ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እመቤታችን የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው!!!
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ
አንቺም በተድላ በደስታዬ ጊዜ ሽልማቴ ሆንሽኝ፡፡ በሐሴትም ጊዜ
ክብሬ ዘውዴ ሐቲም ቀለበቴ ነሽ፡፡ በሐሳቤ ሁሌ አንቺን አደንቃለው
እንዲህም እላለው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህል ጸጋና
ክብር ሰጠ፡፡ እግዚአብሔር አብ ዓለምን ያድን ዘንድ አንድ ልጁን
ወደዚህ ምድር ልኮ ማዳኑን ዐውቄ አደነቅሁ፡፡ አዳም የሰው ልጆች
ሁሉ አባት ነው፡፡ ዓለምን ግን አላዳነም፣ የሰው ልጆች ሁሉ
እናትም ሔዋን ከአዳም ጎን ተፈጠረች እርሷም ዓለምን
አላዳነችም፡፡ ቃየልም እንደሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ
ዓለምን ግን አላዳነም፡፡ እንኳንስ ዓለምን ሊያድን እራሱንስ እንኳን
አልጠቀመም፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ግን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ
ከቅድስተ ቅዱሳን፣ ከንጽሕተ ንጹሓን ከድንግል ማርያም ተወልዶ
ዓለምን ሁሉ አዳነ፡፡
ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል፡፡ ክብር ምሥጋና ለዚህ
ልደት ይገባል፡፡ ጌትነትና ገናንነት፣ ኃያልነት፣ እልልታ፣ ግርግርታ
ለዚህ ልደት ይገባል፡፡ ይህ ጥበብ ዕፁብ ድንቅ ነው ለዚህ አንክሮ
ይገባል፡፡ ይህም የሥጋዌ ምሥጢር ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ?
ለዚህ አንክሮ ይገባል፣ ይህም የሰውን ሥጋ መዋሐድ እጅግ ዕፁብ
ድንቅ ነው፡፡ የሔዋን መዳኛዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ሆይ! የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕፁብ ድንቅ
ነው፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት
እመቤታችን ሆይ! የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡
እሳትና ውኃም በአንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ
ነው፡፡ የሚያስፈራውንም የአንበሳ ደቦል ጸዓዳ በግዕ በክንዷ
መታቀፏ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት
መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በበረትም ለአምላክ ልጅ የሰማይ
ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ዓለምን ሁሉ የመላ አምላክ
በበረት ተወልዶ በጨርቅ ተጠቅልሎ መገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው፡፡
በረት ከጽርሐ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይ ዳርቻ ሠፋ ነቢዩ
ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ነቢዩ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን
በረት በለጠ። ይኸውም አደፍ ጒድፍ ሳይኖርባት ንጽሕት
የወለደችው ንጹሕ በግ ነው፡፡ በረት ለንጹሕ መስዋዕት ሽታ
መሰብሰቢያ ሆነ ሰማይና ምድር የማይወስኑት በረት ቻለው
ወስነውም፡፡ በረት የተመሰገነ ነው የኃያላን ጌታ በውስጡ
ተገኝቷልና።
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች እመቤታችን የተመረጠች
ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው፡፡ የዓለም ጌጽ ሽልማት
የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከእርሷ ተወልዷልና፤
በረት ተመሰገነ ምድርን በውኃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት
ድንግልም የመላእክት አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ
የሚቀመጥ እርሱ በማኅጸኗ ስላደረ፤ በረት ኪሩቤል
እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ፣ ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም
በጎል (በበረት) በጨርቅ ተጠቅልሎ ተገኘ፡፡
ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ፣ ላምና አህያም በወዲህና
በወዲያ በበረቱ ጎንና ጎን በዐራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ
በጎንና በጎኑ እንደ ዐራቱ እንስሶች የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ
ተሠራ፣ ቤተልሔም ሰማይን መሰለች፡፡ እንደ ጸሐይም በቅዱሳን
ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት
የሌለበት ዕውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ፡፡ የብርሃኑም ክበብ
መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ
ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምሥጋና በሁሉ የመላ ነው፡፡
ለዘወትርም የማያጎድል እመቤታችን የተመረጠች ድንግል ማርያም
ተገኘች ከዋክብትም መላእክተ ብርሃንም ታዩ፡፡
ወደዚህ ማኅበር አንድነት እኖር ዘንድ ማን ከፈለኝ? ከመላእክት
ጋር እንዳመሰግን፣ ከአዋላጅቱም ጋር እንዳደንቅ ከእረኞችም
እንዳገለግል፡፡ በረቱንም እጅ አነሳ ዘንድ ማን በከፈለኝ? የሙታን
ሕይወት፣ የኃጥአንም ንጽሕና፣ የቅቡጻን ተስፋ የተጨነቁትም
የሚያድን ጌታ ወደ ተቀመጠበት፡፡ የዓለም ሁሉ መድኃኒት
የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰብትን ምድር እሳለም ዘንድ
ማን በከፈለኝ? ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ
ማን በከፈለኝ? የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን
በከፈለኝ? የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ?
አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች
ድንግል ማርያም ጋር ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሐሳቤን ከዚያ
እንዳለው አድርጌአለውና፡፡ በሥጋ አልነበርኩም በመንፈስ ግን
አለሁ፤ በአኗኗር አልነበርሁም በሃይማኖት አለሁ በገጽ አልነበርኩም
በማመን ግን አለሁ ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያደረግሁ እኔ ዕድለኛ
ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል፡- ሳያዩኝ
የሚያምኑብኝ የተመሰገኑ ናቸው፡፡ እኔ ባርያህ ስለሃይማኖቴ
የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ እምነቴ አይደለም ስለ መረዳቴም
የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ንጽህናዬም አይደለም፣ በእግዚአብሔር
ስም ስለ አመንሁ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ በእናቱም ጸሎት ስለ አመንሁ
ንዑድ ክቡር ነኝ,,,,,፡፡
ምንጭ ፡- መጽሐፈ አርጋኖን ዘ ሰኑይ ምዕ ፬
አዘጋጅ፡-በአዲስ አበባ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት
ቤተክርስቲያን
የምክሐ ደናግል ማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር (ሰንበት ት/
ቤት)
የመረጃ መዛግብትና ኦድዮቪዥዋል ክፍል መካነ ድር ማስተባበሪያ
የተዘጋጀ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
ጥር ፳፻፲፩ ዓ.ም
ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ

ቅድስት ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
:ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው???
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::

በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
*********************************
አካላት
*
1) እራሷ (ሰንበት )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ
በኩረ በዓላት ናት :- የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና
ዓለም የተገኘባት
ወልድ ሰው የሆነባት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::

2) እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: ሉቃ 1÷26
3) ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :- ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና እረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) መንግስተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች ::
" ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እረፍት ይባላል :- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና እረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የእረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::

ማሳሰቢያ
********
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል ::
አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል ::
በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል:: በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::


.........ይቆየን...........

በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

✟ለአዕዛኒከ

ሰላም : ለአዕዛኒከ : እለ : ያጸምዓ : ምሳሌ : ዘሐዋርያት : ቡሩካን : ወዘነቢያት : ሰብአ ኩፋሌ ፤ ተክለ ሃይማኖት ምድራዊ ወመልአክ : ዘሉዓሌ ።
ምሥጠኒ : ውስተ ቤትከ : ዘአረፈቲሀሃ : ቢረሌ ። ከመ : አዕርፍ : ባቲ : እምብካይ : ወወይሌ ።

ትርጉም :- ✟ ለአዕዛኒከ ( ለጆሮሆችህ )

ተክለሃይማኖት ሆይ ፤ በክቡራን ነቢያት የተነገረውን በክቡራን ሐዋርያት የተሰበከውን መልካሙን ምሣሌ ነገር ለሚያደምጡ አዕዛኖችህ ሰላም እላለሁ ።
ቅዱስ አባቴ ሆይ በተፈጥሮ ጠባይህ ምድራዊ ሰው ስትሆን ፤ በሥነ ምግባርህ ሰማያዊ መልአክ ነህኮን ።
ከለቅሶና ከዋይታው በእርሷ ዐርፍ ዘንድ በወርቅና በዕንቁ በተሠራችው በሉዓላዊት ቤትህ
በዚያ ወስደህ አስቀምጠኝ

📜 መልክአ ተክለሃይማኖት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ድኅነት ጥያቄ #መልሶች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ሐሰት
#ምክንያቱም :-ሰው ለመዳን ከማመን ያለፈ የተግባር ሰው (ምግባራትን እና ምሥጢራትን የሚፈጽም) መሆን አለበት:: ምግባራት የሚባሉትም በዋናነት #ጾም #ጸሎት #ስግደት #ምጽዋት ሲሆኑ ምሥጢራቱም #ምሥጢረ_ሜሮን #ቅዱስ_ጥምቀት እና #ቅዱስ_ቁርባን ይጠቀሳሉ #ሃይማኖት ያለ #ምግባራት ጥቅም አልባ የሞተ ነው::
"፤ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ #ከሥራ (ከምግባራት )የተለየ እምነት የሞተ ነው።" (የያዕቆብ መልእክት 2: 26)


#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :-በተለየ አካሉ #ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሶ ነፍስን ተስቶ በፍጽም ተዋህዶ #ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና:: #በምስጢረ ሥላሴ ትምህርታችን #አብ አባት #ወልድ ልጅ #መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ብለን ተምረናል እንዲህም እናምናለን:: ቅዱሳት መጻሕፍትም በተዋህዶ ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት ይነግሩናል:: ለምሳሌ "እግዚአብሔር አንድያ #ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶልና" ዮሐ3÷16

#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :- ምንም እንኳን ድኅነት በዕለተ አርብ በቀራኒዮ አደባባይ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ ለሰው ልጆች የተሰጠ ቢሆንም ከዚህ ከተሰጠው ድኅነት ግን ለመካፈል ሰው የራሱን ጥረት ማድረግ ይገባዋል። ድኅነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተፈጸመ ስለሆነ ብቻ ሰው ሁሉ ያመነውም ያላመነውም በግዴታ ይድናል ማለት አይደለም:: ለመዳን የወደደ ብቻ ከተፈፀመለት የድኅነት ሥራ በምግባራት ተሳትፎ ድኅነትን ያገኛል:: ስለዚህ በድኅነት ውስጥ ሰውም ሊፈጽመው የሚገባ ሂደት ነው::
"፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ #እንደ_ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ፤"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 12)

ልናስተውለው የሚገባን #የታዘዛችሁትን_በመፈጸም የምትለዋ እና #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ የምትለዋን ነው

በመሆኑም የእራሳችንን መዳን መፈጸም የምንችለው እና ከተሰራልን የድኅነት ሥራ የምንካፈለው የታዘዝነውን በመፈፀም ነው:: #የታዘዝነውም 10ቱ ትዕዛዛት 6ቱ ቃላተ ወንጌል ናቸው እነዚህን ለመፈፀም ደግሞ ጊዜ ዘመን ያስፈልገናል:: ይህ ደግሞ ድኅነት በሂደት የሚፈፀም እንጂ በአንድ ቀን በአንድ ቦታ በሰዓት ጌታን በመቀበል ብቻ አለመሆኑን ያስገነዝበናል:: በጥቅሉ ለመዳን ሰው የራሱ ድርሻን መወጣት ይገባዋል።

#ኛ እውነት

#ኛ ሐሰት
ምክንያቱም:-ያልተመለሰለት ጸጋ የለምና::
ፀጋ:-
ልጅነትን:- ከእንግዲ ወዲ ባሮች አትባሉም
ወራሽነትን:-
ገዢነትን(ሥልጣንን):- ግዛ ንዳ የተባለሁ ዓለምና በዓለም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ዛሬም ሰው ከትዕዛዙ ካልራቀ ሕጉን ከጠበቀ ከተፈጥሮ ሁሉ በላይ መግዛት መንዳት የሚችልና ሥልጣኑ ያለው መሆኑን በቅዱሳን ሕይወት መመልከት ይቻላል::


