አትሮኖስ
270K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
434 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
:
:
#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና  ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ ጭንቁርቁስ ቤት ከጭርቁስቁስ ሰዎች ጋር ለመቆየት ታስባለች? ››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ሊዋጥለት አልቻም…፡፡

በፀሎት ከጠፋችበት ቀን አንስቶ በመላ ሀገሪቱ ፍላጋ የተሰማሩትን በመቶ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን የሚመራው ..መረጃ የሚቀበለው አዲስ ቦታ ስምሪት የሚሰጠው እሱ ነው፡፡እና የእሱ እቅድ የሆነ ቦታ መኖሯን በሆነ መንገድ ቀድሞ ቢደርስበት እንደምንም ብሎ የራሱ ሰው በሚስጥር እንዲያገኛት አድርጎ በእጅ አዙር 5 ሚሊዬኑን የሽልማት ገንዘብ ለመቀባበል አቅዶ ከልቡ እየሰራ ነበር...እርግጥ እንደዚህ እያደረገ መሆኑን ቀድመው ቢደርሱበት ያለምንም ማቅማማት ግንባሩን በጥይት እንደሚነድሉት እርግጠኛ ነው…ግን በህይወት የተሻለ ነገር ማግኘት ሪስክ መውሰድ የግድ እንደሆነ የሚያምን ስለሆነ ነገሩን ልክ እንደቁማር ነው ያየው..‹‹ወይ በላለሁ..ወይ ደግሞ እበላለው››ብሎ ነበር ውሳኔ ላይ ደርሶ በተግባር ሲንቀሳቀስ የከረመው፡፡…አሁን ሰውዬው እንደሚሉት ልጅቷ የገመቱት ቦታ የምትገኝ ከሆነ ያ ሁ እቅዱ ውሀ በላው ማለት ነው፡፡ቦታውን ራሳቸው ቀድመው አውቀው ስለነገሩት ሽልማት የሚሰጡበት ምንም ምክንያት የለም….መኪናውን ወደእዛ ሲያሽከረክር በውስጡ በፀሎት የተባለው ቤት በፍፅም እንዳትገኝ እየፀለየ ነበር፡፡እንደደረሰ ከመንገድ ማዶ አስፓልት ጠርዝ ላይ መኪናውን ፓርክ አደረገና የመኪናው መስኮት በከፊል ከፍቶ ማጊሊያ መነፅሩን ወደእነ አቶ ለሜቻ ግቢ አነጣጠረና ገቢ ወጪውን መመልከትና በመሀከልም የተለየ ነገር ያገኘ ሲመስለው በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ጀመረ…
ስራ የጀመረው ከጥዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ቢሆንም እሰከ 10 ሰዓት ሁለት ሶስት ጊዜ አሮጊት ሴት ስትወጣ ስትገባ ከማየት ውጭ በግቢው ውስጥ አይን የሚስብ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም…ሰዓቱ እየረዘመ ሲሄድ ተስፋ እየቆረጠና እየተሰላቸ መጣ…ለዛሬ ይበቃኛል ብሎ 11 ሰዓት ላይ አካባቢውን ለቆ ወደቤቱ ሄደ ..
በማግስቱ በጥዋት ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የመጣው፣እና ሁለት ሰዓት ላይ የሚፈልገውን አገኘ ..ደጋግሞ ፎቶ አነሳው…በቤቱ አንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳላቸው አጣርቷል ..አሁን እየገቡ እየወጡ ያሉት ግን በተቀራራቢ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡አንደኛዋ የቤቱ ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነው…ሁለተኛዋ ግን የሚፈልጋት የባለፀጋው ቅምጥል ልጅ ትሁን አትሁን መለየት አልቻለም…የለበሰችው ልብስ የተለመደ አይነት ነው..በዛ ላይ ፊቷን ጭንቅላቷን ጭምር በሻርፕ ሸፍናለች…ዝም ብሎ ከመኪናው በመውረድና በእግሩ ወደ አጥሩ በመጠጋት ከቅርብ ርቀት በርከት ያለ ፎቶ አነሳና ለአቶ ኃይለ ልኡል ላከላቸው፡፡

አቶ ኃይለልኡል በዚህ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር በሰለሞን በሚሾፈር መኪና ከቢሾፍቱ ወደአዲስ አበባ እየተመለሱ ነበር፡፡ስልካቸው ድምፅ ሲያሰማ ከኪሳቸው አወጡና ተመለከቱት..መልዕክት መሆኑን ሲያዩ ከፈቱት…አይናቸው ተጉረጠረጠ….
‹‹እራሷ ነች ..ልጄ እራሷ ነች….ከጎናቸው ያለችው ሚሳታቸው ላይ ተጠመጠሙና ጉንጮቾን አገላብጠው ይስሙ ጀመር››
‹‹እንዴ ኃይሌ ምን ተፈጠረ..?ምን ተገኘ..አረ ንገረኝ?››
‹‹ይሄውልሽ..እንቺ እይው..ፊቷን ብትሸፋፈንም እራሷ ነች፡፡››ወይዘሮ ስንዱ ስልኩን ከባላቸው እጅ ተቀበሉና አፍጥጠው ተመለከቱ…..ከባላቸው በበለጠ በመደነቅ ኡኡ.አሉ…መኪናዋን በእልልታ አደባላለቁት…ሰለሞን የነገሩ ውል ስላልገባው መሪውን ጠመዘዘና የመንገዱን ዳር አስይዞ መኪናዋን አቆማት…በራፉን ከፍተው ወረዱ….እሱም ተከትሏቸው ወረደ‹‹አረ ለእኔም ንገሩኝ ምንድነው? እንዲህ የሚያስፈነጥዝ ደስታ፡፡››
‹‹ልጃችን የት እንዳለች አወቅን..እያት ተመልከት››ስልኩን ከሚስታቸው ተቀበሉና ለሰለሞን አቀበሉት..አንድ ፊቷ በቅጡ የማይታይ ወጣት ፎቶ ነው…ግን በፀሎት እንደሆነች ወዲያው ነው ያወቃት..ሙሉ ፊቷን ሳያይ እሷ እንደሆነች አንዴት እንዳወቀ አልገባውም…››
‹‹አየህ …ልጃችን እራሷ ነች…ሰው እንዳይለያት ነው ፊቷን የሸፋፈነችው……››
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለችው?››ጠየቀ ሰሎሞን፡፡
‹‹የት እዳለች ቆይ ነግራችኃላው››ብለው ስልኩን ተቀበሉና ደወሉ
‹‹ሄሎ….ፎቶው ደርሶኛል፡፡››
‹‹አዎ ሳስበው እሷ ትመስለኛለች››
‹‹አዎ እሷ እራሷነች…ከቦታው እንዳትንቀሳቀስ..እዛው ጠብቀን…ከቢሾፍቱ እየተመለስን ስለሆነ ከ15 ደቂቃ በኃላ ያለህበት እንደርሳለን››
‹‹ወጥታ ከሄደችስ…?ላስቁማት››
‹‹አይ..ልጄን ቀጥታ እኔው ነኝ የማገኛት..እንዳታስቆማት ትደነግጥብኛለች…ከቤት ከወጣች ዝም ብለህ በርቀት እየተከታተልክ ያለችበትን ታሳውቀኛለህ፡››

‹‹እሺ..ጌታዬ እንዳሉት አደርጋለው››
‹‹ጎበዝ ..እንዳስደሰትከኝ አስደስትሀለው…ቆንጆ ጉርሻ ይጠብቅሀል ››
‹‹እሺ ጌታዬ››ስልኩን ዘጉና‹‹በሉ ጊዜ አናባክን ..ግቡና እንሂድ››
‹‹እንዴ የት አንዳለች ንገረን እንጂ……?››ወ.ሮ ስንዱ ጠየቁ
‹‹ስንድ ልጃችን ሰዎቹ ጋር ነው ያለችው….››
‹‹የትኞቹ ሰዎች››
‹‹እነአቶ ለሜቻ ጋር..ማለቴ የልብ ለጋሾ ቤተሰብ ጋር ነው ያለችው››
‹‹ወይ ጉዴ….አሁን ምንድነው የምናደርገው?››እያሉ ወደመኪናው ገቡ፡፡ አቶ ኃይለልኡልም ተከትለዋቸው ገቡ….ሰለሞን በሰማው ያልተጠበቀ ነገር ግራ እንደተጋባና ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰላሰለ ገቢና ገባ፡፡ መኪናውን አንቀሳቀሳት…ባልና ሚስቶቹ በደስታ ሰክረው እሱን ከቁብ ሳይቆጥሩት እርስ በርስ በፈንጠዝያ ሲጎሻሸምና ሲሳሳሙ እሱ ምን ማድረግ እንዳለበትና ይሄንን ያለጊዜው ያጋጠመውን ነገር እንዴት እንደሚፈታ እያሰላሰለ ነበር የሚነዳው….
አቃቂ አቶ ለሜቻ ቤት ለመድረስ 500 ሜትር ያህል ሲቀራቸው የመኪናውን መሪ ወደግራ ጠመዘዘና ፊት ለፊት ከሚታየው ሆቴል ይዞቸው ገባ..ባልና ሚስቶቹ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሰለሞን…ምን እያደረክ ነው?››አቶ ኃይለልኡል ጠየቁ፡፡
‹መነጋገር አለብን››
‹‹ስለምን?››
‹‹አሁን ልጃቹህ ጋር ከመሄዳችሁ በፊት አረፍ ብለን መነጋገር አለብን››
‹‹ምን መነጋገር ያስፈልጋል…?በቃ እኔና እናቷ ሄደን ልጃችንን ወደቤት ይዘን እንሄዳለን….እንደምታየው  አሁን  ሁሉ  ነገር  ውብ  እና  የተስተካለከለ  ነው..አይዞህ

አታስብ…ከንተጋር  ያለንን  ነገር  እንቀጥላለን..ከሶስት  ቀን  በኃላም  ወደአልከው  ቦታ ትወስደናለህ››
መኪናውን  አቆመና  ሞተሩን  አጥፍቶ  ወደኃላ  ዞረ..ፊት  ለፊት  እያያቸው‹‹ይሄ  ነገር እንደምታስብት ቀላል ይመስላችኃላ?››
‹‹ማለት?››
‹‹አሁን ያለችበት ቤት ሄደችሁ በማንኳኳት..ነይ ልጄ በቃ አግኝተንሻል አሁን ወደቤትሽ ተመለሺ ብትሏት ..እሺ ብላ በደስታ ዘላ የምትጠመጠምባችሁ ይመስላችኃላ…እምቢ መሄድ አልፈልግም ብትል ምን ታደርጋላችሁ ?በግድ በጎረምሳ አሳዝላችሁ መኪና ውስጥ በመክተት ወደቤት ትወስዷታላችሁ….?ከዛስ..?አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፋችሁባት በራፍ ላይ ሁለት ጠብደል ጠባቂ ታቆማላችሁ?እስኪ ንገሩኝ ምንድነው የምደርጉት?››
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ
‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ በጣም ተመችታሀለች መሰለኝ?፡፡››
‹‹መጥቻለው….ምሳ አትጋብዢኝም?፡፡››
‹‹የእውነት መጣህ?››
‹‹አዎ ቢሮሽ ፊት ፊት መኪናዬን አቁሜያለው፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ››ብላ ስልኩን ዘጋች….5 ደቂቃ ነው ያስጠበቀችው፡፡ገና የቢሮዋን የህንፃ ደረጃ ስትወርድ ጀምሮ ነው አይኑ ውስጥ የገባችው…ሙሉ ሮዝ ቀለም ያለው ጉረድ ቀሚስና ኮት ለብሳለች…ፀጉሯ ወደኃላዋ ትከሻዋ ላይ እንዲተኛ ተደርጎል…ውብ ሆናለች….መኪናዋን ስለምታውቃት ብዙም ሳትደነጋገር ቀጥታ ወደእሱ ነው ያመራችው…ይህቺ ሴት እህቱ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው…ጓደኛም እንድትሆነው አይደለም…የፍቅር አጋሩ ሚስቱ ሊያደርጋት ነው ምኞቱ..ይሄ ምኞቱ ደግሞ አሁን በቅርብ በውስጡ የበቀለ ስላልሆነ ህመሙ ቀላል አይደለም…ገና አፍ ፈቶ በኮልታፋ አንደበት መንተባተብ በጀመረበት በጮርቃነት እድሜው ጀመሮ እሷ ሚስቱ እንደሆነች ያስብ ነበር፣እርግጥ በዛን እድሜ ሚስት ማለት እራሱ ትርጉሙ ምን ማለት አንደሆነ አያውቅም ነበር፣ቢሆንም ጭላንጭል የሆነ ግንዛቤ ነበረው…ሚስት ማለት አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ ሁሌ አብራ

የምትተኛ ሴት እንደሆነች ከአባትና ከእናቱ ግንኙነት መረዳት በቻለበት ጊዜ ነው፣ከእሱ ጋር ለዘላለም መተኛት ያለባት ሴት አስቴር እንደሆነች ወስኖ የነበረው፣በዛን የልጅነት ጊዜ እናቷ የቤታቸውን እንጀራ ልትጋግር ስትመጣ አስከትላት ስትመጣ ጀምሮ እዛው እሷን ማስቀረት ምኞቱ ነበር…እና ያ ምኞት ግለቱን ጠብቆ እየፋመ ነበር የቀጠለው…
ጊዜው ሲደርስ ግን ነገሮች ቀደም ብሎ እንዳሰባቸው ቀላል አልነበሩም…ገቢናውን ከፈተላት ገባች.. ጉንጩን አገላብጣ ሳመችው…ሁል ጊዜ የእሷ መሳም ከሌላው መሳም በጣም ይለይበታል…ወፈር ብሎ ወደፊት ግልብጥ ያለው ፍም ከንፈሯ ሰውነቱ ላይ ሲርፍ የተለየ ሙቀት ነው ሰውነቱ የሚያመነጨው…ልክ የጋለ ቢላዋ አካል ላይ ሲያርፍ የሚሰማው አይነት ትሽሽሽ..የሚል የማቃጠል የመለብለብና የመላጠ ስሜት……
‹‹አንተ ወፍረህ ነው የመጣሀው….ስራ ላይ ነበርክ ወይስ ጫጉላ ሽርሽር ላይ?››
‹‹በይው…አንቺም ተመችቶሻል…ምሳ የት አንብላ?››
‹‹ወደ እኔ ቤት ንዳው››
‹‹ምነው ከሰዓት ስራ የለሽም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቅዳሜ እኮ ነው…ግማሽ ቀን ነው የምንሰራው››
‹‹እና አራበሽም ..በልተን ብንሄድ አይሻልም?››
‹‹አይ ሰራተኛዬ አዘጋጅታ እየጠበቀችን ነው…ዘና ብለን ቤታችን ብንበላ ይሻላል….ወንድሜ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል››
‹‹እኔም ከሰዓት ስራ ስለሌለሽ ደስ ብሎኛል››ብሎ መኪናዋን ወደ አስፓልት መሀል አስገባና ነዳት….የእውነትም ከሰዓት ስራ የለኝም ብላ ወደቤቷ ይዛው እየሄደች በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…ከአመታት በኃላ መልሶ ዛሬ እድሉን ይሞክራል፡፡አዎ በስደት ከሄደበት ባእድ ሀገር ተመልሶ የመጣውም ለዚሁ ነው፡፡ከባሎ እንደተለያየችና እሱም በዛ ንዴት ከሀገር ውጭ መሰደዱን ሲሰማ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ የመጣው…አንሆ ተመልሶ በመጣበት ባለፉት ስድስት ወሮች እሷን ከገባችበት ድባቴ እንድትወጣና ያልተሳካ ትዳሯ ከፈጠረባትን የስነልቦና መሰበር እንድታገግም እንደወንድም እንደ ጓደኛም ከዛም አልፎ እንደባለሞያም  ከጎኗ  ሆኖ  ሲያግዛትና  ሲደግፋት  ነበር…አሁን  ግን  ልቧ  ሌላ  ፍቅር

ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ብሎ ያስባል..በዛ ላይ የእሱ እና የእሷ ፍቅር አዲስ ዛሬ የበቀላ ሳይሆን ድሮ በየሁለቱም ልብ ተዳፍኖ ያለ ነው…አሁን ያንን መቆስቆስና መልሶ እንዲቀጣጠል ትንሽ የፍቅር ቤንዚል ማርከፍከፍ ነው…ለዚህ ድርጊት ያበረታታው ሰሞኑን ያየው በአቶ ሃይለልኡል እና በወ.ሮ ስንዱ መካከል የተከሰተው የፍቅር ግርሻ ነው፡፡
‹‹አዎ…አስቴርን አገባታለሁ…ከበፊት ባሏ የወለደችውን አንድ ልጅም እንደልጄ አድርጌ አሳድገዋለው››በውስጡ አልጎመጎመ…‹‹እና በቅርብ ቀን እሷም ወንድሜ የምትለውን ጥሪ ትተውና ባሌ ብላ ትጠራኛለች…ልጇም አጎቴ ብሎ የሚጠራውን አቁሞ አባቴ እንዲለኝ
አደርጋለው››ይሄንን ስላሰበ ብቻ ውስጡ በደስታ ተፍነከነከ..ቤት ሲደርሱ እውነትም እንዳለችው ቆንጆ ምሳ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው፡፡እየተጎራረሱ በሉ፡፡ከምግብ በኃላ ብና ተፈላላቸው..እሷ ሁለት ሲኒ እሱ አንድ ሲና ጠጡና ተጠናቀቀ፡፡
‹‹እዚሁ ልንገራት ወይስ ይዣት ወጣ ልበልና ዘና ያለ ቦታ ወስጄ ዘና ባለ ስሜት ላይ ከሆነች በኃላ ልንገራት ››እያለ ሲወዛገብ ቆየና‹‹እ…ፕሮግራማችን እንዴት ነው….?ወጣ እንበል ወይስ እዚሁ ነው የምንቆየው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ…ወጣ እንላለን..ሱፐርማርኬት ወጥቼ መሸማመት አለብኝ..መጠነኛ ድግስ ደግሳለው፣ማታ እንግዳ አለብኝ››
ንግግሯ ግራ አጋባውም.. ደነገጠም፡፡
‹‹የማታ እንግዳ ምን አይነት ነው?›› our
‹‹አንተም አለህበት…ዛሬ እዚህ ነው አይደል የምታድረው?››
እሷ ጋር እንዲያድር ስለጠየቀችው ደስ ብሏታል ..ግን እንግዳውስ…?ለመሆኑ ማን ነው
…?ሴት ነው ወንድ?፡፡‹‹እሺ ..እዚህ ነው የማድረው…ግን እንግዳውስ?››
‹‹እንግዲህ እሱን ከመጣ በኃላ ነው የምናውቀው…ልደር ካለ ግን እምቢ ማደር አትችልም የምለው አይነት ሰው አይደለም››በማለት ግራ አጋቢ መልስ ሰጠችው፡፡መልሷ ይብልጥ ቁርጠት ለቀቀበት…ይሄኔ ከመስሪያ ቤቷ ባለደረቦች አንዱ ነው….ሀለቃዋ ይሆን እንዴ…?ቢሆንስ ልደር ስላለ እንዴት እሺ ልትለው ትችላለች..?››ወይ ሴቶች ምን አይነት ቅኔ የሆኑ ፍጡሮች እንደሆኑ ሁሌ እንደደነቀው ነው፡፡ወንድም ሴትም በአንድ ላይ ሰው ተብሎ

መፈረጁ  አግባብ  አይደለም….አስተሳሰባችን  እምነትና  ፍላጎታችን  ምኑም  እኮ አይገናኝም››ሲል በውስጡ አብሰለሰለና..ነገሮች እስኪደርሱ ጠብቆ ለማየት ወሰነ…
‹‹ከዛ በፊ የተመቻቸ ጊዜ ካገኘው ነግራታለሁ…እንደውም ከማታው ፕሮግራሞ በፊት የእኔን ሀሳብ መስማት አለባት››የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ‹‹በቃ እንሂዳ››አላት፡፡
‹‹እሺ፣ተነስ ብላ ቦርሳዋን አንጠለጠለችና ተነሳች..ተያይዘው ወጡ ..ያለችው ሱፐር ማርኬት ይዛው ከገባች በኃላ ምትፈልገውን ነገሮች ሁሉ ተገዝተው በመኪናው ከተጫኑ በኃላ.. ማኪያቶ እንጠጣ ብሎ አንድ ፀጥተኛ ካፌ ይዞት ገባና..ፊት ለፊት እንደተቀመጡ እንደምንም እራሱን አጠንክሮ ወደነጥብ መንደርደር ጀመረ
‹‹ለምን ወደውጭ እንደሄድኩ ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ሁለተኛ ዲግሪህን ለመማር ነዋ››
‹‹አይ ያማ ሽፋን ነው….እውነተኛ ምክንያቴን አንቺም በደንብ ታውቂዋለሽ..ወደውጭ የሄድኩት ባንቺ ተበሳጭቼ ነው፡፡››
‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ ግን ምንም ያደረኩት ነገር የለም››
‹‹እሱን ማግባት አልነበረብሽም››
‹‹ለምን …ታዲያ አንተን ወንድሜን ማግባት ነበረብኝ?››
‹‹ምን ችግር አለው?እርግጥ እንደወንድምና እህት አንድቤት አድገናል..ግን የስጋ ትስስር አልነበረንም››
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..

የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ  መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ

እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡

በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡

ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡

ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››

‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››

ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር  ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች

‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ከላይ የተለቀቀው ክፍል 24 ሳይለቀቅ 25  ተለቆ ነበር ክፍል 24 አሁን ተለቋል ለነበረው መዛባት ይቅርታ  እጠይቃለው🙏 ቤተሰቦች


ለሊሴና በፀሎት በእቅዳቸው መሰረት በአንቦ በኩል አድርገው ወንጪ በመድረስ የለሊሴ አጎት ቤት ከደረሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በአካባቢው ያሉ የአቶ ለሜቻ ዘመደች ጋር እየዞሩ ሰላም ማለት እና መጋበዙ እራሱ ማደረስ አልቻሉም…እሷ ብዙ የሀብታም ድግሶችና ፓሪዎችን እንጂ እንዲህ አይነት በየሳር ጎጆውና በየደሳሳ የቆርቆሮ ቤቶች እየዞሩ በግዳጅ መጋበዝ በህይወቷ አይታው የማታውቅ ትዕይንት ስለሆነ በጣም አስገራሚና ትንግርታዊ ነው የሆነባት..በየሄደችበት የሚቀርብላት እርጎ፤ ለወተት…የማር ወለላ…አንጮቴ……ጨጨብሳና  ገንፎ..ሁሉም  ውብ  ነበር፡፡በዚህም  የተነሳ  ወደፓርኩ

ለመሄድና ለመጎብኘት ጊዜ አላገኘችም..ቢሆንም በአካባቢው ቢያንስ የሚመጡትን 15 ቀን ስላምታሳለፍ ሁሉንም ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ እንዳላት ስላወቀች ብዙም አልተጨናነቀችም፡፡
ሰለሞንም የበፀሎትን ወላጆች ይዞ ወደወንጪ እያመራ ነው፡፡በመጀመሪያ እቅዱ ወደላንጋኖ ወይም ሰደሬ ይዞቸው ሊሄድ እንጂ ወንጪ የሚባል ስፍራ ፈፅሞ በአእምሮው አልነበረም..ግን በፀሎት ወደወንጪ እንደሄደች ስትነግረው ግን ወደያው ሀሰቡን ቀየረና ለእነአቶ ኃይለልኡል ሀሳብን ነገራቸው፡፡እነሱ የትም ሆነ የትም ለቦታም ብዙም ግድ ሳልልነበራቸው ወዲያው ነበር ሀሳቡን የተቀበሉት፡፡ከዛ ወዲያው ቻርተር አውሮፕላን ተከራይተው ወንጬ ኢኮቱሪዝም ፓርክ እንግዳ ሆነው ተከሰቱ፡፡ጉዞ ተገባዶ ከቻርተር አውሮፕላኑ እንደወረዱ እነሱን ባሉበት ትቶ ቀጥታ ወደኢንትራንስ ጌት ነው የሄደው
…ስለጠቅላላ የጉብኝቱ ፓኬጅ ማብራሪያ ጠየቀና ሁለት መኝታ ክፍል ተከራየ፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና ተከራይቶ እቃቸውን በመጫን ቀጥታ ወደተከራየበት ሎጅ ይዞቸው ሄደ…
ሰለሞን ወላጆቾን ወደወንጪ ይዞ መምጣቱን ለበፀሎት አልነገራትም፡፡እሷ የምታውቀው ወደላናጋኖ እንደሚሄዱና ሲደርስና ሲመቸው እንደሚደውልላት ነው፡፡
ወንጪ ከአዲስ አበባ በ135 ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ክልል በአንቦ እና በወሊሶ ከተሞች መካከል የሚገኝ ድንቅ ስፍራ ነው ፡፡ወንጪ ሀይቅ ከባህር ወለል በላይ 3000ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ 75 ሜትር ገደማ ጥልቀት ያለው ንፁህ እና ጥርት ያለ ሀይቅ ነው፡፡ሀይቁ ከ3000 ዓመት በፊት በተከሰተ እሳተ ጎመራ የተፈጠረ እንደሆነ ይነገራል፡፡በአካባቢው የሚነገሩ አፈታሪኮች እንደሚያስረዱት በወቅቱ እንደሶደም አይነት ተንቀልቃይ እሳተ ጎመራ ተነስቶ የአካባቢውን ፍጥረት ለረጅም ጊዜ እየበላ ከቆየ በኃላ ድንገት በቦታው አርባ አራት ምንጮች ተፈጥረው የሚንቀለቀለውን ውሀ ካጠፋት በኃላ በእሳተ ጎመራው አማካይነት የተፈጠረውን ረባዳ አካባቢ መሙላት ይጀምራል….ውሀው ግን ሞልቶ በመሀከል ትንሽ ደሴት በውሀ ሳትዋጥ ደረቅ መሬት ሆና ትቀራለች…ከዛ ያንን የታዘብ የአካባቢው ኑዋሪዎች ያቺ መሬት በውሀው ሳትሸፈን የቀረችው የተቀደሰች ስፋራ ስለሆነች ከአሁን በኃላ ቦታዋና እንደማመስገኛና ከፈጣሪ ጋር መገናኛ የተለየች ስፍራ አድርገን እንገለገልባታለን ብለው ይስማማሉ…በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ ቤተክርስቲያን ታንፆበታል፡፡

የውንጪ ኢኮቱሪዝም መዝናኛ..መንገዶቹ ጠባብ ስለሆኑና የመኪና መተረማመስ የአካባቢውን ተፈጥሮ እንዲያበላሽው ስለማይፈለግ .ማንኛውም ጎብኚ በራሱ መኪና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አይችልም…ግን ወደሎጆችም ሆነ ወደመዝናኛ ፓርኮች ወይንም ደግሞ ወደገበሬዎች መኖሪያ ቤት ለመሄድ የፈለገ ሰው የተለያዩ አይነት ቀላል የትራንስፖርት አማራጭ ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል..ለምሳሌ…የፈረስ ትራንስፖርት ..ሳይክል
…ኤሌክትሪክ መኪና ካልሆነም ደግሞ በጠባበቹ የአስፓልት መንገድ ግራ ቀኝ ያለውን ውብ ተፈጥሮና የፓርክ ክፍሎችን በመጎብኘት በእግሩ ወክ እያረገ ስጋውን ማዝናናት ነፍሱንም ማስፈንጠዝ ይችላል፡፡
አጠቃላይ የወንጪ የመንገድ ልማት 70 ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ተራራውን የሚዞር 10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ … ወደ ዲንዲ ሚሄድ ሀይ ወይ …ማራቶን ራጮች እንዲለማመዱበት ታስቦ የተሰራ የሩጫ ትራክ ሁሉም ውብ ነው፡፡በተለይ ተራራውን በሚዞረው መንገድ ላይ ሁለት ሶስት ሆነው ሳይክል እየነዱ ወይም ፈረስ እየጋለቡ ዙሪያ ገባውን መጎብኘት ገነት ደርሶ እንደመመለስ አይነት አስካሪ ስሜት ውስጥ ይከታል፡፡
አንድ ጎብኚ ሎጆቹን የመከራየት አቅም ማይኖረው ከሆነ እዛው ከሪስፕሽን በፓርኩ ግንባታ ምክንያት ከቦታቸው የተነሱ ገበሬዎች በመንግስት በካሳ መልክ የተሰራላቸው ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ ከክፍሎቹ የተወሰኑትን ለቱሪስት እያከራዩ ገቢ እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራላቸው ስለሆነ ቀጥታ እዛው ሬስፕሽን ቡክ ያደረገ ሰው የየትኛው የገበሬ ቤት እንደሚያድር ይነገረውና ቀጥታ እዛ ሄዶ በተመጣጣኝ ዋጋ ማደሪያ ያገኛል፡፡
ወንጪ ውበትን ለመግለፅ እግዜያብሄር እንደምሳሌነት ለማሳያ የፈጠራት ስፍራ ትምስላለች…ውበቷ ሀይቆ ብቻ አይደለም…ዙሪያዋን የከበቡት አረንጋዴ ልብስ የለበሱት ሰንሰለታማ ወጣ ገባ ተራሮች ፣አየሩ ሁሉ ነገር ጠቅላላ ውብ ነው፡፡አሁን ደግሞ ቦታውን የቱሪስት መነኸሪያ ለማድረግ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ይበልጥ ወደፍፁምነት ያስጠጋው ነው፡፡ደረጃቸውን የጠበቁ ሙሉ ተራራውን የሚሽከረከሩ የአስፓልት መንገዶች በእያንዳንዱ ኮርነር ላይ የታነፁ የተላያዩ ታሪክ እንዲሸከሙ ተደርገው በጥንቃቄና በጥበብ እንዲታነፁ የተደረጉ ህንፃዎች፤ ሎጆች፤ ካፌዎች ፤ፈንጠርጠር ብላው ከሩቅ የሚታዩ የገበሬ ቤቶች እርሻዎች …ሁሉ ነገር አይን ሞልቶ የሚፈስ የመንፈስ ትፍስህት ነው፡፡በወንጪ ኢኮቱሪዝም ፤የባንክ አገልግሎት፤ የአካባቢው ልጆች ተደራጅተው የሚሰጡት የሬስቶራንት አገልግሎት ፤የተለያዩ የባህል እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች..ካፍቴሪያ …አነስተኛና ትላልቅ

አዳራሾች…አንፊትያትሮች ሁሉም በአቅሙ ልክ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጎ የተዘጋጀ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ይገኛሉ ፡፡
ወንጪ ኢኮቱሪዝም ባህልና ተፈጥሮን ማእከል አድርጎ የተገነባ ነው፡፡የወንጪ አካባቢ ስድስት ወር አካባቢ ዝናብ የሚዘንብባት ለምለምና እርጥብ ቦታ ነው፡፡እነሰለሞን የተከራዩት ክፍል የእሱ ባለአንድ አልጋ ሲሆን የባልና ሚስቶቹ ግን ሁለት አልጋ በአንድ ክፍል ያለበት ለቀቅ ያለ ዘመናዊና ባህላዊ እቃዎች በስምምነት ተሰባጥረው ያሳመሩት… ለሀይቁም ሆነ የአካባቢውን ተፈጥሮታ ለማየትና ለማድነቅ ውብ እይታ ያለው በአንቦ ድንጋይ ተጠርቦ የተሰራ…በአሻራ ወይም በካርድ የሚከፈት ውብ ክፍል ነው፡፡ መኝታ ክፍሉ ዘመናዊ ማሞቂያ የተገጠመለት ስለሆነ ምቹ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ ተቀምጠው ወይም ተኝተው በተከፈተው መስኮት ቁልቁል ሀይቁን ሲመለከቱ ልብን ጥፍት ያደርጋል፡፡
ምሽት ነው…አራት ሰዓት አካባቢ..አቶ ኃይለ ልኡልና ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ክፍላቸው በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ቁልቁል የጨረቃዋ ብርሀን ወንጪ ሀይቅ ላይ ስታርፍ እና ከሀይቁ ጀርባው ያለውን ውብ ሰንሰለታማ ተራራ እያዩ ያወራሉ
‹‹ሃይሌ..ልጃችን ግን አሁን ወደአዲስአባ እንደተመለስን የምትመጣ ይመስልሀል?››
‹‹አታስቢ….ትመጣለች….››
‹‹እንደማስበው አሁን እሷ እንድንሆንላት የምትፈልገውን አይነት ወላጆች የሆን ይመስለኛል…፡፡››
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

የባልና ሚስቶቹ የምክር አገልግሎት እንደቀጠለ ነው…ዛሬ ወንጪ ከከተሙ አስራአራተኛው ቀን ላይ ሲሆኑ በዚህ የ14 ቀን ጉዞቸው ከፍተኛ ለውጥ ላይ ደርሰዋል…
አሁን በዚህ ሰአት ከሁለቱም ፊት ለፊት ተቀምጦ ተራ በተራ እያያቸው እያተናገረ ነው..
‹‹ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን

ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ደግሞ አስቡት የጋብቻ ዋናው አስፈላጊነትም ይህ ነው ፡፡ወንድ ልጅ በራሱ ፍፅም ወንድ ብቻ አይደለም..75 ፐርሰንት የወንድነት ሆርሞን ሲኖረው 25 ፐርሰንት ግን የሴት ሆርሞን በውስጡ ይዞል..ሴቷም በተመሳሳይ 75 ፐርሰንት የሴት ሆርሞን ሲኖራት 25 ፐርሰንት የወንድ ሆርሞን ይዛለች…አያችሁ የተፈጥሮን ረቅቂነት ..ሁለቱ ሲጣመሩ ...አንድ ሙሉ ወንድና አንድ ሙሉ ሴት ይገኛል ማለት ነው፡፡ለመዋሀድ ደግሞ ፍቅር ዋናው አገኛኝ መሰላል ነው፡፡››
‹‹ግልፅ ነኝ አይደል?››
‹‹አዎ .. ቀጥል››ሲሉ የተናገሩት አቶ ኃይለ ልኡል ናቸው
ሰለሞን ንግሩን ቀጠለ‹‹በአንድ መንደር ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት ሶስት ሽማግሌዎች ከቤቷ አካባቢ ከውጭ በፀጥታ ተቀምጠው ተመለከተች። ሴትዬዎም ከቤቷ ወጣችና ወደሽማግሌዎቹ ቀርባ" እናንተን ከዚህ በፊት አይቼያችሁ አላውቅም።ግን እዚህ በደጃፌ ለረጅም ጊዜ ተቀምጣችኋል። እርግጠኛ ነኝ እርቦችኋል። እባካችሁ ወደቤቴ ዘልቃችሁ ግብና ቤት ያፈራውን ቅመሱ››አለቻቸው።
ከመካከላቸው አንደኛው ሽማግሌ‹‹የቤቱ አባወራ በቤት አለ?››ሲሉ ጠየቋት። እሷም መለሰች‹‹አይ የለም››ስትል መለሰች።
ሽማግሌውም"ስለዚህ ወደቤት መግባት አንችልም።"ሲሉ መለሱላት።
ሴትዬዋም ወደውስጥ ተመልሳ ገባች ።መሸቶ ባሏ እንደመጣ ስለሰዎቹ ነገረችው። ባሏም
‹‹በይ አሁን ሂጂና ወደውስጥ እንዲገብ ጋብዢያቸው››አላት።
እሷም ወጣችና ወደውስጥ እንዲገብ በድጋሚ ጠየቀቻቸው‹‹ባለቤቴ ቤት ነው ያለው..ወደውስጥ እንድትገብም ጋብዛችኋል...እባካችሁ ወደ ውስጥ ዝለቁና የሆነ ነገር ቅመሱ››
‹‹እኛ በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም››አሏት
‹‹ለምን ?››ግራ ገብቷት ጠየቀች።

ከሽማግሌዎቹ አንድ መመለስ ጀመረ "ይሄውልሽ ..."ወደአንደኛው ጓደኛው በጣቱ እየጠቆመ "..እሱ አቶ ሀብት ነው ወደቤትሽ ከገባ ቤትሽ በሀብት ለዘላለም እንደተሞላ ይዘልቃል።...ይሄኛው ደግሞ አቶ ስኬት ነው ከአንቺ ጋር ተከትሎ ወደውስጥ የሚገባው እሱ ከሆነ ቤትሽ በስኬት ይሞላል።እኔ ደግሞ አያ ፍቅር እባላለሁ። እኔ ከገባሁ ደግሞ በዘመንሽ ሁሉ በቤትሽ ፍቅር ሞልቶ ይፈሳል።ክፍቱ ግን አስቀድመን እንደነገርንሽ ሶስታችንም በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም። ስለዚህ ወደቤትሽ ተመለሺና ከባልሽ ጋር በመማከር ከሶስታችን ማንኛችንን ወደውስጥ እንደምታስገብ ወስኑ "በማለት አብራሩላት።
እሷም እንደተባለችው ወደውስጥ ተመልሳ የሰማችውን ሁሉ ለባሏ አስረዳችው። ባሏ በሰማው ነገር ፈነጠዘ‹‹አቶ ሀብትን እንጋብዘው ፤ይግባና ቤታችን በሀብት ይሙላው፤ከእሱ የሚበልጥ ምን አለ?።››አላት።
ሚስትዬው ግን ውሳኔውን ተቃወመች"ለምን ስኬትን አንጋብዘውም፤ከሀብት ይልቅ ስኬት ነው የሚጠቅመን"አለች። እቤት ውስጥ የነበረች የልጃቸው ሚስት ወሬቸውን ስታዳምጥ ስለነበረ ወደእነሱ ቀረበችና‹‹ለምን ፍቅርን አንጋብዘውም..ከሁሉም በላይ በቤታችን ፍቅር ቢሞላ ይሻላል››የሚል ሀሳብ አቀረበች።
ጥቂት ካሠላሠሉ እና ከተከራከሩ በኃላ ባልና ሚስቶቹም በሀሳቧ ተስማሙ ፤ሚስትም ተመልሳ ወጣችና ወደእንግዶቹ ሄደች። ‹‹ከመካከላችው ፍቅርን ለመጋበዝ ወስነናል፤አያ ፍቅር እባክህ ተነስና ወደቤታችን ዘልቀህ ግባ...የተዘጋጀውን መአድም አብረኸን ተቋደስ..ሌሎቻችሁ ስላልመረጥናችሁ ይቅርታ "ስትል ተናገረች።
ፍቅር ተነሳና ወደቤት ለመግባት መንቀሳቀስ ሲጀምር ስኬትና ሀብትም ከተቀመጡበት ተነስተው ከኃላው ተከተሉት። ሴትዬዋ ግራ ገባት ‹‹አብረን መግባት አንችልም.. ከመሀላችን አንዳችንን ምረጪ አላላችሁኝም ነበር እንዴ?"ስትል ጠየቀች።
ከመሀከላቸው አንደኛው ማስረዳት ጀመረ‹‹ልጄ ስትመርጪ ስኬትን ወይም ሀብትን መርጠሽ ቢሆን ኖሮ አንዳችን ብቻ ነበር ወደቤትሽ የምንገባው።አሁን ግን የመረጥሽው ፍቅርን ነው። እኛ ደግሞ ፍቅር በገባበት ሁሉ ተከትለን መግባት ግዴታችን ነው።እኛም እራሳችን የፍቅር ምርኮኞች ነን።በዚህ ምክንያት ሶስታችንም የግድ ወደቤትሽ እንገባለን። ካዘጋጀሽውም መአድ እንቋደሳለን።ቤትሽንም ዘላለም በሚትረፈረፍ ሀብት ፤ስኬትና ፍቅር እንሞላዋለን።"አሏት። እሷም በደስታ እየፈነጠዘች ወደቤቷ ይዛቸው ገባች።

አያችሁ እናነት ሀብታም ናችሁ ስኬታማም ናችሁ…አሁን እየጣርን ያለነው ከመሀከሏችሁ ሾልኮ ተሰዶ ነበረውን ዋናውን ፍቅር ለመመለስ ነው..ፍቅር ከተመለሰ ሁሉ ነገር ሙሉ ይሆናል››
ዛሬ በዚህ በሰጠኋችሁ ምሳሌ በመሀከላችሁ፤በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ፍቅር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እያሰላሰላችሁ እንድታድሩ እፈልጋለው…ነገ እዚህ የምናሳልፍበት የመጨረሻ ቀናችን ነው…ተነገ ወዲያ ወደአዲስ አበባ እንመለሳለን….አሁን ዋናውን ነገር አጠናቀናል…በቀጣይ ቤታችሁ ሆናችሁ ልጃችሁም ተመልሳ ስራችሁን እየሰራች የምናደርገው ይሆናል…››በማለት የእለቱን ፕሮግራም አገባደደ
ባልና ሚስቶቹ ክፍላቸው ተያይዘው ሲገቡ የጠበቃቸው የተለየ ነገር ነበር፡፡የመኝታ ክፍላቸውን ግራና ቀኝ ግድግዳ ታኮ የነበረው ሁለት አልጋ ሁለቱም ወደመሀል ተስቦና አንድ ላይ እንዲገጥም ተደርጎ አንድ አልጋ ሆኗል….ግዙፉ የተዋሀደው አልጋ በነጭ ውብ አልጋ ልብስ ተሸፍኗል.. አልጋ ልብሱ መሀል ላይ በልዩ ዲዛይን የተሰራ ባለቀይ ቀለም የልብ ቅርፅ ይታያል..ሙሉ ወለሉ በቀይ ፅጌረዳ አበባ ከመሞላቱም በተጫማሪ ባለቆርቆሮ ልዩ ሻማ በመሀከል መሀከል ጣልቃ በማስገባት የተለያ ቀለም ያው ብርሀን እየረጩ ነው፡፡አደኛውን ግድግዳ ተጠግቶ በሚታይ ጠረጴዛ ላይ ሻማፓኝ መጠጥ ከውብ ብርጭቆዎች ጋር ይታያል…በሚገፋ ተሸከርካሪ ጠረጴዛ ላይ አስጎምዢ ምግቦች ተደርድረዋል…
ሁለቱም ባልና ሚስት በመጀመሪያ የተሳሳተ ክፍል የገቡ ነበር የመሰላቸው….የገዛ ሻንጣቸውንና ሌሎች የግል እቃዎችን ሲያዩ ተረጋጉና ወደውስጥ ዘልቀው በራፉን ዘጉት፡፡
‹‹ስንድ ይሄ ጉደኛ ልጅ የ20 አመት ጎረምሳ አደረገን እኮ..››
ወ.ሮ ስንዱ እንባቸው እየረገፈ ተናገሩ‹‹ያበቃልኝ መስሎኝ ነበር….እድሜ ለልጄ ይሄው ዳግመኛ ልጃገረድ ሆንኩ››
‹‹እንዴ ስንድ ዛሬ ሳቅና ፈንጠዝያ ነው እንጂ የምን ለቅሶ?››አሉን እጃቸውን ወደባለቤታቸው ጉንጮች በመላክ እንባቸውን ጠረጉላቸውና አቅፈው ሳሞቸው….‹‹በይ ዛሬ ምሽቱ የእኛ መሰለኝ..እንቀመጥ››
‹‹መጀመሪያ ልብሴን ልቀይርና ቀለል ያለ ልብስ ልልበስ…እስከዛ እንተ ቁጭ በል››
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ…

‹‹ሄሎ ሶል ምነው?››

‹‹እባክሽ ስለሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር… እኔ ክፍል ድረስ መምጣት ትችያለሽ?››

‹‹መቼ አሁን?››በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ አሁን››

‹‹እሺ በቃ መጣሁ››

‹‹ስልኩን ዘጋና ከተቀመጠበት ተነሳ…መልሶ ቁጭ አለ‹‹ሰለሞን ምን እያደረክ ነው…?በዚህ ሰአት ስለምን ጉዳይነው የምታወራት.?›እራሱን በብስጭት ጠየቀ፡‹‹፡መልሼ ደውዬ በቃ ተይው ነገ ይደርሳል ማለት አለብኝ..››ወሰነና ስልኩን አነሳ….ቁጥሩን ከመጫኑ በፊት የመኝታ ቤቱ በራፍ ተቆረቆረ…..

