#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
#ምዱካን_ስወራ
ለመሞት ወስኛለሁ፡፡ ግን፣ ደስተኛ የምመስላቸው ቤተሰቦቼ፣ስኬታማ እንደሆንኩ፣ በደስታ እየኖርኩ እንዳለሁ እያሰቡ እንዲቀሩ፣በጥንቃቄ ዱካዬን አጥፍቼ ነው መሞት ያለብኝ፡፡ ልክ ከህይወታችን፣ቀስ በቀስ ጠፍተው እንደተረሱ ሰዎች፣ የት እንዳሉ ምን እንደሆኑ ትዝ እንደማይሉን ሰዎች፣ ዝም፣ ጭጭ፣ ጭልጥ ብዬ መቅረት ነው
ያለብኝ::ጥሩ ደብዛ ማጥፊያ የት ይሆን የሚገኘው? የት ነው አስክሬኔ ወድቆ
ሲገኝ፣ እንደቀልድ ሳይመረመር፣ ማነው? ከየት ነው? ሳይባል ሊቀበር ሚችለው? የት ሊሆን ይችላል?
ገቢና ወጪ ሰው የሚበዛባቸው ከተሞች፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው፣ ማነው? ከየት ነው? መቼ መጣ? ለምን መጣ? ተብሎ ትኩረት ማይስብባቸው ከተማዎች፡፡ የድንበር ከተሞች ናቸው፡፡ በየቀኑ አዳዲስ ሰዎች ሚገቡ፣ ሚወጡባቸው፡፡ ከሀገር የሚወጣ፣ የሚሰደድ የሚሰባሰቡባቸው፡፡ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሚርመሰመሱባቸው፡፡ከነዋሪው በላይ፣ መጪና ሂያጁ ሚበዛባቸው ከተሞች፡፡ እዛነው፣ ሰው እንደዘበት ሚቀበርበት፡፡ ህይወት እርካሽ የሆነበት፡፡ አስክሬን እንደቀልድ አፈር ማስ ማስ ተደርጎ፣ ሚቀበርበት፡፡ አዎ! ወደ እዛ ሄጄ እራሴን
ማጥፋት አለብኝ፡፡
የትኛው የድንበር ከተማ ይሻለኛል? ሞያሌ? መተማ? ሑመራ? አንዳቸውንም ሄጄባቸዋው አላውቅም፡፡ የቱን ልምረጥ? ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ወደ መተማ መሄድ የተሻለ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እዛ ሄጄ፣
እኔነቴን የሚገልፅ መረጃዎቼን ካጠፋሁ በኋላ፣ ሀገራቸውን ተሰናብተው
እንደሚሄዱ ሰዎች፣ እኔም ተሰናብቼ እሄዳለሁ፡፡ እነሱ ይመለሱ ይሆናል፣ እኔ ግን አልመለስም፡፡ እስከ ወዲያኛው እችን አሰልቺና አታካች አለም እሰናበታታለሁ፡፡
በነጋታው ረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ፣ ከአዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ ወደ ማርቆስ የሚሄድ አባዱላ ተሳፈርኩ፡፡ ከኋላ ወንበር አንድ የቀረው መቀመጫ ባዶ ነው፡፡ ተቀመጥኩ፡፡ ባህርዳር፣ ደ/ማርቆስ
ወያላው ይጣራል፡፡ እንደተቀመጥኩ ሞባይሌን አውጥቼ፣ የተለመደ
ፌስቡኬን መበርበር ጀመርኩኝ፡፡ እያነበብኩ ላይክና ኮሜንት አደርጋለሁ፡፡ በዚህም ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ፣ በማነበው ነገር ቅፅበታዊ ንዴትና ደስታ ይሰማኛል፡፡ የማወቅ ፍላጎቴም እንደዛው አለ፡፡ ዓለምን ተጠይፌ፣ ስለ ዓለም ለማወቅ ስልኬን እበረብራለሁ፡፡ ምን አይነት ግራ ነገር ነው፡፡ 'ማምሻም እድሜ ነው፣ ሆኖብኝ ይሆን፡፡ ድንገት፣ “እዚህ
