አትሮኖስ
279K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....የህዝቡ ብዛት….በዚህ ላይ ጨለማ...ያ ሽለምጥማጥ አበራ ፍላጐቱን በቀላሉ ፈፅሞ ከአካባቢው ተሰወረ።..
ጓደኞቹ በሙሉ በመሀሌት ቤት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ከታሰሩበት በኋላ ታደሰ ብቻውን ሊለቀቅ የቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ስውርና ረቂቅ በሆነ መንገድ ሲከታተለው ነበር የሰነበተው፡፡
ባደረገው ክትትል ታደስ የነጣቂው ቡድን ዋነኛ መቅሰፍት መሆኑን እያወቀ መጣ፡፡ መረጃ እየሰበሰበ
ሲያቀብል ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሲወጣ ሲገባ..ራሱን እየለዋወጠ ወንጀልና ወንጀለኛን ለማሳደድ የሚስራውን ሥራ በሙሉ ሲከታተለው ቆይቶ በመጨረሻ ላይ እውነታውን ደረሰበት።

ታደስ ከመረጃ አቀባይነቱ አልፎ ተርፎ እስከ መሸለም መብቃቱን፣
በዚያን እለትም ሌሎቹን ወንጀለኞች በሙሉ ካሳሰረ በኋላ እሱ በነፃ መለቀቁን፣ ለጊዜው የታሰረውም ለሽፋን መሆኑን አረጋገጠ፡፡ በዚሁ መሰረት
ታደሰን ለመበቀል ሲያደባ ቆይቶ ሰላማዊትና ታደሰ ከመኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ትያትር ቤት እስከገቡበት ጊዜ ድረስ በጥብቅ ሲከታተላቸው ዋለና ያን አስከፊ ድርጊት ፈጽሞ አመለጠ፡፡
በከፍተኛ የህዝብ ትብብር
ነፍሰ ጡሯ ግራና ቀኝ ተይዛ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ እንክብካቤ ተደርጉላት ከባሏ ጋር ወደ ሆስፒታል ተወስዱ። በመውደቋ ምክንያት መጠነኛ ንቅናቄ ደርሶባት ስለነበረ ወደ ማህፀን ክፍል ተወሰደች። ታደሰ ደግሞ
ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እንዲገባ ተደረገ፡፡ በግራ ጐኑ የገባችው ጥይት ጉበቱን በስታ በቀኝ ጐኑ ወጥታ ነበር፡፡ ሆስፒታል እንደገባም አጣዳፊ
የሆነ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደረገለትና ደም ከተሰጠው በኋላ ግሉኮስ በግራ ክንዱ ላይ ተሳካለት፡፡
ሰላማዊት የደረሰባት መጠነኛ ጉዳት በመሆኑ በማግስቱ ድና ተነሳች። ታደሰ ግን ክፉኛ ተጐድቷል፡፡ እማማ ወደሬ በጠዋቱ ጉዳቸውን ሲሰሙ
በድንጋጤ ክው ብለው ቀሩ፡ ያ እንደ እናቱ የሚያያቸው፤ ትንሽ ሲያማቸው የሚጨነቅላቸው፣ የዳሩት ልጃቸው የሆነውን ሰሙ። በተለይ ይህ አደጋ በደረሰበት እለት “እንኳን አደረስዎ” ሊላቸው የሚወዷትን ነጭ አረቄ ይዞላቸው ሄዶ ሊያጫውታቸው፣ ሲያስፈነድቃቸው ነበር የዋለው።

“ታዴን! ታዴን! ልጄን! .እኔ እናትህ ድፍት ልበል! የኔ ደም ክንብል
ይበል! ለካ ለዚህ ነው? ለካ አንጀቴን ሲበላው ነው? ምነው ከኔ በፊት? እኔ አሮጊቷ ቁጭ ብዬ...እኔን ያስቀድመኝ...” ልብሳቸውን ሳይቀሩ እየጮሁ ወደ ሆስፒታል ሮጡ አደጋውን የሰሙ
የቅርብ ጓደኞቹ ሲያስታምሙትና ሲጠይቁት ከረሙ:: ታደሰ ግን በየጊዜው የመሻሻል ምልክት ከማሳየት ይልቅ የድካም ምልክቱ እየጨመረ ሄደ። ጉበቱ ክፉኛ ተጐድቶ ነበር፡፡የመዳን ተስፋው የመነመነ መሆኑን ሆስፒታሉ አስታወቀና ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ከሆስፒታል ወጥቶ ህክምናውን በቤቱ ውስጥ እንዲ
ከታተል ተደረገ፡፡ ወይዘሮ ወደሬ ቤታቸውን ዘግተው ንግዳቸውን ርግፍ አድርገው ትተው በአንድ በኩል ነፍስ ጡር ልጃቸውን በሌላ በኩል በሽተኛ ልጃቸውን ለመርዳት ጉለሌ ተጠቃለው ገቡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በአንድ ትልቅ የባህር ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ የሆነ የተንጠለጠለ ነገር በርቀት ይታያል፡፡ በአካባቢው ግርግር እየ
ተፈጠረ ነው፡፡ የሰፈሩ ነዋሪዎች ከህፃናት ጀምሮ ወደ ጫጫታና ግርግሩ ስፍራ እየሮጡ ሲደርሱ ሙሉ ጥቁር ሱፍ የለበሰ፣ ክራቫት ያደረገ መልከ መልካም ወጣት በወፍራም ገመድ ላይ ዘለዓለማዊ የቁም እንቅልፍ አንቀላፍቶ ጠበቃቸው።
ዐይኖቹ ገርበብ ብለው ሲታዩ የሚያዝንለትና የሚያዝንበትን ህዝብ በትዝብት የሚያስተውል ይመስል ነበር፡፡ ቀይ ቀሚስ፣ እጅጌ ጉርድ ሰማያዊ ሹራብ የለበሰች ዕድሜዋ ከአስራ ሰባት ዓመት የማይበልጥ ጠይም መካ
ከለኛ ቁመት ያላት ሴት ልጅ ደግሞ በሟቹ እግር ላይ እየተንከባለለች እዬዬና ዋይታዋን በማሰማት ላይ ነበረች።

