አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


....“አንተ?...” አለች፡፡

ኒኪ አይኗን አጥብባ የምትጠላውን መርማሪ ፖሊስ ፊትን መመልከት
ጀመረች፡፡ ይህ መርማሪ ፖሊስ ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ህይወቷን የማይቻል እና አስቸጋሪ አድርጎባታል። “እዚህ ደግሞ ምን ትሰራለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡

“አንቺ እስክትነቂ ድረስ እየጠበቅኩሽ ነበር” አላት እና አሁንም ፊቱ በደስታg እንዳበራ አፍጥጣ በቁጣ የምታየውን ነገሩን ችላ ብሎ “እግርሽ በቅርቡ ሰላም እንደሚሆን ሰማሁ:: በእውነት ደስ የሚል ነገር ነው ዶክ፡፡ ደግሞም ሁሌም የሚያምሩ እግሮችሽን ይዘሽ ትቆያለሽ” አላት፡፡

ኒኪም በቁጣ አይን እያየችው “ይሄ ሰው ከዘረኝነቱ እና ከተሳዳቢነቱ በተጨማሪ ለሴት የሚባሉና የማይባሉ ነገሮችን ያውቃል ብላ አሰበች።

“አንቺ ሁሌም ደስ የምትይ ቆንጆ ሴት ነሽ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ አንድ አንዴ እንኳን ትንሽ ፈገግ በይበት እስቲ” አላት እና ጆንሰን በመቀጠልም “ማለቴ ድሌን በደንብ እንዳጣጥመው ብታደርጊኝ ደስ ይለኛል፡፡ መቼስ ህይወትሽን ያተረፍኩልሽ እኔ አይደለሁ?”

“ምን ማለትህ ነው ባክህ?” ብላ ኒኪ ከተኛችበት ቀና ብላ በጀርባዋ ትራሷን ተደገፈች። ስለተንቀሳቀሰችም ነው መሰል
የእግሯ ህመም ስለተሰማት ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ እያየችው ቆየች፡፡ ደመነፍሷ እሱን ከክፍሏ ውስጥ ምን እንደተከሰተ እንድትጠይቅ አደረጋት፡፡
“አንተ እንዴት ነው የተከሰተው?” ብላ ጠየቀችው፡፡

ጆንሰንም ልክ እንደ እሷ ቀና ብሎ አያት እና “እውነትሽን ነው ምንም ነገር አታስታውሺም?” ብሎ መለሰላት፡፡

ኒኪም “በእርግጥ አንዳንድ ነገሮችን አስታውሳለሁ” ብላ ግራ እየተጋባች
ኮስተር አለች እና “እዚያ ቦታ የሄድኩት አኔ በርሃው ላይ እያለሁ ደውላ በጣም እንደተጨነቀች እና ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ከነገረችኝ በኋላ ነው።
ቦታው ላይ ስደርስም ዊሊ ባደን ልክ እንደ ቄራ ሥጋ ተሰቅሎ ነው ያገኘሁት።” ብላ ሁኔታውን ስላስታወሰች ፊቷ ኩምትር አለባት።

“እሺ ሌላስ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቃት፡፡
ሁለት ሰዎች መጡና አኔን ወሰዷት። ባሏ ሉዊስ ሮድሪጌዝ እዚያው ነበር። ደብድቧት በግድ ለእኔ እንድትደውልልኝ ያስደረገውም እሱ ነው።”

“አንቺን ብሆን ለእሷ አንድም እምባ አላባክንም ነበር፡፡” አላት እና ጆንሰን
“ብትመታም ባትመታም አንቺ እዛ ስትመጪ ባሏ ምን ሊያደርግሽ
እንደሚችል ታውቅ ነበር እና ልትደውልልሽ ባልተገባ ነበር።”

“ሉዊስ ሁለት ጊዜ በጥይት ሊገድለኝ ነበር” ብላ ኒኪ በስጨት አለች እና
ከዚህም በተጨማሪ ሁሉንም ያደረጋቸውን እና ያስደረጋቸውን ነገሮች
ካርተር በርክሌይን ነገረኝ፡፡ ማለትም ቻርሎቴ እንዲመለከት እንዳደረገ፡፡ ዊሊ ባደን ስላጭበረበረው እንደገደለው እና አኔም እሱን ሲገድል ቪዲዩ እንድትቀርፅ ማድረጉን፣ ብራንዶንን ቅጥር ነፍሰ ገዳይ
አድርጎ ሊያስገድለኝ እንደነበረ እና በስህተት ሊዛ ፍላንገንን እንደገደላት፣
ትሬይ ስለ እኔ መረጃ አልሰጥም ያለ መስሉት እንደገደለው ከነገረኝ በኋላ
ሊገድለኝ ሲል የመጋዘኑ መብራት ጠፋ፡፡ ለዚያም መሰለኝ እግሬን በጥይት የመታኝ። ጭለማው ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ቆለጡን መትቼው እንዳመለጥኩኝ ጭምር አስታውሳለሁ።”

ጆንሰን ራሱን በአዎንታ እየነቀነቀ ትክክል መሆኗን ገለፀላት፡፡ ይሄኔም ፊዮና በመሀል ገብታ “ዶክተር ሮበርትስ ራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ሰውነትሽ ብዙ ደም ስለፈሰሰው እና በተደረገልሽ ቀዶ ጥገና ሁሉ ስላደከመሽ ብዙ...” ብላ ሳትጨርሰው

ኒኪ በእጇ ደህና ነኝ የሚል ምልክት አሳየቻት እና ለጆንሰን ማውራቷን
ቀጠለች።

“እናም መብራቱ በድጋሚ ሲበራ... የእሳት አደጋ መውጫ ደረጃ ላይ
ነበርኩኝ” ብላ ጆንሰንን ስታየው
“ልክ ነሽ” ብሎ አረጋገጠላት።
“ሮድሪጌዝ ሊጨርስኝ ሲል ነው ጉድማን የተከሰተው:: እሱ ነው ህይወቴን ያዳነው” ብላ ጆንሰንን ተመለከተችው እና “ሮድሪጌዝን በጥይት አናቱን አፈንድቶ ገደለው” ብላ ነገረችው፡፡

ጆንስንም “መልካም ከዚያ በኋላስ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ኒኪም ፊቷ ገረጣና መንቀጥቀጥ ጀመረች። አዎን የጉድማን ፊት እሷ ላይ የማላገጡን ሁኔታ
እና አረመኔ አይኑን አስታወሰችና “ከዚያ በኋላ.. ምንም ነገር አላስታውስም።” አለችው፡፡ “እኔ ግን የምታስታውሺ ይመስለኛል።” ብሎ ጆንሰን በመቀጠልም
“ጉድማን ሊገድልሽ ነበር” አላት፡፡

“አልነበረም” አለች ኒኪ ጭንቅላቷን ግራ እና ቀኝ እየወዘወዘች፡፡ “እንደርሱ ሊያደርግ አልነበረም፡፡ ደግሞም አያደርግም፤ እንዴ እኔ እና እሱ
እኮ ጓደኛሞች ነበርን።”

“ማለት ልክ ከብራንዶን ግሮልሽ ጋር ጓደኛ እንደሆናችሁ ሁሉ ማለትሽ ነው?” ብሎ የንዴት ሳቅ ሳቀባትና “ሉው ጉድማን ውሸታም እና አጭበርባሪ ነበር። እኔ በመሀል ገብቼ ባልገላግለው ኖሮ ጭንቅላትሽን ልክ እንደ ሮድሪጌዝ ጭንቅላት ይበትንልሽ ነበር።”

“በፍፁም!” ብላ ተወራጨችና “ይሄ በፍፁም እውነት ሊሆን አይችልም!”
አለችው::

“እውነት ነው እንጂ” አላት እና ጆንሰን ብስጭት ብሎ

“ጉድማን ሮድሪጌዝ እየከፈለው ለሁለት ዓመታት ያህል ወይንም ከዚያ በላይ ተቀጥሮ ሲሰራለት ነበር። ደሀ ሆኖ እንዳደገ ነግሮሻል አይደል? ሁሉን
ነገር ማጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቀው ገና በልጅነቱ ነበር። በቃ
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የህይወቴ ዋስትና ሊሆን የሚገባው ነገር ቢኖር ገንዘብነው ብሎ ማስብ ጀመረ፡፡ ሮድሪጌዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥቂት ሚሊዮን ዶላሮችን ሲሰጠውም በሁለቱ ስግብግብ እጆቹ ተቀበለው፡፡

በዚህም ዴሪክ ዊሊያምስን እና አንቺን ጭምር እስከመግደል ደረጃ ደረሰ”

“እየዋሸሽኝ ነው!” አለችው ኒኪ፡፡

ይሄኔም ነርሷ ማክማኑስ ጣልቃ ገብታ “እባክህን ውጣልን!” ብላ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን ላይ እያፈጠጠችበት፡፡ “እዚህ ክፍል ከመግባትህ በፊት ተነጋግረን ነበር አይደል? ሰውነቷ ስለተጎዳ ማረፍ አለባት። እሷን እንደዚህ እንደምታበሳጫት አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ እንድታገኝህ አላደርግም ነበር።” አለችው፡፡

ጆንሰንም በጣም ተናድዶ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ፍንጥር ብሎ ከተነሳ በኋላ “እኔ ደግሞ እሷ ሁሉን ነገር ካወቀች በኋላ እንኳን እንደዚህ የማታምን ደረቅ መሆኗን ባውቅ ኖሮ የሥራ ባልደረባዬ እና አጋሬ ጉድማን እንዲገድላት ብተወው ጥሩ ነበር!” አላት፡፡

ነርሷ ልታወራ ስትል ጆንሰን በንዴት አቋረጣት እና

“ለማንኛውም የነገርኩሽን ነገሮች የማታምኚኝ ከሆነ ቴሌቪዥኑን ከፍተሽ
ዜናዎችን ማየት ትችያለሽ፡፡ መልካም ዕድል ዶክተር ሮበርትስ” ብሏት በንዴት እየተመናጨቀ ኒኪ ከተኛችበት ክፍል ወጣ፡፡

