አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


“ይሰማኛል ይሰማኛል ቀጥል፡፡” አለ ጀነራሉ በሬድዮው መቀበያ
ላይ አጎንብሶ::

በሬድዮው ክፍል ውስጥ የክፍሉ ሠራተኞች ያልሆኑ ባለሥልጣናት
ከጀኔራሉ ጀርባ ቆመው ይጠባበቃሉ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ያለው አየር ለክፍሉ
ሠራተኞችና ከውጭ ተግተልትለው ለገቡት ለሁሉም የማይበቃ ይመስል
እያንዳንዱ ሰው ትንፋሹን ይዞ በጭንቀት ተወጥሯል፡፡

“ጀኔራል” አለ ከድሬዳዋ.. የቃል ሪፖርት የሚያደርገው አንድሬ ኦማሪ በሚንኮሻኮሻው የሬዲዮ መልዕክት ማስተላለፊያ ውስጥ “ኦኘሬሽኑ
ያለምንም ችግር እየተካሄደ ነው፡፡ መውጫ በሮች ተዘግተዋል፤ ቃል
የገባህልኝ የስልክ ግንኙነት ግን ገና አልተቋረጠም፤ ሰውየውን በተመለከተ
እንዳንድ ፍንጮችን አግኝተናል፡፡ ከባቡር ጣቢያ ከሸሽ በኋላ የገባበትን
መጠጥ ቤት አግኝተን ወደ እንድ ጋራዥ እንደመሩትና ከጋራዥም ባለቤት
ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ደርሰንበታል፡፡ ጊዜው የዓመት በዓል ስለሆነ
የጋራቹን ባለቤት ለማግኘት እቤታቸው ድረስ ልጆቼን ልኬአለሁ፡፡ በተረፈ
በተቻለኝ መጠን አትኩሮት ሳልስብ ፎቶግራፉን የያዙ ሰዎች በከተማው
አሰማርቼ እያሰስኩ ነው፡፡”

ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ የሚለው አንድሬ የደረሰበትን ደረጃ አንድነትና በአንድ በሬድዮው ውስጥ ሲያስተላልፍ አዲስ : አበባ በሬድዮ መቀበያው ክፍል ያሉት ሁሉ በፀጥታ ሲያዳምጡ ቆዩ::

“አንድሬ” አለ ጀኔራሉ “ስልኩን ያላቋረጥኩበት ምክንያት እያንዳንዱን የውጭ ጥሪ እየተከታተልን ስለሆነ መረጃ ለማስተላለፍ ሲሞክር ግንኙነቱን አቋርጠን ስልኩ አድራሻ እንድናጠምደው ስል ነው፡፡ የቤት ለቤት ፍተሻ ለምን እንዳልጀመርክ ግን…”

“አስፈላጊ አይደለም::” አለ አንድሬ ጀኔራሉ መጨረሱን እንዳሳወቀው “በቀላሉ እጄ ላስገባው እችላለሁ:: ከጋራዥ ከገባ በኋላ በተናጠል
የአንድ ሰው አድራሻ ጠይቆ የጋራዥ ባለቤት እንዳመላከቱት ደርሼበታለሁ::
የጋራዥን ባለቤት አግኝቼ አድራሻውን እስካገኘሁ ድረስ ምንም አስጊ ሁኔታ
ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡”

የሬድዮው መልዕክት ተላልፎ እንዳለቀ ከአንድ ሰዓት በኋላ በድጋሚ
የሚቀርበው ሌላ የሬድዮ ሪፖ'ርት እስኪደርስ ድረስ ከሬድዮው ክፍል ውስጥ ተስብስበው የነበሩ ሁሉ ጀኔራሉን ተከትለው ወጡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ናትናኤልና የየምሥራች እናት ከቤት ወጥተው በጠባቧ የከረኮንች መንገድ በዋናው መንገድ አቅጣጫ ራቅ ብለው ሄዱ፡፡ ከአንድ አነስተኛ ቤትዐእንደደረሱ የየምሥራች እናት ከባለቤቶቹ ጋር በኦሮምኛ ቋንቋ እያወሩ አስክትለወት ገቡ፡፡ ከቤት ከገቡ በኋላ የቤቱ ባለቤት ደርባባ ወፍራም ሴትዮ ከፊት ለፊቱ ድክ ድክ እያሉ ስልክ ወዳለበት ክፍል አስገቡት፡፡

ናትናኤል የስልኩን እጀታ አንስቶ አዲስ አበባ ርብቃጋ ደወለ፡፡ የደወለበት ስልክ ሲነሳ ሁለት ጊዜ ቃቃ… ሲል ተሰማው፡፡

ሃሎው… ” አለው ወፈር ያለ የወንድ ድምጽ፡፡
“እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ናትናኤል ስልኩን እንዳትዘጋው። ልናነጋግርህ እንፈልጋለን፡፡» አለ
ያው ወፈር ያለ ድምጽ።
“ማነህ?”
“ማን እንደምሆን መገመት ትችላለህ፡፡ አብርሃምን አስታውስ..
ሌሎቹንም አስታውስ ርብቃ በእጃችን ነች::” ለአንድ አፍታ ሰውየው ዝም
አለ፡፡ “የት ነው ያለኸው? ንገረኝ።” .
“ጫፏን ብትኳት ምስጢራችሁን እንደምነዛው እወቁ! ታዳምጠኛለህ?!” አለ ናትናኤል ድንጋጤውን በቁጣ ለመሽፈን እየታገላ፡፡

ናትናኤል አትችልም::ምንም መንገድ የለህም፡፡ ከድሬዳዋ የሚወጣ :
ማንኛውም የስልክ ጥሪና ፖስታ ሁሉም በቁጥጥራችን ውስጥ ነው፡፡
በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በእጃችን ትገባለህ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት በፈቃድህ
ያለህበትን ቦታ ንገረኝ..ስማ… ”

“ኮሎኔል ትንሽ ድምጽ እንፈልጋለን” አለ ሰውየው በሌላ ስልክ ውስጥ ለሚያዳምጠውና በርብቃ ኣልጋ ጎን ለቆመው ኮሎኔል ማርቆስ፡፡

ናትናኤል የስቃይ ድምጽ ጆሮው ላይ ኣንጫረረበት …እሪታ. የሴት
ልጅ... የስቃይ እዬዬ
“ሰማህ? ርብቃ ነች፡፡ ምን እያደረግናት እንደሆነ ልነግርህ አልሞክርም:: እመነኝ እራስህን ትጠላለህ፡፡ ናትናኤል እመነኝ መፈጠርህን ትጠየፋለህ፡፡ምስጢሩኝ ካልቨርት እንዳገኘኸው እገምታለሁ! . ዓላማችን ለጋራ ጥቅም ነው፡፡ እጅህን ስጠን፡፡ ምንም ጉዳት አይደርስብህም፡፡”

“ርብቃ ምንም አታውቅም!” ናትናኤል ስልኩ ውስጥ አምባረቀ

አዎ ስለማታውቅ ነው ያለማቋረጥ የምናሰቃያት...በአንተ ኃጢያትአበሳዋን የምናሳያት፡፡ የምታውቀው ነገር ቢኖር በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ማንኛውንም ምስጢር ደብቃ መያዝ አትችልም ነበር…ግን አሁንም እጅህን እስካልሰጠኸን ድረስ የጀመርነውን ኣናቋርጥም፡፡ አስታውስ.በማህፀኗ የያዘችውኝ፡፡”