ስልኩን ወደ አልጋው ወረወረና ተንደርድሮ ሄዶ ከፈተላት…በፀሎት ሮዝ ቀለም ያለው ስስና ልስልስ ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች… ፀጉሯን ወደላይ ጠቅልላ በሻሽ አንድ ላይ ጠፍራ አስራዋለች…ውብና መራኪ ሆና ነው እየመጣችው …ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹….ምነው በሰላም ነው…?አስደነገጥከኝ እኮ››

ፊት ለፊቷ ተገትሮ ቆመ….ግራ ገባት
‹‹ሶል ምን ሆነሀል…?.ምንድነው የምትነግረኝ?››ጉጉትና ፍራቻ በተቀየጠበት ስሜት ጠየቀችው፡፡

ተንደረደረና በሁለት እጆቹ አገጯን ግራና ቀኝ ክንዶን ይዞ ወደእሱ አስጠጋት… ከንፈሯ ላይ ተጣበቀ….በቀላሉ አለቀቃትም…ምን ይህል ደቂቃ እንደተሳሳሙ ሁለቱም አያቁም …ምን አልባት አንድ ደቂቃ ሊሆን ይችላል …ምን አልባትም ዘላለምም ሊሆን ይችላል….ግን የሁለቱም ልብ በየውስጣቸው ሲንፈራፈር ታውቋቸዋል…ሁለቱም በአየር ላይ የሚንሳፈፉበት ክንፍ እንዳበቀሉ አይነት ስሜት ተሰምቷቸዋል….ለሁለቱም ያልተጠበቀና ልዩ ክስተት ነበር….ሁለቱም ደግሞ ከገዛ ራሳቸው ጋር እንኳን ተነጋግረው ሳይወስኑ በነገሩ መሆን ተስማምተው በደስታ ፈንጥዘዋል፡፡በፀሎት አራት ተኩል ላይ ሰለሞን ክፍል የሄደች ስድስት ሰዓት ሲሆን ነበር ወደክፍሏ የተመለሰችው፡፡እሱንም ለሊሴ ምን ትለኛለች የሚል ይሉኝታ ቀፍድዷት እንጂ እዛው እቅፉ ውስጥ ሟሙታ እየቀለጠች ቢነጋ ደስ ይላት ነበር፡፡እሱም እንደዛው፡፡
በማግስቱ እስከአራት ሰዓት ከአልጋቸው መውረድ አልቻሉም ነበር፡፡

‹‹ልጁ ምን ይለናል ብዬ ነው እንጂ ቀኑን ሙሉ ከዚህ አልጋ ባልወርድ ደስ ይለኝ ነበር››ወ.ሮ ስንዱ ተናገሩ
‹‹ከአልጋው መውረድ ነው ወይስ ከእኔ እቅፍ መውጣት ነው ያስጠላሽ?››

‹‹አንተ ደግሞ…ለምን ታሳፍራኛለህ?››
‹‹ይሄውልሽ ነገ ወደአዲስአበባ እንመለስ የለ ..የልጃችንን የንቅለተከላ የተደረገላትን አመታዊ የመታሰቢያ በአል ድል አድርገን ከደገስን እና አንዳንድ ነገሮችን ካስተካከልን በኃላ..ለአንድ ወር ሲዊዘርላንድ እንሄዳለን፡፡›

‹ማ እና ማ?››

‹‹እኔ እና አንቺ..፡፡ያው አሁን ዳግመኛ እንደተጋባን እና ጉዞውንም ልክ እንደጫጉላ ሽርሽር ቁጠሪው››

‹‹በጣም አጓጓኸኝ ..ግን እኮ ይሄ ያለንበትም ስፍራ ከሲዊዘርላንድ አይተናነስም››

‹‹ገባኝ… ግን ራቅ ብዬ ካንቺ ጋር መጥፋት ነው የምፈልገው…››

‹‹ውይ የፍቅር ግርሻ እኮ መጥፎ ነገር ነው…ግን እንደምታየው ከልጄ ጋር ላለፈው አንድ ወር አልተገናኘሁም…እኔ ለሌላ አንድ ወር ከእሷ ውጭ ማሳለፍ አልችልም››

‹‹አንቺ ደግ…በቃ ይዘናት እንሄዳለን…ሶስታችን እንደቤተሰብ ከእንደገና አብርን በፍቅር እንቆማለት….›

‹‹እሱ ያስማማኛል፡፡››አሉና ከአልጋቸው ላይ ወረዱ…ተጣጥበውና ተዘጋጅተው ከክፍላቸው ሲወጡ አምስት  ሠዓት ሆኖ ነበር፡፡የሰለሞንን ክፍል ሲያንኳኩ አልነበረም…ደወሉለት

..በደቂቃዎች መጣላቸው፡፡

‹‹እንዴት ነበር አዳር?››

‹‹ዕድሜ ላንተ ሁሉ ነገር ውብና ማራኪ ነበር››አቶ ኃይለልኡል መለሱ፡፡

‹‹ጥሩ …አሁን እርግጠኛ ነኝ እርቦችኃላ?››

‹‹አዎ …የራበን ይመስለኛል›››

‹‹በሉ ተከተሉኝ …ቆንጆ ቁርስና ምሳ አንድ ላይ እንዲዘጋጅላችሁ አድርጌለው…››ብሎ ይዟቸው ሄደ..፡፡

በቀይ መንጣፍ ያሸበረቀ ግዙፍ የሞጃ ሳሎን የመሰለ ክፍል ውስጥ ነው ይዞቸው የገባው….ልክ አዲስ ሙሽሮች እንደሚስተናገዱበት አዳራሽ ውብና ልዩ ተደርጎ ዲኮር ተደርጓል….ግዙፉ ጠረጴዛና ጠረጴዛውን የከበቡት ወንበሮች ከቆዳ የተለበጡ ውብና ልዩ ናቸው…ልዩ ልዩ ባህላዊ ቅርሶች ግድግዳው ሞልተውታል፡፡እየመራ ወሰደና ወንበሩን እየሳበ ሁለቱንም አስቀመጣቸውና ..ከፊት ለፊታቸው ዞሮ ቆመ….
‹‹አቶ ኃይለልኡልና ወ.ሮ ስንዱ…ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው፡፡ማለቴ ከአሁን በኃላ ያለውን ቤታችሁ ተመልሳችሁ መደበኛ ስራችሁን እየሰራችሁ የምናከናውነው ይሆናል፡፡እስከአሁን ላለው ግን በእውነት እናንተ ለእኔ ትልቅ ውለታ ስለዋላችሁልኝ ላመሰግናችሁ እወዳለው..ይሄንን ስራ ከልጃችሁ ከበፀሎት ስቀበል በከፍተኛ ፍራቻና በወረደ የራስ መተማመን ነበር…እናንተ ግን ለልጃችሁ ስትሉ ጠንክራችሁ አጠነከራችሁኝ….በሶስት ወርና በአራት ወር እፈተዋላው ያላልኩትን በመሀከላችሁ ያለውን ውስብስብ ችግር በአንድ ወር አዚህ ደረጃ እንዲደርስ አድርጋችሁ አስደመማችሁኝ..ይህ አንድ ወር ለእኔ ታላቅ ትምህርት

ያገኘሁበት ነው..በሀገራችን የማህበራዊ ስሪትና ባህል የጋብቻ አማካሪ ብሎ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ውጤታማ አይሆንም ተጠቃሚም አይኖርም ብዬ ተስፋ ቆርጬ ድርጅቴን ልዘጋ እያሰብኩ ባለሁበት ወቅት ነው የእናንተን ስራ ያገኘሁት…አሁን ግን ዘመናዊውን ሳይንስ በሀገራችን ተጫባች ሁኔታ አንፃር ቃኝተን በጥበብ ከተጠቀምነው የብዙ ውስብስብ ጋብቻዎችን ችግር ለመቅረፍ እንደሚቻልና ስራዬም ለማህበረሰቡ ጠቃሚ እንደሆነ እንድረዳ አድርጋችሁኛልና አመሰግናለው….በአጭር ቀናት ውስጥ ባሳያችሁት ውጤት ልጃችሁ ብቻ ሳትሆን እኔም ደስተኛ ነኝ፡፡
‹‹ልጄ ..አንተም እንደምትረዳው ወደእዚህ ጉዳይ ስንገባ ..አንተ ስለምትለው በእኔና ስንዱ መሀከል ስላለው ግንኙነት ማሻሻል ምንም አይነት ፍላጎትም ሆነ እምነት የለኝም ነበር…ልጄን ለማግኘት ስል ነበር ሳልወድ በግዴ የተስማማሁት…እያደረ ግን ሀሳቤን ሙሉ በሙሉ እንድቀይር አድርገሐኛል…ጋብቻዬ ጥሩ ባለመሆኑ ሕይወቴም ምን ያህል የተዛባ እና በጭንቀትና በሀዘን የተሞላ እንደሆነ እንዳስተውል አድርገሐኛል…እኔ ምን የህል አጥቼ ቤተሰቦቼንም ምን ያህል እንዳሳጣኋቸው እንዳስብና ወደቀልቤ እንድመለስ አድርገኀኛል..እኔ ነኝ አንተንም ሆነ ስንዱን ማመስገን አያለብኝ…በእውነት የእድሜ ልክ ባለውለታዬ ነህ…አንተ ከአሁን ወዲያ ልክ እንደልጄ ነህ….በማንኛውም ህይወት ጉዞህ እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ ከጎንህ እንደሆን ልታውቅ ይገባል፡፡እርግጠኛ ነኝ ነገ ተነጋ ወዲያ አዲስአበባ እንደተመለስን ልጃችንም ወደቤቷ ትመለሰላች ብዬ ተስፋ አደርጋለው…እሷ ስትመለስ የተቀረውን ነገር እናወራለን፡፡››

ሰለሞን‹‹እሺ ጥሩ አሁን ስለራባችሁ …ከዚህ በላይ በወሬ አልያዛችው ››እጁን ሲያጨበጭብ ነጭ ዩኒፎርም የለበሰ አስተናጋጅ መጣ…..‹‹ምግብ ይቅረብ…መጀመሪያ የእጅ ውሀ አምጡ በላቸው››ሲል አዘዘው…ልጁ በቆመበት በራፍ ላይ ላሉት ልጆች ምልክት ሰጠው፡፡ውብ የሆነ ባህላዊ ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ወጣት ሴቶች ውብ የሆነ ወርቅ ቅብ ማስታጠቢያ በእጃቸው ይዘው መጡና….አንደኛዋ አቶ ኃይለልኡልን ሌለኛዋ ወ.ሮ ስንደን ለማስታጠብ ጎንበስ አሉ…ሁለቱም ታጥበው..ቀና ሲሉ በተመሳሳይ ቅፅበት ነው የአንደኛዋ ፊት
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ድክምክም ብሎታል፡፡ግን ደግሞ አልጋው ላይ ተኝቷ በሀሳብ እየተንገላታ ነው፡፡ ሰለሞን በሁለት በኩል ስለት ባለው ሰይፍ የሚጫወት ህፃን አይነት ሰው እንደሆነ እየተሰማው ነው፡፡ሞያውን በተመለከተ ለሶስት አመት በከፍተኛ የፕሮፌሽናል ደረጃ በምድረ-አሜሪካ ሲሰራ አንድም ጊዜ እንደዚህ አይነት ክፍተት ተከስቶበት አያውቅም..በዛም በራሱ ሲመካና ሲኮራ ኖሮ ነበር፡፡አሁን ግን ወደሀገሩ ተመልሶ ባጋጠሙት የመጀመሪያ ደንበኞቹ ከፍተኛ የሚባል ሽንቁር ተከስቶበታል፡፡አንድ ባለሞያ የሞያውን ስነምግባር አክብሮ ስራውን መስራት የሚገደደው ለደንበኞች ደህንነትንና ጥቅም ሲባል ብቻ አይደለም…ለራሱ ለሞያው ክብርና ተቀባይነትም እያንዳንዱ ባለሞያ የስራ-አፈፃፀም ሁኔታ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡በሙስናና በጥቅማጥቅም የሚታለሉ ዳኞችና አቃቢ-ህጎች በሞሉበት ሀገር ፍርድቤት ሊከበርና ሊታመን አይችልም፡፡ሌላውም ሞያ እንደዛው ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረ ያጋጠመችው ትልቋ ደንበኛው በፀሎት ነች፡፡እርግጥ ቀጥታ ደንበኛው እሷ ሳትሆን ወላጆቾ ናቸው፡፡ከእነሱ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ የሞያው ስነምግባር በሚፈቅደው መንገድ ጥርትና ጥልል አድርጎ እየሰራ ነው፡፡ቢሆንም ቀጥታ ቀጣሪው ልጃቸው በፀሎት ነች፡፡እሷ ፍላጎቱን ተረድታ አፈቅርሀለው ብትለው እንኳን ፍቅሯ እሱ ለወላጆቾ በሚያደርገው የሞያ ድጋፍ ተፅዕኖ ስር የወደቀ ወይንም በይሉኝታ ስሜት የተቀነበበ ሊሆን ይችላል…ይሄንን ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም…በዚህም ምክንያት ከእሷ ጋር ደግሞ ያለው ግንኙነት እየሄደ ያለበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ከሞያ ስነምግባር ውጭም እንደሆነ ያምናል፡፡ይሄ ጉዳይ ነው በጣም እያስጨነቀው ያለው፡፡ ከበፀሎት ጋር የፍቅር ስሜት በተሰማበት ቅፅበት ሁለት ምርጫ ነበረው፡፡አንድም በእሷ ቀጣሪነት ወላጆቾን ለማከም የተዋዋለውን የስራ ውል አፍርሶ ነፃ መውጣትና.. ከልሆነም ልቡን ገስፆ እና ፍቅሩን በውስጡ አክስሞ ስራው ላይ ብቻ አትኩሮ መቀጠል፡፡ቢያንስ ስራውን በተዋዋለው መሰረት ሙሉ በሙሉ አጠናቆ እስኪጨርስ ድረስ እንደዛ ነበር ማድረግ ያለበት፡፡ግን ይሄው ሁለቱንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ‹‹ግን እኮ ይሄ በስራ አለም ቆይታዬ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀምኩት የሞያ ስነምግባር ጥሰት ነው››ሲል እራሱን ለማፅናናት ሞከረ…..፡፡ንግግሩ ግን እራሱንም ሊያሳምነው አልቻለም፡፡ ‹‹ስህተት የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻ ያው ስህተት ነው››የገዛ አእምሮ መልሶ የነገረው ነበር፡፡ ‹‹አሁን ወደኃላ መመለስ አልችልም…ይሄንን ጉዳይ ከዳር ላድርስና ..ከእሷ ጋር ያለኝ የፍቅር ግንኙነት የሚደርስበትን ከፍታ አይቼ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ ምን አልባት ሞያውን በክብር ብለቅና ወደሌላ ዘርፍ ብሸጋገር እንኳን ያዋጣኛል››ሲል ለጊዜው የታየውን መፍትሄ አስቀመጠ…የገዛ አእምሮው ግን ወዲያው ነበር አፍራሽ የሆነ ሀሳብ የሰጠው‹‹ሰውዬ ምን ነካህ..?ይሄንን ሞያ ለቀህ…ነጋዴም ብትሆን …ወይም ደራሲ… ሁሉም ሞያ አይነቱ እና ተጋላጭነቱ በመጠኑ ይለያይ እንደሆን እንጂ የራሱ ህጋዊም ሆኑ ሞራላዊ የስነምግባር ገደቦች አሉበት…በተለይ ፍቅርን በተመለከተ ሁሉም ሞያ ይፈተናል…አስተማሪ ብትሆን ተማሪህ ላይ አይንህን መጣል የለብህም…ማናጀር ሆነህ ፀሀፊህን መጎነታተል ስህተት ነው፡፡ሞያህን ሳይሆን አመለካከትህን ነው መቀየር ያለብህ… ራስህን አታሞኝ፡፡››አለው…. ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ማሰብ አልፈለገም….ጉዳዩን ለጊዜ አሳልፎ ሰጠና ብድርብሱን ተከናንቦ እራሱን ለእንቅልፉን አሳልፎ ሰጠ ....ወዲያው ነበር ያሸለበው…የሚገርመው ደግሞ አይኖቹ በተከደኑ ከሁለት ደቂቃ በኃላ ነበር በፀሎት ነጭ ቬሎ ለብሳ ጭንቅላቷ ላይ የሚያብረቀርቅ የወርቅ አክሊል አጥልቃ ግራና ቀኝ ጎኗ ላይ የበቀሉ ውብ ክንፏቾን እያማታች ከሰማዩ ላይ ሰንጥቃ መጥታ እቅፉ ውስጥ ስትገባ በህልሙ ያየው፡፡
///
በፀሎትና ለሊሴ ከወንጪ ከተመለሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡መሽተዋል…አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው…በፀሎት እና ፊራኦል ግቢው ውስጥ ካለ ግዙፍ የመንጎ ዛፍ ስር ጎን ለጎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው፡፡
‹‹እንዴት ነበር ወንጪ?››
‹‹ውይ ሲዊዘርላድ በለው፡፡››
‹‹እኔ ወንጪን እንጂ ሲዊዘርላንድን አላውቃትም፡፡››
‹‹አኔ ደግሞ አውቃታለዋ ለዛ ነው ያነፃፀርኩልህ..ደግሞ ዘመዶቻችን እንዴት ደግና ቀሽት መሰሉህ?፡፡››
‹‹የእኔም ዘመዶች እኮ ናቸው አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ቢሆንም ..አንተ ምንአልባት ከልጅነትህ ጀምሮ ስለምታውቃቸው …ብዙም ጣእም ላይሰጥህ ይችላል..ማለት ሁለም ሰው እንደእነሱ አይነት ዘመድ ያለው ስለሚመስልህ ተራ ነገር አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ….እንደእኔ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደዛ አይነት ዘመድ ሲኖርህ ግን በቃ ..ከአሁኑ እንዴት እንደናፈቁኝ ብታውቅ››
‹‹ገና በሁለት ቀን››
‹‹አዎ በሁለት ቀን››
‹‹አሁን ከእኛ ስትለይና ወደቤትሽ ስትሄጂ እንናፍቅሻለን ..?ማለት እኔ ናፍቅሻለሁ?››ለቀናት በውስጡ ሲያብሰለስለው የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹ምን ማለት ነው….?ወደየትኛው ቤቴ ነው የምሄደው?››
‹‹ወደቦሌው ቤትሽ››

‹‹ምን….ለሊሴ ነገረችህ››
‹‹እሷ ታውቃለች እንዴ?››
‹‹እሷ ካልነገረችሽ ታዲያ ማን ነገረህ?››
‹‹እራሴ ነኝ የደሰረስኩበት ..ወደ ወንጪ ከመሄዳችሁ በፊት ነው ያወቅኩት››
‹‹እኮ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?››
‹‹ያው እንዳልኩሽ የእህቴን ልብ ከተቀበልሽ በኃላ በሩቅ ሆኜ ለረጅም ጊዜ ስከታተልሽ ነበር..ስለዚህ በደንብ አውቅሻለው…እዚህ ቤት ከመጣሽ ከሳምንት በኃላ ጀምሮ ከፍተኛ ጥርጣሬ አድሮብኝ ነበር..ከዛ ምን አደረኩ አንድ ቀን ስትተኚ ሻርፕሽን ሙሉ በሙሉ ከፊትሽ ላይ ገፍፌ ተመለከትኩሽ…እና ኦርጅናለዋ በፀሎት መሆንሽን አረጋገጥኩ፡፡
‹‹ትገርማለህ..ከዛ ፀጥ አልክ?››
‹‹ምን ላድርግ…ምንም ማለትና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወቅኩም ነበር፡፡››
‹‹አሁንስ አወቅክ?››
‹‹አይ….አንቺ ንገርኝ እስኪ …ምን ልታደርጊ ነው…?እስከመቼ ነው ከወላጆችሽ ምትደበቂው?››
‹‹ወላጆቼን በቀደም አግኝቼቸዋለው..እዚህ መሆኔን ያውቃሉ››ብላ ያልጠበቀውን ዜና ነገረችው፡፡
‹‹ጥሩ..እሺ እነአባዬን እንዴት ልታደርጊ ነው….?እንደዋሸሻቸው ሲያውቅ በጣም ነው የሚያዝኑብሽ…በአንቺ ብቻ ሳይሆን እኛም አውቀን ከነሱ ደብቀን ዝም በማለታችን ምን እንደሚወጥን አላውቅም? በጣም ጨንቆኛል›ብሎ እውነተኛ ስሜቱን ነገራት፡፡
‹‹ይቅርታ ፊራኦል..እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ስላስገባዋችሁ በጣም አዝናልው…ግን በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ውስጥ እፈተዋለው…ማለት እናንተ ቀድማችሁ እንደምታውቁ ሳላሳውቅ እፈተዋለው››
‹‹እስኪ እናያለን…››

‹‹እኔ የእህትህን ልብ የተሸክምኩ በፀሎት መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ምን ተሰማህ?››
‹‹ግማሽ ሀዘን ግማሽ ደስታ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ለረጂም ጊዜ ላናግርሽና ቀርቤ ላወራሽ የምመኝሽ የእህቴን ከፊል አካል የተሸከምሽው በፀሎት የገዛ ቤቴ መጥተሸ ከእኔ ጋር አንድ መአድ እየቆረሽ መሆንሽን ሳውቅ ፍጽም ድስታ ነው የተሰማኝ…በሌላ ጎኑ ደግሞ ያችኛዋን በፀሎት አፍቅሬት ስለነበር….ሌላ በፀሎት እንዳልሆንሽ ሳውቅ ቅር ብሎኛል››
‹‹ከመቀመጫዋ ተነሳችና እላዩ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመችው‹‹….የእኔ ወንድም
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

