አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....አሥር አለቃ ንጉሤ ብድግ
አለ፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉቱ በሙሉ ዐይኖቻቸውን ተከሉበት።
“እህህ..እህ... እናቶቼ ወንድሞቼና እህቶቼ..” ጉሮሮውን አፀዳና ቀጠለ..
“መቼም የዛሬው ደስታ የሁለቱ ሙሽሮቻችን ብቻ ሳይሆን የኛ የሁላችን በዚች ቤት ውስጥ ተሰባስበን ፅዋችንን ያነሳንላቸው ተጋባዦች ጭምር ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። እንደ ባህላችን ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ ጠጁ ተጥሎ ጠላው ተጠምቆ ሻኛ እየተቆረጠ ዘመድ አዝማዱ ያለገደብ እየበላ፣እየጠጣ፣ እየጨፈረ ሃይሎጋ እያለ ጋብቻ ሲፈፀም ለተመልካች ደስ ይላል፡፡ ይህቺ የኛዋ ሠርግ ግን በዚህ በሚቆረጠው ጮማ በሚጣው ጠጅና በወገን ብዛት ደምቆ በሚፈፀመው የጋብቻ ደንብ ውስጥ የምትጣፍና ከቁጥር የምትገባ አይደለችም፡፡ በእውነት ነው የምላችሁ ይቺ በእኛ ሃያ በማንሞላው ሠርገኞች የታደመችው ሠርግ ግን እልፍ
አእላፍ ሠርገኞች የጨፈሩበትን ጋብቻ የምታስንቅበት አንድ ትልቅ ምክንያት አላት። ሁለቱ ልጆቻችን ወይንም ደግሞ ወንድማችን ታደሰና እህታችን ሰላማዊት ያለምንም ፊርማና ያለአንዳች የሃብት ድርድር ፍቅርን ብቻ ዋስትና ጠርተው ፍቅርን ብቻ የጋራ ሃብት አድርገው ትዳር ለመመስረት መወሰናቸው በሁለቱም ልብ ውስጥ ያለው የመተማመንና የመፈቃቀድ ደረጃ ምን ያክል ከፍተኛ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን ነው።

