አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

..ፊሬንዜ ውብ ከተማ ናት፤ የነጻንቴ የነሚኪኤል አንጀሎ ከተማ!

አንዲት ትንሽ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ስንበላ ነበር፡፡ ሲልቪ
ምግቧን ረስታ ወደ ኋላዬ በኩል ትኩር ብላ ማየት ጀመረች።
ሳይታወቃት በግራ እጂ ፀጉሯን አስተካከለች ብቻ መስተካከል
አያስፈልገውም ነበር። ገባኝ። የምትጎመጀው ወንድ አይታ መሆን አለበት። ሹካና ቢላዋን ቁጭ አድርጋ ወይን አንስታ ፉት አለችና፣ ብርጭቆውን መልሳ እንደማስቀመጥ፣ በእጆቿ ውስጥ በዝግታ እያሽከረከረችው ወደዚያው ወደ ኋላዬ ማየቷን ቀጠለች። ቀይ ከንፈሮቿ ገርበብ፣ በወይን ረጠብ ብለው ያስጎመጃሉ

እሷ ወደዚያ ስታይ እኔ እሷን ስመለከት፣ ቆንጆ ፊቷ ቀስ ብሎ
ፈገግ አለ፤ ሰማያዊ ኣይኖቿ ስልምልም ማለት ጀመሩ። ምኞቱ
ውስጤ ሲያድግ ተሰማኝ፡፡ አይኖቿ ከአይኖቼ ጋር ተጋጠሙ፣ ፊቷ መቅላት ጀመረ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ። ሰውየው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ፡ ግን ወደኋላ ከተገላመጥኩ ነገሩ ይበላሻል፣ ስለዚህ ተውኩት

«ፍሬ ይምጣልሽ?» አልኳት
«የለም በቃኝ። አንተ ብላ »
«እኔም በቅቶኛል»
«እንግዲያው እንሂድ?» አለችኝ፣ ወደ ቅድሙ በኩል እያየች
ስንወጣ እሷ ታተኩርበት ወደነበረው በኩል ተመለከትኩ፡፡
በየጠረጴዛው የተበታተኑ አንድ አምስት ወንዶች አሉ፡ የትኛው
ፍላጎቷን እንደ ቀሰቀሰ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግን ፍላጐቷ በሀይል ተቀስቅሷል። አልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን አጠፋችው፣ እየተንገበገበች አቀፈችኝ፤ በመጨረሻ ላይ በእንግሊዝኛ ቃዥች

«Please, my lord! Please, have mercy!

ሌላ ሰው ሆኜ፣ ግን ማን እንደሆንኩ ሳላውቅ፣ በቅንዝርና
በቅናት እየተቃጠልኩ፣ ጥልቅ የሆነ ስጋዊ ደስታን ተደሰትኩ።
በነጋታው ቀኝ ጡቷን እያመማት ዋለ። ሳይታወቀኝ ጨፍልቄው
ኖሯል በሌላ ቀን፣ «ማን ሆኜ ነበር?» አልኳት። ስንበላ በስተኋላዬ አንድ ሰውዬ እይታ ኖሯል። «ልክ ስመ ጥሩውን ባለቅኔ ሎርድ ሳይረንን ይመስል ነበር አለችኝ እንደዚሀ ስንል፣ እሷ ደስ የሚላትን ወንድ ስታይ፤ እኔ በጭለማ እሱን እየሆንኩ ሳቅፋት እሷ ስትቃዥ፣ እኔ ስነክሳት ስጨፈልቃት፣ እንደዚህ ስንል፣ በሰማያዊ, አይኖቿ ብርሀንና በሰፊ አፏ ሳቅ እያሞቀችኝ፣ በውብ ወጣት ገላዋ እያቃጠለችኝ፡የጣልያንን ከተማዎች እያዞረችኝ «Je men fous» አያለች አያሳቀችኝ፣ እንደዚህ ስንል የበጋው እረፍት ወደ ማለቂያው ተቃረበ፡፡ ከፊሬንዜ ሮማ
ከሮማ ናፖሊ፤ ከናፖሊ ኒስ (ፈረንሳይ) ከኒስ ማርሰይ ተጓዝን።

ከማርሰይ እሷ ቤቶቿን ጥየቃ ፓሪስ ሄደች፡፡ ባቡር ጣቢያው
ሄጄ ስሸኛት ልክ የዛሬ ዘጠኝ ቀን ማክሰኞ ኤክስ እገባለሁ፤ ማታ
ቤቴ እጠብቅሀለሁ» አለችኝ
የሲልቪ ናፍቆት የሚገድለኝ መስሎኝ፤ ዘጠኝ ቀን ሙሉ
እንዴት ሊያልፍልኝ ነው? እያልኩ ስሰጋ ነበር፡፡ ግን ባቡሩ ይዟት
እንደሄደ፣ በሀዘን ፈንታ እፎይታ ተሰማኝ፡፡ ማታ አልጋ ውስጥ
ገብቼ ብቻዬን እንደ ልቤ ስገላበጥ፣ ብቸኝነት ሳይሆን ምቾት ተሰማኝ፡፡ ምቾቴ በደምብ እንዲታወቀኝ ስል በብዙ ተገላበጠኩ።ጧት ስነቃ ሲልቪ የለችም፡ ብቻዬን ነኝ፡፡ በናፍቆት ፈንታ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሲልቪ ሰልችታኝ ኖሯል? ወይስ ከሰው ጋር ለመኖር አልተፈጠርኩም? ሊገባኝ አልቻለም

ኤክስ ሄጄ ሲቴ (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አንድ የመኝታ ክፍል
ተቀበልኩ፡ ሁለተኛው አመት ወደ መጀመሩ ነበር ጧት ስነሳ በመስኮቱ ደማቅ ሰማያዊ የሆነ ንፁህ ሰማይ ታየኝ።ደስ አለኝ። ሳይታወቀኝ የኤክስ ውብ ሰማይ ናፍቆኝ ኖሯል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባህራም ከቅርብ

ኤክስ እንደተመለስኩ መጀመሪያ ያገኘሁት ተካን ነበር፡፡ ያው
እንደ ልማዱ ጥፍሩን እየነከሰ፣ የት ነበርክ? ከማን ጋር ነበርክ? ምን
አደረግክ? ምን አየህ? እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ፡፡ ግን ሳየው የጥርሱ መበለዝ የቀነሰ መሰለኝ፡፡ አፉም አልገማኝም፡፡ ጊዜው ከእራት በኋላ ነበር፤ ና ቡና ላጠጣህ ብሎ ወደ ክፍሉ ወሰደኝ፡፡ ቤቱ በጭራሽ
አይገማም!

እንግዲህ፣ የዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤቶች ባለ ሶስት ፎቅ
ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ለሚገኙት ሰላሳ ያህል ክፍሎች የጋራ የሆኑ አንድ የገላ መታጠቢያ ክፍልና፣ አጠገቡ ደግሞ (ልክ ደረጃው መጨረሻ ላይ) አንድ የቡና ማፍያ ምድጃ ያለው ክፍል አላቸው።ተካ ቡናውን ሊጥድ ወደ ማፍያው ክፍል ሲሄድ እኔ የሱን መኝታ ክፍል ተመለከትኩ፡፡ ንፁህ ነው። ፊት መታጠቢያው ዘንድ፡ ግማሹ ያለቀ ኮልጌት የጥርስ ሳሙናና አንድ የጥርስ ብሩሽ አለ። ተካ ጥርሱን ይቦርሻል! ምን ነካው?. ምን ይነካዋል? ያው
የተለመደው መሆን አለበታ! አንድን ጎረምሳ ጥርሱን ሊያስቦርሸው የሚችል ምንድነው? ሴት አይደለችም? ግምቴ ልክ ይሆን? ልክ
መሆን አለበት። አለዚያ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?

አንገቴን በበሩ ብቅ አድርጌ አየሁ። ጨለም ያለው ረዥም
መተላለፊያ ኮሪዶር ባዶውን ነው፡፡ ኮሪዶሩ መጨረሻ ላይ ያለው
የቡና ማፍያ ክፍል ተዘግቷል። ተካ ገና ቡናውን በመጣድ ላይ ነው
ማለት ነው። ጊዜ አለኝ፡፡ በሩን ዘጋሁ፡፡ ቶሎ ወደ አልጋው ራመድ
አልኩ፡፡ አንሶላውን ላመሉ ገለጥ ከደረግኩት። ጎምበስ ብዬ ትራሱን
አሸተተኩት፡፡ የሴት ጠረን። ያለጥርጥር። እንዴት ያለች ትሆን?
ቶሎ አልጋውን አስተካከልኩና፣ ቁጭ ብዬ ጋዜጣ እያነበብኩ
ቆየሁት ቡና ከጠጣን በኋላ ሊሎቹን ሀበሾች ፍለጋ ወጣን
ተካ «ተመስገንን ግን አታገኘውም» አለኝ «ወደ ፓሪስ
ተዛውሯል። ለምን እንደተዛወረ ታውቃለህ?»
«ለምንድነው?» አልኩት
«ነጭ ሴት ሰለቸኝ አለ።»
«ምን?
«ጥቁር ሴት ካላገኘሁ ልማር አልችልም አለ፡፡ እዚህ ኤክስ
ውስጥ ሁለት ጥቁር ሴት ብቻ ነው ያለው፡ ሁለቱም አስቀያሚ
ናቸው። ስለዚህ ፓሪስ መሄዴ ነው:: ቢሆን እግዜር ብሎ አንዲት
ሀበሻ ልጅ ታጋጥመኝ ይሆናል፡፡ ባይሆን ደሞ ሌላ ጥቁር ሴት
አላጣም፣ ብሎ ሄዴ»
ተመስገን እውነቱን ነው። ኤክስ ውስጥ ጥቁር ሴት አይገኝም
ሀበሻ ሴት ይናፍቃል። ያገራችን ሴቶች ትዝ ይሉናል፤
አነጋገራቸው፣ አሳሳቃቸው፣ መሽኮርመማቸው ይናፍቀናል፡ ጥቁር ቆዳቸው፣ ነጭ ጥርሳቸው እንቅልፍ ይነሳናል፡ በሀሳባችን
አረ ንሺ» ሲሉ ይሰማናል።

አንዳንድ ጊዜ ተሰብስበን ስለነሱ እናወራለን፡፡ ናፍቆት ሲበዛብን
እየሳቅን እየጮህን እንዘፍናለን
«አንቺ ጥቁር ድንጋይ ፍቅር አይገባሽ በሰው አገር ሆኜ ተቃጠልኩልሽ»
ሉልሰገድማ “ልጆችዬ፣ አብረን አንዲት እምስ የተቀረፀባት ሻማ ለቁልቢው እናብራለትና » አለን እምስ በፖስታ ላክልን፣
መጋረጃ እናስገባልሀለን፣ እንበለው፡፡ እውነቴን'ኮ ነው! ያገሩ ልጆች ነን፡ ይሰማናል። ኧረ እናታችሁን! ይሄ ምኑ ያስቃል?»

