አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ከዌስት ሊን ተመርጦ የሔደው የሕግ መምሪያ ምክርቤት አባል በጥፋት ከወንበሩ ተባረረ ከሱ በኋላ ደግሞ የዌስት ሊን ሕዝብ ጆን አትሊ የተባለ አንድ በአካባቢው የታወቀ ሰው መርጦ ላከ " እሱም ብዙ ሳይቆይ ሞተና በምትኩ ሌላ እንደ ራሴ መምረጥ አስፈለገ" ማን እንደሚሻል ተመከረበት በአካባቢው የነበሩ ይሆናሉ የተባሉ ሁሉ 'ዳኞችም ሳይቀሩ ተገመገሙ ።

ሚስተር ጀስቲስ ይሻል ይሆን ? እለ · እኔ ያልኩት ይሁን ከማለት በቀር
መተማመን አይሆንለትም ቢሔድም የራሱን ሐሳብ እንጂ የዌስትሊንን ሐሳብ መግለጽ አይችልም። ስኳየር ስፒነርሳ ? እሱ ደግሞ በሕይወቱ በአደባባይ ንግግር አድርጎ አያውቅም " ቀይ ሥር ከማብቀልና ከብት ከማርባት በቀር የሚያውቀው የለውም " ኮሎኔል ቤተል ? ለምርጫው ውድድር የሚያወጣው ገንዘብ አያገኝም » ሰርጆን ዶቢዴ?በጣም አርጅቷል እሱም ራሱ“ከምርጫው ገደብ ኻያ ዓመት አልፏል” ብሎ ሣቀና “ ሁላችንም ብቃት ያላቸውን እየዘለልን በማይሆኑትት ሰዎች ላይ ብቻ ነው ያተኮርነው " ስብሰባችንንኮ ያለዐዋቂዎች ስብሰባ አደረግነው አሁን ከመኻከላችን እንደራሴያችን መሆን የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነው ያለን "

“ ማነው እሱ ? አለ ጉባኤው
“ አርኪባልድ ካርላይል ።
ለምን እንደ ረሱት ሁሉም ገረማቸው -ጥቂት ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ የድጋፍ
ጉርምርምታ አሰሙ ።

“ እሺ ካለን ነው ” አለ ሰር ጆን ። “ ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል ...”

ወዲያው ለጉዳዩ ጊዜ ባይስጡት አንደሚሻል ተስማሙና ተሰባስበው ወደ
ሚስተር ካርላይል ቢሮ አመሩ ። ወደ ቤቱ ሊሔድ ሲል ደረሱበትና በሰፊው እየተወያዩ ብዙ ከቆዩ በኋላ እንዴራሴያችሁ እንደሆን ነው የፈለጋቻችሁኝ ? ለጥቅሜ ሁላችሁንም እሸጣችሁ እንዶ ሆንሳ በምን ታውቃላችሁ ? አላቸው "

ግድ የለም ሚስተር ካርላይል ...እናምንሃለን።

እኔ በአሁኑ ጊዜ ፓርላማ ለመግባት ምንም ሐሳብ አልነበረኝም "

ይኸማ አይሆንም !ይልቁንስ ስምህን ለውድድር እንድናስተላልፍ ፍቀድልን ። ካንተ ሌላ ብቁ ነው የምንለው ሰው የለንም አሁን አንተ እያለህ ከኛ አንዳችንን መምረጥ የማይሆን ነው አውጥን አውርዶን ስናየው ' ከድፍን ዌስትሊን ለዚህ ቦታ አንተን ያህል የሚመጥን ሰው አላገኘንም " ስለዚህ አንተን ለውድድር ለማቅረብ ተስማምተናል ። ነገ ወደ ዌስት ሊን ስትመጣ ግድግዳዎቹ ሁሉ'
ምን ጊዜም ካርላይል በሚሉ መፊክሮች አሽብርቀው ታያቸዋለህ።

እንግዲያውስ ነገሩን ጥቂት እንዳስብበት እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ " ግድግዳዎቹን በመፈክሮች ማስጌጡንም ለአንድ ቀን አዘግዩት '' አላቸው "
“ የለም የለም አሁን ወስንና ንገረን የእሺታ ቃልህን ስጠን።

አሁን ከወሰንኩ በእምቢታዬ እጸናለሁ ይኸ እኮ ጥቂት ማሰብ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው እስከ ነገ ጊዜ ስጡኝ » ምናልባትም ጥያቄያችሁን ለመቀበል እችል ይሆናል
ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ።


ሰዎቹ ከዚያ የተሻለ አማራጭ ስለ አልነበራቸው በቀጠሮዉ ተስማምተው
ሔዱ በውይይቱ ጊዜ አብሮ የነበረው ሚስተር ዲል እጆቹን በርካታ እያፋተገና ሚስተር ካርላይልን ዐይን ዐይኑን እያየ ወደ ኋላ ቀረት አለ "

“ዲል ምነው ? በጣም ደስ ያለሀና ስዎቹ የሚሉኝን እንድቀበል የፌለግህ ትመስላለህ …”

"መቀበል አለብህና" .... ሚስተር አርኪባልድ " ደስ ያለኝ ስለመሆኔ ግን እኔ ብቻ ሳልሆን በዌስት ሊን ውስጥ ደስ የማይለው ሴት ወንድ ልጅ አይገኝም

“ ተው ዲል . . . . በጣም እርግጠኛ አትሁን።
“ ስለምኑ ? እንደራሴያችን ስለ መሆንህ ነው ' ወይስ ስለ ሕዝቡ ደስታ ?
“ስለ ሁለቱም አለው ሚስተር ካርላይል ሣቅ ብሎ ።

ከቢሮው ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጉዳዩን ያብላላው ጀመር " ከፊት ጀምሮ ፓርላማ ለመግባት ማሰቡ እርግጥ ነው ‥የሚወዳደርበትን ጊዜ ግን አልወሰነም " ዘመኑን በሙሉ ለግሉ ሙያ ብቻ የሚወስንበት ምክንያት አልታየውም ። ገንዘብ የማጣት ሥጋት የለበትም » በታወቀው የራሱ ሀብት ላይ ባርባራ ይዛው የገባችው
ሲጨመርበት ከአሁኑ ዐይነት አኗኗራቸው ከሚፈለገው በላይ ነው ሥራውን ለመተው ግን አሳብ የለውም ። ምክንያቱም ሥራው : በራሱም ጠንቃቃ አሠራር
ሳቢያ የሚያስከብረው ከመሆኑም በላይ ጠቀምቀም ያለ ገቢ የሚያገኝበትና ከልቡ
የሚወደው ሙያ ነው " ምንም ቢደረግ ሥራ ፈትቶ ለመኖር አይፈልግም " ነገር
ግን ሁልጊዜ ከሥራ ቦታው እንዳይለይ የሚያስገድደው ሁኔታ የለም ። ሚስተር ዲል
የሱን ያህል መምራት ይችላል እንዲያውም ያገልግሎት ዘመንና የሥራ ልምዱ ከተቆጠረ ይበልጠዋል " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ለፓርላማው ሥራ ወደ ለንደን ሲሔድ ኃላፊነቱን ያለምንም ሥጋት ለዲል ቢተውለት በሚገባ ሊያካሒድለት ይችላል " ፓርላማ መግባቱ ካልቀረ ደግሞ የበለጠ ጥቅምና መስሕብ ካለው ከማንኛውም ቦታ ይልቅ ዌስት ሊንን ወክሎ ቢገባ ይመርጣል አሁን ዌስትሊን አንድ አባል ስለሚያስፈልጋት ለሱ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ ታየው " ጥሩና ብቁ የሕዝብ
አገልጋይ እንደሚሆንም ያምናል " ተሰጥዎው ሰፊ ፡ ንግግሩ አርኪ ነው እውነተኛና ቀና መንፈስ አለው " ወገኖቹን በሙሉ ኃይሉና ችሎታው እንደሚያለግል ያውቃል " እነርሱም ያውቃሉ "

ቅጠላ ቅጠሎቹ ባበቡበት ' ዛፎችና ቁጥቋጦዎች አዲስ ያቆጠቆጠውን ለምለም ቅጠላቸውን በለበሱበት ' በዚያ ደስ በሚለው የጸደይ ምሽት ሁሉም ነገር በተስፋ የተመላ ይመስል ነበር ።

ሚስተር ካርላይልም በቀረበለት ፡ ተስፋ ያለው ዕድል ከልቡ ተደሰተ "

ባርባራ ከሳሎኑ መስኮት ቁማ ትጠብቀው ነበር ሲገባ ደንበክ ደንበክ እያለች ወደሱ ቀርባ በብሩህ ዐይኖቿ ውስጥ የፍቅር ብርሃን እየዋለለ ፊቷን ወደሱ ቀና አደረገች።

'' ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት እንደዚያ ሆና እንደ ቆመች እጆቹን ከወደ ጀርባው
አድርጎ ።

" ምነው ? ደኅና እንዴት አመሸሽ ለማለት አቀበት ከሆነብህ እስከ ሳምንት ድረስ አትስመኝም ልል ሐሳብ አለኝ አርኪባልድ ”

ሚስተር ካርይል በአነጋገሯ ሳማቀና በዚህ የበለጠ የሚቀጣው ማነው ?”
አላት በሹክሹክታ

ባርባራ ለንቦጯን ጣለች እንባዋ ወዲያው በዐይኗ ሞላ “ ባንቺ ይብሳል '
ማለትህ ነው ! ለኔ ደንታ የለህምን አርኪባልድ ?”

በሁለት አጆቹ ጠምጥሞ ይዞ ከደረቱ እቅፍ አደረጋትና መልሶ መላልሶ ሳማት
ላንቺ ማሰብ አለማስቤንማ ታውቂው የለም ? አለት በጆሮዋ "

ይህ ሁሉ ሲሆን ያቺ የፈረደባት ሳቤላ ትመለከት ነበር በዘመኑ ለሷም ሲያደርገው የነበረው ሰላምታ ነው የገረጣው ፊቷ ደም እንደ ለበሰ ልክ እንዳመጣጧ ሹልክ ብላ ሳያዩዋት ወታ ወደ ክፍሏ ተመለሰች " ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ወደ መስኮቱ ሳባትና ክንዱን በሽንጧ ሳይ አድርጎ እንደቆሙ “ስሚ እስቲ ባርባራ ካመት ውስጥ ለጥቂት ወሮች ለንደን ብንቀመጥ ምን ይመስልሻል ?

“ ለንደን ? እኔ እዚሁ በደስታ እኖራለሁ " የምን ለንደን አመጣህ ደግሞ ? ለንደን መቀመጥ አማረኝ እንዳትለኝ "

“ እርግጠኛ አይዶለሁም ግን አንድ ነገር ተጠይቄአለሁ ዌስትሊኖች እንደ ራሴያቸው እንድሆን ይፈልጉኛል " ከስሜ ላይ የፓርላማ አማካሪ የሚል ቅጽል ሲጨመርበት ማየቱ ደስ ይልሻል ?

“ጣም ጥሩ ነው ...አርኪባልድ " ሕዝቡ ወትሮም ቢሆን ይወድሃል አሁን ደግሞ የበለጠ ያከብርሃል " ዘለዓለም የገጠር ጠበቃ ሆኖ መኖር ላንተም ደግ አይደለም " ግን አሁን ለዕለት እንጀራህ ስትማስን አያለሁ " ተመርጠህ ብትሔድ ግን
ዌስት ሊን ላይ ለመሥራት አትችልም " ”
👍15
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ሁለት ሦስት ቀን ቆይቶ ሚስተር ካርላይል ለዌስትሊን ነዋሪዎች ያዘጋጀው ንግግር በአካባቢ ጋዜጦች ወጣ ። ግድግዳዎቹ ሁሉ “ ካርላይልን ምረጡ! ምን
ጊዜም ካርላይል ! በሚሉ ፀባለ ልዩ ልዩ ቀለም ጽሑፎች አጌጡ " ...

ትንግርቶች ማብቂያ የላቸውም ። መገረምም የሰው ልጅ ዕጣ ነው » ሰር ፍራንሲስ ሌቪሰንን የሚያውቁት ሰዎች ሰር ፍራንሲዝ ሌቬሰን ከነበረበት ልማድና ጠባይ ራሱን አላቅቆ እሳት የላስ ፖለቲከኛ ሆነ ሲባል ስምተው እጅግ አድርገው ተደነቁ
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ ፖለቲካ ዓለም የዞረው የጠቅላይ ሚኒስትርነት
ቦታ ተሰጥቶት ወይም ከቁም ነገራም ሰዎች ጋር እንዲሰለፍ ሕሊናው ወቅሶት አይደለም " የገንዘብ ችግር ደረሰበት ። ስለዚህ ደኅና ገንዘብ የሚገኝበት ምንም የማይሠራበት አንድ የሚደገፍበት ነገር አስፈለገው "

የገንዘብ ችግር ! በቅርቡ ከፍተኛ ሀብት የወረሰ ሰው እንዴት ካሁኑ ችግር
ላይ ሊወድቅ ይችላል » የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም " ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚወዳቸውን መዝናኛዎች ለሚወዱ ሁሉ ለክስረት ከዚህ የቀለለ መንገድ አያገኙም " ያጎቱን ማዕረግና ሀብት ሲወርስ እሱ ከጠበቀው የበለጠ ዕዳና ኪሣራ መክፈል ግድ ሆነበት " ሰር ፒተርም በመብቱ ማግኘት ከሚገባው በላይ አንዲት ቤሳ አልተወለትም ዕዳውን በሙሉ ከፍሎ የተረፈውንም ቢሆን በእጁ ከመግባቱ ገና በግራና በቀኝ ይበትነው ጀመረ ጋብቻው ለጥቂት ጊዜ ቢገታውም ተጨማሪ ወጭ ከማስከተሉ በቀር ምንም አላዳነውም " የገንዘብ ዐቅሙን መጥኖ በመኖር ፈንታ እሱና ሚስቱ ከዐቅማቸው በላይ መኖር ጀመሩ ከዚህ ሌላ ከጋብቻው ወዲህ በፈፀረስ
አሽቅድድም በቁማሮችና በልዩ ልዩ ውርርዶች ሁሉ መግባት ጀመረ " ያ ሁሉ
ገንዘብ ያስወጣ ነበር።

በዚህ ዐይነት ጊዜም ሔደ፤ሁኔታዎችም እስኪያቅታቸው ድረስ ተጓዘና ቆሙ።ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በዚህ ጊዜ ነቃ " የነበረው ገንዘብ አንድ ሺልንግ እንኳን ሳይቀር አለቀ ዕቃው ሁሉ ተያዘ ። በነሱ ምትክ ዕዳና ዕዳ ጠያቂዎች ብቻ ቀሩ።
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ባሮኑ የውርስ ተስፈኛ ከነበረዉ ከተራው ፍራንሲዝ
ሌቪሰን የበለጠ ተጨነቀ

ሥራው ሁሉ እንደ ሟቹ ሎርድ ማውንት እሰቨርን ነበር ነገር ግን ፡ ኧርሉ
የሆነ ብልሃት እየፈጠረ ጉዱን እስከ ጊዜ ሞቱ አለባብሶት ዐለፈ " ይኽኛው ግን ጕዱን ይዞ ከችግርና ካስቸጋሪዎች ጋር ተፋጠጠ የሚያደርገው ሲጠፋው ቁማር ቢጀምርም ዕድል ፊቷን አዞረችበት እንደ ምንም አለና ከፈረስ እሽቅድድም ውድድር
ገባ ነገሩ እንኳን ለጥቂት ቀን ይደግፈው ነበር ሆኖም እሱም አቅጣጫውን ለቀቀና እንዲያውም የተጨማሪ ዕዳ ተጠያቂ አደረገው " በመጨረሻ ብዙ ገንዘብ የሚገኝበት ብዙ የማይሠራበት የመንግሥት ሥራ ለመፈለግ በሕግ መወሰኛ የነበሩትን
ሚኒስትሮችን እንደልቡ ለሚያቀያይረው ለሎርድ
ሄድሎት ጸሐፊ ለመሆን የተስፋ ፍንጭ አገኘ " ተስፋው ግን ተጨባጨጨ ሊሆን የሚችለው ሰወየው በመጀመሪያ ፓርላማ የገባ እንደፀሆነ ብቻ ነው " ከዚያ በኋላ ለተጠየቀ ሥራ ብቁ መሆኑ ይገመገማል " ይህ ሁኔታ ነው ወደ አሁኑ ታሪክ ያመጣን ።

በአንድ ፀሐያማ ድኅረ ቀትር ኢቶን አደባባይ ላይ ከነበረ ቤት በጣም ያማረ ሳሎን
ውስጥ አንዲት መልኳ ስልክክ ያለ መልከ መልካም ልጅ እግር እመቤት ተቀምጣለች " በመልካሙ ፊቷ የቁጣና የኩርፊያ መልክ ይታይባታል " በሚያምረው እግሯ ሥጋጃውን ትመታለች ይህች ሴትዮ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪስን ባለቤት ናት።

አንድ ሥራ መልካምም ሆነ ክፉ ይዋል ይደር እንጂ ለሠሪው ፍሬውን አያሳጣወም " ነገሩ ብዙ ዘመን አልፎታል ፍራንሲዝ ሌቪሰን 'ብላንሽ ሻሎነር በተባለች ቆንጆ ልቡ ይጠፋል በፍቅር። ከመኻል ላይ አቋርጦ ለእመቤት ላቤላ ሲል ቸለል ብሏት ይቆያል እንደገና ሳቤላን ጣል አድርጎ ወደ እሷ ተመልሶ የምስጢር ግንኙነት ያደርጋሉ " በምስጢርም ይተጫጫሉ " የብላንሽ እህት ሊዲያ ሻሎነር ትጠራጠርና እኅቷን ትጠይቃታለች ከሌቪሰን ጋር መተጫጨቷን ምላ ተግዝታ ትከዳለች » በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ዘመናት ዐለፉ " ምስኪን ብላንሽ በፍቅሯ ማተብ እንደጸናች ጠበቀች ዕዳውን የገንዘብ ችግሩን ቸልታውን ከሳቤላ ካርላይል ጋር ኰብለላውን ሁሉ እያወቀች ትወደው ነበር ከልቧ ታምነው ነበር ውርሱን ካገኘ በኋላ ወደ ለንደን እንደ ተመለሰ የነበረው ወዳጅነታቸው እንደገና ቀጠለ " ግን በሱ
በኩል የነበረው ፍቅር እንደ ወትሮው ሳይሆን ቀዝቃዛና ጭብጥ የሌለው ቢሆንም
ብላንሽ እንደሚያገባት ትተማመን ነበር አሁንም ከሷ ጋር የነበረው ግንኙነት
እንዲያው ያዝ ለቀቅ ነበር » በምስጢር አለሁልሽ አንለያይም እያለ ' ከቤትም እየዘለቀ ይጠይቃት ነበር " ምናልባትም ግንኙነት ማቆሙን ቢነግራት እብድ እንደምትሆንበት በማወቅ ስለ ፈራ ይሆናል " ብላንሽ እንደ ምንም ብላ ጨከነችና ጋብቻው በቶሎ እንዲሆን ጠየቀችው መቸም ቀጣፊዎች ፈሪዎች
ናቸው ሰር ፍራንሲዝም ግልጽ ያለ ነገር እንዳይናገር ጋብቻው በቅርቡ እንደሚሆን ደኅና ሆኖ በማይሰማ አነጋገር እያልጐመጐመ ነገራት "

