#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
.....አቤል በዮናታን መኪና የአራት ኪሎን ቁልቁለት ሲወርድ፥ ወዴት እንደሚሔድ በውል አያውቅም ነበር ዮናታን በድንገት ከመኝታ ክፍሉ አስጠርተውት ነው የወሰዱት "ዛሬ ከእኔ ጋር ነህ” ከማለት ሌላ ፡ ወዴት እንደሚወስዱት አልነገሩትም እሱም አልጠየቃቸውም ።አብዮት አደባባይ ከመድረሳቸው በፊት በሚገኝ አንድ የመኖሪያ ሕንፃ ጀርባ መኪናቸውን አቁመ የሕንፃውን ደረጃዎች ወጡ ። ሦስተኛው ፎቅ ላይ ሲደርሱ በሩ ላይ “
ቁጥር የተጻፈበትን መኖሪያ ቤት ደውል ደወሉ ። አንዲት ፈረንጅ ከውስጥ በሩን ከፍታ ብቅ አለች ።
“አቤል ማለት እሱ ነው ” አሏት ዮናታን በጀርመንኛ።
ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር ሰላምታ ሰጠችው "
“ ባለቤቴ ናት" አሉት ዮናታን ።
ከትውውቁ በኋላ ወደ ቤት ገብተው ተቀመጡ ። አቤል ዮናታን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ለምን እንዳመጡት ሊገባው
አልቻለም ። በልቡ ብዙ ነገር እያሰበ በግድግዳዎቹ ላይ የተሰቀሉትን ሥዕሎች አንድ በአንድ በዐይኑ አዳረሳቸው ።
ከዮናታን ባለቤት ጋር በዐይን መሣሣቅ ካልሆነ በስተቀር ቃላት መለዋወጥ አልቻሉም ። እንግሊዝኛ ለመግባቢያ
ያህል ትችላለች ። ግን ዮናታን ጀርመንኛ ስለሚያውቁ ቤታቸው ውስጥ የሚነጋገሩት በጀርመንኛ ነው ። አንዳንዴም የምታውቃቸውን ጥቂት የአማርኛ ቃላት በመጠቀም እንግዶቻቸውን እያሣቀች ታዝናናለች "
“ይኽውልህ እዘህ ፎቅ ላይ ተሰቅለን ነው የምንኖረው ” በማለት ዮናታን ፡ ከአቤል ጋር ጨዋታ ከፈቱ።
አቤል ፈገግ አለ ።
“አንተ ወደፊት ምን ዐይነት ቤት ውስጥ መኖር ነው የምትመርጠው ? ” ሲሉ ጠየቁት ።
“ምን ዐይነት ጥያቄ ነው ?” አለ በልቡ ፥ “ አሁን ባለው የቤት ችግር ሁኔታ አንገት ማስገቢያ ይገኝ እንጂ፡ የቤት ምርጫ ይጠየቃል እንዴ ?” ዮናታን ግን እሱን ማጫወት ሲሉ አፋቸው ላይ የመጣላቸው አርዕስት ሆኖ ነው እንጂ
የሚኖሩበትን ሀገር እውነታ አጥተውት አልነበረም ።
“ በአሁኑ ጊዜ አንገት ማስገቢያ ከተገኘ ምን ምርጫ አለ ? ” አላቸው እየተቅለሰለሰ ።
የመመረቂያው ዓመት ላይ ቢሆንም ከዩኒቨርስቲዉ ሲመጣ ስለሚገባበት ቤት አስቦ አያውቅም ። ከቤት ጋር የትዳርም ሐሳብ ይኖራል ። ያንንም ቢሆን አስቦ አያውቅም ። በእርግጥም ስለ ቤት ማሰብ የሚችለው የሥራው ምድብ ቦታ ካወቀ በኋላ ነበር ።
“ አይዞህ ፡ የጊዜ ጉዳይ ነው ” አሉ ዮናታን ፡ “ አሁን ካለንበት ችግር ወጥተን የምርጫችንን የምናገኝበት ጊዜ ይመጣል ። ምን አጣን ብልህ ነው ?ለም መሬት አለን ሀገራችንን ዐልፈው ውጭ የሚፈሱ ወንዞች አሉን : ተፋቅረንና ተባብረን ጠንክረን ከሰራን ብሩህ ተስፋ ይጠብቀናል።
ባለቤታቸው ሻይ ይዛ መጣች ። እሷም ቀስ እያለች ከአቤል ጋር በእንግሊዝኛ መጨዋወት ጀመረች ። ስለ የአቤል ብዙ ነገር ታውቃለችና ሁኔታውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስካሁን ባሏ ያጫውቷት ስለ ነበር፡ ለአቤል ደኅና አመለካከት አላት ሁሉም ለጊዜው ዝም ዝም ቢሉም ፡ እንግድነቱን ለማስታመም ካልሆነ በስተቀር ዝምታው ካለመተዋወቅ
የመነጨ አልነበረም ።
አንዳንድ ማኅበራዊ መግባቢያዎችንና ጨዋታዎችን እየተለዋጡ ሻዩ ተጠጥተው ስኒዎቹ ተነሡ «ከዚያ ዮናታን የቤቱን ክፍሎች ለአቤል ማስጎብኘት ጀመሩ ። ይህ ተግባራቸው ዓላማ ነበረው ። በመጀመሪያ መኝታ ቤቱን ፥ ወጥ ቤቱንና መታጠቢያ ቤቱን አሳዩት ።በመጨረሻም ወደ አንዲት አነስተኛ ክፍል ወሰዱት ። በክፍሏ ውስጥ ብዙ ዕቃ አልነበረም ።፡ አንድ አልጋ እና አነስተኛ ጠረጴዛ ከነወንበሩ ብቻ ይታይበታል ።
“ ይህ ደግሞ የአንተ መኝታ ክፍል ነው ” አሉት ፍርጥም ብለው ።
አቤል ግር አለው ። ድንጋጤ ይሁን ደስታ የተሰማውን ለማወቅ አልቻለም ።
“ ያሉት አልገባኝም ” አላቸው ።
“ ይህ ለአንተ ያዘጋጀሁት መኝታ ክፍል ነው ። ለተወሰነ ጊዜ ከእኔ ጋር እንድትኖር ወስኜአለሁ ። ማንኛውንም ነገር እዚሁ ሊሟላልህ ይችላል ” አሉት " በጥያቄ ሳይሆን በውሳኔ ድምፅ ።
ዮናታን አቤልን እቤታቸው አስቀምጠው ጉዳዩን ለማራአመድ የወሰኑት ሰሞኑን ከባለቤታቸውና ከቢልልኝ ጋር
ተመካክረው ነበር ። በአንድ በኩል የአካባቢ ለውጥ ለአቤል ጤና ይረዳዋል ብለው ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ አቤል
በዚህ ዓመት ትምህርቱን ስለማይቀጥል አጠገባቸው አድርገው ሞራሉን በመጠበቅ ለማበረታታት እንዲመቻቸው
ነው ። ዮናታን ከሚስታቸው ጋር ሆነው ይህን የወሰኑት ስለ አቤል የተደረገው የሥነ ልቡና ጥናት ጥሩ ደረጃ ላይ
መድረሱን ካረጋገጡ በኋላ ፡ የመንፈስ ደስታ አግኝተው ነው ። በአቤል ጐብዝና ባሳቸው የጠነከረ እምነት በቅን፥
ልባቸው የጀመሩት ጉዳይ ከዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ አስደስቷቸው በበለጠ እንዲቀጥሉበት ገፋፍቷቸዋል ።
ዮናታን አቤልን ወደ ቤታቸው ከማምጣታቸው በፊት ይህን ውሳኔአቸውን ያልነገሩት ሆነ ብለው ነው ። ውጭ ቢነግሩት በነገሩ ያመነታ ይሆናል ። ቤት ውስጥ ገብቶ የተዘጋጀለትን ክፍል ካየ በኋላ ግን አንድም ሊወደው ይችላል !ያም ካልሆነ ድካማቸውንና የሰጡትን ክብር በማገናዘብ በእሺታ ይቀበለዋል የሚል ግምት ነበራቸው ። እንዳሰቡትም አቤል ክፍሉን ከተመለከተ በኋላ"የእምቢታ ስሜት አላየለበትም ። ነገር ግን አፉን ሞልቶ “ እሺ ይሁን ” ማለትም አልቻለም ። የተዘበራረቀ ስሜት ሰፈረበት ። ብቸኛኔቲን ይንዳል ። እናም ብቸኛነቱን ሊያስታምምበት የሚችለውን ይህን ክፍል ወድዶታል። ግን ደግሞ የዩኒቨርስቲውን ግቢ መልቀቅ ? ከትዕግሥት ዐይን መራቅ ?
“ እንዴት ነው ? ጥሩ ክፍል ነች ? ” አሉት ዮናታንበላዩ ላይ የሚያንዣብበውን የማመንታት ጥላ በሚገፍ ድምፅ ።
“ ጥሩ ነው ” ሲል ራሱን ነቀነቀ ።
“ የመጻሕፍት ክፍል ከእኔ ጋር በጋራ መጠቀም እንችላለን ” ብለው ፡ ወደ ጥናት ክፍላቸው ወሰዱት ።
መደርደሪያዎቹ በመጽሐፍ ጥቅጥቅ ያሉበት ክፍል ነበር ። መለስተኛ “ላይብራሪ !” የቀለም ትምህርት የፍልሰፍና የምርምር እና ልብ ወለድ መጽሐፎች ፥ እንዲሁም ወርኃዊ መጽሔቶች በመልክ በመልካቸው ተደርድረዋል ።አቤል ስሜቱ ለመንቃት ሲንጠራራ ተሰማው ። ባለ ሦስት ጥራዝ የማርክስ “ ካፒታል ” ከመጽሐፎቹ ሁሉ ጎልቶ ዐይኑን ሳበው ።
ይኸው ነው እንግዲህ ፡ ወደ ማታ ዕቃህን ከካምፓስ ማምጣት እንችላለን ” አሉትና ተመልሰው ወደ ሳሎኑ አመሩ ። አቤልም እግሩን በሐሳብ እየጎተተ ተከተላቸው ።
ሻንጣውን ለማምጣት ከዮናታን ጋር ወደ ዩኒቨርስቲዉ ሲሄድ፡ መንገድ ላይ ልቡ ማመንታቱ አልቀረም ። ዩኒቨርስ
ቲዉን ለቅቆ የመውጣቱን ነገር ልቡ ባይቀበለውም ሁኔታውን ሲያመዛዝን ዮናታን እሱን ለመርዳት ያደረጉለት ጥረት
ከብዶታየው ። እናም በባዶ ግትር እምነት ገደል አፋፍ ላይ የቆመች ሕይወቱ በሰው እጅ ጥበቃ ሥር እየዋለች መሔዷ ታመቀው ። የጥገኝነት ስሜት ተሰማው ። ጥገኝነትን አይወድም ነበር " ከድህነቱ ጋር ሞቶ መቀበር ከልጅነቱ ጀምሮ
ያደረበት ጸባይ ነው ። ግላዊ ነጻነቱን ይሻል ፤ግን የሌላውን እርዳታ ሳይሻ፡ብቸኛ እና ነጻ ሕይወት የኖረ ሰው በዚህ ዓለም
ላይ ማን አለ ?
