ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ መጽሀፍ ቅዱስ #የእስራኤል #ዜግነት ያላት #እስራኤላዊት#በገሊላ ናዝሬት ከተማ ትኖር የነበረች #አይሁዳዊት ወጣት ሴት እንደነበረች ይናገራል [ሉቃ 1፥26] እንዲሁም #ከዳዊት #የዘር #ግንድ የተገኘች መሆኗንም ይናገራል [ማቴ 1፥17 ፣ ኢሳ 11፥1 ፣ ሐዋ 13፥22]።

▶️ ዘመዷ #ኤልሳቤጥ ስትሆን ምን አይነት #ዝምድና እንደነበራቸው ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም [ሉቃ 1-36]። ስለማርያም #ቤተሰቦች #የእነማ ልጅ እንደሆነች፣ የትና መቼ #እንደተወለደች፣ የት #እንዳደገች #መጽሀፍ ቅዱስ አላማው ስላልሆነ የተወሰነ #ፍንጭ ከመስጠት በስተቀር ምንም #አይናገርም
#መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም #ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ #ካበሰራት ቡሀላ እንኳ " #ከመውለዷ ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር #ሰፋ ያለ መረጃ የለም።

▶️ እንደዛ ሆኖ ሳለ #መጽሀፍቅዱስ #ዝም ያለበትን ነገር #ዝም ማለት ሲገባቸው #የመጽሀፍቅዱስን አላማ ሳይገነዘቡ #ግምታዊ #ሃሳቦችን በመስጠት #የተጻፉና #በየአደባባዩ የሚሰበኩ መጽሀፍት #ጥቂቶች አይደሉም።
<< ድንግል ማርያም #ኢትዮጽያዊት ነች>> ብለው በድፍረት የጻፉም እንዳሉ ይታወቃል።
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28 (2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም) *ሱራህ 19, አያህ 27* فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ *ሱራህ 19, አያህ 28* يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ…
▶️ ሌሎች #በኦርቶዶክስ ያሉ #መጽሀፍቶች ደግሞ የተለያዩ #የዘር ግንድ ቆጠራዎችን ይጠቅሳሉ።
" #ድርሳነ #ጽዮን" የተባለው መጽሀፍ #የማርያም የዘር ሃረግን ሲገልጽ👇
ሜሊኪ። "የሐና(የእናቷ)
/ \ |
ሴም ሌዊ። ኤሊ
| |
ሆናሲን። ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን። ማቴን
| |
ኢያቄምን። ሐና
\ /
ማ ር ያ ም ን
ወለዱ ይላል[7]።

▶️ የማቲዎስ ወንጌል እንድምታ ደግሞ ከዚህ የተለየ ይገልጻል።
አኪም
|
ኤልዩድ
|
አልዓዛር
|
ቅዕራ
|
ኢያቄም ይላል[8]።

እንግዲህ እነዚህ #መጽሀፍት ደግሞ #በማርያም #አባት ቢስማሙም #በአያቶቻቸው ግን ፈጽሞ #አይስማሙም

▶️ የአንዳንድ ካቶሊካውያን አመለካከትም። << #ማርያም #ሰማያዊ #ፍጡር>> እንደሆነች ሲገልጹ ይህንንም ሀሳብ #የሰዓታት ጸሐፊና #የተአምረ #ማርያም ጸሐፊም በከፊል የሚቀበሉት ቢሆንም #ሃይማኖተ #አበው ግን በግልጽ ይህን ሃሳብ ያወግዘዋል። << እመቤታችን ከሰው የተለየች #ፍጥረት #ምድራዊት ያልሆነች ቀድሞ #በሰማይ #የነበረች #ሃይል(ፍጡር) ናት የሚል ቢኖር #ውግዝ ይሁን። በቅድስት መጽሀፍት እንደተጻፈው #ቅድስት ድንግል ማርያም #ከዳዊት#ከይሁዳ #ከአብርሃም ዘር እንደሆነች #በእውነት የሚያምን ግን #ከግዝት የተፈታ ይሁን>> ይላል[9]።

▶️ ማርያም ዘመዷ #ኤልሳቤጥ፣ እጮኛዋም #ዮሴፍ የነበረ ሴት እንደሆነች ሃገሯም #ናዝሬት #ገሊላ ሆኖ #ከዳዊት #ዘር እንደነበረች #መጽሀፍቅዱስ እየተናገረ #ሰማያዊ #ፍጡር #ናት ማለት " ህዝቤ #እውቀት #ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል/ሆሴ 4-6/። እንደሚለው #የእውቀት #ማጣት ይመስላል።
መጽሀፍቅዱስ የማርያም #አባት #ኢያቄም ሳይሆን < #ኤሊ> የተባለ #ሰው እንደነበር የሚገልጸው ፍንጭ አለ።
(በሉቃስ 3፥23)
ደግሞ #የማርያም #ገድሎች እንደሚሉት #ለእናት #ለአባቷ #አንዲት #ልጅ ሳትሆን #እህትም እንዳላት #መጽሀፍቅዱስ ይናገራል። 👇

<< ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ #የእናቱም #እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።>> {ዮሐ19፥25}።

<<ለዮሴፍ አባቱም #የማታን ልጅ #የያዕቆብ ልጅ (የማታን የልጅ ልጅ) ነው ብሎ #ማቲዎስ (በማቲ 1-16) #የዘር #ሐረጉን ሲቆጥር ወንጌላዊው #ሉቃስ ደግሞ #የማርያምን #የዘር ሃረግ ተከትሎ #በመቁጠር #የማርያም #አባቷ < #ኤሊ> እንደሆነ አስቀምጧል {ሉቃ 3-23}።

🔆 የዮሴፍ የዘር ሀረግ 🔆

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ........
............................................

