አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...ዮናታን ቤታችው ሲደርሱ፥ ሞኒካ የስብሰባውን ሁኔታ ለመስማት ጓጉታ በሕንፃው መናፈሻ በኩል ቁልቁል እየተመለከተች መምጫቸውን በመጠባበቅ ላይ ነበረች ።

“ እንዴት ነው ? ” አለቻቸው ፡ ከፊቷ ላይ የማይጠፋ ፈገግታዋን ብልጭ አድርጋ "

“ ደስ የሚያሰኝ ስብሰባ ነበር " በብዙ ሰዎች ላይ ቀና ስሜት አሳድረናል” አሏት፡እጅዋን ይዘው ወደ ውስጥ እየገቡ ጥናቱንም ቢልልኝ በጥሩ መልክ አቅርበውታል የጥናቱን ጽሑፍ ከእሳቸው ተውሼ ሰሞኑን አመጣልሻለሁ”

ሞኒካ ስብሰባው ላይ ለመገኘትና በአቤል ላይ የተካሔደውን ጥናት ለማዳመጥ ከፍተኛ ጉጉት ነበራት ጥናቱ የቀረበው በአማርኛ ስለ ነበር በደንብ የማትሰማው ቋንቋ ሆኖባት ነው የቀረችው።

“ አካዳሚክ ኮሚሽኑስ ምን አለ ? ” ስትል ጠየቀቻቸው "

“ የእነሱ መደበኛ ስብሰባ ገና ከአራት ቀን በኋላ ነው ።ሆኖም ስብሰባችን ላይ የነበሩት የኮሚሽኑ አባላት በግል ተስፋ ሰጥተውኛል ። እና ጥሩ ውጤት እጠብቃለሁ ።

ዮናታን ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ልባቸው አቤልን ለማየት ጓጉቶ ነበር • ሳሎን ውስጥ ሲያጡት የት እንዳላ
ለማወቅ ሞኒካን መጠየቅ አላስፈለጋቸው? በቀጥታ ወደ መጻሕፍት ክፍላቸው ሔዱ ። በሩን በዝግታ ከፍተው
ሲገቡ'አቤል በሚያነበው መጽሐፍ ክፉኛ ተመስጦ አገኙት ።
ሊረብሹት አልፈለጉም ። በሩን በዝግታ ዘግተው ለመመለስ ቢያስቡም እጃቸው የበሩን እጀታ መጎተት አልቻለም ለአቤል አንዳች ነገር ሊነግሩት ፈለጉ ። ቀን ምን እንደሚነግሩት ወይም ደስታቸውን እንዴት እንደሚገልጹለት አያውቁም ነበር። አቤል በእሱ ጉዳይ ስብሰባ መካሔዱን አያ
ውቅም ። ጉዳዩ ክብደት ተሰጥቶት አደባባይ መቅረቡ በአንድ በኩል ሊያስደስተው ቢችልም በሌላ በኩል ደግሞ የሚደብቀው የዐይን ፍቅር መጋለጡ ስሜቱን ሊጎዳው ስለሚችል፥ ይህን በማመዛዘን ዮናታን ሆነ ብለው ነበር ያልነገሩት አሁንም ይህን ሊነግሩት አልፈለጉም። እንዲሁ ብቻ በፈገግታ የደስታ ስሜታቸውን ሊያስተላልፉለት አሰቡ ።

ወደ ውስጥ የጫማቸው ድምፅ አቤልን ከተመሰጠበት አባነነውና ካቀረቀረበት መጽሐፍ ቀና አለ ። ፈገግታቸውን
ሲያይ ፡ ምን አገኙ ይሆን ? ብሎ አልተደነቀም ። ንባብ ላይ ተቀምጦ በማግኘታቸው የተደሰቱበት መሰለው ።
“ እንደምን ውለሃል ? ” አሉት ፡ እንዲህ የሳበው መጽሐፍ ምን እንደሆነ ለማወቅ ዐይናቸውን ወደ ርዕሱ እየወረወሩ
ደኅና ፡ ሲገቡ አልሰማሁዎትምኮ ” አላቸው ፡ የደረሰበት ገጽ እንዳይጠፋው ማዕዘኑ ላይ እያጠፈ ።

የሚያነበው “ ማን አገንስት ሄምሰልፍ ! ” “ ሰው ራሱን ሲጻረር ! የሚለው የዶክተር ሜኔንገር መጽሐፍ ነበር " ዮናታን ይህን አርዕስት ሲያዩ ደነገጡ ። ካልጠፋ
መጽሐፍ ይኽን ለምን መረጠው ? የሚል ጥርጣሬ አደረባቸው፤ፈገግታቸው በአንድ አፍታ ጠፋ ። ፈጥነው ሊጠይቁት ግን አልደፈሩም ። ከውጭ ይዘውት የመጡት የደስታ ስሜት ከውስጥ ጥቀርሻ ሲለብስ ተሰማቸው ።

“ ወደ ውጭ ወጣ ብለን እንናፈስ ? ዛሬ ንባብ ላይ ብዙ የቆየህ ይመስለኛል ” አሉት ' ስሜቱ በመጥፎ ነገር ተወጥሮ ከሆነም ወጣ ብሎ መናፈሱ ይሻለዋል በሚል ግምት ።

“ በደስታ!” አላቸው ከተቀመጠበት እየተንጠራራ ።

አመላለሱም ሆነ የፊቱ ብርሃን ከውስጡ መጥፎ ስሜት የወጠረው ሰው አይመስልም ። ዮናታን በግምታቸው ግራ
ተጋቡ ።

ሊብሊንግ ፡ ሽርጥሽን አውልቂና ወጣ እንበል ”አሏት ሚስታቸውን ወደ ሳሎኑ ተመልሰው ።

ሞኒካ ቤት ውስጥ ከሆነች ከወገቧ ነጭ ሽርጥ አይጠፋም።

“ አቤልስ ይመጣል ? ”አለቻቸው ፈቃደኛነቱን ለማረጋግጥ ።

“ አዎ ፡ እወጣለሁ ብሏል ” አሏትና " ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብለው ፥ የዛሬ ውሎው እንዴት ነው ? ” አሏት ፡

የመጽሐፉ አርዕስት እየከነከናቸው ነበር
“ ደኅና ነው የዋለው ። እንዲያውም ንባብ ከመጀመሩ በፊት እሱ ባደገበት አካባቢ ያለውን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት ሲያጫውተኝ ነበር ” አለቻቸው ሽርጧን እየፈታች ።

ዮናታን ውጭ ወለው ቤት ሲገቡ ስለ አቤል ሁኔታ መጠየቅ ልማዳቸው ነበር ። አቤልም ዮናታን ቤት መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ያሳየው ለውጥ ቀላል አልነበረም » እብሯቸው ሲኖር ሳምንት ሆኖታል ። ከእራሱ ጋር መታረቅ ጀምሯል ለውጡ የሞኒካ የድካም ውጤት ነው
ማለት ይቻላል ።

ለመጀመሪያው ሁለት ቀን አቤል ራሱን ገዝቶ ቤት ውስጥ መቀመጡ በጣም አስቸግሮት ነበር " ትዕግሥት በሐሳቡ
እየመጣችበት ብረር ብረር ይለው ነበር ። ሲጠላው የነበረው ዩኒቨርስቲ ይናፍቀዋል ትንሽም ቀለል የሚለው እስክንድር መጥቶ አጫውቶት ሲሔድ ነበር ።

ዮናታንና ሚስታቸውም ይህን ችግሩን ሳይረዱለት አልቀሩም ። ሐሳቡን ከትዕግሥትም ሆነ ከሌላ መጥፎ
ስሜት ለማዘናጋት የተጠቀሙበት ዘዴ መንፈሱ ለሥራ መወጠር ነበር ለቀን ተቀን እንቅስቃሴው ፕሮግራም
አውጥተውለታል ። ሞኒካ ምግብ በምታበስልበት ሰዓት አብሯት ሆኖ የምግብ አሠራሯን እያጠና በአንዳንድ
ማኅበራዊ አርዕስቶች ላይ ይወያያሉ በቀን የተወሰነ ሰዓት እሷ ጀርመንኛ ታስተምረዋሶች ። እሱም በፈንታው
ለተወሰነ ሰዓት አማርኛ ያስተምራታል ። ይህ አቤል ከመምጣቱ በፊት የዮናታን ሥራ ነበር ። ስለዚህ ማታ ማታ ሞኒካ ቀን የተማረቻቸውን አንዳንድ አዳዲስ የአማርኛ ቃላት ስትናገር፥ ዮናታን ወደ አቤል እየመተለከቱ ፥ ጥሩ ረዳት አገኘሁ እንዲያው ከኔ የተሻለ ዘዴ ሳይኖርህ አይቀርም ” በማለት ይክቡታል ። በመጀመሪያ ለንባብ የተመደበለት የተወሰነ ሰዓት ነበረው ውሎ ሲያድር ወደ ንባቡ ፍቅር ሲመለስ ግን፡ለንባብ ከተቀመጠበት ስፍራ የሚነሣው .
በቀስቃሽ ሆነ ። ከንባብ ውጭ ለመዝናናት ያህል በቤት ውስጥ የሚያገኛቸውን የጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሥዕላዊ መግለጌ የያዙ መጻሕፍት ማገላበጠት በመንፈስ
ውስጥ የጥሩ ሕይወት ስሜት ያሳድርበት ነበር ። የሀገር ውስጥና የውጭ ሙዚቃ በሙሉ ጆሮው ሰምቶ ለማድነቅ
የቻለው በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው ። ትርጉሙም ሆነ ጣዕሙ ሲገባው ያልቻለውና ዮናታን የሚያደንቁትና በተመስጦ ያሚያዳምጡት፡የእነ ቫግነርና ቤትሆቭን ክላሲካል ሙዚቃ ነው "
ቤት ውስጥ ሙዚቃ ማዳመጡ ቢያስደሰተውም አንዳንዴ ትካዜ ስለሚጫነው ፥ ለመቆጠብ ወይም ብቸኝነት በማያጠቃው ሰዓት ብቻ ለማዳመጥ ተግዶ ነበር ።

ቀን በዚህ ዐይነት ውሎ ወደ ማታ ላይ ሦስቱም ነፋስ ለመቀበል ወደ ከተማው ጸጥታማ ቦታዎች ብቅ ይላሉ ።
አሰልሠው ሲኒማ ይገባሉ ። ይህን የመሰለው የሕይወት እንቅስቃሴ አቤልን ከብቸኝነት ስሜቱ በማዘናጋት ሐሳቡ
አንድ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር እንዳይሠቃይ ከፋፍሎታል ። ያም ሆኖ ትዕግሥትን እያሰበ ሳይጨነቅ አያድርም
ግን ጭንቀቱ እንደ ቀድሞው አልነበረም ፡ በሥራ በተወጠረ አእምሮ ወይም ደክሞ እንቅልፍ በፈለገ ጭንቅላት ስለሆነ የሚያስባት ፥ ያን ያህል አይረበሽም ።

