አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...የፖሊስ አዛዥ ያዘጋጁትን ንግግር ለመጀመር ጉሮሯቸውን አፀዱ “እህ..እህህ..ውድ የእለቱ የክብር እንግዶች ወንድሞቼ እህቶቼና የሥራ ባልደረቦቼ በዛሬው እለት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኛችሁበት
ይህን ፕሮግራም ማዘጋጀት አስፈላጊ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ያለፈው ዓመት አፈፃፀማችንን በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎናችንን ለመለየት ሲሆን ባለፈው ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክረን የተሻለ
ውጤት ለማስመዝገብና ድክመቶቻችንን በውል ተገንዝበን በማስወገድ በቀጣይ የስራ ዘመናችን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የምንችልበትን
ስትራቴጂ ለመንደፍ ነው፡፡

የተቋማችን ዋነኛ ዓላማ የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በየ አካባቢው እያቆጠቆጠ ያለውን የወንጀል ድርጊት በተቻለ መጠን ለመግታትና ለመቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት ከፊት ለፊታችን ሆነው ይጠብቁናል፡፡ ወንጀል በተለያዩ
መንገዶች የሚገለፅ የማህበረሰቡ ቁስል ነው። ወንጀል አብሮ የመኖር እንቅፋት የመተሳሰብና የመተባበር ነቀርሳ፣ የልማትና የእድገት ፀር ነው። በአጠቃላይ ወንጀል የማህበረሰቡ ክፉ በሽታ ነው። በሽታ ካለ የመንፈስም ሆነ የአካል ጥንካሬ አይገኝም። በሽታን ለማጥፋት ሳይንቲስቶችና
ተመራማሪዎች የእያንዳንዱን በሽታ ባህሪ ለማወቅ የጀርሞች፣ የባክቴሪያና የቫይረሶችን አፈጣጠር በማጥናት መፈወሻ መድኃኒት ለመቀመም ቀን ከለሊት ይማስናሉ። በሽታ ሽባ ያደርጋል፣ በሽታ እብድ ያደርጋል፣
በሽታ የአልጋ ቁራኛ ያደርጋል። በሽታ ይገድላል። ወንጀልና በሽታ አንድ ናቸው፡፡ ወንጀል ከትንሹ ጀምሮ ቀስ በቀስ እያደገና እየሰፋ ሲሄድ ቀሳፊነቱ በዚያው ልክ እያደገ ይሄዳል። በጊዜውና በወቅቱ ያልተቀጨ በሽታ
ህይወት ይዞ እንደሚሄደው ሁሉ በወቅቱና በጊዜው ያልተቀጨ ወንጀል እያደገና እየሰፋ ሲሄድ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። አገራዊ ሰላምን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ወንጀለኛ ከሌላ ወንጀል አይኖርም፡፡ ወንጀል እንዳይስፋፋ አስፈላጊው ጥረት ከተደረገ ደግሞ ወንጀለኛ አይኖርም፡፡ ወንጀልን
በማስወገድ የህብረተሰቡን አጠቃላይ የደህንነት ዋስትና ማረጋገጥ የሚቻለው ሁሉም የህብረተሰብ አባል ለደህንነቱ መረጋገጥ የግልና የቡድን አስ
ተዋፅኦ ሲያደርግና የቆምንለትን ዓላማ መደገፍ ሲችል ብቻ ነው። እኛም እያንዳንዱ ሰው ይሄንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ያለመታከት ማስተማር ይጠበቅብናል።

አብዛኛው ነዋሪ ያለስጋት የሚዘዋወረው አምሽቶ የሚገባውና የሚወጣው እኛ የሱን ሰላም የምናስጠብቅ እንቅፋት ቢመታው ፈጥነን የምንደርስ፣ ያላግባብ በደልና ጥቃት ቢደርስበት ጥብቅና የምንቆም ባለአደራዎች በሰው ልጆች የተፈጠረና ሰዎችን በበላይነት እንዲመራ የተደነገገውን ህግ የምናስከብር አካላት መኖራችንን ተስፋ አድርጎ ነው። በመሆኑም ህጉንና ደንቡን ተላልፈው ወንጀል የሚፈፅሙ ህገወጦችን ለፍርድ
በማቅረብ የተረጋጋና አስተማማኝ የሰላም ዋስትናን ማረጋገጥ እስከሚቻል ድረስ አገልግሎታችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል። የህብረተሰቡን ስላም ለማስጠበቅ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሰላም መጠበቅ ይኖርበታል። ይህን ዓላማችንን እውን ለማድረግ ደግሞ ሰፊ የህዝብ ድጋፍና
ትብብር ያስፈልገናል።

የህብረተሰቡ እርዳታ የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብርና በሌለበት ብቻችንን የምናደርገው ሩጫ በአንድ እጅ እንደማጨብ
ጨብ ነው። ወንጀለኞች በህዝቡ ውስጥ ሆነው ወንጀል በህዝቡ ላይ እየፈፀሙ ተመልሰው ህዝቡ ውስጥ ገብተው የሚሸሸጉ ከሆነ የሚጐዳው ህዝቡ ራሱ ነውና የበለጠ የኃላፊነት ስሜት ተሰምቶት ራሱን ከአደጋ
ለመከላከል ወንጀለኞችን የማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅብናል። ህብረተስቡ ወንጀለኛን የሚያቅፍ፣ የሚሽሽግ ከሆነ ደግሜ እናገራለሁ ድካማችን ሁሉ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ብቻ ሳይሆን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው የሚሆነው። በንግግሬ መሃል አንድ ከዚህ ነጥብ ጋር አብሮ የሚሄድ ትምህርት ይሰጠናል ብዬ የምገምተውን ቀልድ ልንገራችሁ። ሁለት ወንድማማቾች የታጨደ የእህል ክምር ከሌባ ለመጠበቅ ማሳቸው ላይ ገለባ ለብሰው ይተኛሉ። ለሊት ላይ ጅብ ይመጣና
ያንን ገለባ ገላልጦ የአንደኛውን እግር መቆርጠም ይጀምራል። በስማው ድምፅ ግራ የተጋባው ወንድም “ምንድነው የሚሰማኝ ድምፅ?" ብሎ ወንድሙን ይጠይቀዋል።

