አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....ሽመልስ በማግስቱ ለአብዱላሂ ስልክ ደወለለት አብዱላሂ ስልኩን አነሳና ጌትነት ያለመኖሩን በድጋሚ አረጋገጠለት። ሽመልስ ተጨነቀ።
“ምን አጋጥሞት ይሆን?" በሚል ሃሳብ ተዋጠ፡፡ ፈተናው የሚሰጠው ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ባስመዘገበው ስልክ ተደውሎለት ባይገኝ ደግሞ

ለነአቶ አባይነህ ደስታቸው ነው፡፡ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከምሳ ስዓት በኋላ ግን ጌትነት ስለ ሥራው ብቻ ሳይሆን ስለህልውናው ጭምር ጓዙን ጠቅልሎ የሱን ጊዜያዊ ርዳታ ሊጠይቅ ከተፍ አለ።

"እንግዳ ይፈልግሀል ይግባ?"አለች የሽመልስ ፀሐፊ ከውስጥ ስልክ፡፡
"አስገቢው" አላት። እንግዳው ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሽመልስ ዐይኑን ማመን አቃተው፡፡
“ኮንግራጁሌሽን!” አለና ጮኸ፡፡
ጌትነት ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ሆነበት። የሽመልስን ሁኔታ ሲያይ ከደስታው የተነሳ የሆነ ስሜት ስውነቱን ውርር አደረገው፡፡ ሽመልስ አይዞህ ከጎንህ ነኝ እንዳለው አድርጎት ይሆን? እንደመርበትበት እያደረገው የተዘረጋለትን እጅ በደመነፍስ ጨበጠ፡፡
"አረፍ በል እስቲ!"አለና ወንበር ጋበዘው። ጌትነት ከእንግዳ መቀመጫ ወንበሩ ላይ ሄዶ ተቀመጠና በሁለመናው አሰፍስፎ ሽመልስን በጉጉት ይጠባበቀው ጀመር፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ ሳይወስደው ስላደረ ፊቱ ላይ የመጎሳቆል ምልክት ይታይበታል፡፡

"ለመሆኑ የት ጠፍተህ ከረምክ? በተደጋጋሚ ስልክ ደውዬ ሳጣህ ተስፋ
ወደ መቁረጡ ተቃርቤ ነበር። ትግላችን መስመር እየያዘ የመጣ ይመስለኛል። አንተና ፀሀይ በድጋሚ ፈተና እንድትወስዱ መወሰኑን እና ለፈተናው እንድትዘጋጅ ልነግርህ ነበር የፈለኩህ፡ ከየባለስልጣኑና ከአንዳንድ ሰራተኞች ጋር የተናነቅኩት ለዚህ ነበር። የመጨረሻው ውጤት የሰመረ እንደሚሆን ደግሞ ምንም ጥርጥር የለኝም" ሳቅ አለ።
ጌትነት ከመቀመጫው ዘሎ አቅፎ ሊስመው ከጀለ፡፡ ተንበርክኮ እግሩ
ላይ ሊወድቅ ተመኘ፡፡ ፊቱ በደስታ እንደማሽላ ፈካ፡፡ ፍንድቅድቁ ወጣ፡፡ የእድል ገመዱ ስለለች እንጂ አለመበጠሷን አወቀ፡፡ እንደገና አዲስ
የተስፋ ብርሃን፣ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እየሞተ ከሄደው ተስፋው ውስጥ ብቅ ሊል ሲያንስራራ ታወቀው:: ለሱ ለአንድ ምስኪን ተቆርቋሪ ሆኖ በሥራ ህይወቱ ውስጥ ሊጠቅሙትም ሆነ ሊጎዱት ከሚችሉ በርካታ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር ተናንቆ ለዚህ ስላበቃው ሽመልስን የሚያመስግንበት ቋንቋ አጠረው። ሽመልስ ከዚህ ወሳኝ ምዕራፍ
ላይ አድርሶታል፡፡ ፈረስ ያደርሳልንጂ ጦር ይዞ አይዋጋም፡፡ ከዚህ በኋላ የሱ ብርታት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ይህንን የምስራች ከሰማ በኋላ ከአብዱላሂ ቤት መውጣቱንና ለጊዜው ጎኑን የሚያሳርፍበት ቦታ እንኳ እንደሌለው በፍርሃት ተውጦ ገለፀለት።

"አይዞህ ጌትነት አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ ስለማደሪያህ ብዙም አትጨነቅ " በማለት ሞራል ሰጠው፡፡
"የናት አባቴ አምላክ" አለና በልቡ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡ ማምሻውን ተያይዘው ወደ ሽመልስ መኖሪያ ቤት ሄዱ።
ቤቷ ሶስት ክፍሎች ያሏት በንፅህና የተያዘች ናት፡፡ ሽመልስ ሶስት ጉልቻ
ሊመሰርት ቅድመ ሁኔታችን በማጠናቀቅ ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ በጓደኝነት አብራው የቆየችው ኤልሳቤጥን ለማግባት የቤት ዕቃዎችን በሟሟላት ላይ ሲሆን ለጊዜው የሚኖረው በሠራተኛ ነው።
ጌትነት ነፃ ሆኖ ሰውነቱን ታጥቦ የታጠበ ልብስ ቀይሮ ጥሩ በልቶ ጥሩ ጠጥቶ ለፈተናው ሲዘጋጅ አደረ። እኩለ ለሊት ሲሆን የጠዋቱ ተፈታኝ ፈጣሪው በጣለለት ሲሳይ በሽመልስ ላይ ሀሳቡን ጣል አድርጎ በተስፋ የሰላም እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

“ታዲያስ ጌትነት? አዳር ተመቸህ?" ሽመልስ ቀድሞት ተነስቶ ነበር፡፡

“እግዚአብሔር ይመስገን ጋሼ ሽመልስ፡፡ ነጋ እንዴ? የሶስት ቀን የእንቅልፍ ዕዳዬን ሳወራርድ ነው ያደርኩት። መንጋቱን እንኳ አላወቅኩም ነበር" ከአልጋው ውስጥ ለመውጣት ታገለ።
“እባክህ ይሄንን ጋሼ የምትለኝን ነገር ተወኝ። ሽመልስ እያልክ ጥራኝ።
እንደሱ ስትጠራኝ ነው ደስ የሚለኝ"
"ይሻላል ጋሼ ሽመልስ? መዳፈር አይሆንም? እንዴት ብዬ በአንድ ጊዜ?"

"ተውንጂ! አሁንምኮ ጋሼ እያልክ ነው!"
“እሺ…አንተኮ ወንድሜም ጓደኛዬም አባቴም ነህ። ለኔ ይሄንን ያክል የሚጨነቁልኝ አባቴና እናቴ ብቻ ነበሩ"
“ጌትነት አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ፡፡ እኔ የምታገለው፣ የምጨነቀው ላንተ ብቻ ሳይሆን ፀፀት ሰላሜን እንዳይነሳኝ ለራሴ ጭምር ነው።
በአንተ ላይ የደረሰው በደል በኔም ላይ በተመሳሳይ መልኩ ደርሶብኝ ነበረ፡፡ በነገሩ ይበልጥ እንድገፋበት ያደረገኝ አንዱ ምክንያት ያንን በራሴ ላይ ደርሶብኝ የነበረውን በደል የምዋጋበት አጋጣሚ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ሥራ እንደጀመርኩ በሃላፊነት ላይ
የተቀመጡ ሰዎች ወጣት በመሆኔ ብቻ ለሥራ መደቡ ሊከፈል የሚገባው ደመወዝ እንዳይከፈለኝ ተጽዕኖ አድርገውብኝ ነበር። ሥራውን እንድሠራ ነገር ግን ደመወዙን እንዳላገኝ ሆን ብለው በፈጠሩት ተንኮል ሊጎዱኝ ሞከሩ፡፡ ምን ታደርገዋለህ? በብቃት ሳይሆን በዘመድ የተሾሙ በአድልዎና በጉቦ የነበዙ ከንቱዎች ከዚህ የተሻለ እንዲሰሩ
ቅም፡፡ ተምረህ ሲያዩ ደማቸው ይፈላል። ነገ ቦታዬን ይቀማኛል በሚል ስንኩል ፍርሀት ትንሽ ቀና ስትል በኩርኩም ይገጩሀል።ያሸማቅቁሀል፡፡ ደመወዝ የሚወስነው በሥራ ክብደትና በተሰጠህ ሀላፊነት እንጂ በሥጋህ ወይንም በዕድሜህ ክብደት አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ ይሄንን አይገነዘቡትም። ወፍራምና ረጅም ከሆንክ ጥሩ ደመወዝ እንድታገኝ ወጣትና
አጭር ከሆንክ ደግሞ ዝቅተኛ ክፍያ እንዲከፈልህ እስከማድረግ የዘቀጠ
በክብደትና በቁመት ላይ የተመሰረተ የደመወዝ አከፋፈል ሥርአትን
ለመዘርጋት የሚጥሩ ከንቱዎች ናቸው፡፡ እኔም ከዩኒቨርስቲ ተመርቄ ስቀጠር የዚህ የጫጨና የቀጨጨ የድንክ አስተሳሰባቸው ሰለባ ሆኜ ነበር። ወጣት በመሆኔ ብቻ ተመሳሳይ ስራ እየሰራሁ ዝቅተኛ ደመወዝ እንዳገኝ ወስነውብኝ በብዙ ውጣ ውረድና በብዙ ክርክር ነበር መርታት የቻልኩት። ያንተም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም። ወፍራም ጭንቅላት እያለህ እንጀራህን ወፍራም ዘመድ ላለው ሰው አሳልፈው እየሰጡት ነው።ይሄንን ሁኔታ በቸልታ ባልፈው ደግሞ ትናንትና የደረሰብኝን በደል መርሳት፣ እኔነቴን መካድ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ጥረቴ ላንተነትህ በሰጠሁት ግምት ብቻ ሳይሆን ለእኔነቴ ጭምር የከፈልኩት ዋጋ
በመሆኑ እንደ ውለታ አትቁጠረው፡፡ ጌትነት አንተም ይህንን ችግርና
ፈተና አልፈህ በድል ስትወጣ የዚህ ሁሉ ችግር ድምር ውጤት ሰው መሆንህን መርሳት የለብህም፡፡ ችግር የሰው ልጅ እንደ እርሳስ የሚቀረፅበት ትምህርት ቤት ነውና ከዚህ ችግር ልትማርበት ይገባል። የህይወትን ጣፋጭነት የበለጠ የምታጣጥመው ከፈተናዋ ውስጥ በድል አድራጊነት ስትወጣ ነውና ለቀሪው ህይወትህ ጥሩ ትምህርት ይሆንሀል። ስለ ሌሎች እንድታስብ ስለ እውነት እንድትከራከር ስንቅ ይሆንሃልና የኔን
ጥረት ብዙም አትጨነቅበት" አለው።

ጌትነት የሽመልስን ምክር አዳምጦ ቁም ነገሩን በልቡ ኣስቀረና አብረው ቁርስ ሊበሉ ተያይዘው ወጡ፡፡ ቁርሳቸውን አብረው ከበሉ በኋላ ሽመልስ
“መልካም ዕድል!" ብሎት ወደ መስሪያ ቤት ሲሄድ ጌትነት ደግሞ በስድስት ሰዓት ለሚሰጠው ፈተና ሲዘጋጅ አረፈደ።

የሰራተኞቹ ሹክሹክታ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ግማሹ ሽመልስን ያደንቃል፡፡ያመስግነዋል፡፡ገሚሱ"ምቀኛ!እርኩስ!”እያለ ይረግመዋል። አቶ
አባይነህም ይደነፋሉ፡፡ “እከካም የድሃ ልጅ ሁላ ትናንትና እከኩን አራግፈንለት ጥብቆ ሲቀይር ጊዜ ማንነቱን ረሳው ቁርስን በልቶ ምሳውን
👍6
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አስቻለው የተሳፈረበት አንደኛ በራሪ አውቶብስ ከዲላ መውጫ ኬላ ጀምሮ በጩኮ፤ በአፖስቶ በአቢላ እና በአዋሳ ጥቁር ውሃ ፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ፍዳውን
ጨርሶ ከሻሽመኔው ኬላ ላይ ከእረፋዱ አራት ሠዓት አካባቢ ደረሰ። የማይቀረው ዕዳ ሊከፈል ተጓዥ ሁሉ ከመኪና ላይ ወረደ:: ከአስቻለሁ አጠገብ በስተግራ በኩል የመስኮት ጥግ ይዘው ተቀምጠው የነበሩት ወይዘሮ ግን አልወረዱም፡፡

ፈታሾች ከመኪናው ዙሪያ እንደ ልማዳቸው ሲጎማለሉ በርካታ ደቂቃዎችን ከአሳለፉ በኋላ ሁለት ፈታሾች ከመኪናው ፊትና ኋላ በር በኩል ገብተው ለመበርበር
ተዘጋጁ ቀድሞ በፊት በር በኩል የነበረው ፈታሽ የመኪናውን በር መወጣጫ ረግጦ ጠልጠል ሲል እኒያ ሴትዮ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው አገኛቸው፡፡

ምንድነው?» ሲል ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ ጠየቃቸው። ፈታሹ አጠር
ጠየም ያለ ነው፡፡ የፊቱ ወዝ ያብረቀርቃል፡፡ ፊቱ ጠፍጠፍ ያለና አፍንጫው ደፍጠጥ ያለው ጎረምሳ ቢጤ ነው፡፡ የመለዮውን እጅጌ ሰቅስቆት የእጁ ጡንቻ ፍርጥም ብሎ ይታያል። ሰንሰስት የሚያህል የወርቅ ሐብል ደረቱ ላይ ተጋድሞ ይንቀለቀላል፡፡

የኔ ልጅ መውጣት መውረዱ ስልችት ብሎኛል ና እዚሁ ፈትሽ ጎሽ!» አሉት ሴትዮዋ በልመና ዓይነት ፈገግ ብለው ፈታሹን እየተመለከቱት፡፡
«ባክሽ ውረጅ! ምን ትቀልዳለች!" አለና ፈታሹ ቆጣ ብሎ በዓይኑም
ገርመም አደረጋቸው።
ሴትዮዋ ፈገግታቸው ድንገት እልም ብሎ ጠፋና ፊታቸው ኮስተርተር፣ ዓይናቸውም ፍጥጥ አለ። ተናደዱ: በተቀመጡበት ወንበር ላይ እንደ መቅበጥበጥ
እያሉ «እንቺ አትበለኝ አንተ ኧረ ይሄ ደፋር!» አሉት፡፡

«ኣ?» አለ ፈታሹ ወደ ወስጥ ገባ እያለ:: እንደገና «ምን አልሽ አንቺ?» ብሎ ቁልቁል ይመለከታቸው ጀመር፡፡አንቺ አትበለኝ አልኩህ!» አሉና ደሞ ምን ያፈጥብኛል?" ብለው
እሳቸውም አፈጠጡበት::

«ቆይ ምንድነሽ አንቺ?» አላቸው ድፍረታቸው ያልተለመደ ሆኖበት።
ሰው! አውሬ እመስላለሁ?» ፈታሹ ለአፍታ ያህል ፍጥጥ ብሎ ተመለከታቸውና ወደ ውጭ እየተመለከተ
«በቃ ይሄ መኪና ተገትሮ ይውላታል እንጂ ይቺ አሮጊት ሳትወርድ አይፈተሽም።»
ብሎ ከመኪናው ላይ ወረደ:: እንዳትገባ!» ሲል በኋላ በኩል ሊገባ የነበረውንም ፈታሽ ከለከለው።

ተሳፋሪው ሁኔታውን ይከታተል ነበርና ግራ የመጋባት ስሜት አደረበት፡፡ሊጉላሉ ነው:: ግማሹ ፈታሹን ይለምን ጀመር፡፡ ሌላው ደግሞ ከመኪና ሌይ እንዲወርዱ ሴትዮዋን፡፡ ሴትዮዋ ግን ፍንክች አልል አሉ። ይልቁንም በሚለምናቸው ተሳፋሪ ላይ ወረዱበት። «መድሐኒዓለም ይለመነኝ ንቅንቅ አልልም!» አሉና አዳሜ አትጨቅጭቀኝ ወዲያ ሄደህ የምትለምነውን ለምን መቼም አንዴ ወኔህን
ተሰልበህ! ልበ ሙት ሁላ ደሞ እኔንም ይዘኸኝ ሙታ!» አሉ ትንፋሻቸው በርክቶ አፍንጫቸው ነፋ ሞሽሽ፣ ነፋ ሞሽሽ እያለ::
በሁለቱም አቅጣጫ ልመና ያልተሳካለት ተሳፋሪ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነበር፣ ወደ ኬላው ሃሳፊ በመሄድ የተፈጠረውን ሁኔታ ማስታወቅ። በእርግጥም በርካታ ተሳፋሪ ወደ ሃላፊው ቢሮ ተከታትሎ ሄደና አቤቱታውን ማቅረብ ጀመረ፡፡
በዚህ መሀል ግን ብዙ ጊዜ ባከነ፡፡
ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ የኪላው ሃሳፊ ሳይሆን የማይቀር አንድ ፖሊስ የመቶ አለቅነት መለያ ምልክቱን ደርድሮ ከቢሮ ወጣና በለመነው ተሳፋሪ ታጅቦ
ወደ መኪናው አመራ። ቀጠን ያለ ረጅም ነው፡፡ ፈካ ያስ ጠይም ሆኖ ገተር ባለው አፍንጫው ላይ ጥቁር መነጽር አድርጓል። ልክ ከመኪናው የፊት በር አጠገብ
ሲደርስ የተጣላቸውን ፈታሽ ጨምሮ ተሰፋሪው ሀሉ የሚፈጠረውን ሁኔታ ለማየት ዙሪያውን አሰፈሰፈ:: አስቻለውም" ከህዝቡ ፊት ሆኖ ከፈታሾቹ አጠገብ ቆሟል የኬላው ሀላፊ ወደ ውስጥ ሴትየዋን እያየ «ምንድን ነው ችግሩ? » ሲል ጠየቃቸው
«እናቱ እያላችሁ ችግር መች ይጠፋል? ችግር ለመፍጠር አይደል! በየቦታው የተኮለኮላችሁት» አሉ ሴትየዋ ዓይናቸውን አፍጥጠው ቆነጥነጥ እያሉ
«መኪናው አይፈተሽ ነው የሚሉት?»
«እኔ አልወጣኝም፡፡ ስትልጉ መነቃትሩት።» አሉና ሁለመናቸውን አንዘራቸው በል! ስንት አንበሳ የመሳሰለ ጀግና ወልጄ ወልጀ ለወግ ማረግ
ያደረስኩ ሴትዬ አንድ ጓጉንቸር በመሰለ አሽከርህ ልዋረድ!» አሉና ቀሚሳቸውን ቀልጠፍ እያረጉ! ይህ ቅሌታም! አያውቅም እንጂ እኔ አቦነሽ ሃይሌ ስንት ኮረኔል የሚያከብረኝ ሴት ነኝ፡፡ ይህ ባለጌ ባለጌ ያሳደገው! አሉ በማከታተል።
«አሁንም አታርፊ አንቺ አሮጊት!» አላችው ያ መጀመሪያ የተጣላቸው
ፈታሽ በመቶ አለቃው ትክክሻ ላይ አንገቱን ሰገግ አድርጎ ወደ ውስጥ እያየ።ወደ ውስጥ እያየ

ሴትዮዋ እሁንም እየተቅበጠበጡ «አንተ እንደኔ አታረጅ፣ አንት የተረገምክ ዕድሜ እኮ የንጥህና ምልክት ነው። አዳሜን እያስለቀስክ ዛሬ ደረትህ ቢያብጥ
ዘላለም የምትኖር መሰለህ ዛሬ ሰው ቢያቅተው ነገ አንድዬ ይደፋሃል። ምናምንቴ
የምናምንቴ ልጅ! አሉት ወይዘሮ አቦነሽ ሀይሌ። ምናልባት አፍ እላፊ የተናገሩ መስሏቸው ለማካካስ ሳይሆን አይቅርም ከተቀመጡበት ድንገት ብድግ አሉና ግማሽ ጭናቸው እስከሚታይ ድረስ ቀሚሳቸውን እያራገፉ «ቡና ቋጥራለች ብላችሁ
ተሆነ ያው! አቦነሽ ሃይሌ ነጣ!» ብለው ቁጭ እያሉ «ከእንግዲህ ወዲያ አዳሜ ዓይንህን ብታፈጥ የምፈራህ እንዳይመስልህ» አሉ፡፡ እንዳነጋገራቸው የኬላውንም ሀላፊ ነካ እያረጉ ይመስላል።

መቶ አለቃው ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት በማሰብ ላይ ሳለ በሴትዮዋ ቆራጥነትና አነጋገር ልቡ ሲነካ የቆየው አስቻለው ጣልቃ ገባ። «እኔ እምልህ መቶ
አለቃ» አለው አጀቹን በደረቱ ላይ አቆላልፎ የኬላውን ሃላፊ ዓይን ዓይኑን እያየ::
«አንተ እምትለኝ» አለው መቶ አለቃው በንቀት ዓይን እያየው::
«የምትፈልጉት ቡና አለማለፉን ወይስ የተሳፋሪውን ከመኪና ላይ
መውረድና መውጣት?» ሲል ኮስተር ብሎ ጠየቀው::
«አንተ ምንድን ነህ?» አለው ያ መጀመሪያ ከሴትዮዋ ጋር የተጣላ ፈታሽ ጣልቃ ገብቶ። ዓይኑንም አፈጠጠበት።
አስቻለው ውስጡ ተቆጣ፡ ቀድሞም ቢሆን መቶ አለቃው በንቀት ዓይን ሲያየው በስጨት ብሎ ነበርና እሁን ደግሞ የባሰ በመናደድ «ምንድነህ?» ሲል
የፈታሹን ጥያቄ ራሱ ደገመው፡፡
«አዎ ምንድነህ?»
አስቻለው ድንገት ሳያስበው አንድ ነገር በአዕምሮው ብልጭ አለበት። በሆዱ የመጣው ይምጣ እያለ «ካኪ አለመልበሴን አይተህ ከሆነ ተሳስተሃል! እኔ ግን
ሙሉ የፖርቲ አባል ነኝ!» ብሎ በመታወቂያ እንደመፈለግ ዓይነት እጆቹን ከአንድ ኪሱ ወደ ሌላው ያራውጣቸው ጀመር፡፡
ቆይ ጓድ!» አለ መቶ አለቃው ፈጠን ብሎ፡፡ የአስቻለውን ሁለት እጆች በሁለት እጆቹ ያዛቸው።
ደሞ ምንድህ ይለኛል እንዴ ይሄl?» በማለት አስቻለው በፈታሹ ላይ ዓይኑን አፈጠጠ፡፡ ያ ፈታሽ በሀፍረትና በፍርሀት ፊቱ ልውጥውጥ አለ።
«የኛ ችግር እኮ - » ብሉ መቶ አለቃው ንግግር ሲጀምር አስቻለው ቶሎ ብሎ አቋረጠው::
“እ! የእናንተ ችግር?»
«አንዱን አስወርደን ሌላውን ስንተው ሕዝቡ አድሎ አደረጋችሁ እያለ» ብሎ ሳይጨርስ አሁንም አስቻለው አቋረጠው፡፡ ፈጠን ፈጠን ባለ አነጋገር፡፡
1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ጃን ተከል ከወትሮው የበለጠ ሰው ተሰብስቦበታል። ወሬው ሁሉ ስለ ቅዳሜው ግብርና ስለ ምንትዋብ ውበት ነው። ቅዳሜ ዕለት ኣብርሃ ቤተመንግሥት በር ላይ የድኃ ተራ እስኪደርስ ጠብቆ ግብር ተካፍሎ ነበርና በአኮፋዳው
ከየዓይነቱ ምግብ ጠቅጥቆ መጥቶ ጥላዬን እንዲበላ
ሲጋብዘው አልበላም ብሎታል።
አብርሃ ምንትዋብን ባያያትም፣
ስለግብሩ ትልቅነት ሲያወራ አልበቃው በማለቱ ጥላዬ ደከመኝ ልተኛ ብሎት ተለያይተዋል።

ጥላዬ፣ ዋርካው ጠርዝ ላይ ቆሞ፣ “ምንትዋብ ብለው ስም አወጡላት እያሉ ወሬውን ሲቀባበሉ ሰማ። አብርሃን ሲያየው ካንዱ ወደ ሌላው እየሄደ ወሬ ይጨልፋል። ምነው እንደሱ የማላውቃት ባረገኝ። ወደ
ቅጥር ውጭ እኔ ዛፉ ስር ቁሜ አንቺ ነጠላ ተከናንበሽ ገና ኸደጀሰላሙ የልቤን ሳላወጋሽ። የቅርብ ሩቅ ሁኜ ስላንቺ ሰማለሁ። ኸዛ ኸበተክሲያን ወለቴ ምንትዋብ አሉሽ ለኔ ሁሌም ወለቴ ነሽ፡፡ አንድ ቀን ስንኳ ብቅ ስትይ ልቤ ሚተረከከውን ምን ግዝየም አልረሳው። አንድ ቀን ያነን ድንቅ ፊትሽን እሥል ይሆናል። እስተዛው የወፍታው ኻንቺ ጋር ይሁን ብሎ የፍቅራቸውን ምዕራፍ መዝጋት እንዳለበት ለልቡ አስገነዘበ።

አብርሃ የቃረመውን ወሬ ሊነግረው ሲመጣ፣ ጥላዬ መስማት አልፈለገም። “ኸዛው እንኸድና ለሥላሤ ምስጋናዬን ላቅርብ” አለው፣ ወሬውን ሳይጀምር።

“ምናለ፣ እንኸዳ” አለው፣ ግራ የተጋባው አብርሃ።አብርሃ ወደቤቱ ሲሄድ ጥላዬ ቤተክርስቲያኑ ደጅ ላይ ተደፍቶ ምስጋናውን አቀረበ። የተሰበረ ልቡን ሥላሤ እንዲጠግኑለትም ጸሎት
አድርጎ ከዐይኑ ያመለጠውን እንባ ሰው ሳያየው በጋቢው ጠራርጎ ተነሣ።ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ሲቀመጥበት የነበረው ዋንዛ ዛፍ ሥር ተቀምጦአካባቢውን ሲቃኝ፣ የቆሎ ተማሪው ግማሹ የለቀመውን ዕንጨት በእቅፉ
ይዞ ወደቤቱ ይሄዳል፣ ሌላው ውሃ ቀድቶ መመለሱ ነው። በየአጥሩ ጥግ መነኮሳትና አረጋውያን ተቀምጠው ዳዊት ይደግማሉ፣ የቁም ጸሐፊው ብራና ላይ ይጽፋል፣ አንዱ ብራና ሲደጉስ ሌላው ቅዱሳት መጻሕፍትን
ያስጌጣል።

ጥላዬ፣ ለሥራቸው በሚሰጡት ትኩረት ተገረመ። እሱም እንደነሱ
ተቀምጦ ሥራውን የሚሠራበትን ቀን ናፈቀ። አለቃ ሔኖክ ትምህርት
እስኪያስጀምሩት ቸኮለ። እዚያው ግቢውን ሲቃኝ ቆይቶ፣ ከሰዐት
በኋላ፣ ወደ እሳቸው ቤት አመራ።
እሳቸው ስላልነበሩ ደጅ ተቀመጠ። ወርቄ በር ላይ ቆማ የሆነ
ያልሆነውን ስትጠይቀውና ሲመልስ ቆይተው፣ ወደ ውስጥ እንደገባች አለቃ ሔኖክ ቅጥር ግቢው ገቡ።

“አምሽተህ ነው?” ብለውት ወደ ውስጥ ገቡ።ቆየት ብለው ወጥተው ወደ ጓሮ እንዲመጣ በእጃቸው አመለከቱት ኩታውን እያስተካከለ ተከተላቸው። ጎጆውጋ ሲደርሱ፣ “ይህቻት
እንግዲህ ማደሪያህ” አሉት።
"እመቤቴ ትስጥልኝ” አላቸው፣ ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ።

አንገቱን ወደ ውስጥ መዘዝ አድርጎ ተመለከተ። ከአንድ አነስተኛ ቁርበት በስተቀር ጎጆዋ ውስጥ ሌላ ምንም ነገር የለም። የአቧራዋ ሽታ ይሰነፍጣል ።

“እዝች ሁነህ ሥራህን ትሠራለህ። የትምርት ግዝየ ሲደርስ እኔ አለሁ።ምግብ ወርቄ ትሰጥኻለች። አንተ ዛዲያ እንጨት ትለቅምላታለህ፣ ውሃ
ትቀዳላታለህ፣ ልብስም ታጥባለህ” አሉት።

“እረ ምን ገዶኝ!”

