#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
..ባሌ... በሬሳ!
( ከአራት ዓመታት በፊት)
ከቀኑ አስር ሰዓት ተኩል አናቱ ላይ! በፀጥታዋ የምትታወቀው በሬሳ
በኡኡታ ተደበላለቀች። ሰማዩ በነጎድጓድ ድምፅ ታረሰ... በሬሳ ወልዳ አሳድጋ ለከፍተኛ ቁም ነገር ያበቃችው ተወዳጅና ብርቅዬ ልጇን እንደ ክፉ ድመት መልሳ ወደ ማህፀንዋ ልታስገባ አፏን በሰፊው ከፍታ አዛጋች፡፡ መልአከ ሞት አስገምጋሚውን የነጕድጓድ ድምፅ አሰምቶ በመቅስፍት በትሩ የአስካለን ልብ ያለርህራሄ በረቃቀሰው... ልጅዋ ናፍቋት፣
በህልሟ እየተመላለስ ሲያቃዣት ከረመና፣ ናፍቆቱ ዐይኗን ሊያወጣው ደረሰና ዳቦ ቆሎ ቆርጣ አዘጋጅታ ወደ አዲስ አበባ ሄዳ ልጇን እቅፍ
አድርጋ ለመሳም ቸኩላ ዝግጅቷን በማፋጠን ላይ ነበረች። ያ እንደነ
ፍሷ የምትወደው የምትሳሳለት ልጇ ግን መንገዱን ሊያስቀርላት፣ አዲስ አበባ ድረስ ሄዳ እንዳትንከራተት ድካሙን ሊቀንስላት በእንጨት ሳጥን
ተሞሽሮ ወደሷ እየገሰገሰላት ነበር።
ዘይኑን፣ አማረችንና ባልንጀሮቹን የጫነው አውቶቡስ ከቀኑ አስር
ሰዓት ተኩል ላይ በሬሳ ሲደርስ መንደሪቱ በጩኸት ታመሰች። እማዬ! እማምዬ! ጉድ ሆን! ወንድም ጋሼ...ወንድም ጋሼ! ጌትዬ!ጌትሽ!…. የኔ ፍቅር! እናቱ አስካለ አስቀድሞ ምንም ፍንጭ እንዲደርሳት ሳይደረግ ተዘጋጂ! ተጠንቀቂ! ሳትባል ሳይነገራት መአት ወረደባት። ምፅአተ
ቁጣውን ያረገዘው የሰቆቃ ጭጋግ ጥቁር ደመናውን በደሳሳ ጎጆዋ ላይ በድንገት አጥልቶ እንደ ንስር አሞራ ሲያንዣብብ ቆየና በከፍተኛ ጭካኔ መአተ እርግማኑን እንደ በረዶ ያዘንብባት ጀመር።
የመኩሪያ አደራ! ስትል የኖረች እናት ከሷ በፊት ትንሹ ልጇ እሷን ቀድሞ አባቱን ጠያቂ ይሆናል ብላ ለደቂቃ እንኳ አስባ አታውቅም ነበር። እንኳን ሞቱ ረጅም
እንቅልፉ የሚያስጨንቃት ልጅ ጉንፋን ስለመታመሙ ወሬ ሳትሰማ አስከሬኑን እንድትሸከም ሲፈረድባት ምን ይባላል? ያልፍልኛል ብሉ ደፋ ቀና ሲል ከርሞ በማእረግ የተመረቀላት ልጇን ደስታ አጣጥማ ሳትጨርስ ከጎኗ በድንገት ስታጣው የሚስማትን ስሜት ምን ቃላት ሊገልጡት ይችላሉ? ምናልባት በአስካለ ላይ የደረሰባትን ሰቆቃ ምሳ ቋጥሮ እቅፎ ስሞ ትምህርት ቤት የሸኘውን ህፃን ልጁን በመኪና አደጋ የተነጠቀ ወላጅ፣ ለወሊድ ሆስፒታል ይዟት የገባ ጤነኛ ሚስቱን አስከሬን