በፊርማ የሚፈፀመውን ትዳር ለመቃወም አይደለም። ፊርማ
በትዳር ላይ ሊፈፀም የሚችለውን ወንጀል ለመከላከልም ሆነ በተጋቢዎቹ መካከል በራስ መተማመን እንዲኖር የሚያበረክተው ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ይሁን እንጂ የጋብቻ ውል የእስር ሠንሠለት ሆኖ የሚታያቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ከፍቅር በኋላ ውሎ እያደር በሚመጣ አዲስ ስሜት የተነሳ የጋብቻ ውል መፈፀማቸው ከባድ ስህተት ሆኖ የሚታያቸው፣ ትዳር መመስረታቸው የሚያማርራቸውና
ያንን የሚማረሩበትን የጋብቻ ሠንሠለት በጣጥሰው በመጣል በአስቸኳይ ለመለያየት በየፍርድ ቤቱ የሚጓተቱ በርካቶች ናቸው። ለዘላቂ ትዳር ዋናው ቁም ነገር እውነተኛ ፍቅር እንጂ የጋብቻ ውል አይደለም። በከፍተኛ ወጪ ሠርጉ ተደግሶ በሺህ አጀብ ጋብቻው ከተፈፀመ በኋላ በሁለተኛው እና በሦስተኛው ወር ላይ ለፍቺና ለንብረት ክፍፍል በየፍርድ
ቤቱ መሯሯጥ የተለመደ ነው፡፡ ቁም ነገሩ የተጋባዡ ቁጥርና የግብዣው ብዛት ሳይሆን የተጋቢዎቹ ፅኑ ፍላጐትና እምነት ነው። ለእኔ እንደሚገባኝና እንደማምነውም ከሆነ በሁለቱ የዛሬዎቹ ሙሽሮቻችን መካከል
ያለው ሃብት ንብረት ሲኖር አንድና ብቸኛ የሆነው " ፍቅር" ብቻ ነው።
ፍቅር ሳይኖር የሚፈፀም ጋብቻ ከጥሩ ቪላ ቤት ከጥሩ መኪና በአጠቃላይ ከጥሩ ገንዘብ ጋር የሚደረግ ጋብቻ እንጂ ንብረቱን በሚያፈሩት የትዳር ጓደኛሞች መካከል የሚፈፀም ስላልሆነ አንድ ቀን ያ ገንዘብ እንደ
ጉም በንኖ ሲጠፋ የውሽቱ ፍቅርም አብሮ ሰናኝና ጠፊ ይሆናል። ስለዚህ በታደስና በሰላማዊት መካከል ያለው እውነተኛ ፍቅር አብቦ ከዚህ የበለጠ ሆነው ልጅ ወልደው ለመሳም በቅተው አብረው ጥረው ግረው ንብረት ሲያበጁ ደግሞ እምነት አለኝ አስር ልጆች ወልደውም ቢሆን እንኳ
በዛሬዋ እለት አልተደረገም ብለው ቅር የተሰኙበት ነገር ቢኖር በዚያን
ጊዜ እንደ አዲስ ተጋብተው እንደ አዲስ የሙሽራ ልብስ ለብሰው ሰንጋው ተጥሎ ጮማው እየተቆረጠ በሺህ አጃቢ ታጅበው እልል እየተባለላቸው
ጋብቻቸውን በድጋሜ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፡፡ እኛም ዕድለኞች ከሆንና እድሜም ከሰጠን ያንን ደስታ ያንን አለም ለማየት እንበቃ ይሆናል። በእውነት ነው የምላችሁ ይህንን የምናገረው ስሜታዊ ሆኜ ሳይሆን ከዚህ በፊት ያየሁት እና ያጋጠመኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ በድህነትና በችግር ላይ ሆነው ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ሀብት አግኝተው ወልደው
ከብደው በልጆቻቸው ሚዜነት እየታጀቡ እንደ አዲስ ሰርጋቸውን የሰረጉ ብዙ ሰዎች መኖራቸውን ስለማውቅ ነው። የዛሬዎቹ ሙሽሮቻችን የተገናኙበትና ለጋብቻ የተጫጩበት አጋጣሚ ብዙዎች የማይደፍሩት ሆኖ
ሳለ እነሱ ግን ደፍረው ገብተዋልና ዛሬ የጋብቻቸው ቀን ብቻ ሳይሆን
የህይወታቸው አዲስ ምእራፍ የሚጀመርበት ቀን ጭምር ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ አዲስ የህይወት ምእራፍ ውስጥ አዲስ የኑሮ ትግል ጀምረው በድል በመወጣት ወልደውና ከብደው የምናይበት ጊዜ ሩቅ ይሆናል ብዬ አልገምትም፡፡ የዛሬዋን ጋብቻ እግዚአብሔር የአብርሃምና
የሳራ እንዲያደርግላቸው ቤት ንብረት ይዘው እንዲያስጨፍሩን ምኞቴን እየገለፅኩ መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላቸው እላለሁ” አነጋገሩ የብዙዎችን ልብ የነካ በመሆኑ ጭብጨባው ቶሎ አላበቃም ነበር፡፡ በአስር አለቃ
ንግግር አንጀታቸው ቅቤ የጠጣው እማማ ወደሬ ትንሽ ንግግር ለማስማት፣ ልባቸው ላይ የምትንቀለቀል የደስታ ስሜታቸውን በቃላት ለመግለፅ ፈለጉ፡፡ በያዟት አሮጌ መሀረብ ከንፈሮቻቸውን አብስ አብስ አደረጉና የተወለጋገዱ ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉ።