ጥዋት ሶስት ሰዓት አካባቢ ነበር ከክፍሏ ወስደው ለምርመራ አንድ ክፍል ያስገቧት፡፡የሆነ አንድ መርማሪ ፖሊስ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ለመመርመር የምትሄድ ሳይሆን ወደሞት የምትሄድ አይነት መስሎ ነው የተሰማት፡፡ምን አሲረውና ነገሮችን እንዴት እንዴት አጣመው እንደሚጠብቋት ምንም ስላማታውቅ በጣም ነው የፈራችው፡፡በዚህ ሰዓት እንደዛ ያበሳጫት እና በውድቅት ለሊት እቤቷን ለቃ እንድትበር ያደረጋት አላዛር ከጎኗ ቢሆን ተመኘች፡፡እንደምንም ብሎ ከዚህ ነገር እንደሚያወጣትና እንደሚታደጋት እርግጠኛ ነች፡፡ምንም እንኳን የሀዘኗ እና  የብስጭቷ ምንጭ ቢሆንም ከመጠን በላይ እንደሚያፈቅራት እና እሷን ከክፉ ነገር ሁሉ ለመጠበቅ ህይወቱን ጭምር እንደሚሰጥ እርግጠኛ ነች፡፡ለዛም ነው…ጨክና ልትጎዳው የማትደፍረው፤ለዛ ነው ጥላው ለመሄድ አቅም ያጣችው፡፡ከፈለገች  ችግሯን ለህግ አቅርባ ግማሽ ንብረቱን ተካፍላ ልትፈታው እንደምትችል ታውቃለች፡፡ግን እንዴት ብላ…?ይዟት የሄደው ፖሊስ አንድ ክፍል አስገባትና እንድትቀመጥ አዟት ተመልሷ ወጣ፡፡ወዲያው ሽክ ያለ ወታደራዊ ዩኒፎርሙን የለበሰ…ባለማዕረግ መሆኑን ተከሻው ላይ   ባለው የኮከብ ምልክት ማወቅ የሚችል ፖሊስ ገባና   ወደተሸከርካሪ ወንበሩ ሄዷ ተቀመጠ….
ሰሎሜ አንገቷን እንዳቀረቀረች የሚለውን መጠበቅ ጀመረች፡፡

‹‹እሺ ስራችንን እንቀጥል፡፡››ሲል በሻካራ እና በሚያርድ ንግግር ተናገራት፡፡ድምፁ በብርሀን ፍጥነት ነው ተምዘግዝጎ ልቧ ላይ ያረፈው፡፡ፈራ ተባ እያለች ቀና ብላ አየችው፡፡

….አቀርቅሮ እየፃፈ ነው፡፡ድንዝዝ አላት፡፡.ይህ ተአምር ነው፡፡ሄን ሰው ታውቀዋለች፤.ለዛውም ስረ መሰረቱን፤መላ ማንነቱን፤.ውስጡንና ውጩን፤የሚወደውንና የሚጠላውን፤የሚያበሳጨውንና የሚያስቀውን ነገር በጠቅላላ….ሰውነቱ ላይ ያሉትን ጠባሳዎችና የማርያም ስሞሹን በጣቅላላ ቦታቸውን ከነቁጥራቸው ታውቅቸዋለች፡፡

‹‹አሌክሶ….!!››
የሚፅፈውን አቆመና ቀና አለ…በመደነቅ አፍጥጣ የምታየውን ሴት በተራው አፍጥጦ አያት

‹‹ሰሎሜ ነኝ እንዳትይ?››

‹‹አዎ አሌክሶ..ሰሎሜ ነኝ….ወንድሜ ከየት ተገኘህ?››

‹‹በፈጣሪ…ምን አይነት ጉድ ነው..?››መቀመጫውን ለቀቀና ዞሮ ወደእሷ ሄደ፡፡ ተጠመጠመባት…ደረቱ ላይ ለጥፎ ከሰውነቱ አጣብቆ ወዘወዛት፡፡የልቧ ድውድውታ ለልቡ ተሰማው፡፡ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…ከንፈሯ ከመጠን በላይ ጉንጮቹን አጋሉት….ለአስር ደቂቃ መላቀቅ አልቻሉም፡፤የክብር ወንበሩን ሙሉ በሙሉ ዘንግቶ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አለ፡፡
‹‹ወይኔ ሰሎሜ…አንቺ ትዳር እንዲህ ያሳምራል እንዴ?››ሲል እውነታኛ የመደነቅ ስሜቱን ሳይሸሽግ ጠየቃት›፡፡

ቅዝዝ ባለ ድምፅ‹‹እንደዛ ነው ብለህ ነው…?››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹ታዲያ ሌላ ሚስጥር አለው..?ከሆነ እኛም እንጠቀምበት ይነገረን››

‹‹አንተስ ብትሆን ከዚህ በላይ ምን ትሆን..? አምሮብሀል..ቆፍጣናና ወንዳወንድ ሆነሀል..በዛ ላይ ዩኒፎርሙ ያምርብሀል….ባለግርማ ሞገስ አድርጎሀል››አለቸው..

ንግግሯ ከዚህ በፊት ከማንም ሰምቶት ከሚያውቃቸው ሙገሳዎችና አድናቆቶች ሁሉ ወደር የሌላቸውና ልብን የሚያሞቁ ሆነው ነው ያገኘኛቸው፡፡

‹‹ባክሽ አታሳፍሪኝ፡፡››
‹‹ትገርማለህ ግን ..እዚህ ሆነህ ነው ዝም ያልከኝ?ምን አለበት ታዲያ አድራሻዬን ወስደህ ብትደውልልኝ?››

‹‹እኔ እንጃ….እቴቴ አግብታለች ብላ ስትነግረኝ  ደነገጥኩ መሰለኝ አድራሻሽን ሆነ ስልክሽን ልጠይቃት አልቻልኩም፡፡››

‹‹አልቻልኩም ነው ወይስ አልፈለኩም?››

በጀመሩበት ርዕስ እንዲገፋበት ስልፈለገም‹‹አሁንም ነገረኝነትሽ አልተውሽም ማለት ነው?››አላት ፡፡

‹‹አንተ ነገረኛ ነበርኩ እንዴ..?ከአብሮ አደግህ ጋር አትሰደድ የሚባለው እኮ ለዚህ ነው… ለመሆኑ ከተለያየን ስንት አመት ሆነን ማለት ነው?፡፡››

‹‹ስድስት አመት መሰለኝ፡፡››በግምት መለሰላት፡፡

‹‹ግን በዚህ ስድስት አመት ውስጥ አንዴም ልታገኘኝ ሞክረህ አታውቅም፡፡የሚገርመው ደግሞ በየጊዜው ለእናቴ ትደውልላታለህ ….ብር ትልክላታለህ….ብዙ ብዙ ነገር….›› ወደሚሸሸው ርዕስ መልሳ ከተተችው፡፡

‹‹ያው መቼስ እቴቴ ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለእኔም እናቴ ነች፡፡ወላጆቼን ካጣሁ በኋላ እንደራሷ ልጅ ተቀብላ ትምህርቴን እስክጨርስ  ከአንቺ እኩል አሳድጋኛለች…እና እሷን ችላ ማለት አልችልም››

‹‹እኔንስ ..እሺ ከልጅነታችን ጀምሮ ጓደኛ እንደሆን እርሳው …ግን እህትህ አልሆንኩልህም ነበር?እናቴ ለእኔ ያላትን ፍቅር ቀንሳ ላንተ ስትሰጥ ከመደሰት ውጭ ለምን ብዬ ተቃውሞ አሰምቼ አውቃለሁ….?ለምን እኔን ነጥለህ እረሳኸኝ››

‹‹ባክሽ..ይቅር በይኝ….ጉዳዩ የተወሳሰበ ነው….ቀስ ብዬ አስረዳሻለሁ፡፡›

‹‹ምንም ብታስረዳኝ የሚገባኝ አይመስለኝም፡፡››

‹‹አይ እሱስ ትክክል ነሽ..ያው እንደምታውቂው ትምህርት እንደጨረስን  ወዲያው. ፖሊስነት ተቀጥሬ ማሰልጠኛ ገባሁ…ከዛ ከወጣሁ በኋላም  ለአለፉት ሶስት አመት ድሬ ደዋ ነበር የምሰራው..እዚህ ተቀይሬ ከመጣው ገና ሁለት ወሬ ነው፡፡››

‹‹የፖሊስነት ስልጠናውን ጨርሰህ ድሬ ደዋ እንደተመደብክማ አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ እንደውም ድሬ ድረስ ሄጄ ምን እንዳስቀየምኩት ልጠይቀው ብዬ አስብና ደግሞ የማላውቀው ሀገር ሄጄ ባላገኘውስ?አግኝቼው የት አውቅሻለሁ ብሎ ፊት ቢነሳኝስ? ብዬ ብዙ ብዙ ነገር በማሰብ ፈርቼ ተወዋለው፡፡››

አዎ ሰሎሜ እንዳለችው ከቡዙ አመት መጠፋፋት በኃላ ነው  የተገናኙት፡፡ከሰፈር ከለቀቀ  በኃላ አግኝቷትም ሆነ አይቷት አያውቅም፡፡ከሰፈርም ከቤትም ርቆ  የጠፋበት ምክንያት ረጅም ነው፡፡ ግን ድንገት ፖሊስ ቤት ተቀጥሮ  ለስልጠና  ገባ….በምክትል ኢኒስፔክተርነት  ማዕረግ ተመርቆ  መርማሪ ፖሊስ ሆኖ  ከአዲስ አበባ ብዙ ኪሎ ሜትር ርቆ ድሬ ደዋ በመመደብ ስራ ጀመረ፡፡ስለእሱ ይሄንን ታሪክ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡በዚህ  የጊዜ ክፍተት መሀከል  ምን እየሰራና በእንዴት አይነት የህይወት መስመር ሲኖር እንደነበረ አታውቅም፡፡
በእሱ በኩል ግን ስለእሷ ዘወትር ማሰቡንና መተከዙን አላቆመም ነበር፡፡የዛሬ አመት አካባቢ እንደምንም ጨከን ብሎ እናቷን ለመጠየቅ  እቤታቸው ሄዶ ነበር፡፡እናቷን ቢያገኝም እሷ ግን አልነበረችም፡፡ከእናቷ ከእቴቴ ጋር ብዙ ካወጋና ከተጫወተ በኃላ በወሬ በወሬ ስለእሷ ጠየቀ፡፡የገዛ ጓደኛውን   ካገባች አመት እንዳለፋት ተነገረው፡፡በፊትም የሚጠረጥረው እና የሚጠብቀው  ነገር ስለነበር ብዙም አላስገረመውም …የት ነው ያገባችው…?ስልኳን ስጡኝ ወይንም ጥሯትና ላግኛት አላለም…እናትዬውም እንደዛ አይነት ሀሳብ አላቀረቡለትም፡፡ በዛም ምክንያት….በቃ የልቡን በልቡ ይዞ ምንም የተለየ ዓላማ  እንደሌለው ሰው ሌላ ጊዜ በድጋሚ መጥቶ እንደሚጠይቃት ለእናቷ ቃል በመግባት  ሹልክ ብሎ ወጣና ወደ ምድብ ስራው ተመለሰ፡፡
እንግዲህ ከአመት ቆይታ በኃላ መሆኑ ነው በዝውውር ወደ አዲስ አበባ የተመደበው ፡፡አዲስአበባ ከገባ ከሁለት  ወር  በኋላ ድንገት ባልገመተው  ተአምራዊ መንገድ እስረኛው ሆና አገኛት፡፡

ከሀሳብ እንደመባነን አለና  ‹‹ ያገባሽው አላዛርን እንዳደሆነ ሰምቼለሁ፡፡.››አላት

‹‹አድራሻህን ባታጠፋ ኖሮ የመጀመሪያ ሚዜው አንተ ነበርክ…የሚገርመው ደግሞ  ከመጣህ በኋላ እንኳን ለምን ልታገኘን እንዳልፈለክ ነው..?እኔም ሆንኩ  እሱ ጓደኞችህ ነበርን….››ለአመታት ሲከነክናት እና አእምሮዋን ሲበላት የነበረውን ጉዳይ ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቀችው፡፡
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================

ኩማንደር አለማየሁ የአላዛርን ስልክ ተቀብሎ እሷን ወደማረፊያ ክፍል ከላካት በኃላ ጥልቅ ትዝታ ውስጥ ነው የተዘፈቀው፡፡ከእሷ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋር የነበረው የልጅነት እና የወጣትነት ትዝታ በብዙ ውጣ ውረዶች የተሞላ፤ደስታንም ሀዘንንም በውስጡ ያጨቀ ነበር፡፡አዎ አለማየሁ እንደሚያስታውሰው ሰሎሜ ለሶስቱ ወንዶች ልክ እንደጨረቃቸው ነበረች፡፡እነሱ ደግሞ በዙሪያዋ እየተሸከረከሩ ውበቷን የሚያጎሉላት ፍንጥርጣሪ ከዋክብቶች፡፡እናም ሰሎሜ ሶስቱንም ጓደኞቾን የምትወድበት የራሷ የሆነ የተለየ ምክንያት እንደነበራት ይገምታል፡፡ለምሳሌ አላዛርን በውበቱና በልስልስ ባህሪው…እሱን በኮሚክነቱና በድፍረቱ ሁሴንን በጉብዝናው እና በብልሀቱ ፡፡

አሌክስ ፤አላዛር እና ሁሴን ከልጅነታቸው ጀምሮ በእሷ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደገቡ ነበር፡፡አረ ከእነሱም አልፎ ወላጆቻቸውን ጨምሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ችግር ውስጥ ገብተው እንደሚያውቀው ያስታውሳል፡፡አንድ ጊዜ የዘጠኝ አመት ገዳማ ልጆችና የሁለተኛ ክፍል ተማሪ እንደሉ ነበር፡፡ጊዜው የበልግ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ስለሆነ መስኩ ጠቅላላ ውሀ ባቆሩ መሬቶችና ጭቃ ባላቆጡ መንገዶች የተሞላ ነበር፡፡ታዲያ የትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜ ደውል ከተደወለ በኋላ ሰሎሜ ከእነሱ ተነጥላ ሳያዮት ሾልካ ትሔዳች፡፡እደዛ ያደረገችው ሽንቷ ወጥሯት ስለነበረ ወደ ሽንት ቤት ነበር፡፡ስትመለስ ግን ጎረምሳ ጎረምሳ ከሚጫወቱ የስድስተኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እጅ ትወድቃለች፡፡ሴቶቹ እድሜያቸው አስራዎቹ ቤት የገባና በቁጥርም ሶስት ነበሩ፡፡ዙሪያዋን ከበዋት ጆሮዋን እየቆነጠጡ ውሀ ያቆረ ሜዳ ውስጥ በባዶ እግሯቾ ገብታ እያንቦረጨቀች መዝሙር እንድትዘምርላቸው አስገደዷት፡፡
እንዳሏት እየዘለለች ስትዘምር በጭቃ የላቆጠው እና ውሀ ያቆረው መሬት እየተፈናጠረ የለበሰችውን ሙሉ ነጭ ቀሚስ እንዳልነበረ አበላሸባት…፡፡ከዛም አልፏ ፊቷና ጸጉሯ ላይ ሳይቀር ተፈነጣትጥሮባት.. በጭቃ የተሰራች አሻንጉሊት አስመሰሏት ነበር …በንዴትና በፍርሀት እንባዋ እየረገፈ ያሏትን ስታደርግ ቆየች..ልጆቹ የትምህርት ቤት የእርፍት ጊዜ ማለቁን የሚያበስር ደውል ሲደወል ነበር  ጥለዋት የሄዱት …ከዛ ምን ታድርግ ተማሪዎች ሁሉ ወደክፍል ከገቡ በኃላ እያለቀሰች ሄዳ ክፍላቸው ጀርባ  ባለ መቀመጫ ተቀመጠች፡፡እንደዛ ጨቅይታና ልብሷ ጠቅላላ ተበላሽቶ እንዴት ወደክፍል ትግባ..?አስተማሪውስ ምን ይላታል?፡፡ ወደቤት እንዳትሄድ ደግሞ ቦርሳዋ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡
በዚያን ቀን እሱን ጨምሮ  ሁለቱ  ጓደኞቾ እረፍትን ጨምሮ  ክፍል ውስጥ ባለመኖሯ እንዴት ተደናግጠው እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡‹‹የት ሄደች?››የሶስቱም ጥያቄ ነበር፡፡የሚቀርቧትን ሴቶች ሁሉ ቢጠይቁ አይተናታል የሚል ሰው አላገኙም፡፡…አስተማሪ መጥቶ ክፍለጊዜው ከመጀመሩ በፊት እሷን ፍለጋ ክፍሉን ለቀው በመውጣት የትምህርት ቤቱን አጥር ጊቢ በሳምሶማ ሩጫ ማሳስ ጀመሩ፡፡በስተመጨረሻ ከክፍላቸው ጀርባ   እንዳልሆነች  ሆና አገኞት፡፡….ሶስቱም ነበር አብረዋት ያለቀሱት፡፡በዛን ወቅት ሲያያት የተሰማውን ድንጋጤና ንዴት ትዝ አለውና ፈገግ አለ ና ወደ ትዝታው ተመለሰ፡፡
በወቅቱ ወደ ቧንቧ ወሰዷት ..ፊቷንና፤ ፀጉሯን እና እግሮቾንም  በማጣብ  የአንዳቸውን ጃኬት አለበሷት…ሶስቱም ወደክፍላቸው ገብተው የእሷን እና የራሳቸውን ቦርሳ ጭምር በመያዝ ወጡና እሷን መሀከል አድርገው በማፅናናት  ወደቤት ነበር ይዘዋት የሄድት፡፡
ከዛ ምሽቱን ሙሉ በወላጆቻቸው ተገደው ወደቤት  እስኪገቡ ድረስ ‹‹እንዴት አድርገን ነው የእኛን ንግስት ያስለቀሷትን ሴቶች በእጥፍ የምናስለቅሳቸው?›› ብለው ሲማከሩና እቅዶች ሲነድፉ አመሹ ፡፡

የእነሱን ሰሎሜን ያቆሸሾትና  ያስለቀሷት ልጆቹ ሰሚራ፤ ሳራና፤ ሰላም ይባለሉ እንደነበር አሁን ድረስ ስማቸውን ከነመልካቸው ያስታውሰዋል፡፡

‹‹እኛ ሶስት ነን አይደል?››ሲል ነበር አለማየሁ ጓደኞቹን የጠየቀው፡፡

‹‹አዎ››መለሱለት፡፡

‹‹እሺ ሰሎሜን ያስለቀሷትም  ሴቶች ሶስት ናቸው››

‹‹አዎ ትክክል ሶስት ትላልቅ ሴቶች ናቸው››መለሱለት፡፡

‹‹ጥሩ..አንዳ እንድ እንከፋፈላቸዋለን››አለ አለማየሁ፡፡
አላዛር ተቃወመ‹‹አይሆንም እኔ አልስማማም››

‹‹ለምንድነው ማትስማማው?››

‹‹እኔ ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሴት አልፈልግም…..የእኔን ድርሻም ከፈለጋችሁ ተካፈሉና ውሰዷት››ሲል ነበር አቋሙን ያሳወቀው፡፡

‹‹አንተ ጀዝባ የሆንክ ልጅ …የምንካፈላቸው እኮ የእኛ  ልናደርጋቸው አይደለም.. ልናሰቃያቸውና ልናስለቅሳቸው ነው…ለሰሎሜ  ልንበቀልላት ነው፡፡››

ሁሴን ‹‹ገባኝ..ለመበቀል ግን ለምን መከፋፈል አስፈለገ?››ሲል ጠየቀ

‹‹‹ለእያንዳንዳችን የደረሰችንን ሴት የሆነ ዘዴ ፈልገን በተማሪ ፊት እንድታፍር ፤ እንድታለቅስና እንድትፀፀት እናደርጋታላን፡፡ታዲያ ከሶስታችን በጣም በአስቂኝና አስደናቂ መንገድ ተጠቅሞ ማስለቀስ የቻላ የበለጠ ሰሎሜን ያፈቅራታል ማለት ነው፡፡››እንደዚህ አይነት ሀሳብና እቅድ በዛ እድሜ እንዴት ማመንጨት እንደቻለ ዛሬም ሲያስበው በራሱ ይገረማል፡፡

ሁሴን‹‹ተስማምቼለው…እኔ ከሁለታችሁም በላይ ጂኒዬስ ስለሆኑክ ካሁኑ መሸነፋችሁን እመኑ››ሲል ጎረረ፡፡

‹‹ሞኞ በትምህርት ጎበዝ ሆንክ ማለት በእንደዚህ አይነት ነገርም ጎበዝ ነህ ማለት አይደለም?››ሲል ነበር  የመለሰለት፡፡
በክርክራቸው የተሰላቸው አላዘር‹‹እባካችሁ አትጨቃጨቁብኝ. .አሁን እንዴት አድርገን ነው ሴቶቹን ምንካፈላቸው››ሲል ግራ የገባውን ነገር ጠየቀ፡፡

‹‹እጣ እንጥላለን›› ብለው ተስማሙና በዛው መሰረት ተከፋፈሉ…ለሁሉም የአንድ ሰምንት ጊዜ ተሰጣቸው፡፡

ይሄ ውይይት በተደረገ በአራተኛው ቀን ሰላም በምትባለው ልጅ ላይ የመጀመሪያው ጥቃት ደረሰባት፡፡ሁሴን ለመጀመሪያ ሁለት ቀናት ልጆቹን ስር ስራቸው እየሄደ የሆነ ቦታ ተቀምጠው ሲያወሩ በሆነ ከለላ እየተደበቀ የሚያወሩትን በመስማት መረጃ ሰበሰበ፡፡በሶስተኛው ቀን እንደምንም ወደስድስተኛ ክፍል ሾልኮ ገባና ከሰላም ቦርሳ ውስጥ አንድ ደብተር በመስረቅ ወደቤቱ ይዞ ሄዳ፡፡ከዛ ለሁለት ሰዓት ያህል  ፊደል   አጣጣሏንና የእጅ ፅሁፏን ሲለማመድ ቆየ..ከዛ እርግጠኛ ሲሆን ያሰበውን ወደማድረግ ተሸጋገረ፡፡

በእሷ ስም ለአንዱ የክፍሏ ልጅ ደብዳቤ ፃፈ፡፡

ውድ ወንድይራድ…..እንዴት ነህ..?እኔ የአንተ ፅጌረዳ ከአንተ ሀሳብና ናፍቆት በስተቀር ሰላም ነኝ፡፡ይሄንን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ምን ያህል እንደማፈቅርህ ፊት ለፊትህ ቆሜ  ልነግርህ መድፈር ስላቃተኝ ነው፡፡ታውቃለህ ደግሞ እነዛ አስጠሊታ ሁለት ጓደኞቼ ሁል ግዜ እንደተጣበቁብኝ ነው…ሲያስጠሉ፡፡ውዴ ከአሁን በኋላ አንተን ካገኘሁ እነሱ አያስፈልጉኝም…ድሮውም እንደመደበሪያ ነበር የምጠቀምባቸው፡፡ውዴ በእርግጠኝነት አንተም እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ…እንደእኔ አይነት ቆንጆ እንዴት ላታፈቅር ትችላለህ?፡፡ለማንኛውም መልስህን በጉጉት እጠብቃለው፡፡ደግሞ የመልሱን ደብዳቤ ስትሰጠኝ አነዛ ቅናታም  ጓደኞቼ እንዳያዩህ ተጠንቀቅ፡፡
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር ቀኑን ሙሉ ሚስቱን ፍለጋ ሲባዝን ውሎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ስልክ ተደወለለት..ቁጥሩን አያውቀውም…ግን ደግሞ ሰሎሜን ካገኛችሁ ደውሉልኝ ብሎ አደራ በማለት ስልኩን ለብዙ ሰው ስለሰጠ  በትልቅ ተስፋና ጉጉት ነበር በፍጥነት ያነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር ነህ?››ጎርናና ሻካራ የወንድ ድምፅ፡፡

‹‹አዎ ነኝ ፡፡ማን ልበል?››

‹‹ይሄንን ድምፅ አታውቀም?››

ተበሳጨ…ዛሬ የማንንም ሰው ድምፅ ለማወቅ ለአእምሮው የቤት ስራ የሚሰጥበት ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡አንኳን የማያውቀውን ሰው ድምፅ የራሱንም ማንነት ለመርሳት ትንሽ ነው የቀረው‹‹ይቅርታ ማን ልበል..?እየነዳሁ ነው››አለ ኮስተር ብሎ፡፡

‹‹አሌክስ  ነኝ››

በታላቅ ድንጋጤ መኪናውን ወደ ዳር አወጣና አቆማት…..

