ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የነገረ_ማርያም ጥያቄዎች ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ማርያም ማለት እመ ብዙሐን ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ማሪያም በአርብኛ መሪሃም ተብላ ትጠራለች::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ #ማርያም የሚለው ስም #አብርሃም ከሚለው ስም ጋር ከጾታ ልዮነት ባሻገር በትርጉም ደረጃ አንድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ማርያም ማለት:- እመ ብዙኃን ፣የብዙኃን እናት ማለት ነው

#አብርሃም:- ማለት አበ ብዙኃን፣ የብዙኃን አባት ማለት ነው

#ኛ የኤልሳ ማሰሮ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

የኤልሳ ማሰሮ በውስጧ አጣፋጭ ጨው ተገኝቶባታል ከእመቤታችንም እናንተ የዓለም ጨው ናችሁ ብሎ ማጣፈጥን ለቅዱሳን የሰጠ የአዳምንም ሕይወት በከበረ ሞቱ ያጣፈጠ የአማናዊው #ጨው የክርስቶስ መገኛ ሆናለችና የኤልሳ ማሰሮ #የእመቤታችን ምሳሌዋ ነች

#ኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰው ዘር ስለሆነች ጥንተ አብሶ ወይም የመጀመሪያ በደል ነክቷታል::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት
ምንም እንኳን እመቤታችን የሰው ዘር ብትሆንም በመንፈስ ቅዱስ ልዮ ጠብቆት ከጥንተ አብሶ(ከመጀመሪያው በደል) የነጻች ሆናለች::ወርቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው ::ወርቅ መገኛው ከመሬት ከጭቃ ውስጥ ነው ከጭቃ መገኘቱ ግን ወርቅነቱን አያስቀረውም እመቤታችንም በኃጢያት ጭቃ ከተነከሩ ሰዎች የተገኘች የሰው ፍጡር ብትሆንም ነገር ግን ጭቃው ያላቆሸሻት #ንጹዑ_ወርቅ ነችና ጥንተ አብሶ የለባትም፣ አልነካትም::

#ኛ_በመዝሙር 86 ላይ መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ተብሎ የተነረው ለእመቤታችን ቀደምት አያቶቿ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

መጻሕፍትን ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ እንደተባለው ይህንንም ኀሠይለ ቃል አጣመው በወንድ አንቀጽ ቢቀይሩትም እንደ ጥንቱ መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ነው የሚለው ::ይህም ሰሸለ እመቤታችን ቅደምት አያቶች ከፍታና ቅድስና የሚናገር አንቀጽ ነው ::


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 44÷ ከቁር 1 እስከ ያለው ኃይለ ቃል ምን ምን ነገሮችን ያስረዳል
ሀ )የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና
ለ)እመቤታችንን የወለደችሁ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የአብን አንድያ ልጅ ወልድ እግዚአብሔርን ብቻ እንደሆነ::

ሐ) ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ሌላ ልጅ ዳግመኛ እንዳልወለደች

መ)ሁሉም

#ኛ_ከእመቤታችን የዘር ሐረግ ውስጥ የማይካተተው ነገድ የቱ ነው

ሀ) ነገደ ሌዊ
ለ) ነገደ ይሁዳ
ሐ) ነገደ ዳን
መ) ሀ ና ለ

#ኛ_ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ብሎ የተነበየው ነቢይ ማን ነው

ሀ) ነብዮ ሳሙኤል
ለ)ነብዮ ኤርምያስ
ሐ)ነብዮ ኢሳይያስ
መ)ነብዮ ሐጌ

፱ እመቤታችን ለዮሴፍ የታጨችበት ምክንያት ምን ነበር

ሀ) ከውግረት እድትድን
ለ) ለጋብቻ
ሐ) ለጠባቂነት እና ለአገልጋይነት
መ) ከ "ለ" በስተቀር ሁሉም መልስ ነው


#ኛ_ እመቤታችን በቤተ መቅደስ የኖረችው ለስንት ዓመታት ነው

ሀ) ፲ ፪ ዓመታት
ለ) ፫ ዓመት ከ፫ ወር
ሐ) ለ፫ ዓመታት
መ)ለ፲ ፭ ዓመታት


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰው ልጆች ድኅነት ያበረከተችሁን ትልቅ አስተዋጽኦ አብራራ(ሪ)

#መልስ

#ንጽሕናዋን ጠብቃ በመገኘቷ

#ፍቃዶን ስትጠየቅ እሺ ብላ ለድኅነተ ዓለም ምክንያት በመሆነኗ



፲ ፪ #_ድንግል ማርያም በሦስት መሠረታዊ ነገሮች ንጽዕት ነች ::እነዚህ ሦስቱ መሠረታዊ ንጽዕናዋ የምን የምን ንጽዕና ናቸው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#በሥጋዋ (ንጽ ሥጋ )
#በነፍሷ (ንጽኃ ነፍስ )
#በሀሳቧ ( ንጽኃ ልቡና )

፲ ፫ #እመቤታችን " እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትሁልድ ሁሉ ብጽህይት ይሉኛል" ሉቃ 1÷49 ብላ የተናገረችሁ ስለምንድነው? ትውልዱ #ሁሉ ያለችውስ የትኛውን ትውልድ ነው

#ይህን የለችሁ
👉ነቢይት ሰለሆነች የወደፊቱን የማወቅ ፀጋ ስላላት እና በተሰጣት ፀጋ እንደ ሰጣት እንደ ፈጣሪዋ አዋቂ ስለሆነች

ትሁልድ ሁሉ ያለችው ደግሞ አማኝ ትውልድ ሁሉ ማለቷ ሲሆን በመጨረሻ ግን ክብሯ ሲገለጥ ሁሉም ትውልድ እንደሚያመሰግናት አውቃ ይህን አለች

፲ ፬ #_እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስቀድማ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር በፊት በአምላክ ዕሊና ታስባ ትኖር እንደነበር በትምህርቱ መሠረት ቅዱሳት መጻሕፍትን እያመሳከርክ አስረዳ (ጂ)

#መልስ
."እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ እሊና ታስባ ትኖር ነቀር::፡ ለዚህመሸ "ያልተሰራ አካሌን አይኖችህ አዩኝ ፡ የተፈጠሩ ቀኖቸ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመፅሐፍ ተፃፈ" መዝ 138:16
ስለዚህ ዓለም ሳይፈጠር ሁሉም ከተፃፈ እመቤታችንም ተፅፋ ታስባለች ማለት ነው፡፡፡ቅዱሳን ነቢያት(ኤርምያስንና መጥምቁ ዮሐንስን ) ብንመለከት አሰቀድሞ ስለሚያውቃቸው መስክሮላቸዋል፡፡
" በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። " (ኤር1:5)
ስለዚህ የሁሉ አዋቂ ጌታ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰው መሆኑ ከታወቀና ከታሰበ እመቤታችን መታሰብዋን አይዘነጋም፡፡፡
"፤ #ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 4) "፤ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 4)

#15.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ጽዮን" ተብላ የምትጠራበት የመ/ቅዱስ ጥቅስ፡

"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።"
(መዝ 87:5)
" የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። "
(ኢሳ60:14)
" ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል እግዚአብሔር። "
(ኢሳ59:20

#በመልሶቹ ዙሪያ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #_መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአንድ ጊዜ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

2 #_መዝሙረ ዳዊት በከተማ ስም ከተሰየሙ መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

3 #_የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ ትንቢተ ዳንኤል ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

