አትሮኖስ
279K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


#አዲስ_ዓለም

..የመንገዱ መብራቶች ተበላሽተው ብርሃን አይሰጡም። አካባቢው ፀጥ እረጭ ብሏል። ትናንትና ማታ እስከ ስድስት ሰዓት የነበረው ጩኸት፣ ሁካታ የሰካራሞች ልፍለፋ፣ የሴተኛ አዳሪዎች ስድብ፣ በየቀይ መብራቱ ውስጥ የነበዙ ጠጪዎች ዳንኪራና ጭፈራ ትርምሱ ሁሉ እዚህ ቦታ
የነበረ መሆኑ የሚያጠራጥር ነው፡፡ የሥጋ ቤቶቹ ብርሃን ድምቀት፣ከቡና ቤት ቡና ቤት የሚያማርጠው ጠጪ ብዛት፣ የሙዚቃው ጩኽትና የመኪናው ኳኳታ ጆሮ ሲያደነቁር እንዳላመሽ ሁሉ እንደዚህ እንደ አሁኑ እረጭ ብሎ ሲታይ በግርግርና በፀጥታ መካከል ያለውን ልዩነት
ለማሳየት ደፈጣ የያዘ ይመስል ነበር፡፡

የወዳደቀ አጥንት ለመለቃቀም የሚያነፈንፉ ውሾች ውር ውር
ይላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን ያን ሰው የማይታይበትን አካባቢ ፀጥታ በማደፍረስ የጠዋት ገበያዋን ለመላፍ የተጣደፈች ታክሲ ከእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ አቅጣጫ በረረች፡፡ በዚያው ቅጽበት ደግሞ
ቁልቁል ከፒያሳ ወደ እሪ በከንቱ እየዘለለ የሚወርድ ሰው ታዬ። መላ ሰውነቱን ሬንጅና ጥላሸት የተቀባ ፀጉሩ እዚህም እዚያም ተገምዶ እንደ ጭራሮ የቆመ፣ ጎድኖቹ ሥጋ ባልለበሰ አጥንት የገጠጡት እብዱ ምን ሽንሽ! ብቻውን በመንገዱ ግራና ቀኝ ቱር ቱር እያለ እየተሯሯጠ ሽቅብ
ይወጣል ቁልቁል ይወርዳል። ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው ለተመልካች ያስፈራራሉ። ከወገቡ በታች እዚህም እዚያም የተቦጫጨቀ ሱሪ መልበስ
ከተባለ ለብሷል። ቆም ይልና ድንጋይ ይፈነቅላል ያነሳውን መልሶ ይወረውረዋል። ደግሞ ወደታች ይወርዳል። ከዚያም ጉንበስ ይልና የሲጋራ ቁራጭ ለመልቀም ያነፈንፋል።እንደገና ወደ ላይ ይወጣል። የዚያ አስፈሪ
የጨለማ ንጉሥ ሁሉም በየቤቱ በተከተተበት ሰዓት እሱ እየዘለለና እየቦረቀ ብቻውን በየመንገዱ ላይ ሲሯሯጥ ምሽቱን ለብርሃን ለማስረከብ የተዘጋጀ ባለሥልጣን ይመስል ነበር።

ከለሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ሆኗል። ወደየጠቅላይ ግዛቱ የሚጓዙ መንገደኞች አውቶቡስ ተራ ለመድረስ በዋናው አስፋልት መንገድ ላይ ብቅ ብቅ ብለዋል። በዚያ ሰዓት በእግር የሚጓዝ መንገደኛ አንድም በራሱ የተማመነ አሊያም ከወሮበላና ከማጅራት መቺው ሰይፍ እግዚአብሔር እንዲጠብቀው በልቡ ፀሎት እያደረስ በፍርሃት የሚራመድበት እንጂ ልቡ
በድፍረት ተሞልቶ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት አልነበረም፡፡ ለሁሉ ነገር ግድ
የለሌው ለማጅራት መቺው ለብርዱ ለፀሀዩ ለሞትም ለህይወትም ደንታ የሌለው እብዱ ምንሽንሽ ብቻ ነበር። የእሪ በከንቱን ድልድይ ተሻግሮ
ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና አንድ ዕድሜው ከሰላሳ ስምንት እስከ አርባ አመት የሚገመት ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ለመሄድ የሚገስግስ ሰው ብቅ! አለ። ሰውዬው ምንሽንሽን ሲያየው “በስመአብ ወልድ ጌታዬ” አለና
አማተበ፡ የሰይጣን ቤት አጋፋሪ የመሰለውን እብድ ሲመለከት ከመንገዱ ፈንጠር አለና ወደ ዳር ወጣ፡፡ ካደረበት ከዘውዲቱ ሆቴል ቁልቁል ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን መንገድ ሲጀምረው ዳፍንቱ በብርሃን ባለመተካቱ ልቡ ፈራ ተባ እያለ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
የአራት ልጆች አባት የሆነው ጓንጉል ቢሆነኝ አዲስ አበባ የመጣው ያደለባቸውን ሁለት ሠንጋዎች ወልዲያ ገበያ ሸጦ ባገኘው ገንዘብ ለሚስቱና ለልጆቹ ልብስና ጫማ ለራሱ ደግሞ የፋሲካን በዓል መዋያ ልብስ
አማርጦ በርካሽ ዋጋ ገዝቶ ቀሪውን ገንዘብ ለልዩ ልዩ ችግሮች ማቃለያ ሊያደርግና በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነችው የታናሽ እህቱን ልጅ ሊጠይቅ በዚያውም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባን ሊጎበኛት ነው።
በዚሁ መሠረት ጣጣውን ጨርሶ ለአራቱ ልጆቹ ልብስ ሲያማርጥ ቆይቶ ሻንጣ ገዝቶ ከቆጣጠረና አዳሩን ዘውዲቱ ሆቴል ካደረገ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ለመገስገስ ከዚያም ቤት ደርሶ ልጆቹና ሚስቱ ከበውት ሲንጫጩ የኔ ያምራል የኔ ይበልጣል እያሉ ህፃናቱ እርስ በርሳቸው ሲሟገቱ፣ሚስቱ ደግሞ የገዛላትን ቀሚስ እየላካች ረዝሞ ከሆነ ሰነፍ ልኬን እንኳን
የማታውቅ? ስትለው፣ ልኳ ከሆነ ደግሞ እሰይ የኔ አንበሳ” ብላ ስታደንቀው፣ ጉንጬን ሳም ስታደርገው በሀሳቡ እየታየው ቶሎ ሊደርስላቸው ነበር ለሊቱ አልነጋልህ ብሎት ዐይኑ ፈጥጦ ያደረውና ከለሊቱ ለአሥራ
አንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ያውም የረፈደበት መስሎት ልብሱን በፍጥነት ለባብሶ የወጣው...

ጓንጉል ምንሽንሽን ሲያየው በድንገጤ እግሩ ተሽመደመደበት እንደዚህ አይነት አጋንንት መሳይ ሰው ሚልኪው ጥሩ አይደለም አለ በልቡ። የሰው ዘር ሳያይ ዐይኑ ያረፈው በእብዱ ላይ ነበር። እብዱ ምንሽንሽ ወደሱ እንደመጠጋት ብሎ ፊት ለፊት ሲመጣበት በድንጋጤ ወደ ግራ
በኩል እሸሻለሁ ሲል አደናቀፈው።
“ወንዱ!” አለና ፎክሮ ተንገዳገደ። እብዱ ጠጋ አለውና እጁን ዘረጋለት።
ፍራንክ እንደሚጠይቀው አወቀ። ወይ ይቺ ፍራንክ? አለ በልቡ።እብዱም፣ጤነኛውም፣አዋቂውም፣ ህፃኑም ሁሉም ይወዷታል ሲል ተገረመ::
የመጨረሻዋ የስድስት ወር ህፃን ልጁ እንኳን ወሪቀት በግራ እጁ ብር በቀኝ እጁ ይዞ ሲያስጠጋላት እጅዋ ወደ ቀኝ እጁ ነበር የሄደው። ይሄን አስታወሰና ትንሽ እንደ መሳቅ ብሎ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ያገኘውን ድፍን ሃያ አምስት ሣንቲም ኣውጥቶ ወረወረለት። ምንሽንሽ ሳንቲሟን
ለማንሳት ጐንበስ ሲል እሱ ደግሞ አውቶቡሱ እንዳያመልጠው በሩጫ ዳገቱን ተያያዘው፡፡
የሆነ ነገር ውልብ አለበት፡፡ የሰው ቁመና መስለው። ከግራ ወደ ቀኝ
የሮጠ ነገር ነበር፡፡