አለቃ ወደ ቤት ሲመለሱ፣ ቁርበቱ ላይ ጋደም እንዳለ መላ አካላቱ
በሐሳብ ደክሞ ነበርና እንቅልፍ ወሰደው። ምሽት ላይ፣ ወርቄ እራቱን ይዛለት መጣች። ራቱን በልቶ ተኛ።በነጋታው አለቃ ሔኖክ በወርቄ አስጠርተውት ሲገባ እሳቸው መደብ ላይ ተቀምጠዋል። ሰላምታ ሰጥቷቸው በእሳቸው ትይዩ ተቀመጠ።
ወርቄ ቁርስ አቅርባላቸው ከበሉ በኋላ፣ አለቃ ሔኖክ፣ አነስተኛ ብራናና የቀለም ቀንድ ይዘው አብሯቸው ደጅ እንዲወጣ ነገሩት።

“ብራናና ቀለም እኔ ሰጥኻለሁ። ወደፊት ብራና ሆነ ቀለም ራስህ
ታዘጋጃለህ። ቀለም አቀማመም አሳይሀለሁ። ንድፍም አሳይህና በዚያ መሠረት ኸርኩሳኑ መኻል ምትፈልገውን ሠርተህ ታመጣልኛለኸ አሉት።

እጅ ነሥቶ ትኩረቱን እጃቸው ላይ ያለው ብራና ላይ አደረገ።
ቀስ ብለው ንድፍ እንዴት እንደሚሠራና ቀለም እንዴት እንደሚቀባ አሳዩት።
“ለነገሩ ንድፍ አይቸግርህም። በአክርማ ስትሠራ ቆይተህ የለ?”
አሉት፣ እየሳቁ።
ዐይኑን ከብራናውና ንድፉን ከሚሠሩበት የቀርከሀ ስንጥር ላይ
ሳያነሳ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ።

ትምህርቱን ጨርሰው እሳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ እሱ ወደ ቤቱ
ሄደ። ጋቢውን ቁርበቱ ላይ ወርውሮ ደጅ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ፣ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመኝ የኖረው ብራና እጁ በመግባቱ ሊስመው ቃጣው።

ሕይወቱ ዐዲስ ምዕራፍ የያዘ መሰለው።ሥዕሉን በምን እንደሚጀምር አወጣ አወረደ... እባብ? ሳጥናኤል? ቁራ? በመጨረሻም ስለምን ሳጥናኤኔልን አልሰራም አለ፣ ለራሱ።አለቃ ሔኖክ ባሳዩት መሠረት ንድፍ ሞከረ፤ ተንጋደደበት። ብራናውን
ያበላሽ ስለመሰለው ደነገጠ። ሆኖም መሣሉን ቀጠለ። አለቅጥ ረጀም፣ግራና ቀኝ አስፈሪ ቀንዶች ያለው፣ ጆሮዎቹ በጣም ትልልቅና ጭራ ያለው ፍጡር ሣለ። ቤቱ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ፣ ብራናውን ደጋግሞ እየተመለከተ ስቆ እንደማያውቀው ሳቀ። በነጋታው ፈራ ተባ እያለ አለቃ ሔኖክጋ ሲሄድ ወርቄ፣ “ኣፍህን እንድትሽር ልጠራህ ስል መጣህ” አለችው።

“ለመብልማ እስትትጠራ አትጠብቅ። ቤትህ እኮ ነው” አሉት፣ አለቃ ሔኖክ።

ቁርስ አድርገው ከጨረሱ በኋላ፣ “እስቲ ምን ሠራህ?” አሉት።

ብራናውን ብድግ ብሎ ሲያቀብላቸው፣ ቀረብ፣ ራቅ አድርገው ተመለከቱትና ሳቁ። “ሳጥናኤል... ማለፊያ ነው። ንድፉም መልካም ነው። ተሰጥኦ እንዳለህ ያስታውቃል” አሉት።

“ንድፉ ተንጋደደብኝ እንጂ።”

ርኩሳንን ከሀዲያንን፣ አጋንንትንና ክፉዎችን ስትሥል ንድፉ ቢንጋደድ ምንም አዶለም። ባሕሪያቸው ነው፤ መንጋደድ ይስማማቸዋል። ላንተ ግን ዋናው እጅ ማፍታታትህ ነው። ወደፊት ቅዱሳንን፣ መላዕክትንና ሌሎችን ስትሥል ግን ንድፍ ማንሻሽፍ
አይፈቀድም። በል በርታ” ብለው ብራናውን መልሰው ሰጡት።

እጅ ነሥቶ ወጣ።

በሚቀጥሉት ቀናት፣ እሳቸው በነገሩት መሠረት ጥቁር ቀለም ከተለያዩ ዕጽዋት ቀምሞ ሥዕል መሣሉን ተያያዘው። እንደሱ ቢሆን፣ ርኩሳንን ብቻ ሳይሆን የፈለገውን ቢሰራ በመረጠ። ብዙውን ጊዜ የምንትዋብ
መልክ ፊቱ ላይ ድቅን ይላል። እንደበፊቱ እንስሳውን ቤቶቹን ሁሉ
መሣል ይፈልጋል። አንዳንዴ የፈለገውን የሚሥልበት የቤታቸው ጓሮ ይናፍቀዋል።

ሥዕል በማይሥልበት፣ ለወርቄ ውሃ በማይቀዳበት፣ ዕንጨት
በማይለቅምበትና የአለቃ ሔኖክን ልብስ በማያጥብበት ጊዜ፣ ከአብርሃ ጋር ጃን ተከል እየሄደ ወሬ ይሰማል። ጃን ተከል ብቅ ማለት እሱስ ሆኖበታል። ቤተመንግሥት ግብር ሲጣል፣ አብርሃ ምግብ ብቻ ሳይሆን
ስለ ምንትዋብ ወሬ ይዞለት ይመጣል ።

በትምህርቱ እየጎበዘ ሲመጣ፣ አለቃ ሔኖክ በሥራው ቢደሰቱም፣
“መልካም ነው፣ በርታ” ከማለት በስተቀር ብዙ ስለማያብራሩ ጥቂት ቅር ይሰኛል፣ ቢያሞጋግሱት ይመርጣል። የሠራውን ሲመለከቱ፣ ፊታቸው
ላይ የሚንፀባረቀውን አድናቆት ለምን በቃላት እንደማይገልጹለት
ይገርመዋል።

አንድ ቀን አስደሰቱት። ግቢው ውስጥ ተቀምጠዋል። እንዴትና
የት እንደዋለ ከጠየቁት በኋላ፣ “ጥላዬ፣ ሥዕል ኸዠመርህ ወራት
አልፈውሀል። እጅህም ጥሩ ተፍታቷል። እንደነገርሁህ ጥቂት ቆይተህ ቄሶችን፣ መሪጌታዎችን፣ ሊቀጠበብቶችን ቤተክስቲያን አካባቢ ያሉ ሰዎችን መሣል ትዝምራለህ” አሉት።

ደስ ተሰኘ።
👍15😱1
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...አንድ ማታ ኒኮልን ከተማ ሬስቶራንት እራት ጋበዝኳትና ብዙ
ወይን እያጠጣኋት ስለልብ ወለድ መፃህፍትና ስለ ፊልሞች ጨዋታ
እስጀመርኳት። መጀመሪያ ስለምንወዳቸው ደራስያን፣ ስላየናቸው ፊልሞች፣ ስለምናውቃቸው ሰዎች እና በልብ ወለድ መፃህፍት ውስጥ ካገኘናቸው ሰዎች ጋር በምን እንደሚመሳሰሉ ማለት
ስለራሳችን ሳይሆን ስለ ሌላ ነገር ስናወራ፣ ወይን ስንጠጣ፣ ብዙ ጊዜ አሳለፍን። እየለመደችኝ ሄደች። ወይኑም እየሰራ ሄደ። አይናፋርነቷ እየረገፈ፣ እንደ ልቧ ለማውራት እየቻለች ሄደች፡፡ እኔም ፈረንሳይኛ እሷ ስትናገረው በጣም የሚጥም መሆኑን እያስተዋልኩ ሄድኩ።

ቀስ ብዩ ወሬውን ወደ ባህራም ወሰድኩት:: እንዴት ጎበዝ ሆኖ
እንደሚታየኝና፣ ምን ያህል እንደማደንቀው ከነገርኳት በኋላ፣
ባህራም ላንቺ እንዴት ሆኖ ነው የሚታይሽ? አልኳት። ደራሲ
መሆን እንደምፈልግና ስለሰዎች ማወቅ እንዳለብኝ፣ ይልቁንም
ሴቶች ወንዶችን እንዴት እንደሚያዩዋቸው ማጥናት እንደሚገባኝ ስለዚህ፣ እሷ ስለራሷ ብትነግረኝ ለኔ ትልቅ ዋጋ እንዳለው፣ በሰፊው ዘረዘርኩላት። ተቀበለችኝና ስትናገር፣ በቃላትዋ እየተንሳፈፍኩ የድምፅዋ ዜማ እየተመቸኝ አዳመጥኳት
ደራሲ ሳትሆንም ስለራሴ ብነግርህ ግድ የለኝም አለችኝ።
ባሀራም ስላንተ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገር ስለነገረኝ ነው መሰለኝ፣ በጣም የማውቅህ መስሎ ይሰማኛል። ደሞ እወድሀለሁ:: በጣም ተወዳጅ ልጅ ነህ። ብዙ ሴቶች ይህን ነግረውህ የለ? ተናገር፡ (ትስቃለች።እሷ የተናገረችው በንፁህ ልብ ነበር። እኔ ግን ምኞቴ ተቀሰቀሰ፡፡
እግሮቼን አጣመርኩ። የሉልሰገድንና የሷን ታሪክ ባላውቅ ኖሮ አሁን ምኞቴ ይቀሰቀስብኝ ነበር? እንጃ፡፡ ኒኮል ቀጠለችልኝ

«በአስራ ስድስት አመቴ ማርሴል ከሚባል ልጅ ፍቅር ያዘኝ
ማርሴልም ወደደኝ። ቤቶቻችን ሁለቱም ሀብታም ቡርዥም
በመሆናቸው ይከባበሩና ይዋደዱ ስለነበረ፣ በመዋደዳችን እጅግ
ተደሰቱ። እስክንጋባ ቸኮሉ፡፡ ግን
ሁለታችንም የዩኒቨርሲቲ
ትምህርታችንን እስክንጨርስ ላንጋባ ቆረጥን። ቤቶቻችንን ለማስደ ሰት ስንል ተጫጨን፡፡ በዚህ መካከል ማርሴል አየር ሀይል ገባ

«አንቷን ደ ሴንት ኤግዙፔሪን ታውቀው የለ? በኤሮፕላን
ስለመብረር፣ ስለአደጋው፣ ስለክብሩ፣ ስለጀግንነቱ የደረሳቸውን መፃህፍት፣ ማርሴል ደጋግሞ ያነባቸው ነበር፡፡ ከልቡ ሴንት ኤግዙፔሪኝ ያደንቀው ነበር፤ ያመልከው ነበር፡፡ ለዚህ ይመስለኛል አየር ሀይል የገባው፡፡ እኔ ተው አትግባ፤ እንደ ሴንት ኤግዙፔሪ በኤሮፕላን አደጋ ትሞታለህ፣ አልኩት። መሞት የት ይቀራል? አለኝ። የሰው ልጅ ተግባሩ ከሞት ለማምለጥ መጣጣር ሳይሆን፡ ሞት
እስኪመጣ ድረስ ክብር ያለው፣ ኩራት ያለው ኑሮን መኖር ነው፣
አለኝ። አለቀስኩ። እምባዬን ጠረገልኝ። አሮፕላን ነጂ ሆነ
ይህ ሁሉ ሲሆን በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ይሞክር ነበር፡፡ በብዙ
ይለምነኝ ነበር፡፡ ሳንጋባ አይሆንም ብዬ እምቢ አልኩት አንድ ቀን የኤሮፕላን እደጋ ደረሰበት። ሁለት ወር ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ። ከዚያ ወደ ቤቱ መጣ። የአየር ሀይል ኑሮ፣ የሴንት ኤግዙፔሪ አይነት ኑሮ፣ ክብር፣ አደጋና ጉብዝና የሞላበት ኑሮ፣ የጀግኖች አይነት ኑሮ በቃው:: ከአየር ሀይል አሰናበቱት።ምክንያቱም ወገቡ ተሰብሮ እግሮቹ ሽባ ሆኑ። በተሽከርካሪ ወምበር ቁጭ ብሎ፣ እኔ ወይም እናቱ እየገፋነው ነበር አየር ለመቀበል እንኳ የሚወጣው
«ካንጀቴ አዘንኩለት፡ በሀይል ወደድኩት እሱ ግን አሁንም ሽባ ሆኖ የሴንት ኤግዘፔሪን መፃህፍት
ያነብ ነበር። ስለአደጋ፣ ስለጀግንነት፣ ስለክብር ስለሞት ያነብ ነበር።አንድ ቀን ሽጉጡን ጠጥቶ ሞተ ሀዘን ጀመረኝ። ግን ሀዘን ይለመዳል። ወጣት ከሆንክማ ትንሽ ቆይቶም ይረሳል። በተለይ ያጠቃኝ ፀፀት ነበር። ፀፀት አይለመድም፣
አይረሳም፣ የማይጠግብ የማይተኛ ውስጣዊ ትል ነው፡ እድሜ ልክህን ይበላሀል። የቆጨኝ ማርሴል በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ሲፈልግ እምቢ ማለቴ ነው:: እወደው ነበር፡ ስጋዬን ለሱ መስጠት እንዴት አቃተኝ? በሀይል ይቆጨኝ ይሞረሙረኝ ጀመር

ነብስ አባቴ ጋ ሄድኩና ሁሉን ተናዘዝኩ፡፡ የሠራሽው ልክ
ነበር አሉኝ። እኔግን ፍፁም ስህተት እንደነበረ የበለጠ እየተገነዘብኩ ሄድኩ፡፡ ራሴን መቅጣት ጀመርኩ፡፡ ከጠየቀኝ ሁሉ መተኛት
ጀመርኩ። ደሞ ብዙዎች ይጠይቁኝ ጀመር። ርካሽ ሴት ሆንኩ

«ግን አሁንም ፀፀቱ አልተወኝም»

በካሎሪያዬን እንዳለፍኩ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወደ ኤክስ
መጣሁ፡፡ ቤቶቼም ማርሴልን ለመርሳት ካለአቨር ከተማ መራቅ
እንዳለብኝ ስላወቁ ሂጂ አሉኝ። ኤክስ መጥቼ በርካሽነቴ ላይ
ጠጪነት ጨመርኩበት። የፈለገኝ እንግዲህ እስክሰክር ድረስ ማጠጣት አለበት። ብዙ ሰአት ካንዱ ጋር ስጠጣ አመሻለሁ። ጧት ወደ አምስት ሰአት ላይ ስነቃ አልጋው ውስጥ ነኝ፡፡ ሲደሰትብኝ እንዳደረ ይታወቀኛል፣ ግን ምን ምን እንደሰራን እንደ ህልም'ንጂ እንደ ውን ሆኖ አይታየኝም

ካንዲት የኔ ብጤ ርካሽ ጋር ገጠምኩ፣ አብረን መጠጥና
ወንድ ስናሳድድ እናመሽ ጀመር

እንዲህ ስል አመቱ አለፈ፡ ፈተና ወደቅኩ፡ ክፍል ደገምኩ፣
ሁለተኛው አመት ተጀመረ፣ ያንኑ ኑሮዩን ቀጠልኩ

አንድ ረቡእ ጧት እንደ ልማዴ አንዱ እማላውቀው መኝታ
ቤት ነቃሁ። ሰውየው ቁርስ ያቀርባል፡፡ ልዩ ሰው ሆኖ ታየኝ።
ሳይነካኝ አድሯል፡፡ ከመስከሩ የተነሳ ሊነካኝ ባይችል ነው እንዳልል፣ ትላንት ማታ ፓርቲው ጋ ልሰክር ትንሽ ሲቀረኝ ጠጣ እንጂ»
ስለው ሁለታችንም ከሰከርንማ ማን ማንን ይደግፋል?» ሲለኝ
አስታወሰው
“አልጋ ውስጥ እንዳለሁ ቁርስ ከበላን በኋሳ፣ ሰውየው በተሰባበረ
ፈረንሳይኛ
“ እንቁላል ከተሰበረ ወድያ ምንም
እንደማይሆን ታውቂ የለ?» አለኝ፡፡ ምን እንደሚል ሳይገባኝ «አዎን”
አልኩት። ወጣትነትም አንዴ ከተሰበረ ሊጠገን አይችልም» አለኝ

«ምን ማለትህ ነው?» አልኩት

«ያንቺ ወጣትነት ገና አልተሰበረም:: ግን ሊሰበር ትንሽ ነው የቀረው። እንደዚህ አይነት ኑሮ ከቀጠልሽ ከትንሽ ጊዜ በኋላ
ይሰበራል»

ተናደድኩ «ምን አገባህ?» አልኩት
«ምን አገባህ አትበይኝ፡ ፈረንሳይ መሰልኩሽ እንዴ? እናንተ
ፈረንሳዮች ፈሪ ናችሁ፡፡ ግብዝ ናችሁ። ተግባራችሁን መፈፀም
አስቸጋሪ የሆነባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ምን አገባኝ? Ca me regarde pas. ብላችሁ ትተዉታላችሁ፡፡ እኔ ግን እንደሱ አይደለሁም፡፡»

«እና በኔ ህይወት አንተ ምን አገባህ?»

«አንቺ አልጋዬ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? በኔ ህይወት ውስጥ
ገባሽ ማለት አይደለም?» አለኝ። መልስ ስላጣሁ ዝም አልኩ
መጥቶ አልጋው ላይ አጠገቤ ቁጭ እለና፣ አይን አይኔን እያየኝ
«አሁን እስቲ ለሁለት ደቂቃ ፈረንሳይ መሆኑን ተይና ሰው
ሁኚ፡፡ ለሁለት ደቂቃ ብቻ፣ እሺ? አለዚያ ለመናገር አልችልም»
አለኝ፡፡ አንድ አይነት ደግ ፈገግታ አሳየኝ፡፡ ረስቼው የነበረ
አይናፋርነቴ ድንገት ተመልሶ ሽፍን አደረገኝ፡፡ ወደታች ሳይ ፊቴን
በእጆቹ ይዞ ቀና አደረገኝና ግምባሬን ሳመኝ

«አገሬ ኣንቺን የሚያካክሉ ታናናሽ እህቶች አሉኝ፡፡ አንቺ
የምታረጊውን ሲያረጉ ባያቸው ዝም አልላቸውም። ስለዚህ አንቺንም ዝም አልልሽም። ይገባሻል?»
👍28👏2
#ምንዱባን


#ክፍል_አስራ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....«ጌታዬ ይቀመጡ» አለው የጠባቂዎች ኃላፊ:: ሰውዬው እንዲሄድለት ግድግዳውን ተደግፎ ቆመ፤ አላበው፧ መተንፈስ አቃተው፤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡ እንደገና ቁጭ አለ፡፡ የተቀመጠበት ቦታ ትንሽ ዞር ያለ ስለነበር ለሰው በግልፅ አይታይም
ቁጭ እንዳለ አሳቡን የመለወጥ ዝንባሌ ታየበት:: “እስቲ አሁን ማን
አስገድዶኝ ነው የመጣሁት» ሲል አሰበ:: ነገር ግን እንዴት እንደሆነ
ሳያውቀው ቶሎ ብድግ ብሎ በመራመድ ችሎቱ ውስጥ ዳኞች ከነበሩበት አካባቢ ተጠጋ::

አካባቢውን በሚገባ ቃኘው:: ዳኞች ከፊት ለፊት ከፍ ካለው ሥፍራ ተቀምጠዋል:: ጠበቆች አፍጥጠዋል:: ጠባቂ ወታደሮች በየጥጉ ተበታትነው ቆመዋል:: የዳኞች ጠረጴዛ በደማቅ ጨርቅ ተሸፍኖአል:: የበሮች እጄታ
አካባቢ በእድፍ ጠቁሯዋል:: «
ስው ሰራሽ ሕግ እውነትን ያወጣል» በሚል እምነት ከዚያ የነበረ ሁሉ በጥሞና ያዳምጣል:: የሰው ብዛት ከመጠን በላይ
ስለነበር እርሱን ማንም ልብ አላለውም:: ሰው ሁሉ ይመለከት የነበረው ከወንጀለኞች መቆሚያ ላይ በሁለት ጠባቂዎች ታጅቦ ቆሞ የነበረውን ሰው
ነው::

በሁለት ጠባቂዎች ታጅበው የቆሙት ተከሳሹ ሻምፕማቲዩ ነበሩ፡፡መሴይ ማንደላይን አተኩሮ ተመለከታቸው:: በመልክ መመሳሰላቸውን ተገነዘበ፡፡ በእድሜ ግን ከእርሱ በጣም ያረጁ ይመስላል::

እየቀረበ ሲሄድ የመሐል ዳኛውና አቃቤ ሕጉ በጉልህ ስላዩትና
ስለለዩት በአንገት ሰላም አሉት:: ዳኞቹን፣ ሕግ አስከባሪውና እዚያ የነበሩ ጠበቆችና ጠባቂዎች ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት ያያቸው መሆኑን አስታወሰ፡፡
አሁንም ከስንት ዓመት በኋላ ከእነዚህ ሰዎች እጅ ሊወድቅ በመሆኑና ውሳኔያቸው ስለአስፈራው ዓይኑን ጨፈነ፡፡ ከፊት ለፊቱ የቆሙት ተከሳሽ
«ዣን ቫልዣ ናቸው ተብለው ነው የተከሰሱት» የሚል አሳብ ስለተሰረጸበትና ሕሊናው እንደ መሳት ስላለ ቶሎ ብሎ ተቀመጠ፡፡ እንደተቀመጠ ዣቬርን በዓይኑ ፈለገው ፤ አላገኘውም፡፡ ሕግ አስከባሪው መንገድ ላይ ስለተቀመጠ ምስክሮችን ሊያያቸው አልቻለም:: ክፍሉም ቢሆን በመጠኑ ጨለምለም
ያለ እንጂ ቦግ ብሉ የበራ ብርሃን አልነበረውም::

ክርክሩ የፈጀው ወደ ሦስት ሰዓት ገደማ ሲሆን ተከሳሹ ኣንደበተ
ርቱዕ ስልነበሩ የተከሰሱበትን ይካዱ እንጂ በሚገባ አላስረዱም:: እንዲያውም
ብዙውን ጊዜ ጣራ ጣራውን ነበር የሚያዩት:: ሲያዩዋቸው ቂላቂልና
ጅላጅል ቢጤ ይመስላሉ፡፡ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው በእኚህ ሰው ዝምታ የተነሣ ሰው ሁሉ የጠበቀው ከባድ ቅጣት ነው።

ሕግ አስከባሪው የሚከተለውን ተናገረ::

«ተከሳሹ በቅድሚያ ክስ የቀረበባቸው በፍራፍሬ ስርቆት ወንጀል ነበር፡፡ ክሱ ሲመሠረት የቀረበው ማስረጃ 'የሠረቁት ፍሬ ከእነቅጠሉ በእጃቸው ላይ ተገኝቷል' የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ብቻ እንደ ማስረጃ
ተቆጥሮ ለመስረቃቸው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም:: ተከሳሹ ከየት እንዳገኙት ሲጠየቁ ከመሬት ነው ያነሳሁት' ብለዋል፡፡ እርግጥም የፍራፍሬውን
ዛፍ ሌባ ቀጥፎ መንገድ ሊጥለው ይችላል፡፡ ስለዚህ ፍሬዎችን የያዘ
ቅርንጫፍ በመስበር የሰረቁት ሻምፕማትዩ ናቸው ለማለት ያስቸግራል።
ይህም በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ሊከሰሱ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ከእስር ቤት ያመለጠ ወንጀለኛ ለመሆናቸው በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳን
ዣን ቫልዣ ለመሆናቸው ምስክሮች ቢያረጋግጡም ተከሳሹ እስከመጨረሻው ክደዋል፡፡ ክህደቱን ትተው የፍርድ ቤቱን አስተያየት ቢጠይቁ የሚሻላቸው
ለመሆኑ ቢገለጽላቸውም አሻፈረኝ ብለዋል፡፡ በተከሳሹ አመለካከት ስለካዱ ከቅጣት የሚያመልጡ መስሎአቸው ይሆናል፡፡ በዚህ በኩል ተሳስተዋል፡፡ሆኖም ይህ ከእውቀት ማነስ እንጂ ሆን ብሎ የተደረገ ሊሆን አይችልም፡፡
ተከሳሹ በእርግጥ ንቃት ይጉድላቸዋል፡፡ ይህም የሆነው ምናልባት ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ቆይተው በመሰቃየታቸው ከዚያም በኋላ ብዙ ስለተንከራተቱ
ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ በሌላም፣ በሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል።ሆነም ቀረም የእርሳቸው አነጋገር አለማወቅ ወይም ችሎታ ማነስ ከሚሰጠው
ብያኔ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር አይገባም:: ነገር ግን ተከሳሹ ዣን ቫልዣ እንደሆነና የቅጣት ዘመናቸውን ሳይጨርሱ አምልጠው ለመጥፋታቸው
ጥርጥር የለውም:: ስለዚህ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በወንጀለኛ
መቅጫ አንቀጽ መሠረት ተገቢውን ቅጣት ይቀበላሉ፡፡»

ሕግ አስከባሪው ዳኞች ስለሰጡት አስተያየትና ስለፈጸሙት ጥልቅ
ምርምር በቅድሚያ ምስጋናውን አቅርቦአል፡፡ ተከሳሹን ግን የዳኞቹን ትንተና መሠረት በማድረግ በጣም ነቅፎዋቸዋል፡፡ ተከሳሽ ዣን ቫልዣ እንደሆነ
ስለመረጋገጡ ሲያስረዳ «ዝም ማለታቸው ነገሩን አምነው እንደተቀበሉ ያሳያል» አለ፡፡

