ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን!🙏


#እንደምን ከረማችሁልን ውድ የዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ደህና #እግዚአብሔር ይመስገን እንዳላችሁ ተስፋ እናደርጋለን ....እሰከ እዚች ሰዓት በደንነት የጠበቀን አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን አትለይምና እመ አምላከሸ ድንግል ማርያምም ከልጆ ከወዳጇ ጋር የከበረች የተመሰገነች ትሁን ጻድቃን ሰማዕታትም እንደየ ክብራቸው የከበሩ የተመሰገኑ ይሁኑ ለዘለዓለሙ አሜን!!🙏

👉ነገረ ድኅነት
👉ነገረ ማርያም
👉ነገረ ቅዱሳን #መምህር አቤኔ ዘር ማሙሸት እና በዓውደ ምህረት አስተባባሪዎች

👉የመጻሕፍ ቅዱስ ጥናት #በመምህር መስፍን አዳነ

👉ሥነ ፍጥረት #በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው
👉ትምህርተ ሃይማኖት #በመምህር ኢዮብ ክንፈ
👉ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር #በመምህር አቤኔዘር ማሙሸት
👉ባሕረ ሀሳብ #በመምህር ማርቆስ ዓለማየሁ የተሰጡ ሲሆን

#ቅዳሜ ቅዳሜ በሚተላለፈው #ምን እንጠይቅልዎ??? በተሰኘው መርሃ ግብራችን ደግሞ #ኦርቶዶክሳዊ መልሶችን በመስጠት እያገለገሉን የሚገኙት

የተለመዱ ዓይነት ጥያቄዎች በተርቢኖስ(በኃ/ማርያም) እና በአቤኔዘር (በተክለ ማርቆስ)በኩል የሚመለሱ ሲሆን

#ጠንካራና ሕይወት ነክ የሆኑ ጥያቄዎችን ደግሞ

#በመምህር ቢትወደድ ወርቁ እና
#በዲ/ን ሃብታሙ ፍቃዱ በኩል
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ስናስመልስ ቆይተናል ::


ለመምራኖቻችን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን የነፍስ ዋጋ ያድርግልን አሰበ መምህራንን ይክፈልልን !!🙏

#በዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ስምም #ምስጋናችንን እናቀርባለን::

🍒በቀጣይ በምዕራፍ ሁለት ቆይታችንም የጀመሩትን ኮርሶች አጠናቀው #አዳዲስ_ኮርሶችንም እንደሚቀጥሉልንም ስለነገሩን ስለ በጎ ምግባራቸው #በእግዚአብሔር ስም ከልብ እና መሰግናቸዋለን

#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የምዕራፍ #አንድ #ልዮ_የጥያቄና_መልስ_ውድድር
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤


#ሰላም 🙏እንደምን ከረማችሁልን ውድ የዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን እያልን በጉጉት ስንጠብቀው ወደ ቆየነው ወደ አጓጓጊ የ #ጥያቄና መልስ ውድድራችን እናልፋለን ::እስከ ፍጻሜው አብራችሁን እንድትቆዮ ሁላችሁንም #በእግዚአብሔር ስም ጋብዘናችዋል ::🙏


📢#የውድድሩ ሕግና ደንብ🎤

👉 በዓውደ መምህረቱ ከተላለፉት ኮርሶች ውጪ ወይም ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ ውጪ ከማናቸውም ምንጭ የተገኘ ከጥያቄው ጋር የማይገናኝ ምላሽ መስጠት መላሹን ዋጋ ቢስ ያደርገዋል::

👉 #ለመልሶቻችሁ የአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን ከአንድ ሳምንት በኃላ የሚላኩ ማንኛውም መልሶች ዋጋ አይኖራቸውም::

👉 #ከደረቅ ጥያቄዎች ውጪ ላሉ ጥያቄዎች መልሱን የያዙትን ፊደላት #ብቻ መላክ በቂ ነው:

👉#የሚላኩት መልሶች የየትኛው ኮርስ መልስ እንደሆነ በቅድሚያ በርዕሱ ይገለጥ #ሥነ-ፍጥረት ከሆነ ሥነ ፍጥረ #ነገረ ማርያምም ከሆነ ነገረ ማርያም #ተብሎ ይገለጽ::

👉 #አንድ ሰው የመለሰውን መልስ ለሌላው ሰው በመላክ ያለ ምንም ለውጥ መልሶ መላክ ዋጋ እንደሚያሳጣ በትዕትና ለመግለጽ እንወዳለን ::