“ቀስ በል አትጩህ የኔን እግር እየበላ ነው” ሲል በፍርሃት ተውጦ
ይመልስለታል። በዚህ ጊዜ ፎክሮ ይነሳና “አንተ ፈሪ አንተን በልቶ
ሲያበቃ ወደኔ መምጣቱ ይቀራል እንዴ?” በማለት ቆርጥሞ ሳይጨርሰው እሱንም ሳይጀምረው ጅቡን አባረረው ይባላል” በዚህ ጊዜ ሁሉም
በሳቅ ፈነዱ... የተሰብሳቢው ሳቅ ጋብ እስከሚል ድረስ ጠብቀው ቀጠሉ።
“እና ከዚህ ቀልድ ትልቅ ቁም ነገር እንማራለን፡፡ ዛሬ ወንጀለኛን ያቀፈ
ህዝብ ወንድሙ አጠገቡ ሲመታ ሲቆስል ሲሞት እያየ እኔ እስካልተነካሁ ድረስ ምን ቸገረኝ? በማለት ወንጀለኛውን ከማጋለጥ የሚቆጠብ ከሆነና ወንጀለኛን እንደ ጅቡ በጊዜ ማባረር ካልቻለ ተመልሶ በሱ በራሱ ላይ
የሚዘምትበት መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡በዚህ ረገድ የዛሬው ሁለተኛው የስብሰባችን ዋና አላማም ከህዝቡ መካከል ይህንን ተገንዝበው በቀጥታም
ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከእኛ ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመስራት ለከፍተኛ ውጤት ያበቁን ወንድሞቻችንን በመሸለም ለሌሎችም አርአያ እንዲሆኑና ሞራላቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት እነኝህን
ውድ የህዝብ ልጆች ለማታውቋቸው በማስተዋወቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ
ማበረታቻ ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀላቸው ሽልማት በእናንተ ፊት ይስጣቸዋል። ሁላችንም እንደምናውቀው ወንጀል ይበዛባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል ዋነኛው እሪ በከንቱ እንደነበር ግልፅ ነው። ከስም አወጣጣቸው ጀምሮ ዶሮ ማነቂያ፣ እሪ በከንቱ በሚባሉት በእነዚህ ሰፈሮች ውስጥ በርካታ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት ለእሪ ባይ ረዳት የማይደርስበት የሰው ልጅ እንደ ዶሮ ተቆጥሮ በዶሮ ማነቂያ ስም አንገቱ የሚታነ
ቅባቸው አካባቢዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ አካባቢዎች እንደምታውቁት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ሰው በልቡ እምነት አሳድሮ የሚረማመድባቸው አልነበሩም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን እሪ በከንቱነቱና ዶሮ ማነቂያነቱ ቀርቶ ሰዎች
በፈቀዳቸው ሰዓት የሚመላለሱባቸው አልፎ አልፎ በጣም አልፎ አልፎ ንጥቂያዎች ቢፈፀሙ ለእርዳታ ድምፅ የሚያሰማ ፈጥኖ ደራሽ የሚያገ
ኝባቸው የሰላም ቀጠናዎች እየሆኑ መጥተዋል። ይሄ ውጤት የተገኘው በተአምር ሳይሆን ሌት ተቀን ከእኛ ጋር አብረው በተሰለፉ ወንድሞቻችን ድካምና ጥረት ነው፡፡ ለዚህ ውጤት መገኘት በርካታ ተባባሪዎች ቢኖሩንም የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ከዚህ ቀጥሎ አስተዋውቃችኋላሁ”
አሉና ዐይኖቻቸውን ወደ ተሰብሳቢዎቹ መካከል ወረወሩ።ፈገግታ የተላበስ ፊታቸውን ወደ ታደስ በእውነቱ አዞሩና ሁለቱን እጆቻቸውን ዘረጉ።
ታደስ ተነስቶ ቆመ:: ጭብጨባው አስተጋባ፡፡ ታደሰ ወደ መድረኩ ሄደ። “አዎን እሱ ወንድማችን ታደሰ በእውነቱ ይባላል! ወንጀለኞችን መስሎ ወንጀለኞችን ተቀላቅሎ ቀን ከሌሊት ብርቱ ትግል ያደረገና ተደጋጋሚ
ውጤቶችን ያስመዘገበ ወንድማችን ነው!”
👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....«ታፈሡና ሔዋን የሚባሉ ካሉ በአስቸኳይ ቤት ድረስ ይምጡ። የሚል መልዕክተኛ መጥቶ ነው።» አለው፡፡
ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ መልዕክቱን እንደሰማ ወደነታፈሡ ዞር ብሎ ሲያይ ለካ የተነገረውን መልዕክት እነሱም ሰምተውት ኖሮ አቆብቁበው እያዩት ኖሯል። «ምንድነው ሃምሳ አለቃ?» በማለት ታፈሡ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡ ከመደንገጧ ብዛት የቀድሞውን ሃምሳ አለቃ በቀድሞ ማዕረጉ ጠራችው።
«በአስቸኳይ ቤት ድረስ ኑ ተብለዋል ይላል።» አላት ራሱም የድንጋጤ ስሜት እየተነበበበት፡፡
«ኧረ ፍጠኑ ብለዋችኋል!» አለ መልዕክተኛው።
ታፈሡ፣ሔዋንና መርዕድ የምክትል መቶ አለቃውንም ሆነ የድግሱ
ታዳሚዎችን ፈቃድ መጠየቅ የሚያስችል ፋታ እና ጊዜ እላገኙም። በታፈሡ መሪነት የእሽቅድምድም ያህል ተከታትለው ከአዳራሹም ወጡና ወደ ታፈሡ ቤት ሮጡ።
በዚህ ጊዜ የደግሱ ድባብ ፍፁም ተለወጠ፡፡ ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ራሱ ግራ ገብቶት በአለበት ቆሞ ቀረ። ታዳሚዎችም አንዴ በር በሩን ሌላ ጊዜ ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌን በመመልከት ዓይናቸው ይንከራተት ጀመር፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን ጥቂት ፖሊሶች ወደ ታፈሠ ቢት ሄደዉ
የሆነውን ነገር እንዲያጣሩ ታዘዙና የእነታፈሡን ዱካ ተከትለው ገሰገሱ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዕሰተ ረቡዕ ከማለዳ ጀምር የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ቀውጢ ሆኗል። ሰበቡ የመኪና አደጋ ነው። አንዲት በተለምዶ ውይይት በመባል የምትታወቅ ታክሲ በርካታ
የመድሐኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አሳፍራ ከትምህርት ቤቱ በር ላይ በመድረስ ቁማ በማራገፍ ላይ ሳለች አንድ የፍሬን ችግር የነበረበት የከተማ አውቶብስ ከታክሲዋ ላይ በመውረድ ላይ የነበሩ ተማሪዎችን ጨፍልቃቸው ነው። በርካታ ሞተዋል፡፡ ሌሎች ፣ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአደጋ ተረፉ የሚባሉ ተሳፋሪዎች
ብዙ አልነበሩም ከተማሪዎቹ በተጨማሪ ሌሎች መንገደኞችም የሞትና የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የሞቱትም ሆኑ የቆሰሉት ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ነው የተወሰዱት። ይህ አደጋ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ደርሶ እረፈድ እያለ ሲሄድ ደግሞ የአደጋ ሰለባዎች ዘመድ አዝማድ ከቦታው እየደረሱ የሆስፒታሉን ቅጥር ግቢ በለቅሶ በእሪታና በጩኸት እያደበላለቁ የጨበጣ ውጊያ የሚካሄድበት ጦር ሜዳ አስመስለውት አርፍደዋል። ሕይወታቸው ያላለፈ የአደጋው ሰለባዎች የስቃይ ጩህት ከቤተሰቦቻቸው ኡኡታ ጋር ተላምዶ ያ ግቢ ግባተመሬት የሚፈፀምበት የመቃብር ቦታ መስሏል፡፡ የሆስፒታሉ ሐኪሞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ስራ በዝቶባቸው የሚይዙትን የሚጨብጡትን አተው ተዋክበዋል። ቀደም ሲል አልጋ ይዘው ይታከሙ ህሙማን ጨርሶ ተረስተዋል ችግሩ ለአስታማሚዎች ተርፎ እነሱም በጭንቀት ወለሌ ይላሉ።
ከዚህ ችግር ተካፋይ አንዱ በልሁ ተገኔ ነው አስቻለው ደሞ ከሰሞኑ ጀምሮ ህመሙ ፀንቶበት ሰንብቷል በዚያው ልክ በልሁ አጠገቡ በመቆም የሚንከራተቱ የአስቻለውን አይኖች አከታትሎ ማየት የዘወትር ስራው ሆኗል። ሀኪም አይቶት በወጣ ቁጥር ለውጥ ያመጣለት እየመሰለው ቢጓጓም ነገር ግን የአስቻለው ሁኔታ ከዕለት ወደ እለት እያስፈራው ሄዷል።
አደጋው በደረሰበት እለትም የአስቻለው ነፍስና የበልሁ ዓይኖች ተፋጠው አረፈዱ ወትሮም እንደሚያርገው ሁሉ አሰሰቻለው በተኛበት አልጋ አጠገብ ቆሞ ቁልቁል እየተመለከተው ሳለ ከኮሪደር አካባቢ ድንገተኛ ጩህት ተሰማ ቀአደጋው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት የነበረች ልጅ ብዙም ሳትቆይ ህይወቷ አልፎ ኖሯል።ህልፈቷ የተነገራቸው ዘመዶቿ በዚያው አስቻለው በተኛበት ክፍል በር አካባቢ ጩህታቸውን ይለቃሉ የሟች ስም 'ሔለን' ኗሯል አልቃሹም " ሔለን ሔለንዬ ሔሉ" እያሉ ይጯጯሁ ጀመር።
ይህን የለቅሶ ጩኸትና የማቿን ስም እስቻለው በሰመመን ውስጥ ሆኖ ሰምቶት ኖሯል። በልሁ ጠጋ ብሎ እጁን እንዲያዘው ጠቀስው፡፡ በልሁ ጠጋ እንዳለት አስቻለው እጁን ያዝ አደረገና፡-
ሔዋን ምን ሆና ሞተች በልሁ?» ሲል ዓይኑን እያንከራተተ ጠየቀው።
«ምን?» አለ በልሁ ድንግጥ በማለት፡ ስለየትኛዋ ሔዋን ነው
የምታወራው አስቻለው?» ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
አስቻለው ልክ እንደ ጃጀ ሽማግሌ የበልሁን እጀ ጥብቅ አድርጎ በመያዝ ዓይኖቹን እያንከራተተ አትዋሸኝ በልሁ ሔዋን ሞታለች።» አለው።
በልሁ የባስ ተረበሸ፡፡ እሱ በጤናማ ስሜቱ የማቿ ስም ሔለን ስሰመሆኑ እርግጠኛ ቢሆንም ለእስቻለው ግን «ሔዋን የተባለ እንደሚመስለው ሲረዳ ስለ
አስቻለው የእሱ መንፈስ ተሰቃየ። ግን ብቻ ያስተማመንኩ መስሎት
«ሔዋን እኮ በአሁኑ ሠዓት ያለችው ዲላ ነው። ለሃምሳ አለቃ መኮንን
ዳርጌ ሽኝት እንደ ሄደች ገና አልመጣችም። ምናልባት ዛሬ ወደ ማታ ላይ ትመጣና ታያታለህ። አሁን የሚያለቅሱት ሰዎች ሔለን የምትባል ልጅ ሞታባቸው ነው።
ሔዋን አይደለም የሚሉት፡፡ አለው በማከታተልና ሽብር በተቀላቀለበት አነጋገር።