ናትናኤል በስልኩ ውስጥ ድጋሚ የስቃይና የጣር እሪታ ተሰማው፡፡
“ናትናኤል ” ያው ድምጽ ቀጠለ፡፡ “ጊዜ የለንም፡፡ ያለህበትን ቦታ ንገረን፡፡ እዚህ እሷጋ እናመጣሃለን እመነኝ፡፡” “ለሶስተኛ ጊዜ ያው የስቃይ ድምጽ በሩቁ በረጅሙ አንቋረረ፡፡

ናትናኤል ጉሮሮውን ተናነቀው ጭንቅላቱን ነዘረው፡፡ ዓይነ ተጭበረበረበት

“ተዋት! ተዋት! በቃ .. ድሬዳዋ ነኝ”
“አውቃለሁ ድሬዳዋ መሆንህን፡፡ ግን ድሬዳዋ የት?”
“ሰፈሩን አላውቀውም፡፡ ትንንሽ ቤቶች ያሉበት ኣካባቢ ነው፡፡”
ናትናኤል ጭንቅላቱ ውስጥ የሚነዝረውን ስቃይ መቋቋም አቃተው፡፡
“በአካባቢህ ምን የሚታይሀ ነገር አለ? ሆቴል.…ህንፃ ማንኛውም
ምልክት:”
“ቤት ውስጥ ነው ያለሁት፡፡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡”
“ስልክ ቁጥሩን ንገረኝ፡፡”
ናትናኤል የስልክ ቁጥሩን አነበበለት፡፡
“ጥሩ፡፡ የትም ሳትነቃነቅ እዛው ባለህበት ጠብቀን፡፡ ካልቨርት አብሮህ ነው ያለው?”
“አይደለም:: ግን ቅርብ ነው፡፡ ላመጣው እችላለሁ፡፡” አለ ናትናኤል
በጭንቀት እየተውተረተረ፡፡

“ጥሩ፡፡ በፍጥነት ፈጽመው፡፡ : ተጠንቀቅ፡፡ ካልቨርት ሳይነግርህ
እንዳልቀረ እርግጠኛ ነኝ፥ እኛ ብቻ አይደለንም ከተማውን እያሰስን ያለነው፡፡
ናትናኤል በእነሱ እጅ መውደቅ የለብህም፡፡ ነጮቹ:: ተግባባን?”

“አዎ… አዎ አያገኙኝም… በጥንቃቄ አመጣዋለሁ… ብቻ ርብቃን አታሰቃይዋት፡፡ ምንም አታውቅም፡፡”

“ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ማንም የቀሚሷን ጫፍ አይነካም! እመነኝ ናትናኤል፡: ቅሪት የሆነችን ሴት ቀሚስ ገልቦ ማሰቃየት ምን ያህል አስጠሊታና ሰቅጣጭ እንደሆን ብታውቅ ችግሬን ትረዳልኝ ነበር፡፡ በእጄ
ያለችው ሴት ርብቃ እርጉዝ ነች! ለማድረግ የምጠየፈውን እያደረግሁ ነው፡፡ አንተ ብቻ ነህ ልታቆመኝ የምትችል፡፡”

ናትናኤል ስልኩን ዘግቶ ለጥቂት ደቂቃዎች ባለበት ፈዝዞ ቆመ፡፡ በደም የተጨማለቀ፣ ያበጠና የዘጓጎነ ፊት ታየው:: የእርጉዝ ሴት ፊት… የርብቃ:: ሁለት እጆቹን ዓይኖቹ ላይ ጭኖ ፊቱ ላይ የተደቀነውን አስፈሪ ምስል ሊያጠፋው ታገለ። የዘጎነና የበለዘው ምስል ግን ይበልጡን እየደመቀ ደም እየጎረሰ እየደፈረሰ… እየረሰረሰ መጣበት፡፡ ምንም የማታውቀው የእሱ ርብቃ በሱ ኃጢያት ቀሚሷ ይዋ ትቦጫጭቆ ጀርባዋ ተገልቦ ራቁቷን በጅራፍ ስትተለተል ታየችው... ሰውነቱን ኣንቀጠቀጠው፡፡

ፈጠን ብሎ ስልኩ ካለበት ክፍል ወጣና የየምስራችን እናት አስከትሎ በጥድፊያ እየተራመደ ወደ ካልቨርት አመራ፡፡

“ደህና ነች?” አሉት የየምሥራች እናት መንገድ ላይ ከጎን ከጎኑ ሱክ ሱክ እያሉ፡፡

"እ..."

“ደህና ነች ወይ አልኩ… ምስርዬ.… " አሉት ፈገግ ብለው::
“ታገናኘኛለህ ብዬ ስጠብቅህ'ኮ ስልኩን ዘጋህብኝ፤ ምነው?»

“እ…እ… አዎ… አ… ደህና ነች” አላቸው፡፡ ኮረኮንቹ መንገድ እየተወለካከፈ እየተጣደፈ ወደ ካልቨርት፡፡
🥰1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...ዛሬም በሱ የቡድን መሪነት ውስጥ በአባልነት በታቀፈው በሸጋው አንበሴ ቁመናና የዐይኖቹ ውበት ተማርካ በመልከ
መልካምነቱ ልቧ ተሸንፎ በፍቅሩ ነዳለት ጎንቻን ደብቃ ፍቅሯን እያስኮመኮመችው አለማቸውን እየቀጩ ነው።

ይሄንን ያላወቀው ጎንቻ ደግሞ ስሞኑን በብዙ አፈላላጊ ከተገናኘው ሰው ላይ ቀብድ ለመቀበል ተፈልጎ ሄዷል መቀስ ያንን ሹልክ እያለ እየመጣ
የሚቀምሰውን ፍቅር ለመቅመስ በዚያውም ተጨማሪ ገንዘብ ለመበደር ነበር የጎንቻን እግር ጠብቆ የገባው፡፡ እንደተገናኙ ተቃቀፉና አልጋው ላይ ወደቁ፡፡ ያንን የስርቆሽ ፍትወት ከፈፀሙ በኋላ በጀርባቸው ተንጋለሉ። ዓለሚቱ ልቧ ድው ድው ማለት ጀመረ።ስርቆሹን ትወደዋለች፡፡
ይጣፍጣታል።የሚያስከትለውን መዘዝ ስታሰላስለው ግን ትሰጋለች። ትርበተበታለች። በዚያ የስሜት እሳት ውስጥ ገብታ ፍሙን፣ ረመጡን እስከምታጣጥመው ድረስ ምንም አይነት የፍርሃት ስሜት አያድርባትም፡፡አደጋው አይታወሳትም፡፡ ሁሉ ነገር ጎልቶ የሚታያት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ አሁንም የፍትወት ስሜቷን ካረካች በኋላ ስጋቷ በረታና መተንፈስ ግድ ሆነባት።

"አይታወቅም የሱ ነገር ወይ በመሀል ከተፍ ይላል። ቶሎ ቶሎ ተጨዋውተን በጊዜ ብትሄድ አይሻልም?" አለችው፡፡
"ልክ ነሽ፡፡ እውነትሽን ነው። እኔም ሳስበው ነበር። እሱ እኮ ስላቢ ነው፡፡ በድንገት ከች! ሊል ይችላል ፡ጉሮሮ ለጉሮሮ ሳንያያዝና በእጄ ሰበብ ሳይሆንብኝ ብሄድ ይሻላል” አለና ከአልጋው ላይ ተነስቶ ሱሪውን ማጥለቅ ጀመረ፡፡ እሷም ተነሳች፡፡ዓለምዬ ዛሬ ችስታ ወግሮኛል ሁለት መቶ ብር ትጨምሪልኛለሽ፡፡ አንድ
ላይ ወደ አንድ ሺህ መጠጋቱ ነው" አላት፡፡“ትቀልዳለህ እንዴ አንበሴ?! እንዲያውም ስሞኑን የሌለበትን የገንዘብ
መቆጣጠር ፀባይ እያሳየ ነው፡፡ አሁን በድንገት ውለጂ ቢለኝ ምን እመልስለታለሁ? ዛሬ ሁሉንም ይዘህ ትመጣለህ ብዬ ነበር የገመትኩት። አንተ ግን ጭራሽ በላይ በላዩ ልትጨምር ትፈልጋለህ፡ የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታልሆነ አሁንስ!" በስጨት ብላ ተናገረችው።

