አትሮኖስ
271K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

...ካርተር በርክሌይም ቢሆን ሀብታም ነው ይህንን አታውቅ ይሆናል።ዊሊ ባደን እኮ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላርን ለ ኤል.ኤ.ፒዲ የበጎ ሥራ አገልግሎት እንዲውል አስቦ ይለግሰናል።
የካርተር በርክሌይም ባንክ እስከ አሁን ድረስ ከሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለግሶናል።” አለው፡፡

ይሄኔም ጆንሰን ኮስተር ብሎ “ይህንን እንኳን አላውቅም ነበር ጌታዬ”
አለ ጉድማን “እኔም ብሆን ይህንን አላውቅም ነበር” ብሎ መለሰ፡፡

“ታዲያ እነርሱ ይህንን የመሰለ የበጎ እርዳታ ልገሳን ለእኛ በማድረጋቸው
ለእነርሱ የተለየ ነገር ይገባቸዋል ጌታዬ?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡

“ደግሞ በዚህ አይነት ድምፀት እንድታናግረኝ አልፈቅድልህም” ብሎ
ብሩዲ ኮስተር አለ እና “አዎን እነርሱ ይህንን ነገር ለእኛ በማድረጋቸው
የሆነ ነገር ከእኛ የፖሊስ ዲፓርትመንት ይጠብቃሉ። በእርግጥም ደግሞ
እነርሱ እነዚህን ነገሮችን በበጎ ፈቃድ ሥም ለእኛ ሲያደርጉ በምላሹ የእኛን
ዲፓርትመንት ጊዜ ግንዛቤ እና ክብርን ይጠብቃሉ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እነዚህ
ሰዎች ወንጀለኞች ወይንም ደግሞ በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች
አይደሉም። ዶክተር ሮበርትስም ቢሆን ማስረጃህን ሳታቀርብ እንደ ወንጀለኛ
ወይንም እንደ ተጠርጣሪ ልታያት አትችልም” ብሎ ብሩዲ ተናገረው።

ይህን የሰማው ጆንሰንም በቁጣ ፈነዳ እና “ሁሉም የዘረዘርካቸው ሰዎች በሙሉ ወንጀለኛ ሊሆኑ የማይችሉበት ምክንያት የለም።”

“ኒኪ ሮበርትስ ባሏ ከትዳሯ ውጪ ስላለው ግንኙነት ዋሽታናለች።ካርተር በርክሌይም ቢሆን ዛሬ ሆነ ብሎ የፖሊስ ጊዜን አባክኗል። በግድያ ወንጀል ላይ በሚደረግ የምርመራ ሂደት ሲዋሸኝ ነው የዋለው። ባደንም ቢሆን እኔ ባናገርኩት ወቅት ላይ ጠበቃው የሰጠው ስክሪፕት ዝንፍ ሳይል ነበር ይመልስልኝ የነበረው:: ስለዚህ ይሄ ሰውም ወንጀለኛ ላይሆን
የሚችልበት አንዱም ምክንያት አይታየኝም!”

“ይህንን አሁን መስማት አልፈልግም” ብሎ የፖሊስ አዛዡ ብሩዲ እጁን
አነሳ እና “ጆንሰን ለጋሾታችንን ማበሳጨትህን አቁም። ደግሞ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ዐሰዎቻችንንም አታበሻቅጥ፡፡ አንተም ብትሆን ጉድማን
መልመጥመጥህን አቁም፡፡ ለማንኛውም ሁለታችሁም የግሮልሽን ሬሳን
በፍጥነት አግኙ ወይንም ደግሞ ስለመኪና አደጋው የተጨበጠ ነገር አግኙ
ያለበለዚያ ግን ሁለታችሁንም ከዚህ ምርመራ ላይ ላነሳችሁ እገደዳለሁ።”
አላቸው፡፡
ከአለቃቸው ቢሮ ወጥተው በሩን እንደዘጉም ጉድማን በፍጥነት
እየተራመደ ከጆንሰን ፊት ፊት መቅደም ጀመረ።ሀሀሀሀሀ
“እውነቴን ነው እኮ! ይልቅ ነገሮችን በግልፅ እንዳታይ እየከለከለችህ
ነው። ስለዚህ ባሏ ከትዳሯ ውጪ ስላለው ያልተገባ ግንኙነት ጠይቃት
አለው ጆንሰን ጉድማንን እየተከተለው።
ጉድማንም ከፊት ለፊቱ የሚገኘውን ሁለት በር ገፍቶ ወደ መኪና
ማቆሚያው ቦታ ቶሉ ቶሎ እየተራመደ መሸሽ ጀመረ።
“ጠይቃት!” አለው እና ጆንሰን ጉድማንን እየተከተለም
“ትላንትና ማታ አብራችሁ ነበራችሁ አይደል?” አለው።
ጉድማንን ጆንሰን ሊሆን ይችላል ብሎ ያሰበው ነገር እና እሱን ለማናገር
የተጠቀመበት ዘዴ ይሆናል ብሎ አሰበ እና መልስ ሳይመልስለት ወደ
መኪናው ገባ፡፡
“ስለ ባሏ ውሽማ አንድም ነገር አልነገረችህም አይደል? ሰውዬ እሷ
እየተጠቀመችብህ እና እየተጫወተችብህ ነው። ስለዚህ አይንህን ክፈት
እባክህን” አለው፡፡
ጉድማንም መኪናውን አስነስቶ በፍጥነት እያሽከረከረ ከጆንሰን ሲሽሽ
ጆንሰን በመጨረሻ ላይ የተናገረው ነገር ጆሮ ውስጥ እየደወለበት ነበር።

ጉድማን ከፖሊስ ጣቢያው የሆኑ ያህል ብሎክ ከራቀ በኋላ መኪናውን
አቆመ እና ሦስት ጥልቅ ረዥም አየርን ወደ ውስጡ ሳበ፡፡

በአለቃቸው ብሩዲ ቢሮ ውስጥ እያሉ ጆንሰን ስለ ኒኪ ሮበርትስ የተናገረው ነገር ብዙም አላሸበረውም ነበር። ምክንያቱም እሱ ለእሷ ያለው አመለካከት ጆንስን ስለ እሷ ከተናገረው የተለየ በመሆኑ ነው።
መኪናው ውስጥ እንደተቀመጠም ሚክ በኒኪ ሮበትስ ላይ ስላቀረባቸው
ውንጀላዎች ተመስጦ ላለማሰብ ፈለገ። ማለትም ኒኪ ሮበርትስ ባሏ ከትዳሩ
ውጪ ስላለው ግንኙነት በፊት ላይ አስቀድማ በማወቋ የተነሳ የመኪና
አደጋው እንዲደርስ፣ ባሏም ከነ ውሽማው እንዲሞት ማድረጓን እንደዚሁም
ደግሞ ይህንን ብልህ አዕምሮዋን ተጠቅማ የሊዛ ፍላንገን እና የትሬይ
ሬይሞንድን ግድያዎችን ፈጽማለች ብሎ ጆንሰን ያቀረበውን ነገር በተመስጦ
ማስብ አልፈለገም፡፡

በመጨረሻ ላይ ጉድማን ኒኪ ሊዛን እና ትሬይን እንዳልገደለች አመነ፡፡ባሏን እና ውሽማውን መግደሏ ግን ሊሆን ይችላል? ይህንን አምኖ መቀበል አልፈለገም። ያም ቢሆን ግን ጆንሰን በእዚህኛው ጉዳይ ላይ የተለየ እውነታን ለማቅረብ ሞክሯል። ብቻ አሁን ላይ የተቆራረጡ ሀሳቦችን መሰብሰብ እንዳቃተው ያምናል።

“ማን ናት የዶውግ ሮበርት ውሽማ?

ለምንድነው የእሷ ሥም እና ማንነት በወቅቱ በአደጋው ጊዜ ላይ
ያልተገለፀው? ስለ አደጋው የቀረበው ሪፖርት የት ሄደ?

ደግሞ ኒኪ ትላንትና ማታ ነፃ ሆነን በግልፅ እያወራን በነበረበት ጊዜ
ላይ ለምንድነው ባሏ ከትዳሩ ውጪ ስለነበረው ግንኙነት ልትነግረኝ
ያልቻለችው? የሚሉ ጥያቄዎችን በውስጡ እያስተናገደ እያለ ጆንሰን
“እየተጫወተችብህ ነው አይንህን ክፈት እባክህን!” ብሎ ቅድም የተናገረው
ነገር በጆሮው አንቃጨለበት፡፡

ኒኪ ሮበርትስ በእውነት እየተጫወተችበት ነውን?

በዚህ ሀሳብ ውስጥ እያለ ነበር ጉድማን ስልኩን አውጥቶ ወደ ኒኪ ስልክ
የደወለው፡፡

በደበዘዘው ብርሃን በዲስኒ የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ቁጭ ያለችው ኒኪ
ስልኳ ሲጠራ ስልኳን ከቦርሳዋ ውስጥ አወጣች እና ተመለከተችው።
የጉድማንን ሥም ከስክሪኑ ላይ ስለተመለከተች ስልኩን መለሰች እና ስልኳን አጥፍታ ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችው። ቦርሳውን ለኮንስርቱ ብላ ነው
የገዛችው፡፡ ለምሽቱ የኮንሰርት ዝግጅት አስባም ያገዛችው ረዥም ቀሚስ
ሰውነቷ ላይ ልክክ ብሎባታል። ቀሚሱ እሷ ላይ ልክክ በማለቱ ደግሞ
ኮንሰርቱን ለመታደም አዳራሽ ውስጥ ያሉትን የወንዶች አይን ስቦላታል፡፡
ከወንዶች ጋር ያሉት ሴቶችም እሷን በቅናት አይን ነው የሚመለከቷት፡፡

አኔ ቤታማንም የሁለት ሰዓቱን የሙዚቃ ኮንስርት ዝግጅትን በቫዮሊኗ
እየተጫወተች አድምቃዋለች:: አኔ ቫዩሊኗን በሚገርም ችሎታ እና ብቃት
ስትጫወት ኒኪን እና አዳራሹ ውስጥ ኮንሰርቱ ላይ የታደሙትን ሰዎች ሁሉ
ስሜት በደንብ ነበር ይዛ የቆየችው።

ደግሞም የአኔን ድንቅ የሙዚቃ ችሎታን ያ ራስ ወዳዱ ባሏ ይፋ እንዳታወጣው በእንስሳ ማጎሪያ ክፍል ውስጥ ዘግቶ ለብቻው ሊያስቀምጣት መፈለጉ ደግሞ በእውነትም ኪሳራ ነበር ማለት ይቻላል። ኒኪ አኔ ቤታማን ቫዩሊኗን እጅግ በጣም ተመስጣ ስትጫወት በመመልከቷ ስሜቷ
በማታውቀው ሁኔታ ተነካባት እና አይኗ በእምባ ተሞላ። የእምባዋ መምጣት ሙዚቃውን አኔ ቤታማን በድንቅ ሁኔታ እየተጫወተች ስለሆነ ወይንም ደግሞ እሷን ገጥመዋት ከነበሩት የሀዘን ስሜቶች የተነሳ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበረችም፡፡

ትላንትና ማታ ከጉድማን ጋር ያሳለፈችው ምሽት የሆነ መጨረሻ ላይ የደረሰች ያህል ነበር እንዲሰማት ያደረገው። በእውነትም ደግሞ አስገራሚ ሞኝ ሆኖ ነበር ማለት ይቻላል። በግድያው ወንጀል ላይ ምርመራውን ከሚያደርግ ፖሊስ ጋር ለመተኛት እስከምትፈልግና ሞቅ እስከሚላት ድረስ መጠጣቷ ትክክል አልነበረም፡፡ ለመርማሪው ፖሊስ የተሰማት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ስበት ደግሞ ለረዥም ጊዜ ሳይሰማት የቆየ ስሜቷ ስለነበር ገርሟታል። ምንድነው
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....ያች በየጊዜው የምትጠገነውና የማያዘልቅ የገንዘብ መፍጃ ዕድሳት
የሚደረግላት የጉልላት ቮልስዋገን እየተንገጫገጨች መንቆርሰሷ አልቀረም፡፡
አውላላ ሜዳ ላይ ታጋልጠኛለች በማለት ሆዱን ቅር ያለው ዕለት በታክሲና በእግሩ መሔድ ይቀናዋል። አንዳንድ ቀን ተገፍታም ይሁን በበርቺ በርቺ
ተንቀሳቅሳ መሽከርከሯ ስለማይቀር እየተንገራገጨችም ቢሆን ይነዳታል፡፡
መንገድ ላይ ቀጥ ባለች ቁጥር ደግሞ ከየትም ለቃቅሞ ያገዛቸውን ልዩ ልዩ
መፍቻዎች፣ የብረታ ብረት ቅባት ካጠገበ አሮጊ ከረጢት ውስጥ ይዘከዝክና
ለማጠባበቅ ወደ ሞተሯ ይገሠግሣል። ምን ያደርጋል ታዲያ! ያን ውስብስብና
ቁልፍልፍ የብረት ቁልል ሲያይ “አሁን ደግሞ የትኛው ይሆን? ምን ዐይነት
ፍርጃ ነው! » ይልና አንዱን መፍቻ ወርውሮ እንቺ ቅመሽ ይላታል። በዚያው
ደግሞ ሌላ ዕቃ ይቀለጠምና ከናካቴው እንደ አበያ በሬ ለጥ ትላለች፡፡

ከተማዉ ውስጥ ያሉት ሽቃዮች የተሰናከለች ተሽከርካሪ አነፍንፈው ማግኘት ይችሉ ይመስል ወዲያውኑ እንደ ጉንዳን ይከቧታል። እሺ ካለች አለች፡
አለበለዚያም በምንጭሯ አስጎትቶም ይሁን ከወደ ጅራቷ አስጠምዞ አንዱ ጋ
አስጠግቷት ይሔዳል። ለገፉለትም ሆነ ለሳቡለት ሰዎች ስለት እንዳለበት ሰው
የሚሰጠውን ሰጥቶና ኣንጀቱን አሳርሮ በእግሩ ሲንገላወድ የነቀሉት ጭሰኛ
ይመስላል፡፡

እንድ ሰሞን ጥርሱን ነክሶ ስላሳደሳት የመኪና ወጉ ደርሷት ደኅና ስትሽከረከር ሰነበተች። እሱም ሠጋር በቅሉ ላይ እንደ ተቀመጠ የዱሮ መኳንንት ውስጧ ገብቶ ጉብ ይላል፡፡ የወዲያነሽ ጋር ሽርሽር ለመሔድ አስበን ስለ ነበር መኪናውን እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፡፡ 'ውሰድ አለ ቃሉን
ሠፈር አድርጎ በደኅንነቷ እየተመካ፡፡ «በዚህ ሰሞን ውቃቢ ቀርቧታል፡፡
እንዳጋጣሚ ግን በመሏ መጥቶ እንዱ ጋ ቀጥ ብላ ጉድ ካደረገችህ የራስህ
ጉዳይ ነው የለሁበትም!» ብሉኝ ቅዳሜ ማታ ወሰድኳት።

እኔና የወዲያነሽ ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት እንደሆነ ለሁለታችን የሚበቃ ጥቂት ለስላሳ መጠጥና ምግብ ጭነን ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ጎጃም መንገድ ሰማንያ አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ተጓዝንባት፡፡ ምንም እንከንና ጉድለት ሳያጋጥመን ካሰብነው ቦታ እስክንደርስ ድረስ መኪናይቱን እያቆምኩ ባሻገር የሚታዩትን ተራሮችና ኮረብቶች ለጥ ያሉ ለምለም ሜዳዎችና የሽልጥልጥ ሸንተራራማ ገደሉች እያየን፡፡ ምቹ ቦታና መዝናኛ ነው ብዬ ከገመትኩት ሥፍራ ላይ እንደ ደረስኩ የመንገዱን ዳር አስይዤ አቆምኳት፡፡ያ ብዙ ቦታ ላይ በንዝረት የሚገጫገጨው ልል የብረታ ብረት ክፍል ጊዜያዊ ጸጥታ አገኘ። የመኪናይቱ ሙቀት ቀስ በቀስ ቀነሰ። የውስጧ ሞቃት አየር
በመስኮት በኩል በሚገባው ቀዝቃዛ አየር የተገፋ ቦታ ይለቃል፡፡ የመኪናይቱ
ፊት ወደ ሰሜን በመዞሩ በስተምሥራቅ በኩል ባለው መስኮት በከፍተኛ
ፍጥነት እየተግለበለበ የሚገባው አየር በትይዩው መስኮት እየተዥጎደጎደ
ይፈተለካል። የመኪናይቱ መሪ በስተግራ በኩል በመሆኑ የወዲያነሽን እየዳበሰ
የሚመጣው አየር ከላይዋ ላይ የለሰለሰ የሽቶ መዓዛ ያመጣና አወድወድ አድርጎኝ ይከተለባል። ባለፈው አየር እግር የሚተካው አየር ይክሰኛል። በእኔ በኩል ያለውን በር ከፍቼ እግሬን ወደ ውጪ ዘርግቼ ራሴን በየወዲያነሽ ጭን
ላይ አሳረፍኩት፡፡ አንጋጥጬ ስመለከታት አዘቅዝቃ አየችኝ፡፡ አዝራሮቼ በተከፈቱበት በኩል ቀኝ እጅዋን አሾልካ ደረቴን ስትደባብሰኝ የፍቅራዊ ደስታ ሰመመን አጥለቀለቀኝ፡፡ ጋደም እንዳልኩ ዐይኖቼ ተንገረገቡ፡፡ ዐሥራ አምስት ደቂቃ ያህል ቀ-ም እንዳደረግሁ ወደ ከተማ በሚያዘግም የጭነት መኪና ድምፅ ባንኜ ነቃሁ፡፡ ጥቂት ምዕራፎች ወደፊት ነዳሁ።
እንደገና ከመንገድ ገለል አድርጌ አቆምኳት። ሠላሳ ርምጃዎች ያህል
ወጣ ብዬ ስለ ነበር አንዳንድ አጫጭር ቁጥቋጦዎች በመኪናይቱ ተቀለጣጠሙ ጎማው የተሽከረከረባቸው በዚያው ሲቀሩ በመኪናይቱ ሆድ የተለመሰሉት ግን በመጠኑ ጎበጥበጥ ብለው ቀኑ፡፡ ከፊት ለፊታችን ጥቅጥቅ ያለ አጋምና ብሳና ድግጣና ምሥርች ዐልፎ ዐልፎ ኮርች በቅሉ አካባቢውን አይደፈር መሳይ ግርማ አልብሶታል። ወደ ዱሩ የምታስኬደው ቀጭን መንገድ ባረንጓዴ ወረቀት ላይ የተሰመረች ግራጫ መስመር ትመስላለች፡፡በዚቹ መንገድ በኩል ይዣት ልግባ ይሆን ይቅርብኝ እያልኩ ሳመነታ'
ስፈራና ስጠራጠር ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡

አንድ ውሳኔ ለመወሰን ጫካውን አፍጥጬ ስመለከት ጥቂት ራቅ
ብሎ አንድ አፈርቻና ሦስት አራት ያህል ዝንጉርጉር እንስሳት ከጫካው ውስጥ ተከታትለው ብቅ አሉ፡፡

ለጊዜው ልብ ብዬ ባለማየቴ ደንገጥ አልኩና «ምንድናቸው?» አልኩ።
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል ያደረገችው የወዲያነሽ «ፍየሉች ናቸው» አለችኝ፡፡
«እኔስ ሌላ ነገር መስለውኝ» ብዩ ነገሩን ወዲያ ወዲህ እምታታሁ፡፡ ደግነቱ
ስሜቴን ስላላወቀችብኝ ዝም አለች። ጥሎ አይጥሌ ሲረዳኝ አንድ እረኛ ብዙ
ፍየሎች እያንጋጋ ከጫካው ውስጥ ብቅ አለ፡፡ ከመኪና ወጥተን የየወዲያነሽን
እጅ ያዝ አድርጌ እንደቆምኩ እረኛው አጠገባችን ደረሰ። ደረቱ ላይ ሰፋ-ሰፋ
ያለ ኪሶች ያለባት የአቡጀዲ እጀ ጠባብ ለብሷል። የሁለቱም ኪሶቹ አፍ አደፍደፍ ብሎ ጠቁሯል። ሁለት ፍየሎች ተነጥለው ወደ ሌላ አቅጣጫ ስለሄዱ እነሱን ለመመለስ ነይ እሪያ!» ብሎ ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ ልብሱ ከበስተኋላው ቂጡ ላይ ድልህ የነካው ጋቢ መስሏል።

ከጉልበቱ በታች ያለው ሙጭርጭር በደረቀ ጭራሮ የተጠረገ የረገጥ ቤት መስሏል፡፡ በግራ ብብቱ ቀጠን ያለች ብትር አጣብቆ ይዟል። ዋሽንቱን በእጁ ውስጥ እያንከባለለ ያሻሻታል። ፍየሎቹ እየቀነጣጠቡ በአጠገባችን አለፉ፡፡ እረኛውም ከኋላ ከኋላቸው ከተፍ አለ። ልብሱ ላይ ዐልፎ ዐልፎ ጨጎጊት ተጣብቋል። አጋም ሲቃቅምበት የዋለው ከንፈሩ ጠቋቀሯል። እንኩታ ሲቸችግ የዋለ መስሏል።

ለስለስ ባለ ድምፅ "አንተ ልጅ ና እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ አልኩት፡፡ ነባር ፍርሃት ሳይሆን የጥርጣሬ ፍርሃት በፊቱ ላይ እየታየ በዝግታ መጥቶ ቆመ ወደ ጫካው እያመላከትኩት በዚ ጫካ ውስጥ መንገድ አለ እንዴ?ብዬ ጠየኩት? 'አዎ' ብሎ ባጭሩ መለሰልኝ፡፡

«እንግዲያውማ እዚ ቅርቡ መናፈስ ይቻላል፣ አስቸገሩኝ አትበለኝና አንድ ነገር ልለምንህ ነው? ይህን የመብል የመጠጡን ነገር ተወው፡ ነጭ
ሺልንግም እጨምርልሃለሁ ይቺን መኪና ትጠብቅልኛለህ አልኩት።

«ፍየሎቼን ማን ያግድልኛል?» ብሎ መለሰልኝ፡፡ ጓደኛም የለህ እንዴ?
ካለህ ፍየሎቻችሁን ተራ በተራ እየመለሳቹ መኪና ትጠብቁልኛላችሁ» ከማለቴ ጓደኛስ አለኝ» አለኝ፡፡ “ሒድ በል ጥራውና ና » ብዬ በትሕትና አዘዝኩት፡፡ በቀጭኗ መንገድ ወደ ጫካው ወስተ ሄደ፡፡ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ ሰው ጭንቅላቱ ቁልቁል ስለ ወረደች አካባቢው ተዳፋት
እንደሆነ ገባኝ፡፡ ከየወዲያነሽ ጋር የሚረባ ወሬ እንኳ ሳናወራ ጥጆችና ጊደሮች
እየነዱ ከተፍ አሉ፡፡ በመጀመሪያዉ ልጅና በሁለተኛው ልጅ መካከል ትንሽ
የመልክ ልዩነት እንጂ በአለባበስና በአረማመድ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለተኛ
ልጅ ፊቱ ሰልከክ ብላ መጠጥ ያለች ነች፡፡ አፍንጫው ሰልካካ ፀጉሩ ጥቁር
ለስላሳ ነው፡፡ ቆሸሽ ባለችው የእጀ ጠባቡ ኪሶች ኣካባባና እጅጌዎቹ ላይ ልዩ
ልዩ አዝራሮች ተተክለዋል። ሁለቱም ግራና ቀኝ ቆመው እንጠብቅላችኋልን አሉ፡፡

«እንግዲህ አደራችሁን ስመለስ የማደርግላችሁን አታውቁትም አልኩና መኪናይቱን ከፍቼ ምግብና መጠጥ የያዘውን መጠነኛ የእቃ ሻንጣ
አወጣሁ፡፡

ደስ እንዲላቸውኛ በሚያጓጓ ተስፋ እንዲጠብቁልኝ በማሰብ ሁለት
ሁለት ዳቦና አንዳንድ ብርቱካን
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

...ከወደ ጋራው አካባቢ እሪታና ዋይታ ተሰማ፡፡ “ኡ! ኡ!.ኡ.!! የሀገር ያለህ! የመንግሥት ያለህ! የወገን ያለህ! ኡ.ኡ.ኡ. እሪ!” የሚሉ ሰዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ ሄደና የህብረት ጩኸታቸውን ያቀልጡት ጀመር፡፡

የመንደሪቱ ነዋሪዎች ዱላ የያዘ ዱላውን ጠመንጃ ያለው ጠመንጃውን እያነሳ የተጣደፈው ባዶ እጁን ለእርዳታ ወደ ዋይታና እሪታው ቦታ ገስገስ በተፈጠረው ድርጊት በመደናገጥ የበለጠ የሰው ሀይል ለማስባሰብ ተኩስ ተተኮስ፡፡

“ቷ! ቷ! . ዷ! ዷ! ህፃናትና ሴቶች ሲቀሩ ሌላው ግልብጥ ብሎ ወጥቶ አካባቢውን አጣበበው። ድርጊቱ እጅግ የሚያስደነግጥ ፍፁም ዐይን ሊያምነው የማይችል ጆሮ ቢሰማው የሚሰቀጥጥ ሆነ፡፡ የዚህ አይነቱ ወንጀል ለብዙ ሰዎች አዲስ ከመሆኑም ሌላ ወንጀሉ የተፈፀመበት ሰው ገበየሁ መሆኑ ደግሞ ህዝቡን እርስ በርሱ አባለው። አንጫጫው። ቀድሞ እዚያ የደረስው ጭንቅላቱን ይዞ “
እግዚኦ! እግዚኦ! ያንተ ያለህ!” እያለ አንዱ
በሌላው ላይ እየዘለለ ያየው ነገር አስደንግጦት ድርጊቱ አስበርግጎት
ቁጣው ከስማይ እንደወረደ ሁሉ ወደ ስማይ ያንጋጥጣል፡፡ መልካም ባህሪ የነበረው ትህትናው ለአንድ ቀን እንኳን ተጓድሎ የማያውቀው ስሙ በክፉ ተነስቶ የማያውቀው ገበየሁ፣ ለትዳሩ ቀና ደፋ የሚለው ገበየሁ፣ ትዳሩ ለሌሎች ምሳሌነት የሚበቃው ገበየሁ የዚህ አይነቱ አስቃቂ ዕጣ ፈንታ ደርሶበት በጫካ ውስጥ ተደፍቶ ይቀራል ብሎ ማመን እጅግ አስቸጋሪ ሆነባቸው፡፡ መሞቱን የሚጠራጠሩ በፍፁም እሱ ሊሆን አይችልም በማለት የሚከራከሩም አልጠፉም ነበር፡፡ ወዲያና ወዲህ ተሯሩጠው ከብቶቹ መዘረፋቸውን ሲያረጋግጡ ግን ከብቶቹን ለመዝረፍ
በመጣ ወንበዴ እጅ የተገደለ እሱ ራሱ ገበየሁ መሆኑን ሳይወዱ በግድ
እያመኑ መጡ፡፡

“እባካችሁ ጎበዝ! እባካችሁ እስቲ ቶሎ ቶሎ ብላችሁ ቅደሙ! ትኩስ ደም ላይ ከደረሰች ልክፍት ነው የሚገድላት! ድንጋጤው ሰው አያደርጋትም!
እባካችሁ ወደ ቤት እሩጡ! ጉዷን ያላወቀች ወደዚሁ እየመጣች ይሆናል
ዋ! እቴን! እሪታው የቤቷ ጉድ መሆኑን ሳታውቅ ድንገት ደሙ ላይ እንዳትቆምና እንዳትጎዳ ፍጠኑ!” አለ አንዱ የቅርብ ጎረቤት ዓላሚቱ እሪታውን ሰምታ እንዳትመጣ እየሰጋ፡፡
“ጎበዝ! ምናልባት ተጠራጥራ ካስቸገረቻችሁ በጉልበትም ቢሆን ይዛችሁ አቆዩአት። ከሞት ታድነው ደሙ ላይ ደርሳ እንዳትለከፍ! አጉል ራሷን
አደጋ ላይ እንዳትጥል ተጠንቀቁ!” ሲሉ ሌላው ጎረቤት አክለው አሳሰቡ፡፡
በዚሁ መሰረት ደህና ደህና ጡንቻ ያላቸው ስድስት ጎረምሶች ወደ ገበየሁ መኖሪያ ቤት ሮጡ፡፡ ዓለሚቱ ምን እንደተፈጠረ ምን በመፈጠር ላይ እንዳለ ቀድማ አውቃዋለች።ባሏ ከብቶቹን ለግጦሽ ካሰማራበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ ጠንቅቃ ታውቃለች። ጎንቻ እንደፎከረ ያደረገው መሆኑን የተረዳችው ገበየሁ ከብቶቹ እንዲታለቡ ወደ ቤት ይዟቸው
የሚመለስበት ሰዓት ሲያልፍ ነበር፡፡
የተፈፀመውን ድርጊት ፍፁም እንዳላወቀች ሆና ተጨንቃ ሰው ካላስጨነቀች በስተቀር ሀሜትና አሉባልታው እንደማያስቀምጣት ስለምታውቅ ተዘጋጀች።

