አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....“አባቱን ላስገደለ ለርጉም ተክለሃይማኖት ያደረ ርጉም ነው” እየተባሉ ሲታሙ ያዘነላቸውን ያህል፣ ያን ቀን አዘነባቸው፤
ዓመጸባቸው።የሚሉትን ሊፈጽም፣ ሊያነጋግራቸው ቀርቶ፣ በዐይኑ
ሊያያቸው ቸገረው።

ጉልምስና ዕድሜ ላይ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ነገር ተመኝቶ
አደገ - ወለተጊዮርጊስን አግብቶ ሥዕል እየሣለ መኖር፡፡
ወለተጊዮርጊስን ብዙ ጊዜ የሚያያት እሑድ ቤተክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ሲሆን፣ ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውጭ ያለው ዋርካ ስር
ጥምጥሙን አድርጎ፣ ዱላውን መሬት ላይ፣ ዐይኑን ደጀሰላሙ ላይ ተክሎ የሷን ከግቢ መውጣት ይጠባበቃል። በመልኩ ማማርና በቁመቱ ርዝመት የተማረኩ ኮረዶች እሱን እያዩ ሲሽኮረመሙ፣ እሱ ዐይኑ ደጀሰላሙ ላይ ልቡ ወለተጊዮርጊስ ጋ ነው። ነጠላ ተከናንባ ብቅ ስትል ልቡ ይደልቃል። ዐይኖቹ የሚያርፉበት ይጠፋቸዋል ። ከአያቷና
ከእናቷ ኋላ እየተራመደች ዐይኖቻቸው ሲጋጩ ፈገግታ ይመጋገባሉ። ሰላምታ ይለዋወጣሉ።

ይህ ለሳምንት ስንቅ ይሆነዋል።
በዚህ የተነሳ ዋርካውን ይወደዋል ፤ ለእሱ ብቻ የተተከለለት
ይመስለዋል። ዋርካው ሥር ቆሞ የወለተጊዮርጊስን መውጣት
ሲጠባበቅ፣ ብቅ ስትል ልቡ ሲመታ፣ ዐይኑ ማረፊያ ሲያጣ፣ ፍቅሩ ሲግል፣ ምኞቱ ሲበረታ፣ ጊዮርጊስ ዝም ብሎ አይመለከተኝም፣ ያባቴን
ልብ ያራራልኛል እያለ ዐዲስ ተስፋ ውስጡ ሲጫር ይሰማዋል።
ሌሎች ጎረምሶች አጠገቡ ሲቆሙ፣ አቅሉን ያጣል። ወለተጊዮርጊስ ከቤተስኪያኑ ከመውጣቷ በፊት ቢሄዱ ደስ ይለዋል። “እስቲ ዞር በሉ”
ለማለት ይቃጣዋል።

ወለተጊዮርጊስና እሱ ቁጭ ብለው የልባቸውን ተነጋግረው ባያውቁም፣ አባቶቻቸው ቢቀያየሙም፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አብሮ መኖር ዕጣ ተርታቸው እንደሆነ ሁለቱም በልባቸው አምነዋል፤ ሳይነጋገሩ ቃል
ተገባብተዋል። አንዱ ለአንዱ ልቡንና ሕይወቱን ሰጥቷል። ምንም እንኳን እሱ ያ ንፋስ አሸዋውን አንስቶ የተሸፈነበት የእሷ ምስል ልቡ ውስጥ ተቀርጾ አልፎ አልፎ ፍርሐት ቢያሳድርበትም፣ አላገኛት ይሆን?
የሚል ጥርጣሬ ውስጥ ቢከተውም፣ ሁለቱም በአባቶቻቸው መሃል ዕርቅ
ወርዶ የሚጋቡበትን ቀን በተስፋ ተጠባብቀዋል።

ጥላዬ፣ አባቶቻቸው የገቡትን ቃል አጥፈው፣ ለዓመታት እንደ
ጠላት ለመተያየታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ወለተጊዮርጊስን ሳያገባ
ለመቅረቱ ምክንያቱ የእሱው አባት በመሆናቸውና ሥዕል የመሣል
ፍላጎቱን ሊያመክኑበት የሚታገሉትም እኝሁ አባቱ በመሆናቸው ቁርሾ ይዞባቸዋል።


ዐይናቸውን ላለማየት፣ እናቱን በሆነ ባልሆነው ሲጨቀጭቁና ቀን ያገኙትን ሁሉ ማታ ሲራገሙ ላለመስማት፣ ማታ ዳዊታቸውን ደግመው እስኪተኙ ውጭ ጨለማ ውስጥ ተቀምጦ ራቱን በልቶ መግባትና መተኛት፣ ጠዋት ውዳሴ ማርያማቸውንና ዳዊታቸውን ሲይዙ እናቱ
የሚያስጨብጡትን ቂጣ ቋጥሮ መውጣት የዘወትር ተግባሩ ሆነ።

ለእናቱ ቢያዝንም፣ ምኞቱና ፍላጎቱ ሁሉ ከዚያ የቁጭትና የበቀል ስሜት ከተጠናወተውና “የግዞት” ቦታ መሄድ ብቻ ከሆነ ሰንብቷል።የት እንደሚሄድ ያሰላና የወለተጊዮርጊስን ቁርጥ ሳያውቅ ቋራን ጥሎ ለመሄድ አንጀቱ አልችል ይለዋል።
ዛሬ ግን ወለተጊዮርጊስ ለንጉሥ መታጨቷን ሲሰማ ማመን አቃተው፤ ለዘላለም እንዳጣትም አወቀ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ምስሏ በአሸዋ ሲዳፈን የተመለከተው ትዝ አለውና በእርግጥም ያ ንፋስ ንግርት
እንደነበረው ተረዳ ። ሕይወቱ በዐይኑ ሥር ስታልፍ፣ ስታመልጠው ተሰማው። ምንጊዜም ቢሆን የሚፈራውና ባሰበው ቁጥር የሚባንንበት፣
አካሉ ቦታ የማይበቃው የሚመስለው ነገር ዛሬ በመድረሱ አባቱን ወነጀለ።

ወለቴን ንጉሡ አልወሰዱብኝም፡ አባቴ አሳልፈው ሰጡብኝ እንጂ
አለ። እንባውን በኩታው እየጠራረገ፣ ለመሆኑ ወለተጊዮርጊስ ለንጉሡ
መታጨቷን ስትሰማ ምን ብላ ይሆን? መቸም ልብ ለልብ ተገናኝተናልና ምንስ ቢሆን እኔን ሳታስብ ትቀራለች? አለ፣ ሲተያዩ ፊታቸው ላይ የሚዋልለውን ደስታ እያሰበ። ስለምን እስታሁን ተያይዘን አልጠፋንም ነበር? ብንጠፋ ንሮ እኼ ሁሉ አይመጣም ነበር፡፡ ነገሩን እያሰበው ሲመጣ ድንጋጤውና ቁጭቱ ወደ ንዴት ተለወጡበት። ድንገት ንዴቱ እንደ ቋያ እሳት በሠራ አከላቱ ተሰራጨ።

እጆቹ ተንቀጠቀጡ፣ ጉሮሮው ደረቀበት፤ ቁና ቁና ተነፈሰ።
እናቱ ራቱን አመጡለት። መብላት እንደማይፈልግ ነገራቸው። ቤት
ውስጥ ተመልሰው ገብተው ቆሎ በአነስተኛ ቁና፣ ውሃ ደግሞ በቅምጫና ይዘው መጥተው፣ ቅምጫናውን መሬት ላይ አስቀምጠው ቁናውንም
በእጁ እንዲቀበላቸው ጥቂት አባብለው አስይዘውት አጠገቡ ተቀመጡ።

“አይዞህ የኔ ልዥ ። ዕድሜ ኻላነሰው፣ ጊዜ አለው ሰው ይላል ያገሬ ሰው። አንድ ቀን ሰው ትሆናለህ” ብለውት ለመውረድ ያቆበቆበውን እንባቸውን በእጅጌያቸው ጠራረጉ።

“እነየ አትጨነቂ።”

“ያባትህ ነገር መላ የለው ሁኖ አንተም ተቸገርህ። እኔስ እንዳሻው::ኸዝኸ ወዲያ ምን አረጋለሁ። የሳቸው ነገር ያስቸጋሪ በሬ ነገር ሆነ እኮ።”
“ያስቸጋሪ በሬ?”

“የሴቲቱ ባል ማልዶ ተነስቶ ወደርሻ ሲኸድ በሬው ገደል ይገባበታል።ዛዲያ ዳገት ላይ ቁሞ፣ 'ኧረ እርዱኝ በሬየ ገደል ገባ! ብሎ ይጮሀል። ያን ግዝየ ምሽቱ ኸቤት ትወጣና ኸየት ያመጣኸው በሬ ነው? በራሴ
በሬ' ብላው ትገባለች..” ሲሉ ጥላዬ ከት ብሎ ሲስቅ ትን አለው።

“ውሃ ፉት በልበት” አሉና ቅምጫናውን አቀበሉት። ውሃውን ጨልጦ ሲጨርስ ጠብቀው፣ “እናልህ እንደዛ ብላው ቤት ስትገባ ባልየው፣ ኧረ በሬያችን ገደል ገባ እርዱኝ አለ። ሴትየይቱ እንደገና ወጥታ፣ ኸየት
ያመጣኸው በሬ ነውና ነው በሬያችን ምትለው? የድሮ ባሌ የሰጠኝን ብላው ቤት ገባች። በመጨረሻ ሰውየው ሚለው ቢያጣ፣ እረ ያስቸጋሪ በሬ ገደል ገባ እርዱኝ አለ ይባላል አለ” አሉት።

ጥላዬ እንደገና ከት ብሎ ሳቀ። እናቱ ለሁሉ ነገር ምሳሌ የሚሆን
ተረትና ጨዋታ አላቸው። “አይ እነየ” ብሎ መልሶ ሳቀ። “የግዞት”
ቦታ የሚለውን ቤታቸውን እናቱ በተጫዋችነታቸው፣ ነገሮችን ቀለል አድርገው በማየታቸው፣ በተረቶቻቸውና በቀልዶቻቸው ነፍስ ባይዘሩበት ኖሮ፣ ኑሮ ከባላምባራስ ሁነኝ ጋር ምን ያህል አስቸጋሪ ሊሆን ይችል
እንደነበረና እናቱ የቻሉትን፣ የታገሱትን፣ ስቀውና ቀልደው ያሳለፉትን አሰበና፣ “እነየ ስንኳንም አንቺን ሰጠኝ” አላቸው።

ወይዘሮ ጌጤነሽ ሳቅ ብለው፣ “አየ ያንተ ነገር... እንኳንም አንተን
ሰጠኝ እንጂ አለበለዚያማ...” አሉት። ትንሽም ቢሆን ሊያስቁት
በመቻላቸው ደስ ብሏቸው፣ “አሁንስ ራት አትበላም?”

ራሱን በአሉታ ነቀነቀ።

ቅር እያላቸው ወደቤት ሲገቡ እሱ ስለ ሕይወቱ ማሰላሰል ጀመረ።
አንተ የወፍታው ምነው ዝም አልኸኝ? አለ ኹለት ነገር ጠይቄህ
ስንኳ አላውቅ። እኔ ልቤ ውስጥ እሳት አለ - ወለቴና ሥዕል፡ ወለቴን
ኸነጠቅኸኝ፣ ሥዕል መስጠት አቃተህ እኔ ጠበቅሁ፤
ጠበቅሁ፤ ሰው እስተመቸ ይጠብቃል? ለመጠበቅ ብቻ መፈጠርማ የለብኝም፡፡
ኸንግዲህ ምጠብቀው ነገር ስለሌለ ቋራ ሚያስቀምጠኝ ነገር የለም። እሳቸውን ችየ የኖርሁት ወለቴን አገባለሁ ብየ እንጂ፣ እሷ ለንጉሥ ኸተዳረችማ መኸድ በቀር ሌላ ምን አለኝ? ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? አለ፣ ለራሱ።

ወለተጊዮርጊስን ማጣቱና እናቱን ለአባቱ ትቶ መሄድ ማሰቡ
ቢያሳዝነውም በወጣትነት ዕድሜው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ መወሰን መቻሉ ዐቅም ሆነው፤ አደፋፈረው፣ የነፃነት መንፈስ አለበሰው። አባቱ ከፊቱ የደነቀሩበትን ጋሬጣ፣ ዙርያውን የተበተቡበትን ገመድ
በጣጥሶ የወጣ መሰለው።
👍12🔥1
#ትኩሳት


#ክፍል_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


ይሄ ሁሉ ሲሆን ባህራምን አልረሳሁትም ነበር ከምሳ በኋላ Le Monde የተባለውን ስመጥሩ የፈረንሳይ ጋዜጣ እገዛና፣ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ petit creme (ቡና በወተት በሲኒ)
አዝዤ ሀበሾቹ አጠገብ ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን ማንበብ እጀምራለሁ።
ጩኸት፣ ሳቅ፣ ወሬ፣ የሲጋራ ጪስ፣ የሴት ሽቶ ካፌውን
ይሞላዋል። በበጋው ሙቀት ምክንያት መስኮት ሁሉ ይከፈታል፡፡
ሰማያዊ ካኪ የስራ ልብስ የለበሱ የፋብሪካ ሰራተኞች የቡና ማፍያው መኪና የተቀመጠበትን ረዥም ባንኮኒ በክንዳቸው ተደግፈው በተርታ ቆመው ፓስቲስ (ነጭ አረቄ) እየጠጡ፣ የፋብሪካ ዘይት ምናምን ያቆሽሽውን ቀያይ ፀጉራም እጃቸውን በብዙ እያንቀሳቀሱ፣
በአስቂኝ የደቡብ ፈረንሳይኛቸው ያወራሉ። ከባንኮኒው ዳር፣ ከመስተዋት የተሰራው በር አጠገብ፣ የካፌው ባለቤት መስዬ ፖል የቂል ሳቁን እየሳቀ “Merc Bien morosiuro (እግዜር ይስጥልኝ ጌታዬ» እያለ የሚከፍሉትን ገንዘብ ይቀበላል፤ ቴምብርና ሲጋራ ይሸጣል

ከባንኮኒው ኋላ ቆንጆዋ የመስየ ፖል ሚስት ባጭሩ የተቆረጠ
ብጫ ብጤ ቀለም የተቀባ ፀጉሯ እያብለጨለጨ ለሰዎቹ ቡና ወይም ፓስቲስ እያቀበለች፣ ከወጣቶቹ ጋር ፈገግታና ቃላት ትቀባበላለች፣ ትሽኮረመማለች፣ በማርሰይ ዜማ ታወራለች። ሸርሞጥሞጥ የምትል ሴት ናት። ድምፅዋ፣ አስተያየቷ፣ አረማመዷ፣ ሁለመናዋ ወንድ ይጣራል። መስዬ ፖል በብስጭት ነው የሚኖረው ሲባል እሰማለሁ፡፡
ግን ተማሪ ውሽማ ያላትም ይላሉ። ተማሪዎቹ መስዬ ፖልን
ይወዱታል፣ ሚስቱን ሊነኩበት አይፈለጉም፡፡ እሷም ተማሪ
የምትፈልግ አትመስልም፡፡ ውሽሞቿ ጎረምሶችና የፋብሪካ ወይም የኩባ ሰራተኞች ናቸው በበጋው ሙቀት ኮታቸውን አውልቀው የሸሚዛቸውን ቁልፍ በሙሉ ፈተው፣ የደረታቸውን ፀጉርና ጡንቻ እያሳዩና እጅጌያቸውን ሰብስበው ጡንቸኛ ፀጉራም እጃቸውን እያወዛወዙ ካፌ ዶርቢቴል የሚመጡ ጎረምሶች

እጠረጴዛዎቹ መሀል ሁለቱ ሴት ቦዮች ቡና፣ መጠጥ፣ ሲጋራ እየያዙ ይዘዋወራሉ

ሀበሾቹና ባህራም ካንድ ሁለት አፍሪካውያን ወይም ፈረንሳዮች
ጋር ካርታ ሲጫወቱ፣ አጠገባቸው ቁጭ ብዬ ጋዜጣዬን አነባለሁ።
በካርታ የተሸነፉት ሁለት ልጆች፣ ሌሎች ሁለት ተሽንፈውሳቸው
ተራቸውን ለመጫወት እስኪችሉ ድረስ መጥተው ከኔ ጋር ያወራሉ
ተካ ይመጣና ጋዜጣዬን ሳነብ «የማታነበውን ገፅ ልመልከተው
ስቲ» ብሎ ጋዜጣዬን ነጥሎ ግማሹን ይወስድብኛል። የማነበውን ጨርሼ ወደሌላ ገፅ መሄዴ ሲሆን፣ ተካ «ቆይ እቺን ልጨርስና እሰጥሃለሁ» ይለኛል። «አምጣ እንጂ» ስለው «ጋዜጣው ካንተ ጋር ይውላል፣ ትንሽ ባነብ ምናለበት?» ይለኛል። ብሽቅ ብዬ አየዋለሁ፡፡
ጥፍሩን እየነከሰ ያነባል።ጋዜጣው ውስጥ ያሳቀውን ወይም
ያስገረመውን ነገር ያሳየኛል፤ በጭራሽ አያስቅም፣ አያስገርምም።አይ ተካ ብሽቁ! ግን ጥሩ ልጅ ነው፡፡ እሱ ራሱ ጋዜጣ ገዝቶ ያነብ እንደሆነ ጋዜጣውን ይሰጠኝና «የማታነበውን ገፅ ስጠኝ። ሌላውን ካንተ በኋላ ቀስ ብዪ አነበዋለሁ» ይለኛል
አንዳንዴ ሀበሾቹ ተሰብስበው ካርታ ሲጫወቱ ወዳጆቻቸው
ሴቶች አንድ ጠረጴዛ ይዘው እያወሩ ይጠብቁዋቸዋል፡፡ ሲያሰኘኝ ከነሱ ጋር ትንሽ አወራለሁ ከኒኮል ጋር ማውራት እሞክራለሁ፣ ያቅተኛል። በጣም
ታፍራለች፤ ያልለመደችውን ሰው ማናገር አይሆንላትም። ለጊዜው
በጭራሽ ላውቃት አልቻልኩም። ስለዚህ ባሀራም ምን አይቶባት
ይሆን? ለሚለው ጥያቄ የመልስ ጫፍ እንኳ አላገኘሁለትም፡፡
መልኳን አይቶ እንዳልሆነ ግን ግልፅ ነበር፡፡ ውሀ አረንጓዴ አይኖች፣ የተዘረዘሩ ጥቃቅን ጥርሶች፣ ትኩሳት እንደያዛቸው አይነት ቆዳቸው የደረቀ ከናፍር። ድምፅዋ ደስ ይላል። ባህራም ምን አይቶባት ይሆን? እውነት ለገንዘቧ ሲል ይሆን?
ከአማንዳ ጋር ግን ብዙ እናወራለን። ሀበሾቹ አማንዳ ዱቤ ነው የሚሏት፡፡ ሉልሰገድ ይዟት ሊሄድ ሲል ተካ «እንግዲህ ሂድና
ዱባህን አገላብጥ!» ይለዋል። ሉልሰገድ «አንተ ደሞ ከዱባ የተሻለች እስክታገላብጥ ድረስ ስለዱባ ባታወራ ጥሩ ነው!» ብሎት አማንዳን እቅፎ ይሄዳል፡፡ አማንዳ በእንግሊዝኛ «ምንድነው "ሚለው?»
ትለዋለች፡፡ «ተይው ዝም ብሎ ነው» ይላታል።

ጋዜጣዬን እንብቤ፣ ሰዉን አይቼ፣ ባህራምን ተመልክቼ፣ ስለራሱ ለማውራት ዝግጁ እንዳልሆነ ከተገነዘብኩ በኋላ፣ ከካፌው
ወጥቼ ወደ ኩር ሚራቦ በኩል ትንሽ እራመዳለሁ። ወደኋላ ዞሬ፣
ማንም ሀበሻ እንዳልተከተለኝ ካረጋገጥኩ በኋላ፣ እታጠፍና ወደ
ሲልቪ ቤት አመራለሁ

"አንድ ቀን ባህራምን ያዘክው?» አለችኝ
"የለም" አልኳት
"የምትይዘው ይመስልሀል?»
"እርግጠኛ ነኝ»
«የምስራቅ ሰው እንደሆንክ ያስታውቃል፡፡ ጊዜ የሚያመጣውን
ጊዜ እስኪያመጣው ትጠብቃለህ እንጂ ጊዜን ልታጣድፈው
አትሞክርም፡፡ የምእራብ ሰው ብትሆን ግን ባህራምን ሄደህ በብልሀት ታዋራው ታወጣጣው ነበር»
«እንደሱ ካረግኩማ እሱን ራሱን ላውቀው አልችልም፡፡ የማሰብና
የሰዋስው ችሎታውን ብቻ ነው ላውቅ የምችለው»
«ምን የሚል ይመስልሀል?»
«ምን እንደሚልማ ማወቅ ቀላል ነው»
«አንግዲያው ምንድነው የምትጠብቀው?»
«ያ ያልኩሽ ጊዜ ሲመጣ፣ ተጠንቅቄ ምሰማው ቃላቱን
አይደለም ኮ»
«ታድያስ?»
ድምፁን ነው:: ዜማውን፡፡ እጁ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ። ምን
ሲል ድምፁ እንደሚለሰልስ፣ ምን ሲናገር ግምባሩ እንደሚቋጠር።
አንዳንድ ጊዜ እኛ ሳናውቅ ፊታችን ላይ ፈገግታ ወይም ህዘን በገዛ
ራሱ ይጫወት የለ? ያንን ነው ምጠብቀው:: አንድን ሰው
የምናውቀው በሚናገረው ቃላት አይደለም፣ ያን ቃላት ሲናገር
በሚያሳየው ገፅ፣ በሚያሰማው ድምፅ ነው:: እሱን እሱን ለማየት
ነው ባህራምን አድፍጬ የምጠብቀው

ከሰአት በኋላውን ከሷ ጋር አሳልፈዋለሁ፡፡ እንቅልፍ ከወሰደን ወደ አስራ አንድ ላይ እንነቃለን። ወይ እናወራለን፣ ወይ እናነባለን!
ወይ ሙዚቃ እንሰማለን። ሰኞና አርብ በአስር ሰአት ላይ ክፍል
አለባት። አንዳንዴ ተኝቼ ትታኝ ሄዳ ስትመለስ ትቀሰቅሰኛለች።
አንዳንዴ ነቅቼ እንደ ሌላ ቀን ከአርት መፃህፍት አንዱን
እየተመለከትኩ፣ ወይም እያነበብኩ፣ ወይም ሙዚቃ እየሰማሁ አቆያታለሁ

ሲመሽ ተለይቻት እሄዳለሁ። A ጠdemain cheri» («እስከ ነገ
ደህና ሁንልኝ») ምግብ ቤት ሄጄ እራቴን በልቼ፣ ከዚያ ወጥቼ
የቴሌቪዥን ዜና አይቼ ሳበቃ፣ ሆቴሌ ሄጄ ስራ እጀምራለሁ።
(አሜሪካዊቷ መምጣት ትታለች) ወይም ሲኒማ እገባለሁ። ከሲኒማ
በኋላ ለመስራት እሞክራለሁ፡፡ እምቢ ካለኝ፣ የሌሊት ፀጥታ
የዋጣቸውን የኤክስን ጠባብ መንገዶች እዘዋወርባቸዋለሁ፡፡ ንጉሳቸው ነኝ

ጧት ተነስቼ፣ ቁርሴን ሁለት croissant በልቼ፣ ቡና በወተት
ጠጥቼ፣ ወደ ቤተመፃህፍት ሄጄ እስከምሳ ሰአት እሰራለሁ። (ክፍል
መግባት ከተውኩ መቸስ ዘመን የለኝም)
ከምሳ በኋላ ካፌ ዶርቢቴልን ጎብኝቼ ወደ ሲልቪ እሄዳለሁ፡፡
በሰፊ አፏ እየሳቀች ትቀበለኛለች
አያሌ ቀናት ካለፉ በኋላ፣ ተመስገንን እየሳቅኩ
«ሲልቪ እንደወጣች ቀረች?» አልኩት
«ቀረች!» አለኝ «አሁንማ ብትመለስም አልፈልጋት»
«ምነው?»
👍201
#ምንዱባን


#ክፍል_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

አንዳንዴ ኃላፊነትን ከመሸከም አሳልፎ መስጠት

በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ፓሪስ አጠገብ ከሚገኘው ሞንትፌርሜ ከተባለ ሥፍራ አንድ አነስተኛ ሆቴል ቤት ነበር፡፡ ዛሬ ግን የለም:: ሆቴል ቤቱ፡ ዘቴናድዬስ የተባሉ ባልና ሚስት ንብረት ሲሆን የሚገኘው በላንገር ከተባለ ቀጭን መንገድ ላይ ነበር፡፡ ከቤቱ በራፍ ላይ ስዕል
ተንጠልጥለአል:: ስዕለ ላይ ሜዳሊያ የተሰካላትና በደም ተበክሎ የተቦጫጨቀ የጄኔራል ልብስ የለበሰ ሰው ሸክም ተሸክሞ ነው የሚታየው::በተጨማሪም ከምስሉ ባዶ ሥፍራ ላይ ጭስ በብዛት አለ:: የሚያመለክተው
የጦር ሜዳን ሳይሆን አይቀርም:: ከምስሉ ስር «የዋተርሉ ጦር ሜዳ
ጀግና የሃምሳ አለቃ» የሚል ጽሑፍ ተጽፎበታል:: ከዚህ ሆቴል ቤት በራፍ ጋሪ ቆሞ ማየት አዲስ ነገር አልነበረም:: ሆኖም «ከዋተርሉ የጦር ሜዳ ጀግናው የሃምሳ አለቃ» ሆቴል ቤት በራፍ
የተሰባበረ ጋሪ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ዘወትር የሚታይ ትርኢት አይደለም::ጊዜው የፀደይ ወራት ሲሆን ዓመተ ምህረቱ 1818 ዓ.ም ነው፡፡ የጋሪው መንገድ ዘግቶ መቆም ፤ ያን የመሰለ ስዕል ከዚያ ቤት በራፍ መሰቀል በዚያ
ያለፈ የማንኛውም ሰዓሊ ዓይን የሚማርክ ትርዒት ነበር::

ጋሪው ትላልቅ ግንዲላዎችን ጭኖአል፡፡ ታዲያ ይህ ጋሪ ከዚህ ስፍራ ምን ይሠራ ነበር የሚል ጥያቄ ቢነሳ «ከዚያ የተገተረውማ መንገድ ለመዝጋትና የትጉህ ሠራተኞችን ተግባር ለማደናቀፍ ነው» የሚል ትርጉም
ሊያሰጥ ይችላል፡፡

ከጋሪው የእቃ መጫኛ ሥር የተንጠለጠለው ወፍራም ሰንሰለት መሬት ሊነካ ምንም አልቀረው:: አንዲት ሁለት ዓመት ተመንፈቅ የሚሆናት ልጅ ሌላ ዓመት ከስድስት ወር የሚሆናትን ሕፃን ጭንዋ ላይ አሳርፋ
ከሰንሰለቱ ላይ ተቀምጣለች:: ልጆቹ ጅዋጅዌ ላይ እንደወጡ ደስ ብሎአቸዋል፡፡ አንዲት ሴት አቀማመጣቸውን አይታ «ልጆቼ መጫወቻ አገኘ» በማለት ደስ እንደሚላት ማንኛዋም እናት በማተኮር ታያቸዋለች::አተኩሮ ለተመለከታት አንጀት የምትበላ፧ አንዴ እንኳን ለማየት የምትቀፍና
ኑሮ እጅግ ያጎሳቆላት ሌላ ሴት ከበራፉ አጠገብ ተቀምጣለች፡፡ ልጆቹ ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ «ምናልባት ፈረሱ ደምብሮ ይጐዳቸው ይሆን» እያለች
የመጀመሪያዋ ሴት አሁንም እንደማንኛውም እናት ማሰብዋ ኣልቀረም::ሰንሰለቱ በተነቃነቀ ቁጥር ሲጥጥ እያለ ይጮሃል:: ድምፁ ሕፃናቱን አልረሸሻቸወም:: የማታ ጨረር ከልጆቹ ላይ በማረፉ ልብ ብሉ ለተመለከታቸው ዓይንን ይማርካለ::

የልጆቹ እናት በድንገት ድምፅ ትሰማለች:: «እሜቴ ደስ የሚሉ
ልጆች ነው ያሉዎት!»