“የኔ አለኝታ! የኔ መመኪያ ! ምነው? እኔን ለማን ጥለኸኝ? የቀን ጅብ በላኝ እኮ! ሰማዩ ተደፋብኝ...” በሟቹ ምክንያት ስለሚደርስባት ችግር እያወራች ለራሷ የምታለቅስ ትመስላለች። በዚያን ሰሞን በሰፈሩም ሆነ
በመሥሪያ ቤቱ አካባቢ የሰመረ ሞት የሳምንቱ ዐብይ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ሰነበተ። ሰመረ በገዛ ህይወቱ ላይ እንዲፈርድ ያቺን የምታሳሳ ህይወት እንዲንቃት ያስገደደው ምን ይሆን? ምክንያቱን ለማወቅ ሁሉም
ጆሮውን አቁሞ ፍንጩን ለማግኘት አነፈነፈ። ገሚሱ በሰማው ላይ
የራሱን እየጨመረ ወሬውን አራገበ፡፡ ሰመረ ህይወቱን ለማጥፋት ያነሳሳውን ምክንያት ማወቅ አለማወቅ የሚያመጣው ለውጥ ግን አልነበረም።
የሰመረን የልብ ውስጥ ቁስል ከሚያውቁ ጓደኞቹ መካከል የቅርብ ጓደኛው ሳሙኤል ነበር፡፡ ከልጅነት እስከ እውቀት ችግርና ደስታን የተካፈሉ ጓደኛሞች ናቸው፡፡
ሳሙኤል !" ጐረቤቱ ጌዴዎን ነው የጠራው፡፡
“አቤት!” አገር ሰላም ነው ብሎ የጠዋት ፀሀይ ለመሞቅ በረንዳው
ላይ ቁጭ ብሏል፡፡
“አልሰማህም ?”
“ምኑን?”
“የሰመረን?”
“ምን ሆነ?!”
“ሰመረ እኮ . . .”
“መኪና ገጨው እንዳትለኝ ጌዴዎን!!.…” ደንግጦ ተነሳ።
“እ…እ..እኔማ ሰምተህ መስሎኝ፡፡ መኪና አይደለም…ራሱን አጥፍቶ ነው...” ከሳሙኤል የወጣ ትንፋሽ አልነበረም። በድን ሆኗል።
አንጀቱ ድብን ብሏል። ጌዴዎን ሳያውቀው በቀላሉ ሞቱን ያረዳው ሰው ለሳሙኤል የወንድም ያክል ነበር።ቀሳሙኤል ጭንቅላት ውስጥ በርካታ የሰመረ ትዝታዎች ተመላለሱ። ሰመረ በልጅነቱ፣ ስመረ በቄስ ትምህርት ቤት፣ ሰመረ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤት፣ ሰመረ በዩኒቨርስቲ በይዘታቸው አንድ በዓይነታቸው ግን ብዙ ሰመረዎች በዓይነ ህሊናው ላይ ሄዱበት። ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ በቤቱ በረንዳ ጠርዝ ላይ በክርኑ ተደግፎ አንገቱን ቁልቁል ደፍቶ ለረጅም ጊዜ ሲተክዝ ቆየ። ትዝታ የጓደኝነት ፍቅር....ከውስጥ እያቃጠሉት እንባ ያቆረዘዙ
ዐይኖቹ ያዘሉትን ውሃ ወደ ታች ለቀቁት...
ጌዴዎን የጓደኝነታቸውን ደረጃ ሳያጣራ በመናገሩ አዘነ። ድርጊቱ አንድ ችኩል መርዶ አርጂ ከፈፀመው ድርጊት ጋር ተመሳሰለበት፡፡ ሰውዬው
እናቱ የሞተች ባልንጀራውን በደንቡና በሥርዓቱ መሰረት በለሊት እንዲያረዳ ሃላፊነት ይሰጠዋል፡፡ ችኩሉ መርዶ አርጂ ግን እዚያው መሥሪያ ቤቱ ድረስ ይሄድና “ስማ እንጂ! ስለ እናትህ ስማህ እንዴ?”በማለት ይጠይቀዋል። አነጋገሩ ያስደነገጠው ልጅም “ምነው አመማት እንዴ?!”
በማለት መልሶ ጠያቂን ይጠይቀዋል፡፡
“ኽረግ ሊያውቅ ነው መሰል!" ይላል ችኩሉ መርዶ አርጂ። ይህ አባባሉ የበለጠ ያስደነግጠው ሰው "ምነው ባሰባት እንዴ?!” ሲል ደግሞ ይጠይቀዋል፡፡ ከዚያም ችኩሉ መርዶ አርጂ..“ጠረጠረ በለው!” ይላል። በዚህ ጊዜ ልጅ ክፉኛ ይደነግጥና...“ምነው?! ሞተች እንዴ?!” ብሎ በድጋሚ ይጮሃል፡፡ ችኩሉ መርዶ አርጂም “አወቀ በለው!ማን አባቱ
አረዳኝ ሊል ነው?!” አለና ፊቱን አዙሮ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ ጌዴዎንም የሳሙኤልን ሁኔታ ሲመለከት በችኩል መርዶ አርጂነቱ ደንግጦ ሊሮጥ
ቃጥቶት ነበር፡፡ ትውውቃቸውን እንጂ የቅርብ ባልንጀራሞች መሆናቸውን ቢያውቅ ኖሮ ሞቱን እንዲህ በቀላሉ አያረዳውም ነበር። ሳሙኤል በቀብሩ እለት እዬዬ ብሎ አለቀስ። ያቺ ሰመረ ራሱን በሰቀለ እለት እግሩ
👍61👎1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የኑዛዜውን ምስጢር እንዳገኘው ሁሉ የልብ እይታ
ተሰማው በረጅሞ ተንፍሶ ራሱን ወዘወዘ።