እኔም ደስ ብሎኛል! አንጀቴ ቅቤ ጠጥቷል፡፡ ሞት ቀድሞኝ ቢሆን ኖሮ ይህን ዓለም ይህን ሲሳይ አላየውም ነበር፡፡ እመቤቴ ማርያም ጠሎቴን ሰምታ ለዚህ ታበቃችኝ ከእንግዲህ በኋላ ብሞት እንኳ ሞትኩ አይባልም፡፡ ልጅ ወልጄ ለመዳር ማህፀኔ ባይታደልም በስተርጅና በመሞቻ
ጋዜዬ ምስጋና ይግባትና እመቤቴም ሰላማዊትን የመሰለች ልጅ ሰጥታኝ ለዚህ ስትበቃ እንዳይ ስለረዳችኝ ደስታዬን የምገልጥበት ቋንቋ የለኝም።
እንደ ማር እንደ ወተት ያጣፍጣችሁ። ፍቅራችሁ ፍቅር ይሁን። አይለያችሁ። የምታስቀኑ ያድርጋችሁ። በክፉ የሚያያችሁን ዐይኑን ይያዝላችሁ" ብለው መረቁና ተንፈስ አሉ። ሙሽሮቹ እማማ ወደሬ ሲናገሩ
ልባቸው በደስታ ተሸበረ። ዐይኖቻቸው እምባ አቀረሩ... የደስታ እምባ...
እየተበላ እየተጠጣ እስክስታ እየወረዱ ሲደሰቱ ሲጨፍሩ ቆይተው መሸትሸት ሲል ሙሽሪት በአጃቢዎቿ በታደሰና በጓደኞቹ ታጅባ በአንድ ታክሲ ውስጥ ታጭቀው ወደ ታደሰ ቤት በረሩ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አዲሷ ሙሽራ ሰላማዊት አዲሱን ህይወት በመላመድ ላይ ነች፡፡ ከታደስ እውነተኛ ፍቅርና መተሳሰብ ጋር ከዚያ አስቃቂ ኑሮ ከእስር ተላቃ የነፃ ህይወት አየር በመተንፈስ ላይ ነች፡፡ ከውስጥም ከውጭም አማረች፡፡ደመቀች። ታደስ በደላላነት ሥራው ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ነጋዴዎች የቀናቸው እለት በተደሰቱበት ጊዜ የሚስጡት ድጉማ ላሌላ ባይተርፍም ሁለቱን በደስታ ሊያኖራቸው የሚችል ነው፡፡
የፋሲካ በዓል ደርሷል። ህዝቡ በሁሉም መስክ ለዝግጅቱ መሯሯጥ ጀምሯል፡፡ ዓመቱን ሙሉ ሽሮ ያረረበት ለፋሲካ በዓል በቅቤ ያበደችውን ዶሮ ሰርቶ ከጐረቤቱ ከጓደኛው እንዳያንስ ራሱን እየበደለ በቋጠራት ሳንቲም ቢቻል በግ ካልቻለ ደግሞ የቅርጫ ስጋ ተቀራጭቶ ይገባል።
ልጆቹ ሚስቱ የጐረቤት ወጥ እንዳይሽታቸው የሌላ ሰው ቤት እንዳይቀላውጡ የበይ ተመልካች እንዳይሆኑ.. በፋሲካ ሰሞን ሁሉ ነገር ዋጋው እሳት ቢሆንም የአቅሙን ያክል ይዘጋጃል። ለፋሲካ የዶሮ ላባው ይበላ
ይመስል ገብስማ፣ ወሰራ፣ ልበወርቅ፣ ቀይ፣ነጭ.እየተባለ ዋጋው ይሰቀላል። እንደዚያም ሆኖ ግን ሁሉም ጥርሱን ነክሶ ይገዛታል እንጂ አይቀርም፡፡ ምን ዶሮ ብቻ? በበአል ሰሞን ምን የማይወደድ ነገር አለ?
👍4
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....በእራት ሰዓት ግን ዣን ቫልዣ ከሠርጉ ቤት አልነበረም፡፡ ትንሽ
ስላመመው በጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የእርሱ ከዚያ አለመገኘት ኮዜትን ቅር አሰኛት:: ሆኖም የእርሱን ቦታ ማሪየስ በመውሰዱ ሀዘንዋ እየተቃለለ ሄደ፡፡ በመጨረሻ ዣን ቫልዣን እስከ መርሳት ደረሰች::...

