ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ መድኃኒት የሚለው ቃል #በመጽሐፍ #ቅዱስ ውስጥ ያለው #ቦታ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ #ዳዊት ስለዚህ ሲናገር <<እግዚአብሔር አምባዬ አለቴ #መድኃኒቴ ነው>>/2 ሳሙ 22፥2/ ብሏል። በኢሳያስ አንደበትም እግዚአብሔር ለእስራኤል ሲናገር <<እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር #መድኃኒትህ ነኝ... እኔ እግዚአብሔር ነኝ #ከእኔ #ሌላ #የሚያድን የለም>> /ኢሳ 43፥3 ፣11/ ብሏል። እንደዚሁም ነብዩ በሌላ ቦታ ሰዎች እግዚአብሔርን <<የእስራኤል አምላክ #መድኃኒት ሆይ...>> ብለው እንደሚጠሩት ይናገርና በዚያው ክፍል ደግሞ #እግዚአብሔርም ስለራሱ በነቢዩ አንደበት <<እናንተ ከአህዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ተሰብስባችሁ ኑ፤ በአንድነትም ቅረቡ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ ከጥንት ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ጻድቅ አምላክና #መድኃኒት ነኝ ይላል>>/ኢሳ 45፥15 ፣ 20፥21/። በሌሎች ነብያትም <<ከእኔም በቀር ሌላ አምላክና #መድኃኒት የለም>>/ሆሴ 14፥4/ እያለ እግዚአብሔር ያውጅ ነበር። #መድኃኒትነት የእርሱ #ብቻ ነበርና ምንም እንኳን #በብሉይ ኪዳን #ሰንበት#በዓለ ሰዊት፣ #በዓለ መጸለት፣ #በዓለ ፍሥሐ፣ #በዓለ ናእት /የቂጣ በዓል/፣ #ኢዮቤልዩ የሚባሉ ታላላቅ #በዓላት ቢኖሩም ከእነዚህ አንዳቸውም #መድኃኒት አልተባሉም። ከእርሱ #ከእግዚአብሔር ሌላ #መድኃኒት እንደሌለ የተገነዘቡ የዘመኑ ነብያትም <<አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ ማለትም ኃይልህን አንሣ መጥተህም #አድነን>>/መዝ 80፥2/ ይሉ ነበር እንጂ ሰንበትን #መድኃኒታችን ነሽ አላሏትም። በአዲስ ኪዳንም #ድንግል #ማርያም ጌታን በጸነሰች ጊዜ <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ #በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባርይቱን ውርደት ተመልክቷልና>>/ሉቃ 1፥47/ብላለች። ጊዜው ደርሶ ጌታ #በተወለደ ሰዓትም #መላእክት በለሊት መንጋ ለሚጠብቁ እረኞች << ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ #ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ብለው አበሰሩ>>/ሉቃ 2፥11/። #መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላቸው ሲመላለስ ሕይወት ሰጪ ትምህርቱን የሰሙት የሰማርያ ሰዎችም ስለእርሱ ሲናገሩ << እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ #የዓለም #መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን>> ሲሉ ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑን ተናግረዋል/ዩሀ 4፥42/። በእርግጥም #ጌታ እኛን ለማዳን #በመስቀል ላይ #ሞቶ ወደ ከርሠ መቃብር ወርዶ #ሞትን ድል ማድረግ ነበረበትና እንደ #መጻሕፍት ሐሳብ #በኃጢአተኞች እጅ ተሰጥቶ #ሞተ። እንደ እግዚአብሔር አሠራርም #ሞትን #አሸንፎ ተነሣ። ይህንን በዓይናቸው ያዩና የተገነዘቡ #ሐዋርያትም #ጌታ #ካረገ ቡኋላ ስለእርሱ #ለአይሁድ ሸንጎ ሲናገሩ <<እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤ ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ #ራስም #መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው>> ሲሉ ራስና #መድኃኒት ስለመሆኑ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል/ሐዋ 5፥31/። ኢየሱስ ማለት #አዳኝ #መድኃኒት ማለት ነው፤ #ዕለተ #ሰንበት ማዳን ብትችል ኖሮ "ወልደ እግዚአብሔር" #ሰው መሆን ባላስፈለገው ነበር።
#የሐዲስ ኪዳን #ምእመናን #ለመዳን እጆቻቸውን ወደማንም አያነሡም፤ #መዳን #በክርስቶስ ካልሆነ #በቀር በሌላ #በማንም... የለምና/ሐዋ 4፥12/። #እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የሚያስችለውን #ከክርስቶስ ሌላ አማራጭ ቢፈልግ ኖሮ #ከሰንበት ይልቅ ብዙ ታላላቅ #ፍጥረታት ነበሩት፤ ሆኖም ግን #ከፍጥረት ወገን #ለማዳን የሚበቃ አልነበረምና #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ብቻውን #ለሰው ልጆች #መድኃኒት ሆነ።
እንደዚሁም በዚህ መጽሀፍ #ሰንበት <<ለዘላለም ገዥ>> ተብላለች፤ #በመጽሀፍ #ቅዱስ ስንመለከት ግን #ሰንበት ለሰው #ተፈጠረች እንጂ ሰው #ስለሰንበት #አልተፈጠረም። ሰዎችንም #ልትገዛ ከቶ አትችልም፤ #ለዘላለም የመኖር እድልም የላትም፤ የእርሷ #የጥላነት ጊዜ አብቅቶ #አካሉ #ክርስቶስ ተገልጧልና።