እኅቷ ሊድያ ሻሎነር ባሏ ሲሞት በተወላት ገንዘብ እየተረዳች ሚስዝ ዌሪንግ
ተብላ ደኅና ኑሮ ትኖር ነበር" ልጆቹ የሙታን ልጆች ስለ ነበሩ እኅቷ ብላንሽ ሻሎነርንም እሷ ያዘቻት ብላንሽ ወደ ሠላሳ ዓመቷ መቃረቧን የሚጠቁሙ አንዳንድ ምልክቶች ይታዩባት ጀመር ዓመቶቹ ሳይሆኑ የማያቋርጡ የተስፋ እንቅፋቶችና
የሐሳብ ጭንቀት ዱካዎች ይታዩባት ጀመር " ጸጉሯ ሳሳ ፊቷ ምጥጥ ሙግግ አለ"
የሚያምረው የሰውነቷ ቅርጽ ጠፋ „ “ ኧረ ወዲያ ደሞ ይችን ነው የማገባ !
አለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ለራሱ "

አሊሽ ሻሎነር የኻያ ዓመት ቆንጆ የነበረች ታናሽ እኅታቸው ለገና በዓል ልትጠይቃቸው መጣችና ሚስዝ ዌሪንግ ቤት ሰነበተች " በመልኳ ከትልቅ እህቷ ከብላንሽ ሻሎነር በጣም የላቀች ነበረች ገና አንዲት ፍሬ ልጅ ሳለች የተለያት ፍራንሲዝ ሌቪሰን አሁን እንደዚያ አምራና ዳብራ ሲያያት ጊዜ ከሷ ጋር ፍቅር ያዘው ፍቅርም ሲባል ወግ አለው እሱማ ልክ እንደ ጥላዋ እየተከተለ ደስ ደስ የሚሉ የፍቅር ቃላት በጆሮዋ እያንቆረቆረ ልቧን ከማረከ በኋላ ለጋብቻ ጠየቃት " ሳታቅማማ
እሺ አለችው " የጋብቻው ዝግጅት ወዲያው ተጀመረ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
ዝግጅቱን አጣደፈው እሷም ቶሎ መጋባቱን አልጠላችውም "

ከተራ ጓደኝነት የተለየ በፍቅር በጋብቻ መተሳሰር ለሚባል ነገር ጭራሽ
እንደማያውቅ ነገራት በዚህ ረገድ የሰጣትን ተስፋና የገባላትን ቃል
ጭልጥ አድርጎ ካዳት "

መረጃ ማቅረብ አልቻለችም " ከሱ የተጻፈላት ቁራጭ ወረቀት ወይም አንድ
የፍቅር ቃል ሲተነፍስላት ሰማሁ የሚል የጠላትም ሆነ የወዳጅ ምስክር አልነበራትም እሱ በጣም ተጠንቅቆበታል " እሷም ራሷ ምስጢር የጠበቀች መስሏት ከፍራንሲስ ሌቪሰን ምንም 0ይነት ግንኙነት እንዳልነበራት ለእኀቷ አረጋግጣላት ነበር ስለዚህ ለመዳን ተስፋ በሌለው ሁኔታ በመስጠም ላይ ባለች መርከብ ላይ አንደ
👍14😁2
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስተር ካርይልና ባርባራ ቁርስ ላይ እንዳሉ ሚስተር ዲል ሲገባ አዲስ ነገር
ሆነባቸው " እሱን ተከትሎ ጀስቲስ ሔር ጥልቅ አለ » ወዲያው ስኳየር ስፒነር ተከትሎት ግባ " በመጨረሻ ደግሞ ኮሎኔል ቤተል መጣ " አራቱም የመጡት ለየብቻ
ቸው ሲሆን ሁሉም ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ ሲል ማን ቀድሞ እንደሚደርስ የተወዳደሩ ይመስሉ ነበር "

ሁሉም ሲቃ እየተናነቃቸው ሳይደማመጡ ባንድ ላይ ሲናገሩ ሚስተር ካርላይል ሊገባው አልቻለም ።በጣም ተናዶ ይናገር የነበረው የሚስተር ጀስቲስ ሔር
ድምፅ ብቻ ጆሮን ለማደንቆር ይበቃ ነበር ከዚያ ሁሉ ጫጫታ ሚስተር ካርላይል አንድ ቃል ያዘ።

“ ሁለተኛ ሰው ? ተወዳዳሪ ? ይምጣ እንጂ በመጨረሻ ማን እንደሚያሸንፍ ማወቁም እኮ ያስደስታል” አለ ካርላይል በቅን ልቦና "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ ሽማግሌው ማን መሆኑን እኮ አልሰማህም
ዲል “ ከሱ ጋር እኩል ቆሞ መወዳደር ! ” ብሎ ደነፋ ሚስተር ጀስቲስ ሔር ።

“የለም ሰውዬው መሰቀል ይገባዋል” አለ ኮሎኔል ቤተል ከመኻል አቋርጦ"

መዝፈቅ አይቻልም ?” አለ እስኳየር ስፒነር "

ሰዎቹ ተናግረው የሚያበቁ ወይም እየተደማመጡ የሚያወጉ አልመሰለም "
ባርባራ በሁኔታቸው ተገርማ ዐይኗን ካንዱ ወደ ሌላው እያንገዋለለች ታያቸዋለች
“ ይኸ ኃይለኛ ተወዳዳሪ ማነው ? አለ ሚስተር ካርላይል "
ሚስተር አርኪባልድ ” አለ
ዲል ድምፁን ዝቅ አድርጎ " " የቀረበው እጩ ያ ሌቪሰን የሚባለው ሰውዬ ነው ”

ሚስተር ካርላይል ፊቱ ደም ለበሰ ። ባርባራ አንገቷን ደፋች " ዐይኖቿ ግን
በቁጣ ተንቀለቀሉ "

“ ቤንጃሚን ፈረሶቹን ለማንሸርሸር ዛሬ ማለዳ ወደ ከተማ ወጥቶ ነበር '
አለ ጆስቲስ ሔር ከንዴቱ የተነሣ ምላሱ እየተንተባተበ “ ሲመለስ የከተማ
ግድግዳዎች · ሌቪሰን ለዘለዓለም ይኑር ! ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ምረጡ ! በሚሉ ፁሑፎች ተንቆጥቁጠዋል አለኝ “ነደደኝና በጥፊ ላቀምሰው ስል ኧሪ እውነቴን ነው " አንዳንድ ሰዎች አነጋግሬ ነበር ትናንት ማታ ነው አሉ በባቡር ግብቶ ያደረው
አሉኝ "

“ ትናንት ነው በመጨረሻው ባቡር የደረሰው » ያረፈውም ባክስሔድ ሆቴል ነው አለ ሚስተር ዲል " አንድ ወኪል ብጤና አንድ ደግሞ የመንግሥት አባል ነኝ የሚል ሰው አብረውት አሉ ማስታወቂያ አታሚዎቹ ግን ያን ሁሉ ሲያዘጋጁ
ተቀምጠው ሳያድሩ አልቀሩም "

"ገና ሳይጀመር የውድድሩም የድሉም መስክ የኛ ነው እያሉ ጉራቸውን ብትሰሙ
ይገርማችኋል " ሰውየው ግን ራሱን ለውድድር ማቅረቡ ዕብድ ነው?”
አለ ኮሌኔል ቤተል ከዘራውን ወደ መሬት በኃይል በመሰንዘር ።

"ሚስተር ካርላይልን ለመሳደብ ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር ነው ” አለ ስፒነር

"ሁላችንን ለማዋረድ ነው እንጂ! ኧረ ቆይ ሲቀልድ እንደገባው ሲቀልድ አይወጣ።

“ በክስ ሔድ ሆቴል ስብሰባ ስለአለ አብሬአችሁ እግኛለሁ” አለ ሚስተር ካርላይል።

“ በክስ ሔድ ሆቴል ነበር ያልከኝ?ይኸን ደግሞ አልሰማሁም” አለ ስፒነር
ባክስ ሔድ እንደነበር መስማቴን ነው የተናገርኩ” አለ ዲል “ እስካሁን ግን
እሱም መሳሳቱንና ዳኞቹ ቢሰሙ ደግሞ እንደሚቀየሙት ነግሬዋለሁ "ዱሮውንም መሳሳቱን ቢያውቅ ኖሮ ይመልሰው እንደ ነበር ካወቀ ወዲ ደግሞ ባጭር ጊዜ
እንደሚያባርረው ግልጾልኛል።

ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ሰዎቹ ወጡ » ሚስተር ካርላይል ቁርሱን ለመጨረስ ተቀመጠ "

“ አርኪባልድ የዚህ ሰውዬ ደፋር ድርጊት ካሰብከው ፍንክች እንዳያደርግህ”
አለችው ባርባራ "

“ እሱ እኔን ለማጥቃት ገፍቶ መጥቷል " እኔ ደግሞ ከጫማዬ ሥር ካለው
ትቢያ እንኳን አብልጬ አላየውም "

እውነትክን ነው” አለችው ፊቷ በኩራት ቦገግ አለ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ዌስት ሊን ሲሔድ አንድ ሰው በሌላው ላይ ሊፈጽመው የሚችለውን የመጨረሻ ታላቅ በደል የፈጸመበትን የዚያን ክፉ ሰው የውድድር ማስታወቂያ ከሱ ማስታወቂያዎች ጋር ጐን ለጐን ተለጥፎ ተመለከተ "

አርኪባልድ ይህን አሳፋሪ ወሬ ሰምተሃል ? አለች ኮርኒሊያ እንደ ጀልባ እየተንሳፈፈች ደረሰችና "

“ ስምቸዋለሁ ኮርኒሊያ ። ባልሰማስ ግድግዳዎቹ ሊነግሩኝ ይችሉ የለ?”

አብዷል ? ደኅና ግድ የለም በፊት ደስ አላለኝም ነበር !አሁን ግን እንዳትለቅለት " ከእፉኝት አብልጠህ እንዳታየው ዌስትሊን በሙሉ ተነቃንቋል እንደዛሬ ሆኖ አያውቅም።

እውነቷን ነበር ድፍን ዌስት ሊን በድጋፍና በቁጣ ተንቀሳቀሰ ገጠሬው ከተሜው ሁሉ ካርላይል ብሎ ተነሣ " ቢሆንም ዌስት ሊን ውስጥ የመንግሥት ትኩረት ከፍተኛ ነው " የግልና የሕዝብ አስተያየት የመሰለ ቢመስልም ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በጣም ብዙ ድምፅ ይመዘገባል።

ያን ዕለት ጧት ባርባራ ባሏን እስከ ግቢው የውጭ በር ድረስ ሽኝታው ስትመለስ ማዳም ቬንንና ሁለቱን ልጆች አገኘቻቸው ዊልያምም ሻል ያለው ይመስል ነበር።ሁልጊዜም ጧት ት ችግር አልነበረበትም "

· እማማ ” አለች ሎሲ “ የሞቀሽ ትመስያለሽ ፊትሽ ተለወጠ ”
አንድ ሰውዬ ከአባታችሁ ጋር ሊወዳዶር ስለ ተነሣ ተናድጄ ነው
ለመወዳደር መብት የለውም እንዴ አባባ ውድድሩ ለሁሉም ክፍት ነው ሲል ሰምቸዋለሁ ” አለ ዊልያም።

“ ለሱ ካልሆነ በቀር ለሌላው ክፍት ነው ” አለች ባርባራ ንዴቷ አስተያየቷን እየቀደመ “እሱ ክፉ · ማንም የሚንቀው ጥሩ የሚባሉ ሰዎች ሁሉ የሚጠሉትና
የማያስጠጉት ሰው ሆኖ እያለ አሁን ከአባታችሁ ጋር ሊወዳደር ቀረበ

“ ስሙ ማን ይባላል ?”

ባርባራ ትንሽ አሰበችና እሷ ባትነግራቸውም ከሌላ መስማታቸው ስለማይቀር
ካመዛዘነች በኋላ '“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ይባላል ” አለች "

ማቃሰት መደንገጥና መገረም የተቀላቀለበት ድምፅ አሰማች አስተማሪቱ።ባርባራ ዞር ብላ ስታያት አቀርቅራ ፊቷን በመሐረቧ ሸፍና ትስል ስለ ነበር ድንገት ልውጥውጥ ብሎ የገረጣውን ፊቷን ማስተዋል አልቻለችም

አመመሽ እንዴ ? አለቻት ባርባራ "

“ ሕመም እንኳን ደኅና ነኝ " ብቻ አቧራ ብጤ ባፌ ገባ መሰለኝ አሳለኝ። "

ሚስስ ካርላይል ዝም አለች " ሕሊናዋ ግን ዝም አላለም።
ይኸን ስም ስትሰማ ለምን ደነገጠች " ሰውዬውን ታውቀው ኖሮ ይሆን ? የደነጠችው ግን በስሙ መነሣት ነው ? " እያለች ታስብ ጀመር
የሚገርመው ደግሞ ማዳም ቬን የዚያን ለት አላስተማረችም " ስለ ውድድሩ ጉዳይ ቶሎ ከሰሙት አንዱ ሎርድ ማውንት እስቨርን ነበር " ለንደን ውስጥ ከክበቡ
ሆኖ አንድ ማታ ጋዜጣ ሲመለከት ካርላይል ዌስትሊን ” ከሚሉ ስሞች ላይ ዐይኖቹን ያሳርፋል ሚስተር ካርላይል በእጭዎች መቅረቡን ተረድቶ እንዲቀናውም ከልቡ ተመኝቶ ኧርሉ ንባቡን ቀጠለና አንቀጹን አነበበው "

መልሶ መላልሶ አነበበው " ዐይኖቹን አሻሸ " መነጽሩን ወለወለ " በሕልሙ ይሁን በውኑ ለማረጋግጥ ራሱን መረመረ። ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ዌስት ሊን መግባቱን የሚስተር ካርላይል ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረቡንና አሁን የፖለቲካ ንግግር የምርጫ ቅስቀሳ በማካሔድ ላይ መሆኑን አነበበ።

“ ይኸ ጋዜጣው ስለሚለው አሳፋሪ ነገር የምታውቀው አለህ ? አለ አብሮት የነበረውን አንዱን ሰውዬ "
“ እውነት ነው » እኔ ከአንድ ሰዓት በፊት ነበር የሰማሁት ሌቪሰን ብዙ
ድምፅ ማግኘቱ አይቀርም "

ድምዕ ! ” ” ኧርሉ በሰውዬው አነጋገር መንፈሱም አካሉም ተሸበረና “በል እንደዚህ አትበል ይህ ወደል ውሻ እንዲያውም መሰቀል ይገባዋል
👍10👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስ ካርይልና ወይዘሮ ቬን በዚያ በሚግለበለበው ነፋስ መኻል ከመንገዱ መታጠፊያ ቆመው ነበር። ሳቤላ ተደናግጣና ግራ ተጋብታ የመነጽሯን ስብ
ርባሪ ስትለቃቀም 'ሚስ ኮርኒሊያ ደግሞ ተገርማ ያን ነፋስ የገለጠውን ፊት ትመለከታለች። በደንብ የምታውቀው መልክ ነበር " ሆኖም ትኰረቷን የሰር ፍራንሲዝ መዝለቅ ለወጠው።

ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ እነሱ ተጠጋ " ሚስተር ድሬክ ... ሁለተኛው ጓደኛውና ሌሎች
ጥቂት አዳማቂዎች አብረውት ነቀሩ እሱና ኮርኒሊያ ፊት ለፈት ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ነበር " የጥላቻ ግንባሯን ቋጥራ በኩራትና በመራራ ንቀት
ተሞልታ ጠበቀችው እሱ ግን ከነሱ ዘንድ ሲደርስ ለትሕትና ብሎ ይሁን ወይ
ስለ ተደናገጠ ወይም ለማሾፍ አልታወቀም ባርኔጣውን ብድግ አደረገላቸው "

ለሚስ ካርላይል ግን ሊያሾፍ ያደረገው መሰላት ከንዴቷ ተነሣ ከንፈሯ
ዐመድ መሰለ "

“ እኔን ነው እንደዚህ የምትሰድበኝ . . . ፍራንሲዝ ሌቪሰን ? ''

" በመሰለሽ ተርጉሚው ? አላት እሱም ጅንን ብሎ "

አንተ ለኔ ባርኔጣ ልታነሣልኝ ትደፍራለህ ? እኔ ሚስ ካርላይል መሆኔን ረስተኽዋል ?”