ተከታትለው የደረሱትን ወንዶች በጭንቀት መልክ እያስተዋለች... እንዴ! ምነው?! ምንድነው? እንዴ! ምን ተፈጠረ?! ገበየሁ ደህና አይደለም እንዴ!? ወየው ጉዴ! ኸረ ባካችሁ ንገሩኝ?! ምንድነው ግርግሩ?!
ጨኸት…የምን ጩኸት ነው? ወየው! ኸረ ዘንድሮ! እኔ እኮ ሲዘገይብኝ ነው ልቤ የነገረኝ ኸረ! ኡኡ ኡ በዚህ ጊዜ ወንዶቹ የምታብድና ራሷን የምትገድል ስለመሰላቸው ደንግጠው ከግራና ቀኝ ሁለቱንም እጆችዋን አፈፍ ፣አፈፍ አድርገው ያዟት። በዚህ ጊዜ ለየላት። እንባዋ ግድቡን እንደ ጣሰ ጎርፍ መንታ መንታ ሆኖ እየተንዶለዶላ በጥፍሯም በንክሻም የተሰበሰበውን ሰው ሁሉ ትፈጀው ጀመር። ጠቅላላ ቤቱን ቀበሮ የገባበት የበግ መንጋ አስመሰለችው። አተራመሰችው። በዚህ ቅፅበት ወዳጅ ጎረቤቱ መጀመሪያ ቤቷን ከዚያም ቀስ በቀስ ደጁን እየሞላው መጣ፡፡

የቅርብ ዘመድ የሆነው ኡኡታውን እዬዬና ዋይታውን ከርቀት እያስማ መጉረፍ ጀመረ። “ዓለሚቱ ጉድ ሆን! ዓላምዬ እጃችን ተቆረጠ! ዓለምዬ ጉድ ፈላ! ውሽታሙ ገበየሁ! አታላዩ ገበየሁ! ልጆችህን ሳትሰናበት ገበየሁ! እሪ” እያለ ከአንጀቱ አለቀሰ፡፡ ዓለሚቱም ለያዥ ለገናዥ እስከምታስቸግር ድረስ እየጮኽች ደረቷን ደለቀች፡፡ያንን አስደናቂ የማስመሰል ችሎታዋን የታዘበ ሰው የዓለሚቱን እንከን የለሽ መሪ የፊልም ተዋናይነት ያለ አንዳች ጥርጥር ይመሰክርላታል፡፡ ያንን የተዋጣለት ድራማ ሰርታ ካጠናቀቀችና የሚስኪኑ ገበየሁ አሟሟት ለፖሊስ ሪፖርት ተደርጎ አስከሬኑ አሰላ ከተማ ሆስፒታል ተወስዶ ከተመረመረ በኋላ በተወለደ በሰላሳ
ሶስተኛ ዓመት ዕድሜው ወደ ዘለዓለማዊ ቤቱ ወደ መቃብር ወረደ።
“ቤቴን ትዳሬን ልጆቼን ሚስቴን” እንዳለ ሳያስበው እንደወጣ ቀረ። መሪር ሀዘንና የማይጠፋ ፀፀትን በወላጆቹና በወዳጅ ዘመዶቹ ልብ ውስጥ ጥሎ አለፈ... ዓለሚቱ ሀዘኑ ያደከማት፣ የደቆሳት መሰለች።
“ከእንግዲህ ጠንከር በይ እንጂ ዓለሚቱ? ከዚህ በላይ ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ ራስሽን ከዚህ በላይ ጎድተሽ እነዚህ ልጆች ሜዳ ላይ እንዳይቀሩ አስቢ! እሱ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥሽ እንጂ ምን ይደረጋል?! አይ መከራ ሁለት ጨቅላ ልጆቹን አስታቅፏት ጉድ አደርጓት ሄደ
እኮ!...” የሰው ወሬ... ገዳይ ማን እንደሆነ የታወቀው ገበየሁ በሞተ ዕለት ነበር፡፡ ከብቶቹን ፊት ከፊት እያሯሯጠ ሲገሰግስ ሰዎች ተመልክተውት ነበር፡፡ሚስጢሩ
አልተከሰተላቸውም እንጂ፣ ገበየሁን ገድሎ ከብቶቹን ዘርፎ መሄዱን አላወቁም እንጂ አይተውታል።

· “አታውቁትም እንዴ? ጎንቻ የሚባለው ነው እኮ! ኽረ በደንብ እናውቀዋላን! ጥቁር ረዥም? አዎን! ከኢተያ ከተማ አንድም ቀን ጠፍቶ የማያውቅ? ኸረ ሌባ ነው እየተባለ ሲታማ ሰምቻለሁ! ጎንቻ ሌባው ነው እንዴ?! አዎን ጥቁሩ አውቀዋለሁ! ምነው ከወይዘሮ ባንቺይደሩ ቤት የማይጠፋው የሃጂ ቦሩ ልጅ አይደለም እንዴ?! ኸረ ከባለቤቱም ጋር ይታማል ጉድ ነው! ጉድ! አቤት! አቤት!” ውስጥ ውስጡን ሰው ያወራ ጀመር፡፡ ቀስ
በቀስ ደግሞ ጎንቻ ዓለሚቱን የወሸማት መሆኑ ሹክሹክታው ማምለጥ
ጀመረ።

ስልስቱም አርባውም እንደ ቀልድ አለፈ፡፡ ከዓለሚቱ ጭንቅላት ውስጥ የገበየሁ ምስልና ትዝታ ሙሉ ለሙሉ ጠፋ። ትዝታውና ስሙ ያልጠፊው አባባ የታለ? እያሉ ዘወትር ከሚጠይቁት ከእነኝያ በአእምሮም ሆነ በአካል ካልበሰሉ ጨቅላ ህፃናት ጣፋጭ አንደበት ብቻ ነበር።በለቅሶው ዕለት አባታቸው ለዘለዓለም በተለያቸው በዚያን ቀን የነበረው ትርምስና ግርግር ለነሱ ሰርግና ምላሽ ነበር፡፡ ምናልባት የእናታቸው ለቅሶ ቢያስደነግጣቸው እንጂ ከዚያ በኋላ ያለአባት የሚቀሩ የሙት ልጅነታቸው
አልታወቃቸውም ነበር፡፡ ለዚያውም ወንዱ ምትኬ ይሻላል። እሱ ትንሽ ትንሽ በደመነፍሱ ሳይታወቀው አልቀረም፡፡ “እማምዬ አባዬ የታለ አይመታም?”ብሎ ሳይጠይቅ የዋለና ያደረበት ቀን አልነበረም፡፡ ከሁሉ የበለጠ
የምታሳዝነው ደግሞ ትንሿ ሴት ልጁ ነበረች። የዛሬን አይጥራትና በስሟ
ሳይሆን “እናቴ፣ እናቴነሽ” እያለ እያቆላመጠ ነበር የሚጠራት። እሷም
እንደ ወንድሟ አባቷ እየናፈቃት ስለመጣ ታላቅ ወንድሟ የአባቱን ስም እያነሳ ሲጠይቅ የሷም ጥያቄ በመሆኑ ዐይኖቿን በእናቷ ዐይኖች ላይ ታቁለጨልጭ ነበር።

ሁለቱ ህፃናት አባታቸውን ከእናታቸው ዐይኖች ውስጥ እንደሚያገኙት
ሁሉ ዘወትር ዐይን ዐይኖቿን በልምምጥ እያስተዋሉ መወትወታቸውን አላቋረጡም ነበር። የምትመልሳቸው
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...የሰኔ ወር ገብቶ እንዲያውም ተጋመሰ። እዲስ የበጀት ዓመት መቃረቡን ተከትሎ የመንግስት ሠራተኞች የዝውውር ጥያቄ መልስ መስጫው ጊዜም ተዳረሰ፡፡
ከዝውውር ጠያቂዎች አንዱ የሆነው አስቻለው ያን ወቅት በጉጉት ሲጠብቀው ቆይቷልና ከጊዜው መቃረብ የተነሳ ሀሳቡ ሁሉ ስለ ዝውወርና ከዚያ ጋር ተያያዥ ስለሆኑ ነገሮች ብቻ ሆኖ ሰንብቷል። ብዙ ነገሮች ያሳስቡታል። ከዲላ መዛወር
የፈለገው ወዶ አይደለም! ተችግሮ ነው፡፡ ግን በሚዛወርበት ቦታ ዲላ የገጠሙት ችግሮች ከይኖሩ ይሆን? ዲላ የተፈጠሩበት ችግሮች መነሻቸው የግልፅነቱና የተናጋሪነቱ ውጤቶች ናቸው፡፡ ወደ አዲሱ ቦታ ሄዶ ዝም ይል ይሆን? ተናጋሪነቱ የተፈጥሮ ባህሪው ነው፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ የተለያዩ አመሎችን መተው ይሻል
እንደሆነ እንጂ የተፈጥሮ ባህሪውን ግን እንዴት?
ዲላ ከተማ ለአስቻለው በሥራ ሕይወት የኖረባት የመጀመሪያዋ ከተማ ናት፡ ጣፋጭ ማሀበራዊ ሕይወት የጀመረው በዚያችው ከተማ ነው፡፡ ዕድሉ ሆኖ ጥሩና ዕድሜ ልኩን የማይረሳቸው የባዕድ ወገኖች አግኝቶባታል፣ ታፈሡን በልሁና መርዕድን ከእነሱ ተለይቶ መሄዱ ያስጨንቀዋል፡፡ ዝውውር የጠየቀው ወደ ሽዋ
ክፍለ ሀገር ቢሆንም የሚመደብበትን የጤና ተቋም ግን አያውቅም፡፡ ከነታፈሡ በልሁና መርዕድ ጋር በቀላሉ መገናኘት በሚያስቸግር ቦታ ቢሄድስ? ልቡ ይፈራል። ድንገት ትዝ ሲለው ሆዱን ባር ባር ይለዋል።
የሔዋን ጉዳይስ? በወላጆቿ ፈቃድና እውቅና ለፍቅራቸው እልባት ለማግኘት የሚሞክረው ገና ወደፊት ባሉት ወራት ነው! ሐምሌ ወይም ነሐሴ። በእርግጥ
በጉዳዩ ላይ ታፈሡና በልሁ አስበውበታል ምናልባት
ወይዘሮ ዘነቡም ይጨመራሉ፡፡ ግን ይሳካ ይሆን? ወደሚዛወርበት ቦታ ሔዋንን ይዞ መሄድ ይችል
ይሆን?ይህ ጉዳይ ዛሬ ሌሊትም እንቅልፍ ነስቶት አድሯል፤ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ። ሊነጋጋ ሲል ግን ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዶት ኖሯል፡፡ ተኝቶ አረፈደ፡፡
አስቻለው የጠዋት ፈረቃ ሥራ ገቢ መሆኑን የምታውቀው ትርፌ
በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ ለወትሮው ወደ ሥራ ለመሄድ ቀስቃሽ አያስፈልገውም ነበር። ዛሬ ግን ሁኔታው ተለየባት፡፡ ልትቀሰቅሰው እያሰበች ፈራ ተባ ስትል ቆየችና መጨረሻ ላየሰ ግን ልታነቃው ወሰነች።
«.ጋሽ እስቻለው!» አለችው ወደ አልጋው ቀረብ ብላ፡፡ እስቻለው ግን በአንዴ አልሰማትም «ጋሽ አስቻለው!» አሁንም ደግማ፡
አስቻለው ብንን አለ፡፡ ፊቱን ኩብርድ ልብስና አንሶላ ሽፋን ገለጥ አድርጎ ከአንገቱም ቀና በማለት «ወይ» አላት።
«ዛሬ ሥራ የለህም እንዴ?»
«እረፈደ?» በማለት የእጁን ሠዓት አየት ሲያደርግ ከጠዋቱ ሁለት ሠዓት ከአምስት ደቂቃ ሆኗል። «እንዴ!» ብሉ በድንጋጤ ዓይን ትርፌን ፍጥጥ ብሎ ተመለከታት።
እኔ እኮ ሥራ የማትገባ መሰለኝ!» አለችው ትርፌ ሳትቀስቅለው
መትረቷ ቅር ያለው መስሏት አፈር እያለች::
«ምን ነካኝ እባካችሁ?» አለና አንሶላና ብርድ ልብሱን ጣል አድርጎ ከአልጋው ላይ እየተነሳ «ውሃ ውሃ» አላት በችኮላ አነጋገር፡፡
«በረንዳ ላይ አውጥቼልሀለሁ፡፡»
አስቻለሁ በጥድፊያ ልብሱን ለባበሰና ሊታጠብ ወደ በረንዱ ወጣ፡ ቶሎ ቶሎ ታጥቦ አበጣጠረና ወንበር ላይ የሰቀላትን የቆዳ ጃኬት ብድግ አደረገ፡፡
«ቁርስ ሳትበላ አለች ትርፌ እንቅስቃሴውን እየተከታተለች፡፡
«ረፍዷል ትርፌ፤ ቻው » ብሏት በፍጥነት ርምጃ ከቤት ወጥቶ ሄደ።
መንገድ ላይ ሳለ በልቡ እንድ ነገር ያሰላስላል። ካአሁን በፊት ለብዙ ጊዜ እንደተከታተለው የሠራተኞች የሠዓት መቆጣጠሪያ መፈረሚያ ጠዋትም ይሁን ከሰዓት ከቦታው የሚነሳበት ወቅት ከእሱ መፈረም ወይም ያለ መፈረም ጋር ሲያያዝ አይቷል፡፡ እሱ በጠዋት ወይም በጊዜ ገብቶ ከፈረመ ያ የሠዓት
መቆጣጠሪያ መፊረሚያ ለሩብ ሠዓት ያህል በአለበት ቦታ ሊቆይ ይችላል፡፡ እሱ ለደቂቃዎች ያህል
ከዘገየ ግን ለአፍታ እንኳ ሳይቆይ ወደ ቢሮው ይገባል። ዓላማው
እሱ በአርፋጅነት የሚመዘገብበትን ቀናት ለማበርከት እንደሆን ይጠረጥራል.ስለዚህም በጣም ይጠነቀቅ ነበር፡፡ ለዛሬው ግን አልተሳካለትም።ብዙ
ባያስጨንቀውም ነገር ግን ባርናባስ ወይሶነ በመጥፎ ስሜት እያስታወሰ በፍጥነት ርምጃ ግስጋሴውን ቀጠለ::
ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ሲደርስ ሁለት ሠዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ያ ሰዓት ደግሞ የፈረቀው ገቢ የሆኑ የህክምና ባለሙያዎች ከሥራ በፊት የተለመደ ከጭር
ስብሰባ ሊያጠናቅቁ የሚደርሱበት ጊዜ ነው፡፡ ባለቀ ሠዓት ወደ ስብሰባው መግባት አልፈለገም። ዝምብሎ ወደ መልበሻ ክፍል አመራና ጋወኑን ለበሰ፡፡ ቀጥሎም
የሠዓት መፈረሚያው ወደ ሚገኝበት የባርናባስ ወይሶ ፀሃፊ ቢሮ ሄዶ አንኳክቶ ገባ፡፡
“ዛሬ እንኳ አረፈድኩ ከይባልም! ውያለሁ እንጂ!» አለ አስቻለው ፈገግ ብሎ የባርናባስ ወየሶ ፀሃፊ የሆነችውን ሠርካለምን እየተመለከተ፡፡
የአንድ ቀን ደሞዝ ቀለጠች፡፡» አለችው ሠርካዓለም እሷም እንደ አስቻለው ፈገግ ብላ እየቀለደች ሠርካለም የሚያምር ፈገግታ ያላትና ቀጠን ያለች ቀይ ዳማ
ቢጤ ናት። በዕለቱ ጥቁር ኮትና ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች። ዕድሜዋ እስከ ሰላሳ ሊደርስ የሚችል ይመስላል።
«ግድየለም፤ ሌላ ጊዜ ከአልደገምኩ ለዚህ ወር የሃያ ዘጠኙ ቀን ደሞዜ ይበቃኛል::" አለና አስቻለው በቀይ እስክርብቶ የጥያቄ ምልክት ከተደረገበት ጎን
ፊርማውን አስቀመጠ፡፡
ዛሬ ግን ያለ ወትሮህ ከርፍደሃል! በሰላም ነው?» አለችው ሠርክዓለም አንድ በውስጧ የምታውቀውና የአስጨነቃት ጉዳይ ያለ ስለመሆኑ በሚያጠራጥር ስሜት አስቻለውን እያየችው::
«የሆነ ሀሳብ ገብቶኝ ያለ እንቅልፍ አደርኩና ከነጋ በኋላ ድብን አድርጎ
ወሰደኝ:: ሌላ እንኳ ችግር እልነበረበኝም፡፡»
«ምነው? ምን አሳሰበህ?»
«ሀሳብ ይጠፋል ብለሽ ነው» አለና አስቻለው ወደ ውጭ ሊራመድ ሲል ሠርከዓለም ንግግሯን ቀጠለች::
«ፈልጌህ ነበር እስቻለው::»
«በደህና!»
«እስቲ ቁጭ በል፡፡»
አስቻለው የሠርካዓለም ስሜት ጥሩ እንዳልሆነ ገመተ። ይበልጥ ሊያነበው እየተፍጨረጨሪ ዓይኖቹን በዓይኖቿ ላይ ሰክቶ ከሰርካዓለም ጠረጴዛ አጠገብ
በምትገኝ የእንግዳ ወንበር ላይ አረፍ አለና “ስላም ከይደለሽም" ሲል ጠየቃት፡
«እኔ እንኳ ደህና ነኝ»
«ታዲያ ሌላው ምን ሆነ?»
«ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ ለአንተ አንድ ደብዳቤ ስጪ ብለውኝ ቅዳሜና እሁድን በጭንቀት ነው ያሳለፍኩት። ከዛሬ ስለማያልፍ ልስጥህ ብዬ ነው፡፡» አለችው ሠርካለም መንፈሷ ጭንቅ ጥብብ እያለ፡፡
«የምን ደብዳቤ! ዝውወር» አላት አስቻለው በድንጋጤ ዓይኖቹ ጉልንል ብለው በሰርካዓለም'' ላይ በማፍጠጥ፡፡ ትንፋሹም በርከትከት! ፈጠን ፈጠን አለ፡፡
«አይደለም ነገሩ ብዝም ችግር ያለው ሆኖ አይደለም! ምናልባት
ግን አንተ የማትቀበለው ከሆነ በመሀል ችግር እንዳይፈጥርብህ እስቤ ነው።»
«ማን የጻፈው ደብዳቤ ነው?»
ሠርካለም የጻፈው ሰው እገሌ ብላ መግለጽ አልፈለገችም፡፡ ደብዳቤውን ከመሳብያ ውስጥ አውጥታ ሰጠችው።
አስቻለው ደብዳቤውን ተቀብሎ ገጹን በሙሉ ቃኘት ሲያደርገው ሙሉ ፕሮቶኮል የጨበጠ ነው፡፡ የፈረመበት ባርናባስ ወየሶ ነው፡፡ የደብዳቤውን አድራሻ ሲመለከት ለጓድ አስቻለው ፍሰሃ» ይላል፡፡
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ከራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ መሸነፍ በኋላ፣ ሰላም ቀስ በቀስ በሃገሪቱ መልሶ ሰፈነ። ምንትዋብ በነገሠች በዓመቱ እንደ ቀድሞ ነገሥታት የራሷ የሆነ ቤተመንግሥት ለማሠራት ያደረባትን ጽኑ ፍቅርና ፍላጎት
ለማርካት ከባለቤቷ ከአፄ በካፋ ግንብ ጎን ቆማ ያሠራችው የተዋበውና የረቀቀው ፣ እንደ ሌሎቹ ግንቦች ሁሉ ባለ ሰቀሰቁና ባለ ሁለት ደርቡ ቤተመንግሥት የተደነቀ ሆነላት።

አፄ በካፋ በሞቱ በሁለተኛ ዓመታቸው ላይ ያሳደጓት፣ ያስተማሯት፣ በቤተመንግሥት ሥርዐት ሆነ በአስተዳደር ታንጻ እንድትወጣ የረዷት፣ አንደበተ ርቱዕዋ፣ የቤተክህነት ትምህርትና የቤተመንግሥት ወግ አዋቂዋ አያቷ ወይዘሮ ዮልያና ይህችን ምድር ጥለው ሄዱ። እሷ
ሆነች እናቷ መሪር ሐዘን ገባቸው። ዮልያና ታላቅ የቀብር ሥርዐት
ተደርጎላቸው ተቀባሩ። ምንትዋብ ተዝካራቸውንም ታላቅ ድግስ ደግሳ አወጣች።

ዮልያና በሞቱ በስድስተኛ ወራቸው ታናሽ ወንድማቸው ኒቆላዎስ ዐረፈ። ምንትዋብ ተጎዳች። ሆኖም ኒቆላዎስ በታላቅ ለቅሶና ሐዘን ተገቢው ሥርዐት ተደርጎለት ተቀበረ። ቀድሞውንም ቢሆን ለአፄ በካፋ ሁነኛ የነበረና በኋላም፣ ከእሷ ቀጥሎ ትልቁ ባለሥልጣን የነበረ፣አጋሯና በማንኛውም መንገድ ሲያግዛት፣ ሲያማክራትና ትዕዛዞቿን ሁሉ በተገቢው መንገድ ሲያስፈጽምላትና ሲፈጽምላት የቆየ ቀኝ እጇ በመሆኑ፣ የእሱ መሞት በቤተመንግሥት ውስጥ ትልቅ ክፍተት ፈጠረ።

ኒቆላዎስ ከሞተ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ምንትዋብና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዐዲሱ ቤተመንግሥት እልፍኝ ውስጥ እጅ የሚነሱትን መሣፍንትና መኳንንት አሰናብተው ጨርሰው፣ ኢያሱ ከአጃቢዎቹ ጋር ወጥቷል።
ምንትዋብም እልፍኟ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነች፡፡ ደጃዝማች
ወልደልዑል ጫማውን ሳያወልቅ እልፍኝ ዘው ሲል ከአረማመዱ የሆነ ነገር እንደገጠመው አወቀች። ዛሬ ወልድየ ምንን ሁኖ ነው አለወትሮው በችኮላ ሚራመደው አለች፣ ትኩር ብላ እያየችው።

“ችግር አለ” አላት፣ የችኮላ ሰላምታ ከሰጣት በኋላ።

“የምን ችግር ወልድየ?” ከተቀመጠችበት ተነሳች።

“የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ ለውጊያ ታጥቋል።”

“ምን ይሁን ብሎ?” ፊቷ ጥላ ጣለበት። “ምን ይሁን ብሎ ነው አሁን ጦር ይዞ ሚነሳ?”

“ኸኢያሱ ክፍል የለኝም ብሎ። ያው ፊት እንደሰማነው፣ እኒህ
ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ።”

ከቋራ ስለመምጣቷ ከአያቷ ጋር ሲያወሩ፣ “ንቀታቸው... ወደ ፊት
ታቂዋለሽ” ያሉት ትዝ አላትና ራሷን በትዝብት ነቀነቀች። “እኒህ

ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ?” አለችና ከት ብላ የምጸት ሳቅ ሳቀች።

“አዎ እስተመቸ ነው ሚገዙን እያለ ሲቆጭ ቆይቷል” አላትና
እንድትቀመጥ በእጁ ዙፋኗን አመለከታት።

ቀጥል በሚል እጇን አወዛወዘችለት።

“አንዱም ኸተሰጠው የዳሞት ገዥነት ስለወረደ በልቡ ቂም ኣሳድሮ ነው እኼን ሊያረግ የተነሳው። ጥላቻውና እብሪቱ መጠን አጥቶ እዋጋለሁ ብሎ ነገሩን ኻዘጋጀ ሰንብቷል። “
እኼን የኩበት ካብ ሳላፈርስ
ሰው አልባልም ብሏል አሉ።”

“የኩበት ካብ?”

“የንጉሥ ኢያሱንና ያንቺን መንግሥት ማለቱ ነዋ!”

“ዛዲያማ ይጠብቀና” አለች፣ ሌባ ጣቷን እያወዛወዘች።

“ኸመጣሽ ዠምሮ ቋረኞች ላይ ያለው ግምት ምን እንደሁ
ታውቂያለሽ። አንቺም ብትሆኚ አልተሸነፍሽላቸውም፤ ወደፊትም
ታሸንፊያቸዋለሽ። ስሰማ ተንሴ ማሞ ኸዝኸ ሁሉ መጥቶ ግቢውን
አይቶ ነው አሉ የኸደው። ተመልሸ መጣለሁ ብሎ ዝቷል።”

“እንዴት ልቡ አብጧል በል? ይምጣ... ይምጣ... እስቲ እናያለን
የኩበት ካቡን ሲያፈርስ። የልዢን አልጋ ኻላስከበርሁማ እኔ ምንትዋብ ሰው ማዶለሁ” አለች።

ሰውነቷ ጋለ።

“አሳቡ አንቺንና ንጉሥ ኢያሱን መግደል ነው። መንገስ ሚፈልገውን ጠይቆ ሊመጣ ወህኒ ኸዷል። ወንድሙ ተስፋ ማሞም
ኸሱ ጋር አምጿል። ኸጎዣምም ብዙ ሠራዊት ሰብስቧል አሉ። እኛም መዘጋጀት አለብን።”
ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ አየችውና፣ “ሚነግሠውን ያምጣ። የትኛው
አልጋ ላይ እንደሚያስቀምጠው እናያለን። ይልቅስ አሁን ኸመሣፍንቱ፣ ኸመኳንንቱና ኸጦር አበጋዞቹ ጋር እንምከር። ለወሎና ለጎዣም ባላባትም ስለሁኔታው እናመላክታቸው። ዛሬውኑ መልክተኛ እንላክ።ጠንካራ ጦር ስላላቸው ኸነሱ ጋር ተባብረን ነው እኒህን ሰዎች መቋቋም
ምንችለው። ዛሬውኑ ሁነኛ ሰው ላክና እንዲደርሱልን አርግ::”

“በጀ፤ እንደሱ አረጋለሁ” ብሏት እጅ ነስቶ ወጣ።

የእልፍኝ አስከልካዩን ቴዎድሮስን አስጠራች።መኳንንቱና የጦር አበጋዞቹ በአስቸኳይ መሠሪ
እንዲነግራቸው ነገረችው። ኢያሱም ከግቢ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ሰጠች።ቴዎድሮስ እጅ ነስቶ በፍጥነት ወጣ።

ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። “የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ
ለውጊያ ታጥቋል” የሚሉት የወንድሟ ቃላት ጆሮዋ ላይ አቃጨሉ::እሷንና ኢያሱን መግደል መፈለጉ አስገረማት። ኢያሱን መግደል የሚለው ቃል ዘገነናት። ልጄን በደንብ ማስጠበቅ አለብኝ አለች።

አምላኬ ልዤን ዐደራህን አለች፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ
መስኮቱ እየሄደች። በስተቀኝ በኩል በባሏ ግንብና በፈረስ ቤቱ መሃል ያለው ሰፊ ቦታ ላይ ኢያሱ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ባልደራሱ ያነጋግረዋል።ወደ ግቢው በር እየጠቆመ ሌባ ጣቱን ያወዛውዛል። አትውጣ ተብለሀል
ነው ሚለው አለች፣ ምንትዋብ።

በፈረሱ ዙርያ በርካታ የመሣፍንት ልጆች እየተሯሯጡ ይጫወታሉ።
አሁን እስቲ እኼ ትንሽ ልዥ ምን አረገው? ለአልጋ ብሎ ትንሽ ልዥ
ይገድላል? እሱ እንደሆን አይቀመጥበት። ደሞ ማነም ሆነ ማን ኸወህኒ አምባ ቢመጣ የኢያሱን አልጋ አይወስድም. ቁሜ ነው ሙቼ።ልዤንም አልጋውንም እከላከላለሁ አለች። ኢያሱን እያየች፣ እንደነዝኸ ልዥች በመጫወቻው ሰዐት ለሞት ሊዳርግብኝ ባሏ ያስገነቡትን
ግንብ አየችና አስታወሰቻቸው። ለካንስ እንደዝኸ እያመጡ ነው ሰላም ሲነሷቸው የከረሙት.

