"የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።"(1ኛ ዮሐ 3:9)
ቅድስት ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች ጉባኤ ናት።ይህቺ ጉባኤ ደግሞ ለጌታዋ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪት ናት።የሚስት ፈቃድ ወደ ባልዋ እንደሆነ ሁሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን ፈቃድም ሙሽራዋ ወደ ሆነው ወደ ጌታዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።የእርሱን ፍለጋ እየተከተለች ፤ የእርሱን ዱካ እየረገጠች ፤ እርሱ ከገባበት ትገባለች።ይህንን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንና የቅድስት ቤተክርስቲያንን ግንኙነት በራስና በአካል መግለጥም ይቻላል።ራስ(አእምሮ) አካልን እንደሚያዝዝ ፤ክርስቶስም ቅድስት ቤተክርስቲያንን ያዝዛታል።አካልም ለራስ (ለአእምሮ) እንደሚታዘዝ እንዲሁ ቅድስት ቤተክርስቲያንም ለራሷ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዛለች።እርሱ ካዘዛትና ፤ ሠርቶ ካሳያት ፤ ከእርሱ ፈቃድ ውጪም የምታደርገው አንዳች ነገር የለም።አምላካችን ፈጽሞ ካስተማራት ትምህርት ሌላ እንግዳ ትምህርት ፤ ሠርቶ ካሳያትም ትሩፋት ውጪ የምትሠራ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የለችም።
ጌታችን የፈጸማቸው ሥራዎች ሁሉ ዓላማቸው የዲያብሎስን ሥራ ማፍረስና እኛን ማዳን ነው።በሥጋ ማርያም ድንግል ተገልጦ ከፈጸማቸው ሥራዎች መካከል የሰውን መዳን የማይመለከት ምንም የለም።ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ ፤ እኛንም እንዲያድን ከፈጸማቸው ሥራዎች መካከል አንዱ ጾም ነው።
"ከዚያ ወዲያ ጌታችን ኢየሱስ ከዲያቢሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው" : ከጥምቀቱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በሚሆን ፈቃዱ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ ገብቷል።በገዛ ፈቃዱ ተመርቶ የጠፋ አዳምን ፍለጋ ያድነው ዘንድ በፈቃዱ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ ገባ።"ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ" ማለቱም ቀዳማዊ አዳም ከዲያብሎስ ተፈትኖ የወደቀባቸውን ፈተናዎች ድል ይነሣ ዘንድ ነው።እርሱ ከጥምቀቱ በኋላ በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ (የኃጢአት ራሶች)ተፈትኖና ድል ነሥቶ የጥምቀት ልጆች ሁላችን እነዚህ ፈተናዎች እንዳሉብንና ድል መንሣት እንደምንችል ነገረን ። "በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ።ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ" እንዳለው (ዮሐ 16:33)
"አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ" : ዘመን የማይቆጥርለት አምላክ እኛን ዘመን በማይቆጠርባት መንግሥተ ሰማያት ያኖረን ዘንድ አርባ ተብሎ ጊዜ ተቆጠረለት።በአርባ ቀን ያገኛትን ልጅነት አዳም አስወስዶ ነበርና ለሱ ለመካስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጦመ ።"ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው"(መዝ 135:8 ና 9) አምላክ ቀንና ሌሊት ጦመ።አዳም በመብል ቢወድቅ ጌታችን ግን በጾም አነሣው።በሥጋ የተራቡትን በተአምራት በነፍስ የተራቡትን በትምህርት የሚያጠግብ እርሱ በጽድቅ ያጠግበን ዘንድ ተራበ።
"ፈታኝም ቀርቦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው" : ፈቅዶለት ነው እንጂ ዲያቢሎስማ ይህንን ያህል ድፍረት አይደፍርም ነበር።የእግዚአብሔር ባሕርይ ልጅ በዚህ ስስት ከመፈተኑ በፊት የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆቹ አዳምና ሔዋን ተፈትነው ነበር።በዚህ የስስት ፈተና "ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።"(ዘፍ 3:6) ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ግን፦
"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።"
ጌታችን ይህንን የስስት ፈተና በትሕርምት ድል ነሥቶ የዲያቢሎስን ሐሳብና ሥራ አፈረሰ።የዲያቢሎስ ሐሳቡ የክርስቶስን "የእግዚአብሔር ልጅነቱን" ማረጋገጥና ዓለም እንዳይድን በአይሁድ እንዳይሰቀል ማከላከል ሲሆን ሥራው ደግሞ ስስት ነው።ጌታችን ድንጋዮቹን እንጀራ ቢያደርግለት ኖሮ፤የኋላ መናፍቃን ተነሥተው እንደ ጌታ የሰይጣንን ቃል መፈጸም ይገባል ባሉ ነበር ። አዳም የሚኖረው "ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል" ነበር ። ይህቺውም ትእዛዙ ናት።"መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና" (ዘፍ 2:17) ባለው ትእዛዝ ። አዳም ይህቺን ትእዛዝ ቢጠብቅ በሕይወት ይኖር ነበር።"ተብሎ ተጽፎአል"(ዘዳ 8:3) የሚለው አነጋገር ሰይጣን በቃለ መፃሕፍት እንደሚሸነፍ የሚያረጋግጥ ነው።
ስስት የሚበላውን፣የሚጠጣውን፣የሚለበሰውን እጅግ መውደድ (መሳሳት) ነው።ለሚያልፈው የዓለም ነገር ሁሉ መጎምጀት ስስት ነው።ይህንን ፈተና ልክ እንደ ጌታችን በትሕርምት ድል መንሣት ይጠበቅብናል።ሁልጊዜም ቢሆን ስስትን የምናሸንፈው "ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን ቃል ሁሉ" በማሰብ ነው።ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ቃልም፦
የመጀመሪያው በነፍስ የተራቡትን የሚያጠግብ የቅዱስ ወንጌል ትምህርት ነው።ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ "ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ነፍስ ከመብል ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?" በማለት አስተምሯል (ማቴ 6:25) እኔን የምትመስልን ነፍስ ካለመኖር ፈጥሬ ከሰጠኋችሁ ለጥቂት ጊዜ ነፍሳችሁ ከሥጋ ጋር ተዋሕዳ የምትቆይበትን መብል እንዴት እነሣችኋለሁ?፤ሥጋን ከአራቱ ባሕርያት ፈጥሬ ከሰጠኋችሁ ሥጋችሁ የሚለብሰውን አላቂ ልብስ እንዴት እነሣችኋለሁ? ማለቱ ነው።ይህም ብቻ አይደለም ለሰውነታችሁ ቤዛ የሚሆን ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን ከሰጣኋችሁ ፤ በመንግሥተ ሰማያትም የብርሃን ልብስን ካዘጋጀሁላችሁ ለሥጋችሁ የሚሆን መብልና ልብስን እንዴት እነሣችኋለሁ? ማለቱ ነው። እውነት ነው እጅግ ትልቁን የሰጠንን አምላክ በጥቂቱ የምንጠረጥረው ብዙዎች ነን።የጌታችን ተወዳጁ የሚሆን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም "ዓለምንና በዓለም ያለውን አትውደዱ፤ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት..." በማለት በስስት እንዳንሸነፍ መክሮናል።(1ኛ ዮሐ 2:15)
ስስትን "ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል" (ጌታችን ስለጾምና ምጽዋት ባስተማራት ትምህርት) ድል እናደርገዋለን ። " ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።"(ማቴ 6:16) እኛ ያልሳሳንለትን መብልንና ልብስንም ለሌላቸው መስጠት አለብን።በዚህም ጾም ከምጽዋት ጋር ትተባበራለች።
"ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ቃል" ተአምር ነው።ስለዚህ ሰው በእግዚአብሔር ተአምር ጭምር እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም።ጌታችን በዘመነ ኤልያስ በነቢዩ ኤልያስ አድሮ በሰራፕታ ለነበረችው ባልቴት ጥቂቱን ዘይትና እፍኙን ዱቄት እንዳበረከተ እንዲሁ በዘመነ ሐዲስም ሁለት ዓሦችንና አምስት እንጀራዎችን አበርክቶ በተአምር አምስት ሺ ገበያ ሕዝብ አጥግቧል(1ኛ ነገ 17:7-17)።ራሱ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስም የኖረው በእግዚአብሔር ተአምር ነው።"የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ለእርሱ መጣለት።ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፥ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ።ከወንዙም ትጠጣለህ፥ ቍራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ። ሄደም እንደ እግዚአብሔር ቃልም አደረገ። ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተቀመጠ። ቍራዎቹ በየጥዋትና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከወንዙም

"ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፤መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፤ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።"(ማቴ 4:5-6)
በፈቃዱ ሄደለት ለማለት ነው እንጂ ዲያቢሎስስ ጌታን መውሰድ አይቻለውም።ዲያቢሎስ ካህናትን ድል በምነሣበት መቅደስ ቢሆን እኔ ነበርኩ የማሸንፈው ብሎ ቢያሰብ ጌታችን ፈቃዱን ዐውቆ ሄደለት።መዝ 90:11-12 ላይ የተጻፈውን ቃል ጠቅሶ ፈተነው፤ዳዊት ደጋሚ አይመስልም!?ዳዊት ሲደገም ብን ብሎ የሚጠፋ ጠላት ለፈተና ግን ከዳዊት ጠቀሰ።