ዣን ቫልዣ ከቤቱ ሲደርስ ቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም፡፡ ወደ
ኮዜት ክፍል ሲሄድ አልጋዋ አለመነጠፉን ተገነዘበ፡፡ አንሶላዎቹና የትራስ ልብሶች ተነስተዋል፡፡ አንዳንድ የኮዜት የግል እቃዎችም ከዚያ ተወስደዋል፡፡ከዚያ የቀሩት ከባድ የቤት እቃና አራቱ ግድግዳዎች ብቻ ናቸው፡፡ ዣን ቫልዣ ክፍት የነበረውን ሣጥን ዘጋግቶ ከክፍሉ ወጣ፡፡ ክፍሎቹን ሁሉ እየተዘዋወረ ጎበኘ፡፡ ከራሱ መኝታ ቤት ደረሰ፡፡ ወደ አልጋው ሲሄድ ዓይኑ
ከአንድ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ዘወትር ከዓይኑ የማይለየው አነስተኛ ሣጥን ከዚያ ተቀምጧል፡፡ ከአጠገቡ ስለማይለየውና በጣም ስለሚንከባከበው ኮዜት
ትቀናበት ነበር፡፡ ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ ትንሹን ሻንጣ ከፈተው::
ከውስጡ የነበሩትን ልብሶች አወጣ፡፡ በመጀመሪያ ጥቁር ቀሚስ፤ ቀጥሎ ጥቁር እስካርፍ፤ ከዚያም ዛሬም ቢሆን ኮዜት ልታደርገው የምትችል ትልቅ የልጅ ጫማ፤ በመጨረሻ ባለኪስ ሽርጥና የተቀደደ የእግር ሹራቦችን
አወጣ፡፡ ኮዜት ከአሥር ዓመት በፊት ሞንትፌርሜን ለቅቃ ስትወጣ የተቀመጠና እናትዋ ከሞተች በኋላ ኮዜትን ፍለጋ ሲሄድ ዣን ቫልዣ የወሰደላት ጥቁር ልብሶች ናቸው:: ልብሶቹን ከአልጋው ላይ ዘርግቶ
እንዳስቀመጣቸው የኮዜት እናት ትዝ አለችው:: በዚያን ጊዜ ኮዜትም ምን ትመስል እንደነበረና እንዴት ከእዚያ አስከፊ ቤት አስወጥቶ ለእናትዋ ሀዘን
ያመጣላትን ጥቁር ልብስ ለብሳ ምን ትመስል እንደነበረ አስታወሰ፡፡ በእናትዋ ሞት ምክንያት ከል ለብሳ እናትዋ በመንፈስ ስታያት ሳትደሰት አልቀረችም ሲል አሰበ፡፡

ኮዜት ከዣን ቫልዣ ጋር ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ ያቋረጠችውንም
ጫካ አስታወሰ፡፡ ኮዜት ደስ ብሎአት ያንን የገዛላትን ትልቅ አሻንጉሊት ተሸክማና የሀዘን ልብስ ለብሳ ከማታውቀው ሰው ጋር በደስታ ስትጓዝ ምን ትመስል እንደነበር ትዝ አለው:: ሆዱን ባር ባር አለው፡፡ ከአልጋው ላይ
ከዘረጋው የኮዜት ልብስ ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ::
ያን እለት ማታ የሕይወቱን የመጨረሻ ትግል፣ የመጨረሻ ፈተና እንደሆነ ዣን ቫልዣ ተገነዘበ፡፡ እንደ ልማዱ ዣን ቫልዣ ከሌላ ፈተና ውስጥ ገባ፡፡

እንዴት አድርጎ ነው የማሪየስንና የኮዜትን ፍቅር ሳያበላሽ አብሮ
የሚኖረው? ለግል ጥቅሙ ሲል ደንቃራ ይሁን ወይስ ብቻውን ውስጥ ውስጡን ይሰቃይ? ይህ ሁልጊዜም ቤተሰቦችን ያስጨነቀና የብዙ ፍቅረኞችን ሕይወት ያበላሸ ጥያቄ ነው::

በሥጋ ፈቃድ ተመርቶ እርምጃ መውሰድ ውጤቱ ግጭት ነው::
ታዲያ እስከመቼ ነው የነፍስ ተገኝዎች ሆነን የምንቀረው? ዣን ቫልዣ ለሥጋው አድሮ ኮዜትን አልለቅም ይበል ወይስ ለነፍሱ አድሮ ሙሉ በሙሉ ለማሪየስ አሳልፎ ይስጣት?

ግን እኮ ቀላል አይደለም:: እርሱስ ምን ይሁን? ከትቢያ አንስቶ ለዚህ
አደረሳት:: የመንፈስ ልጁ ናት:: በዓለም ላይ ያለ እርስዋ ሌላ ሀብት የለውም:: ወንድሙም፣ እህቱም፣ እናቱም፣ አባቱም፣ ጎረቤቱም፣ ምኑም ምኑም ኮዜት ናት:: ኮዜት ትሂድና ሙልጭ ይውጣ? ታዲያ ምን ይሁን?
ታዲያ ለዣን ቫልዣ ሲባል የኮዚት ሕይወት ይበላሽ?

እንዴ፣ ሕይወትዋ የማን ሆነና?