“ አንቺን አንድ ጊዜ ያየሽ መቸ በቀላሉ ይረሳሻል” አላት በግልጽ እያሾፈ
አብረውት የነበሩት ሁለት ጓዶኞቹ ምን ማለት እንደሆነ ነገሩ አላምር ብሏቸው ይመ
ለከታሉ "

ሳቤላ ፊቷን እንዳያይባት ለመሸሸግ የሚቻላትን ስትሞክር የነሱ' የነገር ምልልስ የሰበሰባቸው ተመልካቾች ደግሞ ሥራዬ ብለው ከበው ያዳምጣሉ " ከነዚያ ተመልካቾች ውስጥ ጥቂት የስኳየር ስፒነር አራሾች ነበሩባቸው "

አንተ የተናቅህ ትል ጮኽችበት ኮርኒሊያ „ “ በማናለብኝነት በዌስት
ሊን እንደምትዘባነንበት በኔም የምትችል ይመስልሃል ? ደፋር መጥፎ አሁን ያዙት ! ብላ ስትጮህ ለሰውየው ፈጣን ቅጣት የሚስጥ አለ ብላ አስባ አልነበረም ከቦ የነበረው ሕዝብ ተዘጋጀቶ ይጠብቅ ኖሯል " ሚስ ካርላይል ደግሞ የፈለገው
0ይነት ጥፋት ቢኖራትም አካባቢው በጣም ያከብራት ነበር " እሁንም እንዲህ በሷ
አነጋገር ተነሣሥተው ይሁን ወይም የነሱ ጌታ እስኳየር ስፒነር ኢስት ሊን መጥቶ
ሳለ ያወሳውን የማድፈቅን ነገር ጠቁሟቸው ይሁን ወይም ከገዛ ስሜታቸው ተነሣሥተወ አይታወቅም እነዚያ ጫንቃ ሰፋፊ አራሾች እንቅስቃሴ ጀመሩ “ድፈቁት " ብሎ ኣንድ ድምፅ ሲጮሀ ሌሎች ያን ቃል እየተቀባበሉ ' ' ድፌቁት ድፈቁት ! ኩሬው ከዚህ ነው ! ማግኘት ከሚገባው ትንሽ እናቅምሰው ይህ ገፋፊ ሚስተር ካርላይልን ለመወዳደር ነው ዌስት ሊን የመጣው ? በእመቤት ሳቤላ የፈጸመው ነገር ምን ነበር ይህን ሥራውን እኛ ዌስት ሊኖች በቀላሉ አናየውም ዌስት ሊን
አይፈልገውም
" ዌስት ሊን እንደሱ
ያለውን ቀጣፊ አይፈልግም
ፊቱ ነጣ ስወነቱ በድንጋጤ ተናጠ " እንደሱ ያሉ ጥቅመ ቢሶች ብዙ ጊዘ ፈሪዎች ናቸው " ወይዘሮ ሳቤላም ስሟ ሲነማ ሰምቲ እንደሆነ እንጃ እንደሱ ትንዘፈዘፍ ጀመር " የዳር አጫፋሪዎቹን ሳይጨምር ኸያ ጥንድ የሚሆኑ ጠንካራ ሸካራ
እጆች ተረባረቡበት በርግጫ በጡጫ ቀጉሽምት ያዋክቡት ጀመር እዚያ የነበረው የቁጥቆጦ አጥር ተጠረማመሰ እሱን ከዚያ ላይ እየጎተቱ መሰዱት ከሚስተር ዴሪክና አብሮት የመጣው ጠበቃው ሁለተኛው ሰው ጠበቃ ነበር ድረገሐቱን ለመግታት ምንም አቅም አልነበራቸው ለመገላገል አስበው አንደኛው መናገር ሲጀምር
የማያርፉ ከሆነ እነሱንም መጨር ነው የሚል ምላሽ ሰሙ አጭር ወፍራም የነበረው ጠበቃ አድራጎቱ ሕገ ወጥ ረብሻ መሆኑን አልጎምጉሞ ካምባጓሮው ቦታ ውልቅ ብሎ ወጣ ሚስ ካርላይል በግርማ ሞገስ ቀጥ ብላ ቁማ ድርጊቱን ትመለከት ጀመር " ለማገላገል ፍላጎት ኖሯት እንደሆነ አልታወቀም
እንጂ መኻል ገብታ ልታላቅቀው ብትሞክርም ኖሮ ሰሚም ተቀባይም አታገኝም ነበር።

እያዳፉ እያንገላቱ ወደ አረንጓዴው ኩሬ ጠርዝ ወሰዱት ልብሱ ብዙ ከመቀዳደዱና ከመዘነጣጠሉ ሌላ የኮቱ ጅራትም ተቆርጦ ሔዶ ነበር " አንዱ ወደፊት ሲጎትተው ሌላው ከበስተኋላው ሲገፈትረው ' ሌላው አንገትያውን ይዞ ሲያንዞረው
የቀሩት ደግሞ በኩርኩም በጥፊ በቁንጥጫ በጉሽምታ መዓታቸውን
አወረዱበት "

“ ክተቱት ጎበዝ !”

ማሩኝ ! ማሩኝ !” አለና ጮኸ ጉልበቶቹን አጥፎ ጥርሶቹን እያንቀጫቀጨ።
“ ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ማሩኝ ስለ ፈጣሪ ” አለ " ውሃው ተንቦጫረቀ ፍራንሲዝ
ሌቪሰን አረንጓዴ ከለበሰው ባሕር ውስጥ ተዘፈቀ » የልዩ ልዩ ነፍሳት መኖሪያና
መራቢያ ከሆነው ቁሻሻ ውሃ ሳይወድ እየጠጣ የደመ ነፍሱን ተፍጨረጨረ
ሰዎቹ እሱን ከተው ሲያበቁ ከዳር ቁሙው እየሣቁ አፌዙበት " ከበው የነበሩት
አዳማቂ ሕፃናት እየጨፈሩ እያጨበጨቡ ኰሬውን ዞሩ።

ነፍሱን ጨርሶ ከመሳቱ በፊት አወጡት » ኩምሽሽ ብሎ የከፋ ነጭ ፊቱ
የሚንዘፈዘፉት እግሮቹና ከመቀደዳቸውም በላይ ከኩሬው ተዘፍቀው ከወጡት ልብሶቹ ጋር ባጠቃላይ ሲታይ ከውሃ ገብታ ከሞተች አይጥ የበለጠ ያስከፋ ነበር "
ገበሬዎቹም የሠሩትን ሠርተው ሔዱ ይጨፍሩ የነበሩት ልጆቹም ከአካባቢው ጠፉ ፤ ሚስ ካርላይልም ሳቤላን አስከትላ መንገዷን ቀጠለች

መከራኛይቱ ሳቤላ
መንቀጥቀጡ አልለቀቃትም
ሚስ ካርላይል ምንም ሳትናገር አንገቷን ቀጥ አድርጋ ወደፊት ገሠገሠች "
ዐልፎ ዐልፎ ብቻ ዞር እያለች የማዳም ቬንን ፊት ታይና '' ይገርማል !ወይ መመሳሰል ... በተለይ ዐይኖቿ' ብላ እያሰበች ከአንድ መነጽር ቤት አጠገብ ደረሱ "
“ መነጽሬን እንዲሠሩልኝ ሰጥቻቸው ልለፍ ” ብላ ጎራ ስትል ሚስ ካርይል
ተከትላት ገባች
መነጽሩ እንዴት ሆኖ መሠራት እንደሚገባው አሳይታ አስረከበችው " ሌላ
ለመማዛት ብትፌልግ ከነጭ በቀር አንድም ባለ ቀለም አልነበረም " ተፈልጎ ተፈ
ልጎ • ከብዙ ዘመን በፊት አንድ ሰው ለማሠራት አምጥቶት ሳይወስደው የቀረ አንድ ጠርዙ አረንጓዴ የሆነ አስቀያሚ መነጽር ተገኘላትና አሱን አደረገች ኮርኒሊያ አሁንም ዐይን ዐይኗን ታያታለች

"ለምንድነው መነጽር የምታደርጊው ? አለቻት ገና ከቤቷ ሲገቡ።

" 0ይኖቼ ይደክብኛል ” አለች ጥቂት አስባ "

“ሲታዬ ጤነኛ ይመስላሉ "ነጩ ለሁሉም ሊያገለግል ይችላል !ለምንድነው
ባለ ቀለም የምትመርጪው ?”

“ ባለቀለም ስለ ለመድኩ ዛሬ ነጭ ለማድረግ ደስ አይለኝም "

ኮርነሊያ ዝም ብላ ቆየችና “ የክርስትና ስምሽ ማነው ማዳም ? አለቻት "

“ ጄን” አለች ሳቤላ ።

“ ኧረ ምን ነገር ነው ? ያ ምንድነው ?

በመንገዱ የሕዝብ ጮኽት ተሰማ ኮርኒሊያ ወደ መስኮቱ ተንደረደረች ሳቤላ
ተአተለቻት " ከሁለቱ ተቃራኒ አቅጣጫ ወደ አንድ መኻል የሚመጡ ይመስሉ ነበር። ባንድ በኩል ቀይና ወይን ጠጅ ዐርማ ያደረጉ የሚስተር ካርላይል ደጋፊዎች ዘለቁ ሎርድ ማውንት አስቨርንና ሚስተር ካርላይል ፊት ፊት ይመሩ ነበር "

የሌላው ወገን ባለ ብጫ ምልክት ሲሆን አመጣጡ
ስርአት የለሽ ትርምስምስ
ያለ ነበር ውሃ የገባች አይጥ የመሰለውን የሕዝቡ ግምባር መሪ አድርገው ጠበቃውና ሚስተር ድሬክ ደግፈው ይዘውት ዘለቁ " ጸጉሩ በሁሉም በኩል ተንዘርፍፎ እግሮቹ እየተንገዳገዱ ጥርሶቹ እየተንቀጫቀጩ ልብሱ ተሸረካክቶና ተዘነጣጥሎ ወደፊት ሲጓዝ መንገዱን አስከ ጫፍ ሞልተው የያዙት
ብዙ ሰዎች የማሾ ፋና የማናናቅ ጩኽትና ፉጨት እያስተጋቡ ተከትለውት ሲጓዙ ኮረሊያና ሳቤላ
ቁመው ተመለከቱ ።
👍13
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ



ናንሲ ሌኔሃን በተከራየችው አይሮፕላን በካናዳ ጠረፍ ላይ ስትበር ለችግሯ መፍትሄ ታያት፡ ወንድሟን መርታት ብቻ ሳይሆን አባቷ
ካስቀመጡላት የህይወት መርህ መውጣት ትፈልጋለች፡ ከመርቪን ጋር
መሆንም ትፈልጋለች፡ ሆኖም የጫማ ፋብሪካውን ትታ መርቪንን ተከትላ
እንግሊዝ ሃገር ሄዳ ብትኖር እንደ ዳያና የባሏን እጅ መጠበቅ የሰለቻት
ሚስት መሆኗ ነው፡

ናት ሪጅዌይ ኩባንያውን በተሻለ ዋጋ እንደሚገዛና በጄኔራል ቴክስታይል ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንደሚሰጣት ነግሯታል፡ ጄኔራል ቴክስታይልስ ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ባብዛኛው በተለይም እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች አለው፡፡ ናት ሪጅዌይ ደግሞ ጦርነቱ ካላበቃ ፋብሪካዎቹን መጎብኘት አይችልም፡፡ ስለዚህ እሷ የፋብሪካ
ዎቹን የአውሮፓ የበላይ ሀላፊነት ቦታ ይሰጣታል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ
ከመርቪን ጋር ለመሆንና ስራ መስራት የሚያስችላት በመሆኑ ጥሩ ነው፡

መፍትሄው ጥሩ ይመስላል፡፡ አንድ የሚያስፈራ ነገር አውሮፓ ጦርነት ውስጥ ስላለች ልትሞት ትችላለች፡፡ ናንሲ ይህን ስታወጣና ስታወርድ
መርቪን ባህሩ ላይ የቆመውን አይሮፕላናቸውን አሳያት፡፡
መርቪን ከአይሮፕላኑ ጋር በሬዲዮ መገናኛ ለመገናኘት ቢሞክርም ምንም ምላሽ አላገኘም፡፡ ናንሲ አይሮፕላኗ ስታንዣብብ አዕምሮዋ ውስጥ የሚመላለሰውን ነገር ተወችው፡፡ ምንድን
ምንድን ነው የተፈጠረው?
አይሮፕላኑ ውስጥ አሉ? አይሮፕላኑ ሲታይ ምንም አልተጎዳም፡፡ ሆኖም
የሰው ዘር ያለበት አይመስልም፡፡

መርቪን ‹‹ምናልባትም ችግር ደርሶባቸው ከሆነ አርፈን ብናያቸው›› አለ፡፡ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡

‹‹የመቀመጫ ቀበቶሽን በደምብ እሰሪ፡፡ ባህሩ ማዕበል ያለበት ስለሆነ
ስናርፍ ይንገጫገጫል፡››
ፓይለታቸው እንደ ፈረስ የሚጋልበው ባህር ላይ አይሮፕላናቸውን
አሳረፈ፡ ናንሲ እንደገመተችው ማዕበሉ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡
አንድ የሞተር ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሯል፡፡ ትልቁ አይሮፕላን በር ላይ አንድ ሰው እጁን ያውለበልባል። ከዚያም እነ መርቪን አይሮፕላናቸውን ከግዙፉ አይሮፕላን ጋር አሰሩት፡፡

ኔድ ‹‹እኔ አይሮፕላኔ ውስጥ እቆያችኋለሁ›› አለ ‹‹እናንተ ውጡ አይሮፕላኑ ምን ችግር እንደደረሰበት አጣሩ›› አላቸው፡፡

‹‹እኔም እመጣለሁ›› አለች ናንሲ፡፡

መርቪን መጀመሪያ ወደ አይሮፕላኑ ዘለለና ለናንሲ እጁን ዘረጋላት፡

በሩ ላይ የቆመውን ሰው ‹‹ምንድን ነው የተፈጠረው?›› ሲል ጠየቀው፡

‹‹ነዳጅ ስላለቀባቸው ነው ባህሩ ላይ ያረፉት›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹በሬዲዮ መገናኛ ላገኛቸው ሞክሬ ነበር፡፡

ሰውዬውም ‹‹ወደ ውስጥ ግባ›› አለው፡

መርቪን ከገባ በኋላ ‹‹ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አይሮፕላኑ ድንገት ነው ያረፈው›› አለ ወጣቱ ሰው ‹‹እኛ አሳ አጥማጆች ነን ስለዚህ ችግሩን ለማጣራት መጥተን ነው››

‹ካፒቴኑን እጠይቀዋለሁ›› አለ መርቪን፡፡

ወጣቱ ሰው በአለባበሱ አሳ አጥማጅ አይመስልም፡፡ ክራቫት አድርጓል፡፡
ናንሲ ሁኔታው አሳቃት፡፡

ወደ ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ መምበሪ በደም ተለውሶ ወለሉ ላይ
ተዘርግቷል፡፡ አፏን ያዘች በድንጋጤ
‹ወይ አምላኬ! ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል መርቪን ጠየቀ ከኋላቸው ያለው ወጣቱ ሰው ‹‹ቀጥሉ ወደፊት›› አለ በቁጣ፡

ናንሲ ዞር ብላ ስታየው ሰውዬው ሽጉጥ ደግኗል፡፡ ‹‹አንተ ነህ እንዲህ ያደረከው?›› ስትል ጠየቀች
‹‹አፍሽን ዝጊና ቀጥ ብለሽ ሂጂ›› አላት፡፡

መብል ክፍል ውስጥ ገቡ፡፡
ሌሎች ሶስት ሽጉጥ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ አዛዣቸው የሚመስል አራተኛ
ሰው ቆሟል፡፡ ትንሹ ልጅ ከመርቪን ሚስት ኋላ ቆሞ ጡቷን ይጎነትላል፡
መርቪን ይህንን ሲያይ ተናደደ፡፡ ሶስተኛው ሰው የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ
የሆነው ሉተር ሲሆን በፕሮፌሰር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡
ካፒቴኑና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ዓይናቸውን
ያቁለጨልጫሉ፡ በርካታ ተሳፋሪዎች ወምበራቸው ላይ እንደተቀመጡ
ሲሆን ወለሉ ላይ የብርጭቆና የሰሃን ስብርባሪ ይታያል፡፡ ናንሲ ዙሪያውን ስታማትር በፍርሃት የተዋጠችው ማርጋሬት አይኗ ገባች፡፡
‹‹ላቭሴይ አምላክ ፊቱን አዙሯል፡፡ አይሮፕላን በምንፈልግበት ጊዜ
ደርሰህልናል፡ እኔን ቪንቺኒንና የእሱን ሰዎች በአይሮፕላን ይዘኸን ትሄዳለህ፡ ኤዲ ዲኪንማ ፖሊስ እጅ ሊጥለን ወጥመድ ሲያሰናዳልን ነው
የከረመው›› አለ ሉተር፡
መርቪን ከመገላመጥ በስተቀር ምንም መልስ አልሰጠውም፡፡

ባለመስመር ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰው ‹‹የባህር ኃይል ወታደሮች
መጥተው ችግር ከመፍጠራቸው በፊት እንሂድ፡፡ ትንሹ ልጅ አንተ ላቭሌይን ይዘህ ና፡፡ ገርል ፍሬንዱ እዚሁ ትቆይ›› አለ፡፡
‹‹እሺ ቪኒ›› አለ ትንሹ ልጅ፡፡
ናንሲ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባታውቅም ወደኋላ መቅረት ግን አልፈለገችም፡፡ መርቪን ችግር ውስጥ የሚገባ ከሆነ ከጎኑ ትሆናለች፡፡

ቪንቺኒ ሌላ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ‹‹ሉተር አንተ ሳይንቲስቱን ይዘህ ና፡›› ወደ ጆ ዞር አለና ‹‹በመጨረሻ ቆንጆዋን ሴት ይዘህ ና›› ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሰውየው ዳያና ላቭሴይ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ‹‹እንሂድ›› አላት እሷ ግን ከቦታዋ ንቅንቅ አልልም አለች፡፡ ናንሲ ሌላ ጥያቄ ጭንቅላቷ ውስጥ አጫረ፡ ዳያናን ለምንድን ነው የሚወስዷት? በኋላ ግን መልሱ ተከሰተላት
ጆ ቀጠለና በሽጉጡ አፈሙዝ የዳያናን ጡት ወጋ ሲያደርገው ጮኸች፡፡

‹‹ቆይ እስቲ›› አለ መርቪን፡፡

ሁሉም እሱ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹ሁላችሁንም በአይሮፕላን እወስዳችኋለሁ። ነገር ግን አንድ ነገር ማሟላት አለባችሁ›› አላቸው

ቪንቺኒም ‹‹አፍህን
ዝጋና ተንቀሳቀስ፡፡ ምንም ቅድመ  ሁኔታ ማስቀመጥ አትችልም›› አለው፡፡

መርቪን እጁን ዘረጋና ‹‹እንግዲያውስ ግደሉኝ›› አለ፡፡

ናንሲ በፍርሃት ጮኸች፡
እነዚህ ሰዎች የሚዳፈራቸውን ሰው
ከመግደል ወደኋላ የሚሉ አይደሉም መርቪን  አላወቃቸውም አለች በሆዷ

‹‹ምንድነው ቅድመ ሁኔታው?›› ሲል ጠየቀ ሉተር

መርቪን ወደ ዳያና
አመለከተና ‹‹እሷ እዚሁ ትቆይ›› አለ ጆ በንዴት መርቪን ላይ አፈጠጠ፡፡

‹‹አንፈልግህም ብዙ የፓን አሜሪን ፓይለቶች ሞልተዋል፡፡ እነሱም
እንዳንተ ማብረር ይችላሉ›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ሁሉም እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹ጠይቋቸው ጊዜ ካላችሁ፡፡›› ወሮበሎቹ እነሱን ያመጣው ፓይለት መኖሩን እንዳላወቁ ተገንዝቧል፡