አንበሴ ያልጠበቀው ነበር፡፡ በሱ ቤት ተደብቆ እየመጣ የሚያቀምሳት ፍቅር ጣፍጧት ስለሚጠይቃት ገንዘብ ደንታ የሌላት መስሎት ነበር።
ተወድጃለሁ የፈለኩትን እንድታደርግልኝ ባዝዛት ትፈፅማለች ባይ ነበር፡፡
ለእንቢታው አንደበቷ የሚፈታ የተጠየቀችውን ገንዘብ ላጥ አድርጎ ለመስጠት እጅዋ የሚያጥር አልመሰለውም ነበር፡፡ በዓለሚቱና በገንዘብ መካከል ግን ቀልድ አልነበረም።
ሲቀር ፍቅሩ ተሽቀንጥሮ ይቀራል እንጂ ብሯን የምትበትን ሆና አልተገኘችም። እንደዚያም ሆኖ ግን ለሱ እጇ ብዙም አይጨክንም ነበር። ከዚያ በፊት ያለውን በደስታ ነው የሰጠችው
ዛሬ በዛባትና ፊት ነሳችው እንጂ፡፡ ባሏ ጎንቻ የቡድኑ ገንዘብ አዛዥ ሆኖ የበለጠውን ድርሻ መውሰዱ ውስጥ ውስጡን በቅናት ቢያቃጥለውም ቁልፉን በእጁ ይዟል። የገንዘቡን ካዝና የዓለሚቱን ልብ ተቆጣጥሯልና
በተዘዋዋሪ መንገድ እየተካስ ይፅናናል።ይሄ በመሆኑ እንጂ እንደ ጎንቻ አያያዝ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ድብልቅልቅ ብለው በተጣሉ ነበር፡፡ ዓለሚቱ ቀስ ትልና ብሩንም ፍቅሩንም እየሰረቀች ትሰጠዋለች። ይቀዘቅዛል፡፡

"ተይ እንጂ ዓለሚቱ! ምን ማለትሽ ነው? ገንዘቡን ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልገው ነው እኮ!ደግሞ ብዙ ችግር እንደሌለብኝ ታውቂያለሽ፡፡ በሙሉ እምነት ነው ወዳንቺ የመጣሁት። ዓለሚቱ ካንቺ ሌላ ማንንም ብድር
መጠየቅ አልፈልግም!"
“አንበሴ ሙት አትቀልድ! ይልቁንስ የወሰድከውን ቶሎ መልስ እንዳን
ጣላ!"
ትቀልጃለሽ እንዴ ዓለሚቱ?"
አልቀለድኩም አንተ ነህ የምትቀልደው!"
“ኧረ በናትሽ ዓለሚቱ?!"
“አይገባህም እንዴ?!" ቁጣዋ ባሰ...የበለጠ ተደናገጠ፡፡ ፕሮግራሙ ሊከሽፍ ነው፡፡ የበርጫውና የጨብሲው... ከአዲሷ የሴት ጓደኛው ጋር የያዘው ቀጠሮ ዜሮ…ደግሞም ባለሥልጣን ነኝ ብሉ የዋሻት፣ ልቡ የወደዳት ቆንጆ ልጅ....
“በቃ እንጣላ?!"
«አንበሴ ሙት በዚህስ እንጣላ! በዚህስ የፈለከውን አምጣ እንጂ አላደርገውም! ትንሽ አታስብም እንዴ?! ያምነኛል እንጂ ገንዘቡን ያውቀዋል እኮ! ምን ልለው ነው በተለይ እንደዚህ መንገብገቡ ከሴት ጋር ቀጠሮ ቢኖረው ነው ብላ ስለገመተች ጨከነችበት።

“በዚህ ላይ አንተ ጋ ያለው ብቻ አይደለም፡፡ በአራጣ ያበደርኳቸው
ብዙዎቹ መክፈል እያቃታቸው አሮጌ ዕቃ እያግበሰበሱልኝ ነው። አሮጌ እቃ ለኔ ምን ያደርግልኛል? የረቡ ዕቃዎች ያየሃቸው ሀብሎችና ቀለበቶች ብቻ ናቸው። ሌላው ዝባዝንኬ ቅራቅንቦ ነው!”
"ገባኝ!... እኔን እኮ እንደሌላው አራጣ ተበዳሪ ማየት የለብሽም። ማወቅ ያለብሽ ነገር ገንዘቡን በጋራ የሰራነው መሆኑን ጭምር ነው! የንዴት ትኩሳት ማተኮስ ጀመረውና ሳያስበው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ የወጣ
ንግግር ተናገራት፡፡

"ኧረ? በጋራ?! በል ተወው! የራስህን ድርሻማ እየላፍከው ሄደሃል። ከዚህ ውስጥ ሰባራ ሳንቲም የባለቤትነት መብት የለህም! በጠየከኝ ቁጥር እያ
ወጣሁ ያስታቀፍኩህ እኮ የተግባባን መስሎኝ ነበር! ለካስ የራስህ ገንዘብ አድርገህ ነዋ እስካሁን ያልመለስከው?! አንበሴ ሙት እንደዚህ አይነት የማይረባ አስተሳሰብ ያለህ ሰው አትመስለኝም ነበር፡፡ ወይ የሰው ነገር? ለካ ሰው እያደር ነው የሚታወቀው?! እና የወሰድከውን ለመመለስ ሀሳብ የለህም ማለት ነው?! እንዴት ያለኸው ቀላል ነህ ባክህ?! ይህንን ያዳፈረህ ጎንቻን ደብቄ ቀሚሴን ስለገለብኩልህ ይሆን እንዴ ? እሱ ይሆናል
እንጂ ያናናቀን! ለምነህ የወሰድከውን ከምስጋና ጋር መመለስ ሲገባህ ጭራሽ..." ፊቷ በንዴት ቀላ፡፡
“እና አሁን አትሰጭኝም?!"
“እስቲ ድብን ያደርግህ እንደሆነም ጉድ አያለሁ! ሰባራ ሳንቲም! " አንበሴ የዓለሚቱን ንዴት ሲመለከት አጉል እልህ ምንም ዋጋ እንደሌለው ተረዳ፡፡ ከብዙ ጉልበት ትንሽ ብልሃት የምትበልጥበትን ጊዜ አሰበ፡፡ በዘዴ አባብሎ ብዙ ነገር ማድረግ ሲችል ብጥብጥ ፈጥሮ ቢሄድ ራሱን ይጎዳል እንጂ እሷን አይጎዳትም ይሄን ማመዛዘን ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ ረገበና ልምምጡን ቀጠለ፡፡ ከውስጡ ንዴትና ብሽቀት ቢያቃጥሉትም ከውጭ ሌላ ሆነ፡፡ ፈገግ አለ፡፡