አቤል ከብርቅነሽ ቀጥሎ በሕይወቱ የገጠመችው ግልጽ ሴት ሞኒካ ነች ። በአንድ ምሽት ዕድሜም ቢሆን
የብርቅነሽ ትሑትና ግልጽ ተፈጥሮ በልቡ ተቀርጿል ። ምናልባትም የብርቅነሽ ግልጽነት ከማይምነቷ ጋር የተያያዘ
የልብ ክፍትነትና የጥሬነት ውጤት ሊሆን ይችላል ። የሞኒካ ግልጽነት ግን ምሁራዊ ጥልቅ ትርጉምና ድምቀት አለው ። ከአኳኋኗ መረዳት እንደሚቻለው “የምንፈጽመው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር የህልውናችን ነጸብራቅ ነው ፤ ስለሆነም
እኛነታችንን ደብቀን መሠቃየት የለብንም ፤ መጥፎ የምንለውን አምቀን ጥሩ የምንለውን ብቻ የምንተነፍስ ከሆነ
ውስጣችን ገምቶ ደማችን ይደፈርሳል የምትል ትመስላለች አቤል በቀላሉ ነው የተግባባት
👍4
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ኒኪ ጠዋት ላይ ከእንቅልፏ ስትነቃ ሙሉ በሙሉ የእረፍት ስሜት ነው የተሰማት:: ምናልባትም ከብዙ ቀናት በኋላ ያልተቋረጠ እንቅልፍ ስለተኛች
ሊሆን ይችላል እንደዚህ አይነት ስሜት ሊሰማት የቻለው። ትላንትና የተሰማት ሀዘን እና ንዴትም በእንቅልፍ ወጥቶላታል፡፡ ትላንትና ማታ ሰውነቷን ያስመታችው ፀሐይ አፍንጫዋን እና ትከሻዋን በደንብ አድርጎ ስለጠበሰው ቀይ ሆኗል፡፡ ስለዚህም የሎዕ ጄል ተቀብታ ለጥቂት ጊዜ ያህል ቆየች እና ገላዋን ታጠበች ቁርሷንም እንቁላል ፍርፍር ከተጠበሰ ፍራፍሬ ጋር በልታ በላዩ ላይ ሁለት ኩባያ ጠንካራውን የኢጣሊያን ቡና ጠጣችበት።

ዛሬ ማታ አኔን ማግኘት አትፈራም፡፡ አኔን ካገኘቻት እና ስለ ሉዊስ አገኘሁት ያለችውን መረጃንም ከአኔ ከተቀበለች በኋላ አኔን በደንብ መክራት እንድትረጋጋ ካደረገቻት በኋላ መረጃውን ለሉው አሳልፋ ትሰጣለች፡፡ ከዚያም ነገሮች እስኪረጋጉ ድረስ ወደ ፓልም ስፕሪንግ፣ ወደ አሪዞና ወይንም ደግሞ ወደ ሆታሆ አምርታ ተደብቃ መቆየት ትችላለች፡፡
ወደ እንግዳ መቀበያው አምርታ “ሲኞራ ማርቼስ አሁን ወጥቼ በጣም አምሽቼ ነው የምመለሰው እና ምናልባት የግቢው በር ቁልፍ ያስፈልግ። ይሆን?”

“አያስፈልግሽም ዶክተር በክፍልሽ ቊልፍ የግቢውን በር መክፈት ትቺያለሽ፡፡ ይልቅ እራት ፍሪጅ ውስጥ ላስቀምጥልሽ?”

“ፍራፍሬ ብቻ ይቀመጥልኝ” ብላቸው ወደ መኪና ማቆሚያው ሥፍራ አመራች። መኪናዋንም አስነስታ ከግቢው መውጣቷን የተመለከቱት ሲኞራ
ማርቼስ የስልኩን እጀታ አንስተው የሆነ ቁጥር ላይ ደወሉና “አሁን ከዚህ
ተነስታለች” ብለው ስልኩን ዘጉ።

ኒኪ መኪናዋን እያሽከረከረች ፓልም ስፕሪንግ ደረሰች እና የክፍያ መንገዱ ውስጥ ከመግባቷ በፊት ነዳጅ ለመቅዳት ነዳጅ ማደያ ቆመች:: ወደ ቦርሳዋም እጇን ሰድዳ የገንዝብ ዋሌቷን ልታወጣ ስትል እጇ የዊሊያምስን ኤንቨሎፕ ነካ። ኤንቨሎፕን ቀደደችውና ውስጡ ያለውን ወረቀት አንድ በአንድ አወጣች።

መሪዋ ላዩ ተደፍታ ሰውነቷ የሚርገፈግፈውን ሴት ያየው የነዳጅ
ማደያው አስተናጋጅ ወደ እሷ ቀረበ እና “ችግር አለ የኔ እመቤት?” ብሎ
ጠየቃት፡፡ ኒኪም ቀና ብላ ስታየው በአንድ ጊዜ እያለቀሰች እና እየሳቀች መሆኗን
አየና ትንሽ ቀለል አለው:: በእጇ ላይ የያዘቸውንም ወረቀት እያሳየችው
“ደረሰኝ (ቢል) እኮ ነው አይገርምም?” ብላ ከት ብላ ሳቀች እና “አይገርምም
እሱ ከሞት መንደር የላከልኝ የመጨረሻው መልዕክት የሚያዚያ እና
የግንቦት ወር ክፍያ መጠየቂያ ቢሉን ነው” ብላ ከት ብላ መሳቋን ቀጠለች።

የነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሴትዮዋ ቢሉን እያሳየችው እንደ ዕብድ የሳቀችበት ምክንያት አልገባውም፡፡ እዚህ ፓልም ስፕሪንግ ውስጥ እንደ እሷ ያሉ ዕብዶችን እያስተናገደ በሚያገኘው ዶላር ዕዳውን የሚከፍለው በሚመጡለት ቢሎች ነውና ቢል ይሄንን ያህል ሊያስቅ አይችልም ብሎ በኒኪ ተበሳጨባት፡፡

ጉድማን ቢሮው ቁጭ ብሎ በዴሪክ ዊሊያምስ ላይ የቀረበውን የፎሬንሲክ
ሪፖርት ደግሞ እያነበበ ነው:: ሪፖርቱ እንደሚገልፀው ከሆነ በሟቹ ላይ
ምንም አይነት አሻራም ሆነ የገዳይ ዲ.ኤን.ኤ ሊገኝ አልቻለም:: የተመታበት
ጥይትም ቢሆን አብዛኛው የሎስ አንጀለስ ህብረተሰብ በሚይዘው የሽጉጥ ጥይት ነው:: ነገር ግን ሽጉጡ ላይ የተገጠመው ሳይለንሰር በጣም ልዩ እና በፍፁም ድምፅ እንዳያሰማ የሚጠቅም በመሆኑ፣ እንዲሁም ደግሞ እነዚህን ልዩ ሳይለንሰር የሚሸጡት የጦር መሳሪያ መደብሮች የሚሽጡለትን ሰው አድራሻ እና ማንነት መዝግበው ስለሚሸጡ፣ ይህንን ሊያጣራ ጆንሰን በከተማው ውስጥ የሚገኙ መደብሮች ውስጥ እየዞረ ይገኛል፡፡

ጉድማን የዴሪክን ገዳይ እንደዚህ በቀላሉ እንደማያገኙት እርግጠኛ ነው።
አሁን እያሳሰበው ያለው ነገር የኒኪ ሮበርትስ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም እሷ
የገባችበትን አደጋ አታውቅም። የእሷ ከተማውን ለቆ መውጣትን ለጆንሰን
አላሳወቀውም። ይሄ ደግሞ ሌላ ችግር ነው የሚፈጥርበት። ምንም እንኳን እሷ በዊሊያምስ ግድያ ውስጥ ባትሳተፍም የግል መርማሪዋ በተገደለ ማግስት ሎስ አንጀለስን ለቅቃ መጥፋቷ ጥሩ ነገር እንዳልሆነ በደንብ ይገባዋል።

በዚህ ሀሳብ ውስጥ እያለም ላቲሻ ሀል የምትባለው የጣቢያው መልዕክት
አቀባይ አንድ የተከፈተ ኤንቨሎፕ አምጥታ ሰጠችው::ጉድማንም የኢንቬሎፑን መከፈት ተመልክቶ “ኢንቨሎፕን አንቺ ነሽ
እንዴ የከፈትሺው!?” ብሎ በቁጣ ጠየቃት፡፡

“ኧረ በፍፁም” ብላ እሷም ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡

“እና ቅድም ከሁለት ሰዓት በፊት ፖስታ በሚከፋፈልበት ጊዜ ለምን
አልሰጠሺኝም?”

“ምክንያቱም መፀዳጃ ቤት በነበርኩበት ጊዜ ነው የሆነ ሰው መጥቶ ዴስኩ ላይ ያስቀመጠው:: ኤንቨሎፕ ላይም ለሎው ጉድማን የሚል ፅሁፍ ስለተፃፈበትም ነው ላንተ ይዤልህ የመጣሁት” አለችው፡፡
ጉድማን ከኤንቬሎፑ ውስጥ ያለውን ወረቀት ሲያወጣው ዴሪክ ዊሊያምስ ለኒኪ የላከው የሚያዚያ/ግንቦት ወር የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ እና
ከደረሰኙ ላይ የተቀደደ እና ኒኪ የፃፈችበት ወረቀትን አገኘ። ከደረሰኙ ጀርባ ላይ 777 የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡ ከደረሰኙ በተቆረጠው ወረቀት ላይ ደግሞ “ይሄን መልዕክት እንደምታገኝው ተስፋ አለኝ፡፡ ነገሩ ከእኔ ይልቅ ለአንተ አስፈላጊ ነው። ሉው
ሁሌም ራስህን ጠብቅ፡ እኔን በፍፁም
እንዳትከተለኝ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ጆንሰን እዚህ ነገር ውስጥ እስከ አፍንጫው
ነው የተዘፈቀበት ኒሮ

የሚለውን መልዕክት እንዳነበበወደ መስኮቱ በፍጥነት አመራና ወደታች ወደ ታች ወደ መኪና ማቆሚያው ተመለከተ፡፡
መንገዱ ግራና ቀኝ ላይ።
ከሚራመዱት ሰዎች ውስጥ ኒኪን በአይኑ ቢፈልጋት ሊያገኛት አልቻለም።
ኒኪ ለጥቂት ከእጁ ስላመለጠችውም በጣም ተናደደ፡፡

ወዳ ላቲሻ ዞሮም “ጆንሰን ጋ ደውይለት:”
“ደውዬ ምን ልበለው?” አለችው ላቲሻ ግራ ተጋብታ፡፡

“በአስቸኳይ ወደ ቢሮ እንዲመጣ ንገሪው።” አላት፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኒኪ ለአኔ የሰጠቻት አድራሻ በሳን ጁሊያን መንገድ ላይ የሚገኝ የድሮ መጋዘን የነበረ ህንፃ ነው። ህንፃው በአንድ ማተሚያ ቤት እና በአንድ የሴቶች ልብስ ስፌት ፋብሪካ መሀከል የሚገኝ ድብቅ ህንፃ ነው::

በእነዚህ ምንም በሌለባቸው ህንፃዎች ውስጥ በፊት ላይ ቤት አልባ
ሰዎች ይኖሩባቸው ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን የከተማው ከንቲባ ለቤት አልባ ሰዎች ማደሪያ ስላዘጋጁላቸው አብዛኛዎቹ እዚህ አካባቢ የሚገኙ ህንፃዎች ባዷቸውን ነው የሚያድሩት።

ኒኪ መኪናዋን በቅርብ ርቀት ከሚገኙት ብሎኮች አጠገብ አቁማ ወደ ቀጠረቻት ህንፃ ስታመራ ለአኔ ይበልጥ መጨነቅ ጀመረች። ኒኪ ጭር ባለ ቦታ አኔ ላግኝሽ እና ላውራሽ ማለቷ በተለይ ደግሞ ይሄንን ቦታ መምረጧ ልታካፍላት ያሰበችው ሚስጥር ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ አብረውም እንዳይታዩ በመፈለጓ የተነሳ ነው ብላ አሰበች፡፡ “ይሄ የመገናኛ ቦታ ሳይሆን የመደበቂያ ቦታ ነው። ግን ከማን ነው የምትደበቀው?”