#በአጭሩ መልሱ

#ኛ #ስለ_ፍጽም_ፍቅሩ
#ለካሳ ለቤዛ
#የዲያብሎስ ጥበብ #በጥበቡ #ለመሻር
#ለምሳሌነት_ለአራያነት
#ድኅነት ሥርዓት ስላለው…

#ኛ #ማመን
#ሥራ (ምግባራት)
#ምሥጢራትን መፈጸም ማር 16:16 ዮሐ 6:54


#ኛ "፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ #በእርሱም ቍስል #እኛ ተፈወስን።"

(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 5)
"፤ #እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ #ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም #የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 6)

ነብዩ ስለ እኔ ብቻ አላለም #እኛ ብሎ አብዝቶ ተናገረ እንጂ:: እኛ ብሎ አብዝቶ መናገሩ የዓለምን ኃጢያት የተሸከመ የዓለም መድኀን መሆኑን ሲገልጥ ነው::

"እነሆ #የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1: 29)


#ኛ #መንግስቱን_ሲወርስ_ስሙን_ሲቀድስ


#ኛ ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው ማለት እንጂ ቅዱሳን አያድኑም ወይም መድኀኒት አይባሉም ለማለት አይደለም:: በቅዱስ መጽሐፍ ሰዎች ሆነው አዳኝ ተብለው የተጠሩ አሉ #ለምሳሌ "፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ #እግዚአብሔርም_የሚያድናቸውን_አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ #ጎቶንያልን_አስነሣላቸው።"
(መጽሐፈ መሳፍንት 3: 9) ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎችን አዳኝ መድኀኒት አድርጎ እንደሚያስነሳ ነው:: መዳን በሌላ በማንም የለም ማለቱ የቅዱሳን አዳኝነት (መድኀኒትነት) ጠፍቶት አይደለም:: ቅዱሳን የጸጋ አዳኝ ናቸው:: ጸጋ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፣የተቸረ ፣የተለገሰ ስጦታ ማለት ነው:: ስለዚህ ቅዱሳን መድኀኒት ቢባሉ በስጦታ ያገኙት ነው። "#እድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን #ሌላ ስም የለም" ማለቱ ደግሞ ቅዱሳን ሲያድኑም በእራሳቸው ኃይል ሳይሆን ማዳንን በሰጣቸው በፈጣሪያቸው ስም ነው ማለቱ ነው:: ቅዱሳን መላእክት አዳኝ (መድኅኒት )ናቸው። ስማቸው ስመ እግዚአብሔር ተሸክሞልና:: ስለሆነም ቅዱስ ሚካኤል አዳነ ማለት እግዚአብሔር አደነ ማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ (ቅዱሳን ሰዎችም) ቢያድኑ የፈጣሪን ስሙን ጠርተው ነው "፤ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ #በናዝሬቱ_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።"
(የሐዋርያት ሥራ 3: 6)
ከዚህም ባሻገር ቅዱሳን ወደ ቅድስና ሲጠሩ ስማቸው ይለወጣል ስመ እግዚአብሔርም ይሆናል:: በመሆኑ እነርሱም በስማቸው ማዳን ይቻላቸዋል "፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #በእኔ_የሚያምን_እኔ_የማደርገውን_ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ #ከዚህም_የሚበልጥ_ያደርጋል፥" (የዮሐንስ ወንጌል 14: 12)
ከእርሱ አብልጦ የሚሰራ የለም ነገር ግን በስሙ ላመኑ እርሱ ያደረገውን ሁሉ የማድረግ ሥልጣን አላቸው ማለቱ ነው።

ይቆየን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሳምንታዊው ከሁሉም ትምህርት የተወጣጡትን ጥያቄዎች እነሆ ይዘን ቀርበናል፡፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡
ሀ. ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ
ለ. ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ
ሐ. በኃጥአን ላይ ይፈርድባቸው ዘንድ
መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ምን ማለት ነው?
ሀ. ሀዘን ማለት ነው፡፡
ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ሐ. ስብከት ማለት ነው፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. 2ኛ ዜና መዋልእ
ለ. ትንቢተ ኤርሚያስ
ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መ.መጽሐፈ አስቴር

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?
ሀ. ሀምሌ 7
ለ. ሰኔ 7
ሐ. ነሐሴ 7
መ. ግንቦት 7

#5
ከሚከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?
ሀ. ብርሃን
ለ. መላእክት
ሐ. 7ቱ ሰማያት
መ. አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስ ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?
ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዳቢሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
ለ. አምላክ ሰው ሳይሆን የዲያብሎስን ሥራ ማፍረሱን፡፡
ሐ. አምላክ ሰው የሆነው የሰው ልጆችን ያስተምር ዘንድ መሆኑን፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ለ. ወደ ሴት መመልከት
ሐ. መመኘት
መ. መሐላ

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ለ. መዝሙረ ዳዊት
ሐ. የሐዋርያት ሥራ
መ. የማቴዎስ ወንጌል

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?
ሀ. 10
ለ. 9
ሐ. 8
መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?
ሀ. ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ
ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ
ሐ. ቅዱስ ኤፍሬም
መ. ቅዱስ ያሬድ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?
ሀ. ቅድስት ሀና
ለ. ቅድስት ደርዲ
ሐ. ቅድስት ሄሜን
መ. ቅድስት ሄርሜላ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?
ሀ. ከመጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ ጋር
ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር
ሐ. ከትንቢተ ኤርሚያስ ጋር
መ. ከትንቢተ ኢሣይያስ ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ውሃ
ለ. ባህር
ሐ. ውቂያኖስ
መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ሀ. በደብረ ዘይት ተራራ
ለ. በሊባኖስ ታራራ
ሐ. በእናት በአባቷ ቤት
መ. በቤተልሔም በከብቶች ግርግም።

መልሶቻችሁን

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡

በሳምንታዊው ጥያቄዎቹ ላይ ለተሳተፋችሁ አባላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን በአምላከ ቅዱሳን ስም እያቀረብን የጥያቄዎቹን መልሶች እነሆ፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡

#መልስ መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
አምላክ ሰው የሆነው ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ፣ ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ፣ የዲያብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ ነው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ማለት ምን ማለት ነው?

#መልስ ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ኤቫንጋሊዮን ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መጽሐፈ ሶስና የሚቆጠረው ከትንቢተ ዳንኤል ጋር አብሮ እንደ አንድ ነው፡፡

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?

#መልስ ሐ. ነሐሴ 7

#5
ከሚከከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ብርሃን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን ብሎ በመናገር ብርሃን ፈጠረ፡፡ ዘፍ 1፡3

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?

#መልስ ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዲብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
የዲያብሎስ ጥበብ በእባብ ቆዳ ተሰውሮ አዳም እና ሄዋንን ማሳት ሲሆን ጌታችን ይህንን ጥበብ ይሽረው ዘንድ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ጌታችን በወንጌል ‹‹አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡... እኔ ግን እላችኋለው በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡›› ማቴ 5፡21 በማለት ከንቱ ቁጣ ወደ መግደል የሚያደርስ በመሆኑ እንዳንቆጣ አርቆ አጥሮልናል፡፡

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ጸሐፊው ዮሐንስ ወንጌላዊ ሲሆን ይዘቱ ደግሞ ያየው ራዕይ ነው፡፡

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?

#መልስ ለ. 11
ጥንተ አበቅቴ ማለት የሌሊቱ ሱባኤ ሲባዛ በሰባት ሲካፈል በሰላሳ የሚመጣው ትርፍ ማለት ነው፡፡ ይህም 23*7 = 161 ይመጣል፡፡ 161/30 ደግሞ 5 ደርሶ 11 ይቀራል፡፡ ቀሪው ጥንተ አበቅቴ ይባላል፡፡


#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?

መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?

መ. ቅድስት ሄርሜላ
እመቤታችን -› ቅ. ሃና -› ቅ. ሄርሜላ -› ቅ.ሲካር -› ቅ.ቶና -› ቅ.ደርዲ -› ቅ.ሄሜን -› ቅ.ቴክታ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?

ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?

መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡
በዕለተ ሰኑይ የተፈጠረው ብቸኛ ሥነ ፍጥረት ጠፈር (በተለምዶ ሰማይ እየተባለ የሚጠራው) ሲሆን የተፈጠረውም ከውሀ ነው፡፡ አዲስ ሥነ ፍጥረት ያሰኘውም አዲስ ባሕሪ ይዞ ስለተፈጠረ ነው፡፡ ውቅያኖስ እና ባሕር ውሀ በመሆናቸው የእለተ እሁድ ሥነ ፍጥረት ናቸው፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ለ. በሊባኖስ ታራራ