በድንገት የታቀፈ አባወራ፣ በሠርጓ ዋዜማ እጮኛዋ በተኛበት አልጋ ላይ እስትንፋሱ ተቋርጣ ያገኘች ሙሽራ የበለጠ ሊረዷት ይችሉ ይሆናል። በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተደረገለት ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ በሶስተኛ ቀኑ በዚያው በሆስፒታሉ ውስጥ እንዳለ ህይወቱ ያለፈው ልጇ አስከሬኑ
ተጭኖ መምጣቱና ከሷ ቀድሞ ከአባቱ መቃብር አጠገብ የቀብር ስርአቱ በህዝብ ፊት በአደባባይ ተፈፅሞ አፈር መልበሱ በገሃድ እየታየ ለደቂቃ እንኳ ሞቱን አምና መቀበል ተስኗት በድን ሆና ቀረች፡፡
በቀብሩ ዕለት የአማረችን አሳዛኝ የለቅሶ ዜማ፣ የእናቱን ሁኔታ፣ የእህቱን እሪታ ሰምቶ አንጀቱ ያልተርገፈገፈ፣በእንባ ያልተራጨ፣ በእዬዬ ጉሮሮው ያልተዘጋ አልነበረም፡፡ ለዚያ ምግባረ ሰናይ ልጅ፣ ላዚያ አመለ ሽጋ ልጅ፣ለዚያ ትህትናው ለተመሰከረለት ልጅ፣ ለዚያ ገና በለጋነቱ የአባቱን አደራ ሊወጣ የቤተሰብ ሃላፊነት ቀንበርን በጫንቃው ተሸክሞ
ሲጎትት ለኖረ ልጅ የማያለቅስ ማን አለ? ከእያንዳንዱ ሰው እንባ እንደ
ውሃ ተቀዳለት፡፡ የሰማይ አእዋፍ ጭምር ተንጫጩለት። አጅሬ ሞት አይረታ የበላውን አይመልስ ሆነ እንጂ....
በዚያን እለት በማህፀኗ የተሸከመችው የአራት ወር ፅንስ ትንሹ ጌትነት ከሆዷ ውስጥ ሆኖ እየረገጣት አማረች የሚከተለውን የሃዘን እንጉርጉሮዋን አሰማች...
ስንዴ ዘርቻለሁ ቡቃያው ያማረ፣
ዛላው ተንዠርጎ ተስፋን ያሳደረ።
ዘሮች ተበትነው በእፍኝ አፈር ላይ፣
ጎልቶ እንዲወጣ ምርጡ እንዲለይ፣
ተመራማሪዎች ተወራረዱና፣
ውጤቱን ለማወቅ አወጡ ፈተና።
እኩል እየበሉ እኩል እየጠጡ፣
አንደኛው ከሌላው ከተበላለጡ፣
ሊመርጡ ፈጣኑን ለልማት ሊያወጡ፣
ተስማሙ ባንድ ድምፅ ሽልማት ሊሰጡ፡፡
አያጠራጥርም ቡቃያዬ አደገ፣
ቀድሞ ለመበላት ለመድረስ ፈለገ፡፡
በከባድ ልዩነት ሁሉንም በለጠ፣
ተፈላጊነቱን በኩራት ገለጠ።
ታዲያ ምን ያደርጋል ሳይታይ ውጤቱ፣
ታጭዶና ተወቅቶ ሳይመዘን ምርቱ፣
አብቦ እንዳሽተ ፍሬ እንዳጋተ፣
ስሩ ተበጠስ ሞተ ተከተተ።
ቡቃያዬ እንጭጩ ቡቃያዬ ሆዴ፣
እጦማለሁ ብዬ ነይ ነይ ከሁዳዴ፣
ተስፋ ያደረግሁት ባንተ አይደለም እንዴ?
ጌትሽ ቡቃያዬ ጌትሽ ቀለበቴ፣
አጊጬ ሳልጠግብህ አድርጌህ ከጣቴ፣
ምነው ሾልከህ ጠፋህ ሆድዬ አንጀቴ?