▶️ መድኃኒትነትም ሆነ #ገዥነት ያለው እርሱ #እግዚአብሔር #ብቻ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ <<ብቻውን የሆነ ገዢ>> የሚለው እርሱን #ብቻ ነው/1ጢሞ 6፥15/። እንደዚሁም <<እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፣ ወገበረ #መድኃኒት በማዕከለ ምድር ማለትም #እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው በምድርም መካከል #መድኃኒትን አደረገ>>/መዝ 74፥12/ የተባለለት የዘለዓለም ንጉሥ አንድ ጌታ ነው እንጂ ሰንበት አይደለችም።
እንደዙሁም ይች #ሰንበት <<ለምኝልን>> ተብላለች። አንዲት የማትሰማና #የጊዜ #መለኪያ ብቻ የሆነችው ^ዕለት^ #አፍ አውጥታ #እንድትናገርና በእግዚአብሄር ፊት ቆማ #እንድታማልድ ወደ እርሷ #እጅን #ዘርግቶ #መማጸን ወደ ልቡ ተመልሶ #ላስተዋለው ሰው ምን ያህል #አሳፋሪ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ቃሉ ግን እኛ ራሳችን #በኢየሱስ #ክርስቶስ #ስም #እግዚአብሔርን እንድለምነው ሲያስተምረን እንደዚህ ይለናል፤ <<ማናቸውንም ነገር #በስሜ #ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ>>/ዩሀ 14፥13/፤ <<የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል>>/ዩሀ 15፥7/፤ <<እውነት እውነት እላቹሀለው #አብ #በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችሀል እስከ አሁን #በስሜ ምንም አለመናችሁም ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ>>/ዩሀ 16፤ 23-24/።
በዚህ መሰረት ወደ ማን #መለመን እንዳለብን ግልጽ ነው፤ በአጠቃላይ #ጸሎታችንና #ልመናችን #በኢየሱስ #በኩል ወደ #አብ እንዲደርስ እንጂ #በሌላ #በኩል ማለትም #በሰንበት ወደ #አብ መግባት እንደማይችል ልንረዳ ይገባል። ጌታም <<በእኔ #በቀር ወደ #አብ የሚመጣ #የለም>> ማለቱ ለዚሁ አይደለምን/ዩሀ 14፥6/?

