ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
69 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
@gedlatnadersanat


ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ በግርጌ ማስታወሻ " #በግሪኩ #የሚማልደው #ነው #የሚለው" ብላ የጻፈችው። ይህ ከሆነ ደግሞ #የአዲስ ኪዳን በኩረ ጽሁፍ(እናት ቋንቋ) #ግእዙ ሳይሆን #ግሪኩ መሆኑ ግልጽ ነው#ግእዙን ጨምሮ ሁሉም #የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት #የትርጉም ሥራቸው የተሰራው #ከግሪኩ በመሆኑ የትኛውም የትርጉም ስራ ሲሰራ #ግሪኩ የሚለውን በማለት ግሪኩ የተወውን በመተው መስራቱ #ለእግዚአብሄር ቃል ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ትልቁ መንገድ ነው#ግሪኩ እንዲህ #አይልም እያሉ ሌላ ነገር መጻፍ #ታማኝ መሆንን አያሳይም።

▶️ ይህ እንዳለ ሆኖ #ጸሀፊው #ከጠቀሱት #መጻሕፍት በፊት " #በዐጼ ሚኒልክ" ጊዜ የታተመው #የ1887 ዕትም #መጽሀፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ እንዴት #አስፍሮት እንዳለ #መመልከቱ መልካም ነው
" #ማን ነው የሚኮንን? ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን? ከሙታን እንኳ የተነሣ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም #ያስምረናል"

አንባቢው ልብ እንዲል የሚገባው ነገር #ሰዎቹ እያሉ ያሉት " #ከጊዜ ቡሀላ #የታተሙት ናቸው እንጂ #ቀደምት ዕትሞች " #ክርስቶስ ያማልዳል" አይሉም የሚል ሲሆን እነርሱ #የቀደሙ ናቸው ከሚሏቸው #ቀድሞ #ለንባብ የበቃው #መጽሀፍ ግን እነርሱ እንዲልላቸው የሚፈልጉትን ሳይሆን #እውነታውን #አስፍሮት ይገኛል።
#ወንድሞቻችን መፈናፈኛ ሲያጡ " #እናንተ የቀየራቹትን ሳይሆን #አባቶቻችን ቀደም ሲል #በግእዝ ጽፈው ያስቀመጡልንን ነው የምንቀበለው" ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚሁ ደግሞ #በግእዝና #በአማርኛ ተዘጋጅቶ #በትንሣኤ #ማተሚያ ቤት የታተመውን #መጽሀፍ በዋናነት የሚጠቅሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ #ግእዙን መሠረት አድርጎ ነው #የታተመው #የሚባለውንና #በ2000 ዓ.ም ለንባብ የበቃውን 80 አሀዱ #መጽሀፍ ቅዱስ ያነሳሉ።
#በግእዝና በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ ምንም እንኳን በአማርኛው
" #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" በማለት ቢያስቀምጡትም ግእዙ ራሱ ግን
" #ወመኑ፡ ውእቱ፡ እንከ፡ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፤ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ፡ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር #ወይትዋቀሥ #በእንቲአነ" በሚል ነው የሰፈረው።(ሮሜ 8፤ 33-34)
📖/፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዐዲስ ኪዳን በግእዝና በዓማርኛ (ዐዲስ አበባ፤ 1994) ገጽ 644።

ሰዎቹ " #ይፈርዳል" እንዲልላቸው የሚጠብቁት ቃል " #ወይትዋቀሥ" የሚለውን ነው
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
🔽 " #ተዋቀሠ" የሚለውን ቃል ትርጉም " #ተሟገተ#ተከራከረ" እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠውታል።
ይህ እንዲህ ሳለ ግን #ሰዎቹ ከመሰረተ ሀሳቡ #ውጭ በሆነ ሁኔታ #ለመተርጎም የተነሳሱበት ምክንያት #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ #ለፈቃዳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ #ሰዎች በመሆናቸው መሆኑ ግልጽ ነው
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፣ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ፣(1948) ገጽ 401።