“በጣም ይቅርታ” እያለች ፊዮና በጣም ተጨንቃ ዶክተር ሮበርትስን ይቅርታ ጠየቀቻት:: ምክንያቱም ዶክተር ራይሌ እሷ ፈቅዳ ፖሊሱ ወደ እዚህ ክፍል ገብቶ ኒኪን ማበሳጨቱን ቢያውቅ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትገምታለች፡፡ “ ውጪ እኮ ሳወራው በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡ በእውነት እንደዚህ የሚያበሳጭሽ ሰው መሆኑን ባውቅ ኖሮ አላስገባውም ነበር”
አለቻት፡፡

ኒኪም “ምንም አይደል” አለቻት እና ጆንስን የነገራትን እያንዳንዱን ነገር
በአዕምሮዋ ማብሰልሰል ጀመረች፡፡ በእርግጥም ደግሞ ጉድማን ሊገድላት
እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ የሆነ ሰው ምናልባትም ጆንሰን ነው ህይወቷን
ሊያድንላት የሚችለው፡፡ አሁን ሉዊስ ሮድሪጌዝም ሆነ ጉድማን በህይወት
የሉም። ስለሆነም ሌሎች የምታውቃቸው ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ህይወታቸውን ሊያጡ ችለዋል ማለት ነው፡፡ ከዶውግ ሌንካ ሊዛ ትሬይ እና ዊሊያምስ ላይ ሁለቱ ሰዎች ጉድማን እና ሮድሪጌዝ
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ጉለሌ አካባቢ ታደሰ የተከራያት ሁለት ክፍል ቤት ለብዙ ጊዜ ተዘግታ የከረመች ሸረሪት ያደራባትና ግድግዳዋ የተላላጠ ነበር፡፡ አሁን ግን ቀለም ተቀብታ ሲረግጡት ቡን... ይል የነበረ ጣውላዋ በሰም ታሽቶ አብረቅርቃለች፡፡ ጠረጴዛና ወንበሮች ተኮልኩለዋል፡፡ ጠጅና ጠላ በጠርሙስ ተሞልቶ ከላይ በነጭ ወረቀት በቄንጥ ተሸፍኖ በየጠረጴዛው ላይ ተደርድራል። ሸክላ ሳህኖች በየጠርሙሶቹ መሀል መደዳውን ተቀምጠዋል፡፡
የሸረሪቶችና የአይጦች መፈንጫ ሆና የከረመችው ጎጆ ሰርገኞች የሚታደሙባት፣ ዋንጫዎቻቸውን እያጋጩ የሚጨፍሩባት፣ ሙሽሮች ደግሞ የፍቅር አክርማቸውን የሚቀጩባት ጫጉላ ቤት ለመሆን ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ ልዩ ሆና ደምቃለች፡፡ አዎን ታደሰ ሰላማዊትን የሚያገባበት ቀን፡፡ ዕለተ እሁድ.…የዛሬዎቹ ሙሽሮች በማዘጋጃ ቤት በሽማግሌ
ዎች ፊት በወረቀት ፊርማ ሳይሆን ተፈቃቅደውና ተማምነው ሊቆራኙ
የተዘጋጁበት ቀን ነው፡፡

ዛሬ ሰላማዊት ከእሥር ቤት ወጥታ ወደ ነፃ ህይወት ለመቀላቀል ከዚያ ስቃይ ከበዛበት የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ተላቃ ከምትወደው ሰው ጋር አብራ ለመኖር እምነትን ብቻ ውል አድርጋ ፍቅርን ብቻ ሰማንያ አድርጋ አዲስ ህይወት ለመጀመር የተዘጋጀችበት ቀን ነው።

እማማ ወደሬ ዕድለኛ ሆኑ። የወይዘሮ ስመኝን እጅ መድኃኒት አድርጎላቸው ከሞት ተረፉና በልባቸው ስቀው፣ አጨብጭበው መርቀው ያስተሳሰሯቸው ልጆቻቸውን ለመዳር በቁ፡፡ እንደተመኙት በጥርሶቻቸው
እየሳቁ በእጆቻቸው እያጨበጨቡና ልባቸው በደስታ እየጨፈረች በአዲስ ነጭ የአገር ባህል ልብስ አጊጠው በእናትነት ወግ ሙሽሪትን ለሙሽራው ለማስረከብ ጉድ ጉድ ለማለት ታደሉ፡፡ ሰላማዊት አምራለች። ተውባለች፡፡ የውቦች ውብ! የቆንጆዎች ቆንጆ! ሆናለች። ባማረ አለባበስ አጊጣ ፀጉሯን በወጉ ተሰርታ ዐይኖቿ ኩል ተኩለው እንደ ጽጌረዳ አበባ ፈክታላች። ሸርሙጣ ከሚል ወራዳ ስም ተላቃ ሙሽሪት የመባል ወግ ማዕግረ ደርሷታል፡፡ የተለያዩ ወንዶችን በወሲብ እያስተናገደች መኖር ከጀመረች ወዲህ ወደር የሌለው ደስታ ያገኘችበትና እንደ አዲስ የተወለደችበት ቀን
ሆኖ የተሰማት ገና ዛሬ ነው። ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ ከምትወደው ሰው ጋር እስከመጨረሻው በፍቅርና በደስታ ልትኖር የእገሌ ሚስት ባለ ትዳር ተብላ ልትጠራ ነው፡፡
"ሰላም እንግዲህ ጣጣችሁን ቶሎ ቶሎ በሉና ጨርሱ። የመምጫ ሰዓታቸው እየደረሰ ነው” አሉ ወይዘሮ ወደሬ ተፍ ተፍ እያሉና የምትኳኳላውን ልጅ በፍቅር እየተመለከቱ።

ዛሬ ሰላማዊትን በማስዋብና አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ በኩል ሙሉ ሃላፊነቱን የወሰደችው ጽጌ ነች።ያቺ
ገበያዋን የዘጋችባት ልጅ
ያቺ ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ምላስ አሳልፋ የሰጠቻት ልጅ ሰፈሩን እስከመጨረሻው ጥላላት ልትሄድላት ነውና ከዚያ በፊት የነበረውን ቂም ከዚያ በፊት የነበረውን የጥላቻ ስሜት ፍፁም እርግፍ አድርጋ ረስታ እንደ ታላቅ እህት እየተንከባከበች የውበቷን እንከን እየነቀሰች አሳምራ
እያዘጋጀቻት ነው።

“እሺ እማማ ጨርሰናል እኮ!" አለች ጽጌ እየተጣደፈች፡፡ ወይዘሮ ወደሬ የዛሬ ሁኔታቸው መቼም ለጉድ ነው። ወልደው አሳድገው ለትዳር እንዳበቋት ልጃገረድ ሰላማዊትን አሥር ጊዜ እየተመለከቱ ውበቷን እያደነቁ
ሁለመናቸው በደስታ ስቋል። የፊታቸው ፈገግታ ከእርጅናቸው ውስጥ ደብዝዞ ብቅ ባለው የልጅነት ውበታቸው ምክንያት ለወትሮው መወላገዱ ከሩቁ ይታይ የነበረው ጥርሳቸውን ሁሉ አሳምሮታል። ሰላማዊት
ጣጣዋን ጨራረሰች።ዝግጁ ሙሽሪት! ሽቅርቅር፣ ዝንጥ አለች። የዛሬው የሰላማዊት ሙሽርነት በሚስጥር ቢያዝም አልፎ አልፎ ማፈትለኩ አልቀረም ነበር፡፡ ጽጌ ለጓደኞቿ ሹክ... ብላቸው ውስጥ ውስጡን ወሬው ተዳርሶ ለአንዳንዶቹ የቡና ማጣጫ ሆኖላቸዋል።

በሰላማዊት ጉዳይ የተነጋገሩባት ሴተኛ አዳሪዎቹ ብቻ አልነበሩም፡፡
ከእማማ ወደሬ መሸታ ቤት ፊት ለፊት ባለው ትልቅ የመኖሪያ ግቢ
ውስጥ የሚኖሩት የነጋዴው የአቶ ዘላለም ልጅ ተማሪዋ ምንተስኖትም የዚሁ የሃሜት ሱሰኞች በሽታ ለክፏት የውጪውን በር ከፍታ ጓደኛዋ ሊባኖን ስታስገባት ሰላማዊትን እያማችላት ነበር፡፡
“ኡ. ኡ. ቴ! የሸርሙጣ ሙሽራ አይተንም ሰምተንም አናውቅ!” ከንፈሯን ወደ ጎን እየሽረመመች፡፡
“በቀደም የነገርሽኝን ነው አይደል? እውነት ልታገባ ነው እንዴ?” አለች
ሊባኖስ ወደ ግቢው እየዘለቀች።

"ከየት የመጣ ፋራ ነው በናትሽ ? የጠላ ቤት ሸርሙጣ ሚስቱ ለማድረግ አበሳውን የሚያይ አይገርምም? አ.ሃ..ሃ..ሃ.ሃ." እንጥሏ እስከሚታይ ድረስ አፏን ከፍታ ሳቀች።
"ፍቅር ከያዘው ምን ታደርጊዋለሽ? እንኳን ሴተኛ አዳሪ ሰው ከወደደ
ቆማጣና እውር ማግባቱ ይቀራል ?” አለች ሊባኖስ፡
“ከሽርሙጣ ቆማጣ ይሻላል።ለጊዜው መደበሪያ ልታደርገው ካልሆነ በስተቀር አብራው ትኖራለች የሚል እምነትም የለኝም" “እንደሱ ብለሽ ባትደምድሚ ይሻላል። አብዛኛዎቹ ሴተኛ አዳሪዎች የችግር ማእበል ገፍትሮ ዳር ላይ ሲጥላቸውና ዙሪያው ገደል ሲሆንባቸው እንጂ ፈልገው የገቡበት አይደለም፡፡
አጋጣሚውን ካገኙ ቤተሰብ
መስርተው በታማኝነት ለመኖር ምንም የሚያግዳቸው ነገር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ቅድስት እንደነገረችኝ ከሆነ ደግሞ ሰላማዊት በጣም የምታሳዝን ልጅ ናት። ወላጆቿ የሞቱባት፣ምን የመሰለ ወንድሟን ማጅራት
መቺዎች ደብድበው ያለረዳት ያስቀሯትና ትምህርቷን አቋርጣ በዚህ ህይወት ውስጥ ለመግባት የተገደደች አሳዛኝ ልጅ መሆኗን አጫውታኛለች። እንደኔ እሷን ያገኘ ባል የታደለ ነው" ስትል ሊባኖስ ምንተስኖትን ተቃወመቻት።

