አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....“ ምናገባህ ? ሞዛዛ ?" ስትለው ድምጿ የብሽቀት ቅላጺ ነበረው ።

“እውነት ብርቄ ፥ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?” አላት ሳምሶን?

"አራት ዓመት!”

"የአራት ዓመት የሥራ ልምድ ! ከሌሎቹ አንጻር ሲታይ ትንሽ ነው ” እላት ሳምሶን "

“ መላጣ ! ” አለችው ፡ ጭንቅላቱን በዐይኗ ቂጥ እያየችው ።

“ በአራት ዓመት ውስጥ ስምሽን ለመለወጥ አልሞክርሽም ? ”አላት እስክንድር ሲቀልድባት ፡ “ እዲስ የከተማ
ስም እንደ ራሄል ኤደን ማርታ ፡ ዓለም ከተሜ ለመሆን እ ? ”

“ሒድ'ደረቅ ! ”

ሒድ፡ደረቅ !ሒድ፡ደረቅ!ደረቅ ማርታ በቅናት ቅንድቧን እያርገበገበች ከፊቱ ድቅን አለችበት ። በሐሳቡ ቁመናዋን ቃኘ በሞቅታ መንፈስ እንደገና አለማት ፡ ኪሱ ባዶ ማለም ብቻ ! ማነጣጠር ብቻ !

"ሒድ ፡ ደረቅ የሴቶች የጋራ ፈሊጽ ” አለ በልቡ ።

የብርቅነሽ ጥሬነት አስገረመው ፡ ስትጫወት የባላገር ለዛ አላት ። ንቅሳቷ ባላገርነቷን ይመሰክራል የባላገር ስሟን
አልለወጠችም " እምብዛም የከተሜ ጭምብል አላጠለቀችም ግን ከሀገርሽ ለምን ወጣሽ ? ” አላት በድንገት ።

“ ሆሆይ !ጋዜጠኛ ነህ እንዴ ?”

ባልሆን ፥ ይህን ሥራ ምን አስመረጠሽ ፡ ማለቴ ነው ። ””

“ ዋ ! ወድጄን መሰለህ ? ግድ ሆኖብኝ እንጂ ” ከማለቷ ፊቷ የኀዘን ጭጋግ ለበሰ

“ ምነው ?እንዴ? ” አላት እስክንድር ስሜቷን ተከትሎ ስሜቱ እየዳመነ።

“ ባልተቤቴ ነው ለነዚ ያበቃኝ ! በሱ ምክንያት ነው ሀገሬን ለቅቄ የወጣሁት እያለች የታሪኳ ዳር ዳር ጨረፈችው
በፍቅር ለቀረባት ሁሉ ታሪኳን ታወራለች
ልስ ልስ ሆኖ ለቀረባት የአንጀቷን ትዘከዝካለች የተማረ መስሎ ለታያት ችግሯን አፍረጥርጣ ትናገራለች ። መፍትሔ ይገኝልኛል ብላ አይደለም :: የውስጧን ተንፍሳ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የመንፈስ እረፍት ታገኛለች።

«« እባክሽ አታጓጊን ፣ በደንብ አጫውቺን" አላት እስክንድር ታሪኳን ለመስማት ተጣድፎ።

“ አያችሁ እናንተ ዕድለኞች ናችሁ : ከደኅና ቤተሰብ በመወለዳችሁ ወይም ከተማ በማደጋችሁ ለመማር በቅታችሆል እኔ የቀለም ትምህርት የለኝም ማንበብና መፃፍ እንኳ የቻልኩት አሁን የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ነው።
የድሀ ገበሬ ልጅ ነኝ ። ያውም በእንጀራ
እናት ያደግኩ !ህም እቴ! ታድያ በአሥራ አራት ዓመቴ ተዳርኩ ። ባሌ ገበሬ ነበር ። እኔ ሁለተኛ ሚስቱ ነኝ ።የመጀመሪያ ሚስቱ ከተጋቡ መንፈቅ እንኳ ሳይሞላቸው ሞታበት ነበር ። ወላጆቼም ሲድሩኝ ይህን ያቃሉ በእድሜ በሰል ያለ ነው ። ጸባዩም ጥሩ ነው ለትዳሩ ታታሪ ነው ” ተባለና ተሰጠሁ ።

“ ጎጆአችንን እያሞቅን ፡ የባላባቶችን ግልምጫና ዱላ በጋራ እየተቀበልን መኖር ጀመርን ፡ ምን ይሆናል ። እግዜር ለትንኮሉ ማሕፀኔን ድፍን እደረገው። ዓመት ጠበቅን ሁለት ዓመት ጠበቅን ልጅ የለም ። በእኔና በባልተቤቴ መሐል ቅሬታ መጣ ያም ሆኖ አልተቃቃርንም ። ድህነት ያስተሳስረን ነበር ። እሱ ከገበሬዎቹ ጋር ውጭ ደክሞ ውሎ ሲመጣ ከቤት ያለሁ
ረዳቱ እኔው ነበርኩ በባላባት ጅራፍ ጀርባው ቆስሎ ሲመጣ አንጀቴ እየተንሰፈሰፈ የማለቅስላት እኔ ነበርኩ ዋ! እቴ ምን ያደርጋል!

እንዲህ እንዲህ እያልን አምስት ዓመት ያህል እንደኖርን አብዮቱ ፈነዳ ። ለውጥ መጣ ። ደክመን ለባላበት መገበሩ ቀረ። እፎይ አለን ። ቤታችን ሙሉ ሆነ እውነቴን ነው ደህና ነገር መብላት መልበስም ጀመርን ። ምን ይሆናል ። ከድህና
ኑሮ ጋር ተያይዞ ነገር መጣ ባልተቤቴ ሌላ ሴት ጋር በስርቆት መሔድ ጀምሯል የሚል ወሬ ሰማሁ ። ስውል ሳድር እኔም
ነገሩን ደረስኩበት። እንዲያውም አንድ ልጅ እንደ ወለደችለት አረጋገጥኩ ። ቀናሁ ! ቅናት አንገበገበኝ ። በሐሳብ
ተብከነከንኩ። ጨስኩ ።ቤት ውስጥ !
መቀመጥ አቃተኝ ብዙም ሳልቆይ ጓዝ ምንጓዝ ሳልል በርሬ ወጥቼ አዲስ አበባ ገበኋት !

“ እዚህ ስደርስ ደግሞ ያዘጋጀሁት ማረፊያ የለኝ ፥ እንደሁ ሜዳ ቀረሁ ። ትንሽ ቀን ሰንብቼ በደላላ አማካይነት
ግርድና ተቀጠርኩ። ስድስት ወር እንደ ሰራሁ ግርድናን እርም ብዬ ተውኩት። አባስኩ እቴ ! የሰው ቤት ሹሮ ሲያልቅ
እኔ ላይ ማፍጠጥ ። ዕቃ ሲጠፉ እኔን መወንጀል ። ምነው ከዚህ ሁሉ ሥጋዬን ሸጨ ባድር አልኩና ሽርሙጥና ጀመርኩ
እላችኋለሁ ።

ብርቅነሽ ስትናገር ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ባሕር ውስጥ የከታቸውን ያኸል ሥስቱም ጸጥ ብለው ነበር ። አሳዘነቻቸው። ምስኪን ጥሬ ፍጥረት ! በመጠጥ ሞቅታ ኃይል ለሁሉ ነገር ግዴለሽ ሆኖ የቆየው አቤል እንኳ፥ ከብርቅነሽ አፍ የድህነት ድምፅ ሲሰማ ቸል ማለት አልቻለም ። ሕዋሳቱ በኀዘን ስሜት ተወራጩ ::

ግን ዝዎም ብለሽ ከምትኮበልይ ፥ ሰላምን በአካባቢሽ በሚገኘው የሴቶች ወይም የገበሬ ማኅበር አመልክተሽ መፍ
ትሔ ኣትፈልጊም ነበር ? ” እላት እስክንድር ፡ ከማዘኑ የተነሣ የሚናገረው ጠፍቶት ።

ዋ እቴ ! ቤት ከፈረሰ ወዲያ ሁሉስ ምን ሊበጅ ? አየህ ፡ ቅናት ከመጣ ቤት ፈረሰ ማለት ነው። ለሁሉም እኔ ለማንም አላማከርኩ ። የሚያለቅሱ ልጆች የሉኝ ' ነጠላ ሰው ምናለበት አልኩና ብር ብዬ አዲስ አበባ ፣ ”

ታዲያ ባልሽ ሊፈልግሽ አልመጣም ” አላትአቤል በሁኔታዋ ስሜቱ ተነክቶ ።

“ ውእእይ • ሥራ አጥቶ ! እንዲያውም ከዚያ ሀገር ለንፀግድ የሚመላለሱ ሰዎች እዚሁ ቡና ቤት አግኝቼ ሲነግሩኝ' ውሽማውን ጠቅልሎ ይዟል አሉኝ • እዩዬ ! ” ብላ ሳትጨርስ ጥሬ ሰማች «

“ ብርቅነሽ ? ! አንቺን'ኮ ነው ? ” የቡና ቤት ባለቢቷ ድምፅ ነበር
“ እመት ! ወይ ጕዱ ዛሬ ! ” እያለች ብርቅነሽ ከተቀመጠችበት ተነሣች

“ እንድዩ ! ሰው ሲገባ አትታዘዥም እንዴ! ምን ይጎልትሻል ? ”

ብርቅነሽ የውስጧን ተንፍሳ ቃጠሎዎን አብርዳ ተነሣች ፡ እስክንድር ተከዘ ቃጠሉዋ ወደ እሱ ተላለፈበት ኀዘኗ ጠልቆ ወጋው ። ቅናት ተፈጥሮአዊ ነው ሀብታምና ድሀ አይልም ። የወደደ ሁሌ ለወደደው ነገር ይቀናል ። ለቀናበት ነገር ይሠዋል ። ብርቅነሽ የቅናትን እሳት ሸሽታ ኮበለለች ። ከቅናት ሸሽታ ሴትኛ አዳሪ ሆነች "

እስክንድር ሐሳቡ ከግላዊነት ወደነማኅበራዊነት መጠቀ ለእሱ ሲጋራ መግዣ መስጠት ያቃታቸው ደሀ እናቱ ላይ ሆኑ፡ሕዝቧን በሰፊው ማስተማር ' በቂ ኢንዱስትሪ ከፍታ እነብርቅነሽን ማሠማራት ያልቻለች ረሀብን ለማጥፋት
ማይምነትን ለማጥፋት ርካሽ ልምዶችን ለማስወገድ በባህል ለማደግና የቴክኖሎጂ ውጤት ተጠቃሚ ለመሆን የልጆቿን እጅ የምትማጠን እናት ሀገር፡እጆቿን ዘርግታ በሐሳቡ ታየችው
ከሐሳቡ ፋታ አግኝቶ እሱነቱን ወዳለበት ሲመልስ ምሶን ዐይኑን አፍጥጦ ተመለከተ ።አስተያየቱ አላማረውም ። በልቡ ምርምርህን እዚያው ዩኒቨርስቲው ውስጥ አድርገው ፥ ይሄ መጠጥ ቤት ነው የሚለው መሰለው "
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

እነሱ ለትህትና ሕይወት እንደዚያ ሲሯሯጡ ደግሞ የእንደሻው ወላጆች ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ ከተች እየተሯሯጡም ብቻ ሳይሆን እየተራወጡ ናቸው። የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር። በተለይ አንዷ ጥይት የራስ ቅሉን በስታው ስላለፈች፤ የአእምሮ ቀውስ
እንዳያስከትልበት፤ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
በተፈጠረው አደጋ ምክንያት የእንደሻው ወላጆችና የአዜብ ወላጆችም ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ...
"ያቺን የተረገመች ልጅ አምጥታ ልጃችንን ልታስገድለው የነበረችው አዜብ ነች በሚል ሲሆን፤ ፀቡን ከአዜብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿ ጭምር አድርገውታል :: እነሱ እንደዚያ ብለው ይናገሩ እንጂ ፤ የአዜብ ወላጆች ሁኔታው ሊፈጠር የቻለው አለሌው ልጃቸው
በፈፀመው ተደጋጋሚ አስነዋሪ ድርጊት ሳቢያ መሆኑን ሲያውቁ የክርስትና ልጃችን ነው በሚል ምክንያት ብቻ ፤ በትህትና ላይ ሊፈርዱባት
አልደፈሩም....
"ሁሉንም ስራው ያውጣው በማለት መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ትህትና ጤናዋ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ጐን ለጐን በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባት፡፡ አዜብና ብሩክ ይህንን እንዳወቁ ቀጣዩ ትኩረታቸው
በምን ላይ መሆን እንዳለበት በስፋት ተመካከሩ፡፡ ከዚያም አንዳንድ
በመከላከያነት ይጠቅማሉ ያሏቸውን ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ፤ ሁለቱም
በየፊናቸው ሩጫ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጉዳይ አበራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገመቱ :: ምክንያቱም አበራ በእንደሻው ክህደት የደረሰበትና፤ በትህትና ላይ ስለተፈፀመው ወንጀል በሚገባ የሚያውቅ የአይን ምስክር ስለነበረ ነው፡፡ አበራ በእንደሻው ስለተፈፀመበት ክህደት ለአገሩ ሁሉ ሲያወራ ለአዜብም አጫውቷት ነበር ፡፡
ከዝምድና ይልቅ ገንዘብን አስበልጦ አስር
አመት ሙሉ ያጠራቀምኩትን ገንዘቤን ወስዶ ከከበረበት በኋላ ከዳኝ፡፡ በጋራ
እናድግበታለን ብሎ የገባውን ቃሉን አፍርሶ አባረረኝ " በማለት በምሬት ነበር የገለፀላት፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ በደል የተፈፀመበት ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ እውነቱንና የሚያውቀውን ከመናገር ወደኋላ ሊል ይችላል? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ በፍፁም ወደኋላ አይልም ስትል ተማመነች፡፡ምክንያቱም እሱ እንደዚያ በንዴት እየተንቀጠቀጠ
ሲነግራት...

“አይዞህ አበራ ተወው፡፡ አንተ ጤና ሁን እንጂ ፤ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው፡፡ በክህደት የተገኘ ገንዘብ ደግሞ የትም አያደርስም፡፡
ከሰራህ ከካደህ ሰው በላይ መሆን ትችላለህ :: አይዞህ! እግዚአብሄር ላንተ ያለውን ምንግዜም አታጣውም " በማለት ትልቅ የማፅነኛ ቃል ለግሳው ነበር፡፡ ያንን
የሰጠችውን የተስፋ ቃል እንኳ አስታውሶ እሺ ይላት ይሆን? ወይንስ እሱም እንደወላጆቹ ተደርቦ ከእውነት ጀርባ ይቆም ይሆን? ልቧ ተጠራጠረ፡፡ ለማንኛውም አለችና ስልክ ደወለችለት :: ስልኩን አነሳና እሷ መሆንዋን ሲያውቅ የሞቀ ሰላምታ አቀረበላት፡፡ ትንሽ እፎይ አለች በልቧ፡፡ለጉዳይ እንደምትፈልገው
ስትገልፅለት፤ በደስታ ተቀብሎ የሚገናኙበትን ቦታ ተቀጣጥረው
ተሰነባበቱ፡፡ በማግስቱ በቀጠሮው ቦታ ቀድሞ የደረሰው እሱ ነበር።
የተፈለገበትን ጉዳይ ስትነግረው...
"ተይ እንጂ አዜብ እቤት ድረስ የወሰድኳት እኮ እኔ ነኝ፡፡በወንጀለኛነት አያስጠይቅህም ነው የምትይኝ?" ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት።
"ስለሱ ከሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል፡፡ አንተን በወንጀል
ተባባሪነት እንዳያስጠይቅህ በቂ ምክንያት ማቅረብ ይቻላል፡፡”
"ለምሳሌ ምን?"
"አበራ ሙት ምንም አትፍራ! በዚህ ጉዳይ አንተ በጥፋተኛነት እንድትጠየቅ የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ፧ አንተ ይዘሃት የሄድከው ወደ ቀጣሪዋ ቤት እንጂ፤ ወንጀል
ወደሚፈጸምበት ጫካ ውስጥ አይደለም፡ቀጣሪዋ ቤት አደረስካት ማለት፤ እንደሻው ደብድቦና፤ አስገድዶ፧ ክብረ ንፅህናዋን እንዲደፍራት አደረክ ማለት አይደለም :: የቀጣሪዋን ቤት የወንጀል መፈፀሚያ ዋሻ ያደረገው ወንጀለኛ ብቻ ነው ለዚህ ተጠያቂ የሚሆነው፡፡ አይዞህ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም፡ አበራን ለማሳመን ብሎ ብሩክ ያስጠናትን ደሰኮረችለት፡፡ አበራ ልቡ ትንሽ ተለሳለሰ፡፡
"በሌላ በኩል ብታየው ደግሞ የቀጣሪዋ ባለቤት ልጅ የቅጥር ውል እንድትፈርም ይዘሃት ና ብሎ አዘዘህ :: አንተም ይህን ነገርካት። እሷም እሺ ብላ ሳታስገድዳት በፈቃደኝነት አብራህ ሄደች። ከዚያም አንተ በሌለህበት እንደሻው ወንጀል ፈፅሞባት ደረስክ፡፡ በቃ፡፡ ይህ አይደለም
ታሪኩ? አንተን የሚያስጠይቅህ ምኑ ነው ታዲያ?" ስትል የማደፋፈሪያ
ሀሳብ አዥጐደጐደችለት፡፡

በልቡ ያሳደረው ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋለትም፤ በአዜብ አቀራረብ ተስማማ፡፡ እንዳለችውም እሱን በቀጥታ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል ጭብጥ እንደሌለ ተሰማው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ያቺ ምስኪን እንጀራ ፈላጊ ልጅ ፤ በደም ተጨማልቃ ወድቃ ያያት እለት የተሰማው ስሜት ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ በተፈፀመባት ወንጀል ከልቡ አዝኖ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ያ ግፈኛ ከሃዲ ከሱቁ ካባረረው በኋላ አሁን አሁን በርካታ ካፒታል በማንቀሳቀስ በቅናት እያቃጠለው
ነው፡፡ በጥይት መቃጠሉን የሰማ እለት " እሰይ የእጁን ነው ያገኘው"ነበር ያለው፡፡ አሁን ደግሞ እሱ ተጠያቂ በማይሆንበት ሁኔታ ለምን ያየውን ከመመስከር ወደ ኋላ ማለት እንደሌለበት ተገነዘበ ፡፡ያየኽውን እውነት መሰከርክ ብሎ የሚፈርድበት ዘመድ እንደማይኖርና፤ ቢኖርም መፅሀፍ ቅዱስ ይዞ በሚፈፅመው መሃላ በውሸት መስክሮ ነፍሱን ማስኮነን እንደሌለበት ተሰማው። እንደሻውን ሊበቀል
የሚችልበትን ይህንን መልካም አጋጣሚ ሊጠቀምበት ወሰነ : እንቢ ቢልስ የት ሊደርስ ? በተለይ አዜብ እየነገረችው
ያለው ፣ ባለስልጣን ፖሊስ ከአዜብ በስተጀርባ መኖሩን ነው፡፡ በተለይ "ሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል"
ስትለው ምን እያለች እንደሆነ
ገብቶታል፡፡አልመሰክርም ቢል በተባባሪ ወንጀለኛነት ተፈርጆ፣ ለፍርድ እንደሚቀርብ እየነገረችው ነው፡፡ ይሄንን ጭምር አስቦ፤ ልቡ ስለፈራ፤ ያየውን ሁሉ በዝርዝር ሊያስረዳና፤ ለትህትና ድንበሩ የመከላከያ ምስክር ሊሆን ቃል ገባላት፡፡ ቃል መግባት ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ ማስረጃ ጠቆማት..