ቃልህን አታጥፍም ብዬ ስኮራብህ፣
ሚስጥር ጠባቂ ነህ ብዬ ስመካብህ፣
አሳፈርከኝ ዛሬ አመኔታም የለህ፡፡
አይታችሁ ያጣችሁ እናንተ ፍረዱ፣
እምነትን ዘርታችሁ ክህደትን ስታጭዱ።
አበቃ ተስፋዬ ሞተ መነመነ፣
የመኖሬ ትርጉም ባዶ ቀፎ ሆነ፡፡
አልችለውምና ጧት ማታ እዬዬ፣
ክብርና ኩራቴ ጥላ ከለላዬ፣
አልቀርም ጠብቀኝ ጌትሽ እጮኛዬ።
የእናቱ የአስካለ ሁኔታ እንዲህ ነበር ተብሎ በቀላሉ የሚገለፅ አል
ሆነም፡፡ የሚያዩ ዐይኖቿ ታወሩ...
የሚሰሙ ጆሮዎቿ ደነቆሩ... የሚናገረው አንደበቷ ተዘጋ፡፡በዚያ በደካማ ሰውነቷ ላይ የወደቀባትን ክምር የስቃይ ሸክም መቋቋም ተስኗት አቅም አጣችና ራሷን ሳተች። ቀወሰች።
ሁለት ቀን ሙሉ ነፍሷ ሳትወጣ የሞተ በድኗ እየተጠበቀ ሳለ በሶስተኛው ቀን ላይ ማንም ሰው ሳያያት በእኩለ ለሊቱ ሹልክ ብላ ሮጣ ወጣችና በባሏና በልጇ መቃብር መካከል ወዲያና ወዲህ ስትንከላወስ ከቆየች በኋላ
የምትወደው ልጇን ተከትላ ባሏ አዘጋጅቶ ወደሚጠብቃቸው አዲስ ዓለም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አብራ ተቀላቀለች። አይ የሰው ነገር?!
ከደሙ ንፁህ መሆኑን ሳያውቅለት ለዘለዓለም አንደበቱ በመዘጋቱ የሸዋዬ ባል ቶሎሳ እንኳ“ሞት ሲያንሰው ነው” ሲል ነበር የፈረደበት።
#የመጨረሻው_መጨረሻ
#ሳኦልና_ጳውሎስ
ታደሰ በእውነቱ ከሆስፒታል እንዲወጣ ተደርጐ በመኖሪያ ቤቱ
ውስጥ አልጋ ላይ ከዋለ ልክ ሳምንቱ.. ለሰው ጥሩ መስራት ለራስ ነው። ታደሰን ለመጠየቅና ለማፅናናት በየጊዜው የሚመጣው ሰው ቁጥሩ
በርካታ ነው፡፡ በጠያቂ ብዛት መዳን ቢቻል ኖሮ ታደሰ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን በቻለ ነበር። ዛሬ ግን እያቃሰተ ህመሙን የሚያዳምጥበት ቀን አልነበረም፡፡ የምራቅ ዕጢዎቹ ማመንጨት አቁመዋል። ከንፈሮቹ ኩበት መስለው ደርቀዋል። ጥቁር መልኩ የጣፊያ ዓይነት መልክ
እየያዘ ሄደ...ወይዘሮ ወደሬ ማዕድ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ እያሉ ነበር።
ለጊዜው ሁለቱ ብቻ ነበሩ። ሰላማዊት የታደሰን ሁኔታ አጤነች፡፡ በየጊዜው እየሰለለች የመጣች ተስፋዋ ልትበጠስ መቃረቧን ተረዳች፡፡ ውድ ባሏ ሊለያት እንደሆነ ጠርጥራ ፍርሃት አደረባት።
“ታዴ! እየበረታህ ነው?” አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ በግራ
መዳፏ ትኩሳቱን እየለካች ጠየቀችው፡፡
“እህ!.. እህ!.. እህ.! ሰላሜ..” ዐይኖቹን በዐይኖቿ ላይ አንከራተ
ታቸው።ከሆስፒታል የወጣው የመዳን ተስፋው እየመነመነ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን አውቆታል፡፡ሚስቱን እያፈቀረና እየወደዳት ብቸኛ አድርጓት ሊሄድ በአስገዳጁ የሞት ጠንካራ ክንድ ተጨምድዶ መያዙን ተገንዝቦታልና ሙሉ ለሙሉ እጁን ከመስጠቱ በፊት አደራ ሊላትና የልቡን ሊነግራት ወሰነ።