ከምግብ ቤቱ በራፍ የተቀመጠችው ሌላዋ ሴትም ልጅ ታቅፋ ነበር::ከባድ የሚመስል እቃ በጀርባዋ አዝላለች:: እርስዋም የታቀፈቻት ልጅ ሁለት ወይም ሦስት ዓመት ቢሆናት ነው:: በአለባበስ ከሁለቱ ልጆች
ምንም ያህል አትለይም:: ሻሽ መሳይ ጨርቅ አስራለች:: የተቦጫጨቀ ቀሚስዋ ቀዳዳው እስከጭንዋ ሊደርስ ምንም አልቀረ:: ሆኖም ጤነኛ ነበረች:: መልክዋ ድምቡሽቡሽ ያለ ስለሆነ ንከሰኝ፣ ንከሰኝ ትላለች፡፡ዓይኖችዋ ትላልቅ ስለነበሩ እንቅልፍ ቢወስዳትም ሙሉ ለመሉ
አልተከደነም:: ለስለስ ካለው የእናትዋ ክንድ ላይ ተመችቶአት ስለተኛች እንቅልፍ ሳይጠግብ ሲቀሰቅሱት እንደማይስማው እንደማንኛውም ሕፃን
እርስዋም ቢቀሰቅሱዋት እንኳ አትሰማም::እናትየዋ ሲያዩዋት የተከፋች ምስኪንና ከተማ ስራ ፍለጋ የመጣች የገጠር ሴት ለመሆንዋ ታስታውቃለች:: በእድሜ ልጅ ናት:: ተፈጥሮ
ውበት ቢቸራትም በዚያ ሁኔታዋ ውበትዋ ጎላ ብሎ አይታይም ፀጉርዋ ዞማ እንደሆነ ቢያስታውቅም ተንጨባሮአል:: የተቀዳደደ ሻሽዋ ተፈትቶ
ሊወድቅ ብሎ ከወደኋላዋ ተንጠልጥሎአል፡፡ የደላው ሲስቅ ነጭ ጥርሱን ያሳያል እንጂ የተከፋ ስለማይስቅ ስለጥርሶችዋ ለመናገር አይቻልም:: ለረጅም
ጊዜ ለማልቀስዋ ዓይኖችዋ ይመሰክራለ:: ገርጥታለች፤ ሰውነትዋ በመዛሉ የደከማት ለመሆነ ያስታውቃል፡፡ ምናልባትም ሳትታመም አልቀረችም::ጭንዋ ላይ የተኛችዋን ልጅ አትኩራ በፍቅር ዓይን ትመለከታታለች፡፡ ልጅዋን ደግፋ የያዘችበት እጅ ሲታይ በሥራ ብዛት ለመሻከሩ ጉልህ ነው::

ጠቅላላ ሀናቴዋ ሲታይ ሩህሩህ ልብ ያላቸው ሁሉ የማያልፍዋት
ዓይነት ስለነበረች አንጀት ትበላለች:: በይበልጥ የሚያሳዝነው ግን ማን
ትሁን፤ ከየት ትምጣ ማንም አለማወቁ ነው:: እርስዋም ራስዋ ብትሆን አባትዋና እናትዋ እነማን እንደሆኑ ማለት ማን እንደወለዳት አታውቅም፡፡ስምዋ ፋንቲን ይባላል፡፡ ቤተሰብ ስላልነበራት የአባት ስም የላትም:: የክርስትና
ስምም አልወጣላትም፡፡ ምክንያቱም በዚያ አካባቢ ቤተክርስቲያን ምን እንደሆነ
አይታወቅም:: ፋንቲን ብሎ ስም ያወጣላት በዚያ ሲያልፍ ያገኛት መንገደኛ ነው ይባላል፡፡ ይህ ሰው ይህችን ሕፃን መንገድ ወድቃ ዝናብ ሲዘንብባት ነው ፋንቲን የሚል ስም ያወጣላት:: «ፋንቲን» ማለት ውሃ ወይም ምንጭ
እንደማለት ነው::

ስለዚህች ሴተ ታሪክ ከዚህ ይበልጥ የሚያውቅ ስለሌላ ስላለፈው ታሪክዋ ከዚህ ይበልጥ መናገር አይቻልም:: ሆኖም ፋንቲን ወደዚህች ዓለም ለስቃይ የመጣች በዚህ ዓይነት ነበር ብሎ ለማጠቃለል ይቻላል፡፡ ወደኋላ
እንደተደረሰበት ደግሞ አሥር ዓመት ገደማ ሲሆናት ከከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኝ መንደር ሥራ ፍለጋ ትሄዳለች:: አሥራ አምስት ዓመትዋ አሁንም ሥራ ፍለጋ ወደ ፓሪስ ከተማ ትመጣለች::

በመጨረሻ ጥርሶችዋ ታዩ ፧ እንደወተት የነጡ ነበሩ፡፡ ሌላ ቢጠፋ የእንጨት መፋቂያ አላጣችም ማለት ነው:: ስታገባ የተሰጣት ሳይሆን አይቀርም የሚያማምሩ ጌጣጌጦች አንገትዋ ላይ አስራለች:: ወይም ደግሞ ሥራ ብጤ አግኝታ ትንሽ ከሠራች በኋላ ፤ የገዛቻቸው ይሆናሉ፡፡ ሴት ናትና ማጌጥ አይቀርም:: እርስዋም እንደ ዓቅምዋ ለመኖር ፈልጋ ሥራ
ይዛ ነበር ማለት ነው:: ለመኖር ሆድ እንጀራ እንደሚርበው ሁሉ ልብም ፍቅር ይርበዋልና ልጅዋን እንደዚያ የምታያት የፍቅር ረሃብዋን ለማርካት ነበር፡፡

ያ ስሜት ለሕፃንዋ የእናት ፍቅር ሲሆን ለእናትዮዋ ግን የስሜት
መገንፈል ነበር፡፡ እናትና ልጅ ከተቀመጡበት አቅራቢያ የሚተላለፉ መንገደኞችና ተማሪዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነበር፡፡ ሕፃን ሆና ሕፃን
የታቀፈችዋን ሴት ሁሉም አይቶ አለፋት እንጂ ከመጤፍ የቆጠራት
አልነበረም::

የሕፃንዋ አባት ልጅቱ፡ እንደተወለደች ሚስቱንና ልጁን ጥሎ ከአገር ይጠፋል፡፡ አባት አንዴ ቤተሰቡን ጥሎ። ከሄደ መመለሱ ያጠራጥራል፡፡
ይህም በመሆኑ ልጅትዋ በብቸኝነት ዓለም ውስጥ እየዋዠቀች ስለነበር ተስፋ ከሚፈጥረው ደስታ ርቃለች:: በአንድ ወቅት ተሳሳተች እንጂ
በአፈጣጠርዋ ገራምና ትምክህት የተለያት ለመሆኑ ገፅታዋ ይመሰክራል በፊትዋ ገጽታ ላይ የሚነበብ ገራምነትዋ ብቻ አልነበረም፡፡ ተስፋ
መቁረጥዋን! ቀባሪና ጧሪ የሌላት መሆኑንና ከባድ ችግር ውስጥ
መዘፈቅዋንም ያሳያል፡፡ ሆኖም ፋንቲን ቆራጥና ጠንካራ ሴት ነበረች:: ወደ ትውልድ አገርዋ የመመለስ አሳብ ነበራት፡፡ ምናልባት እዚያ ከሄደን
ድንገት የሚያውቃት ሰው ይኖርና ሥራ ይሰጠኝ ይሆናል የሚል እምነት አድሮባታል፡፡ ነገር ግን የፈጸመችውን ስህተት መደበቅ ስለነበረባት ልብዋ በሀዘን ቢቆስልም ሀሳብዋን ለመፈጸም ቆረጠች፡፡ በሃያ ሁለት ዓመት
👍21
#ገረገራ


#ክፍል_ስድስት


#በታደለ_አያሌው

...ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ። መቼም ከባልቻ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ እሱን አግኝቼ እስከማማክረዉ ድረስ ትንፋሼን እንኳን ወደ ዉስጥ መሳብ አልሆነልኝም፡፡ ቸኩያለሁ። አይደርሱት የለም ደረስሁና ቢሮዉን በርግጄ ስገባ፣ ባልቻ በወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እንቅልፍ አሸልቦት አገኘሁት።
በተለይም የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ከሆነ በኋላ የግል መኖሪያ ቤቱን አይቶት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዉሎዉም አዳሩም እዚሁ ሆኗል። እዚሁ ምግብ ያስመጣል፣ እዚሁ ወንበሩ ላይ ትንሽ ዕረፍት ያደርጋል። ከስንት አንድ ወደ ዉጪ ቢወጣ እንኳን ምክንያቱ ለዚሁ ለሲራክ ጉዳይ ብቻ
ነዉ፡፡

“ባልቻ!” ብዬ ስጮህበት፣ ብርግግ ብሎ ብድግ አለልኝ።
“ዉብርስት?” አለ ተጨናብሶ፣ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ፡፡
“እሰይ! ‹ዉብርስት?” አልሁት፣ ልጃለሜ የሚለዉ ቁልምጫዉ
መቅረቱ ከንክኖኝ፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ብቻ ሳይሆን ከማንም ቁልምጫ የለመድሁ ሰዉ ነኝ። ቁልምጫዉን ሳይቀር እንደገና በሚያቆላምጥ ቤተሰብ መሀል ነዉ ያደግሁት። ያዉም ዉብዬዋ፣ ‹ዉቤዋ፣ የኔ ዉብ፣ ዓለሜዋ፣ ‹ልጃለሜ› እየተባልሁ። ባልቻ እንዲሁ እንደ ወረደ በስሜ ጠርቶኝ ካለማወቁ የተነሳ፣ ስሜን ሁሉ የሚያዉቀዉ አይመስለኝም
ነበር። ትዝ ሲለኝ እኔ ራሴ ባልቻ ብዬ ነዉ የጠራሁት ለካ። «አባታለም» የሚለዉ ቁልምጫዬስ? የት ተዉሁት?

“ይኸዉ መጣሽ። በስንት ጊዜሽ? ስደዉል ሳታነሺ፣ ሳስጠራሽ ሳትመጪ፣ ስፈልግሽ ሳትገኘ፤ ዛሬ ምን አመጣሽ በይ?”

“እሸቴ ጠፍቷል”

“ጠፋ? ማን እፍ ብሎት ይሆን በናትሽ? ቀድሞስ በርቶ ኖሯል እንዴi” ሲል አላገጠብኝ፡፡

“ማላገጥህ ነዉ?”

“ራስሽ ከመሀል ጀመርሽዋ! እኔና አንቺ እኮ ገና እንደገና መተዋወቅ
አለብን። ቆይ የት አዉቅሻለሁ? አንቺ ታዉቂኛለሽ?”

“በማርያም አባታለም? ፈርቻለሁ። እሽቴ በመንግሥት ደኅንነቶች እጅ
ወድቆ እንዳይሆን ልቤ ሰግቷል”

“እና ምናገባኝ እኔን?”

“ኧረ ባዛኝቱ? እንዴት ነዉ የማያገባህ፤ እሽቴ እኮ ነዉ!”

"የሆነስ እንደሆነ!”

“አዉቃለሁ አሳዝኜሃለሁ። ለዚያም እንዴ ት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም። ቢሆንም ግን በዚህ መሀል እሸቴ በጨካኞች እጅ ወድቆ
ከሆነ አያሳዝንህም?”

“ያሳዝነኛል”

“እኮ አንድ ነገር አድርጋ”

“ምን ላድርግ?”

“የማታስፈልገዉ?”

“እሺ። አስፈልጌ ሳገኘዉስ?”

“ያንተን አላዉቅም። እኔ ግን ተንበርክኬ ይቅርታ እለምነዋለሁ”

“ለምን?”

“ስለሚገባዉ”

“እሺ። መጀመሪያ ግን እንስማማ”

“ንገረኝ በምን?”

“ተንበርክከሽ የምትጠብቀዉ ከሆነና፣ ተሳክቶልኝ ካገኘሁት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ቃል ከገባሽልኝ.…”

“ይኼዉ!” ብዬ ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ ተንበረከክሁ፡፡
“ብቻ አንተ እሺ በለኝ። እገባለሁ። እሄዳለሁ፤ አሁኑኑ ፈልግልኝ!”

“ዉዉዉ-ዉቤ?” የሚል ድምፅ ከኋላዬ ሰማሁ። ማን በተብታባ ድምፁ እንደ ጠራኝ ለማጣራት ዞሬ ማየት ያስፈልገኝ ኖሯል? ኧረ በጭራሽ በጠረኑ ብቻ አዉቀዋለሁ፡፡ እሸቴ ነዉ፡፡ ወይ ባልቻ! ምን ዓይነት ልብ
ነዉ የታደለዉ ግን? መቼም ጨክኖ ማኩረፉን አያውቅበት! ሆነ ብሎ ኖሯል ለካ እሸቴን ከሁላችንም እይታ እንዲጠፋ ያደረገዉ፡፡ እኔ እንደሆነ
እንዳልሞተ ሰዉ የማራክስዉ ነገር የለኝም፡፡ ጊዜ እንኳን ዉድ
የሚሆንብኝ ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳየዉ ብቻ ነዉ። እቃም ቢሆን ከእጅ አምልጦ ካልተሰበረ ወይ ደግሞ ካልተሰረቀ በቀር ዉድነቱ አይታወቀኝም።እሸቴንም ባላጣዉ ኖሮ አልፈልገዉም ነበር። ለዚህ ይመስለኛል ባልቻም
እሸቴን ከዓይኔ እንዲጠፋ ያደረገብኝ። የእሽቴን ዉድነት እንዳምን፣ ከዓይኔ ሠወረብኝ፡፡ እንኳንም ሠወረብኝ፣ እንኳንም ናፈቅሁት፣ እንኳንም
አገኘሁት። ተሳክቶለታል።

ባልቻን በስስትም በኩራትም እያየሁት ሳለ፣ እሸቴ ከፊት ለፊቴ መጥቶ እንደኔዉ በጉልበቱ ወደቀ። ጥዉልግ ብሏል። ከንፈሩ ሳይቀር ኩችር ብሎ ደርቆ ታየኝ፡፡

“እሽቴ?”

“ጨጨጨ ጨከንሽብኝ እኮ
ዉቤ”

“ኹለተኛ አላደርገዉም”

“አአአ አአ አለሽልኝ ግን?”

“አለሁልህ። አለህልኝ?”

የባልቻን መኖር ሁሉ ረስተን፣ አንገት ለአንገት ተቆላልፈን ቆየን፡፡
እንደዚሁ እንዳለን፣ ልክ እሸቴን እንዳገኘልኝ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የገባሁት ቃል ትዝ አለኝ። እስከሚነጋ ቸኮልሁ።

ከአምስት ወር በላይ በሆዴ ፅንስ ይዤ፣ ያዉም እኔ ራሴ የሕክምና
ባለሙያ ሆኜ ፤ እስከ አሁን ግን የሕክምና ክትትል አለመጀመሬ ለግድ የለሽነቱ ወደር የማይገኝልኝ ሴት መሆኔን መስክሮብኛል፡፡ ይኼንን ማንም ሳይነግረኝ አዉቄዋለሁ። ሲሆን ሲሆን እርግዝና ከመፈጠሩ ከዓመት ወይ
ከወራት ቀደም ሲል ጀምሬ ዝግጅት ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እንደኔ እንኳን እርግዝናዉ በድንገት ለተፈጠረበትም ቢሆን፣ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ
ሙሉ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የግድ ነዉ። እኔ ግን ቢያንስ ቅሪት መሆኔን ያወቅሁት ቶሎ ቢሆንም፣ ይኼዉ 22ኛ ሳምንቴን ጭልጥ አድርጌ ነዉ ገና ነገርዮዉን እንኳን በበጎነቱ የተቀበልሁት።

ዛሬ ነዉ ወደ ሆስፒታል ለመምጣት የወሰንሁት። ዛሬ ገና።

ዛሬ ግን ቆርጬ መጥቻለሁ።

በእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ዝነኛ ወደ ሆነዉ ሐሚያሉ ሆስፒታል ገብቼ ካርድ አወጣሁና ወደ ተጠቆምሁት የዶክተር ክፍል አመራሁ። ብዙም ሳልቆይ ወረፋዬ ደረሰኝና፣ መለስ ያለዉን በር ገፍቼ ወደ ዉስጥ ገባሁ። ሆስፒታሉን በበጎ ስሙ መረጥሁት እንጂ፣ የተለየ የሐኪም ምርጫ አላደረግሁም ነበር። ሆኖም ከዉስጥ የጠበቀችኝን ሐኪም ካየሁ በኋላ፤ ሕይወት የአጋጣሚዎች ጋን መሆኗን አመንሁ።

ሐኪሟ ስንቱን አብራኝ ያሳለፈች፣ የቀድሞ ጓደኛዬ ሆና እርፍ!

“ሸዊት!” አልኋት፣ ለረዥም ደቂቃ እጄን አፌ ላይ ጭኜ ስደነቅ ከቆየሁ በኋላ።

"የፈጣሪ ያለህ! ዉብዬ ?” አለች እሷም፣ አሁንም አሁንም ዓይኖቿን
ጨፍና እየገለጠቻቸዉ። ከመልኬ እኩል በሆዴ ያለዉን አስተዉላለች፡፡ ከነጭራሹ የምንገናኝ፣ ያዉም እንዲህ ሆኜ፣ አልጠበቀችኝም ነበር። ለነገሩማ እኔስ እንዴት ብዬ እጠብቃለሁ? በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕክምና
ዶክትሬት ዲግሪያችንን አብረን በተማርንበት ወቅት የነበረንን ጓደኝነት አይቶ ትንሽ ትልቁ እንደዚያ ከዓይን ያዉጣችሁ እንዳላለን ሁሉ፣ እንደዚህ በአንድ ከተማ መኖራችንን እንኳን እስካለመተዋወቅ ድረስ
መራራቃችን ዋዛ ነዉ፡፡ ምን ሆነን ነዉ ግን? ምንም፡፡ ለነገሩ ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቀኝ ወዳጆቼ ማንን አግኝቼ አዉቃለሁ? ከስንት አንድ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር፣ አብዛኞቹ የት እንዳሉ እንኳን አላዉቅም፡፡

“ዋዉ!” አለችኝ፣ እንደ ታቦት እየዞረችኝ፡፡

“እሩ እስኪ ሰላም በዪኝ መጀመሪያ”

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዉብዬ” ብላ መጥታ አንገቴ ሥር ሰረገች፡፡
እንደገና ሆድ ሆዴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ ጭምጭም አድርጋ ሳመችኝ፡፡የምር ደስ ብሏታል። እንባዋ ሳይቀር ጠይም ጉንጮቿን እያራሰ በብርቅዬ አንገቷ በኩል ፈሰሰ።

ሀገር ዉስጥ ነዉ የምትኖሪዉ? ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ?” አልኋት፣

ደስታዋ እንዲጋባብኝ ልቤን እየደቃሁት።

“አይ፤ ቅርብ ጊዜ ነዉ የመጣሁት። ጀርመን ነበርሁ፣ ትምህርት ላይ”

“ተዪ እንጂ? ጀርመን፤ ምን ስፔሻላይዝ አደረግሽ ታዲያ?”

“ይኸዉ እያየሽኝ? ለእር ግዝና ክትትል አይደል እንዴ እኔ ጋ
የመጣሽዉ?”

“አይ አጅሪት! እንዲያ ነዉ እንጂ የኔ እህት! ደግሞ ጥሩ ምርጫ ነዉ”

“አንቺስ ምን አጠናሽ?”
👍481
#ሳቤላ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ዌስትሊን መኻል ተጠጋግተው የተሠሩ ሁለት ቤቶች ይታያሉ " አንዱ ትልቅ ሌላው አነስ ያለ ሲሆን ትልቁ የካርላይል መኖሪያ ትንሹ ደግሞ ቤሮው ነው ካርላይል የሚለው ስም በዚያ አካባቢ በጣም የታወቀ ነው " ካርላይልና ዴቪድስን በአንደኛው ደረጃ የሚቀጠሩ ጠበቆች ነበሩ " ዱሮ ካርላይልና ዴቪድሰን በጋራ
ይዘውት የነበረ ድርጅት ዛሬ አርኪባልድ ካርላይል የብቻው አድርጐታል እነዚ የሥራ ሸሪኮች አምቻዎችም ነበሩ " የጀመሪያይቱ ሚሲዝ ካርላይል የሚስተር
ዴቪድሰን እኅት ነበረች እሷም ኮርኒሊያን ብቻ ከወለደችለት በኋላ ሞተች ኮርኒሊያ ትልቅ ልጅ ከሆነች በኋላ ሚስተር ካርላይል ሁለተኛ ሚስቱን አገባ " ሁላተኛይቱ ሚሲዝ ካርላይል ደግሞ የመጀመሪያ ልጅዋን አርኪባልድ ካርላይልን ወልዳለት ሞተችና እኀቱ ኮርነሊያ ተንከባክባ እንደ እናት ተጨንቃ እሷ በምትፈልገው ዐይነት መርታ አሳደገችው " ልጁም ሌላ እናት አያውቅም ነበርና እማማ ኮርኒ” ይላት ነበር እማማ ኮርኒ ለሱ ማድረግ የነበረባትን ሁሎ ፈጽማለታለች
ነገር ግን ዛሬም ትልቅ ከሆነ በኋላ ልክ እንደ ልጅነቱ በሷ እንዲመራ ትፈልጋለች
ከልማድ መላቀቅ በጣም ከባድ በመሆኑ አርኪባልድም ቢሆን ብዙውን ጊዜ እንዳለችው ይታዘዛታል » በአንዳንድ ነገሮች ደካማ አስተያት ይኑራት እንጂ ባጠቃላይ ግን ብርቱ ሴት ነበረች " ያለ የሌለ ሐሳቧ የአርኪባልድና የንዘብ ማስቀመጥ ፍቅር ብቻ ነበር " ሚስተር ዴቪድሰን ትዳር የሚባል ሳይሞክር ከሥራ ሸሪኩ ከሚስተር ካርላይል ቀደም ብሎ ሲሞት 'ሀብቱን ለኮርነሊያና ለአርኪባልድ እኩል አወረሳቸው " አርኪባልድን ባይዛመደውም በጥሩ ምግባሩ ይወደው ነበር ሚስተር ካርላይል ብዙ ሀብት ሊያከማች የቻለው ሁለተኛዋ ሚስቱ ባመጣችው ኻያ ሺህ ፖውንድ በመሆኑ ይሆናል ለሴት ልጁ ለኮርነሊያ ጥቂት ሰጥቶ አብዛኛውን አርኪባልድ አውርሶት የሞተው "

ሚስ ካርላይል ወይም በከተማው እንደምትጠራው ሚስ ኮርኒ ባል አላገባችም ሰዎች ለትንሽ ወንድሟ የነበራት ፍቅር ሳታገባ ብቸኛ ሆና እንድትቀር ያደረጋት ይመስላቸው ነበር ነገር ግን የባለጸጋው የሚስተር ካርላይል ልጅ ከነጭራሹ ባል የምትፈልግ አትመስልም ነበር " የፍቅር ነገር ይዘው የቀረቧትን ሁሉ አፋቸውን እያስያዘች መልሳቸዋለች የመጨረሻውን ሙከራ ያደረገው አንድ አዲስ የመጣ ቄስ ነበር " የዚያን ጊዜ ዐርባኛ ዐመቷን ይዛ ነበር አንድ ቀን ነጭ ክራባት አስሮ ወይን ጠጅ ቀለም የእጅ ሹራብ አጥልቆ አሸብርቆ ከጧቱ ቀዶም ብሎ ከቤቷ መጣ