🍇#ለሁላችንም_መልካም_ዕድል እና መልካም የመማማሪያ መድረክ እንዲሆንልን አምላከ ቅዱሳን #ቅዱስ_እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን !አሜን🙏

ዓውደ ምህረት የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #_መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአንድ ጊዜ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

2 #_መዝሙረ ዳዊት በከተማ ስም ከተሰየሙ መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

3 #_የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ ትንቢተ ዳንኤል ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

4 #_መጽሐፈ አስቴርን የጻፈችው አስቴር ነች።

ሀ ) እውነት ለ) ሐሰት

5 #_የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ይዘት ምርጫ

6 #_ከሚከተሉት መካከል የታሪክ መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው

ሀ) ግብረ ሐዋርያት
ለ )የማቴዎስ ወንጌል
ሐ )ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች
መ) ሀ እና ለ

7) #ከተዘረዙት መጻሕፍት መካከል #_ሊቀ _ነቢያት ቅዱስ ሙሴ #ያልጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው

ሀ ) መጽሐፈ ኩፋሌ
ለ ) ኦሪት ዘፍጥረት
ሐ ) ኦሪት ዘዳግም
መ ) መጽሐፈ አክሲማሮስ

8) #_የኦ/ተ ቤተ ክርስቲያናችን ምትቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥራቸው ስንት ነው

ሀ ) 46
ለ ) 27
ሐ ) 35
መ ) 81

9 #_መጽሐፈ ምሥጢር ከየትኛው የአዋልድ መጽሐፍ ጋር ይመደባል
ሀ )ድርሳን
ለ )ነገረ ሃይማኖት
ሐ )የሥርዓት
መ )የታሪክ

10 #_"ገና እንደተወለዱ ልጆች የቃሉን ወተት ተመኙ።" 1ጴጥ 2:3 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል

ሀ )መጽሐፍ ቅዱስ ዳኛ መሆኑን
ለ ) መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጽድቅ የሚመራ መሆኑን
ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ ምግበ ነፍስ መሆኑን
መ)መጽሐፍ ቅዱስ የሕግ እና የአስተዳደር ምንጭ መሆኑን

#በአጭሩ መልስ ስጡ

11 #መጽሐፍ_ቅዱስን_ቅዱስ ካሰኙት ነገሮች መካከል ቢያንስ ሦስት ጥረሱ::
#በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሱ ቅዱሳን ሰዎች ስለጻፉት
#ወደ ቅድስና ስለሚመራ
#በቅዱሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለተጻፈ
#ዘመን የማይሽረው መሆኑ
#መጻኤዉንና አላፊውን በትክክልና በእርግጠኛነት የሚናገር ሰለሆነ
#የሌሉሎች መጻሕፍት ዋኘና ምንጭ በመሆኑ

12 #ከመጻሕፍ_ቅዱስ ባህል መካከል ቢያንስ 2ቱ ጠቅሰህ(ሺ)ከሀገራችን ተመሳሳይ ባህል ጋር አንድነቱንና ልዮነቱን አነጻጽር(ሪ)::

እረኝነት:-
ሰርግ:-
ጫማ ማውለቅ:-


13 #አዋልድ_መጻሕፍት ከሚባሉት መካከል 3ቱን ጥቀስና ጥቅማቸውን በአጭሩ አብራራ(ሪ)

#መልስ
#አዋልድ መጻሕፍ የሚባሉ
#ገድል :-
#ተአምር :-
#ድርሳን :-
#መልክዕ :-

#ጥቅማቸው
ከአባታቸው ከመጻሕፍ ቅዱስ ጠባይ ሳይወጡ የቅዱሳንን ተጋሎ ድንቅ ድንቅ ተአምራት እና ተራዳይነት እንዲሁም ክብርን የሚገልጡ በመሆን መጻሕፍ ቅዱስ በጥቂቱ እና በመጠኑ በፍንጭ መልክ የገለጠውን አነርሱ አምልተውና አስፍተው ይተነትኑታይ ማለት ነው::#በአጠቃላይ በደረቁ በንባብ የተጻፈውን ወንጌል በሕይወት ተተግብሮ እያሳዮ ሃይማኖት ያጸናሉ ምግባር ያቀናሉ ይሕወት ይሆናሉ::

14 #የመጻሕፍ_ቅዱስ ዕድሜ ሰንት ነው? መጀመሪያ የተጻፈውስ የመጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?በምንስ ቋንቋ ተጻፈ?

