አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

አንቺ ወደሬሳ ማቆያው ቀድመሽ ሂጂና ሁኔታውን አመቻቺ… እኔ ቀስ ብዬ በጓሮ በኩል  ሄጂ የግቢውን መብራት አጠፋለሁ…ጄኔሬተሩንም አቶማቲኩን ስላበላሸሁት ሄደው አስተካክለው እስከሚያበሩት 10 ደቂቃ ይኖረናል..በዛ ጊዜ ውስጥ ይዘነው እንሄዳለን››

‹‹እሺ ግን ተጠንቀቅ…. ሰው እንዳያይህ››

‹‹እጠነቀቃለሁ..እንቺ ልክ መብራቱ እደጠፋልሽ ቶሎ አዘጋጂውና ከጋሽ ተካ ጋር ይዛችሁት በጎሮ በኩል መኪና መቆሚያው ድረስ ይዛችሁት ኑ..እኔ የመኪናዬን  ሞተር አስነስቼ ዝግጁ ሆኜ እጠብቃችኋለው…››

ተስማምተው እሱ ወደጎሮ  መብራቱን ሊያቆርጥ እና ግቢውን በጨለማ እንዲዋጥ ሊያደርግ እሷ ደግሞ በሽተኛውን ልትረከብ ወደሬሳ ማቆያ ክፍል ሄደች
መብራቱም ጠፍቶ እነሱም ሬሳውን(በሽተኛውን ) ይዘው  በመምጣት በመኪና ውስጥ አድርገው የውጭ ጥበቃዎችን በጥበብ አልፈው ግቢውን ለቀው ለመውጣት 8 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው..

ደ/ር እስክንድር ቀጥታ የነዳው ለዚሁ ጉዳይ ታስቦ ወደተዘጋጀ  ዛሬ ጥዋት ወደተከራዩት አፓርታማ ነበር….ይህን ቤት የተከራዩበት ዋና ምክንያት የሰሚርን ቤት የበሽተኛው ዘመዶች ያውቁታል..እሱ ቤት እንደይወስዱት ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚኖረው…. በዚህ ምክንያት የግድ   ማንም የማያውቀው እና ሰወር ያለ ቦታ ቤት መከራየት ነበረባቸው….
እንደደረሱ….ያው እንደሬሳ ድርቅርቅ ያለውን በሽተኛ ለሁለት እንደምንም ተጋግዘው ከመኪናው አወረዱትና ከሆስፒታል ባመጡት ተሸከርካሪ ጋሪ እየገፉ ወደቤት  አስገቡትና  …መኝታ ቤት የሚገኝ  አልጋ ላይ  ዘረሩት….

ይሄንን ሁሉ እስኪያደርጉ በመካከላቸው በስሜት ከመግባባት እና በምልክት መልእክት ከመለዋወጥ ውጭ ቃላት አልወጣቸውም ነበር….ሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ በድን ሆነዋል

‹‹በይ ቶሎ መድሀኒቶቹን አምጪልኝ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ዓ.ነገር ነበር

ሮጣ ሄደችና ካስቀመጠችለት በማምጣ ፊቱ ያለው ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችለት…

ሁለት መድሀኒቶችን ቀላቅሎ በመርፌ ክንዱ ላይ ወጋው….እና ከጎን ያለ ወንበር  ሳብ በማድረግ አልጋውን ተጠግቶ በመቀመጥ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረ..ሰሚራ ተገትራ  አይኖቾን የተዘረረው ሬሳ ላይ እንደሰካች ነው…ዶክተርም  ቁና ቁና እየተነፈሰ በየሰከንዶች ልዩነት ሰዓቱን እያየ ይቁነጠነጣል..ሰዓቱ ደግሞ መንቀርፈፉ….

‹‹ምነው ዝም አለ…..?››ሰሚራ ጠየቀች

‹‹እኔ እንጃ …መድሀኒቱ በመላ ሰውነቱ እስኪሰራጭና እስኪሰራ 5 ደቂቃ ይወስድበታል››

‹‹ታዲያ ከሰጠሀው እኮ ቆየ…..?››
‹‹መስሎሽ ነው …ገና ሁለት ደቂቃ ነው››

‹‹ሁፍ!!! ሁለት ደቂቃ ማለት ግን ስንት ነው…..?››

‹‹ሁለት ደቂቃ ማለትማ  ያው ሁለት ደቂቃ ነው..ግን አንዳንዴ  እንደዚህ ይበረክታል››አላት በደመነፍስ

…አይደርስ የለ 5 ደቂቃ ሞላ በሽተኛው ንቅንቅ አልል አለ….

‹‹ምን ይሻላል..…..?የሆነ ምልክት ማሳየት ነበረበት››ደ/ር እስክንድር ነው ግራ በመጋባት ለራሱ ይሁን ለሰሚራ በማያስታውቅ ስሜት ያወራው

‹‹አረ የሆነ ነገር አድርግ..ወይኔ ተዋረድን››

‹‹ቆይ እስቲ ተረጋጊ …ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ..››አለና ፊት ለፊቱ ካለ ጠራጴዛ ላይ ከተዘረገፉት መድሀኒቶች ውስጥ አንዱን መርጦ በፊት  ከወጋው በተቃራኒ ባለው ክንዱ ላይ ወጋውና በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ….
አንድ ደቂቃ..ሁለት ደቂቃ…ሶስት ደቂቃ…ምንም የለም..በድን ሬሳ…

‹‹ወይኔ ተበልተናል…ምንድነው የተሸወድኩት…..?››

‹‹እኔ ምን አውቃለሁ…መድሀኒቱ አስተማማኝ ነው …አውቀዋለሁ ብለህኝ ነበር…..?››

‹‹አዎ ብዬሽ ነበር..ግን  አልሆነም››

‹‹ግን አልሆንም ትለኛለህ እንዴ……?ስለሰው ህይወት እኮ ነው እያወራን ያለነው..ገና አለምን በቅጡ መኖር ስላልጀመረ ወጣት››

‹‹መቼስ ይሄ እንዲሆን ፈልገን አይደለም..እንደውም በተቃራኒው የእሱን ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባነው..ሞክረናል  ግን አልቻልንም››

‹‹መቻል ነበረብን …››ከ20 ደቂቃ በላይ ተገትራ ከቆመችበት ቦታ ተነቃነቀችና ወደእሱ ቀረበች ….እሱም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ስጋት ከተቀመጠበት ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ
እንባዋን እያዘራች….‹‹ልታድነው ይገባ ነበር …መሞት አልነበረበትም…ከባድ  ስህተት ነው የፈፀምነው…››ደረቱን እየመታች  በመንሰቅሰቅ እቅፉ ውስጥ ገባች፡

‹‹አንቺ ምን አደረግሽ..…..?ከምትችይው በላይ ልትረጂው እየሞከርሽ ነበር›››

‹‹አይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነበር መሄድ የነበረብኝ…የማይሆን  ነገር ነው የሞከርኩት …..››

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››ያልታሰበ ከሩቅ የሚመስል ድምጽ ተሰማ…. ሁለቱም በድንጋጤ ፈዘው  ወደአልጋው መመልከት ጀመሩ ....መላኩ በተኛበት እልጋ ላይ አይኖቹን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ዙሪያ ገባውን ሲቃኝና በጥያቄ አስተያየት ሲያይ ተመለከቱት

‹‹ወይኔ በአላህ ነቃ ..አደረከው ..አደረከው..››ደ/ር ላይ ተጠመጠመችበት….ለቅሶዋን ማቋረጥ አልቻለችም….ከሳቅ ጋር የተቀላቀለ የደስታ እንባ

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››በሽተኛው ጥያቄውን ደገመው

‹‹አይዞህ… እኔ ሲስተር ሰሚራ እባላለሁ…እሱ ደግሞ ጎደኛዬ ነው ዶ/ር እስክንድር ይባላል…ያንተን ጤንነት የምንከታተለው እኛ ነን››

‹‹ምን ሆኜ ነው…..?››

‹‹አይዞህ ጥቂት ጉዳት ደርሶብህ ነበር.. አሁን ተርፈሀል….››

‹‹ሰላሜስ…..?ሰላምን ጥሪልኝ..››
‹‹አይዞህ ጠራታለሁ .አሁን ራስህን አታድክም .››

‹‹ጥሩ…ልኝ..››እያለ ወደ እንቅልፍ አለም ገባ 

‹‹መተኛቱ ጥሩ ነው….ይገርማል የሰጠነው መድሀኒት ከሞት ብቻም ሳይሆን ሰሞኑንም ከነበረበት ኮማ ጭምር ነው መንጭቆ ያወጣው….እንዲህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር….ግን አሁን መልሶ ከእንቅልፉ ሲነቃ  ስለፍቅረኛው እና  ስለወንድሙ እንዴት ታስረጂዋለሽ…..?››

‹‹አታስብ ዋናው ወደ ህይወት መመለሱ ነው… ሌላው እዳው ገብስ ነው… የሆነ ዘዴ አላጣም..አንተ ግን ድንቅ ሰው ነህ››

‹‹አረ ድንቅነት በአፍንጫዬ ይውጣ ..ሁለተኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት አይዳዳኝም …እንዴ ነፍሴ በአፍንጫዬ ልትወጣ እኮ ነበር››

‹‹ይቅርታ አጨናነቅኩህ አይደል…..?››

‹‹አጨናነቅኩህ ብቻ..ልትውጪኝ እኮ ነበር…ይሄ ልጅማ እንዲህ በቃላሉ ከዚህ ቤት የሚወጣ አይመስለኝም››

‹‹ምን ማለት ነው…..?››

‹‹እኔ እንጃ አይነ ውሀሽ አላማረኝም…ለማንኛውም በየስድስት ሰዓት ልዩነት ይሄንን መድሀኒት ስጭው…ችግር ካለ ደውይልኝ አሁን እኩለ ለሊት ከማለፉ በፊት ወደቤቴ ልሒድ››

‹‹ስላደረክልኝ ነገር በጣም አመሰግናለሁ..ና ልሸኝህ››

‹‹አረ ግድ የለም….ነገ መቼስ ስራ አትመጪም››

‹‹አረ የዓመት ፍቃድ እጠይቃለሁ..እስኪሻለው  ለማን ጥዬው እሔዳለሁ…?››

…ፈገግ ብሎ እየሳቀባት ቤቱን ለቆላት ሄደ 

.በደንብ እስኪሻለው 15 ቀን ፈጀበት..የሆነውን ነገር እና ፍቅረኛውና ወንድሙ ምን እንዳደረጉት የነገረችው እቤቷ በወሰደችው በ3ተኛ ቀን ነበር..የመከዳቱን ነገር ከሰማ በኋላ ለቀጣዬቹ ሶስት ቀናት ህመሙ አገርሽቶበት ለምን ነገርኩት…..? ብላ እስከምትፀፀት ድረስ ነበር እንዲቆጫት ያደረገት..በኋላ ግን ቀስ በቀስ እያገገመ መጣ ..ሲቆይ በእሷ እንክብካቤ እና ማበረታታት ተሻለው….
👍9218🥰5😁4
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ

‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››

‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ

‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ  ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››

‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››

‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት  ጥሩ ነው››

‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ  ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››

‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››

‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት  ከቆየ በኃላ

‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት

‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››

‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››

‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››

በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት

‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….

የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ  አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››

‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ  ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው …  ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር   ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››

‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››

‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››

‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››

‹‹ስራው ይደርሳል››

‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››

‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››

‹‹እግራችን ወደመራን….››

ይቀጥላል
👍1129👎5👏2
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


//
የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ እና የፍቅር ትስሰር  ሙሉውን ታሪክ ለመጨረስ እራሱ አቅም አነሳት...ስለሱ ከማሰብ የሚያሰንፋት መስሎ እየተሰማት ነው….‹‹ለማንኛውም እስቲ  ታሪኩን ልጨርስ›› ብላ ተቀመጠች …ግን ታሪኩን ለመጨረስ  ንስሯ ያስፈልጋታል..እንደምታየው ደግሞ አሁን ጊቢ ውስጥ  ንስሯ አይታያትም …ብዙም ሳያስጠብቃት ከሄደበት ተመልሶ መጣ 

ቀጥታ ወደዛ ወደተለከፈችበት ታሪክ አመራች …አእምሯዋን ከንስሯ አዕምሮ ጋር በተለመደው መንገድ አቆራኘችው..አዎ አገኘዋቸው…ከከተማ እንውጣ ብለው ላንጋኖ ነው የሄድት …በሀይቁ ዳር በታነፀ ላውንጅ  የተዘጋ መኝታ ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡
//////
ህይወት ልክ እንደካርታ ጫወታ ነች…ይበወዝና ተጫዋች ለሆኑት  ኗዋሪዎቾ የሚታደል ዕጣ ፋንታ በሚሉት ምናባዊ ሀዲድ  የምትሸረብ…አጋጣሚ በተባለ የህይወት ሰንሰለታማ  ጉዞ ላይ በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛው ጊዜ አንዱ ካንዱ በመገጣጠም መላተም እና በሌላ ገጽ ላይ  በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ መዘግየት ተፈጥሮ ተፈላልጎም ሳይገናኙ  መተላለፍን በውስጧ የያዘች….

በጣርነው መጠን ማናገኝባት…ባመረትነው መጠን ማንሰበስብባት…በተመኘነው መንገድ ማንጓዝበት..እንደሎተሪ ዕጣ ብዙዎቻችን የምንከስርባት…የተወሰነው በማስተዛዘኛ የምንፅናናባት..ጥቂቶች ደግሞ እንደው ጠብታ  ላባቸውን በአልማዝ ተመንዝሮ እጃቸው ላይ የሚቀመጥላቸው …ውጥናቸውን አለም ጠቅላላ ተረባርቦ ከግብ የሚያደርስልቸው ከእርጥብ እድል ጋር የተፈጠሩ…ንግግራቸውን በደቂቃ አለም የሚያደምጥላቸው…እነሱ ለተከዙት አለም ተንሰቅስቆ የሚያለቅስላቸው …እንዲሁ መርቆ የፈጠራቸው አሉ፡፡ … እና ህይወት የካርታ ጫወታ ነች…የጫወታውን ህግ ግን ተፈጥሮዊ ብቻ አይደለም..ሰው ሰራሽም ጭምር ነው … 
ይሄንን ሀሳብ ያሰበችው ሰሚራ ነች ..ፍቅረኛዋ  መላኩ ደረት ላይ ጋደም ብላ እያሰላሰለች የምትገኘው፡፡እንዴት እንዲህ ልሆን ቻልኩ....?እንዴት ከበሽተኛዬ ጋር ፍቅር ውስጥ ገባሁ…...?አጋጣሚው ነው ወደዛ የገፋኝ ወይስ እራሴ ነኝ ፈቅጄ እና አስቤ ወደዚህ ደረቱ ላይ ወደተጋደምኩት ልጅ ልብ ውስጥ የገባሁት…...?

‹‹ምን እያሰብሽ ነው..?››ድንገት በጠየቃት ጥያቄ ለውስጥ ጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ  አቋረጠችው፡፡

‹‹መቼ ጥለህኝ እንደምትሄድ እያሰብኩ ነው››አለችው…ለምን እንደዛ እንዳለችው ለራሷም አልተገለጸላትም… ..ምክንያም እያሰበች ያለችው ያንን እንዳልሆነ እሷና እግዚያብሄር ያውቃሉ….ሳታስብ ከንፈሯ ላይ የመጣላት ድንገታዊ መልስ የእውነት ስጋቷ አይደለም ማለት ግን አይቻልም…

‹‹የት ነው ጥዬሽ የምሄደው..?››

‹‹ወደኑሮህ ነዋ››

‹‹ኑሮ ማለት እኮ  የህይወት ደስታሽ የሚመረትበት ቦታ ነው….ማንም ሰው በህይወቱ የሚባክነው ያንን ቦታ ፍለጋ ነው…የደስታው ምንጭ የሚፈልቅበትን ጥግ ለማግኘት …የሰው ልጅ ስኬትም የሚለካው በዚህ ነው…እና እኔ እድለኛ ነኝ .ብዙም ሳለፋ በተዐምራዊ አጋጣሚ አንቺን አግኝቼያለሁ….እንዳገኘውሽ ያወቅኩት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በቃ ስትስቂ ልቤ ትቀልጣለች…ትንፋሽሽን ወደውስጤ ስስበው በሰውነቴ ውስጥ በስብሰው  ያበቃላቸው ሴሎቼ እንኳን መልሰው ህይወት ሲዘሩ ራሱ ይታወቀኛል…..ከጎኔ መኖርሽን ሳይ ዓለም ጠቅላላ ተሰብስባ ከእጄ የገባች ይመስለኝና ልቤ በኩራት አብጣ ልትፈነዳ ትደርሳለች..እና ከአንቺ ተለይቼ መሄድ ማለት ወደባዶነት ሸለቆ ተወርውሮ መከስከስ ማለት እንደሆነ ሚጠፋኝ ይመስልሻል …...?አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከንቺ ውጭ ኑሮ ማለት ሲም ካርድ የሌለው ባዶ የሞባይል ቀፎ መሆን ማለት ነው…..››

ከትከት ብላ ሳቀች..ኪ…ኪ..ኪ…እንዴ ‹‹ነገሩን ሁሉ እኮ ስነጽሁፋዊ አደረከው…ከእኔ ከመገናኘትህ በፊት ነጋዴ ነበርኩ ብለሀኝ አልነበር እንዴ..?››

‹‹አዎ በጣም ጎበዝ ነጋዴ ነበርኩ…ምን ተፈጠረ..?››

‹‹አይ ንግግርህ የደራሲ እንጂ የነጋዴ አልመሰለኝ አለኛ…..››

‹‹አታውቂም እንዴ..? ፍቅር እና ችግር ያፈላስፋሉ እኮ….!!!››

‹‹አይ ጥሩ….ለማንኛውም የቀልድህንም ቢሆን በሰማሁት ነገር ደስ ብሎኛል….ምነው በተናገረው መጠን ሊያፈቅረኝ በቻለም ብዬ ተመኝቼያለሁ››

ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ አነሳትና እሱም ከተጋደመበት ቀና ብሎ ተቀመጠ… ወደእሷ ዞሮ አይን ዓይኗን እያየ‹‹አላመንሺኝም እንዴ ..? የምሬን ነው የተናገርኩት….በጣም ነው ያፈቀርኩሽ ..ወደፊት ማግባት የምፈልገው አንቺን ነው….የልጆቼ እናት ላደርግሽም እፈልጋለሁ….. ››
አንገቷን ወደእሱ ዘንበል አድርጋ እጆቾን በመዘርጋት ተጠመጠመችበት ..‹‹በጣም ነው የማፈቅርህ አንተን ስላገኘው እድለኛ ነኝ››
…..
‹‹እሺ አሁን ወጣ ብለን  ቢች ዳር ዘና እንበል…..››አላት በሀሳቡ ተስማማችና ተያይዘው ወጡ…
ላንጋኖ ሀይቅ ላይ ያረፈችው የማታዋ ጀንበር ልዩ ህብረቀለም እየረጨች ስትታይ ለአካባቢው ልዩ ውበት አልብሳዋለች…. ቢች ዳር ኳስ የሚጫወቱ አሉ..ሀይቅ ውስጥ ገብተው የሚዋኙን የሚንቦጫረቁም ጥቂት አይደሉም…… በአካባቢው ደስታ ተመርቶ የሚታደል ወይንም ከንፋሱ ጋር ተቀላቅሎ አየሩን እየሞላው በስፍራው ያለው ሰው ሁሉ እየማገው የሚፈግና የሚደሰት ይመስላል፡፡

‹‹ትዋኚያለሽ …..?››

‹‹አረ ይቅርብኝ …ዝምብለን እዚህ ሳሩ ላይ ቁጭ እንበልና  በማየት እንደሰት..ባይሆን ቆይቶ ከነሸጠኝ አብረን እንገባለን›› አለችውና ቁጭ አለች ..ተከትሎት ከጎኗ ቁጭ አለ…….

ይቀጥላል
👍129👎1514👏6😁2🔥1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን  መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን  ጠባብ  የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው… መላኩ ቶሎ ብሎ የሰሚራን ክንድ ጨምድዶ ያዘና ጎትቶ ከጀርባው በማድረግ አሱ የግንብ ግድግዳ ሆኖ ከፊቷ ተገተረ…..

‹‹አይ አይ ….ካንተ በፊትማ እሷን ነው መግደል  የምፈልገው››

‹‹አይ እንደጀመርከኝ እኔኑ ጨርሰኝ….››

‹‹አይ መጀመሪያማ እንደህጻን ያታለለቺኝን ይቺን ጊንጥ ፊትህ ደፋትና አንተን አስከትላለሁ..››

‹‹ለመሆኑ እዚህ ድረስ እንዴት ተከትለኸን መጣህ..?››መላኩ  ነው ድንጋጤውን እንደምንም   ተቆጣጥሮ  በጣም የገረመውን እና ያልጠበቀው ነገር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ የጠየቀው፡፡

‹‹እግዜር ነው እጄ ላይ የጣላችሁ..እኔማ ሀገር ሰላም ነው ብዬ ልዝናና ነበር እዚህ የመጣሁት
…ግን ሞቶ አልቅሼ በእጄ አፈር
አልብሼ ቀብሬዋለሁ ያልኩት ወንድሜ እዚህ ዘና ብሎ አለሙን ሲቀጭ አገኘሁት…..ለዛውም ገደልኩልህ ብላ 6መቶ ሺ ብሬን ቅርጥፍ አድርጋ ከበላች ቀጣፊ ሴት ጋር…››መለሰለት ሰሎሞን
መላኩ እየተንቀጠቀጠ መናገር ጀመረ‹‹ገራሚ ነህ …አንደኛ በዚህ አፍህ የእግዜያብሄርን ስም ማንሳትህ ትልቅ ድፍረት ነው..እግዚያብሄር እኮ ፍትህ ነው..እግዚያብሄር ፍቅር ነው..እግዜያብሄር የበጎነት የመጨረሻው ጥግ ነው…ታዲያ በምን ስሌት  እግዚያብሄር አንትን ረድቶህ እኛን አንተ እጅ ላይ ይጥለናል ብለህ ታስባለህ …..?ማይሆነውን…..!!!ደግሞ ገንዘቤን የምትለው…ገንዘቡ እኮ የእኔው ነው…ደግሞ እሷ እንደአንተ እና እንደዛች ሴት ከንቱ አትምሰልህ….ገንዘቡን የእኔ መሆኑን በመረዳት ሳትሰስት ሰታኛለች…››
‹‹በቃ ከዚህ በላይ ልፍለፋህን ልስማ  አልፈልግም …..አሁን አይኔ እያየ ሁለታችሁም በአንድ ሳጥን ተዳብላችሁ ትቀበራላችሁ..እዚህ የጀመራችሁት ፍቅር እዛ ያለከልካይ ትኮመኩሙታላችሁ…››ብሎ ወደነሱ የቀሰረውን ሽጉጡን ቀጭ ቀጭ አድርጎ አቀባበለ….ይሄ ቅጭልጭልታ ቀድሞ የተሰማው ለሰሚራ ጆሮ ነበር..ያው ሴት ከወንድ በላይ ንቁ አይደለች….ከሰማችው ድምጽ ጋር እኩል ተሸከርክራ መላኩን  ገፍታር ከፊቱ ተደቀነች.. ሞቱን ቀድማ ልትሞትለት….ተሳካላት…..በዛ ቅፅበት   ዶ..ዶ..የሚል አደንቋሪ ድምጽ ተሰማ  …ወዲያው የብዙ ሰው ጩኸት እና  የሚሮጡ የሰው ኮቴ …ከዛ ሰሚራ ዝልፍልፍ ብላ መላኩ  እጁ ላይ ገንደስ ስትል ይዟት ወደመሬት ሲወርድ ..ሁሉ ነገር የሚሆነው በደመነፍስ ነበር….
////
…ሰሚራ ድንገተኛ እና ያልታሰበ ከነበረው ከዛ አደጋ ከወራት  ህክምና በኃላ ዳነች…መላኩም ወንድሙንና  እና የበፊት ሚስቱን በግድያ ሙከራ እና በእምነት ማጉደል ከሶ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ  ወህኒ እንዲወረወር አድርጎ ንብረቱን መልሶ ተቆጣጥሯል….አዎ እዚህ ድረስ ያሉ ነገሮች ጥሩና መልካም የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ…እንግዲህ ይህ  ድርጊት የተከወነው ከአምስት አመት በፊት ነበር…