ሚስ ኮሮኒ ከልክ ያለ የቤት አያያዝ ዐዋቂ ገረዶቿ ሊፈጽሙት ከሚፈልጉት የበለጠች ጠንቃቃ ነበረች " ለምሳ የሚዘጋጅ ሥጋ የሚጋገር ሊጥ እየመጠነች ስትሰጥና ስለ ዝግጅቱም እያስረዳች ሳለች የምግብ ቤቱ በር ተከፈተ ወዲያው ቄሱ ገባ " የዩልኝታን ነገር እርግፍ አድርጋ የተወችው ሚስ ካርላይል እንግዳ በመምጣቱ ልታጠብ ልለቃለቅ አላለችም- ሊጥ ስትከፋፍልበት የነበረ አንድ ሳህን እንድ ያዘች እንግዳው ዐረፍ ከሚልበት ምግብ ቤት ገባች "

በዐሥራ ሁለት ዓመት በዕድሜ የምትበልጠው መንፈሳዊ ሰው የሚላትን እስክትሰማ ሰሐኑን ጉኗ በነበረው ጠረጴዛ ላይ አሳረፈችው ኮርነሊያ የያዘችውን ሥራ እንዳደበላሽባት ሰውየው ሳይንተባተብባትና ሳይዘበዝብ ቶሎ እንዲወጣላት መፈለጓን
በተዘዋዋሪ መንገድ ስትጠቁመው አልገባው ሲል ቀጥውን በመንገር አጣደፈሻው » እሱ ለአንድ በጎ አድራጐት ድርጅት በረጂ አባልነት እንድትመዘገብ ሊጠይቃት መሰላት » ከሷ በሁለት ስንዝር ያህል አጠር ይል ስለነበር እሁንም ነገር አልቆርጥ በማለቱ ትግሥቷን ጨርሳ ቁልቁል ትመለከተው ጀመር" በመጨረሻ እሷን እንጂ ገንዘቧን ፈልጎ እንዳልመጣ ነገሩን ገልጾ ሲነግራት እሳት ሆነችበት " እሱን የመሰለ ውርጋጥ እሷን ለዚህ ነገር ደፍሮ ሲያስባት ኣለማፈሩን እየነገረች የቁጣ
መዓቷን አወረዶችበትና ያን ከጠረጴዛው ላይ በሰሐን አኑራው የነበረውን ሊጥ ብድግ አድርጋ በረዶ ከመሰለው ነጭ ሸሚዙ ላይ ለደፈችበት » ኃፍረትና ድንጋጤ ኩምሽሽ ያደረገው ካህን እንዴት አድርጎ ከቤት ወጥቶ በዌስት ሊን ቁልቁል ወርዶ ቤቱ እንዶ ደረሰ ለማስታወስ እንኳን አይፈልግም ነበር " ወሬው ግን ባንድ ጊዜ ዳር እስከ ዳር ተዳረሰና ከዚያ ወዲህ ሚስ ኮርኒን ለጋብቻ በመጠየቅ ረገድ ማንም ስው አስቸግሯት አያውቅም "

ሚስተር ካርላይል ከለንደን በተመለሰ ማግሥት ጧቱን ከቢሮው ገብቶ ተቀምጧል " አብዛኛውን ጊዜ ሥራውን የሚያካሒድለት ታማኝ ጸሐፊውና ሥራ አስኪያጁ የሆነው ሚስተር ዲል ከአጠገቡ ቆሟል " ሚስተር ዲል ዐይን አፋር ቢጤ አጭር ' ቀጭንና ራስ መላጣ ነበር " ድሮ በትልቁ ካርላይልና በዴቪድስን ጊዜ ቀጥሮ ገባ ጀምሮ ችሎታውና የሥራ ልምዱ ሳያንሰው ራሱን ችሎ ከመሥራት ይልቅ ሥራ አስኪያጅ እየተባለ በሰው ሥር ሆኖ ደኅና ደመወዝ እያገኘ መኖሩ ምኞቱን ያረካለት ይመስላል " ለመለየት አሳብ አልነበረውም » በዚያው አካባቢ በአንድ
ጥሩ ቤት ሲኖር እሱም እንደ ኮርነሊያ አላገባም ነበር " የሚስ ካርላይል ልባዊ ወዳጅ ስለመሆኑ ይነገር የነበረው ሐሜት በዌስት ሊን ክብደት እያገኘ መጥቶ ነበር
በሩቁ ግን የማምለክ ያህል ነበር የሚያከብራት " ግምቱ እውነት ቢሆንም ባይሆንም ሚስተስ
አርኪባልድ እያለ የሚጠራውን ያሁኑን ጌታውን ይወደው እንደነበር
ግን እርግጥ ነው አሁን ለንደን ሒዶ በሰነበተባቸው ቀኖች ውስጥ በቢሮ አካባቢ የተፈጸሙትን ነገሮች ሲያስረዳው ቆየና ወጣ"መጨረሻው ሲዶርስ «ጆንስና ራሽዎርዝ ተካረዋል " ሁለቱም በየራሳቸው እንድትቆምላቸው ፈልገውህ ትናንት መጥተው ነበር " ዛሬ የምትሰጣቸውን መልስ ለመስማት ይመጣሉ » አለው "

« ለአንዳቸውም አልቆምም " ከነሱ ጋር ምንም ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም እነሱ መጥፎዎች ናቸው " ሀብታቸውም ሁሉ በግፍ የተለበሰበ ስለሆነ
ሰዎች አይደሉም ስለዚህ እኔ ፈቃደኛ አይደለሁምና ሌላ ሰው ይፈልጉ »

« በጣም ጥሩ እሺ» አለው ዲል

« ኰሎኔል ቤተል መጥተዋል
ጌታዬ » አለ አንዱ ጸሐፊ በሩን ከፈት አድርጎ ወዶ ሚስተር ካርላይል እያየ
«ሊያነጋግሯቸው ይችላሉ ? »

ሚስተር ዲል ወደ ተላከው ጸሐፊ ዞር ብሎ' «ኮሎኔሉን እንዲጠብቁ ንገራቸው» አለውና • ሰውየው መልሱን ሰምቶ ሲወጣ አይቶ ወደ ጌታው ምልስ ብሎ «እንግዲህ ይኸው ብቻ መሰለኝ » አለው
« ጥሩ ነው ስማ ዲል ... ሰሞኑን ስለ ኢስት ሊን የባለቤትነት ይዞታ
ስለ ወለድ አግድ ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ከነሙሉ ማስረጃቸው ይቀርቡልሃል "
ለማንም ሳታሳይና ሳትናግር በደንብ አድርገህ እንድታያቸው እፈልጋለሁ ኢስትሊን ባለቤት ሊለወጥ ነው እንደ ሎርድ ማውንት እስቨርን ከመሰለ በችግር ከተወጠሩ ሰዎች ቦታ ሲገዙ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል ስለዚህ ማንም አንዳይሰማ ሆኖ ተጠንቅቀህ እንድትመረምረው በል አሁን ቤቴልን አስገባልኝ »

በሚስተር ካርላይልና በጸሐፊዎቹ ክፍሎች መካከል አንድ አራት ጎኑ እኩል የሆነና ወዶ ዋናው መተላለፌያ የሚያስገባ ሁለተኛ በር የነበረሙ አንድ ትንሽ መተላለፍያ ነበር » በዚያ መተላለፊ በኩል አንድ ጠባብ ክፍል ነበር » ክፍሉ ሚስተር ካርይል በማይኖርበት ወይም እንግዶችን ማያስችል ከባድ ጉዳይ ሲኖርበት ሚስተር ዲል እሱን ተክቶ የሚሸኝበት ልዩ ቢሮው ነበር " ይህ ክፍል የጸሐፊዎቹን ቢሮ የምታሳይ አንዲት ጠባብ መስኮት ነበረችው " ሚስቴር ዲል አንዳንድ ጊዜ በዚያች መስኮት አሹልኮ እየተመለከተ ስላሠቀቃቸው
👍21
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...የሰጠቸው አስተያየት ልባችንን ሊያሞቅ የሚገባው ቢሆንም የእኔን ልብ ግን ድምጽዋ ቀዝቃዛና ግድ የለሽ ነበር፡ በእሷ የውሸት አስተያየት በቀላሉ የምንታለልና አለመደሰቷን የሚረዳ አእምሮ የሌለን አድርጋ ቆጥራናለች ማለት ነው! ብዬ እያሰብኩ ሳለ ቀጥሎ የተናገረቻቸው ቃላት
የሀሳቤን ትክክለኛነት አረጋገጡልኝ፡....

“ጭንቅላታቸው እንደሚሰራ እርግጠኛ ነሽ? ሌላ በአይን የማይታይ የሆነ ጉድለት የለባቸውም?” እናቴ ልክ እንደ እኔ ንዴቷን ውጣ “ምንም እንከን
የለባቸውም እንደምታይው ልጆቼ በአካልም ሆነ በአእምሮ ፍፁም
ጤነኛ ናቸው” አለች ከዚያ ያችን ግራጫ የለበሰች አሮጊት አተኩራ ተመለከተቻትና ከመራመድ ብዛት እግሯ ያበጠባትን የኬሪን ልብስ ልትቀይር ዞራ ተረከዟ ላይ ቁጢጥ አለች እኔም ኮሪ ፊት ለፊት በርከክ ብዬ የጃኬቱን ቁልፍ መፍታት
ጀመርኩ። ክሪስቶፈር ደግሞ አንደኛውን ሻንጣ ከፈተና ሁለት ትናንሽ ቢጫ የሌሊት ልብሶች አወጣ።

ኬሪ የሌሊት ልብሱን እንዲቀይር እያገዝኩት አሮጊቷን አየት አደረግኳት ከሁኔታው ይህች ረጅምና ግዙፍ ሴት አያታችን እንደሆነች ገመትኩ
አሻግሬ እየተመለከትኳት ፊቷ ላይ የተጨማደደ ቆዳ ለማየት ብፈልግም መጀመሪያ የገመትኩትን ያህል አሮጊት እንዳልሆነች አወቅኩ። ፀጉሯ ደስ
በማይል አይነት ከፊቷ ወደ ኋላ በመሰብሰቡ አይኖቿን የፈጠጡና የድመት አስመስሏቸዋል። እያንዳንዱ የፀጉሯ ዘለላ እንዴት ቆዳዋን እንደጎተተው ማየት ይቻላል።

አፍንጫዋ የአሞራ መንቆር ይመስላል፤ ትከሻዋ ሰፊ ሲሆን ከንፈሯ ስስ ሆኖ አፏ በቢላ የተሰነጠቀ ጭረት መሰል ነበር። ቀሚሷ ግራጫ ሆኖ ጠበብ
ካለው አንገትጌው ላይ የአልማዝ ጌጥ አለበት፡ አንዱም ነገሯ ለስላሳና ማራኪ አይደለም፡ ጡቶቿ ሳይቀሩ መንታ ኮረብታዎች የሚመስሉ ናቸው:
ከእናታችንና ከአባታችን ጋር እንደምንጫወተው ከእሷ ጋር ቀልድ የማይታሰብ ነው።

አልወደድኳትም። ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ። ቤቴ መሄድ ፈለግኩ። እንደገና አባቴ በህይወት እንዲኖር ፈለግኩ፡ እንደዚች አይነት ሴት እንዴት እንደ
እናታችን አይነት ተወዳጅና ጣፋጭ ሴት ልትወልድ ቻለች? እናቴ ቁንጅናዋንና ለዛዋን ከማን ወርሳ ነው? እየተንቀጠቀጥኩ በአይኖቼ የሞሉት እምባዎቼ እንዳይወርዱ ሞከርኩ። እናታችን ወንድ አያታችን ለሰው ፍቅር
የሌለው፣ ግድ የለሽና ተቆጪ እንደሆነ አስቀድማ በመንገር አዘጋጅታን ነበር።ነገር ግን መምጣታችንን ያመቻቸችው ሴት አያታችንም መጥፎ የመሆኗ
ነገር አስገራሚ ነበር፡

ደንግጦ የነበረው ክሪስቶፈር አይቶኝ በኋላ እንዳይቀልድብኝ አይኖቼን በማርገብገብ እምባዎቼን መለስኳቸው: እናታችን ግን ሁሉ መልካም የሚሆን
ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሆነን ኮሪን ትልቁ አልጋ ላይ ስታስተኛው በደስታ ፈገግ ብላ ነበር ከዚያ ኬሪንም ከእሱ አጠገብ አስተኛች እዚያ አልጋ ላይ ሮዝ ጉንጭ ያላቸው ትልቅ አሻንጉሊቶች መስለው ተኝተው ሲታዩ እንዴት
እንደሚያምሩ። እናታችን የመንትዮቹን ጎንጮች ሳመችና በእጆቿ ግንባራቸው ላይ የተኛውን ፀጉራቸውን በእጇ ወደ ኋላ መለሰችላቸው: ከዚያ የአልጋ
ልብሱን ወደ አገጫቸው ከፍ አድርጋ ሁላችንም በምናውቀው ጣፋጭ ድምፅዋ
“ደህና እደሩ የኔ ውዶች" ስትል አንሾካሾከች መንትዮቹ አልሰሟትም፡ ገና ድሮ እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር።

እንደተተከለ ዛፍ ቀጥ ብላ ቆማ መንትዮቹ ሲተኙ እንዲሁም እኔና ክሪስቶፈር ተጠጋግተን ስንቀመጥ እያየች የነበረችው አያታችን ደስ እንዳላት በግልፅ ያስታውቃል በጣም ስለደከመን ተደጋግፈን ተቀምጠናል። እንደ ድንጋይ
ከጠነከሩት አይኖቿ ውስጥ የሚነበበው ነገር ደስ አይልም ያልተስማማት አንድ ነገር እንዳለ ከአስተያየቷ መረዳት ይቻላል፡ ፊቷን አጨፍግጋ ዘልቆ
የሚገባ በሚመስል አስተያየት እያየችን የመሆኑ ነገር ለእናቴ የሰጣት የሆነ መልእክት ያለ ይመስላል፡ ወዲያው “ሁለቱ ያደጉት ልጆችሽ አንድ አልጋ ላይ
መተኛት አይችሉም” ስትላት እናቴ ፊቷ በንዴት ደም መሰለ።

እናታችን ባልተለመደ ኃይለኝነት “ገና ልጆች እኮ ናቸው። እማዬ ትንሽ እንኳን አልተቀየርሽም አይደል? አሁንም አስቀያሚ ተጠራጣሪ አእምሮ ነው
ያለሽ፡ ክሪስቶፈርና ካቲ ምንም አያውቁም” አለች።

“ምንም አያውቁም!?” በቁጣ መለሰች፡ የክፋት አስተያየቷ ደም የሚያፈስ ስለት ይመስል ነበር። “እኔና አባትሽም ስለአንቺና ስለ አጎትሽ ሁልጊዜም የምናስበው እንደዚያ ነበር።”

አይኖቼ በሰፊው ተከፍተው ከአንደኛቸው ወደ ሌላኛቸው ተንከራተቱ፡ ወደ ወንድሜ ሳማትር ከእድሜው ላይ አመታት የተቀነሱ ይመስል ልክ እንደ ስድስትና ሰባት አመት ህፃን ረዳት አልባ መስሏል። ከእኔ የበለጠ እንዳልገባው ያስታውቃል።

የሚፋጅ ቁጣ የእናታችንን ቀለም ለዋወጠው “እንደዚያ ካሰብሽ የተለያየ ክፍልና የተለያየ አልጋ ስጫቸዋ! እዚህ ቤት ውስጥ በቂ ክፍል እንዳለ የታወቀ ነው”

“ያ የማይቻል ነው! አጠገቡ መታጠቢያ ያለውና ወዲያ ወዲህ ሲሉ ወይም የሽንት ቤት ውሀ ሲለቁ ባለቤቴ የማይሰማበት ብቸኛ ክፍል ይሄ ብቻ ነው፡ የተለያየ ክፍል ውስጥ ከሆኑ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ድምፃቸው ወይም ጩኸታቸውን ይሰማል ሰራተኞቹም ሊሰሙ ይችላሉ። ይህንን ክፍል ያመቻቸሁት ብዙ ካሰብኩበት በኋላ ነው ደህንነቱ የተጠበቀ ብቸኛው ክፍል
ይህ ብቻ ነው:" አለች አያታችን እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ድምፅዋ።

“ደህንነቱ የተጠበቀ?” ሀያ፣ ሰላሳ፣ አርባ ክፍሎች ባሉበት ትልቅ ቤት ውስጥ ሁላችንም በአንድ ክፍል ውስጥ ታጭቀን እያደርን? በአንድ ክፍል ውስጥ እየኖርን? ቢሆንም ግን አሁን ሳስበው በዚህ ግዙፍ ቤት ብቻዬን አንድ ክፍል
ውስጥ መሆን አልፈልግም
“ሁለቱን ሴቶች አንዱ አልጋ ላይ፣ ሁለቱን ወንዶች ደግሞ ሌላኛው አልጋ ላይ አስተኚ” ስትል አዘዘች
እናታችን ኮሪን አንስታ ሌላኛው አልጋ ላይ አስተኛችው ከያ በኋላ ቀስ በቀስ ሁሉም ነገር አያትየው እንዲሆን እንደምትፈልገው ሆነ። ወንዶቹ ለመታጠቢያ ቤቱ ቅርብ የሆነው አልጋ ላይ፣ እኔና ኬሪ ደግሞ መስኮቱ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ ሆንን።

አሮጊቷ እይታዋን መጀመሪያ ወደ እኔ ከዚያ ደግሞ ወደ ክሪስቶፈር አደረገች ከዚያ ልክ እንደ አዛዥ ወታደር መናገር ጀመረች። “ስሙ! ትንንሾቹን ልጆች ፀጥ እንዲሉ ማድረግን የእናንተን የትልልቆቹ ሀላፊነት ይሆናል፤ ከማወጣቸው
ህሃጎች አንዱንም እንዳትጥሱ የምለውን በጥንቃቄ በአእምሯችሁ ያዙ።
ክፍሉንና መታጠቢያ ቤቱን ልክ ሰው የማይኖርበት በሚመስል አይነት በንፅህና መያዝ ይጠበቅባችኋል። ፀጥ ማለት ግዴታ ነው! መጮህ፣ ማልቀስ ወይም መሮጥ አይቻልም ከዚህ ክፍል ወጥታችሁ መሄድ ስለማይፈቀድና በምንም
ምክንያት ወደ ቤቱ ሌላኛው አካባቢ እንድትሄዱም ስለማልፈልግ እናታችሁና
እኔ አሁን ከዚህ ስንወጣ በሩን ከውጪ እቀረቅረዋለሁ። ወንድ አያታችሁ እዚህ መኖራችሁን ካወቀ በህይወት በመኖራችሁ ብቻ በአስከፊ ሁኔታ ከቀጣችሁ በኋላ አንዲት ሳንቲም ሳይሰጣችሁ አስወጥቶ ይወረውራችኋል!
ስለዚህ እሱ እስከሚሞት ድረስ እዚህ ትቆያላችሁ: ግን እዚህ እንደሌላችሁ ትቆጠራላችሁ”
👍324
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹የሚያስቸኩልሽ ነገር የለም›› አለ ኮንስታብሉ ‹‹አባትሽ ሊወስዱሽ
እየመጡ ነው፡፡››

የማርጋሬት ልብ በድንጋጤ ቀጥ አለ፡ እንዴት ሊሆን ይችላል? አሁን
ያለችበት ቦታ አባቷ የማያውቁት ስለሆነ ደህነኛ ቦታ ነው ብላ ተማምና ነበር፡፡

አባቷን ዝቅ አድርጋ ነበር የገመተቻቸው፡ በዚህ ደቂቃ ውስጥ ሊይዟት ይመጣሉ! ሃሳቡ አንቀጠቀጣት ‹‹የት እንዳለሁ እንዴት አወቀ አባባ?›› አለች፡፡

ወጣቱ ፖሊስ በኩራት ‹‹ትናንት ማታ ስለመጥፋትሽ የቴሌግራም መልዕክት ደርሶን ነበር፡፡ ስመጣ አየሁት፡፡ በጨለማ የመጣሽ ጊዜ
አላወቅኩሽም ነበር፡፡ ስምሽን ግን አስታወስኩት፡፡ ከተገኘሽ ለጌታ ኦክሰንፎርድ
እንዲነገራቸው ቴሌግራሙ ያዛል፡፡ እዚህ እንዳመጣሁሽ ለአባትሽ ደወልኩ››

ማርጋሬት ብድግ አለች፧ ልቧ በጣም ይመታል፡፡ ‹‹እሱን አልጠብቅም
አሁን ነግቷል›› አለች፡፡

ፖሊሱ ስጋት ገባው ‹‹ትንሽ ቆይ›› አለ፡፡ ዞር አለና ‹‹ሃምሳ አለቃ እመቤት ማርጋሬት መሄዴ ነው እያለች ነው›› ብሎ ነገረው፡፡
ሄሪ ማርክስ ‹‹እዚህ ይዘው ሊያቆዩሽ አይችሉም ባንቺ እድሜ ከቤት ጠፍቶ መሄድ ወንጀል ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ መሄድ ከፈለግሽ ቀጥ ብለሽ
ሂጂ›› አላት፡፡

ሃምሳ አለቃውም ‹‹ነገር ግን ጫማ የለሽም፤ ስቶኪንግሽ ተቀዳዷል፡፡ አባትሽ ጋ ልደውልልሽ›› አላት፡፡
ማሰብ ጀመረች፡፡ ጣቢያ እንደደረሰች ነው ለአባቷ ስልክ የተደወለው፡፡
አሁን አንድ ሰዓት አልሞላውም ማለት ነው፡፡ አባቷ ደግሞ ከዚህ በኋላ
እዚህ ለመድረስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በላይ ይፈጅባቸዋል፡ ‹‹ደህና›› አለች ለደጉ ፖሊስ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡››

ሄሪ ወደ ፖሊስ ስታዘግም አየና ‹‹ጅል›› አላት፡፡
ፖሊሱ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ወስዶ አስገባት፡፡ ወንበሮቹ ተራ ናቸው፡
አንድ አግዳሚ ወንበር ይታያታል፡፡ ከላይ ማቀፊያ የሌለው አምፑል ተንጠልጥሏል፡ መስኮቱ በብረት ፍርግርግ ተዘግቷል፡ ሃምሳ አለቃው ይህ
ክፍል ከባለጉዳይ መቀበያው ክፍል የተሻለ ነው ብሎ እንዴት እንዳሰበ
አልገባሽ አላት፡፡ ልትነግረው ዞር ስትል በሩን ፊቷ ላይ ጠረቀመው፡፡ አንድ
ክፉ ነገር እንዳለ በልቧ ጠረጠረችና ፍርሃት ገባት፡፡ ተወርውራ በሩ ጋ ሄዳ
ለመክፈት ታገለች ከዚያም ፍርሃቷም እውነት መሆኑን በሩ ሲቆለፍ አረጋገጠች፡፡ የበሩን እጄታ በሃይል ነቀነቀችው፤ ነገር ግን በሩ የሚከፈት አልሆነም በተስፋ መቁረጥ በሩ ላይ ልጥፍ አለች፡፡

ከውጭ በኩል ሳቅ ይሰማታል፤ ከዚያም ሃሪ ‹‹እናንተ እርጉሞች›› ሲል
ተሰማት ‹‹አፍክን ዝጋ›› አለው ፖሊሱ፡፡

‹ምንም መብት የላችሁም ልጅቷን ለማቆየት፤ አንተም ታውቃለህ አለው።

‹‹አባቷ የተከበሩ ሰው ስለሆኑ ነው እንደዚህ ያደረኩት›› አለ፡

ማርጋሬት ያሰበችው ባለመሳካቱ በምሬት ተንገበገበች፡ የማምለጥ
እቅዷ ውሃ በልቶታል። ይረዱኛል ብላ የገመተቻቸው ሰዎች አታለዋታል ለትንሽ ጊዜ ነፃ
ነበረች አሁን ግን ነፃነቷ አብቅቷላተል ምድር ጦር
መምሪያው መሄድ አለመቻሏ አንገበገባት
ከጦርነቱ ለመሸሽ የፓን አሜሪካ ንብረት በሆነችው አይሮፕላን ተሳፍራ ኒውዮርክ ልትሄድ ነበር። ይህን ያህል ደክማም እድሏ አልሰምር አላት፡፡

ከብዙ ቆይታ በኋላ ከበሩ ወደ መስኮቱ ሄደች። በመስኮት አጮልቃ
ስታይ ምንም ነገር የማይታይበት ጓሮና የሸክላ ግድግዳ ብቻ ነው::
በሽንፈትና በአቅመቢስነት መስኮቱ ጋር ተገትራ የአባቷን መምጣት
ከመጠባበቅ በስተቀር ምንም ምርጫ አልነበራትም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ዲኪን ለአይሮፕላኑ የመጨረሻ ፍተሻ አደረገ እያንዳንዳቸው የ1500 የፈረስ ጉልበት ያላቸው አራቱ ሞተሮች የተቀቡት ዘይት ያብለጨልጫል፡ እያንዳንዱ ሞተር የሰው ቁመት አለው። ኤዲ እያንዳንዱን የሞተር ክፍል መርምሮ ሲጨርስ ዘጋጋና ከመሰላሉ ላይ ወረደ። አይሮፕላኑ ለበረራ ሲዘጋጅ ቱታውን ያወልቅና ሰውነቱን ታጥቦ የአየር መንገዱን የበረራ ዩኒፎርም ይለብሳል።