#መልስ

ዘመኑ በትክክል በውል አይታወቅም መጀመሪያ የተጻፈውም መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተጻፈበት ቋንቋም እንደ ኢትዮጲያዊያን ሊቃውንት ገለጻ #በግዕዝ_ቋንቋ ነው

15 #መጻሕፍ_ቅዱስን እንደ ምንኖርበት ሀገር ባህል ፣ እንደ ደረስንበት የዕውቀት ደረጃ ፣ በሥጋዊ ሀሳብና ፍልስፍ ማንበብእና መተርጎምና የሚያስከትለውን ጥፋት በራስህ(ሺ) አገላለጽ አስረዳ(አስረጂ)

#መልስ

*ወደ ክህደትና ምንፍቅና ይከታል #በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይለያል የሚል መሰል ምላሾችን የሰጣችሁ ሁሉ ትክክል ናችሁ!::

#ለበለጠ_መረጃ የተላለፉ ኮርሶችን ያድምጡ

#በመልሶቻችሁን ዙሪያ ላላችሁ ማንኛውም አሳብ ጥያቄና ጥቆማ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#ስለ ሆሳዕና ከተማ የሆነ ነገር በሉ እንጂ?


“ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?”
ሐዋ9፥4
ክርስቲያኖችን ማሳደድ ክርቶስን ማሳደድ ነው !። ይህ ደግሞ የመውጊያውን ብረት እንደመቃወም የሚብስ ነው።
# ክርቶሳዊያን በሆሳዕና ሲከለከሉ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም ያኜ በክርስቶስ ዘመን የተጀመረ ነው::
# ወደ_ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ # እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው ነበር። "በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር" አሉ ። ይህን ጊዜ ከሕዝብም መካከል #ከፈሪሳውያን_አንዳንዱ፦መምህር ሆይ፥ደቀመዛሙርትህን ዝም እንዲሉ ገሥጻቸው አሉት። # እርሱም መልሶ፦እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው። ሉቃ19÷37-40

#ገዢዎቻችን ባልሰማ ዝም ቢሉም እንኳ #በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው እያለች ሆሳዕና ዛሬም ትጮሃለች !
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ ሉቃ ፩÷፲፱

ቅዱስ ገብርኤል በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ዘንድ ከፍ ያለ መወደድ ያለው መልአክ ነው::ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን አብዝተን የምንወድበት ብዙ ምክንያቶች አሉን

፩. ቤተሰብኡን የሚጠላ ማን አለ ?

ክርስቲያኖች ከቅዱሳን መላእክት ጋር የአንድ ቤተሰብእ ሀገር አባላት አካላት ነን:: በሐዋ ፱÷፲፭ መምህረ አሕዛብ ብርሃነ ዓለም ተብሎ የተመሠከረለት ቅዱስ ጳውሎስ "እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና (ባለሀገሮችና) ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" እንዳለ ኤፌ ፪:፲፱:: ሐዋርያው በዚህ ክፍል ቅዱሳን ከተባሉ መላእክት ጋር ቤተሰብእ እንደሆንን ነገረን ሀገራችንም አንድ መሆኑን ሲመሠክር "ከእነርሱ ጋር ባለሀገሮች ናችሁ " አለን:: ሀገራችን የት ነው ? ብለን ብንጠይቅም ራሱ በፊልጵዩስ መልእክቱ "ሀገራችን በሰማይ ነው" ብሎናል ፊልጵ ፫፥፲፰-፲፱ ::የመላእክት ሀገር መንግሥተ ሰማይ እንደሆነ የእኛም ሀገር በሰማይ ነው::ሐዋርያው "እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" ያለው ቅዱስ ጴጥሮስ "እንግዶችና መጻተኞች ናችሁ" ፩ጴጥ ፪:፲፩ ብሎ በዚህ ኃላፊ ዓለም እንግዶች መሆናችንን የገለጠበትን የዚህ ዓለም እንግዳነታችንንና መጻተኛነታችንን ሳይሆን በሰማይ መንግሥት እንግዶች አለመሆናችንን ለመግለጥ ነው:: ይህ ዓለም ቢበዛ 70 ቢበረታም 80 ዘመን ብቻ የምንኖርበት ጊዜያዊ መኖሪያችን ነው መዝ 89÷10 ::ቅዱሳን መላእክት ቤተሰቦቻችን (እንደ ወንድም አባት እናት እህት) ስለሆኑ በአንዳችን የልብ ንስሐና መመለስ እንኳን ተደስተው በሰማይ ሀሴትን ያደርጋሉ ይዘምራሉ ያሸበሽባሉም :: ይህም የጌታችን በሥጋዌው ወራት ምሥክርነት ነበር ሉቃ ፲፭:፲::ቅዱሳን መላእክት ከምእመናን የማይለዩ እንደ እውነተኛ ወንድም አሳቢ እንደ አባት ጠባቂና ከክፉ የሚያድኑ አገልጋዮችም ናቸው:: መዝ 90÷11 ዳን 4÷12 የሐዋ 12÷5 የሐዋ 27÷23