“እሺ ዓለምዬ እንዳልሽው ይሁን። ማወቅ ያለብሽ ግን እኔን ልቤን የነሳሽው ጣፋጭ ፍቅርሽ እንጂ ገንዘብሽ ያለመሆኑን ነው። ገንዘብ ገደል ይግባ! ፍላጎቴ ፍቅር ሳይሆን ገንዘብ ቢሆን ኖሮ በሴት ብር ብቻ ፎቅ ቤት መስራት እችል ነበር፡፡ ያንን ግን አልፈልገውም፡፡ እዚህ የባልሽን ኮቴ እየጠበኩ ስር ስርሽ የሚያስሮጠኝ ፍቅርሽ ብቻ ነው። አሁንም ቢሆን እኔ የምፈልገው ገንዘብሽን ሳይሆን ፍቅርሽን ነውና አለብህ የም
ትይኝን በሙሉ አምጥቼ እወረውርልሻለሁ። አንቺነትሽን እንደዚህ የለወጣው ገንዘብ ከሆነ ካንቺ የሚተርፍ ገንዘብ አስታቅፍሻለሁ። እውነቴን
ነው የምልሽ ሩቅ ቦታ ስላስቀመጥኩት እንጂ እንኳን ለራሴ ለሌላ የምትርፍ ስው ነኝ ጉራውን ቸረቸረላት።
ዓለሚቱ ልቧ ወከክ... አለ፡፡ እውነትም አንበሴ ገንዘብ በገንዘብ ሲያደርጋት ታያት። በአምስቱ ጣቶቹ ላይ የደረደራቸው የወርቅ ቀለበቶቹ በየቀኑ የሚቀያይራቸው ፋሽን ልብሶቹ ሁሉ ነገሩ የገንዘብ ችግር የሌለበት መሆኑን ይመሰክራሉ። ገንዘብ ስጠኝ ብላ ባለመጠየቋ እንጂ ብትጠይቀው ሊያንበሸብሻት እንደሚችል ተስፋ አደረገች፡፡ በአንድ ጊዜ' በደስታ
👍2😱1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ወደ ሲዳሞ በስተርጅና ዕድሜዬ ብቅ ማለት አስባለሁ፡፡» ካለ በኋላ ወደ ሃምሳ አለቃው ቀና በማለት ፈገግ እያለ
«ግን ደግሞ ከሀገሬ በፊትእኔ ቀድሜ ካረጀሁ » አለው
«አልገባኝም::»
«የሀገር እርጅና፡፡»
አስቻለው ወደ መሬት አቀረቀረና ራሱን ወዘወዘ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከንፈሩን ነከሰ፡፡ ስሮቹ በግንባሩ ላይ ተገተሩ። ፊቱ ተከፋ፡፡
«አስረዳኛ የኔ ወንድም አለው»
የሃምሳ አለቃ ክንዶቹን አቆላልፎ
ጠረጴዛውን በመደገፍ አስቻለውን እየተመለከተ።
«ሀገር በገዳዮቿ መዳፍ ወስጥ እስከ ገባኝ ድረስ ምናልባት እንደ ሰው አትቀበር እንደሆነ እንጂ ማርጀት ቀርቶ ልትሞትም ትችላለች» አለ አስቻለው ፊቱ ክፍት እያለውና ጣሪያ ጣሪያ እያየ፡፡
«ስትል?» ሲል ጠየቀው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ፡ የአስቻለው አነጋገር ሚስጥሩ ለጊዜው ባይገባውም ግን ደግሞ በውስጡ ብዙ ነገር ስለመሆኑ ከወዲሁ ገምቷል።
«አየህ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ቀጠለ እስቻለው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ የህዝብና መንግስት ከተኮራረፈ ምድርና ሰማያዋም ይቀያየማሉ። ያኔ ከዜጎቿ ልብ
ውስጥ ተስፋ ይጠፋል፡፡ ተስፋ የሌለበው ሕዝብ ጭካኔ ይወልዳል።በተለይ ደሃ ከጨከነ
ጠላት የሚያደርገው የገዛ ሀገሩን ነው፡፡ አምባገነኖች የቱንም ያክል
ጡንቻቸው ቢፈረጥም ድሀን ማስተዳደርና መቆጣጠር አይችሉም፡፡ እንዲያውም
በቁጣው እነሱንም ያጠፋቸዋል፡፡ ያኔ ገዢና ተጎዢ አይኖርምና 'ጥፋት ይነግሳል::በዚህ ጊዜ ሀገር መታመም ትጀምራለች። ታዲያ ይህ ከሆነ ሀገር አልሞተችም፣?
የሃምሣ አለቃ ሲል ጠየቀው።
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ባላሰበውና አስቦትም በማያውቅ የተለየ እሳቤ ወስጥ ገባ፡፡ አንዳች አስፈሪ ስሜት ውስጥ ገባ። አንዳች አስፈሪ ስሜት መጣበት እስከዛሬም እንደ ሰው ስለመኖሩ ተጠራጠረ። ፍርሀትና ጭንቀትም አደረበት። በረጅሙ ተነፈሰና
«አስደነገጥከኝ አስቻለው» አለው፡፡
«ሊያስፈራም ሊያስደነግጥም ይችላል ሃምሣ አለቃ። በአሁኑ ሠዓት ሀገራችን ታማለች። ህመም ደግሞ በቶሉ ያስረጃል፡፡ ከሐገሬ በፊት እኔ ካረጀሁ ያልኩህም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አለና አስቻለው የሃምሳ አለቃን ትኩር ብሎ
ተመለከተው።
«ይህ ገባኝ አስቻለው አለና የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እንቆቅልሽ የሆነብኝ ግን ለምን ከዚያ ወዲህ ወደ ዲላ ላለመሄድ እንደነሰንክ ነው፡፡ ምናልባት
ይህም ምስጢር ይኖረው?» ሲል ፈራ ተባ እያለ ጠየቀው።
«ምስጢር የለውም፡፡ እኔ ግን መሄድ አልፈልግም::»
«አይመስለኝም አስቻለው፣ ይህ ውሳኔህ ምስጢር ሳይኖረው አይቀርም፡፡አይዞህ ምስጢር ቢኖረውም በበኩሌ እጠብቅልሃለሁና ንገረኝ፡፡» አለው።
«ወታደር አይደለህ! ለምስጢርማ ማን ብሎህ» አለና አስቻለው ፈገግ አለ፡፡
«ሙያዬ ስለሆነ ሳይሆን ባአንተ በመታመን።»
አስቻለው ጭንቅ አለው። የሃምሳ አለቃው ጥያቄ ከልቧ የመነጨ መሆኑ ይገባዋል ግን ደግሞ የሆዱን ምስጢር ለማንም ላለመናገር ወስኗል የሃምሳ አለቃው ልመና ግን መንፈሱን ወጥሮ ያዘው።ወደ ጣርያ ወደ መሬት ጎንበስ ቀና ካለ በኋላ
በቅድምያ በረጅሙ ተነፈሰ።
የሀምሳ አለቃውንም አየት ሲያደርገው በፊቱ ላይ የጭንቅ ስሜት አነበበበት። መጨነቁም ስለ እሱ መሆኑ ገባው። ከዚያ በኋላ ፍንጭ ሊሰጠው ፈለገ።
«አየህ ሃምሳ አለቃ! እኔ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዲላ ብሄድ ያለ ጊዜዋ