የመጀመሪያ ግምቷ ሉዊስ ነው ሊጎዳት ያስበው የሚል ነበር። ግን ከዚህ
ሁሉ ጊዜ በኋላ ለምንድነው ሉዊስ አኔ ላይ ጉዳት የሚያደርሰው? ምናልባት
ሉዊስ ቀናተኛ እና ሁሉንም ነገሮቿን መቆጣጠር የሚወድ ሰው ስለሆነ
ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ሊያስፈራራት እና ተመልሳ ወደ ቤቷ እንድትሄድ
ማድረግ ነው የሚችለው እንጂ አንድም ቀን እጁን አንስቶባት አያውቅም።
ምክንያቱም በጣም ነው የሚወዳት

ትናንት አኔን በስልክ ስታወራት ከድምጿ ውስጥ ከፍተኛ ፍራቻ እና ተስፋ መቁረጥን
👍1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....ወይዘሮ ወደሬ ከእሪ በከንቱ ወደ ፊት በር በሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ከአፋፉ ላይ በመኖሪያና በመሸታ ቤትነት የሚጠቀሙበት ሁለት ክፍል ቤት አላቸው፡፡ አሻሻጫ ቀን ቀን በግርድና ማታ ማታ ደግሞ ልብሷን ቀያይራ፣ ፀጉሯን አበጣጥራ በሴተኛ አዳሪነት ብቅ የምትለው ጽጌ ነበረች፡፡ ጽጌ ከአካባቢዋ ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ጥሩ መግባባት አላት። ኑሯቸውን እየኖረች ቀን ቀን የቤት ስራተኛ ማታ ማታ ደግሞ ሴተኛ አዳሪ እየሆነች ስትገለባበጥ ኖራለች።
ፅጌ ከኩሽና ንግስትነት እስከ አረግራጊው አልጋ ፊታውራሪነት... ሁለቱንም የህይወት ተሞክሮ እኩል እየኖረች ስፊ ልምድ ያዳበረች ሴት ነች።አዲሷ አሻሻጭ ሰላማዊት ወደ እማማ ወደሬ ቤት ከመምጣቷ በፊት ፅጌ ብቸኛዋ የወንዶች አይን ማረፊያ ነበረች። ሰላማዊት በአሻሻጭነት ስራ
ልትጀምር የአሮጊቷ የእማማ ወደሬን ቤት ከአራት አመታት በፊት ከተቀላቀለች በኋላ ግን የተፈላጊነት ደረጃዋ እያሽቆለቆለ ሄዶ ነበር ሰላማዊት የእማማ ወደሬ ጓደኛ የሆኑት የወይዘሮ አረጋሽ ልጅ የቅድስት ጓደኛ ስትሆን “ እማማ ወደሬ ቤት ይሻልሻል” ብላ ይዛት የሄደችው
ቅድስት ነበረች።
የአሻሻጭ ችግር የነበረባቸው እማማ ወደሬ ቀንበጥ የመሰለችው የቆፍጣናው ገበሬ ልጅ እቤታቸው ድረስ ሰተት ብላ የመጣችላቸው እለት ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ። ገበያቸው በሰላማዊት ምክንያት ሲደራ፣ ሲጧጧፍ ደንበኞቻቸው መሸታ ቤቱን ሲያጣብቡት በሷ የአሻሻጭነት ተግባር ውስጥ የዕለት ገቢያቸው በእጥፍ ድርብ ሲጨምር ወለል ብሎ ታያቸው።
ደንበኞቻቸው ቦታ ቦታቸውን ይዘው እየጠጡ ነበር፡፡ በሞቅታ ሃይል
ግማሹ ይዘፍናል ከፊሉ የቤቱን ጣጣ፣ የሚስቱን ጉድ... የመሥሪያ ቤት ችግሩን... የአለቃውን ተንኮል....ሁሉም የየራሱን ወሬ ያወራል። የሰከረው ብዙውን ጊዜ ከማዳመጥ ይልቅ ማውራት ስለሚቀናው መደማመጥ ይጠፋና አውራው የጠፋበት የንብ መንጋ ይመስል አየሩ በጫጫታ
ይሞላል። የተጀመረው የወሬ ርዕስ መቋጫ ሳያገኝ ሌላ የወሬ ርዕስ ይከፈታል። እሱም በወጉ ሳይሰማ አዲስ ርዕስ ይጀመራል። ምን እንደተወራ ርዕሱ በውል ሳይታወቅ እንደገና ሌላ ርዕስ ይቀጥላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተጀመረው አዲስ ርዕስ ምን እንደሆነ እንኳንስ አድማጩ ተናጋሪው ራሱ በውል አያውቀውም፡፡ ዝም ማለት በህግ የተከለከለ ይመስል ማውራት..
ማውራት.. ማውራት... መጮህ... የአንድ ቀን ትውውቅ የሌለው በስካር መንፈስ መጠጥ ቤት ውስጥ ይተዋወቅና ወዲያውኑ መሳሳም ይጀምራል።ሰክሮ እጁ የማይፈታ፣ የማይጋብዝ፣ ሰክሮ ጥሩ ዘፋኝ፣ ጥሩ ስዓሊ...ጥሩ ደራሲ...ጥሩ የእግር ኳስ ተጫዋች የማይሆን ስለአንበሳ ቦክሰኛነቱ የማያወራ ጥቂቱ ነው። በዚያን ዕለትም እንደተለመደው ጠጪው የእማማ ወደሬን ቤት ከአፍ እስከገደፉ ሞልቶ አጨናንቋት ነበር ደላላው፣ ተሸካሚው፣አናፂው፣ግንበኛው፣ አስተማሪው... በያይነቱ...
እማማ ወደሬ የዶሮ ዓይን የመሰለ ጠላቸውና የነጠረ ካቲካላቸው ለመድኃኒትነት ይፈለጋሉ እየተባለ ዝናን ስላተረፉላቸው ቤታቸው ምንጊዜም ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር፡፡ እማማ ወደሬ ደስ ያላቸው ቀን ከጠጪው መሃል ይደባለቁና ጨዋታውን ያጧጡፉታል። በዚያን ጊዜ የግብዣው መዓት ይወርድላቸዋል፡፡
እሳቸውም ፈታ ብለው ስለ ትኩስ ዘመን የፍቅር ታሪካቸው፣ ስለ ባልንጀሮቻቻው፣ ስለ ውሽሞቻቸው፣ስለ ጣፋጭነታቸው እያነሳሱ እንደ ዋዛ አለፈ እያሉ ጠጪውን ያዝናናሉ፣ ያፍነክንካሉ በጨዋታ ያሰክራሉ። ሰላማዊትን ለገበያ ባቀረቡበት በዚያን ዕለትም ልባቸው በሀሴት ተሞልቶ
ፊታቸው በፈገግታ በርቶ ነበር፡፡ ለደንበኞቻቸው አዲስ ዜና የሚያስ
ሙበት ቀን በመሆኑ በኩራት ትከሻቸው ሁሉ ሰፍቷል። አንድ ሁለት መለኪያ ወስዱና ሳቅ...ፈገግ.…አሉ፡፡

ከወዲያ ማዶ ከትንሽ በርጩማ ላይ ቁጭ እንዳሉ ነበር፡፡ አፋቸውን በቀኝ እጃቸው እብስ እብስ ካደረጉ በኋላም ማስታወቂያውን አሰሙ።
“ልጃገረድ የምሽልመውና ዋጋውን የሚከፍለኝ?” ጠጪዎቹን እየተዟዟሩ
በዐይኖቻቸው ቃኙና ንቅሳታም ጥርሶቻቸውን እንደ ፋኖስ እያበሩ የምስራቹን አበሰሩ። በዚህ ጊዜ ጠጪው በሙሉ በአንድ ላይ በሳቅ አውካካ.
“ምን ያስቃችኋል? ይልቁንስ አትጃጃሉ! ማርያምን እውነቴን ነው” አሉ ከወዲያ ጥግ ተቀምጦ የነበረ አንድ ግንበኛ “እንዴ?! እትዬ ወደሬ ልጃገረዷ እኔው ነኝ እንዳይሉን ብቻ?! ካ! ካ.ካ..ካ” አለና አስካካ:: ሁሉም የግል ወሬአቸውን አቋረጡና ተከትለውት በሳቅ ፈነዱ፡፡
“ግድየላችሁም እትዬ ወደሬ እንደዚህ ደፍረው የሚናገሩት ያለምክንያት አይመስለኝም የሚያውቁት አንድ ሚስጥር ቢኖር ነው” አለ ከጎኑ የተቀመጠ ጓደኛው።

“ጉሽ አንተ ትሻላለህ እንዲያውም ላንተ ነው የምድራት ማርያምን! ሌሎቻችሁ እንደሴቃችሁ ትቀሯታላችሁ” መጋረጃውን ገለጡ። “ሰላማዊት!..ነይ እስቲ ወደዚህ ብቅ በይ የኔ ልጅ፡፡ እንግዲህ ዐይን አፋርነቱ ይበቃል፡፡ ሳምንት ያክል ተደብቀሽ ከረምሽ፡፡ ደፈር ደፈር ማለት ነው እንጂ እስከመቼ ጓዳ ውስጥ ተወሽቀሽ ትዘልቂዋለሽ ልጄ? የኛ ሥራ
ወጣ ወጣ ማለት ያስፈልገዋል። በይ ተደንበኞቼም ጋር ተዋወቂ፡፡ ሳቅ ሳቅ እያልሽ አስተናግጃቸው” ብድግ ብለው ከፊት አስቀደሟት። ከወዲያ ጥግ ፅጌ በአንድ ሰካራም እየተጋበዘችና ጡቶቿ ወተት እስከሚያመነጩ ድረስ እየታሸች በመስለምለም ላይ ነበረች።
የሁሉም ዐይኖች በሰላማዊት ላይ ተተክለው መቅረታቸውን ስታስተውል የሆነ የቅናት ስሜት ቆነጠጣት።ስራዋን ልትጫረትባት “ሀ” ብላ የአሻሻጭነት ስራ የምትጀምረውን ልጅ በጥላቻ ዐይን ተመለከተቻት።
ወንዶቹ ሰላማዊትን ካዩበት ቅፅበት ጀምሮ የምራቅ ዕጢዎቻቸው በከፍተኛ የምርት ሂደት ተጠምደው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ወይዘሮ ወደሬ የሚቀልዱ
መስሏቸው ነበር፡፡በሁለመናዋ የምትስብ ልብ የምትሰርቅ ትንሽ ልጅ! በይብልጥ ዐይኖቻቸው የተሰኩት በዳሌዋ ላይ ነበር፡፡ አቤት ቅርፅ?!...

