ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
@gedlatnadersanat


ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ በግርጌ ማስታወሻ " #በግሪኩ #የሚማልደው #ነው #የሚለው" ብላ የጻፈችው። ይህ ከሆነ ደግሞ #የአዲስ ኪዳን በኩረ ጽሁፍ(እናት ቋንቋ) #ግእዙ ሳይሆን #ግሪኩ መሆኑ ግልጽ ነው። #ግእዙን ጨምሮ ሁሉም #የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት #የትርጉም ሥራቸው የተሰራው #ከግሪኩ በመሆኑ የትኛውም የትርጉም ስራ ሲሰራ #ግሪኩ የሚለውን በማለት ግሪኩ የተወውን በመተው መስራቱ #ለእግዚአብሄር ቃል ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ትልቁ መንገድ ነው። #ግሪኩ እንዲህ #አይልም እያሉ ሌላ ነገር መጻፍ #ታማኝ መሆንን አያሳይም።

▶️ ይህ እንዳለ ሆኖ #ጸሀፊው #ከጠቀሱት #መጻሕፍት በፊት " #በዐጼ ሚኒልክ" ጊዜ የታተመው #የ1887 ዕትም #መጽሀፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ እንዴት #አስፍሮት እንዳለ #መመልከቱ መልካም ነው።
" #ማን ነው የሚኮንን? ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን? ከሙታን እንኳ የተነሣ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም #ያስምረናል"

አንባቢው ልብ እንዲል የሚገባው ነገር #ሰዎቹ እያሉ ያሉት " #ከጊዜ ቡሀላ #የታተሙት ናቸው እንጂ #ቀደምት ዕትሞች " #ክርስቶስ ያማልዳል" አይሉም የሚል ሲሆን እነርሱ #የቀደሙ ናቸው ከሚሏቸው #ቀድሞ #ለንባብ የበቃው #መጽሀፍ ግን እነርሱ እንዲልላቸው የሚፈልጉትን ሳይሆን #እውነታውን #አስፍሮት ይገኛል።
#ወንድሞቻችን መፈናፈኛ ሲያጡ " #እናንተ የቀየራቹትን ሳይሆን #አባቶቻችን ቀደም ሲል #በግእዝ ጽፈው ያስቀመጡልንን ነው የምንቀበለው" ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚሁ ደግሞ #በግእዝና #በአማርኛ ተዘጋጅቶ #በትንሣኤ #ማተሚያ ቤት የታተመውን #መጽሀፍ በዋናነት የሚጠቅሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ #ግእዙን መሠረት አድርጎ ነው #የታተመው #የሚባለውንና #በ2000 ዓ.ም ለንባብ የበቃውን 80 አሀዱ #መጽሀፍ ቅዱስ ያነሳሉ።
#በግእዝና በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ ምንም እንኳን በአማርኛው
" #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" በማለት ቢያስቀምጡትም ግእዙ ራሱ ግን
" #ወመኑ፡ ውእቱ፡ እንከ፡ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፤ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ፡ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር #ወይትዋቀሥ #በእንቲአነ" በሚል ነው የሰፈረው።(ሮሜ 8፤ 33-34)
📖/፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዐዲስ ኪዳን በግእዝና በዓማርኛ (ዐዲስ አበባ፤ 1994) ገጽ 644።

ሰዎቹ " #ይፈርዳል" እንዲልላቸው የሚጠብቁት ቃል " #ወይትዋቀሥ" የሚለውን ነው።
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
🔽 " #ተዋቀሠ" የሚለውን ቃል ትርጉም " #ተሟገተ#ተከራከረ" እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠውታል።
ይህ እንዲህ ሳለ ግን #ሰዎቹ ከመሰረተ ሀሳቡ #ውጭ በሆነ ሁኔታ #ለመተርጎም የተነሳሱበት ምክንያት #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ #ለፈቃዳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ #ሰዎች በመሆናቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፣ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ፣(1948) ገጽ 401።

" #ይከራከል" የሚለው እንዲያውም " #ይማልዳል" ከሚለው በላይ #ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የሚቆም #መካከለኛ መሆኑን #አጠንክሮ ይገልጣል እንጂ #ይፈርዳል ማለትን አያመለክትም፤ #ግእዙን እንኳን የተጠቀምነው #በአገራችን የተለመደ #ጥንታዊ ትርጓሜ ነው በማለት እንጂ #የአዲስ ኪዳን #መጻህፍት ሁሉ በመጀመሪያ በተጻፉበትና ለሁሉም #ትርጓሜዎች መሰረት በሆነው #የግሪክ ቋንቋ በግልጽ #የሚማልደው ተብሎ ተቀምጧል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው #በግሪክ ቋንቋ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም። ይህንን ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለውን ቃል « #የሚፈርደው» ብለው የቀየሩ ሰዎች ራሱ በግሪኩ #የሚያማልደው እንደሚል ራሳቸው ይስማማሉ።(ፎቶው ላይ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ)

@gedlatnadersanat