አትሮኖስ
271K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።

“ዶክ አሁን እንደገባኝ፣ የአዕምሮ በሽታ ከምጠብቀው በላይ በብዛት፣ በዙሪያችን ያለና ብዙ ምስቅልቅሎችን እያስከተለ ያለ፣ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ግንዛቤ የሌለው በሽታ ይመስለኛል፡፡”

“እውነት ብለሃል ያቤዝ፡፡ አሁን ስለ በሽታው በደንብ እየተረዳህ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ብዙ በሽታዎች እንዳሉ ብታውቅ ደግሞ የችግሩ ግዝፈት በደንብ ይታይሃል፡፡”

“ቅድም እንዳልኩህ አልገባኝም እንጂ፣ እቤትህ ያሉትን መፅሃፍት ለማንበብ ሞክሪያለሁ፡፡ ለምሳሌ፤ ስለ ፓራኖይድ፣ ኦብሴሽን፣ዚኮኒያ ምናምን ለማንበብ ሞክሬ ነበር” አልኩኝ በዛው ስለነሱ
እንዲነግረኝ፡፡

“ምነድን ዚኮኒያ ካካካካ...” ዶክተር ለመጀመሪያ ግዜ ከልቡ ሲስቅ
አየሁት፡፡ የበሽታውን ስም ስጠራ እንደተሳሳትኩ ገባኝ፡፡ ዶክተር ሲስቅ
ስላየሁት ግን፣ በመሳሳቴ ደስ አለኝ፡፡

“ዚኮኒያ ... እንደዛ ነገር ያነበብኩ መሰለኝ፡፡” አውቄ ደገምኩለት፡፡
እየተንከተከተ ሳቀ፡፡ ዶክተርን እወደዋለሁ እሱ ለኔ ህይወቴን ያዳነልኝ ጠባቂ መላዕኬ ነው፡፡ ህይወቱን ሙሉ ደስተኛ ቢሆንልኝ ምኞቴ ነው። እሱ ግን ስሜቱ በብዛት የረጋ ነው፡፡ ቶሎ አይደሰትም፣ አይናደድም፡፡ዛሬ በኔ ምክንያት ደስ ስላለው ከልቤ ደስ አለኝ፡፡ ስጦታ የሰጠሁት ያህል ተሰማኝ፡፡ ስቆ ሲጨርስ፤

“ገባኝ፣ ስኪዞፍሬኒያ ለማለት ነው፡፡ የህክምና ቃላቶች ትንሽ ይከብዳሉ፡፡ እንደውም አንተ ጎበዝ ነህ፡፡ ሌሎቹን በትክክል ጠርተሃቸዋል፡፡ እሺ ለማንኛውም እነግርሃለው፡፡ ፓራኖይድ የባህርይ መዛባት ችግር ተብለው ከሚጠሩ ሁኔታዎች አንዱ ነው። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪ ናቸው፡፡ ሰው በተፈጥሮው
ይጠራጠራል፡፡ እንደ ችግር ምንቆጥረው ግን፣ ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ሲጠራጠርና፣ እያንዳንዱ ድርጊታቸው በሌሎች እንጠቃለን ከሚል ከፍተኛና የማያቋርጥ ስጋት፣ አለማመንና ጥርጣሬ የመነጨ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከማንኛውም ሰው ጋር የሚያደርጉት
ግንኙነትና ድርጊታቸው፣ በጥርጣሬ አስተሳሰቦች የተቃኙ ስለሆነ፣
በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በስራቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጠርባቸዋል፡፡

ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በልጅነት ወይም በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ የተለመደ ነው::ፓራኖይድ ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ዝቅ ሊያደርጓቸው፣ ሊጎዷቸው ወይም ሊያስፈራሯቸው እንደሚሞክሩ
ስለሚያስቡ ድርጊታቸው ሁሉ እራሳቸውን በመከላከል የተቃኘ ነው::እነዚህ መሠረተ ቢስ እምነቶች፣ እንዲሁም የማመካኘትና ሌሎችን ያለማመን ባህሪ፣ የቤተሰባዊም ሆነ የስራ ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ
ይስተጓጉላል፡፡ በመሆኑም የፍቅር ህይወታቸው፣ የትዳርና የቤተሰብ
ህይወታቸውን ጨምሮ ማንኛውም ከሰዎች ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት
ከፍተኛ መሰናክል ይሆንባቸዋል፡፡

አነዚህ ግለሰቦች ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶቹም መሃከል፤ሌሎችን ሁል ግዜ መጠራጠር በጣም የሚቀርቧቸውንና ሃኪማቸውን ጨምሮ፣ ሌሎች እነሱን በማታለል ወይም በመበዝበዝ እንደሚጠቀሙ ማሰብና ማመን፤ የግል መረጃዎቻቸው እኔን ለመጉዳት ይውላል በሚል ፍራቻ ለሌሎች መደበቅ፣ ለሰዎች ይቅርታ ማድረግ መቸገር፤ ቂም መያዝ፣ ቁጡና ትችትን በአግባቡ መቀበል መቸገር፤ የሚሰጧቸው አስተያየቶችና የማሻሻያ ሃሳቦች ውስጥ የተደበቁ ትርጉሞችን መፈለግ፣

የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እንደማይታዩ የጥቃት፣ የንቀት ወይም የማስፈራራት ምልክት አድርጎ መረዳት፣ በአፀፋው ለመመለስ መፍጠን፤ እንዲሁም በቁጣ ምላሽ መስጠት፤ የማያቋረጥ ምክንያት
አልባ ጥርጣሬዎችን ማብዛት፣ ይህም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር ጓደኛቸውን በጥርጣሬ ማሰብ፤ ክህደትን ለምከላከል ነገሮችን ሁሉ በጥርጣሬ መመልከት፤ ሁልጊዜ እራሳቸውን ትክክል እንደሆኑ ማመንና በግጭቶች ውስጥ የራሳቸውን ድክመት ወይም አስተዋፅኦ ማየት
አለመቻል፤ አብዛኛውን ግዜ ተቃዋሚዎች ዘና ማለት የሚቸገሩ፣ግትር እና ተከራካሪ ናቸው፡፡ የፓራኖይድ /የምናባዊ/ ጥርጣሬዎችን መለያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

አጠራጣሪውን አስተሳሰብ የሚጋራ ሌላ ሰው ከሌለ፤
ለጥርጣሬ መነሻ ትክክለኛ ማስረጃ ሳይኖር ሲቀር፤
ማስረጃ ባለው ጉዳይ ላይ አልፎ የሚነሳ የጥርጣሬ ሃሳብ፤
ስለጉዳዩ ማሰብ ማቆም የሚከብድ ከሆነ፤
ከሌሎች ማረጋገጫ ተሰጥቶም በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ከቀጠለ፤

ጥርጣሬው ከማስረጃ ይልቅ፣ በስሜቶች እና አሻሚ ክስተቶች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ ይህ ጥርጣሬ ጤነኛ ያልሆነ የፓራኖይድ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪምን ማማከር ከከፋ ችግር ይከላከላል፡፡

ይህ ችግር ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው በመለስተኛ ደረጃ ሊያጋጥማቸው የሚችል ሲሆን የከፋ ጉዳት አያስከትልም ነገር ግን፣በሌላው ጫፍ ሲከሰት በጣም ከባድ ችግርን ሰለሚያመጣ፣ ህክምና
መፈለግ የግድ ነው፡፡” ዶክተር እያወራልኝ ግርማ ትዝ አለኝ፣ በፍቅረኞቻቸው ላይ በአልተጨበጠ ቅናት አሲድ መድፋትና ሌሎች የጭካኔ ወንጀሎችን ሚፈፅሙ ሰዎች በአዕምሮዬ ተመላለሱ፡፡

“ሌላው ደግሞ ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር /ኢኮዲ/የምንለው ነው፡፡ ኦ.ኮ.ዲ. ከመጠን ያለፈ አስጨናቂ የጥርጣሬ ሃሳቦች መከሰትና ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ወይም ለማስተካከል ተመሳሳይ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ለመፈፀም የሚስገድድ ባህሪ ነው፡፡ ግለሰቡ ድርጊቶቹን የሚፈፅመው ወደ አእምሮው ሊቆጣጠረው ከሚችለው በላይ
በተደጋጋሚ እየመጡ በሚያስጨንቁት ሃሳቦች፣ ምስሎች ወይም ፍላጎቶች ምክንያት ነው:: ሃሳቦቹ አስጨናቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን፣በሰውየው አዕምሮ የሚመነጩ እንጂ፣ በነባራዊው አለም የማይከናወኑ
ወይም የሌሉ ናችዉ:: በተጨማሪም፣ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን እንደታዋቂ ወይም ከፍተኛ ደረጃ እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

ኦ.ኮ.ዲ. ምልክቶች በአብዛኛውን ጊዜ በትንሹና ቀስ በቀስ ስለሚጀምሩ፣ ችግሩ ላለበት ሰው፣ የተለመዱ ባህሪዎች ሊመስሉ ይችላሉ:: ድርጊቶቹን ሲፈፅሙ የተወሰነ እፎይታ ይሰማቸዋል፡፡ ነገር
ግን፣ እፎይታው ለትንሽ ጊዜያት ብቻ የሚቆይ ስለሆነ የድርጊቶች
ድግግሞሽ ይቀጥላል። ተደጋጋሚና አስገዳጅ ድርጊቶች በሌሎች ሰዎች
በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በማህበረሰቡ እንደጥዩፍ ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ለግለሰቡ የግዴታ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም፣ ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ እየደጋገሙ ማይታወቃቸው ስለሆነ ነው:: ለምሳሌ፣ ሰው ከጨበጡ ወይም እቃ ከነኩ በኋላ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ሰውን ለመጨበጥ በመፍራት
ሰላምታን በሌላ መልኩ መስጠት፣ የበር መቆለፍን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፣ ልዩ ቃላትን ወይም ጸሎቶችን መደጋገም፣ ደጋግሞ መቁጠር በጣም በተደጋጋሚ የዝግጅት አቀራረቦችን መፈተሽ ናቸው፡፡
እነዚህን ድርጊቶች እንዲፈፅሙ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ፣በጀርሞችን ወይም በቆሻሻ መበከልን በከፍተኛ ደረጃ መፍራት፣ ከመጠን ያለፈ ጥርጣሬ ወይም ስህተት የመስራት ፍርሃት እያደረጉት ላለው ነገር ትክክለኛነት ከሌሎች የማያቋርጥ ማበረታቻና ማረጋገጫ መፈለግና ለስርዐት የበዛና የተጋነነ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡

አንዳንዶቹ ድርጊቶች ሰዎቹ ላይ በቀጥታ ጉዳት ባይኖራቸውም፣አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበትን በመውሰድ፣ በሌሉ ጉዳዮች ላይ በመጨነቅ ውጤታማነትን በእጅጉ ይጎዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ችግር አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበት
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

የግቢው አውራ መንገዶች ጸጥ ረጭ ብለዋል ። ወድዬ ወዲህ የሚዘዋወር
ተማሪ "አይታይም ሁሉም በየምሽጉ
ገብቶ ከወረቀቱ ጋር ፍልሚያ ይዞአል ። አብዛኛው በራሱ ውሳኔ የእንቅልፍ ሰዓቱን አሳጥሮታል ። እንቅልፍ በዐይኑ ሳይዞር የሚያድርም አለ። ውጥረቱና ግብ ግቡ ሲታይ የተማሩትን ለመፈተን ሳይሆን ፥ የሞትን ገደል ለመዝለል የሚደረግ ትንቅንቅ ይመስላል ስለ ግል ጤንነት ስለ አመጋገብ ደንታ የማይኖርበት ሰሞን ነው። በዶርሜቶሪው የጋራ ኑሮ ውስጥ ግዴለሽነት ነግሶ ይታያል ። ልብሶች ከገላ
ሳይወልቁ ውለው ያድራሉ ። የብዙ ተማሪ ፀጉር ከማበጠርያ ተራርቆ ተቆጣጥሮአል እየቆሸሹ በየአልጋው ግርጌ የተጠራቀሙት የእግር ሹራቦች አንሥተው ቢወረውሯቸው ሰው ይፈነክታሉ በስውር የሚገባው የጫተሸ እንጨት ክምር፥ አንዳንድ መኝታ ክፍሎችን መልክ አሳጥቶአቸዋል ።
የፈተና ዋዜማ የገና መአበል ደረስኩ እያለ ተማሪውን የሚያርበተብትበት ሰሞን።

ጓደኝነትና እርስ በእርስ መተማመን ጠፍቷል ። አንዱ ሌላውን ሊያጫውተው ሲጠጋ ከጥናት እንደማዘናጋት ይቆጥራል "ስኬል መስቀል" የሚሉት ፈሊጥ ተማሪው እርስ በእርሱ የጎሪጥ እንዲተያይ አድርጎታል የአንዱ ቀባሪ አብሮ የሚተኛው ጓደኛው ሊሀን ይችላል መሳርያ ባይማዘዙበትም ከፍተኛ ጦርነት ነው ። ሽንት ቤት ደርሰው እስኪ መለሱ የምትቃጠለዋ ጊዜ ታሳሳለች ። ማዕበሉት ማንን ጠርጎ ማንን እንደሚተው በውል ስለማይታወቅ ሁሉም ራሱን ለማውጣት ይፍጨረጨራል ።

ከሴቶች መኝታ ክፍሎች ውስጥ የሽቶ መዓዛ ጠፍቷል ።መስታወት ለማየት ወረፋ ቀርቷል ቅንድብ ለመከርከም
ጊዜ የለም ። የቤት ለቤት ሱሪ ወይም ረዥም ቀሚስ የሰሞኑ የልጃገረዶች ዩኒፎርም ይመስላል ።

ትዕግሥት አቶ ቢልልኝ የጠየቋት ትዝ እያሏትና ከአቤል ጋር እያዛመደቻቸው ብትጨነቅም ሙሉ በሙሉ ከጥናቷ አልተዘናጋችም ። ጥናቷን ጥርሷን ነክሳ ተያይዛዋለች።አቤልን ማየትም ሆነ ስለ አቤል መስማት የማትፈልግበት ሰሞን ነው ።

ማርታም አካባቢው አሸንፎአት ደብተሯ ላይ አቀርቅራለች ። መቼም ትግል ነው ! ቀለሙ ወደ ውስጥ አልጠልቅ ብሎ ጭንቅላቷ ላይ እየነጠረ ሲመለስ ዩኒቨርስቲ የገባችበትን ዕለት ትረግማለች በተለይ የቁጥር ዘር ጠላቷ ነው ። በለማ
በኩል ቤተልሔም ያደረገችላት ሙከራ ቢያጽናናትም እርግጠኛ ለመሆን አልቻለችም ። ጥናቱ ሰልቸት ሲላት ደብተሯን ዘግታ ቀና ትላለች ። ነገር ግን የሚያዋራት ሴት ስታገኝም ደብተሯን እንደ ዘረጋች ስለ እውሮፓ ማለም ትጀምራለች

ቤተልሔም አብራው የምታጠናው ሰው አጥታ ተቸግራለች ። ከለማ ጋር ያላት ግንኙነት በሹክሹክታ ስለ ተሰራጨ የመኝታ ቤትና የክፍል ጓደኞቿ አግልለዋታል እነ ማርታ መኝታ ክፍል እየሔደች ነው የምታጠናው የለማን ኮርስ ደብተር ገልጣውም አታውቅ ፤ ሙሉ እም
ነትዋን በሱ ጥላዋለች ።

እነ አቤል መኝታ ክፍል ውስጥ በፈተና ሰሞን ፍጹም የተላየ ጸባይ የሚኖረው "ድብርት" ነው ። በሚያጠና በት ጊዜ ትንሽ ነገር እንኳ ኮሽ እንድትል አይፈልግም ።አሁንም እንደ ልማዱ የአልጋውን ዙሪያ በጋቢው ጋርዶ የራሱን ጸጥ ያለ ዓለም ፈጥሮ መሸምደድ ይዞአል ማንም እንዲያናግረው አይፈልግም ። ትንሽ ድምፅ ከሰማ መነፋነፉ አይቀርም ። “ ምን እነዚህ ...አበዙት ! ማኅበራዊ
ኑሮ አይገባቸው ” የዘወትር ንፍንፉ ነች ። ሰሞኑን ፍጹም ድምፁ ጠፍቷል ።

ሳምሶን ጉልቤው ለከፋ ሲያምረው የድብርትን የተጋረደ ጋቢ ገለጥ ያደርግበታል ።

ድብርት እየተነፋነፈ ምነው ሲለው ፤
ሳምሶን እየሣቀ ፥ “ ድምፅህ ሲጠፋብኝ ጊዜ፥እያጠናህ በዚያው ሞተህ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው ” እያለ ያበሽቀዋል "
ድብርት ሰላም ለማግኘት ብቻ ሳምሶን ከዩኒቨርስቲው እንዲባረርለት ልቡ ሳይጸልይ አልቀረም ሳምሶን ራሱ ጥናት አስመርሮታል " አንብቦት እንብቦት አልገባህ ሲለው " ይንጋለልና አንዳንዱ በደንብ የሚረዳው ትምህርት ለሌላው ለምን እንደሚያስቸግር መመራመር
ይጀምራል ። ምርምሩ ውጤት ሳያገኝ በዚያው እንቅልፍ ይወስደዋል በፈተና ሰሞን ፈጽሞ የማይረበሽ ሰው ቢኖር እስክንድር ነው ጥናቱን የሚጨርሰው ከፈተናው በፊት ሳምንት ቀደም ብሎ ነው እያንዳንዱን የትምህርት ዐይነት በፕሮግራም በየዕለቱ ቢያንስ አንድ ሰዓት ያህል ስለሚያጠና በፈተና ሰሞን ተቆልሎ ችግር አይፈጥርበትም ከፈተና በፊት ያለችዋን ሳምንት “ ጭንቅላት ማደሻ
ነች” ይላታል ። አሁንም እንደ ልማዱ ፥ ተማሪው በጥናት ተወጥሮ ሲርበደበድ እሱ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ የብርሃኑ ዘርይሁንን ማዕበል በማንበብ ላይ ነው ። ልብወለድ መጽሐፎች ማንበብ በጣም ይወዳል "

የሚይዝ የሚለቀውን ያጣው አቤል ነው እንደ ድብርት ጋቢ ጋርዶ ለመሸምደድ ቢሞክርም አልሆነለትም እንደ እስክንድር ተዝናንቶ ልቦለድ ለማንበብ ሞከረ ።
ሴት ገጸባሕርይ ባጋጠመው ቁጥር ትዕግሥት በሐሳቡ እየመጣች ረበሸችው " እንደ ሳምሶን ተንጋሎ ለመተኛት ሞከረ እንቅልፍ አልወስድ አለው ። ሰው ራሱን
መሆን ሲያቅተው ሌላውን መሆን ይሞክራል ራሱንም መሆን ሲያቅተው ምን ማድረግ ይችላል ?

መኝታ ክፍሉን ለቅቆ ወጣ እስክንድር ቢከተለው ይወድ ነበር ። ሆኖም ልቦለዱን በተመስጦ ያነብ ስለነበር
ሊረብሽው አልፈለገም “ ከክፍሉ እንደ ወጣ ሽንት ቤት
የምመድረስ ሐሳብ መጣለት ጊዜውም እንዲያልፍለት ለውጥም እንዲሆን ነው ወደ ታች ወርዶ ራቅ ካለው ሽንት ቤት
ለመሄድ አሰበ ። ዮናታንን ማየት ሰለሚያፍር ሰሞኑን ከመኝታ ቤቱ ርቆ ግቢው ውስጥ ተዘዋውሮ አያውቅም ።
ፈተና ደርሶ የትምህርት ክፍሉ ባይዘጋ ኖሮ እሳቸውን በመፍራት ምን ጉድጓድ ውስጥ እንደሚገባ ይቸግረው ነበር ። ስለሚያከብራቸውና ስለሚወዳቸው ምክራቸውን ያለ መቀበሉ በፍርሃት እንዲደበቃቸው አድርጎታል።

ደረጃውን ወርዶ ትንሽ እንደሄደ አንድ ተማሪ አገኘ ይህ ተማሪ በግቢው ውስጥ
"ሁለተኛው አምላክ ” በሚል ቅጽል ስም ይጠራል ። «መቼም እጆቹን አኮራምቶ አንገቱን እያቅለሰለሰ ሲሰብክ ላየው ሰው፡ በቀጥታ ከእግዜር ጋር ግንኙነት ወይም የቅርብ ጓደኝነት ያለው ይመስላል። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ለትምህርት ከሚያውለው ጊዜው ሃይማኖታዊ ተልዕኮውን ለማስፋፋት የሚያጠፋው ጊዜ ይበልጣል። በተለይ የፈተና ሰሞን ከማናቸውንም ጊዜ በላይ
በዚህ ስራ ይወጠራል ።

"ወዳንተ እየመጣሁ ነበርኮ አለና አቤልን ጨበጠው።

አበል ሳይወድ በግዱ ነው እጁን የዘረጋለት አንዴ ከያዘው እንደማይለቀው ስለሚያውቅ በሩቁ ሰላም ብሎት ሊሄድ ነበር ።

"ምነው በደህና ነው የፈለከኝ"

አዎ እግዚሐብሔር ይመስገን በደህና ነው ፈጣርያችን ከኛ ገር በመንፈስ እያለ
እጁን ወደ ኋላው አርጎ ባለስልጣን ፊት እንደሚቀርብ አይነት መሽቆጥቆጥ ሲጀምር ፥ አቤል ሐሳቡ ስለገባው ቶሎ
አቋረጠው “

ስል ሃይማኖት እንደሆነ ምንም ነገር እንድታነሳብኝ አልፈልግም።

ከአንጀቱ ተማርሮ ነበር አቤል የተናገረው ውስጡ ስላም አጥቶ መብሰክሰኩ አንሶት ሌላ ሰው ደም እንዲጨቀጭቀሙ አይፈልግም በዚሁ ሰሞን ውስጥ ሌሎች ሁለት ተማሪዎች በመጤ ሃይማኖት ድርጅቶቻቸው ውስጥ አቤንል ለመመልመል ያላደረጉት ሙከራ የለም ።
ሁለተኛው አምላክ ” ሦስተኛ ሰው መሆኑ ነው ። በእኔ ላይ ምን አዩብኝ ? ” ብሎ። አቤል በሽቋል። ሁሉንም ነገር ከዐይን
ፍቅሩ ጋር ስለሚያይዘው ማንም ሰው ሰውን ለመርዳትም ሆና ለመጐዳት ለሚያቀርብለት ጥያቄ ጤናማ አመለካከት።

መጤ ሃይማኖቶችን የማስፋፋት ዘመቻው ግን " በእሱ ላይ የታቀደ አልነበረም ። ምልመላው የሚጧጧፈውና
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....የመከራ ቋት መሆኗ እያማረራት መፈጠሯን እስከመጥላትና ሞቷን እስከመመኘት ብትደርስም፤ ምሬቷን በልቧ አምቃ፣ መጨረሻውን እሱ የፈጠራት አምላኳ እንዲያሳምረው መፀለይዋን አላቋረጠችም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ በፈጠራት ነፍስ ላይ
የሚወስነው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ መቼ እንደሚወስዳት የሚያውቀው እሱ ብቻ ስለሆነ ፤ ዶክተር ባይከዳኝ እንደማትድን ገልጾ ተስፋ ቢያስቆረጣትም፤ ማን ያውቃል? ፈጣሪ በተአምር ሕይወቷን አትርፎላት፣ ሊተዛዘቡ ይበቁ ይሆናል፡፡ ይህንን ስታስብ፤ ሞቱ ተብለው ደረት የተመታላቸው፤ አበቃላቸው ተብለው ሳጥን የተዘጋጀላቸው፣
በአምላክ ረቂቅ ሥራ ህይወት ዘርተው፤ ለረጅም ዕድሜ ባለፀጋነት የበቁ እንዳሉ ሲታወሳት፣ እንኳንስ ተስፋ ያላት እናቷን፤ ከፈለገ ሬሣ የሚቀሰቅሰው አምላክ፤ በህይወት ሊያቆይላት እንደሚችል በመተማመን፤ የዶክተርን ድንፋታ እየናቀችው፤ እናቷን አሳክማ ለማዳን ትግሏን በጠንካራ መንፈስ ለመቀጠል ወሰነች፡፡

ከዚህ ከእናቷ ህመም በተጨማሪ ደግሞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የሷና የሻምበል ፍቅር ገና በለጋነቱ እንዳይጨናገፍ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏታል፡፡
በተለይ የዚያን ዕለት ያየችው ህልም ፍርሃት፤ ፍርሃት፣እንዲላት ዋነኛ ምክንያት ሆኖባታል፡፡
ነገ እሁድ ነው፡፡ ዕሁድ ዕለት እሷና ሻምበል ብሩክ የሚገናኙበት፣ ፍቅር የሚጨዋወቱበት፣ የወደፊት የትዳር ህይወታቸውን እየቀየሱ የሚወያዩበት፤ በአጠቃላይ ሁለቱም በናፍቆት የሚጠብቁትና በሻምበል ብሩክ ቤት በደስታ ውለው የሚያድሩበት ቀን ነው፡፡
ቅዳሜ በጠዋት ተነስታ፤ ለእናቷ አጥሚት አዘጋጅታ፧ ምሣ በሣህን ይዛ፤ ወደ ሆስፒታል ሄደች፡፡ እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ከቆየች በኋላ አንዱዓለምን እናቱ ዘንድ እንዲቆይ አደረገችና፤ ወደዚያች
ችግሯንም ሆነ ደስታዋን እኩል ወደምትካፈልላት ጓደኛዋ ወደ አዜብ
ሄደች፡፡

ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ትናንትና መገናኘታቸውን፣ ከዚያም ቤቱ ይዟት መሄዱን፣ ከዚያም ራሷን ለመፈተሽ ያደረገችውን ሙከራ፣ ከዚያም ዶክተር ባይከዳኝ ሙልጭ አድርጐ ስድቦ ያባረራት መሆኑን አወራችላትና፤ በመጨረሻም ላይ ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው እናቷ መጨረሻ ደረጃ ላይ በደረሰ.... የካንሰር በሽታ መታመሟንና፤
እንደማትድን የገለፀላት መሆኑን፤ አስረዳቻት፡፡
አዜብ እቅፍ አድርጋ አጽናናቻት፡፡ አቤት እንደዛ እቅፍ አድርጋ ስታጽናናት የተሰማት ስሜት! መዋለድ ብቻውን ምን ዋጋ አለው?አንዳንዱ ተዋልዶም ተመልሶ እንደጠላት ይፈላለጋል፡፡ እንደዚህ ያለው
ጓደኝነት ግን ከመዋለድም በላይ ዋጋ ያለው ነው፡፡ መዋለድ ሳይሆን መዋደድ ነው ተብሉ የለ ወትሮውኑ? ፡፡

