ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ተአምረ ማርያም እርግማን እንጂ በረከት የሌለው መጽሐፍ ብዙዎች ተአምረ ማርያም ቅዱስ መጽሐፍ እንደሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንደተጻፈ ይናገራሉ። እነርሱ እንደሚሉት ከሆነና የእግዚአብሔር እስትንፋስ ከሆነ እንደ ቅዱሱ መጽሐፍ ፍቅር ፍቅር የሚሸት፣ የእግዚአብሔር ምህረት የሚታይበት መጽሐፍ መሆን አለበት። ነገር ግን መጽሐፉ ከዚህ ተቃራኒ እንደሆነ እስካሁንም ብዙ እያየን መተናል የሚከተሉት ሃሳቦችም…


#ተአምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ የምንወዳትን ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን #ስድብ እና #ክህደት የሞላበት ስለመሆኑ እርግጥ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ #ከ1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ #አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ #አንገታቸው በጉድጓድ #ተቀብረው #በጭንቅላታቸው ላይ #የፈረስና #የከብት #መንጋ #እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን #እንደተቆረጡ በሚገርም ሁኔታ ራሱ #ተአምረ ማርያም ይመሰክራል።
( #ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121።)
*****************************
***

አብዛኛው የቤተክርስቲያናችን የዋህ ምዕመን እምነቱን የመሠረተ የሚመስለው #በታምረ ማርያም ላይ ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ እንኳ #ታምሯን #ሰምተን እንምጣ እንጂ ወንጌል #ተምረን አንምጣ ብለው አያስቡም አይናገሩም። በተለይ እሁድ እሁድ ታምር የሚያነብ እንጂ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም።
#ከ400,000 ካህናት በላይ እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን #ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥበት አይደለም። በጣም በሚገርም ሁኔታ #ታምሯን #ሰምቶ የሄደ #ሥጋውና #ደሙን #እንደተቀበለ #ይቆጠርለታል የሚለው ባዕድ ወንጌል ስለ ጌታ ራት ከተሰጡት የስህተት ትምህርቶች ውስጥ በዋንኛነት ከሚጠቀሱት #አንዱ ነው።
አረ እንደው በፈጠራቹ ህሊና ያለው ሰው አሁን ይሄን ምን ይላል?
ክርስቲያን የሆነ ሰው አላልኩም
እንደው ህሊና ብቻ ያለው ሰው።

#ብዙ ጊዜ ደግሞ ስህተቱን እያወቁ በዝምታ የሚያልፉ አገልጋዮች አጋጥመውኛል ለምን እውነቱን እንደማይናገሩ ስጠይቅ ለዚህ ጊዜዬን አላጠፋም ወንጌል ሲረዱ እውነቱ ይገለጥላቸዋል የሚል ነው። እንደ እውነቱ ካየነው #የወንጌል #ብርሃን የማይፈታው ጨለማ የለም እንዲሁም ወንጌል ላይ ትኩረት ማድረጉም እደግፈዋለው ነገር አንድ የማልስማማበት ነገር አለ ስንቱን ወደ ዘላለማዊ ሞት እየነዳ ያለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ #የተአምረ ማርያም ዓይነቱ ስጋ ስጋ የሚሸቱ የሰይጣን ሀሳብና ምክሩ የሰፈረበትን በግልፅ መዝለፍ ተገቢ ነው ብዬ አስባለው። ቃሉም እንደዛ ነውና የሚለው
የይሁዳ መልእክት 1:22

አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም #ከእሳት #ነጥቃችሁ አድኑ፥

#ብዙ ሰዎች ይሰድቡኛል ለምን ራስህን አትመለከትም ምናምን እኔ ግን አሁንም ቢሆን በሰው ልብ ውስጥ የነገሰውን በብልሃት የተፈጠረን #ተረትና #መንፈሳዊ #ይዘት ባለው ነገር የሚሰራውን #ክፉ ወገኖቼ ላይ እንዳይሰለጥን የበኩሌን አደርጋለው። የገድላትንም ደባ ባለኝ መረዳትና እግዚአብሔር በሰጠኝ #ፀጋ እጋደላለው በቃ ይሄ ነው የእኔ #አቋም
የገድላትን ደባ በማጋለጥ ሂደት ውስጥ ብዙ ሰዎች መልካም የሆነውን #እውነት ለይተውበታል ለዚህም በውስጥ መስመር የሚደርሰኝ አበረታች ቃላት ወደ ፊት እንድገፋበት ብርታት ሆኖኛል። እናም አጋልጣለው የሚሰማ ባይኖር እንኳ አልተውም። በእርግጥ #ከእውነቱም መሸሽ አይቻልም።

ብቻ ግን ለዛሬ ከላይ በርዕሱ እንደጠቀስኩት #የተአምረ ማርያምን ደባ #ከበለዔ #ሰብ ጋራ ያለውን ታሪክ በተያያዘ የኑሮአችን የመኖሪያ ልክ ወይም ቱንቢ በሆነው በሕያውና በሚሰራው #በቅዱሱ #የእግዚአብሔር #ቃል እንፃር እንመለከታለን መልካም #ንባብ
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28 (2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም) *ሱራህ 19, አያህ 27* فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ *ሱራህ 19, አያህ 28* يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ…
▶️ ሌሎች #በኦርቶዶክስ ያሉ #መጽሀፍቶች ደግሞ የተለያዩ #የዘር ግንድ ቆጠራዎችን ይጠቅሳሉ።
" #ድርሳነ #ጽዮን" የተባለው መጽሀፍ #የማርያም የዘር ሃረግን ሲገልጽ👇
ሜሊኪ። "የሐና(የእናቷ)
/ \ |
ሴም ሌዊ። ኤሊ
| |
ሆናሲን። ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን። ማቴን
| |
ኢያቄምን። ሐና
\ /
ማ ር ያ ም ን
ወለዱ ይላል[7]።

▶️ የማቲዎስ ወንጌል እንድምታ ደግሞ ከዚህ የተለየ ይገልጻል።
አኪም
|
ኤልዩድ
|
አልዓዛር
|
ቅዕራ
|
ኢያቄም ይላል[8]።

እንግዲህ እነዚህ #መጽሀፍት ደግሞ #በማርያም #አባት ቢስማሙም #በአያቶቻቸው ግን ፈጽሞ #አይስማሙም

▶️ የአንዳንድ ካቶሊካውያን አመለካከትም። << #ማርያም #ሰማያዊ #ፍጡር>> እንደሆነች ሲገልጹ ይህንንም ሀሳብ #የሰዓታት ጸሐፊና #የተአምረ #ማርያም ጸሐፊም በከፊል የሚቀበሉት ቢሆንም #ሃይማኖተ #አበው ግን በግልጽ ይህን ሃሳብ ያወግዘዋል። << እመቤታችን ከሰው የተለየች #ፍጥረት #ምድራዊት ያልሆነች ቀድሞ #በሰማይ #የነበረች #ሃይል(ፍጡር) ናት የሚል ቢኖር #ውግዝ ይሁን። በቅድስት መጽሀፍት እንደተጻፈው #ቅድስት ድንግል ማርያም #ከዳዊት#ከይሁዳ #ከአብርሃም ዘር እንደሆነች #በእውነት የሚያምን ግን #ከግዝት የተፈታ ይሁን>> ይላል[9]።

▶️ ማርያም ዘመዷ #ኤልሳቤጥ፣ እጮኛዋም #ዮሴፍ የነበረ ሴት እንደሆነች ሃገሯም #ናዝሬት #ገሊላ ሆኖ #ከዳዊት #ዘር እንደነበረች #መጽሀፍቅዱስ እየተናገረ #ሰማያዊ #ፍጡር #ናት ማለት " ህዝቤ #እውቀት #ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል/ሆሴ 4-6/። እንደሚለው #የእውቀት #ማጣት ይመስላል።
መጽሀፍቅዱስ የማርያም #አባት #ኢያቄም ሳይሆን < #ኤሊ> የተባለ #ሰው እንደነበር የሚገልጸው ፍንጭ አለ።
(በሉቃስ 3፥23)
ደግሞ #የማርያም #ገድሎች እንደሚሉት #ለእናት #ለአባቷ #አንዲት #ልጅ ሳትሆን #እህትም እንዳላት #መጽሀፍቅዱስ ይናገራል። 👇

<< ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ #የእናቱም #እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።>> {ዮሐ19፥25}።

<<ለዮሴፍ አባቱም #የማታን ልጅ #የያዕቆብ ልጅ (የማታን የልጅ ልጅ) ነው ብሎ #ማቲዎስ (በማቲ 1-16) #የዘር #ሐረጉን ሲቆጥር ወንጌላዊው #ሉቃስ ደግሞ #የማርያምን #የዘር ሃረግ ተከትሎ #በመቁጠር #የማርያም #አባቷ < #ኤሊ> እንደሆነ አስቀምጧል {ሉቃ 3-23}።

🔆 የዮሴፍ የዘር ሀረግ 🔆

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ........
............................................

6፤ " እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።"...............................
............................................

15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም #ማታንን ወለደ፤ ማታንም #ያዕቆብን ወለደ፤

16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ #ዮሴፍን ወለደ።