"እኔ ብቻ ሳልሆን በዚያን እለት ሁኔታውን የተመለከተችው የቤት ሰራተኛዋ ወርቅ ያንጥፉም ያየችውን ሁሉ እውነቱን ሳትደብቅ እንድትመሰክር እናደርጋለን :: ደግሞም ትመሰክራለች፡፡ አትጠራጠሪ!
በትህትና ሁኔታ በጣም ነው ያዘነችው፡፡እሷም ስመ እግዚአብሄርን ጠርታ
ያየችውን ሁሉ ትመሰክራለች፡፡ አይዞሽ ! " አላት፡፡ አዜብ ከጠበቀችው በላይ ተባባሪ ሆኖ ስለኣገኘችው፤ በደስታ እቅፍ አደረገችው፡፡ በዚሁ መሰረት አበራና ወርቅ ያንጥፉ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው፤ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደረገ፡፡ ቀኑን፡ ሰአቱን፡ የድርጊቱን አፈፃፀም፡ ዝርዝር ሁኔታውን፤ በሙሉ በአንድ አይነትና ፤ ተመሳሳይ በሆነ ቃል
መሰከሩ። ያም ብቻ ሳይሆን አንዱአለምን ጋርጠው በሚል ቅፅል ስሙ በሚታወቀው ወሮበላ እንዳይሞት፤ እንዳይድን፤ አደርጐ ያስደበደበው
መሆኑን፤ ራሱ እንደሻው በኩራት ሲናገር መስማቱን፧ ጭምር ገለፀ፡፡
በእርግጥም እንደሻው ያንን ለአበራ የተናገረው፤ ይሄ ይመጣብኛል ብሎ ሳይሆን፤ አንተም አርፈህ የማትቀመጥና ወሬ አበዛለሁ የምትል ከሆነ፤ አስወቅጥሀለሁ፤ የሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ አጋጣሚ እንደሻውን የደበደበው ጉልበተኛ
ስለታወቀ፤ ወዲያውኑ ታድኖ እንዲያዝ ሲደረግ ፤ አበራ ማንነቱን በማሳየትና የሚገኝበትን
👍21
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

..... የረር ጎታ ሲቃረቡ ነበር ሲቲና ከእንቅልፏ የተነሳችው፡፡

“ለምን አትተኛም ነበር? ቀንኮ ይደክምሃል» አለችው:: እንቅልፍ
ያሳቀጣቸውን ጉንጮቿን እያሻሸች::

“ተመችቶሽ ተኛሽ? ” አላት ፈገግ ብሎ፡፡
“አመሰግናለህ፡፡ የሚመች ትከሻ አላህ፡፡” አለች እየሳቀች፡፡ ጎንበስ ብላ ከሻንጣዋ ውስጥ ሎሚ አወጣችና አንድ ለእሱ አንድ ለራሷ ወሰደች::
“ሎማ ያነቃቃል፤ ታውቃለሁ? " አለች የያዘችውን ሎሚ እየመጠጠች፡፡

ድሬዳዋ ለገሃሬ ደርሰው ከባቡሩ ሲወርዱ ናትናኤል ተደነጋገረው:: የባቡር ጣቢያው በሰው ተጨናንቋል፡፡ አንድ እርምጃ ለመራመድ ሁለት ሦስት ሰዎች መገፍተር አለባቸው:: ሰው የት ወደየት እንደሚሄድ መለየት ያስቸግራል፡፡ ብቻ ባለበት ይተራመሳል፧ ይገፋፋል ፧ ይታሻሽል። ከኋላው ተቀምጣ የነበረችው ሴት አብሯት ከተቀመጠው ተሳፋሪ ጋር እያወራች ስትወርድ ዞሮ ተመሰክታት:: አብሯትት ካለው ሰው ጋር ታውራ እንጂ
አይኖቿ ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርግጠኛ ነው... ከዚህ ቀደም አያቷታል፡፡

“የት ነው የምታርፈው አለችው
ሲቲና ቀደማ ከባበሩ እየወረደች::

“እ… አልወሰንኩም።” አላት ከጀርባው ተቀምጣ የነበረችውን ሴት ማንነት ለማስታወስ እየጣረ:: እርግጠኛ ነው.. መልኳን ያውቀዋል ግን ራቀበት፡፡
“ማለቴ ዘመድ ጋ ነው... ወይስ ሆቴል?” አለችው ሲቲና::ድንገት ብልጭ ሲልለት ድጋሚ ፊቱን ወደ ሴትየዋ አዙሮ ተመለከታት፡፡ የአብርሃም ሠራተኛ! ዞሮ ተመስከታት:: ሳያውቀው ዓይን ለዓይን ተጋጩ፡፡ ቀድማው ፊቷን መለሰች:: ሴትየዋ ቀድሞ ካላያቸው ሁለት ሰዎች ጋር ስታወራ ተመለከተ፡፡

“እ..ምን አልሺኝ? አይ…. ሆቴል ነው የማርፈው ለጊዜው፡፡” አለ ፊቱን ወደ ስቲና መልሶ፡፡

“ከፈለግህ እኔጋ ማረፍ ትችላለህ፡ባዶ ቤት ነው ያለሁት፡፡”
“እ... አለ አሁንም ፊቱን መልሶ የአብርሃምን ሠራተኛ ባየበት አቅጣጫ ተመለከተ፡፡ ዓይኑን የምትሸሽ መሰለው፡፡ አብረዋት የነበሩት ሦስት ሰዎች በአጠገቧ የሉም፡፡ ሴትየዋ ብቻዋን ጥግ ይዛ ቆማለች፡፡

«ማለቴ ለሁለት ለሦስት ቀን ችግር የለም ማለቴ ነው፡» ከጎኑ ከጎኑ እየሄደች አንገቷን አቀርቅራ ተናገረችው ሲቲና፡፡

ከሰው ግፊያ ወጣ ብለው ወደዳር ላይ የያዟቸውን ሻንጣዎች ከመሬት ላይ አሳርፎ ቀና ሲል ባሻገር ተመለከታት፡፡ ሴትየዋ አሁንም ታየዋለች:: ምናልባት የት እንያምታውቀኝ ጠፍቷት ይሆናል።" ብሎ አሰበ፡፡

“አስቸግርሽ እንደሆነ…” አለ ፊቱን ወደ ሲቲና መልሶ፡፡
“በፍጹም፡፡” አለች ፊቷ በሃፍረት እየቀላ፡፡
“እ... ” ናትናኤል አመነታ፡፡ ሆቴል አለመያዙ ከዓይን የሚያድነው ብቻ ሳይሆን ገንዘብም የሚቆጥብለት ነው፡፡ ግን ይቺን ልጅ ተከትሎ ከቤቷ ሄዶ ምን እንደሚከተል ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ መቼም ምሳና እራት ሊያባላት ወይ ለነፍሷ ብላ እንዳላስጠጋችው ግልጽ ነው፡፡ ግን ቢሆንስ እንዴት ድንገት ልታቀርበው ፈለገች? “ምን መሰለሽ…” አለ ግብዣዋን
እምቢ የሚልበት ዘዴ ጠፍቶት ኣቧራ ያበላሸውን ነጭ ጀለቢያውን
እያራገፈ፡፡

“አስቸግራታለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ ምንም ችግር የለም፡፡ ባዶ ቤት ነው ከፍቼ የምገባው:: ወላሂ አልኩህ፡፡”

“እስቲ እየሄድን እናውራ፡፡” አለ ናትናኤል - የሰው ትፍግፍግ ማለትና የአየሩ ሙቀት ትንፋሽ ቢያሳጥረው።

ጎንበስ ብሎ ሻንጣውን ሲያነሳ ከጎኑ ቆማ የነበረችው ሲቲና ገፍትራ ከመሬት ደባለቀችው፡፡ መሬት ላይ ሁለቴ ተንኮበሉ ቀና ሲል ነበር ነገሩ ጭንቅላቱን የመታው ከጀርባወ ቆመው የነበሩ አንድ አዛውንት በደም የተጨማለቀ ሆዳቸውን ይዘው ወደ ሠሬት ሲያዘቅጡ አያኖቹን አፍጥጦ
ተመለከታቸው!” እሪ አለች ከጎናቸው የነበረች ወጣት ሴት፡፡ ከወደቀበት
ለመነሳት ሲጣደፍ ሲቲና ሸብረክ ብላ ከተከናነበችው ድሪያ ስር ሽጉጥ
መዥረጥ ስታደርግ አያት:: ተቀደመች:: የያዘችው ሽጉጥ እጇ ወስጥ ተፈናጥሮ ሲወረወር እሷ ደረቷን አፍና ወደ ኋላዋ ወደቀች.. ዙሪያውን ረብሻ ሆነ... ጩኸት... ሩጫ.. ኡኡታ... ቶክስ እሪታ ዙሪያወን አደባለቀው..ናትናኤል ከአንገቷ ቀና አደረጋት...

«ሩ...ጥ! ተክትለውሃል... ሩጥ!» አለችው በግራ እጇ በደም የተዘፈቀውን ደረቷን አፍና እንደያዘች ሲር ሲር ከሚለው ትንፋሿ እየቆነጠበች ‹‹ ሩጥ!»

ቀና ሲል አየው:: የጨበጠውን ሽጉጥ ከትከሻው በላይ ይዞ ከፊቱ የሚጋረጡትን ሰዎች አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ እየገፋ እየገፈታተረ ወደ እሱ እየቀረበ ሲመጣ በሚተራመሰው ሕዝብ መሃል በሩቁ አየሁ
ከአብርሃም ሠራተኛ ጋር የነበረውን አንድ ሰውዬ! እንደ ጥንቸል ተፈናጥሮ ከሚደነባበረው ከሚራበሸው ሕዝብ መሃል እየተሹለከለከ በትርምሱ ውስጥ
ሰመጠ... የአብርሃም ሠራተኛ! የፈጣሪ ያለህ! የአብርሃም ሠራተኛ! ከራሱ ጋር እያነበነበ ሮጠ፡፡ ከጀርባው የተኩስ እሩምታ አጀበው::

ወዴት እንደሚሮጥ.. የት እንደሚደርስ ግድ አልነበረውም:: ብቻ ሮጠ፡፡ እራቅ እንዳለ በሩቁ እንዳይለዩት ጭንቅላቱ ላይ የጠመጠመውን ሽርጡን አውልቆ በእጁ ያዘው:: ትንሽ ከራቀ በኋላ ደግሞ ወደ ጥግ ዞር አለና ጀለቢያውን አውልቆ ወርውሮ ከወገቡ በታች ሽርጡን አጥልቆ ከላይ ነጭ ሸሚዙን እንዳደረገ ከራሱ ጋር እያጉተመተመ ሮጠ፡፡ የአብርሃም
ሠሪተኛ! እንዴት ሊከተሉት ቻሉ? ወደ ድሬዳዋ መምጣቱንስ እንደት አወቁ? ሲቲና ባትገፈትረው'ኮ ወደፊቱ ሲወድቅ ባይስቱት'ኮ.. ' በደም የተጨማለቀ ሆዳቸውን ይዘው ያዘቀጡት ሽማግሌ ታዩት:: የፈጣሪ ያለህ! ገለውት ነበር'ኮ የአብርሃም ሠራተኛ! ወያኔ አብርሃም! ለካ ሳያውቀው!

ሲቲና ማነች? ሩጥ…ተከትለውሃል ሩጥ የምስራችን የገደለቻት ሴት ምንድን ነበር ያለችው? ሩጥ!' ሲቲና ማነች? የፈጣሪ ያለህ! ሁሉ ነገር ተወሳሰበበት:: ማሰቡን አቁሞ ሩጫውን ቀጠለ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ያለበት ቦታ የት እንደሆነ ለመረዳት አልቻለም፡፡ በስተግራው መደዳ የተሰሩ ቤቶች ማስታወቂያዎቻቸውን በየቢሮዎቻቸው ላይ እንዳንጠለጠሉ ተደርድረዋል:: ፈቶግራፍ ቤት..የልብስ ሰፊ...ስዓት ማደሻ..በስተቀኙ ደግሞ በረንዳው ላይ የሳጠራ ወንበሮች የተደረደሩበት በሐረግ የተሸፈነ በረንዳ ያለው ቤት ይታያል ድሪዳዋ፡፡

ወደ ቡና ቤቱ፡ ተጠጋና አካባቢያን ለማጥናት ሞክረ፡፡ የፊተኛው ክፍል ሰፊ ቢሆንም ጨለምለም ያለ ነው፡፡ ፈጠን አለና ወደ ውስጥ ገባ፡፡በትናንሽ ጠረጴዛዎች ዙሪያ የተኮለኮሉ ትናንሽ የብረት ወንበሮች ፈንጠር ፈንጠር ብለው ክብ ክብ ሰርተዋል፡፡ በጋዝ የተወለወለው የሲሚንቶ ወለል ቢያብለጨልጭም ሽታው ይከብዳል:: ቁርስ የሚያቂርጉ የቡና ቤቱ ደንበኞች በየወንበሮቻቸው ተቀምጠሁ ያዘዙትን ይስተናግዳሉ፡፡

ባዶ ወረጴዛ ፈለገና ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡

“ምን ልታዘዝም ! በስተቀኝ የተንዘላዘለ ፀጉሯን ጣቷ ላይ እየጠመጠመች እየፈታች ጠየቀችው::

ሻይ አላት ቶሎ ለመገላገል፡፡ ፊቷን መልሳ ሄደች፡፡ ናትናኤል ከራሱ ጋር ምክክር ቀጠለ።

ጊዜ የለውም:: መፍጠን አለበት:: አለበለዚያ ያገኙታል በማያውቀው ከተማ ውስጥ ተደብቆ መቆየት ዘበት ነው ግን እንዴት ተከተሉት? ከርብቃ ቤት አምልጦ ሲሮጥ ተከትለውት ነበር ማለት ነው?
መሆን አለበት፡፡ የአብርሃምስ የቤት ሰራተኛ እዚህ ምን አመጣት? ወይኔ!
አብርሃምን ትከታተለው ነበር ማለት ነው! አሁን ደግሞ

የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዘውን ሻይ አምጥታ ፊቱ አስቀመጠችለት::

እባክሽ የእኔ እመቤት የስልክ ቁጥር ማውጫ ደብተር ይኖራችኋል? “ አላት

“ይቅርታ የለንም ለምን ማዞሪያ አይጠይቁም
👍1
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

ድርጅት የእገታ ማስለቀቂያውን የገንዘብ ክፍያ ከታጋች ቤተሰብ ተቀብለው እና ድርሻቸውን ቆርጠው ለአጋቾች እንደሚሰጡ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ አንደኛው የቢዝነስ አካሄድ ነው፡፡ ሌላኛው ነገር ደግሞ ራሳቸው የወሮበላ ቡድኖቹ አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎቻቸውን ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሰዎች መዝገብ ውስጥ እንዲገቡ ታስደርግላቸዋለች፡፡ ይሄ ደግሞ የሚያሳየው እሷን የሚያግዝ የመንግስት አካል ከውስጥ እንዳላት ነው።

“ከፖሊሶች ውስጥ ማለት ነው?” ብላ ኒኪ ጠየቀች፡፡ ዊሊያምስም ትንሽ ፈገግ አለና “አትገረሚ፡፡ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ ከባድ ልብስ ሲሰቀልበት እንደሚረግብ አሮጌ የልብስ መስቀያ ሆኗል፡፡ ሌላው ደግሞ የጠፉ ልጆችን በህገወጥ መንገድ ከሚያዘዋውሩ ሰዎች እጅ ውስጥ እንደሚገቡ ነው፤ እነዚህ በአየር
መንገዱ የተጠለፉ ህፃናት እና ወጣት ሴቶችም ለሩሲያ የወሲብ ንግድ
አስማሪ የወርበሎች ቡድን ይሸጣሉ የሚል መረጃ አለኝ፡፡ ይህንንም
ላረጋግጥልሽ አልችልም ግን ያው ውስጥ ለውስጥ የሚወራ ነገር ነው፡፡” ኒኪም አይኗን ገርጥጣ “እና ቻርሎቴ ክላንሲ...?” ዊሊያምም ራሱን በአሉታ
ነቅንቆ “አይመስለኝም፤ የወሲብ ንግድ የሚሰሩ ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ
በየሀገሩ የሚያዘዋውሩ ቢዝነሶች አነስተኛ ገቢ ነው ያላቸው፡፡ ቤተሰቦቻቸው
አጥብቀው የማይፈልጓቸውን ህፃናት ወንዶችና ሴቶችን ነው በዚህ ሥራ ላይ
የሚያሰማሩት፡፡ ስለዚህ አንዲት የ18 ዓመት ዕድሜ ሴትን በዚህ ቢዝነስ
ውስጥ ማሰራታቸው ይጎዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም፡፡ ብቻ በአንድም
ሆነ በሌላ መልኩ ይህ የቫላንቲና ቡድን ድርጅት ከፊት ለፊቱ የጠፉ ሰዎችን
የሚያፈላልግ መስሎ ከጀርባ ግን የሚፈልጉትን ሥራ ይሰራሉ። በቫላንቲና
ባደን የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥም ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
ከሚያገኙት (ከሚያስጭኑት) ገንዘብ እጅግ በጣም የላቀ ገንዘብን ያስገባል።”
አላት፡፡

ኒኪ በዝምታ ውስጥ ሆና ዊሊያምስ በወሬ ሰማሁ ያላትን ጓደኛዋ ግሬንቸን እና ገና በወጣትነቷ እህቷን ያጣችውን ቫላንቲና ባደንን ከዚህ ቡድን ጋር ማጣመር አቃታት፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም በዙሪያዋ የሚገኙ ሰዎች በመንፈስና በምግባር ጥንካሬ እየለሰለሱ መሆናቸውን እያየች ቢሆንም ዊሊያምን ተሳስተሃል ለማለት ተቸገረች፡፡

“በማንኛውም መልኩ” ብሎ ዊልያምስ በመሀከላቸው ያለውን ዝምታ ሰበረ እና “ሚስ ባደን እዚህ ነገር ተግባር ላይ እንድትገኝ የሚያደርገው የምትገኘው ዋነኛው ስው ሉዊስ ሮድሪጌዝ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ትኩረቱን ከኮኬይን ላይ አንስቶ ክሮክ ላይ አድርጓል። በዚህም
የኤል.ኤን የዕፅ ገበያን ከሩሲያኖቹ ለመንጠቅ አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ።
እዚህ ከተማ ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች አሉት። በቃ እነርሱ ልክ እንደ ወረርሽኝ ሁሉም ቦታ ላይ ይገኛሉ።” አላት፡፡

ዊልያምስ እነርሱ እንደ ወረርሽኝ ሁሉም ቦታ ላይ ይገኛሉ ብሎ የተናገረውን ነገር ስትሰማ ካርተርን አስታወሰች፡፡ ምክንያቱም ቀን ላይ ካርተር ይገድሉኛል ብሎ ስለሚፈራቸው ሜክሲካውያን ሲነግራት የገለፀላት በዚሁ መንገድ ነበር። ስለዚህ የካርተርን ሀሳብ ማመን ይኖርብኝ ይሆን?”

“ሌላ ግንኙነት። ሌላ የጭለማ ውስጥ የሸረሪት ድር”

ከዚህ የጥልፍልፎሽ ሀሳብ ውስጥ በጠራ አዕምሮ ማሰብ ፈልጋም “እሺ ሉዊስ ያደንዥ ዕፅ ቢዝነስ ውስጥ አለበት እንበል። ግን አኔ ስለዚህ ነገር
ታውቃለች?” ብላ ዊልያምስን ጠየቀችው፡፡

“ሉዊስ የአደንዛዥ ዕፅ ቢዝነስ እንደሚሰራ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህቺ ሚስቱ ይሄን ሁሉ ገንዘብ ከየት እንደሚያመጣው ትወቅ አትወቅ ግን እርግጠኛ አይደለሁም። አንቺ ስለእሷ ከነገርሺኝ ነገር በመነሳት ግን እሷ ይህንን ነገር የምታውቅ አይመስለኝም:: ምክንያቱም ሮድሪጌዝ ሁለት ስብእና ያለው ሰው ነው፡፡ ቢዝነሱን ከግላዊ ኑሮው ለይቶ ማስኬድ ይችላል።”

ይህንንማ ለአኔ መንገር አለብኝ ብላ አሰበች በውስጧ፡፡ ኒኪ የእሷ ባል
ማን እንደሆነ የማወቅ መብት አላት። እያንዳንዷ ሚስት ይህ መብት ሊኖራት ይገባል። እየተዋሸች መኖር የለባትም። ብላ አሰበች፡፡

“እሺ ይህንን የእሱን ሥራ ፖሊሶች ያውቁታል ብለኸኛል? እዚህ
የኤል.ኤ. ፖሊስ እና የኤፍ.ቢ.አይ ሰዎችም ስለ ጉዳዩ ያውቃሉ?”

“በደንብ ነዋ” ብሎ ዊሊያምስ ፈገግ አለ እና ባይገርምሽ የኤሌ.ኤ.ፒ.ዲ የፀረ አደንዛዥ ዕፅ የምርመራ ቡድን ስለ ዴላ ሮዛ እና ስለ ሮድሪጌዝ ክምር ዶሴዎች ሁሉ ሳይኖራቸው ይቀራል ብለሽ ነው?”

“ይሄ ንፁህ የተባለው ክሮክ ከየት እንደሚመጣ በደንብ ያውቁታል።
ምናልባትም ሩሲያውያን ይህንን ሥራ ከሚሰሩት ሜክሲካውያን እንዲሰሩት
ፈልገውም ይሆናል ዝም የሚሉት፡፡ አልያም ደግሞ አንድ ትልቅ የፖሊስ
አለቃ ከእያንዳንዱ የአደንዛዥ ዕፁ ሽያጭ ላይ የሚቆረጥለት ነገር አለ ማለት
ነው።”
ኒክም የሰማችውን ነገር ለጥቂት ሰኮንዶች ያህል ስታመነዥክ ቆየች እና
“አንተ የምትለው ፖሊሶቹ እዚህ ድርድር ውስጥ አሉበት ነው? ማለቴ ልክ
የጠፉ ሰዎችን አፈላላጊ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ እንደሚያደርገው ማለት
ነው?”