ኧረ ደሞ ተንሴ ማሞ ተሹሞ ኸነበረ ላይሻር ኑሯል? ስንቱ ይሻር
የለ? ሹም ሽረት ያለ ነው። ደሞ ሰነባበተ እኮ። እንዴት ያለ በቀለኛ
እያሰበችበት ስትመጣ የጋለ ስሜት በመላ አካላቷ ተሰራጨ። ጉንጫፍም መሰለ።

እኔ ምንትዋብ ምን መስየዋለሁ? ቁጭ ብየ ምጠብቀው ይመስለዋል? ይኼ ኸመጣማ አልመለስለትም፡፡ እስቲ ልዤን እንድች ብሎ ንክች ያርግ ያየኛል፣ ብላ ቀኝ እጇን ጨብጣ የመስኮቱን ደፍ መታ መታ አደረገችው። እስቲ አሁን ሰላም ሆንን ስል... ስንት ነገር ላገሬ ሳስብ እንደዝኸ ያለው ይምጣ ላገሬ ያሰብሁትን ሳላረግማ እሱ አይቀድመኝም ኸመንገዴ ላይማ አይቆምም፤ እፋለመዋለሁ። ግድ የለም መልሸ ሰላም አመጣለሁ። አንዴ የሱን ነገር ልወጣ።

ተመልሳ ሄዳ ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። አሁን ብናደድ ምንም ጥቅም የለው። ይልቅስ ማረግ ያለብኝን ባስብ ነው ሚሻል። በመዠመሪያ የግቢውን በሮች እንዲዘጉ ማረግ አለብኝ መጠለያ እንዳይሆናቸው ደሞ ኸግቢ ውጭ ያሉትን ዛፎች ቅርንጫፍ ሁሉ ማስቆረጥ። አሁን
ይልቅ መሣፍንቱን፣ የጦር አበጋዞቹንና መኳንንቱን ተሎ ላነጋግር።ወልድየም ተሎ ብሎ ወሎና ጎዣም መልክት ይላክ፡
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....እኔ ፓሪስ ሄጀ ቅናት ውስጥ ስንፈላሰስ ኤክስ ውስጥ ምን ምን
ተደረገ? ከባህራም፣ ከተካና ከኒኮል የሰማሁትን ሳገጣጥመው እንደ እሚከተለው ሆነ፡-.

አንድ ማክሰኞ ከሰኣት በኋላ (ኒኮል ከፋሺስቶቹ ተደብቃ
ሰንብታ ከተመለሰች በኋላ) ባህራም የሚሰራበት ትምህርት ቤት ዲሬክተር ቢሮው አስገባውና ከስራዎ ላሰናብትዎ ነው» አለው።
ባህራም «ምነው?» ቢለው “በስራዎ በጣም ተደስቼ ነበር፤ ግን የጋርደን ከተማ የፖሊስ ሹም እንዳሰናብትዎ አዘዘኝ» አለው

«እዚህ ውስጥ የፖሊስ ሹም ምን አገባው?» አለ ባህራም

«አዩ፣ እርስዎ የውጭ አገር ዜጋ እንደመሆንዎ መጠን፣ እዚህ
አገር ስራ ለመያዝ ልዩ ፈቃድ ያስፈልግዎታል። እስካሁን ያለ
ፈቃድ ወረቀት ስለስሩ እርስዎም እኔም ልንቀጣ እንችል ነበር፡፡ ግን
የፖሊስ ሹሙ ጓደኛዬ ነው፡፡

የስራ ፈቃድ እንደሌለኝ እንዴት አወቀ?» አለ ባህራም

ሰው ነገረው:: ይመስለኛል፣ ኤክስ ውስጥ ጠላቶች አሉዎት።»
ባህራም ገባው። ፋሽስቶቹ መሆን አለባቸው

«እሺ ደመወዜን ይስጡኝ አለ። የሁለት ወር ከሶስት ሳምንት
ደመወዝ አለው። ዲሬክተሩ ገንዘቡን ከቢሮው ጠረጴዛ ኪስ አውጥቶ አቀበለው። ባህራም ገንዘቡን ቆጠረ። የተዋዋሉት ገንዘብ ሲሶ ነው።
«ሌላውስ?» አለ ባህራም
ዲሬክተሩ ከጠረጴዛው ኋላ እንደተቀመጠ፣ ቅዝቅዝ ባለ ክፉ
ድምፅ
«የምን ሌላ?» አለው
«ይሄ ሙሉ ደመወዜ አይደለም፡፡ አንድ ሶስተኛው ነው::
«ማን ነው ያለው? ደመወዝህን ሰጥቼሀለሁ፡፡ ከፈለግክ ውሰደው፣
ካልፈለግክ ተወው:: ድሮ አልጄርያ ሳለሁ አረቦቹን ከዚህ ባነሰ
ደመወዝ ነበር የምናሰራችሁ»
ባህራም ረጋ ባለ ድምፅ አረቦቹን ቅኝ ግዛት ስላደረጋችኋቸው
በካልቾ ብለው ካገራቸው አስወጧችሁ፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እኔ አረብ አይደለሁም፡፡ የኢራን ሰው ነኝ፡፡ የኢራን ሰው ሰውን አይነካም። ግን ማንም ሰው የኢራንን ሰው አይበድልም፡፡ ስለዚህ አለና ድንገት
በጠረጴዛው ተንጠራርቶ ሰውዬውን አነቀው፡፡ ሰውየው ራሱን ለማስጣል አልሞከረም፡፡ ባህራም ሲያፈጥበት፣ በደነገጠ ድምፅ

«አይነቁኝ፡፡ አስም በሽታ አለብኝ» አለው ባህራም ለቀቀው፡፡ ሰውዬው ከጠረጴዛው ኪስ ሌላ ገንዘብ አውጥቶ ባህራም ፊት ቆጠረው። ባህራም ገንዘቡን አንስቶ ኪሱ ከተት። ሰውየውን አየው፡፡ ወምበሩ ላይ ተቀምጦ ወደ ላይ ይመለከተዋል። ባህራም አፉ ውስጥ ብዙ ምራቅ ሰበሰበ፡፡ ሰውዬው ፊት ላይ ተፋው፡፡ ሰውዬው መሀረብ ሊያወጣ እጁን ወደ ኪሱ ሲከት ባህራም ትቶት ወጣ

ከዚያ እየጨሰ ወደ ኤክስ የሚወስደውን አቶቡስ ተሳፈረ
ያን ቀን ተካን ባያገኘው ጥሩ ነበር
ተካ በበኩሉ ከአንድ ወር በላይ ሲበሳጭ ሰንብቷል። ጀርመንዋ
ልጅ እየባሰባት ሄደ። በፊት እንኳ ከዚያ ካገሯ ልጅ ጋር የምትወጣው አልፎ አልፎ ነበር፡፡ አሁን ግን ቢያንስ በሳምንት አራት ማታ ከሱ ጋር ነች። ተካ እንግዲህ ቢበዛ በሳምንት ሁለት ማታ ቢያገኛት ነው። ለዚያውም ሁለቱም ማታ የንትርክ ማታ ነው።
ሁልጊዜ ስለጀርመኑ ይጨቃጨቃሉ

«ከሱ ጋር ምን ትሰሪያለሽ?»
በራሴ ህይወት ምን አገባህ?»
አብራችሁ ትተኛላችሁ?»
«ምን አገባህ?»
በጥፊ እየመታት «ንገሪኝ! ይተኛል?» ይላታል
በንዴት «አዎን ይተኛኛል! በል ምን ትሆን!?» ትለዋለች
እንደገና አንድ ሁለት ጥፊ ያቀምሳትና፣ በግድ ታግሎ
ይተኛታል
አንድ ማታ ግን፣ ዝግ ባለ ድምፅ
«ልሰናበትህ ነው የመጣሁት» አለችው
ልቡ እየፈራ «ምነው? የት ልትሄጂ ነው?» አላት
«የትም አልሄድም፡፡ እስቲ
ዛሬ እንኳ ሳንጣላ እንደር፡፡
የመጨረሻችን ሌሊት ነው፡፡ ሄርማን ሊያገባኝ ቆርጧል፡፡ እኔም እሺ ብየዋለሁ።»

በሰላም አደሩ፡፡ ከዚያ በኋላ አነጋግራው አታውቅም
ጀርመንዋ ያስለመደችው ሲቀርበት ጊዜ ያንገበግበው ጀመር፡፡በቶሎ ሴት ማግኘት እንዳለበት ገባው:: ቢመለከት፣ ኒኮል አለች::መልኳ እጅግም ነው፡ ወንድ በብዙ ልትስብ አትችልም፡፡ ለዚህ አይደል ባህራምን በገንዘቧ 'ምታኖረው? ግን አሁን ባህራም
አብዛኛውን ጊዜ ከኤክስ ውጪ ነው:: ስለዚህ ሌላ ወንድ መፈለጓ
አይቀርም። እንድያውም ይህን ጊዜ እሱ (ተካ) ሴት ያስፈለገውን
ያህል እሷም ወንድ መፈለጓ አይቀርም፡፡ ሌላ ሴት እስኪያገኝ ማቆያ ትሆነዋለች። እሷም በበኩሏ ባህራም እስኪመጣላት ማቆያ ይሆናታል፡፡ የጋራ ጥቅም!
ማክሰኞ ከምሳ በኋላ ቤቷ ሄደ
ቡና አፈላችለትና «ዛሬስ ምን ሰማህና ልትጎበኘኝ መጣህ?»
አለችው
«እንድ ነገር አስቤ ነው» አላት
«ምን?»
«እኔንና አንቺን የሚጠቅም ሀሳብ ነው»
«ንገረኛ»
«ደስ ትዪኛለሽ፡፡ ስለዚህ ባህራም በሌለበት ጊዜ እዚህ ብመጣ
ጥሩ ይመስለኛል»
«መጥተህስ?»
«እናወራለን፤ እንጫወታለን» እያለ እጁን እጇ ላይ አስቀመጠ
እጇን እያሸሸች «ለኔ የሚሆን ጨዋታ ያለህ አይመስለኝም»
አለችው
«አለኝ»
«የለህም»
«ከባህራም በምን አንሳለሁ?»
በሁሉም ነገር»
«ሞኝ ነሽ። ይልቅ አንድ አቃጣሪ አረብ እየከፈልሽው
ከሚተኛሽ፣ እኔ ያለ ገንዘብ ብተኛሽ አይሻልሽም?» አላት
ፊቷ በቁጣ እሳት መሰለ፣ ግን ድምፅዋ አልተለወጠም
«ወንድ ከሆንክ ሂድና ባሀራምን አቃጣሪ አረብ ነህ በለው። እኔ
ወንድ ስላልሆንኩ የሚገባህን ቅጣት ልሰጥህ አልችልም። ግን ቆሻሻ ነህ፡፡ አንጎልህም ቆሻሻ ነው፣ ሰውነትህም ቆሻሻ ነው። እግርህ ይገማል፣ አፍህ ከሬሳ እኩል ይቆንሳል። አሁን ቤቴ ሳይገማ ተነስና ሂድልኝ አለችው
ተነሳ። ቁጭ እንዳለች ሳታስበው በጥፊ መታት። ከወምበሯ
ተከነበለች። ከወለሉ ላይ በፀጉሯ ጎትቶ እነሳትና እንገቷን ሳማት።
ስትፍጨረጨር እጁን ጠምዞ ወደ አልጋዋ ወሰዳት። አልጋው ላይ
ጣላትና አንድ ጡቷን ጭብጥ አርጎ ያዘ፡፡ መፍጨርጨሯን ተወች
በኣፏ ብቻ

ተወኝ! ብትተወኝ ይሻልሀል!» እያለች ትፎክራለች እጁን ሰደደና ሙታንቲዋን ሊያወልቅ ሲል እንደገና መፍጨርጨር ጀመረች፡፡ ጡቷን የባሰውን በሀይል ዉበጠው:: ፀጥ አለች፡፡ ሙታንቲዋን አወለቀው። እምባዎ ይወርድ ጀመር፡፡ ቁጣዋ
ወደ ልመና ተለወጠ
እባክህ ተወኝ፡፡ ምን አረግኩህ?»
ልመናዋን ከምንም አልቆጠረውም። ጡቷን ጨብጦ እንደያዘ የሱሪውን ቀበቶ ፈታ
አሁንም እምባዋ እየወረዳ «እባክህን ተወኝ፡፡ እርጉዝ ነኝ፡፡
የሁለት ወር ነብሰ ጡር ነኝ» አለችው

የሱሪውን ቁልፍ ይፈታ የነበረው እጁ ባለበት ደረቀ። ጡቷን ይዞ የነበረው እጁ ለቀቃት፡፡ ሱሪውን መልሶ ቆለፈ፡፡ ትቷት ወጣ

አልጋዋ ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ባህራም ደረሰ፡፡ ከጋርደን
እያበሽቀ መምጣቱ ነበር። በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቷን አየ፡፡
እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ ነገረችው
ተናዶ ተካን ፍለጋ ወጣ፡፡ ኒኮል ተከተለችው። ምናልባት
ኣደገኛ ነገር እንዳይስራ ፈርታለች። እሱ በረዥሙ ሲራመድ እሷ
አልደርስበት ብላ ከኋላው ከሩቅ ሱክ ሱክ ስትል፤ ኤክስን አቋርጠው ሲቴ አጠገብ ሲደርሱ ባህራም ተካን አየው፡፡ ጠራው፡፡ ተካ ቆመ፡፡አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ነበር። ባህራም ደረሰና ቃል ሳይናገር በጥፊ መታው። ተካ ቡጢ ሰነዘረበት። ባህራም ጎምበስ ብሎ አመለጠና፡
በፍጥነት የተካን እጅ ይዞ ጠምዞ በሀይል ወረወረው: ከዛፉ ጋር
አጋጨው። ከዚያ በኋላ ተካ ሊካላከል አልቻለም፤ አንጎሉ ዞሮበታል፡ ባህራም እጅ ውስጥ እንደ ህፃን ሆነ። ባህራም ጭንቅላቱን ይዞ ፊቱን
ከዛፉ ጋር ደጋግሞ ደጋግሞ አጋጨው። የተካ ፊት በደም ተበከለ።ኒኮል ደርሳ ባታስጥለው ኖሮ ምናልባት ይገድለው ነበር
#ምንዱባን


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


...ጫጫታ ከሩቅ ተሰማ:: ዣን ቫልዣ አንዱን ቤት ተጠግቶ ለመደበቅ ፈለገ፡፡ ከሩቅ የሚንቀሳቀስ ጥላ ተመለከተ:: ሰዎች ወደ እርሱ ማምራታቸውን
ተገነዘበ፡፡ ተንጠላጥሎ ድምፅ ወደሚሰማበት አቅጣጫ ተመለከተ፡፡ የዣቬርን ግዙፍ ሰውነት መለየት አላዳገተውም፡፡ በፖሊስ ጥንቃቄ ግራና ቀኝ እያዩ
መራመዳቸውን ተመለከተ፡፡ ቆም እያሉ፣ አካባቢውን እየሰለሉ ነው
የሚሄዱት፡፡ የመደበቂያ ሥፍራ እንዳለ ኣጥርተው እንደሚፈትሹ
ያስታውቃል፡፡ ሰፈሩ ማምለጫ መንገድ የለውም::

በዚያ አካሄዳቸው ሥፍራውን እየፈተሹ ሲመጡ ዣን ቫልዣ
ከነበረበት ለመድረስ ምናልባት ሩብ ሰዓት ቢወስድባቸው ነው:: እጅግ በጣም የሚያስጨንቅ ሰዓት ነበር፡፡ በሕይወቱ ዘመን ለሦስተኛ ጊዜ ከአስፈሪ
ሕይወት ጫፍ ላይ የደረሰ መሰለው፡፡ አሁን ያስጨነቀው የእስር ቤት ኑሮ ብቻ ሳይሆን የኮዜት ከእርሱ መለየት ጭምር ነበር፡፡ ሁለት አማራጭ ነበረው፤ የመለኮት ኃይል አውጣኝ ብሎ መማጠን ወይም ባለው ጉልበት
ተጠቅሞ ሰዎቹን መጋፈጥ፡፡
እስር ቤት ባገኘው ልምድ ዣን ቫልዣ ቀጥ ካለ ግንብ፧ ቁመቱ እንደ ፈለገው ቢረዝም እንኳን፤ በቀላሉ የመውጣት ችሎታ አለው:: ከፊት ለፊቱ የነበረውን ግንብ ርዝማኔ በዓይኑ መተረው:: ወደ አምስት ሜትር ገደማ ይሆናል፡፡ በተጠረበ ድንጋይ የተሠራ ግንብ ነበር፡፡
አሁን የምታስቸግረው ኮዜት ስትሆን ኮዜት ከግንብ ላይ መውጣት አታውቅበትም:: ታዲያ ይተዋት? አሳቡ አንገሸገሸው:: እርስዋን ተሸክሞ መውጣት ደግሞ የማይቻል ነው፡፡

መፍትሔው ትልቅ ገመድ እንደሆነ ተገነዘበ፡፡ ግን ዣን ቫልዣ
ገመድ አልነበረውም:: ታዲያ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገመድ ከየት ሊያመጣ ይችላል? በዚያች ሰዓት ዣን ቫልዣ አገረ ገዢ ቢሆን ግዛቱን በአንድ ወፍራምና ረጅም ገመድ ይለውጥ ነበር፡፡

የሚደንቀው አንዳንድ ጊዜ በጭንቀት ሰዓት የሚያስገርም ወይም ዐለማመን የሚያስቸግር ነገር ይሆናል:: ቫንቫልዣ ግራና ቀኙን ሲቃኝ መብራት የተንጠለጠለበት ገመድ አየ:: በዚያን ብርሃን ባልነበረበት ዘመን በጋዝ የሚሠሩ መብራቶች ከፍ አድርገውና የሚሰቅሉትና የሚያወርዱት በወፍራምና በረጅም ገመድ ነበር፡፡

ዣን ቫልዣ ገመዱ ወደ ተንጠለጠለበት ሮጦ በያዘው ቢላዋ ቆረጠው።ቀደም ሲል እንደተገለጸው በተለይ ያን ምሽት ጨረቃዋ ሙለ ስለነበረች
የመንገድ መብራቶች አልተለኩሰም:: ስለዚህ ዣን ቫልዣ ገመዱን ሲቆርጥ ምናልባት መብራቱ ቢሰበር ልብ የሚለው አልነበረም:: ኣካባቢውም ጭር
ያለ ነበር፡፡ዣን ቫልዣ ከወዲህ ወዲያ ሲሮጥ፤ ዓይኑ ሲቅበዘበዝ አሳብ ሲያስጨንቀው በማየትዋ ኮዜት ደነገጠች:: እርስዋ በመሆንዋ እንጂ ሌላ
ልጅ ብትሆንማ ልቅሶዋን ነበር የምትለቅቀው፡፡ የኮቱን ጭራ አጥብቃ ይዛ ዝም ብላ ነበር የምትከተለው፡፡ በአካባቢው የሚሰማው ድምፅ እየጎላ መጣ።

«አባባ» አለች ኮዜት በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ፤ «ፈራሁ፤ ማነው
የመጣው?

«ዝም በይ፤ ዝም በይ» አለ የተከፋው ሰው፤ «ሚስስ ቴናድዬ
ናት፡፡»

የኮዜት ሰውነት በፍርሃት ተንቀጠቀጠ! ሰውዬው ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ ግን ዝም ነው፤ ካለቀስሽ ወይም ድምፅ ካለማሽ ሚስስ ቴናድዬ ትሰማሻለች፡፡ አንቺን ፍለጋ ነው የመጣችው::»

ዣቬርና ሌሎች ፖሊሶች እነርሱ ከነበሩበት ደርሰው ሊይዟቸው
ስለሚችሉ ጊዜ ማባከኑ ይበልጥ የሚያጋልጥ መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ከረባቱን አውልቆ በከረባቱ የኮዜትን ወገብ አሰረ:: ጫማውንና ካልሲውን አውልቆ ከግንቡ ላይ ወረወረ፡፡ የገመዱን አንዱን ጫፍ ከቋጠረ በኋላ ከኮዜት ወገብ
ላይ ከታሠረው ከረባት ጋር አሰረው:: ከዚያ በኋላ የገመዱን አንድ ጫፍ በእጁ ይዞ ከግንቡ ላይ መውጣት ጀመረ:: ኮዜት ከመሬት ሆና ዝም ብላ ታየዋለች:: የሚስስ ቴናድዬ ስም በመጠቀሱ በጣም ስለደነገጠች ለመናገር
ብትፈልግ እንኳን መናገር አትችልም::

ብዙ አልቆየም ወዲያው እጅግ ዝቅ ባለ ድምፅ ዣን ቫልዣ ሲጠራት ሰማች::

«ጀርባሽን ለግድግዳ ስጪ፡፡»

እንዳዘዛት አደረገች::

«እንዳትናገሪ፧ እንዳትፈሪ» አለ ዣን ቫልዣ ቀጠለና፡፡

ከግንቡ ጫፍ ደረሰች:: ወዲያው ዣን ቫልዣ እቅፍ አደረገና በጀርባው መሬት ለቅቃ ስትንጠለጠል ታወቃት፡፡ የት እንዳለች ሳታውቅ አዘላት:: እጆችዋን በግራ እጁ ያዘ፡፡ እንደገመተው ከግንቡ ኋላ ቤቶች
ነበሩ። በውስጥ በኩል የግንቡ ርቀት እስከዚህም ሩቅ አልነበረም:: ርቀቱን በዓይኑ መተረው፡፡

ልጅትዋን እንዳዘለ በቀላሉ ከአንድ ቤት ጣራ ላይ ለማረፍ ቻለ::

ከላይ ሆኖ ከአጥሩ ውጭ የዣቬርን ድምፅ ሰማ፡፡

«በየመንገዱ ፣ በየሥርቻው ቶሎ ብላችሁ ፈልጉት፡፡ በየቤቱ
እየገባችሁ ፈልጉ፡፡ ስለሚደርሰው ነገር እኔ አልፋለሁ» አለ ዣቬር እየጮኸ

ዣን ቫልዣ ከጣራው ላይ ቁጭ አለ፡፡ ኮዜትን በገመዱ አንጠልጥሉ የዛፍ ግንድ ይዛ በመውረድ መሬት እስክትደርስ ጠበቃት፡፡ ኮዜት ጎብዛም
ይሁን ፈርታ ቃል አልተነፈሰችም:: እጅዋን ሲጨብጣት ግን በጣም አልቦአት ነበር፡፡

ዣን ቫልዣ ከጣራ ወርዶ ሲጓዝ ከአንድ የአትክልት ቦታ ደረሰ
አካባቢው በጣም ጭር ያለ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ጫማውንና ካልሲው
መፈለግ ነበረበት፡፡ ጫማውን ፈልጎ ካጠለቀ በኋላ ከኮዜት ጋር ከዛፍ ስር ተቀመጡ፡፡ ምንጊዜም ቢሆን የሚሸሽ ሰው ያመለጠ ስለማይመስለው ሁልጊዜም እንደ ደነገጠ ነው፡፡ ኮዜት ስለፈራች ከጎኑ ተሸጉጠች:: እነዣቬር ከሁንም ሲጠራሩ አሁንም ይሰማል፡፡ ግን ከሩብ ሰዓት በኋላ ድምፁ እየደከመ ሄደ
ቢሆንም የዣን ቫልዣ ልብ አሁንም አልረጋም፡፡ ኮዜትም ዝምታዋን ቀጠለች ከዚህ መጣ የማይባል ድምዕ በድንገት ተሰማ:: የደናግል ዝማሪ ነበር፡፡ ደናግል ተሰባስበው የሚዘምሩት አትክልት ውስጥ ነበር፡፡ ድምጻቸው ጥርት ብሎ ነው የሚሰማው:: ዣን ቫልዣ ይህን ድምፅ ሲሰማ የድምፁ።
አቅጣጫ ፍለጋ ዞር አለ፡፡

ፊቱን ሲያዞር ከአትክልቱ ውስጥ ሰው መኖሩን አየ:: አንድ ሰው
ጎንበስ ቀና ይላል፡፡ ሰውዬው ሥራ ይዞ መሆን አለበት፧ እቃ ከአንድ
ሥፍራ አንስቶ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚወስድ ሰው ጎንበስ ይልና ቀና ብሎ ጥቂት ይራመዳል፡፡ ተመልሶ መጥቶ ጎንበስ ይልና ቀና ብሉ ይሄዳል።

ዣን ቫልዣ ደነገጠ፡፡ ምናልባት ዣቬርና ተከታዮቹ እዚህም ጠባቂ
ያስቀመጡ መሰለው:: ይህ ሰው የእነርሱ አባል ከሆነ «ሌባ፤ ሌባ» እያለ ቢያሲዘኝስ ሲል አሰበ፡፡ የተኛችውን ኮዜት ቀስ ብሎ አንስቶ ግቢው ውስጥ ከነበረው አሮጌ አግዳሚ መቀመጫ ላይ አሳረፋት:: ኮዜት አልነቃችም፡፡
ከኮዜት አጠገብ ተቀምጦ የሰውዬውን እንቅስቃሴ ተከታተለ፡
የቃጭል ድምፅ ይሰማል፡፡ ሰውዬው አንድ ነገር ለማንሳት ጎንበስ ሲል ቃጭሉ ሲቃጨል እኩል ስለመጣ ዣን ቫልዣ ይህ አጋጣሚ ይቀጥል!እንደሆነ ጠበቀ፡፡ አሁንም እኩል መጣ፤ ጨርሶ አልተዛባም:: ሰውዬው
ሲንቀሳቀስ ቃሉ ድምፅ ያሰማል፡፡ ሲቆም ዝም ይላል፡፡ የሚደንቀው!
ደግሞ ሰውዬው ሥራውን ጨርሶ ሲያርፍ ደወሉም ፀጥ ይላል፡፡ የደወሉ ገመድ ከሰውዬው ወገብ ላይ ታስሮ ይሆን?» ሲል አሰበ፡፡
ይህን እያሰላሰለ የኮዜትን እጅ አሻሽ፡፡ እንደበረዶ ቀዝቅዟል፡፡
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በታደለ_አያሌው

“እንደምን አረፈድሽ የኔ እህት?” አለችኝ አንዲት ደርባባ ሴት፣ እንጀ አጋጣሚ በመንገዱ እያለፈች ሳለ እንደ ዋዛ መለስ ብላ እጅ ነስታኝ።

“እግ..እግዚአብሔር ይመስገ” አልሁኝ፣ እንደ መደናገር ብዬ፡ መልኳ እንግዳ አልሆነብኝም:

“ምነዉ በደህናሽ ነዉ፤ ልጅ ይዘሽ በመንገድ ዳር?”

“ደህና ነኝ” አለሁኝ፣ የሴትዮዋን መልክ አስታዋሽ ልቤ ላይ ብቅ ብሎ
ጥልቅ እያለብኝ፡፡ የት እንደማዉቃት ልጠይቅ አልጠይቅ ብዬ ከራሴ ጋር
ትንሽ ተከራከርሁ፡

“ቱናትስ እንዴት ናት?”

ይኸዋ! እሷ ጭራሽ ከእኔም አልፋ ከማንም ሸሽጌ የማኖራትን ገዳሜን
ሳይቀር ታዉቃለች፡ ኧረ ይቺ ሰዉ ማናት?

“አጠፋሽኝ መሰል”

“አይ ማጥፋት ሳይሆ” አልሁ፣ እሷ በዚህ መጠን አዉቃኝ እኔ አላወቅሁሽም ማለቱ ቢያሳፍረኝ፡

“ምነዉ እንኳን” አለችኝ፣ ጭንቀቴ ገብቷት ልትገላግለኝ፡ “ምነዉ
እንኳን ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተዋዉቀን ?”

"አዎ!” አልሁ፣ ነፍሴን እያሳረፍኋት። “እዚያ ነዉ አይደል
የምንተዋወቀዉ ?»