ዶክተር ባይከዳኝ ሀኪም እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ ስለማሚ ህይወት የሚያውቀው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ደግሞ ታያለሽ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድነው ከዚያ ሆስፒታል ባይወጡ አዜብ ምን አለች ትይኛለሽ ?” እሷን ለማጽናናት ስትል .
ከእግዜሩ መልዕክት ደርሶኛል ለማለት ትንሽ ነበር የቀራት። ትህትናም ትህትናም
ያለችው ይሄንኑ ነበር፡፡ ድሮውንም የእናቷን ነገር ለፈጣሪ ነበር የሰጠችው፡፡ ልቧ ተጽናና፡፡ ወደ ሌላው ዋና ርእሰ ጉዳይ ተሸጋገሩ፡፡
“የተፈጠረውን ሁሉ ፍርጥርጥ አድርጐ እውነቱን መናገር ይሻላል ወይስ ሌላ መንገድ አለው?” ስትል አዜብን አማከረቻት፡፡
“እውነቱን መናገር ባልከፋ ነበር፡፡ ምን ያህል አምኖሽ ይቀበለዋል የሚለው ነው ችግሩ። አላየሽም ዶክተር እንኳን የሆነውን? እሱስ ልጃገረድ ነኝ ስትይው ከከረምሽ በኋላ ያለመሆንሽን ሲያውቅ ምን ይሰማዋል?ስትዘል የኖረች አይልሽም?” መልሳ ጠየቀቻት፡፡ ትህትና
የዶክተር ሁኔታ መጣባት፡፡ አውሬ ነበር የሆነው፡፡ የሻምበልም ከዚህ ሊለይ እንደማይችል ገመተችና ፈራች ::
"እሱስ እውነትሽን ነው አዜቢና፤ ታዲያ ምን አባቴ ማድረግ ይሻለኛል? ጨነቀኝኮ! እንደነገርኩሽ ህልሜም ጥሩ አልነበረም፡፡ ወይኔ ብሩኬ.... የልቤን እንዴት አድርጌ ባሳየሁት?” ተከዘች፡፡
አዜብ ጉዳዩን ከብዙ አቅጣጫ ተመለከተችው፤ መረመረችው፡፡የሆነውን ሁሉ መናገር፤ ወይንም ሌላ ዘዴ መፈለግ.... በመጨረሻ ላይ የመጣላትን ዘዴ ልትነግራት ካለች በኋላ በቅድሚያ ልታሳምናት ፈለገች፡፡
“ ትሁት የእድልሽን ሳትሞክሪ ከወዲሁ ቶሎ ብሎ እጅ መስጠቱ የሚያዋጣ አልመሰለኝም፡፡ ቀድመሽ እንደዚህ ሆንኩ ብለሽ ተናግረሽ፤አልፈልግሽም ካለ እንዳይቆጭሽ ፡፡ አሪፍ ከሆንሽ በአንድ ጊዜ ልታሳኪው ትችያለሽ፡፡ ካልተሳካልሽ ደግሞ ሁለተኛውን እድል ትጠቀሚያለሽ፡፡
የተፈጠረውን ሁሉ በዝርዝር ታስረጂዋለሽ እርግጠኛ ስለሚያፈቅርሽ ችግርሽ ይገባዋል :: ስለዚህ በቅድሚያ አማራጩን ብትጠቀሚ” አለቻት፡፡ ትህትና አማራጩን ለመስማት ጓጓች፡፡
“ፔሬድሽ መጥቷል?”
“አልመጣም”
ጥያቄውን ለምን እንዳቀረበችላት ለማወቅ
ቸኩላለች፡፡
“መቼ ነው የሚመጣው?”
"እሮብ ወይም ሀሙስ ብዬ እገምታለሁ”
“በቃ እሁድ ዕለት አትሂጂ፡፡ ለእሮብ ወይም ለሀሙስ ቅጠሪው። የዚያን ዕለት አብረሽው እደሪና፤ እሪ ብለሽ አልቅሽ”
ትህትና በጥፊ እንደተመታ ሰው ክው ብላ ደነገጠች፡፡
“ውይ አዜቢና ይሄስ የማይሆን ነው” ተቃወመች፡፡
“ወደድሽም፤ ጠላሽም፤ ያለው አማራጭ እሱ ብቻ ነው ትሁት”
“እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዳታለልኩት ካወቀ ደግሞ የባሰ ነው የሚሆነው” በትካዜ ተውጣ፡፡
“ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስንቶቹ ናቸው እንደዚህ የሚሽውዱት ዋናው ያንቺ ቅልጥፍና ነው”
በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው ከተነጋገሩ በኋላ፤ ያለው አማራጭ ይሄና ይሄ ብቻ መሆኑን አሳመነቻት፡፡
ሳምንቱን ሙሉ ከሻምበል ብሩክ ጋር ስልክ ሲደዋወሉ ነበር ያሳለፉት፡፡ ይሁን እንጂ እሷ በእውነተኛ ፍቅር ...
“ብሩኬ " ስትለው፤ እሱ ደግሞ በአንደበቱ “ሀይ ትሁት”ቢላትም፧ በልቡ “አስመሳይ!” ሲላት ነው የከረመው ::
ይሄንን አስመሳይነቷን፤ ሌብነቷን፤ ደርሶበት ቁርጡን እስከሚያውቀው ድረስ በተቻለው መጠን የድሮውን ሻምበል ብሩክን ለመምሰል ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ልቡ ቢሻክርም፤ እንደበቱን ለማለሳለስ
እየታገለ ነው የከረመው ::
ቅዳሜ ዕለት ስልክ ደወለችለትና ከአዜብ ጋር በተመካከሩት መሠረት የእሁድ ፕሮግራማቸውን ወደ እሮብና ወደ ሀሙስ እንዲሸጋገር አሳወቀችው፡፡
“ምነው ምን ተፈጠረ ትሁት?” አላት በመገረም፡፡
“ማዘር ብሶባታል እሁድ እለት ሆስፒታል ነው የማድረው”
“ይሄኔ ከዚያ ጅል ዶክተርሽ ጋር ለማደር ነው” የሚል ስሜት ተሰማውና ቅናት ቅጥል ቢያደርገውም፤ ቻል አድርጐ
“ልምጣ እንዴ?ችግር አለ እንዴ ?” አላት ለማግደርደር ያህል፡፡
“አትድከም ብሩኬ ከቻልክ እሁድ ብቅ በል” አለችው፡፡
ሻምበል ከሶስት ቀናት በፊት ሆስፒታል
ሄዶ ጠይቋታል፡፡ አሁን ብሶባታል ብላ የምትነግረውን ዓይነት አልነበረባትም፡፡ እንዲያውም እየተሳሳቁ፤ እየተጨዋወቱ! ነው የዋሉት፡፡
እሮብ ወይም ሀሙስ ደግሞ ያልተለመደ ቀጠሮ ነው፡፡
“ይሁን እስቲ!” አለና ንዴቱን በልቡ አምቆ፡፡
“ምንም ችግር የለውም ትሁት፡፡ ዋናው የማዘር ጤንነት ነው፡፡ግን እሮብ ወይ ሀሙስ ከምትይኝ ወይ እሮብን፤ ወይ ሀሙስን፤ ለምን አልመረጥሽም? ማለቴ እንድጠብቅሽ?”
“ችግር የለውም ብሩኬ፡፡ ትክክለኛውን ቀን ደውዬ እነግርሃለሁ”
“ይሁን እንዳልሽ” በሃሣቧ የተስማማ በመምሰል አንጀቱ እያረረ እሁድ አልደርስልህ ብሎት በተስፋ ሲጠባበቅ፤ አሁን ደግሞ ይኸውና እሁድ ሲደርስ ተጨማሪ ሶስት ወይም አራት ቀን ጨምራበት ቁጭ አለች፡፡ ይህንን ሁሉ ችሎ፣ እሁድ እለት እዚያው ሆስፒታል ሄዶ፤እናቷን ጠይቆ፤ ልክ
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...“ናትናኤል የቆርቆሮውን የአጥር በር ገፋ አድርጎ ሲገባ ያጋጠመው ሰፊ ግቢ ነበር፡፡ በግራና በቀኝ አያሌ መኪኖች ተደርድረዋል፡፡ የሆቴሉ ህንፃ ውስጥ ገብተው መስተናገድ ያልፈለጉ ደንበኞች ያማራቸውን እዚያው ከየመኪናዎቻቸው ውስጥ አዘው ይጋበዛሉ፡፡ ፍጥነቱን ሳይቀንስ ወደፊት በሆቴሉ ዋና በር እቅጣጫ ገሰገሰ፡፡

ግቢው በጨለማ ቢዋጥም ከፊት ለፊት የሆቴሉ አዳራሽ ብርሃን እውጭ በረንዳው ላይ የምሽቱን እየር እየተነፊሱ የሚጋበዙ እንግዶችን ያሳያል፡፡

በዋናው በር መግባት አደገኛ ነው፡፡ ያለጥርጥር እሱን የሚጠብቅ ድንገት የሚወነጨፍ ወጥመድ ሊኖር ይችላል፡፡

ወደቀኝ እጥፍ ብሎ በሆቴል ቤቱ በስተቀኝ ወደጓሮ ዞረ፡፡

ጭስ፡፡ እዚያና እዚህ ተፍ ተፍ የሚሉ የወጥ ቤት ሴቶች፡፡ማናቸውም ቀና ብለው አላዩትም:: በጨለማው ውስጥ ዘና ብሎ ከኋለኛው በር ደጃፍ ወጣ ብላ ወደቆመች ሴት ጠጋ አለ፡፡

“ታዲያስ!” አላት እንደቤተኛ ተዝናንቶ::
“አለን!” አለች በጨለማው ውስጥ ፊቱን ለማየት እየሞከረች፡፡
“የምሥራችን ምን ነካት ዛሬ?” አለ ጎንበስ ብሎ የእግር ሹራብን ሳብ ሳብ እያደረገ ፊቱን እንዳታየው:: ጨለማው ፊቱን እንደሚከልልለት ቢረዳም መንፈሱ አልረጋጋልህ አለው፡፡

“እንዴት ምን ሆኑ?” አለች ሴትየዋ የእመቤቷ ስም ሲነሳ፡፡
“አላየኋትም፡፡” አለ ፊቱን ወደ ማዕድ ማዘጋጃው ቤት መልሶ፡፡
“ኧረ አሉ፡፡ ከዋናወ ቤት ናቸው ኮ፡፡”
“ከዋናው አዳራሽ?” አለ ለጥቂት ሴኮንዶች ፊቱን መለስ አድርጎ
አይቷት ወዲያው ዞር ብሎ እየተንጠራራ፡፡ ሴትየዋ የምታወቀው ሰው የዘነጋችው ደንበኛ ይሆናል ብላ እንድትጠራጠር አለቅጥ እየተዝናናባት፡፡
“ዋናው አዳራሽማ ገብቼ ነበር፡፡ የለችም፡፡ ክፍል ጨርሳችኋል እንዴ?” አላት
አከታትሎ፡፡

“አልጨረስንም፡፡ ልያዝሎት? ” አለችው::
“አዎ፡፡” ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ሰጣት፡፡
ሴትየዋ ወደ ውስጥ ስትገባ እያፏጨ እየተንጎራደደ ጠበቃት፡፡
ከወዲያ ወዲሀ የሚሯሯጠትን ብቅ ጥልቅ እያሉ እንግዶቻቸውን የሚያስተናግዱትን ሴቶች እየተመለከተ ቆየ::
“አዛሉ! ሁለት ጥብስ አንድ ክትፎ ሶስት ፍርፍር ቶሎ በይ!” አለች አንድ ሴት ከጀርባው ካለ መስኮት ብቅ ብላ፡፡ “ዓለም! ዓለምነሽ! ለሦስት ቁጥር ሰዎች አምቦ ውሃ ወሰጂላቸው እንጂ!” ወደ ውስጥ የገባችው ሴት መልሳ በዛው መስኮት ብቅ ብላ ተጣራች፡፡

“መጣሁ መጣሁ! እዚህም'ኮ ስራ ነው:: ጭቅጭቅ?” ዓለምነሽ እያልጎመጎመች ከማዕድ ቤቱ ወጥታ የአምቦ ውሃ ጨብጣ ወደ ዋናው ቤት ሮጠች፡፡

“ይኽው ሰባት ቁጥርን ያዝኩሎት፡፡” አለችው ቁልፉንና መልስ ገንዘብ የያዘችበትን እጇን ወደፊት ዘርግታ፡፡
ቁልፉን ብቻ ተቀብሎ “ተይው” አላት መልሱን ልትሰጠው ስትከጅል፡፡
“እግዜር ይስጥልኝ፡፡" አለች በጨለማው ውስጥ ፈገግታ ደርባ፡፡
“ምስር ከአዲስ ደንበኞች ጋር ነች መሰለኝ? እኛን ረሳችንሳ፡፡” አለ
የተከራየውን ክፍል ቁልፍ፡ ሌባ ጣቱ ላይ እያሽከረከረ፡፡
“አይ..ከነጋሼ ኪዳኔ ጋር ናቸው...ጓዳ፡፡”
“ኪዳኔ የኛ?” አላት በጭፍን፡፡
“አዎ፡፡” አለችው:: ቤተኛ ነው ብላ እንደደመደመች ግልጽ ሆነለት::
“አይ እነሱስ .. ከሆነ ችግር የለም፡፡ አንድ ሰው ይፈልግሻል በያት፡ክፍሌ ውስጥ ነኝ፡፡” ለመመለስ ጊዜ ሳይሰጣት ፊቱን መልሶ መደዳ ወደተሰሩት የመኝታ ቤቶች አመራ…4..5.6..7 ቁልፉን ከቶ በሩን ከፈተና ወደ ውስጥ ገባ፡፡ በሩን ከዘጋው በኋላ መብራቱን አበራው፡፡

የክፍሉን አብዛኛ ቦታ የያዘው ቀይ ጨርቅ የለበሰ አንድ ሰፊ አልጋ በሁለት ኮመዲኖዎችና ቁምሳጥን ታጅቦ መሃል ላይ ተንጋሏል፡፡ አነስተኛ የፊት መታጠቢያ ሳህን ከነፊት መስታወቱ በስተቀኝ ይታያል፡፡ ከክፍሉ ጀርባ ከአልጋው ራስጌ አንድ የተዘጋ የእንጨት መስኮት አላ:: ናትናኤል ክፍሉን ካጠና በኋላ ወደፊት ራመድ እልና በኮርኒሱ መሃል
የተንጠለጠለችውን አምፖል አላላት፡፡ ጨለማ፡፡

አልጋው ላይ ተቀምጦ መጠባበቅ ያዝ፡፡ ልቡ እየተነሳ ሲፈርጥ ደረቱን ሲነርተው እራሱን ኣሳፈረው፡፡ለሳምንታት አንድ በአንድ ሲያስኬደው የቆየው ዕቅድ ቀላል ሆኖ እንዳልታየው ሁሉ ሰዓቱ ሲደርስ በላብ ይዘፈቅ ጀመር፡፡ …ምንድነው የሚላት? ካልቨርት ያላትን ነው መድገም ያለበት፡፡የካልቨርት ቢጤ ምስኪን ተባራሪ ነው መሆን ያለበት፡፡ ያኔ ነው ካልቨርትን
ባየችበት አይኗ ልታየው የምትችለው፡፡ ባታምነውስ? ብትጮኽስ? ኡ! ኡ!
ብትልስ? ወይ አባብላ የተስማማች መስላ ብታስያዘውስ?. አንዱ ክፍሉ
ውስጥ ከገባች በኋሳ መውጣት የለባትም፡፡ መጀመሪያ መውጣት ያለበት እሱ ነው፡፡ ግን ብትጮህ ምን ያደርጋታል? አፏን አፍኖ ይዞ ማስፈራራት?
አጥፍቷል፡፡ ጩቤ ቢይዝ ጥሩ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያላሰበው ያልጠረጠረው
ሁኔታ ሲከሰትላት ደንገጥ አለ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች አሰላሰለና ድንገት አፈፍ
ብሎ ተነስቶ በሩን ከፍቶ ወደ ማዕድ ቤት ሮጥ ብሎ ሄደ፡፡

“እዛሉ! ዓለምነሽ! ማናችሁ... ምነው ዛሬ ችላ አላችሁን?” ጭንቅላቱን በማዕድ ቤቱ ጠባብ መስኮት ገባ እድርጎ ታጣራ፡፡ ከውስጥ የክፍሉ ብርሃን ሴቶቹን ቁልጭ አድርጎ ቢያሳየውም ከውጭ የቆመው
የእርሱ ፊት ግን በጨለማው ውስጥ እንደተዋጠ ነበር፡፡

“አቤት...ምንድነው?” አለች ኣዛለች ትሁን ዓለምነሽ ያልለያት ሴት በግራዋ መጥበሻ በቀኟ ሳህን እንደያዘች ፊቷን ወደ እርሱ መልሳ፡፡

“ስንቴ ነው የምንልክባችሁ? ቢላ ቢላ! ቢላ! በይ አሁን አንድ ስጪኝ!” አለ እጁን ዘርግቶ እያራገበ::

ዞር ብላ ከጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ የገበታ ቢላ አንስታ አቀበለችው ቢላውን ከተቀበላት በኋላ ፊቱን መልሶ እየተጣደፈ ወደ ተከራየው ክፍል ሲመለስ ከጀርባው ድምጽ ተሰማው፡፡ የክፍሉን በር ከፍቶ እንደያዘ ዞር ብሎ ተመለከተ፡፡

“ማን ነው? ብለዋል እትዬ…ማን ልበላቸው ስሞትን?” አለች የላካት
ልጅ ስሙን ባለማስታወሷ እያፈረች፡፡
“ይሻላል? ህ ህ! ሀ! ሀ!” ልጅቷ ላይ አንቧረቀባት፡፡ “ብላ ብላ ደግሞ ማነው ትለኝ ጀመር? እንደምትያት መታወቂያ ወረቀቴን ብልክ አይሻልም ወይ? ብሏል በያት” ጊዜ ሳይሰጣት ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ “ማነሽ…ደሞ
ሻማና ክብሪት ይሽልኝ ተመለሽ፡ አምፖላችሁ ተቃጥሏል፡፡ እንደው ነው'ኮ
እዚህ የምንመጣ፡፡ የናንተ አስተናጋጅነት ድሮ ቀረ::” በሩን ዘጋው፡፡

አለቅጥ መዝናናቱ ልጅቷን ግራ እንደማያጋባትና እመቤቷ በቅርብ
የሚያውቁት ሰው ነው ብላ እንድታስብ እንደሚያደርጋት ገብቶታል፡፡ ክፍሉ
ውስጥ ከገባ በኋላ ቢላ የጨበጠ ቀኝ እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ አልጋው ላይ
ተቀመጠና ጨሰማው ላይ ኣፈጠጠ፡፡
ቢላውን የጨበጠበት እጁ በላብ ሲጠመቅ አውጥቶ ሱሪው ላይ
ሞዥቀው፡፡ መፍራት የለበትም ቀፍፁም! አሳዳጆቹ ፍርሀት የሚገባቸው ፤
ርህራሄ የሚውጣቸው አይደሉም። አንገቱን አርደው ቱቦ ውስጥ ሊጥሉት
የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ፍርሀት አይበጀውም:: ፍርሀት አያዋጣውም፡፡

ምንድነው የሚላት? ሊያስፈራራት አይገባም፡፡ እሰም እንደ ካልቨርት ተባራሪ መሆኑን ነው ሊያሳምናት የሚገባው፡፡ ያን ጊዜ ነው የምታምነው! ካልቨርትን ባየችበት እይኗ የምታየው:: እንቢ ካለች ግን በራሷ ቢላዋ ያባብላታል፡፡

ያለበት ክፍል በር ወደ ውስጥ ተከፈተ፡፡
“እንዴ! ምነው ጨለማ ውስጥ ?!” ለሴት ጎርነን ያለ ድምፅ፡፡

“አምፖልሽ ተቃጥሏል ምስርዬ፡፡ ሻማ በያት ልጅቷን፡፡” አለ ናትናኤል በጭለማ ውስጥ እንደተቀመጠ ተዝናንቶ፡፡ ልቡ ትቼህ ልብረር ልብረር አለው፡፡

“ማነህ?” አለ ያው ጎርነን ያለ የሴት ድምፅ ጥርጣሬ የገባው በሚመስል ቃና

“እስቲ ሻማው ይምጣና
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


. “እሷን ብሎ እዚህ እናንተ ጋር አይመጣም ነበር?”

“ማንም አይመጣም” ብላ አንጀሊና መለሰች እና ቀጥላም “ብዙውን ጊዜ
አንዲት ጓደኛ ነበረቻት ምናልባትም ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ታሳልፍ የነበረው ከልጆቻችን ጋር ነበር ኮሎኒያ ጀሃሬዝ ውስጥ የምትኖር አንዲት ጓደኛ ነበረቻት
ምንአልባትም ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ታሳልፍ ይሆናል በቃ ከማንም ጋር አይቻት አላውቅም

የልጅትዋ ስም ፍሬድሪክ ነው?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቃት፡፡

“አዎን ልክ ነው ስሟ ፍሬድሪክ ነው፡፡” አለችው አንጀሊና ፈገግ ብላ

“የአባቷን ስም አታውቂም?” ብሎ ዊልያምስ ሲጠይቅ አንጀሊና ኢንክሪቶ
ራስዋን በአሉታ ነቀነቀች

“እኔ አውቀዋለሁ” የሚል የህፃን ድምፅ ድንገት ተሰማ፡፡ ህፃኑም ሙሉ ነጭ የሜዳ ቴኒስ ልብሱን እንደለበሰ ከእነርሱ ጋር ተቀላቀለ

“ዚዳን ነው የአባቷ ስም ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች ስለሆነ ስሙን
አልረሳሁትም”

“አመሰግናለሁ ግን ስምህን ማን ልበል?” ብሎ ዊልያምስ ጠየቀው
“አንቶኒዮ እባላለሁ” ብሎ ከመለስ በኋላ በአዋቂ ወሬ ውስጥ እያወራ ስለሆነ
ደስ አለው፡፡ ወላጆቹ ግን ልጁ ከዊልያምስ ጋር ሲያወራ ማየታቸው
እንደረበሻቸው ከፊታቸው ላይ ይነበብ ነበር፡፡

“ከቻርሎቴ ጋር ሆናችሁ ፍሬድሪክን አግኝታችኋት ታውቃላችሁ አንቶኒዮ?” ብሎ ዊልያምስ ልጁን ጠየቀው

“አዎን ብዙ ጊዜ እናውቃለን”

“የት ነበር የምታገኟት?”

የምናገኛት፡፡ እዚያ ሁሉም ሴቶች ናቸው ግን የውሃ ላይ ሸርተቴ ስላለው
“በመናፈሻው ውስጥ እና እሷ በምትኖርበት ቤት እየሄድን ነበር
...” ብሎ ሊቀጥል ሲል እናቱ አንጀሊና አቋርጣው

“በጣም ነው የምናመሰግነው የኔ ውድ” ብላ ከባልዋ ጋር በአይን እየተነጋገሩ “አሁን ወደ ቴኒስ ጨዋታህ መመለስ ትችላለህ አለችው፡፡”

ዊልያምስ የልጁን እጅ ይዞ “ቤትዋ የት እንደሆነ ታውቃለህ?” ብሎ ጠየቀው።

ይሄኔ አባቱ ጁሃን እንክሪቶ “የሜዳ ቴኒስ የስልጠና ሰአቱ ይረፍድበታል እባክህን ሚስተር ዊልያምስ ልጁ ከአንተ ስራ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ አክብረንም ስላገኘንህ ይሄን ያህልም ልትጫነን አይገባም” አለው።

“ከእኔ ስራ ጋር ይገናኛል እንጂ” ብሎ ዊልያምስ በቁርጠኛ ድምፁም
“ሲኞር ኢንክሪቶ እኔ የልጅቷን ቤት ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም ይቺ ፍሬድሪክ ዚዳን ብቻ ልትሆን ትችላለች በቻርሎቴ ላይ ምን እንደደረስ ልታውቅ የምትችለው፡፡ ምስኪኖቹ የቻርሎቴ ቤተሰቦች በአሁኑ ሰአት ምን
እየተሰማቸው እንደሆነ አስበው እስቲ? የጠፋው ልጅህ ቢሆን ምን ይሰማህ
ነበር?” ብሎ ልሂድ ወይስ ልቅር እያለ ወደሚያመነታው ልጁ ወደ አንቶኒዮ
አመለከተው፡፡

ይሄኔም የልጁ አባት ተረጋጋ፡፡ “እና አንቶኒዮ የልጅትዋ ቤት የት እንደሆነ ታውቃለህ?” ብሎ በእርጋታ ጠየቀው፡፡

“አዎን አውቀዋለሁ!” ብሎ አንቶኒዮ ፈገግ አለ፡፡ “እና እኔ ነገሮቹን አልረሳም፡፡ ከፈለግክ አሁን ቤቷ ልወስድክ እችላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡

ፍሬድሪኩ ዚዳን ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ወጣት ሴት ናት፡፡ፀጉሯ አመድማ ቡኒ እና አጭር ነው፡፡ ፊቷም ሞላ ብሎ ነጣ ያለ ስለሆነ በአርባዎቹ ዕድሜዋ ላይ የምትገኝ ሴት ያስመስላታል፡፡ የለበሰችው ልብስ
ግን ይህንን ነገሯን የሚሸፍንላት አይነት ነው፡፡ የበሩን ደውል ሰምታ ለዊልያምስ ስትከፍትለት ዊልያምስ በጣም አጭር ቀሚሷን፣ ነጭ ቲሸርት እና ከቦዲዋ ስር የሚታየውን የጡት ማስያዣዋን ተመለከተ፡፡ ዊልያምስም የመጣበትን ምክንያት ሲያሳውቃት ፍሬድሪኩ ቤትዋ እንዲገባ በትህትና ጠየቀችው፡፡

“ከበጎ አድራጎት ሀላፊዋ ሴትዮ ውጪ አንተ ብቻ ነህ ስለ ቻርሎቴ ለመጠየቅ እዚህ ድረስ የመጣኸው” ብላው እንዲቀመጥ ሶፋው ላይ ያሉትን
ጨርቆች ወደ አንድ ጎን ሰበሰበችለት።

“የትኛዋ ሴትዮ?”

“የአፈላላጊ ድርጅቱ ሀላፊን ለማለት ነው” ብላ ፍሬድሪኩ ግልፅ አደረገችለት እና በመቀጠልም “እዚህ ካሉት ፖሊሶች በበለጠ መልኩ ቻርሎቴን ፈልጎ ለማግኘት በየቦታው ፎቶዎቿን በመለጠፍ ፍለጋቸውን ሲያደርጉ ነበሩ።”

ይሄ ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም ብሎ ዊልያምስ በውስጡ አሰበ፡፡
“ምክንያቱም ከተከር እና ሜሪ ክላንሲ እንደተረዳው ቫለንቲና ባደን እና የበጎ
አድራጎት ድርጅት በቅርቡ ብቻ እንዳገኟቸው ነው፡፡ ለዚያውም በቴሌቪዥን ቀርበው ስለጠፋችው ልጃቸው እንዲናገሩ ለማድረግ ነው ያገኟቸው።

ቫለንቲና ባደን ገና ቻርሎቴ ከጠፋችበት ጊዜ ጀምሮ በቻርሎቴ ጉዳይ ፍላጎት ኖሯት ትንቀሳቀስ እንደነበር ስላወቀ ጥሩ ነገር አልተሰማውም። ነገሩ ጥሩ ቢሆን ኖሮ ለቻርሎቴ ወላጆች የቻርሎቴን ጓደኛ ፍሬድሪኩን አግኝታ እንዳነጋገረቻት ተነግራቸው ነበር፡፡

የአሜሪካ ፖሊስ በቻርሎቴ መጥፋት ጉዳይ ላይ ምርመራ እንደሚያደርጉ በወቅቱ ተነግሮኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ አንድም ፖሊስ እኔን አላገኘኝም" አለችው ፍሬድሪኩ፡፡

እንግሊዘኛዋን የምትናገረው በፈረንሳይኛ ዘይቤ (ቅላፄ) መሆኑን ያስተዋለው ዊልያምስ ስለ እዚህ ጉዳይ ሲጠይቃት “ልጅ እያለሁ ከቤተሰቤ ነበር የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተማርኩት። አሁን ላይ ደግሞ እስፓኒሽ እና ጣልያንኛ በደንብ መናገር
እችላለሁ፡፡ ስለዚህም ይመስለኛል እዚህ ሀገር ቀለል ብሎኝ የምኖረው።
ቻርሊ ግን እስፓኒሽ ብዙም ስለማትችል ሰዎች ያገልሏት ነበር፡፡ ለስራው አዲስ እና ልጅ ስለነበረች እኔ እንድተረጉምላት ትጠይቀኝ ነበር።በእግዚአብሔር በጣም ነበር የምታሳዝነው፡፡

“እዚህ ለወራት ያህል ለእንክሪቶ ቤተሰብ እየሰራች ስትኖር እንዴት ትኖር እንደነበር ማወቅ እፈልጋለሁ” ብሎ ዊልያምስ ሲጠይቃት ፍሬድሪኩም ወደ እሱ ዘንበል ብላ በጉጉት እየተመለከተችው “እሺ ስለ እሷ ምንድነው ማወቅ የፈለከው?” ብላ ጠየቀችው፡፡

እሷ ትሰራበት የነበረውን ቤተሰብ ቻርሎቴ የወንድ ጓደኛ የላትም ነው ያሉኝ፡፡ ይህ እውነት ነው?”

“እነርሱ ስላላዩ ፍቅረኛ የላትም ቢሉ ችግር የለውም!!!”

“ነገር ግን ቻርሊ ከሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበራት፡፡” ይሄንን ነገር ደግሞ ለፖሊሶች ነግሬያቸው ነበር፡፡የጠፋችውም ያን ምሽት እሱን
ልታገኝ ሄዳ ሳለ ነው ብዬ ብነግራቸውም በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ፖሊሶቹ ምንም አይነት ፍላጎት ሲያሳዩ አላየሁም” አለችው።

“እኔ ስለ እሱ በጣም ማወቅ እፈልጋለሁ” አላት እና ዊልያምስ በመቀጠልም “በአካል አግኝተው ታውቂያለሽ? ስሙንስ ታውቂዋለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ፍሬድሪኩም ራስዋን በአሉታ ነቀነቀች፡፡

“አላውቀውም በቃ ሰውዬው ሚስጥር ነበር፡፡ ቻርሊ ሁሌም ስለእሱ ሳታወራኝ ያደረችበት ቀን የለም፡፡ ፍቅረኛዋ ባለ ትዳር ነው፡፡ በእድሜም ከእሷ በጣም ይበልጣታል፡፡ ስለዚህ ሰውዬውን ልታገናኘኝም ሆነ ስለ እሱ ማንነት ልትነግረኝ አልቻለችም” ብላ ስትነግረው ዊልያምስ በጣም በጉጉት እያዳመጣት ነበር፡፡

“ሜክሲኳዊ ነው ወይስ አሜሪካዊ?”