ወዲያው የሰው ኮቴ ተሰማው፡፡ ወደ አስቻለው ክፍል ዞር ብሎ ሲመለከት ሁለቱ ዶክተሮች ተከታትለው ሲወጡ አየ፡፡ ምን ሊሉት እንደሚችሉ በመጓጓት ትኩር ብሎ ሲመለከታቸው ያ የአስቸለው ዶክተር በእጁ ጠቀስ አደረገውና በልሁም ጠጋ ብሎ- ጆርውን ሲሰጠው «አይዞህ ደህና ነው፡፡» በተረፈ ነርሷ የምትሰጥህን ትዕዛዝ ተቀበል፡፡ ብሎት ወደ ቢሮው አመራ። በልሁ ከነርሷ የሚሰጠውን ትዕዛዝ
ለመስማት ጓጉቶ ከክፍሉ የምትወጣበትን ጊዜ በመጠባበቅ ላይ ሳለ ነርሷ ወዲያው ወጣች፡፡ በሩን መልሳ ዘጋችና እንዲያውም ቆለፈችው፡፡ በልሁ ወደ እሷ ሊራመድ ማሰቡን አውቃ “እዚያው ጠብቀኝ፡፡ አለችው፡፡
በልሁ ቀጥ ብላ ቆመ። ዓይኖቹ ግን በነርሷ ላይ ትክል አሉ። ልቡ
ደንገጥ አለና ከንፈሮቹን በምላሱ ያርስ ጀመር፡፡ ነርሷ ግን ወደ በልሁ ስትጠጋ ፈገግ ብላ ነው፡፡ በዚያው ፈገግታ በተላበሰ ሁኔታዋ የበለጠ ጠጋ አለችውና፡
«ደነገጥክ እንዴ?» ስትል ጠየቀችው።
«ፈራሁ»
«አይዞህ! ምንም አይለው። አሁን አንድ ለየት ያለ መድሐኒት
ሰጥተነዋል። መድሐኒቱ ግን የህመምተኛውን እንቅስቃሴና የትኩረት መለዋወጥ
አይፈልግም። ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት ዕረፍትና የሀሳብ መረጋጋትን ይጠይቃል።ስለዚህ እንተም እንዳትገባ ብዬ በሩን ቆልፈዋለሁ፡፡ እኔ እስከምጠራህ ድረስ ዘወር
ዘወር እያልክ ራስህን አዝናና። እንዲያውም እታች ወርደህ ወደ ክበብ አረፍ ብትል ጥሩ ነው፡፡ እኔም ስፈልግህ በቀላሉ አገኝሀለሁ፡፡» አለችው ረጋ ባለ መንፈስ::
በልሁ አሁንም በረጅሙ ተነፈሰ፡ ምራቁንም ዋጥ አደረገ። የነርሷን
ትዕዛዝ መቀበል እንዳለበት ከዶክተሩም ተነግሮታል። የነርሷም አነጋገር ለዛ የተላበሰ ነው፡፡ ነርሷ ወደ ቢሮዋ ስታመራ እሱም ሶስተኛ ፎቅ ምድር ላይ ወደሚገኘው የሻይ ክበብ አመራ፡፡
ግማሽ ሰዓት ለበልሁ የግማሽ ዓመት ያህል ረዘመባት፡፡ ነገሩ ከጠዋቱ ጀምሮ ምንም ነገር በአፉ አልገባምና ርሀብም ተሰማው። ሰዓቱ ደግሞ ወደ ስድስት
ተኩል ተጠግቷል፡፡ ሻይና ኬክ አዘዘ። ፉት ፉት፣ ጎረስ ጎረስ አደረገ፡፡ ቡናም አዘዘ። ሲቀርብለት አሁንም ፉት ፉት እለ። ግን የሁሉም ነገር ጣዕም እህል ውሃ
አይለውም፡፡ ማጣፈጫው ስኳር ይሁን ጨው አይለይለትም፡፡ ትኩስ ይሁን ቀዝቃዛ
አይሰማውም፡፡ ስሜቱ ሁሉ በአስቻለውና በሁኔታው ዙሪያ ብቻ ሆነ፡፡ በመሀል የሔዋንና የመርዕድ ጉዳይ ትዝ አለው፡፡ «ዛሬም ላይመጡ?» አለ ለብቻው
አየተነጋገረ። «ትንሽ ልጠብቃቸውና ስልክ ደወዩ ችግራቸውን ማወቅ አለብኝ፡፡ ብቻ ነርሷ ስለ አስቻለው የምትነግረኝ ነገር ሰላም ይሁን!» እያለ በማሰብ በማሰላሰል ላይ ሳለ ሠዓቷ ደርሶ ደርሶ ኖሮ ያቺ ነርስ ድንገት ከፋቱ፡ ከች አለች፡፡
«ሻይ ቡና አልክ?» አለችውና ወንበር ሳብ አድርጋ ከአጠገቡ ቁጭ አለች።
«ሁሉንም አደረጉ።» አላት በልሁ በፍርሀት ዓይኑ እየተመለከታት፡፡
ነርሷ ቡና አዘዘች። እስከሚተርብላትም ድረስ ከበልሁ ጋር ጭውውት ጀመረች። ተነጋገሩ። በእርግጥም ብዙ ተወያዩ፡፡ ተግባቡም፡፡ ከዚያች ሠዓት ጀምሮ በልሁ ወደ ዲላ ስልክ ለመደወል ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደረስ፡፡ ከነርሷ ጋር ተሰነባበቱና
እሷ ወደ ስራዋ ስትመለስ በልሁ ደግሞ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ወጥቶ ስልክ ፍለጋ ኪዎስኮችን ይፈልግ ጀመር ።
ስልክ እንዳገኘ በቀጥታ መርዕድን ለማግኘት ወደ የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ደወለ፡፡ ለጊዜው መርዕድን አላገኘውም፡፡ ስልኩን ያነሳው ሰው ግን መርዕድን
ከእሥር ደቂቃ በኃላ ሊያቀርብላት እንደሚችል ነገረው። ለካ ዛሬም ወደ እዲስ አበባ ጉዞ አልጀመሩም፡» አላ በልሁ፡፡ ዲላ ውስጥ እንድ ችግር እንዳለ ገመተ።የሆዱን በሆዱ አድርጎ ወደ አውራጃው ግብርና ጽህፈት ቤት ደወለ። በጓደኞቹ አማካኝነት ለታፈሡ ሊደርስለት የሚፈልገውን መልዕክት አስተላለፈ። ይህ ሁሉ
እስከሚሆንበት ድረስ መርዕድን የቀጠረበትም ሰዓት ደረሰና እንደገና ወደ አፃ ዳዊት
ትምህርት ቤት ደወለ፡፡ መርዕድን አገኘው፡፡