ያላችሁን አስተያየት እና ጥያቄዎች

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ዕረፍተ ቅዱሳን

እንኳን ለብጹዕ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት በሠላም አደረሳችሁ።

ቅዱሳን ከዚህ ዓለም በሥጋ ሲለዩ አረፉ ይባላል። ሞታቸው
ዕረፍታቸው ነውና። ስለ ቅዱሳን ዕረፍት ከማየታችን በፊት ሞትን
በ3 ከፍሎ ማየት ተገቢ ነው።
የሥጋ ሞት:ይህ ሞት ሥጋ ከነፍስ ሲለይ ሥጋ ሞተ
ያሰኘዋል። ያዕ 2:26"ከነፍሰስየተለየች ስጋ የሞተች እንደሆነች
እንዲሁ ደግሞ ከስራ የተለየ ዕምነትም የሞተ ነው።"
የቁም ሞት:ይህ ሞት በቁም ሳሉ እየሄዱ እየቆሙ
እየተቀመጡ እየተኙ እየበሉ እየጠጡ ሥጋ ከነፍስ ሳትለይ ነገር
ግን በኃጥያት ተዘፍቆ ከእግዚአብሔር መለየት ከምግባር
መጉደል ከሃይማኖት በአፋ መሆን የቁም ሞት ይባላል። 1ጢሞ
5:6"ቅምጥሊቱ ግን በህይወት ሳለች የሞተች ናት።" እንዲል።
የነፍስ ሞት:ይህ ሞት በቁም ሳሉ በሰሩት ኃጥያት
እንደቆሸሹ በንስሃ ሳሙና ሳይታጠቡ የስጋ ሞት መቶባቸው
በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ሲኦል በነፍስ ላይ ሲፈረድባት የነፍስ
ሞት ይባላል።
† የቅዱሳን ሞታቸው ግን ለእነርሱ ዕረፍታቸው ስለሆነ ቅዱሳን
ሞቱ አይባልም። ይህም እንደ ምንድን ነው ቢሉ?
1የስጋ ሞት ቅዱሳን በዚህ ዓለም ሳሉ ካደረጉት ተጋድሎ
ህማምና መከራ ወደ ዘላለማዊ ደስታ ዕረፍት መንግስተ ሰማይ
ወደ ፈጠሪያቸው የሚሄዱበት መንገድ ስለሆነ ነው። ፊሊ 2:23
"ልሄድከክርስቶስ ጋር እኖር ዘንድ እናፍቃለው።" እንዳለ
ሐዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ።
2 የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ስለሆነ ነው።
መዝ 115(116):15"የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት
የከበረ ነው።" እንዲል።
3 ቅዱሳን በስጋ ሞት ተወስደው ወደ አምላካቸው ከሄዱ በኋላ
ዕውቀታቸው ምሉዕ ስለሆነ የቅዱሳኑ ሞት ዕረፍት ይባላል።
የቅዱሳን ክብርና ዕውቀት፣ ዕውቀት ሰጭ ከሆነ ከእግዚአብሔር
በተሰጣቸው ጸጋ ሁሉን ያውቃሉ፡፡ ለምሳሌ ኤልሳዕ ነቢይ በዚህ
ዓለም በነበረ ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ በምሥጢር /በስውር/
ከሶሪያዊው ንዕማን ስጦታ መቀበሉን ማንም ሳይነግረውእንዴት
እንዳወቀ በሁለተኛው መጽሐፈ ነገሥት.5፡25-27 መመልከት
ይቻላል፡፡
ሌላም ከሶርያ ንጉሥ ባለሟሎች አንዱ ለንጉሡ ስለ ኤልሳዕ
እንዲህ ሲል ነገር ሠራ"ጌታ ሆይ እንዲህ አይደለም ነገር
ግንበእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእሥራኤል ዘንድ
ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉስ ይነግረዋል"በማለት ኤልሳዕ
በቦታም አንድ አካባቢ ሳይሆኑ በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያውቅ እንደ
ነበረ ተጽፎአል 2ኛነገ.6፡12 በረሀብ ጊዜም የእስራኤል ንጉሥ
ሊያስገድለው መልእክተኛ መላኩን ኤልሳዕ አወቀ። 2ኛነገ.6፡12
በዚህምዓይነት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የሐናንያንና የሰጲራን
ምሥጢራዊ ተንኮል የነገረው ሳይኖር አውቆ በሞት ቀጣቸው።
የሐዋ.5፡3-9
ታዲያ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ ይህ ዕውቀታቸው አይለያቸውም
ይልቁኑ በምድር የነበራቸው ከፊል ዕውቀት ምሉዕ ይሆናሉ።
በነፍሳቸው ሕያዋን እንጂ ሟቾች አይደሉምና ነው፡፡ ለዚህም
ነው ጌታ ከሰዱቃውያን ጋር ስለሙታን ይነጋገር በነበረበት ጊዜ
እግዚአብሔር የአብርሃም የይስሐቅ አምላክ ነው ሲባል እነዚህ
የቀድሞ አባቶች በነፍስ ሕያዋን ስለሆኑ ነው እንጂ እርሱ
የሙታን አምላክ ስለሆነ አይደለም ያለው ለዚህ ነው። ማቴ.
22፡31-32
እስኪቅዱሳን እውቀታቸው በአጸደ ነፍስ ምሉዕ እንደሆነ
የሚያመለክት የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት።
ኤር 15:1–4"እግዚአብሔርምእንዲህ አለኝ ሙሴና ሳሙኤል
በፊቴ ቢቆሙ እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይመለስምና ከፊቴ
አስወግዳቸው ይሂዱ"
ይህ አባባል የሚያመለክተው ከኤርምያስ ዘመን በፊት ከሞቱት
ብዙ ዓመታት ያሳለፉ ሙሴና ሳሙኤል ስለ እስራኤል ዘሥጋ
እግዚአብሔርን ይማጸኑና ይማልዱ የነበሩ መሆናቸውን ነው
የሚያሳየው፡፡
ሉቃ 16:19–30በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ አብርሃም
በገነት ሆኖ በምድር ባለፀጋው ነዌ በድሀው አላዛር ላይ
ያደረገበትን አውቆ አላዛርንም በእቅፉ እንዳኖረው ይናገራል።
ስለዚህ የቅዱሳን ዕውቀት በአፀደ ነፍስ ምሉዕ እንደሆነ መጽሐፍ
ቅዱስ ይመሰክራል።
4 ሞት ለቅዱሳን እንደ እንቅልፍ በመሆኑ ቅዱሳን አረፉ እንጂ
ሞቱ አይባልም። ሰው በዚህ ዓለም ሳለ ከስጋ ድካም በእንቅልፍ
እንደሚያርፍ እንዲሁ ቅዱሳንም በዚህ ዓለም ሳሉ ካደረጉት
ተጋድሎና መከራ በስጋ ሞት ያርፋሉና ነው።
ሐዋ 7:59–60ላይ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስን በድንጋይ
ሲወግሩት "ጌታ ሆይ ይህንን ኃጥያት አትቁጠርባቸው ብሎ
በታላቅ ድምፅ ጮኸ ይህንንም ብሎ አንቀላፋ።" እንዲል።
5 ቅዱሳን በዕረፍታቸው ክብራቸው ይገለጣል። ልዑል
እግዚአብሔርም ቃልኪዳን ይገባላቸዋል። ከቅዱሳን ረድኤት
በረከት ይክፈለን። የጻድቁ አባት የአቡነ ተክለሃይማኖት ምልጃ
አይለየን። የእመቤታችን ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟም በአንደበታችን
ይኑር። ይቆየን።
(አቤኔዘርወልደ ተክለሃይማኖት)

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ይህን ያውቁ ኖሯል?

👉በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጠቀሰ ብቸኛው የቤት እንሰሳ ድመት ነው።(ካለ እስኪ ፈልጉ።)

👉በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሐዋርያት ስራ በሚባለው መጽሐፍ ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም 69 ጊዜ ብቻ የተጻፈ ሲሆን በአንጻሩ የቅዱስ ዻውሎስ ስም ከ135 ጊዜ በላይ ተጽፎ ይገኛል።(ቆጥራችሁ ጥናት ብታረጉበት አይከፋም።) ታዲያ ቅዱስ ዻውሎስ የክርስቶስን ነገር ሸፈነ? አልሸፈነም እንደውም በእርሱ ህይወት ክርስቶስ ተገልጧል ተሰብኳል። ገላ 1:23–24
ዛሬም እኛ ማርያም ማርያም ስንል ክርስቶስን የሸፈንን የእርሱን ክብር ለሷ የሰጠን የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። ለኛ ግን ማይታየውን አምላክ እግዚአብሔርን ያየንባት መስታወታችን ናትና ሁሌም እንጠራታለን እናወድሳታለን እናከብራታለን። ስሟም ይጣፍጣል ትርጉሙም ጣፋጭ ሰማይ ወምድር ነውና።

👉በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር ቅዱሳኑ ስለ ህዝቡ ይማልዱ ወይም ይለምኑ ዘንድ የህዝቡን ኃጥያት ለቅዱሳኑ በምስጢር ያጫውታቸው ነበር። ዘፍ 18:16–33 ፣ 1ሳሙ 3:1 (አይደለም እኛ ለምነናቸው አማልዱን ብለናቸው ይቅርና።)

👉በመጽሐፍ ቅዲስ ላይ መጽሐፈ አስቴር በሚባለው መጽሐፍ ውስጥ አንድም ቦታ እግዚአብሔር የሚል ቃል የሌለው ሲሆን ሙሉ በሙሉ በአስቴር ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ የሚያትት መጽሐፍ ነው።(ቢያነቡት ጥሩ ነው።)


🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit📢
📢 @AwediMeherit📢
📢📢📢📢📢📢📢📢
#ጾመ_ነቢያት

ጾመ ነቢያት ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡ ጾመ ነቢያት በመባሉ ነቢያት ስለጾሙት ጾመ ድኅነት መባሉም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፍቶ ድኅነት የተገኘበት ስለሆነ ነው፡፡

አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት ልጅነቱን ካጣ ከገነት ከወጣ በኋላ ‹‹ወአልቦቱ ካልዕ ኅሊና ዘእንቢብካይ ላዕለ. ኀጢኣቱ›› እንዲል እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ታህል ቦታ በኀጢኣቴ ምክንያት አጣሁ እያለ ሲያዝን ጌታ ኀዘኑን አይቶ ጸሎቱን ሰምቶ በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኀንከ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትያ ‹‹በአምስት ቀን ተኩል ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ሰው ሰውኛውን ኖሬ በመስቀል ተሰቅዬ በሞቴ አድንሀለሁ›› ብሎ ተስፋውን ሰጥቶታል፡፡ መጽሐፈ ቀለሜንጦስ

ከርሱ በኋላ የተነሱ ነቢያት በግዝረታቸው በመስዋዕታቸው መዳን የማይቻላቸው ቢሆን ለአዳም በሰጠው ተስፋ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ በሕማሙ በሞቱ ያድነን ብለው በየዘመናቸው ግብር ገብተው ቀኖና ይዘው አንሥአ ኃይለከ ፈኑ እዴከ ብለዋል፡፡ ጌታም የተናገረውን የማያስቀር ነውና አምስት ቀን ተኩል /አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን/ ሲፈጸም ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ ሰው ሰውኛውን ኖሮ በ፴፫ ዓመቱ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ሁሉ አድኗል፡፡

በመሆኑም ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለሰው መዳን የጾሙትን የጸለዩትን በማዘከር ከበዓለ ልደት አስቀድሞ ያሉትን ስድስት ሳምንታት እንጾማለን፡፡


ምንጭ መዝገበ ታሪክ ቁ ፩

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ደላላዋ ደሊላ

ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ ወገኑ ከዳን ወገን ነው ሚስቱም መካን ነበረች፥ ልጅም አልወለደችም።የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት። እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፥ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። " እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል። " እርሷም የእግዚአብሔር መላእክ እንደ ተገለጠላትና እዳነጋገራት ነገረችው
"፤ ማኑሄም። ጌታ ሆይ፥ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው፥ እባክህ፥ እንደ ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ለሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ተገለጠላት፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርስዋ ጋር አልነበረም። "  ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች ለባልዋም። እነሆ፥ በቀደም ዕለት ወደ እኔ የመጣው ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ ብላ ነገረችው።  "፤ ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተለ፥ ወደ ሰውዮውም መጥቶ። ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? አለው። እርሱም። እኔ ነኝ አለ። ፤ለሚስቱ እንደነገራትም ለእርሱም ደግሞ ነገረው፡፡

"፤ ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው።  ኃይሉንም በጸጉሩ አደረገበት፡፡
(መጽሐፈ መሳፍንት 13÷ 1-24)


"፤ ሶምሶንም ወደ ተምና ወረደ፥ በተምናም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ።  "፤ ወጥቶም ለአባቱና ለእናቱ። በተምና ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አይቻለሁ፤ አሁንም እርስዋን አጋቡኝ አላቸው።  "፤ አባቱና እናቱም። ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለምን? አሉት። ሶምሶንም አባቱን። ለዓይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ አለው። እናትና አባትህን አክብር ያለውን ትዕዛዝ ተላለፈ

፤ ከዚህም  በኋላ ሶምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ደሊላ የተባለች አንዲት ሴትን ወደደ።  "፤ የፍልስጥኤማውያንም መኳንንት ወደ እርስዋ ወጥተው። እርሱን ሸንግለሽ(ደልለሽ) በእርሱ ያለ ታላቅ ኃይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛስ እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ እወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን አሉአት።"፤ ደሊላም ሶምሶንን። ታላቅ ኃይልህ በምን እንደ ሆነ፥ እንድትዋረድስ የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው። "፤ ሶምሶንም። በሰባት ባልደረቀ በእርጥብ ጠፍር ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ አላት። "፤ የፍልስጥኤማውያንም መኳንንት ሰባት ያልደረቀ እርጥብ ጠፍር አመጡላት፥ በእርሱም አሰረችው።"፤ በጓዳዋም ውስጥ ሰዎች ተደብቀው ነበር። እርስዋም። ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። እርሱም የተልባ እግር ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፤ ኃይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም። "፤ ደሊላም ሶምሶንን። እነሆ፥ አታለልኸኝ፥ የነገርኸኝም ሀሰት ነው፤ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለችው።"፤ እርሱም። ሥራ ባልተሠራበት በአዲስ ገመድ ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ አላት።"፤ ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ በእርሱ አሰረችው፤ በጓዳዋም የተደበቁ ሰዎች ተቀምጠው ነበር። እርስዋም። ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ገመዱንም ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው። "፤ ደሊላም ሶምሶንን። እስከ አሁን ድረስ አታለልኸኝ፥ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ የምትታሰርበት ምን እንደ ሆነ ንገረኝ አለችው። እርሱም። የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ብትጐነጕኚው፥ በችካልም ብትቸክዪው፥ እደክማለሁ፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ አላት። "፤ ሶምሶንም በተኛ ጊዜ ደሊላ የራሱን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፥ በችካልም ቸከለችውና። ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቃ፥ ችካሉንም ከነቆንዳላው ድሩንም ነቀለ። "፤ እርስዋም። አንተ። እወድድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው። "፤ ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች።"፤ እርሱም። ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፥ እደክማለሁም፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት።"፤ ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ገለጠላት ባየች ጊዜ። የልቡን ሁሉ ገልጦልኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መኳንንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያን መኳንንትም ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ መጡ።  "፤ እርስዋም በጕልበትዋ ላይ አስተኛችው፤ አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ። " ፤ እርስዋም። ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ። እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ  ተለይቶ ነበርና እንደ ቀድሞ ሊሆን አልቻለም ።