“እንዴ! እትዬ ወደሬ” አንዱ አረቄ ጠጪ በአድናቆት ጮኸና ጓደኛውን ጐሽመው።
እንዴት አይነት መረቅ የሆነች ልጅ ናት በናትህ?” እርስ በርስ ተጐሻ
ሸሙ:: “እትዬ ወደሬ ይሄ በፍፁም ከኔ ማምለጥ የለበትም” የሁልጊዜም ደንበኛቸው አዳሙ ጮኽ፡፡
“እንግዲህ ያልኩትን ቁጭ ማድረግ ከቻልክ ነዋ!” ወይዘሮ ወደሬ መለኪያቸውን አንስተው ጨለጡና የተወለጋገዱ ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉለት።

የፈለገውን እትዬ ወደሬ ምንም ይሁን ምን!”
ኖ...ኖ! እትዬ ወደሬ በቃላችን መሰረት ላንተ ነው ያሉት ለኔ መሆን አለበት፡፡ደግሞ እኔ ሳላዋጣዎ አልቀርም!”ዳንኤል አረቄውን እየጨለጠ ተከራከረ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን ገበያ እንደወጣ በግ በዋጋ የሚከ
ራከሩባት ልጅ ስለምን እንደሚያወሩ ለሷ ግልጽ አልነበረም፡፡ ሄዳ ከአግዳሚው ወንበር ጫፍ ላይ ከአረቄ ጠርሙስ መደርደሪያው አጠገብ ቁጭ አለችና አንገቷን ድፍት አድርጋ መሬት መሬቱን እያየች ተሽኮረመመች፡፡
አጠገቧ የነበረው ደጀኔ እነሱ ሲከራከሩ አጠገቡ መጥታ ቁጭ ያለችለትን እንኮይ ለቀም አደረጋት፡፡ በዋጋ ከመከራከር በእጅ ይዞ እያሻሹና እያሟ
ሟቁ መቀላጠፉ ሳይሻል አይቀርም ሲል ለራሱ አወራ፡፡
👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በልሁ አስር ብር ሰጣትና በተረፈው አንቺ ጠጪ እኔ ግን መንገድ ላይ ደክሞኛልና ወደ ማረፊያዪ ልሂድ አላት።
በጥሩ ስሜትና ፈገግታ ተሰነባበቱ
የበልሁ የማግስቱ የመጀመሪያ ስራ አስተናጋጇ በጠቆመችው
አቅጣጫ ሄዶ ያቺን መናፈሻ ማግኘት ነበር።ብዙ ሳይቸገር
አጎኛት፡፡ ሲያዩዋት ደስ የምትል መናፈሻ የነበረች ትመስላለች፡፡ ግቢዋ በልዩ ልዩ ተክል ያሸበረቀ ነው፡፡ ዋናው ቡና ቤት መሀል ላይ ይገኛሉ፡፡ በአራት ማእዘን ቅርፅ ጥርብ ድንጋይ የተሰራ ነው:: በየአትከልቱ መሀል አልፎ አልፎ
የፈራረሱ መዝናኛ ጎጆዎች ይታያሉ። ከአንዱ ወደ ሌላው መተላለፍያ መንገድ በሲሚንቶ የተሰራ ነው፡፡ አሁን ግን የዛፎቹ ቅርንጫፍ ስለማይከረከም እየተዘጉ ያሉ ይመስላሉ፡፡ በዚያ ላይ የወፎች ኩስ ተንጠባጥቦባቸው
ተዥጎርጉረዋል፡፡
የግቢው ዙሪያ አጥር ከታች አንድ ሚትር ያህል በግንብ፡ ከላይ ደግሞ የዚያኑ ያህል በብረት
ፍርግርግ የታጠረ ነው፡፡ ዋና መግቢያው በር በብረት መዝጊያ ተከርችሟል፡፡ አንድ ሰው ብቻ ይጠብቀዋል፡፡
በልሁ የዚያች መናፈሻ የቀድሞ ገፅታ በአይነ ልቦናው ታየውና እንባ እንባ አለው፡፡ አስቻለውን በዚያ ውስጥ አስታወሰው፡፡ አስቻለው አሁን እዚያ ውስጥ እያለ ነገር ግን ቢጠራው አልሰማ፣ እጁን ቢዘረጋ አልደርስበት ያለው
ይመስል ሆዱ ባባ፡፡ እንባውም ፈሰሰ፡፡ መሀረቡን አውጥቶ አይኑን ጠረግ ሲያደርግ ድንገት ድምፅ ሰማ፡፡ ከመናፈሻዋ በር ጠባቂ በኩል ነበር፡፡
“ምን አሉኝ ጌታዬ?» ሲል በልሁ ወደ ሰውየው እያየ ጠየቀው፡፡
ሰውየው አሁንም ተናገሩ።ነገር ግን በትግርኛ ስለነበር ለበልሁ አልገባውም።
ሰውየው ከስልሳ አለፍ የሚላቸው ይመስላሉ የሰማያዊ ካኪ ቱታ ለብሰው ራሳቸው ላይ የዘበኛ ቆብ
አድርገዋል። እሳቸውም አማርኛ በደንብ አይችሉ ኖሮ በእጃቸው እያመለከቱ « ወዲያ ወዲያ..»
አሉት በልሁም ከዚህ አካባቢ ሂድ ማለታቸው እንደሆነ ገብቶት ከቦታው መራቅ ጀመረ፡፡
ከአባ ሻውል በስተደቡብ አቅጣጫ በሚወስደው አቧራማ መንገድ ላይ ዝም ብሎ ይራመድ ጀመር፡፡ ያ አካባቢ ከሌላው የአስመራ አካል ጋር ሲነጻጸር
ደከም ያሉ ናቸው:: ሞቅ ደመቅ ያሉ ቡና ቤቶች አይታዩበትም ትንንሽ ግሮሰሪዎች ጠላና እንዲሁም አረቄ ቤቶች ይበዙበታል።
በልሁ ድንገት በል በል አለውና ከከንድ ጠላ ቤት ውስጥ ገባ ሰዓቱ ገና ከአራት ብዙም አላለፈም፡፡ ነገር ግን በርካታ ጠጪዎች ቤቱ ውስጥ አሉ፡፡ ባለ ጠላ ቤቷ ሳይሆኑ የማይቀሩ
ወደ ሃምሳ የሚጠጋቸው ቀይ ረጅም ዘንካታ የሆኑ ሴት ወይዘሮ ወንበር ላይ ጉብ ብለው በየመደቡ ላይ ተቀምጠው ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ይጫወታሉ። ቋንቋቸው ትግረኛ ነው።
በልሁ ገብቶ ሲቀመጥ ምን ልታዘዝ የሚል አስተናጋጅ ከፊቱ
አልቀረበም፡፡ ጠላ ቤት ነውና መስተንግዶው የታወቀ ነው፡፡ አንዲት በኑሮዋ ጎስቆል ያለች ልጅ እግር ሴት በጣሳ ጠላ ይዛለት ቀረበች፡፡ በእጁ ሰጠችው፡፡በልሁ ጠላውን ቀመስ ሳያደርግ ወለሉ ላይ ቁጭ አደረገው።
እኒያ ነጫጭ የሀገር ልብስ ለብሰው ወንበር ላይ ቁጭ ያሉት ቀይ መልከ መልካም ሴት በልሁን
አየት አደረጉና «ብርጭቆ ክህቦም» አሉት በትግርኛ። «ምናሉኝ እማማ!» አለና በልሁ «ትግርኛ አልችልም» አላቸው
«ዋይ!» አሉና ሴትዮዋ «ብርጭቆ ይሰጥህ ወይ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አሉት «አያስፈልግም እማማ! አመሰግናለሁ!» አለና ጣሳውን አንስቶ ፉት አለ።
«የሸዋ ሰው ነህ?» ሲሉ ጠየቁት ሴትየዋ ፈገግ እያሉ፡፡
«አዎ» አላቸው፡፡ በልሁ ያቺን የማታዋን አስተናጋጅ አስታወሳት፡፡
«አይዞህ የኔ ልጅ! በል ጠጣ!» አሉትና ሴትዮዋ ወደ ሌለች ጠጪዎች ዞር በማለት ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡
በልሁ አልፎ አልፎ ጠላውን ፉት እያለ የሚያወሩት ነገር ባይገባውም የጠጪዎችን ወሬ ሲያዳምጥ ብዙ ቆየ፡፡ በየመሀሉ ግን ልቡን ዳዳ የሚያረገው
ነገር አለ፡፡ ሊናገር አሁን አሁን ሲል ድንገት ሴትዮዋ ቀድመው አናገሩት:
«ተጫወት የኔ ልጅ!፡፡» አሉት በልሁን ፈገግ ብለው እያዩ፡፡ በልሁ
ጣሳውን እያነሳ ሳለ ሴትዮዋ ቀጠሉ፡፡ «ቋንቋችንን አታውቀው፣ እንዴት እናርግህ?» አሉት እጆቻቸውን በጡቶቻቸው ስር አጣምረው ፊት ለፊት
እየተመለከቱት፡፡
«አረ ይሁን ምንም አይደል» ብሎ በልሁ ወዲያው ደግሞ በዚህ
አካባቢ የሚያውቁት የሚሲዮኖች ሀኪም ቤት ይኖር ይሆን እማማ?» ሲል ጠነቃቸው።
ሴትዮዋ ትንሽ አሰብ አደረጉና «እነዚያ ጥልያኖቹ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡ «ይሆናሉ በእርግጥ ፈረንጆች ናቸው»
«ከዚህ ወደታች በኩል ነበሩ፡፡ ነገር ግን አሁን እኮ ከዚያ ቦታ «ለቀዋል?» በልሁ አሁንም ደንገጥ እያለ
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?
«ቆዩ እኮ!»
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?»
ሴትዮዋ በቀጥታ ለበልሁ ምላሽ ሳይሰጡ ወደ ጠጪዎቹ ዞር በማለት በትግሪኛ ያነጋግሯቸው ጀመር፡፡ ደግመው ደጋግመው ከተመላለሱ በኋላ ሴትዮዋ ፈታቸውን ወደ በልሁ መለስ አድርገው «ከዓመት በላይ ይሆናቸዋል ነው የሚሉኝ» አሉት።
በልሁ እንደገና ወሽመጡ ቁርጥ አለ ፡፡ አጋጣሚዎች ለምን
እንደሚደጋገሙበት ግራ ገባው፡፡ እዝን ባለ ፊት ትክዝ ባለ አነጋገር «በቃ ይተውት እማማ!» እላቸውና ጣሳውን አንስቶ ፉት ካለለት በኋላ መልሶ አስቀመጠው፡፡ ወደ መሬት እጎንብሶ ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘው፡፡
«ልትታከም ኖሯል?» ሲሉ ሲትዮዋ ጠየቁት፡፡
«አይደለም፡፡ እነሱ ጋር ይሰራ የነበረ ሰው እፈልግ ነበር፡፡» አላቸውና አሁንም ጎንበስ አለ።
«አየየ... ለቀዋላ!» ብለውት ሲትዮዋ ወደ ጨዋታቸው ተመለሱ፡፡
በልሁ ከዚያ በኋላ ብዙ መቆየት አልፈለገም፡፡ ውስጡም ተናደደ፡፡
እስከ አሁን ባገኘው መረጃ የአስቻለው ዱካ በቀላሉ እንደማይገኝ፡ ምናልባትም
ጭራሽ ላይገኝም እንደሚችል ፈራ፡፡ ተስፋው እየጨለመ ሄደ፡፡
ወዲያው አንድ ነገር ታየው፡፡ ወደ አረፈበት ሆቴል መብረር፡፡ አዎ
ሄደ፡፡ በጠራራ ፀሐይ በአንሶላና ብርድ ልብስ ጥቅልል ብሎ ተኛ አስቻለውን እንዳያገኝ ከጋረደው የጭንቅ ጉም ያመለጠ መስሎት፡፡
የሰው ልጅ የቱንም ያህል ቢያሰብ፡ ቢጨነቅ ወይም ቢናደድ፡ ቢበሳጭ አልያም ቢፈራ በአጠቃላይ በየትኛውም ስሜት ውስጥ ቢሆን በህይወት
ለመሰንበት የግድ የሚያስፈልገው አንድ ነገር አለ፡ ምግብ፡፡ በልሁ በአንሶላና በብርድ ልብስ ውስጥ ቢደበቅም አላመለጠውም፡ አጅሬ ርሀብ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ የሚነሳ እሳት ነውና አንጀቱን ይሞረሙረው ጀመር፡፡ ከአንድ ጣሳ ጠላ ሌላ የቀመሰው ነገር ባለመኖሩ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ ከተኛበት ሰቅስቆ
አስነሳው:: ምግ አይሉት ራት አደባልቆ ሊበላው ወደ ሆቴሉ ራስቶራንት ወረደ፡፡ ሚሲዮኖቹ ሀኪሞች ይሰሩ ከነበሩበት አካባቢ በመልቀቅ ዜና ተበሳጭቶ
ሳይበላ ሳይጠጣ በመዋሉ መንፈሱ ድክምክም ብሎበት የነበረው በልሁ ምሳ በልቶ ቀዝቀዝ ያለ ለስላሳ ከውሃ ጋር እየቀላቀለ ሲጠጣ በዚያው ልክ ተነቃቃ፡፡
ረጋ ብሎ ማሰብ ጀመረ።
አንድ ነገር ታየው ሚሲዮኖቹ
ሀኪሞች እንደ መሆናቸው መጠን
ከክፍለ ሀገሩ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ጋር በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ታሰበው ምናልባትም የስራ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል " ያ ከሆነ ደግሞ ወቅታዊ ሪፖርቶች ይጠበቅባቸው ይሆናል፡፡ በዚያው መጠን በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብና የአድራሻ ልውውጥ ሊኖር ይችላል “ሚሲዬኖቹ እዚያው አስመራ ካሉም እዚያው
👍131
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የቤት ውስጥ ጦርነት