‹‹አሌክስ አልኬስ…አሌክሶ የእኛ  እንዳትሆን?››

‹‹አዎ አሌክስ ነኝ…አሌክስ የእናንተው…የልጅነት እናም የጉርምስና ጊዜ ጓደኛችሁ››

‹‹ይገርማል…ፈፅሞ ያልጠበቅኩት ጉዳይ ነው…ለመሆኑ አለህ…?

ድሬደዋ እንዳለህ ሰምቼ ነበር..ግን ስልክህን ማግኘት ስላልቻልኩ ልደውልልህ አልቻልኩም፡፡››

‹‹አዎ አሁን ግን አዲስ አበባ ገብቼለሁ››

‹‹በጣም ይገርማል…አሌክሶ አሁን የሆነች ችግር ገጥሞኝ እሷን ለመፍታት እየተሯሯጥኩ ነው…..ይህ ያንተ ቁጥር ከሆነ ቆይቼ ልደውልልህ?››

‹‹ቆይ..እኔም ስለችግርህ ለማውራት ነው የደወልኩልህ››

አላዛር ድንግርግር አለው‹‹አልገባኝም?››

‹‹ችግርህ ስለሰሎሜ አይደለች..ማለቴ እሷን እየፈለክ አይደለህ?›››

የሚስቱን ስም ሲጠራ ይበልጥ ደነገጠ‹‹አዎ ግን እንዴት አወቅክ..ነው ወይስ እቴቴ ደውላልህ ነው?››

‹‹አይ…ከቴቴ ጋር አልተደዋወልንም.ሰሎሜ እኔ ጋር ነች››

አላዛር ይሄንን አረፍተ ነገር ሲሰማ ጭንቅላቱ ላይ ስል ሰይፍ አርፎ ለሁለት የሰነጠቀው ነው የመሰለው..በሰከንዶች ሽርፍራፊ ብዙ ብዙ ነገር ነው ያሰበው፡፡‹‹እንዴት እንዴት ብለው ተገናኙ?ከዚህ በፊትም በድብቅ ይገናኙ ነበር ማለት ነው…?እሱ እጅ ከገባች እንዴት ነው መልሼ የራሴ ላደርጋት የምችለው..?ነው ወይስ እስከወዲያኛው እያጣኋት ይሆን?፡፡››ሲል የስጋት ሀሳብ አሰበ፡፡
አለማየሁ ለረጅም ደቂቃዎች መልስ ሳይሰጠው ዝም ስላለበት ግራ ተጋብቶ ‹‹አላዛር…ምነው ዝም አልክ ..?ሰምተኸኛል?››

‹‹አዎ ሰምቼሀለው…ግን ምንም አልገባኝም…እንዴት ልታገኛት ቻልክ?››

‹‹እሱ ታሪኩ  ረጅም ነው ..ናና እንነጋገራለን››

‹‹የት ነው የምመጣው?››
‹‹ፓሊስ ጣቢያ..ማለቴ…›› ብሎ ትክክለኛ አድራሻውን ነገረው፡፡

‹‹ፖሊስ ጣቢያ ምን ትሰራለች?››

‹‹አንተን ልትከስ መጥታ ልበልህ..?ለማንኛውም  እየጠበቅኩህ ነው.. ፈጠን ብለህ ና››ብሎት ስልኩን ዘጋበት፡፡

አላዛር ድንዝዝ ነው ያለው…መኪናውና አንቀሳቅሶ በፍጥነት መሄድ እንዳለበት እንኳን ማስታወስ አላቻለም….‹‹የምን ክስ …?መቼስ ምንም አይን አውጣ ብትሆን ባሌ ከእኔ ጋር ግንኙነት አላደርግም አለኝ ›ብላ አትከሰኝም…..እንደዛማ አታደርግም…ደግሞ ካልጠፋ ቦታ ስንት ክፍለከተማ አቋርጣ እንዴት እዛ ድረስ …?እስከዛሬ እያወቀች እንዴት መቀየሩን ሳትነግረኝ ..?እንዲሁ እንደተብከነከነ እና የተንዛዙ ጥያቄዎች አእምሮውን አንዳጨናነቀ የተባለው ፓሊስ ጣቢያ ደረሰና መኪናውን  ፓርክ  አድርጎ ወደፖሊስ ጣቢያው ተጠጋ ፡፡በየት እንደሚገባ ግራ ተጋባ በራፍ እንዳለ ሆኖ በሆነ ሜትር ጠጋ ብሎ ደግሞ 5 ሜትር የሚሆን የተደርመሰ አጥር  በግማሽ ቀልቡ እያየ ወደውስጥ ዘለቀና ለአለማየሁ ደወለለት፡፡

የቢሮውን ቁጥር ሲነግረው  ፈራ ተባ እያለ አንኳኳና ወደውስጥ ገባ…ከስድስት አመት በፊት የተለየው የልጅነት ጓደኛውና አብሮ አደጉ ፊቱ በፂም ተሸፍኗ ትልቅ ሰው መስሎ እና የደንብ ልብሱን ለብሶ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ከእሱ ውጭ ክፉሉ ውስጥ ማንም የለም.ሰሎሜንም አገኛታለሁ ብሎ ጠብቆ ነበር…ግን እየታየችው አይደለም፡፡‹‹የት ወስዶ አስቀምጧት ነው?››በውስጡ አጉረመረመ፡፡

እንዴት ብሎ ሰላም እንደሚለው ግራ ገባው…‹‹ጓደኛዬን ለማግኘት ነው የመጣሁት  ወይስ ተከስሼ ቃል ልሰጥ….?››ሲል እራሱን ጠየቀና ተደነጋሮት በራፍ ላይ ፈዞ ቆመ፡፡ አለማየሁ መቀመጫውን ለቆ መጣና ተጠመጠመበት…ከፍራቻው ጋር ሳይፋታ እሱም አቀፈውና የሞቀ ሳላምታ ተለዋወጡ ፡፡ይዞት ወደ ውስጥ ዘለቀና የሚቀመጥበት መቀመጫ ሰጠው..እሱም ከፊቱ ተቀመጠ….፡፡
አለማየሁ ደቂቃዎችን  ወሰደና አላዛርን በትኩረት አየው፡፡አለባበሱ  እንዳአንባሳደሮች ሽክ ያለ ነው..ደግሞ ልክ እንደድሮው …እንደውም ከዛም በላቀ ደረጃ ልቅም ያለቆንጆ ሆኗል፡፡ወንድን ልጅ  ቆንጆ ነው ብሎ  አያውቅም ፡፡ጓደኛውን የአላዛርን ቁንጅና ግን ፍጥጥ ያለ ስለሆነ ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይነት አይደለም፡፡፡

ለንግግሩ አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በቅርብ ነው እዚህ የገባሀኸው?››
‹‹አዎ ገና ሁለት  ወሬ ነው››

‹‹ሁለት  ወር ሙሉ ስትቀመጥ እንዴት አስቻለህ? ነው ወይስ እኔ ብቻ ነኝ ያላገኘሁህ›?›

‹‹አይ ..እዚህ የተመደብኩት በሀላፊነት ቦታ ስለሆነ ነገሮችን እስክለማመዳቸውና እስኪዋሀዱኝ ወዲህ ወዲያ ማለት አልቻልኩም ነበር…መቼ እና እንዴት ላግኛቸው እያልኩ እያሰብኩ ሳለ ነው ድንገት ዛሬ ጥዋት ሰሎሜን ያገኘኋት፡፡››

‹‹ጥዋት?››

‹‹አዎ ጥዋት››

አላዛር ረጅም ትንፋሽ ወደ ውስጡ ሳበና እፎይ አለ…‹‹ለሊት ቀጥታ ከቤት እንደወጣች ወደእሱ ቤት ሄዳ ቢሆንስ ?››የሚል ጥርጣሬ ነበረው…እንደዛ ከሆነ ደግሞ ብዙ የሚፈጠሩና ወደኃላ ሊመለሱ የማይችሉ ችግሮች ይኖሩ እንደነበር ሲያሰላስል ስለቆየ  ከአለማየሁ የሰማው መልስ በጣም ነው ያስደሰተው፡፡

‹‹ታዲያ አሁን የታለች?››

‹‹እስር ላይ ነች››

‹‹ምን?››የሚሰማውን አምኖ ለመቀበል ተቸገረ፡፡

የተሳሳተ ቃል የሰማ ነው የመሰለው….‹‹እሷ እስር ላይ !!እንዴት ተብሎ?››

‹‹ስትገባ ያየሀው መሰለኝ..አጥራችንን ለሊት የናደችው እሷ ነች››

‹‹ተረፈች ታዲያ ..?ተጎድታለች..?ሀኪም ቤት ወሰዳችሃት?››

‹‹አታስብ ..ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባትም….››መኪናዋ ብቻ ትንሽ ተጫራለች…መንገድ ስለዘጋብን አንስተን ወደጎሮ አቁመናታል፡፡››

ከድንጋጤው ትንሽ ተንፈስ ብሎ‹‹መኪናዋ የራሷ ጉዳይ .እሷ ብቻ  እንኳን ተረፈች››አለ ፡፡

‹‹አዎ..ተርፋለች››
ልመና ሳይሆን ትዕዛዝ በመሰለ ቃላት‹‹ላያት እፈልጋለሁ..››ሲል ተናገረ፡፡

‹‹ደህና ነች አልኩህ እኮ››
‹‹በፈጣሪ ካላየኋት አልረጋጋም…..በጓደኝነታችን..እባክህ?››

አለማየሁ ከዚህ በላይ ሊጨክንበት አልፈለገም፡፡‹‹አረ ችግር የለውም… እዚሁ አስመጣታለሁ…››አለና ከመቀመጫው ሳይነሳ  ጠረጴዛው ላይ መጥሪያውን ተጫነው… ወዲያው አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቶት የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅ ጀመረ
ኩማደር አለማሁም‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማን ይዘህልኝ ና››ብሎ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡

ፓሊሱ ወጥቶ ሄደ‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማ  ››ብሎ ሲናገር አላዛር ስቅጥጥ አለው፡፡

‹‹ኩማንደር  ቆይ ግን አጥሩን እኔ በሁለት ቀን ውስጥ ሙሉውን ከበፊቱ በበለጠ አሳምሬ እስገናባዋለሁ….አስፈላጊም ከሆነም  አሁኑኑ ደስ ያላችሁን ብር አስይዛለው..እሷ ማሰር እኮ አስፈላጊ አይደለም….››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

‹‹እናንተ ደግሞ ጅል አትሁኑ…ሰሎሜ ሰው ነች…ሰው ስለሆነች ታማለች…የተመመ ሰው ደግሞ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ህክምና ካላገኘ ይሞታል….ይሄ ሀቅ ለሌላ ሰው ከሰራ  ለሰሎሜም ይሰራል፡፡››ሁሴን ነበር የተናገረው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የምትለው ነገር አለ››አለማየሁ በብስጭት መለሰለት፡፡

‹‹ትክክል ነኛ..ከእናንተ በተሻለ ብዙ ነገር አውቃለሁ…ይልቅስ ሰሎሜ ቀዶ-ጥገናዋን እንድታደርግ እኛ ምን ማድረግ አለብን ?የሚለውን መነጋገር ነው የሚጠቅመን፡፡››

‹‹ትክክል ነህ..የመጣልህ ሀሳብ አለ?››አለማየሁ ነው በጉጉት የጠየቀው፡፡

የቀዶ ጥገና እንዲደረግላት የተወሰነበትንና  እና የገንዘቡን መጠን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘት አለብን›› ሁሴን ሀሳብ አቀረበ፡፡

‹‹አግኝተንስ ምን እናደርገዋለን?››አላዛር ጠየቀ፡፡

‹‹በሰፈር ጠቅላላ ዞረን እንለምናለን…በትምህርት ቤታችንም እንለምናለን፡፡››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን ያንን ሁሉ ብር የምናገኝ ይመስልሀል?››በጥርጣሬ ጠየቁት፡፡

‹‹እስከቻልነው እንሞክራለን…ካልሞላልን ደግሞ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን..አሁን ደብዳቤውን እንዴት እንደምናገኝ ማሰብ አለብን››

‹‹ለምን ሀኪም ቤት ሄደን ሰሎሜን የሚያክማትን ሀኪም አንጠይቀውም…››አላዛር ነው ሀሳቡን ያቀረበው፡፡

‹‹አይ አንተ ጅል የሆንክ ልጅ..አሁን ሄደን ብንጠይቀው ለ13 አመት ልጇች እንዲህ አይነት መረጃ ሚሰጠን ይመስልሀል?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ስለገባኝ እኮ ነው፡፡››

‹‹ለምን እቴቴን አንጠይቃትም..እሷ ደብዳቤውን ልታስወጣልን ትችላለች››

‹‹አሌክስ ትክክል ነው..ጊዜ ሳናባክን አቴቴን እናናግራት››ሁሴን በአለማየሁ ሀሳብ ወዲያው ተስማማ፡፡

‹‹ግን እኮ እሷ ሆስፒታል ነው ያለችው››

‹‹እኮ እንሂዳ››
ተስማሙና ቀጥታ ሰሎሜ ወደተኛችበት ሆስፒታል ነበር የሄዱት፡፡ሰሎሜ የተኛችበት ክፍል ገብተው ያለችበትን ሁኔታ ካዩ በኃላ‹‹እቴቴ አንዴ ውጭ ልናናግርሽ ፈልገን ነበር፡፡››ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ምነው በሰላም?››

‹‹በሰላም ነው..ሰሎሜ ስለተኛች እዚህ ስናወራ እንዳንቀሰቅሳት ነው››አለ ሁሴን፡፡

‹‹እሺ እንዳላችሁ ››በማለት ተስማምታ  ተከትላቸው ወጣች፡፡እዛው ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ካለ አግዳሚ ወንበር ላይ በመደዳ ተቀመጡ፡፡

ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹እሺ ልጆች ..ለምንድነበር የፈለጋችሁኝ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡

‹‹ሰሎሜ እንዴት ነች?››

ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ‹‹ደህና ነች..ምንም አትል››ስትል መለሰችላቸው፡፡

‹‹ማለት ስለቀዶ ጥገናው ነው የምናወራሽ…?እንዴት ነው የሚሆነው…?ያን ያህል ብር ከየት ታመጪያለሽ?››

‹‹ልጇች አትጨነቁ..ከየትም ብዬ ከየትም ይሄንን ብር አግኝቼ ብቸኛ ልጄን ማሳከም አለብኝ….አታስቡ ጓደኛችሁን እንድትድን የተቻለኝን አደርጋለሁ፡፡››ስትል እንባ እየተናነቃት መለሰችላቸው፡፡በእውነት ብሩን ከየት እንደምታመጣው…የትኞቹን ዘመዶቾን እንደምታስቸግር…የትኛውን ንብረቷን ብትሸጥ የተጠየቀችውን ብር ማግኘት እንደምትችል  ምንም አይነት ሀሳብም ሆነ ተስፋ  አልነበራት፡፡ግን ለልጆቹ ይሄንን ምን ብላ በምን አይነት ቋንቋ ልታስረዳቸው ትችላለች፡፡ለዛ ነው በደፈናው ልታፅናናቸው የወሰነችው፡፡

‹‹እቴቴ…ሰሎሜን ለማዳን የተቻለንን ብቻ ሳይሆን ከምንችለው በላይ ነው ማድረግ ያለብን…ሶስታችንም ልክ እንደአንቺ እሷን ለማጣት ዝግጁ አይደለንም…እና የሆነ ነገር ለማድረግ አስበናል፡››ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡

አቴቴ ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው …?እናንተ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?››

‹‹ከሀኪም ቤቱ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት መወሰኑን እና  ለዛም የሚያስፈልገውን ብር የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው››

‹‹ማለት ..ደብዳቤው ምን ያደርግልኛል?››

‹‹አይ ላንቺ አይደለም..ለእኛ ያስፈልገናል››

‹‹ለምን .?.ምን ልታደርጉበት?››
ትምህርት ቤታቸውን ሆነ በሰፈራችን እርዳታ እየዞርን እንጠይቃለን..ከየአንዳንዱ ሰው አንድ  ብርም ሆነ አስር ብር እየዞርን እንሰበስባለን…ለዛ ግን ሰው እንዲያምነን እና ስራችን ቀላል እንዲሆንልን መረጃው ያስፈልገናል፡፡››

በወቅቱ የሰሎሜ እናት ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር…ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ ጉያዋ ውስጥ በመወሸቅ ስቅስቅ ብላ ነበር ማልቀስ የጀመረች፡፡

አለማየሁ ጉንጮ ላይ ያለውን እንባ በመዳፎቹ እየጠረገላት ‹‹እቴቴ አይዞሽ.. አታልቅሺ …ሰሎሜን እናድናታለን…እሷ የእኛ ንግስት ነች..ንግስታችንን ማጣት አንፈልግም፡፡››ሲል አፅናናት ፡፡

‹‹ያስለቀሰኝ  ሀዘን አይደለም ደስታ ነው፡፡ልጄን ወንድም ወይም እህት ሳልወልድላት ብቸኛ አደረኳት ብዬ ብዙ ጊዜ አዝኜና አልቅሼ ነበር፡፡አሁን ግን እንደተሳሳትኩ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ወንድሞች ቢኖሯትም እናንተ ከምትወዷትና ከምትንከባከቧት በላይ ሊንከባከቧት አይችሉም ነበር፡፡
በጣም ነው የማመሰግናችሁ፡፡ እናንተ ስላላችኋት ልጄ በጣም እድለኛ ነች››

‹‹አይ እቴቴ….እሷ ስላለችን እኛ ነን እድለኞች…አሁን መላቀሱ አይጠቅመንም…ሂጂና ዶክተሮቹን ጠይቀሽ ደብዳቤውን አግኚልን፡፡››

‹‹እሺ በቃ ውስጥ ገብታችሁ ጠብቁኝ …መጣሁ››ብላ በነጠላዋ ጫፍ በጉንጮቾ የረገፈ እንባዋን እየጠረገች ወደአስተዳደር ቢሮ ሄደች፡፡

ደብዳቤውን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ሰፈራቸው ወደሚገኝ ባነር መታሚያ ቤት ነበር  የሄድት፡፡ ደብዳቤውን አሳይተውና ሁኔታውን አስረድተው…የሰሎሜ አሳዛኝ ፎቶ የሚታይበትንና ያለችበትን ሁኔታ እጥር ምጥን ባለ ግልፅ ዓረፍተ ነገር አፅፈው ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ባነር አሳተሙ፡፡ ..በማግስቱ ወደትምህርት ቤት ይዘው ሄዱ፡፡ቀጥታ ወደ ዳሪክተሩ ቢሮ ሄዱና ሁኔታውን አስረዱት….፡፡.ተማሪዎች በተሰለፉበት ባነሩ ለሁሉም እንዲታይ ተዘርግቶ ሰሎሜ ያለችበትን ሁኔታና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሁለቱም ፈረቃ ተማሪዎች ተነገረ…፡፡በእለቱ በኪሳቸው ያላቸው ተማሪዎች ወዲያውኑ ማዋጣት ጀመሩ…ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር አካባቢ ተሰበሰበ፡፡በማግስቱ ሁሉም ተማሪ ለወላጆቹ በማስረዳት የቻለውን ይዞ እንዲመጣና በስም ጠሪዎች አማካይነት በየክፍሉ እንዲሰበስብ ተደረገ፡፡
በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ ከመላው ተማሪና አስተማሪዎች 23 ሺ ብር ተሰበሰበ፡፡ትምህርት ቤቱ የሰሎሜን እናት ጠርቶ ቀጥታ ብሩን አስረከባት፡፡  የትምህርት ቤቱን ቅፅር ግቢ በእልልታ አናጋችው….ሶስቱን የልጇን ጓደኞች እያገላላበጠች ሳመቻቸው፡፡ከልቧ መረቀቻቸው፡፡ከነፍሷ ወደደቻቸው፡፡
እነአለማየሁ ግን እንደእሷ ባገኙት ነገር ፍፅም ደስታ አልተሰማቸውም ነበር፡፡የእነሱ ግምት ቢያንስ 40 እና 50 ሺ ብር እናገኛለን የሚል ነበር፡፡ወዲያው ጊዜ ሳያባክኑ ባነሩን ለሁለት ጉን ለጉን ይዘው አንደኛው በአጀንዳ ላይ እያንዳዱ ሰው የሚሰጠውን ስምና ብር  እየመዘገበ  በሰፈር ውስጥ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኩ እና የድርጅቶችንም ቢሮ ዘልቀው እየገቡ  ጭምር መጠየቅ ጀመሩ፡፡
በአራት ቀን ውስጥ ሌላ 20 ሺ ብር አገኙና ለእናትዬው አስረከቧት..፡፡እሷ በፊት ደብተሯ ላይ የነበራትናን ከቢሮዋ ሰራተኞች ተዋጥቶ የተሰጣት አንድ ላይ ሆኖ እነሱ ከሰበሰቡት ጋር  50 ሺ ብር አካባቢ በእጇ ያዘች፡፡
ሶስቱም በአንድ ላይ ተሰብስበው ሄደው ‹‹እቴቴ..አሁን ስንት ብር ሆነልሽ?››ብለው ጠየቋት፡፡
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