በመላኩ ወንድም በሰለሞን  ሽጉጥ ተተኩሶባት ፍቅረኛዋን ቀድማ በተመታችበት ወቅት ከተተኮሱባት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንዱ ሽጉጥ በደረቷ ሌላው ደግሞ በጭነቅላቷ ነበር የገባባት…እና በወቅቱ በደረቷ የገባቸውን የጥይት ቀላሀ በቀላሉ ማውጣት ቢቻልም የጭንቅላቷን ማውጣት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነበር…፡፡
አስቸጋሪነቱ ጭንቅላቷን ቀዶ ጥይቷን  መዞ ማውጣቱ አይደለም….የከበደው ጥይቷ የተቀረቀረችበት ቦታ እንጂ… ጥይቷ ከወጣች የሰሚራ የጤና ሁኔታ በቋሚነት እንደሚበላሽ ….ትውስታዋ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ከዛም አልፎ የማሰብ አቅሞንም እንደሚጎዳው ከፍተኛ ስጋት ስለጣለባቸው….ለጊዜው  ባለበት እንዲቆይ… በየጊዜው የቅርብ የህክምና ክትትል እንድታደርግና በሂደት የሚሆነውን ለማድረግ ተወሰኖ ነበር..
ለአንድ አመት  በየወሩ እየተማመላለሰች ህክምናዋ በመከታል በጥንቃቄ  ካሳለፈች በኃላ ምንም የሚሰማት እና የሚለወጥ ነገር ስላልነበረ ቀስ በቀስ እየተዘናጋችና ምንም አይፈጠረም በሚል እምነት ክትትሉን አቆመች ….
በዛን የጊዜ ክፍተት ውስጥ…መላኩ በንግዱ አለም ከበፊቱ የበለጠ ተሳክቶለት ከሰሚራ ጋር ያየነበረው የፍቅር ትስስር ይበልጥ እየጎመራ ሄዶ ወደጋብቻ ሊሸጋገር ወራቶች ሲቀሩት….ግን ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ድንገት ወድቃ  ሀኪም  ቤት ዳግመኛ ለመግባት ተገደደች…  ምርመራ ባደረገችበት ጊዜ በጭንቅላቷ መሀከላዊ ስፍራ የተቀረቀረችው ጥይት ብቻ ሳትሆን በፊት ያልነበረ ጎን ላይ  አስደንጋጭ እጢ ተፈጥሮ  ታየ..ሀኪሞቹ ተደናገጡ ..ተስፋ እንደሌላት እና ማድረግ የሚችሉት ብዙም ነገር እንደሌለ ለመላኩ ሲነግሩት አንጠልጥሎ ወደውጭ ሀገር ይዞት ሄደ….ግን የረፈደ ውሳኔ ነበር…ጥይቷ እንዲወጣላት ማድረግ ተቻለ ..እጢውም በጨረር ህክምና እንዲሞሞ ማድረግ ብዙም ከባድ አልነበረም…ይ ሁሉ ቢሆን ግን በህይወት ልትቆይ የምትችለው በዛ ቢባል ለቀጣዩ አንድ ወይም ሁለት አመት እንደሆነ አስምረው ነገረዋቸዋል…ከዛ በኃላ ወይ ትሞታለች ወይ ደግሞ በድን ሆና በህይወት እና በሞት መካከል ተንጠልጥላ ለአመታት ትኖራለች…..ሚሻለው ግን ወዲያው ብትሞት ነው…. የሀኪሞቹ ምክር ነበር፡፡ …የምርመራው ወጤቱ ለሁለቱም  ሰቅጣጭ ነበር…

እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኛሞች …ሳቃቸው ከእንባ የተቀላቀለ፤ደስታቸው ከፍራቻ የተጋባ፤ተስፋቸው ጨለማ የገደበው ከሆነ እና በዚህ ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል እና ንስሯ ባመጣላት ታሪክ መሰረት በቀደም የዋና ገንዳ ውስጥ ያገኘችው ፤የፈተነችው እና የፎከረችበት ወጣት ታሪክ እንደዚህ ነው…ታማኝ የሚሆነውም ለዚህች ፍቅረኛው ነው…..አግቢኝ እና ውለጂልኝም የሚላት ይችኑ በጀርመናዊዎቹና በአሜሪካኖቹ ሀኪሞች የ አመት ጊዜ ብቻ የተቆረጠላትን ወጣት  ነው….
ኬድሮን አሰበች‹‹እና ምን ላድርግ ….?እንዳለች ልተዋት….? ትውለድለትና ትሙት…. ከዛ እኔ ለእሱ ሚስት ለልጁ ደግሞ እናት ልሁን…..?ነው ወይስ ላድናት……..?›ከህሊናዋ ጋር ከባድ ፈተና ገባች፡፡በእርግጠኝነት   ንስሯ ከረዳት ለእሷ መዳኛ የሚሆን መድሀኒት ሌላ የአለም ጥግ ማሰስ ሳያስፈልጋት …ከዚህችው ከቅድስቲቷ የኢትዬጵያ ምድር  ቆፍር ቆፈር አድርጋ  ስር ማስ ማስ ፤ ቅጠል በጠስ በጠስ በማድረግ  ልታድናት ትችላለች..፡፡ግን  ለምን ታደርገዋለች…..?ለማንኛወም ጊዜ ወስዳ ልታሰብበት ከራሷ ጋር ተስማማች….

ይቀጥላል….
👍12821👎4😁2🔥1👏1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


////
እየሄደች ነው… ልታናግረው…፡፡ ለምን እሱን ማናገር እንደፈለገች አታውቅም፡፡ ምን አልባት ዳግመኛ አጠገቡ ልትቆምና ያንን ወንዳወንድ ቁመናው እና ቆንጅዬ ባሪያ የሆነ መልኩን በቅርበት ለማየት ፈልጋ ሊሆን ይችላል….ናፍቋትም ሊሆን ይችላል፡፡ 

ንስሯ የት እዳለ በነገራት መሰረት ቀጥታ ቤቱ ነው የሄደችው..የውጩን የጊቢ በር መጥሪያ ስትጫን ዘበኛው ነበር የከፈተላት…‹‹ከመላኩ ጋ ቀጠሮ ነበረኝ ቤት እየጠበኩሽ ነው ብሎ ደውሎልኝ ነበር..?››ብላ ቀላመደች… ዘበኛው ያልተለመደ ነገር ሆኖበት .. ግራ እንደመጋባት አለና በመጠኑ ካቅማማ በኃላ እንድትገባ  ፈቀደላት…
ቀጥታ ቤተኛ እንደሆነ ሰው የተንጣለለውን ግቢ ሰንጥቃ ባለአንድ ፎቅ ከሆነው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት  በረንዳው ላይ ደረሰች… የሳሎኑን በር ገፋ ስታደርገው ተከፈተ…የቀኝ እግሯን አስቀድማ ግራዋን አስከትላ ወደውስጥ ከገባች በኃላ  ወደኃላ ዞሯ በራፉን አንኳኳችው…
‹ከገቡ በኃላ ማንኳኳት ከገደሉ በኃላ ማዘን አይነት አይደለም እንዴ…..?››እራሷው በራሷ ነው የጠየቀችው
መላኩ የሳሎኑ መአከላዊ ስፍራ ላይ  ካለችበት ወደውስጥ 4 ወይም 5 ሜትር ያህል ርቆ በመገረም አፍጥጦ እያያት ነበር….
ማንኳኳቷን ስትቀጥል

‹‹አቤት››የሚል ድምጽ አሰማ

‹‹መግባት ይቻላል..?››

‹‹ገብተሻል እኮ ››

‹‹እሺ ካልክ›› ብላ ቀጥታ የሳሎኑን በር መልሳ ዘግታ ወደእሱ አቅጣጫ አመራች ….በተገተረበት ስለማንነቷ በመመራመር ይመስለል ፈዞ እንደቆመ በስሩ አልፋ ልክ እንደቤተኛ ሶፋው ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች….መጣና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ

‹‹አውቅሻለሁ ልበል..?››

‹‹እኔን የመሰለች ቆንጆ ልጅ እንዴት ልትረሳ ትችላለህ..?››

‹‹ማለት..?››

‹‹ጎበዝ የዋና ተማሪህ ነበርኩ ብዬ ነዋ››

…ድንገት እንደበራለት ሰው በመደነቅ ‹‹እንዴ አንቺ እብድ ..እቤቴን ደግሞ ማን አሳየሽ..?›› አለት ‹‹ቀላል ሰው  አይደለሁም ብዬህ ነበርኮ..?››

‹‹አረባክሽ.. ፉከራሽን እኮ አየነው..እኔማ አንተን ማሳሳት ካቀተኝ እንጠለጠላለው ብለሽ ስለነበረ..በቃ ይቺ ልጅ አልሆንላት ሲል እራሷን አጥፍትለች ማለት ነው..ምን አይነት ለቃሏ ታማኝ ልጅ ነች ብዬ ሳደንቅሽ ነበር የሰነበትኩት፤ለካ ዝም ብለሽ ጉረኛ ነገር ነሽ..?››

‹‹አንተን ማውጣት አቅቶኝ ሳይሆን አሳዝነኸኝ ነው የተውኩህ ››

ግድግዳውን ሰንጥቆ በመውጣት ውጭ ድረስ ለመሰማት ኃይል ባለው አይነት አንቧራቂ ሳቅ ሳቀ‹‹አሳዘንኩሽ…..?ቀልደኛ ነሽ››

‹‹ቀልድ አይደለም…የዛን ቀን የሄደክው ከፍቅረኛህ ጋር ወደሆቴል አልነበር…..?ስለ ጋብቻ ስታወሩ አልነበር....?እንድታገባህ ስትለምናት አልነበር…..?እሷ መጋባቱ ቀርቶባችሁ እስክትሞት ድረስ የቀራትን ህይወት እንደዚሁ እንድታሳልፉ ስትለምንህ አልነበር…..?ከመሞቷ በፊት ካላገባችህ እና መጽናኝ የሚሆን ልጅም ካልወለደችልህ በሞተች ቀን አብረሀት እንደምትሞት እየነገርካት ስትላቀሱ አልነበር……..?››

ይሄንን ስትነግረው እነዛ የኮከብ ክፋይ የሚመስሉ  ደማቅ አይኖቹን ከወዲህ ወዲያ በመገረም እያሽከረከራቸው ነበር…..

‹‹አንቺ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ስታዳምጪኝ ነበር እንዴ..?››በንዴት ጡንቻው ውጥርጥር ሲልና … ልነቃት አልነቃት እያለ ከውስጡ ጋር ሙግት እንደገተመ ከሁኔታው ያስታውቃል….

‹‹አይደለም …ክፍል ውስጥ አልነበርኩም…ግን በአካል ባይሆንም ክፍል ውስጥ ገብቼ  እናንተን ምታዘብበት ሌላ ዘዴ ነበረኝ››

‹‹ምን ..?ካሜራ ..?››
‹‹አይደለም…ምንነቱን ቀስ ብዬ ነግርሀለሁ…አሁን ወደመጣሁበት ጉዳይ እንግባ››

‹‹ወደመጣሁበት ጉዳይ .. ..?በይ ሳትዋረጄ በመጣሽበት እግርሽ ሹልክ ብለሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ..››ከመቀመጨው ቀድሞ ተነሳ…

‹‹ሁለተኛ እንኳን እቤቴ እኔ ባለሁበት አካባቢ  በድንገት ባገኝሽ እወነቴን ነው አጠፋሻለሁ…ሲጥ አድርጌ ነው የምገልሽ….››

ዘና ብላ እንደተቀመጠች መልስ መመለሷን ቀጠለች  ‹‹ዝም ብለህ አትፎክር…በቁጣ እያንቧረቁ መናገር እና ፊትን ማጨማደድ የምትለውን አይነት ጭካኔ እንዲኖርህ አያግዝህም››

‹‹ምን ማለት ነው..?››

‹‹እንኳን እኔን ምንህም  ላይ ያልደረስኩትን ልጅ ይቅርና ሰላምን እንኳን እንደዛ በድላህ ፍቅህን ረግጣ የገዛ ወንድምህን በማግባት ስታወድምህ   ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ምንም ልታደርጋት  አቅም አላገኘህም፡፡››
ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና  ተንበርክኮ አንገቷን በማነቅ እያረገፈገፋ‹‹ማነሽ …....?አንቺን ማነው የላከብኝ....?ማነው ንገሪኝ..?››

‹‹ማንም …ምን አልባት የምታመልከው አምላክ ሊታረቅህ ፈልጎ ይሆናል…ምን አልባት እስዛሬ የፀለይከው ፀሎት አምላክ መንበር ደርሶ መልስ የማግኛህ ጊዜ ደርሶም ሊሆን ይችላል…››
፣እጁን ከአንገቷ ላይ መንጭቃ በማላቀቅ ገፈተረችውና …ዝርፍጥ ብሎ ወለሉ ላይ በቂጡ ቁጭ አለ …እዛው ባለበት አፍጦ እሷን ከማየት በስተቀር ለመነሳት አልሞከረም

‹‹ሰሚራን ባድንልህ ምን  ታደርግልኛለህ..?››

‹‹ምን  እየቀባጠርሽ ነው…...?ደግሞ በእሷ ልትቀልጂብኝ ነው..?››

‹‹አይደለም ..ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኝለህ..?››

‹‹ቅጠል አሽተሸ በመቀባት የምታድኚው ቁስል… ምች መድሀኒት ወይንም ጅንጅብል ጨቅጭቀሽ ከሻይ ጋር አፍልቶ በመጋት  የምታድኚው  ጉንፋን በሽታ  ያመማት መሰለሽ  እንዴ..?››
‹‹አውቃለሁ…ለአመታት በጭንቅላቷ ቆይቶ የነበረው ጥይት እና የጭንቅላት እጢ ተከትሎ…….››
አላስጨረሳትም ‹‹…በፈጠረሽ ማን ነሽ ?ምንድነው ምትፈልጊው....?ይሄን ሁሉ ገበናችኝን ስንት አመት ብትሰልይን ነው ማወቅ የቻልሺው..?››

ጥያቄውን ችላ በማለት  የራሷን ጥያቄ ደግማ ጠየቀችው

‹‹ካዳንኩልህ ምን ታርግልኛለህ..?››

‹‹ እኮ እንዴት ነው የምታዲኚያት…..?የጀርመንና አሜሪካ ጠበብቶች ያቃታቸውን አንቺ እንዴት ብለሽ..?››

‹‹እኔ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ …››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እንድታምነኝ…አንድ አንተ ብቻ የምታውቀው ታሪክ ልንገርህ…እንደውም ለምን ዛሬ ያየኸውን ህልም አልነግረህም ..…››

ንገሪኝም ተይው ማለት አቅቶት በግራ መጋባት ስሜት እየዋለለ ዝም ብሎ እንዳፈጠጠባት ፈዞ ቀረ…

ጣና ሀይቅ መሀል ላይ ያለች ትንሽ ደሴት ትመስልሀለች….እሷን ከብዙ የሀገሪቷ ሀብታሞች ጋር ተወዳደረህ በጫረታ በማሸነፍ ትገዛና …በጣም ውብ የሆነ በባህላዊ መንገድ እጽብ ድንቅ ተደርጎ የታነፀ ቤት ትሰራበታለህ…በዛች ደሴት ላይ አንተ ከሰራሀት ቤት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቤት የለም፤ደሴቱ ሙሉውን በቡና ተክል፣በሙዝ፣በብርቱካን፣በመንደሪን፣በአፕል እና  በመሰሰሉት የሚበሉ ፍራፍሬዋች የተሞላች ነች…አዕዋፍት እና የዱር እንስሳትም  ከደኑ ጋር ስመም ፈጥረው ተፈጥሮን አድምቀው እና በተፈጥሮም ደምቅው የሚኖርበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ድስታ ተሰምቶህ ይሄንን ስጦታ ላዘጋጀህላት ለሰሚራ ትሰጣታለህ…

‹‹ሰሚርዬ ቀሪ ህይወትሽን ምንም እንኳን አጭር ብትሆንም በደስታ የተሞላች እድትሆን ፈልጋለሁ…በዛ ላይ እዚህ ከእኔ እና ከተፈጥሮ ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ ወደ ሌለበትና ወደማይኖርበት ቦታ ሳመጣሽ ቀሪ ዘመንሽን የብቻዬ ብቻ እንድትሆኚ በመፈለግ እና በመሰሰት ነው…ይቺ ስፍራ የእኔ እና የአንቺ ገነት ነች››ትላታለህ፡
👍766😁3🥰2
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹ግን ምን አይነት ዳቢሎስ ነሽ..?››ሙትት ባለ ድምጽ

‹‹ዳቢሎስ እንኳን አይደለሁም…. ምን አልባት የዳቢሎስ ልጅ ልሆን እችላለሁ…ግን የምትወዳትን ልጅ ላድንልህ እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት .. ..?እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር  ዳቢሎስ ያሰኛል እንዴ..?››

‹‹አዎ ዳቢሎስ ፍቅር አያውቅም..ፍቅር የማያውቅ ደግሞ ምንም ነገር በነፃ መስጠት አይችልበትም፤ለሰጠሸ ጥሩ የሚመስል ነገር ሁሉ ተመጣጣኝ የሆነ መከራና ስቃይ ያስከፍሉሻል…››

‹‹አልገባኝም..?››

‹‹ለምሳሌ …ያለፋሽበትን ገንዘብ ተመኝተሸ ስጠኝ ብትይው በደስታ ነው የሚሰጥሽ፤የገንዘብን ባለቤት ግደይና ነጥቀሺው ውስጂ ብሎ መንገድን እና ብልሀቱን ያሳይሻል…ከዛ ትገድይና ገንዘብን ታገኚያለሽ ሀብታም እና በፀፀት የሚሰቃይ ሰው ትሆኚያለሽ፡፡አንቺም ፍቅረኛህን ላድንልህ..እና ልንጠቅህ እያልሺኝ ነው…፡፡ያው እኮ ነው በስጋ ከመሞት ታድኛታለሽ ከዛ ፍቅርን በመንጠቅ በመንፈስ ትገያታለሽ…እኔንም እንደዛው፤ታዲያ አንቺ ዳቢሎስ ካልሆንሽ ማን ይሆናል....?››አላት ምርር ባለ የመጠየፍ ንግግር፡

‹‹እሺ እንግዲያው ይቅርብህ…ሁለተኛ አረብሽህም፤ደህና ሁን››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እንደ አመጣጧ ሳሎኑን ሰንጥቃ  በርፍን ከፍታ ወጣች እና መልሳ ዘግታ መንገዶን ቀጠለች…የግቢው አማካይ ስፍራ ስትደርስ   ነበር የበር መከፈት እና ‹‹ማን ነበር ስምሽ..?››የሚል  ከሙታን  መንፈስ የወጣ የሚመስል ድምጽ  ከጀርባዋ የተሰማው

እርምጃዋን ገታችና ቀኝ ኋላ ዞራ ‹‹ሶፊያ››ስትል መለሰችለት
‹‹ከቻልሽ አድርጊው..አድኚልኝ ፤ተስማም..ቼ…ያ….ለሁ››አላትና ከእሷ ምንም አይነት መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን መልሶ ወደውስጥ በመግባት  በራፉን በመዝጋት ከእይታዋ ተሰወረ ..

‹‹እውነትም ዳቢሎስ ነገር ነኝ እንዴ..?….ምን እያረግኩ ነው…...?››ስትል አሰበች፡፡ቅድም እዚህ እሱ ጋር ስትመጣ ይሄንን ለማድረግ አልነበረም…ዝም ብላ ፍቅረኛው እደምታድንለት ልትነግረው እና በተስፋ ልታስፈነጥዘው ብቻ ነበር ፍላጎቷ…ያደረገችው ግን ተቃራኒውን ነው..በደስታ እና ሀዘን መካከል ነፍሱ ተንጠልጥላ እዲሰቃይ ፈረደችበት …

‹‹የእውነት ግን ያልኩትን አደርገዋለሁ…..?እሷን አድኜ እሱን ነጥቄያት አገባዋለሁ…..?.ማግባትስ በእውነት እኔ የምፈልገው ነገር ነው....?ወይስ በስቃዩ ለመደሰት…..?››ብላ ተደራራቢ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡

ለማንኛውም ዛሬ ማታ ከንስሯ ጋር ለመብረር አቅዳለች….ለልጅቷ የሚሆን መድሀኒት የት እደሚገኝ ፍንጩን አግኝታለች ….ቦረና ባሌ መካከል መዳ ወላቡ አካባቢ ነው ለሰሚራ ፈውስ የሚሆነው መድሀኒት ሚገኘው….፡፡ 
የየትኛውም ሀገር አቨዬሽን  የማይቆጣጠረው በረራ ላይ ነች፡፡ግን ደህንነቱ ፍፅም የተረጋገጠ በረራ ….ከየትኛውም አይሮፕላን ጋር እጋጫለሁ ወይም አሞራና ወፎች ተላትመውብን አቅጣጫ ያስቀይሩናል…ነዳጅ አልቆ ወይም ሞተር ጠፍቶ ችግር ላይ እንወድቃለን  ብላ የማትሰጋበት ዥዋዝዌ የመጫወት ያህል ዘና የሚያደርግ በረራ…. ይሄን አይነት በረራ ሳታካሂድ ሶስት ወራት ስላለፋት ናፍቆት ነበር…
እየሄድ ያለው ከአዲስ አበባ ወደ መዳወላቡ ነው ፡፡መዳወላቡ የት እንደምትኝ መገመት ካቃታችሁ..ኬንያ ድንበር አካባቢ ብትሉት አካባውን ለመገመት ይቀላችኋል ፡፡እየበረሩን ያለነው ከንስሯ ጋር ነው…፡፡እሱ ክንፎች  መሀከል ዘና ብሎ ቁጭ ብላለች….
ከመሬት ያሉበትንን ከፍታ ገምታ ለመናገር አትችልም ..…ግን ትንሽ ግልፅ ለማድረግ  ምሳሌ ለመስጠት ያህል በዚህ ሰዓት ( ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው) ሻሸመኔ ከተማ አካባቢ ደርሰዋል..እላይ ባሉበት ከፍታ ላይ ሆነው ከተማዋ ቁልቁል ስያዮት ከእሷ ቤት ጊቢ ብዙም ሰፍታ አይታያትም….ጭልጭል የሚሉ አንድ ቦታ የተሰበሰቡ መብራቶች ናቸው እንደምልክት የሚታዩት..
የሚፈልገበት ቦታ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት…ከአውሬ ድምጽ እና ከጥቅጥቅ ጨለማ በተጨማሪ ብዙ ድምጽ ይሰማል..የደረቁ ቅጠሎች በንፋስ ተገፍተው ከዛፍ ሲወድቁ ይሰማል…..ካረፍበት ተራራ ወገብ ላይ እየፈለቀ ቁልቁል ወደ ታች እየተምዘገዘገ የሚወርድው  አረፋ ደፋቂ ፏፏቴ ድምጽ በጣም ይሰማል…የብዙ አውሬዎች መጣራራት እና ማስካካተ ድምጽ ይሰማል…. ….

‹‹የቱ ነው መድሀኒቱ….?››ጠየቀችው ንስሯን 
አንድ ከእሷ ቁመት ብዙም የማትበልጥ ቋጥኝ ላይ ዘና ብሎ ቁጭ በማለት ዝም አለት
የሚያስበውን ማወቅ ስለፈለገች..‹‹አዕመሮህን ክፈትልኝ…..….?››ስትል ጠየቀችው… ቁልፍ አደረገና ችላ አለት ..አንዳንዴ እንዲህ ግግም ብሎ ያስቸግራታል..

