ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

✟ለአዕዛኒከ

ሰላም : ለአዕዛኒከ : እለ : ያጸምዓ : ምሳሌ : ዘሐዋርያት : ቡሩካን : ወዘነቢያት : ሰብአ ኩፋሌ ፤ ተክለ ሃይማኖት ምድራዊ ወመልአክ : ዘሉዓሌ ።
ምሥጠኒ : ውስተ ቤትከ : ዘአረፈቲሀሃ : ቢረሌ ። ከመ : አዕርፍ : ባቲ : እምብካይ : ወወይሌ ።

ትርጉም :- ✟ ለአዕዛኒከ ( ለጆሮሆችህ )

ተክለሃይማኖት ሆይ ፤ በክቡራን ነቢያት የተነገረውን በክቡራን ሐዋርያት የተሰበከውን መልካሙን ምሣሌ ነገር ለሚያደምጡ አዕዛኖችህ ሰላም እላለሁ ።
ቅዱስ አባቴ ሆይ በተፈጥሮ ጠባይህ ምድራዊ ሰው ስትሆን ፤ በሥነ ምግባርህ ሰማያዊ መልአክ ነህኮን ።
ከለቅሶና ከዋይታው በእርሷ ዐርፍ ዘንድ በወርቅና በዕንቁ በተሠራችው በሉዓላዊት ቤትህ
በዚያ ወስደህ አስቀምጠኝ

📜 መልክአ ተክለሃይማኖት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ፣ የተበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ "ሁሰት " ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው

ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጢያንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥያንን
መ ) ኃጥያንንና ኃጥያንን

#ኛ_የቅዱሳ መላዕክት አገልግሎት ያልሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም

#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት አማልክት ዘበጸጋ ናቸውና
ሐ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ) ።

፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ

፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልሶቻችሁን
👇👇👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ ፣ የተከበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

ምክንያቱም:- #የባህሪ ቅድስና ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው

#ኛ_ "ሁሰት" ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

ምክንያቱም :-ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር
#ለቅዱሳን መላእክት
#ለቅዱሳን መጻሕፍት
#ለቅዱሳን መካናት ይቀጸላልና

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት
ከፍቃደ ሥጋ ብቻ ሳይሆን #ለበረከት_ከእግዚአብሔር ለማሰናከል #ከሰይጣን #ከአላዊያን ነገስታት #ከጠንቆዮች ጭምር ይገጥማቸዋልና

#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

ሐ)በፍጽምነት የሚገኝ ማዕረግ ነው

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው

ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጥዐንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥዐንን

#ኛ_የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት የሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም

#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
ሐ) የአስተብርኮ ስግደት
መ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

#መልስ
#ከእግዚአብሔር ለበረከት
#ከሥጋ ፍቃዳቸው
#ከአላዊያን ነገስታት
#ከጠንቆዮች
#ከሰይጣን

፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#መልስ
#ጸጣኒነት (ጀማሪ)
#ማዕከላዊነት
#ፍጽምነት
ወይም
#ንጽሐ ሥጋ
#ንጽሐ ነፍስ
#ንጽሐ ልቡናም ተብለው ይጠራሉ
፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
#ሊቀ_ነቢያት_ቅዱስ_ሙሴ በዘመኑ ባልነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መለመኑ እና መልስ ማግኘቱ
"፤ ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ #የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም #አስብ።"
#እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው #ክፋት_ራራ።"
(ኦሪት ዘጸአት 32÷14-14)

፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ

#መልስ
#ኢዮር
#ራማ
#ኤረር

፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
"፤ #እግዚአብሔር#በቅዱሳኑ ላይ #ድንቅ_ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።"
(መዝሙረ ዳዊት 67÷35)

"፤#እግዚአብሔር_በጻድቁ_እንደ_ተገለጠ_እወቁ፤ ።"
(መዝሙረ ዳዊት 3(4)÷3)

#መልሶቹ ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት
👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን ::

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
+++ የክርስቶስ የሆኑትን ሊሳደብ አውሬው አፉን ከፈተ::+++ ራእይ13:5

እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው በፍጹም ሐሳባቸው ሲያመልኩ ኖረው በክብር የተጠሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ስለ ክርስቶስ ሲሰደዱ ሲሰደቡ ኖረዋል እንዲሁም ክርስቶስ የፈጸመልንን መዳን እንድንወርስ እኛን ለማገዝ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክትም በልዩ ልዩ ጊዜ በተነሱ ሐሳባቸው በከፋባቸው ሰዎች ሲሰደቡ ኖረዋል፡፡ ዕብ 1፡14 ስድብ የሰይጣን ማንነት አንዱ መገለጫና መታወቂያም ነው፡፡ ሰይጣን በራሱም ይሳደባል የሰውንም አንደበት ተጠቅሞ ይሳደባል፡፡ ዮሐ 8፡44 ማቴ 12፡24-28 የሰይጣን መጠቀሚያ ሆኖ የስድብ ጎተራና ምንጭ መሆን ደግሞ አለመታደል ነው፡፡እንኳን የእግዚአብሔር የሆኑትን ቀርቶ ማንንም እንዳንሳደብ መጽሐፍ ያስተምረናል ያስጠነቅቀናል፡፡ኤፌ 4፡29 ቢያስጠነቅቀንም የእግዚአብሔር የሆኑቱ ቅዱሳንንም ክብራቸውንም የሚመሰክሩ ምእመናንና መምህራንንም ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንንም ጭምር በሚያጸይፍ ስድቦች እየተጥረገረጉ እያየን እየሰማንም ነው፡፡ሰው በእግዚአብሔር ስም ጉባኤ ዘርግቶ ሰዎችን ሰብስቦ የእግዚአብሔር የሆኑትን እንዴት ይሳደባል ?
+++ ቅዱሳንን መሳደብ የሰይጣን አፍና መሣርያ መሆን ነው!!+++
ዘንዶው ዲያብሎስ ዋና መገለጫው ትእቢትና ስድብ ነው፡፡ ኢሳ 14.12 ፈቃዱን ለሚፈጽሙ ሰዎችም የሚሰጠው ታላቅ ሥልጣን ስድብና የስድብ አፍ ነው፡፡ በፍጻሜ ዘመን ለሚገለጠው በክፉ ግብሩ አውሬ ተብሎ ለተጠራው መለያ ኮዱም 666 ለሆነው የዓመጽ ሰው የጥፋት ልጅም የሰጠው ዋና ሥልጣንም መሳደብን
ሆን የሸለመው መሣርያም የመሳደብያና የማጥረግረጊያ አፍ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን ሲገልጽ ‹ታላቅ ነገርንና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው እግዚአብሔርን ለመሳደብ ስሙንና ማደርያውንም በሰማይ የሚያድሩትንም ሊሳደብ አፉን ከፈተ› ብሏል ራእይ 13.5-6፡፡ አውሬው (666 ሐሳዊ መሲህ) ገና አልተገለጠም መንገድ ጠራጊዎቹ ግን በአገራችን በዓለማችን በቤቱም ጭምር ብቅ ብለው አቆጥቁጠው አብበው ጎምርተዋል፡፡ ለእነርሱ ክርስቶስን ማክበር ቅዱሳኑን መሳደብ ማዋረድ በሥዕላቸው መሳለቅ ቅዱሳኑን የሚወዱትን ማሸማቀቅ ነው፡፡
እስቲ የ facebook ገጻቸውን ተመልከቱ በጥፋት መዝገብ በሚያስመዘግቡ ቅዱሳንን በሚያወግዝ የስድብ ናዳ ተጥለቅልቋል፡፡ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ ያገኛል› ማቴ 10፤40 ‹የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል እናንተን የጣለ እኔን ይጥላል› ሉቃ 10፤16 ብሎ ቅዱሳኑን መስማት መቀበል አንዱ የክርስትና መገለጫ እንደሆነ ነገረን፡፡ ነቢያትና ሐዋርያትም የክርስቶስ የሆኑትን መውደድ ማክበር ብጹዓን ቅዱሳን ንጹኃን ብርሃናት እያሉ ማመስገንም ክርስቶሳዊነት መሆኑን አስተማሩን፡፡ ማቴ 13፤43 መዝ 32(33) ፡ 1 መዝ 105(106) ፡3 ማቴ 5፡1-7 ራዕ 14፡ 12-13፡፡ የምናምነውን እመኑ አንላችሁም በምናምነው መሳለቃችሁ የክርስቶስ የሆኑትን በመሳደባችሁ ግን ስለማይጠቅማችሁና የሰይጣን መሣርያ ከመሆን በዘለለ ክብርም ሽልማትም ስለማያሰጣችሁ ብትሰሙም ባትሰሙም ተዉ እንላችኋለን ፡፡እናቱ እመቤታችን ቅዱሳን መላእክትም እንዲሁም ስለክርስቶስ የተገረፉ የተደበደቡ በስለት የተቆረጡ በድንጋይ የተወገሩ በክብር አርፈው በሰማይ እንደሚኖሩ መጽሐፍ አይነግራችሁምን ?ዕብ 11፡34-38 ራዕይ 7፡13-17 ማቴ 13፡ 43 ራዕ 19፡14 ፡፡ ‹ አክብሯቸው› ዘፍ 12፡1-3 ሮሜ 13፡7-8 1ጢሞ 5፡17 ሮሜ 8፡28-30 ፊልጵ 2፡29 1ሳሙ 2፡29-30 የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል ተላልፋችሁ ለምን ትሰድቧችኋላችሁ ? በዚህ ክርስቶስ ይከብራልን? በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እነርሱን መቀበል ሲገባችሁ በስሙ አምነናል ብላችሁ እነርሱን በመሳደባችሁ የባሰ ፍርድን እንደምትቀበሉ አታውቁምን ?ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጆቹን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመንፈስ ልጆቻቸውንም ጭምር እንደ እናንተ ያሉ በሐሳባቸው የተመረዙ በእምነት ነገር የሳቱ ሰዎች እንደሚሰድቧቸው ነግሯቸዋል ፡፡ ማቴ 5፡11 ራዕ 2፡9-10
+++የስድብ መንፈስ ለሞላባት ለዚያች ሴት ግብር አበር አትሁኑ!!+++
ከላይ እንደተመለከትነው የአውሬው (የሐሳዊ መሲህ) የዘንዶው (የዲያብሎስ) አንዱ መታወቂያቸው እግዚአብሔርን ማደርያውን በሰማይ የሚያድሩትን ቅዱሳኑን መሳደብ ነው፡፡ እንደውም ራሱ ያጌጠውና የተሸለመው ቅዱሳኑን በሚያጥረገርግበት ስድቦች ነው፡፡ራዕ 13፡1-2 በአውሬው ራስ ላይ የተቀመጠችው ያች ክፉ ሴትም (ዛሬ ተንቆለጳጵሳ secularism የተባለች ጾምን ጸሎትን ምጽዋትን ማኅበራዊነትን የምትቃወም የምታጠፋ ግላዊነትን ርኩሰትን የምታስፋፋ ) በስድብ የተሞላች ከአቤል ጀምሮ በፈሰሰ የቅዱሳን ደም የሰከረች በስካሯም ምክንያት ከአፏ የሚወጣውን ከብዕሯ የሚፈልቀውን የማታስተውል የርኩሰት ሁሉ እናት ናት ፡፡ ራዕይ 17፡1-18፡፡ እባካችሁ በግብር አትተባበሯት የክርስቶስ የሆኑትን የሥጋ ሥራና ምኞቱን የሰቀሉ ያሸነፉ ድል ነስተው እንባቸው ታብሶ ፀሐይ ክርስቶስን ለብሰውና መስለው በሰማይ ከእርሱ ጋር ያሉትን ወዳጆቹን ልጆቹን አገልጋዮቹን አትስደቧቸው የሰዎችንም እምነት አትፈትኑ፡፡ ‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ › ማቴ 13፡43 እንደሚል ራዕ 7፡9-17 ራዕ 14፡12-13 ራዕ 6፡9
+++ በባርያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም? ዘጸ 12 ፡8 +++
እግዚአብሔር ለአሮንና ለሙሴ እህት ለማርያም የተናገራቸው የተግሣጽ ቃል ነው ፡፡ አሮንና ማርያም እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሯልን በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን ?ብለው ሙሴን ንቀው አቃለውና ተችተው በስድብ ቃል ተናገሩት በዚህም እግዚአብሔር አዘነ ‹ ቃሌን ስሙ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ ወይም በሕልም አናገግረዋለሁ ባርያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ አናግረዋለሁ በምሳሌ አይደለም የእኔን መልክ ያያል በባርያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለምን አልፈራችሁም ?› ብሎም ተናገራቸው ተቆጣቸውም አሮንን በውስጥ ማርያምንም በውጭ በለምጽ አነደዳቸው ዘኁ 12፡1-10 ዛሬም እግዚአብሔር ቃል በቃል ካናገረው ከሙሴ በላይ በማኅፀኗ የተሸከመችው በጀርባዋ ያዘለችው ጡቶቿንም ያጠባችው እመቤታችን እንዲሁም ወንጌልን በዓለም የሰበኩትን ጣዖት አምልኮን ያጠፉትን ለፈጣሪያቸው የታመኑትን ወዳጆቹ ቅዱሳኑን ያውም በስሙ ‹በኢየሱስ አምነናል› እያላችሁ ስትሳደቡ ዝም የሚል ይመስላችኋልን ?
+++ ተሳደቡ ድብም ወጥቶ ሰባበራቸው 2ነገ 2፡24 +++
ነቢዩ ኤልሳዕ የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ነበር ፡፡ ሁሉን ትቶ ያለውን ንብረትና ከብቶች ሽጦ ለድሆችም ሰጥቶ ፈጣሪውን የተከተለ ስለፈጣሪውም ቤትን ሚስትን ልጅን የተወ አባት ነበር፡፡ 1ነገ 19፡20 ነቢዩ ኤልሳዕ በተሰጠው ጸጋ ሙታንን አሥነስቷል 2ነገ 4፡32 ፡፡ በጸሎቱም በሕዝቡ ላይ የመጣውን ቅጣትና የጠላት ቅጥርን የማፍረስ ሤራ መልሷል ፡፡2ነገ 3፡1-27 በዶታይን መንደር ተቀምጦም በሶርያ ቤተመንግስት ይደረግ የነበረውን ያውቅ ነበር 2ነገ 6፡1-23 በሥጋው ከሞተ በኋላም በአጽሙ ሙት
ዕብ 13፥7 "ዋኖቻችሁን አስቡ"