ሌሊቱን ሌላ ውጊያ ስላልተካሄደ አድመኞቹ የፈራረሰውን ምሽጋቸውን ለማደስና ለማስፋት ጊዜ አገኙ፡፡ ከቁመቱ ትንሽ ጨመሩለት፡፡ ብረት መከላከያም አበጁ፡፡ ወጥ ቤቱን አጸዳድተው የቁስለኛ ማከሚያ ክፍል
አደረጉት:: የሞቱትን ሰዎች አስከሬን አንስተው ጥግ አስያዙ፡፡ በስርቆሹ በር በኩል ያለውን መግቢያና መውጫ በሚገባ ተጠቀመበት፡፡ ቡና ቤቱ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሦስት ሴቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በጓሮ በር በኩል ወጥተው በመሄዳቸው አድመኞቹ እፎይታን አገኙ::

ጎህ ሲቀድ ኢንጆልራስ ሁናቴውን ለመቃኘት በስርቆሹ በር በኩል
ወደ ውጭ ወጣ፡፡ አድመኞቹ «እናሸንፋለን» የሚል እምነት ነበራቸው:: ሆኖም ኢንጆልራስ ከተመለሰ በኋላ ሁኔታው በአንድ ጊዜ ተለወጠ፡፡ ኢንጆልራስ በከተማው የነበረው ጦር በሙሉ እነርሱን ሊያጠቃ መውጣቱን
ሕዝቡ ግን ባለፈው ቀን ገንፍሎ ወጣ እንጂ በእለቱ ሁሉም ከቤቱ መከተቱን ሊነግራቸው መሞቻቸው መቃረቡን ጠረጠሩ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ «ወንድሞቼ ሕዝቡ ሪፑብሊኩን ሲከዳ እኛ ሕዝቡን አንከዳም፡፡ እኛ አሁን
ማድረግ ያለብን ምሽጋችንን አጠናክረን በአለን ኃይል መዋጋት ነው» ብሎ ተናገረ፡፡

እነዚህ ቃሎች የአድመኞቹን ሞራል ገነቡት፡፡ ይህ ቃል የማን እንደነበር
እስከዛሬ አልታወቀም:: ብቻ ቀቢጸ ተስፋ በሚገኝበት ጊዜ ዘወትር አንዱ ብቅ ብሎ ሁኔታውን እንደሚለውጥ ሁሉ ይህም ከዚህ የተለየ አልነበረም::

ያ «የሕዝብ ወገን ነኝ» የሚለው ሁሉ ተቃውሞውን ካሰማ በኋላ
«እድሜ ለሞት፧ ለዚያች ቅጽበት ሁላችንም እንቆይ!» ሲሉ ሁሉም በአንድነት ጮኹ::

«ለምን ሁላችንም?» ሲል ኢንጂልራስ ጠየቀ፡፡

«ሁላችንም! ሁላችንም!» የሚል ድምፅ አስተጋባ፡፡

«ምሽጉ ጥሩ ነው:: ለመመከት ሰላሳ ሰዎች ይበቃሉ:: ለምን አርባ
ሰዎችን እንሰዋለን» በማለት ኢንጆልራስ ተናገረ::

«ምክንያቱማ ከዚህ ለመሄድ የሚፈልግ ሰው ባለመኖሩ ነዋ!» አሉ ሁሉም በአንድነት::

ኢንጆልራስና ኮምብፌሬ ወደ ምድር ቤት ወርደው አራት የወታደር ልብስ ይዘው መጡ፡፡

«ከመካከላችን ቤተሰብ ማለት የሚጦሯቸው እናት! እህት፣ ሚስት፣ ልጆች ያልዋቸው አይጠፉም፡፡ የዚህ ዓይነት ኃላፊነት ያለባቸው ከዚህ
ይሂዱ» ሲሉ ኢንጆልራስ አሳሰበ፡፡

«እውነት ነው! አሁን እርስዎ ቤተሰብ አለዎት! እርስዎ ቢሄዱ»
በማለት አንዱ ወጣት ከአጠገቡ የነበሩ ጠና ያሉትን ሰው መከራቸው፡፡

«ይልቅስ አንተ ሁለት እህቶችህ በአንተ ላይ አይደለም ያሉት?»

ሁሉም በየፊናው «አንተ ሂድ፣ አንቱ ሂዱ» ሲባባል ጫጫታ ሆነ፡፡
«ወንድሞቼ! የምንዋጋው ለሪፑብሊኩ ነው ! አሁን ጭቅጭቀን ተዉና መሄድ ያለባቸው ይሂዱ» አለ ኢንጆልራስ፡፡

አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ሰዎች በኣንድ ድምፅ ተመርጠው እንዲሄዱ ተወሰነ፡፡

«አምስት ናቸው» ሲል ማሪየስ ተናገረ፡፡

የነበረው ዩኒፎርም ግን አራት ነው:: በዚህ ጊዜ ከሰማይ የወረደ
ይመስል አንድ ሌላ ዩኒፎርም ተጣለ፡፡ የአምስተኛው ሰው ሕይወት ዳነ ማለት ነው::
ማሪየስ ልብሱን ማን እንደጣለው ለማየት ቀና ብሎ ሲያይ መሴይ
ፎሽለማንን አየው:: ዣን ቫልዣ ከምሽጉ መግባቱ ነበር፡፡
በጓሮ በኩል ማንም ሳያይ በሚያስገባው መንገድ ነው የገባው:: ያንን መንገድ ቀደም ብሎ ይወቀው ወይም በአጋጣሚ ይድረስበት አይታወቅም፡፡
ከቤቱ ሲወጣ የወታደር ልብስ ለብሶ ስለወጣ ለማለፍ ብዙም አልተቸገረም::

«ይህ ሰው ማነው?» ሲል አንዱ ጠየቀ::

«እሱማ» አለ ኮምብፌሬ የሌሎችን ሕይወት የሚያድን ሰው ነው::

«እኔም አውቀዋለሁ» ሲል ማሪየስ ሀዘን እየተሰማው ተናገረ::

ከዚህ ይበልጥ ሌላ ማረጋገጫ አልተፈለገም:: ኢንጆልራስ ወደ ዣን ቫልዣ ዞረ::

«እንኳን ደህና መጡ፡፡ እንደምንሞት ያውቃሉ?»

ዣን ቫልዣ መልስ ሳይሰጥ ዩኒፎርም የጣለለትን ሰውዬ ያለብስ ጀመር

ምንም እንኳን ጊዜው ረፈድ ቢልም አንድም መስኮት አልተከፈተም።
በሩቁ ግን ሰዎች ከወዲያ ወዲህ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ፡፡ ወሳኙ ሰዓት
እንደቀረበ ያስታውቃል፡፡

ኢንጆልራስ ከመጠጥ ቤቱ በራፍ ድንጋይ ቆልሉአል፡፡ እያንዳንዱ
ሰው ለውጊያ እንዲዘጋጅ አስጠነቀቀ፡፡ ብዙም አልጠበቁም፡፡ ከባድ ጦር
ወደነበሩት ሲመጣ ተመለከቱ፡፡ የተኩስ ድምፅ ተሰማ::

«ተኩስ» ሲል ኢንጆልራስ አዘዘ፡፡

ከዚያ በኋላ ምኑ ቅጡ፤ አገር ተቃጠለ፡፡ ሰማዩ ሁሉ በጭስ ተሸፈኑ።ፊት ለፊት የነበረውን ጣልኩ ሲባል ሌላው ከኋላ ብቅ ይላል::

«ቶሎ ቶሎ እያላችሁ ጠብመንጃችሁን አጉርሱ» ሲል ኢንጆልራስ ጮኸ፡

አድመኞቹ ከባድ መሣሪያ መተኰስ ጀመሩ፡፡ ብዙ ስው ተረፈረፈ።ሁሉም በያለበት «ብራቮ፣ ብራቮ» ሲል ጮኸ፡፡ ሁሉም ተተራመሰ፡፡ ጋቭሮች
እየሮጠ ወደፊት መጣ፡፡ ልጁን ሲያዩ ሁሉም ተበራታ::

«ጓዶች በርቱ» ሲል ጋቭሮች ተናገረ:: «በርቱና ተዋጉ፤ ከየአቅጣጫው ብዙ ጦር እየመጣ ነው።»

«ይኸው ነው፤ እስቲ ሞራል ስጥልኝ!» አለ ኢንጆልራስ፡፡ ጦሩ
ሲመጣባቸው «ጭንቅላታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ደግሞም ወደ ግድግዳው ጠጋ በሉ» በማለት ኢንጆልራስ ምክር ለገሠ፡፡ ከባድ መሣሪያ የያዘ ወጣት
መሣሪያውን እየገፋ ሲመጣ ያዩታል:: ኮምብፌሬ ወጣቱን ሲያየው በጣም አዘነ፡፡