አስቀድሞ በማኅበረ መላእክት ውስጥ ትዕቢትን ከልቡናው አመንጭቶ ሐሰትን በአንደበቱ የተናገረ "የሐሰት አባቷ" ዲያቢሎስ ነው።የሌለውን የባሕርይ አምላክነት ፈልጎ በትዕቢት ወድቋል።ትዕቢት ማለትም ራስን ብቅ (ከፍ) ሌላውን ዝቅ ማድረግ ነው።ሳጥናኤል በልቡ ራሱን ከፍ አድርጎ ከሥላሴ እንደ አንዱ ለመሆን ከጅሏል።ለዚህ ነው ያልፈጠራቸውን መላእክት ፈጠርኳችሁ ብሎ "ሐሰትን" የተናገረው።ትዕቢትና ሐሰት ጓደኛሞች ናቸው፤ተለያይተውም አያውቁም።
እሱ በወደቀበት ትዕቢት እናታችን ሔዋንን ፈትኗታል።ከትዕቢት የማትለይ ሐሰትንም ነግሯታል።"እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።" (ዘፍ 3:4-5) ዲያቢሎስ ቀድሞም ለሔዋን ኋላም ለጌታችን ያቀረበው ፈተና ያልኳችሁን ብታደርጉ ምንም አትሆኑም የሚል ነው።ዛሬም ይህ ፈተና አይቀርልንም። "ይህን ኃጢአት ብታደርግ ምን ትሆናለህ?የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ ፈተና ወርውር እግርህ በኃጢአት እንዳትሰነካከል መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።" በማለት በትዕቢት ይፈትነናል።
ከሌሎች የተሻለ ጥበቃና ከለላ እንደሚደረግልን ማሰብ፤ወይም በአንዳች ነገር ከሌሎች እንደምንሻል መገመት፤ይህን ኃጢአት ብሠራ ማን ያየኛል?ማንስ ከልካይ አለብኝ? ማለት ትዕቢት ነው።ትዕቢት ከእግዚአብሔር ለይቶ ከሰይጣን ያወዳጃል።"በዓይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና በልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም"(መዝ 100:5) ተብሎ የተጻፈውም ለዚህ ነው።ይህ ማለት በትዕቢትና በስስት የተሸነፈ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አይሆንም ማለት ነው።በዘመነ ፍዳ "የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ንቀት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች" ተብሎ እስኪጻፍ ድረስ ባለጠጎችና ትዕቢተኞች የተባሉ አጋንንት እጅጉን በርትተውብን ነበር።(መዝ 122:4)
"ጌታችን ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።" (ማቴ 4:7)መምህረ ትሕትና ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕቢተኛውን በትሕትና አዋረደው።"ምንም አይሳነኝም" ብሎ ራሱን ከመቅደሱ ጫፍ ላይ አልወረወረም።በተአምር ሳይሆን በመጽሐፍ ቃል ድል ነሣው።ልበ አምላክ ክቡር ዳዊትም "አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ" (መዝ 17:27) በማለት እንደዘመረው 5500 ዘመን ሙሉ በአጋንንት የተጠቃውን ሕዝብ ለማዳን የትዕቢተኞቹን (የአጋንንትን) ዓይን በትሕትና አዋርዷል።
እመ ትሕትና ድንግል ማርያም"ትዕቢተኞችን በልባቸው ሐሳብ በትኖአል ...ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል"(ሉቃ 1:51-52) ስትል ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ያዕቆብ በአንድ ቃል "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል"(1ኛ ጴጥ 5:5፤ያዕ 4:6) በማለት ከአምላካቸው እናት ጋር አንድ ዓይነት ሐሳብን ገልጠዋል።ቅዱስ ጳውሎስ "አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል?ያልተቀበልኸውስ ምን አለ?የተቀበልኽ ከሆንክስ እንዳልተቀበለ የምትመካ ስለ ምንድነው?"(1ኛ ቆሮ 4:7) በማለት ከሌላው እንደማንበልጥ፤ያለን ነገር ሁሉ ተሰጥቶን እንጂ ከራሳችን የሆነ እንዳልሆነ፤ባለን ነገርም መመካት እንደማይገባ የትሕትናን ነገር አስተምሮናል።
በትዕቢት (ሌሎችን በመናቅ) የምናገለግለውን አገልግሎት እግዚአብሔር ስለማይቀበለው እጅግ ጠንቃቆች ልንሆን ያስፈልገናል።"ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።"(ማቴ 18:10)ጌታችን እኛ ታናሽ ናቸው ብለን ልንንቃቸው የምንፈልጋቸውን ሰዎች ክብራቸውን በማሳየት "ከመናቅ" እንድንጠነቀቅ አሳስቦናል።ትዕቢት የተሸነፈበትን የጌታችንን ጾም እየጾምን እንኳን የምንታበይ ብዙዎች ነን።ከሌሎች በተሻለ ረዘም ላለ ሰዓት ከእህል ከውኃ ስለተከለከልን የተሻልን ጿሚዎች አይደለንም።ብዙ ገንዘብ ስለመጸወትንም የተለየን መጽዋቾች አይደለንም።በየዕለቱ ለረጅም ሰዓት የተለያዩ ጸሎቶችን ስለጸለይንም ልዩ ክርስቲያኖች አይደለንም።ይህንን ከልብ ማመን ያስፈልጋል።እግዚአብሔር የሚያውቃቸው እኛ የማናውቃቸው በዙሪያችን ያሉ (ከምንም የማንቆጥራቸውን) ወዳጆቹን ትሩፋት ቢገልጽልን፤ገና የጽድቅን "ሀ ፡ ሁ" እንደማናውቅ ይገባን ነበር።ለዚህ ነው "እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር" (ፊል 2:3) በማለት ሐዋርያው ያስጠነቀቀን!!!ጾሙን የትሕትና ያድርግልን አሜን!!!
ኢዮብ ክንፈ
መጋቢት 17/2016 ዓ.ም

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
🛑አዲስ ዝማሬ "አንቺ ነሽ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ ◈New Mezmur "Anchi Nesh" Z Dawit Kibru (Lyrics)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያመሰገነሽ፤
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም
ዛሬ ....
#ለክርስቶስ ጸሀይ ምስራቅ ድንግል #ማርያም የተወለደችበት ቀን ነው ።
(አንቲ ምስራቁ ለክርቶስ እንዲል ቅዱስ ህርያቆስ)
#ለክርስቶስ ዝናብ ደመና ድንግል #ማርያም የተዘረጋችበት ነው ።
(አንቲ በአማን ደመና እንተ አስተርያ ለነ ማየ ዝናም እንዲል ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው)
#ለክርስቶስ መብል ፍሬ ድንግል #ማርያም የተተከለችበት ነው ።
(እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን እንዲል ቅዳሴ ማርያም )
#መልካም_በዓል
#የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው
#ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ
©️ ከመምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ

ለክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት:- ልደታ ለማርያም
እንኳን አደረሳችሁ!!
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ጥንተ አብሶ ካመጣው ፍዳና መርገም ጠብቋታል:: የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ዓለም በጥንተ አብሶ በነበረበት ዘመን በክርስቶስ ማዳን ዋዜማ ሲያበሥራት ቅድስት ኤልሳቤትም በፅንሰቷ ጊዜ ስታመሰግናት ደጋግመው "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ" "አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ።" እያሉ ይህን እውነት መስክረዋል። (ሉቃ፩:፳፮-፵ በጥንተ አብሶና ውጤቱ (origional sin and its effects) ምክንያት ሰዎች "የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል በተባሉበት ዘመን ጸጋን የተመላች ብቸኛ ልዩ እርሷ ነበረች:: ።" (ሮሜ ፫:፳፫) እግዚአብሔር እርሷ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ለመውለድ ፈቃደኛ እንደምትሆን ስለሚያውቅ አስቀድሞ በአካል የሚመስለው በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ አንድያ ልጁን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንድትወልድ ቅድመ ዓለም መርጧታልና የእመቤታችን ልደት (ልደታ ለማርያም) የዓለም መዳን የማይቀር መሆኑ ለታወቀበት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ነው እንላለን። (The nativity of the blessed virgin Mary prepares the way for the birth of Jesus Christ) እንዳለ ሊቁ። (The book of the nativity of Virgin Mary ,) የጌታችን ሰው መሆን "ከዘላለምና (ቅድመ ዓለም) ከትውልዶች ጀምሮ (ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ) ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው።" (ቆላ፩:፳፮) መባሉም የአምላክ ሰው መሆን እንዲሁም የእርሷ እርሱን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ሕሊና የሚታወቅ መሆኑን ያስረዳናል። (ኢሳ ፯:፲፬ ፱:፮) እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ ነው። (መዝ ፻፴፭:፩ ራእ፲፱:፲፮) እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ፈጣሪ ነው:: "ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ያለ እርሱ አልሆነም።" (ዮሐ ፩:፫) "መልካሙን ነገር ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን።" "የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሁኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና።" እንደተባለ:: (ቆላ ፩:፲፭-፲፮፣ ኤፌ ፪:፲) እርሱ ለቅዱሳን የጸጋ አምላክነትን ክብር የሰጠ ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ ነው:: (ዘጸ ፯:፩፣ መዝ ፹፩:፩፣ ዮሐ፲÷፴፬፣ ሮሜ ፱:፭፣ ፩ተሰ ፫:፲፩፣ ቲቶ ፪:፲፩፣ ፩ዮሐ ፭:፳) እርሱ ቸር ከሆነ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአገዛዝ በሥልጣን በሕልውና በመለኮት አንድ ነው:: (ዮሐ ፲:፴፣ ፲፯:፲፣ ማቴ ፲፩:፳፯-፳፱፣ ዮሐ ፲፬:፮-፰) እርሱ ፀሐይ እናቱ ምሥራቅ ናት:: (ሕዝ ፵፬:፩፣ ዮሐ ፰:፲፪፣ ሚል ፬:፪) ምሥራቅ እናቱን ዘወትር መሻታችን የፀሐይ ክርስቶስን በረከት ፍቅርና ቸርነት ለማግኘት ነው:: እንኳንስ እናቱን ነቢዩ ዳዊት ስለ ወዳጆቹ "ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው ስለዚህም ነፍሴ ፈለገቻቸው።" ብሎ ዘምሯል:: (መዝ ፻፲፰:፻፳፭) እርሱ የባሕርይ አምላክ እርሷ ደግሞ ወላዲተ አምላክ ( Theotokos) ናት:: ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም በኋላ መቸም መች አምላክን "ልጄ ወዳጄ" ማለት ከቶ ለማን ተችሏል? እርሱ ፈጣሪ እርሷ ደግሞ ወላዲተ ፈጣሪ ኩሉ ዓለም ናት:: እርሱ እውነተኛ ደስታ እርሷ የደስታ መፍሰሻ ናት። (መዝ ፵፭:፭) እርሱ ሕይወት እርሷ ነቅዐ ሕይወት (የሕይወት ምንጭ) ናት። ይህች ብርሃን ሙዳየ መድኃኒት ቤዛዊተ ኩሉ ብርሃንን ትሰጠን ሕይወት ክርስቶስን ትወልድልን ዘንድ ከተቀደሱ ተራሮች ከአብርሃም ከዳዊት ቤት ተወለደች። (መዝ ፹፰(፹፱):፩)