«ቀደም ሲል ግን ክደው ነበር:: ለመሆኑ ዣን ቫልዣ ማነው? ዣን ቫልዣ የተተፋ፣ አገር የጠላውና ሌላም ሌላም ሰው ነው፡፡»
ሕግ አስከባሪው ይህን ሲናገር ከዚያ የነበረ ሰው ሰውነት ሁሉ
ስቅጥጥ አለ፡፡ «ሻምፕማንቲዩ ማለት ዣን ቫልዣ ነው» ተብሎ ክስ
ሲመሠረት «ዦርናል ደ. ለ ፕሪፊትየር የተባለ ጋዜጣ ዣን ቫልዣ ማን እንደሆነ ሲያስረዳ «ዣን ቫልዣ ማለት ወሮበላ፣ ለማኝ፣ ቀጣፊ፣ መተዳዳሪያ
የሌለው አውደልዳይ፣ ሕይወቱን ወንጀል በመሥራት የሚመራ እንዲሁም ሌላም ሌላም ቅጽል ሊሰጠው የሚገባ ነው» ብሎ እንደጻፈ ተናገረ፡፡

«ይህ ሰው ፍራፍሬ ሠርቆ ቢያዝም አድራጐቱን ክዷል፡፡ እንዲሁም ከእስር ቤት ለማምለጡም ከሕግ ፊት ክዷል፡፡ የሚገርመው የገዛ ስሙን
እንኳን የካደ ሰው ነው:: ምን ያልካደው ነገር አለ! ሕልውናውን ጨምሮ ነው የካደው ለማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እርሱ ሽንጡን ገትሮ ቢክድም አራት ምስክሮች መስክረውበታል: የተከበሩትና ውሽት የማያውቁት የፖሊስ
አዛዥ ዣቬር እንኳን በእርሱ ላይ መስክረዋል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ከተከሳሹ ጋር አብረው ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል ሦስት እስረኞችም መስክረውበታል፡፡ እነዚህ ምስክሮች ከመሰከሩበት በኋላ እንኳን ወንጀሉን አምኖ ይቅርታ አልጠየቀም:: ስለዚህ ማኅበራዊ ኑሮን ሊያፋልስ ታጥቆ
የተነሣ ወንጀለኛ ስለሆነ ቅጣቱ ሊቀልለት አይገባም፡፡»

ሕግ አስከባሪው ይህን ማብራሪያ ሲሰጥ ካህኑ ተከሳሽ አፋቸውን
ከፍተው በመገረምና በመደነቅ አዳመጠ፡፡ ሕግ አስከባሪው አንደበተ ርቱዕ በመሆኑ ቢያደንቁትም በማያውቁት ነገር እንደዚያ ስለወረደባቸው ከልብ
ረገሙት:: ግራ ቀኙን ከቃኙ በኋላ ተከሳሹ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ሕግ አስከባሪው ትችቱን በመቀጠል «ማንም ሰው ወንጀል ሊሠራ ወይም ውሸት ሊናገር ይችላል፡፡ ግን ከሕግ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ይህ ሰው ግን ወንጀል ከመፈጸም አልፎ ከሕግ ለማምለጥ ሞክሮአል፡፡ ይህም
ከባድ ወንጀል በመሆኑ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ አሳብ ኣቀርባለሁ::»

«ስለተሰጠው አስተያየት የምትሰጠው መልስ አለ?» ሲሉ ዳኛው ተከሳሹን ጠየቁዋቸው:: ቆባቸውን ያፍተለትሉ የነበሩት ተከሳሽ ምንም ነገር እንዳልሰማ ዝም አሉ::

ዳኛው ጥያቄውን ደገመላቸው::
አሁን ግን ጥያቄውን ስለሰሙ ዳኛው ምን ማለት እንደፈለጉ ገባቸው::ከእንቅልፍ እንደነቃ ሰው ከወዲያ ወዲህ ተመለከቱ፡፡ ዳኞቹን፣ ሕግ አስከባሪውን፣ ጠበቆቹንና ተመልካቹን ሕዝብ አፍጥጠው ካዩ በኋላ ከፊት
ለፊት የነበረውን መከለያ ብረት አጥብቀው ይዘው በድንገት በከፍተኛ ድምፅ መናገር ጀመሩ፡፡ ቃላት ተሽቀዳድመው «እኔ ልቅደም፧ የለም እኔ ልቅደም» ያልዋቸው ይመስል እየተቻኮሉ በጣም በፍጥነት ተናገሩ፡፡
👍194
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በታደለ_አያሌው


....“ሃያ ስምጉት ሳምንት: ደህና። መቼም ዉሃ እስከሚበቃ ጠጥተሻል አይደለም?” አለችኝ፣ ኮስተር ብላ በአንዴ ከጓደኛነት ወደ ሐኪምምነት እየተሻገረች።.


"አዎ፤ ሽንቴን ለመቋጠር ስቁነጠነጥ አታዪኝም?”

“ደምሽንስ እየተከታተልሽዉ ነዉ፤ ጥሩ ነዉ?”

“እዉነቱን ለመናገ Check አድርጌዉ አላዉቅም ወሰድ መለስ ሲያደርገኝ ሰንብቼ ወደ ቀልቤ የተመለስሁት ገና ዛሬ ነዉ
አልገርምሽም? ቅድም ስንገባ ራሱ ምድር ቤት መለካት እችል ነበር።

ደርሼ ልምጣ እንዴ አሁንም?”

“አይ አይ፤ ኧረ እዚሁ እናየዋለ”
እጅጌዬን ሰበሰብሁና ጠረጴዛዉ ጠርዝ ላይ አስደግፌ ዘረጋሁላት። የደም
ግፊት መለኪያዉን አምጥታ አሰረችልኝ፡

“oK. Nice, right? 128/74 ይላል። ጥሩ ነዉ ያለሽዉ። ሌላ የተለየ
ያጋጠመሽ ነገር የለም አይደል?”

ለመናገር ዳድቼ፣ እንደ መሳቀቅ ብዬ ቀረሁባት።

“ምንድነዉ እሱ፤ አለ እንዴ? "

“አልፎ እልፎ፣ ቀለል ያለ ደም ይፈሰኛል” በዚያ ላይ ቀደም ብሎ ይሰማኝ
የነበረዉ የፅንሱ እቅስቃሴ፣ አሁን እየተሰማኝ አይደለም”

"ምን'? ታዲያ መምጣት አልነበረብሽም? የተለየ ነገር ከገጠመሽ እንድትመጪ ተስማምተን አልነበረ?”

ልክ መሆኗን ስላወቅሁ፣ ምላሽ የሚሆን አላገኘሁላትም። ዝም ብዬ
አቀርቅሬ መሬት መሬቱን አየሁ፡

“እሺ መቼ ነዉ የጀመረሽ?”

“ምኑ?”

“ደም መፍሰሱ”

“እ፤ ደም መፍሰሱ እኳን ትናንት ነዉ የጀመረኝ ገና የእሷ እንቅስቃሴ ግን
ከተሰማኝ ሰንብቷል: አንድ ሳምት አያልፍም ብለሽ ነዉ?”

አስከትላ ማንኛዉም ለእርግዝና ክትትል የመጣ ታካሚ የሚጠየቀዉን ሁሉ ጠየቀችኝ: መቼስ ከሐኪም እና ከንስሐ አባት የሚደበቅ የለም ይባል የለ? ስለ ምግብ፣ ስሜት፣ የአካል እንቅስቃሴ፣ መንፈሳዊ ብርታት እና ስለመሳሰሉት ሁኔታዎቼ ሁሉ እንደ አጠያየቋ በግልጽነት እዉነት ዉነቱን ብቻ መለስሁላት የሁሉም መልስ ግን ያዉ ነዉ በአጭሩ፣
የትኛዎቹም ላይ ግድ የለሽ እንደ ነበርሁ አመንሁላት፡ አሁን እንደ ጓደኛም እንደ ሐኪምም ብትቆጣኝ እንደሚያምርባት ስለማዉቅ ራሴን ለዚያ አመቻችቻለሁ

“ዉብዬ፣ እኔ አንቺን እንዲህ አድርጊ ወይ አታድርጊ አልልሽም" ራስሽ
ታዉቂዋለሽ” ብላ ወደ በሩ እንደ መራመድ ካለች በኋላ፣ በሩን በኃይል ቦርቀቅ አድርጋ ከፍታ አፈጠጠችብኝ

ተከትያት ልነሳ በእጄ እሸቴ ጭን ላይ ስመረኮዝ፣ ስልኩን ሰረቅ አድርጎ አሳየኝ አሁኑኑ የሚል መልእክት ከባልቻ ተልኮለት ኖሮ፣ ምን ይሻላል የሚል ፊቱን አስነበበኝ። ቃል ሳናወጣ አዉርተን፣ አሁኑኑ ወደ ሲራክ ፯ መሄድ እንዳለበት ተማከርን ተግባባን፡

ብድግ አለ

“ወዴት ነዉ እሸቴ? እዚህ እኮ ልትጠብቀን ትችላለህ” አለችዉ፣ በቢሮ መቆየቱ አሳቅቶት የተነሳ መስሏት።

“አይ አይ፤ መሄድ አለብኝ: አጉል አድርጌ የተዉኩት ሥራ ነበረብኝ
አሁኑኑ መሄድ አለብኝ”

“እንዴ! ዉቤን ለብቻዋ ጥለሃት?”

“ምን ታደርጊዋለሽ፤ የእኀጀራ ጉዳይ…”
“ይኼን ያህል? የት ነዉ ግን የምትሠራዉ?”

“እ” ተንተባተበ፡፡ እንዲያዉም እንዲያ ነሽ አሉ ተረተኞች? እንኳን እሱ
እኔም ከእሷ ያልጠበቅሁት ጥያቄ ስለነበር፣ ክዉ ብያለሁ።

“የየየየየየ መንግሥት መሥሪያ ቤት ነዉ የምሠራዉ” አለ ለፊቷ መመለሻ፣ ወዳፉ እንደ መጣለት፡ ጎበዝ አልሁት በምልክት

“ተዉ እንጂ፣ የት?”

“..እ..…ንንንን..ግድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባክ”

“አሪፍ! ባንከሮችማ መናፈሻችሁ ሳይቀር የብር ጫካ ነዉ አላሉም?''

“ሳቅንላት፡ ተሳሳቅን፡ አጋጣሚዋን በመጠቀም፣ እሸቴ በሳቅ እያታለለ
ሹልክ ብሎ ወጣ፡ በቅጡ እንኳን አልተሰናበታትም

"አንቺስ ዉቤ?

“እ..ኔ ምን?” አልኋት፣ የእሸቴን መንተባተብ እኔም እየደገምሁት
የት እንደምትሠሪ መቼ ነገርሽኝ''
“አይ እኔ እንኳ ን ለጊዜዉ ሥራ የለኝም። ምናልባት አንቺ በሆስፒታላችሁ
ታስቀጥሪኝ እደሆነ እንጂ፣ የቤት እመቤት ነኝ”

"አግኝተነሽ ነዉ? በይ ነይ ተነሺ ይልቅ አልትራሳዉድ ክፍል ደርሰን እንምጣ” አለችኝ፣ እንድነሳ በግማሽ ዓይኗ እየደገፈችኝ።

"ውቤ! ሰዓቱን ግን ልብ ብለሽዋል? ባለሙያዉ አልትራሳዉንድ ክፍሉን
ጠርቅሞት ይኼድልሽና በብላሽ መመለስሽ ነዉ: አጅሬዉ ጠዋት ሲገባ
ማርፈዱን እንጂ፣ ከመዉጫ ሰዓቱ እንኳን ደቂቃ ማሳለፉንም አያዉቅበት። ቶሎ በይ፣ እንድረስበት”

እኔ ሆኜባት ነዉ እንጂ፣ አብራ የመዉጣት የመዉረድ ግዴታዋ ሆኖ አይደለም ለየክፍሉ የየራሱ ባለሙያ ስላለዉ፣ ሂጅ ዉጤቱን አሰርተሽ አምጪ ማለት ትችላለች እኔ ግን እኔ ሆንሁባት
እንዳለችዉም፣ ስንደርስ ባለሙያዉ ሊወጣ በር በሩን እያየ ነበር ልክ
ሲያየን ብልጭ አለበት፡ በተለይ እሷን ከፍ ዝቅ አድርጎ ጮኸባት፡ ባለፈዉ በእኔ ጉዳይ ተዋክባ እሷ እሱን በዚሁ ድምፀት ስታናግረዉ ሰማኋት ያን ያህል አልደነገጥሁም፡ ብድሩን ነዉ የመለሰባት፡

“ምን ነካሽ ዶክተር? መዉጫ ሰዓቴን ጠብቀሽ መምጣት ምን የሚሉት
ነገር ፍለጋ ነዉ? ''

“ግድየለም፣ ያን ያህል ጊዜ አልፈጅብህም” አለችዉ፣ ልክ ትርፍ ዉለታ እንደምትጠይቀዉ ሁሉ በመለማመጥ

""ቤቴ የት ሀገር እንደሆነ እያወቅሽ?”

“ነገርኩህ እኮ፤ከመዉጫ ሰዓትህ አንዲት ደቂቃ አላሳልፍብህም ካሳለፍሁብህ ደግሞ ታቋርጠኛለህ። ቶሎ በል ይልቅ አብራዉ አጠፋፍተኸዋል መሰል ደግሞ”

እኔም ጊዜ ለመቆጠብ፣ እስከምታዘዝ ድረስ ሳልጠብቅ ቀልጠፍ ብዬ
አልጋዉ ላይ ለምርመራ ተመቻችቼ የእንግላል ሆንሁላቸዉ
እየተነጫነጨም ቢሆን የፈጀዉን ጊዜ ፈጅቶ፣ ሁሉንም ነገር ዝግጁ አደረገዉ
ከዶክተር ሸዊት የወደድሁላት ጥሩ ጸባይ፣ ያለ ሙያዋ ጥልቅ አትልም ዛሬም ሆነ ባለፈዉ እንዳስተዋልኋት ከሆነ፣ ጣልቃ መግባት ቢያስፈልጋት እንኳን፣ ቢያንስ ቢያንስ ፈቃድ ትጠይቃለች፡ ዛሬም
እንዲህ ባለቀ ሰዓት ዉስጥ ሆና፣ ባለሙያዉን ጠበቀችዉ፡ ለነገሩ
ሙያዉም ያንን አይፈቅድም፡፡ በተለይ አልትራሳዉንድ በባሕሪዉ፣ ለማዳ እጅ ይፈልጋል ዉጤቱን ትክክልም ስሕተትም የሚያመጣዉ ከመሣሪያዉ ዘመናዊነት ይልቅ የባለሙያዉ (የራዲዮሎጂስቱ) ልምድ ያለው እጅ መሆኑ ነው ይባላል።

“እያየሽዉ ነዉ ዶክተ?” አለ ራዲዮሎጂስቱ፣ መከሰቻዉ ላይ ዓይኑን
ሰክቶ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳየ አዉቂያለሁ

“እ፤ እስኪ እስኪ” አለች እሷም፣ ትንፋሿ እየተቆራረጠ፡ ባለሙያዉን
ገፈተረችዉና ራሷ ገባችበት፡ “NO! አይደረግም!” ብላ ጮኸች።
ወዲያዉ ደግሞ በፊቴ መደንገጧ ይበልጥ አስደነገጣት፡ ጀርባዋን ሰጥታኝ
ያልደነገጠች ለመምሰል ብትሞክርም፣ እንደገና ከድንጋጤዋ ለመመለስ
ብትሞክርም፣ የትኛዉም አልሆነላትም

“በቃ፣ ጨርሻለሁ። መዘጋጋት ትችላለህ” አለችዉ ግራ ቀኝ ስትንቆራራጠጥ ቆይታ፣ ከአልጋዉ ላይ ደግፋ እያስነሳችኝ፡፡
“ኧረ ችግር የለም፣ የማግዝሽ ነገር ካለ እንዲያዉም ያን ያህል የሚ ያስቸኩል ጉዳይ የለኝም” አላት፣ እንደዚያ እሳት ለብሶ የነበረዉ ሰዉዬ በአንድ ጊዜ ዉሃ እየሆነ በሐዘኔታ አየኝ፡

“ዉብዬ” አለችኝ፣ የተከሰተዉን እንድመለከተዉ በአገጯ እየጠቆመችኝ
ግብኔን ወደ ጠቆመችኝ መከሰቻ አዞርሁላት። “ያዉ፣ ባለፈዉ እንደ ጠበቅነዉ፤ እንደፈራነዉ ሳይሆን አልቀረም በእርግጥ ያን ጊዜ ምልክቶቹን ባየን ጊዜ፣መልሶ ይቀንሳል የሚል ጭላንጭ ተስፋ ነበረኝ በበኩሌ።ሆኖም ፅንሱን እንደምታይዉ
ባልተመጣጠነ የጭንቅላት የፈሳሽ መጠን የተነሳ፣ ጭንቅላቱ ከመጠን በላይ አድጓል። ይኼ እንዳለ ሆኖ፣ መጀመሪያም ምልክቱን ያየነዉ የጀርባዋ አጥት ክፍተት ደግሞ እየሰፋ መጥቷል”
ትንሽ ተያየን፡፡ ከእሷም በሆዴ ካለችዋም ጋር አጭር ቆይታ አደረግሁ
👍34
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አስራ_አራት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

....ምናልባትም ቅዳሜ ወይም እሁድ መቼ እንደሆነ እየፀፀታት ይሆናል የቀን መቁጠሪያው በትክክል በቀይ የኤክስ ምልክቶች ተሞልቷል የታሰርንባቸው ቀናት፣ ሙቀቱ፣ ብቸኝነቱ፣ የልብ መሰቀሉ
የተጎዳንባቸው ቀናት ላይ በሙሉ ምልክት አድርገንባቸዋል.
ወንበር ላይ ተቀምጣ የሚያምሩ እግሮቿን አነባበረችና ራሷን ለማቀዝቀዝ ልታራግብበት መፅሄት አንሳች ደስ የሚል የፍቅር ፈገግታ ወደኔ አቅጣጫ እያሳየች “ስላስጠበቅኳችሁ ይቅርታ። ጠዋት መጥቼ ላያችሁ ነበር። ግን
አባቴ ሙሉ ትኩረቴን ፈልጎ ስለነበር ከሰዓት ልጎበኛችሁ እቅድ አወጣሁ:: ከዚያ የሄድኩበትን ጉዳይ አሳጥሬ ከእራት በፊት ከልጆቼ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ
እንድችል ብዬ ስሮጥ መጣሁ” አለች: “ሀይቁ ላይ እየቀዘፍኩ ነበር።ወንድሞቼ የዘጠኝ አመት ልጅ ሳለሁ እንዴት እንደምቀዝፍ አስተምረውኝ ነበር ከዚያ አባታችሁ እዚህ ሊኖር ሲመጣ እንዴት መቅዘፍ እንዳለበት
አስተማርኩት ሀይቁ ላይ ብዙ ጊዜ እናሳልፍ ነበር፡ መቅዘፍ ልክ እንደ
መብረር ነው... አስደናቂ ደስታ ይሰጣል” የእሷ ደስታ የእኛን ደስታ እንደሰረቀ አስተውላ መናገሯን አቆመች።

“መቅዘፍ?” ጮህኩ። “ለምን ምድር ቤት ሄደሽ ለወንድ አያትየው ስለኛ አልነገርሽውም? እዚህ ውስጥ ቆልፈሽ የምታስቀምጪን እስከ መቼ ነው?
ለዘለዓለም?”

ሰማያዊ አይኖቿ ክፍሉ ውስጥ ተንከራተቱ ከወንበሩ ላይ ልትነሳ ከጀለች:ክሪስ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል መፅሀፍቶች ተሸክሞ መጣ።

“ካቲ እናትሽ ላይ አትጩሂባት!” አለኝ፡ “ሰላም እማዬ፣ በጣም አምሮብሻል፡'የያዛቸውን መፃህፍት ጠረጴዛ ላይ አደረገና አቀፋት በእናቴ ብቻ ሳይሆን በወንድሜም እንደተጎዳሁ ተሰማኝ፡ ምንም ሳናደርግ በጋው ሊያልቅ ነው።
ሽርሽር ወይም ዋና ቦታ አልሄድንም ወይም ጫካ ውስጥ አልተንሽራሸርንም ጀልባ አላየንም ወይም የዋና ልብስ ለብሰን ጓሮ ያለው የመዋኛ ገንዳ ውስጥ
እንኳን አልተንቦራጨቅንም

“እማዬ!” ጮህኩ፡ በእግሮቼ ቆሜ ለነፃነታችን ለመታገል እየተዘጋጀሁ
“ለአባትሽ ስለኛ ለመንገር ጊዜው ደርሷል ብዬ አስባለሁ! እዚህ ክፍል ውስጥ መኖርና ጣሪያው ስር ያለው ቦታ ላይ መጫወት ሰልችቶኛል! መንትዮቹ |
ንፁህ አየርና የፀሀይ ብርሀን እንዲያገኙ እፈልጋለሁ። እኔም መውጣት እፈልጋለሁ ወንድ አያታችን አባታችንን በማግባትሽ ይቅር ካለሽ ለምን እኛን ሊቀበለን አይችልም? እኛን የስጋ ዘመዶቹ እንደሆንን የማይቆጥረንና
የሚያፍርብን ያን ያህል አስቀያሚ አስቸጋሪ ወይም ደደብ ነን እንዴ?"

ክሪስን ገፋ አድርጋ የተነሳችበት ወንበር ላይ አንገቷን አቀርቅራ ፊቷን በእጆቿ ቀብራ ተቀመጠች: በደመነፍስ ከዚህ በፊት ደብቃን የነበረን የሆነ እውነት ልታወጣው እንደሆነ ገመትኩ። ኮሪና ኬሪን ጠርቼ ጎንና ጎኔ አስቀመጥኳቸው:
ክንዶቼን እያንዳንዳቸው ላይ አደረግኩ፡ ክሪስ ከእናታችን ጎን ይሆናል ብዬ ሳስብ ወደኛ መጥቶ አልጋው ላይ ከኮሪ አጠገብ ተቀመጠ፡ እንደገና እንደ በፊቱ ከባድ ንፋስ ሊወስደን ያለ፣ በልብስ ማስጫ ገመድ ላይ የተቀመጥን ትናንሽ ወፎች መስለን ነበር።

"ካቲ፣ ክሪስቶፈር…” ስትል ጀመረች:: አሁንም አንገቷን እንዳቀረቀረች ነው:
“ለእናንተ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ አልነበርኩም” አለች ልክ ይህን እንዳልገመትኩ ሁሉ፡-

“ዛሬ ለእራት ከእኛ ጋር አትቆይም?” ስል ጠየቅኳት በሆነ ምክንያት ሁሉንም እውነቶች አለማንሳት ፈልጌያለሁ።

“ስለጠየቅሽኝ አመሰግናለሁ መቆየት እፈልግ ነበር ግን ለዚህ ምሽት ሌሎች እቅዶች አሉኝ" ይህ የእኛ ቀን ነው እስኪጨልም ከሷ ጋር የምንሆንበት ጊዜ ትናንትና ከእኛ ጋር የቆየችው ለግማሽ ሰዓት ብቻ ነበር።

“ደብዳቤው” አጉረመረመችና አንገቷን ቀና አደረገች: “ግላድስተን እያለን እናቴ
የፃፈችው ደብዳቤ ላይ እዚህ እንድንኖር ጋብዞናል ግን ደብዳቤው መጨረሻ ላይ አባቴ አጭር ማስታወሻ ፅፎ እንደነበር አልነገርኳችሁም:"

“አዎ” እኔም ገፋፋኋት፡ “መንገር ያለብሽን ንገሪን እንቀበለዋለን” አልኳት።

እናታችን ራሷን የምትቆጣጠር ሴት ናት᎓ ነገር ግን መቆጣጠር የማትችለው አንድ ነገር አለ እሱም እጆቿን ነው: ሁልጊዜም እጆቿ ስሜቶቿን ይከዳሉ።እጆቿ ረፍት የለሽና ልክ እንደሚታጠብ ሰው ይንቀሳቀሳሉ።

“ሴት አያታችሁ ደብዳቤውን ፅፋ ፈረመችው፣ መጨረሻው ላይ ደግሞ አባቴ የራሱን ማስታወሻ ጨመረበት…" አመነታች: አይኖቿን ለአንድ ወይም ለሁለት ሰከንድ ጨፈነች: ከዚያ ከፈተቻቸውና እንደገና አየች። “ወንድ
አያታችሁ ሲፅፍ አባታችሁ በመሞቱ ደስ እንዳለውና ክፉ ሰዎች ሁልጊዜም የሚገባቸውን እንደሚያገኙ፣ ከእኔ ጋብቻ ብቸኛው መልካም ነገር የሰይጣን
ዘሮች አለመፈጠራቸው እንደሆነ ተናግሮ ነበር፡

በፊት ቢሆን “ምንድነው?” ብዬ እጠይቅ ነበር፡ አሁን ግን አውቃለሁ የሰይጣን ዘሮች ማለት ከሰይጣን የተፈለፈሉ ከሚለው ጋር አንድ ነው የሆነ ክፉ፣ የተበላሸ፣ መጥፎ ሆኖ የተወለደ።

ክንዶቼን መንትዮቹ ላይ እንዳደረግኩ አልጋው ላይ ተቀምጬ ወደ ክሪስ
ተመለስኩ፡ ክሪስ ቁርጥ አባታችንን ይመስላል: አባታችን ነጭ የቴኒስ ልብስ የሚለብስ፣ ረጅም፣ ኩሩ፣ ባለ ወርቃማ ፀጉርና ነሀስ የመሰለ ቆዳ ያለው ነበር:
ክፉ የሚባለው ደግሞ ጥቁር፣ ጠማማ፣ ያደፈጠና ትንሽ እንጂ ዋሽተው የማያውቁ ንፁህ ሰማይ የመሰሉ ሰማያዊ አይኖች ያሉትና የሚያምር ፈገግታ ያለው ረጅም ሰው አይደለም።

“እናቴ እናንተን ስለመደበቅ ያላትን እቅድ አባቴ ባላነበበው ደብዳቤ ላይ አሰፈረች" አለችና አጠቃለለች ፊቷ ቀልቶ ነበር።

“አባታችን የወንድሙን ልጅ በማግባቱ ምክንያት ብቻ ነው እንደ ክፉና ምግባረ ብልሹ የተቆጠረው?” ክሪስ ጠየቀ፡ “የሰራው ስህተት ያ ብቻ ነው?
“አዎ!” ብላ ጮኸች የምትወደው ልጇ ስለተረዳት ደስ ብሏታል። “አባታችሁ ህይወቱን ሙሉ አንድ ይቅር የማይባል ኃጢአት ሰርቷል እሱም ከእኔ ጋር በፍቅር መውደቁ ነው ህጉ በአጎትና በወንድም ልጅ መካከል ያለ ጋብቻን
ይከለክላል፤ ዝምድናቸው በግማሽ ቢሆንም እንኳን። እባካችሁ አትርገሙን
እንዴት እንደነበረ ነግሬያችኋለሁ ከሁላችንም አባታችሁ በጣም ምርጥ ነበር” ልታለቅስ ደረሰች በአይኖቿ እየለመነችን ነበር ቀጥሎ የሚመጣውን
አውቄያለሁ:

“ክፋት ምንድነው? ምግባረ ብልሹነት ምንድነው? ሁሉም ያለው በተመልካች አይን ውስጥ ነው:” በእሷ መንገድ እንድናየው በጥድፊያ ቀጠለች። “ወንድ
አያታችሁ መልአክ ላይ ሳይቀር ስህተት ያገኛል። እሱ በሁሉም የቤተሰቡ አባላት ላይ ፍፁምነት የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው እሱ ግን ከፍፁምነት እጅግ የራቀ ነው: ነገር ግን ያንን ልትነግረው ብትሞክር በጥፊ ያጮልሀል
ክሪስቶፈር፣ የሆነ ጊዜ ስላንተ ልነግረው እችላለሁ ብዬ አስባለሁ። እንዴት ጎበዝ ተማሪ እንደሆንክና ሁልጊዜ ትልቅ ማርክ የምታገኝ እንደሆንክ ካቲን ሲያይና ትልቅ የዳንስ ተሰጥኦዋን ሲያውቅ… እነዚህ ሁለት ነገሮች
ብቻ ገና መንትዮቹን ሳያይ እንዲለዝብ ያደርጉታል። እንደማስበውና ተስፋ
እንደማደርገው በቀላሉ ይሸነፍልንና ጋብቻችን ትክክል እንዳልሆነ ማመኑ ስህተት እንደነበረ ይረዳል”
👍314
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


በቢዝነስ ዓለም ውስጥ ያለ ሰው በሌላ ሰው መናደድ ገንዘቡ አይደለም፡፡
ይህን ከረጅም ጊዜ በፊት ተምራለች፡፡ ‹‹ቦስተን በጊዜው አልደርስም፧ ነገር
ግን የኩባንያውን ሽያጭ እዚህ ሆኜ ማስቆም እችላለሁ›› ስትል አሰበች፡፡
ወደ ስልኩ ዞረችና አሁን ቦስተን ውስጥ አንድ ሰዓት ነው፡፡ ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክ ብራይድ ይሄኔ ቤቱ ነው የሚሆነው፡ ለስልከኛው የጠበቃዋን ስልክ ሰጠች.

