#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
«በፍፁም» አለ ዶክተር ደጀኔ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለመግለፅ ጭንቅላቱንም እየወዘወዘ"ቀድሞ ነገር ውድድር አልተካሄደም ነገሩ ከላይ ተወስኖ ነው የመጣው አለው»
«ከላይ ማለት?» ሲል ጠየቀ አስቻለው በእርግጥ የቃሉ ትርጉም ጠፍቶአልና አልነበረም።
ነገር ግን ከዚያው ከአውራጃው ወይስ ከክፍለ ሀገር አለያም ከማዕከል ለማለት ፈልጎ እንጂ።
«ብቻ ከላይ ሌላው ምን ያደርጋል።»ካለ በኋላ ዶክተር ደጀኔ ድንገት ወደ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ገባና መሬት መሬት እያየ
ይተክዝ ጀመር አስቻለው በበኩሉ በንዴት አንጀቱ ተቃጥሎ በእግሩ መሬቱን መታ መታ ያደርግ ጀምር።
«ግን አስቻለው» ሲል ዶክተር ደጀኔ ለራሱ አለና አስቻለውንም አነቃው።
«አቤት ዶክተር»
«ለመሆኑ እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ሰራህ ?»
«ሰባት አመት አለፈኝ!»
«ዝውውር ሞክረክ አታውቅም?»
«አልሞከርኩም»
«አሁንስ ለመሞከር አታስብም?»
«ይሳካል ብለህ ነው ዶክተር?»
«እርግጠኛ ነኝ በዚህ ከተማ ውስጥ የምትጦራቸው አሮጊትና ሽማግሌ የለህም።»
«ምንም » አለ አስቻለው፡፡ ግን ደግሞ ወድያው ሔዋንን ጨምሮ ታፈሡ በልሁና መርዕድ ትዝ አሉት፡፡ ከእናትና አባቱ ባልተናነሰ ሊለያቸው የማይፈልጋቸው የፍቅር ቤተሰቦች ናቸውና።
እንደኔ እንደኔ ከዚህ ሆስፒታል ወደሌላ ብትዛወር የተሻለ ርምጃ መስሎ ይታየኛል፡፡ ለምን መስለህ አስቻለው!»
«እሺ ዶክተር »
አስቻለው በጽሞና እያዳመጠው "መሆኑን የተረዳሁ ዶክተር ደጀኔ ሀሳቡን ቀየር አደረገና በቅድሚያ አንድ ነገር ልጠይቅህና አንተም ትክክለኛውን ንገረኝ::ሲል ፈገግ እያለ በማየት አሳሰበው::
«ምንም አልደብቅም ዶክተር፣»
«ለመሆን እዚህ ከተማ ውስጥ 'የሴት ጓደኛ አለች» ሲል አሁንም ፈገግ ብሎ እያተ ጠየቀ። አስቻለው ድንግጥ ብሎ ድንገት ስሜቱ ሲለዋወጥ አይቶ
ዶክተር ደጀኔ አሁንም ፈገግ እያለ “ምነው ደነገጥክ?» ሲል ደግሞ ጠየቀው፡፡
አስቻለው የምንተነፍረቱን «አይ …ማለት» አለና እንደ መርበትበት
ከአደረገው በኋላ «መኖር አለችኝ ግን ምነው?» ሲል ዶክተር ደጀኔን መልሶ ጠየቀው።
«እስከገባኝ ድረስ አልጅቷ ጋር አብራችሁ አይደላችሁም፡፡ ልጅቷ
ምትኖረው ከእህቷ ጋር ነው። ልክ ነኝ?»
«እንዴት ልታውቅ ቻልክ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በያዘው እስርቢቶ ጠረጴዛጠን መታ መታ አደረገና እንደገና ወደ አስቻለው ቀና በማለት «ቅድም በቤታችንና በግቢያችን ወስጥ የሚከናወነውን እንኳ አናውቅም ብዬህ ተማምነንስ እልነበረም!» እለው፡፡
«ልጅቷ ገና በልቤ ወስጥ ነው ያለችው»
ዶክተር ደጀኔ ድንገት ሃ..ሃ..ሃ...ሃ ብሎ ሳቀና አየህ! ግማሽ አካሏ ከውጭ ቀርቶ ኗሯል አለና አሁንም ሃ ሃ ሃ ሃሃ
«የ'ሷን ነገር ለምን አነሳኸው አለው አስቻለው ዶክተሩ ሳቁን ሲጨርስ፡፡
«ግን እንደው አርግዛብህ ታዉቃለችን።?»
«በፍጹም ዶክተር እንዲያውም አታምነኝ እንደሆነ እንጂ ልጅቷ ገና ድንግል ናት።»
ዶክተር ደጀኔ እንደ መደነቅ ብሎ «ድንግል! ድንግል!»
«ከልቤ ነው የምነግርህ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በመገረም ዓይነት ፍዝዝ ብሎ አስቻለውን ሲመለከት ቆየና ራሱንም ወዘወዘ «ገና ብር አምባር ሰበረልዎ እንላለና»
«እዚያ ካደረሰን! አለና አስቻለው ግን የእሷን ነገር ለምን እንዳነሳህ
አለገባኝም ዶክተር አለ አሁንም ዓይኑን በዶክተር ደጀኔ ላይ እያንከራተተ፡፡
«ምክንያት አለኝ!»
«ምን?»
«ያልተወለደ ገዳይ የሆንከው ከእሷ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡
እኔ ግን ነገሩ አሉባልታ ስለመሆኑ በትክክል ገብቶኛል፡፡» አለው፡፡
«ምኑ ከምን ጋር ተገናኝቶ?»
አሁን አሁን እየተበሳሽ ነው::
«ምኑም ከምንም!» አለና ዶክተር ደጀኔ በአጭር ቃል መለሰለትና ራሱ ቀጠለ፡፡ «እንደሚመስለኝ የአንተና የልጅቷ እህት ግንኙነታችሁ ጥሩ አይደለም፡፡
የልጅቷ እህትና ባርናባስ እንደሚግባቡስ ታውቃለህን?»
«ሰሞኑን ሲደንቀኝ የሰነበተው ይህ ነው ብትነግረኝ ይከብድህ ይሆን?"
«ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ አንድ ቀን ግን እኔና ባርናባስ ከተማ ውስጥ አብረን ስንዘዋወር መንገድ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ተነጋግሮ ወደኔ እንደመጣ
«ህቺ ሴት መምህርት ናት፡ ያቤሎ በነበርኩበት ወቅት እሷም እዚያ ስለነበረች እንተዋወቃለን፡፡ ብቻ ነው ያለኝ አለው ዶክተር ደጀኔ፡፡ አስቻለው የሁለቱን የትውውቅ መሠረት በማውቁ ሳይሆን አይቀርም አንገቱን ደጋግሞ ነቀነቀና «አሁን ብዙ ነገር ገባኝ ዶክተር፡፡» አለው::
«አዎ እስቻለው! የጓደኛህ እህትና ባርናባስ ከፈጠሩት ግንኙነት በመነጨ ነው ያልወሊደ ገዳይነትህ የተወራብህ፡፡ ይህን ደግሞ የነገረኝ ራሱ ባርናባስ ነው!
መምህርቷ ነገረችኝ ብሎ። ግን ደግሞ ይህን ሁሉ የምነግርህ ብዙ ጊዜ አካሄድ ፊትለፊት ስለሆነ ድንገት ሳታውቀው እንዳትጠለፍ ለጥንቃቄ ይረዳሃል ብዬ ነውና
አስብበትት፡፡ የዝውውሩንም ጉዳይ ችላ ባትለው መልካም
ይመስለኛል።» አለው፡፡
እስቻለው በረጅሙ ተንፍሶ ጥቂት ካሰላሰለ በኋላ
«የሰሞኑ እንቆቅልሽ ገና ዛሬውኑ ተፈታልኝ ዶክተር» ብሎ ከንፈሩን ነክሶ ጣሪያ ጣሪያ እያየ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡ የዶክተር ደጀኔን የዝውውር ሃሳብ በቀላሉ አልተመለከተውም፤ እንዲያውም በርካታ ነገሮች በተዘዋዋሪ መንገድ ይህንኑ ጉዳይ ሲያሳስቡት ሰንብተዋል። በልሁና መርዕድ ታፈሡና ሽዋዬን ለማስታረቅ ከሞከሩ በኋላ
ተመልሰው የገለፁለት ነገር ሔዋን በሃሳብ ምን ጊዜም ከአንተ ጋር ናት። ሸዋዩ ባለችበት አካባቢ ግን እንጃ….” የሚል ፍሬ ሃሳብ የነበረው ነው። ከዚያም በላይ
የእርቅ ሙከራ በተደረገ ሶስተኛ ቀን ረፋዱ ላይ ሔዋን ሳያስባት ለዚያውም ፊቷ በእንባ ረስርሶ ወደ ቤቱ መጥታ ነበር።
«ምነው ሔዩ» ነበር የአስቻለው ጥያቄ።
«እንካ ይኸን ወረቀት አንብብ ብላ አንዲት ወረቀት ሰጠችው።
አስቻለው ወረቀቷን ገለጥ አድርጎ ሲያነብ የሚከተለውን መልዕክት
አገኘባት።
«ለተከበራችሁ አባትና እናቴ ለአቶ ተስፋዩ ይርጋ እና ለወይዘር ስንዱ በላቸው፣ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ። እኔ ግን በጣም ተቸግሬያለሁ። እናንተንም እሷንም
ለመርዳት ስል ሔዋን የተባለች ልጃችሁን ወደ ዲላ ይዣት መጥቼ ነበር። እሷ ግን ትምህርቷን እርግፍ አድርጋ ትታ ሥራዋ ወንድ ማባረር ብቻ ሆኗል። እንዲያውም
መዘዟ ለኔ ተርፎ ችግር ላይ ወድቄአለሁ።ከመቸገሬ የተነሳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቤቴ ላባርራት ነው ።ምናልባት ልጃችን ባክና መቅረት የለባትም የምትሉ ከሆነ ከሁለት አንዳቹ መጥታችሁ ውሰዷት። መጥተን እንወስድም ካላችሁ ውርድ ከራሴ።
ልጃችሁ ሽዋዬ ተስፋዬ
አስቻለው ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ በንዴት እሳት ለብሶ እሳት ጉርሶ ፈጠን ባለ አነጋገር ሴትዮዋ ምን እያለች ነው?» ሲል ሔዋንን ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ አስቹ፣ ግራ ገባኝ» ሔዋን እያለቀሰች፡፡
«የት አገኘሽው?»
«ዛሬ ጠዋት ሥራ ስትሄድ ረስታው መሰለኝ አልጋዋ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት።»
«ቀዳድጄ ልጣለው?»
«ተው አስቹ፣ ነገር ይባባስብኛል። ግን አንድ ነገር ላማክርህ?

#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....በመጨረሻም ምንትዋብ ብያታለሁ” ብለው በቀኛቸው ያለው ድንክ አልጋ ላይ
እንድትቀመጥ አደረጓት። እሷን ተከትለው የገቡት አያቷ፣ በካፋን
ለጥ ብለው እጅ ነስተው በእልፍኝ አስከልካዩ መሪነት ከንጉሣውያን
ቤተሰቦች ጋር የተዘጋጀላቸው ቦታ ሄደው ተቀመጡ።
ወዲያው ሙሉ ቤት አዛዥ እንጀራ አሳላፊውንና እንጀራ የያዙ
ተከታዮቹን፣ በወጥ ቤቱ መሪነት ሰታቴ ተሸክመው ወገባቸው
እየተንቀጠቀጠ የሚራመዱትን ሴቶችና ወንዶች፣ ወጥ ቤቶቹንና ወጥ ጨላፊዎቹን፣ የጠጅ መልከኛው የጠጅ ገንቦ፣ ብርሌዎችና ዋንጫዎች የያዙ ጠጅ ቀጅዎቹን፣ ጠላና አረቄ ቤቶቹ ጠላና አረቄ ቀጂዎቹን፣
ግምጃ ቀሚስ ያጠለቀው ሥጋ ቤት ሥጋ ተሸክሞ የተሳለ ቢላዋዎች ያቀፉትንና ዐዋዜና ድቁስ የያዙትን ተከታዮቹን እየመራ ሲገቡ እንግዶቹ ተነሥተው ቆሙ።
እልፍኝ አስከልካዩ ገበታ እንዲወርድ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
ያደገደጉ የእልፍኝ አስከልካዩ ጭፍሮች ንጉሠነገሥቱ የተቀመጡበትን አካባቢ በነጩ መጋረጃ ጋረዱት። ባለ ሦስት ጭፍራው የአስታጣቢ
ሹም አሸርጦ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ላይ ውሃ እንዳይፈናጠቅ ክንዱ ላይ
አንጠልጥሎት የነበረውን ያማረ የእጅ መጥረጊያ ጨርቅ ጭናቸው ላይ አስቀመጠላቸው። ለብ ያለ ውሃ በወርቅ ቅብ ማንቆርቆሪያ አድርጎ፣ የወርቅ ቅብ ሳህን ላይ ሊያስታጥባቸው በርከክ ሲል መሣፍንቱ፣ መኳንንቱና ሌሎቹ እንግዶች እንደቆሙ ፊታቸውን ወደ ውጭ አዙረው በኩታቸው ሸፈኑት። አፄ በካፋ እጃቸውን ከታጠቡ በኋላ፣ አስታጣቢው
ትከሻው ላይ ጣል ያደረገውን እጅ መጥረጊያ ሰጣቸው። እጃቸውን
አድርቀው መልሰው ሲሰጡት ተቀብሎ ከቀኛቸው የተቀመጠችውን
ወለተጊዮርጊስን በርከክ ብሎ አስታጠባት።
ያደገደገ አጋፋሪ በግርዶሽ ተከልሎ፣ በቀኝ እጁ የተከበረውን የንጉሠ ነገሥቱን የወርቅ ዋንጫ፣ በግራ እጁ ፍንጃል ይዞ በሕዝቡ መሃልዐሰንጥቆ ንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ሲደርስ፣ ግራ መዳፉ ላይ ወይን ጠጅ ጠብ አድርጎ ቀመሰና ዋንጫቸውን ሞላላቸው። ዋንጫውን ከእጁ ላይ
ወሰዱ።
ሙሉ ቤት አዛዥ የነጠላውን ጫፍ ከትከሻው ላይ አጠፍ አድርጎ፣
ቀደም ሲል በቀማሽ በኩል ያለፈውን፣ ወርቀ ዘቦ ቀሚስ ባጠለቀ መሶብ የተሰናዳውን እንጀራ ይዞ በቆሙት ታዳሚዎች መሃል፣ “እንጀራ ይስጣችሁ” እያለ አልፏቸው ሄዶ፣ በቀኝና በግራ ረድፎቹ መሃልና ንጉሡ ፊት ለፊት በወርቀ ዘቦ ተሸፍኖ የተቀመጠው የንጉሠ ነገሥቱ መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ አኖረው። ዓይነታቸው ለቁጥር የሚያታክት፣ ዶሮ፣ ቀይ ስጋ፣ ምንቸታብሽ፣ አይብ፣ አልጫና ሌሎችም የወጥ
ዓይነቶች የያዙት አነስተኛ ሸክላ ድስቶች ጠረጴዛው ላይ ቀረቡ። አቡነ ክርስቶዶሉ ተነሥተው መስቀላቸውን ጨብጠው ቡራኬ ከሰጡ በኋላ፣ቆመው የነበሩት እንግዶች ተቀመጡ።
ያን ጊዜ ያሸረጠ አሳላፊ የንጉሠ ነገሥቱን መሶብ ልብስና ክዳን
አንስቶ ከኋላው ለቆመ አስተናጋጅ ሰጠው። ከመሶቡ ጥግ እንጀራ
ቆረስ አድርጎ ግራ እጁ ጀርባ ላይ አስቀመጠ። ወጥ አውጭው ከየድስቱ ውስጥ በትንሹ ጨለፍ እያደረገ እንጀራው ላይ ሲያፈስለት፣ አሳላፊው
እጁ ከንፈሩን እንዳይነካ ተጠንቅቆ ፊቱን ዞሮ ምግቡን ቀመሰ። ወጥ
አውጭው ከየዓይነቱ ወጥ መሶቡ ላይ ሲያደርግ፣ አሳላፊው ንጉሠ
ነገሥቱን ማጉረስ ጀመረ።
ወለተጊዮርጊስም ለመጀመሪያ ጊዜ ከንጉሠ ነገሥት ጋር ማዕድ ተቋደሰች።
ንጉሠ ነገሥቱ፣ ወለተጊዮርጊስና መጋረጃ ውስጥ የተፈቀደላቸው እንግዶች በልተው ካበቁ በኋላ፣ መጋረጃው ሲከፈት
አስተናጋጆች ከመጋረጃ ውጭ ደረጃቸው ተጠብቆ የተቀመጡትን
እንግዶች እንደየክብራቸው እጃቸውን በብር፣ በነሐስ ወይንም በብረት ማስታጠቢያ አስታጠቡ።
በእንጀራ ቤቱ ሥር ያሉት አስተናጋጆች በቀረበው ገበታ ላይ
እንጀራ ሲያደርጉ፣ ወጥ ቤቶቹ የተለያየ ወጥ የያዙ ሰታቴዎችን ይዘው እየተንገዳገዱ ሲቀርቡ፣ ወጥ ጨላፊዎች እየጨለፉ የተዘረጋው እንጀራ ላይ አወጡ፤ እንግዶቹም በፀጥታ መብላት ጀመሩ።
ወጥ ቤቶች እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ወዲህ ወዲያ እየተዘዋወሩ ባዶዎቹን ሰታቴዎች ይዘው በፍጥነት ሲወጡ፣ ሌሎች ወጥ የያዙ ሰታቴዎችን ይዘው ከመቅጽበት ይመጣሉ። ለንጉሠ ነገሥቱ የመጣ ገፀ በረከትና ደጅ መጥኚያ ሙክት፣ ሰንጋ፣ ቅቤና እህል በሙሉ ቤት አዛዥ የበላይ ተቆጣጣሪነት ለድግሱ በመዋሉ፣ የምግቡ ዓይነት ልክ
አልነበረውም።
በትልልቅ ድስቶች ጥብስ እየተንቸሰቸሰ፣ ሽታው እያወደ ሲመጣ፣እንግዶቹ ቀዩን ከጮማው እያማረጡ፣ ዐዋዜ ወይንም ድቁስ ላይ እየተመተሙ፣ በጠጅ አለበለዚያም በአረቄ አወራረዱት።
ቀጥሎም የሥጋ ቤት ሹሙ ተሸክሞት ከመጣው ሥጋ ሻኛው፣
ብርንዶው፣ ጎድን ተዳቢቱ፣ ሽንጡና ሌሎችም ዋና ዋና የሥጋ ብልቶች በየገበታው ሲቀርቡ፣ ቢላዋ ለእያንዳንዱ ሰው ታደለ። ዐዋዜና ድቁስ የያዙት አስተናጋጆች ደግሞ በእያንዳንዱ ገበታ አንፃር ሲያስቀምጡ፣
እንግዶቹ እንደየምርጫቸው እያነሱ ሥጋውን አጣጣሙ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ግርዶሹ እንደ ተከፈተ ነው። ወለተጊዮርጊስ፣ ውስጣዊና ውጫዊ ብርሃን እየረጨች በተመስጦ ዕድምተኛውን ትመለከታለች። ዐይኗን
ከአስተናጋጆቹ ላይ ማንሳት አቅቷታል። በሥራቸው የተካኑት ሙሉ ቤት አዛዥ፣ የእልፍኝ አስከልካዩና ጭፍሮቹ፣ ሰታቴ ተሸካሚዎቹና ወጥ ጨላፊዎቹ፣ የሥጋ ከብቱን ተረክቦ ያሳረደው ሥጋ ቤቱና ጭፍሮቹ
ነጠላቸውን ትከሻቸው ላይ አጣፍተው ወይንም ቡሉኮ ደርበው በየቦታው ተሰማርተው እንደየኃላፊነታቸው በቅልጥፍና ማስተናገዳቸው አስደንቋታል።
ጠጅ አሳላፊው አስተናጋጆቹ የት ሄደው የጎደሉትን ብርሌዎች
መሙላት እንዳለባቸው በዐይኑ ሲጠቁም፣ እንጀራ ቤቱ እንጀራ አለቀ አላለቀ እያለ ከሩቅ መሶብ ሲያማትርና ገበታ ደንገጥ ያለበትን በጥቅሻ ለእንጀራ አሳላፊዎች ሲያመለክት፣ ወጥ ጨላፊዎች እየዞሩ ከየዓይነቱ ወጥ ሲጨልፉ፣ ሥጋ ቤቱ አንጓ አንጓ ሥጋ ተሸክሞ በየገበታው ሲያዞር፣ሥርዓታቸው፣ ትጋታቸው፣ ፍጥነታቸው፣ ቅልጥፍናቸውና ለሥራቸው
ያላቸው ፍቅርና አክብሮት አስደምሟታል።
በልቶ የጨረሰውም እንግዳ ሲወጣ ሌሎች እንደየተራቸው እየገቡ፣ያለግርግርና ያለትርምስ ሁሉም ደንብና ሥርዐት ተከትሎ መደረጉ አስገርሟታል።
ያለ የሌላትን መረጋጋት አጠረቃቅማ ሙሉ ጨረቃ መስላ
ተቀመጠች። ድፍረት እንዳይሆንባት ተጠንቅቃ ንጉሠ ነገሥቱን ሰረቅ አድርጋ አየቻቸው። እንደዚያ በወርቅ ተንቆጥቁጠው፣ ግርማ ሞገስ ተጎናጽፈው፣ ያ ሁሉ ሰው ቁጭ ብድግ የሚልላቸውን ሰውዬ፣ ቋራ እነሱ ቤት መደብ ላይ ተኝተው በወባ ትኩሳት ከተንደፋደፉትና ቤት ያፈራውን እየተመገቡ ካገገሙት ሰውዬ ጋር ማዛመድ አልሆንልሽ
አላት። ለማመንም አቃታት።
ዕጣ ፈንታ ይሁን ሌላ እዚህ ሕይወት ውስጥ የጨመራትን አሰላስላ ተገረመች። እሷ፡ አባቷና የጥላዬ አባት ታርቀው ከጥላዬ ጋር ጎጆ ቀልሰው ለመኖር አልማ ነበር እንጂ እንደዚህ የተንጣለለ ሕይወት ውስጥ እገባለሁ ብላም አልገመተች። ከጥላዬ ውጭ ከሌላ ጋር የመኖር ፍላጎትም ሐሳብም አልነበራት። ጥላዬ ራሱ በዚያን ሰዐት ቢያያት ምን
ሊል እንደሚችል መገመት አቃታት። የንጉሠ ነገሥቱ ታመው ወላጆቿ ቤት መምጣት፣ የእሷ ማስታመምና የእሳቸው አገግሞ መመለስ፣ ለእሷ ቤተመንግሥት መግባት መነሻ ምክንያት መሆኑ ታምር ሆነባት።