ከመኝታ ቤቱ ገብቶ ሻንጣውን ሲያወጣ፡ አቤል ሆዱን ባር ባር አለው ። በዚህ መኝታ ክፍል ውስጥ የሆዱን አውጥቶ ለጓደኞቹ በደንብ ያጫወተበት ቀን ወይም በጋራ ያሳለፉዋቸው ታላላቅ ትውስቶች የሉም ። ነገር ግን ባዶ ትንፋሽም ቢሆን ከለመዱት ሲለዩ ያባባል ። ከርሱ ይበልጥ ሆጹ የባባው እስክንድር ነበር። ሆኖም የዮናታን ጥረት ለእቤል መልካም ሕይወት ስለሆነ፡ ፊቱ ላይ ምንም ዐይነት ቅሬታ እንዳይታይ ከውስጥ እየታገለ

#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ሲንተከተክ የቆየው፤ የብሶት ቋያ የቀቀለው ፤ትኩስ እንባና እልህ እንዴ
እሳተ ገሞራ ገነፈለ፡፡ ከዚያም ኡኡ!! ብሎ እየጮኽ ዋይታውን ማስማት ሲጀምር፤ ከደጅ ተኮልኩሎ ሲጠባበቀው የነበረው ዘመድ አዝማድ በሙሉ ተከታትሎ ወደቤት መግባት ጀመረ፡፡ ስዎች እየተንጋጉ ገቡ፡፡ እሱም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር መቀላቀሉን ሲያውቅ፤ እጅግ ሆድ ብሶት ማንባቱን
ቀጠለ...
“አመልማል ፍቅሬ፡፡ ትዳሬ፡፡ አመልማልዬ ምነው ጨከንሽ? ምነው ደስታዬን ገፈፍሽው? እንግዳ መቀበሉን ስታውቂ ምነው በኔ ልብሽ ጨከነ? አመልማል አስራ አንድ ዓመት ሙሉ የናፈቀሽ ልቤን
ምነው በሀዘን ጉዳሽው እናቴ? ቤቷ ተጨናነቀች፡፡ እዚያ የገቡት በሙሉ እየመጡ እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ ይላቀሱ ጀመር፡፡ የሚያለቅሱት ለሱ ይሁን ለሟቿ አይታወቅም ነበር፡፡ ደስታም ከልክ በላይ ሲሆን ያስለቅሳልና የሚወዱት
መቶ አለቃ ድንበሩ ሞትን ድል ነስቶ ሲያገኙት ቢያለቅሱ ምን ይፈረዳል? የሱ በህይወት መገኘት በአንድ በኩል ታላቅ ደስታን ሲፈጥር፧ እሱ አለችልኝ ብሎ፤ በጉጉት ተውጦ፧ ሊያገኛት የመጣ
ሚስቱን በሞት ተነጥቆ፣ እንደዚያ አንጀቱ እየተርገፈገፈ አንጀት በሚበላ
አለቃቀስ ልቡ ተሰብሮ ሲያዩት፤ የሚፈጥረው የሀዘን ስሜት ከባድ ነው፡፡
ክፍሏ በመርዶና በትንሳኤ መካከል ዋዠቀች፡፡ ለቅሶው ቀለጠ፡፡ እየሄዱ
እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ፤ እዬዬ ሆነ፡፡ ደስታው ሙሉ ደስታ ባለመሆኑ
መቶ አለቃ ድንበሩ አለቃቀሱ እጅግ የሚያሳዝን፤ ብዙዎችን በእንባ
ያራጨ ነበር፡፡
አትጨክንም ነበር አመልማል በእንግዳ
ጀርባዋን ሰጠችኝ አረገችኝ ባዳ፡፡
ሞትን አሸንፌ ስመጣ በናፍቆት
ሸሸችኝ፤ ራቀችኝ፤ ኧረ ምን በደልኳት?
አመልማል ትዳሬ አመልማል ህይወቴ
እባክሽ ወይ በይኝ፤ አትጨክኝ እናቴ፡፡
አለሽልኝ ብዬ በጉጉት ስመጣ
ምነው ጉድ አረግሽኝ ደስታዬ ቅጥ አጣ፡፡
ፋናዬን ትንሿን አንዱዬ አካሌን
የአጥንታችን ፍላጭ ሁለት ልጆቻችን፡፡
ኧረ የትደረሱ እባክሽ ንገሪኝ
አንዴ በሹክሹክታ ድምፅሽን አሰሚኝ፡፡
ፈጣሪዬ ስማኝ ልንገርህ ብሶቴን
ዐይኖቿን አይቼ የምወዳት ሚስቴን፡፡
ፍቀድልኝ ባክህ ናፍቆቴን ልወጣ
ተከትያት በአካል ጠቅልዬ እስክመጣ፡፡
አመልመል አመልማል
የትዳሬ ዋልታ፡፡
እኔ ድፍት ልበል፤ እኔ ልንገላታ፡፡
መከራና ስቃይ ደቁሰው ገደሉሽ?
አይዞሽ እመጣለሁ፡፡
የህይወትን ሽክም
በምድር ባልረዳሽም፡፡
እዚያ አግዝሻለሁ፡፡
ናፍቆቴን ልወጣ
አልቀርም እመጣለሁ፡፡
የሀዘን እንጉርጉሮ አንጐራጐረላት፡፡
በዚያን ሰዓት በሻምበል ብሩክና በትህትና ሰርግ ላይ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው፤ እንደ ወላጅ ሆነው፤ የዳሯቸው የረጅም ጊዜ ጐረቤታቸው አዛውንቱ አቶ ብራቱ በተፈጠረው ሁኔታ በደስታ ሰክረው፤
ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ሆነው፤ ወደ መገናኛ ወደ ትህትና ቤት በታክሲ
እየገሰገሱ ነበር፡፡
አዲሱን፣ አስደናቂውን፣ ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን፣ ታላቅ የምሥራች ይዘው
ትህትና ድንበሩ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በፀሐፊነት ተቀጥራ በማገልገል ላይ የምትገኝ ባለትዳር ስትሆን፤ የአንድ ወንድና፤ የአንዲት ሴት ልጆች እናትም ለመሆን በቅታለች።
በባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ የሚገኘው ዘንካታው ወጣት አንዱዓለም ድንበሩም፤ አንድና ብቸኛ የሆነቸውን፤ እንደ ዓይኑ ብሌን የሚያያት፣ ህይወቷን አሳልፋ የሰጠችለት፤ ታላቅ እህቱን፣ የሚወደውና በቅርቡ የሻለቅነት ማእረግ ያገኘው አማቹ ሻለቃ
ብሩክና፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊያገባት የተዘጋጀው እጮኛው አዜብ ተሾመን፤ ሊጠይቅ፤ የአሥራ አምስት ቀን የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን ወስዶ ከአሰብ ከመጣ አንድ ሣምንት ሆኖት ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ የሻለቃ ብሩክ አጥር በር ተንኳኳ፡፡
ሠራተኛዋ በሩን ከፈተች፡፡ ሁለት ሰዎች ቆመዋል፡፡አታውቃቸውም፡፡
“ሻለቃ አለ?” ሲሉ ጠየቋት ሽማግሌው።
በዚያን ሰዓት አንዱዓለም፣ ትህትና፣ ሻለቃ ብሩክና ወንድሞቹ ስብስብ ብለው እየተሳሳቁ እየተጨዋወቱ፤ እራት እየበሉ ነበር፡፡
“አሉ” ስትል መልስ ሰጠቻቸው፡፡
“አንድ ጊዜ ጥሪልኝ” አሏት ረጋ ብለው፡፡
ሄዳ ብሩክን ጠርታ መጣች፡፡
“እንዴ አባባ ብራቱ ዛሬ ከየት ተገኙ? ይዝለቁ እንጂ!”
ትከሻቸውን እቅፍ እድርጐ እየሳማቸው፡፡
“እሱን አደርሳለሁ ሻለቃ፡፡ አመጣጤ ለብርቱ ጉዳይ.
ነበር። ሥራ ይዘሃል?”
“ሥራስ ብይዝ ምን ችግር አለው ? ደግሞ ለርስዎ? አሁን ግን
ምንም ሥራ አልያዝኩም፡፡ ይግቡዋ ታዲያ” በእጁ ወደ ቤቱ እንዲገቡ
እየጋበዛቸው፡፡
“ባለቤትህስ አለች?”
“ባለቤቴም ፤ወንድሟም፤ ሁላችንም አለን፡፡ ምነው በደህና?”
“እንግዲያውስ አንድ ጊዜ መጣሁ በላቸውና ተመለስ፡፡ በጣም
ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እኔ መሆኔን እንዳትነግራቸው፡፡ አይዞህ በደህና
ነው” አሉት፡፡
ሄዶ የሆነ ምክንያት ሰጥቷቸው ወደ ሽማግሌው ተመለሰ፡፡
ከዚያም ሽማግሌው እጁን ያዝ አደረጉት :: ብሩክ ልቡ በኃይል መታ፡፡
“ምን ሊነግሩኝ ይሆን?” በሚል ጭንቀት ተዋጠ፡፡
ደግነቱ መርዶ በምሽት አይነገርም፡፡
“የውልህ ሻለቃ” አሉና የሆነውን፣ የተፈጠረውን ተአምር ይተርኩለት ጀመር።
የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ፣ ሞቷል ተብሎ ተዝካሩ የተበላለት ሰው በህይወት መግባቱን፣ አሁንም ከድሮው ቤቱ የባለቤቱን መርዶ ተረድቶ መቀመጡን፡ እድርተኛው በሙሉ እንዲሰማ መደረጉን ፡
በሹክሹክታ ሲነግሩት፤ ሻለቃ ብሩክ በህልም ዓለም ያለ ዓይነት ስሜት
ተሰምቶት፤ በአድናቆትና በድንጋጤ ተውጦ አፉ እንደተከፈተ ቀረ፡፡
ተአምር! እውነትም ትንግርት! ይህን ምን ይሉታል?!
