ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የነገረ_ማርያም ጥያቄዎች ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ማርያም ማለት እመ ብዙሐን ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ማሪያም በአርብኛ መሪሃም ተብላ ትጠራለች::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ #ማርያም የሚለው ስም #አብርሃም ከሚለው ስም ጋር ከጾታ ልዮነት ባሻገር በትርጉም ደረጃ አንድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ማርያም ማለት:- እመ ብዙኃን ፣የብዙኃን እናት ማለት ነው

#አብርሃም:- ማለት አበ ብዙኃን፣ የብዙኃን አባት ማለት ነው

#ኛ የኤልሳ ማሰሮ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

የኤልሳ ማሰሮ በውስጧ አጣፋጭ ጨው ተገኝቶባታል ከእመቤታችንም እናንተ የዓለም ጨው ናችሁ ብሎ ማጣፈጥን ለቅዱሳን የሰጠ የአዳምንም ሕይወት በከበረ ሞቱ ያጣፈጠ የአማናዊው #ጨው የክርስቶስ መገኛ ሆናለችና የኤልሳ ማሰሮ #የእመቤታችን ምሳሌዋ ነች

#ኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰው ዘር ስለሆነች ጥንተ አብሶ ወይም የመጀመሪያ በደል ነክቷታል::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት
ምንም እንኳን እመቤታችን የሰው ዘር ብትሆንም በመንፈስ ቅዱስ ልዮ ጠብቆት ከጥንተ አብሶ(ከመጀመሪያው በደል) የነጻች ሆናለች::ወርቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው ::ወርቅ መገኛው ከመሬት ከጭቃ ውስጥ ነው ከጭቃ መገኘቱ ግን ወርቅነቱን አያስቀረውም እመቤታችንም በኃጢያት ጭቃ ከተነከሩ ሰዎች የተገኘች የሰው ፍጡር ብትሆንም ነገር ግን ጭቃው ያላቆሸሻት #ንጹዑ_ወርቅ ነችና ጥንተ አብሶ የለባትም፣ አልነካትም::

#ኛ_በመዝሙር 86 ላይ መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ተብሎ የተነረው ለእመቤታችን ቀደምት አያቶቿ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

መጻሕፍትን ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ እንደተባለው ይህንንም ኀሠይለ ቃል አጣመው በወንድ አንቀጽ ቢቀይሩትም እንደ ጥንቱ መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ነው የሚለው ::ይህም ሰሸለ እመቤታችን ቅደምት አያቶች ከፍታና ቅድስና የሚናገር አንቀጽ ነው ::


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 44÷ ከቁር 1 እስከ ያለው ኃይለ ቃል ምን ምን ነገሮችን ያስረዳል
ሀ )የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና
ለ)እመቤታችንን የወለደችሁ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የአብን አንድያ ልጅ ወልድ እግዚአብሔርን ብቻ እንደሆነ::

ሐ) ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ሌላ ልጅ ዳግመኛ እንዳልወለደች

መ)ሁሉም

#ኛ_ከእመቤታችን የዘር ሐረግ ውስጥ የማይካተተው ነገድ የቱ ነው

ሀ) ነገደ ሌዊ
ለ) ነገደ ይሁዳ
ሐ) ነገደ ዳን
መ) ሀ ና ለ

#ኛ_ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ብሎ የተነበየው ነቢይ ማን ነው

ሀ) ነብዮ ሳሙኤል
ለ)ነብዮ ኤርምያስ
ሐ)ነብዮ ኢሳይያስ
መ)ነብዮ ሐጌ

፱ እመቤታችን ለዮሴፍ የታጨችበት ምክንያት ምን ነበር

ሀ) ከውግረት እድትድን
ለ) ለጋብቻ
ሐ) ለጠባቂነት እና ለአገልጋይነት
መ) ከ "ለ" በስተቀር ሁሉም መልስ ነው


#ኛ_ እመቤታችን በቤተ መቅደስ የኖረችው ለስንት ዓመታት ነው

ሀ) ፲ ፪ ዓመታት
ለ) ፫ ዓመት ከ፫ ወር
ሐ) ለ፫ ዓመታት
መ)ለ፲ ፭ ዓመታት


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰው ልጆች ድኅነት ያበረከተችሁን ትልቅ አስተዋጽኦ አብራራ(ሪ)