መጣችልኝ፡ የቱናትን ሕክምና ለመጀመር ወደ ዘዉዲቱ ሆስፒታል የገባን ዕለት ማታዉን የተዋወቅናት ሴት ናት ከዳር ሀገር መጥታ፣ እዚያ ዘግናኝ ወለል ላይ ወረፋ ጥበቃ ወር ሙሉ ሕመምተኛ ልጇን ይዛ
መቀመጧን ነግራን እንደ ነበር ሁሉ አስታወስሁ፡ አስታወስኋት
የቀድሞዉ ባሌ መተት አስመትቶብኝ፣ ልጄ እንዲህ ሆኖብኝ ቀረ› ብላ ለእመዋ የነገረቻት ሴትዮ ናት።

እዴት ሆነልዎ ... ማነዉ ... እንዴት ሆነለሽ ልጅሽ?” አልኋት አንቱ
ማለት እና አንቺ በማለት መካከል እየዋለልሁ: አሁን አሁን
ምቸገርባቸዉ ነገሮች አንደኛዉ ይኼ ነዉ፡ በምለማመደዉ የምንኩስና ሕይወት ማንኛዉንም ሰዉ አንቱ ብዬ ማክበር እፈልጋለሁ ግን ደግሞ ቀደም ብዬ አንተ ወይ አንቺ እያልሁ የማዉቃቸዉ ሰዎች ግራ
እንዳይጋቡብኝም እሰጋለሁ።

“መቼም ወረፋዉ ደርሶሽ ይሆናል። ዳነልሽ፤ እንዴት ሆነ ልጅሽ?”
“ወረፋዉስ ደርሶኝ ነበር” አለች፣ በቅጽበት አንገቷን እየሰበረች ክፉ ነገር እንዳትነግረኝ እግዚአብሔርን በልቤ ለመንሁት፡ ልጇ እንደዳነላት ብቻ ነዉ መስማት የምፈልገዉ፡
“አልሆነም” አለችኝ፡፡

“እ?”

“አልዳነልኝም ወረፋዉ ደርሶት እንደ ነገ ተቀጥሮልኝ፣ እንደ ዛሬ
ማታዉን እቅፌ ላይ አረፈብኝ” አለችኝ፣ እንባዋን በሺህ መንታ
እያወረደች፡ የእኔም እንባ መቆሚያ አጣ፡ የልጁ ሁኔታ አሁንም ዓይኔ ላይ አለ፡ ምንም እንኳን ልጇን ገጥሞት የነበረዉ ከቱናት ቀለል ባለ ሁኔታ፣ ያልተመጣጠነ የጭንቅላት የዉሃ መጠን (hydrocephalus) ብቻ
ቢሆንም፣ ሁኔታዉ ግን አንጀት ይበላ ነበር፡፡ እሷም ይድንልኛል ብላ ያን ሁሉ መከራ አይታ በመቀርቷ አንጀቴን በላችዉ፡
“አልቅሼ ያልሞትሁትም አንዲት
ማጽናናት የሚያዉቁበት እናት
አባብለዉኝ ነዉ። አሁን እኮ እንዲያዉም እሳቸዉ ጸበል ጸዲቅ
ካልቀመስሽ ብለዉኝ ነዉ የልጄን ሬሳ ይዤ የወጣሁበትን ከተማ
ከመንፈቅ በኋላ ዳግመኛ የተመለስሁበት ያ ጊዜ እሳቸዉ ባይራዱኝ ኖሮ እኮ የልጄን ሬሳ እንኳን ጭኜ ወደ ሀገሬ መዉሰድ ባልቻልሁ ነበር።ዉለታቸዉ አለብኝ። በምን እከፍላቸዉ ይሆን ብለሽ?”

“እግዚአብሔር ዉለታ አዋቂ ነዉ። ግድየለም፣ እሱ በነፍስ ይክስልሻል”አልኋት፣ የተባሉት ሴትዮ ደግነት እያስቀናኝ፡

“ልመልስስ ብል በምን አቅሜ እቴ! እንዲያዉ የማትቸኩይ ከሆነ
እንዲያዉ ባስቸግርሽ፤ አብረን ሄደን ብናመሰግናቸዉ”

“አይ” አልሁ፣ እሺም እምቢ ማለትም እየከበደኝ፡

“እዚያች ዘንድ፣ ያዉና እኮ ቤታቸዉ: ያ በሰፊ ቆርቆሮ የታጠረዉው ግቢ ነዉ ቤታቸዉ መሆኑን ሰዎች የጠቆሙኝ። ነይ እንሂድ እስኪ እባክሽ”።

የእኔ አስፈላጊነት ባይገባኝም፣ እምቢ ማለት ግን አልቻልሁም፡ እሺ ብዬ ባለ ተሽከርካሪዉን የቱናትን አልጋ እያሽከረከርሁ ተከተልኋት። እሷም ጮራዋ የቱናት ዓይኖች ላይ መፈንጠቋን አይታ አላስቻላትም የራሷን ነጠላ ቀልጠፍ ብላ አውልቃ፣ ራስጌዋ ላይ አጠላችላት።

በነበርንበት የመንገዱ ጠርዝ ትንሽ ተራምደን መንገዱን አቋረጥነዉ።
ከዚያ በማቋረጫዉ ፊት ለፊት ባለዉ ቅያስ ትንሽ እንደ ሄድን በቆርቆሮዉ አጥር የታጠረዉን ግቢ በር አገኘነዉ: ቅድም ቆመንበት ከነበረዉ መንገድ
ዳር ሆኖ የታየዉ አጥር እዚህ ድረስ መስፋቱን አይቼ፣ ‹ምን ዓይነት ሴትዮ ቢሆኑ ነዉ? መቼም ሀብታም መሆን አለባቸዉ ልላት ወደ እሷ ስዞር ፊቷን በሳቅ ሞልታ ጠበቀችኝ፡

“ዝግጁ?” አለችኝ፣ በደስታ እየተፍለቀለቀች

“እኮ ሴትዮዋን ለማመስገን?” አልኋት፣ ድንገት ስለ ተሞላችዉ
የደስታዋ ምንጭ ምክንያት እየፈለግሁለት።

“እ" እንደዚያ ነዉ አዎ ግን ምንም ቢገጥምሽ እንዳትደነግጪ። ዝግጁ ነሽ አይደል ለዚያ?”

“ይቅርታ…”

“ይቅርታ አድርጊልኝ ዉብርስት: ትንሽ ዋሽቼሻለሁ: ዉለታ የዋሉልኝ
ሴትዮ የአንቺ እናት፣ እመዋ ናቸዉ። ይኼ በር ሲከፈትም የምናገኘዉ እመዋን እና የእሳቸዉ ዓይነት ዉለታ ዋዮችን ነዉ በእርግጥ ሌላ ያልጠበቅሽዉ ሰዉም ልታይ ትችያለሽ። ምንም ቢሆን ግን እንዳትደነግጪ” አለችኝ፣ እንደ ማቀፍ ጭምር እያደረገችኝ።

ተለዋዋጭ ሁኔታዋን ሳይ ትክክል አልመሰለችኝም፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የሚጎዳ ነገር ዉስጥ እንደማትከተኝ በነፍሴ አምኛታለሁ ለምን እንደሆነ እንጃ ከቅድሙ ሹፌር ይልቅ እሷን በሙሉ ልቤ ነበረ ያመንኋት የልጄን ተሽከርካሪ አልጋ የሚገፉ እጆቼን ጠበቅ አድርጌ ይዤ፣ የሚሆነዉን ሁሉ
ለማየት ዓይኔን በሩ ላይ ተከልሁ። እኔን ያቀፈችበትም ሆነ በሩን
ለመክፈት የሚገፋዉ እጇ ይንቀጠቀጣል፡ ቀስ አድርጋ ከርፈድ አደረገችልኝ፡ አንድ የጠመጠሙ ቄስ ቀድመዉ ዓይኔ ዉስጥ ገቡ።

አሁንም ቀስ አድርጋ መግፋቷን ጨመር ስታደርግልኝ፣ ወዲያ ወዲህ የሚሉ የሰንበት ተማሪዎችን መለዮ የለበሱ ወጣቶች አየሁ ክፍተቱን
ሰፋ ባደረገችዉ ቁጥር፣ ዓይኔ ዉስጥ የሚገባዉም ሰዉ እየጨመረ እየጨመረ መጥቶ ጨርሳ ሙሉ በሙሉ ወለል አድርጋ ስትከፍተዉ፤አንድ ትልቅ ጉባዔ የሚሞላ ብዙ ሰዉ በግቢዉ ተጥለቅልቋል፡ በተለይም በአንደኛዉ ማዕዘን በኩል በድንኳን ዉስጥ ሰብሰብ ብሎ ወደ እኛ የሚመለከተዉን ሕዝብ ተመለከትሁት ነገሩ፣ ትክክለኛ ጉባዔ ነዉ።

“እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ?” አልኋት ወደ ሰዎቹ እንድንሄድ
የመጎተት ያህል ስትመራኝ። “ጭራሽ እመዋም አለችበት? ባልቻም፣ እሸቴም? ኧረ ምንድነዉ ጉዱ?” አልሁኝ፣ በቀረብን ቁጥር እንደ አዲስ እያላበኝ፡ ዓይኔን ከጫፍ እስከ ጫፍ አንከራተትሁት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ጨምሮ፣ ሦስት ጳጳሳት ከጉባያተኛዉ የፊተኛዉ ረድፍ ላይ
ይታዩኛል፡ የጤና ሚኒስትሯን ጨምሮ አንዳንድ የማዉቃቸዉ
የመንግሥት ባለስልጣናትም መኖራቸዉን አስተዋልሁ: በርከት ያሉ ካህናት፣ የማኅበራችን ዋና ሊቀመንበር፣ ባልቻ፣ እሽቴ፣ እመዋ
ሌሎች የማኅበራችንም ሆነ የሲራክ ፯ አባላት ሁሉ አሉበት።

“እንኳን በደህና መጣችሁ” ሲሉ ተቀበሉን፣ ሁሉም: ያልቆመ
የማያጨበጭብ አለ ይሆን?

“ክቡራንና ክቡራት እንግዶቻችን፣ የጉባዔያችን መነሻ ምክንያቶቻችንም ተሟልተዉ ተገኝተዉልናል እንደ ቆማችሁ ማርያም ትቁምላችሁ እባካችሁ በየመቀመጫችሁ አረፍ አረፍ በሉልን” አለ የመርሐ ግብር
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


....ሚስተር ካርላይል ካገባበት ጊዜ ጀምሮ ፍቅርና ቅናት ሁልጊዜ የሚያኝኳት መቆሚያ የሌለው የልብ ሥር ውጋት እሱን ለማግባት የነበራት ምኞትና ተስፋ ከንቱ ሆኖ መቅረትና በዚህም ምክንያት የተሰማት ኃፍረት ሁሉ በአንድነት ተደራርበው ብጥብጥ አደረጓት " የዚያን ቀን ለሚስቱ ሲገልጽላት የነበረው የፍቅር ጭውውትና የነበራቸውንም ደስታ አብራ በማምሸት በዐይኗ ስለ ተመለከተች ልቧን ሰወራት " ሕይወትን ተወዳጅ ሊያደርግ ከሚችል ነገር ሁሉ እንደ ተገለለች ሆኖ ተሰማት የባርባራና የሚስተር ካርላይል ይህን ያል መቀራረብ በእርሷ ላይ ፎቅር ሲያሳድርባት በሱ በኩል ግን እንደ እህቱ እንጂ እንደ ፍቅረኛ አድርጎ አስቧት
አያውቅም እሷ በሐሳብ ማዕበል ስትንገላታና ስትበጠበጥ የዚያ ሁሎ ሁከቷ ምክንያት እሱ መሆኑን ሊገነዘብ ቀርቶ ችግር እንደ ነበረባት ንኳን አላወቀላትም » ስለዚህ እሷ ሲቃ ይዟት ተጨንቃና ተወጥራ እያለ ብሷቷን ባለመረዳት ያልተጨነቀችበትንና ያላሰበችበትን ርዕስ ጣልቃ በማስባት ፡ « አባትሽ ድርቆሹን መች ያስከምሩታል ...ባርባራ?» አላት።

ዝም አለችው " ስሜቷን ለማዳፈን ከራሷ ጋር ስትተናነቅ ሚስተር ካርላይል መልሶ ጠየቃት ባርባራ . . . አባትሽ ድርቆሹን መች እንደሚያስከምሩት ጠይቄሽ ነበር»

አሁንም አልመለሰችለትም መልሶ መናገር አቃታት ጉሮሮዋ ተላወሰ
የአፏ ጡንቻዎች ተኮማተሩ ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ ቀጠለችና ጮኻ መንሰቅሰቅ ጀመረች "

« ባርባራ ...አመመሽ እንዴ ? ምንድነው ? » አላት

ፍቅር ንዴት በደልና ጭንቀት አንድነት ተደባልቀው ይፈሉባት ጀመር ብርክ ያዛት እምታደርገውን ማወቅ ተሳናት " ሚስተር ካርላይል በከፊል ተሸክሞ በከፊል እየሳበ ከአጥሩ መወጣጫ ሁለተኛው ደረጃ በክንዱ ደግፎ ይዞ አሳረፋት " በዚያ ጸጥ ባለው የለሊት ሰዓት ረብሻ መፈጠሩ ለምን እንደሆነ የገረማቸው
አንዲት አሮጊት ላምና ሁለት ጥጆች ወደ ስዎቹ በመቅረብ ትክ ብለው ይመለከቷቸው ጀመር ።

ባርባራ ከስሜቷ ግፊት ጋር ባላት አቅም ተናነቀች እንባዋ ተገታ መብረክረኳና የአቅል መሳት ምልክቶቿ ለቀቅ አደረጓት " ደግፎ የያዛትን ክንዱን ወዲያ ገፍታ አጥሩ ላይ በጀርባዋ ተደግፋ ቆመች " ሚስተር ካርላይል ወደ ኩሬው ሮጦ ውሃ ለማምጣት ቃጣው " ነገር ግን ውሃ የሚያመጣበት ከባርኔጣው በቀር ምንም ነገር አልነበረውም ።

« ተሻለሽ ... ባርባራ ? ምን ነክቶሽ ነው? » አላት "

«ምን ነክቶሽ ነው? » ብላ ጮኸችበት « እንዲህ ብለህ ልትጠይቀኝ ትችላለህ ? »

« ነገሩ አልገባኝም " እኔ
የበደልኩሽ ካለ በውነቱ በጣም አዝናለሁ »

«እንዴታ ! አይጠረጠርም ታዝናለህ እንጂ !ለመሆኑ እኔ ነገ ካፈር ብገባ» አለችው መሬቱን በእግሯ እየደበደበች « አንተ ምን ቸገረህ ? እኔ ምንድነኝና አንተ አንደ ሆንክ ሚስትህ አለችልህ ? የኔ መከራ የኔ ሥቃይ ለአንተ ምንህ ሆነና? ስማህ አርኪባልድ ካርላይል ... እኔ የአሁኑን ኑሮዬን ታግሸ ችየው ለመግፋት ከመድከም ሙቸ ብቀበር ይሻለኛል " ያለሁበት ጭንቅ ከምችለው በላይ ነው»

«ነገርሽ ያልገባኝ ለመምሰል አልፈልግም » አላት ብስጭት ብሎ « ግን ባርባራ እኔ ላንቺ ከማስብልሽና ከማከብርሽ የበለጠ እንድታስቢ ያደረግሁት ነገር የሰጠሁሽ ፍንጭ የለም»

«ምክንያት የሚሆነኝ ፍንጭ አልሰጠኸኝም ! .. እንዶ ጥላ እየተከተልhኝ ከቤታችን ስትመላለስ ይኸን አምጥተህ ስትሸልመኝ » ካባዋን ጣል አድርጋ የወርቅ ጌጥ መያዣዋን እያሳየችው « ከወንድም የበለጠ ስትቀርበኝ !
«አይ ባርባራ ቁም ነገሩን አሁን ገና አመጣሽው እኔ ላንቺ
ከወንድምነት በቀር ሌላ ነገር በሐሳቤ መጥቶብኝ አያውቅም » አላት በተለመደው ቀጥተኛ አነጋገሩ።

«እንደ ወንድም ብቻ ሌላ ምንም» አለች ድምጿ በስሜት እየናረ " ልትቆጣጠረው የቻለች አትመስልም « አንተ ስለኔ ስሜት ምን ቸገረህ ? የኔን ፍቅር
ለማግኘት ለምን ብለህ ትቸገራለህ ? »

« ባሮባራ . . ረጋ በዪ እስኪ ትንሽ አስተውዬ በርግጥ ላንቺ ንጹሕ የሆነ ጥልቅ ስሜትና አክብሮት አለኝ " እኔ ያላሰብኩት ስሜት ሊያድርብሽ የቻለውም በዚህ የተነሣ ሊሆን ይችላል " ስለዚህ ለኔ ሳይታወቀኝ በሐሳቤ የሌለ ስሜት ላንቺ እንዲታወቅሽ እንዲሰማሽ በማድረጌ በጣም አዝናለሁ »

ጥቂት በረድ አለላት " እየለቀቃት ሔደ " ሁኔታዎችን አመዛዘነች ፊቷን ወደ ሚስተር ካርላይል ቀና አድርጋ ተመለከተች "

« እሷ ከመኻላች ባትገባ ኖሮ ትወደኝ ኖሮዋል ? »

« እንጃ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? እኔ አንቺን እንደ እኅቴ እንደ ንጹሕ ባልንጀራዬ ነበር የማይሽ ስለዚህ ግንኙነታችን ከዚህ ሌላ ምን ሊመስል ይችል እንደ ነበር ለማወቅ አልችልም »

« እኔ ኮ ላንተ እንዳልታወቀህ ሁሉ ለሌላውም ባይታወቀው ኖሮ በቻልኩት ነበር • • •አርኪባልድ »

« በውነቱ በጣም አዝናለሁ - አሁንም ሁሉን ነገር እንደምትረሺው ተስፋ አደርጋለሁ " የዛሬ ማታው ንግግራችንም ከአእምሮሽ ይጥፋ " አሁንም ንጹሕ ባልንጀሮች እኅትና ወንድም እንደሆን እንቀጥላለን " ደግሞ አንቺ የተሰማሽን ግልጽልጽ
አድርግሽ በመናገርሽ ባንቺ ላይ ያለኝን ግምት ምንም አልቀነሰውም »

በግርግሩ አጥር ዘሎ ለመሔድ ያሰበ ይመስል ሊንቀሳቀስ ባርባራ ግን ንቅንቅ አላለችም " እንባዋም ዝም ብሎ ይወርድ ጀመር " በዚህ ጊዜ አንድ ነገር ሰሙ "

« አንቺ ነሽ ሚስ ባርባራ ? »

ባርባራ በጥይት የተመታች ያህል ድርቅ አለች " ከአጥሩ በስተውስጥ የቤታቸው የገረዶች አለቃ የነበረችውን ዊልሶንን አዩዋት ሚስዝ ሔር ጃስፐርን ወደ
ባርባራ ከላከችው በኋላ እሱ እስኪመለስ ድረስ መጠበቅ ስለ አልቻለች እንደገና እሷን ስለላከቻት መምጣቷን ነገረቻቸው " ከዚያ ቦታ ምን ያህል ቆይታ ምን ያህል
ምስጢር እንደ ሰማች አይታወቅም ሚስተር ካርላይል ለራሱ ዐለፈና ባርባራንም
እጅዋን ይዞ አሳለፋት "
« ከዚህ በላይስ መሔድ አያስፈልግህም ይብቃህ ተመለስ» አለችው ቀስ ብላ "

« የለም ከቤት አስገባሻለሁ » ብሎ ክንዱን ሰጣትና ተያይዘው በጸጥታ አዘገሙ " ወደ ማድቤት ከሚያስገባው ከዐጸዱ ጀርባ ካለው በር ሲደርሱ ዊልሰን ቀድማቸው ገባች " ሚስተር ካርላይል ባርባራን እጆቿን ይዞ ደኅና እደሪ ባርባራ » አላት "

ባርባራ ትንሽ አሰበች " ያ ሁሉ ስሜታዊ ንዴት በረደላት የፈጸመችው ነገር ከዕብደት የሚቆጠር አሳፋሪ መሆኑ ታወቃት ሚስተር ካርላይልም ምን
ያህል እንደ ተሰማትገባው

« ይህን ሁሉ ነገር ስናገርህ እውነት አብጀ ነበር መሰለኝ እንጂ በደኅናዬ የነበርኩ አይመስለኝም" አንተ ግን እንዳልተፈጸመ እንዳልተነገረ አድርገሀ ቁጠረው

«ስለዚህ ግድየለሽም ሐሳብ አይግባሽ »
ለሚስትህ አትነግርብኝም ? » አለችው እየቃተተች
«እንዴ ባርባራ ! »
«አመሰግንሃለሁ ደኅና እደር »

እሱ ግን እጁን ይዞ ዝም አለ
«ሰማሽ ባርባራ ፍቅርሽን ከኔ በበለጠ ለመቀበል የታደለ በቅርቡ እንደምታገኝ አምናለሁ።»

«በጭራሽ አልቃጣውም እኔ እኮ በቀላሉ አላፈቅርም ፤ በቀላሎም አልረሳም ከእንግዲህ እስከ ዕድሜ ልኬ ባርባራ ሔር እንደ ተባልኩ እኖራታለሁ እንጂ ባል አግብቼ ሚስዝ እገሌ አልባልም

ሚስተር ካርላይል ስለ ደረሰው ሁኔታ እያሰበ ወደ ቤቱ ገሠገሠ እሷ ባሰበችው መንገድ እሱ ሚስቱን በሚያፈቅራት ዐይነት አይሁን እንጂ ባርበራን ይወዳትና
ያከብራት ነበር " ስለዚህ በባርባራ አነጋገር ኀዘን ተሰማው "
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ


“እንዲያውም የእህትህን ቆንጆ ፀጉር የምትሸልተው አንተ
መሆን አለብህ!” ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ ብልጭ አደረገችና በመልበሻው አናት ላይ መቀሱን አስቀመጠች: “ተመልሼ ስመጣ እህትህ ፀጉሯ ተቆርጦ ካገኘሁ
ብቻ አራታችሁም ምግብ የማግኘት እድል ይኖራችኋል።" ስትል ክሪስ እኔ ላይ፣ እኔም ክሪስ ላይ እንዳፈጠጥን ጥላን ሄደች:...

ክሪስ ፈገግ አለ: “አይዞሽ ካቲ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም።እናታችን በየትኛውም ሰአት ተመልሳ ስለምትመጣ እንነግራታለን፡ አይዞሽ አትፍሪ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም::” ሊያቅፈኝ ወደኔ መጣ፡ “በዛ
ላይ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል አንድ ካርቶን ብስኩትና አይብ መደበቃችን መታደል አይደል? ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ይህንን ስለማታውቅ ለዛሬ ምግብ
ይኖረናል:” አለ።

ድንገት እናታችን ካልመጣች ብለን በመስጋት ያን ዕለት ትንሽ ብቻ በላን።ግማሹን ወተትና ጥቂት ብርቱካኖች አስቀመጥን፡ ይሁንና እናታችን ሳትመጣ ቀኑ አለቀ: ምሽቱን ሙሉ አንዴ ስተኛ፣ አንዴ ስነቃ እንዲችው ስገላበጥ
ሌሊቱ ተጋመሰ፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገኝ አሰቃቂ ቅዠት ይመጣብኛል።ኮሪና ኬሪ ጠፍተውብን ክሪስና እኔ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ በጨለማ ስንፈልጋቸው አየሁ ስማቸውን እየጠራን ብንፈልጋቸውም እነሱ
ግን መልስ አይሰጡንም፡ በፍርሀት ውስጥ ሆነን በጨለማ እየሮጥን ነበር።
በጣም የሚያስጨንቅ ህልም ነበር። ስነቃ ክሪስም መንትዮቹም ተኝተዋል።እንደገና እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ፈለግኩ፡ ልከላከለው ሞከርኩ፡ ቀስ እያልኩ
እየሰመጥኩ እየሰመጥኩ እንደገና ጥልቅ ቅዠት የተቀላቀለበት አስፈሪ ህልም ውስጥ ገባሁ፡ በጨለማ እየሮጥኩ በደም የተሞላ ኩሬ ውስጥ ወደቅኩ ደሙ ልክ እንደሬንጅ ያጣብቃል ሽታውም እንደ ሬንጅ ነው: በአልማዝ ያሸበረቀ፣ጭንቅላቱ የወርቅና አይኖቹ ቀይ የሆኑ አሳ እየሳቀ ደም በደም አደረገኝ፡
ከዚያ ደጋግሞ የሚያስተጋባ ድምፅ “እይ! እይ! ማምለጥ አትችይም!” እያለ ጮኸ፡

ማለዳው ቢጫውን የተስፋ ብርሃን ከዘጋው ከባድ መጋረጃ ጀርባ የገረጣ መስሎ ይታያል፡ ኬሪ በእንቅልፍ ልቧ ወደኔ እየተጠጋች “እማዬ፣ ይህንን ቤት አልወደውም” ስትል አጉረመረመች: ኬሪ ያለ እረፍት ስትገላበጥ ላቅፋት ፈልጌ ክንዴን ለመዘርጋት ብሞክርም ማንቀሳቀስ አልቻልኩም:: ምን ሆኛለሁ? ራሴ ልክ ድንጋይ እንደተጫነ አይነት ከበደኝ፡ ከህመሙ የተነሳ ጭንቅላቴ
ሊከፈል መሰለኝ፡ የእግሮቼና የእጆቼ ጣቶች ላይ ይወረኛል። ሰውነቴ ድርቅ ብሏል ግድግዳዎቹ ሁሉ የተጣመሙ ይመስሉኛል። ሁሉም ነገር ቀጥ ያለ መስመር የለውም።

ከአልጋው ባሻገር ባለው በሚያብረቀርቀው መስተዋት ራሴን ለማየት ሞከርኩ::
ሆኖም የከበደኝን ጭንቅላቴን ዞር ላደርገው ብሞክርም አልንቀሳቀስ አለኝ::ሁልጊዜ ከመተኛቴ በፊት ጭንቅላቴን እንደልብ ማዘዋወር እንድችል ፀጉሬን ትራሱ ላይ እበትነዋለሁ ግማሹ ጉንጬ ላይ ያርፋል: እና ደስ የሚል ሽታውና ልስላሴው በጣም ደስ ይለኛል። የፀጉሬ ጉንጬ ላይ መነስነስ ወደ
ጣፋጭ የፍቅር ህልም ይወስደኛል።

ዛሬ ግን ትራሱ ላይ ፀጉር የለም: ፀጉሬ የት ሄዶ ነው?

መቀሱ አሁንም መልበሻው አናት ላይ እንደተቀመጠ ነው: በድንግዝግዝ ይታየኛል፡ ጉሮሮዬን ለማርጠብ ምራቄን ደጋግሜ ዋጥኩና በግድ ትንሽ ድምፅ
አውጥቼ የክሪስን ስም ተጣራሁ። ወንድሜ ክሪስ እንዲሰማኝ እንዲያደርግ ወደ እግዚአብሔር ፀለይኩ። በመጨረሻ እንግዳ በሆነ ድምፅ “ክሪስ፣ የሆነ
ነገር ሆኛለሁ፡” ብዬ በሹክሹክታ መናገር ቻልኩ። ደካማዎቹ ቃላቶቼ እንዴት እንደተሰሙ ባላውቅም ክሪስን አነቁት ከእንቅልፉ በደንብ ሳይነቃ አይኖቹን እያሻሽ ካቲ ምን ፈልገሽ ነው?” አለኝ።

ከአልጋው ላይ አስፈንጥሮ ያስነሳው የሆነ ነገር አልጎመጎምኩ፡ አልጋዬ
አጠገብ ደረሰ፡ ትንፋሹን ውጦ በድንጋጤና በፍርሀት ድምፅ አወጣ፡

“ካቲ… ወይኔ አምላኬ ሆይ!”