+++ የልደቷ ቀን +++
አንተ የራስህን እንዲሁም የምትወዳቸውን ሰዎች ልደት ሻማ አብርተህ ኬክ አስጋግረህ ወዳጅ ዘመዶችህን ጠርተህ በዳንስ በጭፈራና እስክስታ በመውረግረግ ታከብራለህ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ቀን በማሰብ በዓለ ልደቷን የሚያከብሩ ሰዎችን ግን ለምን ያከብራሉ ብለህ ትተቻለህ:: ለመሆኑ አንተ ያንተ የሆኑትን ሰዎች ልደት ተገቢ በሆነ መንገድ ብታከብር አምላክ እንደማያዝንብህ ካወቅህ የእናቱን ልደት እርሱን እያመሰገንን እያወደስን እናቱ "ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል።" (ሉቃ ፩:፵፱) እንዳለችም እርሷንም እያመሰገንን "ብርቱ የሆን እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና።" ብላ እንደመሠከረችም በእርሷ ለሰው ዘር የተደረገውን ታላቅ ሥራ እያሰብን ብናከብር የሚያዝንብን ይመስላሃልን? ከማዳኑስ በላይ ምን ታላቅ ሥራ አለ? ዓለም:- የኤድስ ቀን፣ የጉበት ቀን፣ የኩላሊት ቀን፣ የላብ አደር ቀን፣ የውሃ ቀን፣ የአፈር ቀን፣ የእናቶች ቀን፣ የአባቶች ቀን እያለ በልዩ ልዩ መንገድ ሲያከብር ቅር አይለውም የእናቱ የእመቤታችንን ልደት ለማክበር ግን ያመዋል::
ልደታ ለማርያምን ስናከብር
☞ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት በዳንኪራና በአስረሽ ምስናከብር
ሆን በመንፈሳዊ ሥርዓት እናክብረው ያኔ የልጇ በረከት እጥፍ ድርብ ይሆንልናል። (ምሳ ፲:፯፣ ፩ጴጥ ፪:፲፪)
☞ የቤተክርስቲያን ባልሆነ የልደቷን ነገር በማይገልጥ በማይወክል መንገድ በአምልኮ ባዕድ ጨሌን በየዛፉ ዙርያ አረቄና ቡና በማፍሰስ የሚያከብሩትን ሰዎች በማስተማርና ትክክለኛውንና የክርስትናውን መንገድ በተከተለ መንገድ እንዲያከብሩት በማድረግ ድርሻችንን በመወጣት እናክብር ::
☞ ልደቷ "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ከተባለለት ከዮሐንስ ልደት የሚልቅ መሆኑን እንወቅ። እርሷ የዮሐንስ ፈጣሪ የክርስቶስ እናቱ ናትና። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም " ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ።" እንዳለ:: እርሱ ክርስቶስ "ሁሉን በስሜ አድርጉት" እንዳለን እርሷን በእርሱ ስም ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን ብለን ተቀብለን ልደቷን እንደምናከብር እንረዳ:: (ሉቃ ፩:፲፬)
+++ አድባር +++
አድባር የሚለው ቃል የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም ተራሮች ማለት ነው:: እመቤታችን በሊባኖስ ተራሮች መሐል ተወልዳለችና የልደቷን ወቅት አድባር እንላለን። (መኃ ፬:፰)
🚹የእናቱን በዓለ ልደት ማክበር ማኅበራዊ ፋይዳ 🚹
በዚህ ቀን የአንድ ቀዬ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ጸሎት በማድረግ እግዚአብሔርን በማመስገን እናቱንም በማወደስ ማክበራቸው ከሃይማኖታዊው ፋይዳ ባለፈ በልዩ ልዩ ምክንያት እየደበዘዘና እንደ ዳይኖሰርና ዶዶ ድራሹ እየጠፋ የመጣውን አብሮነት ማኅበራዊ ትስስር የሚያጠነክር መልካም ባሕላችንም ጭምር ነውና አጥብቀን ልንይዘው ይገባናል:: የድንግል ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ የልደት ቀን በረከት ያሳትፈን!!!
©️ መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፲፮ ዓ ም

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Eyob kinfe)
"ዕርገተ ክርስቶስ እንደ ሃይማኖት"
#በጸሎተ ሃይማኖታችን ከምንመሰክራቸው ምስክርነቶች አንዱ "በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ" የሚል ነው።በዚህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ እንዳረገ ማመናችንን እንገልጣለን።ይህንን ሃይማኖታችንን ያገኘነውም "የእግዚአብሔር መንፈስ ካለባቸው" ቅዱሳት መጻሕፍት ነው።(2ኛ ጢሞ 3:16)
ቅዱስ ዳዊት "በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" (መዝ 67:33) ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ "ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ" (ሉቃ 24:51) ብለውናል።እነዚህም የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነቶች ናቸው።
"ዕርገተ ክርስቶስ በነገረ ማርያም"
#የእመቤታችን ወዳጅ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ" ሲል ያመሰግናታል።ይኸውም ለቃል ርደት(መውረድ (ሰው መሆን) ) ለሥጋ ዕርገት ( ከፍ ማለት (አምላክ መሆን) )ምክንያት ድንግል ማርያም ናት ማለት ነው።ቃል ሥጋ ሲሆን ሥጋም ቃልን በመሆን ከፍ ያለው (ያረገው) በማኅፀነ ድንግል ማርያም ነው።ኋላም ከተነሣ በዐርባኛው ቀን ያረገው ከእመቤታችን ሰው በሆነበት ሥጋ ነው።በዕርገቱ ጊዜ ከእናቱ የነሣው (የተዋሐደው) ሥጋ አልተለየውም።"በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ..." በሚለው ኃይለቃል ውስጥ ያለው "ምሥራቅ" የሚለው ቃልም "ሥጋ ማርያም"ን ያሳያል።ጌታ ፀሐየ ጽድቅ ሆኖ ከእርሷ የወጣባት ምሥራቅ ድንግል ማርያም ናትና።ስለዚህ ኃይለ ቃሉ "በድንግል ማርያም ሥጋ ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" ተብሎ ይተረጎማል።
"ዕርገተ ክርስቶስ በአምልኮአችን"
#ቅድስት ቤተክርስቲያን የምትገለጥበት ትልቁ አምልኮዋ ቅዳሴ ነው።የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ "አሜን" ( አሜን ለሃይማኖት ሲሆን ትክክል/እውነት ማለት ነው) እያለች ከምትናገራቸው ምስክርነቶቿ አንዱ "ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ" (ዕርገትህን እናምናለን ሁለተኛ መምጣትህንም) የሚል ነው።እንዲሁም ካህኑ "አልዕሉ አልባቢክሙ" (ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ) በማለት ከፍ ከፍ ያለውን አምላካችንን ሲያሳስበን ዲያቆኑ ደግሞ "ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ" ብሎ የጌታን በምሥራቅ ማረግ ያስታውሰናል።ልቡናን ከፍ ከፍ ማድረግም በዓይነ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር ጌታን ሲያርግ መመልከት ፤ በዕዝነ ልቡና የቅዱሳን መላእክቱን ዝማሬ ማድመጥ፤ በአንፈ ልቡና መዓዛ ዕርገቱን ማሽተት ፤ በእግረ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር በደብረ ዘይት መቆም፤በአብራከ ልቡና ለጌታችን መስገድና በዚህ ሁሉ መደሰት ነው።"እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ" እንዲል (ሉቃ 24:52)
"ዕርገተ ክርስቶስ በክርስቲያናዊ ሕይወት"
#ጌታችን ወደ ላይ ከፍ ከፍ እንዳለ ክርስትናም ከፍ ከፍ የማለት ሕይወት ነው።ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ "በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል" (1ኛ ዮሐ 2:6) እንዳለ ጌታችን ከፍ ከፍ እንዳለ እኛም በቅድስና ከፍ ከፍ ልንል ይገባናል።ይህ የቅድስና ሕይወትም ከሥጋ ንጽሕና ወደ ነፍስ ንጽሕና ከነፍስ ንጽሕና ወደ ልቡና ንጽሕና የሚደረግ ጉዞ ነው።ከሁሉ አስቀድመን ግን ከስድብ ወደ ምስጋና፣ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ከቂም ወደ ይቅርታ፣ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን፣ከፍልስፍና ወደ ሃይማኖት፣ከገዛ አጉል እሳቤአችን ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ ከፍ ከፍ ልንል ያስፈልገናል!!!
"ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ፤ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን።" (2ኛ ተሰ 4:17)
መድኃኔዓለም እንዲህ ያለውን የክብር መነጠቅ በቸርነቱ ያድለን !!!
