አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#ክፍል_ሶስት

#ትንሣኤ
በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት የምርኮኞች ልውውጥ የሚጀመርበት የመጀመሪያው ምዕራፍ......
የድሬዳዋ ከተማ አሸብርቃለች፡፡ ገንደቆሬ፣ ገንደገራዳ፣ መጋላ፣ ከዚራ፣ ለገሀሬ፣ ..... መንደሮች በሙሉ በደስታ ስቀዋል፡፡
በየመንገዱ ግራና ቀኝ ተተክለው ቀዝቃዛና፤ ነፋሻማ አየርን የሚረጩት ዛፎች በደስታ ተውጠው የሚደንሱ ይመስላሉ፡፡ በዚያች ምድር ላይ የተካሄደው ቀውጢ ጦርነት አልፎ፤ ያንን የመሰለ የሰላም አየር መተንፈስ መቻል ዳግማዊ ልደት ነው፡፡
በሐረርጌ ምድር፡፡ በደገሀቡር፣ ቀብሪደሀር፣ መራራሌ፣ በሺላቦ፣
ደቦይን፣ በቆራሄ አሸዋማ ሜዳ፣ በኦጋዴን በረሃ፣ በካራማራ ተራሮችና በሌሎችም ሺህ ሌሊት ሺህ መአልት የፈሰሰው ደም፣ የተከሰከሰው አጥንት፣ያስገኘው ውጤት፡፡
በዚያን ቀውጢ ሰዓት ላይ ለዳር ድንበር ሲሉ ከጠላት ጋር እየተናነቁ አኩሪ ገድል የፈጸሙት፤ በደማቸው ማህተም፤ በአጥንታቸው ክስካሽ፤ ምድሪቱን ያቀሉት...የመስዋዕትነት ፈርጦች! የሚጠበቁበት ዕለት......

ሰማዩ በዚያን ቀውጢ የጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ አየር ሃይል የተሠራውን አስደናቂ ትርኢትና ተአምር አፍ አውጥቶ ሊናገር፣ የታሪክ ምስክርነቱን ሊሰጥ፣ የተዘጋጀ ይመስል አጉረመረመ፡፡ ለሚወዷት እናት አገራቸው ዳር ድንበር ሲሉ የተፋለሙና ልዩ ልዩ ጀብድ ከፈጸሙ በኋላ በጠላት እጅ ወድቀው በባእድ ሀገር በምርኮኝነትና፤ በእስረኝነት ለበርካታ
አመታት ከቆዩ በኋላ በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ዛሬ ወደሚያፈቅሯትና፤ ወደሚወዷት፤ እናት አገራቸው የሚመለሱበት እለት ስለሆነ፤ እነዚህን ውድ የሀገር አለኝታዎችና፤ ጀግኖች፤በልዩና፤ በደማቅ አቀባበል ፤ ሊቀበል ህዝቡ የአውሮፕላን
ማረፊያውን አካባቢ አጥለቅልቆታል....
ማርሽ የሚያሰማው ሠራዊት በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠባበቃል።ባንዲራዎች ይውለበለባሉ፡፡ ህዝቡ ይሯሯጣል፡፡ ይራወጣል። ሰማይ ሰማዩን እያንጋጠጠ ይመለከታል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ትላልቅ አሞራዎች ያሳስታሉ፡፡ የሁሉም ልብ ተንጠልጥሏል፡፡ እነማን ይሆኑ?! ሞቱ ተብለው ደረት
የተመታላቸው፣ ተዝካር የተበላላቸው፣ ማን ያውቃል? በህይወት ሊገኙ
ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ጦርነት በተካሄደባቸው ብዙ አገሮች በተደጋጋሚ
የታየ ክስተት ነው፡፡
ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ሰማዩ እንደገና በከፍተኛ ድምፅ አጉረመረመ፡፡አውሮፕላኗ በርቀት ታየች፡፡ ከዚያም እየጐላች ፤እየጐላች፤ መጣችና፤በማረፊያው ላይ እየዞረች፤ ማንዣባብ ጀመረች።
የሰው ጩኸት ሁካታ... ግርግር... ትርምሱ...ሌላ ሆኗል፡፡ማርሽ በረጅሙ ይሰማል፡፡ አውሮፕላኗ አዘቀዘቀች..... ከዚያም አኮበኮበችና አረፈች፡፡
ጀግኖች የታደሙባት አውሮፕላን! ለዳር ድንበሯ ሱሉ ደማቸውን ያፈሰሱላትን፣ በእስር የማቀቁላትን፣ ጥለው የወደቁላትን፣ ታስረው የተገረፉላትን፣ የጦር ምርኮኞችን ይዛ ይሄውና አውሮፕላኗ መሬት ላይ አረፈች....