" #ይከራከል" የሚለው እንዲያውም " #ይማልዳል" ከሚለው በላይ #ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የሚቆም #መካከለኛ መሆኑን #አጠንክሮ ይገልጣል እንጂ #ይፈርዳል ማለትን አያመለክትም፤ #ግእዙን እንኳን የተጠቀምነው #በአገራችን የተለመደ #ጥንታዊ ትርጓሜ ነው በማለት እንጂ #የአዲስ ኪዳን #መጻህፍት ሁሉ በመጀመሪያ በተጻፉበትና ለሁሉም #ትርጓሜዎች መሰረት በሆነው #የግሪክ ቋንቋ በግልጽ #የሚማልደው ተብሎ ተቀምጧል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው #በግሪክ ቋንቋ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም። ይህንን ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለውን ቃል « #የሚፈርደው» ብለው የቀየሩ ሰዎች ራሱ በግሪኩ #የሚያማልደው እንደሚል ራሳቸው ይስማማሉ።(ፎቶው ላይ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ)

@gedlatnadersanat
Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ሰሞኑን ድርሳነ ማርያም የተሰኘ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ መጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ አስገራሚ ነገሮችን ያነበብኩ ቢሆንም አሁን ያነበብኩትን ግን ለወገኖቼ ማካፈል እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡

በአንዳንዶች እንደሚታመነው ለማርያም ዐስራት ተደርጋ የተሰጠች አገር አለች፡፡ ድርሳነ ማርያም ስለዚህ ሁኔታ እንዲህ ነው ያሰፈረው፡-

"ዐሥራት ትሆነኝ ዘንድ አንዲትን አገር ስጠኝ አለችው፡፡ አዜቡ ይሁንሽ አላት፡፡ ክርስቲያን ነውን? አልሁት፡፡ #አሁን #ክርስቲያን #አልሆኑም #ብዙዎቹ #ለአውሬ#ለድንጋይ #የሚሰግዱ #ናቸው እንጂ፡፡ ከዚህ በሁላ ግን ክርስቲያን ይሆናሉ፡፡ በስሜ ማመናቸውም እንደፀሐይ ያበራል፡፡ በስምሽም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይሠራሉ፡፡ #ይህ #ቦታም #አክሱም #የሚባለው #ነው..." (ድርሳነ ማርያም ገጽ 130)

ከዚህ ውስጥ ሦስት ነጥቦችን ላሳያችሁ፡-

1) አንዳንዶች እንደሚያምኑት አስራት ተደርጋ የተሰጠችው ኢትዮጵያ ናት፡፡ መጽሐፉ ላይ በሰፈረው መሠረት ኢትዮጵያ ልትሆን የምትችለው አክሱም ናት፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት አገር ለማርያም አስራት ተደርጋ ተሰጥታለች የሚለው ስሕተት ነው ማለት ነው፡፡

2) ሌላው እስከዛሬ ጣዖት አምልከን አናውቅም የሚለው ነው፡፡ በድርሳኑ መሠረት ጣዖት ይመለክ የነበረ መሆኑን፡የተናገረው ራሱ ጌታችን ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ውጪ ምንም አምልካ አታውቅም የሚለውም ስሕተት ነው ማለት ነው፡፡

3) ክርስትና ወደ እኛ ጋር የመጣው በጀንደረባው ነው የሚለውም በዚህ ጽሑፍ መሠረት እሳት የነካው ላስቲክ ሆነ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ጀንረባው፡ክርስትና እንዳመጣ የሚታመነው በ34 ዓ.ም. ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የሰፈረው ታሪክ የሰፈረው ማርያም ከሞተች በሁላ ነው፡፡ ይህ ማለት ጀንደረባው ክርስቲያን ከሆነ፡ከብዙ ዓመታት በሁላ ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ገና ለክርስትና ሩቅ ነበረች እያለን ነው፡፡

