አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
477 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

መተዋወቅ አለብኝ፡፡ ውስጤ አሻፈረኝ ሲል ይታወቀኛል።አሁንም ፈዝዤ ዐይኔን እሷ ላይ እንደተከልኩት ነኝ፡፡ ዐይን ለዐይን እየተጋጨን ነው። እንዳሞራ ጆፌዬን እንደጣልኩባት ያወቀች
ይመስለኛል። በእጄ ነይ እዚህ ጋር ብዬ ምልክት ልሰጣት አሰብኩ፡፡ወዲያው ጭንቅላቴ መልሶ፣ አይ እንደዛማ አይሆንም፤ እንደዛ ድፍረት ይመስላል። እሷን መናቅ ይመስላል፡፡ ያቡ ሌላ ዘዴ መፈለግ አለብህ፡፡ምን ብላት ይሻላል..? አዎ!፣ ልደት...!፡፡ ልደቴ ጥሩ መግቢያ በር
ይፈጥርልኛል!፡፡ የልደት ካርዴን ስቤ በደንብ መጫወት አለብኝ..!

ባለቤቷን ጠራሁና፣ “በይ የልደቴን ግብዣ አንድ ብዬ ባንቺ ልጀምር። እስቲ አንድ ሙሉ ተጋበዥልኝ፡፡ልደቴን እንድታደምቅልኝ የጠራሻትን እዛጋር ለተቀመጠችው መላዕክ የመሰለች ቆንጆም ምትፈልገውን ጋብዢልኝ፡፡ ባለልደቱም እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት:
ልታደምቅ መጥታ ጠፍቼባት እንዳይሆን ብቻዋን የተቀመጠችው፤ አልኳት፡፡

“ኪ...ኪ...ኪ... በጣም አመሰግናለሁ!፣ መልካም ልደት በድጋሚ...::”

“አደራ መላእክቷ ልደቴን ታድምቅልኝ...!”

“ጣጣ የለውም፤ ልደቱ እንዲደምቅ የተቻለንን እናደርጋለ፤”ፈገግ እንዳለች ሄደች:: ወደ ውስጥ ገብታ ጫት ይዛ ወጣችና ከቆንጅዬዋ ልጅ ጋር ቁጭ አለች። እየተሳሳቁ ያወራሉ። ልጅቷ ቀና እያለች ወደኔ ትመለከታለች፡፡ ያልኩትን እየነገረቻት መሆን አለበት። ቀና ስትል ጠብቄ በዐይኔ ያዝኳት:: ጎንበስ አለች። ለሁለተኛ ጊዜ ጠበኳት፤ አገኘኋት፤
እድሉን አላባከንኩትም፤ በግንባሬ ሰላምታ ሰጠኋት። አላሳፈረችኝም፣
ከፈገግታ ጋር አፀፋውን መለሰችልኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልጅቷ፣ ቦርሳዋን ይዛ
ከአጠገቤ መጥታ ተቀመጠች፡፡ ባለቤትየዋ ሺሻዋን አምጥታ አጠገባችን አስቀመጠችና፣

“አደራ፣ ዘመዴ ልደቱ ነው፣ በደንብ ተንከባከቢልኝ፤” አለች እየሳቀች፡፡ ስትስቅ ፊቷ አጥንትና ቆዳ ብቻ እንደቀረው ያሳብቃል።

“ዘመድሽ ዘመዴ ነው አታስቢ፡፡” ልጅቱ ፈገግ ብላ መለሰች፡፡

“እሺ፣ ባለ ልደቱ እንዴት ነህ ...?” አለችኝ ወደኔ ዞራ፡፡

“አለሁ፡፡ እንዴት ነሽ ቆንጂት...?”

“ልደት እንዴት ነው ታዲያ...?”

“አጀማመሩ በጣም አሪፍ ይመስላል። እዚህ ብቻዬን ላከብር መጥቼ፣ አንችን መላዕክት የመስልች ቆንጅዬ እግዜሩ ላከልኝ::”

“ምነው ልደትን ሚያክል ነገር በብቸኝነት?”

“ያው ሰው እያለ ሰው ሲጠፍ ምን ይደረጋል? አንቺን መሳይ ቆንጆ በልደቴ ሊሰጠኝ ይሆናላ!”

“ኪ.ኪ.ኪ...ኧረ? ደግሞ ቆንጆ እያልክ አታሙቀኝ፡፡”

የምሬን እኮ ነው በጣም ታምሪያለሽ፡፡ ፀሎቴን ሰምቶ መሆን አለበት፣ በልደት ቀኔ አንቺን ውብ የላከልኝ፡፡ ይቅርታ ግን ሳንተዋወቅ ለፈለፍኩብሽ፣ ስምሽን ማወቅ ይቻላል...?”

“ምስጢር ምትጠብቅ ከሆነ...”

“ምስጢር በመጠበቅስ አልታማም፡፡ ችግሩ እኔ የምነግራቸው ሰዎች ምስጢር አይጠብቁም እንጂ...”

“ኪ...ኪ....ኪ..፣ ሞዛዛ ነገር ነህ ባክህ፡፡ እሺ ሃናን እባላለሁ።”

“እኔ ያቤዝ እባላለሁ።”

እሺ፡፡” ብላ ዝም አለች፡፡

“ተማሪ፣ ሰራተኛ..?” የማልወደው ጥያቄ ሳላስበው አመለጠኝ፡፡ዝም ላለማለት እንጂ፣ ምንም ብትሆን አይገደኝም፡፡

“ሁለቱንም አይደለሁም፡፡”

“ማለት ..?”

“ለግዜው ቦዘኔ ነኝ፡፡” ፈገግ አለች፡፡

“እንዴ! ምንም ሳይሰሩ መኖር ይቻላል እንዴ?”

“እንግዲህ እኔ እየኖርኩ ነኝ ባይ ነኝ፡፡”

“ሃ...ሃ... ከተቻለ፣ ለእኔም ንገሪኝና እንዳቺ አምሮብኝ ልቦዝን፡፡”

“ቀልደኛ ነህ፡፡ ስራን የመሰለ ምን ነገር አለና ነው፣ ልቦዝን ምትለው?”

“አንቺ ነሽ ቀልደኛ፡አንቺን የመሰለ ቆንጆ እንዴት ስራ ያጣል?”

“በቁንጅና ነዉ እንዴ ስራ ሚገኘው? ለነገሩ ለግዜው ነው ያልኩህ፡፡”

“እንደዛ አትዪም ታዲያ፤ እሺ ምን ነበር የምትሰሪው?”

“እንዴ... ምነው እንዲህ አጥብቀህ ጠየከኝ? ልትቀጥረኝ አሰበክ መሆን አለበት? ኪ.ኪ.ኪ...፣ እሺ ፊልም ነበር የምሞክረው።"

“ዋው! በጣም ደስ ይላል። አክትረስ ነሻ?”

“እንደዛ ነገር፣ ሙከራ...።”

“አንተስ ምንድነው የምትሰራው?”

“ዶሮ እርባታ ነገር እየሞከርኩ ነው::”

በቀደም ለሳሚ የነገረኩትን ውሽት ለእሷም ደገምኩላት፡፡ ተስፋ የቆረጠ ስራ ፈትን ማን ይፈልጋል፣ አይደለም እቺን የመሰለች ውብ፡፡ ለወራት የጠፋውን የፆታ
ፍላጎቴን፣ ኬት ጎትታ እንዳመጣችው ገረመኝ፡፡ በባሌም በቦሌም ብዬ መጥበስ አለብኝ፡፡” ብዬ አሰብኩኝ፡፡

“አሪፍ ነው፡፡ ጎበዝ፡፡”

“በደረቁ አደረኩሽ አይደል? ፈታ በይ የፈለግሽውን እዘዢ፡፡ ዛሬ የደስታዬ ቀን ነው፡፡” ሃናን ተግባቢና ቀለል ያለች የደብረ ዘይት ልጅ እንደሆነች ተረዳሁ፡፡ አጥብቆ ጠያቂነቴ ግን አልተመቻትም፡፡ባለቤቷን ጠርቼ ተጨማሪ ሺሻና ምትጠጣውን አዘዝኩላት፡፡ ተቀብላ ማጨስ ጀመረች፡፡ አጭሳ ከአፏ የምታወጣው ጭስ ብዛት ይገርማል፡፡ጭሱን በትኩረት እስከ መጨረሻው በዐይኗ ትከተዋለች፡፡ ጭሱን
አፍጥጣ ስትመለከተው፣ ከውስጡ አንድ የሆነ መልስ ወይም መፍትሄ ምትፈልግ ትመስላለች፡፡ እንደዛ ሆና ሳያት፣ በውብ መልኳና የተመቸው በሚመስለው ሰውነቷ የተጋረደ መከፋት ያየው መሰለኝ፡፡ ሳላስበው እቺን የመሰለች ልጅ ለምን እዚህ ጭስ ውስጥ መደበቅ ፈለገች የሚል ሃሳብ ውስጥ ተዘፈኩ፡፡

“እንካ አጭስ፡፡” ከሄድኩበት ሃሳብ መለሰችኝ፡፡

“እኔ አልወድም፡፡”

“ምንም አይልህም፡፡ ማጨሻ ፒፓ ይምጣልህ?”

“ከሆነማ ያንቺው ፒፓ ይሻለኛል፡፡በዛውም ቆንጆ ከንፈርሽን፣ከፒፓው ላይ እስመዋለሁ፡፡”

“ይሄን ያኸል...? ሞዛዛ፡፡” ብላ ሳቀች፡፡

“የምሬን ነው፣ ከንፈርሽ በጣም ውብ ነው ፤ እንጆሪ ነው ሚመስለው፡፡”

“አመሰግናለሁ!”

“አኔ ደግሞ እንጆሪ በጣም እወዳለሁ፡፡”
ኪ.ኪ.....፣ ደስ ምትል ቀልደኛ ነህ ባክህ፣ ታዲያ ምን ይሻልሃል?”

“ምን እንደሚሻለኝማ በደንብ ታውቂያለሽ የልደቴ ስጦታ ቢሆንልኝ ደስታዬን አልችለውም፤” ብዬ ጠቀስኳት፡፡

“ደረቅ...” ብላ ታፋዬን ቸብ አደረገችኝ፡፡ ሺሻውን ወደኔ ዘረጋችልኝ፡፡ ተቀበልኳትና ለማጨስ ሞከርኩ፡፡ ትን ብሎኝ ያስለኝ
ጀመር፡፡

“ኪ.ኪ.ኪ፣ እውነትም አጭሰህ አታውቅም፧” ብላ ተቀብላኝ ማጨሷን ቀጠለች፡፡ ሳቀርባት ሰተት ብላ እየቀረበችኝ ነው፡፡ ምፈልገው ድረስ ስቤ ብወስዳት ምትጎተትልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ለመሞከር ዝግጁ ሆንኩ፡፡ በደንብ ዘና ብላ መጫወት ጀምራለች፡፡ ባለ ቤትየዋ፣ በየመሃሉ እየመጣች፣ “ተጫወቱ፣ አሁንማ እኔን እረሳችሁኝ፤” ትለናለች፡፡ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ሳወራት፣ ታፋዋን እየነካካው፣ እጆቿን እያሻሸሁ ነው፡፡
ምንም ክልከላ አልገጠመኝም፡፡ ሰዓቴን አየሁና፣

“ስዓቱ እንዴት ሄደ?”

“ስንት ሰዓት ነው?”

“አስራ አንድ ሊሆን ነው፡፡”

“ወሬ ይዘን አልታወቀንም፡፡”

“ኢንስታይን፣ “ከቆንጆ ሴት ጋር ሲሆኑ ሰዓቱ እራሱ ይሮጣል፣ ምቀኛ ነው፧' ያለው እውነቱን ነው ለካ፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ.፣ መቼ ነው የነገረህ?”

“ሃሃሃ...፣ ኧረ የት አግኝቼው? አለ ሲባል ሰምቼ እንጂ፡፡ እዚህ ሃገር ሁሉ ነገር አሉ አይደል...”

እጆቼን ወደ ፈለኩት እየስደድኩ ነው፡፡ አሁንም ክልከላ የለም፡፡ሳማት፣ ሳማት የሚል ስሜት ከቅድም ጀምሮ ወጥሮ ይዞኛል።ልቆጣጠረው የምችለው ስሜት አይደለም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ
አሰብኩ፡፡ ደግነቱ ዛሬ፣ ብዙ ደምበኛ የለም፡፡ ነፃነት ተሰምቶኛል፡፡

“ተጫወት እንጂ! ዝም አልክ፡፡ ምን እያሰብክ ነው?” አለችኝ፡፡

“ያው ስላንቺ ነዋ፡፡ ውበትሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ሳማት፤ሳማት
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ያው ስላንቺ ነዋ፡፡ ውበትሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ሳማት፤ሳማት፤ ይለኛል፡፡ ደግሞ ምርጥ ልጅ ነሽ፡፡ በፍፁም ላስቀይምሽ የማልፈልጋት አይነት ቆንጆ ነሽ፡፡ እንደ ድፍረት ቆጥረሽብኝ እንድታኮረፊኝ ደግሞ አልፈልግም፡፡ ምናባቴ ላድርግ ብዬ እያሰብኩ
ነበር፡፡” ከንፈሯን እያየሁ ደግሜ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡

“አንተ እብድ. አታረገውም አይባልም እኮ፤” አለች ዐይኗን አፍጥጣ፡፡

ዝም ብዬ አየኋት፡፡

«ባይዘዌ ግልፅነትህ በጣም ደስ ብሎኛል። ስሜትህን በግልፅነት
መንገርህ፣ ያንተንም ስልጡንነት ያሳያል፤” አለችኝ ::

ደስ ብለኸኛል...? አሁን መድፈር አለብኝ፡፡ ብስማት ምንም አትለኝም፡፡ ከዚ በላይ ምን እንድነው ምጠብቀው? በመጀመሪያ ቀን ልሳምሽ ስላት፣ አፏን አውጥታ እሺ እንድትለኝ ነው? ስሜቴ ከምቆጣጠረው በላይ ሆነ፡፡ አድርገው አድርገው ይለኛል፡፡ በዐይኔ የቤቱን እንቅስቃሴ እከታተላለው፡፡ አሁን ቤቱ ባዶ ሆኗል፡፡ ባለቤቷም ውጪ
ከወጣች ቆይታለች፡፡ ላድርገው? በድንገት ብትገባብንስ? ደግሜ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ጋድ! አሁን ሂድልኝ ቢባልኮ እንዲህ አይሮጥም፡፡

“ስዐቱ በጣም ሄደ፡፡ ወደ አገርሽ ሄደን ደግሞ፣ ልደቴን በፈሳሽ ብናከብር ምን ይመስልሻል? እዚሁ አስራ ሁለት ሰዓት ሊሆንኮ ነው፡፡”

“እዛማ የማውቀው ሰው ሊያየኝ ይችላል። ባይሆን እዚህ ምታውቀው ቤት ካለ...?”

“ችግር የለም፡፡ መኪና ይዣለሁ፡፡ እዛው ሰው ማያየን ቦታ እወስድሻለሁ።” ዝም አለች፡፡ ዝምታ መስማማት ነው፡፡ ባለቤቷ
መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ባለቤትየው ወዲያው እስክትመጣ አድፍጬ መጠባበቅ ጀመርኩ ባለቤትየዋ ወድያው
ብቅብላ፣

“ተጫወቱ! ዝም አላችሁ፡፡ ምን ይጨመር...?” አለችን፡፡

“ሂሳብ ስሪልን፤” አልኳት፡፡ እዚህ ተጨማሪ ሰዓት ማባከን አልፈፈለኩም፡፡

“እሺ!” ብላ ልትሰራልን ወጣች፡፡ ከሃናን ጋር እየተጠጋጋን ሳናስበው ተጣብቀናል፡፡ ሙቀቷ ይሰማኛል፡፡ ሂሳብ ከፈልኩና፣

ተነሽ እንውጣ!” አልኳት ልብሴን እያረጋገፍኩ፡፡

እሺ ግን፣ አብሬህ አልወጣም፣ አንተ ውጣና ውጪ ጠብቀኝ፡፡”

አላንገራገርኩም፡፡ የመኪናዬን አይነትና ያቆምኩበትን ቦታ ነግሪያት ወጣሁ፡፡ አላስጠበቀችኝም፤ ቶሎ መጣች፡፡ የዱከምን ከተማ ወደኋላ እየተውኩ፣ ወደ ደብረዘይት ነዳሁት። ልደቴን ደስ የሚልና ልዩ እንዳደረገችልኝ፣ ስለ ልዩ ውበቷ፣ ስለ ከንፈሯ ልዩነት እያወራሁ በፍጥነት እከንፋለሁ፡፡ በአንድ እጄ መሪ ይዤ በሌላው እጄ በስስ ታይት የተሸፈኑት ታፋዎቿ መሃል ገባሁ፣ ሙቀቷ ረመጧ ለበለበኝ፡፡ እጄን አወጣሁትና እጆቿን ያዝኳቸው፡፡ በላብ ረስርሰዋል፡፡ ጣቶቼን በጣቶቿ መካከል ሰገሰኳቸው፡፡ አጥብቄ ጨመኳቸው፡፡ ምንም አታወራም ዝም.
ብቻ፡፡ ሁሉም ተፈቅዷል፡፡

በስሜት ባህር ቀልጠን ሰምጠናል፡፡
ወደ ክፍሌ በፍጥነት እየነዳሁ ነው፡፡ ወዴት ነው እንኳ ሳትለኝ ትከተለኛለች፡፡ ልከመርባት ቸኩያለው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ አምናኛለች፡፡ እንደበግ
እየተጎተተችልኝ ነው፡፡ የፈለኩትን ሁሉ ፈቅዳልኛለች፡፡ ከራሴ ሰውነት የሚወጣ ሙቀት በሸሚዜ አልፎ ፊቴን ይልፈኝ ጀመረ፡፡ ወደ ክፍሌ በሚወስደው የውስጥ መንገድ ታጠፍኩ፡፡ አሁንም ምንም አላለችም፡፡ ትንሽ እንደነዳሁ ከፊቴ ያለ ሚኒባስ አስፓልቱ ላይ መንገድ ዘግቶ ቆመ፡፡ ቸኩያለው፡፡ ደርቤ ላልፈው ስል፣ ከፊቴ ሌላ መኪና እየመጣ ነው፡፡
አክለፈለፈኝ፡፡ ወዲያው ሚኒባሱ ተንቀሳቀሰ፡፡ ጠጋ ስል፣ የተሰበሰቡ
ወጣቶች ተቆፍሮ የነበረውን መንገድ ያስተካከሉበት ገንዘብ እየጠየቁ
ነው፡፡ ግዜ የለኝም፣ እጄን ወደ ኪሴ ሰድጄ ያገኘሁትን ብር ሰጠኋቸው፡፡

“ያራዳ ልጅ...፣ ያራዳ ልጅ...

ይመችሽ...፡፡

መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ፡፡”

በዜማ አዘል ምርቃት ሸኙኝ፡፡ ስንት ሰጥቻቸው ይሆን? ለነገሩ ስንትስ ብሰጣቸው፣ እኔ ይሄን የመሰለ መና ወርዶልኝ...፡፡ 'መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ' ያሏት ምርቃት ከእዕምሮዬ ቀርታ በግድ ፈገግ አደረገችኝ፡፡ ቪትሴን ንቀዋት ነው? ለኔ ሃመሬ ናት፡፡

የክፍሉን በር፣ እንዴት ከፍቼ እንደዘጋሁት አላስታውስም፡፡ እንደቆምን በሩን አስደግፌ ተአምረኛውን ከንፈሯን መምጠጥ ጀመርኩ፡፡ በፍጥነት እራቁታችንን ሆንን፡፡ ረጅም ነች፡፡ በቁመት ብዙም አልበልጣትም፡፡ ልከኛ የተነፋፉ ጡቶቿን ለመዋጥ ዝቅ ስል፣ ራቁት
ገላዋን እታች ድረስ ሳየው፣ ከባድ ስሜት ተሰማኝና አልጋው ላይ በጀርባዋ አጋደምኳት፡፡ የገላዋ ልስላሴና የሰውነቷ ሙቀት ስሜቴን አላወሰው፡፡ ከውስጥ ሱሪዋ በስተቀር እራቁቷን ነች፡፡ እላዩዋ ላይ ተለጠፍኩባትና ተንጠራርቼ ከንፈሮቿን ጎረስኳቸው፡፡ በሁለት እጆቿ
ጆሮዎቼን ይዛ፣ ትስመኝ ጀመር፡፡ ትኩሳቴ ሲጨምር ይታወቀኛል፤ ስሜቴ ተንጠራራ፤ እየተሳሳምን እጄን ወደ ፓንቷ ላኩት፡፡ ፓንቷን ላወልቀው ስታገል ተረዳችኝ፡፡ ከንፈሯን ከከንፈሬ ሳታላቅቅ፣ ፓንቷን
እንዳወልቀው፣ እግሮቿን ወደላይ አጥፋ አመቻቸችልኝ፡፡

ስሜቴ በውስጤ ሲፈላ፣ ሲንተከተክ ይሰማኛል፡፡ ዋጣት፤ዋጣት፤ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡ ልውጣት ከከንፈሮቿ ጀመርኩ።
ከንፈሮቿን ሳልጠግብ፣ አንገቷን፣ አንገቷን ሳልጠግብ፣ እየላስኳት ቁልቁል ወደ ጡቶቿ ወረድኩኝ፡፡ እልህ፣ ስግብግብነት፣ ውስጤን ወጥሮታል፡፡ የቱን ይዤ የቱን እንደምለቅ መምረጥ አቅቶኛል።
አንደኛውን ጡቷን እስከቻልኩት ያህል ዋጥኩት፡፡ ከወገቧ ወደላይ
ተንፈራገጠች፡፡ በስሜት ተቃጠልኩ፣ ጨስኩ፣ መትነን ጀመርኩ።መዋጥ አልሆንልህ ሲለኝ፣ እውስጧ መግባት፣ ገብቶ መሰንቀር አማረኝ፡፡ ታፋዎቿን ከፈትኳቸው፤ ያቃጥላሉ፡፡ ይፋጃሉ፡፡ በረጃጅም እግሮቿ፣ በለስላሳ ታፋዎቿ፣ መሀል ተንበረከኩኝ፣ ተርመሰመስኩላት::
በእግሮቿ ወገቤን አቅፋ ጎትታ ከራሱዋ
ጋር አጣበቀችኝ፡፡ እንደተመኘሁት ውስጧ ሰነቀረችኝ፡፡ በሙቀቷ ተቀቀልኩኝ፡፡ እራሳችንን እስክንስት፣ በስሜት ሰረገላ ተመነጠቅን፣ ከአለም ተነጠልን፡፡ ዳግም
የምንገናኝ እስከማይመስል ድረስ፣ ያበጠው ስሜቴ እስኪፈነዳና እስኪተነፍስ ድረስ፣ የቀረን እንጥፍጣፊ ሃይልና ጉልበት አልነበረንም፡፡ እንቅልፍ ወሰደን፡፡ ለእራት እንኳ መነሳት አቅቶን በዛው አደርን፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ፣ እንደሰመመን እንደምታድር በስልክ ስታወራ ስማኋት፡፡

ለሊት ከእንቅልፌ ስባንን አጠገቤ ተኝታለች፡፡ ሳያት በጣም ደስ አለኝ፡፡ ህልም አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ ፀጉሯ ተበታትኗል፣ ረጅምና ማራኪ ሰውነቷ ተበረጋግዷል፡፡ እርሷ ለጥ ብላ ተኝታለች፡፡ አልጋው ውስጥ ተገላብጬ ሰውነቷ ላይ ተለጠፍኩባት። ማታ የጠገብኳት
የመሰለኝ ደክሞኝ ነበር፡፡ ስሜቴ ዳግም ተላወሰ፡፡ አሁንም ውስጤ አልበረደም፡፡ እንድትነቃ አደረኳት፣ እንደ አዲስ እየተንገበገብኩ“እወድሻለሁ፣ በጣም ልዩ ነሽ፣ ስጦጠዬ ነሽ፡፡ እያልኩ እንደተላመደ
ሰው፣ የተለያየ አይነት የወሲብ ልፊያ እየቀያየርን በነፃነት ተላፍተን፣

ተመልሰን ተኛን፡፡ ጥዋት ስነሳ ሰዓቴ አራት ሰዓት ተኩል ይላል።ወላልቀን ስላደርን፣ መነሳት አቅቶን ስንንከባለል አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ ቆየን፡፡ የረሃብ ስሜቱ ሲጠናብን ምግብ ፍለጋ ወጣን፡፡ ምግቡ
በጣም ይጣፍጣል፡፡ተርበን ነበር፡፡ ከበላን በኋላ ድካሙ የባዕ ተጫጫነን፡፡ከትናንት ጀምሮ እረስተነው ወደ ነበረው ወደየ ራሳችን የሃሳብ ዓለም ተመለስን፡፡

“ዛሬም ወደ ቤት አትሸኘኝም?” አለችኝ ሃናን፡፡

“እህ እ! እንዲህ ገድለሽኝ፣ በምን አቅሜ ነው የምሸኝሽ...?” አልኳት ፈገግ ብዬ፡፡

“ኪ.ኪ...ኪ...፣ ጭራሽ እኔ ገዳይ? አላስተረፍከኝም እኮ፣ አውሬ!” የድካም ሳቅ እየሳቀች፡፡
👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


አሁኑኑ መጀመር አለብኝ፤ እንደዋሸኋት ማወቅ የለባትም፡፡ ደስተኛ አድርጋኛለች፡፡ ላጣት ላስቀይማት አልፈልግም፡፡

“እኔ ምልህ ሃብትሽ...፣”

“ወዬ ያቤዝ፡፡”

“ባለፈው ስለ ዶሮ እርባታ ስራ አዋጭነት ስታወሩ ሰምቼ ነበር፡፡”

“አዎ፣ ምነው?”

“እኔም የራሴን ስራ መጀመር እያሰብኩ ነበር፡፡ አዋጭ ከሆነ አግዛችሁኝ እሱን ለምን አልጀምርም?”

“ጥሩ ሃሳብ ነው። ምን ችግር አለው ታዲያ? እናግዝሃለና፡፡ያውም በደስታ!”

ስራውን ለመጀመር ወሰንኩ፡፡ ቤት ኪራይ እንዲፈልጉልኝ ለነአሌክስ ነገርኳቸው፡፡፡ አዳሬ አድካሚ ስለነበር ሳላመሽ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ አልጋ ውስጥ ገብቼም የዶሮ እርባታውን ለመጀመር ሚያስፈልገኝን ገንዘብ በግምት አሰላለሁ፡፡ ስራው ገንዘብ ያስፈልገዋል
የቀረኝ ደግሞ ብዙም አያወላዳም፡፡ ከቤት ኪራይ ሌላ፣ እቃዎችን ጨምሮ
ሌላ ወጪዎች ይኖራሉ፡፡ ገንዘብ ያንሰኛል፡፡ ልበደረው የምችለው ሰው
ደግሞ የለም፡፡ መኪናዬን መሸጥ አለብኝ፡፡ ማሂ ቀድማኝ ደወለች፡፡ አንተ
በቃ ሰው ትዝም አይልህም?' ብላ ወቀሰችኝ፡፡ ለማስተባበል ሞከርኩ፡፡

የሰው ልጅ የህይወት ገመድ ግሩም ነው፣ እጅግም ውስብስብ፡፡ ህይወት ግን መኖር ሰልችቶኝ፣ ፍላጎቴ ጭላንጭል ብቻ ነበረች፡፡ እንደሚበራ ሻማ አይደለችም፡፡ ጭላንጭሉን በቀላሉ እፍ ብሎ ማጥፋት
አልተቻለኝም፡፡ ውስጤ ጨልሞ አስጨናቂና አስፈሪ ሃሳቦችን ብቻ
እንዳላመዠኩ፣ መኖር ከንቱ ልፋት ብሎ ጭንቅላቴ እየነዘነዘ ሰላም እንዳልነሳኝ፣ አሁን ደግሞ ይኸዉ፣ ቀኑንም ለሊቱን ከአንዲት ሴት ጋር የመኖርን አጓጊነት ያሳስበኛል፡፡ መኖርን ያጓጓኛል፡፡ የህይወቴን ገመድ ለመቀጠል ዶሮ እርባታ ስራ ለመጀመር እባዝናለሁ፡፡

ከሃኒ ጋር ጥሩ ተግባባን፡፡ በየቀኑ እንደዋወላለን፡፡ ባጋጣሚ ብንገናኝም፣ ሁለታችንም ሰው ተርበናል፡፡ ከነ አሌክስ ጋር አስተዋወኳት፡፡ እነሱም ወደዋታል። ቆንጅዬና ምርጥ ልጅ ናት፣አፍሰሃል ተባልኩ፡፡ በህይወቴ አዲስ እንደተወለደ ከእርሷ ጋር ማደርገው ሁሉ ብርቅና ልዩ ሆነብኝ፡፡ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እንገናኛለን፡፡ ስሜቴ እሷን ባየ ቁጥር ይለኮሳል፡፡ እናብዳለን፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደከዚህ ቀደሙ ወደ አልጋ አልሮጥንም፡፡ ድሪም ላንድ ሪዞርት ሄደን ተቀመጥን፡፡ቢራችንን እየጠጣን፣ የረጋውን የቢሾፍቱን ሃይቅ ቁልቁል
እየተመከለከትን ከሃይቁ የሚነሳውን ገራም ንፋስ እየተቀበልን እንጨዋወታለን፡፡

“እኔ የምልህ ያቤዝ፣ ልነግርህ የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡”

ስለኬ ጠራ፡፡ አሌክስ ነው፡፡ አነሳሁትና ሃኒ እንዳትሰማኝ ተነስቼ፣ ከእርሷ እራቅ ብዬ ማናገር ጀመርኩ፤ ለስራው ሚሆን ቤት
እንዳገኙልኝ፣ ኪራዩ በወር አራት ሺህ ብር እንደሆነ እና የስድስት ወር ቅድመ ክፍያ እንደሚፈልጉ፣ ከሃብትሽ ጋር ሄደው እንዳዩት፣ ፅድት ያለ ቤት እንደሆነና እንደወደዱት፣ ቶሎ ሄጄ እንዳየውና እንድከራየው ሲነግረኝ፣ ገንዘቡ በጣም ብዙ እንደሆነና ይህን ሚያህል ገንዘብ
እንደሌለኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ስመለስ፣

“ይቅርታ ስላቋረጥኩሽ ሃን፡፡”

“አይ ችግር የለውም፡፡ የሆነ ልነግርህ ምፈልገው ነገር ነበረኝ፤” በቀዘቀዘ ድምፅ፡፡

“ታዲያ ምንችግር አለው፣ ንገሪኛ፡፡”

“ስሜ ሃናን አይደለም፡፡ ማሂ ነው፤” ብላኝ አትኩራ ተመለከተችኝ፡፡

አልመለስኩላትም፡፡ የስም መመሳሰሉ አስደንግጦኝ ዝም አልኩኝ፡፡

“ስለዋሸሁህ በጣም ይቅርታ! ሌላም የዋሸሁህ ነገር አለ፡፡”


“ምንድን ነው?” ውስጤን ፍራት ወረረኝ፡፡ ማላቃትን ልጅ ነው እንዴ የወደድኩት ብዬ አሰብኩ፡፡ መጥፎ ነገር እንዳይሆን
ተመኘሁ፡፡

“ፊልም ነው ምሰራው ያልኩህ...”