አስቻለው የበልሁን ንግግር ከቁብ አልቆጠረውም። ምናልባትም በትክክል እየሰማው ላይሆን ይችላል። የራሱን ንግግር ብቻ ቀጠለ።
«እኔንም እሷ በተቀበረችበት ቤተክርስቲያንና መቃብር ውስጥ ቅበሩኝ፡»
«ቀድሞ እሷ መች ሞተች?»
አስቻለው አሁንም የራሱን ቀጠለ። «በመቃብራችን ላይ እኛ በከንቱ
ሞተናል፥ እናንተ ግን አደራ ብለህ ፃፍበት፡»አለው የበልሁን እጅ ጭምድድ አድርጎ እንደያዘ፡፡
የበልሁ ጭንቀት ከመጨረሻው ጫፍ ላይ ደረሰ፡፡ ከአስቻለው ጋር መነጋገሩ ዋጋ እንደሌለው አመነ፡፡ ቢሆንም ባይሆን ሐኪም መጥራት እንዳለብት ታየው፡፡
እጁን ከአስቻለው እጅ ውስጥ እንደምንም ፈልቅቶ አላቀቀና በፍጥነት በሩን ከፍቶ ወጣ።
ከነርሶቹ ክፍል በር ላይ እንደደረሰ አስቻለውና በአካባቢው የተኙ
ህሙማንን የምትከታተለዋ ነርስ ከውስጥ ወደ ውጭ ስትወጣ አገኛት። የተለያዩ መድሐኒቶችን ይዛ ወደ ድንገተኛ ክፍል በመሄድ ላይ ነበረች።
«እመቤት ልጁ እኮ ደከመብኝ» አላት በልሁ ትንፋሹ በርክቶ እያለከለከ።
ነርሷን ሲስተር ብሎ መጥራት ሲገባው እመቤት ማለቱ መለማመጡና በአክብሮት
ማሳየቱ ነበር።
«ከወትሮው የተለየ ምን ለውጥ አየህበት» ስትል ነርሶም ከእርምጃዋ ቆም ብላ ጠየቀችው። የበልሁ ሁኔታ ትኩረቷን ስቦታል።
«ይቃዥ ጀመር»
«ምን እያለ?»
«ዝም ብሎ የሆነ ያልሆነውን»
«እስቲ ቆይ! ይህን መድሀኒት ድንገተኛ ክፍል ላድርስና መጥቼ አየዋለሁ።» ብላው ወደ ድንገተኛ ክፍል ለመሄድ ከፎቅ ወደ ምድር ቤት ወረደች።
በልሁ ከስጋቱና ከፍርሀቱ የተነሳ ነርሷን ሊያምናት አልቻለም። እድራሻዋ እንዳይጠፋበት ለመከታተል ተከትሏት ወረደ። የገባችበትን ክፍል አረጋግጦ
እስከምትመለስ ድረስ እዚያው በገባችበት ክፍል በር ላይ ቆሞ ይጠብቃት ጀመር፡፡
ነርሷ በዚያ በድንተኛ ክፍል ውስጥ ብዙ አልቆየችም፡፡ መድኒቶችን አድርሳ ከክፍሉ ወጣች። በሩ ላይ በልሁን ስታገኘው ስሜቱ ገብቷት ፈገግ
አለችና «የምቀር መስሎህ ነው አይደል» አለችው
👍7
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ብቻ... የለም... አልሆነም: ይኸው እዚ እኔ ብቻዬን ጣዕር ይዞ ያጣድፈኛል
ብቻዬን! ወይ አምላኬ፣ ወይ አምላኬ ስማኝ፡ ሁለተኛ አላያትም?