እኔና ተካ ሀበሾቹን ሉልሰገድ ቤት እገኘናቸው:: ባህራምና
አንድ ሌላ ኢራናዊ አብረዋቸው አሉ፡፡ ይህ ሌላ ኢራናዊ ጀምሺድ
ይባላል። ረዥም መልከ ቀና ወጣት። ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ
ከቢራቢሮ ክራቫት ጋር ለብሷል። ግብዣ ለመሄድ የተዘጋጀ
ይመስሳል። ረዘም ያላ ፈት፡ ቀጥ ያለ ረዥም አፍንጫ። ከሀር
መሳይ ውብ ቅንድቦቹ በታች ሰማያዊ ትንንሽ አይኖች ሁልጊዜ
ይጨፍራሉ፡፡ ብርሀን ሳቅ፣ ብልጠት የሚፈራረቅባቸው፣ ህይወት የሞላባቸው አይኖች ናቸው፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት፣ ጀምስድ ፈረንሳይ አገር ከመጣ አመት አልፎታል። ታድያ ቢበዛ ስምንት መቶ የፈረንሳይኛ ቃላት ቢያውቅ ነው (የቋንቋ ስጦታ የለውም) ግን እነዚህ ስምንት መቶ ቃላት ለንግግር ኮርተው ይበቁታል። ምክንያቱም ቀጭን ኮሚክ ድምፁና ትንንሽ ብልጮ አይኖቹ፣ ያለ ቃላትም ቢሆን የፈለገውን ይገልፁለታል
👍131
#ትኩሳት


#ክፍል_አስር


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ምጥ


ባህራም በሰኔ ወር የወደቀውን ፈተና እንደገና ለመፈተን
ማጥናት ጀመረ። የራሱ መኝታ ቤት ያረጀና የከረከሰ ሆኖ፣ ደምበኛ ጠረጴዛና ወምበር የለውም፡፡ እዚያ ማጥናት አልቻለም፡፡የዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍት እየሄደ እንዳያጠና፣ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ውር ውር እያሉ ሀሳቡን ይሰርቁታል። ከቀኙ፣ ከግራው፣ከፊቱ፣ ከኋላው ደሞ አስር፣ አስራ አምስት ፍራንክ ያበደሩት ሰዎች ያዩታል፣ ይከብዱታል። እነሉልሰገድ ቤት ሄዶ እንዳያጠና ወሬና
ጫጫታ ይበዛል። እኔ ቤት እየመጣ ያጠና ጀመር። ከሰአት በኋላ ሲኒማ እሄድለታለሁ፣ ሲያጠና ይውላል። ማታ እፅፋለሁ ወይም አነባለሁ፣ ሲያጠና ወይም የማኦ ትዜ ቱንግን መፃህፍት ሲያነብ ያመሻል፡፡ ጧት ግን ምንም ያህል አይሰራም፡፡ ወሬ እናበዛለን።

ጧት ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ መጥቶ፣ በቀስታ በሩን ከፍቶ
ገብቶ፣ ጠረጴዛው ዘንድ ተቀምጦ ሲሰራ ይቆያል። ስነቃ “Bon jour
እለዋለሁ። Bon jour ብሎኝ ቡና ይጥድና ስራውን ይቀጥላል።
አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ትላንት የፃፍኩትን እመለካከታለሁ፤
አርማለሁ፣ እሰርዛለሁ፣ እቀዳለሁ። ሙሉ ሰአት ሲሆን ባህራም «አንድ ጊዜ ዜና ብንሰማ ይረብሽሀል?» ይለኛል፡፡ (የፈረንሳይ ራዲዮ በየሰአቱ አጫጭር ዜና ያሰራጫል) ራስጌዬ ያለችውን ራዲዮ እከፍታታለሁ። ባህራም ያፈላውን ቡና በዱቄት ወተት እየጠጣን ስለቪየትናም ወሬ እንሰማለን። ቪየትኮንግ የደፈጣ አሜሪካኖቹን አጥቅተዋቸው እንደሆን ባህራም ደስ ይለውና ደስታው
አላስጠና ይለዋል። መናገር ይጀምራል።ቬየትኮጎቹ ድል
ማድረጋቸው አይቀርም ይላል፡፡ ንግግሩ ቀስ ብሎ ወደ ኢራን
ይወሳስደዋል።ስለኢራን ሊነግረኝ ይጀምራል። ስለኢራን፣
ስለኮሙኒዝም፣ ስለማኦ ትዜ ቱንግ፣ ስለአሜሪካን ወራሪነትና
አጥቂነት፣ ስለካፒታሊዝም ስናወራ እንቆይና፡ ሙሉ ሰአት ሲደርስ
እንደገና ራዲዮ እንከፍታለን፡፡ ዜናው ያስደስተዋል ወይም
ያበሳጨዋል። ወሬያችንን እንቀጥላለን። የምሳ ሰአት እስኪደርስ እናወራለን፣ እናወራለን ማለት፣ በአብዛኛው እሱ ሲያወራ እኔ አዳምጠዋለሁ፤ እንዳንድ ጊዜ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ፡፡ የነገረኝን
እያንዳንዱን ማታ ልተኛ ስል አንድ ትልቅዬ ደብተር ውስጥ አሰፍረው ነበር

አሁን ያንን ደብተር ሳነበው ባህራም ይታየኛል፡፡ እኔ አልጋ
ውስጥ ትራስ ተደግፌ ቁጭ ብዬ፡ እሱ በሽተኛ ሊጠይቅ የመጣ
ይመስል አጠገቤ ወምበር ላይ ተቀምጦ፣ በብልህ ቡናማ አይኖቹ
እያየኝ፣ ፀጉራም እጆቹን በብዙ እያንቀሳቀሰ፣ በወፍራም ልዝብ
ድምፁና በተሰባበረ ፈረንሳይኛው ሲያወራልኝ፣ ቁልጭ ብሎ
ይታየኛል

ወሬው አንድ መስመር ይዞ አይሄድም። ኢራን፣ ኒኮል፣
የባህራም ቤተሰብ፣ የባህራም ጓደኞች፣ ፈረንሳዮች፣ ጥቁሮች፣
ወጣት ኮሙኒስቶች የተባለ የኢራን አገር ማህበር፣ ትምህርት
ቤት፣ ሴቶች፣ ቡሽቲዎች፣ ጋዜጠኞች ብቻ ባህራም ያየውንና
የሰማውን ነገር፣ በህይወቱ የደረሰበትን ወይም በሌሎች ላይ
የደረሰባቸውን ነገር አሳዛኝ ነገር፣ አስደሳች ነገር፣ አስቂኝ ነገር፣
የሆነ ነገር ያወራልኝ ነበር፡፡ ስንቱን ብዬ ልናገረው እችላለሁ?
ጥቂቱን ብቻ ባጭሩ ላስፍረው፣ እንደ ባህራም ካንዱ ወደ ሌላው
እየዘለልኩ. እንደሚከተለው...

አሜሪካኖቹ ይወድቃሉ (ይላል ባህራም) ታያለህ፡፡ ስንቱን ህዝብ
ጨቁነው፣ ስንቱን አገር ፈትፍተው፣ ስንቱን መንግስት ገዝተው
ይችላሉ? አንድ ቀን ይወድቃሉ። እንኳን እንደነሱ ያለ ቂል ፈረስ
ይቅርና፣ እንደ እንግሊዝ ያለ ተንኮለኛ ቀበሮም ወድቋል። ተነስቶ ሌሎች ህዝቦችን
ጨቁኖ መውደቅ የሚቀርለት የለም፡፡ “አሜሪካኖችም ይወድቃሉ፡፡ ይወድቃሉ። ታይቶ የማይታወቅ አወዳደቅ ይወድቃሉ። ያን ጊዜ የአለም ህዝቦች እልል ይላሉ።
በአሜሪካ አግር ተረግጠው ደክመው እልል ለማለት ያህል አቅም ያነሳቸው ደሞ እፎይ ይላሉ

አሜሪካኖቹን መጀመሪያ
ሆ ቺ ሚን ከቪየትናም ያባርራቸዋል::ቀጥሎ እነ ማኦ ሴቱንግ ወይም ወራሾቹ ከሩቅ ምስራቅ ያስወጡዋቸዋል፡፡ ቀጥሎ እንግዲህ ማን ከየት እንደሚያስወጣቸው አላውቅም:: ብቻ እርግጠኛ ነኝ ያስወጡዋቸዋል። ይህን የሰው አገር ደም ጠጥቶ የወፈረ ቂጣቸውን በካልቾ እየመቱ “Yanked go home!
And stay honte!' (ያንኪ ወደ አገርህ ግባ እና እዚያው ቅር!»)
እያሉ ያስወጡዋቸዋል። ከሰው እድሜ በላይ በኖርኩ! አሜሪካ
ስትወድቅ ለማየት እንድችል ብቻ

ምን ማለትህ ነው? ለምን አልጠላቸውም? አሜሪካኖችን ያልጠላሁ ማንን ልጠላ ነው የነፃነትን ዋጋ እያወቅኩ፣ የተጨቆነ ህዝቤን እየወደድኩ፣ አሜሪካኖችን ካልጠላሁማ ሰው አይደለሁም ማለት ነው። ድንጋይ ነኝ ማለት ነው አሜሪካኖች አንድ የተቀደሰ ተግባር አላቸው:: ይኸውም፣ እባብ ያንዲትን ወፍ እንቁላል መጦ ጨርሶ ቅል ብቻ እንደሚያስቀርላት፣እነሱም ያንዲትን አገር ሀብት መጠው ጨርሰው፣ አፈርና ድንጋይ
ይተዉላታል። የኔን አገር ውሰድ። ዋና ሀብቷ ነዳጅ (ፔትሮል
ነው። ነዳጁን ከመሬት መጦ የሚወስደው አሜሪካ ነው

አንድ ቀን ሞሳዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ተነሳና የኢራን
ሀብት ለኢራን ህዝብ ነው አለ፡፡ አሜሪካኖቹ ተሳስተሀል አሉት፡፡
በቃል ሳይሆን በተግባር፣ የኢራን ሀብት ለአሚሪካ ነው፣ የኢራን
ሀብት ለኢራን ነው ካልክ ኮሙኒስት ነህ ማለት ነው አሉት።
ሲ.አይ.ኤ ልከው ገለበጡት። ሞሳዴግ ተይዞ ሞት ተፈረደበት። ግን ሽማግሌ በመሆኑ፣ የሞት ፍርዱ ወደ እስራት ተሻሻለለት። አሁንም ታስሯል፡፡ የኢራን ሀብት ለአሜሪካኖቹና ለሻህ ነው ያለ ሰው ግን ይሾማል ያሸለማል። ሻህ ማለት በነሲሩስ፣ በነዳርዩሽና በነኻሻር ያዥ ስመ ጥሩ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ኢራንን የሚጨቁን ጋንግስተር ማለት ነው:: አጋዦች አሉት። ህዝቡ ያረሰውን ለመንጠቅ የእርሻ ሚኒስትር ያግዘዋል። ህዝቡ ሲነግድ ከነጋዴው ለመቀማት የንግድ ሚኒስትር
ያግዘዋል። ለልዩ ልዩ አይነት ጭቆና ልዩ ልዩ ሚኒስትር አለው።
ህዝቡ በደስታ እንዲጨቆን፣ ማለትም ተጨቆንኩ ብሎ
እንዳያጉረምርም፣ ፀጥ የሚያሰኙ ያገር ግዛትና የፍርድ ሚኒስትሮች
አሉት

ያሻህን ሻህ ሚኒስትሮች፣ በተለይም የውጭ ጉዳይና ያገር ግዛት ሚኒስትሮቹ፣ ትእዛዛቸውን በቀጥታ ከዋሽንግተን ይቀበላሉ።
ምክንያቱም ኢራን የአሜሪካ የነዳጅ ማእድን ናት። ደሞ ኢራን
የሩሲያ ጎረቤት ስለሆነች፣ አሜሪካኖች በጣም ለኢራን
ይጠነቀቁላታል። አንድ ገበሬ ብዙ የምትታለብ ላም ብትኖረው
አይጠነቀቅላትም?

ሻህ ማለት ውሻ ነው፡፡ አሜሪካኖቹ ኢራንን አርደው ብልቷን ሲያወጡ እፉ ምራቅ እየሞላ በአይኑ ይከተላቸዋል፣ ሳምባ ወይም
ሌላ ቁራጭ ስጋ ጣል ያረጉለታል። እሱ ደሞ ህዝቡን ጨቁኖ
ይይዝላቸዋል። አየህ፣ ህዝቡ ተጨቁኖ ካልተያዘ፣ እንደ ሞሳዴግ
ተነስቶ የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች ይላል። ስለዚህ አሜሪካኖቹ
ለህዝቡ የማይቆረቆር፣ ጥቂት ሚልዮን ብር ቢሰጡት የሚበቃው፣ ህዝቡን ጨቁኖ የሚይዝላቸው ገዥ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ነው ዙፋኑን
የሚጠብቁለት በሞሳዴግ ጊዜ ረብሻ ተነሳ፡፡ ሽህ ሽሽቶ ከአገር ወጣ።አሚሪካኖች መጥተወ «የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች» የሚሉትን የሞሳዴግ ተከታዮች ፈጅተው፣ በዚያውም ያለ የሌለውን ኮሙኒስት አርደው ጨርሰው፣ አገሩን ጸት ካደረጉ በኋላ፣ ና ወደ ዙፋንህ
ተመለስ አሉት፡፡ ወደ ዙፋኑ ተመለሰ
👍22
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ለመሆኑ የትናንቱን ፖሊስ ፍንግል አርገኸው ነበር ለካ
የሮጥከው» አለኝ
«አዎን» አልኩት
«ተነስቶ ቢከተልህስ? እና ካንተ የፈጠነ ሯጭ ቢሆንስ? ወይም
ስትሮጥ ውጋትቢይዝህስ? ወይም ቢተኩስብህስ? ወይ ፊሽካ ቢነፋና
ሌሎች ፖሊሶች ከያለበት ወዳንተ ቢሮጡስ?»