…‹‹በቃ ምንም ማድረግ አንችልም ማለት ነው?››አላዛር ነው በተስፋ መቁረጥ የጠየቀው፡፡

‹‹አይ የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን››ሁሴን ተናገረ

‹አዎ….የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን ..የሆነ ሀብታም ፈልገን ለምን ወግትን ብር አንቀበለውም››የአለማየሁ ሀሳብ ነበር፡፡

‹‹ከዛ የተሻለ ሀሳብ አለኝ..አሁን ወደሰፈር እንሂድ››ሁሴን ነበር መላሹ፡፡

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹ነገ የትምህርት ቤት ተማሪዎችንና ጋዜጠኞችን ይዘን ይሄንን ሆስፒታል እንወረዋለን››

‹‹እንዴት አድርገን...?ተማሪው እሺ ይላል?››

‹‹አዎ ጥሩ ዘዴ ተጠቅመን ከቀሰቀስን ይሳካልናል፡፡
አነአለማየው ቤት ተሰብስበው ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበትን ፅሁፍ ሲያረቁ አመሹ፡፡

እህታችን ከሞት እንታደጋት፡፡
ሰሎሜ  ግርማ በጠና ህመም ታማ ሆስፒታል ከተኛች 15 ቀን እንዳለፋት እናውቃለን፡፡ በቀጣዬቹ 15 ቀናት ቀዶ ጥገና ካላደረገች ..ትምህርት ቤቱን ለአንድ ቀን ዘግተ፤ እጃችንን ወደኃላ አጣምረን ፤ለቀብር ቤተክርስቲያን መዋላችን ማይቀር ነው፡፡

እኛ እሷን ለማዳን ቤተሰቦቻችንን ሁሉ አስቸግረን የተቻለንን ብር አሰባስበናል…50 ሺ ብር በእናትዬው እጅ አለ..ሆስፒታሉ ግን 70 ሺ  ካላሳዚያችሁ በስተቀር ቀዶ ጥገናውን ማድረግ አልችልም ብሏል፡፡ይሄ ምን አይነት ሰባዊነት ነው፡፡ነገ በሰሎሜ ቦታ እኛ ብንታመምስ ተመሳሳዩ አይደል የሚገጥመን…?እኛ ተማሪዎች መብታችንን ማስከበር አለብን፡፡ከአስራአምስት ቀን በሃላ ወደቀብር ከመሄድ በነገው ቀን ልክ በእርፍት ሰዓት ተሰብስበው  ሆስፒታሉን በሰላማዊ ሰልፍ መውረር አለብን..ከዛ መንግስትም  ቢሆን ጣልቃ ገብቶ እህታችን እንድትታከም ማድረግ አለበት፡፡በቦታው ላይ የሬዲዬና የቲቪ ጋዜጠኞች ስለሚኖሩ ድምፃችን በደንብ እንደሚስተጋባ አውቃችሁ ለዚህ ተባባሪ እንድትሆኑ እንጠይቃለን፡፡፡
የሚል መልእክት በእጅ ፅሁፍ አረቀቁና…ኮፒ ቤት ሄደው ለምነው በነፃ አፃፉ፡፡በሰፈር ያሉት ኮፒ ቤቶች ሁሉ አንድ 50 ሌላው መቶ  እያለ ከሶስት መቶ በላይ ኮፒአስደረጉና  ጥዋት አንድ ሰዓት ትምህርት ቤት በራፍ ላይ ተገኙ፡፡ …ከዛ እያንዳንዱ ተማሪ ወደትምህርት ቤት ሲገባ አንድ አንድ ወርቀት እየታደለ ነበር የገባው…በእረፍት ሰዓት ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ቅፅር ጊቢ ውስጥ አልቀረም ነበር፡፡አስተማሪዎችም ሆነ ዘበኞቹ ሁኔታውን ሊቆጣጠሩ ቢሞክሩም ሁሉነገር  ከአቅማቸው በላይ ነበር የሆነው….
የትምህርት ቤቱ ዳሪክተር በኃላ እንዳያስጠይቀው ወዲያው ለአካባቢው ፖሊስ በመደወል ሁኔታውን አስረዳ፡፡፡ከአራት መቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሆስፒታሉን ወረሩት፡፡የተፈጠረውን ነገር ለማጣራትና ከዚህም ከዚያም የተሰበሰቡ ከሺ ባላይ የሚሆኑ  በአካባቢው ሚያልፉ ሰዎች ሰልፉን ተቀላቅለው የበለጠ ደማቅና አስፈሪ አደረጉት፡፡ ….ከተለያየ ጣቢያ የተውጣጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውን ደቅነው በሰልፉ ፊት ለፊት ተኮለኮሉ፡፡አድማ በታኝ ፖሊስና  የእሳት አደጋ መኪና፤አንቡላስ መኪኖች በአካባቢው በቅርብ እርቀት በተጠንቀቅ ቆመው ይታያሉ፡፡ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት ትርምስ ፈጠሩ..ሀኪሞችም ስራቸውን እንዴት እንደሚሰሩ ግራ ተጋቡ…

ከተማሪዎች አንደበት ሚወጣው መፈክር እና  በእጃቸው ፅፈው የያዙት ፅሁፍ ነበር የጉዳዩን ምንነት እንዲያውቁ ያደረገው፡

‹‹ሰሎሜ በገንዘብ እጥረት መሞት የለባትም፡፡››

‹‹ሆስፒታሉ ለሰሎሜ  ህክምና ወጪላይ ቅናሽ ማድረግ አለበት፡፡››

‹‹ሰሎሜ ዛሬውኑ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላት እንፈልጋለን፡፡››

ከቆይታ በኃላ ትንንትና ያናገሩት የሆስፒታሉ ኃላፊ በግንባሩ ላይ ላቡ እየጠንጠባጠበ ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ከሰልፈኛ ተማሪዎች ፊት ለፊት ቆሞ በድምጽ ማጉያ መናገር ጀመረ፡፡

‹‹አንዴ ፀጥታ፡፡በእውነት ጉዳዩ እዚህ መድረስ የለበትም ነበር፡፡የሆስፒታሉ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ከአንድ ሰዓት በኃላ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡እና በእርግጠኝነት የጓደኛችሁ ቀዶ ጥገና  24 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሰራላታል፡፡ይሄንን ቃል የገባሁት በህዝብና በሚዲያ ፊት ስለሆነ ምንም ስጋት አይግባችሁ፡፡አሁን ብዙ በሽተኞች እጃችና ላይ አሉ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ደግሞ ስራችንን መስራት ሰለማንችን…ምንም አይነት ግርግር ሳትፈጥሩ ቀጥታ ወደትምህር ቤታችሁ ተመለሱ…እንደምታዩት  ብዙ ፖሊስ በአካባቢው አለ..ችግር እንዳይፈጠር አደራ….ብሎ ላቡን በመሀረብ እየጠረገ ወደውስጥ ተመለሰ፡፡ተማሪዎችም እርስ በርስ እየተነጋገሩ እንዳመጣጣችው ወደትምህር ቤት ተመለሱ፡፡ በእነሱ ምክንያት የተሰበሰበውም የፀጥታ አካልና ተሸከርካሪም እንደፈሩት ምንም ጉዳት ባለመድረሱ ተደስተው እንደአመጣጠቸው ተመለሱ…ከሰዓታት በኃላ ግን ሙሉ ሚዲያው ጠቅላለ ይሄንን ጉዳይ አስፋፍቶና አጋኖ ማቅረብ ጀመረ….አንዳንዱ ሚዲያ የህክምና ባለሞያ ጋብዞ ስለሀገሪቱ የህክምና ዋጋ ውድነት አስተነተነ..ሌላው የህግ ባለሞያ ጋብዞ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሞከረ..  ሌላው ከጤና ጣቢያ ባለስልጣናትን በስልክ በመጠየቅ የመንግስትን አቋም ለማወቅ ሞከረ፡፡
ሁለት ሰዓት ዜና ላይ ግን ሁሉም የሚፈልገው ምስራች አየሩን ተቋጣጠረው፡፡ ለሰሎሜ እናትና ለጓዶቾ የሚያስፈነጥዝ ዜና ነበር፡፡
የሆስፒታሉ ቦርድ ተሰብስቦ በመነጋገር…የተማሪ ሰሎሜን ኬዝ በልዩ ሁኔታ በመመልከት እናቷ ለብቻዋ የምታሳድጋት በመሆኑና ተማሪ ጓደኞቾ እሷን ለማዳን ገንዘብ ከማዋጣት አንስቶ ያደረጉትን ከፍተኛ ትግለ እና አርአያ ያለው ተግባር ከግንዛቤ በማስገባት ሆስፒታሉ ያለምንም ክፍያ ቀዶ ጥገናውን በነፃ ሊያደርግላት ወስኗል፡፡እናትዬው ለቀዶ ጥገናው ልትከፍለው የነበረውን ብር ልጅቷን ከቀዶ ጥገናው በኃለ በማገገም ሂደት ውስጥ  ለሚያስፈልጋት ወጪ እንዲሆናት ፈቅዷል፡፡››የሚል መግለጫ.. ሰጠ፤ እንዳሉትም..በማግስቱ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ ሰሎሜ ወደቀዶ ጥገና ክፍል ገባች፡፡5 ሰዓት ከፈጀ ውስብስብ ቀዶ ጥገና ቆይታ በኃላ በሽታዋ ተወግዶ ወደ ፅኑ ህክምና ክፍል ተዘዋወረች..በዛ መንገድ ከሞት ሾልካ አመለጠች፡፡ሰሎሜ በጓደኞቾ ጥረት እና ተአምራዊ ትጋት ድና ከወር በኃላ ወደትምህርት ቤት ስትመለስ በትህርት ቤት ውስጥ በጣም ዝነኛና ታዋቂ ሆና ነበር፡፡እሷ ብቻ ሳትሆን ጓደኛቾም ጭምር የተከበሩና የተመሰገኑ ሆኑ፡፡ጥምረታቸውም ‹‹ምን አይነት ጓደኛነት ነው?››እየተባለ ሁሉም የሚቀናበትና  እንደምሳሌ የሚቀርብ ሆኖ  በሁሉም ዘንድ እውቅና አገኘ፡፡

ሁለቱም ከትዝታቸው ሲመለሱ አይኖቻቸው እንባ አቅርረው ነበር…..
ኩማንደር አለማየሁ ጉሮሮውን አፀዳዳና ‹‹አሁን ወደሁለተኛው ጉዳይ እንሸጋገር››ሲል አላዛርንም ከገባበት ትካዜ እንዲወጣ አደረገው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ምንድነው?››ግራ በመጋባትና በፍራቻ ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይማ ዋናው ነው…ይሄን ሁሉ ችግር ያመጣውና ልጅቷን በውድቅት ለሊት ብን ብላ ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት ችግር››

‹‹ዝም ብለህ እኮ ነው..ጊዜዊ የባልናሚስቶች ጭቅጭቅ ነው…ግድ የለም እኔ አስተካክለዋለው…ሁለተኛ  አይደገምም፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››ኮስተርና ቆፍጠን ብሎ ጠየቀው፡፡
አላዛር ደነገጠ‹‹ማለት?››

‹‹አላዛር …ሁሉን ነገር አውቄዋለው…እኔ የአንተም ሆነ የእሷ የሰሎሜ ጓደኛ ነኝ…እዚህ ጋር ምንም የምንደባበቀው ነገር መኖር የለበትም፡፡››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


===============

በሶስተኛው ቀን አለማየሁና ሰሎሜ  ተደዋውለው  ተገናኙ፡፡ማታ አስራሁለት ሰዓት አካባቢ ሆቴል ነው የተገናኙት…ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው፡፡በሞቀና በጋለ ሰላምታ ተቀበላት ፡፡ምግብ አዘው በልተው መጠጥ እየተጎነጩ ወሬ ጀመሩ ፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነሽ..?ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ለጫወታ መጀመሪያ የሚሆን አ.ነገር ሰነዘረ፡፡
‹‹ቆይ እስኪ የእኔ ጉዳይ ይቆይ…ለመሆኑ አንተ እንዴት ነህ?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት..እኔ ደግሞ ምን እሆናለሁ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ማለቴ በቀደም ሳልጠይቅህ ….አገባህ እንዴ?››
‹‹አረ..በፍጽም፣ባገባ ኖሮ ቢያንስ ለእቴቴ ነግራት ነበር..ለእሷ ከነገርኩ ደግሞ ያው ልጇ ስለሆንሽ አትደብቅሽም ነበር፡፡››
‹‹አውቄዋለሁ….!!››
‹‹እንዴት .?ምኑን ነው ያወቅሽው?››
‹‹አንተ በቀላሉ የምትጨበጥ ወንድ አይደለህማ..አንድ ሴት አንተን አሳምና ወደ ጋብቻ ለመውሰድ በጣም ነው የሚከባዳት፡፡እርግጠኛ ነኝ ለማንም ሴት ከባድ ነው የሚሆንባት ፡፡››
‹‹እንዴ ያን ያህል አስቸጋሪ ሰው ነኝ እንዴ?››እሱን በተመለከተ በሰጠችው  አስተያየት የእውነት ገርሞት  ነው የጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እኔ እስከማውቅህ ድረስ፣ሀሳብህና ፍላጎትህ በደቂቃ ውስጥ  ነበር የሚቀያየረው…መቀሌም  ሞያሌም በአንድ ጊዜ መገኘት የምትፈልግ ለመረዳት አስቸጋሪ አይነት ሰው ነህ፡፡ማለቴ ነበርክ..አላውቅም ምን አልባት ባለፉት አምስት.. ስድሰት አመታት ተቀይረህ ሊሆን ይችላል..እኔ የማውቀው አሌክስ  ግን እንደዛ ነበር፡፡››
‹‹በእውነትን እንደዛ አይነት ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ደግሞም አንድ እህት ወንድሟን በተመለከተ ይሄንን የመሰለ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አይነት ነው፡፡፡››
‹‹እንዴት  ..ትክክለኛ ባህሪህን እኮ እየነገርኩህ ነው፡፡ለምሳሌ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሰን ማትሪክ እንደወሰድን  አብረን ተማክረን  ተግባረእድ ተመዝግበን  ነበር፡፡ትምህርት ሲጀመር ግን ብን ብለህ ቤቱንም ከተማውንም ለቀህ ጠፋህ .ፖሊስ  ለመሆን ተመዝግበህ  ማሰልጠኛ መግባትህን እንኳን ለእኔ መንገር አልፈለክም..ከእናቴ ነበር የሰማሁት፡፡ሁል ጊዜ የሆነ ነገር አብረን እናቅዳለን..ትግበራው ላይ ግን ድንገት ታፈነግጣለህ፡፡በዚህ በዚህ ሁሴንና አላዛር ካንተ በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡እነሱ በቃላቸው ይፀናሉ…በተለይ አላዛር››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ..ለገዛ ባልሽ እያደለሽ ነው..?ለመሆኑ ሁሴን አሁን የት ነው ያለው?››
‹‹ያው ከመሀካላችን የተሻለ ጭንቅላት ያለው እሱ ነበር ፡፡አሁን  እንግሊዝ ሀገር የህክምና ዶክተር ሆኖ እየሰራ ነው…ግን በቅርብ ሳይመጣ አይቀርም፡፡››
‹‹አዎ ውጭ መሄዱንማ ሰምቼለሁ….ለማለት የፈለኩት ትደዋወላላችሁ ወይ ለማለት ነው?››
‹‹ከአላዛር ጋር እስክንጋባ ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ከዛ በኃላ ግን  ደውሎልኝ አያውቅም፡፡.እኔም አንድ ሁለቴ ልደውልለት ሞክሬ ነበር ስልኩን ቀይሮታል መሰለኝ አልሰራ አለኝ፡፡››
‹‹ተበሳጭቶብሽ ነዋ?››
‹‹ምን ያበሳጨዋል?››
‹‹በጣም  ያፈቅርሽ ነበር እኮ…!!››
‹‹ያፈቅርሽ ነበር ወይስ ይወድሽ ነበር?››
‹አንቺ ደግሞ …ሶስታችንም ነበር የምናፈቅርሽ..ይሄንን ደግሞ አንቺም በደንብ ታውቂያለሽ፡፡›.
የመደንገጥና ግራ የመጋባት ስሜት በፊቷ ላይ ተንፀባረቀባት ‹‹ምን እያልከኝ ነው…? እየቀለድክ ነው አይደል?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ እየቀለድሽ ያለሽው…፡፡ ሶስታችንም ገና ማፍቀር እራሱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በፊት እናፈቅርሽ ነበር፡፡እድሜያችን በሙሉ ማነው በይበልጥ ሚያፈቅራት እያልን ስንፎካከለርብሽ  ነው ያሳለፍነው፡፡››
‹‹እኔ ትምህርት ጨርሰን እስክንበታተን ድረስ አራታችንም እርስ በርስ የምንዋደድ የልብ ጓደኛሞች እንደሆን ብቻ ነበር የማውቀው፣በተለይ አንተ ወንድሜም ጭምር ስለነበርክ  በዚህ መልኩ ላስብህ አልችልም፡፡ ››
‹‹ይሄን አላዛር እስከአሁን እንዴት ሳይነግርሽ…?ለነገሩ ምን ብሎ ይነግርሻል፤ አውቀሽ እሱ እንዳይከፋ በማሰብ ያላወቅሽ መስለሽ እንደምታስመስይ ነው የሚያስበው፡፡››
‹‹እሺ የሁሴንስ ይሁን ..አንተ የእውነት ታፈቅረኝ ነበር?››
‹‹ለዛውም ልክ በሌለው መጠን ነዋ….ለአንቺ ስል የማላደርገው ምን አለ..ቢያንስ የሞዴሱ ታሪክ ትዝ አይልሽም?››
‹‹አንተ ..ደግሞ ታስታውሰኛለህ እንዴ?ስንት አመት ሙሉ አንተ ምትገዛልኝ እየመሰለኝ አንጀቴን ስትበላው ኖረህ…አለችና በሳቅ ፈረሰች..እሱም ተከተላት፡፡
ሁለቱም በምናባቸው ወደኃላ ተጓዙና ትካዜ ውስጥ ገቡ
ሰሎሜ የወር አበባዋ የመጣው በ14 አመቷ ነበር፡፡ያንን ደግሞ ከግሩፑ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀው አለማየሁ ነበር፡፡የዛም ምክንያት ከሰሎሜ ጋር አንድ ቤት በመኖራቸው ነው፡፡ወር በመጣ ቁጥር ግን ለሞዴስ የሚሆን ብር እናትዬውን መጠየቅ እያሳቀቃት ስትበሳጭ ይሰማና ..ይሄንን ችግር የሚፈታበትን ዘዴ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡
ከዛ ፡አላዛር በዛን ጊዜ   ከትምህር ሰዓት ውጭ የሱቅ ስራ ይሰራ ስለነበረ ወደእዛው ነው የሄደው፡፡
‹‹እሺ ቱጃሩ እንዴት ነህ?››
‹‹ያሄው እንደምታየው ነው....ምነው ብቻህን?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰሎሜን ወይም ሁሴንን አስከትለህ ይምትመጣ መስሎኝ ነበር፡፡››
ከሁለቱን ማንን ይዤ ብመጣ ነበር የምትደሰተው?››ሲል መልሱን እያወቀው ጠየቀው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው…?ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው …ለምን መርጣለሁ?››
‹‹ተው እንጂ …አታስመስል፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ…!››ብሎት ዝም አለ
‹‹ቆይ ..ሞዴስ አለህ እንዴ?››
አላዛር ደንግጦ‹‹የምን ሞዴስ?››ሲል ነበር መልሶ የጠየቀው፡፡
‹‹ሞዴስ ነዋ ..ሴቶች የወርአበባ ሲመጣባቸው ሚጠቀሙበት፡፡››ሲል ብራራለት፡፡
‹‹የለኝም፡፡››
‹‹ለምን አታመጣም..ሴቶች አይጠይቁህም?››
‹‹እሱማ አልፎ አልፎ ይጠይቁኛል፡፡››
‹‹እና ለምን አታመጣም?››
‹‹እንዲሁ…ብዙም አስቤበት አላውቅም…ግን አልገባኝም. .እንዴት ልትጠይቀኝ ቻልክ?፡››
‹‹አይ ሰሎሜ እኮ አላዛር ሞዴስ የሚሸጥ ቢሆን እኮ በየወሩ አንድአንድ ይሰጠኝ ነበር…በየወሩ እቴቴን አላስቸግርም ነበር ስትል ሰምቼት ነው፡፡››
በመደነቅ‹‹በእውነት እንደዛ አለች…?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ ብላለች››ሲል  ነበር ፍርጥም ብሎ የዋሸው፡፡
‹‹ግን የወር አበባ ታያለች ማለት ነው?››
‹‹እንዴ ለምን አታይም ሴት አይደለች?››
‹‹ማለቴ ገና ልጅ ነች ብዬ እኮ ነው፡፡››
‹‹ምነው አንተ መርጨት አልጀመርክም እንዴ?››
‹‹አንተ ደግሞ ታበዛዋለህ፡፡››
‹‹እንደውም ቆየች ..ባይሎጂ ላይ አልተማርክም እንዴ ..?አንድ ሴት እኮ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ የወርአበባ ልታይ ትችላለች፡፡››
‹‹እሱማ አውቃለሁ…በቃ አሁን አደገች ማለት ነው?››
‹‹አዎ ..በደንብ እያደገችልን ነው፡፡››
‹‹በቃ…ከነገ ጀምሮ አመጣለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ ..ለዚህ ወር ተገዝቶላታል..ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ትሰጣታለህ፡፡››
‹‹አዎ..ምንም አታስቢ በላት፡፡››
‹‹እሺ እላታለሁ..የወር አበባዋ የሚመጣው በ22 ወይም በ23 አካባቢ ነው…ስለዚህ በ20 በ20 እየመጣሁ ወስድላታለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ግን እራሷ መጥታ ለምን አትወስድም፡፡››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን
===================