ልክ ይህን ሲያሰላስል በር ተንኳኳ፡

ያን እለት፤ ሰዓቱ ግን ትንሽ ቀደም ይላል፤ ዣን ቫልዣ እንደዚያ ጣዕር ይዞት ሲታገል አሽከር ለማሪየስ ደብዳቤ ያመጣለታል፡ ደብዳቤው ሲሰጠው ማስታወሻውን የሰጠው ሰው ከሳሎን ቤት እንደሚጠብቅ
ይገለጽለታል፡ ደብዳቤውን ከፍቶ አነበበው::

«ጌታዬ፣ እኔም ፈጣሪ ቢልልኝ ኖሮ ባሮን ቴናድዬ በመባል ጌታ የጌታ ልጅ ተብዬ በታወቅሁ ነበር ግን አላለልኝም፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ለምትውልልኝ ውለታ ወይም ለምታደርግልኝ እርዳታ አጸፋ እመልሳለሁ፡፡»

«ስለአንድ ሰው ምሥጢር አውቃለሁ፡፡ ግለሰቡ ከሕይወትህ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ምሥጢሩን ማወቅ ይጠቅምሃል:: እኔ ደግሞ ምሥጢሩን
ለማካፈል ፈቃደኛ ነኝ፡፡ ይህ ሰው የተከበረ ቤተሰብህን ስም የሚያጐድፍ ነው፡: ከክብርት እመቤቴም ጋር ግንኙነት ስለሌለው ከእናንተ መራቅ አለበት: ወንጀለኛው ወንጀሉ ሳይገለጥበት እንዲኖር መፍቀድ የትክክለኛ
ፍርድ ገጽታ አይደለም... ከታላቅ አክብሮት ጋር!››

ደብዳቤው ቴናድ በሚል ስም ተፈርሞአል፡

ማሪየስ በጣም ተረበሸ:: በአንድ በኩል ሲደሰት በሌላ በኩል ተከፋ፡፡ እንደ ሌሎቹ ጠቋሚዎች ሕይወቱን ያዳነለት የውሸት ስው ይዞለት የመጣ መሰለው፡፡ ለማንኛውም ከኪሱ ገንዘብ መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ተጣራ:
አሽከር ገባ::

«ሰውዬውን ይዘኸው ና።»
ደብዳቤውን የላከው ለው ገባ: ማሪየስ እንደ መደነቅ አለ፡፡
አሁን የገባው ሰው «ሕይወትህን ያዳነልህ ሰው ይዤ መጣሁ»
በማለት ቀደም ሲል የመጣ ሳይሆን እንግዳ ሰው ነው።

ጥቁር በጥቁር ነው የለበሰወ ጥቁር መነጽርም አድርጎአል: ከአፍንጫው ደፍጠጥ፣ ከአገጩ ረዘም ያለ ሲሆን በእጁ ባርኔጣ ይዟል።

ማሪየስ የጠበቀውን ሳይሆን ሌላ ሰው ከክፍሉ ውስጥ በመግባቱ
ከፊቱ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ታየበት እርሱን ያስጨነቀው ሕይወቴን ያዳነው ማን ነው የሚል ፕያቄ ሲሆን ጠብቆት የነበረው ሰው ይህን ዜና ይዞልኝ ይመጣል» ብሎ የገመተው ነበር ሰውዬውን ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉር አጤነው::

«ምን ትፈልጋለህ?» ሲል በመኮሳተር ጠየቀው

እንግዳወ በተራው ማሪየስን አጤነው የመረበሽ መልክ አልታየበትም፡: እንዲያውም እጁን ሱሪ ኪስ ውስጥ ጨምሮ ወገቡን ሳያቀና ግምባሩን ብቻ አቅንቶ ነው ማሪየስን ያየው «ጌታዬ፣ የመጣሁበትን አስረዳለሁ:: የምሸጥልህ ምሥጢር አለኝ፡»

«ምሥጢር?»

«አዎን፣ ምስጢር»

«ቀጥል፡››

«ጌታዬ ከቤትህ ውስጥ ሌባና ነፍሰ ገዳይ አለ፡፡»

ማሪየስ ክው አለ

«እኔ ቤት ውስጥ? የለም» ሲል ጮክ ብሎ ተናገረ ነቅነቅ የማይለው ደፋሩ እንግዳ ባርኔጣውን በእጁ ጠረግ ጠረግ
አድርጎ ንግግሩን ቀጠለ፡

«እውነተኛ ስሙን ልነግርህ ነው፡፡ ስሙን በነፃ ያለ ክፍያ ነው የምገልጽልህ፡»

‹‹እየሰማሁ ነው»

«ስሙ ዣን ቫልዣ ይባላል፡፡»

«አውቀዋለሁ »

«አሁን ስነግርህ ነው ያወቅከው::»

«አይደለም፧ከዚያ በፊት አውቀዋለሁ::
እንግዳው በፈገግታ ቀጠለ፡፡
‹‹ጌታዬን መቃወም አልፈልግም፡ ለማንኛውም ብዙ ነገር ማወቄን
መገንዘብ አለብህ አሁን የምነግርህ ጉዳይ ግን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው»

ማሪየስ እንግዳውን ትኩር ብሎ አየው::
«ዣን ቫልዣን የምሥጢር ስም ብቻ ሳይሆን የአንተንም የምሥጢር
ስም አውቃለሁ፡፡ እንዲሁም ትልቁን ምሥጢር አውቀዋለሁ

«ያንተን ስም»

«የእኔን ስም?»

«አዎን፣ ያንተን ስም:»

«ይህ እኮ አስቸጋሪ አይደለም ጌታዬ ከጻፍኩልህ ደብዳቤ ላይ ስሜን
ጽፌ የለም እንዴ?»
"
«'ዬን' አስቀርተሃል»

«እህ?»

«ቴናድዬ::»

«ማነው እሱ?»

አደጋ ሲመጣ ከሰው ጀምሮ እስከ ትንኝ ሁሉም መከላከያውን ያበጃል፡፡"
ዘበኞች ጥግ ይይዛሉ፡ ይህ ሰው ግን መሳቅ ጀመረ።

ማሪየስ ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ወረወረለት:

«አመሰግናለሁ ጌታዬ! አምስት መቶ ፍራንክ!» አለ ቴናድዬ።

ቴናድዬ በመገረም ገንዘቡን አየው፧ ደባበሰው፤ መረመረው: በድጋሚ
«አምስት መቶ ፍራንክ» አለ በመደነቅ:: ቀጥሎ «ይቺ...ቺ ጥሩ ናት» አለ
በማጉረምረም:: ከዚያም በድፍረት «አሁን መነጋገር እንችላለን›› ካለ በኋላ
በጉሬሣ ፍጥነት መነጽሩን አወለቀ አንገቱ ላይ የጠመጠመውንም እስካርፍ
ፈታ፡፡ ዓይኑ በራ፤ ፊቱ አንፀባረቀ:: አፍንጫው ቀጥ አለ፡፡ ያ አስከፊ ፊቱ
ጥምብ ያየ አሞራ ይመስል ቶሎ ተቀያየረ ልክ እንደ ጥምብ አንሳ አሞራ
እርሱም ጥምብ ያገኘ መሰለው፡

«ጌታዬ መቼም አትሳሳትም» አለ ጥርት ባለ ድምፅ፤ «በእርግጥ እኔ ቴናድዬ ነኝ::»