ሰኔ 07/2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ

Forwarded from Eyob kinfe
❤ "ሕይወትን በሚሰጥ አዳኝ በሆነ ከአብ በሠረጸ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን" (ጸሎተ ሃይማኖት)❤
#እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዛሬው ዕለት በእሳትና በነፋስ ተመስሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት ወረደ።ይኸውም በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት የደስታ መፍሰሻ ወላዲተ አምላክን ከብበው በአንድ ልብ ሲጸልዩ ነው።
#ፍስሕት (ደስተኛዪቱን) ይዘው ቢጸልዩ የደስታ መንፈስ የሆነ መንፈስቅዱስ ወረደላቸው።
#መዝገበ ምሥጢር ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ከሣቴ ምሥጢር (ምሥጢርን የሚገልጥ) መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው።በዚህም በሚያውቁት አንድ ቋንቋ ላይ ሰባ አንድ ቋንቋ ተገልጦላቸው ቅዱስ ወንጌልን ሰብከዋል።
#ናዛዚት (የምታረጋጋ) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ናዛዚ (የሚያረጋጋ) መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቷቸዋል።
#ንጽሕት ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ) መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።
#ጽንዕት (የጸናች) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መጽንሒ (የሚያጸና) መንፈስቅዱስን ተቀበሉ።
#መስተሥርዪ ኃጢአት (ኃጢአትን ይቅር የምታስብል) ርኅርኂተ ኅሊና ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ኃጢአትን ይቅር የሚል መንፈስ ቅዱስ በእሳት ተመስሎ ወደ እነርሱ መጣ።
#እናታቸውን ይዘው ምን ሊያጡ ኖሯል?ጽዮንን (እመቤታችንን) ከብበው ቢጸልዩ በደብረ ጽዮን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው።
#ይህቺ ቀን የቅድስት ቤተክርስቲያን የልደት ቀን ናት።ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው እንደ ጌታቸው ሁሉ ጾሙ ጸለዩ።መንፈስ ቅዱስ ያደረበት እንደሚጾም እንደሚጸልይ ያጠይቃል።በዓለም ሁሉ ዞረው ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበኩ።
#አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቸርነቱ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነት ከመፍገምገም ወደ ጽናት ፣ ከኃዘን ወደ ደስታ ፣ ከኃጢአት ወደ ንጽሕና ፣ ከመቅበዝበዝ ወደ መረጋጋት ፣ ከድንቁርና ወደ ዕውቀት ይመልሰን!!! አሜን !!!
#በዓለ ጰራቅሊጦስ
ወርኃ ሰኔ 16 / 2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ
#እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዛሬው ዕለት በእሳትና በነፋስ ተመስሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት ወረደ።ይኸውም በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት የደስታ መፍሰሻ ወላዲተ አምላክን ከብበው በአንድ ልብ ሲጸልዩ ነው።
#ፍስሕት (ደስተኛዪቱን) ይዘው ቢጸልዩ የደስታ መንፈስ የሆነ መንፈስቅዱስ ወረደላቸው።
#መዝገበ ምሥጢር ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ከሣቴ ምሥጢር (ምሥጢርን የሚገልጥ) መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው።በዚህም በሚያውቁት አንድ ቋንቋ ላይ ሰባ አንድ ቋንቋ ተገልጦላቸው ቅዱስ ወንጌልን ሰብከዋል።
#ናዛዚት (የምታረጋጋ) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ናዛዚ (የሚያረጋጋ) መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቷቸዋል።
#ንጽሕት ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ) መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።
#ጽንዕት (የጸናች) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መጽንሒ (የሚያጸና) መንፈስቅዱስን ተቀበሉ።
#መስተሥርዪ ኃጢአት (ኃጢአትን ይቅር የምታስብል) ርኅርኂተ ኅሊና ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ኃጢአትን ይቅር የሚል መንፈስ ቅዱስ በእሳት ተመስሎ ወደ እነርሱ መጣ።
#እናታቸውን ይዘው ምን ሊያጡ ኖሯል?ጽዮንን (እመቤታችንን) ከብበው ቢጸልዩ በደብረ ጽዮን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው።
#ይህቺ ቀን የቅድስት ቤተክርስቲያን የልደት ቀን ናት።ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው እንደ ጌታቸው ሁሉ ጾሙ ጸለዩ።መንፈስ ቅዱስ ያደረበት እንደሚጾም እንደሚጸልይ ያጠይቃል።በዓለም ሁሉ ዞረው ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበኩ።
#አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቸርነቱ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነት ከመፍገምገም ወደ ጽናት ፣ ከኃዘን ወደ ደስታ ፣ ከኃጢአት ወደ ንጽሕና ፣ ከመቅበዝበዝ ወደ መረጋጋት ፣ ከድንቁርና ወደ ዕውቀት ይመልሰን!!! አሜን !!!
#በዓለ ጰራቅሊጦስ
ወርኃ ሰኔ 16 / 2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
YouTube
🛑አዲስ ዝማሬ "አንቺ ነሽ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ ◈New Mezmur "Anchi Nesh" Z Dawit Kibru (Lyrics)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያመሰገነሽ፤
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
YouTube
🔴"በኢዮር በራማ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ | Zemari Dawit Kibru New 'Be Eyor Berama' Orthodox Tewahdo Mezmur
በኢዮር በራማ
በኢዮር በራማ በኤረር ላይ ያለች
የምትመሰገን በክብር የገነነች
የመላእክት ግርማ የክብር አክሊላቸው
የሥላሴ ዙፋን አንቺ ነሽ ጌጣቸው
አዝ.............
በምድረ ሎዛ ያዕቆብ ያየሽ
የወርቅ መሰላል ድንግል አንቺ ነሽ
የአምላክ ማደሪያ እናቱ የሆንሽ
ምዕራገ ጸሎት ንጽሕትም ነሽ
የአሕዛብ በረከት የአብርሃም ዘር
መርገም ተሻረልን /3/ አገኘን በአንቺ ክብር
የተነገረልሽ ትንቢቱ በምድር…
በኢዮር በራማ በኤረር ላይ ያለች
የምትመሰገን በክብር የገነነች
የመላእክት ግርማ የክብር አክሊላቸው
የሥላሴ ዙፋን አንቺ ነሽ ጌጣቸው
አዝ.............
በምድረ ሎዛ ያዕቆብ ያየሽ
የወርቅ መሰላል ድንግል አንቺ ነሽ
የአምላክ ማደሪያ እናቱ የሆንሽ
ምዕራገ ጸሎት ንጽሕትም ነሽ
የአሕዛብ በረከት የአብርሃም ዘር
መርገም ተሻረልን /3/ አገኘን በአንቺ ክብር
የተነገረልሽ ትንቢቱ በምድር…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እንደ ልጇ ተነሥታ ዐርጋለች።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት"(መዝ 131:8) በማለት ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት የጌታችንና የእናቱን የእመቤታችንን ትንሣኤ አስተባብሮ ተናግሯል።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ" ብሎ የጌታን "አንተና የመቅደስህ ታቦት" በማለት ጌታችን ብቻ ሳይሆን እናቱም እንደምትነሣ በእውነት ተነበየ።
#ኋላ ጻድቃን የሚቆሙትን የቀኝ ቁመት እመቤታችን ዛሬ ቆማዋለች።"በወርቅ ልብስ ተሸፋፍና ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" እንዳለ አባቷ ቅዱስ ዳዊት።
#ልጇ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ኋላ ለጻድቃን የሚያወርሳቸውን "ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን" (1ኛ ቆሮ 2:9) ዛሬ ለእናቱ አውርሷታል።
ለነገሩ ራሷ መንግሥተ ሰማያት ናት።ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ንጉሠ ሰማያት ወምድር ማኅፀኗን መናገሻ አድርጎ ነግሦባታልና።
#ልጇ "ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።"(ዮሐ14:3) እንዳለ እርሷም እርሷ ባለችበት እንሆን ዘንድ ከልጇ ታማልደናለች።ማርያም ማለት መርኅ ለመንግሥተ ሰማያት (በቃልኪዳኗ በአማላጅነቷ ረድታ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ) ማለት ነውና።
#ጌታ መጋቢት 27 በመስቀል ላይ ሞቶ መጋቢት 29 በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ እመቤታችንም በጥር 21 ዐርፋ ገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ቆይታ በነሐሴ 14 ቀን በጌቴሴማኒ ተቀብራ በነሐሴ 16 ቀን በክብር፣በይባቤ መላእክት ተነሥታ ዐርጋለች።
#አይ የሞተ አይነሣም ለምትሉ አባታችን ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን በመንፈስ እንጠራዋለን "ነገር ግን ሰው፤ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም።"(1ኛ ቆሮ 15:35) ብሎ ይዘልፍናል።
#ተነሥቶ ወደ ሰማይ አይወጣም የሚል ቢኖር ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን በሃይማኖት እንጠራዋለን፤እንዴትም ወደ ሰማይ እንደወጣ እንጠይቀዋለን።"ሲሄዱም እያዘገሙም ሲጫወቱ፤ እነሆ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።”(2ኛ ነገ 2:11)
ሞቶ ተነሥቶ ያረገ የለም የሚል ማንም ቢኖር ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ
"ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፤ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።"(1ኛ ተሰ 4:16-17) ሲል ይነግርልናል።
#አስተውሉ ያቀረብነው ማስረጃ ጻድቃንን የሚመለከት ነው።ጻድቃን እንዲህ ከከበሩ የጻድቃን እናታቸው የአምላክ እናት ቅደስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምማ ክብሯ ምን ያህል ይሆን !!!!!!!!???
እኛስ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም "አሕዛብ ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናመስግናት" እንላለን!!!
ነሐሴ ኪዳነምሕረት 2016 ዓ.ም

"ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር"
"የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።"
መዝ 115:6
- የዛሬው በዓል ደግሞ ልዩ ነው።የጻድቁ አባት የዓለም ብርሃን የኢትዮጵያ ፀሐይ የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ነውና!!!