“ስለ ዜግነቱ ስታወራ ሰምቼ አላውቅም፤ ግን የዚህ ሀገር ሰው ይመስለኛል ወይም ግምቴ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለብዙ ጊዜያት ወደ ሌሎች ሀገሮች በስራ ምክንያት የሚንቀሳቀስ ይመስለኛል፡፡ ማለቴ ብዙውን ጊዜ ከተማ ውስጥ አይገኝም ነበር፡፡ ባይገርምህ እሱ ወደ ውጪ ሀገር ለስራ በሚወጣባቸው ጊዜያት ልክ ሙጭሊቷ እንደጠፋባት እናት ድመት ነበር ያደርጋት የነበረው።

ዊልያምስ ማስታወሻ እየወሰደ “እንዴት እንደተገናኙ ታውቂያለሽ?” ብሎ
ፍሬድሪኩም ዝም ብላ ለጥቂት ሰከንዶች ስታስብ ቆየችና በመቀጠልም
“ከእሱ ጋር የተገናኙት
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

...አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ ለተለመደው የሥራ ጉዳይ ሳይሆን ለግላዊ ጉዳዩ ወደ አለቃዬ ጽሕፈት ቤት ገባሁ፡፡ በመጠኑ ግልጽ ሆኖ መናገር ፈቃድ በማግኘት በኩል ነገሩን የሚያፋጥንልኝ ስለ መሰለኝ ያጋጠመኝን ጉዳዬ ቀነጫጭቤ በሾላ በድፍን ዘዴ አስረዳሁ፡፡ ንግግሬን እንደ ጀመርኩ የወዲያነሽ ጆሮዬ ላይ ለጠፍ ብላ የምታበረታታኝ መሰለኝ፡፡

አለቃዩ አንደበቱን አለስልሶና የዝቅተኝነትን ስሜት በሚገልጹ ቃላት ተጠቅሞ የሚጠይቃቸውን ሰው ስለሚወዱ ጆሮአቸውን አቁመው ሰሙኝ::
የጉዳዩን አሳሳቢነትና መደረግ የሚገባውን ውጣ ውረድ ሁሉ ከኑሮ ልምዳቸው ስላወቁልኝ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እያመለከትኩ ለመሔድ እንደምችል ካንዳንድ ግዴታዎች ጋር ነገሩኝ፡፡ አዎ ጌታነህ ከባድ ግዴታ ያለብኝ ሰው ነኝ።

የመጀመሪያዋን ቃታ ሳብኩ! ማመልከቻዪን ለዕጓለ ማውታው የበላይ
ባለሥልን ለማቅረብ የሐሳቤ ዝግጅት ተጠናቀቀ። የእኔንና የባለቤቴን
የግንኙነት መነሻ፣ የወላጆቼን የአመለካከት አቋም፣ እንዲሁም የልጃችን
ሕይወት ለምንና እንዴት ለዚያ ዕጓለ ማውታ እንደበቃ ተንትኖ የሚያስረዳ
ጽሑፍ ማዘጋጀት እንዳለብኝ ከየወዲያነሽ ጋር ተነጋገርንበት።

ማታ ከት/ቤት መልስ ግራና ቀኝ ተቀምጠን ሐሳብ ለማቀነባበር
ተፍጨረጨርን፡፡ ከጉዳዩ አፈጻጸም ጋር በጣም ተፃራሪ የሆነ አቋም ቢኖረኝም ሁኔታውን ሁሉ ተቋቁሞ ሌላ አመቺ ሁኔታን መፍጠር ግን የማይቀር ግዴታ ሆነ፡፡ በመጠኑ ሞጫጭሬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ ለወጉ ያህል ጋደም አልኩ።ቁንጫውን ለማራገፍ እንደሚንደባለል ውሻ አልጋዩ ላይ መንከባለል እንጂ እንቅልፍ በማጣቴ ሁለት ሰዓት ያህል ቆይቼ ተነሣሁ፡፡ አካባቢዬ ጸጥ በማለቱ ሐሳቤን በቅደም ተከተል ለማስፈር ውጫዊ ችግር አልገጠመኝም፡፡ ምንም እንኳ የእኔና የወዲያነሽ የሕይወት ገድል በሁለትና በሦስት ገጽ ጽሑፍ ተዘርዝሮ የማያልቅ ቢሆንም መቆነጻጸሉ ግን የግድ አስፈላጊ ነበር፡፡ የወዲያነሽ በወላጆቼ ቤት ውስጥ ሠራተኛ ሆና ማገልገሏን፣ በእርግዝናዋ
ወራት ከቤት መባረሯን፣ የእኔን ማንነትና ያረገዘችውም ከእኔ እንደ ነበር፣
በችግርና በእጦት ተንገላታ ልጅዋን በጭካኔ ሳይሆን በአስገዳጅ የኑሮና የጊዜ ሁኔታ አሳዳጊ እንዲያገኝ ብላ ጥላው መጥፋቷን፣ ከዚያም በወንጀለኛነት ተይዛ አምስት ዓመት መታሰሯን፡ ልጁም በድርጅቱ አማካይነት በማደግ ላይ መሆኑን በልክ በልኩ አሳምሬ ጻፍኩ፡፡ በተጨማሪም እኔና የልጄ እናት በነበረንና ባለን እውነተኛ ፍቅር ትዳር መሥርተን ኣብረን በመኖር ላይ
መሆናችንን አከልኩበት። ቀላል በሆነ አገላለፅ የተቀነባበረ ማመልከቻ
ተዘጋጀ፡፡
በመጨረሻም ድርጅቱ ይህን እስከ ዛሬ ድረስ በጥንቃቄ ያሳደገልንን ልጅ በሕጋዊ መንገድ አስረክቦን ልጃችንን ማሳደግ እንችል ዘንድ የሚጠይቅ ማለፊያ መደምደሚያ አደረግሁለት። ረቂቁን ገልብጬ ስጨርስ ሰማይና መሬት ተላቀቀ። የወዲያነሽ ከእንቅልፏ ነቃች፡፡ አልጋውና የተቀመጥኩበት ወንበር አፍና አፍንጫ ነበሩ። መለስ ብዬ ስመለከታት ካንገቷ ቀና ብላ በድንጋጤ ታስተውለኛለች፡፡ እጆቿን በትከሻዬ ላይ አሳልፋ ጣቶቿን ደረቴ ላይ አንጠለጠለቻቸው። የተበታተነው ጸጉሯ አንገቴ ላይ ሲኩነሰነስ በጣም
እንደ ተጠጋችኝ አወቅሁ፡፡ ተቀምጬ በማደሬ አካላቴ ዝሏል፡፡ የወዲያነሽን
ሐሳብ ላይ ጣልኳት፡፡ በቀኙ ትከሻዬ ላይ ደፋ አለች። በአንገቴ ሥር የተጋደመውን ክንዷን እየደባበስኩ «እንግዲህ አንድ ጊዜ ጀምሬዋለሁ፣ ፍጻሜውን ሳላይ ፊቴን አላዞርም» አልኩና ጽሑፉን አነበብኩላት። የሐሳብ ሰመመን ይዟት ነጎደ። የጻፍኩትን ማመልከቻ ሳጣጥፍ በአእምሮዬ ውስጥ
የተረገዘው ፍላጎቴ ዕለተ ልደቱ እንደ ደረሰ ታወቀኝ፡፡ ውጤቱን በግምት ሳሰላስል የወዲያነሽ ከአልጋው ላይ ወረደች፡፡
ቁርሴን በልቼ ከቤት ስወጣና መኪና አስነሥቼ ስሔድ የማልመለስ ስለ መሰላት ዐይኖቿ ከላዪ ላይ ሳይነቀሉ ተለይቻት ሔድኩ።

ማመልከቻዬን ለባለ ሥልጣኑ ከማቅረቤ በፊት መኪናዬ ውስጥ ሁለት ጊዜ ወጣሁት። የድፍረት ወኔ አጥለቀለቀኝ፡፡ አረማመዴ ጎምላላ ሆነ።አንኳኩቼ ስገባ መላ ሰውነቴ ተሟሟቀ። ማመልከቻዬን ሳቀርብ በሐተታው ርዝመት እንጂ በዘረዘርኩት ከፊል ምስጢር ቅንጣት ታህል አላፈርኩም፡፡አያሳፍርማ!! እንዲያውም ማቀርቀሬና መደንገጤ ቀርቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማቅረብ ተዘጋጀሁ፡፡ ለሦስት ደቂቃዎች ያህል ታሪኩን ያላንዳች እንቅስቃሴ
አነበቡት። የታሪኩ አነሳና አካሔድ ስላስደነቃቸው ራሳቸውን ይነቀንቁ
ጀመር፡፡ ስሜታቸውና ሁኔታቸው ስላፍነከነከኝ የተስፋ ምጥ አጣደፈኝ፡፡
የሚያስደንቅ ዐረፍተ ነገር ሲያጋጥማቸው ንባባቸውን እያቋረጡ ስለሚመለከቱኝ የምትወጂውን ታሚያለሽ እንደ ተባለች ፈሰሰ ሁለመናዬ በደስታ ተነከረ፡፡ ሁለቱን ገጾች ጨርሰው ሦስተኛዉን ሲጀምሩ ወረቀቱን አጠፍ አድርገው ጠረጴዛውን በሁለት ክንዳቸው ተመረኮዙ። ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ጸጉሬ ተመለከቱኝ። እንደገና ደግሞ «ልጄን በችግርና በሥቃይ ከመግደል ይልቅ ምናልባት ርኅሩኅ አሳዳጊና ሰብሳቢ ቢያገኝ ብዩ ብዙ ሕዝብ ከሚተላለፍበት መንገድ
ላይ በጨርቅ ጠቅልዩ ጣልኩት» የሚለውን የእናትየዋን አነጋገር ጽፌው ስለ ነበር ጮክ ብለው አነበቡት።

ምንም እንኳን እሷን ለመርዳትና ልጀንም ለማሳደግ ሙሉ ችሎታ ቢኖረኝም ከቤት የተባረረችው በሌለሁበት ጊዜ ስለነበርና ኋላም አድራሻዋን ለማግኘት ባለመቻሌ ይህ የአንድ ትውልድ የመጥፎ ልማድ ድርሻ ሊደርስብን ቻሏል የሚለውን ሐተታ በቀዳሚው የድምፅ ሁኔታ ደገሙት። አንብበው ከጨረሱ በኋላ ላቀረቡልኝ ጥያቄ የተብራራ ኣጥጋቢ መልስ ሰጠሁ፡፡ ጥያቄ በሚያቀርቡበትና መልስ በሚሰሙበት በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥንቃቄ የጦር ስልት እንዳይበላሽበት የሚከታተልና የውጊያ ስልት ሚዛን የሚቆጣጠር የጦር አበጋዝ ይመስላሉ፡፡ መልሶቼን ሁሉ እያጣጣሙ ተራ በተራ ዋጧቸው::

ለእርሳቸው የአንድ ጉዳይ ተራ ውጥን ቢሆንም፡ ለእኔ ግን አንድ አነስተኛ የትግል ምዕራፍ ነበር፡፡ ሙሉ ተስፋ በማይሰጥ ሁኔታ ቀጠሮ ተቀብዩ ወጣሁ፡፡

ጉዳዩ በቀላሉ የማይፈጸም በመሆኑ ድርጅቱ ጥያቄውን አብላልቶ ከአንድ ውሳኔ ላይ ለመድረስ በጉዳዩ ላይ አተኮረበት።

ደጅ ደጁን ፍሬ ሐሳብ የሚያቀብለኝና በጎደለ የሚሞላልኝ ጉልላት ነበር፡፡ በየቀጠሮው ቀን ስቀርብ የሚጠብቀኝ ጥያቄ ከዕለት ወደ ዕለት እንደ
ስንቅ ሟሸሸ፡፡

አነጣጥሬ የለቀቅሁት የሰላም ቀስት ዒላማውን መታ፡፡ ልክ ባሽመቅሁ
በኻያ አንደኛዉ ቀን የድርጅቱ ደንብ እና ሌላውም ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ልጁን የምረከብበት ቀን ተነገረኝ፡፡ ባለቤትህን ይዘህ እንድትቀርብ
ተብዬ ስለ ነበር የወዲያነሽን ተነሽ አልኳት፡፡ ዶፍ እንደ ወረደበት የፍየል
ግልገል አካላቷ ተሽማቀቀ፡፡ ልማደኛ እንባዋ አትንካት ሲል ተንቆረዘዘ፡፡
አስታራቂ ሐሳብ ስላልነበረ ተረታች፡፡ «እንዴት ብዩ ከሰው ፊት እቀርባለሁ?
ያለፈውን አድራጎቴን ሁሉ ቢጠይቀኝስ ምን እመልሳለሁ? ይቺ ጨካኝ
አረመኔ ቢሉኝስ ምን እላለሁ? አንተን እንዳልኩህ ነው የምላችው?» ብላ
በሥጋት ጠየቀችኝ። እእምሮዋ ተናውጦ እንዳይናጋ የፈጸምሽው ሁሉ በወቅቱ
ባጋጠመሽ አስገዳጅ ሁኔታ የተደረገ ተራ ድርጊት እንጂ ይህን ሁሉ አጓጉል
ስያሜ የሚያሰጥ ባለመሆኑ አታስቢ» ብዩ ካግባባኋት በኋላ ሄድን።

በመንገድ ላይና ድርጅቱም ጽሕፈት ቤት ከመግባታችን በፊት በጣም ስለ አበረታታኋት አራት የድርጅቱ ባለሥልጣኖች በተሰበሰቡበት ክፍል ውስጥ ለጥያቄዎቻቸው ሁሉ መልስ እንድትሰጥና ሐሳቧንም ያላንዳች ግፊት
እንዲሰሙ ጥያት ወጣሁ፡፡ በአስተዋይነቷ ስለምተማመን ምን
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


በሌቱና ወላጆች ቤት ላይ የሥጋት አሞራ ረጃጅም ክንፎቹን ዘርግቶ
በቅርብ ርቀት በማንዣበብ ላይ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ጃኖ ከዛሬ ነገ ምን ያመጣብን ይሆን? ምን ያደርገን ይሆን? በሚል ጭንቀት ተውጠው ከከረሙ በኋላ በተፈጠረው ትንቅንቅ ጉዳት የደረሰበት ባላባት ቱሬ ደግሞ ምን ፍጠሩ? ምን ውለዱ ይለን ይሆን? ምንስ ያስደርገን ይሆን? በሚል ተጨማሪ ጭንቀት ተውጠው እንቅልፍ አጥተው ከርመዋል።

ሴት ልጅ ስትወልድ ወላጆች በደስታ ይፈነድቃሉ። ሴት ልጅ ብር ነች።ሴት ልጅ ንብረት ነች፡፡ ለአቅመ ሄዋን ደርሳ በባህሉ መሰረት ለጋብቻ ስትጠየቅ በገበራ ቤተሰቦቿን ትክሳለች፡፡ በተለይ መልኳ ቀንቶ ዕድሏ ተሳክቶ ባለንብረት ለትዳር የሚጠይቃት ከሆነ ደስታው እጥፍ ድርብ
ነው፡፡ የቁም ከብቶች ከበግና ከፍየል ጀምሮ ሰንጋ ፈረስ ወይንም ምርጥ ሰጋር በቅሎ ለወላጆቿ በገበራ መልክ ታመጣለች ታሸልማለች። የሌቱና
ወላጆች ምኞታቸውና ተስፋቸው ይሄው ነበር፡፡ ሌቱና ተድራ የምታንጋጋው የገበራ ንብረት እየታያቸው በደስታ ነበር የኖሩት፡፡ ሴት ልጅ ለትዳር ምርጫ ዕድል አይሰጣትም፡፡ የወደደችውን ያፈቀረችውን ማግባት አትችልም፡፡ ቢጥማትም ባይጥማትም ወደደችም ጠላችም ፊቷ በነጠላ
ተሸፍኖ ወላጆቿ ከተስማሙበት ጋር ተቆራኝታ መነዳት ግዴታዋ ነው።የሷ ትዳር ጣዕም የሚቀመሰው በወላጆቿ ምላስ ጫፍ ነው። በራሷ ስሜት አጣጥማ የጣፈጣትን የመብላት ያልጣፈጣትን የመተው መብት
ማን ፈቅዶላት? እነሱ ቀምሰው ካጣጣሙላት መቼ አነሳትና?!

ሴቱና ግን ምኞቷና ፍላጎቷ ይሄ እንዲሆን አልነበረም፡፡ ዕድለኛ ሆና
አብሯት ባደገ ወጣት ፍቅር ላይ ከወደቀች ወዲህ ሁል ጊዜም የምትመኘውና የምታልመው እሱን አግብታ ልጅ ወልዳ መሳምን ዘር ዘርቶ መቃምን ነበር፡፡ አዎን ጃኖን! ከጭቃ ማቡካት ጀምሮ አብሯት ያደገው ጃኖን! ለአካለ መጠን ደርሰው መተፋፈር የጀመሩት ጃኖን! የልጅነት ትንሿ ልቧ የደነገጠችለት ጃኖን ብቻ ነው ቀን ከለሊት የምታሰላስለው።
ጃኖም ሌቱናን አግብቶ ልጅ ወልዶ የሚስምበትን በፍቅር ተደስተው የሚኖሩበትን አዲስ ህይወት በዐይነ ህሊናው አሻግሮ እየተመለከተ በተስፋ ሲጠባበቅ ቆየ፡፡ ይሁን እንጂ እሱ እንደሚያስበው ሁሉ እሱ እንደሚመኘው ሁሉ ሌቱናን ታስብ ይሆን? ሌቱናስ ትመኝ ይሆን? ለዚህ ጥያቄው ምላሽ የሚያገኝበትና ቁርጡን የሚያውቅበት ቀን እጅግ ራቀበት። “ጃኖ! አንተ እኮ አብሮ አደግ ወንድሜ ነህ እንዴት እንደዚህ ያለውን ከንቱ ሀሳብ ታስባለህ?” ብላ ቅስሙን የምትሰብረው ወይንም ደግሞ ፍላጎትህ
ፍላጎቴ ምኞትህ ምኞቴ ነው ብላ በደስታ ፈንድቃ እሱንም የምታስፈ
ነድቀውና የምታስቦርቀው ከነኝህ ከሁለቱ አማራጮች አንዱን መርጣ
ቁርጡን የምታሳውቀው ቀን እስከሚደርስለት ድረስ ውስጥ ውስጡን በፍቅር ሲሰቃይ ለብዙ ጊዜ ቆየ፡፡ ጊዜው ይቆይ እንጂ ትዕግስቱ መራራ ሬት ሳይሆን ጣፋጭ የወይን ፍሬ በማፍራት ላይ ነበረች፡፡ ቀስ በቀስ ያቺ ጣፋጭ የፍቅር ወይን በስላ ለመበላት መድረሷን የሚያውቅበት አስገገራሚ ዕለት እየደረሰችለት ነበር፡፡ ምንግዜም ከዐይነ ህሊናው የማትጠፋው ያቺ ውብ ቀን የብሩህ ተስፋ እቅፍ አበባዋን ለጃኖ ይዛ ከተፍ
አለች፡፡

አዝመራው ተንዠርጎ ምርቱን አግቶ ማስጎምጀት በጀመረበት በክረምቱ ወቅት በግብርና ሙያው የሚደነቀው ጃኖ ሹሩባ ማውጣት በመጀመረው የበቆሎ ማሳው ውስጥ ደፋ ቀና እያለ አረሙን በማጭድ በመመንጠር ላይ ነበር፡፡ ዝናቡ ያካፋል፡፡ እሱ ደግሞ እንጉርጉሮውን በዚያ ማለፊያ ድምፁ እያዥጎደጎደ አረሙን ያቀላጥፈዋል።“ጠቀሲስስ መዕስ
ስስስ ..ቋ!...ቋ!” እያደረገ የበቆሎ አገዳውን ግራና ቀኝ እየገፋ ወደሱ የሚመጣ ኮቴ ተሰማው። ጆሮውን አቀና፡፡ፊቱን ድምፅ ወደስማበት አቅጣጫ አዞረ። ማጭዱን አስተካከለና እንደ ማድባት አለ፡፡ ያንን ያማረ ቡቃያውን ሊያጠፋ ጮርቃውን በቆሎ እየገሽለጠ ሊቦጠቡጥ የመጣ ከርከሮ ወይንም ጃርት ይሆናል ብሎ ገመተ።በዚያ በማጭድ አንገቱን ሊቆርጠው አደፈጠ። የሆነ ነገር ውልብ አለበት። ዐይኑ ያየውን ነገር ተጠራጠረ፡፡ ጨፈነውና ገለጠው፡፡ እንደገና እንደገና.. እንደገና የማይታመን ነው። አይኖቹን ተጠራጠረ፡፡ ግን ልክ
ነው። ራሷ ሌቱና ነበረች። ፍልቅ... ፍልቅልቅ.. እያለች ተጠጋችው፡፡
“የትአባቱ! እስከመቼ ድረስ ጫካ ይመስል ሚስጥሬን ደብቄ እኖራለሁ?እስከመቼ ድረስ ውስጥ ውስጡን በፍቅር እነዳለሁ!” ብላ ቁርጡን ተናግራ ቁርጡን ከጃኖ አንደበት ለመስማት ስሜቷ ሂጂ! ሂጂ! ብሉ ገፋፍቷት ደመ ነፍሷ እየነዳ ወሰዳትና ከበቆሎው ማሳ ከአረንጓዴው ሰፊ ሳሎን ከጃኖ የበቆሎ እርሻ ውስጥ አምጥቶ ጣላት። “እኔ እኮ አብሮ አደግ ወንድምሽ ነኝ እንዴት እንደዚህ ታስቢያለሽ? ብሎ የሚያሳፍራት ከሆነም ጉዷን ለማወቅ ቆርጣ ነበር የመጣችው። ካፊያው አበስብሷታል። ጤዛው አርሷታል፡፡ጨጎጊት ቀሚሷ ላይ ተጣብቋል። እሷ ግን አንዱም ስሜት አልሰጣትም፡፡ አልተሰማትም ነበር። ከጃኖ ጋር ያላት ግንኙነት ቁርጡ የሚለይበት የመጨረሻው ቀን ነበርና እንዴት እንደመጣች ዝናቡ እንዴት አድርጎ እንደደበደባት ምንም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ሰው እንደዚያ አድርጎ ይደሰታል ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። ወደ ሰማይ እንጣጥ! ብሎ የደስታ ጮቤ ሊረግጥ ከጀለው። ማጭዱን ዳግም እንደማ ይፈልገው ሁሉ አሽቀንጥሮ ጣለው ..ከርከሮ ወይንም ጃርት መስሉት የተሰበቀው ለካስ በለይቱና ላይ ነበር? “የትአባቱ!” ብሎ ለለይቱና መዘጋጀቱ አናዶት ወደዚያ ወረወረው፡፡

በአካባቢው ያለነሱ በስተቀር ወፍ እንኳን ለምስክርነት በሌለበት በዚያ በካፊያ ውስጥ ሹልክ ብላ ከቤቷ ተደብቃ ወጥታ ገስግሳ የመጣችለትን የፍቅር ልዕልት ፍፁም በሆነ የደስታ ስሜት ተውጦ ወደ ውስጡ ጠቅልሎ ሊያስገባት እጆቹን እንደ አሞራ ክንፍ ግራና ቀኝ ዘረጋላትና
“ቱ!” ብሎ ጮኽ፡፡ ሌቱናም ግራና ቀኝ በተዘረጉት እጆቹ መካከል ሄዳ
ልክክ አለች፡፡ ከሚያካፋው ካፊያ ከቅዝቃዜው እንዲያድናት ጭምር ከተገላጠው ደረቱ ላይ ጥብቅ አለችበት፡፡ ጃኖ በህልሙ እንጂ በውኑ አልመስለውም፡፡ የሱ ሌቱና የሱ ፍቅር የዛሬ አመጣጧ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሳ ቁርጧን ለማወቅ አስባበት መሆኑን አወቀ። እሱ እንደሚያፈቅራት ሁሉ እሷም የምታፈቅረው መሆኑን ተገነዘበ፡፡ እንዳቀፋት ሰውነቱ ሙቀት የሚያመነጭ ጀነሬተር ሆነ። ትኩሳቱ አሻቀበ፡፡ ለዘመናት ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የኖረ ፍቅር ያመነጨው ትኩሳት! ሌቱናም በትኩሳቱ ውስጥ አተኮሰች፡፡ በሙቅ ሰውነቱ ውስጥ በስሜት ፈሰሰች፡፡ ከዚያም
በእፍረት ስሜት በተዋጡት ዐይኖቿ ዐይን ዐይኖቹን ሽቅብ እያየች “ጃኖ! ጃኖ! ትወደኛለህ? ታፈቅረኛለህ? ቁርጡን ብቻ። የመጨረሻውን ንገረኝና
ቁርጤን ልወቀው። አንድ ቃል በቃ... አንድ..ቃል” ዐይኖቿ በእንባ ተሞሉባት። ፀጥ አለች።

ለምን እስከዛሬ ድረስ ቁርጡን አልነገርከኝም፣ ለምን ያንቺው ነኝ አላልክኝም መሆኑ ነው፡፡ እንባና ሳግ ተናነቋትና ልሳኗ ተዘጋ፡፡ ጃኖም ቁልቁል ተመለከታት። በደስታ እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ በስስት አስተዋላት፡ የፍቅሩን ጥልቀት ለመግለፅ ቃላት አጠሩት፡፡ ውስጥ ውስጡን
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...በቀኝ በኩል ታጥፈው ዜሮ ሁለት ቀበሌ ውስጥ 'ግሪን ፓርክ' ተብሎ ከሚጠራው መዝናኛ በታች ወደሚገኘው ቤታቸው ሊያመሩ ሲሉ ሾፈሩ ከመኪናዋ ላይ ወርዶ ወደ እነሱ ሲራመድ አዩት፡፡ ደንገጥ ደንገጥ ብለው እያዩት ሳሉ ከአጠገባቸው ደረሰ።
«ምነው በምሽት ብቻችሁን?» አላቸው ለሰላምታ እጁን በተለይ ወደ ሔዋን እየዘረጋ።
ሔዋን የስውየውን ማንነት ወዲያው አወቀችው፤ በድሉ አሸናፊ ነው፡፡ እጇን መዘርጋት ትታ ወደ ትርፌ ደገፍ አለች፡፡ ዓይኖቿ ግን በበድሉ ላይ ስክት አሉ።

በድሉ አጭር ወፍራም ነው። ከአንገቱ ማጠር የተነሳ ጭንቅላቱ ትከሻው ላይ ቁጭ ያለ ይመስላል። መልኩ ጠቆር ያለ ጠይም ነው፡፡ አራት የፊት ጥርሶቹ
ወጣ ብለው ገጠጥ ያሎና ዓይኖቹ ትናንሽና ድፍርስርስ ያሉ ናቸው፡፡ በዕለቱ ጥቁር ቆዳ ጃኬት በነጭ ቲሸርትና ነጣ ያለ ሱሪ ለብሷል፡፡