የምትረግፍ አበባ አለች፡፡» አለና እንባው ከዓይኑ ላይ ዝርግፍ አለ፡፡
«እንዴት»
«አበባ የምልህ በእርግጥ ተክል አደለችም። ሔዋን ተስፋዬ የምትባል የሰው ልጅ ናት:: የምወዳት የምትወደኝ፣ የምሳሳላት የምትሳሳልኝን የመጀመርያ ፍቅረኛዩና እጮኛዬ ነበረች፡ ልንጋባ ሁለት ወር ሲቀረን ነበር እኔ ድንገት ወደዚህ ወደ አስመራ የመጣሁት።አሁን ግን ይህው እንደምታየኝ ግማሽ አካሌ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ያለ ጊዜዋ ትረግፋለች የምልህም ያቺ አበባ እንዲህ ሁኜ ብታየኝ
የሚፈጠርባት፣ የስሜት ስቃይ ስለማውቅ ነው፡፡ እንደኔ እግሯ ባይቆረጥ እንኔ ፊቷ ባይጠበስ! እንደኔ ጆሮዋ ባይበላሽ፣ እንደኔ ዓይኗ ባይጠፋ እኔን በዚህ ሁኔታ
ካየች ግን በንዴት በቁጭት በብስጭትና በፀፀት የአእምሮ ህመምተኛ ትሆንብኛለች ብዬ እሰጋለሁ። ታዲያ ይህን እያወኩ ሄጄ የዚያችን አበባ ህይወት ላበላሸው ሃምሳ አለቃ?» አለውና በጉንጩ ላይ ይንቆረቆር የነበረ እንባውን በእጁ መዳፍ ሙሉ ሙዥቅ አድርጎ ጠረገው።
«አታልቅስ የኔ ወንድም!» አለው ሃምሣ አለቃ እሱም ዓይኑ በእንባ
እየሞላ።
«እኔማ ገና ብዙ ብዙ አለቅሳለሁ ሀምሳ አስቃ! እኔ ዕድለ ቢሱ ያቺን እድለ ቢስ አድርጊያት ቀርቻለሁ:: ስለ ሔዋን ተስፋዩ ገና ብዙ አለቅሳለሁ::በህይወት እስካለሁ ልረሳት አልችልምና ሳለቅስ እኖራለሁ፡፡» አለና አስቻለው
አሁንም እህህህህ …! በማለት መላ ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በለቅሶ ሲቃ ተርገፈገፈ።
“ምናልባት ትጠየፈኛለች ብለህ ሰግተህ ይሆን የኔ ወንድም?» ሲል ሃምሣ አሐቃ የራሱንም አይን እየጠረገ ጠየቀው።
«ፍጹም ሀምሳ አለቃ! የኔዋ ሔዋን መልኳ አበባ እንደሚመስል ሁሉ
ትጠየፈኛለች ብዬ አይደለም፡፡ የኔዋ ሔዋን እንዲህ ያለ ተፈጥሮ የላትም። በራሴ በኩል ግን ከእንግዲህ እኔ ለእሷ አልገባም ብዬ ወስኛለሁ።» አለ እያለቀሰ።
“ታዲያ እሷ እየጠበቀችህ ቢሆንስ?»
«ተስፋ እንድትቆርጥ ብዩ የበኩሌን አንድ ርምጃ ወስጃለሁ። የምትኖረው በኔ ደመወዝ ስለነበር እንዲቋረጥባት ብዬ የመንግስት ስራ ለቅቄ በአንድ የፈረንጆች
ግብረ ሰናይ ድርጅት ክሊኒክ ውስጥ በአስተርጓሚነት ተቀጥሬአለሁ::»
«ምናልባት ርሀብ ላያሽንፋት ቢችልስ?»
«ይህ እኔንም ያሰጋኛል። ግን ልጅ ናትና ከመቆየት ሀሳቧን ብትቀይር
እያልኩ እጓጓለሁ:: በዚያ ላይ ደግሞ ገና እኔ እዚያው እያለሁ ሊድሯትና ሊያገቧትም እያሰቡ የሚያንዣብበ ሰዎች ነበሩና በእነሱ ጫና ተሸንፋ አዲስ
ህይወት ብትጀምር እያልኩም እፀልያለሁ::»
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ የአስቻለውን ምኞትና ሃሳብ ሲሰማ ቆይቶ ወደ ዲላ ላለመሄድ የወሰኑበት ምክንያት ሲገባው በራሱ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቁስል አመመውና ለአስቻለው ይገልፅለት ዘንድ ስሜቱ ገፋፋው።
«ስማ እስቻለው፡፡» አለው ፍዝዝ ትክዝ ብሎ እየተመለከተው እኔም እንዳተው ተገድጄ ወደዚህ ሀሄገር የመጣሁ ነኝ መጥቼ የፈፀምኩት ነገር ቢኖር ሰው መግደል ነው።እላዬ ላይ የምታየው የሃምሣ አለቅነት መአረግ የተሰጠኝም ሰው በመግደሌ ነው። የገደልኩት ደሞ የሀገሬን ልጆች ወንድሞቼን ነው ሶስት አራት ገድዬ ከሆነ በዛው መጠን በርካታ ዘመድ አዝማዶቻቸውን አስለቅሻለሁ አሳዝኛለሁ በዚህ ስራዬ ደግም ተሸልሜበታለሁ። ታድያ እኔ ይሄን ያህል የህሊና እዳ ተሸክሜ ወደ ሃገሬ ልገባ ስቸኩል አንተ ልታክም መተህ ራስክ ከቆሰልክ ልትረዳ
መጥተህ ራስህ በተጎዳህ ልትጠግን መጥተህ ራስክ ከተሰበርክ ምን የህሊና የፀፀት አለብህና ምን የሚያሳፍር ነገር ሰርተሃልና ከዚህ አይነት አሳዛኝ ውሳኔ ላይ ልትደርስ ቻልክ?» ሲል ጠየቀው።
«ሀሳብህን አደንቃለሁ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ጀመረ አስቻለው «ልዩነቱ ግን አንተ የገደልካቸው ኢትዮጵያውያን ሞተው አርፈዋል። ቤተሰቦቻቸውም እርማቸውን አውተው ተገላግለዋል።ፀፀቴ ያለው በአንተ ልብ ብቻ ነው።
👍10
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ከየቤቱ መስኮት እየተንጠላጠለ ይሳሳቃሉ፣ ወጣቶች የነገሩን ምንነት ሳያጤኑ ጥልቅ ይላሉ፡፡ «ተነስ ተንቀሳቀስ» እያሉ ጩኸት ያስተጋባሉ፡ ሩብ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፓሪስ ከተማ ላይ የሆነውን ላውጋችሁ።
በየአውራ ጎዳናው፣ በየገበያ ቦታ፣ በየመንደሩ ትንፋሽ ያጠራቸው ሰዎች፣ሠራተኞችና ተማሪዎች፣ «ተነስ፣ ተንቀሳቀስ፣ ክንድህን አንሳ» እያለ በአንድ ቋንቋ ይጮሃሉ፡፡ የመንገድ መብራት፣ መስተዋት፣ የመጓጓዣ ጋሪዎችንና
ሠረገላዎችን ይበረብራሉ፣ ድንጋይ ይወረውራሉ፣ ቤት ውስጥ እየገቡ የቤት እቃ ያንኮታከታሉ፣ ሰሌዳ ይዘው በየመንገዱ ይዞራሉ፡፡ ማን
አስተባበራቸው? ማን አነሳሳቸው? ማን ያውቃል!