አሁን ገና ከወገቡ ቀና አለ፡፡ በቴናድዬ አመለካከት በማሪየስና በእርሱ መካከል ገና ንግግሩ አልተጀመረም:: አካሄዱን ለውጦ አዲስ ስልት መቀየስ እንዳለበት አምኖአል፡ ጉዳዩ ብዙም አልተበላሸም:: አምስት መቶ ፍራንክ እንደሆነ ተገኝቷል
«እኔ ቴናድዬ ነኝ» ለ በኋላ ዝም ስላለ ማሪየስ ጣልቃ ይገባል፡

«ቴናድዬ፧ ስምህን ነግሬሃለሁ: አሁን አንተ በተራህ ምሥጢርህን ንገረኝ፡፡ ልትነግረኝ የመጣህበትን እኔ እንድነግርህ ትጠብቃለህ: እኔም እንዳንተው ወሬ የምሰበስብበት መንገድ አለኝ፡፡ ከአንተ ይበልጥ እንደማውቅ አሁን ትገነባለህ እንዳልከው ዣን ቫልዣ ሌባ፤ ቀማኛና ነፍሰ ገዳይ እንደሆነ አውቃለሁ መሴይ ማንደላይን የተባለውን ሁብታም ባለፋብሪካ በመዝረፉና በማክሰሩ ቀማኛ ነው የፖሊስ አዛዥ የዣቬርን ሕይወት
በማጥፋቱ ገዳይ ነው»

ቴናድዬ በተሸፈነ ሰው ዓይን ማሪየስን አየው: ነገር ግን ወዲያው አንድ መላ ስለታየው በኩራት መንፈስ አሁንም ፈገግ እያለ ተናገረ::

«ጌታዬ የተሳሳትን መሰለኝ
‹ምን!» ሲል ማሪየስ መለስ፡ «ይህን ትክዳለህ? ቃሌ እውነትን ያዘለ
ነው፡፡»

«ጌታዬ በማረጋገጥ ነው የምትናገረው፡፡ ለዚህም ስለአንተ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ሆኖም እውነትና ትክክለኛ ፍርድ መውጣት አለባቸው:: ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ሲወነጀሉ መስማት አልፈልግም ጌታዬ፣ ዣን ቫልዣ መሱይ ማንደላይንን አልዘረፈም: ዣን ቫልዣ ዣቬርን አልገደለም»

«እንዴት ነው? ስትናገር አረጋግጠህ ነው!»

«በሁለት ምክንያት»

«በምንና በምን?»

«የመጀ…ሪያው ይኸውልህ፡ ዣን ቫልዣ መሴይ ማንደላይንን አልዘረፈም፤ ምክንያቱም ዣንቫልዣና መሴይ ማንደላይን አንድ ሰው ናቸው:፡›

‹‹ምንድነው የምትነግረኝ?»

‹‹ሁለተኛውን ምክንያት ደግሞ ስማ:: ዣቬርን አልገደለም ምክንያቱም
ዣቬርን የገደለው ራሱ ዣቬር ነው፡

«ምን ማለትህ ነው?»

«ዣቬር ራሱን ነው ያጠፋው፡»

‹ማረጋገጫ፣ ማረጋገጫ አምጣ» ሲል ማሪየስ በኃይል ጮኸ::

ቴናድዬ ቀጠለ፡፡ የሚናገረውን በማራዘም ጫን እያለ ተናገረ:

«የፖ.ሊሱ.... አዛዥ.... ዣ....ቬ...ር …ስም…ጦ ...ከጀ....ልባ .ሥር…ነው...የተገኘው...::»

«አሁንም ማስረጃ አምጣ
ነው የምልህ»

ቴናድዬ ከኪሱ ውስ ኦንድ ፖስታ አወጣ በፖስታው ውስጥ ቀለማቸው የተለያየ የተጣጠፉ ወረቀቶች ነበሩበት።
መረጃዎቼ እኮ ከእጄ ውስጥ ነው ያሉት አለ በዝግታ ስናገር ያለማስሪጃ አልናገርም ደግሞም ስለእጅ ጽሑፍ ማስረጃ አይደለም የማወራው
«እና ማስረጃዎቹ የታተሙ ናቸው።» "

ቴናዲዬ እየተናገረ ከፓስታው ውስጥ
የጋዜጣ ቁራጮችን አውጥቶ
ዘረጋ ወረቀቶቹ ፀሓይ ስለመታቸው ወደ ቢጫነት ተቀይረዋል፡ ከሁለቱ አንደኛው ቁራጭ ጫፍ ጫፉ በመበላቱና በመቀደዱ የቆየ ለመሆኑ በግልጽ
ይታወቃል::
👍18
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...“ስለሷ መናግር አትችይም ማዳም ቬን ”አላት ዊልያም ድርቅ ብሎ „'' አንቺ
እማማን አታውቂያትም " ከዚህ አልነበርሽም "

ትወዳችሁ እንደ ነበር በርግጥ እተማመናለሁ " እኔ ከዚህ የቆየሁት አንድ
ቀን ብቻ ነው ግን ባንድ ጊዜ ለመድኳችሁ " አሁን በጣም እወዳችኋለሁ ” አለችና
በትኩሳት የሚቃጠሉት ጐንጮቹን ሳመችው ይህ ሲሆን 0መፀኛው እንባዋን
ልትገታው ስለ አልቻለች እሱም እንዳሻው እየወረደ ከልጁ ጉንጭ ላይ ያርፍ
ጀመር ።

“እና ምን ያስለቅሻል ? አላት ዊልያም "

"አንተን የመሰለ ልጅ ነበረኝ ሞተብኝ " አሁን በምትኩ አንተን በማግኘቴ የስ ስለአለኝ ነው እሱ ከሞተ ጀምሮ ምንም የምወደው አላገኘሁም ነበር " አለችው

“ ስሙ ማን ነበር ? አላት ዊልያም በጕጕት "

'' ዊልያም ብላ ቃሉ ካፋ ከመውጣቁ አንደዚህ በማለቷ መሳሳቷ ተሰማት

ባርባራ ከቤት ካለች ራት እንደ ተበላ ወደ ሳሎን ከመግባቷ በፊት ከፎቅ ወጥታ ልጅዋን ለጥቂት ደቂቃዎች አይታ መውረድ የዘወትር ልማዷ ነበር » ዛሬ ማታም ልማዷን አድርሳ ስትወርድ ሉሲን በግራ ሳሎን ስታጮልቅ አየቻት "

አሁን መምጣት እንችላለን . . . እማማ ?

አዎን ! ማዳም ቬንም ጥቂት ዘፈኖች እንድትጫወትልን ንገሪያት "

ማዳም ቬን ቆየት ብላ በግድ እየተጨነች ከሳሎኑ በር ስትደርስ ሚስተር
ካርላይል ከምግብ ቤት ተነሥቶ ወደ ሳሎን ሲሔድ ፊት ለፊት ግጥም አሉ " ስታየው ቀጥ አለች ልታፈገፍግም አማራት ሉሲ አስቀድማ ዐልፋ ገብታ ነበር
እሱም እንድታልፍ ከጐን ቁሞ ጠበቃት።

“ማዳም ቬን " አላት እጁን ከመዝጊያው እጄታ አሳርፎ ንግግሩን ዝቅ አድርጎ
ስለ ልጆች በሽታ ብዙ ልምድ ነበረሽ ?” አላት

ልጆቿ አብረዋት በነበሩ ጊዜ ሙሉ ጤነኞች እንደ ነበሩ በማስታወስ “የለም” ብላ ልትመልስለት አሰበችና ሌላ ነገር ትዝ አላት " አራት ልጆች እንደ ሞቱባት
ተናግራ ስለ ነበር ፡ የምትሰጠው መልስ ከዚህ ጋር መስማማት እንዳለበት አሰበች

"የዊልያምን ሳል ስታይው ይህን ያህል አሥጊ ይመስልሻል ?"