«እንዴት ያሳዝናል፧ ምን ዓይነት የጭካኔ ሥራ ነው የሚፈጽሙት።
ምናልባት ንጉሦች ሲጠፉ ጦርነትም ይጠፋ ይሆናል፡፡ ኢንጆልራስ፣ ወጣቱ ላይ ነው እንዴ የምታነጣጥረው ምን ማለትህ ነው? ይህ ወጣት እኮ ገና ለጋ ነው፡፡ ቢበዛ 25 ዓመት ቢሆነው ነው:: ምናልባት የሚጦራቸው አባት ፤ እናት፣ ወንድምና እህት ይኖሩት ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ መልከ ቀና እንደመሆኑ የሚወዳትና የምትወደው ፍቅረኛ ትኖረው ይሆናል።
ደግሞም የእኔ ወይም የአንተ ወንድም ሊሆን ይችላል፡፡»

«እሱማ ነው» ሲል ኢንጆልራስ መለሰለት፡፡

«እንግዲያውማ እርሱን መምታትና መግደል የለብንም።»

«እባክህን ዝም በለኝ፣ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን፡፡

ደም ከመሰለው የኢንጆልራስ ጉንጭ እምባ እንደ ጐርፍ ይወርድ
ጀመር፡፡ ወዲያው የጠመንጃውን ቃታ ሳብ አደረገና ለቀቀው:: ያ ለግላጋ ወጣት ከመሬት ተዘረረ፡፡ አየር ይበላ ይመስል አፉን ከፍቶ ከአንገቱ ቀና አለ፡፡ ይጎትተው ከነበረ ከባድ መሣሪያ ላይ ተደፍቶ ፀጥ እንዳለ ቀረ፡፡ዐከጀርባው ደም ሲፍለቀለቅ ታየ:: የወጣቱ ነፍስ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከሥጋው ተለየች::

ውጊያው ቀጠለ፡፡ ስለውጊያው ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ቢፈለግ ሌላ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ ሆኖም በዚያች ቀውጢ ቀን የነበረው ሁኔታ ስለጦርነቱ ትንሽ መጨመር ያስገድዳል፡፡ የንጉሡ ጦር በሚገባ ተዘጋጅቶ የመጣ ስለነበር የአድመኞቹን ጥይት ለማስጨረስ ፈልጎ ኃይሉን በመበታተን ከተለያየ አቅጣጫ ተኩስ ይከፍታል፡፡ በአንድ ወገን በከባድ መሣሪያ በመጠቀም ምሽጉን አፈራረሰው:: ያንን ለመቋቋም አድመኞቹ
ባላቸው ኃይል በመታኮስ ተከላከሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ጊዜያዊ ድልን ተቀዳጁ፡፡
ሁሉም ደስ አላቸው:: ግን የሚያሳዝነው የነበራቸው ጥይት ተገባድዶ ያገኙታል::
👍16
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ሌሊቴ ነጋ» አየሩ አሁንም እንደ ማታው እንደ ጠገነነው ነው በረዶውም ያለ መጠን መውረዱን ቀጥሏል " ሚስ ካርይል እንኳን አድርጋው የማታውቀውን ቁርሷን ካልጋው ሳትወረድ በላች
ሪቻርድም ከልጋው ቢነሳም
ከመኝታ ክፍሉ ሳይወጣ
ቁርሱን ጆይስ አቀረበችለትና ሲበላ ሚስተር ካርላይል ገብቶ እንዴት እንዳደረ ጠየቀው "

በጣም ድክም ብሎኝ ስለ ነበር በደንብ ተኛሁ እንግዲህ ግን ቶሎ ብዬ
ከዚህ ብጠፋ ይሻለኛል "

የመሔድ ነገር ከማታ በፊት አይሞከርም ቢሆንም አሽከሮች መኖርህን
ሳይሰሙ መሔድ ስለ አለብህ ብዙ አትቆይም። አሁን ሊቨርፑል ወይም ማንቸስተር ነው እሔዳለሁ የምትለው ?

“ወደ ማንኛውም ትልቅ ከተማ ብሄድ ግድ የለኝም መቸም እንደኔ በመሳደድ ላይ ላለ ሰው ሰፊ ከተማ ነው የሚሻለው "

«ለአኔ እንደሚመስለኝ ሪቻርድ ይህ ቶርን የምትለው ሰውዬ ሊያስፈራራህ ብቻ ነው የፈለግው በርግጥ ጥፋተኛ ከሆነ አሱ የሚበጀው ሀርፎ መቀመጥ ነበር አሁንም ቢሆን እሱ መጥፎ ነገር የሚያገኘው አንተ የተያዝክ እንደሆነ ነው ” አለው
ሚስተር ካርላይል "

“ ታዲያ ለምን ያስቸግረኛል ? ለምንድነው ፖሊስ ልኮ እንዲከታተለኝ የሚያደርገው ?

አንተም እንድታስቸግረው ስላልፈለገ በፍራት ሊያባርርህ ይፈልጋል " የፖሊሱ ፍላጎት አንተን ለመያዝ ቢሆን ኖሮ አስካሁን አያቆይህም » ከቦታ ቦታ እየተንከራተተ አይከተልሀም " የምስጢር ሠራተኛ ቢሆን ኖሮ ደግሞ እንደዚህ ሰው
በየደረስክበት ብቅ እያለ ሳይሇን አንተ እንዳታየው እየተጠነቀቀ ነበር የሚከታተልህ "

“ ነገሩ አንተ የምትለው እውነት ነው ” አለ ሪቻርድ ' ' ምክንያቱም እሱ በከፍተኛ ማዕረግ ያለ ሰው ስለሆነ በዚህ ወንጀል መጠርጠሩ ብቻ በአኩያዎቹ ዘንድ
የተናቀ የተዋረደ ያይርገዋል።

"አኔ ግን ሪቻርድ. . . ሰውየው አንተ እንደምትለው ትልቅ ሰው መሆኑን ማመን ይቸግረኛል

በዚህስ ምንም ጥርጥር የለበትም ሚስተር ካርላይል
ስሙን ብጠራልህ ደስ አይልህም ብዬ ነው እንጂ ትናንት ማታ ከማን ጋር ሲሔድ እንዲያውም እንዳየሁት ብነግርህ ይቸግርሃል ?”

“ ተናገር ራቻርድ ንገረኝ ግድ የለም"

"ከሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ሁለት ጊዜ አየሁት " አንድ ጊዜ በቁማር ከሚወራሪድባቸው ክፍሎች በር ቁመው ሲያወሩ ሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ሲሔዱ አገኘኋቸው " ለሚያያቸው በጣም የሚግባቡ ይመስላሉ … ”

በዚህ ጊዜ አንድ የተቆጣ ድምፅ በበረንዳው በኩል ሽቅብ እየጮኸ ሲጣራ ተሰማና ሪቻርድ ሔር ልክ በጥይት የተመታ ያህል ከተቀመጠበት ዘለለ ይጣራ የነበረው የሚስተር ጀስቲስ ሔር ድምፅ ነበር ።

" ካርላይል የት ነህ ? የማይሰማ ጉድ የለ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገር
ይደረጋል " ና እስ ውረድ !”

ሚስተር ካርላይል የሚሆነው ቅጡ ጠፋው በሕይወቱ እንደዚያ ተጨንቆ አያውቅም " ያንን ድምፅ ሲሰማ እሱም ፈጥኖ ብድግ አለ " ሪቻርድ በበኩሉ ወዲያው ባርኔጣውን አንሥቶ የውሸት ሪዙን አጥልቆ ከአልጋው ሥርና ከቁም
ሳጥኑ ውስጥ መሸሸጊያ ያማርጥ ጀመር "

“ እባክህ አትሸበር ሪቻርድ
ምንም አይመጣብህም " እኔ እዛው እሸኛቸዋለሁ ” አለው ሚስተር ካርላይል በጆሮው ሹክ ብሎ "

ሚስተር ሔር ከደጅ ሲጮህ ለካ ሚስስ ካርላይል ልብሷን በመልበስ
ላይ ኖራለች " ሌላውን ሁሉ አብቅታ የሌት ቆቧን ገና ሳታወልቀው አቋርጣ ወጣች ያንን አስገራሚ የሌሊት ቆብ ያየ ቢያየው እሷ ግድ አልነበራትም " ወጥታ ከበረንጀፈዳው ገረገራ ተደገፈች "

“በዚህ ውርጭ የሚያስመጣ ምን ነገር ገጠመህ ?” አለችው በድንጋጤ ድምፅ

“ሚስተር ካርላይልን ለማነጋገር እፈልጋለሁ ። ጥሩ ወሬ ሰምቻለሁ
“ ስለ ምን ? ስለ አን ወይም ስለ ቤተሰቧ የሆነ ነገር አለ ?

የማን አን ? " አለ በሆነ ምክንያት የተበሳጨዉ ዳኛ ያ ልጄ ብዬ እንድጠራው የተገደድኩት ወመኔ ልጅ እዚህ ነው ያለ ይሉኛል " የሱ
ጉዳይ ነው የበጠበጠኝ "

ሚስተር ካርላይል ከፎቅ ደረጃዎቹን አራት አራቱን ባንዴ እየተራመደ ወረደና ሚስተር ጆስቲስ ሔርን ክንዱን ይዞ ወደ ሳሎን አስገባው ።

እንደ ምን አደሩ ? በዚህ በረዶ እንዴት ችለው መጡ?ምነው ደኅናም አይደሉ ? ሲቃ የያዘው ይመስላሉሳ ? ”

“ሲቃ!” ብሎ በጩኸት ተቀብሎ ደገመና የጋለ ጡብ እንደ ረገጠች ድመት እግሮቹን በተራ እየሰቀለ በክፍሉ ውስጥ እየተንጎራዶደ አንተም ሕይወትህ በተረገመ ልጅ ቢበጠበጥ ኖሮ እንደኔ ሲቃ ይይዝህ ነበር " እንዲያው ሰዎች ጭንቅላታቸውን በራሳቸው ጕዳይ ቢበጠብጡና የራሴን ጉዳይ ለራሌ ቢተዉልኝ ምን አለ ?