“ጅብ ነው! ጅብ መሆን አለበት። ከወዲህኛው ገደል ዘሎ ወደዚያኛው መግባቱ ነው! ልክ ነው አውሬ መሆን አለበት! አቋረጠኝ እኮ ልክ ነው ደግሞ ጠቆር ያለ ነገር ነው! ወይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ከዚህ ጉድ ያውጣኝ እንጂ ያጋጠመኝን ሁሉ ቤት ገብቼ ለሚስቴ ነው የማጫውታት፡፡ ገና በጠዋቱ ቀንዳም ጋኔን የመሰለ እብድ ለከፈኝ እሱን ሳልፍ ደግሞ ይኸውና ጥቁር ጅብ አቋረጠኝ። እግዚአብሔር ያውቃል” እያለ በልቡ እያወራ ወደ ድልድዩ ተጠጋ፡፡ ሰግጠጥ እንደማለት
አደረገው። ድልድዩ ላይ ሲደርስ ከበደው፡፡ ገልመጥ፣ ገልመጥ አለ። ሰላም ይመስላል። ፀጥ ረጭ ብሏል። ብቅ ብቅ ብለው መታየት የጀመ ሩት ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሄደዋል። በዚያ መንገድ ላይ ተፍ ተፍ የሚለው እሱ ብቻ ነበር፡፡

“ስው ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ ሰዓት ሰው እዚህ ድንጋይ ውስጥ እገደል ስር ምን ይሰራል? ሰው አይደለም አውሬ መሆን አለበት...” ፈራ ተባ እያለ ወደ ድልድዩ ገባ፡፡ እንደፈራው አይደለም፡፡ ምንም ነገር የለም።
ወደ ኋላው ገልመጥ ብሎ አየ፡፡ እብዱ በተሰጠው ሳንቲም ተደስቶ እየዘለለ ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና ተመለከተው፡፡ አካባቢው ጭር.እረጭ...ያሉ የሞት ጥላ የሚያንዣብብበት መሰለ፡፡ ሁለቱን ሠንጋዎቹን ሸጦ ሸቀጣ ሸቀጥ ከሽመተበት ሌላ በኪሱ ውስጥ ሁለት መቶ አርባ ብር ቀርታዋለች፡፡
እሷንም ጥሩ ቦታ አስቀምጧታል፡፡ መጀመሪያ ከሱሪው ኪስ ከተታት፡፡ ደስ አላለውም፡፡ ወደ ኮቱ የውስጥ ኪስ ወሰዳት። አላመናትም፡፡ የአንድ ዓመት ሙሉ የልፋቱ ውጤት እነዚያ ቤት ቤት የሚያካክሉ ሠንጋዎቹ የተለወጡባት ትንሽ ነገር ብትጠፋ ሁለት ሠንጋዎች ቀለጡ ማለት ነው። በየኪሱ ሁሉ አዟዟራት። በመጨረሻ ላይ ጥሩ የማስቀመጫ ቦታ አገኘላት። በጥንቃቄ የሚደብቀበት አስተማማኝ ቦታ! ወደ ጫማው ወረደ። እንደገና እጁን መለሰው። አሁንም አሰላስለ። ፊቱ ፈካ አለ፡፡የመጨረሻውን አስተማማኝ ቦታ አገኘላት። በመታጠቂያው ዘልቆ በውስጥ ሱሪው መካከል በደንብ አድርጐ አጣጥፎ ቀረቀራት። የአሁኑ ከፍተኛ ሥጋቱ ይቺኑ እንቅልፍ ያጣባትን
👍3