የአውሮፕላኗ በር ተከፍቶ አንድ ረጅም፧ ቀጭን፤ መነጽር ያደረገና በአየር ኃይሉ ውስጥ በጦር ጄት የጠላትን ሃይል ድባቅ
በመምታት በደማቅ ቀለም ታሪክ ያስመዘገበ ምርኮኛ ብቅ አለ፡፡ማርሹ ይሰማል፡፡ እልልታው ቀለጠ!! ግማሹ በሲቃ ያለቅሳል፣ይፈነድቃል፡፡ ምርኮኞቹን ለማየት ሰው በሰው ላይ ይንጠላጠላል፣
ትዕይንቱ ብዙ ነው፡፡ ከዚያም የተዘጋጀውን እቅፍ አበባ ምርኮኛው ተቀበለ፡፡
ምርኮኞቹ ከአውሮፕላኗ እንደወረዱ መሬቷን ይስማሉ። አፈሯን ይልሳሉ፡፡ ያለቅሳሉ፣ ይንከባለላሉ፡፡ የደስታ እንባ... የናፍቆት እንባ... የትዝታ እንባ...
ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ከአገር፤ ከወገን፣ ከቤተሰብ ጋር ተለያይተው ፤ የብቸኝነትንና የመከራ ኑሮን ሲገፉ ከቆዩ በኋላ፤የሚወዱትንና፤ የሚያፈቅሩትን፤ ህዝብና አገር መቀላቀል ዳግም መወለድ
ነውና፤ ምርኮኞች ዳግም የተወለዱ ያህል በደስታ ሰከሩ። እንደዚያ ዳር ድንበርዋን ሊያስከብሩላት፤ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው፡ ሳንጃ ለሳንጃ ተሞዣልቀው፡ ጥለው የወደቁላት፡ የውድ ሀገራቸውን ለም አፈር ለማሽተት በመቻላቸው በደስታ የሚሆኑትን አጡ ...ህዝቡም በእልልታና በሆታ የጀግና አቀባበል አደረገላቸው፡፡ ደስ የሚል ከህሊና የማይጠፋ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት......
ለተወሰኑ ቀናቶች በድሬዳዋ ከተማ እረፍት አድርገው ከቆዩና መንፈሳቸው ከተረጋጋ በኋላ፣ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሊቀላቀሉ የቸኮሉት ቀድመው ተንቀሳቀሱ፡፡


እለተ ቅዳሜ! አዲስ አበባ!! የኢትዮጵያ ዋና ከተማ! ቀዝቃዛ ንፋስ ይነፍስባታል ። በተለይ የባህር ማዶው ዛፍ ለቅዝቃዜው የራሱን ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል፡፡
ባቡሩ መንገደኞቹን ጣቢያው አራገፈ፡፡ ግፊያው ለጉድ ነው፡፡ግማሹ ሲመጣ ግማሹ ሲሄድ... የገቢና ወጪ መንገደኞች ምልልስ የማያቋርጥበት አምባ......