ማክ የወንድም ያህል ነው ለእሷ ባሏ የሞተ ጊዜ ሁሉን ነገር አድርጎላታል፤ ቀብሩን ማስፈፀም፣ የባሏን ኑዛዜ እና የግል ገንዘቧን
መቆጣጠርና መከታተል፣ ልጆቿንም ወደ መጫወቻ ቦታ በመውሰድ በትምህርት ቤት የተወኑትን ድራማ በማየት፣ ኮሌጅ ሲገቡ የሚመርጡትን
ትምህርትና ኮሌጅ ካጠናቀቁም በኋላ የሚይዙትን የስራ አይነት በማማከር በኩል የአባት ያህል ሚና ተጫውቷል፡፡ ስለወሲብ ማወቅ የሚገባቸውን ነገር
እንኳን አልደበቃቸውም፡፡ የፒተርና የናንሲ አባት የሞተ ጊዜ ፒተር የኩባንያው ሊቀ መንበር እንዳይሆን የተቻላትን ማድረግ እንዳለባት መክሯት
ነበር፡፡ እሷ ግን የነገራትን በወቅቱ አልተቀበለችውም፡ አሁን የደረሰው ነገር ታዲያ ማክ በዚያ ጊዜ ያለው ትክክል መሆኑን አሳይቷታል ማክ እንደሚወዳትም ታውቃለች፡፡ ማክ አጥባቂ ካቶሊክ ሲሆን ለሚስቱ ታማኝ አይደለም ለፈስፈስ ያለና ራሰ በራ ነው፡፡ እሷ የምትፈልገው ቆፍጣናና
ፀጉረ ሙሉ ወንዶችን ነው ልክ እንደ ናት ሪጅ ዌይ ያሉ፡፡

የስልክ ግንኙነት እስከሚገኝ ድረስ ያለችበትን ሁኔታ ማውጠንጠን ጀመረች፡፡ ከፒተር ጋር አብሮ ሴራ የሚያውጠነጥነው የአባቷ ምክትልና የአንድ ወቅት ፍቅረኛዋ የነበረው ናት ሪጅ ዌይ ነው፡፡ ናት የኩባንያውን ዋና ኃላፊነት ቦታ ሲያጣ ኩባንያውንና ናንሲን እርግፍ አድርጎ እብስ አለ፡ አሁን ደግሞ የጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ ፕሬዚዳንት በመሆኑ የብላክ ጫማ ኩባንያን ለራሱ ለማድረግ ይመኛል፡፡

ናት የጫማ ሳምፕሎች ሊሰበስብ ፓሪስ መምጣቱን ታውቃለች፧ ምንም እንኳን ባታገኘውም፡፡ ፒተር ከእሱ ጋር ተገናኝቶ ስምምነት እንዳደረጉ ገምታለች፡፡ ናንሲ ደግሞ ይህን አልጠረጠረችም ምን ያህል በቀላሉ እንደተታለለች ስታውቅ በፒተርም በናትም በጣም ተናደደች በይበልጥ ግን በራሷ።

ስልኩ ጮኸና አነሳችው፡፡ ዛሬ የስልክ እድሏ ሰምሮላታል፡
ማክ አፉን በምግብ ሞልቶ ሃሎ አላት፡፡
‹‹ማክ ናንሲ ነኝ››
የጎረሰውን ዋጥ አደረገና ‹‹ይመስገነው መደወልሽ፡፡ አውሮፓ ውስጥ አንቺን በስልክ ያልፈለኩበት ቦታ የለም፡፡ ፒተር. አለ፡፡

‹‹አውቄያለሁ አሁን ሰማሁ›› ስትል አቋረጠችው ‹‹ምንድን ነው
ስምምነታቸው?››

‹‹ለብላክ ጫማ አምስት አክሲዮኖች ከጄኔራል ቴክስታይልስ አንድ አክሲዮን ከ27 ሳንቲም ጋር››

‹‹በኢየሱስ ይሄማ በነፃ መስጠት ነው!››

‹‹አሁን ከምታገኙት ትርፍ አንፃር ፒተር ያቀረበው ዋጋ ትንሽ አይደለም፡፡››

‹‹ታዲያ የእኛ የቋሚ ንብረት ዋጋ እኮ ከፍተኛ ነው›› አለች ናንሲ ጮሃ።

‹‹እንዴ ከእኔ ጋር እኮ አይደለም ጠብሽ›› አላት ለስለስ ብሎ

‹‹ይቅርታ ማክዬ ተናድጄ ነው››

‹‹ይገባኛል፡፡››

በስልኩ ውስጥ ልጆቹ ሲንጫጩ ይሰማታል፡፡ አምስት ልጆች አሉት ሁሉም ሴቶች ናቸው፡፡ ሬዲዮና ጀበና ሲያፏጭ ይሰማታል፡፡
‹‹ፒተር ያቀረበው ዋጋ ዝቅተኛ እንደሆነ አሁን ገብቶኛል፡ ብላክ ጫማዎች ኩባንያው የሚገኘውን ትርፍ እንዲህ ያለውን ቋሚ ንብረትና የወደፊት እምቅ ሃይል ግምት ውስጥ አላስገባም›› አለ ‹‹ሌላም ነገር አለ››

‹‹ምንድን ነው?››

‹‹ጄኔራል ቴክስታይልስ የእናንተን ኩባንያ ከተረከበ በኋላ አምስት አመት ድረስ ፒተር እንደሚያስተዳድረውና አንቺም ቦታ እንደሌለሽ
ተስማምተዋል፡››

ናንሲ ዓይኗን ጨፈነች፡፡ እንደዚህ አይነት ጥቃት ደርሶባት አያውቅም፡፡
ህመም ተሰማት፡፡እስከዛሬም ወንድሟ ደካማነቱ እንዳይታወቅ በኃላፊነት እንዲቆይ ስትረዳውና ኩባንያውም ከስሮ ከገበያ እንዳይወጣ ስትለፋ ኖራ እሷ ከስራ ትባረር! ‹‹እንዴት ይሄንን ደባ በእኔ ላይ ይፈፅማል?›› አለች፡፡

‹‹ወንድሜ አይደለም?››
‹‹ናን በደረሰብሽ ዱብ ዕዳ አዝናለሁ››
‹‹አመሰግናለሁ ማክ›› አለች፡፡
‹‹እኔ መቼም ከድሮም ፒተርን አላምነውም ነበር››
‹‹አባታችን ይህን ቢዝነስ ለዓመታት ሲገነባ ኖረ›› ስትል አለቀሰች፡:
‹‹ፒተር ይህን ኩባንያ ማጥፋት የለበትም››
‹‹ምን ላድርግልሽ እኔ ታዲያ?›› አለ ማክ
‹‹ይህን ደባ ማስቆም እንችላለን?››
‹‹የቦርድ ስብሰባው ላይ ብትደርሺ የአክስትሽና የዳኒ ሪሌይን ሃሳብ ማስለወጥ የምትችይ ይመስልሻል?››
‹‹በሰዓቱ መድረስ አልችልም ችግሬ ይሄ ነው፡፡ አንተ ልታሳምናቸው አትችልም?››
‹‹እችል ይሆናል ነገር ግን ምን ሊፈይድ፡፡ ፒተር ባለው የአክሲዮን ድርሻ የአክስቱን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ይችላል፡ የአክስቱና የዳኒ አክሲዮን ቢደመር 20 በመቶ የእሱ ደግሞ 40 በመቶ ነው፡፡››

‹‹አንተ እኔን ወክለህ ድምፅ መስጠት አትችልም?›

‹‹የአንቺ ውክልና የለኝም››
‹‹በስልክ ድምፅ መስጠት እችላለሁ?››

‹‹ይሄ ሃሳብ ምናልባት ያስኬድ ይሆናል፡፡ የቦርዱ ውሳኔ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ፒተር ባለው ሃይል ሃሳቡን ውድቅ ማድረግ ይችላል፡››

ሁለቱም አዕምሮዋቸው በሃሳብ ሲርመሰመስ ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ሰፈነ፤
በዚህ ጊዜ ይሉኝታ ማጣቷ ታወሳትና ‹‹ቤተሰብ እንዴት ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ልጆቹ ደህና ናቸው፤ ቤቲም አርግዛለች››

‹‹አሁንም?›› ልጅ መውለድ ያቆሙ መስሏት ነበር፡ ‹‹የመጨረሻው ልጅ ገና አምስት አመቱ አይደለም እንዴ?›› ስትል ጠየቀችው:

‹‹የችግሩን መፍትሄ አሁን ገና ነው ያገኘሁት›› አለ፡፡
ናንሲ ሳቀች ‹‹እንኳን ደስ አለህ!››
‹‹አመሰግናለሁ፡ ቤቲ ደስታም ሀዘንም ተሰምቷታል››
‹‹ደመወዝህ ግን ቤተሰብ ለማስተዳደር ይበቃሃል?››
‹‹ይበቃኛል፡፡ አይሮፕላን እንደማታገኚ ግን አረጋግጠሻል?››

ናንሲ ጫን ጫን ተነፈሰችና ‹‹አሁን ያለሁት ሊቨርፑል ነው፡ ሳውዝ ሃምፕተን ከሊቨርፑል 200 ኪ.ሜ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ እናም አይሮፕላኑ ሊነሳ የቀረው ሰዓት ከ2 ሰዓት አይበልጥም፡፡ አይቻልም››

‹‹ሊቨርፑል ከአየርላንድ እኮ ብዙ አይርቅም››
‹‹እባክህ ተወኝ ጂኦግራፊውን›› አለች፡፡
‹‹በራሪ ጀልባው አየርላንድ ያርፍ የለም እንዴ?››
የናንሲ ልብ ዘለለ ‹‹እርግጠኛ ነህ?››
‹‹ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ››
ማክ የሰጣት አስተያየት ልቧን አነሳሳው፡ ተስፋዋም ለመለመ፡፡ ‹‹የት ነው የሚያርፈው ደብሊን ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹አይደለም፡፡ በምዕራብ የባህር ዳርቻ የሆነ ቦታ፧ ስሙን ረሳሁት ያም
ሆነ ይህ ትደርሻለሽ›› አላት
‹‹አረጋግጬ እደውልልሃለሁ ባይ ባይ››
‹‹ናንሲ››
‹‹ምንድን ነው?››
‹‹መልካም ልደት››
ናንሲ ፈገግ አለች ‹‹አንተ የምትገርም ነህ፤ መቼም አትረሳም፡፡››
‹‹መልካም ዕድል››

‹‹ደህና ሁን›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡ ወደ እንግዳ ተቀባዩም ሄደች ሰውዬውን ልክ ልኩን ልትነግረው ፈልጋ ነበር፤ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት እርዳታውን ስለምትፈልግ የባሰ እንዳይተበትባት ማድረግ ነው ያለባት፡
‹‹በራሪ ጀልባው አየርላንድ ውስጥ ያርፋል አይደል?›› አለች ተለሳልሳ፡፡
‹ልክ ነው የኔ እመቤት፡፡ ፎየንስ የሚባል ቦታ፡››
‹ለምንድን ነው ታዲያ ቅድም ይህን ያልነገርከኝ አንተ ጉረኛ› ልትለው ፈልጋ ነበር ነገር ግን ፈገግ ብላ በስንት ሰዓት?› ስትል ጠየቀች፡
👍16
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ኤዲ በመጨረሻ ጉዳዩን ለአንድ ሰው ማዋየት እንዳለበት ተገንዝቧል
በጣም ለሚያምነው ሰው፤ ምስጢሩን መጠበቅ ለሚችል፡፡ ከዚህ በፊት
እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥመው ለካሮል አን ነው የሚነግራት፡ ምስጢረኛው
ናት፡፡ አባቱ በህይወት በነበሩ ጊዜ እንኳን ሚስጢር አያወሩም፡፡ አባቱ
‹ደካማ› እንዲሉት አይፈልግም፡፡ ታዲያ የሚያምነው ሰው ያገኝ ይሆን?

ካፒቴን ቤከርን አሰበ፡፡ ካፒቴን ቤከር ተሳፋሪዎች ገና ሲያዩት የሚወዱት አይነት፣ መልከ መልካም፣ በራሱ የሚተማመንና ሚዛናዊ ሰው ነው፡፡ ኤዲ ቤከርን ይወደዋል፣ ያከብረዋልም፡፡ ነገር ግን ቤከር ታማኝነቱ
ለአይሮፕላኑና ለተሳፋሪዎች ደህንነት ሲሆን ከደንብ ውልፍት አይልም፡
ያሰበውን ለእሱ ቢነግረው በቀጥታ አንጠልጥሎ ለፖሊስ ነው የሚሰጠው::
ካፒቴን ቤከርን ማማከር አይሆንም፡፡ ‹ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል?,

ስቲቭ አፕል ባይ

ስቲቭ ቁመቱ ሎጋና ፈርጣማ ሲሆን አባቱ የእንጨት መሰንጠቂያ
ባለሙያ ናቸው በባህር ኃይል ኮሌጅ ከኤዲ ጋር አብረው ተምረዋል፡ትምህርት የጀመሩ ዕለት ዩኒቨርሲቲ ካፍቴሪያ ተዋወቁና ጓደኝነት
መሰረቱ፡፡ ሌሎች ተማሪዎች የማሰልጠኛውን ምግብ
ሲንቁ ምግቡ የተስማማው አንድ ተማሪ የበላበትን ሰሃን እንደሱ ሲያጥብ አየ ያም ልጅ ስቲቭ ነው፡፡ ዓይን ለዓይን ተገጣጠሙና ተግባቡ፡፡

ሁለቱ ወጣቶች የኮሌጅ ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ
ጓደኝነታቸው አልተቋረጠም፡ በኋላም ፐርል ሃርበር
ሰርተዋል፡፡ ስቲቭ ሲያገባ ሚዜው ኤዲ ነበር፤ ኤዲ ሲያገባ ሚዜው ስቲቭ
ነበር፡፡ ስቲቭ አሁንም የባህር ኃይል ባልደረባ ነው፡፡ አሁን አሁን ብዙ
ባይገናኙም ጓደኝነታቸው አልተቋረጠም: አንድ የተለየ ነገር ካልኖረ በስተቀር ደብዳቤ ባይፃፃፉም ኒውዮርክ ያሉ ጊዜ ግን ተፈላልገው ራት ይገባበዛሉ
ወይም ከረንቦላ አብረው ይጫወታሉ፡፡የሚለያዩበት ቀን እስኪደርስ አይላቀቁም፡፡ ኤዲ በዚህ ምድር ላይ የሚያምነው ሰው ስቲቭን ብቻ ነው፡፡

ኤዲ የሆዱን ሊተነፍስለት ስቲቭን ለማግኘት ወሰነ፡፡ ይህንንም መወሰን
በመቻሉ እረፍት አገኘና ወደ ሆቴሉ ሮጠ፡

ኤዲ የሆቴሉ እንግዳ ተቀባይዋጋ ሄዶ የባህር ኃይሉን ኮሌጅ ስልክ
አስመዘገበና ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡ መስመር ሲገኝ ትጠራዋለች፡

ቱታውን አወላልቆ ባኞ ቤት ገባና ፊቱንና እግሩን ታጥቦ ዩኒፎርሙን ለበሰ፡፡ አእምሮው ሰላም አጥቷል፡፡ ስቲቭ ምን እንደሚል ባያውቅም ችግሩን
ለእሱ ማካፈል መጠነኛ እፎይታ ይሰጠዋል፡፡

ትንሽ ቆይቶም ስልክ እንደሚፈልገው ተነገረውና ደረጃውን በሩጫ
ወርዶ ስልኩን አነሳ ‹‹ከስቲቭ አፕልባይ ጋር ብታገናኚኝ›› አላት የኮሌጁን
ስልከኛ፡

‹‹መቶ አለቃ አፕልባይ በዚህ ሰዓት በስልክ አይገኝም›› አለችው፡፡ ኤዲ ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡፡ ‹‹ሲመጣ ምን ልበልሎት?››

ኤዲ በእጅጉ ሀዘን ተሰማው፡፡ ስቲቭ በአስማት ካሮል አንን እጁ ላይ
አምጥቶ እንደማይጥልለት ያውቃል፡፡ ነገር ግን የደረሰበትን ዱብዳ
ቢያማክረው ስቲቭ አንድ የሆነ ሀሳብ ይሰጠዋል፡፡

‹‹የኔ እመቤት ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልጌው ነበር አሁን የት ነው ያለው?››

‹‹ማን ልበል እርስዎን?››

‹‹ኤዲ ዲኪን እባላለሁ››

‹‹ኤዲ እንደምን አለህ? የእሱ ሚዜ የነበርከው አይደለህም? እኔ ላውራ
ግሮስ እኮ ነኝ፧ ከዚህ ቀደም ተገናኝተናል፤ ስቲቭ ዛሬ ከካምፕ ወጥቶ ነው
ያደረው›› አለች እሱ መሆኑን በማወቋ የስልከኛ ንግግሯን ትታ፡

ኤዲ በሆዱ አጉተመተመ፡፡ ‹‹በስንት ሰዓት ይመለሳል?››

‹‹ጎህ ሲቀድ መመለስ ነበረበት ግን እስካሁን አልመጣም›› አለች፡
‹‹ኔላን ታስታውሳታለህ? አሁን ጸሐፊ ሆናለች፤ ቆይ አንድ ጊዜ ከእሷ ጋር
ላገናኝህ››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ›› ለኔላ መቼም ነገሩን አይነግራትም ነገር ግን ስቲቭ የት እንዳለ ታውቅ ይሆናል፡፡ ስልከኛዋ ከኔላ ጋር እስከምታገናኘው
ድረስ በትዕግስት ማጣት መሬቱን በጫማው ይጠበጥባል፡፡ ኔላ ትዝ
አለችው፤ ፀጉረ ረጅም፣ ጨረቃ ፊትና ሩህሩህ፡፡

‹‹ሄሎ›› አለች ኔላ፡፡
‹‹ኄላ እንደምነሽ?››
‹‹እንዴት ነህ ኤዲ? የት ነህ ያለኸው?››
‹‹ከእንግሊዝ አገር ነው የምደውለው‥ ኔላ ስቲቭ የት ነው ያለው?››
‹‹ከእንግሊዝ! ወይ ጉድ! ስቲቭ አሁን ካምፕ የለም፤ ምነው ችግር አለ
እንዴ?››
‹‹አይ፤ በስንት ሰዓት ይመጣል?››
‹‹ዛሬ ጧት ምናልባት አንድ ሰዓት ላይ፡፡ ኤዲ ድምፅህ አንድ ችግር እንደገጠመህ ያመለክታል፤ ምንድነው እሱ?››
‹‹ሲመለስ ይደውልልኝ›› አለና የሆቴሉን ስልክ ሰጣት፡፡
‹‹ኤዲ ምን ችግር እንደገጠመህ አትነግረኝም?››
‹‹አልችልም፧ ሲመጣ እንዲደውልልኝ ንገሪው፤ ለበረራ አንድ ሰዓት
ብቻ ነው የሚቀረኝ፤ ከዚያ በኋላ ወደ ኒውዮርክ እበራለሁ››

‹‹እንዳልክ›› አለች ኔላ፤ ‹ካሮል አን እንዴት ነች?

‹‹ሄድኩኝ ኔላ ቻው›› አለና ምላሿን ሳይጠብቅ ስልኩን ዘጋ፡፡ አነጋሩ ስርዓት የጎደለው መሆኑን ያውቃል፡፡ ነገር ግን ከዚያ በላይ የሚያስጨንቀው ነገር ስላለ ግድ አልሰጠውም:፡ ሆዱ በጭንቀት ተወጥሯል፡

የሚያደርገው ቢያጣ ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡ ስልኩ ሲጮህ እንዲስማው በሩን
ገርበብ አድርጎ ትቶ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ፡፡ ትልቅ ከሆነ ወዲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓይኑ በእምባ ተሞላ፡፡ ራሱን ሁለት እጆቹ ውስጥ ወሽቆ እንግዲህ ምንድነው የሚደረገው?› አለ፡፡

ከሰባት ዓመት በፊት አትላንቲክ ውቅያኖስን ለብቻው በርሮ ያቋረጠው
የሊንድበርግ ልጅ እገታ ትዝ አለው፡፡ በዚያ ጊዜ ጋዜጣው በሙሉ
የሚያወራው ይህንኑ ነበር፡፡ አጋቾቹ የጠየቁት
አልፈጸም ሲላቸው
የሊንድበርግን ልጅ ገድለው ጣሉት፡፡ ‹አምላኬ ካሮል አንን ጠብቃት› አለ።

አሁን አሁን ጸልዮ አያውቅም፡፡ ጸሎት ለአባትና ለእናቱ ምንም
አልፈየደላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ይረዳል ብሎ አያምንም፡፡ በዚህም ጊዜ ወደ ሃይማኖት መመለስ አይፈልግም፡፡ አንድ ነገር ነው ማድረግ ያለበት፡፡

ካሮል አንን ያገቷት ሰዎች ኤዲ አይሮፕላኑ ላይ እንዲገኝላቸው ይፈልጋሉ፡ ይህን ያህል አረጋግጧል፡፡ ምናልባትም ዛሬ አይሮፕላኑ ላይ እንዳይሳፈር ይሄ በቂ ምክንያት ሊሆን ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን እሱ
አይሮፕላኑ ውስጥ ከሌለ ቶም ሉተርን ስለማያገኘው ሰዎቹ ምን እንደፈለጉ
ሊያውቅ አይችልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሁኔታው ከእሱ ቁጥጥር ውጭ
ይሆናል፡

ትንሿ ሻንጣ ውስጥ ጢም መላጫውን፣ ፒጃማውንና ሳሙና ከተተ ጸጉሩን ሲያበጥር ልቡ ካሮል አን ጋር ነበር፡፡

ስልኩ አቃጨለ፡፡
ፈጠን ብሎ ከክፍሉ ወጣ፡ ደረጃውን በሩጫ ወረደና ስልኩጋ ደረሰ ነገር ግን ሌላ ሰው ይዞታል፡፡ በንዴት ተመለሰ፡፡

የሆኑ ሰዎች ሚስቱን አግተዋታል፤ ኤዲ ደግሞ የሚፈልጉትን ካደረገላቸው እሷን ማስለቀቅ ይችላል፡፡ ከዚህ ማጥ ውስጥ ማንም
የሚያወጣው የለም፡፡

የተለያት ቀን ተጣልተው እንደነበር ሲያስበው ልቡ በሃዘን ተሰበረ ይህ ደግሞ ዕድሜ ልኩን ሲጸጽተው ይኖራል፡፡ ምን ነበር የዚያን ቀን ያጣላቸው?› ከዚህ በኋላ ከእሷጋ አይጣላም፡፡ ብቻ ደህና ትመለስ፡፡

ይሄ የተረገመ ስልክ ለምን አይጮህም?›
በሩ ተንኳኳና ሚኪ የበረራ ዩኒፎርሙን ለብሶ ሻንጣውን ይዞ ገባ፡፡
‹‹ተዘጋጅተሃል?›› ሲል ጠየቀው
ኤዲ ብርክ ያዘው፡፡ ‹‹ሰዓት ደረሰ እንዴ?››
‹‹ደርሷል››
‹‹ምን አይነት ነገር ነው!››
‹‹ምን ሆነሃል? እዚህ መሆን ፈለግህ? እዚህ ሆነህ ጀርመኖችን ልትዋጋ ነው?›› ሲል ቀለደበት፡፡
👍201👏1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ደልቲ ገልዲ በካርለት ባህል አፍራሽነት ቆሽቱ አርሮ የነበረውን ያህል አሁን ግን አእምሮው መዝናናት ጀምሯል" መቼም እሱ
የያዘው ነገር መስተካከሉ የማይቀር በመሆኑ እንግዳዋ እሱን መቅረብ
ከጀመረችና ግንኙነት ካደረጉ በኋላ ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋን አወላልቃ ጥላ ቆዳ መልበሷ፣ በባዶ እግሯ ካለ ጫማ መሄዷ፣ እንደ
ሐመር ልጃገረዶች ጸጕሯን አሳጥራ በጨሌና አምባር ማጌጥ መጀመሯ፣ እሱን ፍርሃት እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት እንደማይኖራት ስለ ተገነዘበ ደስታ እየተሰማው፣ «ኧረ ገና ይቀራታል» ብሎ
ፎክሮባታል።

ካርለት የከሎ ሆራ ከብት ዘለላ ወቅት ከልጃገረዶች መሃል ሆና አንጋዞች ሲገርፏት ግርፊያውን ፈርታ ስትንቀጠቀጥ የነበረውንና
ከተገረፈችም በኋሳ የጮኸችውን ደልቲ ገልዲ ሰምቶ ሐፍረት
ተሰምቶቷል፣ «ባለጌ! ልጃገረድ እንዴት ለግርፋት ትንቀጠቀጣለች? ...ቆይ ብቻ ልክ ሳላገባት ከቀረሁማ እኔ አይደለሁም! እያለ ተማሮባታል"

ደልቲ ገልዲ የእንግዳዋ ልጃገረድ አቀራረብ ልቡን የሚያራራ ሆኖ ቢያገኘውም፣ የሐመር ልጃገረዶች የሚያሟሉትን ባህላዊ ደንብ
ባለማሟላቷ ግን ቅር መሰኘቱ አለቀረም" ደልቲ መቼም አንዴ ከአፉ
አውጥቶ ሊያገባት በመወሰኑ እንጂ ልቡ ያለው ከሌላ ልጃገረድ ጋር
ነው። ያችን ልጃገረድ ሊያገባትና የግሉ ሊያደርጋት ቢችል ኖሮ
መቼም በሕይወቱ ቀረኝ የሚለው ነገር ባልነበረም ነበር። ግን ልጃገረዷን ሊያገባት አይችልም" አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ የልጅቷ
እናት የካርላ ጎሳ አባል ናት። እሱም ከዚሁ ቤተሰብ ነው። የካርላ ጎሳ የጉለትን ጎሳ ሊያገባ ይችላል" የካርላ ጎሳ የካርላን ጎሳ፣ የጉለት ጎሳ የጉለትን ጎሳ ግን ሊያገባ አይችልም" ሊጋቡ የሚችሉት ፀንጋዞች
(ባዕዳን) ብቻ ናቸው" ይህም ሆኖ ግን ደልቲ ሊያገባት ባይችልም
ሊወሽማት ይችላልI ችሏልም" ጉድ የሚፈላው ግን ባል አግብታ የሄደች እንደሆነ ነው።

