አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገ/የሱስ


የታላቁ ምሥሪቅ አፍሪቃ ስምጥ ሸለቆ አካል በሆነ ተራራማ ቦታ ላይ በተቆረቆረችው ዲላ ከተማ ውስጥ መኖር ከጀመረ ስባት ዓመት ሞላው፡፡ ነገር ግን
በብርዳማነቷ በምትታወቀው መሀል ሜዳ ከተማ ተወልዶ ያደገ በመሆኑ የዲላ ከተማን ሙቀት በቅጡ ሊላመደው አልቻለም:: በተለይ ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስክ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ የሚወርደው ያጸሃይ ንዳድ መላ ሰውነቱን እንደ ሰም እያቀላጠ ያቅለበልበዋል፡፡ እንደ መፍትሄ የሚጠቀምበት ዘዴ አካላቱን በቀዝቃዛ ውሃ መለቃለቅ ብቻ ነው፡፡

ነርስ አስቻለው ፍስሀ ዛሬም ከሚሰራበት ዲላ ሆስፒታል ወደ ዜሮ አምስት ቀበሌ የሚገስግሰው ከቤቱ ደርሶ አካላቱን ቀዝቀዝ ባለ ውሃ እስከሚለቃለቅ ድረስ እየቸኮለ ነው። ወሩ ታህሳስ፣ ሰዓቱ ደግሞ ዘጠኝ አካባቢ በመሆኑ፡ ሙቀቱ ወደር አልነበረውም፡፡ ጥቁር ቆዳ ጃኪቱን ትከሻው ላይ በማንጠልጠል በጥቁር ቡኒ ሱሪው ላይ ነጭ ሽሚዝ ለብሶ ከሩቅ እያንቦገቦገ በመገስገስ ደርሶ ተዘግቶ የዋለ ቤቱን
ሲከፍተው፡ ግን የችኮላና የድካሙን ያህል በደስታ አልተቀበለውም፡፡

'ፐ' ምን ጉድ ነው ባካችሁ?» አለ በሩን ከፈት አድርጎ እጀታውን
እንደያዘ። ወደ ወስጥ መልከት ሲል ወለሉ አስጠላው፡፡ ትናንት ማታ የቅርብ ጓደኞቹ የሆኑት በልሁ ተገኔና መርዕድ እሸቴ ጫት ሲቅሙበት አምሽተዋል፡፡ የዚያ
ውጤት የሆኑ የጫት ገራባ፣ የክሰል ማንደጃ ከነአመዱ፣ የሻይ ማፊያ በራድ፣መጠጫ ብርጭቆዎች ሁሉ በወለሉ ላይ ብትንትን፣ ዝርክርክ እንዳሉ ናቸው፡፡ የወንደ ላጤ አልጋው እንኳ አልተነጠፈም ፣ አንሶላና ብርድ ልብሰ ምስቅልቅል
ልብሱም በአንድ ወገን ተንዘርፏል፡ በቃ የኔ ነገር እንዲህ ሆኖ
ይቅር!?» አለና በር ላይ ቆሞ ለረጂም ጊዜ ተመስካተው::

«አዬ ትርፊ!» አለ እንደገና ወደ ውስጥ ገባ እያለ፡፡ በአንድ እጁ ጃኬቱን በሌላው ሽንጡን ያዝ አድርጎ መሀል ወለሉ ላይ በመቆም «አጉል ልማድ ካስለመድሽኝ በኋላ ጥለሽኝ ጠፍተሽ እንዲህ ታዘበራርቂኝ?» ሲል ከበርካታ ወራት በፊት ድንገትና በማያውቃው ምክንያት የጠፋችበትን የቤት ሰራተኛውን አማረራት። ጃኬቱን ወንበር ላይ ጣል አድርጎ ያንን ቤት ለማስተካካል ቃጣ። ግን ደግሞ በጣም ስለደከመው ትንሽ ለማረፍ ፈልጎ ወጀዠደ አልጋው አለፈ:: የተንዘረፈፈውን የአልጋ ልብስ ብቻ ስብስብ አድርጎ ጫማውን ሳያወልቅ እግሩን በጎን በኩል አንጠልጥሎ በጀርባው ጋለል አለ። ትርፌን አሁንም አሰባት፡፡ በእሷ አለመኖር ኑሮው
ከመመሰቃቀሉም በላይ አጠፋፏ ድንገት ስለነበረ የደህንነቷም ነገር ያሳስበው ጀመር፡፡