ጩኸቱ በፍርሀት አሳቀቀኝ

'ካቲ ‥. ወይኔ ካቲ" ሲል አቃሰተ።

አይኖቹ እንዲህ በድንጋጤ እንዲፈጡ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ አልታዘዝ ያሉኝን ክንዶቼንና ያበጠ የመሰለኝን ከባድ ጭንቅላቴን ለማንቀሳቀስ
ሞከርኩ፡ እንደምንም እጄን ማንሳት ቻልኩ ከዚያ ለመሰማት የሚችል ጮክ ያለ ድምጽ አገኘሁና የእውነት ጮህኩ። ደግሜ ደጋግሜ ጮህኩ ክሪስ
በክንዶቹ አቅፎ እስኪያባብለኝ ድረስ ልክ አእምሮው እንደተነካ ሰው እየጮህኩ ነበር።

“እባክሽ አቁሚ… እባክሽ” ተንሰቀሰቀ። “ስለ መንትዮቹ ስትይ... የባሰ አታስፈራሪያቸው.
እባክሽ ካቲ አትጩሂ፡ ያሳለፉት
ይበቃቸዋል።እስከመጨረሻው ፈሪ እንዲሆኑ እንደማትፈልጊ አውቃለሁ: ካልተረጋጋሽ
ይደነግጣሉ። እመኚኝ በህይወቴ እምልልሻለሁ። ዛሬ እንደምንም ሬንጁን ከፀጉርሽ ላይ አስለቅቅልሻለሁ "

አያትየው ከእንቅልፌ እንዳልነቃ የሆነ መድኃኒት የወጋችኝን ምልክት ክንዴ ላይ አገኘሁ እና እንደተኛሁ ትኩስ ሬንጅ ፀጉሬ ላይ አፍስሳብኛለች: አንድም
ዘለላ እንዳይቀር ሬንጁን ከመጠቀሟ በፊት ፀጉሬን በደንብ ሳትሰበስበው አልቀረችም።

ክሪስ መስተዋት እንዳላይ ቢከለክለኝም ገፍትሬው መስታወቱ ላይ ተሰየምኩ።
ጭንቅላቴ አስፈሪ ጥቁር ጓል የተቀመጠበት መስሎ ሳይ አፌ በድንጋጤ ተከፈተ በመጀመሪያ የነቃው ኮሪ ነበር የተዘጋውን መጋረጃ ገለጥ አድርጎ ከእሱ
የተሸሸገችውን ፀሀይ ለማየት ከአልጋው ወጥቶ ወደ መስኮቱ እየሮጠ ሳለ ድንገት ሲያየኝ አይኖቹ ፈጠጡ፡ ከዚያ ትንንሽ እጆቹ አይኖቹን ለማሻሽት
ከፍ አሉና ባለማመን እንደገና አተኩሮ ተመልክቶኝ፡-

"ካቲ አንቺ ነሽ?” አለ፡

“አዎ”

“ፀጉርሽ ለምን ጥቁር ሆነ?"
ለዚያ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት ኬሪ ነቃች። “ወይኔ!” ስትል ጮኸች። ካቲ ጭንቅላትሽ ምን ሆኖ ነው?! ትልልቅ እምባዎች ከአይኖቿ ወደ ጉንጮቿ ወረዱ፡ “አሁን ጭንቅላትሽን አልወደድኩትም” ስትል ሬንጁ እሷ
ፀጉር ላይ እንደሆነ ሁሉ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

“ተረጋጊ ኬሪ” አለ ክሪስ በተረጋጋ ድምጽ። ካቲ ፀጉር ላይ ያለው ሬንጅ ነው: አሁን ስትታጠብና ሻምፑ ስታደርግበት ልክ እንደ ትናንቱ ይሆናል፡ እሷ ስትታጠብ እናንተ ሁለታችሁ ደግሞ ቁርስ እስኪቀርብ ብርቱካን እየበላችሁ
ቲቪ ተመልከቱ፡ በኋላ የካቲ ፀጉር ንፁህ ሲሆን ሁላችንም ቁርሳችንን
እንበላለን፡" አለ፡ ስለ ሁኔታችን የባሰ ፍርሀት እንዳይሰማቸው በማለት የአያታችንን ስም አልጠቀሰም ስለዚህ ወለሉ ላይ ተጠጋግተው በመቀመጥ
እርስ በርስ እየተረዳዱ ብርቱካኑን እየላጡ እየበሉ ራሳቸውን በቴሌቭዥን በሚተላለፈው የቅዳሜ ጠዋት የካርቱን ፊልም ውስጥ ከተቱ..

ክሪስ ገንዳው ውስጥ የሞቀ ውሀ ሞላልኝ: በዚያ በሚፋጅ ውሀ ውስጥ ፀጉሬን ደግሜ ደጋግሜ ነከርኩት። ክሪስ ደግሞ ሬንጁ እንዲላላ ለማድረግ ሻምፑ እያደረገ ነበር። ሬንጁ ቢላላም ከፀጉሬ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም:
ጣቶቹ በሚያጣብቀው የሬንጅ ክምር ውስጥ ገቡ። ፀጉሮቼን ሳይነቅል ሬንጁን
ለማውጣት እየሞከረ ነው: ግብግቡ ስላደከመኝ ማሰብ የቻልኩት ስለ መቀሱ ብቻ ነው: አያትየው መልበሻው አናት ላይ ስላስቀመጠችው የሚያንፀባርቅ
መቀስ።

ክሪስ ገንዳው አጠገብ ተንበርክኮ የሬንጁን ክምር ከፀጉሬ ውስጥ ሲያወጣ ሬንጁ በፀጉሮቼ የተሸፈነ ነበር፡ ሬንጁን ከፀጉሬ ውስጥ ለማውጣት ስንሞክር
ከሁለት ሰዓት በላይ ሆኖን ነበር። “መቀሱን መጠቀም አለብህ!” ብዬ ጮህኩ።

“አይሆንም መቀስ የመጨረሻ ምርጫችን ነው” አለ እናታችን ያመጣችለትን የኬሚስትሪ ዕቃዎች በመጠቀም ፀጉሬ ሳይጎዳ ሬንጁን የሚያሟሟ ኬሚካል መቀመም እንደሚችል አስቧል።
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት.

መርቪንም ‹‹ከእዚያ ማጥ ውስጥ ወጥተው በዓይኔ በብረቱ ማየቴ ደስ
ብሎኛል፡ አዩ ጠፉ ሲባል እኛ ክፉ ነገር ደርሶባቸዋል ብለን ነበር የገመትነው በነገራችን ላይ እኔ መርቪን
ላቭሴይ እባላለሁ›› አላቸው:

‹‹ይሄ ጓደኛዬ ባሮን ጋቦን ይባላል፡ በህይወት እንዳመልጥ የረዳኝ እሱ
ነው አሉ ሃርትማንም።

መርቪንም ሁለቱንም ለስንብት ጨበጠና ‹‹ከዚህ በላይ አልረብሻችሁም
ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የተከሰተው ነገር ገርሟት የሚስቱን እግር በእግር መከታተል ተግባር ለደቂቃዎችም ቢሆን ያዘናጉት ሃርትማን
የተባሉት ሰው ታዋቂ ሰው ሳይሆኑ አይቀርም ስትል አስበችና ‹‹ማናቸው እኒህ ሰው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ካርል ሃርትማን በዓለም ታዋቂው የፊዚክስ ሳይንቲስት›› አላት፡ ‹‹አቶምን ለሁለት ለመሰንጠቅ በሚደረገው ምርምር ላይ የሚሰሩ
ሰው ነበሩ፡፡ ከናዚዎች ጋር የፖለቲካ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ስለነበር
ዓለም በሙሉ ከአፈር ተደባልቀዋል ብሎ ነው የገመተው አላት
‹‹ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ፊዚክስ ነበር የማጠናው፡፡ በዚያ ጊዜ ሳይንቲስት ለመሆን ነበር ምኞቴ፡፡ ግን ለዚህ ዓይነት ስራ ትዕግስት አልነበረኝም: ይሁን እንጂ በዚህ መስክ አልተውኩም፡፡ ታዲያ በዚህ የሳይንስ ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት አስደናቂ የሚደረጉትን ግስጋሴዎች መከታተል
ግኝቶች ተገኝተዋል፡፡››

‹‹ለምሳሌ?›› ስትል ጠየቀች ናንሲ፡

‹‹ሊዝ ሜይትነር የምትባል ኦስትሪያዊት ሳይንቲስት ከናዚዎች አምልጣ
በኮፐንሄገን በስደት የምትኖር ተጠቃሽ ናት፡፡ እሷም በምርምር ስራዋ
የዩራኒየምን አተም ባሪየምና ክሪፕተን ወደተባሉ ትንንሽ አተሞች መከፋፈል
ችላለች፡፡››

‹‹አተሞች የማይከፋፈሉ ነበር የሚመስለኝ›› አለች ናንሲ፡

‹‹እስከቅርብ ጊዜ እኛም እንዲህ ነበር የሚመስለን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ራበሳይንስ ትልቅ ግስጋሴ ተደረገ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው የወታደራዊው መስክ ይህን የሳይንስ ውጤት በእጅጉ የሚፈለገው፡፡ ስለዚህ የዚህን ሂደት መቆጣጠር ከቻሉ በዓለም ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል ያለውን ቦምብ መስራት ቻሉ ማለት ነው፡››

ናንሲ እንደ ቆቅ የሚደነብሩትንና ሰውን ሁሉ በፍርሃት የሚመለከቱትን እኒህን ሰው አንገቷን አዙራ አየት አደረገቻቸው፡፡ ‹‹እንዲህ ያሉ ሰው ያለ ጠባቂ ብቻቸውን እንዲሄዱ እንዴት እንደፈቀዱ የሚገርም ነው!›› አለች።

‹‹ብቻቸውን ናቸው ብዬ አልገምትም›› አለ መርቪን እዚያ ፈንጠር ብሎ የቆመውን ሰው ተመልከቺ፡፡,

የመርቪንን የግምባር ጥቅሻ ተከትላ ከመንገዱ ባሻገር አይኗን አማተረች፡ ሌላ ረጅም ቆብ የደፋና
ሙሉ ልብስ ከነሰደርያው የለበሰ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ተመለከተች፡:

‹‹ይህ ሰው የሳይንቲስቱ ጠባቂ ነው ብለህ ትገምታለህ?››

መርቪን ትከሻውን ነቀነቀና
‹‹ነጭ ለባሽ ይመስላል፡፡ ሃርትማን የሚጠበቁ መሆናቸውን አያውቁም ይሆናል፡፡ ሆኖም ጠባቂ ሳይኖራቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ›› አላት፡

hዚህ ቀደም መርቪን ያን ያክል ነገሮችን ይከታተላል ብላ አትገምትም ነበር፡፡

‹‹ቡና ቤቱ ይሄ ሳይሆን አይቀርም›› አለ መርቪን የውይይታቸውን ርዕስ ለውጦ፡፡ በኋላም በሩጋ ደርሶ ቆመ።

‹‹መልካም ዕድል›› አለችው ናንሲ ከልቧ፡ አናዳጅ ባህሪ ቢኖረውም ሰውየውን እየወደደችው እንደመጣች አሰበች፡፡

ፈገግ አለና ‹‹አመሰግናለሁ ላንቺም መልካም ዕድል እመኝልሻለሁ›› አላትና እሱ ወደ ቡና ቤቱ ሲገባ እሷ መንገዱን ይዛ ነጎደች።

ህንጻው ውስጥ አንድ ወጣት የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኛ ወዳለበት እንደነገሩ የተሰራ ቢሮ አየችና ወደ እሱ ሄደች፡
‹‹ወደ ኒውዮርክ ነው የምሄደው ቲኬት ብትሰጠኝ›› አለች፡
‹‹ቲኬት ፈልገው ነው? አልቋል›› አላት

ናንሲ ለወጣቱ ፈገግ አለችለት፡፡ ፈገግ ማለት የቢሮክራሲውን ማነቆ
ሊያለዝብ የሚችልበት ጊዜ አለ፡፡

‹‹አየህ የኔ ወንድም፤ ቲኬት ማለት ብጣሽ ወረቀት ነው›› አለችው
‹የቲኬቱን ዋጋ ልስጥህና አይሮፕላኑ ላይ ጫነኝ አይመስልህም?››

እሱም በፈገግታ ጥርሱን ብልጭ አደረገ፡ የሚችል ከሆነ እንደሚረዳት
ገመተች፡፡

‹‹አይሮፕላኑ ሙሉ ባይሆን እጭንዎት ነበር›› አላት፡፡

“ምን አይነት ነገር ነው! ስትል አጉተመተመች፡ ሰማይ የተደፋባት መሰላት፡፡ እስካሁን የደከመችው እንዲያው ነው እንዴ! ሆኖም ገና እጇን አልሰጠችም፡፡ በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለባትም፡፡

‹‹አንድ የሆነ ነገር መኖር አለበት›› አለች፡፡ ለመኝታ የሚሆን ቦታ ባይኖርም ግዴለም መቀመጫ ላይ እተኛለሁ፡፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች
ወንበር ቢሆንም ግድ የለኝም››
‹‹የሰራተኛ ወንበር ላይ ተሳፋሪ እንዲቀመጥ አይፈቀድም አንድ ያልተያዘ ቦታ ያለው የሙሽሮች ክፍል ብቻ ነው።
‹‹እሱን ቦታ ትሰጡኛላችሁ?›› ስትል ጠየቀች ተስፋዋ ለምልሞ
‹‹ምን ችግር አለ፤ ዋጋው ስንት እንደሆነ አላውቅም እንጂ››
‹‹እባክህ ጠይቅልኝ›› አለችው አስተዛዝና፡

‹‹ምናልባትም የሁለት መቀመጫ ዋጋ ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ማለትም
ሰባት መቶ ሃምሳ ዶላር የመሄጃ ብቻ፡፡ ምናልባትም ይበልጥ ይሆናል› አላት፡፡

ናንሲ ዋጋው ሰባት ሺ አምስት መቶ ዶላር ቢሆን ግድ የላትም፡፡ ‹‹ባዶ ቼክ እሰጥሃለሁ የፈለከውን ዋጋ መሙላት እንድትችል›› አለች በጉጉት ‹‹ነገ ኒውዮርክ መድረስ የምፈልግበት ብርቱ ጉዳይ አለብኝ›› አለች
የምትሄድበትን ጉዳይ ለመግለጽ ከዚህ የተሻለ አባባል አጥታ፡

‹‹እስቲ ካፒቴኑን ልጠይቅ›› አለ ወጣቱ ‹‹ከኔ ጋር ይምጡ፣ የኔ እመቤት››

ናንሲ የመወሰን ስልጣን የሌለው ሰው ጥረቴን ሁሉ መና ያስቀርብኝ
ይሆን ብላ እየሰጋች ሰውየውን ተከተለችው ምን ምርጫ አላት፡

አንድ ፎቅ ላይ የሚገኝ ቢሮ ውስጥ ገቡ፡፡ ቢሮው ውስጥ ሲጋራ እያጨሱና ቡና እየጠጡ የአየር ጠባይ ሁኔታ ቻርት ይዘው የሚወያዩ ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ የአዘቦት ልብሳቸውን የለበሱ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አሉ፡፡ ወጣቱ ሰራተኛም ናንሲን የአይሮፕላኑ ካፒቴን መርቪን ቤከር ጋ ወስዶ አቀረባት፡

ወጣቱ ሰው ‹‹ካፒቴን ወይዘሮ ሌኔሃን ወደ ኒውዮርክ የሚያስኬደኝ
ብርቱ ጉዳይ ስላለኝ የሙሽሮችን ክፍል ዋጋ ከፍዬም ቢሆን እሄዳለሁ እያሉ ነው፡፡ እንውሰዳቸው?›› ሲል ጠየቀ፡

ናንሲ የካፒቴኑን መልስ በጉጉት ጠበቀች፡፡ ካፒቴኑም ‹‹ወይዘሮ ሌኔሃን
ባለቤትሽ አብሮሽ አለ?›› ሲል ጠየቃት፡

‹‹ባለቤቴ ሞቷል ካፒቴን››
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


የቀይ አፈር መንደር ገና እያዛጋች ነው፡፡ ካርለት ጥቁርና ቡናማ ቀለም ያለው የፍዬል ቆዳዋን ለብሳ አንባሯን ጨሌዋን
አንገቷ ላይ ደርድራ ቀለበቶችዋን በጣቶችዋ ሰክታ ጥልፍልፍ ነጠላ
ጫማዋን ተጫምታ
እቃዋን በጀርባዋ በማዘል ከከተማው ቁልቁል
በሚወስደው መንገድ ትንሽ ሄደችና ሰፊውን የአርባምንጭ መንገድ
ትታ ወደ ግራዋ በመታጠፍ ወደ ዲመካ የሚወስደውን ጎዳና ይዛ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

በሾላ ቆንጥር ዘረማይ ሶውት• ዲሎ ጉርዶ  ሶቆላ… የተሞላውን ጫካ ግራና ቀኝ እያየች የድርጭት ጭልፊት ቁራ
አቲ ሴሌ አርክሻ… አዕዋፍ ዝማሬ እያዳመጠች ልቧ በደስታ እየዘለለ ነጎደች፡፡

የእግር ጉዞ ትወዳለች፡፡ አቀበት ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ! ላብ በጀርባዋ ተንቆርቁሮ, ሰውነቷ ዝሎ. ካሰበችበት ስትደርስ
የአሸናፊነት ስሜት  ይሰማታል፡፡ በራሷ ትኮራለች ህይወቷ ይታደሳል፤ ልቧ በደስታ ይዘላል።

በተለያዩ ቦታዎች ተራራ ወጥታለች በበረሃ አሸዋ
ተጉዛለች በበረዶ ተንሸራታለች ስለዚህ አካሏ ብቻ ሳይሆን የህሊናዋ ጡንቻም ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ ነው።

በሰዓት በአማካይ ከአራት እስከ አምስት ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች፡፡ ከቀይ አፈር መንደር እስከ ዲመካ ያለው ርቀት ሃምሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ሃምሳውን ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ይፈጅባታል፡፡ በየመካከሉ ግን እረፍት
ማድረጓ ስለማይቀር የመድረሻ ሰዓቷ በሁለትና ሶስት ሰዓት ይጨምር ይሆናል፡፡

የለበሰችው የሐመር ባህላዊ ልብስ አምሮባታል፡ ከኋላዋ በኩል የለበሰችው ቆዳ ውን ውን የሚል ሲሆን ከፊት ለፊቷ ግን አጭር ነው፡ ጭኖችዋ ለፀሐይ እንብዛም ተጋልጠው ስላልከረሙ እንደ ፋርኖ ነጭ ሆነው ያስጎመጃሉ፡፡ አንድ ወቅት ፀሐዩ ጠብሷቸው እንሶስላ መስለው ነበር፡፡

በየመንገዱ የሚያገኝዋት መንገደኞች እንግዳነቷን ገምተው ተደንቀው ቆም ብለው ሲያይዋት

ነጋ ያ” ትላቸዋለች፡

ጋ ያኒ" ይሏታል፡፡

“ነኖኖምቤ ቀለሎምቤ
ፈያዎ…" በነጭዋ ሐመር
ይገረማሉ፡ በደስታም ፈገግ ይሉና፡“ፈያኔ! ያ ፈያዎ! ይሏታል፡ ሰላምታዋን አቅርባ ከብቶች… ደህና ብላ ስትጠይቃቸው፡፡ እነሱም የእሷን ደህንነት ሲጠይቋት፡-

“ኢንታ ፊያዋ…” ብላ መንገዷን ትቀጥላለች፡እነሱም በአይናቸው ይሸኝዋታል፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰላምታ ከተለዋወጡ ደህንነታቸውን ከተነጋገሩ በኋላ፡

“ናቢ ናሞ አይኔ? ይሏታል ስምሽ ማነው ለማለት በሐመርኛ፡፡

“ኢንታው! ፈገግ ትላለች የእኔ  ስም በማለት፡፡ እየሳቁ
እራሳቸውን ሲወዘውዙ፡

ናሞ አይኔ ካርለት ስትላቸው ይከብዳቸዋል፡ እንደገና
እየደጋገመች የእኔ ስም ካርለት ነው፡" ትላቸውና ተጨዋውተው
ደሞ ይለያያሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንዲያውም ከደስታቸው ብዛት ሮጠው ሄደው በለሻ ወተት ይዘውላት ይመጣሉ፡ እነሱ ዘንድ እንድትውል
እንድታድርም ይጠይቋታል፡፡ “ምነው እዚች ምድር ያለው ሁሉ እንደእናንተ ቅን በሆነ! ብቻ ግን ሁሉም እንዲህ ቢተዛዘን ምናልባት
የህይወት ጣምናውን መግለጽ ይከብድ ይሆናል" እያለች ታስባለች፡፡

ስለዚህ ደግነታቸው  አቀባበላቸው ሞራል ስለሚሆናት ስትጓዝ ድካም አይሰማትም፡፡ ላብ ብቻ፡፡ የትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ
ማለት ብቻ… ውስጧ ግን ብርቱ ነው፡፡ ብረት ሞራሏም እንደአለት ጥንካሬው እያደገ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ hብቶችን የሚጠብቁ አፍላ ጎረምሶች
ያጋጥሟታል፡፡መፉቂያቸውን አፋቸው ውስጥ ሰክተው
የሚያብለጨልጭ ጭናቸውን ሳንቃ ደረታቸው ላይ ጨሌያቸውን
ያንዠረገጉ ይቀርቧትና ሞቼ ጉምዛ ክሮጃ  መፋቂያ  ጨሌ ይሸልሟትና፡-

“እጮኛ አለ?” ይሏታል፡፡

“አዎ!” ትላቸዋለች፡፡

“ሐመር ነው?”

“ከዎ፡፡

“ማን ይባላል?"

“ደልቲ ጉልዲ…"

“ይእ- አንች ነሽ ነጭዋ ሐመር?"

“አዎ"

ካርለት የምትባይው አንቺ ነሻ?

“አዎ-” ይገረሙና
“አንችንማ በስም የማያውቅ ማን አለ! ይእ!.." ሲሏት ካርለት ደስ ይላታል፡፡

ቀኑ እንኳን መሽቶ ከጨለመ በኋላ ሲያገኝዋት ጠጋ ብለው ያነጋግሯትና ሽኝተዋት ይመለሳሉ፡፡ በዚህ በጉዞው ወቅት ቀበሮ
ጅብ… ሲጮሁ ይሰሟታል፡፡ ግን አልፈራችም፡፡ አውሬዎች የሚያጠቁት ፊሪን ነው፡፡ የዓላማ ዕፅት ያለውን ያከብሩታል፡፡

ካርለት ዲመካ ለመድረስ ወደ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲቀራት ደከመች፡፡ በሐመር ባህል ልጃገረድ በምሽትም ሆነ
በቀን ብትጓዝ የሚደፍራት እንደሌለ ጠንቅቃ ታውቃለች:: ስለዚህ
በጉዞዋ ብትቀጥል የሚያሰጋት ነገር የለም፤ ድካሙ ሲጠነክርባት ግን
አንድ በቆሎ እርሻ ውስጥ ገብታ ለወፍ: መጠበቂያ ከተዘጋጀው ማማ ላይ ወጣች ትንሽ ብስኩትና ቼኮሌት ተመግባ በኮዳ ከያዘችው ውሃ ተጎንጭታ “ስልፒንግ ባጓ" ውስጥ ገብታ ከዋክብትን እያየች,
ተወርዋሪ ኮቦችን እየቆጠረች የእንቁራሪቶችን የኮኮሮችን ዝማሬ
እያዳመጠች እንቅልፍ እያባበለ ይዟት ጭልጥ አለ

ካርለት ከእንቅልፏ ስትነቃ ለጊዜው የት እንዳለች ድንግርግር አለባት፡፡ አይኖችዋን ከድና ስታስብ ከየት ተነስታ ወዴት
እንደምትጓዝ መቼ እንደደከማትና ማማው ላይ እንዴት እንደወጣች
ትዝ አላት፡ ራቅ ብለው ጎረምሶችና ህፃናት ይጫወቱ ነበር፡፡ ከማማው
ለመውረድ ስትሞክር ግን ሁሉም ዘወር ብለው አይዋት፡፡ ሻንጣዋን
ማማው ላይ ይዛ መውጣቱ ስለከበዳት ማማው ስር ነበር ጥላው የወጣችው፡ ማማው ከመንገዱ ብዙም  ስለማይርቅ እሷንም ሆነ
እቃዋን ብዙ ተላላፊዎች እያዩ ነው ያለፉት፡፡ ሐመር ውስጥ ግን የአንዱን ንብረት ሌላው አይነካም ወድቆ እንኳን ቢያገኝ ዛፍ ላይ
አንጠልጥሎት ይሄዳል፡፡ የጠፋው ተመልሶ እንዲያገኘው

ካርለት ልጆችንና ጎረምሶችን ሰላም ስትል አንድ ልጅ እግር ከቡዱኑ ነጠል ብሉሎ ሄደና፡-

“አይቶ!  እረ ኦይቶ" ብሎ ተጣራ፡፡

“ዬ!” የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡
“ይዘሽው ነይ እንግዳዋ ልትሄድ ነው" ሲል በሐመርኛ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ካርለት ሰንደል ጫማዋን ቆልፋ ሳትጨርስ
አንዲት ልጃገረድ በዛጎልና ጨሌ የተዋበውን ቆዳዋን እያንሿሿች በቀጭኗ መንገድ እየሮጠች መጣች፡፡ በእጅዋ የወተት መያዣ ዶላ በሾርቃ ደግሞ የማሽላ ጭብጦ ይዛለች፡፡
ካርለት ልጃገረዷ ወደ እሷ ስትመጣ በአድናቆት
ተመለከተቻት፡፡ ኦይቶ ሰላም ብላት የወተቱን ዶላ ሰጠቻት፡፡ በሐመር ባህል የቁጥ ቁጥ ስጦታ የለም ያን የምታውቀው ነጭዋ ሐመር ዶላውንና ሾርቃውን ተቀበለቻት፡ ርቧታል፡፡ የዶላውን ክዳን ደፍታ
በ“ዶንግ" የታጠነውን ትኩስ ወተት በክዳኑ ቀዳቸና አንዱን ለጥሟ ጠጣች፡ ከዚያ ጭብጦውን በወተቱ እያማገች በላችና፡-

“ባይሮ ኢሜ” እግዜር ይስጥልኝ ብላ አመስግና ዶለውንና ሾርቃውን ለልጃገረዷ መልሳ ሁሉንም ተሰናብታ አሁንም “ሁላችንም ምን ነበረ እንደ እናንተ ብንሆን! ብላ እየተመኘች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ወፎች ይዘምራሉ እሷም ትዘምራለች ከብቶች ያገሳሉ
ተፈጥሮም እንዲሁ. የሙዚቃው  ህብረ ዜማ ተዋህዶ በሐመር
ቀዬዎች ያስተጋባሉ አይ ሕይወት! ተፈጥሮ የቃኘችው የህይወት
ለዛ.... ሳያቋርጥ እንደ ምንጭ ውሃ ከአድማስ አድማስ ይንቆረቆራል።

ምህረትየለሽ ቴክኖሉጂ አየሩን ከመበከሉ
ስግብግብነትንና ጦርነትን ከማስፋፋቱ ሌላ ተፈጥሮን ሊያዛባ አሁንም ባልተዳረሰበት ሁሉ ሃዲዱን ዘርግቶ ባህላዊ ህይወትን ሊጨፈልቅ ወደ ሐመር ሲምዘገዘግ ታያት፡፡

“አይ አፍሪካ! አለች ካርለት ከግብፅ እስከ ደቡብ አፍሪካ፧.ከኢትዮጵያ እስከ ሞሪታንያ ያሉትን የአፍሪካ አገሮች እያሰበች፡፡
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_አራት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ከደብረብርሀን ከተመለስኩ በአራተኛው ቀን ይመስለኛል ማታ ከስራ ተመልሼ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ለመተኛት እየተገላበጥኩ ሳለ ልጄ ደወለች..አነሳሁና ስለእናቷ ስለቤተሰቡ ብዙ ብዙ ነገር ካወራን በኃላ

‹‹እናት…እናትሽ ከመጣች በኃላ እኮ ያቺን ነገር መላክ አቆምሽ››ስል ወቀስኳት

‹‹ምንድነው አባዬ?››

‹‹የእናትሽን ደብዳቤ ነዋ….ነው ወይስ ነጠቀችሽ?››

‹‹አይ አልነጠቀቺኝም እኔው ጋር ነው. ያለው...ግን እኮ አንድ ገፅ ብቻ ነች የቀረቺው..እሷን አሁን እልክልሀለሁ››

‹‹እሺ የእኔ ማር …እጠብቃለሁ..ደህና አደሪልኝ››

ከተሰናበትኳት ከ10 ደቂቃ በኃላ ቃሏን አክብራ የመጨረሻ ያለችውን ቅጠል በተለመደው መንገድ ላከችልኝ..እስኪ ከመተኛቴ በፊት የሪቾን የመጨረሻ ኑዛዜ አብረን እናንብባት፡፡
 
ሀምሌ 20/2008 ዓ.ም
ተስፋ መቁረጥ ብቻም ሳይሆን እግዚያብሄርን በጣም ነው የተቀየምኩት…. ወደ እዚህ ጉድ ከመግባት  እንዲታደገኝ እቤቱ ተመላልሼ አቧራ ላይ እየተንከባለልኩ ብዙ ቀን ተማፅኜዋለሁ…. በመሰናክሉም ተሰናክሎ ላለመውደቅ ያቅሜን ያህል ሞክሬያለሁ፡፡

የማላፈቅረውን ሰው በተክሊል እስከማግባት ድረስ ሄጄለሁ፣እኔ ይሄንን ሁሉ ስጥር እግዚያብሄር ምን ረዳኝ…..?እንደውም በተቃራኒው ላልተገባ ሀጥያት አሳልፎ ሰጠኝ……..ምንአልባት ጥንቱን ሲፈጥረኝ ለሲኦል አጭቶኝ ስለሆነ ይሆናል….ስለዚህ እጅ ሰጥቼያለሁ……በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ ህይወቴ ያለኝ ተስፋ ፈርሶል፡፡አሁን ነፍሴ ሴይጣን ይንገስባት….. በተሰነካከለ ተስፋዬም  ዳቢሎስ ይደሰትበት ብዬ እራሴን ረገምኩ……
ከዛ በሃላ ብቸኛው ያስጨነቀኝ ጉዳይ የቤተሰቦቼ ሀዘን ነው…የእናቴ ቅስም መሰበር ነው…..እና እንደፈራሁትም በክስተቱ ቤተሰቦቼ የመጨረሻውን  ሀዘን አዘኑ ..እናትና አባቴ የ30 አመት ትዳራቸውን በተኑ……በወቅቱ ሁሉን  ነገር ጣጥዬ እራሴን ለማጥፍት  ወስኜ ነበር……ግን  ደግሞ ፈራሁ ..የፍራቻዬ ምክንያት ደግሞ የሚያስቅ ነው…‹‹ከሞትኩ በኃላ   እዬቤ ቢናፍቀኝስ…..?እውነት ይሄ ልክፍት ነው…፡፡አንድ የሁለት ልጆች እናት የሆነች  ባለ ጤነኛ አዕምሮ ሴት በሆነ ችግር እራሷን ለማጥፋት ስትነሳ ሊያሳስባት የሚገባው የመጀመሪያው ነገር ‹‹እኔ ከሞትኩ በኃላ ልጆቼ እንዴት ይሆናሉ?›› የሚለው ስጋት መሆን ነበረበት፡፡እኔ ግን ፈፅሞ እንደዛ አይት ሀሳብ አላስጨንቀኝም
…….ስላማያስጨንቀኝ ግን አፍራለሁ….እውነትም በጣም አፍራለሁ፡፡
በዛ መወዛገብ ውስጥ እያለሁ እዬብ የተአምር አባት እንደሆነ ሲያውቅ ማቄን ጨርቄን ሳይል እብስ ብሎ ጠፋ …ለአንድ ወር ፈለኩት እስከሀለማያ ሄጄ ፈለኩት…አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም አይደል የሚባለው…ሊገኝ አልቻለም፡፡
በቃ ሁሉን ነገር ጣጥዬ በደስታ ሳይሆነ በሀዘን ተቆራምጄ..በተስፋ ሳይሆን  በተሰባበረ ልብ ወደአሜሪካ ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡   ……አዎ እራሴን ማጥፋት ካልቻልኩ እራሴን መርሳት አለብኝ …እራስ ለመርሳት ደግሞ አሜሪካ ምቹ ቦታ ትመስለኛለች፡፡አዎ እዛ ሄጄ እራሴን በስራ እጠምዳለሁ ……ልክ ከአሜሪካ ሮቦቶች ማካከል እንደአንዱ እሆናለሁ ……በቃ ከሶስት ቀን በኃላ ሁሉን ነገር ጣጥዬ የፈረሰ ተስፋዬን እና የቆሰለ ልቤን ይዤ ወደአሜሪካ… እዛ እንደረስኩ ከምፈታው ባሌ ጋር እበራለሁ..

