አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
458 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


#ከሁለት_ወራት_በኋላ

እንደሻው በቀለንና ራሷን በጥይት አቁስላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ከቆየች በኋላ በሁለተኛው ወሯ ሙሉ ለሙሉ ዳነች፡፡
በዚያ ጥይት ምክንያት ከላይኛው መንጋጋ ጥርሶቿ ላይ ሁለቱን አጥታለች፡፡ የግራ ጆሮዋ በመስማት በኩል ትንሽ ቅር ቢለውም ሙሉ ለሙሉ አልደነቆረም፡፡
ጥይቶቹ በተከታታይ ሾልከው የወጡበት ቀዳዳ መጠነኛ ጠባሳን ጥሉባት አለፈ እንጂ፤ ውበቷን እምብዛም የሚፈታተነው አልነበረም፡፡
ከዚህ ሁሉ ሥቃይ በኋላ ግን እቤቷ ገብታ አላረፈችም፡፡ ወንጀለኛ ናትና በቀጥታ በማረፊያ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ህግ ከሳሽነት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህጉ ተከሳሽ ሆን ብላ ተዘጋጅታ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ በአራት ጥይቶች ያቆሰለችው መሆኑንና እራሷንም ለመግደል ሙከራ ማድረጓን ከገለፀ በኋላ፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ አስፈላጊው ቅጣት እንዲወሰንባት
የተመሰረተ ክስ መሆኑን በማተት አቀረበ፡፡
ትህትና ድንበሩ ተከሳሽ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ዕለት፤ ታናሽ ወንድሟ በችሎቱ ላይ በመገኘት ክሱን
አብሯት አዳመጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላት፡፡
ስምሽ?”
“ትህትና ድንበሩ”
“ዕድሜሽ?”
"አሥራ ሰባት ዓመት”
“አድራሻ?”
“አዲስ አበባ
“ሥራሽ?”
“ሥራ ፈላጊ”
“ወላጆችሽ በህይወት አሉ?”
“አባቴ ሞቷል እናቴም የአልጋ ቁራኛ ነች”
ይህንንና መሰል ጥያቄዎችን ከተጠየቀች በኋላ “የክሱ ቻርጅ ደርሶሻል?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት፡፡
“አዎን ደርሶኛል”
ከዚያም የመሐል ዳኛው መነጽራቸውን ዝቅ አድርገው በግንባራቸው ዐይዋትና........
“ወይዘሪት ትህትና ለተመስረተብሽ ክስ እራስሽ ትከራከሪያለሽ ወይስ?
ጠበቃ ታቆሚያለሽ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡላት፡፡
ቀስ ብላ ሻምበል ብሩክን አየችው፡፡ የመከራትን አስታወሰች፡፡
“ድሃ ስለሆንኩ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ?” የሚል መልስ ሰጠች፡፡
ይህንን መልስ ስትሰጥ በተቻላት መጠን ድምጿ እንዲሰማ ጮክ ብላ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ በጥብቅና ሙያው የታወቀው አቶ ምንውዬለት ተዘራ ለተከሳሽ ጠበቃ እንዲሆንላት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ አቶ ምንውዬለትም ትእዛዙን በደስታ ተቀበለ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰችበት ወንጀል በንባብ እንዲሰማ ተደረገ፡፡
“በተመሰረተብሽ ወንጀል ጥፋተኛ ነሽ አይደለሽም?” ተብላ ተጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ጠበቃው አቶ ምንውዬለት ጥቁር ካባውን እንደለበሰ
ብድግ ብሎ ቆመ፡፡
“ጥፋተኛ አይደለችም ክቡር ፍርድ ቤቱ” ሲል መልስ ሰጠ፡፡ ዳኛው መልሱን ከመዘገቡ በኋላ፤ ጠበቃው “ክቡር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስ መብቷ ተጠብቆ እንድትከራከር ይፍቀድልኝ” ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ፤ ተከሳሽ በማረፊያ
ቤት ቆይታ እንድትከራከር በመወሰንና፤ ዐቃቤ ህጉ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ አበቃ፡፡
ትህትና እዚያ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ
ቆማ ስትቁለጨለጭ፣እንዳንድ ጊዜ በፍርሃት ተውጣ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ፣
ድምጿ ሲርገበገብ፣ ሲያልባት፡ እያየች አዜብ እንባ እየተናነቃት ነበር፡፡ ሆኖም አልቅሳ ልትረብሻት አልፈለገችም፡፡ ይልቁንም ሳቅ ፈገግ እያለች ሞራል ልትሰጣት ሞከረች፡፡
እውነትም እንደዚያ ሰውነቷ በፍርሃት ሲሸበርባት፣ ልቧ ድው ድው ሲል፣ ሻምበል ብሩክን፣ ወንድሟንና አዜብን ቀስ ብላ ታያቸዋለች፡፡ እነሱ ፈገግ ይሉና በ“አይዞሽ” ምልክት ሲያበረታቷት “አይዞኝ” በሚል ስሜት እራሷን ስታጠናክር ከቆየች በኋላ ችሎቱ ሲያበቃ በአጃቢ ፓላስ ታጅባ ወጣች፡፡
ከዚያም በአንዱአለም ጠያቂነት አብረው ምሣ ይበሉ ዘንድ ሻምበል ብሩክ አጃቢ ፓሊሱን አነጋገረውና አብረው ምሣ ለመብላት ፈቃድ ስለ አገኙ ፤ እዚያው አካባቢ በሚገኝ ወደ አንድ ሆቴል ገቡ፡፡
አንዱአለም የዛሬውን ምሣ ለመጋበዝ የፈለገበት ምክንያት ነበረው፡፡ የሚፈለገው ምግብና መጠጥ ታዘዘ፡፡
ከባህር ኃይሉ የተሰጠው የኪስ ገንዘብ ስለነበረው ምሣ የጋበዘው እሱ ነበር፡፡ አንዱአለምን ብሎ ጋባዥ በመገኘቱ እየተሳሳቁ፣እየተጨዋወቱ፣ ግብዣውን በደስታ ተቀበሉት፡፡ አጃቢ ፓሊሱ በሻምበል ብሩክ ላይ እምነት ስለጣላ እስረኛዋ ታመልጣላች የሚል ሥጋት አላደረበትም፡፡ እንደዚሁ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ.......