“እና ምንድን ነው የምትሰሪው...?”

“አሜሪካ ነበርኩኝ፤ አሁን ትቼው መጥቼ ነው::”

“ለምንድን ነው ትተሽው የመጣሽው..?

“ከዚህ ስሄድም ሳልፈልገው፣ በድንገት ነው የሄድኩት፡፡ የአዋላጅ ነርስ ነኝ፤ እዚህ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ውጪ ስለመሄድ አስቤም፣ ጓጉቼም አላውቅም፡፡ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ እርሱ ደግሞ በተቃራኒው፣ ህልሙ አሜሪካ ነበረች፡፡ እዚህ እየኖረ ነበር ማለት ይከብዳል፡፡ ፌርማታ ጋር ቁጭ ብሎ ባስ እነደሚጠብቅ ሰው፣ አሜሪካ እስኪሄድ ሲጠባበቅ ነበር፡፡ አሜሪካ ለመሄድ ያልሞከረው ነገር የለም፡፡ አንድ ዓመት ላይ ዲቪ ሲከፈት፣
አብረን እንሙላ አለኝ፡፡ ሞልቼ አላውቅም፣ ትዝም አይለኝ ነበር፡፡ እንደባልና ሚስት ሞላን፣ ባጋጣሚ ደረስን፡፡ ብዙ ሰው እንድለኛ ነሽ አለኝ፡፡ እልል ተባለ። በተለይ ነርስ መሆኔ ብዙ እንደሚጠቅመኝ ነገሩኝ፡፡ፕሮሰሱን ጨርሰን አሜሪካ ገባን፡፡

እንደሄድን ከጓደኛዬ ቀድሜ እኔ ቶሎ ስራ አገኘሁ፡፡ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል፡፡ ጓደኛዬም ብዙም አልቆየም፣ ሌላ ስቴት ላይ ስራ አገኘ፡፡ አንድ መጋዘን ውስጥ ተቆጣጣሪ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ በመጀመሪያ ሁሉ ነገር ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ የሆስፒታሉ ንፅህና፣
አደረጃጀት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ክፍያው፣ ብቻ ሁሉም ነገር በጣም ደስ አለኝ፡፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ፣ እርሱም ቢዚ እየሆነ፣ መገናኘት እየከበደ፣ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ እርሱ፣ በትርፍ ሰዓቱ ሌላ ተጨማሪ ስራ መስራት ሲጀመር፣ የምንገናኝበት ጊዜ በጣም ቀነሰ፡፡ ከሳምንታት ወደ ወራት ረዘመ:: ሲደውልልኝም፣ ከድምፁ የምሰማው ናፈቆት ሳይሆን ድካምና መሰልቸት ሆነ፡፡ ለእኔ ቦታ እንደሌለው እየተሰማኝ መጣ፡፡ ብዙ እንጨቃጨቅ፤ እንጣላ ጀመርን፡፡ አትወደኝም እለዋለሁ፤ አትረጂኝም፤
ይለኛል። ሲኒማ እንኳ ከሰው ጋር መግባት ናፈቀኝ፡፡ ማውቃቸው ሰዎች ጋር ደውዬ ሲኒማ እንግባ ስላቸው፣ እስቲ ፕሮግራም ልይ ይሉና፣
(Next Month the last Sundayi am free, we can meet and do it)
የሚቀጥለው ወር የመጨረሻው እሁድ እረፍት ነኝ፣ መገናኝት እንችላለን
ይሉኛል፡፡

እኔ ደግሞ ሰው ነው የራበኝ፡፡ እረሃብ ደግሞ ግዜ አይሰጥም፡፡ሰው ስናፈቀኝ በሁለት ወር ሰው ማግኘት ሰለቸኝ፡፡ ስሜት አልባ በሆኑ፣ በቁሳዊ ነገሮች በሚደሰቱ ሰዎች ብቻ የተከበብኩ ያህል ተሰማኝ፡፡ ጓደኛዬ ከኔ ይልቅ፣ ፍቅር ያለውጠ ለዳላር ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ሁሉም machine
people, with machine brain and machine hearts መስለው ታዩኝ፡፡
የሰው ተፈጥሮ የሌላቸው በውስጣቸው፣ የሰው ፍቅር ርሀብ ማይሰማቸው፣ ዓለምን አስደናቂ፣ ግሩምና ሳቢ የሚደርጓት ቁሶች
ሳይሆኑ፣ ሰውና ተፈጥሮ እንደሆኑ ያልገባቸው ሮሆቦት ሆኑብኝ፡፡ በሰው
መሀል ሆኜ ሰው እራበኝ፡፡ ጥዬው መጣሁ፡፡”

በትካዜ ስሜት ውስጥ ሆና አወራችኝ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አለች፡፡ ደስተኛ ትመስለኝ ነበር፣ ንፁህ ያልደማ ልብ ያላት። ከትረካዋ እርሷም ቁስለኛ እንደሆነች ተረዳሁ፡፡ ላቋርጣት አልፈለኩም፡፡ይውጣላት፡፡ ትተንፍስ ብዬ፣ ዝም አልኳት፡፡ ቀጠለች፡፡

“ለእኔ ህይወት ቁስ አይደለም፣ ማፍቀር ነው! To live is love”! ከጓደኛዬ ተጣላን፡፡ የአሜሪካ ኑሮ በእኔ ዕይን፣ እድሜህን ለመቼ እንደሆነ ለማይታውቀው ነገ ቁስ እየሰበሰብክ፣ ዛሬህን የምታባክንበት ህይወት ነው፡፡ የእኔ ሀገር እዛ አይደለም! ወሰንኩ፡፡ ግን፣ ከባድ ውሳኔ፡፡ብነግራቸው፣ ባስረዳቸው ሚረዳኝ አጣሁ፡፡ ጭራሽ እንደ እብድ ቆጠሩኝ፡፡ጥዬው መጣሁ፡፡ ከመጣሁ አስር ወር አለፈኝ፡፡ እዚህ ስራ ለመጀመር
ወስኜ ነው የተመለስኩት፡፡ ውሳኔዬ ማንንም ደስተኛ አላደረገም፡፡ቤተሰብ፣ ጎሮቤት፣ ጓደኛ፡፡ ሁሉም በእራሳቸው ምኞት፣ ለክተው እያሰቡና እየመዘኑ ስህተት ነሽ ይሉኛል፡፡ ሊመክሩኝ፣ ሊያሳምኑኝ ይጨቀጭቁኛል
👍5
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

ባለፈው ስናወራ፣ ሰው ሞልቶ፣ ሰው ሲጠፋ ምን ይደረግ ስትለኝ፣እንደኔው ሰው እንደራበህ ተሰማኝ፡፡ ሁሉም እንዲሆን በደስታ ፈቀድኩልህ፡፡ እንዲህ እንግባባለን ብዬ ስላልገመትኩ የውሸት ስምና ስራ ፈጥሬ ተዋወኩህ፡፡ ለዛ ነበር የዋሸሁህ፡፡” ዝም አልኳት፡፡

“በቃ ይሄው ነው፤” አለችኝ፡፡

“አንድ ነገር ልንገርሽ”

“እሺ ንገረኝ፡፡"

“ስለዋሸሽኝ አልተቀየምኩሽም፡፡ ግን እኔ ካሁን በኋላም ቢሆን፣ሃኒ ብዬ ነው ምጠራሽ፡፡ ማሂ ሚባል ስም ቆሌዬ አይወደውም፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ...፣ እሺ ባክህ፣ ባለ ቆሌ፣ አንተ ደስ እንዳለህ ጥራኝ፡፡” በአንዴ ፊቷ ከትካዜ ተላቀቀ፡፡ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና “ሃኒዬ፣ ያደረግሺው ሁላ፣ ትክክል ነው፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰንሽው፡፡ ህይወት አንዴ ናት፡፡
አትደገምም፡፡ የአዕምሮ ደስታን፣የመንፈስ እርካታን የማይፈጥሩልሽን ቁሶች ስትሰበስቢ፣ ነብስሽ የምትሻውን ሳታገኚና ሳታጣጥሚ ለመሞት፣መኖር የለብሽም፡፡ ሚዛኑን መጠበቅ አስፈላጊ ነው!መኪና፣ ቤትና፣ሌሎች ቁሶች፣ ቋሚ ደስታ ሚፈጥሩ ሚመስሏቸው፣ እነርሱ ሳይገባቸው ሊያስረዱሽ የሚሞክሩ፣ ስላላዩት ሀገር የሚያወሩሽ፣ ሳይደርሱበት በርቀት እያዩ፣ በምኞት እረሀብ የሚቃጠሉና የሚቃዡ ናቸው፡፡ ተያቸው፡፡ ግራ ገብቷቸው ነው፣ ግራ ሚያጋቡሽ፡፡ እርሻቸው።” ፊቷ ላይ የደስታ ብርሃን
መፈንጠቅ ጀመረ፡፡

ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ “ያቡዬ ስለተረዳኸኝ በጣም አመሰግናለሁ!! አንተ ትክክል ነሽ፣ ያልከኝ የመጀመሪያው ሰው ነህ።እራሴን መጠራጠር ጀምሬ ነበር፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ ትክክል እንደሆንኩ
እንዲሰማኝ አደረከኝ፡፡ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ጥሩ እንዲስማኝ አድርገኸኛል። እወድሃለው፡፡”

ግንባሯን ሳምኳትና፣ “ደስተኛ እንደሆንሽ ስለነገርሽኝ፣አመሰግናለሁ፡፡ እኔም፣ በህይወቴ ተሰምቶኝ የማላውቀውን ደስታ
ሰጥተሽኛል፡፡ አንቺ በጣም ልዩ ሴት ነሽ፡፡ ስላንቺ በደንብ አስብያለሁ፡፡እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፣ የልቤ ንግስት አንጓነሽ፡፡ መቼም በምንም ምክንያት ላጣሽ አልፈልግም፡፡ ከአሁን በኋላ ሁሌም፣ በሁሉም ነገር አብሬሽ ነኝ፡፡ አንቺን ለማስደሰት ምንም አደርጋለሁ፡፡ ምንም!፡፡ አንቺ ለእኔ ልዩ ስጦታዬ ነሽ፡፡ ቀኑ ሲደርስ፣እኔም እንዳንቺ ሙሉ ታሪኬን እነግርሻለሁ። እስከዛው ግን እጅግ በጣም እወድሻለሁ፡፡” እንደዚህ የውስጥ ስሜታችንን ስናወራ አምሽተን ሸኘኋት፡፡

ከሃኒ ጋር በተደጋጋሚ እንገናኛለን፡፡ ሲከፋት፣ ሚረዳት ስታጣ እኔ ጋር ትደውላለች፡፡ የሙያ ፍቃዷ ስለተቃጠለ፣ ስራ መጀመር ከብዷታል፡፡ ቤተሰብ ደግሞ፣ በስራ መፍታቷ አመካኝቶ ያንገበግቧታል።ውሳኔዋ ስህተት እንደነበር እንድታምን በአሽሙር ይወጓታል፡፡ ተከፍታ መጥታ እኔ ጋር አምሽታ ሁሉን እረስታ ወደቤቷ ትመለሳለች። እኔም በእርሷ በጣም ደስተኛ ሆኛለሁ። የእኔ መኖር የሚጠቅመው፣ሚያስፈልገው ህይወት አገኘሁ፡፡ ተደስታ ስትሄድ ማላውቀው ደስታ ውስጤን ይሰማኛል። ስለሷ ማሰብ የህይወቴ ዋና ክፍል ሆኗል፡፡

ከእርሷ ጋር መኖርን ያጓጓኛል። አሁን መኖር አለብኝ፡፡ህይወቴን ሙሉ እርሷን ደስተኛ እያደረኩ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ የሃኒ
ተስፋዋ፣ መከታዋ እኔ ነኝ፡፡ በየቀኑ ከምትነግረኝ ብሶት ልገላግላት ምችለው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ሆቴል ቁጭ ብዬ፣ ገቢ የሌለው ወጪ ብቻ የሆነ፣ ተስፋ የቆረጠ ሰው ንሮዬን አብቅቼ፣ ሰው ሆኜ ለእርሷም
ለመትረፍ በፍጥነት ስራ መጀመር አለብኝ፡፡ የዶሮ እርባታውን ስራ
ማፍጠን አለብኝ፡፡ መነሻ ስንት ብር ያስፈልገኝ ይሆን? አሌክስ ባለፈው
የነገረኝ የቤት ኪራይ ውድ ነው፡፡ ሌላስ የምን ወጪ አለ? ሃብታሙን ደውዬ ያለበት ቦታ ሄጄ አገኘሁት፡፡ ጭንቅላቴ ወር ሙሉ ሲያንቀላፋ ከርሞ፣ አሁን ያጣድፈኝ ጀመር፡፡ እንዳገኘሁት በቀጥታ ወደ ጉዳዩ
ገባሁ፡፡

“ሃብትሽ ያን ጉዳይ ዝም አላችሁኝ እኮ፡”
“የቱን ነው ያቤዝ?”

“የዶሮ ስራውን ነዋ፡፡ ጭራሽ በኛ ጣለው ብላችሁ ዝም አላችሁኝኮ፡፡”

“እ...፣ እሱንማ አንተው ነህ ዝም ያልከው፡፡ ባለፈው አሌክስ ቤት አገኘን ሲልህ፣ ሄደህ እንኳ አላይ ስትል የተውከው መሰለን፡፡”

“እሱኮ ውድ ሆኖብኝ ነው ሃብትሽዬ፡፡”

እሺ፣ ምን አይነት ዶሮ ነው ማርባት ምትፈልገው?”

“ማለት? ዶሮ ነዋ፡፡ ዶሮ ምን አይነት አለው?”

“አለው እንጂ ፤ የስጋ ዶሮ ነው፣ ወይስ የእንቁላል ማርባት ምትፈልገው?”

“እንደዛ ሚባል ነገርም አለ እንዴ? ሃብትሽዬ እኔ ምንም እውቀቱ የለኝም፡፡ ሚሻለውን እናተ ምረጡልኝ፡፡ ፕሊስ ሃብትሽ.”

“እኔ የእንቁላል ዶሮ ብትጀምር እመክርሃለው። ምክንያቱም፣ የእንቁላል ገበያ አመቱን ሙሉ አለ፡፡ ያ ደግሞ፣ አመቱን ሙሉ በወጥነት የሆነ ያህል ቢሆንም ገቢ አለህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ፣ እንደቤት ኪራይና ሌሎች የወር ወጪዎችን ሊሸፍንልህ ይችላል፡፡ ያው ትንሽ በዛ ሚለው የምግብ ወጪያቸው ነው፣ እሱን ፈልጎ ከአቅራቢ መግዛት ነው፡፡ የስጋዎቹን ካረባህ፣ ምታገኘው ገቢ በአመት በተወሰነ ግዜ በአል ጠብቀህ
ብቻ ነው፡፡ ደግሞ ስንት ለፍተህ፣ በሽታ አንድ ነገር ቢያደርጋቸው፣እንዳትነሳ ሆነህ ትጎዳለህ፡፡” አለኝ፡፡

“እውነትህን ነው ሃብትሽ፤ የእንቁላል ይሻለኛል፡፡ አሌክስ ጋር ደውልለትና እረከስ ያለ ቤት ቶሎ ይፈልግልኝ፡፡ ምንም ስራ ሳልጀምር እጄ ላይ ያለው ብር ሊያልቅኮ ነው፡፡ በናትህ ሃብትሽ ቅበሩኝ፡፡” ተጣድፌ አጣደፍኩት፡፡

አሌክስን ደወለለትና፤ ይዤው ቤት ፍለጋ ከከተማው ጫፍ እስከ ጫፍ መዞር ጀመርን፡፡ በሁለት ቀን ከተማ ውስጥ ያሉትን ሰፈሮች አካለልናቸው፡፡ ቤት ውድ ነው፡፡ ለንግድ ሲሆን ደግሞ፣ ከስድስት ወር በታች ቅድመ ክፍያ አይቀበሉም፡፡ በመጨረሻም፣ በወር ሁለት ሺህ ብር
ለስድስት ወር አስራ ሁለት ሺህ ብር ከፍለን ተከራየን፡፡ ቤቱ ባለ ሶስት ክፍል ሲሆን፣ አንዱ እንደመጋዘን ሰፊና አራት መአዘን ነው፡፡ እሱን አናፂ ቀጥረን በስስ ሽቦ ወደ ስምንት የዶሮ መኖሪያ ክፍሎች ቀየርነው፡፡ተስፋ ቢስና ስልቹ የነበርኩት ልጅ፣ እነ ሃብትሽና አሌክስ እስኪሰለቹኝ፣
ጉዳዬን ሳልቋጭ ማይደክመኝ ተስፈኛ ሆንኩ፡፡ እንቁላል ጣይ ጫጩት በርካሽ ገዝቼ ከመጠበቅ አንድ መቶ እንቁላል ለመጣል የደረሱ ዶሮዎችን መርጬ ገዛሁና ስራ ጀመርኩ፡፡ ለአልጋ በየቀኑ የማወጣውን ወጪ ለመቆጠብ፣ አንዱን ክፍል ፍራሽና ብርድ ልብስ ገዝቼ መኖሪያዬ አደረኩት። ሃኒ ምግብ ማብሰያ እቃዎች ገዝታ፣ እቤት እየተመላለሰች
ታበስልልኝ ጀመር፡፡ በዛውም፣ እቤት ያስከፏትን ብሶቷን ስትነግረኝ አምሽታ እራት አብልታኝ ትሄዳለች፡፡

ከሁለተኛው ሳምንት በኋላ፣ እጄ ላይ ገንዘብ ጨረስኩኝ፡፡የዶሮዎቹን ምግብና የእኔን የቀን ወጪ መሸፈን አቃተኝ፡፡ ለሃብትሽ ሳማክረው፣ ስራው ጥሩ ትርፍ የሚኖረው፣ አምስት መቶና ከዛ በላይ
እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሲኖር እንደሆነ ነገረኝ፡፡ እርሱ የነገረኝን ከማመንና ከመፈፀም፣ ወደ ፊት ከመሄድ ውጪ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡ ያንን ለማድረግ ደግሞ መኪናዬን መሸጥ አለብኝ፡፡ ለመሸጥ ያላገባ ሳወጣ፣ እናቴ መኪና ልሽጥ እንደሆነ ጠርጥራ፤ 'ተው ልጄ ተው፣ ምን ሆንኩ ብለህ ነው ንብረት ምትሸጠው? ተው ንብረት ዝም ተብሎ አይሸጥም፡፡ ተው ልጄ፡፡" አለችኝ፡፡ ምክሯን ከቁብ ሳልቆጥረው፣ቆም ብዬ ሌላ አማራጭ እንኳ ለማየት ሳልሞክር መኪናዬን ሸጥኩኝ፡፡ተጨማሪ አራት መቶ እንቁላል መጣል የደረሱ ዶሮዎችንና ምግባቸውን በጅምላ ገዛሁ፡፡

አሁን በገንዘብ እጥረት ሚሰማኝ ስጋት ጠፋ፡፡ ኪሴ ወፍሯል፡፡ግን ገና ከቤት ለመውጣት ሳስብ፣ የታክሲ ጥበቃውና ፀሃዩን
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ጉዞ ወደ አርባምንጭ፤በጥዋት ተነስተን በሚኒ ባስ ተሳፍረን ጉዞ ጀመርን፡፡ሃኒ ከአዲስ አበባ ስንነሳ ጀምሮ መኪናው አልተመቻትም፤ ስትንቆራጠጥ ነው ሻሸመኔ ደረስን አደርን፡፡ ከሻሸመኔ ደግሞ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሳፍረን፣ በወላይታ
ሶዶ አድርገን፣ ጉዞ ወደ አርባ ምንጭ፡፡ መኪናው እላይ አድርሶ ያፈርጠናል፡፡ ደጋግሜ አይዞሽ እላታለሁ፡፡ በእርግጥ እንደዛ ከማለት ውጪ፣ ምንም ማድረግ ምችለው ነገርም የለም፡፡

“መዝናናት ሳይሆን መጉላላት ሆነብሽ?” አልኳት የሚሰማትን ማውቅ ፈልጌ፡፡

“ለምንድነው ግን፣ በቱር መኪና ያልመጣነው?” አለች፡፡

“አቅም ነዋ ሃኒዬ፣ አቅም..! በጣም ውድኮ ነው፡፡ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር፣ አይከብድም...?”

“ኖ...! እንደሱ ሳይሆን፣ ኮስትር በጋራ ከሌላ ጎብኒዎች ጋር ሆነን ማለቴ ነው፡፡”

“እንደዛ አይነት ፓኬጅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሰምቼ አላውቅም፡፡
ሙሉ ኮስትር ግን ይባስ ውድ ነው፡፡”
“ለምን እንከራየዋለን? እንደኛ አርባ ምንጭን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጓዦችን አሰባስቦ የሚሄድ፣ የአስጎብኚ ድርጅቱ ጋር ሁለት ትኬት ገዝተን ብንሄድ ነው ምልህ፡፡ እንደውም፣ አስጎብኚ ስለሚኖር ብዙ ነገሮችን ማየት እንችላለን፡፡”

“እንደምትዪው አይነት ጉዞ ሰምቼ አላውቅም፡፡ በአስጎብኚዎች የሚዘጋጅ፣ የግሩፕ የጉብኝት ጉዞ እድል ያለው፣ ወደ እስራኤልና ሲሸል ለማስጎብኘት ሲሆን፣እንጂ ሀገራችን አልተለመደም፡፡ ሀገራችንን ለማየት፣ ያለን አማራጭ፣ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ከፍሎ፣ ላንድክሩዘር መከራየት ይጠይቃል ወይም
እንደዚህ በተለመደው የህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረሽ፣ ለመዝናናት
እየተጉላላሽ መሄድ ነው፡፡ የግሩፕ ጉዞ ቢኖር ኖሮማ፣ይሄኔ ሀገሬን ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምስራቅ እስከምዕራብ ማየት እችል ነበር፡፡”

“እንዴ ይኼ እኮ አሪፍ ቢዝነስ ነው፡፡ እና ወደ አርባ ምንጭም ሆነ፣ ወደተለያዩ የሀገራችን ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህብ ያላቸውን ቦታዎች በተደራጀ መልኩ፣ ቅስቀሳ አድርገው፣ በተመጣጣኝ ዋጋ
የማስጎብኘት ስራ የሚሰሩ ድርጀቶች የሉም እያልከኝ ነው?”

“በእርግጥ፣ ይሄ አካሄድ ገዳማትን ለማስጎብኘት በየታክሲው፣በከተማዋ ግድግዳዎችና የስልክ ቋሚዎች ላይ በሚለጠፉ ቅስቀሳዎች፣ፍላጎቱ ያላቸውን ሰዎችን አሰባስበው በማደራጀት በተመጣጣኝ ዋጋ ጉብኝቶችን ሲያዘጋጁ አይቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን አካሄድ፣ በጥቂቱ አዘምነው፣ ሀይማኖታዊ ላልሆኑትም ለሌሎች የሀገሪቱ መስህቦችን ለማስጎብኘት ብንጠቀምበት፣ ማህበረሰቡን በተመጣጣኝ ዋጋ የተለዩ የሀገራችንን መስህቦች ለማስጎብኘት እድል ይሰጣል፡፡ በሂደቱም፣ ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ነገርግን፣ ይህ የተለመደ ባለመሆኑ፣ ላሊበላን፣
አክሱምን፣ የጀጎል ግንብን፣ የባሌ ብሄራዊ ፓርክን፣ ነጭሳር ፓርክን
እና ሌሎች ልዩ እና ድንቅ የሆኑ የሀገራችን ውበቶችና ኩራቶች ከዜጎቻችን ይልቅ በውጪ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ፡፡ ትውልዱም ሀገሩን የማወቅ እድል ስለሌለው፣ በሀገሩ መኩራት ሲገባው፣ ባለማወቁ ፀምክንያት ያፍርባታል፡፡”

“ይኸውልህ ያቡ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ያለው ውጣ ውረድ አድካሚ እና የሚያጉላላ ከመሆኑም በተጨማሪ በየቦታው የሚገኙ መስህቦችን ቆም ብሎ ለማየት፣ ለማድነቅና ፎቶ ለማንሳት አይመችም፡፡በመሆኑም ጉብኝቱን የተሟላ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ እንደምትነግረኝ ከሆነ፣ የአስጎብኚ ድርጅቶች አደረጃጀት የውጪ ዜጎችንና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ብቻ ያማከለ ይመስላል፡፡ ይህም የመጎብኘት
ባህላችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ጉብኝትን እንደቅንጦት እንዲቆጠር
ያደርጋል፡፡ እራስን አድሶ ለቀጣይ ስራ እራስን ከማዘጋጀትም በላይ፣
በመጎብኘት ውስጥ በጣም ብዙ አዲስ እውቀት፣ የፈጠራ ሀሳቦችና የልምድ ልውውጦች አሉ፡፡”

“ትክክል ብለሻል ሃኒዬ፡፡ እንደማህበረሰብ የመጎብኘት ባህላችን መሻሻል አለበት። እንዳልሺው መጎብኘት ከመዝናናት በዘለለ ብዙ ፋይዳዎች አሉት፡፡ አንዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያየሽውን ባህልና እሴት ቀምረሽ፣ በህይወት ለሌሎች ችግሮችም እንደ መፍትሄ ልትጠቀሚበት
ትችያለሽ፡፡ ነገር ግን እንዳለ መታደል ሆኖ፣ በማህበረሰባችን መጎብኘትን
እንደቅንጦት፣ ለመጎብኘት የሚያወጣን ወጪ እንደ ማባከን የሚቆጥረው
ቁጥሩ ቀላል ሚባሉ አይደሉም፡፡”

እየተጫወትን ለመርሳት የመኪናውን እንግልት እንዲህ ሞከርን፡፡ ሲደክማት ጋደም እያለችብኝ፣ አስር ሰአት አርባ ምንጭ ከተማ ገባን፡፡ እንደደረስን ቱሪስት ሆቴል አልጋ ያዝን፡፡ ቢደክመንም፣ ሃኒ
ከተማውን ለማየት ካላት ጉጉት የተነሳ፣ ሳናርፍ ሻወር ወስደን ወጣን፡፡በቅርብ የተሰራ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ለከተማዋ አዲስ ውበት ሰጥቷል፡፡ አርባ ምንጭ ግርግር ያልበዛበት ደርባባ ከተማ ነች፡፡ በባጃጅ ተዘዋውረን ከተማዋን ለማየት ሞከርን፡፡ ከተማዋ ሁለት ጫፎች አሏት፡፡የዩኒቨርስቲውን መስፋፋት ተከትሎ የተመሰረተውና የቀደመው መንደር ደረጃውን በጠበቀ የአስፓልት መንገድ በቅርብ እንደተገናኘ ያስታውቃል፡፡
አስፓልቱ ሳይሰራ ከተማዋን አሰብኳት፡፡ የአባይና ጫሞ ትልልቅ ሀይቆች ሀገር፣ የነጭ ሳር ፓርክ፤ የአዞ ገበያ፣ የሙዝና የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ የቱሪስት መናኸሪያ ሀገር፣ አርባ ምንጭ የረባ የአስፓልት
መንገድ ለዓመታት ብርቋ ነበር፡፡

ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ወክ እያደረግን ወደ ቱሪስት ሆቴል ተመለስን፡፡ ወደ ሆቴሉ እንደገባን ረሃብ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እራት
ለመብላት ዞርዞር ብለን ቦታ መፈለግ ጀመርን፡፡ አንድ ጥግ ላይ ክፍት ቦታ አገኘንና ተቀመጥን፡፡ አስተናጋጅ እየጠበቅን፣ ግቢውን ቃኘነው፡፡

“ግማሽ በግማሽ ፈረንጅ አይደል እንዴ?” አለች ሃኒ፡፡

“ያው ቱሪስት ሆቴል አይደል፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ..፣ እና ለዛ ነው?”

ማለቴ አርባ ምንጭ እኮ ምድራዊ ገነት ናት፡፡” አስተናጋጁ መጥቶ “ምን ልታዘዝ!” አለን፡፡

“ምን እንብላ ሃኒዬ?”

“እንዴ! አርባ ምንጭ መጥተንማ፣ ከአሳ ውጪ መብላት...”

“እሺ! አንድ ለብለብ አንድ ጉላሽ ይሁን?”