እዚህ ላይ ሪች ብዙ ነገር ሸፋፍና እና በጥቅሉ ጠቃቅሳ  አልፋቸዋለች…. ለዛውም ዋናውን አስኳል  ነገር ..እርግጠኛ ነኝ ሰለዛ ስታስብ  እእምሮዋ ከተገቢው በላይ እየተጨናነቀባት አስቸግሯት በምልሰት እያስታወሰች መፃፍ ከብዶት መሰለኝ እንደዛ ያደረገቺው፡፡
እኔና ሪች ለመጀመሪያ ጊዜ  ወደ ጻታዊ ግንኙነት ሰተት ብለን የገባናው ካገባች ከ10 ኛው ቀን በኃላ ነው፡:፡ሰርጉ አልፎ እኛ ቤትም መልስ ተጠርተው  ከተመለሱ በኃላ  እና ቤታቸው  ገብተው ኑሮን አህድ ብለው እንደጀመሩ መስፍኔ  አንድ ጎጃም ፍኖተሰላም ሚኖሩ አጎቱ ሞተው መርዶ ተነገረው፡፡
ከመሄዱ በፊት እኔን በአካል አግኝቶኝ በከፍተኛ አደራ ሪችን እንዳስተዳድራትና ቀንም ቢሆን ብቻዋን እንዳልተዋት በልመና ተማፀነኝ‹‹በሬ ከአራጁ ይውላል ይሎችኋል እንዲህ አይነቱን ነው››

…ለአስራአምስት ምናምን አመት  አንድ አልጋ ላይ አብረን ተኝተን ምንም ያላደረግን ሰዎች..ይሄው ከሰርጎ በኃላ አብረን በተኛን በመጀመሪያው ቀን እንዲህ  የሰማይ መስኮት ተከፍቶ የጥፋት ዘንዶ በላያችን ተጠመጠመ… ከሲኦል ድንገት የተረጨ ሚመስል የመርገምት እሳት ሁለታችንንም ለብልቦ አቃለጠን፡፡
.በመጀመሪያ ቀን ወሲብ ፈፅመን ነግቶ በማግስቱ ስንነሳ  ከመተፋፈራችን የተነሳ አይን ለአይን መተያየትም ሆነ ቃል አውጥተን ምንም  ነገር ማውራት አልቻልንም ነበር…፡፡ሁለታችንም ቀኑን ሙሉ በፀፀት ስንብሰለሰልና  እና ግራ በመጋባት  ደንዝዘን  ነበር የዋልነው…፡፡

የሚገርመው ግን መሽቶ መልሰን ስንተኛ መልሰን ተመሳሳዩን ከመፈፀም እራሳችንን መግታት አልቻልንም…፡፡በአጠቃላይ ጥቅምት ላይ የዩኒቨርሲቲ ትመህርት ተከፍቶ  ተመልሼ ወደ አለማይ እስከምሄድ ድረስ ከሰባት ወይም  ስምንት ቀን በላይ ፍቅር ሰርተናል፤እና ደግሞ በስድስተኛው ወር ሊጠይቁኝ ሀለማያ ድረስ ከመስፍኔ ጋር  መጥተው እራሱ እሱን   ለሆነ ሰዓት ሸውደን ለብቻችን የመንሆንበትን ሁኔታ በማመቻቸት  ፍቅር ሰርተናል፡፡ስሜቱ አስቀያሚ  ግን ደግሞ በጣም ጣፋጭ ነበር..በተለይ መስፍኔን ፊት ለፊት ማየት ልብን ይሰብራል.፡፡
የሚገርመው ደግሞ በጣም ብዙ ብዙ ቀናት እሷ መሀል ሆና ሶስታችንም በአንድ አልጋ ላይ አንዳችንን በግራ እጇ ሌላችንን በቀኝ እጇ  እያቀፈች ብዙ በጣም ብዙ የመሳቀቅ ለሊቶችን እንድናሳልፍ አድርጋናለች…አይ ወንዶች በፍቅር አይናችን ከተጋረደ እኮ በቃ በጣም የዋህና ገራሞች ነን፡፡ከዛ ያው እሷ  እንደነገረቻችሁ የአሜሪካው ጉዳይ መጣና ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ምናምን ተባለ ሁሉን ነገር አደፈራረሰው..ሀጥያታችንን ፀሀይ ላይ ተሰጣ…..ሁሉ ነገር እንደምታውቁት ሆነ፡፡

ይቀጥላል
#ባል_አስይዞ_ቁማር
:
:
#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

በማግስቱ ነው…እሷ ገንዳ ውስጥ ገብታ ትዋኛለች እሱ እየሠረቀ ይመለከታታል..
‹‹ለምን ገብተህ አብረሀት አትዋኝም?"
"አብረሀት ማለት?"ስኳር ሲሰርቅ እንደተያዘ ህፃን በርግጎ ጠየቃት፡፡

"እንዴ በአይንህ እኮ ዋጥካት"

"ስርዓት ያዢ እንጂ… የራስሽው ጓደኛ መስላኝ?"

"እሱማ እዚህ ከመምጣታችን በፊት ነዋ ..አሁንማ ቀማሀኝ..ለማንኛውም ይመቻችሁ"አለችውና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ጉንጩን ሳመችውና መራመድ ጀመረች፡፡
ደንግጦ"እንዴ! ወዴት ነው?"

"እግሬን ላፍታታ"
‹‹ልከተልሻ"አለ ከመቀመጫው እንኳን ለመንቀሳቀስ ሳይሞክር

"አይ ብቻዬን ይሻለኛል ››

‹‹ እሺ እዚሁ እንጠብቅሻለን›› ብሎ ሸኛት...ደስ አለት።ደስ ያለት ተንኮል ስላሠበች ነው።

ትንሽ እራቅ እንዳለች እንዳያዮት ተጠንቅቃ በዛፍ ተከልላ ተጠማዘዘችና ወደመኝታ ክፍል አመራች፡፡ ...እንደደረሰች  ልብሷን ቀያየረች ።ሻንጣዋን አዘጋጅታ ።ከቦርሳዋ  ዘወትር እንደምታደርገው እነዛን የድመት አይን የመሰሉ ካሜራዎችን ድብቅ ቦታ አስተካክላ አስቀመጠች..ወደጊፊቲ ክፍል ስትሄድ ፅዳቷ እያጸዳች ነበር፡፡

‹‹…ይሄንን ቻርጅ ከጎደኛዬ ተውሼ ልመልስላት ነበር..››አለችና ዝም ብላ ገብታ ኮመዲኖ ላይ ቻርጁን አስቀመጠች… የእሷን እይታ በሰውነቷን ጋርዳ እዛው ኮመዲኖ አጠገብ ካለ የቴሌቪዥን ጠርዝ ላይ የካሜራውን አይን ለጠፈችው….መልሳ ቻርጀሩን አነሳችና‹‹እንደውም ሀሳቤን ቀየርኩ እስክትመጣ ብጠቀምበት ይሻላል›› ብላ ወጥታ ሄደች….ቀጥታ የመኪናውን ቁልፍ እያወዛወዘች ወደ መድሀኔ መኪና ነው ያመራችው..ከፈተችና ገባች… መኪናውን አስነስታ ኩሪፍቱን ለቃ ወጣች ።30 ደቂቃ ከነዳች በኃላ ስልኳን አወጣችና…፡፡
‹‹መኪናህን ይዤ ከጊቢ ወጥቼያለሁ ከሁለት ሰዓት በኃላ እመለሳለሁ ››ብላ መልዕክት ላከችለትና ስልኳን አጠፍችው።
////
አዲስአበባ ገብታ እቤቷ ከደረስች በኃላ ነበር. ስልኳን ስትከፍት ሰዓቱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር ..ከከፈተች ከአስር ደቂቃ በኃላ ተደወለላት።

‹‹አንቺ የት ነሽ?››

"እቤቴ›››

‹‹ ማለት?"

"እቤቴ ነዋ.. አዲስአበባ..."
" ግን ጤነኛ ነሽ...?ምን ሆንኩኝ ብለሽ ነው?"ከንዴቱ ብዛት ድምፁ እየተቆራረጠ እና እየተርገበገበ ነበር..፡፡
"ምንም ..አሰኘኝ አደረኩት ..ለማንኛውም ለሹፌርህ ነግሬልሀለው...አሁን እቤት መጥቶ መኪናህን ወስዷል …ጥዋት እስከሁለት ሰዓት ይደርስልሀል፡፡"

"በጣም ታበሳጪያለሽ…  እኔስ ይሁን አንዴ ፈርዶብኛል.. የሠው ሠው ከቤቷ አክለፍልፈሽ አምጥተሽ  ባዶ ሜዳ ላይ ጥለሻት ትሄጂያለሽ?››

"ባዶ ሜዳ ላይ አይደለም  አንተ ላይ ነው ጥያት የመጣሁት...አንተ ማለት ደግሞ እኔ ነህ...ምነው ተሳሳትኩ እንዴ?››
"አሽሟጠጥሽ ማለት ነው...በይ ቻው"ብሎ ጠረቀመባት ።

እሷ ግን ሁሉም ነገር በእቅዷ መሠረት እየሄደ ስለሆነ  ደስ አላት።
///
"ሶስት ሰዓት የጀመረች ይሄው እስከአራት ሰዓት ተኩል ላፓቶፖን  አስተካክላ ወደክፍላቸው እስኪገብ እየጠበቀች ነው። ‹‹ውይ ተመስገን››አለች…
የጊፍቲ ክፍል ተከፈተና ገባች ...የእሱም ተከፈተ ገባና ዘጋው።ልዩ መልሳ ተበሳጨች…፡፡እቅዴ አልሰራም ወይም ግምቶ ትክክል አልነበረም፡፡ በተለይ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ወደ ክፍላቸው ሳይመለሱ መቆየታቸው ተስፍ ሰጥቷት ነበር ፡፡እነሱ ግን ይሄው ጨዋነታቸውን እንደጠበቁ በየክፍላቸው ገቡ..፡፡ይሄ ጉዳይ ደግሞ ልዩን ተስፋ ሲያስቆርጣት …የእሷን ላፕቶፕ ሀክ በምድረግ እሷንም ሰደሬ ያሉትን እነጊፍቲንም እየተመለከተ ያለው ቃል ደግሞ ፈገግ አለ፡፡
ልዩ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ… ››ብላ ትኩረቷን መድሀኔ ክፍል ውስጥ ትኩረት ደረገች፡፡ እሱ ላይ ምንም የመረጋጋት መንፈስ አይታይበትም፡፡ ዝም ብሎ ወለሉ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሠ ደቂቃዎችን አሳለፈ... ጊፍቲ ምንም የሚነበብባት የተለየ ስሜት የለም፡፡ ልብሷን አወለቀችና በፓንት ብቻ እርቃኗን ቆመች‹‹...ዋው ሰውነቷ ለእኔ ለሴቷም ያጓጓል..፡፡እርግጥ ከመጠን ትንሽ ተረፍረፍ ያለ ውፍረት ይታይባታል ቢሆንም ታምራለች፡፡››በማለት አድናቆቶን ተናገረች …ቃል ደግሞ በግማሽ ትኩረት የሚያውቀውን ገላ እየተመለከተ በገማሽ ቀልቡ ደግሞ የልዩን ጉሩምሩምታና መቁነጥነጥ እየታዘበ ቀጣዩን ትዕይንት ለማየት በጉጉት መከታተሉን ቀጠለ...
ጊፍቲ ከሻንጣዋ ውስጥ ሙሉ ቢጃማ ቀሚስ አወጣችና ለበሰች..ከዛ ሎሺን አወጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ከባቷ ጀምሮ ወደታች እግሮቾን መቀበባት ጀመረች...
መድህኔ  አሁንም ክፍሉ ውስጥ ሆኖ መንጎራደድን አላቆመም ..በውስጡ ከፍተኛ የሀሳብ ፍጭት እየተደረገ ይመስላል.. ድንገት እንደመባነን አለና ወደ ጠረጰዛው ሄደ ..ብዙም ያልተጠጣለት ብላክ ሌብል ውስኪ ነበር ..አንስቶ ያዘው..ትናንት ማታ ልዩ ይሄን መጠጥ ስለምትወድ  ለእሷ ብሎ ነበር  የገዛላት። ሊያንደቀድቀው ነው ብላ ስትጠብቅ ሁለት ብርጭቆ ይዞ ከክፍሉ ወጣ...የቃልም ሆነ የልዩ ልብ በየአሉበት ተንጠለጠለ… ሁለቱም የሚቀጥለውን ትዕይንት ለማየት ተነቃቁ ..የጊፍቲ ክፍል ተንኳኳ

"ማነው?"

"ጊፍቲ መድህኔ ነኝ"
ያለምንም ማቅማማት ቀልጠፍ ብላ ሄዳ ከፈተችለትና በራፍን ይዛ ቆመች..ከካሜራው ስለራቁ የሚያወሩት እየተሠማቸው አይደለም .ከደቂቃዎች ብኃላ ከበራፉ ገለል አለችና እሱን አስገባችው፡፡ በራፍን ዘግታ ወደነበረችበት የአልጋ ጠርዝ ተመልሳ ተቀመጠች...እሱ ውስኪውን ከነጠርሙሶቹ እንደያዘ ቆሟል።

‹‹እንዴ ቁጭ በል እንጂ?››

"እሺ"አለና በሁለቱም ብርጭቆ ቀዳና አንዱን አቀብሏት አንዱን ይዞ ከፊት ለፊቷ ያለ ደረቀ ወንበር ላይ ተቀመጠ...፡፡

"የጠጣሁት ወይን እራሱ አድክሞኛል..."

"አይዞሽ ምንም አይልሽ...ደግሞ አልጋሽ ላይ ነው ያለሽው ከደከመሽ ወደኃላ ክንብል ብሎ መተኛት ነው፡፡"

"እኔስ ክፍሌ ነኝ ክንብል ብዬ ተኛው...አንተስ በሰለም ወደቤትህ መግባትህን ቅድሚያ ማረጋገጥ የለብኝም?።››አለችው፡፡
"ለዛ አታስቢ  ..ከእዚህ ክፍሌ እስከሚደርስ ምን ያጋጥመዋል ብለሽ የምትሰጊ ከሆነ እዚሁ ከእግርሽ ስር እጥፍጥፍጥፍ ብዬ እተኛለሁ›› አላት፡፡
ጊፍቲ ከት ብላ የመገረም ሳቅ ሳቀች ."ይህቺ ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ነው ...ሰውዬ በል ጠጣ ጠጣ አድርግና ወደ ክላስህ" አለችው ….
መልስ ሊመልስላት አፉን ሲከፍት የእሷ ስልክ ጠራ…እርብትብት አለች….መድህኔ  እየተከታተላት ነው…ስልኩን አላነሳችውም፡፡ ስልኩም እስከመጨረሻው ድረስ አልጠራም…በመሀከል ተቋራጠ፡፡ስልኩን የደወለው ቃል ነው..ይሄንን ያደረገው ሆነብሎ ስሜቱ እንደዛ እንዲያረግ ስለገፋፋው ነው፡፡
‹‹ወይ….በፈጣሪ!!›አለች፡፡
‹‹ምነው ?ማነው የደወለልሽ?››
ልዩም በላችበት ሆነ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማወቅ ፈልጋ ነበር
‹‹ጓደኛዬ ነው፡፡››መለሰች ጊፍቲ፡፡
‹‹ጓደኛሽ ማለት ፍቅረኛሽ?››
‹‹በለው.. አዎ ፍቅረኛዬ››
‹‹ይሄን ያህል አደገኛ ነው እንዴ;?››
‹‹አዎ….ማለቴ ምንም ብታደርግ ምንም አይናገርህም…አያኮርፍህም ..አይቆጣህም..በቃ ዝም ብሎ ነው የሚያልፍህ››
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
ለሊት ተኝታ በአልጋዋ በላይ ያለው መስኮት ይቆረቆራል…ባነነችና ማዳመጥ ጀመረች..ደጋግሞ ሲቆረቆር ግራ ገባት..ያለምንም ፍርሀት መስኮቱን በርግዳ ከፈተች… ንስሯ ነው፡፡

‹‹እንዴ ምን እየሰራ…?››ዓረፍተ ነገሩን መጨረስ አልቻለችም…የአንድ ሰው ጭንቅላት በመንቀቁሩ አንጠልጥሎ አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ከአልጋው ፊት ለፊት ያለው  ወለል ላይ ጥሎላት ተመልሶ በሮ ወጣ….ትኩር ብላ አየችው..የተንጨበረረ ፀጉር ..ተጉረጥርጦ ወደ ውጭ የወጣ አይን… በደም የተበከለ የተጎመደ አንገት….አጥወለወላትና አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች…ምን አይነት ተአምር ነው..?ስትል አሰበች፡፡ ይህንን ነገር እራሷ ልታደርገው ትናንትና ወስና ነበር...አሁን ግን እንዳሰበችው ቀላል ስራ እንዳልነበረ ገባት…እርግጥ አሁንም ገና ሁለት የሚቆረጥ ጭንቅላት ይቀራታል….ግን እንዴት አድርጋ ነው የሰውን አንገት እንዲህ ምትከትፈው? ለነገሩ ከባድ ሆኖ የታየኝ ሰው የመሆን ዲኤን.ኤ በውስጤ ስላለ ሳይሆን አይቀርም…?ግን ነው እንዴ? በዚህ ጉዳይ ሰው ከሌላው ከማንኛውም ፍጡር በላይ ገዳይ አራጅ አይደለምን?የሚል ጥያቄ መጣባት.. 
ከሀሳቧ ሳትወጣ እግሯ ስር …ዷ ብሎ የወደቀ ነገር ተሰማተና ነቃ ብላ ትኩረቷን ሰበሰበች… ቀኝ እግሯ ስር አንድ ከአንገቱ የተቆረጠ ሰው በግራ እግሯ  ደግሞ ሌላ ጭንቅላት ቀደም ብሎ ደግሞ የመጣው ትንሽ ከእሷ ራቅ ብሎ በአጠቃላይ በዛች ትንሸ መኝታ ቤት  አንገታቸው የተቆረጠና ጭንቅላቻው ብቻ የቀረ ሶስት ሰዎች ተረፍርፈዋል፡፡ የንስሯ መንቁሩ በደም ተጨማልቆ በኩራትና በልበ ሙሉነት አፍጥጦ እያያት ነው፡፡

‹‹ምንድነው የሰራሀው?››

‹‹ልፋትሽን አቃለልኩልሽ››

‹‹እነዚህን ሁሉ በአንድ ቀን ከየት አገኘሀቸው?››

‹‹ምን ደግሞ ወንጀልና ገዳይ በበዛበት ሀገር ሶስት ሰዎች ማግኘት ይከብዳል?››

‹‹አሁን እነዚህ.. በተለይ እኚ ሁለቱ እንኳን ሰው ዶሮ ለሚስታቸው አርደው ያውቃሉ….እንዴ ይህቺኛዋ ደግሞ  ሴት ነች እንዴ?››

‹‹አዎ ሁለት ወንድሞቾን ጨምሮ  10 ሰዎችን በመርዝ ገድላለች፡፡››

‹‹ምን ለማግኘት?››

‹ብር ነዋ ሀብታም ለመሆን…ለውርስ ብላ››

‹‹ይገርማል..››

‹‹አሁን መገረምሽን አቁሚና እነዚህን ሶስት ጭንቅላቶች እናትሽ አልጋ ስር ቅበሪያቸው››

‹እንዴት አድርጌ ?››

‹‹ይህቺማ ቀላል ስራ ነች..ለማንኛውም ይንጋ…አሁን ተመልሰሽ ተኚ.. እኔም እነዚህን ጨካኞች ሳድን ድክም ብሎኛል አላት…

‹‹ውይ እውነትህን ነው የእኔ ጀግና ..ና አለችና በደም  የጨቀየውን መንቁሩን ታጥቦና ተጣጥፎ በተቀመጠው ነጭ ፎጣዋ  ጠራርጋ አፀዳችለትና ወደአልጋው እንዲሄድ አድርገ መስኮቱን በመዝጋት እሷም ወደአልጋዋ በማምራት ወደ ላይ ወጣች. ብርድልብሱን ለበሰችና ንስሯንም አለበሰችው፡፡ከዛ ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳት፡
ጥዋት ሳሎን ቤተሰቦቾ ሲንጫጩ ነው ከእንቅልፏ የባነነችው..ከጎኗ ንስሯ እንደተኛ ነው…በርግጋ ተነሳችና ከአልጋ ላይ ወርዳ ቆመች.. ወለሉ ቅንጣት የደም ጠብታ የሌለው ንፅህ ከመሆኑም በላይ  ባዶ ነው….ምንም ጭንቅላት የለም፡፡
ንስሯ ተነስቶ እያያት ነበር..

‹‹ምን ተፈጠረ ጭንቅላቶቹስ ?››
ምንም መልስ ላለመስጠት አእምሮውን ዘጋባት

‹‹መልስልኝ እንጂ››ልክ በባሏ ተግባር እንደተበሳጨች ጮሂ ሚስት አንቧረቀችበት፡፡

ንስሩ ግን ዝም

‹‹ቀበርካቸው እንዴ…?››

አሁንም እምሮውን እደቆለፈ ነው፡
በራ ክፍሏን ለቃ ወጣችና እናቷ ወደተኛችበት ክፍል አመራች፡፡
ባልተረጋጋ ስሜትና በተንቀዠቀዠ አነጋገር‹‹ሀርሜ እንዴት አደርሽ?;››አለች

‹ሰላም ነኝ ልጄ.አንቺ ደህና ነሽ ?ምነው የደነገጥሽ ትመስያለሽ?››

‹‹አይ ደህና ነኝ…ንስሬ እዚህ አንቺ ጋር መጥቶ ነበረ..?››

‹‹የት እዚህ.. አረ አልመጣም››

‹‹ከክፍልሽ ወጥተሸ ነበረ…››

‹‹እንዴ ምን ነክቶሻል? እንዴት ብዬ ወጣለሁ…?››

‹‹አይ ማለቴ እንቅልፍ ወስዶሽ መጥቶ ሄዶ ከሆነ ብዬ ነው…››

‹‹አረ ተረጋጊ ለሊት አንቺ ከዚህ ከሄደሸ ጀምሮ እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም እና ንስርሽም እልመጣም…ምን አልባት አደን ሄዶ እንዳይሆን?››

‹‹አይ አልሄደም… እሱማ እኔ ክፍል ነው ያለው››

የልጅቷ ቅብዥርዥር ያለ ወሬ ግራ ስላጋባት ‹‹ልጄ ግን ደህና ነሽ?ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ደህና ነኝ ሀርሜ… ››አለችና በርክ ብላ አንገቷን በመድፋት አልጋ ስር ገባችና ወሉን ማየት ጀመረች …ምንም የተቆፈረ …ምንም የተነካካ ነገር የለም…?››

‹‹መጣው እናቴ…ሰላም ነኝ አታስቢ›› ብላ ወደክፍሏ ተመለሰች..ንስሯ አሁንም አልጋው ላይ ተኮፍሶ እንደተቀመጠ ነው፡፡
እንደገባች ‹‹ለምን ታበሳጨኛለህ ?አለችው የእውነትም ተበሳጭታ፡፡

አእምሮውን ከፈተላትና እንድትረጋጋ ወደእምሮዋ መልዕክት አስተላለፈላት

‹‹ዝም ብዬ እንዴት እረጋጋለሁ…?ምንድነው የሆነው…?ለሊት የሶስት ሰዎች አንገት ቆርጠህ አምጥተህልኝ ነበር..እንደውም መንቁርህ በደም ተነክሮ በምወደው ነጭ ፎጣ ነው የጠራረኩልህ .››አለችና በደም የተበከለውን ፎጣ ስታስታውስ  ፎጣው ወደተቀመጠበት ጠረጴዛ ስትሄድ እንደተጣጠፈና  ግራ እንደመጋባት ብላ አነሳችና ፈታችው… ምንም የደም ጠብታ የለበትም… ከትናንት ወዲያ አጥባ አጣጥፋ እንዳስቀመጠችው ነው…‹‹.እንዴ ህልም ነበር እንዴ?››ብላ ግራ በመጋባት አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ይሄ የአንተ እና የአባቴ ስራ ነው አይደል….?በል አሁን ተዘጋጅ የሚገደል ሰው ፍለጋ እንሄዳለን… ምን ያህል ቀን እንደሚፈጅብን አላውቅም››አለችው፡
በንስሩ የአእምሮ ሰሌዳ ላይ አያስፈልግም የሚል መልእክት አነበበች፡፡

‹‹እንዴት የእናቴ ህይወት እኮ ነው…?››

‹‹እኮ በሌለ መንገድ አንድ አመት እንድትታገኝ ማድረግ ተችሏል ..በሶስት ቀን ውስጥ ድና ትነሳለች፡፡››

‹‹እውነትህን ነው?››

‹‹እውነቴን እንደሆነ ታውቂያለሽ›› አላት፡፡

በደስታ አቀፈችውና እየሳመች ወደእናቷ ክፍል ይዛው ሄደች፤እናትዬው ከቅድሙ ሁኔታዋ በተቃራኒ እየሳቀችና እየፈነደቀች ንስሯን አቅፋ ሰታገኛት ተደሰተች‹‹ልጄ ከመቼው ወደ ፈንጠዝያ ገባሽ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹እማ በጣም ደስ ብሎኛል…ለምን መሰለሽ? አንቺ ስለምትድኚልኝ.››
‹‹አይ ልጄ ..ብዙም ተስፋ አታድርጊ››