ከአይሮፕላን ማረፊያ ወደቡ ወጥቶ ሲሄድ ፀሀይ ገና አልጠለቀችም፡ከዚያም የስራ ባልደረቦቹ ወደሚገኙበት ሆቴል አመራ: በአይሮፕላኑና
በሚሰራው ስራ ይኮራል። አትላንቲክ አቋራጭ በረራ ከሁሉም የበረራ ስራ
የበለጠ ስለሆነ አየር መንገዱ ያሰማራው አሉ የሚላቸውን የበረራ ሰዎች
ነው።

ሆኖም ይህን ስራ በቅርቡ ለመተው አቅዷል፡ አሁን እድሜው ሰላሳ ሲሆን ትዳር ከያዘ ዓመት ሆኖታል። ሚስቱ ካሮል አን ነፍሰ ጡር ናት ይህ ስራ ለወንደላጤ ምንም አይልም እሱ ግን ከቤተሰቡ ርቆ መኖር
አይፈልግም፡ የራሱን ስራ ለመጀመር በቂ ገንዘብ አጠራቅሟል፡ አሜሪካ
ውስጥ ይህን ስራ ለመስራት የሚያስችለው አየር ማረፊያ አለ፡፡" አይሮፕላን ይጠግናል፣ ነዳጅ ይሸጣል፡ በኋላም አይሮፕላን ገዝቶ ያከራያል፡

ሆቴሉ ውስጥ ሲገባ ረዳት ኢንጂነሩን ሚኪን አገኘው፡ ሚኪ ተጫዋች ሲሆን ኤዲን በችሎታው ይወደዋል። ሚኪ ስልክ እየተነጋገረ ሳለ ኤዲንን
ሲያይ ‹‹እድለኛ ነህ አሁን መጥቷል ላገናኝህ›› አለው ለደዋዩ ‹‹አንተን ነው
የሚፈልገው›› ብሎ የስልኩን መነጋገሪያ ለኤዲ ሰጠና ብቻውን መነጋገር
እንዲችል ጥሎት ሄደ።
ኤዲም ስልኩን ተቀበለና ‹‹ሄሎ?›› አለ፡

‹‹ኤድዋርድ ዲኒኪን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ደዋዩ፡፡

ኤዲ ግንባሩን በግርታ ቋጠረ፡ በስልክ የሚሰማው ድምጽ አዲስ ሆነበት ከዚህ በፊትም ማንም ኤድዋርድ ብሎት አያውቅም፡፡ ‹አዎ ነኝ
ማን ልበል?›› አለ፡

‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቀኝ ባለቤትህን ላገናኝህ አጠገቤ ነው ያለችው›› የኤዲ ልብ ተንጠለጠለ ካሮል አን ለምንድነው ከአሜሪካ የደወለችልኝ ችግር አለ ማለት ነው?› ሲል ተጨነቀ፡፡

ከአፍታ በኋላ የካሮል አን ድምጿ ተሰማ ‹‹ኤዲ›› አለች እምባ እየተናነቃት፡

‹‹እንዴት ነሽ ማርዬ ምን ሆነሻል?››

ካሮል አን የባልዋን ድምጽ ስትሰማ ለቅሶዋን ለቀቀችው።

ኤዲ በዚያች ደቂቃ ውስጥ ክፉ ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለበት፡
‹ካሮሌ ላይ ምን ደርሶባት ይሆን? ውርጃ ገጠማት ይሆን? ቤቱ ተቃጠለ?
ማን ይሆን የሞተው? የሚሉ ሃሳቦች በአንድ ላይ መጡበት፡፡

«ካሮል ተረጋጊ ደህናም አይደለሽ?››

‹‹አይ ምንም አልሆንኩም›› አለች እየተነፋረቀች፡

‹‹ታዲያ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው?›› አለ ሆዱ በፍርሃት እየተንቦጫቦጨ፡

‹‹ምን ተፈጠረ ንገሪኝ የኔ ውድ?››

‹‹እነዚህ ሰዎች እቤት መጡ››

ኤዲ ይህን ሲሰማ በድንጋጤ የበረዶ ክምር ሆነ ‹‹የምን ሰዎች? ምን
አደረጉሽ?››

‹‹መኪና ውስጥ ከተው ወሰዱኝ››

‹‹ወይ አምላኬ! ማን ናቸው?›› ንዴቱ ደረቱ ላይ ውጋት ለቀቀበትና
መተንፈስ አቃተው፡

‹‹ጎድተውሻል?››

‹‹አይ ደህና ነኝ፡ ነገር ግን ኤዲ ሰዎቹ ያስፈራሉ››
ምን እንደሚል ጨነቀው፡ ብዙ ነገሮች አዕምሮው ውስጥ መጡበት፡፡"
የሆኑ ሰዎች ሚስቱን አግተዋታል፡፡ ምንድነው ነገሩ? በመጨረሻም
‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹ምክንያቱን አልነገሩኝም››

‹‹ምን አሉሽ?››

‹‹ኤዲዬ የሚሉህን በሙሉ አርግላቸው፡፡ የማውቀው ይህን ብቻ ነው››

ንዴትና ፍርሃት እየተፈራረቁበት ‹‹አንቺን ከሚያሰቃዩብኝ ያሉትን
አደርግላቸዋለሁ›› አለ፡፡

‹‹እውነት?››

‹‹አዎ የኔ ማር››

‹‹ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል›› አለች ካሮል አን።

‹‹መቼ ነው ያገቱሽ?››

‹‹ከሁለት ሰዓት በፊት››

‹‹አሁን የት ነው ያለሽው?››

‹‹ከኛ ቤት ብዙም አይርቅም.›› ብላ ሳትጨርስ የድንጋጤ ጩኸት
አሰማች፡፡
👍212
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ዲመካና ቱርሚ ሁለቱም የሐመር አውራጃ የገጠር ከተሞች ናቸው" ለቆላማው የሐመር ክፍል ቱርሚ፣ ለደጋማው ደግሞ ዲመካ
አማካዮች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ደረቅና ቁጥቋጦ የበዛበት መሬት ያላቸው ናቸው። ቱርሚ መንገድ ዳር ያለ ከተማ ሲሆን፣ ከዲመካ ይልቅ ሁለት ትናንሽ ምግብ ቤቶች፣ ወደ አምስት የሚደርሱ ሻይና ቂጣ
መሸጫ ቤቶች፣ ሁለት በመጠን ከፍ ያሉና ትናንሽ ሳሙና፣ ባትሪ ድንጋይ፣ ክብሪት...የሚሸጥባቸው መንገድ ላይ የሚዘረጉ ሱቆች አሉ። በተለይም በገበያ ቀን ከተማዋ ደመቅዐመቅ ብላ ትታያለች
ገበያ ውስጥ ለመጠጥ ቦርዴና የአበሻ አረቄ፣ ግልድም የሚሆን ከጥጥ
ተሠርቶ ከኮንሶ በነጋዴዎች የሚመጣ ሳዳጎራ፣ ጨሌና አንባር፣በቆሎና ማሽላ ዓይነተኛ ሸቀጦች ናቸው" ቱርሚ፣ በከብት እርባታና
በቁፋሮ ምርት ለሚተዳደረው የሐመር ሕዝብ ድል ያለች ከተማ፣
ታምሮና ተውቦ የሚታዩባት፣ ጐረምሳና ሴቱ አብሮ መሸታ ገብቶ የሚደባበስባት፣ የተጣላ የሚታረቅባት፣ ሽማግሎች ተሰባስበው
የሚመክሩባት፣ ብርቅዬ ከተማ ናት ለሐመሮች።

ዲመካ ግን፣ ከዋናው መንገድ ወጣ ብላ፣ ሰቀላ ቤቶች በአራት ማዕዘን ተሰትረው የሚታዩባት ከተማ ናት። በየሰቀላ ቤቶች ፊት ለፊትና በስተኋላ የግራር፣ የብርብራ.ዛፍ ያለ ሲሆን ከከተማው ግርጌ፣ ከወንዙ ጥግ በሚስዮናውያኑ የተተከለ በፀሐይ ብርሃን በሚንቀሳቀስ መስኖ የለማ የፍራፍሬ፣ የበቆሎና ሌሎችም ወቅታዊ
አዝርእቶች የሚታይ ሲሆን፣ ከጎን በኩልም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንፃና ጋራዡ፣ ዲመካን አንድ ዓይና ከመሆን አድኗታል"የገበያ ቀን፣ በየሰቀላ ቤቱ ጠጅ የሚሸጥ ሲሆን፣ ምግብ ቤት ግን ከናካቴው የለም" ደግነቱ፣ እንግዳ ብርቅ በመሆኑ ጋባዡ ብዙ ስለሆነ
እግር የጣለው ሰው ሕቅ ብሎ ሲያዝን አይሰማም" በተረፈ ገበያ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ከቱርሚ ጋር ተመሳሳይ ነው ሁለቱንም ከተሞች ቡስካ ስር ካሉት ላላና ሻንቆ እስከ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዳ
መንደር ድረስ የሚያገናኛቸው የማኅበረሰብ ሕይወት የሆነው የከስኪ ወንዝ ነው ከብቱ፣ ፍየሉ፣ በጉ፣ ሰው፣ አዕዋፍ...ሁሉም ጥሙን
ይቈርጥበታል።

ካርለትና ከሎ ሆራ ከዲመካ ወጣ ብላ ከምትገኘው የሻንዛ መንደር መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራት አለፋቸው የክልሉ ኗሪዎ
ከሎ ሆራን እንዳዩ፣ «የሆራ ሻላ ልጅ» እያሉ፣ ሰላምታና ስጦታ አጐረፉለት ቆዳ ለባሽ እናቱና እኅቶቹም ደረታቸውን በመድቃት
የደስታ እንባ እያነቡ አስተናገዱት።

ካርለት፣ በቆይታዋ የተለያዩ ልምዶችን አገኘች። ከዘመናዊ ሕይወቷ እንደ ባንዲራ ወርዳለችI ይህን አጋጣሚዋን ግን በግላዊ
ትርጕሟ እንደ መጥፎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰዷ የሚሰማት ስሜት የደስታ ስሜት ነው። ይህ ደግ
ማኅበረሰቡን ለመቅረብና ለመርዳት እንድትጣጣር አድርጓታል ስለዚህ፣ ካርለት የከሎ ሆራን እናትና እኅቶች፣ የአካባቢው ሴቶችና ወንዶች ለመቅረብ የቋንቋ ትምህርቷን በማጠናከር ልትግባባ ሞክራለች ቢሆንም ግን፣ በወደፊቱ ጥናቷ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት
እየሆነባት የመጣው በሴቶች ላይ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖ እንደ ጋለ ብረት ምጣድ አላስጠጋሽ አላት"¸

በማኅበረሰቡ፣ ሴት ሣቂታ ወንድ ኰስታራ ነው" ሴት በልጃገረድነቷ የአባቷ፣ ባል ካአገባች ደግሞ የባሏ ጥገኛ ናት" ስለዚህ
በልባዊ ኵራት የተሞሉት የሐመር ወንዶች ካርለት ሴት ሆና እንዴት ባሏን ወይንም አባቷን ጥላ ወደ እነሱ እንደ መጣች በጣም
አስገርሟቸዋል" ሽማግሎች እንዲያውም፣ «ይእ! እሷ ምን ታድርግ? አባቷ ወይም ባሏ፣ ብቻዋን መልቀቃቸው ከቶ ምን ያሉ ነፈዞች ቢሆኑ ነው» ብለው አውግዘዋል"
ስለሆነም፣ ካርለት የጥናት ኮተቷን ይዛ ለጥያቄ ቀረብ ባለቻቸው ቍጥር የደስታ ገጽ ስለማታይባቸው ለተወሰነ ቀን ግራ ተጋብታ
ነበር" አንድ ቀን ግን ወንዶች ሊያደርጉት ባሰቡት ስብሰባ ለመካፈል ሄደች። ገላጣ ስፍራ ላይ ካለ ትልቅ ግራር ጥላ ሥር፣ የሻንቆ መንደር
ሽማግሌ፣ አባወራ፣ ጐረምሶች ተሰብስበዋል" ከወገብ በላይ ራቁት
ሆነው፣ ቆዳቸው የተሸበሸበ፣ ጸጕራቸው ገለል ብሎ ሽበት ጣል
ጣል ያደረገበት አዛውንት በሁለት ወገን ጦር የተሰካበት ብትር ይዘው፣ መሬቱን ወጋ ነቀል እያደረጉ ወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ
ንግግር ሲያደርጉ ሁሉም ጸጥ ብሎ በተመስጦ ሲያዳምጥI ካርለት
ስብሰባውን ለመካፈል ጓጕታ ቀስ እያለች ተጠግታ ልትቀመጥ ስትል
ሁሉም ዘወር ብለው አይዋትና በስብሰባው መካፈል እንደማትችል
ነገሯት"

ካርለት፣ ወንዶችን ለመቅረብ አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን፣ ሴቶችም
ምሥጢራቸውን ሊገልጹላት ባለመቻላቸው ግራ ተጋብታ ቅር ተሰኘች" በተለይ ደግሞ፣ ለመሳተፍ ጓጕታለት በነበረው የወንዶች
ስብሰባ ልትካፈል ባለመቻሏ ጥልቅ ኀዘን ከመስማት አልፎ ለወደፊቱ አደርገዋለሁ ብላ የደከመችለት ጥናት ሊሳካ አይችልም ብላ ሠጋች"
ስለዚህ፣ ዓይኗ ቁንዶ በርበሬ መስሎ እስኪቀላ ድረስ እያለቀሰች፣ «ከሎ! ለምን ወንዶች ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ
አይሆኑም? ለምንስ በስብሰባቸው እንዳልካፈል ይከለክሉኛል? በዚህ
ዓይነት ጥናቴንስ እንዴት ማድረግ እችላለሁ? » ብላ ጠየቀችው።

«በሐመር ማኅበረሰብ ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል የተፈጠረች ጸጋ ናት። ለወንዶች ትንባሆ ታዘጋጃለች ልጃገረድ
ከሆነችም ታርሳለች፤ የከብቶችን በረት ታጸዳለች ሕፃናትን ትንከባከባለች ምግብ ታበስላለች.እንጂ ከወንድ ጎን ተቀምጣ ስለ
ማኅበረሰቡ ችግር በመነጋገርና በመምከር መፍትሔ መፈለግና ጦርነት
መግጠም አትችልም።

«ካርለት፣ አንቺ ወንድ ብትሆኚ ኖሮ ምንም ችግር ላያጋጥምሽ ይችል ነበር" ሆኖም ግን አንቺ ሴት ነሽ። ለሐመር ሴቶች የወጣው
ደንብ ማንኛዋንም ሴት ያጠቃልላል፣ ብለው ስለሚያምኑ በስብሰባቸው እንድትካፈይ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን፣ የምትጠይ
ቂያቸውንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም" እኔም
ይህ ችግርሽ እጀ ሰባራ ሊያደርግሽ እንደሚችል እየተሰማኝ መጥቷል" ምናልባትም ችግሩ ግልጽ ከሆነልሽ የግልሽን መፍትሔ
ውሰጂ» አላት"

ካርለት ፈጽሞ ያልጠበቀችውን መልስ በማግኘቷ በባህላዊ
ልዩነቱ በጣም ተሸማቀቀች በአሁኑ የጥናት አያያዟ በእርግጥ ለመቀጠል አለመቻሏ ቁልጭ ብሎ ታያት በአእምሮዋ አውጥታ
አውርዳ የወሰነችው ውሳኔ፣ እስከ አሁን ያደረገችው ጥረትና ጒዞ ጥሩ የድንጋይ ምት እንዳረፈበት መስተዋት ከሽ ብሎ ሊሰበር
የተቃረበ መስሎ ታያት። ያ ችሎታዋንና ጥንካሬዋን የሚያስመሰክረው፣ ማንነቷን የሚያረጋግጠው፣ ብቃቷን ማያዋ መስተዋት
እንዲሰበር ግን ጭራሽ አትፈቅድም። በዚህም ተባለ በዚያ የጀመረችውን ከግቡ ለማድረስ ሕሊናዋ እሷን ወደፊት መግፋት
አለበት" ሰዎች ከጎሪላና ከእፉኝት፣ ከአንበሳና ከተኩላ ጋር በሐሩርና
በረዶ መኖር መቻላቸውን አስመስክረዋል" እሷም ዓላማዋን ከግቡ
ለማድረስ ተጣጣፊና ጠንካራ ለመሆን ከራሷ ጋር ተማማላች" ግን ምን መላ ትምታ? ለተወሰነ ቀን ካለ ዕረፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ስታስብ ከቆየች በኋላ ምንም እንኳ የችግር ኮተቱን ዓይኗን ጨፍና አላይም
ብትልም፣ የሚያጋጥማት ሥቃይ ከባድ መሆኑን አውቃ ቀበቶዋን አጠበቀች

ከዚያም፣ ያሰበችውን መላ ለመጀመር ያስችላት ዘንድ ባል አለማግባቷን የሚገልጽ ወሬ ለአገኘችው ሁሉ አወራች" ወሬው ተዛምቶ በየመንደሩ መዳረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ጐረምሶች፣ ወጣት
ባለትዳር ወንዶች፣ ያላገቡና ባለ እጮኛ ልጃገረዶች ምሽትን ተገን አድርገው ወደሚቦርቁበት የምሽት ጭፈራ «ኢቫንጋዲ» ለመካፈል ነኢማ ከምትባለው የከሎ ሆራ እኀት ጋር ስትሄድ ምንም ተቃውሞ ሳይደርስባት ቀረ።
👍271
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

መጀመሪያ የደራረቀ እንጨትና ግንድ ቀጥላ ለጉልቻ የሚሆን ሦስት ድንጋይ አቅርባ እሳት አቀጣጠለችና ውሃ የያዘውን
ቶፋ ወደ አንደ በኩል ዘንበል አድርጋ ጣደችው ከዚያ በለሻ እንዲበላ ስታቀብለው “አንችስ ብይ እንጂ ተወተቱም ጠጭ…"
አላት ጭብጦውን እያላመጠ።

ይእ! ይልቅ አታስቀምጠው ጠጣው። የኔ በኋላ ይደርሳል“ ብላ በጨንዋዛ ቅጠል የተቋጠረውን ሽፈሮ ቡና ፈታ በሚቆለቆሰው
እሳት በመቅጃው የቅል ጭልፋ ዙሪያ ትጉልጉል የሚለውን እንፋሉት እንዳያቃጥላት ተጠንቅቃ የቡና ገለባውን ጨመረች:

ሰማዩ ላይ እንደ ጨሌና ዛጎል ከዋክብት ሆጨጭ ብለዋል። በስተ ሰሜን በኩል ደግሞ ብናኝ ዳመና አቅፎ የያቸው ከዋክብት
ብልጭ ድርግም... ይላሉ: የምሽት በራሪዎች የሌሊት ወፍ ጉጉት የማታ ተረኞች ሆነው ወዲህ ወዲያ ይበራሉ: ጅብ ይጮሃል
አንበሳው ያገሳል... ጦጣና ዝንጀሮ ፀጥ ብለዋል: ጉሬዛዎች ግን እንደ ዶሮ ሰዓት እየጠበቁ “ጉርር ጉርር. ጉርርርር..." እየተቀባበሉ ያውካኩና ጸጥ እረጭ ይላሉ።

ዳራና ደልቲ በሚነደው የሳት ወላፈን እሷ አንድ ጉልበቷን
አጥፋ መሬት ላይ አጋድማ፧ ሌላውን ጉልበቷን አጥፋ አቁማ አልፎ አልፎ እንጨቱን ቆስቆስ እያደረገች አይኖችዋን ጨለማው ውስጥ ተክላለች።

ደልቲ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ የአባቱን ከዋክብት እንደ እሳት እየተንቦገቦጉ ቁልቁል ተወርውረው የሚጠፉትን “ሚቲዎሮች”
እያየ ያስባል።

በሁለቱ መካከል ንግግር የለም:: ፀጥታ ሆኗል: በሐመር ባህል የቡና ሥነሥርዓት እርጋታና ፀጥታ የሰፈነበት ነው:: ህፃናት
እንኳን ይህን ስለሚያውቁ  ቡረቃቸውን ገተው ያደፍጣሉ። ሴቷ ወንዱ ሽማግሌው ከራሳቸው
ጋር የሚነጋገሩበት ራሳቸውን የሚመዝኑበት አደብ የሚገዙበት በጎና እኩይ ተግባራቸውን የሚፈትሹበት... ነው የቡና ሥነ ሥርዓት ለሐመሮችሽማግሌ
ትናንትን የሚያደንቅበት ዛሬን የሚያመሰግንበት ነገን በተስፋ የሚጠባበቅበት ግለሰቡ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሰላምን፡ ጥጋብን የሚመኝበት የአባት የአያት ደንብ ወደ ልጅ የሚሸጋገርበት ጠላትና ወዳጅ ጠንቅቆ የሚታወቅበት ምላስ አጥራ ህሊና ገዝፎ መግባባት የሚመጣበት ነው የቡና ሥነ ሥርዓት። ይህ የቡና ሥነሥርዓት ለህፃን ለወጣት ለአዋቂ ለሽማግሌ ለእንግዳ ክፍት ነው። ያሻው ሁሉ ይሳተፋል እድሜና ደረጃውን ጠብቆ ይዳረሳል። የሐመር በር መዝጊያ የለውም። የሐመር ሕይወት ጓዳ የለውም፡ የሐመር ማህበረሰብ “ከሌላው ኪስ ወስደህ የኔን ኪስ ሙላ በሚል ስግብግብነት ምኞት ላይ አልተመሰረተም።

ደስታ ችግር ጦርነት... የጋራ ነው: የአንዱ ምርኩዝ ሌላው ነው: ግለሰብ ህብረተሰብን አይረሳም። ህብረተሰቡም ግለሰቡን
አይጥልም ያሳድገዋል ሃብት ያካፍለዋል ይድረዋል ለጀግንነቱም
ያሞግሰዋል...

ስሰዚህ ደልቲና ዳራ ምንም እንኳ ጫካ መሃል ብቻቸውን ቢሆኑም ህሊናቸውና አካላቸው ግን በባህላቸው ደንብና ሥርዓት
የተገነባ ነው: ፀጥታው ተጠብቆ ዝምታው ሰፍኖ እሱም ሆነ እሷ ትናንትን ቃኝተው ዛሬን አስታውሰው ነገን ሲያልሙ በሐሳብ
ተውጠው ቆዩ።

ከዚያ ዳራ ሾርቃውን ጠረግ ጠረግ አረገችና የቅል ማንኪያውን አንስታ ቶፋው ውስጥ ጨምራ ከቡናው ሁለቴ ቀድታ ሰጠችው ደልቲ ቡናውን ለማብረድ ግራና ቀኝ ጎለል አደረገና ፉት ብሎ “ፕስስ ፕስስ.." እያለ ወደ ምስራቅ ምዕራብና ወደ መሬት የሸፈሮ ቡናውን አርከፍክፎ- “የአባቴ ሰማይ ዝናብ ይጣል በሽታዎች ከሐመር ምድር ይጥፉ፤ ከብቶች  ፍየሎች በጎች
አያገሱ  በሰላም ይግቡ ይውጡ..." ብሎ መረቀና ወደ  ዳራ ዞሮ ቡናውን ፉት ብሎ “ፕስስ..” አለና ሽፈሮ ቡናውን አርከፈከፈባት፡

ዳራ ደንገጥም አፈርም ሳትል አይኗን ከወረወረችበት
ሳትመልስ በሃሣብ እንደሰመጠች
“..ተባረኪ... ዘርሽን ያብዛው የአባትሽ የሐመር ምድር የልጆችሽ መቦረቂያ ይሁን... የባልሽ ጥገት ይብዛ" ብሎ መረቃትና ቡናውን በፀጥታ መጠጣት ጀመረ።

ሰረቅ አድርጋ አየችው: በውስጧ እንደ ህፃን የሚላወሰው እሱ ነው ከፊት ለፊቷም የተቀመጠው እሱ ነው፡ ፍቅር የሰጣት የመረቃት እሱ ነው። ስለሱ ያላትን ስሜት አሁንም በእርግጠኝነት አጤነች ስለ ጀግናው የሚባለውንም አስታወሰች።

ጥጃና ፍየል ስትጠብቅ ወንዶች የድሜ ጓደኞችዋ እነሱ ጠመንጃ እያሉ እንጨት ቆርጠው እየተሸከሙ እንደ ጥይት ዳውላ እየወረወሩ ይሄ ከብት የኔ ያ እርሻ የኔ... እየተባባሉ ሲጫወቱ። እሷም የእድሜ እኩዮችዋ ከሆኑት ልጃገረዶች ጋር ከከስኬ ወንዝ
የጭሮሽ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየለቀሙ, ልጅ እያቀፉ... ሲጫወቱ
ይቆዩና ጫካው መሃል ሚስትና ባል ሲባባሉ ቆይተው ዘፈን ሲጀምሩ
ስለ ሐመር ተራራ ስለ  ሐመር ሰማይና ምድር... ስለከብቶች ሲያዜሙ ይቆዩና የሐመር ጀግኖችን ህፃናቱ ሲያወድሱ የደልቲ ስም የደልቲ ጀግንነት... ይነሳል። ወንዶች ህፃናት “እኔ ነኝ እሱ እኔ ነኝ
ሲባባሉ እሷም ከሌሎች የእድሜ ጓደኞችዋ ጋር “ደልቲን የሆነውን ወንድ እኔ ነኝ የማገባው ! እኔ ነኝ የማገባው" ሲባባሉ አንዳንዴ ሁለት አንዳንዴ ሦስት እየሆኑ ሲያገቡት የነበረው የልጅነት ዘመኗ
ታወሳት። እንዲህ ዳሌዋ ሰፍቶ ጡቶችዋ አጎጥጉጠው ሰውነቷ
አምሮ ባለበት የቡረቃ ዘመኗ ያ ስም አብሯት አደገ:: የዚያ ጀግና መግነጢሳዊ የፍቅር ሃይል በውስጧ እየተገለባበጠ  ሲያስጨንቃት ኖረ።

ገበያ ስታየው ትንፋሽዋ ቁርጥ ያለባት ሲመስላት  ስሙ ሲነሳ እንደ አውሬ  ስትደነብር  ፍትወት ሲያስቸግራት ከልቧ
አውጥታ ጉያዋ ውስጥ በሰመመን ስታስገባው፤ በፍቅሩ ወዲያ ወዲህ
ስትንገላታ ኖረች: ነገ ነገን ሲተካ የሷ አምሮትም ከቀን ወደ ቀን ሲጨምር ከስኬ ወንዝ አሸዋ ጭራ ጭሮሽ ውሃ ስትቀዳ ያ በውስጧ
አብሯት ያደገው ጀግና ድንገት ሽቅብ ወደ ቡስካ ተራራ ሲወጣ አየችው ደነገጠች! ግራ ገባት: “አያ ደልቲ! እሱ ኮ ነው…..የኔው.." ብላ ቀባጠረች። ጓደኞችዋ ሳቁባት አላየቻቸውም።
አልሰማቻቸውም እሱም የለም: ጫካው ሰወረው። እሷ ግን ታየዋለች።አካሉ ቢሄድ እሱ ልቧ አለ፡ አወጣችው አየችው ወደደችው! አቀፈችው...