“እሺ፣አሪፍ ነው፡፡”

“የሚጠጣ ሁለት ጊዮርጊስ ቢራ፡፡”

አስተናጋጁ እየተዋከበ ከአጠገባችን ሄደ፡፡ ግቢውን በዐይኔ ቃኘሁት፡፡ በግቢው የመዝናናት መንፈስ ሰፍኗል፡፡ ሰው ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ይጫወታል፡፡ ከሃኒ ጀርባ የተቀመጡ ሁለት ነጭ ሴቶችን አየሁ፡፡ ከኔ ትይዩ ያለችው ፈረንጅ
👍3
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ (MD)

አልጋችን ውስጥ ገብተን ተኛን፡፡ እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም፡፡ከነጮቹ ጋር ያደረኩት ስሜታዊ ድርጊት ምን እንደሆነ ማስብ ጀመርኩ፡፡እንዴት ማሂ እያለች እንደዚህ አይነት ስሜት ይሰማኛል? እንዴት
ቢያንስ ማሂ ፊት ስሜቴን መደበቅ አቃተኝ? ከማሂ ጋር ተኝቼ ውስጤ
ኢቫን በወሲባዊ ስሜት ያስባል፡፡ ምን አይነት እብደት ነው?፡፡ እንቅልፍ
ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ተነስተን ተጣጠብንና ቁርስ በልተን ሁለት ሰዓት ላይ ወጣን፡፡ ባጃጅ ይዘን፣ አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ሄድን፡፡ የዶርዜ ሎጅ መጎብኘት እንደምንፈልግ ነገርነው፡፡

“ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ?”

“አዎ!”

“የሞላ መኪና አለ፡፡ ሂሳብ ክፈሉ።” የተጠየቅነውን ክፍያ ከፈልን፡፡ ባለድርጅቱ ከሌላ ልጅ ጋር አገናኘን፤

“ኑ፣ ፍጠኑ፡፡ እድለኛ ናችሁ፡፡”ተከተልነው።

“ከዚህ ይርቃል እንዴ?”

“ብዙም አይርቅም፡፡ ሰላሳ ኪ.ሜ. አካባቢ፡፡”

መኪናው ጋር አደረስን፡፡ እውነቱን ነበር፡፡ እንዳለው ሚኒባሱ ሞልቷል፡፡ ሁሉም በሚባል መልኩ፣ አብዛኛው ጎብኚ ፈረንጆች ናቸው።

ክፍት የነበረው የመጨረሻ ወንበር ላይ ሄደን ተቀመጥን፡፡ ወዲያው መኪናው ጉዞውን ጀመረ፡፡ የምናልፍበት ቦታ ሁሉ አረንጓዴ ነው።በየመንገዱ ማይሸጥ የፍራፍሬ አይነት የለም፡፡ ሙዝ፣ ሎሚ፣ አቡካዶ፣መንደሪንና የመሳሰሉት፡፡ የቦታው አረንጓዴነት፣ ከመሬቱ አቀማመጥ
ጋር እጅግ ውብ፣ መንፈስን የሚያድስ ነው፡፡

ሃኒ በምታየው ነገር ሁሉ፣ “ኦ... ሎርድ፣ እንዴት ያምራል!” ትላለች፡፡

“ምድራዊ ገነት ነች ያልኩሽ ዋሸሁ?”

“በፍፁም...!! እውነትም ምድራዊ ገነት፡፡ እንኳን እዚህ መጣን፡፡ሎርድ...ያቢዬ በናትህ ፎቶ ላንሳ ቦታ ቀይረኝ፤”

“እንዴ፣ እኔ አላነሳም እንዴ?”

ካሜራዬን አውጥቼ ማንሳት ጀመርኩ፡፡ ሃኒ “ዋው..፣ ይሄን ተራራ አንሳው፣ ሰማዩን አብረህ አስገባው፣ ዛፉን በከፊል...” ትላለች።

መልሳ ደግሞ፣ “ወይኔ ይሄኛው ሲያምር፣ እስቲ እኔም ላንሳ በናትህ፣” ተቁነጠነጠች፡፡ ቦታውን ቀየርኳት፤ ካሜራውን ሰጠኋት፤ ብዙ ፎቶዎችን
አነሳን፡፡ እያበላለጥን፣ እየተፎካከርን፣ እያደነቅን፣ ተደሰትን፡፡ እጅግ የሚገርም ብዙ ቅፅበታዊ ደስታዎች፡፡ በተፈጥሮ ተማርከን፤ ተዋጥን፣በደስታ ተንሳፈፍን፡፡ አስጎብኚያችን “አሁን ወደ ዶርዜ መንደር
ደርሰናል፤” ሲል ከሄድንበት የራሳችን የደስታ አለም ተመለስን፡፡አይተን፣ ተደስተን፣ አንስተን ግን፣ አልጠገብንም ነበር፡፡

ከመኪናው እንደወረድን፣ ሃኒ፣

“ዋ...ይ..!” ብላ ጮሃ ተጠምጥማብኝ፣ “እየው ያቡዬ” ትለኛለች፣ እጆቿን ወደ ፊታችን ቀስራ፡፡

“ኦ...፣ ማይ ጋድ! ምንድነው...? ሰው ነው?››

“ኖ ኖ...፣ እዚህ አሳ በብዛት ስላለ፣ አሳ ነው ሚሆነው::በአሳ ቅርፅ ነው የሰሩት፡፡ ሎርድ!”

“በጣም ግዙፍ እኮ ነው፡፡” ማንንም እየሰማን አይደለም፤ ቀስ ብለን እየተጠጋነው ነው፡፡ ምን አይነት ትልቅነት ነው? ምን አይነት ከፍታ ነው...?

“ጭንቅላት አለው፤ አፍንጫ አለው፤ አፍ አለው፤ ጆሮ አለው፤”ሃኒ በስሜት ሆና ትቆጥራለች፡፡

“ሃኒዬ ልንገርሽ? ይሄ የዝሆን ቅርፅ ነው፡፡”

“የስ..!፣ አሁን በትክክል ተመልሷል፡፡” ፈነጠዘች...!

“እስቲ ዝም ብለሽ እዪው:: ግዙፍነቱ፣ ወደ ላይ ያለው ከፍታ፣ኩንቢው፣ በረንዳው ነው:: አፉ በር ነው:: ጆሮዎቹ መስኮቶች ናቸው።
“... ፣ ሎርድ!፣ ምን አይነት ጥበብ ነው...! ምን አይነት እውቀት ነው...? ልቤ ልትቆም ሳግ ተናነቀኝ፡፡”

“ኧረ ፎቶ ሳንነሳ...!” ጮኸች ሃኒ፡፡

ውስጡ ገባን፤ እየዞርን አየነው፤ተሻሸነው፣ ታቀፍነው፣ እጅግ በጣም ብዙ ፎቶዎች ተነሳን፡፡ በተመለከትነው ኢትዮጲያዊ ድንቅ ጥበብ ነብሳችን ሃሴትን አደረገች፡፡ ፈረንጆቹ እንደ ተአምር ተደንቀው
ይመለከቱታል። ፎቶ ያነሱታል፡፡ የከተማ ህንፃዎች ለምን እንደዚህ አይነት የስነ ህንፃ ዲዛይን እንደማይጠቀሙ ገረመን፡፡ የምንችለውን ያክል ተዟዙረን አየነው:: በፎቶ ማስቀረት የቻልነውን ያክል አስቀረን፡፡ዶርዜዎች ለጥበብ የተፈጠሩ ህዝቦች ናቸው!፡፡ መመለስ ስላለብን
ተመለስን፡፡ ነብሳችን ግን እዛው ቀረች፤ አልተመለሰችም፡፡ ስላየነው ድንቅ ጥበብ ብቻ ስናወራ ተመልሰን አርባ ምንጭ ገባን፡፡ ደስታችን፣እርካታችን ቅጥ አጣ፡፡ እራት በላን፣ ከደስታችን የተነሳ የድካምም ስሜት አልተሰማንም፡፡ በየመጠጥ ቤቱና በየጭፈራ ቤቱ መዝናናት ጀመርን፡፡

እየጠጣን፣ ጨፈርን፣ ቤት እየቀያርን ተዝናናን፡፡ ደስ የሚል ልዩ ስሜት፡፡ እኩለ ለሊት እየሆነ ነው፡፡ የመጨረሻ አንድ ቤት እንይ ብለን የገባንበት ቤት፣ ደረጃውን የጠበቀና በቅርቡ እንደተከፈተ
የሚያስታውቅ፣ ሞቅ ያለ ጭፈራ ቤት ነው፡፡ ሙዚቃዉ ደርቷል፡፡በሚያምር የጭፈራ መብራቶች ታጅበው፣ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚጨፍሩ ሰዎች፣ አለባበሳቸውም ሆነ ውበታቸው አትለፉኝ፣
አትለፉኝ የሚሉ ቆነጃጂት ቤቱን ሞልተውታል፡፡ ከሃኒ ጋር እየተሽሎኮሎክን ወንበር ፈልገን ተቀመጥን፡፡ ሁለት ደብል ብላክ ሌብል አዝዘን፣ ሂሳብ በቅድሚያ ከፍለን እየጠጣን፣ ከቤቱ ጋር እስክንግባባ ወንበራችን ላይ ሆነን በቀስታ መደነስ ጀመርን፡፡ ስንገባም ሞቅ ስላለን፣ከቤቱ ጥሩ የሙዚቃ ምርጫ ጋር ተደምሮ የሞቀ ጭፈራ ጀመርን፡፡
ድንገት እነ ኢቫን ከበሩ በስተ ግራ በኩል ሆነው እንደ እብድ ሲደንሱ አየሁ፡፡ ከሃኒ ጋር እየጨፈርኩ፣ ልቤ ግን ኢቫ ጋር ሄዷል፡፡ ለምክንያት ሽንት ልሽናና ልምጣ ብዬ ወጣሁና ስመለስ ኢቫን አስደንሼያት
ተመለስኩ፡፡ ትንሽ ቆይቼ፣ ወደነሱ
ጋር ቦታ እንድንቀይርና እንድንቀላቀል አደረኩ፡፡ ደጋግሜ ኢቫን ወሲብ ቀስቃሽ ዳንስ አስደነስኳት፡፡ እያስደነስኳት እንደተማረኩባት ነገርኳት፡፡ እብደቱ
ብሶብኛል፡፡ ሃኒና ወፍራሟ ፈረንጅ ብዙ ሰዓት አብረው ይደንሳሉ፡፡ ከኢቫ
ጋር ተግባብተናል፡፡ አልጋ ይዜ ልምጣ አልኳት፡፡ አልተግደረደረችም፡፡
ይዤ መጣሁ፡፡

ውጪና ጠብቂኝ፡፡” በጆሮዋ አንሾካሾኩላት፡፡ በተራዋ ለጓደኛዋ
አንሾካሹካ ወጣች፡፡ ትንሽ ቆይቼ እኔም፣

“ሃኒዬ መጣሁ፣ ሽንት፡፡” ብያት ልወጣ ስል

“ያቡ ሰክረሀል ጠንቀቅ በል፧” አለችኝ፡፡

“ሃኒዬ፣ እኔን በዚች ሰክረሃል?”

“እሺ ለማንኛውም ጠንቀቅ በል፡፡”

“እሺ!” ብዬ ወጣሁ፡፡ እንደውጣሁ ኢቫን ወደ ያዝኩት ክፍል እያከነፍኩ ወሰድኳት፡፡ የተሰረቀ ነገር ሆኖብኝ አንገበገበኝ፡፡ በቁማችን ጀመርነው ልብሳችንን ተጋግዘን
አወልቀን፣ አልጋው ላይ ተወረወርንበት፡፡ ለዘመናት የተጠራቀም፣ የወሲብ አምሮት ያለብኝ እሰኪመስል፣ ሀይልና ስግብግብነት የተቀላቀለት ወሲብ ተዋሰብን፡፡ስንጨርስ ከውስጤ የወሲብ ሰንኮፍ ተነቅሎ የወጣ መስሎ ተሰማኝ፡፡
ስካሬ ለቀቀኝ፣ በምትኩ ሀፍረት ወረረኝ፡፡ ልብሴን በፍጥነት ለብሼ ቻው እንኳ ሳልላት ልወጣ፣ በሩን ሳብ ሳደርገው፣ አልተቆለፈም፡፡ ምን አይንት አብደት ነው፡፡ ሃኒን እንዴት ብዬ ነው ማያት፡፡ ቆይተን ይሆን? ትጠረጥረኝ ይሆን?፣ በፍጥነት ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡

“ቆየሁ ሃኒዬ?”

“አይ ትንሽ፡፡ ደህና ነህ አይደል?”

“ደህና ነኝ፡፡ ሸንቼ ስመጣ ኢቫ ሲጋራ እያጨሰች አገኘኋት።

ንፋስ ለመውሰድ ትንሽ አወራኋት፡፡ የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡

“አይ እንኳን ንፋስ ወሰድክ፡፡ አሁን ስካርህ የለቀቀህ ትመስላለህ፡፡” በአሽሙር እየተናገረችኝ መሰለኝ፡፡

“ሰከርክ ሰከርክ አትበይኝ እኔ ድሮም አልሰከርኩም፡፡” በእኔ ብሶ ኸኩኝ፡፡ ድካም ተሰምቶኛል፣ ፀፀት ተጨምሮበት እንደቅድሙ እየተጫወትኩኝ አደለም። አሁን የምፈልገው መውጣትና መሄድ ነው። ድንገት ቤቱ ውስጥ ትርምስና
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ምን እያደረክ ነው?” የሚል ድምፅ ሰምቼ ቀና ስል፣ ግዙፍ ቅልብ ጎረምሳ ፊትለፊቴ ቆሟል፡፡ ልቤ ፀጥ ልትልብኝ ነው፡፡

“ዕቃ ወድቆብኝ እየፈለኩ፡፡”

“መጀመሪውኑ ባጃጄ ውስጥ ምን ፈልገህ ገባህ ነው የምልህ?”

“ባለ ባጃጁ አንተ ነህ? ጭፈራው ቤት ነበርን፡፡ ብጥብጥ ሲነሳ ኮንትራት ፈልገን ስንመጣ የለህም፡፡ እንድታደርሰን ቁጭ ብለን እየጠበቅንህ ነው፡፡” ብዬ፣ ከሾፌሩ ወንበር ላይ ቀስ ብዬ ጠጋ አልኩና
ቦታውን ለቀኩለት። ከኋላ ዞር ብሎ ሲመለከት ብቻዬን እንዳልሆንኩ
ተገነዘበ፤

“ወዴት ናችሁ?”

“ቱሪስት ሆቴል።”

“መቶ ብር ትከፍላላችሁ፡፡”

“ችግር የለውም፡፡” ኡፈይ አልኩ በውስጤ፡፡

ቁልፉን አውጥቶ ባጃጇን ለማስነሳት ሞከረ፣ ምንም ድምፅ የለም፡፡ ደጋግሞ ሞከረ፣ ምንም የለም፡፡ ደነገጥኩ፡፡ እኔ ስጎትት ወደ የነበረበት ጎንበስ ብሎ አየ፡፡ ላብ አጠመቀኝ፡፡ ስካሬ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ገመድ በጥሼ ይሆን እንዴ? የሆነ ነገር ነካካ፡፡ መልሶ ቁልፉን ሞከረ፡፡ ባጃጇ
ተረክ ብላ ተነሳች፡፡ ተመስገን...፣ ከግንባሬ ላይ ላቤን ጠራረኩ፡፡

እንግዶች ናችሁ?”

“አዎ፡፡”

“አርባ ምንጭ ሰላማዊ ከተማ ነች፡፡ የቅድሙ ፀብ አጋጣሚ ነው፡፡ በሴት ተጣልተው ነው፡፡ አትደንግጡ፡፡ እንደዚህ ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ ዘና በሉ፡፡ ከፈለጋችሁኝ ስልኬን ውሰዱ፡፡”
“እሺ እናመሰግናለን፡፡ ስልክ ቁጥርህን ስጠን፤” አልኩት፡፡ሆቴላችን አድርሶን፣ ሂሳብ ከፍለን ቁጥሩን ተቀብለን ወረድን፡፡ ባጃጁ ከሄደ በኋላ፣ ሦስቱም ያደረኩትን እያስታወሱ፣ ያሽኩብኝ ጀመር፡፡

“ቆይ ባጃጇን ምን ልታደረጋት ፈልገህ ነው፣ እንደዛ የተንፈራፈርከው?” ከት... ከት... ከት

“በተለይ ባጃጇ በቁልፉ አልነሳም ስትልማ የደነገጥኩት ድንጋጤ... ” ከት... ከት ከት..

“ደግሞ እኮ ተው ሲባል አይሰማም፡፡” ከት ከት...

“እኔማ ይሄ ልጅ፣ ዛሬ እስር ቤት አሳደረን እያልኩ ነበር፡፡” ከት..ከት..

የሰራሁት የእብድ ስራ መልሶ እኔንም ያስቀኝ ጀመር፡፡

አብሪያቸው እስቃለሁ፡፡ እስኪደክማቸው፣ እንባ እሰኪወጣቸው ሳቁብኝ፡፡

“ኧረ ሰዓቱን እዩት፡፡ ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አልፏልኮ፡፡” አልኩኝ እንደደከመው ሚስቁብኝን ለማስቆም፡፡ ወደ ክፍላችን ገባን፡፡ ልንተኛ ስል፣ ቅድም ከነጮ ጋር ባደረኩት የተሰማኝ ፀፀት ጠፍቶ፣ ስሜቴ.
እንደገና ሲያገረሽ ተሰማኝ፡፡ ምክንያት ፈልጌ መውጣት ፈለኩ፡፡ ምን ብዬ እወጣለሁ፡፡ ሽንት ቤቱ እዚሁ ነው፡፡ ሌላ ምን ምክንያት እፈጥራለሁ፡፡ ኢቫም እንደኔው እያሰበችኝ ነው ብዬ ገመትኩ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ ውጪ ያለ የተለየ እንቅስቃሴ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡ በር ላይ የቆመ ሰው እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ሃኒ ተኝታለች፡፡ ቀስ ብዬ ከአልጋ ውስጥ
ወጣሁ፡፡ ከአልጋው ብድግ ስል፧ “እንቅልፍ እንቢ አለህ እንዴ ያቡ”
አለች ሃኒ፡፡ አልተኛችም፡፤

“አይ ይሄን ቢራ ልፈን ሽንቴ..”

ለይስሙላ ሽንት ቤት ደርሼ ተመልሼ ተኛሁ፡፡ በንጋታው በጣም የድካም ስሜት ተሰማን፡፡ ከአልጋችን ላይ አርፍደን ተነሳን፡፡ ቁርስ እንደነገሩ ቀማመስን፡፡ ሁለታችንም የምግብ ፍላጎት አልነበረንም፡፡ ሃኒም ከኔ እኩል ድካም ተሰምቷታል፡፡ ከሰዓት በአብዛኛው እክፍላችን ተኝተን አሳለፍነው፡፡ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ተነስተን ከክፍላችን ወጣን፡፡

“ሃኒዬ እርቦኛል፡፡”

እኔም ልልህ ነበር፡፡ የሆነ ነገር እንብላ፡፡”

“ምን እንብላ?”

“አሳ እንዳይሆን እንጂ፣ የፈለገከውን፡፡”

“ከአሳ ውጪ እንዳላልሽ፣ ሰለቸሽ?”

“ሳይሆን፣ ቅድመ ጥንቃቄ ነው፡፡”

ወጥተን ምሳችንን እንደነገሩ በላን፤ ቡና ጠጥተን ሰውነታችንን ለማፍታታት ከሆቴላችን ወጣን፡፡ ስለ ሀገሩ ለምነት እያወራን፣ በትናንትናው እብደት እየሳቅን፣ ነገ ነጭ ሳር ፓርክን ለማየት እያቀድን
የአርባ ምንጭን የምሽት ንፁህ አየር እየማግን፣ በእግራችን ብዙ
ተንቀሳቀስን፡፡
በንጋታው በጥዋት የበቀደሙ አስጎብኚ ድርጅት ጋር ሄድን፡፡

“ሄይ እንዴት ነህ አለቃ?" አልኩት፡፡

“አለሁ፤ አለሁ...፤ እንዴት ናችሁ ዘመዶች?"

“ይመስገነው! ይኸው ያንተ ናፍቆት መልሶ አመጣን”

“እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ምን እንታዘዝ ” አለ እጆቹን እያሸሽ፡፡

ነጭ ሳር ፓርክን ማየት ፈልገን ነበር፡፡ እንዴት እንደከረመ ጠይቀነው እንምጣ?”

“ታዲያ ምን ችግር አለ፡፡ እንደ ንጉስ አስጎብኝተን እንመልሳችኋለን፡፡ በጀልባ ይሁንላችሁ በመኪና?”

“በጀልባ” አለች ሃኒ ከአፉ ነጥቃ፡፡

“በጀልባ፣ ሶስት ሺህ ብር ብቻ ያስከፍላችኋል፡፡”

እችን ትወዳለች.... እኛ አንተን ደንበኛ ብለን መርጠንህ ብንመጣ፣ ጭራሽ ታሰወድዳለህ?”

“እንደውም ደምበኝነታችሁን ብዬ ነው፡፡አልተወደደም፡፡”

“እንዴ! በጣም ውድ ነው እንጂ፣ በጣም!”
“እንደዛ ነው ዋጋው፡፡ ጀልባው አራት ሰው ነው የሚጭነው፡፡

ሁለት ሰው ካገኛችሁ ሂሳቡን ተካፍላችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡”

“እኛ ሰው ከየት እናመጣለን? ባይሆን እሺ እሱን ፈልግ፡፡”

“እዛ ጋር የቆሙት ሁለቱ ነጮች፣ እንደናንተው ዋጋው በዛ ብለው ነው፣ ካልደበራችሁ አናግሯቸው፡፡” አለኝ ፈንጠር ብለው ወደ ቆሙ ሁለት ፈረንጆች እየጠቆመኝ፡፡ አውርቶ ሳይጨርስ፣ ቆመው ከነበሩት ፈረንጆች ወንድየው ወደኛ መምጣት ጀመረ፡፡ ሰላምታ
ሰጠንና፤

“ወደ ነጭ ሳር መሄድ ፈልጋችሁ ነው?” አለን በእግሊዝኛ፡፡

አዎ፡፡ ግን ዋጋው በዛብን፡፡”

“እኛም ዋጋው በዝቶብን ነው፡፡ ዋጋውን ተካፍለን አብረን ብንሄድ፣ ይስማማችኋል?”

“ጥሩ ነው፡፡ እንደዛ ይሻላል፡፡” አልኩ ሃኒን እያየሁ፡፡

መስማማቷን ጭንቅላቷን በመነቅነቅ ገለጠችልኝ፡፡

ሦስት ሺህ ብሩን እኩል አዋጥተን ትኬት ቆረጥን፡፡ ወደ ሀይቁ ለመሄድ፣ ከከተማ ለታክሲ አራት መቶ ብር ተጠየቅን፡፡ ፈረንጆቹ ቀድመው መረጃ ሰብስበዋል፡፡ በባጃጅ በሁለት መቶ ብር መሄድ
እንደሚቻል ነግረውን፣ ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን፡፡ የከተማው ዋና መንገድ
ላይ ቆመን፣ ባጃጅ እየጠበቅን፣ በመንገድ ላይ ጫት እየቃሙ ሚያልፉ ወጣቶችን ፈረንጆቹ ተመልክተው፣

“ወጣቶቹ ሚበሉት ቅጠል ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ፡፡

“ጫት ይባላል፤” አልኳቸው፡፡

“ያለው ጥቅም ምንድን ነው?”

“ያነቃቃል፡፡ ደስተኛ ያደርጋል፡፡”

“እንዴት ያነቃቃል?” ሰውየው አጥብቆ ጠየቀኝ፡፡

“ማለት?”

“ውስጡ ያለው ንጥረ ቅመም ምንድን ነው? ሴሮቶኒን /የደስታ ንጥረ ቅመም/ አለው?”

“ስለ ሴሮቶኒን ንጥረ ቅመም ብዙም አላውቅም፡፡ ግን ካቲን የተባለ ቅመም አለው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡”

በተባለው ዋጋ ወደ ሃይቁ የሚያደርሰን ባጃጅ አግኝተን ጉዟችንን ጀመርን፡፡ መንገዱ በጣም ቁልቁለታማ፣ ጥምዝምዝ የበዛው፣ ግማሽ ፒስታ በሚባል ደረጃ፣ የፈራረሰና ጠባብ መንገድ ነው፡፡ ወደ ሀይቁ ስንቀርብ፣ መንገዱ ጭራሽ ጭቃ የበዛው ረግረጋማ ሆነ፡፡ ከዚህ በፊት ሰምጠው የተያዙ ተሽከርካሪዎች ጎማ ቅርፅ ይታያል፡፡

“ሌላ የተሻለ አማራጭ መንገድ የለም?” አለች፤ አብራው ያለችው ፈረንጅ፡፡

አይመስለንም፤” አልኳት።

በጭቃው መንገድ ውስጥ ትንሽ እንደሄድን፣ ባጃጁ ቆመና እዚህ
ጋር ነው መውረጃው አለን ሹፌሩ፡፡ ሀይቁ በትልልቅ ዛፎች ተከቦ ይታያል፡፡ ወደ ፓርክ እየገባን እንደሆነ ሚያሳይ፣ አንዳችም ምልክት የለም፡፡ ሂሳብ ከፍለን ወረድን፡፡
“ምልክት ሚሆን መግቢያ በር የለውም እንዴ?” አለችኝ ሃኒ፡፡

“ሌላ መግቢያ ይኖረው ይሆናል፡፡”

“እንዴ፣ ቢኖረውስ፣ ቱሪስት ሚገባበት እስከሆነ ድረስ፣ ምልክት መኖር አለበት፡፡ በዛውም
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“አዎ፣ ወደዛ ቤት እየሄድኩ እንደሆነ ሳስብ...” ከቤተሰብ ጋር መሆን ታክቷታል፡፡

“አይዞሽ ሃኒዬ፡፡ በቃ እርሻቸው፡፡ እንደሌሉ አስቢያቸው::እንዳልሰማሽ እለፊያቸው፡፡”

“አይ ያቡ፣ እንደዛ ሳልሞክር ቀርቼ መሰለህ? የሚቻል አይደለም፡፡ ከባድ ነው፡፡ በተለይ ታላቅ እህት ተብዬዋ፣ እዛ ሆኜ ስንት ነገር እንዳላደረኩላት ዛሬ የምትናገረኝ ቅስሜን እስኪጠዘጥዘኝ ድረስ ነው፡፡ ነገሩ ልብን ይሰብራል፡፡” ስታወራ እንባዋ መጣ፡፡ ወሬውን
አስቀይሬ መቀባጠር ጀመርኩ፡፡ ሞጆን አልፈን ወደ ቢሾፍቱ ስንጠጋ፤

“ያቡዬ..?” አለችኝ ምቀባጥረውን አቋርጣኝ፡፡

“ወዬ ሃን...”

“አንተ ግን ለምን አታገባም?”

“ማለት...?” ተደናበርኩ፡፡ ያላሰብኩት ዱብዳ ነው፡፡

“ብቻህን ነው ምትኖረው፡፡ በዛ ላይ የቅርብ ሰው እንኳ ባጠገብህ የለም፡፡ ስለዚህ ለምን አንዷን አታገባም?”

“እ...፣ እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ ግን..”

“ይኼ ምን ግን ያስፈልገዋል?” ሳይታወቃት ጮኸች፡፡

“ንሮዬን እያየሽው አይደል፡፡ ገና ለመቆም ድክ ድክ እያልኩ፡፡ባይሆን ስራው መስመር ከያዘልኝ በኋላ...”

ቁርጠኝነቱ ቢኖርህ፣ አሁን እዚህ በሳምንት ያወጣነው፣ለሁለት ሰው ንሮን ለመመስረት በቂ ነው፡፡ አቅም ሳይሆን ቁርጠኝነቱ ነው የሌለህ፡፡”

የምመልሰው አልነበረኝም፡፡ ዝም አልኩ፡፡ እርሷም ዝም አለች፡፡መናኸሪያ እስክንደርስ ምንም አላወራንም፡፡
ወደየቤታችን ከመለያየታችን በፊት አቀፍኳትና፣

“አይዞሽ የኔ ፍቅር፣ ሁሉ ነገር ይገባኛል፡፡ እረዳሻለሁኮ፡፡ ጠንከር በይ፡፡ ትንሽ ግዜ ብቻ ታገሺኝ፣” ጉንጫን ሳምኳት፡፡ ከልቤ ነበር ያልኳት። ከሷ በፊት ስለማንም ደንታ ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ ማታ እንዴት እንደሆነች ደውዬ ጠየኳት፡፡እንደተለመደው ነው አለችኝ፡፡

ከአርባምንጭ መልስ የኔ ስሜት ጥሩ ሆኗል፡፡ የሃኒ ደግሞ ጭራሽ ብሶባታል፡፡ በስልክም በአካልም መነፍረቅ አመሏ ሆኗል፡፡ ድብርቱ እንዳይጋባብኝ፣ በየቀኑ ውሎዬን ከነ ሃብትሽ ጋር አደረኩ፡፡
ዛሬም፣ ለአራተኛ ቀን ምሳ እየበላን፣ ጃምቦ እየላፍን፣ ከአርባምንጭ
የተረፈ ወሬ አየገረብን ነው፡፡ መሃል ላይ ወሬው ሲቀዘቅዝ፣ ሳሚ ትዝ አለኝ፡፡ ተጠፋፍተናል፡፡ ደወልኩለት፣

ሳሚሻ የጠፋ ሰው፣ እንዴት ነው ባክህ?” አልኩት፡፡

ጎረምሳው፣ በዚህ ፍጥነት ሰው ትረሳለህ?”

“እውነት ሳሚሻ ቢዚ ሆኜ ነው፡፡ ብረሳ፣ ብረሳ አንተን እረሳለሁ?” ተጎዘጎዝኩኝ፡፡

“እኔ ምልህ፣ የአለቃህን ነገር ሰማህ?”

“የትኛው አለቃዬ? ሼባው?”

“አዎ ሼባው፡፡”

“ኧረ ምንም አልሰማሁም፡፡ ምን ተፈጠረ?”

“ጮማ ወሬ አምልጦሃላ..?” ካ..ካ..ካ... የተለመደች ካንገት በላይ ሳቁን፡፡

“ይነገረኛ! እዛ የቀረኸኝ ዘመድ አንተ ብቻ ነህ፡፡ ማን ይነግረኛል ብለህ ነው?”