«ሀሎ መርዕድ!»
«እቤት!»
«አንተና ሔዋን እንመጣለን ያላችሁት ባለፈው ሰኞ አልነበረም እንዴ?
ነገር ግን ይኸው እስከዛሬ አልተነሳችሁም፡ ችግሩ ምንድነው?» ሲል ጠየቀው፡፡
መርዕድ ለበልሁ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የተቸገረ በሚመስል አኳኋን ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እንደ መርበትበትም እያደረገው
«እ..እ...ካለ በኋላ «ግን እኮ ነገ ልንመጣ ተነስተናል» አለው፡፡

«ሔዋን ግን ደህና ናት?»
«ደህና ናት፡፡»
«በእርግጥ ነገ ወደዚህ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ትጀምራላችሁ?»
«እዎ፡ ወስነናል፡፡ »
«ጥሩ እሺ! እንዳትቀሩ፣ እጠብቃችኋለሁ፡፡»
ስልኩ ከሁለቱም በኩል ተዘጋ፡፡
የዕረቡ ቀትር ተጠናቀቀ፡፡ ፀሐይ ወደ ምዕራብ አዘቀዘቀች፡፡ አድማሱን አቅልታ ጨረሯን ወደ ላይ በመዘርጋት እሷ ግን ቁልቁል ሸሸች፡፡ ብላ ብላም ጠለቀች፡፡ ለዓይን መያዝም ጀመረ፡፡ የመንገድ መብራቶች ሁሉ በሩ፡፡
ከዋክብትና ጨረቃ የሰማይ ቦታቸውን ተረከቡ፡፡ ሌሊቱም ተጀመረ፡፡
ለበልሁ ግን ሁሉም ነገር ያው የቀን ያህል ነው፡፡ እንቅልፍ
እላስፈለገውም፡ በንቃት ያስባል፡፡ ዕረፍትም አላገኘም፡ የዘመኑን የሰዓት እላፊ ገደብ በራሱ ጥሶ በአዲስ አበባ አውራ መንገዶች ላይ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣል፡፡ በሀሳቡ ሔዋንና መርዕድ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ስንቅና
ልብሳቸውን ሲያዘጋጁ እየታየ እሱ ደግሞ ማለዳ ተነስቶ ወደ ዲላ ለመብረር የኮንትራት መኪና ለማግኘት ይለፋል ወደ እኩለ ሌሊት ላይ የሚፈልገውን የመኪና ዓይነት አገኘ፡ ፈጣንና ጠንካራዋን
ባለ እንድ ጋቢና ቶዮታ መኪና በእርግጥም ገና ጎህ ሳይቀድ
ተሳፈረባት ከጨለማው ቅልቅል ጉዞ ወደ ዲላ ጀመረ፡፡
ከአፍንጫው መገተር የተነሳ "መጥረቢያ ፊት ሊባል በሚችል ብቄ ባለሙያ ሾፌር በምትነዳው
ቶዮታ መኪና ማልዳ በመነሳት የአዲስ አበባ መንገዶችን በግላጭ አግኝታ እንደ ንስር ትወረወርባቸው ጀመር ከአዲስ
አበባ ወጥታ አቃቂን፡ ዱከም፣ ደብረዘይትንና ሞጆን አቆራርጣ ወደ ሲዳሞ መስመር መታጠፊያውን መንገድ ስትይዝ ገና ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እንኳ
በወጉ አልሞላም፡፡ከፍጥነቷ የተነሳ ከገመድ የተረፈው የሸራ ሽፋኗ
እየተርገበገብ ሳጮህ የእውቅ ዜመኛ ፉክራ ይመስላል፡፡ ጋቢናዋ በዝምታ ተሞልቶ ከኋላ በኩል ግን ድንቅ የተፈጥሮ ሙዚቃ እየተሰማባት ቶዮታዋ ወደ
ቆጋ ተጠጋች የአዋሽ ወንዝንም ገና በጠዋቱ ተሻገራቸው ከዚያም አልፎ ወደ አለም ጤና፡፡ ሾፌሩና በልሁ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገሩት ዝዋይ ከተማ ሊደርሱ ሲሉ ነው፡፡
«ስማ ሾፌር ቁርስ ያስፈልግህ ከሆነ ዝዋይ ከተማ ላይ አረፍ ብንል፡፡እሱን ካለፋን ዲላ ሳንደርስ የረባ ነገር አይገኝም፡፡» አለው በልሁ፡፡
«ለኔ ሳንይሆን ለአንተ ያስፈልግሃል፡፡ እኔ በጠዋት መብላት ብዙም አልወድም" : አንተ ቁርስ የምታደርግ ከሆን ልቁም» አለው ልክ እንደ
እንደ አፍንጫው ቅንድቡም ወጣ ወጣ ብሎ አስፈሪ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ሾፈር፡፡
👍10🔥1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ቴናድዬ ንግግሩን የጨረሰው ቁራጩን እራፊ ከኪሱ በማውጣት ነበር ጨርቁ በደረቀ ደምና በቆሻሻ ተጨማልቋል ቀለሙ ጥቁር ሲሆን ማሪየስ እንዲያየው ወደ ዓይኑ አስጠጋለት።