ቀለል ያሉ ሌሎች ጫወታዎችን  ሲጫወቱ  አመሹና  እቤቷ ድረስ ሸኝቷት በብዙ ነገር ተወስውሶ  ወደቤት ተመልሶ  ገባና የወንደላጤ ቤቱን ከፍቶ ባዶ ቤት ውስጥ ባዶ አልጋ ላይ ብቻውን ተኝቶ  ማሰላሰል ጀመረ፡፡

ሰሎሜ ደጋግማ እንደጠየቀችው..ከተማውንም ሆነ ሁሉንም ጓደኞቹን ድንገት ጣጥሎ ፖሊስ ማሰልጠኛ  የገባበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው..በቂና ጠንካራ ምክንያት ነበረው::
አለማየው  የፈራረሰና ጣሪያው የዛገ ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ  ከእናትና አባቱ እና ከታናሽ ወንድሙ እና የሴት አያቱ ጋር የድህነት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሳቅና ደስታ የሞላበት ኑሮ ይኖር ነበር፡፡ነበር እንዲህ ህልም ሆኖ አይን ጨፍኖ ሲገልጡ እንደሚበን ማሰብ ይከብደል፡፡ያ ሞቀትና የደመቀ… በፍቅር ሀውልት የተገናባ የቤተሰብ ትስስር በአንድ ወር ውስጥ ነው ድርምስምሱ ወጥቶ የፈረሰው፡፡በወቅቱ እሱ የ13 አመት ወጣት እና የ7 ክፍል ተማሪ ነበር፡፡ድንገት አባትዬው ታመምኩ አለና አልጋ ያዘ፡፡በሶስተኛው ቀን ሰፈር ያለ ጤና ጣቢያ ወሰዱት ፡፡አንድ ቀን አድሮ እስከወዲያኛው አሸለበ፡፡ ያልተጠበቀ ስለነበረ ሁኔታው ጠቅላላ ለቤተሰቡ እንደመቅሰፍት ነበር ፡፡በተለይ ለእናቱ…፡፡አባትዬው በሞተ በማግስቱ ተቀበረ፡፡ከቀብር መልስ እናትዬው ወደ ድንኳን ውስጥ ገብታ በተነጠፈላት የሀዘንተኛ ፍራሽ ላይ ተቀምጣ ሊያስተዛዝኗት የመጣውን የሩቅም ሆነ የቅርብ እንግዶችን በመቀበል ፋንታ ወደቤት ገብታ ከባሏ ጋር ትተኛበት የነበረበት አልጋዋ ላይ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡.በሶስተኛው ቀን እስትንፋሷ በውስጧ አልነበረም…፡፡ጉድ ተባለ..፡፡ፍቅር እስከመቃብር….ማለት ይሄ ነው ተባለ…፡፡
የአለማየሁና የወንድሙ እጣ ፋንታ ግን በደካማና እድሜዋ በጋፋ ተጦሪ አያቱ እጅ ነበር የወደቀው፡፡፡ድሮም የድህነት  መቀመቅ ላይ የነበረ ቤተሰብ ውሉ የጠፋበት ሆነ፡፡ ምርጫ አልነበረም፡፡አለማየሁና ታናሹ ለመለያየት ተገደዱ፡፡አያትዬው ጎንደር ለሚኖር ሌለኛው ልጃቸው..‹‹ቢያንስ አንደኛውን ልጅ ውሰድልኝ ››ብለው ተማፀኑት..አጎትዬው ታናሹ ይሻለኛል ብለው መረጡና እሱን  ወሰዱት፡፡አለማየሁና አያትዬው ቀሩ..፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግድግዳ ሚጋሩት ቀጥሎ ካለው የቀበሌ ቤት የሚኖሩት ሰሎሜና እናትዬው ከጎናቸው ነበሩ፡፡በማፅናናቱም ካላቸው ላይ ቆረስ እያደረጉ በማጉረሱም አልተለዬቸውም ነበር፡፡ከዛ አያትዬው ሁለመናው ጭልምልም ሲልባቸው.የሰሎሜ እናት እቴቴን ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው‹‹ …እኔ በቃኝ፡፡ ለራሴ ማልሆን ሰው የልጅ ልጄን ጠቅመዋለው ብዬ እዚህ  አልቀመጥም…፡፡ጭራሽ ሸክም ነው የምሆንበት፡፡አንቺ ለእናቱ ጎደኛዋ ነበርሽ…አለማየሁንም ልክ ከሰሎሜ እኩል አንቺም አሳድገሽዋል ፡፡..ልጅሽ ነው…፡፡አሁንም አንቺው ነሽ ምታጎርሺን.. ስለዚህ እኔ የልጅ ልጄን ላንቺ ጥዬ ወደ ገዳም መሄዴ ነው…ባይሆን እዛ ሄጄ ፀልይልሻለሁ››በማለት አለማየሁን  ለሰሎሜ እናት ጥለውት ጠቅልለው ገዳም ገቡ፡፡አለማየሁ ብቻውን ቀረ …፡፡
ከዛ ሁሉ ከሞላ ቤተሰብ አመት ባልሞላ ጊዜ ቀስ በቀስ እየበነኑ ጥለውት በመሄዳ ባዶውን አስቀሩት፡፡ በቃ ባዶውን…፡፡ግን ሰሎሜና እናትዬው ከመጠን በላይ እንዲሰበርና አልፈቀዱለትም፡፡ለሰሎሜም እህት ለእሳቸውም ሁለተኛ ልጅ ሆነ ፡፡በመሀከል የሚያዋስናቸውን ግድግዳ ቀደው የውስጥ ለውስጥ በር አበጁለትና አንደኛውን በር ዘጉት፡፡ሁለት የተለያ ክፍል የነበረው ቤት ሁለት  ክፍል ያለው አንድ ቤት ሆነ፡፡
እሱ ከትምህርት ቤት በተረፈው ጊዜ ሰፈር ውስጥ እየተሯሯጠና እየተላላከ በሚያገኘው ብር እራሱን መደጎም ቀጠለ፡፡የሰሎሜ እናት በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ስለሆኑና ቆሚ ደሞዝ ስላላቸው..ምንም እንኳን የተትረፈረፈ ኑሮ ባይኖራቸውም ለሁለቱ ልጆችና ለእራሳቸው ለለት ጉርስ የሚቸግራቸው አይነት ሰው እልነበሩም…አለማየሁን ከልጃቸው እኩል ለማኖር የእለት ጉርስንና የአመት ልብሱን ለመሸፈን ቸግሯቸው አያውቅም፡፡በዛ ላይ አለማየሁን ከልጅነት ጀምሮ ሚወዱትና ከእናትዬው ጋር ካላቸው ቅርበት የተነሳ ብቸኛ ልጃቸውን ክርስትና የነሳቸው የእሱ እናት ስለሆነች ልጄ ወንድም ይሆናታል  በሚል አመለካከት ከልባቸው ነበር የተቀበሉት፡፡በዛ ላይ ከዚህ በፊት ልጃቸው በህይወትና በሞት መካከል ሆና ሆሲፒታል በገባች ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እሷን ለማትረፍ ያደረጉትን ታሪካዊ ድርጊት መቼም አይረሱትም…እናም ደግሞ ለሌላ ለማንም ሰው የማይነግሩት ተጨማሪ ዋና ምክንያትም ነበራቸው፡፡
.ከዛ ቀስ በቀን ከሰሎሜ ጋር ያለውን ግንኙነት እያላላ ከእናትዬውን ግን በወጉና በስርኣቱ በስልክ እየጠየቀ ስልጠናውን ጨርሶ በምክትል መቶ ሀለቅነት ተመረቀ..ከዛ አዲስ አበባ አካባቢ የመመደብ እድል ቢኖረውም በራሱ ምርጫ ድሬደዋ እንዲመድቡት አድርጎ እርቆ ሄደ፡፡ይሄንን ታሪክ ሰሎሜ ሆነች ሌሎች ጓደኞቹ አያውቁም..አይደለም በዛ ጊዜ ዛሬም እንዲህ ነበር ብሎ ሊነግራትና ሊያብራራላት አይችልም….ከባድ ነው፡፡በሀሳብ ሰውነቱ ስለዛለ ለመተኛት ወደ መኝታ ቤቱ ሄዶ …ድንገት ሳያስበው የአላዛር  ምስል በአእምሮ ተሰነቀረ፡፡

‹‹አሁን አላዛር ህክምናው ባይሳካለትስ…?ሰሎሜ ወደፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዛ እንድትሄድ መክራታለው ወይስ ምን አደርጋለው….? ፍርድ ቤቱ እንዲፋቱ ከወሰነስ በኋላ ከእሷ ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው የሚሆነው…?አሁን ሳይቸግረኝ ሳፈቅራት እንደኖርኩና አሁንም እንደማፈቅራት ነገሬታለሁ…እና በቀጣይ ፡፡ ርቃታለሁ ወይስ የበለጠ ከእሷ ጋር ያለኝን ጓደኝነት አጠናክራለሁ….?እና ከዛስ…አሁን ተራው የእኔ ነው አግቢኝ እላታለሁ? ወይስ ?››..እራሱን አመመው፡፡

ስለምንም ነገር ማሰብ አቁሞ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ለመተኛት በመፈለግ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ቢጃማ እየቀያየረ ሳለ ስልኩ  ድምጽ አሰማ..አነሳውና አየው… መልዕክት ነው፡፡ሰሎሜ ነች የላከችው፡፡

‹‹አሌክሶ ..በሰላም እቤት ገባህ..?››ይላል፡፡

‹‹አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለና  መልስ ፅፎ ላከላት‹‹አዎ….ቢራ ቢሮዋ  ሰላም ገብቼለሁ?››

ከልጅቷ ጀምሮ በጣም ቀጭን እና በንፋስ ግፊት በአየር ላይ ተንሳፋ የምትበር ስለምትመስል ቢራቢሮ የሚል ቅፅል ስም አላት…ብዙውን ጊዜ እሱ በዚህ ስም ነው የሚጠራት፡፡

‹‹ጥሩ…ደስ የሚል ምሽት ነበር ያሳለፍነው…አመሰግናለሁ››

‹‹እኔም የልጅነት ጊዜዬን ወደኋላ ተመልሼ እንዳስታውስ ስላደረግሺኝ  ደስ ቢለኝም የተዳፈነ የልጅነት ፍቅሬን ስለቀሰቀሺብኝ ችግር ላይ ነኝ፡፡››ብሎ  ፃፍላና ላከላት፡፡

‹‹አንተ ባለትዳር እኮ ነኝ…ለምን ታሽኮረምመኛለህ?››

‹‹ይቅርታ ምን ላድረግ..?እንደምታውቂው ፍቅር  ይሉኝታ ቢስ ስሜት ነው፤ለማንኛውም አላዛርን ሰላም በይልኝ››

‹‹አይ …እራስ ደውለህ ሰላም በለው፤.ሌላ ነገር እንዲያስብ አልፈልግም…በመጀመሪያ ጉዳዩን ስለነገርኩህ እራሱ በጣም ቅር ብሎታል?፡፡››

‹‹አይ ታዲያ ምን ማድረግ ትችይ ነበር..?እስከመቼ ለብቻሽ በጉዳዩ መሰቃየት ትችያለሽ?››

‹‹አየህ አንተ ከልጅነቱ ጀምሮ የምታውቀው ጓደኛው ነህ.. ሁለታችሁም በጋራ የምታውቋቸው በርካታ ሰዎች አሉ ....ይሄንን ጉዳይ አንተ አወቅከው ማለት ሌሎች እሱንና አንተን የሚያውቁ ሰዎችም የማወቅ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው. .ይሄ ደግሞ ስነልቦናውን ይበልጥ ይጎዳል…..በዛ ላይ እንደምታውቀው የእናንተ የወንዶች ኢጎ ከፍተኛ ነው፡፡››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
:
:
#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

‹‹እሺ ቻው ሁሴን…››ስልኩን ዘጋ፡፡ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር ነው፡፡ድብልቅልቅ የሆነ የሚረብሽ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው፡፡ደስታም መረበሽም ….አሁንም ሶስቱም  አንድ ላይ ተገናኝተው  ሰሎሜን ከበው ሲቀመጡ ምን እንደሚሰማቸውና ምንስ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አልቻለም፡፡

እርግጥ አሁን እንደድሮው አይደለም ሰሎሜ የአላዛር ህጋዊ ሚስት ሆናለች፡፡ግን ደግሞ በመሀከላቸው ያለው ሸለቆ ስምጥና  እሩቅ ነው፡፡እና አላዛር ከበሽታው ማገገም ተስኖት ሁለቱ ከተፋቱ ሰሎሜን መልሶ ለማግኘት ሁለቱ ይፎካከራሉ ማለት ነው…አለማየሁና  ሁሴን…..‹‹ምን አልባት እሱ እስካሁን ባለበት ሀገር አንዷን ወዶና አጭቶ ወይንም አግብቶ ሊሆን ይችላል… እንደዛ ከሆነ ግልግል ››ሲል አሰበና እራሱን እንደምንም ለማረጋጋት ጥረት ማድረግ ጀመረ፡፡
የሁሴንን ድምፅ በስልክ ከሰማ በኃላ  የአላዛርን የህክምና ውጤት ለማወቅ በጣም ነው የጓጓው…ደውሎ ሊጠይቀው አስበና ደግሞ ምን ብሎ እንደሚጠይቀው ስላልገባው  ሀሳቡን ሰረዘ፡፡

…‹‹እራሱን ወይም ልቡን አሞት ቢሆን ኖሮ በቀላሉ ደውዬ የድሮ ጎደኛዬ ልብህን እንዴት ሆንክ ..?አሁን ምን ይሰማሀል…?ምርመራው ምን ውጤት አስገኘ….?ምናምን እያልኩ በዝርዝር እጠይቀው ነበር፡፡››ሲል ተነጫነጨ…ድንገት ብልጭ አለለትና ከተኛበት አልጋ ተነሳና ቁጭ አለ.. ስልኩን ከተቀመጠበት አነሳና ዳታ አበራ…..
ስንፈተ ወሲብ ብሎ ሰርች ሲያደርግ ብዛት ያላቸው መረጃዎች ተዘረገፉለት…የመጀመሪያውን ከፈተ፡፡
ስንፈተ ወሲብ ወይም የወንድ ብልት አለመቆም ችግር ለወንዶች አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ ችግር የወንዶችን በራስ መተማመን የሚቀንስና ፍርሃት የሚያሳድር ነው። ስንፈተ ወሲብ ማለት በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የወንድ ልጅ ብልት በደንብ መቆም አለመቻል ነው።
ንባቡን አቆመና ማሰብ ጀመረ..‹‹የእሱ ግን ያለመቆም ችግር ነው እንዴ..?ነው ወይስ ሙሉ በሙሉ ፍላጎት ማጣት…?.››መረጃው ስለሌለው ማሰቡን አቁሞ ንባቡን ቀጠለ፡፡
ስንፈተ ወሲብን ማከም የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
•  ስኳር የበዛባቸው ምግቦች የወሲብ መነሳሳትን ወይም የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ስለሚችሉ ብዙ ስኳርንና ከፍተኛ ካርቦሀይድሬት ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ።
•  የኮሌስትሮል መጠናችን ጤነኛ በሚባለው ደረጃ መቆጣጠር።
•  የደም ፍሰትን ለመጨመር ከፍተኛ አሚኖ አሲድ ያላችው ምግቦችን መጠቀም።
•  በዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም የቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዲመረት የሚረዱ ሰፕልመንቶችን መውሰድ።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች ቀለል ያለ የስንፈተ ወሲብ ችግር ላለባቸው ሰዎች እንደመፍትሄ የተቀመጠ ሲሆን ከዛ ከፍ ያለና አሳሳቢ የሆነ ስንፈተ ወሲብ ችግር ካለብዎ የሜዲካል ህክምና ማግኘት እንደ  ኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክም ማግኘት ይገባል ይላል፡፡የኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክምና የታካሚው ብልት ውግት አድርጎ በመያዝ ዝቅተኛ ኢንተንሲቲ ባለው ግፊት ሞገድ ወደ 4000 ሾክ በወንዱ ብልት 4 ቦታ ላይ የብልት የደምስሮችን ለማነቃቃት ይሰጣል። በዚህ ህክምና ታካሚው በሳምንት ከ1-2 ጊዜ በተከታታይ ለ12 ሳምንት ህክምናውን መውሰድ አለበት።
የሚያነበው ነገር ሁሉ ምንም እየገባው አይደለም…ልክ ያንቀላፋ ያለን ልብ በኤልኬትሪክ ሾክ መንጭቆ እንደማስነሳት አይነት ህክምና ይሆን እንዴ..?ልክ እንደዛ በብልት ዙሪያ  የኤሌክትሪክ ንዝረት በመልቀቅ ተመንጭቆ እንዲነሳና እንዲያቆም ማድረግ ይሆን እንዴ….?ተመንጭቆ ተነስቶ አልተኛም ቢልስ?››በራሱ ጥያቄ እራሱ ሳቀ፡፡

እግዚያብሄር ከዚህ አይነት በሽታ አንዲሰውረው  በመፀለይ ስልኩን አጠፋና መልሶ ተኛ፡፡

በሶስተኛው ቀን ከስራ ወደቤት እየተመለሰ  መንገድ ላይ እያለ  አላዛር ደወለለት፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር እንዴት ነህ?››

‹‹ምንም አልል ሰላም ነኝ››
ምን ሊነግረው እንደደወለለት  ለማወቅ በከፍተኛ ጉጉት ‹‹አይ ጥሩ ነው…ምነው ፈለከኝ….?.››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አዎ …ነገ ማታ እራት ብጋብዝህ ብዬ አሰብኩ››

‹‹ይቻላል….የትና በስንት ሰዓት እንደምንገኛኝ ንገረኝ..እገኛለሁ››

‹‹ጥሩ …ቴክስት አደርግልሀለው››

‹‹እሺ እጠብቃለሁ….ግን ሰላም ነው አይደል…?ማለቴ የተነጋገርነው ህክምና በተመለከተ አዲስ ነገር አለ?››በመከራና በጭንቀት ጥያቄውን አፈረጠው…
እስከነገ እንዴት  ብሎ አምቆ ይያዘው…?‹‹የእራት ግብዣው ሙሉ በሙሉ ተፈወስኩ ብሎ የምስራች ሊለኝ ቢሆንስ?.››ሲል አሰበና ተጨነቀ፡፡ የእሱ የምስራች ማለት ለእሱ በተዘዋወሪ  መርዶ ነው….

‹‹አሌክስ  ያው በተነጋገርነው መሰረት ቀናቶች አሉኝ አይደል?››

‹‹አዎ ..20 ቀን አለህ…እንዲሁ ሂደቱ እንዴት እየሄደልህ ነው የሚለውን ለማወቅ ነው››

‹‹ለጊዜው ሁሉ ነገር በሂደት ላይ ስላለ መጨራሻውን በእርግጠኝነት አላውቅም ..ሀኪሞቹም የሚያውቁ አይመስለኝም››

‹‹ጥሩ ..በእኔ በኩል ላግዝህ የምትፈልገው ነገር ካለ ሁሉ ጊዜ አለሁልህ…አሁን መራራቃችንን ሳይሆን የልጅነት ቅርበታችንን  አስበህ ምንም ነገር ልትጠይቀኝ ትችላለህ….ይሄ ነገር ተስተካክሎ ሁለት የልጅነት ጓደኞቼ ደስተኛ የሆነ ትዳራቸውን እንዲያስቀጥሉ እፈልጋለው…ሁለታችሁንም ስል ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ››አለው…ንግግሩ ለራሱ  ጆሮ እንግዳ ስሜት ነው የፈጠረበት፡፡
‹‹በእውነት አሌክስ ይህንን መስማቴ ደስ ብሎኛል…በቀደም ቢሮህ ተገናኝተን  በጉዳዩ  ላይ ስንወያይ ንግግርህ ጨከን ያለ ነበር…ይቅርታ አድርግልኝና እንደውም…የሄ ልጅ የእኛን መለያየት ይፈልጋል እንዴ?ብዬ እንዳስብ ነበር ያደረከኝ..ያንን ስሜቴን ደግሞ በእለቱ ነግሬሀለው››ሲል እውነቱን አፍርጦ ነገረው፡፡

እንደዛ ሲለው ዛሬም መደንገጡ አልቀረም….ያን ያህል እስከሚያስታውቅበት እንደዘባረቀ አልተሰማውም ነበር…..ማስተባበሉን ቀጠለ‹‹እንዴ ምን ነካህ ?ለምንድነው እንድትለያዩ የምፈልገው?››

‹‹ያው ታውቃለህ አይደል…..?››

‹‹ምኑን ነው የማውቀው?››

‹‹ያው ልጅ ሆነን ጀምሮ ሶስታችንም ነበር የምናፈቅራት››

‹‹ልጅ ሆነን ነበራ ››

‹‹አሁን እንደውም በይበልጥ ውብና ማራኪ ሆናለች እኮ…እንደውም በበለጠ በፍቅር የምታማልለው አሁን ነው…ማለቴ ስሜቱን በራሴ አውቀዋለው..በየጊዜው ትንሽ ባደገችና እድሜ በጨመረች ቁጥር ውብና ማሪኪ እየሆነች እኔም አምርሬ እያፈቀርኳት ነው እየሄድኩ ያለሁት››

‹‹አላአዛር…አንተ እኮ እንደዛ ቢሰማህ ሚስትህ ስለሆነች ነው…..እኛን በተመለከተ የምታወራው ግን የልጅነትና ያለፈ ታሪክ ነው››

‹‹ለማንኛውም እንደዛ ስላሰብኩህ ይቅርታ…በእውነት ያንተን እገዛና ማበረታቻ በጣም ነው የሚያስፈልገኝ…በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንተ በተሻለ የሚረዳኝና የሚያግዘኝ ሰው እደሌለ እኔም  አምናለው››

‹‹አዎ እንደዛ ጥሩ ነው..በል አሁን ቻው …ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹.ቻው እሺ ..አመሰግናለሁ፡፡››
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁ በቀጠሮው መሰረት  ከአላዛርና አለማየሁ ጋር ከተገናኘ በኋላ ‹‹እሺ ባላና ሚስቶች ለምንድነው የፈለጋችሁኝ….?ለጥሩ ነገር እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡››ሲል የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ..አንተ ንገረው አንቺ ንገሪው እየተባባሉ የሚገባበዙ ይመስላል አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት ሁሴን እንደሚመጣ ታውቃለህ አይደል?››