‹‹ምን እያሰብክ ነው… ….?ለሊቱን እዚሁ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እናሳልፍ እንዴ…….?››ጠየቀችው
አዕምሮው ውስጥ ሰርስሯ እንዳትገባ እንደከረቸመባት በሹፈት መልክ አንገቱን አሸከረከረባትና ጀርባውን ሰጣት…በቃ ምንም ማድረግ አልችለችም …እስኪለቀው ድረስ መጠበቅ እንዳለባት ስለተረዳች እራሷን አረጋጋች..የሆነ የሚጠብቀው ወይም ለጊዜው ያልጣመው ነገር አለ ማለት ነው ስትል አሰበች..ተወችውና አካባቢውን በመቃኘት ዘና ማለት ጀመረች..
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ስታይ.. በአካባቢው በቅርብ ርቀት  ከሚገኙ የገጠር መንደሮች ጭል ጭል የሚሉትን  የኩራዝና የፍኖስ መብራቶችን  ..ወደ ላይ አንጋጣ የዘወትር አጫዋቾን ጨረቃን ስትመለከት ሰዓቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆነ …ንስሯ ፀባይ ላይ ምንም የተለወጠ ነገር የለም …አሁንም የነበረበት ቋጥኝ  ላይ በተመስጦ… አረ እንደውም የፀሎት በሚመስል ሁኔታ ያለእንቅስቃሴ አንገቱን ወደጨረቃዋ አንጋጦ ተደምሟል ..
የተቀመጠችበት የወደቀ የግንድ ጉማጅ ቂጧን ስላሳመመት ተነሳችና ቀስ እያለች እሾህ እንዳይቧጭራ እና አውሬ ጉድጋድ ውስጥ ተንሸራታ እንዳትገባ እየተጠነቀቀች ወደ ፏፏቴው ተራመደች… እንደደረሰች ሙሉ ልብሷን ፓንቷንም ሳታስቀር ውልቅልቅ አድርጋ ገባችበት… ፏፏቴው ከላይ ከአለቱ እየተላተመ መቶ ጭንቅላቷ ላይ ሲያርፍ ያለውን ኃይል መቋቋም አቅቶት ልትወድቅ ነበር.. ለጥቂት ነው በአቅራቢያዋ የጋጠማትን የግንድ ቅርንጫፍ ይዛ የተረፈችው‹‹..ደግሞ ውሀው እንዴት አባቱ ይሞቃል…….?››አለችና ድክም እስኪላት ድረስ ሰውነቷን እየተገለባበጠች አስመታችውና ወጥታ ልብሷን ለብሳ ወደ ንስሯ ተመለሰች፡፡
ስሩ እንደደረሰች  ከፊት ለፊቱ ቆማ በትኩረት አየችው…መልኩ ተለየባት… የሆነ አመድ ላይ የተንከባለለ አህያ መስሏል..እንዴ ምን ላይ ተንከባሎ ነው….?..እዚህ ሰውነት ላይ ነው እንዴ ተጭኜ የመጣሁት…….?ነው ወይስ እኔ ውሀ ውስጥ  ሳለው የሆነ ነገር ከሰማይ አመድ ነፋበት..….?አረ አመድ ብቻ አይደለምል  አንገቱንም መሸከም አቅቶታል…››ስለንስሷ ቴና ሀሳ ገብቷት መነብሰልሰል ጀመረች

‹‹ምን ሆንክ….?››
አዕምሮውን ቀስ እያለ ከፈተላት፡፡እሷም እንደምንም እራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ወደአዕምሮው ገባች…አዎ መድሀኒቷን አየቻት …እሷ ካለችበት በ5 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች…የተለየች አይነት ልዩ ተክል ነች ….?የአንድ ሰው የማህል ጣትን ነው የምታክለው…የበቀለችው ሌላ ትልቅ የብሳና ዛፍ ላይ ጥገኛ ሆና ነው….የሆነ ሀመራዊ አይነት የተለየ ብርሀን  ትረጫለች…
👍7112😁1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

‹‹የአባትሽ ዘመዶች ነው ያልከው….?››

‹‹አዎ የአባትሽ ወገኖች … ይሄንን ተክል በምድር ላይ  እንዲበቅል አድርገው ሲበትኑት ለመድሀኒትነት እንዲሆን አስበው አይደለም…››

‹‹እና ለምድነው….?››

‹‹አንቺን ለማግኘት….››ብሎ ጭራሽ ግራ አጋባት

‹‹እንዴት አድርገው ነው እኔን የሚያገኑኝ…….?ደግሞ የት ናቸው….?››

‹‹የት እንዳሉማ ታውቂለሽ….››

‹‹እና እንዴት ነው የሚያገኙኝ ….?››

‹‹ልክ  ያቺን ተክል ስትቀነጥሺ ቀጥታ መልእክቱ እነሱ ጋር ይደርሳል››

‹‹እወነትህን ነው….?››ውስጧ ፈነጠዘች..አባቷ የማግኘት ምኞት ሳታስበው አዘለላት..የእናቷን እውነት የማረጋጋጥ ፍላጎት…

‹‹እና አሪፍ ነዋ..ያለሁበትን ካወቁ ይመጣሉ አይደለ..….?አባቴም ይመጣል አይደል….?››ጠየቀችው

‹‹አይ አባትሽ በጥብቅ እስር ላይ ስላላ መምጣት አይችልም.. ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ ሳይፈቀድለት  ከሰው ጋር በፍቅር በመቆራኘትና አንቺን ስለወለደ ይሄው ባንቺ እድሜ ሙሉ እንደታሰረ ነው››አንጀቷ ተላወሰ..በምድር ላይ ታስሮ ቢሆን ኖሮ  የፈጀውን ያህል   ይፍጅ  እንጂ   መንግስትንም ገልብጣ ቢሆን አባቷን ታስፈታው ነበር

‹‹እና ታዲያ ዘመዶቹም ቢሆን ይምጡ ምን  ችግር አለው….?››

‹‹ሚመጡት  አንቺን ለመውሰድ ነው››

ደስ አለት..ደነገጠችም ‹‹ወዴየት ነው የሚወስድኝ….?››

‹‹ወደራሳቸው አለም….››

‹‹እኔ መሄድ ካልፈለኩስ….?››
‹‹ፈለግሽም አልፈለግሽም ይወስዱሻል …ምንም አይነት ምደራዊ ኃይል አንቺን ከመውሰድ አያግዳቸውም….››

ለአምስት ደቂቃ በትካዜ  ውስጥ ገባች…ሌላ አለም የማየት ፍላጎት… አባቷን እና ዘመዶቹን የማወቅ ፍላጎት..ደግሞ ይህቺን ምድርስ….?

‹‹ቆይ ሄጄ ሁሉን ነገር ካየሁ በኃላ ተመልሼ ወደምድር መምጣት አልችልም….?››

‹‹አይመስለኝም… ብትመለሺም እንደዚህ ሆነሽ አይደለም…ሙሉ በሙሉ ተቀይረሽ.. ሙሉ በሙሉ እነሱን ሆነሽ..የእነሱን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው ሚሆነው.ያ በእነሱ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ነው.ከፈለጉ እስከወዲያኛው ዳግመኛ ምድርን ላትረግጪ ትችያለሽ፡፡››

‹‹በቃ ይሁን.. ለእኛም እዛ መኖር ይሻለናል..የተለየ ዓለም  እኮ አሪፍ ነው..ይቺን ዓለም እንደሆነ በተቻለ መጠን በርብረናታል…ምን ይቀርብናል….?››

‹‹እና ወሰንሽ››

‹‹አዎ ባክህ እንደውም አሪፍ እድል ነው››
እንግዲያው ተዘጋጂ… ከአምስት ደቂቃ በኃላ ሄደሽ መቀንጠስ ትችያለሽ..ከቀነጠስሽ በኃላ ግን አንድ ሳምንት ብቻ ነው በምድር የመቆየት እድል የሚኖርሽ… ልክ የዛሬ ሳምንት በዚህን ሰዓት ካለሽበት ቦታ መጥተው ይዘውሽ ይፈተለካሉ››

‹‹አንድ ሰምንት..አንድ ሳምንት ፈጠነ..ግን ቢሆንም ቀላል ቀን አይደለም….ብዙ ነገር እንሰራበታለን…እናቴን ሄደን እንሰናበታለን..የልጅነት ጎደኞቼን እሰናበታለሁ… አሪፍ ነው..አንድ ሳምንት ይበቃናል..››አለችና ወደተክሏ ተራመደች..
ደረሰችና ልክ ድፍን  6 ሰዓት ሲሆን  ከብሳናው ዛፍ ቅርንጫፎች መካከል  እጇን ዘረጋችውና ጨበጠችው… ቀነጥሰዋለሁ ስትል በእጇ ሟሞና እንደቅባት ተሙለጭልጮ ወደሰውነቷ ሲገባ ታወቀት… ደነገጠች የቀነጠስችው መስሏት ነበር… እጇ ላይ ግን ምንም ነገር የለም… እጇ  የተለየ ቀለም እያመጣ ነው ..ሀመራዊ እሳት መሰል ቀለም… በመላ ሰውነቷ እየተራወጣ ከተዳረሰ በኃላ አንዘርዝሮና አንቀጥቅጦት በአፏ የቴንስ መጫወቻ የምታክል ድብልብል እሳት ብልቅ ብሎ በመውጣት እንደሮኬት ተተኩሶ ወደሰማይ ተምዘገዘገ ..እያየችው  አየሩን ሰንጥቆ ተሰወረ..ግራ ጋባት …እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረች ወደንሰሯ አዕምሮ ተመለስችና ‹‹ምን እየሆነ ነው….?››ጠየቀችው
‹‹በቃ ጨርሰናል እንሄድ››
‹‹እንዴ መቀንጠስ አልቻልኩም እኮ ..እጄ ላይ ምንም የለም….?››
‹‹እጅሽ ላይ ምን ያደርግልሻል …ተክሉ እኮ በመላ ሰውነትሽ ገብቶ ተዋሀደሽ..አሁን መዳኒቱ ተክሉ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ነሽ..በዚህ የሳምንት ጊዚ ውስጥ የፈለግሽውን ማዳንም የፈለከግሽውን መግደልም  ትችያለሽ..››

‹‹ደስ ሲል ››

‹‹ደስ አይልም…››አለና ከመጣ ጀምሮ ተዘፍዝፎበት ከነበረው ቋጥኝ ላይ ክንፉን አርገፍግፎ ተነሳን ማጅራቷን ይዞ ወደሰማይ ተምዘገዘገ  ….ወደጀርባዋ ዞረና ተጣበቀባት…  ወደ አዲስአባ ተመልሰው እቤታችን ሲደርሱ ከምሽቱ 8 ሰዓት አልፎ ነበር… …

‹‹ወይኔ ድክም ብሎኛል..ግን መድሀኒቱን ስላገኘን ከአባቴ ወገኖችም ጋር ልንገናኝ ስለሆነ ደስ ብሎኛል…አንተስ ደስ አላላህም….?››ለመተኛት ወደ አልጋዋ እያመራች ነበር ምትናገረው

‹‹በጣም ከፍቶኛል››አላት ንስሯ

ደነገጠች‹‹ለምን….?››

‹‹ከንቺ ጋር የምኖረው ..በህይወትም የምቆየው ለሳምንት ብቻ ስለሆነ››

በህይወቷ እንደዚህ አይነት ድንጋጤ ደንግጣ አታውቅም.‹‹.እንዴ የእኔ ንስር ሟች ፍጡር ነው እንዴ…….?›ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰበችብት ጊዜ ነው

‹‹ጥዬህ የምሄድ መስሎህ ነው..አብረን እኮ ነው የምንሄደው››

‹‹ይዘሺኝ መሄድ አትቺይም››

‹‹ለምን….?››

‹‹እኔ መጀመሪያም ከዛ ነው የመጣሁት…ለአባትሽ ብዬ እና አሁን ተመልሼ ለመሄድ ፍፅም አይፈቀድልኝም፡፡››

‹‹በቃ ይቀራላ ..እስከዛሬ ካንተ  ጋር እንጂ ከእነሱ ጋር አልኖርኩ.. ምን  ያደርጉልናል እነሱ መቅረት ይችላሉ››

‹‹እሱማ ጊዜው አለፈ..ቅድም ከአፍሽ የወጣችው እሳት አነሱ ጋር መልዕክት ይዛ የምትሄድ ነች…ወደድሽም ጠላሽም አንቺን ይወስዱሻል..እኔ ደግሞ ካለአንቺ ህይወት የለኝም …ተነጥለሺኝ እንደሄድሽ ወዲያው በዛኑ ሰዓት እሞታለሁ..››

‹‹እንዴ  እሞታለሁ ማለት ምን ማለት ነው….?ይሄንን ታዲያ ተክሉን ከመቀንጠሴ በፊት ለምን አልነገርከኝም….?››

‹‹ውሳኔሽ በእኔ ላይ እንዲመሰረት ስላልፈለኩ ››

‹‹ያምሀል እንዴ . ….?.ካንተ ሚበልጥብኝ ነገር አለ…….?

ህይወቴ እኮ ነህ..››አበደች ጮህች ፕሮፌሰሩ ከእንቅልፋቸው ባነው በራፏን እስኪያንኮኩ ድረስ ግቢውን አተረማመችው …፡፡

ይቀጥላል….

#አደራ በዛውም YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ እያደረጋቹ አይደለም አያስከፍልም እባካቹ እያረጋቹ ለሚለቀቁት ታሪኮች እንደክፍያ ቁጠሩት👇
https://www.youtube.com/@atronose

#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://tttttt.me/atronosee
👍111😢3120🔥5👏5🥰4
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ለሊቱ ያለእንቅልፍ ነው ያለፈው….የጣር ለሊት…የስቃይ ለሊት…፡፡ደግነቱ ፕሮፌሰሩ ለሊቱን ሙሉ አብረዋት ነው ያሳለፍት…..ይሁን እንጂ እሷ ባዘነች መጠን አብረዋት እያዘኑ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም..ግን በታታሪት ሲያዳምጧት እና ደረቅ አልኳል ሲያጣጧት ነበር..  ወፎች የለሊቱን መንጋት የምስራች ሊያበስሩ ሲንጫጩ ድምጻቸው የተሰማው…
ሁለት ጠርሙስ ብላክ ሌብል  ጠርሙስ ጨርሰዋል..እሷ አንድ ጠርሙስ ከግማሹን ሳትጨርስ አልቀርም፡፡በንዴት፤ በስጋትና በብስጭት ያወራችው ወሬ ቢቀረብ እና ወደ መጻሀፍ ቢገለበጥ አንድ ደለብ ያለ መጽሀፍ ይወጣዋል፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ምን አቀበጠኝና ተክሉን ቀነጠስኩ..….?ምን ቅብጥ አደረገኝ….?››

‹‹እንደነገርሺኝ እኮ ሙሉ በሙሉ ሚያመጣውን መዘዝ አልተረዳሽም ነበር››

‹‹እኮ ረጋ ብዬ ጊዜ ወስጄ ማሰብ ነበረብኝ…ንስሬ እንኳን ሊነግረኝ ባይፈልግ…ጎትጉቼ ሙሉውን  መዘዝ መረዳት ነበረብኝ፡፡››

‹‹ግን እርግጠኛ ነሽ ..እንደዚህ ያለ ንስርሽ ለመሄድ እንደምትገደጂ ብታውቂ ኖሮ ተክሏን ከመቀንጠስ ትታቀቢ ነበር….?››

‹‹ይቀልዳሉ እንዴ ፕሮፌሰር..ጭርሽ ለማሰብ እንኳን አልሞክርም…እንዴ ንስሬን ጥዬ እንኳን የማላውቃቸው ..ምን አይነት ፍጡር እንደሆኑ እንኳን እርግጠኛ ወዳልሆንኩባቸው..ይመቹኝ አይመቹኝ  መገመት ወደማልችላቸው  የአባቴ ዘመዶች ይቅርና እግዚያብሄርም ቢጠራኝ  ንስሬን ጥዬ በፍቃደኝነት  ለመሄድ አልፈልግም››

‹‹በቃ ተረጋጊ..ያው በሞትም መለየት እኮ አለ››አሏት ፕሮፈሰሩ …በእሳቸው ቤት እሷን የሚያጽናና ቃል መናገራቸው ነው፡፡

‹‹አይ ፕሮፌሰር …ይቀልዱብኛል አይደል?ይሄም እኮ ያው ሞት  ነው…ሞት ማለት የራስ ከሆኑ ሰዎችና ከሚኖሩበት ዓለም ለዘላለም ተለይቶ በስጋ ወደመሬት ውስጥ መግባት በነፍስ ደግሞ ወደማይታወቅ አለም መጓዝ ማለት አይደል…?አሁን እኔም ከሳምንት በኃላ የሚገጥመኝ  ደግሞ በስጋም በነፍስም ከዚህች ምድርም ሆነ  የእኔ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ  ተለይቼ ለዘላለም ወደማይታወቅ አለም በስጋም በነፍስም መጓዝ ነው…ታዲያ ይሄ እንደውም ሙሉ ሞት አይደለም..….?ማንም ሰው ስናፍቀው እንኳን መቃብሬ ጋር ሄዶ በማልቀስ ወይም አበባ በማኖር ሊያጽናና ዕድሉ አይኖረውም …. ነፍሴንም ስጋዬንም ይዤ ነው የምሄደው…››

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው››

‹‹አዎ ዋናው ችግር  ግን ይሄ አይደለም..ዋናው ንስሬን ጥዬ መሄድ ያለመፈለጌ ነው..እሱን..››ንግግሯን አቋረጧት፡፡  
‹‹እኔ እኮ በህይወት እስካለሁ ድረስ ልንከባከብልሽ እችላለሁ፡፡››

‹‹አይ አይችሉም… እርሶ የሚችሉት በስርዓት የቀብር ሰርዓቱን ማስፈፀም ብቻ ነው››

‹‹አልገባኝም..››አሏት ደንግጠው፡፡
‹‹እኔ  ጥዬው በሄድኩ ቀን እሱም እደሚሞት ነግሮኛል››

‹‹እንዴት ሆኖ ነው የሚሞተው….?››
‹‹እኔ እንጃ ግን  እኔን ከወሰዱኝ በኃላ ለአንድ ቀንም እንኳን በህይወት መኖር እንደማይችል እርግጠኛ ሆኖ ነግሮኛል››

‹‹አይዞሽ ሳምንት እኮ ብዙ ቀን ነው..የሆነ መውጫ መንገድ ልናገኝ እንችላለን..በተለይ ንስርሽ መላ ሚያጣ አይመስለኝም››

‹‹እኔ እንጃ …. እንደዛ ተስፋ አላደርግም …››

‹‹አይዞሽ…ደግሞ ይሄ ጉዳይን እንደመስዋዕትነት ቁጠሪው..ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ወጥመድ ውስጥ የገባሽው››

‹‹መስዋዕት አሉኝ….መስዋዕትነትማ እንዲህ በቀልድ አይገለጽም..እኔ ከመስዋዕትነት ይልቅ ክስረት ነው የሚሰማኝ…መስዋዕትነት እኮ ለአንድ ክብር አለማ አቅዶና አስቦ ሕይወትንም ጭምር መስጠት ማለት ነው…ህይወትንም ጭምር ቢሆን አጥቶ ሌላውን ለማኖር ቀድሞም አምኖና ወስኖ መተግበር ማለት ነው…

‹‹ልክ እንደ አርበኞቻችን ማለትሽ ነው….?››

‹‹አዎ እንደውም ዛሬ ለሀገር መስዋዕትነት ስለከፈሉ ሰዎች ምስጋና የምናቀርብበት ቀን አይደል…ሀገር ከምትደፈር የእኔ ህይወት ትቀጠፍ ብለው…ለልጆችና ለልጅ ልጆቻችን ባርነትን ከምናወርስ እኛ ዛሬ ደማችንን እረጭተን አጥንታችንን በትነን ነጻነትና ኩራትን እናወርሳቸው ብለው ታሪክ እንደሰሩት አባቶቻችን   ነው መስዋዕትነት….ልክ እንደ በላይ ዘለቀ፡፡ ከገዛ አብራክ ልጅ ይልቅ ሀገርን ወይም ህዝብን ማስቀደም ማለት ነው…ለሀገር ክብር እና ለወገን መድህን ሆኖ መውደቅ ማለት ነው…ከስኬት በኃላም ላደረጉት ነገር የተለየ ክብር እና ሹመት አለመፈለግ ማለት ነው..ለሚወዱት ነገር ያለንን ነገር ሁሉ ህይወትንም ጭምር በነፃ መስጠት ማለት ነው….
እንደዛአይነት መስዋዕትነት ሚስጥሩ ከባድ ነው….ከድል በኃላ የበላይን ይሄንን ለሀገሩ በነፃ የሰጠውን መስዋዕትነት  ሸፍጠኞቹ እና ባንዳዎቹ አልወደዱለትም ነበር..ምክንያም ስለእሱ ዝናና ታሪክ ሲሰሙ የእነሱን ሆዳምነት እና  ትንሽነታቸውን በየጊዜው ስለሚያሳብቅባቸው ከንጉሱ አላትመው በአደባባይ እንዲሰቀል አደረጉት..ከጠላት በክብር የተረፈች ነፍሱ በገዛ ህዝቦቹ ምቀኝነት እና ክፍት ተነጠቀች…ይሄ ነው መስዋዕትነትን መራር የሚያደርገው…ለዚህ ነው መስዋዕትነት የሚለው ቃል ሚያስጠላኝ፡፡

‹‹ትክክል ነሽ ልጄ…ይሄ የበላይ  ታሪክ የእንግሊዞች ቢሆን፤ይሄ የበላይ  ታሪክ የአሜሪካኖች ቢሆን  ኖሮ አንድ ሺ ፊልም እና አስር ሺ መጽሀፍ ተጽፎበት ነበር…?ስንት መንገድ እና ስንት ዩኒቨርሲቲ በስሙ ተሰይሞለት ነበር…?››
እኚህ  ለሊቱን ከፕሮፌሰሩ ጋር በመጠጥ እያወራረድ በእሷ ለቅሷ ታጅበው  ሲያወሩ ከነበሩት ነጥቦች ጥቂቶቹ  ነበሩ..….

አሁን ሰዕቱ ከማለዳ 12፡45 ይላል…ፕሮፈሰሩ በመጠጥ እና በእሷ ወሬ ተዳክመው ይመስላል እዛው የተቀመጡበት ሶፋ ላይ ደገፍ እንደሉ እንቅልፍ ይዞቸው ጭልጥ ብሏል….ንስሯ ያለው መኝታ ቤት ውሰጥ ነው ከእሷ በላይ ትካዜና ቁዘማ ውስጥ ነው…ልትነካካው አልፈለገችም
እየተንገዳገደች እቤቱን ለቃ ወጣችና ወደ መኪና ማቆሚያ አመራች…‹‹ከጠጡ አይንዱ›› የሚለውን የትራፊኮችን ዋና ምክር አዘል መመሪያ ከቁብም ሳትቆጥር መኪናዋን አስነሳችና ግቢው ለቃ ተፈተለከች..ቀጥታ ወደመላኩ ቤት ነው ያመራችው…
እንደደረሰች ወደጊቢው አጥር አስጠጋችና መንገድ እንዳይዘጋ አስተካክላ መኪናዋን ካቆመች በኃላ ሞተሩን በማጥፋት ከመኪናዋ ወረደችና  የግቢውን በራፍ መጥሪያ በሰከንድ ሽርፋራፊ ውስጥ  ደጋግማ አንጣረረችው ፡፡ከጠበቀችው በፈጠነ  ሁኔታ ተከፈተላተት..ከእንቅልፉ የባነነ እና በአንድ እጁ አይኖቹን እያሻሸ በሌላ እጁ የበራፍን እጄታ ይዞ ‹‹ምን ፈለግሽ….? ›› የሚላት ሰው ስትጠብቅ .. ንቁ እንቅልፍ በዓይኑ እንዳልዞረ የሚያስታውቅ..አይ እንደውም እያለቀሰ የነበረ ከዚህ በፊትም ያየችት ዘበኛ ከፈተላትና…ምንም ነገር ሳይጠይቃት እንድትገባ መንገዱን ዞር ብሎ ለቀቀለት …አልፋ ገባችና መንገዷን ቀጠለች ..በፍጥነት ዘግቷ ከኃላዋ ተከተላት፡፡

‹‹ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው…….?ሰው ሁሉ ሲያለቅስ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድርበት ቀን ነው እንዴ….?››ከዘበኛው ሁኔታ ተነስታ ውስጧን እየጠየቀች ነው…  እራሷን ለመቆጣጠር በዚህ በተወለካከፈ እርምጃ አንድ ነገር አደናቅፏኝ እንዳትደፋ  እየፈራች ስትራመድ ዘበኛው በታፈነ ድምጽ መናገር ጀመረ

‹‹ጋሼ ደውለውልሽ ነው….?››

‹‹አዎ›› አለችው….ምንም ሳታስብበት

‹‹አይ ቢጨንቃቸው እኮ ነው ..በቃ እኮ 10 ደቂቃም ዕድሜ አይራቸውም …አብቅቶላቸዋል…››

‹‹ማን ነው ያበቃለት ….?››ደንግጣ
👍9410🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.?  ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…

እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን  የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን  እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡ 

…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ  እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…

‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት  ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡

‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)

‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)

‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››

‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ  አያምርብሽም››

‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር  ነው››

‹‹እኮ ምንድነው….?››

‹‹ልሄድ ነው››

ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ  ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››

‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››

ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት  ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?

‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››

‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››

ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ  ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››

‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ  ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡

‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››

‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡

አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..

‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››

‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››

‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››

የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ

‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት

‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››

‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››

‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር አይችልም››
👍10610🥰1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////

ወደሸገር ተመልሰዋል..ማለት እሷ እና ንስሯ ፡፡ለእናቷ በመጨረሻው ቀን ተመልሳ እንደምታያትና ወደአባቷ ዘመዶችም በምትሄድበት ቀን አጠገቧ እንድትሆን እንደምትፈልግ   ነግራትና ቃል ገብታላት ነው የመጣችው፡፡
እስከዛው ያሉትን ቀጣዬቹን በስስት እየተሸራረፉ በመርገፍና በማለቅ ላይ ያሉትን ቀሪ 5  የሰቀቀን ቀናቶችን ሸገር ልታሳልፍ ወስናለች….ምን አልባትም አይታውቅም… በመሀል ሀሳቧን ልትቀይር ትችላለች፡፡
ግን አሁን ተረጋግታ እቤቷ መቀመጥ አልቻለችም … ሰዓቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ቢያልፍም ልትቆጣጠረው የማትችለው ከውስጧ ሚመነጭ ስውር ስሜት ውጪ ውጪ ይላት ጀመር….ልብሷን ቀያየረችና መኪናዋን ወዳለችበት መራመድ ከጀመረች በኃላ ሀሳቧን ቀየረችና ስልኳን አውጥታ ደወለች..አዎ ነፃ መሆን ነው የምትፈልገው….ላዳ ያለው የምታውቀው ልጅ ጋር ነው የደወለችው፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹ሰላም ነው… .ፈልጌህ ነበር…የት ነህ ያለኸው?››

‹‹ይቅርታ ዛሬ ስራ ላይ አይደለሁም መኪናዬ ተበላሽታ ገራዥ ነች››

‹‹በቃ አንተ ናልኛ ..የእኔ መኪና ስላለች ትይዝልኛለህ …ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ መንዳት አልፈለኩም››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር.. ግን ያው ስራ የለኝም ብዬ ከከተማ ወጣ ብያለሁ…..ከፈለግሽ አንድ ጓደኛዬን ልልክልሽ እችላለሁ››

‹‹ደስ ይለኛል››

‹‹በቃ ንገረውና ቁጥርሽን ሰጠዋለሁ…ይደውልልሻል››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ››ስልኳን ዘጋችውና ጊቢዋ ውስጥ እየተዘዋወረች እስኪደወልላት መጠበቅ ጀመረች….፡፡
ብዙም ሳይቆይ ስልኳ ላይ የማታውቀው ቁጥር ተንጫረረ …አነሳችው..አናገረችው ….በ15 ደቂቃ እንደሚደርስ ነገራት…..መጠበቅ ጀመረች…..

‹‹አዎ በዚህ ለሊት ምን አልባት ለመጨረሻ ጊዜ ማበድ እፈልጋለሁ..አዎ ብዙ ነገር ማድረግ አምሮኛል…የማሰብ አቅሜን አዳክሞ ጭንቀቴን የሚቀንስልኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ እፈልጋለሁ…..መጠጣትና መስከር …መቁላላትና መዋሰብ እፈልጋለሁ…መጣላትና መደባደብም ካገኘሁ አልጠላም…››
እግዜር ይስጠው የመኪና ጥሩንባ ድምጽ ሰማች...ጎበዝ ልጅ ነው… በነገረችው ምልክት መሰረት ሳይሳሳት መምጣቱ አስደሰታት… በራፍን ከፈተችና ወጣች…በምልክት ጠራት … የላዳውን በራፍ ከፈተላትና ገባች፡፡

‹‹ወዴት ልውሰድሽ….?››

‹‹መጠጣት ነው የምፈልገው››አለችው፡፡

‹‹መጠጣት›› አላት ግራ ተጋብቶ፡፡

‹‹መጠጣት ስልህ …ብሽቅጥ እስክል መጠጣት ነው የምፈልገው…የፈለከውን ያህል ከፍልሀለሁ እስከንጋትም ቢሆን አብረኸኝ ትቆይና እቤቴ ታስገባኛለህ››

‹‹ይመችሽ ››አላት….

እንዲሁ ወደደችው…አንድን ሰው አይተን በውስጣችን ስለሰውዬው ደስ የሚል ስሜት ሲሰማን ውቃቢዬ ወዶታል  የምንለው ነገር አለ አይደል..….? እሷም ይሄን የላዳ ሹፌር  እንዳየችው  እንደዛ ነው የተሰማት፡፡

‹‹ምርጫሽ የት አካባቢ ነው?››

‹‹የፈለክበት ውሰደኝ ››

‹‹ቺቺኚያ ይመችሻል››

‹‹ይመችህ››

ነዳው….ንስሯ አምኗት እቤት ሊቀር አልቻለም  …ከፊት ለፊታቸው  በላዳዋ   ፍጥነት መጠን  ሲበር በመኪናዋ መስታወት አሻግራ አየችው….

ደረሱና መኪናዋን ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀበት ቦታ ፓርክ አድርገው አንዱ ጭፈራ ቤት ገቡ……እሷ ደረቅ አልኮለሏን ስታዝ እሱ ዉሀ አዘዘ..

‹‹ለምን ትንሽ አትሞከርም….? ››

‹‹አይ …የሞያዬ ስነምግባር አይፈቅድልኝም›› ሲል መለሰላት በቀልድ መልክ

..ዝም አለችው… በላይ በላዩ መለጋቱን ቀጠለች….የሙዚቃው ከጣሪያ በላይ ጩኸት…የለሊት ንገስታቶች በገዢ መሳይ  ወንዶች ዙሪያ መሽከርከር፤  በስካር የሚናውዙና የሚደንሱ ወንዶችና ሴቶች የሆቴሉን ወለል መሙላት…የሆነ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚታየው….በዛ ላይ መብራቱ በአምስት አይነት ቀለም በመፈራረቅ ቦግ ብልጭ ሲል  እይታን ብዥ ያደርጋል…….ግን በምትፈልገው መጠን ባይሆንም ተመችቷታል ፡፡ቢሆንም ደስታዋን ሙሉ ማድረግ ፈለገች…

‹‹ሌላ ጓደኛ የለህም….?››ድንገት ከመሬት ተነስታ ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን አይነት….?››

‹‹ሹፌር››..

‹‹ምን ያደርግልሻል….?››

‹‹ያንተን መኪና የሚነዳልን››

‹‹እኔስ….?››አላት በጥያቄዋ ግራ ተጋብቶ

‹‹አይ አንተማ እንድታጣጣኝ ፈልጌ ነው..ብቻዬን ደበረኝ››

‹‹እ ..ቆይ እስኪ ደዋውዬ ልሞክር››አለና ስልኩን እየጎረጎረ ከሆቴሉ ወጣ..ሲወጣ ከጀርባው ሳታየው ነበር…ቁመናው መስጧታል..በቃ የተለመደው ችግሯ እያገረሸባት ነው..ጭኗ መካከል አሳከካት…ምን አይነት መጥፎ አመል ነው…እዛም አባቷ  አለም ስትሄድ እንዲህ የሚበላት ነገር ወቅት እየጠበቀ ይፈታተናት  ይሆን እንደዛ ከሆነ ምንድነው የምታደርገው….….?

ሀሳቧን ሳትጨርስ መጣና መቀመጫው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ..‹‹ተሳክቶል…ተቀላቅዬሻለሁ››አላት

በደስታ እየፈገገች‹‹ምን ይምጣልህ..?››ሥትል ምርጫውን ጠየቀችው፡፡

‹‹አንቺ የያዝሺውን…››
ሙሉ ጠርሙስ አዘዙ…መጣላቸው…… ይገለብጡት ጀመረ…እየደነሱ እየተቀመጡ …ደግሞ ተመልሰው በመነሳት እየደነሱ ..ውልቅልቃቸው እስኪወጣ ድረስ አስነኩት‹‹  …አቤት ዳንሱ !!ፕሮፌሽናል ነው ፡፡ልቤን ስልብ ነው ያደረገኝ…›አለች በዳንስ ችሎታው ተመስጣ፡፡ይበልጥ ሰውነቱ ላይ ተለጥፋ በተሸሻችው መጠን የጭኗ መብላላ  አደብ እየነሳት ነው…በትርምሱ መካከል በዳንስ ስልት በማሳበብ እጣቷን  ወደጭኗ በመስደድ   ይሉኝታ እስክታጣ ድረስ እያሻሸች  ነው..ደግነቱ ሁሉም በመጠጥ የደመቀ እና በመብራቱ ቦግ ብልጭ ብዥ ያለበት መሆኑ በጃት …
ከለሊቱ አምስት  ሰዓት አካባቢ ሲሆን ግን ተዳከሙ…

‹‹ቤት እንቀይር ….?››አለችው… ቤት መቀየር የፈለገችው ሙዳችውንም ጭምር መቀየር ስለፈለገች  ነው… ተስማማ ..ሂሳብ ዘግተው ወጡ…

‹‹ጭፈራ ቤት ሳይሆን ዝም ብለን የምንጠጣበት ቦታ ነው የምፈልገው…››

ወደላዳዋ ይዟት ሄደ …ቅድም ተጠርቶ የመጣው ጓዳኛውን ገቢና ቁጭ ብሎ ጫቱን ሲቀመቅም  አገኙት..ሁለቱም ተደጋግፈው ከኃላ ገቡ… ላዳዋ ተንቀሳቀሰች… በመስኮቱ አንጋጣ ሰማዮን ሰታይ ንስሯን ቀድሟት ለመብረር ሲያኮበኩብ አየችው…ሰካራሙ ጓደኛው እይታዋን ተከትሎ ወደውጭ በተመሳሳይ ሁኔታ  ካየ በኃላ‹‹ አይገርምም ይሄ አሞራ ቅድምም ስንመጣ ከፊት ለፊታችን ሲበር  ነበር….እርግጠኛ ነኝ የተለየ ከለር ስላለው አስተውዬው ነበር››አለ

‹‹አሞራ አይደለም..ንስር ነው››አረመችው 

‹‹እንዴ.. አዎ ንስር ነው ትክክል ..አንቺ ግን እንዴት አወቅሽ….?››

‹‹የእኔ ነው››በልበ ሙሉነት መለሰችለት፡፡

‹‹የእኔ ነው ስትይ….?››ያዝ ያዝ በሚያደርገው የስካር አንደበት ጠየቃት 

‹‹ወንድሜ ነው››

ሁለቱም ተንከትክተው ሳቁ

‹‹..ቀልደኛ ነሽ..ይበልጥ ስትጠጪ  ደግሞ ይብልጥ ቀልደኛ የመሆን ተስፋ አለሽ ማለት ነው››አላት፡፡

….አስረድቶ ማሰማንም ሆነ ተከራክሮ ማሸንፈ እንደማትችል ስለተረዳች‹‹ይሁንልህ›› አለችው ፡፡
መገናኛ አካባቢ ደርሱ… ብዙም ትርምስ የሌለበት እሷ የማታውቀው ሁለቱ ግን የሚያውቁት ሆቴል ይዘዋት ገቡ..ሹፌሩ ከላዳዋ አልወረደም…‹‹ጫቴን ብቅም ይሻለኝል›› ብሎ ቀረ …እነሱ ተያይዘው ገቡና የተገነጠለ እና ከታዳሚ የራቀ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡
👍8611😁2👎1🤔1😱1😢1
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ በቀኝ ፊቷ ላይ ከሚታየው የተላላጠ ጠባሳ በስተቀር ሙሉ ለሙሉ ከደረሰባት አደጋ አገግማለች ፡፡ወደ ስራዋ መመለስ ብትፈልግም የታዲዬስ ልጆች ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አቆይተዋታል፡፡ለዚህም ሰበባቸው የፅዬንን የምረቃ በዓል አብራቸው እንድታከብር ስለፈለጉ ነው፡፡ፅዬን የሙዚቃ ባለሞያ ብትሆንም በህግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከሁለት ቀን በፊት ተመርቃለች ..ዛሬ ደግሞ በታዲዬስ ቤት የእንኳን ለዚህ አበቃሽ ዝግጅት ተዘጋጅቶላታል፡፡

ዶ/ር ሶፊያም እንግዳ ከአሜሪካ ድረስ መጥቶባት አዲስአባ እሷ ቤት ቁጭ ብሎ እየጠበቃት እንደሆነ ተደውሎ የተነገራት ቢሆንም ይሄንን ዝግጅት ረግጣ ችላ ብላ መሄድ ስላልተቻላት ከጉዞዋ ቀርታለች፡፡
የዝግጅቱ ዋና አቀናጆች አላዓዛር ፣ቤተልሄም እና የታዲዬስ ልጆች ሲሆኑ የወጪውን 9ዐፐርሰንት የሸፈነው ታዲዬስ ነው፡፡ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶ በመጠናቀቅ ወደ ዝግጅቱ የተገባው ከምሽቱ 1 ሰዓት ነው፡፡ዝግጅቱን ከታደሙት ውስጥ የውጭ ሰዎች ሶስት ብቻ ናቸው፤ሌሎች ጠቅላላ የቤተሰቡ አባል ናቸው፡፡

የእራት ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኃላ፤ የፕሮግራሙ መሪ መምህር ዓላዛር ወደ ፊት ወጣ ‹‹እንግዲህ የዛሬውን ፕሮግራም የጀግናዋ እህታችን የምረቃ ክብረ በዓል በማስመልከት የተዘጋጀ ነው...እንኳን አደረሰሽ..እንኳን ደስ ያለሽ እያልናት ነው፡፡ ፂ ለእኛ ምርጥ እህታችን ብቻ ሳትሆን መልካም አርአያችንም ነች፡፡ይቺን የእሷን የስኬት ቀን ለማክበር እነ ሄለን ለአንድ ወር ሲጥሩ እና ሲዘጋጁ ነበር፡፡ይሄ ዝግጅት በዋናነት የእነሱ ስለሆነ እያንዳንዳቸው ለእሷ ያላቸውን መልካም ምኞት እንዲገልጹላት መድረኩን ተራ በተራ እሰጣቸዋለሁ፡፡መጀመሪያ ሚጡ ወደ እዚህ ነይና ለጺ የምትያት ነገር ካለ እድሉን ልስጥሽ፡፡››

ሚጡ ቆንጆ ሆና፣ነጭ የአበሻ ቀሚስ ለብሳ፣ትንሽ ሞዴል ወይዘሮ መስላ አላዓዛር ወደ ቆመበት ቦታ መጣችና ቆመች፡፡በእጇ አንድ ወረቀት ይዛለች፡፡ሁሉም ሰው እሷ ላይ ሲያተኩርባት ተደነጋገራት፡፡ወደ ታዲዬስ ፊቷን አዞረች ፡፡‹‹...በርቺ.. አይዞሽ >>ብሎ አበረታታት፡፡መናገር ጀመረች፡፡

.....‹‹ፅዬን እንኳን አደረሰሽ፡፡እኔ በጣም ነው
የምወድሽ፡፡ እኔንም እንደ እነ ሄለንና ሀሊማ ሙዚቃ እንድታለማምጂኝ በጣም እፈልጋለሁ፡፡

ፒያኖ ስትጫወቺም፣ ስትዘፈኚም ደስ ትይኛለሽ፡፡ዛሬ ተመርቀሽ የለበሽው ጥቁር ቀሚስም በጣም ያምርብሻል እና ደግሞ
እኔም እንዳንቺ በደንብ ተምሬ አሁን የለበሽውን
መልበስ እፈልጋለሁ፡፡…››ለተወሰነ ሰከንድ ፀጥ
ብላ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች፡፡‹‹...ላንቺ አንድ ግጥም ገጥሜልሻላሁ ...ማን
እንደምታስፈቅድ ባይታወቅም‹….ላንብብ ? >
አላችና ጠየቀች.. ፡፡ሁሉም በአንድ ላይ ‹‹..ጎበዝ አንብቢ….አንብቢ›› አበረታቷት ….ጀመረች፡፡

የግጥሜ ርዕስ

‹ጥቁር ቀሚስ› ነው

‹ጥቁር ቀሚስ›

ኮንግራ ብያለሁ... ፅዮንዬ እናቴ በጣም ነው ምወድሽ… ፍፁም ከአንጀቴ ምርጥ ሙዚቀኛ….ድንቅ መምህር ነሽ ከጎኔ ስትሆኚ ....ደስ ትይኛለሽ ጥቁር ቀሚስ ልበሽ ...ኮፍያም አጥልቂ የላብሽ ውጤት ነው...ኩሪ ተነቃቂ እንኳን አደረሰሽ... ፅዮን ወድሻለሁ እንደአንቺ ለመሆን ...በርትቼ አጠናለሁ፡፡

‹‹...ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ›› አለችና ወደ ፅዬን በመሄድ ጉንጯን ሳመቻትና ግጥም የተፃፈበትን ወረቀት በእጇ አስጨበጠቻት.. ፅዬንም በተራዋ ወደራሷ ጎትታ፣ከደረቷ ለጥፋ በማቀፍ ሙጭምጭ አድርጋ ትንፋሽ እስኪያጥራት አገላብጣ ሳመቻትና‹‹እኔም በጣም ነው የምወድሽ›› አለቻት፡፡

ቀጥሎ ዕድሉ የተሰጣት ለሰላም ነበር፡፡ሰለም እያነከሰች ቢሆንም በእጇ ለፅዬን ያዘጋጀችላትን ስዕል ይዛ ወደ ፊት ወጠችና ንግግር ጀመረች‹‹እኔ እንደምታዩኝ ሸንካላ ነኝ...›› ድንገተኛ ሳቅ በቤቱ ፈነዳ.…ሁሉንም ያሳቃቸው የእሷ እግር አንካሳነት ሳይሆን አገላለጿ ነበር ፡፡ ‹‹....አዎ እውነቴን ነው ...በፊት በፊት በዚህ ጉዳይ በጣም እበሳጭ ነበር፤ይህን እግሬን እንዲህ ያደረገኝ የገዛ አባቴ ነው....ግን ብቻውን ያደረገው አይመስለኝም ነበር፡፡አዎ እግዚያብሄርም ያገዘው ይመስለኝና ሁል ጊዜ ተደብቄ በማልቀስ ሁለቱንም እወቅስና አማርር ነበር ፡፡ በተለይ ትምህርት ቤት አንዳንድ ልጆች



ሲያሾፍብኝ..እንደእነሱ ዘልዬና ተሯሩጬ መጫወት እያማረኝ ያንን ማድረግ ሳልችል ስቀር ..በጣም ያበሳጨኝ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት ይሄንን የውስጥ ንዴቴን

ይበልጥ የሚያባብስ ስም ሁሉ አውጥተውልኝ

ነበር < ካንጋሮ› ነበር የሚሉኝ፡፡ አረማመድሽ

የካጋሮን ይመስላል ማለታቸው መሰለኝ፡፡ ብቻ

በወቅቱ ታዲዬስን እየፈራሁ እንጂ ትምህርቱ

ከነጭራሹ ቢቀርብኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ውሎ

አድሮ ግን ከዚህ ሁሉ ስቃይ እንድወጣ ፅዬን

አርአዬ ሆነች፡፡በቃላት እየመከረች አይደለም

ያስተማረቺኝ ፤በምግባሯ እንጂ፡፡ሁለት ዓይኖቿ

አያዩላትም፤ግን ከሚያዩት በላይ

ታስተውላለች፣ከዓይናማዎቹ በላይ ውጤታማ

ነች፡፡ማድረግ የፈለገችውን ነገር ለማድረግ

ዓይኖቿን ሰበብ በማድረግ ስታማርር እና

ስትሰንፍ አይቻት አላውቅም፡፡ታዲያ እኔስ

የተሰናከለችብኝን አንድ እግር እያሰብኩ ቀሪ

ህይወቴን ሙሉ እንዴት ጓዶሎ አደርጋለሁ..?

ብዬ ጠነከርኩ፡፡ የሚያሾፉብኝን ልጆች በፊት
ሲያሾፍብኝ..እንደእነሱ ዘልዬና ተሯሩጬ መጫወት እያማረኝ ያንን ማድረግ ሳልችል ስቀር ..በጣም ያበሳጨኝ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት ይሄንን የውስጥ ንዴቴን ይበልጥ የሚያባብስ ስም ሁሉ አውጥተውልኝ ነበር < ካንጋሮ› ነበር የሚሉኝ፡፡ አረማመድሽ የካጋሮን ይመስላል ማለታቸው መሰለኝ፡፡ ብቻ በወቅቱ ታዲዬስን እየፈራሁ እንጂ ትምህርቱ ከነጭራሹ ቢቀርብኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ውሎ አድሮ ግን ከዚህ ሁሉ ስቃይ እንድወጣ ፅዬን
አርአዬ ሆነች፡፡በቃላት እየመከረች አይደለም

ያስተማረቺኝ ፤በምግባሯ እንጂ፡፡ሁለት ዓይኖቿ
አያዩላትም፤ግን ከሚያዩት በላይ ታስተውላለች፣ ከዓይናማዎቹ በላይ ውጤታማ ነች፡፡ማድረግ የፈለገችውን ነገር ለማድረግ
ዓይኖቿን ሰበብ በማድረግ ስታማርር እና ስትሰንፍ አይቻት አላውቅም፡፡ታዲያ እኔስ የተሰናከለችብኝን አንድ እግር እያሰብኩ ቀሪ
ህይወቴን ሙሉ እንዴት ጓዶሎ አደርጋለሁ..?
ብዬ ጠነከርኩ፡፡ የሚያሾፉብኝን ልጆች በፊት
አዝንባቸው ነበር ፤አሁን ግን አዝንላቸው ጀምሬያለሁ፡፡.ባለማወቃው ነው .፡፡

ሰው ለሀገሩም ለቤተሰቦቹም ሸክም የሚሆነው የአካል ጉዳተኛ ስለሆነ ሳይሆን ፤ የአስተሳሰብ ጉዳተኛ ሲሆን ነው፡፡ፅዬን ያንን እንድረዳ ስላረግሺኝ አመሰግናለሁ፡፡ እንኳን ደስ ያለሽ፡፡ይሄ ስጦታዬ ነው›› ብላ ወደ እሷ በመሄድ በገዛ እጆቿ የተሳላውን ስዕል አበረከተችላት... ሁሉም በጭብጨባ አጀቧት፡፡

ቀጥሎ የጽዮን የሙዚቃ ተማሪ የሆኑት ሄለን እና ሀሊማ ናቸው ወደ መድረክ የወጡት፤ ግን አልተናገሩም፡፡ ከታዳሚዎቹ ፊት ለፊት ወደሚታዩት ፒያኖ እና ጊታር ነው የሄዱት፡፡ ሀሊማ ጊታሩን ስትይዝ ሄለን ፒያኖውን ያዘች፡፡ ከዛ መጫወት ጀመሩ ፡፡ኮሽታ እንኳን አልነበረም፡፡ ፀጥ ባለ ድባብ በፍፅም ተመስጦ ነበር ሁሉም ጆሮውን ሰጥቶ ሚያዳምጣቸው ፡፡ ሙዚቃው ለሁሉም ጆሮ አዲስ ልዩ ጣዕም ያለው የሚያንሳፍፍ ነበር፡፡ከሁሉም ዕድምተኛ በተለየ መልኩ በዚህ ሙዚቃ የጽዮንን ያህል የተመሰጠ ፣የተገረመና ግራ የተጋባ ሰው አልነበረም፡፡ከየት አገኙት…? ማ
አለማመዳቸው…?ይሄን ድንቅ የሙዚቃ ድርሰትስ ማን ደረሰላቸው....? የዚህን ያህል ደረጃቸው እንዳደገ ገምታ አታውቅም ነበር.፡፡
👍599🤔3
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዶ/ር ሶፊያ ግማሽ ልቧን ታዲዬስ ጋር ጥላ እሩብ ልቧን ወደ ትንግርት ልካ በሩብ ልቧ ነው ከሀዋሳ ተመልሳ ቤቷ የደረሰችው፡፡የሳሎኑን በር ከፍታ ስትገባ ፕሮፌሰር ዬሴፍ ሶፋ ላይ ጋደም ብሎ ፊልም እየተመለከተ ነበር፡፡ እንደገባች በፍቅር እና በመፍቀለቅለቅ ተጠመጠመባት ..ከንፈሯን ሳመት…ዝም ብላ ሳትስመው ተሳመችለት፡፡ ሰላምታውን ከጨረሱ በኃላ የፊቷን መገባበጥ ሲመከት በጣም ደነገጠ ‹‹እንዴ ቤቢ.… ምንድነው ይሄ.....? ምን አጋጠመሽ?::<<

‹‹ትንሽ የመኪና ግጭት ነው፡፡››ዋሸችው፡፡

‹‹ታዲያ ተረፍሽ..…?››

‹‹አዎ ቀላል ግጭት እኮ ነው ..ግን አንተ እንዴት መጣህ?››

‹‹አንቺ ጋር ነዋ፡፡››

‹‹እሱማ በስልክ ነገርከኝ ...ማለቴ እንምትመጣ አልገርከኝም ብዬ ነው?››

‹‹ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈልጌ ነዋ፡፡››

‹‹እብድ እኮ ነህ.....ሰው እንኳን ከአሜሪካ ከደብረዘይት ሲመጣ ይናገራል…፡፡››

‹‹ልጅቷስ የት ሄደች ?››አለችው..ከመጣች ሰራተኛዋን ስላላየቻት ግራ ተጋብታ፡፡

‹‹አለች ..ቢራ እንድትገዛልኝ ልኬያት ነው፡፡››

‹‹ፍሪጅ ውስጥ የለም እንዴ?››

‹‹ጨረስኩታ... ከመጣው እኮ ሶስት ቀን ሆነኝ፡፡››

‹‹እስቲ መጣው በጣም ሞቆኛል... ሰውነቴን ለቅለቅ ልበል››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ወለሉ ላይ አስቀምጣ የነበረውን ሻንጣዋን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡

ዬሴፍ ከኃላዋ መላ አቋሟን እና የሚሞናደለውን መቀመጫዋን በአትኩሮት ተመልክቶ‹‹አማላይ ነሽ….›አለና ምራቁን ዋጠ፡፡ በእድለኝነቱም አምላኩን አመሰገነ፡፡ በአንድ ወር ውስጥ ደስ በሚል ሁኔታ ድል ባለ ሰርግ ያገባትና መልሶ ወደአሜሪካ ይዟት ይሄዳል..ወደአሜሪካ የመሄዱን ሀሳብ አልቀበልም ብትለው እንኳን ከእሷ የሚበልጥበት ነገር ስለሌለ እሱ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሶ ከእሷ ጋር ይኖራል ..፡፡አሁን በሱ ህይወት የጎደለችው እሷ ብቻ ነች፡፡የሚፈልገውን አይነት ትምህርት ተምሯል፣የሚፈልገውን ዓይነት ስራ እየሰራ ነው፣የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ አጠራቅሟል፣በዚህ ሁሉ ስኬት ላይ ሶፊን ማግባት ከቻለ…እሷ ደግሞ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ ከወለደችለት ..በቃ በዚህ ምድር ላይ ከእሱ በላይ ዕድለኛ ሰው ከየት ይገኛል?፡፡

ሶፊ መኝታ ቤቷ እንደገባች በቁሟ ነበር አልጋዋ ላይ የተዘረረችው፡፡የሶስት ዓመት
ፍቅረኛዋ በእሷ ትልቅ ተስፋ አድርጎ ውቅያኖስ ተሻግሮ በመምጣት ሳሎኗ ውስጥ ይገኛል፡፡ እሷ ግን በአካል ስታገኘው ውስጧን ደስታ አልተሰማትም…እንደውም በተቃራኒው የቅሬታና የመረበሽ ስሜት ነው በደም ስሯጰየተሰራጨው..በውስጧ የተፈጠረውን ስሜት ልትቆጣጠረው የምትችለው ዓይነት አይደለም፡፡ብቻ ውስጧ በነውጥ እየተናጋ ነው፡፡በልቧ ኃይለኛ ወጀብ ሲደበላለቅ ይሰማታል፡፡ከሚጡ ፣ከሰላም፣ ከሄለን ፣ከሀሊማ እና ከሙሴ ጀርባ የታዲዬስ ምስል በትልቁ ይታያታል፤ፅዬን ደግሞ እሱ ጭንቅላት ላይ ጉብ ብላ ስትደባብሰው.. በውስጧ የተፈጠረው ብስጭት ጭንቅላቷን አቃጠላት፤ከእዛ ሀሳብ ስትሸሽ ደግሞ ትንግርት ተቀበለቻት...ተፈናጥራ ከመኝታዋ ተነሳችና ልብሷን በማወላለቅ ወለሉ ላይ አዝረክርካ ወደ ሻወር አመራች ..የሰውነቷን ሙቀት ብቻ ሳይሆን በአዕምሮዋ የሚተረማመስ ሀሳብ ለማቀዝቀዝ፡፡
ፀጉሯን በላስቲክ ሸፍና ቧንቧውን ከፈተች፤ውሀው ካላይ እየተንፎለፎለ ሰውነቷን ሲያረጥበው ቀስ በቀስ የጋለው ገላዋን አቀዘቀዘላት..ያም ብቻ ሳይሆን የተረበሸ መንፈሷም እየተረጋጋላት መጣ፡፡ በመሀከል ‹‹ቤቢ..ቤብ››የሚለው የፕሮፌሰር ዬሴፍ የጥሪ ድምፅ ከነበረችበት የተመስጦ ድባብ አናጠባት፡፡

‹‹...ቤቢ አልጨረሽም እንዴ?››እያለ መኝታ ቤቱን አልፎ ወደ ሻወር ቤቱ ተጠጋ፡፡

እዛው እንዲጠብቃት በሚፈልግ ስሜት ‹‹ጨርሼያለሁ ...መጣሁ›› አለችው፡፡ እሱ ግን የሻወር ቤቱን መዝጊያ ገፋ አደረገና አንገቱን ወደውስጥ አሰገገ....ዕርቃን ሰውነቷን ሲያይ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመለከታት ሁሉ ድንዝዝ በሚያደርግ ስሜት ተውጦ የፈጠጡ ዓይኖቹን እንደተከለባት ለደቂቃዎች ቆመ…፡፡ እሷን ግን ከበዳት፤ ለማታውቀው መንገደኛ ሰው ዕርቃን ሰውነቷን ያሰጣች መሰላት..የተቀሰሩት ጡቶቿን በእጆቿ ሸፈነቻቸው፡፡

‹‹ዬሲ መጣሁ አልኩህ እኮ..!! ሳሎን ጠብቀኝ››ሳታስበው እንደመቆጣት አለች፡፡

‹‹ሶሪ.…››አለና ከደነዘዘበት በመከራ ነቅቶ በራፉን ዘጋላትና በፍቅረኛው ያልተለመደ ሁኔታ ግራ እየተጋባ ወደ ሳሎን ተመለሰ..በፊት ቢሆን ጎትታ ነበር ወደ ውስጥ ምታስገባው.፡፡

.‹‹አይ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች ይሆናል፡፡››ሲል እራሱን አፅናና፡፡

ሁሉን ነገር ጨርሳ ቢጃማዋን ለብሳ ሳሎን ስትመለስ...ሰራተኛዋ ሲኒ ደርድራ ቡና እየቆላች ነበር፡፡ ዬሴፍ ደግሞ እንደበፊቱ ሶፋው ላይ ጋደም ብሎ ቢራውን ይጐነጫል፡፡

‹‹ቤቢ መጣሽ..?›› አለት..ዩሴፍ በፊት

ከኢትጵያ ወደ አሜሪካ ሄዶ ከሶፊያ ጋር በተገናኙ እና ፍቅር በጀመሩበት ጊዜ ‹እናት› ብሎ ነበር የሚጠራት ...እናቴን ትመስያለሽ ለማለት..ከዓመታት በኃላ ግን አገሩን ሲላመድ እና የፈረንጆቹ ባህሪ ሲጋባበት..እናትን እረሳውና በቤቢ ቀየረው…ምሁራዊ የባህል ዕድገት …፡፡

‹‹አዎ ፡፡ >>አለችውና ከእሱ ፈንጠር ብላ ተቀመጠች፡፡

‹‹ቢራ ይከፈትልሽ ቤብ?››

‹‹አይ ይቅርብኝ ..ቡና ነው ያሰኘኝ፡፡››

‹‹እራት ቀርቦ በልተው የተፈላውን ቡና ጠጥተው አጠናቀቁና ተያይዘው ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡ዮሴፍ ለ7 ወራት ያላገኘው ... በጣም የናፈቀውን ገላ ዳግም የሚያጣጥምበት ሰከንድ መቅረቡን ሲያስብ ውስጡ በደስታ ተጥለቀለቀ….የሰውነቱ ግለትም ለራሱ ተሰማው፡፡ከሁሉም በፊት ግን ያመጣላትን ስጦታ ሊያበረከትላት ፈለገ ፡፡
መኝታ ቤት አስገብቶ ካስቀመጣቸው 3 ሻንጣዎች ውስጥ ግዙፉን ሻንጣ ከፈተ‹‹ቤብ እነዚህ ልብሷች እና ጫማዎች ያንቺ ናቸው..ከግምቴ ትንሽ ወፈር ብለሽ ነው ያገኘሁሽ ስለዚህ አንዳንዶቹ ሊጠቡሽ ይችላሉ››አላት፡፡

ደስ እንዲለው ለቁጥር ከሚያዳግቱ ልብሶች መካከል አንድ ሶስቱን አንሳችና እንደነገሩ ሞከረች..ግን ውስጧን ደስ አላለውም... ‹ከሚያስፈልግሽ በላይ መሰብሰብ ስግብግብነት ነው፤፤››የሚለው የሰላም ንግግር አእምሮዋን ወቀራት፡፡አይደለም ባላት ላይ ተጨምሮ ይቅርና አሁን ፊት ለፊቷ በሻንጣው የታጨቀው ልብስ ብቻ ለሀያ ሴቶች በደንብ ይበቃል‹‹እውነትም ስግብግብነት…፡፡››አለች ..ሳይታወቃት ድምፅ አውጥታ፡፡

‹‹አናገርሽኝ ቤቢ..?››አላት ያናገረችው መስሎት፡፡
‹‹አይ... ያምራል ማለቴ ነው..ለማኛውም ሌሎቹን ነገ ተረጋግቼ እለካቸዋለሁ... አሁን ደክሞኛል፡፡››

‹‹አንደርእስታንድ አረግሻለሁ....ግን ከመተኛታችን በፊት ሌላ አንድ ነገር ላሳይሽ እፈልጋለሁ››

‹‹ምንድነው ዬሴፍ..አሳየኝ ?›አለችው ፡፡

ሁለተኛውን ሻንጣ ከፈተ..ውስጡ ያለውን አወጣ… በጣም ደነገጠች ‹‹..ምንድነው ?››

‹‹ለሰርጋችን ቀን የምትለብሽው ..ከፓሪስ በትዕዛዝ የተሰራ ልዩ ቬሎ..፡፡››

ሰውነቷ ዝልፍልፍ አለባት.. የምትለውን የምትናገረውን አጣች፡፡ዬሴፍም ግራ ገባው..በፊቷ ላይ ያረበበው ድንጋጤ የደስታ ነው ወይስ የቅሬታ? መለየት አልቻለው…፡፡

‹‹ቤብ..ምነው? ፈዘዝሽ እኮ!!!››

‹‹ይሄንን ከማድረግህ በፊት ልታማክረኝ ይገባ ነበር..እኔና አንተ እኮ ስለፍቅር እንጂ ስለጋብቻ አውርተን አናውቅም፡፡››
👍556
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዶ/ር ሶፊያ ቢሮዋ ቁጭ ብላ የእለቱን ስራዋን በመስራት ላይ እያለች ፀሀፊዋ ወደእሷ መጣችና እንግዳ ሊያናግራት እንደሚፈልግ ነገረቻት.. እንድታስገባው ፍቃድ ሰጠቻት፡፡ እንግዳው ሲፈቀድለት ወደ ውስጥ ገባ ..ከመቀመጫዋ ተነስታ በክብር ጨብጣ ተቀበለችውና እንዲቀመጣም ጋዘችው፡፡

ለስራ ጉዳይ የመጣ መስሏት‹‹ምን ልታዘዝ ጌታዬ ..?››አለችው፡፡

‹‹የመጣሁት ለስራ ጉዳይ አይደለም ..ለግል ጉዳይ ነበር፡፡››

ግራ ገባት‹‹ይቅርታ ስለምን እንደሆነ ማወቅ እችላለሁ?›.›

‹‹አዎ በመጀመሪያ ግን እራሴን አላስተዋወቅኩም መሰለኝ ...ሁሴን እባላለሁ..

የትንግርት ባለቤት ነኝ፡፡››

ወንበሯ ላይ ወደኋላዋ በድንጋጤ ተለጠጠችና በረጅሙ ተነፈሰች.....ከዛ እራሷን እንደምንም አረጋጋታ <<ውጭ ሀገር ትምህርት ላይ መስለኸኝ ነበር?››

‹‹ከተመለስኩ 3 ቀን አለፈኝ፡፡››

‹‹ምነው በሰላም…?››

‹‹ምን ሰላም አለ ብለሽ ነው..የአንቺን ወደ ኢትየጵያ መመለስ ከዛም አልፎ ከትንግርት ጋር በአካል መገናኘት ስሰማ ተረጋቼ መማር አልሆነልኝም ..ስለዚህ ትምህርቱን አቋርጬ

‹‹ያን ያህል..?››

‹‹ከዛም በላይ...>>

‹‹እና አሁን ምን ልታዘዝ?››

‹‹እንድንነጋገር እፈልጋለሁ?››

‹‹ምንን በተመለከተ?

‹‹ዶ/ር ሶፊያ እኔ ትንግርትን በጣም አፈቅራታለሁ..በመሀከላችሁ ባለው የቀደመ ግንኙነት የተነሳ በህይወቷ ከበቂ በላይ መስዋዕትት ከፍላለች...ከዛ አዘቅት በከፍተኛ ጥረት ወጥታ በብዙ ትግል ነው ማገገም የቻለችው ፡፡ መልሳ ወደ እዛ ህይወት እንድትገባ በፍፁም አልፈልግም….ከዛ በላይ መሰቃየት አይገባትም፡፡ ለራሴ ብቻ አስቤ አይደለም እኔን ትተወኛለች ብዬ በመስጋት ቀንቼም አይደለም፤አንቺንም ጥፋተኛ ነበርሽ ብዬ ልኮንንሽ ወይም ልፈርድብሽም አይደለም…ግን በምንም አይነት ዳግመኛ ወደአንቺ ተመልሳ  እንድትቀጥሉ ስለማልፈግ ነው፤ እሷን በሙሉ አቅሜ ከሚመጣው ጥፋት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ ....››

‹‹እና እኔ ምን ልተባበርህ?››

‹‹አሁን የስራ ቦታ ስለሆነ ሁሉን ነገር በተረጋጋ ሁኔታ ለመነጋገር ምቹ አይደለም ..እኔ እና አንቺ እንደሰለጠነ ሰው ቁጭ ብለን እንድንነጋገር ቦታ ንገሪኝ፡፡›› እፈልጋለሁ፤የሚመችሽን ጊዜና

ዶ/ር ሶፊያ ለደቂቃዎች እንደማሰብ አለችና በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ለእሷም የወደፊት ህይወት መረጋጋት እንደሚጠቅማት ስለገመተች በሀሳብ ተስማማችና ቢዝነስ ካርዷን አውጥታ ሰጠችው‹‹ነገ በተመቸህ ሰዓት ደውልልኝና ፕሮግራሜን አመቻችቼ የምንገናኝበትን ጊዜ እና ቦታ እነግርሀለሁ››

ከመቀመጫው ተነሳና ለስንብት እጁን እየዘረጋ‹‹በትህትና ስላስተናገድሺኝ አመሰግናለሁ፤ ይሄንን በመሀከላችን ያለውን ግንኙነት ትንግርት አታውቅም፤ምን አልባት የምትገናኙ ከሆነ ባትነግሪያት ደስ ይለኛል፡፡›› አላት፡፡

‹‹አትስጋ አቶ ሁሴን ..አልነግራትም፡፡›› አለችው ፤አንገናኝም ነበር ለማለት የፈለገችው... ግን እጅ መስጠት ስላልፈለገች አልነግራትም አለችው፡፡ደግሞ ሁሴንን ወዳላታለች... ‹‹ደስ የሚል ወንዳወንድ ቁመና ያለው አማላይ ባል ነው ያገኘችው፡፡››አለች እና የሆነ የመጐምዠት አይነት ስሜት ልቧን ጠቅ ሲያደርጋት ተሰማት….እንዴ ምን አይነት ነገር ነው እያሰብኩ ያለውት..? ብላ ራሷን ለመገሰፅ ሞከረች....ግን የሁሴንን ምስል ከአዕምሮዋ አውጥታ ጥላ ጀምራ የነበረውን ሰራ መቀጠል አልተቻላትም... በዚህም የተነሳ እራሷን ለማረጋጋት ቢሮዋን ለቃ ወጥታ ወደ ቤቷ አመራች፡፡

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሰሎሞን እና ሁሴን ካሳንቺስ ከሚገኝ አንዱ ሆቴል ጥግ ይዘው ውስኪያቸውን እየተጐነጩ የናፍቆት ወሬ እያወሩ ናቸው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ቀላህ እኮ !! ከፈረንጅ ሀገር ዕውቀታቸውን ልትኮርጅ ሄደህ የቆዳ ቀለማቸውን ኮርጀህ መጣህ እንዴ?››

‹‹ምን ይደረግ ብለህ ነው...እንደሚታወቀው እኛ ኢትዬጵያውያን ኩረጃ ላይ ቀሺም ነን…..ግን ምን በጣም ናፍቆኝ እንደነበረ ታውቃለህ?››

‹‹አውቃለሁ.. እኔ ነኛ በጣም የናፈቅኩህ፡፡››

‹‹ጉረኛ…አንተ ደግሞ ጭቅጭቅህ ካለሆነ ሌላ ምን የሚናፍቅ ደህና ነገር አለህ ?እነዚህ ጠያይም ወዛና ያላቸው ልዕልት የሀገሬ ሴቶች በዓይኔ ላይ እየሄዱ ፈተና ነበር የሆኑብኝ፡፡››አለው ወደ አስተናጋጆቹ በአገጩ እያመለከተው፡፡

‹‹እንዴ!! እዛስ የፈረንጅ ቆንጆ ሞልቶልህ የለም እንዴ?››

‹‹የሰው ቆንጆ ለእኔ ምን ይሰራል? እኔ ምንም ብትለኝ ምንም እንደሀገሬ ሴት የተለየ ውበት ያላቸው የሉም ባይ ነኝ…የእኛ ሀገር ፉንጋዋ እንኳን የራሷ የሆነ ማግኔታዊ ደም ግባት
ይኖራታል ...ብቻ የትም ብትሄድ የትም የሀገሬ ሴቶች አንደኛ ናቸው፡፡››

‹‹ይሁንልህ... ይሄንን ዲስኩርህን ትንግርት ብቻ እንዳትሰማህ፡፡ >>

‹‹ብትሰማስ ምን አጠፋው ?ያሀገሬን ሴቶች ውበት ነው ያደነቅኩት፡፡››

‹‹አድናቆትህ ወሲባዊ ሆነብኛ፡፡››

‹‹የእኔ አድናቆት ሳይሆን ያንተ ጆሮ አደማመጥ ነው ወሲባዊ ያደረገው... ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ እንግባ ዳግመኛ ወደ ሆቴልህ ተመለስክ አሉ፡፡››

‹‹አዎ ምን ላድርግ ?ሴቶች እና እኔ ልንገናኝ አልቻልንም፡፡ አገኘኋቸው ስል ይሾልኩብኛል አወቅኳቸው ስል ይጠፉብኛል.... ባክህ እነሱን በተመለከተ ግራ ግብት ብሎኛል፡፡

‹‹አይዞህ ጓዴ ...ይሄ ያንተ ችግር ብቻ አይደለም የአብዛኛው ወንድ ችግር ነው፡፡

ይኖራታል ...ብቻ የትም ብትሄድ የትም የሀገሬ ሴቶች አንደኛ ናቸው፡፡››

‹‹ይሁንልህ... ይሄንን ዲስኩርህን ትንግርት ብቻ እንዳትሰማህ፡፡ >>

‹‹ብትሰማስ ምን አጠፋው ?ያሀገሬን ሴቶች ውበት ነው ያደነቅኩት፡፡››

‹‹አድናቆትህ ወሲባዊ ሆነብኛ፡፡››

‹‹የእኔ አድናቆት ሳይሆን ያንተ ጆሮ አደማመጥ ነው ወሲባዊ ያደረገው... ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ እንግባ ዳግመኛ ወደ ሆቴልህ ተመለስክ አሉ፡፡››

‹‹አዎ ምን ላድርግ ?ሴቶች እና እኔ ልንገናኝ አልቻልንም፡፡ አገኘኋቸው ስል ይሾልኩብኛል ..አወቅኳቸው ስል ይጠፉብኛል.... ባክህ እነሱን በተመለከተ ግራ ግብት ብሎኛል፡፡

‹‹አይዞህ ጓዴ ...ይሄ ያንተ ችግር ብቻ አይደለም የአብዛኛው ወንድ ችግር ነው፡፡

የአሁኑ ግን የእኔ ጥፋት ነው፡፡››

‹‹አንተ ደግሞ ምን አደረግክ…?››

‹‹እኔ ወደ ሀዋሳ ሂድ ባልልህ ይሄ ችግር አይፈጠርም ነበር፡፡››

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ... እኔ ኖርኩም አልኖርኩም እርግዝናዋ ከመጨንገፍ ይድናል ብለህ ታስባለህ?፡፡››

‹‹እሱ ሊሆን ይችላል ...ምንም ሆነ ምንም ግን አጠገቧ ብትሆን ኖሮ እሷ እንዲህ አታመርም ነበር፤አንተም አኮ ትንሽ አጥፍተሀል››

‹‹ምን አድርጌ አጠፋሁ?››

‹‹ስደውልልህ የእሷን መታመም ብትነግረኝ ሌላ ሰው እልክ ነበር፡፡››

‹‹እሱ ሰበብ ነው.. እናቷ፣አባቷ፣ እህቷ.. ከአስር ሰው በላይ ዙሪያዋን ከቧት ነበር ..ደግሞ በጣም ተሸሏት ወደኖርማል ጤንነቷ
በተመለሰች ጊዜ ነው ተነስቼ የሄድኩት፡፡መልሳ እንደምትታመም እና ይሄ ነገር እንደሚፈጠር ጠንቋይ አልቀልብ በምን ላውቅ እችላለሁ? እንደውም ይሄንን ሰበብ አድርጋ ጋብቻውን ለማፈረስ በምክንያትነት ተጠቀመችበት እንጂ በፊቱኑም ከእኔጋ መኖር የሰለቻት ይመስለኛል፡፡ይሄን ያህል ይቅርታ የማያሰጥ ጥፋት አጥፍቼያለሁ ብዬ አላስብም፤ የጠፋው የእኔም ልጅ ነው፤ ወንድ ልጅ በመሆኑ እንዴት ተደስቼ እንደነበረ…እንዴት በናፍቆት ወደእዚህች ምድር የመምጫውን ቀን እጠብቅ እንደነበረ ከማንም በላይ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ በተፈጠረው
👍69
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሰሎሞን ድቅቅ ካደረገው እንቅልፍ ቢነቃም

ዓይኖቹ አልገለጥ ስላሉት አሻሽቶ ሊያነቃቸው
ፈልጐ ቀኝ እጁን ለማንቀሳቀስ ሲሞክር
አልተቻለውም፤የሆነ እጁ ላይ የተጫነ ነገር አለ፤የሆነ ሰው አቅፎል..‹‹ወይ እዳዬ !!ማታ ተሳሳትኩ መሰለኝ... ሴት ይዤ ገብቼያለሁ ማለት ነው፡፡›› ሲል አሰበ፤ እሱን ተወውና
ግራውን ሞከረ ተመሳሳይ ነው፡፡በዚህን ጊዜ ደነገጠ ..እንዴት ሁለት ሴት ልገዛ እችላለው?›› ድንጋጤው አይኖቹ ተበርግደው እንዲከፈቱ አገዘው ፡፡ወደ ቀኙ ዞረና አየ…..ልጁ ዕፀ-ህይወት ናት ዝርግትግት ብላ ክንዱን
ተንተርሳ በነጻነት ተኝታለች...ወደ ግራው
ዞረ..ሌለኛዋ ልጁ ዕፀ‐ፍቅር በተመሳሳይ ሁኔታ ግራ ክንዱ ላይ ተመቻችታ ተኝታለች፡፡ከእሷ ቀጥሎ ቢጃማ ለባሽ የሆነች ገዘፍ ያለች ሴት ከአንሶላው ሳትወጣ ቁጭ ብላ መፅሀፍ
እያነበበች ነው፡፡

‹‹የፈጣሪ ያለህ!!››አለ የልጆቹ ሲገርመው ከአመታት በፊት የፈታት ሚስቱን ከጎኑ ሲመለከት፡፡ ‹‹ምን ልትሰራ እሱ ቤርጓ ተገኘች?..የቤቱን ዙሪያ ገባ በግርምት ቃኘ... ቤርጎው አይደለም ያለው ፤ የድሮ ቤቱ... የበፊት መኝታው ክፍሉ ውስጥ..የበፊት አልጋው ላይ ከበፊት ሚስቱ ጋር…የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡

‹‹እየቃዠው መሆን አለበት?››ድምፅ አውጥቶ ተናገረ፡፡

የውብዳር የተናገረውን በትክክል አጥርታ ባትሰማም የሆነ ነገር እንዳለ ድምፁ ጆሮዋ ጋር ስለደረሰ የምታነበውን መጽሀፍ ቅዱስ በመክደን ያቀረቀረ ግንባሯን ወደ ላይ ቀና አደረገችና << ነቃህ እንዴ….?እንዴት ነው ሰላም አደርክ?››አለችው በፍጹም ትህትና ፡፡

ለእሷ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የራሱን ጥያቄ አስቀደመ ‹‹የት ነው ያለሁት?››ጠየቃት፡፡

‹‹ቤትህ ነዋ፡፡››

እንደመበርገግ አለና ልጆቹን ከክንዶቹ ላይ አንሻራቶ እራሱን ነጻ በማድረግ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ተቀመጠ፡፡

‹‹ቀስ... ቀስ.. ልጆቸህን ትቀሰቅሳቸዋለህ››አለችው በለሆሳሳ፡፡

‹‹ቆይ ማታ ሰክሬ ነው አይደል የመጣሁት .. ? በጣም እረበሽኳችሁ እንዴ....? ስትረብሽ ልጆችህም አይተውህ ነበር እንዳትይኝ ብቻ… አዝናለሁ፡፡ እንዲህ ለማድረግ ፈልጌ አልነበረም፡፡ ትንሽ ተበሳጭቼ ስለነበር በዛ ላይ መጠጥ አብዝቼ ስወስድበት እራሴን አስቶኝ ነበር ማለት ነው..አንቺም እኮ ትክክል አይደለሽም፤ስመጣ ዝም ብለሽ ታስገቢኛለሽ እንዴ…? ገና ከውጭ በራፍን አልፌ ሳልገባ ዘበኛው እንዲመልሰኝ አታደርጊም ነበር?››

ዝም ብላ በፍዘት ስታዳምጠው ከቆየች በኃላ << ማታ ስለሆነው ሁሉ ምንም ነገር አታስታውስም ማለት ነው?›.አለችው፤ የሆነ ሀይለኛ የሚቀስፍ ስጋት እና የሚቀዘቅዝ ፍርሀት በሰውነቷ እየተሰራጨባት፡፡

‹‹ቆይ ቆይ..ማታ እኔ ቤርጎ አንቺ…››የሆነ እንደህልም አይነት ትዝታ በአዕምሮዎ ብልጭ ድርግም አለበት፡፡

‹‹አዎ መጥቼ ነበር፡፡››

‹‹አዎ እንደ እሱ በይኝ.. እንጂማ ያን ያህል ላብድ አልችልም፡፡ >>

‹‹የምን እብደት አመጣህብኝ?››

‹‹...ቀጥታ ዝም ብዬ እዚህ በመምጣት ካላደርኩ አልልማ ... አንቺን እዛ ሳይ ተከትዬሽ መጥቼ እንጂ..፡››

‹‹እንደዛም አይደለም፡፡››

‹‹ታዲያ እንዴት ነው?››

‹‹እኔ ነኝ ለምኜህ ማለት ይቅርታ ጠይቄህ ይዤህ የመጣሁት...››

‹‹እየቀለድሽ አይደለም አይደል?››

‹‹እውነቴን ነው ሶል... ተነጋግረን ተስማምተን ነበር የመጣሀው፡፡ጥፋት ያጠፋህ መስሎ ከተሰማህ እንኳን ጥፋቱ የእኔ ነው እንጂ ያአንተ አይደለም፡፡ አንተ ምንም አላደረግክም …እኔም ግን ወድጄ አይደለም ፤ እስቲ ልጆቻችንን እያቸው፤ዛሬ ከጎናቸው ብትሆን እንዴት የሰላም እንቅልፍ እንደተኙ.. አቤት ማታ ቀስቅሰህ መጥቼያለሁ ስትላቸው የተደሰቱት መደሰት ልነግርህ አልችልም..ታዲያ ለእነሱ ስትል ይቅር ብትለኝ ምን አለበት..?በቃ ምንም ልበድልህ ... ምንም ላጥፋ ለእነሱ ስትል ልትረሳልኝ አትችልም?››

‹‹ኧረ ቆይ.. አንቺ ባጠፋሽው መጠን እኮ እኔም አጥፍቼያለሁ›..