«ታድያ እንዴት ማድረግ ነበረብኝ?» አልኩት
«አታውቅምን ?»
«አላውቅም»
«እንግዲያው ነገ ጧት በአስራ አንድ ተኩል ቤቴ ና....
ከዚያ በኋላ አራት ወር ሙሉ ጧት ጧት ካስራ አንድ ተኩል እስከ
አንድ ተኩል ድረስ የሚያውቀውን ሁሉ አስተማረኝ፡፡ ከሱ እኩል
ከሆንኩ በኋላ፣ አንድ ሌሊት ማጅራት መቺዎች የሚበዙበት
ሰፈር ወሰደኝና እኔ እንግዲህ አላግዝህም፣ ዝም ብዬ ማየት ነው።ይሄ የመጨረሻ ፈተናህ ነው አለኝ

አንድ ቦታ ስድስት ዱርዬዎች ከበቡና ማኑ «ወዲህ በኩል
ያሉት ሁለቱ የኔ ናቹው፣ አራቱን ውሰድ አለኝ በእንግሊዝኛ።
የኔን ሶስቱን አጋደምኳቸው፣ አንዱ ሸሸ። ፈተናዬን አለፍኩ

ግን አንድ ሌሊት አክስ ውስጥ ብቻዬን ስዘዋወር፣ ሶስት
አሜሪካኖች ግድግዳ ላይ ሲፅፍ ይዘውት፣ ሊደበድቡት እንደ ጀመሩ
ድንጋይ በመወርወር አስጥዬዋለሁ። ይህን የአምባጓሮ ችሎታውን ለምን ከነሱ ለማምለጥ አልተጠቀመበትም? ማወቅ ፈለግኩ፣ ግን አልጠየቅኩትም። ከፈለገ እሱ ራሱ እንደሚነግረኝ አውቃለሁ)

ማኑ አንድ ሊላ ነገር አስተኖሮኛል (አለ ባህራም) አየህ፣ ድሮ ሻህ ግርማ ሞገስ ያለው፣ ከነሲሩስ ከነዳርዮሽ የሚስተካከል ንጉስ
መስሎኝ ነበር። እና እየጠላሁትም አከብረው እፈራው ነበር። በማኑ
ቀልድ እየሳቅኩ በማኑ አይን ሳየው ግን ሽህ ምንም ግርማ ሞገስ የለውም። በነዳርዮሽ ዙፋን ላይ ተቀመጠ እንጂ፣ የነዳርዮሽ ደም ወይም ክብር ወይም ጀግንነት የለውም፡፡ የአንበሳ ቆዳ የለበሰ ውሻ ነው

ብኝ እሱን ተወው

አንድ ጊዜ የኮረምሻህር ወደብ ከተማ የሰራተኞች ማርበር
ሰላማዊ ሰልፍና ንግግር ለማድረግ በህግ ተፈቀደለት። የኛ ፓርቲ ላያግዛቸው ወስኖ፣ እኔና ማኑ በባቡር ሄድን፡፡ ስነ ስርአቱ
የሚካሄደው በታጠረ ኳስ ሜዳ ውስጥ ነበር። ቦታ ቦታችንን ይዘን
ንግግሩ የሚደረግበት ሰአት ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው፣ ብዙ ብዙ
ፖሊሶች በትልቁ በር ሲገቡ አየሁ። እንደገቡ ፊታቸው ያገኙትን
በዱላ መጨፍጨፍ ጀመሩ
ማኑን «እንሂድ?» አልኩት
«አንተ ሂድ አለኝ
«አንተስ?» አልኩት
«እኔ ደህና ቦታ እንድይዝና ካለቆቻችን ትእዛዝ ካልመጣ
በስተቀር እንዳልለቅ ታዝዣለሁ»
ይህን ጊዜ ሜዳውን ጩኸትና ትርምስምስ ሞልቶታል
“አለቆቻችን የተፈቀደላቸው መስሏቸው ነበር፡፡ ግን ፈቃዱ
ወጥመድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እዚህ መቆም ምንም ጥቅም የለውም፡፡
«ና እንሂድ» አልኩት
«አልሄድም፡፡ ኮሙኒስት ነኝ። አለቆቼ ሽሽ ካላሉኝ ልሸሽ
አልችልም» አለኝ
«እዚህ መቆምህ ጥቅም የለውማ!» አልኩት
“ምን ታውቃለህ? ይልቅ ሂድ ፖሊሶቹ እዚህ ሊደርሱ ነው።
በወዲያ በኩል ዝለልና አምልጥ» አለኝ
«አንተ ካልሄድክ አልሄድም» አልኩት
«እኔ አለቆቼን እታዘዛለሁ። አንተም አለቃህን ታዘዝ፡፡ አለቃህ
እኔ ነኝ፡፡ በል አሁን ሂድ። ሂድ!» አለኝ ሄድኩ። አጥሩን ልዘል ስል ዘወር ብዬ አየሁት። ዙሪያውን
ፖሊሱና ሰዉ ሲተራመስ ሲከታከት፣ እሱ ሁለት እጆቹን ደረቱ ላይ አጣምሮ እንደ ሀውልት ቆሟል። በአጥሩ ዘለልኩ
ማኑ ፖሊሶቹ ደብድበውት ሶስት ሳምንት ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ
መሀል ጣቱ ተሰብሮ ቀረ። አሁን ሊያጥፈው ኣይችልም
ማኑ እንዴት ኮሙኒስት እንደሆነ ልንገርህ?
አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ ነበረው። ጓደኝየው በጣም ጥሩ
ልጅ ነው:: ቆንጆ ቆንጆ ግጥሞችን ይደርሳል። ግን ድሀ ብጤ ነው።
ከዚህም በላይ እጅግ የተዋበ!

አንድ ቀን የዚህ ልጅ አባት ታሰሩ። በሽተኛ ሚስት፣ ስድስት
ትንንሽ ልጆች ኣሏቸው። እሱ የመጀመሪያ ልጃቸው ነው። አባትየው ታስረው ልጆቹ ምን ይብሉ? ልጁ ጨነቀው። ያባትየውን ጉዳይ የሚከታተለው የፖሊስ ሹም ቢሮ ሄደና እያለቀሰ የቤቱን ችግር ነገረው። ፖሊሱ ደግ ነበር። የልጁ ችግር ገባው። ጉዳዩ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ አባትህን ዝም ብዬ ነፃ ብለቃቸው፣ የበላይ ሹማምንት ይቀጡኛል፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዛሬ ማታ ለእራት ቤቴ ብቅ በልና እንመካከርበታለን» አለው
ሲመሽ ልጁ ፖሊሱ ቤት ሄደ፡፡ እራት ከበሉ በኋላ ፖሊሱ
ልጁን ያሻሽው ጀመር። ልጁ በመጀመሪያ ደነገጠ፤ በኋላ ተቆጣ::ይኸኔ የፖሊሱ ፊት ተለወጠ። ደግ የነበረው በሀይል ክፉ ሆነ፡፡ ረጋ ባለ ድምፅ ልጁን እንዲህ እላው
«አባትህ በኔ እጅ ነው:: ላስገድለውም እችላለሁ፣ ላሳስረውም እችላለሁ፣ ላስፈታውም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ አባትህ ባንተ እጅ ነው
ማለት ነው:: እዚህ ከኔ ጋር ካደርክና ካስደሰትከኝ፣ ነገ አባትህ
ለምሳ ቤቱ ይመጣል፣ ተነገ ወዲያ መስሪያ ቤቱ ይሄዳል፣ በስህተት
መያዙን አስመሰክርለታለሁ፡ ቤቶችህ የሚበሉትን ያገኛሉ። እኔን
እምቢ ካልከኝ ግን አባትህ ወየውለት! ትንንሽ ወንድሞችህና
እህቶችህም ምን እንደሚውጣቸው አላውቅም፡፡ ባንተ አጅ ናቸው።
ሁሉም ባንተ እጅ ነው»
ልጁ እሺ እርስዎ እንዳሉኝ አደርጋለሁ አለ። አባትየው ተፈታ።
መስሪያ ቤቱም ተቀበሉት
ልጅየው ውርደቱን ተሸክሞ መጣና የተፈፀመበትን ግፍ
እያለቀሰ ለማኑ አጫወተው። ምን ባደርግ ይሻለኛል? አለው
አየሀ፣ ሲለያዩ ፖሊሱ ምን ብሎታል «እኔ የተገደልኩ ወይም
የተጎዳሁ እንደሆነ፣ ሁለት ሌሎች የፖሊስ ሹማምንት አሉ፤ ጓደኞቼ
ናቸው፡ ኣንተ እንደጎዳኸኝ ያውቃሉ፤
ስለዚህ አባትህን እነሱ
መልሰው ያሳስሩታል። ያን ጊዜስ አባትህን አያርገኝ፣ ቤቶችህን
አያርገኝ! ስለዚህ በኔ ላይ የበቀል ሀሳብ ባታስብ ጥሩ ነው።
ብሉታል። ልጁ ምን ይሁን? የተዋረደ ክብሩን ሊበቀል አልቻለም።
ግን ውርደቱ ሊረሳ የሚችል አይነት አይደለም። ልጁ አልቻለም።
በዛበት፡፡ ከሚችለው በላይ በዛበት፡ አበደ። አበደ በቃ! እብድ ሆነ።
ቤቶቹ በድህነታቸው ላይ ሀዘን ተጨመረጣቸው:: ደግሞስ ማን
ያውቃል? ኢራንም አንድ ታላቅ ደራሲ ባጭሩ ተቀጨባት ማለት
ይሆናል'ኮ
አይ ኢራን! ስንቱን ጉድ ትችያለሽ! ኢራን ውቢቱ! እንዴት
መሰለችህ! አቤት ህዝቡን ብታውቀው! ቋንቋውን ብትሰማው! አይ ህዝብ! እንደ ምንም ብዬ ከሻህና ከጋንግስተሮቹ ነፃ ባወጣው'ኮ የኢራን ህዝብ በደስታ ሊኖር የሚችል ህዝብ ነው። ክብሩን ልመልስለት ብችል፡ ማንንም ሳይፈራ ሰርቶ ለመብላት ቢችል፤ ህግ ካልጣስ ማንም ሊያስረው እንደማይችል እርግጠኛ ለመሆን ቢችል!
ሻህና አሜሪካኖቹ ሀብቱን ባይነጥቁት! ብቻዬን እንዳልመስልህ! በጭራሽ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ እኔ ያየሁትን ያዩ፣ እንደኔ የሚቆረቆሩ፣ እንደኔ የተናደዱ፣ እንደኔ ደም ለማፍሰስ ዝግጁ የሆኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ኢራናውያን አሉ። አሉ! አሉ!
የሚመራቸውን ይጠብቃሉ! (አለ ባህራም)
ባህራምና እኔ ከተዋወቅን ጀምሮ እስከተለያየን ድረስ ስለኢራን
ያወራልኝ ነበር። ኢራን፣ ኢራን፣ ኢራን። አልሰለቸኝም ግን ይበዛብኝ ነበር። ይልቁንም የአገሩ መበስበስ ያንገሸግሸኝ ነበር፡፡ ሁሉ ነገር በጉቦ ነው። ፖሊሱ፣ ጃኛው፣ አስተማሪው ሳይቀር ጉቦ ይበላል።
👍17🔥2
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...ይህን ሁሉ ሲልና ከአሜሪካኖቹ ጋር ሲከራከር፣ እኔ ዝም ብዬ
እሰማለሁ። ምሳዬን ወይም እራቴን እየበላሁ። አንድ ግዜ ግን ከአንድ ጉረኛ አሜሪካን ጋር ክርክር ገጠመ