ከዚያም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከሽማግሌው ጋር በእርጋታ ተመካከሩ፡፡ በመጨረሻም ሲነጋ በሌሊቱ ሁለቱን ልጆቹን ወደ ድሮ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከአባታቸው ጋር ለማገናኘት በፈጠሩት ምክንያት ተስማምተው ተሰነባበቱ፡፡ ሻለቃ ብሩክ ከሽማግሌው ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረት
በጠዋቱ ትህትና ከሁለቱ ልጆቿ ጋር አንዱዓለምንም እንደዚሁ ልብሳቸውን እንዲለባብሱ አደረገ፡፡
“አባባ ብራቱ ጠበል እንድንቀምስላቸው በጠዋት ድረሱ ስለአሉን
እንዳይቀየሙን ቶሎ ቶሎ ልበሱ” በማለት አጣድፎ አለባበሳቸውና፤ይዟቸው በታክሲ ወደ ድሮ ሠፈራቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡ አባባ ብራቱ ደግሞ በቀጠሮአቸው መሰረት ቤታቸው ሆነው መምጫቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ እንዳልሆነ ሻለቃ በሚገባ አውቆታል፡፡ ዛሬ
ሞቷል ተብሎ የተለቀሰለት አባታቸው አፈሩን አራግፎ የመጣበት ቀን ነው፡፡ አፈር ለብሳ፤ አፈር ሆና፤ የቀረችው እናታቸው ግን ዳግም ላትነሳ ነው የሄደችው፡፡ ሶስቱ ሲገናኙ በዚያን በሚያስገርም ወደር በሌለው
ደሰታቸው መካከል፤ የተለየቻቸው የእናታቸው ናፍቆት እንደ አዲስ
ተቀስቅሶ፤ በእንባ እንደሚራጩላት አውቋል፡፡
ከልክ በላይ ሲሆን፤ ከሀዘን
ደስታም የበለጠ በእንባ ያንፈቀፍቃል። በተለይ ደግሞ እንደ መቶ አለቃ ድንበሩ ያለ የሚወደድ፤ የሚናፈቅ ፤አባት ሞትን አሽንፎ ሲመጣ ድንጋጤው ብቻ በሽታ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው፡፡ዛሬ ትንሳኤና መርዶ እዚያች ግቢ ውስጥ መንገሳቸው የማይቀር ነው፡፡ ሻለቃ ብሩክ ካሜራውን አዘጋጅቶ ይዟል፡፡ ትህትና እና ወንድሟ
የሚሄዱት ወደ ድግስ እንጂ ወደ አባታቸው ዘንድ መሆኑን እንዴት
ጠርጥረውት? የሞተ ሰው ከመቃብር ተነስቶ አቀባበል ሊያደርግላቸው
እየተጠባበቃቸው መሆኑን እንዴት ገምተውት? ጭቃ እያቦኩ፤ ውሃ
እየተራጩ ባደጉባት፡ በፍቅርና በመተሳሰብ የደስታ ጊአዜአቸውን
ባሳለፉባት፤ አልቅሰው የእናታቸውን ተዝካር ባወጡባት፤ በዚያች የድሮ
ቤታቸው ውስጥ በአካል ተገኝቶ በናፍቆት

👍1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....“ልክ ነህ” ጉድማን ፈገግ ካለ በኋላ እኛ በሁለት የሰዎች ግድያዎች ላይ
ምርመራችንን የምናደርግ ፖሊሶች ስለሆንን አሁንም ስራችንን በመስራት
ላይ እንገኛለን፡፡ አንተ ልትሰራው ፈልገህ አለቆቻችን ሊቀጥሩህ ያልቻሉትን
የምትቋምጥለትን ስራ የምንሰራ... ስንት ጊዜ ነበር በፖሊስነት አመልክተህ
ያልተሳካልህ? አታስታውስ አንተ ደግሞ... ምን ነበር ቃሉ?” ብሎ ጉድ ማን ጣቶቹን እያጮኸ ቆየና አዎን ድንኳን ሰባሪ ነህ እርግጠኛ ነኝ የተጋበዝክበትን ደብዳቤ ወይም ካርድ ልታሳየኝ አትችልም” አለው፡፡
ዊልያምስ ከንፈሩን ነክሶ ቢችል በቦክስ ጥርሱን ቢያረግፈው እና የሚሞጣሞጥበትን አፉን ደም በደም ቢያደርገው ደስ ባለው፡፡ ዊልያምስም
“ውጪ እንውጣ እና የማሳይህ ነገር አለኝ ልጁ” አለው፡፡
ጉድማንም ቅንድቡን በግርምት እያነሳ “እየቀለድክ ባልሆነ?” አለው፡፡
ይመስልሃል?” ብሎ ዊልያምስ በብሽቀት ከመለሰላት በኋላ “ከኒኪ ጋር ያለህ
ነገር እንዴት እየሄደልህ ነው? እስከአሁን እንዳልተኛችህ ነው የነገረችኝ ይሄ
ደግሞ ያማል አይደል? ከፍለሃት ካልሆነ በስተቀር አንተ ለመጨረሻ ጊዜ
ከሴት ጋር የተኛኸው መቼ ነበር?” ጉድ ማን እያሾፈ “እኔ እንዳንተ አይደለሁም ስለዚህ በአእምሮዬ ነው የማስበው” አለው፡፡ ዊልያምስ “እኔ ከኒኪ ጋር ወሲብ አልፈልግም፡፡ እኔ እሷን ልረዳት እየሞከርኩ ነው፡፡ለዚያም መሰለኝ እኔን አምና ለአንተ እና ለዚያ አጋስስ አጋርህ በህልምዋም ቢሆን እንኳ ልታካፍላችሁ የማትፈልገውን ሚስጥሮቿን ለኔ የምትነግረኝ” አለው፡፡ በጆንሰን አቅጣጫ በአፍንጫው እየጠቆመው በነገር ሲወጋው የጉድ ማን ፊት በንዴት ሲቀላ ተመለከተና የደስታ ስሜት ተሰማው፡፡ ጉድ ማን በቁጣ እንዳበጠ ዊልያምስን “ሳልጠፈንግህ በፊት ከዚህ ጉዳይ ውጣ!” አለና አንባረቀበት፡፡
ዊልያምስም “ለምንድን ነው የምታስረኝ?” ብሎ ጠየቀውና ለወደፊቱ
ሌሎች ከጉድ ማን ጋር የሚጠብቁት ጸቦች እንዳሉ ሲገባው የአሁኑን ጸብ
መተው እንዳለበት ራሱን አሳምኖ “ሌላ ጊዜ አገኝሃለሁ” አለው፡፡
እኔ ነኝ ቀድሜ የማገኝህ” ብሎ ጉድማን መለሰለት፡፡ ዊልያምስ ኮቱን አንስቶ እየተንጀባረረ ከአዳራሹ ወጣ፡፡ ዊልያምስ ከአዳራሽ እንደወጣም የአኔ ቤታማን ቫዮሊን የመጀመሪያው ሶሎ ሙዚቃ መሰማት ጀመረ፡፡
ወንበሯ ላይ ደገፍ ብላ የነበረችው ኒኪም አኔ ቫዬሊኗን ለስለስ አድርጋ ቁጭ ብላ እና አይኗን ጨፍና ቫዬሊን መምቻዋን ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መጫወት ስትጀምር አዳራሹ ጸጥ አለ፡፡ አኔ መድረኩ ላይ አንድ ወንበር ላይ እየሰበቀች መጫወቷን ቀጠለች፡፡ ሙዚቃው የታላቁ እንግሊዛዊ ሙዚቃ አዘጋጁ የቫውጋን ዊልያምስ ሲሆን ይህንን ሙዚቃ ደግሞ ባለቤትዋ ዶውግ በጣም የሚወደው ሙዚቃ ነበር፡፡ ይህንን ሙዚቃ ለቁጥር ለሚያታክት
ጊዜያት ያህል እሁድ እሁድ የቁርሳቸውን ፓን ኬክ እየሰሩ በመኪና ረጅም
ጉዞን ሲጓዙ እና የጫጉላ ጊዜያቸውን ከአልጋቸው ሳይወጡ ፍቅር እየሰሩ
በሚያሳልፉባቸው ጊዜያቶች ሁሉ አብረው ያዳምጡት ነበር፡፡
በድንገት የናፍቆት እና የሃዘን ስሜት የሞላው ሰውነቷን ወረራት::በሚያሳፍር ሁኔታም ድምጽ አውጥታ
እየተንቀሳቀሰችና እየተርገፈገፈች ጠረጴዛው ላይ ክንዷን ዘርግታ ጭንቅላቷን አንተራሰችበት::
“ሰላም አይደለሽም ውዴ?” ብሎ አጠገቧ የሚገኘው ኒሮሳይንቲስት
