✍✍
የአገራችን ቅዱሳን እውን መንፈሳዊ ናቸው ??
#በአገራችን ቅዱሳን ተብለው ታቦት ተቀርጾ -ቀን ተሰይሞ -ገድል ተጽፎላቸው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል እየተባሉ ከወር እስከወር የሰው ልብ ላይ ነግሰው የአምላክ ገንዘብ የሆነውን ስግደትና ዝማሬ መስዋእትም በጸጋ ስም የሚኮመኩሙ የቡልጋ የትግራይና የጎጃም ተወላጅ የሆኑ አፈጣጠራቸው አኑዋኑዋራቸውና ትምህርታቸው አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያልተሰማ #ክንፍ ያወጡ/#ሰውነታቸው ተበሳስቶ አሳ የሚሾልክበት/ #ከተወለዱ በሶስተኛው ቀን ያማተቡ/#ከተፈጠሩ ምግብ ያልቀመሱ/#ባህር ውስጥ 12 አመት #ምድር ላይ ሰባት አመት በአንድ እግራቸው ቆመው የጸለዩ ይገኙበታል።
የእነዚህ ሰዎች መንፈሳዊነት አጠያያቂ እየሆነ መጥቶአል። መንፈሳዊ ሊሆኑ የማይችሉ ይልቁንም የክርስቶስን ክብር እንዲጋርዱ ሰይጣን የተጠቀመባቸው እንደሆኑ ለዛሬ በ6 ምክንያቶች እንመልከት….
⚜1፦ እድሜአቸው -
#ዘፍ 6-3 “የሰው ዘመኖቹ መቶ ሃያ አመት ይሆናሉ“በማለት የእድሜ ጣራ ተበጅቶአል.
#መዝ 90-10 “የዘመኖቻችንም እድሜ ሰባ ቢበረታም ሰማኒያ ነው“ይላል. እውነትም እንደ አብረሃም፣ ዳዊት፣ ሙሴ ያሉ ታላላቅ አባቶች እንኩዋን ከዚህ አልዘለሉም።
#አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ግን 562 #ክርስቶስ ሰምራ 375 አመት ኖሩ ተብለናል።
⚜2፦ አፈጣጠራቸው፦
#ዘፍ 1-25 እግዚአብሄር ሁሉን እንደወገኑ እንደፈጠረ ይናገራል. ክንፍ ለአእዋፍ ወገን እንጂ ለሰው ወገን ተሰጥቶ አያውቅም። ተክልዬ ግን 6 ክንፍ እንደተሸለሙ በገድላቸው ተጽፎአል። እንደውም አንዳንድ ሸርዳጆች “የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት“ን እየጠቀሱ “እግር የላቸው ክንፍ አማራቸው “ ሲሉ ሰምቻለሁ። ደግሞስ የት በረሩበት?? እግዚአብሄር ግዜአዊ ችግርን ለመቅረፍ ተፈጥሮን አይቀይርም። ቀይሮም አያቅም። ትልቅ የእግዚአብሄር አጀንዳ የተሸከመው ጳውሎስ እንኳን በደማስቆ ሊይዙት ባሉ ግዜ በቅጥሩ ላይ በቅርጫት ወረደ እንጂ ያለፍጥረቱ ክንፍ አልተሰጠውም። ጌታን ራሱ ሊይዙት ሲሉ በመካከላቸው አልፎ ይሄድ ነበር እንጂ ሌላ አካል አልተገጠመለትም ወይም ክንፍ አላበቀለም። ኤልያስ ከኤልዛቤል በተደበቀ ግዜ ክንፍ ባለው ቁራ ስጋ ይመጣለት ነበር እንጂ ክንፍ አልወሰደም።
የአቡየ በህይወት ዘመን እህል አለመቅመስ ተረት ነው።
ጌታ “ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም“ አለ እንጂ ያለምግብ ይኖራል አላለም።
#ጌታም ተርቧል
#ኤልያስም እንዲሁ……ስጋ ያለምግብ መኖር አይችልምና
ሉቃ 7-34 “መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላ የወይን ጠጅም ሳይጠጣ መጥቶ ነበርና። ጋኔን አለበት አላችሁት።“እንዳለው ጋኔን ያለበት ካልሆነ በቀር……ማርያም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መቀመጫ ሰገራ እንዳይመጣባቸው ደፈነች የሚለውም የሌለ ነው። ሰው ይበላል ይጸዳዳል። ጌታም ሰይጣን በህመም የደፈነውን መቀመጫ ይከፍታል እንጂ አይደፍንም።
⚜3፦ ለሰይጣን ያላቸው ፍቅር-እነዚህ ሰዎች ለሰይጣን አንጀታቸው ስፍስፍ ነው የሚለው። ክርስቶስ ሰምራ መንፈሳዊ ከሆነች #2ቆሮ 6-15 “ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው??“-#ዘፍ 3-15 “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ“የሚለውን በማወቅ ሰይጣንን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ አትሞክርም ነበር።
ተክልዬም “ባህረ አልቅም“ የተባለውን ሰይጣን ከባህር አውጥተው “ክርስቶስ ሐረዬ“(ክርስቶስ የመረጠው) ብለው ስሙን ቀይረው አገልጋይ አያደርጉትም ነበር።