ይህን ኃይለቃል ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስቅዱስ ተቃኝቶ በረድኤተ እግዚአብሔር ተጎብኝቶ ተናግሮታል። አስቀድሞም "የጸኑትን አስቡ" በማለት መክሮናል(ዕብ 12፥3)። ስለምን ማሰብ ማንንስ ማሰብ እንዳለብን ግራ ለገባን ለእኛ ይህን መልእክት ጽፎልናል። ኃጢአት ከሚሠራባቸው መንገዶች አንዱ ሀሳብ ነው። ለዚህ ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኅል እኔ ግን እላችኅለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" በማለት ወደ መግደል የሚወስደውንና በሀሳብ ሊሠራ የሚችለውን ቁጣ የተባለ ኃጢአት የከለከለው(ማቴ 5፥22)። ዋኖችን(ቅዱሳንን) ማሰብ እኩይ ሀሳብን በማሰብ ከመባከን ያድናል። ቅዱስ ጳውሎስን በድንቅ አጠራሩ የጠራ ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ስብከቱ "ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀመዝሙሬ ስም የሚያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም" (ማቴ10፥42) ብሎ የተናገረው ደቀመዛሙርትን (ቅዱሳንን) ማሰብ እንደሚገባን ሲያስረዳን ነው። ሀሳብ ለጽድቅም ለኃጢአትም መነሻ መሆኑን በሚገባ ማስተዋል ያስፈልጋል።" መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል ክፉም ሰው ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል.የተባለውም ለዚሁ ነው(ማቴ12፥35)። ቅዱሳንን በማሰብ ብቻ ግን መዳን አይቻልም። አስቦ በሃይማኖት በምግባር በመምሰል እንጂ።

#ለምን ቅዱሳንን አስቡ ተባልን?

፨በምኞት ተስበን በኃጢአት እንዳንወድቅ። ቅዱሳንን በማሰብ የተጠመደ አእምሮ ያልተገባ ጉዳይን ለማሰብ ጊዜ አይኖረውምና።
፨እንድንመስላቸው። "የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" ዕብ 13፥7።
፨ከቃልኪዳናቸው ለመጠቀም። "ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።" መዝ 88፥3
፨እግዚአብሔርን እንድናስብና እንድናደንቅ። "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67፥35።
፨ቅዱሳኑ ለእግዚአብሔር ያሳዩትን ፍጹም ፍቅርና መገዛት ተመልክተን በጥቂቱ ለእግዚአብሔር መገዛት ያልቻለ እኛነታችንን ወቅሰን በንስሐ እንድንመለስ። "ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ።" ኢሳ 51፥2
፨በባዶነታችን የምንታበይ እኛ ትሕትናን እንድንማር። አበ ብዙኃን ሥርወ ሃይማኖት የተባለ አብርሃም አመድና ትቢያ ነኝ ካለ፤ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም ካለ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ጭንጋፍ ነኝ ካለ (ዘፍ 18፥27፤መዝ 21፥6 ፤1ኛ ቆሮ 15፥8) እኛ ማንነን እንበል?

#ቅዱሳንን እንዴት እናስብ?

፨በሚከብሩበት ዕለት ታቦታቸውን በማንገሥ።
፨ገድላቸውን፣ተአምራታቸውን በማንበብ።
፨በስማቸው ነዳያንን በመመጽወት።
፨በስማቸው በታነጸው ቤተክርስቲያን መባ (ዕጣን፣ጣፍ፣ዘቢብ፣ዣንጥላ፣መጋረጃ) በመስጠት።
፨በመንፈሳዊ ዝማሬ ቅዱሳንን አስበን፣ መስለን ስሙን ለመቀደስ መንግሥቱን ለመውረስ ልዑል አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን።

አሜን።

በወንድችማን #ኢዮብ ክንፍ

በአማላጅ እና በመማጸኛ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ?