“አዎን እንደዚያ ነው ብዬ አምናለሁ” አላት እና ዊሊያምስ በመቀጠልም ፖሊሶቹ እናም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እዚህ የአደንዛዥ ዕፅ ሽያጭ ላይ ይኖሩበታል፡፡ ሮድሪጌዝ ደግሞ ልክ ሜክሲኮ ውስጥ ሲያደርግ የነበረውን
ነገር እዚህም በማድረግ ላይ ይገኛል። ወንዶችን ማፍራት፣ በእጅ መሄድን
ያውቅበታል። በዚያ ላይ ደግሞ በአደንዛዥ ዕፅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለድሆችም የልገሳ እጁን በስፋት በመዘርጋት ላይ ይገኛል።”

ሃሳቡን እየተናገረ እያለ ኒኪ በትኩረት ስትከታተለው ስላየ ከተጣላችኝም
ይለይለት አለና “የሜክሲኮ አደንዛዥ ዕፅ አምራቾች ከትሬይ እና ከሊዛ ፍላንገን ግድያዎች በስተጀርባ እንደሚገኝ አልጠራጠርም፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ
ምናልባትም በባለቤትሽም ግድያ ላይ እጃቸው ሊኖርበት ስለሚችል ለዚህም
ራስሽን አዘጋጂ” አላት፡፡

ኒኪ ይህን ስትሰማ አይኗ በራ። ምናልባት የባለቤትሽ ግድያ ውስጥ የሊዊስ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል ማለቱን አልወደደችለትም፡፡ ምክንያቱም
ከባሏ እና ከውሽማው ግድያ ጋር በተያያዘ የእሷ ታካሚ የሆነችው ከአኔ
ባለቤት ሉዊስ ሮድሪጌዝ ጋር እንዲገናኝ አትፈልግም፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን
ይችላል? ብላ አሰበች፡፡

“ለማንኛውም ማጠቃለያ ይህንን ይመስላል” ብሎ ባወራት ነገር የረካው
ዊሊያምስ ወደ ኋላ ወንበሩ ላይ እየተለጠጠ “በሚቀጥለው ምን ላይ አተኩሬ ሥራዬን እንድሠራ ትፈልጊያለሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ኒኪ ዝም ብላ ስታየው
ዊሊያምስ ነገሩን ማብራራት ጀመረ “በዚህ ሳምንት ትኩረቴን ትሬድ ላይ
አድርጌ ነው ምርመራዬን ላካሂድ የፈለግኩት።” አላት እና ዊሊያምስ
በመቀጠልም ከነገ ጀምሮ ሊና ፍላንገን ላይ ትኩረቴን ለማድረግ አስቤያለሁ፡፡ ማለትም ስለ በፊቱ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀሟ ምናልባትም ከሆነ ትልቅ የዕፅ አዘዋዋሪ ጋር ስላላት ግንኙነት ወይም ደግሞ ከዊሊ ቡድን ጋር ስላላት ግንኙነት ምናልባትም ደግሞ እኔ ካሰብኩት በላይ የዊሊ እና ቫለንቲና ቡድን እዚህ የአደንዛዥ ዕፅ ቢዝነስ ውስጥ ሊኖሩበት ይችሉ ይሆናል፡፡ አሊያም ደግሞ ፖሊሶች የአንቺ የቀድሞ ታካሚ ከሆነው ብራንዶን ግሮልሽ ላይ አትኩሮታቸውን አድርገው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ
በማወቅ ላይ አትኩሮቴን ማድረግ እፈልጋለሁ። ደግሞም መርማሪ ፖሊስ
ጆንሰን ይሄ ዘረኛ እጁ እዚህ ነገር ውስጥ በሙስና
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

....ጋሻዬነህ ከእናቴ ጋር ውሉ አደረ፡፡ የየወዲያነሽ የእናትነት አንጀት በናፍቆት ተላወሰ፡፡ ሮብ ጧት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን «ምነው ዝም አልክ ጌታነህ? ረሳኸው እንዴ? ከጋሼ ጉልላት ጋር ምን ምን ነበር የተባባላችሁት?
ሂድና አምጣው እንጂ» አለችኝ፡፡

“ምናልባት ዛሬ የውብነሽ ታመጣው ይሆናል» አልኩና እንደገና ደግሞ
«ምናለባት ጋሻዬነህን ለእነርሱ ብንሰጣቸውና እኔና አንቺ ደግሞ….ሌላ» ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ ደረቷን ሁለት ጊዜ በጥፊ ደቃችና «ህ! እንዴት ያለህው ዓለመኛ ነህ! ምነው ምን በወጣኝ! ዕድሜ ላንተ እያልኩ ዐይን ዐይኑን እንዳላይ ነው!» ብላ ከነጥርጣሬዋ ዝም አለች።

ሐሳብን ማሻሻልና ፈጽሞም መለወጥ አንድ ዐይነት ዕድገት በሆኑ የሐሳቧ መለወጥና ተቃውሞዋ ደስ አለኝ፡፡ ለጥያቄዋ መልስ ሳልሰጥ ወደ ሥራ ሄድኩ፡፡
የውብነሽ ቀንም ሆነ ማታ ብቅ ሳትል ቀረች፡፡ የሮብ ጀንበር ጠልቃ የሐሙሷ ተወለደች፡፡ አዲሱ የፍርሃት ሸክም ከየወዲያነሽ ይልቅ እኔን ከበደኝ፡፡ ከማታ
ትምህርት መልስ ሻይ እየጠጣን ስናወራ አንዱን ተረስቶ የቀረ የጋሻዬነህን የሒሳብ ደብተር እያገላበጠች «እሷ መች ሥራ አጣችና ነው ይዛው ትመጣለች
የምትለው? እኔ እኮ ነገሩ የገባኝ የመማሪያ ደብተሩን ይዛ ስትሒድ ነው» ብላ ወደ ራሷ ደብተሮች መለስ አለች፡፡

«እኔን ያሠጋኝ ሌላው አይደለም.....አባባ ይመለሳል ከተባለበት ቀን ቀደም ብሎ ቢመለስና ይኸ ልጅ የማን ነው ልጅ? ብሎ ቢጠየቅ ምን ይላሉ?
እናቴ ገና እንማከራለን ነው ያለችኝ እንጂ ሌላ የተነጋገርነው ነገር የለም ከማለቴ፣ የማን ልጅ እንዲባልልህ ትፈልጋለህ? የጌታነህ ልጅ ነው ብለው
ይነግሩልሃላ» ብላ ኩታ አጣፍቶ የመልበስ ያህል ጉዳዩን አቃልላ መለሰችልኝ።

«እንዴት አንቺ? እኔ እኮ ገና ብዙ ግብግብና ትግል ይጠብቀኛል።
የሙሉ ድሌ ቀኔ ገና ነው:: ምኑ ተያዘና!ምኑ ተነካና! እንዴት አድርጌ እንደምገጥመውና ድል እንደማደርገው ዕቅድና ብልሃቴ አልተጠናቀቀም፡፡ወደፊት የሚቀረኝ የትግል ጉራንጉር ያለፉትን የመከራና የትግል ገድሎች ሁሉ ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ ቀሪው ትግል በዕድልና በአጋጣሚ የማምንበት ነገር
የለም፡፡ የሚጠብቀኝ ውጣ ውረድ ሁሉ በበቂ ምክንያትና በተግባር የሚመራ ነው። «የዘልማድ ዝላይና ባወጣ ያውጣኝ በቃው! በቂ ምክንያት ጥሩ የተግባር
ዋስትና» ብዬ በመጀመር ለወደፊት ከሚያጋጠሙኝ አንደንድ ችግሮች መኻል አንዳንዶቹን በከፊል አዋየኋት፡፡

ዓርብ ከጧቱ ሁለት ሰዓት ላይ የውብነሽ ጋሻዬነህን ይዛ መጣች።
የሚያምር አዲስ ልብስ ለብሶ
ከፈገግታው ጋር ሲታይ የመስከረም ዝናብ ያጠባት
የለጋ ዘንባባ ተክል መስሏል። የወዲያነሽ ግልገሏን አስከትላ ጢሻ ውስጥ እንደምትገባ ሰስ ልጅዋን አስከትላ ወደ ጓዳ ገባች። እኔና የውብነሽ ወጣ ብለን ሰበሰቡ ላይ እንደቆምን «አባባ የነገ ሳምንት ከሰዓት በኋላ ይገባል፡፡ ባለቢትህን እንዴት አድርገን እሱ ፊት እንደምናቀርባት፡ አንተም ምንና ምን እያልክ መናገርና ማስረዳት እንዳለብህ አንድ ባንድ አውጥተን አውርደን ጨርሰናል» ብላ ስለ እኛ ሕይወት እኔና ባለቤቴ ያልተካፈልንበትን የአፈጻጸም ዕቅድ አረዳችኝ፡፡
የችግሬን ዐይነትና ዓላማዬን የማውቀው እኔ ሆኜ ሳለሁ መወከልና ማስፈጸም
የማይገባቸው እኅቴና እናቴ አፈ ቀላጤ ሆነን እንገኝ ሲሉ በመስማቴ ተናደድኩ፡፡
አልተዋጠልኝም፡፡

የአባቴ ግብዝነትና ቁጣዉ፣ ግትርነቱንና የመጣ ይምጣ ባይነቱ፣ እንደ ጨካኝ አገረ ገዢ ፊት ለፊት ቆሞ እንደ እሳት ፈጀኝ፡፡ «ማታ ከትምህርት ቤት
መልስ ከየወዲያነሽ ጋር እንድትመጡ፣ ነገሩን አብራራልሃለሁ። አሁን ግን
ቸኩያለሁ ደኀና ዋል» ብላኝ ቶሉ ብለህ ና እንደ ተባለ መልእክተኛ ጥላኝ ሄደች። አእምሮዬ በሐሳብ ተወቃ፡፡ ሁለመናዬ ብው ብሎ ጋመ፡፡ አዳዲስ ጭንቀቶች በውስጤ ተራወጡ፡፡ የሐሳቤ አድማስ ለመጥበብም ሆነ ለመስፋት ባለመቻሉ መረጋጊያ አጣሁ፡፡

ጎርፍ እንደ ገረሰሰው ዛፍ ግድግዳውን ተደግፌ ቆምኩ፡፡ የወዲያነሽ ከወደ ውስጥ መጥታ «ከምን ጊዜው ሄደች? ያንተ ነገር እኮ...አናደድካት እንዴ?» ብላ
በሥጋት አዘል ሁኔታ ጠየቀችኝ፡፡ «ቸኩላ ነበር፡ ታናድደኛለች እንጂ ምን አናድዳታለሁ፡፡ የማይጠቅሙሽ እጠቅምሻለሁ፣ የሚያጠፉሽ አለማሻለሁ፣
የሚገድሉሽ አድንሻለሁ ሲሉሽ አትናደጂም? አሁን የነገረችኝን ማታ ስትነግረኝ ትሰሚያታለሽ፡፡ አሁን ወደ ሥራሽ ሂጂ» ብያት ዝም አልኩ፡፡ የእርሷ ከአጠገቤ
ገለል ማለት የሚረዳኝ ስለ መሰላት ተመልሳ ገባች፡፡ በአካባቢዬ የሚገኙት ነገሮች
ሁሉ ለችግሮች ማቃለያ የሚሆን ብልሃት ያቀርቡልኝ ይመስል ትክ ብዬ አየኋቸው:: ሆኖም ከበድን መልስ የለምና አፍጥጨ ቀረሁ። ሳላስበው ከቤት ወጣ ብዬ ቆምኩ፡፡ የማለዳዋ ፀሐይ ደጋናማ ጉዞዋን ጀምራለች፡፡ ደመና የማይታይበትን ሰማይ ትኩር ብሎ ላየው ኣስፈሪነቱ አይጣል! ዘልዓለም የሚሉት ይህን ርቀትና
ጥልቀት ይሆን? አንጋጥጬ ስመለከት ሐሳብ አሽቆልቁሎ አየኝ፡፡ አካባቢዬን ፈራሁት፡፡ ጥቂት ርምጃ ተራምጄ ግቢው መኻል ተገተርኩ፡፡ ከመሬት ውስጥ
መልስ ይፈልቅልኝ ይመስል ደቃቁን አፈርና ኮረት ባይኔ ሰለልኩት። ቀዝቃዛና ለስላሳ ትንሽ እጅ የቀኝ እጄን ከበስተኋላዬ ስትነካው ከፍዘቴ ነቃሁ። ጋሻዬነህን እጁን ስቤ ወደፊት አዞርኩት፡፡ ከፍ ብለው የሚበርሩ አዕዋፋትን እንደሚከታተል
ወፍ ጠባቂ ዐይኖቼን አሻቅቦ ከፈለገ በኋላ ና ቶሎ! አሁኑኑ ና ቶሎ ብላሃለች እማማዬ» ብሎ መልሴን ለመስማት ኣፉን እንደ ከፈተ ዝም አለ፡፡ ከቁመቱ ጋር ለማስተካከል ጉልበቴን አጥፈ ቁጢጥ አልኩና፣ እኔን ነው እማማዬህን ነው የምትወደው ጋሻዬነህ?» አልኩት።ፊቱ በፈገግታ ፈክቶ የደብር ጉልላት የሚመስሉት ዐይኖቹ በሰፊው ተከፈቱ። «አንተንም እማማዬንም እወዳችኋለሁ...ያንን ቀይ ሽጉጥ እገዛልሃለሁ አላልከኝም ነበር፡ መቼ ትገዛልኛለህ?» ብሎ ዐይን ዐይኔን ሲያይ ዐይኖቹ በዐይኖቼ ውስጥ ሠረጉ፡፡ ትልቋ እማማስ እዚያ ትልቁ ቤት ውስጥ ያየሃቸው
የእኔ እናት አያትህ ጥሩ ናቸው? በል እስኪ ንገረኝ፡ ያንን ሽጉጥ እንድገዛልህ?»አልኩት። ከንፈሩን ትንሽ ሾል ካደረገ በኋላ «እሳቸው ደግሞ በጣም ደስ ሊሉኝ፡
ጥሩ ናቸው፡፡ ያንተ እማማ ናቸው እንዴ? እወዳቸዋለሁ» ካለ በኋላ ትልቅ በመሆኔ ከእናት ያልተወለድኩ ይመስል አወጣጧ የምታምር ሞንሟና ሣቅ ሣቀ።

«እስኪ ትወደኝ እንደሆነ ሳመኝ?» አልኩት፡፡ ጉንጩን ተራ በተራ ሳመ። «ኧረ እባካችሁ ኑ ግቡ! እባትና ልጅ ምን ትማከራላችሁ? እኔ እንዳልሰማችሁ ነው?» የሚል ድምፅ ከወደ ቤት ተሰማ፡፡ የወዲያነሽ ፍቅራዊ ትእዛዝ ስለሆነብኝ ጋሻዬነህን ይዤ ገባሁ፡፡ ቁርስ ይዛ ከተፍ አለች፡፡ የጀመረችውን ሥራ ለመዉረስ
መለስ ስትል «በይ አንሺና ይዘሽው ሂጂ!» ብዩ የካንገት በላይ ቁጣን በሚገልጽ
ስሜት ተናገርኩ፡፡ ደንገጥ ብላ ተመለሰችና «ምነው? ምን አጠፋሁ? የት ልሄድ
ነው? እደርሳለሁ ብዬ ነው ! » በማለት በፍርሃት ሳይሆን በፍቅራዊ ስሜት ትኩር
👍6
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...የተቃራኒ ፆታ ሱስ እስከሚያንጠራራው ድረስ ተጨነቀ ጭኖቹ በጭኖቿ መካከል ነበሩ አልቻለም፡፡ ከንፈሮቿን እየሳመ ቀስ ብሎ የሆነ ነገር በጆሮዋ ሹክ አላት፡በዚህ ጊዜ አማረች በጣም ተበሳጨች፡፡

ሂድ! ባለጌ! ወንዶች ስትባሉ ይሄው ናችሁ። ፍቅር ሲሏችሁ ዘላችሁ የምትሰፍሩት እዚያ ላይ ነው፡፡ ፍቅር ማለት እሱ ብቻ ነው የሚመስላችሁ፡፡ እኔኮ አንተን ለብዙ ነገር ነበር የምመኝህ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ልጃገረድ መሆኔን ማወቅ አለብህ!ባንተ ዘንድ ረከስኩ እንጂ ውድ ነበርኩ፡፡ ሽርሙጣ አይደለሁም፡፡ ገባህ?!" ጮኽችበት። ደነገጠ።

“እንደሱ አይደለም የኔ ቆንጆ። በሌላ መልክ አይቼሽ አይደለም፡፡ በጣም ስለምወድሽ ነው በጣም አማረች.." ቃላት አጥረውት ተጨነቀ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ስውነቱ በስሜት ግሏል። ነዷል። "እኔኮ እኔኮ . እወድሻለሁ.... እስከ መጨረሻው የኔ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ" አፉ ሲወተውት
ጣቶቹ ባልተፈቀደላቸው ድንበር ዘለው ገብተው አሰሳ ማካሄዳቸውን አላቋረጡም ነበር፡፡ ድርጊቱ አማረችን የበለጠ አናደዳት።

"ልቀቀኝ! ልቀቀኝ!" መንጭቃው ተነሳች። "እኔው ነኝ ወረዳዋ! አንተ
ምን አደረክ? በለሊቱ በርህን አንኳኩቼ የገባሁት እኔ! ጥፋተኛዋ እኔ!" ፀጉሯን እየነሰነሰች….ያንን ውብ ዳሌዋን እያውረገረገች ከአልጋው ላይ ወረደች፡፡ በድንጋጤ ዐይኖቹ ፈጠጡ። የሚናገረው ጠፍቶበት በፈፀመው የብልግና ድርጊት ራሱን ወቀሰ፡፡ በስሜት ግፊት ተሸንፎ ከፍላጎትዋ ውጭ በፈፀመው ድርጊት ተፀፀተ።

ቆይ!!. . ቆይ! . ቆይ! " እጆቹን ዘርግቶ ተከትሏት ብድግ አለ።
“ሂድ!" በሩን አላትማ ወጣች።
“አማ.አማረች..አንዴ .ምን…. መሆንሽ ነው?ቆይ እስቲ..." ሲወራጭ የአልጋው ብረት ቅዝቃዜ እንደ ኤሌክትሪክ ነዘረውና ብንን አለ። ጭንቀቱ..
ቅዠቱ.. ላብ በላብ አድርጎት ነበር፡፡
“በስመአብ ወልድ!“ ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ ቀስ ብሎ ያየውን ህልም ይመረምር ጀመር፡፡ ያንን የማይጨበጥ ጉም የማይዳሰስ ተስፋ መጨረሻው ባያምርም እቅፍ አድርጎ
በላይዋ ላይ እየተንፈላሰለ እንጆሪ ከንፈሮቿን የቀሰመበት ዓለም እንደ
ሰቀቀን ሆኖ አለፈ። ዐይኖቹን ጭፍን ክድን ጭፍን ክድን አደረጋቸው። መብራቱን አበራና ሁለቱንም ትራሶች ደራርቦ ከወገቡ በላይ ራቁቱን ሆነ፡ ዐይኖቹን ፊት ለፊቱ አማረችን በጋረደበት ግድግድ ላይ በንዴት ተክሎ በሀሳብ እሷ ክፍል ገባ፡፡ እንደ ንዴቱና እንደ ብሽቀቱ ቢሆን ኖሮ
ከዐይኖቹ የሚወረወሩት ጨረሮች ያንን የግንብ ግድግዳ የጤፍ መንፊያ ወንፊት ባደረጉት ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ እንቅልፍ በዐይኑ ሳይዞር ቀሪውን ጊዜ በመቀመጥና በመገላበጥ አሳለፈው፡፡ ጠዋት ቁርሳቸውን እዚያው በሉና በፕሮግራማቸው መሰረት ወደ ላንጋኖ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ዛሬ አማረች
የዋና ተለማማጅና የህይወት አድን ሰራተኛ ፈላጊ ሆና ለመቅረብ አቅዳለች። ለዘዴዋ፡፡ ላንጋኖ ደርስው ለዋና ተዘጋጁ፡፡ አማረች ልብሷን አወላልቃ በውስጥ ሱሪ ብቻ ወደ ሃይቁ መጣች፡፡ ጌትነት ያንን ውብ ተክለ ቁመናዋን የሚያጓጓ ራቁት ገላዋን በውስጥ ሱሪ ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ
አየው። ልቡ ወደ ሰማይ ወጥታ እንደ እምቧይ ፈረጠች፡፡ ወደር የሌለው አፍ የሚያስከፍት ቅርፅ.. ስምንት ቁጥር ቁጭቁጭ.ያሉ ጡቶቿ ዐይኖቻቸውን አፍጠው ምራቃቸውን በሚውጡ ተመልካቾቿ ድርጊት ተቆጥተው እንደ ነብር ያበጡ ይመስላሉ። ጌትነት ዘወር ዘወር ብሎ ሲመለከት የበርካታ ዋናተኞች አፎች ተከፍተው መቅረታቸውን አስተዋለ። ቅንአት ቢጤ ቆነጠጠው...

"እውን የኔ ትሆኝ ይሆን ?"አለ በልቡ። ይሄንን ልቡ የተመኘውን ምኞት ዐይኑ እንዳያሳብቅበት ፈራና ለመሸፋፈን ጥረት አደረገ፡፡ ተወት ያደረጋት ለመምሰል ማዶ ማዶውን ማየት አበዛ... አማረች ደግሞ የጌትነትን አንጀት ለመብላት ስትል አንድ አላስፈላጊ ድርጊት ፈፀመች። ጡት ማስ
ያዣዋን በመጠኑ ዝቅ አደረገች። ማግኔት!!