ጊዜው ለዐይን ያዝ ማድረግ የጀመረበት ሰዓት ነው፡፡
አንድ ቁመቱ ረዘም ያለ፣ ሰውነቱ በበረሃ ግርፋትና በእስር ስቃይ ምክንያት የተለበለበ ግንድ ቢመስልም፤ በሰላሙ ጊዜ ማራኪ መልክና ቁመና እንደነበረው አሁንም በግልጽ የሚታየው ትክለ ሰውነቱ
ዐቢይ ምስክርነቱን የሚሰጥለት፤ ከሲታ ሰው ከባቡሩ ወረደ፡፡
ደረቱ ሰፋ ያለ፣ ፀጉረ ዞማና ዐይኖቹ ጐላ ጐላ ብለው የሚታዩ ረጅም ሰው ነው፡፡ ሻንጣ አንጠልጥሏል፡፡ ከተሰጠው የኪስ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ያዋለው ለሁለት ሴቶችና፤ ለአንድ ወንድ የሚሆኑ ልብሶችን በመግዛት ነው፡፡ ከባቡሩ ወርዶ፤ በአምባሳደር ቲያትር በኩል መጥቶ ፤ ወደ ኦርማ ጋራዥ አቀና፡፡ የሚራመደው በደመነፍስ ዐይነት ነው፡፡
በህልም ዓለም የሚራመድ ይመስላል፡፡
እሱ እራሱ የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን ተጠራጥሯል።ግራና ቀኙን በዓይኑ ያማትራል፡፡ ሰዎችን ይቃኛል፡፡ ምናልባት የማውቀው ሰው ካገኘሁ በሚል ግምት ነው፡፡ ግን ማንም የሚያውቀው ሰው አላገኘም፡፡ ድሮ የሚያውቁት ሲያዩት እንኳን፤ በቀላሉ ሊለዩት አይችሉም፡፡ ተለውጧል፡፡ ተጉሳቁሏል፡፡
መንገዶቹ የጠበቡ፣ ቤቶቹም ከምዕተ ዓመት በፊት የነበሩ መስለው ታዩት፡፡ በየመንገዱ ላይ ከሚያያቸው ሰዎች ውስጥ ሶስት ሰዎችን ለማግኘት በናፍቆትና በጉጉት ደጋግሞ ይቃኛል፡፡
የሱ ብርቅዬ፤ ድንቅዬዎች፡፡ ልዩ የህይወቱ ቅመሞች፡፡ የተዳፈነ የናፍቆቱ እምቅ ሊፈነዳ ተቃረበ፡፡ ልቡ ተሸበረ... እየተቃረበ ሲመጣ ልቡ ድው ድው የሚል ድምጽ ሰጠ፡፡ ትንፋሽ አጠረው፡፡
እጅግ አስገራሚ ነው! አስደናቂ
የማይጠበቀው ሰው ፤ እንደዚህ ባልተጠበቀ ሰዓት ከች! ሲል፤ እነሱ
ከአንጀቱ የሚያፈቅራቸው፣ የሚወዳቸው፣ የሚሞትላቸው ቤተሰቦቹ እንዴት ሆነው ይሆን? የሚወዳት ሚስቱ፣ የሚወዳቸው ልጆቹ እንዴት ሆነው ይሆን? ሲለያቸው በነበራቸው ዕድሜ ላይ አስራ አንድ ዓመት ሲጨመርበት የትየለሌ ነው፡፡ ምን መስለው ይሆን?
አቤቱ ፈጣሪ ያንተ ተአምር እንዴት ተወርቶ ያልቅ ይሆን? አደራህን ሁሉንም ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን ዐይናቸውን አይቼው
እንድሞት እርዳኝ፡፡ አንተ ታውቃለህ፡፡
ወባ እንደያዘው ሰው እየተቃረበ መጣ፡፡ ቤቱ ጋ ሲደርስ ሰውነቱ ተንዘፈዘፈበት :: ልቡ በፍጥነት ይመታ ጀመር፡፡
ግቢው ...ያ ...ግቢ የሚወደው ግቢ...እዚያ ውስጥ ያሉት እነ.. መራመድ አልቻለም፡፡ ቆመ፡፡ እንደሀውልት ተገትሮ ቀረ፡፡ ከዚያም ለዘመናት በወስጡ ሲንተከተክ የነበረው እንባ በድንገት ገንፍሉ ወጣ፡፡
ከደስታ ብዛት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ቤቱን አየው፡፡ ልጆቹን አቅፎ የሳመበትን፣ ከሚያፈቅራት ባለቤቱ ጋር ደስታን ያሳለፈበትን፣ በመጨረሻም ወደ ጦርነት ሲሄድ ከቤተሰቦቹ ጋር ተላቅሶ
👍2🔥1