«የእግዚአብሔር ሰላምታም ልነፈግ እንዴ?» አላት በድሉ የዘረጋውን እጁን ወደ ክንዷ አዙሮ
ያዝ እያደረጋት።
«ልቀቀኝ!» አለችው ሔዋን በጨለማው ውስጥ ፊቷን ጭምድድ አድርጋ እያየችው።
«የማነጋግርሽ ጉዳይ አለኝ፡፡» አላት ክንዷን ጠበቅ አድርጎ በመያዝ፡፡
«ስለምን ጉዳይ?»
«ቅድም አዳራሽ ውስጥ ያለቀስሽው እኔ ስላወላከፍኩሽ ከሆነ ይቅርታ ልጠይቅ እፈልጋለሁ»
«አይ! በእሱ አይደለም»
«ታዲያ ምን ሆነሽ ነው?»
«ዝምብዬ!»
«ዝምብሎማ ለቅሶ የለም !
የሆንሽው ነገር ካለ ንገሪኝ' ምናልባት ልረዳሽም እችላለሁ»
«አይ አይ ምንም ዕርዳታ አልፈልግም፡፡ ልቀቀኝና እንሂድ መሽቶብናል፡፡»አለችው ሔዋን አሁንም ክንዷን ለማስለቀቅ እየታገለች።
«በመኪና አደርሳችኋለሁ»
«አያስፈልገንም ቤታችን ቅርብ ነው»
«ቅርብ ከሆነ ታዲያ ምን አስቸኮላሽ»
ሔዋንን ንድድ አላት፡፡ ክንዷን ደግሞ ጥብቅ አድርጎ ነው የያዛት፡፡ አሁንም እየታገለች ልቀቀኝ አለበለዚያ እጮሀለሁ!» አለችው።
«እጮሀለሁ? ሲል በድሉ የሔዋንን ቃል ደገመው፡፡
«አዎ፣ እንዳልጮህ ከፈለክ ልቀቀኝ»
«እኔም እጮሀለሁ አለች ትርፌም፡፡» እስካሁን ድረስ ከአሁን አሁን የሚለቃት መስሏት ዝም ብትልም አሁን ግን የበድሉ አያያዝ አላምር አላት።
«አሃ! እንደ ከዚህ ቀደሙ ልታስደበድቢኝ ነዋ!» አላት በድሉ በተለይ ሔዋንን አየት እያረገ፡፡
«መቼ እስደብድቤህ አውቃለሁ?»
«ረሳሽው?»
ሔዋን በድሉ ምን እያለ እንደሆነ ሊገባት አልቻለም:: በእርግጥም ጩሂ ጩሂ የሚል ስሜት መጣባት። ነገር ግን በዚያ ጭር ባለ ቦታና ሰዓት ግን ማን
ሊደርስላት እንደሚችል አታውቅም::
«በእናትህ ልቀቀኝ!» አለች አዝኖ እንዲለቃት ለመለማመጥ።
«በልሁ ለሚባለው ሰውዬ ስለኔ ምን ብለሽ ነግረሽው ነው ሊደበድበኝ የተነሳው
««እሱ ሰው አይደባደብም»
«የተሞከረብኝ እኮእኔ ነኝ»
ነበር «ምን አደረክ ብሎ ይደበድብሃል?» በማለት ትኩር ብላ ስትመለከተው በድሉ የታችኛውን ከንፈሩን ነክሶ መሬት መሬት እያየ ያስብ ጀመር፡፡
" ያስታውሳል' በድሉ ሔዋንን በሽዋ ቤት ውስጥ እጇን ጎትቶ ፍራሽ ላይ ሊያስቀምጣት በሞክረበት ሳምንት ውስጥ ነበር፡፡ ከአንድ ቡና ቤት ውስጥ ብቻውን
ቁጭ ብሎ በሚጠጣበት ወቅት በልሁ በዚያ ቡና ቤት ውስጥ ገባ ሲል ሁለቱ ይተያያሉ፡፡ በልሁ ጠጋ ብሎ ስላም ካለው በኋላ አጠገቡ ቁጭ ይላል፡፡ ወዲያው
ያናግረዋል፡፡
«ይቅርታ የኔ ወንድም ፣ መቸም በዓይን እንተዋወቃለን»
«አዎ፡፡» ይለዋል በድሉ ፈዘዝ ብሎ ከነበረበት ስሜት ነቃ እያለ፡፡
«ላናጋግርህ የምፈልገው አንድ ጉዳይ ነበር፡፡»
«የምን ዓይነት ጉዳይ?»
«ሸዋዬ የምትባል መምህርት ታውቃለህ?» ሲል ይጠይቀዋል፡፡
«አልፎ አልፎም ቢሆን ወደ እሷ ቤት የምትሄድ መሰለኝ»
«ምነው?»
«ሔዋን የምትባል እህቷ ጋር የተለየ ጉዳይ አለህ? ወይ ደሞ ሊኖርህ የምትፈልገው ነገር ይኖር ይሆን?»
«አልገባኝም የኔ ወንድም» ካለ በኋሳ በድሉ በደረቁ ፈገግ ብሎ በልሁን እያየ እርግጠኛ ነኝ ፖሊስ አይደለህም"
«ትክክል። ፖሊስ አይደለሁም::
ልነግርህ የምፈልገው ግን ያቺ ልጅ
እጮኛ አላት ስለዚህ ላትጠቅምህ ነገር አንተም ባትለፋ እሷን" ባታስቸግራት ልልህ ፈልጌ ነው፡፡ ቅር ይልሀል?
ይህንንም ለመግለፅ ራሷ ልጅቷ ትበቃለች። የእንተ ጣልቃ መግባት
ያስፈልግ አልመሰለኝም"» ይላል በድሉ ፊቱን ኮስተር አድርጎ፡፡
«ጣልቃ መግባት እይደለም በድሉ፣ ጣልቃ ገቦችን ማስጠንቀቅ ፈልጌ ነው።
ሳታውቅ ላደረከው ነገር ይቅርታ ይደረግልሀል፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ብትሞክር ግን ሰው እየተዳፈርክ መሆኑን አውቀህ ብታስብበት ብዬ ነው
«ብታስብበት።» በማለት በድሉ ቃሉን ይደጋግማል «ጨርሻለሁ» ብሎ በልሁ ትቶት ይወጣል።
ይህ ብቻ አልነበረም በወቅቱ በድሉን ትዝ ያለው ነገር፡፡ እንድ ዕቅዱም እንደከሸፈበት አስታወሰ፡፡ ሔዋን ጓዟን ጠቅልላ ከቤቷ በወጣች ዕለት ሽዋዬ ያላሰበችው ዱብ ዕዳ ሆናባት የምታደርገውን አጥታ ተሸብራ ነበር፡፡ ሔዋን
ለታፈሡ ቤት የገባች መስሏት ዓይኗን በጨው አጥባ ካታፈሡ ቤት በመግባት ታፊሡን ራሷን ጠይቃት ነበር። ታፈሡ የሰጠቻት መልስ ደግሞ ሔዋን እኔ ቤት
ልትኖር አትችልም፡፡ የራሷን መኖሪያ አግኝታለች። ከእንግዲህ አታገኚያትምና ባትለፌ ጥሩ ነው የሚል ነበር። የታፈሡ መልስ እና የሔዋን ድራሽ መጥፋት
በማግስቱ ደሞ መሠረተ ትምህርት ወደ ምታስተምርበት ጣቢያ ሄዳ እግኝታት «የት ነው የሄድሽው አንቺ» ስትል ነበር ዓይኗን አፍጣ ጥርሷን አግጥጣ
የጠየቀቻ
«እዚሁ ዲላ ውስጥ ነኝ»
«ወደ ቤትሽ ትመለሻለሽ ወይስ አትመስሽም?»
«ፈጽሞ አልመስም»
አስደንጋጭ አቋም ነበር ለሽዋዬ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ስትብከነከን ቆይታ መጨረሻ ላይ በተለይ ከባርናባስና በድሉ ጋር በመሆን የቀቢፀ ተስፋ ምክክር አድርገው ስምምነት ላይ የደረሱበትም ዕቅድ ነበር። ሸዋዬ ያለ እስታራቂ ሔዋንን ለምናም ቢሆን ልትታረቃት፣ እናታችን ጠርታናለች ክብረ መንግስት ደርሰን
እንምጣ ብላ ልታታልላት! ሔዋን ስራዬስ ያለቻት እንደሆነ በአንድ ቀን አድርሶ የሚመልስን ሰው አለ ልትላት፣ እሺ ካለች በድሉ አለታ ወንዶ ድረስ ይዟቸው ሊሄድና እዚያው እለታ ወንዶ ከተማ ውስጥ መኪናዬ ተበላሸች ብሎ እየጎረጎረ ሊያስመሻቸው ከዚያም ማረፊያ ሆቴል ይዘው ሊያድሩና በድሉ ሔዋንን ሊደፍራት፡፡ ከዚያም እዚያው አለታ ወንዶ ስነባብተው ሔዋንን ሊያባብሉና
ሊያለማምዱ አስበው ነበር።
በእርግጥም ሽዋዬ ሔዋንን ለማታለል ብዙ ጥራ ነበር፡፡ ሔዋን ግን ፍንክች አላለችም፡፡ የእናቷ ጥሪ ትንሽ አሳስቧት በማማከር ሽዋዬ ያስቻትን ሁሉ
ለታፈሡ፣ ለበልሁና ለመርዕድም ነግራቸው ነበር፡፡ በተለይ በልሁ በአንድ ቀን አድርሶና የሚመልስ ሰው አለ የሚለው ቢነገርም ገብቶት በጣም ይናደዳል። አንድ ቀን መርዕድን አስከትሎ ወደ ሸዋ ቤት ይሄዳል፡፡ በአጋጣሚ ሸዋዬና በድሉ ፍራሽ ላይ ቁጭ ብለው ሲቅም ያገኛቸዋል፡፡ ቁጭ ሳይል በቋሙ ስሚ እንቺ!» ብሏት ነበር ሸዋዬን።
«አቤት!» ሸዋዬ በድንጋጤ ክረምትምት እያለች፡፡
እየሰራሽ ያለሽው ነገር ያልታወቁ እንዲይመስልሽ ዳግም ሔዋን ወደምትሰራበት ቦታ ብቅ ትዬና
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....ምንትዋብ አልጣሽ የተባለችውን ሁለተኛ ልጇን ወልዳ ከአራስ ቤት እንደወጣች እንደገና በግዛት ዘመኗ ልትፈጽማቸው ያሰበቻቸው ነገሮች ላይ ትኩረት አደረገች።

ትምህርት ቁስቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማስጀመር ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር መከረች። ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት አንድ ቀን እንግዳ መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል።

ትክ ብላ አየችው። ፈንጣጣ ፊቱ ላይ ምንም ምልክት ሳይተው
ማለፉ ገረማት። በቁስቋም ረድኤት መዳኒቱ ሠርቷል። ይኸን የመሰለ መልኩን ሊያበላሽብኝ እሷ የቁስቋሟ ማረችልኝ፡፡ አሁን ኢያሱን የመሰለ ልዥ አለ? የተባረኩ እያለች በሐሳብ ጭልጥ ብላ ሄደች።

ኢያሱ በሐሳብ እንደነጎደች ኣውቆ ከሄደችበት እስክትመለስ ዐይን
ዐይኗን እያየ ጠበቃት።

“አያትህ ታላቁ ኢያሱ ለትምርት ብዙ ዋጋ ሚሰጡ ሰው ነበሩ…
አለችው፣ ከሄደችበት ስትመለስ።

“አውቃለሁ። አንቺም ነገርሽ ሁላ እንደሳቸው ነው። ደሞስ የሳቸው
ስም መቸ ኻፍሽ ጠፍቶ ያውቃል?”

ከት ብላ ስትስቅ እሱም ሳቀ።

“ስለ ትምርት ላወራህ ፈልጌ ነው የሳቸውን ስም ያነሳሁ” አለችው፣
ፈገግ ብላ። “በሳቸው ዘመን የተማሮች ቁጥር ኸዝኸ ኸደብረሥላሤ ስንኳ ብዙ ነበር ይላሉ። ስንክሳርም በብዛት የተጣፈው በሳቸው ግዝየ
ነው። እንደ ክፍለ ዮሐንስ የመሰሉ ሊቃውንትም ኸጎዣም ያመጡ
እሳቸው ናቸው። ሊቁ አዛዥ ከናፍሮም ቢሆኑ በሳቸው ግዝየ ነው የነበሩ። ዛዲያ ልነግርህ የፈለግሁት ቁስቋም ውስጥ ትምርት ቤት ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ ለተማሮቹና ላስተማሮቹ ድጋፍ ማረግ አለብን
ሚለውን ነው።”
“እኔም ስለሱ ነግርሻለሁ እያልሁ ነበር። ሌላ ደሞ ባለፈው መጻሕፍት ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ እንዲመለሱ ፈልጋለሁ ስትይ
ማልነበር?”

"ትርጉም.... አዎ ስል ነበር። ሁሉ ባግባቡ ነው። ባለፈው መላከ
ጠሐይ ሮብዓምን ትርጉም ላይ ቢበረታ ብያቸው ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ሚመልሱ ሰዎች አምጥተው ሥራ እንዲዠምሩ ተደርጓል።
ለእነመላከ ጠሐይ ሃይማኖትን ሚያስተምረውንና ላገር ሚጠቅመውን ሁሉ እንዲያስተረጉሙ ነግሬያቸው እነሱ ተመካክረው ወስነዋል።”

"የትርጉም ሥራ ለገዳማቱ ቢሰጥ ጥሩ ነው ሲሉ ሰምቸ።”

“ዛዲያ ምን አለ... ይሰጣል ። በጎ አሳብ ነው። ትዛዝ ሰጣለሁ። እኔ
መቸም ቢሞላልኝ አገር ሁሉ መጻፍ በመጻፍ እንዲሆንና ትምርት
እንዲስፋፋ ነው ምፈልግ። እኔ ራሴም ብሆን አንድ ቀን ስለ እመቤታችን ማርያም ታምር አስጥፋለሁ ብየ አስባለሁ። ደሞ እሑድ እሑድ ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ግብር እናግባላቸው። አንተም ለነሱ ትልቅ ክብር አለህ። ቅኔም ተምረሀል። ቅኔ እውቀቴ እንዳንተ ባይሆንም፣ሊቃውንቱ ቅኔ ሲቀኙ ስሰማ መንፈሴ ሁሉ ይታደሳል። በተለይማ
የአክስትህን ልዥ እመት ወለተብርሃንን ስሰማ እንዳው እንደሳቸው ቅኔ በቻልሁ እላለሁ፡፡ አንተማ ኸኔም የበለጠ ትወዳቸዋለህ።”

የአክስቱ ልጅ ነገር ሲነሳ ፈገግ አለ። “ውነትሽ ነው እመት ወለተብርሃን ታላቅ የቅኔ ሊቅ ናቸው። እሑድ እሑድ ግብር ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ማግባት ያልሽው ተገቢ ነው። በተነጋገርነው መሠረትም በአካባቢው ወይን እንዲተከል ቦታ ብታስጠኚ። ቃሮዳ አየሩ ለወይን ተስማሚ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ቅርብም ነው።”

“ውነትህ ነው። ዛሬውኑ ሰው ይላካል።”

ሁለቱም ዝም አሉ።

“ግና ካህናቱና ሊቃውንቱ... ምናለ ልብሳቸውን ቢያጠዱ?” አላት።

ያልጠበቀችው በመሆኑ ከት ብላ ሳቀች። “ልብሳቸውን እንዲያጥቡ
ማረግ ይቻላል ። በጐንደር ዙርያና በየገዳማቱ እንዶድ ኣስተክለን
ልብሳቸውን እንዲያጥቡ እናረጋለና” አለችው፣ አሁንም እየሳቀች።

“ዋናዎቹ ካህናት ደሞ የወርቅ ጫማ እንዲያረጉ ፈልጋለሁ።”

“ወርቅ አሳብ ነው። ይታዘዝላቸዋል። የአክብሮትህ ምልክት ነው።

እንደገና ዝም ብለው ተቀመጡ። ኢያሱ ሐሳብ የገባው ይመስላል።
እሷም ዝም ብላ ታየዋለች።

ዐይን ዐይኗን እያየ፣ “አደን ብኸድ ትፈቅጅልኛለሽ?” እናቱን ፈሪና
አክባሪ ነው።

ዕጢዋ ዱብ አለ። አፏ ተያዘ። ሊመጣበት የሚችለው አደጋ
አሳሰባት። ጥያቄው ግን አንድ ቀን እንደሚመጣ ታውቃለች።

“ኣባትህ ስንኳ በኸዱ ቁጥር እጨነቅ ነበር። ኢያሱ እንድትኸድ
አልፈልግም፤ ጭንቀቱን አልችለውም።”

“ምን ችግር አለው?”

“ባትኸድ መርጣለሁ። ኢያሱ አልጋውን እኮ ባየነቁራኛ ሚጠባበቅአለ!”

“ሁሉስ እያደኑ ማዶል እንዴ የኖሩት?”

“ገና ልዥ እኮ ነህ ኢያሱ።”
ድምጽዋ ተርበተበተ።

“አትጨነቂ። ምንም ሚመጣ ነገር የለም። ሰዎች ይዠ ነው ምኸደው
በዝኸ ላይ ደሞ አልቆይም።”

“ኻንተ መለየት አልፈቅድም ኢያሱ ... መቸ ትነሳለህ?”
ነገ።”
“ነገ?”
“አዎ! ነገ።”
“ታሰብህበት ቆይተሀል ማለት ነዋ! መቸስ ምን ኣረጋለሁ። ቁስቋም
ደሕና ትመልስህ። በጠሎቴ አልለይህም።”

አይዞሽ አትጨነቂ። በጠዋት ስለምኸድ ካሁኑ ልሰናበትሽ” አላት፣ጠዋት መጥቶ ቢሰናበታት እንባዋን ማየት ስለማይችል። ተነስታ ወደ እልፍኟ ስትሄድ በጭንቀት ተመለከታት።

በማግስቱ ጠዋት ከእናቷ ጋር በመስኮት ቆመው የአደን ዕቃው
በቅሎ ላይ ሲጫን አይተው ሆዳቸው ባባ። ኢያሱ ፈረሱ ቀርቦለት፡ በሹሩባው ዙርያ ነጭ ሻሽ አስሮ፣ ካባውን ደርቦ ከዐጀቡ ጋር ብቅ ሲል፣ የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ ወታደሩ፣ ጋሻ ጃግሬውና ሌላው ሰገደ።ምንትዋብና እናቷ ግን ሲቃ ያዛቸው።
ከቤተመንግሥት ግቢ ሲወጣ፣
ምንትዋብ ጩሂ ጩሂ አላት። እንኰዬ ትከሻዋን መታ መታ አደረጓት።እሳቸውም እንባ እንባ ብሏቸዋል፤ ግን እሷን ማረጋጋት መረጡ።

ሁለቱም በየክፍላቸው ገብተው ወገባቸውን በገመድ አስረው ሱባዔ ገቡ። መሬት ላይ ተኙ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ጸሎታቸው ሠምሮ ኢያሱ በሰላም ተመለሰ። እናትና ልጅ ገመድ ትጥቃቸውን ፈቱ።የነበሩበትን ጭንቀት ሳይናገሩ በደስታ ተቀበሉት።

እያደር የአደን ፍቅር በረታበት፤ መዝናኛው አደረገው። በሄደ ቁጥር
እናቱና አያቱ ወገባቸውን በገመድ ጠፍረው መሬት መተኛትና ሱባዔ
መግባት፣ ሲመጣ ደግሞ ገመዳቸውን ፈትተው መጣል፣ ጸማቸውን መፍታት ልማድ አደረጉት። እንደዚህ እያለም ኢያሱ የከፋ ነገር ሳይገጥመው ቀለል ያለ አደን ማካሄዱን ቀጠለ።

ከእናቱ ጋር በተስማሙት መሠረት ከንባብ ቤት እስከ ትርጓሜ ቤት
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያምን በትምህርት ለማደራጀት ወጡ ወረዱ።ሁለት መቶ የሚጠጉ ምርጥ ሊቃውንት ከጐንደር ገዳማትና ከሌላ የሃገሪቱ ክፍሎች እየመጡ ወንበር ዘረጉ
የተማሪ ጎጆዎች ተቀለሱ። ትምህርት ከቁስቋም ሌላ በየገዳማቱና በየደብሮቹ ተስፋፋ። ወሬውን የሰማ ተማሪ ከየቦታው ፈልሶ ጐንደር ገባ፡፡ ጐንደር ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የሊቃውንት ማፍሪያና
መሰብሰቢያ ሆነች። ከጐንደር ውጭም ትምህርት ቤቶች ተስፋፉ።

የዜማ ሊቃውንት ድርጎ በማግኘታቸው ሙያቸውን አበለፀጉ ቤተክርስቲያንን አገለገሉ፤ ቤተመንግሥትንም አዝናኑ።

የሥዕል ሥራ በአያሌው አደገ። ቀለም አጠቃቀም ጥንት ከነበረው
ለውጥ አመጣ፣ የአቀራረብና የይዘት ለውጦች መጡ። ሠዓሊዎች ድጎማ እየተደረገላቸው አብያተ ክርስቲያናትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስጌጡ።
#ምንዱባን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


.....ማሪየስ ፤ ሰማህ? አንተ ብሎ ባሮን እነዚያ ሽፍቶች ፤ ቀማኞች ፧ አታላዮች ፤ አታላዮች ፤ አታላዮች እውነተኛውን ንጉስ
ከድተው ቦናገርቴን የተከተሉ ፈሪዎች ፧ የፈሪ ፈሪዎች ናቸው:: ዋተርሉ ላይ ጠላቶችን ፈርተው የሸሹ ወርቦለች! ይኽ ነው እኔ የማውቀው::አባትህ ከነዚህ ዉስጥ ከሆነ አዝናለሁ አላውቀውም ብል ይሻላል

መሴይ ጊልኖርማንድ በቃላት ወናፍ ሲያራግቡት ማሪየስ በተራው ጨሰ፣ ተናደደ ፤ ቁጣው ገነፈለ፡፡ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ የሚያደርገውን አጣ፤ የሚናገረውም ጠፋው፡፡ የአባቱ ስም ከፊቱ ተረገጠ፤ ተናቀ፡፡ በማን
በአያቱ፡፡ ታዲያ እንዴት ይበቀል? አያቱን መልሶ እንዳይሰድብ ያስነውራል::ዝም እንዳይልም አሳቡ ዘገነነው፡፡ በአንድ በኩል የአባቱ መቃብር በሌላ በኩል የአያቱ ሽበት ታየው፡፡ ነገሩ ሁሉ ስለተምታታበት ፈዝዞ ቀረ ።
ጥቂት ቆይቶ ቀና በማለት አያቱን አፍጥጦ አያቸው::

«በርበኖችና ትልቁ አሳማ ልዊ 18ኛ ይውደሙ» ሲል በታላቅ ቁጣና ጩኸት ተናገረ::

ንጉሡ ልዊ 18ኛ ከሞቱ አራት ዓመት አልፎአል:: ግን ለማሪየስ
ለውጥ አላመጣም::

ሽማግሌው በድንገት ፊታቸው በንዴት ብዛት ከፀጉራቸው ጀምሮ
ጠቆረ፡፡ ከዚያም ቃል ሳይናገሩ አንዴ ወደ መስኮት፧ አንዴ ወደ በሩ
በዝግታ ተራመዱ፡፡ ቀጥሉም እንዳረጀ በግ ድምብርብራቸው ወደ ወጣው ሴት ልጃቸው ዞር ብለው ፈገግ በማለት የሚቀጥለውን ተናገሩ፡:

«እንደ መሴይ ያለ ባሮን እንደ እኔ ያለ ቡርጓዥዋ ከአንድ ጣራ ስር
ለማኖር ያዳግታል፡፡» ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠና ቁጣቸው እንደነበልባል ከፊታቸው
ላይ እየሰራ ቀጥ ብለው ቆሙ:: እጃቸውን ወደ ማሪየስ ዘርግተው «ከዚህ ቤት ውጣልኝ» ሲሉ ጮሁ:: ማሪየስ ከቤቱ ወጣ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ለሴት ልጃቸው ሲናገሩ «ለዚህ ደም መጣጭ
በየስድስት ወር ስልሣ ፒስትልስ ትልኪለታለሽ፤ ለእኔ ግን ሁለተኛ ምንም ነገር እንዳታነሺ» ሲሉ አዘዙ፡፡

ነገሩ በጣም ስላሳዘናቸውና ስላናደዳቸው በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አሳጣቸው:: ሴት ልጃቸውን ሲያነጋግሩ እንኳን እጅግ ቀዝቀዝ ብለው ነበር፡፡

ማሪየስ ከቤቱ የወጣው ወደዚያ ቦታ ነው የምሄደው ሳይል ነበር
እነርሱም የት እንደሚሄድ አልጠየቁትም:: ጋሪ ተከራይቶ ዘልሉ ከገባ በኋሳ ጋሪው ወደ መራው ሄደ፡፡

ማሪየስ ምን ሊያደርግ ነው?

የእህቤሴ ጓደኞች

ማሪየስ ከቤቱ በወጣበት ጊዜ የለውጥ አየር ይነፍስ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ሳይታወቀው ንቅናቄ ውስጥ እየገባ አብዮተኛ ሆኖኣል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ፡፡ ንጉሣውያን ቤተሰብ እንኳን ሳይቀሩ በነገሩ ገቡ።ሰዎች ከጊዜ በኋላ ናፖሊዮንንና ነፃነትን እንደ አምላክ የማምለክ ስሜት አደረባቸው:: ሌሎች ደግሞ ዓለም ፍጹም እንድትሆን ተመኙ::
የዛሬው ምኞት ነገ ሥጋና ደም ለብሶ እሙን እንደሚሆን አመኑ፡፡

የአህቤሴ ጓደኞች እነማን ናቸው? አህቤሴ የተረገጡ፤ የተከፉና
የተረሱ ጭቁኖች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች በፖለቲካው እንቅስቃሴ ሳቢያ ብዙ ወዳጆች ያፈሩ ናቸው:: ጓደኞቻቸወም ከወደቁበት እንዲነሱ ከልብ ተመኙ:: ሰዎቹ ብዙ አልነበሩም:: ፓሪስ ከተማ ውስጥ ሃሌስና ኮርኒት ከተባሉ ሥፍራዎች በየጊዜው ከአንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ
ይሰበሰባሉ: ሥፍራው ወዛደሮች የሚኖሩበት አካባቢ ነው:: በዚያ አካባቢ ተማሪዎችም በብዛት ይገኛሉ፡፡ የአህቤሴ ጓደኞች የሚሰበሰቡበት ቡና ቤት
«ካፌ ሙሴን» ይባላል፡፡ ቡና ቤቱ ሰፊ ጓዳ ስለነበረው የአህቤቴ ጓደኞች ከዚያ ክፍል ውስጥ ይሰበሰባሉ:: ክፍሉ ከዋናው መጠጫ ክፍል ትንሽ ራቅ
ያለ ነበር፡፡ በጓሮ በኩል ወደ ውጭ የሚያስወጣ በር አለው::

ጓደኛሞቹ ከዚያች ክፍል ውስጥ ይጠጣሉ፤ ሲጃራ ያጨሳሉ:፧
ይጫወታሉ፤ የፖለቲካ ወሬ ያወራሉ:: የማያነሱት ነጥብ የለም፡ከክፍለ ግድግዳ ላይ የበፊቱን የፈረንሳይ ሪፑብሊክ ካርታ ሰቅለዋል።

የዚህ ቡድን አባሎች አብዛኞቹ ተማሪዎች ሲሆኑ ጥቂት ወዛደሮችም ነበሩበት፡፡ ጥቂት ቀንደኛ መሪዎች አሉዋቸው:: ከመሪዎቹ መካከል ኔንጀልራስ የተባለው የሀብታም ልጅ ቀንደኛ መሪ ሲሆን ደስ የሚልና
መልከ መልካም ወጣት ነው:: ደግሞም በጣም አዋቂ ከመሆኑም በላይ ወኔው ለጉድ ነው:: ከቀንደኛው መሪ ከኢንጆልራስ ጎን የተሰለፉ ሌሎችም ረዳት መሪዎች አሉ::
አንዳንዶቹ በፖለቲካው ሌሎቹ ደግሞ በሰው ልጅ ፍቅር የሰከሩ ናቸው:: አንዳንዶቹ ‹‹ጭቁኖችን ነፃ እናወጣለን ብለው የተነሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ «አገራችን ውስጥ አድልዎ የተለየው ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰፍን ጽኑ እምነታችን ነው» የሚሉ ናቸው::

ሆኖም በመካከላቸው አንድ ተጠራጣሪ ሰው ነበር፡፡ ታዲያ የሕዝቦችና የግለሰብ መብት፧ የፈረንሳይ አብዮት ፧ ሪፑብሊክ ፧ ዲሞክራሲ ፧ ለሰው ሥልጣኔ፤ ሃይማኖት፧ መሻሻልና የመሳሰሉት ቃላት ለእርሱ ትርጉም የላቸውም:: እነዚህን ቃላት በሰማ ቁጥር ይስቃል:: ታዲያ ከነዚህ የተለየ ዓላማ ካላቸው ሰዎች መካከል ይህ ሰው እንዴት ሊደባለቅ ቻለ?