የአድመኞቹ ወላፈን እንደ ጭድ እሳት ተቀጣጠለ፡፡ በሦስት ሰዓት
ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑትን ስፍራዎች ከቁጥጥራቸው ሥር አደረጉ፡፡ ከሰዓት በኋላ ወደ አሥራ አንድ ሰዓት ገደማ የፓሪስ ከተማን |
ሦስት አራተኛ የሚሆነውን ክፍል ያዘ:: ይህም ከድንጋይ ውርወራ ወደ ጦር መሣሪያ መጨበጥ አሸጋገራቸው:: አድመኞቹ የመሣሪያ መጋዘን ስለማረኩ የጦር መሣሪያ ከዚያ ዘረፉ:: በአሥራ ሁለት ሰዓት ቅልጥ ያለ ዝርፊያ
ተጀመረ።

በአንድ ፊት አድመኞቹ በሌላ አቅጣጫ የመንግሥት ወታደሮች
ሥፍራ ሥፍራቸውን ያዙ፡፡ ተኩሰ ተጧጧፈ፡፡ ለወሬ ሞትኩ ያለ፣
ወደፊት በሚሆነው እጠቀማለሁ ብሎ ያለመ፤ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ
ጭምር ሁኔታውን ለማየት እየተሽሎከሎከ ወደ ጦር ሜዳው አመሩ፡፡እንደ እነቪክተር ህዩጎ ያለ አልጠግብ ባይ ከእሳተ ገሞራ ውስጥ ገብቶ መውጫ በማጣት ተቅበዘበዘ፡፡ ከጦርነቱ፡ መካከል በመግባታቸው ጥግ ይዘው
አውጣን» ከማለት በስተቀር ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡ ቅልጥ ያለ ጥይት እሩምታ ግማሽ ሰዓት ወሰደ:: የጦሩ ክፍል በያለበት መሯሯጥ፣መንቀሳቀስ ሆነ፡፡ ከጦር ሜዳው በብዛት የጦር ኃይል ጎረፈ:: ውጊያው ፓሪስ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

የጦር ኃይሉ እንዳላ መንቀሳቀሱን የተመለከተ ሕዝብ ወደኋላ መሸሽ
ጀመረ፡፡ በየአቅጣጫው ተንሰራፍቶ የነበረው ሰልፈኛ እንደመበተን አለ::ትርምስምሱ ወጣ:: አንዳንዱማ ፈሪ በሩጫ እግሬ አውጪኝ አለ፡፡

ዝናብ በሀይል ይጥላል:: ከዚህ ትርምስ ውስጥ አንድ ልጅ ውራጅ
እቃ ከሚሽጥበት ሱቅ አካባቢ ብቅ አለ፡፡ አንዲት አሮጊት ሽጉጥ ይዘው መቀመጣቸውን ስለተመለከተ ልጁ ወደ ሴትዮዋ ሮጠ
«እማማ፣ አንድ ጊዜ ሽጉጥዎን ያውሱኛል?» ሲል ጠየቃቸው:::

ሽጉጡን ለማግኘት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ወዲያው መሣሪያውን ከእጁ አስገብቶ ወደ መጣበት ተመልሶ ሮጠ፡፡

ልጁ ከአሁን ቀደም ያነሳነው ሚስተር ቴናድዩ ከእስር ቤት እንዲያመልጥ የረዳውና ጋቭሮች የሚባለው ነበር፡፡ መንገድ ከጀመረ በኋላ ነበር ሽጉጡ
ጥይት እንደሌለው የተገነዘበው:: ቢሆንም መንገዱን ቀጠለ፡፡

እነ ኩርፌይራክና ኤንጆልሪስ ከቁጥጥራቸው ስር ካደረጉት ሰፈር ደረሰ:: ከሌላ አቅጣጫ ሌሎች በድኖች የሚመሩት የአድመኞች ቡድን መጥቶ ሲደባለቅ ተመለከተ፡፡ ጋቭሮችም አብሮ ከሰልፈኞቹ ጋር ተደባለቀ::

««ወዴት ነው የምንሄደው?» ሲል ጠየቀ::

‹‹ተከተለን» ሲል ኩርፌይራክ መለሰለት::

የረብሻው ቀንደኛ መሪዎች ከአፍ እስከ ገደፍ ታጥቀዋል:: ከኋላ
የተከተላቸው ጀሌ አንዳንዱ የጦር መሣሪያ ሲይዝ አንዳንዱ ዱላ ብቻ ነው የያዘውን ፡፡ ከሠራዊቱ መካከል አንድ በእድሜ የገፉ ሽማግሌዎም ነበሩ::
ሽማግሌው ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ አልያዘም:: ግን በጣም እየተቻኮለ ነበር የሚሄዱት፡፡ ፊታቸውን ሲያዩት ከአሳብ ባህር የሰመጠ ይመስላል፡፡

ጋቭሮች ከሩቁ አያቸው::
«ያ ማነው?» ሲል ኩርፌይራክን ጠየቀው::
«አንድ ሽማግሌ ነዋ!» ሲል መለሰለት::
ከአሁን ቀደም ያየናቸው መሴይ ማብዩፍ ነበሩ::
ሽማግሌው ፊት ለፊት ከሚሄደው መስመር ሊደርሱ ምንም ያህል
አልቀራቸውም::

«ምን ዓይነት ቆራጥ ሽማግሌ ናቸው!» ሲሉ ተማሪዎቹ አጉረመረሙ። ማን እንደሆኑ ለማወቅ ተማሪዎቹ ጊዜ አልወሰደባቸውም ገዳም ውስጥ
ይኖሩ እንደነበር የሚያውቋቸው ሰዎች በሹክሹክታ ስማቸውን አስተጋቡ ሠራዊቱ አንዱን ጎዳና ጨርሶ ወደ ሌላው ተሸጋገረ፡፡ ጋቭሮችም መጓዙን ቀጠለ።

ብዙ በተጓዘ ቁጥር የሠራዊቱ ቁጥር እየጨመረ ሄደ፡፡ አንድ ግዙፍ ሰውነት ያለው ረጅም ሰው መጥቶ ተደባለቀ፡፡ ሽበት ጣል ጣል አድርጎበታል ፡መሪዎቹ ይህ ሰው ማን እንደሆነ አላወቁትም፡፡ ግን ወደ እነርሱ ለመጠጋት
በጣም ይፈልጋል፡፡ ጋቭሮች በሚያዜመው መዝሙር ተመስጦ ስለነበረ ሰውዬውን ልብ አላለውም፡፡ ልጁ መዝሙር ሲሰለቸው ያፏጫል፤ አንዳንዴ
ያንን ጥይት የሌለውን ሽጉጡን ያሻሻል፡፡

ሰልፈኛው መንገዱን ቀጥሎ እንደአጋጣሚ ሆኖ በኩርፌይራክ መኖሪያ ቤት ደጃፍ ያልፋል፡፡

«ጥሩ አጋጣሚ ነው» ይላል ኩርፌይራክ፡፡ «ቆቤ ጠፍቷል፤ ጠዋት ደግሞ ቦርሳዬን ረስቼ ነው የመጣሁት፡፡»

ከሰልፈኛው ተገንጥሎ ደረጃዎቹን በእጥፍ እየዘለለ ወደ ቤቱ ገባ
አንድ አሮጌ ቆብና የኪስ ቦርሳውን አነሳ፡፡ ከቆሻሻ ልብስ ውስጥ
የነበረ ሌላ አነስተኛ የእጅ ቦርሳም ወሰደ:: ደረጃውን በችኮላ ሲወርድ በጨለማ ውስጥ አንድ ሰው «ሊያነጋግርህ የሚፈልግ ሰው አለ» ሲል ነገረው፡፡