4 #_መጽሐፈ አስቴርን የጻፈችው አስቴር ነች።

ሀ ) እውነት ለ) ሐሰት

5 #_የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ይዘት ምርጫ

6 #_ከሚከተሉት መካከል የታሪክ መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው

ሀ) ግብረ ሐዋርያት
ለ )የማቴዎስ ወንጌል
ሐ )ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች
መ) ሀ እና ለ

7) #ከተዘረዙት መጻሕፍት መካከል #_ሊቀ _ነቢያት ቅዱስ ሙሴ #ያልጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው

ሀ ) መጽሐፈ ኩፋሌ
ለ ) ኦሪት ዘፍጥረት
ሐ ) ኦሪት ዘዳግም
መ ) መጽሐፈ አክሲማሮስ

8) #_የኦ/ተ ቤተ ክርስቲያናችን ምትቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥራቸው ስንት ነው

ሀ ) 46
ለ ) 27
ሐ ) 35
መ ) 81

9 #_መጽሐፈ ምሥጢር ከየትኛው የአዋልድ መጽሐፍ ጋር ይመደባል
ሀ )ድርሳን
ለ )ነገረ ሃይማኖት
ሐ )የሥርዓት
መ )የታሪክ

10 #_"ገና እንደተወለዱ ልጆች የቃሉን ወተት ተመኙ።" 1ጴጥ 2:3 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል

ሀ )መጽሐፍ ቅዱስ ዳኛ መሆኑን
ለ ) መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጽድቅ የሚመራ መሆኑን
ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ ምግበ ነፍስ መሆኑን
መ)መጽሐፍ ቅዱስ የሕግ እና የአስተዳደር ምንጭ መሆኑን

#በአጭሩ መልስ ስጡ

11 #መጽሐፍ_ቅዱስን_ቅዱስ ካሰኙት ነገሮች መካከል ቢያንስ ሦስት ጥረሱ::
#በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሱ ቅዱሳን ሰዎች ስለጻፉት
#ወደ ቅድስና ስለሚመራ
#በቅዱሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለተጻፈ
#ዘመን የማይሽረው መሆኑ
#መጻኤዉንና አላፊውን በትክክልና በእርግጠኛነት የሚናገር ሰለሆነ
#የሌሉሎች መጻሕፍት ዋኘና ምንጭ በመሆኑ

12 #ከመጻሕፍ_ቅዱስ ባህል መካከል ቢያንስ 2ቱ ጠቅሰህ(ሺ)ከሀገራችን ተመሳሳይ ባህል ጋር አንድነቱንና ልዮነቱን አነጻጽር(ሪ)::

እረኝነት:-
ሰርግ:-
ጫማ ማውለቅ:-


13 #አዋልድ_መጻሕፍት ከሚባሉት መካከል 3ቱን ጥቀስና ጥቅማቸውን በአጭሩ አብራራ(ሪ)

#መልስ
#አዋልድ መጻሕፍ የሚባሉ
#ገድል :-
#ተአምር :-
#ድርሳን :-
#መልክዕ :-

#ጥቅማቸው
ከአባታቸው ከመጻሕፍ ቅዱስ ጠባይ ሳይወጡ የቅዱሳንን ተጋሎ ድንቅ ድንቅ ተአምራት እና ተራዳይነት እንዲሁም ክብርን የሚገልጡ በመሆን መጻሕፍ ቅዱስ በጥቂቱ እና በመጠኑ በፍንጭ መልክ የገለጠውን አነርሱ አምልተውና አስፍተው ይተነትኑታይ ማለት ነው::#በአጠቃላይ በደረቁ በንባብ የተጻፈውን ወንጌል በሕይወት ተተግብሮ እያሳዮ ሃይማኖት ያጸናሉ ምግባር ያቀናሉ ይሕወት ይሆናሉ::

14 #የመጻሕፍ_ቅዱስ ዕድሜ ሰንት ነው? መጀመሪያ የተጻፈውስ የመጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?በምንስ ቋንቋ ተጻፈ?

#መልስ

ዘመኑ በትክክል በውል አይታወቅም መጀመሪያ የተጻፈውም መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተጻፈበት ቋንቋም እንደ ኢትዮጲያዊያን ሊቃውንት ገለጻ #በግዕዝ_ቋንቋ ነው

15 #መጻሕፍ_ቅዱስን እንደ ምንኖርበት ሀገር ባህል ፣ እንደ ደረስንበት የዕውቀት ደረጃ ፣ በሥጋዊ ሀሳብና ፍልስፍ ማንበብእና መተርጎምና የሚያስከትለውን ጥፋት በራስህ(ሺ) አገላለጽ አስረዳ(አስረጂ)

#መልስ

*ወደ ክህደትና ምንፍቅና ይከታል #በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይለያል የሚል መሰል ምላሾችን የሰጣችሁ ሁሉ ትክክል ናችሁ!::

#ለበለጠ_መረጃ የተላለፉ ኮርሶችን ያድምጡ

#በመልሶቻችሁን ዙሪያ ላላችሁ ማንኛውም አሳብ ጥያቄና ጥቆማ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች መልስ

1 ማቴ 1:1–17 እና ሉቃ 3:23-38 ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ የዘር ሐረጉን ይተነትናል። እነዚህ ሁለት የዘር ሐረግ ትንተናዎች በዮሴፍ በኩል የተቆጠሩ ናቸው። በዮሴፍ በኩል የተቆጠሩበት ምክኒያት ምንድን ነው? ማቴዮስ የዮሴፍን አባት ያዕቆብ ይለዋል። ሉቃስ ደግሞ ዔሊ ይለዋል። እነዚህ እንዴት ይስማማሉ? ለአንድ ሰው ሁለት አባት ሊኖሩት ይችላሉ?

#መልስ
በማቴ 1:1-17 በዚህ ክፍል ማቴዎስ ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ድረስ 42 ትውልድ ቆጥሯል። የትውልዱ አቆጣጠር በእመቤታችን በኩል ሳይሆን በዮሴፍ በኩል ነው። ምክኒያቱ ምንድን ነው ቢሉ የሀረገ ትውልድ አቆጣጠር ልማድ መሰረት ትውልድ የሚቆጠረው በወንድ በኩል ስለሆነ ነው። በተጨማሪም ዮሴፍ ከእመቤታችን ጋር በአንድ የትውልድ ሀረግ ውስጥ ስለሆነ በዮሴፍ በኩል መቆጠሩ ሀረገ ትውልዱን አይለውጠውም።
ሉቃ 3:23–38 ሉቃስ "እንደመሰላቸው" (የዮሴፍ ልጅ) ብሎ በመግለጽ ከራሱ ከዮሴፍ ጀምሮ ወደ ላይ እስከ አዳም ድረስ 78 ትውልድ ይቆጥራል። ከማቴዎስ ጋር የሚገናኝበትም የሚለያይበትም አለ። ይህ እንዴት ነው ቢሉ ማቴዎስ የዮሴፍን አባት ያዕቆብ ይለዋል ሉቃስ ደግሞ የዮሴፍ አባት ኤሊ ይለዋል። ሲያዩት የሚጋጭ ይመስላል ግን አይጋጭም። እንዴት ቢሉ ዳዊት ናታን እና ሰሎሞን ሚባሉ ሁለት ልጆች አሉት ማቴዎስ የቆጠረው በሰለሞን የወረደውን ነው። ሉቃስ ደግሞ በናታን በኩል ቆጠረ። እንዲም ቢሆን ዮሴፍ ሁለት አባት አለው ማለት አይደለም። ማቴዎስ በልደት ሥጋዊ ቆጠረ። ይህ ማለት ያዕቆብ የዮሴፍ የሥጋ አባት ነው። ሉቃስ በልደት ሕጋዊ ቆጠረ። እንዴት እንደሆነ እንመልከት