መስዋዕትነት መትነን ነው፣ ለመደሰት መሰቃየት አለ፤ ይህን መፈጸም ማለት ደግሞ ከጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ነው:: ግን ካጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ከቻለ ዓለምን ከቁጥጥር ስር ማድረግ ይሆናላ!

ዣን ቫልዣ ፍልስፍናውን ትቶ ተስፋ በመቁረጥ ጋደም አለ፡፡ ነገሩን
ሁሉ ለካው፣ መዘነው:: ከዉሳኔ አሳብ ላይ ደረሰ፡፡ እርሱና ጨለማ
ብቻቸውን ቀሩ፡፡

በሠርግ ማግሥት ሁሉም ነገር ጭር ይላል:: ለፍቅረኞች እድል
ለመስጠት ታስቦ ይመስል ሁሉም አርፍዶ ነው ከመኝታው የሚነሳው::ዣን ቫልዣ ግን በጠዋት ተነስቶ ወደ ማሪየስና ኮዜት ቤት ሄደ::

«እርስዎ ነዎት አባባ!» አለ ማሪየስ ዣን ቫልዣ ከነበረበት መጥቶ::
ማሪየስ ብዙም ስላልተኛ በጣም ከብዶታል፡፡

«ምነው በጠዋቱ? ኮዜት ገና አልተነሳችም፡፡ ማታ ቶሎ በመሄድዎ በጣም ቅር አለን፡፡ ስለእርስዎ ብዙ ተጫወትን፡፡ ኮዜት በጣም ትወድዎታለች:
ከዚሁ ጥሩ ክፍል እንደተዘጋጀልዎት ቀደም ብዩ ነግራዎት ነበር፡፡ ከእኛ ጋር መቀመጥ አለብዎት:: ከዚያ ብቻዎን ምን ያደርጋለ? እንዲያውም ከዛሬ ጀምሮ ከዚሁ ነው የሚሆነት:: አባባንም እንደሆነ በመንፈስ ገዝተወታል፡፡ እርሱ የእርስዎ ነገር አይሆንለትም:: በጣም ነው
የሚያከብርዎትና የሚወድዎት፡፡ አብረን የኖርን ተደስተን ነው የምንኖረው።
እርስዎ ደግሞ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው:: አሁን እንሂድ ቁርስ ቀርቦአል» አለ፡፡

«ሰማሀ ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «አንድ የምነግርህ ነገር አለ፡፡ እኔ
እንደሆንኩ አሮጌና ሽማግሌ ወንጀለኛ ነኝ::»

አንዳንድ ጊዜ ጆሮ ለመስማት የማይፈልገውን አይሰማም፡፡ በተለይም ካልተጠበቀ ምንጭ የሚወጣ የማይሆን ወሬ ጆሮ ያልፈዋል፡፡ “ወንጀለኛ ነኝ" የሚለውን ዜና ከ መሴይ ፎሽለማ የሚጠበቅ ስላልሆነ የማሪየስ ጆሮ ሊሰማው አልፈቀደም አንድ ነገር ግን እንደሰማ ስለሚያውቅ ፈዝዞ ቀረ።

ምን ማለትዎ ነው?» ሲል በማጉረምረም ይጠይቃል፡፡
«ይህም ማለት» አለ ዣን ቫልዣ ፣ «ወህኒ ቤት ነበርኩ ማለት ነው፡፡»
ምነው እኔን ለማሞኘት ነው?» ሲል ማሪየስ ቅሬታውን ገለጸ፡፡
«ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ፣ «ከወህኒ ቤት አሥራ ዘጠኝ ዓመት
ኖሬአለሁ:: በሌብነት ወንጀል ተከስሼ ነው የታሰርኩት:: በመጨረሻ ላደረስኩት ጥፋት የእድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶብኝ ነበር፡፡ ሆኖም አምልጬ
በመውጣቴ አሁንም ወንጀለኛ ነኝ::

ማሪየስ አሁን መከራከሩ ዋጋ እንደሌለው ስላመነ ዝም ብሎ ይሰማ ጀመር፡፡ ነገሩ እየገባው ሄደ፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው ራሱም ፈራ፡፡