"ጌትሽ ይሄኛው ጥልቅ ነው እኔ እዚህ አልዋኝም፡፡ እሰምጣለሁ። እዚ ቅርቡ ጋ ሄደን እንዋኝ?” ሰው ወደሌለበት አካባቢ በአገጭዋ እያሳየችው አካባቢውን ጠቆመችው። ወደዚያ እሷ ወዳለችው የሃይቁ ዳርቻ ተያይዘው ሄዱ፡፡ አማረች አዲስ ዋና ተማሪ ሆና ቁጭ አለች፡፡ ወይ አበሳው?!
ያንን መጠጋት የፈራውን እፍኝ የማይሞላ ወገቧን ይዞ ከፍ ዝቅ ወደ..ፊት ወደ ኋላ... እያደረገ ያለማምዳት ጀመር። በሷ እንቅስቃሴ አቅጣጫ
እየተመራች የሱም ልብ ከቦታዋ ለቃ እየተንከራተተች ነበር፡፡
ጌትነት የትናንትናው ህልም ዓለም ክፍል ሁለት እንዳይሆን ዐይኖቹን
ተጠራጠረ፡፡ ሲፈራው የኖረ ውብ ገላዋን በኒያ አለንጋ መሳይ ጣቶቹ
እያሻሽ አንዳንዴም ልቡ ሲከዳው ጣቶቹ ደግሞ ሳይታዘዙ ወደ ጡቶቿ እያዘገሙ ከዚያም ድንግጥ ብሎ ሲመልሳቸው ደግሞም ላያስበው በስሜት
ሌላ ሃሳብ ውስጥ ይገባና ወደ ዳሌዋ አድርሶ ሲመልሳቸው.. በአማረች ፈተና እንደያዘችው ቁም ስቅሉን ሲያይ ዋለ፡፡ እሷ አውቃ ስትፈራገጥ እሱም ጎበዝ አሰልጣኝ ለመሆን ሲታገል ሲተሻሹ ሲደባበሱ..ብዙ ቆዩ።
ሰው እንደ ጨው የሚሟሟ ቢሆን ኖሮ ሟሙተው ሟሙተው በጠፉ
ነበር፡፡ የሱ ጣቶች በገላዋ ላይ በሚርመሰመሱበት ጊዜ አማረች በከፍተኛ የፍቅር ስሜት ውስጥ ነበረች። ከውጭ ቀዝቃዛው ውሃ ባያቀዘቅዛት ኖሮ ውስጧ በስሜት እየጋለ እየነደደ ሄዶ እንደ ስም ቀልጣ በፈሰሰች ነበር፡፡

የሁለት ዓመት የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ከአንገቷ ቀና አድርጎ ዐይን
ዐይኖቿን በፍቅር እያየ አበባ ከንፈሮችዋን ለመቅሰም ያልታደለ ንብ ሆኖ አንገቱን እያቀረቀረ እሷ በጉጉት ስትጠብቀው እያሳፈራት ሁለት አመታት እንደ ዋዛ አለፉ፡፡ እሱ እንደዚያ ማድረግ ቢችል ኖሮ ከወዲሁ ስሜቷን ቢረዳላት ኖሮ ያንን ያክል የሚባክን ጊዜ ባልተፈጠረ ነበር፡፡ ገና
ከጅምሩ ፍላጎትዋን አውቆ በአንደኛና በሁለተኛው ወር ላይ በአፉ ባያወጣው እንኳ ሚስጥሩን በዐይኖቹ ቢገልፅላት ኖሮ ተቀላጥፋ ምላሹን በደስታ በገለፀችለት ነበር፡፡ እሱ ግን ያንን ማድረግ ባለመቻሉ ግንኙነታቸው በጥናት ላይ ብቻ ተወሰነና ጊዜው ተላለፈና በእህትነት በወንድምት
በሚል ፈሊጥ ምኞታቸውን ከመገላለፅ ተቆጠቡ።

በልባቸው እየተፈላለጉ ከአሁን በኋላ ምን ይለኝ? ምን ትለኝ? በመባባል ተፈራርተው በመካከላቸው አፏን ከፍታ የምታዛጋውን ፍቅር ሁለት
ዓመት ሙሉ በሱስ እንድትሰቃይ አደረጓት። በይሉኝታ ገመድ በመታሰር ምን ይለኛል ምን ትለኛለች በሚል ፍራቻ ግልፅነት ሲጠፋ ትርፉ ውስጥ ውስጡን መሰቃየት ነውና አማረችና ጌትነት የዚህ የፍቅር ጋግርት የይሉኝታ ሰለባዎች ሆኑና የሱን ልወቀው ከሷ ይምጣ እየተባባሉ የመፈላለግ ደረጃቸው ገሃድ ሳይወጣ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።

በማህበረሰቡ ዘንድ ሴት ልጅ ስትለመን፣ ደጅ ስታስጠና፣ ስትሽኮረመም ትወደዳለች የሚል አመለካከት በስፋት የሚንፀባረቅ በመሆኑ ፍቅሯን አስቀድማ ለመግለፅ ትቸገራለች። አማረችንም አፏን ያፈነው ይሄው
ነበር፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎቹ የተረታላት መሆኑን ብታውቅም አስጠናኝ ብዬ በግድ የቀረብኩት ልጅ ቀድሜ ወደድኩህ ብለውና "አልፈልግሽም ዞር በይ" ቢለኝስ? በሚል ፍራቻ ዝምታን መርጣ ቆየች። እሺ እንደ ሃሳብሽ ቢላት እንኳ ወደ ፊት አንድ ቀን “እሷ ራሷ ወደድኩህ አበድኩልህ ብላ ተለማምጣኝ ነው" ብሎ ሊያወራ ነው። ከዚህ ሁሉ እንደተከባበርን ቢቀርስ? ከዚህ ሁሉ ነገሩ ከሱ ገፍቶ እስከሚመጣ ድረስ በትዕግስት ብጠብቅስ? በማለት ሁለት ዓመት ሙሉ ታገሰች። ከጌትነት በኩል ገሀድ የሚወጣ
👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ሸዋዬ በህዳር ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ ቆማ የመጀመርያው መንፈቅ ትምህርት አልቆ ለአጭር ጊዜ እረፍት ትምህርት ቤት የሚዘጋበትን የጥር ወር መጨረሻ በናፍቆት ትጠባበቃለች። ከብረ መንግስት የምትደርስበት ቀን ሳይቀር ተወስኗል።እቅዷ ከሔዋን
ወይም ከወላጆቿ ተቃውሞ ቢገጥመው ማሳመኛ ይሆናል የምታስበውን እያዘጋጀች ነው። ዘዴና ብልሀት በልቧ ይውጠነጠናል።

ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል እንዲሉ ወንድሟ አስራት ተስፋዬ ባላሰበችው ቀንና ሰአት ከቤቷ ከች ብሎ ያደረሳት ብሥራት ግን ሰጋትና ፍርሃቷን ሁሉ ከልቧ ውስጥ እንደ እድፍ አጠበው። ሔዋን የልብ ህመምተኛ ሆናለች በሰው ላይ ክፉ ደግ አለና መተሽ እያት ከማለት ውጭ ስለ ሔዋን ሁኔታ ምንም አይነት ፍንጭ ለሸዋዬ እንዳይሰጥ በተለይ በእናቱ አደራ የተባለው አስራት የልጅ ነገር ሆኖበት አንዳንድ ነገሮችን ማፈንዳቱ አልቀረም ሔዋን ዛፍ ስር ተቀምጣ መዋል ማዘውተሯን በሀሳብ እየተዋጠች ቤተሰቧን ማሳሰቧንና በተለይ በህመሟ ምክንያት አገር ብትቀይር የተሻለ መሆኑ መታመኑን ሁሉ አልደበቃትም።

የሔዋን አገር መቀየር አስፈላጊነት የታመነበት ስለመሆኑ መስማቷ ሸዋዬን ከምንም ነገር በላይ አስፈነጠዛት። ሔዋን አገር መቀየር ካለባት ቀላሉ ከክብረ መንግስት ወደ ዲላ ነው ይህ ደግሞ በቤተሰቦቿ ዘንድ ተፈጥሮ ይሆናል ብላ ከምታስበው ቅሬታ ነፃ የምትሆንበት አጋጣሚን ይፈጥራልና ወቅትና ጊዜ ያለ ሽማግሌ ሲያስታርቃት በመቅረቡ አምላኳን አመሰገነች፡፡ ወደ ክብረ መንግስት ልትሄድ በልቧ ይዛው የነበረውን የጊዜ ቀጠሮ አሳጠረችው፡፡ ወንድሟ አስራት
ከቤቷ በደረሰ በአራተኛው ቀን እንዲሆን አደረገችው:: በመሀል ያሉት ሁለት ቀኖችም የዝግጅት ጊዜ ሆነ::
ብሥራቱን ያካፈለቻችው በድሉና ማንደፍሮ በእነዚህ ሁለት ቀናት
አልተለዮትም፡፡ ወደ ክበር መንግስት አካሄዷን ሊያሳምሩ ሽርጉድ አሉ። አብረዋት
እየዋሉ አብረዋት አመሹ። በየገበያው ቦታ አብረዋት ዞሩ። አዘጋጇት፤ አዘገጃጇት ጠዋት ወደ ክበረ መንግስት ልትሄድ ሻንጣዋ የያዘውን ይዞ ማታውኑ ተቆለፈ
የማግስቷ ጀምበር ክብረ መንግስት የምታደርስ የልቧ መብራት ሆነች::

ልክ በዚያ ዕለት ምሽት ላይ ክብረ መንግስት ሌላ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው። የሄዋን አባትና እናት ሔዋን ወደ ዲላ መሄድ ያለ መሄድ ፍላጎቷን ለመጠየቅ ሊያነጋግሯት በተመካከሩበት መሠረት ውይይቱ ተጀመረ፡፡
«እሙዬ !» ሲሉ ጠሯት ለስለስ ባለ አነጋገር።
«አቤት እማ» አለቻቸው ሔዋን ከአጠገባቸው መደብ ላይ ገደም ብላ ሳለች። አባቷ ደግሞ ከባላቤታቸው ፊት ለፊት ምድጃኑ እጠገብ ተቀምጠው እሳት ይሞቃሉ።
«እንደው ይቺ ልብሽ ያስቸገረችሽ ይኸን አገር ጠልታብሽ ይሆን? እማስበው ባጣ ይህን ነገር በእሊናዬ አውጠነጥነው ጀመር ልጄ? አሏት ጉልበታቸውን በሁለት
እጆቻቸው ደገፍ በማድረግ ዓይን ዓይኗን እየተመለከቱ፡፡
«አዩ! እማ ቢቸግርሽ!»
«ቸገረኝ ልጄ! በጣም ችግረኝ፡፡»
«የት ልሂድ ታዲያ እማ»
«እውነትሽ ነው:: መሄጃማ ይቸግራል የኔ ልጅ፡፡» ካሉ በኋላ የሔዋን እናት ወደ አቶ ተስፋዩ ዞር በማለት «እንደው ወደ ዲላ ትሂድ ይሆን አቶ ተስፋዬ» ሲሉ ጠየቋቸው።
«ተሆነማ ወደዚያው ነው ኋላማ መይት ትሄደዋለች? ከዚያ ሌላ አገር አታውቅ አሉ አቶ ተስፋዬ አንገታቸውን ወደ እሳቱ ደፋ አድርገው፡፡
«ከማን ጋር ልኖር?»ስትል ሔዋን ጠየቀቻቸው፡፡
«በኔ ልብማ ከነዚያ ከነታፈሡ ጋር ትንሽ ተጨዋውተሽ ትመለሽ እንደሆን ብዬ ነዋ!»አሉ እናቷ ለስለስ ባለ አነጋገር።
«እህቷስ አለች አይደል! »አሉ አቶ ተስፋዬ ወደ እሳቱ እንዳቀረቀሩ።
«እንደገና ከእታ አበባ ጋር?» አለች ሔዋን ደንገጥ ብላ።
«እሷን ለሰበብ ተዚያ በኋላ ደግሞ ከእነዚያ ልጆች ጋር አንዳንድ ጊዜ
መጫወቱ ትንሽ ያፍታታሽና ልብሽም እየተወችሽ ትሄድ እንደሆነ ብዬ እኮ ነው፡፡»
አሉ እናቷ የሔዋንን ቁጣ ለመመለስ ረጋ ብለው።
«ተይ እማ! እንዲህማ አይሆንም::»
«ቀለብሽን ተሆነ እኔ እችላለሁ ሔዋኔ ከቶ የአንቺ ጤና ይመለስ እንጂ፣ደሞ ላንቺ ያልሆነ አዱኒያ ምን ሊያደርግልኝ! ላም ተሆነች ላም! በሬ ተሆነም በሬ ይሸጣል :: አይዞሽ!» አሉ የሔዋን አባት በቆራጥነት።
«እናንተ የማታወቁት ልላም ችግር አለ:: አለች ሔዋን፡፡
«ብትነግሪን አይፈታም?» አሏት እናቷ፡፡ ግን ትዝ ያላቸው ነገር አለ፤ ያኔ ታፈሡ በማትፈልገው ሰው ልታስደፍራት ያለቻቸው ነገር። ፈታ ብላ ብታወባና ሁኔታውን በግልጽ ቢረዱት ፈለጉ፡፡
«እኔና እት-አባበ አብረን መኖር አንችልም፡፡» አለች ሔዋን ነገሩን ደፈንፈን አድርጋ።
«ኧረ ተይ ሔዋኔ፣ በእትማማቾች መካከል ቂም ተያይዞ አይኖርም!» አሉ አባቷ አሻግረው መልከት እያሏት፡፡
«ከበድኳችሁ እንዴ አባዬ?»
«ለአንቺ ብለን ነው እንጂ እሙዬ ደሞ አንቺ ምን ትከብጅናለሽ የኔ ልጅ?»
አሏት እናቷ በማሳዘን ዓይነት አነጋገር፡፡
«እንግዲያው እዚሁ ብሆን ይሻለኛል፡፡» አለችና ሔዋን በረጅሙ ተነፈስች።

የሔዎን እናትና አባት ግራ ተጋቡ። ልጃቸው ወደ ዲላ ለመሄድ ፈቃደኛ አለመሆኗ ገባቸው። ከዚያ በኋላ ምንም ሳይነጋገሩ ጊዜው መሸ፡፡ እንደ ተዳፈጡ ተኙ፡፡ ሌሊቱ በሀሳብ ነግቶ ቀኑም በትካዜ አለቀ።

የደስታ ፈረስ ጋልባ ሶምሶማ ስትጋልብ የዋለችው ሸዋዬ ከቤተሰቦቿ ቤት የደረሰችው ከአመሻሹ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ በዚያ ሠዓት አባቷ
ከብቶቻቸውን ይዘው ከመስክ እየተመለሱ ነው። እናቷ ደግሞ ምናልባት ሔዋን ሸዋዬ ስትመጣ ሀሳቧን የቀየረች እንደሆነ ብለው ለወደፊቱ ግንኙነት እንዲያመች
የዘመድ ስልክ ቁጥር ሊያመጡ ወደ ከተማ ሄደው እየተመለሱ ገና በመንገድ ላይ ናቸው:: ሽዋዬና አባቷ በር ላይ ተገናኝተው በመሳሳም ናፍቆታቸውን አውጥተው እየተነጋገሩ ወደ ቤት ሲገቡ ሔዋን በጎሮ በር በኩል ወደ ቤት ስትገባ ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ።

"እማሃይዬ! አለች ሔዋን ሸዋዬን ስታይ ደንግጣ። የትናንት ማታው ወሬ መሰረቱ ምን እንደነበር ልቧ ጠረጠረ።
«እህትሽ መጣች ሔዋኔ!» አሉ አባቷ ቀድመው::
«ጠፋሁባት ይሆን?» በማለት ሽዋዬም ሳቅ እያለች ወደ ቤት ገባችና በሔዋን ላይ ጥምጥም ብላ ሳመቻት::
«አንቺ! አለቻት አጠገቧ ቆማ ከእግር እስከ ራሷ እየተመለከተቻት፡፡
«አቤት» አለች ሔዋን ወደ መሬት እንዳቀረቀረች::
«በቃ አንዲህ ሆነሽ ቀረሽ?»
ሔዋን ሽዋዩ ምን እያለች እንደሆነ አልገባትም፡፡ ጠቁራባት ይሁን
ከስታባት ብቻ ያየችባትን አካላዊ ለውጥ ገና ትነግራት እንደሆነ እንጂ ለጊዜው አለየላትም።
ሸዋዬ እንደ መናደድ ዓይነት እጆቿን ጨብ ጨብ ጨብ እያረገች ዋይ-ዋይ-ዋይ-ዋይ…አለች ደጋግማ:: በአባታቸው ግብዣ
ሁሉም በመደብ ላይ ተቀመጡ።

«ሔዋኔ ክብረ መንግስት እንዳላደገችበት ሁሉ ዛሬ ዛሬ አልስማማት ብሏል የሸዋ!» አሉ የሔዋን አባት የሸዋዬ ቁጭት መነሻው የሔዋን መጎሳቆል መስሏቸው።
«ለመሆኑ ያምሻል?» ስትል ሸዋዬ ሔዋንን ጠየቀቻት፡፡
«እል አልፎ ልቢን ያመኛል::
👍51
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ለዓመታት በርካታ የመንፈስ ድል ስትቀዳጅ ቆይታ ልጇ ከሞተ በኋላ፣ ይኸው ድል ወደ ሽንፈት የተቀየረ በመሰላት ሰዐት እሱን በማግኘቷ ልቧ ተነሳስቶ ኸንግዲህ ሞት እንጂ ሌላ አይለየንም አለች።
አስተናጋጅ ወይን ጠጅ አምጥቶ ቀድቶላቸው ወጣ።

“ጠጣ እስቲ!” አለችው፣ ፈገግ ብላ።

የትካዜው ድባብ ተገፈፈ።

“ለመሆኑ ሥዕል እንዴት ዠመርህ?”

“ቋራ ሁኘ ነው የዠመርሁት” አለና ስለግድግዳው ታሪክ ነገራት።

ከት ብላ ሳቀች። “ሥዕል ትሥል እንደነበር ዛዲያ እንዴት
አላወቅሁም?”

“አባባ ለምሠራው ነገር ቁብ ሰጥተውት አያውቁም ነበር። ወዲያው ያጠፉት ነበረ። ቋራን ትቸ ጐንደር ዘልቄ እመኝ የነበረውን ሥዕል መማር ዠመርሁ። ኋላም ደብረ ወርቅ ማርያም ኸድሁ። መቸም በርስዎና በንጉሥ ኢያሱ ዘመን ሥዕል አደገ። ጐንደር ውስጥ የባሕር ማዶ ሰዎች ኸመጡ ወዲያ ሥዕል ለውጥ ኣምጥቶ ነበረ...” ብሎ ከጠጁ
ተጎነጨ።

“እንዴት?”

“የቀድሞዎቹን ሥዕሎች ያስተዋሉ እንደሆን መለኮታዊ ይዘት
ያላቸውና ታሪክ ተራኪ ነበሩ። ኋላ ግን መለኮታዊ ብቻ ሳይሆን ሥዕል ወደ ሰው ወረደ። ሥጋ ለባሾች... ነገሥታት ሚሣሉበት ዘመን ላይ መጣን። የቀለም አጠቃቀም ሁሉ ለውጥ አመጣ። መቸም የአጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመንም በትምርትም ሆነ በሥዕል ብዙ ለውጥ የመጣበት
ዘመን ነበር። ቁም ጸሐፊው፣ ደብተራው ቁጭ ማለት ያመጣበት ግዝየ ስለነበረ ቁጭ ሲባል ፉክክር፣ ክርክርና አሳብ ለአሳብ መለዋወጥ መጣ።እንዲያም ብሎ አንድምታ ትምርት ተዠመረ። ይኸ አሳብን መግለጽ ወደ ሥዕለም መጣ።”

“እንዴት ያለ ነገር ነገርኸኝ? ሁሉ ሚሆነው በግዝየው ነው መሰለኝ
ብላ ፈገግ አለች።
“አዎ ሁሉ ሚሆነው በግዝየና በቦታ ነው። አለግዝየውና አለቦታው ሚሆን ምን አለ?”

“ግዝየ ምንድነው?”

“ግዝየ እኛ ነን።”

“የግዝየ ነገር ይገርመኛል።”

“የሰው ነገር ይገርመኛል ማለትዎ ነው? ግዝየን ሆነ ቦታን ምንፈጥር
እኛ ሰዎች እኮ ነን። እዝጊሃር ምድርና ሰማይን ፈጠረ። እኛ ደሞ
ግዝየንና ቦታን ፈጠርን። ግዝየ ሆነ ቦታ አለኛ የሉም? ቦታም ግዝየም እኛ ነን። እኛ ጥሩ ስንሆን ግዝየም ጥሩ ይሆናል። እኛ ጥሩ ስንሆን የሰማዩም ደስ ይለዋል፣ ምድርም ለፍጥረታት ሁሉ ምቹ ቦታ
ትሆናለች።”

“አሳብህ ገባኝ። ግዝየ ሳይሆን እኛ ነን ምንገርመው ማለትህ ነው?
እንግዲያማ የሰው ነገር ይገርመኛል።”

“አየ እቴጌ ዝናዎን ሰምቻለሁ። ሊቃውንት ሆኑ ካህናት ያደንቅዎታል።እርስዎ የጠለቀ ዕውቀት... ትምርት ያለዎ... አንደበታምና ታሪክ
አስተካካይ... የሰው ባሕርይ ይግረምዎ?”

“አንተ የሥዕል ንጉሥ፣ የሰማዩንም የምድሩንም ብራና ላይ
ምታስቀምጥ እስቲ ንገረኝ። ሰው ማለት ምን ማለት ነው?”

“እቴጌ ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ኻወቅሁማ ፈጣሪን ሆንሁ።እኛ ሰዎች መሆን የነበረብን ሚዛኑ ከፍ አለና እኛ አነስን። መሆን ሚገባንን መሆን አልቻልንም። መቸም ጉድለት አለን ብንል ፈጣሪ ጉድለት ያለው ፈጠረ ማለት ይሆንብናል። ሙሉ ግን ማዶለን።”

“ዛዲያ የተሟላን መሆን ቢያቅተን፣ ኸሚዛኑ ብንጎድል፣ ለመሙላት
አንጥርምን?”