በዚህ ጊዜ አንድ የተቦጫጨቀ የሴት ቀሚስ ከላይ ያጠለቀ ወንድ
ከወደ ውስጥ ብቅ ብሎ አነጋገረው:: ድምፁ የሴት እንጂ የወንድ አይመስልም:: በጣም ቀጭን ነው::

«ማሪየስን አይተውታል?»
«የለም፤ ከቤት አልመጣም::»
«ማታ ይመጣ ይሆን?»
«እኔ እንጃ፡፡ እኔ ግን ዛሬ ወደቤት አልመለስም::»
አለባበሱና ድምፁ ሴት ያስመስለው ወጣት ኩርፌይራክን አፍጥጦ አየው
ለምን አይመለሱም?» ሲል በድፍረት ጠየቀው::
«ምክንያቱም...»
«እንግዲያው አንተ ወዴት ነው የምትሄደው?» በማለት ጣልቃ ገባ፡፡
«ምን ያደርግልሃል?»
«ቦርሳህን ልያዝልህ?»
«ወደ ጦርነቱ ቦታ ነው የምሄደው?»
«አብሬህ ብሄድ ትፈቅድልኛለህ?»
«ከፈለግህ፣ እኔ ምን ቸገረኝ» ሲል ኩርፌይራክ መለሰለት:: «መንገዱ
ነጻ፣ ጎዳናው የጋራ!»

ኩርፌይራክ ይህን እንደተናገረ ከጓደኞቹ ለመድረስ በሩጫ ወጣ፡፡
እንደደረሰም የእጅ ቦርሳውን እንዲይዝለት ለአንዱ ጓደኛው ሰጠው:: ከሩብ ሰዓት ጉዞ በኋላ መለስ ቢል ወጣቱ እንደተከተለው ተገነዘበ፡፡
ለአመዕ የተነሳሳ ሰልፈኛ ብዙውን ጊዜ የሚመራው በነፋስ ስለሆነ
አንዳንዴ ወደፈለገበት ሳይሆን ወደ አልፈለገበት አቅጣጫ ነው የሚጓዘው::ይህም በመሆኑ ይህ ሰልፈኛ ሴንትሜሪ ከተባለ ሥፍራ ለመሄድ ፈልጎ ሳይታወቀው ይህን ቦታ አልፎ ከሴንት ዴኒስ ይደርሳል፡፡

ከሰላሳ ዓመታት በፊት አንድ መንገደኛ ሴንት ዴኒስ ከተባለ ሥፍራ ቢያልፍ መንገዱ እየጠበበ ሄዶ በመጨረሻ እንደ አቁማዳ ጫፍ መደፈኑን ይገነዘብ ነበር፡፡ አካባቢውን አጥርቶ የማያውቅ ከሆነማ በግራና በቀኝ በኩል
የጨለማ መንገድ መኖሩን ስለማይረዳ መድረሻ ያጣል:: ውስጥ አዋቂ ግን በእነዚህ ጠባብ የጨለማ መንገዶች ተሹለክልኮ ሊያልፍ ይችላል፡፡ በስተቀኝ
በኩል ያለውን የቀኝ መንገድ ይዞ ሲጓዝ ከአንድ መሸታና ምግብ ቤት
👍14😁2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ዳያና ላቭሴይ እውነተኛ ፍቅር በአጭር ጊዜ እንደማይለቅ በሃዘን
አስታወሰች፡፡ መርቪን በፍቅሯ የተነደፈ ጊዜ የጠየቀችውን ነገር ሁሉ
በፍጥነት ለማድረግ ደስተኛ ነበር፡፡ አንድ ነገር ከፈለገች በመኪና በመሄድ ያመጣላት ነበር፡፡ ሲኒማ አምሮኛል ካለች ከስራውም ቀርቶም ቢሆን ይዟት ይገባ ነበር፡፡ ከባሰም ለጉብኝት ፓሪስ ይወስዳት ነበር፡ የፈለገችው ሻርፕ እስኪገኝ ድረስ በማንቼስተር ሱቆች እግሩ እስኪቀጥን እየዞረ ሲያስስ ቢውል አይደክመውም፡፡ ቴአትር ቤት ገብተው በመሃል ደበረኝ ካለችው ሳይጨርሱ ቢወጡ ቅር አይለውም፡፡ ታዲያ ይሄ ታዛዥነት ከተጋቡ በኋላ ቀስ በቀስእንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ ከዚያ በኋላ የጠየቀችውን ባይነሳትም ያደርግ የነበረው
ግን በዳተኝነት ነበር፡፡ ግድ የለም ልታገስ ብሎ እንጂ እንደ በፊቱ በፍቅር
ማድረጉን እየተወ መጣ፡፡ በመጨረሻ እንደውም ትዕግስት እያጣ ሲመጣ
ሚስቱን ጭራሹን ‹‹ዞር በይ›› ማለት አመጣ፡፡
ታዲያ ማርክም እንዲህ ሊያደርገኝ ይችላል የሚል ፍርሃት አጫረባት፡

ማርክ እንግሊዝ አገር በቆየበት ጊዜ ባሪያዋ ሆኖ ነው የስነበተው
በጠፉ በሁለተኛው ቀን ተጣልተው መኝታ ለይተውነበር፡ ሆኖም እኩለ
ሌሊት ላይ እውጭ ያለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ አይሮፕላኑን እንዳልተገራ
ፈረስ ሲያሰግረው ዳያና በጣም ፈራችና ዓይኗን በጨው አጥባና ክብሯን ሽጣ ወደ ማርክ መኝታ ሄደች፡፡ እንደዚያም ሆኖ ውጤቱ አላማረም፡፡ በኋላ ወደ እኔ ይመጣል ብላ ብትጠብቅም እሱም ኩራት ልቡን ነፍቶት ሳይመጣ
በመቅረቱ በንዴት ኤሌክትሪክ ልትጨብጥ ምንም አልቀራትም:

ዛሬ ጧት ምንም አልተነጋገሩም ማለት ይቻላል፡፡ ጧት ከእንቅልፏ
የነቃችው አይሮፕላኑ ቦትውድ ሲያርፍ ሲሆን ከአልጋዋ ስትነሳ ማርክ
ወጥቶ መሄዱን አወቀች፡፡ ጧት ቁርስ ላይ መሳ ለመሳ ተቀምጠው በሃሳብ
ተውጠው ምግባቸውን ሲቆነጣጥሩ ነበር፡፡
ዳያናን መርቪን ከናንሲ ጋር የሙሽሮች ክፍልን ተጋርተው ማደራቸው
ለምን እንደዚህ እንዳናደዳት አልገባትም፡ ማርክ በዚህ ረገድ ቢያግዛት
በወደደች። በተቃራኒ አሁንም መርቪንን ትወጂዋለሽ እንዴ?ሲል
ጠይቋታል፡፡ ትዳሯንና ቤት ንብረቷን ትታ ከእሱ ጋር መኮብለሏን እያወቀ
ማርክ እንዲህ ማለቱ አናዷታል፡፡

ዙሪያዋን ስትመለከት በቀኝዋ የተቀመጡት ልዕልት ላቪኒያና ሉሉ ቤል
የቆጡን የባጡን ያወራሉ፡፡ ሁለቱም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ ስላደረ እንቅልፍ
ባይናቸው ሳይዞር ስለነጋባቸው ተዳክመዋል፡፡ በግራ በኩል የኤፍ.ቢ.አዩ ሰው ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንኪ ጎርዲኖ በጸጥታ ምግባቸውን ይበላሉ።