“ብዙ ጥንቃቄ የሚያስፌልገው ይመስለኛል በተለይ ሌሊት እኔስ ከኔ ክፍል ውስጥ እንዲተኛ እንዲፈቀድለት ልጠይቅ ነበር " አልጋው በቀላሉ ይዛወራል እኔም ከማንኛዋም የበለጠ እጠብቀዋለሁ "

ምንም ቢሆን ይህን ያሀል ልናስቸግርሽ አንፈልግም ልጁ ደግሞ የሌሊት ጥበቃ እስከሚያስፈልገው ድረስ አልታመመም ቢያስፈልግም ሠራተኞቹ እምነት ሚጣልባቸው ናቸው

“ እኔ ልጆች እወዳለሁ ይህንን ልጅም ካየሁት ጀምሮ ወደድኩት " ስለዚህ
ጤንነቱን ቀንና ሌሊት ብንከባከበው ደስ ይለኛል "

"አንቺ በውነት በጣም ደግ ሰው ነሽ " ነገር ግን ሚስዝ ካርላይል ሐሳብሺን እንደማትቀበለው እርግጠኛ ነኝ ችግርና ድካም ልትፈጥርብሽ አትፈልግም ”

አነጋገሩ ቁርጥ ያለ ነበር " ከዚያ በሩን ከፍቶ አሳለፋት።

አሁን ደግሞ ከሁሉ ይበልጥ የፈራችው ፒያኖ መጫወቱን ነው ድሮ ለባሏ ስትዘፍንለት ነበር አሁን ልዝፈን ብትል ድምጿ ትዝ ይለው እንደሆነ ብላ ሠጋች ስለዚህም ከድሮ ዘፈኖቿ አንዳቸውንም ላትሞክራቸው ወሰነች ደግነቱ ወዲያው ከመግባቷ ጀስቲስ ሔር መጣ ሙዚቃ የሚባል ነገር ምንም ስሜት ስለማይስጠው እሱ ካለ ዘፈን የለም ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ተነሥተው ተቀበሉት ወደ መቀመጫው ሲያመራ በማዳም ቬን አጠገብ ስለ ዐለፈ ባርባራ አስተዋወቀችው።

" እኔ ፌረንሳይኛ መናገር አልችል ” አላት መላቅጥ በሌለው የቃላት አገባብና ድምፅ።

« እኔ እንግሊዛዊት እንጂ ፈረንሳዊት አይደለሁም ስለዚህ ፈረንሳይኛ
እንዲናገሩ የሚያስገድድዎ ነገር የለም ” አለችው እንደ መሣቅ ብላ "

“እኔ ኮ አንዲት ፈረንሳዊት ልትመጣ ነው ሲባል ሰምቸ ነው " አንቺም ብትሆኚ በስምሽ ጭምር ፈረንሳዊት ትመስያለሽ" ሆኖም ባለመሆንሽ በጣም ደስ አለኝ ፈረንሳዊት መምህር ከቤት ማስገባት ደግ አይደለም " እነሱን በሩቁ ነው ” አለና ዱሮ ለልጆቹ መምህርነት የቀጠራት አንዲት አስተማሪ በምግብ ጊዜ እንቁራሪት እየተሠራ ካልቀረበ እያለች ስታስቸግር መኖሯንና በኋላም ከጦር ሜዳ ቆስሎ ከሱ ቤት ይቀመጥ ከነበረው አንድ ወንድሙ ጋር ፍቅር ገጥማ ስለ አገኛት ' ሁለቱንም
ማባረሩን ነገራቸ “ ኧረ እንኳን አልሆንሽ እኔ አሁን ፈረንሳይ አገር ብቀመጥና
መስዬ ሔር እየተባልኩ ብጠራ ለልጄ እንኳን የፈረንሳይ እንቁራሪት መስዬ ብታየው አልቀየመውም " አለቸው "

ሉሲ ባነጋገሩ እያጨበጨበች ከትከት ብላ ሣቀች "

"አንቺ ግድ የለም ሣቂ " ግን ለፈረንሳዊት አስተማሪ ቢሰጡሽ እስካሁን ወደ
አንቁራሪትነት ወይም ከዚያ ወደባሰ ነገር ትለወጭ ነበር " ያቺ ያልታደለች እናትሽ እንኳን በልጅነቷ ፈረንሳዊት አስተማሪ ባትኖራት ኖሮ በመጨረሻ እንዲያ ያለ ሥራ አትሠራም ነበር ። በሉ ይብቃን " ስሚ እስኪ ባርባራ ምን ነገር ነው ያሳሰብሻት ?”

“ ምን ማለትህ እንደሆነ አልገባኝም " እኔና አርኪባልድ አንተ ከለንደን እስክትመለስ ድረስ ከእኛ ጋር እንድትሰነብት እንፈልጋለን " ምናልባት የጠየቅኸው ይኸን ከሆነ ?

“ ጌትዮውም እመቤቲቱም በሌሉባት ቤቴ የሠራተኞች መጨፈሪያ እንዲሆን ነው " እናንተ ወጣቶችኮ ከጥጆች የተሻለ አታስቡም " እናንተ ዘንድ ከአንድ ቀን በላይ እንድትቆይ ከፈለጋችሁ ለምን እኔ እያለሁ እንድትመጣ አታደርጓትም?

“ እንደሱ እንዳይሆንማ እሷም ትታህ ለመምጣት እሺ እንደማትል አንተም
ታውቃለህ » እሷን የመሰለች ሚስት እኮ ታይታ አታውቅም " አሁን እኔ ለአርኪባልድ ከብዙ ዘመን በኋላ የሷን ግማሽ ያህል እንኳን ብሆንለት ዕድሌን ማመስገን ይኖርበታል አባባ
ሁልጊዜ አንተ ባልከው ነው የሚሆንልህ !እስኪ ዛሬ
ደግሞ የኛን ፈቃድ ፈጽምልን እማማ እኛ ዘንድ ለመምጣት ትፈልጋለችና እባክህ እሽ በል " ቤቱና የቤቱ ሠራተኞች ምንም አይሆኑም ፤ በኔ ይሁንብህ"
"ለውጥ እኮ ያስፈልጋቸዋል ጌታዬ አለ ሚስተር ካርላይል የባለቤቱዎን የጭንቀት ኑሮ ያውቁታል"

"ሁልጊዜ ስለዚያ ወሮበላ ስታስብ ነዋ !ለምን አትተወውም "

"እሳቸውኮ ለእርስዎ አዛኝና አፍቃሪ ሚስትም ናቸው "
አይደለችም አላልኩም "
“ እንግዳያውማ ጥቂት ቀን ከእኛ ጋር እንዲቆዩ ይንገሯቸው " ለውጡ ራሱ
በጣም ይበጃቸዋል " ከባርባራ ጋር ሲሆኑ ብዙ ይረዳቸዋል " እንዴት እንደሚወዷት እርስዎ ያውቃሉ ።