‹‹ሴትዬዋን ተዋት›› አለ ሉተር፡፡

ጆ በንዴት ፊቱ ቀላ፡፡

‹‹ለምን?››

‹‹እሷን ተዋት›› ሲል ጮኸ ሉተር፡፡ ‹‹እኔ ገንዘብ የከፈልኩህ ሃርትማንን እንድታፍንልኝ ነው እንጂ ሴት እንድትደፍርልኝ ነው እንዴ››

‹‹ሉተር ልክ ነው ጆ፡ በኋላ ሌላ ሴት ታገኛለህ›› አለው ቪንቺኒም:

‹‹እሺ›› አለ ጆ፡

ዳያና በእፎይታ አለቀሰች።

‹‹ጊዜ የለንም ከዚህ እንውጣ›› ሲል ቪንቺኒ አዘዘ፡፡

ናንሲ ‹መርቪንን ዳግመኛ አየው ይሆን?› አለች በሃሳቧ
ከውጭ ክላክስ ተሰማ፡፡ የጀልባው ነጂ ነው ክላክስ ያደረገው።
👍192
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
👍192🔥2🥰2🤔1
#​​ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

‹‹ለማንኛውም ልድገምልሽ ኤርምያስ እባላለሁ…ለ15 ዓመት ያህል በማንዴላ ሀገር በሆነችው ደቡቡ አፍሪካ ጀሆንስበርግ ኖሬያለሁ… ወደሀገሬ ከተመለስኩ  ሁለት ዓመት ከግማሽ ሆኖኛል፡፡የ20ዓመት አፍላ ፍንዳታ ሆኜ ሄጄ የ35 ዓመት ሙሉ  ደንዳና ወጣት ሆኜ ተመለስኩ….››

‹‹አሀ ዲያስፖራ ነሀ….?››

‹‹አይ ዲያስፖራ ..!!! ‹ጽድቁ ቀርቶብኝ  በቅጡ በኮነነኝ ›ትላለች እናቴ… ለማንኛውም  እወነቱን ንገረኝ ካልሺኝ … በእነዛ ዓመታት ውስጥ በሰው ሀገር ላይ  ስዳክር ..ሞራሌን ከማንቆሻቆሽ…ሰው ሆኜ መፈጠሬን ከመጠየፍ እና ወጣትነቴ ላይ ጢቢ ጢቢ ከመጫወት ውጭ ምንም ያተረፍኩት ነገር አልነበረም…ብዙ ህልም በልቤ ብዙ ምኞት በውስጤ አጭቄ ነበር የተጓዘኩት …እርባነቢስ ሆኜ ባዶ እጄን በሀገሬ ለመሞት ብቻ ብዬ  ነበር የተመለስኩት …ይገርማል አይደል?

ሰው እንዴት ለመሞት ብሎ ከደብቡ አፍሪካ ድረስ ኪሎሜትሮችን አቆርጦ ይመጣል ትይኝ  ይሆናል..….?ለእኔ ግን ትርጉም ነበረው..››

‹‹ንገረኝ እስኪ ትርጉሙን…››ከሳዕታት ትርኪ ሚርኪ ወሬ እና መዛለል በኃላ ድንገት ምርር ወዳለ የህይወት ታሪክ ሀተታ መግባቱ አስደምሟታል አስደስቷታልም…አሁን እየነገራት  ያለውን ታሪክ እሱ ሳይነግራት እንደተለመደው  ወጭ እየጠበቀት ያለውን ንስሯን እንዲረዳት አድርጋ በዝርዝር ማወቅ ትችላለች..ግን አልፈለገችም …እንዲሁ እየጓጓችና ቀጥሎ ምን እንደሚናገር እየገመተች ቀጥታ ከራሱ አንደበት መስማቱ የሆነ የተለየ ስሜት ስለፈጠረባት ደስ ብሏታል…
ቀጠለ ‹‹በህይወቴ እያለሁ የመኖር ምኞቴ ሰልበው በድን አድርገውኝ …ወጣትነቴን ከንቱ አስቀርተውብኝ የመጨረሻውን ክስረት ማክሰራቸው ሳይበቃቸው …ከሞቴም በኃላ ክብር ስጋዬን  ለሀገራቸው ምድር  ልገብር …?አላደርገውም ፡፡ለዘላለም የባዕድ ሀገር አፈር ሆኜ መቅረት  አልፈለኩም  ..ይህ  መልካም አይደለም…ቢያንስ አገሬ እትብቴን በክብር በወርቃማ አፈሯ ውስጥ ቀብራ ከማንነቷ ጋር እንዳወሀደችው ሁሉ ስሞትም በድኔን በክብር ልትቀበለኝ እና ለዘላለም በጉያዋ ልትሸሽገኝ ይገባል..አዎ እንደዛ ነው መሆን ያለበት..በዛ ላይ እናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ማየት እፈልጋለሁ… አያየኋት መሰናበት፤ስሮ በመኖር  እና እሷን መጦር ችዬ ላስደስታት  ባልታደልም… እጇ ላይ ሞቼ አልቅሳ ልትቀብረኝ እና እርሟን ለማውጣት እንድትችል ግን እድሉን ላመቻችላት ይገባል..አዎ ስመጣ እንደዛ ብዬ  እና እንደዛ ወስኜ ነበር …

‹‹ከዛስ….?››

‹‹ከደረስኩ ኋላማ … ቆይ ዛሬ ስል …ቆይ ትንሽ ልሰንብት ስል ..የመኖር ጉጉቴ ቀስ በቀስ ከሞተበት  እያንሰራራ እና እየተቀሰቀሰ መጣ..ምንም አግኝቼ አልነበረም ..ከእናቴ የማገኘው ተንሰፍሳፊ ፍቅር  እና ከጓደኞቼ የማገኘው ማፃናኛ …››

‹‹በጣም አሪፍ ታሪክ ነው ያለህ››
‹‹አዎ መራር የህይወት ገጠመኞች  ለሰሚው ወይም ለፅሀፊው ሳቢ ታሪክ ይወጣቸዋል…››

‹‹ከዛስ እንዴት ሀሳብህምን ሙሉ በሙሉ ልትቀይር ቻልክ….?››
‹‹አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተውኩትም…አሁንም  የመሞት እቅዴ በውስጤ አለ…››

‹‹እሺ እንዴት ልታራዝመው ቻልክ….?››ጥያቄውን አስተካከለችለት፡፡

‹‹እንዴት መሰለሽ….ከዛ ከሰው ሀገር  በገንዘብም በመንፈስም ክስርስር ብዬ የመጣሁ ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ሚስኪን የልጅነት ጓደኞቼ  አዋጥተው አሁን የምጠቀምባትን ላዳ ገዝተው ሰጡኝ..በቃ የመሞት ሀሳቤን አራዘምኩት ..ለራሴ ሁለተኛ እድል ሰጠሁት..ቢያንስ ለጊዜው ሰርቼ ስጋዬን የማኖርበትን  ካገኘሁ አንድ ቀን ምን አልባት ሁለተኛውን የህይወት ምኞቴን በሆነ ተአምር ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል…ብዬ ተስፋ አደረኩና መጨረሻውን እስከማይ ሁለት ዓመት ተኩል በሀገሬ ኖርኩ..ዘና ብዬ ለማንም ለምንም ሳልጨነቅ…ባሳኘኝ ሰዓት እየሰራሁ ሲያሰኘኝ ደግሞ እየተኛው..የእናቴን ሽሮ እየበላሁ ተስፋዬን በመጠበቅ እንሆ አለሁልሽ››

‹‹ምንድነው ተስፋህ..ማለቴ ይሳከልኛል ብለህ የምትጠብቀው….?››

‹‹የልጅነት ፍቅሬን… ..አንድ ቀን ቀና ብላ ታየኛለች የሚል ተስፋ..አንድ ቀን ከቄስ ትምህርት ቤት ጀምሮ እንደማፋቅራት እና ዕድሜዬን ሙሉ በልቤ ተሸክሜያት ስዞር እንደኖርኩ  ተረድታ በእቅፎ ታስገባኛለች ብዬ ተስፋ  በማድረግ..አንድ ቀን እጄ ትገባለች በሚል ተስፋ…..››

‹‹ወየው ጉዴ!!›አለኝች በውስጧ፡ በዚህ ቅርብ ጊዜ ውስጥ የምትቀርባቸውና የምትመኛቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት እንዴት ሆኖና  ምንስ በሚሉት አጋጣሚ   እንደዚህ በፍቅር ስክር ያሉና የታወሩ ሆነው እንደሚገኙ ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም...?‹‹ይሄኛውንስ ዛሬ አልምረውም…በፍጽም፡፡››ስትል ፎከረችው፡፡

‹‹ይቅርታ ሙሉ ታሪኩን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ….››

‹‹እየነገርኩሽ እኮ ነው …እየተረተርኩልሽ…..ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አይደል የሚባለው››

‹‹አይ እዚህ አይደለም…እኔ ቤት እንሂድና ተረጋግተን እየጠጣን ታወራልኛለህ….አሁን ሆቴሉም ሊዘጋ መሰለኝ››

‹‹ይቻላል››ይከራከረኛል  ወይም ይቃወመኛል ብላ ነበር የጠበቀችው ..ቀድሟት ተነሳ ..ሂሳብ ከፍላ ተከተለችው …. እየተወለጋገድና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ላደው ድረስ ሄድ ..ሹፌሩ ተቀብሏቸው እቤት ድረስ አደረሳቸውና የለሊቱን ግዳጅ ጨረሶ  ተለያቸው.. 
እሷም ዛሬ ለዛውም ከመሸ ያወቀችውን ባለ ላዳ ይዛው  ወደቤቷ ገባች…..

ይቀጥላል

#YouTube ቻናሌን አ.ረ.ረ..ረ!!!subscribe እያደረጋቹ😔
👇
https://www.youtube.com/@atronose

#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://tttttt.me/atronosee

Follow my channel on WhatsApp 👇👇

https://whatsapp.com/channel/0029VaDdoKaJENxsTyh8E43Z
👍12111🤔7🔥3😁2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ  አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..

‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››

‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል

‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››

‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ  ነበር ያቆምኩት….?››

‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››

‹‹አዎ….አይገርምሽም …

እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››

‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››

‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..

‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ  አይነት በሽታ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››

‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ  በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና  የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን   .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››

‹‹ይገርማል!!››

‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር  የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ  ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር  ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››

‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት

‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ   ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር  የተነሳ….››

አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ

‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ  አብሬት በምማርበት  በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ  በስደትም እያለው እንደዛ ነበር  እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ  ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ  ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት  ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት  ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ  ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን   ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ  ሰላምታ  ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን  እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››

‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር  ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ  እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት  ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››

‹‹ምን ተከሰተ….?››

‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ   ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ  አቁሜ እኔም ላዳዬ  ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ  የእብድ ድርጊት መስሎኝ  በርግጌ ተነሳሁና  አንገቴን በመስኮት አስግጌ  ወደ ኃላው ተመለከተኩ…

‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››

‹‹ክፈትልኝ››

‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..

‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ  …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና  ነደሁት

‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት

‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት

-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው  የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››

‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ  ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ  አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም  ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡ 
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና  ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡
👍858😁2👏1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

‹‹ከተለየኋት በኋላ ስለእሷ ማሰብ ላቆም አልቻልኩም ነበር..እንዴት አድርጌ ከዚህ ሀዘን ላወጣት  እችላለሁ….?እንዴት አድርጌ ላግዛት እችላለሁ….? የግድ አባቷ እስኪመጡ መጠበቅ የለብኝም..አባቷ ስል አባቷ ብቻ አይደሉም እናቷም ጭምር.. ጓደኛዋም ጭምር እንደሆኑ መላ ሰፈሩ ያውቃል..ብቻቸውን ነው ያሳደጎት….እድሜ ልኳን ከአባቷ ተለይታ ኖራ አታውቅም..ይሄንን ማንም ያውቃል…ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ደርሷት መለያየት ግድ በሆነበት ጊዜ እንኳን  እሷ ከአንተ ተለይቼ መሄድ ስለማልችል ትቼዋለሁ ስትል..አባቷም እውነትሽን ነው አንቺ ትምህርትሽን ከምትተይ እኔ አብሬሽ ሄዳለሁ በማለት…ስራቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር በመቀየር አብረዋት ዘምተዋል…ይህ ሀገር የሚያውቀው ሀቅ ነው……..አሁን አባቷ ለጉዳይ ወደውጭ ሀገር እንደሄዱ ነግራኛለች….ስጨነቅ አንግቼ  በማግስቱ ያለውን ቀንም በተመሳሳይ መሸበር አሳለፍኩ

…..ግን……?››

ድንገት ንግሩን አቋረጥኩትና ‹‹አልደከመህም መኝታ ቤት ሄደን አልጋ ላይ አረፍ ብለን የቀረውን ትጨርስልኝ….?››አለችው  

‹‹በቀላሉ  ያልቃል ብለሽ ነው….?››

‹‹እንሞክረው….?››

ደስ እንዳሽ ብሎ ብርጭቆውን ይዞ ተነሳ.. ቀድማው ወደመኝታ ቤት አመራች፤ እየተንጋዳገደ ከኃላ ተከተላት….የእሱና የሰላም የፍቅር ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእሷ እና የእሱንም መጨረሻ እንዴት እንደሚጠናቃቅ ማወቅ አጓጓት
///

መኝታ ቤት ገብተው አልጋ ላይ ጎን ለጎን ትራስ በመደገፍ ጋደም ብለው ከተመቻቹ በኃላ ወሬውን ካቆሙበት ቀጠሉ፡፡

‹‹እና እንደነገርኩሽ በእሷ ጉዳይ ስጨነቅ አድሬ ስጨነቅ ውዬ …ከእንደገና መልሼ መጥፎ ለሊት ካሳለፍኩ በኃ
ኋላ ዛሬ ጥዋት ስልኬ ጠራ …አነሳሁት‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ››

‹‹ማን ልበል….?››ስል ጠየቅኩ፡፡

‹‹ትናንት ማታ ያደረስከኝ ልጅ ነኝ..ቁጥርህን ከተውክልኝ ካርድ ላይ አግኝቼው  ነው››አለቺኝ.…

እንደዛ በፍጥነት ትደውልልኛለች ብዬ አላሳብኩም ነበር..ትናንትና ስልክ ቁጥሬን ፅፌ ትቼላት ሰወጣ ለምን አልባቱ ብዬ ነበር..ምን አልባት በዛ ስካር ውስጥ  ሆና የሰጠኋትን ወረቀት ቀዳዳም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ልትጥለው ትችላላች የሚልም ግምት ነበርኝ..እና ደወለችልኝ ..ለዛውም ገና በጥዋት4 ሰዓት…እንደደረስኩ መኪናዬን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳሁ…ከፈተችልኝ….

‹‹እሺ ደህና ነሽ ግን….?››
ጥያቄዬን ችላ ብላ ‹‹አሁን እየጠበቅኩህ ነው ና››አለችኝ 

‹‹አቤት….?››አልኳት ይበልጥ እንድታብራራልኝ ፈልጌ 
እሷ እቴ ስልኩን  ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችው

‹‹ይህቺ ልጅ ጤናም የላትም እንዴ . ….?.››አልኩና የላዳዬን ሞተር በማስነሳት ወደቤቷ ተፈተለኩ..እንዴ እሷ ና ብላኝ እንዴት እዘገያለሁ….?፡፡ 

‹‹ታዲያ እቤት ስትሄድ አገኘሀት….?››ኬድሮን ነች የጠየቀችው በእጇ ከያዘችው ብርጭቆ መጠጥ አንዴ እየተጎነጨች
‹‹አዎ ..እንደደረስኩ መኪናዋን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳው…እራሷ ከፈተችልኝ….ጉስቁልናዋ እንዳለ ነበር..ስልችት ብሏታል…የሆነ ልቧን ስብብርብረ ያደረገው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ..እንደውም የፍቅር ነገር ይመስለኛል….››

‹‹እሺ ማን ነበረ ስምህ….?›› አለችኝ ግድ የለሽ እና አናዳጅ በሆነ የድምጽ ቅላፄ….አይገርምሽም ዕድሜሽን ሙሉ ያመለክሽው ልጅ… ስንት ቀን እና ሌት የናፈቃሽው እና በትዝታው የተሰቃየሽለት ልጅ -ማን ነበር ስምሽ ሲልሽ…..….?

በውስጥሽ  የሚፈጥረው ስሜት ግማሽ ህልውናሽ  የመደምሰስ አይነት ነው …..እመኚኝ በጣም ነው የሚያመው …እሷ ግን ለእኔ የስሜት መጎዳት ቁብ ሳይኖራት፤.መልሴንም ለመስማት ትግስት አጥታ ወደትዕዛዞ ተሸጋገረች

‹‹ካላስቸገርኩህ የሆነ ቦታ ትወስደኛለህ…….?››

‹‹የፈለግሺው ባታ …ተዘጋጂና ነይ መኪና ውስጥ እጠብቅሻለሁ››ብዬ ወደላዳዬ ፊቴን አዞርኩ‹‹አይ ላዳህን ወደግቢው አስገባት እና አቁማት.. በእኔ መኪና ነው የምንሄደው፤ ከከተማ ወጣ ማለት ነው የፈለግኩት…..››አለቺኝ፡
ግራ ግብት እንዳለኝ ወደኃላዬ ተመለስኩና ላዳዬ ውስጥ ስገባ እሷ ደግሞ የውጩን በራፍ ከፈተችልኝ…ወደ ጊቢ ውሰጥ አስገባኋትና ሚጢጢ ላዳዬን  ግዙፍ የእሷ ላንድኩሩዘር መኪና ጎን አቆምኳትና ሞተሩን አጥፍቼ ወጣሁ… በሩን ዘግቼ ቆምኩ..
‹‹እሷ ወደሳሎን ተመልሳ እየገባች ነበር…ደግሞ የሰውነቷ ቅርፅ ከቁመቷ ጋር ያለው ምጣኔ እንዴት አባቱ ያምር ነበር መሰለሽ…..5 ደቂቃ ሳትቆይ ተመልሳ ወጣችና የሳሎኑን በራፍ መቆለፍ ጀመረች ….በእጇ ካንጠለጠለችው ቦርሳ በስተቀር ምንም  የያዘችውም ሆነ የቀየረችው ነገር አልነበረም… እንደነበረችው ነው ተመልሳ የመጣችው..ዝንጥንጥ ብላ የምትመጣ መስሎኝ ነበር..ግን በለበሰችው ቱታ ሱሪ እና ቲሸረት ነው አሁንም ያለችው..ስሬ እንደደረሰች ከቦርሳዋ ውስጥ ቁልፍ አወጣችና ወረወረችልኝ …በአየር ላይ ቀለብኩና ወደመኪናዋ ተንቀሳቀስኩ…..ሞተሩን እስነስቼ ከግቢሁ ከወጣሁ በኋላ አቁሜ ጠበቅኳት… የውጩውን በራፍ  በመዝጋት እና በመቆለፍ መጣችና ጋቢና  በመግባት ከጎኔ ትቀመጣለች ብዬ ስጠብቅ  የኃላውን በራፍ ከፍታ ገባች……››

‹‹ምነው እዚህ አይሻልሽም….?›› ልላት ነበር ..ግን አንደበቴን ማላቀቅ አልቻልኩም…በእስፖኪዬ ወደኃላ ተመለከትኳት ….ግማሽ እሷነቷ ሞቶ ግማሽ እሷነቷ ብቻ በህይወት እና በሞት መካከል ያለ ይመስላል..ልክ እኔ  ለመሞት ወደሀገሬ ልግባ ብዬ በወሰንኩበት በዛ ጭለማ ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔታ አስታወሰችኝ ….