ይህ ሰው ተጠራጣሪ ቢሆንም የራሰ እምነት ነበረው:: እምነቱ
በኢንጂልራስ ላይ ነው:: ኢንጂልራስን ይወደዋል፣ ያደንቀዋል፣ ያምንበታል::
ለዚህ ነው በዓላማ አንድ ከነበሩና እንደ ቤተሰብ ከሚተያዩ ሰዎች መካከል ሊገባ የቻለው:: ኢንጆልራስ ይህን ተጠራጣሪ በፍልስፍና ወይም በነበረው
የተለየ አሳብ ሳይሆን በጠባዩ ነው የገዛው፡፡

አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፤ ሕይወት በአጋጣሚ የተሞላች ናትና፧
አንድ ነገር በአጋጣሚ ይሆናል፡፡ ከፈረንሳይ አብዮት ጠንሳሾች መካከል አንዱ ከካፌ ሙሴን በራፍ ግድግዳ ተደግፎ ቆሞአል:: እርሱ ከዚያ እንደቆመ ጋሪ በዚያ በኩል ያልፋል፡፡ ይህ ሌግል የተባለ ወጣት ጋሪውን ሲመለከተው
በጣም ዝግ ብሎ ስለሚሄድ አንድ ነገር እንደሚፈልግ ጠረጠረ:: አነስተኛ ሻንጣ የያዘ ሰው ጋሪው ላይ ከነጂው ጎን ቁጭ ብሎአል፡፡ ሻንጣው ላይ ማሪየስ ፓንትመርሲ የሚል ጽሑፍ በጉልህ ተጽፎበት ስለነበር ሌግል ጽሑፉን ያነባል::

ማሪየስ ፓንትመርሲ የሚለው ስም በጣም ማረከው:: ጋሪው ከአጠገቡ ሲደርስ «መሴይ ማሪየስ ፓንትመርሲ» ሲል ተጣራ:: ጋሪው ቆመ:: ጋሪው
ላይ የነበረውና በአሳብ መጥቆ ሄዶ የነበረው ወጣት ቀና አለ፡፡
«ምን ነበር?» ሲል ጠየቀ፡፡
«መሴይ ማሪየስ ፓንትመርሲ ማለት አንተ ነህ?»
«ነኝ፡፡»
«ስፈልግህ ነበር፡፡»
«እንዴት ሊሆን ይችላል? አታውቀኝ፤ አላውቅህ» ሲል ማሪየስ ጠየቀው
«ትናንት ትምህርት ቤት አልመጣህም፡፡»
«ላልመጣ እችላለሁ::»
««በርግጥ አልመጣህም::
‹‹ተማሪ ነህ አንተም?»
«አዎን፧ እንዳንተው ተማሪ ነኝ:: ከትናንት ወዲያ ልክ ወደ ክፍል
ልገባ ስል፧ አለ አይደል አንዳንዴ አስተማሪዎች ሦስት ጊዜ ስምህን ሲጠሩ አቤት ካላልክ ይሠርዙሃል፡፡ ስልሣ ፍራንክ ቀለጠች ማለት ነው::»
ማሪየስ ዝም ብሎ ይሰማል:: ሌግል ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«ብሎንዳው የሚባለው አስተማሪ ነበር ስም የሚጠራው፡፡ አስተማሪውን ታውቀዋለህ አይደል? ያ እንኳን ቀፋፊና ግትር አፍንጫ ያለው! የቀረ ተማሪ
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

..ሚስተር ካርይልና ሳቤላ ዊልሰንን አስከትለው በምዕራብ ፈረንሳይ ቡሎን በምትባል ከተማ ደርሰው ወደ ቤንስ ሆቴል አመሩ " ፒተር የሚስ ካርላይል አሽከር
የነበረ ሲሆን ወደ ኢስትሊን ሲዛወሩ ወደነሱ ዙሮ እንደ ነበር እዚህ መጥቀሱ ተግቢ ይሆናል " ቡሎኝ እንደገቡ ወደ ቤንስ ሆቴል ሔደው ሚስዝ ዱሲ መኖሯን ጠየቁ ቀድማ ዴርሳ ልትቀበላቸውና ሳቤላንም ልታላምድ ታስባ የነበረችው ሚስዝ ዱሲ በቤተሰብ ችግር ምክንያት ወደ ጀርመን መሔዷን ከተወችላት ደብዳቤ ተረዱ"

“ ፊቱንም ቢሆን ማወቅ ነበረብኝ እንደሷ በቃሏ የማትገኝ ሴት የለችም አለች ሳቤላ "

ሚስተር ካርላይልም እሷ ከሌለች ወደ ትሩቪል መሔድ መሻሉን አማክሯት ነበር ሳቤላ ግን አንድ ጊዜ ቡሎኝ ከገባች ከዚያው መቆየቱን መረጠች " እሱም
ቤንስ ሆቴል ግርግር ይበዛበት ስለነበር፡ ጸጥታና ክብር ያለበትን ሆቴል ፈልጎ በኤኩ መንግድ በኩል ከወደቡ አጠገብ አንድ በጣም ጥሩ ሆቴል አገኘና ወዶፈደዚያ ተዛወሩ ወዟ ቶሎ ምልስ ሲል አይቶ ሚስተር ካርላይል ጉዞው ደኅና የረዳት መሰለው እሷም ብርታት እንደ ተሰማት ነገረችው አንድ ቀን ብቻ ውሎ ለመመለስ የመጣውን
የብርታቷ መታደስና የፊቷ መለምለም ሲያይ ስለ ተደሰተ የዚያች ወጭ ወራጅ አላፊ አግዳሚ የበዛባትና የተጨናነቀችውን ከተማ ሁኔታ እያየ ጭምር ሦስት ቀን አደረ።

“ እኔ እዚህ ከማንም ጋር ለመተዋወቅ አልፈልግም
አለችው ሳቤላ ከወደቡ መድረክ አንድ ጫፍ ላይ ተቀምጠው ባጠገባቸው እየተጋፉ ሲያልፉ የነበሩትን ብዙ ደስተኛ ሥራ ፈቶችን እየተመለከቱ "

“ በደፈናው እንደዚህ ማለቱ እንኳን ደግ አይሆንም ” አላት ሲመልስላት እንዳጋጣሚ የምታውቂው ሰው ታገኚ ይሆናል " ብዙ ዐይነት ሰዎች ወደዚህ
ይመጣሉ አንዳንዶቹ ሐቀኞችና የተከበሩ ሆነው ለተከበረ ዓላማ ይመጣሉ አንዳንዶቹ ደግሞ በተግላቢጦሹ በመጥፎ ጠባያቸው ዕዳና ዱቤ በማብዛታቸው ኢንግላንድ ውስጥ መኖር ስለአልቻሉ ካገር እየሸሹ በሀብት የከበሩና የቅዱሳን ኑሮ የሚኖሩ መስለው የሚታዩ አጭበርባሪዎች ናቸው "

“ አንተ ወደ ባሕር ማዶ እንኳን መጥተህ አታውቅም እንዴት ታውቃቸለህ.. አርኪባልድ ?”

“ ቦታውን ከሚያውቁ ብዙ ሰዎች ጋር እገናኛለሁ ለምሳሌ ባክስታንን ተመልከቼው እሱም አይቶኛል " ወደፊት በመምጣት ወይም ወደ ኋላ በመሸሽ መካከል ሊቆርጥ አልቻለም ።

"ማን ? የቱ ነው እሱ ?”

“ ያ ረጂም ጸጉረ ቀይ ደኅና ልብስ ለብሶ በሰዓቱ ማሰሪያ ብዙ ጌጥ ያንጠለጠለው " ሚስቱ ደግሞ ከሌሎች ሴቶች ጋር ሆና ስትከተለው ተመልከቻት
የለበሰችው ልብስ ያጠለቀቻቸው ሐብሎችና በእጅዋ ያደረገቻቸው አምባሮች ሁሉ ሰው አማኝ ከሆኑ ነጋዴዎች በማጭበርበር የተወሰዱ ናቸው " እዚህ ባለው የእንግሊዝ ኅብረተሰብ መኻል ግን ትልልቅ ስዎች መስለው ለመታየት እንደሚሞክሩ አይጠረጠርም ደከመሽ እንዴ ? አላት ።

"አዎን ትንሽ ! እንግዲህ ወደ ቤት ብገባ ይሻለኛል "

ከወደቡ መድረክ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ቀስ እያሉ ሲወርዱ በጠቅላላ ሁኔታቸው ዐይነ ገቦች ሆኑና ብዙ ሰው አተኩሮ ይመለከታቸው ጀመር "

በበነጋው ጧት በሁለት ሰዓት በሚነሣው ጀልባ ወደ ኢንግላንድ ለመመለስ ሲሰናበታት : “ ደኅና ሁኚ . . . የኔ ፍቅር” አላትና ዝቅ ብሎ ከሳማት በኋላ “ራስሽን ጠብቂ አላት ።

“ ልጆቼን ሳምልኝ ... አርኪባልድ እና እ ... እና .. እ. እ” “ እና ምን ? ” አላት “ ሰዓት ደረሰብኝ ”

“ እኔ አለመኖሬን አይተህ ከባርባራ ሔር ጋር እንዳትዳራ ” አለችው የቀ
ለደች መስላ " እሱም እንደ ቀልድ ወሰደውና እየሣቀ ወጣ አነጋሯ ከልቧ መሆኑ አልገባውም "

ሳቤላ ተነሥታ ለቁርስ እንደ ተቀመጠች የቀሩትን ሳምንቶች እንዴት እንደ ምታሳልፋቸው ጨንቋት ትተክዝ ጀመር ። ከደሬሰችበት ቀን ጀምሮ ሁለት ጊዜ ከባሕሩ ሔዳ ታጥባ ነበር : ግን ጭንቀትና እንቅጥቅጥ ለቀቀባትና የሚስማማት ስላልመሰላት አቋረጠችው "

አየሩ በጣምደስ የሚል ስለነበር ማታ ከባሏ ጋር ካመሹበት የወደብ መድረክ ዘልቃ ለመሞከር አሰበች " ስለዚህም ፒተርን አስከትላ ሔዳ ከተቀመጠች በኋላ አንድ ሰዓት ቆይቶ እንዲመጣ ነግራ መለሰችው እሷ ከዚያ የተለያዩ ተላላፊዎችን ትመለከት ጀመር " አንድ እግረ በሺተኛ ሰውዬ በጨርቅ ማማ ሲሔድ አየች " ቀጠሉና ሦስት ቆነጃጂት ከሞግዚታቸው ጋር ብቅ አሉ ከዚያ ዴግሞ ዳንዴ ዳንዴ የሆኑ ጎረምሶች የአደን ጃኪት ለብሰው መነጽር አድርገው መጡ ሳቤላን ትንሽ ትኩር አድርገው ካዩዋት በኋላ ዐልፈው ሔዱ " ከነሱ በኋላ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ከሁኔታው ትልቅ ሰው የመሰለ · አንድ ረጂም መልከኛ ሰውዬ ዘለቀ » ሳቤላ
ገና ስታየው ዐይኖቿን ጣለችበት " ያ እስከዚያ ድረስ ገና ከልቧ ያልጠፋው ሰው መሆኑን ስታይ ' የጠቅላላ ሰውነቷ ሥሮች ተርገፈገፉ።

ካፔቴን ሌቪስን በበኩሉ ገና ሲያያት እንዴት ያለች ቆንጆ ነች ? ማን ትሆን?” እያለ ወደ ተቀመጠችበት መድረክ አድናቆቱንና አክብሮቱን በግንባሩ እየገለጸ ሲጠጋ ማን መሆኗን አወቃት ወዲያው ባርኔጣውን አንሥቶ' ፊቱ በፈገግታ ፈክቶ
እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ፡ “ ከእመቤት ሳቤላ ቬን ጋር እንደገና ለመገናኘት እንደታደልኩ አልጠራጠርም ” አላት

እሷም መንፈሷ ተሸብሮ የምትናገረው ጠፋት » እጅዋን ለሰላምታ ስትዘረጋላት ጥቂት ቃሎች በማልጐምጐም መለሰችለት "

ይቅርታ አድርጊልኝ ... እመቤት ሳቤላ ፡ ካርላይል ማለት ነበረብኝ ከተለያየን ብዙ ጊዜ ሆነና አሁን እንዲህ ድንገት ሳገኝሽ ጊዜ ከደስታዬ ብዛት የተነሣ
አንቺን ያሰብኩሽ ልክ ያን ዘመን እንደ ነበርሽው አድርጌ ነው "

እንደገና ተቀመጠች " በስሜት ፍላት ጉንጮቿን አልብሷት የነበረው ቅላት ቀስ በቀስ ለቀቀ " ፍራንሊዝ ሌቪሰን ከዚያ በፊት ካያት ጀምሮ እንደሷ ያማረ ፊት
አይቶ የሚያውቅ አልመሰለውም።

ከዚህ ምን እግር ጣለሽ ?” አላት ከጐኗ እየተቀመጠ ።

አመመኝና ወደ ባሕር ዳርቻ እንድሔድ ታዘዝኩ ሚስዝ ዱሊን ከዚህ እናገኛታለን ብለን ባንጠብቅ ኖሮ አንመጣም ነበር ሚስተር ካርላይልም አብሮኝ መጥቶ ሦስት ቀን ቆየና ዛሬ ጧት ተመልሶ ሔደ „

ሚስዝ ዱሲማ ወደ ኤምዝ ሄዶች እነሱን ዐልፎ 0ልፎ አያቸዋለሁ
ለጥቂት ጊዜ ፓሪስ ተቀምጠው ነበር " እውነትም የታመምሽ ትመስያለሽ ልጄ " ኣላት አስተዛዝኖ “ በጣም ታመሻል " እኔ የምረዳሽ ነገር አለ ?

እሱን ስታይ ድንገት የያዛት ድንጋጤና የመንፈስ መረበሽ እየለቀቃት ሲሔድ ደም መስሎ የነበረው ፊቷ ዐመድ ሲያለብሰው ከመጠን በላይ የታመመች
መምሰሏን ለሷም ታውቋት ነበር ። ከሱ ጋር ስለ ተገናኘች መንፈሷ በመረበሹ በራሷ በጣም ተናደደች እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ለፍራንሲዝ ሌቬስን የተዳፈነ ስሜት ይዛ መኖሯን አልታወቃትም ነበር።

“ምናልባት በጥዋት ለመምጣት በመድፈሬ ይሆናል " አለችው እንዳዲስ ያመማት ለመምሰሏ ምክንያት ስትሰጥ “ ልመለስ መሰለኝ " አሽከሬን አገኘዋለሁ " ደኅና ዋል .. . ካፒቴን ሌቪሰን”

ግን ብቻሺን በእግርሽ ችለሽ መሔድ የምትችይ አትመስይም ስለዚህ ከቤትሽ ድረስ እንድሸኝሽ ፈቃድሽ ይሁን "

ድሮ ሲገናኙ ያደርገው እንደ ነበረው ክንዷን ሳብ አድርጎ ከብብቱ አስገብቶ
ከወደቡ መድረክ እየደገፈ አወረዳት በርግጥ ከሱ ጋር እንዶዚያ ተያይዛ መሔዱ'
ደግ ያለ መሆኑ ቢታወቃትም እሱም የቤተሰቧ ዘመድ ብዙ ስለሆነ ክንዷን ለመከልከል የምትሰጠው ምክንያት አልተገለጸላትም
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ

...ልታገኝ ስለምትፈልገው ነገር ስትል ድራማ የምትሰራ አድርጌ የማስባት ለምንድነው? እኔን ችላ ብላ ክሪስን ተመለከተች።

ለሚቀጥለው ልደትህ ኢንሳይክሎፒድያ አዝዤልሀለው። ማተምያው ድረስ ራሴ ሄጄ ነው ያዘዝኩት ስምህንና ቀኑን ሰጥቺያቸዋለሁ ግን ወደዚህ በቀጥታ መላክ አይችሉም:: የሆነ ሰው ሊቀበላቸው ይገባል ልክ ሁልጊዜ ራስህን ለማስተማር ምርጡን ልሰጥህ እንደምፈልግ ሁሉ የሚያስደስትህን ስጦታ ሳስብ ሳስብ ቆይቼ ነው ያዘዝኩልህ”

ክሪስ የሚናገረውን አጣ ፊቱ ላይ የሚታየው ድብልቅልቅ ስሜት ነበር፤አይኖቹ ግራ የተጋቡና የፈዘዙ መሰሉ። አምላኬ! ካደረገችው ነገር በኋላ እንኳን ይወዳታል ማለት ነው::

ስሜቶቹ ቀጥታ ናቸው:: በቁጣ ነደድኩ እንደዚህ አይነት መፅሀፍት ከአንድ
ሺ ዶላር በላይ ይፈጃል: ምናልባትም ሁለት ወይም ሶስት ሺም ሊፈጅ ይችላል። ይህንን ገንዘብ ለምን የማምለጫ ገንዘባችን ውስጥ አትጨምረውም?
ልክ ኬሪ ስትቃወም እንደምታደርገው ልጮህ ስል ክሪስ አይኖች ላይ ያየሁት ነገር አፌን እንድዘጋ አደረገኝ፡ ሁልጊዜ እነዚያ መፃህፍት እንዲኖሩት ይፈልግ ነበር፡ በዚያ ላይ አንድ ጊዜ ታዟል: አሁን ለሷ ገንዘብ ምኗም አይደለም፧
ምናልባት እንዲያው ምናልባት አያታችን ዛሬ ወይም ነገ ሊሞት ስለሚችል አፓርታማ መከራየትም ሆነ ቤት መግዛት አያስፈልጋት ይሆናል፡

ጥርጣሬዬ ተሰምቷታል።

እናታችን ጭንቅላቷን ቀና አደረገችና ወደ በሩ ተራመደች። ስጦታዎቻችንን
ገና አልከፈትንም፤ ስንከፍት የሚኖረንን ስሜት ለመመልከትም አልቆየችም።
እየጠላኋት ለምንድነው በውስጤ የማለቅሰው? አሁን አልወዳትም አልወዳትም።

በሩጋ ደርሳ እየከፈተች “ዛሬ ስለፈጠራችሁብኝ ህመም ስታስቡና እንደገና
በፍቅርና በአክብሮት ልታስተናግዱኝ ስትችሉ ተመልሼ እመጣለሁ ከዚያ
በፊት ግን አይሆንም::” አለች።

መጣች።

ሄደች።

መጥታ ስትመለስ
ኬሪና ኮሪን አልነካቻቸውም አልሳመቻቸውም አላናገረቻቸውም ለምን እንደሆነ አውቄያለሁ፤ ሀብት ማግኘት መንትዮቹን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው ማየት መቋቋም ባለመቻሏ ነበር።

ከጠረጴዛው አጠገብ ተነስተው እየሮጡ ወደ እኔ መጡና ቀሚሴን እየጎተቱ
ፊቴ ላይ አፈጠጡ ትንንሽ ፊቶቻቸው ጭንቀትና ፍርሀት አጥልቶባቸዋል።
እነሱም ደስታ እንዲሰማቸው መደሰቴን ለማየት ፊቴን እያጠኑ ነው:
ተንበርክኬ እሷ የጎዳቻቸውን በመሳምና በማቀፍ አጥለቀለቅኳቸው።
መልካችን ያስጠላል?" ጠየቀች ኬሪ በመጨነቅ፤ ትንንሽ እጆቿ እጄን
ይዘውኛል

“አይ በጭራሽ! አንቺና ኮሪ ቤት ውስጥ ብዙ በመቆየታችሁ ትንሽ የገረጣችሁ ትመስላላችሁ”

“በደንብ አድገናል?”

“አዎ፣ አዎ አድጋችኋል” እየዋሸሁ እንኳን ፈገግ ብያለሁ: በዚያ የማስመሰል
ደስታና የውሸት ፈገግታ ወለሉ ላይ ከክሪስና ከመንትዮቹ ጋር ተቀምጠን
አራታችንም ልክ እንደ ገና ቀን ስጦታዎቻችንን መክፈት ጀመርን። ሁሉም
በውድ የስጦታ ወረቀቶች በሚያምር ሁኔታ የታሸጉ ናቸው።

ወረቀቱን ቀደድን ሪቫኑን ጥለን የታሸጉበትን ካርቶኖች ገነጣጥለን ውስጡ ያለውን አወጣን... በውስጡ ለእያንዳንዳችን የሚያማምሩ ልብሶች ነበሩ:
አዳዲስ መፃህፍት፣ መጫወቻዎች፣ አንድ አይነት ቅጠል የሚስል ቅርፅ ያላቸው በትልቅ ካርቶን ውስጥ የታሸጉ የስኳር ከረሜላዎች።

እንደምታስብልን ማሳያው ይኸው! ሁላችንንም በደንብ ታውቀናለች።ከመጠኖቹ በስተቀር ፍላጎታችንን፣ ማድረግ የምንፈልገውን ሁሉ ታውቃለች።
በፈቃደኝነት ሞተን ስንቀበር ማየት ደስ በሚላት ጠንቋይ አያታችን ጥበቃ ስር የተተውንባቸውን እነዚያን ባዶና ረጃጅም ወራት በስጦታዎቹ ከፈለችን።

በዚያ ላይ እናቷ ምን አይነት እናት እንደሆነች እያወቀች... የምትሰራው ሁሉ በልቧ ትክክል እንዳልሆነ እያወቀች በመጫወቻዎቹና በአሻንጉሊቶቹ
ልትደልለንና ይቅርታ ልትጠይቀን ፈለገች
በጣፋጭ የስኳር ከረሜላ መራራውን ብቸኝነታችንን ከአፋችን፣ ከልባችንና
ከአእምሯችን ልትወስድ ተስፋ አደረገች ምንም እንኳን ክሪስ መላጨት
የሚያስፈልገው እኔም ጡት መያዣ መልበስ የሚገባን እድሜ ላይ የደረስን
ቢሆንም በእሷ አስተሳሰብ አሁንም ልጆች ነን ልክ በምታመጣው መፃህፍት
ርዕስ ትንሽ አድርጋ ለዘለዓለም ልታስቀምጠን ትፈልጋለች፡

ኬሪን አዲስ ቀይ ቀሚስ ሳለብሳትና ሀምራዊ ሪቫን ሳደርግላት ፈገግ እንዳልኩ
ነበር አሁን ሁልጊዜ እንደምትፈልገው አይነት ለብሳለች የምትወዳቸውን
ቀለማት እግሮቿ ላይ ሀምራዊ ካልሲ ከነጭ አዲስ ስኒhር ጋር አለበስኳት “በጣም ታምሪያለሽ ኬሪ” እሷም ብሩህ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሷ ተደስታለች።

ቀጥሎ ኮሪን ቀይ አጭር ሱሪና ኪሱ ቀይ የሆነ ነጭ ካኒቴራ አለበስኩት፡

ከዚያ “አንተንም ላልብስህ ክሪስቶፈር?” ስል ቀለድኩ

“ልብሽ ከፈቀደ ቆዳዬን ገልብጠሸ ማልበስ ትችያለሽ”

“ጋጠ ወጥ አትሁን!”

ኮሪ ሌላ የሙዚቃ መሳሪያ መጣለት፡ እሱ የሙዚቃ መሳሪያውን እየነካካ ኬሪ
ትዘፍንለታለች።

ሁሉም ነገር ላይ ያለኝን ደስታ የሚወስዱብኝ እግዚአብሔር የሰጠኝ ክፉ
ሀላቦች ነበሩኝ: ማንም የማያያቸው ከሆነ ቆንጆ ልብሶች ምን ይጠቅማሉ?
እኔ የምፈልገው በሚያምሩ ወረቀቶች ያልተጠቀለሉ፣ በሪቫን ያልታሰሩ፣ ሱቆች ውስጥ በካርቶን ያልተቀመጡ ነገሮችን ነው፧ የምፈልገው ገንዘብ
ሊገዛቸው የማይችላቸውን ነገሮች ነው: ጸጉሬ ከፊቴ በአጭሩ መቆረጡን
አስተውላለች? እንዴት እንደሳሳ አይታለች?የገረጣና የሳሳው ቆዳችንን እያየች
ጤነኛ እንደሆንን ታስባለች?

ለእኔ የተባሉትን ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች ተመለከትኩ፡ ሰማያዊ ቬልቬት ቀሚስ፣ ለግብዣ የሚለበስ ሮዝና ሰማያዊ የምሽት ጋዋን አብሮት ከሚሄድ ጫማ ጋር፧ እዚያ ተቀምጬ ከረሜላውን እየበላሁ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
“ኢንሳክሎፒዲያ!” ለዘለዓለም እዚህ ልንኖር ይሆን?

የስኳር ከረሜላ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህንን የከረሜላ
ካርቶን ያመጣችው ለኔ ነበር ለኔ፡ እኔ ግን መብላት የቻልኩት አንድ ብቻ
ነበር። ያንንም በጣም በችግር።

የከረሜላው ካርቶን መሀል ላይ ተቀምጦ ክሪስ ኮሪና ኬሪ ከበውት ተቀምጠው
በጣም በመደሰት ከረሜላዎቹን እያጣጣሙ ነበር፡ “ከረሜላዎቹን ሁሉ
መጨረስ አለባችሁ ለረጅም በጣም ለረጅም ጊዜ የማታዩት የመጨረሻ
ከረሜላችሁ ነው፡” አልኳቸው በመረረ ጥላቻ

ክሪስ አየት አደረገኝ ሰማያዊ አይኖቹ ደስተኛና የሚያበሩ ሆነዋል።
እምነቶቹና መተማመኑ ሁሉ እናታችን ለአጭር ጊዜ ባደረገችው ጉብኝት
እንደተመለሱለት ለማየት ቀላል ነበር፡ ስጦታዎቹ እሷ ከዚህ በኋላ ለእኛ ግድ የሌላት የመሆኑን ሀቅ የመደበቂያ መንገድ እንደሆነ ለምን ማየት አልቻለም? ከዚህ በፊት እንደነበርነው አሁን ለእሷ እውነት እንዳልሆንን እኔ
እንዳወቅኩት እንዴት አያውቅም? እኛ ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንዳሉት አይጦች፣ ሰዎች ሊነጋገሩባቸው ከማይፈልጓቸው ደስ የማይሉ ርዕሶች ውስጥ ነን፡

“እዚያ ቁጭ ብለሽ የማይናገር ምሰይ” አለ፡ ክሪስ ደስታውን እኔ ላይ እያንፀባረቀ: “እኛ ሶስታችን አይጦቹ መጥተው ከመብላታቸው በፊት አምሮታችንን ስንወጣ አንቺ ከረሜላውን እምቢ በይ: አንቺ ቁጭ ብለሽ ስታለቅሺ፣ ለራስሽ
ስታዝኚና ራስን መስዋዕት በማድረግ ሁኔታችንን መለወጥ እንደምትችይ ስታስመስይ ኮሪ፣ ኬሪና እኔ በልተን ጨርሰን ጥርሶቻችንን እናፀዳለን፡ ቀጥይ
ካቲ አልቅሺ! ሰማዕት ሁኚ! ተሰቃይ! ጭንቅላትሽን ከግድግዳ አላትሚ! ጩኺ እኛ እንደሆነ ወንድ አያታችን እስኪሞት እዚህ መሆናችን የማይቀር ነው::በዚያ ላይ ከረሜላዎቹ ሁሉ ያልቃሉ! ያልቃሉ! ያልቃሉ”
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"

ባሮን ጋቦን ፊታቸው በድንጋጤ አመድ መስሏል ለሎርዱ መልስ ሊሰጡ አሰቡና ትተውት ፊታቸውን ወደ ሃርትማን መለሱ፡
ሆዳቸው እያረረ በፈገግታ አለፉት፡ ነገር ግን እሳቸው ከናዚ ጀርመን አምልጠው የመጡ በመሆናቸው ከዚህ በላይ ብዙ ክፉ ነገር የደረሰባቸው ስለሆነ ይህ ስድብ ለእሳቸው እንደ ምርቃት የሚቆጠር ነው።

ማርጋሬት ባሮን ጋቦንን ተመለከተች፡ ሎርዱ ያሉትን ከምንም ባለመቁጠር ማንኪያቸውን አንስተው ሾርባቸውን መጠጣታቸውን ቢቀጥሉም እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ስላስቸገራቸው ሰደርያቸው ላይ ሾርባው ተንጠባጠበ፡፡ውስጣቸው
የሚንተከተከው ንዴት ግን
መጠጣት ስላላስቻላቸው ማንኪያቸውን አስቀመጡት።

ማርጋሬት የባሮኑ ብስጭት ልቧን ነካው። በአባቷም ስድብ በጣም ተናደደችና ‹‹ድፍን አውሮፓ የሚያከብራቸውን ሁለት ትላልቅ ሰዎች እንደዚህ መሳደብ የለብህም›› አለቻቸው በድፍረት።

‹‹ሁለት የታወቁ ይሁዲዎች በይ›› አሉ አባቷ።

‹‹ይሁዳዊያን አያቴን ረሳሃቸው አባባ?›› አለ ፔርሲ ሁሉን ነገር ቀልድ አድርጎ።

አባት ወደ ልጃቸው ዞሩና ጣታቸውን ፔርሲ ላይ እያወዛወዙ ‹‹እንዲህ
ያለውን የማይረባ ቀልድህን ተወኝ ሰማኸኝ!›› ሲሉ አፈጠጡበት

ፔርሲ ነገሩ ስላላማረው ‹‹መጸዳጃ ቤት ልሂድ አሞኛል›› አለና ትቷቸው ሄደ፡ ማርጋሬት እሷና ፔርሲ አባታቸውን መቃወም እንደሚችሉና ምንም እንደማያመጡ አውቃለች፡ ይህም አንድ እድገት ነው ስትል አሰበች፡