እግዚአብሄር ሰው ቢያጣ እንኳን ሰይጣንን ለአገልግሎት አይመርጥም።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ሰይጣንን ድንጋይ አሸክመው አያሰሩም ነበር።
አቡነ አረጋዊም እንደዛሬው ዳን ቴክኖክራፍት ሊፍት በዘንዶ አቀበት አይወጡም ነበር።
ምናልባት ይህን ክፍል አላነበቡትም ይሆናል ብለን እናልፋቸዋለን.. 👇
የማቴዎስ ወንጌል 25:41
በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ #ለሰይጣንና ለመላእክቱ #ወደ #ተዘጋጀ ወደ #ዘላለም #እሳት ከእኔ ሂዱ።
ሲኦል ራሱ የተዘጋጀው ለሰይጣን ነው መንግስተ ሰማያት ለሰይጣን ቦታ የለም።
⚜4፦ በአንድ አካባቢና ግዜ የተወሰኑ ናቸው፦
የእነዚህ ሰዎች አገልግሎት ከቡልጋና ከአክሱም አልወጣም።
#የተክልዬን ዝክር አሻሮ ያሸተተ ይጸድቃል
#በደብረሊባኖስ የተቀበረ ይድናል -…ወዘተ የሚሉ አሻሮና ደብረሊባኖስ የማታወቅበትን አህጉርና አለም ያላማከሉ አግልግሎቶች(Localized) ናቸው።
እንግሊዝ/ናይጀሪያ/ካናዳ ዝክርና አሻሮ አያውቁም። ሌላው በቅርብ አመታት ክንፍ ያላቸው ፣
በአንድ እግራቸው 7 አመት የሚቆሙ -
ሰውነታቸው ተበሳስቶ አሳ የሚሹለከለክበት ቅዱሳን እንዴት የሉም የሚል ጥያቄ ያስነሳል።
⚜5፦ መንፈሳዊ ውጊያቸው
#2ቆሮ 10-3 “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤“ እንደሚል ክርስቲያን ስጋና ደም ከሌለው ጠላት ጋር ስለሚዋጋ የጦር እቃው ጦርና ጋሻ አይደለም።
አቡየ ገ/መንፈስ ቅዱስ ግን ዝቋላ ተራራ ላይ ከሰይጣን ጋር በመብረቅ ይዋጉ ነበር።
⚜6፦ ቃል ኪዳናቸው -የእግዚአብሄር የመዳንና የዘላለም ህይወት መንገድ አንድና በግልጽ የተነገረ ነው። እሱም በልጁ በኢየሱስ አምኖ ... ይሁንና የቅዱሳን ቃልኪዳን የሚባለው ኢ-መጽሃፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን ሰዎች በሃጢአታቸው እንዲሞቱና ሲኦል የሚጨምር የሰይጣን ምክር አለበት። የእከሌን ገድል ያነበበ-ያስነበበ-የተረጎመ እስከ 10 ትውልድ ምሬልሃለሁ የሚል -#በአቡነ አረጋዊ ስም የተማጸነ 15 ትውልድ ምሬለታለሁ የሚል ምንፍቅና ነው።
ወገኖቼ ሆይ ይህንን እውነት ስንናገር እነሱ ግን የእግዚአብሄር ጠላት ሆነው የቅዱሳን ጠላት ይላሉ። እባካችሁ ከዚህ አዚም ውጡና በሙሉ ልባችሁ ንስሀ ገብታቹ እግዚአብሄርን አክብሩ አምልኩ።
#ተሃድሶ ለተረታተረት
እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/
@gedlatnadersanat @teeod

ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
@gedlatnadersanat
✍
ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ በግርጌ ማስታወሻ " #በግሪኩ #የሚማልደው #ነው #የሚለው" ብላ የጻፈችው። ይህ ከሆነ ደግሞ #የአዲስ ኪዳን በኩረ ጽሁፍ(እናት ቋንቋ) #ግእዙ ሳይሆን #ግሪኩ መሆኑ ግልጽ ነው። #ግእዙን ጨምሮ ሁሉም #የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት #የትርጉም ሥራቸው የተሰራው #ከግሪኩ በመሆኑ የትኛውም የትርጉም ስራ ሲሰራ #ግሪኩ የሚለውን በማለት ግሪኩ የተወውን በመተው መስራቱ #ለእግዚአብሄር ቃል ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ትልቁ መንገድ ነው። #ግሪኩ እንዲህ #አይልም እያሉ ሌላ ነገር መጻፍ #ታማኝ መሆንን አያሳይም።
▶️ ይህ እንዳለ ሆኖ #ጸሀፊው #ከጠቀሱት #መጻሕፍት በፊት " #በዐጼ ሚኒልክ" ጊዜ የታተመው #የ1887 ዕትም #መጽሀፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ እንዴት #አስፍሮት እንዳለ #መመልከቱ መልካም ነው።
" #ማን ነው የሚኮንን? ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን? ከሙታን እንኳ የተነሣ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም #ያስምረናል"