ባህራም እንደልማዱ ከሙግቱ ጋር ቀልድና ሳቅ ሊቀላቅል ሞከረ። ከሜሪካኑ ግን በሀይል አምርሮ ስለ አሜሪካን የጦር ሀይል ሲሸልል ፣ ስንት የጦር መርከብ ስንት የጦር አውሮፕላን እንዳላቸው ሲያወራ ፣ እንኳን ሆ ቺ ሚን ክሮስቾብና ማኦ እንደዚሁም ሌሎች ችጋራሞች ኮሚኒስቶች ተሰብስበው ቢመጡ አሜሪካ ብቻዋን ድምጥማጣቸውን እንደምታጠፋቸው የዚህም ማስረጃ በ 61 ዓ.ም የኩባ ፍጥጫ ላይ ኬኔዲ ኮሚኒስቶቹን ፈሳቸውን አስረጭቶ ከኩባ እንዳባረረ እንደዚ እያለ ጉራውን ሲነፋ አበሸቀኝ። ባህራምም መሳቁን ትቶ ዝም ብሎ ይሰማዋል። አሜሪካኑ

«አሁን ብንፈልግ ሆ ቺ ሚኒንና ቪየትኮንጎቹን በአንድ ሳምንት
ውስጥ እናስፈሳቸዋለን!» ሲል፣ ምን እንደነካኝ ሳላውቅ እዚህ ላይ አንድ ነገር አለ አልኩ። እስካሁን አንድ ቃል ሳልተነፍስ ስለቆየሁ፣ ባህራምም፣ አሜሪካኑም፣ ሌሎቹም ገበታችን ላይ የነበሩት፣ ወደኔ አዩ። አጭር ዝምታ

ታሪክን ብናስታውስ» አልኩ በ480 አመተ አለም፣ ብዛቱ በሚሊዮን የሚገመት የፋርስ ጦር ስራዊት ግሪኮችን ለመውረር መጣ። ቴርሞፒሌ ላይ ሌዎኒዳስ የተባለው የስፓርታ ንጉስ አራት
መቶ ወታደሮቹን አሰልፎ ሲጠብቅ፣ ከፋርስ ንጉስ ወይም ከጦር አበጋዙ እንዲህ የሚል ማስፈራሪያ ደረሰው። 'እጅህን ብትሰጥ ይሻልሀል፡፡ የኛ ቀስተኞች ሲተኩሱ፣ ፍላፃዎቹ ከመብዛታቸው
የተነሳ፣ ፀሀይዋን ይሸፍኗታል፡፡
እና ሌዎኒዳስ ምን አለ ይመስላችኋል?»

አሜሪካኑ «ምን አለ?» አለኝ

«መልካም ነው:: እኔና አራት መቶዎቼም ጥላ ውስጥ ሆነን
ብንዋጋ እንመርጣለን» አለ

ዝም አሉ፡፡ የምግብ ቤቱ ጩኸት ከቦናል

ባህራም «ቀጥል» ኣለኝ
«ምን እቀጥላለሁ? ታውቁታላችሁኮ። ሌዎኒዳስና አራት መቶው አለቁ፡፡ ሆኖም ግን የፋርስን ቁጥር-የለሽ ሰራዊት ገትረው በመያዛቸው የውጊያው ሚዛን በነሌዎኒዳስ መስዋእትነት ወደነሱ ስላደላ፣ ግሪኮቹ ወራሪውን ሰራዊት ድል አድርገው አባረሩት። ታድያ በጦር ብዛት ቢሆን ኖሮ፣ ፋርስ ያን ጊዜ የአለምን ጦር በሙሉ ሊያሸንፍ ይችል ነበር። ግን የሰው ልጅ ለነፃነት ሲዋጋ፣ በጦር መሳሪያ ብቻ ሳይሆን በወኔው፣ በንዴቱ፣ በወንድነቱ ጭምር ስለሚዋጋ፣ ማንም ትልቅ ጦር አይችለውም። ለዚህ ነው እነሆቺሚን ሊሸነፉ የማይችሉት፡፡»

ይህን ጊዜ ምሳችንን ጨርሰን ስለነበረ ባህራም እየሳቀ
አሜሪካኑን «ለዚህ መልስ ለማግኘት አትሞክር። እውነት ስለሆነ መልስ አይገኝለትም» አለው ይልቅ ለኬነዲ ሀቁን ንገረው። እና አንድ ሌላ ነገር አለ ለኬነዲ መንገር ያለብህ፡፡ ማኦ የቻይናን ህዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጅ ብሎ ማዘዙን ታውቅ የለ? ደሞ የቻይና ህዝብ በማኦ ትእዛዝ ዋና በመማር ላይ ይገኛል፡፡ በየቀኑ ሰባት ሚልዮን ቻይናዎች የዋና ልምምድ ያደርጋሉ። አሮጊትና ሽማግሌው ባኞ ውስጥ ይዋኛል። ልምምዳቸውን ከጨረሱ በኋላ
እንግዲህ ምን እንደሚያደርጉ ታውቃለህ? ማኦ እየመራቸው
የፓሲፊክን ውቅያኖስ በዋና ያቋርጡና፣ እናንተን በአለንጋ አርባ
ገርፈው ሲያበቁ፣ አሻንጉሊቶቻችሁን በሙሉ ይቀሟችኋል። ጥሩ ልጆች የሆናችሁ እንደሆነ፣ አሻንጉሊቶቻችሁን እንመልስላችኋልን፡
አለዚያ ግን መጫወቻ ታጣላችሁ፡፡ ልባርጉ» ብለዋችሁ ሲያበቁ፣
ወደአገራቸው ተመልሰው በሰላም ይኖራሉ። ይህን ለኪነዲ ንገረው
አለውና እኔን እንሂድ አለኝ። አሜሪካ ለመሳቅም አልቻለ፣
ለመናደድም አልቻለ። ግራ ገብቶት ባህራምን አየው
እኔና ባሀራም ትተነው ከምግብ ቤቱ ወጣን። መኝታ ቤት
ሄደን ቡና ከጠጣን በኋላ፣ እንዲያጠና ወይም ስለሪቮሉሽን
እንዲያነብ ትቼው ወጥቼ ሲኒማ ለመግባት ወደ ከ ሜሪብ በኩል
አመራሁ ግን ሲኒማ አልገባሁም፡፡ በካፈ ዶርቢቴል በር ሳልፍ፣ ውስጥ ሲልቪን አየኋት:: ፊቷን ወደበር በኩል አርጋ ተቀምጣ ጋዜጣ ስታነብ ነበር፣ አየችኝ። የፈገግታዋን ወሰት ረስቼው ኖሯል፤ አሁን ሳየው በጣም ደስ አለኝ፡፡ ወደኔ መጣች። ስትራመድ እንገቷን እያወዛወዘች ስለሆነ፣ ከረዥም ነጭ አንገቷ በስተኋላ የተለቀቀው ጥቁር ሀር ፀጉሯ ዥው ዥው ይጫወታል፡፡ ይህንንም ረስቼው ኖሯል። መጣችና ጉንጬን ስማኝ

«ከነገ ወድያ ነበር ልመጣ ያቀድኩት፡ ግን በሀይል ናፈቅከኝ-
አለችኝ፡፡ እሷ ስትናገረው ፈረንሳይኛው መጣፈጡ! ወደ ቤቷ በኩል እየተራመድን፡

“እንኳን መጣሽ! በሀይል ናፍቀሽኝ ነበር» አልኳት

እንደ ልማዷ «ዣማንፉ» ሳቋን እያሳቀች እኔን የምታስረሳን
ሴት አላገኝህም? አለችኝ፡፡ እንዳላገኘው ታውቃለች። መቸም
ኣንደማላገኝ እርግጠኛ ነች።

«ሴት የሚሉት ነገር ዘወር ብዬም አላየሁ» አልኳት
“አንግዲያው ምን ስትሰራ ሰነበትክ?» ጫማዋ መንገዱን ኳ! ኳ! ሲያረገው ይሰማኛል፡ ከጎኔ ድምፅዋ ይሰማኛል፣ ሰፊ አፏ ላይ ውብ ፈገግታዋ ይታየኛል፣ ደስታ ይሰማኛል

«ሲኒማ ሳይ፡፡ እና ከባህራም ጋር ሳወራ»

«ምን ምን አወራችሁ?»
«ኦ --! ብዙ ነው»
«ንገረኝ»
«ጊዜ የለኝም፡፡ ዛሬ ካንቺ ጋራ ማውራት አልፈልግም» አልኳት
ምኞቱ ውስጤ ማበጥ ጀምሯል። ቤቷ እስክደርስ ቸኩያለሁ

«ማውራት አለብህ፤ ሌላ ነገር ለመስራት አትችልም» አለችኝ
«ለምን?» ብዬ አየኋት፡፡ ከጎኔ ስትራመድ ጭንቅላቷ ይወዛወዛል
ወደኔ አታይም፡፡ ፊቷ በጣም ቀልቷል። አፍራለች፡፡ ዝም አለች
«ለምን? ለመመንኮስ ቆርጠሻል እንዴ?» ዝም አለች፡፡ «ምን
ሆነሻል?»
«አሞኛል»
«ምንሽን?»
«አንተ የምትጠይቀውን ጥያቄ መቸስ የመንደር ቂል እንኳን
አይጠይቀውም፡፡»
«አትቆጪ። ምን ሆነሽ ነው? ማለቴ -»
«ነገሩ ትንሽ ነው፡፡ ሀኪም አይቶኝ መድሀኒት ሰጥቶኛል።
ከአንድ አምስት ቀን በኋላ ይድናል ብሎኛል።» ድንገት ሳቀች።
«ብቻ ቂጥኝ ወይም ጨብጦ እንዳልሆነ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ።
ኣለችኝ፣ ሳቋን ትታ «ይልቅስ ስለባህራም ንገረኝ፡፡»
ስለባህራም ሳጫውታት፣ ተነሳስቶ የነበረ ስሜቴን ረሳሁት።
ቤቷ ገብተን፣ ቡና በወተት አፍልታ ጠጥተን፣ ለብዙ ጊዜ አወራሁላት ስጨርስ አስተያየቷን ባጭሩ ገለፀችልኝ
«ይሄ ባህራም እንደ ፖል አይነት ሰው ይመስላል» አለች
«ለመሆኑ ስለፖል ትሰሚያለሽ?»
«ፓሪስ ስሄድ አንድ ደብዳቤ አገኘሁ፡፡ ፖል በቪየትናምና
በላኦስ መካከል እየተመላለሰ የደፈጣ ተዋጊዎቹን ያግዛል። በይፋ ባይታወቅ ነው እንጂ፣ አሜሪካኖቹ ላኦስ ውስጥም ይዋጋሉ። የደፈጣ ተዋጊዎቹ ፖልን ኮሎኔል ነው የሚሉት፡፡ በጣም ይወዱታል፡፡»
«ሌላስ ምን አለ?»
«ምንም አላለ። እሱን ተወውና ናፍቄህ አንደሆነ አሳየኝ እስቲ»
አለችኝ። ውብ ፊቷ ላይ ቅንዝረኛ ፈገግታ ይርበተበታል። እነ ፖልን
ባንዳፍታ ረሳኋቸው። እሷ እንደተቀመጠች ከፊቷ ተምበርከኬ አንገቷን እስመው ጀመር፡፡ አንገበገበኝ፡፡ ተለይታኝ ስለቆየችና አሁንም ላገኛት ባለመቻሌ፡ ስሜቱ እንደ እብድ አደረገኝ፡ ምንም ማድረግ እንደማልችል እያወቅኩም ልብሷን አስወለቅኳት። ናፍቆኝ
የነበረውን ውብ ገላዋን ማየትና መቃጠል አማረኝ። በልዩ ጥንቃቄ
👍16
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

#እንደወረደ_ነውና_ለአንባቢ
#የማይመቹ_እና_ፀያፍ_የምንላቸው
#ቃላቶች_አሉትና_አሁንም
#በድጋሚ_እንደምናገረው
#የማይመቸው_እንዳታነቡት
#እመክራለሁ

በጣም ፀያፍ ቃሉት አሉት

ኒኮል
ፍትወት


ባህራም ወደ ጋርደን ሲሄድ ኒኮልን ብቸኝነት እንዳይሰማት አደራችሁን ብሎን ሄደ በተለይም ሉልሰገድን አደራ አለው፡፡ ኒኮል
አይናፋርና ሰውን ቶሎ የማትላመድ በመሆኗ ከሉልሰገድና ከጀምሺድ ጋር ብቻ ነበር በመጠኑ የምትጫወተው

አንድ ምሽት ከእራት በኋላ፣ እኔ፣ ሉልሰገድ፣ ጀምሺድ፣ ተካ ካፌ ዶርቢቴል ቁጭ ብለን የሲኒማ ሰአት እስኪደርስ ስናወራ፣
ኒኮል ግራጫ ሱፍ ኮትና ጉርድ ከአረንጓዴ ሸሚዝ ጋር ለብሳ መጣች ሉልሰገድ ተነስቶ ከሌላ ጠረጴዛ ወምበር ሲስብላት፣
ጀምሺድ ተነሳና Bon soir ብሎ ሊጨብጣት እጁን ዘረጋ Bon soir ብላ እጇን ሰጠችው ጨበጣት

«አይ!» ብላ እጇን ማሻሸት ጀመረች

«ምንድነሽ?» አላት «ምን ሆንሽ?» ማለቱ ነው

«ወጋኸኝ» አለችው፣ ሉልሰገድ ያመጣላት ወምበር ላይ
እየተቀመጠች

«እንደት ወጋሁሽ?»