ይእ!  እሰይ እሱንም ከውስጤ ያለውንም አየሁት..." ቀና ብላ ፀሐይን ሰማዩን... ቦርጆን አመሰገነች።

“እይ! እሽ ምን ልሁን! እሽ ምን ላርገው.." ጓደኞቿ እንደገና ሳቁባት። ጆሮዋ ግን አይሰማም አይኗ አያይም... ሁሉም ጀግናዋን ሊዳብሱ ሄደዋል። ውስጧ ያለው የፍቅር ሃይል ለፍንዳታ ተዘጋጀ ተቀባበለ። ሃይሉ ናጣት ወዘወዛት, አሻት... አዞራት አሽከረከራት... ዛፍ ጥላ ስር በደመ ነፍስ ሄዳ አረፈች መረጋጋት ስትጀምር ቡስካ ተራራን ቀና ብላ አየችው: ነይ" አላት። ወሰነች
ለመሄድ ጀግናዋን ጫካ መሃል ለመፈለግ  ቆረጠች። ሄደች “አቅጣጫ ያላት ጀልባ ንፋሱም ይረዳታል ይባል የለ አገኘችው::

ደልቲ ዳራ የቀዳችለትን ሸፈሮ ቡና አራት ጊዜ እየተቀበለ ጠጣና  ሾርቃውን ከፊት ለፊቱ አስቀመጠው: በሐመር ደንብ የጠጡበትን እቃ ማቀበል ጨምሩልኝ ሲሆን ማስቀመጥ ግን በቃኝ ማለት ነው:: ዳራ ለራሷ መጠጣት ጀመረች። በሐመር ባሀል ወንድ በሐመር ባሀል ወንድ
አንበሳ ነው ሴቷ አንበሳ መጀመሪያ ግዳይ ትጥላለች: ወንዱ ጎፈር
አንበሳ ግን ቀድሞ ይባርካል ይበላል፤ ይጠግባል፤ ተንጎማሉ ሄዶ
ለመከታነቱ ተዘጋጅቶ ይጋደማል። ሴቷ አንበሳና ደባሎችዋ የጎፈር
አንበሳው ግሣት ደህንነታቸው ህልውናቸው ነው... እሱ ሲጠግብ
እሱ ሲጠነክር ይረካሉ። ዳራም አንበሳዋ ከጠገበ በኋላ ጭብጦዋን በላች ቡናዋን ጠጣች ከዚያ እቃውን ሸካከፈች።
👍37👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ስድስት



#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ከሀያ ቀን በኃላ ፤ስለእሷ ማሰብ ካቆምኩ በኃላ ...ኦልሞስት ከረሳኋት በኃላ  ድንገት ተከሰተች። እለቱ ቅዳሜ ነው ፤ቅዳሜ ለአብዛኛው ሰራተኛ የደመቀች ቀን ነች። ፈገግታ የሚፈስባት ..ሙዚቃ የሚንቆረቆርባት..የዳንስ ጥበብ  የሚጠበብባት ወሲብ የሚወሰብባት በስራ ሳይሆን በመዝናናት ብዛት የሚደከምባት...በወጪ ብዛት ኪስ የሚታጠብባት አዲስ ፍቅረኛ የሚጠባበስባት ክንድ ላይ ያለ ፍቅረኛ ድንገት ሾልኮ የሚሰወርበት… የታሪክ መፃፊያ ቀን ነች።
ከቅዳሜው የተትረፈረፈው ወደ እሁድ ይዘዋወራል።

ያው ከላይ በገለፅኩላችሁ ምክንያት ለእኛ ለአስተናጋጆች ዋና የስራ ቀናችን ነው።እና በዛው ልክ ወከባ አለ፡፡ ከአንዱ ወደሌላው  ጠረጴዛ መስፈንጠር ..ከአንዱ ተስተናጋጅ ትዕዛዝ ወደሌላው...ብቻ ከባድ ግን ደግሞ ወሳኝ ቀን ነች።ከባድ ያልኩት የስራውን ጫና ፤ የተስተናጋጆቹ ወከባ፤ የትዕዛዝ መደበላለቅ፤ የሰከራሙ ትንኮሳ፤የሂሳብ መጉደል የመሳሰሉትን ጫና አስቤ ነው። ወሳኝ ያልኩት ሳምንቱን ሙሉ የማናገኘውን ቲፕ እና መሠል ተጨማሪ ገቢ የምናገኝበት ቀን ስለሆነ ነው።ዛሬም እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት እንደወትሮ የተለመደ ስራዬን እየሠራሁ ሳለ ጋሼ አስጠረኝ።

‹‹አቤት ጋሼ፡፡››

‹‹ወንበርህን ለሌሎቹ አስረክብና    ቪ.አይ.ፒ ቁጥር 4 ያሉትን እንግዶች አስተናግድ"

ፈጠን ብዬ ‹‹እሺ ጋሼ "አልኩና በደቂቃ ውስጥ ወንበሬን ለጓደኞቼ አስረክቤ ወደታዘዝኩት ቦታ ሄድኩ ፡፡  በእኛ ሆቴል ስድስት የቪ.አይ.ፒ ቦታዎች አሉ።ልክ እንደትያትር ቤት በሆቴሉ ሰፊ አዳራሽ አራቱ ኮርነሮች ላይ  ከፍ ብሎ የተገነብ ሲሆን ወደ እዛ የሚወጣው ከሆቴሉ ሳይገባ በውጭ በኩል ባለ እስቴር ነው።የሁሉም መግቢያ ለየብቻ ሲሆን ቀጥታ በጓሮ በር ገብቶ መልሶ በጎሮ መውጣት ያስችላል..የቤቱ ዙሪያ በጠንካራ ኮንክሪት ግድግዳ የተገነባ ሲሆን አንድ ጎን ማለት ወደሆቴሉ ያለው ጥይት በማይበሳው  መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ነው ..፡፡መስታወቱ እታች ሆቴል ያለውን እንቅስቃሴ ጭፈራውንና እያንዳንድን እድምተኛ ቁልጭ አድርጎ ሲያሳይ ከሆቴል ወደላይ ግን ድፍን ጥቁር መስታወት ግድግዳ ብቻ ነው የሚታየው።ክፍሉ በጣም ዘመናዊ፤ ምቹ ሶፋዋች እና እንደ አማራጭ የባለጌ ወንበሮች ከምቹ ባልኮኒ ጋር ተገጥሞላቸዋል
መብራቶቹም በምርጫ የሚቀያየሩ  ተደርገው የተሠሩ ሲሆን ሙዚቃን በተመለከተ ቀጥታ እታች የሚለቀቀው በጥራት የሚመጣበት ወይም ያንን ዘግቶ እዛው የራሳቸውን የተመረጠ ሙዚቃ የሚጠቀሙበት አማራጭ አለው። እዛ ክፍል …ተጠቃሚዎች ወይ በራፍ ላይ  ቆሞ ወይ ውስጥ ተቀምጧ የሚያስተናግዳቸው  የብቻቸው አስተናጋጅ ይመደብላቸዋል። የተለየ ፕራይቬሲ ከፈለጉ ደግሞ  አስተናጋጅ ከክፍሉ ውጭ  ይሆንና ልክ መጥሪያውን ተጭነው ከመድገማቸው በፊት ተስፈንጥሮ በመግባት ትዛዛቸውን ተቀብሎ የሚፈልጉትን ያመጣላቸዋል።

ይህን  ክፍል የሚጠቀሙት ለደህንነታቸው ወይም ለስማቸው አብዝተው የሚጨነቁ ትላልቅ የቢዝነስ ሰዎች፤ዝነኞችና እና ባለስልጣኖች ናቸው። ቢሆንም ለሁሉም አገልግሎቶች ከመደበኛው  ከአራት እጥፍ በላይ ያስከፋላል ።አስተናጋጅም ብዙን ጊዜ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛል።እናም ሁሉም እዚህ ቦታ ሲመደብ በደስታና  በፈንጠዝያ ነው የሚቀበለው።

ደረስኩ ..በራፋን እንደመቆርቆር አደረኩና ገፋ አድርጌ ስከፍት ደነገጥኩ...፡፡እንደጠበቅኩት ቀለል ያሉ ሰዎች አይደሉም የገጠሙኝ። እርግጥ ሴቲቷ ጀርባዎን ሰጥታኝ የተቀመጠች በመሆኑ ፊቷ አይታየኝም፡፡ግን ዝንጥ ብላለች።ደማቅ ሰማያዊ ረጅም ቀሚስ፤ መካከለኛ ታኮ ካለው ሰማያዊ ጫማ ጋር አስማምታ ለብሳለች። ፀጉሯ የእውነት የእሷ ከሆነ ውብ መሆኑን  በቀላሉ መናገር ይቻላል ፤ወገቧ ላይ ተበትኖ  ይታያል .፡፡

.ሰውዬው ከእኔ ፊት ለፊት ናቸው ያሉት ፤ትልቅ ሰው ናቸው።ቆፍጣና ፤ኮስታራና አስፈሪ  ..ፀጉራቸው ገብስማ ነው..፡፡ሙሉ ዠንጉርጉር የመከላከያ ልብስ ለብሰዋል።ትከሻቸው ላይ አራት ኮከብ ወደጎን ተደርድሯል።መቼስ በዚህ አለባበስ የሆነ ስብሰባ ላይ ወይም ወሳኝ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ አምሽተው ከጊዜ መጣበብ የተነሳ ወደቤታቸው ጎራ ብለው ለመቀየር ሳይችሉ ቀጥታ መተው ነው እንጂ ይሄ የክብር ልብስ ቦታው አይመስለኝም"በውስጤ አጉረመረምኩ ...

እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደፊት የተወሰነ እርምጃ ጠጋ አልኩና ‹‹ጌታዬ የጎደለ ነገር አለ?››ብዬ ጠየቅኳቸው፡

"ሚበላ ምን አላችሁ?"ጎርናና እና ሻካራ ድምፅ...እኚ ጄኔራልማ እቤታቸው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን አስቀምጠው ነው ከዚህች ኮረዳ ጋር የሚማግጡት› በሆዴ አማኋቸው፡፡እስቲ አሁን ምን አውቄ ነው ለሰከንድ ያየኋቸውን ሰዎዬ ወደማማትና መፈረጅ የገባሁት ብዬ እራሴን ወቀስኩ።

"ጌታዬ ሜኑ ላምጣ"

"አይ አንድ ክትፎ አምጣልን...ክትፎቸው አሪፍ ነው" አለች ሴቲቱ...አሁንም  በደበዘዘው ብርሀን ከእኔ በተቃራኒ የዞረ ፊቷ እየታየኝ አይደለም ።ድምፆ ግን የሚነዝር ኃይል ነበረው። የሚያደነዝዝ...በምን ምክንያት ነዘረኝ...?ስለምንስ ውስጤ ተናጠ... ?

"በቃ ጎረምሳው እንዳለችህ አድርግ"አሉኝ ጄኔራሉ ..ንግግራቸው  ብቻውን ምሽግ የሚንድ አይነት ነው፤ተስፈንጥሬ ወጣሁ።በተቻለ ፍጥነት በልዩ ሁኔታ ክትፎውን አሰርቼ ይዤ ተመለስኩ።

"የእጅ ውሀ እዚሁ ልታመጣልን ትችላለህ?"ሴቲቱ ነች ጠያቂዋ፡

"ይቻላል እመቤቴ.. አሁን አመጣለሁ"አልኩና በደቂቃ ውስጥ የእጅ ውሀ ይዤ መጣሁ። ተንደርድሬ ሄጄ በክብር ጎንበስ ብዬ ልክ እማማ ኢትዬጰያን እያስታጠብኩ እንደሆነ ኩራት እየተሠማኝ ጄኔራሉን አስታጠብኩና ወደ ሴቲቱ ዞር ስል ፊት ለፊት አይን ለአይን ግጥም ...ምን ተአምር ነው?...ልደሰት ወይስ ልዘን? ላልቅስ ወይስ ልሳቅ ?

ጎንበስ ብዬ እያስታጠብኳት ቢሆንም ግን በደመነፍስ ነው። ድምፅ አውጥቼ ላወራት አልቻልኩም  ? አውቅሻለሁ... ጋብዘሺኛል.. እርቃን ገላሽን በዓይኖቼ አይቻለሁ...በጣቶቼ ዳብሼሻለሁ ልላት ፈፅሞ አልቻልኩም።

‹‹አይ የጎረምሳ ነገር....ውሀውን ደፍተህ ጨረስከው እኮ"አሉኝ ጀኔራሉ እንደመሳቅ ብለው። ለካ እሷ መታጠብን ጨርሳ እጇን ብትሰበስብም እኔ ግን አይኔን አይኖቾ ላይ እንደተከልኩ ፈዝዤ ውሀውን ማንጮርጮሬን ቀጥያለሁ...በጄኔራሉ ንግግር ባነንኩና ተስፈንጥሬ ከስራቸው ወደበሩ መራመድ ጀመርኩ።

"በራፋ አካባቢ ነኝ፤ ስትፈልጉኝ መጥሪያውን ተጫኑ ››አልኩና  ክፍሉን ዘግቼላቸው  ወጣሁ።የእጅ ማስታጠቢያውን አስቀምጬ በረንዳው ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተሸከረከርኩ መብሰልሰል ጀመርኩ፡፡

"ፍፅም እንደማታውቀኝ እኮ ነው የሆነችው...ምን አይነቷ ባለጌ ነች?" ከንፈሬን በብስጭት ነከስኩ ..‹‹አንድ ለሊትም ቢሆን እኮ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር  አልነበረንም ያሳለፍነው..? ነው ወይስ ውሽማዋን ፈርታ ነው?››

"ብትፈራ ይፈረድባታል .. ጄኔራሉ እኮ እንኳን በጎናቸው የሸጎጡት ሽጉጥ ተጨምሮበት ይቅርና እንዲሁ ያን ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ሲያደርጉት ያርበደብዳሉ...እኔስ ሀይ ሰላም ነሽ የሚል አጭር ሰላምታ እንኳን ለመስጠት ድፍረት ያጣሁት እሳቸውን ከመፍራት አይደል?።ግን ውሽማዎ ናቸው ነው ያልኳችሁ ..?ያንን በምን አወቅኩ ?አልነገሩኝ...ሲሳሳሙ እንኳን አላየሁም"

የመጥሪያው መንጣረር ከሀሳቤ አናጠበኝ። ፈጥኜ ወደውስጥ ገባሁና መሽቆጥቆጤን ሳልቀንስ "አቤት ጌታዬ"አልኩኝ፡፡
👍56👎21👏1
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ካርለት ድንኳናን ዘግታ ስትፅፍ የሰው ኮቴ የሰማች መሰላትና ጆሮዋን አቁማ አዳመጠች

"ካርለት?"

"የስ" ብላ ቶሎ በማስተካከል "ዬ! አለች - እንደ ሐመር ልጃገረዶችı ካርለት የጠራት ሰው ማን እንደሆነ አውቃዋለች
ደልቲ ነው ቀብራራው ጀግና የድንኳኗን ዚፕ ከፍታ ፈገግ ብላ አየችው" ሰውነቱ በአኖ (ከኦሞ ወንዝ ዳር በመጣ የተላቆጠ አፈር)
ተዥጎርጉሯል፥ ጴሮው (መሃል አናቱ ላይ ባለው ጌጥ) ላይ የተሰካው
የቀጭኔ ላባ በንፋስ ይርገበገባል ... እሱ ግን ፊቱን ዞሮ በርኮታው
ላይ ቁጭ ብሎ ጥርሱን በልምጭ ይፍቃል"

አንቺ ንብ አደለሽ
ምነው ቀፎሽን ዘጋግተሽ መቀመጥሽ

"ደልቲ ንፋሱ: ልጆችም
እንዳያስቸግሩኝ አለችው
ፈገግ ብላ እያየችው" እሱ ግን መልሷ አልተዋጠለትም ይህች ሰው! ነፋስና ልጅ የምትጠላ ምን ልትወድ ነው እህ! ብሎ ቆሽቱ
እያረረ ሃሣቡን ሳይናገር ከታጠቀው ዝናር አንድ ቀላህ አውጥቶ
ውታፏን ከፈተና በአውራ ጣቱ ጀርባ የትንባሆ ዱቄት ፈሰስ አድርጎ ጎንበስ ብሎ በአፍንጫው ቀዳዶች ሞዠቅ ሞዠቅ አድርጎ ሽቅብ ማገና በዐይኖቹ እንባ ፍጭጭ ብሎ ደጋግሞ ካስነጠሰው በኋላ
ትንባሆውን ለካርለት አቀበላት በሐመር ሴት ልጅ ትንባሆ መሳቧ ነውር የለውም! በፍቅረኞች መካከል ትንባሆ (ሱረት) መሰጣጣት ደግሞ አንዱ የመግባባታቸው ምልክት ነው።

"ሽማግሎች ለዛሬ ከብት ውጋ ብለውኝ ይኸው በሬዬን ይዠ መጣሁ" አላት ካርለት ትንባሆው ካስነጠሳት በኋላ ምክንያቱን የሰማች ቢሆንም ከእሱ አንደበት ለመስማት ብላ።

"ምነው  ምናጠፋህ?" ስትለው  መፋቂያውን አኘክ አኘክ አድርጎ ተፋና ረጋ ብሎ፣

"አንች ሰው ምነው ሥርዓት ቢኖርሽ ሴት በየት አገር ነው
የወንድን ጥፋት የምትጠይቀው?" አላት ደልቲ ካርለት እንዲህ
ስታጠፋ ጎንበስ ብላ እግሯን
እንድትይዝ አድርጎ ጡቷን
እንዳይመታ እየተጠነቀቀ ሁለት ሶስት ቀን በባራዛ አርጩሜ ደህና አድርጎ እየገረፈ ቢገራት ልክ እንደ ስልጡን አህያ ትሰግር እንደነበር አስታውሶ እህ! ሽማግሎች እንዳሉትስ በመታረሚያዋ ጊዜ
ስታጠፉ እኔ እንጂ ሌላ ማን ይታዘንበታል! ብሎ አዝኖ ጢቅ አድርጎ ምራቁን ተፋና ጥርሱን ይፍቅ ገባ።

"ጎይቲ ስታለቅስ ነው የምትውል አይተሃት ታውቃለህ?"አለችው ካርለት በጥያቄዋ ጎርጉራ አንድ አዲስ ነገር ባገኝ ብላ።

"ሰማሁ! እኔን እህቴን ምን የከፋ ችግር መጣባት! አዘነ
ደልቲ።

"ለዚህ ምን መፍትሔ አለው ታዲያ?" ስትል ካርለት ደልቲ
ሰረቅ አድርጎ አይቷት

"ምን መፍትሄ ይኖረዋል  ሽማግሌ ያለውን መቀበል ነው እንጂ።

"ጎይቲ ከከሎ ጋር ከተጋቡ ወዲህ እኮ ሌላ ወንድ አታውቅም "እንደገና ለዓመል ያህል ሰረቅ አድርጎ እንደዘበት አያት የለበሰችው
ቆዳ የፊተኛው ክፍል ጉያዋ ውስጥ ተሸጉጦ: የቀኝ ጭኗ ውስጥ ክፍል እንደ ጥጥ ንጥት ብሎ ታየው"

"ተታናናሽ ወንድሞቹ ጋርስ  አልቀበጠችም?"

"ከሎ ታናሽ ወንድም እኮ የለውም ሁሉም የእሱ ታላላቆች ናቸው"" ስትለው ታናሽ ወንድም እንደሌለው እያወቀ የረሳበት ምክንያት እየገረመው
"ተዘመዱ ወንዶችስ ጋር?" ካርለት የሰጎን ላባ የሰካበት ጴሮ  የተተለተለውን ሳንቃ ደረቱን እንደ አቦ ሸማኔ ቀጠን ያለ ወገቡን አይታ ምራቋን ከምላሷ ስር መጣ ዋጠችና,

"ከማንም ጋር አልቀበጠችም ካለ ከሎ በቀር" አለችው

"እህ!" ሲል ካርለት ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ጆሮዋን መዘዘች እሱ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችውን ጥያቄ

"የምጠጣው ውሃ ትሰጭኝ?" አለ ከኮዳዋ በኩባያ ቀድታ ውሃ
ስትሰጠው ቀና ብሎ አይቷት

"እሱን አንች ጠጭው፤ ለኔ በሾርቃ ስጭኝ" አላት ካርለት ውሃ ለማምጣት ሄደች ደልቲ አረማመዷን÷ ዳሌዋን ወገቧን ከኋላዋ የሚወናወነውን ቆዳዋን ጥርሱን እየፋቀ አየና ምራቁን ጢቅ አድርጎ ተፋና የበረቱ ከብቶች ቀለማቸው የተለያዬ ነው  ቀይ፥
ዳልቻ: ነብርማ: ነጭ የካርለትም ቀለሟ ነጭ መሆኑ ሚስቶቹን
እንደ ከብቶቹ ቀለም ማሳመሩን ሲያስብ የደስታ ስሜት ተሰማው መልሶ ደግሞ የሐመር ልጃገረዶች እንዳለቁ ሁሉ ከዚች አግድም አደግ ጋር ቢቀርብኝስ ብሎ አሰበ አንዴ ግን አገባሻለሁ ብሏል1
ስለዚህ ቃሉን ማጠፍ አልፈለገም ግዴለም አገባታለሁ ድምጿ ግን
ምነው ተዛሬ ነገ ቃናው አይጣፍጥ?  ብልግናዋና ድምጿ እንጂ ሴትነቷስ  እያለ ሲያስብ ካርለት ውሃ በሾርቃ ይዛለት ብቅ አለች

ከርቀት እያያት  ደሞ ደህና ገብሮ የነበረው ሰውነቷ እንደ ምስጥ ንጉስ ተመልሶ ለሰለሰ እያለ ሲያስብ ካርለት ሰው ጠርቷት
ዘወር ስትል የጀርባዋ ሰንበር ታየው  ከሎ ከብት ሲዘል የተገረፈችው"
ደልቲ ትንሽ ፈርጠም ብሎ ሳቅ  አለ ካርለት
አላየችውም ትዝ አለው ስትገረፍ ሰውነቷ የተንቀጠቀጠው ወድቃ
የተዘረረችው

ባለጌ! ብሎ ተቆጨና መልሶ ደግሞ አዘነላት ጀርባዋ ላይ
ያሉት የግርፊያ ሰንበሮች ጥቂት ናቸው ለሐመር ልጃገረድ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበር ሌላው ውበቷ ሲሆን ዳንስ ቦታና ጫካ ውስጥ ወንዱ
እንደ አኮርዲዎን መጫወቻ ሰንበሮቹን በጣቱ እየነካካ የፍቅረኛውን የፍቅር ቅላፄ በማስተካከል የጋራ የፍቅር ስሜት የሚፈጥሩበት ነው
ሴቷና ወንዱ

በልጃገረድ ጀርባ ላይ ባለ የግርፊያ ሰንበር ላይ ሻካራ የእጅ ጣት ጫፎችን ማንቀሳቀስ ትናጋው በፍቅረኛው ምላስ የተነካ ያህል በስሜት ንዝረት መላ ሰውነቱ ያረግዳል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበሯ ጀርባዋ ላይ የበዛ ዘመደ ብዙ' ካነሰ ደግሞ ዘመደ ትንሽ ናት ይባላል ብዙ ጊዜ ልጃገረዶች እርስ በርስ
ስለዚህ ሲጨዋወቱ

ይእ! ይሄ ሁሉ ማን ሲዘል የተገረፍሽው  ነው? ተብላ
የተጠየቀች እንደሆነ እጅዋን አዙራ ጀርባዋን እየዳሰሰች

ይእ! ይሄ የባልዳምቤ
ይሄ የሸረምቤ ይሄ የላሎምቤ …እያለች ትዘረዝራለች ልጃገረዷ በእነዚህ ሁሉ ዘመዶችዋ ስትፎክርና ሳትፈራ ስትገረፍ ያያት ደግሞ ስንትና ስንቱ ወንድ ተመኝቷታል ከስንቱ ጋርስ ቀብጣለች ሊያገባት የፈለገውስ እንዴት እንደሚበዛ መገመቱ አይቸግርም አንድ
የሐመር ወንድ ደግሞ ሌላው የተመኛትን ያፈቀራትን የራሱ አድርጎ ከማግባት የበለጠ ትልቅ
ክብር የለም  በሐመር የጋብቻ አለም።

ካርለት ግን የተገረፈችው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፤ የዛን ቀንም  ግረፉኝ ብላ አልፎከረችም  ስትገረፍም ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ
ስታለቅስ በመጨረሻም ህሊናዋን ስታ ስትወድቅ ምድረ ጎረምሳ ተሳስቆባታል እንጂ ማንም ለፍቅር አልተመኛትም ደልቲ ይህን
አስታውሶ

ወዲህ ወዲያ ስትል እንደ ፍየል ጅራት ስትወናወን እንጂ እሷስ ብትሆን ስንትና ስንት ዘመዶችዋ ከብት ሲዘሉ ብትኖር ኖሮ
የመገረፉ እድል መች ያመልጣት ነበር! እያለ ሲትከነከን ካርለት
አጠገቡ ደርሳ ውሃ የያዘ ሾርቃውን አቀበለችው
እየተጉመጠመጠ ደጋግሞ ተፋና ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ ባይሮ ኢሜ ብሎ
አመሰገናት እግዜር ይስጥልኝ ለማለት

ካርለት ሾርቃውን
ሾርቃውን ልትመልስ ሄደች ያን ጊዜ ደልቲ ደሙ ፈላ  ነደደው ተቀብላ ፈንጠቅ አድርጋ ደፋችውና
ይህች አሳሳች! ብሎ እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ ከመቀመጫው ተነሳ

"ይእ! እህ የታል አያ ደልቲ?  አለ አሁን ውሃ ብሎኝ
ሰጥቸው መጣሁ አላልሽኝ?" አለች ጎይቲ ከካርለት ጋር ወደ ድንኳኗ
እየተጠጉ
"ጎይቲ  አሁን እኮ እዚህ  ቁጭ ብሎ ስናወራ ቆይተን ውሃ ስጭኝ ብሎኝ ሰጥቸው ሾርቃውን መልሼ: አንችን ጠርቸሽ መጣን በዚህ ቅፅበት የት ሄደ?"