‹‹ከቤታችን አባረው እንድንሰደድ ያደረጉን እነዚህ ሰዎች መሆናቸውን
እንዳትረሺ›› አሏት አባት ማርጋሬትን፡፡ ‹‹ከኛ ጋር የሚሄዱ ከሆነ ስርዓት
መማር አለባቸው›› አሉ፡

‹‹ቃ!›› ሲል ተደመጠ አንድ ድምጽ

ማርጋሬት ድምጹ ወደመጣበት አቅጣጫ ዞረች፡ ይህን ያለው ፎየንስ
ላይ የተሳፈረው መርቪን ላቭሴይ ነው፡፡ መርቪን እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ
የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ ጠረጴዛ ተደግፎ ቆሟል። አስተናጋጆቹ በድንጋጤ
ደርቀው ቆመዋል፡ ጠብ ይነሳል ብለው ፈርተዋል፡ ላቭሴይ የሰማይ ስባሪ
የሚያክል፣ ዕድሜው በአርባዎቹ ውስጥ የሚገመትና ጸጉሩ ገብስማ መልከ መልካም ሰው ነው፡፡ ሲያዩት የሚፈራው ነገር ያለ አይመስልም፡ የለበስው
ልብስ ውድ መሆኑ ያስታውቃል፡

‹‹ይህን አመለካከትህን ለራስህ ያዘው›› አላቸው በሚያስፈራ ድምጽ“

‹‹አንተን አያገባህም!›› አሉ ኦክሰንፎርድ።
‹‹ያገባኛል!››
ማርጋሬት አስተናጋጁ ውልቅ ብሎ ሲሄድ አየችው፡ የአይሮፕላኑን አስተናጋጆች ሊጠራ እንደሄደ ተገንዝባለች፡፡

‹ስለ እኚህ ሰውዬ ምንም አታውቅም፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማን ባንተ አፍ የሚጠሩ ሰው አይደሉም፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ሳይንቲስት ናቸው››
አለ ከመቆርቆር በመነጨ ብርቱ ስሜት፡

‹‹የፈለገውን ቢሆን ግድ የለኝም›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡
‹‹አንተ ግድ ባይኖርህ እኔ ግድ ይኖረኛል፡ ስለዚህ ይህን የከረፋ አስተሳሰብህን አስተካክል›› አለ ላቭሴይ፡

እኔ የፈለኩትን ማለት እችላለሁ›› አሉና ኦክሰንፎርድ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡
ላቭሴይ በጠንካራ እጁ የኦክሰንፎርድን ትከሻ ተጫነና አስቀመጣቸው፡፡
እንዳንተ ካሉ ሰዎች ጋር ነው ጦርነት የገጠምነው›› አለ፡፡

ኦክስንፎርድም በደከመ ድምጽ ‹‹ልቀቀኝ! ልቀቀኝ!›› ሲሉ ተወራጩ።

‹‹አፍህን የምትዘጋ ከሆነ ነው የምለቅህ››

‹ካፒቴኑን እጠራለሁ›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡

‹‹አያስፈልግም!›› አለ ሌላ ድምጽ፡ ካፒቴን ቤከር ሙሉ ዩኒፎርሙን ለብሶ ቆሟል የአዛዥነት መንፈስ ይታይበታል፡ ‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ ብትመለስ?›› አለ፡

‹‹እኔ ወደ ቦታዬ እመለሳለሁ›› አለ ላቭሴይ ‹‹ነገር ግን በመላው
አውሮፓ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው ሳይንቲስት በዚህ ሰካራም ሲሰደቡ
በዝምታ ማለፍ አልችልም፡››

‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ›› አለ ቤከር፡

ላቭሴይ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ወደ ኦክሰንፎርድ ዞር አለና ‹‹ሎርድ ኦክሰንፎርድ የተናገሩት
ነገር አስነዋሪ ነው፡ አንድ ተሳፋሪ ሌላውን ተሳፋሪ መስደብ አይችልም፡››

ማርጋሬት አባቷ የቤከርን ምክር እንዲቀበሉ ብትፈልግም እሳቸው ግን
ጠብ ጠብ እንዳላቸው ነው፡፡

‹‹አንተ ይሁዲ ብዬ ነው የጠራሁት፡፡ ይሁዲነቱን ሊክድ ነው!›› ሲሉ
አምባረቁ፡፡

‹‹አባባ ምነው ዝም ብትል›› ስትል ተቆጣች ማርጋሬት፡

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ማንንም እንዲሳደቡ አልፈቅድም›› አለ ቤከር፡

አባት ስድባቸውን ቀጠሉ ‹‹በይሁዲነቱ ያፍራል እንዴ?›› አሉ፡

ቤከር በቁጣ ገነፈለ፡፡ ‹‹ይሄ የአሜሪካ አይሮፕላን ነው ጌታዬ እኛ ደግሞ ጥብቅ የስነ ምግባር ደንብ እንከተላለን፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎችን መሳደብ
ካላቆሙ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው በሚያርፍበት ቦታ ላይ ለፖሊስ አስረክቦታለሁ፡፡ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም እንዲህ
አይነት ነገር ሲገጥም አየር መንገዱ ህግ የጣሱ ሰዎችን ይከሳል›››

ሎርዱ የክስ ነገር ሲነሳ ፍርሃት ፍርሃት አላቸው፡ የሚመጣውን በመፍራትም አፋቸውን ዘጉ፡፡ ማርጋሬት በእጅጉ በሃፍረት ተሽማቀቀች አባቷን ዝም ለማሰኘት ብዙ ብትጥርም የአባቷ አድራጎት አንገት
አስደፍቷታል ቅሌት ውስጥ የገቡት አባቷ ስለሆኑ::

‹‹ወደ መቀመጫችን እንመለስ›› አሉና አባት ተነሱ ወደ ሚስታቸውም ዞር ብለው ‹‹አንሄድም የኔ ውድ?›› አሏቸው።

ሁሉም ሰው ማርጋሬት ላይ አፈጠጠባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ከየተ መጣ ሳይባል ከመቀመጫዋ ኋላ መጥቶ ወምበሯን ያዝ አደረገላት” ሌዳ ማርጋሬት›› አለ በአክብሮት በመጠኑ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ማርጋሬት በሄሪ አድራጎት ልቧ ተነካ፡፡

እናት ጅንን ብለው ፊታቸው ላይ ምንም የእፍረት ምልክት ሳይታይባቸው ባላቸውን አስከትለው ወጡ፡፡

ሄሪ ለማርጋሬት በጨዋ ደምብ ክንዱን ሲሰጣት ክንዷን ከክንጿ ጋ ቆላለፈች፡፡ ይሄ ትልቅ ነገር ባይሆንም ለእሷ ግን አንድ የሆነ መተማመን ፈጥሮላታል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በእፍረት ቁንጫ አክላ የነበረችው ማርጋሬት በመጨረሻ በሄሪ እርዳታ በክብር ወደ ቦታዋ ተሸኘች፡፡ ከሄሪ ጋ ወደ መቀመጫዋ ስትመለስ ድምጹን አጥፍቶ አምባጓሮውን እንደ ትርኢት
ሲመለከት የነበረው ተሳፋሪ ከኋላ ሲንሾካሽክ ሰማች፡

‹‹አንተ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም›› አለችው
ሄሪን፡፡

‹‹የተፈጠረውን አታካሮ ስመለከት ነበር፡፡ በአባትሽ አድራጎት አንገትሽን
ስትደፊ ሳይ አሳዘንሽኝ፡፡››

‹‹እንደዚህ ቀን በሃፍረት ተሸማቅቄ አላውቅም›› አለች እየተንገፈገፈች

አባቷ ግን አሁንም አደብ አልገዙም፡፡ ‹‹አንድ ቀን ይቅርታ ይጠይቁ ይሆናል እነዚህ ጅሎች!›› አሉ፡ ሚስታቸው አንድ ቃል ሳይተነፍሱ እጥግ
ተቀምጠው ባላቸውን በአግራሞት ያይዋቸዋል፡፡

‹‹ይህ ጦርነት ያበቃና! ምናለ በሉኝ›› አሉ
አባት፡፡
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ሶራ ሲያገኛት በጭቃ ልውስውስ ብላ ሰው አትመስልም። ጦርሷቿ ይፏጫሉ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል አካሏ የማታዝበት በድን ሆኗል። በጀርባው ያዘለውን ፈቶ በፕላስቲክ የተጠቀለለ ስሊፒግ ባግ አውጥቶ የበሰበሰና በጭቃ የተለወሰ ልብሷን አውልቆ ፎጣ አልብሶ ስሊፒግ ባግ ውስጥ እየጎተተ አስገባት።

በውርርድ ደረቅ ቦታ የለም ደለሉ በሙሉ ጨቅይቷል ውሃ ተኝቶበታል ስለዚህ ሶራ በቶሎ ከዚህ አካባቢ መራቅ እንዳለበት አምኖ ጀልባዋን ለማምጣት ሄደ።

ሶራ የፕላስቲክ ጀልባዋን በኦሞ ወንዝ ዳር ለዳር እየቀዘፈ ኮንችት ወዳለችበት ሄደ።ከጀልባዋ ወርዷ ወደኮንቺት ሲጠጋ አትሰማም። እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዷታል።
የጀርባ ቦርሳቸውን ከጫነ በኋላ እሷን ጀርባው ላይ
አስተካክሎ በሰፊ ቀበቶ ከገላው ጋር አሰራትና የጀልባዋን ገመድ ፈቶ
ቀስ ብሎ ጀልባዋ ላይ ወጣ፡ hዚያ ጆልባዋ ወለል ላይ ትራስ አድርጎ
አጋደማትና ከጀልባዋ በስተኋላ እግሩን አንፈራጦ ቁጭ ካለ በኋላ መቅዘፍ ጀመረ"

ቀኑ ፀሐያማና ነፋሻማ ነው፡፡ ኮንችት ወዲያ ወዲህ ሳትል
ተንጋላለች፡ ሶራ ትንሽ ሲቀዝፍ ይቆይና ጆሮ'ውን ልቧ ላይ ይደቅናል። ከዚያ ተመልሶ ደግሞ ይቀዝፋል…
የሞላው የኦሞ ወንዝም ቁልቁል መግፋቱን እየረዳው እስከ ቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ ተጓዘ፡፡

ኮንችት በስፓኒሽ “ውኀ" ትለውና አንገቷን ቀና አድርጎ
ሰሰጣት ጎንጨት ታደርግና ትተኛለች፡ ርሃቡ ራሱ ሊጎዳት እንደሚችል ቢያምንም ጀልባዋን ሊያቆምበት የሚችል የተሻለ ቦታ በማጣቱ እግር ጉልበት እየጨመረለት ብዙ እንደተጓዘ ሜዳማ ደረቅ• ጨሌ ሣርና ጥላቸው ዘርፈፍ ያሉ ዛፎች ዘንድ ደረሰ፡፡ ቀስ ብሎ  እየቀዘፈ ጀልባዋን ወደ ዳር አስጠጋና ኮንችትን እንዳይጫናት
ተጠንቅቆ በጀርባው አዘላትና ቀስ ብሎ
ቁጭ አለ፡፡ ጀልባዋ
ስለምትንቀሳቀስ ጀልባዋን እንደገና ወደዳር
ይበልጥ አስጠግቶ
እንደተቀመጠ ተንጠራርቶ ወንዙ ዳር ላይ ያለ የዋርካ ሥር ያዘ ያለው እድል ያ ብቻ ነበር።

መቅዘፊያውን ከጀልባዋ ላይ ፈቶ ወደ ውሃው ውስጥ ከቶ ለካው፡፡ መሬቱን ነክቶ ለመሻገር ኮንችትን አዝሉ እስከ አንገቱ ውሃ
ውስጥ መነከር አለበት፡፡ ምናልባት ከታች ያለው መሬት ድቡሽት
ከሆነ ስለሚሰምጥ እሷን ይዞ ለመዳን ይፍጨረጨር ይሆናል፡፡ እሷን አዝሎ ግን ካልተመቸው እንደተመኘው ሁለቱም እንደተዛዘሉ
አብረው ከአስቸጋሪው ሕይወት ለዘላለም ያርፋሉ፡፡ሶራ አሁን አልፈራም፡፡ ተለያይቶ ከመሞት አብሮ መሞትን ይመረጣል፡፡
በአርግጥ ሞትን ሊያመልጥ ብዙ ተጉዟል፡ ብዙ ሸሽቷል፡፡ ሞትን ግን ሊያመልጠው አልቻለም፡፡ ለሁሉም ወረቀት ፅፎ ሊያስቀምጥ ፈለገ፡ አዎ የሷም ሆኑ የእሱ ዘመዶች ሙት እንደሆናቸው መጠን እንደማንኛውም ሰው  መሞታቸውን አውቀው ልሳቸውን በማውጣት በነሱ ላይ ያላቸው አጉል የተስፋ ህልማቸው ሊቆም ያስፈልጋል የእሱንም
የእሷንም ስም አድራሻ… ፃፈና በላስቲከ አስሮ ወገቡ ላይ ባሰረው ውሃ የማይገባው ላይነን ቀረጢት ከተተው፡፡

ከዚያ ውሃው ሲወስዳቸው እንዳይለያዩ በሌላ የዕቃ ማሰሪያ ቀበቶ በሷና እሱ ትከሻና ጉያ ስር አሰረው፡፡
“እፎይ  ድሮ ሞትን እንዴት እፈራው ነበር፡፡ አሁን ግን
ቢያንስ መሞቴ እንደማይቀርልኝ አመንሁ! ከማንም ሰው  በላይ
የመሞቻ ጊዜዬ መድረሱን ከነደቂቃው አውቄያለሁ, ከፍቅረኛ ጋር ደግሞ ወደ ሞት መሄዴ የሙት ዕድለኛ ያደርገኛል" ብሎ እዕዋቱን
ሰማዩን የማታዋን ጀንበር ከማህደሩ መግደያ ሰይፉን በመምዝ ላይ ያለውን የኦሞን ወንዝ አየና የዋርካ ስሩን ጠበቅ አድርጎ ይዞ
ከጀልባዋ ወደ ውሃው ውስጥ ገባ፡፡

የኢትዮጵያዊውን አያቷን እትብት የተቀበረበትን ለመፈለግ ደክማ ያልተሳካላትን ቆንጆ ውሃው ውስጥ እየገባ አያት፡፡ ከዚያ
ውሃው አሰመጠው? እንደፈራው ከደረቱ አላለፈም፡፡ ስለዚህ በዛፉ
ሥር አማካኝነት እየተጎተተ ወደ ውጭ ወጣ፡፡ መከራና ስቃይን ውጦ እንደጨረሰ ሁሉ ፊቱ በደስታ ፀዳል በራ፡ በቅፅበት ከመከራ
ወደ ደስታ ተመለሰ፡፡

ከዚያ ጫካ ውስጥ ገብቶ የደራረቁ እንጨቶችን ለቅሞ
አመጣና ውኃ የማያበላሸውን ክብሪት ጭሮ እሳት አቀጣጠለ፡፡
ከጀልባዋ ላይ ያለውን የጀርባ ሻንጣ አውርዶ ለኮንችት ፓንት ሣይቀር ቀይሮ እሳቱ ዳር አስተኛትና ለችግር ጊዜ ብለው የያዟትን
ትንሽ ድንኳን ዘረጋ፡፡

ከጀርባ ሻንጣው ተጣጣፊ መጥበሻና ብረት ድስት አውጥቶ ለችግር ጊዜ ካስቀመጡት ምግብ መካከል የሚበላ አዘጋጀና ሻይ  አፈላ ኮንችት ቀስ በቀስ ዓይኖቿን መግለጥ ስትጀምር የአይብና አሳ ሳንዲዊች ወደ አፏ አስጠጋላት ከጭኖቹ ደገፍ እንዳለች ሳንዱቹን ገመጠች ሻየለንም መጠጣት ጀመረች።

ከዚያ የራስ ምታታ መድሃኒት እንደዋጠች ፈሳሽ ቅባት ጀርባዋን ጭኖቿን ክንዷን ፊቷን እያሸላት  እቅልፍ ይዟት ሄደ ቀስ አድርጎ አቀፈና ድንኳን ውስጥ አስተኛት።

የሱ እስሊፒግ ባግ ካንጠለጠለበት ዛፍ ላይ ንፋሱ ሲያወዛውዘው ጠፈፍ እስኪልለት እሳቱ ዳር ጋደም አለና ሽቅብ ወደ ሰማይ አየ። ሰማዩ ጥርት ያለ ደመና አልባ ነው አየሩ በደንብ እንደበዘቀዘ እርጎ የሚገመጥ ነው ተወርዋሪ ኮኮቦች ይወረወራሉ ጨረቃ ትንሳፈፊለች ድንቁ ተፈጥሮ እንደገና የሚያስጓመጅ ሆኗል ቀናት ያልፋሉ ዛሬም አይቀርም ያልፋል ግን በሚያልፍ ጊዜ ስንቱ አዝኖ ስንቱ ይደሰታል?

እኩለ ሌሊት ላይ የትንሿ ድንኳን ዚፕ ጢዝዝዝ ብሎ ተከፈተ ጨለማው በጨረቃ ብርሃን ድል ተነስቷል የእሳቱ ነበልባል ጠፍቷል ፍሙ ግን አለ አጠገቡ ኩርምትምት ብሎ የተኛው ሶራ ነገር አለሙን ዘንግቶ እንቅለሰፉን ይለዋል።

ኮንቺት እጇን ግንባሩ ላይ አስቀመጠች ሶራ አልተንቀሳቀሰም ዝቅ ብላ አየችው። ተመልሳ ደግሞ የሆነውን ሁሉ ለማስታወስ ሞከረች ሰመመናዊ ህልሟ ሳይቀር።

ሶራ ከዚያ መአትና የጫካ አውሬ አፍ አውጥቷታል አሁን ግን ያሉበት ተፈጥሮ እየነፈሰ ስሜትን የሚኮረኩር ነው። እንደገና አየችው ሶራ የለበሰው ስሊፒግ ባግ እርጥብ በጭቃ የተለወሰ ነው።

ዝቅ ብላ ከንፈሩን ሳመችውና ቀና ብላ ላፈቅርህ በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል አለችው እንደዚያ እንደ ዘቢብ የጣፈጠ አባባሏን ቢሰማ ኖሮ ምንኛ በደስታ በፈነጠዘ የተቃጠለ አንጀቱ እንዴት በራሰ ግን አልሰማትም መልካም ነገር እንዲህ በቀላሉ መቼ
ይሰማል!

ኮንችት ቀስ ብላ የሞቀ ትኩስ  ትንፋሽዋን በጆሮ ግንዱ እያንቦለቦለች

“ሶራ ሶራ..." አለችውና ጭቃ የተቀባባውን አንገቱን
ግንባሩን ስትስመው አይኖቹን እንደምንም ብሎ ከፈተደ።

“ሶራ" ያ ሙዚቃዊ ጣዕም ያለው ድምፅ ጆሮው ላይ
አዜመ። ለመንቃት ታገለና አያት

ኮንችት! ጥርሱ ሳቀና አይኑ እንባ ሞልቶ ወደ ጎን ወደ
ጆሮ ግንዱ ፈሰሰ፡ ኮንችት እንባውን በምላሷ ቀመሰችው በፍቅር
የተቀመመ ጣፋጭ ነው  እንባው!

“አፈቅርሃለሁ የእኔ ማር!'' አለችው። ሶራ አባባሏ
“አታፍቅሪኝ ኮንችት!  ካፈቀርሽኝ ፍቅሬ ይከብድሻል ከከበደሽ ደግሞ ወርውረሽ ትጥይውና ትጠፊብኛለሽ:: ያኔ መከራ ይውጠኛል: ስለዚህ…" ከንፈሩን በከንፈሯ ከደነችው:: ከንፈሯ
ትንፋሽዋ ምላሷ. ሙቅ ነው።

ፍቅር ይከብደኛል!
ስፈራው ስሸሸው ኖሪያለሁ:
ካለፍቅር መሞት አልፈልግም የሞትን በር ሳንኳኳ+ የሚከፍቱት
ሲንቀራፈፉ አንተ ነጥቀህ መለስኸኝ። እኔ ደግሞ ፍቅሬን ዘንጥፌ
ልሰጥህ ወሰንኩ! ላለማፍቀር ስሸሽ እንደኖርኩት! ለማፍቀር ደግሞ ቅንጣት ታክል ፍርሃት የሌለኝ ደፋር ነኝ!

ሶራ ተምታታበት፤  ሳታፈቅረው እንዳፈቀራት አብሯት ቢዞር መከራም ገፍቶ ቢመጣ ቀድሟት ቢሞት ደስተኛ ነው።
ፍቅሯን እንደተሸከመው ሁሉ አሷም ፍቅሩን ብትሸከመው ሸክሟን ወርውራ ትሸሸው ይሆን?
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጥዋት የበረፍ መንኳኳት ነው ከእንቅልፌ ያባነነኘ…በርግጌ ተነሳሁና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ…አሁንም በራፉ ይንኳኳል ግን የውጭ በራፍ ሳይሆን ከአያቴ ጋር የምንወሰነበት ተከፍቶ ያማያውቀው የውስጡ በራፍ ነው የሚንኳኳው…‹‹ውይ ልጅቷን ረስቼያት… በፈጣሪ ምን አይነት ዝፍዝፍ ሰው ነኝ? .እስከ አሁን እንግዳ እያለብኝ እንዲህ ነገር አለሙን ችላ ብዬ እተኛለሁ…?ይሄኔ እኮ እርቧት ይሆናል….?››

‹‹ማራናታ… ደህና አደርሽ?.››

‹‹አዎ ደህና አድሬያለሁ….ልግባ…ልብስህን ለብሰሀል?፡፡››ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቀቺኝ፡፡

‹‹ውይ እሱ በራፍ የታሸገ ነው …ቆይ በፊት ለፊት ዞሬ መጣሁ..››

‹‹አይ እሽጉን ትናንት አያቴ አስነስቶት ነው የሄደው››…ከሚል ድምፅ ጋር የበር መንሳጠጥ ተሰማና ወለል ብሎ ተከፈተ..ውይ የተሰማኝ ስሜት…. በቅዱሳን መላዕክቱ የገነት በር ሲከፈት ፊት ለፊት በአይኖቼ እያየሁ  ያለሁ   ነው የመሰለኝ...እና ከበሩ መከፈትም በላይ በተከፈተው በራፍ አንገቷን አስቀድማ በማስገግ ብቅ ብላ ወደእኔ ግዛት የገባቸው ልጅ…  በፈጣሪ ሰይጣን አይደል እንዴ የምትመስለው፣ሰይጣን ክብሩን ከመገፈፉ በፊት…ለነገሩ ክብሩን ከተገፈፈም በኃላም ውበቱን አልተነጠቀም…

‹‹አንቺ ይገርማል..አያቴን አይደል እንዴ የምትመስይው?››ሳላስበው አድናቆት ከአንደበቴ አፈትልኮ ወጣ
‹‹ሽማግሌ ፊት ነው ያለሽ እያልከኝ ነው?››

‹‹ይቅርታ …ማለቴ በጣም ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው….››አዎ እውነቴን ነው …ልጅቷ ልክ አያቴን ነው የምትመስለው…ልቅም ያለች የጥቁር   ልጥልጥ  ውብ ነች…፡፡ልክ እንዳየኋት ልቤ ቢጫ ወባ እንደነደፈው ሰው ነው በደቂቃ ውስጥ ፍርፍር ስትል የተሰማኝ፡፡
‹‹ለማንኛወም ቁርስ መብላት ከፈለክ ና ቀርቧል….››ብላኝ በራፉን ክፍት ጥላ ተመልሳ ወደውስጥ ገባች፡፡እንግዳ ሲያፍር ባለቤት ይጋብዛል አሉ….ሲሆን ሲሆን ለሊት ተነስቶ ቁርስ በመስራት እሷን መቀስቀስ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ..ዳሩ አጅሪቷ በየት አሲይዛ …በሁሉ ነገር ጥድፍ ጥድፍ ትላለች፡፡በፈጣሪ በዚህ አይነት አጀማመር ይህቺን አንድ ወር እንዴት ነው ተቋቁሜ የምዘልቀው…? አያቴ ምን ነካቸው..?ይሄንንማ አውቀው ሆነ ብለው እኔን ለመፈተን ያደረጉት ነገር ነው፡፡ወይ እዳዬ ለዘመናት ከዳከርኩበት እና ፍዳዬን ካየሁበት የፍቅር ታሪክ ገና ትናንትና መደምደማሚያ አበጅቼለት ተገላገልኩ ስል….

‹‹እዬቤ...››ጥሪው ከተዘፈዘፍኩበት ሀሳብ መዞ  አነቃኝ

‹‹አቤት››

‹‹ቁርሱ ቀዘቀዘ እኮ….በዛ ላይ እርቦኛል››

ተንደርድሬ ተነሳሁና ፊቴን ተለቃልቄ ልብሴንም ሳልቀይር በለበስኩት ቢጃማ ተንንርድሬ ሚቀጥለው ክፍል ገባሁ…..እንግዲህ ይታያችሁ እዚህ ቤት መኖር ከጀምርኩ ሶስተኛ አመቴ ውስጥ ብሆንም አሁን ያለሁበትን ክፍል ስረግጥና የውስጥ ገፅታውን ሳይ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኔ ነው፡ክፍሉ በስርአት ቦታቸውን ይዘው በተቀመጡ የቤት እቃዎች የተሞላ ነው፡፡ ቢያንስ ሶስት ቦታ በመፅሀፎች የተሞሉ መደርደሪያዎች ይታያሉ…አልጋው በስርኣት ተነጥፏል፡፡  አልጋውን ተጠግቶ ያለው መካከለኛ መጠን ያለው ጠረጴዛ በምግብ ተሞልቷል…

‹‹ምን ይገትርሀል አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በል ››አለችኝ

የእሷን  ግብዣ ችላ አልኩና ግድግዳ ተደግፎ ያተቀመጠ አንድ ደረቅ ወንበር በማንሳት ወደምግብ ጠረጴዛው አስጠግቼ በመቀመጥ አንዴ የቤቱን ዙሪያ መልሼ ደግሞ እሷን ከስር አስከላይ መቃኘት ጀመርኩ… አቀራርባ ስትጨርስ ፊት ለፊቴ አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በማለት እሷም ለመብላት ዝግጁ ሆና እጇን ወደምግቡ እየሰደደች‹‹..በል ብላ››.አለችኝ..