ምስጢር ለሁሉ አይገለጥም (አይነገርም)የቀደመች እናታች ሔዋን በእግዚአብሔር እና በእነርሱ መካከል ያለን ቃል ኪዳንን አጋልጣ ለእባብ በመናገሯ ከፀጋ እግዚአብሔር ተራቁታለች ዲቢሎስም ምርኮ ሆና ወድቃለ ነበር ሶምሶምም የተሸፈነው ምስጢሩን ወደድኳት ላለው ለደሊላ በመግለጡ ከጠላቶቹ እጅ እንዲወድቅ አድርጎታል በቤተ ክርስቲያናችን ለሁሉ የማይነገሩና ለሁሉ የማይፈፀሙ ብዙ ምስጢራት አሉ::እነዚህን ምስጢራት ለማያምኑ ሰዎች መናገር እንደ ሔዋን እና እንደ ሶምሶም ዋጋ ያስከፍላል አንዳንድ ሰው አትንገር ብላችሁ ስትነግሩት ለመናገር ያለው ጉጉት ይጨምራል ጌታችንም በወንጌል አላስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ያደረገውን ተአምራት ለሌሎች እዳይናገሩ ያሳስባቸው ነበር ሆኖም ግን ከትዕዛዙ እየወጡ አብዙተው ያወሩ ነበር::"፤ ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት። " ማር 7÷ 36 ወሬ ከእግዚአብሔር መንግስት በአፋ ያደርጋል እንደ ወደ ሄማሁስም ያሰድዳል

ፍልስጥኤማውያንም ሶምሶምን ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፤ ዐይን የተባሉት ብሉይና ሐዲስ ናቸው አንድም ሃይማኖትና ምግባር ናቸው ሰው ምስጢር ሲያወጣ ብሉያት ይጠፉበታል አዲሳት ይሰወሩበታል ሃይማኖት ይጸንበታል ምግባር ይጠምበታል:: ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።፤ሶምሶም ምስጢር በመግለጡ ይህ ሁሉ ችግር ደርሶበታል::በዚህም ምክንያት ዳግማዊ ሶምሶም የሚባል የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢርን ከማያምኑ ከመናፍቃን እንዴት መደበቅ እደሚገባን አስተማረን "በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።" ማቴ7÷6
ዛሬ ዓለም የክርስትና ምስጢር ምን ይጠቅማል ብላ እንደ ሄሳው ብኩርና ምስጢራትን የምታቃልል የምጠ
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
 ብዙዎችን ደስ ያሰኘን ልደት

የእግዚኃርያ እና የፀጋ ዘ አብ ቤት ዛሬ በደስታ ተመልታለች ምክንያቱም ዛሬ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚያበራ አንድ ሲሆን ብዙ ብቸኛ ሲሆን ከሰው አልፎ ለእልፍ አህላፍ መላእክት ወንድማቸው የሚሆን ታናሽ ብላቴና ሳለ ለብዙዎች መካር የሚሆን ደገኛ ልጅን ወልደዋልና ነው :: ቤታቸው አስቀድመው ባለመውለዳቸው ምክንያት እንደ ኃጢያተኛ ቆጥሮ መጠቆሚያ ባደረጋቸው ሰዎች እና እጅግ በሚያከብሯቸው እንዲሁም በሚወዷቸው ሰዎች ተጨናንቃለች ::ዓለም እንዲ አይደለች?::
ይህ የፍሰሐ ጺዮን መወለድ ዛሬ ለእግዚአርያና ለፀጋ ዘአብ የደስ ቀን ቢሆንም ግን ዝም ተብሎ የተገኘ ቀን አይደለም በጾም በጸሎትና በምጽዋት የተገኘ የደስታ ቀን ነው በይበልጥ ለእናታችን ለእግዚኃርያ ያሳለፋችሁ ልጅ አልባ የትዳር ጊዜ ከባድ ነበር ዛሬ ሃያ ልጆችን ወልደው ግን በትዳር መኖር የከበዳቸው ብዙች ናቸው እናታችን ያልወለደች መካን እንደ በቅሎ የማትወልድ እያሉ ሲያሟት ሲሰድቧ እንኳ ትዳር መፍታትን እንደ መፍትሄ አልቆጠረችም ምን አልባት ይህን ስድብና ነቀፋ ችላ በመልካምነት እና በትእግስት እግዚአብሔርን ባትጠብቅ ኖሮ አባታችንን ተክለ ሃይማኖትን የሚያክሉ አባት ባላገኘን ነበር :: የሚገርመው እርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይታ እንኳን ያለቀሰችበት ጊዜ ነበር ስለዚህ ይን በይበልጥ ለእናታችን ልዮ ነው::
ልደት የሕይወት መግቢያ በር ነው በመጽሐፍ ቅዱስ በልደታቸው (በመወለዳቸው ብዙዎችን ደስ ያሰኙ ቅዱሳን ሰዎችእንዳሉ ይነግረናል ለምሳሌ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን መመልከት እንችላለን በቅዱሳን ሰዎች መወለድ ከወላጆቻቸው በተጨማሪ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆኑ ሁሉ ደስ ይሰኙባቸዋል ::በአባታችን በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ውልደት በመጀመሪያ ደረጃ የተደሰው እግዚአብሔር አምላክ ነው ምክንያቱም
"፤ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል" ..ና ነው ::" ሉቃ1÷17
ከእግዚአብሔር በመቀጠል በመወለዱ ደስ የተሰኘችሁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች ክብሯን ዘላለማዊ ድንግልናዋን አማላጅነቷን መላዲተ አምላክነቷን በመናፍቃን ፊት ይመሰክራልና አንድም ፍሰሀ ጺዮን ነውና የጺዮን የእመቤታችን ደስታ የሚሆን ስመ ትርጓሜ አለውና ነው ከእመቤታችን ቀጥሎ በመወለዱ የአህላፍ ቅዱሳን የደስታ ምንጭ ነው ሰው ከሃይማኖት በአፋ ሲሆን ከምግባር የተጣመመ ሲሆን በወንጌል መረብነት አጥምዶ ወደ ንሰሐ የሚመልስ ካህን ነውና ቅዱሳን መላእክት በዚህ ስራው እጅግ ሃሴትን ስለሚያደርጉ ነው ለዚህ ማሳያ"፤ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። " ሉቃ 15÷10 እንዲል ጻድቁ በሚመልሳቸው ኃጢያን መላእክተ ይደሰታሉ ሌላው በመወለዱ ደስ የሚላቸው ቅዱሳን ሰዎች ናቸው በሃይማኖት በምግባር በገድል በትሩፋት የሚመሰላቸውን ወንድም አግኝተዋልና ደስ ይላቸል :: በአንጻሩ ጥቂት ከፉ ሰዎች በቅዱሳን ሰዎች ውልደት ይበሳጫሉ ይከፋሉ የዲያቢሎስ የግብ ልጆቹ ናቸውና ለዚህ ነው "በመወለዱ ሁሉም ሰዎች ደስ ይላቸዋል" ተብሎ ሳይሆን "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" ተብሎ ብቻ የተጻፈለፈን ሉቃ1÷14 በቅዱሳን ዉልደት ለቅዱሳን ብቻ ሳይሆን ለሕዝብም የደስታ ምንጭ ነው:: "፤ ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል። "መጽሐፈ ምሳሌ 29÷ 2 እግዚአብሔር አምላክ የሚወለዱ ቅዱሳንን ቁጥር በእጅጉ አብዝቶ ከማልቀስ ይሰውረን :: አሜን

......ይቆየን........

ከጻድቁ አባታችን እረድኤት እና በረከትን ይክፈለን::አሜን!

ተርቢኖስ ሰብስቤ (ኃይለ ማርያም)
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
የኖኅ መርከብ ከደብረ አሚን ሰማይ ሥር

የአራራት ተራራ ይህ ይሆንን??


በዘመነ ኖኅ ሰው ኃጢያትን አብዝቶ ሰራ በኃጢያቱም ብዛት  እግዚአብሔር  ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ ብሎ ተነገረለት:: ይህም የሰው ፍጥረት ሁሉ ፈጽሞ ከምድር ላይ እንዲያጠፋ ምክንያት ሆነው ቢሆንም፡ግን እግዚአብሔር አምላክ ፈታዬ በጽድቅ ኮናኔ በርትዕ ነውና  ጻድቁን ከኃጥሁ ደብልቆ አይፈርድባቸውም ኃጥሁንም ከጻድቅ ቀላቅሎ አይፈርድላቸውም እና ለሁሉም እንደ ሥራው ሰጠው   "፤  ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ። " ዘፍ 6÷9 ስለዚህ ኖኅ ና ቤተሰቦቹ የሚድኑበትን መርከብ እንዲሰራ ታዘዘ "፤ ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ፤ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ፥ በውስጥም በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት።  "፤ እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ፤ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። "  ዘፍ 6÷14:: ገና ከመቶ ሃያ ዓመት በኃላ ለሚዘንብ ተራ ዝናብ መርከብ የሚሰራ ብኩን የሚል የሰዎችን ስድብ ትችትና ነቀፋ ሳይበግረው ኖኅ በእምነትም በደረቅ መሬት ላይ እንደታዘዘው መርከብን ሰራ  መጻሕፍ " ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። " ሐዋ ሥራ 14: 17 እንዲል ለምሥክር ይሆኑ ዘንድም ከአዋፍ ከአራዊት ከእስሳት ወገን ሁለት ሁለቱን ተባህትና አንስት እያደረገ በመርቡ ውስ ከተተ ከሰባት ቀንም በኃላ አርባ ለሊትና አርባ ቀን የቆየ የንፍር ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ዘንቦ ፍጥረትን በሙሉ አጠፋ::

 እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዊቱን ሁሉ፥ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ፤ እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፋስን አሳለፈ፥ ውኃውም ጎደለ፤  ፤ የቀላዩም ምንጮች የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፥ ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ "፤ ውኃውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፥ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጎደለ። ፤ መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች። "

ይህ የአራራት ተራራ መገኛ ቦታ በብዙ ምሁራን ዘንድ  የታሪክ ውዝግብን ሲያሰነሳ ቆይቷል ሁሉም የራሱን መረጃና ማሰረጃ ይሆናል የሚለውን ነገር እያነሳ ተራራው በሀገሬ ይገኛል ሲል ይሰማል መጻሕፍ ቅዱስም ቢሆን የተራራውን ሰም ከመግለጥ በዘለለ በየት አገር እንዳለ ፍንጭ አይሰጥም በአራራት ስም የሚጠሩ ቡዙ ተራሮች በየ ሀገራቱ መገኘት በመቻላቸውም ነገሩን አከራካሪ ያደርገዋል ::



የአራራት ክልል፣ በቱርክ ምሥራቃዊ ክፍል ያለውንና በአሁኑ ጊዜ አራራት
ተብሎ የሚጠራውን ረጅም ተራራ ይጨምራል፤ ይህ ተራራ የሚገኘው በአርሜኒያ እና በኢራን ድንበር አቅራቢያ ነው። በርካታ ሰዎች በዚህ አካባቢ የኖኅን መርከብ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ በኋላ  ግርምትን ጫሪ ሐሳቦችን የሰነዘሩ ቢሆንም ተጨባጭ ማስረጃ ያቀረበ አንድም ሰው የለም ። ከአውሮፕላን ላይ የተነሱ አስገራሚ ፎቶግራፎችና መርከቡ እንደታየ የሚናገሩ ሪፖርቶች መኖራቸው እንዲሁም በቅጥራን የተሸፈኑ የእንጨት ቁርጥራጮች መገኘታቸው ሰዎች ይበልጥ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ለማግኘት እንዲነሳሱ አድርገዋቸዋል። ይሁንና ፍለጋው ቀላል አልሆነም። በመጀመሪያ ደረጃ መርከቡ አርፎበታል ተብሎ በአብዛኛው የሚጠቀሰው
የአራራት ተራራ ክፍል ወደ 4,600 ሜትር ከፍታ አለው። በአንደኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. የኖረው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ፣ በአራራት ክልል ባሉ ተራሮች ላይ መርከቡ እንደሚታይ ስለተናገሩ የተለያዩ የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች ጠቅሷል ።እንዲያውም ሰዎች በቅጥራን የተሸፈኑ የእንጨት ቁርጥራጮችን ለማስታወሻነት ይወስዱ እንደነበር የብዙዎችን ትኩረት ከሳቡት ሪፖርቶች መካከል አንዱ፣ ባለፈው መቶ ዘመን ጆርጅ ሃጎፕያን የተባሉ አርመናዊ የተናገሩት ነገር ነው። እኚህ ሰው፣ ልጅ ሳሉ ማለትም በ1900ዎቹ
መጀመሪያ አካባቢ ከአጎታቸው ጋር ሆነው መርከቡ ያለበት ቦታ እንደሄዱ አልፎ ተርፎም መርከቡ ላይ እንደወጡ ተናግረዋል። ሃጎፕያን በ1972 የሞቱ ቢሆንም እሳቸው የተናገሩት ነገር አሁንም ድረስ ብዙዎች የኖኅን መርከብ ለማግኘት እንዲጓጉና ስለ መርከቡ እንዲጠይቁ አነሳስቷቸዋል።