‹‹ሰላም ወዴት ነው የምንሄደው..….?››ብዬ ጠየቅኳት

‹‹አቤት›› አለችኝ እንደመባነን ብላ
‹‹ወዴት ልንዳው ነው ያልኩሽ….?››

‹‹ወደ ፈለከው…. ግን ከከተማ ውጭ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይሁን እንጂ ወደየትም ይሁን …..››
‹‹እሺ››
‹‹ግን ስሜን መቼ ነው የነገርኩህ….….?ሰላም ብለህ የጠራህኝ መሰለኝ….?››

‹‹ነግረሺኝ አይደለም…››

‹‹እና እንዴት  አወቅከው…..….?››

‹‹አውቄውም አይደለም…ሰላም ማለት ለእድሜ ልኬ ያፈቀርኳት..አሁንም ድረስ የማፈቅራት ከህጻንነቴ ጀምሮ የማውቃት ፤መቼም ልረሳት የማልችላት  ልጅ ስም ነው…እና ያው ፍቅሯ ጅል አደርርጎኛል መሰለኝ ብዙ ሴቶችን ሰላም ብዬ መጥራት እወዳለሁ…››አልኳት….ሽሙጤ ሳይገባት….ፈገግ አለችና‹‹ ይገርማል እንደአጋጣሚ የእኔም ስም ሰላም ነው››አለችኝ 

‹‹አውቃለሁ››

‹‹ማለት›….?›››መልሶ  ግር ብሏት

‹‹በመልክም በጣም ትመሳሰላላችሁ ልልሽ ፈልጌ ነው››
ዝም አለች….በጦር ኃይሎች አድርገን በ18 ማዞሪያ ታጥፈን በአንቦ መስመር አሸዋ ሜዳን አቆርጠን ወደቡራዬ ተጓዝን…እሷ እውነትም እንዳለችው ወደየትም ብነዳው ግድ ያላት አትመስልም ነበር..አይኗን በመኪናው መስታወት ወደውጭ ልካ በየመንገዱ ዳር ያለውን ትዕይንት ምታይ ትመስላለች ….ግን አታይም እሳቤዋም እይታዋም ከውስጧ ጋር እንደሆነ ያስታውቃል…ብራዩንም አለፍን ፣እኔም አላቆምኩም እሷም አቁም አላለችኝ…ግን ጊንጪ ልንደርስ ኪሎ ሜትሮች ሲቀረን  የሆነ ለጥ ያለ ሜዳ ጋር ስንደርስ…..‹‹ይቅርታ ማን ነበር ስምህ...….?››ስትል ከሳዕታት ዝምታ በኃላ አብሻቂ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀችኝ….
👍936
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹አዎ…እናቴ እና ሰላም ያልኩሽ የማፈቅራት ልጅ ትዝ ሲሉኝ››
-‹‹በዛ ሰዓት ላይ ሁለቱም ባይኖሩ ኖሮ…..መቼም እንዳማታገኛቸው እርግጠኛ ሆነህ ቢሆን ኖሮስ….?››ዘግናኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ

‹‹እኔ እንጃ…እንዳልሞት የሚያደርገኝ ምንም ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም››ስል በታማኝነት መለስኩላት፡፡

‹‹ለምን….?››ጠየቀችኝ
‹‹ሁለቱ መላ አለሜ ናቸው…እነዚህ የነገርኩሽ ሁለቱ ሴቶች እና ሌላው ዓለም እኔንም ጨምሮ በሌላ ሚዛን ቢሆን ሚዛን ሚደፉት እነሱ ናቸው…..ስለዚህ እነሱ  የሌሉበት  ዓለም ምን ይረባኛል…››

‹‹አየህ ትክክል ብለሀል..እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ አንተ አንደገለጽከው ነው…እስከአሁን እራሱ ለምን እንደቆየሁ አላውቅም…….?››ብላ የሆነ አዲስ ነገር እንደተገለጽላት ተመራማሪ  ፈገግ ብላ ከተቀመጠችበት  ተነሳች ‹‹ እንሂድ ›› ብላ ጠርሙሷን ይዛ ምንጣፉን ባለበት ጥለ መራመድ ጀመረች…

-‹‹እንዴ ወዴት….? ››

‹‹ወደቤት ….ወደቤት መልሰኝ››

ደነገጥኩ…. ሳላስበው የማይሆን ነገር እንደተናገርኩ ገባኝ…ገደል አፋፍ ላይ ያለን ሰው ከኃላ መግፋት አይነት የቀሺም ሰው ተግባር ነው የሰራሁት..

‹‹ምንጣፉስ..››

ግዴለሽ በሆነ የድምፅ ቃና‹‹ከፈለከው ያዘው›› አለችኝ፡፡ጠቅለል ጠቅለል አደረኩና ወስጄ ኮፈን ውስጥ ከተትኩት፡፡ከዛ ወደመኪናው ገባሁና ወደኃላ አዙሬ የመልስ ጉዞ ….ብራዩ እንደደረስን የሆነ ነገር ማድረግና አሁን ካለችበት ስሜት እንድትዘናጋ ማድረግ እንዳለብኝ   ወሰንኩ…

‹‹..በጣም አመመኝ..››አልኳት …ቀና ብላ አየችኝና ምንም ሳትናገር መልሳ ወደ ሃሳቧ ተመለሰች…..መኪናዋን ወደዳር አውጥቼ አቆምኩ

‹‹ምነው….?››ኮስተር ብላ

‹‹ሆዴን ቆረጠኝ ››

‹‹ማለት….?››

‹‹እኔ እንጃ እራበኝ መሰለኝ..ከነጋ ምንም አልቀመስኩም… ለዛ ይሆናል..ረሀብ ደግሞ አልችልም››

‹‹እና ምን ይሻላል ….?››አለች እንደመበሳጨት ብላ

‹‹በቃ እኔ ሳልበላ መንዳት አልችልም….››

‹‹እሺ ጥሩ  ቁልፉን ስጠኝ…. እኔ ጊዜ ማባከን አልፈልግም …አንተ ብላና በትራንስፖርት ና››የሚል ሀሳብ አቀረበች

‹‹ለምን የሚሆን ጊዜ ነው ማባካን የማትፈልጊው….?››ስል ጠየቅኳት፡፡

‹‹እቤት ተመልሼ በፍጥነት ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ››

‹‹እሺ ነይ…አልኩና ቁልፉን ነቅዬ ከመኪናው ወረድኩ.. እሷም ካለችበተ የኋላ ወንበር ወርዳ ወደጋቢናው ስታመራ ፈጠን ብዬ ሁሉንም በር ጠረቀምኩትና ቁልፍን እያንቀጫጨልኩ   በአካባቢው ወደአለ ሆቴል ጉዞ ጀመርኩ

‹‹ምን እያደረክ ነው….?››

‹‹ምሳ በልቼ እቤትሽ አደርስሻለሁ..አንቺ ስለጠጣሽ መንዳት አትችይም…››

‹‹ምኑ ነህ..….?አሁን ለአንድ ቀን ባትበላ አትሞት…ደግሞ ብትሞትስ ከመኖር ምን ሲገኝ…››

‹‹ግድ የለም.. ልብላና አብሬሽ እሞታለሁ››

‹‹መቀለድህ  ነው..….?››ተከተለችኝና ከፊት ለፊቴ ወንበር ስባ ተቀመጠች…ምግብ አዘዝኩ እስኪመጣ ወሬ ጀመርን 
‹‹በነገራችን ላይ አባትሽን በቅርብ አይቼው አላውቅም..?››

‹‹የለም››

‹‹የት ሄዱ….?››

‹‹ወደ ውጭ ሄዷል››

‹‹አሀ …ለዛ ነዋ እንዲህ ዓለም ድብልቅልቅ ያለችብሽ….?››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ….?››

‹‹በአባትሽ እና በአንቺ መካከል ያለውን ግንኙነት እና ቀረቤታ እኮ ሙሉ ሰፈሩ ነው የሚያውቀው.. እንኳን እኔ ቀርቶ የዛሬ አመት እዛ ሰፍር የገባ ሰው ሳይቀር ያውቃል…››

‹‹አንዴ አንተም እኛ ሰፈር በቅርብ የገባህ መስሎኝ….  ባልሳሳት ሁለት  አመት ..ከዛ ይበልጥሀል..?››

‹‹የእውነትሽን ነው..አታውቂኝም….?›› በእድሜዬ  ከደነገጥኩት በበለጠ መጠን ደንግጬና ተሸማቅቄ ጠየኳት

‹‹ማለት አንተ ታውቀኛለህ እንዴ….?››

……የምመልሰው ነገር ሲጠፋኝ  ሳቅኩ

‹‹የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ እንዴ…››

‹‹አይ ታውቀኛለህ ስትይ ገርሞኝ ነው….ራስህን ታውቃለህ ወይ ብለሽ ብትጠይቂኝ ይሻላል..ግንባርሽ ላይ ያለውን ስንጥቅ ጠባሳ ምን እንደሆነ ልንገርሽ…….?››

‹‹እንዴት ልትነግረኝ ትችላለህ..….?

እሱ እኮ እፃን ሆኜ የሆነ ነገር ነው››

‹‹አዎ ቄስ ትምህርት ቤት አባ ገብረክርስቶስ ጋር ስንማር ድብብቆሽ በምንጫወትበት ጊዜ ልትደበቂ ስትሮጪ  አደናቅፎች ወድቀሽ ብረት ግንባርሽን ሰንጥቆሽ አይደል…?››

አይኖቾ ፈጠጡ ‹‹እንዴ !!!አዎ ትክክል ነህ ..ማነህ አንተ….?..››

‹‹ኤርሚያስ››

‹‹ኤርሚያስ ..ኤርሚያስ እንዴ ኤርሚያስ ካሳ እንዳትሆን……….?››የሆነ የቆየ ህልም የማስታወስ ያህል ተደንቃ

‹‹አዎ ነኝ››

‹‹ታዲያ በጣም እኮ ነው የተቀያየርከው…አረጀህ… በጣም…ደግሞ ከሀገር  ወጥተህ አልነበር…..….?››

‹‹ኦዋ ሁለት  ዓመት አለፈኝ  ተመልሼ   ከመጣሁ..››

‹‹እና ይሄን ሁሉ ጊዜ   ሳታናግረኝ…….?››

‹‹እኔ እንጃ እንደመጣው ጥሩ ስሜት ላይ ስላልነበርኩ ላናግርሽ ጉልበቱ አልነበረኝም….››

‹‹ትክክል አልሰራህም…ጓደኛች ነበርን አይደል….….?.››መገረሟ ሳይገታ የታዘዘው ምግብ መጣ..እሷ ለምግቡ  ደንታም ሳይሰጣት ብላክ ሌብል ታመጣልኝ አለችው አስተናጋጁን….

‹‹አይቻልም..››አልኳት ቆፈጠን ብዬ
‹‹ለምን…….?ዝም በለውና አምጣልኝ ››አምጣላት …ግን ከበላሽ ነው የምትጠጪው..

‹‹አረ ባክህ ››

‹‹እውነቴን ነው››

‹‹እሺ ..››አለች.. እየቆነጠረች ከምግቡ ለመቅመስ ሞከረች እኔ እየለመንኩም እያስገደድኩም አንድ ሶስት ደህና ጉርሻ አጎረስኳት…
ከዛ መጠጧን ጀመረች ‹‹….ይገርማል  ..ዱርዬ ነበርክ እኮ …አሁን የተለየ እና የተረጋጋ ሰው ሆነሀል››

‹‹ምን ታደርጊዋለሽ ህይወት ትገራሻለች… ኑሮ ይሞርድሻል…መከራ ያስተካክልሻል ወይም ያበላሽሻል፡፡››

‹‹ለምን አንተም አትጠጣም….?››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን መኪናውን ማን ይነዳል…….?››

‹‹ግድ የለም ..የሆነ መላ እንፈልጋለን..….?››ልክ ቅድም ላንቺ ታዝዤ አብሬሽ መጠጣት እንደጀመርኩ ..ለእሷም ተስማምቼ አዘዝኩ …የልጅነት ነገር ምንም ሳይነሳ የቀረ ትውስታ የለም..ከማስበው በላይ ስለልጅነታችን ታስታውሳለች…ያ ደግሞ ደስታ ፈጠረብኝ….እሷም ከነበረችበት ስሜት በሆነ ጠብታ ቢሆንም የመረጋጋት ሁኔታ  ታየባት
ተመልሰን ቅድም ለቀነው ወደወጣነው ቤት የሄድን
 
‹‹እየተቆነጠረ የሚመጣው ውስኪ ሊያረካን ስላልቻለ..ሙሉውን አዘዝን…››

ኬድሮን ቆይ ቆይ ..››ብላ አስቋመችው 

‹‹ምነው ደከመሽ..እንተኛ?››

‹‹አይ አንዴ ሽንቴን….›› አለችና ከመኝታዋ ወርዳ ወደሽንት ቤት ሳይሆን ወደሳሎን ሄደች….ይህቺ ታሪኳ ለሊቱን ሙሉ የተነገረላት  ፍቅረኛው የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እየተሰማት ነው ..አዎ ስሜቷ እየነገራት ነው….ለዚህ ነው ወደሳሎን የሄደችው …ንስሯን ፈልጋ..‹‹አይ የኔ ነገር ..››አለች . የዚህ ባለ ላዳ ታሪክ ንስሯንም እንድትዘናጋ ስላደረጋት እራሷን ታዘበች…ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት እንዳለ ተኝቷል….አስነሳችው….‹‹ ‹‹አብሮኝ ያለው ልጅ ፍቅረኛ..ማለቴ የሚወዳት ልጅ ችግር ላይ ትመስለኛለች..አሁኑኑ ሄደህ ያለችበትን ሁኔታ አጣራልኝና  ና…አሁኑኑ……ትንሽ ከዘገየን የሚረፍድብን ይመስለኛ…››
👍839😁4👎2
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››
👍12010🥰1👏1🎉1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን  አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ

‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››

ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››

‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››

ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ

ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት  ጥያቄ  ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና  ሳይጠይቃት መለሰችለት….

‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››

‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት

‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን  አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››

‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ  ነበር የቀራት….. 

እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች   ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው

‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡

‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››

‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን  ለቆ ወጣ……

‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች

….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን  የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና  ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////

ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ  ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን  እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››

‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ›› 

‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››

‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››

‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››

‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››

‹‹ወዴት....?››

‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››

‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››

ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››

‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››

‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ  ሰውና በ20  ደቂቃ  ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው

‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››

‹‹እራስህንማ  እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››

‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት  ኮስተር ብሎ

‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››

‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ  ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ  ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››

‹‹ከዛ ምን…..?››

‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››

‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››

‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››

‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ  በመግባት  እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ  ጉብ አለ….

ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..

‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›

‹‹የማታው ንስር አይደል..?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ምን ይሰራል  እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››

‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››

‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት  

‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››

‹‹እኔና ንስሬ››

ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››

‹‹የምሬን ነው…›

‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን  ማወቅ አልቻልኩም››
👍11015😁4👏2😱2👎1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››
👍8910🥰3👎1🔥1😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››

‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት

‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም  ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ

‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ  ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት

ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…

‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››

‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››

‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››

‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ 

ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ  በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ  ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››

‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ

‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን  ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››

‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?›› 

‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም  ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…

መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ  እያመሩ ሳለ…

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት

‹‹ያው ላንተ ስል ነው››

‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን  እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››

‹‹ለምን…?››

‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››

‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››

‹‹ምን ለመሆን…?››

‹‹ለመብረር…››

‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››

‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….

እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….

‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››

‹‹ምንም ››

‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ  ግን ቅር አሰኝቶኛል››

‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››

‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////

የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…

ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም..  የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ  ተክል   ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡

‹‹አትመጪም…  ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…

‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ  አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ  እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››

‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡

የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…

‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››

‹‹ውሀ ››

‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል

‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››

‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡

‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር  ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ  እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች  ናቸው…››

‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››

‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና  እንከን አልባ  ስፍራ  ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው  ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን  እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን  ነው፡፡
👍918👏4😢4🔥2🥰2🤔1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር  ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…

አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች   …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን  ኖሮ ይሄን  ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ  ጎረምሳ አግብቼ  መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ  ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና  ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት  ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን  እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡

ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ   ላይ ያለ አሉ  በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ። 
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ  ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት  ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…

….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት… 

ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡

ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ  የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል  ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡
👍7010😢2😁1🤔1
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ታዲዬስ የፅዮንን ቀኝ እጇን እንደጨበጠ በቀስታ ደረጃውን ይዟት እየወጣ 1ኛ ፎቅ ላይ ወደተከራየው መኝታ ክፍሉ ወሰዳት….፡፡

‹‹የሚያምር ክፍል ነው >>አለችው ወደ ውስጥ መግባቷን ካረጋገጠች በኃላ::

‹‹የእኔ አይደለም የባለ ሆቴሎቹ ነው፡፡››

‹‹አውቃለሁ....ሁለት አልጋ ያለው ክፍል መከራየትህን ወድጄልሀለሁ.››

‹‹.ተሳስተሸል ....ባለ አንድ አልጋ ነው››አላት እየሳቀባት፡፡

‹‹አታይም ብለህ ትሸውደኛለህ እንዴ?››

‹‹ግን እንዴት ልታውቂ ቻልሽ..?ቅድም ነግሬሻለሁ ማለት ነው?››

‹‹አልነገርከኝም…ግን ክፍሉ በጣም ሰፊ ነው ... በዚህ ስፋት ደግሞ አንድ አልጋ ብቻ አይዘረጋም፡፡››

‹‹ስፋትን በሽታ መለየት ትችያለሽ ማለት ነው?››

‹‹ኖኖ.. በጆሮዬ ነው::››

‹‹አድናቂሽ ነኝ፡፡››

‹‹አመሰግናለሁ››አለችው እየፈገገች፡፡

‹‹እንደቆምሽ እኮ ነሽ ....ቁጭ በይ እንጂ››በዳበሳ ወደ አልጋው ተጠጋችና ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹የምትፈልጊው ነገር አለ ወይስ እንተኛ?››

‹‹ኧረ ምንም አልፈልግም እንተኛ ....እኩለ ለሊት እኮ ሆኗል....ለሁለተኛ ቀን ካንተ ጋር ለመተኛት በጣም ጓጉቼያለሁ፡፡››

‹‹ተይ እንደባለፈው ዝም ብሎኝ እየተቃጠለ ይተኛል ብለሽ አስበሽ ከሆነ ካሁኑ ላስጠንቅቅሽ፡፡››

‹‹ባክህ አታደርገውም …እንደዛ ሰክረህ ያልተሳሳትክ ዛሬ በሰላሙ? >>

‹‹ስካር እኮ ማሳበቢያ ነች..እኔ ሰው ይሄንን ስህተት የሰራውት ሰክሬ ነው፣ከሰው የተደባደብኩት ሰክሬ ነው፣እንትናን የደፈርኩት ሰክሬ ስለነበር ነው፣ካለ ኮንደም የወጣውለት ሰክሬ ነው..ወዘተ ሲባል አያሳምነኝም፡፡ያ ሰው መጀመሪያውኑ ለእነዛ ነገሮች የተመቻቸ ስነ- ልቦና ያለው ሰው ቢሆን እንጂ በመጠጥ ብቻ ለወንጀል የሚዳረግ ሰው መኖሩን እጠራጠራለሁ.. እርግጥ መጠጥ ሲበዛ ብርታት ይሰጠው ይሆናል እንጂ ለስህተት ማቅለያ በቂ ምክንያት ሆኖ አይታየኝም....የእውነት ሆኖ እንኳን ስካር ለዛን ያህል ተፅዕኖ የሚያጋልጠው ከሆነ.... ያ ሰው መጠጥ በዞረበት መዞር የለበትም የሚል አቋም አለኝ፡፡

‹‹ስለዚህ እኔ በራሴ እተማመናለሁ… ንክችም አላደርግሽ እያልከኝ ነው?››አለችው፡፡

‹‹አልወጣኝም..እኔ ያልኩት ምናልባት የማደርገው ከሆነ ቀድሞውኑም ለማድረግ
ዕቅድና ፍላጎት ስላለኝ እንጂ ስለጠጣሁና
lስላልጠጣሁ አይደለም እያልኩሽ ነው፡፡›› አላትና ከተቀመጠበት ተነስቶ በቁሙ ልብሱን ማወላለቅ
ጀመረ…ጨረሰ፡፡ወደ እሷ ቀረበና ከላይ የለበሰችውን ሻርፕ አንስቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ቀጥሎ የለበሳችውን ቲሸርት

ጠርዙን ይዞ ወደ ላይ ሳበው..በጭንቅላቷ

ተሞሽልቆ ሲወልቅ ሀር መሳይ ሉጫ ፀጉሯን ብትን ብሎ አየሩን ሞላው ..እጇን ይዞ አቆማት፤በዝምታ ቆመችለት፤የለበሰችውን
ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ ለማውለቅ መጀመሪያ ቀበቶውን ፈታ፣ቀጥሎ ቁልፉን አላቀቀ፣ዚፑን ቁልቁል አንሸራተተው፣ከዛ ወደታች ጎተተው...ሮዝ ፓንት ላይዋ ላይ ቀረ ..ወደ ላይ ተመለሰና
ጡት ማስያዣዋንም አወለቀላት::

‹‹..አሁን ወደ አልጋው መሄድ እንችላለን?››አላት፡፡

<< በነካ እጅህ ጨርሰው እንጂ?››

‹‹ፓንቱንም..?››

‹‹አዎ ምነው አንተ አላወለቅክም እንዴ? ››ብላ እጇን ወደእሱ ስትዘረጋ ሳታስበው እንደ ብረት የተገተረ ለስላሳ እርቃን ብልቱ አፈፍ አደረገች፡፡

‹‹አንተ ምነው እንዲህ እንደ ሚሳዬል ተቀሰረ..እውነትም ዛሬ ጉዴ ፈልቷል፡፡›› ብላ ወደ
እሱ ልጥፍ አለችበትና ከንፈሯን ወደ ከንፈሩ አስጠግታ ትንፋሿን ለቀቀችበት..ታዲዬስም
ጭምቅ አድርጐ አቀፋትና ከንፈሮቿን ዋጣቸው... ያለማቋረጥ በረረረረረረጅሙ
ከንፈሯን እየመጠጠ እጆቹን ወደታች አወረደና በኃላ በኩል ፓንቷ ውስጥ ሰቅስቆ አስገብቶ

ከወንዝ ወዲህ ማዶ እና ከወንዝ ወዲያ ማዶ በትይዩ መስመር ጉብ ያሉ ተራሮች የሚመስሉትን መቀመጫዋን እስኪያማት
ጨመቃቸው.. የተጎረሰው ከንፈሯ ሳያግዳት አቃተተች... እሷም እጆቿን በጭንቅላቱ

በጀርባው እያሽከረከረች ትዳብሰውና ትታገለው
ጀመር…እንትኑ ግን እየወጋት ነው፤ደግሞ እንዴት
ነው ጥንካሬው….?አቤት መቀመጫዋን ጨመቅ
ለቀቅ መልሶ ደግሞ ጨመቅ ሲያደርግላት   የምታሰማው የደስታ መቃተት፤ፓንቷን ወደታች ሳበላት ልታግዘው እግሯን ወደ ላይ ሰቀለችለት ተራ በተራ ከእግሮቿ አሾልኮ አወጣውና እዛው ወለሉ ላይ ጣለው፡፡ እስከአሁን አልጋውን አልያዙም እደቆሙ ነው፡፡ወደራሱ በኃይል ሳባትና ከሰውነቱ ጋር አጣበቃት፤ሁለቱ የሚፈላለጉና የሚሳሳቡ ሸለቆና ጉብታ ሳይዋሀዱ ውጫዊ በሆነ ንክኪ ሲፋተጉ ጉብታው ላይ የበቀለው ችፍግ ያለ ደን ሸለቆ አካባቢ ያለውን ሜዳ ላይ አርፎ በሚያደርገው የፍትጊያ ንክኪ ፅዮንን ልዩ ስሜት ተሰማት… ስሜት ብቻ ሳይሆን ሸለቆውም በደስታ ምንጭ አፍልቆ አካባቢውን በፈሳሽ አረሰረሰው፡፡››

እንደምንም ከንፈሯን ከከንፈሩ አላቀቀችና‹የእኔ ጌታ በጣም ነው የማፈቅርህ ..በቃ አድርገው..

‹‹እርግጠኛ ነሽ?››አላት ይሄን ሁሉ መንገድ ከተጓዙ በኃላ እርግጠኛ ነሽ ብሎ መጠየቁ ለራሱም እየገረመው….፡፡

ከስር ሰቅስቆ ተሸከማትና አልጋው ላይ ዘረራት ..….ተከትሎ እግሮቿ መካከል ገባ...የጠነከረ ጉብታውን ሸለቆዋ ውስጥ ለመጨመር በራፍ አካባቢ ሲያሽከረክረው‹‹የእኔ ጌታ ፈራሁ..ታውቃለህ የመጀመሪያዬ እኮ ነው... ያ..መ..ኝ ይሆን?››ጠየቀችው፡፡

‹‹‹አይዞሽ አያምሽም ቀስ ብዬ…. አስታምሜ ነው፡፡››

‹‹እሺ እንደፈ..ለግክ...ግን የሀያ ስምንት አመት ድንግል ሴት በዚህ ዘመን አጋጥሞህ ያውቃል?››

‹‹እኔ አጋጥሞኝ አያውቅም.. ፡፡››እያለ በድርጊቱ ገፋበት፡፡
…እንደጠረጠረው ግን እየሆነለት አይደለም... በፊት ሲገምት ከንባብም ባገኘው መረጃ መሰረት ዕድሜ ከፍ እያለ ሲሄድ ድንግልና በራሱ ይወገዳል ወይም በጣም የመሳሳቱ ዕድል ሰፊ ነው የሚል ነበር..የፅዮን ግን ድፍን ነው..ቢለው ቢለው ከክርክሩ አልፎ ሊገባለት አልቻለም…፡፡

‹‹የእኔ ጌታ አመመኝ››አለችው ፅዬን ፡፡

‹‹እኔንም እያመመኝ ነው...ሳልላጥ አልቀረሁም... ሲወራ እንደሰማሁት ሊያቅተኝ ነው መሰለኝ፡፡››

‹‹ኧረ አያቅትህም የእኔ ጀግና ...ሰውነቴን ጨምድጄብህ ይሆናል... ይሄው ብላ እግሮቿን እስከ መጨረሻው በረጋግዳለት ዘና ለማለት ሙከራ አደረገች..እሱም በአዲስ መልኩ ወደ ውስጠቷ ለመጥለቅ እየተዘጋጀ ሳለ የመኝታ ቤቱ በራ ተንኳኳ..እንቅስቃሴውን አቋርጦ በገረሜታ አዳመጠ‹‹..በዚህ ለሊት ማነው የሚያንኳኳው?››

መንኳኳቱ ጠንከር እያለ መጣ‹‹ ...የእኔ ጌታ ተነስ ክፈት፡፡››

‹‹በዚህ ሰዓት ማን ነው..?ይቅርታ አጣርቼ ልምጣ፡፡››ብሏት ከጭኗ መካከል ወጣና ኮመዲኖው ላይ ያለውን ፎጣ አንስቶ በማገልደም ወደ በራፉ ሄዶ ከውስጥ የተሰካውን ቁልፍ አሽከርክሮ ከፈተና << ማነው?››ብሎ እይታውን ወደ ውጭ ሲወረውር ርብቃን ተገትራ አያት፡፡

በራፉን ሳያስብ ሙሉ በሙሉ በረገደውና ‹‹እንዴ !!ምን ሆንሽ..?ምን ተፈጠረ?›› ብሎ ወደ ውስጥ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘጋው፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አልሆንኩም ..መጀመሪያ የከፈትከውን ጭን ዝጋና እናወራለን ››አለችው አይኖቿን የፅዮን እርቃን ገላ ላይ ሰክታ፡፡

ተንደርድሮ ሄደና ከላይ ዕርቃኗን የተዘረጋጋችውን ፅዬንን አልጋ ልብሱን በአንድ በኩል ገለጠና አለበሳት…እሷም ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ ሳታሰማ ባለችበት ሁኔታ በዝምታ ያለምንም እንቅስቃሴ እንዳደረጋት ሆነችለት፡፡
👍797
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የዶ/ርን ስልክ እንደዘጋ ርብቃ ጋር ነው የደወለው<<መቼስ እሁድ ስለሆነ ቤት ትኖሪያለሽ ብዬ ነው?››

‹‹አዎ ቤት ነኝ ..እየመጣህ ነው እንዴ?››

‹‹አዎ ፈልጌሽ ነበር?››

<<ና አለውልህ››አለችው፡፡ ስልኩን ዘጋውና ታክሲ ውስጥ ገባ፡፡

ሲደርስ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ ጠበቀችው፤ በጣም የገረመው ያገኛት በህልሙ የመጣችበት ጊዜ የለበሰችውን ቀሚስ ለብሳ ነበር ፡፡

ከቁርስ በኃላ

‹‹አረፍ እንበል እንዴ? >> አለችው በአገጯ ወደ መኝታ ቤቷ እየጠቆመችው….፡፡

‹‹አይ እስቲ መጀመሪያ እዚሁ ሳሎን ሆነን እንነጋገር።

<<እንነጋገር?>>

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹እኔ እንጃ እኔና አንተ እንነጋገር ብለን ተነጋግረን አናውቅም ብዬ ነዋ ..እኔ እንነጋገር ሲሉኝ ይጨንቀኛል...፡፡ የሆነ ችግር..የሆነ የተበላሸ ነገር ያለ መስሎ ነው የሚሰማኝ…ይገርምሀል እናትና አባቴ ሁል ጊዜ እንነጋገር እንዳሉና በጠረጴዛ ዙሪያ እንደተቀመጡ ነው... ግን አንድም ቀን በመግባባት አጠናቀውት አያውቁም...እና ቃሉ ያስጠላኛል፡፡››

‹‹እና ካልፈለግሽ ልተወው?››

‹‹አይደለም ..ዝም ብለህ በፊት እንደምታደርገው ቀለል አድርገህ በጨዋታ መልክ አውራኝ ነው ያልኩህ››

‹‹እሺ›› አለ ፈገግ ብሎ‹‹…ባለፈው አንድ ጨዋታ በስልክ ጀምሬልሽ ነበር….ስለ እኔ እና ስለ ፅዮን››

‹‹አስታወስኩት….፡፡››

‹‹እንድንጋባ ትፈልጋለች፡፡››

‹‹በጣም አፍቅራሀለች ማለት ነው ?አደራ ግን እዳትጎዳት... አንተ በጣም ምርጥ ጓደኛ መሆን እንደምትችል እኔ ምስክር ነኝ ..ለእሷ ደግሞ ምርጥ ባል ለመሆን ሞክር፡፡››

‹‹እሞክራለሁ….ከዛ በፊት ግን አንቺ ብታገቢኝ ምን አለበት ብዬ ልጠይቅሽ ነበር የመጣሁት››

<<እኔ....? ጋብቻ>>

‹‹አዎ ጋብቻ...ካፈቀርሺኝ ማለቴ ነው?››

‹‹ስለማፈቅርህማ ነው የማላገባህ..አየህ ታዲ እኔ ስላንተ ምንም አይነት ቆሻሻ ትዝታ እንዲኖረኝ አልፈልግም..7 አመት ሙሉ ህይወቴን በፍቅር አጣፍጠህልኛል...አንተን በማግኘቴ በጣም እጅግ በጣም እድለኛ ሰው ነኝ... ወደ ጋብቻ ¶ይዤህ ገብቼ የሆነ ነገር ታስቀይመኝና ይሄንን ስለአንተ ስገነባ የኖርኩትን የፍቅር ሀውልቴን ታፈርስብኛለህ ብዬ እሰጋለሁ.. ስለዚህ ይቅርብኝ፡፡››

‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?››

‹‹አዎ ከዚህ በፊት አንተን ለማግባት ሁለት ሶስት ጊዜ አስቤ ነበር፤ቀድሜ ሁሉ ልጅ ልወልድልህ ፈልጌም ነበር፤ከዛ እንድታገባኝ ማለት ነው››

<<ሎጅ?>>

‹‹አዎ ልጅ ልወልድልህ ....ከዛ ላገባህ፡፡››

‹‹እና ሀሳብሽን ለምን ቀየርሽ?››

‹‹ተረጋግቼ ሳስበው የጅል ሴት ዘዴ ሆኖ አገኘሁት..አይህ ወንድ ልጅ እንዲያገባህ የተሳሳትክ መስለህ ማርገዝ ትክክለኛ ዘዴ አይደለም ፡፡ምን አልባት አፍሮ፣ይሉኝታ ይዞት፣አዘኔታ አንጀቱን አላውሶት..ወይም ለልጁ ካለው ፍቅር አንፃር በሁኔታዎች አስገዳጅነት ወደ ጋብቻ ተስማምቶ ሊገባ ይችል ይሆናል..ነገር ግን ቆየት ብሎ ጋብቻው ችግር ላይ መውደቁ አይቀርም፤አይደለም በሆነ ሰበብ አስገዳጅነት ይቅርና በፍፁማዊ ፍቀር እና በሙሉ ፍላጐት የገቡበት ጋብቻ እንኳን አስተማማኝ አይደለም፡፡››

«እና?»