የሚንቀጠቀጠው እጁን ትከሻዋ ላይ አኑሮ “ ውጪ ወጥተሽ ትንሽ አየር
ትወስጂ?” አላት፡፡
ኒኪም ራሷን በአሉታ በመነቅነቅ ምንም እንደማትፈልግና ጉዳይዋ በእምባ የተሸፈነ እንደሆነ አሳወቀችው፡፡ በቅርብ ወራቶች ውስጥ በዙሪያዋ ባሉ ሰዎች ላይ በደረሱት አሰቃቂ ነገሮች የተነሳ የዶውግን ሃዘን ዘንግታው ነበር፡፡ አሁን ግን ዕድሜ ለአኔ ምርጥ የቫዩሊን ሙዚቃ! ውስጧ ታምቆ የነበረው የሃዘን ስሜት ቁልፍ ተከፈተ፡፡ አሁን ወደ ኋላ መመለስ የለም፡፡ እየተንዠቀዠቀ የሚፈስሰው እምባዋን ማቆም አትችልም፡፡ የሚርገፈገፍ ትከሻዋንና መላው ሰውነቷን በስልቱ እያስኬደች ለሁለት የሚሰነጥቃትን ሃዘን እና መከፋትን እንዲሁ እንደ ቀልድ ማቆም አትችልም፡፡
“ፕሮፌሰር ጀምሰን አትቸገር” የሚለው የሀዶን ዶፎ ጥልቀትና ስሜታዊ
ድምፅ በጆሮዋ ያንቃጭልባታል “እኔ እረጋጋለሁ” ሲል ይሰማታል፡፡
ኒኪ የሀዶንን እርዳታም ቢሆን አትፈልግም ነበር፤ ነገር ግን እምቢታዋን
እንደ ፕሮፌሰሩ ሳይቀበል ቀርቶ ክንዷን ይዞ አነሳትና እያለቀሰች ለእሳት
አደጋ መውጫ በተዘጋጀው በር በኩል ይዟት ከአዳራሹ ወጣ፡፡ ከአዳራሹ
ጀርባ በሚገኝ መናፈሻ ውስጥም ይዟት ገባ፡፡ እናም በትንሹ ከሚንፎለፎል
ፏፏቴ አጠገብ ከሚገኝ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብላ የአይኗ ሜክአፕ እስከሚበላሽ
ድረስ አምርራ ታለቅስ ጀመር፡፡ ሳጓ እና የትከሻዋ መርገፍገፍ እየቀነሰ መጣ
እና በመጨረሻ ላይ “እፎይ” ብላ ፀጥ አለች፡፡
“ምን ሆነሽ ነው?” ብሎ ሀዶን አጠገቧ እየተቀመጠ ጠየቃት። ፀጉሯን
ከፊቷ ላይ አንስቶ ከኪሱ የራሱን መሃረብ አውጥቶ አቀበላት፡፡
እኔ እንጃ ብላ ኒኪ መሃረቡን ተቀብላ ፊቷንና አፍንጫዋን ካፀዳች በኋላ
“ሙዚቃው መሰለኝ በቃ ስለ ዶውግ እንዳስብ አደረገኝ፡፡ በጣም ከፋኝ ሀዶን
ዶውግ እኮ ላይመለስ ነው የሄደው፡፡ ይህንን ደግሞ ልቋቋመው አልቻልኩም”
አለችው::
ሀዶንም በክንዱ እቅፍ አደረጋት እና ወደ ራሱ እያስጠጋት “ምስኪን የኔ ቆንጆ” አላት፡፡
በጣም የደከማት ኒኪም ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች፡፡ ታላቅ ወንድም ባይኖራትም ሀዶንን የምታየው እንደዚያ ነው፡፡
ሀዶንም በጆሮዋ “አንቺ እኮ ለእሱ አትገቢውም ኒኪ፡፡ በእውነት እሱ
ላንቺ የሚገባ ሰው አልነበረም” ብሎ ማንሾካሾክ ጀመረ፡፡ ድምፁ ምቾት
የሚሰጥ ስለነበረ እና ጭንቅላቷም ይዞርባት ስለነበረ የተናገረውን ነገር
በደንብ አልተረዳችውም፡፡
ነገር ግን ቀሚሷን ወደ ላይ ሰብስቦ እጁን ከጭኖቿ መሀል ለመክተት በሚያቃጥሉት ስግብግብ ጣቶቹ ወደ ላይ መሰርሰር ሲጀምር ባነነች፡፡
“ሀዶን” ብላ ልትገፋው ብትሞክርም ጥብቅ አድርጎ ስለያዛት አልቻለችም፡፡ “ምን እያደረግክ ነው አንተ?” “ከአመታት በፊት ማድረግ የሚገባኝን ነገር ነዋ” ብሎ እያጉረመረመ በስሜት ባበደ ድምፅም እያቃተተ አትታገይኝ ኒኪ ይህን ነገር ትፈልጊዋለሽ፡፡ ሁለታችንም እንፈልገዋለን፡፡ከበፊት ጀምሮ በጣም ነበር የማፈቅርሽ...”
“ሀዶን አይሆንም ተው” ብላ በድንጋጤ በረዶ ሆነችበት። ሀዶንም ወደ ፊት ቀርቦ ከንፈሯን በከንፈሩ ግጥም አድርጎ እየተስገበገበ ይስማት ጀመር፡፡”
“አይሆንም” ብላ እየታገለችውም እንዳለ “እዚህ ችግር አለ!” የሚለው
የመርማሪ ፖሊስ ጉድማን ድምፅ ጨለማውን ሲስነጥቀው ሀዶን ዶፎ ዘልሎ ከላይዋ ላይ ተነሳ፡፡ ኒኪም ቀና ብላ ጉድማንን በእፎይታ ስሜት
ተመለከተችው:: ያኔ ከጥቁሩ ላንድክሩዘር መኪና ያዳናትን የቀዩ ስፖርት መኪና አሽክርካሪን ስታገኝ የተሰማት አይነት የእፎይታ ስሜት ነበር አሁንም
የተሰማት፡፡
“ሁሉም ነገር ሰላም ነው” ብላ ኒኪ ፀጉሯን እና ቀሚሷን እያስተካከለች
ተነሳች፡፡ በሀዶን ድንገተኛ ድርጊት ከተሰማት ድንጋጤ ውስጥ ሳትወጣም
ሀዶንን አየችው፡፡ እኔ እንደምፈልገው ያምናል ማለት ነው? እንደዚያ ነው
ኣይደል ያለኝ? ይህንን ነገር ትፈልጊዋለሽ ሁለታችንም እንፈልገዋለን ነው አይደል፡፡ እንዴ ሀሳቡ እራሱ ይዘገንናል እኮ! ሀዶን የዶውግ የልብ ጓደኛ የነበረ ሰው ነው እኮ ነው ኦ!' እያለች በውስጧ አሰበች፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ሀዶን ኒኪን የእውነት ይወዳት ከነበረ በዶውግ የተካደ እና የተታለለ ስለ

👍4
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የጨሻው መጀመርያ
“ምን እንደነገረቻቸው ገምቺ…” ክሪስ ቀጠለ “ክፍሉ በወሩ መጨረሻ
በሚመጣው አርብ እንዳይፀዳ የፈለገችበትን ምክንያት ገምቺ።
“እንዴት መገመት እችላለሁ? እኔ የእሷ አይነት አእምሮ የለኝም:" ጭንቅላቴን ነቀነቅኩ። ሠራተኞቹ ወደዚህ መምጣት ካቆሙ ብዙ ጊዜያቸው ነው እነዚያን
አስፈሪ የመጀመሪያ ሳምንታት ረስቻቸው ነበር፡
“አይጦች ካቲ...” አለ ክሪስ ሰማያዊ አይኖቹ ቀዝቃዛና ጠንካራ ሆነዋል
“አይጦች አያትየው የፈጠረቻቸው ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶ የሚቆጠሩ አይጦች ከሁለተኛ ፎቅ በደረጃ ወደታች የሚወርዱ
ትናንሽ ብልጥ አይጦች፣ አርሰኒክ የተደረገበት ምግብ ትታላቸው በሩን
ቆልፋባቸው ልትሄድ የምትገደድባቸው ትንንሽ ጨካኝ አይጦች”
ሠራተኞቹ እዚህ አካባቢ እንዳይደርሱ ግሩምና ድንቅ ታሪክ እንደሆነ አሰብኩ ጣራው ስር ያለው ክፍል በአይጥ ተሞልቷል። አይጦቹ በደረጃውም
ይወርዳሉ።
“አርስኒክ ነጭ ነው ካቲ፣ ከተፈጨ ስኳር ጋር ሲቀላቀል ምሬቱ አያስታውቅም
ጭንቅላቴ ተሽከረከረ! በየቀኑ በሚመጣልን አራት ዶናት ላይ ያለው የተፈጨ
ስኳር! ለእያንዳንዳችን አንድ አንድ: አሁን ግን ቅርጫቱ ውስጥ ሶስት ብቻ ነው: “ግን ክሪስ ታሪክህ ምንም ስሜት አይሰጥም አያትየው በአንድ ጊዜ ብዙ መርዝ ሰጥታ ልትገድለን ስትችል ለምን ቀስ በቀስ ትመርዘናለች? ለምን
በአንዴ አትገላግለንም?”