ጋር ሰው አለ?” የሚል ድምፅ ተሰማኝ፡፡ ቀና አላልኩም፡፡ ጭንቅላቴን
በመወዝወዝ የለም የሚል ምልክት ሰጠሁ፡፡
የማነበው ነገር ትኩረቴን ስቦታል፡፡ ፌስቡክ የሀገራችንን የፖለቲካ መዘወሪያ መስሏል፡፡ ሰው ሁሉ ፖለቲከኛና አክቲቪስት ሆኗል፡፡ ሀገሪቷ የሚያስፈልጋት ሙያ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ እንደሆነ፣ ሁሉም ሙያውን ትቶ ተመራጭ ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ተንታኝና
አክቲቪስት ለመሆን ይታትራሉ፡፡ ምን እየሆንን ነው?፣ ፖለቲከኛ ባልሆንም እንደመረጃ ስለዓለም ጉዳይ ባገኘሁት አጋጣሚ እከታተላለሁ፡፡ሶሻል ሚዲያ አላማው የተሻለ ተጠያቂነትና ዲሞክራሲ መገንባትና ማስፈን እንደሆነ እሰማለሁ፡፡ በጣም ጠቃሚ ፈጠራም እንደሆነ ግልፅ
ነው፡፡ ግን የተሻለ ቁጥጥር ሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ ሶሻል ሚዲያ በዓለማችን ከተስፋፋ በኋላ፣ ዓለማችን ይበልጥ በቀውስ የተሞላች ይመስለኛል፡፡ ከቱኒዚያ የተነሳው የአረብ አብዮት፣ ሊቢያ፣ ግብፅ፣ የመን እያለ ሀገራችን ገብቷል፡፡ አሁን አሁን ሳስበው አሜሪካንና ዌስተርኖች በእርዳታና በሌላ ዲፕሎማቲክ ጫና ያስፈጽሙት የነበረው የአንጋሽነት “King Maker” ሚና ሀገራቶች ከቻይና ጋር በመተባበር በቀላሉ
አልጠመዘዝ ሲሏቸው ያመጡት አማራጭ ይመስለኛል፡፡
በእርግጥ አሁን አሁን፣ አሜሪካንም ሆነ አውሮፓውያን በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አህጉራት ስላሉ ታዳጊ ሀገራት እድገትና
ዴሞክራሲ ይጨነቃሉ ብዬ ማመን እየከበደኝ ነው፡፡ ሀያላን ሀገራቱ፣
ዋናው የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ሀገራት ቋሚ ጥቅምን ማረጋጥ
ይመስላል፡፡ በሊቢያ፣ በኢራቅ፣ በየመንና በሶሪያ የተከሰተውን በዓለም
ታሪክ ታይቶ ማይታወቅ የሰበአዊ ቀውሶችን አይተው እንዳላየ መሆናቸው፣ እነዚህ ሀያላን ሀገራት አላማችን፣ ዓለምን ለሰው ልጆች ሁሉ ለኑሮ የተመቸች ማድረግ ነው' የሚለው ዲስኩር፣ ለሽፋንነት የሚደረግ ባዶ ሽንገላ እንደሆነ እንድናስብ ያስገድዳል፡፡
እንደዚህ እያሰብኩ መኪናችን ሞልቶ፣ መንገድ ጀምረን፣እንጦጦ ኬላ ለፍተሻ እንድንወርድ ታዘዝን፡፡ ከሄድኩበት ሃሳብ ባነንኩ፡፡ፍተሻውን ጨርሰን ወደ መኪናችን ተመልሰን ገባን፡፡እኔ የተቀመጥኩት
ወንበር ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣለች፡፡ እግሯን ዘወር አድርጋ፣
ወደቦታዬ እንድገባ አሳለፈችኝ፡፡ ቅድም “እዚህ ጋር ሰው አለው?” ያለችኝ
እርሷ ነበረች፡፡ ቀይ፣ ወጣት፣ ቆንጆ ነች፡፡ ሰሞኑን፣ በህይወቴ የመጣብኝ