«ይቀጥሉ፤ ይቀጥሉ፤ ሁሉንም ይንገሩኝ» ሲል ተናገረ፡፡ «እርስዎ
የኮዜት አባት ነዎት!»
ፍርሃቱን ለመግለጽ ሁለት እርምጃ ወደኋላ ተራመደ፡፡
ዣን ቫልዣ በኩራት መንፈስ ጭንቅላቱን ወደ ጣራ አቅንቶ ያለምንም ማፈር ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ምንም እንኳን የምለው ነገር የሚዋጥና የሚጥም ባይሆንም
እንድታምነኝ ያስፈልጋል::)
እዚህ ላይ ዣን ቫልገዥ ጥቂት ቆም ብሎ ንግግሩን በዝግታና ግርማ ሞገስ በተሞላበት አንደበት ቀጠለ፡፡

«ታምነኛለህ ፧ እኔ የኮዜት አባት ነኝ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ግን
አባትዋ አይደለሁም:: ፌቨሮል ከሚባል ሥፍራ ገበሬ ነበርኩ፡፡ ሥራዬ አትክልት መከርከም ነበር:: ስሜ ፎሽለማ ሳይሆን ዣን ቫልዣ ነው:: ከኮዜት ጋር ዝምድና የለንም:: ኣእምርህን ሰብሰብ አድርግ፡፡»
ለማሪየስ እድል ለመስጠት ንግግሩን ካቋረጠ በኋላ እንደገና ጀመረ፡፡
«ታዲያ ለኮዜት ምንዋ ነኝ?አዛኝ! ከአሥር ዓመት በፊት በሕይወት
መኖርዋን እንኳን አላውቅም ነበር፡፡ በእርግጥ እወዳታለሁ፡፡ የሙት ልጅ ስለሆነች አባትና እናት የላትም:: የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ የእኔን እርዳታ በጣም ያስፈልጋት ስለነበር እርስዋን ማፍቀር ጀመርኩ፡፡ ልጆች ደካሞች
👍19
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹አዎ…እናቴ እና ሰላም ያልኩሽ የማፈቅራት ልጅ ትዝ ሲሉኝ››
-‹‹በዛ ሰዓት ላይ ሁለቱም ባይኖሩ ኖሮ…..መቼም እንዳማታገኛቸው እርግጠኛ ሆነህ ቢሆን ኖሮስ….?››ዘግናኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ

‹‹እኔ እንጃ…እንዳልሞት የሚያደርገኝ ምንም ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም››ስል በታማኝነት መለስኩላት፡፡

‹‹ለምን….?››ጠየቀችኝ
‹‹ሁለቱ መላ አለሜ ናቸው…እነዚህ የነገርኩሽ ሁለቱ ሴቶች እና ሌላው ዓለም እኔንም ጨምሮ በሌላ ሚዛን ቢሆን ሚዛን ሚደፉት እነሱ ናቸው…..ስለዚህ እነሱ  የሌሉበት  ዓለም ምን ይረባኛል…››

‹‹አየህ ትክክል ብለሀል..እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ አንተ አንደገለጽከው ነው…እስከአሁን እራሱ ለምን እንደቆየሁ አላውቅም…….?››ብላ የሆነ አዲስ ነገር እንደተገለጽላት ተመራማሪ  ፈገግ ብላ ከተቀመጠችበት  ተነሳች ‹‹ እንሂድ ›› ብላ ጠርሙሷን ይዛ ምንጣፉን ባለበት ጥለ መራመድ ጀመረች…

-‹‹እንዴ ወዴት….? ››

‹‹ወደቤት ….ወደቤት መልሰኝ››

ደነገጥኩ…. ሳላስበው የማይሆን ነገር እንደተናገርኩ ገባኝ…ገደል አፋፍ ላይ ያለን ሰው ከኃላ መግፋት አይነት የቀሺም ሰው ተግባር ነው የሰራሁት..

‹‹ምንጣፉስ..››

ግዴለሽ በሆነ የድምፅ ቃና‹‹ከፈለከው ያዘው›› አለችኝ፡፡ጠቅለል ጠቅለል አደረኩና ወስጄ ኮፈን ውስጥ ከተትኩት፡፡ከዛ ወደመኪናው ገባሁና ወደኃላ አዙሬ የመልስ ጉዞ ….ብራዩ እንደደረስን የሆነ ነገር ማድረግና አሁን ካለችበት ስሜት እንድትዘናጋ ማድረግ እንዳለብኝ   ወሰንኩ…

‹‹..በጣም አመመኝ..››አልኳት …ቀና ብላ አየችኝና ምንም ሳትናገር መልሳ ወደ ሃሳቧ ተመለሰች…..መኪናዋን ወደዳር አውጥቼ አቆምኩ