በትርፌ አለመኖር በቤት ወስጥ የተከሰተበትን አለመመቸት ሲያስብ ቆይቶ የመስሪያ ቤቱም ሁኔታ ድንገት ከፊቱ ድቅን አለበት፡፡ አስቻለው በዲላ ሆስፒታል
ውስጥ ሰላም የለውም፤ የሰው ተባይ እየነክሰው ተቸግሯል። በዚያው ልክ የስራ ሞራሉ እየወደቀና እየተሸረሸረ ሄዶበታል፡፡
ለዚህ ሁኔታ ዋና መነሻ የሆነው ከሶስት ዓመታት በፊት በዲላና አካባቢዋ ተከስቶ የነበረው የማጅራት ገትር ወረርሽኝ በሽታ ነበር። በተለይ በከተማዋ በርካታ
ህጻናንት እየሞቱ በየቀኑ ቀብር ሆኖ በየቦታው ድንኳን እየተተከለ ህዝቡ እልቃሽን ሀዘንተኛ ሆኖ ዲላ ከተማ መዓት የወረደባት መስላ ነበር፡፡
ዘመኑ ደግሞ በራሱ በሽተኛ፡ አምባገነኖች ዘውድ ሳይጭኑ የነገሱበት እውር ድንብራቸውን ሀገርን የሚመሩበት፡ ሳያውቁ የሚፈላሰፉበትና በተለይ
ካድሬዎቻቸው በሶስት ዓይነት ካኪ ቀለም ልብስ ራሳቸውን እየጀቦኑ ምርጥ ዜግነታቸውን በይፋ ያወጁበት ወቅት ነበር። በዚያው መጠን ዜጎች በሞትና በስደት እንግልትና ውክቢያ አበሳ የማያዩበትና መላ አገሪቱ በመጤ ፖለቲከኛ ወረርሽኝ የምትታመስበት የቅስፈት ዘመን ነው:: ከማጅራት ገትር ወረርሽን ጋር ተያይዞ በዲላ ሆስፒታል ሰራተኞች ላይ የሥነ ልቦና ቀውስ ያስከተለ መመሪያም ተላልፏል::.…የህክምናም ሆነ የክትባት አገልግሎት ቅድሚያ ለጓዶችና
ለቤተሰቦቻቸው ይሰጥ የሚል።