“ያቺ ጉደኛ ሜሪ፣ ሼባውን ጉድ ሰራችው፡፡ እሷን ሊያገባ ሚስቱን ፈታ::”

“ምን?” ጆሮዬን አላመንኩም፡፡

“አዎ፡፡ ፍርድ ቤት ፍቺ ጨርሰው፣ ንብረት በሽማግሌ ተካፈሉ ሲባሉ፣ ሽማግሌ ሁነኝ አይለኝም?”

“በጣም ሚገርም ነገር ነው የምትነግረኝ፡፡ ግን ቆይ፣ ሚሪ እሺ
ባትለውስ? አባቷን የሚያህል ሽማግሌ፣ ምን አጥታ ነው ምታገባው? እሺ ደግሞ ልጆቹስ?” ሁሉ ነገር ግራ ገባኝ፡፡

“ልጆቹን ምን ሊደርግ እንዳሰበ እኔ አላውቅም፡፡ ሜሪ ግን ከቤተሰቧጋ ወጥታ ተከራይቶላት ካስቀመጣት ቆየ፡፡ እሱንም
አልሰማህማ? ከብዙ መረጃዎች እርቀሃላ ወንድሜ፡፡” ካካካ...፡፡ ብዙ ከተጫወትን በኋላ፣

“በል እንደዚህ ብዙ መረጃ እንዳያመልጥህ፣ ቶሎ ቶሎ ደውል፡፡
ሲደወልልህም ደግሞ ስልክ አንሳ፤” አለኝ፡፡

“ኧረ እኔው እደውላለሁ፡፡ አዲሱን ስራ መስመር ለማስያዝ በት በት ስል እየረሳውኮ ነው፡፡ አሁን መስመር እየያዘልኝ ነው፡፡ አልጠፋም፧
እደውላለሁ፡፡”

ስልኩን ዘግቼ ለነ ሃብትሽ፣ ስለ ቀድሞ አለቃዬ ሙሉ ታሪኩን ነግሪያቸው፣ በእርሱም በሜሪም ድርጊት ስንገረም አመሸን፡፡ ማታ እቤቴ ስገባ እንደተለመደው ለሃኒ ልደውል ስልኬን ሳወጣ፣ በጣም ብዙ ግዜ ደውላ ነበር፡፡ ወሬ ይዘን አልሰማነውም፡፡ የቴክስት መልዕክት ልካልኛለች፡፡ ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ!” ይላል፡፡ መልሼ ደጋግሜ
ደወልኩላት፡፡ ስልኳ ዝግ ነው፡፡ እንቅልፌን ተኛሁ፡፡ ጠዋት ስነሳ እጅግ አስደንጋጭ ዜና ሰማሁ፡፡ ሃኒ ትናንት ማታ መርዝ ጠጥታ እራሷን አጠፋች፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ አዞረኝ፡፡ በቀጥታ እቤታቸው ሄድኩኝ፡፡ ሃኒ እራሷን ማጥፋቷ እውነት ነው፡፡ ቤታቸው በለቀስተኛ
ተሞልቷል፡፡ አብዛኛው የሰፈር ሰው በጣም አዝኗል፣ ከልቡ ያለቅሳል፡፡
ማያለቅስ ለቀስተኛ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለነገሩ ባያዝኑና ባያለቅሱ ነበር ሚገርመው፡፡ ገና በልጅነቷ ነው የተቀጨችው ፤ በዛ ላይ ምታጓጓ ቆንጅ።
ነበረች፡፡ መሞቷ፣ እራሷን ማጥፋቷ ያላስደነገጠው የለም፡፡ አልቅሺ አልወጣልህ አለኝ፡፡ ሃዘኑ ቅስሜን ሰርስሮ ገባ፡፡ ከቀብሯ ጀምሮ እስከሰልስት፣ የሚያቀኝ ሰው ባይኖርም፣ ከለቀስተኛው መሃል ሆኜ ስቅስቅ ብዬ አነባሁ፡፡ ልቤ በሃዘን ተሰበረ፡፡ ከፍተኛ ጫና እንዳለባት
አውቅ ነበር፡፡ በተለይ ታላቅ እህቷን እንደገዳይ አየኋት፡፡ ስታለቅስ አይቻት፣ ለቅሶና ሃዘኗን አስመሳይ የአዛ እንባ ሆነብኝ፡፡ ሄጄ ማነቅ አሰኘኝ፡፡ ያስጨንቋት እንደነበር ተረድቼ ነበር፡፡ እራሷን እስክታጠፋ ይደርሳል ብዬ ግን በፍፁም አልገመትኩም፡፡ ልደርስላት፣ ልከላከላት
ይገባ ነበር፡፡ ከኔ ውጪ የሚረዳት፣ ሚከላከልላት፣ ሚደርስላት ሰው
አልነበራትም፡፡ እንዳግዛት ነግራኝ ነበር፡፡ አብረን እንኑር ብላኝ ነበር፡፡አልተረዳኋትም፤ አልደረስኩላትም፡፡ ላድናት ስችል አላደረኩትም፡፡
ልረሳው የማልችለው ከባድ ሃዘን በውስጤ ነገሰብኝ፡፡

ከሞተች ሦስት ሳምንት ሙሉ በዚህ ስሜት ተሰቃየሁ። በአዕምሮዬ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች ይዘንባሉ፡፡ ለምንድን ነው ህይወት እንዲህ ግራ የሆነችብኝ? ለምንድነው ተስፋዬ በተደጋጋሚ እየበራ ሚጠፋው? ለምንድን ነው በተደጋጋሚ ሚጨልምብኝ? ሃኒ
ደስተኛ አድርጋኝ ነበረ፡፡ የምኖርላት ምክንያቴ ሆና ነበረ፡፡ ለምን እርሷን
ይወስድብኛል? ለምን? ለምን? ለምን?! የማያባሩ ጥያቄዎች፣ ልሸከመው፣ ልቋቋመው የማልችለው የልብ ስብራት፡፡

እራሴን በአልኮል ደብቁ ለማለፍ ሞከርኩ፡፡ ጭንቀትና ድባቴው ግን እየባሰብኝ መጣ፡፡ህይወት መልሳ እንደቀድሞው ባዶና ተስፋ ቢስ ሆነችብኝ፡፡ ልቋቋመው ማልችለው ፀፀት ያላምጠኛል፡፡ ስልኩን ባነሳው ኖሮ ታተርፋት ነበር ይለኛል። በእርሷ ምክንያት፣ የተውኩት፣ የጣልኩት እራሴን የማጥፋት እቅድ፣ አቧራውን አራግፎ፣ የችግሬ የመጀመሪያ ተመራጩ መፍትሄ
ሆኖ ታየኝ፡፡ ተከተላት ይለኛል፡፡ እዕምሮዬ ሌላ ነገር ማሰብ አቁሟል፡፡ በየቀኑ፣ በየሰዐቱ፣ በየደቂቃው ይነተርከኛል፣ ይጠዘጥዘኛል፡፡ ከዚች ጭለማ ህይወት ሞት በስንት ጠዓሙ ይለኛል፡፡ በስተመጨረሻ ተሸነፍኩለት፡፡ የተውኩትን እቅዴን በድጋሜ በጥንቃቄ ለመፈፀም
መዘጋጀት ጀመርኩኝ፡፡ በእጄ ከቀረኝ ገንዘብ አብዛኛውን ለእናቴ ላኩላት፣ የዶሮ ቤቱን ለነ ሃብትሽ እንደባለፈው ሰው እንዲያመጡና እንዲከታተሉት አደረኩኝ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ምዱካን_ስወራ

ለመሞት ወስኛለሁ፡፡ ግን፣ ደስተኛ የምመስላቸው ቤተሰቦቼ፣ስኬታማ እንደሆንኩ፣ በደስታ እየኖርኩ እንዳለሁ እያሰቡ እንዲቀሩ፣በጥንቃቄ ዱካዬን አጥፍቼ ነው መሞት ያለብኝ፡፡ ልክ ከህይወታችን፣ቀስ በቀስ ጠፍተው እንደተረሱ ሰዎች፣ የት እንዳሉ ምን እንደሆኑ ትዝ እንደማይሉን ሰዎች፣ ዝም፣ ጭጭ፣ ጭልጥ ብዬ መቅረት ነው
ያለብኝ::ጥሩ ደብዛ ማጥፊያ የት ይሆን የሚገኘው? የት ነው አስክሬኔ ወድቆ
ሲገኝ፣ እንደቀልድ ሳይመረመር፣ ማነው? ከየት ነው? ሳይባል ሊቀበር ሚችለው? የት ሊሆን ይችላል?

ገቢና ወጪ ሰው የሚበዛባቸው ከተሞች፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው፣ ማነው? ከየት ነው? መቼ መጣ? ለምን መጣ? ተብሎ ትኩረት ማይስብባቸው ከተማዎች፡፡ የድንበር ከተሞች ናቸው፡፡ በየቀኑ አዳዲስ ሰዎች ሚገቡ፣ ሚወጡባቸው፡፡ ከሀገር የሚወጣ፣ የሚሰደድ የሚሰባሰቡባቸው፡፡ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሚርመሰመሱባቸው፡፡ከነዋሪው በላይ፣ መጪና ሂያጁ ሚበዛባቸው ከተሞች፡፡ እዛነው፣ ሰው እንደዘበት ሚቀበርበት፡፡ ህይወት እርካሽ የሆነበት፡፡ አስክሬን እንደቀልድ አፈር ማስ ማስ ተደርጎ፣ ሚቀበርበት፡፡ አዎ! ወደ እዛ ሄጄ እራሴን
ማጥፋት አለብኝ፡፡

የትኛው የድንበር ከተማ ይሻለኛል? ሞያሌ? መተማ? ሑመራ? አንዳቸውንም ሄጄባቸዋው አላውቅም፡፡ የቱን ልምረጥ? ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ወደ መተማ መሄድ የተሻለ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እዛ ሄጄ፣
እኔነቴን የሚገልፅ መረጃዎቼን ካጠፋሁ በኋላ፣ ሀገራቸውን ተሰናብተው
እንደሚሄዱ ሰዎች፣ እኔም ተሰናብቼ እሄዳለሁ፡፡ እነሱ ይመለሱ ይሆናል፣ እኔ ግን አልመለስም፡፡ እስከ ወዲያኛው እችን አሰልቺና አታካች አለም እሰናበታታለሁ፡፡

በነጋታው ረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ፣ ከአዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ ወደ ማርቆስ የሚሄድ አባዱላ ተሳፈርኩ፡፡ ከኋላ ወንበር አንድ የቀረው መቀመጫ ባዶ ነው፡፡ ተቀመጥኩ፡፡ ባህርዳር፣ ደ/ማርቆስ
ወያላው ይጣራል፡፡ እንደተቀመጥኩ ሞባይሌን አውጥቼ፣ የተለመደ
ፌስቡኬን መበርበር ጀመርኩኝ፡፡ እያነበብኩ ላይክና ኮሜንት አደርጋለሁ፡፡ በዚህም ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ፣ በማነበው ነገር ቅፅበታዊ ንዴትና ደስታ ይሰማኛል፡፡ የማወቅ ፍላጎቴም እንደዛው አለ፡፡ ዓለምን ተጠይፌ፣ ስለ ዓለም ለማወቅ ስልኬን እበረብራለሁ፡፡ ምን አይነት ግራ ነገር ነው፡፡ 'ማምሻም እድሜ ነው፣ ሆኖብኝ ይሆን፡፡ ድንገት፣ “እዚህ
ጋር ሰው አለ?” የሚል ድምፅ ተሰማኝ፡፡ ቀና አላልኩም፡፡ ጭንቅላቴን
በመወዝወዝ የለም የሚል ምልክት ሰጠሁ፡፡

የማነበው ነገር ትኩረቴን ስቦታል፡፡ ፌስቡክ የሀገራችንን የፖለቲካ መዘወሪያ መስሏል፡፡ ሰው ሁሉ ፖለቲከኛና አክቲቪስት ሆኗል፡፡ ሀገሪቷ የሚያስፈልጋት ሙያ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ እንደሆነ፣ ሁሉም ሙያውን ትቶ ተመራጭ ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ተንታኝና
አክቲቪስት ለመሆን ይታትራሉ፡፡ ምን እየሆንን ነው?፣ ፖለቲከኛ ባልሆንም እንደመረጃ ስለዓለም ጉዳይ ባገኘሁት አጋጣሚ እከታተላለሁ፡፡ሶሻል ሚዲያ አላማው የተሻለ ተጠያቂነትና ዲሞክራሲ መገንባትና ማስፈን እንደሆነ እሰማለሁ፡፡ በጣም ጠቃሚ ፈጠራም እንደሆነ ግልፅ
ነው፡፡ ግን የተሻለ ቁጥጥር ሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ ሶሻል ሚዲያ በዓለማችን ከተስፋፋ በኋላ፣ ዓለማችን ይበልጥ በቀውስ የተሞላች ይመስለኛል፡፡ ከቱኒዚያ የተነሳው የአረብ አብዮት፣ ሊቢያ፣ ግብፅ፣ የመን እያለ ሀገራችን ገብቷል፡፡ አሁን አሁን ሳስበው አሜሪካንና ዌስተርኖች በእርዳታና በሌላ ዲፕሎማቲክ ጫና ያስፈጽሙት የነበረው የአንጋሽነት “King Maker” ሚና ሀገራቶች ከቻይና ጋር በመተባበር በቀላሉ
አልጠመዘዝ ሲሏቸው ያመጡት አማራጭ ይመስለኛል፡፡

በእርግጥ አሁን አሁን፣ አሜሪካንም ሆነ አውሮፓውያን በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አህጉራት ስላሉ ታዳጊ ሀገራት እድገትና
ዴሞክራሲ ይጨነቃሉ ብዬ ማመን እየከበደኝ ነው፡፡ ሀያላን ሀገራቱ፣
ዋናው የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ሀገራት ቋሚ ጥቅምን ማረጋጥ
ይመስላል፡፡ በሊቢያ፣ በኢራቅ፣ በየመንና በሶሪያ የተከሰተውን በዓለም
ታሪክ ታይቶ ማይታወቅ የሰበአዊ ቀውሶችን አይተው እንዳላየ መሆናቸው፣ እነዚህ ሀያላን ሀገራት አላማችን፣ ዓለምን ለሰው ልጆች ሁሉ ለኑሮ የተመቸች ማድረግ ነው' የሚለው ዲስኩር፣ ለሽፋንነት የሚደረግ ባዶ ሽንገላ እንደሆነ እንድናስብ ያስገድዳል፡፡

እንደዚህ እያሰብኩ መኪናችን ሞልቶ፣ መንገድ ጀምረን፣እንጦጦ ኬላ ለፍተሻ እንድንወርድ ታዘዝን፡፡ ከሄድኩበት ሃሳብ ባነንኩ፡፡ፍተሻውን ጨርሰን ወደ መኪናችን ተመልሰን ገባን፡፡እኔ የተቀመጥኩት
ወንበር ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣለች፡፡ እግሯን ዘወር አድርጋ፣
ወደቦታዬ እንድገባ አሳለፈችኝ፡፡ ቅድም “እዚህ ጋር ሰው አለው?” ያለችኝ
እርሷ ነበረች፡፡ ቀይ፣ ወጣት፣ ቆንጆ ነች፡፡ ሰሞኑን፣ በህይወቴ የመጣብኝ
ምስቅልቅሎሽ ከሴቶች ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ሴቶች
መጥፊያዬ ናቸው ብያለሁ፡፡ላልደርስባቸው ምያለሁ፡፡ አሁን ሰይጣን
በዚህች የቀይ ቆንጆ ሊፈትነኝ አጠገቤ አስቀምጧታል፡፡ አላደርገውም ብዬ ስልኬን መበርበሬን ቀጠልኩ፡፡ የፌስ ቡክ ወሬ እንደቅድሙ አልጥም አለኝ፡፡ ሃሳቤ ከእርሷ አልወጣ አለ፡፡ የሚሞት ሰው ይፈራል እንዴ?፣ባክህ ዝም ብለህ እድልህን ሞክር ይለኛል ውስጤ፡፡ የስልኬን ዳታ አጠፋሁት፡፡ እንደሚያድን ነብር፣ ሁሉ ነገሬን ወደ እርሷ ቀሰርኩ።
በደንብ ተመለከትኳት፡፡ ጅንስ ሱሪና ኮት ለብሳለች፡፡ እድሜዋ ቢበዛ ሃያዎቹ መጀመሪያ ቢሆን ነው፡፡ ለመተዋወቅ ወሰንኩ፡፡ እንዴት ልጀምር እያልኩ ሳስብ፣ ታፋዎቿ ላይ መፅሀፍ አየሁ፡፡ ታፋዋን ጎሸም አደረኩና፣

“ልየው?” አልኳት፣ እጄን ወደ መፅሐፉ እየጠቆምኩ፡፡

ይቻላል በሚል ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ፡፡ መፅሀፉን አነሳሁት::የፊት ገፅ ሽፋኑ ላይ ጓድ ኮርኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱት ፎቶ ይታያል፡፡ የመፅሀፉ ርዕስ ነበር
ይላል፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ ይህን መፅሀፍ ብዙ ጊዜ መፅሐፍ አዟሪዎች ላይ አይቼዋለሁ፡፡ አንስቼ የጀርባ ፅሁፉን ለማንበብ እንኳ ተነሳሽነቱ አልነበረኝም፡፡ የዛ ትውልድን መፅሐፍት ፈልጌ ነበር የማነበው።ይገርሙኛል፤ ያስቀኑኛል፤ ይደንቁኛልም፡፡ በመንግስት አፍንጫ ስር
የመደራጀት ጥበባቸው፣ ዲሲፕሊናቸው፣ ለድርጅታቸው ያላቸው ፍፁማዊ ታማኝነት፣ ይደንቀኛል፡፡ ስለዚህ፣ ፈልጌ አነባቸዋለሁ።የመንግስቱ ኃ/ማርያምን ጨፍጫፊነትን ይቅር የምልበት ምክንያት
ፍለጋ ግን አላነብም፡፡ ልቤ ዝግ ነው፡፡ ስለዚህ አልገዛሁትም፡፡ እንኳን መፅሐፉን ገዝቼ ላነበው፣ ሚያነበው ሰው ያለ ፀአይመስለኝም ነበር፡፡

“ያንቺ ነው?” አልኳት ተገርሜ፡፡

“አሁን አይደል ከኔ የወሰድከው?” አለችኝ፣ በፈገግታ ነጫጭ ጥርሶቿን ፍልቅቅ አድርጋ፡፡ ፈገግታዋ የልብን ምት የሚጨምር ጨረር ይረጫል፡፡

“ማለቴ ልታነቢው ነው?” በመገረም ጠየኳት፡፡

“እንዴ...! አዎ! ምነው? ችግር አለው?”

ደግማ ፈገግ እያለች፡፡

“ኢሰፓ ቤተሰብ አለሽ?”

“ኧረ የለኝም፡፡” ኪ.ኪ.ኪ...

“ግን፣ ለምን እንዲህ አልከኝ?”

“ሴት፣ የፖለቲካ መፅሀፍ፣ ደግሞ የመንስቱ ኃ/ማርያም ታሪክ፣ በጣም ደንቆኝ ነው!”

“መፅሐፉን አንብበኸዋል ግን?”

“ኧረ በጭራሽ! ሳየው ገና ያንገሸግሸኛል!”

“ብታነበው ግን፣ እርግጠኛ ነኝ እንደዚህ አትጠላውም፡፡”

“ምን ፈልጌ ነው ማነበው?

አልጨፈጨፍኩም እንዲለኝ? ወይስ
ቀይ ሽብር ፅድቅ ነው እንዲለኝ? ለማንኛውም ተይው፡፡ ወዴት ነሽ?”

“ባህርዳር፡፡ አንተስ?”

“ባህር ዳር፣ ከዛ ጎንደር
👍3
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞይዞራል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ አባይ፣ አባይ ሲባል እየሰማሁ ነው ያደኩት፡፡ በውስጤ አባይ ግዙፍ ነው፡፡ ወደ ድልድዩ እየተጠጋን ነው፡፡ አሁን በደንብ ወንዙ ይታየኛል፡፡ የአለም እረጅሙን ወንዝ አባይ...፣ በሱዳን አቋርጦ፣ ግብፅን አጠጥቶ፣ ተርፎ
ሜድትራያንያን ባህር የሚገባው አባይ... ፣ በሁሉም አቅጣጫ ለማየት ሞከርኩ፣ በደንብ ተንጠራራሁ፣ አባይ እንደጠበኩት ግዙፍ አልሆንልህ አለኝ፡፡ ውስጤ አግዝፌው ስለነበር ይሆን?፣ ወይስ ገና ከዚህ ወዲያ ነው ሚገዝፈው...? ይሄን እንዴት እስከዛሬ ሳንገድብ ቆየን? እነዚህ
ሃሳቦች በውስጤ ተሯሯጡ፡፡

ልጅቷ ነቃች፡፡ ዐይኗን እያሻሸች ቀና ብላ አየችኝ፡፡

“እንቅልፋም!” አልኳት፡፡

ፈገግ ብላ፣ “ብዙ ተኛሁ እንዴ?”

“እንጃ፣ እያነበብኩ ነበር፤ አላስተዋልኩም፡፡”

“መፅሀፉ አሪፍ ነው አይደል?”

“በጣም ምርጥ ነው፡፡ ይቅርታ ተሳስቻለሁ፡፡”

“ችግር የለውም፡፡ እንኳን ተመቸህ፡፡”

“እንደውም አልሰጥሽም፤ ወስጄዋለሁ፤” አልኩኝ ፈገግ ብዬ፡፡

“ችግር የለውም፡፡ ሌላ እገዛለሁ፡፡”

“ዋጋውን ግን፣ በእጥፍ እከፍላሁ::”

“በጭራሽ አይሆንም፡፡ እንደውም ስጦታዬ ነው፡፡”

“እንዴ ለምን?፣ምን አድርጌልሽ?››

«እንደ ፍራሽ ተኝቼብህ ለመጣሁት፡፡”

“ከተማሪማ ስጦታ አልቀበልም፤” አልኩኝ ሆን ብዬ፤ ገና አሁን እንተዋወቅ ላለማለት፡፡

“ማነው ተማሪ ናት ያለህ?”

“ውይ ለካ በደንብ ሳንተዋወቅ ነው፤ ወደ ወሬ የገባነው፡፡ ያቤዝ እባላለሁ።”

“ህይወት፡፡ ስምህ ደስ ሲል፡፡ ምን ማለት ነው?”

“እ...፣ በችግር ውስጥ የተወለደና ለችግሩ መፍትሄ የሆነ ማለት
ነው ሲሉ ሰምቻለው፡፡”

“ትርጉሙም ስሙም በጣም ደስ ይላል፡፡”

“ይሆናል፡፡ እኔ ግን እስካሁን ችግር እንጂ፣ የችግር መፍትሄ ሆኜ አላውቅም፡፡”

“ወደፊት ትሆናለሃ፡፡”

ሃሃሃ...ወደፊት ትሆናለህ'፣ ወደፊቴን ላጠፋው እየሄድኩ እንደሆነ ብታውቂ..፣ በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ ዳግሞ መፅሀፉን ገለጥኩት፡፡ አላባበለኝም፡፡ በፍጥነት ጭልጥ አድርጎ አስመጠኝ፡፡ ላድናት ጥፍሬን ያሾልኩለት ቆንጅዬ፣ ዳግም አጠገቤ እንደሌለች እረሳኋት፡፡
መልሳ ጋደም አለችብኝ፡፡ አሁን ቤተኛ ሆነናል፡፡ ቀጥታ ታፋዎቼ ላይ ተጋደመች፡፡ ቀይ፣ ለጋና ሰልካካ ፊቷን አየሁት፡፡ ያስጎመዣል፡፡ የሹራብ ጃኬቴን አውልቄ እንድትንተራሰው ሰጠኋት፡፡ ተቀበለችኝ፡፡ መፅሀፉ ግን ማግኔት ነው፡፡ መልሶ ወደ ራሱ ይጎትተኛል፡፡ ወታደሩ የህዝቡን አመፅ እንዴት ወደራሱ ጠምዝዞ እንደቀለበሰው፣ አተራረኩ ይገርማል፡፡ ሻለቃ መንግስቱ በደርጉ ምስረታ ስብሰባ ላይ ባደረገው ዲስኩር፣ እንዴት የሰው
ልብ እንደገዛ ማንበብ ይመስጣል፡፡ የዚያው የመጀምሪያ ቀን ዲስኩር
ማሳረጊያ 'ኢትዮጵያ ትቅደም' መፈክር፣ የሀገሪቷ የአስራ ሰባት ዓመት ቋንቋ መሆኑን ማንበብ ይደንቃል፡፡ አብዛኛውም የሃገራችን ፖለቲካ መዘወሪያ ሃሳቦች እንደዚህ ባሉ ቅፅበታዊና ስሜታዊ ሁኔታ ሚፈጠሩ ይሆን እንዴ ብዬ አሰላሰልኩ፡፡

ህይወት ትገላበጣለች፡፡ ታፋዎቼ መሀል ሞቀኝ፡፡ አሁን ትኩረቴ ሲበተን ታወቀኝ፡፡ የሚሰማኝ ሙቀት፣ ካሰመጠኝ ድንቅ መፅሀፍ፣ እየጎተተ አውጥቶ፣ ትኩረቴን ወደ እርሷ እያደረገው ነው፡፡ ስለእርሷ
ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እያነበብኩ፣ አንድ እጄን ጭንቅላቷ ላይ ጣልኩት፡፡

ፀጉሯን መደባበስ ጀመርኩ፡፡ በስሱ ፊቷን ዳበስኩት፡፡ ያፍንጫዋን ስልካካነት ወደታች በስሱ ወረድኩት፣ እናት ልጇን እንደምትዳብሰው፤ ፍቅረኛማቾች እንደሚደባበሱት፣ የከንፈሮቿን ጠርዝ እየተከተልኩ በጣቶቼ ጫፍ ዳበስኳቸው፡፡ ዝም፣ ጭጭ፡፡ መልሼ፣ በፀጉሮቿ መሀል
ጣቶቼን ላኳቸው፡፡ አሁን፣ መፅሀፉን ለይስሙላ ነው የያዝኩት፡፡ እያነበብኩት አይደለም፡፡

ስሜቴ እየሞቀ መጥቷል፡፡ እንቅልፍ ካልወሰዳት፣ የተኛችበት ታፋዎቼ መሀከል ያለው እንቅስቃሴ፣ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ አዎ እንቅልፍ ካልወሰዳት፣ እኔ ምንም መናገር አይጠበቅብኝም፡፡ መፅሀፉን ዘግቼ አስቀመጥኩት፡፡ ትኩር ብዬ፣ ቁልቁል እንደ ፍቅረኛ እያየኋት
ነው፡፡ የሌሎች ተሳፋሪዎችን ዐይንና ቀልብ ከሳብን ቆይተናል፡፡ አብረን
የመጣን ፍቅረኛሞች፣ ባልና ሚስት እንጂ፣ በድንገት እዚሁ የተገናኘን
አንመስልም፡፡ ተሳፋሪዎች በአግራሞት እየተመለከቱን ነው፡፡ ህይወት በጣም ቀላል፣ተግባቢና መስህብ ያላት ቆንጆ ነች፡፡ በጣም የምንዋደድ ፍቅረኛሞች እንመስላለን፡፡

ትወስደዋለህ፤ እስጥሃለሁ፤ ያለችኝ ውልብ አለብኝ፡፡ አሁን ለእኔ ጊዜ ስጠኝ መፅሀፉን ሌላ ጊዜ ታነበዋለህ ማለቷ ይሆን? ስሜቴ ሲያድግ ታወቀኝ፡፡ አሁን እንኳን ማንበብ፣ ዐይኔን እንኳ ከእርሷ መንቀል አልቻልኩም፡፡ እዳብሳታለሁ፡፡ እየሰማች ከሆነ፣ ታፋዎቼ መሀከል
የተፈጠረው እሳተ ጎሞራ፣ ስሜቴን በማያወላዳ መልኩ ያሳብቅልኛል፡፡

ማስረዳት አይጠበቅብኝም፡፡ እንቅልፍ እንዳልወስዳት ማረጋገጥ አለብኝ፡፡
ስሜቴን እየሰማችው መሆን አለመሆኑን ማወቅ አለብኝ፡፡ ትኩር ብዬ አየኋት፡፡ ቁልቁል የተንሰለከከ አፍንጫዋን በጣቶቼ በፍቅር እየዳሰስኩት ወረድኩኝ፡፡ ቁልቁል ወርጄ ጫፍ ላይ ስደርስ፣ በጣቶቼ ቀስ ብዬ አፍንጫዋን ጭምቅ፣ እፍን አደረኳት፡፡ ወዲያው ቀና ብላ፣

“ልትገለኝ ነው እንዴ?” አለችኝ፡፡

ፈገግ ብዬ፣ “እና ጥለሽኝ ስትተኚ...”

“አንተስ ጥለኸኝ በመፅሃፉ ስትመሰጥ አልነበር፡፡”

“የእውነት፡፡ መፅሀፉ ውበትሽን ሚገዳደር ነው፡፡”

“ፖለቲካ ትወዳለህ ማለት ነው፡፡”

“እንደዛ ሳይሆን፣ የያ ትውልድ ታሪክ ይማርከኛል፡፡

ችሎታቸው፣ ዲሲፕሊናቸው፣ የሀገር ፍቅራቸው፣ አሁን እንኳን ሀገር እየመሩም እየተቃወሙም ያሉት እነሱ እኮ ናቸው፡፡”

“አሁን ወጣቱ ሁሉ ፖለቲከኛ አይደል እንዴ?”