‹‹ታዲያ በቃ ይቅር እንባባላ..በቃ በስካር
መንፈስም ቢሆን ወደ ቤትህ አንዴ ገብተሀል
..በፈጠረህ በዚህ በምታምንበት መጽሀፍ
ቅዱስ ልለምንህ ፤ ተመልሰህ ከቤትህ
አትውጣ... ከልጆችህ ጋር ኑር...አንተ
ከምትወጣ እኔ ብወጣ ይሻለኛል...ሴት ልጆች
አባታቸውን አብልጠው ይወዳሉ ሲባል አባባል
ብቻ ይመስለኝ ነበር..በራሴ ልጆች ነው እውነት
መሆኑን ያረጋገጥኩት... አንተን አጥተው መኖር
በጣም ነው የሚከብዳቸው... ስለዚህ
ባክህ..ባክህ››በማለት በቃላትም ...በአይኖቿ
እርግብግብታም ተለማመጠችው፡፡እጁን ላካና አቅፎ ወደ ራሱ በመጎተት ደረቱ ላይ ለጥፎት በጆሮዋ ‹‹እኔም የትም አልሄድ ..አንቺ
እንዳልሽው በቃ ያለፈውን እንርሳው... የውሾን
ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን››አላት፡፡

‹‹እሺ የእኔ ጌታ አመሰግናለሁ››አለችውና የሚንጠባጠበውን እንባዋን በቀኝ እጇ እያበሰች ከእቅፉ ወጥታ አልጋውን ለቃ ወረደች፡፡በዚህ ጊዜ በመሀከላቸው ያለችው ዕፀ- ህይወት ከእንቅልፏ ባና ዓይኖቿን ከመግለጧ በፊት መጀመሪያ የጠየቀችው ጥያቄ‹‹አባቴስ?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹አለሁልሽ የእኔ ቆንጆ >> ብሎ ወደ ራሱ አስጠግቶ አቀፋት... ሙሉ በሙሉ ነቃችና እላዩ ላይ ተንጠልጥላ እያገላበጠች ትስመው ጀመር፡፡ በዚህም አረካችም መንታ እህቷንም ቀሰቀሰቻት ..ሰሎሞን ተይ ትተኛ ቢላትም ልታዳምጠው አልፈለገችም፡፡ ሁለቱም ልጆቹ ለመጀመሪያ ቀን ያዩት ይመስል ትንፋሽ እስኪያጥረው እና ድክም እሲኪለው ተላፉት ፣ሳሙት፣እላዩ ላይ ጨፈሩ፡፡ በመጨረሻ የውብዳር ነበረች በግድ አላቃ ለቁርስ መኝታ ቤቱን ለቀው ወደ ምግብ መመገቢያ ቤት እንዲሄዱ ያስገደቻቸው፡፡

በፊት አብሯቸው ይኖር በነበረበት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ዓመታት በእጇ ትሰራለት የነበረውን እና እሱም በጣም እየወደደውና እሷንም እያመሰገነው ይበላው የነበረውን ምግብ ነበር ሰርታ ለቁርስ ያቀረበችው ፡፡በሳቅ እና በጨወታ ታጅበው
ቁርሳቸውን እየበሉ ግማሽ እንደደረሱ የሳሎኑ በራፍ ተንኳኳ፡፡

‹‹ይግቡ ..ክፍት ነው›› አለች የውብዳር ከመቀመጫዋ ሳትነሳ.፡

በራፉ ተከፈተ..ሁሴን ነበረ የመጣው ፡፡

‹‹እየተጣራጠርኩ ነው የመጣሁት ስልክሽ አይሰ......››ንግግሩን አቋረጠ፡፡እርምጃውንም መሀል ሳሎን ላይ ገታው፡፡የሰሎሞን እዛ ቤት ውስጥ መገኘት ፍጽም ከግምቱ ውጭ የሆነ ክስተት ነበር... የሆነ ውሽማው ቤት ሊሰርቅ የሄደ ሰው ከባልዬው ጋር የመፋጠጥ አጋጣሚ እንዳጋጠመው ሰው ነው አደነጋገጡ፡፡

<< ና እንጂ ....አንተ እንወድሀለን ማለት ነው .. ቁርስ ላይ ደረስክ.…‹ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ መልሰኝ› የሚባለው እንደዚህ ነው››አለችው የውብዳር፡፡

ሁሴን ግን የእሷን ወሬ አልሰማም‹‹ይሄ ሰውዬ
እዚህ ምን ይሰራል? ››አላት እንደምንም እግሮቹን አነቃንቆ ወደ እነሱ እየተጠጋ።

‹‹እቤቱ ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ ቁርስ እየበላ ነዋ››

‹‹..ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር >> ልትል አስባ ነበር ያልተረጋገጠውን የሚስትነት ማዕረጓን መልሳ የዋጠችው›› የምታድርበት ሆቴል እኮ ሁለቴ ነዋ የመጣሁት ስልክህም ዝግ ነው ..ግራ ሲገባኝ ጊዜዬን ከማባክን እነዚህ ልጆች ልይ ብዬ ወደ እዚህ ጎራ ማለቴ እኮ ነበር..እንጂማ.. ››በማለት ለልጆች ይዞላቸው የመጣውን ቸኮሌት አከፋፈሏቸው ወንበር ስቦ ተቀመጠ ፤አመስግነው ተቀበሉት፡፡
👍686
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፅዮን እና ታዲዬስ እሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብላው እሷ ለስላሳ እሱ ቢራ አዛው እየተጐነጩ ያዘዙትን መክሰስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡የምረቃ በዓሉ ካለፈ በኃላ በሣምንታቸው ዛሬ መገናኘታቸው ነው፡፡‹‹እሺ ፅዮን ለምን ግን ወይን ነገር አትሞክሪም ነበር?››

<<አንደኛ አልኮል የሚባል ነገር ሞክሬ አላውቅም ...ሁለተኛ የማያየው ዓይኔ ሳያንስ ጠጥቼ እምሮዬንም እንዳያይ አድርጌ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አይ ሳታበዢ ማለቴ እኮ ነው፡፡››

‹‹ያው መጠጣት ከጀመርኩ ቢያንስ አንድ ብርጭቆ መጨረሴ ይቀራል..ያ ማለት ደግሞ እኔን ለማስከር በቂ መጠን ነው…ግድ የለህም ለስላሳው ይብቃኝ፡፡››

‹‹ያው ብትሰክሪም እኮ እኔ አብሬሽ አለሁ ብዬ ነው፡፡››

‹‹አይ እኔ በራሴ ድክመት እራሴን ጥዬ ሰውን ደግፉኝ ማለት አይመቸኝም፡፡››

‹‹ተቀብያለሁ››አለ በጠንካራ መንፈሷ ተደስቶባት፡፡

‹‹ፂ ስለበቀደሙ ጉዳይ እንድናወራ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ››ወደዋናው ቁምነገር ድንገት ገባ።

‹‹ይመቸኛል..እኔም እንደዛ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ነው የመጣሁት..ቀጥል፡፡››

‹‹እንዴት እንደምቀጥል አላውቅም፤ብቻ…..››

‹‹ታዲ ..እኔ የ28 ዓመት ወጣት ነኝ፤በህይወቴ ብዙ ውጣ ውረድ ያየው ሰው ነኝ.. ህይወት ነጩንም ሆነ ጥቁሩን ክፍሎቿን በማፈራረቅ አሳይታኛለች፡፡አንድን ነገር ፈልጌዋለሁና የግድ አገኘዋለሁ ማለት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡››

‹‹በህይወትማ ምንም ነገር ከልብሽ አገኘዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ ታገኚዋለሽ፡፡››

‹‹አውቃለሁ....የሆነ ነገር አገኛለሁ ብለህ ከልብህ ከተመኘህ፤ ምኞትህንም ለማሳካት በሙሉ ጉልበትህ ከተንቀሳቀስክ የማይሳካልህ ነገር እንደሌለ እኔም አምናለሁ፤ይሄ ግን ፍቅር ላይ ሲሆን ከሚሰራበት ጊዜ ይልቅ የማይሰራበት ጊዜ ይበልጣል፡፡››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትይ ቻልሽ…?ከፍቅር አምላክ ጋር ትንሽ የተቀያየማችሁ ይመስላል፡፡››

‹‹ትንሽ አልከው...ምን ትንሽ ብቻ ...ለአምስት አመት ተኮራርፈን በደረሰበት ላልደርስ ተማምለን… ሳይደርስብኝ ሳልደርስበት ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ነበር ፡፡››

‹‹ታዲያ እንዴት ሆናችሁ?››

‹‹ምን እንዴት ሆናችሁ አለው... አንተን ሳገኝ መሀላዬን አፍርሼ ደጅ እየፀናሁ እያየኸኝ?››

‹‹ደጅ ጽናት አልሽው፤ለማንኛውም እስኪ በምን ተኮራርፋችሁ እንደነበረ ብትነግሪኝ ? ማለት ደስ ካለሽ…..››

ዝም አለች... ጭንቅላቷ ወደታች ተደፋ‹‹…ምን መሰለህ......››ብላ ልትቀጥል ስትል ያዘዙት መክሰስ መጣና ቀረበላቸው፡እየተጎራረሱ በሉ..ከጨረሡ በኃላ አብረው ወደ እጅ መታጠቢያው በመሄድ ታጠቡና ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ታዲዬስ ሁለተኛ ቢራውን አዘዘ..ዛሬ ካለወትሮው ጠጣ ጠጣ አሰኝቶታል፡፡

‹‹ምነው ዝም አልከኝ ...?››አለችው ልትጀምርለት የነበረውን ታሪኳን እንድትቀጥልለት ባለመጠየቁ ቅር ብሏት...

‹‹ኧረ ዝም አላልኩሽም ….ዝም ስላልሽ እኮ ዝምታሽን ላለመረበሽ ብዬ ነው፤እኔ ዝምታዬን ከሚረቡሹኝ ንግግሬን ቢያቋርጡኝ ይሻለኛል፡፡››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ግን አሁን ዝምታ ውስጥ ስላልሆንኩ አትረብሸኝም

...ይሄውልህ ታዲ እኔ የሻሸመኔ ልጅ ነኝ፡፡ ትውልዴ እስከተወሰነ ጊዜም እድገቴም እዛ ነው፡፡ አባቴን እና እናቴን አላውቃቸውም ማለቴ በአካል አላውቃቸውም...ያሳደገችኝ የአባቴ እናት አያቴ ነች ... እናቴ ገና አንድ አመት ሳይሞላኝ ነው አባቴ ክንድ ላይ ጥላኝ ሀገሩን ጥላ የጠፋችው፡፡ ከአንድ አመት በኃላ አባቴም በተራው ሁኔታዎች ስልችት ሲሉት እኔን ለእናቱ ሰጥቶኝ ውትድርና ተቀጥሮ ለጦርነት ወደ ሰሜን ይሄዳል፡፡

ከዛ በኃላ አያቴ ያለቻትን አንድ ክፍል ቤት በደባልነት አንድ ደደፎ ለሚባል ከገጠር ለትምህርት ለመጣ ልጅ አከራይታ ከእሱ ከምታገኘው ገቢ በተጨማሪም በደካማ አቅሟ ጠላ እየጠመቀች አንዳንዴም አረቄ እያወጣች በመሸጥ እኔን ማሳደግ ትጀምራለች ፡፡ስምንት ዓመት ሲሞላኝ ግን ያልታሰበ ችግር ተፈጠረ..

ዓይኖቼን ይጋርደኝ ጀመር ..በወቅቱ አያቴ እንኳን ለህክምና ለሆዴም መሙያ የሚሆን ሳንቲም ለማግኘት በመከራ ነበር ሚሳካላት…፡፡

ባቅሟ የቻለችውን ፀበሉንም የባህል መድሀኒቱንም ብትሞክርልኝም ከቀን ወደቀን እየባሰብኝ መጥቶ ከአንድ አመት በኃላ ሙሉ በሙሉ ሁለቱም አይኖቼ ታወሩ..ከዛ ትምህርቴንም ከሁለተኛ ክፍል ግማሽ ላይ አቆረጥኩ፡፡አያቴ ግራ ገባት ፡፡በሚመጣው አመት ግን ያ እቤታችን በደባልነት ይኖር የነበር ያልኩህ ተማሪው ልጅ ሚሽኖቹ ጋር ተሯሩጦ በአዳሪነት አስገባኝ፡፡ ይገርምሀል አያቴን ልክ እንደእናቱ ነበር የሚወዳት... እሷም ከእኔ ለይታ አታየውም ነበር እንዲሁ ስሙ ተከራይ ተባለ እንጂ እኛ የምንበላውን ይበላል እሱ የሚበላውን እንበላለን ስናጣ አብረን እንራባለን፡

እኔ ሚሽን በአዳሪነት ከገባሁ በኃላ አያቴ ጋር እኖር ከነበረው ኑሮ በተሻለ ሁኔታ እኖር ጀመር፤ ትምህርቴንም በጥሩ ሁኔታ መከታተል ጀመርኩ፤ድንገት ግን ምን እንደተፈጠረ ታውቃለህ? ብቸኛ ዘመዴ የሆነችው አያቴ ሞተች፡፡በወቅቱ የ5ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ… ዕድሜዬም ወደ 14 አካባቢ ተጠግቶ ነበር ..በጣም ነው የከበደኝ፡፡ ለመጽናናት በጣም አስቸግሬ ነበር፡፡ይገርምሀል እቤታችንን ተከራይቶ ነበር ያልኩህ ልጅ በወቅቱ አስረኛ ክፍል ደርሶ ነበር፡፡በአያቴን ሞት በጣም ነበር ያዘነው…፡፡

ከዛ እኔን መንከባከብ የእሱ ኃላፊነት እንደሆነ ነበር የሚያስበው፤ በሳምንት ሁለት ቀን እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር፤ደግሞ ሲመጣ ባዶ እጁን አይመጣም..ደብተር፣እስኪሪብቶ፣የፀጉር ቅባት፣ማበጠሪያ፣ፓንት ...ብቻ የማይገዛልኝ ነገር አልነበረም፤ካጣ ካጣ የ 25 ሳንቲም ማስቲካም ቢሆን ይዞልኝ ይመጣል..ደግሞ እኮ የሚገርመው እሱም ምንም የሌለው የደሀ ገበሬ ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ግማሽ ቀን ይማራል ኑሮውን ለመደጎም ደግሞ ግማሽ ቀን ጋራዥ ይሰራል...ከዛ በሚያገኛት ሽርፍራፊ ገንዘብ ነበር ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ይገዛልኝ የነበርው፡፡

በዛ ላይ የቤት ኪራዬን በየወሩ ቀን እንኳን ሳያስተጎጉል አምጥቶ ይሰጠኛል…ተወው ይቅር አያስፈልገኝም ብለውም አይሰማኝም...‹ነገ ብትቸገሪ ለአንድ ነገር ይሆንሻል.. አስቀምጪው >> ይለኛል...እኔ ደግሞ የተለየ ወጪ ስለሌለኝ እጄ ላይ እየተጠራቀመ ሲበዛብኝ አንድ የምወዳት አስተማሪዬ ጋር ማስቀመጥ ጀመርኩ፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ቀናቶች እየነጐዱ እኔም እያደግኩ በትምህርቴም እየገፋሁ መጣሁ..በነገራችን ላይ ሙዚቃ መሳሪያ መነካካት የጀመርኩት እዛው ሻሸመኔ አይነስውራን ትምህርት ቤት እያለሁ ነበር፡፡

ስምንተኛ ክፍል ስደርስ ደደፎ 12ተኛ ክፍል ጨርሶ ነጥብ ስላልመጣለት መንጃ ፍቃድ አውጥቶ ሹፌር ሆነ፡፡በዚህን ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን መምጣቱን አቁሞ በሳምንት አንዴ
..አንዳንዴም በአስራአምስት ቀን አንዴ ይመጣ
ጀመር፡፡ሲመጣ ታዲያ ይዞልኝ የሚመጣውን
ነገር አትጠይቀኝ ... ምንም የሚቀረው ነገር
አልነበረም፤ለእኔ አይደለም ለጓደኞቼ እራሱ ይተርፍ ነበር፡፡ የጽዮን ወንድም መጣ ከተባለ ጓደኞቼ በሙሉ ጥርስ በጥርስ ነበር
👍728
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሁድ ቀን ነው 8 ሰአት ከካባቢ ደደፎ እንግዳ ይዞ ቤት መጣ፤ምን ዓይነት እንግዳ መሰለህ ? ... የሚያስጠላ ቀፋፊ ድምፅ ያላት፤ሾካካ አረማመድ የምትራመድ፤ባለ ሻካራ ድምፅ ሴት፡፡ ምን አልባት ያልኳትን አይነት ሴት ላትሆን ትችላለች፤በወቅቱ ለእኔ የተሰማኝ ግን እንደዛ ዓይነት ሴት እንደሆነች ነበር፡፡››

‹‹ኪያ ተዋወቂያት ፀዳለ ትባላለች..ፀዳለ እሷ ደግሞ ጽዮን ትባላለች እህቴ ነች፡፡ ››አላት፡፡

‹‹ተዋወቅንና ቁጭ አሉ…ውይ ኪያ ሳልነግርሽ ….ከፀዳለ ጋር አንድ መስሪያ ቤት ነው
የምንሰራው አሁን ግን….››ብሎ ንግግሩን አንጠልጥሎ ተወው፡
እኔም የልጅቷን ድምጽ ከሰማሁበት ደቂቃ ጀምሮ የሆነ ቅፍፍ ብሎኛልና‹‹አሁን ግን ምን…?››ብዬ ጠየቅኩት፡፡

‹‹ፍቅረኛዬ ሆናለች….እሺ ካለቺኝ በቅርብ እንጋባና ትቀላቀለናለች፡፡››አለኝ፡፡

መሀከል ወለል ላይ ቆሜ ነበር የሚያወራውን ሳዳምጥ የነበረው ... ወዲያው ግን ብዥ አለብኝ...ልቤን ሲያጥወለውለኝ ወደ ጓዳ ለመግባት ቀኝ እግሬን አነሳሁና መልሼ መሬት ለማሳረፍ ስሞክር መሬቱ የጥልቅ ገደል ያህል በኪሎ ሜትሮች ራቀብኝ፡፡ከዛ ዥው ብዬ ወደ ኃላዬ እየወደቅኩ ሳለ ደፎ ተንደርድሮ ከመሬቱ ከመላተሜ በፊት ሲታደገኝ..ከዛ ማንነቴም ሲጠፋኝ፡፡

ከደቂቃዎች በኃላ ስነቃ ደደፎ በድንጋጤ በፎጣ ውሃ እየነከረ እራሴን ልቤን ሲያቀዘቅዝልኛል ሴትዬዋ በዛ ቀፋፊ ድምጿ < አይዞህ ይሻላታል …አትደንግጥ፡፡›› እያለች ስታፅናናው ሰማሁ ፡፡ የእሷን ድምጽ
የማልሰማበት የት ልሂድ....? ደሞ ያበሳጨኝ የእኔ መታመም ሳይሆን የእሱ ለእኔ መጨነቅ ስላስጨነቃት ነበር ፡፡ እንደምንም አንደበቴን አላቅቄ‹‹.. ደፍ ሰላም ነኝ እራሴን ስላመመኝ ትንሽ ልተኛበት ..ይተወኛል› አልኩት፡፡

በመናገሬ ደስ እያለው ብርድልብሱን አለባበሰኝና ያቺን ባለቀፋፊ ድምፅ ሴት
ከመኝታ ቤት ይዞልኝ ወጣ፡፡እኔም የምፈልገው

እሱን ነበር፡፡ግን ምን ነካኝ….?የእሱ ፍቅረኛ
መያዝ እኔን እራሴን እስክስት ድረስ እንዴት
ሊያደርሰኝ ቻለ... ? ለእኔ ወንድሜ አይደል እንዴ..?አይደለም፡፡ ለእኔ ዘመዴ አይደለ እንዴ….? አይደለም፤እና አፈቅረዋለው ማለት ነው...?. መጠርጠሩስ፡፡ በቃ የልቤን ጥያቄ እና የአዕምሮዬን መልስ ስሰማ ሰማይ ምድሩ
ተደበላለቀብኝ፤ምን ይሻለኛል….?እንዴት ነው
ለዓመታት እሱን አቅፌ የሰላም እንቅልፍ
በተኛሁበት አልጋ ላይ ሌላ ሴት መጥታ እኔን
ሳሎን ወዳለው ፍራሽ ላይ ወርውራኝ እሷ እሱን
አቅፋ የምትተኛው…? በፍፅም አይሆንም፡፡
ይሄንን ቤት ለቅቄ መውጣት አለብኝ…? ወጥቼ ወዴት ነው የምሄደው? አለሜ ጠቅላላ ..ዘመዴ መሸሸጊያ እሱው ነው፡፡ ቢሆንም እሱን ከሌላ ሴት ጋር እያየሁ መኖር አልችልም ::

መቻል አለብሽ... እሱ እኮ እንደ ታናሽ እህቱ አይቶሽ ነው በህይወቱ ሙሉ ሲንከባከብሽ የኖረው ፡፡ታዲያ ውለታውን እንዲህ ነው እንዴ የምትመልሺው..… ?ዕድሜሽን በሙሉ ያንን ሁሉ በምንም የማይለካ ደስታ ሲመግብሽ ቆይቶ ዛሬ አንቺ ውለታውን እንዲህ ነው የምትመልሺው...? የእሱ ደስታ እንዴት ነው እንዲህ ሊያበሰጭሽ የቻለው..? እስከመቼ ሳያፈቅር እና ሳያገባ ላንቺ ሲል ተቆራምዶ ይኖራል…?››አይምሮዬና ልቤ ጦርነት ጀመሩ ግን ቆረጥኩ… በቃ፡፡