‹‹እናማ ሀሳቤን ሰረዝኩ፡፡››

‹‹ለእኔ ልጅ የመውለዱን?››

‹‹....ኧረ አንተን ማግባቱንም ጭምር፡፡››

‹‹አሁን ግን እኮ ልጅ አርግዘሽልኛል፡፡››

‹‹የምን ልጅ?››

‹‹ልጅ ነዋ... እርጉዝ ነሽ፡፡››

‹‹አንተ እኮ ምላስህ ጥቁር ነው..በእናትህ አታሟርትብኝ፡፡››

‹‹ማሟረት አይደለም.. የእውነቴን ነው…፡፡አሁን የለበስሽውን ቀሚስ ለብሰሽ በህልሜ መጥተሸ ነበር..ለዚህ ነው በጥዋት ወደአንቺ የመጣሁት፡፡››

‹‹ይሄንን ቀሚስ አታውቀውም እኮ ከሶስት ቀን በፊት ነው የገዛሁት..በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ደግሞ ካንተ ጋር አልተገናኘሁም፡፡››

‹‹እኔም የገረመኝ እሱ ነው..ጥምዝ የወርቅ ሀብል በፍቅር አጠለቅሺልኝ.. ስሜቴ እንደሚተረጉምልኝ ከሆነ ልጅ ሳታረግዢልኝ አልቀረሺም፡፡ >>

‹‹እንዴ ሀብል አጠለቅኩልህ ማለት እሺ እንዳልከው ልጅ ይሁን ..ከፅዬን እንደሆነስ ..? የግድ እኔ ስላጠለቅኩልህ ከእኔ ነው ማለት ይቻላል?››

‹‹አይ ከፅዮን ጋር መዋሀድ እንደማንችል አይቼያለሁ..በዛ ላይ ሀብሉ ሁለት ተመሳሳይ አንድ ላይ የተጠቀለለ ነበር ...አንዱን እራስሽ አንገት ላይ ስታጠልቂ አንዱን እኔ አንገት ላይ ነው ያደረግሽው፡፡››

‹‹ጥሩ ህልም ነው ፤ግን አንድ የዘነጋሀው ነገር ቢኖር እኔ በየሶስት ወሩ ሳላሰልስ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንየተወጋው መሆኔን ነው፡፡››

‹‹አውቃለሁ.... ያ ማለት ግን ላለማርገዝሽ መቶ ፐርሰንት ማስተማመኛ ነው ማለት አይደለም..እዚህ ሰፈር በቅርብ ክሊኒክ አለ?››

‹‹አዎ ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹ተነሽ ሄደን ቼክ እናድርግ?››

‹‹ምኑን?››

‹‹ማርገዝ አለማርገዝሽን >>

‹‹የምርህን ነው እንዴ?›› አለችው በፍራቻም በመጠራጠርም ጭምር.. ምክንያቱም ከዚህ በፊት ታዲዬስ ተመሳሳይ ከህልም የመነጩ ትንቢቶችን ነግሯት እሱ እንዳለው ተግባራዊ ሲሆኑ ደጋግማ ታዝባለች፡፡

‹‹ተነሽ እንጂ፡፡››ትንሽ ካቅማማች በኃላ ተስማምታ ተነሳች.... ተያይዘው ወጡ፡፡

ከአንድ ሰአት በኃላ..ወደቤት ተመልሰው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡

‹‹..ጭራሽ የሶስት ወር እርጉዝ?››በንዴት ተንጨረጨረች፡፡

‹‹ርብቃ አይዞኝ ተረጋጊ እንጂ፡፡››

‹‹እንዴት ልረጋጋ..?እኔ ገና ለገና ስራና ገንዘብ ስላለኝ ብቻ አባት የሌለው ልጅ መውለድ አልፈልገውም፡፡>>

‹‹ምን ማለት ነው? አባቱ እኮ አለሁ... እኔ ነኝ::››

‹‹አንተማ የሌላ ሰው ባል ልትሆን ነው››

‹‹እርሺው ..እኔ እንኳን ልጅ ኖሮኝ ቀድሞውንም ያንቺን ፍላጐት ላክብር ብዬ ነው እንጂ የማፈቅረው ማግባትም የምፈልገው አንቺን ብቻ ነው››...አፍጥጣ በአድናቆት አየችውና‹‹ፅዮንስ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አስረዳታለዋ››

‹‹ምን ብለህ …?ሞራሏ እኮ ሊነካ ይችላል?››

‹‹ጋብቻ የሰው ሞራል ለመገንባት ወይም ለይሉኝታ ሲባል የሚገባበት አይደለም፡፡››

‹‹ቢሆንም እኔ እንጃ ምን ማለት እንዳለብኝ እንኳን ማወቅ አልቻልኩም››

‹‹አባት የመሆን ብቃቴ ተጠራጥረሽ ነው አይደል፡፡››

አይ እሱን እንኮን ፍፁም ልጠራጠር አልችልም..ያንተን አባት የመሆን ብቃት ከተጠራጠርኩማ እኔ የአለም ትልቋ ደደብ ነኝ ማለት ነው..አንተ እኮ የአለም ምርጥ አባትነት ብትወዳደር እንደምታሸንፍ አውቃው››

‹‹እና ምንድነው ችግሩ››

ችግሩማ ምንም እንኳን በአባትነትህ ቅንጣት ጥርጣሬ ባይኖረኝም በባልነትህ ግን እኔ እንጃ..አንተ የትዳር ሰው ይወጣሀል ብዬ ማሰብ ይከብደኛል፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍7516😱3🔥2🥰2👎1
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡.

ዶ/ር ሶፊያ እና ትንግርት ኮንትኔንታል ሆቴል ምሳ በልተው ከጨረሱ በኃላ መጠጥ እየተጎነጩ ጨዋታ ይዘዋል፡፡

‹‹እሺ ትንግርቴ ህይወት እንዴት ነው?››

ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንደምታይው ነው፡፡››

‹‹ላገባ እኮ ነው ..ነግሬሻለሁ አይደል?››

‹‹አላስተዋወቅሽኝም እንጂ ነግረሺኛል፡፡››

‹‹አስቤ ነበር ግን ወደ አሜሪካ በረረ ..ያው ጣጣውን ጨርሶ አንደኛውኑ ከ15 ቀን በኃላ ወደ ሀገር ቤት ይመጣል ...ሊያገባኝ ፡፡የዛኔ አስተዋውቅሻለሁ፡፡››

‹‹ቆንጆ ነው?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡:

‹‹ያንቺን ያህል አያምርም እንጂ ቆንጆስ ቆንጆ ነው፡፡››እንዲህ ስትላት የትንግርት ፊቷ ቀላ፡፡

‹‹የሆንሽ ብሽቅ ነገር እኮ ነሽ...ሰውን መተንኮስ መቼም አታቆሚም፡፡››

እውነተኛ ስሜቴን እኮ ነው እየነገርኩሽ ያለሁት..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡..እንደዛ የሚሰማኝ ደግሞ አንቺን ሳይ ብቻ
ነው፡፡››

‹‹ታድዬ፡፡››አለቻት በማሾፍ፤ቀጠለች‹‹ግን ሁሌ አንድ ነገር ጠይቅሻለሁ እያልኩ ሳገኝሽ እረሳዋለሁ፡፡›››

‹‹ምንድነው አሁን ጠይቂኛ?››

‹‹ሀዋሳ ከመገናኘታችን በፊት ለስድስት ወራት ያህል በሚሴጅ ታጨናንቂኝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ አይደል?››

‹‹አዎ እኔ ነኝ...ማን መስሎሽ ነበር?››

‹‹እኔ እንጃ.... ብቻ ከድሮ የሽርሙጥና ህይወት ካፈራዋቸው ደንበኞቼ መሀከል የፍቅር ግርሻ ናላውን ያዞረው አንዱ ጀግና መስሎኝ ነበር፡፡››

‹‹ትንግርቴ..በእኔ ተረብሸሽ የማትፈልጊው ህይወት ውስጥ ተሰንቅረሽ ሶስት የባከኑ ዓመታት በማሳለፍሽ ግን በጣም አዝናለሁ፡፡››

‹‹የባከኑ አልሻቸው..እነዛ አመታት ፍፁም የባከኑ የሚባሉ አልነበሩም ...የህይወት ልምዶች ያገኘሁባቸው እና ስብዕናዬን የሞረድኩባቸው ዓመታት ነበሩ፤ያን ስል መከራ አልነበረውም፡፡...ስቃይ
አልተቀበልኩበትም፣አልተሰደብኩበትም፣አልተደ በደብኩበትም ፣አልተዋረድኩበትም ማለቴ አይደለም ግን ከተሰቃየሁት ስቃይ ይልቅ ያተረፍኩት በጎ ነገር ሚዛን ይደፋል እያልኩሽ ነው፡፡››

‹‹ግን በመሀል ህይወት አስጠልታሽ ማለቴ ተስፋ ቆርጠሸ አታውቅም?›› ትንግርት እየፈገገች‹‹ታስቂያለሽ..አንድ በጣም የምወዳት አማረች የምትባል ጓደኛዬ አንድ የሚያምር ንግግር ትናገር ነበር …ምን እንደምትል ታውቂያለሽ

<<ተስፋ የሌለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም››ምን ለማለት እንደፈለገች መጀመሪያ አይገባኝም ነበር... በኃላ ግን ከገዛ ህይወቴ ጋር አቆራኝቼ ሳሰላሰለው ተገለፀልኝ…፡፡ እኔ ከዛች ከተለያየንበት ደቂቃ ጀመሮ ተስፋ ሚባል ነገር ከውስጤ ወድሞ ባዶ ንብ የሌለበት ቀፎ ሆኜ ነበር፡፡ሶስቱን አመት ሙሉ ያለምንም ተስፋ ነበር የኖርኩት..ለዛም ነው ያልተቸገርኩት…ምንም አጣለሁ ብዬ የምጨነቅለት፡፡..እዚህ ቦታ መድረስ አለብኝ ብዬ የምጥርበት..ይሄንን ነገር ማግኘት አለብኝ ብዬ የምጓጓለት ነገር አልነበረኝም፡፡››

‹‹ያሳዝናል...ትንግርቴ፡፡››

‹‹አትዘኚ...በህይወት ዝቅታ ወይም ከፍታ ላይ በአጋጣሚ ትንጠለጠያለሽ፡፡ከከፍታው
በምታገኚው ምቾት ተጠምደሽ ወይም ከዝቅታው ውስጥ በሚያጋጥምሽ መከራ ተደቁሰሽ አልባሌ ሰው ሆነሽ እንዳትቀሪ ግን የራስሽ ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ከፍታውም ሆነ ዝቅታው የራሱ የሆነ አውንታዊ አና አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡አሉታዊ ጎኑን ተቋቁመን ጠቃሚውን ነገር መቅሰም የእኛ ፋንታ ነው፡፡››ትንግርት እንዲህ ስትናገር ዶ/ር ሶፊያ እንባዋን እያንጣባጠበች ነበር፡፡

‹‹ቢሆንም ትንግርቴ ይህ ላንቺ ፍፁም የሚገባ ህይወት አልነበረም፡፡››

‹‹ላንቺም እኮ ብር ከፍሎ ሰውን ማስገደል የሚገባሽ ህይወት አልነበረም፤ አሜሪካ ሄዶ ለስድስት ወር በአዕምሮ ህመም ማገገሚያ ሆስፒታል ውስጥ ታግቶ መኖር፤የማትፈልጊያቸውን ኪኒኖች እየጎመዘዘሽ መቃም፤በድንዛዜና በብዥታ ቀናቶችን መግፋት ላንቺም የሚገባ አልነበረም፤አየሽ ሶፊ ‹ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን› የሚባለው በትክክል የሚሰራው በሶሰሻሎስቶች የመፈክር ባነር ላይ በቲዬሪ ደረጃ ብቻ ነው፡፡…እንደውም
በተቃራኒው ተፈጥሮ ነች እኛን ባብዛኛው የምትቆጣጠረን…የህይወት መስመርሽን አንቺ በፈለግሽው መንገድ ብቻ ማስኬድ አይቻልሽም፡፡ቤተሰብ ወደዚህ ይጎትትሻል፣ጓደኞችሽ ወደዛ ይስቡሻል፣ሀገርሽ ወደ ላይ ታወጣሻለች፣ያላሰብሻቸው አጋጣሚዎች ወደታች ያወርዱሻል፣ስለዚህ የሆነው ሁሉ ሆኗል፤በመሆኑም ደግሞ ለበጎነው ብለን መቀበልና ወደፊት መጓዝ ብቻ ነው የሚበጀን፡፡››

‹‹ለበጎ ነው ስትይ?››

‹‹በምንም ምክንያት ሆነ በምንም አንቺ ጥለሽኝ መሄድሽ በጊዜው ፈተናው ከባድ ቢሆንም በስተመጨረሻ ያመጣው ውጤት ዛሬ ህይወታችን እንዲህ ኖርማል እንዲሆን ስላደረገ ውጤቱ ጥሩ ሆኗል ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ግን እኮ ሁለታችንም የምንፈልገው ያንን ኖርማል ያልሆነውን ህይወት ነበር፡፡››

‹‹ቢሆንም ዘላቂ ውጤቱ መልካም አይሆንም ነበር…ማህበረሰብ እንዴት ነበር የሚያሰቃየን...?
መቼ ነው የምታገቡት..?ኧረ ቆማችሁ ቀራችሁ፤ በዛ ላይ የልጅ መውለድ ጉዳይ አለ...


✂️✂️✂️?????????✂️✂️✂️

‹‹...እሱን እኮ ነው የምልሽ ...አደገኛ የሆኑ ውስብስብ የማህበራዊ ህይወት ቀውስ የሚያመጡብን ችግሮች ውስጥ መግባታችን አይቀርም ነበር፡፡››

‹‹ያልሻቸው ነገሮች እንደሚከሰቱ አውቃለሁ ... ቢሆንም ግን ምርጫ ቢቀርብልኝ አንቺን
ከማጣት ያንን ፈተና መጋፈጥን እመርጥ ነበር፡፡››

‹‹ይሆናል…ግን አሁን ሁሉም አልፏል ...መሆን ያለበት ሁሉ አሁን እንደሆነው ሆኗል... በመሆኑም ትክክል ነው፡፡››

‹‹እንዳልሽ ይሁን .…እሺ ግን ሳገባ ሚዜ ትሆኚኛለሽ››ዶክተር ነች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹በሰርግ ነው እንዴ የምታገቢው?››

‹‹እስከአሁን አልወሰንኩም…. ግን አንድ ሃያ ሰው ጠርቼ የእራት ግብዣም ቢሆን ማድረጌ ይቀራል?››

‹‹ታዲያ ያገባች ሴት እኮ ሚዜ አትሆንም፡፡››

«ለምን?»

‹‹ባህላችን ነዋ...መነሻ ሀሳቡን ባላውቅም ምክንያቱን ስገምት ግን ያላገባች ሴት ሚዜ ስትሆን እግረ መንገዷን የራሷን አዳም የምታገኝበትን ዕድል እንድታመቻች ታስቦ የተቀየሰ ስውር ዘዴ ይመስለኛል፡፡››

‹‹አንቺ ...ትንታኔሽ አሳማኝ ይመስላል..በቃ እንደዛ ከሆነ ሌሎቹን ሁለት ሚዜዎች ያላገቡ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ያንቺ ግን የግድ ነው፡፡››ተሳሳቁ፡፡

‹‹ካልሽ ምንቸገረኝ..የእኔን ልጅም ክርስትና ታነሺያለሽ፡፡››

‹‹እንዴ!!! አረገዝሽ እንዴ?››

‹‹አዎ 1 ወር ከ15 ቀን ሆነኝ፡፡››

‹‹ኦ!!! ፈጣሪ የእኔ ቆንጆ እንኳን ደስ አለሽ፡፡›››ከመቀመጫዋ በመነሳት ተጠምጥማባት እያገላበጠች ሳመቻት እና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡

‹‹ክርስትና ግን ስትይ ..ሁሴን ኦርቶዶክስ ሆነ እንዴ?››

‹‹ኧረ አልሆነም፡፡››

<<እና>>

‹‹ምን እና አለው ..ያው እሱም ሀይማኖት የለሽ እንደሆነ የእኔ ሀይማኖት ደግሞ አለየለትም፡፡››

‹‹ግን በኑሮችሁ ምንም ችግር አልፈጠረባችሁም?››

‹‹ያው እስከ አሁን በፍቅር ጥላ ስር ስለሆንን ችግር አልፈጠረብንም… በሚያስማማን እየተስማማን በልዩነታችን ደግሞ እንደልዩነታችን እየኖርን ነው፡፡ፍቅር እኮ ሁሉንም ክፍተቶችሽን ይደፍንልሻል...ፍቅር ሲሸረሸር ነው ሜዳ ሁሉ ገደል፣ነጩ ሁሉ ጥቁር፣ንግግሩ ሁሉ ጭቅጭቅ መስሎ ሚታይሽ፡፡››
👍7511😁2😢2👎1
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም::

ለታዲዬስ ፣ትንግርት፣ሁሴን፣ዶ/ር ሶፊያ፣ፎዚያ እና ኤልያስ ዛሬ ልዩ ቀን ነች፡፡ለስድስት ወር የለፉበትን ...እንቅልፍ አጥተው ገንዘባቸውንም ዕውቀታቸውንም ያፈሰሱበት የድርጅታቸው የመጀመሪያ ፍሬ እነሱም የሚያዩበት ለማህበረሰቡም የሚያስተዋውቁበት ቀን ነው፡፡

ዝግጅቱ በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ፣የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች፣የኤንባሲ ሰዎች፣ታዋቂ ሙዚቀኞች፣የፊልም አክተሮች፣አትሌቶች፣ነጋዴዎች፣
ለዚህ ድርጅት ከምስረታው እሰከአሁን ከፍተኛ እገዛ ካደረጉት ከየተለያዩ የፌስ ቡክ ግሩፖች የተወከሉ ወጣቶች፣ከተለያዩ ሚዲያዎች የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች እና ካሜራ ማኖች..አዳራሹን
ሞልተውታል፡፡

የዛሬው ዝግጅት ዓለማ በዋናነት ሁለት ሲሆን ሌላም አንድ ንዑስ ዝግጅት አለ፡፡መድረኩን የሚመራው ጋዜጠኛ ሁሴን ነው..ማይኩን ይዞ ወደ መድረክ ወጣና ጉሮሮውን ሞርዶ ንግግሩን
ጀመረ::

‹‹ክቡራን እና ክብሯት ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እዚህ የተገኛችሁ ሁላችሁም እንዲሁም በየቤታችሁ ሆናችሁ ዝግጅቱን በቀጥታ በቴሌቨዥን ስርጭት እየተከታተላችሁ ያላችሁ በአጠቃላይ በድርጅታችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን እስከፍፃሜውም በፅሞና እንድትከታተሉን እየጠየቅን በቀጥታ ወደ ዝግጅቱ እንገባለን፡፡በቅድሚያ የድርጅታችን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሶፍያ ፕሮግራሙን በንግግር እንዲከፍቱልን እንጠይቃለን… ዶ/ርን ወደ መድረክ ሸኙልን፡፡››ዶ/ር ሶፊያ በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ ወጣችና ማይኩን ከሁሴን ተቀብላ ንግግሯን ማሰማት ቀጠለች፡፡

‹‹ክቡራን እና ክቡራት የመንግስት ባለስልጣናት፣የሀይማኖት አባቶች፣ከተለያዩ የማህበራት ዘርፎችን በመወከል
የተገኛችሁ፣በየቤታችሁም በመሆን እየተከታተላችሁን ያላችሁ በአጠቃላይ..እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰን አላለሁ፡፡

የዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት ዓላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው የወላጆች እና ልጆች የምረቃ በዓል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለድርጅታችን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ነው..እኔ አሁን አትኩሬ የተወሰነ ማብራሪያ ልሰጣችሁ የምፈልገው በመጀመሪያው ላይ ነው..ሁለተኛውን በተመለከተ አቶ ታዲዬስ ቆየት ብሎ ያብራራላችኋል፡፡