#መልስ

#ንጽሕናዋን ጠብቃ በመገኘቷ

#ፍቃዶን ስትጠየቅ እሺ ብላ ለድኅነተ ዓለም ምክንያት በመሆነኗ



፲ ፪ #_ድንግል ማርያም በሦስት መሠረታዊ ነገሮች ንጽዕት ነች ::እነዚህ ሦስቱ መሠረታዊ ንጽዕናዋ የምን የምን ንጽዕና ናቸው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#በሥጋዋ (ንጽ ሥጋ )
#በነፍሷ (ንጽኃ ነፍስ )
#በሀሳቧ ( ንጽኃ ልቡና )

፲ ፫ #እመቤታችን " እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትሁልድ ሁሉ ብጽህይት ይሉኛል" ሉቃ 1÷49 ብላ የተናገረችሁ ስለምንድነው? ትውልዱ #ሁሉ ያለችውስ የትኛውን ትውልድ ነው

#ይህን የለችሁ
👉ነቢይት ሰለሆነች የወደፊቱን የማወቅ ፀጋ ስላላት እና በተሰጣት ፀጋ እንደ ሰጣት እንደ ፈጣሪዋ አዋቂ ስለሆነች

ትሁልድ ሁሉ ያለችው ደግሞ አማኝ ትውልድ ሁሉ ማለቷ ሲሆን በመጨረሻ ግን ክብሯ ሲገለጥ ሁሉም ትውልድ እንደሚያመሰግናት አውቃ ይህን አለች

፲ ፬ #_እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስቀድማ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር በፊት በአምላክ ዕሊና ታስባ ትኖር እንደነበር በትምህርቱ መሠረት ቅዱሳት መጻሕፍትን እያመሳከርክ አስረዳ (ጂ)

#መልስ
."እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ እሊና ታስባ ትኖር ነቀር::፡ ለዚህመሸ "ያልተሰራ አካሌን አይኖችህ አዩኝ ፡ የተፈጠሩ ቀኖቸ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመፅሐፍ ተፃፈ" መዝ 138:16
ስለዚህ ዓለም ሳይፈጠር ሁሉም ከተፃፈ እመቤታችንም ተፅፋ ታስባለች ማለት ነው፡፡፡ቅዱሳን ነቢያት(ኤርምያስንና መጥምቁ ዮሐንስን ) ብንመለከት አሰቀድሞ ስለሚያውቃቸው መስክሮላቸዋል፡፡
" በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። " (ኤር1:5)
ስለዚህ የሁሉ አዋቂ ጌታ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰው መሆኑ ከታወቀና ከታሰበ እመቤታችን መታሰብዋን አይዘነጋም፡፡፡
"፤ #ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 4) "፤ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 4)

#15.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ጽዮን" ተብላ የምትጠራበት የመ/ቅዱስ ጥቅስ፡

"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።"
(መዝ 87:5)
" የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። "
(ኢሳ60:14)
" ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል እግዚአብሔር። "
(ኢሳ59:20

#በመልሶቹ ዙሪያ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ክርስቶስ #የግል_አዳኝ ወይስ #መዳኃኔዓለም?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ዛሬ በፕሮቴስታንቱ ዓለም "ጌታን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል።" የሚለው አባባል መስማት የተለመደ ሆኗል። ክርስቶስን "የግል አዳኜ" ሲሉም ይስተዋላል። ይህን ቋንቋ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አመክንዮ ስንመለከተው ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አናገኘውም። የትኛውም ሐዋርያ ሰዎችን በክርስቶስ የግል አዳኝነት እንዲያምኑ ሲያደርግ አላየንም አልሰማንም። ነገር ግን ሁሉም የተባበሩበት በአንድ መንፈስ ቅዱስ ተነድተው የተናገሩት የጻፉትና ያስተማሩት የክርስቶስን #መድኃኔዓለም መሆንን ነው። እስኪ የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት…