- ለጻድቁ ክብርም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ክብርት ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን፣15ቱ ነቢያትን፣12ቱ ሐዋርያትን ብዙዎች የሰማይ ሠራዊትን ይዞ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደሚገኙበት የደብረ አስቦ ዋሻ ወርዶ ብዙ ቃልኪዳንን ሰጥቷቸዋል።
- የጻድቁስ ሐሳብ በሰማዕትነት አደባባይ ለክርስቶስ ፍቅር ደማቸውን አፍስሰው፣ሥጋቸው ተቆራርጦ፣አጥንታቸው ተከስክሶ ለማረፍ ነበር።በጣም የሚገርመው ይህንን ሐሳባቸውን ለጌታ የነገሩት የቀራቸው ምንም ዓይነት ተጋድሎ ሳይኖር ነበር።ነገር ግን ጌታ ጻድቁ ለእርሱ ያላቸውን ጽኑ ፍቅር ያውቃልና ምንም የቀራቸው እንደሌለና በከፍተኛ የሆድ ሕመም እንደሚያርፉ፤ይህንንም እንደ ስቅለቱና እንደ ሰማዕታት ደም እንደሚቆጥርላቸው ነግሯቸው በዚያ በክብር ዐርፈዋል።
- ዋሻዪቱን ሊነገርና ሊሰማ የማይችል ብርሃንና በዚህ ዓለም የሌለ የልዩ ልዩ የሽቱና የዕጣን መዓዛ ሞልቶባት፤ምድሪቱም እየተንቀጠቀጠች፤የሰማይ ሠራዊት ቅዱስ ዳዊት"ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።"ሲል እንደተናገረ (መዝ 41፥4) በክቡር ዳዊት ምስጋና“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።”በማለት እያመሰኑ የጻድቁ ነፍስ ከሥጋቸው ተለየች።(መዝ 117፥24)
- ጌታችን የጻድቁን ነፍስ በክብር ተቀብሎ አቅፎ ሳማት።"የጸራሽ ንጽሕት ነፍስ ሆይ" ሲልም አመሰገናት።አባታችንን በሕይወተ ሥጋ ሳለ እንደነገራቸው በ15ቱ የገነትና በ5ቱ የመንግሥተ ሰማያት አህጉር ላይ ሾመው።አስቀድሞ በቅዱስ ወንጌል
“በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” ያለ አምላክ ለጻድቁ የመንፈስ ልጆች ይሆኑ ዘንድ በእነዚህ ሁሉ ላይ ሾመው።(ዮሐ 14፥2)
- በጻድቁ ስም ለተራበ ያበላ፤ለተጠማ ያጠጣ፤የየታረዘውን ያለበሰ፤ገድላቸውን የጻፈ ያጻፈ የሰማ፤ለቤተ ክርስቲያናቸው ዕጣን፣ዘቢብ፣ወይን፣ ሜሮን፣ንጹሕ ስንዴ ልዩ ልዩ መባዕ ያገባ፤ለበዓላቸው ለሚዘጋጀው ዝክር ውኃ በመቅዳት፣እንጨት በመፍለጥ፣ቅጠል በመቁረጥ የተራዳ፤በዓላቸውን ደስ ብሎት ያከበረ፤ከእነዚህ ሁሉ ባይቻለው በበዓላቸው ቀን የታመመ የጠየቀ ወይም ያዘነውን ያጽናና፤ በበዓላቸው ቀን ከ ቅዱስ ሥጋው ከክቡር ደሙ የተቀበለውን፤ይህንንም ባይችል ለበዓላቸው ከተዘጋጀው ዝክር የቀምሰ፤ከእነዚህ ሁሉ የተቻለውን አንዱን ቢፈጽም እንደሚምርላቸው ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
- ለቅዱሳኑ የሚሰጠውን ቃልኪዳን በተመለከተ ራሱ ጌታችን እንዲህ ሲል ተናግሯል"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ዋጋው አይጠፋበትም።"(ማቴ 10:40-42)
- የእግዚአብሔር የምሕረቱ ብዛት እንዴት ብዙና ጥልቅ ነው።ጻድቁን የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን!!!
ጻድቁም በጸሎታቸው በበረከታቸው ይጎብኙን፤በፍጹም ሰማያዊ መስቀላቸውም ይባርኩን፤በፍጹም ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነታቸውም ከኃጢአት ማሠሪያ የተፈታን ንጹሐን ለመንግሥተ ሰማያትም የተዘጋጀን ድልዋን ያድርጉን!!! አሜን!!!
#ኢዮብ ክንፈ
ነሐሴ ተክለሃይማኖት/2016 ዓ.ም

+++ እርሷ መድኃኒታችሁ ናትና!!" +++
ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናት ዓመታዊ በዓል (ብዙኃን ማርያም) እንኳን አደረሰን!!
(በትዕግሥት ሆነው ያንብቡት፣ ለሌላውም በማጋራት ሃይማኖታዊ ግዴታዎን ይወጡ)
ላለመማርና ላለማወቅ አእምሯቸውን አሳልፈው የሰጡ ኦርቶዶክሳዊነትንና ኦርቶዶክሳውያንን አምርረው የጠሉ ሰዎች "ድንግል ማርያም ምክንያተ ድኂን እንጂ መድኃኒት አትባልም" ሲሉ ለይቶላቸው የወጡቱ ደግሞ ጥቅሶችን ከዓውድና ከተነገሩበት ዓላማ ውጭ በመጥቀስ "ማርያምን መድኃኒት ቤዛ አድኝን" አትበሏት ብለው በአፍም በመጽሐፍም ይናገራሉ:: ኦርቶዶክሳውያን ድንግል ማርያምን "መድኃኒት፣ ቤዛ" ብለን ስንጠራት በውስጥም በአፋ ያሉ ብዙዎች ባልተረዱት ባላወቁት ባልመረመሩት ነገር እርሷን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያተካከልናት በእርሱ የማዳን ዙፋን ያስቀመጥናት አድርገው ያስባሉ ይናገራሉም:: ከዚያም አልፈው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ላይ የተንሸዋረረ እውቀትና እምነት እንዳለን አድርገው በሌሎች ዘንድ ያጠለሹናል:: ኦርቶዶክሳውያን ያዳነን ማን እንደሆነ ከምን እንዳዳነን ለምን እንዳዳነንና በማዳኑም ሥራ ውስጥ ማዳኑ የተፈጸመለት የሰው ልጅ ሱታፌና ድርሻ ምን መሆን እንደሚገባው ቤተክርስቲያን ታስተምረናለች:: ድንግል ማርያምና ቅዱሳኑን በመንቀፍና በመጥላት ስለ እነርሱም ላለመናገር ዳተኛ በመሆን ለክርስቶስ ያለኝን "ፍቅር" እገልጻለሁ ብሎ መድከም ምንኛ አለመታደል ነው? ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የ"ፓስተሮቻቸውን የ"መጋቤዎቻቸውን" የ"ነቢያቶቻቸውን" የ"ያድናሉ" መልእክት በፖስተር በብሮሸርና በትላልቅ "ባነሮች" እየለጠፋ ወደ የመስብሰቢያ አዳራሾቻቸው ሰዎችን ይጋብዛሉ : በየጉባኤዎቻቸውም የሚያምኑበትን የራሳቸውን ትምህርት ከማስተማር ይልቅ ኦርቶዶክሳዊነትን እያጨለሙና እያጠለሹ የሌለ ስም እየሰጡ ይሰብካሉ:: ኢየሱስ ክርስቶስ ከምንና ለምን አዳነን? እርሱ ካዳነን ከእኛ ምን ይጠበቃል? የሚሉትን ሀሳቦች ማየቱ እጅግ ሰፊ በመሆኑ ለጊዜው አቆይተነው ወደ ነጥባችን እንመለስ :-
+++ ድንግል ማርያም መድኃኒት አትባልምን ? +++
መልሱ ግልጽ ነው::መድኃኒት ትባላለች:: እርሷ መድኃኒት ማለታችን ግን ከክርስቶስ ጋር አስተካከልናት ማለት አይደለም ሊሆንም አይችልም::በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ብርሃን ተብሏል ቅዱሳንም ብርሃን ተብለዋል:: (ማቴ 5:14 ዮሐ 5:38፣ 8:12) እናስተውል እርሱን ብርሃን ስንለውና እነርሱን ብርሃናት ስንላቸው አንድ አይደለም:: እርሱን ብርሃን ስንለው ቃሉ እንደ አምላክነቱ ይረቃል ይመጥቃል ይረቃልም:: እነርሱን ብርሃናት ስንላቸውም እንደ ማዕረጋቸው እንደ ቅድስና ደረጃቸው ነው። (ማቴ 13: 8 1ቆሮ 15:41) ያ ባይሆን ቅዱስ መጽሐፍ ክርስቶስንም ብርሃን አገልጋዮቹንም ብርሃን በማለቱ እርሱንና ቅዱሳኑን አፎካከረ ያሰኝ ነበር:: ወዳጆቹን ብርሃናት ማለት የእርሱን ብርሃንነት መካድ አይደለም:: እርሱ እንደውም የብርሃናት (የቅዱሳን) አባት ተብሏል:: (ያዕ 1:17) ይህን እንደ መነሻ ካልን እርሷ መድኃኒት መባል እንደሚገባት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገን በንጽጽር እንመልከት::
+++ ቤዛ እስራኤል ቤዛዊተ ዓለም +++
በብሉይ ኪዳን እስራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣ በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ ለሕዝቡ ቤዛ የሆነ ጠላቶቻቸውን የጣለ እርሱ እግዚአብሔር ነው::እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ሲያወጣ ነፃ ካወጣቸውም በኋላ የነፃነት ጉዞ ሲያደርጉ መላእክት ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን እንደሚመራቸው ተነግሯቸው ነበር:: (ዘጸ 14:19 ዘጸ 23:20) በዚህ ነጻ የመውጣት ጉዞ ውስጥ ታላቅ ሚናና ድርሻ የነበረው ሰው መስፍኑ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነበር :: ሕዝቡን ይመራና ያስተዳድር ስለእነርሱም ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ነበር:: (ዘጸ 32:32) በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር የሆኑት እስራኤላውያን "የሙሴ ሕዝብ" ሲባሉ ሙሴም በፈጣሪው "የሕዝቡ ነፃ አውጪ" ተብሏል:: (ዘጸ 32:7-8) እስራኤል እግዚአብሔርን ባሳዘኑት ጊዜ ሙሴ ስለ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ነበር:: (መዝ 105:23) ከዚህ ሁሉ የተነሳ እግዚአብሔር ሙሴን ምክንያት አድርጎ ሕዝቡን ከባርነት ነጻ ስላወጣቸው ሙሴ "የእስራኤል ነፃ አውጪና ቤዛ" ተብሏል:: (ዘጸ 32:7-8፣ የሐዋ 7:35) ይህንም መጽሐፍ ሲመሠክር " ይህ ሰው (ሙሴ) በግብጽ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው" ብሏል :: (የሐዋ 7:36)