ይቀጥላል
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በትንግርት እና በሁሴን መካከል ሲካሔድ የነበረው የድብብቆሽ ጨዋታ እልባት ካገኘ እንሆ ዛሬ ድፍን አንድ አመት ሞላው፡፡ይህ የጊዜ ባቡር ለአንድ አመት በሀዲዱ ላይ እየተጠማዘዘ ተጉዞ ዛሬ ላይ እስኪደርስ በመሀከል የተከሰቱ ዋና ዋና ክስተቶች

1/ ከደብረዘይት መልስ ሁሴን ቤት ከተከሰተው ድራማዊ ምሽት ጀምሮ ትንግርት እና ሁሴን የትዳር ጥንዶች ሆነዋል፡፡ከሁሴን ጋር ተጋብተው በመከባበር እና በፍቅር በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡ትዳራቸው ግን ከተለመደው ለየት ያለና ዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ሁሉ ግራ የሚያጋባ አይነት ነው፡፡ ለምሳሌ ሳሪስ የሚገኘውን የእሷን ቤት አሁንም ትኖርበታለች፡፡በሳምንት ሁለት ቀን ሳሪስ እሷ ቤት አብረው ያድራሉ..ሌላውን ሁለት ቀን ልደታ እሱ ቤት ተያይዘው ያድራሉ ..ሌላውን ሶስት ቀን ደግሞ ተለያይተው በየራሳቸው ቤት ለየብቻ ያድራሉ፤ቀኑ እንደየሁኔታው ሊቀያየር ይችላል፡፡ይህ ጉዳይ ሁለቱን ባልና ሚስቶችን በጣም የተመቻቸው እና ያለቅሬታ እየኖሩት ያለ ህይወት ቢሆንም ለሌሎች ሰዎች ግን ሊገባቸው የሚችል ሚስጥር ሆኖ አልተገኘም ፡፡ በተረፈ ትንግርት ሁለተኛ ዲግሪዋንም በጆርናሊዝም መማር ጀምራለች፡፡

2/ከሁሴን የፍቅር አገዛዝ ነፃ የወጣችው ኤደን እና ከየውብዳር የጋብቻ እቅፍ ሾልኮ ያመለጠው ሰሎሞን ተፈቃቅደው ድል ባለ ድግስ ከተጋቡ ስምንት ወር አልፏቸዋል፡፡በዚህ የጋብቻ ጥምረታቸው የወደፊቱን እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚችል ሰው ባይኖርም ለጊዜው ሁለቱም ደስተኞች ይመስላሉ፡፡በቅርቡም የጋራ ልጅ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ኤደን የአምስት ወር እርጉዝ ነች፡፡ ኤደን ለአመታት ስታፈቅረውና ህይወቷን ሙሉ ከእሱ ጋር ለመኖር ወስና በተስፋ ስትጠብቀው የነበረችው ሁሴን እሷን ችላ ብሎ ድራማዊ በሆነ መልኩ ትንግርትን ካገባ በኃላ ሙሉ በሙሉ ሀሳቧን ሰብስባ የሰሎሞንን ጥያቄ በመቀበል ስትመኘው ወደነበረው ትዳር ገባች፡፡አሁንም ታዲያ ሁሴንን ስታገኘውና እሱ ባለበት አካባቢ ስትሆን በውስጧ የተዳፈነው የጥንት ፍቅሯ እየተቆሰቆሰ ሽው ቢልባትም መልሳ በውስጧ በመቅበር የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ያለእንቅፋት እንዲቀጥል ሁሌ ትጥራለች፤እስከአሁንም ተሳክቶላታል፤የወደፊቱን ደግሞ ጊዜ ይመልሰዋል ፡፡

3/ፎዚያ የኮሌጅ ትምህርቷን አጠናቃ በፍኖተ- ጥበብ ጋዜጣ በፅሀፊነት ተቀጥራ መስራት ከጀመረች ስድስት ወር ጨርሳ ሰባተኛ ውስጥ ገብታለች፡፡አሁንም የምትኖረው ከሁሴንና ከትንግርት ጋር ነው፡፡በዚህ ሁኔታ ሶስቱም ሰዎች ደስተኞች ናቸው፡፡ፎዚያ ሁሴንን እንደሥጋ ወንድሟ እንደምታየው ሁሉ ትንግርትንም እንደስጋ እህቷ በፍቅር ተቀብላታለች፡፡በቅርብ ግን ይሄንን የፍቅር ሙዳ የሚቆረጥበትን ቤት ቅር እያላትም ቢሆን ሳትለቅ አትቀርም፤ምክንያቱም ፍቅር ይዞታል፡፡ እረፍት የሚነሳ ፍቅር፡፡እሷም ማግባት አሰኝቷታል፤አዎ ማግባቷ አይቀርም፤ ለጊዜው ግን ሚስጢር ነው፡፡ትንሽም ቅር እያሰኛት ያለው የትንግርት በሙሉ ልቧ ጠቅልላ ሁሴን ቤት መግባት አለመቻሏ ነው፡፡ሁሴንም በዚህ ጉዳይ ለምን ተቃውሞ እንደማያነሳ ሁሌ ስታስበው ግራ ይገባትና ‹‹ሁለት እብዶች፡፡›› ብላ በውስጧ ታዝባ ታልፈዋለች፡፡

4/የውብዳር አሁንም በቤትና በንብረቷ ውስጥ ከሁለት መንታ ልጆቿ ጋር እየኖረች ቢሆንም ከህይወቷ ግን ደስታ ብን ብሎ ጠፍቷል፡፡ ከስታለች፤ ተጐሳቁላለች፤ እራሷን ጥላለች፡፡ በፀፀትና በቁጭት ውስጥ ተዘፍቃ ህይወቷን እየገፋች ነው፡፡

ዛሬ

ሁሴን እና ትንግርት በጋብቻ ተሳስረው አንድ ቤትም ባይሆንም አንድ ላይ መኖር የጀመሩበት የአንደኛ ዓመት ክብረ በዓል የሚያከብሩበት ቀን ነው፡፡በቤታቸው ድል ያለ የሚባል አይነት ባይሆንም መጠነኛ ድግስ
ተዘጋጅቷል፡፡ይሄን ድግስ እንዲህ ለማቀናጀት ትንግርት እና ፎዚያ አንድ ሳምንት ሙሉ ለፍተውበታል፡፡እርግጥ ድግሱ ወይም የእራት ግብዣ ፕሮግራሙ የጋብቻ የልደት በዓላቸውን በማስመልከት ብቻ አይደለም የተዘጋጀው፤ ሌላም በደባልነት የሚከበር ጉዳይ አለ፤የሁሴን የሽኝት ፕሮግራም፡፡ሁሴን ሦስተኛ ዲግሪውን ለመስራት የሲዊዘርላድ ዩኒቨርሲቲ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ለአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ ወደ ውጭ ከሰሞኑ ይጓዛል፡፡

ድግሱ ላይ የታደሙት የቅርብ የሚባሉ ስምንት ያህል ሰዎች ናቸው፡፡ሰሎሞን፣ባለቤቱ ኤደን፣ፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ የሚሰሩ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ጋዜጠኞች ፣ አንድ የትንግርት የድሮ የቡና ቤት ጓደኛዋ.. በቃ፡፡

ዝግጅቱ ላይ ትናንት ለሰሎሞን እንዲታደም ‹‹ነገ አንድ ሰዓት የእራት ግብዣ ስላሰናዳን ከኤደን ጋር እንድትመጡ››በማለት
ሲነግረው‹‹ምንን አስመልክቶ?››ብሎ ነበር ሰሎሞን የጠየቀው::

<<የአንደኛ አመት የጋብቻ በዓላችንን ልናከብር ነው::>>

<<ትቀልዳለህ?››

‹‹እንዴት ? ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››ሁሴን ግራ በመጋባት መልሶ ይጠይቀዋል፡፡

‹‹የትኛውን ጋብቻችሁን ነው የምናከብረው? ጋብቻን ማላገጫ አደረጋችሁት እንዴ?አንድ ከተማ እየኖሩ ያለምክንያት በሳምንት አራት እና አምስት ቀን ተለያይተው እያደሩ፤ሁለት የተለያየ ቤት እየኖሩ፤ድንቄም ጋብቻ!!››

‹‹ዋናው እኮ ጋብቻን ጋብቻ የሚያደርገው የቤትና የቁሳቁስ መቀላቀል አይደለም ፤ የልብ መቀላቀል እንጂ፡፡››

‹‹ባክህ አትመፃደቅብኝ፤ ታስተካክሉ እንደሆነ አስተካክሉ፡፡በጋብቻ ስም አንድ አመት አላገጣችሁ፤ አሁን ይበቃል፡፡አንዱን ቤት አከራዩና ወደ አንዱ ቤት ተጠቃላችሁ ግቡ፡፡››

‹‹እሺ እናስብበታለን፤ ለማንኛውም ነገ እንዳትቀር፡፡››

‹‹ለነገው እመጣለሁ፤ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀጠላችሁ በሚመጣው አመት አብሮን ያከብራል ብላችሁ እንዳትጠብቁ፡፡›› በማለት ነበር ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር ግብዣውን የተቀበለው፡፡

ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን ኤደን እና ሰሎሞን ተያይዘው ደረሱ፡፡ ወዲያው ተከታትለው የፍኖተ-ጥበብ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው በመግተልተል ገቡ ፡፡ትንሽ አርፍዳ የደረሰችው አለም የምትባለው የትንግርት ጓደኛ ነበረች፡፡ ከምግብ እና መጠጥ ዝግጅት በተጨማሪ ቤቱ በሚያምር ሁኔታ ደምቋል፡፡

ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ
የሁሴን ሙሀመድ እና የትንግርት ካሳ የአንደኛ ዓመት የጋብቻ ክብረ በዓል

ከስር ደግሞ

እንኳን ለአንደኛ አመት የፍቅር /ጋብቻ በዓላችሁ አደረሳችሁ፡፡

የሚል በትልቅ ባነር የተሰራ ጽሁፍ ተሰቅሎ ይታያል፡፡ይሄንን ያሰራችው ፎዚያ ነች፡፡በራሷ እንደ ስጦታ እንዲቆጠርላት::

ከፊት ለፊቱ ግድግዳ ተጠግቶ ካለ አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ ገዘፍ ያለ አንድ ቁጥር ሻማ ተለኩሶ እየተንቦገቦገ ነው፡፡

ትንግርት በዚህች ምሽት ሁለት የተቀላቀለ ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ለአንድ አመት ከሁሴን ጋር ባሳለፈቻቸው አስደሳች ቀኖች በጣም ረክታለች፡፡ እንደሚስትም ብቻ ሳትሆን እንደጓደኛም፣ እንደስራ ባልደረባውም ሆና በተዋጣለት ጥምረት እስከአሁን አብራው ቆይታለች ፡፡

በዚህ አንድ አመት የጊዜ ሂደት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድም እጅግ ተደናቂና ታዋቂ ለመሆን በቅታለች፡፡ለዚህም የረዳት እንደበፊቱ በምስጢር ሳይሆን በግልፅ ፣በብዕር ስም ሳይሆን በራሷ ስም በፍኖተ- ጥበብ ጋዜጣ ላይ የምትጽፋቸው ልብ-ወለድ የሆኑና ሌሎች ኢ‐ልብወለድ ስራዎች ሲሆን በተጨማሪም በህይወት ታሪኳ ላይ ያጠነጠነ ረጅም ተከታታይ ዘገባ በሁሴን አማካይት ጋዜጣው ላይ በመቅረቡ ይበልጥ እንድትታወቅ አግዟታል፡፡የስዕል ስራዋንም ለሁለት ጊዜያቶች ለህዝብ አቅርባለች፡፡ በአጠቃላይ አንድ የጥበብ ሰው በአስር አመት ልፋት የማያገኘውን ዕውቅና እሷ በአንድ አመት
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


      ትዝታ-ከ10 አመት በፊት

  አዲሱን ስራ ለመጀመር ወደ ስልጠና የገባችበት የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ አዎ ወደዚህ አዘቅት ውስጥ ወደ አስገባት ስራ ቀጥታ ከመግባቷ በፊት ምርጥና አስደሳች የሆኑ 3 የስልጠና ወራቶችን አሳልፋ ነበር፡፡ በእነዛ ወራቶች የተማረችው ትምህርት እና ያገኘችው የህይወት ልምድ አራት አመት በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ካገኘችው እውቀትና ልምድ ጋር ብዙም የማይተናነስ  ነበር፡፡ አጭር በጣም ጣፋጭና ልዩ አይነት ልምድ ያጎናፀፋትና የህይወት ምልከታዋን ሙሉ በሙሉ የቀየራት ነበር፡፡ትዝ ይላታል  ለመጀመሪያ  ቀን ከአደረችበት  ሆቴል  በለሊት መጥቶ ጥሩ ቁርስ ጋብዞ ስልጠና የሚወስዱበት አፓርታማ ድረስ የወሰዳት ደምሳሽ ነበር፡፡
በወቅቱ ሳባ ሁለት ሻንጣ ልብሷን ይዛ ለስልጠና በተዘጋጀላት አፓርታማ ደርሳ  ከመኪና እንደወረደች ፊት ለፊቷ ያየችው ሰገንን ነበር

"እንኳን በሰላም መጣሽ" በሚል የሞቀ  ሰላምታ  ነበር  የተቀበለቻት።

ሳባም "እንኳን ደህና ቆያችሁኝ"አለችና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ አቅፋት ወደ ውስጥ ይዛት ገባች። ደምሳሽ ሻንጣዋን ከመኪናው ኪስ እያወረደ ወደተዘጋጀላት መኝታ ቤቷ ይዞላት ገባ፡፡ በስርአት አስቀምጦላት ወደስራው ተመለሰ፡፡ ሳባ የገባችበት ክፍል የሳሎን ይዞታ ያለው ሲሆን  ምቹ ሶፋ እና ደረቅ ወንበሮች ነበሩበት በሶፋው ላይ ራቅ ራቅ ብለው ሁለት ወጣት  ሴቶች ተቀምጠዋል፡፡ በግምት 40  አመት የሚሆናት ደርባባ.ባለ ግርማ ሞገስ ሴት ፈንጠር ብላ ደረቅ ወንበር.ላይ ተቀምጣለች፡፡ ፊት ለፊቷ መለስተኛ ጠረጴዛ አለ …እዛ ላይ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ተቀምጧል…ከጭንቅላቷ በስተጀርባ ባለው ግድግዳ ፕሮጀክተር ተለጥፏል፡፡
  ሰገን ወደእሷ ተጠጋች፡፡ ‹‹እንግዲህ ሶስተኛዋ ሰልጣኝ እሷ ነች፡፡ ሳባ ትባላለች፡፡ለሁላችሁም መልካም የስልጠና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ…አልፎ አልፎም ቢሆን ከእኔ ጋር እንገናኛለን፡፡በሉ ደህና ሁኑ ..ሳባ ተቀመጪ››ብላ
ወጥታ ሄደች፡፡ሳባም ክፍት ወደሆነው የሶፋ መቀመጫ ሄደችና ተቀመጠች፡፡ እርስ በርስ ለመተዋወቅ 10 የሚሆኑ ደቂቃዎችን ካባከኑ በኃላ ቀጥታ ወደስልጠናው ነበር የገቡት፡፡

አሰልጣኟ ራሷን ከማስተዋወቅ ጀመረች፡፡ ማህደር እባላለሁ፡፡ ቀድሞ እንደተነገራችሁ ጠቅላላ ስልጠናው ሶስት ወር የሚፈጅ ሲሆን እንግዲህ ቀጣዬችን ሁለት ወር ተኩል ከእኔ ጋር እናሳልፋለን፡፡ የመጨረሻዎቹ 15  ቀናት  ደግሞ  ያው ከእኔ ጋር በነበራችሁ ቆይታ የቀሰማችሁትን እውቀትና ጥበብ በተግባር የምትፈተኑበት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በድርጅታችን ሶስት የማሳጅ  መስጫ ቦታዎች አሉን ሶስቱም ደረጃቸው የሚገኝባቸው ጥቅምም ይለያያል በስልጠናው ላይ በምታስመዘግቡት ብቃትና በመጨረሻው የተግባር ላይ ኢቫሉዌሽን መሰረት በማድረግ ምደባችሁ ይከናወናል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ደረጃ አንድ የሚመደበው ማን ነው? ደረጃ ሁለትስ…? ሶስት ወር ጠብቀን የምናውቀው ይሆናል…ለሁላችሁም ‹‹መልካም እድል›› ብላ ነበር ወደ እለቱ ትምህርት የገባችው፡፡ እንግዲህ ትምህርታችን አራት ዘርፍ ይኖረዋል፡፡ የመጀመሪያው ስለማሳጅ እንማራለን..ይሄ የስልጠናው ዋናው ክፍል ስለሆነ አንድ ወር ይፈጃል..ሁለተኛው ክፍል ስለ‹‹ፍቅርና ወሲብ››ይሆናል፤ ይሄም  ሀያ ቀን ይፈጅብናል…ሶስተኛው ስለ‹‹ተግባቦት››አስር ቀን እንማራለን ከዛ መልሰን ስለማሳጅ 15 ቀን በመማር ከእኔ ጋር ያለንን ቆይታ እናጠቀልላን፡፡ለመጀመር ያህል ዘሬ ማሳጅ ምንድነው? ከሚለው እንጀምር፡፡
ማሳጅ ከሰው  ልጅ  ጥንታዊ  ታሪክ  ጋር  ከፍተኛ  ቁርኝት  ያለው  ግኝት   ነው፡፡ማሳጅ ለተዝናኖት ከመጥቀሙም በተጨማሪ አጠቃላይ የሰው ልጅን የጤና ችግር የሚያስተካክል የጎንዬሽ ጉዳት የሌለው ውጤታማና ተፈጥሮአዊ ዘዴ ነው፡፡ማሳጅ ከ4ሺ አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና ተጀምሮ ወደተለያዩ የምስራቁ አለም ክፍል ወደ ሆኑት ህንድ፤ጃፓን፤ታይላንድ የመሳሰሉት አገሮች የተስፋፋ ሲሆን በኋላም ወደአውሮፓ በመሻገር ከየሀገሮቹ ባህልና ወግ ጋር በመዋሀድ ቅርፁን በመቀያየር ቀስ በቀስም ቢሆን ሊስፋፋና ሊዛመት ችሏል፡፡
በዛሬው ጊዜ ማሳጅ በተለያየ የአለም ክፍሎች የተለያየ ስምና ቅርፅ ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ አማራጭ የህክምና ዘርፍ በመሆን ግልጋሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከተወሰኑ የማሳጅ አይነቶች ጥቂቶቹ ስዊዲሽ ማሳጅ፤ ዲፕ ቲሹ ማሳጅ፤ስፖርት.ማሳጅ፤ሞሮኮ ማሳጅ፤የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ለምሳሌ ሲዊዲሽ ማሳጅ በአሁኑ ጊዜ በመላው አለም በስፋት በተግባር ላይ እየዋለ የሚገኝ የማሳጅ አይነት ሲሆን ጠቅላላ የሰውነት ክፍልን በተዝናኖት ውስጥ ለመክትት ታቅዶ ዲዘይን የተደረገ ሲሆን  በምዕራባዊያን የሰውነት  መዋቅርቨእውቀትና የስነ-ልቦና ሳይንስ ላይ መሰረት አድርጎ የተቃኘ ነው፡፡  ሎሽን ወይም ቅባት ይጠቀማል፤የደም ዝውውርን ማሳለጥና የደም ስሮች  ላይ  ያለውን ውጥረት እንዲረግብ ያደርጋል፡፡
ሌላው የስፖርት  ማሳጅ ነው፡፡ ይሄ የስፖረት ማሳጅ ለአትሌቶች የብቃታቸው ጫፍ ላይ እንዲደርሱ፤ጡንቻዎቻቸውን በማፈርጠምና ትንፋሻቸውን በማጎልበት እገዛ ሚያደርግላቸው ከመሆኑም በላይ ከአደጋና ከዝለት የሚታደጋቸው ነው ከዛም በተጨማሪ ጉዳት ላይ በሚወድቁበት ጊዜ በፍጥነት እንዲያገግሙ ይጠቀሙበታል ሌላው አኩባንቸር የሚባለው የማሳጅ አይነት ሲሆን፡፡ በአብዛኛው በህንድ አካባቢ የሚሰጥ ሲሆን የሰውነትንና የአዕምሮን ባላንስ ለመጠበቅ ዲዛይን የተደረገ የማሳጅ አይነት ነው፡፡

ለግዜው ለመግቢያ ያህል እነዚህን ካልን ይበቃል ፤በቀጣይ ግን እያንዳንዳቸውን በተናጠል እያነሳን በተግባርም እየሞከርን በጥልቀት እናሰራችኋለን፡፡ ምክንያቱም ዋናው ስራችን ስለሆነ፡፡
   ከዛ እንዳለችው እያንዳንዱን የሰውነት ክፍል እየለየን፤የት ጋር ሲታሽ የት ጋር.እንደሚሰማን…ለምን አይነት ችግር ምን አይነት ማሳጅ እንደምንሰራ… የትኛው ጡንቻ ከየትኛው ግንኙነት እንዳለው በተግባር እናያለን፡፡

እንዳለችውም ለ15 ቀን ያለማቋረጥ ሶስት የተለያዩ ወንዶች እየተቀያየሩ የማሳጅ ጠረጴዛቸው ላይ እንዲተኙ ይደረግና መምህሯ ለሶስቱ ሴቶች እያንዳንድን የሠውነት ክፍል እየለያየች በማሳየት እያንዳንዱን    የሰውነት መገጣጠሚያ እየጨፈላለቀች እየገጣጠመች...የደም.ስሮችን አቀማመጥና አሰራር በቪዲዬ በ3ዲ ቪዲዬ በመታገዝ እያሳየቻቸው ፤ስለሰው ልጅ የሠውነት መዋቅር ስለሴትና ወንድ የሰውነት መዋቅር ልዩነት እስኪደነቁና እስኪፈዙ ድረስ ካስተማረቻቸው በኃላ ለቀጣዩ 10 ቀን ደግሞ በየቀኑ የተለያየ የሰውነት አቋም ውፍረትና ቅርፅ ያላቸውን ወንዶች በማምጣት የት ጋር እንዴት አድርገው ማሸት እንዳለባቸው እጃቸው እስኪዝልና አእምሯቸው እስኪደነዝዝ ሰለጠኑ፡፡ ላባቸው እስኪንጠፈጠፍ እግራቸው እስኪንቀጠቀጥ ለአንድ ወር አጠቃለሉና ወደ ሁለተኛ የስልጠና ርዕስ ተሸጋገሩ
..//

ቀጣዩ የስልጠናው  ርዕስ ስለወሲብ ነበር
እስኪ ስለ ወሲብ በወፍ በረር  እንይ  የወሲብ  አብሮነት  የጋራ  ስሜትና ፍቅራቸውን እንዲያስታውሱና በትዝታውም ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፤ወደተሻለ የፍቅር እርካብ ያሻግራቸዋል፤ይበልጥ ልብ ለልብ
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አራት
፡፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የተወሰነ አርፈው ናፈቆታቸውን ካቀዘቀዙ በኃላ ናኦል‹‹እህቴ ዛሬ ቀኑን ታውቂያለሽ….››ሲል ግራ ያጋባትን ጥያቄ ጠያቃት፡፡
ወንድሜ ደግሞ መንጋትና መምሸቱን ካልሆነ በስተቀር እለቱና ቀኑኑ መለየት ካቀምኩ ቆየሁ…ለካ በህይወታችን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ነገሮች በመከራ ቀኖቻችን ውስጥ ስንሆን ትርጉም አይኖራቸውም፡፡››
‹‹እንግዲያው ልንገርሽ ዛሬ ጥር 11 ነው …ልደታችን ነው፡፡››

ያልጠበቀችውን ዜና ነው የነገራት….መላ ሰውነቷን ነው የወረራት‹‹ኦ …ደሰስ ይላል…››መልሰው ተንጫጩ …..
ምስራቅ‹‹እናንተ ለምን እነዚህ አስተናጋጆቻችንን ጥቂት ውለታ አንጠይቃቸውም…››የሚል ድንገቴ ሀሰብ አቀረበች፡፡
‹‹ምን ››

ልደታችሁን  ለማክበር  የሚሆን  ጥቂት  ሻማ  …የተወሰነ  ከረሜላ  ካለ…ኬክም  ቢገኝ አንጠላም…ኮኬይንም  ቢያቀርቡልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው…››አላች…ተሳሳቁ፡፡
‹‹ሌላውን አላውቅም.. ኮከይኑ ግን አይጨክኑብንም…..›› ምስራቅ ወደ መጥሪያው ሄደችና ተጫነችው…
‹‹እንዴት ፍቅር ምን ፈልገሽ ነው››ናኦል ምስራቅን ጠየቃት..ኑሀሚ ሁለቱንም አፈራረቀች ና       በገረሜታ ታያቸው ጀመር..ምስራቅ የእሷን ምልከታ ሳታስተውል ‹‹ትቀልዳላችሁ እንዴ.. ከመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቃራል፡፡ሲባል አልሰማችሁም፡፡››በማለት በራፉ በድጋሚ ለማንኳኳት እጇን ስትሰነዝር  ….በድንገት በራፉ ተከፈተ…፡፡
ኑሀሚን ያመጣት ወጣቱ ልጅ ነው በራፉን የከፈተው…. የሚፈልጉትን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሀለቃዬን ጠይቄ ከፈቀደ የሚሆነውን አደርጋለው››ብሎ መልሶ በራፉን ዘግቶ ሄደ….፡፡ኑሀሚ ግን  በነበረችበት እንደፈዘዘች ነው፡፡
‹‹ምንድነው ያፈዘዘሽ››

‹‹የእኔ ፍቅር አለሽ እኮ…አንቺም ወዬ አልሺው ››

‹‹እና ›

‹‹እኔ እዚህ በአማዞን ጫካ ከአውሬውም ከሰው አውሬውም ለማምለጥ በመጣር ፍዳዬን በማይበት ሰዓት እናንተ ፍቅሬ ማሬ መባባል ጀመረችሁ››
‹‹ታዲያ በመሀከላችን ያለውን ለዘመናት የታፈነ ፍቅር ጭረን ካላቀጣጠልነው አንቺን ለመፈለግና ለማግኘት የሚያስችለንን ብልሀትና ጥንካሬ ከየት እናመጣን…. በነገራችን ላይ ያው አንቺ ወደ እዚህ እንደመጣሽ ሰሞን ነው የተጋባነው…››
‹‹የተጋባነው››

አዎ …ወዳሻንጣዋ ሄደችና የጋብቻ ሰርተ ፍኬታቸውን አውጥታ አሳየቻት…..ማመን አልቻለችም…ምስራቅ የሚያደርጉትን ሆነ የሚያወሩትን ሁሉ ሰዎቻቸው እየተመለከቷቸው እንደሆነ ታውቃለች….የጀመሩትን ማስመሰል አስከወዲያኛው መቀጠል አለባቸው….አዎ ከዚህ እስኪወጡ ከናኦል ጋር ባልና ሚስቶች ናቸው….ከወጡስ በኃላ አንዴት ይሆናል የሚለውን እርግጠኛ አይደለችም…..ልጁን በፊት ከምትወደው በተለየ መንገድ ወዳወለች…..ጠረኑ ክፉኛ ለምዳዋለች…..ፍቅሩ ልቧ ውስጥ እየተንጠባንጠበ ነው…..ይሄንን የጋብቻ ሰርተፍኬት እንደቀልደ በቃ አሁን ጉዛችን አበቅቶለታል ብላ ቀዳዳ የወረቀት ቅርጫት ውስጥ ለመክተት ጥንካሬው መቼም ቢሆን የሚኖራት አይመስላትም፡፡
ከተረጋጉ በኃላ ኑሀሚ ሰውቷን ለመታጠብ ፈለገች እና ወደሻወር ቤት ገባች፡፡ታጥባና ነፅታ ስትወጣ ክፍላቸው ውስጥ የተለየ ነገር ነበር የጠበቃት….በርከት ያሉ የሴት ቀሚሶች እና ሙሉ የወንድ ሱፍ ሱሪ የያዘ ተሸከርካሪ የልብስ መደርደሪያ ወለሉ መሀከል ላይ ተቀምጦ ናአልና ምስራቅ ፊት ለፊቱ  ቆመው በአድናቆት እየተመለከቱት ደረሰች፡፡
ያገለደመችውን ፎጣ በደንብ አጥብቃ አሰረችና ‹‹ምንድነው ይሄ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ይህን ያመጣው ልጅ..በጠየቃችሁት ጥያቄ መሰረት ልዳታችሁን ለማክበር ተፈቅዷል…..ከዚህ የሚሆናችሁን ልብስ መርጣችሁ ልበሱና ልደቱ ወደሚከበርበት ቦታ ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስዳችኃላው›› ብሎል፤ብለው አስረዷት፡፡
‹‹አንቺ ሰዎቻችን ደግ ናቸው…….መጀመሪያ በደንብ አስደስተውን የምንፈልገውን ነገር እንድናደርግ ከፈቀዱልን በኃላ ከዛ አመስግነናቸው እንድንሞት ነው የፈለጉት፡፡››አለች ምስራቅ፡፡
‹‹እሱስ ቢሆን ማን አየበት  ይመስገን ነው››….ብላ ካመጣጡላቸው ቀሚሶች መካከል ለእሷ
የሚሆናትን መምረጥ ጀመረች….በሀያ ደቂቃ ውስጥ ሶስቱም ልክ እቤተ-መንግስት ከንግሱ ጋር የእራት ግብዣ እንዳላባቸው መኮንንቶች ሽክ ብለው ዘንጠውና አምረው በቀጣይ
የሚሆነው መጠበቅ ጀመሩ፡፡