ቢያንስ አሁን ትልቅ ሰው ነኝ.. ከአያቴ ቤት ኪራይ ለዓመታት የተጠራቀመልኝ 5ዐሺ ብር ባንክ ቤት አለኝ ፤ በዛ ላይ ከቸገረኝ የአያቴን ቤት እሸጠዋለሁ፡፡ያ ደግሞ ትምህርቴን እስክጨርስ በርግጠኝነት ይበቃኛል.. ለጊዜው
የሚከራይ ቤት እስካገኝ ጓደኞቼ ጋር አርፋለሁ ፡፡ከዚህ ቤት ግን ዛሬውኑ መልቀቅ አለብኝ፡፡ አዎ አሁን ሊሸኛት ሄዷል ፤ ከመምጣቱ በፊት መፍጠን አለብኝ > አልኩና ከተኛሁበት ተነስቼ ሻንጣዬን በዳበሳ ፈለግኩና ፊት ለፊት ያገኘሁትን እና መሰብሰብ የቻልኳቸውን የእኔ የሆኑ እቃዎችን ከታተትኩና ሻንጣዬን በአንድ እጅ የገንዘብ ቦርሳዬን በትከሻዬ፤ ዘንጌን በሌላው እጄ ይዤ ከመኝታ ቤት አልፌ የሳሎኑን ደጃፋ በጥበብ ተሸግሬ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ለቅቄ ልወጣ ስል‹‹እንዴ ወዴት ነው?››የሚለው የደደፎ ድምጽ አንዱን እገሬን በአየር ላይ ተንከርፍፎ እንዲቀር አደረገው፡፡ ተንደርድሮ መጣና ክንዴን አጥብቆ ያዘኝ፡፡

‹‹ኪያ ምን እየሰራሽ ነው?›› ሲጠይቀኝ ሰውነቱ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ እንደሆነ በያዘኝ እጆቹ ንዝረት ተረዳሁ፤ አሳዘነኝ፡፡

‹‹ንገሪኝ እንጂ የት ነው?››

‹‹በቃ ልታገባ አይደል እንዴ? ቤቱን ልለቅልህ ነዋ፡፡››

በጥፊ አላሰኝ... አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ ..አቤት የተደሰትኩት መደሰት..አቤት የተሰማኝ ቅብዥርዥር ስሜት፡፡ ከተዋወቅንበት ቀን አንስቶ እንኳን ሊመታኝ ክፉ ቃል እንኳን ተናግሮኝ አያውቅም ...የደነገጥኩት ለዛ ነው፡፡ የተደሰትኩት ደግሞ የመታኝ ስለሚፈልገኝ ነው የሚል ስሜት ስለተሰማኝ ነበር፡፡ከዛ ቦርሳውንም ሻንጣውንም ነጥቆኝ እየገፈተረ ወደ ውስጥ አስገባኝ እና ወንበር ላይ ገፍትሮ አስቀመጠኝ..››

‹‹እየሰማኸኝ ነው አይደል ታዲ?››

‹‹በጣም እየሰማሁሽ ነው.፡፡ በሰው ወሬ መካከል እሺ ..ከዛስ ..ምናምን ማለት ስለማልወድ ነው..፡፡››

ከዛ እየተንዘረዘረ‹‹እኔ አንቺን ከቤት አስወጥቼ ነው ሚስት የማገባው?እንዴት እንዴት ነው የምታስቢው…? በቀላሉ እንድታገባ አልፈልግም አትይኝም?››

‹‹እንድታገባ አልፈልግም ብልህ እሺ ትለኛለህ?››

‹‹በትክክል እልሻለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንድታገባ አልፈልግም..አንተን ከሌላ ሴት ጋር እንዳይህ ፈጽሞ አልፈልግም››አልኩት፡፡ ፀጥ አለኝ ፡፡ ፀጥታው አስር ለሚሆኑ ደቂቃዎች ነው የቆየው... ግን የአስር ሺ አመትን ያህል ርዝመት ነበረው፡፡ ግራ የሚያጋባ የሚያስደነግጥ ፀጥታ….ነፍስን የሚያፍን ፀጥታ እንደምንም ያለኝን ጉልበት አጠራቅሜ‹‹ይሄው አላልኩህም… እሺ አትልም አላልኩህም .. ?እኔ እዚህ ቤት መኖር አልፈልግም በቃ…››ተንጣጣሁበት፡፡

‹‹ባክሽ ዝም በይ፤እሺ ብዬሻለሁ፤በቃ ትቼያታለሁ፡፡ ፍቅረኛዬም እንዳልሆነች
እንደማላገባትም ነገ እነግራታለሁ...አሁን ለምቦጭሽን አትጣይብኝ፡፡›› አለኝ፡፡

ከተቀመጥኩበት ተንደርድሬ በመነሳት ተጠምጥሜበት ልስመው ስል አንድ ኩርሲ ነገር አደናቀፈኝና ልዘረገፍ ስል በአየር ላይ ተቀበልኝ ...በአንድ ቀን ለሁለተኛ ጊዜ ከመፈጥፈጥ ታደገኝ፡፡ ለዛም ምስጋና እንዲሆንልኝ ወደራሴ ጎትቼ ጉንጩን ሳምኩት…፡፡

ከዛ .... ከአንድ ወር በኋላ ነበር ነገሩን አንስተን ዳግም የተነጋገርንበት፡፡

እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ‹‹ኪያ ታፈቅሪኛለሽ እንዴ?›› አለኝ፡፡

‹‹አንተ ምን ይመስልሀል?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ገብቶኝ እኮ ነው የጠየቅኩሽ .. ምን አልባት አንቺ ድሮ አይንሽ በሚያይበት ወቅት ጎረምሳ ስለነበርኩ አሁንም ልክ እንደዛው አድርገሽ ስለሺኝ ተሸውደሽ  እንዳይሆን ....ቢያንስ ከአስር አመት በላይ በዕድሜ እበልጥሻለሁ... አረጅብሻለሁ፡፡››

‹‹እንጂ ታፈቅረኝ ነበር.?

‹‹.እኔማ በጣም ነው ማፈቅርሽ….ግን ደግሞ ሳስብ በብዙ ነገር የምገባሽ አይደለሁም፡፡ እኔ አንድ ተራ ሹፌር ነኝ..አንቺ ደግሞ ነገ ብሩህ ሕይወት የሚጠብቅሽ በጣም ዝነኛ የመሆን ዕድል ያለሽ ሴት ነሽ፡፡ አየሽ ነገ ይሄ በውለታ አስሯት አታሏት ህይወቷን አበላሸባት፤ደግሞ ሽማግሌ እኮ ነው!!! በዛ ላይ፤ እያሉ እንዲሳለቁብኝ እና አንቺም ወይኔ ብለሽ እንድትፀፀቺ ስለማልፈልግ እንጂ እኔማ መች አንቺን ሳላፈቅር ቀርቼ አውቃለሁ፡፡››ብሎ ቁጭ አለ፡፡… አቤት የዛን ቀን የተደሰትኩት መደሰት፣አቤት
👍819🥰8😁3
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከሆቴል ይዟት ሲወጣ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡55 ሆኖ ነበር፡፡‹‹ፂ በጣም እኮ ጨልሞል... በዛ ላይ የከተማው መብራት እንዳለ ጠፍቷል የግድ ቤትሽ ድረስ ልሸኝሽ ይገባል፡፡››

‹‹መብራት ባይጠፋ ኖሮስ ?››

‹‹መብራት ባይጠፋማ ነፃነት ሆቴል ድረስ ከሸኘሁሽ ከዛ ወዲያ ቅርብ ስለሆነ እንቺም ወደ ቤትሽ እኔም ወደቤቴ እንበታተን ነበር››

‹‹ተው እንጂ ?እያሾፍክብኝ ነው አይደል?››

‹‹ለምን አሾፍብሻለሁ?››

‹‹ጨልሞል መብራት ጠፍቷል ..ያ ታዲያ ለእኔ ምኔ ነው..?ሁለቱም አይመለከቱኝም እኮ፡፡ ስትተኙ ተኝቼ ስትነሱ የምነሳው እኮ መቼስ ህይወቴም ስራዬም ከዓይናማዎቹ ጋር ነዋና ሰዓቴን ከእናንተ ሰዓት ጋር አስተካክዬ ልጠቀም ብዬ ነው እንጂ፤ ቀን በምትሉበት ሰዓት ተኝቼ በማታው ብሰራ ለእኔ ለውጥ የለውም፡፡ቀንና ለሊት የጨለማ እና የብርሀን መፈራረቅ ነው አይደል በእኔ ህይወት ሁለቱም አይፈራረቁም ጭርሱኑ የሉም…››

‹‹አይ የእኔ ነገር ..!!አንቺ እኮ ሁል ጊዜ በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በአካልም ሙሉ መስለሽ ስለምትታይኝ ነው..በዛ ላይ ካለወትሮዬ አራት ቢራ መጠጣቴን አትዘንጊ፡፡››

‹‹ሰክሬያለሁ ለማለት ነው?››

‹‹ያው እንደዛው በይው››

እያወሩ ፅዮን ቤት በራፍ ጋር ደረሱ፤የቤቷን መክፈቻ ቁልፍ ከቦርሳዋ በርብራ አወጣችና በመክፈት ወደውስጥ አልፋ ከገባች በኃላ ‹‹ግባ እንጂ >> አለችው፡፡

‹‹እንዴት ልግባ?››

‹‹እኔ እንደገባሁት ነዋ…ምን እንደህንዶቹ ፀሎት ተደርጎልህ ግንባርህን ቀለም ካላስነኩህ ደጃፉን አታልፍም?››

‹‹እሱን አላልኩም እኔ እንዳንቺ በጨለማ የመጓዝ ችሎታ የለኝም..፡፡››

‹‹ወይኔ ወይኔ…አለችና ወደ ኋላ ተመልሳ በራፉ አቅራቢያ ኮርነር ላይ የሚገኘውን ማብሪያ ማጥፊያ በዳበሳ ተጫነችው፡፡››

‹‹ይሄው ግባ››

‹‹ባክሽ አሁንም አልበራም.. እውነትም ዛሬ ሰክሬያለሁ መሰለኝ መብራት እንደጠፋ ቅድም ስነግርሽ ቆይቼ አሁን ደግሞ መብራት ውለጂ ማለቴ...፡፡››

‹‹ግዴለህም ቆይ እንደ ፓውዛ ያበራል ብለው የሚያደንቁት ባትሪ አለኝ፡፡›› ብላ ወደ ውስጥ ዘለቀችና ባትሪውን አበራችለት... እውነትም ፓውዛ እንዳለችው ቤቱን በብርሀን ሞላው፡፡ከዛ እሱም ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ክፍሉ አንድ ክፍል ቢሆንም የመለስተኛ ሳሎን ያህል ስፋት ኖሮት በዕቃ የተሞላ ነው፡፡
‹‹የሚመችህ ቦታ ቁጭ በል››አለችውና ወደ ቁም ሳጥኑ በማምራት ከፈተችው፡፡እሱ ከአልጋው ፊት ለፊት ካለው ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡

ፅዮን ከከፈተችው ቁም ሳጥን ቢጃማ ሱሪና ሹራብ አወጣች..ቀሚሷን ሳታወልቅ በፊት ቀድማ ቢጃማ ሱሪውን ለበሰች፤ከዛ ቀሚሷን አወለቀች.... በዚህን ጊዜ ግማሽ አካሏ ለእይታ ተጋለጠ...ጡት ማስያዣያም አላደረገች፡፡ የቢጃማ ሹራቧን አነሳችና ለመልበስ ጭንቅላቷን አስገብታ ወደ ታች እየሳበች‹‹ምነው አፍጥጠህ አየኸኝ?›› አለችው፡፡

ደነገጠ‹‹ምን አልሺኝ?››

‹‹ዓይንህ ሰውነቴን አቃጠለኝ፡፡››

‹‹መቼም ወንድ ነው... ወንዶች ደግሞ የሴት ዕርቃን ፊት ለፊታቸው ከተጋረጠ ማፍጠጣቸው አይቀሬ ነው ብለሽ ነው አይደል?››

‹‹እና እያየሁሽ አይደለም እያልከኝ ነው?››

‹‹ከጠረጴዛሽ ላይ አልበም አግኝቼ እሱን እያየሁ ነው››አላት፡፡ እውነታው ልክ እሱ እንደሚለው ቢሆንም በጎሪጥ እየሰረቀ አንድ ሁለቴ ግማሽ እርቃን ገላዋን አላያትም ማለት ግን አይደለም፡፡

‹‹እሺ ይሁንልህ ሻይ ወይስ ቡና ላፍላ ?››

‹‹ኧረ ምንም አልፈልግም… ቤትሽን እኮ ልይልሽ ብዬ ነው ወደ ውስጥ የዘለቅኩት ባይሆን ሌላ ቀን እመጣለሁ... አሁን ልሂድ››

‹‹ስንት ሰዓት ነው?››

<<4:25>>

መሽቷል እኮ ለልጆቹ ትርንጎ አለች አይደለም?

(ትርንጐ ልጆቹን እንድትንከባከብ የታዲዬስ ቤተስብ የተቀላቀለች ወጣት ልጅ ነች) >>

‹‹ብትኖርስ…? እዚህ ነው የማድረው?››

‹‹አዎ፡፡ ምን አለበት..?አልጋው እንደሆነ እንደምታየው ባለ ሜትር ከሰማንያ ነው፡፡››

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው..እንግዲያው ለትርንጎ ደውዬ ልንገራታ.. ታውቂያለሽ ስልክ አልያዝኩም ያንቺን ስልክ ልጠቀም?››

‹‹ቦርሳዬ ውስጥ አለልህ ፤ተጠቀም፡፡››

ከተቀመጠበት ተነሳና ቦርሳውን ከጠረጴዛው አንስቶ ያለችበት ቦታ ድረስ ወስዶ ሰጣት፡፡

‹‹ምነው?››

አውጪና ስጪኛ..የሴት ቦርሳ በርብሮ ዕቃ ከማግኘት ከሙሉ መጋዘን ውስጥ የሆነ ዕቃ ፈልጐ ማግኘት ይቀላል..ግምሽ ንብረታችሁን እኮ በቦርሳችሁ ነው ይዛችሁ የምትዞሩት፡፡››

‹‹ለካ እንዲህ ነገረኛ ነህ?››አለችና አውጥታ ሰጠችው፡፡ ደውሎ እንደማይመጣ ተናግሮ ስልኩን ዘጋና ወደ መቀመጫው ተመልሶ ቁጭ እንዳለ መብራቱ መጣ፡፡

‹‹እሺ አሁንስ ማደርህ ተረጋግጧል .. ቡና ነው ሻይ?>>

‹‹እኔ ምንም አልፈልግ..መተኛት ብቻ፡፡››

‹‹የእኔ ቢጃማ ይሆንህ ይሆን?

‹‹ቅር ካላለሽ እኔ ቢጃማ ለብሼ መተኛት አልወድም... እንቅልፍም አይወስደኝም፡፡››

‹‹በፓንት ብቻ ነው ሁሌ የምትተኛው?››

‹‹ኧረ እኔ ፓንት የሚባል ኖሮኝ አያውቅም?››

ከትከት ብላ ሳቀችበት‹‹እያሻፍክብኝ ነው አይደል?››

‹‹የእውነቴን ነው ... ሰውዬውም በሰፊ ሱሪ ውስጥ በነፃነት ሲጨፍር ነው የሚውለው... ለዛሬው ግን አይዞሽ አትስጊ አንሶላውን ተጠቅልዬ እተኛለሁ››

‹‹ኧረ ያንተ ነገር ገርሞኝ ነው እንጂ ለእኔ ችግር የለውም፡፡››

ልብሱን ሙሉ በሙሉ አወለቀና መላ መላውን ወደ አልጋው ሲራመድ

‹‹አንተ በጣም ትልቅ ነው አለችው›› ደነገጠና በሁለት እጁ አፈፍ አድርጎ ሸፈነው...ትዝ ሲለው

መልሶ ለቀቀውና በሳቅ ፈረሰ፡፡

‹‹በጣም ተንኮለኛ ነሽ ..የእውነት ያየሺኝ እኮ ነው የመሰለኝ››ብሏት ወደ አልጋው ሄዶ ከውስጥ ገብቶ ተኛ ..እንዳለውም አንሶላውን ተጠቅልሎ አንደኛውን ጠርዝ ይዞ ነበር የተኛው፡፡እሷም ከደቂቃዎች በኃላ ተከተለችው ፤በመካላቸው የ5ዐ ሴ.ሜትር ክፍተት ነበር

‹‹መብራቱን ላጥፋው?››ጠየቃት፡፡

‹‹መብራት መጥቷል እንዴ ?››

‹‹አዎ መጥቷል?››

‹‹እንደፈለግክ፡፡››

‹‹አይ አንቺ የቱ ይሻልሻል?››

‹‹አንተ ልጅ ዛሬ ምን ነክቶሀል? መብራቱ እኮ ለአንተ ሲል ነው የበራው፡፡››

‹‹እውነትም የሆነ የነካኝ ነገር አለ፡፡›› አለና ተንጠራርቶ አጠፋው፤ ፊቱን አዙሮ ተኛ፤እሷም

ፊቷን ወደ እሱ አዙራ ክፍተቱን እንደጠበቀች

ከ1ዐ ደቂቃዎች ዝምታ በኃላ‹‹ታዲያ..እንቅልፍ ወሰደህ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አልወሰደኝም››መለሰላት፡፡

‹‹ማውራት ትፈልጋለህ?››

‹‹አዎ እስቲ አውሪኝ ..ዛሬ ቢራው ነው መሰለኝ የወሬ አፒታይቴን ክፍትፍት አድርጎልኛል››

‹‹ወሬ አይደለም ጥያቄ ልጠይቅህ ነው?››

‹‹ጠይቂኝ››

‹‹ታዲ የዛሬው ፕሮግራም እኮ በዕቅዳችን መሰረት አይደለም የተፈፀመው፡፡የተገናኘነው የሁለታችን ጉዳይ ለማውራት ነበር፤ ጊዜው ያለፈው ግን በእኔ ያለፈ ታሪክ ትረካ ነው፡፡››

‹‹እና ጥያቄሽ ምንድነው?››

‹‹ጓደኛ አለህ እንዴ? ማለቴ የፍቅር ጓደኛ?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ እንጃ ማለት እኮ አለኝምም የለኝምም የሚል አሻሚ መልስ ነው፡፡››

‹‹አዎ እንደዛው ነው፡፡››

‹‹እሺ ያለችውን ታፈቅራታለህ?››

‹‹ይመስለኛል ያለፉትን 1ዐ ዓመታት ያለመሳለቻቸት አብረን አሳልፈናል…ከእሷ ውጭ ማንም ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም፤ባላፈቅራት ኖሮ እንደዛ አላደርግም የሚል ግምት አለኝ፡፡››

‹‹ትክክል ነህ... እሷስ ታፈቅርሀለች?››
👍949👎3👏3
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን ልክ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ጊዮን ደርሶ ለዶ/ር ሶፊያ ሲደውልላት ቀድማው ተገኝታ ነበር፡፡ያለችበትን ቦታ ጠቆመችውና ወደዛው አመራ፡፡በጣም በፈካ ፈገግታ እና በደመቀ የወዳጅነት መንፈስ ነበር የተቀበለችው:: እሱም በተመሳሳይ ስሜት ሰላምታውን መለሰላትና ከፊት ለፊቷ ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡እሷ ቀድማ አዛ ስለነበር እሱም የሚፈልገውን አዘዘና ወደ ጨዋታቸው ገቡ፡፡ለማውራት ቅድሚያውን የወሰደችው ዶ/ር ሶፊያ ነበረች፡፡

‹‹አቶ ሁሴን…..ግርማ ሞገስህ በጣም የሚማርክ ዓይነት ሰው ሆነህ ነው ያገኘውህ:: ከትንግርት በፊት ተገናኝተን ቢሆን ኖሮ አልምርህም ነበር፡፡›› አለችው በፈገግታ እንደተሞላች፡፡

‹‹ኧረ እንኳንም አላገኘሺኝ፡፡››አላት እንደመደንገጥ ብሎ..የጨዋታ ርእስ አከፋፈቷ ከገመተው በተቃራኒው ስለሆነበት ተገርሞባታል፡፡

‹‹ምነው? ያንተ ታይፕ አይደለሁም እንዴ?››

‹‹እንደዛው በይው….እኔ ትንግርትን ባላገኝ ቆሜ የምቀር አይነት ሰው ነበርኩ፡፡››

<ታድላ!!!>>

<<እኔ ነኝ የታደልኩት፡፡እሷ እኔንም ባታገኝ ብዙ ከእኔ የተሻለ ሰው በርግጠኝነት ታገኛለች..እኔ እሷን ባላገኝ ኖሮ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም፡፡››

‹‹እንደዛ እንኳን ብዬ ማመን ይከብደኛል፡፡››

‹‹አይክበድሽ..የማወራሽ ስለ ሴት አይደለም፤ መንፈሴን ሰርስራ ስለምትረዳኝ፣የውስጥ ፍላጎቴን ገና ወደ ውጭ ወጥቶ በቃላት ከመመንዘሩ በፊት አንብባ ስለምትፈፅምልኝ አይነት ሴት ነው የማወራሽ ፤እንጂማ ሴት ከሆነ ከተማው ሙሉ ሴት ነው፤ወንድም እንደዛው፡፡››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው...ትንግርት እንኳን አሁን በአዕምሮም በዕድሜም በስላ ይቅርና ድሮም
አፍላ ወጣት ሆና ከእኔ ጋር እያለንም ልዩ ሰው ነበረች..ሰው ከእሷ ጋር መኖር ለምዶ ከሌላ ሰው ጋር ለመግባባት በጣም ነው የሚከብደው... ይሄውና እኔ እስከዛሬ ድረስ የእዛ ችግር ተጠቂ እንደሆንኩ ነው፤ሁል ግዜ ለሆነ ግንኙነት የምቀርበው ሰው ውስጥ እሷን ነው የምፈልገው..እሷ ታደርግልኝ የነበረውን እንዲያደርግልኝ፣እሷ ትፈልገኝ በነበረው መጠን እንዲፈልገኝ ነው ምኞቴ ...ግን አይሳካልኝም፡፡››

ቀስ በቀስ ወደሚፈልገው ርእስ መጣችለት‹‹ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?››

‹‹የፈለግከውን፡፡››

‹‹ ትንግርትን ትወጃት ነበር?..››

‹‹ትወጃት ነበር ትለኛለህ እንዴ..?ፍቅር መቼስ ረቂቅ መንፈስ ነው፤ .ይሄን ያህል ነው ተብሎ በመጠን አይገለጽም…እንዴትም ብዬ ላስረዳህ…?ከውቅያኖስ በጠለቀ እና ከሰማይ በራቀ በማይተመን መጠን ነው የምወዳት፡፡ >>

‹‹ታዲያ ለምን ጥለሻት ወደ መጣሽበት አሜሪካ ተመልሰሽ ሄድሽ?››

‹‹ተገድጄ፡፡››

‹‹ማነው ያስገደደሽ ?››

‹‹አንድ አፍቅርሻለው የሚል እብድ፡፡››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ በእኔ ፍቅር እብድ እስኪል ቆሻሻ ፍቅር የያዘው ሰው ነበር... በተወሰነ መልኩ ልጁን ትንግርትም ታውቀው ነበር ፡፡ካሌብ ይባላል..፡፡... ታዲያ ይሄ ልጅ ሲከታተለኝ ሲለማመጠኝ እና መግቢያ መውጪያዬን ሲከታተል ከሁለት ዓመት በላይ ከቆየ በኃላ እኔና ትንግርት ጓደኛሞች እንደሆን ይደርስበታል..እኔን ከእሷ ነጥሎ ለራሱ ለማድረግ ባለ በሌለ ኃይል መፋለም ቀጠለ፡፡››

‹‹እንዴት ሊደርስበት ቻለ ?>>

‹‹እሱ ለእኔም እስከዛሬ ጥያቄ እንደሆነብኝ ነው ?ከዛ ቀጥታ ወደ እኔ መጣና አናገረኝ..ወይ ተያት ወይ እገድላታለሁ ..››ብሎ አለኝ ...ንቄ ችላ አልኩት፡፡

‹‹እሱ ግን ዙሩን አከረረው….ሀብታም ስለሆነ የገንዘብ ችግር የለበትም...በየሄደችበት የሚከታተሏት ሁለት ወጠምሻ ጓረምሶች ቀጠረባት፡፡በየቀኑ ሙሉ እንቅስቃሴዋን ፣የት እንደዋለች... ? ምሳዋን ምን እንደበላች… ?በምን ሰዓት ጭር ያለ ቦታ እንደነበረች…?እዛጋ ልትገደል ትችል እንደ ነበር፡፡››በየቀኑ አዋዋሏን በተመለከተ ሙሉ ሪፖርት ያቀርብልኝ ጀመር ... ግራ ገባኝ፡፡

ለትንግርት እንዳልነግራት ጭራሽ ማስበርገግ ይሆናል ብዬ ሰጋሁ....በቃ ጉዳዩን ወደ ህግ መውሰዱ የተሻለ ውጤት ያመጣል ብዬ አመንኩና ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩ፤…ግን ተሳስቼ ነበር ..የሰማኝም ሰው አልነበረ፡፡ መረጃሽ ምንድነው.. ?ምስክር አለሽ ወይ ? ጭራሽ እኔኑ ሲያዋክቡኝ ተውኩት፡፡ይገርምሀል