ማቲ የተባለው ሰው ዔሊን ወለዶ ይሞታል። ሉቃ 3:24 ማታን የማቲን ሚስት አግብቶ ያዕቆብን ይወልዳል። ያዕቆብ እና ኤሊ በእናት የሚገናኙ ወንድማማቾች ናቸው። ዔሊ ታላቅ ነው ያዕቆብ ታናሽ። በእስራኤል ልማድ ታላቅ ሳያገባ ታናሽ አያገባም። ኤሊ አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ይሞታል። የኤሊን ሚስት ደግሞ ለያዕቆብ ያጋቡታል። የሙት ወንድምን ሚስት ማግባት በእስራኤል ልማድ ነው። ስለዚህ ሉቃስ ኤሊን የቆጠረው በልደት ሕጋዊ ነው። ኤሊ ዮሴፍን ባይወልደውም ሕጋዊ አባቱ ነው። ያዕቆብ ደግሞ ሥጋዊ አባቱ ነው።

ወደ እመቤታችን ሀረገ ትውልድ ስንመጣ ግን ከአላዛር እንጀምራለን። ማቴ 1:15

አላዛር ማታን እና ቅስራን ይወልዳል። ማታን ያዕቆብን ያዕቆብ ዮሴፍን ይወልዳል። ቅስራ ደግሞ የእመቤታችንን አባት ኢያቄምን ይወልዳል።

2 ዘዳ 34:4–5 "የእግዚአብሔር ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ። በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሞዓብ ምድር በሸለቆው ውስጥ ተቀበረ፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም አላወቀም።" እንዲሁም ኢዮብ 42:16-17 "ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ተውልድ ድረስ አየ። ኢዮብም ሸምግሎ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ።" ይላል። የኦሪት ዘዳግም ጸሐፊ ሙሴ ሲሆን የመጽሐፈ ኢዮብ ጸሐፊ ደግሞ ኢዮብ ነው። ሁለቱም ስለሞታቸው በመጽሐፋቸው እንዴት ጻፉ?

#መልስ
እግዚአብሔር አምላክ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲሁም ለጻድቁ ኢዮብ ከሰጣቸው ጸጋ አንዱ ነቢይነት ነው። ነቢይ ወደ ፊት የሚደረጉትን ነገሮች በሙሉ እግዚአብሔር ገልጦለት ያውቃል። በዚህም መሰረት ሙሴ እና ኢዮብም ነቢያት ስለሆኑ አሟሟታቸውንም ጭምር ያውቃሉ።

3 ዮሐ 14: 27 "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።" ይላል በማቴ 10:34 ላይ ደግሞ ጌታችን "በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።" ይላል። በአንድ ቦታ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ሌላ ቦታ ሰላምን ሳይሆን ሰይፍን ለማምጣት መጣሁ ይላል። እነዚህ ኃይለ ቃላት ይጋጫሉ? ካልተጋጩ እንዴት?

#መልስ
ክርስቶስ ወደዚህ ምድር በመምጣቱ ሰላማችን መረጋገጡ ምንም ጥያቄ የሌለው ነገር ነው። ኢሳ 9:6 ሉቃ 2:14 ኤፌ 2:14
ነገር ግን በማቴ 10:34 ላይ ሰይፍን ይዤ ወደ ምድር መጣሁ ማለቱ ሰይፍ በቁሙ የተሳለው ብረት ሳይሆን #ቃለ_እግዚአብሔርን ነው። ቃለ እግዚአብሔር እንደ ሰይፍ በማሰብ በመናገር በመስራት የተሰራውን የሰውን ኃጢአት መርምሮ ኃጥኡን ከጻድቁ ይለያል እንዲሁም ይፈርዳልና ነው። ዮሐ 12:48 ራዕ 1:16 ዕብ 4:12–16 ኤፌ 6:17

4 ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ ላይ ስለ ካህኑ መልከጸዴቅ ሲናገር "አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። " ዕብ 7: 3 አለው። ሰው ያለ እናት እና አባት ሊወለድ ይችላል? ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ስለ መልከጸዴቅ ስለምን ተናገረ?

#መልስ
ለመልከ ጸዴቅ እናቱ እገሊት አባቱ እገሌ ነው ተብሎ የተነገረለት እንዲሁም በዚህ ቀን ተወለደ በዚህ ቀን ዐረፈ ተብሎ በሌዋውያን ወይም በእስራኤላዊያን ዘንድ የተጻፈ ምንም መጽሐፍ የለም። ስለ ነገረ ትውልዱም በእስራኤላዊያን ዘንድ አይታወቅም። የዘር ሀረጉም ከሌዋውያን ዘንድ አይቆጠርም። ዕብ 7:6 ነገር ግን መልከ ጸዴቅ የካም የዘር ግንድ ነው ያለው። ለዘመኑ ፍጻሜ የለውም የሚለውም የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ሰው አይደለም ለማለት እንዳልሆነ ማስተዋል ይገባል። ሰው ከሆነ በሥጋ መሞቱ የማይቀር ነገር ነው። ያ ማለት ግን ከዚህ በፊት ሞቷል ማለት አይደለም። ዕብ 7:8 በመጽሐፍ ቅዱስ እነ ሄኖክ እነ ኤልያስ ሞትን ሳያዩ እንደተወሰዱ ይታወቃል። መልከ ጸዴቅም ከእነርሱ መካከል አንዱ ነው። በሌዋውያን መጽሐፍ ጥንቱም ሆነ ፍጻሜው ባለመጻፉ ምክኒያት ለህይወቱ ፍጻሜ የለውም ሲል ጽፏል። በዚህም ምክኒያት መልከጸዴቅ ለጌታችን ምሳሌ ሆኗል።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ከዚህ ቀደም በዓውደ ምህረት ዘተዋሕዶ በ #ምን_እንጠይቅልዎ ከተሰኘው አምዳችን ካስተናገድናቸው ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹን በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሱትን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

#ጥያቄ ሰላም ለእናንተ ይሁን የክርስቶስ ቤተሰቦች እንኳን ለዳግመ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
እኔ የምጠይቀው ጥያቄ የወቅቱ ባይሆንም ግን ሁል ጊዜ በልቤ የሚመላለስ ጥያቄ ነው ዛሬ ያነሳሁት ሰሞኑ በመንፈሳዊ እና በአለማዊ የቴሌቪዥን መስኮት ያየሁ ነገር የበለጠ እንድጠይቅ አስገድዶኝ ነው።
ጥያቄ ከስርአተ ቤተ ክርስቲያን የተያታዘ ነው እኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ስንማር የሚዘመሩ መዝሙሮች እንኳን ተለይቶ ተሰጥቶን ነው ምንዘምረው የነበረው ዛሬ ዛሬ ግን የማንም ተራ አርቲስት ተነስተው መዝሙር ይዘምራሉ ዘምረው ዘማሪት ዘማሪ ይባላሉ ንስሀ ግብተው ወደ እግዚአብሔር ቤት ተመልሰው ነው እንዳንል በሌላኛው ቀን በሜካፕ በአጭር ቀሚስ በቃ ምን አለፋሽ በአጭሩ በአለም ውስጥ እናያቸዋለን ይባስ ብለው ማህተባቸውም አውልቀው አይተናል ይሄ ነገር ከተዋህዶ ስርአተ አስተምሮ እንዴት ይታያል ቤተክርስቲያናችን ይሄ ነገር እንዴት ታየዋለች

#መልስ
ጠያቂያችንን ከልብ እናመሰግናለን የሕይወትን ቃል ያሰማልን!!