ጭንቅላቴ በመዳፎቹ መሀከል ሆኖ በረጃጅም ጣቶቹ ፀጉሬን እየዳበሰኝ ነበር።ቀስ ባለ ድምፅ ተናገረ “በቲቪ ያየነው የሆነ ያረጀ ፊልም አስታውሺ
አስታውሺ ለሽማግሌው ለሀብታሙ ሰውዬ ቤት የምትጠብቅለትን ያቺን ትንሽ ሴት ካመኗት፣ ከወደዷትና ኑዛዜያቸው ውስጥ ካስገቧት በኋላ
በየቀኑ ትንሽ ትንሽ አርሰኒክ ትመግባቸው አልነበር? በየቀኑ ትንሽ ትንሽ
አርሰኒክ ሲወሰድ ቀስ በቀስ ወደ ሰውነታችን ይሰርግና በየቀኑ ተጠቂው ትንሽ ትንሽ እያመመው ይመጣል፤ በጣም ብዙ ግን አይታመምም ትንንሽ
የራስ ምታቶች የአንጀት መቆጣት እና የመሳሰሉት በቀላሉ መገለፅ የሚችሉ
ህመሞች ያጋጥሙታል ተጠቂው ሲሞት፣ ለምሳሌ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን
መጀመሪያውኑ ከስቶ፣ ደም ማነስ ይዞትና ረጅም የህመም ታሪክ፣ የጉንፋን
አይነት ትኩሳት፣ ብርድና የመሳሰሉት ይታዩበታል እና ተጠቂው የሳምባ ምች ምልክቶችን ሁሉ ቢያሳይም ልክ እዛ ፊልም ላይ እንዳየነው ዶክተሮቹ
መመረዝ መሆኑን አይጠራጠሩም:”
ኮሪ!” ትንፋሽ አጠረኝ: “ኮሪ የሞተው በአርሰኒክ ተመርዞ ነው? እናታችን የገደለው የሳምባ ምች ነው ብላን ነበር”
“የምትፈልገውን ልትነግረን አትችልም? እውነቱ መናገሯን በምን
እናውቃለን? ምናልባት ሆስፒታል ወስዳውም ላይሆን ይችላል። ወስዳውም ከሆነ ዶክተሮቹ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ሞት መሆኑን አልጠረጠሩም ማለት ነው። እንደዛ ባይሆን ኖሮ አሁን እስር ቤት ትሆን ነበር”
“ግን ክሪስ” ተቃወምኩ። “እናታችን አያትየው መርዝ እንድታበላን አትፈቅድም! ያንን ገንዘብ እንደምትፈልገው አውቃለሁ፤ በፊት የምትወደንን ያህል እንደማትወደንም ይገባኛል፤ ግን አሁንም ልትገለን አትፈልግም”
ክሪስ ጭንቅላቱን ወደጎን ዘምበል አደረገ፡ “እሺ አንድ ሙከራ እናድርግ፤ ለኮሪ ጓደኛ አይጥ ትንሽ የተፈጨ ስኳር ያለበት ዶናት እንስጠው”
“አይሆንም! በሚወደንና በሚያምነን ላይ እንደዚህ ማድረግ አንችልም ኮሪ
ያንን ግራጫ አይጥ ይወደው ነበር። ክሪስ፣ ሌላ አይጥ እንይዛለን” ካቲ አይጡ አርጅቷል፡ በዚያ ላይ እግሩ ሽባ ነው፡፡ አይጥን ከነህይወቱ መያዝ ደግሞ ከባድ እንደሆነ ታውቂያለሽ፡ ከዚህ ስንሄድ ነፃ ስንለቀው አሁን የቤት እንስሳ ስለሆነ መኖር አይችልም በእኛ ላይ ጥገኛ ሆኗል።"
ከእኛ ጋር ይዘነው እንድንሄድ አስቤ ነበር
“በዚህ መንገድ ተመልከቺው ካቲ። ኮሪ ሞቷል፣ ገና መኖር እንኳን አልጀመረም ነበር። ዶናቶቹ መርዝ ከሌለባቸው አይጡ በህይወት ይቆያል፡ ከዚያ ይዘነው መሄድ እንችላለን፡ የግድ ካልሽ ማለቴ ነው: አንድ ነገር እርግጥ ነው፣ማወቅ አለብን፡ ለኬሪ ስንል እርግጠኛ መሆን አለብን: ተመልከቻት፡ እሷም
"እየሞተች እንደሆነ አይታይሽም? ከቀን ቀን ጤና እያጣች ነው። እኛም እንደዚያው
ተጠግቶ እኛን፣ ያ ትንሽ ፍጥረት በሶስቱ ጤናማ እግሮቹ እያነከስ ወደ እኛ መጣ። ወደ ክሪስ ጣቶች ተጠግቶ እኛን፣ ጌቶቹን፣ ወላጆቹን፣ ጓደኞቹን አምኖ ቁንጥር አድርጎ በላ፡፡ ያንን ማየቱ ራሱ ያሳምማል።
አልሞተም! ወዲያውኑ አልሞተም፡ ቀርፋፋ፣ ፈዛዛ፣ ፍላጎት ያጣ ሆነ። በኋላ እንዲያቃስት ያደረገው ትንሽ ህመም ተሰማው፡ በጥቂት ስዓታት ውስጥ ድርቅ ብሎና ቀዝቅዞ በጀርባው ተጋደመ: ሮዝ ጣቶቹ ተቆለመሙ፤ ትናንሽ ጥቁር አይኖቹ ጎደጎዱ። አሁን አወቅን... በእርግጠኝነት ኮሪን የወሰደው
እግዚአብሔር አይደለም!
“አይጡንና የቀሩትን ሁለት ዶናቶች በኪስ ወረቀት ውስጥ አድርገን ወደ
ፖሊስ እንወስደዋለን" አለ ክሪስ በሚያስተማምን አይነት አይኖቹን ከእኔ ዞር እያደረገ፡“አያትየውን እስር ቤት ያስገቧታል” አልኩት
“አዎ” አለና ጀርባውን አዞረ:
“ክሪስ፣ የሆነ ነገር ደብቀኸኛል፡ ምንድነው?”
“በኋላ... ከሄድን በኋላ፡ አሁን ማለት የምችለውን ሁሉ ሳያስመልሰኝ
ተናግሬያለሁ። ነገ በማለዳ ከዚህ እንሄዳለን፡” አለ ምንም አልተናገርኩም እጆቼን በሁለት እጆቹ ይዞ ጭምቅ አደረጋቸውና “በተቻለ ፍጥነት ኬሪን ወደ
ዶክተር መውሰድ አለብን ራሳችንንም ጭምር” አለ ቀኑ በጣም ረጅም ሆነብን፡ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተን ስለጨረስን ለመጨረሻ ጊዜ ቲቪው ላይ ከማፍጠጥ በስተቀር ምንም የምንሰራው አልነበረንም ኬሪ
ጥጉ ላይ እንደተቀመጠች ሁለታችን ደግሞ በተለያየ አልጋ ላይ ጋደም ብለን የምንወደውን ተከታታይ የቴሌቭዥን ፊልም እያየን ነው: ሲያልቅ ክሪስ እዚህ ፊልም ውስጥ ያሉት ሰዎች ልክ እንደኛ ናቸው: እምብዛም ወደ ውጪ
አይወጡም ሊወጡም መውጣታቸውን እንሰማለን እንጂ አናይም ሳሎንና መኝታ ቤት ውስጥ ሲንጎራደዱ፣ ወጥ ቤት ቁጭ ብለው ቡና ሲጠጡ ወይም
ቆመው ብራንዲያቸውን ሲጠጡ ነው የምናያቸው: ግን በፍፁም ውጪ ወጥተው አይተናቸው አናውቅም፡ የሆነ ጥሩ ነገር ተፈጥሮ በመጨረሻ ደስተኛ እንደሚሆን ባሰቡ ቁጥር የሆነ መቅሰፍት ይመጣና ተስፋቸውን ሁሉ ያጠፋዋል” አልኩት ድንገት የሆነ ሰው ክፍሉ ውስጥ እንዳለ ተሰማኝ፡ ትንፋሽ አጥሮኝ ዞር ስል
አያትየው ቆማለች: አቋቋሟና ከጨካኝና ንቀት የሚያሳዩ አይኖቿ ለሆነ ጊዜ ያህል እዚያው እንደነበረች ነገሩኝ።
በቀዝቃዛው ድምጽዋ ተናገረች “ከአለም ተነጥላችሁም እያላችሁ ሁለታችሁም እንዴት ሰልጥናችኋል! ህይወት እንዴት እንደሆነ በቀልድ መልክ እያጋነናችሁ ነበር በትክክል ነው የገመታችሁት ምንም ነገር እናንተ በምታስቡት መንገድ
አይሰራም: በመጨረሻ ሁልጊዜም ታዝናላችሁ” አለች:
እኔና ክሪስ አተኩረን ተመለከትናት: ሁለታችንም ፈርተናል። ፀሀዩዋ
አፍንጫዋን ወደ ምሽቱ ውስጥ እየደበቀች ነው:: የምትፈልገውን ተናግራለች: ስለዚህ ወጣችና በሩን ቆለፈች: አልጋዎቻችን ላይ ተቀመጥን፡ ኬሪም ጥጉ
ላይ ተቀምጣለች።
ካቲ፣ የተሸነፍሽ አትምሰይ! እንደገና ተስፋ ልታስቆርጠን እየሞከረች ብቻ
ነው። ምናልባት ምንም ነገር በትክክል አልሄደላት ይሆናል። ያ ማለት ግን እኛ እንሞታለን ማለት አይደለም ምንም ፍፁም የሆነ ነገር እናገኛለን ብለን ሳንጠብቅ እንሂድ። ትንሽ ደስታ እንደሚኖረን ብቻ እንጠብቅ። ተስፋ አንቆርጥም:”

👍47🥰5👏1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
አንድ ቀን ጀንበሯ ለመጥለቅ በምትሽለቆለቅበት አመሻሽ ላይ ሚስተርና ሚስዝ ሔር ከባርባራ ጋር ምግብ ላይ እንደ ተቀመጡ አባትየው እየተሳደበ ያስለቅሳታል ።
እናቲቱ ደግሞ ምንም እንኳን በልቧ ለባርባራ ብታደላም ጀስቲን ሔር
ባርባራን ከቤት ዘግተን እናቃጥላት ቢላትም መቃወም የሚባል ስለማይቃጣት አሁንም ከባሏ ሐሳብ ጋር ተስማምታና ተደርባ አብራ ትቆጣት ነበር "
ባርባራ ጥሩ እጮኛ እየመጣላት እምቢ ብላ በመመለስ አባቷን ደጋግማ አስቀይማዋለች » እሱ ደግሞ ለምን እንዲህ ይደረጋል ብሎ እብድ ይሆንባታል " ሴቶች
ልጆቹ ሳይዳሩ ጠውልገውና መንምነው ቢያረጁ ወይም ተድረውና ተኩለው የቤት
እመቤቶች ቢሆኑ ለሚስተር ጀስቲስ ሔር ስሜት አይሰጠውም " እንዲያውም "ባርባራ ከቤት በመኖሯ ልትከብደው ቀርቶ ከነጭራሹም እንድትርቀው አይፈልግም ነበር " የሀብት ፍላጎትም አይደለም " ባርባራ ብታገባም ባታግባም የሚበቃ ሀብት
አላት " ባርባራ ለጋብቻ ስትጠየቅ ባለ መቀበሏ አባቷ የሚቆጣት ምክንያት
እነዚህን ከመሰሉ ተራ ነገሮች የተለየ ነበር
የዊስትሊን ሰው በማያገባው ነገር ሁሉ በየሰዉ የግል ሕይወትና ኑሮ እየገባ አሉባልታ ሳያናፍስ መኖር አይሆንለትም ባርባራ ሔር አግብታ በባሏ ስም ሚስዝ
እገሌ መባል ሲገባት ስሟን ሳትለውጥ ባርባራ ሔር ሁና በመቅረቷ ሁሉም በይፋ
ስሟን አነሣው በውበቷ በመልካሙ ጠባይዋና በሀብቷ ከሆነ ካገሩ ቆነጃጅት ሁሉ የሚወዳዶራት አልነበረም እሷ ሳትያዝ ሌላ ልጃገረድ ትታጫለች ብሎ ለማመን
የሚያስቸግር ይመስል ነበር " ነገር ግን እስከ ዛሬ ይኸው ባርባራ ሔር እንደሆነች አለች » አሁን አሉባልተኞች ምክንያቱን ለማወቅ አንገት ላንገት ገጥመው ሲያቶኮትኩ በመጨረሻ ቆማ የቀረችበት ብቸኛው ምክንያት ወንድሟ የፈጸመሡ አሳዛኝ ወንጀል ነው እየተባለ ተወራ " ይህ አጉል መሬ በተወራበት አልቀረም ሲል ሲል
ጀስቲስ ሔር ጆሮ ዶረሰ ጀስቲስ ሔር ደግሞ ምርር ብሎ የሚጠላው ነገር ቢኖር ያን ጥቁር ነጥብ የተወበት አሲቃቂ ድርጊት ነው እሱ የሚጠላው ያው ፍጡር አለ ከተባለ ደግሞ ያን ዕድለ ቢሱ ልጁን ነው " ባርባራ ጠያቂ አጥታ የቀሪችው በወንድሟ ወንጀል ነው የሚለው ወሬ ለጀስቲስ ሔር እንዶ ሐሞት መሪሪው መንፈሱን እንደ
ቅንቅን ቦረቦረው » ከብሽቀቱ የተነሣ በቅርብ ከሚገኘው ኩሬ አሽቀንጥሮ ቢጥለው ወይም ሪቻርድን አግቶ አንገቱን አንቆ ለፍርድ ቢያቀርበው ወይም የሚነፍሰወን አሎባልታ ለማስቀረት ባርባራን ወዲያው ድሮ ቢያርፍ ደስታውን አይችለውም ነበር " አሷ ግን የሚመጡላትን ባሎች ሁሉ በእምቢታ ስትመልስ አራተኛ ጊዜዋ ስለሆነ አባቷን በጣም አበሳጨችው
“ አንቺ እኮ ይህን የምታደርጊው ሆን ብለሽ 'እኔን ለማበሳጨት ነው ” ብሎ እንደ መብረቅ ጮኸባትና ጠረጴዛወን በቡጢ ሲመታው ፍንጃሎቹ ተንቀቀጫቀጩ
“ ኧረ አይዶለም ... አባባ ” አለችው ባርባራ እየተንሰቀሰቀች
ታዲያ ለምን እንደዚህ አደረግሽ ?