"ምነው ጠበቃ ሆንሽላት በናትሽ ? እኔ በበኩሌ በየቀኑ አዳዲስ ባሎችን እያገባችና ገላዋን እየቸረቸረች የኖረች ሴት ስፊ ልማዷን እርግፍ አድርጋ
በጠባብ ጐጆ ውስጥ ዲቃላዋን እያጫወተች መኖርን በቀላሉ ትለምደዋ ለች ብዬ አላስብም”

“ምን እያልሽ ነው ምንተስኖት? በአልኮል የተሟሽ የሰካራም አፍ ጠረን እንደ ሰንደል እየታጠኑ የአባለዘር በሽታን በጅምላና በችርቻሮ ከሚያከፋፍሉ ዝሙተኞች ጋር ለግብረ ሥጋ መውደቅና መነሳት ኑሮ መሆኑ
ነው እንዴ? ሰፊ ልማድ የምትይውስ ከፍላጐት ውጪ ስሜት አልባ ገላን እየቸረቸሩ ሳንቲም በመለቃቀም የሚገኝ ነው እንዴ? በየቀኑ መኳኳሉና
አዳዲስ ልብስ መቀያየሩ ትርጉም ያለው መሰለሽ? ውጫዊ መብለጭለጭ እኮ ውስጣዊ መብለጭለጭን አያመጣም፡፡ ቢከፍቱት ተልባ ነው፡፡ የምትወጂውና የሚወድሽ የትዳር ጓደኛ ስታገኚ፣ተስመው የማይጠገቡ ህፃናት እናት ሆነሽ መኖር ስትጀምሪ ብቻ ነው ኑሮ ኑሮ የሚሆነው። ትዳሬን ሚስቴን ልጆቼን የሚል አሳቢ ባል ካገኘሽ ደግሞ ከዚያ በላይ ደስታ ከዚያ
በላይ እርካታ ይኖራል ብዬ አላስብም”

“አንቺ እንደምትይው አይነት ባል እንደዚህ በቀላሉ የሚገኝ ቢሆን እሰየው ነበር፡፡ ትዳሬን፣ ልጆቼን የሚልና ከራሱ በፊት ለትዳሩና ለልጆቹ የሚያስብ ወንድ ደግሞ ሚስት ለማግባት የጠላ ቤት ሽርሙጣን የመጀመሪያ
ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም” አለች ምንተስኖት ባለመሸነፍ ስሜት ።
👍21
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አስቻለውም እያለቀሰ በሀሳብ ደግሞ ወደ ዲላ ነጎደ፡፡ የሔዋንን አኳኋን
በእዝነ-ልቦናው ይመለከትው ጀመር፡፡ ከዓይኗ የሚፈሰው እንባዋ በስሜት ቆጠቆጠው:: የታሰረችበት እግር ብረት የእሱን እጅና እግር ሲከረክረው
ተሰማው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳች እንግዳ ስሜት ተፈጠረበትና ተነስ! ሂድ! ብረር ወደ ሲዳሞ!! » አለው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታፈሡ እንግዳሰው ከተፈጠረች ጀምሮ እንደ ሰሞኑ በሀሳብና በጭንቀት መንፈሷ ተናውጦ አያውቅም፡፡ ችግሩ የጀመራት የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ
ስለ አስቻለው አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር ከገለፀላቸው ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ አስመራ ከሄደ በኋላ ደግሞ ብሶባት ሰንብታለች፡፡ስጋቷም
በልሁ አስቻለውን ያገኘው ይሆን ወይስ ያጣው ይሆን? ቢያገኘው
እሺ ብሎ ይመጣላት ይሆን? ቢመጣስ የሔዋን ስሜታዊ ምላሽ ምን ሊሆን ይችል ይሆን? ከሚል ስጋትና ፍርሀት የሚመነጭ ነው፡፡
በእነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች በቂ ምላሽ ሳታገኝላቸው ውስጥ ውስጡን ሲበሏት፤ ሲያስጨንቋትና ሲያሳስቧት ድፍን አሥራ ሰባት ቀናት አልፉ፡፡ ዛሬ ግን ከሁሉም ነገር መቋጫ ቀን ላይ ደርሳለች፡ በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ
አስመራ ከሄደበት ቀን ጀምሮ ሲቆጠር አሥራ ስምንተኛ ቀን በእለተ ቅዳሜ፡፡
በተለይ ሔዋን በማታውቀው ሁኔታ ታፈሡ እንግዶች አሉብኝ
በማለት ማለዳ ተነስታ የድግስ ስራ ጀምራለች፡፡ ስጋና የመጠጥ ዓይነቶችን ጨምሮ በርካታ የምግብ ሸቀጦችን ገዝታ ሔዋንና ትርፌን በስራ ወጥራቸዋለች፡፡ ከአንድም ሁለትና ሦስት ምድጃዎችን በመጠቀም ይከትፋሉ፣ ያቁላላሉ፣ ይቀቅላሉ፡፡
የታፈሡ እጆች በስራ ይጠመዱ አንጂ ቀልቧ በቤት ውስጥ ወይም
በስራው ላይ አልነበረም፡፡ ሀሳቧ ሁሉ ይበታተናል፡፡ ከሔዋንና ከትርፈ ጋር የምትለዋወጠውን ጭውውት ከልቧ አታዳምጠውም፡፡ ብትስቅ እንኳ ሳቋ ለዛ የለውም፡፡ ለጭውውቱ የምትሰጠው ምላሽ ከርእሰ ጉዳዩ ጋር ብዙም አይጣጣምም፡፡ አልፎ አልፎ ከሀሳቧ ብንን ስትል ብቻ •ጭውውቱን እንደ አዲስ
ትጀምረዋለች፡፡
በግምት ከቀኑ አምስት ሠዓት አካባቢ ሳይሆን አይቀርም ታፈሡ ሌላ አስፈሪና አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረባት፡፡ ነገሩ የመነጨው ከወደ ሔዋን አካባቢ ነው፡፡
ሔዋን በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ አስመራ ስለመሄዱ አታውቅም፡፡ምናልባት አስቻለው ወደ ዲላ ባለመመለስ አቋሙ የፀና እንደሆነ፡ ወይም ጭራሽ ያልተገኘ እንደሆነ ደስታ በሽታ ሆኖ እንዳያሳቅቃት ሁኔታው ለእሷ
ድብቅ ነበር፡፡ በልሁ ቤተሰብ ሊጠይቅ ወደ ደብረ ብርሃን እንደ ሄደ ነው የተነገራት፡፡ እናም የበልሁን መምጣት የምትጠብቀው ከደብረ ብርሃን
እንደሚሆን አድርጋ ነው፡፡ ታፈሡን አናግራ ያስደነገጠቻትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው፡፡
ታፈሠዬ!ስትል ጠራቻት ሔዋን ትርክክ ባለ የከሰል ፍም ላይ
የተጣደ ድስት በረጅም ማማሳያ እያማሰለች፡፡
«ወዬ የኔ ወርቅ አለቻት ታፈሡ ወደ ሔዋን ዞር በማለት በዚያች
ሰዓት የሶፋ ጌጦች እያስተካከለች ነበር፡፡
«ዛሬ ሕልም አየሁ»
«ምን ዓይነት ሕልም ሔዩ?»
«በልሁ ከደብረ ብርሃን የመጣ ይመስለኛል፡፡ መንገድ ላይ ከረሜላ ገዝቶ ሲያላምጥ ቆይቶ ኖሮ ልክ እዚህ ሲደርስ የከረሜላዋን እላቂ ከአፉ
አውጥቶ ይሰጠኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እጄ ላይ ሊያስቀምጣት ሲል ድንገት አምልጣኝ መሬት ላይ ትወድቅበታለች ብፈልጋትም አጣታለሁ፡፡ ወዲያው ደግሞ እኔም ያለሁበት ቦታ ይጠፋኛል፡፡» አለችና «ፍችው ምን ይሆን
ታፈሡዬ”? ስትል ጠየቀቻት፡፡
ኣ? አለች ታፈሡ ድንገት ሳታስበው፡፡ በሁለት እጆቿ ሽንጥና
ሽንጧን በመያዝ ቆማ ሔዋንን አተኩራ ታያት ጀመር፡፡
«መጥፎ ህልም ነው እንዴ ታፈሠዬ»
ለነገሩ የህልም ጥሩና መጥፎ የለውም፡ ህልም እንደ ፈቺው ነው ይባል የለ አለችና አሁንም ስሜቷን እፍን እድርጋ ወደ ሶፋ ማስጌጥ ስራዋ ተመለሰች፡፡
ግን ደግሞ ሃሳባ ሁለ ጥቅልል ብሎ ወደ ትናንት ምሽት ሁኔታዋ ነጎደ፡፡