ግን ከዚህ ሁሉ ተሰቅሎልኝ ቢሆን ኖሮ መቸ ይህ ሁሉ ይመጣብኝ ነበር "

“ ምነው ምን ነገር መጣ ? አለ ሚስተር ካርላይል "


"የመጣው ነገር ይኸውልህ አለና አንድ ደብዳቤ ከጠረጴዛው ላይ ወረወረለት " " ይኽንን አሁን ፖስተኛው አመጣልኝ " እንደዚህ የሚስደስት ወሬይዞልኝ መጣ "

ሚስተር ካርላይል ወረቀቱን አንሥቶ አነበበው " ሁኔታው ከተቆርቋሪ ዘመድ የተላከ ይመስል ነበር መልእክቱ ወንጀለኛዉ ልጅ እስካሁን ዌስት ሊን ያልደረሰ
ከሆነ በሚመጡት አንድ ሁለት ቀን ውስጥ ሊደርስ ይችላል "ዌስትሊን መግባቱ ከተሰማ ደግሞ ወዲያው ሊያዝ ስለሚችል አባትየው ተጠባብቆ መዲያሙኑ መልሶ
አስወጥቶ እንዲሰደው የሚምክር ነበር "

ይኽ ዴብዳቤ የሐኀፊው ስም አልተጻፈበትም አለ ሚስተር ካርላይል

" አዎ የለውም !እና ቢሆንሳ ? አለ ጀስቲስ ሔር ።

" እኔ ስም ላልተፃፈበት ደብዳቤ የማደርገው ጥንቃቄ ከእሳት መጨመር ብቻ " አለው ሚስተር ካርይል።

“ ግን ማን ጻፈው ? አለ ጀስቲስ ሔር “ ሪቻርድስ አሁን ዌስት ሊን ላይ ነዎይ ነው ዋናው ጥያቄው

“ አሁን ሲያስቡት ወደ ዌስት ሊን የሚመጣ ይመስለዎታል እንዲያው ግልጽ ያለ አስተያየቴን ብሰጠዎ ይቀየሙኛል ? ”

“ የት አባቱ ይኸ ዕብድ ደሞ ዌስት ሊን ላይ ሊታይ?ሰተት ብሎ ሮጦ ከሞት መንጋጋ ሊገባ ? አዬ ምነው እጀጄ ላይ በጣለውና በሕግ ሥር አውዬ ባረፍኩት ”

“ እኔ ልነግርዎ የፈለግሁትይህን ሁሉ ንዴት በራስዎ ላይ የሚያመጡት በገዛ እጅዎ መሆኑን ነው”

“ ለምን እንዲህ ትለኛለህ .... ሚስተር ካርላይል? ሆሊጀንን የገደልኩ እኔ ነኝ ? ከሕግ የሸሸሁት እኔ ነኝ ? የት እንደሆነ ቤልዘቡብ ይወቀው እንጂ ' የተደበቅሁት እኔ ነኝ ? አባቴ በሰላም እንዳይኖርበት የአራሽ ቡቲቶ ለብሼ ወደ ተወለድኩበት መንደር እየመጣሁ ያባቴን ስም የማስነሣው እኔ ነኝ? ስም ያልተጻፈባቸው ደብዳቤዎች እጽፋለሁ ? እስቲ በል ንገረኝ ሚስተር ካርላይል እንዴት አድርጌ
ነው በራሴ ላይ ንዴት የማመጣው ?

“ ይስሙኝማ አንድ ጊዜ ስለ ተናደዱ የልጅዎ ስም በፈለገው ምክንያት ቢነሳም ይበሳጫሉ " እንደኔ ደግሞ ይህን የመሰለ ደብዳቤ የሚጽፍልዎ እርስዎን ለማናደድ ታጥቆ የተነሣ ሰው ነው ምናልባትም ዌስት ሊን ውስጥ አብሮን የሚኖረው ሰው ሊሆን ይችላል ”

“ ይሀ ጭራሽ የማይመስል ነገር ነው "

“ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ማን ስለመሆኑ ምንም ፍንጭ እንደማይሰጥ ማወቅ አለብዎ እኔ ብሆን ደብዳቤውን እሳት ውስጥ እከትና ስለሱ ማሰቤን አቆም ነበር
አሁን እርስዎ በዚህ በረዶ እየዳከሩ ሲመጡ ተንኮለኞች ከዚህ ከኛው አካባቢ ከሆኑ ደብዳቤውን ይዘው እኔን ለማማከር እንደሚመጡ ስለሚያውቁ ይህን ጊዜ አሻግረው
እያዩዎ ይሣሣቁ ይሆናል "
👍161
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡

አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ።

ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡
ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር አይሮፕላኑ ሰላማዊ መንገዱን ይጓዝ ነበር
አሁን ግን ምንም ሆነ ምን ችግሩ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጦ መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደተሳፋሪ መብረር ካልሆነ በስተቀር የበረራ መሀንዲስ መሆን አይችልም፡፡ አልቆለታል። በንዴት ስህተት እንዳይሰራ
መጠንቀቅ አለበት፡ ይህን ዕቅድ በርጋት መከወን አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ
ህይወቱን ያመሰቃቀሉበት ርጉሞች ላይ ይዘምታል።

አይሮፕላኑ በድንገት ባህር ላይ ማረፍ ሊገደድ ነው: ሚስቱን ያገቱበት ወሮበሎች አይሮፕላኑ ላይ ይወጡና ፍራንክ ጎርዲኖን ያስፈታሉ፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነው አይታወቅም:፡ ካሮል አን ደህና ስለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወሮበሎቹ ወደ አይሮፕላኑ ሲመጡ የጠረፍ ጠባቂ
ፖሊሶች አደጋ ይጥሉባቸው ይሆናል፡፡ ኤዲ በዚህ ስራ ውስጥ ለፈጸመው እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እሱ እጣ ፈንታው ሆኖ እዚህ ውስጥ በመግባቱ ነው
ለእስር  የሚበቃው።ካሮል አንን በደህና እጁ እንዳስገባ ሌላ የሚፈልገው ነገር የለም::

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ቀጥ ካሉ ከአፍታ በኋላ የካፒቴን ቤከር ድምጽ በጆሮ ማዳመጫው መጣና ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ በድንጋጤ አፉ ስለደረቀበት ከመናገሩ በፊት ሁለት ጊዜ ምራቁን ዋጥ አደረገ ‹‹ገና አላወቅሁትም›› አለና  መለሰ፤ ነገር ግን መልሱን ያውቃል፡ ሞተሮቹ መስራት ያቆሙት ነዳጅ ስላለቀ ነው፡፡ እሱ ነው ነዳጅ
ወደ ሞተሮቹ እንዳይደርስ ሆን ብሎ ያደረገው። አይሮፕላኑ ስድስት የነዳጅ
ታንከሮች ያሉት ሲሆን ነዳጅ ወደ ሞተሮቹ የሚያደርሰው ክንፉ ላይ ባሉት
ታንከሮች አማካይነት ነው፡፡ ወደ ሞተሮቹ ነዳጅ
የሚያመጡትን ፓምፖች ሆን ብሎ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ሌላ ኢንጂነር
ቢያየው ሆን ብሎ እንዳይሰሩ እንደተደረጉ ያውቅበታል፡

ረዳት ኢንጂነሩ ሚኪ ፊን ተራው ባይደርስም ድንገት ሊመጣ ይችላል ብሎ ተጨንቋል፡ ነገር ግን ሚኪ እንቅልፉን እየለጠጠ ይሆናል ይህን ጊዜ፡
በረራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ ውጭ ያሉ
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ይተኛሉ፡

ሼዲያክ ላይ ሁለት ጊዜ አስፈሪ የፖሊስ ምርመራዎች ነበሩ፡
የመጀመሪያው ፖሊሶች አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረውን የፍራንኪ ጎርዲኖ
ግብረ አበር ስም ማወቃቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ኤዲ ሉተርን ማለታቸውን
ገምቷል በዚህም ምክንያት ሉተር  አልቆለታል ብሎ  ካሮል አንን የሚያስለቅቅበትን ሌላ ስልት ማውጠንጠን ጀምሮ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ
ፖሊሶቹ ሄሪ ቫንዴርፖስትን እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ኤዲ ጮቤ ረገጠ፡፡ከድንጋጤው መለስ ሲል ከሃብታም ቤተሰብ የተወለደ የሚመስለው ቫንዴርፖስት ለምን በሀሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ ገርሞታል፡የፖሊሶችን ትኩረት ከሉተር ወደ ራሱ እንዲዞር በማድረጉ ቫንዴርፖስትን በሆዱ እግዚአብሔር ይስጥህ  ብሎታል፡።
ፖሊሶችም በምርመራው  ብዙም ሳይገፉበት ርግፍ አድርገው ተዉት፡ ስለዚህ ሉተር ተረዳና በዕቅዱ መሰረት እነ ኤዲ የጀመሩትን ሊያከናውኑ ተነሱ፡፡
የፖሊሶችን

ለካፒቴን ቤከር ግን የተፈጸመው ሁሉ ጥርጣሬን የሚቀሰቅስ ሆኖበታል፡፡ ኤዲ ገና ከድንጋጤው ሳያገግም አንድ ድንገተኛ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ላይ ጎርዲኖ
ተባባሪ አለው ማለት እሱን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ሰው አለ ሲል ደመደመ፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖን ከአይሮፕላኑ ላይ ማስወረድ ፈለገ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤዲ እቅድ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡

ህግ እንዳይከበር በማድረጉ በህግ እንደሚጠይቀው የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድ ካፒቴን ቤከር ላይ ዝቶ ነበር፡፡ በመጨረሻ ካፒቴኑ ኒውዮርክ ለሚገኘው ለፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ስልክ ደውሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ አየር መንገዱም ጎርዲኖ በአይሮፕላኑ
መጓዙን እንዲቀጥል ሲፈቅድለት ኤዲም በእፎይታ ተነፈሰ፡፡

ሼዲያክ ላይ አንድ አስደሳች መልዕክት ደረሰው፡፡ የመጣው የኮድ
መልዕክት ከጓደኛው ስቲቭ አፕል ባይ መሆኑ አያጠራጥርም፡ መልዕክቱም አንድ የባህር ኃይል ጀልባ አይሮፕላኑ የሚያርፍበት አካባቢ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንና እንዳይታወቅ ከእይታ ውጭ ሆኖ ወደ አይሮፕላኑ የሚጠጋ ማንኛውንም ጀልባ ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡

ይሄ ለኤዲ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በኋላ ወሮበሎቹ ከህግ እንደማያመልጡ
ማረጋገጫ ቢሰጠውም ዕቅዱ ግን ያለምንም እንከን ባሰበው መልኩ
እንዲጠናቀቅ እንቅፋት እንዳይፈጠር ምኞቱ ነው፡፡
ካፒቴን ቤከር ወደ ኤዲ መጣ፡፡ ኤዲ እጁ እየተንቀጠቀጠ ለሞተሩ ነዳጅ የሚመግበውን ፓምፕ ከፈተውና ‹‹ታንከሩ ባዶ ስለሆነ ሞተሩ አልነሳ አለ›› አለው::

‹‹ለምን?›› ሲል ካፒቴኑ ተቆጣ፡፡

ኤዲ መልስ አልነበረውም፡፡
የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች በመጠባበቂያ ነዳጅና በመጋቢ ቧንቧዎቹ
መካከል የነዳጅ እንቅስቃሴ ወይም ግፊት መኖሩን አያሳዩም፡ ፓይለቶቹ ጋ
ግን የነዳጅ ሁኔታን የሚያሳዩ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች አሉ ካፒቴኑ ሁሉንም በየተራ አየና ‹‹ምንም ነዳጅ የለም›› አለ፡፡ ‹‹በክንፉ ላይ ባለው
ታንከር ውስጥ ምን ያህል ነዳጅ አለን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ትንሽ ነው የቀረው - የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ብቻ የሚያስኬድ››
‹‹እንዴት ነው ይህን ያላስተዋልከው?›› ሲል ጠየቀ በቁጣ፡