«በሀይል ጨበጥከኝና ቀለበቴ ወጋኝ»

«ኦ!» አለና፣ ይቅርታ እንደመጠየቅ ዛሬ ከሰአት በኋላ የሚከራይ አፓርትመንት ቤት እየፈለግኩ ብቻዬን» አለ። ትንንሽ ሰማያዊ አይኖቹ እንደልማዳቸው በሳቅ ይጨፍራሉ፡፡ ቀጠለ፡-
አንድ አፓርትመንት ፎቅ ወር ማለቴ ወጥቼ፣ የባለቤት የበር
ደወል። በእጄ መግፋት ውስጥ ደወል። ቀጭን ደወል ኪል! ኪል
ቆንጆ ደወል። በር ክፍት! የደወልኩት በር አይደለም፡፡ ሌላ በር:: ከግራ በኩል ከበሩ ብቅ። አንድ ሽማግሌ ዶክተር። ነጭ የዶክተር ልብስ። በአይኑ መነፅር በራሱ መላጣ በከንፈሩ ሙስታሽ በእጁ መርፌ

ዶክተር እኔን «ወዲህ ይግቡ፣ ልውጋህ»

እኔ «እኔ መርፌ አይፈልጉም። እኔ በሽታ የለም። እኔ ጤነኛ
እኔ ቤት መፈለግ፡፡ የአፓርትመንት ባለቤት መፈለግ። ለቤት
ኪራይ፡»

ዶክተር «ግድ የለህም፡፡ ና ግቡ ልውጋህ፡፡ እኔ አዋቂ መርፌ
ወጊ ብሉ መርፌ እንደ ጋንግስተር ሽጉጥ ወደኔ እኔ ዶክተር! እኔ አሁን መርፌ አይፈልጉም፡፡ ነገ እመጣለዚህ
እሺ?
ዶክተር «እኔ ነገ አይሰሩም። አሁን ና ልውጋህ፡፡ በኋላ ይቆጭሀል አላስከፍልም፡፡ አሁን ልውጋህ። ነገ ሀይድሮጅን ቦምብ ፓሪስ ላይ ፑፍ!

እኔ «ዶክተር፣ አሁን መጣሁ» ብዬ በሩጫ ፎቁን መውረድ
ዶክተር በሀይል ጩኸት ድምፅ ታድያ እኔ ማንን ይወጋል?
አንተ ከሄድክ እኔ ማንን ይወጋል?»

እኔ መልስ አልሰጥም ለዶክተር፡ በልቤ «እንጃ፣ ምናልባት ከኔ
በኋላ ሌላ ሰው አፓርትመንት ፈላጊ። ደወል ሲደውል ኪል! hል!
ዶክተር ቅስ ብሉ መርፌ ጠቅ! ከኋላ፡፡»

ጀምሺድ ሲያስቀን ከቆየ በኋላ ሁላችንም ሲኒማ ሄድን። አንድ
ነገር አስተዋልኩ፡፡ ሉልሰገድ በትልልቅ ጥቋቁር አይኖቹ ኒኮልን
ያያታል። ኒኮል በአረንጓዴ አይኖቿ ጀምሺድን ታየዋለች። ጀምሺድ
በብልጮ ሰማያዊ አይኖቹ ማዳም ፖልን ያያታል። ማዳም ፖል ብጫ ቅብ ፀጉሯን እያብለጨለጨች ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች
በጠረጴዛዎቹ መሀል ጉድ ጉድ ትላለች፡፡ አንድ ጊዜ ከጀምሺድ ኋላ ስታልፍ መንገዷን የዘጋባት አስመስላ ትከሻው ላይ እጆቿን አሳረፈችና "Pardon monsieur" አላቸው "Derien madame" ብሎ አሳለፋት፡፡ ብዙ ጊዜ እየከበብነው ሲያስቀን ስለምታይ፣ አይኗን ጣል
አድርጋበታለች። መስየ ፖል በሩ አጠገብ ቆሞ ገንዘብ እየተቀበለ
ሀጂውን ሰው በየዋህ ድምፅ
“Au revoir!' ወይም “A bient” ይላል

አማንዳ ወደ አገሯ እንደሄደች ሉልሰገድ አንዲት ኢጣልያዊት
ልጅ ያዘ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት ሳምንት እንዳለፈ ልጂቱ
አረገዘች። የፈረንሳይ ህግ ማስወረድ ስለሚከለክል፣ ሉልሰገድ ከኔ፣ ከጀምሺድና ከሌሎች ገንዘብ ተበድሮ ልጅቱን ወደ ስዊስ አገር ላካት። በዚያው አገሯ ገባች።

አንድ ቀን፣ ባቡር ጣቢያው አጠገብ ያለችው ትንሽ ካፌ በረንዳ
ላይ ቁጭ ብለን፣ ሉልሰገድ የሚወደውን ቡና አይነቱን የስኮትላንድ ቢራ እየጠጣን ስናወራ፣ ድንገት ተነሳና «ቆየኝ መጣሁ። ካልመጣሁ
ቤትህ እንገናኝ ብሎኝ፣ ባቡር መንገዱን ተሻግሮ ሁለት ኮረዳዎችን አቆመና ትንሽ አነጋገራቸው። ተለይተውት ሲሄዱ መሬት መሬቱን እያየ ወደኔ ተመለሰ

«እምስ የሸተተኝ መስሉኝ ነበር፡፡ ተሳስቼ ነው » አለኝ፡፡ አንድ
ነገር ሊነግረኝ እንደፈለገ ታወቀኝ፡፡ ዝም አልኩና ቢራውን ቀዳሁለት። ጎልዋዝ ሲጋራ አፉ ላይ ሲሰካ፣ ክብሪቱን ከጠረጴዛው ላይ አንስቼ አቀጣጠልኩለት መከራ ነው ባክህ። ሴቶቹ እምቢ አሉኝ። እንደዚህ ሰሞን እምስ ቸግሮኝ እያውቅም፡፡ እኔ ደሞ እንደምታውቀኝ ነኝ፣ ያለሱ
መኖር አልችልም፡፡ ለኔ መንግስተ ሰማያት ማለት በየሜዳው ላይ፣
በየዛፉ ስር፣ በየመንገዱ ዳር፣ በየግድግዳው ጥግ እምስ የሚበቅልበት አገር ነው:: ገሀነም ደሞ ፈፅሞ እምስ የማይገኝበት እርኩስ ቦታ ነው:: እምስ ዘርተውት ቢበቅል ኖሮ ገበሬ እሆን ነበር፡፡»

ሌላ ቢራ አዘዝኩለት

«እኔ ምልህ! ስለኒኮል ምን ይመስልሀል?» አለኝ
«ምንም»
“ምንም? እንግዲያው አታውቅም»
“ምን ማለትህ ነው?»
«እኔ እንደሷ ያለች ሴት አጋጥሞኝ አያውቅም:: አየህ፣
መጀመርያ ስታያት ስሜት አትሰጥህም፡፡ አመዳም ፀጉር የኔ
አይነት ጥቃቅን ጥርስ፣ የደረቀ ከንፈር፡፡ ታድያ እየለመድካት
እየለመድካት ስትሂድ ደሞ ስትለያት ትናፍቅሀለች። ታድያ ጤነኛ ናፍቆት አይደለም፡፡»

«ዋ! አንተ ልጅ፣ ፍቅር የያዘህ ትመስላለህ»

«ፍቅር አይደለም። ቅንዝር ነው፡፡ የሚያቅበጠብጥ ቅንዝር::
ባህራምን እወደዋለሁ፡፡ ጎበዝ ስለሆነ አደንቀዋለሁ፡፡ ደሞ አምኖን አደራ ኒኮልን አጫውታት ብሎኝ ነው የሄደው:: ግን አልቻልኩም። በጭራሽ አልቻልኩም፡፡ እኔ ልለምናት ነው»

«እምቢ ብትልህስ?»

«የምትለኝ አይመስለኝም። እሷም የምትፈልገኝ ይመስለኛል።
ትላንትና ማታ ሲኒግ ወስጃት፣ ፊልሙን አላየሁትም፡፡ ሽቶዋ
ከለከለኝ፡፡ ቀስ ኣድርጌ እጄን ጭኗ ላይ አሳረፍኩ፣ አልገፋችኝም።
ትንሽ ቆይቼ እጇን አመጣሁና የተገተረ ቁላዬ ላይ አስቀመጥኩት።
በሱሪው ላይ፡፡ እጇን እዚያው ተወችው። ታድያ ክፋቱ፣ በጭራሽ
አላሻሸችኝም፡፡ እጄን ወደ ቀሚሷ ውስጥ ላስገባ ስል ከለከለችኝ።
ለመከልከል እጇን ከቁላዬ ላይ አነሳች፡፡ እንደገና መድፈር
አልቻልኩም፡፡ ... ስቃይ ነው የኒኮል ነገር፡፡»

ከአራት ቀን በኋላ ሉልሰገድ ኒኮልን አፍ አውጥቶ፣ “ፍቅር ይዞኛል ቤትሽ መጥቼ ልደር?» አላት
«አኔ እሺ አልልህም። ግን እሺ ብልህም በኋላ ለባህራም
እነግረዋለሁ» አለችው::
ለምን ቢላት
«ባህራምን ላታልለው
አልፈቅድም» አለችው
«ከባህራም ጋር መፋረስ አምሮሽ እንደሆነ አንቺው ራስሽ
ምክንያት ፈልጊ እንጂ እኔን ሰበብ እንድታደርጊኝ አልፈቅድልሽም
እላት ሉልሰገድ ይህን ሲያጫውተኝ ሆ! ባህራምን ለምን እንጀራ ከምታበላው ሴት ጋር ላጣላው? ምን በደለኝ?» አለ
«እንግዲያው ምን በደለህና ኒኮልን ልትበዳበት ትፈልጋለህ?”
አልኩት እየሳቅኩ

«በጭራሽ አንድ አይደለም» አለኝ መጀመርያ ነገር ብበዳት አያልቅበትም። እንኳን ልጨርስበት አላሰፋበትም፡፡ አንድ ቀን
ገላውን ታጥቦ ሙታንቲውን ሲቀይር አይቼ፣ ጀላ ነው የተሸከመው። የኔ ግትር ብሎ ቆሞ እንኳ ያንን አያክልም፡፡ ታድያ ተኝቶ ተንጠልጥሎ ነው ያየሁት። እናትክን! ምናባክ ያስቅሀል? እኔን አይቶ ሊቆምበት ኖሯል?»
👍391🥰1
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...አንድ ማታ ኒኮልን ከተማ ሬስቶራንት እራት ጋበዝኳትና ብዙ
ወይን እያጠጣኋት ስለልብ ወለድ መፃህፍትና ስለ ፊልሞች ጨዋታ
እስጀመርኳት። መጀመሪያ ስለምንወዳቸው ደራስያን፣ ስላየናቸው ፊልሞች፣ ስለምናውቃቸው ሰዎች እና በልብ ወለድ መፃህፍት ውስጥ ካገኘናቸው ሰዎች ጋር በምን እንደሚመሳሰሉ ማለት
ስለራሳችን ሳይሆን ስለ ሌላ ነገር ስናወራ፣ ወይን ስንጠጣ፣ ብዙ ጊዜ አሳለፍን። እየለመደችኝ ሄደች። ወይኑም እየሰራ ሄደ። አይናፋርነቷ እየረገፈ፣ እንደ ልቧ ለማውራት እየቻለች ሄደች፡፡ እኔም ፈረንሳይኛ እሷ ስትናገረው በጣም የሚጥም መሆኑን እያስተዋልኩ ሄድኩ።