      በዕድሜ ጠገብነቷ እና በታሪክ ቀደምትነቷ ስሟ ሳይነሳ የማታልው የሰው ዘር መገኛ የሆነችሁ ሀገራችን ኢትዮጲያም ስለ አራራት ተራራ እና ስለ ኖኅ መርከብ መዳረሻ እንዲ ትላለች
      ኖኅ በጣና ነበረ።ኖኅ እሰከ ሚሞትበት ጊዜ ድረስ ይኖር የነበረው በአራራት ተራራ ነው ። የኖኅ መርከብ ያረፈችበት ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል ።  (ገድለ አዳም፣157-167፣ኩፋሌ 8፥1)
አራራት ተራራ 150 ሜትር ርዝመት አንባ ሊኖረው ግድ ይላል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐመር አሠራር የሚነግረን ይህንን ነው።
ሌላው አራራት ተራራ ተያያዥነት ያለው ተራራማ ነው።መርከቧ ያረፈችበት እና ኖኅ ወይን የተከለበት ተራራ ነው ። ኖኅ አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ ። የትም አልሄድም ኖኅ ካምን ይዞ ወደ አፍሪካ ምድር ሄደ የሚለው ልቦለድ ድርስት ነው ። ሌላው የኖኅ መቃብር ከአራራት ተራራ አይርቅም።እርሱም በአሁኗ ጎንደር ከተማ ሲሞት
በመቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር።ሆኖም ፈጣሪ ለኖኅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተመንግሥት አሳቦ የኖኅ መቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ። ምንጭ ፡-(ያሬድ ግርማ,የጎንደር ታሪክ 1999 ዓ.ም.)
የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው ። በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች ። ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል። ሉባር የሚባል ከተራሮች መሃል የሚገኘው ጣና እንጅ ከአርመኒያው ቦታ የለም። የነጮች የፈጠራ ውሸት ነው።ያልተፈጠረን ታሪክ ሲነግሩን የቆዩት የአራራትን ተራራ ታሪክ ለመሻማት መሆኑ ግልጽ ነው።
መጽሐፈ ኩፋሌ 9 ላይ እንደተጻፈው ኖኅ ለልጆቹ ርስት ሲያከፋፍል ለሴም ጣናን እና አባይን ተንተርሶ እስከ ግብፅ ዕጣ እንደወጣለት ይታወቃል ።ግብፅ ለመነሻው ቦታ ሰሜን ናት።ግብፅ ለእስያ ምድር ሰሜን አትሆንም።
አራራት ተራራ ለማየት በባህርዳር ከተማ ፊትለፊት 3 ዝቅተኛ ተራራዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ማየት ይቻላል ። ወይንም በዘጌ በኩል ሦስቱ ተራሮች ከሥር በኩል አንድ ሆነው ከላይ በኩል ተለያይተው ይታያሉ ። መርከቧ ያረፈችበት ቦታ ደልዳላ ሲሆን የመርከቧን ስፋትም መገመት ይቻላል።
ወይንም አራራት ተራራ የይጋንዳ ተክለሃይማኖት ቤተ ከርስቲያን ያለበት ነው ። መርከቧ ያረፈችው ከቤተ ክርስቲያኑ ጥግ ነው።መርከቧ ያረፈችበት ሉባር ተራራና ሌሎችም ቦታዎች እስከ አሁን ድረስ በአትክልት የታጀቡ ናቸው።

ዋናውና መቅደም ያለበት ነገር ግን የኖኅ መርከብ ወደ ምትባል ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀርቦ ከጥፋት ውኃ መዳኑ ላይ   ተራራውም መርከቧም በሀገራችን ቢኖሩ ለሀገር ዕድገት ይጠቅሙ ይሆናል እንጂ ለነፍ ዕድገት አይረቡንም ሳያዮ የሚያምኑ ብጽሐን ናቸው ተብሎ የተነገረልን ድንቅ ሕዝቦች እና የብዙ ቅርሥ ባለቤቶች ነንና  ማንም ነጭ አይቶና ጎብኝቶ የጨርቅ እላቂ  የሳንቲም ድቃቂ እንዲለግሰን አንፈልግም..

 በኖኅ የሚመሰሉ የካህናት የአባቶቻችንን ምክር ሰምተን ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን ተቀብለን ማዕበል በሚያናውጣት ግን ፈጽሞ የማያሰጥማት መርከባችን ወደ ሆነች  ቤተ ክርስቲያን በጊዜ እንግባ !

              .......  ይቆየን......
      ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ለአስተያየታችሁ
@YEAWEDIMER
ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ

ቅድስት ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
:ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው???
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::

በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
*********************************
አካላት
*
1) እራሷ (ሰንበት )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ
በኩረ በዓላት ናት :- የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና
ዓለም የተገኘባት
ወልድ ሰው የሆነባት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::

2) እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: ሉቃ 1÷26
3) ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :- ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና እረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) መንግስተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች ::
" ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እረፍት ይባላል :- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና እረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የእረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::

ማሳሰቢያ
********
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል ::
አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል ::
በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል:: በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::


.........ይቆየን...........

በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ:
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የዓውደ ምህረት ቤተሰቦች ሳምንታዊው የምን እንጠይቅልዎ መርሐ ግብራችን እነሆ ሰዓቱን ጠብቆ ተጀምሯል::
ለዛሬ ባሳለፍነው ሳምንት ከቀረቡልን ጥያቄዎች መካከል በቅደም ተከተላቸው መሠረት ለሁለት ጠያቂዎች ምላሽ ይዘን መተናል::


👉 ለሳምንት ሌሎች ጥያቄዎችን ለማቅረብ ለምትፈልጉ በዚህ አድራሻ ጥያቄዎን ሊሰዱልን ይችላሉ::
👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

የዛሬዎቹ ጥያቄዎች



ስማቸው እንዳይጠቀስ የተፈለጉ የአንድ ታዳሚ ጥያቄ



1⃣Selam wendemea

Yewere Abeba laye tehuno mesegede yechalale?

Beken snte mesegede alebene...lemene?


መልስ

በመጀመሪያ ጠያቂያችንን እናመሰግናለን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን::

ይህን መሰል ጉዳይ በምክረ ካህና(በንስሐ አባት በኩል የሚያልቅ ነገር ነው ስለዚህ ጠያቄያችን የንሰሐ አባትዎን በማነጋገር እንደ ትዕዛዛቸው መተግበር ይገባዎታል ::ሆኖም በዚህ ዙሪያ የግልም ሆነ እንደ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋ ነገር ስለሌለ ይህ ነው ብዙ አቅጣጫ መስጠቱ ሥርዓተ ቤተ ክርስትያንና ሥሥልጣናችን ስላልሆነ የተደመደመ ሀሳብ አንሰጥበትም በአጭሩ ከነፍስ አባቶዎ ጋር በመነጋገር የሚፈታ ችግር ነው:: ነገር ግን ነገሩን ካነሳን አይቀር በዚህ በወር አበባ ጊዜ ሴቶች ከምን ከምን ይከለከላሉ በሚል ንሁስ ርዕስ ጥቂት ዕውቀቶችን ልናካፍልዎ ወደደን....::