‹‹እኔ ፓምፕ እያደረገ ነው የመሰለኝ›› አለ ኤዲ በተቆራረጠ ድምጽ
ይህ መልስ ግን ካፒቴኑን አላጠገበውም፡፡

‹‹ሶስቱም ፓምፖች እንዴት ባንድ ጊዜ ስራ ሊያቆሙ እንደቻሉ አልገባኝም›› አለ ካፒቴኑ።

‹‹ቶሎ ባህር ላይ ካላረፍን የቀረው ነዳጅ ተንጠፍጥፎ አይሮፕላኑ ሊወድቅ ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡

‹‹ባህር ላይ ልናርፍ ስለሆነ ሁላችሁም ተዘጋጁ›› አለ ቤከር፡፡ ጣቱንም ኤዲ ላይ እያወዛወዘ ‹‹አንተ አታስፈልገኝም አላምንህም›› አለው፡

ኤዲ ሞቱን ተመኘ፡፡ ካፒቴኑ ላይ ክህደት ለመፈጸም በቂ ምክንያት እንዳለው ቢያውቅም የፈጸመውን ድርጊት አልወደደውም፡ ህይወቱን በሙሉ
ሃቀኛ ሆኖ ነው የኖረው:: አጭበርባሪዎችንና አታላዮችን አጥብቆ ይጠላ
ነበር፡፡ አሁን ግን የሚጠላውን ነገር ለማድረግ ተገዷል፡
ካፒቴኑ ናቪጌተሩ ጋ በመሄድ ቻርቱ ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ኤዲን በግርምታ ገረመመውና ‹‹አሁን ያለነው እዚህ ላይ ነው››
ብሎ ቻርቱ ላይ በመጠቆም ለካፒቴኑ አሳየው፡፡

የኤዲ ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው አይሮፕላኑ እሱ ባሰበው ቦታ ከወረደ
ነው፡፡ ወሮበሎቹ እዚህ ቦታ ላይ ነው የሚጠብቁት፡፡ ነገር ግን ድንገት
የሚፈጠር ነገር ካለ ከታሰበው ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ካፒቴኑ ሌላ ቦታ
ከመረጠ ግን ኤዲ እሱ ያለው ቦታ የተሻለ ስለሆነ እዚያ ማረፍ እንዳለበት
ካፒቴኑን ማሳሰቡ አይቀርም፡፡ ካፒቴኑ ሊጠረጥር ቢችልም እዚህ ቦታ ከማረፍ የተሻለ ነገር እንደሌለ በሎጂክ መቀበል ይኖርበታል፡ ሌላ ቦታ
እንዲያርፍ የሚያደርግ ከሆነ ግን ትክክል የማይሆነው እሱ ነው፡፡ ስለዚህ የእሱ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹እዚህ ጋ ነው የምናርፈው›› አለ ካፒቴኑ፡
👍19
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.?  ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…

እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን  የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን  እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡ 

…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ  እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…

‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት  ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡

‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)

‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)

‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››

‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ  አያምርብሽም››

‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር  ነው››

‹‹እኮ ምንድነው….?››

‹‹ልሄድ ነው››

ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ  ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››

‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››

ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት  ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?

‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››

‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››

ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ  ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››

‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ  ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡

‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››

‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡

አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..

‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››

‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››

‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››

የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ

‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት

‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››

‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››

‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር አይችልም››
👍10610🥰1
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን እና ዶ/ር ሶፊያ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ...ቤቱ ለሁለት ባልና ሚስቶች የእርቅ በዓል የተሰናዳ የእራት ግብዣ ሳይሆን መለስተኛ ሠርግ ነበር የሚመስለው..ሁሴን እራሱ በጣም ደነገጠ፡፡ እሱ ይኖራሉ ብሎ ከጠበቀው የሰው ብዛት በእጥፍ ቁጥር ብልጫ ያለው እንግዳ ሰፊውን ሳሎን አጨናንቆታል..የውብዳር ሰሎሞን፣ሁለቱ ልጆቻቸው፣ ኤልያስ፣ታዲዬስ ከነልጆቹ..በተለይ የታዲዬስ እና የአምስቱ ልጆች እዚህ የእራት ግብዣ ላይ መገኘት ማንም ያልጠበቀው ነው፡፡ ለነገሩ እስከ 1ዐ ሰዓት ትንግርትም አታውቅም ነበር፡፡እንዳጋጣሚ ስትደውልለት ከነልጆቹ አዲስ አበባ እንዳለ ነገራት…ጊዜዋ የተጨናነቀ ቢሆንም እንደምንም ሰዓቷን አብቃቅታ ያረፈበት ሆቴል ድረስ ሄዳ ለምና እዚህ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፍ አግባባችው.. ኤልያስን ግን የጋበዘችው ፎዚያ ነች፡፡

‹‹እንዴ እናንተ የእራት ግብዣውን ወደ ሰርግነት ቀየራችሁት እንዴ?›› አለ እያንዳንዳቸውን በመጨበጥ ሰላምታ እየሰጠቸው..ዶ/ር ምን እሱን እየተከተለች ተመሳሳዩን ፈፀመች....በወቅቱ ትዕንግርት አልነበረችም ፡፡ ማዕድ ቤት ለዝግጅቱ ከፎዚያ ጋር ተፍ ተፍ እያለች ነው፡፡

‹ ‹እንዴ ታዲ መች መጣህ?››ዶ/ር ነች ጠያቂዋ፡፡

‹‹ዛሬ... ስምንት ሰዓት አካባቢ ነው የገባነው፡፡››

‹‹ለምን ሳትደውልልኝ ታዲያ?›› መምጣቱን ሳታውቅ ያላሰበችው ቦታ ስላገኘችው ቅር ብሏት…፡፡

‹‹ለአምስት ቀን እኮ ነው የመጣነው..አረፍ ካልኩ በኃላ ነገ ተነገወዲያ እደውላለሁ ብዬ ነው…ትንግርትም ድንገት ነው ያገኘችኝ..ደግሞ የአዲስ አበባ ሰዎች እንግዳ እንደሚመጣ ከወር በፊት ቀጠሮ ካላስያዘና ለሚቆይበት ጊዜ በጀት ካልተመደበለት በስተቀር ድንገት ሲሄድባቸው ፊት ይነሳሉ ብለው ሲያሟችሁ ሰምቼ ነው፡፡››

‹‹እንዴ ታዲዬስ እንደዛማ አትለንም.. እንደዛ የሚያደርጉት በቅርብ ሀብታም ለመሆን እቅድ ይዘው ተፍ ተፍ የሚሉት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው ፡፡እኛ መቼም ሀብታም የመሆን ዕቅድ የሌለን ዛሬን ብቻ የምንኖረው ጋር ብትደውል ችግር የለውም ነበር...ካለን ያለንን ትበላለህ ከሌለን ይዘህ የመጣህውን እናባላሀለን›››አለው ኤልያስ… ሁሉም ተሳሳቁ፡፡

‹‹እንዴ እናንተ ሚስቴን አስረሳችሁኝ ትንግርትስ?››ጠየቀ ሁሴን፡፡

‹‹ወደማዕድ ቤት አካባቢ ነች መሰለኝ፡፡››የውብዳር መለሰችለት፡፡

‹‹ተጫወቱ ዓይኗን አይቼ ልምጣ..ናፍቃኛለች፡፡ ››ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ ማዕድቤት ሄደ....::

ፎዚያና ትዕንግርት ተፍ ተፍ ሲሉ ደረሰ‹‹ሀይ የእኔ ፍቅር?›› ብሎ ከንፈሯን ሳማት..፡፡

‹‹ሀይ እህት አለም..የሰላት ሰዓት ደርሶብሻል እኮ አላት፡፡››ፎዚያን፡፡

‹‹ኧረ ባክህ አሁን ስንት ሰዓት ነው..? ልታስታውሰኝ ከፈለግክ ቀደም ብለህ መምጣት ነበረብህ፡፡ >>አለችው ፎዚያ፡፡

‹‹ቆይ ለመሆኑ ይሄው ሁሉ ጉድ ምንድነው..? እንዴት እንዴት አድርጋችሁ እራት ልታበሏቸው ነው?>>

‹‹አይዞህ አታስብ .... የተወሰነውን ሰራን.. የተወሰነውን ደግሞ ከሆቴል አመጣን፡፡››

‹‹የምትገርሙ ናችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ሳረሳው...የመጠጥ ሂሳቡን አንተ ነህ የምትዘጋው 18ዐዐ ብር ቆጥሮብሀል፡፡››

‹‹18ዐዐ ብር ሙሉ ብቻዬን?››

‹‹2ዐዐ ውን እኔ አግዝሀለሁ፡፡›› አለችው ፎዚያ፡፡

‹‹እሺ 18ዐዐ ቀረ አንቺስ የእኔ ፍቅር ስንት ታግዢኛለሽ?››

‹‹እራስህን ቻል... የምግብ ጉዳዩን ጠቅላላ በእኔ ነው የተሸፈነው፡፡››አለችው እየሳቀች፡፡

‹‹ይሁን እንግዲህ ከጨከንሽ ... ከአለም ባንክንም ቢሆን የማይመለስ ብድር እጠይቃቸኋለዋ››

‹‹ትችላለህ..አረ እንግዶቹ ጋር ሂድና አጫውታቸው፡፡››

‹‹እሺ ግን የእኔ ፍቅር አንድ እንግዳ ይዤ መጥቼያለሁ››

‹‹እንደዛማ ከሆነ እዳህ ይጨምራል፡››

‹‹እውነቴን ነው፡፡››

‹‹እኮ ታዲያ ምን ችግር አለው ..?ለመሆነ ማነው የማውቀው ሰው ነው?››

‹‹አዎ፡፡››

<ማነው?>>

‹‹ዶ/ር ሶፊያ››

ትንግርት የያዘችውን ጎድጓዳ ሰሀን በቁሟ ለቀቀችው፡፡

‹‹‹ተረጋጊ ፍቅር፡፡››

‹‹እውነትህን ነው ግን?››

‹‹አዎ ፍቅር ከእሷ ጋር ነው እስከአሁን የቆየሁት..ሁሉን ነገር ነግራኛለች፡፡››

‹‹ትንገርህ ታዲያ ... እኔ ምን አገባኝ?››

‹‹አይደለም እኮ ...እሷ ጋርም አንቺ የማታውቂው እውነት አለ..እኔን አሳምናኛለች፡፡››

<< ይሄ እኮ ያንተ እና የእሷ ጉዳይ ሳይሆን የእኔ እና የእሷ ጉዳይ ነው.....ፎዚያ እንዳደረግሽ አድርጊ እኔ መሄዴ ነው፡፡›› ብላ ሽርጧን ማወላለቅ ጀመረች፡፡

‹‹ወዴት ትሄጂያለሽ?››

‹‹ሳሪስ ሄዳለሁ እቤቴ..ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ፡፡››

ፎዚያ ደንግጣ ትለምናት ጀመረ‹‹ትንግርቴ በአላህ ሌሎቹን እንኳን ተያቸው በስንት ጉትጎታ

‹‹‹ተረጋጊ ፍቅር፡፡››

ቤትሽ ለመጀመሪያ ቀን የመጣው የምታከብሪው ታዲዬስ ምን ይሰማዋል…?››

‹‹እሺ ይሄ ወንድምሽ ሴትዬዋን ከዚህ ቤት ያውጣትና ካመጣበት ወስዶ ይጣልልኝ፡፡››

‹‹ኧረ ትንግርት በፍቅራችን››ጉልበቷ ላይ ወደቀ

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1119🤔5🔥1