ቀስ ብዩ ወሬውን ወደ ባህራም ወሰድኩት:: እንዴት ጎበዝ ሆኖ
እንደሚታየኝና፣ ምን ያህል እንደማደንቀው ከነገርኳት በኋላ፣
ባህራም ላንቺ እንዴት ሆኖ ነው የሚታይሽ? አልኳት። ደራሲ
መሆን እንደምፈልግና ስለሰዎች ማወቅ እንዳለብኝ፣ ይልቁንም
ሴቶች ወንዶችን እንዴት እንደሚያዩዋቸው ማጥናት እንደሚገባኝ ስለዚህ፣ እሷ ስለራሷ ብትነግረኝ ለኔ ትልቅ ዋጋ እንዳለው፣ በሰፊው ዘረዘርኩላት። ተቀበለችኝና ስትናገር፣ በቃላትዋ እየተንሳፈፍኩ የድምፅዋ ዜማ እየተመቸኝ አዳመጥኳት
ደራሲ ሳትሆንም ስለራሴ ብነግርህ ግድ የለኝም አለችኝ።
ባሀራም ስላንተ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገር ስለነገረኝ ነው መሰለኝ፣ በጣም የማውቅህ መስሎ ይሰማኛል። ደሞ እወድሀለሁ:: በጣም ተወዳጅ ልጅ ነህ። ብዙ ሴቶች ይህን ነግረውህ የለ? ተናገር፡ (ትስቃለች።እሷ የተናገረችው በንፁህ ልብ ነበር። እኔ ግን ምኞቴ ተቀሰቀሰ፡፡
እግሮቼን አጣመርኩ። የሉልሰገድንና የሷን ታሪክ ባላውቅ ኖሮ አሁን ምኞቴ ይቀሰቀስብኝ ነበር? እንጃ፡፡ ኒኮል ቀጠለችልኝ

«በአስራ ስድስት አመቴ ማርሴል ከሚባል ልጅ ፍቅር ያዘኝ
ማርሴልም ወደደኝ። ቤቶቻችን ሁለቱም ሀብታም ቡርዥም
በመሆናቸው ይከባበሩና ይዋደዱ ስለነበረ፣ በመዋደዳችን እጅግ
ተደሰቱ። እስክንጋባ ቸኮሉ፡፡ ግን
ሁለታችንም የዩኒቨርሲቲ
ትምህርታችንን እስክንጨርስ ላንጋባ ቆረጥን። ቤቶቻችንን ለማስደ ሰት ስንል ተጫጨን፡፡ በዚህ መካከል ማርሴል አየር ሀይል ገባ

«አንቷን ደ ሴንት ኤግዙፔሪን ታውቀው የለ? በኤሮፕላን
ስለመብረር፣ ስለአደጋው፣ ስለክብሩ፣ ስለጀግንነቱ የደረሳቸውን መፃህፍት፣ ማርሴል ደጋግሞ ያነባቸው ነበር፡፡ ከልቡ ሴንት ኤግዙፔሪኝ ያደንቀው ነበር፤ ያመልከው ነበር፡፡ ለዚህ ይመስለኛል አየር ሀይል የገባው፡፡ እኔ ተው አትግባ፤ እንደ ሴንት ኤግዙፔሪ በኤሮፕላን አደጋ ትሞታለህ፣ አልኩት። መሞት የት ይቀራል? አለኝ። የሰው ልጅ ተግባሩ ከሞት ለማምለጥ መጣጣር ሳይሆን፡ ሞት
እስኪመጣ ድረስ ክብር ያለው፣ ኩራት ያለው ኑሮን መኖር ነው፣
አለኝ። አለቀስኩ። እምባዬን ጠረገልኝ። አሮፕላን ነጂ ሆነ
ይህ ሁሉ ሲሆን በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ይሞክር ነበር፡፡ በብዙ
ይለምነኝ ነበር፡፡ ሳንጋባ አይሆንም ብዬ እምቢ አልኩት አንድ ቀን የኤሮፕላን እደጋ ደረሰበት። ሁለት ወር ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ። ከዚያ ወደ ቤቱ መጣ። የአየር ሀይል ኑሮ፣ የሴንት ኤግዙፔሪ አይነት ኑሮ፣ ክብር፣ አደጋና ጉብዝና የሞላበት ኑሮ፣ የጀግኖች አይነት ኑሮ በቃው:: ከአየር ሀይል አሰናበቱት።ምክንያቱም ወገቡ ተሰብሮ እግሮቹ ሽባ ሆኑ። በተሽከርካሪ ወምበር ቁጭ ብሎ፣ እኔ ወይም እናቱ እየገፋነው ነበር አየር ለመቀበል እንኳ የሚወጣው
«ካንጀቴ አዘንኩለት፡ በሀይል ወደድኩት እሱ ግን አሁንም ሽባ ሆኖ የሴንት ኤግዘፔሪን መፃህፍት
ያነብ ነበር። ስለአደጋ፣ ስለጀግንነት፣ ስለክብር ስለሞት ያነብ ነበር።አንድ ቀን ሽጉጡን ጠጥቶ ሞተ ሀዘን ጀመረኝ። ግን ሀዘን ይለመዳል። ወጣት ከሆንክማ ትንሽ ቆይቶም ይረሳል። በተለይ ያጠቃኝ ፀፀት ነበር። ፀፀት አይለመድም፣
አይረሳም፣ የማይጠግብ የማይተኛ ውስጣዊ ትል ነው፡ እድሜ ልክህን ይበላሀል። የቆጨኝ ማርሴል በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ሲፈልግ እምቢ ማለቴ ነው:: እወደው ነበር፡ ስጋዬን ለሱ መስጠት እንዴት አቃተኝ? በሀይል ይቆጨኝ ይሞረሙረኝ ጀመር

ነብስ አባቴ ጋ ሄድኩና ሁሉን ተናዘዝኩ፡፡ የሠራሽው ልክ
ነበር አሉኝ። እኔግን ፍፁም ስህተት እንደነበረ የበለጠ እየተገነዘብኩ ሄድኩ፡፡ ራሴን መቅጣት ጀመርኩ፡፡ ከጠየቀኝ ሁሉ መተኛት
ጀመርኩ። ደሞ ብዙዎች ይጠይቁኝ ጀመር። ርካሽ ሴት ሆንኩ

«ግን አሁንም ፀፀቱ አልተወኝም»

በካሎሪያዬን እንዳለፍኩ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወደ ኤክስ
መጣሁ፡፡ ቤቶቼም ማርሴልን ለመርሳት ካለአቨር ከተማ መራቅ
እንዳለብኝ ስላወቁ ሂጂ አሉኝ። ኤክስ መጥቼ በርካሽነቴ ላይ
ጠጪነት ጨመርኩበት። የፈለገኝ እንግዲህ እስክሰክር ድረስ ማጠጣት አለበት። ብዙ ሰአት ካንዱ ጋር ስጠጣ አመሻለሁ። ጧት ወደ አምስት ሰአት ላይ ስነቃ አልጋው ውስጥ ነኝ፡፡ ሲደሰትብኝ እንዳደረ ይታወቀኛል፣ ግን ምን ምን እንደሰራን እንደ ህልም'ንጂ እንደ ውን ሆኖ አይታየኝም

ካንዲት የኔ ብጤ ርካሽ ጋር ገጠምኩ፣ አብረን መጠጥና
ወንድ ስናሳድድ እናመሽ ጀመር

እንዲህ ስል አመቱ አለፈ፡ ፈተና ወደቅኩ፡ ክፍል ደገምኩ፣
ሁለተኛው አመት ተጀመረ፣ ያንኑ ኑሮዩን ቀጠልኩ

አንድ ረቡእ ጧት እንደ ልማዴ አንዱ እማላውቀው መኝታ
ቤት ነቃሁ። ሰውየው ቁርስ ያቀርባል፡፡ ልዩ ሰው ሆኖ ታየኝ።
ሳይነካኝ አድሯል፡፡ ከመስከሩ የተነሳ ሊነካኝ ባይችል ነው እንዳልል፣ ትላንት ማታ ፓርቲው ጋ ልሰክር ትንሽ ሲቀረኝ ጠጣ እንጂ»
ስለው ሁለታችንም ከሰከርንማ ማን ማንን ይደግፋል?» ሲለኝ
አስታወሰው
“አልጋ ውስጥ እንዳለሁ ቁርስ ከበላን በኋሳ፣ ሰውየው በተሰባበረ
ፈረንሳይኛ
“ እንቁላል ከተሰበረ ወድያ ምንም
እንደማይሆን ታውቂ የለ?» አለኝ፡፡ ምን እንደሚል ሳይገባኝ «አዎን”
አልኩት። ወጣትነትም አንዴ ከተሰበረ ሊጠገን አይችልም» አለኝ

«ምን ማለትህ ነው?» አልኩት

«ያንቺ ወጣትነት ገና አልተሰበረም:: ግን ሊሰበር ትንሽ ነው የቀረው። እንደዚህ አይነት ኑሮ ከቀጠልሽ ከትንሽ ጊዜ በኋላ
ይሰበራል»

ተናደድኩ «ምን አገባህ?» አልኩት
«ምን አገባህ አትበይኝ፡ ፈረንሳይ መሰልኩሽ እንዴ? እናንተ
ፈረንሳዮች ፈሪ ናችሁ፡፡ ግብዝ ናችሁ። ተግባራችሁን መፈፀም
አስቸጋሪ የሆነባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ምን አገባኝ? Ca me regarde pas. ብላችሁ ትተዉታላችሁ፡፡ እኔ ግን እንደሱ አይደለሁም፡፡»

«እና በኔ ህይወት አንተ ምን አገባህ?»

«አንቺ አልጋዬ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? በኔ ህይወት ውስጥ
ገባሽ ማለት አይደለም?» አለኝ። መልስ ስላጣሁ ዝም አልኩ
መጥቶ አልጋው ላይ አጠገቤ ቁጭ እለና፣ አይን አይኔን እያየኝ
«አሁን እስቲ ለሁለት ደቂቃ ፈረንሳይ መሆኑን ተይና ሰው
ሁኚ፡፡ ለሁለት ደቂቃ ብቻ፣ እሺ? አለዚያ ለመናገር አልችልም»
አለኝ፡፡ አንድ አይነት ደግ ፈገግታ አሳየኝ፡፡ ረስቼው የነበረ
አይናፋርነቴ ድንገት ተመልሶ ሽፍን አደረገኝ፡፡ ወደታች ሳይ ፊቴን
በእጆቹ ይዞ ቀና አደረገኝና ግምባሬን ሳመኝ

«አገሬ ኣንቺን የሚያካክሉ ታናናሽ እህቶች አሉኝ፡፡ አንቺ
የምታረጊውን ሲያረጉ ባያቸው ዝም አልላቸውም። ስለዚህ አንቺንም ዝም አልልሽም። ይገባሻል?»
👍28👏2
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ሞት

ያን ሰሞን ጀምሺድ ታሞ ተኛ፡፡ ልጠይቀው ወደ ቤቱ ሄድኩ።
ሌሎቹ በሚጠይቁት ሰአት ብሄድ ምንም አልጠቅመውም በማለት፣
በትምህርት ሰአት ሄድኩ። ፎቁን ወጥቼ በሩን ብሞክረው ተቆልፏል። ደወሉን ተጫንኩት፣ ውስጥ ሲደውል ተሰማኝ፡፡ ቆየሁ
የጀምሺድ ቤት ሳይሆን፣ በግራ በኩል ያለው የጎረቤቱ በር
ተከፈተ። መነፅር ያደረገ መላጣ ሽማግሌ ሀኪም አንገቱን ብቅ ከርጎ አየኝ፡፡ አየሁት። ከበሩ ወጣ፡፡ ነጭ የሀኪም ኮቱ በጣም ንፁህ ነው፡፡በእጁ መርፌ ይዟል። ጀምሺድ የነገረኝን ታሪክ አስታወስኩ ሀኪሙ ዙሪያውን ተገላመጠና ሲያበቃ፣ ማንም እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ፣ በሹክሹክታ