ባርባራ ዝም አለች።
“ድሮውንስ ምን ልትይ ኖሯል የምታቀርቢው ምክንያት የለሽማ ! እስኪ አሁን
ለሻለቃ ቶርን ምን ሊወጣለት ነው ? በይ እስቲ ተናገሪ "
“ አልወደውም
ብላ ተንተባተበች »
“ እሱን ተይው ! ትወጅዋለሽ « እዚህ በመጣ ቁጥር ትወጂው ነበር " ለምን
" እንደ ማንም ዕውቂያ እንጂ ለባልነት አልወደውም
“ ለባልነት አልወደውም ?
ወይ አንተ ! ግድ የላችሁም ልጅቱ ማበዷ ነው" አሁንስ ቢሆን ገና ሳታግቢው ማን ውደጅው ብሎ ጠየቀሽ?እስኪ ማን ይሙት
አንዲት ልጃገረድ ባሏ የሚሆነውን ሰው ሳታገባ መውደድ አለባት ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ ? ”
"ባርባራ ግራ ገባት "
ይኸውና አገር ምድሩ ማግባት አትችልም በዚያ እርጉም ስሙን እኮ
ስጠራው ዘገነነኝ ወንጀል የተነሣ ማንም አይፈልጋትም እያለ ያወራል " ታዲያ ይኸ ራሱ ከባድ ውርደት አይደለም ? ''
“ ግን እኮ ውሸት ነው ፤ ሰዎች ይጠይቁኛል ”
“ ታዲያ አንቺ እምቢ እያልሽ ከመለስሻቸው ምን ያደርጋል ? ሰዎች እንደ
ጠይቁሽ የምታሳውቂው እንዲህ በመናገር ነው ? አንቺ እኮ የሚነገርሺን የማትሰሚ እንደ ልቧ አዳሪ ዐመፀኛ ነሽ " ደግሞ እንደዚህ ሆነሽ መቅረትሽን
ዕወቂው "
የባርባራ እንባ እንደ ውሃ ወረደ" ጀስቲስ ሔር የሻይ ዕቃውን ከጠረጴዛው
እንዲያነሡት ጠርቶ ለማዘዝ የደወሉን እጅታ በቡጢ መታው" ዕቃዎቹ ከተነሡ
በኋላ ነገሩ እንደገና ተቀሰቀሰ " የባርባራ ለቅሶም ባሰ " የጀስቲስ ሔር አንዱ መጥፎ ጠባዩ ይኸው ነበር " ደግነቱ ሁልጊዜ ከልቡ አይበሳጭም እንጂ አንድ ጊዜ ባንድ ነገር ቅሬታ ከተሰማው ንዝንዙ ማቆሚያ የለውም » በባርባራ ላይ የቁጣውን መዓት ሲያወርድበት ሚስተር ካርላይል ገባ "
ያለፉት ኻያ አንድ ወሮች በግራና ቀኝ የራስ ጸጉሩን ላይ ሽበት ጣል ጣል
እንዲልበት ከማድረጋቸው በቀር እምብዛም ለውጥ አላደረሱበትም ባርባራ
ልትወጣ ተነሣች
አትሔጅም '' አለ ጀስቲስ ሔር በሷና በመዝጊያው መኻል ተገድግዶ።“እኔ
በቁም ነገር እያነጋገርኩሽ አንቺ ጥለሽኝ ተነሻለሽ " መሔድ የለም " ቁጭ በይ"
ድንገት ጥቂት ብታፍሪ ጉድሽን ሁሉ ከሚስተር ካርላይል ፊት ነው የምነግርሽ "
ባርባራ ተመልሳ ተቀመጠኛ " ሚስተር ካርላይል ምን እንዳገኛት ለማወቅ
እየፈለገ ተቀመጠ "
" በኛ ላይ የወረደውን አስደንጋጭ መከራ አሳፋሪ ውርደት አንተ ታውቃለህ
ሚስተር ካርላይል " ሕዝቡ ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ የሚያወራው ቢያጣ ወደ ባርባራ ዞረና አንድም ባል ልሁን ብሎ የሚጠይቃት ያጣችው ወንድሟ የፈጠረው ኃፍረትና ውርደት በሷም ስለ አንጸባረቀ ነው " እያለ ማውራት ጀመረልህ " ይህን እየሰማች ይህን መጥፎ ስም ይዛ ለአሎባልተኞች ወሬ ተመቻችታ ተቀመጠች
የቤተክርስቲያን ተላላኪም ቢሆን ማግባት አለባት በሚባልበት ጊዜ እንዴት እንዴት ያሉ ዶኅና ደኅና ሰዎች ሊቀርቡ አሻፈረኝ እያለች መለሰቻቸው " አሁን ዛሬም ከሻለቃ ቶርን የቀረበላትን ጥያቄ እናት አባቴ ያውቃሉ ማለት ሲገባት እኛን ሳታማክር በሥልጣኗ እምቢ” ብላ መለሰችሙ » አሁን እስቲ
ምን ይባላል ? አንተስ ምን ትላለህ? ”
«ምናልባት የቤት እመቤትነት ላባርባራ ደስ ይላት ይሆናል ” አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሣቅ ብሎ "
“ እሷ መጀሪያ ምን ደስ የሚላት አለና ? ነግሯ ሁሎ የተግላቢጦሽ ነው ኧረ
የሆነስ ሆነና ” አለ ጀስቲስ ሔር አንድ ሐሳብ በአእምሮው ብልጭ ስላለበት ይዞት የነበረውን ጭቅጭቅ ተወት በማድረግ “ትናንት በክስ ሔድ ሁኜ ስምህን ከጋብቻ ጋር ሲያግናኙት ሰማሁ አለው ወደ ሰርጀን ዶቢድ የምትመላለሰው ለልጃቸው
ሚስ ዶባድን ስትል ነው ይላሉ „ ”
“ በክስ ሔድ በዚህ ሲሥቅ አምሽቷላ? በርግጥ ግን ሚስ ዶቢድ ስለምታገባ
የውል ሰነድ እያረቀቅሁ ነው
"የለም የለም እሷንስ ሰመርሴትን እንደምታገባ ሁሉ ዐውቆታል " ሌላይቱን ነው እንጂ ሎዊዛ ነው የምልህ መቸም ቆንጆ ልጅ ናት... ካርላይል ...
“ በጣም ” አለና ሚስተር ካርላይል ዝም አለ ጃስቲስ ሔር ከቤት መቀመጥ

👍14👏1
#ታምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን ጠባብ የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው… መላኩ ቶሎ ብሎ የሰሚራን ክንድ ጨምድዶ ያዘና ጎትቶ ከጀርባው በማድረግ አሱ የግንብ ግድግዳ ሆኖ ከፊቷ ተገተረ…..