ቤተ ክርስቲያናችን ባህረ ጥበባት የጥበባት ባህር ናት በመሆኑም ጥበብንና ጥበበኞችን አትቃምም አትደግፍም : :አብዛኛውን ጊዜ እንደውም ለጥበብ ባለ ውለታ ሆና ትገኛለች በየ ቴሌ ቪዥን መስኮት የምንመለከታቸው አብዛኞቹ አርቲስቶችም ከቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህር ቤቶች የተገኙ የማህጸኗ ፍሬ ናቸው:: እዚህ እየዘመሩ እዚያ መዝፈናቸው እዚህ የሀገር ልብስ ለብሰው እዛ ሚኒ እስከርት እዚይህ በማዕተም እዛ ማውለቃቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጥርጥር የሌለው ስህተት ነው:: ሆኖም እንደዚህ ከሆናችሁ አንዱን ያዙት ወይ ዝፈኑ ወይ ዘምሩ ብለን ግን ልንፈርድባቸው አይገባንም ዝም ብሎ ከመዝፈን እየዘመሩ መዝፈን የተሻለ ነው :: ማን ያውቃል ይመልሳቸው ይሆናል

ተዋናይነት ለአንዳንዶች ሕይወታችው መደበኛ ስራቸው የሆኑ ብዙ ተዋንያን ሊኖሩ ይችላሉ ስለሆነም አንዱን ያዙ ወይ ዘምሩ ወይ ዝፈኑ ብሎ ማስጨነቁ ግሮሮዋቸው ላይ ቆሞ የሕይወታቸው እልውና መፈታተን ነው:: እግዚአብሔር አምላክ በስተ መጨረሻ ሥራ ሊሰራባቸው ይችላል ስለዚህ እየተወኑ ይዘምሩልን እየዘፈኑ ያመስግኑልን በታሪክ እንደምናውቀው አንዳንዶች በስተ መጨረሻ ንስሐ ሲገቡ ዘማሪ ሲሆኑ ይታያል በዚህም እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ተከታዮቻቸው(አድናቂዎቻቸውንም ) ጭምር የሚመልሱ ይሆናሉ:: የሚገርመው የተዋንያኖቹ ሳይሆን የአዘጋጆችና ካሜራ ማን የሆኑ ሰዎች አመለካከት ነው ሰይጣን ክርስቲያኖችን አብዝቶ መፈተኑ አይቀርም:: የየ ሰንበት ትምህር ቤቱ ወጣት ሁሉ ተዋንያን ለመሆን ሲፈልግ ለምን መስቀሉን ከአንገቱ እንዲያወልቅ ይገደዳል? ትወና ማለት እኮ ማስመሰል እንጂ መሆን አይደለም :: አንዳንድ ዘፋኖች ሲዘፍኑ እጃችሁን ወደላይ ወደላይ ይላሉ አሉ ሕዝቤም እውነት መስሎት እጁን ሲያነሳ ጓደኞቻቸው ኪስ እየገቡ ብዙዎችን እንደሚያጥቧቸው ሰምቻለሁ ታድያ አዘጋጆችስ (producer ) ምን ነካቸው ለቀረጻ ስለማይመች መስቀልህን መስቀልሽን አውልቂ አውልቅ እያሉ ለሌባው ዲያቢሎስ ሕይወታችንን የሚሰርቁት ለምንድነው? ከሳጥናኤል ጋር ተመሳጥረው ይሆን???


ሌላውን ትተን ሁል ጊዜ በየ ምሽቱ ቤታችንን እያንኳኳ "ቤቶች" የሚለንን ተከታታይ ሲት ኮም የቴሌ ቪዢን ድራማን እንኳን መስቀል አድርገው እንዳይቀረጹ ተዋንያን ይከለከሉ ነበር:: የሰውን ዘር ሁሉ እንዳይጠፋ የሚጠብቅ መስቀል አውልቁ ካልሆነ አትሰሩም እያለ ዘሩ ዘራችንን አቀለጠ::ለነገሩ መስቀል የሌለው ስለ መስቀል ክብር ሊያውቅ ሊረዳ አይችልም::

በዚህ ሁኔታ ታድያ በአገኙት አጋጣሚ ዕውቅናቸውን ለእግዚአብሔር ዕውቅና ያዋሉ ተዋንያን ዘማሪዎቻችንን ልናመሰግናቸውና በርቱ ጠንክሩልን ልንላቸው ይገባል እንጂ ልንወቅሳቸው አይገባም ባይ ነኝ::
እንደውም ዝማሬ መላእክትን ያሰማለን እስከ መጨረሻው በቤቱ ይትከልልን🙏አሜን

#ጥያቄ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉሻል የተባለው ለድንግል ማርያም ነው ወይስ ለኢየሩስ አሌም ነው?

#መልስ
ቃሉ የተናገረችሁ እሯሷ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት የተናረገችሁም ስለ እራሷ ነው

"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 48)


እንዴ ስለ እሯሷ እንዲ ተናገረች ቢሉ
1) እውነተኛው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሴቶች ሁሉ የተለየች እንደሆነች ስለነገራት

2) እመቤታችን ነቢይት ስለሆነች ፀጋን የተሞላች ነችና የጉደላት ፀጋ የለም በመሆኑም ወደፊት የሚሆነውን የሚደረገውን አውቃ በአንድ በቅዱስ ገብርኤልና በአንድ ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል አለች በዚም እውነት ተናገረች ትውልዱ ሁሉ ብጽይት እንላታለንና

ምነው ይህ ሁሉ ሃይማኖት ይህ ሁሉ መናፍቅ ባለበት ዓለም እንዴት ሁሉ ብጽይት ይሉኛል አለች ብለው ቢጠይቁ

ሁሉ ያለችሁ

1) አማኝ ትውልድን ሁሉ ማለቷ ነው ወላዲተ አምላክነቷን ዘላለማዊ ድንግልናዋን አማላጅነቷን ያመኑ ሁሉ ምዕመናን ያመሰግኑኛል ማለቷ ነው:: ይህም የመጻሕፍ ቅዱስ የአገላለጽ ባህል ነው ለምሳሌ በሉቃስ ወንጌል 2÷1 ላይ እንዲ ተብሎ ተጽፎል

"፤ በዚያም ወራት 👉ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች። "

አውግስጦስ ቄሳር ዓለምን በሙሉ አልገዛም በዓለም ታሪክም እስከ ዛሬ ድረስ ዓለምን አንድ ንጉስ ጠቅልሎ አልገዛትም


አውግስጦስ ቄሳር ትዛዙን ያወጣው ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ብሎ ነው :: ምን ማለቱ ብለን ልንጠይቅ ይገባል አውግስጦስ ቄሳር ዓለሙ ሁሉ ይጻፍ ዘንድ ያለው በግዛቱ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሳይቀሩ ለማለት ነው እንጂ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያሉ ሰዎች ሁሉ ይጻፉ ማለቱ አይደለም