2. ቅዱስ ገብርኤል መምህራችንም ነው

ቅዱስ ገብርኤል በቅዱሳት መጻሕፍት ከተገለጡልን ሥራዎቹ አንዱ የቅዱሳን ነቢያት እንዲሁም ምእመናን አስተማሪ መካሪ ጥበብ ገላጭ መሆኑ ነው :: እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን ያለውን ነገር በምልአት በስፋት የተናገረ ነቢዩ ዳንኤል "ገብርኤል ወደ እኔ እየበረረ መጣ በማታም በመሥዋእት ጊዜ ተናገረኝ አስተማረኝም እንዲህም አለኝ ዳንኤል ሆይ ጥበብና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ" ዳን 9:22 እንዳለ :: ቅዱስ ገብርኤል ምሥጢርን ጥበብን የመግለጥ ጸጋ ሀብት እንደተሰጠው ትመለከታላችሁን ? ዛሬ ላለን ምእመናን የክርስቶስ እናቱ እመቤታችንን "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ" እያልን እናመሰግናት ዘንድ ያስተማረን እርሱ አይደለምን ? ሉቃ 1:26-40 :: "በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን" ማለታችንም ለዚሁ ነው::

3 . አረጋጊ አጽናኝ ፍርሃትንም የሚያርቅ መልአክ ነው

አንዱ የቅዱስ ገብርኤል ሥራ ፍርሃትን ማራቅ የታወኩትንም ማረጋጋት ነው :: ስለሆነም ወደ ሰዎች በመጣ ጊዜ "አትፍሩ" እያለ ያረጋጋቸዋል :: እንኮዋ በዚህ ዓለም ሀሳብና የሥጋ ነገር የታወክነውን ቀርቶ መንፈሳዊውን ሰው ነቢዩ ዳንኤልን "አትፍራ" ብሎ ፍርሃትን አርቆለታል ዳን 8:15 ; 10:12 :: የአምላክ እናት ድንግል ማርያምንም ሲያበሥራት "ማርያም ሆይ አትፍሪ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና" ሉቃ 1:29-40 እያለ ነበር ::

4 . ስለ ምእመናን በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም (የሚለምን የሚማልድ) መልአክ ነው "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ" እንዳለ ሉቃ 1:19

5 . ደጋግ ሰዎችን ለንስሐ እንዲበቁ ከስህተታቸው እንዲታረሙ እንደ አባት የሚቀጣ መልአክ ነው :: ካህኑ ዘካርያስን ዲዳ እንዲሆን እንደቀጣውና ልጁ በተወለደ ጊዜም አንደበቱ እንደሚፈታለት እንደነገረው መጽሐፍ ይነግረናል ሉቃ 1:19-25 :: "ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት በፊቱም ተጠንቀቁ" ተብሎም ከኃጢአታቸው የማይመለሱትን እንደሚቀጣ ተነግሮናል ዘጸ 23:20

6 . በእባቦች ላይ በገነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው ተብሎም ተነግሮናል ሔኖክ 6:7-8 :: እንግዲህ ምን እንላለን ? የመላእክት አለቃ የአብሣሬ ትስብእት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃ አይለየን አሜን!!

#ቢትወደድ ወርቁ
የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ ም
ድጋሚ የተለጠፈ
"የእግዚአብሔር መልአክ"

#በስሙ ስመ እግዚአብሔርን የተሸከመ መልአክ ማለት ነው።ሚካኤል፣ገብርኤል፣ሩፋኤል ወ.ዘ.ተ የሚሉት ስሞች ውስጥ "ኤል" የሚለው ቃል አምላክ ማለት ነውና።“ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ።”ዘጸ 23፥21
እንዲል።

#በልቡ ስብሐተ እግዚአብሔርን የያዘ በአንደበቱም
እግዚአብሔርን የሚያመሰግን መልአክ ነው።“አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።”(ኢሳ 6፥3) እንዳለ ነቢዩ።