የታፈሡ እንግዳሰው የትናንት ምሽት ሁኔታ የተለየ ነበር፡፡ ሰበቡ
በልሁ አስቻለውን ይዞ ዲላ ከተማ መግባቱ ነው:: በልሁ እስቻለውን ይዞ ከቀኑ ስምንት ሠዓት አካባቢ ዲላ እንደገባ በቀጥታ ወደ ታፈሡ ቤት ይዞት መሂድ አልፈለገም:: አማሆ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ አሳረፈው፡፡ ለዚህ
ምክንያቱ አስቻለው አሁን በሚገኝበት ሁኔታ ላይ ሔዋን ብታየው ሊደርስባት
የሚችለውን የመንፈስ ስብራት በምን መልኩ መቀነስ እንደሚቻል ከታፈሡም ሆነ ከሌሎች ጋር መመካከር የሚያስችል ጊዜ ለመግዛት ነበር፡፡
በዚሁ መሠረት በዕለቱ ከአመሻሸ አስር ሰዓት አካባቢ ታፈሡ ወደ
ሆቴሉ ጎራ እንድትል በሚስጥር ላካባት፡፡ እሷም ጥሪውን ስትሰማ ከመደንገጧ የተነሳ ምን እንዳደረገች ሳይታወቃት የቤት ልብሷን እንደለበሰች፣ ነጠላ
ጫማዋን እንዳደረገች ብፌ ላይ ጣል አድርጋት የነበረች የአንገት ልብሷን ብድግ አድርጋ ነበር ወደ ሆቴሉ የበረረችው፡፡ 'ሰዎች ተጣልተው ድረሽልኝ ብለውኝ ነው' ብላ ባትናገር ኖሮ ያበደች መስሏቸው ሔዋንና ትርፌም
በተከተሏት ነበር፡፡ ብቻ ወደተነገራት ሆቴል ሮጣ ስትደርስ ወደ አልቤርጎው ማለፊያ አቅጣጫ እንኳ ጠፍቷት ነበር፡፡ በአመላካች እርዳታ እንደ ምንም
ገባች:: ፊትለፊት ወደ አልጋ ክፍሎች ስትመለከት በልሁ፣ መርዕድና የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከአንድ የአልቤርጎ ክፍል በር አጠገብ በረንዳ ላይ ቆመው አየች። እጅግ በሚያስገርም ጩኽት በልሁዪ !» ስትል ከርቀት ተጣራች።
ረጋ በይ ታፈሥ፡፡» አላት በልሁ ከአሯሯጧ በተጨማሪ የጥሪዋ
ድምፀት ውስጣዊ ስሜቷን አስረድቶት፡፡
ታፈሡ የበልሁን ማሳሰቢያ ከቁብ አልቆጠረችውም፡፡ ጆላላ የቤት ውስጥ ቀሚሷን ወደ ጉያዋ ሰብሰብ አድርጋ በመሮጥ ከመሀላቸው ጥልቅ አለች።
ወዲያው በበልሁ አንገት ወስጥ ተሸጉጣ ገና የአስቻለውን ሁኔታ ሳታውቀው በመባባት ስሜት ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ጀመር።
«አይዞሽ ታፈሥ» አላት በልሁ እሱም ፊቱን በትከሻዋ ላይ እስደግፎ በእጁ ጀርባዋን እያሻሽ፡፡
«እናስ በልሁ?» አላችው ታፈሡ፡፡ የአስቻለውን ሁኔታ በድፍኑ
መጠየቋ ነው:: አሰቻለውን እገኘኸው? ይዘኸው መጣህ? ብሳ በዝርዝር ብትጠይቀው ምናልባት ምላሽ አሉታዊ ቢሆን ብላ ሰጋች፡፡
«እስቲ ነይ ወደ ውስጥ ግቢ፡፡ አለና በልሁ ወዳ አልቤርጎው ክፍል ፊቱን መልሶ ወደ ውስጥ ተራመደ፡፡ ታፈሡ ከፍርሀቷ የተነሳ በጥንቃቄ እርምጃ ከኋላው ተከተለችው፡፡ የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌና መርዕድም ወደ ክፍሉ ገቡ።
ታፈሡ ከክፍሉ ውስጥ ገብታ ወደ አልጋው ስትመለከት አንድ ሰው
ተኝቶ አየች፡፡ ከአንገቱ በታች ያለው ሰውነቱ አልጋው ላይ የሚታይ
አይመስልም፡፡ የድዱ ስጋ አልቆ ጥርሶቹ ገጥጠዋል፡፡ የፊቱ ላይ አጥንቶችም እንደዚሁ፡፡ ዓይኖቹ እንባ አቅረው ሲያዩዋት አየች፡፡ የግራ ፊቱ ጠባሳ ያ የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የገለጸውን መልክ ያንፀባርቃል፡፡ ታፈሡ ያ ሰው
አስቻለው ስለመሆኑ ማመን ቢያዳግታትም በተለይ የፊቱ ጠባሳ፣ የግራ ዓይኑ
ልትጠፋ የደረሰች መሆኗ፣ የግራ ጆሮው ልጣፊ ስጋ መስሳ መታየቷና ከራስጌው በኩል ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ክራንች መታየቱ የግዷን እንድትቀበለው አደረጋት፡፡ ብቻ አሁንም ጨርሳ ላለማመኗ ምስክር የሚሆን
👍8
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የልጅ ልጅና አያቱ

ማሪየስ ለረጅም ጊዜ ስለታመመ መሞቱ ወይም በሕይወት መኖሩ
ሳይታወቅ ለረጅም ጊዜ ቆየ:: ለብዙ ሳምንታት ትኩሳቱ አልበረደለትም::አንዳንዴም ያቃዠዋል:: የአያቱ የመሴይ ጊልኖርማንድም ሁኔታ ከማሪየስ
የተለየ አልነበረም:: የልጁ ጉዳይ እስኪለይ ድረስ እርሳቸውም ከአልጋው አጠገብ እየተቀመጡ በሞትና በሽረት መካከል ኖሩ::

በየቀኑ አንዳንዴም በቀን ሁለት ጊዜ አንድ ሽበት የወረረው አዛውንት እየመጣ ይጠይቀዋል:: የሰውየው አለባበስ በጣም ሸጋ ሲሆን ከማረየስ ቤት በመጣ ቁጥር አንድ ነገር ይዞ ነው የሚመጣው::

በመጨረሻ ልክ በታመመ በሦስት ወሩ የማሪየስ በሽታ የማያሰጋ
ለመሆኑ በሐኪሙ ተገለጸ ፤ አያቱ ፈነጠዘ፡፡ ወደ ላይና ወደ ታች ሮጠ፡፡በዚሁ የተነሣ አንድ ቀን ለጎረቤታቸው የደስታ መግለጫ በመላካቸው ሰው ሁሉ ተገረመ:: ሌላው ቀርቶ ማሪየስን «ጌታው» እያለ ይጠሩት ጀመር፡፡
ከነአካቴው ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር» ብሉ እስከመጮህ ደረሱ፡፡ በአጭሩ ጮቤ መቱ።

በማሪየስ በኩል የነበረው አሳብ አንድ ነበር፡፡ ሲያክሙት፣ ቁስሉን
ሲጠግነት፣ እህል ሲቀርብለት፣ አዲስ ሰው ብቅ ሲልም ሆነ በማንኛውም ሰዓት ትዝ የምትለውና እረፍት የምትነሳው ኮዜት ነበረች፡፡ ለእርሱ ሕይወትና ኮዜት አንድ ናቸው:: ኮዜት ከሌለች ሕይወት የለችም:: ከሁለት
አንደኛቸው ከሌሉ ሁለቱም እንደሌሉ በልቡ ወስኖአል::

ማሪየስ ነፍስ ከዘራ በኋላ አንድም ቀን ቢሆን «አባባ» ብሎ ስላልጠራቸው መሴይ ጊልኖርማንድ ይታዘባሉ፡፡ ነገር ግን ጤናው በጣም ተመልሶአል::
አንድ ቀን ከአልጋው ላይ ቁጭ እንዳለ አያቱ ላይ ያፈጥጣል፡፡ ሁለቱ ተያዩ፡፡ ንግግር የሚጀምር ግን ጠፋ:: በመጨረሻ ማሪየስ ዝምታውን ይሰብራል፡፡

‹‹የምነግርህ ነገር ነበረኝ::>

«ምንድነው እሱ?»

«ትዳር ለመያዝ እፈልጋለሁ::»

«ጠርጥሬአለሁ» አሉ አያቱ:: ከዚያም ከት ብለው ሳቁ::

«እንዴት ጠረጠርክ?»

ቀደም ሲል አውቄዋለሁ ፤ አታመልጥህም ታገባታለህ::
ማሪየስ በደስታ ፈነደቀ፡፡ ፊቱ እንደ ማታ ጀምበር እዩኝ እዩኝ አለ::"
እንደ ጠዋት ፀሐይም በራ:: ልቡ እንደ ከበሮ ራሱን ሲደልቅ በውጭ
አልታየም እንጂ በኃይል ተማታ::

አያቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ::

«አዎን፣ ያቺ ለግላጋ ፣ ያቺ ሽንኩርት የመሰለች ቆንጆ ያንተው
ትሆናለች:: እንደ አሮጊት ለብሳ ሁናቴህን ለመጠየቅ በየቀኑ ትመላለሳለች።ቆስለህ ከተመለስክ ጀምሮ በየቀኑ እየመጣች አልቅሳ ነው የምትመለሰው::ማን እንደሆነች አጠያያቄ ደርሼበታለሁ:: አድራሻዋንም አወቅሁት፡፡ ለማንኛውም እኛ ተዘጋጅተናል፤ አንተም ፈልገሃል:: እርስዋም ሳትፈልግ አትቀርም፡፡
ስለዚህ ከዚህ በኋላ የቀረው አንድ ነገር ነው! ትዳር መመሥረት፡፡ ነገሩን ስታነሳብኝ እየፈራህ ነው የተናገርከው፡፡ የምጮህብህና የምቆጣህ መስሎህ ነው! አይፈረድብህም:: የለም! አልቆጣም፡፡ ኮዜት ትሁን ወይም ሌላ ፍቅር ብቻ ይስፈን፡፡ አግብተሃት ደስ ብሎህ ኑር ልጄ፡፡»

ሽማግሌው ይህን እንዳሉ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። እያለቀሱ የማሪየስን ፀጉር አሻሹ፡፡ በዛለ የሽማግሌ እጃቸው አቀፉት፡፡ የደስታ ብዛት መጨረሻው
ለቅሶ ነውና ሁለቱም ለረጅም ጊዜ ተላቀሱ::

‹‹አባባ» አለ ማሪየስ፡፡
«እንግዲያውማ አልጠላኸኝም ማለት ነዋ!» አሉ አያቱ፡፡
ተቃቅፈው ስለቀሩ መነጋገር አልቻሉም:: ቆይተው፣ ቆይተው ግን ሽማግሌው ተናገሩ፡፡
«በል ና፤ ጋሬጣው ተገልጧል፡፡»
ማሪየስ ከተሸሸገበት ከአያቱ ጉያ ብቅ አለ፡፡
«እንግዲያውስ አባባ ሄጄ ልያት፤ አሁን ተሽሎኛል::»
«ይህንንም ጠርጥሬአለሁ፤ ነገ ሄደህ ታያታለህ፡፡»
«አባባ!»
«ምነው?»
«ለምን ዛሬ አይሆንም?»
የሚከለክለን የለም፧ ይህንንም ጠርጥሬአለሀ:::»