‹‹ይሄን ሁሉ ምን ጊዜ ሰራሺው?››የገረመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት.፡፡

‹‹እቤትህ ሰዓት የለም እንዴ..?ሶስት ሰዓት ሊሆን እኮ ነው››አመሏ ከመልኳ ተቃራኒ ነው..እስከአሁን እንዳየሆት ለየትኛውም ጥያቄ ቀና መልስ መስጠት አይሆንላትም…

‹‹ይቅርታ .እንቅልፍ ጣለኝ››

‹‹አያቴ ጠንካራ ሰራተኛ ነው እያለ ሲፎክርብህ የነበረው እንዲህ እየተኛህ ነው እንዴ?››

‹‹አጋጣሚ ሆኖ ነው..›› የጠቀለልኩትን ምግብ እየጎረስኩ መለስኩላት፡

‹‹እሺ ቢሾፍቱ ዛሬ ትወስደኛለህ ?››አዲስ ርዕስ ከፈተች

‹‹ለምን…?መሄድ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አይ የስራህ ቦታ እዛ አይደለ? ስራ ከሄድክ አብሬህ ለመሄድ ብዬ ነው››
‹‹እ ….እንደዛ ነው….ዛሬ ሳይሆን ነገ ነው የምሄደው ….ነገ አብረን እንሄዳለን….ዛሬ የሆነ ጓደኛዬን ከአገር ውጭ ስለምትሄድ እሷን እንሸኛለን››

‹‹እ… .ጄኔራሏን?››

‹‹ምን….?በምን አወቅሽ…?››.ደንግጬ

‹‹ይሄውልህ ስለአንተ የማላውቀው እንዲህ ቆንጆ መሆንህን ብቻ ነበር… አሁን ደግሞ እሱኑም አወቅኩ››ብለኝ እርፍ
‹‹እንዴት…?አሀ ይሄን ሁሉ የነገሩሽ አያቴ ናቸው?››

‹‹አዎ  አያትህ…በነገራችን ላይ አያቴ በየደብዳቤው ስለአንተ ሲዘበዝብልኝ በጣም እበሳጭበት ነበር››

‹‹ለምን? ቀንተሸ?››

‹‹አዎ ብቀና ይፈረድብኛል..?እኔ በአያቴ ቀልድ አላቅም...እና ብቸኛ የልጅ ልጁ ሆኜ መቀጠል ነበር ምፈልገው..››

‹‹እና አሁንስ?››ስል ጠየቅኳት በመገረም፡፡

‹‹አሁንማ አንደኛ አባቴ ከዛች የተረገመች ሚስቱ ሌላ ልጅ ስለወለደ ብቸኛ የልጅ ልጁ መሆኔ ማክተሙን አምኜ ተቀበልኩ ….ሁለተኛ እኔም ሳላስበው ታሪክህን ቀስ በቀስ ሲያስጠናኝ የእውነትም አያቴ አያትህ ይመስለኝ ጀመር…››

ተበሳጨሁ… ልጎርስ አፌ ላይ ያደረስኩትን ምግብ መልሼ ትሪው ላይ በትኜ ተነሳሁና‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው..?››አፈጠጥኩባት

‹‹አቦ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ማለት ምን ማለት ነው?››እሷስ መች የዋዛ ሆነችና በተቀመጠችበት መልሳ አፈጠጠችብኝ፡፡

‹‹አያቴ ስል ለማሾፍ ወይም ለፉገራ ይመስልሻል…?የእውነት አንቺ ከእኔ በላይ እራስሽን ባለመብት አድርገሽ መጎረርሽ ነው..?››ወረድኩባት
‹‹ባለመብቱንማ በተግባር አየነው እኮ…. እኔ እኮ አይደለሁም የአንድ ሚሊዬን ብር ቼክ የተፃፈልኝ…አሁን እንብር እንብር አትበል ቁጭ በልና ቁርስህን ጨርስ .ደግሞ አያቴን የነጠቅከኝ ሳያንስ ስድብ ትመርቅልኛለህ….አረ አይነፋም…››

በንግግሯ ተሸነፍኩና ተመልሼ ቁጭ አልኩ…ገና በመጀመሪያው ቀን ይሄን ያህል ከተጮጮህን ዋል አደር ስንል..ወይኔ ጉዴ…ጨነቀኝ፡፡

አንድ ክፍል ቀረው
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ከክስተቱ በኃላ መድህኔ ልዩ ቤት ድረስ አይኑን በጨው አጥቦ ሊያናግራትና ይቅርታ ሊጠይቃት መጥቶ ነበር..የመኝታ ቤቷን በራፍ ግን ልትከፍትለት አልፈቀደችም…ለእናቷም የሰርግ ዝግጅቱን እንዲያቆሙና ከመድህኔ ጋርም  ፍፅም እንደማትጋባ ስትነግራቸው. መጀመሪያ በጊዜያዊ ንዴት ተገፋፍታ የተናገረችው ነው ብለው ትኩረት አልሰጡትም ነበር…ውሎ አድሮም ምንም አይነት የመርገብም ሆነ የመረጋጋት ሁኔታ ስላልታየባት እየደነገጡ ሄዱ….ከዛ ምክንያቱን እንድትነግራቸው አምርረው ጨቀጨቋት…‹‹ከጓደኛዬ ጋር ሲማግጡ አንድ አልጋ ላይ ያዝኳቸው›› ብላ እቅጩን ነገረቻቸው…ባለማመን እራሱ መድህኔ ጋር ደውለው ጠየቁት…አላደረኩትም ብሎ ሊክዳቸው አልቻለም...ከዛ እሷቸውም እጥፍ በሆነ ምሬት መድሀኔን ተቀየሙት… እሷን መጨቅጨቁንም ሆነ የሰርጉን ወሬ እርግፍ አድርገው በመተው ልጃቸው ብቻ በብስጭት አንድ ነገር እንዳትሆንባቸው  በስስት መከታተላቸውን  ቀጠሉ፡፡

ስለጊፍቲ ሁኔታ ደግሞ ቃል አንድ ሁለት ቀን  እቤቷ ድረስ በመሄድ እንዳገኛትና ያለችበት ሁኔታ የከፋ የሚባል እንደሆነ ነገሯታል….መድሀኔና ጊፍቲም ተገናኝተው እንደማያውቁ ሲነግራት ስጋት ውስጥ ገብታለች።

‹‹በዚህ የቃል ሀዘኔታ  ጊፍቲ እግሩ ላይ ወድቃ ይቅርታ ብትጠይቀው አይኑን ሳያሽ ነው ይቅር የሚላት።››ስትል ስጋት ውስጥ ነች፡፡ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ተጋብታለች፡፡

ጊዜ ተለዋዋጭ ነው…በተለያ ሁኔታ ውስጥ ሊለጠጥና ሊኮማተር ሊረዘምና ሊያጥር ይችላል፡፡ጊዜ በተለያዩ የሰማይ አካላት ላይ ባላቸው ፍጥነት መጠን ልክ የተለያየ መጠን አለው፡አንድ ዓመት ርዝመት  በምድር ላይ እና በማርስ ላይ በጠጣም የተለያየ ነው…
በፍጥነት በሚጓዙ .የሰማይ አካላት  ላይ ሰዓት ሲኮማተር ዝግ በሚሉ ብለው በሚጓዙት ላይ ደግሞ ጊዜ ይለጠጣል ወይም ይረዝማል፡፡
አልበርት አንስታይን በቴኦሪ ኦፍ ሪላቲቪቲ መሰረት  የአንድ ቁስ ጉዞ ከብርሀን ፍጥነት በላይ በሚሆንበት ጊዜ ወደ ትናንና  ይጓዛል የሚለውን አረጋግጧል..ይሄ ማለት   የታይም ትራቭለር ሀሳብ  በዚህ ስሌት የሚሰላ ነው ፡፡
ይሄን ያሰበችው ቃልን ከማግኘቷ በፊት ያሳለፈችው ጊዜ ሲቆጠር ረጅም አሰልቺ አይነት ሲሆን አሱን  ካገኘች በኃላ ያሳለፈችው በሚዛኑ የቀኝና የግራ ሰሀን ላይ ቢቀመጥ  የትኛው በልጦ ይገኛል? ፡፡
ከቃል ጋር እያወራች ነው..እራሱ ደውሎ ነው ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት..ምክንያቱም በጣም ልቧ ተሰብሯል…ምክንያቱም የእሱ ጓደኛና እጮኛ የእሷን እጮኛ አማግጣባታለች...ወይንም እርስ በረሻቸው ተመጋግጠዋል….ስለዚህ አፅናኝ ትፈልጋለቸ፡፡ይሄው አሁን ቃል እያደረገ ያለውም ያንን ነው፡
‹‹ልዩ የምሬን ነው በጣም ነው ያዘንኩት ..ልብሽ እንዲሰበር ስላደረኩ ይቅርታ›› አላት አንጀት በሚበላ  አሳዛኝ ንግግር፡፡
"አንተ ምን አደረክ...?እንደውም ከእኔ እኩል ተጠቂ ነህ።"
"አይ የእኔና ያንቺ አንድ አይደለም .›አላት፡፡
.‹‹ምን? የእኔ የራሴ ጥፍት ነው"ምን ለማለት እንደፈለገ ግልፅ አልሆነላትም‹ምን ማለትህ ነው?›ስትል ጠየቀችው፡፡
"ኃላፊነቴን ባለመወጣቴ ምንም ነገር ብታደርግ በእሷ ላይ ጣቴን የመቀሰር ሞራል የለኝም..ብቻ ከአንቺ  እጮኛ ጋር ለምን እንዳደረገችው ነው ሊገባኝ ያልቻለው?"
"ከእኔ እጮኛ ጋር ሆነ ከሌላ ጋር ምን ለውጥ አለው ..ክህደት ያው ክህደት ነው?"

"አይ እኔ ከድታኛለች ብዬ አላስብም...ጊፍቲ መቼም እኔን ልትከዳኝ አትችልም...ግን ከእኔ የምትጠብቀውን ለዘመናት ጠብቃ ስላጣች..ያደረገችውን ማድረጓ  ያንስባት እንደሆነ እንጂ  አይበዛባትም፡፡"

"እና አሁን ወደአንተ መጥታ ይቅርታ የምትጠይቅህ አይመስልህም"
"ይቅርታ..."
የመደነጋገር ስሜት ታየበት..‹‹ጊፈቲና መድህኔ ተበዳይ እእጂ በዳይ እይደሉም..ይቅርታ መጠየቅ ያለብን እኔና አንቺ ነን..››በማለት በውስጡ አያሰበ በአንደበቱ ግን"አይ ይቅርታ  የምጠይቃት እኔ ነኝ...... ጥፋተኛው እኔ ስለሆንኩ ላባከንኩት ጊዜዋ፤ላልከሰከስኩት ተስፋዋ፤ለሁሉም ነገር  ይቅርታ እጠይቃታለሁ።"አላት፡፡
ልዩ ሰውነቷ ሁሉ በፍርሀት መንዘርዘር ጀምሯል...ያ ሁሉ ልፋቷ ያ ሁሉ ጥረቷ   በዚህ ሰው አጉል የዎህነት ገደል  ሊገባባት እንደሆነ ታሰባትና ውስጧ በንዴት ተቃጠለ።እንዲህማ አያደርገኝም....፡፡
"እና ይቅርታህን ከተቀበለች በኃላ እንደድሯችን እንሁን ብትልህ እሺ ትላለህ?"
"ምን አልሽ? እንደውም እንደድሯችን መሆን አንችልም  ካለቺኝ  ነው እሺ ማልላት...እንደዛ መቼም አይሆንም፡፡"
"እንዴ ይሄ ምን የሚሉት ግራ የተጋባ ነገር ነው...ከእኔ ባል ጋር ፍቅር ይዞት ከሆነስ ...?እሱን ለማግባት ፈልጋለሁ ብትልህስ?›› ስትል ጭርጭር በሚያደርግ የንዴት  ጠየቀችው፡፡
"እሱን ማለቴ አይደለም... እንዳልሽው እሱን ታፍቅረውም ለማግባት ትሞክርም.. የእሷ  የራሷ መብቷ ነው። ያንን ምርጫዋን ሆነ ውሳኔዎን አከብርላታለሁ።ግን እሺ ማልላት ጓደኝነታችንን እናበላሽ ካለቺኝ ነው።…አዎ ሲሆን ሲሆን ይቅር ብላኝ ብታገባኝ ደስ ይለኛል.ከልሆና እንዳልሺው አሱን ወዳውም ከሆነ ችግር የለም ዋናው የእሷ ምቾት ነው››አላት…ቃል ንግግሩን ሆነ ብሎ የልዩን የአሸናፊነትና የስኬት ስነልቦና ለመናድ አልሞ ነው እየሰነዘረ ያለው.. እናም ደግሞ ተሳክቶለታል..ልዩ በተሸናፊነት መንፈስ እየተናጠችና በፍርሀት ስሜት እየተንቀጠቀጠች ነው፡፡

‹‹እና አንተን ጥላ መድሀኔንም አግብታ ቢሆን እንደበፊቱ ጓደኛዋ ሆነህ የመቀጠል ፅናቱ ይኖርሀል።››
"እንደዛ ካላደረኩ እኮ መጀመሪያውኑ  አልወዳትም ነበር ማለት ነው"አለትና አስደመማት።
ዝም አለች..."እኔ አሁን የመድህኔ መሳሳት የእኔ ስውር እጅ ስላለበት ይሉኝታ ይዞኝ ትንሽ ቀዝቀዝ አልኩ እንጂ ከእኔ እውቅና ውጭ  ወስልቶብኝ ቢሆን ኖሮ  ዘልዝዬ አልበላውም ነበር?›ስትል በውስጧ እራሷን ጠየቀች..፡፡
" እኔ ግን   መቼም ቢሆን መቼም ይቅር ልለውና  መልሼ እንደድሮችን ልቀበለው አልችልም።››ስትል ፍርጥም ብላ አቋሟን ለቃል ነገረችው፡
"እንደእጮኛ  ተቀበይው ብዬ  ላስገድድሽ አልችልም...ግን ከእዚህ በፊት እንዳጫወትሺኝ ከሆነ መድህኔ ፍቅረኛሽ ከመሆኑ በፊት የልጅነት ጓደኛሽ ነው። በጓደኝነት ህይወታችሁ  ብዙ መልካም ቀናትን… ብሩህ የሆኑ ትዝታዎችን አሳልፋችኋል...እና እሱን ከውስጥሽ እስከወዲያኛው ፈንቅለሽ ስትጥይ የራስሽንም መልካም ትዝታዎችንና ወርቃማ ትናንቶችሽን ነው አብረሽ የምትደመስሼያቸው... እሱን በጎዳሽው መጠን አንቺም ተጎጂያለሽ፡፡.››
"እና ምን እያልከኝ ነው?"
ከደረት ኪሱ እስኪረሪብቶና ብጣሽ ወረቀት አወጣና ሰጣት.::ግራ በመጋባት‹‹ምን ላድርገው?››ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹የምነግርሽን ነገሮች ለመፃፍ ተዘጋጂ››አላት፡፡
ምን ሊለኝ ነው በሚል ጉጉት እስኪርብቶውን ወረቀቱ ላይ ቀስራ መጠባበቅ ጀመርረች፡፡
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ…››
ቀና ብላ አየችው..
‹‹ፃፊው…፡፡››
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ››ብላ  ፃፈች፡
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡

‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡››

‹‹ፎቶው አለሽ?›› 

‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ‹‹ተከተይኝ ››አለቻት እና  ወደበረንዳው ወጡ…ንስሯ ተረጋግቶ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ስታየው እንደመፍራትም ግራ እንደመጋባትም አለችና፡፡

‹‹ምን አይነት አሞራ ነው..አይፈራም እንዴ? ››

‹‹የእኔ ነው››

‹‹አሞራው?››

‹‹አዎ…ግን አሞራ ሳይሆን  ንስር ነው…የእኔ ንሰር ፡፡››

‹‹ምን ያደርግልሻል?፡፡››

‹‹እሱማ ለእኔ ብዙ ነገሬ ነው… የፈለኩትን ነገር ያደርግልኛል..እኔ እንደውም የሚገርመኝ እኔ ለእሱ ምን አደርግለታለሁ ሚለውን ነው››

‹‹ይቅርታ ግን ያስፈራል…. .በተለይ አይኖቹ እና መንቁሩ…››እሷን ችላ አለቻትና ሞባይሏ ላይ ያለውን የልጅቷን ፍቅረኛ ፎቶ ለንስሯ እያሳየች ‹‹….እንርዳት መሰለኝ…እወነቱን ማወቅ መብት አላት››ስትለው ክንፎቹን አርገፈገፈና   መቀመጫውን ለቆ በአየር ላይ ተንሳፈፈ…እሷ  በርግጋ ወደኃላዋ አፈገፈገች….ወደላይ ተምዘግዝጎ አየሩን እየሰነጠቀ ከፍታውን ለአይን መታየት እሰከማይችል ድረስ ርቆ ተሰወረ፡

‹‹ቁጭ በይ› አለቻትና በረንዳው ላይ ካለው ወንበር አንዱን እያሳየቻት እሷ ንስሯ በለቀቀላት ወንበር ላይ እየተቀመጠች፡፡

‹‹ሄደብሽ እኮ …እንዲህ እርቆ ሄዶ አሁን አውቆ ተመልሶ ይመጣል?፡፡››

‹‹አዎ የእኔ እወቀት ዘጠና ፐርሰንቱ ከእሱ የማገኘው ነው…ንስሮች በተፈጥሮቸው በጣም ልዩ የሆኑ የአእዋፋት ዝርያዎች ናቸው፡፡እይታቸውም ጥልቅ አስተሳሰባቸውም ስል እና የተሞረደ  ነው፡፡ከዛም በላይ ግን የእኔ ንስር የተለየ ነው፡፡እንዴት የሚለውን ነገር ላብራራልሽ አልችልም..ግን አሁን የሚያደርገውን ታያለሽ ..ከዛ እራስሽ ትፈርጂያለሽ››

‹‹እንዴት?››

‹‹አሁን ፍቅረኛሽን ፎቶ እያሳየሁት ሳወራው አላየሽም?››

‹‹አይቻለው.ግን እናቴም ሲጨንቃት እና በሆዷ ነገር ሲገባ ከምታልባት ላም  ጋር ታወራ ነበር…እንደውም ለእሱ ስታወሪ እናቴ ነች ትዝ ያለችኝ፡፡››

‹‹አይ ይሄ ይለያል..አሁን ያንችን ችግር ማለት ስለፍቅረኛሽ ትክክለኛ ነገር እንዲያጣራልኝ ነው የላኩት››

‹‹እንዲት አድርጎ››

‹‹በቃ የተለየ ችሎታ አለው… ማንኛውም ነገር ካተኮረበት የውስጡን ሀሳብ እና ጠቅላላ ታሪኩን ማንበብ ይችላል…እኔ ደግሞ ከሱ አዕምሮ ማንበብ እችላለሁ..ወይም እንዳውቀው አዕምሮውን ይከፍትልኛል..ቅድም ያንቺን ታሪክ ላውቅ የቻልኩት ከእሱ ነው፡፡››

‹‹እኔ አላምንም ..ንስር ይሄን ሁሉ…. እንዴት  ተደርጎ?››

‹‹አየሽ እንዳልኩሽ የእኔ ንስር ልዩ ነው..ከእኔ  ጋር ያለውም ትስስር ከተፈጥሮ ክስተቶች እንደ አንድ ነው..ያም ሆኖ ግን እንዲሁ ንስር እና የሰው ልጅ ከጥንትም ጀመሮ የመንፈስ ትስስር እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡፡ሌላውን ተይና  በሀገራችን ጥንታዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ንስር የትንሳኤ ምልክት ነበር… በምጥቀት ማሰብ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር መንፈስ ተምሳሌ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡በግብጽ ደግሞ መቃብራቸውን ጋንኤል እንዳይደፍረው የንስር ምስል ከመቃብሩ በራፍ ላይ ያስቀምጡ ነበር…ያ የንስር ምስል የጋንኤሉ መንፈስ አልፎት ወደውስጥ ሊጋባ ስለማይችል እሬሳቸው ከጥቃት የተጠበቀ ይሆናል ብለው ያምናሉ..፡፡
የጲላጦስ ሀገር የሆነችው ግሪክ ደግሞ ከአመልክቶቾ ውስጥ አንድ የሆነው የአማልዕክቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው ዜዎስ በንስር ይመሰል እንደነበረ ይነገራል፡፡በጥንት ጊዜ አሜሪካኖች  ደግሞ እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው ያለቸውን ጥልቅ ፍቅር ሚገልጽት የንስር ላባ በመስጠት ነው፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ሲራክም  ሶስት እራስ እና አስራ ሁለት ክንፎች ሳላለው ንስር በህልሙ ራዕይ አይቶ ነበር….የራዕይው ፍቺ በየተራ ስለሚነግሱ ነገስታት ሲገለጽለት ነበር…ንስር የኃይልን እና የስልጣን ምልክት ነው፡፡…››ስብከት የመሰለ ንግግሯዋን ተናግራ ሳትጨርስ….ዶክተሩ በራፋቸውን ከፍተው ወጡና ወደእነሱ መጡ

…‹‹.ሶፊ ደህና ነሽ?››

‹‹እንዴት አደሩ ዶክተር?››
‹‹አለሁ….ዛሬ እንግዳ ከየት አገኘሽ ?››አለት እንግዳዋ ላይ በማተኮር፡፡

‹‹አያውቋትም?››

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት ግን ያየኋት ይመስለኛል››

‹‹አዎ ከባሌ የመጣች የአክስቴ ልጅ ነች…ከዚህ በፊትም መጥታ ስለነበረ.. ተገናኝታችኋል››
‹‹ለዛ ነዋ ፊቷ አዲስ ያልሆነብኝ….በሉ ተጫወቱ አንዲት ቀጠሮ አላለችብኝ ..ከሰዓት እንገናኛለን ..›ብለው ተሰናብተዋቸው ወደመኪናቸው ማቆሚያ ጥለዋቸው ሄዱ
ሶፊያ ሳቋ  አፍኗት  ስለነበር እንደራቁላት ለቀቀችው

…‹‹ሳያውቁኝ ቀርተው ነው ወይስ አውቀው ነው?››

‹‹አይ ተምታቶባቸዋል…ያው ማታ መጠጥም ስለሚወሳስዱ ነው ቅር አይበልሽ››

‹‹አረ ምን ቅር ይለኛል ነገራቸው ገርሞኝ እንጂ››ብትልም ቅር እንዳላት ግን በግልፅ ከንግግሯ ቃና በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እዚህ ቤት ከጥዋት ጀምሮ የሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ይገርማል አይደል?››

‹‹ምን መገረም ብቻ ከአዕምሮም በላይ ነው….እኔ እንዲህ….››ንግግሯን ሳትጨርስ  ንስሩ እየተምዘገዘገ መጣና ከእነሱ ፊት ለፊት በአምስት ሜትር ርቀት ያህል በሚገኝ የጽድ ዛፍ ላይ ሲያርፍ ስለተመለከተች  አቆረጠችና …ምን እንደሚከሰት ለማወቅ መጎጎቷን በሚያስታውቅባት መንፈስ‹‹መጣ ››አለቻት፡፡

‹‹ትንሽ ታገሺኝ ››አለቻትና አዕምሮዋን ሰብሰባ  ትኩረቷን በሙሉ  ከንስሯ ጋር በማቋራኘት እምሮውን  ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መምጣትሽን ፍቅረኛሽ አያውቅም አይደል?፡፡››

‹‹አዎ..አንዴ በእሱ ክህደትና ዘረፋ የሞትኩት አንሶኝ ጭራሽ መምጣቴን ነግሬው ስሩ ቆሜ ሁለተኛ ሞት ልሙት እንዴ? አላደርገውም ….ፍቅሬን መልስልኝ ብዬ ልማፀነው..?ወይስ ብሬን መልስልኝ ልበለው?››

በንስሯ አእምሮ አሻግራ እያየች ያለችው ታሪክ አሰገርሟት፡፡‹‹ቆይ ቆይ…በዚህ ሰዓት ፍቅረኛሽ ምን እየሰራ እንደሆነ ታውቂያለሽ…?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን እየሰራ ነው..?.ከሚስቱ እየተዳራ ወይም ልጁን እያጫወተ ይሆናል››ብስጭት እና ቅናት በተቀላቀለበት ድምፀት መለሰችላት፡፡

‹‹አይደለም …ትናንትና ወደ  ጊኒጪ ሄዶ እናትሽን  አምጥቶ ግሩም ጠቅላላ  ሆስፒታል እያሳከማቸው ነው…››

‹‹የእኔን እናት .. ?ምን ሆና ነው…?››በድንጋጤና በመገረም .እናም ደግሞ ባለማመን ጠየቀች፡፡

‹‹አትደንግጪ ያው የተለመደው በሽታዋ ነው….ድሮም ከፍተኛ የጨጎራ ቁስለት እንዳለባት ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹ግን እኔን እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ያሰጠጉታል …እናቴ ምንም የሚያስታምማት እና ሚያሳክማት ሰው ብታጣ እንዴት ልጇን ከከዳ ሰው ጋር ትተባበረለች…?እኔ ይሄን ማመን አልችልም …፡፡ሌላው ይቅር እናቴ እንኳን ለስላሳ እና የዋህ ስለሆነች  ይቅር ልትለው ትችላለች… እህቴ ግን እርግጠኛ ነኝ ይቅር አትለውም ፤ እርግጥ ሁሉም ለእሱ የላኩለትን ብር አያውቁም …ግን በጣም እንደማፈቅረውና ላገባውም  እንደምፈልግ ከዛም አልፎ ቃል እንደተግባባን ግን በደንብ ያውቃሉ፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ…በጣም ነው የሚያፈቅርሽ፡፡››
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ በማግስቱ ከምሽቱ 12፡3ዐ ላይ መኪናዋን እያሽከረከረች ታዲዮስ ቤት ደረሰች፡፡ሦስት ኩርቱ ፔስታል ሙሉ ስጦታ ይዛለች ፤ለአምስቱም ልጆች ፡፡በመከራ እየተንገዳገደች ነበር ዕቃዎቹን ተሸክማ በረንዳው ላይ ማድረስ የቻለችው፡፡መሬት አስቀመጠችውና በራፉን አንኳኳች፡፡ ሃያ አምስት ዓመት የሚሆነው ባለ ሹሩባ ፀጉር መልከ መልካም ወጣት ከፈተላት፡፡

‹‹አቤት ምን ነበር?››ዓይኑ ያልተለመደ ነገር በማየቱ የመገረም ፊት እያሳያት፡፡

‹‹ታዲዬስን ፈልጌው ነበር፡፡››

‹‹ይቅርታ ታዲ ከአንድ ሰዓት በኃላ ነው የሚመጣው፡፡››

<< አመጣጤማ ሰላምን ልጠይቃት ነበር፤የታዲ ዘመድ ነኝ፤ማታ እዚህ በነበርኩበት ሰዓት የሰላምን መታመም አይቼ ስለነበር አሳስቦኝ ነው፡፡››

ፈራ ተባ እያለ በራፉን በሰፊው ከፈተላት እና አንዱን ፔስታል ለእሷ ትቶ ሁለቱን ወደ ሳሎን ውስጥ በማስገባት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠላት‹‹እህት .. እንግዲህ አረፍ በይ ትንሽ ስራ ላይ ነን፡፡ ››ብሏት ጥሏት ሄደና በመደዳ ካሉት ክፍሎች መሀከል ወደ መጀመሪያው ክፍል ገባ፡፡ ሶፋው ላይ ቁጭ አለች፡፡ልጁ ከገባበት ክፍል አካባቢ የፒያኖ ድምፅ ይሰማታል፤የሚመስጥ ክላሲካል ሙዚቃ፡፡ዝም ብላ በደመነፍስ ባዶውን ሳሎን ለቃ የሙዚቃውን ድምፅ ተከትላ ወደ ክፍሎቹ መራመድ ጀመረች፡፡የመጀመሪያው ክፍል በራፍ አጠገብ ስትደርስ እርምጃዋን ገታችና ቆመች፡፡በራፉ ገርበብ ብሎ ስለነበር አንገቷን አሰገገች፡፡
እንደመጣች በራፉን የከፈተላትን ልጅ ሹሩባ ቀድሞ ታያት፡፡ይበልጥ ስትጠጋ ሠላምን አየቻት፡፡ በሹክሹክታ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች፡፡ሠላም ወንበር ላይ ቁጭ ብላለች፡፡ ከፊቷ የስዕል ሸራ ተወጥሮላት ፊቷ በቀረበላት የተዘበራረቀ ቀለም በቀጫጫ እጆቿ የያዘችውን ብሩሽ እያጠቀሰች የሆነ ስዕል ትስላለች፡፡ወጣቱ ቀና ብሎ ሶፊያን ተመለከታትና መልሶ ቀልቡን ሰላም ወደምትስለው ስዕል መለሰ፡፡ ልትረብሻቸው ስላልፈለገች ክፍሉን በቀስታ ለቃ ወጣች፡፡

ወደ ሳሎን ልትመለስ ካሰበች በኃላ የፒያኖው ድምፅ የሚንቆረቆረው ከሚቀጥለው ክፍል እንደሆነ ስታውቅ ሀሳቧን ቀየረችና ወደዛው አመራች፡፡ገርበብ ያለውን ክፍል በተመሳሳይ ገፋ አድርጋ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ መሀከል ወለል ላይ አንድ መለስተኛ ፒያኖ ተመለከተች፡፡ አንድ ወጣት ግን አይነስውር የሆነች ምታምር ሴት ሁለቱን ሴት ህፃናት ተራ በተራ ጣታቸውን እየያዘች ታለማምዳቸዋለች፡፡ ግድግዳውን ተደግፋ በተመስጦ ትከታተላቸው
ጀመር፡፡ከአስር ደቂቃ ቆይታ በኃላ ዓይነ ስውሯ
አስተማሪ አዳምጡ አለቻቸውና ሁለቱን ሴት
ልጆች መቀመጫቸውን ይዘው እንዲቀመጡ

በማድረግ ጣቶቾን ፒያኖው ላይ ማርመስመስ ጀመረች፡፡ልጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ዶ/ር ሶፊያም
ድንዝዝ ብላ ነው የተከታተለቻችው፡፡እሷ
እራሷም ከሙዚቃው ስልት ጋር ከወዲህ ወዲህ አንገቷን ስታወናጭፍ እረጅም ጥቁር ፀጉሯ በአየሩ ላይ ይበተናል፡፡የተመልካች ልብን
ስልብ ያደርጋል ፡፡ስትጨርስና ጣቶቾን
ስትሰበስብ ሳታስበው አጨበጨበችላት፡፡

ሁለቱም ህፃናት ልጆቹ እያቀፋ በመሳም
ፍቅራቸውን ገለፁላት፡፡
ሄለን ‹‹ፅዬንዬ እኔም ሳድግ እንደአንቺ መጫወት እፈልጋለሁ፡፡አንቺን መሆን ነው የምፈልገው፡፡››አለቻት፡፡
ፅዬን በግምት እጇን ወደ እሷ ላከቻና የለበሰችውን ጃኬት ይዛ ወደ ራሷ ጎትታት ጉያዋ ውስጥ ሸጉጣ አቀፈቻት ‹‹በቅርብ ቀን
እንደ እኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔም በላይ ትጫወቺያለሽ፡፡ አንቺ ምርጥ ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ሀሊማ ደግሞ ምርጥ ድምፃዊ እንደምትሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡››ብላ በማበረታታት ጉንጯን ሳመቻት፡፡

ዶ/ር ሶፊያ ቀስ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣችና ሶስተኛው ክፍል ገባች፡፡ አንድ የአስራ ስምንት አመት ወጣት ሴት የአማርኛ ፊደል ተራ በተራ ብላክ ቦርድ ላይ እየፃፉች ሚጣን እያስተማረቻት ነው፡፡

እስከአሁን ያላየችው ወንዱን ልጅ ብቻ ነው፡፡ እሱ አራተኛው ክፍል ውስጥ ይሆናል›› ስትል ገመተች‹‹ለመሆኑ እሱስ ምን እየተማረ ይሆን?›› ለማወቅ በጣም ጓጓች.. ወደ አራተኛ ክፍል አመራች ፡፡እስከአሁን ካየቻቸው ሶስቱም ክፍሎች በተሻለ ይሄኛው በእጥፍ ሰፋት አለው፡፡ ግን ቤት ሳይሆን ኳተት ማጠራቀሚያ ክፍል ነው ማለት ይቻላል፡፡በኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣በብረታ ብረት ቁርጥራጮች፣በተበላሹ ቴሌቨዢኖች፣ሬዲዬኖች
ገመዳ ገመዶች ተሞልቷል፡፡ዕድሜው ከ1ዐ የማይበልጠው የሰውነቱ ግዙፍነት ግን የ15 ዓመት ታዳጊ የሚያስመስለው ድንቡሽቡሽ ልጁ ኮተቶቹ መሀከል ወለል ላይ ተዘርፍጦ ላፕቶፕ ኮምፒተር ላይ አፍጥጧል፡፡ድምፅ ብታሰማውም ሊሰማት አልቻለም፡፡ሹክክ ብላ ወጥታ ወደ ሳሎን ተመለሰች እና ስላየችው ነገር በግርምት ማሰላሰል ጀመረች፡፡

አንድ ሰዓት ሲሆን ሁሉም የእለት ስራቸውን አጠናቀው ከየአስተማሪዎቻቸው ጋር ከየክፍላቸው ወጡ፤ ከወንድዬው ልጅ በስተቀር፡፡ ሠላምንም አስተማሪዋ ደግፎት አመጣትና ከእሷ ጐን እንድትቀመጥ ከረዳት በኃላ‹‹ይቅርታ ቅድም በስራ መሀል ስለነበርኩ በቅጡ አላናገርኩሽም…የቤቱ ህግ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ስራ ይቀድማል፡፡አላዛር እባላለሁ፡፡››በማለት እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት፡፡ እሷም እየጨበጠችው‹‹ሶፊያ እባላለሁ›› አለችው፡፡

‹‹አሁን ሠላምን መጠየቅ ትችያለሽ..ያው ከጎንሽ አስቀምጪልሻለሁ፡፡ እኔ ሽንት ቤት ደርሼ መጣው›› ብሎ ወደ ጓሮ ሄደ ::

‹‹አመሰግናለሁ››ብላው የሰላምን ግንባሯን ሳመቻት፡፡

‹‹ትመጪያለሽ ብዬ ስጠብቅሽ ነበር ::>> አለቻት ሠላም በመምጣቷ መደሰቷን በፈገግታዋ እያረጋገጠችላት፡፡

‹‹ይሄው መጣሁልሽ፤ ለመሆኑ የሚያምሽ ተሻለሽ?»