ማሪየስ ብድግ አለ:: ፊቱ በአንድ ጊዜ አመድ መሰለ፡፡ መተንፈስ አቃተው፡ ዓይኑ ከጨርቁ ላይ ተተከለ: መናገር አልቻለም: ዓይኑን ከጨርቁ ሳያነሳ ወደኋላ ሸሸ፡፡ ቀኝ እጁን ከኪሱ አስገብቶ ቁልፍ አወጣ
በቁልፉ ከዚያ የነበረ አነስተኛ ቁምሣጥን ከፈተ አሁንም ዓይኑን ከቁራጩ ጨርቅ ላይ አላነሳም፡ በዚህ ጊዜ ቴናድዬ ቀጠለ።

«ጌታዬ፣ ሟቹ ወጣት በኪሱ ብዙ ገንዘብ ይዞ እንደነበረና ዣን ቫልዣ በጥበቡ አጥምዶ እንደ ገደለው ብርቱ የሆነ እምነት አለኝ፡»

«ወጣቱ የምትለው እኔው ራሴ ነኝ፤ ኮቱም ያውልህ! ሲል ማሪየስ ጩኸቱን ለቀቀው:: በደም የተጨማለቀውን ኮት ከምንጣፍ ላይ ጣለው»

ከዚያም ቁራጩን ጨርቅ ከቴናድዬ እጅ ነጠቀ:: ጎንበስ ብሎ ቁራጩን
ጨርቅና የኮቱ ቀዳዳ ይገጥሙ እንደሆነ ለካ፡፡ ጨርቁ ከቀዳዳው ልክክ በማለቱ የኮቱን ቀዳዳ በትክክል ደፈነው::

ቴናድዬ አመዱ ቡን አለ፡፡ ‹‹ተበላሁ» ሲል አሰበ፡፡

ማሪየስ ከተቀመጠበት ገንፍሎ ተነሳ:: በአሳብ ረመጥ ተቃጠለ፡፡

ቶሎ ብሎ ከኪሱ ውስጥ ገባ እጁን ከኪሱ ሳያወጣ መንቆራጠጥ ጀመረ: ግሥላ መስሎ በቀጥታ ወደ ቴናድዬ ሄደ: ከኪሱ ውስጥ ያወጣን አንድ ሺህ አምስት መቶ ፍራንክ የቴናድዬን እጅ በማስነካት አሳየው

«ርኩስ ነህ! ውሸታም ነህ! ስም አጥፊ ነህ! ተንኮለኛ ነህ ምቀኛ ነህ! ይህን ሰው ለመክሰስ ነው የመጣኸው፤ ግን ትክክለኛና እውነተኛ ሰው
መሆኑን ነው የመሰከርክለት፡፡ ልታጠፋውና ስሙን ልታጕድፈው ፈልገህ
ነበር፤ ግን ክብር ነው ያጕናጸፍከው:: አንተ ነህ ሌባ! አንተ ነህ ነፍሰ ገዳይ
አንተ ነህ እንጂ እርሱ አይደለም ወደ ሆስፒታሉ ከሚወስደው ጎዳና አጠገብ ከሚገኘው ትኖርበት ከነበረው ዋሻ ውስጥ ጣራ ላይ ተንጠልጥዬ የሠራኸውን ሁሉ አይቼሃለሁ፣ ዦንድሬ! ቴናድዬ: ብፈልግ አንተን ለማሳሰር
የሚያስችል በቂ ማስረጃ አለኝ ግን
ምን ያደርግልኛል! አሁን ብቻ ከዚህ
ጥፋልኝ:፡ እንካ ለማኝ ስለሆንክ ይህን አንድ ሺህ ፍራንክ ጨምረህ ውሰድና
ውጣልኝ፡»

ገንዘቡን ወረወረለት

«ስማ ዦንድሬ! ቴናድዬ፣ አንተ እቡይ! ይህ ትምህት ሊሆንህ ይገባል የእኛ ምሥጢረኛ፣ የእኛ የጨለማ ነጋዴ፣ አንተ የተረገምክ ይህንንም አምስት መቶ ፍራንክ ወሰድና ብቻ ከዚህ ውጣልኝ ሂድ፣ ሂድ ከዚህ ቤት ውጣ ከዓይኔ ብቻ ተሰወር ደስ ይበልህ ይህን ብቻ ነው የምፈልገው ውይ ርኩስ! እንዲያውም ሦስት ሺህ ፍራንክ በተጨማሪ እንካ! ውሰዳቸው፡ አንተ ሽፍታ! ነገ ወደ አሜሪካ ትሄዳለህ እኔ ደግሞ አገር ጥለህ መሄድህን እከታተላለሁ: አገር ጥለህ ከወጣህ ሌላ ሃያ ሺ ፍራንክ እሰጥሃለሁ ሂድና እዚያው ተጨማለቅ!»

«ክቡር ጌታዬ» ሲል ቴናድዬ ግራ እንደተጋባና እንደተከዘ ምንም ነገር
ሳይገባው ገንዘቡን ተሸክሞ ሄደ
በጣም ክው ነው ያለው፤ ሆኖም ደስ ብሎታል ከአሁን በኋላ ስለዚህ
ሰው በአጭሩ ተናግረን ብናቆም ይሻላል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በማሪየስ እርዳታ ልጁን አዜልማን ይዞና ስሙን ቀይሮ ወደ አሜሪካ ሄደ:ማሪየስ ቃል የገባለትን ገንዘብ ሰጠው: አሜሪካም ከገባ በኋላ ያ ርኩስ ጠባዩ አልለቀቀውም፡፡ ብዙ ጊዜ የደካማና የክፉ ሰው ድርጊት የደህናውን ሰው በጎ ተግባር ስለሚያበላሽና ይህም ከመጥፎ ውጤት ላይ ስለሚያደርሰው ማሪየስ በሰጠው ገንዘብ ቴናድዬ አሜሪካ ውስጥ የባሪያ ንግድ አጧጧፈበት᎓