ነርስ አስቻለው ፍሰሀ ቀድሞም ቢሆን በካኪ ለባሾች ላይ ጥሩ አመለካከት አልነበረው፡፡ ከዓመታት በፊት በገንዘብ ይረዳው የነበረውን ወንድሙን ገድለውበት
ተቸግሮ እንዲማር አድርገመታል። ከዚያም በላይ እልፍ አእላፍን እንደ ገደሉ ሌልቦናጡ ያውቃልና ፖለቲካዊ መሠረታቸውም በመግደልና በማስገደል ላይ የተገነባ መሆኑን ይረዳል። ራስ ወዳድ የሆናቸውን በውል ተገንዝቦታል፡፡ በዚያ ሰሞን
ያስተላለፉት መመሪያም የዚሁ ማንነታቸው ገላጫ ነውና አስቻለው በሁኔታው አንጀቱ ተቃጥሏል። አንድ ቀን ጠዋት ደግሞ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን
ተራ በተራ እያወራ የህክምና እርዳታ ይሰጥ በነበረበት ክፍል ውስጥ አንዲት ኑሮ ደልቷት የወፈረች፤ ጉንጯ ሊፈነዳ የደረሰ፣ ቀላ ያለች ሴት ክፍሉን ከፍታ ገባች።
በአንገቷ ላይ የተጋደመው የወርቅ ሀብልና በጣቶቿ ላይ የተደረደሩት የአልማዝ ጌጣጌጦች እንደ ፀሐይ ያበራሉ፡፡
እስቻለው በአጋጣሚ የሴትዮዋን ቤተሰባዊ መሰረት ያውቃል፡፡ አመጣጧ የዚያ መመሪያ ውጤት መሆኑ ስለገባው ሰውነቱ በንዴት ተለዋውጦ በዚሁ ንዴት ውስጥ ሆኖ <<ማን ጠራዎት?» ሲል አፈጠጠባት፡፡
ሴትዮዋ ለአስቻለው ቁጣ ቦታ አልሰጠችውም፣ እንዲያውም ኮራ ብሳ ወደ አስቻለው ጠጋ ማለት አንዲት ወረቀት ዘረጋችለት፡፡ ወረቀቷን የንጥቂያ ያህል ከእጇ ወስዶ ሲያነባት የዘጠኝ ስዎች ስም ተዘርዝሮ ቅድሚያ የክትባት አገልግሎት እንዲሰጣቸው የታዘዘበት ማስታወሻ ሆና አገኛት። ወረቀቷን ለሴትዮዋ መልሶ
በመዘርጋት «ይቅርታ የኔ እመቤት፣ በቅድሚያ በበሽታው ተይዘው የሚሰቃዩትን ልርዳና የእርስዎን በኋላ! ውጭ ይጠብቁኝ፡፡» አላት::
ወይዘሮዋ በቁጣ ስሜት ግንባሯ ቁጥርጥር አለ፡፡ ለጠጥ ብላ ወረቀቷ ከአስቻለው እጅ እየተቀበለች «ጓድ ባርናባስን ልጥራቸው እንዴ?» ስትል
ጠየቀችው፡፡

ለኔ አያስፈልገኝም:: የሚረዳዎት ነገር ካለ እዚያው ጨርሱ! አለና
ፊቱን ከሴትዮዋ ላይ መልሶ ስራውን ቀጠለ፡፡ ወይዘሮዋ ከክፍሉ ወጣች። ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ግን ያቺ ሴትና ባርናባስ የአስቻለውን ቤሮ ከፍተው ተከታትለው ገቡ ባርናባስ ብጭጭ ያለ ቀይ ነው፤ ዕድሜው ወደ ሃምሳ አምስት የሚጠጋ
ቀጭን ረጅም፡፡ ደማቁን ሰማያዊ ካኪ ለብሶ ወርቃማ ቀለም ያላት ጠበብ ያለች መነፅር አድርጓል፡፡ የሆስፒታሉ የአስተዳደር አገልግሎት ሃላፊና የፓርቲ መሠረታ ድርጅት አንደኛ ፀሃፊ ነው፡፡
«አቶ አስቻለው!» ሲል ጠራው ባርናባስ ኮራ ባለ አነጋገር፡፡
አቤት አለው አስቻለው በንቀት ስሜት።
"የወይዘሮ ጥበቧን ማንነት አታወቅም እንዴ?"
"በትክክል አላውቅም"
"የአውራጃችን ፓርቲ ኮሚቴ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆነው የጓድ ሙሉነህ ባለቤት ናት እኮ!
"ታዲያ ይኼ የምንነት እንጂ የማንነት መገለጫ ነው እንዴ?"
“ምን?" አለ ባርናባስ ድንገት ክም ብሎ። መነፅሩን አውልቆ እስቻለው በሌጣ ዓይኑ እየተመለከተ ምንድነው ልዩነቱ?» ሲልም እንደገና ጠየቀው፡፡
"አሁን ምን ልርዳችሁ? ክትባቱን በተመለከተ ከሆነ ለወይዘሮዋ
ነግሬያቸዋለሁ::» አለ አስቻለው ዓይኑን በሁለቱም ላይ ሰካ ነቀል እያደረጉ።

«መመሪያ አትቀበልም ማለት ነው?

«በበኩሌ ቅድሚያ ህይወት ማዳን የሚለውን የህክምና መርህና ሥነ-ምግባር ማክበሬ ነው!»