"ይእ! እኔን ትጠይቂያለሽ ደሞ ይልቅ አንች ምንሽ  ውስጥ ከተትሽው? አያ ደልቲ መቼም ካለ ነገር እንዲህ ሹልክ ብሎ እንደ
ሌባ አይጠፋም ተቀያየማችሁ?"

"ኧረ በጭራሽ"
👍272
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››
እታች ምድር ቤት ሁሉም ከየክፍሉ እየወጣ እሷ ወደአለችበት የመጀመሪያ ፎቅ የሚያስወጣውን መወጣጫ  ግር ብለው በመምጣት መክበብ ጀመሩ…. እናቷ ከእሷ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤቷ  ልብሳቸውን እንኳን በቅጡ ሳይለብስ በተለመደ ድንጋጤዋ እያለከለከች
‹‹ምን ተፈጠረ ልጄ.?ደግሞ ምን  ሆነሽ ነው?››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ያሳደግሺኝ?››ጮህችባቸው፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ልጄ …እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው.?››

‹‹እኔ ለምንድነው እንደሌላው ሰው ጥሩ መሆን የማልችለው…? እኔ ለምንድነው ስርዓት የሌለኝ? አለሌ የሆንኩበት ምክንያት ምንድነው›?

እናቷ የምትለፈልፈውን  ሌሎች ሰራተኞች እንዳይሰሙ በመጨናነቅ  ይመስላል እቅፍ አረጓትና የሚወራጩ  እጆቾን አንድ ላይ በዛ ግዙፍ ሰውነታቸው በመጭመቅ  አንጠልጥለው ወደመኝታ ቤታቸው አስገቧትና  አልጋዋ  ላይ በማሳረፍ በራፍን ሄደው ዘጉት…እሷም ከንዴቷ እንደመብረድ ብላ ሹክክ ብላ ተነሳችና ሙሉ በሙሉ ወደ አልጋዋ ላይ ወጣች..፡፡ከውስጥ ገባችና ተኛች…፡፡በቃ ደከማት..እናቷም እንደእሷው አደረጉ፡፡ ቀስብላው ወደአልጋው ላይ ወጡና ከጎኗ በመተኛት ክንዳቸውን አንተርሰው ከራሳቸውጋር ልጥፍ አደረጓት፡፡
ሰው ሲከፋው እንዲህ እንደእሷ ሮጦ የሚወሸቅበት ጉያ ወይም ተንተርሶ  የሚተኛበት ክንድ ወይም እቅፋ ውስጥ ገብቶ የውስጥ ቁጣውንና ለቅሷውን የሚያቀዘቅዘዝዝት ምሽግ ካላው እድለኛ ነው። ሲከፍ ወደ  መጠጥ ቤት ሮጦ አልኮል ከመጎንጨት የሚያፈቅሩት ሰው እቅፍ ውስጥ ኩርምትምት ብሎ በማልቀስ የመረጋጋት አማራጭን መጠቀም ውጤታማና ብልሀት የታከለበት ውሳኔ  ነው።በተለይ ያ ክንድ እንዲህ እንደልዩ የእናት ሲሆን የቀጥታም ሆነ የጎንዬሽ ጉዳቱ ለዜሮ የቀረበ ነው።

‹‹የእኔ እርግብ…. አንቺን የሚስተካከል ደግ የለም እኮ…ከአንቺም እኩል  ለሰው አዛኝ እና ሰናይ ምግባር ያለው ልጅ ማግኘት ከባድ ነው….ይሄን  እኔ ብቻ  አይደለሁም ሀገር ምድሩ ነው የሚያወራው…እዚህ ቤት የሚርመሰመሱ ሰራተኞች አንቺ ሲያምሽ አብረው ሚታመሙት፤ ፈገግ ስትይ ሲገለፍጡ የሚውሉ ናቸው እኮ...የሰፈሩ አሮጌት ምረቃትን  ካንቺ እኩል የተመረቀ ማን አለ..?ከአኔ ከእናትሽ ቦርሳ እየመዠረጥሽ ለሰፈር አሮጊትና ሽማጊሌ ብሬን ስታድይ፤ የተመመ ችግረኛ ስታሳክሚ ፤መማር ላቃተቻው ህፃናት ደብተርና ዩኒፎርም እየገዛሽ ስታድይ አይደል እንዴ የኖርሽው?
ልጄ እኔ እንደውም ይሄ ሁሉ ደግነትና ቸርነት ከየት አምጥታው ነው ?እያልኩ ዘወትር እንደተደምኩብሽና እንደኮራሁብሽ ነው..አንቺ ይሄ ክፍ አመል ባይጠናወትሽና ባይለክፍሽ እንከን አልባ መልአክ እኮ ነበርሽ..ልጄ ታዲያ ምን ላድርግሽ እንድትፈወሺልኝ ያልሞከርኩት ህክምና የላጠጣሁሽ ጠበል የለም..የእኔ ቆንጆ ሰው ሲቸገር ምንም ነገር ለመሞከር ይደፍራል፤አጣብቂኝ  የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል፤ የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል፤የትኛውንም የሚወደውን ነገር  አሳልፎ ይሰጣል።አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል።እኔም በዚሁ በአንቺ ችግር ምክንያት የሰራሁትን ዛሬ ልንገርሽ…ሚስጥር አድርጌ ይዤው ነበር.. እግዜር ይቅር ይበለኝና ይሄውልሽ ጠንቆይ ቤት ሁሉ እኮ መፍቴ ይሰጠኝ መስሎኝ ሄጄ ጠይቄያለሁ….ግን መፍትሄ አልተገኘም፡፡
‹‹እጄን አስቆርጪው…በእጄ አይደለ ምሰርቀው…በቃ አልፈልጋቸውም.. ሁለቱ እጆቼ ይቆረጡ፡፡››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ ..በስመአብ…የሚነሳው በእጅ ቢሆንም ቀድሞ  የሚሰርቀው  እኮ እዕምሮ ነው..እምሮሽን አላስቆርጥ?››
›‹‹እማዬ  ብቻ እኔ አንዲህ እየተዋረዱ መኖር ሰልችቶኛል…ትንሽ ጊዜ ነው የምሰጥሽ ….ካለበለዚያ..››
‹‹ካበለዚያ ምን?››
‹‹እራሴን አጠፋልሻለሁ..ከዛ ግልግል ነው፡፡››
‹‹አረ ተይ ልጄ…. ተይ እኔ እናትሽ እንኳን አላሳዝንሽም..?ሌላ ትርፍ ልጅ እንዳለው ሰው እንዲህ ትያለሽ..? አንቺ እኮ ከታችም ከላይም የሌለሽ ብቸኛ ልጄ የአይኔ ማረፊያ ነሽ…እኔ ባለኝ ሀብት በአለም በየትኛውም ጥግ ለዚህ ፈውስ ቢኖር የምሰስት ይመስልሻል ?ለምን ብዬ…ከሰባራ ሳንቲም አንስቶ ሙሉ ካማፓኒው ያንቺው ነው..እኔ ከአሁን ወዲህ የምኖረው እራሴን ለማስደሰት ሳይሆን አንቺ በሁሉ ነገር የተሳካልሽ ሆነሽ ስትስቂ ለማየት ነው…፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን አድርጊ እያልሺኝ ነው?››
‹‹ካልሆነ ለሁለተኛ ጊዜ እዛው አሜሪካ ሂጂና ትሞክሪ ይሆን ?››
‹‹እማዬ እኔ የትም ሀገር መሄድ አልፈልግም..ደግሞ የፈረንጆች የቅዠት ሀሳበ መሞከሪያ መሆን ሰልችቶኛል፡፡››
‹‹እሺ.በቃ ከመድህኔ ጋር ተማከሬ የሆነ ነገር አደርጋለሁ፡፡›› 
‹‹ከእሱ ጋር አትማከሪ በራስሽ ከቻልሽ አድርጊ ካለበለዚያ…፡፡››
‹‹በቃ በቃ. እሱን ለእኔ ተይውና ተኚ.›
እጃቸውን ፀጉሯ ውስጥ ከተው ሲዳብሷት የሆነ ፀጥ ያለ ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኘች ያለች መሰላት…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

  ይቀጥላል
👍10216👏3😁3
#ህያብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በኤርሚ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"
👍488🥰2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

‹‹ጎሽ ጥለኸኝ አልተሰወርክም…አጠገቤ አለህ ማለት ነው? ››ስትል የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰችና…በከፍተኛ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ዓይኖቾን ገለጠች…..ወንዝ የሚባል ነገር ስራቸው  የለም…የሲኦል ምልክትም አይታያትም…. በሳር ፤ በትናንሽ አረንጓዴ ቁጥቆጦች እና የሚያማምሩ በቀለማት  በተሸቆጠቆጡ አበቦች የተሞላ ወብ ቦታ ነው…ግን ግራ አጋቢ ቦታ…፡፡
ከስር መሬት ከላይም መሬት ነው የሚታያት ..ግዙፍ ዋሻ መሰል  ነው እንዳትል ምኑም ዋሻ አይመስልም…የተለመደው አይነት ምድርና ሰማይ ነው የሚታየኝ ብላም እንዳትገምት በቆመችበት መሬት እና ወደላይ አንጋጣ  በምታየው መሬት(ሰማይ)  መካከል ያለው ልዩነት  የሚታወቀውን   ሰማይ  ከመሬት የሚርቀውን ያህል እርቆ አይደለም የሚገኘው…በግምት ከመቶ ሜትር አይበልጥም፣
‹‹ተገልብጠን ከምድር ስር ይሆን እንዴ ያለነው….?ማለቴ ምድርን ከታች ወደ ላይ የምናያት..ማለቴ አሁን ላለሁበት ሚስጥራዊ ቦታ ምድር ሰማይ  ትሆን እንዴ…?›ስትል በውስጧ ብትጠይቅም ለመግለጽ የፈለገችውን  ሀሳቡ ለእሷው ለራሷ ተምታታባት…

ትክክለኛ መልስ ለመግኘት ወደ እሱ ዞረችና ‹‹የት ነው ያለነው…..?›› ስትል ጠየቀችው

‹‹እቤቴ››አላት

አበባ.. ትንንሽ ቁጥቋጦች.. እዚህም እዛም የሚፈልቁ  ምንጮች… ለጥ ያለ ማለቂያው የማይታወቅ ሜዳ ነው የሚታያት‹‹ ….ይሄ ነው ቤትህ…..?››

‹‹አይ አይደለም….››አላት ፍርጥም ብሎ

‹‹….ቆይ ቆይ…›› እሰከአሁን በሁኔታው ተመስጣ ልብ ያላለችውን  ነገር አየች…., ልብስ ለብሶም ሆነ እንደዚህ ሙሉ እርቃኑን ፊት ለፊቷ ቆሞ አይታው አታውቅም ነበር….እስከዛሬ ግምሽ አካሉ በውሀ እንደተሸፈን ከእምብርቱ በላይ ነበር የምታየው….በጣም ተገረመች…የምታየው ፍጥረት  ሰው አይደለም….….?ሰው ካልሆነ ታዲያ ምንድነው ከተባለ መልሱ ለመግለፅ በጣም ይከብዳል…?፡፡ ምን ተብሎ እንደምትገለጽው እሷም ምንም አልገባትም  ..እንደዚህ አይነት ፍጡር እሷ አይታ አታውቅም…፡፡እግሮቹ  ጣት አልባ ናቸው… ልሙጥ እና እንደሰፌድ የተዘረጉ…ወይም የዓሳ ክንፍ የመሰሉ …..ብልቱ ደግሞ ምታህለው…ያልተገረዘች የሴት ቂንጥር በሏት… ወደ ፊት እንደባቄላ  ነው አጎንቁላ  የምትታየው…
ወይኔ ጉዴ››አለችና ሳቋ አመለጣት…ያሳቀት …?ስንት ቀን አሁን ቢደፍረኝስ .. ?እያለች የተጨነቀችው አጉል  መጨነቅ በምናቧ መጥቶባት ነው …‹‹አሁን በዚች እንኳን መድፈር ሽንቱንስ መሽናት ይችላል…?›› የሚል ሀሳብ አሰበችና ሳቋን አረዘመችው …
ሌላው በትክክል ሰው አይደለም ብላ ያሰበችው ዋናው ምክንያት  ባለጭራ መሆኑ ነው..ጭራ አለው፡፡ ጭራው ደግሞ ከኃላ ከመቀመጫው የላይኛው ክፍል በቅሎ ወደታች በመሄድ በእግሮቹ መካከል አልፎ ወደፊት ተቆልምሟል.‹‹.እንደውም ከእውነተኛው ብልቱ ይልቅ ጭራውን እንደብልትነት ቢጠቀምበት ያዋጣዋል›› ስትል በውስጧ  አሰበችና ድጋሚ  ፈገግ አለች፡፡

‹‹ስለእኔ ተፈጥሮ አስበሽ እና ተመራምረሽ ጨረሽ?››ብሎ አስበረገጋት
‹‹አይ ምን እመራመራለሁ….?እንዲሁ አዲስ  ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ..››በአፍረት መለሰችለት፡፡
‹‹ግን አልፈራሺኝም…››
‹ለምን እንዳልፈራውህ እኔንም ገርሞኛል…?››የእውነትም ለምን እንዳልተንቀጠቀጠች…?ለምን ፊቷን አዙራ ወደተንጣለለው ሜዳ ፈርጥጣ እንዳልሮጠች …?ለምን ያንን ጆሮ ሰንጣቂ የዘወትር ጩኸቷን እንዳላስነካችው ?ለእሷም አልገባትም…በቃ ከመደነቅና ከመገረም ውጭ በስሜቷ ላይ ያስከተለው የጥላቻውም ሆነ የፍራቻ ስሜት አልነበረም….
‹‹ስለዚህ ወደቤት መሄድ እንችላለን?›› አለና ጎንበስ ብሎ የቆመበትን አካባቢ መሬት በእጁ ሲነካ በአስገራሚ ፍጥነት አብረቅራቂ የወርቅ ሳጥን ከተሰነጠቀው መሬት ተፈልቅቆ  ወጣ…..
‹‹ፓንትሽን  አውልቂ››አላት
‹‹ለምን …? ምን አስበህ ነው…?››ስትል ግራ በተጋባ ስሜት ጠየቀችው፡
‹‹በዚህች ዕቃዬ ምን አስባለሁ?›› አላት እና አሳፈራት….እሷም ልትለው የፈለገችው  በዚህ ዕቃህ ምን ለማድረግ አስበህ  ነው…›ነበር..ያው ልቧን በትክክል ነው ያነበበው፡ 

‹‹እንደዚህ ሆነሽ ወደ እኔ ቤቴ መግባት አትችይም  …..ጨረር ይጎዳሻል››

መከራከሯን ትታ ፓንቷን አወለቅችና እጆቾን እፍረቷ ላይ አደራርባ ቆምች….በእጁ ካንጠለጠለው ሳጥን  የሆነ ሰማያዊ መልከ ያለው የጠፈርተኞችን የሚመስል ልብስ አወጣና  አለበሳት….ሙሉ በሙሉ በልብሱ ተጠቀለለች …ከዛ እጁን ወደ ፊት ሲዘረጋ  እስከአሁን እይታዋ ውስጥ ያልገባ ግን ከቆመችበት በአንድ ሜትር ርቀት የነበረ ወርቅማ የብረት በር ወለል ብሎ ተበረገደ……ከዛ እቤት ሳይሆን አይታ የማታውቀው በምናቧ እንኳን ገምታው የማታውቀው በተረት አለም ብቻ የሚገኝ አይነት ምትሀታዊ የዘመነ ፤ የፀዳ  እና ፀጥ ረጭ ያለ ከተማ ከፊታቸው ተነጠፈ…‹‹..እርግጠኛ ነኝ ይሄ ሁሉ እስከአሁን የሆነውና ያያሁት እውነት አይደለም….ህልም ላይ ነኝ ..ገና ከእንቅልፌም አልተነሳሁም›› በማለት እራሷን ለማፅናናትም ለማረጋጋትም ሞከረች….፡፡ግን አልተሳካላትም፡፡

…ምንም አይነት እሱን መሳይም ሆነ ሌላ ፍጡር ሳታይ ነው በወርቃማ ብርሀን ያሸበረቀውን ከተማ ሰንጥቀው እሱ ቤት የደረሱት፡፡ ይዞት የገባው አንድ  ከግድግዳው ሰማያዊው ብርሀን የሚተፋ  ቤት ውስጥ ነው ፡፡አራት ክፍል ቢኖሩትም ሁሉም  ባዶ ነበሩ..ምንም ዕቃ የላቸውም…

‹‹እንዴ…ይሄ ነው ቤትህ..?››

‹‹አዎ ምነው… ?

አልወደድሺውም…?››

‹‹አይ ቤቱማ አሪፍ ነው..ግን ባዶ እኮ ነው….ቤትን ቤት የሚያሰኘው ደግሞ ጣሪያና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ውስጡም የሚገኝ መጠቀሚያ ቁሳቁስ ነው….››

‹‹ባዶ…››አለና ወደውስጥ ገብቶ ግድግዳውን ተጠጋና ማብሪያ ማጥፊያ የሚመስል ነገር ተጫነ..
ተአምር ተፈጠረ…ድፍን ግድጋዳው እየተከፋፈተ ፍሪጅ …ቴሊቭዝን የመሳሰሉት ዕቃዎች… ወለሉም እየተከፈተ ጠረጵዛ ወንበር በመውጣት እቤቱን ሞሉት…. አደመቁት….. 

ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን ነገር ችላ ብሎ‹‹አረፍ በይ …››አላት 

‹‹ምን ጉድ ነው….!!እስኪ መኝታ ቤትህን አሳየኝ..?››ሌላ ተአምር ለማየት ከመጓጓት የመነጨ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

መጣና እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ይዟት ሄደ …ወደ ቀጣዩ ክፍል….በተመሳሳይ ባዶ ነበር…
-‹‹የትኛውን ልጫን …››አለችው ግድግዳ ላይ ወደተለጠፉት ማብሪያ ማጥፊያ እጇን እየሰነዘረች
‹‹አልጋ ከፈለግሽ ነጩን ተጫኚ..››

ተጫነችው፡፡

ከእምነበረድ ይሁን ከእንጨት ይሰራ ለጊዜው መለየት ያቃታትን   ነጭ አንሶላ ….ነጭ አልጋልብስ የለበሰ አልጋ ከወለሉ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ ክስተት በመውጣት  ተዘረጋ…..

‹‹ወይ እዚህ ላይስ መተኛት እፈልጋለሁ..››

‹‹ታዲያ ተኚያ …ማን ከለከለሽ››

‹‹ግን ይሄንን የለበስኩትን ደባሪ ልብስ ማውለቅ እችላለሁ?››

‹‹ቆይ… ››ብሎ ወደሳሎን ሄደ…. ምን እንዳደረገ ባታውቅም ወዲያው ሰማያዊው የነበረው የቤቱ መብራት  ወደ ብርማ አይነት ተለወጠ…እሱ ተመልሶ እሷ ወዳለችበት መጣ

‹‹አሁን ትችያለሽ አውልቂው››አላት፡፡ 
‹‹ወይ እንዴት ደባሪ መሰለህ ››አለችና ለማውለቅ ብትሞክርም  የተቆላለፉትን ነገሮች እንዴት ልትፈታታቸው እንደምችል አልገባትም... ምታደርገው ግራ ገባት

‹‹አቦ ምን ቆመህ ታየኛለህ ? ናና ከእዚህ  ወጥመድ ውስጥ አውጣኝ እንጂ››ቁጣ የተቀላቀለበት ልመና አሰማች፡፡
👍11913🤔5👎2👏2😢1
#ትንግርት


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡

የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡

‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን ማን አሳየህ?›› ወደ እሱ እየተራመደች ነበር የምትናገረው፡፡

ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳሙ በኋላ ግማሽ እርምጃ ራቅ በማለት አስተዋላት፡፡ ድንቡሽቡሽ ያለች የምትበላ ብስል ቀይ ወይዘሮ ነች፡፡ ያገለደመችው ሮዝ ቀለም ያለው ፎጣ ከወገቧ እስከ ጉልበቷ ሸፍኗታል፡፡ ሌላው አካሏ እንደተጋለጠ ነው፡፡ ጡቶቿ አሁንም እንደልጃገረድነቷ እንዳጎጠጎጡ ናቸው፡፡ የቆዳዋ ጥራትም አስደምሟታል፡፡

‹‹ምን ያፈዝሀል? ቁጭ በል እንጂ›› አለችው፡፡ በእሷ ውበት መደመሙን ስታስብ ውስጧን የንዝረት ስሜት ተሰማት፡፡

‹‹ለምን አልፈዝ፡፡ ጓደኛዬ ለካ ይሄንን ሠውነት እንደ አሞሌ ጨው ሲልስ እያደረ ነው እንዲህ

‹‹ኡ . ኡ . ቴ <ቅጡም የምንኩስና ነው› አለች አክስቴ.... ለማንኛውም ልብሴን ለብሼ ልምጣ.... የሚጠጣ ከፈለክ ፍሪጁን ከፈት አድርግ፡፡›› በማለት እየተውረገረገች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ሁሴን ፍሪጁን ከፍቶ ቢራ አወጣና እየተጎነጨ ማሠብ ጀመረ፡፡ ስለ ሰሎሞን ነበር የሚያስበው፡፡ በመጀመሪያ የውብዳርን ያፈቀራት ጊዜ ጨርቁን መጣል ነበር የቀረው፡፡ እሷን ማግባት ካልቻለ በህይወት መኖር
እንደማይችል ደጋግሞ ሲምል ነበር፡፡ በወቅቱ ደግሞ የእሷ ቤተሠቦች ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የእሱ ፍቅር ብርታትና መስዋዕትነት የመክፈል ፅናቱ እሷንም ሙሉ በሙሉ በፍቅሩ እንድትጠመድና ከቤተሠቦቿ ፍቃድ ውጭ አሻፈረኝ ብላ እቤቱ እንድትገባ አስገደዳት፡፡ እናም ትዳራቸው በእንደዛ አይነት ሁኔታ በጽኑ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ ደስታ ተጀመረ፡፡ ንብረት መጣ፣ልጆች ተወለዱ፣ሁሉ ነገር የሰመረ መሰለ፡፡ዳሩ ግን ውሎ አድሮ አካል ሲቀራረብ ፍቅር ቀስ በቀስ ከመሀከል ሾልካ ተነነች፤አንዳቸው ለአንዳቸው የወዳጅ ጠላት ሆኑ፡፡

‹‹እሺ አቶ ሁሴን... ደህና ነህ?›› እስከተረከዟ የሚደርስ ረጅም አብረቅራቂ ጥቁር ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ዊግ የተቀላቀለበት ሹሩባዋ ያምራል፡፡ የሁለት ጡቶቿ አካፋይ የስምጥ ሸለቆ ስንጥቅ መስሎ በከፊል ይታያል፡፡ የተቀባችው ሽቶ የሳሎኑን አየር በሠከንድ ነበር የቀየረው፡፡

‹‹አለሁልሽ... ከውዱ ባለቤትሽ ጋር ነበር የመጣነው ግን ከበራፍ ተመለሰ፡፡››

‹‹ምነው ውሽማው ጠራችው እንዴ?›. ግዴለሽ በሆነ አሽሞጣጭ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ! ውሽማው ጋር ነው የሄደው፤ወይዘሪት ገንዘብ ጋር ።

‹‹እነ ዕፀ-ህይወት ትምህርት ቤት ናቸው እንዴ? ... የጫወታውን አቅጣጫ ወደ መጣበት ጉዳይ እንዲያመራላት ነበር ጥያቄውን የሠነዘረው፡፡››

<<አዋ>>

‹‹ልደታቸው ደረሠ አሉ፡፡ ለምን ዝግጅቱ በእናንተ ወጪ እኔ ቤት አይሆንም? በዛውም እኔ አገባበታለሁ፡፡ ‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር ያገባል› አይደል የሚባለው፡፡›› ፈገግ አለች... ስለመጨቃጨቃቸው እንደሰማ እርግጠኛ ሆነች‹‹ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከጓደኛህ ይሻላል፡፡››

‹‹የእሱ ሀሳብ እንዴት ነው?››

‹‹እንደነገረህ ነዋ ..! ሆቴል ይዘጋጅ ነው የሚለው፡፡ አሁን አሁን ምን እያሠብኩ እንደመጣሁ ታውቃለህ፤ ለእሱ ስል ይሄንን ሳሎን ወደ ሆቴልነት በመቀየር በመጠጥ ሞልቼ ለእሱ እንዲመች ማድረግ… ፡፡››