“ቢሆንልንማ እንዲያ ነበር።”

“እኔስ እንዲያው በተለየ አሁን ያለንበትን ሳስብ ክፋትና ደግነት
አብረውን የተወለዱ ናቸው ነው እምል።”

“ስለ ሰው ባሕርይ ተመራምረን ምንደርስበት አይመስለኝም::”
አለ ጥላዬ ከጠጁ አሁንም ጎንጨት ብሎ። እሷ የቀረበላትን ጠጅ አልነካችውም። “ይጠጡ እንጂ” እንዳይላት ድፍረት መሰለው።

“እኔ ለነገሩ ሰው ማለት ምን ማለት ነው ብየ የጠየቅሁት እንዳው
ያገራችን ነገር አሳስቦኝ ነው። ይረዳሉ ብለህ ያሰብኻቸው ሁሉ
አንተንም አገርንም ሲጎዱ ስታይ ይገርማል። ሰላም ጠፋ።”

“ርግጥ ነው ... ርግጥ ነው እቴጌ... ሁላችንን ሚያሳስበን ይኸው ነው” አለ፣ በሐሳብ ተውጦ ሳይመልስላት በመቅረቱ ደንገጥ ብሎ። “እቴጌ በእርስዎና በንጉሥ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዘመን ደግ ግዝየ አለፈ።
እናንተ ደግ ጥሩ ነበራችሁና ግዝየውን ደግ... ጥሩ አረጋችሁ።
አዋቂው እንዳለው እኛ መልካም ስንሆን ግዝየውም መልካም ይሆናል። ከቶም ያገሩ ንጉሥ ወይም ገዥ ደግ ተኾነ ሕዝቡም ደግ ነው ሚኾን፤ገዥው ተከፋም ሕዝቡም አብሮ ይከፋል። “እስመ ከመ መኰንና ለአገር ከማሁ ይገብሩ እለ ውስቴታ ይላል፤ አገረ ገዥው የሚያደርገውን ነገር ሁሉ በአገሪቱ ያሉ ያደርጋሉ ሲል ነው። መቸም በሩቅም ቢሆን
ስለእርስዎ ደግነት ብዙ ሰምቻለሁ ሁሉ ያመሰግንዎታል። እርስዎ
ለምለም ልቡና ያለዎና ልበ ጽኑ በመሆንዎ አምላክ መንግሥትዎን
ሥሙር አርጎልዎ፣ አቅንቶልዎ ለዐርባ ዓመት ገደማ ሰላም የመላበት ዘመን ሰጡን። አጤ ኢያሱ ካደጉ በኋላ እርስዎም እሳቸውም ባሳያችሁት
ትጋት እፎይ ብለን ዐርፈን አለሥጋት ተማርን፤ ሠራን። አሁን ግን ይኸው ተኝተን ሳይሆን በቁማችን እንባንናለን።”

“የኛ ዘመን ... መቸም ዕድለኛ ሁነን...”

“ዕድለኛስ አይበሉ እቴጌ! ነገርዎን አቋረጥሁ እንጂ..”

“ኧረ ግዴለህም እህትህ ነኝ እንደ ሹመኛ አትሽቆጥቆጥብኝ
አለችው፣ በፈገግታና በሚያቀራርብ ቅላጼ።

“አይ ግዴለዎትም ቀስ እያልሁ እዘናለሁ፤ ክብረት ይስጥልኝ። ደሞስ መሽቆጥቆጥ ለካህናተ ደብተራ ወግ ማዶል” ብሎ ፈገግታውን እንደያዘ ነገሩን ቀጠለ። “ንጉሥ ኢያሱ ልዥ በነበሩ ግዝየ ያን ሁሉ ትጋትዎን አይተን... ሰምተን ማልነበር? እሳቸውም ካደጉ በኋላ ተባብራችሁ
አገራችንን ሰላም አረጋችሁ፤ ደከማችሁላት። የጥጋብ ዘመን ሰጣችሁን።ሰዉም ወደዳችሁ። የሰው መውደድ ብል አጤ በካፋስ እያሉ ቢሆን እርስዎ ተወዳጅ ነበሩ። ጠንካራም ይባሉ ነበር። ይኸ ዛዲያ እንደምን ስለ ዕድል ይቆጠራል? እኔማ ቢጠይቁኝ ዕድል ሚሄድበትን ያቃል እላለሁ። ያኔ በለጋነቴ እምብዛም አይገባኝም ነበር። አንዴ ዛዲያ
መምህሬ የነበሩት አለቃ ሔኖክ ዕድል ከሰማይ አይወድቅም' ዕድል እንደ ሥዕል ነው። የሚገባውጋ ነው ሚኸድ። ማይሆነው... ዝግጁ ሆኖ
ማይጠብቀውጋ ኣይኸድም' ብለውኝ ያውቃሉ።”

“እኔም እሚታ ዮልያና ዕድል ኸሰማይ ይወድቃል?' ስትል
ሰምቻለሁ። አሳቡ አንድ ነው። እኔ ግን ዕድል ሚሰጠን እዝጊሃር ነው
እላለሁ።”

“ግና ማንችለውን አይሰጠንም። ማንችለውን ሰጥቶን ብንወድቅ...
ሳንችል ብንቀር ማን ሊጠየቅ ነው?”

“አየ ጥላዬ... ሰውን ትፈታተናለህ መሰል” አለችና ከት ብላ ሳቀች።

“እቴጌ... በመንበርዎ ትንሽ በቆዩ ኑሮ አሁን ኸመጣብን መቅሰፍት
እንድን ነበር” አለ፣ ጨዋታውን ለውጦ። “ድኻውም እኮ ቢሆን እርስዎን ተገን አርጎ ነበር የኖረ። ዛሬ ለሱ ሚያስብለት ማን አለው? ጉያዎ ደብቀው ያቆይዋትም አገር ይኸው አሁን መፈንጫ ሆነች። አሳቢ ጠፋ። አዋቂ ጠፋ። የዕውቀት ውጤቱ ሰላምና ቅንነት ነው፤ የዕውቀት ደግነቱ ማስተዋል ነው ብሎም ማልነበር ፈላስፋው? አሁን ሰላምም፣ ቅንነትም፣ ማስተዋልም የለ።”

ምንትዋብ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች። “አእምሮ ለነፍስ መዳኒቷ ነው፤ የልብ ሽልማት አእምሮ ነው' ይል የለ ፈላስፋው?”
👍14
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ከፕሎሜ ጎዳና ላይ ያለ ቤት

ፕሎሜ ከተባለ ጎዳና ላይ ንብረትነቱ የመንግሥት ባለሥልጣን የሆነ ባለአንድ ፎቅ ቤት ነበር፡፡ ቤቱ ሁለት ክፍል ቤት ከፎቁ ላይ፣ ሁለት ክፍል
ደግሞ ከምድር ቤት ነበረው፡፡ በተጨማሪ እንደ ወጥ ቤት የሚያገለግል ተጨማሪ ክፍል ፎቁ ላይ ነበረው:: ከዋናው ጎዳና ጋር የተያያዘ ትልቅ የውጭ በር ሲኖረው በአበባ ያጌጠ ሰፊ ግቢ አለው:: ከበስተጓሮው እንደ
እቃና ማድቤቶች ሊጠቅሙ የሚችሉ ሌሎች ሦስት ክፍሎች ነበሩ:: በጓሮ በኩል ደግሞ የምሥጢር በር አለው::
ምስጢሩን ለሚያውቅ እንጂ ይህ
በር፣ በር መሆኑ በቀላሉ አይታይም:: ቤቱ ብዙ ጊዜ ሰው አይከራየውም::

በ1829 ዓ.ም አንድ በእድሜ በሰል ያለ ሰው መጥቶ ይህን ቤት
ይከራየዋል፡፡ ሰውዬው ብቻውን አልነበረም:: አንዲት ወጣት አብራው ነበረች፡፡ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ነው:: ወጣትዋ ልጅ ደግሞ ኮዜት ናት፡፡ ቀደም ሲል ዣን ቫልዣ ይረዳት የነበረችው አሮጊት ደግሞ አብራቸው ናት:: ስምዋ ቱሴይ ይባላል:: ዣን ቫልዣ ቤቱን የተከራየው መሴይ ፎሽለማ በሚል ስም ነው::

ዣን ቫልዣ ለረጅም ጊዜ የኖረበትን ገዳም ለቅቆ ከወጣ በኋላ ምን
ተፈጸመ ቢባል ምንም የሆነ ነገር የለም:: እንደሚታወሰው ዣን ቫልዣ ገዳሙ ውስጥ ደስ ብሎት ነበር የሚኖረው:: በየቀኑ፡ ኮዜትን ያገኛታል።በተገናኙ ቁጥር ፍቅራቸው እየጠናና የአባትነት ስሜቱ እየዳበረ ይሄዳል፡፡
ልጅትዋን ፈጣሪ የሰጠው ፀጋ እንደሆነች ከማነ ባሻገር ይህችን ልጅ ከእርሱ ማንም ሊለያት እንደማይችል ገምቷል:: እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ከእርሱ የማትለይ ፍጡር ለመሆንዋ አልተጠራጠረም:: ይህም ደስታውን እጥፍ አደረገለት፡፡ ነገር ግን ልጅትዋን የግሉ ሀብት አድርጎ በመቀበልና የደስታው ምንጭ እንድትሆን በማድረጉ በመጠኑም ቢሆን የሕሊና ወቀሣ
ነበረበት::

ይህቺ ልጅ ገና እምቡጥ ናት:: ምንም ነገር አታውቅም:: ሕይወትዋን እንደፈቀደ የሚመራው ዣን ቫልዣ ነው:: ይህንንም ያደረገው ከክፉ ነገር
ላይ እንዳትወድቅ በማሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ዓይነቱ አስተዳደግ የዓለምን ምንነት ለማወቅ እድል አልሰጣትም:: የራስዋን እድል ራስዋ ልትወስን አልቻለችም:: እንደ እውነቱ ከሆነ ሰውዬው ይህቺን ልጅ እንደ ቦይ ውሃ የመራት ከእርሱ እንዳትሄድ እንጂ ሙሉ በመሉ ለእርስዋ ብሎ አልነበረም፡፡
ይህ ነው የሕሊና ወቀሣ ያስከተለበት::
ከመነኩሴ ትምህርት ቤት ያስገባት እርሱ ነው:: መነኩሲት እንድትሆን የወሰነው እርሱ በመሆኑ ምናልባት ስታድግ በዚህ የተነሣ ልትጠላው ትችላለትች፡ ይህንና ይህን የመሳሰለ አሳቦች ናቸው ገዳሙን ለቅቆ እንዲወጣ
ያደረጉት:: ከዚህ ለመውጣት ከውሳኔ አሳብ ከደረሰ በኋላ አልቆየም::ግቢውን ለቅቆ ለመውጣት ጥሩ አጋጣሚ እየጠበቀ ሳለ ሽማግሌው ፎሽለማ መሞታቸው በዚሁ ሳቢያ ግቢውን ለቅቆ ወጣ፡፡

ከገዳሙ ሲወጣ ለገዳሙ አለቃ የነገራቸው ወንድሙ በመሞታቸውና እንደ እርሳቸውም መሞት የተነሣ መጠነኛ ሀብት ስለወረሰ ሌላ ቦታ ሄዶ መኖር የሚችል መሆኑን ነበር፡፡ ስለዚህ ልጁን ይዞ ያለ ብዙ ድካም ከሌላ
ቦታ ለመኖር የወሰነ መሆኑን ሲነግራቸው አልተቃወሙትም:: ልጅትዋን በማስተማር ገዳሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ ለገዳሙ አምስት ሺህ ፍራንክ በስጦታ መልክ ሰጥቶ ነው የወጣው::

ከገዳሙ ሲወጣ የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅና ማንንም ሳያስቸግር
ያቺን ትንሽ ሳጥን እርሱ ራሱ በእጁ ይዞ ነው የወጣው:: የሳጥንዋን ቁልፍ ዘወትር ከእርሱ አይለያትም:: ስለሳጥንዋ ኮዜት ሁልጊዜም ትገረማለች፡፡አንድ ዓይነት የተለየ ጠረን አላት:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሳጥንዋን ከራሱ አይለያትም:: ሁልጊዜም የሚያስቀምጣት ከራሱ ክፍል ውስጥ ነው:: ከቦታ ወደ ቦታ በተዘዋወሩ ቀጥር እርስዋን ብቻ ነው አንጠልጥሉ የሚሄደው::
ኮዜት «ይህቺን ሣጥን ቀናሁባት» እያለች አንዳንዴ ብቻዋን ትስቃለች::

ከጊዜ በኋላ ዣን ቫልዣ ወደ ከተማ በወጣ ቁጥር እየተጨነቀ እንጂ
መዝናናትን ከተወ ሰንበት ብሉአል:: ፕሎሜ ጎዳና ላይ ካለው ቤት ውስጥ ከገባ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ከቤት አይወጣም:: ከዚያ ቤት ውስጥ እያለ ስሙ የሚታወቀው ኧልቲስ ፎሽለማ በሚል ስያሜ ነው::

እዚያው ቤት ውስጥ እያለ ሌሉች ሁለት አነስተኛ ቤቶች ከተለያዩ
ሰፈር ተከራይቶ በስሙ ይይዛል:: አልፎ አልፎ ወደ እነዚህ ቤቶች ተራ በተራ አንድ ጊዜ ከአንደኛው በሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለተኛው እየሄደ ወርም ሁለት ወርም ኮዜትን ይዞ ይቀመጣል:: አሮጊትዋን ግን ይዟት አይሄድም፡፡ይህንንም ያደረገው ከፖሊሶች ለመሰወር ነበር፡፡

ከቤት ውስጥ ሲሆኑ ቤቱን የምትመራው ኮዜት ናት ገዳም ውስጥ እያለች ስለቤት አያያዝ ትምህርት ቀስማለች:: ብዙውን ጊዜ ዣን ቫልዣ በጓሮ በኩል ከነበሩት ቤቶች ውስጥ ሲቀመጥ ኮዜት ከትልቁ ቤት ውስጥ
ፎቅ ላይ ነው የምትቀመጠው:: በየቀኑ ዣን ቫልዣ የኮዜትን እጅ እየያዘ ከዚያ ከተንጣለለውና ስአበባ ከአጌጠው ግቢያቸው ውስጥ ይንሸራሽራሉ፡፡
ወደ ከተማ የሚወጠበት ቀን
ውሰን ነው:: እሑድ እሑድ ግን
ወደ ውጭ ወጣ ብለው ይንሸራሸራሉ በዚህ ጊዜ የኮዜትን ቁንጅና ተመልካች እየበዛ መጣ በርግጥ እርሷም ሁሌ የምታስበው ነው ለሽርሽር በወጡ ቁጥር ወንዶች ሰብሰብ ብለው አንዱን አፍጥጣ ስታይ አንድ ሰው ‹‹በእርግጥም ቆንጆ ነሽ የሚላት መሰላት::ትንሽ ተሽኮረመመች:: ያን እለት ማታ ጥሩ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ ከተኛች በኋላ «እውነትም ቆንጆ ነኝ፤ የወንዶች ልብ አሁን እኔን ይመኛል?»
ስትል ብዙ አሰበች:: ገዳም ውስጥ በነበረችበት ጊዜ የምታውቃቸውን ጓደኞችዋን በማስታወስ መልክዋን ከእነርሱ መልክ ጋር ማነፃፀር ጀመረች::
«እኔ እኮ ከእገሊት አላንስም፡፡ እገሊትም ብትሆን እስከዚህም የምትደነቅ ልጅ አይደለችም፡፡ ውይ እገሊት ግን በጣም ቆንጆ ናት:: እኔን ትበልጠኛለች ብቻ ምንዋ ነው ከእኔ የሚበልጠው?» እያለች ስለውበትዋ ታሰላስል
ጀመር::

አንድ ቀን ከግቢው ውስጥ እየተንሸራሸረች ሳለ አሮጊትዋ ቱሴይ
«ጌታዬ ይህቺ ልጅ እንዴት እየቆነጀች እንደሄደች ልብ ብለዋል?» ብላ ስትናገር ትሰማለች:: አባትዋ ምን መልስ እንደሰጠ ግን አልሰማችም::
የቱሴይ ንግግር ግን ስሜትዋን ነካው:: እየሮጠች ወደ ክፍልዋ ሄደች::
ከመስታወት ፊት ቆማ መልክዋን አየችው:: መስታወት በማየት መልክዋ ካስደነገጣት አንድ ሦስት ወር ያህል አልፎአል፡፡ የመጀመሪያው ቀን ሰው
ሳያያት ትንሽ አልቅሳለች:: የምታየው ራስዋን ሳይሆን የሌላ ሰው መስሎአት ነበር።

በጣም ቆንጆ ለመሆንዋ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጠች:: መስታወቱና
ቱሴይ ያሉት ነገር ትክክል እንደሆነ አልተጠራጠረችም:: ቅርጽዋ፣ የቆዳዋ ቀለም፣ ፀጉርዋ፣ ዓይንዋ፣ ጥርስዋ፣ አፍንጫዋ ይህ ቀረሽ የምትባል ልጅ አልነበረችም:: ውበትዋ እንደጠዋት ፀሐይ ፊትዋ ላይ በራ፤ ተንጸባረቀ፣ ደመቀ፡፡ ወደ አበባው ቦታ ተመለሰች:፡ ወፎች ስለእርስዋ የሚዘምሩ መሰላት።
ራስዋንም እንደ ንግሥት ለመቁጠር ቃጣች::

ተመልሳ ስትመጣ ዣን ቫልዣ በአያት ጊዜ ልቡ ደነገጠ፡፡ የኮዚት
👍194
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

ውድ አንባብያን #የጣሪያ_ስር_አበቦች የተሰኘው መፅሀፍ #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ድርሰት ነው ስለዚህ እውነተኛ ታሪክ ደሞ የሚቀናነስ ነገር አይኖረውም ከባህላችን ምናምን አትበሉ እኛም በየቤታችን ስንት ጉድ አለ ያልወጣ ያልታተመ...መልካም ንባብ



...ይገባዋል እንዳልል እንኳን አእምሮው ውስጥ ያለውን ሙሉ በሙሉ አልተረዳሁትም። ያለውን ያደርጋል ብዬ ግን አስባለሁ ስሜት ግን ሰውን
የሚቆጣጠርበት መንገድ አለው ሁለታችንም ወለሉ ላይ ወደቅን ልታገለው ሞከርኩ። ታገልን፣ ተገለባበጥን፣
መንፈራገጥና መጨነቅ ያለበት የፀጥታ ትግል የእሱ ጥንካሬ ከእኔ ጋር።ፍልምያ አልነበረም።

እኔ ጠንካራ የዳንሰኛ እግሮች አሉኝ፡᎓ እሱ ትልቅ ክብደትና ቁመት አለው... በዛ ላይ ከእኔ የበለጠ የሆነ የጋለ ያበጠና ጠንካራ ነገር ለመጠቀም ማስተዋሉንና
ጤንነቱን የሰረቀው ቆራጥነት ነበረው
እወደዋለሁ ያንን ያህል የሚፈልገው ከሆነ እሱ የሚፈልገውን እኔም
እፈልገዋለሁ ትክክልም ይሁን ስህተት᎓ የሆነው ሆኖ ከዚህ ምሽት በፊት
ፍቅረኞችን የማያውቀው አሮጌ፣ ቆሻሻና የሚሸት ፍራሽ ላይ አረፍን፡ እዛ
ነው የወሰደኝ እና መርካት ያለበትን ያንን ያበጠ፣ ጠንካራ የወንድ የወሲብ
አካል በግድ ያስገባው: ጥብቅና የተቋቋመውን አካሌን ቀዶትና አድምቶት
ወደ ውስጥ ገባ።

አሁን በጭራሽ አናደርገውም ብለን የማልንበትን ነገር አደረግን።

አሁን ለዘለዓለም ተፈርዶብናል። ለዘለዓለም በእሳት ልንጠበስ ተረግመናል።በማያቋርጠው የገሀነም እሳት ውስጥ እርቃናችንን ተዘቅዝቀን እንሰቀላለን
ልክ አያትየው ከረጅም ጊዜ በፊት እንደተነበየችው ሆንን ኃጢአተኞች!