“ አዎን ከሚገባት በላይ ትወዳታለች » አሁንማ ይችም ከኔ ቁጥጥር ውጭ
የሆነች መሰላትና ያለመጠን ተዝናናችብኝ " አለ ጀስቲስ ሔር

"በኔ ቁጥጥር ውስጥ ስለሆነች ልክ አስገባታለሁ በዚህ አያስቡ ' አለ ሚስተር ካርሳይል ።

ዐውቃለሁ አለ አባትዮው ቆጣ ብሉ ። እሷን ልክ ከማስገባትህ በፊት
መረን ለቀሀ አቅብጠህ ትገድላታለህ ”

ለጀስቲስ ሔር መጠጥ ቀረበለት " በዚህ መኻል ሳቤላ ወደ ሚስዝ ካርላይል
ጠጋ ብላ ለመሔድ ይፈቀድላት እንደሆነ ጠየቀች ሚስዝ ካርላይል በጎ ፈቃዷ ሆኖ ጥያቄዋን ተቀብላ ለቀቀቻት "

ከግራጫዉ ሳሎን ገብታ ብቻዋን አመሸች " በጸጸት በኀዘን በንዴት በቁጭት የተመላ መራራ ምሽት በሦስትና በአራት ሰዓት መካከል ከመኝታ ቤቷ ገብታ ለማረፍ እየተሳበች ወደ ፎቅ ወጣች ከክፍሏ ልትግባ ስትል የዊልሰንን ረዳት ላራን ስታልፍ ብታገኛት ድንገተኛ ሐሳብ ድቅን አለባት -የዊልያምን መኝታ ቤት ጠይቃት አሳየቻትና ወርዳ ወደዚያው ሔደች ሳቤላ የሳራን መሔድ አረጋግጣ ከዊልያም ክፍል ቀስ ብላ ገባች ዊልያም አንድ ትንሽ ነጭ አልጋ ላይ ተኝቷል " ፊቱ ቦግ ብሎ ወዝቷል ። ትኩሳት
👍14😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን  አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ

‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››

ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››

‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››

ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ

ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት  ጥያቄ  ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና  ሳይጠይቃት መለሰችለት….

‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››

‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት

‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን  አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››

‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ  ነበር የቀራት….. 

እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች   ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው

‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡

‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››

‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን  ለቆ ወጣ……

‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች

….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን  የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና  ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////

ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ  ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን  እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››

‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ›› 

‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››

‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››

‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››

‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››

‹‹ወዴት....?››

‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››

‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››

ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››

‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››

‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ  ሰውና በ20  ደቂቃ  ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው

‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››

‹‹እራስህንማ  እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››

‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት  ኮስተር ብሎ

‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››

‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ  ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ  ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››

‹‹ከዛ ምን…..?››

‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››

‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››

‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››

‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ  በመግባት  እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ  ጉብ አለ….

ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..

‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›

‹‹የማታው ንስር አይደል..?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ምን ይሰራል  እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››

‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››

‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት  

‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››

‹‹እኔና ንስሬ››

ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››

‹‹የምሬን ነው…›

‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን  ማወቅ አልቻልኩም››
👍11015😁4👏2😱2👎1
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን ሰዓሊ ሰላም ነች.. ሰዓሊ ሰላም ወደ መድረክ…፡፡››

ሰላም ሸንከል ሸንከል እያለች ወደ መድረክ ስትወጣ ትንግርት ከኃላዋ 120 ሳ.ሜ በ 60 ሳ.ሜ ስፋት ባለው በሸራ ላይ የተሳለ ስዕል ይዛ ተከትላት ወጣች፡፡ስዕሉ ለህዝብ እይታ ቀረበ፡፡

<<እኛ ለእኛ›› የሚል ርዕስ አለው፡፡

አንድ ህፃን የተቦተራረፈ ልብስ እና የቆሸሸ ፊት ይዞ አስፓልት ዳር ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ
ጠርዝ ላይ ቂቢብ ብሎ በመውጣት ሞልቶ በመትረፍ አካባቢውን ሙሉ ከሸፈነው ቆሻሻ ላይ የተጣለ ምግብ ጎንበስ ብሎ የሚፈልግ ይመስላል፤አንደኛው እጁ ግን ወደ አስፓልቱ ተቀስሯል፤በተቀሰረው እጁ አቅጣጫ የቆመች የቤት መኪና ትታያለች፣ከመኪናዋ ውስጥ አንድ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኝ የፀዳ ልብስ የለበሰና የተመቸው ህፃን በመስኮት ተንጠራርቶ መፅሀፍ እና ዳቦ ለጎስቆላው ልጅ ሊያቀብለው ሲንጠራራ ያሳያል፡፡

ሁሴን ቃላ መጠየቅ ሊያደርጋት ወደ ሰላም ተጠጋ

‹‹ስምሽን ብታስተዋውቂን?››

‹‹ሰላም እባላለሁ..ሰላም ታዲዬስ፡፡››

‹‹ሰላም እሺ ..…ለምንድነው ወደዚህ መድረክ የወጣሽው?››

‹‹ይሄንን ስዕል ለድርጅቱ በስጦታ ላማበረክት፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ነው ..ማነው የሳለው?››

<<እኔ ነኛ፡››

‹‹ለምን ርዕሱን ..እኛ ለእኛ አልሽው?››

‹‹ለእኛ ከእኛ ውጭ ማንም ስለሌለ ነዋ...ታዲዬስ አባት ባይሆነኝ እኔ ይሄኔ እዚህ

መድረክ ላይ ሳይሆን ሀዋሳ መንገድ ዳር ቁራሽ ዳቦ መግዣ ሳንቲም እየለመንኩ ነበር
ምታገኙኝ…..እባካችሁ የኢትዮጰያ ህዝቦች በጠቅላላ መጥናችሁ ውለዱ፤ልመና የሞራል
ነቀርሳ ነው ማንም ህፃን እንዲለምን አትፍቀዱ፤ጎዳናዎች ከቦታ ወደ ቦታ መተላለፊያዎች እንጂ ፈጽሞ የህጻናት መኖሪያዎች መሆን የለባቸውም፤ታዲ አባቴ ከዛ
የጎዳና ሰቆቃ አውጥተህ ሰው ስላደረግከኝ አመሰግንሀለው እሺ ... ደግሞ በጣም ነው
የምወድህ....ሁላችንም ልጆችህ
እንወድሀለን..ሁሉም የዓለም አባቶች እንደ አንተ እንዲሆኑ እንፈልጋለን..››ይሄን ስትናገር እንባዋን መግታት ስላልቻለች መድረኩ ጥላ ወረደች..አዳራሹን የሞላው ህዝብ ዓይኞች ሁሉ
በዕንባ ፈሳሽ ተሞሉ፡፡ሁሴን ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ መናገር
ጀመረ‹‹እሺ ሰላምን እንደሰማችኋት ይሄንን በነዛ
ትናንሽ እጆቿ የተሳለውን ድንቅ ስዕሏን በስጦታ አቅርባልናለች.. እናም ለጨረታ እናቀርበዋለን..፡፡
ሰላም ማለት የታዲዬስ ልጅ ነች..ቅድም ልዩ ጥኡመ ዜማ ለጆሮችን ያሰሙን ሀሊማ እና
ሄለንም የታዲዬስ ልጆች ናቸው፤ሚጡና ሙሴ
የሚባሉም ልጆች አሉት...በተለይ ሙሴ የልጅ ሳይንቲስት ነው…ስለሱ ሳስብ ምን እንደሚታሰበኝ ታውቃላችሁ ሰው ከሞተ በኋላ
ነፍሱ በሌላ ሰው አካል ሆና ዳግም ወደዚህ ምድር ትመጣለች የሚል እምነት የሚያራምዱ
ማህበረሰቦች አሉ ፤ያ እምነት እውነት ከሆነ የታዲዬስ ልጅ የሆነው ሙሴ የቶማስ ኤዲሰንን
ነፍስ ይዞ ለኢትዬጵያውያን ተስፋ ሊሆን የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ…. በአጠቃላይ ቅድም ታዲዬስ
የተናገረው ንግግር ለመናገር ብቻ ሳይሆን እሱ በተግባር ስለፈተነው ህጻናትን ከመሰረቱ ኮተኩተን ካሳደግናቸው ገና ከጥዋቱ ፍሬያቸው እንደምናይ ስላረጋገጠ ነው..፡፡