እንደተባሉት ያው ልጅ ቤቱን ከፍቶ ይዞቸው ወጣ፡፡ቀጥታ ከህንፃው በጎሮ በኩል ካለ እስካአሁን ካላዩት በአበቦች ያሸበረቀ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ስፋት ያለው የተንጣለለ  የመዋኛ ገንዳ ያለበት ቦታ ነው የወሰዳቸው፡፡ ገንዳው ዳር ባለ በሰራሚክ ንጣፍ ባማረ ጎጆ የምግብ አይነትና፤ የመጠጥ አይነቶች ሞልተውበታል….ዙሪያውን መቀመጫዎች ሲኖሩ አስተናጋጅ መሰል ሁለት ሴትና አንድ ወንድ ዝግጅቱን ለማሳመር ከላይ ወደታች ይሯሯጣሉ፡፡ይዞቸው የመጣው ሰው ለገንዳው እይታ ምቹ የሆነ መቀመጫ ሰጣችውና ሶስቱም በተርታ ተቀመጡ፡፡
..በትካሻቸው ከባድ መሳሪያ የተሸከሙ ሰዎች በአከባቢ ራቅ ካለ ስፍራ በየተወሰነ ርቀት ፈንጠር ፈንጠር ብለው ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲቃኙ ይታያል ፡፡ጥርት ካለው ከአማዞን ደን ሚነፍሰው ልስልና እርጥብ አየር ጋር አብሮ የሚነፍስ ጥኡም የላቲን ሙዚቃ እየተሰማ ነው፡፡በአካባቢው ሌላ ሰው የለም፡፡ድንገት ከገንዳው ብልቅ ብሎ ወደ ዳር የሚወጣ ሰው ተመለከቱ… ከእነሱ በ5 ሜትር  ርቀት ላይ ስለሆነ ማንነቱ ጥርት ብሎ ይታያቸዋል፡፡
ወደ ኑሀሚ በፈገግታ እየተመለከተ‹‹በሰላም ተመልሰሽ ወደቤትሽ በመምጣትሽ ደስ ብሎኛ››አላት፡፡
‹‹እንዴት አልመጣ ….ብጨክን ብጨክን ባንተ ጨክኜ መቅረት እችላላሁ››ብላ ምፀቱን በምፀት መለሰችለት…መልሷ በጣም አሳቀው፡፡
‹‹በጣም ናፍቀሺኝ ነበር….በህይወቴ እንደአንቺ ለማግኘት ያስቸገረኝ ሰው የለም….ድሮም ውድ ነገር ለማግኘት በጣም ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል…ለማንኛውም መልካም ልደት ለሁለታችሁም…..ሰዎቹ  መሰናዶቸውን እስኪያጠናቅቁ ትንሽ ልዋኝ.. ከመሀከላችሁ መዋኘት    …የሚፈለግ ሰው ካለ ግን መጥቶ መወኘት ይችለል፡፡››ብሎ ወደገንደው መሀል እየዋኘ ሄደ፡፡
ምስራቅ ብድግ ብላ ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች….ሁለቱም መንትያዎች ‹‹ሴትዬዋ አበደች እንዴ›› የሚል እይታ አፍጥጠው ያዮት ጀመር…፡፡
‹‹ፍቅር..ምን እየሰራሽ ነው››ናኦል ነው የጠየቃት…በእነዚ ሰው በላ አውሬ በሆኑ ሽፍቶች ፊት እርቃን ሰውነቷን ማሳየቱን ጥሩ ሆኖ አላገኘውም፡፡፡
‹‹ምን ነካችሁ ዛሬ እኮ የአናንተ ልደት ብቻ አይደለም..ጥምቀትም ጭምር ነው..ታዲያ ባገኘነው አጋጣሚ ብንጠመቅ ምን ይላችኃል?፡፡›› ብላ ጎንበስ በማለት ጫማዋን አወለቀችና ወለሉን እየነካካች ወደ ገንደው ተንቀሳቀሰች….ኑሀሚ ተነሳችና እሷ አንዳደረገችው ልብሷን በፍጥነት አወላለቀች.‹‹ሴቶቹ ጤናም የላቸው እንዴ››በማለት አልጎምጉሞ ባለበት መንቋራጠጡን ቀጠለ…ኑሀሚ ልብሷን አውልቃ እንዳጠናቀቀች ሄደችና ምስራቅ ጎን ቆመች…ዳግላስ ገንዳው መሀከል ባለ ከመነደሪ ላይ ተኝቶ ጭንቅላቱን በክንዱ ደገፍ በማድረግ አይኖቹን ሁለቱ እንሰት ላይ ተክሎ በገረሜታ ከሩቅ ይመለከታቸው…እንዲሁ ለማለት ያህል ጋበዛቸው እንጂ ያደርጉታል ብሎ አልጠበቀም ነበር…የኑሀሚን ሙሉ ተክለ ቁመና ሲያይ በሰውነቱ ሁሉ ሙቀት ተረጨና ውጥርጥር አለ…ለሳምንታት ሲያልመውና ሲመኘው የነበረው ገላ ይሄው በእሱ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከፊት ለፊቱ እየታየው ነው….እሱ የእዚህ አካባቢ ገዢና አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን የዚህ አካባቢ አምላክ ..ሁሉን አድራጊ..ሁሉን ፈጣሪ እንደሆነ ነው
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ከላይ የተለቀቀው ክፍል 24 ሳይለቀቅ 25  ተለቆ ነበር ክፍል 24 አሁን ተለቋል ለነበረው መዛባት ይቅርታ  እጠይቃለው🙏 ቤተሰቦች


ለሊሴና በፀሎት በእቅዳቸው መሰረት በአንቦ በኩል አድርገው ወንጪ በመድረስ የለሊሴ አጎት ቤት ከደረሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በአካባቢው ያሉ የአቶ ለሜቻ ዘመደች ጋር እየዞሩ ሰላም ማለት እና መጋበዙ እራሱ ማደረስ አልቻሉም…እሷ ብዙ የሀብታም ድግሶችና ፓሪዎችን እንጂ እንዲህ አይነት በየሳር ጎጆውና በየደሳሳ የቆርቆሮ ቤቶች እየዞሩ በግዳጅ መጋበዝ በህይወቷ አይታው የማታውቅ ትዕይንት ስለሆነ በጣም አስገራሚና ትንግርታዊ ነው የሆነባት..በየሄደችበት የሚቀርብላት እርጎ፤ ለወተት…የማር ወለላ…አንጮቴ……ጨጨብሳና  ገንፎ..ሁሉም  ውብ  ነበር፡፡በዚህም  የተነሳ  ወደፓርኩ

ለመሄድና ለመጎብኘት ጊዜ አላገኘችም..ቢሆንም በአካባቢው ቢያንስ የሚመጡትን 15 ቀን ስላምታሳለፍ ሁሉንም ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ እንዳላት ስላወቀች ብዙም አልተጨናነቀችም፡፡
ሰለሞንም የበፀሎትን ወላጆች ይዞ ወደወንጪ እያመራ ነው፡፡በመጀመሪያ እቅዱ ወደላንጋኖ ወይም ሰደሬ ይዞቸው ሊሄድ እንጂ ወንጪ የሚባል ስፍራ ፈፅሞ በአእምሮው አልነበረም..ግን በፀሎት ወደወንጪ እንደሄደች ስትነግረው ግን ወደያው ሀሰቡን ቀየረና ለእነአቶ ኃይለልኡል ሀሳብን ነገራቸው፡፡እነሱ የትም ሆነ የትም ለቦታም ብዙም ግድ ሳልልነበራቸው ወዲያው ነበር ሀሳቡን የተቀበሉት፡፡ከዛ ወዲያው ቻርተር አውሮፕላን ተከራይተው ወንጬ ኢኮቱሪዝም ፓርክ እንግዳ ሆነው ተከሰቱ፡፡ጉዞ ተገባዶ ከቻርተር አውሮፕላኑ እንደወረዱ እነሱን ባሉበት ትቶ ቀጥታ ወደኢንትራንስ ጌት ነው የሄደው
…ስለጠቅላላ የጉብኝቱ ፓኬጅ ማብራሪያ ጠየቀና ሁለት መኝታ ክፍል ተከራየ፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና ተከራይቶ እቃቸውን በመጫን ቀጥታ ወደተከራየበት ሎጅ ይዞቸው ሄደ…
ሰለሞን ወላጆቾን ወደወንጪ ይዞ መምጣቱን ለበፀሎት አልነገራትም፡፡እሷ የምታውቀው ወደላናጋኖ እንደሚሄዱና ሲደርስና ሲመቸው እንደሚደውልላት ነው፡፡
ወንጪ ከአዲስ አበባ በ135 ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ክልል በአንቦ እና በወሊሶ ከተሞች መካከል የሚገኝ ድንቅ ስፍራ ነው ፡፡ወንጪ ሀይቅ ከባህር ወለል በላይ 3000ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ 75 ሜትር ገደማ ጥልቀት ያለው ንፁህ እና ጥርት ያለ ሀይቅ ነው፡፡ሀይቁ ከ3000 ዓመት በፊት በተከሰተ እሳተ ጎመራ የተፈጠረ እንደሆነ ይነገራል፡፡በአካባቢው የሚነገሩ አፈታሪኮች እንደሚያስረዱት በወቅቱ እንደሶደም አይነት ተንቀልቃይ እሳተ ጎመራ ተነስቶ የአካባቢውን ፍጥረት ለረጅም ጊዜ እየበላ ከቆየ በኃላ ድንገት በቦታው አርባ አራት ምንጮች ተፈጥረው የሚንቀለቀለውን ውሀ ካጠፋት በኃላ በእሳተ ጎመራው አማካይነት የተፈጠረውን ረባዳ አካባቢ መሙላት ይጀምራል….ውሀው ግን ሞልቶ በመሀከል ትንሽ ደሴት በውሀ ሳትዋጥ ደረቅ መሬት ሆና ትቀራለች…ከዛ ያንን የታዘብ የአካባቢው ኑዋሪዎች ያቺ መሬት በውሀው ሳትሸፈን የቀረችው የተቀደሰች ስፋራ ስለሆነች ከአሁን በኃላ ቦታዋና እንደማመስገኛና ከፈጣሪ ጋር መገናኛ የተለየች ስፍራ አድርገን እንገለገልባታለን ብለው ይስማማሉ…በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ ቤተክርስቲያን ታንፆበታል፡፡

የውንጪ ኢኮቱሪዝም መዝናኛ..መንገዶቹ ጠባብ ስለሆኑና የመኪና መተረማመስ የአካባቢውን ተፈጥሮ እንዲያበላሽው ስለማይፈለግ .ማንኛውም ጎብኚ በራሱ መኪና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አይችልም…ግን ወደሎጆችም ሆነ ወደመዝናኛ ፓርኮች ወይንም ደግሞ ወደገበሬዎች መኖሪያ ቤት ለመሄድ የፈለገ ሰው የተለያዩ አይነት ቀላል የትራንስፖርት አማራጭ ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል..ለምሳሌ…የፈረስ ትራንስፖርት ..ሳይክል
…ኤሌክትሪክ መኪና ካልሆነም ደግሞ በጠባበቹ የአስፓልት መንገድ ግራ ቀኝ ያለውን ውብ ተፈጥሮና የፓርክ ክፍሎችን በመጎብኘት በእግሩ ወክ እያረገ ስጋውን ማዝናናት ነፍሱንም ማስፈንጠዝ ይችላል፡፡
አጠቃላይ የወንጪ የመንገድ ልማት 70 ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ተራራውን የሚዞር 10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ … ወደ ዲንዲ ሚሄድ ሀይ ወይ …ማራቶን ራጮች እንዲለማመዱበት ታስቦ የተሰራ የሩጫ ትራክ ሁሉም ውብ ነው፡፡በተለይ ተራራውን በሚዞረው መንገድ ላይ ሁለት ሶስት ሆነው ሳይክል እየነዱ ወይም ፈረስ እየጋለቡ ዙሪያ ገባውን መጎብኘት ገነት ደርሶ እንደመመለስ አይነት አስካሪ ስሜት ውስጥ ይከታል፡፡
አንድ ጎብኚ ሎጆቹን የመከራየት አቅም ማይኖረው ከሆነ እዛው ከሪስፕሽን በፓርኩ ግንባታ ምክንያት ከቦታቸው የተነሱ ገበሬዎች በመንግስት በካሳ መልክ የተሰራላቸው ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ ከክፍሎቹ የተወሰኑትን ለቱሪስት እያከራዩ ገቢ እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራላቸው ስለሆነ ቀጥታ እዛው ሬስፕሽን ቡክ ያደረገ ሰው የየትኛው የገበሬ ቤት እንደሚያድር ይነገረውና ቀጥታ እዛ ሄዶ በተመጣጣኝ ዋጋ ማደሪያ ያገኛል፡፡
ወንጪ ውበትን ለመግለፅ እግዜያብሄር እንደምሳሌነት ለማሳያ የፈጠራት ስፍራ ትምስላለች…ውበቷ ሀይቆ ብቻ አይደለም…ዙሪያዋን የከበቡት አረንጋዴ ልብስ የለበሱት ሰንሰለታማ ወጣ ገባ ተራሮች ፣አየሩ ሁሉ ነገር ጠቅላላ ውብ ነው፡፡አሁን ደግሞ ቦታውን የቱሪስት መነኸሪያ ለማድረግ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ይበልጥ ወደፍፁምነት ያስጠጋው ነው፡፡ደረጃቸውን የጠበቁ ሙሉ ተራራውን የሚሽከረከሩ የአስፓልት መንገዶች በእያንዳንዱ ኮርነር ላይ የታነፁ የተላያዩ ታሪክ እንዲሸከሙ ተደርገው በጥንቃቄና በጥበብ እንዲታነፁ የተደረጉ ህንፃዎች፤ ሎጆች፤ ካፌዎች ፤ፈንጠርጠር ብላው ከሩቅ የሚታዩ የገበሬ ቤቶች እርሻዎች …ሁሉ ነገር አይን ሞልቶ የሚፈስ የመንፈስ ትፍስህት ነው፡፡በወንጪ ኢኮቱሪዝም ፤የባንክ አገልግሎት፤ የአካባቢው ልጆች ተደራጅተው የሚሰጡት የሬስቶራንት አገልግሎት ፤የተለያዩ የባህል እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች..ካፍቴሪያ …አነስተኛና ትላልቅ

አዳራሾች…አንፊትያትሮች ሁሉም በአቅሙ ልክ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጎ የተዘጋጀ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ይገኛሉ ፡፡
ወንጪ ኢኮቱሪዝም ባህልና ተፈጥሮን ማእከል አድርጎ የተገነባ ነው፡፡የወንጪ አካባቢ ስድስት ወር አካባቢ ዝናብ የሚዘንብባት ለምለምና እርጥብ ቦታ ነው፡፡እነሰለሞን የተከራዩት ክፍል የእሱ ባለአንድ አልጋ ሲሆን የባልና ሚስቶቹ ግን ሁለት አልጋ በአንድ ክፍል ያለበት ለቀቅ ያለ ዘመናዊና ባህላዊ እቃዎች በስምምነት ተሰባጥረው ያሳመሩት… ለሀይቁም ሆነ የአካባቢውን ተፈጥሮታ ለማየትና ለማድነቅ ውብ እይታ ያለው በአንቦ ድንጋይ ተጠርቦ የተሰራ…በአሻራ ወይም በካርድ የሚከፈት ውብ ክፍል ነው፡፡ መኝታ ክፍሉ ዘመናዊ ማሞቂያ የተገጠመለት ስለሆነ ምቹ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ ተቀምጠው ወይም ተኝተው በተከፈተው መስኮት ቁልቁል ሀይቁን ሲመለከቱ ልብን ጥፍት ያደርጋል፡፡
ምሽት ነው…አራት ሰዓት አካባቢ..አቶ ኃይለ ልኡልና ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ክፍላቸው በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ቁልቁል የጨረቃዋ ብርሀን ወንጪ ሀይቅ ላይ ስታርፍ እና ከሀይቁ ጀርባው ያለውን ውብ ሰንሰለታማ ተራራ እያዩ ያወራሉ
‹‹ሃይሌ..ልጃችን ግን አሁን ወደአዲስአባ እንደተመለስን የምትመጣ ይመስልሀል?››
‹‹አታስቢ….ትመጣለች….››
‹‹እንደማስበው አሁን እሷ እንድንሆንላት የምትፈልገውን አይነት ወላጆች የሆን ይመስለኛል…፡፡››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

…‹‹በቃ ምንም ማድረግ አንችልም ማለት ነው?››አላዛር ነው በተስፋ መቁረጥ የጠየቀው፡፡

‹‹አይ የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን››ሁሴን ተናገረ

‹አዎ….የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን ..የሆነ ሀብታም ፈልገን ለምን ወግትን ብር አንቀበለውም››የአለማየሁ ሀሳብ ነበር፡፡

‹‹ከዛ የተሻለ ሀሳብ አለኝ..አሁን ወደሰፈር እንሂድ››ሁሴን ነበር መላሹ፡፡

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹ነገ የትምህርት ቤት ተማሪዎችንና ጋዜጠኞችን ይዘን ይሄንን ሆስፒታል እንወረዋለን››

‹‹እንዴት አድርገን...?ተማሪው እሺ ይላል?››

‹‹አዎ ጥሩ ዘዴ ተጠቅመን ከቀሰቀስን ይሳካልናል፡፡
አነአለማየው ቤት ተሰብስበው ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበትን ፅሁፍ ሲያረቁ አመሹ፡፡

እህታችን ከሞት እንታደጋት፡፡
ሰሎሜ  ግርማ በጠና ህመም ታማ ሆስፒታል ከተኛች 15 ቀን እንዳለፋት እናውቃለን፡፡ በቀጣዬቹ 15 ቀናት ቀዶ ጥገና ካላደረገች ..ትምህርት ቤቱን ለአንድ ቀን ዘግተ፤ እጃችንን ወደኃላ አጣምረን ፤ለቀብር ቤተክርስቲያን መዋላችን ማይቀር ነው፡፡

እኛ እሷን ለማዳን ቤተሰቦቻችንን ሁሉ አስቸግረን የተቻለንን ብር አሰባስበናል…50 ሺ ብር በእናትዬው እጅ አለ..ሆስፒታሉ ግን 70 ሺ  ካላሳዚያችሁ በስተቀር ቀዶ ጥገናውን ማድረግ አልችልም ብሏል፡፡ይሄ ምን አይነት ሰባዊነት ነው፡፡ነገ በሰሎሜ ቦታ እኛ ብንታመምስ ተመሳሳዩ አይደል የሚገጥመን…?እኛ ተማሪዎች መብታችንን ማስከበር አለብን፡፡ከአስራአምስት ቀን በሃላ ወደቀብር ከመሄድ በነገው ቀን ልክ በእርፍት ሰዓት ተሰብስበው  ሆስፒታሉን በሰላማዊ ሰልፍ መውረር አለብን..ከዛ መንግስትም  ቢሆን ጣልቃ ገብቶ እህታችን እንድትታከም ማድረግ አለበት፡፡በቦታው ላይ የሬዲዬና የቲቪ ጋዜጠኞች ስለሚኖሩ ድምፃችን በደንብ እንደሚስተጋባ አውቃችሁ ለዚህ ተባባሪ እንድትሆኑ እንጠይቃለን፡፡፡
የሚል መልእክት በእጅ ፅሁፍ አረቀቁና…ኮፒ ቤት ሄደው ለምነው በነፃ አፃፉ፡፡በሰፈር ያሉት ኮፒ ቤቶች ሁሉ አንድ 50 ሌላው መቶ  እያለ ከሶስት መቶ በላይ ኮፒአስደረጉና  ጥዋት አንድ ሰዓት ትምህርት ቤት በራፍ ላይ ተገኙ፡፡ …ከዛ እያንዳንዱ ተማሪ ወደትምህርት ቤት ሲገባ አንድ አንድ ወርቀት እየታደለ ነበር የገባው…በእረፍት ሰዓት ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ቅፅር ጊቢ ውስጥ አልቀረም ነበር፡፡አስተማሪዎችም ሆነ ዘበኞቹ ሁኔታውን ሊቆጣጠሩ ቢሞክሩም ሁሉነገር  ከአቅማቸው በላይ ነበር የሆነው….
የትምህርት ቤቱ ዳሪክተር በኃላ እንዳያስጠይቀው ወዲያው ለአካባቢው ፖሊስ በመደወል ሁኔታውን አስረዳ፡፡፡ከአራት መቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሆስፒታሉን ወረሩት፡፡የተፈጠረውን ነገር ለማጣራትና ከዚህም ከዚያም የተሰበሰቡ ከሺ ባላይ የሚሆኑ  በአካባቢው ሚያልፉ ሰዎች ሰልፉን ተቀላቅለው የበለጠ ደማቅና አስፈሪ አደረጉት፡፡ ….ከተለያየ ጣቢያ የተውጣጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውን ደቅነው በሰልፉ ፊት ለፊት ተኮለኮሉ፡፡አድማ በታኝ ፖሊስና  የእሳት አደጋ መኪና፤አንቡላስ መኪኖች በአካባቢው በቅርብ እርቀት በተጠንቀቅ ቆመው ይታያሉ፡፡ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት ትርምስ ፈጠሩ..ሀኪሞችም ስራቸውን እንዴት እንደሚሰሩ ግራ ተጋቡ…

ከተማሪዎች አንደበት ሚወጣው መፈክር እና  በእጃቸው ፅፈው የያዙት ፅሁፍ ነበር የጉዳዩን ምንነት እንዲያውቁ ያደረገው፡

‹‹ሰሎሜ በገንዘብ እጥረት መሞት የለባትም፡፡››

‹‹ሆስፒታሉ ለሰሎሜ  ህክምና ወጪላይ ቅናሽ ማድረግ አለበት፡፡››

‹‹ሰሎሜ ዛሬውኑ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላት እንፈልጋለን፡፡››

ከቆይታ በኃላ ትንንትና ያናገሩት የሆስፒታሉ ኃላፊ በግንባሩ ላይ ላቡ እየጠንጠባጠበ ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ከሰልፈኛ ተማሪዎች ፊት ለፊት ቆሞ በድምጽ ማጉያ መናገር ጀመረ፡፡

‹‹አንዴ ፀጥታ፡፡በእውነት ጉዳዩ እዚህ መድረስ የለበትም ነበር፡፡የሆስፒታሉ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ከአንድ ሰዓት በኃላ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡እና በእርግጠኝነት የጓደኛችሁ ቀዶ ጥገና  24 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሰራላታል፡፡ይሄንን ቃል የገባሁት በህዝብና በሚዲያ ፊት ስለሆነ ምንም ስጋት አይግባችሁ፡፡አሁን ብዙ በሽተኞች እጃችና ላይ አሉ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ደግሞ ስራችንን መስራት ሰለማንችን…ምንም አይነት ግርግር ሳትፈጥሩ ቀጥታ ወደትምህር ቤታችሁ ተመለሱ…እንደምታዩት  ብዙ ፖሊስ በአካባቢው አለ..ችግር እንዳይፈጠር አደራ….ብሎ ላቡን በመሀረብ እየጠረገ ወደውስጥ ተመለሰ፡፡ተማሪዎችም እርስ በርስ እየተነጋገሩ እንዳመጣጣችው ወደትምህር ቤት ተመለሱ፡፡ በእነሱ ምክንያት የተሰበሰበውም የፀጥታ አካልና ተሸከርካሪም እንደፈሩት ምንም ጉዳት ባለመድረሱ ተደስተው እንደአመጣጠቸው ተመለሱ…ከሰዓታት በኃላ ግን ሙሉ ሚዲያው ጠቅላለ ይሄንን ጉዳይ አስፋፍቶና አጋኖ ማቅረብ ጀመረ….አንዳንዱ ሚዲያ የህክምና ባለሞያ ጋብዞ ስለሀገሪቱ የህክምና ዋጋ ውድነት አስተነተነ..ሌላው የህግ ባለሞያ ጋብዞ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሞከረ..  ሌላው ከጤና ጣቢያ ባለስልጣናትን በስልክ በመጠየቅ የመንግስትን አቋም ለማወቅ ሞከረ፡፡
ሁለት ሰዓት ዜና ላይ ግን ሁሉም የሚፈልገው ምስራች አየሩን ተቋጣጠረው፡፡ ለሰሎሜ እናትና ለጓዶቾ የሚያስፈነጥዝ ዜና ነበር፡፡
የሆስፒታሉ ቦርድ ተሰብስቦ በመነጋገር…የተማሪ ሰሎሜን ኬዝ በልዩ ሁኔታ በመመልከት እናቷ ለብቻዋ የምታሳድጋት በመሆኑና ተማሪ ጓደኞቾ እሷን ለማዳን ገንዘብ ከማዋጣት አንስቶ ያደረጉትን ከፍተኛ ትግለ እና አርአያ ያለው ተግባር ከግንዛቤ በማስገባት ሆስፒታሉ ያለምንም ክፍያ ቀዶ ጥገናውን በነፃ ሊያደርግላት ወስኗል፡፡እናትዬው ለቀዶ ጥገናው ልትከፍለው የነበረውን ብር ልጅቷን ከቀዶ ጥገናው በኃለ በማገገም ሂደት ውስጥ  ለሚያስፈልጋት ወጪ እንዲሆናት ፈቅዷል፡፡››የሚል መግለጫ.. ሰጠ፤ እንዳሉትም..በማግስቱ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ ሰሎሜ ወደቀዶ ጥገና ክፍል ገባች፡፡5 ሰዓት ከፈጀ ውስብስብ ቀዶ ጥገና ቆይታ በኃላ በሽታዋ ተወግዶ ወደ ፅኑ ህክምና ክፍል ተዘዋወረች..በዛ መንገድ ከሞት ሾልካ አመለጠች፡፡ሰሎሜ በጓደኞቾ ጥረት እና ተአምራዊ ትጋት ድና ከወር በኃላ ወደትምህርት ቤት ስትመለስ በትህርት ቤት ውስጥ በጣም ዝነኛና ታዋቂ ሆና ነበር፡፡እሷ ብቻ ሳትሆን ጓደኛቾም ጭምር የተከበሩና የተመሰገኑ ሆኑ፡፡ጥምረታቸውም ‹‹ምን አይነት ጓደኛነት ነው?››እየተባለ ሁሉም የሚቀናበትና  እንደምሳሌ የሚቀርብ ሆኖ  በሁሉም ዘንድ እውቅና አገኘ፡፡

ሁለቱም ከትዝታቸው ሲመለሱ አይኖቻቸው እንባ አቅርረው ነበር…..
ኩማንደር አለማየሁ ጉሮሮውን አፀዳዳና ‹‹አሁን ወደሁለተኛው ጉዳይ እንሸጋገር››ሲል አላዛርንም ከገባበት ትካዜ እንዲወጣ አደረገው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ምንድነው?››ግራ በመጋባትና በፍራቻ ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይማ ዋናው ነው…ይሄን ሁሉ ችግር ያመጣውና ልጅቷን በውድቅት ለሊት ብን ብላ ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት ችግር››

‹‹ዝም ብለህ እኮ ነው..ጊዜዊ የባልናሚስቶች ጭቅጭቅ ነው…ግድ የለም እኔ አስተካክለዋለው…ሁለተኛ  አይደገምም፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››ኮስተርና ቆፍጠን ብሎ ጠየቀው፡፡
አላዛር ደነገጠ‹‹ማለት?››

‹‹አላዛር …ሁሉን ነገር አውቄዋለው…እኔ የአንተም ሆነ የእሷ የሰሎሜ ጓደኛ ነኝ…እዚህ ጋር ምንም የምንደባበቀው ነገር መኖር የለበትም፡፡››