እንግዲህ እንደመነሻ ይሆነን ዘንድ የዛሬ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን አካባቢ በበጎ ፍቃደኝነት አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናትን እናሳድጋለን ብለው ከተመዘገቡ በብዙ ሺዋች ከሚቆጠሩ ባለቀና ልቦች መካከል ለጊዜው አቅማችንን መሰረት አድርገን 15ዐ ግለሰቦችንና በቡድን ከመጡት መካከል ደግሞ 5ዐ ዎቹን ወደ ስልጠና አስገብተን ነበር፡፡እንግዲህ በአንድ ወር ስልጠና ውስጥ በድርጅቱ ህግና የስልጠና ማኑዋል የተሰጣቸውን ስልጠና በመከታተል ከ15ዐ ዎቹ ግለሰቦች መካከል 43 በቡድን ሆነው ከመጡት መካከል ደግሞ 31 መስፈርቱን ማሟላት ስላልቻሉ ከይቅርታ ጋር እንደ ፍላጎታቸው ህፃናትን እንዲያሳድጉ ልንፈቅድላቸው አልቻልንም፡፡የተቀሩት እንግዲህ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው እንሆ ዛሬ በእናንተ ፊት መርቀን ልጆቻቸውን በአደራ እናስረክባቸዋለን፡፡››

የደመቀ ጭብጨባ ከአዳራሹ...ቀጠለች ዶ/ር ‹‹ዛሬ አሁን ለነገርኳችሁ ወላጆች የምናስረክባቸውን ልጆችም ለ3 ወር በካምፕ በማስገባት ስልጠና ሰጥተናቸዋል፡፡ልዩነቱ ህፃናቱን አንዴ ወደ ማሰልጠኛ ካስገባናቸው:: የምንፈልገውን ብቃት እስክናገኝባቸው ድረስ የፈጀውን ያህል ይፍጅ እንለፋባቸዋለን፡፡ ልጆቹን ከበሸቀጠ የድህነት መንደር እንዲሁም በስነ- ምግባር እና በሞራል ከዘቀጠ ጎዳና ላይ ነው የምንሰበስባቸው፤አመላቸውን ማረቅ፣ ስነ- ልቦናቸውን መገንባት፣ጤንነታቸውን ማስተካከል፣ ተስጥኦቸውን ለይቶ ማወቅ፤ወዘተ እንደሀሳባችን እስክናሳካ 3 ወር ፈጀብንም ሶስት
አመት ተስፋ አንቆርጥባቸውም፡፡ የራሱ ጉዳይም ብለንም እርግጠኛ ባልሆንበት ሁኔታ ለአሳዳጊ ወላጅ አሳልፈን አንሰጣቸውም፡፡ይህ ነው ልዩ የሚያደርገን.. እንጂማ መአት በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እንዳሉ እናውቃለን...፡፡.››

ወላጅ ለመሆን ስልጠናውን ወስደው መስፈርቱን አላሟላችሁም ብለን ከመለስናቸው ውስጥ የተወሰኑት በጣም ተበሳጭተውብን ነበር፤ላሳድግ ባልኩ መልካም ልስራ ባልኩ እንዴት እከለከላለሁ?የሚል መከራከሪያ ሀሳብ
ነበራቸው፡፡ግን እኛም ያንን ስናደርግ እያዘንን ነው... እየገነባን ያለነው የወደፊቱን ትውልድ
ነው፡፡አንድ ሰው ገንዘብና ፍላጎት ስላለው ብቻ ዝግጁ የሆነ ስነልቦና እንዲሁም የወላጅ ባህሪ
ሳይኖረው ልጅን ያህል ነገር አሳድግ ብለን አንስተን አንሰጠውም..በፍፁም እንደዛ
አናደርግም፡፡በእኛ መአከል ሰልጥነው ልጅ የተረከቡ ሰዎች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት
ከዚህ ከእኛ ጋር ለወሰዷቸው ልጆችም ብቻ ሳይሆን ከአብራካቸው ለወጡትም
ህፃናት፣ለዘመዶቻቸው ልጆች ፣ለጎረቤቶቻቸው ልጆችም ያገኙትን ዕውቀት እንዲጠቀሙበት
እንፈልጋለን፡፡አርአያ እንዲሆኑበት እንፈልጋለን፡፡ ለዛ ነው ማኑዋሉንም አዘጋጅትን ለእያንዳንዱ ያደልነው፡፡

‹‹ልጅ ማሳደግ ማብላትና ማጠጣት ብቻ ሳይሆን..የወደፊት የህይወት ዓላማቸውን፤ ተሰጥኦዋቸውን ከስር ከመሰረቱ እያጎለበቱ መንገድ ማስያዝን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን ነው ጠቅላላ የሀገራችን ወላጆች ሊከተሉት የሚገባው መንገድ፡፡ ህብረተሰቡም እንደህብረተሰብ...መንግስትም እንደመንግስት የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ ምረቃ በዓሉ እንሄዳለን፤ ክብር የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ ለተመራቂ ወላጅ እና ህፃናት የምስክር ወረቀት ይሰጡልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡››

ሚንስቴሩ በሙሉ ሱፍ ሽክ ብለው በከረባት እንደታነቁ በተጀነነ እርምጃ ወደ መድረክ ወጥተው ከዶ/ር ጎን ቆሙ ፡፡ሁሴን የተመራቂዎቹን ስም ተራ በተራ ሲጠራ ወላጆቹ ከተረከቧቸው ህጻናት ጋር በመምጣት የምስክር
ወረቃታቸውን እየወሰዱ ወደ መቀመጫቸው ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ..ሰሎሞንና የውብዳር አንድ ወንድ ልጅ(እነሱ የጠየቁት ሁለት ቢሆንም በታዲዬስ የሚመራው ቴክኒክ ብድን ግን በዚህ በአንዱ ልጅ ላይ የሚያሳዩት አፈፃፀም ታይቶ ከአመት በኃላ ሌላ ልጅ ሊጨመርላቸው ይችላል እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ከአንድ ልጅ በላይ አይፈቀድላችሁም በማለት ከለከሏቸው) ሌላው..ዶር ሶፊያና ከፕ/ዬሴፍ ጋር አንድ ሴት ልጅ፣ፎዚያ እና ኤልያስ አንድ ሴት ልጅ፣ፅዮን እና ዓላዛር ..ትንግርት እና ሁሴን አንድ ልጅ በመረከብ ከራሳቸው በመጀመር አርዓያነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም ሲጠናቀቅ የክብር እንግዳውንና ዶ/ር ሶፊያ መድረኩን ለቀው ወደ መቀመጫቸው ሄዱ.... ሁሴን ቀጣዩን ፕሮግራም ማስተዋወቅ ጀመረ…፡፡

‹‹ክብሯን እንግዶች ወደ ቀጣዩ ፕሮግራማችን ከመሸጋገራችን በፊት የሙዚቃ እረፍት

እናደርጋለን..ድምፃዊ ሀሊማ እና ሄለን ወደ መድረክ፡፡››

በአካልም በየቤቱም እየተከታተሉ ያሉ አይኖቻቸውን ወደ መድረኩ ላኩ፡፡

የተባሉት ሙዚቀኞች ወደ መድረክ ሲመጡ ታዩ …ሀሊማ ጊታሯን ይዛ ወንበር ስባ ተቀመጠችና ማይኩን ወደ አፏ አስተካክላ አመቻቸች፡፡ሄለን ወደ ፒያኖው አመራች፡፡አብዛኛው ህዝብ አስታወሳቸው፡፡ ባለፈውም በቴሌቨዥን ቃለ መጠየቅ የተደረገላቸው ጊዜ ብቃታቸውን አሳይተዋል፤በአይድል ውድድርም እንደዛው…፡፡ ጀመሩ ሄለን ፒያኖውን ስታናግረው ሀሊማ ጊታሯን እየተጫወተች በድምጿም ታንቆረቁር ጀመር..
👍6311
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን ሰዓሊ ሰላም ነች.. ሰዓሊ ሰላም ወደ መድረክ…፡፡››

ሰላም ሸንከል ሸንከል እያለች ወደ መድረክ ስትወጣ ትንግርት ከኃላዋ 120 ሳ.ሜ በ 60 ሳ.ሜ ስፋት ባለው በሸራ ላይ የተሳለ ስዕል ይዛ ተከትላት ወጣች፡፡ስዕሉ ለህዝብ እይታ ቀረበ፡፡

<<እኛ ለእኛ›› የሚል ርዕስ አለው፡፡

አንድ ህፃን የተቦተራረፈ ልብስ እና የቆሸሸ ፊት ይዞ አስፓልት ዳር ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ
ጠርዝ ላይ ቂቢብ ብሎ በመውጣት ሞልቶ በመትረፍ አካባቢውን ሙሉ ከሸፈነው ቆሻሻ ላይ የተጣለ ምግብ ጎንበስ ብሎ የሚፈልግ ይመስላል፤አንደኛው እጁ ግን ወደ አስፓልቱ ተቀስሯል፤በተቀሰረው እጁ አቅጣጫ የቆመች የቤት መኪና ትታያለች፣ከመኪናዋ ውስጥ አንድ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኝ የፀዳ ልብስ የለበሰና የተመቸው ህፃን በመስኮት ተንጠራርቶ መፅሀፍ እና ዳቦ ለጎስቆላው ልጅ ሊያቀብለው ሲንጠራራ ያሳያል፡፡

ሁሴን ቃላ መጠየቅ ሊያደርጋት ወደ ሰላም ተጠጋ

‹‹ስምሽን ብታስተዋውቂን?››

‹‹ሰላም እባላለሁ..ሰላም ታዲዬስ፡፡››

‹‹ሰላም እሺ ..…ለምንድነው ወደዚህ መድረክ የወጣሽው?››

‹‹ይሄንን ስዕል ለድርጅቱ በስጦታ ላማበረክት፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ነው ..ማነው የሳለው?››

<<እኔ ነኛ፡››

‹‹ለምን ርዕሱን ..እኛ ለእኛ አልሽው?››

‹‹ለእኛ ከእኛ ውጭ ማንም ስለሌለ ነዋ...ታዲዬስ አባት ባይሆነኝ እኔ ይሄኔ እዚህ

መድረክ ላይ ሳይሆን ሀዋሳ መንገድ ዳር ቁራሽ ዳቦ መግዣ ሳንቲም እየለመንኩ ነበር
ምታገኙኝ…..እባካችሁ የኢትዮጰያ ህዝቦች በጠቅላላ መጥናችሁ ውለዱ፤ልመና የሞራል
ነቀርሳ ነው ማንም ህፃን እንዲለምን አትፍቀዱ፤ጎዳናዎች ከቦታ ወደ ቦታ መተላለፊያዎች እንጂ ፈጽሞ የህጻናት መኖሪያዎች መሆን የለባቸውም፤ታዲ አባቴ ከዛ
የጎዳና ሰቆቃ አውጥተህ ሰው ስላደረግከኝ አመሰግንሀለው እሺ ... ደግሞ በጣም ነው
የምወድህ....ሁላችንም ልጆችህ
እንወድሀለን..ሁሉም የዓለም አባቶች እንደ አንተ እንዲሆኑ እንፈልጋለን..››ይሄን ስትናገር እንባዋን መግታት ስላልቻለች መድረኩ ጥላ ወረደች..አዳራሹን የሞላው ህዝብ ዓይኞች ሁሉ
በዕንባ ፈሳሽ ተሞሉ፡፡ሁሴን ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ መናገር
ጀመረ‹‹እሺ ሰላምን እንደሰማችኋት ይሄንን በነዛ
ትናንሽ እጆቿ የተሳለውን ድንቅ ስዕሏን በስጦታ አቅርባልናለች.. እናም ለጨረታ እናቀርበዋለን..፡፡
ሰላም ማለት የታዲዬስ ልጅ ነች..ቅድም ልዩ ጥኡመ ዜማ ለጆሮችን ያሰሙን ሀሊማ እና
ሄለንም የታዲዬስ ልጆች ናቸው፤ሚጡና ሙሴ
የሚባሉም ልጆች አሉት...በተለይ ሙሴ የልጅ ሳይንቲስት ነው…ስለሱ ሳስብ ምን እንደሚታሰበኝ ታውቃላችሁ ሰው ከሞተ በኋላ
ነፍሱ በሌላ ሰው አካል ሆና ዳግም ወደዚህ ምድር ትመጣለች የሚል እምነት የሚያራምዱ
ማህበረሰቦች አሉ ፤ያ እምነት እውነት ከሆነ የታዲዬስ ልጅ የሆነው ሙሴ የቶማስ ኤዲሰንን
ነፍስ ይዞ ለኢትዬጵያውያን ተስፋ ሊሆን የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ…. በአጠቃላይ ቅድም ታዲዬስ
የተናገረው ንግግር ለመናገር ብቻ ሳይሆን እሱ በተግባር ስለፈተነው ህጻናትን ከመሰረቱ ኮተኩተን ካሳደግናቸው ገና ከጥዋቱ ፍሬያቸው እንደምናይ ስላረጋገጠ ነው..፡፡

አሁን ወደ ሰላም ሥዕል ጨረታ እንግባ..በነገራችን ላይ ከዚህ ፕሮግራም በኋላ የሰላምን ሌሎች ድንቅ ስዕሎችን ማየት ከፈለጋች በሚቀጥለው ክፍል ጎራ በሉ..(ይሄንን ሲናገር በየቤታቸው ሆነው ዝግጅቱን በቴሌቨዠን ለሚከታተሉት ካሜራው የሰላም ስዕል ወደ ሚገኙበት ክፍል በማዞር ማስቃኘት ጀመረ ..13 የሚሆኑ የተለያየ ርዕስ እና መጠን ያላቸው ስዕሎች በግድግዳው ላይ ተሰባጥረው ለዕይታ ምቹ ሆነው ተሰቅለው አሳየ፡፡

ሰላም ለድርጅቱ በስጦታ ያበረከተችው ስዕል ከሸራተን ሆቴል አልወጣም..በሼኩ ትዕዛዝ ይመስላል በ1ዐዐ ሺ ብር መነሻ የተጀመረውን ጫረታ ፉክክር ዝግጅቱ ላይ ታድመው የነበሩት የሜድሮኩ ስራ አስኪያጅ በሁለት ሚሊዬን ብር እዛው አስቀሩት..ድርጅቶችም ግለሰቦችም ያቅማቸውን ወረወሩ..አጠቃላይ ቃል የተገባውና እጅ በእጅ የተሰጠው በድምሩ 25 ሚሊዬን ብር ሆነ፡፡

ሁሴን ፕሮግራሙን ወደ ሶስተኛው ዝግጅት ሊያሸጋግር ፈለገ‹‹ቅድሚያ ግን ሄለን እና ሀሊማ ወደ መድረክ ዳግም እንዲወጡ አደረገ...የቴዲ አፍሮን ላምባዲና ነው ያቀረቡት፤ ልክ እንዳጠናቀቁ ሁለተኛውን ሙዚቃ ሊቀጥሉ ሲሉ ትንግርት በምልክት አስቆመቻቸው እና ወደ መድረክ ወጣች ፡

‹‹ይቅርታ ለየት ያለ ዜና በስልክ ስለደረሰኝ ነው ወደ መድረክ የወጣሁት..ቴዲ አፍሮ ከሄለን እና ሀሊማ ጋር አዲስ አበባ ላይ አንድ ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን ለድርጅቱ እንዲሚያስገባ ነግሮናል.. ለጊዜው 1ዐዐ ሺ ብርም በአካውንታችን ዛሬውኑ እንደሚያስገባ አብስሮናል፤እንግዲህ እዚህ ዝግጅት ላይ የታደሙ ድምጻዊያኖቻችን እና ኮሜዲያኖችም ቅድም እንደሰማችሁት አንድ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁልን ቃል ገብተው ነበር..ይሄ ሁለተኛ ኮንሰርት መሆኑ ነው፡፡እናመስግናለን ››ብላ ወረደች፡

..በዚህ ዜና በጣም የፈነጠዙት ሀሊማ እና ሄለን ናቸው ፤ከሚወዱትና ከሚያደንቁት ለእነሱ እንደ ህልም ከሆነው ቴዲ አፍሮ ጋር በአንድ መድረክ ሊሰሩ ነው..በደስታ በተጥለቀለቀው ስሜታቸው የሚቀጥለውን ሙዚቃ መጫወት ጀመሩ.. የሰርግ ዘፈን ነው‹‹..ሙሽራዬ ሙሽራዬ ... የወይን አበባዬ››ሙዚቃውን ተከትሎ ከጀርባ ካለው በር ወደ መድረክ ሲወጣ የታየው ታዲዬስ ነው፡፡ ቅድም ከለበሰው ልብስ በተለየ አለባበስ ሙሉ ሱፍ ለብሶ ቀኝ እግሩን አስቀድሞ ታየ.. ከኃላው ነጭ የተንዘረፈፈ ቬሎ የለበሰች ወጣት ተከትላዋላች... ርብቃ ነኝ..፡፡እጅ ለእጅ ተቆላልፈው በዝግታ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ወደ መድረኩ ወጡ…ጥጉን ይዘው እንደተጣበቁ ቆሙ፡፡

ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው..ሌሎች ጥንዶች በተመሳሳይ ሁኔታ በተመሳሳይ አለባበስ ወጡ ዶ/ር ሶፊያ እና ፕ/ዬሴፍ ናቸው፡፡ ከነ ታዲዬስ ጎን ቆሙ..አሁንም ሌላ ጥንዶች ተከተሉ ፎዚያና ኤልያስ(የእነ ኤልያስ ጋብቻ ልዩነታቸውን በምን ሁኔታ ፈተው ወይም ለመፍታት ተስማምተው ለዚህ ጥምረት እንደበቁ ለጊዜው ከጥንዶቹ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው የለም) ህዝብ ከፍተኛ መደመም ወስጥ ገብቷል..በመጨረሻ ጥንድ ሆነው የወጡት የነ ሀሊማ የሙዚቃ አስተማሪዋ አይነ ስውሯ ፅዬን እና የሰላም የስዕል አስተማሪው ዓልዓዛር ናቸው፡፡ሙዚቃው አልቆ ተቋረጠ..ከዛ አምስቱም የታዲዬስ ልጆች ከያሉበት ወደመድረክ ወጡና ታዲዬስን እና አዲሷን እናታቸውን ርብቃን ከበው ቆሙ..በተመሳሳይ ሌሎች ጥንዶችም ዛሬ ለማሳዳግ የተረከቧቸው ልጆች ወደ መድረክ ወጥተው በእያንዳንዱ ጥንዶቹ መካከል በፈገግታ ቆሙ..ህዝቡ በደስታ እና በዕልልታ አዳራሹን አደበላለቀው፡፡

ሁሴን ወደ መድረኩ ወጣና መናገር ጀመረ….
👍7614🤔2👎1