አሁን መልሶች ሁሉ አሉኝ፡

አሁን ልጅ ሊኖር ይችላል፡ ለእንደኛ አይነቶቹ የተዘጋጀውን ዘለአለማዊ
የገሀነም እሳት ሳይጠብቅ በህይወት ስለኃጢአታችን የሚያስከፍለን ልጅ
ይመጣል። ተራራቅንና እርስ በርስ ተያየን: ፊቶቻችን በድንጋጤ የደነዘዙና
የገረጡ ሆነዋል። ልብሶቻችንን ስናስተካክል መነጋገር እንኳን አልቻልንም

አዝናለሁ ማለት አያስፈልገውም ሁሉ ነገሩ ላይ ይታያል... የሚንቀጠቀጥበት
መንገድ፣ ልብሶቹን ለመቆለፍ ሲሞክር እጆቹ የሚንቀጠቀጡበት መንገድ
መደንገጡን ይናገራሉ፡

ቆይቶ ወደ ጣራው ላይ ወጣን።

ረጃጅም የደመና መስመሮች የድፍኗን ጨረቃ ፊት እያቋረጡ ነው እሷም
ትደበቅና እንደገና ትወጣለች:: ጣራው ላይ ሆነን ለፍቅረኞች በተዘጋጀው ምሽት ተቃቅፈን ተላቀስን ሊያደርገው ፈልጎ አልነበረም፡ እኔም ልፈቅድለት ፈልጌ አልነበረም ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ደም ካለው ሰው ጋር አንድ ጊዜ ባደረግነው ነገር ልጅ የመምጣቱ ፍርሀት ወደ ጉሮሮዬ መጥቶ ምላሴ ላይ ቀረ: ከገሀነም ወይም ከእግዚአብሔር ቁጣ በላይ የሆነው ከባዱ ፍርሀቴ ጭራቅ የሚመስል፣ ቅርፁ የተበላሸና ደደብ ልጅ መውለድ አስፈርቶኛል። ግን
እንዴት ስለዚህ ጉዳይ ለክሪስ መናገር እችላለሁ? በበቂ ሁኔታ እየተሰቃየ
ነው: ሆኖም ግን መንገር አለብኝ ምክንያቱም የእሱ ሀሳቦች ከእኔ በተሻለ
በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

“በአንድ ጊዜ መፀነስ አይኖርም:: ምንም ነገር ቢፈጠር ሌላ ጊዜ እንደማይሆን
እምልልሻለሁ፡ ይህ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ራሴን አኮላሻለሁ! አለኝ፡ ከዚያ
ወደ እሱ ሳበኝና የጎን አጥንቶቼ የሚሰበሩ እስኪመስለኝ ድረስ አጥብቆ አቀፈኝ። “አትጥይኝ ካቲ… እባክሽ እንዳትጠይኝ፡ ልደፍርሽ ፈልጌ አልነበረም
በእግዚአብሔር እምልልሻለሁ። ብዙ ጊዜ ተፈትኜ አውቃለሁ ግን ብዙ ጊዜ ክፍሉን እለቃለሁ ወይም ወደ መታጠቢያ ቤት እገባለሁ አለዚያም ጣራው
ስር ወዳለው ክፍል እወጣለሁ ወይም እስክረጋጋ ድረስ አፍንጫዬን መፅሀፍ ውስጥ እቀብራለሁ እና ማለፍ ችዬ ነበር:”

በቻልኩት መጠን ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት። “አልጠላህም ክሪስ” ስል አንሾካሾኩ ጭንቅላቴን ደረቱ ላይ አድርጌያለሁ: “አልደፈርከኝም፤ የምሬን ብፈልግ ኖሮ ላስቆምህ እችል ነበር ማድረግ ያለብኝ ጉልበቴን ጥንክር አድርጌ ወደላይ ማድረግ ብቻ ነበር፡ የኔም ጥፋት ነው” አዎ የኔም ጥፋት ነው። የእናቴን
መልከመልካም ወጣት ባል ከመሳም የተሻለ ነገር ማወቅ ነበረብኝ፡ የወንድ
ጥንካሬ አካላዊ ፍላጎቶች ባሉትና ሁልጊዜ በሁሉም ነገርና በሁሉም ሰው
ተስፋ በቆረጠ ሰው ዙሪያ ወንድሜም ቢሆን እንኳን ሰውነትን የሚያሳይ ልብስ
መልበስ አልነበረብኝም: በፍላጎቶቹ እየተጫወትኩ፣ ሴትነቴን እየሞከርኩ፣
የራሴን የሚቃጠል የመርካት ፍላጎት እያየሁ ብቻ ነበር።

ይህ የተለየ አይነት ምሽት ነው፤ ልክ ዕድል ከረጅም ጊዜ በፊት ይህንን ቀን
ያቀደው ይመስላል እና ይህ ምሽት ትክክልም ይሁን ስህተት እጣ ፈንታችን
ነው:

ንፋሱና ቅጠሎቹ ዜማ አልባ ሙዚቃ ያሰማሉ: ሙዚቃው ያው ነው: ሰው የመሰለ አፍቃሪ የሆነ ፍጥረት እንዴት በዚህ ቆንጆ ምሽት አስቀያሚ ሊሆን
ይችላል?

ምናልባት ጣሪያው ላይ ብዙ ቆይተናል፡

የመስከረም መግቢያ በመሆኑ ጣሪያው ቀዝቃዛ፣ ጠንካራና ሻካራ ሆኗል።
ቅጠሎቹ መርገፍ ጀምረዋል ጣራው ስር ያለው ክፍል ልክ እንደ ገሀነም ያቃጥላል ጣራው ላይ ግን በጣም በጣም ይቀዘቅዛል
እኔና ክሪስ ለደህንነትና ለሙቀት ተቃቅፈን ተቀምጠናል። በጣም መጥፎ ወጣቶችና ኃጢአተኞች:: ያለማቋረጥ በመጠጋጋት በጣም ተወጥረው በቀጠኑ
ታሪኮች የራሳችንን ክብር አሽቀንጥረን ጥለነዋል፡ በአንድ ወቅት በራሳችን
ስሜታዊ ተፈጥሮ አብዝተን የተፈተንን ቢሆንም... በዚያ ወቅት እንኳን እሱ እኔም ስሜታዊ መሆኔን አላውቅም ነበር፡ ልቤን የሚሰውርና ሽንጤን
እንድሰብቅ የሚያደርገኝ ቆንጆ ሙዚቃ ብቻ ይመስለኝ ነበር፡ በጣም ተጨባጭ የሆነ ሌላ ነገር እንዳለ አላውቅም ነበር።

ልክ አንድ ልብ እንደምንጋራ ሁሉ በሰራነው ስራ ራስን የመቅጣት አሳዛኝ ቅኝት
እየደለቅን ነበር ቀዝቃዛው ነፋስ የረገፈ ቅጠል ወደ ጣራው አምጥቶ ድንገት
ፀጉሬ ውስጥ እንዲያዝ አደረገው:: ክሪስ ሊያነሳው ሲሞክር ደርቆና ተሰባብሮ
ወደቀ ህይወቱ ቅጠሉ በንፋስ መብረር እንዴት እንደሆነ በሚያውቀው
ሚስጥር ላይ የተመሰረተ ይመስል ክሪስ ቅጠሉን አተኩሮ እየተመለከተ
ነበር: እጆችም ክንፎችም የሉትም... ግን ሞቶም መብረር ይችላል።

“ካቲ” በሚደነቃቀፍ ደረቅ ድምፅ ጠራኝ፡ “አሁን ልክ ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት
ዶላር ከአርባ አምስት ሳንቲም አለን በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል።
በልካችን የሆነ የክረምት ኮት ወይም ጫማዎች የሉንም፧ መንትዮቹ ደግሞ
ደካማ ስለሆኑ በቀላሉ ብርድ ሊያሳምማቸውና ከዚያ ወደ ኒሞኒያ ሊለወጥባቸው
ይችላል ሌሊት ነቅቼ ስለእነሱ እጨነቃለሁ እና አንቺንም አልጋሽ ላይ
ሆነሽ ኬሪን አተኩረሽ ስትመለከቻት አይሻለሁ፡ አንቺም ተጨንቀሽ መሆን
አለበት። አሁን ከእናታችን ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ ገንዘብ የማግኘታችንን
ነገር እጠራጠራለሁ። ሠራተኞች ገንዘብ እየሰረቋቸው እንደሆነ ጠርጥረዋል።አሁን ምናልባት እናታችን አንቺ ልትሆኚ እንደምትችይ ትጠራጠር ይሆናል አላውቅም... እንደማይሆን ተስፋ አለኝ።

“እነሱ ምንም ቢያስቡ በሚቀጥለው ለመስረቅ ስሄድ ጌጣጌጧን ለመስረቅ
እገደዳለሁ። ትልቅ ነገር እወስድና ከዚያ እናመልጣለን ልክ ርቀን እንደሄድን በቂ ገንዘብ ስለሚኖረን መንትዮቹን ወደ ዶክተር እንወስዳቸዋለን፡” አለ፡

“ጌጣጌጦቹን ውሰድ።” እንዲወስድ ብዙ ጊዜ ለምኜው ነበር። በመጨረሻ
ሊያደርገው ነው እናታችን ልታገኘው የታገለችለትን ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ
ጌጥ ታጣለች በዚያ ሂደት ውስጥ እኛንም ታጣለች: ግን ግድ ይኖራት
ይሆን?
👍402👏2
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...ቀኑ ሰኞ ማታ ነው አየሩ ለሰስ ብሏል " ጨረቃ ፍንትው ብላ ወጥታለች "
እንዳይታይ ሠግቶ አንገቱን ደፍቶ ተገን እየመረጠ በእግሩ ከሚጓዘው ብቸኛ የሩቅ መንገደኛ ላይ የሚያበሩት ከዋክብትም ጥርት ብለው ደምቀዋል " ሰውየው የሥራ ካፖርቱን ለብሶ ሶሉ ምስማር የተጠቀጠቀበት ጫማ አድርጎ የጉልበት ሠራተኛ
ይመስላል " ረጅምና ጥቁር ሪዙ ታችኛውን ፊቱን ሲሸፍነው ክፈፈ ሰፊው ባርኔጣው ደግሞ ግንባሩን ዐልፎ ወርዷል " ወደ ሚስተር ሔር ቤት ተጠግቶ ግራና ቀኙን ደኅና አድርጎ ተመልክቶ በአጥር ተንጠልጥሎ ገብቶ ወደ አትክልቱ ቦታ መጣና ዛፎቹ መኻል ተጠግቶ ቆመ።

ሚስተር ሔር እቤት እንግዶች ካልመጡበት በቀር በዓመት ሁለት ቀን
እንኳን አድርጎት የማያውቅውን የዚያን ቀን ከቤቱ አምሽቷል ባርባራ የወንድሟን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአባቷ ከቤት ማምሸት በጣም አስጨንቋታል ካሁን አሁን በመጣ እያለች ስትመኝ እሱ ወንበሩን ወደ መስኮቱ አስጠግቶ ረጂም ፒፓውን ካፉ ሰክቶ ሰው ሠራሽ ጸጉሩን ወደ አንድ በኩል
ገደድ አድርጎ በአትክልት ቦታውና በዐፀዱ ሙሉ ትይዩ ተቀምጦ ይመለከታል

“ ዛሬ አትወጣም እንዴ . . . ሪቻርድ '' አለችው ሚስዝ ሔር ፈራ ተባ እያለች

አልወጣም "
“ እማማ . . .የመስኮቱን መከለያዎች ላስዘጋቸው ? አለች ባርባራ "

“ ይዘጉ ?” ብሎ አጉረመረመ " “ ማነው ይህች ጨረቃ እያለች የሚዘጋው የኛ ቆንጆ ብትፈልጊ ፋኖሱ ከዚያ ጥግ አለልሽ ከዚያው ሔዶሽ ተቀመጭ ”

አባትው እንደዚያ በሚመለከትበት ጊዜ ሪቻርድ በድኑንም ይዘልቅና ያየው እንደሆን ብላ በጣም ሠጋች እንደ ፈራችው ምልክቱ መጣ ሲንቀሳቀስ ታያት "ባርባራ ተጨነቀች ነጭ ዐመዷ ቡን አለ » ከንፈሯ ደረቀ ።
አቤት በጣም ምቀኝ ! እኔስ በአትልቱ ቦታ ትንሽ ነፋስ ተቀብዬ ልምጣ መሰለኝ " አለች የመውጫ ምክንያት ፈልጋ "

ጠቆር ባለው የሐር ቀሚሷ ላይ ጠቆር ያለ መደረቢያ ጣል አድርጋ ሹልክ ብላ ወጣችና አባቷ አስተውሎ እንዳይመለከታት እየተጠነቀቀች ሪቻርድን ወዳየችበት ቦታ ሔዳ ተግናኙ ፊቱ ነጥቶ ከስቶ ስታየው በጣም አዘነች " ጸጉሩም እንዳለ
ሸበት መሆኑን ነገራት "

ሪቻርድ አሁን አላነጋግርህም " ዛሬ አባባ ያለ ወትሮው ከቤት አምሽቷል ስለዚሀ ነገ ማታ ተመለስ ”

ለሁለተኛ ምሽት ወደዚህ መምጣት ደስ አይለኝም ... ባርባራ የዚ አካባቢ ምድር በእያንዳንዱ ስንዝር ርቀት አደጋ አለበት

“መቆየትማ አለብህ ...
ሪቻርድ ! ያ ይህን ሁሉ ተንኮል የፈጸመው ቶርን
ዌስት ሊን መጥቷል” እሱ ሆነም አልሆነም ቶርን የሚባል ሰው እዚህ ይገኛል
እኔና ሚስተር ካርላይል
እሱ መሆኑን አምነንበታል
አንተም እንድታየው
እንፈልጋለን እንዴት አይተህ ልታረጋግጥ እንደምትችል ግን ሚስተር ካርላይል
ይነግረናል" ምንም እንኳን ሰውየው አንተ የምትለው ቶርን መሆኑ ስለ ተረጋገጠ
ብቻ አንተን ነፃ ለማድረግ በችኮላ የሚፈጸም ባይሆንም አንድ ትልቅ ነጥብ አጣርቶ መጠበቅም ቀላል ነገር አይደለም ግን አትረሳውም ? እንደምታውቀው እርግጠኛ ነኝ ትጠራጠራለህ?"

“አባቴን አላውቀውማ ! አንቺ አሁን ትጠፊኛለሻ ! አሱንም እንደዚሁ
እይው i ግን እንዴትና መቸ ነው ላየው የምችል ... ባርባራ ?

ሚስተር ካርላይልን እስክጠይቀው ድረስ ልነግርህ አልችልም አንተ ነገ
ማታ በጣም ሳይመሽብሀ እንደ ተመቸህ እዚሀ ድረስ እንድትመጣ " አባባም ከቤት አይኖርም ምናልባት.."

ነጎድጓድ የመሰለው የጀስቲስ ሔር ድምፅ በመስኮቱ አስተጋባ „ “
ባርባራ ብርድ እንዲመታሽ ነው እዚያ የምትንከለከይው አሁን ነይ ግቢ ነው የምልሽ.

“አዝናለሁ ሪቻርድ? . . . ልለይህ ነው” አለችውና በጆሮው “ ነገ ግን
አባባ ከቤት እንደማያመሽ አትጠራጠር ቢሞት አከታትሎ ሁለት ቀን ከቤት
አያመሽም " ደህና እደር ።

አሁን እንግዲህ መጣደፍ አስፈላጊ ሆነባት " የማንንም ሐሜትና ትችት ሳትፈራ ጧት ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ደረሰች " እንደዚያ እየተጣደፈች ?ስትደርስ ሚስተር ካርላይል አልገባም ። ጸሐፊዎቹም የሚገባበትን ሰዓት አላወቁም ።

"ሚስተር ዲል” አለች ባርባራ ሰውየው ሰላም ሊላት ወደሷ ሲመጣ“ ሚስተር ካርላይልን ማግኘት አለብኝ " በጣም እፈልገዋለሁ ”

“ ከሰዓት በኋላ ያውም ቆየት ብሎ ነው የሚገባው ከዚያ በፊት አይመጣም "
እኔ ልረዳሽ የምችለው ጉዳይ ነው?”
“ አይደለም ፣ አይደለም " አለችው በረጅሙ ተነፈሰችና

ሁለቱ ቁመው ሲነጋገሩ ሳቤላ ልጅዋን ትንሿ ሳቤላን ይዛ በሠረገላ ስታልፍ አየቻቸውና ለባርባራ ጅንን ብላ በንቀት እጅ ስትነሣት ለሚስተር ዲል ደግሞ ደመቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለችው "

ባርባራ ሚስተር ካርላይልን በዐሥር ሰዓት ላይ አገኘችውና የሪቻርድን መምጣት ነገረችው

ሚስተር ካርላይል ማንኛውንም ማታለልና ማጭበርበር በጣም ይጠላ ነበር አሁን ግን ቶርን በነበረበት ችግር አመካኝቶ ከቢሮው ማስጠራት እሱ ሳያውቅ ሪቻርድ እንዲያየው ማድረግ አማራጭ ያልነበረው ተገቢ ሥራ መሆኑን አመነበት"ስለዚህ ሪቻርድን በቀጠረችው ሰዓት ሲመጣ ወደሱ እንድትልከው ነገራት » እሱም በበኩሉ ጀፈርሰን ቤት የነበረበትን የራት ጥሪ ሰርዞ ካፔቴን ቶርን አማክሮት ስለ ነበረው ጉዳይ ማታ በሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ እንዲመጣ ላከበት ” እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ቀኑን ከቢሮ ባለመዋሉ አልላከበትም እንጂ ስለሱ ጉዳይ ጧቱን
አግባብ ካላቸው ጋር ተነጋግሮ መፍትሔ አግኝቶለት ነበር።

የሚስተር ካርላይልን አስቸኳይ ውሳኔ የሚጠይብቅ ብዙ ጉዳዮች ከቢሮ ይጠብቁት ነበር። ስለዚህ ወደ ቤቱ ከመሄዱ በፊት አስራ አንድ ሰአት ሆነ ከራት ጥሪው መገኘት አለመቻሉን ገና ለሚስቱ አልነገራትም " ስለዚህ ከቢሮው የነበረውን ውዝፍ ሥራ ሳይጨርስ ወደ ቤቱ መሔድ ግድ ሆነበት "

ሚስተር ካርላይል የግል ደስታውን ለወዳጅነትም ሆነ ለሥራ ለመሠዋት የማያወላውል ሰው ነበር ።

ከሰረገላው ተዘጋጅቶ ከበሩ ቁሞ ሳቤላም ልብሷን ለብሳ ከመልበሻ ክፍሏ ተቀምጣ ስትጠብቀው መጣ “ ጀፈርሰን ቤት ራት የሚጀመረው ባሥራ ሁለት ሰዓት መሆኑን ረሳኸው ? አለችው በሰላምታ ፈንታ

“ አልረሳሁትም. . .ሳቤላ ግን ከዚህ ቀድሜ መድረስ አልቻልኩም " አሁንም ቀደም ብዬ የደረስኩት አብሬሽ ለመሔድ ስለ አልተመቸኝ ሚስዝ ጀፈርሰንን ይቅርታ እንድትጠይቂልኝ ልነግርሽ ነው " ዛሬ ማታ ሌላ ሰው ሊሠራልኝ የማይችል ሥራ ስለ አጋጠመኝ አሁን ራት እንደ በላሁ ተመልሼ ወደ ቢሮ እሔዳለሁ " ሳቤላ
ሲላት ሳቤላ ፊቷ ተለዋወጠ " እሷን ወዝውዞ ሊገድላት የሆነው ልዩ ልዩ ሰበብ እየፈጠረ ጊዜውን ከባርባራ ሔር ጋር ለማሳለፍ ስለሚፈልግ ነው የሚለው እምነቷ ነበር "

“ አትቆጭ . . . ሳቤላ እውነቴን ነው ወድጄ አይደለም ። ለሌላ ቀን የማይተላለፍ ዲልም ሊፈጽመው የማይችል ብርቱ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው በዚህ አጉል ሰዓት እንደዚህ ያለ ነገር በመፈጠሩ በጣም ነው የማዝነው።

"አለ ዛሬ ከመሸ በኋላ ወደ ቢሮ ተመልሰህ ገብተህ አታውቅም ”

“ እውነትሽን ነው " ምክንያቱም ማታ ወደ ቢሮ የሚያስገባ ነገር ቢፈጠርም
ዲል ሊሠራው የሚችል ነበር " የዛሬው ግን እኔ ራሴ መሥራት ያለብኝ ጉዳይ ስለ
ሆነ ነው ' '

ባይሆን ስትሠራ ቆይተህ ስትጨርስ አዛው ድረስ አትመጣም ?

በውነቱ የምደርስ አይመስለኝም ”
👍18👎1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ሌኔሃን ከማታውቀው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መተኛቷ
ሰላም ሳይነሳት አልቀረም:

ምንም እንኳን ክፍሉ የሙሽሮች ክፍል ቢሆንም አልጋዎቹ ተደራራቢ ናቸው፡፡ በሩ ክፍት እንዲሆን ቢፈልጉም በወጀቡ ምክንያት በሩ እየተወረወረ
ይዘጋል፡፡ ስለዚህ አስሬ ሲዘጋ እየተነሱ ከመክፈት ይልቅ አንድ ጊዜ ዘግቶ
መተዉ የሰውን ትኩረት አይስብም:፡

ናንሲ በጊዜ ላለመተኛት ብዙ ጥራለች። በዋናው ሳሎን ሄዳ ለመቀመጥ
ብትፈልግም ወንዶች ብቻ ናቸው የተሰባሰቡት፡፡ ቦታው በሲጋራ ጭስ ታፍኗል፧ በዊስኪ ሽታ ታውዷል፡ በተጨማሪም የካርታ ተጫዋቾች ስድብና
ጫጫታ ጆሮ ይሰነጥቃል፤ ቦታው ለሴት ልጅ የሚሆን አይደለም፤ ስለዚህ
‹መተኛት ሳይሻል አይቀርም› ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።

ስለዚህ መርቪንና ናንሲ መብራቱን አጠፉና በየአልጋቸው ላይ ሰፈሩ።
ናንሲ ዓይኖቿን ብትጨፍንም እንቅልፍ በአይኗ hልዞር አለ፡፡ ወጣቱ ሄሪ ማርክስ ያመጣላት አንድ መለኪያ ዊስኪ እንኳን ለመተኛት የረዳት ነገር
የለም፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም በዓይኗ እንቅልፍ አልኳል ብሏል፡

መርቪንም እንቅልፍ እንዳልያዘው አውቃለች፡ የላይኛው ቆጥ ላይ
ሰፍሮ ይገላበጣል፡፡ እንደ ሌሎች መኝታዎች የሙሽሮቹ አልጋዎች በመጋረጃ የተሸፈኑ ባለመሆናቸው ላለመታየት ያላት ምርጫ መብራቱን ማጥፋት ነው፡፡

እንቅልፍ አልመጣላት ሲል ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በሀሳቧ መጣች ማርጋሬት በጣም ወጣት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ የማይገባትና ወደፊት
ስለሚገጥማት ነገር ቅንጣት ታህል የማታውቅ ልጅ ናት። ከማርጋሬት
በጥርጣሬ የተሞላ ፊት ላይ ያነበበችው ግን ከፍተኛ ነፃ የመሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ወጣት በነበረችበት ጊዜ የገጠማት አይነት ችግር ነው፡፡ ናንሲም በዚያ ወቅት ከወላጆቿ ጋር አተካራ ውስጥ ገብታ ነበር፧
በተለይ ከእናቷ ጋር፡ እናቷ የተከበረ የቦስተን ቤተሰብ ልጅ እንድታገባ
ብትፈልግም እሷ ግን ገና አስራ ስድስት አመት ሲሞላት ሾን ሌኔሃን
ከሚባል የህክምና ትምህርት ከተማረ ከአባቷ ፋብሪካ ውስጥ ከሚሰራ ካቦ ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ እናትዬው ናንሲ ይህን ልጅ እንዳታገባው ልጁ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንደሚማግጥ፣ እናት አባቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ
እንደሚሳደብና በየጊዜው እንደሚያመው ሀሜት ብታስወራም ናንሲ ግን
የሚነዛውን ሀሜት እንዳልሰማች በማሳለፍ ሾንን አግብታ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አብራው ኖራለች፡፡