6፤ " እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።"...............................
............................................

15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም #ማታንን ወለደ፤ ማታንም #ያዕቆብን ወለደ፤

16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ #ዮሴፍን ወለደ።
▶️ ኤልሳቤጥ በጸነሰች #በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል #ልጅ #የመውለድ #መልእክት ይዞ ወደ እሷ መጣ። በዚህ ጊዜ #መልእክቱ የመጣው #በገሊላ አውራጃ ከምትገኝ #በናዝሬት ከተማ ለምትኖርና ስሟ #ማርያም ለምትባል #ድንግል ልጃገረድ ነበር። #ማርያም #ከይሁዳ ነገድ #ከዳዊት ትውልድ የሆነች #አይሁዳዊት #ድንግል ነበረች (ኢሳ 7፥14)። #በናዝሬት ከተማ #በአናጺነት ሙያ ለሚተዳደር #ዮሴፍ ለተባለ #ሰው የታጨች ስትሆን (ማቴ 13፥55) ሁለቱም ድሆች ነበሩ (ሉቃ 2፥24 ፣ ዘሌ 12፥8)።

▶️ ከሉቃስ ወንጌል #ምዕራፍ 1፤ 26-33 #የቅዱስ ገብርኤልን #ሰላምታ በደንብ ስንመለከተው #ማርያም ለጊዜው #እንደፈራችና #ግራ እንደተጋባች ያስረዳል። <<ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው>> አላት። #መልአኩ #ሠላምታ ሊሥጣት የመጣው ለምንድን ነው?? #ጸጋ የሞላባትስ በምን #መንገድ ነው? #እግዚአብሔር #ከእሷ ጋር የሆነውስ #እንዴት ነው??..

▶️ የማርያም #ምላሽ #በእግዚአብሄር ፊት #ትሁትና #እውነተኛ እንደነበረ ያሳያል። ከቶውንም #ከመልአክ ጋር እንደምትነጋገርና #ከሰማይ ልዩ #ጸጋዎችን እንደምታገኝ አልጠበቀችም። #የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #የሉቃስ ወንጌል #አንድምታው እንደሚለው <<ማርያም #የኢሳያስን #ትንቢት የሆነውን ኢሳ 7፥14 ስታነብ ያቺን #ሴት ምነው እኔ #በሆንኩ አላለችም። እንደውም ምነው #ከጊዜዋ ደርሼ #ወጥቼ #ወርጄ አገልግያት በማለት #ታስብ እንደነበር ይገልጻል[1]። እንዲህ አይነት #ሁኔታዎች እንዲፈጸምላት የሚያደርግ #ምንም የተለየ ነገር አልነበራትም። አንዳንድ የስነ መለኮት #አስተማሪዎችም እንደሚናገሩት <<ማርያም #ከሌሎች አይሁዳውያን #ሴቶችና #ልጃገረዶች #የተለየች ብትሆን ኖሮ <<መልካም እንግዲህ #ጊዜው #ደርሷል! እስከአሁንም #ስጠብቀው ቆይቻለሁ! ትል ነበር። ነገር ግን #በፍጹም አላለችም[2]!!! ሁሉ ነገር ለእሷ #አዲስና #አስደናቂ #ዱብእዳ ስለነበረ ግራ #ተጋብታለች#ፈርታለች#ደንግጣለችም <<ይህ እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው?>> በማለትም አስባለች። #ቅዱስ ገብርኤልም #አትፍሪ በማለት #የማረጋጋት ተግባር ሲያከናውን ይታያል።

▶️ ከዚያም #መልአኩ ገብርኤል #መልካሙን #ዜና ያበሰራት #ኢየሱስን (አዳኝ፣ መድኃኒት) ማቲ 1፥21 ብላ የምትሰይመውን #መሲህ እንደምትወልድ ነበር። በመቀጠልም #መልአኩ የኢየሱስን #አምላክነትና #ሰብአዊነት አስረግጦ በመንገር #የምትወልደው #ልጅ ታላቅ እንደሆነና እንደሚሆን እንጂ በእርሷ ታላቅነት ላይ አላተኮረም {ሉቃ 1፥31}።

▶️ የሚወለደው ህጻን(ኢየሱስ) #ንጉስ ሆኖ #የዳዊትን #ዙፋን በመውረስ #ለዘላለም በእስራኤል ላይ #ይነግሳል#እግዚአብሔር #ከዳዊት ጋር የገባውን #ቃል #ኪዳን (2ኛሳሙ 7) እና ለእስራኤል #ህዝብ የሰጠውን #የመንግስት የተስፋ #ቃሎች #እያመለከተ ነበር {ኢሳ 9፤1-7፣ 11-12 ፣ 61 ፣ 66፣ ኤር 33}።