ያልጠበቀውን ርዕስ ነው ያነሳበት‹‹ትክክለኛውን ቀን አላውቅም እንጂ  እንደሚመጣ አዎ በቀደም ደውሎልኝ ነበር..››

‹‹ጥሩ እንግዲህ ..እናቱም አባቱም እንደሞቱ ታውቃለህ…..እዚህ ሌላ ዘመድ የለውም ..ከፋም ለማም የልጅነት ጓደኞቹና የቅርቡ ሰዎች እኛ ሶስታችን ነን››

በውስጡ ‹‹የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች›› የሚለውን ተረት  እየተረተበት ‹‹አዎ ትክክል››ሲል መለሰ፡፡

‹‹እና እንዴት እንቀበለው የሚለውን ለመነጋገር ነው፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ይሄ የድሮ ጓደኛችንን የመቀበል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኛም መልሰን ለአመታት ተራርቀን ከቆየንበት ለመቀራረብና መልሰን ጓደኝነታችንን ለማደስ ያግዘናል….››አለ
…እንደዛ ሲል በውስጡ ያለው ከአላዛር ወይም ከሁሴን ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ድሮ ጓፈደኛነታችው የመመለስ ጉጉት ኖሮት አይደለም..ከዛ ይልቅ ስለሰሎሜ በውስጡ እያሰበ ነው፡፡

‹‹በጥሩ ሁኔታ ብንቀበለው ደስ ይለኛል…እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ….ዝግጅቱን እኔ ቤት ማድረግ እንችላለን››አለ…

‹‹አይ ከአንተ ቤት የእኛ ቤት ይሻል ይመስለኛል….ማለት የወንደላጤን ቤት ማድመቅ ይከብዳል›› ሰሎሜ  ነች ተናጋሪዋ፡

‹‹እሺ እንዳልሽ…እኔ  ቤት ብንቀበለው በዛውም የራሱን ነገር እስከሚያመቻች አኔ ጋር መቆየት ይችላል ብዬ ነው፡፡››

‹‹እኛ ጋርስ ለመቆየት ምን ይከለክለዋል…?እቤታችን እንደሆነ እንኳን እሱንና  አንተም ብትጨመር በቂ ክፍት ክፍሎች አሉን ….እንደምታውቀው እዛ አፓርታማ ቤት ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ነን....ልጅ የለን ምን የለን››

በሰሎሜ ንግግር አላዛር ሽምቅቅ አለ..ሆነ ብላ አስባበት የተናገረችው እንደሆነ   ያውቃል….ግን ዋጥ አድርጎ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ ምርጫ እንደሌለው ያውቃል፣ያደረገውም እንደዛ ነው፡፡
አለማየሁ‹‹በቃ እሺ እጅ ሰጥቼለው››ሲል በሀሳባቸው ተስማማ፡፡

‹‹ጥሩ  በቃ …እንደዛ ከሆነ በፊታችን እሁድ ቤት ናና ስለዝርዝሩ እንነጋገርበታለን››

‹‹ጥሩ..እንደውም በሰበቡ ቤታችሁን አያለሁ››

‹‹አዎ ››
ከዛ በኃላ ብዙም ያወሩት ነገረ የለም ፡፡ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡

‹‹አላዛር እና ሰሎሜ በአንድ መኪና ገብተው ወደቤታቸው እየተጓዙ ወሬ ጀመሩ‹‹ግን እርግጠኛ ነህ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምኑን?››

‹‹ማለቴ  የሁሴን እኛ ቤት ማረፍ….ነው ወይስ አንድ ሁለት ቀን እኛ ጋር ካደረ በኃላ ሌላ ማረፊያ ፈልግ ልንለወው ነው፡?››

‹‹ለምን …አንቺን ካልደበረሽ እቤታቸን ሰፊ ነው…ሁሴን የማናውቀው ሰው አይደለም ….ለሁለታችንም ቅርብ የሆነ ሰው ነው፡፡››

‹‹ገባኝ….በደንብ አስበህበታል ወይ ለማለት ነው…?.እኔማ ደስ ይለኛል..ግን እወቅ እንደነገረኝ ከሆነ እስከሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡››

‹‹ችግር የለውም..ታውቂያለሽ የሆነ የእኛ የምንለው ሰው አብሮን እንዲኖር እንዴት እፈልግ እንደነበረ…እህቶቼም ሁለቱም ስላገቡ ወደቤታችን ላመጣቸው አልቻልኩም…የአንቺም እናት  አሻፈረኝ ብላለች..እስኪ አሁን በጓደኛችን እንሞክረው፡፡››

‹‹እማዬ እኮ ከእናንተ ጋር አልኖርም አላለችም..እሷ ያለችው ልጅ ስትወልዱ እሱን ለማሳደግ መጣለሁ…አሁን ግን መጥቼ የእናንተ ሞግዚት መሆን አልፈልግም ነው ያለችው››።

‹‹እና በሞግዚት ኑሪ እንጂ  ሞግዚት ሁኚን  መች አልናት?››

‹‹ተወው አሁን… ለምን የማይሆን ጭቅጭቅ ውስጥ እንገባለን…ቁርጥ አድርጋ አቋሟን አሳውቃለች…መውለድ ስንችል ትመጣለች››

‹‹ይሁን እሺ… ለማንኛውም ስለሁሴን አትጨነቂ… ሁኔታዎች ካልተመቹት እኮ እራሱ አማራጭ ይፈልጋል፡፡››በማለት የተጣመመውን ርእስ እንደምንም ብሎ አቃናው፡፡

‹‹ጥሩ..ለእኛም ከብቸኝነት ጋር ከመታገል በተወሰነ መንገድ ይታደገናል…›› ስትል መለሰች፡፡

‹‹እኔም እሱን አስቤ ነው ››አላት..ግን ሁለቱም ስጋታቸው ሌላ እንደሆነ ግልፅ ነው…ሁሴን ልክ እንደአላዛር ሁሉ የሰሎሜ የልጅነት አፍቃሪዎ እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ለሁለቱም እኩል ጓደኛቸው ቢሆንም ለእሷ ግን በተለየ መልኩ አፍቃሪዋም ጭምር ነው…እና አሁን አንድ ቤት እሱን ጎትቶ ማምጣት ለዛውም አሁን ባልና ሚስቶቹ ባሉበት ሁኔታ ላይ አደጋ እንዳለውና የልታሰበ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል…ለሁለቱም ግልፅ ነው….እና ሰሎሜ ደጋግማ ስለውሳኔው እርግጠኝነት እየጠየቀችው ያለው..ነገ አንድ ነገር ቢከሰት  ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡

እሷ ያላወቀችው ግን የእሱን እቅድ ነው…እሱ ሁሴን ወደቤት  እንዲመጣ ሲወስን መዘዙንም አስቦና አስልቶ ነው፡፡ምን አልባት የጀመረው የህክምና ጉዳይ ባይሳካለት ሊያደርግ የሚችለውን እቅድ አስቦና አስልቶ ጨርሷል..በቃ እራስ ወዳድ መሆን እንደሌለበት ገብቶታል…እየወደደም ቢሆን ከሰሎሜን ህይወት ሾልኳ መውጣት  እንዳለበት ወስኗል.. ከህይወቱ ሲሸኛት ግን በተሰበረ ልብ ሆና  ስነልቦናዋ ተጎድቶ መሆን እንደሌለበትም ነው የሚያምነው..ለእሱ መሆን ካልቻለች ከሁለት የልጅነት ጓደኞቾና ከልብ ከሚያፈቅሯት መቼም ቢሆን ሊጎዶት ለማይችሉት ለአንዱ ሊያስረክባት ነው ያሰበው….ለዛም ጥሪጊያ መንገድ ለመፍጠር ሁሴን በእንግድነት እሱ ቤት ማረፍ እንዳለበት ማድረግ እንዳለበት ተሰምቶታል፡፡፡ያንን ካደረገ ደግሞ አለማየሁም በተደጋጋሚ ወደእሱ ቤት ለመመላለስና ከሰሎሜ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመገናኘት እድል ይኖራዋል፣በሂደት ከሁለት አንዱ ከእሷ ጋር በተሻለ መቀራረብ ይፈጥሩና ልቧን ማግኘት ይችሉ ይሆናል….ከዛ አንዱ ያገኛታል ማለት ነው፡፡ከዛ እሱ ሀዘኑን ለብቻው ያዝናል..ማጣቱን በማስታመም ቀሪ የብቸኝነት ዘመኑን ይገፋል…….፡፡እግዚያብሄር ቀንቶት ከተፈወሰ ደግሞ በቃ ምን ይፈልጋል…እና አሁን እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ይሄ ነው ሰሎሜን ያልገባት፡፡

ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከሰሎሜ ይልቅ አለማየሁን ነው ፍፅም ግራ ያጋባው‹‹ሰውዬው ምን እየሰራ ነው?››የሚለው ሀሳብ በውስጡ መጉላላት የጀመረው ገና ከእነሱ እንደተለየ ነው፡፡እና ደግሞ አልተመቸውም….በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሴን ወደሀገር ቤት ተመልሶ መምጣት ደስ አላሰኘውም ነበር፡፡፡በእሱ እምነት አላዛር ካልተሳካለት ቀጥታ ሰሎሜን የእሱ የማድረጉን ትግል በብቸኝነት ለመወጣት ነበር ዕቅዱም ምኞቱም..ሁሴን ደውሎ እንደሚመጣ ከነገረው በኋላ ግን ሌላ ተፋላሚ እየመጣበት እንደሆነ ነው ወዲያው የገባው…እንደውም መምጣቱ እራሱ ያጋጣሚ ነገር ሳይሆን  ሆነ ብሎ የታሰበበት እንደሆነ ነው የሚጠረጥረው…ሰሎሜ አላዛርን ከማግባቷ በፊት ከእሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደምትደዋወል ነግራዋለች..በእሷ እና  በባሏ መካከል ያለውን ቦንብ ሚስጥር ለእሱ በተገናኙበት በመጀመሪያው ቀን ከነገረችው…ለረጅም ጊዜ ስትደዋወል ለነበረው ለዛውም ከባህር ማዶ ላለው ሁሴን ላትነግረው የምትችልበት ምክንያት ምንም እየታየው አይደለም…እንደጠረጠረው ነግራው ከሆነ ደግሞ በተለይ የሰሞኑን ግር ግር አብራርታለት ከሆነ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ አጋጣሚውን ለመጠቀም እንደመጣ ነው የሚያምነው..እና ከእሱ ጋር
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

..ፎጣዋን አገልድማ ስትወጣ እሱ ደግሞ ለመግባት እርቃን ሰውነቱን በፓንት ብቻ ሆኖ ወደእሷ አቅጣጫ ሲመጣ አየችው…ዞር ብላ መንገዱን ለቀቀችለት …ቀጥታ ወደውስጥ ገባና የሻወሩን በራፍ ዘጋው…
ባለቤቷን እንዲህ እርቃኑን ስታየው ሁሌ እንደአዲስ እንደገረማት ነው፡፡ሰለብሪቲ አክተር ወይም ታዋቂ ሞዴል እኮ ነው የሚመስለው፡፡እዚህ አካባቢ እንደዚህ ቢሆን የሚባል ቅር የሚያሰኝ የአካል ክፍል የለውም‹‹ሆሆ..ለናሙና የተፈጠረ እኮ ነው የሚመስለው››አለችና ሰውነቷን አደራርቃ በምሽቱ ሶስቱን የእድሜ ልክ አድናቂዎቾና አፍቃሪዎቾ ወንዶችን ያስደምማል ያለችውን አለባበስ ለበሰች፡፡ፀጉሯን አስተካከለች፡፡የተወሰነ ሜካፕ ተጠቀመችና ሽቶ እላዮ ላይ ነስንሳ ወደሳሎን ወጣች፡፡
አለማየሁ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ  ዝንጥ ብሎ  ሳሎን ቁጭ ብሎ እስኪወጡ እየጠበቃቸው ነበር፡፡
እንዳየችው ‹‹እንዴ ኩማንደር….አምባሳደር መስለሀል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹የወደፊት እጣ ፋንታዬ ምን አልባት አምባአሳደር ሊሆን ይችላል፡፡››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምነው አፍጥጠህ አየሀኝ…ልብሱ አልሄደብኝም እንዴ?››ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት፡፡

‹‹አረ የሚያስደነግጥ አለባበስ ነው … እንከን አይወጣለትም ..በጣም ያምራል፡፡››

‹‹ልብሱ ብቻ ነው ሚያምረው?››ስትል ልስልስ በሆነ ቅንዝራም ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹ስለአንቺ አላዛር ሲመጣ ይነግርሻል….ያንን አስተያየት የመስጠት መብት ለጊዜው የእሱ ነው፡፡››

ግንባሯን ቋጠረች‹‹ለጊዜው ስትል…?››

‹‹ይሄ ጥያቄ ይዝለለኝ፡፡››

‹‹በጣም ተቀይረሀል ..ድሮ እንደዚህ አልነበርክም››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ከእኔ ጋር ለምትነጋገረው ነገር ስትጠነቀቅ አይቼህ አላውቅም ..እንደመጣልህ በነፃነት ነበር የምናወራው፡፡ትዝ ይልሀል ..አንተ እኮ ጓደኛዬ ብቻ አልነበርክም….አንድ ቤት ውስጥ አብረኸኝ ያደክ ወንድሜ ነህ፡፡››

‹‹አዎ..በልጆቼን በሞት ሳጣና አያቴም በቃኝ ብላ ገዳም ጥላኝ ስትገባ ..አንተም ልጄ ነህ ..ከልጄ ጋር አሳድግሀለው ብላ የወሰደችኝ እናትሽ እቴቴ ነች፡፡በእውነት ለእሷ በሚገባው መጠን አልተንከባከብኳትም…፡፡››

‹‹ተው ተው..እቴቴንማ በጣም ነው የተንከባከብካት፡፡.በየጊዜው ብር እንደምትልክላት ማላውቅ ይመስልሀል፡፡እዚህ ከተቀየርክ በኃላ  እንኳን እሷን ደጋግመህ አግኝተህ እኛን ግን ለማግኘት ፍቃደኛ አልነበርክም፡፡ካንተ ደግሞ ይልቅ ደግሞ የሚገርመኝ የእሷ ያንተ ተባባሪ ሆና መደበቅ፡፡ …እንደውም አንዳንዴ ከእቴቴ ጋር ስንጣላ እኮ…‹‹ከአንቺ ይልቅ የእኔን እናትነት የተረዳው አለማየሁ ነው…››እያለች ታበሳጨኛለች፡፡እና እሷ በአንተ ደስተኛ ነች…ትንሽ ቅር ሚላት በየጊዜው በአካል ሄደህ ስለማትጠይቃት ነው፡፡በዛ ከአንተ እኔ እሻላለሁ….፡፡››

‹‹ቢሆንልኝ…ለእሷ ምንም ነገር ባደርግ ይገባታል፡፡››

‹‹ለእኔስ…ለስድስት አመት የት እንዳለህ እንኳን ደውለህ አሳውቀሐኝ አታውቅም…አለማየሁ ደወሎ እንዲህ አለ…አለማየሁ ደውሎ በባንክ ይሄንን ላከ ሲባል እንጂ አንድ ቀን ሰሎሜ ሰላም ብሎሻል…?ሰሎሜ አለማየሁ ሰለአንቺ እንዲህ  ያስባል ብሎ የነገረኝ ሰው የለም..ሁል ጊዜ አእመሮዬን እንደበላኝ ነው…‹‹ምን አድርጌዋለው…?መቼ ቀን ነው ያስከፋሁት …?.የቱ ጋር ነው የተቀየመኝ? ብዬ እንደተከዝኩ ነበር..እወነቱን ለመናገር በጣም ተቀይሜህ ነበር ..ባገኝህ እንደማላናግርህ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር..ግን በእንደዛ አይነት ሁኔታ ስንገናኝ…ምንም ማድረግ አልቻልኩም...ተቀይሜህ እንደነበረ ራሱ ከእስር ተፈትቼ ቤቴ ከገባው በኃላ ነው ያስታወስኩት፡፡››

‹‹ጥሩ ነው፣ ቂመኛ አይደለሽም ማለት ነው…አንቺን ያላገኘሁሽ ግን ላላገኝሽ ስላልፈለኩ ሳይሆን ተገድጄ ነው››

‹‹ተገድጄ ስትል?››

‹‹ማለቴ….››ንግግሩን እንዳንጠለጠለ አላዛር ከእነሱ በበለጠ.. ልክ እንደእለቱ ሙሽራ ዝንጥ ብሎ ወደእነሱ ሲመጣ ስለተመለከተ ለንግግር የተከፈተ አፉን መልሶ ዘጋ፡፡

‹‹በሉ…እንሂድና …ቀደም ብለን እዛው አካባቢ ደርሰን ብንጠብቀው ይሻለል፡፡››

አለማየሁ አላዛር መጥቶ ማውራት ከማይፈልገው ነገር ስለገላገለው በመደሰት ‹‹ጥሩ …እንሂድ››አለና ከተቀመጠበት  ተነሳ፡፡ርምጃውን ከአላዛር አስተካክሎ ወደውጭ መራመድ ጀመረ.፡፡ሰሎሜ ከኃላ ሁለቱንም በትኩረት እያየች ተከተለቻቸው፡፡ሁለቱም ፈርጣማና ወንዳወንድ የሚባሉ ናቸው፡፡ግን አላዛር ወደላይ የተሳበ መለሎ ነው፡፡
//
ከ30 ደቂቃ ጥበቃ  በኋላ የተጠበቀው ሁሴን ግዙፍ ሻንጣውን በጋሪ እየገፋ ከተርሚናሉ ሲወጣ ሶስቱም በእኩል አዩት…በደስታና በጩኸት እንዲያያቸው እጃቸውን አውለበለቡለት…ሁሴን ከዛሬ ስድስት   አመት  በፊት እደሚያውቁት አይነት ነው፡፡ እንዳዛው ውልምጭምጭ ቀጫጫ…ባለትልቅ ጭንቅላትና ሉጫ ፀጉር…የህፃን የመሰለ ፍልቅልቅ ፊት…ነጭ ከሩቅ አይን የሚስብ  በረዶ መሳይ ጥርስ ……
ሶስቱም በየተራ እየተጠመጠሙበት ሰላምታ ከሰጡትና ይዘው የመጡትን የእንኳን በሰላም መጣህ ምኞታቸውን የሚገልፅ  አበባ አስታቀፉት፡፡ከዛ በኃላ አለማየሁና አላዘር ሻንጣውን ተቀብለው  ወደመኪናው ወሰዱና ከኋላ ጫኑለት፡፡…በአላዛር ሹፌርነት ሰሎሜ ገቢና ከእሱ ጎን ተቀምጣ አለማየሁና ሁሴን ከኋላ ሆነው ወደቤት ጉዞ ጀመሩ፡፡

ድንገት‹‹ይገርማል…?››አለ ሁሴን፡፡

አለማየሁ‹‹ምኑ ነው የገረመህ?ከተማዋ ልደቷን የምታከብር የቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ መሰለችህ አይደል…?››አለው፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹አሸብርቃና ተኳኩላ …በደማቅ መብራቷች ተንቆጥቁጣ ስታያት ገርሞህ እንደሆነ ብዬ ነዋ?››

‹‹..አዎ ያልከው ነገር በጣም አስገርሞኛል..ግን እኔ ለማውራት የፈለኩት ሶስታችሁን በአንድነት መጥታችሁ ትቀበሉኛላቹሁ የሚል ምንም አይነት ግምት ስላልነበረኝ በዛ መደነቄን ነው፡፡፡፡›

ልክ እንደሁሴን እሷም ሶስቱም የልጅነት እና የአፍላ ወጣትነት ጓደኞቾ እና አፍቃሪዎቾ ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲህ አንድ ላይ ተሰብስበው አይናቸው እሷ ላይ ሲያቁለጨለጩ በመመለከቷ እየተገረመች‹‹ምን ማለት ነው? ሶስታችንም እኩል ጓደኞችህ አይደለንም እንዴ…?ለመሆኑ መጥቶ ይቀበለኛል ብለህ የገመትከው ማንን ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው አሌክስን ነበር፡፡እናንተን በማግስቱ ባገኛችሁ ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡››

‹‹አንተ …ከእኛ ይልቅ አሌክስ ቁምነገረኛ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው…?ነው ሰው ሀገር ከሄድክ በኃላ ፀባያችን ተምታታብህ››አለችው ሰሎሜ በመገረም፡፡

አለማየው በፈገግታ‹‹አንቺ …ሰው ሁሉ ስለእኔ ልክ እንደአንቺ የተሳሳተ ግምት ያለው ይመስልሻል እንዴ?››አላት፡፡

‹‹ተው ተው…ከመሀከላችንማ አንደኛው ቁምነገረኛና ኃላፊነትን የሚወስደው አላዛር ነው…አንተ እንደውም በዚህ ጉዳይ  የመጨረሻው ሰው ነህ››አለው ሁሴን፡፡

‹‹አንተ ዲያስፖራ ለመሆኑ ዜግነትህን ቀይረሀል?››ሲል ጠየቀው፡፡
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለተጠየቀው ግራ ተጋባ‹‹አይ አልቀየርኩም…ግን ለምን ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ኢትዬጵያዊ ዲያስፖራ ከሆንክ  የሚጮህልህ ኤምባሲ ስለሌለ ለዚህ ንግግርህ የሆነ ሰበብ ፈልጌ ከርቸሌ ልወረውርህ ነዋ….እንደድሮ አለማየሁ ብቻ አይደለሁም..ኩማንደር አለማየሁ ነኝ፡፡››
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ

‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ

ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…

ፀደይ  ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››

‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡

ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››

‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››

‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››

‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››

‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን  እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን  ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡

እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…

‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት

‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን  ወንጀል የፈፀመው?››

‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ  አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››

‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ  ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››

‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት  ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡

‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡

‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው  ሁለታችንንም ያነቃን….

እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና  አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….

‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ  ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡

‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….

‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ

‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት

‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››

‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት  አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ  ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡

ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን  እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››