#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
...ይህን ሁሉ ሲልና ከአሜሪካኖቹ ጋር ሲከራከር፣ እኔ ዝም ብዬ
እሰማለሁ። ምሳዬን ወይም እራቴን እየበላሁ። አንድ ግዜ ግን ከአንድ ጉረኛ አሜሪካን ጋር ክርክር ገጠመ
ባህራም እንደልማዱ ከሙግቱ ጋር ቀልድና ሳቅ ሊቀላቅል ሞከረ። ከሜሪካኑ ግን በሀይል አምርሮ ስለ አሜሪካን የጦር ሀይል ሲሸልል ፣ ስንት የጦር መርከብ ስንት የጦር አውሮፕላን እንዳላቸው ሲያወራ ፣ እንኳን ሆ ቺ ሚን ክሮስቾብና ማኦ እንደዚሁም ሌሎች ችጋራሞች ኮሚኒስቶች ተሰብስበው ቢመጡ አሜሪካ ብቻዋን ድምጥማጣቸውን እንደምታጠፋቸው የዚህም ማስረጃ በ 61 ዓ.ም የኩባ ፍጥጫ ላይ ኬኔዲ ኮሚኒስቶቹን ፈሳቸውን አስረጭቶ ከኩባ እንዳባረረ እንደዚ እያለ ጉራውን ሲነፋ አበሸቀኝ። ባህራምም መሳቁን ትቶ ዝም ብሎ ይሰማዋል። አሜሪካኑ
«አሁን ብንፈልግ ሆ ቺ ሚኒንና ቪየትኮንጎቹን በአንድ ሳምንት
ውስጥ እናስፈሳቸዋለን!» ሲል፣ ምን እንደነካኝ ሳላውቅ እዚህ ላይ አንድ ነገር አለ አልኩ። እስካሁን አንድ ቃል ሳልተነፍስ ስለቆየሁ፣ ባህራምም፣ አሜሪካኑም፣ ሌሎቹም ገበታችን ላይ የነበሩት፣ ወደኔ አዩ። አጭር ዝምታ
ታሪክን ብናስታውስ» አልኩ በ480 አመተ አለም፣ ብዛቱ በሚሊዮን የሚገመት የፋርስ ጦር ስራዊት ግሪኮችን ለመውረር መጣ። ቴርሞፒሌ ላይ ሌዎኒዳስ የተባለው የስፓርታ ንጉስ አራት
መቶ ወታደሮቹን አሰልፎ ሲጠብቅ፣ ከፋርስ ንጉስ ወይም ከጦር አበጋዙ እንዲህ የሚል ማስፈራሪያ ደረሰው። 'እጅህን ብትሰጥ ይሻልሀል፡፡ የኛ ቀስተኞች ሲተኩሱ፣ ፍላፃዎቹ ከመብዛታቸው
የተነሳ፣ ፀሀይዋን ይሸፍኗታል፡፡
እና ሌዎኒዳስ ምን አለ ይመስላችኋል?»
አሜሪካኑ «ምን አለ?» አለኝ
«መልካም ነው:: እኔና አራት መቶዎቼም ጥላ ውስጥ ሆነን
ብንዋጋ እንመርጣለን» አለ
ዝም አሉ፡፡ የምግብ ቤቱ ጩኸት ከቦናል
ባህራም «ቀጥል» ኣለኝ
«ምን እቀጥላለሁ? ታውቁታላችሁኮ። ሌዎኒዳስና አራት መቶው አለቁ፡፡ ሆኖም ግን የፋርስን ቁጥር-የለሽ ሰራዊት ገትረው በመያዛቸው የውጊያው ሚዛን በነሌዎኒዳስ መስዋእትነት ወደነሱ ስላደላ፣ ግሪኮቹ ወራሪውን ሰራዊት ድል አድርገው አባረሩት። ታድያ በጦር ብዛት ቢሆን ኖሮ፣ ፋርስ ያን ጊዜ የአለምን ጦር በሙሉ ሊያሸንፍ ይችል ነበር። ግን የሰው ልጅ ለነፃነት ሲዋጋ፣ በጦር መሳሪያ ብቻ ሳይሆን በወኔው፣ በንዴቱ፣ በወንድነቱ ጭምር ስለሚዋጋ፣ ማንም ትልቅ ጦር አይችለውም። ለዚህ ነው እነሆቺሚን ሊሸነፉ የማይችሉት፡፡»
ይህን ጊዜ ምሳችንን ጨርሰን ስለነበረ ባህራም እየሳቀ
አሜሪካኑን «ለዚህ መልስ ለማግኘት አትሞክር። እውነት ስለሆነ መልስ አይገኝለትም» አለው ይልቅ ለኬነዲ ሀቁን ንገረው። እና አንድ ሌላ ነገር አለ ለኬነዲ መንገር ያለብህ፡፡ ማኦ የቻይናን ህዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጅ ብሎ ማዘዙን ታውቅ የለ? ደሞ የቻይና ህዝብ በማኦ ትእዛዝ ዋና በመማር ላይ ይገኛል፡፡ በየቀኑ ሰባት ሚልዮን ቻይናዎች የዋና ልምምድ ያደርጋሉ። አሮጊትና ሽማግሌው ባኞ ውስጥ ይዋኛል። ልምምዳቸውን ከጨረሱ በኋላ
እንግዲህ ምን እንደሚያደርጉ ታውቃለህ? ማኦ እየመራቸው
የፓሲፊክን ውቅያኖስ በዋና ያቋርጡና፣ እናንተን በአለንጋ አርባ
ገርፈው ሲያበቁ፣ አሻንጉሊቶቻችሁን በሙሉ ይቀሟችኋል። ጥሩ ልጆች የሆናችሁ እንደሆነ፣ አሻንጉሊቶቻችሁን እንመልስላችኋልን፡
አለዚያ ግን መጫወቻ ታጣላችሁ፡፡ ልባርጉ» ብለዋችሁ ሲያበቁ፣
ወደአገራቸው ተመልሰው በሰላም ይኖራሉ። ይህን ለኪነዲ ንገረው
አለውና እኔን እንሂድ አለኝ። አሜሪካ ለመሳቅም አልቻለ፣
ለመናደድም አልቻለ። ግራ ገብቶት ባህራምን አየው
እኔና ባሀራም ትተነው ከምግብ ቤቱ ወጣን። መኝታ ቤት
ሄደን ቡና ከጠጣን በኋላ፣ እንዲያጠና ወይም ስለሪቮሉሽን
እንዲያነብ ትቼው ወጥቼ ሲኒማ ለመግባት ወደ ከ ሜሪብ በኩል
አመራሁ ግን ሲኒማ አልገባሁም፡፡ በካፈ ዶርቢቴል በር ሳልፍ፣ ውስጥ ሲልቪን አየኋት:: ፊቷን ወደበር በኩል አርጋ ተቀምጣ ጋዜጣ ስታነብ ነበር፣ አየችኝ። የፈገግታዋን ወሰት ረስቼው ኖሯል፤ አሁን ሳየው በጣም ደስ አለኝ፡፡ ወደኔ መጣች። ስትራመድ እንገቷን እያወዛወዘች ስለሆነ፣ ከረዥም ነጭ አንገቷ በስተኋላ የተለቀቀው ጥቁር ሀር ፀጉሯ ዥው ዥው ይጫወታል፡፡ ይህንንም ረስቼው ኖሯል። መጣችና ጉንጬን ስማኝ
«ከነገ ወድያ ነበር ልመጣ ያቀድኩት፡ ግን በሀይል ናፈቅከኝ-
አለችኝ፡፡ እሷ ስትናገረው ፈረንሳይኛው መጣፈጡ! ወደ ቤቷ በኩል እየተራመድን፡
“እንኳን መጣሽ! በሀይል ናፍቀሽኝ ነበር» አልኳት
እንደ ልማዷ «ዣማንፉ» ሳቋን እያሳቀች እኔን የምታስረሳን
ሴት አላገኝህም? አለችኝ፡፡ እንዳላገኘው ታውቃለች። መቸም
ኣንደማላገኝ እርግጠኛ ነች።
«ሴት የሚሉት ነገር ዘወር ብዬም አላየሁ» አልኳት
“አንግዲያው ምን ስትሰራ ሰነበትክ?» ጫማዋ መንገዱን ኳ! ኳ! ሲያረገው ይሰማኛል፡ ከጎኔ ድምፅዋ ይሰማኛል፣ ሰፊ አፏ ላይ ውብ ፈገግታዋ ይታየኛል፣ ደስታ ይሰማኛል
«ሲኒማ ሳይ፡፡ እና ከባህራም ጋር ሳወራ»
«ምን ምን አወራችሁ?»
«ኦ --! ብዙ ነው»
«ንገረኝ»
«ጊዜ የለኝም፡፡ ዛሬ ካንቺ ጋራ ማውራት አልፈልግም» አልኳት
ምኞቱ ውስጤ ማበጥ ጀምሯል። ቤቷ እስክደርስ ቸኩያለሁ
«ማውራት አለብህ፤ ሌላ ነገር ለመስራት አትችልም» አለችኝ
«ለምን?» ብዬ አየኋት፡፡ ከጎኔ ስትራመድ ጭንቅላቷ ይወዛወዛል
ወደኔ አታይም፡፡ ፊቷ በጣም ቀልቷል። አፍራለች፡፡ ዝም አለች
«ለምን? ለመመንኮስ ቆርጠሻል እንዴ?» ዝም አለች፡፡ «ምን
ሆነሻል?»
«አሞኛል»
«ምንሽን?»
«አንተ የምትጠይቀውን ጥያቄ መቸስ የመንደር ቂል እንኳን
አይጠይቀውም፡፡»
«አትቆጪ። ምን ሆነሽ ነው? ማለቴ -»
«ነገሩ ትንሽ ነው፡፡ ሀኪም አይቶኝ መድሀኒት ሰጥቶኛል።
ከአንድ አምስት ቀን በኋላ ይድናል ብሎኛል።» ድንገት ሳቀች።
«ብቻ ቂጥኝ ወይም ጨብጦ እንዳልሆነ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ።
ኣለችኝ፣ ሳቋን ትታ «ይልቅስ ስለባህራም ንገረኝ፡፡»
ስለባህራም ሳጫውታት፣ ተነሳስቶ የነበረ ስሜቴን ረሳሁት።
ቤቷ ገብተን፣ ቡና በወተት አፍልታ ጠጥተን፣ ለብዙ ጊዜ አወራሁላት ስጨርስ አስተያየቷን ባጭሩ ገለፀችልኝ
«ይሄ ባህራም እንደ ፖል አይነት ሰው ይመስላል» አለች
«ለመሆኑ ስለፖል ትሰሚያለሽ?»
«ፓሪስ ስሄድ አንድ ደብዳቤ አገኘሁ፡፡ ፖል በቪየትናምና
በላኦስ መካከል እየተመላለሰ የደፈጣ ተዋጊዎቹን ያግዛል። በይፋ ባይታወቅ ነው እንጂ፣ አሜሪካኖቹ ላኦስ ውስጥም ይዋጋሉ። የደፈጣ ተዋጊዎቹ ፖልን ኮሎኔል ነው የሚሉት፡፡ በጣም ይወዱታል፡፡»
«ሌላስ ምን አለ?»
«ምንም አላለ። እሱን ተወውና ናፍቄህ አንደሆነ አሳየኝ እስቲ»
አለችኝ። ውብ ፊቷ ላይ ቅንዝረኛ ፈገግታ ይርበተበታል። እነ ፖልን
ባንዳፍታ ረሳኋቸው። እሷ እንደተቀመጠች ከፊቷ ተምበርከኬ አንገቷን እስመው ጀመር፡፡ አንገበገበኝ፡፡ ተለይታኝ ስለቆየችና አሁንም ላገኛት ባለመቻሌ፡ ስሜቱ እንደ እብድ አደረገኝ፡ ምንም ማድረግ እንደማልችል እያወቅኩም ልብሷን አስወለቅኳት። ናፍቆኝ
የነበረውን ውብ ገላዋን ማየትና መቃጠል አማረኝ። በልዩ ጥንቃቄ

#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
የሻምፕማትዩ ጉዳይ
የታሪኩ አንባቢ እስካሁን በተነገረው መሴይ ማንደላይን ማለት ዣን ቫልዣ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ዣን ቫልዣ ማለት ራሱ እንደሆነ እያወቀ አሁን ሌላ ሰው ዣን ቫልዣ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉት ምን ይሰማው ይሆን? ሕሊናው ምን ይላል? ምን ዓይነትስ ፈተና ውስጥ ነው የገባው? ከባሕር ጥልቀትና ከሰማይ ርቀት የላቀው የሰው አእምሮ የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ሲገጥመው ውስጣዊ ስሜቱ ምን ይመስል ይሆን?
እስከዚያን እለት ድረስ ከልቡ ውስጥ ቀብሮ የያዘውን ጉዳይ በድንገት ዣቬር ስላነሳው መሴይ ማንደላይን ከቢሮው ውስጥ ቁጭ እንዳለ መላ ሰውነቱ ራደ:: «መጨረሻዬ ምን ይሆን» ሲል አሰበ:: ውሽንፍር እንደሚያወዛውዘው ዋርካና ከባድ ጦር እንደገጠመው ወታደር ልቡ ከወዲያ ወዲህ ተንከራተተ:: ዣቬር ነገሩን አራዝሞ ከቢሮው አልወጣ ብሎት ሲናገር የአገር ደመና ተሰባስቦ ከባድ ዝናብና መብረቅ ከጭንቅላቱ ላይ
የሚያዘንብ መሰለው፡፡ ዣቬር እያነጋገረው «ሂድ ፤ ተነሳ፤ ሩጥ!
ሻምፕማቲዩን ነፃ አውጣ፤ ወደኋላ አትበል፤ ራስህን አጋልጥ» የሚል
ስሜት አደረበት፡፡
«አባ ሻምፕማትዩን ከእስር ቤት አስወጥተህ በእርሳቸው እግር አንተ ተተካ» የሚለው አሳብ ከሕሊናው አልወጣ አለው:: ሆኖም ቀላል ውሳኔ ሆኖ አላገኘውም:: ሀሳቡ ልክ ኣንድ ስለት ያለው ነገር አካል ውስጥ ዘልቆ ሲገባ የሚሰማው ዓይነት ስሜት አሳደረበት:: መጨረሻውን እንያ!» ሲል እርስ በራስ ተነጋገረ፡፡ በሌላ በኩል የምን ጀግንነት ነው» ሲል ከራሱ ጋር ተሟገተ፡፡ በዚህ ዓይነት ሕሊናውና ሥጋው ግብግብ ገጠመ፡፡
ገና ድሮ ከእስር ቤት እንደወጣ እኚያ ጳጳስ አጥንት የሚሰብር ንግግር ባይናገሩት ኖሮ የዚህ ዓይነቱ፡ ግብግብ ባልገጠመው ነበር፡፡ አንድ ጎኑ
«የሚበቃህን ያህል ተሰቃይተሃል፤ አሁን ራስህን አውጣ» ሲለው ሌላውዐጎኑ «እንዴት ባንተ ምክንያት ሌላ ሰው ይጐዳል» እያለ ወተውተው፡፡
ዣቬር ከቢሮው እስከወጣ ድረስ ስሜቱን ለመቆጣጠርና የተዝናና ለመምሰል ብዙ ታገለ፡፡ ዣቬር እንደወጣ ፋንቲንን ለመጠየቅ ወደ ተኛችበት ክፍል ሄደ፡፡ ከሌላው ቀን ይበልጥ ጊዜ ወስዶ አጫወታት:: ሴሮቹ የተለየ ጥንቃቄ
እንዲያደርጉላት በማሳሰብ ምናልባት እራስ ወደ ተባለ ሥፍራ ሊሄድ እንደሚችል ገለጸላቸው:: ከዚያም ገበታ ቀርቦለት እንክት አድርጎ በላ፡፡
ወደ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ኣሳቡን ሰበሰበ፡፡ ሁኔታውን በአሳብ ሲገመግመው ከዚያ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ
ዓይነት ሆነበት:: ድንገት ሳያስበው ከመቀመጫው ብድግ ብሎ የነበረበትን ክፍል በር ቆለፈ:: በሩ የተቆለፈ እንደሆነ ማንም ገብቶ ሊያስፈራራው እንደማይችል አመነ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የክፍሉን መብራት አጠፋ::
መብራቱ ራሰ ኣናደደው:: መብራት አበራ አንድ ስው ከውጭ ሆኖ
ሊያየው እንደሚችል ተገነዘበ፡፡
«ማን? የትኛው ሰው?»
የሚገርመው ግን እንዳያየው የፈለገው ሰው ሁሉ አየው:: የቆለፈው በር ሁሉ ወለል አለ፡፡ ማን ከፈተው? ማን አየው? ሕሊናው::
ሕሊናው ማለት ሁሉንም የሚያይ አምላክ አየው:: በመጀመሪያ ራሱን ለማታለል ሞከረ:: ከተቆለፈ ቤት ውስጥ ብቻውን ራሱን ከደበቀ
ማንም የሚያገኘው አልመሰለውም ነበር፡፡ በሩ ተቆልፎአል፤ መብራቱ ጠፍቶአል፡፡ ታዲያ ማን ሊያየው ይችላል?
ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ያዘና ክርኑን ጠረጴዛ ላይ በማስደገፍ
ጨለማ ውስጥ ያሰላስል ገባ፡፡ አሳቡን ለማሰባሰብ ሲፈልግም አንጎሉ በቂ ኃይል አጣ፡፡ ሕሊናው ውስጥ የነበረው አሳብ ሁሉ እንደ ማዕበል ተወራጨ፡፡
አሳቡን ለማቆም ይችል ይመስል ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ጥብቅ አድርጎ ያዘ፡፡ ሆኖም በአሳብ ነጎደ እንጂ ከተጨበጠ ውሳኔ ይ ሊደርስ አልቻለም:: ጭንቀቱ እየጐላ ሄደ:: ጭንቅላቱ በእሳት ተያይዞ የሚቃጠል መሰለው::
ወደ መስኮቱ ሄዶ መስኮቱን በኃይል ከፈተው:: ሰማይ ላይ አንዲት ኮኮብ እንኳን አትታይም:: ተመልሶ እንደበፊቱ ጭንቅላቱን ይዞ ተቀመጠ፡፡ አንድ ሰዓት አለፈ::
ቀስ በቀስ አሳብ ተሰብስቦ ወደ አንድ ውሳኔ አመራ:: እኚያ ካህን
የገቡበትን ወጥመድ በጉልህ ለማየት ቻለ:: ከቅዠት ዓለም የነቃ መሰለው:: እኚህ ሰው የእርሱን ጦስ፣ የእርሱን እዳ ተሸክመው በአሳብ አያቸው::
እርሱ መግባት ከነበረበት አዘቅት ውስጥ ሊጣሉ ተመለከታቸው፡፡ ከዚያ የመከራ አዘቅት ውስጥ እንዳይገቡ አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት አመነ ይህን ሊያደርግ የሚችል እርሱ ወይም አንድ ሌላ ሰው መሆን ይኖርበታል::
ግን ከእርሱ ሌላ ማነው ይህን ለመፈጸም የሚችለው?
ነገር ተምታታበት፤ የሚችለው ጉዳይ አልሆነም፡፡ ተጨነቀ፤ ተጠበቡ::አንጎሉ በጭንቀትና በአሳብ ብዛት ሊፈነዳ ሆነ፡፡ ማንም ሰው ቢሆን ከዚያ
በፊት ከእንደዚያ ያለ ፈተና ውስጥ የገባ አልመሰለውም:: ሕሊናው
አሳደደው፤ እረፍት ነሳው:: «ማሽላ እያረረ ይስቃልና» የፌዝ ሳቅ ሳቀ::
በችኮላ መብራቱን እንደገና አበራው::
«ታዲያ፣ ምን ይጠበስ!» አለ። «ምን አርበተበተኝ? ምንስ አስጨነቀኝ? እኔ እንደሆነ ምንም አልሆንኩም:: ነገሩ ከፍጻሜ ደርሷል:: አንድ ግለሰብ
በደል ቢሠራ ጥፋቱ የእኔ አይደል! እኔ እንደሆነ ክብር ያለኝ ሰው ነኝ:: ይህ የፈጣሪ ሥራ ነው:: የእርሱ ፈቃድ ይህ ከሆነ እኔ ምን አገባኝ! እርሱ አስተካክሉ የቀየሰውን እኔ ማፍረስ እችላለሁ! ታዲያ ምን ጥልቅ አደረገኝ? አያገባኝም:: በሕይወቴ ዘመን በሕልሜም በውኔም የተመኘሁት ነገር ቢኖር
የኑሮ ዋስትና ነበር፡፡ የአምላክ ፈቃድ ሆኖ ያንን አግኝቻለሁ:: ይህን በአምላክ ፈቃድ ያገኘሁትን የኑሮ ዋስትና ማበላሸት የለብኝም:: ታዲያ ለምንድነው የጀመርኩትን እንዳልቀጥል፣ ለሰዎች በጎ ተግባር እንዳልፈጽም፣ ለሌሎች ሰዎች አርአያ እንዳልሆንና የአሳለፍኩት የረጅም ዘመን ስቃይ
ውጤት ደስታ እንዳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆነው? ለማንኛውም
ያለቀ ጉዳይ ነው:: በእግዚአብሔር ሥራ እኔ ልገባ አልችልም::»
ተጨባጭ የሆነ መፍትሔ ሲያጣ ከመቀመጫው ብድግ ብሎ ክፍሉ
ውስጥ ተንቆራጠጠ፡፡ ና ወዳጄ ፣ ከዚህ ይበልጥ ራስህን አታሰቃይ» አለ እርሱ በራሱ ሲነጋገር፡፡ ሆኖም የመንፈስ እረፍት ሊያገኝ አልቻለም፡፡እንዲያውም ከነአካቴው ከመጠን በላይ ተጨነቀ፡፡ የጭንቀቱም ውጤት
ብስጭት ሆነ፡፡
ማንም ሰው ቢሆን የባህርን ውሃ ወደ ዳር እንዳይወጣ ለማገድ
እንደማይችል ሁሉ አእምሮውም ውስጥ አሳብ እንዳይገባ ለመከልከል አይችልም፡፡ በኃይል እየገፋ የሚመጣውን ውሃ ማዕበል እንለዋለን፡፡ ወንጀል ተሠርቶ የሚደርሰውን ሰቆቃና ጭንቀት ደግሞ የሕሊና ወቀሳ እንለዋለን፡፡
ተፈጥሮ ነፍስን ውሃን በልዩ ጥበቡ ወደታችና ወደላይ ያነጥራቸዋል፡፡
ጊዜው እያለፈ ሲሄድ እርስ በራሱ መነጋገሩን ቀጥሎ ተናጋሪም
ሰሚም ራሱ ሆነ፡፡ ግን በጣም የሚያስገርመው የሚናገረው ለመስማት የማይፈልገውን ሲሆን ለመናገር አፉን የሚከፍተው ደግሞ ከምንም ጊዜ
ይበልጥ ፀጥታ በፈለገስት ወቅት ነበር፡፡
«ይህ ሰው በዚያን ጊዜ የት ነበር? ይሄ ያለቀለት ጉዳይ አይደለም?»

#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
....“ራስህ ነህ፤ አዎ: ግን እንዴት?” አልሁት መኪናዉን የቤተመንግሥት ታርጋ እንዳየሁበት አስታዉሼ። ለነገሩ ባልቻ የማያልፍበት ምን የመርፌ ቀዳዳ አለና ነዉ? ልክ ወደ መዉጫዉ በር ስንቃረብ፣
መኪናዉን ድንገት ሲጢጥ አድርጎ አቆመዉ።
"አይሆንም በዚህ መልኩ መዉጣት አንችልም። ይኸኔእኮ በሩ ተከርችሞ ወታደሮችም በጥፍሮቻቸዉ ቆመዉ እየጠበቁሽ ይሆናል: ኮሎኔሉ ሳይቀር መሬቱን እየጠለዘ በመንቆራጠጥ ላይ ነዉ የሚሆነዉ።ምክንያቱም ከግብጽ ትሆኚ ከኤርትራ፣ አሸባሪ ትሆኚ ተገዳዳሪ፤ ምንነትሽን እንኳ ን በቅጡ ያላወቁሽ አንቺ ከእጃቸዉ ስላመለጥሽባቸዉ እታሰስሽ ነዉ የምትሆኝዉ: ስለዚህ በየትኛዉም በር መዉጣት አንችልም ደኅነት እና ወታደር ሁሉ ተነስንሶ እያፈላለገሽ ከሆነ ደግሞ አስቢዉ፣ግቢም ደግሞ መቆየት አንችልም: አጣብቂኝ ዉስጥ ነን”
አለኝ፣ እንደ መረታት ብሎ።
“እንዲህ ብናደርግስ?” አልሁት፣ ሰዓቱን እንዲመለከት እየጠቆምሁት።
“በመርሐ ግብሩ መሠረት፣ በአዳራሽ የነበሩት እንግዶች መዉጫቸዉ ነዉ: በእርግጥ አልፏል: የፈለገ በየሰበቡ አንዛዝተዉ ቢያቆዩአቸዉ
እንኳን፣ መዉጣታቸዉ ግን አይቀርም: መቼሰ እዚሁ አያሳድሯቸዉ።ይወጣሉ። እነሱ እስከሚወጡ ድረስ ጠብቀን በየመኪናቸዉ ተከታትለዉ
ሲወጡ እኛም ተደባልቀን መዉጣት እንችላለ”
“ፍተሻዉ ቀላል ይሆናል ብለሽ ነዉ?” አለ የመኪናዉን መብራቶች
አጠፋፍቶ በዝግታ ወደ ተነሳንበት ቦታ ወደ ኋላ እያሽከረከረ ወደ ሰፊዉ የመኪና ማቆሚያ ተመልሰን ልክ ከመቆማችን፣ የጋቢናዉ በር ተንኳኳ።
ስአሊ ለነ! መኪና ማቆሚያዉ ጠባቂ እንዳለዉ እንዴት አልገመትንም?እንኳንስ የቤተ መንግሥቱ ተራ የመንገድ ዳር መኪኖችስ ጠባቂ አላቸዉ
አይደል እንዴ? ቀሽሞች ነን! የኔስ እሺ፣ ባልቻ እንዴት ልብ አላለዉም
ይኼን?
ጋቢናዉ በድጋሚ ተንኳኳ
“አቤት?” አለ ባልቻ እኔን ወንበር ሥር እንድደበቅ በዳበሳ ምልክት
ከሰጠኝ በኋላ፣ መስታዎቱን ዝቅ አድርጎ፡
“ችግር አለ?” አለ ጠባቂዉ፣ በትሕትና
“እህህ” ብሎ የማስመሰል ሳቅ አስቀደመ፣ ባልቻ። “እህህ… ያዉ
ታዉቀዉ የለ የኛን ሥራ? አለቆቼ አድ ቦታ ላኩኝና እየወጣሁ ሳለ ደግሞ እንደገና እንድተወዉ ደዉለዉልኝ ነዉ እንጂ ችግር የለም: የማደርሳቸዉ እንግዶች ሳይኖሩ አይቀርም”
“አይደል? ተደዉሎልህ?” አለ ሰዉዬዉ ልብ በሚወጋ ስላቅ።
ወዲያዉኑ በአቅራቢያ የሚያልፉ ኹለት ወታደሮችን አፏጨላቸዉ።
እየበረሩ እንደ መጡ ኮቴያቸዉ ነግሮኛል።
“ይቅርታ ጌቶቼ፣ የሚያጠራጥር ነገር ካለ አሳዉቅ ተብዬ ነበር። መቼም ሰዉ ያለ ምክንያት መብራት አጥፍቶ ወደ ኋላ አይነዳም: ምናልባት
የምትፈልጉት ዓይነት ሰዉ እንደሆነ ብዬ ነዉ” አላቸዉ፣ ወደ ባልቻ እየጠቆመ። መሣሪያቸዉን አነጣጥረዉ ከመኪናዉ በቀስታ እንዲወርድ አዘዙት።
“እንዳትሳሳቱ፣ እኔ ተራ ሹፌር ነኝ: ከዚህ ሁሉ ለምን ጉቦዳን
አትጠይቁትም?”
ምን አስቦ እንደሆነ ባይገባኝም፣ አመላለሱ ግን ሆነ ብሎ ጥርጣሬያቸዉን የሚያጎላ ነዉ ምክንያቱም ገና አንድ ጥያቄ እንኳን ሳይጠይቁት፣
በዉስብስብ ጥያቄዎች እንዳስመረሩት ሁሉ መቀለማመዱ ከባልቻ የሚጠበቅ አይደለም: እንዲያዉም እሱ ራሱ “ጅል ለስለላ ሄዶ ምግብ
ቢያቀርቡለት ስለላ ላይ ነኝ ብሎአረፈዉ” ብሎ በተልካሻ የመረጃ አነፍናፊዎች ሲስቅ ሰምቼዋለሁ። የእሱ የተቻኮለ መልስ ግን ከጅሉ በላይ
ቢብስ እንጂ አይተናነስም
“ጉቦዳን ጠይቁት”
“ማነዉ ደግሞ ጉቦዳ?”
“ጉቦዳ የመኪና ስምሪት ኃላፊዉ ነዋ: አታዉቁትም? ጉቦዳ ?”
“ና ቅደም እስኪ ለማንኛዉም” ብለዉ ወሰዱት እርስ በእርስ ትንሽ
ከተመካከሩ በኋላ።
እኔን ማንም ሳያየኝ መኪና ዉስጥ ቀረሁ አሁን ሐሳቡ የገባኝ መሰለኝ፡ ኹለታችንም ከምንያዝ፣ እኔን አትርፎ ራሱን ማጋለጡ ነዉ። ባልቻ አይደል ሰዉዬዉ? መhራዬን መዉሰድ ያዉቅበት የለ? መንገድ አብረን እየሄድን ድንገት ጋሬጣ ሲያደናቅፈኝ ‹እኔን ባዩ ሰዉ! ለማለቱማ ማንም ሰዉ ይለኝ ይሆናል፣ ከልቡ መሆኑን ግን ከእሱ በቀር የማምነዉ ማን
አለኝ? ከእናቴ ቀጥሎ ከሰዉ ማንም እንደሱ የለም ባልቻ ብቻ!
ባልቻን በወሰዱበት መንገድ አፍጥጬ እንባ እያፈሰስሁ ለደቂቃዎች በድንዛዜ ቆየሁ ከዚያ እንደ ምንም እንባዬን ጠራርጌ ዓይነ ልቡናዬን እንዲያበራልኝ አጭር ጸሎት ማድረስ ስጀምር፣ በርከት ያለ ድምፅ ሰማሁ። እንግዶች መዉጣት ጀምረዋል። አሁን የዕቅድ ለዉጥ አድርጌም
ቢሆን ከዚህ ግቢ ቶሎ ማምለጥ አለብኝ፡ እንዴት? መቼም እንግዶቹ
ሲወጡ በር ላይ ጠበቅ ያለ ፍተሻ መኖሩ የማይቀር ነዉ። ያን ጊዜ
ትኩረቱ ሁሉ ወደ በሩ ይሆናል ማለት ነዉ፡ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ እኔ በአጥር መዝለል እችላለሁ፡ በእርግጥ እንኳንስ በአጥሩ መዝለል ይቅርና፣ አጥሩ አጠገብ መድረሱ በራሱ ዋዛ እንደማይሆንልኝ አልጠፋኝም: ነገር ግን ከጥበቃ ማማዎች ወደሚቀርበኝ ቃኚ ወታደር መስዬ እያዘናጋሁ እቀርበዉና ያቺን የሰመመን መርዝ ጠቅ አደርግበታለሁ። ይወድቅልኝ
የለ? ያን ጊዜ ከራሱ ማማ እመር ብዬ ወደ ዉጪ እዘላለሁ፡ ምናልባት በግራና በቀኝ በኩል ባሉ ማማዎች ያሉ ወታደሮች ቢተኩሱብኝ ነዉ ቢሆንም ግን የመጨረሻዉ ቀላል ማምለጫ ይኼ ብቻ ነዉ ሌላ አልታየኝም:
ያቀድሁት ሁሉ ሰምሮልኝ ዘልዬ ወደ ዉጪ ከመዉደቄ እንደ ጠበቅሁት የተኩስ እሩምታ ይዘንብብኝ ጀመር። እየተንከባለልሁ ወደ ዋናዉ ጎዳና
ስወርድ፣ ማንነቱ የማይታይ ሰዉ አንዲት ሚኒባስ ታክሲ እያበረረ
አጠገቤ አድርሶ በሯን ከፈተልኝ፡ የሲራክ፯ አባላትን የምታግባባዋን
የመኪና ጥሩምባ ቀድሞ ስለነፋልኝ፣ ለእኔ የመጣ መሆኑን አወቅሁና ሳላቅማማ ተወርዉሬ ገባሁባት ነዳጁን ረግጦ ከግቢ ገብርኤል በታች ወዳለዉ የመንደር መንገድ ወሰደኝ።
አመለጥሁ።
ከቤተ መንግሥቱ መራቃችንን ሲያዉቅ፣ ሹፌሩ የመኪናዉን የዉስጥ መብራት አብርቶ በድል አድራጊነት አየኝ፡ አየሁት።
“አ-ባ-ቴ?!” ብዬ በጩኸት አቀለጥሁት ባልቻ ነዉ። በምን ተአምር እንዳመለጠ ልጠይቀዉ ወይስ ዝም ብዬ ከአንበሳ ጉሮሮም ቢሆን የሚያተርፈንን አምላክ ላመስግን? ቸገረኝ እኮ፡ ሰአሊ ለነ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ባልቻ ነዋ ሰዉዬዉ! እንዴት አያመልጥ?” ሲል አቋረጠኝ፣ ቢራራ እኔም ልክ አሁን የሆነ ያህል ነበር በስሜት ያጫወትሁት።
በዚህ እና ከዚህ በባሱ መዐት ሞቶች መካከል አልፌ የማዉቀዋ እኔ፣ ዛሬ ግን ፈራሁ። እዉነትስ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ የሚለዉ አባባል ይመለከተኛል? በጭራሽ! በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አልፏል።
“እንግዲያዉ ለምን ፈራሁ አሁን? አንተ እስክትሳለቅብኝ ድረስ ለምን
ተንቀጠቀጥሁ?”
“ይኼን ስትነግሪኝ ምን እንደመጣብኝ ታዉቂያለሽ?ስለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጴጥሮስ ያነበብሁት አንድ ምዕራፍ” አለ፣ በሞባይሉ መጽሐፍ ቅዱስ እየከፈተ። የሚፈልገዉን ምዕራፍ ሲያገኘዉ፤ “ከዚህ ጀምረሽ
አንብቢዉማ” ብሎ ሞባይሉን አቀበለኝ። ታሪኩ ጌታችን ኹለት ዓሣ እና አምስት እንጀራ አበርክቶ ሕጻናቱንና ሴቶቹን ሳይጨምር አምስት ሺ ወንዶችን ያጠገበ ዕለት፤ ሌሊቱን የሆነ ነዉ።