ምስቅልቅሎሽ ከሴቶች ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ሴቶች
መጥፊያዬ ናቸው ብያለሁ፡፡ላልደርስባቸው ምያለሁ፡፡ አሁን ሰይጣን
በዚህች የቀይ ቆንጆ ሊፈትነኝ አጠገቤ አስቀምጧታል፡፡ አላደርገውም ብዬ ስልኬን መበርበሬን ቀጠልኩ፡፡ የፌስ ቡክ ወሬ እንደቅድሙ አልጥም አለኝ፡፡ ሃሳቤ ከእርሷ አልወጣ አለ፡፡ የሚሞት ሰው ይፈራል እንዴ?፣ባክህ ዝም ብለህ እድልህን ሞክር ይለኛል ውስጤ፡፡ የስልኬን ዳታ አጠፋሁት፡፡ እንደሚያድን ነብር፣ ሁሉ ነገሬን ወደ እርሷ ቀሰርኩ።
በደንብ ተመለከትኳት፡፡ ጅንስ ሱሪና ኮት ለብሳለች፡፡ እድሜዋ ቢበዛ ሃያዎቹ መጀመሪያ ቢሆን ነው፡፡ ለመተዋወቅ ወሰንኩ፡፡ እንዴት ልጀምር እያልኩ ሳስብ፣ ታፋዎቿ ላይ መፅሀፍ አየሁ፡፡ ታፋዋን ጎሸም አደረኩና፣
“ልየው?” አልኳት፣ እጄን ወደ መፅሐፉ እየጠቆምኩ፡፡
ይቻላል በሚል ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ፡፡ መፅሀፉን አነሳሁት::የፊት ገፅ ሽፋኑ ላይ ጓድ ኮርኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱት ፎቶ ይታያል፡፡ የመፅሀፉ ርዕስ ነበር
ይላል፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ ይህን መፅሀፍ ብዙ ጊዜ መፅሐፍ አዟሪዎች ላይ አይቼዋለሁ፡፡ አንስቼ የጀርባ ፅሁፉን ለማንበብ እንኳ ተነሳሽነቱ አልነበረኝም፡፡ የዛ ትውልድን መፅሐፍት ፈልጌ ነበር የማነበው።ይገርሙኛል፤ ያስቀኑኛል፤ ይደንቁኛልም፡፡ በመንግስት አፍንጫ ስር
የመደራጀት ጥበባቸው፣ ዲሲፕሊናቸው፣ ለድርጅታቸው ያላቸው ፍፁማዊ ታማኝነት፣ ይደንቀኛል፡፡ ስለዚህ፣ ፈልጌ አነባቸዋለሁ።የመንግስቱ ኃ/ማርያምን ጨፍጫፊነትን ይቅር የምልበት ምክንያት
ፍለጋ ግን አላነብም፡፡ ልቤ ዝግ ነው፡፡ ስለዚህ አልገዛሁትም፡፡ እንኳን መፅሐፉን ገዝቼ ላነበው፣ ሚያነበው ሰው ያለ ፀአይመስለኝም ነበር፡፡
“ያንቺ ነው?” አልኳት ተገርሜ፡፡
“አሁን አይደል ከኔ የወሰድከው?” አለችኝ፣ በፈገግታ ነጫጭ ጥርሶቿን ፍልቅቅ አድርጋ፡፡ ፈገግታዋ የልብን ምት የሚጨምር ጨረር ይረጫል፡፡
“ማለቴ ልታነቢው ነው?” በመገረም ጠየኳት፡፡
“እንዴ...! አዎ! ምነው? ችግር አለው?”
ደግማ ፈገግ እያለች፡፡
“ኢሰፓ ቤተሰብ አለሽ?”
“ኧረ የለኝም፡፡” ኪ.ኪ.ኪ...
“ግን፣ ለምን እንዲህ አልከኝ?”
“ሴት፣ የፖለቲካ መፅሀፍ፣ ደግሞ የመንስቱ ኃ/ማርያም ታሪክ፣ በጣም ደንቆኝ ነው!”
“መፅሐፉን አንብበኸዋል ግን?”
“ኧረ በጭራሽ! ሳየው ገና ያንገሸግሸኛል!”
“ብታነበው ግን፣ እርግጠኛ ነኝ እንደዚህ አትጠላውም፡፡”
“ምን ፈልጌ ነው ማነበው?
አልጨፈጨፍኩም እንዲለኝ? ወይስ
ቀይ ሽብር ፅድቅ ነው እንዲለኝ? ለማንኛውም ተይው፡፡ ወዴት ነሽ?”
“ባህርዳር፡፡ አንተስ?”
“ባህር ዳር፣ ከዛ ጎንደር

👍3