ኮዜትና ማሪየስ እንደገና ተገናኙ፡፡ ሲገናኙ ምን እንደተጠያየቁ
ለመግለጸ አንሞክርም:: አንዳንድ ጊዜ አንባቢ ተመራምሮ ማወቅ ያለበትን በመዘርዘር ከሰው ሥራ ወስጥ አንገባም:: እናንተው አስቡት::

በእለቱ ኮዜት ማሪየስን ለመጠየቅ ስትመጣ የቤት ሰው በሙሉ
አንድም ሳይቀር ከማሪየስ ክፍል ይጠብቃታል:: ልክ እርስዋ ከክፍሉ ውስጥ ልትገባ ስትል ሽማግሌ ሊያስነጥሳቸው ይላል፡፡ በመሃረባቸው አፋቸውን
እፍን አደረጉ::
«አይ ቁንጅና!» ይላሉ እርስ በራሳቸው ሲነጋገሩ::

ውስጣዊ ደስታ ፊትን እንደ ብርሃን እንዲበራ ያደርጋል ቢባል የኮዜት
ፊት ማስረጃ ይሆናል:: ኮዜት በደስታ ብዛት ቆነጀች:: ተቅበጠበጠች፣ ሰከረች፣ ዘልላ ሄዳ ከማሪየስ አንገት ላይ ብትጠመጠም ደስ ይላታል፡፡ ግን
ሰው እያለ ፍቅርዋን አደባባይ ማውጣቱ አሳፈራት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍቅረኞች ላይ እንጨክናለን፡፡ እነርሱ ብቻቸውን መሆን ሲፈልጉ እኛ የሙጥኝ
በማለት አብረን እንቀመጣለን፡፡ እኛ እንፈልጋቸዋለን፤ እነርሱ ግን
አይፈልጉንም

ከኮዜት ጋር አብሮ የመጣ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው አባባ ሸበቶ ነው::
ይህ ሰው መሴይ ማንደላይን ነው:: ይህ ሰው መሴይ ፎሽለማ ነው፡፡ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ነው:: ዣን ቫልዣ ፊቱን በፈገግታ አስውቦና እሱነቱን በሽበት አስከብሮ ኮዜትን በመከተል ነበር ከቤቱ የገባው:: ሽክ ብሎ ለብሷል፡፡ጥቁር ሱፍ ለብሶ ነጭ ከረቫት አስሮአል::

ሰኔ 6 ቀን እንደዚያ ተጎሳቁሎና ቆሽሾ ማሪየስን ተሸክሞ የመጣው
ሰው ለመሆኑ ሠራተኛው አልጠረጠረም:: ጌታ የጌታ ልጅ መስሎታል ዣን ቫልዣ የተቀመጠው ከበር አጠገብ ሲሆን ከብብቱ ስር እንደ
መጽሐፍ ያለ የተጠቀለለ ነገር ይዟል፡፡ ይህን ያየች የማሪየስ አክስት ወደ አባትዋ ተጠግታ አንድ ነገር ትናገራለች::

«ይህ ሰው ዘወትር መጽሐፍ ይሸከማል?»

መጽሐፍ የሚባል ነገር ጠላትዋ ነው::

«ምን ያድርገው ብለሽ፤ ምሑር እኮ ነው፤ ጥፋት የለበትም» ሲሉ
የማሪየስ አያት መለሰላት::

«መሴይ ፍችለሹ» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ::

ስሙን አሳስተው የጠሩት ሽማግሌው ሆን ብለው አልነበረም:: እንደ እርሳቸው የለመዱት የመኳንንት ስሞችን እንጂ እንደ «ፎሽለማ» ያለ ደረሰ
ያልታወቀ ዘር ስም አስተካክሎ መጥራት አይሆንላቸውም::
«መሴይ ፍችለሽ፣ ልጅህን ለልጄ እንድትሰጠኝ እለምናለሁ::»

መሴይ ፎሽለማ ጎንበስ ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ «ተስማምቻለሁ» አለ፡፡

«ተጫወቱ» ብለው ሽማግሌዎቹ ከክፍሉ ውስጥ ጥለዋቸው ወጡ፡፡ኮዜትና ማሪየስ አንገት ለአንገት ለመተቃቀፍ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡
ንግግር አላስፈለጋቸውም:: መተያየትና መታሻሸቱ በቂ ነበር፡፡

መሴይ ጊልኖርማንድ ልጅትዋን በማድነቅ አወሱ፡፡ ስለውበትዋና
ስለቁንጅናዋ ብዙ ተናገሩ:: ፍቅራቸው የፀና እንዲሆንና እርስ በርስ እንዲከባበሩ መከሩ:: ፍቅር ሰዎች ቂል የሚሆኑበትና የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገለጽበት ነገር እንደሆነ አስረዱ፡፡

«ብቻ» አሉ ቀጥለው ሊናገሩ፧ «ብቻ እኔ በሕይወት እስካለሁ ድረስ በቂ መተዳዳሪያ ይኖራችኋል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን እንጃ! ትቸገራላችሁ፡፡
አሁን በኋላ ፈጣሪ የሀያ ዓመት እድሜ ቢለግሰኝ እንኳን ያለው ንብረት ይበቃል::

«አይጨነቁ፤ ኮዜት ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ አላት::
የዣን ቫልዣ ድምፅ ነበር፡፡
«እኔ!» ስትል ኮዜት ጮኸች::
«ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ?» ሲሉ መሴይ ጊልኖርማንድ ጠየቁ፡፡
«አዎን፤ ስድስት መቶ ሺህ.… ብቻ ምናልባት አሥራ አራት ወይም
አሥራ አምስት ሺህ ፍራንክ ቢቀነስ ነው» ሲል ዣን ቫልዣ ተናገረ፡፡
👍192
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...በመጨረሻ እንዲህ ሆነ " ሚስዢ ላቲመር የምትባል የዌስትሊን ነዋሪ የሆነች
ወይዘሮ እንደ ገረድና አነጋጋሪም እንድትሆናት አፊ ሆሊጆንን አስከትላ ወደ
እስታልክንበርግ መጣች አፊ ከመቤቲቱ ጋር አብራ ትቀመጣለች ወይም ትበላለች ማለት ሳይሆን ከብዙ እመቤቶች ደንገጡሮች የተሻለ የመቅረብ ዕድል ነበራት እሷ ደግሞ ይህንን ጫፍ በመያዝ ጓደኛዋ እንደ ሆነች አድርጋ ታወራ ነበር » ሚስዝ ላቲመር ደግ ሰው ነበረች አፊም አባቷ በተገደለበት ጊዜ በነበረው
ሁኔታ የራሷን ታሪክ እያሠማመረች ለመቤቲቱ ታጫውታት ስለ ነበር በጣም ወደደቻት የሚስዝ ላቲመር ክፍል ከሚስዝ ክሮስቢ ቀጥሎ ስለ ነበር ' ሁለቱ ሴቶች ከመተዋወቅ ዐልፈው ባልንጀሮች ሆኑ " የመጀመሪያዋ ሎድዊግ ከገባች ሳምንት ሳይሆናት ምናልባት ሁለቱም ከሌሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንዳደረጉት
ለዘለዓለም እትማማችነት ቃል ተጋቡ

ወይዘሮ ሳቤላ ከአትክልቱ ጓሮ ትገባና ሰው ወደሚያዘወትረው ጥግ ሒዳ መቀመጥ ትወድ ነበር ሔለና ክሮስቢ እንደምታገባ የነገረቻት ጊዜ ጨለማው ለዐይን መያዝ ጀምሯል እንደ ተለመደው እያዘገመች ሔዳ ከአንድ አግዳሚ ወንበር
ተቀመጠች እንዳጋጣሚ ሆኖ አፊ ሆሊጆንም በዚያው መንገድ እየተንጐራደደች መጣች » እሷም በበኩሏ ብቻዋን መሆኗ አስጨንቋታል።

ያቺ ደሞ ማን ናት ? ስትል አሰበች ወደ ወይዘሮ ሳቤላ እየተመለከተች አሃ ! ዐወቅኋት የክሮስቢ ልጅ አስተማሪ ናት በደፋችው ያሮጊት ቆብ ከሩቅ ትለያለች
ሔጄ ከሷ ጋር ላውጋ አለች።

አንዳለችውም ስለ ይሉኝታ ምንም የማትጨነቀው አፊ ሰተት ብላ ሒዳ ከሳቤላ ጐን ቁጭ አለች ደኅና አመሸሽ ማዳም ቬን ? አለቻት "

“ደኅና ፤እንደ ምን አመሸሽ ? አለቻት ሳቤላ በትሕትና ሴትዮዋን የማን እንደሆነች ጨርሳ ዐላወቀቻትም።

ያወቅሽኝ አልመሰለኝም አለቻት የሳቤላን አመለካከት በመገምገም “እኔ እኮ የሚስዝ ላቲመር ጓደኛ ነኝ ዛሬ ከሚስዝ ክሮስቢ ዘንድ ገብታ እዚያው ማምሸቷ ነው " ይኸ እስታልከንበርግ እንዴት ይሰለቻል !

“ እውነት ? እስከዚህ ድረስ ?

"ለኔ አዎን አየሽ ጀርመንኛም ሆነ ፈረንሣይኛ መናገር አልችልም " እዚህ
ያሉት የማናቸውም ቤተስቦች ተከታዮች አብዛኞቹ እንግሊዝኛ አይናገሩም ስለዚህ ዝም ብዬ ድብልቅ እያልኩ እንደ ጒጒት አፈጣለሁ " እዚህ የመጣሁት አሞኝ ነበር ግን የፈለገውን ያድርገኝ እንጂ ወደ ዌስት ሊን ብመለስ ይሻለኛል።”

ሳቤላ ይህችን ሴትዮ እንድታወራት በንግግርም ሆነ በገጽታ አላደፋፈረቻትም ነበር " የመጨረሻውን ዐረፍተ ነገር ስትስማ ግን ልቧ ከውስጧ ዘለለ የናፍቆት ትኩሳት ተነሣባት ።

"ከዌስት ሊን ነው የመጣሽው?"