#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
በማውንት እስቨርን ኧርል ዕረፍትና ቀብር መካከል የነበረው ጋዜ ውስጥ ሁኔታዎች ቶሎ ቶሎ ተከታተሉ " አንባቢ ከነዚህ ሁኔታዎች አንዱን ከእውነተኛ
ሕይወት ጋር የማይዛመድና መሠረት የሌለው ነገር ነው ይል ይሆናል ካለ ስሕተት ነው " ሁኔታዎቹ ደርሰው ታይተዋል "
ዊልያም ቬን ዓርብ ጥዋት ንጋት ላይ ዐረፈ " ወሬው ወዲያው ተዛመተ ትልቅ ሰው ሲሞት ምን ጊዜም ይኸው ነው የዚያኑለት ለንደን ላይ ተሰማ " ስለዚ ሟቹ በሕይወት ቢኖር ኖሮ «መንቻኮች» ይላቸው የነበሩት ብዙ ሰዎች ኢስት ሊንን ለመክበብ ቅዳሜ ማለዳ ደረሱ የጥቂት ገንዘብ ባለዕዳዎችም የብዙ ገንዘብ ባለዕዳዎችም ነበሩባቸው " ከአምስት እስከ ዐሥር ፓውንድ የሚጠይቁ ' ከአምስት እስከ አሥር ሺ የሚፈልጉም ሁሉ ነበሩባቸው አንዳንዶቹ ሰላማዊ ሰዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ትዕግሥት የሌላቸው አንዳንዶቹ ለፍላፊዎች ሥነ ሥርዓት
የሌላቸውና ቁጡዎች ሌሎች ደግሞ እዚያው ላይ እርምጃ ለመውሰድ አንዳንዶቹ አስከሬኑን በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ የመጡ ነበሩ።
የመጨረሻው ድርጊት በዘዴ ነበር የተፈጸመው " ሁለት አፍንጫ ቈልማማ ሰዎች ከግርግሩና ከሽብሩ ሹልክ ብለው በጓሮ በር አለፉና ሲደውሉ አንዲት የማድ ቤት ሠራተኛ ከፈተችላቸው።
« የሬሳው ሳጥን ገና አልመጣም እንዴ ? » አሉ
« የሬሳ ሳጥን ? የለም ሚስተር ጆንስ ከሦስት በፊት እመጣለሁ አላለም "አሁን ገና ሁለት ሰዓት እንኳን አልሞላም » አለቻቸው።
« እሱስ አሁን ይዶርሳል እመንገድ ላይ ነው " ስለዚህ ወደ ክቡርነታቸው ክፍል አቅንተን አስከሬኑን እያዘጋጀን እንቆያለን » አሏት ሠራተኛዋ የቢት አዛዡን ጠርታ « ከቀብር አስፈጻሚው ከጆንስ ዘንድ የመጡ ሁለት ሰዎች ሳጥኑ እስኪደርስ ከላይ ወጥው ሬሳውን አሰናድተው ለመቆየት ይፈልጋሉ » አለችው ።
አዛዡም ሰዎቹን እየመራ ወስዶ አስከሬኑ ከነበረበት ክፍል ካስገባቸው በኋላ
« ይበቃሃል » አሉት አብሮ ለመግባት ሲል «እዚህ በመቆየት አናስቸግርህም » ሲሉት ምንም ሳይጠረጥር ወጣላቸው ። እነሱም ክፍሉን ዘግተው ከሬሳው ግራና
ቀኝ ተቀምጠው ሲያበቁ ጥያቄያቸው ካልተሟላ በቀር ሬሳውን እንዶማይለቁ አስ
ታወቁ ከአንድ ሰዓት በኋላ ( ሳቤላ ከክፍሏ ወጥታ ምንም ድምፅ ሳታሰማ ያባቷ ሬሳ ካረፈበት ክፍል ስትገባ ሁለት የማይታወቁና የሚቀፉ ሰዎች ባጠገቡ ተቀምጠው ስታገኛቸው ጊዜ ክው ብላ ደነገጠች "
መጀመሪያ ነገሩ ተገቢ ባይሆንም እንኳን'ለወሬ የቸኮሉና ሁኔታውን ለማየት የጓጉ የመንደር ሰዎች መስለዋት ነበር " ቢሆንም ትክክለኛውን ነገር ከነሱ አግኝታ ለማረጋገጥ ፈለገችና « እዚህ የምትፈልጉት ነገር አላችሁ ? » አለቻቸው "
« ስለ ጠየቅሺን እናመሰግናለን " እመቤት ) ደኅና ነን ምንም አትቸገሪ » አሏት " ሥራቸውም አነጋገራቸውም ፍጹም ያልተለመደና ያልተጠበቀ ሆነባት
ጨነቃት » ይህን ተናግረው ቢደነግጡም የወግ ነበር ከዚያ ገብተው ቁጭ ለማለት መብትና ሥልጣን ያገኙ ይመስል ተደላድለው እንደ ተቀመጡ ዝም አሉ።
« እዚሀ ምን አመጣችሁ ? ምን እያደረጋችሁ ነው ? » አለቻቸው።
« እንደ መሰለን አንች ልጃቸው ነሽ ብንነግርሺም ግድ የለንም » አላት
አንደኛው በግራ አውራ ጣቱ በስተኋላው ወደነበረው አስከሬን የኋሊት እያመለከተ"
« ባጠገባቸው ሌላ የቅርብ ዘመድ እንዶሌላቸው ስምተናል አሁን እኛ እዚህ የመጣነው በጣም ብዙ ዕዳ ስለ ነበረባቸው ገንዘባቸውን ያላገኙ አበዳሪዎቻቸው መሞታቸውን ሲሰሙ ሬሳውን በዕዳ መያዣ እንድናስከብር ቀጥረው ልከውን ነው » አላት
ድንጋጤና ፍርሃት በአስጨናቂው መከራዋ ላይ ተደምረው የምትለውን አስጠፋት » እንደዚያ ያለ ጉድ ሰምታ አታውቅም » ብታውቅም አታምንም ነበር "
ሬሳን በእስረኝነት መያዝ ? ምን ለማድረግ » ቁና ቁና እየተነፈሰች ከክፍሉ ወጥታ ስትወርድ ሚሲዝ ሜዞንን ከደረጃው ስታልፍ አኘቻትና በሁለት እጆቿ ጥምጥም
አድርጋ ይዛ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ራሷን መቈጣጠር አልቻለችም አስተካክላ መናገርም አልሆነላትም።
« እነዚያ ሰዎች እዚያ ! » አለች እየቃተተች "
« የምን ሰዎች ናቸው . . . የኔ እመቤት ? »
« ኧረ እኔስ እንጃ ! ኧረ እኔስ እንጃ ! ከዚያ የሚወጡም አልመሰሉኝም አባባን በዕዳ ይዘነዋል ይላሉ። የቤት ጠባቂዋም ነገሩ አስገርሟት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ሁኔታውን በዐይኗ ለማየት ሔደች " ሳቤላ ግን ከዚያ ለመነቃነቅ ፈራች ሰውነቷ ዛለባት ከደረጃው መደገፊያዎች ላይ ተደግፋ ብቻዋን ቀረች ሁኔታው ደስ
የማይል ሌላ ብጥብጥ በምድር ቤት በኩል ሰማች » ማንነታቸው ያልታወቁ እንዲያውም ከማያገባቸው ገብተው ነገር የሚያዳንቁ ሰዎች ከምድር ቤቱ አዳራሽ ዘልቀው ሲያማርሩ ' ሲፎክሩ ሲደነፉ ተሰማት ፍራቷ እየጨመረ መጣ " በደንብ ለማዳመጥ ትንፋሿን ያዝ አደረገች።
« ይህች ልጅ ከናንተ ፊት ብትቀርብ ጥቅማችሁ ምንድነው ? እሷ ስለ አባቷ
ጉዳዮች ምን ታውቃለች ? አሁን ለራሷ በከባድ ኀዘን ላይ እያለች በተጨማሪ ባታስጨንቋት ምናለበት ? » እያለ የቤት አዛዡ ሲያነጋግራቸው ከጆሮዋ ገባ "
« የፈለገው ይምጣ እሷን ማየት አለብኝ » ይላል አንድ ችክ ያለ ድምፅ «እዚሀ ድረስ ወርዳ አንድ ሁለት ጥያቄዎች ለመመለስ ክብሯ የሚዋረድ ከሆነ
ካለችበት ድረስ በግድ እገባለሁ " ገንዘባችን የተጭበረበረብን ምስኪኖች ከዚች ልጅ በቀር ልናነጋግረው የምንችል ማንም እንደሌለ እየተነገረን ከነሷው ደግሞ አታስቸግሯት ለምን ትሉናላችሁ ? ገንዘባችንን ለማጫረስ አባቷን ስትረዳ ግን አልተቸገረችም " እዚህ ድረስ መጥታ ልታነጋግረን ካልፈቀደች የሴት ወይዘሮ ስሜትም
ክብርም የላትም »
ስሜቷን አምቃ ይዛ ደረጃዎቹን ወረዶችና የቤቱን አዛዥ ወደሷ ጠራችው "
« ምንድነው ይህ ሁሉ ሽብር ? ማወቅ እፈልጋለሁ " »
« ተይ እመቤቴ አትሒጂ " ሥነ ሥርዓት የላቸውም ያንቺ ከመኻከላቸው መገኘት የሚያስታግሣቸው አይደሉም ። እኔ ለሚስተር ካርላይል ስለ ላክሁባቸው አሁን ይመጣሉ ስለዚህ አንቺ እነዚህ ሰዎች ሳያዩሽ ግቢ » አላት።
« ግን አባባ ከነዚህ ሁሉ ገንዘብ ወስዷል ማለት ነው? »
« አዎን ሳይወስዱ የቀሩ አይመስለኝም » አላት።
ሳቤላ ቀጥታ ወደነሱ ሔዴች ከመተላለፊያው ተበታትነው የነበሩትን 0ልፋ ብዙዎቹ ተሰብስበው ከቆሙበት ጩኸትና ጫጫታ ከበዛበት ከምግብ ቤት
ገባች " ሁሉም ሲያዩዋት ጸጥ አሉ የሚያምር የጧት ልብስ ለብሳ፡ ቆንጆው ፊቷ በተዘናፈለው ጸጉሯ ተጋርዶ ሲያዩዋት በዚያ ሁኔታቸው ከነሱ ጋር መልስ ልትለዋወጥ
ቀርቶ ጕዳዬም ሊገባት የማይችል ምንም ነግር የማታውቅ ገና ልጅ አድርገው ገመቷት " በደላቸውን የብሶታቸውን ያሀል በመዘርዘር ፋንታ ሁሉም ጸጥ አሉ።
« አንድ ሰው እኔን ለማየት እንደሚፈልግ ሲናገር ስምቸ ነበር» አለች ንግግሯ እየተቆራረጠ « ከኔ ምን ትፈልጋላችሁ? » ሁሉም ረጋ ባለ አነጋግር የየራሱን ጉዳይ ሰነዘረ ። እስኪያጥወለሡላት ድረስ በጥምና አዳመጠቻቸው " ብዙ የከፍተኛ ገንዘብ ጥያቄዎች ቀረቡ ። በተወሰነ ጊዜ
የሚመለስ የብድር ሰነዶች ባለዕዳነት መተማመኛዎች የጊዜ ገደባቸው ያለፈና ያልደረሰ ሒሳቦች ፡ በጠቅላላው ለቤት ጣጣ ለአሽከች የደንብ ልብስ ለውጭ ከትልቅ እስከ ትንሽ ይህ ነው የማይባል ብዙ ብዙ ዕዳ
አሽከሮች ደሞዝ ተዘረዘረ ።

#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...ለመሄድ እየተነሳች "አሁን መሄዴ ነው"ስትል መንትዮቹ ተላቀሱ
“እማዬ አትሂጂ! አትተይን! ሁለቱም በትናንሽ ክንዶቻቸው እግሮቿ ላይ ተጠመጠሙ: ወደ እኔ እየተመለከተች “የምችለውን እንደማደርግ ቃል እገባለሁ እናንተ መውጣት የምትፈልጉትን ያህል እኔም ከዚህ ቤት እንድትወጡ እፈልጋለሁ:"
በሩ ጋ ስትደርስ የቆሰለ ጀርባዋን ማየታችን ምን ያህል አያታችን ጨካኝ እንደሆነች እንድናውቅ ስለሚያደርገን ጥሩ መሆኑን ነገረችን፡ “ስለእግዚአብሔር
ህጎቿን ጠብቁ: መታጠቢያ ቤት ስትጠቀሙ ስርአት ይኑራችሁ። ክፉ የምትሆነው ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእኔ ለሆኑት ሁሉ እንደሆነ አስታውሱ”አለች ከዚያ ለሁላችንም ክንዶቿን ዘረጋችልንና ሁላችንም ወደ እሷ ሮጥንና
አቀፍናት። “ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ:” ስትል ተንሰቀሰቀች። “ይሄንን ልብ በሉ… እምላለሁ ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ ሁኔታ ምን ያህል እንደምወዳችሁ አሳያችኋለሁ፡ እኔም ልክ እናንተ የሆናችሁትን ያህል እስረኛ ነኝ። ልክ እናንተ በሁኔታዎች እንደተጠመዳችሁት እኔም እንደዚያው ነኝ። ዛሬ ማታ ደስ የሚል ሀሳብ እያሰባችሁ ወደ መኝታችሁ ሂዱ። ምንም ያህል መጥፎ ቢመስልም እንኳን ሁሉም ነገር ያን ያህል መጥፎ አይደለም።
ተወዳጅ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። አንድ ወቅት ላይ አባቴ እጅግ በጣም ይወደኝ ነበር፡ ያ እንደገና እኔን የመውደዱን ነገር ቀላል ያደርግለታል ብዬ አስባለሁ፤ አይደል እንዴ?” አለችን።
አዎ አዎ ያደርግላታል።
“እኔ ነገ እዚያ ትምህርት ቤት ከገባሁ በኋላ እዚህ ክፍል ውስጥ ለሰዓታት ስትቀመጡ እንዳይሰለቻችሁና ደስተኞች እንድትሆኑ ወደ ሱቅ እሄድና አዳዲስ አሻንጉሊቶችና መጫወቻዎች ገዝቼላችሁ እንደምመጣ አስታውሱ፡ አባቴ
እንደገና እንዲወደኝና ስለሁሉም ነገር ይቅርታ እንዲያደርግልኝ ለማድረግ ብዙ ጊዜ አይወስድብኝም:”
“እማዬ… ግን ለእኛ መጫወቻ ለመግዛት የሚሆን በቂ ገንዘብ አለሽ?” አልኳት
“አዎ” አለች በፍጥነት። “በቂ ገንዘብ አለኝ፡ አባቴና እናቴ ኩሩ ሰዎች ናቸው በጓደኞቻቸውና በጎረቤቶቻቸው ፊት አንሼም ሆነ የቆሸሸ ለብሼ እንድታይ
አይፈልጉም፡ ስለዚህ ገንዘብ ይሰጡኛል፡ እኔ ደግሞ ለእናንተ መጫወቻ እገዛላችኋለሁ: የሚተርፈኝን እያንዳንዱን ደቂቃና ያልተጠቀምኩበትን እያንዳንዱን ብር አስቀምጠውና በፊት እንደነበርነው የራሳችን ቤት ሲኖረንና እንደገና አንድ ቤተሰብ ስንሆን እንድንጠቀምበት እቅድ አወጣለሁ።አለች
እነዚህ ከመውጣቷ በፊት የነገረችን ቃላቶች ነበሩ: ከዚያ በሩን ዘጋችና ቆለፈችው: ከተቆለፈ በር ጀርባ ሁለተኛ ምሽታችን ነበር።
አሁን ብዙ ነገር አውቀናል ... ምናልባትም በጣም ብዙ።
እናታችን ከሄደች በኋላ እኔና ክሪስ ሁለታችንም አልጋዎቻችን ውስጥ ገባን::ክሪስ አይኖቹ በእንቅልፍ እንደተዳከሙ ወደ እኔ ዞሮ አይኖቹን እየጨፈነ “ደህና እደሪ ካቲ ቁንጮቹ እንዳይበሉሽ አድርጊ: ብሎ አጉረመረመ።
ክሪስቶፈር ከተኛ በኋላ እኔም የኬሪን ትንሽዬና ሞቃት ሰውነት እቅፍ አድርጌና ፊቴን ወደ ለስላሳው ፀጉሯ ዝቅ አድርጌ ተኛሁ።
እንቅልፍ ሊወስደኝ ስላልቻለ ወዲያው በጀርባዬ ተኛሁና ወደ ላይ አፈጠጥኩ::እዚህ ግዙፍ ቤት ውስጥ ያለው ፀጥታ ተሰማኝ በግዙፉ ቤት ውስጥ ከሩቅ
የሚሰማ የስልክ ጥሪ ወይም ደግሞ የወጥ ቤት ዕቃዎች መንኳኳት ድምፅም ሆነ ምንም አይነት እንቅስቃሴም የለም ከውጪ ውሻ እንኳን ሲጮህ ወይም መኪና ሲያልፍ ድንገት ብልጭ የሚያረገው መብራት እንኳን በትልልቆቹ መጋረጃዎች አልፎ አይታይም።
የማንፈለግ፣ የተቆለፈብን.. ከሰይጣን የተፈለፈልን መሆናችንን የሚነግረኝ መጥፎ ሀሳብ መጣብኝ፡ ሀሳቦቹ በጭንቅላቴ እየተመላለሱ አበሳጩኝ።
ከጭንቅላቴ ለማስወጣት የሆነ
መንገድ መፈለግ አለብኝ፡ እናታችን ትወደናለች…ትፈልገናለች ጥሩ ፀሀፊ ለመሆን እየሞከረች ነው: አያቶቻችን ከእኛ ሊያርቋት የሚፈልጉበትን መንገድ እንደምትቋቋም አምናለሁ።
“እባክህ እግዚአብሔር እማዬ ፈጥና እንድትማር እርዳት” ብዬ ፀለይኩ ክፍሉ በጣም የሚሞቅና የሚያስጨንቅ ነው: ውጪ ንፋሱ ቅጠሎችን ሲያንቀሳቅስ ይሰማኛል ግን እዚህ ገብቶ እኛን ለማቀዝቀዝ አልቻለም የንፋሱ ድምፅ ውጪው ቀዝቃዛ እንደሆነ እና እኛም መስኮቶቹን መክፈት ብንችል ወደ ውስጥ መግባት እንደሚችል እየነገረን ነው: ንፁህ አየር በመናፈቅና በመመኘት
ተነፈስኩ። ተራራማ ቦታ በበጋም ጭምር ሁልጊዜ ቀዝቃዛ እንደሆነ እናታችን ነግራን አልነበረም? አሁን እኮ በጋ ነው ግን መስኮቶቹ ሁሉ ስለተዘጋጉ አይቀዘቅዝም:
በደብዛዛው ብርሃን ክሪስ በሹክሹክታ ጠራኝና “ምን እያሰብሽ ነው?” አለኝ።
“ስለ ንፋሱ” አልኩት
“እንደዚያ አይነት ሀሳብ እንደምታስቢ አውቃለሁ"
“ሌላም ሀሳብ አለኝ የሚያንሾካሹኩት ነፍሳት እንደሞቱ ሰዎች ነፍሶች የሆነ ነገር ሊነግሩን እየሞከሩ ነው:"
ተናደደ “አሁን አድምጪኝ ካተሪን ዶል (አንድ ቀን እንደምጠቀምበት
ያቀድኩት ስም ነው፡) ተኝተሽ አስፈሪ አሳቦችን ከማሰብ፣ እያንዳንዱን ሰዓት እንዳመጣጡ እንውሰደውና የሚቀጥለውን ለማሰብ ቆም እንበል። ይህንን ዘዴ
መጠቀም በቀናትና በሳምንታት ከማሰብ እጅግ የሚቀል ነው ስለ ሙዚቃ፣ስለ ዳንስና ስለ መዝፈን አስቢ ሙዚቃ አእምሮሽ ውስጥ ሲደንስ ሀዘን እንደማይሰማሽ ስትናገሪ ሰምቼ የለ?”
“አንተስ ስለምን ታስባለህ?”
“እንቅልፌ በደንብ ካልመጣ ብዙ አይነት ሀሳቦችን አስባለሁ ግን አሁን እንደምታይኝ መልስ ለመስጠት ደክሞኛል። ለማንኛውም አላማዬን ታውቂዋለሽ ከአሁን ጀምሮ ለመጫወት ጊዜ ስለምናገኝለት ጨዋታ አስባለሁ” አፋሽኮ
ከተንጠራራና ወደ እኔ እያየ ፈገግ ካለ በኋላ “አጎቶች የወንድሞቻቸውን ልጆች አግብተው ስለሚወልዷቸው ሸኮና፣ ጅራትና ቀንዶች ስላሏቸው ልጆች ምን ታስቢያለሽ?”
“እንዴ! ሁሉንም እውቀቶች ፈላጊና የወደፊት ሀኪም አይደለህ እንዴ…
በህክምና ሳይንስ የሚሆን ይመስልሀል?”
“በፍፁም!” መለሰልኝ፡ ልክ በዚያ ርዕስ በደንብ የተማረ ይመስል ነበር። “እንደዚያ ቢሆን ኖሮ አለም ዲያቢሎስን በሚመስሉ ፍጥረታት የተሞላች ትሆን ነበር፡ እና እውነቱን ለመናገር ዲያቢሎስን አንድ ጊዜ ላየው እፈልጋለሁ”
“እኔ ሁልጊዜ በህልሜ አየዋለሁ።”
“አሀ! አንቺና ያበዱ ህልሞችሽ! ግን መንትዮቹ አልገረሙሽም? ያቺን ግድንግድ አያታችንን እንዴት በድፍረት እንደተጋፈጧት… እኔማ በጣም ኮርቼባቸዋለሁ፡ እንደ ንዴቷ. የሆነ የከፋ ነገር ታደርጋለች ብዬ ፈርቼ ነበር።”
“ያደረገችው ነገር የከፋ አይደለም እንዴ? ኬሪን እኮ ፀጉሯን ይዛ ነው
ያንጠለጠለቻት። እንዴት እንደሚያም ባወቅክ… ኮሪን ደግሞ በጥፊ መትታ ጣለችው። ያም ያሳምማል ከዚህ የበለጠ ምን ትፈልጋለች?"
“የከፋ ነገር ማድረግ ትችል ነበር"
“ራሷም እብድ ሳትሆን አትቀርም”
“ልክ ነሽ” እያንቀላፋ ነው፡
“መንትዮቹ ህፃናት ናቸው ኮሪ ኬሪን እየተከላከለ ብቻ ነበር። ታውቃለህ እሱ ስለሷ፣ እሷ ስለሱ እንዴት እንደሚሆኑ?” አመነታሁ። “ክሪስ እናታችንና አባታችን በፍቅር በመውደቃቸው ልክ የሰሩ ይመስልሀል? ለማስቆም የሆነ
ነገር ማደረግ አይችሉም ነበር?”
“አላውቅም: የማይመች ስሜት ስለሚያሳድርብኝ ስለዚያ አናውራ”
“ለዚያ ነው ለካ ሁላችንም ሰማያዊ አይኖችና ወርቃማ ፀጉር የኖረን”
“አዎ” አፋሸከ “የድሬስደን አሻንጉሊቶች እኛ ነን፡”
“ልክ ነህ። ሁልጊዜም ቀኑን ሙሉ መጫወት እፈልግ ነበር። እና አሁን
እናታችን ያንን አዲሱን መጫወቻ ስታመጣልን ቢያንስ ጨዋታውን ለመጨረስ በቂ ጊዜ ይኖረናል።”

#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
...መርከቡን የሚሳፈሩበት ሳውዝ ሃምፕተን ከተማ ሆቴል ውስጥ ወደ ወደቡ የሚወስዳቸውን ታክሲ በድል አድራጊነትና ነፃነት እየጠበቁ ነው፡፡
ሆቴሉ ውስጥ ያለው ሁሉ ዓይኑን ከእሷ ላይ አልነቅል ብሏል፡፡ አንድ ከእሷ አስር አመት የሚያንስ ወጣት ዓይኑን ሳይሰብር ያያታል፡ እሷ ግን እንዲህም አይነት ነገር ዘወትር ስለሚያጋጥማት ለምዳዋለች፡፡ ጥሩ የለበሰች
ጊዜ ይኸው ነው የሚያጋጥማት፡፡ ዛሬ ደግሞ አለባበሷ ልብ ይሰቅላል፡፡
የለበሰችው ቀይ ነጠብጣብ ያለው የበጋ ጊዜ ቀሚሷ ሄዶባታል፡፡ ራሷ ላይ
የደፋችው ኮፍያ ደግሞ ውበት ጨምሮላታል፡፡ ከንፈሯን የተቀባችው
ብርቱካናማ ሊፒስቲክና ጥፍር ቀለሟ ቀሚሷ ላይ ከሚታዩት ነጠብጣቦች ጋር ተጣጥመዋል፡፡ ቀይ ጫማ ለመጫማት አስባ ሴተኛ አዳሪ ያስመስለኛል ብላ ትታዋለች፡፡
መቼም ልብሶቿን በሻንጣ ሸካክፋ መጓዝ ትወዳለች: አዳዲስ ሰው እንድትተዋወቅና አዳዲስ ቦታ እንድትታይ ዕድል ይሰጣታል፡፡ በአይሮፕላን
መሄድ ቢያስፈራትም በዚያኛው አትላንቲክ ዳርቻ ያለችው አሜሪካ መሄድ
ግን ከጉዞዎች ሁሉ አስደሳች ጉዞ በመሆኑ ለብቻው ነው፡፡ ስለአሜሪካ ያላት እውቀት ፊልም ቤት ያየችው ብቻ ነው በአይነ ህሊናዋ መስታወት
በመስታወት የሆነ ቤት፣ ዩኒፎርም የለበሰች የቤት አገልጋይ ፀጉራማ ኮት
ስታለብሳት፣ አንድ ጥቁር ሹፌር ወደ ናይት ክለብ ሊወስዳት ሞተሩ የተነሳ
መኪና ይዞ ሲጠብቃት፣ ናይት ክለብ ቁጭ ብላ የጃዝ ባንድ ሙዚቃ እያየች
ደረቅ ማርቲንዋን ስትጨልጥ ታያት፡፡ ይሄ በምናቧ የሚታያትን አኗኗር
አሜሪካ ሄዳ በእውን ለማግኘት ልቧ ቆሟል፡፡ደ
ጦርነቱ የጀመረ ሰሞን ከእንግሊዝ መሰደድና አለመሰደድ መካከል ልቧ
ይዋልል ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ መሰደድ ቦቅቧቃ ቢያስመስልም መሄዱ ግን አጓጊ ነበር፡፡
ዳያና በርካታ ይሁዳውያንን ታውቃለች፡፡ ማንቼስተር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የይሁዳውያን ማህበረሰብ አለ፡፡ ማንቼስተር ያሉ ይሁዳውያን በአውሮፓ አይሁዳውያን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ በፍርሃትና
በጭንቀት እየተከታተሉ ነው፡፡ ናዚዎችና ፋሺስቶች ይሁዳውያንን ብቻ
ሳይሆን ጂፕሲዎችን፣ ክልሶችንና ለየት ያለውን ሁሉ ይጠሉታል፡፡
ጦርነት ውስጥ የገባችውን አገሯን በወታደርነት ለመታደግ ብትፈልግም
ዕድሜዋ አይፈቅድም ሆኖም ማንቼስተር ቆይታ የቀይ መስቀል የበጎ
አድራጎት አባል ሆና ቁስለኞችን የማከም አስተዋፅኦ ማበርከት ፈልጋ ነበር።
ይህም ቢሆን በሃሳቧ እንጂ በእውን እንደማይሆን አውቃለች፡፡ ነገር ግን
እሷም የልጆች እናት ልትሆን ነው፡፡ በፓን አሜሪካን አይሮፕላን መሄዷን
ስታስበው በደስታ ተፍነከነከች፡፡
ጋዜጣው ስለዚህ በራሪ ጀልባ የፃፈውን ሁሉ ብታነብም እኔም እበርበታለሁ ብላ አልማ አታውቅም ነበር፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ኒውዮርክ
መድረሱ ተዓምር ሆኖባታል፡፡
ቤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለቃ ስትሄድ ለመርቪን ይህን የሚል ደብዳቤ ጽፋ አስቀምጣለች፡፡
‹‹ዉዱ መርቪን ትቼህ ሄጃለሁ ከቀን ወደ ቀን ግግር በረዶነትህ ይለቅሃል
እያልኩ ብጠብቅም አንተ ግን ያው ነህ:፡ ሌላ ሰው አፍቅሬያለሁ፤ ይህን
ደብዳቤ በምታነብበት ጊዜ እኔ አሜሪካ ነኝ፡፡ ልጎዳህ ፈስጌ ባይሆንም
በከፊል ጥፋቱ ያንተ ነው::
ዳያና››
በመጀመሪያ መልዕክቱን በቀላሉ እንዲያገኘው ወረቀቱን መብል ቤት
ጠረጴዛው ላይ ልታስቀምጥለት ፈልጋ ነበር፡፡ ወዲያው ወደ ክለብ የመሄዱን ሃሳብ ለውጦ ወደ ቤት ከተመለሰ ደብዳቤውን ያገኝና ከማርክ ጋር አገር ለቃ ሳትሄድ ችግር ይፈጥር ይሆናል ብላ በመፍራቷ ደብዳቤውን በመስሪያ ቤቱ አድራሻ በፖስታ ላከችለት፡፡ ባሏ ሰዓት አክባሪ እንድትሆን ስጦታ የሰጣትን የእጅ ሰዓቷን ተመለከተች፡፡ የዘወትር ልማዱን ታውቃለች፡፡ ጧት ጧት ማምረቻ ክፍል ይቆይና እኩለ ቀን አካባቢ ቢሮው ገብቶ ለምሳ ከመውጣቱ
በፊት ደብዳቤዎችን ያነባል፡፡ ደብዳቤው ላይ የግል› የሚል ስለፃፈችበት
ጸሐፊው አትከፍተውም፡፡ ይህን ጊዜ ደብዳቤዋ ጠረጴዛው ላይ ካሉት
ደረሰኞች፣ የስራ ትዕዛዞች፣ ደብዳቤዎችና ማስታወሻዎች መሃከል ይሆናል፡፡የጻፈችለትን ደብዳቤ ስታስብ በባሏ ላይ የፈጸመችው ክህደት ህሊናዋን ቢሸነቁጣትም ከእሱ ከሁለት መቶ ኪ.ሜ በላይ በመራቋ በአንጻሩ እረፍት ተሰምቷታል።
‹‹ታክሲው መጣ፣ እንሂድ›› አላት ማርክ፡፡
ጭንቀቷን ዋጥ አድርጋ፣ የቡና ሲኒዋን አስቀምጣ በፈገግታ ብድግ
አለች ‹‹እሺ›› አለች በደስታ ‹‹መብረራችን ነው›› አለች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ሴቶች ፊት ሲሆን ያፍራል፡፡
ከአናፖሊስ የባህር ኃይል አካዳሚ ሲመረቅ የሴት ልጅ እጅ እንኳን ጨብጦ አያውቅም፡፡ ከኮሌጅ ተመርቆ በፐርል ሃርበር ስራ ሲጀምር ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አሸሼ ገዳሜ ማለት ጀመረ። ባህር ኃይል መስሪያ ቤትን ሲለቅ ብቸኝነት ስላጠቃው ጓደኛ ፍለጋ ቡና ቤት መሄድ አዘወተረ፡፡ ካሮል በዚያን ጊዜ ኒውዮርክ በሚገኝ አየር መንገድ ውስጥ በእንግዳ ተቀባይነት
ትሰራ ነበር፡፡ ካሮል ጸጉሯ ቡናማ ሲሆን አይኗ ደግሞ ሰማያዊ ነው፡፡ ኤዲ
እሷን ‹‹ልጋብዝሽ›› ብሎ ለመጠየቅ በፈራ ተባ ብዙ ጊዜ አጠፋ፡፡ አንድ ቀን
አንድ ጓደኛው ቴአትር ቤት መግቢያ ሁለት ቲኬት ሲሰጠው አንዱን ቲኬት
ምን እንደሚያደርገው ሲያስብ ጓደኛው ካሮል አንን አብራው ትገባ እንደሆን
ሲጠይቃት ‹‹እሺ›› አለች፡፡ ኤዲ ባነጋገሯ እንደ እሱው ገጠር አደግ እንደሆነች ተገነዘበ፡፡
ታሪኳን ሲያጠና ብቸኛና ገጠሬ በመሆኗ የከተማ ውጥንቅጥ ስጋት ላይ
የጣላት መሆኑን አወቀ፡፡ ምንም እንኳን በሆዷ ፍላጎት ቢኖርም ወንዶች አፍ አውጥተው እናውጣሽ ብለው ሲጠይቋት በማፈር ታኮርፋለች፡፡ ሰዎች
ይህን እምቢተኛነቷን ስለሚያውቁ አይጠይቋትም፡፡
ኤዲ ይህን ያውቅ ስለነበር ክንዷን ከክንዱ ጋር አቆላልፎ ይንጎራደዳል፡፡
ራት ይጋብዛትና እቤቷ በታክሲ ያደርሳታል፡ ቤቷ ደጃፍ ላይ ቆመው
ስላሳለፉት አስደሳች ምሽት ያመሰግናትና ጉንጮቿን በድፍረት ይስማቸዋል፡፡
እሷም እምባ እየተናነቃት በመላው ኒውዮርክ እንደ እሱ ዓይነት ጨዋ ሰው
እንዳላጋጠማት ትነግረዋለች። እሱ ለሌላ ቀን ቀጠሮ ይጠይቃታል
ቀስ በቀስም ፍቅር ያዘው፡ አንድ ቀን ሊያዝናናት ወደ አንድ ደሴት ይዟት ሄደ፡፡ ከእሱጋ መታየት የሚያኮራት መሆኑን ተገንዝቧል፡፡ የሄዱበት ቦታም አይስክሬም ሲልሱ፣ በሽክርክሪት ሲጫወቱና ፍቅራቸውን ሲለዋወጡ
ዋሉ፡፡ ሽርሽራቸውን ጨርሰው ወደ ቤቷ ሲሸኛት እንደዚህ ቀን ደስ ብሎት
እንደማያውቅ ካንጀቱ ሲነግራት እሷም ‹‹እኔም ደስ ብሎኛል›› አለችው::
ካሮል አን ለፍቶ አዳሪ ደሃ ቤተሰቦቿጋ ወስዳ አስተዋወቀችው፡፡ እነሱን
ሲያይ ቤተሰቦቹ ትዝ አሉት፡፡ ልጃችን እንዴት ቆንጆ ብትሆን ነው ኤዲን የመሰለ መኳንንት የማረከችው! ሲሉ ተደነቁ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ማረፊያ ሆቴሉ ውስጥ ሆኖ በሃሳቡ መጣችበት፡ የሄደ ቀን ተጋጭተው ነበር፡፡ የእሱን ሸሚዝ ለብሳ ከውስጥ ሌላ ነገር ሳትለብስ ሶፋው ላይ ቁጭ
ብላ መጽሐፍ ታነባለች፡፡ ለስላሳው ረጅሙ ጸጉሯ ትከሻዋ ላይ ተዘናፍሏል፡
ጡቶቿ ትንንሽ ቢሆኑም ጉች ጉች ያሉ ናቸው፡፡ በሽሚዟ ስር እጁን ሰደደና
የጡቶቿን ጫፎች አፍተለተላቸው፡፡ እሷ ግን ማንበቧን ቀጥላለች፡

#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሎ ሆራ ጨርቆሉ ማዝ ሆኖ ደም፣ ወተት፣ ሥጋና ማር እየተቀለበ፣ ከሰልና ቅቤ ተቀላቅሎ ፊቱንና የተላጨውን ራሱን
ተቀብቶ፣ ከሚዜው ጋር ውሎው ጫካ ነው። ከሎ የወገኖቹን ባህላዊ
የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ለመጀመር ምክንያቱ አንድ ነበር ፍቅር። ሥነ ሥርዓቱን እያሟላ ሲመጣ ግን፣ አዲስ ስሜት አእምሮው ማፍለቅ ጀመረ።
ወገኖቹ የሆኑት ሐመሮች በአንድ ወቅት ከማኅበረሰባቸው
አግልለውት ነበር" ያውም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣ እንዲሞት ተደርጎ ተጥሏል። ከሚወዳቸው ወላጆቹና እኅት ወንድሞቹ፣ ከሚያፈቅረው የፍየልና ጥጃ ጥበቃው፣ ከቦረቀበትና ከተጫወተበት ማራኪ
የሐመር ምድር ተጎትቶ ተወስዶ፣ በጦር ተወግቶ፣ ወደ ገደልም ተገፍቶ፣ የሞትን ጽዋ ጕድጓድ ውስጥ እንዲቀምስ ተደርጎ ነበር።
የሕፃንና የወጣትነት አእምሮው ይህን የደረሰበትን መራራ ጽዋ
ጠንጥኖ በገዛ አእምሮው የዛን ጊዜውን መሪ ተዋናይ ሲያስታውሰው አፉን ደም ደም ይለዋልI ልሳኑ ይዘጋበታል ሕይወቱ የላሸቀ፣ የተበላሸ እንቍላል ሆኖ ባለመጥቀሙ ተሽቀንጥሮ የተወረወረ
ይመስለዋል።
የዛኔው የቍስል ስሜት ምልክት ጥሎ ካለፈ ዓመታት ቢቈጠሩም
ሁሌም አጋጣሚውን ባስታወሰ ቍጥር ሥቃዩ ይጀምረዋል" ሞት
ጒሮሮው ላይ ቆሞ ስለታም ሰይፉን ጕሮሮው ውስጥ ሊቀረቅርበት ሲመጣ ይታየውና ይባባል፤ መሸሻ፣ መደበቂያ፣ ማምለጫ መንገድ ያጣል። ከራስ ሕሊና የሚፈጠር አስፈሪ ነገር በምን አንቀጽ
ይከሰሳል! ምን ዓይነት ጠንካራ በር ያግደዋል?
«እኮ ለምን? ምን ባደረኳቸው በእንቦቀቅላነቴ ወቅት ልሸከመው
የማልችለውን ሞትና ፍርሃት አሸከሙኝ ምን ባደረኳቸው ከእናት ጉያ ነጥለው፣ አብሬአቸው ከምዘላቸው ጓደኞቼ ለይተው ለመከራ
ዳረጉኝ?» ባለፈው ሕይወቱ ከሎ ሆራ ራሱን በራሱ እየጠየቀ መልስ ያጣበት ጉዳይ ነው" ለብዙ ዓመታት የዕለት ተዕለት ትዕይንት ሆኖ የሚቀርበውን የቆየ ትዝታ ባስታወሰ ቍጥር የመጨረሻውን ረድፍ
ይዘው የሚደረደሩት ጥያቄዎች ከላይ የተዘረዘሩት ሲሆኑ መልሳቸው ግን ሰው ወይንም መዝገበ ቃላት ሳይመልሰው እስከ ዛሬ አብረውት ዘልቀዋል"
ከሎ ሆራ በሕይወቱ ሙሉ ያምንበት የነበረው አሁን ግን እንደ አጉም እየበነነ አልጨበጥልህ ይለው ጀምሯል" ወደ ወገኖቹ ብቻ
ሳይሆን ወደ ሐመር ምድር ለመመለስ አልሞም አያውቅም። የኖረው
እነሱን ሲረግምና ሲሸሽ ነው። አሥራ ሁለተኛ ክፍል እንደ ጨረሰ በአገር አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻውም ወቅት፣ ከዘመቻው መቅረት ወይንም መለወጥ አልቻልህ ብሎት እንጂ እግሩንም
ለማንሣት አያስብም ነበር" የዛኔም ቢሆን ደግሞ፣ «ጌታዋን የተማመነች በግ...» እንዲሉ፣ መንግሥትን ተማምኖ እንጂ እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ዕድሉ ሌላው ሁሉ ነገር ቢቀር ወደ ሐመር
ተመልሶ ለመምጣት አያስብም። በቆይታውም አይጥና ድመት ሆነው
ቆዩ እንጂ አልተቀራረቡም።
አሁን ግን ከሎ ሆራ አይጡም ድመቱም እሱ እንደሆነ በመቁጠር ወደ ቤቱና ወደ ባለቤቶቹ መመለስ ይከጃጅለዋል"
ከሎ ሆራ በእርግጥ አሁን ያለው ሐመር ነው" ሐመሮች በተለይም ዘመዶቹ ባዩት ቍጥር ይሳሱለታል" ወላጅ እናቱ ልክ እንደ ልጅነቱ እጆቹን እያፍተለተሉ እንባቸውን ያፈሱለታል ያላቸውንና
ቤት ያፈራውን ጎጆው ድረስ ተሸከመው ያመጡለታል፤ ከብት ለመዝለል በየዘመዶቹ ቤት ሲዞር እንደ ብርቅ ስመው አስተናግደውታል ከብት በሚዘለልበትም ወቅት ዘመዶቹ ዝግጅቱን በማሟላትና በለምለም ቅጠል መልካም ዕድልን በመመኘት አብረውት
ተጨንቀዋል ልጃገረድ ዘመዶቹም የዝምናድ ምልክት የሆነውን
ግርፋት በወኔና በፍላጎት ተገርፈውለታል።
ከሎ ሆራ ይህን ሁሉ ካመዛዘነ በኋላ ለዘመናት በአእምሮው ተቀብረው
የኖሩትን ጥያቄዎች ከመቃብራቸው እያወጣ መጣል ጀምሯል እናቱ እንደ ብርቅዬ ልጃቸው፣ ወንድምና እኅቶቹ እንደ
ተወዳጅ ወንድማቸው አድርገው ይቈጥሩታል“ ታዲያ ማንን ይጥላ?
ለሥቃዩ ሁሉ ተጠያቂው ማን ሊሆን? ለምንስ እንዲሞት አድርገው
ጣሉት?
ከሎ ሆራ አእምሮው ለጥያቄዎቹ መልስ አገኘ" ለመጣል ያበቃው ባህል ነው። እሱን ለመጉዳት፣ ከእናቱ ጉያ ለመነጠል የደፈሩት የአገር ሽማግሎች አንኳን ለሱ ከሜዳ ተነሥተው hፉ አላሰቡም”
የሐመር ሕዝብ ባህሉን አክባሪ፣ ካለ ዘመናዊ ሕግና ደምብ በባህላዊ ደምቦችና ሥርዓቶች የሚመራ፣ ተፋቅሮና ተዛዝኖ የሚኖር
ማኅበረሰብ ነው። ማንንም የማያገል፣ ባህሉን ከመከተል ዝንፍ
የማይል ሕዝብ መሆኑን አረጋግጧል። «ታዲያ ወገኖቼ በእኔ ላይ
ብቻ ልዩ ቅጣት አልፈጸሙብኝማ። ባህላዊው ደንብ መሟላት
ነበረበትና ተገደልኩ፤ ከሙትነት ተነሥቼ ስመጣ ግን ተቀበሉኝ" አሁን የተቀበሉኝ ስለ ተማርሁ፣ ከእነሱ የተለየ ሕይወት ስላየሁ አይደለም ባህሉ ስለሚፈቅድ ብቻ ነው ታዲያ ባህል ባመጣው ጦስ ወገኖቼን መጥላት አለብኝ?» ጨርቆሌ ማዝ ተብሎ ጫካ ለጫካ
የሚዞረው ከሎ ሆራ ዕድሜ ልኩን አእምሮውን ሰንገው ይዘው ያስጨንቁት የነበሩትን ጥያቄዎች መመለስ ጀመረ።
።።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሰው ራሱን ማስተማር የሚችል ታላቅ ፍጡር ነው" በተለይም ታታሪ ሰዎች ከአምላክ የተሰጠውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ
እየተጣጣሩ ናቸው። እየተሳካላቸውም ነው
በምርምር እንደ እብድ ያልለፈለፈ ፈላስፋ፣ ቀንና ሌሊት በምርምርና በሙከራ እልሁን ያልጨረሰ ሳይንቲስት፣ እንደ
ሚፈጥራቸው ገጸባሕርያት ስቅስቅ ብሎ ያላዘነ አሊያም በደስታ ያልተፍነከነከ ደራሲ፣ የሚሥለውን ሥዕል የተዋጣ ለማድረግ
ረቂቁን የተፈጥሮ ምሥጢር ለማወቅ በመጣጣር ያልዳከረ ሠዓሊ
l ሊኖር አይችልም" ካለም ከነሆድ አምላኩ ወገን የሆነ አስመሳይ መሆኑ ነው"
ካርለት የሐመር ሴቶችን ሕይወትና ማኅበራዊ ተሳትፎ የምታጠና
ወጣት አንትሮፖሎጂስት ናት ያለችበት ዘመን ሳይንስና ተክኖሎጂ የመጠቀበት፣ የሰው ልጆች በአዲስ ግኝቶች የሚንበሸበሹበት ወቅት ነው„
«እንደ ዱሮው ዘመን ይህን ይህን ማድረግ ያስቸግራል የሚል አዳማጭም ሆነ ተመልካች አያገኝም" መሆን አለበት ብዬ ብዙ
ሞከርኩኝ ፈተናና ሥቃይም ገጠመኝ፤ በመጨረሻ ግን ተሳካልኝ ሲባል አድናቆታዊው ጭብጨባ መቅለጡን አውቃለሁ። የሰው ልጅ በውኃ ውስጥ በባቡር መጓዝ በቻለበት፣ ሕዋ ላይ ከተማ በከተመበት፣አይጥና ድመት አብረው እንዲጫወቱ በተደረገበት ወቅት እኔስ
ሰውነቴ ቢቈስል፣ የአእምሮ ጭንቀት ቢደርስብኝ፣ ብገረፍ፣ ባል ባገባ ምኑ አዲስ ነገር ነው። ከዚህስ የቀለለ የዓላማ መሥዋዕትነት ምን
ሊኖር ይችላል?» ካርለት መኝታዋ ላይ ተጋድማ የምታስበው ነበር
ካርለት ለአንድ ወር ያክል በከብት ዝላይ ወቅት የተገረፈችው ቁስል አሠቃያት ጫማ የለመደውን እግሯንም እንቅፋቱና እሾሁ
እየተተካካ አንሰፈሰፋት" እየቆየ ሲመጣ ግን ይህ ሁሉ ሥቃይ እየታገሠ፣ ቍስሉም እየደረቀ፣ እግሯም እየደነደነ መጣ ካርለት በቃን በማይሉት ማስታወሻዎቿ የየዕለት ገጠመኞቿን
እያሰፈረች፣ በካሜራዋ እይታዋን እያጠናከረች፣ በድንኳኗ አካባቢ
አገገመች ካርለት አልፈርድ ልብሶቿን በሻንጣዋ ቆልፋ፣ ቆዳዋን በመልበስ፣ በባዶ እግሯ በጨሌና አንባር አጊጣ ስትወጣ ብዙ አዲስ

#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሮፕላን እያጉረመረመ ከለንደኑ ሒትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ የለንደኑን ዳመና በአፍንጫው
እየበረቃቀሰ አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ካርለት ከሎና ጎይቲ እንደ ሌሎቹ መንገደኞች ሣቅ ጨዋታ አላበዙም።
ካርለትና ጎይቲ እየቆዩ ጫን ጫን ይተነፍሳሉ። ሶስቱም
የተቀመጡት በአሮፕላኑ መካከል ባሉት መቀመጫዎች ጎን ለጎን
ሲሆን ከፊት ለፊታቸውና ከኋላቸው ነጮችአሉ በስተቀኝ በኩል
አንድ ኢትዮጵያዊና አንድ ነጭ፤ በስተግራ በኩል ደግሞ የንጉሥ
ኃይለስላሴን ምስል ደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉ ፀጉራቸውን እንደ ባህታዊ ጎንጉነው የኢትዮጵያ ባንዲራ የጠመጠሙ ጃማይካውያን
ተቀምጠዋል።
ካርለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚታተመውን “ሰላምታ" መጽሔት እያነበበች ሳለች።
“ይቅርታ” የሚል ድምፅ ሰምታ ቀና ስትል የአሮፕላኑ
አስተናጋጅ ፈገግ ብላ የምግብ ማስቀመጫውን እንዲዘረጉ ጠይቃ
ለሶስቱም የሚሆነውን ምግብ በፊታቸው አስቀመጠች።
በአጭር ጊዜ ውስጥ በኤሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተሳፋሪ መመገብ ጀመረ: ጎይቲ ልትበላ አልፈለገችም: ካርለት ግን፡-
“ጎይቲ እባክሽ ትንሽ ለመብላት ሞክሪ?" አለቻት፡
“ካርለት እህል መች ራበኝ። ይልቅንስ አንች ብይ" አለቻት ፈርጠም ብላ ጎይቲ።
ባይሆን ይሄ ደረቅ ስለሆነ ብስኩቱን ብይ እስፕራይቱንም
ጠጪ" ስትላት።
“ይእ! አቤት! የምግባችሁ ስሙ ብዛቱ። አፍ ላይ
ይጣፍጥና ውስጥ ሲገባ እንደ ነፍሰ ጡር ማቅለሽለሽ። አሁንስ ወደ
አገሬ እሄድሁ ነው:: ለኔ ያደግሁበት ኩርኩፋ ትኩስ ወተቴ ይሻለኛል፡" ጎይቲ ኮስተር አለች።
ከሎና ካርለት ተያዩ: ጎይቲ አንዴ ከወሰነች ውሳኔዋን
እንደማታጥፍ ስላወቁ የየበኩላቸውን መመገብ ጀመሩ::
ጎይቲ ወዲያ ወዲህ ሄድ መለስ የሚሉትን እያየች ቆየችና፡-
“ፈረንጅና ህፃን ልጅ አንድ ነው፡ አንድ ጊዜ እስኪጠግብ አይበላ! አሁንም አሁንም መለካከፍ! ሁሉን መላስ ብቻ አንዴ
ጥሩ አርጎ አይጎርስ አይ ደንብ እቴ: ይእ! - ደግሞ የልብሳቸወ ብዛት:: ልብስን ቢያበዙት ትርፍ የለው: ከብት ቢገዙት ይራባል
በረት ይሞላል፤ ተዚያ ወተቱ ስጋው ይጠቅማል። ለዘመድ ወገን ቢሸልሙት ደስ ይላል።
“እነሱ ቤታቸውን ኮሮጆአቸውን የሞላው የሚያልቅ ቅራቅንቦ ብቻ! እና እኒህ ከህፃን በምን ይሻላሉ። እንደ ቀበሮ
የሚፈልጉትን እየተሯሯጡ ሲያነፈነፉ ይውሉና በዚያ ተግቶ በሚውለው ዋሻቸው ገብተው ማድፈጥ: እርስ በርስ አይዋደዱ አንዱ ሌላው ዘንድ አይደርስ ሲጫወቱ ለከት የላቸው:: ጆሮ እሚያደነቁር ነገር ይከፍቱና ዛር እንደያዘው ሰው አንዱ ከመሬት
መፈጥፈጥ ሌላው እንደ ጠገበ እንቦሳ መዝለል... ወንድና ሴቱ ደግሞ አይታወቅ ሁለቱም እቤት ውስጥ ተከተው አንድ አልጋ
ላይ ወጥተው መተኛት። ሴት ወንድን እንደህፃን ልጅ አቅፋ ተኝታ ሲያንኮራፋ ማየት።
“ደሞ የዚህ የኔው ጉድ የከሎ ይባስ እንጂ! ወዷቸው ሊሞት! ሳያርፍ ደሞ መኖርስ እዚህ ነበር' ይበለኝ፡ መጨከኑ
እንደ ዶሮ ሲጠጡ ማንጋጠጥ ሲበሉ አንገት መድፋት ከዚያ መሮጥ እንደ እብድ እየተገፋፉ መክላፍለፍ ተመልሶ ዋሻን ዘግቶ መቀመጥ ይህ የቀበሮ ኑሮ ምን ይወደዳል? ይእ! እነ አያ ደልቲ! ሐመሮች እዚህ ውስጥ መኖሬን ብነግራቸው እውን ሰው ያረጉኛል።ዳሩ እኒስ ምን ጥሩ አለው ብዬ አወራቸዋለሁ። ብቻ እንድረስ!"ጎይቲ ስለ ነጮች አኗኗር ማሰቧም ዘገነናት።
ጎይቲ አይኖችዋ ቡዝዝ ብለው ቢከፈቱም አያዩም: እሷ የምታየው የሐመር ተራራን ሜዳን... የጀግኖችን ቁንጮ ደልቲ ገልዲን ነው::
ቱር እያሉ የሚበሩ አዕዋፍ በነፋስ ጎንበስ ቀና የሚሉት
እዕዋት... ሳራቸውን የሚያመነዥኩ ከብቶች በጎችና ፍየሎች በጨረቃ ብርሃን ተቃቅፈው የሚጨፍሩት ልጃገረዶችና ጎረምሶች በአይነ ህሊናዋ ይመጡባታል፧ ይታይዋታል::
ደልቲን ለዳንስ ስትጋብዘው አየሩን እየቀዘፈ የወተት አረፋ የመሰለ ጥርሱን በጨረቃዋ ብርሃን እያብለጨለጨ ሲመጣ ከወገቧ እየረገረገች ጡቶችዋን እያስነጠረች ስልቱ ባልተዘበራረቀ እንቅስቃሴ መሬት እስኪጨንቃት እየረገጠ ሲጠጋትና ስትሾር... እንደ ብረት የጠነከሩት እጆቹ ትከሻዋን ሲደገፉ እንደ ባልጩት የሚለሰልሰው
ጭኑ ወደ ጭኗ ሲዘልቅ የብልቷ በር ደጋግሞ ሲንኳኳ... ከዚያ ወደ
ተፈጥሮ መኝታ ቤት ወደ ጫካው ሲገቡ በሩ ተከፍቶ ጋ ተደርጎ ሲቀረቀር የፍቅር ማራቸውን ሲላላሱ እንዳይሰላቹ ተሰነባብተው
እሷ ወደ ጎጆዋ እሱ ወደ ማማው ሲያመሩ ታያት።
ይህን ጊዜ ጎይቲ
ካርለት! ምነው ይኸ ነገር ቆመ፤ ምነው የሰው ጭንቀት ቢገባው ፤ምናለ! ከሐመር ቀዬ ቶሎ በሮ ቢያደርሰኝ!... አለቻት
መሳሳቋን ሳትደብቅ።
“እንደ ወፍ እየበረርን ነው'ኮ ጎይቲ! አይዞሽ ወደ ናፈቅሽው ቶሎ ትደርሻለሽ: ከሎን አታየውም? አለቻት እንድትረጋጋ በማሰብ
“ይእ! እሱማ ለማዳ ነው። ታቦቱ ደንብ የወረሰው የለም ለኔ የጨነቀኝ ለሱ ደስታ ፈጥሮለታል። ብቻ ተይኝ! እንዲያው እሚሰሙሽ ከሆነ ይኸ ነገሩ በቋራጭ በአቋራጭ አድርጎ ከሐመር
hእባቴ ተራራ ከቡስካ እንዲጥለኝ ንገሪው:: ከዚያስ ወዲያ ችግር
ቀናም ብዬ ሳላየው እየቦረቅሁ ተቀየዬ
ከዘመዶቼ ከጀግናዬ ጋር እገናኛለሁ፡ እና! እስቲ ንገሪቸው? አለች ጎይቲ፡
ካርለት ሳቅ ብላ፦
“ኤሮፕላኑ የራሱ የተወሰነ ፍጥነት ኦለው..." ስትል ጎይቲ አቋረጣት።
"አቤት! የደንባችሁ ብዛቱ። አቤት ስትፈራሩ… በይ ተይው እኔስ እንግዲህ ለአንድ ጊዜ እችለዋለሁ። መጥኔ ለናንተ! አለቻትና
ወደ ህልሟ ገባች። ከሎ ከጃማይካዎች ጋር ይጫወታል ይከራhራል...ይሳሳቃል።
የጎይቲ አስተያየት
ካርለት እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስገረማት። የጎይቲን ገሀዳዊ ህይወት አይታዋለች: ሐመሮች
በጥቁር ቆዳ የተሸፈነ አልማዝ ጥቅማ ጥቅም ያልበከለው ንፁህ ህሊና ያልተበከለ ባህል ካለ ዘመናዊ ህግና ፖሊሲ ተስማምተው
የሚኖሩ ተፈጥሮን የማይቃረኑ ህዝቦች መሆናቸውን አብራቸው
ኖራ አይታለች።
ሐመር ውስጥ ስሜት በህሊና እንጂ ሰዎች ባወጡት ህግ
አልተለጎመም: እውነት ራቁቷን ናት! እነሱም ራቁታቸውን ናቸው!
ተፈጥሮም አልተበከለችም! መሬት የፈለገችውን እፅዋት ታበቅላለች!የተጠጓትን አውሬዎች ደስ ብሉአቸው እንዲኖሩ ታረጋለች
የተፈጥሮ አበባ አካባቢውን እንዳስዋበው ነው። ሰማዩ ግን በአይሮፕላን ጢስ እየቆሸሸ መኪናው አራዊትን እያስበረገገ ነው።ስልጣኔ የተፈጥሮ ሚዛንን ለማዛባት ኬላውን ለመጣስ እየጣረ ነው ያኔ በራስ መተማመን በራሱ ይቆማል! ህክምና አልባው የመምስል
በሽታ ይጠናወታል! ማንነት ይጠፋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመስኮቱ መጋረጃ እንደተዘጋ ነው: የመኝታ ክፍሉ ግን በማለዳ ፀሐይ ብርሃን ደምቋል። ካርለት ተንጠራርታ አይኖችዋን
ስትከፍት ነጭ ቀለም የተቀባውን የመኝታ ክፍል ከጣራው እስከ ወለሉ የሚደርሰውን ሰፊ ቁምሳጥን ሰፊውን አልጋ.. ቃኝታ ዘወር ስትል ከስቲቭ ጋር ተያዩ::
ተንጠራርታ ወደሱ ጠጋ አለችና በፀጉር ከተሸፈነው ደረቱ ላይ ተለጥፋ አቀፈችው። እሱም ያቀፈበትን ክንዱን ሳብ ሳብ አድርጎ በግራ እጁ ፀጉሯን ዳበሰላት።
መቀሽቀሻ ስዓቷ ዲሪሪን… ዲሪሪን.ዲሪሪን' ስትል ስቲቭ ቀና ብሎ ድምፅ ሲያሰማት ፀጥ አለች እነሱም ሙቀታቸውን
እየተጋሩ ተቃቅፈው ፀጥ አሉ።
መቀሽቀሻ ሰዓቷ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ደግማ ዲሪሪን…..ዲሪሪን...' ስትል ካርለት የስቲቭን ከንፈር ሳም አድርጋ ቢጃማዋን
ሳትለብስ እርቃኗን መታጠቢያ ክፍል ገባች።

#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹እኔ እዬብ እኮ ነኝ.›› ብዬ ቃላት ከአንደበቴ ለማውጣት አፌን ስከፍት ከንፈሯ ከንፈሬን ጎረሰው…ተአምር ነው በዚህ ሀገር ስንት ሴት ጄኔራሎች አሉ…?ከእነዚህ ውስጥ ከ ጄኔራሎች ጋር ፍቅር ለመጋራት ስንት የአዳም ልጅ እድል አግኝቷል.?.ልቤ በትዕቢት ስታብጥ ታወቀኝ…፡፡እጄን በወገቧ ዙረያ ጠምጥሜ ይበልጥ ወደሰውነቴ አጣበቅኳት..ብስጭቴ ሁሉ ከጭንቅላቴ እየተነነ አየሩን ሲሞላ ታየኝ…ውስጤ ተንፈቅፍቆ መሳቅ ጀምሯል…
ከከንፈሯን አላቃ በአንድ እጇ ብቻ ወገቤን ይዛ ወደላይ አንጠለጠለችኝና አልጋው ላይ ወረወረችኝ…፡፡ወይኔ ዛሬ በቃ እስከመጨረሻው ነው…ቆይ ልብሴን ላውልቅ ብዬ ልነሳ ቀና ስል ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቅናለች..መልሼ በድንጋጤ በመደንዝ አልጋው ላይ ተዘረርኩ፡
‹‹ሽጉጥ እንኳን ሊደቀንብኝ በህይወቴ በፊት ለፊቴ አይቼው አላውቅም በፊልም እና በፎቶ ብቻ ነው የማውቀው..እና የጋለው ሰውነቴ ቀዘቀዘ…››
‹‹እንዴ ምን አጠፋሁ..?››
‹‹ሌባ ነህ..››
‹‹እኔ እዬብ እኮ
ነኝ››ለስንተኛ ጊዜ ይሆን ስሜን የነገርኳት?፡፡
‹‹አዎ ልቤንም የሰረቅከው እዬብ የተባልከው አስተናጋጅ አንተ አይደለህ?››
‹‹ይቅርታ የእኔም ልብ እኮ የለም ›አልኳት በአሳዛኝ ድምፅ ሽጉጡን ከግንባሬ አንስታ ትራሷ ስር ሸጎጠችና ከጎኔ ተኛች
‹‹በፈጣሪ ምነው ምን አድርጌሽ ነው እንዲህ ምታስደነግጪኝ.?››
‹‹ይቅርታ››
‹‹እስከአሁን እንዴት ሳትተኚ››
‹‹አየጠበቅኩህ ነበር››
‹‹እንዴት …ወደቤት ሁሉ ሄጄ ተኝቼ ነበር.
‹‹እናስ?››
.እናማ እንቅልፍ አልወስድም ሲለኝ ተመልሼ መጣዋ››
‹‹መጀመሪያ ለምን ሄድክ? አኩርፈሀኝ ነበር አይደል?››
‹‹አዎ በጣም ነበር የተበሳጨሁብሽ ..ደግሞ ዛሬ ነው ያየሁት..ወታደር መሆንሽን ብትነግሪኝ ምን አለበት ?ለዘውም ጄኔራል.››
‹‹ምን ይጠቅምሀል… እኔ ከአንተ ጋ እየተገናኘሁ ያለሁት ጄኔራል ሆኜ ሳይሆን ዜና-ወርቅን ብቻ ሆኜ ነው..››
‹‹ኸረ ተይ በናትሽ..ከቀድሞ አውቄ ቢሆን ልቤን መች እንዲህ አዝረከርካት ነበር…››
‹‹ምን ወታደር አይመችህም እንዴ?.››
‹‹አረ እንደዛ ማለቴ
አይደለም ግን ይከብዳል…በተለይ ለአንቺ የሚከብድ ይመስለኛል..አለ አይደለ እኔ እንጃ ብቻ.››
‹‹ለማለት የፈለከው ገብቶኛል.ግን አታስብ በቅረብ ጡረታ ልወጣ ነው..››
‹ጡረታ ምነው በዚህ ዕድሜሽ.?ለዛውም የማአረግ እድገት ባገኘሽበት ማግስት ››
‹ ምክንቱን ሌላ ጊዜ እንግርሀለሁ …ግን ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ከሰራዊቱ እሰናበትና ሌላ የሲብል ስራ ላይ የምመደብ ይመስለኛል…››
‹‹አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ…መቼስ ጡረታ ከወጣሽ በኃላ ችላ አትይኚም አይደል?››
‹‹አይ አልልህም….ግን አንድ ልደብቅህ ማልፈልገው ነገር አለ››
ስለጄኔራሉ ፍቅረኛዋ የሆነ ነገር ልትለኝ ነው ብዬ በታፈነ ስሜት‹‹ ምን?›› ስል ጠየቅኳት
‹‹አንተን በተመለከተ በጣም የተወዛገበ ስሜት ነው የሚሰማኝ…የሆነ ድሮ የማውቀው የጠፋ ዘመዴ ወይም ወንድሜ ነው ምትመስለኝ››ብላኝ እርፍ፡፡
‹‹ባክሽ አትቀልጂ …ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹እኔ እንጃ …ሁል ጊዜ ላገኝህና ላቅፍህ እፈልጋለው..አግኝቼ ሳቅፍህ ደግሞ ታናሽ ወንድምሽ እኮ ነው የሚል ስሜት ይተናነቀኛል፡፡››
‹‹ምነው የጠፋ ወንድም ነበረሽ እንዴ?››
‹‹ኸረ ፍፅም.. እኔ ምንም የጠፋም ያልጠፋም ወንድም ኖሮኝ አያውቅም››
ኮስተር ብዬ‹‹ተይው በቃ ይህ የእህት ነገር እጣ-
ክፍሌ አይደለም..ለጊዜው ጓደኞች ከሆን ይበቃል›› አልኳት …ውስጤ ግን ምንም አይነት ከእሷ ጋር ጓደኛ የመሆን ጉጉት የለውም…
በተረጋጋ አንደበት‹‹እንደዛ ከሆነ እንተኛ››አለችኝ፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›አልኳት፡፡
እሺ ብላ አልጋው ላይ ቆመች…የለበሰችውን ቢጃማ አወላለቀችና በሰማያዊ ፓንት ቆመች.እኔ በተኛሁበት ከስር ወደላይ እያየኋት ነው..ይገርማል በቴቪ በዛ ግርማ ሞገስ ያያት ሰው አሁን እንዲህ እርቃኗን ቆማ ከነሙሉ ውበቷና ደምግባቷ ቢያያት ደግሞ ምን ይል ይሆን?፡እኔም በተኛሁበት ልብሴን አወላልቄ ወደጠረጳዛው ወረወርኩና ከውስጥ ገባሁ ..ቀድማኝ ገብታ ነበር፡፡ መብራቱን አጠፈሁና ከሰውነቷ ተጣበቅኩ፡፡እና ከየት እየተንቀዠቀዠች እንደመጣች ሳላውቅ የተአምር እናት በምናቤ ተሰነቀረች…የሴት ልጅን ገላ ሳቅፍ እንዲህ አይነት የሚነዝርና የሚያሾር አይንት ስሜት ሚሰማኝ ከእሷ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ዳሩ ነገሮች ባለምኳቸው መጠን እድገት አላሳዩም.. ሊቱን በሙሉ በመተቃቀፍ ገደብ ባይኖረውም ከዛ እልፎ ወደ ጭን መፈላለቅ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ‹‹በፈጣሪ አሁን እኔ ምኔነው የእሷ ወንድም የሚመስለው?››ይሁን እስቲ ….ማምሻም ዕድሜ ነው ይባል የለ፡፡
…በማግስቱ ማታ
//
ከምሽቱም አምስት ሰዓት ከስራ መልስ ነው፡፡አልጋዬ ላይ ወጥቼ ከብርድልብሴ ስር ገብቼ ስለነበር ስልኬን ካስቀመጥኩበት አነሳሁና ተነጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁ፡፡ብርድልብሱን ተከናነብኩና ሞባይሌን ከፈትኩ ፡፡ቅድም ልጄ ተአምር ልካልኝ የነበረው ቴሌግራም ከፈትኩ….እናቷ ስለእኔ የፃፈችው ቀጣይ ፀሁፍ ነው….የእሷን ፅሁፍ ማንበብ የቡና ሱስ ነው የሆነብኝ፡፡ ተመቻችቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡
ግንቦታ 16/2008 ዓ.ም
እዬቤ ከእህቶቼ በላይ ነው ማቀርበው…ከእህቶቼም በላይ ነው የምወደው..እሱ ለእኔ የሚስጥር ተጋሪዬ ነው..እሱ ለእኔ የትምህርት ቤትም ጓደኛዬ ነው።እርቃኔን እህቶቼ ፊት ስቆም ሰውነቴን ይበላኛል...እዬቤ ፊት ሲሆን ግን የራሴን ሰውነት በራሴ አይን እያየሁ ነው የሚመስለኝ።ለምን እንደዛ ሆነ ?ለእኔም ለራሴ ግራ ይገባኛል። ለምሳሌ ልብስ ለእህቶቼ ተገዝቶ ለእኔ ባይገዛ ችግር የለውም..ለእኔ ተገዝቶ ለእሱ ላይገዛ ግን አይችልም።በቃ ያንን ልብስ በምንም አይነት አለብሰውም።እሱም እንደዛው ነው።አንዳንዴ ያው የሙት ልጅ ነው በሚል ስሌትም ከቤተሠቦቹ ቤት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ ስላለ በሚል ስሌትም ብቻ ምክንያን አላውቅም ለእሱ ለብቻው ልብስ ይገዛለታል..እሺ ብሎ ይቀበልና አጣጥፎ ያስቀምጣታል"ለእኔ እስኪገዛልኝ ስድስት ወርም ቢፈጅ አይለብሳትም ።ከዛ በቤተሠብ ሁሉ ተለመደና ለሁለታችንም መግዛት እስኪችሉ ነጥለው መግዛት አቆሙ..
ከእዬቤ ጋር እድሜያችንም ተቀራራቢ በመሆኑ ክፍላችንም አንድ ነው። የምንቀመጠውም አንድ መቀመጫ ላይ ነው።ያው ግን ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት በጣም የተለያየ ነው።እዬቤ ከአንደኛ ክፍል አንስቶ እስከመጨረሻው አንደኛ ወይም ሁለተኛ ነው የሚወጣው..ተሳስቶ እንኳን 3 ተኛ መውጣቱን አላስታውስም ።ብዙ አያጠናም ..ክፍል ውስጥ አስተማሪ የሚያስተምረውን በፅሞና ያዳምጣል..የቤት ስራ ሳይረሳ ይሰራል፤ ፈተና ሲቃረበ ያጠናል በቃ...እኔ ግን ተውኝ "አንድ ቤት እየኖራችሁ አንድ ክፍል እየተማራችሁ አንድ አስተማሪ እያስተማራችሁ ይሄ ሁሉ ልዩነት ምንድነው?"የአባቴ የዘወትር ጥያቄ ነበር
"ቆይ አንድ ክፍል አይደል እንዴ የምትኖሩት? ለምን አብራችሁ አታጠኑም?" አባቴ ይጠይቀዋል
‹‹ጋሼ አብረን ነው የምናጠናው..ግን እሺ አትለኝም..እያጠናን ትተኛለች..ወይም ትረብሻለች"

#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
በፊት ፍቅር ማለት....?ብለው ሲጠይቋት በመራቀቅ እና በልበ ሙሉነት ትዘረዝር ነበር::አሁን ከዚህ ልጅ ጋር በአጋጣሚ ከተላተመች በኃላ ግን...ፍቅር ማለት ...?ብለው ሲጠይቋት መልሷ ረጅም ዝምታ ነው።እንደዛ ማድረጓ ፈልጋ አይደለም …ከእሱ ጋር ከተጋራችው ስሜት አንፃር ፍቅርን ለመተንተን ብቁ የሆነ ሀሳቧን የሚመጥን ቃል በከንፈራ ላይ ስለሌለ ነው።
በቀደም ሜቅዶኒያ በሄድ ቀን በጣም አሪፍ ሚባል ጊዜ ነበር ያሳለፉት…ከአባቱ ጋር አስተዋወቃት…አብረው ከሁለት ሰዓት በላይ አዛውንቶቸን በመንከባከብ የሚሰሩ የበጎ ስራ አገልግሎት ሰራዎችን ሰሩ፡፡
ይሄ ተግባር ለቃል የዘወትር የእለተ እሁድ የግማሽ ቀን ተግባሩ ነው…ለልዩ ግን የመጀመሪያ ኤክስፒሪያንሶ ነበር..እና ከጠበቀችው በተቃራኒ እጅግ አስደሳችና ጭፈራ ቤት አምሽቶ ከመዝናናት በላይ በተሻለ ጥልቅ የሆነ ደስታ የሚሰጥ ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ስራቸውን ጨርሰው በአባቱ ተመርቀው እና ተሰናብተው ከወጡ በኃላ መንገድ ላይ‹‹ምንም ነገረ ሳይከፈል ምንም ነገር ጥቅም ሳይገኝበት እንዲህ አይነት ፈታኝ ስራዎችን መስራት የሚገርም ስብዕናን የሚጠይቅ ነው››አለችው፡፡
‹‹ አይ በነፃ ይመስልሸል እንጄ በነፃ አይደለም…በዚህ ምድር ላይ ያደረግሽው ሁሉ ይመለሰልሻል.አሁን እነዚሀ የአረጋዊያንን ልብስ አጥበሽ በምርቃት ብቻ ተቀብለሽ ስትሄጂ በነፃ ያገለገልሽ መስሎሽ ይሆናል..ግን በሌላ መንገድ ታገኚዋለሽ…ለምሳሌ አሁን አይበለውና መኪናሽ ከሆነ መኪና ጋር ተጋጭታ አደጋ ደርሶብን ሆስፒታል ብንገባ አንድ የማናውቀው ሰው ለሁለታችንም በናፃ ደም ለግሶን ከሞት ሊያተርፈን ይችላል፡፡ …ያደረግሽው በጎ ነገር ሁሉ ይፍጠንም ይዘግይም ይመለስልሻል…መጥፎውም ነገር እንደዛው›› እንደዛ ነበር ያላት፡፡
ያው እሷ በሰዓቱ ምንም እንኳን በንግግሩ ብትደመምም በትክክለኝነቱ ግን ሙሉ በሙሉ አላመነችበትም..ቢሆንም የሰማችው ግን በፅሞናና በመመሰጥ ነበር…ባለው ነገር ሙሉ እምነት ያልተሰማት ምክንያት ዕድሜያቸውን ሁሉ ክፍ ስራ እየሰሩ ግን ደግሞ በሰላም የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በዙሪያዋ ስለምታውቅ ነው፡፡ለቃል ግን እንዳዛ አላለችውም…፡፡ምን አልባት እንደዛ ብላው ቢሆን ‹‹በሰላም እየኖሩ መሆናቸውን በምን አወቅሽ…? ሰላም ማለት እኮ ትርጉሙ ሰፊ ነው..በህይወታቸው ደስተኛ ናቸው…?ጥሩና ሰላማዊ እንቅልፍ እየተኙ ነው…? አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ በእጅ አዙር ይመልስላት እንደነበር እርግጠኛ ነበረች፡፡
ከዛን ከሰአት እንጦጦ ሄድ.. በየካፌውና ሬስቶራንቶቹ እየቀያየሩ ድንቁና አረንጓዴ የሆነውን ወጣ ገባ መልካ ምድር እየጎበኙ ንፅህንና ነፋሻማውን አየር እየማጉ በደስታ ሲፈነጥዙ ዋሉና ማታ አንድ ሰዓት እቤቱ በራፍ ድረስ አድርሳው ቅር እያላት ወደቤቷ ሄደች…፡፡
ከዛን ወዲህ ሁለት ቀን ተገናኝተው ሻይ ቡና ብለዋል…አሁን ግን ካየችው ሌላ ሁለት ቀን አለፋት ፡፡ናፍቆታል፡፡‹‹
‹‹አይገርምም ..አሁን ናፍቆኛል ስል መድህኔ ቢሰማ ምን ያህል ልቡ ይሰበራል?››ሳታስበው እራሱ ዝግንን አላት…፡፡ቢሆንም ግን መናፈቋ የማይካድ ሀቅ ነው: አሁን በዚህ ምሽት እያደረገች ያለችው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች ስለእሱ ማሰላሰል ነው..ስለመድህኔ አይደለም…ስለቃል እንጂ ፡፡
‹‹አዎ እስኪ አይኑን ልየው›› አለችና ከመኝታዋ ተነስታ ላፕቶፖን ከተቀመጠበት አመጣች፡፡ ወደቦታዋ ተመልሳ ከፈትችው፡፡
እንዲህ አይነት ስራዎችን በተለያዩ ሰዎች ላይ እንደምትሰራ የምታውቅ አንድ የትምህር ቤት ጓደኛዋ‹‹ ለምን ግን ደህንነት መስሪያ ቤት ሲርቪስን አታስገቢም፤አንቺ እኮ የተፈጠርሽው ሰላይ ለመሆን ነው፡፡ ብልሀቱንም፤ተንኮሉንም ማስመሰሉንም ተክነሽበታል››ትላት ነበር…፡፡በወቅቱ አስተያየቷን ብትቃወማትም አሁን ሳታስበው ግን እውነቷን ነው ብላ ማመን ጀምራለች፡፡
..ከእሱ መኝታ ቤት የቀበረችው ካሜራ ጋር የሚያገናኘውን ቁልፍ ተጭና እሱ ወደ መኝታ ቤቱ እስኪገባ መጠበቅ ጀመረች፡፡የፊት ለፊቱ ክፍል እንዳለ አውቃለች፡፡ ሙዚቃና አንዳንድ የሚንጋጉ ድምፅች ከሚቀጠልው ክፍል ውስጥ መኖሩን ያሳብቃሉ…፡፡
መኝታ ቤቱ ተከፈተ…ቃል ገባና በራፉን ዘጋው…፡፡ትኩረቷን ሰብስባ መከታተል ጀመረች፡፡ወደ ቁም ሳጥኑ ቀረበ፡፡ከፈተ.. ፡፡ቢጃማ አወጣ..፡፡
‹‹ውይ ልብሱን ሊቀይር ነው…፡፡››አለች..ግራገባት…ምን ታድርግ..?፡፡
‹‹ለጊዜው ቀይሮ እስኪጨርስ ላፕቶፑን ልዝጋው..ወይስ እኔ ከስሩ ዞር ልበል..?፡፡›› ውሳኔ ላይ ሳትደርስ ከላይ የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀና በስነስርአት አጣጥፎ ጥግ ላይ ካለች ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠ..ሲሊፐሩን አወለቀና ባዶ እግሩ ምንጣፍ ላይ ቆመ፡፡ ሱሪውን መዥርጦ አወለቀ…ሰማያዊ ፓንት እየታያት ነው፡፡
‹‹..ወይ ምን እየሰራሁ ነው….?.ሱሪውን በተመሳሳይ አጣጥፎ አስቀመጠ…፡፡
‹‹እንዴ ሌላ ነገር ሊያወልቅነው እንዴ?›› ስትል እግዜር ይስጠው አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ፒጀማ አነሳና በየተራ ለበሰ…፡፡መሀል ወለል ምንጣፍ ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ… …፡፡
‹‹እንዴ ምን እየሰራ ነው..?ስትል እጁን ወደፊቱ ዘረጋ….ከዛ ድምፅ አውጥቶ ከዚህ በፊት ሰምታው የማታውቀው አይነት አዲስ ፀሎት መፀለይ ጀመረ..‹‹ታድሎ የየትኛው ሀይማኖት ፀሎት ይሆን ..?ምን አልባት አንድ ቀን በደንብ ስንግባባ ጠይቀው ይሆናል..እናም አብሬውም ከጎኑ ተንበርክኬ እጆቹን በእጆቼ ይዤ እፀልይ ይሆናል፡፡››ስትል ተመኘችና ፀሎቱን በጥሞና መከታተል ጀመረች፡፡
///
የውበቶች ሁሉ ድምር ውበት...የሙዚቃዎች ሁሉ ጥቅል ዜማ....የብርሀን ሁሉ ብርሀን ...የሠው ልጆች ሁሉ ጥምር እስትንፍስ ...እሱ እግዚያብሄር ነው።መላእክቶች ቅርንጫፍ ላይ የበቀሉ ወረቃማ ቅጠሎች ናቸው። ፀሀይ ከልብ አንድ ጥግ መንጭታ ለአጥናፍ አለሙ ብርሀንና ሙቀት የምትለግስ የህይወት ምንጭ ነች። ጨረቃ ከአይኖቹ ብሌን ጫፍ የምትገኝ የውበት ፈርጥ ነች..ከዋክብቱ ግንባሩ ላይ ልክ እንደፀጉር የተበተኑ ድንቆች ናቸው ....እኛ የሰው ልጆች የአእምሮው ህብረሰረሰር ቅንጣት ህዋስ ነን።የእኛ ኢምንት ሀሳቦቻች ከሱ እልቆ መሳፍርት ሀሳብ እየተሸረፍ ሚበተኑ ህልሞቻችን ናቸው። አፅናፍ አለም በእጅ መዳፍ ላይ የተበተኑ የሚነበብና የሚተነተኑ መስመሮች ናቸው። የምድር ደኖችና ተክሎች እግሮቹ ላይ የበቀሉ ፀጉሮች ናቸው። የፍጥረታት ነፍስ ከትንፍሹ የተሸረፈች የህይወት እርግብግቢት ነች።እግዚያብሄር ሁሉም እና አጠቃላዪ ማለት ነው። ጥልቀቱ ወሰን አልባ ርዝመት የማይደረስበት ...ልኩ ይሄን ያህል ነው የማይባል ... የነገሮች ሁሉ የመጨረሻው ቅንጣት ኢነርጂ ... በጊዜ የማይገመት በቦታ የማይታጠር ኤልሻዳይ አምላክ ነው።
/
ከዛ ፀሎቱን እንደጨረሰ ትንፋሽ በጥልቀት ወደውስጥ እየሳበ ከዛ አምቆ ይቆይና ወደውጭ ይለቀዋል…መልሶ ወደውስጥ ይስብና ወደውጭ ይለቀዋል.. ያለመታከትና መሰልቸት ለአስር ያህል ደቂቃ እንደዛ ካደረገ በኃላ...ባለበት ያለምንም እንቅስቃሴ አይኖቹን ጨፍኖ ፀጥ አለ…፡

#ህያበ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ኤርሚ
"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።
"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"
"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።
ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ...
"አንደርስም እንዴ ደግሞ እኮ አይኔን በጨርቅ አስረህዋል። የት ነው የምንሄደው ራቀብኝ? ያ ውሻ የት ነው ያለው?"
"አይንሽን ከገለጥሽ ከኔ ጋ ትጣያለሽ ማርያምን የምሬን ነው። ታገሽ ትንሽ ነው የቀረን ደርሰናል" ጥቂት ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ መኪናውን አቆመው
"አሁን ጨርቁን ማንሳት ትችያለሽ" ቶሎ ብዬ ፈታሁት... ሰው የሌለበት ቦታ ነው።
"ምንድነው ቢኒ እየቀለድክብኝ ነው" ፊቴን አዙሬ በንዴት አየሁት
"ውረጂ.,. ያውልሽ እዛጋ ይታይሻል...( በወዳደቁ ነገሮች የተሰራች ቤት) እዛ ውስጥ አለልሽ ውረጂና የፈለግሽውን አድርጊው" ሳላቅማማ ወረድኩ። በእልህና ንዴት እየተራመድኩ ወደቤቱ ተጠጋሁ ልገባ ስል
"እባቷ ነኝ ባሏ. ... ሀ ሀ ሀ... ንገሩኝ እስኪ እናቷን አግብቶ ልጁን ያስረገዘ አባት ታውቃላችሁ... አታውቁም? ሙትቻ ለምንድነው የምታፈጡብኝ... መልሱልኝ... ኧረ ተውኝ ኡ ኡ ኡ..." ጩኸቱ አስደንግጦኝ ወደኋላ ተመለስኩ። ትንሽ ተራምጄ ቆምኩና ልጄን አሰብኳት "እገለዋለሁ" ወደ ቤቷ ተመለስኩና ከፍቼ ጎንበስ ብዬ ገባሁ። የቤቱ ጠረን ይገፈትራል ሰው የመጣም አልመሰለው ዝምም ብሎ ልፍለፋውን ቀጥሏል። የማላውቃቸውን ብዙ የሴት ስሞች ይጠራል... ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይራገማል፣ ድንገት ደግሞ አስደንጋጭ ጩኸቱን ይለቀዋል። ለደቂቃዎች ዝምምም ብዬ ሰማሁት... በብዙው የቤቱ ቀዳዳ በሚገባ ብርሀን አየሁት ከድምፁ ውጪ ምኑም እሱን አይመስልም። ልብሱ ተቀዳዷል፣ ፊቱ ጠቁሮ ከሰል መስሏል፣ ፀጉሩ ተንጨባሯል፣ እላዩ ላይ ተፀዳድቶ መሬቱ ጭምር በሽንትና ሰገራ ተበክሏል። ዮኒ እኔ ልሰጠው ካሰብኩት ሞት በላይ በቁሙ ሞቷል... ልቤን ሽው የሚል የሀዘኔታ ጦር ወጋኝ። ወዲያው ደግሞ ልጄን የከዳኋት መሰለኝ... እየሮጥኩ ከቤቱ ወጣሁ... ልፍለፋው ከኋላዬ ይሰማኛል... እያለቀስኩ መኪናውን ከፍቼ ስገባ
"አደረግሺው ህያብ ገደልሽው" አለኝ
"ሞቷል እኮ ቢኒ የሞተን ሰው ድጋሚ እንዴት እገለዋለሁ" ድፍት ብዬ ተንሰቀሰቅሁ
"ቢኒ እባክህ ምንም ሰላም ሊሰማኝ አልቻለም ዮኒን ሆስፒታል እንውሰደው" ደረቱ ላይ ተኝቼ ለቀናት ከራሴ ጋ ስከራከርበት የነበረውን ሀሳብ ነገርኩት
"እኔ የማውቃትም የምወዳትም ህያብ ይቺ ናት ለጠላቷ ሳይቀር የምትራራ። አታስቢ የኔ ቆንጆ ዛሬውኑ እናደርገዋለን" እዛው ቦታ ተመልን ሄድን። ወደዛች ቤት ገባን አጠገቡ ዳቦ ቁጭ ብሏል። ለነፍሱ ያደረ ሰው እንደሚመግበው ገባኝ። መለፍለፉን አላቆመም እንጂ ተዳክሟል... ይዘናቸው የሄድነው ባለሞያዎች በግድ አንስተው ስትሬቸር ላይ አደረጉት... ከኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት ወደቀ፤ ቀልጠፍ ብዬ አነሳሁትና ዞር ብዬ ከፈትኩት በትልቁ ርዕስ "ፀፀት" ይላል። ከስሩ ደግሞ "ለማታዩኝ እኔ ግን በየቀኑ ለማያችሁ ለበደልኳችሁ ሁሉ" ይላል... ትርጉም ያለው ነገር ሊሆን ቢችልም ማንበብ አልፈለኩም... ሌላ ሸክም መሸከም አልፈልግም... እጄ ላይ ያለውን ሶስት ገፅ ወረቀት ቀዳድጄ ዱቄት አደረኩትና ለነፋስ ሰጠሁት ብትትንን... አምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ። ሰላም ተሰማኝ
አዳራሹ በእንግዶች ጢም ብሎ ተሞልቷል። ቃል የሚያገባቡን ቄስ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።
"በሀዘን በደስታዋ በህመም በጤናዋ..." ቢኒ ቃል ገባ እሱ ያለውን መልሰው እኔንም አስባሉኝ።
የጋብቻ ቀለበት ጣቴ ላይ አደረገልኝ እኔም እንደዛው አደረኩለት.....
ገና ወደሰውነት ቅርፅ ያልተቀየረው የአምስት ሳምንት ልጄ ደስ ብሏት/ብሎት ይሆን ሆዴን ዳበስኩት። የልጄ አባት ቢኒ ፈገግ ብሎ አየኝ
"ተመስገን" አልኩ በልቤ የማያልፉ የመሰሉኝ ሁሉ አለፉ... ዛሬ ደስተኛ ነኝ... ነገን አምላክ ያውቃል።
✨ተ ፈ ፀ መ ✨

#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
የድባለ አባት ኬድሮንን እንዳያት.. እጁን እንዳንከረፈፈ ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹ኬድሮን ምን ተፈጠረ…?ምን ሆንሽ ?›› እያለ ወንበሩን ለቆ ወደእሷ ቀረበ፡፡
ሴትዬዋ መለፍለፏን አላቆመችም….‹‹ምንድነች ማነች…? ታውቃታለህ እንዴ…?ነው ሚስትህ ነች የላከቻት..?››
‹‹አይ አይደለም…ተረጋጊ የጎረቤት ልጅ ነች.?››
‹ትሁና ..ነይ ውጪልኝ…ቤቴን ማንም እንዲደፍረው አልፈልግም …ከፈለክ ውጭ አናግራት ›› ብላ ክንዷን ይዛ ልትጎትታት ብትሞክርም ንቅንቅ ልታደርጋት አልቻለችም…ሴትዮዋ ግራ ግብቷት እራሷን አጠንክራ ደግመኛ ሞከረች….ግዙፍ የዋርካ ግንድ የማነቃነቅ አይነት ነው የሆነባት፡፡
‹‹ምንድነች ይህቺ ጉድ …ውስጧ ጋንኤል አለ እንዴ?››ስትል የድብአለ አባት በቆመበት ደንዝዞ ሚገባበት ጠፍቶት ኩምሽሽ አለ...የድብአለ አባት በእነኬድሮን ሰፈር ኬድሮን ከመወለዷ በፊት የገባ በመሆኑ ስለእሷ ታሪክና ሀሚቶችንም ጨምሮ በዝርዝር ስለሚያውቅ ነው የተጨነቀው…ሴትዬዋ ደግሞ ገና ወደ ደሎ ከተማ ከገባች 6 ወርም ያላለፋት በመሆኑ ስለ እንደዚህ አይነት ታሪክ ምንም ምታውቀው ነገር የላትም፡፡
‹‹ጋሼ ለአዲሷ ሚስትህ ስለእኔ አልነግርካትም እንዴ?፡፡››
ሰውዬው ልክ በጣም ሚፈራውን ባለስልጣን እንደሚያናግር ሰው አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ፡፡
በጥርጥሬ ልጅቷን አትኩራ እየተመለከተች‹‹ምንድነው ያልነገርከኝ…?ነው ልጅህ ነች…?›ስትል ጠየቀች ፡፡
‹‹አይ የእሱ ልጅ አይደለሁም…እናቴ በሬዱ ትባላለች፡፡ በሬዱ ዲንቃ….አባቴ ደግሞ ዳቢሎሰ ነው…እና ለአዲሱ ባልሽ መልእክት ለመናገር ነው የመጣሁት….ሚስትህ ልጆቾን ይዛ ወደሀገሯ ልትሄድ ነው..እኔ ደግሞ ድባአለ ጓደኛዬ ስለሆነ እንዲሄድ አልፈልግም…ማለቴ እውነቱን ለመናገር እኔ እንኳን ቢሄድ ብዙ ግድ የለኝም.. ግን እሱ እኔን ጥሎ መሄድ እንደማይፈልግ እያለቀሰ ነው የነገረኝ…እውነቱን መሆኑን ደግሞ አይኖቹን አይቼ አምኜዋለሁ፡፡ ስለዚህ እንዲሄዱ አልፈልግም…እንዳይሄዱ ደግሞ አንተ እሷን ይቅርታ ጠይቀህ ወደልጆችህ ትመለሳለህ፡
‹‹አንቺ ምን አይነት ጉድ ነሽ…በዚህ ዕድሜሽ ስለ እንዲዚህ አይነት ነገሮች ምኑን አውቀሽ ነው ምትዘባርቂው…ይሄኔ ቤተሰቦችሽ ጠፍተሸባቸው እየፈለጉሽ ነው…በይ አሁን ቤቴን ለቀሽ ወደቤትሽ ሂጂ››ሴትዬዋ ተንዘረዘረች …
የድባአለ አባት ምንም ለመናገር አልደፈረም፡፡
ኬድሮን መናገር ጀመረች..‹‹አንዳልሺው እሄዳለሁ....አሁን ሁለታችሁም ዘና ብላችሁ የጀመራችሁትን እራት ብሉ… ከዛ ስትተኙ ያልኩትን ባተፈፅሙ ምን እንደሚያጋጥማችሁ ቀድመ ማስጠንቂያ እንዲያሳያችሁ ለዳቢሎሱ አባቴ አሁን ነግሬዋለሁ…እና ምርጫውን የእናንተ ነው…እርግጠኛ ነኝ የዱብአለ አባት ነገ ለእራት ቆቅ ወይም ጅግራ አድኜ አመጣና ወደልጆችህ መመለስህን በማስመልከት አብረን እራት እንበላለን….አንቺም ሌላ ሚስት የሌለው ባል እንደምታገኚ እምነቴ ነው.››ብላ ፊቷን አዙራ ስትወጣ ሰውየው ከደነዘበት እንደመባነን ብሎ ‹‹ኬድሮን ልሸኝሽ ?መሽቷል እኮ›አላት፡፡
‹‹አይ ጋሼ እንደማልፈራ ታውቃለህ አይደል? ›
‹‹አዎ እሱስ አውነትሽን ነው፤ደህና እደሪ››ብሎ በቆመበት ሸኛት፡፡
እቤቱን ለቃ እንደወጣች ሴትዬዋ ተንደርድራ በራፏን ከቀረቀረች በኃላ ወደውሽማዋ ዞራ
‹‹ምን ጉድ ነው ?ማነች ይህቺ ልጅ….?ደግሞ የዳቢሎስ ልጅ ነኝ ትበለኝ እንዴ …?በእሷ ቤት ማስፈራራቷ ነው?ወላጆቾ በዳቢሎስ እያሰፈራሩ ነው ያሳደጓት መሰለኝ?››
‹‹እውነቷን ነው…እናቷ ከዳቢሎስ ነው የፀነሰቻት ተብሎ ይወራል›› ብሎ በመጀመር ሙሉ ታሪኳን ከመጀመሪያው አንስቶ በሚያውቀውና በሰማው መጠን ብትንትን አድርጎ አስረዳት….ሴትዬዋ ይበልጥ በነገራት ቁጥር ይበልጥ በፍራቻ እየተንዘፈዘፈችና እተንቀጠቀጠች ነበር..
‹‹ምን አይነት ጣጣ ውስጥ ነው የገባሁት..?እና ምን ይሻለናል…?››
‹‹ለማንኛውም አሁን እንተኛና.. ነገ የሚሆነውን አይተን እንወስናለን››
አልተከተራከረችውም…እንደቅዱሙ ጩሀቱም ወኔውም ከውስጧ ተሰልቦ ባዶ ሆኗል፡፡ ሹክክ ብላ ወደ አልጋው ሄደች፡፡ እሱም ተከተላትና እንደወትሯቸው ተቃቅፈው ግን ደግሞ በዝምታ ተኙ፡፡
ኬድሮን ቤታቸውን ለቃ ወደቤቷ በድቅድቅ ጨላማው ውስጥ ሰንጥቃ በምታሄደበት ጊዜ‹‹የት እንደሆንክ ማላውቀው አባቴ እንግዲህ ይሄንን ጉዳይ ቀለል ባለ መንገድ እድጨርሰው እርዳኝ….ማለት አሪፍ የሆነ አሳማኝ ህልም እንዲያዩ አድርግልኝ›.ካልሆነ ግን ታውቃለህ ሌላ ዘዴ እጠቀማለሁ…በዛ ደግሞ የሆነ ሰው ይጎዳል...እኔ እንኳን ማንም ቢጎዳ ብዙም ደንታ እንደሌለኝ ታውቃለህ ግን እናቴ ትከፋብኛለች...ለእሷ ስል ነው ደግና ጥሩ ሰው ለመሆን የምሞክረው እና አግዘኝ›በማለት መልእክት ይሁን ፀሎት ባለየለት ንግግር ነበር መልኩንም ሆነ ማንነቱን በቅጡ የማታውቀው አባቷን ፌበር እየጠየቀች ወደቤቷ የተመለሰችው፡፡ኬድሮን ብዙ ጊዜ ስለአባቷ ከሰው ጋር ስታወራ ዳቢሎስ ነው አባቴ ብላ በድፍረት የምትናገረው የእውነት እንደዛ ብላ ስለምታምን ሳይሆን እንሱ እንደዛ ብለው ስለሚያሟትና ከአንደበቷ አውጥታ ስታረጋግጥላቸው በፊታቸው ላይ የምታየውን ድንጋጤና በአካላቸው ላይ የምትመለከተው መንቀጥቀጥ ስለሚያረካት እና በእነሱ ላይ የበለጠ ኃይልና የበለጠ የበላይነት ስለሚያጎናፅፋት ነው፡፡
✨ይቀጥላል✨

#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሁሴንና ሰሎሞን ለመዝናናት ተያይዘው ወጥተዋል፡፡ቦታው ሃያ ሁለት አካባቢ ነው፡፡ ሠዓቱ ከምሽቱ 4፡45 ሆኗል፡፡ ያሉበት ጭፈራ ቤት በጠጪዎችና በቡና ቤት ሴቶች ተሞልቷል፡፡ በዲጄው ፍላጎት በሚለቀቁ ሙዚቃዎች የተወሠኑ ሠዎች ይውረገረጋሉ፡፡ ሠሎሞንና ሁሴን አንድ ጥግ ይዘው መጠጣቸውን ከጨዋታ ጋር እያወራረዱት ነው፡፡
‹‹ቆይ አንተ ጨክነህ እንደ እኔ ወንደላጤ ሆንክ ማለት ነው?›› ሁሴን ነበር ጠያቂው፡
‹‹ኧረ !!ትቀልዳለህ እንዴ! እስከዛሬም የተጃጃልኩት ለልጆቼ ስል ነበር፡፡››
‹‹ቆይ በቤተክርስቲያን ስርዓት አይደል እንዴ ያገባሀት? እና ዝም ብሎ መፋታት ይቻላል…?
ከምትፈራውስ ከፈጣሪ ጋርስ አያቀያይምህም?››
‹‹ዝም ብለህ አትበለኝ፤ዝም ብዬ አይደለም የፈታኋት፡፡ በእኛ ሀይማኖት ፍቺ የሚፈቀዱባቸው ሦስት መሰረታዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንደኛው ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት፣ ሁለተኛ ከሁለት አንዱ በዝሙት ኃጥያት ከወደቀ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ የማይድን የአዕምሮ በሽተኛ ሲኮን ነው፡፡››
ሁሴን ከአፉ ተቀበለው፡፡ ‹‹ገባኝ... ገባኝ... ታዲያ እኔ እስከማውቀው ድረስ ያንተዋ አልሞተች ወይም የአዕምሮ ህመምተኛ አልሆነችም የቀረው ዝሙት ያልከው ጉዳይ ደግሞ አንተም እየተንቦራጨክበት ነው፡፡ >>
‹‹ቢሆንም እኮ እኔ ወንድ ነኝ፡፡››
‹‹መፅሀፉ ለወንዶች ልዩ ፍቃድ ይሰጣል ማለት ነው?>>
‹‹ባክህ ነገር አታጣም፡፡ ያው እንደምታውቀው እኔ ሆነ ብዬ ሳይሆን አንዳንዴ ስጠጣና ስበሳጭ የምፈፅመው ስህተት ነው፡፡ ለዛውም ከቡና ቤት ሴቶች ጋር ነው፡፡ አንዴ ያወጣኋትን ሴት መልሼ እንደማልደግማት ታውቃለህ፡፡ ይሄንን የማደርገው ደግሞ ከማንም ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር እንዳይዘኝ ስለምፈራ ነው፡፡ እሷ ግን ሥጋዋንም ልቧንም ጠቅላላ እሷነቷንም ነው ያስረከበችው፡፡ ስለዚህ ለእኔ ምን ይተርፈኛል? ምንም … ፡፡ባዶ በድን ገላና የተራቆተ ልብ...
በቃ፡፡››
‹‹እኔ በበኩሌ ለውሳኔህ ያቀረብከው ምክንያት አላሳመነኝም፡፡ የሀይማኖቱን አላውቅም፡፡ በሞራል በኩል ግን ኢፍትሃዊነት ይመስለኛል፡፡››
ሠሎሞን ተበሳጨ <<አቦ በቃ ጨዋታ ቀይር፤ልዝናና ነው የመጣሁት፤በደስታ ልጠጣበት ፡፡››
ሁለቱም ፊት ለፊታቸው ያለውን የቢራ ጠርሙስ አነሱና ወደ ጉሮሮአቸው ካንቆረቆሩለት በኃላ መልሰው አስቀመጡ፡፡ አዲስ የጨዋታ ርዕስ ለማምጣት የቀደመው አሁንም ሠሎሞን ነበር፡፡
<<ለመሆኑ የመጽሀፉ ሽያጭ እንዴት እየሆነ ነው?>>
‹‹አትጠይቀን ባክህ ... የተአምር ያህል ነው፡፡ በቅርብ ሁለተኛ ዕትም ማሳተማችን የግድ ነው፡፡ በየጋዜጣውና የየሬዲዮ ጣቢያው መነጋገሪያ ርዕስም ሆኗል፡፡ የድርሰቱ ምርጥነት ብቻም ሳይሆን የደራሲዋ ማንነት አለመታወቅ ያልተለመደ ክስተት በመሆኑ መነጋገሪያ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽኦ ሳያደርግ አይቀርም፡፡››
‹‹ቆይ ደውላልህ አታውቅም?››
<<ማ? >>
‹‹ጣኦትህ ነቻ...ደራሲዋ?››
‹‹መፅሀፉ ከታተመ ወዲህ አንዴ ደውላልኝ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ስሜት የለሽ ሆና ነበር ያናገረችኝ፡፡ መቼም አንድ ጤነኛ ሠው የመጀመሪያ ልጁን ሲወልድ እንደሚፈነጥዝ ሁሉ አንድም ደራሲ የመጀመሪያ መፅሐፉ ሲታተምለት በደስታ መፍነክነኩ የሚጠበቅ ነው፡፡ እሷ ግን ደንታም የሠጣት አይመስለኝም፡፡ ስለ ሌላ ነገር ነበር የምታወራልኝ፡፡››
‹‹አሁንም ልታገኝህ አትፈልግም ማለት ነው?››
‹‹እሷን ለማግኘት አንድ አማራጭ ብቻ እንዳለ ነግራኛለች፡፡››
‹‹ምንድነው .. እንዴት አይነት አማራጭ?››
‹‹አልነገረችኝም...ትንሽ ታገስ አለችኝ፡፡››
‹‹አሁንስ አበዛችው…ቆይ እሷ እንደኛው ሠው አይደለችም እንዴ? ነው ወይስ የመላዕክት ዝርያ አለባት ይሆን?... ብቻ እኔን ለማየት አርባ ቀንና ለሊት ፁምእንዳትልህ!››
‹‹ምን ችግር አለው…እጾማለኋ፡፡ ጣኦቴ አይደለች? ሠው ለጣኦቱ ነፍሱንስ ለመስዋዕትነት ይለግስ የለ?››
‹‹ወይ ጉድ!! በሕወቴ ማየት እፈልግ የነበረው አንድ ነገር ያንተን በሴት ፍቅር ተንበርክከህ ስትንገላወድ ማየት ነበር፡፡ አንድ ቀን እንደሚሆን እምነቴ ቢሆንም እንዲህ መላ ቅጡ በጠፋ መልኩ ይሆናል ብዬ ግን ፍፁም ግምቱ አልነበረኝም፡፡ በነገራችን ላይ ይህቺ ደራሲህን ሳስብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ የመጽሐፍ ምረቃው ቀን ፎዚያን በጣም ስከታተላት ነበር፤ ስታነብ ታሪኩ የራሷ ይመስል ተመስጣ ነበር፡፡››
‹‹አዋ እኔም ያንን ታዝቤለሁ፡፡››
‹‹ቆይ የሥነ ጽሁፍ ችሎታ አላት እንዴ?››
‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ የላትም፤አንባቢ እንደሆነች ግን አውቃለው….ግን ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ የሆነ ጥርጣሬ ነገር በውስጤ ተጭሮ ነው፡፡ >>
ሁሴን ተንከትክቶ ሳቀ፡፡ ‹‹ደራሲዋ ፎዚያ ነች ልትል ነው?››
‹‹ነች አላልኩም፤ ተጠራጠርኩ እንጂ፡፡ አንዳንዴ በዚህ ዓለም ላይ ሊሆን አይችልም የምትለው ነገር ሆኖ ታገኘዋለህ…።››
‹‹እሱ ትክክል ነህ፡፡ ጥርጣሬህ ግን መሰረተ ቢስ ነው …፡፡›ንግግሩን ሳይጨርስ በዙሪያቸው ስትሽከረከር የቆየች አንዲት የ18 ዓመት ውብ ወጣት እጎናቸው ባለው ባዶ ወንበር ላይ ሳታስፈቅድ ተቀመጠች፡፡ እርግጥ ለመቀመጥ እንድትደፍር ያደረጋት የሰሎሞን ዓይኖች ለተደጋጋሚ ጊዜ መላ አካሏቷ ላይ ሲሽከረከር ደጋግማ ስለያዘችው ነው፡፡
በመኮሳተር ንግግሯን ጀመረች፡፡‹‹ቆይ እናንተ የመጣችሁት ልትዝናኑ ነው ወይስ የፓርላማ ውይይት ልታካሂዱ?›› ሁለቱም በአግራሞት አፍጥጠው ቢመለከቷትም መልስ ለመስጠት የቀደመው ግን ሲያፈጥባት የቆየው ሠሎሞን ነՈԸ::
‹‹እስከ አሁን ስትሰልይን ነበር እንዴ?››
‹‹ምን እሰልላችኋለሁ... ገርማችሁኝ እንጂ ፡፡ አሁንም እስቲ በደረቁ አታናዙኝ…ጋብዙኝ፡፡››
‹‹እዘዢ›› ሁሴን ነበር የፈቀደላት፡፡ አስተናጋጁን ጠርታ ቢራ አዘዘች፡፡
ሠሎሞን‹‹ቆንጆ ነሽ፡፡›› አላት ፡፡
ትላልቅ አይኖቿን አንከባለለችበትና ፈገግ ብላ ‹‹ሊበሏት ያሠቧትን ወፍ ጅግራ ነሽ ይሏታል፡፡›› አለ ያገሬ ሠው ስትል›› ተረተች
‹‹እንዴት ማለት?›› አላት ሠሎሞን፡፡
‹‹አይገባህም... ቅኔ አልተማርክም እንዴ?››
‹‹ተይው እሱ ስለ ስሚንቶና ድንጋይ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡›› የሁሴን ንግግር ነበር፡፡
‹‹ግምበኛ ነው እንዴ?›› ከቢራዋ እየተጎነጨች በፈገግታ ጠየቀች፡፡
‹‹ትክክል ነሽ..…የግንበኞች ሀለቃ ነው››
‹‹እሺ አንተስ?››
ሠሎሞን ብድሩን ለመመለስ ተሽቀዳደመ፡፡ ‹‹እሱማ ያው ወሬ ለቃቃሚ ነው ... ወሬ ይገዛል፤ ይሸጣል፡፡››
‹‹ኧረ... እኔ ጋር ብዙ ወሬ አለ፤ ለምን አትገዛኝም.. ? ግን ደስ የምትሉ ጓደኛሞች ናችሁ፤ተረባችሁ ደስ ይላል፡፡››
ሠሎሞን እጁን አንስቶ ጭኗ ላይ በማስቀመጥ ጨመቅ እያደረጋት ወሬውን ቀጠለ ‹‹ተረብ እኮ አይደለም ...እውነቴን ነው የወሬ ነጋዴ ነው ...እሱና መሰሎቹ ግን ለራሳቸው ቆንጆ ስም ሠይመዋል፡፡ ስራችሁ ምንድነው ? ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው ጋዜጠኛ ይላሉ… ።››
ሁሴን ተቀበለው፡፡ ‹‹ልክ እናንተም ስትጠየቁ ኢንጅነር እንደምትሉት ሁሉ፡፡››
‹‹በቃ ይበቃችኋል እኔ ስለማንነታችሁ በቂ መረጃ አግኝቼያለሁ፡፡››
‹‹ኮሚሽን እፈልጋለሁ፡፡›› አላት ሁሴን፡፡
<<ለምኑ?>>
‹‹አያያዙን ሳየው የሚለቅሽ አይመስለኝም፤ ታዲያ ስትደራደሩ ምን ያህል መክፈል እንደሚችል እንድታውቂ መረጃ ሠጥቼሻለሁ፡፡››
‹‹ባክህ ስንት ቀብቃባ ኢንጅነር አይተናል መሰለህ!!>>

#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/አማዞን ወንዝ ላይ
ዳግላስ ሚስቱ የሰጠችውን መድሀኒት ወስዶ ከተኛ ከሁለት ሰዓት በኃላ ነቃ፡፡አይኑን ሲገልጥ የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ ብቻዋን ነው ያለው፡፡ ከነቃም በኃላ አይኑን ብቻ ገልጦ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ባለበት ሆኖ 15 ደቂቃ አሳለፈ፡፡፡ከዛ ተነሳና በራፉን ከፍቶ ‹‹ማሪያ…ማሪያ እያ ተጣራ››ስሙ ሳያስበው ነው አፉ ውስጥ የገባለት፡፡ ሚስቱ ተንደርድራ መጣችን ፊቱ ቆመች፡፡ ወደራሱ ጎትቶ አቀፋትና ደረቱ ላይ ለጥፎ ከንፈሯን ለረጅም ደቂቃ መጠጣት፡፡እሷም እጆቾን ዘርግታ በአንገቷ ዙሪያ አሽከርክራ አቀፈችውና እላዩ ላይ ተንጠለጠለችበት፡፡
‹‹ማሪያ የእኔ ውድ ..አንጀሊናስ?››
‹‹ከእነ ሳንዲያጎ ጋር ነች፡፡እጇን ይዞ እየጎተተ ወደጀልባዋ በረንዳ ወጣ፡፡ሲደርስ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ አስፈሪ ጠባቂዎች ከየተቀመጡበት በድንጋጤ ተነሱና ቀጥ ብለው ቆሙ….አንጀሊና አባቷን ስታይ ወደእሱ ተንደረደረች…በአየር ላይ ቀለባትና ግራና ቀኝ ክንዶን ይዞ አሽከረከራት፡፡ መርከቡ ላይ ያሉት ሁሉ ደስ አላቸው፡፡አሁን እራሱን ዳግላስን ሆኖል ማለት ነው፡፡ከልጁ ና ከሚስቱ ጋር ሀያ ለሚሆኑ ደቂቃዎች በማሳለፍ በመጠኑ ናፍቆቱን ከተወጣ በኃላ እነሱን ወደውስጥ ገብተው እንዲጠብቁት አዞ …ቀጥታ መርከቡ ላይ ካሉት 5 ታጣቂዎች ጋር ስብሰባ ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ እየሰማዋችሁ ነው፡፡››
የታጣቂዎች ሀለቃ የሚመስለው ግዝፍ ሰው አንገቱን እንደደፋ መናገር ጀመረ‹‹ሀለቃ በተፈጠረው ነገር በጣም እናዝናለን፡፡በእውነቱ ችግሩ እንደተፈጠረ ስንሰማ ወዲያው ነበር እርምጃ የወሰድነው››
‹‹እኮ ምን አደረጋችሁ?››
‹‹ያው ብራዚሊያ አየር ማረፊያ ገብታችሁ ነበር… አንተ ወደፕሌኑ ማለፍ ብትችልም አብሮህ የነበረው ፓብሎ ግን በፖሊስ እጅ ወደቀ፡፡አንተን ማሳለፍ ቢችልም እሱ እራሱን ግን ከፖሊሶች እጅ ማስመለጥ አልቻለም፡፡እና ምንም ልንረዳው ባለመቻላችን…ጠበቀ ያለ ምርመራ ሲደረግበት ስለአንተ የሆነ ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ብለን ስለሰጋን እዛው የገባበት እስር ቤት እርምጃ እንዲወሰድበት አድርገናል፡፡
አንተን ወደ ብራዚሊያ ይዛ የሚበረው አውሮፕላን በአየር ፀባይ ምክንያት ኢኩዩቶስ እንደረፈ ስንሰማ እኔ እራሴ ነኝ አንድ ቡድን እየመራሁ በቻርተር አውሮፕላን ወደዛ ያመራሁት፡፡ከዛ ምን አልባት የመንግስት ሰዎች ሆኑ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች እጅ እንዳትገባ ተጠንቅቀን ከሆቴል ስትወጣ አፈነንህ ከኢኩዬቶስ አስወጣንህ፡፡
‹‹ጥሩ ስራ ነው….እርግጠኛ ነኝ ምንም ያዝረከረካችሁት ነገር የለም፡፡››
‹‹አረ የለም..ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ነው የተከወነው…ግን….››
‹‹‹ግን ምን?››
‹‹አንድ የአንተን ውሳኔ የሚጠብቅ ጉዳይ አለን፡፡››
‹‹ምንድ ነው?››
‹‹ልጅቷን ምን እናድረጋት …?ምን አልባት የምትለው ነገር ይኖራል ብለን..ወደ ዋናው ሳንቺዋሪ እየወሰድናት ነው፡፡አሁን ላቲሲያ ደርሰዋል፡፡ለሁለት ቀን እዛ ቆይተው…ወደሳንቹዋሪ ይዘዋት ይመጣሉ፡፡
‹‹ምንድነው የምታወራው ..?የቷ ልጅ?››
ሰውዬው አንዴ ዳግላስን አንዴ ደግሞ ወደመርከቡ የውስጠኛ በራፍ እያየ ለመናገር ጊዜ ወሰደ‹‹እየጠየቅኩህ እኮ ነው..የምን ልጅ?››
ድምፁን ቀነሰና …‹‹ሆቴል ስናገኝህ ከሆነች አፍሪካዊት ልጅ ጋር ነበርክ….፡፡ ከኤርፖርት አብራችሁ ወጥታችሁ ሆቴልም አንድ ክፍል ነው ያደራችሁት፡፡››ለምን ድምፁ ቀንሶ እንደሚያወራ አሁን ገባው፡፡ከሴት ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደሩን ሚስቱ ሰምታ ግርግር እንዳትፈጥር ነው፡፡አሱ ግን ያ ብዙ አላስጨነቀውም፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ..እንደዛ አድርጌለሁ?››
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ…ምን አልባት ስለአንተ ማንነት ያወቀችው ነገር ይኖር ይሆናል ብለን ስለሰጋን ልንለቃት አልፈለግንም፡፡››
‹‹እና አሁን ወደሴንቸዋሪ ከሚጓዘው ቡዱን ጋር እየወሰድናት ነው እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹አዎ፡፡››
‹‹ሽጉጥህን ስጠኝ ፡፡››ኮሰተር ያለ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ሁሉም በያለበት ሽምቅቅ አሉ፡፡ዳግላስ ሽጉጥ ስጠኝ ካለ የሆነ ችግር ሊፈጠር እንደሆነ ሁሉም ያውቃሉ፡፡ሽጉጥ እጁ ከገባ ይተኩሳል፡፡ሲተኩስ ደግሞ አየር ላይ አይደለም..ወይ አንዱ ደረት ላይ ወይ ደግሞ ጭንቅላት ላይ ነው የሚያሳርፈው፡፡በሚንቀጠቀጡ እጆቹ ሽጉጡን ከጎኑ መዞ ሰጠው…ግንባሩ ላይ ደቀነበት፡፡
‹‹እንዴት አንድ ምንነቷን የማታውቃትን መንገደኛ ሴት እየነዱ ወደግዛቴ ይዘዋት እንዲመጡ ትዕዛዝ ታስተላልፋለህ….?ምን ተልዕኮ እንዳላት ታውቃለህ…?ማን እንዳሰማራትስ?››
‹‹ጌታዬ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገናል…ሙሉ እቃዋን ሆነ ጠቅላላ ሰውነቷን አብጠርጥረን ፈትሸናል፡፡ አታስፈልግም ካልከን አሁን ባለችበት እንዲያስወግዶት ማድረግ እችላለሁ፡፡››በፍርሀት በራደና በሚንቀጠቀት ድምፅ ሊያስረዳው ሞከረ፡፡
‹‹አይ መጀመሪያ አንተን አስወግድህና ትዕዛዙን እራሴ አስተላላፋለሁ፡፡››የሽጉጡን መጠበቂያ አላቀቀ….እጠቱን ምላጩ ላይ አሳረፈ…በዚህ ቅፅበት ልጁ‹‹አባዬ…አባዬ›› እያለች የጀልባውን በራፉ ከፍታ ወደእሱ ተንደረደረች….ቶሎ ብሎ የደቀነውን ሽጉጥ ከሰውዬው ግንባር ላይ አላቀቀና ጠረጴዛ ላይ ወርውሮ ከተቀመጠበት በመነሳት ወደ ልጅ ተንደረደረ፡፡አቃፋትና አባበላት፡፡ዝም ስትል ወደ ታጣቂዎች ዞረና ትዕዛዙን አሰስተላለፈ‹‹ በሉ አሁን ጉዞ እንቀጥል፡፡ እስከአሁን ያባከነው ሰዓት ይበቃል ፡፡ዛሬ ካምፕ ገብተን ማደር አለብን፡፡››
‹‹እሺ ጌታዬ ..ልጅቷን በተመለከተ ትዛዙን ላስተላልፍ?፡፡››
እንደማሰብ አለና‹‹..አይ ያንን ዕድልማ አጥተኸዋል…አሁን እራሴ የሚሆነውን አደርጋለው፡፡››ብሎ ወደውስጥ ገባ…..ጀልባዋም ተንቀሳቀሰችና ጉዞ ጀመረች፡፡
ወዲያው ነበር እጃቸው ላይ ያለችውን ሴት ገድለው ማንም እንዳያገኛት አድርገው እንዲቀብሯት ላቲሲያ ለሚገኙት ገዳዬቹ ትዕዛዝ የስተላለፈው፡፡
ኮለምቢያ
/ላቲሲ(አማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች በአሳ ምርቶ የምትጣወቅ ከተማ) ካርሎስ ከገዳይ አጋሮቹ ፈንጠር ብሎ አንድ ግዙፍ ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ የቀን ውሎውንና ገጠመኞቹን በምጥን ቃላት እያሰፈረ ሳለ በቡድኑ ሀለቃ ተጠራ፡፡ማስተወሻ ደብተሩን አጣጥፎ ጎኑ ያለው የጉዞ ቦርሳው ውስጥ ከተተና መሳሪያውን በአንድ ተከሻው አንጠልጥሎ ቦርሳውን በእጁ ይዞ ወደተጠራበት ቦታ ሄደ፡፡
ቀጥታ ‹‹ግባና ግደላት፡፡››የሚል ትዕዛዝ ነበር የሰጠው፡፡
‹‹ምን ?››ካርሎስ ሀላቀውን በድንጋጤ ጠየቀ፡፡
‹‹ትልቁ ሀለቃችን ትገደል ብሏል…ግባና ግደላት፡፡››ኮስተር ብሎ በድጋሚ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡
‹‹እርግጠኛ ናችሁ ትገደል ብሏል?››
‹‹ሰውዬ ያምሀል እንዴ? እኔ የተሳሳተ ትዕዛዝ ሳስተላልፈ አይተሀኝ ታቃለህ..?ነው ወይስ ፈራህ?ከፈራህ ግድ የለም ሌላ ሰው በደስታ ያድርገዋል፡፡እኔ እኮ ስለምትወዳት በፍቅር እንድትገድላት እድሉን ልስጥህ ብዬ ነው እንጂ ሌሎች በደስታ የሚፈፅሙት ትዕዛዝ መሆኑን አጥቼው አይደለም …ምንም ቢሆን እሷን እዚህ ድረስ በማጓጓዙ ከአንተ እኩል የለፋ የለም፡፡››

#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡
‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››
‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››
‹‹እኮ ተነስና አድርግ››
‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››
‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››
‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››
ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡
‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡
‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››
‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ
‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኋላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው
ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡
‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ ፈራ ተባ እለች… ስልኳን ከተቀመጠበት አነሳችና ለመደወል ስትዘጋጅ ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››
‹‹አዎ ልጆች ሁላችሁም ተቀምጡ….ለሊሴ እስኪ ሲኒውን አቀራርቢና ቢና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ
‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሸት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም
‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››
‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››
‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››
ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››
‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››
‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››
‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››
‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››
‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››
‹‹ታዲያ ልግዛልሽ…ማለቴ በራስሽው ብር የምትፈልጊውን አይነት ስልክ ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››
‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››
‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››
‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››
‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››
‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ ነበር…አሁን ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው የምፈልገው
….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››
‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››
‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ
በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…

#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
ጭንቅ
ደጅ ፣ ደጁን አስሬ እየወጣች ትመለከታለች፡፡ የጣደችውን ቡና እየተንተከተከ ሳታነሳው አራት ሰዓት ሆነው፡፡
በህሊናዋ የተለያየ ሃሳብ እየተመላለሰ ረብሿታል፡፡ ምን ገጥሟቸው ይሆን ? እንዴው መኪና ተገልብጦ ይሆን? ከሰው ተጣልተው ይሆን? ነጋዴው አልመጣላቸው ይሆን ? ጥሩውንም መጥፎውንም ልቧ የገመተውንም ሁሉ እያወጣች እያወረደች ከራሷ ሃሳቧ ትሟገታለች፡፡
ኮሽ ባለቁጥር እየወጣች እየገባች እንቅልፍ የሚባል በአይኗ ሳይዞር ከአሁን አሁን ይመጣሉ እያለች ሌሊቱን ሳታምነው ቁጭ ብላ የማደር ያህል አነጋች፡፡ ጭንቀቱ ውሎም አድሮም አልተፋታትም፡፡
ተመስገንና ያሬድ ወሬያቸው እና ብቅታቸውም ሳይታይ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

አበበች ሃሳብና ጭንቀቷ እየባሰባት ቢሄድም መፍትሄ አላገኘችም፡፡ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
የቻለው አባት አለች፡፡ አቶ ጎሹን በበራቸው ላይ ከብቶች ይዘው ሲያልፉ ድንገት አይታ፡፡ ታዲያ አቶ ጎሹን የቻለው አባት ብላ መጣራቷ በልጃቸው ስም ስለምጠራቸው ነበር፡፡
አቶ ጎሹ የቻለው አባት ወደ አለው ድምፅ መለስ አሉ፡፡ "ጠራሽኝ ልበል" ? አሉ ፤ ለአበበች፡፡
አዎ ፤ እኔ ነኝ የጠራዎት፡፡ ብላ ቀኑም እረፍዶ ስለነበር ሰላም አረፈዱ የቻለው አባት" አለች፡፡
"ሰላም አረፈድሽ አበበች፡፡ ምነው ደህና አይደለሽም ኖሯል? አሏት፡፡ አይን አይኗን እየተመለከቱ፡፡
"አይ! እኔ እንኳን ደህናነኝ፡፡ ባለቤቴ ከተመስገን ጋር ውሎ ገባ እንመለሳለን ብለው ወደ ድሬደዋ ሄደው ነበር፡፡ ይኸው ውሎ ገባ ሳይመለሱ ሰነበቱ፡፡ አሁንም ብቅታቸውም ጠፋ፡፡ እንዴው የማደርገው ሲጠፋኝ ነው፡፡ እርሶዎን የጠራዎት" አለች፡፡ መሬት መሬት እየተመለከተች፡፡
አቶ ጎሹ ታዲያ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው፡፡ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም የሄዱበት ሳይሳካላቸው ቀርቶ አድረው ለመምጣት አስበው ይሆናል፡፡ ለማንኛውም ምንም ማሰብ ፣ መጨነቅ የለብሽም፡፡ ደግሞ ወንድ ልጆች ናቸው፡፡ አድረው ይገኛሉ፡፡ ሴት ልጆች ቢሆኑ እንኳን አድረው አይገኙም ይባላል፡፡ ማታ ሊመጡ ይችላሉ ብለው አፅናንተዋት ወደ ከብቶቻቸው ተመለሱ፡፡
አበበች የመለሱላትን የማፅናኛ መልስ በትንሹም ቢሆን ለመረጋጋት ሞክራ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ነጋዴው ሳይመጣ ቀርቶ ሰንብተው ይሆናል፡፡ ብላ በማሰብ ተመልሳ ወደ ቤቷ ገባች ፡፡
አበበች ማታ ይመጣሉ እያለች ስትጠብቅ የሷ ማታ ሳያልቅ ማታና ማታ ተደምሮ አምስት ማታ ቢሆንም እንኳን ያሬድና ተመስገን ሊመጡ አይደለም አየናቸው የሚል ሳታገኝ..ቆየች
ህልምነው ቅዠት ;
"አዎ ፤ ነግቷል ወፍ እየተንጫጫ ነው፡፡ ምነው ሰላም አላደርሽም እንዴ? አሉ፡፡ ቄስ መልካሙ ለባለቤታቸው፡፡ በሌሊት ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ እየተነሳሱ፡፡
"እንዴው ዛሬ ደግሞ ሲያቃዠኝ ነው ያደረው" አሉ ፤ ቄስ
"ኧረ ! እኔንም ሲያቃዠኝ ነው ያደረው፡፡ ያ ተመስገን ደህና አይደል ይሆን? ከያሬድ ጋር የምንሄድበት አለ ብሎኝ ነበር የሄደው፡፡ ማታ ይመጣል ብዬ ጠብቄው ነበር፡፡ ይሄው ሳይመጣ ዛሬ አምስት ቀኑን ያዘ" አሉ፡፡ አይናቸውን በሸማቸው እየጠራረጉ፡፡
"ከያሬድ ጋር ከሄደ ምን ይሆናል ፤ ብለሽ ነው?፡፡ ያሬድ ነጋዴም አይደል ፤ ምን አልባት አብሮት ይዞት ሄዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም እመቤቴ እንደፍቃዷ፡፡ እንግዴህ ቼር ነገር ታሰማን ፡፡ ዛሬ ደግሞ ተረኛ ገቢ ነኝ፡፡ ለቅዳሴ ሳይረፍድብኝ ልሂድ ፤ አንችም ተመስገን ካልመጣ ለከብቶቹ የሚበላ ፤ የታሰሩበት ስጫቸው፡፡ ስመለስ ውሃ አጠጣቸዋለሁ፡፡ ብለው ነጠላቸውን ለባብሰው ፤ ዘንጋቸውን ይዘው ፣ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሄዱ፡፡
"እንዴው ዛሬ ደግሞ ምን ልታሰማኝ ይሆን ? ውስጤ የሚረበሸው ፣ እንግዴህ እመብርሃን አንች ታውቂያለሽ ፡፡ ያለዐንች ማን አለኝ እያሉ የጥዋት ፀሎታቸውን በቤታቸው የእንጨት ምሰሶ ስር በፊታቸው ተደፍተው የሚወዷትን የአገራቸውን ታቦት ጥሩ ነገር እንድ ታሰማቸው ተማፀኑዋት፡፡
ከተንበረከኩበት የእንጨት ምሰሶ ስር ተነሱ፡፡ ቤታቸውን በዶዶሆ ቅጠል ጠረግ ፣ ጠረግ አደረጉ፡፡ የሳር ድርቆሽ ከዓውድማ አምጥተው ለከብቶቻቸው ሰጡ፡፡ ሲያቃዣቸው ያደረውን ህልም ይሁን ቅዠት በሃሳባቸው እያወጡ እያወረዱ ለመፍታት ይግተረተራሉ፡፡ አንዴ በጥሩ ፣ አንዳንዴ በመጥፎ ፣ እየፈቱ እንደገና ደግሞ ህልም እንደፈችው ነው እያሉ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ይከራከራሉ፡፡
ታዲያ ወ/ሮ አሰገደች ሳይታወቃቸው ሰዓቱ እረፍዷል፡፡ ቁርስ እንኳን ሳይቀምሱ ባለቤታቸው ከቤተክርስቲያን የመምጫቸው ሰዓት ተቃርቧል፡፡
ቄስ መልካሙ ከቅዳሴ እንደ ወጡ ዛቲ ቀምሰው ለምዕመናኑ አሳርገው ፣ ከብቶቻቸውን ውሃ የሚያጠጣላቸው ስለሌለ ፣ እንዳይረፍድባቸው ሰንበቴያቸውን ቀምሰው ገበታ እንደተነሳ ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
ከብቶቻቸው ከማሰሪያቸው ሳይፈቱ ደረሱ፡፡ የተሰጣቸውን የሳር ድርቆሽ መብላታቸውን ትተው ቆመዋል፡፡ ያ! ተመስገን አልመጣም ማለት ነው፡፡ ቢመጣ ከብቶቹን ውሃ ያጠጣቸው ነበር እያሉ ወደ ቤት ገቡ፡፡
"ዛሬ ደግሞ ሰንበቴ ሳትገባ ነው እንዴ የመጣኸው"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡
"አልቆየሁም ፤ እንጅ ደረስ ብያለሁ፡፡ ከቅዳሴም ስንወጣ አረፈድን ፤ ዝክርና ክርስትና ስለነበር ፤ሰንበቴ ቶሎ አልገባንም፡፡ ብለው ተመስገን አልመጣም እንዴ"? አሉ፡፡
"እስከ አሁን አልመጣም፡፡ እኔም አበበች ጋር ሄጀ እጠይቃለሁ ብዬ ነበር፡፡ ከቤትም ሳልወጣ እየተንደፋደፍኩ ምንም የረባ ስራ እንኳን ሳልሰራ አንተም መጣህ"፡፡
ከብቶቹን ላጠጣና እስከምመለስ ካልመጣ አይተን እኔ አበበች ጋር ሄጄ እጠይቃታለሁ፡፡ ብለው ከብቶቻቸውን ከታሰሩበት ፈትተው ውሃ ለማጠጣት ወደ ወንዝ ወረዱ ፤ ቄስ መልካሙ፡፡
ወ/ሮ አሰገደች ባለቤታቸው ከወንዝ እስኪመለሱ ቡና አፍልተው ጠበቋቸው፡፡
ከብቶቻቸውን አጠጥተው ተመለሱ፡፡ የጤፍ ጭድ የሚበላ ሰተው ፈልቶ የጠበቃቸውን ቡና ከባለቤታቸው ጋር እየጠጡ ነው፡፡
እንዴው ያ! ማንደፍሮ የሚሸጥ ባህርዛፍ አለ ብሎኝ ነበር፡፡ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን አግኝቸው እጠይቀዋለሁ ብዬ ሳልጠይቀው እረሳሁት፡፡ አሁን ደረስ ብዬ ልምጣ መሰለኝ ፡፡
"እንዴ! ቅድም አበበች ጋር ሄጀ እመጣለሁ አላልከኝም?፡፡ እማንደፍሮ ጋር በሌላ ቀን አይደርስም"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡
"ምን ያህል እቆያለሁ፡፡ በቁሜ ደረስ ብዬ የሚሸጠውን ባህርዛፍ አይቼ ቶሎ ስመለስ እሄዳለሁ፡፡
ታዲያ ቄስ መልካሙ ባለቤታቸው ያሉትን ለጊዜው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ተነስተው ወደ ማንደፍሮ ቤት አቀኑ፡፡
ወ/ሮ አሰገደች ከአዳራቸው አንስተው ቀኑን ሁሉ ውስጣቸው ሲረበሽ መዋሉ እረብሿቸዋል፡፡ ልጀ ምን ሆኖ ይሆን ? እንዴው ከቤት እንኳን ወጥቶ አያውቅ፡፡ ከያሬድ ጋር ከተማ መሃል ተጠፋፍተው ይሆን ? ክልብ ክልብ ሲል መኪና ባልገጨብኝ ብቻ፡፡
ለአስር ዓመታት የተለየቻቸውን ብርቅየ የአንጀታቸው ክፋይ የሆነችው ልጃቸውን እድላዊትን ወደ ኋላ፤ ተመልሰው አስታወሱ፡፡ እንባቸው በሁለቱም አይኖቻቸው ግጥም አለ፡፡ ለመመለስ በውስጥ
ቀሚሳቸው ጠራርጉት፡፡ ከአንጀታቸው የመጣ እንባ መመለስ ግን አቃታቸው፡፡ በተቀመጡበት እንደ እንኳይ ኮለል እያለ እንባቸው ይዘረገፍ ጀመር፡፡
ቄስ መልካሙ ቆይተው ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ከአመት በኃላ
አላዛር በግንባታው ዘርፍም በፍጥነት እየቀናውና እያደገ ሄዶ በሁለት አመት የኮንስትራክሽን ስራው ደራጃ -4 መድረስ ቻለ፡፡በስራ ዓለም ብቻ ሳይሆን እህቶቹንም በማገዝ የተዋጣለት ነበር …አንደኛዋን አህቱን ደግሶ ጥሩ የሚባል ትዳር ሲያሲዛት ሌለኛዋን ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እያስተማራት ነው፡፡
…በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሰሎሜን አግቢኝ ብሎ ለመጠየቅ በተሻለ ብቃት ድፍረቱን ማሰባሰብ የጀመረው፡፡እንደውም ይሄንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በጣም ቆይቶል፡፡ከአመት በፊት ሁሴን ጨርቄን ማቄን ሳይል ወደውጭ እንደሄደ ነበር ወዲያው ሊያደርገው የወሰነው፡፡ግን ቆይ ከዛሬ ነገር ሲል…መጀመሪያ ይህቺን ነገር ላሞላ ብሎ ከራሱ ጋር ሲሟገት ከአመት በላይ ጊዜ ፈጀበት፡፡አሁን ግን አግቢኝ ብሎ ሰሎሜን ለመጠየቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሁኔታዎች ጠቅላላ ለእሱ ያደሉ እየሆኑ ነው ፡፡
እስከአሁን በዋናነት የያዘው ከበፊት ጀምሮ ሰሎሜን ካገባው በኃላ አኖርበታለሁ ብሎ ያልም የነበረውን አፓርታማ እስኪገዛ ድረስ ነበር፡፡ያንን ለማድረግ ለሶስት አመት ያህል ወገቡን አስሮ ገንዘብ ማጠራቀም ነበረበት ..አሁን ግን ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ገንዘቡም ሞልቶለት ውብ የሆነ አፓርታማ ገዝቶ በእጁ አስገብቷል፡፡
አሁን እዛ ኮንደሚኒዬም ቤት ውስጥ የሚኖረው ከእሷ ላለመለየት ብቻ ብሎ እንጂ በቅርብ የገዛውን አፓርታማ ቤት የሚስተካከለውን ነገር ቶሎ አስተክሎ ወደዛው መዘዋወር ይችል ነበር፡፡ ፡፡ለጊዜው ግን አፓርታማውን ባለበት አቆይቶ የእሷ ጎረቤት ሆኖ መኖሩን ቀጥሏል፡፡
ሁለተኛ እሷን እንዲጠይቃት ገፊ ምክንያት ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ እሷን የራሳቸው ለማድረግ አብረውት ሲፎካከሩት የነበሩት የእሱም የእሷም ምርጥ ጓደኞች በከተማው አለመኖር ነው፡፡
ሁሴን ለትምህርት ከአገር ውጭ የወጣበት አለማየሁ ደግሞ ፖሊስ ሆኖ ተመርቆ የት እንኳን እንደተመደበ የማያውቅበት ጊዜ ላይ ነበር፡፡እናም በዚህ ጊዜ እነዚህ ሁለት ተፎካካሪዎቹ እስከወዲያኛው ከመንገዱ ገለል እንዳሉ እርግጠኛ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች የእሷ ብቸኛ ጓደኛ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚ ላይ በመገኘቱ ክፍተቱን ለመጠቀም ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነ አእምሮውም ሆነ ልቡ በእኩል ተስማምተው እየጨቀጨቁት ነው፡፡
ሌላው እሱ ቢዝነሱ ሁሉ መስመር ይዞ በኢኮኖሚ ጠንክሮ የካማፓኒ ባለቤት እና የብዙ ንብረት ባለቤት መሆን ችሏል ፡፡ በተጨማሪም እሷ ስራ አጥታ ካፌ በአስተናጋጅነት እየሰራች ብስጭት የምትልበት ጊዜ ላይ በመሆኗ ግራ ቀኙን አመዛዝኖ እሺ እንድትለው የሚያግዙትን ሌሎች እርምጃዎችን ቀድሞ ለማድረግ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ሁለት ጥንዶች ወደጋብቻ ከሚገብባቸው ዋነኛው ምክንያት መካከል አንድ በመካከላቸው የተፈጠረውን ጓደኝነት እድሜ ለመስጠት እና በመካከላቸው የበቀለውንም ፍቅር አድጎና አብቦ ፍሬ እንዲያፈራና እንዲጎመራ ለማድረግ ነው፡፡በዚህ ሰበበ-ምክንያት ጥንዶቹ ወደጋብቻ ከገቡ በኃላ አንዳቸው ለአንዳቸው ረጅም ጊዜ ይሰጣጣሉ፤ስሜታቸውን በተሻለ ግለት ይጋራሉ፤ በጋራ ስቀው በጋራ ያለቅሳሉ፡፡ለዚህም ሲሉ በጋብቻ እቅፍ ውስጥ አንድ የፍቅር ብሉኮ ለሁለት ለብሰው ህይወት በመደጋገፍ ይስኬዱታል፡፡
ሌላው ጥንዶች ወደጋብቻ የሚገቡበት ሁለተኛው ምክንያት ለህጋዊ ጉዳዬችና ለጥቅማ ጥቅም ሲሉ ነው፡፡ሁለት ጥንዶች ፤ከመንግስት ለሚያኙት ጥቅማ ጥቅም ሲሉ፤ለሚያገኙት ውርስ ሲሉ፤ከፖለቲካ ለሚያገኙት ተርፍና ክብር ሲሉ ወደጋብቻ ሊገቡ ይችላሉ፡፡በሶስተኛ ደረጃ ለጋብቻ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ልጆችና ቤተሰብ ለማፍራት ሲባል ነው፡፡አንዳንድ ተጣማሪዎች በግላቸው በነበራቸው ጉዞ በህይወት ሁሉ ነገር ይሳካላቸውና ግን ደግሞ ዘራቸውን ተክተው ለማለፍ ወይም ያላቸውንን ንብረት ወይም ሌጋሲያቸውን ሚወርስ ልጅ እንደሚያስፈልጋቸው ትዝ ሲላቸው..ያንን ለማግኘት አቅደው ወደጋብቻ ይገባሉ፡፡ ልጆች ለመውለድና ቤተሰብ ለመሰረት ሲሉ፡፡በአራተኛ ደረጃ እንደምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ ለሀይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ጉዳዬች ሲባል የሚደረግ ጋብቻ ነው፡፡ሁለት ተመሳሳይ ሀይማኖት ወይም ባህላዊ እሴት የሚጋሩ ጥንዶች ምንም እንኳን በመካከላቸው ወደትዳር አንደርድሮ የሚከት የፍቅር መሳሳብ ባይኖርም በሀይማታዊ ጉዳዬች ምክንያት ወይም በባህላዊ መንገድ በቤተሰቦቻቸው ፍቃድ ብቻ ወይም በጎሳ መሪዎቻቸው ልዩ ትዕዛዝ ወደጋብቻ ሳያቅማሙ የሚገብበት አጋጣሚ አለ፡፡በአሁኑ ዘመን በብት የሚተገበረው አምስተኛው ምክንያት ደግሞ
እራስን ለማሻሻል የሚደረግ የጋብቻ አይነት ነው፡፡ውጥረት በበዛበት በዘመናዊው አለም በተለይ በተጨናነቁ ዋና ከተሞች የሚኖሩ ጥንዶች በመካከላቸው የተወሰነ መግባባት ከተፈጠረ..አስቸጋሪውን የኑሮ ዳገት ተጋግዞ ለመግፋትና ወደፊት ትንሽ ፈቅ ለማድረግ ሲሉ ወደጋብቻ የሚገቡበት አጋጣሚ የተለመደና በቁጥርም ቀላል የሚባል አይደለም…የቤት ኪራይ ወጪ ለመጋራት…የቤት ውስጥ የስራ ጫናን ለመተጋገዝ፤አብሮ በመረዳዳት ወደተሻለ ህይወት ለመሸጋገር ሲባል በመነጋገርና በመደራደር ወደጋብቻ ተያይዞ ይገባል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ለጋብቻ ገፊ ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋኖቹ ናቸው እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም..ደግሞም አንድ ሰው ለአንዱ ምክንያት ሲል ወደጋብቻ ሲገባ ሌሎቹን ፈፅሞ አይፈልጋቸውም ወይም አያገኛቸውም ማለት ሳይሆን ዋና ትኩረቱንና ከጋብቻው ጥምረት በዋናነት ሊያተርፍ የሚፈልገውን ነገርን ለመግለጽ ነው፡፡ለልጆች ብሎ ወደጋብቻ የገባ ሰው..ልጁንም ፤በሂደት ደግሞ ከመቀረረብ ብዛት ፍቅርንም…ከዛም አልፎ ተጋግዞ ከመስራትና ተሳስቦ ከመኖር ብዛት የተሻለ ህይወትንም ሊያገኝ ይችላል፡፡
አላዛርም ሰሎሜን ሊያገባ የፈለገበት ዋናውና አንገብጋቢው ምክንያት ለእሷ ያለውን ፍቅር ለዘላለም ለመንከባከብና ለመጠበቅ ሲል ብቻ ነው፡፡በዋናነት በአእምሮው ያለው ምክንያት ያ ነው፡፡ቢሆንም ግን ከእሷ ምርጥና ተወዳጅ ልጆችን ማግኘትም ይፈልጋል…እሱ ከቤተሰቡ ያለገኘውን ፍቅርና እንክብካቤ ከእሷ ጋር ለሚመሰርተው አዲስ ቤተሰብ መስጠትና ለልጆቹ ምርጥና ተወዳጅ አባት ለእሷ ደግሞ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ አባወራ መሆን መቻሉን ማረጋገጥ ይፈልጋል….በኑሮ እንድትረዳውና እንድትደግፈው ፍጽም አይፈልግም…ይልቅ በተቃራኒው ለዘላለም እንደንግስት ሊንከባከባትና ሊያቀማጥላት ነው ምኞቱ፡፡አዎ ሊያነግሳት ነው የሚያገባት፡፡
አዎ በእቅዱ መሰረት ቅድሚያ የሚደረጉ ነገሮችን አድርጎ እንደሚያፈቅራት ነግሯት እንድታገባው ቢጠይቃት .. ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ልታቅማማ ብትችልም ጨክና እምቢ ልትለው እንደማትችል ጠንከር ያለ እምነት አድሮበታል፡፡…
ሰሎሜን ደወለና ቀጠራት፡፡አዲሱ ሰፈራቸው የሚገኝ በብዛት አዘውትረው የሚጠቀሙበት ካፌ ቁጭ ብሎ ስለእሷው እያሰበ ስክትመጣ እየጠበቃት ነው፡፡ከመንገድ ማዶ በሩቁ ወደእሱ ስትመጣ ሲያያት ነው ውስጡ በደስታ የተተራመሰው፡፡እንደቀረበችው ከመቀመጫው ተነሳና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡እሷ ፊት ለፊቱ ስትቀመጥ የጥዋት ፀሀይ ወጥታ ሰውነቱን እየዳበሰችው እንዳለ ህፃን መላ ሴሎቹ ይነቃቃሉ፡፡አላዛር ሰሎሜን ዛሬ እንዲህ አብባ እና አሽታ ሲያያት ይደንቀዋል፡፡እንደልጅነታቸው ሊቀርባት ሊያቅፋት ሊስማት ሁሉ ይመኛል፡፡ግን ደግሞ ይፈራል፡፡በዚህም ረጅም ብስጭት ይሰማዋል፡፡

#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ከአስር ቀን በኃላ ያሉት ባለስልጣን ከሳምንት በኃላ ደወሉለት..አልጠበቀው ነበር፡፡‹‹ሚካኤል አንድ ጥሩ ዜና አለኝ››
‹‹ምንድነው ጌታዬ?››በጉጉት ጠየቀ፡፡
‹‹ነገ ሰባት ሰዓት ላይ አባትህን እንድታገኝ ከእስርቤቱ አስተዳዳሪ ፍቃድ አግንቼልሀለው፡፡››
‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው›..እግዜር ይስጥልኝ››
‹‹አዎ በሰአቱ ሂድና…ቀጥታ አሁን በምልክልህ ስልክ እዛ እንደደረስ ደውልለት… አስተዳዳሪው ራሱ ይቀበልህና ሚሆነውን ያደርጋል….ሌሎች ነገሮችን እየሰራሁባቸው ነው….እስከዛው በዚህ ተፅናና…››
‹‹እሺ ጌታ ..በጣም ነው የማመሰግነው››
ስልኩን ዘጋና በደስታ ዘለለ…ልጇን እያጠባች ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው አዲስአለም ..‹‹ምን ተገኘ..ሎቶሪ ወጣልህ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹በይው…ነገ አባዬን እንድጠይቀው ተፈቀደልኝ››
‹‹በእውነት..በጣም ደስ ይላል››
‹‹አዎ….ምንድነው ይዤለት የምሄደው…..?››ሲል ከፈንጠዝያው ሳይወጣ ጠየቀ፡፡
‹‹አንተ ምን አልባት ቅያሪ ልብስ የላቸውም ይሆናል..ልብስ ምናም አዘጋጅ..እኔ ደግሞ የሚበላ ነገር አዘጋጃለው፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ ..የእኔ ማር በጣም ደስ ብሎኛል….››
‹‹ደስ ይላል..ግን ያው አባትህ እስር ቤት ከገቡ ጀምሮ ልትጠይቃቸው በሄድክ ቁጥር በምን አይነት አቀባበል እንደሚቀበሉህ ታውቃለህ…እንዲህ በመፈንጠዝ ሄደህ በኃላ አላናገረኝም….መጥተህ አትጠይቀኝ አለኝ…ምናምን ብለህ እንዳትበሳጭ››ስትል ስጋቷን ገለፀችለት፡፡
‹‹አረ…የፈለገ ይበል እኔ አይኑን ማየት ብቻ ነው የምፈልገው….ከፈለገ ለምን ልትጠይቀኝ መጣህ ብሎ በቡጢ አይነርተኝም ..ግድ አይሰጠኝም››
አሳዘናት…‹‹ሁሉም ሰው ምናለ እንዳአንተ ሰው ወዳጅና ሌላውን የሚረዳ ቢሆን››ስትል በውስጦ አሰበች‹አይ እንደዛ ከተዘጋጀህ ጥሩ››አለችው፡፡
‹‹በቃ ወጣው ….በዛው ለአባዬ የሚሆን ልብስ ገዛዛለሁ››ብሎ ሚስቱን ጉንጯን ልጁን ግንባሩን ሳመና ወጥቶ ሄደ፡፡
ሚካኤል ለአባቱ ልብስና የሚበሉ የተለያዩ ትኩስ ምግቦችን ተሸክሞ ልክ በተባለው ሰዓት ወህኒ ቤት ጊቢ ደርሶ ስልኩን ደወለ፡፡
‹‹ሄሎ ኩማንደር …ሚካኤል ነኝ…ቀጠሮ ነበረኝ፡፡››
‹‹እ ሚካኤል ….ጥበቃ ላይ ካሉት ፖሊሶች አስርሀለቃ ላቀው በልና ንገረው …ነግሪዋለው ወደእኔ ይዞህ ይመጣል፡፡››የሚል አስደሳች መልስ አገኘ፡፡
‹‹እሺ ኩማንደር አመሰግናለው››
ስልኩን ዘጋና ፊት ለፊቱ ያለውን ፖሊስ ‹አስር ሀለቃ ላቀውን› እንዲያሳየው ጠየቀው….እዛው በቅርብ የነበረ ፖሊስ ጠቆመው፡፡ማንነቱን ለፖሊሱ ነገረና ..ለአባቱ ይዞ የመጣውን እቃ እንዲያስረክ ካደረገ በኃላ ቀጥታ ወደኮማንደር ቢሮ ይዞት ሄዳ፡፡ፖሊሱ ክፉሉን ቆርቆሮ ከፍቶ አስገባውና መልሶ ሄደ፡፡
ሲገባ የገጠመው ግዙፍና ግርማ ሞገስ ያለው ቢሮ ነው፡፡እዚህ ቀፋፊ ወህኒ ቤት ውስጥ እንዲህ አይነት የሚያምር ቢሮ ይኖራል ብሎ ገምቶ አያውቅም፡፡ፀጉራቸው ሙሉ በሙሉ ቀለሙን ቀይሮ ነጭ የሆነው ግዙፉ ጠይም ቆፍታምና ሰው ከግዙፉ ጠረጴዛ ኃላ ባለ የቆዳ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው ይታያሉ….በጎርናና እና ሻካራ ድምጻቸው ‹‹ግባ አቶ ሚካኤል…..››አሉት
ሄደና ወደእሳቸው ቀርቦ ለሰላምታ እጁን ዘረጋላቸው…በመጠኑ ከመቀመጫቸው እንደመነሳት አሉና እጃቸውን ዘርግተው ጨበጡትና‹‹ተቀመጥ አቶ ሚካኤል›
እሺ ብሎ አንዱን ወንበር ሳበና ተቀመጠ‹‹ኩማንደር ስለአስቸገርኩት ይቅርታ….ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለሆነብኝ ነው››ሲል ተናገረ፡፡
‹‹ይገባኛል…እንደውም ጥሩ ልጅ ስለሆንክ መመስገን አለብህ…መቼስ ማረሚያ ቤታችን በአባትህ ላይ የወሰደው አቋም ለምን እንደሆነ ይገባሀል አይደል?አዎ ይገባሀል እንጂ …በእኛ ልትበሳጭ ፍፅም አትችልም፡፡››
‹‹አዎ በትክክል ይገባኛል….››ሲል በአጭሩ መለሰ፡፡
‹‹አሁን ያው ከአንተ ጋር እየተነጋገርን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንሞክራለን….ዋናው አንተ አባትህንን ምን ያህል ?ማገዝ ትፈልገለህ የሚለው ነው››አሉና ፈገግ ብለው በሲጋራ የበለዘ ጥርሳቸውን አሳዩት፡፡
‹‹ኮማንደር አባቴ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት መሞቻ ቀኑን የሚጠብቅ ሰው ነው…እና ያ ቀን አስኪደርስ ድረስ በተቻለ መጠን በተመቻቸ ሁኔታ እንዲያሳልፍ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ ነኝ፡፡አባቴ ይሄንን ቀፋፊ ወንጀል ሰርቶ ወህኒ ቤት ከመግቱ በፊት ለቤተቡ አይደለም ቸገረኝ ላለ ሰው ሁሉ ልብ የሚያዝንና እጁ የሚፈታ መልካምና የተከበረ ሰው ነበር…..ምንም ሆነ ምንም ፍፃሚዊ እንዲህ አሳዛኝ መሆን የለበትም፡፡
‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ ማድረግ ይምንችለውን ሁሉ እናያለን፡፡››አሉን ወደፊት ተንጠራርተው መጥሪያውን ተጫኑ..አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠ…‹‹ሳጂን ታራሚ ቅጣውን እዚህ አስመጣልን››ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ
ፖሊሱ ትዕዛዙን ተቀበለና ተመልሶ ወጥቶ ሄደ….ከ5 ደቂቃ በኃላ እስከአሁን ያለሳተዋለው በኩማንደሩ መቀመጫ በቀኝ በኩል የምትገኝ ጠበብ የጀርባ በራፍ ተቆረቀረ…ኮማንደሩ ዝርጥት ሰውነታቸው እየከበዳቸው በመከራ ተነሱና በራፉ ከውስጥ ከፍተው ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ አይኖቹን የተከፈተው በራፍ ላይ እንደተከለ መጠበቅ ጀመረ…ሰው ከማየቱበፊት ብረት ቅጭልጭልታ በጇሮው ሞላ..…ከዛ በተቀመጠበት ደንዝዞ ቀረ..አባቱን ከስድስት ወራት በፊት ነው ያየው…ሰው በስድስት ወር በዚህ መጠና ሊቀየር እንደሚችል ግምቱ የለውም ፡ፀጉሩ ተንጨፍርሮ ተንጨፍርሮ ጉድሮ ሆኖ ግንባሩ ላይ ተደፍቷል…ፂሙ አድጎ ግማሽ ፊቱን ሸፍኖት ያረጀ አንበሳ አስመስሎታል…ከመክሳቱ የተነሳ ሁለቱ ጉንጮቹ አንድ ላይ የተጣበቁ ይመስላል፡፡አይኖቹ ጥልቅ ጉድጓዱ ውስጥ ያሉ ደማቅ አንፖሎች ነው የሚመስሉት…ሚካኤል እንባው ዝርግፍ አለ..ኮማደሩ ከተቀመጡበት ተነሱና ..ለብቻችሁ ጊዜ ልስጣችሁ..አንድሰዓት አላችሁ……በፊት ለፊተኛው በራፍ ክፉሉን ለቀውላቸው ወጡና ከውጭ ቀርቅረውባቸው ብቻቸውን ተዋቸው…
እንደምንም እራሱን አበረታቶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደአባቱ ሄደ…ልጅ እያለ ባለግርማ ሞገሳሙ አባቱ ወደ ቤት መምጣቱን የሚያውቀው የመኪናውን ክላክስ ሲሰማ ነበር..ካዛ ከወንድሙ ጋር ሮጠው ከቤት ይወጡና ወደእሱ ይንደረደራሉ…ከዛ ለልጆቹ የገዛላቸውን ፍራፍሬ ወይም ሌሎች ጣፍጭ ነገሮች የያዘ ፔስታል ይዞ ከመኪናው ሲወርድ እሱን ጨምሮ ሶስቱም ልጆቹ በሽሚያ አንዱ ቀኝ እግሩን ሌላው ግራ እሩን ያቅፍትና በልዩ ፈንጠዝያ ይቀበሉታል…እሱም ስራቸው ይንበረከክና አንዱን ጉንጩን ሌላዋን ግንባሩን እያሳመና እየዳበሰ ይዞቸው ወደቤት ይገባል…አባትዬው ለልጆቹ እንስፍስፍ የሚባል አባት ነበር..በተለይ ዬቱ ታላቅ የሆነችውን ሴት ልጁን በልዩነት ንው የሚወዳት…እሷም በአባቷ በምንም አይነት ሁኔታ የማትደራደር የእሱ ተመራጭ ልጅ ነበረች…እና እንደዛ ኩሩና ሽቅርቅር የነበረው አባቱ አሁን አፅሙ ብቻ ነው ያለው..ሄዶ በፍራቻ ተጠመጠመበት.. ጠረኑ ወደኃላ ይገፋተራል…አባትዬው ምንም አይነት ምላሽ አላሳየውም..እየጎተተ ወደወንበሮቹ ወሰደውና አስቀመጠውና ከፊት ለፊቱ ተቀመጠ፡፡
‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››
ለእሱ መልስ ከመስጠት ይልቅ ‹‹ለምን እንደዚህ አደረክ?››ሲል አንቧረቀበት፡፡
‹‹ማለት? ምን አደረኩ?››ምን ስህተት እንደሰራ ባለማወቅ በፍራቻ ጠየቀ፡፡
‹‹ለምን አገኘኸኝ..?እንዴት እንደተቀጣሁና ምን አይነት ቀፋፊ አውሬ እንደሆንኩ ለማየት ነው የመጣኸው?››