ክፍል -1

አማላጅ ህልውና ያለው እኔባይ ስለ አንድ አካል ለሌላ አካል መለመን ፣ መማጸንና ማስታረቅ የሚችል ነው።
መማጸኛ ህልውና ያለው ሊሆንም ላይሆንም የሚችል ነው። ለምሳሌ ስም ፣ ቅዱስ መስቀል ፣ ስጋ ወደሙ ፣ ከተሞች የመሳሰሉት ህልውና የሌላቸው መማጸኛ ሲሆኑ እግዚአብሔር (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) እና ቅዱሳን ደግሞ ህልውና ያላቸው መማጸኛ ናቸው።

መማጸኛን ተጠቅሞ መጸለይ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ነው። ታዲያ መማጸኛ ማለት አማላጅ ማለት አይደለም። ለምሳሌ አንድን ሰው "በእናትህ" ብለን ብንለምነው የሰውዬውን እናት መማጸኛ አድርገን ለመንን እንጂ እሳቸው አማላጅ ናቸው ማለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስም ብዙ መማጸኛዎችን ተጠቅመው የተጸለዩ ጸሎቶችና መማጸኛዎችን መመልከት እንችላለን። ለአብነትም ጥቂቶቹን እነሆ
❖ መዝ 131(132):10 "ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ ብለህ የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ።"
በዚህ ክፍል ላይ የቅዱስ ዳዊት ስም መማጸኛ ሆኖ ቀርቧል። የዳዊት ስም መማጸኛ እንጂ አማላጅ አይደለም።
❖ ኢሳ 37:35 " ስለ እኔም ስለ ባርያዬ ስለ ዳዊትም ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።"
እግዚአብሔር ራሱንና ዳዊትን መማጸኛ አድርጎ አቅርቧል። ስለዚህ አማላጅ አይደሉም።
❖ ዳን 9:17 "አሁንም አምላካችን ሆይ የባርያህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ በፈረሰው በመቅደስህ ላይ ስለአንተ ስትል ፊትህን አብራ።"
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል ሲጸልይ እግዚአብሔርን መማጸኛ አድርጎ ነው። "ስለ አንተ" ብሎ። በመሆኑም ስመ እግዚአብሔርን አልያም አምላክን መማጸኛ ልናደርገው እንችላለን። ነገር ግን አማላጅ አንለውም። ጌታችን አምላካችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መማጸኛ እንጂ አማላጅ አይደለም።
❖ ዮሀ 16:26 "በዚያ ቀን በስሜ ትለምናላችሁ። እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም።"
በግልፅ እንደሚነግረን ከትንሳኤና ከዕርገት በኋላ ስሙን መማጸኛ አድርገን እንደምንለምን እርሱም አማላጅ እንዳልሆነ ነግሮናል። ቅዱሳንን ግን እንደ መማጸኛም እንደ አማላጅም ልንጠቀማቸው እንችላለን። ማማለድ ከፈጣሪ ያገኙት ጸጋ ነውና።
ስለዚህ ስለ አንተ ፣ ስለ እናትህ ፣ ሰለ ቅዱሳንህ ፣ ስለ ፈሰሰው ደምህ ፣ ስለ ተቆረሰው ስጋህ ፣ ስለ ቅዱስ መስቀልህ ... ብለን መማጸኛዎችን በመጠቀም ስንጸልይ መማጸኛዎቹን አማላጅ አያሰኛቸውም።

-ይቀጥላል-

አዘጋጅ - አቤኔዘር ማሙሸት
ኤዲተር - ዳዊት ክብሩ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
 ብዙዎችን ደስ ያሰኘን ልደት

የእግዚኃርያ እና የፀጋ ዘ አብ ቤት ዛሬ በደስታ ተመልታለች ምክንያቱም ዛሬ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚያበራ አንድ ሲሆን ብዙ ብቸኛ ሲሆን ከሰው አልፎ ለእልፍ አህላፍ መላእክት ወንድማቸው የሚሆን ታናሽ ብላቴና ሳለ ለብዙዎች መካር የሚሆን ደገኛ ልጅን ወልደዋልና ነው :: ቤታቸው አስቀድመው ባለመውለዳቸው ምክንያት እንደ ኃጢያተኛ ቆጥሮ መጠቆሚያ ባደረጋቸው ሰዎች እና እጅግ በሚያከብሯቸው እንዲሁም በሚወዷቸው ሰዎች ተጨናንቃለች ::ዓለም እንዲ አይደለች?::
ይህ የፍሰሐ ጺዮን መወለድ ዛሬ ለእግዚአርያና ለፀጋ ዘአብ የደስ ቀን ቢሆንም ግን ዝም ተብሎ የተገኘ ቀን አይደለም በጾም በጸሎትና በምጽዋት የተገኘ የደስታ ቀን ነው በይበልጥ ለእናታችን ለእግዚኃርያ ያሳለፋችሁ ልጅ አልባ የትዳር ጊዜ ከባድ ነበር ዛሬ ሃያ ልጆችን ወልደው ግን በትዳር መኖር የከበዳቸው ብዙች ናቸው እናታችን ያልወለደች መካን እንደ በቅሎ የማትወልድ እያሉ ሲያሟት ሲሰድቧ እንኳ ትዳር መፍታትን እንደ መፍትሄ አልቆጠረችም ምን አልባት ይህን ስድብና ነቀፋ ችላ በመልካምነት እና በትእግስት እግዚአብሔርን ባትጠብቅ ኖሮ አባታችንን ተክለ ሃይማኖትን የሚያክሉ አባት ባላገኘን ነበር :: የሚገርመው እርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይታ እንኳን ያለቀሰችበት ጊዜ ነበር ስለዚህ ይን በይበልጥ ለእናታችን ልዮ ነው::
ልደት የሕይወት መግቢያ በር ነው በመጽሐፍ ቅዱስ በልደታቸው (በመወለዳቸው ብዙዎችን ደስ ያሰኙ ቅዱሳን ሰዎችእንዳሉ ይነግረናል ለምሳሌ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን መመልከት እንችላለን በቅዱሳን ሰዎች መወለድ ከወላጆቻቸው በተጨማሪ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆኑ ሁሉ ደስ ይሰኙባቸዋል ::በአባታችን በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ውልደት በመጀመሪያ ደረጃ የተደሰው እግዚአብሔር አምላክ ነው ምክንያቱም
"፤ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል" ..ና ነው ::" ሉቃ1÷17
ከእግዚአብሔር በመቀጠል በመወለዱ ደስ የተሰኘችሁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች ክብሯን ዘላለማዊ ድንግልናዋን አማላጅነቷን መላዲተ አምላክነቷን በመናፍቃን ፊት ይመሰክራልና አንድም ፍሰሀ ጺዮን ነውና የጺዮን የእመቤታችን ደስታ የሚሆን ስመ ትርጓሜ አለውና ነው ከእመቤታችን ቀጥሎ በመወለዱ የአህላፍ ቅዱሳን የደስታ ምንጭ ነው ሰው ከሃይማኖት በአፋ ሲሆን ከምግባር የተጣመመ ሲሆን በወንጌል መረብነት አጥምዶ ወደ ንሰሐ የሚመልስ ካህን ነውና ቅዱሳን መላእክት በዚህ ስራው እጅግ ሃሴትን ስለሚያደርጉ ነው ለዚህ ማሳያ"፤ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። " ሉቃ 15÷10 እንዲል ጻድቁ በሚመልሳቸው ኃጢያን መላእክተ ይደሰታሉ ሌላው በመወለዱ ደስ የሚላቸው ቅዱሳን ሰዎች ናቸው በሃይማኖት በምግባር በገድል በትሩፋት የሚመሰላቸውን ወንድም አግኝተዋልና ደስ ይላቸል :: በአንጻሩ ጥቂት ከፉ ሰዎች በቅዱሳን ሰዎች ውልደት ይበሳጫሉ ይከፋሉ የዲያቢሎስ የግብ ልጆቹ ናቸውና ለዚህ ነው "በመወለዱ ሁሉም ሰዎች ደስ ይላቸዋል" ተብሎ ሳይሆን "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" ተብሎ ብቻ የተጻፈለፈን ሉቃ1÷14 በቅዱሳን ዉልደት ለቅዱሳን ብቻ ሳይሆን ለሕዝብም የደስታ ምንጭ ነው:: "፤ ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል። "መጽሐፈ ምሳሌ 29÷ 2 እግዚአብሔር አምላክ የሚወለዱ ቅዱሳንን ቁጥር በእጅጉ አብዝቶ ከማልቀስ ይሰውረን :: አሜን

......ይቆየን........

ከጻድቁ አባታችን እረድኤት እና በረከትን ይክፈለን::አሜን!

ተርቢኖስ ሰብስቤ (ኃይለ ማርያም)
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ

ቅድስት ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
:ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው???
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::

በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
*********************************
አካላት
*
1) እራሷ (ሰንበት )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ
በኩረ በዓላት ናት :- የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና
ዓለም የተገኘባት
ወልድ ሰው የሆነባት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::

2) እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: ሉቃ 1÷26
3) ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :- ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና እረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) መንግስተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች ::
" ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እረፍት ይባላል :- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና እረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የእረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን
ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::

ማሳሰቢያ
********
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል ::
አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል ::
በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል:: በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::

.........ይቆየን...........

በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ለም ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ዘስጋ እንጅ መምህረ እስራኤል ዘነፍስ አይደለም፡ ክርስትና አለቃና ባሪያን አንድ እንደምታደርግ አያውቅምና የጎደለውን ፍለጋ መጣ ገላ 3 26፡፡ ያለውን ሳይሆን ያጣውን የሞላለትን ሳይሆን የጎደለውን ፍለጋ መጣ፡፡ዕውቀት ብቻውን ምሉእ አያደርግም፡፡ አለቅነትም ቢሆን ገደብ አለው፡፡የሕይወቱን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አንድ ክርስቶስ ብቻ ነውና ጎደሎነቱን አምኖ መጣ፡፡ የሚጎድለኝ ምንድን ነው? ብሎ እንደጠየቀው እንደዚያ ሰው ጎደሎን ማመን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው ማቴ 18 21፡፡ በአብዛኞቻችን የሚታየውና ክርስትናችንን አገልግሎታችንን ቤተክርስትያናችንን እየተፈታተነ ያለ ችግር ጎደሎዎቻችንን አለማወቅና ምሉእ ነኝ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምንም እንዳልሆኑ አውቆ ራስን ለክርስቶስ፣ ራስን ለመርዐተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሳልፎ መስጠት ምንኛ መታደል ነው!
አልዕሎ ልቡና (ልቡናንን ከፍ ማድረግ)
ኒቆዲሞስ ይዞ የመጣው ስጋዊ ህዋሳቱን ነበር፡፡ጌታችን ግን አመጣጡ ለመልካም እንደሆነ አውቆ ለስጋዊ ዕውቀት እጅግ የሚከብደውን ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ መጀመሪያ ይህን ምስጢር ለመቀበል አልተቻለውም ነበር፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ምስጢሩን ፍንትው አድርጎ ሲያብራራለት ግን ልቡናው ይህን ምስጢር ለመቀበል ከፍ ከፍ አለ፡፡ ምስጢራትን ለመቀበል ልቦናን ከፍ ከፍ ማድረግ ይገባል፡፡የእምነታች መሰረት በስጋ ዓይን ማየት በስጋ ጆሮ መስማት በስጋ እጅ መዳሰስ ብቻ ከሆነ ልክ እንደ እንቦይ ካብ ሆነ ማለት ነው፡፡ ትንሽ ነፋስ ትንሽ ተፅዕኖ ሲያርፍበት መፈራረስ መናድ ይጀምራል፡፡ ኒቆዲሞስም ምስጢሩ መጀመሪያ ቢከብደውም ቅሉ በኋላ ላይ ልቦናውን ወደ ሰማያዊው ምስጢር ከፍ ስላደረገ ምስጢሩ ተገለጸለት፡፡ ቤተክርስቲያንን ሲፈታተኗትና እየተፈታተኗት ያሉ አካላት በሙሉ የስህተታቸው ምንጭ እንደ ግያዝ ከአካባቢያቸውና ከምናየው አካል (ቁሳዊ ዓለም) ውጭ መመልከት አለመቻል ነው 2ነገ 6- 17፡፡ ለዚህም ነው ካህኑ በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ የቁርባኑ ምስጢር እንዲገለጽልን «አልዕሉ አልባቢክሙ (ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ)» የሚሉን፡፡
የእውነት ምስክር (ስምዐ ጽድቅ) መሆን
ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሃፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡እውነትንና ፀሐይን ፈርቶ የትም መድረስ አይቻልም፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ በመሪዎች ፊት በታላላቅ ሰዎች ፊት እውነትን መመስከር ክርስትናችን የሚያስገድደን ቁም ነገር ነው ሉቃ 12 8፡፡ ቤተክርስቲያን ሰማዕታት እያለች የምትዘክራቸው በሙሉ ለእውነት ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳንን ነው፡፡በፍርሐትና በሀፍረት በይሉኝታና በሀዘኔታ እውነትን አለመመስከር በክርስቶስ ፊት ያስጠይቃል እንጅ አያስመሰግንም ማቴ 10 32፡፡ «ለእውነት እንጅ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልም» እንዳለ 2ቆር 13 8፡፡
ትግሃ ሌሊት
እንደ ሌሊት ለመንፈሳዊ ህሊና ለተመስጦ የሚመች ጊዜ የለም ፡፡ ቀን ለስጋ ሲራወጥ የነበረ አካልና መንፈስ ሌሊቱን ለነፍስ በምገዛት ስጋውን መጎሰም አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኑን በቅዳሴ ሌሊቱን ደግሞ በማኅሌት በሰዓታት በኪዳን እግዚአብሔርን ስታምሰግን የምታድረው፡፡ ቅዱስ ማር ይስሐቅ ሌሊትስ ጌታን ለማመስገን የተፈጠረ ድንቅ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያቱን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሏቸዋል ማቴ 26፡፡ አሁንም ቤተክርስቲያን እንደ ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ለኪዳን ለማኅሌት ለጸሎት የሚመጣን ምዕመን ትፈልጋለች፡፡
እስከ መጨረሻ መጽናት
ጌታችንን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ሺህ ሕዝብ ቢከተለውም እስከመስቀሉ አብረውት የነበሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የተወሰነው ሕዝብ ቀድሞም የተከተለው ለምግበ ስጋ ነበርና ቀራንዮ ላይ አልተገኘም፡፡ ቀራንዮ ላይ ምግበ ነፍስ እንጅ ምግበ ስጋ የለም፡፡ ሌሎችም በቤተሰብ በሀብት በፍርሀት ምክንያትነት መስቀሉ ስር አልተገኙም፡፡ ምንም እንኳ ኒቆዲሞስ በስድስት ሰዐት ባይገኝም የክርስቶስ ስጋ ከነፍሱ በምትለይበት ሰዐት ክርስቶስን ከመስቀል አውርዶ ለሐዲስ መቃብር ያበቃው እሱ ነበር፡፡ በዚህ የመከራ ሰዐት ከዮሐንስና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ውጭ ማንም እንዳልነበረ መጻሕፍት ከገለጹልን በኋላ የምናገኛቸው የቁርጥ ቀን ልጆች ዮሴፍንና ኒቆዲሞስን ነው፡፡ ይህም ፈተናውን ሁሉ ተቋቁሞ እስከ መጨረሻው ለመጽናቱ ምስክር ነው፡፡ በክርስትና ሕይወታችንም የምናያቸው ነገሮች ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡በምቹ ጊዜ የምናገለግል ፈተና ሲመጣ ጨርቃችን(አገልግሎታችንን) ጥለን የምንሮጥ ማር 14-51 ሰበብ አስባብ ፈልገን የምናፈገፍግ ብዙዎች ነን፡፡ ዕውቀት ጣዖት ሆኖበት መሀል መንገድ የቀረው ሀብት ጣዖት ሆኖበት ሩጫ ያቋረጠውን ጊዜ ጣዖት ሆኖበት ቅዳሴ የሚቀረውን ቆጥረን እንጨርሰው ይሆን? ጌታ በትምህርቱ «ለዘአዝለፈ ትዕግስቶ ውእቱ ይድኅን -እስከ መጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል » እንዳለ ማቴ 2413፡፡ ክርስትና ለጀመሩት ሳይሆን ለጨረሱት ለወጠኑት ሳይሆን ለፈጸሙት የድል አክሊል የምትሰጥ መንገድ እንጅ የመሮጫ መሙን ጠበበን ሩጫው ረዘመብን ለሚሉ ዴማሶች ቦታ የላትም፡፡2ጢሞ 4-9
በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡ የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ አሜን 👉❤️