ባል እንዳታገባ ደግሞ ሊያግዳት አይችልም" ይህን ላድረግ ካለ አባትየው አይቀበለውም" አባቷ ከልጁ ባል ጥሎሽ ማግኘት አለበት" ጥሎሹን ካገኘ ደግሞ የሷ ጉዳይ «ጉም መዝገን» መሆኑ ነው።
በእርግጥ ደልቲ ሌላ ባል መጥቶ ከሚወስዳት እጥፍ የሆነ ጥሎሽ ከፍሎ ሊወስዳት ይችል ነበር። ችግሩ ግን ይህ አልነበረም፤ የሱ ችግር እሷና እሱ የአንድ ጎሳ አባል በመሆናቸው ጋብቻ ሊፈጽሙ አለመቻላቸው ነው። ከሎ ሆራ ግን የጉለት ጎሳ በመሆኑና ጎይቲ
አንተነህ የካርላ ጎሳ በመሆኗ ሁለቱ ፀንጋዞች (ባዕዳን) ስለሆኑ መጋባት
ይችላሉ።

ጎይቲ አንተነህም እንደ ደልቲ ገልዲ በውኗ መቃዠቷ አልቀረም። ብዙ ወንዶች ታውቃለች፤ እንደሱ ግን ልቧን የሰረቀባት
ወንድ የለም" መጀመሪያም ቢሆን ከእሱ ጋር አካል ለአካል ከመነካካታቸው በፊት የወሮን መንደር ኗሪ እንደ አውሎ ነፋስ
በነፈሰው ወሬ የደልቲ ገልዲ ጀግንነት እየተወራ፣ ዘፈኑና ሙገሳው ሲቀልጥ፣ በዝናው በእጅጉ መጐምዠቷ አልቀረም
ከልጅነቷ ጀምሮ ከአባቷ እየሰማች ያደገችው የጀግንነት ታሪክ፣
ጀግንነት ውሎ፣ የጀግንነት ሞት ነው" ስለዚህ፣ ጀግና ትወዳለች፣ ገዳይ ታከብራለች" በየወንዙና በየእንጨት ለቀማው፣ ማንነቱን ገና ያላወቀችውን ጀግና ስም በሐመር ጫካና ተራራ ድምፅዋ እያስተጋባ
ዘፍናለታለች" ከልጃገረዶች ጋርም ገና ሳያዩት እየተሣሣቁ፣ «የኔ
ነው የኔ ነው» ተባብለው ተነታርከውበታል"

ጎይቲ አንተነህ ይህን ሰው የምትወደውና የምታደንቀው ከልቧ
ነበር። የሌሎችን ልጃገረዶች እውነተኛ ስሜት ግን አታውቅም። ያ ሰው ግን እንዲያ በቀላሉ ሊከሰትላትና ልታየው አልቻለችም"

አንድ ቀን ከሌሎች ልጃገረዶች ጋር ገበያ ውላ ስትመስ ግን ከወንዶች መሃል ሳዳጉራውን (ሽርጡን) ለብሶ፣ በላዩ ላይ ዝናር የታጠቀ፣ በአንገቱ ልጃገረዶች የሸለሙትን ጨሌ ለማስታወሻ አጥልቆ፣ ክናዱ ላይ አንባር፣ ጣቱ ላይ ደግሞ የመዳብ ቀለበት ያጠለቀ፣ ጸጕሩን በባህሉ መሠረት ተሠርቶ የሰጎን ላባ የሻጠ ሸበላ ላይ ልጃገረዶች ሲጠቋቆሙ፣ «ይእ! ምንድን ነው? ማነው?» ብላ
ጠየቀች  ጎይቲ። ልጃገረዶች «ይእ! አታውቂውም ማለት ነው? »
ተሣሣቁባት አፈረችና፣ «በቃ አላወቅሁትም ንገሩኝ» አለቻቸው
“ደለቲ ገልዲን ነው የማታውቂው? ይልቅስ አታሹፊብን» አሏት።

ያን ሁሌ የምታልመውን ሰው፣ እንዲህ እንደ ዘበት አይታው ልታልፍ፣ «እሱ ነው ለካ፣ አፈር በሆንኩት!» አለች ጎይቲ፣ ለምን
እንደዚያ እንዳለች ግን አልገባትም። «አሁን ይሄ እውነት ሰው ነው?
አቤት ውበት! አቤት ቁመና!» በማለት አፏን ከፍታ ማየቷን ቀጠለች" ጓደኞቿ እርስ በርስ እየተጨዋወቱ፣ እሷም አብራ ያለች መስሏቸው የተለመደ የወሬ ፍትፍታቸውን መጐራረስ ቀጠሉ።

«እከሌን ታውቂዋለሽ? »
«ይእ! እንዴት ነው ታውቂዋለሽ?»
«ግንኙነት አላችሁ? »
«አዎና!»
«አንችስ? »
«እኔም አዎን አውቀዋለሁ።» ይሣሣቃሉ። ደግሞ እንደገና
ሌላውን ይጠያየቃሉ። መቼም በሐመር ልጃገረዶች አንድ ላንድ ብቻ መወሰን ጥላቻንም ሊፈጥር ይችላል። የኔይቱ ቆንጆ ባትሆን ነው፣የኔው ቆንጆ ባይሆን ነው፣ ሌላው (ሌላይቱ) ያልፈለገው (ያልፈለገችው) ስለሚባባሉ መራራቅ በመሃላቸው ሊፈጠር ይችላል" በሐመር
ማኅበረሰብ ፍቅር ነፃ ጨረታ ነው" የጨረታው ዕጣ ግን በሴቷ ፍላጎት
ይወሰናል" ስለዚህ አንዲት ልጃገረድ ለብዙ ወንዶች፣ ብዙ ልጃገረዶች በአጠቃላይ ለመንደሩ ጐረምሶች ይሆኑና መቃበጥ ነው።

ጎይቲ አንተነህ ከልጃገረዶች ተለይታ ደልቲ ገልዲን እንደ
ተአምር ስትመለከት፣ ጓደኞቿን ረሳቻቸው ደልቲ ገልዲ ይህ ሁሉ ሲሆን አላያትም ነበር፤ በኋላ ግን ድንገት ዓይኑን ወርወር ሲያደርግ ዓይኗን ቀድሞ ተመለከተው አያት፤ አየችው፤ እንደገና አያት፣
እሷም አየችው። ብዙ ከቆዩ በኋላ ለሰላምታ አንገቱን አወዛወዘሳት"እሷም አጸፋውን መለሰች።

በሐመር ባህል ሰላምታ ከዕረፍት በኋላ ነው። ወዳጅም ሆነ ዘመድ
ድንገት ሲገናኝ ሮጦ አይተቃቀፍም፤ ሰላምታ አይለዋወጥም"
የሚደረገው ራቅ ራቅ ብሎ መቀጥ ወይንም መቆም ነው።ከሩቅ አካባቢ የመጣ ከሆነ እንዲያውም ካለምንም የቃል ልውውጥ ቁርቀት ይነጠፍለትና ለመቀመጫም፣ ለትራስም የሚገለገልበትን በርኮታ
ተንተርሶ ይተኛና ዕረፍት ይወስዳል። በሐመር ማኅበረሰብ መንቀዥቀዥ፣ መዘባረቅ የለም። ሁሉም የሚፈጸመው በሥርዓት ነው።

ስለዚህ እንግዳው፣ «እንደምን ናችሁ?» ይላል።
«ደህና ነን፤ እናንተስ እንደምን ናችሁ?» ይላል አባወራው ወይንም የቤተሰቡ አባል።

«ደህና ነን። ከብቶችስ ደህና ናቸው? » እንግዳው ደግሞ
ይጠይቃል።

«ደህና ናቸው። የእናንተስ?»
«ደህና ናቸው።»

«የአባካቢያችሁ ሰላምስ እንዴት ነው?»

«ደህና ነው" እናንተስ ዘንድ?»እየተባባሉ ጨዋታቸውን በሥርዓትና በእርጋታ ይቀጥላሉ እንጂ አፍ እንዳመጣ መዘላበድና
«ሲበሉ እንደላኩት» ያንንም ይህንንም ያዝ ለቀቅ ማድረግ የለም።ከዚያ በኋላ የሚበላ ይቀርብና ሚስት ለብቻዋ ወይንም ከልጆች ጋር፣ባለቤቷና እንግዳውም ለየብቻቸው ቤት ያፈራውን ይቀማምሳሉ።
👍243
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ቀኑ ቅዳሜ ነው። ሴቬሊያ ከተማ ላይ አንዣቦ የከረመው ዳመና ተበታትኖ ሰማያዊው ሰማይ በፀሐይ ብርሃን ተጥለቅልቆ ኗሪው በደስታ ሲንቀሳቀስ ይታያል።
ሶራ ከመኝው የተነሳው ዘግየት ብሎ ሲሆን ከመኝታው ተነስቶ ሳሎኑ ሲገባ አብረውት የሚኖሩት ሁለቱ የክፍል ጓደኞቹ
ሞዛምቢካዊው ኢናሲዬ እና ሴኔጋላው ዲያንካ ሲከራከሩ አገኛቸው:

“...አየህ የኛ የአፍሪካውያን ችግር በእለት ችግሮቻችን ላይ ካልሆነ በህልማችን በሐሳባችን... ላይ በትዕግስት መወያየት
መከራከር አንችልም: በግልፍተኝነት ስለ ዛሬ እናወራለን ዛሬ በምንፈፅመው እናዝናለን ወይንም እንረካለን።

ዛሬን ከትናንትና ከነገ ጋር ማነፃፀር ስለማንችል መቻቻሉም ያቅተናል: እና እኛ አፍሪውያን ከጊዜ የቁም እስር እራሳችንን ነፃ
አድርገን ጊዜን መጠቀም ስንጀምር! ሽንፈትና ድልን ልዩነቱን ስናውቅ በቅድሚያ ችግሮቻችንን እንፈታለን…” አለ ሞዛምቢካዊው
ኢናሲዬ:

“…በሃሣብህ እኮ እስማማለሁ፡ ችግሩ ግን እንደ ቡችላ ያለው አይናችንን ለመክፈት ገና ስናስብ  የሰለጠኑት ህዝቦች ባለፉት ጊዜያት ከተጠቀሙበት መሳሪያ በተሻለና በረከሰ የረቀቀ መረብ እየጠለፉ ይጥሉናል: ለዚህ መፍትሄው ምን
ይሁን ነው? እኛ ፊደል እንዴት እንቁጠር ስንል አንዱ እርስ በራሳችን እንማማር ሌላው  የሰለጠኑት ህዝቦች እንዲያስተምሩን
እንለምን... ሲል ጊዜያት ከነፉ፤ የጥቁር ህዝብ ህልም እንደ
ኪሊማንጃሮ ተራራ ቢከመር ጠብታ ተግባር ካልወጣው! አንዱ ሌላውን ወንድሙን ገሉ ማቅራራቱንና መፎከሩን ካላቆምንና ራሳችንን መግዛት ካቃተን ጥሩ ተገዥ መሆን ይሻለናል” ብሎ
የምፀት ሳቁን ሳቀ  ሁለቱም ተሳሳቁ፡

“ጥሩ! ማን በማን ላይ እንደሳቀ ዳኝነቱን ወደፊት
እስከገልፅ አንዴ ይቅርታ ይደረግልኝ..."

“ሶራ!  ሁለቱም እንደተመካከሩ ሀሉ በአድናቆት ዞረው
ጠሩትና

ዛሬ ምነው ምሽግን አለቅም ብለህ ዋልህ?  ያች ኢትዬ
ስፔናዊት የምትሰራው የቤት ስራም ሰጥታህ
ነበር መሰል ሞዛምቢካዊው ኢናሊዬ የጓደኛውን ጉልበት  መታ አድርጎ ቤቱን
ለሁለት በሣቅ አነቃነቁት።

ከባድ የቤት ሥራ ነበር የሰጠችኝ፡ ጥያቄዋን ሽ ጊዜ አነበብኩት በቃሌ  አነበብኩት! መልሱ ግን ጠፋኝ። ጥያቄዋን
ካለእሷ ሊመልሰው የሚችል የለም:"

“ስለዚህ መልሱን ከመምህርት ኢትዮ ስፔናዊት ለማግኘት
ልትሄድ ነዋ!” ነዋ!

ቶሉ መሄድ! የጠፋኝን ቶሉ ማወቅ ከዚያ ጎበዝ
ደቀ መዝሙሯ መሆን እፈልጋለሁ።” የሁለቱንም ትከሻ መታ መ+ አድርጎ። ወደ ውስጥ ገብቶ ለባብሶ ወጣና፡-

“አጭርና ያልተንዛዛ  አስተያየት አላማረብኝም አላቸዎሸ በየተራ እያያቸው።

“መልሱን ካለ  አንድ ሰው አይመልሰውም" ሲል ዲያንካ

“እሷም መምህርት ኢትዮ ስፔናዊት ብቻ ናት..." አለ ኢናልዬ

“ትክክል!'' ብሎ የኢናሲዬን ትከሻ መታ መታ አድርጎ በሩን ከፍቶ ሲወጣ ሳቃቸው ከኋላው ተከተለው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሶራና ኮንችት ከተዋወቁ በኋላ ኮንችት ቤት ማድሪድ
በሚገኘው ፒካሶ ሆቴል... ደጋግመው ተገናኝተዋል። ኮንችት በሶራ ግልፅነት በጎደለው ይሉኝታ በተበተበው ባህሪው ብዙ ጊዜ ትበሽቃለች።

ሶራ መብላት ትፈልጋለህ?" ስትለው

“አንችስ?” ሲላት በብስጭት

"እፈልጋለሁ! ወይንም አልፈልግም። ስለእኔ እኔ ስለአንተ ደግሞ አንተ መመለስ በቃ። የአንተ መፈለግ አለመፈለግ ከእኔ ጋር ምን አገናኘው" ትለዋለች

“የዛሬ ግብዣ የኔ ነው"

“ጥሩ ስለግብዣ ሃሳብህ  አመሰግንሃለሁ። የት ነው የምትጋብዘኝ?

“የት ልጋብዝሽ?”
“ኦ! - አምላኬ!” በንዴት ትጦፍና፦

“ሰውን ልትጋብዝ ስትፈልግ በቅድሚያ የት ምን
እንደምትጋብዘው አስብ እሽ ፊቷ በንዴት እንደቀላ ትነግረዋለች

“ምነው ዝም አልሽ?

“ለምን ጠየቅከኝ?

“ስለማትጫወቺ ስለማትስቂ...”

"ሰው ቤት ከመሄድህ በፊት ልትገናኙ መቻል አለመቻላችሁን ደውለህ ፈቃድ ጠይቅ ! እኛ ሰዎች ለስራ ለጨዋታ
ለእረፍት... የምንመድበው ጊዜ አለ:: ሰዎችን በፕርግራማቸው
እንዳይጠቀሙ እንቅፋት መሆን ትልቅ ሃጢያት ነው: ገባህ!” ትለዋለች።

“የያዝሽውን እቃ ልያዝልሽ?

“ለምን?

“ይከብድሻል…”

“ፖልፋቮር /ይቅርታ/ እኔ ጡጦ የምታጠባው ህፃን ልጅህ አይደለሁም የሚከብደኝን መጀመሪያውንም አልይዝም።እሺ
በንዴት ትንጨረጨርበታለች ሶራ ባህሪዋ ሙልጭልጭ ይልበታል ሲያዝንላት ሲንከባከባት ሲሞክርና እንዲቀራረቡ ጥረት ሲያደርግ? አባባሉን በተቃራኒ ተረድታ በግሳፄ የህሊና ድዱን በርግጫ
ታወልቀዋለች:

እሱ ግን ይችላታል: ሆዱ እየተቀየመ አንደበቱ ግን
ያልፋታል።

“ዲስኮ ዳንስ ቤት ብዙ መቆየት አልወድም"

“ሶራ!  ከኔ ጋር ግን'ኮ አብረህ…"

“ላስከፋሽ ስላልፈለግሁ"

“እብድ ነህ! የማትፈልገውን ለኔ ብለህ የምታደርግ?”

“ብቻሽን ትቼሽ መሄድ ስላልፈለግሁ"

“በቃህ አንተ ኖርህ አልኖር ለኔ ለውጥ የለውም 7
ገባህ! መዝናናት ስፈልግ ዘበኛ አላስከትልም: ማንንም ካለፍላጎቱ እንደ
ከዘራ ቆልምሜ የኔ ምርኩዝ ማድረግ አልሻም.." ታፈጥበታለች።

አብሯት ለመሆን እንደሚጓጓው ሁሉ ከሷ መለየቱንም ይፈልገዋል: ልዩነታቸው ብዙ ነው።

ኮንችት ባህሪው ግልፅ
ነው ሣቋን አንደ ጥሩ ሙዚቃ በስሜት ይደንስበታል: ችግሩ ድንገት እሳት ወዲያው ውሃ
ትሆንበታለች:: እሳት ስትሆን ሊሸሻት ይፈልጋል! ውሃ ስትሆን ደግሞ እንደ ፀበል በጨዋታዋ ይጠመቃል!

ሶራ ሜዳ ይሁን ገደል ስሜቱ በደመ ነፍሱ ሲጋልብም እሷ
ለሁሉም ነገር ምክንያት ትፈልጋለች: እየተሞላቀቀች

ጭኖችዋን ፓንቷን.. ስታሳየውና ጉሮሮውን ስታስጮህበት ስሜቱን
ስታስነጥስበት ትቆይና መላውን ሳትለው ድንገት

“መተኛት እፈልጋለሁ" ትለዋለች።

ትንሽ አንጫወትም?"

...የሰው ፍላጎት ሊገባህ ይገባል እሽ?" ቀልቡን ገፋበት መኝታ ቤቷ ትገባለች። እሱም ወጥቶ ይሄዳል። ቤቱ ሲሄድ ግን
ህሊናው እረፍት ሲነሳው ሰውነቱ እንደ እሳት ሲቀጣጠልበት
መታጠቢያ ቤት ይገባና ቀዝቃዛ ሻወር ገላው ላይ ያፈሳል፡ ለአያቷ
አገር ለኢትዮጵያ ያላት ናፍቆት ግልፅነቷ ሳቋ… ተክለ ቁመናዋ
እያወዛወዘው ሲያንጨዋልለው ፍላጎቱ  ለእሷ ያለው ቀረቤታ
ከጓደኝነት ያለፈ ይሆንበታል።

ኮንችት ደጋግማ
የነገረችው ስሜትህንና ፍላጎትህን አትደብቅ ነው። ስለዚህ እየዋለ ባደረ ቁጥር ናፍቆቱ ጤና ሲነሳው
ስሜቱን ሊገልፅላት አሰበ: ድፍረቱና አጋጣሚው ጠፍቶ ለቀናት ተሰቃዩ:: አንድ ቀን ግን ደፈረ:

“ኮንችት?”

“አቤት" ያ እንደ ንስር አይን ተልቆ የሚበረበረው አይኗ
ከመናገሩ በፊት እየበሳሳው ውስጠ ሚስጥሩን አየበት።

“አፈቅርሻለሁ አላት ባጭሩ። ኮንችት ግን ይህን ስሜቱንና አባባሉን ቀደም ብላ እንደተረዳች ሀሉ፡

“ለምን አፈቀርኸኝ? በአባባሉ ሳትደነቅ ጠየቀችው

ተቁነጠነጠ! ግልጽ ሁን ብላ ወትውታ ግልፅ ሲሆን ደግሞ ዓለምን ያስጨነቀ ጥያቄ “ለምን?" እያለች በማስቸገሯ ተማረረባት።

ለምን አፈቀርኝ? ደግማ ጠየቀችው

“አስተሳሰብሽ ደስ ይለኛል” አንገቱ ላይ እንደቆሙበት ውሻ አይኑ እየተቁለጨለጨ መለሰላት።

“አስተሳሰቤን ገና መች ተረዳኸው። እኔ የማስበው ለአንተ እንግዳ ነው: የአንተ ደግሞ ለእኔ እንዲሁ አይገባኝም። ታዲያ
ሳንግባባ እንዴት አስተሳሰቤን አውቀህ አፈቀርኸኝ:"

“የምልሽ  ፀባይሽም ደስ ይለኛል"

“ፀባዬ ምን አይነት ነው?"

“ግልፅ

“ፀባዬን እንዳልወደድኸው ግን ብዙ ምልክቶች አይቸብሃለሁ

"ቁመናሽ ደስ ይለኛል..."

“አንድን ሰው በማፍቀርና በመፈለግ መካከል ያለውን ልይነት ግን ታውቃለህ?"
👍28👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_አስራ_አራት

/////

እለተ እሁድ ነው፡፡ረፋድ ላይ ቁርሴን ከበላሁ በኃላ ወደአልገዬ ተመልሼ ልጄ የላከችልኝን የእናቷን ማስታወሻ በተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡ይሄ ታሪክ የአፈላነት ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡ትኩስ ወጣት ሆነን የኖርነው፡፡ወጣትነት ውስጥ የሚንፎለፎል ኃይል አለ።"ልክ የኒዩክሌር ኃይል አይነት።ወደማብራት ኃይል ተቀይሮ ልማትን ሚያሳልጥ...ወደአውዳሚ ቦንብ ተቀይሮ   ለጦርነት ውሎ ከተማን የሚያፈርስ  ወጣትነት ከተራራ የሚገዝፍ ነገሮችን የማድረግ ጉጉት እና   ሳይታክቱ የመሞከር ትጋት ..ቢወድቁ በፍጥነት ተነስቶ የመቆም ፅናት፡፡ አዎ  ከሰው ልጅ የዕድሜ እርከኖች ጎልደን ኤጅ የሚባለው ነው ወጣትነት፡፡ ህፃንነትና ታዳጊነት ከኃላው ትቶ ጎልማሳነትና አዛውንትነትን ከፊቱ አስቀምጦ  ከህይወት ዘንግ የመሀል አንጓ ላይ ያለ በዕንቁ  ያሸበረበቀ ጌጥ ነው።

ወጣትነት ውበት በመጨረሻው እንጥፍጣፊ አቅሙ የሚጎመራበት ስሜት ክላይማክሱን ገጭቶ የሚንፎለልበት የአበባነት እድሜ ነው።የፍቅር  ኮንሰርት ቢዘጋጅ የዳንሱን መድረክ የሚሞላው ወጣት ነው...የጦርነት ነጋሪት ቢመታ ለመስዋዕትነት ግር ብሎ የጦር ካንፑን የሚያጨናንቀው ወጣት ነው።አብዬት አንስቶ ከተማውን በድንጋይ አጥሮ አስፓልቱን በጎማ ጭስ የሚያጥነው ወጣት ነው....ለድጋፍ ሰልፍ ቲሸርትና ኬፕ ገድግዶ ጎዳናውን በመፈክርና  በባንዲራ የሚያጣብበውም ያው ወጣት ነው። በቀደድለት ቦይ የሚፈስ ፤ባሳዩት መንገድ የሚነጉድ ወጣት ነው።ቤተ እምነቱ የሚሻማው ቤተመንግስቱም የሚፈራው ያው ወጣት ነው...፡፡ ወጣት ሆነህ ጥበብ  ቀድሞ ከበራልህ ቤተእምነትም ሆነ ቤተመንግስት  አያታልሉህም....፡፡ፓለቲከኛው በስሜትህ ጢባጢብ አይጫወትብህም ...፡፡አዎ የነቃህ ወጣት ከሆንክ  ለእሱ ወደስልጣን ማማ መስፈንጠሪያ እስፕሪንጉ ለመሆን በምንም አይነት ሁኔታ ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም" ግን ወጣትነት በብዙ ችኮላ ፤ፋታ በማይሰጥ ጉጉት፤ ስር ባልሰደደ ዕውቀትና ልምድ የሚጓዝ በመሆኑ ከስህተት ሊፀዳ አይችልም፡፡እርግጥ ሙሉ የሰው ልጅ ከስህተት ጋር የእድሜ ልክ ትስስር አለው…ወጣትነት ላይ ግን  ይለያል..እኔም እንደአብዛኛው ሰው ህይወቴን ያጨመላለቅኩት በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በሰራሁት ስህተት ነው፡፡ውይ እስቲ መዘበራረቁን

ገታ አድርጌ እጄ ላይ አንከርፍፌ የያዝኩትን ከሪች ማስታወሻ ፎቶ ተንስቶ በልጄ አማካይነት በቴሌግራም የተላከልኝን ቀጣይ ታሪክ ላንብብላችሁ፡፡

ሰኔ 5 2008 ዓ.ም
11 ኛ ክፍል ሆነን ነው፡፡ማታ 11 ሰዓት ሆኖ ከትምህርት ቤት ከገባን በኃላ በምን ሰዓት በየት እንደሄደ ሳላውቅ እዬብ ከቤት ወጥቶ ጠፋ..ሰፈር ዞር ዞር ብዬ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም.ግራ ገባኝ…ማታ እራት ሰአት ላይም ተመልሶ አልመጣም.. እነእማዬ ሲጠይቁኝ ጓዳኛዬ ጋ አብረን እናጠናለን ሲል ሰምቼለሁ ብዬ ዋሸሁ…የቤቱ ሰው ሁሉ ከተኛ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ የክፍላችን መስኮት ከፈትኩለት.ዘሎ ገባ፡፡

‹‹እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?››

‹አፈር ብላ…ዝም ብለህ ከቤት ወጥተህ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ትቆያለህ?››

‹‹የእኔ ውድ እህት …አሳስብኩሽ እንዴ ..?

ድንገተኛ በረከት አጋጥሞኝ ነው፡፡››

‹‹የምን በረከት ነው?››

‹‹ባክሽ ሶፊያ ጋር ነበርኩ››
አቤት የደነገጥኩት
ድንጋጤ‹‹ሶፊያ የት? .ለምን?.ከእሷ ጋር ምን አባህ ትሰራለህ?››

ተንሰረዘረኩበት ፤አዎ ሶፊያን በደንብ አውቃታለሁ...አረ እንደውም. የክፍላችን ልጅና ለእኔም ጓደኛዬ ነች..የተበሳጨሁበት ጉዳይ ግን ወደጎን ነው፡፡ሶፊያ እዬብዬን በጣም እንደምትወደው አውቃለሁ፡፡.ማለት እንደምታፈቅረው አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ ደጋግማ ‹ወንድምሽን አፈቅረዋለሁ› …ብላ ነግራኝ ፊት ነስቻታለሁ፡፡እንደዛ ስትለኝ የማቀርብላት ምክንያት ‹ወንድሜ ጎበዝ ተማሪ ነው..ያለጊዜው ፍቅር ምናምን እያልሽ እንድታዘናጊው አልፈልግም› የሚል ነበር››ዋናው ምክንያቴ ግን ያ አልነበረም…እዬብን ፍቅረኛም ሆነ ጓደኛ በሚል የብእር ስም አንድ ሴት መሀከላችን ገብታ እንድትሻማኝ አልፈልግም፡፡

‹‹እረጋ በይ እቤቷ ነበርን››አለኝ.በሚያበሳጭ የድምፅ ቃና..