“አዎን የተረገመ ቦታ ! ከሚስዝ ላቲመር ጋር መኖር እንደ ጀመርኩ ወዲያው መኖሪያዋን ዌስት ሊን አደረገች " ወደዚያ ከመምጣት ወደ አንድ የግዞት ሥፍራ ብትሔድ ኖሮ ይሻል ነበር "

"ግን ለምን ጠላሺው ?

“ ስለማልወደው ነዋ ?”

ኢስት ሊንንሳ ታውቂዋለሽ ?” አለች ሳቤላ ልትጠይቃት የምትፈልጋቸውን ነገሮች ስታስብ ልቧ እየደለቀ ።

ዐውቀዋለሁ እንጂ እኅቴ ሚስ ሆሊጆን የዚያ ቤት የሠራተኞች አለቃ ናት አንቺም ታውቂዋለሽ ማለት ነው ....ሚስዝ ቬን ?”

ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚያ አካባቢ ለአጭር ጊዜ ተቀምጬ ነበር » ስለ ካርላይል ቤተሰቦች ደኅንነት ለመስማት ደስ ይለኝ ነበር " ጥሩ ሰዎች ነበሩ ”

አፊ ራሷን ወዝወዝ አደረገች እንደሚመስለኝ አንቺ የምታውቂያቸው የእመቤት ሳቤላ ጊዜ ከሆነ አሁን ብዙ ነገር ተለዋውጧል።

“ እመቤት ሳቤላ?” አለቻት ጥቂት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ " አዎን ' ትዝ አለችኝ !የሚስተር ካርላይል ሚስት ነበረች "

እንዴት ያለች ሚስቱ ነበረች መስለሽ ? አለች አፊ በማሾፍ " መቼም ከሰው ተለይተሽ ጫካ ካልኖርሽ በቀር ታሪኳን ሳትሰሚ አትቀሪም ልጆቿን ሁሉ አፍስሳለት ከሌላ ወንድ ጋር ኮበለለች »

" ልጆቹስ በሕይወት አሉ ?

“ አሉ ያልታደሉ ምስኪኖች አንዱን የሳምባ በሽታ እያመነመነው ነው እህቴ ጆይስ ግን እንዲ ብዬ ስናገር በሽታው ይበረታበታል ብላ ትቆጣኛለች "

የትኛው ልጅ ይሆን ? አለች ሳቤላ የወረዛውን ግንባሯን እየጠረገች “ሳቤላ ትሆን

“ ሳቤላ የምትባል ልጅ የለችም " ያለች አንዲት ሴት ናት እሷም ሉሲ ነው የምትባል።

"ዱሮ እኔ ሳውቃቸው አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች ነበሩ እና ሴቲቱ ሳቤላ ስትባል ትዝ ይለኛል።

"ቆይ እስቲ ምን ነበር የሰማሁት አዎን ዊልሰን ሞግዚቲቱ እንደ ነገረችኝ ሚስቲቱ የኮበለለች ሌሊት ሚስተር ካርላይል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ልጅቷ በሁለተኛ ስሟ ሉሲ ተብላ እንድትጠራ አዘዘ " ይኸንም ማድረጉ አያስገርምም አለች አፊ " እሱም ያንን ስም እየሰማ መኖር አይችልም " ልጂቱም በናቷ ስም ስትጠራ በትዝታዋ እንድትሠቃይ አልፈለገም "

“ እውነት ነው አያስገርምም ለመሆኑ የትኛው ልጅ ነው የታመመው ? አለች ሳቤላ

“ ዊልያም የሚባለው ትልቁ ልጅ ነው " ታመመ እንኳን አይባልም " ግን ሣር መስሎ ቀጥኗል ፊቱ ያለ መጠን ብጭጭ ብሏል ዐይኖቹ እንደ መስታወት ያብረቀርቃሉ " ጆይስ የፊቱ ብጭጭ ማለት የናቱም ከዚያ ይብስ ነበር ትለኛለች እኔ ግን ከሷ የበለጠ ዐውቃለሁ ጤነኞች የዚያን ዐይነት መፍለቅለቅ አይታይባቸውም "

“ እመቤት ሳቤላን አይተሻት ታውቂ ነበር ? ”

“ ኧረ እኔ!” አለቻት አፊ “ እሷን ማየቱንም እንደ ውርደት ነበር የምቆጥረው " አየሽ ማዳም ቬን ... እሷን ከመሰለ ቅሌታም ጋር መግናኘት ምን ያስፈልጋል ?

ሌላ ደግሞ አንድ ትንሽ ልጅ ነበር " ስሙም አርኪባልድ ይመስለኛል እሱስ ?”

“ ያ ረባሽ ጐረምሳ ! እሱ ምንም የለበትም " መቸም ብታይው ቁርጥ አባቱን
ነው " ታዲያ ' ዌስት ሊን ላይ ትንሽ ከቆየሽ የኔንም ስም በመጥፎ ሲያነሱት
ሰምተሽ ይሆናላ ?

“ የሰማሁ ይመስለኛል ግን ዝርዝር ነገሩን አላስታውሰውም "

አባቴ በሰው መገደሉን ሰምተሻል ? ”

“ አዎን አስታውሳለሁ "

“ አንድ ሪቻርድ ሔር የተባለ ሰው ገደለውና ወዲያው ካገር ጠፋ " ቤተሰቦቹን
ታውቂያቸው ይሆናል " እኔም ቦታው አስጠላኝና አባቴን እንዳስቀበርኩ ለቅቄ
ሄድኩ” ለካ ሰዉ ከሪቻርድ ሔር ጋር ኮበለለች ብሎ ያማኝ ኖሯል እንዲህ መባሌን በጊዜ ብሰማ ኖሮ ሁሉንም ልክ ልኩን እነግረው ነበር ” እስቲ እንዴት አድርጌካባቴ ግዳይ ጋር እሔዳለሁ !? ከዌስት ሊን አሉባልተኞች ጥቂቶቹ እንኳን ቢንጠለጠሉ
ለብዙዎቹ ትምህርት ይሆን ነበር ብዬ ለሚስተር ካርላይል ስነግረው ሣቀና' መስቀል አሉባልታን አያስቀርም አለኝ » ከዚያ ሁሉ ሕዝብ ከሪቻርድ ሔር ጋር አለመሔዴን ያመነልኝ እሱ ብቻ ነበር እንዴት ያለ ቀጥኛ ሰው መሰለሽ ?”

" አንቺ ግን በሥራ ላይ ነበርሽ አይደለም ?

“ አዎን ካንድም ሁለት ቦታ ነዋ መጀመሪያ ካንዲት ባልቴት ጋር እንደ ጓደኛ ሁኘ ኖርኩ " በጣም ትወደኝ ስለነበር ስትሞት ደኅና ገንዘብ ተናዘዘችልኝ
ከዚያም ከካውንተስ ማውንት እስቨርን ጋር ሁለት ዓመት ተቀመጥኩ

“ ካውንተስ ማውንት ስቨርን ? እሷማ ከሚስተር ካርላይል ሚስት ጋር በባሏ
በኩል ዝምድና ነበራት » ሎርድ ማውንት እስቨርን ራሱ ዘመድ ነበር "
👍16
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

‹‹ከተለየኋት በኋላ ስለእሷ ማሰብ ላቆም አልቻልኩም ነበር..እንዴት አድርጌ ከዚህ ሀዘን ላወጣት  እችላለሁ….?እንዴት አድርጌ ላግዛት እችላለሁ….? የግድ አባቷ እስኪመጡ መጠበቅ የለብኝም..አባቷ ስል አባቷ ብቻ አይደሉም እናቷም ጭምር.. ጓደኛዋም ጭምር እንደሆኑ መላ ሰፈሩ ያውቃል..ብቻቸውን ነው ያሳደጎት….እድሜ ልኳን ከአባቷ ተለይታ ኖራ አታውቅም..ይሄንን ማንም ያውቃል…ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ደርሷት መለያየት ግድ በሆነበት ጊዜ እንኳን  እሷ ከአንተ ተለይቼ መሄድ ስለማልችል ትቼዋለሁ ስትል..አባቷም እውነትሽን ነው አንቺ ትምህርትሽን ከምትተይ እኔ አብሬሽ ሄዳለሁ በማለት…ስራቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር በመቀየር አብረዋት ዘምተዋል…ይህ ሀገር የሚያውቀው ሀቅ ነው……..አሁን አባቷ ለጉዳይ ወደውጭ ሀገር እንደሄዱ ነግራኛለች….ስጨነቅ አንግቼ  በማግስቱ ያለውን ቀንም በተመሳሳይ መሸበር አሳለፍኩ

…..ግን……?››

ድንገት ንግሩን አቋረጥኩትና ‹‹አልደከመህም መኝታ ቤት ሄደን አልጋ ላይ አረፍ ብለን የቀረውን ትጨርስልኝ….?››አለችው  

‹‹በቀላሉ  ያልቃል ብለሽ ነው….?››

‹‹እንሞክረው….?››

ደስ እንዳሽ ብሎ ብርጭቆውን ይዞ ተነሳ.. ቀድማው ወደመኝታ ቤት አመራች፤ እየተንጋዳገደ ከኃላ ተከተላት….የእሱና የሰላም የፍቅር ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእሷ እና የእሱንም መጨረሻ እንዴት እንደሚጠናቃቅ ማወቅ አጓጓት
///

መኝታ ቤት ገብተው አልጋ ላይ ጎን ለጎን ትራስ በመደገፍ ጋደም ብለው ከተመቻቹ በኃላ ወሬውን ካቆሙበት ቀጠሉ፡፡

‹‹እና እንደነገርኩሽ በእሷ ጉዳይ ስጨነቅ አድሬ ስጨነቅ ውዬ …ከእንደገና መልሼ መጥፎ ለሊት ካሳለፍኩ በኃ
ኋላ ዛሬ ጥዋት ስልኬ ጠራ …አነሳሁት‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ››

‹‹ማን ልበል….?››ስል ጠየቅኩ፡፡

‹‹ትናንት ማታ ያደረስከኝ ልጅ ነኝ..ቁጥርህን ከተውክልኝ ካርድ ላይ አግኝቼው  ነው››አለቺኝ.…

እንደዛ በፍጥነት ትደውልልኛለች ብዬ አላሳብኩም ነበር..ትናንትና ስልክ ቁጥሬን ፅፌ ትቼላት ሰወጣ ለምን አልባቱ ብዬ ነበር..ምን አልባት በዛ ስካር ውስጥ  ሆና የሰጠኋትን ወረቀት ቀዳዳም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ልትጥለው ትችላላች የሚልም ግምት ነበርኝ..እና ደወለችልኝ ..ለዛውም ገና በጥዋት4 ሰዓት…እንደደረስኩ መኪናዬን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳሁ…ከፈተችልኝ….