‹‹አይ አይ ….ካንተ በፊትማ እሷን ነው መግደል የምፈልገው››
‹‹አይ እንደጀመርከኝ እኔኑ ጨርሰኝ….››
‹‹አይ መጀመሪያማ እንደህጻን ያታለለቺኝን ይቺን ጊንጥ ፊትህ ደፋትና አንተን አስከትላለሁ..››
‹‹ለመሆኑ እዚህ ድረስ እንዴት ተከትለኸን መጣህ..?››መላኩ ነው ድንጋጤውን እንደምንም ተቆጣጥሮ በጣም የገረመውን እና ያልጠበቀው ነገር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ የጠየቀው፡፡
‹‹እግዜር ነው እጄ ላይ የጣላችሁ..እኔማ ሀገር ሰላም ነው ብዬ ልዝናና ነበር እዚህ የመጣሁት
…ግን ሞቶ አልቅሼ በእጄ አፈር
አልብሼ ቀብሬዋለሁ ያልኩት ወንድሜ እዚህ ዘና ብሎ አለሙን ሲቀጭ አገኘሁት…..ለዛውም ገደልኩልህ ብላ 6መቶ ሺ ብሬን ቅርጥፍ አድርጋ ከበላች ቀጣፊ ሴት ጋር…››መለሰለት ሰሎሞን
መላኩ እየተንቀጠቀጠ መናገር ጀመረ‹‹ገራሚ ነህ …አንደኛ በዚህ አፍህ የእግዜያብሄርን ስም ማንሳትህ ትልቅ ድፍረት ነው..እግዚያብሄር እኮ ፍትህ ነው..እግዚያብሄር ፍቅር ነው..እግዜያብሄር የበጎነት የመጨረሻው ጥግ ነው…ታዲያ በምን ስሌት እግዚያብሄር አንትን ረድቶህ እኛን አንተ እጅ ላይ ይጥለናል ብለህ ታስባለህ …..?ማይሆነውን…..!!!ደግሞ ገንዘቤን የምትለው…ገንዘቡ እኮ የእኔው ነው…ደግሞ እሷ እንደአንተ እና እንደዛች ሴት ከንቱ አትምሰልህ….ገንዘቡን የእኔ መሆኑን በመረዳት ሳትሰስት ሰታኛለች…››
‹‹በቃ ከዚህ በላይ ልፍለፋህን ልስማ አልፈልግም …..አሁን አይኔ እያየ ሁለታችሁም በአንድ ሳጥን ተዳብላችሁ ትቀበራላችሁ..እዚህ የጀመራችሁት ፍቅር እዛ ያለከልካይ ትኮመኩሙታላችሁ…››ብሎ ወደነሱ የቀሰረውን ሽጉጡን ቀጭ ቀጭ አድርጎ አቀባበለ….ይሄ ቅጭልጭልታ ቀድሞ የተሰማው ለሰሚራ ጆሮ ነበር..ያው ሴት ከወንድ በላይ ንቁ አይደለች….ከሰማችው ድምጽ ጋር እኩል ተሸከርክራ መላኩን ገፍታር ከፊቱ ተደቀነች.. ሞቱን ቀድማ ልትሞትለት….ተሳካላት…..በዛ ቅፅበት ዶ..ዶ..የሚል አደንቋሪ ድምጽ ተሰማ …ወዲያው የብዙ ሰው ጩኸት እና የሚሮጡ የሰው ኮቴ …ከዛ ሰሚራ ዝልፍልፍ ብላ መላኩ እጁ ላይ ገንደስ ስትል ይዟት ወደመሬት ሲወርድ ..ሁሉ ነገር የሚሆነው በደመነፍስ ነበር….
////
…ሰሚራ ድንገተኛ እና ያልታሰበ ከነበረው ከዛ አደጋ ከወራት ህክምና በኃላ ዳነች…መላኩም ወንድሙንና እና የበፊት ሚስቱን በግድያ ሙከራ እና በእምነት ማጉደል ከሶ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ ወህኒ እንዲወረወር አድርጎ ንብረቱን መልሶ ተቆጣጥሯል….አዎ እዚህ ድረስ ያሉ ነገሮች ጥሩና መልካም የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ…እንግዲህ ይህ ድርጊት የተከወነው ከአምስት አመት በፊት ነበር…
በመላኩ ወንድም በሰለሞን ሽጉጥ ተተኩሶባት ፍቅረኛዋን ቀድማ በተመታችበት ወቅት ከተተኮሱባት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንዱ ሽጉጥ በደረቷ ሌላው ደግሞ በጭነቅላቷ ነበር የገባባት…እና በወቅቱ በደረቷ የገባቸውን የጥይት ቀላሀ በቀላሉ ማውጣት ቢቻልም የጭንቅላቷን ማውጣት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነበር…፡፡
አስቸጋሪነቱ ጭንቅላቷን ቀዶ ጥይቷን መዞ ማውጣቱ አይደለም….የከበደው ጥይቷ የተቀረቀረችበት ቦታ እንጂ… ጥይቷ ከወጣች የሰሚራ የጤና ሁኔታ በቋሚነት እንደሚበላሽ ….ትውስታዋ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ከዛም አልፎ የማሰብ አቅሞንም እንደሚጎዳው ከፍተኛ ስጋት ስለጣለባቸው….ለጊዜው ባለበት እንዲቆይ… በየጊዜው የቅርብ የህክምና ክትትል እንድታደርግና በሂደት የሚሆነውን ለማድረግ ተወሰኖ ነበር..
ለአንድ አመት በየወሩ እየተማመላለሰች ህክምናዋ በመከታል በጥንቃቄ ካሳለፈች በኃላ ምንም የሚሰማት እና የሚለወጥ ነገር ስላልነበረ ቀስ በቀስ እየተዘናጋችና ምንም አይፈጠረም በሚል እምነት ክትትሉን አቆመች ….
በዛን የጊዜ ክፍተት ውስጥ…መላኩ በንግዱ አለም ከበፊቱ የበለጠ ተሳክቶለት ከሰሚራ ጋር ያየነበረው የፍቅር ትስስር ይበልጥ እየጎመራ ሄዶ ወደጋብቻ ሊሸጋገር ወራቶች ሲቀሩት….ግን ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ድንገት ወድቃ ሀኪም ቤት ዳግመኛ ለመግባት ተገደደች… ምርመራ ባደረገችበት ጊዜ በጭንቅላቷ መሀከላዊ ስፍራ የተቀረቀረችው ጥይት ብቻ ሳትሆን በፊት ያልነበረ ጎን ላይ አስደንጋጭ እጢ ተፈጥሮ ታየ..ሀኪሞቹ ተደናገጡ ..ተስፋ እንደሌላት እና ማድረግ የሚችሉት ብዙም ነገር እንደሌለ ለመላኩ ሲነግሩት አንጠልጥሎ ወደውጭ ሀገር ይዞት ሄደ….ግን የረፈደ ውሳኔ ነበር…ጥይቷ እንዲወጣላት ማድረግ ተቻለ ..እጢውም በጨረር ህክምና እንዲሞሞ ማድረግ ብዙም ከባድ አልነበረም…ይ ሁሉ ቢሆን ግን በህይወት ልትቆይ የምትችለው በዛ ቢባል ለቀጣዩ አንድ ወይም ሁለት አመት እንደሆነ አስምረው ነገረዋቸዋል…ከዛ በኃላ ወይ ትሞታለች ወይ ደግሞ በድን ሆና በህይወት እና በሞት መካከል ተንጠልጥላ ለአመታት ትኖራለች…..ሚሻለው ግን ወዲያው ብትሞት ነው…. የሀኪሞቹ ምክር ነበር፡፡ …የምርመራው ወጤቱ ለሁለቱም ሰቅጣጭ ነበር…
እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኛሞች …ሳቃቸው ከእንባ የተቀላቀለ፤ደስታቸው ከፍራቻ የተጋባ፤ተስፋቸው ጨለማ የገደበው ከሆነ እና በዚህ ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል እና ንስሯ ባመጣላት ታሪክ መሰረት በቀደም የዋና ገንዳ ውስጥ ያገኘችው ፤የፈተነችው እና የፎከረችበት ወጣት ታሪክ እንደዚህ ነው…ታማኝ የሚሆነውም ለዚህች ፍቅረኛው ነው…..አግቢኝ እና ውለጂልኝም የሚላት ይችኑ በጀርመናዊዎቹና በአሜሪካኖቹ ሀኪሞች የ አመት ጊዜ ብቻ የተቆረጠላትን ወጣት ነው….
ኬድሮን አሰበች‹‹እና ምን ላድርግ ….?እንዳለች ልተዋት….? ትውለድለትና ትሙት…. ከዛ እኔ ለእሱ ሚስት ለልጁ ደግሞ እናት ልሁን…..?ነው ወይስ ላድናት……..?›ከህሊናዋ ጋር ከባድ ፈተና ገባች፡፡በእርግጠኝነት ንስሯ ከረዳት ለእሷ መዳኛ የሚሆን መድሀኒት ሌላ የአለም ጥግ ማሰስ ሳያስፈልጋት …ከዚህችው ከቅድስቲቷ የኢትዬጵያ ምድር ቆፍር ቆፈር አድርጋ ስር ማስ ማስ ፤ ቅጠል በጠስ በጠስ በማድረግ ልታድናት ትችላለች..፡፡ግን ለምን ታደርገዋለች…..?ለማንኛወም ጊዜ ወስዳ ልታሰብበት ከራሷ ጋር ተስማማች….