ይህ ሁሉ የእኔ ሐሳብ አይደለም፡፡ ከመጽሐፉ ላይ ያለውን ነው ግልጽ ያደረኩት፡፡

https://tttttt.me/tewoderosdemelash/381
Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ዳንኤል ክብረት በ2011 ለንባብ ባበቃው "ኢትዮጵያዊው ሱራፊ" ላይ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሚባል የለም የሚል ሐሳብ ሲያቀርብ ይታያል፡፡ ለዚህም ‹‹ #የሄደም #የተመለሰም #ሰሎሞናዊ #መንግሥት #የለም፡፡… ከእስራኤል ዘር ጋር ማገናኘት የሕዝባችን ባህል መሆኑን የምናየው በታሪክ ነገሥታቱ ብቻ ሳይሆን በገድለ ቅዱሳኑም ይህንኑ ባህል ማገኘታችን ነው፡፡ በባህላዊው የዘር ቈጠራ ውስጥም አለ፡፡ #ስለዚህም #ነገሥታቱን #‹ሰሎሞናዊ› #የሆነና #ያልሆነ #ብሎ #መከፋፈሉ #አዋጪ #አይደለም›› (ገጽ 27) በሚል ያሰፈረውን መመልከት ይቻላል፡፡

ታዲያ ከሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ጋር በተያያዘ ስመ ገናና የሆነው ክብረ ነገሥት ለምን ተጻፈ? የሚል ጥያቄ ቢነሣ ዳንኤል የሚከተለውን መልስ ይሰጣል፡-

#"...ለዐዲሱ #የይኩኖ #አምላክ #ሥርወ #መንግሥት #ታሪካዊ#ሃይማኖታዊ #መደላድል #መፍጠር… የዐረብ ምንጮችን መሠረት አደርጎ በቃላዊ መረጃዎችና በተራረፉ የጸሑፍ መዛግብት ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ #አገራዊ #መጽሐፍ #ነው፡፡… ሁለተኛው ዓላማው ለኢትዮጵያ ነገሥታት የማንነት መሠረት መስጠት ነው፡፡ ንግሥናን ከእስራኤል ዘር በሚገኝ የዘር ተዋርዶ ብቻ እንዲሆን የሕግ መሠረት አስቀመጠ፡፡ ‹ሰሎሞናዊ› የሚለውም ሐሳብ በሚገባ ጎልቶ ወጣ፡፡ ይኩኖ አምላክም የሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት መላሽ ተባለ፡፡… ንቡረ ዕድ ይስሐቅና የዘመኑ ሊቃውንት ክብረ ነገሥትን የተረጎሙበት አንዱ ምክንያት ለኢትዮጵያ ዐዲስ ማንነትን ለመስጠት ነው፡፡ ያችኛዋ እስራኤል ፈረሳለች፣ ክርስትናንም አልተቀበለችም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ዐዲሷ እስራኤል ናት፡፡ በመሆኑም ለእስራኤል የተሰጠው ቃል ኪዳን ለኢትዮጵያ ተላልፏል፣ ይህም በሰሎሞንና በንግሥት ሳባ በኩል ተፈጽሟል፡፡ የቃል ኪዳኑ ታቦትም በኢትዮጵያ ነው፡፡ ስለዚህ #ኢትዮጵያ #የአፍሪካ #ጽዮን #ናት #የሚለውን #ለመመሥረት #ነው (ገጽ 25 እና 302 የግርጌ ማስታወሻ 804 እና 325)፡፡


በዚህ በዳንኤል እምነትና ምስክርነት መሠረት ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሚባል ከሌለ፣ ክብረ መንግሥትም ለሌላ ዓላማ ከተጻፈ የሰሎሞን ልጅ ነው የሚባለው የቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ እና በእሱ አማካይነት ወደ ሀገራችን መጥቷል የሚባለው ታቦት ታሪክ ውሃ በላው ማለት ነዋ!!!???

https://tttttt.me/tewoderosdemelash/586