‹‹ምነው….?››ኮስተር ብላ

‹‹ሆዴን ቆረጠኝ ››

‹‹ማለት….?››

‹‹እኔ እንጃ እራበኝ መሰለኝ..ከነጋ ምንም አልቀመስኩም… ለዛ ይሆናል..ረሀብ ደግሞ አልችልም››

‹‹እና ምን ይሻላል ….?››አለች እንደመበሳጨት ብላ

‹‹በቃ እኔ ሳልበላ መንዳት አልችልም….››

‹‹እሺ ጥሩ  ቁልፉን ስጠኝ…. እኔ ጊዜ ማባከን አልፈልግም …አንተ ብላና በትራንስፖርት ና››የሚል ሀሳብ አቀረበች

‹‹ለምን የሚሆን ጊዜ ነው ማባካን የማትፈልጊው….?››ስል ጠየቅኳት፡፡

‹‹እቤት ተመልሼ በፍጥነት ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ››

‹‹እሺ ነይ…አልኩና ቁልፉን ነቅዬ ከመኪናው ወረድኩ.. እሷም ካለችበተ የኋላ ወንበር ወርዳ ወደጋቢናው ስታመራ ፈጠን ብዬ ሁሉንም በር ጠረቀምኩትና ቁልፍን እያንቀጫጨልኩ   በአካባቢው ወደአለ ሆቴል ጉዞ ጀመርኩ

‹‹ምን እያደረክ ነው….?››

‹‹ምሳ በልቼ እቤትሽ አደርስሻለሁ..አንቺ ስለጠጣሽ መንዳት አትችይም…››

‹‹ምኑ ነህ..….?አሁን ለአንድ ቀን ባትበላ አትሞት…ደግሞ ብትሞትስ ከመኖር ምን ሲገኝ…››

‹‹ግድ የለም.. ልብላና አብሬሽ እሞታለሁ››

‹‹መቀለድህ  ነው..….?››ተከተለችኝና ከፊት ለፊቴ ወንበር ስባ ተቀመጠች…ምግብ አዘዝኩ እስኪመጣ ወሬ ጀመርን 
‹‹በነገራችን ላይ አባትሽን በቅርብ አይቼው አላውቅም..?››

‹‹የለም››

‹‹የት ሄዱ….?››

‹‹ወደ ውጭ ሄዷል››

‹‹አሀ …ለዛ ነዋ እንዲህ ዓለም ድብልቅልቅ ያለችብሽ….?››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ….?››

‹‹በአባትሽ እና በአንቺ መካከል ያለውን ግንኙነት እና ቀረቤታ እኮ ሙሉ ሰፈሩ ነው የሚያውቀው.. እንኳን እኔ ቀርቶ የዛሬ አመት እዛ ሰፍር የገባ ሰው ሳይቀር ያውቃል…››

‹‹አንዴ አንተም እኛ ሰፈር በቅርብ የገባህ መስሎኝ….  ባልሳሳት ሁለት  አመት ..ከዛ ይበልጥሀል..?››

‹‹የእውነትሽን ነው..አታውቂኝም….?›› በእድሜዬ  ከደነገጥኩት በበለጠ መጠን ደንግጬና ተሸማቅቄ ጠየኳት

‹‹ማለት አንተ ታውቀኛለህ እንዴ….?››

……የምመልሰው ነገር ሲጠፋኝ  ሳቅኩ

‹‹የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ እንዴ…››

‹‹አይ ታውቀኛለህ ስትይ ገርሞኝ ነው….ራስህን ታውቃለህ ወይ ብለሽ ብትጠይቂኝ ይሻላል..ግንባርሽ ላይ ያለውን ስንጥቅ ጠባሳ ምን እንደሆነ ልንገርሽ…….?››

‹‹እንዴት ልትነግረኝ ትችላለህ..….?