👍10
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሚስተር ካርይልና ባርባራ ቁርስ ላይ እንዳሉ ሚስተር ዲል ሲገባ አዲስ ነገር
ሆነባቸው " እሱን ተከትሎ ጀስቲስ ሔር ጥልቅ አለ » ወዲያው ስኳየር ስፒነር ተከትሎት ግባ " በመጨረሻ ደግሞ ኮሎኔል ቤተል መጣ " አራቱም የመጡት ለየብቻ
ቸው ሲሆን ሁሉም ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ ሲል ማን ቀድሞ እንደሚደርስ የተወዳደሩ ይመስሉ ነበር "
ሁሉም ሲቃ እየተናነቃቸው ሳይደማመጡ ባንድ ላይ ሲናገሩ ሚስተር ካርላይል ሊገባው አልቻለም ።በጣም ተናዶ ይናገር የነበረው የሚስተር ጀስቲስ ሔር
ድምፅ ብቻ ጆሮን ለማደንቆር ይበቃ ነበር ከዚያ ሁሉ ጫጫታ ሚስተር ካርላይል አንድ ቃል ያዘ።
“ ሁለተኛ ሰው ? ተወዳዳሪ ? ይምጣ እንጂ በመጨረሻ ማን እንደሚያሸንፍ ማወቁም እኮ ያስደስታል” አለ ካርላይል በቅን ልቦና "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ ሽማግሌው ማን መሆኑን እኮ አልሰማህም
ዲል “ ከሱ ጋር እኩል ቆሞ መወዳደር ! ” ብሎ ደነፋ ሚስተር ጀስቲስ ሔር ።
“የለም ሰውዬው መሰቀል ይገባዋል” አለ ኮሎኔል ቤተል ከመኻል አቋርጦ"
መዝፈቅ አይቻልም ?” አለ እስኳየር ስፒነር "
ሰዎቹ ተናግረው የሚያበቁ ወይም እየተደማመጡ የሚያወጉ አልመሰለም "
ባርባራ በሁኔታቸው ተገርማ ዐይኗን ካንዱ ወደ ሌላው እያንገዋለለች ታያቸዋለች
“ ይኸ ኃይለኛ ተወዳዳሪ ማነው ? አለ ሚስተር ካርላይል "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ
ዲል ድምፁን ዝቅ አድርጎ " " የቀረበው እጩ ያ ሌቪሰን የሚባለው ሰውዬ ነው ”
ሚስተር ካርላይል ፊቱ ደም ለበሰ ። ባርባራ አንገቷን ደፋች " ዐይኖቿ ግን
በቁጣ ተንቀለቀሉ "
“ ቤንጃሚን ፈረሶቹን ለማንሸርሸር ዛሬ ማለዳ ወደ ከተማ ወጥቶ ነበር '
አለ ጆስቲስ ሔር ከንዴቱ የተነሣ ምላሱ እየተንተባተበ “ ሲመለስ የከተማ
ግድግዳዎች · ሌቪሰን ለዘለዓለም ይኑር ! ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ምረጡ ! በሚሉ ፁሑፎች ተንቆጥቁጠዋል አለኝ “ነደደኝና በጥፊ ላቀምሰው ስል ኧሪ እውነቴን ነው " አንዳንድ ሰዎች አነጋግሬ ነበር ትናንት ማታ ነው አሉ በባቡር ግብቶ ያደረው
አሉኝ "
“ ትናንት ነው በመጨረሻው ባቡር የደረሰው » ያረፈውም ባክስሔድ ሆቴል ነው አለ ሚስተር ዲል " አንድ ወኪል ብጤና አንድ ደግሞ የመንግሥት አባል ነኝ የሚል ሰው አብረውት አሉ ማስታወቂያ አታሚዎቹ ግን ያን ሁሉ ሲያዘጋጁ
ተቀምጠው ሳያድሩ አልቀሩም "
"ገና ሳይጀመር የውድድሩም የድሉም መስክ የኛ ነው እያሉ ጉራቸውን ብትሰሙ
ይገርማችኋል " ሰውየው ግን ራሱን ለውድድር ማቅረቡ ዕብድ ነው?”