“ማለቴ፣ አሁን ያለችው ኢትዮጵያ የዛ ትውልድ የአዕምሮ ውጤትና የእጅ ስራ እየሆነችኮ ነው፡፡ ያ ትውልድ መሬት ላራሹ ብሎ ፊውዳሊዝምን በታተነ፡፡ ኢትዮጵያዊ ማነው ብሎ ሞግቶ፣ የብሄር ብሄረሰብን መልክ፣ መልኬ ነው ብላ እምትቀበል ኢትዮጵያን እጇን ጠምዝዞ እየገነባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረስብ ነች ብለው፣ መሀል አዲስ አበባ ላይ የብሄር ብሄረሰብ አደባባይ አኑረዋል፡፡ ወደድንም ጠላንም
አሻራ ያላቸው ትልቅ ትውልዶች ናቸው፡፡ እኛ በእነሱ ጥላ ተከልለን አሻራ ቢስ ሆነን ልናልፍ ነው፡፡”

“ግን ያ ትውልድ፣ ያልከው ብቻ አይደለም እኮ፡፡ አስተዋዩና ባለ ልዩ አምሮ ያልከው ያ ትውልድ፣ እርስ በርሱ ተባልቷል፡፡ ወንድም ወንድሙን ገሏል፧ ኢትዮጵያዊ ባህል ባልሆነ ጭካኔ ሀገሪቷ የደም
አኬልዳማ አድርጓታል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ በላይ አማኝ በሆነ ማሀበረሰብ፣ ከማርክስ ሌኒኒስት አስተምሮ ተነስቶ፣ ሀይማኖት የቀኝ ገዢዎች የማህበረሰብ ማደንዘዣ ድሪቶ ነው፤ አውልቁና ጣሉት አለ፡፡ ማህበረሰቡን እሴት አልባ አደረገው፡፡ መሰረቅ ባህላችን ሆነ፡፡አረ ስንቱን ..::”

“የእርስ በእርስ ጦርነቱን እንኳን ተይው፣ እንደ አንድ የማህበረሰቡ ባህልና እሴት አብሮን የኖረ ነው፡፡ ግን ቆይ ቆይ፣ ሀይማኖት ማህበረሰባችን አላደነዘዘም እያልሽኝ ነው? የሆነ ችግር ሲያጋጥመው
ለመፍታት ከመጣር ይልቅ፣ ሁሉ ለበጎ ነው ብሎ ችግሩን ተላምዶ እንዲኖር ሀይማኖት አላደረገውም እያልሽኝ ነው?”

‹‹ሀይማኖታችን የሚለው ያልሰራ እርሱ አይብላ ነው፡፡››

“ኧረ..? እና ለዚህ ነው፣ ባልጠፋ ጊዜ በታህሳስ የዘራውን ሰብል እንዳይሰበስብ የሰማይ ወፎች አይዘሩም አያጭዱም የሰማይ አባታቸው ይመግባቸዋል እንጂ፤ ብሎ የሚስብክ ቤተክርስቲያን ማህበረሰብን
👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ጨዋታ እንቀይር፡፡ በሀይማኖት ተከራክሮ፣ መቀያየም ካልሆነ መተማመን ማይታሰብ ነው፡፡”

“እሺ! ደስ እንዳለህ፡፡ ግን ሳስብህ ልብህ በውጪው ባህል የሸፈተ ይመስላል፡፡ ሚስትህ ፈረንጅ ነች እንዴ...?”

“ኧረ ሚስት የለኝም፡፡”

“ሚስትም ባይሆን ፍቅረኛ፡፡”

“ፍቅረኛም የለኝም፡፡”

“እሺ፣ ፈረንጅ ጠብሰህ ታውቃለህ?” ያን ፈገግታዋን ፍልቅቅ አደረገችልኝ፡፡

“እንደሱማ፣ አንድ ሁለቴ አይጠፋም፡፡”

“እውነት..?! ምናቸው ደስ ብሎህ?

ከአበሻ እንዴት በለጡብህ?”

ፊቷን ኮሶ እንደሚጠጣ ሰው ከስክሳ አከታትላ ጠየቀችኝ፡፡

“እንደኔ እብድ ናቸው፡፡ ከፈለጉሽ እራሳቸው ይጠብሱሻል፡፡ አስር
ገሰስ አያበዙም፡፡”

“እራሳቸው ይጠብሳሉ? እንደሱ አጋጥሞህ ያውቃል? በናትህ
ንገረኝ?” እንዳወራት ፍልቅልቅ ፈገግታዋን ቀብድ ከፈለችኝ፡፡

“እሺ፡፡ አንዴ አብራኝ የምትስራ ባልደረባ
ነበረችኝ፡፡ እንቀራረባለን፡፡”

“እሺ...”

“አብረን እንሰራለን፤ አብረን እንበላለን፡፡ አንድ ቀን፣ አስቸኳይ ስራ እየሰራን፣ ምሳ ደረሰ፡፡ እራበን፡፡ ስራው አሰቸኳይ ስለነበር ላፕቶፑን ይዘን እየሰራን ምሳ ልንበላ ወጣን፡፡”

“እሺ..”

እየሰራን ምሳ መጣ፡፡ እኔ እየበላሁ ሃሳብ አዋጣለሁ፡፡ እርሷ እየፃፈች አልፎ አልፎ ትጎርሳለች፡፡ ትንሽ እንደበላን፤
'አበሻ ጥሩ ባህል አለው፤ አለችኝ ::

ምንድን ነው እሱ?” አልኳት፡፡

ሲበላ ይጎራረሳል፡፡ አለችኝ፡፡

በአሽሙሯ በጣም ተገርሜ ሳቅኩና አጎርሳት ጀመር፡፡ ሳጎርሳት ሆን ብላ፣ ጣቶቼንም በስስ ከንፈሮቿ ላሰቻቸው፡፡ ቀና ብዬ ሳያት፣በመሽኮርመም ፈገግ አለች፡፡ የሆነ አዲስ ስሜት ወረረኝ፡፡ ከስራ
ባልደረባነቷ በተለየ፣ በሌላ ስሜት አሰብኳት፡፡ ማታ አስቸኳይ ስራውን
ስለጨረስን፣ እናክብረው፣ ልጋብዝህ አለችኝና ሞቅ እስኪለን ስንጠጣ፣
ስንጫወት፣ ስንስቅ አመሸን፡፡ ሲመሽ መኪናዋ ድረስ ሸኘኋት፡፡ እንድገባ ጋበዘችኝ፡፡ ገባሁ፤ ሳታስፈቅደኝ ትስመኝ ጀመር፡፡ አለተቃወምኳትም፡፡በቃ ተጀመረ፡ ከዛ ቀን በኋላ፣ ዛሬኮ የደሞዝ ቀን ነው፣ አርብ ነው፣ ደብሮናል፣ ብዙ ስራ ሰርተናል...፣ ተያይዞ መውጣት ሆነ፡፡”

“እብድ ነህ፡፡”

“አንዳንዴ አዎ፡፡ ግን፣ ሁሌም እብድ ብሆን ደስ ይለኛል፡፡”

“ማለት?”

“ደስ ደስ የሚሉ ነገሮችን የምሰራው፣ እብድ ስሆን ነዋ፡፡ ያለበለዛ ይሰለቸኛል፤ ያስጠላኛል፤ ውስጤ ይጠወልጋል፤ የመኖር ለዛው ይጠፋብኛል፡፡”

“ሆ ...፣ ቆይ አሁን እብድ ነህ...?” ሳቀችብኝ፡፡

“ሃ...ሃ...ሃ.... በጣም አታስቂኝ፤ ልትሸሺኝ ነው?” ድንገት ንዴት ተሰማኝ፡፡

“እና...፣ አስፈራራኸኝ እኮ፡፡” ይባስ ተበሳጨሁ። የተማረች አንባቢ ብዬ አፌን የከፈትኩላት፣ ቀልድ ማይገባት እንጭጭ ነች፡፡

“አታስቢ እናቱ፣ እኔው ቀድሜ እሸሽሻለሁ፡፡”

“ኧረ ባክህ?” አለችኝ፡፡

አልመለስኩላትም፡፡ ወደ ውስጤ ተወሸኩኝ፡፡ ባወራሁላት ነገር ማንነቴን የገመተችኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እየቆየ በጣም እየተናደድኩና እየተበሳጨሁ መጣሁ፡፡ በዝምታዬ ውስጥ ንዴቴ ይንቀለቀል ጀመር፡፡ዝምታዬ ያሰፈራል። ደንግጣ ፀጥ አለች፡፡ ወሬ ጠፋባት፡፡ ልጅቷ በአንዴ አስጠላችኝ፡፡ እረጅም መንገድ በፀጥታ ተጓዝን፡፡ አስራ ሁለት ሰዐት አልፎ ለዐይን ያዝ ማድረግ ጀምሯል፡፡ እንደዛ ልቤንና ውስጤን ያቆመ
ውበቷ፣ እንደጉም በኖ ጠፋ። ማርቆስ ደረስን፡፡

“እንቺ መፅሃፍሽን!” አልኳት፡፡

“ስጦታዬ ነው፣ አንብበው፡፡”

“አመሰግናለሁ! ገዝቼ አነበዋለሁ፤ ስጦታሽ አያስፈልገኝም፡፡” ብዬ መፅሃፉን ገፈተርኩላት፡፡

“ቆይ ምንድን ነው ያስቀየምኩህ?
በአንዴ እንዲህ የተለወጥከው፡፡”

“ምንም አላጠፋሽም፡፡ ፈልጌው ነው፡፡”

“ኧረ ይደብራል፡፡ እሺ ካስቀየምኩህ ይቅርታ!”

“አላስቀየምሽኝም፡፡ ይቅርታም አያስፈልግም፡፡”

መኪናው ሰው ለማውረድ ቆመ፡፡ አሳልፊኝ ብዬ፣ ገፈታትሪያት ልወርድ ስል፣ መኪናው ተመልሶ ሲንቀሳቀስ፣ በጀርባዬ ልደፋ ስል፣ ከኋላ ደገፈችኝ፡፡ መንጭቂያት፣ በራሴ እንደቆመ ሆንኩኝ፡፡

ሰዉ “ኧረ ቆይ ወራጅ አለ!” ብሎ ጮኸ፡፡

“ዐይን የለህም?፣ ወራጅ እየወረደ ምትነዳው? መሃይም” አምባረኩበት፡፡

“የወረደው ሰውዬ ነው፣ ወራጅ ያለኝ፤” አለ እረዳቱ፣ በሩን እየከፈተልኝ፡፡

“እና፣ ዞር ብለህ አታይም! ደደብ! እዚህ የማንም መሃይም ከየትም መንጃ ፍቃድ ይለቃቅምና፣ ስለሰው ደንታ የላቸውም፡፡”
እየተሳደብኩ ወረድኩ፡፡

በአንዴ፣ እንዲህ ምን እንዳበሳጨኝ እኔም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሰሞኑን፣ በትንሽ ነገር እናደድና ቀስ በቀስ ብስጭቴ
ከመጠን ያለፈ ይሆናል፡፡ ያናደደኝን በቅጡ ይሄ ነው ብዬ መለየት እስከማልችል ድረስ፡፡ የቀባጠርኩላት ደጋግሞ ወደ ጭንቅላቴ እየመጣ፣
ስህተት ነበርክ፤ ቀሽም ነህ፤ በነገረካት ደካማ ጎንህ አላገጠችብህ፤” እያለ
ይነዘንዘኛል፡፡ ከለቀቀኝ ብዬ አልጋ ይዤ ሻወር ወሰድኩ፡፡ ለውጥ የለም፡፡
ሃሳቦቹ እንደ ንፋስ ውልብ እያሉ መጥፎ ስሜት ይለቁብኛል፡፡ በመጠጥ
ለመደበቅ ወሰንኩኝ፡፡ እራቴን በልቼ፣ ንዴቴና ብስጭቴ እስኪጠፋ፣ እስክስክርና እስክደነዝዝ፣ ድረስ፣ መጠጦችን እየቀያርኩ ስጠጣ አደርኩ፡፡
በንጋታው አረፋፍጄ ባህር ዳር ምሳ በልቼ ጎንደር ገብቼ አደረኩ፡፡

ጉዞ ወደ መተማ ዮሀንስ

መተማ ለመሄድ፣ ከጎንደር አዘዞ መናኸሪያ ሚኒባስ ተሳፈርኩኝ፡፡ ሚኒባሱ ወደ መሙላቱ ነው፡፡ አብዛኛው መኪናው ላይ የተሳፈሩት ወጣቶች ናቸው፡፡ ከአጠገቤ የተቀመጠው ወጣት እድሜው
በግምት ስላሳ አካባቢ ይሆናል፡፡የለበሰው ልብስ ወይቧል፡፡ ከተማ ቀመስ ይመስላል በመስኮት አጠገብ ለመቀመጥ ቦታ እንዲቀይረኝ ጠየኩት።ሳያቅማማ ቦታውን ቀየረኝ፡፡ ታክሲው እስክንተፋፈግ ድረስ ትርፍ ጭኖ መንገድ ጀመረ፡፡ የያዝኩት ገንዘብ፣ በየቀኑ እየሳሳ፣ እየመነመነ፣ አሁን ያሳሰበኝ ጀምሯል፡፡ አሁን ሃሳቤን ብቀይር እንኳ፣ መልሼ መቋቋም
ማልችልበት ደረጃ ደርሻለሁ፡፡ መፍጠን አለብኝ፡፡ መተፋፈጉን ለመርሳት፣ በመኪናው መስኮት አሻግሬ ሃሳብ የሚይዝ ነገር ፍለጋ ዐይኔን ላኩት፡፡ ምንም ቀልብ ሚይዝ ሚታይ ነገር የለም፡፡

ግማሽ መንገድ እንደሄድን ታክሲው ቆመ፡፡ ሾፌሩ የአርሴማን በረከት መያዝ የምትፈልጉ ሃያ ደቂቃ ብሎ ወረደ፡፡ ተሳፋሪው በሙሉ ተከተለው፡፡ ህብስት ዳቦ፣ ብርቱካን፣ ማንጎ፣ ይዘው የሚሸጡ ወጣቶች፣
የቅድስት አርሴማ በረከት እያሉ በመስኮት በኩል ያሳዩኛል። በቀኝ በኩል ተደርድረው የተሰሩ የጭቃ ቤቶች ይታያሉ፡፡እንደሱቅና ካፍቴሪያ እየሰሩ ነው፡፡ በስተግራ በደን የተሸፈነ ተራራ ይታያል፡፡ ከተራራው ስር
ምንጮች ይፈሳሉ፡፡ ሰዎች ተሰባስበው በምንጮቹ ውሃ ልብስ ያጥባሉ፡፡
ውሃ በጀሪካን ይቀዳሉ፡፡ ተራራው ጫፍ ላይ ትልቅ የተሰቀላ መስቀል በርቀት ይታያል፡፡ ተሳፋሪዎች፣ ህብስት ዳቦ እየበሉ፣ የገዟቸውን በረከቶች በፌስታል ጠቅልለው ገቡ፡፡ ሹፌሩ የቀረ ሰው እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

አጠገቤ የተቀመጠው ልጅ፣ “ስለቅድስት አርሴማ!” ብሎ ህብስት ዳቦ ወደ እኔ ዘረጋልኝ፡፡ትንሽ ቆንጥሬ አርሴማ ትስጥልኝ አልኩት፡፡እስካሁን እንዳያወራኝ መንገድ ስዘጋበት ነበር፡፡ ሰሞኑን ድብርቴ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል፡፡ ማንንም ማናገር አስጠልቶኛል፡፡ ምግብና መጠጥ ሳዝ
እንኳ መመላለስ ሰልችቶኛል፡፡ላለመነጋገር፣ ያዘዝኩትን እንኳ ቀይረው
ሲያመጡልኝ፣ ንዴቴን ውጩ፣ ያመጡልኝን እጠቀማለሁ፡፡ ግን አሁን የቆምንበትን ምክንያት ማወቅ ፈለኩኝ፡፡

አጠገቤ የተቀመጠውን ወጣት “ለምንድነው የቆምነው?” ብዬ
ጠየኩት፡፡
👍21
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ወደ ዚህ ስትመጣ የመጀመሪያህ ነው?”

“አዎ።”

“ትቆያለህ?”

ሳምንት አካባቢ።”

“እዚያ ማዶ ሚታየው አፄ ዮሐንስ አንገታቸው የተቀላበት ቦታ ነው።” እጁን ከመንገዱ በላይ እየጠቆመ::

“መተማ ዮሐንስ ደረስን ማለት ነው?”

“አዎ፡፡ አሁን ገብተናል፡፡” ልቤ ድንግጥ ድንግጥ አለብኝ፡፡ ሚኒባሱ እየቆመ፣ ሰዎችን ያወርዳል። እስከዛሬ ያልተሰማኝ ፍርሀት እየተሰማኝ ነው፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ወደ ስንብት እየተጠጋሁ ነው፡፡
የማውራትም የማወቅም ፍላጎት የለኝም፡፡ ዝም ብዬ በዐይኔ ከተማውን መፈለግ ጀምረኩ፡፡ በግራና በቀኝ የተደረደሩ የጭቃ ቤቶች፣ ጭር ያለ ከተማ ነው፡፡ እንደጠበኩት ግርግር የበዛበት ከተማ አይደለም፡፡ ሰዐቴን አየሁ፤ አስር ተኩል፡፡ አብዛኛው ሰው ወርዶ አልቋል፡፡

“መናኸሪያ ትገባለህ?” ወያላው ፊቱን አዙሮ ጠየቀኝ፡፡

“አይ አልገባም፡፡”

“ካልገባህ መጨረሻው እዚህ ነው።”

“እሺ አውርደኝ!”

በጭራሽ እንደገመትኩት አይደለም፡፡ ለማደሪያ ሚሆን አልጋ ቤት እንኳን እስካሁን አላየሁም፡፡ ከተማዋ ትሞቃለች። አስራ አንድ ሰዓት እየሆነ ቢሆንም፣ በጣም ይወብቃል፡፡ ፍርሀት ነው መሰል፣ በጣም እያላበኝ ነው። ዝም ብዬ ዋና መንገዱን ይዤ፣ አልጋ ቤት ፍለጋ
ተጓዝኩኝ፡፡ ነጋዴ የሚርመሰመስበት፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው
ከዐይን የማይገባበት ብዬ የገመትኩት ከተማ፣ ትንሽዬ መንደር ሆና አገኘኋት፡፡ መንገድ ዳር በብሎኬት የታጠረ ሰፊ ግቢ ያለው ሆቴል አየሁ፡፡ ሰላም ሆቴል ይላል፡፡ አላንገራገርኩም፡፡ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ብቻ
አልጋ በኖረ፡፡

“አልጋ አለ?”

“አለ፡፡”

“እስቲ አሳዩኝ?”

“ባለሻወር ነው፣ ያለሻወር?”

“ባለሻወር፡፡” ቁልፍ አመጣችና አሳየችኝ፡፡

“ስንት ነው?”

“አንድ መቶ ሃምሳ ብር፡፡” ብሩን ሰጠኋትና ቦርሳዬን አስቀመጥኩ።

ሻወር ቤት ገብቼ ሻወር ቼክ ሳደርግ ውሀ የለችም፡፡ ዞር ስል፣ውሀ በባልዲ ተቀምጧል፡፡ በጣም አልቦኛል፣ ተለቃለኩኝ፡፡ እራት በልቼ ቢራ መጠጣት ጀመርኩ፡፡ ሙቀት ስለሆነ ተጠጣልኝ፡፡ ማታ ጥሩ እንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ፡፡ ቀን ወጥቼ ከተማውን ዙሪያውን ሳይ ዋልኩ፡፡
በፍፁም እኔ እንዳሰብኩት አይደለም፡፡ የከተማው ዙሪያ ለጥ ያለ ለእርሻ የሚውል ሜዳ ሲሆን፣ ዛፎች በእርቀት ነው የሚገኙት፡፡ ስዞር ውዬ አመሻሹ ላይ፣ ቢራዬን እየጠጣሁ ምን እንደሚችል ሳስብ፣ አርሴማ ገዳም የሚል ሀሳብ መጣብኝ፡፡

#ኑሮ_በገዳም

ሽቅብ ዝግዛግ ሆኖ በተሰራውን የጥረጊያ መንገድረገ፣ በግራና በቀኝ በዛፎች ተከቧል፡፡ ከፊት ለፊቴ፣ አጠር ያለ ወጣት፣ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ስዕል ያለበት ጥቁር የጨርቅ ሻንጣ በጀርባው ተሸክሞ በዝግታ ያዘግማል። እየተከታተልን ወደ ገዳሙ ዘልቀን ገባን። ከገዳሙ መግቢያ
በር ትንሽ ፈቅ ብላ ያለች የጭቃ ቤት ጋር ስንደርስ፤

“እንኳን ደህና መጣችሁ። ምዝገባ ቢጤ አለች።” አለን ፊቱ መጠጥ ያለ ጠይም ወጣት፡፡

“እሺ!” ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ልጁን መዝግቦ ከጨርሰ በኋላ፣ ትንሽ ቆየኝ ብሎት እኔን መመዝግብ ጀመረ፡፡ ስም፣ እድሜ፣ የመጡበት አድራሻ፣ የአደጋ ግዜ ተጠሪ...፣ ሁሉንም ቀይሬ ነገርኩት፡፡

“ለስንት ግዜ ነው ሚቆዩት?”

“ለሦስት ሳምንት፡፡”

“መታወቂያ ይዘዋል?”

“አልያዝኩም፡፡” አልተጫነኝም፡፡
“እሺ፣ እንግዶቻችን፣ እኔ መልካሙ እባላለሁ፡፡ በገዳሙ አስተባባሪ ነኝ፡፡ አሁን ማደሪያ ቦታ እሰጣችኋለው፡፡ ገዳሙን
አስጎበኛችኋለው፤ ስለ ገዳሙ ታሪክ፣ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች መረጃዎችን እነግራችኋለው፡፡ እዚህ ገዳም፣ ማንኛውም አዲስ ሱባኤተኛ ሲገባ እናንተ እንዳደረጋችሁት ተመዝግቦ ነው፡፡ ገዳሙ የአርምሞ ገዳም ነው:: ማውራት ክልክል ነው፡፡ አስገዳጅ ነገር ካላጋጠማችሁ በስተቀር፣ ማውራት አይቻልም፡፡ የግድ ማውራት ካስፈለገ እንኳ፣ ዝግ ባለ ድምፅ፣ በለሆሳስ ነው ማውራት ሚቻለው፡፡ እዚህ መዳን የሚገኘው በአርምሞ ውስጥ ነው፡፡”

ከኛ ውጪ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ፣ በሆዱ እንደሚያወራ፣ በጣም ዝግ ባለ ድምፅ ያወራናል፡፡ በአርምሞና በለሆሳስ ማለት እንዲህ ነው' ብዬ አሰብኩ፡፡ የሚያወራው እንዲሰማን፣ አንገታችንን ወደሱ አሰገግን፡፡ እያወራን ወደ ማደሪያችን ወሰደን፡፡ እያንዳንዱ ከሁለት መቶ ምዕመን በላይ የሚይዝ፣ አራት የማደሪያ አዳራሾች አሉ፡፡ ሁለቱ የወንድ፣ ሁለቱ የሴት እንደሆነ ነገረን፡፡ ቦታ ሊሰጠን ወደ አንደኛው አዳራሽ ይዞን ገባ፡፡ በውስጡ ከመቶ ሚበልጡ ምዕመናን አሉ፡፡አሰላሁት። በግምት በገዳሙ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሱባኤያተኛ ምዕመናን
እንዳሉ ገመትኩኝ፡፡ ገዳሙ ግን ሰው ያለው አይመስልም፡፡ ዝም፣ ጭጭ፣ ያለ ነው፡፡ ሁሉም በለሆሳስ ፀሎት ላይ ነው፡፡ ሰላምታ እንኳ፣ ጎንበስ ቀና በመባባል ብቻ ነው፡፡ ምንም አይነት የሰው ድምፅ አይሰማም፡፡የወፎች ጭጭታና የዛፎች ሽው ሽውታ ብቻ ነው፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡መንፈስን ያድሳል፡፡ አዕምሮን ያረጋጋል፡፡ ፈውስ በመንፈስ ቅዱስ
ባይላክም እንኳ፣ የቦታው ድባብ ፈውስን ይሰጣል።

“እና ሌላው...” አለ መልካሙ ቦታችንን ሰጥቶን ከአዳራሹ ይዞን እየወጣ፣ “ማንኛውም ምእመን ወደ ገዳሙ ለሱባኤ ሲገባ፤ ፀጉሩን መላጨት፣ ንስሀ መግባትና ስግደት መውሰድ አለበት፡፡” አለን እኔን እኔን እየተመለከተ፡፡

“እሺ፡፡ ማን ነው ሚላጨን?”

“እርስ በእረስ ነው ምትለጫጩት፡፡ ፈራህ እንዴ..? አንተን እኔ ቆንጆ አድርጌ እላጭሃለው፡፡” የከተማ ልጅ መሆኔን አውቆ ነው መሰል፣ ከገባን ጀምሮ እኔን እኔን እየተመለከተ ነው ሲያወራ የነበረው፡፡

“እሺ” አልኩት፡፡ አሁን ስለራሴ ብዙም ግድ የለኝም፡፡ ምላጭ ግቢ ካለው ሱቅ ተገዝቶ ሁለታችንንም ላጨን፡፡ ነብስ ካወኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን ተላጨሁ፡፡ እየላጨንም ስለ ገዳሙ መተዳደሪያ ደንብ ይነግረናል።

“በገዳሙ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የሚበላው፡፡ ጥዋት ቅዳሴ እንዳለቀና ማታ አስራ ሁለት ሰዐት። አስራ ሁለት ሰዐት ካለፈ መመገብ አይቻልም፡፡ ገዳሙ መብራት ስለሌለው፣ ማታ ማታ ሻማ ነው
ምትጠቀሙት። ሻማ ከዚህ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ የማታ ሦስት ሰዓት ፀሎት ካበቃ ቦሃላ ሻማ ማብራት አይቻልም፡፡ የእንቅልፍ ሰዓት ነው፡፡ እንዳያችሁት፣ የቦታ ጥበት ስላለ አንድ ሰው፣ በአንድ መዳበሪያ በታ ላይ ነው መተኛት ያለበት፡፡ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት ላይ ሁሉም
ምዕመን መገኘት ግዴታ ነው፡፡” ሁለታችንንም ላጭቶ ሲጨርስ አስራ
አንድ ሰዐት ሆኖ የሰርክ ፕሮግራም ተጀመረ።

“በሉ ተነሱ እንሂድ፣ የሚቸግራችሁ ነገር ካለ እዚሁ ስላለን በፈለጋችሁት ሰዓት ጠይቁኝ ፤ ” ብሎ ፕሮግራሙ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ወሰደን፡፡

የገዳም ኑሮዬ ተጀመረ፡፡ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት መነሳት በጣም ከባድ ነው፡፡ ግን፣ አማራጭ የለም፡፡ አስተባባሪዎች እየዞሩ ይቀሰቅሳሉ።ያልተነሳ ሰው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ይረጫሉ፡፡ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ
በጣም ከበደኝ፡፡ ከእንቅልፍ ሳልነቃ ውሃ ሲረጩኝ እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝረኛል፡፡ ሁለት ሦስት ቀን ሲደጋግሙኝ፣ ገና ድምፃቸውን ስሰማ መነሳት ጀመርኩ፡፡ ፀሎትና ምህላው እስከ ጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ይደረጋል፤ ከዛ ወደ ፀበል።

ገዳሙን ቅጥር ግቢ በደንብ ለማማወቅ እየተዟዟርኩ ማየት ጀመርኩ፡፡ የአርሴማ ገዳም በሃገራችን እንዳሉት አብዛኞቹ ገዳማት፣በተራራማ ቦታ ላይ ከየተመሰረተ ነው፡፡ የገዳሙ መስራችና አስተዳዳሪ
የሆኑት መነኩሴ፣ እድሜያቸው ሃምሳ ዓመት ቢሆን ነው፡፡ ገዳሙ በእውቀት እንዲለማ በደንብ አስበውበት እንደመሰረቱት ገዳሙ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ከመሰረቱት
1👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

የገዳሙ ምዕራብ ክፍል በጥቅጥቅ ደኖች የተሞላ ሲሆን፣ምዕመኑ በየዛፉ ስር ተጠልለው በአርምሞ ፀሎት ያደርጋሉ፡፡ ፀበል ይጠጣሉ። ደቡባዊው ክፍሉ ደግሞ፣ ከፍተኛ ተራራ ላይ ያለ ሲሆን፣
ወደታች ያለው የሚያሰፈራ መጨረሻው ማይታይ ጥልቅ ገደል ነው።
ለገዳሙ እንደአጥር ያገለግላል፡፡ እዚህ አካባቢ የበቀሉ ትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፍ ከግቢው አልፎ ወደ ገደሉ ይዘናፈላሉ፡፡ በዚህ አቅጣጫ ገደላማና በረሃማ ስለሆነ፣የሰው ዘር ዝር ብሎበት ሚያውቅ
አይመስልም፡፡ ገና ሳየው፣ በውስጤ እራሴን ማጠፋበት ትክክለኛው ቦታ
እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ጠጋ ብዬ ለወራት የተዘጋጀሁበትን ሰው ሳያየኝ የምፈፅምበትን ዛፍ መምረጥ ጀመርኩ። ውስጤ ምንም አይነት ፍርሃት እየተሰማኝ አይደለም፡፡ አሁን ውስጤ የሚፈልገውን ቦታ አግኝቷል፡፡
ስህተት ላለመፍጠር፣ የግቢውን እንቅስቃሴ በደንብ ማወቅ፣ ተስማሚ
ሰዓት ለመምረጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ እዛ አካባቢ ያሉ ዛፎች ስር ቁጭ ብዬ ሰው ጭር የሚልበትን አመቺ ሁኔታ እያጠናሁ፣ የገዛሁትን ፎጣ ለአሰብኩት አላማ እንዲመቸኝ በመቀስ እየቆረጥኩ በሚገባ
አስተካክዬዋለሁ፡፡ ከወራት በኋላ፣ የመጨረሻው መጨረሻ ደርሷል፡፡
ሰዎች እንዳይጠራጠሩኝ ምእመኑ ሚያደርጉትን ሁሉ እፈፅማለሁ፡፡ ሁሌ ሰርክ አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ የግቢው ዋና አስተባባሪና ሰባኪ፣ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እረጅም ቀጠን ያለ፣ ጥሩ
ተናጋሪ ጎልማሳ ነው፡፡ በስብከቱ ሰዓት ከፕሮግራሙ የሚቀር አንድም ሰው የለም፡፡ ትክክለኛው ሰዓት እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ አንድ ቀን፣የመጨረሻ ከኔ ጋር የቀሩትን የትምህርት ማስረጃዬን ጨምሮ፣ ማስራጃ ሊሆኑ ሚችሉትን፣ እንዳይገኙ ቆፍሬ ስቀብር ዋልኩ፡፡ ማታ ምዕመኑ ለጉባዔ ሲሄድ እኔ የተለመደው ቦታዬ ቁጭ ብዬ የእቅዴን መጨረሻ
ለመፈፀም አደፈጥኩ፡፡ እንደጠበኩት ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ተነስቼ ያስተካከልኩትን ፎጣ ቼክ አድርጌ፣ ወደ መረጥኩት ዛፍ ሄድኩ፡፡ ድንገት ኬት እንደመጣ ያላስተዋልኩት አስተባባሪ፤

“እንዴት አመሸህ?” አለኝ፡፡

“እግዚአብሄር ይመስገን!” በንዴት መለስኩ፡፡

“የምሽት ጉባኤ ተጀምሯል እኮ፣ አትሄድም እንዴ?”