በዚሁ በንጉሡ ትዕዛዝ እና በቅዱስ ሉቃስ አገላለጽ ዓለሙ ሁሉ የተባለው በግዛቱ ሥር የሚገኙት ሰዎች ለማለት እንደሆነ እመቤታቸንም ትውልዱ ሁሉ ስትል ሁሉን በአንድ ጨፍልቃ ሳይሆን አማኝ ትውልድ ሁሉ ማለቷ መሆኑን መገንዘብ ያሻል:: በእርግጥ በስተ መጨረሻ እመቤታችንን የማያመሰግናት ትሁልድ የለም ክብሯ ሲገባው አማላጅነቷ ሲታወቀው ሁሉ ብጽይት ይሏታል ይሰግዱላታልም::
"፤ የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። " ተብሎ በነቢይ ተነግሮላታልና::

(ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 14)
#ጥያቄ የኔ ጥያቄ 1ኛ ሎቱ ስብሀት ማለት ምን ማለት ነው? ሰው ሲል እሰማለው እኔ ግን ብዬ አላውቅም ትርጉሙን ስለ ማላቀው።

2ኛ በመፅሀፍ ቅደስ ከ 10ቱ ትእዛዛት ውስጥ 1 እትግደል ነው በወንጌልም ክርስቶስ ሲያስተምር ወንድሙን ጨርቃም ብሎ ሚሰድብ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ይላል ከዛም አልፎ ግራህን ሲመታህ ቀኝህን ስጠው ይላል. ታዲያ ለሀገር ዘብ ሚቆሙ ወታደሮች በጥምርነት ብዙ ነፍ ያጠፍሉ ይህ ነገር ትእዛዙን ማፍረስ አይደል እንዴ ታዲያ ቤተክርስቲያን እንዴት ነው አስተምሬትዋ በዚ ዙርያ ??

#መልስ
እሺ ጠያቄያችን በጣም እናመሰግናለን ጥያቄውን ለመመለስ ያክል

#ሎቱ ስብሐት ማለት ክብር ምስጋና ይግባው ማለት ነው:: ቃሉን የምንጠቀመው ለወንድ አንቀጽ ሲሆን ሎቱ ስብሐት እንላለን እንዲሁ ለሴት ሲሆን ደግሞ #ላቲ ስብሐት እንላለን ክብር ምስጋና ይግባት ማለታችን ነው::

ቃሉን የምንጠቀምበት ሁኔታ ስለ ስለ አምላካችን ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ ነክ ነግግሮችን እነ እከሌ እንዲ ይላሉ ከማለታችን አስቀድመን ክብር ምስጋና ይግባውና እነ እገሌ(መናፍቃን) እንዲ ይሉታል እርሱ ግን እንዲ አይባልም ለማለትና ላቲ ስብሐት ክብር ምስጋና ይግባትና እመቤታችንን እነ እገሌ እንዲ ይሏታል እርሶ ግን እንዲ አትባልም ለማለት እንጠቀመዋለን:: በአጠቃላይ አባቶቻችን የደፋሮችን የትቢተኞችን ንግግር እንዲ አሉ ብለው ለመናገር ሲሉ እንኳን ስመ እግዚአብሔርን አጥብቀው ስለሚያከብሩ አስቀድመው ክብርንና ምስጋናን በማቅረብ ጸያፉን የሰነፎች ንግግር ያስከትላሉ ይህም አርቆ ማጠር ነው::አባቶቻችን ተሳዳቢሆች እንዲ አሉ ብለው የተሳዳቢዎችን ግግር ቃል በቃል አይናገሩም ምክንያቱ እነሱ ያሉትን ለማስተማርም ቢሆነ እንደ እራሳቸው ንግግር አድርገው መናገር አይፈልጉምና አገለ አለ እንጂ እኔ አልልም እርሱ ክብር ምስጋና የማገባወ አምላክ ነው ሲሉ የመናፍቃንን ንግግር በሙሉ ከመናገራቸው በፊት ሎቱ ስብሐት ክብር ምስጋና ይግባውና ብለው ይጀምራሉ ለእመቤታችን ከሆነ ደግሞ ላቲ ስብሐት ይላሉ :: ከሰደበኝ የደገመኝ ነውና የመናፍቃንን ንግግር እንደወረደ እንዲሁ ማቅረብ አይገባም::

ለምሳሌ:- አባቶቻችን ስመ እግዚአብሔርን ሲጠሩ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለው አክብረው ይጠሩታል:: ደፋሮቹ መናፍቃን ግን ወዴ ወዳጄ ከማለታቸውም አልፈው ኢየሱሴ ብለው በነጠላው ይጠሩታል ይህ ግን ነውር ነው :: ለባሊ እንኳን ማንጠልጠያ አለው:: ስለዚህ አንድ ሰባኪ መናፍቃን የፈጣሪን ስም ሲጠሩ ሎቱ ስብሐት ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና በነጠላው ኢየሱስ ብለው ነው ብሎ ቅድሚያ እራሱ ክብር ሰቶ አስከትሎ አጸያፊ ንግግራቸውን ይናገራል እንጂ ዝም ብሎ መናፍቃን እንዲ ይላሉ ብቻ ማለት ከእራሳቸው ከመናፍቃን አለመሻል ነው::

ሁለተኛው ደግሞ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ሕግና ደንቦች ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ያገለግላሉ ወይም ሙሉ በሙሉ ይፈጸምባችዋል አይባልም::

ለምሳሌ ያክል በማቴዎስ ወንጌል 16÷16 ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃነታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል "ብሎ ትዕዛዝ አስተላልፎል ይህ ትዕዛዝ ግን ለሁሉ ይሰራል ማለት አይደለም የማይመለከታቸው አካላት አሉና ለምሳሌ ሕጻናት ሕጻናት በ40እና በ80ቀናቸው የልጅነት ጥምቀትን ይጠመቃሉ መቼ ተምረው? መቼ አምነው ነው የሚጠመቁት ሊያስብል ይችላል ስለዚ ይህ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ለሕጻናት አይሰራም ማለት ነው::

ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሀገር የሚጠብቁ ደንበር የሚያስከብሩም የሀገር ዘብ የሆኑ (ወታደሮች) አትግደል የሚለው ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ አይተገበርባቸውም በመጻሕፍ ቅዱስ ከፎ አድራጊዎችን በመግደላቸው እንደ ጽድቅ የተቆጠርላቸው ሰዎች እንዳሉ መመልከት እንችላለን ::በአገራችን ታሪክ በአድዋ ጦርነት ጊዜ እቴጌ ጣይቱ ለዘመቻ የተሰበሰበውን ወታደር ጠርተው ሀገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ወራሪ ጠላት መቶብናልና ሁሉችሁም በድፍረት ተዋጉ ለሀገር ለወገን መሞት ሰማዕትነት ነው ብለው እንዳበረታቶቸውና በሕይወት ተርፈው ከተመለሱ እንደሚሸለሙ ከሞቱም የጀግና አቀባበር እንደሚያደርጉ ልጆቻቸውን እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተው እንዳዘመቷቸው የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ " ባለጌን ካሳደገው የገደለው ይጸድቃል" እንዲሉ

በወንጌል መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወታደሮች(ጭፍሮች)ቀርበው እኛስ የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ምን እንደርግ ዘንድ ትወዳለህ ብለው በጠየቁት ጊዜ ሰው አትግደሉ ብሎ አልመከራቸውም ሥራቸው ከሰው መግደል ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ያውቃልና ከዛ ይልቅ ሌሎች ትዕዛዛትን እንዲጠብቁ አዘዛቸው እንጂ
"፤ ጭፍሮችም ደግሞ። እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም። በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው። " (የሉቃስ ወንጌል 3: 14)

ሌላው ወታደር ብለን ካነሳን ቅዱሳን መላእክትም የሰራዊት ጌታ የቅዱስ እግዚአብሔር ወታደሮች ናቸው ትዕዛዝ የጠበቀውን በረከትን ሲሰጡ ትዕዛዝ ያፈረሱት ደግሞ ይቀጣሉ ይገላሉ ::

"፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። "
(ኦሪት ዘጸአት 23: 21)

ስለዚህ ወታደሮች አትግደል ከሚለው ትዕዛዝ ወጣ ያሉ ናቸው ይህ ማለት ግን ያለ ምክንያት የዓይን ውኃ አላማረኝም ወይም ደግሞ ጥይቴ እንደሚሰራ ላረጋግጥ ብለው ሰወችን መግደል ይችላሉ ማለት አይደለም::!!!!