«ይምጡ ልውጋዎት» አለኝ
ዝም ብዬ አየሁት
ካልፈለጉ ላስገድድዎት አልችልም፡፡ ነፃነትሳ? ዳሩ፤ ለኔ ያው ነው፡፡ ደሞ ደንታ የለኝም እንጂ» እያለ ለራሱ እያጉረመረመ ወደ ጀምሺድ ተኝቷል መሰለኝ ብዬ ደረጃውን መውረድ ስጀምር
በሩ ተከፈተ። ዘወር ስል ኒኮል ነች
“ይቅርታህን። አስጠበቅኩህ? ሽንት ቤት ነበርኩ» አለችኝ::
አመዳም ፀጉሯ ተሞነጫጭሯል። ሸሚዟ በአንድ በኩል ከጉርዷ
ወጥቷል። ገባኝ፡፡ ጀምሺድ አልጋው ውስጥ ትራስ ተደግፎ
እንደተቀመጠ፣ እየሳቀ
ዶክተር ሽቫይትዘር መርፌ ይውጉህ?» አለኝ፡፡ የሱም ፀጉር
ተሞነጫጭሯል ግምባሩ ላይ ወድቋል፡፡ ግን ፈፅሞ የታመመ
አይመስልም።
ኒኮልና ጀምሺድ እየተሻሙ ስለዶክተሩ ነገሩኝ። ሰውን
የማይጎዳ ሰላማዊ እብድ ነው፡፡ የመጣውን ሁሉ መርፌ ልውጋዎት? እያለ ይጠይቃል፣ አሉኝ። አነጋገራቸው አንድ ነገር ለመደበቅ የፈለገ ሰው አነጋገር ይመስላል

ትንሽ ቆይታ ኒኮል ከፍል አለብኝ ብላ ሄደች፡፡ ጀምሺድ
ስለጎረቤቱ ዶክተር ኮሚክ ወሬ እያወራ ሲያስቀኝ ቆየና ተነስቶ ወደ ሽንት ቤት ገባ
በፍጥነት በፀጥታ ተነስቼ የራስጌውን ፍራሽ አነሳሁ፡፡ አልጋው ሽቦ ላይ አንድ ጥቁር የሴት ሙታንቲ፡፡ ሙታንቲው ኣጠገብ አንድ አምስት የተጨማደደ ለስላሳ ክሊኔክስ ወረቀት ወረቀቶቹ ፅጌረዳ አይነት ስለሆኑ ርጥበታቸው ለአይን ያስታውቃል። ጎምበስ
ብዬ ወረቀቶቹን አሸተትኩ፡፡ የግብረ ስጋ ሽታ። ያለጥርጥር፡፡
ተመልሼ ወምበሬ ላይ ከተቀመጥኩ በኋላ፣ ተነስቼ የሰው ጉድ ሳሽት ታየኝና፣ ለራሴ ሸርሎክ ሆምዝ!» ብዬ በሀይል መሳቅ
ጀመርኩ ጀምሺድ ከሽንት ቤቱ «ለምን መሳቅ?» አለኝ
«መርፌ መውጋት» አልኩትና ሳቄን ቀጠልኩ
ሉልሰገድ ስለኒኮል ባይነግረኝ ኖሮ፣ ኒኮልንና ጀምሺድን እጠረጥር ነበር? አይመስለኝም
በጀምስድ አገር ደምብ የሚያፈላው ሻይ በጣም ይጣፍጣል።
እሱን እየጠጣን ወሬ ጀመርን
ጀምሺድ እንደሚለው ከሆነ፣ በቁማር መክበር አይቻልም።
በቁማር የሚከብር ቁማር ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ምንም ያህል ብትበላ
ያችን የበላ ሀትን ተመልሰህ እስክታስበላ ያቁነጠንጥሀል። በቁማር ለመክሰር እንጂ ለመክበር አይቻልም። እንዲህ ከሆነ ጀምሺድ ለምን
ቁማር ይጫወታል? ... ሰካራሙ ለምን ይጠጣል?ለጀምሺድ እንደሚታየው፣ ኑሮ ጨቅጫቃ ሚስት ናት፡ ና ምግብ ብላ፣ ና ተኛ፣ ና ሽንት ቤት ሂድ፣ ና ትምህርት ተማር፣ ና ይህን አድርግ፣ ና ያንን ፈፅም፣ እያለች መነዝነዝ ነው ስራዋ፡፡ ታድያ የሰው ልጅ ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ለመሸሽ አንዳንድ ጊዜ ቢሰክር ይፈረድበታል?

ጀምሺድ ዮኑሮን ችኮነት ሊረሳ የሚችለው ቁማር ቤት የሄደ
እንደሆነ ነው። ቁማር ቤት ውስጥ ያለችው ኑሮ፣ ነዝናዛ ችኮ ሚስት
ሳትሆን፣ የማትጠገብ፣ ለዛዋ ሁልጊዜ የሚታደስ ውሽማ ናት። ኮት የምታስሽጥ ውብ ውሽማ!

«እኔ ቁማር ስጫወት መኖሬን እረሳለሁ፡፡ መኖሬን ሲረሳ፣ ያን
ጊዜ ኑሮን ኖርኳት ነኝ ማለት ነው:: ሌላ ጊዜ ኑሮን ሲኖራት፣ እኔን
እያታለልኩ ነው ችኮ ናት ደስታ የለም፡፡ ቁማር ጊዜ ግን፣ ቁማር
ፈፅሞ ሲውጠኝ ሳለ። ኑሮ መሀል ውስጥ እገባ፣ ከንቱ አይደለች፣
እላያትም እኖራታለሁ ማለት»

ጀምሺድ ስለቁማር ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም

እንስሳ ኑሮ አይሰለቸውም (ይሄ የጀምሺድ አስተሳሰብ ነው)
ምክንያቱም እንሰሳ ይኖራል እንጂ መኖሩን አያውቅም። ስለዚህ ኑሮ
አይመረውምም አይሰለቸውምም። ስለዚህ ነው እንሰሳ ራሱን የማይገለው። «በሬ ወይም አህያ ወይም አይጥ ወይም ውሻ ወይም ሌላ፣ ራሱ ገደለ እሱ ሰምተሀቸዋል ታውቃለህ?» ሰውን ከእንሰሳ
የሚለየው ማሰቡ አይደለም፡፡ በመጠኑ ይሁን እንጂ እንሰሳም
ያስባል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው በመሳቁ አይደለም። ዝንጀሮም
ይስቃል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው፣ ህይወቱን እየኖራት እንደሚኖራት በማወቁ፣ ከህይወት በኋላ ሞት መከተሉን በማወቁ፤ እነዚህም እውቀቶች ለሰው ልጅ ኑሮን ከንቱ፣ ሞትን መራራ በማድረጋቸው በዚህ ነው ሰው ከእንሰሳ የሚለየው

በመሰረቱ ህይወት ግሩም ስጦታ ናት። ኑሮ ግን ይሰለቻል።
ሀዘን ሞልቶበታል፡፡ ብስጭት ይበዛበታል፡፡ በሽታ ወሮታል። ሞት
ደሞ ይቆያል እንጂ አይቀርም። ስለዚህ መሞት ላይቀር፣
ብስጭት ሊበዛ፣ ለምን አሁኑኑ
አንሞትም? ለምን ራሳችንን አንገድልም? ችኮ የሆነ ሀዘን፣ ብስጭት የወረሰው እውቀት ምኑ ይወደዳል? ራሳችንን የማንገድለው ሞትን
ስለምንፈራ ብቻ ነው። ፈሪ ነን በቃ፡፡ ይኸው ነው ስለዚህ፤ ልናደንቀው የሚገባ ሰው ማን ነው? ራሱን ለመግደል የደፈረ ሰው ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው። እኛሳ ዋናው አላማችን ምን መሆን አለበት? ይህን የመሰልቸት ቀሚስ አውልቀን ወዲያ መጣል
በተቻለ ፍጥነት ራሳችንን መግደል
«እኔ ራሴ ለመግደል ዋና ምኞት፡፡ ግን እስካሁን ድፍረት የለም፡፡ አንድ ቀን ግን ለመድፈር ተስፋ! ያን ጊዜ እኔ ሰው::እውነተኛ ሰው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን ከንቱ ቁማርተኛ።»

ጀምሺድ ራስን ስለመግደል ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም

በልግ ከዛፎቹ ላይ ቡናማ፣ ቀይና ወርቃማ ቀለማቱን ሰብስቦ
የሙቀትና የውበት ጓዙን ጠቅሎ ኤክስን ለቆ ሊሄድ ተነሳ የኤክስ አየር መብረድ ጀመረ። ሽማግሌዎቹ፣ አሮጊቶቹና
ጥቁሮቹ፣ ሹራብ መደረብ ካፖርት መልበስ ጀመርን። ወጣቶቹ
ፈረንጆች ግን ገና ብርዱ ሊሰማቸው አልጀመረም
ሉልሰገድን ኒኮል እምቢ ስትለው እኔጋ መጥቶ «ካፌ ኒኮል»
ይወስደኝና፣ እየቀረበን በመጣው የክረምት ብርድ ምክንያት፣ ቤት
ውስጥ ገብተን ቁጭ ብለን ስለኒኮል ያወራልኛል። የጭገሯ ፀጉር እንደራሷ ፀጉር አመዳም ሳይሆን፣ ንፁህ ወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ወተት የመሰለው ነጭ ቆዳዋ ላይ ረዣዥም የተጠላለፈ ውብ ወርቃማ ሀረግ መስሎ በቅሏል። ታዲያ እምሷ ዳር የበቀሉት ፀጉሮች፣ ውሀ ዳር እንደበቀለ ቄጠማ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ከሁለቱ ከናፍር ተንጠራርተው ተጠላልፈው፣ ጎምበስ ብለው እምሷ ውስጥ
የፍቅር ውሀ ይጠጣሉ. .. ወዘተርፈ

አንድ ቀን ግን፡ ስለሷ ያወራልኛል ብዬ ስጠብቅ ስለጀምሺድ
ሊነግረኝ ጀመረ፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ሆነዋል። ጀምሺድ ቁማር
ለመጫወት ካዚኖ ሲሄድ ሉልሰገድን ይዞት ይሄዳል። ከዚህም በላይ ሉልሰገድ የጀምሺድ ሻይ ሱስ ይዞታል። ሁለቱም ሻይውን የሚጠ
ጡት በኢራን አገር ወግ ነው። በፊት ከአራት ማእዘኑ ስኳር ላይ
ይገምጡና፣ ቀጥሎ ሻይ ፉት ይሉበታል፣ እንጂ ስኳሩን ሻይው
ውስጥ አይጨምሩትም
👍232
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ከዚሀ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤
ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና
ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ..

