ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
🔽▶️ *⃣ #ሮሜ 8፥34 እና #የመናፍቃኑ እርስ በእርስ አለመግባባት፦ ‹‹ #የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡34)፡፡ #በልማድ ለያዙት #የተሳሳተ ትምህርት አልመች ያለውና #በምንፍቅና #ጎዳና ላይ ሆነው #የአዳኛችንን #የኢየሱስ ክርስቶስ #የማዳን ግብር የሆነው #የምልጃ ሥራውን ሽምጥጥ አድርገው…
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽

#ቀደም ሲል ከቀረበው "ምንባቡ #ይማልዳል ሳይሆን #ይፈርዳል ነው ማለት የነበረበት" በሚል ከተቀመጠው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" #ሐሳብ የተለየ #ሐሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ #ይማልዳል የሚለውን ይቀበሉና እንዲህ ይላሉ..

〽️ 2፦ ‹‹[መናፍቃን] ለማታለል ሲሉ #በግእዝ #ይማልዳል ብለው ጽፈውታል፤ ቃሉ #ግእዝ ነው #ግእዝና #ፍቺውን የማያውቅ #ሊታለል ይችላል፡፡ እነርሱ ግን ግእዝን ይቃወማሉ፤ #ለማወናበጃ ግን #ሊጠቀሙበት ይሞክራሉ፡፡ #ቅዱስ ዳዊት ግን የቃልህ ፍቺ ያበራል… እንዳለ #ፍቺው ይመሰክርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም
/ #ይማልዳል/ የሚለው #የግእዝ #ቃል ሲሆን #ፍቺው / #ይፈርዳል/ ነው፡፡ አማላጅ ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ በግልጽ ዐማርኛ ‹ #ያማልዳል› ብሎ በጻፈ ነበር፡፡… እስኪ ፍረዱኝ››
📖/፤ (ደምሰው ዘውዴ (መምህር)፣ " ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ" (2001) ገጽ 30)፡፡

▶️ ጸሀፊው መጽሐፍ ቅዱስ በዐማርኛ የተጻፈ መስሏቸው ይሆን? ወይስ ምናልባት #አብርሃም ኢትዮጵያዊ ነው፣ #መልከ #ጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው፣ #ማርያም ኢትዮጵያዊት ናት፣… እንደሚባለው #ሐዋርያው ቅዱስ #ጳውሎስም ኢትዮጵያዊ ነው እያለ ይሆን? እነርሱ እንደ መሰላቸው መጽሐፍ ቅዱስ #በዐማርኛ #ቋንቋ የተጻፈ አይደለም፡፡ ይህን ማንም የሚያውቀው እውነት ነው። #ብሉይ ኪዳን #በዕብራይስጥ #ዐዲስ ኪዳን ደግሞ #በግሪክ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን መላው #ዓለም (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከእነዚህ #ቋንቋዎች ነው ወደ #የሀገራቸው #ቋንቋ የተረጐሙት፡፡ #የእኛ ሀገር ሰዎች (በተለይ ቤተ ክርስቲያናችን) ግን መጽሐፉን ወደ #ዐማርኛ ሲተረጉሙት #የግሪኩ የማይለውን #በማስፈር #እንግዳ ትምህርት ለማስተማር #ምክንያት ሆኑ እንጂ፡፡ ግሪኩስ የሚለው "ኢየሱስ ይማልዳል" ነው። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጉ #በ2000 ዓ.ም #የታተመውን 80 አሀዱ #በሮሜ 8፥34 የግርጌ ማስታወሻ ላይ "ግሪኩ <የሚማልደው> ይላል" የሚለውን ፎቶው ላይ ይመልከቱ።

ሌላው የኚህ ጸሀፊ አስጋራሚ ነገር ከላይ ከቀበረው የተለየ ሐሳብ ካላቸው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" ጋር #አለመስማማታቸው ነው፡፡ ቀደም ሲል ያየነው " #የሚማልደው ሳይሆን #የሚፈርደው ነው መሆን ያለበት #የሚማልደው የሚለው የተቀየረ ነው። #መናፍቃን የጨመሩት ነው ሲል" ከዚህ የተለየ ሀሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ " #የሚማልደው ነው መሆን ያለበት ምክንያቱም #የግእዝ ቃል ነውና፡፡ በግእዙ #የሚማልደው ማለት #የሚፈርደው ማለት ነው" በማለት ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

▶️ በክፍል 2(የኢየሱስ አማላጅነት) ላይ #የምልጃ ትርጉም መቅረቡ ይታወሳል። በዛ #ትርጉም መሰረት #ይማልዳል የሚለው ቃል #ይፈርዳል ተብሎ ሊተረጎም የሚችልበት ምንም ዓይነት አግባብ እንደ ሌለ መመልከት ይቻላል። በመሆኑም ጸሀፊው የሌለ #ትርጉም በመስጠት ሰውን #ለማሳሳት እየሞከሩ ነው ከማለት ያለፈ ሊባል የሚችል ምንም ነገር የለም።

ይቀጥላል...(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ብዙ ሴቶች #ማርያም በሚል ስም ይጠራሉ[1]። [ለምሳሌ]👇 〽️ 1፦ "የሙሴ እህት ማርያም" /ዘጸ 2፥4-8/ ▶️ የዚችን #ማርያም ታሪክ #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ስናይ #ወንድሟ #ሙሴ በወንዝ #ዳር #በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን #ለማወቅ ስትመለከት ወደ ወንዙ የመጣችውን #የፈርኦንን #ልጅ #በጥበብ አነጋግራና #እንድታጠባው የገዛ #እናታቸውን #በሞግዚትነት ስም አገናኝታ…
▶️ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ለ"ማርያም" ለሚለው ስም የተሰጡ #ትርጉሞች #የቤተስክርስቲያን #አባቶችም ሆኑ #ወጣት #ሰባኪያንና #ህዝቡም በብዛት የሚያውቁት #የተለመደ #ትርጉም ነው። የሚገርመው ደሞ #የስሙ #ትርጉሞች ብዙ #ማርያም የተባሉ #ሴቶች እያሉ ማእከል ያደረገው ግን #የጌታችን #እናት #ድንግል #ማርያምን ብቻ ይመስላል። እነዚን #ትርጉሞች ይዘን ለሌሎች < #ማርያም> ለተባሉ #ሴቶች ትርጉሙን ብንሰጣቸው #የትርጉሙ #ባለቤቶች ራሱ #ይሸማቀቁበታል። [ለምሳሌ]፦
#በስም #ደረጃ ከክርስቶስ እናት ጋር #ምንም #ልዩነት ላልነበራት #ለመግደላዊት #ማርያም ትርጓሜውን ብንሰጣት
< #ማርያም> ማለት < #ፍጽምት ማለት ነው>። #መልክ #ከደም #ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን #ንጽሐ ሥጋ #ንጽሐ ነፍስ #በድንጋሌ ሥጋ #በድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችንና ብንል #በወንጌል እንደተገለጸው #መግደላዊት #ማርያም #ድንግል አልነበረችም።

▶️ ሌላውንም #ትርጉም ብናይ (ጸጋ ወሀብት) ለሰው ሁሉ #ጸጋ ሆና #ተሰታለችና#የመንግስተ #ሰማይም #መሪ ናት፤ " #ከፈጣሪ በታች #ከፍጡራን በላይም ነች"፤ #ለሰውና #ለእግዚአብሄር #ተላኪ ናት ብንል፤ ምኗ #ለሰው #ሁሉ #ጸጋ ሆኖ #እንደተሰጠ፣ ማንንስ #መንግስተ #ሰማይ #መርታ እንዳስገባች፣ #ከፍጡራን በላይ ያደረጋትስ ምንድነው ብንል #ሊቃውንት ነን የሚሉ ሰዎች #የተምታታና #የተጋጨ ወይም #የእፍረት መልስ ካልሆነ በቀር #መልስና #ማስረጃ የሌለው ነገር ነው። በመሆኑም ከላይ እንደተጠቀሰውም " #ማርያም" የሚለውን #የስም ትርጉም ለሌሎች " #ማርያም" ለተባሉ ሴቶች #ትርጉሙን ብንሰጠው #የማያስኬድና #ስህተት ሆኖ እናገኘዋለን።

️የስም #ለውጥ ባይኖረውም ብቻ #ትርጉሙ የሚሰራው ለጌታችን እናት #ለድንግል #ማርያም ብቻ ነው #ብንል #እንኳን
" ማርያም << #ፍጽምት በስጋም በነፍስም ነች>> ማለት #ጻድቅ #የለም አንድስኳ {ሮሜ 3፥11} ከተባለው እና ከሌሎች #የመጽሀፍቅዱስ ክፍሎች ጋር የሚቃረን ይሆናል።
በምድር ላይ #ኃጢአትን አላደረኩም፤ #የውርስ #ኃጢአት የለብኝም የሚል #ፍጹም ወይም #ፍጽምት ቢገኝ ኖሮ #ክርስቶስ ራሱ #መምጣት ባላስፈለገው ነበር።

▶️ ሁለተኛውን ትርጉም ደሞ ብናይ #ጸጋና #ሀብት ሆኖ #ለምድር የተሰጠው፤ የተዘጋውንም #የገነትን #ደጅ #በከበረ ሞቱ ከፍቶ #ከተሰቀለው #ወንበዴ አንዱን እንኳ #እየመራ #መንግስተ #ሰማያት ያስገባ፤ #በእግዚአብሄርና #በሰው መካከል ሆኖ #የመካከለኛ አገልግሎት #የሰጠውና #የሚሰጠው ጌታችን መድሃኒታችን #ኢየሱስ እንጅ ሌላ #ማንም አይደለም። ለዚህም እባክዎትን #መጽሀፍ #ቅዱስዎትን ገልጠው እነዚህን #የተጠቀሱ ጥቅሶችን ያንብቡ። {ቲቶ 2፥11-14፣ ኤፌ 2፥8፣ ሮሜ 5፥17፣ ዩሐ 3፥16፣ ሉቃ 23፤ 42-43፣ 1ጢሞ 2፥5፣ ዕብ 7፥24}።