ይቀቆየን ስለነበረን ጊዜ የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ስም ከእናቱ ከእመቤታችንና ከወዳጆቹ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር የከበረ የተመሰገነ ይሆን ለዘለዓለሙ አሜን🙏
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ከዚህ ቀደም በምን እንጠይቅሎ ዓምዳችን ከተጠየቁት ጥያቄዎች መካከል በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሰውን መልስ እነሆ።

#ጥያቄ
ዘፈን ሀጢያት ነዉ። ታዲያ ለምንድን ነው መፅሀፍ ቅዱስ ላይ እና የፀሎት መፅሀፍ ላይ ዘፈን የሚፃፈዉ አብራሩልኝ?

#መልስ
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን መዝ 150÷8
ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘፈንን ትከለክላለች ለምን ቢሉ

* ፍጡር ለፍጡር የሚያቀርበው በመሆኑ ዘፈን መዝፈንን ቤተክርስቲያን ትከለክላለች። ይህም እንደ አምልኮተ ጣኦት ይቆጠራል። አማልክት ዘበ ሀሰት ከሚባሉት አንዱ ደግሞ ሴት ወይም ወንድ ናቸው። (ሴት ለወንድ ስዘፍን እንዳመለከችው ይቆጠራል። ወንድም ለሴት እንደዛው።)

ሌላው ስጋዊ ደስታን በመፍጠር ስህተት እንድንሰራ ከክብር እንድናንስ( ዝሙት እንድንፈጽም) ያደርጋል። ዲና ክብሯን ያጣችው የአህዛብን ዘፈን ለመመልከት ስትወጣ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። የዮሐንስም አንገት የተቆረጠው የሄሮድያዳ ልጅ ባቀረበችው ዘፈን የተነሳ ነው። ዘፍ 34:1 እና ማቴ 14


የእህታችን ጥያቄ ግን ከዚህ ይለያል መዝፈን እንደማይቻልና እደተከለከለ ታውቃለች የሷ ጥያቄ ለምን ታድያ መጻሕፍ ቅዱስ ዘፈን እያለ ይናገራል ነው?

ከጅምሩ መጻሕፍ ቅዱስ አንድ ሰው ዘመረ ለማለት ዘፈነ ብሎ አያቅም ዘፋኙን ዘፋኝ ዘማሪውንም ዘማሪ ይላል እንጂ
በመዝሙረ ዳዊት 150÷5-አካባቢ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔርን ድምጹ መልካም በሆነ ጸናጽልና በዘፈን አመስግኑ ያለ ይመስላል ገልጣችሁ ብታነቡት በዘፈን አመስግኑ የሚል ቃል ቁልጭ ብሎ ታገኛላችሁ ቅዱስ ዳዊት እርሱ እግዚአብሔርን በበገናና በመዝሙር አመስግኖ እኛን በፍጹም በዘፈን አመስግኑ ሊለን አይችልም ታድያ ከየት መጣ???
የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች በሥርዋጽ (በድብቅ ያለ ዕውቀት) የከተቱት የሀሰት ገጸ ንባብ ነው በጥንቱ የግእዝ መጻሕፍት ይህ አይነት ገጸ ንባብ በጭራሽ የለውም
ለሆዳቸውና ለሥጋቸው ያደሩ የመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን የአጋንንት ማደሪያ የሆኑ ሊቅ ተብዬዎች ሁሉ ሳይቀሩ የበሉበትን የዕውቀት ወጪት ሰባሪ የሆኑ የእስሯ ንባቧን ትርጓሜዋን ድጓ ጾመ ድጓዋን ተምረው የዕውቀቷን ጽዋ ጠጥተው በገንዘብ የሸጧት የውስጥ ቁስል የእናት ጡት ነካሾች ያስገቡት የሀሰት ትምህር ነው ::እንኳን መጻሕፍ ቅዱስ መጻሕፍ ቅዱስን የምንፈታበት የአንድምት መጻሕፍት ሁሉ ሳይቀሪ ተመሰቃቅለዋል መጻሕፍት መበረዝ ዛሬ የመጣ አይደለም ስለዚህ አንደነቅም መናፍቃንቢነሱ ቢነሱ ርዕሰ መናፍቃን ከተባለው ከአርዮስ የበለጠ ሊቅ መናፍቅ አይነሳም እርሱም ቢሆን እንኳን ነቅንቆ ሊጥላት አልተቻለውም መሠረቷ የጠበቀው የክርስቶስ ደም ነውና "የገሀነምም ደጆች አይችሏትም" እንዳለ ማቴ 16÷15
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የመናፍቃንን ድብቅ ሴራ ያውቅ ነበርና እንዲ ብሎ መክሮናል


" በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።"
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:16)


አይ መጻፍ ቅዱስ ዘመረ ለማለት ዘፈነ እያለ ተጠቅሞል የሚሉ ካሉም ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ታስማማዋለች

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፈን የሚለውን ቃል እንደየአገባቡ ይፈታል። ይህም መዝሙር ተብሎ። ለምሳሌ ዳዊት ዘፈነ ቢባል ዘመረ ማለት ነው እንጂ አቀነቀነ ማለት አይደለም። ግን ዘፈን የሚለው ቃል መዝሙር ተብሎ የማይተረጎምበት ቦታ አለ። ለምሳሌ
ኦሪት ዘጸአት 32 :5 – 6
"አሮንም ባየው ጊዜ መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም።ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው ሲል አወጀ። በነጋውም ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የደኅነትም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ።"

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:7 "ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።"

"፤ በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ፥ ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችም በዚያ ይኖራሉ፥ በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 13: 21)

ከላይ በተጠቀሱት ቃላት መሠረት ዘፈን ኃጢአት ነው የተባለው ለዛ ነው።

ሌላ ለመጥምቁ ዮሐንስ አንገት መቆረጥ የሆነው ሥጋዊው ዘፈን መሆኑ ግልጥ ነው። ማቴ 14:6

ስለዚህ ዘፈን የሚለውን ቃል እንደ አገባቡ መተርጎም ይገባል። ሲቀጥል ዘፈን ማለት በስልት በዜማ የሚጮህ ጩኸት ማለት ነው። መዝሙርም የሚለው በቃል ፍቺ ተመሳሳይነት አለው።

ይቆየን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ጥያቄ

ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ ተገቢ ነውን? ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ የተፈቀደ ነው ወይስ ኑዛዜ አያስፈልግም?