‹‹አዎ ...ዛሬ ሚጠዘጥዘኝ ትቶኛል፡፡››

‹‹አይ ጥሩ ነው፡፡››ንግግሯን ሳትጨርስ ሌሎቹ ልጆች ከያሉበት መጥተው ወረሯት ፡፡ግማሹ ግንባሯን ግማሹ ጉንጮን ሳሟት፡፡እሷም በየተራ ሳመቻቸው፡፡ለሚያያቸው ዕውቂያቸው የአንድ ቀን ብቻ አይመስልም፡፡

አላዛር ከጓሮ ተመለሰና ከሚጠብቁት ጓደኞቹ ጋር ከተቀላቀለ በኃላ ድምፅን ከፍ አድርጐ << ሶፊ ልንሄድ ነው››ሲላት ልጆቹን ‹‹ቆይ አንዴ መጣሁ >>ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ እነ አላዛር ሄደች፡፡

‹‹ይቅርታ እኔ የታዲ ዘመድ ነኝ፤ ከሁላችሁም ጋር ብተዋወቅ ደስ ይለኛል፡፡››

አይነስውሯ ቀድማ ለሰላምታ እጇን እየዘረጋችላት‹‹ፅዬን እባላለሁ›› አለቻት፡፡

‹‹ዶ/ር ሶፍያና፡፡››
‹‹ቤቲ..ቤተልሄም፡፡›› እባላለሁ..ሌላዋ ቀጠለች፡፡
አላዛር መሀል ገብቶ ማብራሪያ በመስጠት ቀጠለ ‹‹...ፂ እንዳየሻት አሪፍ የሙዚቃ ሰው ነች፡፡ጊታር እና ፒያኖ ነፍስ አድርጋ ትጫወታለች፡፡የያሬድ ግርፋ ነች፤ በሞያዋ የሙዚቃ አስተማሪ ነች፡፡እዚህም እንዳየሻት የሄለን እና የሚኪያ የሙዚቃ አስተማሪ ነች፡፡…

ቤቲ ደግሞ ሀይ‐ስኩል አማርኛ ቲቸር ነች፡፡
የስድስት ኪሎ ምሩቅ ነች፡፡እዚህ ያሉትን ህፃናት አማርኛም ሆነ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፕሮግራም
ታስተምራቸዋለች፡፡አንዳንዴ
ሂሳብም ቀልቀል ለማድረግ ትሞክራለች ግን ቀሺም ነች፡፡ሂሳብ እና ጠቅላላ ዕውቀትን በተመለከተ ጂኒዬሱ ነው የሚያስተምራቸው፡፡

ጂኒዬሱ ስል ታዲዬስን ማለቴ ነው፡፡እኔ ያው
እዚህ ቤት የቀለም ሽታ የምትወድ አንድ ሰላም
የምትባል ልዩ ነፍስ ያላት ልጅ አለች ፤እሷን ስዕል አስተምራታለሁ፡፡አስተምራታለሁ ማለት
እንኳን ይከብዳል ስትስል
አያታለው፤የምትፈልገውን ቁሳቁስ አቀብላታለው ማለቱ ነው የሚሻለው ፡፡

ምክንያቱም አሁን ባለንበት ሁኔታ ችሎታችን እኩል ነው፤ከስድስት ወር በኃላ ደግሞ እኔ ቁጭ ብዬ ከእሷ መማሬ አይቀርም፡፡››
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ በጀመረች ሶስት ወርም ሳይሞላት በፊት ነበር፡፡ምክንያቱም ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ትክክለኛ ያልበተበረዘና ያልተከለሰ ማሳጅ 25 ፐርሰንትም አይሆንም...አሱ ሽፋን ነው፡፡
ወደስራው ጠልቃ ከገባች በኃላ ብዙ ብዙ ገራሚ ገጠመኞችን አስትናግዳለች… አንዳንዶቹ እስከህይወቷ ፍፃሜ የማትዘነጋቸው አይነት ናቸው፡፡
ከበርካታ ያልተለመዱ አይነት ገጠመኞቾ መካከል  አንድን ለምሳሌ ያህል ለማየት ብንችል ነገሮችን ግልፅ ያደርግልናል፡፡ስራ በጀመረች በአራተኛው አመት ነው፡፡ደምበኛ እንዳላት ተነግሯት በሰዓቷ ስራ ቦታዋ ተገኝታ እየጠበቀች ነው፡፡ እንደተባለውም በሰዓቱ በራፍ ተንኳኳ… ከፈተች፡፡በራፍ ላይ በመግባትና ተመልሶ ሮጦ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ውዝግብ ውስጥ የገባ ስሜት ላይ ያለ ጎልማሳ  ሰው  ቆሟል..ሰውዬውን  ታውቀዋለች… በአካል አይደለም..ታዋቂ ሰው ነው..ግን ምንድነው?  ተዋናይ  ነው?  ፖለቲከኛ ነው…? ግልፅ ብሎ ሊታወሳት አልቻለም፡፡‹‹ጌታዬ እንኳን ደህና መጡ ይግቡ.›› አለችና በራፉን በሰፊው ከፈተችለት..የመዝለል ያህል ፍንጥር አለና ወደ ውስጥ ገባ…እሷም በራፉን ዘጋችና  ተከተለችው…እቤቱ  ውስጥ  ከወዲህ  ወዲያ መንጎራደድ ጀመረ‹‹…ጌታይ ችግር አለ? ››ጠየቀችው፡፡

‹‹እዚህ መምጣቴ ትክክል ነው ወይስ ስህተት አላውቅም››

‹‹ጌታዬ ስህትም  ሆነ  ትክክል  አንዴ  መጥተዋል..አረፍ  ይበሉና  ትንሽ ይረጋጉ..እዚህ መምጣቶት ስህተትም ቢሆን የሆነ ጥቅም አይጠፋውም….ደግሞ ነገሮች እንደአጠቃቀማችን ይወሰናሉ…የህይወት ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ዳካሮ መውጣት የብርሀኗን ውበት የበለጠ እንድናጣጥም  ግንዛቤያችንን ይጨምርልናል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡››ብሎ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ፡፡ሳባም ወደፍሪጁ ሄደችና የታሸገ ውሀ በማምጣት ከጎኑ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለት..ከፈተና ገርገጭ.ገርገጭ አድርጎ ግማሽ ያህሉን ከጠጣለት በኃላ ከደነና መልሶ አስቀመጠው፡፡ለእኔ እዚህ ቦታ መምጣት ቀላል አይደለም…እዚህ እንድመጣ የጠቆመኝ አንድ ወዳጄ ነው….

‹‹ጥሩ ነው…ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚፈልጉት…ሙሉ ማሳጅ ..የእግር ማሳጅ አለ…ከአንገት በላይ ማሳጅ አለን…ሌሎች አገልግሎቶቹም አሉን.መጠጥና
…››
‹‹አይ እንዳዛ አይደለም…የዘረዘርሻቸውንም ሁሉ አንዳቸውንም አልፈልግም…እኔ የምፈልገው እንድታዳምጪኝ ብቻ ነው…ቆይ አሉና እጃቸውን ወደ ኮት ኪሳቸው በመክተት አንድ መለስተኛ ጥራዝ ያለው መፅሀፍ  አወጡና  ዘረጉላት፡፡ግራ በመጋባት ተቀበለችና አነበበችው›

‹‹የኢየሱስ ተአምራዊ የማዳን ስራ››የሚል ርዕስ አለው፡፡ጀርባውን ገልብጣ አየችው ፀሀፊ-ፓስተር ጴጥሮስ ዳንሳ ይላል፡፡ ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ፎቶ ገጭ ብሎበታል…እንደአዲስ ደነገጠች..ሰውዬው በደንብ ታውቀዋለች..በፕሮቴሰታንቱ መንደር በጣም ታዋቂና ዝነኘ ፓስተር ነው…በዛ ላይ የራሱ ሆነ ቴሌቬዥን ጣቢያ ስላለው.በተደጋጋሚ ስብከቱን በቴሌቪዥን መስኮት አዳምጣለች፤አሷ  ጋር መምጣቱ ለምን እንደዚህ እንደከበደው ወዲያው ነበር ግልፅ  የሆነላት..ኸረ መምጣቱ ለእሷ ለራሷ በጣም ገርሟታል..››

‹‹ፓስተር.በእውነት የአርሷ እዚህ  መምጣት  ለእኔ  ትልቅ  ክብር  ነው….እና እንዳሉኝ የሚፈልጉት እንዳዳምጧት ከሆነ በሙሉ ነፍሴ  የለምንም  ፍርድና ትዝብት እንደማዳምጧት እርግጠኛ ይሁኑ››

‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ .ማወራሽ ስለመፅሀፉ ነው፡፡በእጅሽ ስለያዝሺው መፅሀፍ ፡፡ መፅሀፉ እውነተኛ የህይወት ገጠመኜ የሰፈረበት ነው፡ይሄ ገጠመኝ ምንም ማጣፈጫ ያልተጨመረበት ንፅህ እውነት ነው ብዬ  አምን  ነበር።ላለፍት  9 ዓመታት ሰፋ ያለ ህዝብ በታደመበት አውደ ምህረት ላይ  ያለመሰልቸት ተርኬዋለሁ። ምዕመኑም አንዳንድ ሶስቴ ሌላውም 13ቴ ደጋግሞ ሰምተውታል። ግን አይ ሰልችቶኛል የሚል የለም፡፡ ከእልልታው ጥቂት ዝንጣፊ የሚቀንስ የለም።በጌታ ሰው አንደበት የሚነገር የጌታ ተአምር እንዴት ሰለቸኝ ማለት ይቻላል...?መታሰብስ።

የዛሬ 14 አመት ለአገልግሎት ደቡብ ኢትዬጰያና ሱዳን ድንበር  አካባቢ  ወደሉ ጎሳዎች እሄዳለሁ።እርግጥ ብቻዬን ሳይሆን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ነበር።እና ጉዞችን ጥቅጥቅ ደን የምናቋርጥበት ከአውሬ ጋር ድብብቆሽ የምንጫወትበት አስደናቂና አስፈሪ ነበር..ግን ደግሞ ጌታ ከእኛ ጋር ስለነበር በዝምታ ሳይሆን በዝማሬ ነበር የተጓዝነው። መንገድ ከሚገኝበት የሁለት ቀን የእግር መንገድ ተሂዶ ነው የሚደረሰው። ጌታ ይመስገን በሰላም ደረስን።ጌታን አገለገልን በሶስት ወር ቆይታችን 10 ብቻ የነበሩትን አማኞች ወደ ሶስት መቶ አሳድገን በመንደሩና በአካባቢው  የጌታ  አገልጋዬች  አድርገን  ጉባኤ  አደራጅተን  ቤተክርስቲያን መስርተን አንደኛውን ጓደኛችንን እዛው  እንዲያገለግል  ትተን  የመልስ  ጉዞ ጀመርን።

በመሀል ደረቀ ጉሮሮውን ለማርጠብ ከጎኑ ካለው ጠረጴዛ ውሀውን አነሳና ላይ የተቀመጠለትን ሀይላደንድ ውሀ በመክፈት እየተጎነጨ በተመስጦና በስሜት ትረካውን ቀጥሏል…፡
…በሁለተኛው ቀን ከጓደኞቼ ነጥለው ጠለፍኝ።አንድ መፅሀፍ ቅድስ ብቻ ነበር በእጄ የያዝኩት፡፡ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀኝ አልኩ።የጠለፍኝ ሰዎች ቋንቋቸው የማይገባ እጅግ ከሰው ተነጥለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የሚኖሩ 2መቶ የማይሞላ ቁጥር ያላቸው አባላት ያላቸው ጎሳዎች ናቸው።
ከወሰዱኝ በኃላ አንድ ጠባብ ጎጆ ውስጥ ጠርቅመውብኝ በራፍን ገንጥዬ እንዳላመልጥ ሁለት ጦር የቀሰሩ ጠባቂዎች በራፍ  ላይ  አስቀመጡ።መፅሀፍ ቁዱሴን ደረቴ ላይ ለጥፌ እኔ ፀልያለሁ...ያለማቆረጥ ከጌታ ጋር አወራለሁ።ሶስታ ቀንና ሶስት ለሊት  እዛች  ጠባብ ጎጆ  ውስጥ  አሳደሩኝ፡፡  በአራተኛው ቀን የተለየ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ውጭ ታላቅ  ክብረ  በዓል  ለማዘጋጀት  ትርምስ  ላይ እንደሆኑ ይታየኛል።‹‹ጌታ ሆይ  ተአምራትህን  በዚህ  ዝግጅት  ላይ  አድርግ›› እያልኩ ፀሎቴን ቀጠልኩ.. ሲጨልም ምቀምሰውን ምግብ አንድ ልጃገረድ ይዛልኝ መጣች፡፡ ጠባቂዎቹ ወደውስጥ እንድታልፍ ፈቀድላት...:: ጎምበስ ብላ ምግብን እያቀረበችልኝ
"አይዞህ"አለችኝ፡፡

‹‹ እንዴ ጌታ ስራውን መስራት ጀመረ ››አልኩ...አማርኛ ትችላለች..

"ለምንድነው የያዙኝ...?ከእኔ ምን ፈልገው ነው ?"ከእሷ ባነሰ ደካማ ድምፅ ጠየቅኳት።
"ለመስዎእትነት..ለአማልዕክቱ ሊያቀርብህ ነው" አለችኝ... ያልጠበቅኩትን መልስ ነበር ያገኘሁት…የጌታ ጥበቃ በዙሪያዬ እንዳለ ባምንም..የልጅቷ በዛን ሰዓት

ከአማርኛ  ችሎታ  ጋር  ስሬ  መከሰት  አንድ  ምልክት  እንደሆነ  ባልጠራጠርም
...ሰውነቴ በፍራቻ መራድ፤አፌም በድንጋጤ መድረቁ አልቀረም ነበር።"
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

..ፎጣዋን አገልድማ ስትወጣ እሱ ደግሞ ለመግባት እርቃን ሰውነቱን በፓንት ብቻ ሆኖ ወደእሷ አቅጣጫ ሲመጣ አየችው…ዞር ብላ መንገዱን ለቀቀችለት …ቀጥታ ወደውስጥ ገባና የሻወሩን በራፍ ዘጋው…
ባለቤቷን እንዲህ እርቃኑን ስታየው ሁሌ እንደአዲስ እንደገረማት ነው፡፡ሰለብሪቲ አክተር ወይም ታዋቂ ሞዴል እኮ ነው የሚመስለው፡፡እዚህ አካባቢ እንደዚህ ቢሆን የሚባል ቅር የሚያሰኝ የአካል ክፍል የለውም‹‹ሆሆ..ለናሙና የተፈጠረ እኮ ነው የሚመስለው››አለችና ሰውነቷን አደራርቃ በምሽቱ ሶስቱን የእድሜ ልክ አድናቂዎቾና አፍቃሪዎቾ ወንዶችን ያስደምማል ያለችውን አለባበስ ለበሰች፡፡ፀጉሯን አስተካከለች፡፡የተወሰነ ሜካፕ ተጠቀመችና ሽቶ እላዮ ላይ ነስንሳ ወደሳሎን ወጣች፡፡
አለማየሁ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ  ዝንጥ ብሎ  ሳሎን ቁጭ ብሎ እስኪወጡ እየጠበቃቸው ነበር፡፡
እንዳየችው ‹‹እንዴ ኩማንደር….አምባሳደር መስለሀል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹የወደፊት እጣ ፋንታዬ ምን አልባት አምባአሳደር ሊሆን ይችላል፡፡››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምነው አፍጥጠህ አየሀኝ…ልብሱ አልሄደብኝም እንዴ?››ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት፡፡

‹‹አረ የሚያስደነግጥ አለባበስ ነው … እንከን አይወጣለትም ..በጣም ያምራል፡፡››

‹‹ልብሱ ብቻ ነው ሚያምረው?››ስትል ልስልስ በሆነ ቅንዝራም ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹ስለአንቺ አላዛር ሲመጣ ይነግርሻል….ያንን አስተያየት የመስጠት መብት ለጊዜው የእሱ ነው፡፡››

ግንባሯን ቋጠረች‹‹ለጊዜው ስትል…?››

‹‹ይሄ ጥያቄ ይዝለለኝ፡፡››

‹‹በጣም ተቀይረሀል ..ድሮ እንደዚህ አልነበርክም››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ከእኔ ጋር ለምትነጋገረው ነገር ስትጠነቀቅ አይቼህ አላውቅም ..እንደመጣልህ በነፃነት ነበር የምናወራው፡፡ትዝ ይልሀል ..አንተ እኮ ጓደኛዬ ብቻ አልነበርክም….አንድ ቤት ውስጥ አብረኸኝ ያደክ ወንድሜ ነህ፡፡››

‹‹አዎ..በልጆቼን በሞት ሳጣና አያቴም በቃኝ ብላ ገዳም ጥላኝ ስትገባ ..አንተም ልጄ ነህ ..ከልጄ ጋር አሳድግሀለው ብላ የወሰደችኝ እናትሽ እቴቴ ነች፡፡በእውነት ለእሷ በሚገባው መጠን አልተንከባከብኳትም…፡፡››

‹‹ተው ተው..እቴቴንማ በጣም ነው የተንከባከብካት፡፡.በየጊዜው ብር እንደምትልክላት ማላውቅ ይመስልሀል፡፡እዚህ ከተቀየርክ በኃላ  እንኳን እሷን ደጋግመህ አግኝተህ እኛን ግን ለማግኘት ፍቃደኛ አልነበርክም፡፡ካንተ ደግሞ ይልቅ ደግሞ የሚገርመኝ የእሷ ያንተ ተባባሪ ሆና መደበቅ፡፡ …እንደውም አንዳንዴ ከእቴቴ ጋር ስንጣላ እኮ…‹‹ከአንቺ ይልቅ የእኔን እናትነት የተረዳው አለማየሁ ነው…››እያለች ታበሳጨኛለች፡፡እና እሷ በአንተ ደስተኛ ነች…ትንሽ ቅር ሚላት በየጊዜው በአካል ሄደህ ስለማትጠይቃት ነው፡፡በዛ ከአንተ እኔ እሻላለሁ….፡፡››

‹‹ቢሆንልኝ…ለእሷ ምንም ነገር ባደርግ ይገባታል፡፡››

‹‹ለእኔስ…ለስድስት አመት የት እንዳለህ እንኳን ደውለህ አሳውቀሐኝ አታውቅም…አለማየሁ ደወሎ እንዲህ አለ…አለማየሁ ደውሎ በባንክ ይሄንን ላከ ሲባል እንጂ አንድ ቀን ሰሎሜ ሰላም ብሎሻል…?ሰሎሜ አለማየሁ ሰለአንቺ እንዲህ  ያስባል ብሎ የነገረኝ ሰው የለም..ሁል ጊዜ አእመሮዬን እንደበላኝ ነው…‹‹ምን አድርጌዋለው…?መቼ ቀን ነው ያስከፋሁት …?.የቱ ጋር ነው የተቀየመኝ? ብዬ እንደተከዝኩ ነበር..እወነቱን ለመናገር በጣም ተቀይሜህ ነበር ..ባገኝህ እንደማላናግርህ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር..ግን በእንደዛ አይነት ሁኔታ ስንገናኝ…ምንም ማድረግ አልቻልኩም...ተቀይሜህ እንደነበረ ራሱ ከእስር ተፈትቼ ቤቴ ከገባው በኃላ ነው ያስታወስኩት፡፡››

‹‹ጥሩ ነው፣ ቂመኛ አይደለሽም ማለት ነው…አንቺን ያላገኘሁሽ ግን ላላገኝሽ ስላልፈለኩ ሳይሆን ተገድጄ ነው››

‹‹ተገድጄ ስትል?››

‹‹ማለቴ….››ንግግሩን እንዳንጠለጠለ አላዛር ከእነሱ በበለጠ.. ልክ እንደእለቱ ሙሽራ ዝንጥ ብሎ ወደእነሱ ሲመጣ ስለተመለከተ ለንግግር የተከፈተ አፉን መልሶ ዘጋ፡፡

‹‹በሉ…እንሂድና …ቀደም ብለን እዛው አካባቢ ደርሰን ብንጠብቀው ይሻለል፡፡››

አለማየሁ አላዛር መጥቶ ማውራት ከማይፈልገው ነገር ስለገላገለው በመደሰት ‹‹ጥሩ …እንሂድ››አለና ከተቀመጠበት  ተነሳ፡፡ርምጃውን ከአላዛር አስተካክሎ ወደውጭ መራመድ ጀመረ.፡፡ሰሎሜ ከኃላ ሁለቱንም በትኩረት እያየች ተከተለቻቸው፡፡ሁለቱም ፈርጣማና ወንዳወንድ የሚባሉ ናቸው፡፡ግን አላዛር ወደላይ የተሳበ መለሎ ነው፡፡
//
ከ30 ደቂቃ ጥበቃ  በኋላ የተጠበቀው ሁሴን ግዙፍ ሻንጣውን በጋሪ እየገፋ ከተርሚናሉ ሲወጣ ሶስቱም በእኩል አዩት…በደስታና በጩኸት እንዲያያቸው እጃቸውን አውለበለቡለት…ሁሴን ከዛሬ ስድስት   አመት  በፊት እደሚያውቁት አይነት ነው፡፡ እንዳዛው ውልምጭምጭ ቀጫጫ…ባለትልቅ ጭንቅላትና ሉጫ ፀጉር…የህፃን የመሰለ ፍልቅልቅ ፊት…ነጭ ከሩቅ አይን የሚስብ  በረዶ መሳይ ጥርስ ……
ሶስቱም በየተራ እየተጠመጠሙበት ሰላምታ ከሰጡትና ይዘው የመጡትን የእንኳን በሰላም መጣህ ምኞታቸውን የሚገልፅ  አበባ አስታቀፉት፡፡ከዛ በኃላ አለማየሁና አላዘር ሻንጣውን ተቀብለው  ወደመኪናው ወሰዱና ከኋላ ጫኑለት፡፡…በአላዛር ሹፌርነት ሰሎሜ ገቢና ከእሱ ጎን ተቀምጣ አለማየሁና ሁሴን ከኋላ ሆነው ወደቤት ጉዞ ጀመሩ፡፡

ድንገት‹‹ይገርማል…?››አለ ሁሴን፡፡

አለማየሁ‹‹ምኑ ነው የገረመህ?ከተማዋ ልደቷን የምታከብር የቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ መሰለችህ አይደል…?››አለው፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹አሸብርቃና ተኳኩላ …በደማቅ መብራቷች ተንቆጥቁጣ ስታያት ገርሞህ እንደሆነ ብዬ ነዋ?››

‹‹..አዎ ያልከው ነገር በጣም አስገርሞኛል..ግን እኔ ለማውራት የፈለኩት ሶስታችሁን በአንድነት መጥታችሁ ትቀበሉኛላቹሁ የሚል ምንም አይነት ግምት ስላልነበረኝ በዛ መደነቄን ነው፡፡፡፡›

ልክ እንደሁሴን እሷም ሶስቱም የልጅነት እና የአፍላ ወጣትነት ጓደኞቾ እና አፍቃሪዎቾ ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲህ አንድ ላይ ተሰብስበው አይናቸው እሷ ላይ ሲያቁለጨለጩ በመመለከቷ እየተገረመች‹‹ምን ማለት ነው? ሶስታችንም እኩል ጓደኞችህ አይደለንም እንዴ…?ለመሆኑ መጥቶ ይቀበለኛል ብለህ የገመትከው ማንን ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው አሌክስን ነበር፡፡እናንተን በማግስቱ ባገኛችሁ ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡››

‹‹አንተ …ከእኛ ይልቅ አሌክስ ቁምነገረኛ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው…?ነው ሰው ሀገር ከሄድክ በኃላ ፀባያችን ተምታታብህ››አለችው ሰሎሜ በመገረም፡፡

አለማየው በፈገግታ‹‹አንቺ …ሰው ሁሉ ስለእኔ ልክ እንደአንቺ የተሳሳተ ግምት ያለው ይመስልሻል እንዴ?››አላት፡፡

‹‹ተው ተው…ከመሀከላችንማ አንደኛው ቁምነገረኛና ኃላፊነትን የሚወስደው አላዛር ነው…አንተ እንደውም በዚህ ጉዳይ  የመጨረሻው ሰው ነህ››አለው ሁሴን፡፡

‹‹አንተ ዲያስፖራ ለመሆኑ ዜግነትህን ቀይረሀል?››ሲል ጠየቀው፡፡
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለተጠየቀው ግራ ተጋባ‹‹አይ አልቀየርኩም…ግን ለምን ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ኢትዬጵያዊ ዲያስፖራ ከሆንክ  የሚጮህልህ ኤምባሲ ስለሌለ ለዚህ ንግግርህ የሆነ ሰበብ ፈልጌ ከርቸሌ ልወረውርህ ነዋ….እንደድሮ አለማየሁ ብቻ አይደለሁም..ኩማንደር አለማየሁ ነኝ፡፡››