‹‹እንግዲያው ከጓሮ ያሉትን ሰርቪስ ክፍሎችም ወደቤርጎ ቀይሪልን፤ እኔም አንዳንዴ ሴቶችን ሸጎጥ አድርጌ መጣና አረፍ እልበታለሁ።

‹‹ምን አንተስ የእሱ ጓደኛ አይደለህ፡፡››

‹‹ከእሱ በፊት እኮ የአንቺ ጓደኛ ነበርኩ…ኧረ እንደውም የዕቃ ዕቃ ባልሽ አልነበርኩ እንዴ?››

ፊቷ ቀላ፡፡ የውብዳር ሁል ጊዜ ስለ እሷ እና ስለ ሁሴን የልጅነት ታሪክ ስታስብ የሠውነቷ ሙቀት ይጨምራል፡፡ በተቀራራቢ ጊዜ አንድ ሠፈር ውስጥ ከማደጋቸው አንፃር ጣፋጭ የሆነ የልጅነት፤ ከዛም ዘሎ እስከ አሁን የዘለቀ የጓደኝነት ቁርኝት በመሀከላቸው አለ፡፡ ከሠሎሞን ጋር እንዲገናኙ መሠላል የሆናቸውም እሱ ነበር፡፡

ካለፈ ትውስታቸው እንደመባነን አለችና ‹‹አዋ እሱማ ለእኔም ጓደኛዬ ነህ፡፡ካንተ ጓደኝነት ያተረፍኳቸው ሦስት ትላልቅ ነገሮች ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ምርጥ ተወዳጅ ልጆች፣ብዙ ብር እና የምሁር ደደብ የሆነ ባል ናቸው፡፡ እና ላማርርህም ሆነ ላመሠግንህ ግራ ይገባኛል፡፡ ባይገርምህ ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስብ የዛን ጊዜ ከእሱ ይልቅ አንተን ለምን እንዳልጠበስኩህ ድንቅ ይለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ሆነን አብረን ማደጋችን እንደወንድምና እህት እንድንተያይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እንደ አሁኑ በሳል
ሆኜ ቢሆን ኖሮ መቶ ጊዜ ደጋግሜ አንተን ነበር የምጠብሰው

‹‹ድሮም ሆነ አሁን ዱርዬ እንደሆንኩ እኮ ደጋግመሽ ነገርሽኝ ነበር››፡›› ሁሴን የድንጋጤ ንግግር ነበር የተናገረው፡፡ የውብዳር ስለ እሱ እንደዚህ አይነት ስሜት እንደሚሰማት ገምቶ አያውቅም፡፡

‹‹ዱርዬማ ዱርዬ ነህ፡፡ ግን ንፁህ ዱርዬ ነህ፡፡ አፍቃሪም ነህ፡፡ ከተረጋጋ ማህበራዊ ሕይወት ይልቅ በማዕበል የሚናወጽ ግን በደስታ የተጥለቀለቀ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ደስታ በሕይወት ለመኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የምትረዳው ባጣኸው ጊዜ ነው፡፡ ፍቅር አልባ ሕይወት እኮ በቃ..… ንብ አልባ ባዶ ቀፎ ማለት ነው፤ንብ የሌለበት ባዶ ቀፎ ደግሞ ማር ሊመረትበት አይችልም፡፡ ብር ምን እንደሚያደርግልህ ታውቃለህ፡፡ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያስገኝልሀል፡፡ ውጫዊ ችግሮችህን ሁሉ በቀላሉ ታስወግዳለህ፡፡ ሀብታም ሆነህ ሳለ የፍቅር ካዝናህ ባዶ ከሆነ ግን ..በቃ ቀንና ሌት ስለ እሱ ብቻ ታስባለህ፡፡ ሌሎች ፍላጎቶችህ ሁሉ ስለተሟሉ ሌላ የምትጨነቅበት ጉዳይ አይኖርማ፡፡ ስለዚህ ይበልጥ በፍቅር እጦትህ እንድትሠቃይ ትሆናለህ፡፡››

‹‹ቆይ ይሄንን ያህል እስክትማረሩ ድረስ ምን
ትሠራላችሁ፡፡ ለምን አትነጋገሩም?፡፡ የተከሰቱ
ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ጥረት ለምን
አታደርጉም ? ፍቅር እኮ ዘላለማዊ ነገር አይደለም፡፡ ይወለዳል .. ያድጋል .. ይሞታል፡፡በልጅነቱ .. በወጣትነቱ አልያም አርጅቶ ሊሞት ይችላል፡፡ የዕድሜውን ርዝመት የሚወስነው ግን ሁለቱ ፍቅረኛሞች ስለፍቅር ባላቸው ግንዛቤና ለፍቅራቸው በሚያደርጉለት
እንክብካቤ መጠን ነው፡፡ እናንተም አያያዙን
ያወቃችሁበት አይመስለኝም፡፡ ሲጋቡ
አይታችሁ ተጣድፋችሁ ተጋባችሁ፤ ይሄው
ጀርባ ለመሠጣጣትም ብዙ አልዘገያችሁም፡፡ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ጊዜ በእርጋታ ቁጭ ብለን በሠፊው እንነጋገርበታን፡፡

አሁን ወደ መጣሁበት ጉዳይ እንመለስ
መግባባት ስላቃታችሁ የልጆቹ የልደት ዝግጅት ጉዳይ….፡፡››

‹‹እንዳልክ እሺ፡፡መቼስ አንተ ጠይቀኸኝ ምንም ነገር እምቢ ማለት እንደማልችል ስለሚያውቅ ነው የላከህ፡፡ ከዛ በፊት ግን ስለራበኝ የሚበላ ነገር እንድታመጣ ሠራተኛዋን ልዘዛት›› በማለት ወደ ማብሠያ ክፍል አመራች፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍13013👏5🔥3🎉2🤔1😢1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን ሀውልት ታሳድሳለች..አካባቢውን ታፀዳለች..በሀውልቱ ላይ ደርቀው የከሰሙ አበቦችን አስወግዳ በምትካቸው አዲስ ትተክላለች..ያሉትንም ውሀ  ታጠጣለች...ቤት ውስጥ በድግሱ የእንጀራ እናቷን ትረዳለች...በዕለቱ ታዲያ አንድም ችግረኛና የኔ ቢጤ በከተማው አይቀርም፤ ቀኑን ሙሉ ወደእነሡ ቤት ሲጓዙና ከድግሱ በልተው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን በፌስታል ተቋጥሮላቸው የሞተውንም ነፍስ ይማር ብለው እነሱንም መርቀው ይሄዳሉ።ይሄ መታሰቢያ ባለፉት ስድስት አመታት በጠቅላላው በአሰላ ከተማ የታወቀ ነው። እሷ ግን ይሄው የዘንድሮውን ረሳችው፡፡ከአይኖቿ የሚንጠባጠበውን እንባ እያበሰች "አባዬ በጣም ይቅርታ፡፡›› አለች፡፡

በዚህ ጊዜ ቱሉ ዲምቱ የክፍያ ጣቢያ ደርሳ የክፍያ ትኬት ለመቀበል መኪናዋን አቁማ ነበር።ታናሽ ወንድሟን ካወራች በኃላ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም።ወደቤቷ ሄዳ እንኳን ቅያሪ ልብስ ለመያዝ አልሞከረችም።ጭራሽ በሀሳቧም አልመጣ፡፡ቀጥታ መኪናዋን አዙራ ወደአሰላ መሄድ ብቻ ነበር የታያት፤እያደረገች ያለውም ያንን ነው።የቤታቸው የውጭ በራፍ ጋር የመኪናዋን አፍንጫ አስጠግታ የመኪናዋን ክላክስ ስታስጓራ አስር ሰዓት  ተኩል  ሆኖ  ነበር። ከሰፈሩ  በግርማ  ሞገሡ  አንደኛ የሆነውን ፊት ለፊቷ የሚታያትን የግንብ አጥር እና ፍረንች ዶር ያሰራችው እሷ ነበረች...አጥሩን ብቻ ሳይሆን ከድሮ ቤታቸው ማለት እትብቷ ከተቀበረበት እና ካደገችበት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ቪላ ቤት ያሰራችው እሷ ነች።ግን ይህን ሁሉ ያደረገችው ውድ አባቷ ከሞተ በኋላ ነው።በህይወት እያለ የሚወደውንና መላ ህይወቱን የለፋበትን ግቢ እንዲህ አሳምራውና ቀይራው ቢያይላት ኖሮ እንዴት ይደሰት እንደነበረ ትገምትና የብስጭት እንባዋን  ትዘራለች።ሁሌ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አንስተው ከስንዱ ጋር ሲያወሩ"አሁንም  እኮ መንፈሱ ያይሻል...ለእኔና ለወንድምሽ በምታረጊው ነገር ባለበት ሆኖ ይመርቅሻል..ልክ በህይወት እያለ ይኮራብሽ እንደነበረው  አሁንም  ይኮራብሻል..››እያለች ልታፅናናትና ከገባችበት ሀዘን መንጭቃ ልታወጣት  ትሞክራለች።ግን ይህ አይነቱ  የእንጀራ እናቷ የማፅናኛ ንግግር እሷን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነው ሀዘን ውስጥ ነው ጎትቶ የሚሸጉጣት

‹‹አባቴ ባለበት ሆኖ እኔን የሚያየኝ ከሆነማ በጣም ነው የሚያፍርብኝ...በእውነት ይህቺ ልጅ እኔ ያሳደኳት ከአብራኬ የወጣች ልጅ ነች ?››ብሎ መጠየቁ አይቀርም...ምክንያቱም በትክክልም ባለበት ሆኖ ስራዬን የሚያይ ከሆነ ቤቱን ማሳመሬን ብቻ አይደለም የሚያየው..ሚስቱን እና ልጁን መንከባከቤንና መርዳቴን ብቻ አይደለም የሚያየው አመት እየጠበቅኩ በስሙ የአሰላን ድሆች ማብላቴን ብቻ አይደለም የሚያየው...እርግጥ እነዚህን ስራዎቼን ባየ ቁጥር ፈገግ ሊል ይችል ይሆናል፡፡ግን ደግሞ በየዕለቱ በስራ  ህይወቴ  የማሳልፈውን ነገሮች ካየስ..?.በእየዕለት ህይወቴ የሆንኩትንና እየሆንኩ ያለሁትን የሚያይ ከሆነስ..?ልጁ አጨበርባሪ እንደሆነች ሲያይስ.?ልጁ እልል ያለች ፕሮፌሽናል ሸርሙጣ መሆኗን ሲያይስ? ከዛም  አልፎ  ገዳይና  ቂመኛ  መሆኗን ሲያይስ?››እኚህንና መሠል ነገሮችን በውስጧ እያሰበች ሽምቅቅ ትላለች።አባቷ በሄደበት በዛው እንዲመቸውና ፊቱን ወደኃላ ዞሮ እንዳያያት ዘወትር ትፀልያለች።አዎ አባቷም  ሆነ  ሌሎች የሚወዷት ሰዎች ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችውን ሳባን ብቻ አውቀው በዛ ትዝታ እንዲኖሩ እንጂ ካዛ ወዲህ እንደ አዲስ በውስጧ በቅላ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረቻትን አውሬዋን ሳባን እንዲያውቁ ፈፅሞ አትፈልግም...

የአሁኗን ሳባ ከእነሱ ለመደበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በሀሳብ ጭልጥ ካለችበት የበራፍ መከፈት ነው ያባነናት፡፡ራጂ ነበር ..የከፈተላት።መኪናዋ አዲስ ስለሆነች አይቷት አያውቅም።ማንነቷን ስላለየ  ወጣና ቀረባት፤እህቱ መሆኗን ሲያውቅ እየፈነጠዘ ሰላምም ሳይላት  ወደውስጥ ሮጠ.‹‹..እናቴ ማን እንደመጣ እይ ? እናቴ አላልኩሽም እህቴ  መጣች...እህቴ መጣች" ደስታውንና ፈንጠዝያውን ስታይ ውስጧ ርብሽብሽ አለባት፡፡
‹‹እንደዚህ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሠቦች እያሉኝ ለምንድነው ብቸኝነት ውስጤን የሚከታትፈው? ›› ስትል እያሠበች ከገቢናው ከፍታ ወረደችና ወንድሟ  ክፍት ጥሎት በሄደው ትንሹ በር ገብታ እራሷ የመኪናውን መግቢያ በራፍ ከፈተችና መኪናዋን ወደ ግቢ ውስጥ አስገብታ ገና በቅጡ ሳታቆም ስንዱ ልጇን አስከትላ እጇን እንደ ክንፍ እያርገፈገፈች ስትመጣ አየቻትና ፈጠን ብላ  መኪናዋን በማቆም ወረደችና… ወደእሷ ተንደረደረች፡

አይን  ለአይን  ሳይተያዩ ገና ሁለት ወርም በቅጡ ያልደፈነ ቢሆንም አሁን በሰላምታ ተቃቅፈው ሲላቀሱ ላያቸው ባለፈው ሁለት አመት ጭራሽ ያልተገናኙ ነው የሚመስለው፡፡

‹‹ለመሆኑ.አለሽ…?ምነው.ከሳሽ?››ፊቷን.እየዳበሰች.በመንሰፍሰፍ.ጠየቀቻት…ስንዱ የሳባ እኩያ ብትሆንም አባቷን በማግባቷና  በዛም  ምክንያት እናቷ መሆን በመቻሏ  ሁሌ  ንግግራቸው የሀያ አመት ልዩነት በመሀከላቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ቤት እንደገባች ምግብ ተሰርቶ በልታ ቡና ተፈልቶላት ጠጥታ  ለነገው  ድግስ የሰፈር ሰው ሁሉ ቤታቸው ስራ ላይ  ስለነበረ  እነሱን  ተቀላቅላ  ማገዝ ብትፈልግም ራስ ምታቷ ስለተቀሰቀሰባትና ከሰው ተቀላቅላ ሆይ ሆይታ ውስጥ መሳተፉን ስላልቻለች በስንዱ ገፋፊነት እሷ መኝታ  ቤት  ገብታ እንድትተኛ አድርጋት ወንድሟም እየመጣ እንዳይረብሻት አስጠንቅቃው በራፉን ከውጭ ዘገታባት ወደስራዋ ሄደች፡፡

ሳባም የድሮ የአባቷ መኝታ  ክፍል  አባቷ ይተኛበት የነበረ አልጋ ላይ ወጥታ ኩርምት ብላ ተኛች የተወሰነ  ድካም  ቢኖርባትም እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡እስከአሁን ሁለት ጊዜ በዶክተሩ የታዘዘላትን ለሳምንት ያህል በተከታታይ ስትወሰደው የነበረውን መድሀኒት መውሰድ ነበረባት..ጥዋት ለህክምና ብላ ከቤት እንደወጣች ስላልተመለሰች አልያዘችውም ዛሬ የታዘዘላትንም ተጨማሪ መድሀኒት  ወደፋርማሲ  ጎራ  በማለት  ልትገዛ አልቻለችም..ጭራሽ ትዝም አላላት፡፡

‹‹የራሱ ጉዳይ አለችና ››ወደሀሳቧ ተመለሰች፡፡
እዚህ ቤት መምጣት .ከዛም በላይ እዚህ ክፍል መግባት… ከዛም በላይ  እዚህ አልጋ ላይ ተኝቶ ስለአባቷ  ማሰብ  አንኳን  አሁን  እንደዚህ  አእምሮዋ  በጭንቀት እና በድባቴ ምስቅልቅል ባለበት ጊዜ ይቅርና በፊትም ራሷን መግዛትና ስሜቷን ማረቅ በምትችል ጊዜ በጣም ነበር የሚረብሻት…በጣም ነበር ሀዘን ውስጥ የሚጨምራት፡፡ይሄ ቤት የተወለደችበት ነው፡፡እናቷ የሞተችው እሷ ከተወለደች ከአንድ አመት በኃላ ነበር፡፡አዎ  የአንድ  አመት  የልደት  በዓሏ  ሊከበርላት  አንድ ቀን በቀረበት ጊዜ ነው፡እናትዬው ከመሞቷ በፊት ለእሷ የልደት ክብረበዓል የሚሆኑ ሁሉንም ዝግጅት አሰናድታ ጨርሳ ነበር.በድንገተኛ በሽታ ማታ ሁለት ሰዓት አመማት..ወዲያው አፋፍሰው አሰላ ሆስፒታል አስገቧት…አምስት ሰዓት ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛ አባትዬው ለብቻው ሆኖ ነጭ ላቡን ጠብ በማድረግ ምንም እንዳይጎልባት አድርጎ አሳደጋት፡፡ታዲያ ሁል  ጊዜ  የእሷ  ልደት 
👍7913👏1😁1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፔሩ/አማዞን ወንዝ
ዳግላስን ከኑሀሚ ነጥለው በአማዞን ወንዝ ላይ የተወሰነ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ሌላ እጅግ በጣም የተቀናጣ ግን ደግሞ መለስተኛ ዘመናዊ ጀልባ አጠገብ አቆሙና አሸጋገሩት፡፡ምንም እየገባው ነገር ባይኖርም ግን ደግሞ መከራከርና መጨቃጨቅ ባለመፈለጉ እንዳደረጉት እየሆነላቸው ነው፡፡ልክ ከትንሿ ጀልባ ወደቅንጡ ውሀና ዘመናዊው ጀልባ አሸጋግረውት ገና ወለሉ ላይ እንዳረፈ..አንድ ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ፤ደማቅ ጥቁር ፀጉሯ መቀመጫዋ ላይ የደረሰ ፤መልኳ ጉርድርድ ያለ ግን ደግሞ ሳቢ የሚባል የደም ግባት ያላት ሴት ከውስጥ ወጣችና ተንደርድራ መጥታ ተጠመጠመችበት፡፡ግራ ገባው፡፡ብዥም አለበት፡፡ይህችን ሰውነቱ ላይ ተጠምጥማ በእንባ በመታጀብ እየሳመችው ያለችውን ልጅ የሆነ ቦታ የሆነ ጊዜ ያውቃታል..አዎ በአእምሮ ብልጭ ድርግም እያለችበት ነው ..ግን የት እና እንዴት እንደሚያውቃት ምንም ትዝ ያለው ነገር የለም፡፡
‹‹ቤብ..ሰላም ነህ…?ወይኔ በኢየሱስ……ምንም አልሆንክም…?›› መላ እሱነቱን እየተሸከረከረች አያች  ግንባሩን ጉንጮቹን እጆቹን እያፈራረቀችና እያገለባበጠች ትሰመው ጀመር፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ወጠምሻና አብረቅራቂ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አንገታቸውን አቀርቅረው ዙሪያቸውን ከበው እየሆነ ያለውን በቆረጣ እየተመለከቱ ናቸው፡፡ልጅቷ እየጎተተች ወደውስጥ ይዛው ገባች ፡፡ደረጃውን እየወረዱ ወደውስጠኛው መኝታ ክፍል ይዛው ገባች፡፡ ሰፊውን ክፍል አልፋ አልጋ ወደ ተነጠፈበት መለሰተኛ ክፍል ይዛው ገባቸው፡፡ባለመሳሪያዎቹ ባሉበት በረንዳ እንደቀሩ ናቸው፡፡

ዳግላስ በገባበት የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ የምታምር ድንብሽብሽ ያለች በግምት ሶስት ወይም አራት አመት የሚሆናት ጥቁር ሉጫ ፀጉሯ ግንባሯ ላይ ድፍት ብሎ ግማሽ ፊቷን የሸፈናት ልጅ ጭልጥ ያለ የሰላም እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ህፃኗን በትኩረት ሲያያት የሆነ ብዙ ቀለማቶች በአእምሮው ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያሉ ይረብሹት ጀመረ፡፡በፀጥታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና ቀኝ እጁን ወደ ልጅቷ ልኮ በቀስታ ግንባሯ ላይ የተደፋውን ፀጉሯን ከግንባሯ ላይ እያነሳ ትራሱ ላይ አስተኛው..እናትዬዋ ስሩ በፀጥታ ቆማ የሚያደርገውን እየተመለከተች ነው፡፡አሁን ሙሉ በሙሉ የልጅቷ ገፅታ ይታያል፡፡ይህቺ ልጅ ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም እንዳለች እርግጠኛ ነው፡፡ይሄንን የተረዳው ደመነፍሳዊ በሆነ ስሜቱ ነው፡፡በትክክለኛው ግን ምንም ትዝ እያለው ያለ ነገር የለም፡፡
አንገቱን ቀና አደረገና ጎኑ የቆመችውን አማላይ ሴት ተመለከታት‹‹የምታግዢኝ ነገር የለም?››ሲል ጠየቃት፡፡
የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ፍቃደኛ እንደሆነች በሚያረጋግጥ ንግግር ‹‹ምን ላድርግልህ የእኔ ፍቅር? የፈለከውን ጠይቀኝ››አለችው፡፡
‹‹አሞኛል ..በፊት የምወስዳው መድሀኒት ወይም ኪኒን ነገር ይኖራል?፡፡››
ደነገጠች….የእሷን   መደንገጥ  ተከትሎ  እሱም  ደነገጠምም  ግራ ተጋባምም‹‹ዛሬ መድሀኒትህን አልወሰድክም እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እስከማስታውሰው ድረስ ለበርካታ ቀናት ምንም አይነት መድሀኒት የወሰድኩ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ይሄ የፓብሎ ተግባር ነበር፡፡ግን እሱ ራሱ የት እንደገባ ምንም የሚታያውቅ ነገር የለም፡፡ቆይ መጣሁ›› ብላ ሔደችና ከሁለት ደቂቃ በኃላ ሁለት ኪኒኒ ከእሽግ ውሀ ጋር ይዛ መጣች፡፡ኪኒኖቹን ከእሽጉ ፈልቅቃ አቀበለችው….‹‹ውሀውን ከፈተችና በል ዋጥና ለአንድ ሰዓት ያህል ጋደም በል… ስትነሳ ሰላም ትሆናለህ….››
‹‹አልገባሽም ..አመመኝ ስልሽ እኮ ህመም አይደለም..ምንም የማስታውሰው ነገር የለም እያልኩሽ ነው..አንቺን ጭምር ማንንም አላስታውስም››የተረዳችው ስላልመሰለው ፍርጥ አድርጎ እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ገባኝ የእኔ ፍቅር ..ሁሉ ነገር ይስተካከላል… ብቻ ያልኩህን አድርግ… መድሀኒቱን ዋጥና ከልጅህ ጎን ተኛ፡፡››እንዳለችው መድሀኒቱን ተቀበላትና ዋጠ፡፡ጫማውን አወለቀና ቀስ ብሎ አልጋው ላይ ወጣና ከልጁ ጎን ተኛ፡፡ፊት ለፊት ካለው የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ አልጋ ልብስ አወጣችና አለበሰችው፡፡ ቀስ ብላ ክፍሉን ዘግታለት ወጣችና ከጠባቂዎቹ ራቅ ብላ የጀልባዋ በረንዳ ላይ ባላ ወንበር ተቀምጣ ከወንዙ ባሻገር ያለውን ጥቅጥቅ የአማዞን ደን በተመስጦ መመልከቷን ቀጠለች፡፡

ኑሀሚ ያለችበት ጎጆ የተወታተፈ በራፍ ሲከፈት ሰማችና የጨፈነ አይኗን ከፈተች፡፡ከአጋቾቾ መካከል አንዱ ነው፡፡፡አሁን እጆ ላይ ተጣብቆ ከወዲህ ወዲያ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ቅጭልቅል እያለ የሚረብሻትን ሰንሰለት ተቆራኝቷት የነበረው ልጅ ነው፡፡በእጁ የሚበላ ነገር በሰሀን እና የሚጠጣ ውሀ በላስቲክ ኩባያ ይዞል፡፡ወደእሷ ተጠጋና በርከክ ብሎ ምግብን አስጠግቶ አስቀመጠላትና የስፓንሽ ቋንቋ ዘየ በተጫነው ግን ደግሞ ባልተደነቃቀፈ እንግሊዘኛ፡፡‹‹ተነሽ ይሄን ምግብ ብይ…ከጥቂት ጊዜ በኃላ በእግር ረጅም መንገድ መጓዛችንን ስለምንቀጥል ጥንካሬው ያስፈልግሻል፡፡››አላት፡፡
ጎኑ ላይ የያዘውን አብረቅራቂ ኮልት ሽጉጥ በጎሪጥ እየተመለከተች‹‹ወደየት ነው የምትወስዱኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እሱን ለአንቺ ለመናገር ፍቃዱ የለኝም፡፡››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹እባክህ…እህት የለህም..እኔ እኮ በጣም ከሩቅ አህጉር የመጣው ምስኪን ወጣት ነኝ…ምን ላደርግላችሁ ነው እንዲህ ከእኔ ጋር የምትሰቃዩት?››አሳዛኝ መስላ ለመቅረብ ሞከረች፡፡
‹‹እህት አለኝ ….ግን ላደርግልሽ የምችለው ነገር ቢኖር  አንድ ምክር ላንቺ መስጠት ብቻ ነው፡፡››

‹‹ምንድነው? እባክ ንገረኝ፡፡››

‹‹ፈፅሞ የሞኝ ስራ እንዳትሰሪ…››
ያልጠበቀችው የምክር አይነት ስለነበር‹‹ምን ማለት ነው?››በማለት ጠየቀችው፡፡

‹‹ጥዋት በምንጓዝበት ጊዜ በየመሀከሉ ሁኔታሽን ስከታተለው ነበር… ለማምለጥ ወይም ለመፋለም የመፈለግ አዝማሚያ አይቼብሻለው፡፡ በእርግጠኝነት ትንሽ እንቅስቃሴ ወይም ሙከራ ካደረግሽ ከመሀከላችን አንድ ወዲያው ነው የሚደፋሽ… እመኚኝ ሌሎቹ እንደእኔ ልስልስ እና ደካማ ነገር አይደሉም፡፡ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ጭካኔም ያላቸውና ሰውን በመግደልና ድመት በመግደል መካለከል ምንም ልዩነት የማይታያቸው ገዳዬች ናቸው..እንደውም አጋነንከው ከላልሺኝ ለእነሱ ወሲብ ማድረግና ሰውን መግደል ተመሳሳይ አይነት እርካታ ነው የሚያጎናፅፋቸው፡፡››ሲል መስማት ከምትፈለገው ተቃራኒ የሆነ አስቀያሚ ዜና ነገራት፡፡

‹‹እና መጨረሻዬን ምንም ሳላውቅ ልክ እንደፋሲካ በግ ዝም ብዬ ልነዳ ?››

‹‹እኔ እንግዲህ እንደዛ የሚሻል ይመስለኛል፡፡በህይወት ነገ ተነገ ወዲያ ምን እንደሚከሰት አይታወቅም፡፡ነገ ይዛ የምትመጣውን እድል ለመጠበቅ ደግሞ ዛሬ በህይወት ቆይቶ ነገ ላይ መገኘት ያስፈልጋል፡፡በይ እንዳልኩሽ የቀረበልሽን ብይ…  የእግር ኮቴ እየተሰማኝ ነው፡፡
‹‹ልሂድ››ብሎ ቁጢጥ ካለበት ምንጭቅ ብሎ ተነሳና በራፉን ከፍቶ እንደአመጣጡ ተመልሶ ሄደ፡፡
👍827👎1👏1😱1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡

ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡

‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡

በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››

‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››

ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡

‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››

‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››

‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡

‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡

መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..

‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን  አልባትም  ወደቀልባቸው  እንዲመለሱ  ምክንያት  ሊሆናቸው  ይችል
ይሆናል… ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡ ‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡

‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…

‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት

‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡

‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት›› በማለት መለሰችለት፡፡

‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..

‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››

‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡

እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡

እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡

‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…
‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ››

‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡
👍5510
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ደላላው

ያዋጣኝ ይሆን ? ወይስ ያከስረኝ ? ይሆን ? ተጠራጠረ ፤ የአልባሳት ንግዱ ግን ውጤታማ አድርጎታል፡፡ እየተመላለሰ መነገዱን ቀጥሏል፡፡

የባልጪ መኪና ቶሎ ያሬድ ወደ ድሬድዋ ሊሄድ ረፍዶበት ተቻኩሏል፡፡ መኪናው ግን ሳይሞላ መውጣት አልቻም፡፡ አዳማ አርፍዶ ደረሰ፡፡ ወደ ድሬደዋ በጥዋት የሚወጣው መኪና አምልጦታል፡፡

ተናደደ ፣ ተበሳጨ፡፡ ምነው ዛሬ ባልመጣሁ ኖሯል፡፡ እንደሚረፍድብኝ እያወቅሁ፡፡ ከባልጪ መመለስ ሲኖርብኝ፡፡ ወደ አዳማ መንከርፈፍ ምን ይሉታል? ራሱን እየወቀሰ ከአሰላ መውጫ መነሃሪያ ወጥቶ በስተቀኝ በኩል ወደ ምትገኝ አንድ ሻይ ቤት አመራ፡፡

አንድን ጠቆር ያለ ወጣት ነው፡፡ ቁመተ አጭር ዳክየ፡፡ የተከረከመ ጉቶ ይመስላል፡፡ ፀጉሩ በአቧራ የተለወሰ ፣ የተንጨበረረ ፣ ቁጥርጥር ፀጉራም፡፡

ከመነሃሪያ ውጭ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው የቀረው እያለ ይለፈልፋል፡፡
ቀኝ እግሩን አንስቶ ግራ እግሩን አልደገመም፡፡ ድሬ አንድ ሰው የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ ወደ ፊት መራመዱን ትቶ ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ ብስጭትና ንዴቱ ለቀቀው፡፡ እየተጣደፈ ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው እያለ ወደ ሚለፈልፈው ደላላ ተጠጋ፡፡ እኔ አለሁ ድሬ አለ፡፡

"ኧረ! ድሬ ነህ ና ተከተለኝ፡፡ አሁን ልንወጣ ነው"፡፡ ብሎት ወደ መኪናው ወሰደው፡፡ ሂሳብ ክፈልና እዚህኛው መኪና ግባ አለው፡፡

ለመሳፈሪያ ብሎ ለይቶ ካስቀመጠው የሱሪ ኪሱ አውጥቶ ከፈለ፡፡ ደረሰኝ ግን አልተቀበለም፡፡ ደላላው ገንዘቡን ተቀብሎት ታጠፈ፡፡

ያሬድ ግባ ወደ ተባለበት አውቶቢስ ገባ፡፡ እውነትም አንድ ሰው ብቻ ነበር የቀረው፡፡ አንድ ተሳፋሪ ቀርቷት የነበረች ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡

እረዳቱ የአውቶቢሱን በር ዘጋ፡፡ ሹፌሩ መኪናውን አስነሳ፡፡ ጉዞው ከአዳማ ወደ ድሬደዋ ተጀመረ፡፡

"ምዕመናን ሂሳብ ወጣ! ወጣ! አድርጉ አለ እረዳቱ፡፡ እየተቀበለ ያሬድ ጋር ደረሰ፡፡

"ለእኔ ደረሰኝ ብቻ ስጠኝ ገንዘቡን ከፍያለሁ አለ ያሬድ፡፡

"ለማነው የከፈልከው አለ እረዳቱ?፡፡

"ሊያሳፍረኝ ይዞኝ ለመጣው ሰውየ ፡፡

"አባት የከፈሉት ሂሳብ ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ አሁን ለእኔ ይክፈሉኝ አለ፡፡ ትህትና በተሞላበት ንግግር፡፡

"አልከፍልም" አለ ያሬድ፡፡

"እባክዎት ይክፈሉኝ" አባት ቢልም ፤ ምንም ቢል ያሬድ ሊሰማ አልቻለም፡፡ ክፈል ፣ ጭቅጭቅና ንትርኩ ተባባሰ፡፡ ሹፌር መኪናውን መንዳቱን አቆመ፡፡ በረዳቱና በያሬድ መሃል ጣልቃ ገባ

"ለምንድ ነው የማከፍለው? በነፃ ተሳፍረህ የምትሄደው የአባትህ ፈረስ አደረግከው አለ ሹፌሩ፡፡ በፊቱ ላይ የደም ስሮቹ ተወጣጠሩ፡፡

"የአባቴ ፈረስ ባይሆንም ገንዘብ ከፍየ ነው የተሳፈርኩት፡፡ ያጭበረበራችሁኝ እናንተ ናችሁ፡፡ በማስፈራራት ደግማችሁ ልታስከፍሉኝ ነው? አልከፍልም፡፡ ወደ ህግ እንሄዳለን እንጅ አለ ያሬድ፡፡

ከመኪናው ውስጥ ጎትተው አወጡት፡፡ ሊደበድቡት ተጋበዙ፡፡ ተሳፋሪዎቹ ገላገሏቸው፡፡ ክርክሩና ንትርኩ አላቋረጠም፡፡

አቶ ላንቻ ባልቻ የሚባሉ ከያሬድ ጋር አንድ ወንበር ላይ አብረው ተቀምጠዋል፡፡ ጭቅጭቁ አበሳጭቷቸዋል፡፡ ቶሎ ለመድረስ ያሰቡበት ቦታ እየረፈደባቸው ነው፡፡

"ለረዳቱ በቃ! ተወው እኔ እከፍለዋለሁ፡፡ ንትርኩን ተውና ቶሎ ቶሎ ንዳ፡፡ እውነት ይሄ ሰውዬ ሳይከፍልም የተከራከረ አይመስለኝም፡፡ የአዳማ ሞጭላፋ ጩልሌዎች ጨልፈውት ይሆናል፡፡ እንኳን የክፍለ ሃገር ሰው አግኝተው አይደለም ወፍ ከሰማይ ያወርዳሉ፡፡ ይዞት የመጣው ደላላ የሻይ ሲጠይቀው የመሳፈሪያውን ሂሳብ ተቀብሎት ላፍ ብሎ ይሆናል፡፡ ብለው የሚያጨቃጭቀውን የያሬድን ሂሳብ ከደረት ሸሚዝ ኪሳቸው አውጥተው ከፈሉለት፡፡

"አጭበርብረውኝ ነው፡፡ እንጅ እኔ እኮ ገንዘቡን ከፍያቸዋለሁ አባት አለ፡፡ እንደ መፀፀት ብሎ፡፡

"ያጭበረበሩህ ባለ መኪናዎቹ አይደሉም፡፡ ዱርዬዎች ናቸው፡፡ አንተም መኪና ውስጥ ሳትገባ መክፈል አልነበረብህም፡፡ ወይም ስትከፍል ደረሰኝ መቀበል ነበረብህ::

"እኔ መቼ አወኩ፡፡ እንደዚህ መሆኑን የት አውቄ፡፡ የእነሱ አጋዥ መስሎኝ ነው፡፡ የከፈልኩት፡፡ መቼ ሰባራ ሳንቲም አቀምሰው ነበር፡፡ ብሎ ስህተቱ የራሱ መሆኑን አውቆ የከፈሉለትን ገንዘብ ሊከፍል ከኪሱ አወጣ፡፡
አባት አመሰግናለሁ ገንዘቡን እንኩ አለ፡፡ በፊቱ ላይ የይቅርታ ምልክት እያሳየ፡፡

ገንዘቡን ለመቀበል አልፈለጉም፡፡ ተወው ችግር የለውም፡፡ አንተም ተወስዶብህ ነው፡፡ እንጅ አውቀህ አይደለም፡፡ አሁን ያወጣኸውን ገንዘብ መልሰህ ወደ ኪስህ አስገባ እኔ አልቀበልም አሉ አቶ ላንቻ፡፡

አቶ ላንቻ ከድሬደዋ አዳማ እየተመላለሱ የሚነግዱ የታወቁ ቱጃር አልባሳ ነጋዴ ናቸው፡፡ ጨዋታቸው እየሞቀ ሄደ፡፡ አቶ ላንቻ ከተደገፉበት ወንበር ቀና አሉ፡፡

"ስምህን ማን አልከኝ"? አሉት፡፡ መጀመሪያ ነግሯቸው በጭዋታ የተነሳ ዘንግተውት ይሁን ተመስሎባቸው ደግመው መጠየቃቸው፡፡

"ያሬድ እባላለሁ አለ፡፡ ፊቱን ወደ አቶ ላንቻ መለስ አድርጎ፡፡

"አሁን ወዴት ነው የምትሄደው"? ፡፡

"ወደ ድሬ የምሄደው"፡፡

"እዛው ነዋሪ ነህ ወይስ ለስራ ነው የምትሄደው?፡፡

"አይ! ለስራ ነው፡፡ ነገ እመለሳለሁ፡፡ እቤት ከመቀመጥ ብዬ ትንሽ ሳልባጅ ቢጤ ጀምሬ ነበር፡፡ ሞልቶ ለማይሞላ ነገር ስንት ገዛኸው ዘጠኝ ፤ ስንት ሸጥከው ዘጠኝ ፤ ትርፉስ ምንድነው? ዘጥ ዘጥ እንደሚባለው የበሰለውን ከማጥፋት ውጭ ድካም ነው፡፡ ውጤት የለውም አላቸው፡፡ ንግግሩ የሚያስቅ ስለነበር ፈገግ አደረጋቸው፡፡

አቶ ላንቻ አለመተዋወቅ እንጅ አልባሳት ከሆነ የምትነግደው እኔ አዳማ ድረስ አመጣልህ ነበር አሉ፡፡

"አልባሳት ይነግዳሉ እንዴ? አለ ያሬድ፡፡

"አዎ፤ ነጋዴ ነኝ፡፡ አሁንም አራግፌ እየተመለስኩ ነው፡፡

"ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እንዴው የሰው መተዋወቂያው መንገዱ ብዙ ነው አለ ያሬድ፡፡ ያገናኛቸው አጋጣሚ እያስገረመው፡፡

"ድሬ ደንበኛ አለህ የምትረከብበት"? ፡፡

"ደንበኛ እንኳን የለኝም፡፡ የጀመርኩት ቅርብ ጊዜ ስለሆነ ደንበኛ አላበጀሁም፡፡ ከአሸዋ ሜዳ ነው የምገዛው ፡፡

የዛሬ መገናኘታችን ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ አሁን እየደረስን ስለሆነ መነሃርያ ሳንገባ ወርደን አረፍ ብለን እንነጋገራለን" አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

ከመኪና ወርደው ወደ አንድ ሪስቶራንት አመሩ፡፡ አረፍ ብለው የሚጠጣ ለስላሳ አዘዙ፡፡ በመኪና ላይ የጀመሩትን ጭውውታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

"አዳማ ውስጥ የራስዎ ቡቲክ አሎት እንዴ? አለ ያሬድ፡፡

"የራሴ እንኳን ቡቲክ የለኝም፡፡ አዳማ መነሃሪያ አካባቢ ቢያድግልኝ የሚባል የጅምላ አከፋፋይ ሱቅ አጠገብ የተከራየሁት ቡቲክ አለኝ፡፡ እዛ ነው የምሸጠው፡፡ ቦታውን ነገ አብረን ስንሄድ አሳይሃለሁ፡፡ አሁን እንሂድና እዚህ ድሬ ውስጥ ያለኝን ቡቲክ ላሳይህ፡፡ የሚያስፈልግህንም ገዝተህ እኔ በምጭንበት መኪና ጭነህ ነገ አብረን አንሄዳለን፡፡

ያሬድ ያገናኘውን አጋጣሚ እየመረቀ እንዴው ምን ዓይነት ደግ ሰው ነው፡፡ ያጋጠመኝ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ እያለ "አይደህና ነው፡፡ ለእኔም እዚህ ድረስ ከምለፋ ጥሩና መልካም ነው፡፡ እንዴው ውለታዎን ለመክፈል ያብቃኝ" አለ፡፡ ቀለስለስ እያለ፡፡

"አይ! ምንም ማለት አይደለም፡፡ የራሴም ስራ ነው፡፡ አሁን ከአንተ የምጠብቀው ታማኝ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው"፡፡ ብለውት ሊያሳድሩት ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡

በነጋታው በጥዋት ተነሱ፡፡ በተነጋገሩት መሰረት የሚያስፈልገውን ልብሶች ገዝቶ አብረው ወደ አዳማ ተጓዙ፡፡
👍6410😁1
#አላገባህም


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል ከሰዓታት በፊት የሰርጉን ስፍራ ለቆ መሄድ ነበረበት። ነገር ግን ከፀአዳ ተለይቶ መራመድ አልቻለም። ከሳምንት በፊት በእንጥልጥል የተወውን ጉዳይ መቋጫ ማበጀት አለበት፡፡በልቡ ጭራበት የሄደችው ሲኦል እሳት እየተንበለበለች መላ ሰውነቱ ትኩሳት እንደለቀቀችበት ነው…እንዴትም አድርጎ እንዴት  እሱን  ማስተካከል ያስፈልገዋል. ዛሬ ማታ።

ፀአዳ ለዘሚካኤል ቃል በገባችለት መሰረት ወደእሱ ለመሄድ ከውስጥ ወደአዳራሹ በተመለሰች ጊዜ በብዙ ውብና አማላይ ሴቶች ተከቦ ሲያውካካ ተመለከተችውና  ከመንገዱ  ለመራቅ ወሰነች - ባየችው ነገር ክፍት ነው ያላት…እንደዛ የማድረግ መብት የላትም ..ግን   ከማንም ለመፎካከርና እሱን ሻሞ ለመሻማት ምንም አይነት እቅድ የላትም..እና እግሯና ወደኃላ ጎተተችና  የአስተባባሪነቱን ስራዋን በትኩረት መስራቷን ጀመረች፡፡እራሷን ማሞኘት አልፈለገችም።

እሱ በእጁ ይዞ የነበረውን ባዶ ብርጭቆ በአጠገቡ በሚያልፈው አስተናጋጅ ትሪ ላይ አስቀመጠና ዓይኑን ወደ ህዝቡ መሀከል አንከራተተ። የሙሽሮቹ ዋና ተጠሪ እንደመሆኗ   መጠን መጥፋት አልቻለችም። ግን   እሱን ከእይታዋ ለማስወገድ እየሞከረች እንደሆነ ያስታውቅባታል፡፡‹‹እንደዛ እንድታደርጊማ አልፈቅድልሽም››ሲል ፎከረ፡፡ይሄ በእሱ ልምድ  አዲስ ተሞክሮ ነበር።አንድ በሆነ አጋጣሚ ከንፈሩን የቀመሰች ሴት መልሳ ልታገኘው መከራዋን ስታይና ስትንሰፈሰፍ ነበር የሚያውቀው፣ከከበቡት ልጃገረዶች በዘዴ ተለየና  እሷን ለማግኘት መጣር ጀመረ፡፡

ፀደይ ግራ በመጋባት ያለአላማ ከወዲህ ወዲያ ስትሽከረከር . ድንገት አይን አዲስ ወደእሷ ጠራቻት‹‹እ ምን ፈለግሽ?››

‹‹እኔ ምንም አልፈለኩም… ለምን ከእሱ ትደበቂያለሽ ?››

‹‹ አልተደበቅኩም›› አለች ፀአዳ፡፡

‹‹እሺ እንደዚያ ከሆነ፣ ለምንድነው ከእሱ ጎን ሆነሽ አንድ ብርጭቆ ሻምፓኝ የማትጎነጪው?ምንድነው የሚያስፈራሽ?››

‹‹እንደምታይው እሱ ብቸኛ ሰው አይደለም….ሁሉም ሰው የእሱን እዚህ ሰርግ ላይ ስለመገኘት ነው  የሚያወራው -..እና ወደሰርግ አዳራሹ ከገባበት ደቂቃ አንስቶ በሰው በተለይ በሴቶች እንደተከበበ ነው››

‹‹እና ውድድሩን አላሸንፍም ብለሽ ሰጋሽ …?አዎ  ከባድ ውድድር እንዳለብሽ እኔም ገምታለው።ግን እኮ ይሄንን ለመሰለ ጠንበልል አማቼ… መፋለም መቻል በራሱ እድል ነው?››

‹‹አረ በካሽ…እኔ ፀደይ ነኝ፡፡ ወንድ ለማግኘት ከሌላ ሴት ጋር የምናጠቀው። እንደው እንዳልሺው ፊልሚያ ውስጥ ልግባ ብልስ እሱ ፍላጎት ከሌለው የሚሆን ይመስልሻል…?እናስ ከእነዛ ከከተመዋ አማላይና ስብር ቅንጥስ ከሚሉ ወዳጆችሽ ጎልቼ በአይኑ የምገባ ይመስልሻል...›› በብስጭት ተንዘረዘረች፡፡

‹‹ገባሽ እኮ ..ቀድመሽ በከንፈሩ ገባሽ….ይልቅ አትንቀርፋፊ..በሰርጌ ቀን ካንቺ ጋር ከዚህ በላይ መዳረቅ አልችልም..ባሌ አየጠራኝ ነው፡፡ቻው››ብላት በቆመችበት ጥላት ሄደች፡፡

ፀደይ ለተወሰነ ደቂቃ ድንዘዝዝ አለች‹‹…ምን ላድርግ?››እራሷን ጠየቀች..፡፡ምንም ያህል ችላ ልትለውና ልትርቀው ብትሞክርም ልቧ ግን ልክ እንደማግኔት ወደእሱ እየጎተታት ነው…ወደአለበት  ሄዳ ከሰውዬው ጋር ለመነጋገር ድፍረት አልነበራትም።ፊቷን አዙራም ከእሱ ርቃ ለመሰወር ብትጥርም ከዚህ የበለጠ ተጫማሪ ሳዕታትን ከእሱ ተደብቃ መቆየት እንደማትችል ልቧ ያውቃል፡፡ድንገት ስታየው ብቻውን ሆኖ ስላየችው  ወደኋላ ተመለሰችና ቅዱስን ከሞግዚቷ ተቀብላ በማቀፍ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደእሱ ሄደች፡፡

‹‹እንዴት ነሽ…?መምጣትሽን በናፍቆት ስጠብቅ ነበር››ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ልቧን በቀላሉ ማቅለጥ አቅም ነበራቸው፡፡

‹‹አልደበረህም አይደል?››

‹‹በመጠኑ…ግን በጣም የሚፈልጉትን ነገር ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መጠበቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው….እና አልከፋኝም››አላት፡፡

ዝም አለች…ምን እንደምትል ግራ ተገባች‹‹ከወንድምህ ልጅ ከቅዱስ ጋር ላስተዋውቅህ።››አለችው

ዘሚካኤል  በተራው በዝምታ ተዋጠና  ህፃኑን በትኩረት ማየቱን ቀጠለ። የሆነ የማያውቀው መከፋት ስሜት ውስጡን ሲያተረማምሰው ተሰማው፡፡ህፃኑን እቅፉ የተንጠለጠሉትን ውብ ጉንጮቹን እያገላበጠ ቢሰመው ደስ ይለው ነበር፤አዎ እንደዛ አይነት ፍላጎት ነበር የተሰማው፡፡ግን ከተቀመጠበት መነቃነቅ ሆነ እጆቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡እንዲህ መሆን የለበትም ነበር፡፡እሱ በቤተሰቡ ላይ ያን አይነት መአት ከመድረሱ በፊት በጣም ሰው ወዳጅ በተለይ ዘመድ ለተባለ ሰው ልቡ ትርክክ የሚል በፍቅር የሞላ ልጅ ነበር፡፡ከክስተቱ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ነው የሆነው፡፡ከዘመድ ጋር መነካካት መርዝ እንደመጎንጨት የሚያንገፈግፈው ነገር ሆኖል…ቢሆንም እንዲህ በጮርቃ ህፃን ላይ እንኳን የተለየ አቋም ሊኖረው አይገባም  ነበር፡፡

‹‹አይዞህ አትጨናነቅ..በሂደት ጥሩ አጎቱ ትሆናለህ››አለችው፡፡

‹‹ልጁን በተመለከተ እንደጨነቀኝ እንዴት አወቀች?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

‹‹አሁንም ብቻህን ጥዬህ ልሄድ ነው..ግን አልቆይም..ህፃኑን ለእናቱ አስረክቤ መጣሁ…››

በረጅሙ ተነፈሰ‹‹አዎ እንደዛ ይሻላል..አታስቢ ስለአንቺ እያሰብኩ ጠብቅሻለሁ፡፡››አላት፡፡

ፈገግ አለችለትና ህፃኑን ቅዱስን አቅፋ ተነስታ ሄደች፡፡ከኃላ አይኑን ተክሎ ተመለከታት..አቋሞ ልዩ ነው፡፡ተረከዘ ሎሚ የምትባል አይነት ነች..እንዲህ አይነት እግር ያላት ሴት ከድሮውም በጣም ነው የምትማርከው…ደግሞ ከሁሉም በላይ እሱ ጋር ከሚመላለሱት ሴቶች ተቃራኒ በሆነ መልኩ ምንም አይነት መዋቢያና መኳኳያ አትጠቀምም…ለምን እንደሆነ ሊገባው አልቻለም…ብትጠቀም እኮ የበለጠ ውብ ትሆን ነበር?››ሲል አሰበ፡፡‹‹ግን አንኳንም አልተጠቀመች››ሲል ደመደመ፡፡

ልጁን ለሞግዚቷ አስረክባ ብቻዋን  ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ የወንድሙን ሚስት አስከትላ መጣች፡፡

አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል… በመምጣትህ በጣም ደስ ብሎናል … ዛሬ ማታ ቤታችን በተዘጋጀው የእራት ግብዣ  ላይ ብትገኝ እንዴት ደስ ይለናል መሰለህ …ግን ምቾት የማይሰማህ  ከሆነ እንረዳሀለን….እዚህ ስለመጣህ እራሱ በእውነት በጣም ደስተኛ አድርገሀናል….ሰርጋችንም የማይረሳና የታደመው ሰው ሁሉ መቼም የሚያስታወስው እንዲሆን አድርገሀል ።››

ዘሚካኤል ደቂቃ ወስዶ እንደማሰብ ሲያደርግ ፀአዳ ጣልቃ ገብታ‹‹እባክህ እሺ ብለህ ቆይ…አይዞህ እንደአሁኑ  ጣል ጣል አናደርግህም…ቃል እገባልሀለው››አለችው፡፡

ንግግሯን ስታጠናቅቅ አዲስአለምም ሆነች ዘሚካኤል አፍጥጠው እየተመለከቷት ነበር…‹‹ምንድነው የሚያስቀበጥረኝ ?››ስትል በውስጧ እራሷን ወቀሰች፡፡

ዘሚካኤል መናገር ጀመረ‹‹እሺ እቆያለው››ሲል ተናገረ፡፡

አዲስአለም ፊት በደስታ በራ‹‹አመሰግናለው..በቃ አሁን ጥያችሁ ልሂድ …አብረሽው ቆይና ይዘሽውን ነይ››አለችና ተመልሳ ሄደች፡፡

ፀአዳ ከእፍረቷ ሳትላቀቅ በዝግታ ተቀመጠችና፡፡‹‹እሺ ትላለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››አለችው፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር እኔም እሺ እላለው የሚል ግምት አልነበረኝም….ቃልሽን አምኜ ነው እሺ ያልኩት››አላት፡፡

‹‹ማለት የምን ቃል?››

‹‹እንደእስካሁኑ  ብቻህን በመተው እንድትደበር አላደርግህም…ከመጀመሪያው እስከፍጻሜው ከጎንህ አልለይም…›ብለሽ  የገባሽልኝን ቃል ነዋ››

‹‹አንተ ይሄን ሁሉ መቼ ነው የተናገርኩት.››

‹‹.አሁን ከደቂቃዎች በፊት››

‹‹ይሁን..ለማንኛውም ማትቆጭበት ውሳኔ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው››
👍639🥰2