‹ለመሆኑ እስከዚህን ሰአት እቤቷ ጎረምሳ ስታቆይ እቤተሰቦቾ ምንም አይሏትም?››

‹‹አታስቢ የእኔ እህት… ብቻዋን ነበረች››

‹‹ብቻዋን?››

‹‹አዎ ምነው ደነገጥሽ…ገጠር ሄደዋል… ብቻዋን ስለምታድር ነው የጠራቺኝ››
‹‹እና ምነው ብቻዋን ጥለኸት መጣህ ..የሆነ ነገር ቢያስደነግጣትስ…?አብረሀት አታድርም ነበር?››
‹‹እንኳን አድሬ ላመሸሁትም ሞቼልሻለሁ…አንቺ ጓደኛሽ እንዳንቺ መሰለችሽ.. አስጮኸችኝ እኮ››

‹እስጮኸችኝ ማለት…?መታህ ነው
አስደንግጣህ?››

‹‹አይ አንቺ ልጅ በቀላሉ አይገባሽም…ወሲብ ፈፀምን ….ወሲብ እንደዚህ እንደሚጥም ዛሬ በእሷ አወቅኩ፡፡››

‹ወሲብ .ወይኔ እቴትዬ…ወይ እግዚያብሄር ድረስ..ከተቀመጥኩበት አልጋ ተነሳሁ .እንባዬ አራት መስመር ሰርቶ በጉንጮቼ ላይ መፍሰስ ጀመረ…ወለሉ ላይ ተዘርፍጬ መሬቱን አሰስኩት..እዬቤ ያላሰበው ዱብ እዳ ነው የገጠመው...በጣም ግራ ገባውም በጣምም ደነገጠ.

‹‹አንዴ ምን ሆነሻል.?አረ ደምፅሽን ቀንሺ.እነቴቴ አንዲሰሙ ተፈልጊያለሽ እንዴ?›

‹‹አንተ እንዴት እንዲህ ትሰራለህ…?ምን ነክቶህ ነው?››

‹‹ምን ችግር አለው ?ይሄ እኮ ማንም ወጣት የሚሰራው ኖርማል ነገር ነው›

‹አይደለም እኔስ ወጣት አይደለሁ ለምን ሳልሰራሁም…?ለምን ቆይ?
‹‹እሱን እግዲህ እራስሽን መጠየቅ ነው››

‹‹አይደለም..በሽታውስ እንዴት እንዲህ እንዝላል ትሆናለህ.?.በዛ ላይ ብታረግዝብህስ…?ምን አባህ ልታደርግ ነው…ደግሞ ቤተክረስቲያን ይሄን ሁሉ ዘመን የተመላለስከው ለዚህ ነው፡፡ይሄ እኮ ዝሙት ነው..››

‹‹አረ በፈጠረሽ..እኔ ፀፀት እንዲሰማኝ ለማድረግ የሚያስቸልሽን አንድም ምክንያት እኮ አልቀረሽም..እኔ እኮ አስቤበት አልነበረም አሷ ጋር የሄድኩት..ድንገት ነው ሳናስበው ወደወሲብ የገባነው….ጥሩነቱ ግን እሷ ሁሉንም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችኝ.››

‹‹ሁሉንም ማለት?››

‹ኮንደም ነበራት..ልታረግዝ አትችልም አትፍሪ... በሽታውም እንደዛው…››

‹‹እሷማ አዎ እንደዛ ታደርጋለች …ልምድ ያላት ሸርሙጣ ነች፡፡እሺ የእግዚያብሄር ቃልን መጣሱስ? ዝሙቱስ?›
‹እሱን አንግዲህ አንዴ ተሳሳትኩ ወደኃላ መልሼ አልውጠው…ማድረግ የምችለው ንሰሀ መግባት ነው…እሱን አስብበታለሁ…አሁን እንተኛ ደክሞኛል አለኝና ልብሱን ፊቴ አወላልቆ ከውስጥ ገባና ከጭቅጭቄ ለማምለጥም ጭምር መሰለኝ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡
‹‹እኔማ ከሻርሙጣ ጋር አብሬ አልተኛም›› አልኩና አልጋ ልብሱን ከላዩ ገፍፌው ትራሴን ወሰድኩና ምንጣፍን ወለሉ ላይ ዘርግቼ ተኛሁ…ተነስቶ እንዲለምነኝ ፤ጉንጬን፤ ግንባሬን እየሳመ ይቅርታ እንዲጠየቀኝ…እቅፍ አድርጎ ፀጉሬን እያሻሸ ሁለተኛ አልመለስበትም ብሎ በስሜ እየማለ ቃል እንዲገባልኝ ፈልጌ ነበር….እሱ እቴ ዝም አለኝ….ደረቅ ወለል ላይ ብገላበጥ..እህህ ብል ምንም ጭራሽ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ ማንኮራፋት ጀመረ..
👍37
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በተለያየ ጊዜ ከሶስት ከሚበልጡ ወንዶች ጋር የመተሻሸት እና የመሳሳም አጋጣሚዎች አሳልፋለች። ከእነሱም መካከል አንድ መድህኔ ነው። ግን ከቃል ጋር ቁጭ ብሎ ማውራትን ያህል ንዝረቱ ለነፍሷ ተሰምቷት አያውቅም።ቃል አፈቅርሻለሁ ብሏት አያውቅም...እሷም እንደምታፈቅረው ነግራው አታውቅም። ሲገናኙ ፍቅር የወሬያቸው ዋና ማጠንጠኛ ሆኖ አያውቅም።
ግን ቃል ስለምንም ያውራ ስለምንም ወደእሷ አነጣጥሮ የሚረጨው ስውር ኃይል አለ..ሳታስበው ሙላት ይሰማታል... በሰውነቷ የሚለቀው ንዝረት ተርገብግቦ ተርገብግቦ ሲሰክን ከወሲብ እርካታ እጥፍ የሆነ ደስታን ይረጫል...ይሄ ልምድ ለእሷ ገራሚ ነው ።እናም ደግሞ ሱስ አስይዟታል።
….ብዙውን ጊዜ ከስራ ሲመለስ በራፍ ላይ መኪናዋን አቁማ ትጠብቀዋለች..ተከትላው ወደቤት ትገባና ሲጫወትና የባጥ የቆጡን ሲያወሩ ቆይተው ከምሽቱ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ላይ ወደቤቷ ትሄዳለች… አልያም መኪናዋ ውስጥ ታስገባውና ይዛው ወደ መሰላት ቦታ ወስደው እስከተቻላት ሰዓት ድረስ አብራው ትቆያለች.››
አሁን ያሉት ኢትዬጵያ ሆቴል ነው…ሰዓቱ 12፤40 ሆኗል ..መክሰስ ከበሉ በኃላ…ለስላሳ ነገር እየጠጡ ጫወታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ከብዙ ጫወታ በኃላ ድንገት አዲስ ርዕስ ከፈተች‹‹እና ጓደኛህን መች ነው ምታስተዋውቀኝ?››ፍቅረኛህን ለማለት ፈልጋ ነበር ግን ደግሞ ተናነቃት፡፡
‹‹እነግራትና የሚመቻትን ጊዜ ጠይቄ እነግርሻለሁ››አላት፡
‹‹አዎ አስተዋውቀን..እሷም መቼስ እንደአንተ አይነት ከሆነች የዕድሜ ልክ ጓደኛ ነው የማደርጋት››አለችው…በውስጧ ፍራቻና ንዴት እየተቀጣጠለ፡፡
‹‹እንደእኔማ እንዴት ልትሆን ትችላለች….?ደግሞ እንደእኔ አይነት ሌላ ምን ያደርግልሻል.. እኔው አለሁ አይደል?››አለት፡፡
‹‹እና አንተን የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ እንዳደርግ እየመከርከኝ ነው››አለችው በውስጧ ሌላ ምቀኝነት ተንኮል እያብሰለሰለች…፡፡
‹‹እንደእሱ ነገር..እሷን ደግሞ በራሷዋ ማንነት ትቀበያታለሽ ማለት ነው፡፡››
‹‹ግን ምንድነው የምትሰራው ..?ተማሪ ነች?››
‹‹አይ የመንግስት ሰራተኛ ነች….ውጭ ጉዳይ ውስጥ በፀሀፊነት ነው የምትሰራው››ደስ አለት….ለምን እንደሆነ ግን አታውቅም፡፡
‹‹አይ ጥሩ ነው..ታዲያ ስራ ካላት አኮ እስከአሁን መጋባት ነበረባችሁ…የዘመኑ ወንዶች መቼስ ጋብቻን እንደመቅሰፍት ነው የምትፈሩት..››
‹‹አይ እኔ አልፈራም..መጋባትም እፈልጋለሁ…እሷ ግን ?››ንግግሩን አንጠልጥሎ ተወው፡
‹‹እሷ ምን….?››መልሱን ለመስማት ተስገበበች፡
‹‹እሷ የልጅነት እቅድ ነበራት ..ገና ልጆች እያለን ምን አልባት እሷ የ13 እኔ ደግሞ የ14 አመት ታዳጊዎች ሳለን እንደማፈቅራት ነግሬያት ወደፊት እሷን አግብቼ መኖር እንደምፈልግ ነግሬያት ነበር››
‹‹ታዲያ እሷ ምን አለችህ…?እርግጠኛ ነኝ እሺ ነው የምትልህ›› አለችው..በምን ስሌት ነው እሺ እንደምትለው እርግጠኛ መሆን የቻለችው...?ልጅቷ ቀይ ትሁን ጥቁር….ቆንጆ ትሁን አስቀያሚ አታውቃትም፡፡ብቻ እኔ ብሆን በሚል እሳቤ መዝና ነው ሀሳቧን የሰነዘረችው፡፡ እሱም ለምን እንደዛ እንዳለች ገብቶታል፡፡
‹አዎ ግን በተለየ መልኩ ነው እሺ ያለቺኝ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹እንዴት?››
ብዙ አመት ወደኃላ ተመልሶ ትዝታውን ይተርክላት ጀመረ‹‹ያንን ጥያቄ ስጠይቃት ነገ መልስልሀለሁ ብላ ነበር በእለቱ የተለያየነው...በማግስቱ ወደቤተክርስቲያን ይዛኝ ሄደች.. ከዛ የእናቷ መቃብር ጋር ወሰደችኝ፡፡በጣም ነበር የደነገጥኩት.ይታይሽ በ14 አመት ከምትወጂያት ልጅ ጋር እናቷ መቃብር ስር ቁጭ ብለሽ ስለፍቅር ስታወሪ..…ግን ፍራቻዬን በውስጤ አፍኜ ያስቀመጠቺኝ ቦታ ቁጨ በማለት የምትለኝን በፅሞና መስማቴን ቀጠልኩ፡፡እና በወቅቱ እንዲህ ነበር ያለቺኝ፡፡‹‹….ይሄውልህ ቃል አኔም በጣም ነው የምወድህ ፤ማግባትም የምፈልገው አንተንና አንተን ብቻ ነው.. ግን ለእናቴ ቃል ገብቼላታለሁ…የእራሴ አሪፍ ቤት ሳይኖረኝ ባል ባገባ የአንቺን እናትነት እንደካድኩ ይቆጠርና እጥንትሽም ይውቀሰኝ ብዬ …ይሄንን ቃል ያስገባቺኝ ልትሞት በጣር ላይ በነበረቺበት በመጨረሻው ቀን ነው…እናም ከዛሬ ጀምሮ አንተም እንደምታፈቅረኝ እኔም እንደማፈቅርህ አውቀናል.. ዳግመኛ ሰለእዚህ ጉዳይ አንስተን የምናወራው ግን ከሁለት አንዳችን የግላችን የሆነ ቤት መስራት ወይም መግዛት የቻልን ጊዜ ብቻ ነው፡፡›አለችኝ፡፡
‹‹ካልቻላችሁስ?››
‹‹እኔም ይሄን ጥያቄ የዛኑ ቀን ነበር የጠየቅኳት.እሷ ግን ቆፍጠን ብላ ካልቻልን ምንም ማደረግ አንችልም… እንደተፋቀርን እንለያያለን ማለት ነው….ግን የግድ መቻል አለብን .እግዚያብሄርም ይረዳናል፡፡›› አለችኝ.፡፡
‹‹እና አንተም ተስማማህ?››
‹‹ይሄ እኮ የእሷ የማይሻር ውሳኔ ነው…የእኔ መስማማትና አለመስማማት ቦታ የለውም››
‹‹ቆይ ያልገባኝ እናተዬው እንደዛ አይነት ግራ የተጋባው ቃል ለምንድነው ያስገባቻት….ለዛውም ገና ለአቅመሄዋን እንኳን ባልደረሰችበት ዕድሜ ላይ›››
‹‹እናትዬውማ እንደዛ ያደረጉት እራሳቸው ከገጠማቸው የህይወት ገጠመኝ በመነሳት ይመስለኛል፡፡ የእሳቸው እጣ በልጃቸውም እንዳይደገም ከመፍራት የተነሳ…እናትዬው ከአባቷ ጋር ተፋቃቅረው በኪራይ ቤት ነበር የተጋቡት…ከዛ ቃል እና አንድ ታናሽ ወንድሟ ተወለዱ፤ቃል የአምስት አመት ወንድሟ የሁለት አመት እያሉ አባትዬው ድንገት ታሞ ይሞታል…ቤተሰቡ ሙሉ በሙሉ የሚተዳደሩት በአባትዬው ገቢ ስለነበር ከፍተኛ ችግር ላይ ይወድቃሉ.መጀመሪያ ተከራይተው ከሚኖሩበት ሶስት ክፍል ቤት ወደሁለት ክፍል፤ ከዛ ወደአንድ ክፍል እያሉ መጨረሻ በረንዳ እስከመውጣት ሁሉ ደርሰዋል ፡፡በዛ ስቃይ መካከል ነው ወንድሟና እናቷ በተከታታይ የሞቱት..እና እናትየው እንደሚያምኑት ቢያንስ አንደ ክፍል የራሳችን ቤት ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸውን የጉልበት ስራም ቢሆን በመስራት ማሳደግ የችሉ እንደነበረ ነው….እና ለዛ ነው ልጅቷንም በእሷቸው የደረሰ የልጆችን ስቃይ የማየት መከራ በእሷ እንዳይደርስ ከመፈለጋቸው የተነሳ በእንደዚህ አይነት ቃል ኪዳን ያሰሯት፡፡››
‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው?›፡ያለበትን አጣብቂኝ አሰበችና አሳዘናት፡፡ቢሆንም ግን ይሄንን ክፍተት ልትጠቀምበት እንደምትችል አሰበችና ፈገግ አለች፡

ይቀጥላል
👍13114🔥5🤔4👎1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ኬደሮን ከደሎ ወጥታ ሌላ ከተማ ስታይ ይሄ መጀመሪያ ገጠመኞ ነበር፡፡ትራንስፖርቱ አይሱዙ ጭነት መሆኑ በአካባቢው የተመደበ ትራንስፖርት ስለሆነ ነው፤ከመንገዱ አስቸጋሪነት የተነሳ ዋናው የትንስፖርት አይነቶች አይሱዙ ጭነት፤ኤፍ.ኤስ. አር ጭነት ፤ፒካፕ መኪና ሲሆን አልፎ አልፎ አይሱዙ ቅጥቅጥ ይገኛል...ከዛ ውጭ የተለመደው አይነት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስና ሎንቺን፤ብሎም ሚኒባስ ያንን መንገድ አያስቡትም፡፡አይደለም እነሱ እራሳቸው የአይሱዙ ሹፌሮቹ ቢሆንም እያንዳንዱን የመንገዷን ወጣ ገባና  ኩርባ፤ ዝቅታና ከፍታ አብጠርጥረው የሚያውቁ ሰለሆነ ነው የሚወጡት.እዛ መንገድ ላይ ለመሾፈር ቅድሚያ በረደትነት አራትና አምስት አመት ቀጥቅጦ ማገልገልገልና የመኪናውን ብቻ ሳይሆን የመንገዱንም ፀባይ አብጠርጥሮ  ማወቅ የሚጠይቅ የጀግና ስራ ነው፡፡

እና አይሱዚውን ከሞሉት ተሳፋሪዎች መካከል ሆነ እናቷ ያለበሰቻትን ወፍራም ጋቢ ተከናንባ እንደለበሰች  አይኖቾን ወደውጩ ወርውራ አንዴ በቀኝ ያለውን የመሬት ውበት ደግሞ በግራ ያለውን ጭው ያለ ገደል እየተመለከተች ስትደነቅ የሀንጋሶን ተራራ ጨርሰው የፓርኩን ክልል ሰንጥቀው አልፈው የሪራን መንደር ከሩቅ አሻግራ እያየች ጠመዝማዛውን ገደል እያወረዱ ሳለ ድንገት መኪናው ሰሌሜ ሰሌሜ እንደሚጨፍር የወላይታ የባህል ቡድን መዋዣቅ ሲጀምር ልክ እንደሸቀጥ ታጭቀው ተጭነው የነበሩ 26 የሚሆኑ ሰዎች በድንጋጤና ግራ በመጋባት መተረማመሰና መጮህ ጀመሩ….፡፡እንደምንም መኪናዋ እንደመስተካክል አለችና መንገዱን ይዛ ልትጠመዘዝ ስትል ቀኝ ጎማው ሳተና ወደገደሉ ተንሸራተተ… እመልሳለሁ ብሎ መሪውን ወደግራ ሲጠመዝዝ ሙሉ በሙሉ መንገዱን ሳተና የኋላውም ጓማ ወደገደሉ ተንጠለጠላ..ከዛ አምስት ሚሆኑ ሰዎች ከመኪና ዘለሉ .የተቀሩትም ለመዝል እየተሰናዱ ሳለ መኪናዋ ገደሉን ጥሳ ቁልቁል መጨረሻው በአይን እዚህ ላይ  ያቆማል ተብሎ ወደማይታየው ገደል መምዘግዘግ ጀመረች..የተወሰኑ ሰዎች መዝለላቸውን  ቢቀጥሉም አብዛኛው ግን ዘለልኩ ሲል እየተጎተተ መኪና ውስጥ በመግባት ከመጨፍለቅ ውጭ እራሳቸውን ማትረፍ አልቻሉም ነበር… ኬድሮን በትርምሱና በጩኸቱ መሀከል ሆና ወዲህ ወዲያ ከመቁለጨጭለጭ ውጭ የምታደርገው ጠፍቷት እንደደነዘች ነበር…ሮጦ ማምለጥ ቢሆን ሚቀድማት አልነበረም….ሰላሳና አርባ ሜትር ዛፍ መውጣት ቢሆንም ይሄኔ ከማንም ቀድማ ከጫፍ ደርሳ  በመረጋጋት ተቀምጣ ነበር… አውሬን ማደንም  ለእሷ ከጓደኞቾ ጋር ድብብቆሽ አንደመጫወት ቀላልና አዝናኝ እስፖርት ነው…ወደገደል ከሚምዘገዘግ መኪና እንዴት ማምለጥ እንዳለባት ግን ምንም አይነት ልምድ አልነበራትም….የሚዘሉትም ሰዎች ሲጨፈላለቁ እያየች ስለሆነ ልታደርገው አልደፈረችም..መጨረሻ ግን ምርጫ አልነበራትም...መኪናዋ የገደሉ አጋማሽ አካባቢ ሲደርስ ከሆነ አለት ጋር ተላትሞ የፊት ጎማው ሲቀረቀር ተሳፋፈሪዎቹን ልክ በካሶኒው የጫነውን  ቁልል አፈር ወደኋላ እንደሚገለብጥ ገልባጭ መኪና እስከ አሁን መኪናው ላይ የቀሩትን ሰዎች በአየር ላይ ወደፊት አሽቀንጥሮ ዘረገፋቸው….ሶፍያ ሃያ ሜትር  ያህል ወደፊት በአየር ላይ ተሳፈንጥራ ወደታች ቁልቁል ወደምድር ስትምዘገዘግ ይታወቃታል…ከስሯ እንደጦር የሾለ ትክል ድንጋይ ላይ ልትሰካ አንድ ሜትር ያህል ሲቀራት በጭንቀትና በጣር ‹‹አባቴ ድረስልኝ ››የሚል የመጨረሻ ጣር ድምፅ ስታሰማ የሆነ ነገር የለበሰችውን ጃኬት እጅጌ ያዘና ወደላይ አንጠልጥሎ በአየር ላይ አቆያትና ከመፈጥፈጥ አዳናት...ሌሎች ከድንጋዩ እየተጋጩ በቋጥኞች እየተላተሙ  እየተሰበሩና እየተሰነጣቁ በደም እየታጠቡ ህይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲነጠቁ ቁልቅል አዘቅዝቃ ሚዘገንነውን ትዕይት ልክ እንደተዋጣለት አክሽን ፊልም በፍራቻና በመንቀጥቀጥ መመልከት ጀመረች….ማመን አልቻለችም…፡፡

‹‹.እንዴት እኔስ ሳልወድቅ ?››እራሷን ጠየቀች፡፡

የሆነ የዛፍ ቅርንጫፍ የጃኬቷን  ኮሌታ ውስጥ ተቀርቅሮ በአየር ላይ ያንጠለጠላትና ለጊዜው ከመፈጥፈጥና እንደሌሎቹ ተሰባብሮና ከመቆራረጥ እንዲሁም ከሞት እንደተረፈች አሰበች...ለማረጋገጥ ወደኃላ ዞራ ዛፉን ለማየት ብትሞክርም መዞር አልቻለችም፡፡ ይባስ ብሎ የያዛት ነገር ወደላይ ይዟት ሰማዩን ሰንጥቆ እየተመነጠቀ ነው…‹‹.ውይ በቃ አባቴ ወደሆነ ቦታ እየወሰደኝ ነው...ምን አልባትም ወደሲኦል ሊሆን ይችላል››ስትል ገመተች…፡፡
ከሆነ ከፍታ በኋላ አንጠልጥሏት ነበረው .ነገር እንደመወዝወዝ አርገፈገፋትና አሽቀንጥሮ ወደላይ ወረወራት….‹‹ወይ ጭራሽ ከዚህ ርቀት ከወረወረኝ አጥንቴ እንኳን ለቀብር አይገኝም›› ብላ አሳባ ሳትጨርስ ጀርባዋ ላይ ሰርስሮ የሚገባ ነገር ተሰማት….ምንድነው ሰውነቴን  ሰንጥቆ የሚገባው››ወዲያው በግራና ቀኞ የተዘረጋና ነጭ ጣል ጣል ያደረገበት ጥቁር ክንፍ ታያት…የንጉስ ሰረገላ ላይ እንደተሳፈረች አይነት ንግስት የመመቸትና የመድላት ስሜት ተሰማት‹‹….ምን አይነት ተአምር ነው? ››አለችና በአየር ላይ እንደተንጠለጠለች እጆቾን ወደጀርባዋ አዙራ ፈተሸች..አዎ ክንፉ የራሷ ነው፡፡ …ወዲያው ግዙፍ እላዬ ላይ የተሰካው ክንፍ በራሱ አቅጣጫውን እያስተካከለ  ..ንፋሱን እየሰነጠቀ..ያንን ውብ ተፈጥሮና ጥቅጥቅ ደን ወደ ኋላው እየጣለ  ይዟት ነጎደ…ከ20 ወይም  ከ30 ደቂቃ በኃላ እናቷ ቤት በራፍ ላይ  በእንክብካቤ አሳረፋት..ማመን አልቻለችም…፡፡

ጀርባዋ ላይ ተሰክቶ በመዘርጋት እቤቷ በራፍ ድረስ ያመጣት ክንፍ እየተሰበሰበና እያነሰ መጣና ከእሷ ጋር የተያያዘበትን ልክ ብሎን  እንደመፍታት አይነት አለያየና እራሱን ችሎ በአየር ላይ በረረ… ከበላዮ 10 ሜትር ያህል እርቋት አንዴ አካባቢውን ዞረና መጥቶ ከእግሯ ስር አረፈ…ከእስከ አሁኑ በላይ አስገራሚ ነገር ነው እያየች ያለችው…መጀመሪያ አሞራ መስሏት ነበር…ግን አሁን በቅርቧ ስታየው ንስር መሆኑን አረጋገጠች..ንስር ሰውነቷ ላይ ተጣብቆ ምን አልባትም መንቁሩን ጀርባዋ ላይ ሰክቶ ክንፍ ሆኖ እንድትበር ሲያግዛት…
እሷም ባለፉት ሰላሳና አርባ በሚሆኑ ደቂቃዎች የደረሰባትን ሰቅጣች አደጋና የተረፈችበትን ተአምራዊ መንገድ አሁን አጠገቧ ካለው ተአምራዊ እንግዳ ፍጡር ጋር አያይዛ ‹‹እንዴት እንደዚህ ?እያለች በመብሰልሰል ባለችበት ደንዝዛ ቆማለች…ንስሩም ከስሯ አልሄደም እግሯ ስር ነው ያለው….ግን ደግሞ መጠኑ እሷን መሸከም የሚችል አይነት አይደለም፡፡ህልም ላይ እሆን እንዴ? ብላ እሱን እዛው በራፉ ላይ ጥላው ወደውስጥ ገባች. .ሴት አያቷና አጎቶቾ እቤት ነበሩ ..‹‹እንኳን ሰላም መጣሽ? ››ብለው እያቀፉ በመሳም ተቀበሏት..
‹‹በዚህ ሰዓት እንዴት ደረሳችሁ..?.ሶስት ሰዓት እኮ ነው.›ሁሉም የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር..ምክንያቱም ከጎባ ለሊት 11 ሰዓት የተነሳ መኪና እንኳን በጣም ከፈጠነ አራት ሰዓትና አራት ተኩል ነው ሊደርስ የሚችለው፡፡ይሄ ከመንገድ እርቀት የተነሳ ሳይሆን ከአስቸጋሪነቱ የተነሳ ቀስ እያሉ ስለሚጓዙ ነው፡፡አሁን ኬድሮን ቤት የደረሰችበትን ሰዓት ሪራ በተባለችው የገጠር ከተማ ታርፎ ቁርስ የሚበላበት ሰዓት ነው፡፡
👍858😱3
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከሌላ ፕላኔት የመጣ ፍጡር ይሆን እንዴ?›› ስል አሰብኩ፡፡ መጨረሻዬም አጓጓኝ፡፡ በዚህ ቅፅበት እጁን ወደ ጃኬት ኪሱ ሲሠድ በጨረፍታ ተመለከትኩ፡፡ ብሞት ግድ የሌለኝ መስሎ ይሠማኝ ነበር፡፡ ይህቺን አለም ገና እንዳልጠገብኳት የተረዳሁት ግን በዚህ ክስተት ነው፡፡የሚያብረቀርቅ ጩቤ አወጣ ፤የራሱን እጅ በጭካኔ ሸረከተው፡፡ ደሙ መስመር ሰርቶ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የተለያዩ ህብረ - ቀለማት አይኖቼ ላይ ተመላለሱብኝ፤ቀስ በቀስ ከማንነቴ እየተነጠልኩ..እየተፋው ሲሄድ ይታወቀኛል፡፡