አለ ኮሌኔል ቤተል ከዘራውን ወደ መሬት በኃይል በመሰንዘር ።
"ሚስተር ካርላይልን ለመሳደብ ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር ነው ” አለ ስፒነር
"ሁላችንን ለማዋረድ ነው እንጂ! ኧረ ቆይ ሲቀልድ እንደገባው ሲቀልድ አይወጣ።
“ በክስ ሔድ ሆቴል ስብሰባ ስለአለ አብሬአችሁ እግኛለሁ” አለ ሚስተር ካርላይል።
“ በክስ ሔድ ሆቴል ነበር ያልከኝ?ይኸን ደግሞ አልሰማሁም” አለ ስፒነር
ባክስ ሔድ እንደነበር መስማቴን ነው የተናገርኩ” አለ ዲል “ እስካሁን ግን
እሱም መሳሳቱንና ዳኞቹ ቢሰሙ ደግሞ እንደሚቀየሙት ነግሬዋለሁ "ዱሮውንም መሳሳቱን ቢያውቅ ኖሮ ይመልሰው እንደ ነበር ካወቀ ወዲ ደግሞ ባጭር ጊዜ
እንደሚያባርረው ግልጾልኛል።
ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ሰዎቹ ወጡ » ሚስተር ካርላይል ቁርሱን ለመጨረስ ተቀመጠ "
“ አርኪባልድ የዚህ ሰውዬ ደፋር ድርጊት ካሰብከው ፍንክች እንዳያደርግህ”
አለችው ባርባራ "
“ እሱ እኔን ለማጥቃት ገፍቶ መጥቷል " እኔ ደግሞ ከጫማዬ ሥር ካለው
ትቢያ እንኳን አብልጬ አላየውም "
እውነትክን ነው” አለችው ፊቷ በኩራት ቦገግ አለ።
ሚስተር ካርላይል ወደ ዌስት ሊን ሲሔድ አንድ ሰው በሌላው ላይ ሊፈጽመው የሚችለውን የመጨረሻ ታላቅ በደል የፈጸመበትን የዚያን ክፉ ሰው የውድድር ማስታወቂያ ከሱ ማስታወቂያዎች ጋር ጐን ለጐን ተለጥፎ ተመለከተ "
አርኪባልድ ይህን አሳፋሪ ወሬ ሰምተሃል ? አለች ኮርኒሊያ እንደ ጀልባ እየተንሳፈፈች ደረሰችና "
“ ስምቸዋለሁ ኮርኒሊያ ። ባልሰማስ ግድግዳዎቹ ሊነግሩኝ ይችሉ የለ?”
አብዷል ? ደኅና ግድ የለም በፊት ደስ አላለኝም ነበር !አሁን ግን እንዳትለቅለት " ከእፉኝት አብልጠህ እንዳታየው ዌስትሊን በሙሉ ተነቃንቋል እንደዛሬ ሆኖ አያውቅም።
እውነቷን ነበር ድፍን ዌስት ሊን በድጋፍና በቁጣ ተንቀሳቀሰ ገጠሬው ከተሜው ሁሉ ካርላይል ብሎ ተነሣ " ቢሆንም ዌስት ሊን ውስጥ የመንግሥት ትኩረት ከፍተኛ ነው " የግልና የሕዝብ አስተያየት የመሰለ ቢመስልም ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በጣም ብዙ ድምፅ ይመዘገባል።
ያን ዕለት ጧት ባርባራ ባሏን እስከ ግቢው የውጭ በር ድረስ ሽኝታው ስትመለስ ማዳም ቬንንና ሁለቱን ልጆች አገኘቻቸው ዊልያምም ሻል ያለው ይመስል ነበር።ሁልጊዜም ጧት ት ችግር አልነበረበትም "
· እማማ ” አለች ሎሲ “ የሞቀሽ ትመስያለሽ ፊትሽ ተለወጠ ”
አንድ ሰውዬ ከአባታችሁ ጋር ሊወዳዶር ስለ ተነሣ ተናድጄ ነው
ለመወዳደር መብት የለውም እንዴ አባባ ውድድሩ ለሁሉም ክፍት ነው ሲል ሰምቸዋለሁ ” አለ ዊልያም።
“ ለሱ ካልሆነ በቀር ለሌላው ክፍት ነው ” አለች ባርባራ ንዴቷ አስተያየቷን እየቀደመ “እሱ ክፉ · ማንም የሚንቀው ጥሩ የሚባሉ ሰዎች ሁሉ የሚጠሉትና
የማያስጠጉት ሰው ሆኖ እያለ አሁን ከአባታችሁ ጋር ሊወዳደር ቀረበ
“ ስሙ ማን ይባላል ?”