ለካ እሱ ቀድሞውኑም በደንብ ተዘጋጅቶበት የአካባቢውን ፖሊሶቹ ሁሉ በእጁ አድርጎ ነበር፡፡

የመጨረሻ ውሳኔዬ ላይ ያደረሰኝ ጉዳይ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? የእኔም የትንግርትም የጋራ ጓደኛ የሆነች ልጅ ታገባ ስለነበር ሁለታችንም ሚዜ ሆነን በልጅቷ ተመርጠን ነበር፡፡ እሷ አንደኛ ሚዜ እኔ ሁለተኛ ሚዜ ..ሰርጉ የት ነበር መሰለህ ?ዲላ ...ከሰውዬው ለሶስት ቀንም ቢሆን በመገላገሌ እንደ እረፍት ቆጥሬው ነበር፡፡ካለስጋትና መሳቀቅ የማሳልፋቸው ሶስት የሰላም ቀኖች እንደሚሆኑ ተስፋ አድርጌ ከትንግርቴ ጋር ወደ ዲላ አመራን፡፡ ልክ የሠርጉ እለት ማታ እኛም ሆንን ሙሉ ሠርገኛው ጭፈራ ላይ እያለ አንድ ጠንካራ ክንድ ጀርባዬን ጨምድዶ ነቀነቀኝ ...ዞር ስል የማላውቀው ሰው ነበር ...ግራ በመጋባት አፍጥጬ ስመለከተው‹‹ሰው ይፈልግሻል

››አለኝ፡፡

‹‹ማን….?ምን አይነት ሰው..? >>

በጣቱ አቅጣጫውን ጠቆመኝ…ሰርግ ቤቱ ግቢ ውስጥ ሆኖ ግን ደግሞ ጨለም ወዳለ ቦታ ተወሽቆ ወደ ነበር አንድ ሰው... ልሂድ አልሂድ በሚል መንታ ስሜት በሚዋልል ግማሽ ልቤ እግሬን እየጐተትኩ ሄድኩ…ስደርስ ማን ቢሆን ጥሩ ነው ?ካሌብ ፡፡ከአዳማ ዲላ ድረስ ተከትሎኝ መጥቷል…፡፡ አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ....ሰውዬው ጤነኛ እንዳልሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማሰብ ተገደድኩ፡፡››

‹‹ምነው ?ምን ልታደርግ መጣህ ?››የሞት ሞቴን ጠየቅኩት፡፡

‹‹የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልሰጥሽ ነው የመጣሁት››

‹‹የምን ማስጠንቀቂያ ....የአንተን ማስጠንቀቂያ እኮ ከመቶ ጊዜ በላይ ሰማሁህ ..የቀረም ካለ ከሁለት ቀን በኃላ እዛው አዳማ እመጣልሀለው ..ምን አስቸኮለህ..…?››

‹‹አይ.. አይ... እንደተለመደው አይነት ቃላዊ ማስጠንቀቂያ አይደለም ....ተግባራዊ ነው››

‹‹ሰርግ ቤቱን በቦንብ ልታፈነዳና ልታጠፋን ነው ?>>

‹‹አይደለም... ያቺ ከእናንተ ጋር ሶስተኛ ሚዜ የሆነችውን ልጅ ማነው ስሟ ? >>

‹‹እሷ ደግሞ እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አደረጋት…ሳራ ትባላለች ?>>

‹‹አዎ ሳራ... ነፍሷን እግዜር ይቀባላት እና ነገ ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ከዘገየ ደግሞ ስድስት ሰዓት ድረስ ትሞታለች፡፡››

ምን ማለት ነው... ?ደግሞ የሰውን መሞቻ ቀን የምትተነብይ ነብይ ሆንክ እንዴ ?››

‹‹አይደለም.... ባንቺ እንቢተኝነት ምክንያት የተሰዋች የአብረሀም በግ ነች…መቼስ በጣም እወድሽ የለ፤ ያንቺዋን ትንግርትን ከመግደሌ በፊት መግደል እንደምችልም እንድታውቂ ቅድሚያ ምልክት ይሆንሽ ዘንድ ያልኩሽን ልጅ ከ12-16 ሰዓት የጊዜ ሂደት ውስጥ የሚገድል መርዝ ተሰጥቷታል፡፡››

‹‹አንተ ጨካኝ አታደርገውም…..አሁን እዚህ ጮኼ ላሲዝህ?››
👍666
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን እና ዶ/ር ሶፊያ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ...ቤቱ ለሁለት ባልና ሚስቶች የእርቅ በዓል የተሰናዳ የእራት ግብዣ ሳይሆን መለስተኛ ሠርግ ነበር የሚመስለው..ሁሴን እራሱ በጣም ደነገጠ፡፡ እሱ ይኖራሉ ብሎ ከጠበቀው የሰው ብዛት በእጥፍ ቁጥር ብልጫ ያለው እንግዳ ሰፊውን ሳሎን አጨናንቆታል..የውብዳር ሰሎሞን፣ሁለቱ ልጆቻቸው፣ ኤልያስ፣ታዲዬስ ከነልጆቹ..በተለይ የታዲዬስ እና የአምስቱ ልጆች እዚህ የእራት ግብዣ ላይ መገኘት ማንም ያልጠበቀው ነው፡፡ ለነገሩ እስከ 1ዐ ሰዓት ትንግርትም አታውቅም ነበር፡፡እንዳጋጣሚ ስትደውልለት ከነልጆቹ አዲስ አበባ እንዳለ ነገራት…ጊዜዋ የተጨናነቀ ቢሆንም እንደምንም ሰዓቷን አብቃቅታ ያረፈበት ሆቴል ድረስ ሄዳ ለምና እዚህ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፍ አግባባችው.. ኤልያስን ግን የጋበዘችው ፎዚያ ነች፡፡

‹‹እንዴ እናንተ የእራት ግብዣውን ወደ ሰርግነት ቀየራችሁት እንዴ?›› አለ እያንዳንዳቸውን በመጨበጥ ሰላምታ እየሰጠቸው..ዶ/ር ምን እሱን እየተከተለች ተመሳሳዩን ፈፀመች....በወቅቱ ትዕንግርት አልነበረችም ፡፡ ማዕድ ቤት ለዝግጅቱ ከፎዚያ ጋር ተፍ ተፍ እያለች ነው፡፡

‹ ‹እንዴ ታዲ መች መጣህ?››ዶ/ር ነች ጠያቂዋ፡፡

‹‹ዛሬ... ስምንት ሰዓት አካባቢ ነው የገባነው፡፡››

‹‹ለምን ሳትደውልልኝ ታዲያ?›› መምጣቱን ሳታውቅ ያላሰበችው ቦታ ስላገኘችው ቅር ብሏት…፡፡

‹‹ለአምስት ቀን እኮ ነው የመጣነው..አረፍ ካልኩ በኃላ ነገ ተነገወዲያ እደውላለሁ ብዬ ነው…ትንግርትም ድንገት ነው ያገኘችኝ..ደግሞ የአዲስ አበባ ሰዎች እንግዳ እንደሚመጣ ከወር በፊት ቀጠሮ ካላስያዘና ለሚቆይበት ጊዜ በጀት ካልተመደበለት በስተቀር ድንገት ሲሄድባቸው ፊት ይነሳሉ ብለው ሲያሟችሁ ሰምቼ ነው፡፡››

‹‹እንዴ ታዲዬስ እንደዛማ አትለንም.. እንደዛ የሚያደርጉት በቅርብ ሀብታም ለመሆን እቅድ ይዘው ተፍ ተፍ የሚሉት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው ፡፡እኛ መቼም ሀብታም የመሆን ዕቅድ የሌለን ዛሬን ብቻ የምንኖረው ጋር ብትደውል ችግር የለውም ነበር...ካለን ያለንን ትበላለህ ከሌለን ይዘህ የመጣህውን እናባላሀለን›››አለው ኤልያስ… ሁሉም ተሳሳቁ፡፡

‹‹እንዴ እናንተ ሚስቴን አስረሳችሁኝ ትንግርትስ?››ጠየቀ ሁሴን፡፡

‹‹ወደማዕድ ቤት አካባቢ ነች መሰለኝ፡፡››የውብዳር መለሰችለት፡፡

‹‹ተጫወቱ ዓይኗን አይቼ ልምጣ..ናፍቃኛለች፡፡ ››ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ ማዕድቤት ሄደ....::

ፎዚያና ትዕንግርት ተፍ ተፍ ሲሉ ደረሰ‹‹ሀይ የእኔ ፍቅር?›› ብሎ ከንፈሯን ሳማት..፡፡

‹‹ሀይ እህት አለም..የሰላት ሰዓት ደርሶብሻል እኮ አላት፡፡››ፎዚያን፡፡

‹‹ኧረ ባክህ አሁን ስንት ሰዓት ነው..? ልታስታውሰኝ ከፈለግክ ቀደም ብለህ መምጣት ነበረብህ፡፡ >>አለችው ፎዚያ፡፡

‹‹ቆይ ለመሆኑ ይሄው ሁሉ ጉድ ምንድነው..? እንዴት እንዴት አድርጋችሁ እራት ልታበሏቸው ነው?>>

‹‹አይዞህ አታስብ .... የተወሰነውን ሰራን.. የተወሰነውን ደግሞ ከሆቴል አመጣን፡፡››

‹‹የምትገርሙ ናችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ሳረሳው...የመጠጥ ሂሳቡን አንተ ነህ የምትዘጋው 18ዐዐ ብር ቆጥሮብሀል፡፡››

‹‹18ዐዐ ብር ሙሉ ብቻዬን?››

‹‹2ዐዐ ውን እኔ አግዝሀለሁ፡፡›› አለችው ፎዚያ፡፡

‹‹እሺ 18ዐዐ ቀረ አንቺስ የእኔ ፍቅር ስንት ታግዢኛለሽ?››

‹‹እራስህን ቻል... የምግብ ጉዳዩን ጠቅላላ በእኔ ነው የተሸፈነው፡፡››አለችው እየሳቀች፡፡

‹‹ይሁን እንግዲህ ከጨከንሽ ... ከአለም ባንክንም ቢሆን የማይመለስ ብድር እጠይቃቸኋለዋ››

‹‹ትችላለህ..አረ እንግዶቹ ጋር ሂድና አጫውታቸው፡፡››

‹‹እሺ ግን የእኔ ፍቅር አንድ እንግዳ ይዤ መጥቼያለሁ››

‹‹እንደዛማ ከሆነ እዳህ ይጨምራል፡››

‹‹እውነቴን ነው፡፡››

‹‹እኮ ታዲያ ምን ችግር አለው ..?ለመሆነ ማነው የማውቀው ሰው ነው?››

‹‹አዎ፡፡››

<ማነው?>>

‹‹ዶ/ር ሶፊያ››

ትንግርት የያዘችውን ጎድጓዳ ሰሀን በቁሟ ለቀቀችው፡፡

‹‹‹ተረጋጊ ፍቅር፡፡››

‹‹እውነትህን ነው ግን?››

‹‹አዎ ፍቅር ከእሷ ጋር ነው እስከአሁን የቆየሁት..ሁሉን ነገር ነግራኛለች፡፡››

‹‹ትንገርህ ታዲያ ... እኔ ምን አገባኝ?››

‹‹አይደለም እኮ ...እሷ ጋርም አንቺ የማታውቂው እውነት አለ..እኔን አሳምናኛለች፡፡››

<< ይሄ እኮ ያንተ እና የእሷ ጉዳይ ሳይሆን የእኔ እና የእሷ ጉዳይ ነው.....ፎዚያ እንዳደረግሽ አድርጊ እኔ መሄዴ ነው፡፡›› ብላ ሽርጧን ማወላለቅ ጀመረች፡፡

‹‹ወዴት ትሄጂያለሽ?››

‹‹ሳሪስ ሄዳለሁ እቤቴ..ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ፡፡››

ፎዚያ ደንግጣ ትለምናት ጀመረ‹‹ትንግርቴ በአላህ ሌሎቹን እንኳን ተያቸው በስንት ጉትጎታ

‹‹‹ተረጋጊ ፍቅር፡፡››

ቤትሽ ለመጀመሪያ ቀን የመጣው የምታከብሪው ታዲዬስ ምን ይሰማዋል…?››

‹‹እሺ ይሄ ወንድምሽ ሴትዬዋን ከዚህ ቤት ያውጣትና ካመጣበት ወስዶ ይጣልልኝ፡፡››

‹‹ኧረ ትንግርት በፍቅራችን››ጉልበቷ ላይ ወደቀ

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1119🤔5🔥1
# ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እንግዶቹ ሳሎን ውስጥ እንደከተሙ ቢራ የሚጠጣው ቢራ የተቀረው ለስላሳ እየተጎነጩ እየተጫወቱ ነው፡፡

‹‹ታዲ ለዛ ጉዳይ ነው የመጣሀው?››
‹‹አዎ.. ስትጨቀጭቁኝ ጊዜ ደጋግሜ አሰብኩበት...የእኔ እና የልጆቼ ታሪክ በሌላው ዜጋ ላይ መነሳሳት ፈጥሮ ብዙ ወላጅ አልባና ችግረኛ ህፃናቶችን አጋዥ ሚያስገኝላቸው ከሆነ ለኢ.ቢ.ኤስ ቶክሾው የቴሌቨዠን ፕሮግራም
እኔም ሆንኩ ልጆቼ ቃለ መጠየቁን ብናደርግ አይከፋም ብዬ ነው፡፡በዛ ላይ ያው እነ ሄለንም በሙዚቃው .....እነ ሰላምም በስዕሉ በሞራል እየሰሩ ለመዝለቅ ከህዝብ ጋር በይበልጥ
መተዋወቅ የስራቸውን ውጤት ለህዝብ ማቅረብ ስላለባቸው ለዛ ደግሞ ሚዲያው ወሳኝ መሆኑን
አምኜበት ነው..ስለዛ ነው ሀሳቤን ቀይሬ የተስማማሁት፡፡››
‹‹በእውነት ጥሩ ወስነሀል..ይህ ነገር መስፋፋት አለበት... ባይገርምህ እኔም ፕሮፖዛሌን ጨርሼ እንቅስቃሴም ጀምሬያለሁ፡፡››አለችው ዶ/ር ሶፊያ፡

‹‹ምንድነው እኛም እንሳተፍበት ይሆናል... ገለጽለፅ አድርጉልን እንጂ?››አለ ሰሎሞን፡፡

‹‹እሺ ፕሮፖዛሌ በድህነት ምክንያት የሚባክኑ ሕፃናትን ከኢትዬጵያ ማጥፋት ነው.. ሀሳቡን የወሰድኩት ሙሉ በሙሉ ከታዲዬስ ነው፡፡እሱ ብቻውን አምስት ልጆችን እያሳደገ ..ማሳደግ ሲባል ደግሞ ማንም ኢትዬጵያዊ ልጁን ከሚያሳድገው እጅግ በሚበልጥ እና ለማንም ምሳሌ በሆነ መልኩ ነው፡፡ ሄለን ሀይለኛ ፒያኒስት ነች፣ሀሊማ ጊታሩን ታናገረዋለች..በዛ ላይ ድምጸ መረዋ ነች፣ሚጡ ከአሁኑ አሪፍ ገጣሚ ነች፣ሰላም የሚያማልል ስዕሎች ትስላለች፣ሙሴ የእሱን አትጠይቁኝ..የዬፎ አይነት ጭንቅላት ያለው ድንቅ የልጅ ሳይንቲስት ነው፤ እስቲ ተመልከቱ ከእነዚህ ልጆች መካከል አንድም የባከነ ይታያችኋል....?

ማንም ሰው የተትረፈረፈ ሀብት ኖሮት አምስት ልጆች ቢወልድ ቢያንስ ሁለቱ ወይም ሶስቱ ዝም
ብለው እየቦዘኑ መኖራቸው የሚጠበቅ ነው…

ታዲዬስ ጋር ግን ይሄ አይሰራም …እኔ እንደተረዳሁት ልዩ ፍጡሮችን መሰብሰብ ስለቻለ ሳይሆን ..ማንም ሰው ሲፈጠር አብሮት ወደ እዚህ ምድር ይዞት የመጣው ልዩ ስጦታ
ወይም ከሌላው በተሻለ የሚችለው ነገር አለው
ብሎ ያምናል፡፡ ..የታዲዬስ ልዩ ብቃት ደግሞ
አንድ ህጻን ሲድህ ጀምሮ እየተከታተለ የህይወት
መስመሩን ብዙም ሳይለፍ እንዲያገኝ ማድረግና
ማገዝ መቻሉ ነው፡፡ታዲዬስ እኮ ለልጆቹ ምግብና መጠለያ መስጠቱ ብቻ በጣም
ሚያስወድሰው ሰናይ ተግባር ነው... እሱ ግን ከከርሳቸው መሙላት በላይ ለአዕምሮቸው
መጎልበት ነው አብዝቶ የሚጨነቀው፡፡››..

የውብዳር ለዚህ ወሬም ሆነ ስለታዲዬስ ታሪክ አዲስ ስለሆነች ግራ ተጋባች፤ ታዲዬስና ልጆቹን ካየች ጀምሮ ጥያቄ በውስጧ ተቀብሮ ነበር፡፡፡

ዳ/ር ንግግሯን አራዘመች << እንግዲህ የእኔ ፕሮፕዛል ቀንጨብ አድርጌ ለማብራራ...›› ስትል  
ከወደ ጓዲያ ጠንከር ያለ ድምጽ ሲሰማ ንግግሯን አቆመች፡

‹‹ምንድነው ሰዎቹ እራት ጋብዘውን ማእድ ቤት ተከተው ቀሩኮ..ዶ/ር ይቅርታ የፕሮፖዛልሽን ሀሳቡ በጣም መስማት ስለምፈልግ እስክመጣ አቆይልኝ አይቻቸው ልምጣ፡፡›› ብሎ ከመቀመጫው ተነሳና ወደ ማዕድ ቤት ሊያመራ መንገድ ሲጀምር ዶ/ር ሶፊያ‹‹ይቅርታ አቶ ሰሎሞን እኔ ብሄድ ይሻላል›› ብል ተነሳች ፡፡

ታዲዬስ ግራ ገባው‹‹...እሱ ቢሄድ አይሻልም፡፡››

‹‹ግድ የለም ካልደፈረሰ አይጠራም ብሎኝ ነው ሁሴን ይዞኝ የመጣው..ልሂድና በደንብ ይደፍርስ… ከጠራ እመጣለሁ››
‹‹አይ.... አሁንም ተፈነካክታችሁ እራታችንን ሳንበላ በለሊት ሆስፒታል ለሆስፒታል እንዳታንከራተቱን፡፡››

‹‹ከሆነም መቻል ነው››በማለት አሻፈረኝ ብላ እነ ትንግርት ወደሚገኙበት በመሄድ ዘው ብላ ስትገባ ፎዚያ ፈዛ ቆማ ትንግርትን ስትለምናት   ነበር የደረሰችው.... ሁሴን ደግሞ ጉልበቷ ላይ ተደፍቶ ‹‹የእኔ ፍቅር እኔ እኮ ምክንያቷን ሰምቼ ስላሳመነችኝ... እኔን ያሳመነኝ ምክንያት ደግሞ አንቺንም ያሳምንሻል ብዬ በእርግጠኝነት ስላመንኩ ነው፤ ተማምኜብሽ ነው ይዤያት የመጣሁት ..የዛሬን››

‹‹ደህና አመሸሽ ትንግርት››...ስድስት ያፈጠጡ ዓይኖች ግንባሯ ላይ ሲተከልባት ሚጥሚጣ በዓይኑ ገብቶ እንደለበለበው ሰው የራሷን ዓይን አርገበገበች ‹‹ይቅርታ ለድፍረቴ... ሁሴን እና ፎዚያ እኛ እንነጋገር አንዴ ወደ ሳሎን ትሄዱልን፡፡››

‹‹ችግር የለም ዶ/ር አንቺ ሳሎን ሁኚ ...>>

<<ኖ ሁሴን እመነኝ እንደፈለገች ታድርገኝ...5 ደቂቃ ላናግራት እና ፤ካልሆነ እኔ ወደቤቴ ሄዳለሁ በእኔ ምክንያት ይሄን የመሰለ ዝግጅት መበላሸት የለበትም፡፡››

‹‹ይሻላል ፍቅር? ››አላት ወደ ትንግርት እያየ በመለማመጥ፡፡
ትንግርትም በግንባሯ ንቅንቅታ እንደሚሻል አረጋገጠችለት..ሁሴንና ፎዚ ግራ በገባው ሁኔታ ማዕድ ቤቱን ለቀው ወጡላቸው፡፡እንደወጡ ዶክተር ሶፊያ ከውስጥ ቀረቀረችው…ሁሴን ዶ/ ር ሶፊን በመጋበዙ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማው ለሚፈጠረው ችግር ሁሉ ኃላፊነቱን የራሱ እንደሆነ እያሰብ ሳሎን ሄዶ ከእንግዶቹ ጋር ተቀላቀለ ፡፡ ፎዚያ በጭንቀት ኮርደሩ ላይ ወዲህና ወዲያ ትንጎራደድ ጀመር፡፡

‹‹እንዴ ጥለሀቸው መጣህ እንዴ?››ሰሎሞን ነው የጠየቀው፡፡

‹‹አዎ ምርጫ የለኝም ፡፡>>

‹‹አጠገባቸው ፎዚያ አለች አይደል?››

‹‹ኧረ እሷንም አስወጥተው እራሳቸው ላይ ቆልፈዋል፡፡››

ሰሎሞን ብድግ አለ ..መልሶ ቁጭ አለ‹‹አብደሀል እንዴ..?ወይኔ የውብ መክሰስ በልተን እንሂድ ስልሽ እንቢ ብለሽ አሩጠሸ አምጥተሸኝ...በቃ አሁን እኮ ቀጥታ አንድ በደም የተሸፈነ ሰው ይዘን ሆስፒታል መሄዳችን አይቀሬ ነው፡፡››

‹‹ቆይ አልገባኝም... ይሄን ያህል አንዷ ያንዷን አባት ገድላለች እንዴ….?ግራ አጋባሀኝ እኮ!!›› አለችው የውብዳር ፡፡

‹‹ኧረ ከዛም በላይ ናቸው ..ቅድም ዶ/ር ግንባር ላይ ጠባሳ አላየሽም፤ባለፈው ትንግርት በቢራ ጠርሙስ በርግዳት ነው አኮ፡፡ አሁን ደግሞ... ለመሆኑ ማዕድ ቤት ውስጥ ቢላዋ ፊት ለፊት አለ?»

‹‹አይ ብዙም የለ... አንድ አራት ወይም አምስት ብቻ ቢሆን ነው››አለው ሁሴን ጥያቄው አበሳጭቶት፡፡

በዚህ ጊዜ ከታዲዬስ ጎን የተቀመጠው ሙሴ ከመቀመጫው ተነሳና ወደውጭ ሲሄድ ታዲዬስ ተከተለው ፡፡

‹‹ወዴት ነው?››ኤልያስ ነው ጠያቂው፡፡

‹‹ሙሴ ትንሽ በግርግሩ ሳይጨናነቅ አይቀርም አብሬው ውጭ ነኝ... ለማንኛውም አትጨነቁ ከዛ ክፍል በሰላም ተግባብተው ነው የሚወጡት፡፡ >>

‹‹እንደአፍህ ያድርግልን >>አሉት ሁሉም በአንድነት፡፡

ከአስጨናቂ የ15 ደቂቃ ቆይታ በኃላ የማዕድ ቤቱ በራፍ ተከፈተ ...ቀድማ የወጣችው ዶ/ር ሶፊያ ነች ..በተፍለቀለቀ ፊት በሚያበራ ፈገግታ ወደ ሳሎን ገባች፡፡

ፊቷና ሁኔታዎ ግን ለየቅል ነበር... ከላይ

የለበሰችው ሽሮ መልክ ቲሸርት የሰላምን ጅምር የስዕል መሳያ ሸራ መስሏል ፡፡በርግጠኝነት

አንድ ሙሉ ጎድጓዳ ሰሀን ቀይ ወጥ ነው እላይዋ ላይ የተደፋው ፡፡ሁሴን ተንደርድሮ
ከመቀመጫው በመነሳት ስሯ ደረሰና‹‹ ምን ሆንሽ ...?ምን ተፈጠረ? ››እያለ በድንጋጤ ዙሪያወን ሲሽከረከር ትንግርት ከኃላው ደረሰችና‹‹ደህና ነች ባክህ›› ብላ የሶፊያን እጆች

ይዛ ወደ መኝታ ቤት ይዛት ገባች...... እሱም እንደፈዘዘ መሀል ሳሎን ላይ ተገትሮ ቀረ ፡፡

‹‹አቦ ይሄ ድራማ መች ነው የሚያልቀው ..?አኔ እኮ በርሀብ ልሞት ነው››ሰሎሞን ተነጫነጨ፡፡

‹‹ኧረ ዛሬ እንኳን ስለከርስህ ማሰብ አቁም፡፡››አለው ሁሴን በብስጭት፡፡
👍815🥰1👏1😁1