ወደ ጥልቅ ገደል እየተንሸራተትኩ ምጓዝ

መስሎ ተሠማኝ፡፡

ለምን ያህል ጊዜ እራሴን ስቼ እንደቆየሁ ትዝ አይለኝም፡፡ አይኖቼን በፍራቻ ስከፍታቸው ባዶ ክፍል ውስጥ ባዶ ሆኜ ብቻዬን ነው ያለሁት፡፡ ዙሪያ ገባውን በጥንቃቄ ቃኘሁ፡፡ የቤቱ ግድግዳ በቀይ ቀለም ተዥጎርጉሯል፡፡ ፅሁፍ ነው፡፡ የሚነበብ ፅሁፍ፡፡ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ‹‹አፈቅርሻለሁ...አምርሬም እጠላሻለሁ›› የሚል ፅሁፍ አነበብኩ፡፡አይኖቼን ወደ ራቁት ሠውነቴ ስመልስ እንደ ግድግዳው በፅሁፍ ሳይሆን በምልክት ተዥጎርጉሯል፡፡ ሁለቱ ጡቶቼ የራይት ምልክት አለባቸው፣ እንብርቴ አካባቢ የኤክስ ምልክት ይታያል፡፡ግራ ገባኝ እስከዛን ግዜ እጆቼ እንደተጠፈሩ አፌ እንደተለጎመ ነበር፤ የተለየው ነገር የአእምሮዬ በመጠኑ መረጋጋት ነው፡፡ እጁን ሲቆርጥ ያየሁትን ምስል ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስታውስ ይሄ ሁሉ ግድግዳው ላይና ሠውነቴ ላይ ያቀለመው በራሱ ደም እንደሆነ ገባኝ፡፡ ሠውነቴ ላይ ያረፉት የራይትና የኤክስ ምልክቶች ፍቺ ግን በቀላሉ ሊገለፅልኝ አልቻለም፡፡እንደ ድንገት ወደ ጎኔ ስዞር በቀኝ  በኩል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ሌላ ፅሑፍ አነበብኩ፡፡

‹‹40 ፐርሰንት ብቻ ከእሷ ጋር ትመሳሰላለች፡፡ ስለዚህ አትወክላትም... ያበሳጫል...ይቺን መግደል ትርጉም አይሰጥም፡፡›› ይላል... ዳግመኛ አዞረኝ፡፡ የሚገላትን ሴት በመፈለግ ላይ ያለ ወፈፌ ነው ያጋጠመኝ፡፡ የምልክቶቹም ፍቺ ተገለፀልኝ፡፡ ከሚያውቃት ወይም ካስከፋችው ሴት ጋር እያመሳሰለኝ ነበር፡፡ እየተንፏቀኩ ሄጄ በራፉን በደከመ ጉልበቴ ደበደብኩ፡፡ ዘበኛው ሠምቶ ከፈተልኝና ከእስራቴ ነፃ አደረገኝ፡፡እየተንቀጠቀትኩ ልብሴን በመልበስ ላይ ሳለው ቅድም ያለየሁት ሌላ ምልክት ብልቴ አካባቢ አየሁ፡፡ ጥያቄ ምልክት አስቀምጦበታል፡፡ ኮንትራት ታክሲ አስጠርቼ እቤቴ አደረሠኝ፡፡ እቤቴ ስገባ ልክ ከለሊቱ ስምንት ሠዓት ነበር፡፡ ሠውነቴን ታጠብኩ፡፡ከፍራቻዬ ለመገላገል ለሊቱን ሙሉ ስጠጣ አደርኩ፡፡ እያነበበችለት ያለውን ዲያሪ አጥፋ እያስቀመጠች.....ይሄው ነው አለችው፡፡

በጉንጮቹ ላይ ያለ ፍቃድ የወረደ እንባውን እየጠረገ ‹‹ልብ ወለድ ነው እውነት?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ልብ ወለድ በዲያሪ ይፃፋል እንዴ?››

‹‹በቃ ምንም አላውቅሽም ነበር ማለት ነው….? እራሴን አመመኝ ልሂድ፡፡›› በማለት ከመቀመጫው ተነሳና ግንባሯን በመሳም ተሠናብቷት ወጣ፡፡ እሷም በተቀመጠችበት በስስት በሚንከራተቱ አይኖቿ ሸኘችው፡፡

የሠጠችውን ፖስታ ለመቅደድ እቤቱ እስኪደርስ አላስቻለውም፡፡ ከሠፈሩ ትንሽ ወጣ እንዳለ ነበር ወደ አንድ ሆቴል ጎራ በማለት መኪናውን አቁሞ ከውስጥ ሳይወጣ የከፈተው፡፡ የሚያየው ነገር ግራ ገብቶታል፡፡ አንድ ወረቀት እና መዓት ብሮች! ባለ መቶ፤ሃምሳ እና አስር ብር በየመጠናቸው ለየብቻ በብር ላስቲክ ተጠፍንገው እጁ ላይ ተዘረገፉ፡፡ብሮቹን ትቶ ወረቀቱን አነሳና ማንበብ ጀመረ፡፡

‹‹አንተን ከመጀመሪያ ጀምሬ የቀረብኩህ ሸርሙጣ ስለሆንኩ ሳይሆን ስለማፈቅርህ ነው፡፡ ብር የምቀበልህ ከአንተ ፍቅር እንደያዘኝ በፍፁም እንድታውቅ ስለማልፈልግ ነበር፡፡ ቢሆንም ብሩን ተጠቅሜው ቢሆን ኖሮ ፍቅር ሳይሆን ሽርሙጥና ይሆን ነበር… እና ለሁለት ዓመት ደንበኛዬ ነበርክ፡፡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አርባ ዘጠኝ ቀን አብረኸኝ አድረሀል፡፡

ከዚህ ውስጥ አስራ አምስቱን ቀን ብር ስላልነበረህ አልከፈልከኝም፡፡

ለዘጠኝ ቀን -> 5ዐዐ ብር ከፈልከኝ  500×19  9500 ብር ይሆናል

አስራ ሁለት ቀን  4ዐዐ ብር ከፈልከኝ  400×12  4800 ብር ይሆናል

ሦስት ቀን  15ዐ ብር ነው የከፈልከኝ 150x3  45ዐ ብር ይሆናል፡፡ እንግዲህ በድምሩ አስራ አራት ሺ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር መሆኑ ነው፡፡ ይሄ ብር እንግዲህ ለመውጫ የምትከፍለውን አርባ.. አርባ ብር አያጠቃልልም፡፡ ቻው፡፡›› ይላል፡፡

አንብቦ ሲጨርስ ወረቀቱን ጨምድዶ አፉ ውስጥ ከተተው፤አኘከው..አደቀቀው  አልተፋውም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሠዓቱ ከምሽቱ 2፡30 ሆኗል፡፡ ሠሎሞንና ኤደን ቦሌ በሚገኘው ታዋቂው አቢሲኒያ ሬስቶራንት እራት በአክሱማይት ወይን እያወራረዱ በመመገብ ላይ ናቸው፡፡ የተገናኙት በቀጠሮ አልነበረም፡፡ ሁለቱም በጋራ የሚያውቁት ሠርግ ላይ በመታደማቸው ነበር ድንገት የተገጣጠሙት፡፡ ሠሎሞን እንደ ወትሮው ሙሉ ሱፍ ከሠማያዊ ሸሚዝና ጥቁር መደብ ኖሮት በነጭ መስመር ከተዥጎረጎረ ክራባት ጋር ለብሶ ሙሽራ ባይሆንም ሚዜ መስሏል፡፡

ኤደንም ከሱ ባልተናነሰ ሁኔታ ዘንጣለች፡፡ ጥቁር ቀለም ያለው ከጉልበቷ በላይ የሚቀር ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች፣ ከላይ ከሠውነቷ ጋር የተጣበቀ ሮዝ ከለር ያለውና የጡቷን ቅርፅ የሚያጎላና ግማሽ የሚሆን የጀርባዋን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ‹ፓክ አውት›
ለብሳለች፣ጆሮዋ ላይ ያንጠለጠለችው ጌጥ አርቲፊሻል ቢሆንም ለውበቷ የራሱ የሆነ ድርሻ
ነበረው፣በፊትም ጎላ ጎላ ብለው ሚታዩ አይኖቿን በስሱ ተኩላቸው ይበልጥ ቀልብ ሳቢ ሆነዋል፣የፀጉር አሠራሯም ልዩ ነው፡፡

‹‹ቬሎ ስላለበሽ ነው እንጂ ሙሽራዋ እኮ አንቺ መስለሽኝ ነበር፡፡››

‹‹ኧረ ባክህ! ለእንደዛ አይነት ወግማ መች ታደልን፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?›› አላት ሠሎሞን በግራ እጁ አንገቱ ላይ የተሸመቀቀውን ክራባት እያላላ፡፡

‹‹እብድ አፍቅረን ከእሱ ጋር ስንጃጃል ውዱ ጊዜያችን በከንቱ አልፎ በፈነዳንበትም ወቅት የነበረንን አንፀባራቂ ውበት መጠቀም አቅቶን ዛሬ ከጠወለግን በኃላ ካንቀላፋንበት ስንባንን ረፍዶብን አገኘነው...ምን ማድረግ እንችላለን፤ አረጀን! ማን ይፈልገናል፤ ያው ቆመን መቅረታችን ሳይሆን ይቀራል?›› ትካዜዋን
ከቆነጠረችው ምግብ ጋር ወደ አፏ ልካ አላመጠችው፡፡

ሠሎሞን መናገር ጀመረ ‹‹ለመሆኑ ፊትሽን የምትመለከቺበት መስታወት ቤትሽ የለሽም እንዴ? የአስራ ስድስት አመት ልጃገረድ ነኝ ብትይ እኮ ማንም የሚጠረጥርሽ አይኖርም ፤‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ ነው እንጂ› መች ላንቺ የሚሆን ባል ጠፋ ብለሽ ነው ... ለማንኛውም ምግቡን ብይ፡፡››

<<ባክህ በቃኝ::>>

‹‹ምነው?መች ተነካና?››

‹‹ግድ የለህም ይብቃኝ.... ባይሆን ወይኑን እደጋግማለሁ፡፡››

‹‹ኧረ ይቻላል! በስንት ወራችን እኮ ነው የተገናኘነው፤ዛሬማ መላቀቅ የለም፡፡››

‹‹ተስማምቼያለሁ፡፡›› አለች ኤደን የወይን ብርጭቆዋን አንስታ እየተጎነጨችለት፡፡
ሠሎሞን የዘወትር ገረሜታው አሁንም እንደገ አገርሸቶበት የኤደንን ውበት በጎሪጥ እየቃኝ በውስጡ ያብሠለሠላል፡፡
👍889👎3😁3
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ኮሎምቢያ/አማዞን ደን ውስጥ

ኑሀሚና ካርሎስ አምስት ሰዓት ያለምንም ረፍትና መንቀርፈፍ ነው የተጓዙት፡፡በቀንም ቢሆን እንኳን ፀሀይ የተንጣለሉትን የግዙፍ ዛፎችን ቅርንጫፍ ሰንጥቃ ወደመሬት መድረስ አይሆንላትም፤ ማታ ሲሆን ደግሞ ለጨረቃዋ በጣም ከባድ ስራ ነው የሚሆንባት፡፡ በዚህም ምክንያት በማታ አይደለም በቀንም ከፍተኛ ሀይል ያለው ባትሪ ሳይጠቀሙ መጓዝ አዳጋች እና በቀላሉ ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ ነው፡፡
‹‹አሁን ማረፍ ያለብን ይመስለኛል››አላት ካርሎስ

‹‹ይሻላል ብለህ ነው?››አለችው በዛለና በደከመ ድምጽ፡፡

‹‹አዎ አሁን የተወሰነ የራቅናቸው ይምስለኛል…ባይሆነ ለሊቱን አርፈን ንጊት ላይ በሙሉ አቅም ጉዞችንን እንቀጥላለን፡፡››አላትና ተስማሙ፡፡ቅጠል እየቆረጠች ግዘፉ ግንድ ስር መጓዝጎዝ ጀመረች፡፡
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?፡፡››

‹‹መሬት ላይ ከመቀመጥ ቅጠሉ ይሻለናል ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹እዚህ የአማዞን እንብርት ላይ መሬት ላይ ተዝናተን መተኛት አንችልም…››

‹‹ለምን? ጃጓር ምናምን ፈርተህ ነው?››

‹‹እሱም አንድ ነገር ነው..ካዛ በላይ ግን ጥቃቅን መርዛማ ነፍሳቶች ናቸው የሚያስፈሩት…..ለምሳሌ የአማዞን ሸረሪት ሰውነትሽን ጥቂት ከጫረችሽ ወይ ከቦጨቀችሽ….በቀጥታ እራስሽን ለሞት ማዘጋጀት መጀመር ነው ያለብሽ፡፡በጣም ብርቱ ከሆንሽ አንድ ሰዓት ብቻ ነው የምትኖሪው፡፡መርዙን አርክሶ ከሞት የሚያድንሽ ምንም አይነት ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ መድሀኒት የለም፡፡እና ይህችን ሸረሪት በቁጥር አንድ ደረጃ ነው የምፈራት፡፡››
ፍራቻው ወደእሷም ተጋባበትና‹‹እና ምን እናድርግ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ሊያስተኛን የሚችል ዛፍ ነው መፈለግ ያለብን ..››ብሎ አይኖቹን በአካባቢው ወደሉት ግዙፍ ዛፎች ባትሪውና በማብራት መምረጥ ጀመረ…ከዛ ‹‹አዎ ይሄኛው የተሻለ ነው….፡፡››ስል ምራጫውን አሳወቃት፡፡
‹‹እንዴት አድርገን ነው እዚህ ላይ ምንወጣው?››

‹‹እንደምንም መውጣት ነዋ….መቼስ ቢከብድ ቢከብድ የሰው ህይወት ከማጥፋት በላይ አይከብድም፡፡››
በንግግሩ ድንግጥ አለች፡፡እስከአሁን እዛ ለእሷ በተቆፈረው መቃብር አካባቢ ስለሆነው ነገር አንሰተው አላወሩም‹‹ሰው መግደሉን ፈልጌው ወይም ቀላል ሆኖልኝ መሰለህ..?ጨንቆኝና የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩ…?ይሄም የህይወት እና የሞት ትግል ነው፡፡ከዚህ ደን በአውሬ ሳንበላ ወይም በነፍሳት ሳንነደፉ በሰላም ወጥተን የሆነ መንግስት የሚቆጣጠረው ትንሽዬም ቢሆን ከተማ ወይም መንደር እስክንገባ የህይወትና የሞት ሽረት ላይ እንደሆን እንዳትዘነጊ…. በይ ቦርሳሽን ለእኔ ስጪኝና ለመውጣት ተዘጋጂ …እኔ ከኃላ ሆኜ እደግፍሻለሁ፡፡››
የተወሰነ ጊዜ እንደማሰብ አለችና ትከሻዋ ላይ ያንጠለጠለችውን ቦርሳ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና ካንጠለጠለው ቦርሳ ጋር አንድ ላይ በቀኝ ትከሻው ደርቦ አንጠለጠለው፡፡በግራ ትከሻው ላይ ክላሽ አለ፡፡
እሷ በረጅሙ ትንፋሽ ወሰደችና ለመውጣት ዝግጁ ሆነች፡፡ቀኝ እግሯን አስቀደመች…ወገቧን ይዞ ደጋፋት፡፡ በእጆቿ ቅርብ ያለውን ቅርንጫፍ ተንጠራርታ ያዘችና ግራ እግሯን አስከተለች፡፡ እንዳዛ እያለች ወደ ላይ መንቀሳቀሷን ቀጠለች፡፡እሱ ከስር ሆኖ ትወድቅ ይሆን በሚል ስጋት በጭንቀት እየተከታተላት ነው፡፡እንደፈራው ሳይሆን እንደውም ይበልጥ አንድ ርምጃ ወደላይ ከፍ ባለች ቁጥር ይበልጥ እየፈጠነችና በራስ መተማመን እየታየባት መጣች፡፡ ለመተኛት ምቹ ነው ብሎ ያሰበበት ቦታ ስትደርስ ‹‹በቃሽ…እዛው ጠብቂኝ›› አላት፡፡እሱም በእፎይታ ወደላይ መውጣት ጀመረ፡፡እሱ ከልጅነቱ ጀምሮ የብዙ አመት ልምድ ስላለው ዛፍ መውጣት ለእሱ በምድር እንደመራመድ ቀላሉ እና ተራ ነገር ነው፡፡
ስሯ ደረሰና ከጎኗ ቁጭ ብሎ የእሷንም የእሱንም ቦርሳ ከአንደኛው ቅርንጫፍ ላይ አሰረው፡፡መሳሪያውንም እንደዛው አንጠለጠለውና በእፎይታ ደገፍ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ካልተመቸሽ እግርሽን በቅረንጫፉ መሀከል አድርጊና ጭንቅላትሽን እኔ ላይ አስደግፊ አላት፡፡››እንዳለት አደረገች፡፡ጭንቅላቷን ደረቱ ላይ ለጥፋ አረፍ ስትል የልብ ምቱ ድውድውታ ተሰማት፡፡
‹‹ልብህ በጣም ይመታል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹አንቺን የመሰለች ፀይም መልዐክ ደረቴ ላይ ተኝታ የልብ ምቴ ባይጨምር ነበር የሚገርመው››አላት፡፡
‹‹አይገርምም …የዛሬን አያድረገውና አለቃህም በሰላሙ ቀን ፀይም መልአክ ብሎኝ ነበር››

‹‹እንደዘ በማለቱ እንኳን ተሳስቷል ማለት አልችልም…የእሱም ልብ እንደእኔው በውበትሽ ደንዝዛ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በዚህ ጣር ላይ ሆነህ ትቀልዳለህ አይደል?››

‹‹በጣር ላይ ሆንሽ በምቾት ላይ ልብሽ ጉዳዩ አይደለም እኮ …ከተነካ ተነካ ነው..በሲኦሉ ውስጥም ሆነ በገነት እጅ መስጠቱ አይቀርም፡፡››
‹‹ይሁንልህ…ውሀው አለቀች እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡ውሀ ጠምቷት ብቻ ሳይሆን የጀመሩትን የወሬ ርዕስ አቅጣጫ ማስቀየርም ስለፈለገች ነው፡፡የእሱን ልብ አታውቅም የእሷ ልብ ግን በዚህ ጊዜ ነፍሷን ለወንድሟ ስትል ከማትረፍ ውጭ ሌላ ተልዕኮ የላትም፡፡እጁን ወደተንጠለጠለው ቦርሳ ሰደደና ኮዳውን አውጥቶ ሰጣት፡፡ክዳኑን ከፈተችና ተጎነጨችለት፡፡መልሳ ከድና አቀበለችው፡፡ወደቦታው መለሰ፡፡
‹‹አሁን የት ነው ያለነው?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ነዋ፡፡››

‹‹እሱንእማ እያየሁት ነው…ሀገሩን ነው የጠየቅኩት፡፡
‹‹ብራዚል እና ኮሎምቢያ ድንበር ላይ ነን፡፡››
‹‹እንዴ …!ወደየት ነው እየሄድን ያለነው?››

‹‹ወደብራዚል ነው…››

‹‹ወደኮሎምቢያ ወይም ወደመጣንበት ወደፔሩ የምንሄድ ነበር የመሰለኝ፡፡››

‹‹አይ …ያንን ማድረግ አልመረጥኩም…ከፔሩ ፤ኮሎምቢያ ሜክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ ሰውዬው በብዙ ሺ የሚሆኑ ሰዎች አሉት…በየደረስንበት ሁለ ታዳኞች ነው የምንሆነው፡፡ይሄኔ ሁሉም እኛን በደረስንበት ቀጨም አድርጎ ወይ በህይወት ካለሆን ደግሞ እሬሳችንን ለእሱ በማስረከብ እና ደለብ ያለ ሽልማቱን ለመቀበል ቋምጠው እየጠበቁን ነው፡፡››
‹‹ብራዚልስ ሰው የለውም?››

‹‹አይ ብራዚል ተፅእኖው በጣም የሳሳ ነው፡፡በዛ ላይ አሁን እየተጓዝን ያለነው ወደግዙፍ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ነው..በቀደም እንደነገርኩሽ 60 ፐርሰንቱ የአማዞን ደን ያለው ብራዚል ውስጥ ነው፡፡ወደእዛ ጠልቀው ይገባሉ ብሎ ማንም አያስብም፡፡ገብተዋል ብለው ቢያስብ እንኳን ያን ሁሉ ደን ሰንጥቀን ከአውሬዎቹም ከተናዳፊ መራዛማ ነፍሳትም ተርፈን በህይወት የሆነ ቦታ እንደማንደርስ እርግጠኞች ናቸው..ስለዚህ ወደዚህ አይፈልጉንም፡፡ለዛ ነው በጣም ከባዱን መንገድ የመረጥኩት፡፡በህይወት እንዲሳካልሽ አንዳንዴ ቀላሉን መንገድ መምረጥ አዋጪ አይደለም…፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹አሳምነኸኛል..ግን አንተስ ከፊታችን እንደፓስፊክ ውቅያኖስ የተዘረጋውን አስፈሪ ጥቅጥቅ ደን ሰርቫይቭ አድረገን ሕይወታችንን እንደምናተርፍ እንዴት ልታምን ቻልክ?፡፡››
‹‹በቀደም በነገርሺኝ ታሪክ ነዋ››

‹‹የትኛው ታሪክ?፡፡››

‹‹የሴትዬዋ… ጨካኝ ንጉስ ያለበት ግዛት ውስጥ ከመኖር አዳኝ ነበር ያለበት ጫካ ውስጥ መኖር እንደሚሻል መምረጦን የነገርሺኝን…››
በጨለማ ውስጥ ፈገግ ብላ‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ፡፡››አለችው ፡፡

‹‹አዎ ጥሩ ተማሪ ነኝ..በዛ ላይ ሶስት ነገሮች ያግዙናል ብዬ አስባለው፡፡››

‹‹እስኪ ንገረኝ እነዚሀ ሶስት ነገሮች ምንድናቸው?፡፡››
👍793👎1🥰1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ የሚሞከር ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡

ነገሩ ቀልድ እንዳልሆነ የተረዳው ልክ በተነገረው መሰረት ከሶስት ቀን በኃላ ተመሳሳይ ስልክ ሲደወልለት ነው፡፡በጉጉት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ..አወቅከኝ?››

‹‹መሰለኝ… አደናጋሪዋ ልጅ ነሽ አይደል?››

‹‹መሰለኝ….የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ?››

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹በተነጋገርነው መሰረት ስራ ማስጀመሪያ መቶ ሺ ብሩን እንድልክልህ ነዋ››

‹‹እንዴ? ስራው ምን እንደሆነ ሳላውቅ…ልስራው አልስራው መወሰን የምችለው እኮ ስራውን ሳውቅ ነው…መጀመሪያ በአካል ተገናኝነተን ስለስራው ማውራት አለብን››

‹‹ለጊዜው በአካል ላገኝህ አልችልም…ስራው በአባትና እናቴ መካከል ያለውን ችግር መቅረፍ ነው…እናትና አባቴ ያለፉትን 28 አመታት በጋብቻ አሳልፈዋል….እኔ ሀያ አንድ አመቴን ጨርሼ 22 ዓመት ውስጥ ነኝ…በእድሜዬ አንድም ቀን ሰላም ሆነው አይቻቸው አላውቅም…መኝታ  ለይተው  በየራሳቸው  መኝታ  ቤት  ነው  የሚያድሩት….ሁል  ጊዜ
እንደተጣሉና እንደተጨቃጨቁ ነው.ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድም እስከመፈለግ የሚያደርስ ጥላቻ በመካከላቸው አለ..ወይ አይፋቱ ወይ እንደሰው የእውነት አብረው አይኖሩ፣….እና የፈለኩህ ይሄንን የሻገተና የበሰበሰ ጋብቻ የበሰበሰውን ቅጠል ከላዩ አራግፈህ የደረቀውን የጋብቻ ግንድ ቆርጠህ ከስር አዲስ የፍቅር ቅርንጫፍ እንዲያቆጠቁጥ እንድታደርግ ነው…ቢያንስ እንደባለትዳር መልሰው መተቃቀፍ ባይችሉ እራሱ እንደጓደኛሞች እንዲጨባበጡ ማድረግ እንድትችል ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የእኔ የህይወቴ ትልቁ አላማ ነው…እባክህ ይሄንን ጉዳይ እንደጉዳይህ ልትይዘው ትችላለህ….?›››

‹‹በእውነቱ ከጠበቅኩት በተቃራኒ የሆነ መሳጭ ነገር እየነገርሺን ስለሆነ ቀልቤን ገዝተሸዋል…የምትይውን በደንብ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡፡ለመሆኑ እኔን የምታናግሪው አባትሽ ወክለሽ ነው ወይስ እናትሽን…..?ማለት እኔን ለስራው እንድታናግሪኝ የጠየቀሽ ማን ነው?፡፡››

‹‹በእውነቱ ሁለቱም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር የለም….›

‹‹ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል..እሺ ቆይ ለመሆኑ እኔን ለምን…?እንዴት እኔን መረጥሽ?››

‹‹ለጊዜው ማንነቱን ልነግርህ የማልችለው አንድ አንተን የሚያውቅ ሰው ነው ሰለአንተ በሆነ ጉዳይ አንስተን ስንጨዋወት በጋብቻ ጉዳይ ላይ እንደምትሰራና በጉብዝናህም እንደሚተማመንብህ የነገረኝ..እንዳአጋጣ ሚ ሆኖ ደግሞ ያንን ሰው እኔ አምነዋለው…እሱ ጎበዝ ነህ ካለህ ጎበዝ ነህ ማለት ነው…

ተመለሰልህ?፡››

‹‹በከፊል አዎ…ግን እንደነገርሺኝ በወላጆችሽ መካከል ያለው ችግር ለረጅም አመት የተከማቸ የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙም ነው፡፡››

‹‹በትክክል ገልፀኸዋል››

‹‹ችግሩ ምን መሰለሽ..በቀደም እንደነገርኩሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በጋብቻ መካከል የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት የሚችለው ሁለቱም ተጋቢዎች በመሀከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ያንን ለማስተካከል ከአማካሪው ጋር ለመተባበር ሙሉ ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው…አሁን ያንቺን ጉዳይ ስንመለከት ወላጆችሽ ጉዳዩን እንኳን አያውቁትም..ቢያውቁትም ፈፅሞ ከእኔ ጋር ለመስራት ላይቀበሉት ይችላሉ.››.