👉 ሉቃ 2:10–11 "መልአኩም እንዲህ አላቸው ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
ይህን ቃል የተናገረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። የክርስቶስን ወደዚህ ዓለም መምጣት ለእረኞቹ ባበሰረበት ቃሉ #ለህዝቡ_ሁሉ_የሚሆን#መድኃኒት ተወለደላችሁ በማለት ነበር። መልአኩ ለህዝቡ ሁሉ አለ እንጂ ለአንተ ወይም ለአንቺ የግል አዳኝህ አዳኝሽ የሚሆን ክርስቶስ ተወለደ አላለም። እርሱ መድኃኔ ዓለም መድኃኒትነቱ ለዓለሙ (ለህዝቡ) ሁሉ ነውና። መልዓኩ ከዚህ ቀደም ለጻድቁ ዮሴፍ በህልሙ በተገለጠለትም ጊዜ "እርሱ #ህዝቡን_ሁሉ ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" ነበር ያለው። ማቴ 1:21 መልአኩ የክርስቶስን መድኃኔዓለም መሆን ከነገረን #የግል_አዳኜ የሚለው ምን የሚሉት ፈሊጥ ይሆን???

👉 ዮሐ 4:42 “አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።” የሰማርያ ሰዎች በግልጽ ንግግር ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው ብለው ምስክርነት ከሰጡ #የግል_አዳኝ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም መቃረን መሆኑን ልናውቅ ይገባል።

👉 ዮሐ 1፥29 “ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ ወደ አጥማቂው ለስንብት በመጣ ጊዜ ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክርስቶስ መድኃኔዓለም መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠለት #የዓለሙን_ኃጢአት_የሚያስተሰርይ ብሎ መሰከረ። በመንፈሰ እግዚአብሔር የሚመራውን መንገደ ክርስቶስን የጠረገውን መጥምቁን እንቀበል ወይስ ሉተርን????

👉 ዮሐ 3:16–17 "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ #ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። #ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።" የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው ዓለሙን ሁሉ ያድን ዘንድ ነው በማለት ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እየነገረን #ጌታን_እንደ_ግል_አዳኝ_አድርገህ_ተቀበል የሚለው አስተምሮ ጤነኝነት ነው ብላችሁ ታስቡ ይሆን??? አይመስለኝም።

👉 ይሁ 1:3 "ወዳጆች ሆይ ስለምንካፈለው ስለመዳናችን እጽፍላችሁ ዘንድ እጅግ ተግቼ ሳለሁ…" ሐዋርያው በማያሻማ ቃል #መዳናችን በማለት ክርስቶስ የፈጸመው የማዳን ሥራ ለሁሉም መሆኑን ተናገረ። ሰው ሁሉ አንድ ጊዜ ክርስቶስ ከፈጸመለት የማዳን ሥራ የሚካፈል እንጂ ክርስቶስን አንደ ግል አዳኝ አድርጎ የሚቀበለው እንዳልሆነ የሐዋርያው ንግግር ልብ ይለዋል።

👉 1ኛ ጢሞ 4፥10 “ይህን ለማግኘት እንደክማለንና ስለዚህም እንሰደባለን ይህም #ሰውን_ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን #በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።” በግልጽ ቃል ሰውን ሁሉ የሚያድን በማለት ግላዊነት አስተሳሰብን ሳያንጸባርቅ ክርስቶስ አዳኝነቱ የዓለም መሆኑን ያስረዳናል።

👉 1ኛ ዮሐ 4፥14 “እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።” እንዳለ ሐዋርያው እኛም ያመነውን እንመሰክራለን። ምንመሰክረውንም ደግሞ እናምናለን። የሐዋርያውን ዐይን ዐይናችን አድርገን ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ አንዳዳነ ዐይተናልና መድኃኔዓለም አንለዋለን።

በመጨረሻ ሥሮቿ በምድር ምዕመናን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ቅዱሳኑ እና መላእክት ራሷ ደግሞ ክርስቶስ የሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መላእክት የመሰከሩትን ሐዋርያት የተባበሩበትን ክርስቶስ መድኃኔዓለም ሆኖ ደሙን ለዓለሙ ሁሉ ማፍሰሱን አምና ታሳምናለች። እኛም ክርስቶስን አንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውን ትምህርት በመቃወም የግላዊነት አስተሳሰብን አስወግደን ከክርስቶስና እርሱን ከመሰሉ ከቅዱሳን ሐዋርያት እንደተማርነው መድኃኔዓለም ብለን እናምናለን እንታመናለን።

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ
የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር
የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ሕብረት አንድነት አይለየን።

አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን።

ይቆየን።

አዘጋጅ: #አቤኔዘር

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit