ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28 (2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም) *ሱራህ 19, አያህ 27* فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ *ሱራህ 19, አያህ 28* يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ…
▶️ ሌሎች #በኦርቶዶክስ ያሉ #መጽሀፍቶች ደግሞ የተለያዩ #የዘር ግንድ ቆጠራዎችን ይጠቅሳሉ።
" #ድርሳነ #ጽዮን" የተባለው መጽሀፍ #የማርያም የዘር ሃረግን ሲገልጽ👇
ሜሊኪ። "የሐና(የእናቷ)
/ \ |
ሴም ሌዊ። ኤሊ
| |
ሆናሲን። ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን። ማቴን
| |
ኢያቄምን። ሐና
\ /
ማ ር ያ ም ን
ወለዱ ይላል[7]።

▶️ የማቲዎስ ወንጌል እንድምታ ደግሞ ከዚህ የተለየ ይገልጻል።
አኪም
|
ኤልዩድ
|
አልዓዛር
|
ቅዕራ
|
ኢያቄም ይላል[8]።

እንግዲህ እነዚህ #መጽሀፍት ደግሞ #በማርያም #አባት ቢስማሙም #በአያቶቻቸው ግን ፈጽሞ #አይስማሙም

▶️ የአንዳንድ ካቶሊካውያን አመለካከትም። << #ማርያም #ሰማያዊ #ፍጡር>> እንደሆነች ሲገልጹ ይህንንም ሀሳብ #የሰዓታት ጸሐፊና #የተአምረ #ማርያም ጸሐፊም በከፊል የሚቀበሉት ቢሆንም #ሃይማኖተ #አበው ግን በግልጽ ይህን ሃሳብ ያወግዘዋል። << እመቤታችን ከሰው የተለየች #ፍጥረት #ምድራዊት ያልሆነች ቀድሞ #በሰማይ #የነበረች #ሃይል(ፍጡር) ናት የሚል ቢኖር #ውግዝ ይሁን። በቅድስት መጽሀፍት እንደተጻፈው #ቅድስት ድንግል ማርያም #ከዳዊት#ከይሁዳ #ከአብርሃም ዘር እንደሆነች #በእውነት የሚያምን ግን #ከግዝት የተፈታ ይሁን>> ይላል[9]።

▶️ ማርያም ዘመዷ #ኤልሳቤጥ፣ እጮኛዋም #ዮሴፍ የነበረ ሴት እንደሆነች ሃገሯም #ናዝሬት #ገሊላ ሆኖ #ከዳዊት #ዘር እንደነበረች #መጽሀፍቅዱስ እየተናገረ #ሰማያዊ #ፍጡር #ናት ማለት " ህዝቤ #እውቀት #ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል/ሆሴ 4-6/። እንደሚለው #የእውቀት #ማጣት ይመስላል።
መጽሀፍቅዱስ የማርያም #አባት #ኢያቄም ሳይሆን < #ኤሊ> የተባለ #ሰው እንደነበር የሚገልጸው ፍንጭ አለ።
(በሉቃስ 3፥23)
ደግሞ #የማርያም #ገድሎች እንደሚሉት #ለእናት #ለአባቷ #አንዲት #ልጅ ሳትሆን #እህትም እንዳላት #መጽሀፍቅዱስ ይናገራል። 👇

<< ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ #የእናቱም #እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።>> {ዮሐ19፥25}።

<<ለዮሴፍ አባቱም #የማታን ልጅ #የያዕቆብ ልጅ (የማታን የልጅ ልጅ) ነው ብሎ #ማቲዎስ (በማቲ 1-16) #የዘር #ሐረጉን ሲቆጥር ወንጌላዊው #ሉቃስ ደግሞ #የማርያምን #የዘር ሃረግ ተከትሎ #በመቁጠር #የማርያም #አባቷ < #ኤሊ> እንደሆነ አስቀምጧል {ሉቃ 3-23}።

🔆 የዮሴፍ የዘር ሀረግ 🔆

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ........
............................................

6፤ " እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።"...............................
............................................

15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም #ማታንን ወለደ፤ ማታንም #ያዕቆብን ወለደ፤

16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ #ዮሴፍን ወለደ።
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ብዙ ሴቶች #ማርያም በሚል ስም ይጠራሉ[1]። [ለምሳሌ]👇

〽️ 1፦ "የሙሴ እህት ማርያም"
/ዘጸ 2፥4-8/

▶️ የዚችን #ማርያም ታሪክ #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ስናይ #ወንድሟ #ሙሴ በወንዝ #ዳር #በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን #ለማወቅ ስትመለከት ወደ ወንዙ የመጣችውን #የፈርኦንን #ልጅ #በጥበብ አነጋግራና #እንድታጠባው የገዛ #እናታቸውን #በሞግዚትነት ስም አገናኝታ ወንድሟ #ሙሴ እንዲያድግ #አስተዋጽኦ ያደረገች ናት። #ሙሴም በዚህ እድልና በእግዚአብሄር #አላማ አድጎ #እስራኤላውያንን #የኤርትራን #ባህር ካሻገራቸው በኋላ #ነብይት ሆና #ሴቶችን #በመዝሙርና #በምስጋና መርታለች {ዘጸ 15፥20}። ከዛ ግን #ማርያም #የሙሴን የበላይነት ካለመውደዷ የተነሳ #ኢትዮጵያዊት #ሚስቱን ምክንያት አድርጋ #አማችው#እግዚአብሔር ግን #በለምጽ #ቀጣት {ዘኅ 12 ; ዘዳ 24፥9}። በመጨረሻም #እስራኤላውያን ገና በጉዞ ሳሉ #በቃዴስ #በረሃ #ሞተች በዚያው #ተቀበረች። {ዘኅ 20፥1}።

〽️ 2፦ "የዩቴር ልጅ የዕዝራ የልጅ ልጅ ማርያም" {1ዜና 4፥17} ፦

▶️ የዚች #ማርያም ታሪክና ተግባሯ ብዙም አልተጠቀሰም

〽️ 3፦ "የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም" {ሉቃ 1፤ 26-27} ፦

▶️ ሙሉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ታሪኳ <13🌐☑️ ቅድስት ድንግል ማርያም በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ> በሚለው ርእስ ስር ይቀርባል።

〽️ 4፦ "የማርታና የዓላዛር እህት ማርያም" {ዩሐ 11፥1} ፦

▶️ ከኢየሩሳሌም አጠገብ ባለው #ቢታንያ በተባለው #መንደር #ከእህቷ #ማርታና ከወንድሟ #አላአዛር ጋር ትኖር ነበር። አንድ ቀን #ጌታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስም ወደ ቤታቸው ሄዶ ሲጠይቃቸው ይህቺ #ማርያም ወደ እርሱ #ቀርባ ቃሉን #በጽሞና #ስለሰማችና #ስለተማረች #ክርስቶስ አመስግኗታል {ሉቃ 10፤ 39-42}። ወንድሟ #አላአዛርም #ከሙታን በተነሳ ጊዜ #ከጌታ #ኢየሱስ ጋር ብዙ ተነጋግራለች {ዩሐ 11}። ቀድም ብሎም ይቺ #ማርያም #ጌታችን እንደሚሞት አውቃ #በናርዶስ #ሽቶ #እግሩን ቀብታውም ነበር። {ዩሐ 12፤ 1-8}።

〽️ 5፦ "መግደላዊት ማርያም"፦

▶️ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ሰባት #አጋንንት ከእርሷ ካወጣላት ቡኃላ ታገለግለው ነበር {ሉቃ 8፥2 , ማር 15፥40}። ይህቺ #ሴት ለክርስቶስ #መሰቀልና #መነሳት #ምስክር ነበረች {ማቴ 27፤፦55 ፣ 56 ፣ 61, ማር 15፤ 40-47 ፣ ዩሐ 19፤25 ፣ ማቲ 28፤ 1-10 ፣ ማር 16፤ 1-8፣ ሉቃ 24፤10}። #ከትንሳኤውም ቡሀላ #በአትክልት ቦታ ለብቻዋ #ክርስቶስን #ካየችውና #ካነጋገረችው ቡሀላ የመጀመሪያዋ #ትንሳኤውን #መስካሪ ሆናለች {ዩሐ 20፤ 1-18}።

〽️ 6፦ "የቀለዩጳ ሚስት ማርያም "፤

▶️ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ #ከመስቀሉ #አጠገብ ቆማ ነበር {ዩሐ 19፤25}።

〽️ 7፦ "የማርቆስ እናት ማርያም"፤

▶️ ሐዋሪያት ተሰብስበው በቤቷ #ይጸልዩና #ይመካከሩ ነበር {ሐዋ 12፥12}።

እንደምናየው #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ #ብቻ #ማርያም ተብለው የሚጠሩ #ሰባት #ሴቶች አሉ። #እስራኤላውያንም #ለልጆቻቸው #ስም ሲያወጡም ሆነ #ለራሳቸው የሆነ #ስያሜ #ሲመርጡ ከልዩ #የሕይወት #ታሪካቸው ጋር #የተያያዘውን ነው።
አንዳንዶች በተለይ " #ማርያም" የሚለውን ስም #የጌታችን #የኢየሱስ #ክርስቶስን #እናት ብቻ #ማእከል አድርገው በሚገርም ሁኔታ #ተርጉመው #ሌላ #ትምህርት ለዛውም #ከእግዚአብሄር #ብቸኛ የማዳን #ተግባር ጋር #የሚጋጭ አርገው እንዲህ ተርጉመውታል።👇👇

🔆 1ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት " #ፍጽምት" ማለት ነው። መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን #ንጽሐ ሥጋ #ንጽሐ ነፍስ #በድንጋሌ ሥጋ #በድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና።

🔆 2ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት #ጸጋ #ወሀብት(ጸጋና ሀብት) ማለት ነው። #ለእናት #ለአባቷ #ጸጋ ሆና ተሰጣለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ #ጸጋ ሆና #ተሰጥታለች

🔆 3ኛ ትርጉም፦

" #ማርያም" ማለት #መርሕ #ለመንግሥተ ሰማያት(የመንግሥተ ሰማያት መሪ) ማለት ነው። ምዕመናንን መርታ #ገነት #መንግስተ #ሰማያት አግብታለችና።

🔆 4ኛ ትርጉም፦

"ማርያም" ማለት #ልዕልት ማለት ነው። #መትሕተ ፈጣሪ #መልዕልተ ፍጡራን(ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) ይሏታልና።

🔆 5ኛ ትርጉም፦

ተላአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ {#የእግዚአብሄርና #የህዝብ #ተላኪ ማለት ነው።[2]