‹‹እሱን ለእኔ ተወውና አሁን የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ… ገንዘቡን ትራንስፈር ላድርግልህ››

‹‹ይሄውልሽ ፣እኔ በነገርሺን ታሪክ በጣም ተስቤያለሁ…አንድ ወጣት ሴት በወላጆቾ ግንኙነት ተረብሻ እንዲህ ነገሮችን ለማስተካከል ስትጥር እኔም የበኩሌን እገዛ ለማድረግ ፍጽም ፍቃደኛ ነኝ..እዚህ ላይ ዋናው ገንዘብ አይደለም.. እሱ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው…አሁን መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ወላጆችሽን ከቻልሽ አንድ ላይ አስቀምጠሸ ካልሆነም ለየብቻ ያሰብሽውን ንገሪያቸውና ለማሳመን ሞክሪ..እነሱ ፍቃደኛ ከሆኑ በኃላ ደውይልኝ..ከዛ ፕሮግራም እናወጣና ያለውን ችግር እያየን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡››

‹‹እነሱን በቀጥታ ማናገር አልችልም››

‹‹ለምን?››

‹‹ስሜ በፀሎት ኃይለልኡል ይባላል››

‹‹እሺ በፀሎት…ለምንድነው ወላጆችሽን ማናገር የማትችይው..?እነሱን ማናገር የማትቺይ ከሆነ እንዴት አድርጌ ነው ወላጆችሽን መርዳት የምችለው?››

‹‹ማለት ስሜን የነገርኩህ ስለእኔ የተወሰነ መረጃ እንዲኖርህ ነው..በፀሎት ኃይለልኡል በልና ድህረገፆች ላይ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈልግ ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መልሼ ደውልልሀለው፡፡››አለችና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡

ስልኩ ቢዘጋም እሱ ግን ስልኩ ላይ እንዳፈጠጠ ነው…የገባው የመሰለው የልጅቷ ሁኔታ መልሶ እየተበታተነበት ነው‹‹…ድህረ-ገፅ ላይ ስለእሷ ምን…?ታዋቂ ሰው ነች ማለት ነው…?››

ጎግል ከፍቶ ››በፀሎት ኃይለመለኮት››ብሎ ሰርች መድረግ ጀመረ..በርካታ መረጃዎች ተዘረገፉ….እውነትም ይህቺ ልጅ ታዋቂ ነች መሰለኝ..ብሎ የመጀመሪያውን ሲያነብ

‹‹የታዋቂ ቢሊዬነሩ የኃይለመለኮት ብቸኛ ወራሽ በውድቅት ለሊት ከቤት ወጥታ ከጠፋች 14 ቀን አልፏታል፡፡››

‹‹ታዋቂው ቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ በፀሎት ለምን ከቤቷ ጠፋች?››
‹‹በጸሎት ኃይለመለኮትን ያለችበትን የጠቆመ የ5 ሚሊዬን ብር  ሽልማት እንደሚሸልሙ አባቷ ለፋና ቴልቨዥን በሰጡት መግለጫ አሳወቁ››

በሚያነበው ዜና ሁሉ ደነዘዘ…..ማንበቡን አቆመና..ደወለላት

‹‹ሄሎ ..››

‹‹አሁን በመጠኑ ገባህ?››

‹‹ማለት አሁንም እንደጠፋሽ አይደለሽም አይደል…..?ማለቴ ወደቤት ተመልሰሻል?››

‹‹አይ  አልተመለስኩም…ወደቤት  እንድመለስም  እንደወጣው  በዛው  እንድቀርም የምታደርገኝ አንተ ነህ፡፡››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ከእቤት የጠፋሁት የወላጆቼ ጭቅጭቅና የእርስ በርስ ጥላቻ ምርር ብሎኝ ነው….እኔ የእነሱን ሀብታቸውንም ሆነ ውርሳቸውን አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅራቸውን ነው..ቢያንስ የሁለት ጓደኛሞችን አይነት እርስ በርስ የመግባባት እና የመረዳዳት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ወደዛ ቤት አልመለስም…እና እቅዴ ምን መሰለህ..ለእነሱ ደብዳቤ ፅፌ ልክልሀለው….በዛ ደብዳቤ ላይ ግልፅ የሆነ ፍላጎቴን አሰፍራለሁ…ማለቴ በግልፅ ከአንተ ጋር ሰርተው በማሀከላቸው ያለውን ግንኙነት ካስተካከሉ…እናም ያንን አንተ ካረጋገጥክልኝ ወደቤት እመለሳለው..ካለበለዚያ በቃ እኔም እነሱን እረሳለው አነሱም እኔን ይረሱኛል ማለት ነው፡፡›

‹‹በተሰቀለው..ነገሩ ካሰብኩት በላይ የተወሳሰበና ..አደገኛም ጭምር ነው፡፡››

‹‹ለዚህ እኮ ነው አምስት ሚሊዬን ብር እንድታገኝ የማደርግህ..ገብቷሀል አይደል አባቴ እኔን ላገኘ ወይም ያለሁበትን ለጠቆመ ሰው የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ..ያ ማለት ነገሮች እንደተሳኩ እርግጠኛ በሆንኩ ጊዜ አንተ እንድታገኘኝና ለቤተሰቦቼ እንድታስረክበኝ አደርጋለሁ…እናም ለሽልማት የተዘጋጀውን ብር ከአባቴ ተቀብዬ ለአንተ አስረክብሀለው፡፡››
👍61🥰123
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

አይንሽን ላፈር

አይ! ሰው ለሰው ሞት አነሰው ብላ የተረተችው ቀበሮ ወዳም አይደለም፡፡ ለካ ለሁሉም የሚተረትለት ችግሩ በቤቱ ሲደርስበት ኖሯል፡፡ ለነሱ ብዬ ስሜ በማንም አፈኛ በየገብያውና በየቤቱ ይነሳል፡፡ እቤት ተዘፍዝፋ ባሏ ዲቃላ ያንጠባጥባል፡፡ ምን አይነት ግፍንት ነች እየተባልኩ የማንም መሳቂያና መተረቻ ልሁን? ከሰውም ጋር ባይሆንም ከራሷ ሃሳብ ጋር ያወራችው ነበር ፡፡

ስሙን ሳነሳሳና ሳማው መጣ እንዴ? ከውጭ በኩል አበበች የሚል የወንድ ድምፅ ሰምታ ተመስገን መስሏት ነበር፡፡ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወጣች፡፡

ግን ተመስገን ሳይሆን ወላጅ አባቷ አቶ አሸናፊ ነበር፡፡

"ደህና አረፈዳችሁ"? አለ ፤ አቶ አሸናፊ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አረፈድህ አባባ ፤ ግባ ወደ ቤት" አለች፡፡

ወደ እቤት እየገቡ "ያሬድ የለም እንዴ"? አለ፡፡

"የለም፤ በጥዋት መጣሁ ብሎኝ እንደ ሄደ አልተመለሰም፡፡ የሄደበትንም አልነገረኝም፡፡ ምነው ደህና አይደለህም?፡፡

"እኔስ ደህናነኝ፡፡ ከብቶቹ እፀሃይ ላይ ታስረው ሳይ ለምን አልፈታቸውም ብዬ ነው"፡፡

"እኔም ብዬ አሁን ነበር የሚበላ የሰጠኋቸው፡፡ ውሃ ጠምቷቸው ነው መሰለኝ አልበሉትም፡፡ እሱም ውሃ እንዳያጠጣቸው ብቅታውም ጠፋ፡፡ ወይ እቆያለሁ አጠጫቸው እንኳን አላለኝ፡፡ ቶሎ እንደሚመለስ ሰው ሳይነግረኝ መሔዱ አለች፡፡

"መቼ ጉዳይ ብሎ ነው፡፡ ከብት አጠጥቶ የሚያውቀው፡፡ አንዴ ነጋዴ ነኝ ፤ አንዴ ባለጉዳይ ነኝ
እያለ ፤ መንደር ለመንደርና ከተማ ለከተማ እያሽካካና እየዞረ አላት፡፡

"እንዴው እቤት ካለ ብዬ ነው እንጂ ለማጠጣቱማ አዲስ አይደለሁም፡፡ አሁን ለአንተ ቡና ላፍላና አጠጣቸዋለሁ፡፡

"እኔ ቡና አልጠጣም፡፡ አታፍሊ ፡፡

"ለምን አትጠጣም? ምነው ደህና አይደለህም? እንዴ አለችው፡፡ አባቷ ተኮሳትሮ መናገሩ አስፈርቷታል፡፡

አቶ አሸናፊ በሚወራው የሰፈር ወሬ ማንነቱን ያስደፈረው ይመስላል፡፡ ወደ ልጁ ቤት የመጣው እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ለበጎ ሳይሆን ለነገር እንደመጣ በፊቱ ላይ የሚነበበው የመኮሳተር ምልክት የሚያስይ መሆኑ ጥርጥር የለውም ነበር፡፡

"አንቺ ወራዳ ፤ አንቺ ተዋርደሽ እኔንም አዋረድሽኝ፡፡ ባልሽ አንቺን የቤት ገረድ አድርጎ ዲቃላውን በሔደበት ይፈለፍላል፡፡ ከሰማሽ በኋላ፤ እንኳን ጥለሽ መምጣት አቅቶሽ ነው" አለ፡፡ በዱላ እንደ መምታት ያህል በሚሰማ ንግግር፡፡

አበበች የፈራችው አልቀረም፡፡ በትዳሯ ላይ እሳት ሲለኮስ ታያት፡፡ የአባቷ ንግግር ከያሬድ ጋር እንድትቀጥል የሚፈልግ አይመስልም፡፡ ለተመስገን እሽ ያለችበትን ቀን አምርራ ብትረግምም ያቺን ቀን ግን ተመልሳ ልታገኛት አልቻለችም፡፡ መልስ ሳትሰጥ አይኞቿ በእንባ ተሞሉ፡፡

"አሁን ምንድ ነው ሃሳብሽ ? የባልሽ ገረድ ሆኖ መቀጠል ይሻላል?፡፡ ወይስ ለቆ መውጣት ይሻላል?፡፡ መነፋረቁን ትተሸ ተናገሪ አለ፡፡ አሁንም ቁጣና ንዴት በተቀላቀለበት ንግግር፡፡

"አባባ የማታውቀው ነገር ስላለ እኮ ነው ብላ..

"የማላውቀው ምንድ ነው ባክሽ?፡፡ ከቄስ መልካሙ ልጅ ባልሽ መውለዱን ነው፤ የማላቀው? ወይስ በማንም ጨምላቃ አፍ በየቡና ቤቱ ላይ በአንች የተነሳ ስሜ መነሳቱን ነው የማላውቀው?፡፡ ለነገሩ እኔ የተዋረድኩት ዛሬ ሳይሆን አንቺን የወለድሁ ቀን ነው አላት፡፡

ሚስጥሩን ለአባቷ ለመንገር ብትፈልግም አባቷ ግን ምንም አይነት ምክንያት የሚቀበል አይደለም፡፡

"ትዳሬን እንዴት ባልሰራሁት ለቅቄ እሄዳለሁ?

ልጄን ያለ አባት ማሳደግ አልፈልግም፡፡ ነገ እውነቱ ሲወጣ ጥፋተኛ ማን እንደሆነ ያኔ ታውቃለህ አለች፡፡ ደፍራ በመናገሯ አይኑን ላለማየት ወደ መሬት አቀርቅራ፡፡

አቶ አሸናፊ የባሰ በንዴት ቆሽታቸው አረረ፡፡ አንች ወራዳ አታፍሪም ደግሞ ነገ እውነቱ ይወጣል ስትይኝ?፡፡ አንገታቸውን እየነቀነቁ አይ! አለመታደል ይሄ! ልክስክስ ባልሽ ካዋጣሽ ከዛሬ ጀምሮ! ልጄ! አይደለሽም፡፡ ብሞትም እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ፡፡ ብሏት፤ የወለዳትን ልጅ ረግሞ እንዳልወለዳት ልጄ አይደለሽም ብሎ እያለቀሰች ትቷት ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

ታዲያ አበበች ስታለቅስ አይን አይኗን እያዬ የሚቁለጨለጨው ልጇ ለተመለከተው ከሷ ለቅሶ ይልቅ የልጇ አይኖች ሲንከራተቱ ያስለቅሱ ነበር፡፡

"ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው"? አለ ፤ ያሬድ፡፡ ባለቤቱን ጥዋት ትቷት ሲወጣ ደህና ብትሆንም ሲመለስ ግን እያለቀሰች ስላገኛት፡፡ በምን እንደምታለቅስ ግራ ገባው፡፡ ልጁን ከእቅፏ ላይ አንስቶ ታቀፈው፡፡ ባየው ነገር ሆዱ ባባ፡፡ ከየት መጣ ሳይባል እንባ ከአይኖቹ ተንጠባጠቡ፡፡

የተፈጠረውን ለማውቅ ደግሞ "ምንድ ነው የሆሽው? ለምን አትነግሪኝም? አለ ፤ እንደ መቆጣት ብሎ፡፡

አበበች እንባዋን እየጠራረገች አባባ አሁን መጥቶ ነበር አለች፡፡

"ታዲያ ምን አሉሽ ?፡፡

"ምን ይለኛል፡፡ ያው እየፈራን ላደረግነው ነገር አይንሽን ለአፈር አለኝ፡፡ አንቺ የባልሽ ገረድ ሆነሽ ባልሽ ዲቃላውን ይፈለፍላል፡፡ አሁን ባሌ ይሻለኛል ካልሽ ከዛሬ ጀምሮ ልጄ አይደለሽም፡፡ ብሞት እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ ብሎኝ እያለቀስኩ አሁን ነው ጥሎኝ የወጣው፡፡

"ሚስጥሩን ነገርሻቸው እንዴ"?፡፡

"እኔ ልነግረው አስቤ ነበር፡፡ እሱ ግን የሚሰማኝ ስላልመሰለኝ አልነገርኩትም፡፡

"ድሮም እግዚአብሔርን ብለን እንጅ ይሄ እንደሚመጣ እያወቅን የገባንበት ነው፡፡ አሁን እውነቱ
እስከሚወጣ ድረስ የምናደርገው ምንም አይኖርም፡፡

ሚስጥሩ መውጣት ያለበት የእነሱም ቤተሰቦች የእኛም ቤተሰቦች ተሰብስበው ነው፡፡ እኔም ትላንትና አልነገርኩሽም እንጅ ከገበያ ስመጣ ወንድምሽ ከመንገድ አድፍጦ ሊገለኝ ሲል እሮጨ ነው ያመለጥኩት፡፡ ሁሉም ነገር ጥፋቱ የእኔ እስከሆነ ድረስ በእነሱ የምይዝባቸው ቂም የለኝም፡፡ ከአሁን በኋላ፤ እናትሽም ቢመጡም ሚስጥሩን እንዳትነግሪ፡፡ ምክንያቱም ወሬው በውጭ ከተወራ ተመስገንና እድላዊት ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ እነሱ ከሌሉ ሁሉም ነገር ጨለማ ለብሶ ሳይገለጥ ተዳፍኖ እንዳይቀር ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡

ወዶዘማች

ወደ ጠጁ ቤቱ ጎራ አለ፡፡ አንድ ብርሌ ጠጅ አዘዘ፡፡ ሁለት አውቶቢስ አንድ ሚኒባስ ከላይዋ ላይ ድምፅ ማጉሊያ ጭና ከፊት ለፊት ቀድማ ትከንፋለች፡፡ የአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በከፍተኛ ድምፅ ተለቋል፡፡ የአረርቲ ከተማን ከዳር እስከ ዳርም አናውጧታል፡፡ ታዲያ ሽለላና ቀረርቶው በጥቂቱ እንዲህ ይል ነበር፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

እንኳን በለው ብለው ልከው ሰደውት፤

ከወገብ ላይ ሆኖ ያኮራል ጥይት፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ከአፈሙዙ ዘቅዘቅ ከሰደፉ ቀና አድርገው የተኮሱ እንደሆን፤

ጥይት ሰው አይፈራም ምን ደንደሳም ቢሆን፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘሩ የመርዙ ትውልድ፤

አምሶ ይቀብራል እንደ እሳት ሰደድ፤

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ሀገሬ ኢትዮጵያ ኩሪ ይገባሻል፤

የማያስደፍሩ ጀግና ልጅ ወልደሻል፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

አገሬን ኢትዮጵያ እሳት ይዞረዋል፤

ለመጥፋት ነው እንጅ ምን ይሻገረዋል፡፡

ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘራፍ የተጎረፈው በጠመንጃው ፊት ሰው የማያልፈው፤ ሳይነካኳቸው እየደረሱ ይመለሳሉ እየቀመሱ ፤

ታንክ ቢያሽካካ መድፍ ቢያጓራ፤

የሚጋፈጠው በሮ እንደ አሞራ፡፡….

ከአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በተጨማሪ ጋዜጠኛ ገረመው ይታያል እሱም እንዲህ ይል ነበር፡፡
👍529
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6610🥰1
የግዜርየአደራልጅ…


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ከብዙ ድካምና ልፋት በኃላ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባበሰቢያ ቀን ደረሰ፡፡አሁን በግዙፉ እና ነፋሻማው በወላጆቿ ቤት ሁሉም አይነት ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው‹‹እርግጠኛ ነህ ምንም ነገር የጎደለ የለም?›› ራሔል ሮቤልን ለአራተኛ ጊዜ ጠየቀችው።

በሙሉ የራስ መተማመን‹‹ሁሉ ነገር በቁጥጥር ስር ነው…አንቺ ምንም አታስቢ›› ሲል መለሰላት፡፡
ራሄል የመጀመሪያ እንግዶች በእርሻ ቦታው ላይ በሰዓቱ ሲደርሱ ስትመለከት ተደሰተች። እሷ እንደዚህ ቀደሞቹ ዝግጅቶች ሙሉ ቁጥጥር አልነበራትም። በዚህም ምክንያት በሁሉ ነገር ላይ በቀላሉ  እርግጠኛ መሆን አልቻለችም፡፡
በነገራት ነገር እንዳላመነችው የተረዳው ሮቤል‹‹ ደህና ነን። ነገሮች ጥሩ ናቸው። ሁሉም ሰው በጥሩ ሁኔታ ስራውን እየሰራ ነው። ምንም አትጨናነቂ ዘና በይ …  ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች  ገንዘብ  መሰብሰብ ሲጀመር የፋውንዴሽናችን ካዝና ሞልቶ ይፈሳል፡፡ ››አላት፡፡

ከመጠን ያለፈ በራስ መተማመኑን አልወደደችለትም፡፡ቢሆንም ማድረግ የምትችለው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ያልታሰብ ችግር እንዳይፈጠር መፀለይ ብቻ ነው፡፡ግን ችግሩ መፀለዩም ለእሷ በቀላሉ መደረግ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡

ቀስ በቀስ ግቢው በእንግዶች እየተሞላ መጣ…የቅርቧ ሰዎች ጓደኞቾና ዘመዶቾን ጨምሮ ከዚህ በፊት በዝግጅቷቾ ላይ ተገኝተው የማያውቁ ሚዲያ ብቻ ማታውቃቸው በርካታ ታዋቂ እና ዝነኛ ሰዎች እዚህምእዛም ስታይ በጣም ተገረመች…የሚዲያ ሰዎች በየቦታው እየተሹለከለኩ የመረጡትን ሰው ፎቶ በማነሳትና ቃለመጠየው በማድረግ ተጠምደዋል፡፡

የሚገርም ሁኔታ ቀስ በቀስ  የበለጠ ነፃነት፣ እና ቀላል ያለ  ስሜት እየተሰማት መጣ።ስሯ ያለችው ፀጋ እጇን ስትይዛት ወደቀልቧ ተመለሰች እና ወደታች አጎንብሳ ተመለከተቻት።

በጣቷ ወደ ግራ እየጠቆመቻት‹‹ኤሊ..ኤሊ››አለቻት፡፡ራሄል ጥቆማዋን ተከትላ እይታዋን ወደዛው አዞረች፡፡ዶ/ር ኤልያስ ወደእነሱ እየመጣ ነው፡፡ጥቁር ሙሉ ሱፍ ለብሶ ሽክ ብሏል፡፡ስራቸው ሲደርስ

‹‹ኤሊ. ኤሊ. መጣህ››ትሁት ጮኸች.

የራሄል ልብ ዘለለ፡፡ ዔሊያስ ጎንበስ ብሎ ፀጋን በእቅፉ አስገባትና ስሞ መልሷ አስቀመጣት…። በዚህ ጊዜ ሮቤል ራሄል ጀርባ ደርሶ የሁነ ነገር በሹክሹክታ እየነገራት ነበር፡፡

የኤልያስ የደመቁ ጥቁር ዓይኖቹ ወደ ሮቤል በረሩ፣ ‹‹ኤሊ  ሮቤል ይባላል  … ረዳቴ ነው .››ብላ አስተዋወቀችው፡፡

‹‹ሮቤል እሱ ደግሞ ዶ/ር ኤልያስ ይባላል…››በቀደም  ከንፈሬን የሳመኝ እሱ ነው› የሚለውን ተጨማሪ ንግግር በውስጧ አከለችበት ,፡፡

ዔሊያስ  የሮቤልን እጅ   እየጨበጠው‹‹ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል።››አለው፡፡

ሮቤል በደማቅ ፈገግታ ተሞልቶ በቀልድ መልክ  ››ራሔል ስራዎቾን በውክልና ለእኛ አሳላፋ መስጠት እየተማረች ነው። በተቻለህ መጠን ከእኛ አርቀህ ብትይዝልን ደግሞ ነገሮች ከዚህ በላይ እየተሻሻሉ ይሄዳሉ ››አለው

ኤልያስ የሮቤልን ንግግር እያዳመጠ   ዓይኖቹ  ራሔል ላይ ተከለ።

‹‹እንዳልከው አደርጋለው.››አለው ዔሊያስ…ሮቤል ተሰናብቶቸው ወደስራው ተመለሰ፡፡
ብቻቸውን ሲሆኑ ራሄል ቀሚሷን ወደታች እየጎተተች ያስቸገረቻትን  ፀጋን  ወደላይ አንስታ አቀፈቻት እና‹‹በመምጣትህ ደስ ብሎኛል››አለችው ።

‹‹አመሰግናለው››አላት

ፀጋ ፀጉሮሯን እየነጨችና ፊቷን እየቧጨረች አስቸገረቻት‹‹አንቺ ሞኝ  ልጅ ..እረፊ… ፀጉሬን ነቀልሽው እኮ››አለቻት  ራሄል ።

ፀጋ በደስታ ሳቀች ።

‹‹አውርጂኝ ›› ብላ ጠየቀች እና ዔሊያስም እንድታወርዳት ነገራት።እንዳወረደቻት  ለመጫወት ከእነሱ ራቅ ብላ ወደ ሜዳው ኩስ ኩስ እያለች ሄደች፡፡

ራሄል ፀጋ  የበታተነችባትን ፀጉር ለማስተካከል እየሞከረች ‹‹መጀመሪያ ወደ ቤት ሄጄ ፀጉሬን መልሼ መስራት አለብኝ›› አለችው፡፡

ዔሊያስ  ከፀጉሯ ላይ ያረፈች ሳር እያነሳ  ‹‹ባታስተካክይውም ቆንጆ ነሽ ››አላት፡፡

ጉንጯ በእፍረት ቀላ‹‹ አመሰግናለው..ግን እንደምታየው ልብሴንም መቀየር አለብኝ?››

ራሄል አለባበሷ ለስራ ከምትለብሰው ልብስ ጋር ሲነፃፀር የተለመደ ነው ግን ሰሞኑን እቤት ስትውል ከምትለብሳቸው  ልብሰች አንፃር በጣም ያጌጠና ያመረ የሚባል ነው፡፡

የዔሊያስ ተንኮል አዘል ፈገግታ ተፈታተናት፣ እጁ ዘንበል ብሎ አገጯን እየነካካ ‹‹ጸጉርሽን እንዲህ ስትለቂው   ደስ ይለኛል.››ሲላት ለአፍታ ልብን የሚያቆም ፍርሀት ወረራት፡፡

‹‹እንደገና ሊስማኝ  ነው እንዴ?›› ብላ  በውስጧ አሰበች። እንዲያደርገው  ፈለገች።

ፍርሀቷን  በሳቅ ለመሸፈን እየጣረች  ‹‹ፀጋ ሳትርቅ ብንሄድ ይሻለናል››አለችው፡፡
ወደፀጋ ሄዱና እያንዳንዳቸው አንዳንድ እጃን ያዙ. ራሄል ከሩቅ ለሚያያቸው ሰው ልክ ወደ ወ.ሮ ላምሮት ቤት ሲሄድ  እንደነበሩት ቀን  ቤተሰብ እንደሚመስሉ አሰበች። ።ወደጎን   ዞር ብላ ስታየው  ዓይናቸው ተገናኘ። ቢፌ በተደረደረበት ግዙፍ ጠረጴዛ አጠገብ ሲያልፉ  የ ሰላጣ ሳህኖች ባዶ ሆነው አየችና እንደመበሳጨት ብላ‹‹ይቅርታ አድርግልኝ..ይህን ማስተካከል  አለብኝ.››አለችውና ተለይታቸው ልትሄድ ስትል ዔሊያስ  ፈጠን አለና  እጇን በእጁ ያዘ።

‹‹አይ, ይሄ የአንቺ   ስራ አይደለም, ሮቤል እና አዲሷ ረዳትሽ ሁሉንም ነገር በቁጥጥራቸው ስር አድርገውታል…ለእነሱ ተይላቸው.››አላት፡፡ራሄል ፊቷን አኮሰታተረች እና ተቃውሞዋን ልታሰማ ስትል አንዲት ተለቅ ያለች ነጭ ዩኒፎርም  የለበሰች ሴት በላስቲክ የተሸፈነ ሳህን ይዛ መጣችና   ባዶውን የሰላጣ ሳህን ስትሞለ ተመለከተች፡፡

ኤሊያስ ቅንድቡን ከፍ አድርጎ ‹‹አየሽ…ዘና በይ ..ሁሉ ነገር አሪፍ ይሆናል?››ሲል  ተናገረ።ራሄል በራሷ ችኮነት አፍራ ሳቀች።

‹‹እሺ በቃ ዘና እላለሁ ።››አለችና  ረዥሙ ትንፋሽ ሳበች ፣ ዙሪያውን ተመለከተች እና ይህንን እንደምትለምድ ተገነዘበች። የገቢ ማሰባሰቢያ  ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የተጣደፈ ፣ የተቸኮለ  ነበር፣አሁን የምታው ግን የተረጋጋ እና ዘና ያለ ሆኖ ነው ያገኘችው  ፡፡አሁንም እየፈገገ ያለውን ዔሊን ተመለከተች እና ከሰዎች ጋር በቀላሉ መዋሀድ  መቻል እንዴት ጥሩ እንደሆነ አሰበች። ዔሊም እያንዳንዱን እንግዳ ስታናግር  ከጎኗ እንዲሆን ፈለገች።

ራሄል በሳቅ ፈገግታ ተጥለቅልቃ‹‹አስደናቂ ቀን ይሆናል ብዬ አስባለሁ››አለችው ።

ኤልያስም‹‹እንደዛ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ።››ሲል ተጨማሪ ጥንካሬ ሰጣት።ከዚያም ራሄል ይቅርታ ጠየቀችውና  አዲስ ወደገቡት እንግዶች ሄደች፡፡እሱ ፀጋን እንደያዘ በተወሰነ ርቀት ወደኃላ ቀረ፡፡ እንግዶቹን እያወራች   ትኩረቷ በዔሊ ላይ ነበር። 

ኤልያስ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ የራሱን ትዝብት መውሰድ ጀመረ…አዎ እሱም እንደማንኛውም ሰው የራሱ እቅድ ነበረው፣ ነገር ግን ከዚህ ህዝብ ጋር ለመስማማት ትንሽ ከፍ ብሎ ማቀድ፣ ትንሽ መስራት፣ የአምስት አመት እቅድን ቢያንስ ወደ አስር አመት ማስፋፋት ይኖርበታል።እና የዛን ጊዜ በእንደዚህ አይነት ዝግጅት ላይ ከሚሳተፉ ከላይኛው ማህበረሰብ ሰዎች ጋር በደንብ ተቀላቅሎ ዘና ብሎ ማውራት ይችል ይሆናል..እስከዛው ግን   እንደተነጠለ መቆየት መርጧል፡፡

በሀሳብ ተውጦ ሳለ ድንገት ከኋላው መጣችና‹‹ሰላም ነህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ደህና ነኝ። ትንሽ የመጨናነቅ ስሜት እየተሰማኝ ነው።›› ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ብዙ አዲስ ፊቶች ሲመጡ እያየው ነው›› አለች ራሄል ። ‹‹ግን ከጊዜ በኋላ ታውቋቸዋለህ። ››
60👍1