ማሪየስ ወዲያው ቴናድዬን እንደሸኘ ኮዜት ከነበረችበት የአትክልት ቦታ እየተጣደፈ ሄደ።

«ኮዜት! ኮዜት!» ሲል ተጣራ፡ «ነይ ቶሎ በይ፤ ፍጠኝ! እንሂድ:: ባስክ ቶሎ በል ሠረገላ አስመጣ፧ ፈጠን በል! ያንተ ያለህ! ለካስ እሱ ነው ሕይወቴን ያዳናት ደቂቃ አናጥፋ፤ ቶሎ ብለሽ ነጠላ ነገር ከላይሽ ላይ ጣል አድርጊ፡፡»

ኮዜት፣ ማሪየስ ያበደ መሰላት፡ ሆኖም ትእዛዙን ተቀብላ ራስዋን በቶሎ አዘጋጀት፡

ማሪየስ መተንፈስ አቃተው የሚዘልለውን ልቡ ለማብረድ እጁን ደረቱ ላይ አኖረ: ከወዲህ ወዲያ ተንቆራጠጠ ኮዜትን ዘልሎ አቀፋት «እንጃልኝ ኮዜት! ከአሁን በኋላ የተከፋሁ ሰው ነው የምሆነው» ሲል ተናገረ::

የዣን ቫልዣን ትልቅነት፣ የዣን ቫልዣን ክቡርነት የዣን ቫልዣን ስቃይ በጉልህ ስላየ ማሪየስ ፈዘዘ ወንጀለኛው ከርኩስነት ወደ ቅዱስነት ተቀየረበት ይህም በጣም አስደነቀው:: ከሕሊናው ውስጥ የሚተራመሰው ነገር ግልጽ ሊሆንለት አልቻለም ሆኖም የዣን ቫልዣን ክቡርነት
አልተጠራጠረም

ብዙም ሳይቆይ ሠረገው መጣ ኮዜትን በመደገፍ ካሳፈራት በኋላ ራሱም ዘልሎ ከሠረገላው ላይ ወጣ
«ቶሎ በል፤ ፍጠን» ሲል ባለ ሠረገላውን አዘዘው፡፡ «የምንሄደው
አርሜ ጎዳና የቤት ቁጥር 7 ነው»
ባለሠረገላው መንገዱን ቀጠለ፡፡...

በሩ ሲንኳ ሲሰማ ዣን ቫልዣ ፊቱን አዞረ: በደከመ ድምፁ ‹‹ግቡ» አለ፡፡

በሩ ተከፈተ:፡ ኮዜትና ማሪየስ ብቅ አሉ ኮዜት ቀደም ቀደም ብላ በችኮላ በመራመድ ከክፍሉ ውስጥ ገባች ማሪየስ ግን የበሩን እጄታ ይዞ ከበሩ ላይ ቀረ

«ኮዜት!» አለ ዣን ቫልዣ ብድግ ብሎ እጆቹን ሲዘረጋቸው ተንቀጠቀጡ፡፡ እጅግ በጣም ቢዳከምም ዓይኖቹ ውስጥ የደስታ ምልክት ታየው ኮዜት በስሜት ተውጣ ከደረቱ ላይ ሄዳ ዘፍ አለች ከዚያም «አባዬ» በማለት ስትናገር ዝግ ብሎ መለሰላት፡

«ኮዜት! እውነትም እርስዋ ናት? አንቺ ነሽ እመቤቴ! አንቺው ነሽ ኮዜት? ያንተ አለህ!» ብሎ እጆችዋን ጥርቅም አድርጎ ያዘ: ቀጥሎም ያንኑ ጥያቄ በመድገም «አንቺ ነሽ ኮዜት? መጣሽ» ይቅርታ አድርገሽልኛላ!›› ሲል ተናገረ::

ማሪየስ ከዓይኑ ላይ ያቀረረው እምባ ዱብ እንዳይል በርግብግቢቱ ዓይኑን ከጨመቀ በኋላ ወደፊት ተራመደ፡፡ እንዳያለቅስ ስሜቱን በኃይል እየተቆጣጠረ በጣም በደከመ ድምፅ አባባ» አለ

«አንተም ይቅር ብለኸኛል!» አለ ዣን ቫልዣ:

ማሪየስ ቃል ለመናገር አልቻለም፡ ዣን ቫልዣ በመቀጠል አመሰግናለሁ» ሲል ተናገረ

ኮዜት ነጠላዋን ጣል አደረገች: ከዚያም የዣን ቫልዣን ሽበት ማሻሸት ጀመረች ቀጥሎም ግምባሩን ሳመችው፡ እሱም ዝም አላት እርስዋም የማሪየስን እዳ የምትከፍል እየመሰላት ማሻሸቱን ቀጠለች::

መጣሃ፣ መሴይ ፓንትመርሲ፤ ይቅር ብለኸኛላ! ሲል ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል የተናገረውን ደገመ:፡

ዣን ቫልዣ ያለውን ደግሞ ሲናገር ማሪየስ አልቻለም፤ ፈነዳ

«ኮዜት ትሰሚያለሽ? ይሄ ነው የእርሳቸው ጠባይ! እኔን ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡ ኮዜት
ያደረጉልኝን ታውቂያለሽ? ሕይወቴን ያዳንዋት እኮ እርሳቸው ናቸው፡: ከዚህም
ይበልጥ ነው ያደረጉት አንቺን ለእኔ አሳልፈው ሰጥተውኛል፡ የእኔን ሕይወት ካዳኑና አንቺን ለእኔ አሳልፈው ከሰጡ
በኋላሳ ምን አደረጉ! ራሳቸውን በደሉ:: ይሄ ነው ሰው ማለት፡፡ እና ለእኔ
ለውለታቢሱ፤ ለእኔ ለረሺው፤ ለእኔ ለማይታዘንለት፤ ለእኔ ለወንጀለኛ
ምስጋና ያቀርባሉ፡ ሰማሽ ሕይወቴ ከእኚህ ሰው ጫማ ስር ተደፍታ ብትቀር እንኳን በቂ አይሆንም ያ ምሽግ፣ ያ የቆሻሻ መውረጃ፣ ጨለማ፣ ያ ስቃይ! ያ ሁሉ መከራ የተቀበሉት ለእኔ ሲሉ ነው፡፡ ሕይወቴን በሕይወታቸው ነው የዋጁት ጀግንነት፣ ደግነት፣ ድፍረትና ቅድስና ሁሉ
የእርሳቸው ቢሆን አይበዛባቸውም፡፡ ኮዜት እኚህ ፍጡር መልአክ እንጂ ሰው አይደሉም»
👍15
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ከዌስት ሊን ተመርጦ የሔደው የሕግ መምሪያ ምክርቤት አባል በጥፋት ከወንበሩ ተባረረ ከሱ በኋላ ደግሞ የዌስት ሊን ሕዝብ ጆን አትሊ የተባለ አንድ በአካባቢው የታወቀ ሰው መርጦ ላከ " እሱም ብዙ ሳይቆይ ሞተና በምትኩ ሌላ እንደ ራሴ መምረጥ አስፈለገ" ማን እንደሚሻል ተመከረበት በአካባቢው የነበሩ ይሆናሉ የተባሉ ሁሉ 'ዳኞችም ሳይቀሩ ተገመገሙ ።