@gedlatnadersanat
▶️ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን #ደቀመዛሙርቶቹ ተሰብስበው #ስለጸሎት እንዲያስተምራቸው በጠየቁት ጊዜ እንግዲህ እናንተ እንዲህ #ጸልዩ፦ <<በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ፥ #ስምህ #ይቀደስ#መንግሥትህ #ትምጣ፤ ፈቃድህ #በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ #በምድር ትሁን፤ የዕለት #እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን #ይቅር እንደምንል በደላችንን #ይቅር በለን፤ ከክፉም #አድነን እንጂ ወደ #ፈተና አታግባን፤ #መንግሥት ያንተ ናትና #ኃይልም #ክብርም #ለዘለዓለሙ፤ አሜን።>> በሉ በማለት አስተምሯል። [ማቴ 6፤ 9-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]።

▶️ ከዚህ ጌታ #ኢየሱስ ከሰጠው #የጸሎት #መመሪያ ላይ በመቀጠል #አድራሻው ወደ #ማርያም የሆነ፦ <<እመቤታችን ቅድስት #ድንግል #ማርያም ሆይ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ....>> ምናምን የሚለው #ጸሎት ቢኖሮ ኖሮ ወይም መኖር ቢኖርበት ኖሮ ደቀመዛሙርቱ #ጸሎት #አስተምረን ባሉት ጊዜ ባገኘው ምርጥ #አጋጣሚ ወደ #ማርያም #መጸለይ #ትክክል ወይም #ተገቢ መሆኑን ባሳየ ነበር። #ዝንጋኤ የሌለበት በማስተዋልም #ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ <<መንግስት ያንተ ነውና ኃይልና ክብርም ለዘላለሙ አሜን>> ብሎ #የመዝጊያ #ቃል አስቀምጦ ባልደመደመውም ነበር።

▶️ መምህራችንና #ሊቃችን አንድ እርሱም #ክርስቶስ የሆነው #ጌታ [ማቴ 23፤ 8-11] ያላስተማረውን #ትምህርት ከእርሱ ይልቅ #ሊቅ ለመሆን #በመሞከርና #በመጨመር ሌላ ድርሰት ማምጣት #ከንቱ #ድካምና #ፍሬ #ቢስ ከመሆኑም በላይ የሚያመጣው #ፋይዳ (ጥቅም) አይኖርምና <<እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን #በቃሉ አንዳች #አትጨምር።>> [ምሳ 30፥6]።

▶️ በመሰረቱ <<አባታችን ሆይ>> በሚለው #የማህበር #ጸሎት ላይ <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን ብቻ ሳይሆን <<ሊቃውንቶች>> የጨማመሩት #ሠላም #ለኪን#ውዳሴ #ማርያምን#አንቀጸ #ብርሃንን#ይወድስዋ #መላዕክትን#መልክዓ #ማርያምን....ወ.ዘ.ተ ደራርበውበታል።

▶️ የካቶሊክ #ቤተክርስቲያንና ሌሎች #እህትማማች ተብለው የሚጠሩት #አብያተ #ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ካለው የ<<እመቤታችን.... ሆይ>> ጸሎት #የቃላትና #የይዘት #ልዩነት አለው። የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትለው፦ <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እንዲሁም ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታውን ለምኝልን ኃጢታትችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን[1]።>> የሚል ሲሆን #የካቶሊክና#የእህትማማች #አብያተ ክርስቲያናት (የግሪክ፣ የህንድ፣ የአርመን የግብጽ. . .ኦርቶዶክስ) ደግሞ <<ድንግል ወላዲት ሆይ! ማርያም ሆይ፣ ጸጋ የሞላሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የነፍሳችንን አዳኝ ተሸክመሻልና ደስ ይበልሽ[2]>> #ብቻ ነው የሚለው። ይህ ግን #መጽሀፍ ቅዱስ የማይቀበለውና #መጽሀፍ ቅዱሳዊ #ማስረጃ የሌለው ከንቱ #ፈጠራ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ ጌታቸው አየነው (መምህር)፤ "የዘውትር ጸሎት በአማርኛ"፥ ገጽ 5 ፥አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጽ/ጠ/ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ስራ መምሪያ ፤ "ሕያው እግዚአብሔር" ፤አማርኛ ትርጉም ገጽ 316፤ በገላውዲዎስ ተቋም በአባ ጳውሎስ ጻድዋ ካርዲናል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እንዲታተም የተፈቀደ፤ ማስተር ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።