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-ማህበረ ቅዱሳን መካነ ድህር
ዓውደ ምህረት የእናንተ
አስተያየት ጥቆማና የከበረ ሀሳብዎን በዚህ ይስደዱልን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
፩) ሰማዕት ‹‹ሰምዐ› › ከሚል የግእዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም
ያየነውን፣ የሰማነውን መመስክር መቻል እንደሆነ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ
መጽሐፈ ስዋስወ ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ 671 ይነግረናል፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹እኔ ለእውነት ለመመስከር
መጥቻለሁ›› በማለት እውነትን እንድንመሰክር አብነት ሆኖናል /
ዮሐ.18፥37/፡፡
ሰማዕትነት በሃይማኖታዊ ትርጉሙ ስንመለከተው ስለ እግዚአብሔር፣
ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ ሃይማኖታቸው በእውነት
በመመስከራቸው ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት፣
እግራቸውን ለሰንሰለት፣ አንገታቸውን ለስለት አሳልፈው ለሰጡ፤
በድንጊያ ተወግረው በመንኮራኩር ተፈጭተው በጦር ተወግተው
አልያም በግዞትና በስደት በዱር በገደል ተንከራተው ለዐረፉ ቅዱሳን
አባቶችና ቅዱሳት እናቶች የሚሰጥና ተጋድሎአቸውን ጠቅለል አድርጎ
የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው እመቤታችንን
ባመሰገነበት ድርሳኑ “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት
ናቁ፤ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ስለ መንግሥተ
ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ” በማለት የሰማዕታት ተጋድሎአቸው
መራራ እንደሆነ ገልጿል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)
ጌታችን ‹‹በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት
ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡ በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ
ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ›› ሲል ስለ
ሃይማኖታችን የምንመሰክረው ከሰማዕትነት ጋር ያለውን ቁርኝት
ነግሮናል፡፡ /ማቴ.10፥32-33/፡፡ ከዚህ አንጻር ያለ ክርስትና
ሰማዕትነት ያለ ሰማዕትነት ክርስትና የለም ማለት ነው፡፡
ሰማዕትነት መመስከር ከሆነ እንዴት ነውየምንመሰክረው የሚል ጥያቄ
ማንሳታችን አይቀርም፡፡ ለዚህ ጥያቄያችን መልስ የምናገኝባቸው
ሦስት የመመስከሪያ መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
በአንደበታችን
እግዚአብሔር አምላካችን አንደበት የሰጠን እውነትን በመመስከር
ለክብር እንድንበቃበት እንጂ ውሸት በመናገር አምላካችንን
እንድናሳዝንበት አይደለም፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ‹‹አንደበቱን
ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው
ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው›› በማለት በአንደበታችን
እውነትን እንድንመሰክርበት ይመክረናል /ያዕ. 1$26/፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉ መስክሮም
ይድናልና›› እያለ እውነትን መመስከር ለመጽደቅና ለመዳን ወሳኝ
ጉዳይ ነው ይለናል /ሮሜ 10፥10/፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን
በዓለም ዞረው ያስተማሩት በአንደበት መመስከር ያለውን ሰማያዊ
ዋጋ ስለተረዱ ነው፡፡ አንደበታችን እውነትን በመመስከር ለሰማዕትነት
የሚያበቃን መሆኑን ተገንዝበን አንደበታችን ሰዎችን ከማማት፤
ያለሥራቸው ስም ከመስጠት ሊቆጠብ ይገባዋል፡፡
በሕይወታችን
በሕይወት መመስከር ያላመኑትን ወደ ማመን የሚያመጣ ትልቅ
መሣሪያ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መመሪያችን ነው፡፡
በሕይወት መመስከር ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትን
ሕግጋትና ትእዛዛት በተግባር ለውጦ ማሳየት መቻል ነው፡፡ ለስም
አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በተራራ ላይ ስብከቱ ያስተማረን ‹‹መልካሙን ሥራችሁን
አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ›› በማለት ነው /ማቴ.5፥16/፡፡ በቅዱሳን
የሕይወት ምስክርነት እግዚአብሔር ታይቷል፡፡ በእኛ ሕይወት
እግዚአብሔር ታይቷል ወይ ብለን ሁላችን ራሳችንን ልንመረምር
ያስፈልጋል፡፡
በአላውያን ፊት
ከባዱና ታላቁ ሰማዕትነት በአላውያን ነገሥታትና እግዚአብሔርን
በማያምኑ ሰዎች ፊት ያመኑትን እምነት ሳይፈሩ መመስከር መቻል
ነው፡፡ አላውያን ነገሥታት የእግዚአብሔርን አምላክነትና ፈጣሪነት
ስለማያምኑ ሰማዕታትን ያሰቃያሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሰማዕት
የሚሆኑት ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ሰማያዊ ክብር ስለሚያስቡ ወደ
እሳት ቢጣሉ፣ በሰይፍ ቢቆረጡ፣ በድንጋይ ቢወገሩ ምንም
አይመስላቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት የኖሩ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ
የተፈጸመው ግፍና ስቃይ ለዚህ አባባላችን መሳያ ነው፡፡ ቀዳሜ
ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ እውነትን በሐሰት ለውጠው
የእግዚአብሔርን አምላክነት በመካድ በሥልጣናቸው ተመክተው
ለነበሩ አይሁድ ያላንዳች ፍርሃት ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ
አምላክነት በመመስከሩ በድንጋይ ሲወግሩት፣ ዓይናቸው በኃጢአት
ለታወረ አይሁድ ‹‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› በማለት
ለወጋሪዎቹ ምሕረትን ለምኗል /የሐዋ. ሥራ 7፥60/፡፡
የሰማዕትነት ዓይነቶች
የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሰማዕትነት ዓይነቶች ሁለት ናቸው
ይሉናል፤ ሲተነትኑትም ሰማዕት ዘእንበለ ደም (ደማቸውን ሳያፈሱ
ሰማዕት የሆኑ) እና ደመ ሰማዕታት (ደማቸውን በማፍሰስ ሰማዕት
የሆኑ) በማለት በሁለት አበይት ክፍሎች መድበውታል፡፡ እነዚህ
ብያኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ሰማዕትነትን ከአፈጻጸም አንጻር
በሦስት መሠረታዊ ቀለሞች ይመስሉታል፡፡ (ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሐመረ
ተዋሕዶ፤ ገጽ 130 ነሐሴ 2002 ዓ.ም.)
አረንጓዴ ሰማዕትነት
እንደማንኛውም ሰው በከተማ እየኖሩ ዓለምን ለማሸነፍ የሚጥሩ
ከራሳቸው ጋር ታግለው ዲያብሎስን ድል ማድረግ የቻሉ አረንጓዴ
ሰማዕታት ይባላሉ፡፡ የሚበላ፣ የሚጠጣ ሳያጡ ሁሉን የሰጣቸውን
ፈጣሪ እያመሰገኑ ራሳቸውን በጾምና በጸሎት በመወሰን ያጡ የተቸገሩ
ወገኖቻቸውን ለመርዳት የማይሰለቹ የጽድቅ ሥራ በመሥራት
የሚያገኙትን ሰማያዊ ጸጋ በማሰብ የሚደሰቱ ናቸው፡፡ ከዚህ መልካም
ሥራቸው የተነሣ ስድብ፣ ነቀፌታ፣ ስደት፣ እስራት ሲደርስባቸው
መከራውን ሁሉ በአኮቴት (በምስጋና) ተቀብለው ፈጣሪያቸውን
የሚያመሰግኑ ናቸው፡፡
ነጭ ሰማዕትነት
ይህን ዓለም አሸንፈው ግርማ ሌሊትን ጸብአ አጋንንትን ታግሰው በዱር
በገደል የኖሩ አባቶቻችን ሕይወት የምናይበት ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ማንም
ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ትቶ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን
አይችልም›› ብሎ የተናገረውን ቃል በተግባር ያሳዩትን የሚወክል
ነው /ሉቃ 14$27/፡፡ ይህ የሰማዕትነት ጥሪ ለሁላችንም የቀረበ
እንደሆነ እንድንረዳው ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› ብሎናል /ማቴ. 16፥24/፡፡
ስለሆነም ራሳችንን ከውስጣዊ ፈተና ለማዳንና ከልቦና ኃጢአት
ለመጠበቅ በጾም፣ በጸሎት፣ በትኅርምት በትሕትና ጸንተን በመዓልትና
በሌሊት እግዚአብሔርን እያመሰገን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡
ቀይ ሰማዕትነት
ይህ ሰማዕትነት በደም የሚመጣ የሰማዕትነት ዓይነት ነው፡፡
እግዚአብሔርን በማምለካችን፣ ቅዱሳንን በማክበራችን፣ ማተብ
በማሠራችንና በአጠቃላይ ክርስቲያን በመሆናችን የሚመጣብንን
መከራና ስቃይ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር በመታገስ በሰይፍ ተቀልተን፤
በመንኮራኩር ተፈጭተን፤ ወደ እቶን እሳት ተጥለን የሕይወት
መስዋዕትነት በመክፈል የምናገኘው ክብር ነው፡፡ ይሔ ሰማዕትነት
የመጨረሻ ደረጃ ነው፡፡ (ያረጋል አበጋዝና አሉላ ጥላሁን፤ ነገረ
ቅዱሳን፤ ገጽ 26-30፤ 1997 ዓ.ም.)

፪ ) ቢቻላት ትከናነብ ሳይሆን በግዴታ መከናነብ እንዳለባት ነው ሐዋርያው የተናገረው ጸጉርን ለመሸፋፈን መቻል አለ መቻል ብሎ ነገር የለም ጸጉሯን መሸፈን የማትችል ወይም የሚያዳግታት ሴት የለችምና ምን አልባት አላማዋ መታየት መገላለጥ መፈለግ ካልሆነ በቀር

"፤ በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን? "

ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ዋኖቻችሁን አስቡ። ዕብ 13:7

ይህን ኃይለ ቃል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች በላከው መልዕክቱ ያሰፈረው ሲሆን ፍጻሜው ግን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለኛ ለምዕመናን ሁሉ ነው።

ዋኖቻችን እነማን ናቸው? በአጭር ቃል ሐዋርያው «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁ» በማለት መልሶልናል። እነርሱም ከቀደምት አበው ጀምሮ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ቅዱሳን ናቸው።

ቅዱሳንን ማሰብ ለምን ይጠቅማል?

1 ከሀሳብ ኃጢአት እንጠበቃለን። ኃጢአት በሀሳብ ይጸነሳል። በነቢብ (በመናገር) ደግሞ ይወለዳል ኋላም በተግባር ሲፈጸም ይጎለብታል ከእግዚአብሔር ይጣላል። ሰው ቅዱሳንን በማሰብ ጊዜውን የሚያሳልፍ ከሆነ ኃጢአትን ለማሰብ ጊዜ አይኖረውም።

2 ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት እናገኛለን። ጠቢቡ ሰለሞን በምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 7 ላይ «የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።» እንዲል ።

3 ቅዱሳንን አርአያችን በማድረግ እነርሱን ለመምሰል እንጥራለን። ፈጣሪያችን በኦሪቱ «እኔ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።» እና በሐዲስ ኪዳንም «የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ ፍጹማን ሁኑ።» በማለት የቅድስና ጥሪን ለሰው ልጆች አቅርቧል። ሰው ቅዱስ መሆን የማይችል ቢሆን ይህንን ጥሪ አምላካችን ባላቀረበ ነበር። ነገር ግን ሰዎች ይህንን የቅድስና ጥሪ ተቀብለው በጽድቅ በቅድስናና በንጽሕና መኖር እንደሚቻል ያሳዩን ቅዱሳን ናቸው። ይህንን የቅድስና ጥሪን ተቀብለው በኑሮአቸው ቅዱሳን የሆኑትን ስንመልከት ለጽድቅ ለትሩፋት እንነሳለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «እኔ ክርስቶስን እንድመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።» 1ቆሮ 11:1 ላይ እንዳለን እነርሱን በማሰብ የበምግባር በሃይማኖት እነርሱን ለመምሰለል እንጥራለን። ጥረታችንም ተሳክቶ ለቅድስና እንበቃለን። ኋላም እነርሱ የገቡበት እንገባለን። እነርሱ የወረሱትን እንወርሳለን።

4 በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነትና ተስፋ እንዲጠነክር ያደርጋል። ለምሳሌ ልጅ ባለመውለድ እየተፈተኑ ያሉ ሰዎች አብርሃምና ሳራን በማሰብ እነርሱን ያልተወ በእርጅናቸው ወራት ልጅ የሰጠ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በእምነት ይጸናሉ።

እንዴት እናስብ?