“አንድ ጊዜ” አለና አንዱአለም ትንፋሹን ሰብሰብ፣ ምራቁን ዋጥ አደረገ፡፡
አራቱም በፀጥታ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ከወትሮው ለየት ያለ ስሜት ይታይበታል፡፡ እነሱ ከተቀመጡበት አካባቢ ትንሽ ራቅ ብለው በርከት ያሉ እየተጨዋወቱ የሚሳሳቁ ሰዎች ድምጽ ብቻ ይሰማል፡፡
“ይህቺ የምሣ ግብዣ በአንድ በኩል እታለም ለመጀመሪያ ጊዜ
ፍርድ ቤት በቀረበችበት ቀን ተገኝቼ እውነተኛ ፍትህን አግኝታ በነፃ
እንድትለቀቅ መልካም ምኞቴን የምገልጽበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ
ለራሴ መሸኛ በማድረግ በግል ውሣኔዬ መሠረት ለነገው ጉዞዬ መቃናት
እንድትመርቁኝና፤ የወጪ እንድላችሁ በማሰብ የተደረገች ግብዣ ነች”
አለ፡፡ ስለምን እንደሚያወራ ቶሎ ማወቅ አልቻሉም :: “የምን ጉዞ? የምን መሸኛ?. “ምንድነው የምትለው አንዱዬ?” በድንጋጤና በጥርጣሬ ተውጣ አዜብ ጠየቀችው፡፡ “ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቄአለሁ፡፡
ከአንድ ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሬ ለስልጠና
መሄዱ ነው” ሲል ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚያ ጨዋታ መካከል ይህንን መርዶ አምጥቶ ሲጥልባቸው ልባቸው ክፉኛ አዘነ፡፡ በተለይ ትህትና የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ ጭውው አለባት፡፡ ግማሽ አካሏ፣ የምትወደው ታናሽ ወንድሟ ምንም እንኳን እስረኛ ብትሆንም በየጊዜው እየመጣላት ዐይኖቹን ስታየው
የምትጽናናበት አለኝታዋ ነበር፤ በሁኔታው መሪር ሀዘን ተሰምቷት አለቀሰች፡፡
አዜብም እንደዚያው፡ ሻምበል ብሩክም ክፉኛ ነበር የደነገጠው፡፡
ይህ ትንሽ ልጅ የዚህ ዐይነት ከባድ ውሣኔ ላይ ይደርሳል ብሎ ጭራሽ አልገመተም ነበር፡፡ የሱ ፍላጐት አንዱአለም በትምህርቱ ጠንክሮ ዩኒቨርስቲ
እንዲገባ እንጂ እንደዚህ በመሀሉ አቋርጦ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄድ አልነበረም፡፡ ከረጅም ፀጥታ በኋላ......
“እንደሱ ይሻላል አልክ አንዱአለም?” አለው ሻምበል በትካዜ አንደበት።
ትህትና እና አዜብ በእንባ ይንፈቀፈቃሉ፡፡ አጃቢ ፓሊሱ ግራ ተጋብቶ ሁሉንም በዐይኑ ይቃኛል፡፡
“በቃ ብንሄድስ” የሚል ፍላጉት አድሮበታል፡፡ ሞትም ቢሆን በተሰማበት ቅጽበት በድንጋጤ ያደርቃል እንጂ፤ ቀስ በቀስ መለመዱ አይቀርምና፤
ውስጥ ውስጡን እየተቃጠሉ፤ እንባቸውን እየጠራረጉ፤ዐይን፤ ዐይኑን፧ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ውሣኔው የፀና፣ ጉዳዩ ያበቃለት መሆኑን ቁርጥ አድርጉ ነገራቸው፡፡
እስከዛሬ ድረስ የቆየው እህቱ ፍርድ ቤት ስትቆምና የተከሰሰችበት ወንጀል ሲሰማ አብሯት ለመገኘት ፍቃድ በመውሰድ መሆኑን፣ ነገ በጠዋት በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝቶ ወደ ማሰልጠኛው ጉዞ የሚጀምርከ መሆኑን፣ለሻምበል ሲያስረዳው ለትህትና እና ለአዜብ ደግሞ የመርዶ ያህል ካረዳቸው በኋላ በአጃቢ ፓሊሱ አሳሳቢነት ተነስተው ወጡ፡፡
“እሺ አሥር አለቃ ስለተባበርከኝ በጣም ነው የማመሰግንህ አለው ሻምበል የአጃቢ ፓሊሱን ትከሻ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡
“እሺ ጌታዬ አኔም የርስዎ ነገር ሆኖብኝ እንጂ፤ ህግ መጋፋቴን አልዘነጋሁትም” አሥር አለቃ ጥላዬ እግረ መንገዱን ውለታውን
👍1