“ሴቶች (በልማደ አንስት ) በወር አበባ ጊዜ ከምን ከምን ይከለከላሉ?”
ሔዋንንም አላት ይውረድ ካንቺ ደም፣
ይኸው እስከ ዛሬ ለሴት አልቀረም፣
በወር ሰባት ቀን አለባት ሕመም፡፡
(“መስዋዕተ ኦሪት እንጂ ሕገ ኦሪት አልተሻረም” በሚል ርእስ ከታተመች መጽሐፍ ገጽ 5 ላይ የተገኘች የጎንደር አዝማሪ ግጥም)
ይህ ጽሑፍ የሚዳስሳቸው ነጥቦች፡
† የወር አበባ ስያሜው ምን ማለት ነው? የወር አበባ ጥንተ ታሪኩና ሕመሙ…? የወር አበባ ርኩሰት ነውን? በወር አበባ ወቅት
መከልከል የሚገባው ከምን ከምን ነው?
አንዲት የክታበ ገጽ/ፌስቡክ/ ወዳጄ በወር አበባ ወቅት ሴቶች ከምን ከምን እንደሚከለከሉ እንዳብራራላት ጠይቃኝ የነበረ ሲሆን
እኔም በዚህች እኅት አነሳሽነት ይህችን ጽሑፍ አዘጋጅቼ ለሁሉም ይጠቅማል በሚል ለጥፌዋለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ወንዶች ለአቅመ አዳም፣ ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ሲደርሱ ዕድገታቸውን የሚያመለክቱ የተለያዩ አካላዊም ሆነ ሥነ ልቡናዊ የሆኑ
ተፈጥሯዊ ክስተቶችን በላያቸው ላይ እናስተውላለን፡፡ በሴቶች ላይ ከሚስተዋሉ አዲስ ልማዶች አንዱ የወር አበባ መታየት ነው፡፡
† የወር አበባ የሚለው ስያሜ
የወር አበባ “ወር”ና “አበባ” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው፡፡ “የወር” የተባለበት ምክንያት በየወሩ የሚከሰት በመሆኑ ነው፡፡
“አበባ” የተባለበት ምክንያት ደግሞ ሴቶች ልጆች በዕፅ፣ በየወሩ የሚያዩት ደም በአበባ፣ የሚወልዷቸው ልጆች ደግሞ በፍሬ
ስለሚመሰሉ ነው፡፡ መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት ከመጽሐፈ ምሥጢር ጠቅሶ ይህንን ሲያስረዳ “እስመ ዕፅ ይቀድሞ ለጽጌ ወይተልዎ
ፍሬ ወለአንስትኒ ይቀድሞን ጽጌ ይመትክቶን ወይተልዎን ፍሬ ውሉድ” ይላል፡፡ ትርጉሙም “ለአንድ ተክል አበባው ቀድሞ ፍሬው
እንደሚከተል ለሴቶች ልጆችም በመጀመሪያ የወር አበባ ቀድሞ ይታያቸውና በኋላ ልጅ ለመውለድ ይበቃሉ” ማለት ነው፡፡
(ሕይወተ ወራዙት ክፍል አንድ፣ ዲያቆን ኅብረጽ የሺጥላ)
የወር አበባ በሌሎች የተለያዩ ስያሜዎች ተጠርቷል/ይጠራል፡-
+ ልማደ አንስት - ዘፍ.18፡11
+ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ - ዘፍ. 31፡35
+ ደመ ትክቶ (አደፍ) - ሕዝ. 18፡7-9
+ ደመ ጽጌ - የአበባ ደም ማለት ሲሆን ሴቶች በሚያብቡበት ጊዜ የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት መምህራን የሚጠሩበት ስም
ነው፡፡
† የወር አበባ ጥንተ ታሪኩ
የወር አበባ አዳምና ሔዋን በገነት በነበሩበት ጊዜ በሔዋን ላይ አልተከሰተም ነበር፡፡ ምንም እንኳን በውስጧ ደመ ጽጌ ሆኖ
ቢኖርም ወደ ውጭ ግን የሚፈስ አልነበረም፡፡ በጥንተ አብሶ እግዚአብሔርን በድለው ከገነት ከተባረሩና ወደ ምድር ከተጣሉ
በኋላ ግን የበደል ውጤት ሆኖ በየወሩ መፍሰስ ጀመረ፡፡ ይህም ዕፀ በለስን በልተው ሲበድሉ ሔዋን ደመ ዕፀ በለስን አፍስሳለችና
“ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕፅ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ/ የዕፀ በለስን ደመ ዕፅ እንዳፈሰስሽ ደምሽ በየወሩ እንዲፈስ ይሁን”
ተብላ ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ስለፈረደባት ሔዋን ከገነት ውጭ ሆና ስትኖር ደሟ በየወሩ ይፈስ ጀመር፡፡
† በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም ሕመምና ለሴቷ የሚደረግ ድጋፍ
ሴቶች ደመ ጽጌን/ የወር አበባን በሚያዩበት ወቅት የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ (ድካም) ያጋጥማቸዋል፡፡ የጀርባ/ የወገብ
ሕመም፣ ሆድ ቁርጠት፣ የምግብ መንሸራሸር ችግር፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ራስ ምታት፣ ማስመለስና የመሳሰሉት
ይስተዋልባቸዋል፡፡ (በርግጥ ምንም የማይሰማቸው ጥቂቶች ይኖራሉ)፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ አስፈላጊው ድጋፍና በቂ ረፍት
ያስፈልጋቸዋል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ትውፊት ወንዶችም ሆነ ሌሎች ሴቶች በወር አበባ ወቅት ላይ ያሉ እኅቶችን መደገፍ እንደሚገባን ያስተምራል፡፡
በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 31 ቁጥር 35 ላይ ላባ የተባለ ሰው የጠፋበትን ዕቃ በሚፈልግበት ጊዜ በወር አበባ ላይ ትገኝ
የነበረችውን ልጁን ራሔልን ከተቀመጠችበት ቦታ ላለማሥነሳት የተቀመጠችበትን ስፍራ ከመበርበር ተቆጥቧል፡፡ በምን አውቆ
ቢባል እርሷም አባቷን “በፊትህ ለመቆም ስላልቻልኩ አትቆጣብኝ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል” አለችው ስለሚል ከዚህ
የይቅር በለኝ ቃሏ ያለችበትን ሁኔታ ለመገንዘብ ችሎ ነው፡፡
† የወር አበባ ርኩሰት ነውን?
አንዳንድ ሴቶች በወር አበባ ወቅት “ርኩስ ነኝ” በሚል ሰበብ መስቀል አይሳለሙም፤ ከጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብ
የሚቆጠቡም አሉ፤ አንዳንዶቹም ለጸበል ጸዲቅ የሚሆን ማናቸውንም ሥራ ከመሥራት ይከለከላሉ፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ስህተትና
የሥርዐተ ቤተክርስቲያን ምንጭ የሌለው ተግባር ነው፡፡
በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የምታይን ሴት
ለመጥቀስ “በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች” እና “ባለ መርገም ሴት” ሲል ይገኛል፡፡ ዘሌ. 18፡19 ፤ 20፡18፡፡ ከወር አበባ የነጻችን ሴት
ለመጥቀስ ደግሞ “ከርኩሰቷ ነጽታ ነበርና” በማለት ይገልጻል፡፡ 1 ሳሙ.11፡4 ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች የወር አበባ በኦሪት የርኩሰት
ምልክት እንደነበር የሚጠቁሙን ናቸው፡፡ ለነገሩ በኦሪት እንኳንስ የወር አበባ ይቅርና ጽድቁም እንደ መርገም ነበር፡፡ ለዚህም ነው
ነቢዩ ኢሳይያስ “ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፣ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው” በማለት የተናገረው፡፡ ኢሳ.
64፡6 ፡፡
በአዲስ ኪዳን ግን የወር አበባን ርኩሰት ነው ማለት ቀርቶ መታሰብም የለበትም፡፡ እንደውም የወር አበባን ርኩሰት ነው ማለት
ከኃጢአትም አልፎ ከባድ ክህደትም ነው፡፡ ምክንያቱም መርገምንና ርኩሰትን ያስወገደልንን የክርስቶስን ቤዛነት መጠራጠር ብሎም
መካድ ነውና፡፡
መዘንጋት የሌለበት ነጥብ ግን የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም አደፍ ነው፡፡ ርኩሰትና አደፍ ከፍተኛ ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት
ውሳጣዊ ሲሆን የሚጠራው በንስሐ ነው፡፡ አደፍ ግን በመታጠብ የሚጠራ ውጫዊ ነው፡፡
የወር አበባ በሰውነት ውስጥ እስካለ ድረስ አደፍ አይባልም፡፡ እን

"ሐሰተኞች ናችሁ እንጂ ከተክለ ሃይማኖት ወገን ልጆች አይደላችሁም "


ገድለ ተ/ሃይማኖት 61÷1-10
ነሐሴ 1989 ዓ/ም ዕትም
ከአባታችን ልጆች ደግሞ ሁለቱ ወደ ኢየሩሳሌም ወረዱ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ደርሰውም ከእርሱ ተባረኩ ከወድሄት ናችሁ? አላቸው ከኢትዮጵያ ነን አሉት የእግዚአብሔር ሰው የተክለ ሃይማኖትን መቃብር ታውቁታላችሁን? አላቸውአዎን እናውቀዋለን ከዛ መጣን አሉት ሊቀ ጳጳሱም ሰምቶ ተነስቶ ሰገደላቸው እግራቸውንም ሳመ በምን ነገር ከዚህ መጣችሁ አላቸው የነፍሳችንን ድኅነት ልንሻ አሉት :: ጮሆም ወይ ሰው የነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ለካ ይጎዳልን? መድኃኔታችሁን ተዋችሁ ሕይወታችሁንም ጠላችሁት ጌታ ለተክለ ሃይማኖት በአጽሙ ቦታ የተቀበረውን ዘወትር ከእርሷ ዘንድ የሚኖር የሁለተኛይቱ ቀን በግልጽ ከአንተ ጋር ይለፍ ያለውን አልሰማችሁምን? አላቸው::ከሊቀ ጳጳሱም ንግግር የተነሳ መነኮሳቱ አደነቁ ::
ለእኔ ምን ታደርጉልኛላችሁ ተመልሳችሁ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ አላቸው እኛ ካንተ ጋር እንኖራለን እንጂ አንመለስም አሉት ምን ሥራ ታውቃላችሁ አላቸው? የወይን ተክል ሥራ መኮትኮት እናውቃለን አሉት የወይንም ቦታ ሥራ እንዲያዮ ላካቸው :: ከዛም በደረሱ ጊዜ በእጃቸው ሳይነኩት ገና በዐይናቸው ቢያዮት ያ በቦታው ያለው ወይን ደረቀ ለሊቀ ጳጳሱም ይህን ነገሩት ሊቀ ጳጳሱም ሰምቶ እጅግ ደነገጠ እነዚያንም መነኮሳት ጠርቶ ባያችሁት ጊዜ የወይን አትክልት ቦታዬ እንደደረቀ ስለ እናንተ ነግረውኛል ፍጥረታችሁ ከምንድነው? አላቸው ችግረኞች ሰዎች ነን እኛስ ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን ነን አሉ ሊቀ ጳጳሱም ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን ብትሆኑ ደረቁ እንኳን እርጥብ በሆነ ነበር እርጥቡ የቦታዬ ወይን ባያችሁት ጊዜ የደረቀ አይደለምን "ሐሰተኞች ናችሁ እንጂ ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን አይደላችሁም " አላቸው አባታች ሆይ ሐሰት እንዳልተናገርን ነፍሳችን በእጁ ያለ እግዚአብሔር ምሥክራችን ነው አሉት:: እንኪያስ የቦታዬ ወይን ስለምን ደረቀ አላቸው እንጃ የሆነውንስ ነገር አናውቅም አሉት የተክለ ሃይማኖትን መቃብር የተሾሙ አበ ምኒት ተሰናብታችውታልን? አላቸው አልተሰናበትነውም አሉት ሊቀ ጳጳሱም እጆቹን አጨበጨበ ና የቦታዬ ወይን ስለዚህ ነገር እደ ደረቀ አሁን ገና አወቅሁ አለ ሊቀጳጳሱም በመላእክቶቹና በእግዚአብሔር ዘንድ ተክለሃይማኖት የክቡር ነው ዘወትርም መንፈስ ቅዱስ በመቃብሩ ላይ ይረባል በተክለ ሃይማኖት ወንበር የተቀመጠ ተክለ ሃይማኖት ነው አሁንም ወደዛ ሂዱ ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም የወይኔንም ቦታ አታጥፉሁ አላቸው ከእርሱም ተባርከው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ:: በእውነት እኛንም ከተሰደድንበት የክህደት መንገድ ይመልሰን ዛሬ ከቅዱሳን መቃብር ይቀው የቅዱሳኑን አጽም ተጸይፈው የሚጸድቁ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው ከቅዱሳኑ አጽም ጋር ግን እግዚአብሔር እንዳለ አያሰውሉም "፤ የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው እግዚአብሔር ከሁሉ ያድናቸዋል እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። " መዝ 33 (34)÷20 በቅዱሳኑም አጽም ድንቅ እንደሚያደርግ አያምኑም "የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። " መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 13÷21 ስለዚህም ዓለሙ ከቅዱሳን አጽም ይልቅ የሚሊዮን ዓመት ቅሪተ አካል የነ ሉሲና የነ አርዲ እንዲሁም የነ ሠላምን አጽም ማክበሮ እና በመስታወት እጥሮ ዕለተ ዕለት መጎብኘቱን ይመርጣል ከነ ሉሲ አጥንት ጋር ግን እግዚአብሔር የለም አይጠብቃቸውምም ስለዚህ ከከፊል ቅሪት አጽም ያለፈ ሙሉ አጽማቸው ሊገኝ አልቻለም አፈር በልቶት ብል ሰባብሮት ጠፍቷልና የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል የኃጥህ ስም ግን ይጠፋል እንዳለ መጻሕፍ:: ምሳ10÷7