እስቲ ጥያቄ እናንሣ እስራኤልን ነፃ ያወጣ ማነው? ሙሴ እንዴት ነፃ አውጪ ተባለ? የእስራኤል ቤዛ ማነው? ሙሴ እንዴት የእስራኤል ቤዛ ተባለ? እስራኤል የማን ሕዝብ ናቸው? የእግዚአብሔር የሆኑት ሕዝቡ እንዴት የሙሴ ሕዝብ ተባሉ? ሙሴ በሕዝቡ መካከል ድንቅና ምልክት ካደረገ "ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ድንቅና ምልክቶችን አድርጋለች።" ተብሎ ሲነገር "ይህማ አይሆንም!" ብሎ ሽንጥ ገትሮ መከራከርን ምን አመጣው? (ማር 16:17 ዮሐ 14:15 ::) በሐዲስ ኪዳን ግብጽ የሲኦል እስራኤላውያን የምእመናነ ሐዲስ ጉዟቸው የጉዟችን የገጠሟቸው ፈተናዎች የፈተናዎቻችን ምሳሌዎች እንደሆኑ ተነግሮናል:: (1ቆሮ 10:1-5) በሙሴ ምስፍና እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ ባርነት ነፃ እንዳወጣ ከእርሷ ከድንግል ማርያም በነሳው (በተዋሐደው) ሥጋ እኛን ከሰይጣን አገዛዝ ከሲኦል ባርነት ነፃ አውጥቶናል:: (ዕብ 2:14-16 1ጴጥ 3:19 ዮሐ 1:14-15) በሙሴ ተልእኮ እስራኤል ከግብጽ ወጡ ከድንግል በነሳው ሥጋ ዓለም ከሲኦል ነፃ ወጣ:: በሙሴ ተልእኮ ፈርኦን ተሸነፈ ከድንግል በተዋሐደው ሥጋ በፈጸመው የማዳን ሥራ ዲያብሎስ አፈረ በመስቀሉም ተጠረቀ:: (ቆላ 2:14-16) እስራኤል ከሥጋ ባርነት ከፈርኦን አገዛዝ ነፃ ከወጡበት መንገድ ዓለም ከነፍስ ባርነት ከሰይጣን አገዛዝ የዳነበት መንገድ ይበልጣል :: በእርሱ ምክንያት በተፈጸመው እስራኤልን ነጻ የማውጣት ጉዞ ሙሴ ቤዛ ነጻ አውጪ ከተባለ በድንግል ማርያም በተፈጸመው የማዳን ሥራ ቤዛዊተ ዓለም ብትባል ምን ያንስባታል? እራሷ " ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ ( ማዳኑን ) አድርጓልና።" እንዳለች (ሉቃ 1:49-50)
+++ እርሷ መድኃኒታችሁ ናት +++
በተአምረ ማርያም መቅድም ከሠፈሩ እመቤታችንን እንድንወዳት ከሚያስገነዝቡን ኃይለ ቃላት አንዱ "ውደዷት እርሷ መድኃኒታችሁ ናት" ይላል:: እንግዲህ ይህን አንብበው ነው ሰዎቹ ለምን እንዲህ ትላላችሁ ብለው እንደ ጥህሎ ሊውጡን እንደ እንቀት ሊጠጡን የሚነሥሡብን ሳይመረምሩና ሳይገነዘቡም የሚተቹን :: እነዚህ ክፍሎች እርሷን እንዴት መድኃኒት ትሏታላችሁ? ብለውም ጉንጭ አልፋ መከራከርያ ያነሣሉ:: እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት አዳኝ ነው:: ማዳን የባሕርይው የሆነ እርሱ የወደዳቸውን በፍጹም ልባቸው ያመለኩት ወዳጆቹን ምክንያት አድርጎ በልዩ ልዩ መንገድ ማዳኑን ስለገለጠባቸው መድኃኒት አዳኝ እንዲባሉ ፈቀደ ያድኑም ዘንድ የማዳኑን ጥበብ ገለጠላቸው ኃይሉንም አስታጠቃቸው መንገዳቸውንም አቃና:: እስቲ የሚከተሉትን ለግንዛቤ እንመልከት
👇-ይቀጥላል-👇

🔴ከተጠሩት መሐል እንዳልሄድ ኮብልዬ በ1987ዓ.ም የተዘመረ#Ethiopian Orthodox Tewabido Old Mezmur
መጥቅዕ ሚዲያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ ቀኖና ትውፊት እና ሥርዓት የጠበቁ የቅዱስ ያሬድ መዐዛ ያላቸውን ዝማሬዎችን አውደ ስብከቶችን የበጎ አድራጎት ክንውኖችን በመንፈሳዊ ህይወት እንዲጠነክሩ የሚያስችል ተግባራዊ የህይወት ተሞክሮዎችን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ክንውኖችን እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው፤
ማኅቶት ቲዩብ, ኢቲአርት ሚዲያ, ታቦር ቲዩብ, ንቁ የጸሎትና…
ማኅቶት ቲዩብ, ኢቲአርት ሚዲያ, ታቦር ቲዩብ, ንቁ የጸሎትና…
#ደስ ይበልሽ#
-ቀዳሚት ሔዋንን ሰይጣንን ሸንግሎ ሞት ወደ ዓለም ገባ ፤ ዳግሚት ሔዋን ድንግል #ማርያምን ግን ቅዱስ #ገብርኤል አብሥሯት ሕይወት ተወለደልን።
-ሔዋንን ሰይጣን ሲያታልላት ብዙ መጠየቅ
እየቻለች አመነችው ፤ #እመቤታችንን ግን ቅዱስ #ገብርኤል ሲያበሥራት መረመረችው።
- ሔዋን መልአከ ጽልመትን አምና ነፍሰ ገዳዩ ቃየንን ወለደች ፤ ድንግል #ማርያም ግን ብርሃናዊውን መልአክ አምና ነፍሳችንን የሚያድነውን ወለደች።
- በሔዋን ከጸጋ መጉደልን ዐወቅን ፤ #በእመቤታችን በድንግል #ማርያም ግን በጸጋ መሞላትን ተረዳን።
"ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርህ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው።ወደ እኛ የመጣ (ሰው የሆነን) የጌታን ልደት ነገርኸን ለድንግል #ማርያምም ጸጋን የተመላሽ ሆይ #እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሠርካት" (ውዳሴ #ማርያም ዘረቡዕ)
- ከሔዋን የተረፈውን ኃዘን ልጆቿ ሁሉ ለ5500 ዘመናት ተካፈሉ ፤ #ከእመቤታችን የተረፈውን ደስታ ግን ዓለም ሁሉ ተካፈለ።
-እኛም ከቅዱስ #ገብርኤል ጋር "ጸጋን የተመላሽ ደስተኛዪቱ ሆይ ደስ ይበልሽ"
-ከቅዱስ #ኤፍሬም ጋር "በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ ፤ የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ" እንልሻለን።
#እመቤታችን #ማርያም ሆይ መልአከ ብሥራት አንቺን ደስ እንዳሰኘሽ ፤ በዛሬዪቱ ቀን ያዘንን እኛን ደስ አሰኚን!!!
-አማናዊ በዓለ ሱታፌ ያድርግልን አሜን!!!
#ኢዮብ ክንፈ
#ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም

#ሁለተኛውን_ልደቱን_አስደናቂ_አደረገው!
📍እግዚአብሔር እልፍ ድንቅ ነገሮችን ትላንት አድርጓል፣ ዛሬም እያደረገ ነው ለወደፊትም ያደርጋል። ከድንቆች በላይ ግን ምንድነው ከተባለ ይህ ነው።
አምላክ ሰው የሆነበት፣ ሰውም አምላክን የሆነበት፣ ረቂቁ
ግዙፍ የሆነበት፣ ልዑሉ ትሑት የሆነበት ይህ ሁለተኛው ልደቱ
እጅግ ይደንቃል።
ታላቅነቱን በታናሽነት፣ ኃያልነቱን በደካማ ሥጋ ሰውሮ
መምጣቱ በጣሙን ይገርማል።
ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በማኅፀነ ማርያም መወሰኑ
እጅግ ያስደንቃል።
ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነችለት አምላክ የዕለት
ጽንስ ሆኖ በማኅፀነ ማርያም ማደሩ በጣሙን ያስደንቃል።
የአስራ አምስት ዓመት ብላቴና እንድትሸከመው መፍቀዱ እጅግ ያስደንቃል።
የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ተብሎ መጠራቱ እጅግ
ያስደንቃል።
እኛን ወደሰማይ ሊያወጣ እርሱ ወደመሬት መውረዱ በጣም
ያስደንቃል።
እኛን ከክብር ዙፋን ላይ ሊያስቀምጥ እርሱ በውርደት በረት
መጣሉ እጅጉን ያስደንቃል።
እኛ ከመላእክት ጋራ እንድንዘምር እርሱ ከእንስሳት ጋራ በበረት
ማደሩ ያስደንቃል።
ባለዙፋን ባለበረት ሲሆን ማየት እጅግ ያስደንቃል።
ኃያል አምላክ ሕጻን ሆኖ መወለዱ ያስደንቃል። (ኢሳይያስ ሕጻን ተወለደልን አለ ማቴዎስ ደግሞ የተወለደው ንጉሥ ነው ይለናል። ሰብአ ሰገል ለዚህ ዘውዳቸውን አንሥተው ለሕጻኑ ሰግደዋል። በሚታይ ዕድሜ ቢሆን ኖሮ አይታሰብም አይሞከርም ነበር።)
#በሚታይ ሕጻንነቱ ግን ዘለዓለማዊ አባትነት አለው፣
#በሚታይ ሕጻንነት ዘለዓለማዊ ንግሥና አለው፣
#በሚታይ ሕጻንነት ዘለዓለማዊ አምላክነት ስላለው ዘውዳቸውን አንሥተው ለሕጻኑ ሰገዱለት።
ኃያል አምላክ ሕጻን ሆኖ መወለዱ እጅግ ያስደንቃል።
የዘለዓለም አባት "አንድ" ተብሎ ዘመን ሲቆጠርለት አረ
በጣሙን ያስደንቃል።
ከአንዲት ታናሽ ብላቴና ምግብ ሲለምን ማየት በጣም
ያስደንቃል።
ከአንዲት ታናሽ ብላቴና ምግብን ፈልጎ ማልቀሱ እጅግ
ያስደንቃል። እግዚአብሔርም አለቀሰ ሲባል እጅግ ያስደንቃል።
የእርሱ ማልቀስ የእርሷ እሹሩሩ ብሎ ማባበል እጅግ በጣም
ያስደንቃል።
.