እሱ እኮ እፃን ሆኜ የሆነ ነገር ነው››

‹‹አዎ ቄስ ትምህርት ቤት አባ ገብረክርስቶስ ጋር ስንማር ድብብቆሽ በምንጫወትበት ጊዜ ልትደበቂ ስትሮጪ  አደናቅፎች ወድቀሽ ብረት ግንባርሽን ሰንጥቆሽ አይደል…?››

አይኖቾ ፈጠጡ ‹‹እንዴ !!!አዎ ትክክል ነህ ..ማነህ አንተ….?..››

‹‹ኤርሚያስ››

‹‹ኤርሚያስ ..ኤርሚያስ እንዴ ኤርሚያስ ካሳ እንዳትሆን……….?››የሆነ የቆየ ህልም የማስታወስ ያህል ተደንቃ

‹‹አዎ ነኝ››

‹‹ታዲያ በጣም እኮ ነው የተቀያየርከው…አረጀህ… በጣም…ደግሞ ከሀገር  ወጥተህ አልነበር…..….?››

‹‹ኦዋ ሁለት  ዓመት አለፈኝ  ተመልሼ   ከመጣሁ..››

‹‹እና ይሄን ሁሉ ጊዜ   ሳታናግረኝ…….?››

‹‹እኔ እንጃ እንደመጣው ጥሩ ስሜት ላይ ስላልነበርኩ ላናግርሽ ጉልበቱ አልነበረኝም….››

‹‹ትክክል አልሰራህም…ጓደኛች ነበርን አይደል….….?.››መገረሟ ሳይገታ የታዘዘው ምግብ መጣ..እሷ ለምግቡ  ደንታም ሳይሰጣት ብላክ ሌብል ታመጣልኝ አለችው አስተናጋጁን….

‹‹አይቻልም..››አልኳት ቆፈጠን ብዬ
‹‹ለምን…….?ዝም በለውና አምጣልኝ ››አምጣላት …ግን ከበላሽ ነው የምትጠጪው..

‹‹አረ ባክህ ››

‹‹እውነቴን ነው››

‹‹እሺ ..››አለች.. እየቆነጠረች ከምግቡ ለመቅመስ ሞከረች እኔ እየለመንኩም እያስገደድኩም አንድ ሶስት ደህና ጉርሻ አጎረስኳት…
ከዛ መጠጧን ጀመረች ‹‹….ይገርማል  ..ዱርዬ ነበርክ እኮ …አሁን የተለየ እና የተረጋጋ ሰው ሆነሀል››

‹‹ምን ታደርጊዋለሽ ህይወት ትገራሻለች… ኑሮ ይሞርድሻል…መከራ ያስተካክልሻል ወይም ያበላሽሻል፡፡››

‹‹ለምን አንተም አትጠጣም….?››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን መኪናውን ማን ይነዳል…….?››

‹‹ግድ የለም ..የሆነ መላ እንፈልጋለን..….?››ልክ ቅድም ላንቺ ታዝዤ አብሬሽ መጠጣት እንደጀመርኩ ..ለእሷም ተስማምቼ አዘዝኩ …የልጅነት ነገር ምንም ሳይነሳ የቀረ ትውስታ የለም..ከማስበው በላይ ስለልጅነታችን ታስታውሳለች…ያ ደግሞ ደስታ ፈጠረብኝ….እሷም ከነበረችበት ስሜት በሆነ ጠብታ ቢሆንም የመረጋጋት ሁኔታ  ታየባት
ተመልሰን ቅድም ለቀነው ወደወጣነው ቤት የሄድን
 
‹‹እየተቆነጠረ የሚመጣው ውስኪ ሊያረካን ስላልቻለ..ሙሉውን አዘዝን…››

ኬድሮን ቆይ ቆይ ..››ብላ አስቋመችው 

‹‹ምነው ደከመሽ..እንተኛ?››

‹‹አይ አንዴ ሽንቴን….›› አለችና ከመኝታዋ ወርዳ ወደሽንት ቤት ሳይሆን ወደሳሎን ሄደች….ይህቺ ታሪኳ ለሊቱን ሙሉ የተነገረላት  ፍቅረኛው የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እየተሰማት ነው ..አዎ ስሜቷ እየነገራት ነው….ለዚህ ነው ወደሳሎን የሄደችው …ንስሯን ፈልጋ..‹‹አይ የኔ ነገር ..››አለች . የዚህ ባለ ላዳ ታሪክ ንስሯንም እንድትዘናጋ ስላደረጋት እራሷን ታዘበች…ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት እንዳለ ተኝቷል….አስነሳችው….‹‹ ‹‹አብሮኝ ያለው ልጅ ፍቅረኛ..ማለቴ የሚወዳት ልጅ ችግር ላይ ትመስለኛለች..አሁኑኑ ሄደህ ያለችበትን ሁኔታ አጣራልኝና  ና…አሁኑኑ……ትንሽ ከዘገየን የሚረፍድብን ይመስለኛ…››
👍839😁4👎2