ባርናባስ ከዚያ በኋላ ምንም አላለም፡፡ ስስ ከንፈሮቹን እንደ እንሽላሊት ጅራት ወዲያ ወዲህ እያንቀሳቀስ ቀጫጭን ዓይኖቹን በአስቻለው ላይ ስክቶ ለአፍታ
ያሀል ከተመለከተው በኋላ ሴትየዋን አስከትሎ ከክፍሉ ወጣ።
👍6
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገ

...አፍንጫ ጎራዳነቷ ውበቷን አደመቀው እንጂ አላደበዘዘውም፡፡ ስላማዊት ብዙ ሰው ቢረባረብባትም ከሁሉ የበለጠ የምትቀርበውና ወዳጇ
መሆኑ በብዙዎቹ ዘንድ እየታወቀ የመጣው ታደሰ ነው። ታደሰ መልኩ ጥቁር ሆኖ ረዘም ያለ ጉብል ነው፡፡ እሱ ሲመጣ ሰላማዊት ማንንም አታነጋግርም፡፡ ሄዳ እሱ ላይ ጥብቅ ነው። ይሄ ሁኔታ በፅጌ አማካኝነት ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ሁሉ ስለተወራ ታደሰ ብቅ ማለቱን ሲያዩ ስሟን
እንደማስቲካ ሲያኝኩት ይውላሉ።
“አሳበዳት እንጂ! ነፍሷን አጠፋላት!ታደሰን አታውቂውም እንዴ? ደላላ ነው እኮ! ኸረ በሌላም የሚጠረጠር ሰው ነው አሉ። አንዱ ውሽማዬ ስለሱ ነግሮኛል።ነጭ ለባሽ ነው ተብሎ ይጠረጠራል ብሎ አጫውቶኛል”
“አረ እባክሽ?! ነጭ ለባሽ ?ምን አስነክቷት ይሆን እንደዚህ በፍቅር የከነፈችለት?”
“ትቀልጃለሽ እንዴ? ያቅማታላ! ብር እንደ አሸዋ ይበትንላታላ! እስቲ ይታይሽ? ደላላ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ በነጭ ለባሽነቱ መንግሥት ይከፍለዋል! ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ነው
“ምን እያቀመሰቻቸው ይሆን ወንዶቹ ሁሉ እንደዚህ በሷ ላይ የሚረባረቡት በናትሽ?”
“ወረት ነው እባክሽ! ወረት! አዲስ ጀማሪ አይደለችም? በወረት ነው እንደ ንብ የሚከቧት”
የታደሰ ደግሞ ባሰ፡፡ ፍቅር ድብን አድርጎ ገድሎታል እኮ፡፡ ምን ማለትሽ ነው? አሁን አሁንማ ግንባሯን ሳይሳለም አይውልምኮ! እኔም ሳላየው የዋልኩበት ቀን የለም”
“ምን ታደርጊዋለሽ አጅሬ የወረት ፍቅር ነዋ!” ተንሾካሾኩባት። እውነትም ከዚያ ሁሉ የወንድ መንጋ መካከል ለታደስ ልዩ ፍቅር ነበራት። ታደሰ ፍቅሩን በብዙ መልኩ የሚገለፅላትና የሚያስፈልጋትን ሁሉ የሚያሟላላት የስካር ሳይሆን እውነተኛ ጓደኛዋ ነበር።
ዛሬም እንደ ወትሮው ካፖርቱን ከላይ ጣል አድርጉ ባርኔጣውን ደፍቶ አንገቱ ላይ ሻርፕ ጠምጥሞ ተፍተፍ የሚለው ወደሷ ነበር፡፡ ከሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቀኝ ተገንጥሎ ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን ቀጭን የአስፋልት መንገድ ተከትሎ ወደ ፍቅረኛው ወደ ሰላማዊት ለመድረስ እየተጣደፈ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኗል። በአላፊ አግዳሚ ላይ ዐይኖቻቸውን እያፈጠጡ የሚያስፈራሩ ሴተኛ አዳሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። በዚህ
ሰዓት እብዱ ምንሽንሽ ከአካባቢው አይታጣም ነበር፡፡ አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ እየዘለለ ድንጋይ እያነሳ ድንጋይ እየጣለ ይሯሯጥ ነበር፡፡ ሣንቲም
ይለምናል። ከሰጡት ይቀበላል፡፡ ዝም ካሉት ደንታም የለው። የሱ ቁም ነገር መዝለል፣ መዝለል፣ ድንጋይ መፈንቀል፣ ድንጋይ ማንሳት ድንጋይ መጣል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ግን በሱ ምትክ ሰካራሙ ታከለ ያንን የማያስከፍል ድራማውን እያሳየ ለሴተኛ አዳሪዎች መሳለቂያና መደበሪያ ሆኖላቸው ነበር፡፡ መጀመሪያ ቀይ አጣብቂኝ ሱሪ ለብሳ ፀጉሯን እንደ ገዳይ ጐፈሬ ወዳቆመችው ሴት ቤት ጥልቅ ብሎ ገባ..
ሰካራሙ ታከለ ትዳሩን በመጠጥ ምክንያት ካፈረሰ በኋላ መቅኖ አጥቶ በደሞዝ ሰሞን ሲጠጣ፣ያገኘውን ሲጋብዝ፣ ሲሸልም፣ ሲበትን ይከርምና
ባዶ ኪሱን ጨረቃ አስመስሎ መውጣት ልማዱ ነው። እንደምንሽንሽ ሲለይለት አንድ ሀሙስ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ሴትዮዋ በሯን ዘጋችና...
“እሺ ሂሣብ በቅድሚያ!” አለችው።
“ም. ን. ድ. ነው... ቅርሚያ ቅርሚያ! የምትይው? እኔን አታ..
አታምኝ.. ኝ.. ኝምምም?” አላት ልፍድድ ባለ የስካር ንግግር።
“ኡፋ! ሰውዬ ወሬ አታብዛ ! የምትከፍል ከሆነ በቅድሚያ ክፈልና እሺ። አለበለዚያ ውጣልኝ!ገበያዬን አትዝጋ!” አለችና አንባረቀችበት። ታከለ በጠጅና በአረቄ ብዛት የደነበሹ ዐይኖቹን ብልጥጥ አድርጎ ሲመለከታት ተንኮል የቋጠረ አመፀኛ ዝንጀሮ እንጂ ለጉዳይ የገባ እንግዳ አይመስልም ነበር።
በል ተናገር?! ያለበለዚያ ውጣ!” የዘጋችውን በር መልሳ እየከፈተች ጭኽችበት።
“ቆይ .. እ- ሺ ቆይ! ቆይ!” አለና ወደ ኪሱ ገባ፡፡ ያገኘው ሰላሳ አምስት ሣንቲም ብቻ ነበር።
እሺ ያው..ልሽ!
አትፈልጊምምም.?” እየተንተባተበ፡፡ ብልጭ አለባት።
ከኋላው አሽቀንጥራ ስትወረውረው ከፊት ለፊቱ ካለው ቆሻሻ ውሃ ከሚ ወርድበት ቦይ ውስጥ ሂዶ ተወተፈ፡፡ ከዚያም እየተውተረተረ ተነሳና ሣንቲምቹን መለቃቀም ጀመረ፡፡ እንደምንም ብሎ ሃያ አምስት ሣንቲም አገኘ።