ባርባራ ትንሽ አሰበችና እሷ ባትነግራቸውም ከሌላ መስማታቸው ስለማይቀር
ካመዛዘነች በኋላ '“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ይባላል ” አለች "
ማቃሰት መደንገጥና መገረም የተቀላቀለበት ድምፅ አሰማች አስተማሪቱ።ባርባራ ዞር ብላ ስታያት አቀርቅራ ፊቷን በመሐረቧ ሸፍና ትስል ስለ ነበር ድንገት ልውጥውጥ ብሎ የገረጣውን ፊቷን ማስተዋል አልቻለችም
አመመሽ እንዴ ? አለቻት ባርባራ "
“ ሕመም እንኳን ደኅና ነኝ " ብቻ አቧራ ብጤ ባፌ ገባ መሰለኝ አሳለኝ። "
ሚስስ ካርላይል ዝም አለች " ሕሊናዋ ግን ዝም አላለም።
ይኸን ስም ስትሰማ ለምን ደነገጠች " ሰውዬውን ታውቀው ኖሮ ይሆን ? የደነጠችው ግን በስሙ መነሣት ነው ? " እያለች ታስብ ጀመር
የሚገርመው ደግሞ ማዳም ቬን የዚያን ለት አላስተማረችም " ስለ ውድድሩ ጉዳይ ቶሎ ከሰሙት አንዱ ሎርድ ማውንት እስቨርን ነበር " ለንደን ውስጥ ከክበቡ
ሆኖ አንድ ማታ ጋዜጣ ሲመለከት ካርላይል ዌስትሊን ” ከሚሉ ስሞች ላይ ዐይኖቹን ያሳርፋል ሚስተር ካርላይል በእጭዎች መቅረቡን ተረድቶ እንዲቀናውም ከልቡ ተመኝቶ ኧርሉ ንባቡን ቀጠለና አንቀጹን አነበበው "
መልሶ መላልሶ አነበበው " ዐይኖቹን አሻሸ " መነጽሩን ወለወለ " በሕልሙ ይሁን በውኑ ለማረጋግጥ ራሱን መረመረ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ዌስት ሊን መግባቱን የሚስተር ካርላይል ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረቡንና አሁን የፖለቲካ ንግግር የምርጫ ቅስቀሳ በማካሔድ ላይ መሆኑን አነበበ።
“ ይኸ ጋዜጣው ስለሚለው አሳፋሪ ነገር የምታውቀው አለህ ? አለ አብሮት የነበረውን አንዱን ሰውዬ "
“ እውነት ነው » እኔ ከአንድ ሰዓት በፊት ነበር የሰማሁት ሌቪሰን ብዙ
ድምፅ ማግኘቱ አይቀርም "
ድምዕ ! ” ” ኧርሉ በሰውዬው አነጋገር መንፈሱም አካሉም ተሸበረና “በል እንደዚህ አትበል ይህ ወደል ውሻ እንዲያውም መሰቀል ይገባዋል

👍10👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…
አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን ኖሮ ይሄን ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ ጎረምሳ አግብቼ መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡
ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ ላይ ያለ አሉ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ።
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡
ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…
….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት…
ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡
ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡

👍70❤10😢2😁1🤔1