#ፈቃደ እግዚአብሔርን የሚፈጽም ማለት ነው።ማር ያለውን ይምራል ፤ ቅሰፍ ያለውን ይቀስፋልና።

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።”(መዝ33፥7)

“ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ።”ሐዋ12፥23
ተብሎ እንደተጻፈ።

#የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ መልአክ ነው።“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።” (መዝ 18፥1) በሚለው ኃይለ ቃል ውስጥ "ሰማያት" የሚለው ቃል በምሥጢር መላእክት ማለት ነው።ይኸውም “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።”
(ሉቃ2፥14) ባለው ኃይለ ቃል ውስጥ ካለው "አርያም" ከሚለው ቃል ጋር አንድ ነው።

#የእግዚአብሔርን ሕዝብ መርቶ ወደ ተዘጋጀላቸው ስፍራ የሚያገባ መልአክ ነው።“በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።”
( ዘጸ 23፥20) እንዲል።

#በእግዚአብሔር የሚታመነውን ሰው እግሩ በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቹ የሚያነሣ መልአክ ነው።"በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
(መዝ 90:11-12)

#ሰዎች ሁሉ መዳንን (መንግሥተ እግዚአብሔርን) እንዲወርሱ ለማገዝ የሚላክ፤የሚያገለግልም መልአክ ነው።“ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?”(ዕብ 1፥14) እንዳለ ሐዋርያው።

#በኃጢአተኞች መዳንም የሚደሰት መልአክ ማለት ነው።“ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”ሉቃ15፥10

ይኸውም ሰውን እጅግ እጅግ እጅግ የሚወድድ መልአከ ምሕረት፣መልአከ ፍስሐ፣መልአከ ሰላም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነው!!!በረከቱ ይደርብን!!!

#ኢዮብ ክንፈ
#ኅዳር ሚካኤል/2017 ዓ.ም
ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ (መዝ103፥27)

#ፍጥረት ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔርን ተስፋ ያደርጋል።ምርጫ አይደለም የህልውና ጉዳይ እንጂ።በደመነፍስ ሕያዋን ሆነው የሚኖሩት እንስሳት፣አራዊት፣አዋዕፍ፣ዓሦችና አንበሪዎች እርሱ እግዚአብሔር ባወቀ ተስፋ ያደርጉታል።እርሱም ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸዋል።ከቸር እጆቹ ጠግበው ያመሰግኑታል።

#ሰውም እንደ መላእክት ሁሉ "ተስፋ" የተሰጠው ታላቅ ፍጡር ነው።ተስፋውም በሕግ ቃልኪዳን ላይ የተመሠረተ ነው።“ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”(ዘፍ 2፥17) ሲል ጌታ ለሰው ማዘዙ የሰው የሕይወት ተስፋው ሕጉን በመጠበቅ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያስረዳል።

#ኋላም በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት የተሰጠው “ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ።” (ዘጸ 20፥6) የሚለው ቃል ከላይ ያነሣነውን ሐሳብ ያጠናክረዋል።

#በእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተወደደ ሰው የሚባል ፍጡር ለሕይወቱ የተሰጠውን ሕግ አፍርሶ ቢበድል እንኳን ይቅር የመባል ተስፋ አለው። ስለዚህ የሚተማመነው "በእግዚአብሔር ምሕረት" ላይ እንጂ በራሱ ሕግ የመጠበቅ ብቃት ላይ አይሆንም።

#ተስፋ ቆርጫለሁ

#የሚለው ድምፅ እዚህና እዚያ ይሰማል።ተስፋ ማለት እግዚአብሔር ከሆነ ተስፋ ቆርጫለሁ ማለት እግዚአብሔርን ትቼአለሁ ማለት ይሆናል።ተስፋ ለመቁረጥ ተስፋ ማድረግ ያስፈልጋል።ሰው ተስፋ የሚያደርጋቸው ጊዜአዊ ነገሮች ከእውነተኛ ተስፋው ከእግዚአብሔር ጋር ይምታቱበትና፤ያልተሳኩ እንደሆነ
ተስፋ ቆረጥሁ ይላል።መማርን፣አንድ ቦታ ተቀጥሮ መሥራትን፣እገሌን ወይ እገሊትን ማግባትን፣ልጆች መውለድን፣ባህር ማዶ ተሻግሮ መኖርን ወ.ዘ.ተ።