የአባታችን የተክለሃይማኖት አጽም ለ57ዓመት በደብረ አስቡ (አሰቦት ገዳም ) ከቆየ በኃላ በፍቃደ እግዚአብሔር ግንቦት 12 ቀን በዛሬዋ እለት ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹ በተገኙበት ወደ ደብረ ሊባኖስ ፈልሷል ይህም የሆነው ደብረ አሰቦት ጠባብ በመሆኗና በዓሉን ለማክበርም ሆነ በቅዱሱ አጽም ጥላ ሥር ተከልለው ለመኖር የሚመጡ ሰዎች ብዙ ሊሆኑ ስለሚችል ቦታዋ እንዳትጠባቸው በማሰብ ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊሊባኖስ ሊፈልስ ችሏል (ተጨማሪ መረጃ ገ/ተ/ሃይማኖት ምዕራፍ 56 ይመልከቱ) እስካሁንም የጻድቁ አጽም በዚያ አለች::ታዲያ እነዚያ ሁለት መነኮሳት ከዚህች የተቀደሰች ሥፍራ ኮብልለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ ሄደው ግን ፍሬ ሊያፈሩ አልቻሉም እንዲያውም ያፈራውን የወይን ቦታ ሰላዮት ብቻ ደርቆ ተገኝቷል::ይገርማል ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተክል ከተክለ ሃይማኖት ተለይቶ ፍሬ ማፍራት አይቻልም ዛሬ ብዙዎች ከቅዱሳን ቤት ወጥተው ፍሬ ለማፍራት ይሞክራሉ ግን አይቻላቸውም :: መነኮሳቱ ከተክለ ሃይማኖት የመቃብር ሥፍራ መጣን ብለው ነበር ነገር ግን የበለጠውን ጥለው መተዋልና ሊቀ ጳጳሱ ተቆጣ በቤቱ ካደጉት ይልቅም ስለ አባታችን የአጽም(የመቃብር ሥፍራ) ቃል ኪዳን እየነገረ ይበልጡኑ አስገረማቸው አብረውት የኖሩ ቢሆኑም እዳማያውቁት ሆነባቸው ተደነቁም ጥለነው የመጣነው ከመጣንበት ነገር የሚበልጥ ሆኖ ስናገኘው የእንደሚሰማን ዓይነት ስሜት አደረባቸው ዛሬስ አብረነው የምንኖር ግን የማናውቀው ስንቶች እንሆን? ያለ "እኔ አዳች ልታደርጉ አትችሉም እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ" እንዳለ ከግንዳችን የተለየን ፍሬ ማፍራት የማንችል ጭራሮች ብዙ ነን :: የዛፍ ቅርንጫፍ ከዛፉ እስካለ ድረስ ቅርንጫፍ ይባላል ከዛፉ ተቆርጦ ከወደቀ ወዲያ ግን ጭራሮ እንጂ ቅርንጫፍ አይባልም በፀሐይ ደርቆ በንፋስ ተወስዶ ይጣላል ወይም ወደ እሳት ይጣላል:: "፤ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሐ 15÷5 ተክለ ሃይማኖት የሕይወት ዛፍ ናቸው::የሚጠጋቸውም (30)(60)(100) ያማረ ፍሬዎችን አፍርቶ ይገኛል ወደ እሳትም ሳይሆን ወደ ዘላለም ደስታ ይገባል :: መነኮሳቱ ያዮት የአትክልት ቦታ ደርቆ በመገኘታቸው ሊቀ ጳጳሱን አሳዘነው እነዚያንም መነኮሳት ጠርቶ ባያችሁት ጊዜ የወይን አትክልት ቦታዬ እንደደረቀ ስለ እናንተ ነግረውኛል ፍጥረታችሁ ከምንድነው? አላቸው ችግረኞች ሰዎች ነን እኛስ ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን ነን አሉ ሊቀ ጳጳሱም ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን ብትሆኑ ደረቁ እንኳን እርጥብ በሆነ ነበር እርጥቡ የቦታዬ ወይን ባያችሁት ጊዜ የደረቀ አይደለምን "ሐሰተኞች ናችሁ እንጂ ከተክለ ሃይማኖት ልጆች ወገን አይደላችሁም " አላቸው ዛሬም ልብ ተክንኖውን ለብሰን ስንቀድስ ስንዘምር ስናገለግል ያየን ቤቱ ስንመላለስ የተመለከተን ነገር ግን የተክልዬ ልጆች ናቸው ተብሎ ለመጠራት የማንመጥን ብዙ አለን:: የማያፈራ ተክል እራሱ ከመነቀሉ በተጨማሪም ያደገበትን ቦታ ያቦሳቁላል ያደርቃል ሊሎችም ተክሏች እንዳያፈሩ ቢያፈሩም በአረም ተሞልተው ፍሪያቸው እንዳይታይ ያደርጋል :: ፈሪሳዊያንና ጸአፍት አብርሃም አባታችን ዳዊት መንግሥታችን እያሉ ይታበዮ ነበር የአብርሃምን እምነት ግን አአልተከሉም የዳዊትን ፍሬ ግን አላፈሩም እንዲህ ከመሆን ጻድቁ የእምነት ገበሬ ተክለ አይማኖት አባታችን ይጠብቁን በሃይማኖት ይትከሉን በምግባር ይኮትኩቱን በረድኤታቸው ያረስርሱን "ሐሰተኞች ናችሁ እንጂ
፩) ሰማዕት ‹‹ሰምዐ› › ከሚል የግእዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም
ያየነውን፣ የሰማነውን መመስክር መቻል እንደሆነ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ
መጽሐፈ ስዋስወ ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ 671 ይነግረናል፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹እኔ ለእውነት ለመመስከር
መጥቻለሁ›› በማለት እውነትን እንድንመሰክር አብነት ሆኖናል /
ዮሐ.18፥37/፡፡
ሰማዕትነት በሃይማኖታዊ ትርጉሙ ስንመለከተው ስለ እግዚአብሔር፣
ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ ሃይማኖታቸው በእውነት
በመመስከራቸው ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት፣
እግራቸውን ለሰንሰለት፣ አንገታቸውን ለስለት አሳልፈው ለሰጡ፤
በድንጊያ ተወግረው በመንኮራኩር ተፈጭተው በጦር ተወግተው
አልያም በግዞትና በስደት በዱር በገደል ተንከራተው ለዐረፉ ቅዱሳን
አባቶችና ቅዱሳት እናቶች የሚሰጥና ተጋድሎአቸውን ጠቅለል አድርጎ
የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው እመቤታችንን
ባመሰገነበት ድርሳኑ “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት
ናቁ፤ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ስለ መንግሥተ
ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ” በማለት የሰማዕታት ተጋድሎአቸው
መራራ እንደሆነ ገልጿል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)
ጌታችን ‹‹በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት
ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡ በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ
ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ›› ሲል ስለ
ሃይማኖታችን የምንመሰክረው ከሰማዕትነት ጋር ያለውን ቁርኝት
ነግሮናል፡፡ /ማቴ.10፥32-33/፡፡ ከዚህ አንጻር ያለ ክርስትና
ሰማዕትነት ያለ ሰማዕትነት ክርስትና የለም ማለት ነው፡፡
ሰማዕትነት መመስከር ከሆነ እንዴት ነውየምንመሰክረው የሚል ጥያቄ
ማንሳታችን አይቀርም፡፡ ለዚህ ጥያቄያችን መልስ የምናገኝባቸው
ሦስት የመመስከሪያ መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
በአንደበታችን
እግዚአብሔር አምላካችን አንደበት የሰጠን እውነትን በመመስከር
ለክብር እንድንበቃበት እንጂ ውሸት በመናገር አምላካችንን
እንድናሳዝንበት አይደለም፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ‹‹አንደበቱን
ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው
ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው›› በማለት በአንደበታችን
እውነትን እንድንመሰክርበት ይመክረናል /ያዕ. 1$26/፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉ መስክሮም
ይድናልና›› እያለ እውነትን መመስከር ለመጽደቅና ለመዳን ወሳኝ
ጉዳይ ነው ይለናል /ሮሜ 10፥10/፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን
በዓለም ዞረው ያስተማሩት በአንደበት መመስከር ያለውን ሰማያዊ
ዋጋ ስለተረዱ ነው፡፡ አንደበታችን እውነትን በመመስከር ለሰማዕትነት
የሚያበቃን መሆኑን ተገንዝበን አንደበታችን ሰዎችን ከማማት፤
ያለሥራቸው ስም ከመስጠት ሊቆጠብ ይገባዋል፡፡
በሕይወታችን
በሕይወት መመስከር ያላመኑትን ወደ ማመን የሚያመጣ ትልቅ
መሣሪያ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መመሪያችን ነው፡፡
በሕይወት መመስከር ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትን
ሕግጋትና ትእዛዛት በተግባር ለውጦ ማሳየት መቻል ነው፡፡ ለስም
አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በተራራ ላይ ስብከቱ ያስተማረን ‹‹መልካሙን ሥራችሁን
አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ›› በማለት ነው /ማቴ.5፥16/፡፡ በቅዱሳን
የሕይወት ምስክርነት እግዚአብሔር ታይቷል፡፡ በእኛ ሕይወት
እግዚአብሔር ታይቷል ወይ ብለን ሁላችን ራሳችንን ልንመረምር
ያስፈልጋል፡፡
በአላውያን ፊት
ከባዱና ታላቁ ሰማዕትነት በአላውያን ነገሥታትና እግዚአብሔርን
በማያምኑ ሰዎች ፊት ያመኑትን እምነት ሳይፈሩ መመስከር መቻል
ነው፡፡ አላውያን ነገሥታት የእግዚአብሔርን አምላክነትና ፈጣሪነት
ስለማያምኑ ሰማዕታትን ያሰቃያሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሰማዕት
የሚሆኑት ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ሰማያዊ ክብር ስለሚያስቡ ወደ
እሳት ቢጣሉ፣ በሰይፍ ቢቆረጡ፣ በድንጋይ ቢወገሩ ምንም
አይመስላቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት የኖሩ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ
የተፈጸመው ግፍና ስቃይ ለዚህ አባባላችን መሳያ ነው፡፡ ቀዳሜ
ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ እውነትን በሐሰት ለውጠው
የእግዚአብሔርን አምላክነት በመካድ በሥልጣናቸው ተመክተው
ለነበሩ አይሁድ ያላንዳች ፍርሃት ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ
አምላክነት በመመስከሩ በድንጋይ ሲወግሩት፣ ዓይናቸው በኃጢአት
ለታወረ አይሁድ ‹‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› በማለት
ለወጋሪዎቹ ምሕረትን ለምኗል /የሐዋ. ሥራ 7፥60/፡፡
የሰማዕትነት ዓይነቶች
የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሰማዕትነት ዓይነቶች ሁለት ናቸው
ይሉናል፤ ሲተነትኑትም ሰማዕት ዘእንበለ ደም (ደማቸውን ሳያፈሱ
ሰማዕት የሆኑ) እና ደመ ሰማዕታት (ደማቸውን በማፍሰስ ሰማዕት
የሆኑ) በማለት በሁለት አበይት ክፍሎች መድበውታል፡፡ እነዚህ
ብያኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ሰማዕትነትን ከአፈጻጸም አንጻር
በሦስት መሠረታዊ ቀለሞች ይመስሉታል፡፡ (ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሐመረ
ተዋሕዶ፤ ገጽ 130 ነሐሴ 2002 ዓ.ም.)
አረንጓዴ ሰማዕትነት
እንደማንኛውም ሰው በከተማ እየኖሩ ዓለምን ለማሸነፍ የሚጥሩ
ከራሳቸው ጋር ታግለው ዲያብሎስን ድል ማድረግ የቻሉ አረንጓዴ
ሰማዕታት ይባላሉ፡፡ የሚበላ፣ የሚጠጣ ሳያጡ ሁሉን የሰጣቸውን
ፈጣሪ እያመሰገኑ ራሳቸውን በጾምና በጸሎት በመወሰን ያጡ የተቸገሩ
ወገኖቻቸውን ለመርዳት የማይሰለቹ የጽድቅ ሥራ በመሥራት
የሚያገኙትን ሰማያዊ ጸጋ በማሰብ የሚደሰቱ ናቸው፡፡ ከዚህ መልካም
ሥራቸው የተነሣ ስድብ፣ ነቀፌታ፣ ስደት፣ እስራት ሲደርስባቸው
መከራውን ሁሉ በአኮቴት (በምስጋና) ተቀብለው ፈጣሪያቸውን
የሚያመሰግኑ ናቸው፡፡
ነጭ ሰማዕትነት
ይህን ዓለም አሸንፈው ግርማ ሌሊትን ጸብአ አጋንንትን ታግሰው በዱር
በገደል የኖሩ አባቶቻችን ሕይወት የምናይበት ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ማንም
ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ትቶ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን
አይችልም›› ብሎ የተናገረውን ቃል በተግባር ያሳዩትን የሚወክል
ነው /ሉቃ 14$27/፡፡ ይህ የሰማዕትነት ጥሪ ለሁላችንም የቀረበ
እንደሆነ እንድንረዳው ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› ብሎናል /ማቴ. 16፥24/፡፡
ስለሆነም ራሳችንን ከውስጣዊ ፈተና ለማዳንና ከልቦና ኃጢአት
ለመጠበቅ በጾም፣ በጸሎት፣ በትኅርምት በትሕትና ጸንተን በመዓልትና
በሌሊት እግዚአብሔርን እያመሰገን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡
ቀይ ሰማዕትነት
ይህ ሰማዕትነት በደም የሚመጣ የሰማዕትነት ዓይነት ነው፡፡
እግዚአብሔርን በማምለካችን፣ ቅዱሳንን በማክበራችን፣ ማተብ
በማሠራችንና በአጠቃላይ ክርስቲያን በመሆናችን የሚመጣብንን
መከራና ስቃይ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር በመታገስ በሰይፍ ተቀልተን፤
በመንኮራኩር ተፈጭተን፤ ወደ እቶን እሳት ተጥለን የሕይወት
መስዋዕትነት በመክፈል የምናገኘው ክብር ነው፡፡ ይሔ ሰማዕትነት
የመጨረሻ ደረጃ ነው፡፡ (ያረጋል አበጋዝና አሉላ ጥላሁን፤ ነገረ
ቅዱሳን፤ ገጽ 26-30፤ 1997 ዓ.ም.)