አንባቢው ልብ እንዲል የሚገባው ነገር #ሰዎቹ እያሉ ያሉት " #ከጊዜ ቡሀላ #የታተሙት ናቸው እንጂ #ቀደምት ዕትሞች " #ክርስቶስ ያማልዳል" አይሉም የሚል ሲሆን እነርሱ #የቀደሙ ናቸው ከሚሏቸው #ቀድሞ #ለንባብ የበቃው #መጽሀፍ ግን እነርሱ እንዲልላቸው የሚፈልጉትን ሳይሆን #እውነታውን #አስፍሮት ይገኛል።
#ወንድሞቻችን መፈናፈኛ ሲያጡ " #እናንተ የቀየራቹትን ሳይሆን #አባቶቻችን ቀደም ሲል #በግእዝ ጽፈው ያስቀመጡልንን ነው የምንቀበለው" ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚሁ ደግሞ #በግእዝና #በአማርኛ ተዘጋጅቶ #በትንሣኤ #ማተሚያ ቤት የታተመውን #መጽሀፍ በዋናነት የሚጠቅሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ #ግእዙን መሠረት አድርጎ ነው #የታተመው #የሚባለውንና #በ2000 ዓ.ም ለንባብ የበቃውን 80 አሀዱ #መጽሀፍ ቅዱስ ያነሳሉ።
#በግእዝና በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ ምንም እንኳን በአማርኛው
" #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" በማለት ቢያስቀምጡትም ግእዙ ራሱ ግን
" #ወመኑ፡ ውእቱ፡ እንከ፡ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፤ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ፡ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር #ወይትዋቀሥ #በእንቲአነ" በሚል ነው የሰፈረው።(ሮሜ 8፤ 33-34)
📖/፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዐዲስ ኪዳን በግእዝና በዓማርኛ (ዐዲስ አበባ፤ 1994) ገጽ 644።
ሰዎቹ " #ይፈርዳል" እንዲልላቸው የሚጠብቁት ቃል " #ወይትዋቀሥ" የሚለውን ነው።
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
🔽 " #ተዋቀሠ" የሚለውን ቃል ትርጉም " #ተሟገተ፣ #ተከራከረ" እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠውታል።
ይህ እንዲህ ሳለ ግን #ሰዎቹ ከመሰረተ ሀሳቡ #ውጭ በሆነ ሁኔታ #ለመተርጎም የተነሳሱበት ምክንያት #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ #ለፈቃዳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ #ሰዎች በመሆናቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፣ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ፣(1948) ገጽ 401።
" #ይከራከል" የሚለው እንዲያውም " #ይማልዳል" ከሚለው በላይ #ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የሚቆም #መካከለኛ መሆኑን #አጠንክሮ ይገልጣል እንጂ #ይፈርዳል ማለትን አያመለክትም፤ #ግእዙን እንኳን የተጠቀምነው #በአገራችን የተለመደ #ጥንታዊ ትርጓሜ ነው በማለት እንጂ #የአዲስ ኪዳን #መጻህፍት ሁሉ በመጀመሪያ በተጻፉበትና ለሁሉም #ትርጓሜዎች መሰረት በሆነው #የግሪክ ቋንቋ በግልጽ #የሚማልደው ተብሎ ተቀምጧል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው #በግሪክ ቋንቋ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም። ይህንን ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለውን ቃል « #የሚፈርደው» ብለው የቀየሩ ሰዎች ራሱ በግሪኩ #የሚያማልደው እንደሚል ራሳቸው ይስማማሉ።(ፎቶው ላይ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ)