ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
Photo


#ስለዚህም ይህ " #መናፍቅ #የጨመሩት ነው" የሚለው ንግግር ሆን ብሎ ሰውን ለማሳሳት #የተፈጠረ መላምት ነው ከማለት ያለፈ ሊባል የሚቻለው ሌላ ነገር የለም። ይህ ራሱ #የአንዳንዶች #የማታለያ #ዘዴ ብቻ ነው እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቃሉ #እውነት እንደሆነ #ከጥንትም እንደነበረ ራሳቸውም ማመናቸው ተራጋግጧል።
ለምሳሌ፦
#ማኅበረ ቅዱሳን #ለተሐድሶ መልስ እሰጥበታለሁ ብሎ በለቀቀው ድምፅ ወምስል (ቪሲዲ) ላይ " #ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ" ይህን ጥቅስ በተመለከተ ‹‹ #ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለው ቃሉ አለ፤ #ከጥንቱም #ከግሪኩ አለ›› የሚል #አስተያየታቸውን መስጠታቸውን መመልከት ይቻላል፡፡
(ማኅበረ ቅዱሳን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን ብለው የተነሡ ፕሮቴስታንቶች በሚያነሧቸው ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መልስ 2ኛው ድምፅ ወምስል፣ (መስከረም 2010)፣ 8፡11-8፡15 ደቂቃ፡፡)

ዞሮ ዞሮ ይህም የሆነው #እውነትን ደብቆ #መቀመጥ ስለማይቻል ብቻ ነው። ከዚህም በተጨማሪ #አባቶቼ እያሉ የሚጠሯቸው ፣ #መታሰቢያም የሰሩላቸው #አባቶች ይህን ቃል የተረዱት የዛሬዎቹ አንዳንድ መምህር ተብዬዎች ከሚያስቡት በተቃራኒ ነው።
@ ለምሳሌ፦
#ዮሐንስ አፈወርቅን ብንመለከት #የሮሜ መልእክትን በተረጎመበት
/" #ድርሳን 15" ይህን ቃል #እንደወረደ ተጠቅሞታል።
እንዲህ ብሏል ፦
<< #ቅዱስ ጳውሎስ " #ስለ እኛ #የሚማልደው"ብሎ #ለሥጋ እንደሚገባ አድርጎ የተናገረው #ፍቅሩን #ይገልጽ ዘንድ #በታላቅ #ትህትና የገለጸው ነው>>
ብሎ ጽፏል።
#አስተውሉ #ዮሐንስ #አፈወርቅ #የጳውሎስ ጹሕፍ ምን እንደነበረ
#ሲገልጽ እነመለከታለን።
#ጳውሎስ " #የሚማልደው"ብሎ እንደጻፈ ይህም የክርስቶስን #ትሕትና እና #በሥጋው ወይም #በሰውነቱ #አንጻር #የተነገረ እነደሆነ እና #ጌታ ለእኛ ያለውን #ፍቅር #ለሚያስረዳት የተጻፈ #መሆኑን ገልጿል።
አስተውሉ!!
#ዮሐንስ አፈወርቅ #መናፍቅ ነበር እንዴ? ነው ወይስ
#የመናፍቃንን #መጽሐፍ ቅዱስ
ነው የተረጎመው? ነው ወይስ
#እናንተ #አባታችን ከምትሉት #ዮሐንስ አፈወርቅ #ትበልጣላችሁ? ነው ወይስ
#ተሳስቶ ነበር? ምንድን ነው #የምትመልሱት?
*
#ይህም ብቻ አይደለም የክርስቶስ #አማላጅነት #ከአብ #ያንሳል ማለት እንዳልሆነ
፣እኛን ለመርዳት አቅም ስለሌለው #መለመን አስፈልጎት እንዳልሆነ ነገር ግን
ለእኛ ያለውን #ፍቅር ለማሳየት እንደሆነ ገልጿል።
#ይህን ቢገልጽም #የጳውሎስን
#ቃል #መናፍቃን #የጨመሩት ነው አላለም።
ነገር ግን ከጳውሎስ #የሰማውን ቃል #እርሱም ተቀበሎ እየደጋገመ ይናገረዋል ።
ለምሳሌ ፦

<< #ክርስቶስ አሁን #በክብሩ #የሚታይ ቢሆንም #ርኅራኄውን ከእኛ #አላራቀም #ስለእኛ
#ይማልዳል #እንጅ>>


<< #እንግዲህ #መንፈስቅዱስ ራሱ #በማይነገር #መቃተት #የሚማልድልን ከሆነ #ኢየሱስም #ሞቶ #የሚያማልደን ከሆነ #አብም #ለአንተ ሲባል #ለልጁ #ካልራራለት #አንተን #ከመረጠህ #ካጸደቀህ ከዚህ ሌላ በምን #ትፈራለህ?>>


<< #እግዚአብሔር #ዘውዱን አቀዳጅቶናል። #የሚኮንነንስ #ማነው? #ክርስቶስ #ሞቶልናል #መሞት ብቻ አይደለም ከዚህም በኋላ #ለእኛ #ስለሚማልድ ማን
#ይኮንነናል? >>
📖/፤ ሐመረ መጽሄት ሐምሌ 2007 ገጽ 10
በማለት ያብራራዋል።
#ለመሆኑ > #ዮሐንስ #አፈወርቅ< እንዲህ እየገለጸው እያለ
#መናፍቃን #የጨመሩት ነው #የምትሉት ከየት አምጥታቹ ነው? እናንተ #ሰዎች ሆይ #ከስህተታችሁ ታረሙ።
#ይህ " #ዮሐንስ #አፈወርቅ" ዕብራውያን 7:25ን በተረጎመበት ድርሳን 13 ላይ
የሮሜን መልእክት ለማስረጃ ጠቅሶታል።
ሮሜ8:34 ላይ የተጻፈውና ዕብ7:25 ላይ የተጻፈው ቃል #ተመሳሳይ እንደሆነ ያስረዳል። ይህ ዮሐንስ አፈወርቅ
#የክርስቶስን #አማላጅነት #ከፍቅር #አንጻር ይመለከተዋል ለምሳሌ፦
ዮሐ17:9-21
ያለውን #የጌታን #ምልጃ እንዲህ ገልጾታል ፦
*
<< "I pray not that You should take them out of the world, but
that You should keep them from the evil."
Again He simplifies His language; again He renders it more
clear; which is the act of one showing, by making entreaty
for them with exactness, nothing else but this, that He has a
very tender care for them. Yet He Himself had told them,
that the Father would do all things whatsoever they should
ask. How then does He here pray for them? As I said, for
no other purpose than to show His love .>>
በማለት የጸለየው የፍቅር መገለጫ መሆኑን በድርሳን 82 ገልጾታል ።
ራሱን ያለምስክር የማይተው ጌታ በእነዚህ ሰዎች ሞስክር አአስቀምጧል ።

እንግዲህ መጀመሪያ #በግሪክ የጻፈው #ሐዋርያ ስለእኛ #የሚማልደው ካለ አባቶቻችንም ይህንን #እውነት ካጸኑልን ታድያ ይህንን #በመንፈስ ቅዱስ በተሰጠ #ሐዋርያዊ ስልጣን የተጻፈን ቃል #የመለወጥ ስልጣን ያለው አለን? #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን #እንመን? #ወይስ #እነርሱን?
አስቡበት!!

#ይህም ብቻ ሳይሆን ‹ #ስለ እኛ #ይፈርዳል› ተብሎ የተተረጐመው ቃል #ስሕተት የሆነው ንባቡ በመተርጎሙ ብቻ ሳይሆን፤ #በሕገ #ሰዋስው መሠረት ሲታይ ሐረጉ #በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ እንዲገልጽ #የተፈለገውን ሐሳብ ስለማይገልጽና ሌላ #ትርጕም ስለሚሰጥም #ጭምር ነው እንጂ፡፡ በዐማርኛ ሰዋስው ‹ #ስለ እኛ ይፈርዳል› የሚል ንባብ " #ለእኛ ይፈርዳል› ወይም " #በእኛ ይፈርዳል" የሚል #ትርጕም ሊሰጥ አይችልም፡፡ የሚሰጠው #ፍቺ በእኛ ምትክ፣ #እኛን #ወክሎ #ይፈርዳል የሚል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቃሉን የለወጡት ሰዎች ቃሉ እንዲናገርላቸው የፈለጉትን ‹ #ለእኛ ይፈርዳል› ወይም " #በእኛ ይፈርዳል" የሚለውን #ሐሳብ አይጠራላቸውም፡፡ እንዲያውም ያልጠበቁትን #ትርጕም ይሰጥባቸዋል፡፡ የተፈለገውን #ትርጕም ይሰጥ ዘንድ ‹ #ስለ› የሚለው መስተዋድድ #ይፈርዳል ከሚለው ግስ ጋር ሳይሆን #ይማልዳል ወይም #ይከራከራል ከሚለው #ግሥ ጋር ነው ሊሄድ የሚችለው››፡፡

ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
<<ሁሉም ወደ #አምላኩ ወደ #እግዚአብሔር አንጋጦ #ሲለምን በአየን ጊዜ #መንፈሳዊ #ቅንዓትን ቀንቶ #ገሰጻቸው። በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች #አምላክን ወደ ወለደች ወደ ክብርት #እመቤታችን #ማርያም ለምን #እርዳታ አትሹም እርሱዋ #ከቅዱሳን ሁሉ #ድንቅ ድንቅ #ተአምራትን የምታደርግ፣ #ፈጥና #የምታደርስ #ልመናን የምትሰማ ናትና አላቸው። በዚያችም ጊዜ #ተአምራትን ወደ ምታደርግ #በድንጋሌ #ስጋ #በድንጋሌ #ነፍስ ወደ ጸናች ወደ ክብርት እመቤታችን #ማርያም ለመኑ .... የሃገሩም ሰዎች #እመቤታችንን አመሰገኑ[1]።>>

<<እግዚአብሔር #ሲመሰገን #ግሣጼ መጣ #ስለማርያም ግን #ምስጋና ሽልማት ይሆናል #ቀሲስ #እንድርያስም #የማርያምን #ቅዳሴ #ዘወትር ይቀድሳል #ከእርሷም #በቀር ሌላ #ቅዳሴ አያውቅም ነበር ... #ኤጲስቆጶሱ ጠርቶ ሁልጊዜ #ከአንድ #ቅዳሴ በቀር ለምን #ለእግዚአብሄር #አትቀድስም ብሎ ተቆጥቶ #እንዳይቀድስ ቢከለክለው #ማርያም ተገልጣ #የእኔን #ቅዳሴ ሲቀደስ አገልጋዩን #ያወገዝከው ለምንድን ነው? ... #በክፉ #አሟሟት እንድትሞት #በእውነት እነግርሃለው አለችው #ኤጲስቆጶሱም ከዛሬ ጀምሮ #ከእመቤታችን #ቅዳሴ በቀር ሌላ #ቅዳሴ #አትቀድስ አለው[2]።>>

▶️ ከላይ ያየነው ሁሉ #ስለማርያም የሚናገሩት #አዋልድ #መጽሀፍት #ከእግዚአብሄር ይልቅ #ማርያምን የሚያስበልጡና እርሷን #ስለማምለክ የሚያሳዩ የጠቀስናቸው #ጥቂት #አጸያፊ #ክፍሎች ሲሆኑ ከዚህ በታች ደግሞ #ከእግዚአብሄር ጋር ባልተናነሰ መልኩ #ስትመለክና #ስትመሰገን የሚያሳዩ #ጥቂት #ክፍሎችን ደግሞ #በመገረም እንመልከት፦

<< #ለአብ #ምስጋና ይገባል፣ #ለወልድ #ምስጋና ይገባል፣ #ለመንፈስ ቅዱስም #ምስጋና ይገባል፣ #አምላክን #ለወለደች #ለእመቤታችን #ድንግል #ማርያም #ምስጋና ይገባል[3]>>

ይህም ማለት #ከአብ #ከወልድና #ከመንፈስቅዱስ ጋር #እኩል #ምስጋና የምትቀበል #የስላሴ 4ተኛ #አካል ሆነች ማለት ነው። በሌላ መጽሐፍም
<<ወላዲተ አምላክ ማርያም ሆይ፥ ጧት ስነሳ #እግዚአብሔርንና #አንቺን እመቤቴን #በጸሎት #እንዳመሰግን የሚያነቃቃ መንፈስ ኅሊና አሳድሪብኝ፤[4]>> ይላል።

▶️ ከዚህም የከፋ #ማርያም እንደ #አምላክ #እግዚአብሔር ደግሞ ከእርሷ #ዝቅ ብሎ #እንደመማለጃዋ ሆኖም የቀረበበትን #መጽሀፍ ደግሞ እስኪ እንታዘብ ፦

<< #ዘጠኝ ወር #የተሸከምሽው ከሃሊ በሚሆን #ከጡትሽ #ወተቱን ባጠባሽውም #ልጅሽም #በሰው ልጅ ላይ #ቸርነቱና #ይቅርታው በበዛ #በአባቱ... #በእግዚአብሄርም #እማጸንሻለው #እማልድሻለሁ #እለምንሻለሁ[5]>> ይላል።

▶️ ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊና #አጸያፊ የሆኑ #አዋልድ መጽሀፍት ይዞ እግዚአብሔርን #አመልካለሁ ማለት ራስን #ማታለል ነው። እግዚአብሔር ግን <<እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ>> |ኢሳ 40፥25] ደግሞም <<እንደ እኔ ያለ ማን ነው ይነሳና ይጣራ ይናገርም>> ይላል እግዚአብሔር [ኢሳ 44፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
___________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ህማማት፤ ዘረቡዕ በ1 ሰአት በነግህ የሚነበብ፤ ገጽ 394፤ ቁጥር 1-13፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፥ 1996 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ሕማማት" ዘሐሙስ በመዓልት በ11 ሠዐት የሚነበብ፤ ገጽ 587 - 588 ቁጥር 1፤ 10 ፤ 1996 ዓ.ም።

[3] 📚፤ ተስፋ ገብረስላሴ፤ "ውዳሴ ማርያም ምስለ መልክዓ ማርያም በአማርኛ"፤ የዘውትር ጸሎት፤ ገጽ 6 ፥1986 ዓ.ም።

[4] እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 15።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ 3ተኛ ዕትም፥ ምዕ 102፥7፤ ገጽ 170፤ ትንሳዔ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።