1 ገድላቸውንና ዜና ሕይወታቸውን በማንበብ። “ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ።” ኢሳ 51፥2 እነርሱ በሥጋ ከተለዩን ብዙ ዓመታት ነውና እንደምን ልናያቸው እንችላለን? አብርሃምን በእምነት መነጽር ለማየት ገድለ አብርሃምን ማንበብ ያስፈልጋል።

2 በዓላቸው በማክበር በስማቸው ለመታሰቢያ በታነጸ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ማስቀደስ፣ መሳለም፣ ጠበል መጠጣት፣ እጣንና ጧፍ በመስጠት ማሰብ ያስፈልጋል።

3 በስማቸው ዝክርን በመዘከር (መታሰቢያን በማድረግ) ነድያንን ማብላትና ማጠጣት። ማቴ 10:41

በመጨረሻም ሐዋርያው እንዳለ ቅዱሳኑን አስበን የነሱን አሰረ ፍኖት ተከትለን በምግባር በሃይማኖት እንድንመስላቸው አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ፍቅሯን በልባችን ጧሟን በአንደበታችን ታኑርልን። ቅዱስ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤታቸውን በረከታቸውን ያሳድሩብን።

ይቆየን።

(አቤኔዘር ወልደ ተክለሃይማኖት)

ሰኔ 04 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
+++ ታማልደናለች +++

ሐዋርያው ስለ ቅዱሳን “ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።” (2ኛ ቆሮ 9፥14) በማለት የተናገረውን ያነበበ የአምላክ እናት ምልጃን እንዴት ያስተባብላል?
+++++
እመቤታችን የነገሥታቱን ንጉሥ የጌቶቹን ጌታ የኃያላኑን ኃያል የጸጋ አማልክት የተባሉ የቅዱሳኑን አምላክ እርሱን የወለደች ውሆችን በእፍኙ የሠፈረ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ የእርሱ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ናትና እንወዳታለን እናከብራታለን ።(ኢሳ 40:12 ራእይ 19:16 1ጢሞ 6:15) ጠላት የክርስቶስ እናቱ የድንግል ማርያም ወዳጆችን በባሕር አሸዋ በተመሰለ በዚህ ዓለም እንደ አሸን ፈልተው በተበተኑ እኩያን ሰዎች ልቡና አድሮ እንደሚዋጋቸው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል። (ራእይ 12:17) ጥላቻ ደረጃ አለው ዲያብሎስ ሁሉንም የሰው ዘር ይጠላል ከፍ ሲልም ቅዱሳንን አምርሮ ይጠላል ለድንግል ማርያም ያለው ጥላቻ ግን ወሰን ገደብና ጥግ የለውም ። የጥላቻው መገለጫ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ደግሞ ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣትን ምሉዕ ጸጋ ማስተባበል ማጠራጠር ማስካድና እርሷንም መሣርያ ባደረጋቸው ሰዎች አንደበት ማሰደብ ነው:: የምልጃዋን ጣዕም የቀመሰ ደግሞ ስለ አማላጅነቷ ከሕይወቱ በላይ ምስክር የለውምና እንዲህ ይላል :-
++ ታማልጅን ዘንድ ላንቺ ይገባል ++
የእመቤታችንን አማላጅነት መቃወም እግዚአብሔርን መቃወም መጻሕፍትንም ማስተባበል ነው:: ለምን ? ቢሉ
፩. በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዎች መማለድ መለመን ታላቅ ጸጋ ነው :: የእግዚአብሔር ጸጋ ያልተሰጠው ያልበዛለት በእርሱ ፊት ቆሞ እርሱን ሊለምን አይችልምና :: አባታችን አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ቢያገኝ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዶምና ለገሞራ እንደማለደ መጽሐፍ ይመሰክራል ። (ዘፍ 18:18-29) ሊቀ ነቢያት ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለምኖላቸዋል ። (ዘጸ 32:1-32) ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ይህን ታሪክ አውስቶ ሲናገር "እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ ባይቆም (ባይለምን) ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።" (መዝ 105(106)÷23) ማለቱ ሐሳባችንን ያጠነክርልናል:: የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሉዕ ጸጋን አግኝታለች:: ከሰማያውያኑ ቅዱስ ገብርኤል ከምድራውያኑ ቅድስት ኤልሳቤት "ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ ።" (ሉቃ 1÷30:43) ብለው እንደመሠከሩ:: ድንግል ማርያም ያልተሰጣት የቀረባት ምን ጸጋ አለ? እርስዋ አታማልድም የሚሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በመቃወም ክብር ይግባትና "የሚጎድላት ጸጋ አለ" እያሉ እንደሆነ እንገንዘብ:: ይህ ደግሞ ራሳቸው ምን ያህል ከጸጋው እንደተራቆቱ ያሳያል:: ከቅዱሳን ሁሉ ክብር የማርያም ክብር ይበልጣልና ::
፪. በሐዲስ ኪዳን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማማለድን ጸጋ ለቅዱሳን እንደሰጠ ሐዋርያው ሲመሠክር "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ (ህልው ሆኖ) ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር :: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ።" 2ቆሮ 5÷17-20 ብሏል:: ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ በሙሉ ለእመቤታችን ተሰጥቷታል ለእርሷ የተሰጠ ጸጋ ግን ለሐዋርያት አልተሰጠም:: ከፍጥረታት ወገን " ጸጋን የተሞላሽ" የተባለ ከእርሷ ሌላ ማን አለ? ታዲያ ማማለድ ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ ተልእኮም ከሆነ ድንግል ማርያም ደግሞ በጸጋ የተሞላች ከሆነች "አታማልድም" የሚሉ አያፍሩምን? የቅዱሳን ሐዋርያትን የማማለድ ጸጋ መጽሐፍ እየነገረን የእርስዋን ማማለድ ለመቀበል መቸገር ምን ይሉታል?
፫ . በሐዲስ ኪዳን ስለ ክርስቶስ በዓላውያን ነገሥታት የታረዱ በሰማይ በክብር የተገለጡ ሰማዕታት በክፉዎች ላይ እንደለመኑባቸው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል ። (ራእይ 6÷9)ስለ ልጇ "በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ።" (ሉቃ2÷35) የተባለች የሰማዕታት እናት ድንግል ማርያም ሰይጣን ክፉ ዓለም የሥጋ ፈቃድ ለሚፈትናቸው ክርስቲያኖች አትማልድምን ?
፬. ደፋሮች በድፍረትና በትእቢት በመናቅም እንደ ተራ ታሪክ ቢመለከቱትም ቅዱስ ዮሐንስ "የምልክቶች መጀመሪያ ጌታችንም ክብሩን የገለጠበት" ብሎ በመሠከረበት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ልጅዋን ወዳጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ለምና ተራውን ውሃ ወደሚጣፍጥ ወይን እንዲለወጥ አድርጋለች ። (ዮሐ ፪÷፩-፲፪)ክብርና ጸጋዋ ያልተገለጠላቸው ሰዎች የእርሷን የማማለድ ጸጋ እያስተባበሉ "እንጸልይላችሁ" "እናድናችሁ" "እንፈውሳችሁ" ሲሉ ማየትና መስማት " ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ ።" (ምሳ 30÷13) ተብሎ የተነገረው ትንቢታዊ ኃይለ ቃለ እንዲፈጸምባቸው እየተጉ መሆኑን ያሳየናል:: ዛሬም በኑሯችን በሥራችን በትዳራችን በትምህርታችን ጣዕም ያጣን ሁሉ በአማላጅነቷ በጥዑም ስሟና ከልጇ በተሰጣት ጸጋ አምነን እንቅረብ !! እርሷ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የክርስቶስ እናቱ ናትና::

አዘጋጅ መምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።”
መዝ 4፥3

ብዙዎች እግዚአብሔር በጻድቃን እንደሚገለጥ ባለማወቅ የቅዱሳኑ ነገር የእግዚአብሔርን ነገር በልጦ የሸፈነው ይመስላቸዋል :: ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም ውኃን ከጥሩ (ከጠራው) ነገርን ከሥሩ እንዲሉ የጻድቅን ትርጉም በመጀመሪያ በአጭሩ እንመልከት::
ጻድቅ የሚለው ግሥ እውነተኛ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለብዙ ቁጥር ስንጠቀመው ጻድቃን ብለን ማናበብ እንችላለን እውነተኞች ማለታችን ነው!::
በእውነቱ "ጻድቅ" የሚለውን መቀጽል በመጀመሪያ በተገባ የሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው :: እግዚአብሔር አምላክ እቀደስ አይል ቅዱስ እጸድቅም አይል ነገር ጻድቅ ነው ጽድቁም እንደ ቅዱሳን የጸጋ (የስጦታ) እንደ ሰይጣንም የሐሰት ሳይሆን ማንም ያልሰጠው ማንም የማይቀማው በባህሪው ጻድቅ እውነተኛ ቅዱስም አምላክ ነው ::“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ #አምላካችንም_ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” እንዲል መጽሐፍ 1ኛ ሳሙ 2፥2