“እየሄድኩ ነው፡፡” ኬት ነው የመጣው ባካቹ ኮቴ ቢስ፡፡ ሄጄ የተለመደውን ስብከት ተከታተልኩ፡፡

ከጉባኤ ስመለስ መልካሙን አገኘሁት፡፡ ከገባንበት ቀን ጀምሮ ባገኘኝ ቁጥር ያወራኛል፡፡ የገባሁ ቀን ስለ ላጨኝ የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቼዋለሁ፡፡ ሊቀርበኝ ይሞክራል፡፡ ለሻወር ውሃ ላምጣልህ ይለኛል፡፡ሲያመጣ የተወሰነ ነገር እሰጠዋለሁ፡፡ በዛ አምኖኝ ነው መሰል፣ ስለ ገዳሙ ጥሩም መጥፎም የሚሰማውን ይነግረኛል፡፡ የገዳሙ አባት
ከፍተኛ ሀይል እንዳላቸው፣ እርሳቸው ሲመጡ፣ በግቢ ውስጥ ሰይጣን
ያለበት ሁሉ እንደሚጫኽ፣ ከከፍተኛ የባለስልጣን ሚስቶች ጀምሮ የውጪ ሃገር ዜጎች እዚህ እንደሚመጡ ይነግረኛል፡፡ ወራትን የቆዩ ምዕመናን አስተባባሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ ግን አንዳንዶች ያልሆነ ወሬ ስለሚያወሩ መባረር እንደሚያሰጋቸው ያጫውተኛል፡፡ ቢወጡ መሄጂያ፣መጠጊያ ስለሌላቸው እዛ መሆንን እንደመረጡ፣ ተሸሎኝ ወደ መኖሪያዬ ስመለስ እንድጠይቀው፣ እዚህ ኑሮ ከባድ እንደሆነ፣ ከቤት ውጪ ሌላ
ደሞዝ እንደሌላቸው፣ እንደኔ ያሉ አንዳንድ ምዕመናን በሚያደርጉላቸው ድጎማ እንደሚኖሩ አጫወተኝ፡፡

አብዛኛው በገዳሙ የሚገኙት ምዕመናን ወጣት ናቸው፡፡ አማካኝ ዕድሜ ቢስላ ከሰላሳዎቹ መጀመሪያ አይዘልም፡፡ አብዛኞቹ ለሳምንታትና ለወራት ሚቆዩ ናቸው። ባገኘሁት አጋጣሚ ብዙኃኑ ሰው የመጣበት ምክንያት፣ ሰይጣን አለብኝ ብሎ በመጨነቅ፣ በህይወት አለመቃናት
የተከሰተ ጭንቀትና ሌሎች ዓለማዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በገዳሙ ሁለተኛ ሳምንት እንዳለፈኝ፣ አይታወቅምኮ እኔም ስይጣን አሞኝ ይሆናል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ሰው እንዴት በሀገር ሰላም እራሴን ላጥፋ ብሎ፣ ይሄን ሁሉ ሀገር አቋርጦ ይመጣል? ለማንኛውም፣ ፀሎት
መድሃኒት ነው ብዬ፣ ለሱባኤ ዋሻ ገባሁ፡፡

የዋሻው አስተባባሪ መነኩሲት፣ ስለዋሻው ህግና ደንብ ትነግረኛለች፤ አፍጥጬ አያታለሁ፡፡ እጅግ ዘመናዊ የምትመስል፣ ሴት ናት፡፡ ጥርት ያለው የፊቷ ቆዳ፣ የገዳማዊ ሴት ሳይሆን፣ ሜክ አፕ
የተቀባች፣ ኑሮ የደላት፣ የከተማ ልጅ ፊት ይመስላል፡፡ ከተሸፈነችበት ነጭ ነጠላ፣ አልፎ ሚታየው ንፁህ፣ ሉጫና ደማቅ ጥቁር ፀጉሯን ሳይ መሀል አዲስ አበባ እንጂ፣ ገዳም ውስጥ ያለሁ አልመሰልህ አለኝ፡፡እያወራች ስታየኝ በሃዘኔታ የምትመለከተኝ መሰለኝ፡፡ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስንት ጊዜ እንደምፀለይ፣ እንደሚሰገድ፣ እግዚኦ ሲባል እንዴት
ጣት እንደሚቆጠር፣ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት በእርሷ እየተመራን እንደምንፀልይ አስረዳችኝ፡፡

እኔ ይህች ለጋ ሴት እዚህ ምን ትሰራለች እያልኩ በመገረም አያታለሁ፡፡ አይደለም ስግደት፣ ፆም ባለፈበት አልፋ ምታውቅ
አልመስልህ አለኝ፡፡ እኔ እዚህ ከመጣሁ፣ በሁለት ሳምንት ብቻ ብዙ እንደከሳው ታውቆኛል፡፡ የሱሪዬን ቀበቶ ቀዳዳ ሁለቴ ቀይሬያለሁ፡፡በዋሻው ሚቆየው ሦስት፣ ሰባት፣ አስራ አራት እና ሃያ አንድ ቀን ነው፡፡በሱባኤው ጊዜ፣ ለምትፀልይበት ጉዳይ አርሴማ በአምሳል ተገልጣ
መፍትሄ ትስጥሃለች አለችኝ፡፡ እንደታዘዝኩት መፀለይኩ፣ መሰገድ
ጀመርኩ፡፡ በጣም ከባድ ነው፡፡ እረሃብ አጠወለገኝ፤ ስግደቱ አወላለቀኝ፡፡
የለሊቱ ቅዝቃዜ ይጠዘጥዛል፡፡ መሬቱ በጣም የቆረቁራል፡፡ እንቅልፍ ማይታሰብ ነው፡፡ እዚህ አንዱ ቀን በጣም እረጅም ነው፡፡ ከሦስት ቀን በፊት መውጣት ቢቻል፣ ሲነጋ ውልቅ እል ነበር፡፡ በዛ ላይ ፣ትንሽ ሸለብ ሲያደርገኝ፣ ሰይጣን ክፋቱ መነኩሲቱን እያመጣብኝ ይፈትነኛል፡፡
ሦስቱን ቀን እንደምንም ጨረስኩኝ፡፡ ልወጣ ስል እንዳገባቤ መነኩሲቷ፣
አናገረችኝ::

“እንዴት ነበር ሱባኤህ?

ጥሩ ነበር አልከትና ከዋሻው ወጥቼ ወደ አዳራሼ ተመለስኩኝ፡፡ማታ እንቅልፍ አልወሰደኝም፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ታክቶኛል። ባለፈው ያ አስተባባሪ ነው ከመንገዴ ያቆመኝ፡፡ አሁን መሳሳት የለብኝም፡፡
የባለፈውን ስህተት ላለመድገም ለሊቱን እያቀድኩ እስኪነጋልኝ ቸኮልኩኝ፡፡ እንቅልፍ በዐይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ አስር ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ ሙሉ ትጥቄን ይዤ ወጣሁ፡፡ ያቀድኩትን ለመፈፀም ገመዱን አስተካክዬ ዛፉ ላይ ካስርኩ ቦሃላ፣ እስኪጨልም ለመደበቂያነት ወዳሰብኩት
የሚያስፈራው ተራራ ጀርባ ቀስ ብዬ ለመውረድ ስል፣ አፈሩ እየተናደ ቁልቁል ሲዖል ወደ ሚመስለው ጥልቅ ገደል ይዞኝ መውረድ ጀመርኩኝ፡፡


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#የመጨረሻው_መጨረሻ

ድንገት ስነቃ እራሴን አልጋ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ አገኘሁት፡፡ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ እራሴ አካባቢ፣ በቀኝ በኩል ሰውነቴን፣ፊቴን ይጠዘጥዘኛል፡፡ ዐይኖቼን ለመክፈት ሞከርኩ፡፡ የቀኝ ዐይኔን
ህመም ተሰማኝ፡፡ አልከፈት አለኝ፡፡ ዐይኔ ምን እንደሆነ ለመዳበስ፣ የቀኝ እጄን ለማንሳት ስሞክር፣ እ...ህ... ከፍተኛ ህመም፡፡ ማንቀሳቀስም፣ ማንሳትም አልቻልኩም፡፡ እጄስ ምን ሆኖ ነው...? ወደ እጄ ዞር ስል፣አንገቴ ከሆነ ነገር ጋር ታስሯል፡፡ ምን ሆኜ ነው..? የት ነው ያለሁት..? ማን ነው እዚህ ያመጣኝ...? በግራ እጄ ላይ የግልኮስ ገመድ
ተንጠልጥሎ አየሁ፡፡ ሆስፒታል ነው ያለሁት። የት ሆስፒታል ነው ያለሁት?፣ ምን ሆኜ ነው...? ለማስታወስ ሞከርኩ፡፡ ብዙ ጥያቄዎች በፍጥነት በጭንቅላቴ ተመላለሱብኝ፡፡ በበር በኩል፣ በርቀት አንድ ነጭ ገዋን የለበሰ ሰው ሲገባ አየሁ፡፡ እንዲስማኝ፣ አ...ብዬ አቃሰትኩ፡፡
እንደገመትኩት ድምፄን ሰምቶ ነው መሰል፣ በቀጥታ ወደ እኔ መጣ፡፡

“ኦ...ነቃህ?፣ በጣም ደስ ይላል፡፡ እንዴት ነህ?፣ ምን ይሰማሃል?” አለኝ፡፡

“ደህና ነኝ፡፡ ትንሽ እራሴ አካባቢ...” በደከመ ድምፅ፡፡

“ቆይ መጣሁ፡፡” ብሎኝ ሄደና፣ ብዙም ሳይቆይ የታካሚ ካርድ ይዞ ተመለሰ፡፡

የግራ እጄን ይዞ የልብ ምቴን ቆጠረ፡፡ በደም መለኪያ የደም ግፊቴን ለካ፡፡ ዐይኖቼን ከፍቶ አያቸው፡፡ ደረቴን በማዳመጫ አዳመጠ፡፡እግሮቼን አንቀሳቅስ እያለኝ፣ እግሮቼን በሹል ነገር እየወጋኝ፣ በሙሉ ስውነቴን መረመረኝ፡፡

“የት እንዳለህ አውቀሃል?” ጠየቀኝ፡፡

“ሆሰፒታል ነኝ መሰለኝ..."

“በጣም ጥሩ። እኔን ታውቀኛለህ?”

“አላውቅህም፡፡ ግን ዶክተር ትመስለኛለህ፡፡”

“እሺ፤ አሁን ስንት ሰዐት ይመስልሃል?”

“ሰዓቱን አላውቅም፡፡”

“በግምት፣ ጥዋት ከሰዓት ወይስ ምሽት ይመስልሃል?”

“መገመት ይከብደኛል።” አጠገቤ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠና መፃፍ ጀመረ፡፡ ለደቂቃዎች ከፃፈ በኋላ፣ “አይዞህ፡፡ ትንሽ አደጋ ደርሶብህ ነው፡፡ አሁን ደህና ነህ፤
ተርፈሃል፡፡ እራስህና እጅህ አካባቢ ትንሽ ጉዳት ደርሶብሃል፡፡ ግን እድለኛ ነህ... ተረፈሃል ለህመምህ ማስታገሻ እንሰጥሃለን አይዞህ ብሎኝ ማስታገሻ መርፌ እንድወጋ አደረገ፡፡ ከብዙ ህመም ቦሃላ መልሶ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ፣ እረጅም እንቅልፍ እንደተኛው ተሰማኝ፡፡ ቀጣዮቹም ቀናት እጅግ በጣም ከባድ ነበሩ። ያለፈውን፣ የተፈጠረውን፣ መቀበልም መቋቋም አልቻልኩም፡፡ እራሴን በቁሜ
ቦርቡሬ፣ ገዝግዤ ጨርሼዋለሁ፡፡ ዳግመኛ እንዳልነሳ እንዳላንሰራራ
አድርጌ ቀብሬዋለሁ፡፡ አሁን ለኔ መኖር ከቀደመው የባሰ ሲኦል ነው፡፡ አሁን መሞት በጣም ያስፈልገኛል፡፡ ተሰምቶኝ ማያውቅ ጭንቀት እየተሰማኝ መጥቷል፡፡ . ትንሽ ድምፅ ይረብሸኛል። እንቅልፍ አይወስደኝም፡፡ ነገርግን፣ እንኳን እራሴን ላጠፋ፣ እራሴን ማንቀሳቀስ
ማልችል እንደሆንኩ ሳስብ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ጭንቅላቴ
ሊፈነዳ ይደርሳል፡፡ በእንዲህ ባለ ሁኔታ ቀናቶች አለፉ፡፡ ዶክተሮች መጥተው ይከታተሉኛል፤ መድሀኒት ያዙልኛል። ጥዋት ጥዋት፣ የፊቴ ቁስል ይጠረግልኛል፡፡

አንድ ቀን እንደተለመደው ዶክተሮች ከጎበኙኝ ቦሃላ ሌላ እስፔሻሊስት ዶክተር መጥቶ እንደሚያየኝ ነግረውኝ ሄዱ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ሚከታተለኝ ወጣት ዶክተር እንደርሱ ነጭ ገዋን ከለበሰ ወጣት ጋር
ተመልሶ መጣ፡፡ አዲሱ ዶክተር ካርዴን ተቀብሎ አገላብጦ አነበበው፡፡

“ማን ነው እዚህ ያመጣው?” አዲሱ ዶክተር ጠየቀ፡፡

“አምስት ቀን ሆነው፡፡ ገዳም አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው አምጥተውት የሄዱት።”

ዝም አልኩኝ፡፡ በራሴ አፈርኩ፤ ዐይኔን ጨፈንኩ፡፡ አዲሱ ዶክተር፣ እኔን ሳያናግረኝ በእጁ ግራ እጄን እያሻሸ፣ ከስራ ባልደረባው ጋር ያወራል፡፡ በእጁ እንቅስቃሴ፣ ልስላሴና ሙቀት፣ በውስጡ እያዘነልኝ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

“ዶ/ር ሄኖክ እባላለሁ፡፡ ሄኖክ ብለህ ልትጠራኝ ትችላለህ፡፡ የስነ-አዕምሮ ህክምና ክፍል፣ የመጨረሻ አመት የድህረ ምረቃ ሃኪም ነኝ፡፡አንተስ ስምህን ትነግረኛለህ?” ፊቱ፣ ድምፁ፣ ሁሉ ነገሩ ላይ ሃዘኔታና ርህራሄ የሚነበብ መሰለኝ፡፡

“ያቤዝ እባላለሁ፡፡”

“ያቤዝ ማን?”

“ያቤዝ አለማየሁ፡፡”

“እድሜ ?”

“ሠላሳ አራት፡፡”

“እራስህን ልታጠፋ ሞክረህ እንደነበር፣ ምታስታውሰው ነገር አለ?”

ዝም አልኩ፡፡ ጭንቅላቴ ይወቅረኝ ጀመር፡፡

“ደህና ነህ ያቤዝ?”

“ደህና ነኝ ዶክተር።”

“እሺ ያቤዝ፣ ለህክምናህ ስለሚረዳኝ የሆነውን ነገር ልትነግረኝ ትችላለህ?፡፡ ልትነግረኝ ምትፈልገውን፣ ግን ትክክለኛውን ብቻ ንገረኝ፡፡ እያንዳንዱ የምትነግረኝ መረጃ ካንተ ፍቃድ ውጪ፣ ለማንኛም ሶስተኛ ወገን በፍፁም አይደርስም፡፡ ለቤተሰብህም ቢሆን እንኳን፡፡ መናገር የማትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ እለፋቸው፣ እንዳትዋሸኝ፡፡››
“እሺ!” አልኩት በደከመ ድምፅ፡፡ ውስጤ በጣም እየተረበሸ ነው፡፡ምን ብዬ ነው የምነግረው? ከየት ነው የምጀምረው? የተፈጠረውን ወደ ኋላ ሳስበው፣ እንባ እየተናነቀኝ መጣ፡፡

“ያቤዝ እየጠበኩህ ነው፡፡ የሆነውን፣ የተፈጠረውን ንገረኝ፡፡እራስህን ልታጠፋ ለምን ሞከርክ?”

ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ ዶክተር ሊያባብለኝ ሞከረ፡፡ ውስጤ ጭራሽ ገነፈለ፡፡ “እኔ ከሞትኩ ቆይቻለሁ፡፡ በቁሜ የአርባና ሰማንያ ተዝካሬን አውጥቻለሁ፡፡ ሀብትና ንብረቴን ነፍስ ይማር ብዬ በትኜዋለሁ፡፡ለወራት ስንከራተት የከረምኩት፣ አስክሬኔን የምቀብርበት ምቹ ቦታ ፍለጋ ነበር እንጂ፣ ላለመሞት አልነበረም፡፡ እንዴት ተረፍኩኝ...? ለምን..? እኔ
መኖር አልፈልግም...!” እየጮኸኩ ተንሰቀሰኩ፡፡ ቢያባብሉኝም፣ ማቆም
አልቻልኩም፡፡ እንባዬ የፊቴን ቁስል እየለበለበኝ ይወርዳል፡፡ ዶክተሮቹ
ከወንበራቸው ሲነሱ፣ ኮቴ ሲበዛ፣ ግርግር ሲፈጠር፣ እጄ ላይ በተቀጠለው ግሉኮስ፣ መድሃኒት ሲስጠኝ ይሰማኛል፡፡ የማለቅስበት ሃይል እየከዳኝ፣ ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ከዛች ቀን ጀምሮ የዶክተር ሄኖክ ክትትል በጣም የተለየ ነበረ፡፡እንደቤተሰብ ብዙ ሰዓታት ከኔ ጋር ያሳልፋል። ጥሩ ተቀራርበናል፤የሚሰማኝን የህመም ስሜት እነግረዋለሁ፡፡ መድሃኒት ያዝልኛል፡፡
ያዘዘልኝ መድሃኒቶች፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድተኛ እያገዙኝ ነው፡፡እኔ ሳልፈልጋቸው ወደ ጭንቅላቴ እንደፈለጉ ሚፈነጩብኝ፣ እነዛ ተላምጠው ማያልቁ አስጨናቂና ተስፋቢስ ሃሳቦች እንደ ሀምሌ ዝናብ
እኝኝ ማለታቸውን አየቀነሱልኝ ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ በተለየ አቅርቦት ይንከባከበኛል፡፡ እንደታካሚው ሳይሆን፣ እንደታላቅ ወንድም፣ እንደቤተሰብ፣ በሁሉም ነገር እያገዘኝ ነው፡፡ ከሁሉም ታካሚዎች ቀድሞ እኔን ይጎበኘኛል የሚያስታምመኝ ቤተሰብ ስለሌለ ይሁን አዛኝ ተፈጥሮ
ኖሮት ባላውቅም፣ ካወቀኝ ጀምሮ ከኔ አልተለየም፡፡ የህክምና ወጪዬንም
እየሸፈነ እንደሆነ አውቂያለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ምግብ ከውጪ ያስመጣልኛል፤ አብዛኛውን ግዜ ስራውን ሲጨርስ፣ በተለየ ርህራሄና ፍቅር ያጫውተኛል፤ ያበረታታኛል፡፡ ተስፋንና ጥንካሬን በውስጤ ይረጨል፡፡ ቀናቶች ሲያልፉ፣ እየተሻለኝ መጥቷል፡፡ የፊቴና የእጄ
ቁስሎች ለውጥ አላቸው፡፡ ህመሞቼ እየቀነሱ፣ ለውጥ እያመጣሁ፣ የሞተው፣ የተቀበረው ተስፋዬ ዳግም ያቆጠቁጥ ጀመር፡፡

እጄን ሁለት ጊዜ ራጅ ተነሳሁ፡፡የተሰበረው አጥንቴ ጥሩ ሆኖ ጠግኗል፡፡ የታሰረልኝ ጄሶ ሊፈታልኝ ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ የፊቴ ቁስል ህመሙ ጠፍቷል፡፡ በእጆቼ ዳበስኩት፤ ይሻክራል፡፡ ፊቴ ላይ ትልቅ
የማይሽር
👍4
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ብዬ አስረዳለሁ...? ዶክተር ድንገት አጠገቤ ቁጭ ሲል ከሄድኩበት ሃሳብ
ተመለስኩ፡፡

“እንዴት አደርክ ያቤዝ?” አለኝ፡፡

“እንዴት አደርክ ዶ/ር፡፡”

“ምነው በሀሳብ ነጉደሀል? ምን እያሰብክ ነው?”

“ለወራትኮ ማሰብ አቁሜ ነበር ዶክተር፡፡ አሁን ማሰብ ስጀምር፣ ውዝፍ ሀሳብ ሁሉ ይመጣብኛል። ምን ማላስበው ነገር አለ?”

“ብዙ አትጨነቅ፡፡ ሁሉም በጊዜው፣ ቀስ በቀስ ይፈታል፡፡ ዋናው በርታ በርታ ማለት ነው፡፡” እሱ ሲያወራኝ የመረጋጋት ስሜት
ይሰማኛል፡፡

ቀጠል አደረገናም “ያቤዝ፣ አሁን ቁስሎችህ እየሻሩ ነው፡፡ ነገር ግን ስለመሰረታዊ ችግርህ እስከዛሬ በደንብ አላወራንም፡፡ ባለፈው ስጠይቅህ በጣም ስለተረበሽክ፣ እንዲያግዝህ ስሜት ማረጋጊያና ጭንቀት መቀነሻ መድሃኒትቶችን እንድትወስድ እያደረኩ ነው የቆየሁት፡፡ ካልረበሸህ፣ ባለፈው እንደጠየኩህ፣ ለምን እራስህን ለማጥፋት
ደግሜም ያልጠየኩህ እስክትረጋጋ ብዬ ነው፡፡ አሁን ለውጥ አለህ ካልረበሸህ ባለፈው እን።ጠየቁህ ለምን ራስህን ለማጥፋት እንደሞከርክ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ፡፡” ብሎ ዐይን ዐይኔን ይመለከተኝ ጀመረ፡፡

እውነቱን ነው፡፡ ለውጥ አለኝ፡፡ አሁን ሁሉን ነገር፣ ቀስ በቀስ ለምጄዋለሁ፡፡ እንባ አልተናነቀኝም፡፡ ነገርግን፣ ከየት እንደምጀምርለት ግራ ገብቶኛል፡፡ መቼም፣ ዝም ብዬ ከሞቀ ህይወቴ፣ እራሴን ላጥፋ ብዬ አልተነሳሁም፡፡ እንኳን እራስን ማጥፋት፣ በቃኝ ብሎ መመነን ብዙ ታስቦነት፣ ታኝኮና ተላምጦ ነው ሚወሰነው፡፡ ከየት ጀምሬ ልንገረው?፣
እንዴት እዚህ ውሳኔ ላይ ደረስኩ፣ እንዴት ላስረዳው?

“ያቤዝ እየጠበኩህ ነው፡፡”

“እሺ ዶክተር፡፡ ከየት እንደምጀምር ግራ ገብቶኝ ነውኮ፡፡ ታሪኩ ረጅም ነው፡፡”

“ችግር የለውም፤ ደስ ካለህ ጀምረው፡፡ ደስ ያለህን፣ ትዝ ያለህን ንገረኝ፡፡ ብቻ እውነቱን ንገረኝ፡፡ ከዛ ውስጥ እኔ የሚጠቅመኝን እወስዳለሁ፡፡”

“እሺ፡፡ እኔ በማኔጅመንት ሁለት ዲግሪ አለኝ፡፡ አስር አመታት አካባቢ በስራ ላይ ቆይቻለሁ፡፡ ህይወቴ መጥፎ ሚባል አልነበረም።ውስጤ ግን፣ ወቅት እየጠበቀ ደስታ ቢስ፣ ተስፋ ቢስ ይሆናል።ህይወትን በየመሀሉ በጥቁር መነፅር ብቻ እመለከታታለሁ። ጨለምተኛ
እሆናለሁ፡፡ የመኖር ፍላጎቴ ባዶና ገለባ ይሆንብኛል፡፡ አንዳንዴ ድግሞ፣ ህይወት ዳግመኛ ውብና አጓጊ ትሆንብኛለች፡፡ የማያቸው ነገሮች ሁሉ ያጓጉኛል፡፡ እነሱን ለማግኘት ከፍ ያለ ፍላጎትና ሃይል ይኖረኛል። ደርስባቸዋለሁ እንደጓጓሁ ስደርስባቸው፣ ሳገኛቸውና ሳቃቸው
ለተወሰነ ግዜ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግን፣ ደስታውና እርካታው መልሶ ይጠፋል። ሁሉም ማስመሰል፣ ከንቱና ባዶ ሆኖ ይመለስብኛል። አዕምሮዬ ከጥሩ ነገር ይልቅ፣ መጥፎና አስጨናቂ
ነገሮች ላይ አመዝኖ እንዳስብ ያደርጋል፡፡ እንዲህ ሲሰማኝ ስራዬን ደጋግሜ ለቅቂያለሁ፡፡ አዕምሮዬ ሚያስጨንቅ ሃሳብ ያላምጣል፣ ያመነዥካል። ያስጨንቀኛል፡፡ ሞቼ መገላገል እስክመርጥ፡፡

መጀመሪያ አካባቢ እነዚህን ስሜቶች ያዝ ለቀቅ ነበር ሚያደርጉኝ፡፡ ዛሬ ደስታ ነገ ድብርት፣ ዛሬ ብርሀን ነገ ጨለማ፣ እንደዛ
ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ከሁሉም ነገር ላይ መጥፎውን መመልከት ጀመርኩ፡፡
ቤተሰብና ጓደኝነት ከንቱ መስለው ይታዩኝ ጀመር፡፡ ሰዎችን ሸሸሁ። ስራዬ አስጠላኝ፡፡ ለቅቄ ብቸኝነቴን መረጥኩኝ፡፡ ሁሉም አርቴፊሻል የማስመሰል፣ የውሸት ኑሮ ሆነብኝ፡፡ ይህን መጥፎ ስሜት ለመሸሽ
ወደ ሱስ ገባሁኝ፡፡ ለግዜው ከጭንቀቴ፣ ከድብርቴ ቀለል እንዲለኝ አገዘኝ፡፡
በየእለቱ በሚባል ሁኔታ መቃም ጀመርኩኝ ሲመሽ መጠጣት፡፡ ጓደኞቼ
በሙሉ የሚቅሙና ሚጠጡ ሆኑ፡፡

አዎ ወራቶች አለፉ ዳግም ህይወቴ አሰልቺ ሆነችብኝ ደስታ ቢስ ሆንኩኝ፡፡ ለእዚህ አሰልቺ ህይወት ስትወጣ ስትወርድ መኖር የለብህም፣ የሚል ሀሳብ በጭንቅላቴ እንደ ሀምሌ ዝናብ ቀንና ለሊት ይዘንብብኝ ጀመር፡፡ ልቆጣጠረው አልቻልኩም፡፡ አመንኩኝ፡፡ በየቀኑ
እየቃምኩ፣ ከቤተሰቦቼ ደብዛዬን አጥፍቼ፣ እንዴት እራሴን ማጥፋት እንዳለብኝ አሰብኩ፤ እቅድ አወጣሁ፡፡ ስለዚህም፣ ከምኖርበት ራቅ ያለ ቦታ፣ የጠረፍ ከተማ፣ የተሻለ እንደሆነ አሰብኩኝ፡፡ መተማን መረጥኩ፡፡ወደ መተማ ስጓዝ አንድ ገዳም አየሁ፡፡ ጥቅጥቅ ጫካው ትክክለኛ ቦታው
እዚህ ነው ብዬ ወሰንኩ፡፡ ከዛም ያሰብኩትን ሞክርኩ፡፡” ሳበቃ ቀና ብዬ
ዶ/ርን አየሁት፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞልተዋል፡፡

“አይዞህ ያቤዝ! አይዞህ! አሁን ተርፈሃል፡፡ ህይወት ዳግመኛ የመኖር እድልን ሰጥታሀለች፡፡ ብዙዎች አንተ የሆንከውን የሆኑ ይህን እድል አያገኙም፡፡ እድለኛ ነህ፡፡ ጎበዝ ልጅም ነህ፡፡ ባይፖላር የተባለ
የአዕምሮ ህመም አለብህ፡፡ የነገርከኝ፣ በአንተ ላይ የሆነው አብዛኛው ነገር ሁሉ፣ ካለብህ የአዕምሮ በሽታ የተነሳ ነው።”

“በሽታ ነው ያልከኝ ዶ/ር? እኔኮ ምንም አይነት የህመም ስሜት ኖሮኝ አያውቅም፡፡”

“አይደለም ያቤዝ፡፡ ባይፖላር የተባለ የአዕምሮ በሽታ አለብህ፡፡የነዚህ በሽታዎች የህመም ምልክቶች እንደ ሌሎች በሽታዎች ትኩሳት፣እራስ ምታትና ቁረጠት የመሳሰሉት አይደሉም፡፡ ለዛም ነው የህመም ስሜት የለኝም ያልከኝ እንጂ፣ የህመም ምልክቶችማ በተደጋጋሚ ነበረህ፡፡ ከመጠን ያለፈ የባህሪ መለዋወጥ፣ ስለ አንድ ጉዳይ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ማሰብና መጨነቅ፣ አብዝቶ ብቸኝነትን መምረጥ፣ እራስን
የማጥፋት ሃሳቦች ሁሉ የህመም ምልክቶች ናቸው።” ዝም ብዬ ወደ
ራሴ ማሰብ ጀመርኩ፡፡

“ያቤዝ አውቃለሁ ስራህን አጥተሃል፣
ንብረቶችህን አጥፍተሀል፤ ከቤተሰቦችህንና ከጓደኜችህ እርቀህ ተሰውረሃል፡፡ ቢሆንም ግን፣ አንተ በጣም እድለኛ ነህ፡፡ በማህበረሰባችን ባለው የግንዛቤ እጥረት ምክንያት መፍትሄ ብለህ የመረጥካቸው ሁሉ፣ ለግዜው ቀለል ያደረጉልህ ቢመስልህም፣ በመሰረቱ ችግሩን የሚያባብሱ ነበሩ። ሰዎች ሲጨነቁ፣ ሲከፉቸውም ሆነ ሲደሰቱ የአልኮል መጠጦችን መጠቀም
መጥፎ ማህበራዊ ልማድ ነው፡፡ እነዚህ ሱሶች በተደጋጋሚ የሚከሰት የስሜት መረበሽ ሲኖር ግዜያዊ መፍትሄ ቢመስሉም፣ ሲቆዩ ወደ ተባባሰና ወደከፋ ስነ አዕምሯዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይዳርጋሉ፡፡

ስለዚህም ካሁን በኋላ የጀመርኩልህን መድሀኒቶችን መውሰድ፣ ክትትልም በደንብ ማድረግ አለብህ፡፡ አንተ ገና በጣም ወጣት ነህ፡፡ በዚህ እድሜ ገና ትምህርት ቤት ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ህይወትን እንደገና መጀመር ትችላለህ፡፡ ሁሉንም ነገር ያጠፋህ ቢመስልህም፣ በጣም ብዙ ያልጠፉ ነገሮችም አሉህ፡፡ ለምሳሌ፤ ትምህርትህ፣ ጥሩ የስራ ልምድህ አሁንም በጣም ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደገና መኖር አለብህ። አንተ ለቤተሰቦችህ፣ ለጓደኞችህ፣ ለማህበረሰብህና ለሀገርህ ታስፈልጋለህ፡፡ሰሞኑን ህክምናህን ጨርሰህ ትወጣለህ በርታ በርታ በል ፤ " ብሎኝ ወጣ፡፡

ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣና፣ ከዛሬ ጀመሮ አንደኛው መድሃኒት በሌላ
እንደተቀየረልኝ ነግሮኝ፣ አዲሱን መድሃኒት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮው ሄደ::

እኔ ስለነገረኝ በሽታ ሳብሰለስል ውዬ አደርኩ፡፡ መድሃኒት ከተቀየረልኝ በኋላ፣ የበለጠ የተረጋጋ ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡ ምሽት ምሽት ከዶክተር ጋር የሆስፒታል ግቢ ውስጥ እየተንቀሳቀስን ንፋስ
መውሰድን ልምድ አድርገነዋል፡፡ ስለ ባይፖላር በሽታ በደንብ የማወቅ
ፍላጎቴ ጨመረ፡፡ ነገር ግን፣ ስለበሽታው መረጃ ለማግኘት ስልክ ወይም መፅሃፍ በእጄ ላይ የለም፡፡ አንድ ጥዋት ዶክተር ወደ መኝታ ክፍል መጥቶ፣

“ታዲያስ ያቤዝ፣ እንዴት ነህ?”
“ደህና ነኝ ዶክ፣ እንዴት ነህ አንተስ?”
“ደህና ነኝ
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


......ከተደጋጋሚ ጥዝ የሚል አስፈሪ ድምፅና መንቀጥቀጥ በኋላ ጄሶው ተፈልቅቆ ወጣ፡፡ እጄን እንድዘረጋውና እንዳጥፈው አዘዘችኝ፡፡ የቀደመውን ያህል አይታጠፍም አይዘረጋም፡፡ ዶክተሯ እጄ
ላይ የቀረውን ጥጥና ቆሻሻ በአልኮል እያፀዳችልኝ፡፡

“ጥሩ ነው፡፡ በየቀኑ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንደዚህ እያደረክ ካለማመድከው፣ ወደ ቀድሞው ቦታ ይመለሳል፤” አለችኝ፣ በእጆቿ እጄን እጥፍ ዘርጋ እያደረገች እያሳየችኝ፡፡

“እሱን ሃላፊነት እኔ እወስዳለሁ፡፡ አመሰግናለሁ ዶክ፤” አላት ዶክተር ሄኖክ ፈገግ ብሎ፡፡ ወደኔ ዞር አለና፣
“እንኳን ደስ አለህ ያቤዝ! አሁን ህክምናህን ጨርሰሃል፡፡” አለኝ
እጄን ይዞ እየወጣ፡፡ ምንም
አልመለስኩም፡፡ አሁን ከሆስፒታል ውጣ
ከተባልኩ የት እንደምሄድ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሃሳብ በአንዴ በድን አደረገኝ፡፡ እጄን እንደያዘኝ የሆስፒታሉን ዋና በር አልፈን ወጣን፡፡ዝምታዬን ሊሰብር፣

“ሆስፒታላችንን እንዴት አየኸው?” አለኝ፡፡
“አሪፍ ነው፡፡” በአጭሩ መለስኩ፡፡ የት እንደምሄድ፣ በምን ገንዘብ እንደምሄድ ጨንቆኛል፡፡ ለዚህም ዶክተርን ማስቸገር እንደሌለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ የሆስፒታሉ በር አካባቢ ወደ ቆሙ ታክሲዎች ሄድን፡፡
ፒያሳ፣ አራዳ እያሉ ይጣራሉ፡፡ ሁሉም ሃገር ፒያሳ አለ ማለት ነው?
ከዚህ በፊት የት ነበር የሰማሁት? አዎ፣ ደሴ፡፡ ስለ ፒያሳ ማሰብ ጀመርኩ። ከሚያስጨንቀኝ ሃሳቤ ፒያሳ ነፃ አወጣችኝ፡፡ ዶክተር አንዱ ታክሲ ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ታክሲው የት እንደጠራ አልሰማሁም፡፡ ከቀልቤ አልነበርኩም፡፡ የጎንደርን ፒያሳ ምን እንደምትመስል ለማየት ጓጓው::የተወሰነ እንደሄድን፣ የታክሲው እረዳት፣

“አስራ ስምንት ወራጅ አለ?” ብሎ ጠየቀ፡፡

“አዎ፡፡ ና እዚህ ነን፤” ብሎኝ ዶክተር መውረድ ጀመረ።ተከተልኩት፡፡ ከታክሲው ወርደን ትንሽ እንደተጓዝን፣
“አሁን የምንሄደው ወደኔ ቤት ነው :: ወደ ቤተሰብም ለመሄድ ሆነ ስራ ለመጀመር ተረጋግተህ እስክትወስን እኔ ጋር ትሆናለህ፡፡ ካሁን በኋላ እንደ ሃኪምህ ሳይሆን፣ እንደ ወንድምህ፣ እንደ ጓደኛህ ልታስበኝ ትችላለህ፡፡ ምንም ነገር አታስብ፤ ምትፈልገው ነገር ካለ ምንም
ሳትጨነቅ ልትጠይቀኝ ትችላለህ፡፡”

“አመሰግናለሁ ዶክተር፡፡ መቼም የማልከፍለው ውለታህ አለብኝ፡፡ የት እንደምሄድ በጣም ጨንቆኝ ነበር፡፡”
ትልቅ የብረት በር ያለው ግቢ ጋር ስንደርስ፣ ዶክተር በሩን በቁልፍ ከፍቶ ገባን፡፡ ሰፊ ንፁህ ግቢ፣ መሃል ላይ የቆመ ትልቅ ቪላ፣ ዙሪያውን የተደረደሩ ስርቪስ ቤቶች፣ ዶክተር ቪላውን አልፎ ጥግ ላይ
ያለች ሰርቪስ ክፍል ከፍቶ ገባ፡፡

“ግባ፡፡ እንግዲህ የወንደ ላጤ ቤቴ ይቺ ናት፡፡ ብቻዬን ነው ምኖረው፡፡ ካሁን በኋላ እንጋራታለን፡፡ አንድ ቁልፍ እንካ፡፡”

“ደስ ትላለች፡፡” አልኩኝ ወደ ውስጥ ገብቼ ዙሪያውን እየቃኘሁ፡፡መለስተኛ አንድ ክፍል ቤት፣ መሃል ላይ በመጋረጃ ተከፍላለች።ከመጋረጃው ጀርባ አልጋ እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ቴሌቪዥን፣ በመፅሃፍት የተሞላ የመፅሃፍት መደርደሪያ፣ ዱካዎች፣ እቤት እንደሚያበስል የሚናገሩ እቃዎች፡፡ ዶክተር አንዲህ እንደሚኖር ገምቼም አላውቅም፡፡እኔ ከዚህ በጣም የተሻለ ንሮ ነበረኝ፡፡

“ቁጭ በል እንጂ፤ ቆመህ ቀረህ እኮ...” አለኝ ዶክተር ወደ ዱካዎች እያመለከተኝ፡፡ አንዱን ስቤ ተቀመጥኩ፡፡ወዲያው ዶክተር
ምግብ ማብሰል ጀመረ፡፡ አንዳንድ ነገር እያቀበልኩት ቆንጆ ሽሮ ወጥ ሰርቶ ምሳ በላን፡፡ በጣም ይጣፍጣል፡፡ የቤት ምግብ ናፍቆኝ ነበር፡፡ እቃ በማጠብ የቤተኝነት ስሜት እንደተሰማኝ ለማሳየት ሞከርኩ። ስንጨርስ ፒያሳ ወስዶ ከተማውን አሳየኝ፡፡ ፑል ተጫወትን፤ ሲመሻሽ ከፒያሳ
ወደቤት ወክ እያደረግን ተመለስን፡፡ ስንመለስ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ
ነው መሰለኝ፣ ቅርብ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

ህይወት እንዲህ ቀጠለች፡፡ የኪስ ገንዘብ ይሰጠኛል፡፡ እርሱ ወደ ስራ ሲሄድ ከተማ ወጣ ብዬ ሻይ ቡና እላለሁ፡፡ እረፍት ሲሆን ከተማ ወጥተን ሻይ ቡና ብለን ፑል ተጫውተን እንመለሳለን፡፡ ስራ ከዋለ፣
ከስራ ሲመጣ ወክ እያደረግን እንጨዋወታለን፡፡ ዶክተር የሰጠኝ ፍቅር
አሁንም የሚፈልጉኝ ሰዎች እንዳሉ ተሰማኝ፡፡ እንድነቃቃና መኖር እንዳለብኝ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ በጣም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው::ስራ መጀመር እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው፡፡ እርሱ ስራ ሲሄድ፣ በብዛት
ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እያነሳሁ፣ ስለ ባይፖላር ለመረዳት በብዛት በቤቱ ከደረደራቸው የስነ አዕምሮ መፅሃፍት እየመረጥኩ ሳነብብ እውላለሁ፡፡

#ህመም_አልባው_በሽታ

ዶክተር የባይ ፖላር በሽታ አለበህ ካለኝ ቀን ጀምሮ፣ ስለ ባይፖላር የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል፡፡ መድሃኒት ከጀመርኩኝ በኋላ እያየሁ ያለሁት ለውጥ ጥሩ ስሜት ፈጥሮልኛል፣ ከቀደመው ስሜቴ
ጋር ሳነፃፅረው፣ አሁን የተለየ የተረጋጋሁ ይመስለኛል። አለምን የማይበትን መነፅር የቀየርኩ ያህል ልዩነት ይሰማኛል፡፡ ባይ ፖላር ግን ምን ማለት ነው...? እብድ ማለት ነው...? ወፈፌ...? ቀውስ ማለት
ይሆን...? ሆ...ሆ... ኧረ በጭራሽ...! እኔማ ቀውስ አይደለሁም፡፡
እንትና ቀውሱ፣ እንትና እብዱ፣ ያ ሾጡ፣ ቅብርጥሱ፣ ምናምን ሲሉ እሰማለሁ፡፡ ህመሞች ይሁኑ ስድቦች አይገቡኝም፡፡ እኔን ማንም እንዲህ ሲለኝ አልሰማሁም፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ሆኖ ይሆን እንዴ?
ኖ.ኖ. እብድማ ብዙ ግዜ ተብዬ አውቃለሁ፡፡ እና ባይፖላር እብድ
ማለት ነው? ስለበሽታዬ ለማወቅ በየቀኑ አሰላስላለሁ። ዶክተር እንዳለው፣ ታምሜ ከነበር ይኼ በሽታ ህመም አልባ በሽታ ነው፡፡ ዶክተር ስራ ሲሄድ፣ እቤት ያለውን ስራ ጨርስና፣ ከተደረደሩት የስነ አዕምሮ
መፅሃፍት፣ እየቀያየርኩ አነበብኩኝ፡፡ አብዛኞቹ በሽታዎች ተመሳሳይ ሆኑብኝ፡፡ አንዱን ከአንዱ መለየት ቸገረኝ፡፡ ዶክተርን ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ሚመቸውን ቀን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡

አንድ ቀን ዶክተር አዳር ስርቶ ጥዋት መጣ፡፡ ከሰዐት ምሳ በልተን ፀሃዩ በረድ ሲል እንደተለመደው ወክ ልናደርግ ከቤት ወጣን፡፡በአባ ሳሙኤል አድርገን ቁልቁል ወደ እየሱስ መውረድ ጀመርን፡፡ ዛሬ
ለቀናት ያጠራቀምኳቸውን ጥያቄዎች ላዘንብበት ተዘጋጀሁ፡፡ ከግቢ
ወጥተን ትንሽ እንደተጓዝን፤

“ዶክ ጥያቄ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር”

“ጣድያ ምን ችግር አለው፣ ጠይቀኛ፡፡”

“ዶክ ባይፖላር አለብህ ካልከኝ ጀምሮ ስለበሽታው ለማወቅ ብዙ ሞክሬያለሁ፡፡ ብዙ አነበብኩ፤ ግን አልገባኝም፡፡ አስረዳኝ?”

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


...“በጣም ጎበዝ ያቤዝ፡፡ ስለ አለብህ የጤና ችግር ለማውቅ መፈለግ በጣም ጉብዝና ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጥቅም አለው፡፡ ባይፖላር ዲስኦርደር ማለት፣ ሰዎች ሁለት የስሜት ዋልታዎች መፈራረቅን ተከትሎ፣ተደጋጋሚ የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ሲያጋጥማቸው ነው።
መለዋወጦቹም፧ በስሜት ከፍታዎች እና በስሜት ዝቅታዎች መካከል የሚከሰት ነው:: በመሆኑም ይህ ችግር ያለበት ሰው፣ ባለበት የስሜት ከፍታ ወይም ዝቅታ መሰረት አሰተሳሰቡ፣ ውሳኔ አሰጣጡ፣ በነገሮች ላይ የሚኖረው ፍላጎት፣ ድርጊቶችን ለማድረግ የሚኖረው ሀይልና ጉልበት፣ በአጠቃላይ የህይወት አመለካከቱና አረዳዱ በሰዐቱ እንዳለው
የስሜት ሁኔታ የተለያየ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ
ሰዎች ውስጣዊ ለውጦች ሊኖራቸው፣ አካባቢያቸው የተለወጠ ስለሚመስላቸው የሚሰጡት ምላሽ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፡፡

የዚህ ችግር ተጠቂዎች የስሜት ከፍታ ሲኖራቸው ማኒያ ወይም ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡ ማኒያ ከሃይፖማኒያ ተመሳሳይ ምልክት ቢኖረውም፣ ማኒያ በህመም ደረጃው ከበድ ያለ በሽታ ነው፡፡ ይህ
የባህሪዎች መለዋወጥ፣ ችግሩ ያለባቸውን ሰዎች በስራ፣ በትምህርት፣
በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው እና ግንኙነቶቻቸው ላይ ችግሮች
ማወቅ እንዲከሰቱ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ የስሜት ከፍታ ላይ ሲሆኑ፤ በፊት
ብዙም ትኩረት ማይሰጡትን ጉዳይ የማየት፣ የመስማትና የማወቅ ፍላጎት መጨመርን ያሳያሉ፤ ከነበራቸው ማህበራዊ መግባባት የጨመረ
የመቀራረብና የመግባባት ባህሪ ያሳያሉ፣ የማይጨበጡ፣ ወይም

ቶሎቶሎ ሚቀያየሩ አዳዲስ ሀሳቦችንና ንድፎችን በማምጣት ያወራሉ፤አንድ ቦታና አንድ ሃሳብ ላይ በጥልቀት ማስብ ስለሚያስጨንቃቸው ቶሎ ከሃሳብ ወደ ሃሳብ ይቀያይራሉ፣ በጥቃቅን ነገሮች አክርረው ይጨቃጨቃሉ፣ ነገሮቹ ከነርሱ ህይወት ጋር ጠቃሚ ግንኙነት ባይኖራቸውም፣ ስለሚሰሟቸው ነገር ከፍተኛ የማወቅ ፍፈላጎት ያሳያሉ፤ ለነገሮች ከተገቢው በላይ ይናደዳሉ፣ ይበሳጨሉ፣ ከብሰጭት ስሜት መውጣት ይቸገራሉ፣ የተጋነነ በራስ የመተማመን ስሜት ይኖራቸዋል፤ የሚያመጧቸውን ሀሳቦች ፍፁም አድርገው ያስባሉ፡፡
ትችትና አስተያየት መቀበል ይከብዳቸዋል እንደሚተገብሯቸው እርግጠኛ መሆን፡፡ የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ፤ በፊት ከሚተኙበት ሰዓት ዘግይቶ መተኛትና ባልተለመደ ንቁ መሆን፤ ያልተለመደ
ወሬኛነት፤ ከማይግባቧቸውና ከማያቋቸው ሰዎች ጋር ጭምር
ያልተለመደ የማውራት ፍላጎት፤ ነገሮችን አብዝቶ ማቅለል፤ ደካማ ውሳኔ መስጠት ያስከትላል፡፡ የመሳስሉትን ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች ሃይፖማኒያ ይባላል፡፡”

“ስለዚህ ዶክ፣ አንድ ሰው የተዘረዘሩት ምልክቶች በሙሉ ሊኖርበት ነው ይሄ ችግሩ አለበት ሚባለው?”

“ኖኖ! እንደዛ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ከላይ ከዘረዘርኳቸው ውስጥ፣ ሶስቱን ወይም ከዚያ በላይ ምልክቶች ካሳየና በሃኪም
ከተረጋገጠ ሃይፖማኒያ አለበት ልንል እንችላለን፡፡” በውስጤ አሰላሰልኩ፡፡ እነዚህ ስሜቶች ሶስቱ ሳይሆን ሁሉም ግዜ ጠብቀው፣እብደቴ ሲነሳ በደስታ ማስተናግዳቸው ሲሜቶች ናቸው፡፡

“ዶክ ከእነዚህ ስሜቶች አብዛኞቹ በተደጋጋ እኔን ሲስሙኝ ኖረዋል። ታዲያ ሃይፖማንያ ሳይሆን ለምን ባይፖላር አለብህ አልከኝ?”

ትክክል ነህ ያቤዝ፡፡ አንተ እነዚህ ስሜቶች ሲሰሙህ እንደከረሙ ነግረኸኛል፡፡ ነገር ግን፣ ሃይፖማንያ ሚባሉት እነዚህን
ስሜቶች ብቻ ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንተ ግን፣ እነዚህ ስሜቶች ብቻ አይደሉም ሲሰሙህ የነበረው፡፡ ሌላም ስሜቶች ነበሩህ፡፡”

“ሌላ ስሜትም ስትለኝ፣ ሌላ ምን አይነት ስሜት?"

“አንተ የሃይፖኒያ ስሜቶች ብቻ ሳይሆን የነበረህ፣ ግዜን ጠብቆ ሚፈራረቅ የስሜት ዝቅታ ወይም የዲፕረሽን ምልክቶችም ነበሩህ፡፡”

“የስሜት ዝቅታ /የዲፕረሽን/ ምልክቶችስ ምን ምን ናቸው?"

“የዲፕረሽን ምልክቶች የምንላቸው፤ ከፍተኛ ብስጭት፣ማህበራዊ መነጠል፣ ብቸኝነት ማብዛት፤ ከፍተኛ ምክንያት የለሽ የድካም ስሜት፧ የጡንቻ መዛል፤ ቁርጥማት፣ የጀርባ ህመም፤ የመረበሽ
ስሜት ፣ በስራ፣ በትምህርትና ቤተሰባዊ ሃላፊነቶች ከተገቢው በላይ መጨነቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የመዝናናት የፍላጎት ማጣት፣ እንዲሁም፣ የጥፋተኝነት ስሜቶች፣ ዋጋቢስ እና ተገቢ ያልሆነ ራስን መቅጣት፣ በራስ የመተማመን ስሜት መቀነስ፣ ደካማ እና የቀነሰ ትኩረት፣ አፍራሽ እና መጥፎ ሃሳቦችን በተደጋጋሚ ማሰብ፣ ራስን የማጥፋት አስተሳሰብ እና ራስን የመጉዳት ወይም ራስን የመግደል ሙከራዎች እና የመሳሰሉት ምልክቶች ካሉበት፤ የዲፕረሽን ችግር አለበት ይባላል”

እነዚህ የበሽታ ምልክቶች ከሆኑማ
ታምሜያለሁ፣ሲፈራረቁብኝ ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ብዙ ሰው እንደዛ ሚሰማው
ይመስለኛል፡፡ ሃኒ በአምሮዬ ውልብ አለች፡፡ ትበሳጭ ነበር፤ ትናደድ ነበር፤ ብቻዋን መደበቅ ፈልጋ ስትመጣ ነው የተገናኘነው፣ እራሷን አጥፍታለች። እና ሃኒም እንደኔ የዲፕረሽን ታማሚ ነበረች ማለት ነው?፣ እራሷን ለማጥፋት ያደረሳት ይህ ህመም አልባ በሽታ ነበር ማለት ነው?

“እና ዲፕረሽን አሁን ከጠቀስካቸው ምልክት ሶስቱን ማሳየት ማለት ነው?”

“አይደለም፡፡ ዲፕረሽን እንደ ሃይፖ ማንያ በሶስት ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች መካከል አምስቱን ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት አንድ ስው ደጋግሞ ሲኖረውና የእለት ተለት ህይወቱን እንዳይመራ ተፅእኖ ሊኖራቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች
ሃኪም ሳያማክሩ ምልክት በመቁጠር ብቻ እንዲህ ነኝ እንዲያ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ግን ምልክቶቹ ከተደጋገሙና ከቆዩ ሃኪም ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡”

“እነዚህም ምልክቶች እኮ በደንብ እንደነበሩኝ ነግሬሃለው ዶክተር፡፡ ታድያ ለምን ዲፕረሽንም አለብህ አላልከኝም? ህይወቴን እዚህ ያደረሱት እኮ አሁን የጠቀስካቸው ምልክቶች ሲስሙኝ ነው። ያማል፣ያላምጣል፣ ያመነዥካል፣ ሞት እንደ ጣፋጭ መድሃኒት ይናፍቃ፡ ዶክ፣
ስለዚህ እኔ ያለብኝ ችግር እንደውም ዲፕረሽን ነው፡፡”

“አየህ ያቤዝ፣ ቅድም ለዛ ነበር ሃኪም ሳያማክሩ ምልክቶችን ቆጥሮ ይሄ ነው፣ ያ ነው ያለብኝ፣ ማለት አይቻልም ያልኩህ፡፡ አንተ የሃይፖማንያም የዲፕረሽንም ምልክቶች እየተቀያየሩብህ አሳይተሃል፡፡
አንድ ስው የሃይፖማንያ ምልክት ብቻ ካለው፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ ሃይፖማንያ አለበት ይባላል፤ የድባቴ ምልክቶች ብቻ ካሉበት፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የድባቴ ችግር አለበት ይባላል፤ የሁለቱ በሽታዎች ምልክት እየተፈራረቁ ከተሰሙት ደግሞ፣ በሃኪም ከተረጋገጠ በኋላ የባይፖላር ችግር አለበት ይባላል፡፡”

አሁን ለቀናት ሳነብ አልገለጥልህ ያለኝ ተገለጠልኝ፡፡ አይኔ በራ፡፡ዶክተር እያወራ ነው፡፡ “ባይፖላር ዲስኦርደር የዕድሜ ልክ ሁኔታ ቢሆንም፣ሕክምና በመከታተል የስሜት መለዋወጥን እና ሌሎች
ምልክቶችን በመቆጣጠርና መሰናክሎችን በማስቀረት በህይወት ስኬታማ መሆን ይቻላል፡፡ ባይፖላር
ዲስኦርደር በስነ ልቦና ምክር (ሳይኮቴራፒ)እና በመድኃኒቶች ይታከማል፡፡

በግማሽ ልቤ ነው ማዳምጠው፡፡ እኔ ወደ ውስጤ ተወሽቄያለሁ።ወደኋላ ተመልሼ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ ነው፡፡ ዶክተር እውነቱን ነው::ቅድም የጠቀሳቸው ስሜቶች ብዙ ግዜ ተፈራርቀውብኛል። ባይፖላር ዲስኦርደር፣ በጋና ክረምት የሚመሰሉ ስሜቶች መፈራረቅን ተከትሎ
የሚመጣ የባህሪ መለዋወጥ ነው፡፡ በጋ፣ ብርሀን ነው ፧ ተስፋ ነው ፤ በጋ ሙቀት ነው ፤ ሀይል ነው፤ መቦረቅ ነው፡፡ ክረምት ግን፣ ብርድ ነው ፤መሸሸግ፣ መኮራመት ነው፡፡ አዎ! የኔ
👍3😁1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳናውቀው እርቀን ሄደናል፡፡ ዞብልን አልፈን ቸቸላ ሆስፒታል ልንደርስ ምንም አልቀረን፡፡

“እርቀን መጣን፡፡ እንመለስ?”

“ደከመህ? እሺ” ብሎ ዞረ፡፡ ዶክተር እረጅም ወክ ይወዳል።

“ዶክ አሁን እንደገባኝ፣ የአዕምሮ በሽታ ከምጠብቀው በላይ በብዛት፣ በዙሪያችን ያለና ብዙ ምስቅልቅሎችን እያስከተለ ያለ፣ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ግንዛቤ የሌለው በሽታ ይመስለኛል፡፡”

“እውነት ብለሃል ያቤዝ፡፡ አሁን ስለ በሽታው በደንብ እየተረዳህ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ብዙ በሽታዎች እንዳሉ ብታውቅ ደግሞ የችግሩ ግዝፈት በደንብ ይታይሃል፡፡”

“ቅድም እንዳልኩህ አልገባኝም እንጂ፣ እቤትህ ያሉትን መፅሃፍት ለማንበብ ሞክሪያለሁ፡፡ ለምሳሌ፤ ስለ ፓራኖይድ፣ ኦብሴሽን፣ዚኮኒያ ምናምን ለማንበብ ሞክሬ ነበር” አልኩኝ በዛው ስለነሱ
እንዲነግረኝ፡፡

“ምነድን ዚኮኒያ ካካካካ...” ዶክተር ለመጀመሪያ ግዜ ከልቡ ሲስቅ
አየሁት፡፡ የበሽታውን ስም ስጠራ እንደተሳሳትኩ ገባኝ፡፡ ዶክተር ሲስቅ
ስላየሁት ግን፣ በመሳሳቴ ደስ አለኝ፡፡

“ዚኮኒያ ... እንደዛ ነገር ያነበብኩ መሰለኝ፡፡” አውቄ ደገምኩለት፡፡
እየተንከተከተ ሳቀ፡፡ ዶክተርን እወደዋለሁ እሱ ለኔ ህይወቴን ያዳነልኝ ጠባቂ መላዕኬ ነው፡፡ ህይወቱን ሙሉ ደስተኛ ቢሆንልኝ ምኞቴ ነው። እሱ ግን ስሜቱ በብዛት የረጋ ነው፡፡ ቶሎ አይደሰትም፣ አይናደድም፡፡ዛሬ በኔ ምክንያት ደስ ስላለው ከልቤ ደስ አለኝ፡፡ ስጦታ የሰጠሁት ያህል ተሰማኝ፡፡ ስቆ ሲጨርስ፤

“ገባኝ፣ ስኪዞፍሬኒያ ለማለት ነው፡፡ የህክምና ቃላቶች ትንሽ ይከብዳሉ፡፡ እንደውም አንተ ጎበዝ ነህ፡፡ ሌሎቹን በትክክል ጠርተሃቸዋል፡፡ እሺ ለማንኛውም እነግርሃለው፡፡ ፓራኖይድ የባህርይ መዛባት ችግር ተብለው ከሚጠሩ ሁኔታዎች አንዱ ነው። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪ ናቸው፡፡ ሰው በተፈጥሮው
ይጠራጠራል፡፡ እንደ ችግር ምንቆጥረው ግን፣ ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ሲጠራጠርና፣ እያንዳንዱ ድርጊታቸው በሌሎች እንጠቃለን ከሚል ከፍተኛና የማያቋርጥ ስጋት፣ አለማመንና ጥርጣሬ የመነጨ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከማንኛውም ሰው ጋር የሚያደርጉት
ግንኙነትና ድርጊታቸው፣ በጥርጣሬ አስተሳሰቦች የተቃኙ ስለሆነ፣
በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በስራቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጠርባቸዋል፡፡

ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በልጅነት ወይም በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ የተለመደ ነው::ፓራኖይድ ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎች እነርሱን ዝቅ ሊያደርጓቸው፣ ሊጎዷቸው ወይም ሊያስፈራሯቸው እንደሚሞክሩ
ስለሚያስቡ ድርጊታቸው ሁሉ እራሳቸውን በመከላከል የተቃኘ ነው::እነዚህ መሠረተ ቢስ እምነቶች፣ እንዲሁም የማመካኘትና ሌሎችን ያለማመን ባህሪ፣ የቤተሰባዊም ሆነ የስራ ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ
ይስተጓጉላል፡፡ በመሆኑም የፍቅር ህይወታቸው፣ የትዳርና የቤተሰብ
ህይወታቸውን ጨምሮ ማንኛውም ከሰዎች ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት
ከፍተኛ መሰናክል ይሆንባቸዋል፡፡

አነዚህ ግለሰቦች ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶቹም መሃከል፤ሌሎችን ሁል ግዜ መጠራጠር በጣም የሚቀርቧቸውንና ሃኪማቸውን ጨምሮ፣ ሌሎች እነሱን በማታለል ወይም በመበዝበዝ እንደሚጠቀሙ ማሰብና ማመን፤ የግል መረጃዎቻቸው እኔን ለመጉዳት ይውላል በሚል ፍራቻ ለሌሎች መደበቅ፣ ለሰዎች ይቅርታ ማድረግ መቸገር፤ ቂም መያዝ፣ ቁጡና ትችትን በአግባቡ መቀበል መቸገር፤ የሚሰጧቸው አስተያየቶችና የማሻሻያ ሃሳቦች ውስጥ የተደበቁ ትርጉሞችን መፈለግ፣

የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እንደማይታዩ የጥቃት፣ የንቀት ወይም የማስፈራራት ምልክት አድርጎ መረዳት፣ በአፀፋው ለመመለስ መፍጠን፤ እንዲሁም በቁጣ ምላሽ መስጠት፤ የማያቋረጥ ምክንያት
አልባ ጥርጣሬዎችን ማብዛት፣ ይህም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር ጓደኛቸውን በጥርጣሬ ማሰብ፤ ክህደትን ለምከላከል ነገሮችን ሁሉ በጥርጣሬ መመልከት፤ ሁልጊዜ እራሳቸውን ትክክል እንደሆኑ ማመንና በግጭቶች ውስጥ የራሳቸውን ድክመት ወይም አስተዋፅኦ ማየት
አለመቻል፤ አብዛኛውን ግዜ ተቃዋሚዎች ዘና ማለት የሚቸገሩ፣ግትር እና ተከራካሪ ናቸው፡፡ የፓራኖይድ /የምናባዊ/ ጥርጣሬዎችን መለያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤

አጠራጣሪውን አስተሳሰብ የሚጋራ ሌላ ሰው ከሌለ፤
ለጥርጣሬ መነሻ ትክክለኛ ማስረጃ ሳይኖር ሲቀር፤
ማስረጃ ባለው ጉዳይ ላይ አልፎ የሚነሳ የጥርጣሬ ሃሳብ፤
ስለጉዳዩ ማሰብ ማቆም የሚከብድ ከሆነ፤
ከሌሎች ማረጋገጫ ተሰጥቶም በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ ከቀጠለ፤

ጥርጣሬው ከማስረጃ ይልቅ፣ በስሜቶች እና አሻሚ ክስተቶች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ ይህ ጥርጣሬ ጤነኛ ያልሆነ የፓራኖይድ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪምን ማማከር ከከፋ ችግር ይከላከላል፡፡

ይህ ችግር ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው በመለስተኛ ደረጃ ሊያጋጥማቸው የሚችል ሲሆን የከፋ ጉዳት አያስከትልም ነገር ግን፣በሌላው ጫፍ ሲከሰት በጣም ከባድ ችግርን ሰለሚያመጣ፣ ህክምና
መፈለግ የግድ ነው፡፡” ዶክተር እያወራልኝ ግርማ ትዝ አለኝ፣ በፍቅረኞቻቸው ላይ በአልተጨበጠ ቅናት አሲድ መድፋትና ሌሎች የጭካኔ ወንጀሎችን ሚፈፅሙ ሰዎች በአዕምሮዬ ተመላለሱ፡፡

“ሌላው ደግሞ ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር /ኢኮዲ/የምንለው ነው፡፡ ኦ.ኮ.ዲ. ከመጠን ያለፈ አስጨናቂ የጥርጣሬ ሃሳቦች መከሰትና ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ወይም ለማስተካከል ተመሳሳይ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ለመፈፀም የሚስገድድ ባህሪ ነው፡፡ ግለሰቡ ድርጊቶቹን የሚፈፅመው ወደ አእምሮው ሊቆጣጠረው ከሚችለው በላይ
በተደጋጋሚ እየመጡ በሚያስጨንቁት ሃሳቦች፣ ምስሎች ወይም ፍላጎቶች ምክንያት ነው:: ሃሳቦቹ አስጨናቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን፣በሰውየው አዕምሮ የሚመነጩ እንጂ፣ በነባራዊው አለም የማይከናወኑ
ወይም የሌሉ ናችዉ:: በተጨማሪም፣ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን እንደታዋቂ ወይም ከፍተኛ ደረጃ እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

ኦ.ኮ.ዲ. ምልክቶች በአብዛኛውን ጊዜ በትንሹና ቀስ በቀስ ስለሚጀምሩ፣ ችግሩ ላለበት ሰው፣ የተለመዱ ባህሪዎች ሊመስሉ ይችላሉ:: ድርጊቶቹን ሲፈፅሙ የተወሰነ እፎይታ ይሰማቸዋል፡፡ ነገር
ግን፣ እፎይታው ለትንሽ ጊዜያት ብቻ የሚቆይ ስለሆነ የድርጊቶች
ድግግሞሽ ይቀጥላል። ተደጋጋሚና አስገዳጅ ድርጊቶች በሌሎች ሰዎች
በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፤ በማህበረሰቡ እንደጥዩፍ ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ለግለሰቡ የግዴታ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም፣ ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ እየደጋገሙ ማይታወቃቸው ስለሆነ ነው:: ለምሳሌ፣ ሰው ከጨበጡ ወይም እቃ ከነኩ በኋላ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ሰውን ለመጨበጥ በመፍራት
ሰላምታን በሌላ መልኩ መስጠት፣ የበር መቆለፍን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፣ ልዩ ቃላትን ወይም ጸሎቶችን መደጋገም፣ ደጋግሞ መቁጠር በጣም በተደጋጋሚ የዝግጅት አቀራረቦችን መፈተሽ ናቸው፡፡
እነዚህን ድርጊቶች እንዲፈፅሙ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ፣በጀርሞችን ወይም በቆሻሻ መበከልን በከፍተኛ ደረጃ መፍራት፣ ከመጠን ያለፈ ጥርጣሬ ወይም ስህተት የመስራት ፍርሃት እያደረጉት ላለው ነገር ትክክለኛነት ከሌሎች የማያቋርጥ ማበረታቻና ማረጋገጫ መፈለግና ለስርዐት የበዛና የተጋነነ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡

አንዳንዶቹ ድርጊቶች ሰዎቹ ላይ በቀጥታ ጉዳት ባይኖራቸውም፣አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበትን በመውሰድ፣ በሌሉ ጉዳዮች ላይ በመጨነቅ ውጤታማነትን በእጅጉ ይጎዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ችግር አላስፈላጊ ግዜንና ጉልበት
👍3
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


በመጨረሻም ስኪዞፍሬኒያ ፤” ብሎ ቀጠለ፡፡ እኔ እሱን በግማሽ ልቤ እያዳመጥኩት ይህን ቃል የት እንደስማሁት ለማስታወስ፣የአዕምሮዬን ጓዳ እበረብራለሁ፡፡ “ይህ በሽታ ከቀደሙት ሁሉ ከባዱ ሲሆን፣ ሰዎች የእውነታውን አለም በቋሚነት በተሳሳተ መንገድ የሚረዱበትና የሚተረጉሙበት የአዕምሮ ችግር ነው። ስኪዞፍሬንያ
ያለባቸው ሰዎች በጣም ያልተለመደ አስተሳሰብ እና ባህሪ ያሳያሉ፡፡
የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን መተግበር አይችሉም፡፡ በመሆኑምከሌሎች የአእምሮ ችግሮች በላይ ማህበረሰቡ ይሄ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በቀላሉ ይለያል፡፡ ችግሩ ግን በማህበረሰባችን ያለው በጣም አናሳና የተሳሳተ የአዕምሮ ችግሮች ግንዛቤ እነዚህ ሰዎችን ወደ ህክምና ከማምጣት ይልቅ ወደ ሌሎች ቦታዎች መውሰድና ማግለል ሚያበረታታ
ነው፡፡ ነገር ግን፣ ይህም ችግር ህክምና ያለው ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ከባድ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ህክምና መጀመር ምልክቶችን ለመቆጣጠር እና ከባድ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

ምልክቶቹም፤ የግል ንፅህናንዉን ችላ ማልት፤ ስሜት የጎደለው የሚመስል ምላሽ መስጠት፤ የዓይን ለዓይን ግንኙነት አለማድረግ፣በንግግር ወቅት ስሜት አልባ የፊት ገፅታዎች ማሳየት፣ በማኅበራዊ
ኑሮ ደስታን ማጣት፤ ማኅበራዊ ግንኙነት መሻከር፤ በነባራዊው ቦታ የሌሉ ነገሮችን ማየት ወይም መስማትና ለነሱ ምላሽ መስጠት፤ ከፍተኛ ብስጭት፣ ያልተለመደ ሃይለኝነትና ለፀብ መጋበዝ፤ ያልተደራጀ
አስተሳሰብና ንግግር፣ የሚሰጡት መልስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የማይገናኝ መሆን፤ በንግግር የማይታወቁ፣ ትርጉም የለሽ ቃላትን አሰባስቦ መናገር፣ ያልተለመደ የልጆች ከሚመስል ሞኝነት እስከ ለመረዳት የሚከብድ ብስጭት፤ ምክንያት የለሽ ፈጣን እንቅስቃሴዎችን
ማሳየት፣ በስራም ሆነ በተለያየ ቦታዎች መመሪያዎችን መቃወም፣ያልተለመደ ወይም ተገቢ ያልሆነ አቀማመጥ ወይም አቋቋም ማሳየት፣የእብሪት ስሜቶችና ለመታዘዝ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ባህሪያትን ማሳየት የመሳሰሉት ናቸው፡፡” ብሎኝ ጨረሰ፡፡

“አስታወስኩት!” ሳይታወቀኝ ጮኸኩኝ፡፡
“ምኑን ያቤዝ?” አለኝ ዶክተር ደንገጥ ብሎ፡፡ “ሴሮቶኒን ያለኝን ሰው፡፡ የሆነ ፈረንጅ ነበር፡፡ ጫት ያነቃቃል ስለው፣ ውስጡ ሴሮቶኒን አለው ወይ ያለኝ፡፡ አላውቅም ምናልባት ፈረንጁ ዶክተር ይሆናል።”

“አይ ያቤዝ ላይሆንም ይችላል፡፡ ጤና ከመሰረታዊ እውቀቶች አንዱ ነው። ሁሉም ሰው ስለ ጤና እውቀት ሊኖረው ይገባል። ስለ መኪናችን ስለ ኮምፑተር ለማወቅ የምንጥረውን ያክል፣ ዶክተሩን
ለመተካት ሳይሆን እራሳችንን ከከፋ ጉዳት ለመከላከል፣ ሃኪማችን
የሚለንን በአግባቡ ለመረዳት ሁሉም ሰው ስለ ህክምና መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ ያደጉት ሃገራት ማህበረሰቡ እንደዛ ነው ለዛ ሊሆን ያልከው ሰው ያወቀው፡፡ እንዳልኩህ እኛ ሃገር ብዙ ሰው

ከሙያው በተጨማሪ፣ ስላለው መኪና፣ ስለ ቤቱ፣ ስለ ኮምፑተር ከባለሙያው ጎን ለጎን የተወሰነ እውቀት አለው፡፡ ነገር ግን፣ መሰረታዊ ስለሆነው ጤናው ግን ለጤና ባለሙያዎች ብቻ ተቶ ተቀምጧል።
እንደዚህ ስል ግን፣ አንተንና እንዳንተ ያሉትን ስለ በሽታቸው ለማወቅ ብዙ ጥረት ሚያደርጉም እንዳሉ አልዘነጋም፡፡ ግን ጥቂት ናቸው።መስተካከል ያለበት ይመስለኛል፡፡”

“ትክክል ብለሃል ዶክ፡፡ መኪናም ቤትም ጤና ሲኖር ነው፡፡ ግን እኔ ምልህ ዶክተር ”

“ወዬ ያቤዝ”

“እነዚህ ያስረዳኸኝን በሽታዎች ማህበረሰባችን ያውቃቸዋል? መጥቶስ ይታከማል?”

“በቂ መረጃ አለ ብዬ ለማለት ይከብደኛል፡፡ በሃገራችን እነዚህ
ችግሮች ያለባቸው ሰዎች በሚሊዬን የሚቆጠሩ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ነገር ግን ህክምና ፈልገው ሚመጡት በጣም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኞች፣ ሲያፍሱ ሲበትኑ፣ ወደፊት እንዳይጓዙ መሰናክል ሆኗቸው፣ እታገሉ በየመስሪያ ቤቱ አሉ። ገሚሶቹ ደግሞ፣ ከእምነት ጋር አያይዘውት በህይወት ያጋጠማቸው መሰናክል፤ በሽታ ሳይሆን መንፈስ አድርገው ሌላ አማራጮችን ፍለጋ እተንከራተቱ ናቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነኝ ግን፣ ስለ በሽታውና በሽታው ባለባቸው
ሰዎች ላይ ያለው አሉታዊ አመለካከት ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች አክመን ደግፈን ውጤታማ ማድረግ ሲገባን፣ እያንጓጠጥናቸው ምናባብስባቸውን
ሳይ፣ እስከመቼ እያልኩ ልቤ ይደማል፡፡” አለኝ በትካዜ መሬት መሬቱን እያየ፣ በእግሮቹ ጠጠሮችን እንደ ኳስ እየመታና እያንከባለለ፡፡

ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደቤት ደረስን፡፡ የዶክተር ቁጭት፣ እንደ ኤሌክትሪክ ነዝሮኝ ወደኔም ሲተላለፍ ተሰማኝ፡፡ እቤት ገብተንም ሁለታችንም በሃሳብ ሄድን፡፡ አዎ ይሄን በሽታ እኔም ሁሉ ነገሬን ወስዶብኛል፡፡ ስራዬን፣ ያፈራሁትን ሃብት ንብረቴን እንደ ሰላቢና እንደ ድግምት ለፍቼ ያመጣሁትን አመድ አድርጎብኛል፡፡ እድሜዬን ነጥቆኛል፣ ነብሴን ሊቀማኝ ሲል በተአምር ነው የተረፍኩት፡፡ ከሁሉም
በላይ ግን፣ ግማሽ ህይወቴን፣ የምወዳትን ሃኒን ቀምቶኛል። አሁን እኔ
ታምሜ እንደነበር ማን ይጠረጥራል?፣ በቅርበት የሚያቀኝ ሳሚ እንደታመምኩ መች አወቀ?፣ እናቴስ መች አወቀች? እንደኔ፣ እንደ ሃኒ፣ እንደ ኤፍሬምና ሌሎች ዶክተር በነገረኝና ባልነገረኝ በሽታዎች
ሚስቃዩ ሚሊዮኖችን አሰብኩ፡፡ ካሁን ቦሃላ፣ እኔም ይህን በሽታ በምችለው ሁሉ ልታገለው ይገባኛልና ልዋጋው ይገባል፡፡ በዝምታ ሆነን እንደተለመደው እየተጋገዝን እራት ሰርተን በላን፡፡ የተጓዝነው ረጅም የእግር ጉዞ አድክሞናል ስለነበር፣ እራት እንደበላን ቶሎ ተኛን፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ቶሎ ወደ ሃገሬ ለመመለስና ህይወቴን እንደገና እንዴት መጀመር እንደምችል ማሰብ ጀመርኩ፡፡
በየመሃሉ የአእምሮ ጤና ጉዳይ በከፍተኛ እልህ አስባለሁ።አነባለሁ። ኤፍሬም ይህ ችግር ገጥሞት ሊሆን ይችላል ለማለት
የሚያበቃኝ እውቀት ማግኘት አልቻልኩም ነገር ግን፣ ባነበብኳቸው
በሽታዎች ሁሉ ትንሽ ቁጥር የማይባሉ ሰዎችን ከጓደኞቼም ከቤተሰቤም ጭምር፣ እከሌ የዚህ ችግር ይኖርበት/ባት ይሆን እንዴ ብዬ አስቤያለሁ።
እከሌ እንዲህ የሚቸገረው በዚህ ጉዳይ ቢሆንስ፣ እያልኩ አሰላስያለሁ፡፡እንደኔ ብዙ ሰዎች ሳያውቁት በነዚህ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሆነ ዶከተር የነገረኝ እውነቱን ነው፡፡ እንደ ሃገር የሚያጋጥሙን
ምክንያቶች አንዱ ቢሆንስ ብዬም አሰብኩ፤

አለመግባባትና የፀብ በየመስሪያ ቤትና በየቤተሰቡ(እንደ ሃኒ) የፀብ መክረር ምክንያትስ ቢሆን..፡፡

እንዴት ግን መንግስትን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላት በዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ሰፊ ስራ መስራት አልቻሉም?፣ ስንቶች የመስራት አቅም እያላቸው፣ ትንሽ ታክመው ውጤታማ መሆን ሚችሉ፣ እንደኤፍሬም ወደ ረመጡ ተገፍተዋል?፣ ስንቶች በዚህ ምክንያት እየተሰናከሉ ሲወድቁ፣ ሌላ ምክንያት ላይ ጣታቸውን
እየቀሰሩ፣ ምርታማ እድሜያቸውን እያባከኑ አሉ?፣ ማን ያውቃል፤ ብዙዎች ይህ ችግር እስከነመኖሩም መረጃው የላቸው ይሆናል፣ ስንቶች ይሆኑ የአዕምሮ ችግር ሲባል ጨርቅ መጣል ብቻ ሚመስላቸው?፣ስንቶች ይሆኑ ይህ በሽታ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ
እንደሚያስከትል ሚረዱ?፣ ስንቶች ይሆኑ ችግሩ እንዳለባቸው ሚገነዘቡ፣ የህልማቸው መሰናክል እንደሆነ ያወቁ፤ ታክመው ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ የተረዱ፣ ስንቶች ናቸው? ማሰላሰል ጀመርኩኝ፡፡

ሰው አዕምሮው ጤነኛ ካልሆነ፣ ሌላው አካሉ ምን ያህል ጤነኛ ቢሆን፣ ምን ሊሆነው፣ ምን ሊበጀው?

“ጭንቅላት አይክዳህ ...” ነበር ያለኝ ያ ጓደኛዬ?...

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
😁1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ድህረ_ታሪክ

አራት አመት አለፈኝ፡፡ የህክምና ክትትል አደርጋለሁ፡፡ እድሜ ለነ ሃብትሽ፣ አደራ የሰጠኋቸውን የዶሮ እርባታ በቅንነትና በታማኝነት ሰርተው ከነ ፍሬው ጠበቁኝ፡፡ መልሼ ለመቋቋም በቃሁኝ፡፡ ለዶክተር
ለህክምናዬ ያወጣውን ግማሹን ቢሸፍን እንኳ ብዬ የተወሰነ ገንዘብ ላኩለት፡፡ አሁን ውስጤ በጣም የተረጋጋ ስሜት ይሰማኛል። የግል ስራዬን አስፋፍቼ ንሮዬን አዲስ አበባ አድርጌያለሁ፡፡ ነገሮች እንደበፊቱ ቶሎ አይረብሹኝም እንደውም፣ አሁን የሰዎችን ህመም አዳማጭና
መካሪ ሆኛለሁ፡፡ አንዳንዴማ፣ እንደ ዶክተርም ሊቃጣኝ ይሞክራል፡፡ሰዎች
በማይረባው ነገር ተረብሸው፣
ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸው፣ የማትረባዋን ነገር አግዝፈው ሲያኝኩ፣ ሲያብሰለስሉ ሳይ፣ ሰዎች ሁሉ ተደራጅተው ሊያጠቁኝ ነው ብለው እያሰቡ ሲጨነቁ ሳይ፣ ወደራሳቸው ማየት ሲያቅታቸው፣ ወላፈኑ እየለበለባቸዉ
ሲመስለኝ፣ ከነበልባሉ፣ ከእረመጡ ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ፣ መፍትሄ
እንዲያገኙ ሃኪም እንዲያማክሩ እመክራለሁ፡፡

አሁን ዐይኔ በርቶልኛል፡፡ በአጠገቤና በአካባቢዬ በጣም ብዙ ሰዎች ላይ ምልክቱን አያለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ልረዳቸው አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አሁን ግን፣ ይሄ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እየተሰማኝ ነው።
ቁጭ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላስልኩ ነው፡፡ ከጎረቤት የተከፈተው የዳንኤል አምደሚካኤል መዝሙር ይሰማኛል፡፡ አብሬ ማንጎራጎር ጀመርኩ፡፡

“ዐይኔ በርቶልኛል፣ ሁሉን አይቻለሁ፡፡

ከዚህ የበለጠ ምን እፈልጋለሁ..::

እናገራለሁኝ...፣ አልታክትም ሁሌ..
.
ስለዚህ ሳወራ..አ..ሃ..ሃ፣ ከቶ አልደክምም እኔ።”

ከዶ/ር ሄኖክ ጋር እየተደዋወልን እንጠያየቃለን፡፡ በእድሜም ስለምንቀራረብ ነው መሰለኝ፣ ግንኙነታችን ጠብቋል፡፡ ከሳምንት በፊት፣
ደውሎልኝ ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረና ሊመጣ እንደሆነ ሲነግረኝ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ውለታው የሚመለስ ባይሆንም፣ ለሱ ያለኝን ክብርና ፍቅር የምገልጥበት አጋጣሚ እንዳገኘሁ ተሰማኝ፡፡ ሲመጣ እኔ ጋር
እንዲያርፍ ተቀበልኩት፡፡ ተከራይቼ ምኖርበት፣ ሳር ቤት መቻሬ ኮንዶሚኒየም ወሰድኩት::


“ዶክ ተዋወቃት ባለቤቴ ናት፡፡”

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡ ግባ፡፡ ማሂ እባላለሁ፡፡” አለችው ባለቤቴ
እየጨበጠችው፡፡

“እንኳን ደህና ቆየሽኝ፡፡ ሄኖክ፡፡ እንዴት ነሽ?"

“ዶክ ይህንንም ጎረምሳ ተዋወቀው፡፡ ልጄ ነው፡፡”

‹‹እንዴ! ከመቼው ይሄን አደረስክ?” ልጄን እየሳመው በመገረም ጠየቀኝ፡፡

ሁሌም ከአምናችን ይዘን ምንሻገረው ጥሩም መጥፎም ነገር ይኖራል፡፡ አንድ ጥሩ ነገር ቤቢ ነው፡፡ ይህ ትልቅ የፊቴ ጠባሳ ደግሞ ሌላው፡፡” ማሂ በፈገግታ ታስተናግደናለች፡፡

ዶክተርን ከማሂ ጋር ሆነን በምንችለው አቅም በደንብ አስተናገድነው፡፡ በህይወቴ ባሳየሁት ለውጥ በጣም ደስተኛ እንደሆነ
ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ለሳምንት የራሱን ቤት እስኪያመቻች ከኛ ጋር ቆየ፡፡ደስ የሚል ግዜን አሳለፍን፡፡ ቤት አፈላለኩለት፣ እቃዎችን አጋዛሁት፣ባገኘሁት አጋጣሚ ያለኝን ፍቅርና ክብር ለማሳየት ሞከርኩ፡፡ ያለኝን ትርፍ ሰዓት አብረን እናሳልፋለን፡፡ ወክ እናደርጋለን፣ ሃሳብ እንለዋወጣለን፡፡ ነገ ወደ ተከራየው አዲሱ ቤት ይገባል፡፡ ዛሬ የሰፈራችንን የመጨረሻውን ወክ ልናደርግ ወጣን፡፡

“ያቤዝ...”

“ወዬ ዶክ፡፡”

“ሰሞኑን አንተ ላይ ባየኋቸው ለውጦች ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ስነግርህ ቆይቻለው፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደ አዲስ ሙሉ የህይወት ታሪክህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”

“ማለት? አልገባኝም ዶክ፡፡”

“በቃ ህይወትህን፣ ከልጅነትህ ጀምረህ እንድትተርክልኝ እፈልጋለሁ።”

“እንዴ! ለምን?”

“ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ካየሁህ፣ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ስላንተ በጥልቀት ማወቅ ፈልጌያለሁ፡፡ ስላንተ ብዙ አስባለሁ፤ እገምታለሁ፡፡ እስከዛሬ ግዜው እንዳልነበር ይሰማኝ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን፣
ከመቼውም ግዜ በላይ ደስተኛና የተረጋጋህ እንደሆንክ አይቻለው፡፡
ስለዚህ ብትነግረኝና ብሰማኸ ደስ ይለኛል፡፡

“ዶክ፣ አንተን ይህን ያህል ካስደሰትህ፣ እንኳን ይሄን ሌላም
አደርግልሃለው፡፡ መቼም ከፍዬው ማልጨርሰው ውለታህ አለብኝ፡፡”

“ኧረ በፍፁም! እንደዛ ሁለተኛ እንዳትለኝ፡፡ እኔ ምንም አላደረኩልህም፡፡ አንተ ጎበዝና ጠንክራ ሰው ስለሆንክ ነው፡፡”

“እሺ እንዳልክ፡፡ ብቻ ግን ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ፡፡”

“አሁን የጠየኩህን፣ ታሪክህን ንገረኝ፡፡”

“እሺ! ያቤዝ እባላለሁ፡፡ ሰላሳ ስምንት አመቴ ነው። በልጅነቴ ዝምተኛም፣ አስቸጋሪም ልጅ ነበርኩ፡፡ ደግሞም ጎበዝ ተማሪ፡፡.” ከመቻሬ ኮንዶሚኒየም ወጥተን የጦር ሀይሎች አጥርን ታከን ቁልቁል
የካርል አደባባይን እየወረድን ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ ዝም ብሎ ያዳምጠኛል፡፡ገብርኤልን አልፈን፣ በቶታል ማዞሪያ ቁልቁል ወደ መካኒሳ እየወረድን፣ከልጅነት እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ከመመረቅ እስከ ከፍተኛ ሀላፊነት፣ ደስታና ሃዘን መውጣትና መውረዶች፣ ከእሱ ጋር እስከተዋወቅንበት ያለውን የማስታውሰውን ያህል ነገርኩት፡፡ በየመሀሉ የሚሰማኝን የጥፋተኝነትና
የቁጭት ስሜቶች ከፊቴ እንዳያነብብኝ፣ ቀና ብዬ ሳላየው በተመስጦ ተረኩለት፡፡ ስጨርስ ዝም አልኩኝ፡፡

“እንዙር፡፡” አለኝ፡፡ እርቀን ሄደናል፡፡ እሺ ሳልለው ዝም ብዬ ዞረኩኝ፡፡ ምንም እያወራ አይደለም፡፡

“በቃ ይኸው ነው፡፡ ከዛ ህይወቴን አንተ ቀጠልከው:: አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ ቀድሜ ህክምና ብጀምር ብዙ ጉዳቶቼን ማስቀረት እችል ነበር፡፡ ግን፣ ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም፡፡ እንዴት እንደምመልስው ባላውቅም፣ ውለታህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አልረሳውም፡፡”

“የምን ውለታ ነው ምትለው ያቤዝ፣ መልስህ እንዲህ ደስተኛና ስኬታማ ሆነህ በማየቴ ብቻ፣ በምንም ከፍዬ ማላገኘው ደስታ ነው::ታሪክህ ደግሞ ከጠበኩት በላይ ይገርማል፡፡ መፅሀፍ እየተረክልኝ
እስኪመስለኝ፣ ተመስጬ ነበር ያዳመጥኩህ፡፡”

“እንዴት..?”

“በህይወትህ የባይፖላር ምልክቶችን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ተፈራርቀውብሃል፡፡በማህበረሰባችን የስነ አዕምሮ የግንዛቤ እጥረት ሰፊ ስለሆነ እንጂ፣ ይሄን ሁሉ ቀውስ ሳታሳልፍ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል ነበር፤” ብሎ ትክዝ አለ፡፡

“እውነትህን ነው፡፡ አሁን፣ እኔም የቀድሞ እኔን ካሁኑ ጋር ሳነፃፅረው እንደዛ ይሰማኛል፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ ለበጎ ነው ብሎ ከማለፍ ውጪ፡፡”

“ማድረግማ መቻል አለብን፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣በሃገራችን ከአራት ሰዎች አንዱ የሆነ አይነት የአዕምሮ ችግር አለበት፡፡በዚህ ሰዐት እንዳንተ ብዙ ሴ ሰዎች፣ በስራቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ባለው የመረጃ እጥረትና የተዛባ አመለካከት፣ ብዙ ሰዎች ችግሩ እንዳለባቸው አይገነዘቡም፣ ችግሩም ህክምና እንዳለው አያውቁም፣ ማህበረሰባችን በዚህ ጉዳይ ሃኪም ማናገር ይፈራል፡፡ በዚህ ምክንያት ስንቶች፣ ከሚገባቸው ስኬት በታች ሆነው፣መድረስ ካለባቸው ከፍታ በታች ወርደው፣ በሚገፉት ህይወት
የሚሰማቸውን ቁጭትና ህመም ሳይ፣ ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ እንዳልሆነ ይሰማኛል። በጣም አዝናለሁ፡፡ የችግሩን መጠንና ስፋት ስመለከት ደግሞ፣ ነብሴን ትጨነቃለች። የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፤” አለኝ አሁንም በትካዜ ውስጥ ሆኖ፡፡ እነዛ አስጨናቂና አስፈሪ፣ ላቆማቸው የማልችላቸው የባዶነት፣የተስፋ ቢስነት፣ ሀሳቦች ትዝ አሉኝ፡፡ አሁን የሉም፡፡ ጠፍተዋል።
ውስጤ ስላምና የተረጋጋ ነው፡፡ አሁን፣ ለእኔ አለም ጨለማ
👍2🥰2🔥1