ትርዒቱን እያዩ ወደሚሳሳቁት ግራና ቀኙን ወደተኮለኮሉ ሴተኛ አዳሪዎች እየተመለከተ“ይህቺን... ፈላጊ!.. ይህቺን... ይህቺን.” እያለ ሳንቲ ሞቹን ሽክ... ሽክ... ሽክ ሲያደርጋቸው የበለጠ በሳቅ ፈነዱ።
“አንተ ጠንባራ ሰካራም ድራሽህ ይጥፋ! የቀረችህ እሷ ናት። ሂድና ለሚስትህ ቀሚስ ግዛበት ፉዞ!” የስድብ መአት አወረዱበት። እሱም እየተንገዳገደ ቁልቁል ወረደ። ታደሰ ይህ ትርዒት የሚካሄድበትን አካባቢ
አልፎ ወደ ሰላማዊት ዘንድ ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል። አስፋልቱን ከመሻገሩ በፊት ግን ቆም ብሎ ምን ይዞላት እንደሚሄድ አሰላሰለ። እንደ
ሴተኛ አዳሪነቷ ሳይሆን እንደ ሚስቱ ያስብላት ስለጀመረ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚሄድ አባወራ እንጂ ወደ መሸታ ቤት የሚሄድ ጠጪ አይመስልም ነበር፡፡ ሰላማዊትም ከልቧ ስለምትወደው እሱ ከመጣ ሌላው ጠጪ
ሰው መስሎ አይታያትም፡፡ እንደሚጨነቅላት ስለምታውቅ አፀፋውን ፍቅር እየሰጠችው ነው፡፡ ታደስ ከእማማ ወደሬ ቤት ከፍ ብሎ ወደሚገኘው ሉካንዳ ቤት ገባና ከሽንጥ ሥጋ ላይ ሁለት ኪሎ ግራም አስቆርጦ አስጠቅልሎ ሄደ። ወይዘሮ ወደሬ የታደሰ ውለታ እየከበዳቸው ስለመጣ በሱ ምክንያት ሰላማዊትን ማክበርና መፍራት ጀምረዋል። ታደሰ ወደ ቤት ሊገባ ካለ በኋላ ምናምን እንዳቋረጠው ሰው ወደ ኋላው ሰግጠጥ አለና ቆመ፡፡ቀስ ብሎ በጓሮ በኩል ዞረ። የጓሮውን በር ያለሱ የሚደፍረው የለም።