#መልስ

ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ

† የሰው ልጅ ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ለሰራው ኃጢአት ቅጣቱን ይቀበላል። የሰራውን ኃጢአት ለንስሐ አባቱ በመናዘዝ በካህኑ ፊት መናዘዝ በራሱ ቅጣት ነው። ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ሲተገበር የነበረ እና በሐዲስ ኪዳንም ተጠናክሮ የቀጠለ ንስሐን የመፈጸሚያ ሥርአት ነው።

ኃጢአትን አምኖ ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሔር መናዘዝ ነው። ኢያ 7:19 "ኢያሱም አካንን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጥ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው።"

ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት የንስሐ ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የሰሩትን ኃጢያት ይናዘዙ ነበር። ማቴ 3:5 "ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ ይጠመቁ ነበር።" ኑዛዜ ተገቢ በመሆኑ ዮሐንስ መጥምቅ እያናዘዛቸው የንስሐን ጥምቀት አጠመቃቸው። ማር 1:5

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማሰር፣ የመፍታት እንዲሁም ኑዛዜን የመቀበል ጸጋን ለካህናት ሰጥቷቸዋል። ሉቃ 5:14 ማቴ 18:18

ሐዋርያት አባቶቻችንም ኑዛዜን በመፈጸም ኃጢአታችን እንደሚሰረይ አስተምረውናል። ያዕ 5:15–16

☞ በመሆኑም ኃጢአትን ለንስሐ አባታችን መናዘዝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ኃጢአታችንን ለንስሐ አባታችን ተናዘን በንስሐ ሳሙና ታጥበን የንስሐ ፍሬን አፍርተን አዲስ ሰው እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን።

ይቆየን!

በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ባለፈው ዓመት በምን እንጠይቅልዎ አምድ ከተጠየቁ እና በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሰ ብለሽ ጻፊበት። የሀሳብ እና የፊደል ምናምን መፋለስ ካለው አስተካክዪው። አውደ ምህረት ላይ ሚፖሰት ነው።

#ጥያቄ

ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ እህት ወንድሞቸ ፍጹም በወደደና ናሰባሰበን በልዑል እግዚአብሔር ሰላም እንዴት አደራችሁ
በእውነት ለሁላችሁም ጸጋውን ያብዛላችሁ ሰማያዊ ዋጋን ይክፈልልን እኛም የሰማነውን 30 60 100 ያማረ ፍሬ አፍርተን ቃሉን እንድንማር እግዚአብሔር ይርዳን ጥያቄ ነበረኝ ጸጋው የበዛላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች አብራሩልኝ።
ቃልኪዳን ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ለምሳሌ ለጻድቃንና ለሰማዕታት የኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው ቃል ኪዳን አለ ለምሳሌ እነ ቅድስት አርሴማ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ለነዚህና ለመሳሰሉት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል። ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን ምንድነው
ለመምህር ግርማና ላባ ዮሐንስ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ሰቷቸው ነው ወይስ እግዚአብሔር ጸጋውን አድሏቸው ነው⁉️ ብዙ ሰወች እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለሰጣቸው ነው ይሉናል ለነዚህ አይነት ሰወች ምን መልስ መስጠት እዳለብን ብታብራሩልን?

#መልስ

ቃል ኪዳን ማለት #ውል #ስምምነት #መዕላ ማለት ነው።

ሰው የሚምለው የሚዋዋለው ስምምነት የሚፈጥረው ከመረጠው ከወዳጁ ጋር ነው እንጂ ከወጪ ወራጁ #ከመንገደኛው #ሁሉ ጋር አይደለም::ልክ እንዲሁ #እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳን የሚገባው #ለመረጣቸው ሰዎች ብቻ ነው::
"#ከመረጥሁት ጋር #ቃል ኪዳኔን #አደረግሁ፥ " ብሎ እደተናገረ #መዝ 88÷3

ስለዚህ ቃል ኪዳን የተገባው ለሁሉ አይደለም ጸድቃን ቅዱሳን ቢመረጡ ከእራሳቸው ይልቅ ክርስቶስን ሰብከው ነው ::እንደ ዘመናችን አጥማቂ ነኝ ባዮች በክርስቶስ ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው እራሳቸውን የሚሰብኩ መቁጠሪያና ሲዲ ቸብችበው አይደለም::
አጋንንት ያለ ጾምና ጸሎት በመቁጠሪያ እና በስልክ አይወጣም ዛሬ ዛሬ በስልክ አጋንንትን እናስለቅቃለን የሚሉ አሉ:: አጋንንትም ያወጣ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም
"፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 21)

"የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ #ጥቂቶች " "፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።" (የማቴዎስ ወንጌል 22: 14) እንደተባለ የተመረጡት ቃል ኪዳን ያላቸው ከንቱ ውዳሴን የሚጠየፉት ጽላት የተቀረጸላቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸላቸው ገድልና ተአምር የተጻፈላቸው የጥንቶቹ እነ አቡነ #ተክለ ሃይማኖት ናቸው

የክርስቶስ ማለያ ለብሰው ለዲያቢሎስ #የሚጫወቱ አሳዊያን(አሰተኞች )በዝተዋልና በእጁጉ እንጠንቀቅ መልክታችን ነው:: "፤ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 5)

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ..... #ይቆየን 🙏

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ከዚህ ቀደም በምን እንጠይቅልዎ አምዳችን ከተጠየቁ ጥያቄዎች በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሱትን መልሶች ይዘን ቀርበናል።

#ጥያቄ
መምህር አንድ ጥያቄ ነበረኝ
መኖክሳት የሚለብሱት ብጫ ልብስ የምን ምሳሌ ነው
ወይም ብጫ ልብስ ለምን ይለብሳሉ?

#መልስ
በቅድሚያ ስለ ጥያቄዎት #እናመሰግናለን🙏

መነኮሳት ቢጫ ልብስ የሚለብሱበት ምክንያት ቢጫ ብርሃናዊ ነው አንተም እንደተናገርከው ብርሃናዊ አምላክ ነክ ሲሉ ነው "፤ ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8: 12)

#አንድም ጻድቃን በአባታቸው መንግስት እንደ ፀሐይ ያበራሉ ተብሎ እንደተጻፈው በአባታችን ቤት እንደ ፀሐይ እናበራለን ሲሉ ቢጫ ልብስን ይለብሳሉ "፤ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 13: 43)

በሌላ መልኩ ቢጫ የብሩህነት የተስፋ ምልክት እንደሆነ ብሩህ የሆነች መንግስትህት ታወርሰን ዘንድ ተስፋ አለን ሲሉ ይለብሱታል

"፤ በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን #የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤"
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1: 2-3)

#ጥያቄ
ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ እህት ወንድሞቸ ፍጹም በወደደና ናሰባሰበን በልዑል እግዚአብሔር ሰላም እንዴት አደራችሁ
በእውነት ለሁላችሁም ጸጋውን ያብዛላችሁ ሰማያዊ ዋጋን ይክፈልልን እኛም የሰማነውን 30 60 100 ያማረ ፍሬ አፍርተን ቃሉን እንድንማር እግዚአብሔር ይርዳን። ጥያቄ ነበረኝ ጸጋው የበዛላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች አብራሩልኝ
1.ቃልኪዳን ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ለምሳሌ ለጻድቃንና ለሰማዕታት የኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው ቃል ኪዳን አለ ለምሳሌ እነ ቅድስት አርሴማ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ለነዚህና ለመሳሰሉት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል። ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን ምንድነው
ለመምህር ግርማና ላባ ዮሐንስ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ሰቷቸው ነው ወይስ እግዚአብሔር ጸጋውን አድሏቸው ነው⁉️ ብዙ ሰወች እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለሰጣቸው ነው ይሉናል ለነዚህ አይነት ሰወች ምን መልስ መስጠት እዳለብን ብታብራሩልን?