ጻድቅ ወይም እውነተኛ ለመሆን በእውነት ማመን ፣ ስለ እውነት መናገር፣ ስለ እውነት ማስተማር፣ ስለ እውነት መኖር ይጠይቃል :: ታዲያ ይህ እውነት ማነው ካልን እግዚአብሔር ነው:: “እኔ መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ” ዮሐ14፥6

ከእነዚህ እውነተኞቹ ጻድቃን መካከል የጽላሎሹ ኮከብ የእግዚ አርያ ዐይን ማረፊያ የፀጋ ዘአብ አብራክ የምመናን እረኛ የወንጌል አርበኛ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ግምባር ቀደም ናቸው:: ድካምን በማብዛት እንደ ነቢያት ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት በመገረፍ እንደ ሰማዕታት መሰለ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር በጻም በድካም ሌት ተቀን ተጉ 22ዓመት በሁለት እግራቸው ከቆሙ በኃላ ከመቆም ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራ ወደቀች በዚህም ለአፍታ ሳይዘናጉ ለ7ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው በትዕግሥት 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: መጻሕፍ “እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን” ያዕ5፥11 ብሏልና " #ብፁህ " አልናቸው :: የሥራዬን ጽናት የሃይማኖቴን ደግነት ግለጥ እያሉ በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ክርስቶስን ሲሰብኩ ቆይተዋል እንዲያውም በከተታ አውራጃ በዚህ በታመኑለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያስተምሩ ሀገሪው ሰምቶ ለዛፍ መስገድን ሊያስቆሙን ነው ከፈጣሪያችን ሊያጣሉን ነው ብለው እንደ አንበሳ ሊውጧቸው ተነሱ አባታችን ግን በልበ ሰፊነት በነገር አሳላፊነት እያለዛዘበ አስተማሯቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸው:: ይህ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ምን ያክል ድንቅ እንደሆነ የሚያመላክት ነው እንጂ የቅዱሳኑ ሕይወት የእግዚአብሔር ነገር ነገረ እግዚአብሔርን የሸፈነ አይደለም ጻድቃን ቅዱሳን “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፥” የሚሉ ናቸውና 1ኛ ቆሮ1፥23

እንደ ልቤ የተባለውም ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔር #በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።”መዝ 67(68)፥35 ሲል የጻድቃን ሕይወት ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር የተገለጠበት ድንቅም የሚያደርግበት ለሕዝብም ኃይልን የሚያድልበት መሆኑን መስክሮልናል በዚህም ነገር እግዚአብሔር ይመሰገንበታል :: “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሎ ያዘዛቸውም በእነርሱ መልካም ሕይወት የሰማይ አባታቸው እግዚአብሔር ስለሚገለጥበት ነው። ማቴ 5፥16

አንዳንድ አካላት ግን ይህን ባለ መገንዘብ ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ይልቅ ቅዱስ ጳውሎስን ከነገረ እግዚአብሔር ይልቅም ነገረ ቅዱሳንን አስበልጣ ትሰብካለች ይላሉ:: ነገሩ ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያለ ነገር ነውና የትም አያደርስም :: ይህ ዓይነቱ አካሄድ የዋልዮሽ አካሄድ በመሆኑ መጨረሻው ገደል ነው:: የዚህ ትምህርት ምንጭም ክርስቶስ ብቻ በቂዬ ነው የምትለው የመናፍቁ ዓለም ጨዋታ ነች :: ለክርስቶስ የተቆረቆሩ በማስመሰል ምርጦቹ ቅዱሳኑን ለማራቅ አያስፈልጉም ለማለት የሚደረግ ዳርዳርታ ነች :: ቅዱሳን ማሰብ በስማቸው ዝክር ማዘከር ስማቸውን መጥራት ገድላቸውን መስማት ማሰማት የተገባ ደገኛ ሥርዓት ነው ሙሽራው ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ሚዜዎቹ ቅዱሳንንም መቀበል ይገባል::
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10፥40-41 መቀበል ከነ ሚዜዎቹ ነው ማነው? እስቲ ከውጪ የመጣ ወዳጁን አንተ ና ወደ ቤቴ ግባ የያዝከው የሻንጣ ገንዘብ ግን ከቤቴ አይገባም ብሎ ወዳጁን ስለ ገንዘቡ አልቀበልም የሚለው? ቅዱሳን የክርስቶስ ገንዘቡ ናቸው :: ያለ እነርሱ ልንቀበለው አንችልም::

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን #ዋኖቻችሁን_አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”ዕብ 13፥7 እንግዚህ እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያቀለዋል ?
“በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ በቤቱና በቅጥሩ የማይጠፋ የዘላለም የመታሰቢያ ስም የሰጣቸው እራሱ ባለቤቱ ነው ኢሳይ56፥5
እግዚአብሔር ለጻድቃን የሰጣቸው ወይም የሚሰጣቸው ክብር በሕይወተ ሥጋ ብቻ ሳሉ አይደለም ለሞታቸውና ለአጸደ ነፍሳቸውም ጭምር የሚሆን ከብረው የሚያከብሩበት ዘላለማዊ ሥጦታ ጭምር ነው እንጂ:: “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ116፥15

ጻድቁም ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሄጄ በስምህ ሰማዕትነትን እቀበል ዘንድ አውዳለውና ያን እንዳደርግ እዘዝ አሉት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መቀዳደምክን ጨረስክ ከሞት በቀር የቀረህ የለም ሁሉን ፈጽመሃል ሞትህንም እንደ ሰማዕታት ሙት አድርጌ እቀበለዋለው አላቸው :: ብዙ ቃል ኪዳንም ከሰጣቸው በኃላ አባታችን ነሐሴ 24 ቀን በ99 ዓመት ከ10ወር 10ቀናቸው ቅዱስት ነፍሳቸው ከቅዱስ ሥጋቸው ተለየች::
#የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን !::አሜን!

#የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” ዘኍልቁ 23፥10

.............#ይቆየን..........
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 24 ቀን 2012ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#ዛቲ_ዕለት_ቅድስት_ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
#ቅድስት_ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው?
_________________________
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::
በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
***********************************
1) (ሰንበት ክርስቲያን )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
*ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ በኩረ በዓላት ናት :-
* #የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና ዓለም የተገኘባት
* #ወልድ ሰው የሆነባት
* # ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
* #ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::
2) #እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች
____________________________

ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: #ሉቃ 1÷26
3) #ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) #ቅድስት_ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :-
__________________________________
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) #መንግሥተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች
_______________________________
እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች :: " ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዕረፍት ይባላል :-
___________________________________
" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና ዕረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የዕረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::
#የግርጌ_ማስታወሻ
++++++++++++++
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል :: አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል :: በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል::
በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::
.........ይቆየን...........
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ /ማርያም
የካቲት 12/2010 ዓም
" #እነሆ_መንገድህ_በፊቴ_ጠማማ_ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
_____________________________________________
#ዘኍ ፳ ፪ ÷፴ ፪

ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው #ሊቀ_መላእኩ_ቅዱስ_ሚካኤል ነው ። የተናገረውም ለተራጋሚው በልዓም ስለተባለ ሰው ነው:: ቃሉን ጽፎ ያስቀመጠልን ሊቀ ነብያት ቅዱስ ሙሴ ነው::

#በልዓም ሃብተ መርገም ያለው የረገመው በቶሎ የሚደርስለት ሰው ነበር :: በዚህም ጸጋው ተጠቅሞ እስራኤልን ይረግም ዘንድ እጅ መንሻ ገንዘብን እንዲሰጡት ባላቅ ሰዎች ላከበት "፤ የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት። " #ዘኍ ፳ ፪÷ ፯
በልዓምም የተሰጠውን ሃብተ መርገም በገንዘብ ቀይሮ ሕዝበ #እግዚአብሔርን እስራኤልን ለመርገም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሽማግሌዎቹንም ከዋላው አስከትሎ ጉዞ ጀመረ ::ጥቂት እንደሄደ ግን አህያው አንድ ባታ ላይ ቆማ አልንቀሳቀስም አለችሁ:: #የእግዚአብሔር_መላእክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከፊቷ ቆሞ አይታዋለችና:: በልዓም ግን አህያይቱን አብዝቶ ደበደባት አህያይቱም ወደፊት ላለመሄድ ወደጉን ወደ እርሻው ተጠጋች

"፤ አህያይቱም #የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ደግሞ መታት። " #ዘኍ ፳ ፪÷፳ ፭

#እግዚአብሔር አምላክ የሚረግሙህን እረግማለው የሚባእኩህንም እባርካለው ብሎ ቃል የገባላቸው የነ አብርሃም የነ ይስሐቅ የነ ያዕቆብ ዘር ናቸውና ሕዝበ እስራኤል እንዲረገሙ አልፈቀደም::ዘፍ 12÷3

የበላዓም ዓይኖች አሁንም አልተከፈቱም ልቦናውም ከአህያይቱ ልብ አልተሻለም አሁንም አብዝቶ ደበደባት ይህን ጊዜ በሰው አንደበት እንዲ ብላ ተናገረችው ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው። "፤ በለዓምም አህያይቱን። #ስላላገጥሽብኝ_ነው_በእጄስ_ሰይፍ_ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት።