.
.
.
አባ ጊዮርጊስ "የመጀመሪያውን ልደቱን (ከአብ ያለ እናት) ረቂቅ አደረገው። ሁለተኛውን ልደቱን (ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት) አስደናቂ አደረገው።" ብሎ እንደተናገረ በእውነት ይህ ሁለተኛ ልደቱ እጅጉን ድንቅ ነው!!
ምድር እስከ ተዘረጋችበት ውኃም እስከፈሰሰበት ድረስ ያላችሁ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የሆናችሁ ሁሉ እንኳን ለልደቱ ለእግዚእነ አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!!🤲🤲
©️ከ ስምዓ ጽድቅ አርአያ የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

#ዛሬ የኪዳናት ሁሉ ፍጻሜ #ኪዳነ #ምሕረት ናት።ለቅዱሳኑ ለአዳም፣ለኖኅ፣ለመልከጼዲቅ፣ለአብር
ሃም፣ለዳዊት የተገባው ቃልኪዳን ሁሉ በእግዝእትነ ድንግል ማርያም ፍጻሜውን አገኘ።ይህ ኪዳነ እግዚአብሔር ምንድነው? ቢሉ የእግዚአብሔር ወልድ ሰው መሆን ነው።ሰው ሆኖም መዳናችንን መፈጸም ነው።
#ቅዱስ ዳዊት “ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።” መዝ 3፥8
ብሎ እንደተናገረው ሰውን ከተፈረደበት የሞት ፍርድ ማዳን የሚቻለው የፈረደበት እግዚአብሔር ነው።
#“ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።”(መዝ 33፥5) በሚለው ቃልም ምን እግዚአብሔር ሰውን ማዳን(ጽድቅ) ቢችልም ፍርድንም ይወድዳል።ሰውን በቸርነቱ የማዳን ፈቃዱ ጽድቅ ሲሆን፤የበደለ ሰው ነውና ሊክስ የሚገባውም ሰው ነው፦ይህ ፍርድ ይባላል።
ሰው ደግሞ ራሱ የሞት ፍርድ ስላለበት ሰውን ማዳን የማይቻለው ነው።ታዲያ ምን ተሻለ? የሞት ፍርድ የሌለበት፤የባሕርይ ጉስቁልና (fallen nature)፤መርገመ አዳም መርገመ ሔዋን ያላገኘው ንጹሕና ቅዱስ ሰው ነዋ !!! ይህንን ነቢዩ ኢሳይያስ
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።”
(ኢሳ1፥9) በማለት የገለጸው ከላይ ካነሣናቸው ጉዳዮች የቀረች ንጹሕ ዘር ታስፈልግ ነበር።ከዚህች ንጹሕ ዘር ነው ራሱ እግዚአብሔር የነሣውን ሥጋዋን ነፍሷን ተዋሕዶ የሚያድነን።
#ይህቺ አዳምና ሔዋን በበደሉት በደል ከመጣው ጣጣ ሁሉ ከአዳም ልጆች በተለየ መልኩ ያስቀራት ዘር እመቤታችን ናት።ልብ በሉ "ዘርን ባያስቀርልን" አለ እንጂ "ዘሮችን" አላለም።ዘርዪቱ አንዲት ናት።ልዩ ናት!!!አትደገምም፤አትነገርም።ይህቺ ሰዎች ሁሉ ላይ ከመጣው የሞት ዕዳ የቀረች (የተረፈች) ዘር እመቤታችን ለመሆኗ ሰማያውያን መላእክትን ምድራውያን ጻድቃንን ምስክር እናቆማለን።“እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ።”(ኢሳ 1፥2)
1.“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
(ዘፍ 3፥15) የሰማዮች ሰማይ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ነው።ይህቺ ከእባቡ (ከሰይጣን) ጋር ጠላትነት ውስጥ የምትገባ ዘር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።ሔዋን ከመሰለችህ ተሳስተሃል።ስለ እርሷማ ቅዱስ ኤፍሬም "ከይሲ ዲያቢሎስ ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ፃዕርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት"ብሎ ተናገረ ።በምክረ ሰይጣን የተስማማ ሰው ከሰይጣን ጋር ጠላትነት ውስጥ ሊገባም አይችልም።ይህ የእመቤታችንና የሰይጣን ጠላትነት “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ”
(ራእይ 12፥17) ተብሎ ተጽፎለታል።ዘንዶው ማንነው? ካልክ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።”(ራእይ 12፥9) በማለት የቀደመው እባብ (ሰይጣን) መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ ይነግርሃል።ሴቲቱስ?“ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”ራእይ 12፥1
የተባላለት ድንግል ማርያም ናት።በዘፍጥረት በሴቲቱና በእባቡ ጠላትነት እንደሚደረግ እግዚአብሔር ነገረን።ቅዱስ ዮሐንስ ይህን ጠላትነት በተግባራዊ መልኩ በራእዩ አስረዳን።
2. “ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።”(መዝ 45፥4) ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያውን ለየ፤አመሰገነ፤አከበረ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ማደሪያው የምትሆን ድንግል ማርያምን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠበቀ ፤ በመጠበቁም አከበረ።
3.“ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።”ሉቃ1፥27
ቅዱስ ገብርኤል የተላከው "ከደናግል ወደ አንዲቱ" አይደለም፤ወደ "አንዲት ድንግል" እንጂ!!!በሥጋ ደናግል የሆኑ ሴቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እነዚህ ግን እንደ ማንኛውም የሰው ዘር መርገመ አዳም ወሔዋን ደርሶባቸዋል።እመቤታችን ግን ከዚህ ሁሉ ንጽሕት ናትና "አንዲት ድንግል" አላት።"አንዲት ድንግል" ማለትም "ብቸኛዪቱ ድንግል" ማለት ነው።ይህ ዓይነቱ ድንግልና ነው "የድንግልናሽ ምስጋናና ክብር ታላቅ ነው" ተብሎ የተመሰገነ።
4. “መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።”(ሉቃ 1፥28)
ሰው ሁሉ ኃዘን አግኝቶት "ደስ ይበልሽ" የተባለች፤ሰው ሁሉ ከጸጋ እግዚአብሔር ጎድሎ "ጸጋ የሞላብሽ ሆይ" ተብላ የተመሰገነች፤በበደል በደሉንም ተከትሎ በደረሰብን መርገም ከእግዚአብሔር ተለይተን በነበርን ጊዜ መርገምም ሆነ በደል ካላገኛት ከእመቤታችን ጋር ጌታ እግዚአብሔር ነበር።ከሌሎች ሴቶች መካከል የተባረከች ናት እመቤታችን።መባረክ የመረገም ተቃራኒ መሆኑ ግልጥ ነው።ሌሎች ሴቶች ላይ “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።” (ዘፍ 3፥16) የተባለው መርገም ሲደርስባቸው በእመቤታችን ግን ይህ ሁሉ የለባትም።
#በእውኑ #የእመቤታችን ሥጋ የወደቀው የአዳም ሥጋ እንዳልሆነ፤አዳም ሳይበድል የነበረው ሥጋ እንደሆነ ዐወቅን ተረዳን!!!ይህንን የገለጠልን ለእመቤታችን የምሕረት ቃል ኪዳን የሰጠ ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን!!!
#የካቲት #ኪዳነ #ምሕረት /2017 ዓ.ም

#ምስጋና ቢስ ጤና
----------------------------
በሽታውን ለምዶ ለኖረ በጠና
መዳን መታመም ነው መቆየት በጤና
ሕመመ ለምዶ ለምዶ
እኸኸን ለምዶ ለምዶ
ወንጀል ይመስለዋል የዳነ ተገዶ
ከለመደው ሕመመ ካከረመው በደል
ማንም ቢነጣጠል ጸናበት ነው እንጂ
ተፈወሰ አትበል
ጤና ለራቀው ሰው ሕመም ነው ጤንነት
ከለመደው መኖር እኸኸ ከሚልበት
አለመታመም ነው የሱ መጻጉነት
ስለዚህ ወዳጄ
ማዳንን ስለቻልክ መፈወስ ስላወክ
ልፈውስ አትበለው ሕመሙን አርቀህ ጤናውን እያወክ
ያ ደጉ ጌታ እንኳ ለማዳን የመጣው
ልድን ተወዳለህ? ብሎ ያስፈቀደው
ላንዳንዱ በሽታው
ጤናው እንደሆነ አስቀድሞ አውቆ ነው
መዳን ጤና የሚሆን ላንዳንዱ ብቻ ነው
ጤናው ጤና ነስቶት በሽታ የሆነበት
ኁልቁ ሰው አለልህ ለቁጥር የሚያዳግት
ያዳነውን መድኅን ሽቅብ የሚያንጓጥጥ
ያዳነኝ ያ ሰው ነው ብሎ የጠቆመው
መድኅኑን በሰው ፊት ኮንኖ ያቆመው
ተኝቶኮ አይደለም በአልጋ ቁራኛ
መጻጉዕ ድኖ ነው የሆነ ሕመምተኛ
እናማ የታመምክም ብትሆ በአልጋ የወደክ
ጤናህን በማጣት በጅጉ የደከምክ
አታማር ግድ የለም
ያንተ ጤንነትህ በደዌክ ውስጥ ነው
መናልባት ሕመም ቀና ያልክ ቀን ነው
#ማስታወሻነቱ :- በደዌ ደኛ በአልጋ ቁራኛ ለተያዙ ሁሉ ይሁንልኝ!