ሚስተር ጀስቲስ ይሻል ይሆን ? እለ · እኔ ያልኩት ይሁን ከማለት በቀር
መተማመን አይሆንለትም ቢሔድም የራሱን ሐሳብ እንጂ የዌስትሊንን ሐሳብ መግለጽ አይችልም። ስኳየር ስፒነርሳ ? እሱ ደግሞ በሕይወቱ በአደባባይ ንግግር አድርጎ አያውቅም " ቀይ ሥር ከማብቀልና ከብት ከማርባት በቀር የሚያውቀው የለውም " ኮሎኔል ቤተል ? ለምርጫው ውድድር የሚያወጣው ገንዘብ አያገኝም » ሰርጆን ዶቢዴ?በጣም አርጅቷል እሱም ራሱ“ከምርጫው ገደብ ኻያ ዓመት አልፏል” ብሎ ሣቀና “ ሁላችንም ብቃት ያላቸውን እየዘለልን በማይሆኑትት ሰዎች ላይ ብቻ ነው ያተኮርነው " ስብሰባችንንኮ ያለዐዋቂዎች ስብሰባ አደረግነው አሁን ከመኻከላችን እንደራሴያችን መሆን የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነው ያለን "

“ ማነው እሱ ? አለ ጉባኤው
“ አርኪባልድ ካርላይል ።
ለምን እንደ ረሱት ሁሉም ገረማቸው -ጥቂት ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ የድጋፍ
ጉርምርምታ አሰሙ ።

“ እሺ ካለን ነው ” አለ ሰር ጆን ። “ ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል ...”

ወዲያው ለጉዳዩ ጊዜ ባይስጡት አንደሚሻል ተስማሙና ተሰባስበው ወደ
ሚስተር ካርላይል ቢሮ አመሩ ። ወደ ቤቱ ሊሔድ ሲል ደረሱበትና በሰፊው እየተወያዩ ብዙ ከቆዩ በኋላ እንዴራሴያችሁ እንደሆን ነው የፈለጋቻችሁኝ ? ለጥቅሜ ሁላችሁንም እሸጣችሁ እንዶ ሆንሳ በምን ታውቃላችሁ ? አላቸው "

ግድ የለም ሚስተር ካርላይል ...እናምንሃለን።

እኔ በአሁኑ ጊዜ ፓርላማ ለመግባት ምንም ሐሳብ አልነበረኝም "

ይኸማ አይሆንም !ይልቁንስ ስምህን ለውድድር እንድናስተላልፍ ፍቀድልን ። ካንተ ሌላ ብቁ ነው የምንለው ሰው የለንም አሁን አንተ እያለህ ከኛ አንዳችንን መምረጥ የማይሆን ነው አውጥን አውርዶን ስናየው ' ከድፍን ዌስትሊን ለዚህ ቦታ አንተን ያህል የሚመጥን ሰው አላገኘንም " ስለዚህ አንተን ለውድድር ለማቅረብ ተስማምተናል ። ነገ ወደ ዌስት ሊን ስትመጣ ግድግዳዎቹ ሁሉ'
ምን ጊዜም ካርላይል በሚሉ መፊክሮች አሽብርቀው ታያቸዋለህ።

እንግዲያውስ ነገሩን ጥቂት እንዳስብበት እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ " ግድግዳዎቹን በመፈክሮች ማስጌጡንም ለአንድ ቀን አዘግዩት '' አላቸው "
“ የለም የለም አሁን ወስንና ንገረን የእሺታ ቃልህን ስጠን።

አሁን ከወሰንኩ በእምቢታዬ እጸናለሁ ይኸ እኮ ጥቂት ማሰብ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ » ምናልባትም ጥያቄያችሁን ለመቀበል እችል ይሆናል
ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ።


ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ አማራጭ ስለ አልነበራቸው በቀጠሮዉ ተስማምተው
ሔዱ በውይይቱ ጊዜ አብሮ የነበረው ሚስተር ዲል እጆቹን በርካታ እያፋተገና ሚስተር ካርላይልን ዐይን ዐይኑን እያየ ወደ ኋላ ቀረት አለ "

“ዲል ምነው ? በጣም ደስ ያለሀና ስዎቹ የሚሉኝን እንድቀበል የፌለግህ ትመስላለህ …”

"መቀበል አለብህና" .... ሚስተር አርኪባልድ " ደስ ያለኝ ስለመሆኔ ግን እኔ ብቻ ሳልሆን በዌስት ሊን ውስጥ ደስ የማይለው ሴት ወንድ ልጅ አይገኝም

“ ተው ዲል . . . . በጣም እርግጠኛ አትሁን።
“ ስለምኑ ? እንደራሴያችን ስለ መሆንህ ነው ' ወይስ ስለ ሕዝቡ ደስታ ?
“ስለ ሁለቱም አለው ሚስተር ካርላይል ሣቅ ብሎ ።