✨ይቀጥላል….✨

👍128❤21👎4😁2🔥1👏1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሰሎሞን ድቅቅ ካደረገው እንቅልፍ ቢነቃም
ዓይኖቹ አልገለጥ ስላሉት አሻሽቶ ሊያነቃቸው
ፈልጐ ቀኝ እጁን ለማንቀሳቀስ ሲሞክር
አልተቻለውም፤የሆነ እጁ ላይ የተጫነ ነገር አለ፤የሆነ ሰው አቅፎል..‹‹ወይ እዳዬ !!ማታ ተሳሳትኩ መሰለኝ... ሴት ይዤ ገብቼያለሁ ማለት ነው፡፡›› ሲል አሰበ፤ እሱን ተወውና
ግራውን ሞከረ ተመሳሳይ ነው፡፡በዚህን ጊዜ ደነገጠ ..እንዴት ሁለት ሴት ልገዛ እችላለው?›› ድንጋጤው አይኖቹ ተበርግደው እንዲከፈቱ አገዘው ፡፡ወደ ቀኙ ዞረና አየ…..ልጁ ዕፀ-ህይወት ናት ዝርግትግት ብላ ክንዱን
ተንተርሳ በነጻነት ተኝታለች...ወደ ግራው
ዞረ..ሌለኛዋ ልጁ ዕፀ‐ፍቅር በተመሳሳይ ሁኔታ ግራ ክንዱ ላይ ተመቻችታ ተኝታለች፡፡ከእሷ ቀጥሎ ቢጃማ ለባሽ የሆነች ገዘፍ ያለች ሴት ከአንሶላው ሳትወጣ ቁጭ ብላ መፅሀፍ
እያነበበች ነው፡፡
‹‹የፈጣሪ ያለህ!!››አለ የልጆቹ ሲገርመው ከአመታት በፊት የፈታት ሚስቱን ከጎኑ ሲመለከት፡፡ ‹‹ምን ልትሰራ እሱ ቤርጓ ተገኘች?..የቤቱን ዙሪያ ገባ በግርምት ቃኘ... ቤርጎው አይደለም ያለው ፤ የድሮ ቤቱ... የበፊት መኝታው ክፍሉ ውስጥ..የበፊት አልጋው ላይ ከበፊት ሚስቱ ጋር…የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡
‹‹እየቃዠው መሆን አለበት?››ድምፅ አውጥቶ ተናገረ፡፡
የውብዳር የተናገረውን በትክክል አጥርታ ባትሰማም የሆነ ነገር እንዳለ ድምፁ ጆሮዋ ጋር ስለደረሰ የምታነበውን መጽሀፍ ቅዱስ በመክደን ያቀረቀረ ግንባሯን ወደ ላይ ቀና አደረገችና << ነቃህ እንዴ….?እንዴት ነው ሰላም አደርክ?››አለችው በፍጹም ትህትና ፡፡
ለእሷ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የራሱን ጥያቄ አስቀደመ ‹‹የት ነው ያለሁት?››ጠየቃት፡፡
‹‹ቤትህ ነዋ፡፡››
እንደመበርገግ አለና ልጆቹን ከክንዶቹ ላይ አንሻራቶ እራሱን ነጻ በማድረግ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ተቀመጠ፡፡
‹‹ቀስ... ቀስ.. ልጆቸህን ትቀሰቅሳቸዋለህ››አለችው በለሆሳሳ፡፡
‹‹ቆይ ማታ ሰክሬ ነው አይደል የመጣሁት .. ? በጣም እረበሽኳችሁ እንዴ....? ስትረብሽ ልጆችህም አይተውህ ነበር እንዳትይኝ ብቻ… አዝናለሁ፡፡ እንዲህ ለማድረግ ፈልጌ አልነበረም፡፡ ትንሽ ተበሳጭቼ ስለነበር በዛ ላይ መጠጥ አብዝቼ ስወስድበት እራሴን አስቶኝ ነበር ማለት ነው..አንቺም እኮ ትክክል አይደለሽም፤ስመጣ ዝም ብለሽ ታስገቢኛለሽ እንዴ…? ገና ከውጭ በራፍን አልፌ ሳልገባ ዘበኛው እንዲመልሰኝ አታደርጊም ነበር?››
ዝም ብላ በፍዘት ስታዳምጠው ከቆየች በኃላ << ማታ ስለሆነው ሁሉ ምንም ነገር አታስታውስም ማለት ነው?›.አለችው፤ የሆነ ሀይለኛ የሚቀስፍ ስጋት እና የሚቀዘቅዝ ፍርሀት በሰውነቷ እየተሰራጨባት፡፡
‹‹ቆይ ቆይ..ማታ እኔ ቤርጎ አንቺ…››የሆነ እንደህልም አይነት ትዝታ በአዕምሮዎ ብልጭ ድርግም አለበት፡፡
‹‹አዎ መጥቼ ነበር፡፡››
‹‹አዎ እንደ እሱ በይኝ.. እንጂማ ያን ያህል ላብድ አልችልም፡፡ >>
‹‹የምን እብደት አመጣህብኝ?››
‹‹...ቀጥታ ዝም ብዬ እዚህ በመምጣት ካላደርኩ አልልማ ... አንቺን እዛ ሳይ ተከትዬሽ መጥቼ እንጂ..፡››
‹‹እንደዛም አይደለም፡፡››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው?››
‹‹እኔ ነኝ ለምኜህ ማለት ይቅርታ ጠይቄህ ይዤህ የመጣሁት...››
‹‹እየቀለድሽ አይደለም አይደል?››
‹‹እውነቴን ነው ሶል... ተነጋግረን ተስማምተን ነበር የመጣሀው፡፡ጥፋት ያጠፋህ መስሎ ከተሰማህ እንኳን ጥፋቱ የእኔ ነው እንጂ ያአንተ አይደለም፡፡ አንተ ምንም አላደረግክም …እኔም ግን ወድጄ አይደለም ፤ እስቲ ልጆቻችንን እያቸው፤ዛሬ ከጎናቸው ብትሆን እንዴት የሰላም እንቅልፍ እንደተኙ.. አቤት ማታ ቀስቅሰህ መጥቼያለሁ ስትላቸው የተደሰቱት መደሰት ልነግርህ አልችልም..ታዲያ ለእነሱ ስትል ይቅር ብትለኝ ምን አለበት..?በቃ ምንም ልበድልህ ... ምንም ላጥፋ ለእነሱ ስትል ልትረሳልኝ አትችልም?››
‹‹ኧረ ቆይ.. አንቺ ባጠፋሽው መጠን እኮ እኔም አጥፍቼያለሁ›..
‹‹ታዲያ በቃ ይቅር እንባባላ..በቃ በስካር
መንፈስም ቢሆን ወደ ቤትህ አንዴ ገብተሀል
..በፈጠረህ በዚህ በምታምንበት መጽሀፍ
ቅዱስ ልለምንህ ፤ ተመልሰህ ከቤትህ
አትውጣ... ከልጆችህ ጋር ኑር...አንተ
ከምትወጣ እኔ ብወጣ ይሻለኛል...ሴት ልጆች
አባታቸውን አብልጠው ይወዳሉ ሲባል አባባል
ብቻ ይመስለኝ ነበር..በራሴ ልጆች ነው እውነት
መሆኑን ያረጋገጥኩት... አንተን አጥተው መኖር
በጣም ነው የሚከብዳቸው... ስለዚህ
ባክህ..ባክህ››በማለት በቃላትም ...በአይኖቿ
እርግብግብታም ተለማመጠችው፡፡እጁን ላካና አቅፎ ወደ ራሱ በመጎተት ደረቱ ላይ ለጥፎት በጆሮዋ ‹‹እኔም የትም አልሄድ ..አንቺ
እንዳልሽው በቃ ያለፈውን እንርሳው... የውሾን
ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን››አላት፡፡
‹‹እሺ የእኔ ጌታ አመሰግናለሁ››አለችውና የሚንጠባጠበውን እንባዋን በቀኝ እጇ እያበሰች ከእቅፉ ወጥታ አልጋውን ለቃ ወረደች፡፡በዚህ ጊዜ በመሀከላቸው ያለችው ዕፀ- ህይወት ከእንቅልፏ ባና ዓይኖቿን ከመግለጧ በፊት መጀመሪያ የጠየቀችው ጥያቄ‹‹አባቴስ?›› የሚል ነበር፡፡
‹‹አለሁልሽ የእኔ ቆንጆ >> ብሎ ወደ ራሱ አስጠግቶ አቀፋት... ሙሉ በሙሉ ነቃችና እላዩ ላይ ተንጠልጥላ እያገላበጠች ትስመው ጀመር፡፡ በዚህም አረካችም መንታ እህቷንም ቀሰቀሰቻት ..ሰሎሞን ተይ ትተኛ ቢላትም ልታዳምጠው አልፈለገችም፡፡ ሁለቱም ልጆቹ ለመጀመሪያ ቀን ያዩት ይመስል ትንፋሽ እስኪያጥረው እና ድክም እሲኪለው ተላፉት ፣ሳሙት፣እላዩ ላይ ጨፈሩ፡፡ በመጨረሻ የውብዳር ነበረች በግድ አላቃ ለቁርስ መኝታ ቤቱን ለቀው ወደ ምግብ መመገቢያ ቤት እንዲሄዱ ያስገደቻቸው፡፡
በፊት አብሯቸው ይኖር በነበረበት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ዓመታት በእጇ ትሰራለት የነበረውን እና እሱም በጣም እየወደደውና እሷንም እያመሰገነው ይበላው የነበረውን ምግብ ነበር ሰርታ ለቁርስ ያቀረበችው ፡፡በሳቅ እና በጨወታ ታጅበው
ቁርሳቸውን እየበሉ ግማሽ እንደደረሱ የሳሎኑ በራፍ ተንኳኳ፡፡
‹‹ይግቡ ..ክፍት ነው›› አለች የውብዳር ከመቀመጫዋ ሳትነሳ.፡
በራፉ ተከፈተ..ሁሴን ነበረ የመጣው ፡፡
‹‹እየተጣራጠርኩ ነው የመጣሁት ስልክሽ አይሰ......››ንግግሩን አቋረጠ፡፡እርምጃውንም መሀል ሳሎን ላይ ገታው፡፡የሰሎሞን እዛ ቤት ውስጥ መገኘት ፍጽም ከግምቱ ውጭ የሆነ ክስተት ነበር... የሆነ ውሽማው ቤት ሊሰርቅ የሄደ ሰው ከባልዬው ጋር የመፋጠጥ አጋጣሚ እንዳጋጠመው ሰው ነው አደነጋገጡ፡፡
<< ና እንጂ ....አንተ እንወድሀለን ማለት ነው .. ቁርስ ላይ ደረስክ.…‹ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ መልሰኝ› የሚባለው እንደዚህ ነው››አለችው የውብዳር፡፡
ሁሴን ግን የእሷን ወሬ አልሰማም‹‹ይሄ ሰውዬ
እዚህ ምን ይሰራል? ››አላት እንደምንም እግሮቹን አነቃንቆ ወደ እነሱ እየተጠጋ።
‹‹እቤቱ ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ ቁርስ እየበላ ነዋ››
‹‹..ከልጆቹ እና ከሚስቱ ጋር >> ልትል አስባ ነበር ያልተረጋገጠውን የሚስትነት ማዕረጓን መልሳ የዋጠችው›› የምታድርበት ሆቴል እኮ ሁለቴ ነዋ የመጣሁት ስልክህም ዝግ ነው ..ግራ ሲገባኝ ጊዜዬን ከማባክን እነዚህ ልጆች ልይ ብዬ ወደ እዚህ ጎራ ማለቴ እኮ ነበር..እንጂማ.. ››በማለት ለልጆች ይዞላቸው የመጣውን ቸኮሌት አከፋፈሏቸው ወንበር ስቦ ተቀመጠ ፤አመስግነው ተቀበሉት፡፡

👍68❤6