▶️ ሌሎች #ሊቃውንትና #ተርጓሚዎችም << ማርያም ማለት በዚህ ዓለም #ከሚመገቡት ሁሉ #ምግብ #ለአፍ የሚጥም #ለልብ የሚመጥን < #ማር> ነው፤ #በገነትም #በህይወት ለተዘጋጁ #ጻድቃንና #ቅዱሳን < #ያም> የሚባል #ምግብ አላቸው፤ ስለዚህ ሁለቱን < #ማር" እና #ያም> የተባሉትን #ሁለት ፊደላት ስናገጣጥማቸው #ማርያም የሚል ስም #ተገኝቷል ምክንያቱም #እናትና #አባቷ አንቺ ከዚህም ኩሉ #የበለጥሽ #ጣፋጭ #የከበርሽ ነሽ ሲሉ #ማርያም ብለዋታል>> ይላሉ።

▶️ አሁንም ሌላ #ትርጉማቸውን ይቀጥሉና " #ማርያም ማለት #ሠረገላ #ፀሐይ ማለት ነው፤ #መንግስተ #ሰማያት ታገባለችና ፤ አንድም #ማርያም ማለት #ውኅብት #ወስጥወት (የተሰጠች) ማለት ነው፤ እመቤታችን እግዚእትነ ማርያም የተወለደች ዕለት በአባት እናቷ ቤት ውኅብት ወስጥወት ሆና ተገኝታለች፤ ኋላም በዓለሙ ሁሉ #አማላጅ ሆና #ሞታለችና ስለዚህ ውኅብት ወስጥወት (የተሰጠች) ናት" ይላሉ[3]።

️አሁንም እነዚህ #ሁለት #ትርጉሞች የአንድ ሰውን #የጌታችን የመድሃኒታችን #የኢየሱስ #ክርስቶስን #እናት #ድንግል #ማርያምን #ማእከል ያደረገ እንጅ ሌሎቹን #የማርያምን #ስም የያዙትን #ሴቶች ያገናዘበ አይደለም። ሆኖም ግን #የአማርኛውን ፊደል ወይም #ሐረግ ብቻ ተከትሎ < #ማር> እና < #ያም> በሚል የተከፋፈለ #ትርጉም መስጠት #አዋጭነት የለውም። ምክንያቱም ስያሜው #የእብራይስጥ #ቋንቋ እንጅ #የአማርኛ ወይም #የግእዝ አይደለም። እንደዛም እንኳን ቢሆንና ብንወስደው < #ያም> የሚባል #ቅዱሳኑ የሚበሉት #ምግብ አለ" ስለተባለው ሁኔታ #መጽሀፍ #ቅዱስም ሆነ ሌሎች መጽሀፍት #በሰማይ #ምግብ እንዳለ አይናገሩም። እንደውም #መጽሀፍ ቅዱስ #እግዚአብሔር #ምግቦችን ሁሉ #በምድር እንዳደረገ ነው የሚናገረው። {ዘፍ 1፤29-31} በተጨማሪም #የእግዚአብሔር ቃል << #መብል #ለሆድ ነው #ሆድም #ለመብል ነው እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንንም #ያጠፋቸዋል>> ይላል {1ቆሮ 6-13}።
በመሆኑም #መብል የእግዚአብሔር ዘላለማዊ #እቅዱ ስላልሆነ #በመንግስተ #ሰማያት አስቤዛ መግዛት መለዋወጥ ምግብ ማብሰል ... የለም፤ #አይኖርምም#አልተጻፈምም። በመሆኑም < #ማር" እና " #ያም> ብሎ ከፋፍሎ #የስም #ትርጉም መስጠቱ #ትርጉም የለሽ ይሆናል።

▶️ ሌላው << #ለዓለሙ ሁሉ #አማላጅ ሆና #ሞታለችና #ማርያም ማለት #ስጦታ ማለት ነው>> ብሎ መናገርና መጻፍ #ስለበደላችንና #ስለሐጢአታችን #በቀራኒዮ #መስቀል አደባባይ ላይ #የሞተውን ለይቶ #አለማወቅ ወይም #ክህደት ነው። #ለዓለም ሁሉ #ኃጢአት #አስታራቂ እንዲሆን የተሰጠንና ከአባቱም ጋር #ያስታረቀን ስለበደላችን #የሞተልን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ብቻና ደግሜ እላለሁ #ብቻ ነው። {1ጢሞ 1፥15፣ ሮሜ 3፥23፣ ሮሜ 5፥8፣ ሮሜ 8፥34፣ ዕብ 7፥24}።