‹‹እሺ ደህና ነሽ ግን….?››
ጥያቄዬን ችላ ብላ ‹‹አሁን እየጠበቅኩህ ነው ና››አለችኝ 

‹‹አቤት….?››አልኳት ይበልጥ እንድታብራራልኝ ፈልጌ 
እሷ እቴ ስልኩን  ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችው

‹‹ይህቺ ልጅ ጤናም የላትም እንዴ . ….?.››አልኩና የላዳዬን ሞተር በማስነሳት ወደቤቷ ተፈተለኩ..እንዴ እሷ ና ብላኝ እንዴት እዘገያለሁ….?፡፡ 

‹‹ታዲያ እቤት ስትሄድ አገኘሀት….?››ኬድሮን ነች የጠየቀችው በእጇ ከያዘችው ብርጭቆ መጠጥ አንዴ እየተጎነጨች
‹‹አዎ ..እንደደረስኩ መኪናዋን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳው…እራሷ ከፈተችልኝ….ጉስቁልናዋ እንዳለ ነበር..ስልችት ብሏታል…የሆነ ልቧን ስብብርብረ ያደረገው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ..እንደውም የፍቅር ነገር ይመስለኛል….››

‹‹እሺ ማን ነበረ ስምህ….?›› አለችኝ ግድ የለሽ እና አናዳጅ በሆነ የድምጽ ቅላፄ….አይገርምሽም ዕድሜሽን ሙሉ ያመለክሽው ልጅ… ስንት ቀን እና ሌት የናፈቃሽው እና በትዝታው የተሰቃየሽለት ልጅ -ማን ነበር ስምሽ ሲልሽ…..….?

በውስጥሽ  የሚፈጥረው ስሜት ግማሽ ህልውናሽ  የመደምሰስ አይነት ነው …..እመኚኝ በጣም ነው የሚያመው …እሷ ግን ለእኔ የስሜት መጎዳት ቁብ ሳይኖራት፤.መልሴንም ለመስማት ትግስት አጥታ ወደትዕዛዞ ተሸጋገረች

‹‹ካላስቸገርኩህ የሆነ ቦታ ትወስደኛለህ…….?››

‹‹የፈለግሺው ባታ …ተዘጋጂና ነይ መኪና ውስጥ እጠብቅሻለሁ››ብዬ ወደላዳዬ ፊቴን አዞርኩ‹‹አይ ላዳህን ወደግቢው አስገባት እና አቁማት.. በእኔ መኪና ነው የምንሄደው፤ ከከተማ ወጣ ማለት ነው የፈለግኩት…..››አለቺኝ፡
ግራ ግብት እንዳለኝ ወደኃላዬ ተመለስኩና ላዳዬ ውስጥ ስገባ እሷ ደግሞ የውጩን በራፍ ከፈተችልኝ…ወደ ጊቢ ውሰጥ አስገባኋትና ሚጢጢ ላዳዬን  ግዙፍ የእሷ ላንድኩሩዘር መኪና ጎን አቆምኳትና ሞተሩን አጥፍቼ ወጣሁ… በሩን ዘግቼ ቆምኩ..
‹‹እሷ ወደሳሎን ተመልሳ እየገባች ነበር…ደግሞ የሰውነቷ ቅርፅ ከቁመቷ ጋር ያለው ምጣኔ እንዴት አባቱ ያምር ነበር መሰለሽ…..5 ደቂቃ ሳትቆይ ተመልሳ ወጣችና የሳሎኑን በራፍ መቆለፍ ጀመረች ….በእጇ ካንጠለጠለችው ቦርሳ በስተቀር ምንም  የያዘችውም ሆነ የቀየረችው ነገር አልነበረም… እንደነበረችው ነው ተመልሳ የመጣችው..ዝንጥንጥ ብላ የምትመጣ መስሎኝ ነበር..ግን በለበሰችው ቱታ ሱሪ እና ቲሸረት ነው አሁንም ያለችው..ስሬ እንደደረሰች ከቦርሳዋ ውስጥ ቁልፍ አወጣችና ወረወረችልኝ …በአየር ላይ ቀለብኩና ወደመኪናዋ ተንቀሳቀስኩ…..ሞተሩን እስነስቼ ከግቢሁ ከወጣሁ በኋላ አቁሜ ጠበቅኳት… የውጩውን በራፍ  በመዝጋት እና በመቆለፍ መጣችና ጋቢና  በመግባት ከጎኔ ትቀመጣለች ብዬ ስጠብቅ  የኃላውን በራፍ ከፍታ ገባች……››

‹‹ምነው እዚህ አይሻልሽም….?›› ልላት ነበር ..ግን አንደበቴን ማላቀቅ አልቻልኩም…በእስፖኪዬ ወደኃላ ተመለከትኳት ….ግማሽ እሷነቷ ሞቶ ግማሽ እሷነቷ ብቻ በህይወት እና በሞት መካከል ያለ ይመስላል..ልክ እኔ  ለመሞት ወደሀገሬ ልግባ ብዬ በወሰንኩበት በዛ ጭለማ ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔታ አስታወሰችኝ ….

‹‹ሰላም ወዴት ነው የምንሄደው..….?››ብዬ ጠየቅኳት

‹‹አቤት›› አለችኝ እንደመባነን ብላ
‹‹ወዴት ልንዳው ነው ያልኩሽ….?››

‹‹ወደ ፈለከው…. ግን ከከተማ ውጭ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይሁን እንጂ ወደየትም ይሁን …..››
‹‹እሺ››
‹‹ግን ስሜን መቼ ነው የነገርኩህ….….?ሰላም ብለህ የጠራህኝ መሰለኝ….?››

‹‹ነግረሺኝ አይደለም…››

‹‹እና እንዴት  አወቅከው…..….?››

‹‹አውቄውም አይደለም…ሰላም ማለት ለእድሜ ልኬ ያፈቀርኳት..አሁንም ድረስ የማፈቅራት ከህጻንነቴ ጀምሮ የማውቃት ፤መቼም ልረሳት የማልችላት  ልጅ ስም ነው…እና ያው ፍቅሯ ጅል አደርርጎኛል መሰለኝ ብዙ ሴቶችን ሰላም ብዬ መጥራት እወዳለሁ…››አልኳት….ሽሙጤ ሳይገባት….ፈገግ አለችና‹‹ ይገርማል እንደአጋጣሚ የእኔም ስም ሰላም ነው››አለችኝ 

‹‹አውቃለሁ››

‹‹ማለት›….?›››መልሶ  ግር ብሏት

‹‹በመልክም በጣም ትመሳሰላላችሁ ልልሽ ፈልጌ ነው››
ዝም አለች….በጦር ኃይሎች አድርገን በ18 ማዞሪያ ታጥፈን በአንቦ መስመር አሸዋ ሜዳን አቆርጠን ወደቡራዬ ተጓዝን…እሷ እውነትም እንዳለችው ወደየትም ብነዳው ግድ ያላት አትመስልም ነበር..አይኗን በመኪናው መስታወት ወደውጭ ልካ በየመንገዱ ዳር ያለውን ትዕይንት ምታይ ትመስላለች ….ግን አታይም እሳቤዋም እይታዋም ከውስጧ ጋር እንደሆነ ያስታውቃል…ብራዩንም አለፍን ፣እኔም አላቆምኩም እሷም አቁም አላለችኝ…ግን ጊንጪ ልንደርስ ኪሎ ሜትሮች ሲቀረን  የሆነ ለጥ ያለ ሜዳ ጋር ስንደርስ…..‹‹ይቅርታ ማን ነበር ስምህ...….?››ስትል ከሳዕታት ዝምታ በኃላ አብሻቂ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀችኝ….
👍936
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡.

ዶ/ር ሶፊያ እና ትንግርት ኮንትኔንታል ሆቴል ምሳ በልተው ከጨረሱ በኃላ መጠጥ እየተጎነጩ ጨዋታ ይዘዋል፡፡

‹‹እሺ ትንግርቴ ህይወት እንዴት ነው?››

ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንደምታይው ነው፡፡››

‹‹ላገባ እኮ ነው ..ነግሬሻለሁ አይደል?››

‹‹አላስተዋወቅሽኝም እንጂ ነግረሺኛል፡፡››

‹‹አስቤ ነበር ግን ወደ አሜሪካ በረረ ..ያው ጣጣውን ጨርሶ አንደኛውኑ ከ15 ቀን በኃላ ወደ ሀገር ቤት ይመጣል ...ሊያገባኝ ፡፡የዛኔ አስተዋውቅሻለሁ፡፡››

‹‹ቆንጆ ነው?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡:

‹‹ያንቺን ያህል አያምርም እንጂ ቆንጆስ ቆንጆ ነው፡፡››እንዲህ ስትላት የትንግርት ፊቷ ቀላ፡፡

‹‹የሆንሽ ብሽቅ ነገር እኮ ነሽ...ሰውን መተንኮስ መቼም አታቆሚም፡፡››

እውነተኛ ስሜቴን እኮ ነው እየነገርኩሽ ያለሁት..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡..እንደዛ የሚሰማኝ ደግሞ አንቺን ሳይ ብቻ
ነው፡፡››

‹‹ታድዬ፡፡››አለቻት በማሾፍ፤ቀጠለች‹‹ግን ሁሌ አንድ ነገር ጠይቅሻለሁ እያልኩ ሳገኝሽ እረሳዋለሁ፡፡›››

‹‹ምንድነው አሁን ጠይቂኛ?››

‹‹ሀዋሳ ከመገናኘታችን በፊት ለስድስት ወራት ያህል በሚሴጅ ታጨናንቂኝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ አይደል?››

‹‹አዎ እኔ ነኝ...ማን መስሎሽ ነበር?››

‹‹እኔ እንጃ.... ብቻ ከድሮ የሽርሙጥና ህይወት ካፈራዋቸው ደንበኞቼ መሀከል የፍቅር ግርሻ ናላውን ያዞረው አንዱ ጀግና መስሎኝ ነበር፡፡››

‹‹ትንግርቴ..በእኔ ተረብሸሽ የማትፈልጊው ህይወት ውስጥ ተሰንቅረሽ ሶስት የባከኑ ዓመታት በማሳለፍሽ ግን በጣም አዝናለሁ፡፡››

‹‹የባከኑ አልሻቸው..እነዛ አመታት ፍፁም የባከኑ የሚባሉ አልነበሩም ...የህይወት ልምዶች ያገኘሁባቸው እና ስብዕናዬን የሞረድኩባቸው ዓመታት ነበሩ፤ያን ስል መከራ አልነበረውም፡፡...ስቃይ
አልተቀበልኩበትም፣አልተሰደብኩበትም፣አልተደ በደብኩበትም ፣አልተዋረድኩበትም ማለቴ አይደለም ግን ከተሰቃየሁት ስቃይ ይልቅ ያተረፍኩት በጎ ነገር ሚዛን ይደፋል እያልኩሽ ነው፡፡››

‹‹ግን በመሀል ህይወት አስጠልታሽ ማለቴ ተስፋ ቆርጠሸ አታውቅም?›› ትንግርት እየፈገገች‹‹ታስቂያለሽ..አንድ በጣም የምወዳት አማረች የምትባል ጓደኛዬ አንድ የሚያምር ንግግር ትናገር ነበር …ምን እንደምትል ታውቂያለሽ

<<ተስፋ የሌለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም››ምን ለማለት እንደፈለገች መጀመሪያ አይገባኝም ነበር... በኃላ ግን ከገዛ ህይወቴ ጋር አቆራኝቼ ሳሰላሰለው ተገለፀልኝ…፡፡ እኔ ከዛች ከተለያየንበት ደቂቃ ጀመሮ ተስፋ ሚባል ነገር ከውስጤ ወድሞ ባዶ ንብ የሌለበት ቀፎ ሆኜ ነበር፡፡ሶስቱን አመት ሙሉ ያለምንም ተስፋ ነበር የኖርኩት..ለዛም ነው ያልተቸገርኩት…ምንም አጣለሁ ብዬ የምጨነቅለት፡፡..እዚህ ቦታ መድረስ አለብኝ ብዬ የምጥርበት..ይሄንን ነገር ማግኘት አለብኝ ብዬ የምጓጓለት ነገር አልነበረኝም፡፡››

‹‹ያሳዝናል...ትንግርቴ፡፡››

‹‹አትዘኚ...በህይወት ዝቅታ ወይም ከፍታ ላይ በአጋጣሚ ትንጠለጠያለሽ፡፡ከከፍታው
በምታገኚው ምቾት ተጠምደሽ ወይም ከዝቅታው ውስጥ በሚያጋጥምሽ መከራ ተደቁሰሽ አልባሌ ሰው ሆነሽ እንዳትቀሪ ግን የራስሽ ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ከፍታውም ሆነ ዝቅታው የራሱ የሆነ አውንታዊ አና አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡አሉታዊ ጎኑን ተቋቁመን ጠቃሚውን ነገር መቅሰም የእኛ ፋንታ ነው፡፡››ትንግርት እንዲህ ስትናገር ዶ/ር ሶፊያ እንባዋን እያንጣባጠበች ነበር፡፡

‹‹ቢሆንም ትንግርቴ ይህ ላንቺ ፍፁም የሚገባ ህይወት አልነበረም፡፡››

‹‹ላንቺም እኮ ብር ከፍሎ ሰውን ማስገደል የሚገባሽ ህይወት አልነበረም፤ አሜሪካ ሄዶ ለስድስት ወር በአዕምሮ ህመም ማገገሚያ ሆስፒታል ውስጥ ታግቶ መኖር፤የማትፈልጊያቸውን ኪኒኖች እየጎመዘዘሽ መቃም፤በድንዛዜና በብዥታ ቀናቶችን መግፋት ላንቺም የሚገባ አልነበረም፤አየሽ ሶፊ ‹ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን› የሚባለው በትክክል የሚሰራው በሶሰሻሎስቶች የመፈክር ባነር ላይ በቲዬሪ ደረጃ ብቻ ነው፡፡…እንደውም
በተቃራኒው ተፈጥሮ ነች እኛን ባብዛኛው የምትቆጣጠረን…የህይወት መስመርሽን አንቺ በፈለግሽው መንገድ ብቻ ማስኬድ አይቻልሽም፡፡ቤተሰብ ወደዚህ ይጎትትሻል፣ጓደኞችሽ ወደዛ ይስቡሻል፣ሀገርሽ ወደ ላይ ታወጣሻለች፣ያላሰብሻቸው አጋጣሚዎች ወደታች ያወርዱሻል፣ስለዚህ የሆነው ሁሉ ሆኗል፤በመሆኑም ደግሞ ለበጎነው ብለን መቀበልና ወደፊት መጓዝ ብቻ ነው የሚበጀን፡፡››

‹‹ለበጎ ነው ስትይ?››

‹‹በምንም ምክንያት ሆነ በምንም አንቺ ጥለሽኝ መሄድሽ በጊዜው ፈተናው ከባድ ቢሆንም በስተመጨረሻ ያመጣው ውጤት ዛሬ ህይወታችን እንዲህ ኖርማል እንዲሆን ስላደረገ ውጤቱ ጥሩ ሆኗል ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ግን እኮ ሁለታችንም የምንፈልገው ያንን ኖርማል ያልሆነውን ህይወት ነበር፡፡››

‹‹ቢሆንም ዘላቂ ውጤቱ መልካም አይሆንም ነበር…ማህበረሰብ እንዴት ነበር የሚያሰቃየን...?
መቼ ነው የምታገቡት..?ኧረ ቆማችሁ ቀራችሁ፤ በዛ ላይ የልጅ መውለድ ጉዳይ አለ...


✂️✂️✂️?????????✂️✂️✂️

‹‹...እሱን እኮ ነው የምልሽ ...አደገኛ የሆኑ ውስብስብ የማህበራዊ ህይወት ቀውስ የሚያመጡብን ችግሮች ውስጥ መግባታችን አይቀርም ነበር፡፡››

‹‹ያልሻቸው ነገሮች እንደሚከሰቱ አውቃለሁ ... ቢሆንም ግን ምርጫ ቢቀርብልኝ አንቺን
ከማጣት ያንን ፈተና መጋፈጥን እመርጥ ነበር፡፡››

‹‹ይሆናል…ግን አሁን ሁሉም አልፏል ...መሆን ያለበት ሁሉ አሁን እንደሆነው ሆኗል... በመሆኑም ትክክል ነው፡፡››

‹‹እንዳልሽ ይሁን .…እሺ ግን ሳገባ ሚዜ ትሆኚኛለሽ››ዶክተር ነች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹በሰርግ ነው እንዴ የምታገቢው?››

‹‹እስከአሁን አልወሰንኩም…. ግን አንድ ሃያ ሰው ጠርቼ የእራት ግብዣም ቢሆን ማድረጌ ይቀራል?››

‹‹ታዲያ ያገባች ሴት እኮ ሚዜ አትሆንም፡፡››

«ለምን?»

‹‹ባህላችን ነዋ...መነሻ ሀሳቡን ባላውቅም ምክንያቱን ስገምት ግን ያላገባች ሴት ሚዜ ስትሆን እግረ መንገዷን የራሷን አዳም የምታገኝበትን ዕድል እንድታመቻች ታስቦ የተቀየሰ ስውር ዘዴ ይመስለኛል፡፡››

‹‹አንቺ ...ትንታኔሽ አሳማኝ ይመስላል..በቃ እንደዛ ከሆነ ሌሎቹን ሁለት ሚዜዎች ያላገቡ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ያንቺ ግን የግድ ነው፡፡››ተሳሳቁ፡፡

‹‹ካልሽ ምንቸገረኝ..የእኔን ልጅም ክርስትና ታነሺያለሽ፡፡››

‹‹እንዴ!!! አረገዝሽ እንዴ?››

‹‹አዎ 1 ወር ከ15 ቀን ሆነኝ፡፡››

‹‹ኦ!!! ፈጣሪ የእኔ ቆንጆ እንኳን ደስ አለሽ፡፡›››ከመቀመጫዋ በመነሳት ተጠምጥማባት እያገላበጠች ሳመቻት እና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡

‹‹ክርስትና ግን ስትይ ..ሁሴን ኦርቶዶክስ ሆነ እንዴ?››

‹‹ኧረ አልሆነም፡፡››

<<እና>>

‹‹ምን እና አለው ..ያው እሱም ሀይማኖት የለሽ እንደሆነ የእኔ ሀይማኖት ደግሞ አለየለትም፡፡››

‹‹ግን በኑሮችሁ ምንም ችግር አልፈጠረባችሁም?››

‹‹ያው እስከ አሁን በፍቅር ጥላ ስር ስለሆንን ችግር አልፈጠረብንም… በሚያስማማን እየተስማማን በልዩነታችን ደግሞ እንደልዩነታችን እየኖርን ነው፡፡ፍቅር እኮ ሁሉንም ክፍተቶችሽን ይደፍንልሻል...ፍቅር ሲሸረሸር ነው ሜዳ ሁሉ ገደል፣ነጩ ሁሉ ጥቁር፣ንግግሩ ሁሉ ጭቅጭቅ መስሎ ሚታይሽ፡፡››
👍7511😁2😢2👎1