#መልስ
ቃል ኪዳን ማለት #ውል #ስምምነት #መዕላ ማለት ነው

ሰው የሚምለው የሚዋዋለው ስምምነት የሚፈጥረው ከመረጠው ከወዳጁ ጋር ነው እንጂ ከወጪ ወራጁ #ከመንገደኛው #ሁሉ ጋር አይደለም::ልክ እንዲሁ #እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳን የሚገባው #ለመረጣቸው ሰዎች ብቻ ነው::
"#ከመረጥሁት ጋር #ቃል ኪዳኔን #አደረግሁ፥ " ብሎ እደተናገረ #መዝ 88÷3

ስለዚህ ቃል ኪዳን የተገባው ለሁሉ አይደለም ጸድቃን ቅዱሳን ቢመረጡ ከእራሳቸው ይልቅ ክርስቶስን ሰብከው ነው ::እንደ ዘመናችን አጥማቂ ነኝ ባዮች በክርስቶስ ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው እራሳቸውን የሚሰብኩ መቁጠሪያና ሲዲ ቸብችበው አይደለም::
አጋንንት ያለ ጾምና ጸሎት በመቁጠሪያ እና በስልክ አይወጣም ዛሬ ዛሬ በስልክ አጋንንትን እናስለቅቃለን የሚሉ አሉ:: አጋንንትም ያወጣ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም
"፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 21)

"የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ #ጥቂቶች " "፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።" (የማቴዎስ ወንጌል 22: 14) እንደተባለ የተመረጡት ቃል ኪዳን ያላቸው ከንቱ ውዳሴን የሚጠየፉት ጽላት የተቀረጸላቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸላቸው ገድልና ተአምር የተጻፈላቸው የጥንቶቹ እነ አቡነ #ተክለ ሃይማኖት ናቸው

የክርስቶስ ማለያ ለብሰው ለዲያቢሎስ #የሚጫወቱ አሳዊያን(አሰተኞች )በዝተዋልና በእጁጉ እንጠንቀቅ መልክታችን ነው:: "፤ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 5)

"፤ በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 7: 22)

ለመጨመር ያህል ቅዱሳን ቃልኪዳንን የሚቀበሉት በከበረ ዕረፍታቸው ነው።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ..... #ይቆየን 🙏

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ ፣ የተከበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

ምክንያቱም:- #የባህሪ ቅድስና ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው

#ኛ_ "ሁሰት" ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት


#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

ምክንያቱም :-ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር
#ለቅዱሳን መላእክት
#ለቅዱሳን መጻሕፍት
#ለቅዱሳን መካናት ይቀጸላልና

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት
ከፍቃደ ሥጋ ብቻ ሳይሆን #ለበረከት_ከእግዚአብሔር ለማሰናከል #ከሰይጣን #ከአላዊያን ነገስታት #ከጠንቆዮች ጭምር ይገጥማቸዋልና


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

ሐ)በፍጽምነት የሚገኝ ማዕረግ ነው

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው


ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጥዐንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥዐንን

#ኛ_የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት የሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም


#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
ሐ) የአስተብርኮ ስግደት
መ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

#መልስ
#ከእግዚአብሔር ለበረከት
#ከሥጋ ፍቃዳቸው
#ከአላዊያን ነገስታት
#ከጠንቆዮች
#ከሰይጣን


፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#መልስ
#ጸጣኒነት (ጀማሪ)
#ማዕከላዊነት
#ፍጽምነት
ወይም
#ንጽሐ ሥጋ
#ንጽሐ ነፍስ
#ንጽሐ ልቡናም ተብለው ይጠራሉ
፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
#ሊቀ_ነቢያት_ቅዱስ_ሙሴ በዘመኑ ባልነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መለመኑ እና መልስ ማግኘቱ
"፤ ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ #የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም #አስብ።"
#እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው #ክፋት_ራራ።"
(ኦሪት ዘጸአት 32÷14-14)


፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ

#መልስ
#ኢዮር
#ራማ
#ኤረር


፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
"፤ #እግዚአብሔር#በቅዱሳኑ ላይ #ድንቅ_ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።"
(መዝሙረ ዳዊት 67÷35)


"፤#እግዚአብሔር_በጻድቁ_እንደ_ተገለጠ_እወቁ፤ ።"
(መዝሙረ ዳዊት 3(4)÷3)


#መልሶቹ ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት
👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን ::

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡

በሳምንታዊው ጥያቄዎቹ ላይ ለተሳተፋችሁ አባላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን በአምላከ ቅዱሳን ስም እያቀረብን የጥያቄዎቹን መልሶች እነሆ፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡

#መልስ መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
አምላክ ሰው የሆነው ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ፣ ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ፣ የዲያብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ ነው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ማለት ምን ማለት ነው?

#መልስ ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ኤቫንጋሊዮን ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መጽሐፈ ሶስና የሚቆጠረው ከትንቢተ ዳንኤል ጋር አብሮ እንደ አንድ ነው፡፡

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?

#መልስ ሐ. ነሐሴ 7

#5
ከሚከከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ብርሃን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን ብሎ በመናገር ብርሃን ፈጠረ፡፡ ዘፍ 1፡3

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?

#መልስ ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዲብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
የዲያብሎስ ጥበብ በእባብ ቆዳ ተሰውሮ አዳም እና ሄዋንን ማሳት ሲሆን ጌታችን ይህንን ጥበብ ይሽረው ዘንድ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ጌታችን በወንጌል ‹‹አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡... እኔ ግን እላችኋለው በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡›› ማቴ 5፡21 በማለት ከንቱ ቁጣ ወደ መግደል የሚያደርስ በመሆኑ እንዳንቆጣ አርቆ አጥሮልናል፡፡

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ጸሐፊው ዮሐንስ ወንጌላዊ ሲሆን ይዘቱ ደግሞ ያየው ራዕይ ነው፡፡

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?

#መልስ ለ. 11
ጥንተ አበቅቴ ማለት የሌሊቱ ሱባኤ ሲባዛ በሰባት ሲካፈል በሰላሳ የሚመጣው ትርፍ ማለት ነው፡፡ ይህም 23*7 = 161 ይመጣል፡፡ 161/30 ደግሞ 5 ደርሶ 11 ይቀራል፡፡ ቀሪው ጥንተ አበቅቴ ይባላል፡፡


#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?

መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?

መ. ቅድስት ሄርሜላ
እመቤታችን -› ቅ. ሃና -› ቅ. ሄርሜላ -› ቅ.ሲካር -› ቅ.ቶና -› ቅ.ደርዲ -› ቅ.ሄሜን -› ቅ.ቴክታ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?

ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?

መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡
በዕለተ ሰኑይ የተፈጠረው ብቸኛ ሥነ ፍጥረት ጠፈር (በተለምዶ ሰማይ እየተባለ የሚጠራው) ሲሆን የተፈጠረውም ከውሀ ነው፡፡ አዲስ ሥነ ፍጥረት ያሰኘውም አዲስ ባሕሪ ይዞ ስለተፈጠረ ነው፡፡ ውቅያኖስ እና ባሕር ውሀ በመሆናቸው የእለተ እሁድ ሥነ ፍጥረት ናቸው፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ለ. በሊባኖስ ታራራ

ያላችሁን አስተያየት እና ጥያቄዎች

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit