አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሦስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ሆቴል ፍለጋ ብዙም አራቅንም ..እዛው ዞር ብለን ዋቤ ሸበሌ ነበር የገባነው…እንደተቀመጥን ነው የምንበላውን በማዘዝ ወደጭቅጭቃችን የገባነው…እኔን ፍለጋ ይሄን ያህል መንገድ ይጓዛል ብዬ አልገመትኩም ነበር…እርግጥ ነገሮችን በፍጥነት እንዲህ እንዲሆኑ አድርጌ ስልኬንም፤ አድራሻዬንም አጠፋፍቼ ከመስሪያ ቤቴ የጠፋውት አውቄ ነው …ለእሱ የማሰቢያ እና የመረጋጊያ ጊዜ እንዲያገኝ በማሰብ ….እንጂማ ስራዬን እሱ ስላለ መልቀቄ አይደለም..እንደዛማ አይታሰብም…ሰው በገዛ ግዛቱ ውስጥ በታነፀ ቤተመንግስት ሊነግስበት ያሰበውን ወንበር ሌላ ተቀናቃኝ ልቀቅ ስላለው በቀላሉ ይለቃል…አይ በፍፁም ይሄ የነገስታት ባህሪ አይደለም..እሱ በንግስናው ኃይል ተማምኖ ወግጂልኝ ቢለኝ እኔ በቀላሉ ምኞቱን ላሳካለት አልችልም..ምክንያቱም እኔም ከእሱ እኩል ኃይል ያለኝ ንግስት ስለሆንኩ…
‹‹እኔን ፍለጋ እንዲህ መባከንህ አስደስቶኛል››አልኩት
‹‹ጉረኛ አትሁኚ… ስለአንቺ አንዳንድ ነገር ሳጣራ ከበፊትም ጀመሮ በካምፓኒው አንቺን በተመለከተ ያለው ነገር ትክክል ስላልመሰለኝ ያንን ለማስተካከል ነው..የአንድ አዲስ መሪ ስራ የወደፊት የካምፓኒውን አካሄድ ማስተካከል ብቻ ሳይሆን ወደኃላም ተመልሶ በባለፍት መሪዎች አላግባብ የተሰሩ ስራዎች ካሉ ለእነዛ እርማት እንዲደረግ ማሰድረግም ጭምር ነው…
‹‹ስለመሪነት ጥሩ ግንዛቤ እያገኘህ ነው››
‹‹አዎ…አስተዳደግሽ፤ የቤተሰቦችሽ ሁኔታ እና የህይወት ገጠመኞችሽ የፈጠሩብሽ ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ ካምፓኒያችንም ላንቺ የሰጠው ቦታ ለህይወትሽ መበላሸት አንድ አስዋፅኦ እንዳበረከተ ተሰምቶኛል..እኔም ነገሩን በደነብ ሳላጣራ በእሳቱ ላይ ቤንዚል ጨመርኩበት››አለኝ እጆቹን እያፍተለተለ…አይገርማችሁም አንዳንድ ሰው ወደ ህይታችሁ ድንገት ከመንገድ ጎራ ብሎ ይገባና ገና በሁለት እግሩ እንኳን ተስተካክሎ ሳይቆም አፍርሼ ልስራችሁ ይላል፡፡
‹‹ያው ቸኩሎ መፍረድ የአንተ ብቻ ሳይሆን…የእኛ ኢትዬጵያውያን ዋና ችግር ነው.. ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሆነ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን የማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ እኛ ግን እንደዛ አናደርግም…በዛም ምክንያት ውሳኔያችን ቡዙ ግዜ የጥድፊያና በስህተት የተሞላ ነው››አልኩት… ከገባው ብዬ
‹‹አዎ ትክክል ነሽ››አለኝ ኮራና ጀነን ብሎ
‹‹አየህ አሁንም ተሳሳትክ..ትክክል መሆኔን እንዴት በዚህ ቅፅበት ልታረጋግጥ ቻልክ….?››
ግራ ገባውና ‹‹ማለቴ….››ብሎ ሊያብራራልኝ ሲሞክር መልሼ ጣልቃ ገባውና
‹‹ግዴለም ብታስረዳኝም አታሳምነኝም..ይልቅ ህይወቴ እንደተበላሸ ስትናገር ነበር…እስቲ እንዴት እንዲያ ልታስብ እንደቻልክ አስረዳኝ..….?››
‹‹ይሄ ምን ማስረዳት ያስፈልገዋል…በዛ ነጥብ ዲግሪ ተመርቀሽ በትንሽ ደሞዝ በፀሀፊነት እየሰራሽ ነው..በቀደም አያትሽ ከሚሆን ሰው ጋር አግኝቼሻለው…ዛሬ ደግሞ ተራ የሽያጭ ሰራተኛ ሆነሽ መጽሀፍ ስትቸረችሪ ነው ያገኘውሽ…ህይወትሽ እርጋታ የሌለው ምስቅልቅሉ የወጣ ነው….ከዚህ በላይ የህይወት መበለሻሸት ከየት ይመጣል››በቃ በእሱ ቤት የእኔን ህይወት ብጥርጥር አድርጎ አጥንቶ ጨርሶል..
‹‹እውነት ግን ምንድነው ….?››ጠየቅኩት
ግራ ተጋባ‹‹….ምን አልሺኝ….?››
‹‹እውነት ምንድነው..….?››ፍጥጥ ብዬ ጥያቄዬን ደገምኩለት
‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው….….?እውነት ሀቅ ነው…በትክክል የተተገበረ ወይም የተነገረ ክንውን ነው..በቃ ይሄው ነው፡፡››
‹‹እሱ ብቻማ አይደለም…እውነት እረቂቅ ነው..እውነት ጥልቅ ነው…የሰማህው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን አይችልም..ለምን ይመስልሀል እኔ እና አንተ አንድ አይነት ነገር ከአንድ ሰው በእኩል ሰዓት ብንሰማ የምንረዳበት መንገድ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም…ምክንያም ሁለታችንም በየራሳችን አዕምሮ ተጠቅመን ነው ተርጉመን ነገሩን ለመገንዘብ የምንጥረው…..ስንተረጉም ደግሞ የበፊት የህይወት ልምዳችን..የምንከተለው የሀይማኖት አይዲኦሎጂ፤ ከተወለድንበት አካባቢ ማህበረሰብ የቀሰምነው ባህል፤ የራሳችን ፍላጎት…..እነዚህና ሌሎችም በአተረጋጎማችን ላይ የየራሳቸውን ስውር ተፅዕኖ ያሳድራብናል…… የሰማነው እውነት በግማሽ ይበረዛል ማለት ነው…ያየነውም እንደዛ..፡፡ሌላ ምሳሌ ልስጥህ የአንድ ወጣት ልጃገረድ ፎቶን ሶስት ወጣት ወንዶች ቢያዩት እና ከሳዕታት ቡኃላ ምን እንዳዩ ቢጠየቁ..አንድ የተቀሰረ አስጎሚዥ ጡቶች ያላት ወጣት ይልሀል…ሌላው የሚያምረ መቀመጫ ያላት ሞዴል መሆን የምትችል ወጣት ይልሀል…ሌላው ደግሞ የሚያምር ቁንጅና ያላት ግን ልቧ በሀዘን የተሰበረ፤የእኔ ያለችውን ነገር በመጠበቅ በናፍቆ እየተሰቃየች መሆኖን አይኖቾ ውስጥ ያጋቱት እናባዋ የሚመሰክሩ ፤ ግን ደግሞ ያልሸነፍ ባይነት እና የራስን ስሜት የመቆጣጠር ጥረት በፊቷ ላይ የሚነበብባት፤ከዕድሜዋ በላይ የምታውቅ ወጣት ነች ይላል፡፡አየህ ሶስቱንም አስተያየት ሰጪዎች አንድ አይነት ስዕል ከአንድ አይነት እርቀት ላይ አይተው የተረዱት ነገር የተለያየ ነው፡፡እውነቱ የማናኛቸው ነው…….?አየህ እውነት እንደሽንኩርት ነው ሚባለው ለዛ ነው…በላጥከው ቁጥር ሌላ አዲስ ነገር..አሁንም ስትልጠው ሌላ ሚስጥር…..አንዳንዴማ ማብቂያ ሁሉ ላይኖረው ይችላል….ጲላጦስ እኮ እኔ ማውቀው አለማወቄን ነው ያለውም አንድም ለዛ ነው….ያወቀ የመሰለው ሁሉ እሱ ገና ጀማሪ ተማሪ ነው….
‹‹ወይ አንቺ ልጅ…እያወራን የነበረውን ቁም ነገር እኮ አወሳስበሽ ድራሹን አጠፋሽው….››
‹‹አይ አሁን ያወራውት ነው ትክክለኛው ቁም ነገር….አየህ የእኔ ህይወት ብልሽትሽት ማለቱን ለመወሰን በአንድ ሰምንት ውስጥ ያየሀቸው ወይም የሰማሀቸው ቅንጭብጫቢ ታሪኮች ላንተ በቂዎች መሆናቸው አስገራሚ ነው››
‹‹እኛ ካምፓኒ በፀሀፊነት እንደምትሰሪ ማንም ተናገረው ማንም እውነት ነው…..በቢዝነስ ማነጅመንት ዲግሪ እንዳለሽም አንቺ እራስሽ አትክጂም…ሹገር ዳዲሽንም በአይኔ ነው ያየውት››
በዚህ ጊዜ ምግቡ ቀርቦልን እየበላን ነበር እያወራን ያለነው..ሁሉን ነገር ጨርሶ ሳያውቅ እንደአወቀ የሚያወራው ነገር ብሽቅ አደረገኝ ‹‹ሌላውን ተወው ….ሹገር ዳዲዬ መሆኑን በምን አረጋገጥክ…….?››
‹‹አይቼሻለው አልኩሽ እኮ..አንቺም አረጋግጠሽልኛል…››
‹‹ዋሽቼህ ቢሆንስ…….?››
‹‹በምን ምክንያት ትወሺኛለሽ ….?››
‹‹ላስቀናህ ፈልጌ››
ሳቁን ለቀቀው…
‹‹ምን ያስቅሀል….?››
‹‹ለምን ብዬ ቀናለው…አፈቅሬሽ ነበር እንዴ….?››
‹‹እኔ እንጃ… ሰው አንድ ሰውን ላይ ካለምክንያት ትኩረት ካደረገና ምክንያት እየፈለገ ጥዋትና ቀን የሚነጫነጭበት ከሆነ ያው በእኔ ግምት ፍቅር ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡››
‹‹እንደ ህይወትሽ ለራስሽ ያለሽ ግምት የተዘበራረቀ ነው…አንዳዴ መሬት የሚወረድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ልንጠልጠል የሚል…›› አለኝ …በመበሳጨትና ስሜቱን ለመቆጣጠር በሚጥር የስሜት መደበላለቅ
‹‹እሺ ተሳስቼ ይሆናል..ለምን
👍1
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ሦስት (🔞)


#ከናንተ_መሐል_ጻድቅ_የሆነ
#መጀመርያዋን_ድንጋይ_ይወርውር

መጋቢት 8፣ 1998

በኮዚ ክለብ መስራት ከጀመርኩ እንድ ዓመት አልፎኛል፤ስጀምር አካባር አርብ፣ቅዳሜ እና እሁድን ብቻ ነበር
በክለቡ ውስጥ የምሰራው፡፡ይህን ያህል ጊዜ የቆየሁበት ሌላ ቤት የለም፡፡ጥሎብኝ በአንድ ቤት ለረጅም ጊዜ መቆየት አልችልም። ስልቹ ነኝ መሰለኝ።
ድሮም ቢሆን እዚህ ህይወት ውስጥ ሳልገባ ከአንድ ወንድ ጋር ሙጭጭ ማለት አይሆንልኝም ነበር፡፡ ወንዶች ቶሎ ይሰለቹኛል። በሕይወቴ መቀየር የምችለውን ነገር ሁሉ መቀየር ብችል ደስ ይለኛል፡፡ ጸጉሬን ደጋግሜ የምቆረጠውም ለዚህ ይመስለኛል፡፡ጓደኞቼ ግን የሚያምረውን ጸጉሬን ስቆርጠው ያበድኩ ይመስላቸዋል፡፡እንኳን ጸጉሬን ቁመቴንም እሰለቸዋለሁ፤
አንዳንድ ጊዜ ቁመቴን መቁረጥ እንደሚያምረኝ ማን በነገራቸው፡፡ ሰው እንደ ግመል ሜትር ከ 75 ሆኖ
ይፈጠራል በማርያም"ይህን ቁመትሽን ወይ ቁንጅና አልተወዳደርሸበት ወይ አውሮፕላን አላበረርሽበት"
ትለኛለች ራኪ፡፡ ብዙ ሀበሻ ወንዶች ከኔ ጋር መቆም ምቾት የማይሰጣቸውም ለዚሁ ነው:: ያነሱ ይመስላቸዋል፡፡ «ይህቺ ቆጥ እምስ» እያሉ ያሙኛል፡፡ ምን ላድርግ…ቁመቴን እኔ ኮትኩቼ አላሳደኩት፡፡

ኮዚ ክለብ ብዙም ሐበሻ ስለማያዘወትረው ተመችቶኛል፤ በዚያ ላይ አሪፍ ቢዝነስ አለ፤አሪፍ አሪፍ ሰዎች
ሚኒስትሮች ከስብሰባ በኃላ"ጌዳውን" ሲያምራቸው በጊዜ ከዚህ ቤት ይሰየማሉ፡፡ እንደ ሌሎች ቤቶች
ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ፊቶች አይበዙም፡፡ ለምሳሌ በየምሸቱ አዳዲስ ተጋባዥ ዲጂዎች ይኖራሉ።
በየእለቱ ከአዳዲስ ደምበኞች ጋር እንደመውጣቴ የተለያዩ አገር ስጦታዎች ይመጡልኛል፡፡ ተመሳሳይ ፊት አይቼ አላውቅም፡፡ አዲሳባ ለአጭር ጊዜ ስብሰባ ወይም የስራ ጉብኝት የሚመጡ ሰዎች ናቸው ኮዚን በብዛት የሚያዘወትሩት፡፡

የሰዉ ዓመልም በኮዚ የዛኑ ያህል ለየቅል ነው፤ አንዳንዱ ጡትሽን እንደ ህጻን እየጠባሁ ልደር ይላል፤ሌላው ቂጥሽን ሌሊቱን ሙሉ ልንተራሰውና የፈለግሽውን ልከፈልሽ ይላል፡፡ የኔ መፍሳትአለመፍሳት
አያሳስበውም፡፡አንዳንዱ ሰው የቅንዝር ለሃጭ ጭንቅላቱን ሲጋርደው ሰው መሆኔንም ይረሳል መሰለኝ።
ተንበርከከን እንላስልሽ የሚሉኝ ብዙ ናቸው፡፡በተለይ አረቦች ጭንቅላታቸውን ጭኔ ውስጥ ቀብረውት ማደር ይወዳሉ፡፡ ራኪ ይህን ጉዳይ ስነግራት « አረብ ነዳጅ ካላየ ያን ያህል የሴት ጭን ውስጥ አይደፋም፤ አስቆፍሪው» ትለኛለች፡፡ እሷ ጫወታ አያልቅባትም፡፡ ነዳጅ ቀርቶ አንድ ከርሳም አረብ እዚያው ትንፋሽ
አጥሮት ድብን ብሎ ሰበብ እንዳይሆንብኝ እንጂ ለኔስ ብዙም ከባድ አልነበረም፡፡ በኮዚ የማይገጥመኝ ጉድ የለም፤አንዳንድ ጊዜ የሚገርመኝ ነገር ከመብዛቱ የተነሳ መገረም ሁሉ አቆማለሁ፡፡ ግን ይኸው ለውጥ
ይመስለኛል እዚህ ያከረመኝ፡፡

የኮዚ ክለብ እለታዊ ፕሮግራም ተለዋዋጭ ነው፤ በብዛት ግን ምሽት
2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ለስላሳ የጃዝ ሙዚቃ ይቀርባል፤ በዚህ ሰዓት የሚገቡት ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ናቸው ከሰሞኑ ደግሞ እትሌቶች መምጣት ጀምረዋል። አሁን ማን ይሙት በቀደም ስንት ሺ ሜትር ነው ሮጦ ወርቅ ያመጣው ባላገር ልጅ እንዴት ሆኖ ነው ጃዝ ሙዚቃ ገብቶት እዚህ ቤት ማዘውተር የጀመረው ይሄ አትሌት በመጣ ቁጥር ቶሎ ራኪ ጋር እንሰባሰባለን፡፡ በጣም ነው ሙድ የምትይዝበት፡፡ ለነገሩ እሱ ላይ በመቀለድ አፉን ያልፈታ የቤቱ ሰራተኛ የለም፡፡ ደግነቱ ዘወትር ምሽት የሚያዘው ወይ ሃይላንድ ግፋ ቢል
ሬድቡል መሆኑ በጀው እንጂ እንደሌላው ቀምቅሞ ቢለፋደድ ከሰው አፍ ይገባና ያርፈው ነበር፡፡ አትሌቱ አንድ ሳምንት በተከታታይ ይመጣና ከዚያ ለእንድ ለሁለት ወር ይጠፋል፡፡ ባለፈው ወር አምለሰትን ልጋብዝሽ ብሏት አብረው እየተጫወቱ ድንገት ዘሎ ለምን “ከዚህ ስራ አትወጪም… ምናምን ብሎ
ሊመከራት አልዳዳውም? ጌጃ! አምለሰትን እያወቃትም ማለት ነው "ሆድዬ! እንተ ሩጫ ስታቆም ነው
እኔ ይህን ስራ የማቆመው» ብላው አመዱን ቡን አደረገችው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ እዚህ ቤት ሴት ጋብዞ አያውቅም፡፡ ብቻውን እዛች ዲጄው መስኮት ጥግ ተቀምጦ ይሄን ዉሃውን ይጋታል፡፡ የጌጃነቱ ጌጃነት እዚህ ቤት የስፖርት ቱታ ለብሶ ይወጣል፡፡ ንክር ባላገር!

ኮዚ ባር ከ5፡30 ጀምሮ ደግሞ ዲጀ ዲክ ከዕለቱ ተጋባዥ ዲጄ ጋር በመሆን በአለም ሙዚቃ ያምነሸንሹናል፡
ክልሱን ዲጄ ዲከን የማያውቀው የለም፡፡ በእንግሊዝኛው ኤፍ ኤም የራሱ የአየር ሰዓት ስላለው ብዙ የዲፕሎማት ሴት ልጆች እርሱን በአካል ለማየት ከዚሁ ሰዓት ጀምሮ ቤቱን ይሞሉታል፡፡ ከሱ ጋር ለማደር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ እሱ ሸክላውን ከሚያጫውትበት መስኮት ፊት ሆነው ቂጣቸውን እየቆሉ
ይደንሱለታል፡፡ እሱ ብዙም ግድ አይሰጠውም፡፡ የፈለጋትን ሴት በፈቀደው ሰዓት ማግኘት እንደሚችል
አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ሲኮራ ይበልጥ ያምርበታል፡፡ ለነገሩ የሚያምር ሰውነት ነው ያለው፡፡ እኔ ግን ለምን
እንደሆነ እንጃ እንደ ወንድሜ እንጂ በሌላ ተመኝቼው አላውቅም፡፡ በጣም እንቀራረባለን፡፡ ቀልድ ጫወታ ስለሚችል ደስ ይለኛል፡፡

እኩለ ሌሊት አካባቢ ቢዝነስ እጀምራለሁ ፡አፍሪካውያን፣ አረቦች፣ አውሮፖውያንና አሜሪካውያ ከጥቂት ዲታ ኢትዮጵያዊያኑ ጋር ቤቷን በአንድ እግሯ ያቆሟታል፡፡ በእስካሁኑ ልምዱ እንደዚህ ቤት
የምናማር ሴቶችን ብቻ በብዛትና በጥራት የሚያቀርብ አላውቅም፡፡ ለነገሩ የኛም የሾርትና የአዳር ዋጋ በከተማዋ ሁሉ የማይቀመሰው ነው ይላሉ፡፡ ኮዚ እየሰሩ ሾርትና አዳር እየተልፈሰፈሰ በመጣው የብር ዋጋ መተመን የማይታሰብ ነው፤ ከ5:30 ጀምሮ ቋንቋው ሁሉ በዶላር ይሆናል፡፡ሪያል የምንቀበለው ራሱ አረብ ቂጣችንን እየላሰ ሲለማመጠን ብቻ ነው:: አንኳን ለዜጋ ለሀገር ልጆችም በዶላር ተምነን ነው የምቀበላቸው:: ከዚያ ዶላሩ ጠርቀም ሲልልን ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ በሳምንት አንድ ጊዜ ሰኞ ሰኞ መንዝረነው እንመጣለን፡፡ ያ ሁሉ ዶላር የት እንደሚገባ በበኩሌ አይገባኝም፡፡ ለምን
ይሆን የማይበረከትልኝ? ለሁላችንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ የምናገኘው ብር በረከት ኖሮት አያውቅም፡፡ ሸሌን
ጌታ ረግሞታል፣ ንስሀ ግቡ” ትለናለች ሸሌዋ ጓደኛችን ትርሲት፡፡

በስካሁኑ ቆይታዬ በርካታ ዓለም አቀፍ ደንበኞችን አፍርቼአለሁ። ዜጋ ደንበኛ በማብዛቴ ጓደኞቼ "ኮፊ ሀናን" በሚል ቅጽል ስም ነው የማጠሩኝ።ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን ጋር አያይዞ ዲጄ ዲክ ነው መጀመሪያ ይህንን ቅፅል ስም ያወጣልኝ። በኮዚ እንደ ዲጄ ዲክ ተረበኛ ሰው የለም መቼለታ ስቱዲዮ ጠርቶኝ ተኪላ ከጋበዘኝ በኋላ "ሮዚ ቆንጆ ይሄ ፓስፖርት የመሰለ እምስሽን የስንት አገር ቪዛ ነው የምታስደበድቢው?" ብሎ ተረበኝ። "አንተ ክፉ" ብዬው እየሳኩ ወደ ደንበኛዬ ፋሩቅ
ሄድኩኝ፡፡ ፋሩቅ ግብጻዊ ኦርቶዶክስ አረብ ነው ቀልዱን በእንግሊዘኛ ተርጉሜ ነገርጉትና ሌሊቱን ሙሉ ሲስቅ አደረ፡፡ ቁላው በቆመበት ቁጥር ታድያ..Rozina may i have your passport please? wanna issue my visa....እያለ ተላጠብኝ፡፡

በእኔ በኩል ደንበኛን የማብዛቱ ቀመር አሁንም አልተለወጠም፤ ብዙ ደንበኛ የማፈራበት ምክንያት ብዙ የወንድ ሳይኮሎጂ ላይ የተጻፉ መጻሕፍትን በማንበቤ ይመስለኛል፡፡ ወንድ ሲፈጥረው ጉረኛ ነው። ጉራውን ሲቸረችር
ሳይሰለቹ እህ! ብሎ መስማት ዋናው ቁም ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜም ወንዶች ከሌሎች ወንዶች የተለዩ አስደናቂና ስኬታማ እንደሆኑ እነግራቸዋለሁ፡፡ ወዲያው
👍62
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ሲሳይ_ራስታ

የመኪናን ፍቅር ደሜ ውስጥ እንዲዋሃድ ያደረገው ማነው ቢባል "ሲሳይ ራስታ" ነው። ጓደኛዬ ሲስ ሰዓሊ ነው፤ ፀጉሩ ድሬድ ነው፣ አንደበቱ ጣፋጭ ነው፣ አእምሮው አስተዋይ ነው፣ ምላሱ ተረበኛ ነው፤ እና ደግሞ ሆዱ የዋህ ነው። ሲስ የዓለምን ሕዝብ ሁሉ ይወዳል። ኢህአዴግን ግን አይወድም። ግርም ይለኛል።

ከወንዶች ጋር እስከዚህም ነው፣ ብዙ ወንዶችን አይቀርብም፣ እነሱም እንዲሁ። ቢያንስ እንደሚቀኑበት ግን አውቃለሁ። ዉሎና አዳሩ ከኛ ከሴቶች ጋር ነው። በተለይ ከኔና ከሸዊት ጋር እጅግ ከመላመዱ የተነሳ አንድ ክፍል ውስጥ አብሮን ቁጭ ብሎ ጡት መያዣችንን እንፈታለን። በኋላ ነው ድንግጥ የምንለው። እሱ ብዙም ግድ አይሰጠውም፤ አይረበሽም። እንዲያውም «Ladies Don't worry
ስቱዲዮዬ ራቁት ሴት አጋድሜ ስስል ነው የማድረው relax! » ይለናል ድንገት ጡታችንን እንዳያይብን በመዳፋችን ስንሸፍን ካየ፣ ወይም ደግሞ የተጨነቅን ከመሰለው።

ከሲስ ጋር የሆነ ሰሞን ቅልጥ ያልን ጓደኛሞች ሆነን ነበር። የሚያውቁን ሰዎች ግን በሌላ ነገር ጠረጠሩን።
ስቱዲዮው ይዞኝ ይሄዳል፤ ከዚያ የማነበውን መጽሐፍ ይሰጠኝና እሱ ቡሩሹን ይዞ ከሐሳብ ጋር ይታገላል። ጋለሪ እራት ይጋብዘኛል፣ አሪፍ የአርት ኤግዚቢሽን ሲኖር ይወስደኛል ሺሻ ያስጨሰኛል. ከሊያንስ የጃዝ ሙዚቃ ያስኮመኩመኛል…ከሁሉም በላይ ደግሞ የማሊ ሙዚቃ እንዴት እንደምወድ
ስለሚያውቅ ታዋቂ የማሊ ዘፋኞች ኢትዮጵያ ሲመጡ ራሱ ወስዶ ያስተዋውቀኛል…።

በወር ቢያንስ አንድ ጊዜ እሱ ቤት ሄደን አንድ ከሰዓት አብረን እናሳልፋለን፤ አሪፍ አሪፍ መጽሐፍት

ይሰጠናል፤ ከአማርኛ ሁለታችንም የስብሐት አድናቂዎች ነን፡፡ ከእንግሊዝኛ ፓውሎ ኮሂሎን ይወዳል። ከስብሐት ጋር ሁልጊዜ ወስጄ አስተዋውቅሻለሁ ይለኛል፤ ግን ተሳክቶለት አያውቅም። ከሱ
ጋር ይተዋወቃሉ።ስለሱ መአት ቀልድ ነው የሚነግረኝ።ችግሩ ወሬ ቶሎ ነው የምረሳው።

አንድ ግዜ ስብሐት ታክሲ ተሳፈረ...."አለኝ

ወያላው ግን ብሽቅ ኾነበት። ሲለው አራተኛ ወንበር ላይ ሲያስቀምጠው፣ ሲለው ደግሞ ሼባው ተጠጋ እሰኪ ቅርብ ወራጅአለ!” እያለ ሲያንገላታው ጋሽ ስብሐት ነቀለ። ከዚያም ባለጌ ጣቱን አውጥቶ ወያላውን እንካ ይሄ ይግባልህ!” ይለዋል። ወያላው እንዴት በዚህ ጨርጫሳ ሽማግሌ እሰደባለሁ ብሎ
ስብሐትን ካልደበደብኩ አለ። ይህን ጊዜ ስብሐትን የሚያውቁ ተሳፋሪዎች ወያላውን… “አንተ እሱ እኮ
ስብሐት የሚባለው ደራሲ ነው፣ አታውቀውም እንዴ?” ይሉታል። ወያላው ስብሐትን በዴዜ ብዳታና እንዲሁ በብዙ የብልግና ቀልዶች በዝና ያውቀው ስለነበር ድንግጥ ብሎ… “አባባ ይቅርታ ስላላወቅኮት ነው እንዲያውም ጋቢና ይግቡ ይለዋል። ይሄኔ ስብሐት ምን ቢለው ጥሩ ነው?… "

ምን አለው?” አልኩ ተስገብግቤ

“በቃ እኔም ቅድም የሰካሁልህን ነቅዬልሀለሁ”

በሳቅ እሞታለሁ።

ሲስ ነፍሴ አወራሩ ሁሉ ስለሚያስቅ ሁሌም እንዳፍነከነከኝ ነው። ይህንኑ ቀልድ ከ10 ደቂቃ በኋላ ደግሞ ቢነግረኝ ልክ እንደ አዲስ እስቃለሁ።

ሮዝ!"

አቤት!"

".. ስብሐትን ብዙ ጊዜ አንደማገኘው ነግሬሻለሁ?”

"እኔንጃ መሰለኝ”

“እሱን የምንወድ ልጆች ሁልጊዜም ከጕልበቱ ሥር አንጠፋም። በተለይ እኔን “ጃን ትመስለኛለህ!”

ይለኝ ስለነበር እወደዋለሁ። እሱ ከራስ ተፈሪያንስ የባሰ የተቃጠለ የጃ አድናቂ ነው በነገራችን ላይ። ስለሳቸው አውርቶ አይጠግብም። እንዴ እኔና ተፌ ባሪያው ብሔራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት ከርካሳ መፅሀፍት ቤት ቁጭ ብሎ ሊጋዜጣ ጽሑፍ ሲጽፍ አግኝተነው የነገረንን ቀልድ ልንገርሽ።

"ቀጥል የኔ ቆንጆ"

"..የሆነ የገጠር ሀይስኩል ቲቸር ነው ሊያስተምር ትምህርት ቤት ይሄዳል።ሚስቱን ቤት ትቶ ማለት ነው። ትምህርት ቤት ሲደርስ ዛሬ ቾክ ስላለቀ ትምህርት የለም!” ተባለ። ምንም ማድረግ ስላልቻለ ወደቤቱ ይመለሳል። ለካንስ ሚስቱ ወሲባም ነገር ናት። የሰፈራቸው ወጠምሻ ሲሸከሽካት አይደርስ መሰለሽ። እነሱ እቴ ስሜት ዉስጥ ሆነው ጭራሽ የአቶ ባልን መምጣት ሁሉ አላዩትም። ወጠምሻው ከላይ የቲቸሩ ሚስት ከታች ሆነው ይናጩልሻል።

ከዚያ ቲቸር ባል በንዴት ጦፈ።ጥርሱን ነክሶ ወደነሱ ተጠጋ ከዚያ ከላይ የነበረውን ወጠምሻ በርግጫ
ቂጡ ላይ ሊጨፈልቀው ብሎ ተወው።

ለምን እንደተወው ታዉቂያለሽ?”

"አላውቅም"

“ነገሩን ማባባስ ይሆናል ብሎ”

መጀመርያ ቀልዱ አልገባኝም ነበር። ቆይቶ ሲገባኝ ግን እንደ ጅል ዝም ብሎ መሳቅ ሆነ ስራዬ። ያን ቀልድ ከነገረኝ በኋላ ባለ ትዳር ከሚመስሉ ወንዶች ጋር ስወጣ ሁልጊዜም ይሄ ቀልድ ስለሚመጣብኝ ሳቅ ያመልጠኛል። ለሲስ ግን ይህን ነግሬው አላውቅም።

ሲስና እኔን ሰዎች ሲያዩን በሌላ ይጠረጥሩናል። አንድም ቀን ግን በጾታ ፈልጎኝ አያውቅም።እንዲያውም መንገድ ላይ አሪፍ ቂጥ ሲያይ እኔኑ ጎሸም አድርጎ- «ከልሚውማ ይሄን ስፖንዳ….አጃኢብ ይደልአ!? ይሄንን ሸራ ላይ ነበር መወጠር…» እያለ ይጎመዣል። ትንሽ ቅናት ቢጤ እየቆነጠጠኝም
ቢሆን እስቃለሁ።

ሲስ «ራቫ 4» አለችው። ከሚስላቸው ስዕሎች ቀጥሎ የሚወደው እሷን ነው። ከመኪናው ጋር እጅግ

ይሰደዳሉ። እጅግ ይተሳሰባሉ። ሲያይዋቸው የጫጉላ ሽርሽር ላይ ያሉ አዲስ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉት። እሱ ደግሞ ድሬድ ስለሆነ መኪና ሲነዳ ያምርበታል። ይጣጣማሉ። በምድር ላይ አንድ ያለው ንብረት መኪናው ናት። ከዚያ ዉጭ የሚወዳቸው ስዕሎች ብቻ ናቸው ያሉት። እናቱንም አባቱንም በቀይ ሽብር አጥቷል። ዘመድ የሚባል ነገር የለውም። ዘመዱ መኪናው ናት።

"ራቫዋ እኮ ለሱ ካልሆነ ለማንም አትነሳም» እየተባለ ይቀለዳል።

በቁልፍ እኮ አይደለም፣ በቁላው ነው የሚያስነሳት” ትላለች ራኪ፤

እሱ መኪናዋን እንደሚንከባከባት ወላጆች ልጆቻቸውን ቢንከባከቡ ፣ እኛም ሸሌ አንሆንም ነበር ማርያምን የምሬን ነው!” ትላለች ሸዊት።

ሲስ እኮ ሴት አይበዳም፣ ራቫዋን ነው ፓርኪንግ ሎት እያስገባ አስፈንድዶ…» እያሉ ያሙታል የአሪዞና ጋርዶች፣

አኛ ጋር በንጹህ ጓደኝነት በመቀራረቡ የሚቀኑበት ወንዶች ብዙ ናቸው። እሱ ግን ግድ የለውም። በራሱ ዓለም የሚኖር እውነተኛ አርቲስት ነው።

ሜይ 5 ለዓለም የጋዜጣ ቀን ሲስ ራዲሰን ጋለሪ ውስጥ ኤግዚቢሽን አሳይቶ ነበር። ሁላችንንም ጋብዞን ነበር፤ ኾኖም ከኔ በስተቀር ማንም አልመጣለትም። ሸዊትም ራኪም ስዕል አይወዱም።
ወይም አይገባቸውም። በተለይ ከጣይቱ በኋላ እርም ብለዋል። የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ጣይቱ ስዕል ኤግዚቢሽን ሁላችንንም ጋብዞን ሰፍ ብለን ሄደን ምንም ሳይገባን ነበር የተመለስነው። በዚህ የተነሳ ሲስን ምድረ ሸሌ ስትሞልጨው ነው የከረመችው። «የማንም እብድ መደበርያ ነን እንዴ…» ይሉታል ከዚያ በኋላ ስዕል ሲጋብዛቸው። «እኔን የሚገርሙኝ የሚቸከቸኩት ሳይሆኑ በቁም ነገር የሚያዩቱ
ናቸው» ትላለች ሸዊት። በርግጥም የጣይቱ ቀን የአብስትራክት ስእል ብዙ ስለነበረ ሁላችንም ግራ ገብቶን ነበር።

ይሄ የራዲሰኑ ኤግዚቢሽን እንዳለቀ ሲስ ወደ ቦሌ ጫፍ ይዞኝ ሄደ፡፡ ካልዲስ ማክያቶ ልንጠጣ ነበር አካሄዳችን፡ እዚያ ስንደርስ ራቫውን የሚያቆምበት ፓርኪንግ ተቸገረ። ቦታ እስኪያገኝ ብሎ መኪና
ደርቦ ቆመ። አንድ ቀጭን ትራፊክ ማዶ ላይ ቆሞ ሲስ ደርቦ መቆሙን እያየ እንዳላየ አልፎት ሄደ።

“ሮዝ!እዪውማ ያንን ትራፊኪ…! አያሳዝንም? እነሱ ሲበሉ እሱን አስረውት አይመስልሽም? እቁብ አላስገባ
ብለውት ይሆናል ይሄኔ…ሮዝ ሙች ቀጭን ትራፊክ ሳይ አንጀቴ ይንሰፈሰፋል።
👍6
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ

በእርግጥ እናቴ እሷ መሆኗን እስካወቅኩበት ቀን ድረስ እናትና አባቴ ሞተውብኝ ከሩቅ ሀገር አምጥተው የሚያሳድጉኝ ጥያቄ አልባ
ቀኖች የነበሩኝ ህፃን ነበርኩ:: አባባ የምለው አሳዳጊዬ እግዚአብሔርን በመፍራቱና በደግነቱ ትንሿ ያደግኩባት የገጠር ከተማ ድፍን ነዋሪ የመሰከረለት፣ ሚስቱ የምትኮራበት፣ ልጆቹ የሚመፃደቁበት፣ እኔን ጨምሮ ቤቱ የምንኖር አገልጋዮቹ የምንመካበት ሰው ነበር፡፡ በልጅነቴ ውስጥ ያለው አሳዳጊዬ ይህ ነው፡፡ የልጅነትን ቡረቃ ተሰናብቼ መብሰልና ህልም ማለም ስጀምር ለክብሩ እንጂ ለእኔ ግድ ከሌለው አያቴ ጋር ተዋወቅን፡፡በእርግጥ በቸርነታቸው ከሚያሳድጉኝ መልካም አሳዳጊዎቼን
ላሳዩኝ በጎነት በልቤ የማመሰግን፣ ለውለታቸው ክፍያ በአቅሜ
የማገለግል አገልጋያቸው እንጂ ለጎደለው
የማማርርበት መብትም ሆነ ይገባኛል የምለው አንዳች ያልነበረኝ ትንሽዬ ልጅ ነበርኩ። ቢቆጡኝ፣ ቢሰድቡኝ፣ ቢያንቋሽሹኝ ትምህርት፣ ቢሰድቡኝ ትምህርት እንድማር ሳይፈቅዱልኝ ከማንበብና መፃፍ የዘለለ ባላውቅም፣ እንደልጅ ለመጫወት ባይፈቅዱልኝ
መሄጃ የለሽ ወላጅ አልባ ህፃን ለሚያሳድጉ ደግ አሳዳጊዎቼልክ ነገር መሆኑ ነበር የሚገባኝ፡፡

በአስራ አራት ዓመቴ ገደማ ለአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ሁሉም ቤተሰብ ተሰብስቧል። አክስቴና እሷ ከአዲስ አበባ ነበር የመጡት:: ሴትነቴ ያበበበት ወቅት ነው።የሰፈራችን ጎረምሶች
በአጠገቤ ሲያልፉ ቂጤን ገፍተር፣ ያጎጠጎጠ ጡቴን ቆንጠር እያደረጉ ያሽኮረምሙኛል፡፡ አመሻሹን ከብቶች ከሜዳ ይዤ ስመለስ ችፍ ያለው የሰንሰል ተክል አጠገብ አዳነ ቆሟል። ጎትቶ
ወደራሱ አስጠጋኝ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: ጡቴን እንዳስነካው ያባብለኛል። ብዙ አላስለምነውም:: ሲነካካኝ ደስ ስለሚለኝ እፈቅድለታለሁ።

"እረፍ አዳነ ቤት ሁሉም አሉ። እየጠበቁኝ ነው ልቀቀኝ" ብዬው ነበር አልሰማኝም። እንደሌላ ቀኑ አላባበለኝም:: ወደ ሰንሰሉ
ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ከላዬ የለበስኩትን ልብስ ወደ ላይ ሰብስቦ ጡቴን ሲነካካኝ የምከለክልበት አቅምም ምክንያትም ከዳኝ። ሳሩ ላይ አጋድሞኝ ጡቴን በአፉ ሙሉ እየጎረሰ ሲተፋው እያቃሰትኩ
ነበር። ድንገት አቁሞ ሲበረግግ የጨፈንኳቸውን ዓይኖቼን ገለጥኳቸው።ያየሁትን ደግሜ ላለማየት ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው። መልሼ አጮልቄ አየሁ። ከተጋደምኩበት ሆኜ ሳየው ጋሼ (የአባባ ብቸኛ ወንድ ልጅ) ከሰማይ ላይ ተወርውሮ የተንጠለጠለ መስሎ ዓይኑን ጎልጎሎ አፍጥጦብናል። አዳነ ፓንቱ እስኪቀደድ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሲሮጥ ጋሼ ማጅራቴን ጨምድዶ ይዞኝ ወደቤት ገባ። በቤቱ ጣራ ስር ያሉትን ሁሉ
በጩኸቱ ስብስቦ እንደ ክፉ ወንጀለኛ ፊትለፊታቸው አቆመኝ፡፡የት እንዳገኘኝ እና ምን ስሰራ እንደነበረ በሚዘገንን ፀያፍ ቃል ለሁሉም ተናግሮ እንዳበቃ ተራ በተራ የምላሳቸውን መርዝ ተፉት። እሷ ምንም አልተናገረችም።ዓይኖቿ ውስጥ የነበረው መፀየፍ ግን ከእነርሱ ስድብ በላይ ህመም ነበረው።የሚያውቁትን ስድብና ቁጣ ሁላ ጨርሰው ፀጥ ሲሉ ወደ ጎዳ ገባሁ።እሷም ሲጋራዋን ልታጨስ ወደ ውጪ ወጣች።ጋሼም ተከተላት።በጎሮ በር አድርጌ ወጣሁ።ልሰማቸው ፈልጌ ባይሆንም ሲጯጯሁ ይሰማኛል። የመደናቆራቸው መንስኤ እኔ መሆኔን ሳውቅ ጆሮዬን ጥዬ መስማት ጀመርኩ፡፡

እንቺ የወረወርሻትን ዲቃላ እድሜ ለአባቴ በይ አሳደግንልሽ፡፡ እሷ ይዛብን የምትመጣውን ዲቃላ ማን ሊሸከምልሽ ነው?ካንቺም ብሶ እንዳለማች ቆጥረሽ ዝም ትያታለሽ? ባንቺ ነው የወጣችው! ገና ቂጧን ሳትጠርግ በየሳሩ ትሸረሙጣለች፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯን እየጠበቅኩ የከፈተችውን እግሯን አልገጥምም።ከፈለግሽ ወስደሽ የምታደርጊውን አድርጊያት:: " ከእውነታው እኩል የመረጣቸው ፀያፍ ቃላት አስደነገጡኝ፡፡ የሰማሁት
እውነት መሆኑን መቀበል አቃተኝ፡፡ እሷ አትመልስለትም።አጎቴ አንዴ እህቱን አንዴ እኔን እየሞለጨ ደቂቃዎች አለፉ፡፡
ደጋግሞ ከተናገረው እሷ እናቴ መሆኗን እና ለእነሱ ጥላኝ እንደሄደች ገባኝ፡፡

"እናቴ አንቺ ነሽ? አባባ አያቴ ነው?" አልኩኝ ተኮራርፈው ሳሎን እንደተቀመጡ ሁሉም ነብር እንዳየ ጥንቸል ዓይናቸው
ተጎልጉሎ ጆሮአቸው ቆመ።የመለሰልኝ የለም፡፡

ውጪ ያወራችሁትን እንዳለ ሰምቻለሁ::" አልኳቸው፡፡

እና የሰማሽ እንደው ምን ይሁን? እኔ እናትሽ አይደለሁም ስትለኝ እናቴ መሆኗን ስሰማ ተንሰራፍቶ የነበረውን
ብልጭታ ደስታ በተነችው:: አጠገቧ ተጠግቼ እጇን ስይዛት መንጭቃ ገፈተረችኝ፡፡ እናቴ መሆኗን ሳላውቅም በፊት ይዣት አውቃለሁ፡፡ እንደዚህ አስጠልቻት አይቻት አላውቅም፡፡ እነ አባባ ጋር የምትመጣው ከስንት
ዓመት አንዴ ቢሆንም የምትለብሳቸው ልብሶች፣ ሲጋራ አጫጫሷ፣ ቁመቷ፣ አካሄዷ...
ባየኋት ቁጥር እንደርሷ መሆን የምመኝላት ነበረች::ስትመጣ እንግዳ ሲመጣ እንደማደርገው እግሯን የማጥባት እኔ ነበርኩ፡፡ ከስንት ዓመት አንዴ ለአዲስ ዘመን መለወጫ ስትመጣ
አዲስ ልብስ እቤት ላለነው ሁሉ ስትገዛ ለእኔም ገዝታልኝ ታውቃለች:: እንደዛ ቀን በጥላቻ አመናጭቃኝ አታውቅም።

በእርግጥ የምትፈልገውን ነገር ልታዝዘኝ ካልሆነ በቀር በፍቅር ወይ በክብርም አናግራኝ ማወቋን አላስታውስም፡፡
በደስታ፣በተስፋ እና ግራ በመጋባት መሃል ዋለልኩ:: በጥያቄ መዓት ተበታተንኩ፡፡ ተራ በተራ አፍ አፌን ብለው አባረሩኝ፡፡
ዓይኗን እንኳን መልሼ ሳላየው ተመልሳ ወደ አዲስ አበባ ሄደች።

ባልገባኝ ምክንያት ከዚያን ቀን በኋላ ከአባባ በቀር ሁሉም ያመናጭቀኝ ጀመር። ለምን የስጋቸው ክፋይ መሆኔ
እንዳሳፈራቸው ግራ ተጋባሁ:: ምንስ ቢሆን ደግሞ የእኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው? ከቀናት በኋላ አባባን እያለቀስኩ እውነቱን
እንዲነግረኝ ጠየቅኩት። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ከሆነ ጎረምሳ ጋር ተጣልታ ከባድ ጉዳት ስላደረሰችበት አስር ወር ተፈርዶባት መታሰሯን ነገረኝ። ማንም የተፈጠረውን አያውቅም፡፡ ሊጠይቋት ሲመላለሱ ማናቸውንም ለማግኘት ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርዷን ጨርሳ ወደ ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ነበር ምጥ የጀመራት:: ማናቸውም ማርገዟን ሳያውቁ እቤት እንደደረሰች ወለደችኝ፡፡ አባቷ ወግ አጥባቂ እና
ክብሩን ወዳድ ስለነበረ ተዋረድኩ ብሎ ያዙዙኝ ልቀቁኝ አለ፡፡
(ይሄን ሲነግረኝ በቁጭት ነበር) አንዲትም ቀን አላደረችም፡፡ለማንም ምንም ሳትል ከነደሜ ጥላኝ ጠፋች:: ከቤተሰቦቿ ጋር
መልሳ ስትገናኝ አድጌ በእግሬ ድክ ድክ እል ነበር። ሁሉም በዲቃላነቴ ደስተኛ ስላልነበሩ እናቴ መሆኗን እንዳላውቅ
የሰጠችው ማስጠንቀቂያ ተስማማቸው:: አብዛኛዎቹ የቤት አገልጋዮች እንደሚጠሩት ከስሜ የማስከትለው የአባባን ስም ነው:: የእኔ መወለድ ሌላ ሴት እንድትሆን እንዳደረጋት አባባ ሲነግረኝ ለቤተሰቡም ሆነ ለእናቴ ክፉ እጣ እንደሆንኩ ደጋገመልኝ እናቴ እኔን ከመውለዷ በፊት ከወንድ ልጁ ይልቅ በራስ መተማመኗ የሚያስተማምነው፣ ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች ቤት ተከራይቶላት ከተማ የሚያስተምራት መኩሪያው፣ ትልቅ
ቦታ ትደርስልኛለች ብሎ የሚመካበት የዓይኑ ማረፊያ፣ ማንም ደፋር ቀና ብሎ የማያያት ጉልበተኛ እና ደፋር እንደነበረች
በትካዜ ፊቱ ደብዝዞ አወራኝ፡፡ እኔን ከወለደች በኋላ ጠፍታ ስትመለስ የማያውቋት ሌላ ሴት ሆና መምጣቷን ጨመረልኝ፡፡

"አባባ አባቴ ማን ነው?" አልኩት:: ምናልባት አባቴ ልጁን በፍቅር ክንዱን ሊዘረጋልኝ ይችላል ብዬ እያሰብኩ፡፡

"አናውቀውም:: ከእርሷ ውጪ የሚያውቅ የለም:: ስለአንቺም ሆነ ስለአባትሽ ጥያቄ ሲነሳባት ጣረሞት እንዳየ ሰው
ትንፈራገጣለች::” አለኝ፡፡

አባባ ከነገረኝ ያልተሟላ ታሪክ
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ያው ስላንቺ ነዋ፡፡ ውበትሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ሳማት፤ሳማት፤ ይለኛል፡፡ ደግሞ ምርጥ ልጅ ነሽ፡፡ በፍፁም ላስቀይምሽ የማልፈልጋት አይነት ቆንጆ ነሽ፡፡ እንደ ድፍረት ቆጥረሽብኝ እንድታኮረፊኝ ደግሞ አልፈልግም፡፡ ምናባቴ ላድርግ ብዬ እያሰብኩ
ነበር፡፡” ከንፈሯን እያየሁ ደግሜ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡

“አንተ እብድ. አታረገውም አይባልም እኮ፤” አለች ዐይኗን አፍጥጣ፡፡

ዝም ብዬ አየኋት፡፡

«ባይዘዌ ግልፅነትህ በጣም ደስ ብሎኛል። ስሜትህን በግልፅነት
መንገርህ፣ ያንተንም ስልጡንነት ያሳያል፤” አለችኝ ::

ደስ ብለኸኛል...? አሁን መድፈር አለብኝ፡፡ ብስማት ምንም አትለኝም፡፡ ከዚ በላይ ምን እንድነው ምጠብቀው? በመጀመሪያ ቀን ልሳምሽ ስላት፣ አፏን አውጥታ እሺ እንድትለኝ ነው? ስሜቴ ከምቆጣጠረው በላይ ሆነ፡፡ አድርገው አድርገው ይለኛል፡፡ በዐይኔ የቤቱን እንቅስቃሴ እከታተላለው፡፡ አሁን ቤቱ ባዶ ሆኗል፡፡ ባለቤቷም ውጪ
ከወጣች ቆይታለች፡፡ ላድርገው? በድንገት ብትገባብንስ? ደግሜ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ጋድ! አሁን ሂድልኝ ቢባልኮ እንዲህ አይሮጥም፡፡

“ስዐቱ በጣም ሄደ፡፡ ወደ አገርሽ ሄደን ደግሞ፣ ልደቴን በፈሳሽ ብናከብር ምን ይመስልሻል? እዚሁ አስራ ሁለት ሰዓት ሊሆንኮ ነው፡፡”

“እዛማ የማውቀው ሰው ሊያየኝ ይችላል። ባይሆን እዚህ ምታውቀው ቤት ካለ...?”

“ችግር የለም፡፡ መኪና ይዣለሁ፡፡ እዛው ሰው ማያየን ቦታ እወስድሻለሁ።” ዝም አለች፡፡ ዝምታ መስማማት ነው፡፡ ባለቤቷ
መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ባለቤትየው ወዲያው እስክትመጣ አድፍጬ መጠባበቅ ጀመርኩ ባለቤትየዋ ወድያው
ብቅብላ፣

“ተጫወቱ! ዝም አላችሁ፡፡ ምን ይጨመር...?” አለችን፡፡

“ሂሳብ ስሪልን፤” አልኳት፡፡ እዚህ ተጨማሪ ሰዓት ማባከን አልፈፈለኩም፡፡

“እሺ!” ብላ ልትሰራልን ወጣች፡፡ ከሃናን ጋር እየተጠጋጋን ሳናስበው ተጣብቀናል፡፡ ሙቀቷ ይሰማኛል፡፡ ሂሳብ ከፈልኩና፣

ተነሽ እንውጣ!” አልኳት ልብሴን እያረጋገፍኩ፡፡

እሺ ግን፣ አብሬህ አልወጣም፣ አንተ ውጣና ውጪ ጠብቀኝ፡፡”

አላንገራገርኩም፡፡ የመኪናዬን አይነትና ያቆምኩበትን ቦታ ነግሪያት ወጣሁ፡፡ አላስጠበቀችኝም፤ ቶሎ መጣች፡፡ የዱከምን ከተማ ወደኋላ እየተውኩ፣ ወደ ደብረዘይት ነዳሁት። ልደቴን ደስ የሚልና ልዩ እንዳደረገችልኝ፣ ስለ ልዩ ውበቷ፣ ስለ ከንፈሯ ልዩነት እያወራሁ በፍጥነት እከንፋለሁ፡፡ በአንድ እጄ መሪ ይዤ በሌላው እጄ በስስ ታይት የተሸፈኑት ታፋዎቿ መሃል ገባሁ፣ ሙቀቷ ረመጧ ለበለበኝ፡፡ እጄን አወጣሁትና እጆቿን ያዝኳቸው፡፡ በላብ ረስርሰዋል፡፡ ጣቶቼን በጣቶቿ መካከል ሰገሰኳቸው፡፡ አጥብቄ ጨመኳቸው፡፡ ምንም አታወራም ዝም.
ብቻ፡፡ ሁሉም ተፈቅዷል፡፡

በስሜት ባህር ቀልጠን ሰምጠናል፡፡
ወደ ክፍሌ በፍጥነት እየነዳሁ ነው፡፡ ወዴት ነው እንኳ ሳትለኝ ትከተለኛለች፡፡ ልከመርባት ቸኩያለው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ አምናኛለች፡፡ እንደበግ
እየተጎተተችልኝ ነው፡፡ የፈለኩትን ሁሉ ፈቅዳልኛለች፡፡ ከራሴ ሰውነት የሚወጣ ሙቀት በሸሚዜ አልፎ ፊቴን ይልፈኝ ጀመረ፡፡ ወደ ክፍሌ በሚወስደው የውስጥ መንገድ ታጠፍኩ፡፡ አሁንም ምንም አላለችም፡፡ ትንሽ እንደነዳሁ ከፊቴ ያለ ሚኒባስ አስፓልቱ ላይ መንገድ ዘግቶ ቆመ፡፡ ቸኩያለው፡፡ ደርቤ ላልፈው ስል፣ ከፊቴ ሌላ መኪና እየመጣ ነው፡፡
አክለፈለፈኝ፡፡ ወዲያው ሚኒባሱ ተንቀሳቀሰ፡፡ ጠጋ ስል፣ የተሰበሰቡ
ወጣቶች ተቆፍሮ የነበረውን መንገድ ያስተካከሉበት ገንዘብ እየጠየቁ
ነው፡፡ ግዜ የለኝም፣ እጄን ወደ ኪሴ ሰድጄ ያገኘሁትን ብር ሰጠኋቸው፡፡

“ያራዳ ልጅ...፣ ያራዳ ልጅ...

ይመችሽ...፡፡

መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ፡፡”

በዜማ አዘል ምርቃት ሸኙኝ፡፡ ስንት ሰጥቻቸው ይሆን? ለነገሩ ስንትስ ብሰጣቸው፣ እኔ ይሄን የመሰለ መና ወርዶልኝ...፡፡ 'መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ' ያሏት ምርቃት ከእዕምሮዬ ቀርታ በግድ ፈገግ አደረገችኝ፡፡ ቪትሴን ንቀዋት ነው? ለኔ ሃመሬ ናት፡፡

የክፍሉን በር፣ እንዴት ከፍቼ እንደዘጋሁት አላስታውስም፡፡ እንደቆምን በሩን አስደግፌ ተአምረኛውን ከንፈሯን መምጠጥ ጀመርኩ፡፡ በፍጥነት እራቁታችንን ሆንን፡፡ ረጅም ነች፡፡ በቁመት ብዙም አልበልጣትም፡፡ ልከኛ የተነፋፉ ጡቶቿን ለመዋጥ ዝቅ ስል፣ ራቁት
ገላዋን እታች ድረስ ሳየው፣ ከባድ ስሜት ተሰማኝና አልጋው ላይ በጀርባዋ አጋደምኳት፡፡ የገላዋ ልስላሴና የሰውነቷ ሙቀት ስሜቴን አላወሰው፡፡ ከውስጥ ሱሪዋ በስተቀር እራቁቷን ነች፡፡ እላዩዋ ላይ ተለጠፍኩባትና ተንጠራርቼ ከንፈሮቿን ጎረስኳቸው፡፡ በሁለት እጆቿ
ጆሮዎቼን ይዛ፣ ትስመኝ ጀመር፡፡ ትኩሳቴ ሲጨምር ይታወቀኛል፤ ስሜቴ ተንጠራራ፤ እየተሳሳምን እጄን ወደ ፓንቷ ላኩት፡፡ ፓንቷን ላወልቀው ስታገል ተረዳችኝ፡፡ ከንፈሯን ከከንፈሬ ሳታላቅቅ፣ ፓንቷን
እንዳወልቀው፣ እግሮቿን ወደላይ አጥፋ አመቻቸችልኝ፡፡

ስሜቴ በውስጤ ሲፈላ፣ ሲንተከተክ ይሰማኛል፡፡ ዋጣት፤ዋጣት፤ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡ ልውጣት ከከንፈሮቿ ጀመርኩ።
ከንፈሮቿን ሳልጠግብ፣ አንገቷን፣ አንገቷን ሳልጠግብ፣ እየላስኳት ቁልቁል ወደ ጡቶቿ ወረድኩኝ፡፡ እልህ፣ ስግብግብነት፣ ውስጤን ወጥሮታል፡፡ የቱን ይዤ የቱን እንደምለቅ መምረጥ አቅቶኛል።
አንደኛውን ጡቷን እስከቻልኩት ያህል ዋጥኩት፡፡ ከወገቧ ወደላይ
ተንፈራገጠች፡፡ በስሜት ተቃጠልኩ፣ ጨስኩ፣ መትነን ጀመርኩ።መዋጥ አልሆንልህ ሲለኝ፣ እውስጧ መግባት፣ ገብቶ መሰንቀር አማረኝ፡፡ ታፋዎቿን ከፈትኳቸው፤ ያቃጥላሉ፡፡ ይፋጃሉ፡፡ በረጃጅም እግሮቿ፣ በለስላሳ ታፋዎቿ፣ መሀል ተንበረከኩኝ፣ ተርመሰመስኩላት::
በእግሮቿ ወገቤን አቅፋ ጎትታ ከራሱዋ
ጋር አጣበቀችኝ፡፡ እንደተመኘሁት ውስጧ ሰነቀረችኝ፡፡ በሙቀቷ ተቀቀልኩኝ፡፡ እራሳችንን እስክንስት፣ በስሜት ሰረገላ ተመነጠቅን፣ ከአለም ተነጠልን፡፡ ዳግም
የምንገናኝ እስከማይመስል ድረስ፣ ያበጠው ስሜቴ እስኪፈነዳና እስኪተነፍስ ድረስ፣ የቀረን እንጥፍጣፊ ሃይልና ጉልበት አልነበረንም፡፡ እንቅልፍ ወሰደን፡፡ ለእራት እንኳ መነሳት አቅቶን በዛው አደርን፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ፣ እንደሰመመን እንደምታድር በስልክ ስታወራ ስማኋት፡፡

ለሊት ከእንቅልፌ ስባንን አጠገቤ ተኝታለች፡፡ ሳያት በጣም ደስ አለኝ፡፡ ህልም አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ ፀጉሯ ተበታትኗል፣ ረጅምና ማራኪ ሰውነቷ ተበረጋግዷል፡፡ እርሷ ለጥ ብላ ተኝታለች፡፡ አልጋው ውስጥ ተገላብጬ ሰውነቷ ላይ ተለጠፍኩባት። ማታ የጠገብኳት
የመሰለኝ ደክሞኝ ነበር፡፡ ስሜቴ ዳግም ተላወሰ፡፡ አሁንም ውስጤ አልበረደም፡፡ እንድትነቃ አደረኳት፣ እንደ አዲስ እየተንገበገብኩ“እወድሻለሁ፣ በጣም ልዩ ነሽ፣ ስጦጠዬ ነሽ፡፡ እያልኩ እንደተላመደ
ሰው፣ የተለያየ አይነት የወሲብ ልፊያ እየቀያየርን በነፃነት ተላፍተን፣

ተመልሰን ተኛን፡፡ ጥዋት ስነሳ ሰዓቴ አራት ሰዓት ተኩል ይላል።ወላልቀን ስላደርን፣ መነሳት አቅቶን ስንንከባለል አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ ቆየን፡፡ የረሃብ ስሜቱ ሲጠናብን ምግብ ፍለጋ ወጣን፡፡ ምግቡ
በጣም ይጣፍጣል፡፡ተርበን ነበር፡፡ ከበላን በኋላ ድካሙ የባዕ ተጫጫነን፡፡ከትናንት ጀምሮ እረስተነው ወደ ነበረው ወደየ ራሳችን የሃሳብ ዓለም ተመለስን፡፡

“ዛሬም ወደ ቤት አትሸኘኝም?” አለችኝ ሃናን፡፡

“እህ እ! እንዲህ ገድለሽኝ፣ በምን አቅሜ ነው የምሸኝሽ...?” አልኳት ፈገግ ብዬ፡፡

“ኪ.ኪ...ኪ...፣ ጭራሽ እኔ ገዳይ? አላስተረፍከኝም እኮ፣ አውሬ!” የድካም ሳቅ እየሳቀች፡፡
👍4
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


በዚህ ጊዜ መላኩ ሁሉም ነገር የተደረሰበትና ያበቃለት መሰለው፡፡
ከአሁን በኋላ መቀላመድ ምናልባትም የታችኛው መንጋጭላውን በሽጉጥ
ሰደፍ ከማስገመስ በስተቀር ውጤት እንደማይኖረው ተረዳ፡፡
አሉ...ሁሉም አሉ.....እ...ጫት እየቃሙ ናቸው ቄራ... እንትና..ቤት. ስንዱ ቤት....አሳይሃለሁ....”ያልተጠየቀውን ሁሉ ይቀበጣጥር ጀመር፡፡

ቅደም” አለና በሽጉጡ አፈሙዝ ሲገፈትረው፤ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ፤ በጉምሩክ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በኩል አድርጐ፤ እንደ
ጥሩ በቅሎ ይሰግር ጀመር፡፡

ፖሊሱ ሽጉጡን መልሶ ከቦታው አስቀመጠና፤ በለስ ቀንቶት በእጁ
የገባለትን ሌባ ከፊት ከፊት አስቀድሞ ይነዳው ጀመር፡፡ መላኩ በድንጋጤ
ነበር፡፡ እንደዚያ እየተገፈተረ በፖሊስ ሲነዳ ድንገት የሚያውቀው ሰው እንዳያጋጥመው በልቡ ፀሎት እያደረሰ፤ እንደተዋጊ በሬ አቀርቅሮ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ከቦርሣው ውስጥ ምንድነው ያገኛችሁት? ” ጠየቀው፡፡ ከዚያ ቦርሣ
ውስጥ የተገኘውን በሙሉ ዘረዘረለት፡፡
የስርቆሹን ሂደት አንድም ሳያስቀር ተነተነለት፡፡ የ፶ አለቃ ውብሸት
በአጋጣሚው ተደስቶ፤ ድካሙን ለቆጠረለት አምላክ ምስጋና አቀረበና
መላኩን ይዞ በታክሲ ወደ አዲሱ ቄራ፤ ወደ ስንዱ ቤት በረሩ።

አሁን ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሆኗል፡፡ ጫቱ በጊዜ ስለተጀመረ አንዳንዶቹ መርቅነዋል፡
ስንዱ እጅጌ ጉርድ ነጭ ስስ ሹራብ፣ አጠር ያለ ቢጫ ጉርድ ቀሚስ ለብሣ በነጠላ ጫማ ሽር ጉድ እያለች፤ በጐደለው ታሟላለች ጫት ቃሚዎቹ ከሙቀቱ የተነሣ በላብ ተጠምቀዋል፡፡ ከዚህም ከዚያም የሚወረወሩት ቀልዶች ያፍነከንካሉ፡፡ የስንዱ ባለ ሁለት ስፒከር ቴፕ በተለይ በጫት ላይ መንፈስ የሚሰርቀውን የመሀመድ ወርዲን የሱዳንኛ ያንቆረቁራል፡፡ ማርታ የካዳሚነት ወጉን አውቃበታለች ለፕሮግራሙ ድምቀት የበኩሏን ድርሻ አበርክታለች፡፡

በጋሪ የተነገረው ቀልድ የሁሉንም ጫት ቃሚዎች ድድ አስገልፍጦ፣ከዚያ ጥግ የተለኮሰው የሣቅ ችቦ፤ ከወዲህኛው ጋር ተቀላቅሎ፤ ክፍሏ ተደምራ እየተቀጣጠለች በመንደድ ላይ እያለችና፤

የማያቋርጥ የሣቅ ፏፏቴ እየተስተጋባ፤ በመፍነክነክ ላይ እንዳሉ፣ የስንዱ
ዐይኖች በድንጋጤ ተበልጥጠው በሩ ላይ በቆመው ሰውዬ ላይ እንደተተከሉ ቀሩ፡፡
ወዲያውም መላኩ ጭራውን ወደ ውስጥ ሸጉጦ ኩምምሽ ብሎ አንገቱን አቀርቅሮ ገባ፡፡
የ፶ አለቃ ውብሸትን አስከትሎ በጓሮ በር በኩል ነበር የገባው፡፡ ምንም እንኳን ያንን ያክል የሚያሰጋ ነገር ይፈጠራል ብለው ባይገምቱም፧ ስንዱ በድንገት ሳቋን አቋርጣ፤ ፊቷ በድንጋጤ አመድ ሲለብስ በማየታቸው ፤ ደንግጠው፣ እሷ እሷን ሲመለከቱ ቀላ ረዘም ያለ ሰው መላኩን
ወደፊት ገፈተረና፡-
“እንዳትንቀሳቀሱ !” ብሎ በሁሉም ላይ ሽጉጡን ደቀነ፡፡ መላኩ ተንደራደረና ሄደ ስንዱ አልጋ ላይ በግንባሩ ወደቀ፡፡
ማርታ ቀስ ብላ ከስንዱ አልጋ ሥር ገብታ ተደበቀች፡፡ስንዱ አፏ ተከፍቶ መቅረቱን አላስተዋለችም፡፡
ጋሪና ኪኖ... ይሄ የውሻ ልጅ አስበላን” ተባባሉና በመላኩ ላይ ያደረባቸውን ቁጭት ተንሾካሾኩ፡፡ወይዛዝርቱ በየጓደኞቻቸው ብብት ሥር ተሸጉጠው ሲታዩ፤ ከጭልፊት ንጥቂያ ለማምለጥ እናታቸው ጉያ ስር የሚደበቁ ጫጩቶች ይመስሉ ነበር፡፡
በድንጋጤ ፀጉራቸው ቆሟል፡፡ በተለይም አንዱዓለም በሚያየው ያልተጠበቀ ሁኔታ ተደናግጦ አንዴ ሰውዬውን፤ አንዴ
ደግሞ ሂሩትን፤ ከዚያም እዚያ የተሰባሰቡትን በሙሉ በጥርጣሬ ዐይኑ
ይመለከታቸው ጀመር፡፡
“የትነው ያመጣሽኝ?” በሂሩት ላይ ጮኸባት፡፡
ከሁሉም የተለየችው ግን ሜርኩሪ ነበረች፡፡ ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው
ተገፍትሮ አልጋ ላይ በወደቀው በመላኩ ሁኔታ ልቧ አዝኖ ፈዛለች፡፡ስንዱ ከዚያ ከገባችበት ድንጋጤ ወጥታ ልቧ በትክክል መምታት ሲጀምር ምንድነው ነገሩ?” ስትል በ፶ አለቃ ውብሸት ላይ አፈጠጠች፡፡
በአስቸኳይ ልብሳችሁን ልበሱ! ሌላውን በኋላ እንነጋገራለን?” ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ሰው በቤቱ መጫወት አይችልም ማለት ነው፡፡?"ስንዱ በመገረም ጠየቀችው፡፡
እሱን ፖሊስ ጣቢያ ስንደርስ እንነጋገርበታለን አሁን ግን የምላችሁን
ብቻ እንድትፈጽሙ እጠይቃለሁ፡፡ ሕጋዊ ፖሊስ ለመሆኔ መታወቂያዬ
ይሄውላችሁ፡፡ ከዚህ በኋላ አንጃ ግራንጃ ለመፍጠር የሚሞክር ቢኖር ችግር ላይ ይወድቃል” አለና መታወቂያውን አሳያቸው፡፡

ሁሉም በድንጋጤና በብርክ ተውጠው፤ በታዘዙት መሠረት ልብሳቸውን መልበስ ጀመሩ፡፡

ስንዱ ከብስጭቷ የተነሣ ነይ ውጭ ከዚህ! ምን አባሽ ይወሽቅሻል ?” አለችና ማርታን ከአልጋው ሥር ጐትታ አስወጣቻት፡፡ በማርታ ሁኔታ የ፶ አለቃ ውብሸት የመጣበትን ሳቅ ዋጠው፡፡ እዚያች ትንሽ አልጋ ስር ያቺን የምታክል
ወፍራም ሴት ትኖራለች ብሎ አልገመትም ነበር፡፡፡
የጋሪ መንቀዥቀዥ አላማረውም፡፡
"ለማምለጥ እሞክራለሁ ያለ በህይወቱ ላይ ይቁረጥ!” ሽጉጡን በፊታቸው ሲያቀባብለው....
“ ዋ. ይ!” አለችና የኬኖ ጓደኛ ስንዱ ላይ ልጥፍ አለችባት፡፡
ሂጅ ወደዛ! ምን አባቷ ትጨማለቃለች?! አመነጫጭቃ ገፈተረቻት፡፡
የአሁኑን አያድርገውና ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በፍቅር ሲላላሱ ነበር፡፡ያ ሁሉ ፍቅር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተረሳ ::ከዚያም ከቤት ወጥተው እንደ መንጋ እየተነዱ ጉዞ ጀመሩ፡፡ እንደዚያ ሆነው ቢታዩ ለነሱ
ውርደት ነበር፡፡ ደግነቱ ምሽት ስለሆነ ብዙም ሰው አላያቸውም፡፡

የ፶ አለቃ ውብሸት አንድ ውይይት ታክሲ ተኮናተረና፤ ሁሉንም አሳፍሮ፤ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አቀኑ :: ከዚያም ፖሊስ ጣቢያ ሲደርሱ፤ ሴቶቹ ወደ ሴቶች እስር ቤት ሲገቡ፤ እነ ኬኖም ወደለመዱት የዘወትር
ቤታቸው እንዲገቡ ተደረገ፡፡ከወንዶቹ መካከል እስር ቤት ምን እንደሆነ የማያውቀውና ዛሬም በማያውቀው ነገር እዚህ ጣጣ ውስጥ የገባው አንዱዓለም ድንበሩ ብቻ ነው፡፡
ተረኛው ፖሊስ እሱን ከሌሎቹ ነጥሎ ይዞት ከሄደ በኋላ፤ አንዱን የእስር ቤት በር ከፍቶ ወደ ውስጥ ገፈተረውና በሩን መልሶ ዘጋው፡፡
አንዱዓለም የገባበት ክፍል የታፈነና እንደ ሲኦል የከበደ ከመሆኑም ሌላ፤ የሚሰነፍጥ መጥፎ ጠረን አፍንጫውን ስለሰረሰረው፤ አስነጠሰው፡፡ክፍሉ ለተወሰኑ ሰኮንዶች እንደሙታን አምባ ፀጥ ረጭ ያለ ቢመስልም፣ዐይኖቹ ጨለማውን ተለማምደው፤ ትንሽ በትንሹ ማየት ሲጀምሩ፤በጥርጣሬ የቆሙት ጆሮዎቹ የሆነ የሚርመሰመስ ድምጽ አስተላለፉለት።
ዐይኖቹን በቀኝ እጁ አሽት፤ አሸት፤ አድርጉ ክፍሉን ለመቃኘት ሲሞክር፤ አንድ ጠንከር ያለ መዳፍ፤ በታችኛው አገጩ ከመንጋጋው ላይ ሲያርፍበት፤ በትክክል ፊቱ ወደ ኋላ መዞሩን አመነ፡፡ ወዲያውም አይነ ስቡ ላይ የተከደነበት ጥፊ እሳት መሣይ ነገር ብልጭ አደረገለት፡፡

“ወይኔ እማዬ” አለና እያለቀሰ ወደታች ወረደ፡፡ከዚያም ጡንቻው ፊቱ የተጠባበሰ፣ ወጠምሻ ከበላዩ
የፈረጠመ ፤ ቁመቱ ረዘም ያለ
መቆሙን አስተዋለ፡፡
“ ምነው? ምን አደረኩኝ? “ አለው እያለቀሰ፡፡
የሻማ ! " ሲል እጁን ዘረጋላት :: አልገባውም፡፡
የምን ሻማ ? “
“ ገንዘብ ! "
አልነበረውም፡፡
ጮኸበት፡፡ እሱ እንደሆነ በኪሱ ውስጥ ሰባራ ሳንቲም አልነበረውም።
ምንም ገንዘብ የለኝም፡፡ ከፈለክ ፈትሽኝ፡፡ " አለና ዙሪያ ገባውን ተመለከተ፡፡
የበርካታ እስረኞች ዐይኖች ሲቁለጨለጩ አየ፡፡ ወጠምሻው ኮሌታውን ጨምድዶ አስነሳና ኪሶቹን እየገለበጠ ፈተሻቸው፡፡ ምንም አጣ፡፡
"እዚያ አስረክቦ ነው የመጣው ፈላ!” በንዴት ማጅራቱን አንቆ ሲወርውረው፤ ተስፈንጥሮ የሆነ ጥግ ላይ ተወተፈ፡፡

በዚህ ጊዜ ያ በርቀት የሚሰነፍጠው ሽታ በቅርበት አግኝቶት አፍንጫውን እንደጦር ይወጋው ጀመር፡፡
1👍1👎1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

የምትለው፡፡ በረጅሙ ተነፈሰ ናትናኤል በጨለማው ውስጥ ማጅራቱን
እያሻሽ፡፡

ምን ያህል እንደቆየ ትዝ አይለውም፡፡ • 'ዝ ፡ ዝ ዮሚለው የማያቋርጥ የትንኝ ድምጽ ጆሮው ላይ አዜመበት። ድንገት የክፍሉ
መብራት ቦግ አለ፡፡ መብራቱን ያበሩት ከውጭ እንደሆነ ገባው። በጊዜ ጥግህን ያዝ ነው ነገሩ ብሎ አሰበ፡፡

በጠቧቧ ክፍል ውስጥ ለአይን የሚስብ ምንም ነገር አይታይም፡፡
ከወዲያ ጥግ ከበሩ ትይዩ በሥነሥርዓት የተነጠፈ ጠባብ አልጋ አለ፡፡
ይኸው ነው:: ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ ወደፊት ተራምዶ ኣልጋው ጫፍ ላይ
ተቀመጠና ጭንቅላቱን ሁለት መዳፎቹ መሃል ቀብሮ ያስብ ጀመር:: ብዙ
አልቆየም እንደፈራው የክፍሉ መብራት ጠፋ፡፡ ናትናኤልን ግን ከሃሳቡ
ኣልቀሰቅሰውም፡፡

አንድ ነገር አግኝቶ መሆን ኣልበት አብርሃም የደወለለት፡፡ ከቻለ ሊረዳው ቃል ገብቶለት ነበር፡፡ ቀን ምሳ በልተው አብርሃም “በዘጠኝ ሰዓት ከጓደኛዬ ጋር ኢትዮጵያ ሆቴል ቀጠሮ አለኝ…” ስላለው እዚያው ካደረሰው በኋላ ፍንጭ ካገኘ ሊደውልለት ተስማምተው ነበር፡፡

“አብርሃም ለማለት የፈለግኸው ገብቶኛል... ሁኔታው ውስብስብና
አደገኛም ነው.. ግን በማቀርበው ሪፖርት ላይ ነገሩን አደባብሼ ማለፉን አልፈልግም… ገባህ? .… ስለዚህ የሚጠቅመኝ አዲስ ሃሣብ ካገኘህ ደውልልኝ እ?” ነበር ያለው ናትናኤል መኪናውን ኢትዮጵያ ሆቴል በራፍ ላይ
አቁሞ ከመሰነባበታቸው በፊት፡፡

“ምን ቸገረኝ ናትናኤል.… እንቆቅልሹን ብፈታውኮ እኔም ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ራሴን ለአደጋ ማጋለጥ አልፈልግም.. ደግሞ ፈጠነም
ዘገየ አባት መሆኛዬ ደርሷል። ፈገግ አለ አብርሃም፡፡ “ልጄ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ አባት ይፈልጋል፡፡”

“ውለታ መላሽ ያድርገኝ፡፡” ናትናኤል እጁን ዘረጋለት ተጨባበጡ፡፡

“እ... በነገራችን ላይ ከተገናኘን አይቀር ለምን አልነግርህም እንዳልኩህ ጥቅምት ላይ ማግባቴ ነው» አለ ኣብርሃም ፈገግ ብሎ ጺመን በኩራት እየላጉ፡፡ «ሃ! ሃ! ሃ! ሃ! ሚዜዩ እንድትሆን ብጠይቅህስ?”

“ቸኮልኩኝ!” ናትናኤል ስሜቱን መደበቅ አልሆነለትም::
“አብሮ ማደግ ቀላል ነገር አይደለም፡፡” የጓደኛውን ትከሻ ቸብ አድርጎ አብርሃም ከመኪናው ወረደ፡፡ “ቻው ናቲ! እደውልልሃለሁ ለማንኛውም::” .

'ደወለ፡፡ ግን ምን ፈልጎ ደወለ? ምን ሊነግረው ደወለ? ምን አግኝቶ ደወለ?' ናትናኤል በመቆያ ቤቱ ኣልጋ ላይ ቁጭ ብሎ ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ ክንዶቹን ጉልበቶቹ ላይ ቸክሎ ለጥያቄው መልስ ፈለገ፡፡ ለምን ደወለ?..
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ስልኩ ሲያንቃጭል ጋለል ካለችበት ፎቴ ላይ በርግጋ ተነሳች::
በመጨረሻ… ሸለብ አድርጓት ነበር፡፡
ሌሊቱን ቁጭ ብላ ነበር ያደረቸው፡፡ ማታ እንደሄደ . 'ቶሎ ይመለሳል' ብላ ስላሰበች ተመልሳ አልጋ ውስጥ ገብታ ተኛች:: ብንን ስትልና ሰዓቷን ስትመለከት ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ከአስር ነበር፡፡ ዞር ብላ ከጎኗ ተኝቶ እንደሆነ በጨለማው , ውስጥ አልጋውን ዳሰሰችው፡፡ አልተመለሰም፡፡
መብራቱን አብርታ ድጋሚ ሰዓቷን ተመለከተች:: ልክ ነች፡፡ ከሶስት ሰዓት
በላይ ሆኖታል ከሄደ፡፡ ቅንድቦቿን ኣጠጋግታ ለማሰብ ሞከረች፡፡ እስካሁን
እንዴት ያቆያል፤ , ችግር አጋጥሞት ይሆን ኣብርሃም? ታዲያ ችግር ሲያጋጥመውስ እንዴት ደውሎ እንዲህ ነው አይላትም…. ርብቃ አልጋው መሃል ቁጭ ብላ ታወጣ ታወርድ ጀመር፡፡ እሱ እራሱስ እንደዚያ ተቻኩሎ ሲሄድ አደጋ ገጥሞት እንደሆነስ? ገብሬልዬ! ሆዷ ውስጥ ያለው ልጅ የተላወሰ መሰላት፡፡ ዳበስ አደረገችው ሳይታወቃት፡፡ ስጋት ይጠረጥራት ጀመር፡፡ ግንኮ ከዚህ ታኝታ ቢደውልምኮ አትሰማውም፡፡ እስካሁንስ ደውሎ አቅቶት እንደሆነስ?'

ፈጠን ብላ ብርድ ልብሱን ከላይዋ ላይ ገፋ ከእልጋው ተነሳች፡፡ ፒጃማዋ ላይ የጠዋት ልብሷን ደረበችና ወደ ሳሎን ገባች፡፡ ከስልኩ አጠገብ ፎቴ ላይ ተቀመጠችና አይኖቿን ከፊት ለፊት ካለው የናትናኤል ፎቶግራፍ ላይ ኣሳረፈቻቸው::
ምን ሆኖ ይሆን? እንዴት ኣይደውልም? ሰው ያስባልም ኣይል? ሰዓቷን ተመለከተች ሰባት ከሃያ።

ጊዜው እየተሽረሸረ ሌሊቱ እየተናደ ሰሄደ ቁጥር የርብቃም ሆድ . እየተከፋ ሄደ፡፡ ሁለቴ መታጠቢያ ቤት ደርሳ ተመለሰች:፡ እውነት በጤናው ይሆን?' ሰዓቷን ተመለከተች ዘጠኝ ከሩብ፡፡ ክፉው ታሰባት፡፡ “ቀስ ብለህ ንዳ” ሲሉት አይሰማ! በዛ ዝናብ ሲሮጥ… ገብሬልዩ! ሰዓቷን ተመለከተች ዘጠኝ ከሃያ::
ሌሊቱ የሸሸ ንጋቱ እየቀረበ ሄደ ናትናኤል አልተመለሰም ፤ አልደወለም፡፡

ስልኩ መልሶ አምባረቀባት፡፡ ፈራችው:: ሶስተኛ ጊዜ እሪ አለ ፈጠን ብላ አነሳችው
“ሃሎ"
“ሃሎ ርብቃ…? ”
“ናቲ! ደህና ነህ?” አለች ድምፁን ስትሰማ፡፡
“ደህና ነኝ ርብቃ::” -
“ትንሽ አታስብም ሰው ያስባል ብለህ!” ኣቋረጠችው:: የአገር ንዴት ጉሮሮዋ ውስጥ ተማገደ፡፡ የእፎይታና የመረጋጋት ስሜት ሰውነቷን ሲወረው ሳይታወቃት አይኖቿ በእንባ ተሞሉ፡፡

“ርብቃ ስሚኝ.… ችግር አጋጥሞኝ ነው:: ቆይ ርብቃ ስሚኝ…” አላ ድጋሚ ልታቋርጠው ስትል ተሽቀዳድሞ፡፡ «ርብቃ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ነኝ፡፡»

“ፖሊስ ጣቢያ?!” ጮህ አቋረጠች፡፡ የሰማቸውን ማመን አልቻለችም፡፡ “ታስሬአለሁ ነው የምትለኝ?!” ደነገጠች፡፡ ፖሊስ ጣቢያ? ፖሊስ ሌባ.… ለአንድ አፍታ የእሷን ናትናኤል የፊጢኝ እስረው ፀጉሩን ላጭተው'አየገፈተሩ ከወረበሎች ታዛ ሲደባልቁት ታያት፡፡

“ርብቃ እባክሽ ረጋ ብለሽ ኣዳምጪኝ፡፡ ማታ መንጃ ፈቃድ ረስቼ ስለወጣሁ ነው እዚሁ ያሳደሩኝ፡፡ ይልቅ መታወቂያዬንና የመንጃ ፈቃዴን ይዘሽልኝ ነይ፡፡ የመኪናዋን ሊብሬም እዚያው ታገኚዋለሽ፡፡ ታውቂዋሽ አይደል ኣምስተኛን?''
“ማንን?”
“እምስተኛን?”
“አምስተኛ! ” ግራ ገባት ርብቃ፡፡
“ኣምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ!” ናትናኤል ትዕግስቱ እልቅ አለበት፡፡
“የት ነው? አላውቀውም ናቲ”
“እይው... ሜክሲኮ አደባባይጋ ከደረስሽ በኋላ… ”
ርብቃ ከየት ወዴት ልብሷን እንደቀያየረች ትዝ አይላትም፡፡
'ውሸቱን ነው! ሰው መንጃ ፈቃድ ረሳህ ተብሎ እስር ቤት አይገባም!
ውሸቱን ነው:: አንድ ነገር አለ፡፡ ሆዷ ተንጓጓባት፡፡ መታጠቢያ ቤት ቶሎቶሎ ቀሚስ... በጭንቅላቷ… ጫማዎቿ ውስጥ ዘላ ገባች ቶሎ.... ቦርሳዋን ይዛ ወጣች፡፡ የኣፓርትመንቱን በር ከውጭ ስትቆልፍ፡
የረሳችው ትዝ አላት መንጃ ፈቃድ! መታወቂያ! የናቲ! በሩን ከፍታ
ገባች፡፡ ወደ መኝታ ቤት ሮጣ የራስጌ ኮመዲኖ ፈተሸች፡፡ የለም፡፡
መሳቢውያን ስባ አየች:: የለም:: ቆም ብላ ኣሰሰች:: የት ነው አስቀምጦ የሄደው? ኣሃ! ቁም ሳጥነ!! ራመድ ብላ ቁም ሳጥኑን ክፈተች፡፡ የላይኛው መደርደሪያ የመሃለኛው የታች የለም:: ርብቃ ግራ ገባት:: መኝታ ቤቲ መሃል ቆማ ቀረች፡፡ ዙሪያውን ተመለከተች:: የት ነው ያስቀመጠው? ኮቱን አነሳቸው:: ኡፍ… ፍ!
የገንዘብ ቦርሳውን አወጣች፡፡ ከፈተችው፡፡ ሳንቲሞች ተዘረገፉ ቅጭልጭል እያሉ በየስርቻው ተበተኑ:: መታወቂያ ወረቀት? አዎ የመንጃ ፈቃድ? አዎ፡ ሮጣ ወጣች - መንገዱ ጭር እንዳለ ነው::

ታክሲ ተሳፍራ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ደረሰች፡፡

“ምንድንነው?” አላት በር ላይ የቆመው ፖሊስ እጆቹን ከኪሱ ሳያወጣ ፡

“ስልክ ደውለው ጠርተውኝ ነው፡፡ ልግባ?”
“ማንን ነው የፈለግሽው?”
“ሰው፡፡ እዚህ ያደረ፡፡” አለች ርብቃ እስረኛ ማለቱ ሲቀፋት፡፡
. “እስረኛ ነው?”
“እ... ” 'ናቲ እግዜር ይይልህ!'
“ታዲያ እንደሱ አትይም… ግቢ፡፡” አለ ጭንቅላቱን ወደጎን መታ
👍1
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...ስሜቴ በመጠኑ በመለወጡ ደስታ መሰል ሁኔታ ተሰማኝ። ደስታዬ እርሷ በመታስሯ ሳይሆን እርሷ ትሆን በማለት ሲዋልል የሰነበተው ጥርጣሬዬ ወደ
አንድ መጠነኛ ውጤት በመቃረቡ ነበር፡፡ ወደ ውጪ ወጣ ብዬ ወደ ግራ ተጠመዘዝኩ። ጥቂት ርምጃዎች እንደ ተራመድኩ ፊቴን ወደ ሰሜን መለስኩ፡፡
እስር ቤቱ ከፖሊስ ጣቢያው በስተጀርባ ነው፡፡ አረማመዴ ፈጠን ያለ ስለነበር
ጠበንጃ ይዞ የቆመው ዘብ «ቁም ወዴት ትሄዳለህ?» አለኝ። ሥርዓት እንደጣስኩ
ገባኝ፡፡

ቃሉ ቃለ ሕግ በመሆኗ ቀጥ አልኩ፡፡ ቀጠን ሳለች አስደንጋጭ የቁጣ
ድምፅ «ማንን ነው የምትፈልገው?» አለኝ።

«አንዲት ሴት እስረኛ ለመጠየቅ ነው?» ብዬ ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ
መለስኩለት። ለአካባቢው ፍፁም እንግዳ መሆኔ ገባው:: ውስጡ ትሁት እንደሆነ
ተሰማኝ፡፡ ፈገግ አለልኝ። ፈገግታው እለመቆጣቱን ስላስረዳኝ አራት እርምጃዎች ወደፊት ቀጠልኩ፡፡ እሷ መሆኗን ባላረጋግጥም የወዲያነሽን እስረኛ በማለቴ የልቤ ግርማ ሞገስ ተገፈፈ፡፡ በወታደሩና በእኔ መካከል ከስድስት ደኅና ደኅና ርምጃ
የማይበልጥ ርቀት ነበር፡፡

«ምን ይዘሃል? ባዶ እጅህን ነው እንዴ እስረኛ ጥሩልኝ የምትለው? እስረኛ እኮ በማንኛውም ሰዓት አይጠየቅም፡፡ የተወሰነ ጊዜ አለው» አለ አሁንም
በመጠነኛ ፈገግታ። አነጋገሩ የሰውየውን የፈቃደኝነት ስሜት ስላስረዳኝ ሁለት
እርምጃዎች ጨመርኩ፡፡

«ገና እርሷ መሆኗንም አላረጋገጥኩ፡ መጀመሪያ ላረጋግጥ ብዬ» ሳልጨርስ አይኖቼ ዕንባ አቀረሩ፡፡ ጊዜም አልሰጡኝ፡ ተንጠባጠቡ። እምብዛም ጥልቅ ኀዘን በማይታይበት ፊቴ ላይ ዕንባ ሲወርድ በማየቱ፣

«ምነው ምን ነካህ? ወንድ ልጅ ያውም አንተን የሚያህል ያለቅሳል እንዴ?» አለኝ፡፡

«ምንም አልሆንኩ፡ እንዲያው ብቻ...»
«ለመሆኑ ማን ትባላለች?»
«የወዲያነሽ ትባላለች?»።
«እረግ! ኧረ! ያቺን ዕብድ አይሏት ጤነኛ ነው እንዴ? እሷማ ያቻትልህ! ያቺው ተጨብጣ ተቀምጣልሃለች! በል ሂድ! ፈጠን በል! ታዲያ ሥርዓቱን ባለማወቅህና እደጅ በመሆኗ ነው እንጂ እቤት ውስጥ ብትሆን ኖሮ
አይፈቀድም ነበር። እዚህ ድረስም አይመጣም ሰዓቱም ገና ነው» ብሎ አደራ አዘል ፈቃድ ሰጠኝ። አጠገቧ ከመድረሴ በፊት ትንሽ ራቅ ብዬ ቆምኩ::
ሲሽመደመድ የሰነበተው ጥርጣሬዩ ቀና አለ፡፡

ቀሚሷ ተዘነጣጥሎ ተቀዷል፡፡ እግሯ በእሳት የተለበለበ የክትክታ ዕንጨት መስሎ ዐልፎ አልፎ ልብሷ ላይ ጭቃ ተለጥፏል። የተራቆተው ግራ ቀኝ ክንዷ ዐመድ የተነሰነሰበት መስሎ ጽጉሯ እዚህና እዚያ የተነቀለ የጓያ ማሳ
መስሏል። መናገርም መራመድም አቃተኝ፡፡ የወዲያነሽ ጉስቁልና ለሁለተኛ ጊዜ አናቴ ላይ ተከመረ፡፡

ጥርጣሬዬ ጥርጣሬ መሆኑ ቀረ። ለየለት። የወጺያነሽ ተገኘች! ያም ሆነ ይህ የፍቅር ዐይኖቼ አላምጠው ዋጧት እንጂ አልተጸየፏትም። አእምሮዬ ውስጥ
የፍቅር ደማቅ ነበልባል በራ እንጂ የጥላቻና የንቀት ጥቁር ማቅ አልተሸመነም።አንድ ቀጠን ያለ ድምፅ ከበስተጀርባዬ ቶሉ በል እንጂ ሰውዩ!» ሲለኝ ሰማሁ:: በሐሳብ ከማንቀላፋበት አጭር ሰመመን ባነንኩ፡፡ ወደፊት ራመድ ብዪ ከወዲያነሽ አጠገብ ቆምኩ፡፡ ጉልበቷ ላይ ተደፍታ ስለነበር ድንገት ስናገር እንዳትደነግጥ የቆምኩበትን ሸካራ ንጥፍ ድንጋይ በቀኝ እግሬ ረመረምኩት።የፈራሁት አልቀረም፣ በድንጋጤ ባንና ተነሣች። በጣም ከስታለች። ፊቷ ጢስ የጠገበ ቋንጣ መስሏል፡፡ ልብ ብሎ ባላየ ዓይን ቀና ብላ አየችኝ። ማን መሆኔን አላወቀችም፡፡

አገጯን በእግሮቿ መሃል አስገብታ እግር እግሬን እየተመከለተች
«ምነው? ምን አጠፋሁ? ወድጀ እኮ አይደለም! ምን አባቴ ላድርግ! የሚላስና
የሚቀመስ በማጣቴ በረሃብና በችግር ከሚሞት ለነፍሴ ያለ ወስዶ እንዲያሳድገው ብዬ መንገድ ዳር አስቀመጥኩት፡፡ ምነው ሞቴን ባቀረበው?» ብላ ንግግሯን እንደ
ጨረሰች ቀና ስትል የሻገተ እንቀልባ በመሰለው ጉንጫ ላይ ዕንባዋ ተዝረበረበ።

በቁጣ ስሜት ዐይኗን አፍጥጣ «ከዚህ ወዲያ ምን እሆናለሁ ግደሉኝ!
ስቀሉኝ! አንጠልጥለኝ?» አለችና ጉልበቷ ላይ ደፋ አለች።

ጐንበስ ብዬ የቀኝ እጅ ክንፏን ያዝኩና «እኔ ነኝ እኮ የወዲያነሽ፣ እኔ ጌታነህ እኮ ነኝ» አልኳት፡፡ ቀስ ብላ ቀና ካለች በኋላ አፏን በፍርሃትና በድንጋጤ ከፈተችው፡፡ በሰውነቷ ውስጥ ይገኛል ተብሎ በማይገመት እንቅስቃሴ ተነስታ
አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ አይፈቀድም ያለኝ ፖሊስ
ምን ይል ይሆን በማለት ፈራሁ፡፡ መንማና ክንዶቿ ሥጋው ተፈቅፍቆ የወደቀ አጥንት እንጂ ሥጋ የለበሱ አይመስሉም፡፡ አንገቴ ላይ ተጠምጥማ እዬዬዋን ለቀቀችው፡፡ ተንሰቀሰቀች። የሟሸሹ ጉንጮችዋን ሳምኳቸው:: ደርቆና ተሰነጣጥቆ
ያረረ ደረቆት የሚመስለው ከንፈሯ ሻካራ ድንጋይ መስሏል። ያ ዝንፍልፍልና
የውበቷ ደረባ የነበረው ጸጉሯ ተሸላልቷል። አምክ እምክ የሚሽተው ጠረኗ የሥቃይዋን፡ ብዛት ያስረዳል፡፡ አይቼ ሳልጠግባትና አንዳች ነገር እንኳ ጠይቄ ሳልረዳ ፖሊሱ “በቃህ!» ብሎኝ ተመለስኩ:: እንባዋን እየረጨችና እያለቀሰች ተለያየን።

"እኔና የወዲያነሽ ተለያይተን የምንቆየው እስከ መቼ ይሆን ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። እጅ እግር ላልነበረው ለዚህ ድፍን ጥያቄ አሁን በአሁን መልስ አላገኘሁም፡፡ አዲስ የፈተናና የስራ ገፅ ተከፈተ። ወደ ቤቴ ከመመለሴና የወዲያነሽንም መታሰር ለጉልላት ከመንገሬ ቀደም ብዬ አንድ ነገር ለማከናወን ወሰንኩ። በኪሴ ውስጥ የነበረችኝን የገንዘብ ልክ ዐወቅሁ፡፡ ከዚያም አራዳ ልብስ ተራ ገባሁ፡፡ በግምት አንድ ጥሩ ቀሚስ እና የውስጥ ልብስ፡ በቀድሞ ቁጥሯ አንድ ተራ ጫማ፣ ዋጋው ቀነስ ያለ የብርድ ልብስ ወዲያ ወዲህ ተሯሩጬ ገዛሁ፡፡

ኀዘንና ደስታዬ በመስተካከሉ መፈንጠዣና መተከዣ የሚሆን ምክንያት አገኘሁ፡፡ የገዛሁትን ልብስ በፖሊስ አስመርምሬ ለየወዲያነሽ ሰጥቻት ተመለስኩ፡፡

ከዚያች ዕለት ጀምሮ በየሣልስቱና ባመቸኝ ቁጥር እየተመላለስኩ
መጠየቄን ቀጠልኩ። አብዳለች፣ ወፍፏታል የተባለው ሁሉ ጠንባራ ስሕተት
መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ከሁኔታዎቿ አረጋገጥኩ፡፡

ከግራና ቀኝ የቆሰለ ሰው ሁለቱንም ቁስሎቹን ተራ በተራ እንደሚያይና እንደሚያክም ሰው፡ እኔም ልክ ከዐሥር ቀን በኋላ እንደገና ወደ ጋንዲ ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ የተስፋ ቅራሪ ሳይሆን የርግጠኛነት ድፍድፍ ይዣለሁ፡፡
ልክ ሁለትና ሁለት ኣራት እንደሆነ ሁሉ ጋንዲ ሆስፒታል ውስጥ የተኛው ሕፃን
የየወዲያነሽ ልጅ መሆኑን ከዚህም ከዚያም እጅግ በሚገባ አረጋግጫለሁ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የአጥንቴን ክፋይና የሥጋዬን ቁራጭ በአንዲት አነስተኛ ጠባብ ኣልጋ ላይ ደስ በሚያሰኝ ጥንቃቄና አኳኋን ተኝቶ አየሁት።

የወዲያነሽ መታሰር ልጁም ልጅዋ መሆኑን ማመኗ አብስለሰለኝ፡፡ ይህ
ሁሉ ከመሆኑ በፊት ባገኘኋት ኖሮ!!... እያልኩ በማሰብ፣ እከሌ እኮ እንዲህ
ቢደረግለት ኖሮ አይሞትም ነበር እያሉ ስለ ሞተ ሰው እንደሚጸጸቱ ሰዎች
በጸጸት ተቃጠልኩ፡፡ ዐመድ እንደገና ዕንጨት አይሆንምና ሐሳቤ በነነ፡፡ ያም ሆነ ይህ ሕይወት እጆቿን ዘርግታ ክቡር ስጦታ ሰጠችኝ! የእኔና የየወዲያነሽ ፍቅር
ጊዚያዊ መሪር ፍሬ አፈራ።

አስታማሚዋ አጠገቤ እንደ ቆመች ጎንበስ ብዬ ደጋግሜ ግንባሩን ሳምኩ፡፡ ከወዲያነሽ ማሕፀን የተገኘውን ክቡር ፍሬ እሷን በሳምኩበት ከንፈሬ
በመሳሜ ልቤ በደስታ ቦረቀች። በሕይወት መቃብር ውስጥ የሚፍለከለከው የወዲያነሽ ኑሮ ግን መንጠቆውን ይዞ አንጠለጠለኝ፡፡ በጸጥታ የሚያንቀላፋውን ሕፃን እየተመለከትኩ 'ጌታነህ! አንተ ጌታነህ! ዛሬ ደግሞ ሌላ
👍3
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


..ካዛንችስ ማታ ማታ ትርምሱና ጫጫታው ልዩ ነው። ስሪ ዶርስ..
ፋይቭ ዶርስ የቀኑ እንደ ምሽቱ ባይሆንም ግርግር ይበዛል። ዛሬ ጌትነት የተወዳደረበት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ከየአቅጣጫው ተሰባስ በው በሰርቪሱ ውስጥ ግጥም ብለው ሞልተው ወደ ካንዛንቺስ በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡ ሁሉም የየራሱን ወሬ ያወራል፡፡ ያወካል፡፡ ይስቃል። ይሳሳቃል። የዕለቱ አቢይ የጋራ አጀንዳ ሆኖ ብዙዎችን ሲያወያያቸው የነበ
ረው ግን የአቶ ሽመልስና የአቶ አባይነህ ክርክር ጉዳይ ነበር፡፡
"ምነው እሱ ጥምድ አድርጎ ያዛት በናትሽ? ጠይቋት እምቢ ብላው ይሆን
እንዴ?" አንዷ ለሌላዋ...
"ምን አውቄለት እንደዚህ የጉሮሮ አጥንት የሆነባት ያለምክንያት ይሆናል ብለሽ ነው? ምቀኛ ! የሷን እንጀራ እሱ አይበላው?!"
"ይገርምሻል! አስተዳዳሪውንም ወንጅሏቸዋል ነውኮ የሚባለው!"
“አይ አንቺ እንግዳ ሆኜ ነው እንደ አዲስ የምትነግሪኝ? ከመወንጀል አልፎ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን አጣርቶ ለዋና ሥራ አስኪያጅ አቅርቦት የለም እንዴ?" ለቀባሪው አረዱት መሆኑን አብራራችላት፡፡
"ተይ እንጂ” ዐይኗን አፍጥጣ ።
“ሽመልስን የዋዛ ደራቁቻ አድርገሽዋል ለካ!ትናንትና ነበር የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል የተባለው። ከዚያ በኋላ የሆነውን እንኳ ገና አልሰማሁም"
ወይ ጣጣ! ሰውዬው ያለምክንያት ተንቀዠቀዠ ብለሽ ነው?" ከወዲያ
ማዶ የተቀመጡት ስለ ሽመልስ የሚያወሩት የተለየ ነበር፡፡
"ሰምተሽልኛል? የሚከራከርለት ልጅ ዘመዱ ነው አሉ። የአጎቱ ልጅ ነው
እየተባለ ይወራል። ኽረ ሌላም ይባላል። አስቀጥርሃለሁ ብሎ ጉቦ ተቀብሎታል የሚል ሃሜትም አለ፡፡ ብቻ ወሬው ብዙ ነው"
"ወቸ ጉድ! በጣም ይገርማል። ሽመልስ እኮ እንደዚህ ያለ ምቀኛና ተንኮለኛ አይመስለኝም ነበር?!"
“እስከዛሬ ድረስ እንዴት ሳታውቂው ቀረሽ? አንዴ ሙጭጭ ካላ መቼ
ይለቃል? የደረቀ ችኮ አይደለም እንዴ?!" በእነ አቶ አባይነህ የነቀዘ አስተዳደር ምክንያት የትውውቅ ቅጥር የበዛበት መ/ቤት በመሆኑ ከጋቢናው አካባቢ የተቀመጡት ወንዶችም የዚሁ ትኩስ ወሬ ተጋሪዎች ነበሩ።
“አንበሳው ያንን ቦርጫም ሠራለት አይደለም?!"
"ሰራለት ትላለህ? ጉድ አደረገው እንጂ! የአክስትና የአጎቶቹን ልጆች እያግበሰበስ ያልፈነጨውን ያክል ጉድ አደረገው!"
"እንደዚህ ከተጋለጠ ከሥራ ሳይባረር ይቀራል ብለህ ነው?"
ድርጊቱ ከሥራ የሚያስወጣው ቢሆንም ይሯሯጣል። አባይነህ የዋዛ ሰው እንዳይመስልህ! በወዳጅ በአማላጅ ይማፀናል” ምን ዋጋ አለው ታዲያ? ያ ሁሉ ማጣራት? ያ ሁሉ ድካም? "
“እንደዚያ ሽንጡን ገትሮ የተሟገተለት ያለምክንያት ይመስልሃል?"
“እሱን እንኳ መጠርጠር ነው! ያለ በቂ ምክንያት ማን ለማን እንደዚህ
ይሟሟታል?”
“ተው እባክህ ሁሉም እንደ ሽመልስ ስለእውነት ቢታገል ምንኛ መልካም
ነበር" አለ ሌላው የተለየ አስተያየቱን እየሰነዘረ።
“ወንድ ነው! ዐባይነህን ከመሰለ ዝሆን ጋር ታግሎ ለዚህ መብቃቱ የሚያስገርም ነው!” አለና ሃሳቡን አጠናከረለት ሌላው፡፡
“አሁን ሊለይለት አይደል? ድጋሚ ፈተናው ከሁለትና ሶስት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሊሰጥ ነው አሉ"
“እኔ እዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ አስር ዓመት በላይ ሳገለግል ይህንን
የመሰለ ፍትሃዊ እርምጃ ሲወሰድ ያየሁት አሁን ገና ነው
“እኔ ግን በሌላ መስሪያ ቤት ተመሳሳይ ሁኔታ አጋጥሞኛል። አንዱ እንደዚሁ ለአስተዳዳሪው ጉቦ ሰጥቶ ተቀጠረና የአንድ ወር ደሞዙን ሳይበላ እሱም አስተዳዳሪውም በአንድ ደብዳቤ ከሥራ ተባረሩ። ተወዳዳሪው ጮማ ዘመድ ነበረው። አስተዳዳሪው ቁልፍ ቦታ የያዘ ዘመድ እንዳለው ሳያውቅ ፈተናውን ያለፈውን ሰው ይጥልና ጉቦ የሰጠውን ሰው ይቀጥራል። ከዚያማ ምን ትጠይቀኛለህ? አስተዳዳሪዋን ከላይ ከታች አጣደፏት።ሁኔታው እላይ ድረስ ተሳቅሎ ያለምንም ተጨማሪ ማጣራት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀጣሪም ተቀጣሪም በአንድ ላይ ተሸኙ "
"ግን ሽመልስ የልጁ ዘመድ አይደለም ብለህ ታስባለህ?
“እምልልሃለሁ! ምኑም አይደለም። ከዚህ በፊት አይቶት እንኳ እንደማያውቅ ከራሱ ከሽመልስ አንደበት ነው የሰማሁት። ለምን አይን ያወጣ አድልዎ ይፈፀማል? ተወዳዳሪዎቹ ተመጣጣኝ ሆነው ቢገኙ ኖሮ ቅር አይለኝም ነበር ይሄ አይን ያወጣ ብቻ ሳይሆን ቀንድ ያወጣ በደል
ስለሆነ በቀላሉ አንላቀቅም እያለ በቁጭት ሲናገር ሰምቼዋለሁ" ሠራተኛው በሙሉ እያንሾካሾከ ስርቪሱ ከመስሪያ ቤት ደረሰ፡፡ ሽመልስ የበላይ ሃላፊው የስጡትን ውሳኔ እንደሰማ ወዲያውኑ ለጌትነት ስልክ ደወለለት፡፡ ስልኩን ያነሳችው የአብዱላሂ ሚስት ፋጡማ ነበረች።ጌትነት ያለመኖሩን ስትገልፅለት ጠዋት እደውላለሁ እንዲጠብቀኝ ንገሪው ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡ በማግስቱ ከሰው በፊት ቀድሞ ቢሮው የገባው ፋጡማ መልዕክቱን በትክክል ስለማድረሷ ምንም ጥርጣሬ ሳያድርበት ውሳኔውን በጠዋቱ ሊያስታውቀውና ለሁለተኛው ዙር ፍልሚያ ራሱን እንዲያ
ዘጋጅ ሊያሳስበው ነበር፡፡ ፍልሚያው በገሃድ በፀሃይና በጌትነት መካከል
የሚካሄድ ቢሆንም በስውር ደግሞ በእሱና በአቶ አባይነህ ወይንም
ደግሞ በእውነትና በሃስት መካከል የሚጧጧፍ በመሆኑ ለውጤቱ
ተቁነጥንጧል፡፡ ቢሮው እንደገባ በቀጥታ ወደ ስልኩ ሮጠ፡፡
"ሃሉ! ባክዎ ጌትነትን?" አብዱላሂ ቁርሱን እየበላ ነበር፡፡
"ሃሎ! አቶ ሽመልስ ነህ? እንደምን አደርክ? ጌትነት ወደ ዘመዶቹ ሄዷል።
ተሰናብቶን ነው የወጣው።ወደዚህ የሚመለስ አይመስለኝም"
"እንደምን አደርክ ጌታዬ ማን ልበል?"
“አብዱላሂ እባላለሁ ሁል ጊዜ ጌትነት ስላንተ ያጫውተኝ ነበር፡፡ የሚረዳኝ ጥሩ ወንድሜ ነው እያለ ይነግረኝ ነበር።
"ደህና ታዲያ እንዴት ነው ላገኘው የምችለው የኔ ወንድም?"
“ምነው?ቀናው እንዴ?!” አብዱላሂ ጮኸ፡፡
“አዝማሚያው ወደዚያው ነው። የት ብዬ ላገኘው እችላለሁ ባክህ . '
ሽመልሽ እየተጨነቀ ጠየቀው።
“በተቻለ መጠን ልናገኘው እንሞክራለና! ይሄ እዕድል ሊያመልጠው አይገባም" አለ አብዱላሂ።
“እባክህ በተቻለህ መጠን ልታገኘው ሞክር። ወደ ማታ ላይ መልሼ እደ
ውላለሁ" አለና ስልኩን ዘጋው።
“ኦ! በጣም ግሩም ነው አላህ ይርዳው! በሌላ አመል ቢታማም ጌትነት
ጥሩ ልጅ ነው፡፡ ሰው መቼም በሁሉ ነገሩ ጥሩ ሊሆን አይችልም፡፡ከብዙ ጥሩ ፀባዮቹ መካከል አንድ መጥፎ ነገር ሊኖርበት ይችላል። ኣላህ እንዲረዳው ዱአ አድርጌለታለሁ። ወላሂ! እኔ የተለማመንኩለት ዱአ ያደረ
ኩለት ሰው ሁሉ ይቀናዋል።እስቲ አሁን የት ተብሉ ይፈለጋል ታዲያ?
አድራሻውን አልገረን?"እሱም ተጨነቀለት፡፡ጌትነት አብዱላሂን ተሰናብቶ
የወጣው አድራሻ አዘጋጅቶ አማራጭ አግኝቶ አልነበረም፡፡ ይልቁንም የህይወት ዕጣ ፈንታው በምትመራው ጠባብ መንገድ ላይ ሆኖ ያንን የአባቱን የአደራ ቃል ለመወጣት የሚያስችለው የሥራ ዕድል እስከሚያገኝ ድረስ ችግሩን እየተጋፈጠ ወደ ፊት ለመጓዝ ነበር።

የቶሎሳን ቤት ጥሎ ጭልጥ ብሎ እንደቀረው ሁሉ አሁን ደግሞ የአብዱ
ላሂን ቤት ጥሎ ጭው እልም ብሎ ሄደ። እናቱ ከላከችለት ገንዘብ ውስጥ
ሃያ ብሯን አላጠፋትም ነበር፡፡ በኪሱ ውስጥ ያቺ ሃያ ብር አለች።
እሷን ተማምኖ ነው የአብዱላሂን ሃያ ብር ላለመቀበል የደፈረው በዚያች
የማትረሳ መጥፎ ቀን. የሽዋዬ ወጥመድና አረቂ የገባበት ጠላ ያስከ
ተለበት ጦስ ከአንዱ ወደ አንዱ ያንከራትቱታል፡፡ ጌትነት በምሽቱ ከአ
ብዱላሂ ቤት እንደወጣ እየተካካከዘ በቀጥታ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ
ወረደ.. በልቡ ብዙ ነገሮችን እያወጣ እያወረደ ወደማያውቀው አቅጣጫ ወደ ፊት ነጎደ

“አዎን የዛሬን እንደምንም ብዬ ፖሊስ ጣቢያ
👍2
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....ሠራተኛዬ ሁሉ የትም መበተኑ ነው፡፡ ለሌሎች መኖር
ዋጋ የሚሆንው ለዚህ አይደል? ብዙ ቤተሰቦች እንዳይፋቱ፡፡ ልጆቻቸው የሰው እጅ እንዳያዩ፣ እናቶች በሰቀቀን ማኅፀናቸው እንዳይደርቅ ብዩ ራሴን ሳላጋልጥ ብቀር ሰዎች በእኔ ላይ ይፈርዳሉ? ሕሊናዩስ ወደፊት ይገስጸኝ ይሆን? ምን ዓይነት ጣጣ ነው እባካችሁ!»

እንደገና ብድግ ብሎ ከወዲያ ወዲህ መንጎራደድ ጀመረ፡፡ አሁን ግን የሚንጎራደደው አንደ በፊቱ፡ ከጭንቀት ማጥ ውስጥ በመርመጥመጥ ሳይሆን በረጋ መንፈስ ነበር።

እንቁ ጨለማ ከወረሰውና ጥልቀት ካለው መሬት ወስጥ ተፈልፍሎ
እንደሚገኝ ሁሉ እውነትም ከማሰብና ከማሰላሰል ብዛት ይደረስበታል፡፡መሴይ ማንደላይንም ከመጨነቅ፣ ከመጠበብና ከማሰብ ብዛት ከእውነት የደረሰ መሰለው፡፡ ይህም ትክክለኛውን ጎዳና እንዳያይ ጋረደለት:

«አልተሳሳትኩም» አለ ለራሱ፤ «ይኸው ነው ትክክለኛ ጎዳና:: ትክክለኛውን አቅጣጫ ነው የያገዝኩት፡፡ ለጭንቀቴ መፍትሔ አገኘሁለት:: ከእነዚህ
አሳብ ላይ መጽናት አለብኝ፡፡ ምርጫዬ ይኸው ነው፤ ወስኛለሁ:: ከዚህ ወዲያ ስለነገሩ ማውጣትና ማወረድ ወይም መጨነቅ አያስፈልግም::ይህንንም የምለው ለራሴ በማሰብ ብቻ ሳይሆን ለኅብረተሰቤም በመጨነቅ
ጭምር ነው:: እኔ ማንደላይን ስለሆንኩ በማንደላይንነቴ እጸናለሁ:: ይብላኝ ለዣን ቫልዣ! ከአሁን ወዲያ እኔና ዣን ቫልዣ አንድ ሰው አይደለንም::
የዣን ቫልዣን ማንነት አላውቅም:: ዣን ቫልዣ ነው ተብሎ የተጠረጠረው ሰው ራሱን ያውጣ እንጂ እኔ ምን አገባኝ:: አዎን፤ ከዚህ ውሳኔና መደምደሚያ
ላይ በመድረሴ መንፈሴ ረካ፡፡ አሁን ገና የተለየ ሰው መሆኔን ተረዳሁ::"

ጥቂት እንደ መራመድ ብሎ ድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ::

«ኧረ ወዲያ» አለ፡፡ «ከጥሩ ውሳኔ ላይ ነው የደረስኩት፧ ከዚህች
ውሳኔ ነቅነቅ የለም:: ብቻ አሁንም ቢሆንኮ አሳቡ ጨርሶ ከሕሊናዬ ውስጥ ተነቅሎ አልወጣም:: ቢሆንም መወገድ ያለበት ነው:: ከእዚህ ቤት ውስጥ እንደ ምስክር ሆነው ሊናገሩ፤ በአየኋቸው ቁጥር የዚህችን ሰዓት ጭንቀቴን
ሊያስታውሱ የሚችሉ ብዙ እቃዎች ስላሉ አሳቤ ብቻ ሳይሆን እነርሱም ጭምር ከዚህ መወገድ አለባቸው::»

ኪሱን ዳብሶ ቦርሳውን ካወጣ በኋላ ከውስጡ አንዲት ትንሽ ቁልፍ አወጣ፡፡ መክፈቻዋ በግድ ከምትታይ የቁልፍ መግቢያ ቀዳዳ ውስጥ ቁልፉን ጨምሮ ሳጥኑን ከፈተው:: ብዙ እቃ አልነበረበትም:: ያረጀ ሱሪ፣ የተበጣጠሰ ጫማ፣ የተቀዳደደ ሸሚዝና እንዲሁም አሮጌ ኮረጆ መሳይ ነገርና ያኔ አሁን
ወዳለበት ከተማ ሲገባ ይዞት የነበረው ዱላ ከዚያ ተቀምጠዋል፡፡ መቼ
እንዳስቀመጣቸው አስታወሰ፡፡
ወደ በሩ ተመለከተ፡፡ ምንም እንኳን በሩ በሚገባ ተቀርቅር ቢዘጋም የሚከፈት መስሉት ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡ ልብሱን፣ ጫማውን፣ ከረጢቱና
ዱላው በቅጡ እንኳን ሳይመለከታቸው ቶሎ ብሎ እሳት ውስጥ ጨመራቸው፡፡ እስከዚያን እለት ድረስ በክብር አስቀምጧቸው ነበር፡፡ በጥቂት
ሰከንድ ውስጥ ቤቱ ብርሃን በብርሃን ሆነ፡፡ ሁሉም ጋየ፡፡ ዱላው እየተሰነጣጠቀ
ሲነድ የእሳት ብልጭታ ራቅ ወዳለው ሥፍራ ሁሉ ይበተን ጀመር::

ከረጢቱ እየነደደ አንድ የሚያብረቀርቅ ነገር ከአመዱ ውስጥ ታየ:: ጠጋ ብሎ ቢመለከት የብር እቃ መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ከእኚያ ጳጳስ ቤት የሠረቀው እቃ ለመሆኑ ታወሰው:: ወደ እሳቱ መመልከቱን ተወ፡፡ እርምጃውን ሳያዛባ ከወዲህ ወዲያ
መንቆራጠጡን ቀጠለ፡፡ ወደ እሳቱ ዞር ብሎ ቢያይ እነዚያ ሁለት ከብር የተሠሩ የሻማ ማብሪያዎች መሆናቸውን አረጋገጠ፡፡
«ቆይ እስቲ» በማለት ወደ አሳቡ ተመለሰ፡፡ «ዣን ቫልዣ ማን
እንደሆነ የሚያስታውሱ ስለሆነ እነርሱም መጥፋት አለባቸው» ሲል አሰበ::ነገር ግን እሳቱ ኃይለኛ ስለነበር ሊያቀልጣቸው ካልሆነም ደብዛቸው እስኪጠፋ ሊያበላሻቸው እንደሚችል ስለገመተ የሻማ ማንደጃዎቹን ቀስ ብሎ ከእሳቱ ውስጥ አወጣቸው:: ወደ እሳቱ ጠጋ ሲል ሰውነቱን ትንሽ ስለሞቀው ደስ አለው:: «እንዴት ደስ ይላል» ሲል ተናገረ፡፡
የሻማ ማንደጃዎቹን እያገላበጠ አያቸው:: ለአንድ ደቂቃ ቢቆይ እሳቱ ውስጥ መልሶ ይጨምራቸው ነበር፡፡ ግን ወዲያው ከመቅጽበት «ዣን
ቫልዣ ፣ ዣን ቫልዣ» ተብሎ የተጠራ መስሉት ጆሮውን አቀና፡፡
ፀጉሩ ቆመ፤ መርዶ የተረዳ መሰለው::

«አዎን! ይኸው ነው፤ አልቋል» በማለት ድምፅ ያሰማው ነገር
ንግግሩን ቀጠለ፡፡ «የጀመርከውን ብትጨርስ ይሻላል፡፡ የሻማ ማንደጃዎቹንም አቃጥላቸው:: እነርሱም አንተነትህን የሚያስታወሱ ስለሆኑ አጥፋቸው፡፡ እኚያ ጳጳስንም እርሳቸው! ሁሉንም ነገር እርሳ! በሻምፕማትዩ ሕይወት
ላይ ፍረድ፣ አዎን ብትፈርድ ይሻልሃል! ብራቮ፣ መልካም ሥራ! ይኸው ነው፣ አልቋል፡፡ ምን አለ! ይህ ሰው ምናልባት ንጹህ ሰው ሊሆን ይችላል።
ብቻ እድሉ ሆነና በአንተ ስም ተጠርጥሮ አዘቅት ውስጥ ሊገባ ነው።የአንተን ኃጥያት በመሸከሙ ብቻ መጨረሻው የከፋ፣ የስቃይና የመከራ ዘመን ሊያሳልፍ ነው:: ምን አለ፤ ይሁና! አንተማ ሰዎች በይበልጥ ሊያከብሩ |
'አንተን ያኑርልን፧ ሺህ ዓመት ከንቲባ ሁነህ ኑር፣ የተጠማን አጠጣ፤የተራበን ኣብላ፤ እናት አባት የሌለውን ጡር፤ ተባረክ! የሰው ፍቅር ይስጥህ' ሊሉህ ነው፡፡ እና አንተ እዚህ ስትደሰት፣ ስትዝዝናና አንድ ሰው ግን የአንተን የጥንት ልብስ ለብሶ፧ ባለማወቅ ስምህን ወርሶ የአንተን
የኃጢአት ሰንሰለት እየጎተተ ጨለማ ውስጥ ሊኖር ነው፡፡ ድንቅ፣ ዕጹብ ድንቅ ሥራ! እንዴት ያለው ድርድር ነው! አንተ ርኩስ!»
ፊቱ ላብ በላብ ሆነ:: የሻማ ማንደጃዎቹን በደበዘዘ ዓይኑ
ተመለከታቸው፡፡ ከውስጡ የሚወጣው ድምፅ አልተቋረጠም፤ ቀጠለ።
«ዣን ቫልዣ ፣ ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉ የሚናገሩ ብዙ ድምፆች
ይኖራሉ፡፡ ድምፆቹ ለዘላለም ይጮሃሉ፤ አንተንም ያሞግሳሉ፡፡ ግን ከእነዚህ ድምዖች መካከል አንዱ ብቻ ሌሎች ሳይሰሙት አንተን ያሳድድሃል፤ በጨለማ ሁሉ ይከተልሃል፡፡ ስማ አንተ ርኩስ፤ የተረገምክ! ይሄ ሁሉ ሙገሣ፣ ይሄ ሁሉ አክብሮትና አድናቆት ሰማይ ቤት ሳይደርስ ይጠፋል፡፡
ርግማኑ ግን እስከ እግዚአብሔር ፊት ድረስ ይከተልሃል፡፡»

ስውር ሕሊናው ውስጥ በዝግታ የጀመረው ድምፅ ቀስ እያለ እየጎላና ለጆሮው እየቀረበ መጣ፡፡ ያ ድምፅ ንግግሩን ሲጀምር ከራሱ ሕሊና የሚወጣ መሆኑን ቢታወቀውም ከቃላቱ ኃይለኛነት፣ ከድምፁ ጥራትና ጉልህነት
የተነሳ እውነትም ከአጠገቡ ሰው ቆሞ የሚገስጸው ስለመሰለው ክፍሉ ውስጥ ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ሲፈራ ሲቸር እየተገላመጠ አየ::

«ማነው?» ሲል ተጣራ:: መጣራቱ ራሱን ስላስገረመው ከት ብሉ
የቂል ሳቅ ሳቀ፡፡ «ምን ጅል ነኝ እባካችሁ! ከዚህ ውስጥ ማንም ሊገባ እንደማይችል እያወቅሁ!» ነገር ግን ከክፍሉ ውስጥ አንድ ዓይነት ኃይል ነበር፡፡ ሆኖም ያ ኃይል ለሰዎች ዓይን ጉልህ አልነበረም::

የሻማ ማንደጃዎቹን ከፍ ካለ ሥፍራ ላይ አስቀመጣቸው:: በየተራ የተፈራረቁበትን የተለያዩ ሁለት አሳቦችን አገናዘበ፡፡ ሁለቱም አሳቦች እጅግ የሚያስፈሩ ሆኖ አገኛቸው:: አንዱ ከሌላው አይሻልም:: ሻምፕማቲዩ
👍15🔥1
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በታደለ_አያሌው


....“አንድ ጊዜ ከባልቻ ጋር እዚህ መጥታችሁ ነበር አይደል?” አለችኝ እንደ ዋዛ፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት በቅንድቧ እየጠቆመችኝ፡

“አዎ” አልኋት፣ እኔም እንደ ዋዛ፡ “እ?” አልኋት ወዲያዉ፣ ዉሃ ሆኜ ምን ምን? ያለችዉን ነገር እኮ ገና አሁን ነዉ ልብ ያደረግሁበት::
ከማን ጋር ምንድነዉ ያለችኝ? ባልቻ? እርፍ! እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ? በድንጋጤ ተዝለፍልፌ አለመዉደቄ፣ ለራሴ ደነቀኝ፡ መሬቱን ይዤ አረፍ ማለትም አሰብሁ፡ ቢሆንም ግን ቸኩሎ መደናገጥን የሲራክ ፯ ማንነቴ
ስለማይፈቅድልኝ ማስጨረስ አለብኝ፡ ጥርሴን ነክሼ እንደ ምንም ተበራታሁ።

“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ወደ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር እያስገባችኝ
ወደ ቤተ መዘክሩ ስመጣ የመጀመሪያዬ ስላልሆነ ብርቅ አልሆነብኝም እንጂ፣ እንደዚህ ማንኛዉንም ሰዉ መንፈሳዊ የሚያደርግ ወደረኛ ቦታ
አለ ቢሉኝ አላምንም ሲጀመር በከተማ ዉስጥ ካሉ ገዳማት እንደዚህ የጸጥታ እና የአርምሞ ገዳም አላዉቅም። በበርሐ ካሉትም የሚስተካከል
ትክክለኛ የገዳም ይዞታ ያለዉ ግቢ ነዉ፡ ዕድሜ በጠገቡ እና ራሳቸዉ ታሪክ በሠሩ ጽዶች የተሞላ ስለሆነ፣ እዚህ ግቢ የገባ ሰዉ ዉጣ ዉጣ አይለዉም እንኳንስ ለአማኝ እና ለተማጻኝ ይቅርና፣ ለማንኛዉም ሰዉ
መረጋጋትን የሚሰጥ ገራሚ ሥፍራ ነዉ።

ቤተ መዘክሩ ዐሥር ብር የከፈለ ማንኛዉም ታሪክ ወዳጅ የሚጎበኘዉ ሕዝባዊ ቤት ቢሆንም፣ የሚገኘዉ ግን በዋናዉ የገዳሙ ሕንጻ ምድር ቤት ነዉ፡ ስለዚህ ወደ ቤተ መዘክሩ ለመግባት የግድ ጫማ አዉል
በቅኔ ማኅሌቱ በኩል ማለፍ ይጠይቃል። በዋናነት የዳግማዊ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የእቴጌ ዘዉዲቱ፣ የአቡነ ማቴዎስ
ግብጻዊ የልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ ዐጽሞች በየራሳቸዉ ወርቃማ ሳጥን ዉስጥ ተከብረዉ የተቀመጡበት ሲሆን፣ ዓይነተ ብዙ የካህናት እና የነገሥታት ቅርሳ ቅርሶችም አሉበት ከነዚህም መካከል ሮማዊዉ ሊቀ ጳጳስ ለአፄ ምኒልክ የላኩላቸዉ የሚካኤል አንጀሎን ትክክለኛ የእጅ ሥዕል ጨምሮ ብዙ የሚነገርላቸዉ ከሩስያ ከግሪክ ከጣልያን እና ከተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን የተበረከቱ ቅርሶች
ሞልተዉ ተትረፍርፈዉበታል። እንዲሁም ንግሥተ ነገሥታት ዘዉዲቱ ለጸሎት ይጠቀሙበት የነበረ ወንበር፣ የእጅ ጽሑፋቸዉ ያለበት ዉዳሴ ማርያም እና ሌሎች የብራና መጻሕፍት እና ለእሳቸዉ የተሰጡ ታሪዊ ስጦታዎች ጭምር አሉበት። ለአድዋ ዘመቻ ሲታወጅ የተጎሰመዉ ነጋሪት፣ አድዋ
ድረስ የዘመተችዋ ድል አድራጊዋ የጃንሆይ መቀመጫ ወንበር ሁሉ
የሚገኙት በሌላ አይደለም፡ እዚሁ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር ዉስጥ
ነዉ።

ያም ሆኖ ግን ቤተ መዘክሩን የሚጎበኘዉ ሰዉ በታሪኩ ልክ ብዙ ነዉ ማለት አይቻልም እስከዚህም ነዉ ያን ያህል ንጉሥ ንጉሥም፣ ካህን ካህንም የሚሸት እና ቢናገሩለት የማያልቅ የቅርስ ክምችት እንዳልሞላበት
ሁሉ፣ ጎብኚ ግን ከስንት አንድ ነዉ ብቅ የሚልበት። ያዉም የዉጪ
ሀገር ሰዉ፡ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ከነጭራሹ ማንንም አላየሁበትም። አስጎብኚዎቹም እንኳን በአካባቢዉ የሉም

“እና፣ ወደ ቤተ መንግሥቱ ያመጣችሁን ጉዳይ እንደሚሆን እንደሚሆን ከዉናችሁት ልትወጡ ስትሉ ተይዛችሁ ነበር አሉ?” አለችኝ እመዋ፣ በዚያ የዉድ ዉድ እቃዎች ክምር መካከል ለብቻችን ስንዋኝ።

ዝም ብዬ ባዳምጣት ይሻለኛል ምን ልል እችላለሁ? ጭጭ እርጭ ብዬ አዳመጥኋት። ጭራሽ ተዪዛችሁ ነዉ ያለችዉ? በስመ አብ!

“ከዚያ ባልቻ አቺን ደብቆ ራሱን አጋለጠ። አንቺ ይኸኔ የእሱ መጨረሻ እያሳሰበሽ እንደ ምንም ከቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ስታመልጪ ቀድሞሽ ውጪ አገኘሽዉ በምን ተአምር ከእነሱ እጅ እንዳመለጠ ግን እስከ
አሁንም ድረስ ባሰብሽዉ ቁጥር ይገርምሻል አይደለም? በእርግጥም ግን እኮ ይገርማል። የመንግሥት ደኅነቶች ለመያዝ ዘገምተኞች ናቸዉ እንጂ ከያዙ እኮ አይለቁም ይባላል”

እመዋን አላዉቃትም ለካ በእርግጥ ግን ይቺ ሰዉ እመዋ ራሷ ናት ከንግግሩ አነጋገሯ ከአነጋገሯ ሁኔታዋ! እሷ ማለት ለኔ የስልሳ አራት ዓመት አሮጊት፣ ከጾምና ከምሕላ ሌላ የምታዉቀዉ የሌላት ምስኪን
ሃይማኖተኛ ናት፡ እንዲያዉ አዳሯ በገዛ ቤቷ ከመሆኑ በቀር፣ ሙሉ
ሕይወቷ ከመናኝ አይተናነስም፡ በቤተ መንግሥት ዙሪያዉን ባሉ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት፣ ለትንሽ ለትልቁ የምትታዘዝ ገዳማዊት ብቻ ናት። በጭራሽ እናቴን አላዉቃትም በቃ።

“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ከሩስያዉ የመጨረሻ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ኒኮላስ ለኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የተላh መሆኑን የሚያመላክት ጽሑፍ በግርጌ ወደ ሰፈረበት ጽዋዕ እየወሰደችኝ
ከዚህ ቀደም ቤተ መዘክሩን በጎበኘሁ ጊዜ አስጎብኚዉ ስለ ጽዋዉ ያብራራልኝን አልረሳሁትም ከጽዋዉም አልፎ ጽዋዉን ስለላከዉ የሩስያ ንጉሥ ጭምር ገልጾልኛል። ለሃያ ሦስት ዓመታት ገደማ በሩስያ መንገሡን፣ የሩስያ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድረስ በቅዱስነቱ እንደምታወሳዉ፣ ዝነኛዉ የሀገሩ አብዮት ዘመኑን እንደ ቀጨበት
ያብራራልኝን ከነፊቱ ገጽ አስታዉሰዋለሁ። ስለ ንጉሡ ያልነገረኝ አልነበረም።
ይኼ ሩስያዊ ንጉሥ ለሐበሻዉ ንጉሥ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ስትደርስ፣እመዋ ፈገግ ብላ አየችኝ። ደግሞ ምን ልትለኝ ይሆን?

“ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም”

ስትል በፊቴ አንጎራጎረች፣ የሩስያዉ ንጉሥ ለአፄ ምኒልክ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ቆማ ፊቷ የፈገግታ ብርሃን እንደ ፈነጠቀበት

“ዳዊት እደግማለሁ ቆሜ ገረገራ
እመቤቴ ማር ያም ኢትዮጵያን አደራ
ነይ ነይ እምዬ ማርያም”

ከመሬት ተነስታ እንዳልዘመረችዉ ይገባኛል። ምንም እንኳን መዝሙሩ ነባር እና ሕዝባዊ መዝሙር ቢሆንም፣ የእሷን ምክንያት ግን አግኝቼዋለሁ በሲራክ ፯ ማዕከል ዉስጥ ሥራዎቻችንን ጨርሰን ትንሽ
ፋታ ያገኘን እንደሆነ፣ አባላቱ ሁሉ ከበዉ የሚያዘምሩኝ እኔም እንደ
ጸሎት የምቆጥረዉ መዝሙር ነዉ። ከዚህ በላይ፣ ራሷ አፍ አዉጥታ የሲራክ ፯ አባል ነኝ እስከምትለኝ ልጠብቅ ካላልሁ በቀር፣ እናቴ ግን እንደማስባት ዓይነት ሰዉ ብቻ አለመሆኗን በተግባር ጭምር
አሳይታኛለች፡

“ተከተዪኝ” አለችኝ ጽዋዉን ትኩር ብላ ስታይ ቆይታ፣ ዘወር ብሎ
ወዳለዉ ሥዕል ደግሞ እየተራመደች። ልክ ከፊት ለፊቱ ስትቆም፣ ነፋስ የነካዉ ያህል ሥዕሉ መወዛወዝ አመጣ፡ ዓይኔን ተክዬ የሚሆነዉን ሁሉ
ተጠባበቅሁ: አፍታ ያህል ሲወዛወዝ ከቆየ በኋላ፣ የድምፅ ፍጥነትን በሚስተካከል ፍጥነት ተገልብጦ የፊቱ ወደ ጀርባ፣ የጀርባዉ ወደ ፊት ተለወጠ። ሥዕሉ ግን አሁንም ያዉ የቅድሙ ዓይነት ነዉ።

የሆነዉ ሆኖ ሥዕሉ ሥዕል ብቻ፣ እመዋም እመዋ ብቻ እንዳልሆነች
ገብቶኛል።

“አሁን ባልቻ እንዴት እንዳመለጠ ሳይገባሽ አልቀረም” አለችኝ
በፈገግታ።

ወደ ቤተ መንግሥቱ ግቢ የሚዘልቅ የዋሻ መንገድ አለ ማለት ነዉ?አፌን ከፍቼ፣ ዓይኔን በልጥጬ እንዳፈጠጥሁባት ቀረሁ እየቆየ የባሰ እየደነቀኝ፣ ሁሉም ነገር ቅዠት እየመሰለኝ መጣ፡ ጭንቅላቴ በጥያቄ
መዐት ተጠቃ። ሚሊዮን ጥያቄ በዉስጤ እየተዥጎደጎደ፣ አንደኛዉ ከሌላኛዉ ተሽቀዳደመብኝ፡ የሲራክ ፯ አባል ነሽ? እሺ አባል ከሆንሽ ምን
👍21🥰31
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

..ናንሲ ሌኔሃን የሰውነቷ ክብደት መጨመሩ ታወቃት፡፡ ያለችው
ሊቨርፑል ከተማ አዴልፊ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ ናንሲ አስጠሊታም ቆንጆም
አይደለችም፧ አፍንጫዋ ሰልካካና ጸጉሯ የተዘናፈለ በመሆኑ የደስ ደስ
አላት፡ ደህና ልብስ ስትለብስ ዓይን ትስባለች፡፡ ይሄ ደግሞ የሁልጊዜ
ገጽታዋ ነው፡፡ ኮቷ ስለጠበባት ቁልፎቹ ሲቆለፉ ቀፈት ቢጤ ይወጣባታል:
ይህ የሆነው ሰሞኑን ለአንድ ወር ያህል በፓሪስ ምግብ ቤቶች እየዞረች ምግብ መሰልቀጥ ስላበዛች ነው፡፡ አትላንቲክን በመርከብ ስታቋርጥ ግን ስባት
ያለበት ምግብ ላለመብላት ወስናለች፡፡ ኒውዮርክ ስትደርስ የቀድሞው
ሽንቅጥናዋ ይመለሳል።

ከዚህ በፊት ውፍረት ችግሯ አልነበረም፡፡ ጥሩ ምግብ ብትወድም ብዙ አታግበሰብስም፡፡ አሁን አሁን ውፍረት የእርጅና ምልክት ነው ብላ መፍራት
ጀምራለች፡

ዛሬ አርባኛ አመቷን ደፍናለች፡፡

ሁልጊዜም ሸንቃጣ ነበረች፡፡ ውድ ልብስ ገዝቶ ወይም አሰፍቶ መልበስ ጫማ መግዛት ትወዳለች፡፡ በፋሽን እቃዎች ንግድ ላይ በመሰማራቷ ጥሩ
ነገር መልበስ እንዳለባት ታውቃለች፡፡

ናንሊ የተወለደችው በ1899 ዓ.ም ሲሆን ይህ ወቅት አባቷ የጫማ ፋብሪካ ከፍተው ንግዱን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ ከእንግሊዝ አገር ጥራት ያላቸውን ጫማዎች አስመጥተው አስመስሎ በመስራት በርካሽ ዋጋ ይሸጣሉ፡፡ ሃያ ዘጠኝ ዶላር የሚያወጣውን የለንደን ጫማ አስር ዶላር
ከሚያወጣው የራሳቸው ጫማ ጋር ጎን ለጎን እያስቀመጡ ‹‹እነዚህ
ጫማዎች ልዩነታቸው ምንድን ነው?›› እያሉ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፡ ጥሩ ጥሩ ጫማ በማምረት እውቅና እያገኙ ሲመጡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት
ሲቀሰቀስ የወታደር ጫማ አቅርቦት ትእዛዝ ጨረታ አሸናፊ ሆኑ።

በ1920 ዓ.ም አሜሪካ ኒው ኢንግላንድ ስቴት ውስጥ በርካታ ሱቆች በመክፈት ራሳቸው የሚያመርቱትን ጫማ ብቻ መሸጡን ተያያዙት፡፡ በ1930 ዓ.ም በተከሰተው የኢኮኖሚ
ድቀት ምክንያት ገበያው
ስለቀዘቀዘ የሚፈበረኩትን የስታይል ዓይነቶች መቀነስ ተገደዱ፡፡ ኢኮኖሚው እያንሰራራ ሲመጣ ለተለያዩ ስታይል ጫማዎች አንድ ዓይነት ዋጋ በመቁረጥ ገበያውን ተቆጣጠሩት፡፡ በዚህ ብልጠታቸው በመጠቀም ሌሎች ነጋዴዎችን ከገበያ
በማስወጣት በትርፍ ላይ ትርፍ ማጋበሱን ቀጠሉ።

የናንሲ አባት ‹‹መጥፎ ጫማ ለመስራት የሚወጣው ወጪ ጥሩ ጫማ ለማምረት ከሚወጣው ወጪ አይተናነስም›› ይሉ ነበር፡፡
ለናንሲ ጥሩ ጫማ ማምረት ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር፣ ጥሩ መልበስና ማጌጥ፣ ጥሩ ጥሩ መኪና መንዳትና በየጊዜው መደገስ ማለት ነው፡፡ወንድሟ ሰላሳ ስምንት ዓመቱ ነው፡፡ አባታቸው ለሁለቱ ልጆቻቸው
ለእያንዳንዳቸው 40 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ አውርሰዋቸው ከሞቱ አምስት ዓመት ሞላቸው፡፡ የአባታቸው እህት አክስታቸው 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ሲወርሱ ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በታማኝነት ላገለገሏቸው አዛውንት ጠበቃ ደርሷቸዋል፡፡

ናንሲ አባታቸው ሲሞቱ የኩባንያውን ኃላፊነት ቦታ ለእሷ እንደሚሰጡ
ትገምት ነበር፡ ሴት የኩባንያ ኃላፊነት ቦታ መያዟ ባይለመድም አባቷ
ከፒተር ይልቅ ቢዝነሱን እንድትመራ እሷን ይመርጡ ነበር።

አባቷ ናት ሪጅዌይ የሚባል እሳት የላሰ ምክትል ነበራቸው፡፡ እሱ በበኩሉ የብላክ ቡትስ ጫማ ፋብሪካ ዋና ኃላፊ መሆን ይመኛል።

ፒተርም የኃላፊነቱን ቦታ መከጀሉ አልቀረም፡፡ እሱ ደግሞ የቤተሰቡ ወንድ ልጅ ነው ናንሲ አባቷ ከፒተር ይልቅ ስለሚያቀርቧት ሁልጊዜ ትሸማቀቅ ነበር፡ ፒተር በአባቱ እግር ካልተተካ በጣም እንደሚያዝን ጥርጥር የለውም፡፡ ናንሲም እሱ ከሚያዝን በማለት ኃላፊነቱን እንዲወስድ
ቦታውን ለቀቀችለት፡፡ እሷና ወንድሟ በድምሩ 80 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ
ይዘዋል፡፡

ናት ሪጅዌይ በዚህ ተቀይሞ ኒውዮርክ የሚገኘው ጄኔራል ቴክስታይልስ
የተባለ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ተቀጠረ፡፡ የእሱ ኩባንያውን ለቆ መሄድ
ክስረቱ ለብላክ ቡትስ ብቻ ሳይሆን ለናንሲ ጭምር ነበር፤ አባቷ ሊሞቱ
አካባቢ ከናንሲ ጋር ወዳጅነት ጀምሮ ነበር፡፡
ናንሲ ባሏ ከሞተ ወዲህ ከማንም ወንድ ጋር ወዳጅነት አልመሰረተችም
ነበር፡፡ ናት ፤ደግሞ "በትክክለኛው ጊዜ ነው የደረሰላት ባሏ ከሞተ አምስት ዓመት በኋላ ህይወቷ ሁሉ ስራ ብቻ በሆነበትና የወንድ ፍቅርና የገላ ጠረን እየናፈቃት በመጣበት ዘመን፡፡ በወቅቱ የተወሰኑ ቀናት ራት ጋብዟታል ቴአትር ቤትም ወስዷታል አንድ ቀን ቤቷ ሲሸኛት ምጥጥ አድርጋ
ስማዋለች፡፡ ነገር ግን ይህ ግንኙነት ብዙም ሳይዘልቅ ናት ሪጅዌይ ጥሏት
እብስ አለ፡፡ መሸወዷን ስታውቅ ክፉኛ በሸቀች፡

ከዚያ በኋላ ናት ረጂዌይ
በጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ ታዋቂነትን አትርፎ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ለመሆን በቃ፡፡ከዚያ በኋላ ከናንሲ አስር ዓመት የምታንስ ቆንጆ ሴት አገባና ናንሲን አሳፈራት፡፡

ፒተር የኃላፊነቱን ቦታ መወጣት አልቻለም፡፡ የኩባንያው ስራ
አስኪያጅነት ቦታ በእጁ በሆነበት አምስት ዓመት ጊዜ የኩባንያው ገቢ
ቁልቁል ወረደ ሱቆቹ በሙሉ ዋናቸውን ከማስመለስ በስተቀር ትርፍ ማግኘት አቃታቸው ኒውዮርክ ውስጥ የሴቶች ጫማ መሸጫ
ቢከፍትም ይህም ሱቅ ከኪሳራ አልዳነም፡፡

ናንሲ የምትመራው ፋብሪካ ብቻ ነው አትራፊ የነበረው:: አገሪቱ የኢኮኖሚ አዘቅት እየወጣች ባለችበት በአስራ ዘጠኝ ሰላሳዎቹ አጋማሽ
ዓመታት ክፍት የሴቶች ሰንደል ጫማ ማምረት ጀመረችና በአንድ ጊዜ
ተወዳጅ ሆነላት፤ ወደፊት የሴቶች ጫማ ገበያ የደራ እንደሚሆን ተገነዘበች
የማምረት አቅሙ ቢኖራት አሁን ከምትሸጠው የጫማ ቁጥር እጥፍ ትሸጥ ነበር፡፡ ነገር ግን እሷ ያመጣችው ትርፍ በፒተር ኪሳራ ስለሚዋጥ ፋብሪካውን ማስፋፋት አልቻለችም፡፡
ናንሲ የጫማ ንግዱን ከኪሳራ ለማዳን አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት
ተገነዘበች፡፡

የማስፋፊያ ካፒታል ለመፍጠር የጫማ መደብሮቹ ለኃላፊዎቹ መሸጥ አለባቸው፡፡ ከመደብሮቹ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ፋብሪካውን ለማዘመንና ለማስፋፋት ስራ ላይ ይውላል ፒተር ደግሞ የስራ አስኪያጅነቱን ቦታ
ለእሷ ይለቅና የወጪ ገደብ ጣሪያ ተሰጥቶት የኒውዮርኩን መደብር ብቻ
ያንቀሳቅሳል፡፡

ፒተር የኩባንያውን ሊቀመንበርነት ከነሙሉ ክብሩና ጥቅሙ ይዞ
እንዲቆይ፣ የፒተርን መደብ ከእሷ ኩባንያ ከሚገኘው ትርፍ በገደብ ልትደጉም ሆኖም እውነተኛ ስልጣኑን እንዲለቅ ልታደርገው ፈልጋለች፡

እነዚህን እቅዶቿን ለሌሎች ሳታሳውቅ ለፒተር ለብቻው አቀረበችለት እሱም አስቦበት መልስ እንደሚሰጣት ቃል ገባ፡፡ የኩባንያው ገቢ መቀነስ
በዚሁ ሁኔታ መቀጠል እንደማይገባው በዚህ እቅድ የማይስማማ ከሆነ እሱን
አልፋ ለቦርድ በማቅረብ እሱን አስነስታ ቦታውን እንደምትይዝ በእርጋታ
አስጠነቀቀችው፡፡ ይህን ሳይቀበል ቀርቶ አምባጓሮ ማንሳት ከመረጠ አሳፋሪ
ሽንፈት እንደሚገጥመውና ምናልባትም ከእህቱ ጋር ተቆራርጦ እንደሚቀር
ጥርጥር የለውም
እስካሁንም ምንም ጥቃት አልከፈተም::የተረጋጋ ተቆርቋሪና ተጫዋች መሰለ፡ ፓሪስ ላይ ፒተር ለመደብሮቹ የወቅቱን ፋሽን የተከተሉ ጫማዎች ሲሸምት እሷ ደግሞ ለራሷ ጫማዎች ስትገዛ የፒተርን ወጪ በጥንቃቄ አጠናች፡

ሁሉም እንደሚያደርገው ወንድምና እህት ወደ አሜሪካ መመለስ
እንዳለባቸው ወሰኑ

ቦታው ሁሉ ስለተያዘ በአይሮፕላን ለመሄድ ደግሞ አልተቻለም፡፡
በመጨረሻ ከሊቨርፑል የሚነሳ ውርከብ ቲኬት ገዛች፡፡ ከፓሪስ በባቡር ረጅም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ በጀልባ ወደ ለንደን አመሩ፡

ዛሬ በአየር በራሪው ጀልባ ሊበሩ ነው፡፡
👍231
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ከሎ ሆራ በጨርቆሌ ማዝነት በደንብ እየተቀለበ ከቆየ በኋላ ሚዜው ሰውነቱ እንደ ተመለሰ አረጋገጠ። ስለዚህ ከሎ ሆራና ሚዜው
ከተሪ (ዲክ ዲክ) ቆዳ የተተለተለ ቀበቶ መሳይና ኩርኩፋ ይዘው
በደንቡ መሠረት ጎይቲ አንተነህን በድብቅ ማሳደድ ጀመሩ።

ጎይቲ አንተነህ ከሎን አልወደደችውም እሷ ልቧ የጠፋባት ለዚያ ጀግና ለደልቲ ገልዲ ነው" መሬቱን በልበሙሉነት እየረገጠ
ሲንጐማለል፣ የሷንም ልብ እንደ ጠረማመሰው ሁሉ በፍቅር ታቃስታለች።

በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት አንዳንዴ መንደራቸው ብቅ ካለ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑትን ሌሎቹን የዳንስ ምቶች ከሌሎች ጋር
ብትጨፍርም ጭንን በጭን የማግባቱ ጊዜ ቀድማ የምትጋብዘው እሱን ነው። ጭኑን በጭኗ ውስጥ ሲያስገባ የአእምሮዋን እንቅስቃሴ ያዛባና በቍጥጥሩ ስር ያደርጋታል" ከወገቧ ልጥጥ ብላ ወንድ ብልቱ ላይ ትለጠፍበታለች" በዚያ ወቅት ስሜት እንደ ቅቤ ይቀልጥና እሱም እሽት፣ እሷም አሽት፣ እሱም እሽት...ሲደራረጉ ይቆዩና
ሁለቱም ሲሸነፉ፣ ውጥረት ሲበዛባቸው ተያይዘው ወደ ጫካ፣ ወደ ልዩው የተፈጥሮ መኝታ ክፍል ጐራ ይላሉ“

ጫካው ውስጥ ወፎች፣ አራዊት፣ እባቦችና ሰዎችም ጭምር ፍቅራቸውን በነፃነት ይለዋወጣሉ ጫካ ውስጥ ትርዒት አቅራቢ እንጂ
ተመልካች አይኖርም። «ሁሉም ለየራሱ…» ብቻ መባባል ነው።

ጎይቲ አንተነህ ታዲያ ያ አራዊትን፣ ሰውን የገደለ ጀግና የፍቅርም ጀግና ሆኖ አግኝታዋለች" ጠምዘዝ አድርጎ በጠንካራ እጆቹ ወደ እሱ እያስጠጋ ትንፋሿ እስኪቋረጥ የሚስማትና እንደ ሕፃን ልጅ አቅፎ የሚያጫውታት ሁሉ ትዝታን ያልፈጠረባት እፎይታን ያልሰጣት ጊዜ የለም።

ከሎ ሆራ፣ ጎይቲ አንተነህን ባየ ቍጥር ከፍቅሩ ፅናት አንፃር ሰውነቱ እየተልፈሰፈሰ ቢርበተበትም ተፈቃሪዋ ግን ኵሩ ሆና ኵሩ ወንድ፣ ጅንን ጀግና፣ ስሙ የገነነ ወንድ ፈላጊ ነበረችና እሱ ለእሷ
ሲል ልብሱን አውልቆ ራቁቱን ቢሄድም፣ ሊያደርገው ያላሰበውን
እንዲያደርግ ፍቅሯ ቢያስገድደውም፣ እሷ ግን ለሱ ቁብ የማይሰማት
ሆነችበት"

የጎይቲ አንተነህ ልብ ያለው ደልቲ ገልዲ ላይ ሲሆን፣ የከሎ ሆራ ልብ የማለለው ደግሞ፣ ለጎይቲ አንተነህ ነው። ቢሆንም ከሎ
ሆራ እሷን የማግኘት ተስፋው አልጨለመበትም" እሱም ሆነ ሽያው
(ሚዜው) ከቀናቸው ጎይቲ አንተነህን ብቻዋን ሰከም ሰከም ስትል ሊያገኟት ይችላሉ።

አንድ ቀን በሬ ጠምዳ ስታርስ፣ አጥማጆቿ በርቀት ቍጥቋጦው ውስጥ ተደብቀው ሲከተሏት ዋሉ። መቼም እንደዚያን ቀን በከፊል የተመቻቸ ቀን ከዚህ በፊት አላጋጠማቸውም" በሬዎችን በጅራፍ ሸንቆጥ በማድረግ፣ ከወገቧ ወደ ጎንና ጎን ለጠጥ፣ ዳሌዎቿን ወጣ  ገባ....እያደረገች ስለ ሐመር ጀግኖች፣ ስለ ከስኬ ወንዝ፣ ስለ በልጉ ታንጐራጕራለች። አጠገቧ የአጎቷ ልጅ ብቻ ነው ያለው፤ እሱ ዘወር ካለላቸው ፈጥነው ሊይዟትና የልባቸውን ሊያደርሱ ይችላሉ " እሱ እያለ ግን ምንም መሥራት አይችሉም ጎይቲ የተዘጋጀላትን ወጥመድ በጭራሽ አላወቀችም ዝም ብላ እርሻዋን ታርሳለች። አፍቃሪዋም፣ ከዘምባባው ዙሪያ ካለው ሰንበሌጥ ውስጥ ሆኖ በገዛ ምራቁ ይታነቃል።

አጥጆቿ፣ የኦጎቷን ልጅ ቦርጆ (አምላክ) ከዚያ አካባቢ ዘወር እንዲያደርገው ይመኛሉ" የአጎቷ ልጅ ደግሞ፣ ጎይቲ አንተነህ ልጃገረድ በመሆኗ ብቻዋን ትቷት ቢሄድ ሊደርስባት የሚችለውን
አጋጣሚ አሰበ" ኋላ እሱና ሌሎች ጐረምሳ ዘመዶቿ መጠበቅ ተስኗቸው ጀግንነት፣ ሀብት ከሌለው አንዱ ቢተናኮላት የሌሎች
ልጃገረዶች ማሽሟጠጥና በጓደኞቹ «ፈሪ» ተብሎ መናቁ፣ እሱንና ዘመዶቹን ስለሚያናድዳቸው ብቻዋን ትቷት ለመሄድ አልፈለገም።
ስለዚህ አዳኞች ታዳኟን በቍጥጥር ሥር እንዳያውሉ የአጎቷ ልጅ
«ጕሮሮ አጥንት» ሆኖባቸው ሳይሳካላቸው ቀረ።

በሌላ ቀናትም ውኃ ለመቅዳት ስትሄድ፣ ገበያ ስትመላለስ ትክለ
ቁመናዋን፣ ፈገግታዋን፣ የሚነጥረውን መቀመጫዋን ቀምሶ
ያልጠገበውና እያየ በመሳሳት ላይ ያለው የመንደሯ ጐረምሳ፣ እንደ
ሴት ውሻ ከቦ ስለሚከታተላት በድብቅ ለሚከታተሏት እንቅፋት
ሆኖባቸው ሰነበተ።

ከሎ ሆራ ከሚዜው ጋር ጫካ ለጫካ ሲዞርና ጎይቲ አንተነህን  ሲከታተል ጕሮሮው ሲጮህበት ቢውልም፣ እየቆየ ግን መሰላቸት ጀመረ። ፊት ለፊት ሄዶ የደንቡን ለመፈጸም ያስብና ባህሉን ባለማክካበሩ የሚደርስበትን ውግዘትና ቅጣት እያሰበ፣ ሐሳቡን ከሕሊናው አውጥቶ ያሽቀነጥራል"

አንድ ቀን ግን፣ ጎይቲ አንተነህ ደንገዝገዝ ባለ ምሽት፣ ከቤቷ ወጥታ መንገዱን ስትነካው እነከሎ ተከተሏት" ከመንደሯ ዘወር
እንዳለች የመሮጥ ያህል እየተራመደች ወደፊት ገሰገሰች" ከሎ ሆራ፣
«የት እየሄደች ይሆን? ብቻዋን ካለፍርሃት እንዴት ትሄዳለች» በማለት ግራ ገባው ከወሮ ራቅ ብለው ካሉት መንደሮች ለመድረስ
ከመቻሏ በፊት ግን እነሱ ያቀዱትን ከመፈጸም የሚያግዳቸው የለም።

«አቤት ለስንት ጊዜ እንዳለፋን በግላጭ አገኘናት» ተባብለው
ከሎና ሚዜው ተቃቅፈው ደስታቸውን ተገላለጹና ፍጥነት ጨምረው
ለመያዝ ወደ ፊት ሽምጥ ሮጡ" እሷ ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ግን
ሁለቱም ሩጫቸውን ገትተው ቆሙ ከግራር ጥላው ሥር መሣሪያ የያዘና በርኮታው ላየ የተቀመጠ ሰው ያዩ መሰላቸው» አበሸቃቸው፣ ገረማቸውም፣ «ማን ይሆን?» ጠየቀ ከሎ፣ «እንጃ!» አለ ሚዜው። ስለዚህ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ቃጫው ተክል ገባ ብለው አደፈጡ። ጎይቲ አንተነህ ወደዚያ
ሰው እየቀረበች ስትሄድ እየተደነባበረች የሰካራም ጕዞ ጀመረች ሰውየው መጀመሪያ አላያትም ነበር። ዱካዋን ሲሰማ ግን
ከተቀመጠበት ፈንጠር ብሎ ተነሥቶ መሣሪያውን ሲደግን፣ ወደሱ
የምትገሰግሰው ጎይቲ አንተነህ ናት። መሣሪያውን አቃንቶ፣ እጁን ከፍቶ ጠበቃት፤ ያው እንደ ልማዱ እንደ ቀንድ የቆመው ጡቷን
ከሰውነቱ ስታሻሽለት፣ እሱም የኰራውን ዳሌዋን በሁለት እጁ ወደ
እሱ ይበልጥ እየሳበ፣ ትንፋሿ እስኪቈረጥ ድረስ ሳማት። እሷም ሆነ እሱ በተፈጠረው ሙቀት እንደ ቅቤ ቀለጡ።

ከሎ ሆራ፣ ይህን ትርዒት ራሱ እንደሚሠራ ሁሉ፣ እሱም ባለበት ደነዘዘ። ሰውነቱ ሁሉ ባለበት ሲወጣጠር ታወቀው። በእሱ ላይ የተለጠፈችበትና አቅፎ የሚስማት መሰለው። ዋና ተዋናይዎቹ ግን ወደ ዋናው እርካታ ጕዟቸው ለመሄድ አንዱ በሌላው ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ከሎ ከሰመመኑ ነቃ። የሚወዳት ጎይቲ አንተነህ ከሱ ጋር
ሳይሆን ያለችው ከሌላ ሰው ጋር ነው። እሱ ያቀፈውና የሳመው ለካ ግንዱን ነው" እሱ ግንድ አቅፎ ሲስም፣ እሷ ሰው አቅፋ
ትቃበጣለች፣ «ዳሚት» አለ ከሎ፣ ሊቈጣጠረው በማይችለው ስሜት ተወጥሮ።

ከሎ ሆራ ሰውዬውን በደንብ ቢያስተውለውም ሊለየው
አልቻለም። ሚዜው ግን ነገረው፣ «አያ ደልቲ ገልዲ ነው» አለው።

"አዎ እሱ ነው ካለሱ እሷን እንዲህ የሚያደነባብራትና
ትንፋሿን የሚያሳጣት ወንድ የለም» በማለት፣ በእልህ ወደ ተዋጠ ሰሜት ውስጥ ገባ" ሚዜው ግን፣ ከርቀት የሚታየው ቅብጠት አፉን
አስከፍቶታል።

ፍቅረኛሞች የፍቅር ጥማቸውን ለማርካት እየደጋገሙ ሲጫወቱ ቆዩና ተለያዩ" ጎይቲ አንተነህ ወደ መንደሯ ስትመለስ ከኋላ የቀረባት ሰው እንዳለ ሁሉ ልቧ ተንጠልጥሎ አልፈጠነችም። መንደሯ
👍22🥰2
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሶራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዓመተ ምህረት ነው። ከዚያም በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና በረጂ ድርጅቶች ሰርቷል። ሥራ መቀያየሩ ግን ሆዱን እንደ እንቁራሪት ሆድ ከማሳበጥ በስተቀር ያገኘው የሕይወት እርካታ
የለም። የት ቢሄድ ምን
ቢሆን የህሊና እርካታ እንደሚያገኝ
አያውቅም ዩኒቨርስቲ ውስጥ እያለ  ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንትን የመረጠው በጓደኞቹ ምክርና ግፊት ነው።

"...አትሞኝ! ጥሩ ደመወዝ ለማግኘት አዲሳባ ለመመደብ ዕድልተህ እንዲሰፋ ከፈለግህ" እያሉ የሰማይ ጥገት የሚመኙ ጓደኞቹ እየነዱ ወደ አልተመኘው ዲፓርትመንት
ሃሳቡን አኮላሽተው
አስገቡት።

ከአደገበት· ቀዬ ከተንቦራቸበት የኤርቦሬ ምድርም ዳግመኛ ሳይመለስ የውሃ ሽታ ሆኖ ወደ መጣበት ተመልሶ መግባት የማይታሰብ ገደል ሆነበት። በልጅነቱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ሊሄድ
ጥብቆ ሲለብስ
ሽማግሌዎችም ሲመርቁት

“…እንደ ጅብ በነጋበት የምትቀር አትሁን። የአያት የቅድመ አያቶችህን ደንብ አክባሪ ለወገንህ ተቆርቋሪ መሆንህን የምታስመሰክር ሁን ብትጠፋ እንኳ የእነሱ ዘር ነው የሚያሰኝህን
ኤርቦሬነትህን አታጥፋ።
ኤርቦሬ ውስጥ  ሪስ  ፋርቶ ሃልዝጋለች አልሞቅ  ሩፍ ህፀንቴ ኤቡሬ ጋሮራ
ጋራንጉዶ ጋርሌ ዲሳ የሚባል ዘር አለ ወደምትሄድበት አገር ስትደርስ የከብት ጆሮ
አበሳሳችሁ እንዴት ነው? ህፃን ልጅ እንደ ተወለደስ መጀመሪያ የምታቀምሱት ምንድን ነው?ብዙ ጊዜ የምትጋቡትስ ከማን
ከማን ጋር ነው?..." ብለህ ጠይቅ።

“...የአንተ ዘር የከብት ጆሮ አበሳስ ታችኛውን የጆሮ ክፍል ከውስጥ ወደ ውጭ በመብሳት ሲሆን! ህፃን ልጅ እንደተወለደ የቡና
ፍሬ ማሽላ የከብት ጥፍር ከህፃኑ ልጅ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ ይሰጠዋል። ብዙ ጊዜ ጋብቻ ከቦረናና ፀማይ ጋር ነው። ስለዚህ
ይህን በሄድህበት ሁሉ እየነገርህ ዘርህን ብትጠይቅ ካለጥርጥር
ታገኛቸዋለህ: ከዚያ የቤተስባችሁ አባል ከሌላ  አገር ስለመጣ ተቀበሉት ብለው ከዘሮችህ ያደባልቁሃል:

ወደ ሌላ አገር የሄደና የሞተ አንድ ነው እስካልታዩ ድረስ:: ልዩነቱ ያልሞተ ከሄደበት ይመለሳል ! ያኔ ወደ ቤተሰቡ ከመቀላቀሉ በፊት የመንደሩ ሰዎች ማንም ሰው ጠጥቶበት
በማያውቅ ቅል ውሃ ሞልተው ይይዙና ከፊት ለፊቱ ውሃውን እየደፉ መሬቱን በማርጠብ እርጥቡን  እግር"  ከቤተሰቡ ጋር ይደባልቁታል! ካለበለዚያ ግን ማንም የቤተሰቡ አባል ቢያየውም
ሰላም አይለውም:: እና!  አንተም ክሄድክበት ስትመለስ ይኸ ደንብ
እንደሚሰራልህ አትርሳ: ከደንቡ በኋላ ከኤርቦሬ ወንድሞችህ ጋር ጫካ ትወርድና ያገኘኸውን አውሬ ገለህ ስትመጣ ከወላጆችህ በር ፊት ለፊት የእድሜ ጓደኞችህ "ዘውትር ምሽት እየዘፈኑ እያቅራሩ አንዱ የሌላውን ጀርባ ሸፍኖ እየተቀመጠ የአባትህ ቤት የጀግና ቤት መሆኑን እያወደሱ ሲያደምቁት ይሰነብታሉ… ከዚያ ተድረህ ወልደህ ከብደህ ጋንደሩባ ኡላም ሙራል ወይም እጉዴ ትኖራለህ።

“ ኤርቦሬ በአሁኑ ጊዜ ስልጣን የያዘው የኦጌልሻ ሄር ሲሆን ኦጌልሻ ሄር ስልጣነን የተረከበው ከሜልባሳ ሄር ነው።

“በአባትህ ባህል በአርባ ዓመት አንድ ጊዜ አሮጌው ገዥ ሄር በአዲሱ ገዥ ሄር ይተካል:: ይህም ኦቤርሻ ጂም ጊድማ ጂም
ማሮሌ ጂምና ዋተኛ ጂም ሲሆን የመጀመሪያው ጂም ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ሲሆኑ ኦቤርሻ ጂም ይባላሉ: ከዚያ ከጨቅላነት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት ህፃናት
አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት አመት ሲሞላቸው ጊድማ ጂም ይሆናሉ። ያም ማለት ከኦቤርሻ ጂም እስከ ጊድማ ጂም ዘጠኝ ዓመት
ይሆናል ቀጥሎ ደግሞ ከጊድማ ጂም በታች ካሉት ጨቅላዎች እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር አመት እስከ አስራ ስምንት  ዓመት ሲሞላቸው ማሮሌ ጂምን ይመሰርታሉ።
ይህም ዘጠኝ ዓመት
ይፈጃል። ከማሮሌ በታች ያሉት ከጨቅላነት እስከ "ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ ዋተኛ ጂም ይባላሉ።

“ስለዚህ ኦቤርሻ ጂም ዘጠኝ ጊዴማ ጅም ዘጠኝ ማርሌና የአራቱን ጂም
ዋተኛ ጂም እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ዘጠኝ ስለሚቆዩ
ለመፈፀም ሰላሳ ስድስት አመት የሚፈጅ ሲሆን አሮጌውን የገዥ ሄር
ከተለያዩ እድሜ ከሴትና ወንድ በእኩል የተሰባሰበውን አዲስ ሄር
አጠቃላይ የኤርቦራ ማህበረሰብ በተሰበሰበበት በተለያዩ ባህላዊ ስነስርዓቶች ስልጣን ከአሮጌው ሄር ይረከብና በጋንደሩባ ኩላም
ሙራልና እጉዴ አንዳንድ ከርነት (ጠቅላይ ሚኒስቴር) ይመረጣል። ከርነት ሆኖ የተመረጠው ሰው ካለ  ግልድም በስተቀር ልብስ
አይለብስም። ባህሪውም የተመሰገነ ትሁት... መሆን ይገባዋል። ይህ ሰው የአባት ደንብና አሁን ያለው የኤርቦሬ ህዝብ የአደራ ቀንበር የሚጫንበት በሬ ነው: ጎረምሶችም የራሳቸውን የጦርነት ጊዜ
አዝማች 'መሪናኔት' መርጠው የነብር ቆዳ ያለብሱታል: ይህም ሰው
በጦርነት ጊዜ ስልት አውጭና ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ለህዝቡ መከታ
የሚሆን ነው።

“ከዚያ የፖለቲካ መሪ የሚሆኑት አራቱ ከርነቶች
ከመንፈሳዊ መሪዎች (ቃውቶች) የአገር ሽማግሌዎች (ጃላቦች) ጋር
ስልጣናቸውን ለሚቀጥለው ወጣት ሄር ያስረክባሉ። ስለዚህ አንተ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦጌልሻ ሄር አባል በመሆንህ ቶሎ ተመልሰህ
ማህበረሰብህን መርዳትህን አትዘንጋ: እስከዚያው ግን
ወገኖችህ ፀሐይ ወጥታ እስክትገባ ሳንሰለች እንጠብቅሃለን፡፡ ይህ ኸሊናህ ሳይጎድፍ ተመልሰህ ናና ከማህበረሰብህ ተቀላቀል...” ብለውት ነበር።

አካሉ እያደገ ህሊናው እየበሰለ ሲሄድ ግን ከዘመዶቹ አደራ በላይ የአገሩ የአህጉሩ ባጠቃላይ የሰው ልጆችን የመርዳት አደራ ፕላኔቷን የመጠበቅ ግዴታ... እንዳለበት እንኳን ተረድቶ ነበር። በጎ
አስተሳሰቡን ግን ውሃ በላው። አፍንጫው ጥቅም ውስጥ እየተሰነቀረ
ሆዱ ለእለት ደስታ እየተነጠፈ አስቸገረው መቆፈሪያ አንስቶ
የድህነት ተራራ ለመናድ የማንዴላ እናት አምጣ እንድትወልደው ኃይልን እንድታቀብለው ፈለገ እየቆየ ግን አንድ ሃሣብ በህሊናው
ማውጣት ማውረድ ጀመረ።: ቢያንስ በግሉ አንድ ሆዝብን ሊረዳ
ድርጅት መክፈት። ለዚህም ደግሞ ገንዘብ ያሻዋል። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች መዳፍ ገብቶ እንደ ቆሎ እያሹ ጉልበቱን ቆረጣጥመው ምስጥ
እንደበላው ግንድ ገንድሰው እንዲጥሉት ግን አልፈለገም
ነፃ መሆንን መረጠ፡

ለዚህ ግን አልታደለም። ያለበት ዘመን ህይወት በገንዘብ የሚተመንበት የገንዘብ ኃይል ነጋሪት እየተጎሰመ በሚለፈፍበት ጊዜ ነው። ዓላማውን ለማሳካት ግን አንድ አማራጭ አለው: ሰርቶ
የማግኛ ስደት: "ስደት ግን ሽሽት ነው" ብሎ ያምን ነበር: ከዚህ ህዝብ ጋር የበላውን በልቶ የጠጣውን ጠጥቶ ከንፈር እየመጠጡ
ማስተዛኑም ደግሞ ድፍረት እንዳልሆነ ተረዳ። ኤርቦሬ አደራ ይዞ ወጣ፤ አልተመለሰም እና! አደራውን በላ: ከአገሩ ሰርቶ
ለማግኘት ብሎ ሄዶ ፍርፋሬ ቢጥመውስ፤ አዲስ ምኞት ህሊናው ቢያረግዝስ እንደገና ክህደት ሊፈፅም? ስለዚህ ለመወሰን ብዙ
አማጠ ከወሰነ በኋላም ህልሙን እውን ለማድረግ ብዙ ጣረ፤ ግን ተሳካለት። እንደ ደረቀ እንጨት የተለዬ ሆነ እንጂ።
👍21