“ሰላምን ጥሪያት” አላት ላፅጌ። ሰላማዊት ፅጌ ስትነግራት ሮጣ መጣች።
“ውይ ታዴ!”እቅፍ አድርጋ ሳመችውና በእጁ የያዘውን ተቀበለችው።
በጓሮ በኩል ዞሮ የገባው የያዘውን ሊሰጣት መሰላት። ድርጊቱ የበለጠ ገረማት። ማንም እሱ የሚያደርገውን አያደርግላትም። የፈለገውን ያክል ገንዘብ አስታቅፈዋት ቢሄዱ ታደሰ የሚያስበውን ያክል አስበውላት አያውቁም፡፡ በበዓላት ቀን ሹልክ ብሎ ይመጣና ገንዘብ ይሰጣታል። እንዳይደብርሽ እያለ ትያትርና ሙዚቃ ቤት ወስዶ ያዝናናታል፡፡
“አይ ታደሰ?አሁንስ አበዛው ምነው እሱ እንዲህ ተጨነቀ? እኔ ውለታ
ሲበዛብኝ ደስ አይለኝም፡፡ ይከብደኛል። ከሌላው የተለየ ለሱ ምን የተደረገለት ነገር አለ?” ወይዘሮ ወደሬ ስለታደሰ ተጨነቁ፡፡
“ታድዬ እቤት ትገባለህ ወይስ እዚሁ ጠላ ይዤልህ ልምጣ?” ስትል ጠየቀችው።
“እቤት አልገባም እዚችው ጓሮ ቁጭ ብለን ትንሽ አጫውቺኝና ጠላ ጠጥቼ እሄዳለሁ” አሁን አሁን የገባው ጠጪ ሁሉ እንደፈለገው እየጎተተ ሲያሻሻት፣ ሲያቅፋት፣ ሲስማት፣ ሲደባብሳት ማየት እያስጠላው መጥቷል።

“እሺ የኔ ቆንጆ ይዤልህ ልምጣ” አለችና ተመልሳ ገባች።
“ታዴ ወደ ቤት አይገባም እንዴ ሰላም?” አሉ ወይዘሮ ወደሬ።
“ውጭ ይሻለኛል ብሉኝ እኮ ነው”