ማርጋሬት የእሷን ያህል ጥንካሬ ያላት ልጅ አትመስልም፡፡ ከአባቷ ጋር
ካልተስማማች ከቤታቸው መውጣት ትችላለች፡፡ ይቺ ልጅ በየጊዜው ችግር
እያነሳች እንዳታላዝንና ራሷን ለመቻል እንድትጥር የሚመክራት ሰው ያስፈልጋታል፡ እኔ በእሷ እድሜ የሁለት ህጻናት እናት ነበርኩ› አለች በሃሳቧ፡

ስለዚህ ማርጋሬት ራሷን እንድትችል ጠበቅ ያለ ምክር ለግሳታለች እሷም ቃሏን በመጠበቅ ስራ ልትሰጣት ተስፋ አድርጋለች፡፡

ይሄ ሁሉ ደግሞ የሚወሰነው ከወንድሟ ጋር ባላት ጠብ የሀይል
ሚዛኑን በጨበጠው በአጭበርባሪው ሽማግሌ በዳኒ ሪሌይ ነው፡፡ ናንሲ
እንደገና ወደ ጭንቀቷ ተመለሰች፡፡ ጠበቃዋ ማክ ዳኒ ሪሌይን ይኸኔ
አግኝቶት ይሆን? ከአገኘውስ ስለቀድሞው ወንጀሉ ሲነግረው ምን አለ? ይህ ሁሉ ሴራ እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ የተጠነሰሰ መሆኑን ጠርጥሮ ይሆን?›
እነዚህን ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ስታወጣ ስታወርድ እንቅልፍ አጥታ
አልጋዋ ላይ ትገላበጣለች፡፡

የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦትውድ ከተማ ነው፡፡ ኒውፋውንድ ስትደርስ ማክጋ ስልክ ደውላ ታረጋግጣለች፡፡በዚያ ጊዜ ሁሉ ነገር ይለይለታል፡

አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲንገጫገጭ ናንሲ መላ አካልዋ ተረበሸ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበታል፡ በአይሮፕላን በተደጋጋሚ ብትሄድም ከዚህ ቀደም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ግዙፉ አይሮፕላን በንፋሱና
በወጀቡ ሲወዛወዝ ስጋት ገብቷት ተወርውራ እንዳትወድቅ የአልጋውን ብረት አጥብቃ ያዘች፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ብዙ ችግር ገጥሟታል፤ ‹አሁን ጉልበቴ
በርታ በርታ› ማለት አለበት፤ ነገር ግን የአይሮፕላኑ መንዘፍዘፍ ክንፎቹን
ይገነጥል፣ ሞተሩን ሰብሮ ይጥለው ይሆን?› እያለች መፍራቷ አልቀረም፡፡
ፍርሃቷን ይቋቋምላት ይመስል ትራሷን በጥርሷ ነክሳ ያዘች፡፡ ድንገት
አይሮፕላኑ ቁልቁል ወረደ፡፡ ቁልቁል መውረዱ እንዲቆም በእጅጉ ብትመኝም
መውረዱን ቀጥሏል፡ ይህ ሁኔታ ክፉኛ አስደነገጣት፡፡ ከዚያም ዘጭ አለና
ቀጥ ብሎ መብረር ጀመረ፡
መርቪን እጁን ሰዶ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ንፋሱ የፈጠረው ወጀብ ነው አይሮፕላኑን እንዲህ የሚያደርገው›› አለ ‹‹ከዚህ የባሰ ሁኔታ እኔ ብዙ
ገጥሞኛል፤ አይዞሽ አትፍሪ›› ሲል አጽናናት፡፡

እጁን በእጇ ፈልጋ አጥብቃ ያዝ አደረገችው፡፡ ከአልጋው ወረደና እሷ አልጋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ ፀጉሯን ይደባብስ ገባ፡፡ አሁንም ፍርሃቷ ሙሉ በሙሉ ባይለቃትም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ መርቪን ያዝ ስላደረጋት በመጠኑ
ቀለል አላት፡፡

ምን ያህል ጊዜ እንደተያያዙ አላወቀችም:: ትንሽ ቆይቶ ወጀቡ ተነሳ፡፡በደምብ ስትረጋጋ የመርቪንን እጅ
ለቀቅ አደረገችው፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አላወቀችም።

ናንሲ መብራቱን አበራችና ከአልጋዋ ውስጥ ወጣች፡፡ ከላይ የሆነ ልብስ ደረብ አደረገችና መስታወቱ ፊት ቁጭ አለች፡፡ ሁልጊዜም
ጭንቀት ሲይዛት እንደምታደርገው ፀጉሯን አበጠረች፡፡ በጭንቀቷ ጊዜ የመርቪንን እጅ መያዟ አሳፈራት፡ በዚያ ጊዜ ክብሯን ሸጣ እጁን ለጥቂት ጊዜ በመያዟ በሆዷ
ብታመሰግነውም አሁን ፍርሃቷ ሲለቃት ግን ነገሩ አስፈራት፡፡ እሱም ስሜቷን በመረዳት እፍረቷ እንዲለቃት ብሎ ለጊዜው ክፍሉን ለቆላት ወጣ፡፡

መርቪን ትንሽ ቆይቶ ጠርሙስ ብራንዲ ከሁለት መለኪያ ጋር አመጣና
መጠጡን ቀድቶ አንዱን ሰጣት፡፡ አይሮፕላኑ ትንሽ ይወዛወዝ ስለነበር
በአንድ እጇ መለኪያውን በሌላ እጇ ደግሞ የአልጋውን ብረት ይዛለች:
የለበሰው አስቂኝ ልብስ ባያስቃት ኖሮ ድንጋጤው ቶሎ አይለቃትም አስቂኝ ቢሆንም ልክ ሱፍ ለብሶ
እንደሚንጎራደድ ሁሉ ምንም አልመሰለውም፡፡ ሰው ሞኝ ነው ቢለው ግድ
የለውም፡፡ ልበ ሙሉነቱ አስደስቷታል፡፡

ብራንዲዋን ስትጨልጥ በሰራ አካላቷ ሙቀት ስለፈጠረላት ደጋግማ
ተጎነጨች፡፡

መርቪን ወሬ ለመጀመር ብሎ ‹‹እዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ የሆነ
እንግዳ ነገር አየሁ›› አለ ‹‹እኔ ወደ መታጠቢያ ክፍል ስገባ አንድ በድንጋጤ
ቀልቡ የተገፈፈ ተሳፋሪ ሲወጣ አየሁ፡፡ የመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት ተሰብሯል የበረራ መሀንዲሱ ደግሞ ጥፋት ሲፈጸም የተያዘ ሰው መስሎ እዚያ ቆሟል፡፡ መስኮቱ የተሰበረው ከአይሮፕላኑ ውጭ ተወርውሮ በገባ
የበረዶ ቋጥኝ መሆኑን ሊታመን የማይችል ታሪክ ነገረኝ፡፡ እኔ ግን ሁለ±
ሲደባደቡ እንደነበር መገመት አላቃተኝም፡፡››

ናንሲ እዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚቀመጡ ታሪክ ስለነገራት በሆዷ
መርቪንን አመሰገነችው፡፡ ‹‹የትኛው የበረራ መሀንዲስ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹እንደ እኔ ቁመቱ ሎጋ የሆነና ፀጉሩ ቃጫ የመሰለ መልከ መልካም ወጣት››
‹‹መሀንዲሱን አወቅሁት፤ ተሳፋሪውስ ማን ነው?››
‹‹ስሙን አላውቀውም፤ ነጋዴ ይመስላል፤ አመድማ ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰውዬ ነው›› አለና መርቪን ተነስቶ ብራንዲ ብርጭቆዋ ውስጥ
ጨመረላት፡፡
👍20🥰1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹ከምን ያህል የጊዜ ደንዛዜ ውስጥ እንደቆየች አታውቅም .የሳሎኑ በራፍ ተበርግዶ ሲከፈት ነው ከሀሳቧ ውስጥ በመከራ የወጣችው…ጊፍቲ ከፊት መድህኔ ከኋላ እያለከለኩ ተከታትለው ገቡ
በመጠጥ ተዳክሞ በተቆላለፈ አንደበቷ ‹‹ነይ እንጂ ኑ ብያለሁ››አለቻት..ያልጠበቀችን እና ከነመፈጠሩም ጭሩሱኑ ረስታው የነበረውን መድሀኔን ስታየው ብሶቷ በእጥፍ ጨመረባት፡

ጊፊቲም በራሷ ድንጋጤ ላይ ስለሆነች እሷ የምትለውን እየሰማቻት አይደለም..ጥያቄዋን አዥጎደጎደችው‹‹እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው…?ቃልዬ የት አለ….?አመመው እንዴ….?››ተንደርድራ አልፋ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፈተችና ወደ ውስጥ አየች… ባዶ መሆኑን ስታይ ወደ ልዩ ተመለሰችና‹‹…ልዩ ንገሪኝ እንጂ…ተጣልታችሁ ነው….?አሁን እሱ የት ሄደ?››
ዝም ብላ አየቻት..ሆዷ ወደፊት እየገፋ ነው…በሶስት ወር ፣‹‹እንዲህ ያስታውቃል እንዴ…?››ስትል አሰበች ግራ ከመጋባቷ የተነሳ የማያሳስበው እያሳሰበት ነው፡፡መድህኔ እጁን በደረቱ ላይ አጣጥፎ ግራ በማጋባት ዝምብሎ ቁልቁል እያየት ነው፡፡አሳዝናዋለች.በጣም ነው ያሳዘነችው..ስሯ ተንበርክኮ ወደደረቱ አስጠግቶ እቅፍ አድርጎ ቢያፅናናት ደስ ይለዋል.ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም…
‹‹ልዩ አረ በፈጠረሽ …አናግሪኝ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው?››አለች ጊፊቲ
‹‹ቃል ከዛሬ ጀምሮ የለም››
‹‹የለም ማለት ምን ማለት ነው?››
‹‹መልሱ መኝታ ቤት ግቢና አልጋው ላይ አለልሽ››
ከተንበረከከችበት ተነስታ ተንደርድራ ወደመኝታ ቤት ስትገባ መድህኔ ‹‹ልጄን…›› አለ .አንድ ነገር እንዳይሆንበት የተሳቀቀ በሚመስል ሰውነቱን አሸማቆና ፊቱን አጨማዶ‹‹አረ ማሬ ቀስ በይ..ቀስ…..››
ፖስታውን በእጇ እያገላበጠች ተመልሳ መጣች፡፡‹‹የመጨረሻ ስንብት ማለት ምን ማለት ነው? ››ተንዘረዘረችባት
‹‹ወይዘሮ ጊፍቲ ብታነቢው እኮ የምትፈልጊውን  መልስ  ከውስጡ ታገኚያለሽ..››
ከፈተችውና ማንበብ እንደጀመረች እንደማዞር አደረጋት ፡፡ ተንገዳገደች….ተንደርድሮ ሄደና ክንዷን ያዛት …መድህኔ የልዩ የድሮ ፍቅር …ቃልን የማታገኝ መስሏት ለሌላ ሴት አሳልፋ የሸለመችው የልጅነት ጓደኛዋ …የረጅም ዘመን ፍቅረኛዋ… እየጎተተ ወሰዳትና  ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ለማንኛውም ብሎ ልክ እንደባለስልጣን ጋርድ ከጎኗ በተጠንቀቅ ቆመ ..እንደምንም ብላ ማንበቧን ቀጠለች…ልዩም መጠጧን እየሳበች እየተከታተለቻት ነው፡፡ ጨረሰችና ደብዳቤውን ወደመሬት ጣለችው›
‹‹አንብቤያለሁ ግን ምንም አልገባኝም››
‹‹እኔም እኮ አልገባኝ ብሎ ነው የጠራሁሽ..አንቺ ምን አልባት የልጅነት ጓደኛው ስለሆንሽ ጠባዩንና ድርጊቱን ከኔ በተሻላ ትረጂያለሽ ብዬ ስለማስብ  እንድታስረጂኝ ነበረ  …አንቺ ግን መልሰሽ እኔን እየጠየቅሽ ነው፡፡››
‹‹ቀስ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና እየተጎተተች ሄዳ ከልዩ  ጎን ተዘረፈጠች…..የውስኪውን ጠርሙስ አንስታ ልትጋተው ወደላይ ስታነሳ..ልክ አንደ እግር ኳስ በረኛ ካለበት ተንደረድሮ ሸርተቴ በመግባት ከእጇ ላይ ቀለበው…
‹‹ምን ነካሽ..?እርጉዝ እኮ ነሸ››
‹‹ይቅርታ መድህኔ …ግራ ስለተጋባሁ ነው..እንዴት ነው ቃል ህይወቱን ጥሎ፤ ስራውን ጥሎ፤ አባቱን ጥሎ፤ እኛን ጥሎ ገዳም  የገባው…ገዳም መግባት ማለት ምን ማለት ነው…?››የመለሰላት የለም…..
መድህኔ ከሁለቱም ፊት ለፊት ቆሞ በጭንቀት እያፈራረቀ እያየቸው ነው..ምን እየተሰማው እንደሆን ልቡ ውስጥ ገብታ ማንበብ ብትችል ደስ ይለታል ..የድሮ ፍቅረኛውና የአሁኑ እጮኛው ሌላ ወንድ ጥሎን ገዳም ገባ በሚል ሰበብ ስብብርብር ብለው እንዲህ ሲነፈርቁ….በጣም ከባድ ነው……፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር በቃ አንተ ወደስራህ ሂድ…..››
‹‹እንዴ እንዲህ ጥያችሁ እንዴት…..››
‹‹ግድ የለህም ..ሂድ ..እኛ ምንም አንሆንም…››
‹‹እውነቷን ነው እንደውም ብቻችንን ብትተወን ውለታ እንደዋልክልን ነው የምቆጥረው…›.አለችው
‹‹በቃ..የሆነች አጭር ስብሰባ አለቺብኝ..እሷን እንደጨረስኩ ተመልሼ እመጣና ወሰድችሓለው…፡፡
‹‹ሚስትህን መጥተህ መውሰድ ትችላለህ ..እኔ ግን የማድረው እዚህ ነው….ባይሆን ለእማዬ ደውለህ የሆነ ምክንያት ስጣትና እንደማድር ንገርልኝ››
እኔም እሷን ጥያት ስለማልሄድ ..ለዛሬ ተወን..ከፈለግንህ እንደውልልሀለን…› አለችው…››ጊፍቲ
‹‹ካላችሁ እሺ…ስልክሽ ግን እንዳይዘጋ….ቻው››   ቅር እያለው ወጥቶ ሄደ
የእግሩ ኮቴ መራቁን አረጋግጠው ሁለቱም የተነጋሩ ይመስል   እርስ በርስ ተቃቀፍና እየነፈረቁ ማልቀስ ቀጠሉ….ልክ የጋራ ቅርብ ዘመዳችው ሞቶ  ተረድተው ነው የሚመስለው….
‹‹በጣም አፍቅሬው ነበር እኮ……››አለቻት
‹‹አዎ ጠርጥሬ ነበር…በጣም አዝናለሁ››
‹‹እሺ አሁንም ምን ይሻለኛል….?እንዴት ነው የማደርገው?››
‹‹እኔ አላውቅም የእኔ ማር..እኔም ያለእሱ ምክርና ማበረታቻ ህይወትን መኖር አለመድኩበትም…እንዴትም እንደሚዘለቅ አላውቅም….››>
ማኒቲሱ የሚባል ነፍሳት አለ፡፡ የፌንጣ ዝርያ ነው፡፡የፍቅር ታሪካቸው በጣም ልብ ሰባሪ ነወ፡፡ ሴቷ ወንድ ዙሪያውን በመሽከርከር ስትደንስና ክንፎቾን እያማታች ስታማልልው  የወንዱ ስሜቱ ቀስ በቀስ ተነቃቅቶ በፈቅር ቅልጥልጥ ይላል..ከዛ እራሱን ከግንድና ካገኘው ጠንካራ ነገር ጋር ደጋግሞ ባማጋጨት ከሌላው ሰውነቱ በመለየት ቀንጥሶ ይጥለዋል..ምክንያም እንደዛ ሲያደርግ ብቻ ነው ከእሷ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ በማድረግ ከውጥረቱ መርካት ሚችለው…..እና እንዳሰበው ከፍቅር መቅደስ ገብቶ ወሲባዊ መዝምር ዘምሮ …ፍፅማዊ እርካታ ይረካል..ግን ወደህይወት መመለስ አይችልም….ዳግመኛ የተቀነጠሰ አንገቱን ለብቻው ከተዘረረ ሰውነቱ ጋ የማጣበቅ ምንም አይነት ተፈጥሮአዊ ችሎታ የለውም..በዚህም ምክንያት የህይወት ፍፃሜው ይሆናል፡፡
‹‹እና ምን ማለት ነው?››
እኔም እንደዛ ሆኜለሁ…እንደሴቷ ሳይሆን እንደወንዱ…ቃልን አገኛለሁ ብዬ በክንዱ እቅፍ ውስጥ ለአንድ ቀን እንኳን ለመግባትን በፍቅር ትንፋሹን ለመማግ ቋምጬ አንገቴን ከሌላው ሰውነቴ ቀንጥሼ ጥያለሁ..ግን የሚገርመው እንደ ፌንጣው እንኳን የአንድ ቅፅበት እድል አላገኘሁም…ከእነ ፍቅር አምሮቴ ሕይወቴ አከተመላት…ይህ ከበደል ሁሉ የከረፋ በደል ነው፡፡ይቅርታ ማያሰጥ  ሀጥያት  ነው  የፈፀመብኝ››
‹‹ተይ ተይ ከእግዚያብሄር ጋር ለምን ታላትሚዋለሽ..››አለቻት ለቃል በመቆርቆር
‹‹እና ከሰይጣን ጋር ላድርገው..የሄደው እግዚያብሄርን ብሎ አይደል…?ታዲያ እግዚያብሄር ከእኔ ጋር የጀመረውን ጉዳይ አያውቅም ..እሱን ለማግኘት በመቋመጥ አንገቴን ከአከላቴ ቀንጥሼ መጣሌን አላየም..ተው    ግዴለህም እዛው ቆይላት አይለውም ነበር፡፡››

ይቀጥላል
👍102😢36😁95👎3🥰3
​​#ተአምረተ_ኬድሮነ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

ቀጥታ  ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን  ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ  ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን  እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን  በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ  የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት  በሀገሩ ህግ  መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና  እያመነ ሲሄድ  አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ  የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡

ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ  በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡

እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና  የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር  ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን  ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ   ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን  በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ  ተስማምታ  የታማሚውን  ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና  ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን  መኪና ገዝታ  ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን  ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና  ድምቀት  በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ  እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ  አቅዳና   ተከፍሏት ግድያ  ፈፅማ ይቅርና  እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር  ይሆን እንዴ….….?›› 
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ  ስቃዮ  ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት  በሽተኛ  ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

ይቀጥላል
👍88👎96👏4😁1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከ8 ሰዓት እራስን የመሳት ሂደት በኃላ ዶ/ር ሶፊያ ስትነቃ ከአንደበቷ ሾልኮ የወጣው የመጀመሪ ቃል <<ትንግርት››የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ አጠገቧ የነበረው ታዲዬስ ነበር፡፡ ግንባሯ በቀኝ በኩል በከፊል በፋሻ ተሸፍኗል፡፡ እንደምንም ተረጋግታ ያለችበትን ሁኔታ አጣራችና በደከመ ድምፅ << ታዲ >> ብላ ተጣራች ፡፡

‹‹አቤት…ምን ፈለግሽ?››

‹‹ትን..ግር ትስ?››

‹‹ሰላም ነች..አንቺ እራስሽን አረጋጊ፡።››

‹‹ንገረኝ ..የት ነው ያለችው..?ጥራልኝ በናትህ..ላገኛት እፈልጋለው፡፡››

‹‹አሁን እኮ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው..ነገ ታገኚያታለሽ››

‹‹አሁን ነው የምፈልጋት.. ታዲ በፈጠረህ ደውልላት፡፡››

‹‹ሞባይል ቁጥሯ የለኝም፡፡››

‹‹እኔ ሞባይል ውስጥ አለ፡፡››

ሊነግራት ባይፈልግም ስላስጨነቀችው ምንም ማድረግ አልቻለም ‹‹ታስራለች፡፡››አላት ፡፡

‹‹ወይኔ በጌታ ..!!!ማን አሰራ..ት?››አለች... ከተኛችበት ለመነሳት ብትጣጣርም ተራራ በጭንቅላተቷ የተሸከመች ይመስል የገዛ ራሷን ማነቃነቅ እንኳን አልተቻላትም፡፡

‹‹ህግ ነዋ ያሰራት...ልትገልሽ ሁሉ ትችል ነበር.::>>

‹‹ብትገድለኝም ይገባኛል..በፍፅም መታሰር የለባትም፡፡››

‹‹እሱ ያንቺ ፍላጎት ሊሆን ይችላል…ህግ ደግሞ እንደዛ አይልም፡፡››

‹‹ወይኔ ታዲ..አሁን ምን ይሻለናል?››

‹‹ስለምኑ?››

‹‹እንድትታሰር አልፈልግም፡፡››አለችው ደግማ፡፡

‹‹እንግዲ ሲነጋ የሚሆነውን እናያላን..ክስ ልትመሰርቺባት ካልፈለግሽ ምን አልባት በሽምግልና እንጨርሳለን ብለን ልናስፈታት እንችል ይሆናል፤አሁን ግን አንቺ ገና አላገገምሽም አረፍ በይ ፡፡››

‹‹ታዲ ...አንተ ግን ለምን ወደ ቤት ሳትሄድ…? ልጆችህስ?››

‹‹እንዲህ ሆነሽ እንዴት ጥዬሽ እሄዳለሁ…? ለልጆቹም ደውዬ ነግሬያቸዋለው፤ በጣም ነው ያዘኑት ፡፡ቶሎ እንድታገግሚ መልካም ምኞታቸው እንዳደርስላቸው ጠይቀውኛል፡፡ በገዛ እንግዳ እንዲህ በመሆንሽ አዝናለሁ፡፡››

‹‹ፍፅም ማዘን የለብህም...ይሄ የማንም ስህተት አይደለም፤ ለማንኛውም አብረኸኝ
ስለሆንክ ደስ ብሎኛል... አመሰግናለሁ፡፡››አለችውና አይኖቿን በድካም ከደነቻቸው.... እሱም የጀመረውን መጽሀፍ ማንበቡን ቀጠለ፡፡

ከለሊቱ 11 ሰአት ላይ ፎዚያ ተነስታ እየለባበሰች ሳለ ከውጭ የመኪና ጡሩንባ ጩኸት ሰማች... በጣም ነው የደነገጠችው፡፡ ‹‹በዚህን ሰዓት ማን ነው የመጠው..?››ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠባት፡፡‹‹የምን መርዶ ይዘውብኝ መጡ...?::>>

የመኝታ ቤቷን መስኮት ከፍታ ወደውጩ ስታማትር ዘበኛው የውጩን በር እየከፈተ ነበር፡፡ከዛ መኪናዋ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች .. የሰሎሞን መኪና ነች፡፡ሮጣ ወደ ውጭ ወጣች፡፡እሱ ሞተሩን አጥፍቶ ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እሷ ስሩ ደርሳ ‹‹ምን ተፈጠረ…? ምን ሆንክ..?ኤዲስ ደህና ነች…?››

‹‹አረ ተረጋጊ .…ሁሉም ሰላም ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ምነው በዚህን ሰዓት?››

‹‹አብሬሽ ሀዋሳ ልሄድ ነው፡፡››

«ለምን?»

‹‹ለሽርሽር፡፡››አሾፈባት፡፡

‹‹ማለቴ ማን ነገረህ?››

‹‹አንቺ ብትደብቂኝም ሁሴን ደወለልኝ..ይገርማል ሀገር ውስጥ የተሰራ ታሪክ በአሜሪካ ዞሮ ስሰማው››

‹‹እኔ እኮ ኤደን አሟታል ስትለኝ ላስጨንቅህ ስላልፈለኩ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም መስማት ነበረብኝ..አሁን በይ ተዘጋጂና እንሂድ፡፡››

‹‹እሺ ጨርሻለሁ ...አምስት ደቂቃ ብቻ፡፡››አለችውና ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች፡፡

ዝዋይ ሲደርሱ ከጥዋቱ 1፡4ዐ ነበር፡፡‹‹ቁርስ እንሞክር እንዴ?››አላት ሰሎሞን፡፡

‹‹ኧረ ገና ጥዋት ነው… እንቀጥል፡፡›› አለችው..ተስማማና ነዳው፡፡

‹‹ግን ኤደን ታማ እያለ ጥለሀት ስትመጣ አልከፋትም?›› ጠየቀችው... ፎዚያ ፡፡

‹‹ከፍቷታል... ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ሁሴን ሂድና እያት ብሎኝ ምክንያት ፈጥሬ እምቢ ልለው አልችልም፡፡ በዛ ላይ እኔ ኖርኩም አልኖርኩም ለውጥ የለውም፤ቤተሰቦቿ ዙሪያዋን ከበዋታል፡፡››

‹‹ቢሆንም.... ቤተሰብ ሌላ ባለቤት ሌላ፡፡››

‹‹ጉረኛ ...ስለባል ደግሞ ምን ታውቂያለሽ?››

‹‹ለምን አላውቅም፤ ስለባለትዳሮች ለማወቅ እኮ የግድ ባለትዳር መሆን የለብኝም፡፡››

‹‹መስሎሻል.. እኛም ሁለት ጊዜ ያገባነው እንኳን አሁንም ስለትዳር ምንም አልገባንም፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ባክሽ ሴቶችን ማወቅ በጣም ነው እየከበደኝ ያለው፡፡››

‹‹ይህቺ ነገር..!!!!ምነው ከኤደን ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ?››

‹‹እኔ እንጃ ባክሽ.. ከባለፉት ሁለት ወራቶች ወዲህ ንጭንጯን ልቋቋመው እየከበደኝ ነው....?»

‹‹መነሻውን አታውቅም? >>

‹‹ውሀ ቀጠነ ነው…ግን ቅዳሜ እና ዕሁድን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ ከጀመርኩ ወዲህ ይመስለኛል ነገሩ የጀመረው፡፡››

‹‹ከልጆቼ ጋር ስትል..ወደ ድሮ ሚስትህ እየሄድክ ማለት ነው?››

‹‹ኖ..ኖ ቅዳሜ እኔ ጋር ይመጣሉ. አብረውኝ አድረው እሁድ ማታ እመልሳቸዋለሁ.. ከእናታቸው ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም፡፡››

‹‹ታዲያ እሷን ምኑ ነው የደበራት?››

‹‹እኔም ያልገባኝ እሱ ነው፡፡እንግዲህ መጀመሪያም ልጆች እንዳሉኝ እያወቀች ነው ያገባችኝ...ከሚስቴ ተፋተው እንጂ ከልጆቼ አልተፋታውም፤ ምኑ ቅር እያሰኛት አንደሆነ አልገባኝም፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ...ልጆቹን መተው የሚያሳልፉት አብረዋችሁ ቤት አይደል..?››

‹‹በፊት ነበር…በኃላ ግን ቅዳሜና እሁድን መጥተው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ ቅር እያላት ፊቷን እያጠቆረችባቸው ስታሳቅቃቸው ..ነገርኳትና ውጭ ማለቴ ሶደሬ ፤ላንጋኖ ካልተቻለም ደግሞ እዛው አዲስ አበባ ሆቴል አብሬያቸው ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡

በነገራችን ላይ በሳምንት ሁለቱን ቀን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ እንዳለብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳሰበኝ ሁሴን ነው ፤ ከመሄዱ በፊት ሊሰናታቸው ቤት ሄዶ በናፍቆት በጣም ተጎድተውና ተሳቀው ስላገኛቸው እኔም ኤደንም ባለንበት ሁኔታውን በማስረዳት አሳምኖን ሄደ፡፡እኔም ሁኔታውን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ነበር የፀፀተኝ ‹‹እንዴት ልጆቼን ችላ ልል እንደቻልኩ ድንቅ ነበር ያለኝ….በአጠቃላይ ሁኔታው ሁሉ እንደዛ ነው እልሻለው፡፡››

‹‹አይ ቢሆንም ተነጋገሩበት…እሷም ነገሩን መቀበል መቻል አለባት፡፡ ቅሬታም ካላት በግልፅ ትንገርህና መፍትሄ ፈልጉለት፡፡››

‹‹እስቲ እሞክራለሁ....ምን አልባት የራሷን ልጅ ስትወልድ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ስለሚገባት ያን ጊዜ ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››

‹‹እንድትረዳህ እመኝልሀለው...ካለበለዚያ ስታገባ ሰትትፈታ መኖርህ ነው፡፡››ብላ አሾፈችበት፡፡

‹‹እጣ ክፍሌ ከሆነ ምን አደርጋለሁ፡፡››

3 ሰዓት ሀዋሳ ደረሱ፡፡ኤልያስ ሲጠብቃቸው ስለነበረ ወዲያው ወደ ትንግርት ይዞቸው ሄደ፡፡

‹‹ተራማጆቹ ፀሀፊዎች በፖለቲካ በሚታሰሩበት ዘመን አንቺ በፈንካችነት ትቀላቀያቸዋለሽ..? ምነው ምነው?››አላት ሰሎሞን ገና ከፖሊሶቹ ፍቃድ አግኝተው ፊት ለፊት እንደተገናኙ፡፡

‹‹ምን ይደረግ ....ይህቺ ሀገር ፀሀፊ ሳይሆን ጀግና ነው ያጣችው ብዬ ነዋ!!››ብላ መለሰችለት፡፡

የሚነጋገሩት ፖሊሶቹ ጆሮ ይደርሳል... አይደርስም የሚለውን ለማጣራት ግራ ቀኙን ተገለማመጠ

‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡

‹‹ልጄ ለምን አልፈራ..በስህተት እንኳን አንድ ቀን እስር ቤት ባድር ፈንድቼ የምሞት ነው የሚመስለኝ፡፡››

‹‹ለመሆኑ እንዴት ነሽ…?ምን አሉሽ?›› አለቻት ፎዚያ በጭንቀትና በሀዘኔታ፡፡
👍819😁4
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው።

‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ  እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ
"እውነቴን እኮ ነው"

""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።››

"ምንድነው ስራው?"

"ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ      ወንድሜም      እርግጠኛ      ነኝ      ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።››

"በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡"

"ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች።
ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡

ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል  "

‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም"

"ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?"

"እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ  ብር  እናገኛለን፡፡  ከዛ   አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡››

"መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር።

"የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።››

"እሱን  ገና  አልወሰንኩም...ይሄን  አይነት  ሀሳብ   እራሱ   ወደ   አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።"

"አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?"

"የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት   የህይወት   አላማ   የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ
እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።"

‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...››

‹‹ጠይቂኝ".

‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..."

የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?››

‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…››

‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?››

‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?"

የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን  ..?ደሴ? ምን ለመስራት?"

"ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት  መንገድ  መሄድ  የለብህም..እነሱ  በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ  የሆኑ  ሰዎች  ናቸው።እንዳልከው  እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ  ብቻ አይመስለኝም?"

በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?"

"ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…"

"ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?"

"አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን  አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።"

‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.."

‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ  ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ…  ይሄ  ጓደኛዬ  ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ  ቅንጣት  ሴሎች  ነን፡፡ከመወለዳችን  በፊት  የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን  ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ  ነው  ያለን…  ቦታችን  እንቅስቃሴ  ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…››
‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት   በእግዚያብሄር   ዘንድ   ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ››
‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ"

‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?"
"እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ"

"ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት  አደጋ  ደርሷባቸው  አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት  ደረጃ  ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና  ተሰናብተዋት  ይሄዳሉ። እርግጥ  ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር  የሚሆኑ  ሰዎችን  ነው  የያዘችው..እኔ  አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች  እግዚያብሄር  ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ
አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡››

‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ  መገናኘታችን  እንዲሁ  በዘፈቀደ  የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡››

‹‹አልገባኝም››
👍1067👎1😁1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ቤቱ ቅልጥ ያለ ድግስ ላይ ነው፡፡ግቢ ውስጥ ግዙፍና ዘመናዊ ድንኳን ተደኩኖ በዲኮር አሸብርቋል፡፡በዝግጅቱ የሰሎሜ ፤ የእቴቴ የአላዛር እና የአለማየሁ አንድም ወዳጅና የስራ ባለደረቦች አልቀረም…ከ500 በላይ ሰው ነው የተጠራው፡፡እርግጥ ይሄ ድግስ እንዲደገስ ቀጠሮ የተያዘለት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን ከሰማች ከሳምንት በኃላ ነበር፡፡ግን ባልተጠበቀ ፕሮግራም ዜናው ከተሳማ ከሦስት ቀን በኃላ አለማየው ለአጭር ጊዜ ስለልጠና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪት እንዲሄድ በመስሪያ ቤቱ ስለታዘዘ ድግሱ በሁለት ወር እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

ይሄ ድግስ በዋናነት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን በማወቋ እና ዘመናት ለማወቅ ስታልመው የነበረው የአባቷን ማንነት በማወቋ የተፈጠረባትን ፈንጠዝያ ለማክበር ነበር..ሌላው ለህይወቷ በጣም አስጊ የሆነውን በሽታ ታክማ መዳን በመቻሏም ለተንከባከቧት ሰዎች ሆነ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ለሌላው ሶስተኛ ነገር ደግሞ ትዳር በያዘችባቸው ሶስት አመቷ ውስጥ ስትሰቃይበት የነበረችው ከአላዛር ላይ ተከስቶ የነበረው ስንፈተ ወሲብ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ  ልክ እንደአዲስ ሙሽራ ቀንና ለሊት ሳይለዩ በፊት ያበከኑትን ጊዜ ማካካስ በሚመስል መልኩ እልካቸውን እየተወጡበት ስለሆነ በዛ ጉዳይ የተፈጠረባቸውን ደስታ በይፋ ለማክበር ነው፡፡ያም መሆኑ ለሁለቱም ከፍተኛ ደስታና አዲስ የህይወት እርካታ አጎናፅፏቸዋል፡፡ከሁለቱም ልብ እየተበተነ ያለ ደስታ በዙሪያቸው ያለውን ሰው ላይ ሁሉ የሚጋባ አይነት ሆኗል፡፡ይሄም ድግሱ ደማቅና ሰፊ እንዲሆን አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ድግሱ ለሁለት ወር በመራዘሙ ምክንያት ሌላም ሊከበር የሚገባው ተደራራቢ ምክንያትና በረከት ተፈጥሮል፡፡

ድግሱ ላይ የታደሙት 500  ያህል የቅርብ ሰዎች ምሳ ከበሉ በኃላ ሰሎሜ የተፍለቀለቀ ፊቷን በፈገግታ አጅባ ወደመድረኩ ወጣች፡፡

ማይኩን ድግሱን በሙዚቃ እያደመቀ ካለው ዲጄ  ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹ወዳጆቼ ዘመዶቼ ይሄ ድግስን አስመልክቶ ጥቂት ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡››ስትል ሁሉም የምትለውን ነገር ለመስማት የእርስ በርስ ወሬያቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ወደእሷ አዞሩ….ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ..እናቴ እቴቴ ..ባለቤቴ አላዛር….ወንድሜ አለማየሁ….ጓደኛዬ ሁሴን ..ሁላችሁም ወደዚህ መድረክ ኑና ከጎኔ ያለው የፊት ፊት መቀመጫ ላይ እንድትቀመጡ እፈልጋለው፡፡የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡

ሁሉም እየተያያዙ መጡና ፊታቸውን ወደእድምተኞች አዙረው መድረክ ላይ በተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተቀመጡ፡፡

ሰሎሜ ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንግዲህ እነዚህ አራት ሰዎች ወደእዚህ ምድር ከመጣሁበት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ከጎኔ ነበሩ…ሰሎሜ ሰሎሜ እንድትሆን ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡እኔ ማለት የእነሱ ውጤት ነኝ፡፡እናቴ እቴቴ … ከልጅነቴ ጀምሮ ያለአባት  በጀግንነት አሳድጋኛለች፡፡ላደረግሺልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡በጣም ነው የምወድሽ፡፡
በህይወቴ ሁለት ጊዜ በከባድ በሽታ ሆስፒታል ገብቻለሁ፡፡ልጅ ሆኜ በታመምኩ ጊዜ ለህክምናው 70 ሺ ብር ተጠይቆ ነበር፡፡በወቅቱ እናቴ የነበራት ከ7ሺ ብር የማይበልጥ ብር ነበር፡፡ቀሪውን ብር በትምህርት ቤትና በየመንደሩ እየዞሩ ለምነው ያሳከሙኝ..እንዚህ ከፊት ለፊት ተቀምጠው የምታዬቸው የልጅነት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ከሶስት ወር በፊትም ተመሳሳይ አይነት ፈታኝ ህመም አሞኝ ነበር፡፡ ከአካሉ አካል ቆርሶ በመስጠት ደግመኛ ዛሬን እንደዚህ ከፊት ለፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ወንድሜ አለማየሁ ነው፡፡ይሄም ዝግጅት እንዲጋጅ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ‹‹ወንድሜም ስለሆንክ…ከህመሜም እንድፈወስ ስላደረከኝ››አመሰግናለው ለማለት ነው፡፡

ሌላው የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ  ሁሴን በሁለቱም የህይወቴ ጨለማ ቀናቶች ከጎኔ ስለነበርክ አንተንም በጣም አመስገናለሁ፡፡በጣም እንደምትወደኝ አውቃለው….እኔም በጣም እወድሀለው….እናም ከሶስት ቀን በኃላ ተመልሰህ ወደውጭ እንደምትሄድ ስለማውቅ ዳግመኛ ሙሉ ጓዝህን ጠቅልለህ ወደሀገር እስክትመለስ እና አብረሀን መኖር አስክትጀምር ድረስ  ይሄ እንደሽኝት ፕሮግራም እንዲታይልኝ እፈልጋለው፡፡
ከፍተኛ የሞቀ ጭብጨባ ተከተላት…ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ሌላው የእድሜ ልክ ጓደኛዬ እና አንድም አመት ቢሆን ከስሬ ተለይቶኝ የማያውቀው መከራዬንም ሆነ ደስታዬን አብሮኝ ያሳለፈው የምወደው ባለቤቴ  አላዛር  ..ስለተንከባከብከኝ. .ለአስቸጋሪው ፀባዬ ጠቅላላ ትዕግስት አድርገህ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ እስከአሁን አብሬህ እንድኖር ሚስትህ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግናለው..ለዚህም ድንቅ አበርክቶትህ ከእኔ ከሚስትህ በዚህ ሁሉ ወዳጅ ዘመድ ፊት አንድ ስጦታ ላበረክትልህ እፈልጋለው፡፡››አለችና ንግግሯን ገታ አደረገች…አላዛር ግራ ተጋባ..ሌሎችም የሽልማቱን ምንነት ለማወቅ ጉጉት አሳዩ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ ወደእኔ ና››ስትል ጠየቀችው፡፡

ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ….በእጆ የያዘችውን ፖስታ አቀበለችው፡፡ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቷት ዝም ብሎ እያገላበጠ ያየው ጀመር፡፡

ሁሴን እና አለማየሁ‹‹ይከፈት ይከፈት››አሉ..ሌሎችም እድምተኞች ተከተሏቸው፡፡አላዛር ምርጫ ስላሌለው በቀስታ ፖስታውን ሸረከተው፡፡አንድ ነጠላ ወረቀት ነው ውስጡ ያለው፡፡ አወጣውና  ተመለከተው ፡፡ ምንም አልገባውም‹‹ምንድነው ፍቅር?››ሲል እሷኑ መልሶ ጠየቃት፡፡

‹‹አንብበዋ››አለችው፡፡

‹‹እንድምንም ትክረቱን ሰብስቦ ማንበብ ጀመረ…አይኑ ፈጠጠ…‹‹ምንድነው ፍቅር..? የማየው ነገር እውነት ነው…?››ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡ተንደረደረና ተጠጋት፡፡ዝቅ ብሎ ጉልበቷ አካባቢ በእጆቹ ያዛትና ወደላይ አንስቶ አሽከረከራት፡፡ሰው ሁሉ ሽልማቱ ምን ቢሆን ነው በሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ መወዛገብን ቀጠለ፡፡እንደምንም እንዲያወርዳት ካደረገች በኃላ ጠረጴዛ ላይ ያለውን  ማይክሮፎኑን ወደአፈዋ አስጠጋችና ‹አዎ እውነት ነው..ውድ ባለቤቴ ሽልማትህ ልጅ ነው..እኔ ሚስትህ የሁለት ወር እርጉዝ ነኝ፡፡››በማለት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ታዳሚው የምስራቹን አበሰረች፡፡መጀመሪያ እልልታዋን ያቀለጠችው እናቷ እቴቴ ነች….ከዛ ሙሉ ዱንኳኑ በእልልታና በጭብጨባ ተደበላለቀ፡፡.አለማየሁም ሆነ ሁሴን ከመጠን በላይ ተደሰቱና ተንደርድረው ባልና ሙስቶቹ ላይ ተጠመጠሙባቸው፡፡ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ልዩ አይነት ዝግጅት ሆኖ አለፈ…፡፡

እንግዶቹ ከተሸኙ በኋላ ቤተሰቡ ድግሱንና ፈንጠዝያውን ቀጠሉበት፡፡ሁሴን ወደመጣበት እንግሊዝ ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ ከዛ ቤት የሄደ ሰው አልነበረም፡፡.እቴቴ ለአመታት ቃል በገባችው መሰረት ብቸኛ ልጆን በእርግዝና ወቅቷ ለመንከባከብና ከወለደችም በኃላ የልጅ ልጆን ለማሳደግ ስትል የራሷን ቤት ዘግታ ሙሉ በሙሉ ባልና ሚስቱ ጋር ተጠቃላ ገባች፡፡አለማሁም ከእንግዳ ክፍሎቹ ውስጥ አንዱ ክፍል ተመርጧ የእሱ ቆሚ ክፍል ሆኖ እንዲደራጅ ተደረገና ቢያንስ በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን እየመጣ እነሱ ጋር ማደር ጀመረ፡፡እሱ እንቢ ብሎ እንጂ እነሱማ ቢያንስ የራስህን ሴት አግኝተህ ሚስት እስክታገባ ሙሉ በሙሉ የተከራየኸውን ቤት ልቀቅና  እዚሁ እኛ ጋር ተጠቃለህ ግባ ና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንኑር ብለውት ነበር፡፡እሱ ግን ሙሉ በሙሉ በሚለው ሊስማማ አልቻለም፡፡በአጠቃላይ እንደዛ የጭቅጭቅ መናኸሪያ ሆኖ ቀዝቅዞ የነበረው ቤት አሁን ደምቆና በቤተሰብ
👍7513👏4🥰3👎1😱1