አሁን ወደ ሰላም ሥዕል ጨረታ እንግባ..በነገራችን ላይ ከዚህ ፕሮግራም በኋላ የሰላምን ሌሎች ድንቅ ስዕሎችን ማየት ከፈለጋች በሚቀጥለው ክፍል ጎራ በሉ..(ይሄንን ሲናገር በየቤታቸው ሆነው ዝግጅቱን በቴሌቨዠን ለሚከታተሉት ካሜራው የሰላም ስዕል ወደ ሚገኙበት ክፍል በማዞር ማስቃኘት ጀመረ ..13 የሚሆኑ የተለያየ ርዕስ እና መጠን ያላቸው ስዕሎች በግድግዳው ላይ ተሰባጥረው ለዕይታ ምቹ ሆነው ተሰቅለው አሳየ፡፡

ሰላም ለድርጅቱ በስጦታ ያበረከተችው ስዕል ከሸራተን ሆቴል አልወጣም..በሼኩ ትዕዛዝ ይመስላል በ1ዐዐ ሺ ብር መነሻ የተጀመረውን ጫረታ ፉክክር ዝግጅቱ ላይ ታድመው የነበሩት የሜድሮኩ ስራ አስኪያጅ በሁለት ሚሊዬን ብር እዛው አስቀሩት..ድርጅቶችም ግለሰቦችም ያቅማቸውን ወረወሩ..አጠቃላይ ቃል የተገባውና እጅ በእጅ የተሰጠው በድምሩ 25 ሚሊዬን ብር ሆነ፡፡

ሁሴን ፕሮግራሙን ወደ ሶስተኛው ዝግጅት ሊያሸጋግር ፈለገ‹‹ቅድሚያ ግን ሄለን እና ሀሊማ ወደ መድረክ ዳግም እንዲወጡ አደረገ...የቴዲ አፍሮን ላምባዲና ነው ያቀረቡት፤ ልክ እንዳጠናቀቁ ሁለተኛውን ሙዚቃ ሊቀጥሉ ሲሉ ትንግርት በምልክት አስቆመቻቸው እና ወደ መድረክ ወጣች ፡

‹‹ይቅርታ ለየት ያለ ዜና በስልክ ስለደረሰኝ ነው ወደ መድረክ የወጣሁት..ቴዲ አፍሮ ከሄለን እና ሀሊማ ጋር አዲስ አበባ ላይ አንድ ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን ለድርጅቱ እንዲሚያስገባ ነግሮናል.. ለጊዜው 1ዐዐ ሺ ብርም በአካውንታችን ዛሬውኑ እንደሚያስገባ አብስሮናል፤እንግዲህ እዚህ ዝግጅት ላይ የታደሙ ድምጻዊያኖቻችን እና ኮሜዲያኖችም ቅድም እንደሰማችሁት አንድ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁልን ቃል ገብተው ነበር..ይሄ ሁለተኛ ኮንሰርት መሆኑ ነው፡፡እናመስግናለን ››ብላ ወረደች፡

..በዚህ ዜና በጣም የፈነጠዙት ሀሊማ እና ሄለን ናቸው ፤ከሚወዱትና ከሚያደንቁት ለእነሱ እንደ ህልም ከሆነው ቴዲ አፍሮ ጋር በአንድ መድረክ ሊሰሩ ነው..በደስታ በተጥለቀለቀው ስሜታቸው የሚቀጥለውን ሙዚቃ መጫወት ጀመሩ.. የሰርግ ዘፈን ነው‹‹..ሙሽራዬ ሙሽራዬ ... የወይን አበባዬ››ሙዚቃውን ተከትሎ ከጀርባ ካለው በር ወደ መድረክ ሲወጣ የታየው ታዲዬስ ነው፡፡ ቅድም ከለበሰው ልብስ በተለየ አለባበስ ሙሉ ሱፍ ለብሶ ቀኝ እግሩን አስቀድሞ ታየ.. ከኃላው ነጭ የተንዘረፈፈ ቬሎ የለበሰች ወጣት ተከትላዋላች... ርብቃ ነኝ..፡፡እጅ ለእጅ ተቆላልፈው በዝግታ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ወደ መድረኩ ወጡ…ጥጉን ይዘው እንደተጣበቁ ቆሙ፡፡

ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው..ሌሎች ጥንዶች በተመሳሳይ ሁኔታ በተመሳሳይ አለባበስ ወጡ ዶ/ር ሶፊያ እና ፕ/ዬሴፍ ናቸው፡፡ ከነ ታዲዬስ ጎን ቆሙ..አሁንም ሌላ ጥንዶች ተከተሉ ፎዚያና ኤልያስ(የእነ ኤልያስ ጋብቻ ልዩነታቸውን በምን ሁኔታ ፈተው ወይም ለመፍታት ተስማምተው ለዚህ ጥምረት እንደበቁ ለጊዜው ከጥንዶቹ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው የለም) ህዝብ ከፍተኛ መደመም ወስጥ ገብቷል..በመጨረሻ ጥንድ ሆነው የወጡት የነ ሀሊማ የሙዚቃ አስተማሪዋ አይነ ስውሯ ፅዬን እና የሰላም የስዕል አስተማሪው ዓልዓዛር ናቸው፡፡ሙዚቃው አልቆ ተቋረጠ..ከዛ አምስቱም የታዲዬስ ልጆች ከያሉበት ወደመድረክ ወጡና ታዲዬስን እና አዲሷን እናታቸውን ርብቃን ከበው ቆሙ..በተመሳሳይ ሌሎች ጥንዶችም ዛሬ ለማሳዳግ የተረከቧቸው ልጆች ወደ መድረክ ወጥተው በእያንዳንዱ ጥንዶቹ መካከል በፈገግታ ቆሙ..ህዝቡ በደስታ እና በዕልልታ አዳራሹን አደበላለቀው፡፡

ሁሴን ወደ መድረኩ ወጣና መናገር ጀመረ….
👍7614🤔2👎1