"፤ አህያይቱም በለዓምን። ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም ። እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት። እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
#የእግዚአብሔርም_መልአክ። አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ አህያህ አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ ባትል ኖሮ በገደልኩ ነበር አለው ደግሞም በለዓምን ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ መልአኩ እየነገረው እስራኤልን ሊረግም ሄዶ መርቆ ተመለሰ::

#የእግዚአብሔር ሥራ ይገርማል ። የበልዓም አህያ የመላእኩን ክብር በማወቋና በመገንዘቧ የበላህምን ሕይወት ታድጋለች ዛሬ የቅዱሳን መላእክትን ክብር የማያውቁ የጸጋ ስግደት የማይሰግዱ አማላጅነታቸውን የማይቀበሉ ከአህያ ያነሱ ሰዎች በዝተዋል እግዚአብሔር አምላክ እንደ በልዓም ዓይነ ልቦናቸውን ከፍቶ ክብረ መላእክትን አውቀው ቅዱሳንን መርገም ትተው አንገታቸውን ደፍተው እንዲሰግዱ ያድርጋቸው ... .....ሌላ ምን እንላለን ከጌታችን የተማርነው ይህን ነውና

"፤ #የሚረግሙአችሁንም_መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። "
(ሉቃ ፮÷ ፳ ፰ )
....#ይቆየን......
በዛሬው ዕለት ለበልዓምና ለአህያው የተገለጠበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ የሚከበርለት የሊቀ መላእኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና ምልጃው አይለየን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
መጋቢት ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፲ ዓ.ም የተጻፈ
ለም ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ዘስጋ እንጅ መምህረ እስራኤል ዘነፍስ አይደለም፡ ክርስትና አለቃና ባሪያን አንድ እንደምታደርግ አያውቅምና የጎደለውን ፍለጋ መጣ ገላ 3 26፡፡ ያለውን ሳይሆን ያጣውን የሞላለትን ሳይሆን የጎደለውን ፍለጋ መጣ፡፡ዕውቀት ብቻውን ምሉእ አያደርግም፡፡ አለቅነትም ቢሆን ገደብ አለው፡፡የሕይወቱን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አንድ ክርስቶስ ብቻ ነውና ጎደሎነቱን አምኖ መጣ፡፡ የሚጎድለኝ ምንድን ነው? ብሎ እንደጠየቀው እንደዚያ ሰው ጎደሎን ማመን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው ማቴ 18 21፡፡ በአብዛኞቻችን የሚታየውና ክርስትናችንን አገልግሎታችንን ቤተክርስትያናችንን እየተፈታተነ ያለ ችግር ጎደሎዎቻችንን አለማወቅና ምሉእ ነኝ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምንም እንዳልሆኑ አውቆ ራስን ለክርስቶስ፣ ራስን ለመርዐተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሳልፎ መስጠት ምንኛ መታደል ነው!
አልዕሎ ልቡና (ልቡናንን ከፍ ማድረግ)
ኒቆዲሞስ ይዞ የመጣው ስጋዊ ህዋሳቱን ነበር፡፡ጌታችን ግን አመጣጡ ለመልካም እንደሆነ አውቆ ለስጋዊ ዕውቀት እጅግ የሚከብደውን ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ መጀመሪያ ይህን ምስጢር ለመቀበል አልተቻለውም ነበር፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ምስጢሩን ፍንትው አድርጎ ሲያብራራለት ግን ልቡናው ይህን ምስጢር ለመቀበል ከፍ ከፍ አለ፡፡ ምስጢራትን ለመቀበል ልቦናን ከፍ ከፍ ማድረግ ይገባል፡፡የእምነታች መሰረት በስጋ ዓይን ማየት በስጋ ጆሮ መስማት በስጋ እጅ መዳሰስ ብቻ ከሆነ ልክ እንደ እንቦይ ካብ ሆነ ማለት ነው፡፡ ትንሽ ነፋስ ትንሽ ተፅዕኖ ሲያርፍበት መፈራረስ መናድ ይጀምራል፡፡ ኒቆዲሞስም ምስጢሩ መጀመሪያ ቢከብደውም ቅሉ በኋላ ላይ ልቦናውን ወደ ሰማያዊው ምስጢር ከፍ ስላደረገ ምስጢሩ ተገለጸለት፡፡ ቤተክርስቲያንን ሲፈታተኗትና እየተፈታተኗት ያሉ አካላት በሙሉ የስህተታቸው ምንጭ እንደ ግያዝ ከአካባቢያቸውና ከምናየው አካል (ቁሳዊ ዓለም) ውጭ መመልከት አለመቻል ነው 2ነገ 6- 17፡፡ ለዚህም ነው ካህኑ በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ የቁርባኑ ምስጢር እንዲገለጽልን «አልዕሉ አልባቢክሙ (ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ)» የሚሉን፡፡
የእውነት ምስክር (ስምዐ ጽድቅ) መሆን
ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሃፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡እውነትንና ፀሐይን ፈርቶ የትም መድረስ አይቻልም፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ በመሪዎች ፊት በታላላቅ ሰዎች ፊት እውነትን መመስከር ክርስትናችን የሚያስገድደን ቁም ነገር ነው ሉቃ 12 8፡፡ ቤተክርስቲያን ሰማዕታት እያለች የምትዘክራቸው በሙሉ ለእውነት ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳንን ነው፡፡በፍርሐትና በሀፍረት በይሉኝታና በሀዘኔታ እውነትን አለመመስከር በክርስቶስ ፊት ያስጠይቃል እንጅ አያስመሰግንም ማቴ 10 32፡፡ «ለእውነት እንጅ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልም» እንዳለ 2ቆር 13 8፡፡
ትግሃ ሌሊት
እንደ ሌሊት ለመንፈሳዊ ህሊና ለተመስጦ የሚመች ጊዜ የለም ፡፡ ቀን ለስጋ ሲራወጥ የነበረ አካልና መንፈስ ሌሊቱን ለነፍስ በምገዛት ስጋውን መጎሰም አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኑን በቅዳሴ ሌሊቱን ደግሞ በማኅሌት በሰዓታት በኪዳን እግዚአብሔርን ስታምሰግን የምታድረው፡፡ ቅዱስ ማር ይስሐቅ ሌሊትስ ጌታን ለማመስገን የተፈጠረ ድንቅ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያቱን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሏቸዋል ማቴ 26፡፡ አሁንም ቤተክርስቲያን እንደ ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ለኪዳን ለማኅሌት ለጸሎት የሚመጣን ምዕመን ትፈልጋለች፡፡
እስከ መጨረሻ መጽናት
ጌታችንን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ሺህ ሕዝብ ቢከተለውም እስከመስቀሉ አብረውት የነበሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የተወሰነው ሕዝብ ቀድሞም የተከተለው ለምግበ ስጋ ነበርና ቀራንዮ ላይ አልተገኘም፡፡ ቀራንዮ ላይ ምግበ ነፍስ እንጅ ምግበ ስጋ የለም፡፡ ሌሎችም በቤተሰብ በሀብት በፍርሀት ምክንያትነት መስቀሉ ስር አልተገኙም፡፡ ምንም እንኳ ኒቆዲሞስ በስድስት ሰዐት ባይገኝም የክርስቶስ ስጋ ከነፍሱ በምትለይበት ሰዐት ክርስቶስን ከመስቀል አውርዶ ለሐዲስ መቃብር ያበቃው እሱ ነበር፡፡ በዚህ የመከራ ሰዐት ከዮሐንስና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ውጭ ማንም እንዳልነበረ መጻሕፍት ከገለጹልን በኋላ የምናገኛቸው የቁርጥ ቀን ልጆች ዮሴፍንና ኒቆዲሞስን ነው፡፡ ይህም ፈተናውን ሁሉ ተቋቁሞ እስከ መጨረሻው ለመጽናቱ ምስክር ነው፡፡ በክርስትና ሕይወታችንም የምናያቸው ነገሮች ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡በምቹ ጊዜ የምናገለግል ፈተና ሲመጣ ጨርቃችን(አገልግሎታችንን) ጥለን የምንሮጥ ማር 14-51 ሰበብ አስባብ ፈልገን የምናፈገፍግ ብዙዎች ነን፡፡ ዕውቀት ጣዖት ሆኖበት መሀል መንገድ የቀረው ሀብት ጣዖት ሆኖበት ሩጫ ያቋረጠውን ጊዜ ጣዖት ሆኖበት ቅዳሴ የሚቀረውን ቆጥረን እንጨርሰው ይሆን? ጌታ በትምህርቱ «ለዘአዝለፈ ትዕግስቶ ውእቱ ይድኅን -እስከ መጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል » እንዳለ ማቴ 2413፡፡ ክርስትና ለጀመሩት ሳይሆን ለጨረሱት ለወጠኑት ሳይሆን ለፈጸሙት የድል አክሊል የምትሰጥ መንገድ እንጅ የመሮጫ መሙን ጠበበን ሩጫው ረዘመብን ለሚሉ ዴማሶች ቦታ የላትም፡፡2ጢሞ 4-9
በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡ የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ አሜን 👉❤️

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-ማህበረ ቅዱሳን መካነ ድህር
ዓውደ ምህረት የእናንተ
አስተያየት ጥቆማና የከበረ ሀሳብዎን በዚህ ይስደዱልን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
" #እነሆ_መንገድህ_በፊቴ_ጠማማ_ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
_________