የጎርዲኖ እግር በእግረ ሙቅ ከመቀመጫው ጋር ተጠፍሯል፡ሁሉም
በድካም የዛሉና ነጭናጫ ሆነዋል፡፡ እንዲህ ያለ አለቅጥ የረዘመ ሌሊት
ገጥሟቸው አያውቅም፡፡
አስተናጋጁ ዴቪ ቁርስ የተበላባቸውን ሰሃኖችና ቁሳቁሶች እየሰበሰበ
ነው፡፡ ልዕልት ላቪኒያ ‹‹እንቁላሉ አልበሰለም ሞርቶዴላው ደግሞ በጣም
ሙክክ ብሏል›› በማለት ስሞታ ያሰማሉ፡ ዴቪ ቡና ቢያመጣም ዳያና
አልጠጣችም::

ማርክን ሰረቅ አድርጋ አይታ ፈገግ ስትል እሱም በፈገግታ ተቀበላት
‹‹ከነጋ አንዴ እንኳን አላናገርከኝም›› አለችው፡፡
‹‹ምክንያቱም ከኔ ይልቅ ለመርቪን ልብሽ መጥፋቱን ስላወቅሁ ነው›
ወዲያው ጸጸት ገባት፡፡ መቅናቱ ትክክል ነው፡ ‹‹ይቅር በለኝ ማርክዬ›
አለች ‹‹ልቤ ያለው ካንተጋ ብቻ ነው እውነቴን ነው››
እጁን ሰዶ እጇን ያዝ አደረገና ‹‹እውነትሽን ነው?››
‹‹እውነቴን ነው፡፡ ትናንት ምን እንደነካኝ አላውቅም››

‹‹እሺ›› አለ ማርክ፡፡
ሁለቱም አፍቃሪዎቿ አፍጥጠውባታል፡፡ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ
እንዳለባት አውቃለች፡ ከመርቪን ጋር ብቻዋን ብትነጋገር ማርክን
አስከፋዋለሁ ብላ ገምታለች፡፡ አሁን መርቪንን ትቼ ከማርክ ጋር ነው
ያለሁት ስለዚህ ማርክን ነው መደገፍ ያለብኝ ስትል አሰበች፡፡

ልቧ  ከበሮ  እየደለቀ ‹‹ማርክ ፊት የማታናግረኝ ከሆነ ልሰማው አልፈልግም›› አለችው፡:

መርቪን ደንገጥ አለና ‹‹እሺ›› አለ በብስጭት፡፡ ወዲያው ራሱን አረጋጋና ‹‹ከዚህ በፊት ያልሺኝን ተገንዝቤያለሁ፤ምን ያህል ቀዝቃዛ እንደነበርኩ አንቺም ምን ያህል ብቸኝነት ይሰማሽ እንደነበር…›› ንግግሩንቆም አደረገ፤ ዳያና ምንም መልስ አልሰጠችም፡፡ ይቅርታ ማለት ወይም መጸጸትን መግለጽ የመርቪን ባህሪ አይደለም፡፡ ምን ሊል ነው?› አለች ዳያና በሆዷ።

‹‹እስካሁን ላደረግሁት ሁሉ ይቅር በይኝ›› አለ መርቪን፡ ዳያና የመርቪን አባባል ቢገርማትም እውነቱን መናገሩን አውቃለች፡ ‹ይህ ሁሉ ለውጥ ከየት መጣ?›

መርቪን ቀጠለና ‹‹የተዋወቅን ሰሞን አንቺን ለማስደሰት ጥረት አደርግ
ነበር፡፡ እንዲከፋሽ አልፈልግም ነበር፡፡ አሁን ኑሮሽን ጨለማ ማድረጌ
ተሰምቶኛል፡ ደስታ ማግኘት መብትሽ ነው፡፡ የሰው ሁሉ ዓይን ማረፊያ እንደሆንሽ አውቃለሁ፡››

ዳያና ይህን ስትሰማ እምባዋ በዓይኗ ሞላ፡፡ የወንዶችን ዓይን መሳቧ
እውነት ነው፡፡

‹‹አንቺን ማሳዘኔ ሀጢያት ነው›› አለ መርቪን፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አንቺን ለማስደሰት እጥራለሁ፡››

ከዚህ በኋላ ጥሩ እሆናለሁ› ማለቱ ፍርሃት ለቀቀባት፡ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ እሷ ግን እንዲጠይቃት እንኳን
አትፈልግም፡፡ ‹‹ወደ አንተ ተመልሼ አልመጣም›› አለች ዳያና፡

‹‹ከማርክ ጋር ደስተኛ ህይወት የምትኖሪ ይመስልሻል?››

ዳያና ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች፡፡

‹‹ያስብልኛል ብለሽ ታምኛለሽ?››

‹‹አዎ ያስብልኛል››

ማርክ ጣልቃ ገባና ‹‹እኔን እንደ እቃ ቆጥራችሁ ስለኔ ትናገራላችሁ? አለ፡፡

ዳያና የማርክን እጅ ለቀም አድርጋ ያዘችና ‹‹እንዋደዳለን›› አለችው:
‹‹አይ!›› አለ መርቪን፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፊቱ ላይ የለበጣ ፈገግታ
ተነበበ ‹‹ትዋደዳላችሁ›› አለ፡፡
መርቪን የተለሳለሰ መሰለ፡፡ ይሄ የእሱ ባህሪ አይደለም፡፡
ወይዘሮ ሌኔሃን ሄደህ ከሚስትህ ጋር ተነጋገር አለችህ እንዴ?›› አለች ዳያና ተጠራጥራ።
አላለችም፡፡ ሆኖም ልናገር እንደምችል ታውቃለች››
‹‹ታዲያ ፈጠን ብለህ ተናገረውና ይውጣልህ›› አለ ማርክ፡፡
መርቪን ማርክን ገላመጠውና ‹ጎረምሳው አንተን እዚህ ነገር ውስጥ
የሚያገባህ ነገር የለም፤ ዳያና እኮ አሁንም ባለቤቴ ናት›› አለ፡፡

ማርክ ፍቅረኛውን ለማገዝ ‹‹ተው እባክህ!  ከዚህ በኋላ ከእጅህ ወጥታለች፤ ደግሞ ጎረምሳው አትበለኝ ሽ
ሽሜ›› አለው መርቪንን፡፡

‹‹መርቪን እዚህ አምባጓሮ ማንሳት አትችልም የምትለው ካለህ
አውጣና ተናገረው፤ አለበለዚያ አንድ ዓይነት ኃይል ያለህ አታስመስል››
አለችው ዳያና፡፡
‹‹ደህና፧ ነገሩ እንዲህ ነው›› ትንፋሹን ዋጥ አደረገና ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፤ ወደ ቤትሽ እንድትመለሺ ስጠይቅሽ ‹ምን ሲደረግ ብለሻል፧ ይሄ ሰው እኔ ማድረግ የማልችለውን አድርጎ ከሆነና ከእሱ ጋር
መኖር ደስታ የሚሰጥሽ ከሆነ መልካም እድል ይግጠማችሁ፡፡ መልካሙን
እመኝላችኋለሁ ይሄው ነው›› አለ፡፡ ከዚያም ጸጥታ ነገሰ፡

ማርክ ሊናገር ሲል ዳያና አቋረጠችውና ‹‹አንተ የተረገምክ እምነተ ቢስ
የሆንክ ሰው!›› አለች ‹‹እንዴት ያለኸው ደፋር ነህ!›› አለችና ምራቋን ጢቅ
አደረገች፡፡

መርቪን አባባሏ ግራ አጋባውና ‹‹ምነው?›› አላት፡፡
👍223🥰1