ከቢሮው ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጉዳዩን ያብላላው ጀመር " ከፊት ጀምሮ ፓርላማ ለመግባት ማሰቡ እርግጥ ነው ‥የሚወዳደርበትን ጊዜ ግን አልወሰነም " ዘመኑን በሙሉ ለግሉ ሙያ ብቻ የሚወስንበት ምክንያት አልታየውም ። ገንዘብ የማጣት ሥጋት የለበትም » በታወቀው የራሱ ሀብት ላይ ባርባራ ይዛው የገባችው
ሲጨመርበት ከአሁኑ ዐይነት አኗኗራቸው ከሚፈለገው በላይ ነው ሥራውን ለመተው ግን አሳብ የለውም ። ምክንያቱም ሥራው : በራሱም ጠንቃቃ አሠራር
ሳቢያ የሚያስከብረው ከመሆኑም በላይ ጠቀምቀም ያለ ገቢ የሚያገኝበትና ከልቡ
የሚወደው ሙያ ነው " ምንም ቢደረግ ሥራ ፈትቶ ለመኖር አይፈልግም " ነገር
ግን ሁልጊዜ ከሥራ ቦታው እንዳይለይ የሚያስገድደው ሁኔታ የለም ። ሚስተር ዲል
የሱን ያህል መምራት ይችላል እንዲያውም ያገልግሎት ዘመንና የሥራ ልምዱ ከተቆጠረ ይበልጠዋል " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ለፓርላማው ሥራ ወደ ለንደን ሲሔድ ኃላፊነቱን ያለምንም ሥጋት ለዲል ቢተውለት በሚገባ ሊያካሒድለት ይችላል " ፓርላማ መግባቱ ካልቀረ ደግሞ የበለጠ ጥቅምና መስሕብ ካለው ከማንኛውም ቦታ ይልቅ ዌስት ሊንን ወክሎ ቢገባ ይመርጣል አሁን ዌስትሊን አንድ አባል ስለሚያስፈልጋት ለሱ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ ታየው " ጥሩና ብቁ የሕዝብ
አገልጋይ እንደሚሆንም ያምናል " ተሰጥዎው ሰፊ ፡ ንግግሩ አርኪ ነው እውነተኛና ቀና መንፈስ አለው " ወገኖቹን በሙሉ ኃይሉና ችሎታው እንደሚያለግል ያውቃል " እነርሱም ያውቃሉ "

ቅጠላ ቅጠሎቹ ባበቡበት ' ዛፎችና ቁጥቋጦዎች አዲስ ያቆጠቆጠውን ለምለም ቅጠላቸውን በለበሱበት ' በዚያ ደስ በሚለው የጸደይ ምሽት ሁሉም ነገር በተስፋ የተመላ ይመስል ነበር ።

ሚስተር ካርላይልም በቀረበለት ፡ ተስፋ ያለው ዕድል ከልቡ ተደሰተ "

ባርባራ ከሳሎኑ መስኮት ቁማ ትጠብቀው ነበር ሲገባ ደንበክ ደንበክ እያለች ወደሱ ቀርባ በብሩህ ዐይኖቿ ውስጥ የፍቅር ብርሃን እየዋለለ ፊቷን ወደሱ ቀና አደረገች።

'' ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት እንደዚያ ሆና እንደ ቆመች እጆቹን ከወደ ጀርባው
አድርጎ ።

" ምነው ? ደኅና እንዴት አመሸሽ ለማለት አቀበት ከሆነብህ እስከ ሳምንት ድረስ አትስመኝም ልል ሐሳብ አለኝ አርኪባልድ ”

ሚስተር ካርይል በአነጋገሯ ሳማቀና በዚህ የበለጠ የሚቀጣው ማነው ?”
አላት በሹክሹክታ

ባርባራ ለንቦጯን ጣለች እንባዋ ወዲያው በዐይኗ ሞላ “ ባንቺ ይብሳል '
ማለትህ ነው ! ለኔ ደንታ የለህምን አርኪባልድ ?”

በሁለት አጆቹ ጠምጥሞ ይዞ ከደረቱ እቅፍ አደረጋትና መልሶ መላልሶ ሳማት
ላንቺ ማሰብ አለማስቤንማ ታውቂው የለም ? አለት በጆሮዋ "

ይህ ሁሉ ሲሆን ያቺ የፈረደባት ሳቤላ ትመለከት ነበር በዘመኑ ለሷም ሲያደርገው የነበረው ሰላምታ ነው የገረጣው ፊቷ ደም እንደ ለበሰ ልክ እንዳመጣጧ ሹልክ ብላ ሳያዩዋት ወታ ወደ ክፍሏ ተመለሰች " ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ወደ መስኮቱ ሳባትና ክንዱን በሽንጧ ሳይ አድርጎ እንደቆሙ “ስሚ እስቲ ባርባራ ካመት ውስጥ ለጥቂት ወሮች ለንደን ብንቀመጥ ምን ይመስልሻል ?

“ ለንደን ? እኔ እዚሁ በደስታ እኖራለሁ " የምን ለንደን አመጣህ ደግሞ ? ለንደን መቀመጥ አማረኝ እንዳትለኝ "

“ እርግጠኛ አይዶለሁም ግን አንድ ነገር ተጠይቄአለሁ ዌስትሊኖች እንደ ራሴያቸው እንድሆን ይፈልጉኛል " ከስሜ ላይ የፓርላማ አማካሪ የሚል ቅጽል ሲጨመርበት ማየቱ ደስ ይልሻል ?

“ጣም ጥሩ ነው ...አርኪባልድ " ሕዝቡ ወትሮም ቢሆን ይወድሃል አሁን ደግሞ የበለጠ ያከብርሃል " ዘለዓለም የገጠር ጠበቃ ሆኖ መኖር ላንተም ደግ አይደለም " ግን አሁን ለዕለት እንጀራህ ስትማስን አያለሁ " ተመርጠህ ብትሔድ ግን
ዌስት ሊን ላይ ለመሥራት አትችልም " ”
👍15
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››
👍8910🥰3👎1🔥1😁1