#የምሕረት-እናት-ድንግል-ማርያም ምሕረቱን ትላክላችሁ:: የወይን ጠጅ አኮ የላቸውም ብሎ አዲስ የወይን ጠጅ ባሰጠ አንደበቷ ዛሬም ጤናኮ የላቸውም ብላ ከቀድሞው የበለጠ አዲሰ ጤናን ታሰጣችሁ ታሰጠን! አሜን!
አ.አ ኢትዮጵያ
ከተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
መጋቢት ፲ ፫ ቀን ፳ ፻ ፲ ፬ ዓ.ም ጥንተ ጽሕፈቱ

++ ለክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ++
እንኳን አደረሳችሁ!!
☞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ጥንተ አብሶ ካመጣው ፍዳና መርገም ጠብቋታል:: የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ዓለም በጥንተ አብሶ በነበረበት ዘመን በክርስቶስ ማዳን ዋዜማ ሲያበሥራት፤ ቅድስት ኤልሳቤትም በፅንሰቷ ጊዜ ስታመሰግናት ደጋግመው "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ" "አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ።" እያሉ ይህን እውነት መስክረዋል። (ሉቃ፩:፳፮-፵)
☞ በጥንተ አብሶና ውጤቱ (origional sin and its effects) ምክንያት ሰዎች "የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል በተባሉበት ዘመን ጸጋን የተመላች ብቸኛ ልዩ እርሷ ነበረች::" (ሮሜ ፫:፳፫) እግዚአብሔር እርሷ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ለመውለድ ፈቃደኛ እንደምትሆን ስለሚያውቅ አስቀድሞ በአካል የሚመስለው በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ አንድያ ልጁን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንድትወልድ ቅድመ ዓለም መርጧታልና የእመቤታችን ልደት (ልደታ ለማርያም) የዓለም መዳን የማይቀር መሆኑ ለታወቀበት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ነው እንላለን። (The nativity of the blessed virgin Mary prepares the way for the birth of Jesus Christ) እንዳለ ሊቁ። (The book of the nativity of Virgin Mary)
☞ የጌታችን ሰው መሆን "ከዘላለምና (ቅድመ ዓለም) ከትውልዶች ጀምሮ (ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ) ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው።" መባሉም የአምላክ ሰው መሆን እንዲሁም የእርሷ እርሱን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ሕሊና የሚታወቅ መሆኑን ያስረዳናል። (ቆላ፩:፳፮፣ኢሳ ፯:፲፬ ፱:፮)
☞ እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶች ጌታ፣ የአማልክት አምላክ ነው። (መዝ ፻፴፭:፩ ራእ፲፱:፲፮)
☞ እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ፈጣሪ ነው:: "ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ያለ እርሱ አልሆነም።" (ዮሐ ፩:፫)፤ "መልካሙን ነገር ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን።"፤ "የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሁኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና።" እንደተባለ:: (ቆላ ፩:፲፭-፲፮፣ ኤፌ ፪:፲)
☞ እርሱ ለቅዱሳን የጸጋ አምላክነትን ክብር የሰጠ ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ ነው:: (ዘጸ ፯:፩፣ መዝ ፹፩:፩፣ ዮሐ፲÷፴፬፣ ሮሜ ፱:፭፣ ፩ተሰ ፫:፲፩፣ ቲቶ ፪:፲፩፣ ፩ዮሐ ፭:፳)
☞ እርሱ ቸር ከሆነ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአገዛዝ በሥልጣን በሕልውና በመለኮት አንድ ነው:: (ዮሐ ፲:፴፣ ፲፯:፲፣ ማቴ ፲፩:፳፯-፳፱፣ ዮሐ ፲፬:፮-፰)
☞ እርሱ ፀሐይ እናቱ ምሥራቅ ናት:: (ሕዝ ፵፬:፩፣ ዮሐ ፰:፲፪፣ ሚል ፬:፪) ምሥራቅ እናቱን ዘወትር መሻታችን የፀሐይ ክርስቶስን በረከት ፍቅርና ቸርነት ለማግኘት ነው:: እንኳንስ እናቱን ነቢዩ ዳዊት ስለ ወዳጆቹ "ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው ስለዚህም ነፍሴ ፈለገቻቸው።" ብሎ ዘምሯል:: (መዝ ፻፲፰:፻፳፭)
☞ እርሱ የባሕርይ አምላክ እርሷ ደግሞ ወላዲተ አምላክ ( Theotokos) ናት:: ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም በኋላ መቸም መች አምላክን "ልጄ ወዳጄ" ማለት ከቶ ለማን ተችሏል? እርሱ ፈጣሪ እርሷ ደግሞ ወላዲተ ፈጣሪ ኩሉ ዓለም ናት::
☞ እርሱ እውነተኛ ደስታ እርሷ የደስታ መፍሰሻ ናት። (መዝ ፵፭:፭)
☞ እርሱ ሕይወት እርሷ ነቅዐ ሕይወት (የሕይወት ምንጭ) ናት። ይህች ብርሃን ሙዳየ መድኃኒት ቤዛዊተ ኩሉ ብርሃንን ትሰጠን ሕይወት ክርስቶስን ትወልድልን ዘንድ ከተቀደሱ ተራሮች ከአብርሃም ከዳዊት ቤት ተወለደች። (መዝ ፹፰(፹፱):፩)
+++ የልደቷ ቀን +++
አንተ የራስህን እንዲሁም የምትወዳቸውን ሰዎች ልደት ሻማ አብርተህ፣ ኬክ አስጋግረህ፣ ወዳጅ ዘመዶችህን ጠርተህ፣ በዳንስ በጭፈራና እስክስታ በመውረግረግ ታከብራለህ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ቀን በማሰብ በዓለ ልደቷን የሚያከብሩ ሰዎችን ግን ለምን ያከብራሉ? ብለህ ትተቻለህ::
የእናቱን ልደት እርሱን እያመሰገንን፣ እያወደስን እናቱ "ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል።" (ሉቃ ፩:፵፱) እንዳለችም እርሷንም እያመሰገንን "ብርቱ የሆን እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና።" ብላ እንደመሠከረችም በእርሷ ለሰው ዘር የተደረገውን ታላቅ ሥራ እያሰብን ብናከብር የሚያዝንብን ይመስላሃልን? ከማዳኑስ በላይ ምን ታላቅ ሥራ አለ? ዓለም:- የኤድስ ቀን፣ የጉበት ቀን፣ የኩላሊት ቀን፣ የላብ አደር ቀን፣ የውሃ ቀን፣ የአፈር ቀን፣ የእናቶች ቀን፣ የአባቶች ቀን እያለ በልዩ ልዩ መንገድ ሲያከብር ቅር አይለውም የእናቱ የእመቤታችንን ልደት ለማክበር ግን ያመዋል::
ልደታ ለማርያምን ስናከብር
☞ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት በዳንኪራና በአስረሽ ምስናከብር
ሆን በመንፈሳዊ ሥርዓት እናክብረው ያኔ የልጇ በረከት እጥፍ ድርብ ይሆንልናል። (ምሳ ፲:፯፣ ፩ጴጥ ፪:፲፪)
☞ የቤተክርስቲያን ባልሆነ የልደቷን ነገር በማይገልጥ በማይወክል መንገድ በአምልኮ ባዕድ፣ በየዛፉ ዙርያ አረቄና ቡና በማፍሰስ የሚያከብሩትን ሰዎች በማስተማርና ትክክለኛውንና የክርስትናውን መንገድ በተከተለ መንገድ እንዲያከብሩት በማድረግ ድርሻችንን በመወጣት እናክብር ::
☞ ልደቷ "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ከተባለለት ከዮሐንስ ልደት የሚልቅ መሆኑን እንወቅ። እርሷ የዮሐንስ ፈጣሪ የክርስቶስ እናቱ ናትና። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም " ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ።" እንዳለ:: እርሱ ክርስቶስ "ሁሉን በስሜ አድርጉት" እንዳለን እርሷን በእርሱ ስም ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን ብለን ተቀብለን ልደቷን እንደምናከብር እንረዳ:: (ሉቃ ፩:፲፬)
+++ አድባር +++
አድባር የሚለው ቃል የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም ተራሮች ማለት ነው:: እመቤታችን በሊባኖስ ተራሮች መሐል ተወልዳለችና የልደቷን ወቅት አድባር እንላለን። (መኃ ፬:፰)
🚹የእናቱን በዓለ ልደት ማክበር ማኅበራዊ ፋይዳ 🚹
በዚህ ቀን የአንድ ቀዬ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ጸሎት በማድረግ እግዚአብሔርን በማመስገን እናቱንም በማወደስ ማክበራቸው ከሃይማኖታዊው ፋይዳ ባለፈ በልዩ ልዩ ምክንያት እየደበዘዘና እንደ ዳይኖሰርና ዶዶ ድራሹ እየጠፋ የመጣውን አብሮነት ማኅበራዊ ትስስር የሚያጠነክር መልካም ባሕላችንም ጭምር ነውና አጥብቀን ልንይዘው ይገባናል:: የድንግል ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ የልደት ቀን በረከት ያሳትፈን!!!
ቢትወደድ ወርቁ
ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፲፯ ዓ ም