#አሁንስ ደከመኝ፣ታከትኩ፣ከዚህ በላይስ አልሄድም፣
በቃኝ ... የሚሉ ንግግሮች ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች አለመሳካት የሚነገሩ ናቸው።"እናንተ ስለፈለጋችሁ የሚሆን ነገር የለም፤ሆኑ አልሆኑ የእግረ መንገድ ጉዳዮች ናቸው።እነዚህ ጉዳዮች እንደ ሕፃናት ማቆያዎች (Day cares) ናቸው።የተፈጠራችሁላቸው ዓላማዎች አይደሉም።" እያለ ሕፃንነታችንን እየነገረን ከሆነስ!? "ፈቃድህ ይሁን" ብለን በፈቃዱ ሲከለክለን ማዘን አይገባም።

#ኑሮው!!! ኧረ ውድነቱ!!! "እግዚአብሔር ሆይ ወዴት ነህ???" "አንተን በማኖር ግብር ነኝ" ይልሃላ።ወይ ግሩም እስከዛሬ ታዲያ በኑሮ ርካሽነት ነበር እንዴ የኖርነው!?በእኔ ዕድሜ ሳውቅ በየጊዜው "ኑሮ ተወደደ" ነው የሚባለው።ሲወደድ እንጂ ሲረክስ ያየሁት ነገር የለም (ከሰው(ከእኔ) በቀር 😭)።ግን በቸርነቱ አለን!!!ግሩም ነው መቼስ!!!

#ለነፍሳችን ለማደር ከኃጢአት ጋር በምናደርገው ትግልም ተመሳሳዩ ነገር ይገጥመናል።"ከዚህ በኋላ ይህንን ያህል በድለህ እግዚአብሔር ይቅር የሚልህ መሰለህ" የሚል ሐሳብ በኅሊናህ ሲመጣ "አዎን ይቅር ይለኛል" በለው።ገድለህ "አዎን"፤አመንዝረህ "አዎን"፤ዘሙተህ "አዎን"፤ሰርቀህ "አዎን"፤"ዋሽተህ" አዎን!!!

#ታዲያ የእግዚአብሔር ፍርድ ወዴት አለ?

#ቅዱስ ዳዊት “መንገድህ በባህር ውስጥ ነው፥ ፍለጋህም በብዙ ውኆች ነው፥ አረማመድህም አልታወቀም።”(መዝ 76፥19) ሲል የእግዚአብሔር አሠረ ፍትሑ (የፍርዱ መንገድ) እንደማይታወቅ ተናግሯል።ቅዱስ ጳውሎስም “የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።”(ሮሜ 11 ፥ 33) በማለት የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመረመሬነት ገልጧል።ስለዚህ "የእግዚአብሔር ፍርድ ወዴት አለ?" ለሚለው ጥያቄ መልሱ "በራሱ ዘንድ ነው" የሚል ነው።

#ይህንን ሁሉ አጥፈተህማ እግዚአብሔር ሳይቀጣህ አይቀርም" የሚል ድምፅ ኅሊናህ ውስጥ ሲመላለስ፤"እግዚአብሔር ደግ አባቴ ነውና በደንብ ይቅጣኝ፤አንዴ አይደለም መቶ ጊዜ ይቅጣኝ።ብቻ ለአንተ ለከይሲው አሳልፎ አይሰጠኝ።እንኳን የእኔ የአንዱ በደል ከአዳም ጀምሮ እስከ ኅልፈተ ዓለም የሚሠራው ኃጢአት የደጉ አባቴን የእግዚአብሔርን አንዲቱን የምሕረት ጠብታ አያህልም!!!" በለው። እንዲህ ብለን በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ እግዚአብሔር ደስ ይለዋል።ቁጣውን ሁሉ ይተወዋል።ሰው ራሱ ላይ ከልቡ ሲፈርድ እግዚአብሔር ፍርዱን ይተውለታል!!!
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።”(መዝ 11፥7) እንዳለ መዝሙረኛው በጽድቅ ራሳችን ላይ ፈርደን፤በልብ ቅንነት ራሳችንን ጻድቅ ለሆነ እግዚአብሔር ስንሰጥ፤እግዚአብሔር ደግሞ የምሕረት ፊቱን ያሳየናል።ይህንንም በልባችን በሚመላብን ፍጹም ሰላምና ደስታ እናውቃለን!!!

"#ሳለ #መድኃኔዓለም" የምወዳት የእናቶቼ ብሂል ናት።እውነትም "#ሳለ #መድኃኔዓለም" #አምላከ #ተክለሃይማኖት!!!

#ኢዮብ ክንፈ
#ኅዳር 13/2017 ዓ.ም