፪ ) ቢቻላት ትከናነብ ሳይሆን በግዴታ መከናነብ እንዳለባት ነው ሐዋርያው የተናገረው ጸጉርን ለመሸፋፈን መቻል አለ መቻል ብሎ ነገር የለም ጸጉሯን መሸፈን የማትችል ወይም የሚያዳግታት ሴት የለችምና ምን አልባት አላማዋ መታየት መገላለጥ መፈለግ ካልሆነ በቀር

"፤ በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን? "

ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥
" #አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል"
" #መስቀሌን በመስቀልያ ቦታ አስቀምጥ"
መጽሐፈ #ጤፉት


መስቀሌን በመስቀልያ ቦታ አስቀምጥ የሚለው ትዕዛዝ ለአፄ ዘር ያዕቆብ የተነገረ ቢሆንም ቅሉ ለኛ ለክርስቲያኖችም የታዘዘ ኃይለ ቃል ነው። የሰው ልጅ ቃጥ ብሎ ቆሞ እጆቹን ወደ ግራና ወደ ቀኝ ቢዘረጋ ሁነኛ የመስቀል ቅርጽ ያለው መስቀልያ ቦታ መሆኑን ይረዳ ነበር። ብዙዎች ግን በprotocol ሰበብ ለቀረጻ አይመችም !፣ ለሰርግ አይሆንም ፣ ውበት ይደብቃል እያሉ መስቀሉን ከመስቀልያ ቦታ አውርደው ጥለውታል። ቅዱስ መስቀሉ ግን "እንወደው ዘንድ ደም ግባት የለውም" ኢሳ53÷1-12 እስኪባልለት ድረስ መዳኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ደም ግባት ያለን ያደርገን ዘንድ ወዝና ደሙን ያንጠፈጠፈበት ውበታችን ነበር ። #ስለዚህ_ዛሬም "አንብሩ መስቀልየ በዲበ መስቀል" እየተባልን ነው። #መድኃኔዓለም በዕለተ ዓርብ ከቀኔ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ከለየ በኋላ በኋላ ከመስቀሉ አውርደው ቀበሩት ፡፡ በ፫ኛው ቀን ሲነሣ ተሰቅሎ የነበረው የእንጨት መስቀል ሌት ተቀን በሙሉ ሳያቋርጥ እንደፀሐይ ሲያበራ በተጨማሪም አጋንንት ሲያባርር ድውይ ሲፈውስ ሙት ሲያነሣ ቤተ እሥራኤል አይሁድ ቀንተው በዓዋጅ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በመቅበር የቤት ጥራጊና አመድ ጠቅላላ የቆሻሻ መከማቻ እንዲሆን ወሰኑ፡፡

ከዚያ ዘመን ጀመሮ እስከ ሦስት መቶ ዘመን ድረስ የተከማቸው ቆሻሻ እንደተራራ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት እሌኒ ንግሥት የተባለች ደግ ሴት የክርስቶስን መስቀል መስከረም ፲፯ ቀን ፫፻፳ ዓ.ም. ላይ በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተ መቅደስ ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው ። ይህ መስቀልም ከዚያ ዘመን ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ተአምራትን እየሠራ ሙት እያነሳ ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡ ይህንንም ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው። በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ምዕመናን የሮማውን ንጉሥ ሕርቃልን ዕርዳታ በመጠየቅ እንዲመለስ አድርገው በኢየሩሳሌም ብዙ ዘመን ሲኖር እንደገና ኃያላን ነገሥታት ይህን መስቀል እኔ እወስድ እኔእወስድ እያሉ ጠብ ፈጠሩ። በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም፤የቁስጥንጥንያ፤የአንጾኪያ፤የኤፌሶን፤የአርማንያ ፤ የግሪክ ፤ የእስክንድርያ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት ከዚህም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስ መስቀል ከ፬ ከፍለው በዕጣ አድርገው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎቹ ታሪካዊ ንዋያት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት፡፡ የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡ ይህ ግማደ መስቀልም ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሄደ። በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ሥቃይ ያጸኑባቸው ጀመር ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግሥልን ብለው ጠየቁት” ። ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክት ለእስላሞች ላኩ። በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ የሕይወታችሁ መሠረት የሆነውንም የዓባይን ወንዝ ገድቤ በርሃብ ነው የምፈጃችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ላኩ ፡፡

የንጉሡ መልዕክት ለእስላሞች እንደደረሳቸው ፈርተው እንደጥንቱ በየሃይማኖታቸው ፀንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡መታረቃቸውን ዳግማዊ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ በጣም ደስ አላቸው እግዚአብሔርንም አመሰገኑ የዓባይንም ወንዝ እንደ ቀድሞ ለቀቁላቸው በግብፅ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ ተመልከተው ደስ ኣላቸው። ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፉ በግብፅ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝን ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም። የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ በኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረውን መስቀልና የቅዱሳንን አፅም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው የሚል ነበር፡፡ በእስክንድርያም ያሉ ምእመናን ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን አጽምና ንዋየ ቅድሳት ጋር አሁን በመለሰው ፲፪ ወቄት ወርቅ የብርና የንሐስ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው ተስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው አስረከቧቸው። በጊዜውም በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሉት ይህም የሆነው መስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያም ታለቅ ብርሃን ሌት ተቀን ፫ ቀን ሙሉ ሲበራ ሰነበተ፡፡ ነገር ግን ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዓፄ ዳዊት ስናር ላይ አረፉ፡፡ ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት አስፈለገው፡፡

ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዘርአ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ሥናር ሔደው ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት ጋር አምጥተው በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተ መቅደስ ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ ።በሕልማቸው አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል ወዳጄ ዘርአ ያዕቆብ ሆይ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ የሚል ሕልም አዩ ፡፡ ንጉሡም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ መስቀለኛ ቦታ በመፈለግ ከብዙ ቦታ ላይ አስቀምጠውት ነበር ። ለምሳሌ በሸዋ በደርሄ ማርያም ፤ በመናገሻ ማርያም ፤ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ያላገኙ በመሆኑ በራዕይ እየደጋገገመ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡ዓፄ ዘርአያዕቆብም ለ፯ ቀናት ያህል ሱባዔ ገቡ በዚያም የተገለፀላቸው መስቀልኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምድ ብርሃን ይመጣል አላቸው እርሳቸው ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ ዓምደ ብርሃን ከፊታቸው መጥቶ ቆመ በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል መርቶ አደረሳቸው ፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ሁና ስለአገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው ፡፡ በዚያችም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ በመጀመሪያም ይህ ግማደ መስቀል ከእስክንድርያ ስናር የገባው መ
#ዛቲ_ዕለት_ቅድስት_ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
#ቅድስት_ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው?
_________________________
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::
በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
***********************************
1) (ሰንበት ክርስቲያን )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
*ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ በኩረ በዓላት ናት :-
* #የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና ዓለም የተገኘባት
* #ወልድ ሰው የሆነባት
* # ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
* #ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::
2) #እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች
____________________________

ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: #ሉቃ 1÷26
3) #ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) #ቅድስት_ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :-
__________________________________
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) #መንግሥተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች
_______________________________
እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች :: " ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዕረፍት ይባላል :-
___________________________________
" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና ዕረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የዕረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::
#የግርጌ_ማስታወሻ
++++++++++++++
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል :: አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል :: በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል::
በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::
.........ይቆየን...........
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ /ማርያም
የካቲት 12/2010 ዓም
የተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን መቼ ዐውቀዋለሁ? ብዬ ስለው፤ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አሉልህ ብሎ ይለኛል። ወደ ምሥራቅ ስሄድ፥ የደብረ አሚን ተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ቤተ ክርስቲያን ዐየሁ። ከቤተ ክርስቲያኑ ደረጃ ላይ ሦስት መነኰሳት አገኛለሁ። ሁለቱ ይይዙኝና አንደኛው እንደ ቱቦ ባለ ነገር ሲያጠምቀኝ ዐየሁ።
አረ ለቀቅሁኝ ለቀቅሁኝ እያልሁ የምጮኽ ይመስለኛል። በሕልሜ ስጮኽ ድምፄ ተሰምቷቸው ሴትዮይቱ ዳጃፉን ቆፍቁፈው (ቆርቁረው)፥ ምን ሁነህ ትለፈልፋለህ? አሉኝ። ለፈለፍሁ? አልዃቸው። አዎ አሉኝ። ኧረ ሕልም ታይቶኝ ነው አልኋቸው።
ወዲያውም ተክለሃይማኖት ከዚህ ሀገር አለ ወይ? አልዃቸው። አዎን አሉኝ። ወዴት ናቸው? ብዬ ብላቸው፥ ወደ ጸሐይ መውጫ ናቸው ያሉት ቅርብ ናቸው ብለው አሉኝ። ጠበል
አላቸው ወይ ብዬ ብላቸው አዎን አለ፤ ማንም የክፍለ ሀገር ሕዝብ እየመጣ የሚድንባቸው ናቸው። በጋዜጣም ተጽፏል አሉኝ። እንግዲያስ ማለዳ እንዲያሳዩኝ አልዃቸው።

ማልዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውኝ ሲመጡ፥ ከቅጽረ ጊቢው ልገባ ስል፤ ከቤተ ክርስቲያኑ (ፊቴ) . . . ፊት ለፊት ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ዐየሁ። መሄድ አቅቶኝ ተጎንብሼ ከትከሻዬ ላይ ትልቅ ሸክም የተሸከምኩ የመሰለኝ ሰው፤ ቀስተ ደመናውን እንዳየሁ፥ ሸክሙ ወርዶ ከጀርባዬ ሲወድቅ ተሰማኝ። ምን ዕቃ ጣልሁ? ብዬ ወደ ኋላዬ ዘወር ብል፥ ባዶ ሆነ። ከዚያ በኋላ ትከሻዬን ስለ ለቀቀኝ ቀና አልሁ። ቤተ ክርስቲያ ሄጄ ተሳልሜ በመስቀል አማተብሁ።
በስመ አብ ብዬ ለመጸለይ በቃሁ። የዕለት ውዳሴ ማርያም መጽሐፈ ጎልጎታ ደገምሁ። ከዚህ በኋላ ወደ ጠበሉ ገባሁ። ባዩህና አሰፋ ከየት እንደ መጣሁ ጠየቁኝ። ከጎንደር አልኋቸው። አስታማሚ የለኝም ብዬ ብነግራቸው፥ በነጻ ትጠመቃለህ ማደሪያ ፈልግ ተባልሁ። እሺ ብዬ ተጠመቅሁ። ምንም ሳያስጮኸኝ አንደበቴም ሕሊናዬም ተመለሰልኝ።

ከሴትዮይቱ ቤት እያደርሁ ሰባት ቀን በተከታታይ ተጠመቅሁ። ሴትዮይቱም
እንዳልከብዳቸው ራሴን ስለቻልሁ ማደሪያ ቤት ስጡኝ ብዬ እነባዩህን (እንባዬን)
ለመንኋቸው። ለሰባት ቀን ብቻ ከአዳሹ ግባ አሉኝና ገባሁ።
ሰባት ቀን ተጠመቅሁ። እነሱም ውጣም አላሉኝ። ጠበሉን ስለወደድሁት እንደ ሱባኤ አድርጌ ጸሎት እያደረግሁ ተጠመቅሁ። ጤናዬን ካገኘሁ አገሬ አልሄድም ብዬ እስከ አሁን አለሁ። ከሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ጀምሮ፥ እስከ ዛሬ የካቲን ፫ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. ድረስ እዚሁ ጠበል ቤት እየተጠመቅሁ፤ በቤተ ክርስቲያንም እያገለገልሁ አለሁ። ልብሴም ጉርሴም አባቴ ተክሃይማኖት ሁነውኝ እስከ አሁን አለሁ።

ምንጭ :- ምክሖን ለደናግል Mkhon Ledenagil