ክረምት እየተንፏቀቀ መጣና፣ ከወርቃማው በልግ ጋር ተቃቅፋ
የነበረችውን የኤክስ ከተማ እንደ ቀናተኛ ሌላ ውሽማ በብርድ
ይገርፋት ጀመር፡፡ ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ከየመንገዱና
ከየመናፈሻው አባረሯቸው። ልጃገረዶቹ ቆንጆ ስስ ቀሚሳቸውን
ትተው ወፍራም ሱፍ ቀሚስ፣ ሱሪና ወፍራም ሹራብ፣ ካፖርት
እየለበሱ፣ ውብ ቅርፃቸውን ከክረምቱ አይን እየሽሽጉ በበጋ ቀያይ ወይም ብር መሳይ የጥፍር ቀለም ተቀብተው ሲውለበለቡ የነበሩትን ጣቶቻቸውን በወፍራም ጓንቲ ውስጥ እየደበቁ፤ ከክፍል ወደ ምግብ ቤት፣ ከምግብ ቤት ወደ መኝታ ቤት በፍጥነት ኩስ ኩስ ይሉ ጀመር። ውብ ዳሊያቸውን እያወዛወዙ በዝግታ መራመድ፣ ፅጌረዳ ጉንጫቸውን እያሳዩ፣ በቀያይ ከንፈራቸው እየሳቁ፣ በተኳላ አይን
ጎረምሳውን መቃኘት ቀረ፡፡ (ኩሉንና የከንፈር ቀለሙን ብርድ
ስለሚሰነጣጥቀው ለአይን ደስ አይልም።) ደም የሽሽውን ነጭ
ጉንጫቸውን ግራጫ ብጤ የጎሽ ፀጉር ወረረው በየመንገዱ ዳር በተርታ የተተከሉት ዛፎች ራቁታቸውን ቆመው
የኤክስን ንፁህ ሰማይ በጭራሮዋቸው ይቧጥጡታል። ቅጠሎቹ በሙሉ ረግፈው የባቡር መንገዱን ዳርና የሰው መተላለፊያውን ሞልተውታል። ሰው በፍጥነት ሲራመድ በቡት ጫማው ይፈጫቸዋል

አንዳንድ ቀን በረዶው እንደ ጥጥ በዝግታ ይወርድና ኤክስን
በንፁህ ነጭ ሻሽ ይገንዛታል። በሱፍ የተከናነቡት ልጃገረዶችና
ጎረምሶች ሜዳ ወጥተው በረዶውን እያድቦለቦሉ ይፈነካከታሉ ይሳሳቃሉ። ትንፋሻቸው እንደ ጉም ከአፋቸው ቡልቅ ቡልቅ! ሲል ይታያል። ጥቁሮቹ በረዶው ላይ እየሆኑ ፎቶግራፍ ይነሳሉ የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ሰአት እንደ ልጃገረዶች ጉንጭ ይቀላል። የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፡ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው፣ ሁልጊዜ ውብ ነው፤ ሁልጊዚ ሰሳማዊ ነው። ማታ ማታ የአልማዝ ከዋክብትና የፀጥታ ሰላም ይለብሳል

ክረምት ሲሆን ሌሊቶቹ ይረዝማሉ፣ ቀኖቹ ያጥራሉ፤ ፀሀይዋ ጧት ወደ አንድ ሰአት ተኩል ላይ ትወጣና ከሰአት በኋላ ወደ አስር ተኩል ላይ መጥለቅ ትጀምራለች፤ በሽታ እንደያዘው እየማቀቀች እየደከመች ትሄዳለች። ሩቅ፣ ሩቅ ሩቅ በጣም ሩቅ ሆና ኮሳሳ ብርሀን ትልካለች። እቺ ፀሀይ በበጋው የሙቀት ምንጭ ነበረች፡ለኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች የህይወት ተስፋ ነበረች፣ አሁን ግን
ሰማዩ ተበስቶ ከውጭ የብርድ ጮራዎች የሚያስገባ ይመስላል

ብርዱ መላውን ፍጥረት ጨብጦ ያዘ፡፡ የሁላችንም ህይወት
በክረምቱ ብርድ ታሰረ፣ በቆፈን ተቋጠረ፡፡ ፀደይና ፀሀይ መጥተው
እስኪያስፈቱንና እስክንንቀሳቀስ ድረስ፣ የህይወታችን ታሪክ በያለበት ረጋ:: ተካና ጀርመኗ እኔ የማላውቀውን ግንኙነታቸውን ቀጠሉ፡፡ጀምሺድና ሉልሰገድ በኒኮል የፍትወት ገመድ ተሳስረው መለያየት አቅቷቸው፣ ጤና የለሽ ጓደኝነታቸውን ቀጠሉ፤ ለገና እረፍት ባህራም ወደ ኤክስ ሲመለስ ጊዜ፤ ኒኮልን ትተውለት ሁለቱ ተያይዘው ወደ ሞንቴ ካርሎ ሽሹ። እኔና ሲልቪ አልፎ አልፎ
እየተገናኘን፣ የቀረውን ጊዜ ስንፅፍ እንሰነብት ነበር በብርዱ ምክንያት የህይወታችን ታሪክ መፍሰሱን መለዋወጡን ትቶ፣ በያለበት ረጋ
አዳሞ የተባለው ዘፋኝ
"Tombe la neige
Tu ne viendras pas ce soir
Tombe la neige
Me crie mon desespoir..."
(በረዶው ይወርዳል
እንግዲህ ዛሬ ማታ አትመጪም
በረዶው ይወርዳል
ተስፋ መቁረጤ ይነግረኛል .. .»)
እያለ የክረምት እንጉርጉሮውን ያዜማል ..
ፀሀይዋ ቀስ በቀስ የሸሸችንን ያህል ቀስ በቀስ ትጠጋን
ጀመር። አየተቀነሰ የሚሄደው ብርድ፣ ቀጥሎም እየበረታ የሚሄደው ሙቀት፣ ረግቶ የነበረውን የፍጥረት ደም ቀስ በቀስ ያፍታታው ጀመር። መጀመሪያ አንዳንዷ ደፋር ቅጠል ብርዱን አሽንፋ አንገቷን
ብቅ ታደርጋለች፣ ራቁታቸውን የከረሙት ጭራሮ ቅርንጫፎች ላይ ስትታይ ታስደንቃለች፡ ታስደስታለች፤ የድል አድራጊው ህይወት ፊታውራሪ ነች፡ ምስጢራዊ ተአምር ነች። እንግዲህ ሌሎቹ ቅጠሎች
ይከተሉዋታል፡ የኤክስ ዛፎች በራቁት ጭራሮዋቸው ሰማዩን
መቧጨር ትተው፣ በለምለም አረንጓዴ ልብሳቸው ይወለውሉታል፣ ያፀዱታል። የኤክስ ጎረምሶችና ኮረዳዎች መጀመሪያ ካፖርትና
ጓንቲያቸውን አወለቁ፤ ቀጥሎ ሹራባቸውን አውልቀው መሳሳቅ
ጀመሩ። አንዳንድ ደፋር አሮጊት ወይም ሽማግሌ ካፖርቱን
እንደለበሰ መንገድ ላይ ይታይ ጀመር፡፡ ክረምቱ አለፈ ..

ፀደይ መጣ፡፡ የኤስ ልጃገረዶች ከባድ የክረምት ልብሳቸውን ገፈው ጥላው፣ ክረምቱ አልብሷቸው የነበረውን
አስቀያሚ ነጭ ጎሽ ፀጉር ኣራግፈው፤ የተፈጥሮ ውበታቸውን
መልበስ አመጡ፡፡ ፀጉራቸው ጭንቅላታቸው ላይ ተቆልሎ ወይም ወደ ኋላቸው እየፈሰሰ፣ ቆዳቸው ልስልስ ብሎ የፅጌረዳ ቀለም እየለበሰ፣ በቀይ ከንፈራቸው የተከበበ ጥርሳቸው በፈገግታ እያብለጨለጨ፡ ተሸሽጎ የከረመው ወጣት ቅርፃቸው እየፋፋ፣ ሹል ጡታቸው
ከፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ያበጠ ዳሌያቸው ከኋላ እየተወዛወዘ፣ ይሄ ሁሉ ፀጋ የፀደይን መልካም ብርሀን ለብሶ በየመንገዱ እየተዘዋወረ፣ የኤክስን ጎረምሶች ምራቃቸውን ያስውጣቸው ጀመር። በብርድ ተኮራምተው የከረሙት ኮረዳዎች አሁን በሙቀት ተዝናኑ፤ እየተጯጯሁ በሳሩ ሜዳ ይፈነጩ
ይንከባለሉ ጀመር። ከጎረምሶቹ ጋር ልፊያና መተቃቀፍ ተጀመረ

ሽማግሌዎቹና አሮጊቶቹ እየወጡ የኩር ሚራሶንና የመናፈሻውን
አግዳሚ ወምበሮች ሰፈሩባቸው። እርጅና ከወጣትነት ጋር እየታከከ
የኤክስን መንገዶች በጎባጣ ጨምዳዳ እርምጃው ይንፏቀቅባቸው ጀመር የክረምቱ ብርድ ገድቦ ይዞት የነበረው ታሪካችን አሁን በፀደይ
ውቀት እንደገና መፍሰስ ጀመረ

ፀደይ ለኤክስ ብርሀንና ሙቀት ከአረንጓዴ ቀሚስ ጋር ይዞላት
ሲመጣ፤ ለተካ ችግር ይዞለት
መጣ። ባለውስታሿ ጀርመን
ታስቸግረው ጀመር። ከአንድ ያገሯ ልጅ ጋር መውጣት አመጣች፡፡
ታዛ ምን ትሽረሙ@ያለሽ? አላት። መሸርሞጥ አይደለም ማማረጥ ነው» አለችው:: እና የትኛችን ይሻላል?» አላት::በአንዳንድ ነገር እሱ ይሻላል፤ በሌላ ደሞ አንተ ትሻላለህ»አለችው። ተካን ቅናት ይሞረሙረው ጀመር

ጥፍሩን እየነከሰ «አሁን ምን ማድረግ ይሻለኛል እባክህን?»
አለኝ

«ትወዳታለህ?» አልኩት
«አዎን። ብዙ ነገር ይገባታል፡»
እሷስ ትወድሀለች?»
«አዎን»
«እንግዲያው አግባታ»
“አብደሀል? ነጭ ሚስት ይዤ ብመለስ አባቴ አይታነቅም?»
«እንግዲያው ተዋት»
እንዴት አድርጌ ልተዋት? በፊት እንኳ ቢሆን ልተዋት እችል
ነበር። አሁን ግን፣ ከዚያ ከንፍጣም ጀርመን ጋር መውጣት
ከጀመረች ወዲህ፡ ከምተዋት ብገድላት እመርጣለሁ፡፡»
«የሀበሻ ምቀኝነት ነው?» አልኩት
«አይደለም፡፡»
«ታድያስ?»
«እህ! ስለቅናት አታውቅም እንዴ? እንግዲያው ልንገርህ፡፡
አየህ፣ ስትቀና ልጅቷን በሀይል ትጠላታለህ። ብትገድላት ፈቃድህ
ነው፡፡ ግን በዚህ አለም ላይ ምን ትፈልጋለህ ቢሉህ፤ እሷን ነው
ምትፈልገው ሁሉ ነገር ይቅር ብቻ እሷ ትምጣ፡፡ ገባህ የምልህ?
ለምሳሌ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱ ጋር የወጣች ጊዜ፣ ቤቷ ወሰድኳትና አንድ ጥፊ አላስኳት፡፡ ወዳ እስክትጠላ ልደበድባት ቆርጬ ኮቴን አወለቅኩ። ታዲያ ዳግማዊ ጥፊ ላወርድባት ስል
👍162
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ.

ተነሳና ወደ ሽንት ቤት በኩል መራመድ ጀመረ። አንዱ
ጎረምሳ ፋሺስት ከዚያው ሲመለስ ነበር ባህራምን የገጨው፡፡ ፋሺስቴ ሳያስብበት በልማድ “Pardon” ብሎት ሲያልፍ፣ ባህራም

«አንተ!» ብሎ ጮኸበት። ፋሺስቶቹ ወሬያቸውን አቆሙ::
ካፌው በሙሉ በፀጥታ ባህራምን ማየት ጀመረ። የገጨው ፋሺስት
ወደ ባህራም ዞሯል ባህራም

«ለምን ገጨኸኝ?» አለው

ፋሺስቱ «አንተ ነህ እንጂ የገጨኸኝ አለው

«ውሽታም ፋሺስት! ውሻ ፋሺስት! ፈሪ ፋሺስት! ወንድ ከሆንክ ተከላከል። ልገርፍህ ነው» አለና ዘሎ ትግል ያዘው። የፋሺስቱ ጀርባ ወደኔ ስለነበረ፣ ባህራም ምን እንዳደረገው ለማየት
አልቻልኩም፡፡ ብቻ ምንም ያህል ሳይታገሉ ፋሺስቱ ፍስስ ብሎ ወደ
መሬት ወደቀ፡፡ ባህራም ከበላዩ እንደቆመ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ከፋሺስቶቹ ማንም አልተነሳም
ባህራም ፋሺስቶቹን እያየ «ማንም ፋሽስት እንዲገጨኝ አልፈቅድለትም፡፡ ከንግዲህ ሌላ ፋሺስት የገጨኝ እንደሆነ፣ ፂሙን
ነው ምላጭለት አለና የወደቀውን ፋሺስት ተሻግሮ ወደኔ መጣ፡፡
አብረን ወጣን
(ፋሺስቶቹ እኔን ሌላ ጊዜ ቢያገኙኝ ይደበድቡኝ ይሆን? ብዬ
ትንሽ ፈራሁ፡፡ ግን ደፍረው ጥቁር ተማሪ የሚደበድቡ አልመሰለኝም፡፡ ምክንያቱም እኛ የፈረንሳይ መንግስት እንግዶች
ማለት ነን፡፡)
ባህራም ኤክስ ውስጥ አራት ቀን ቆየ፡፡ ቀን ቀን ኮሙኒስቶቹን
ሲመካክራቸው፣ እንዴት አድርገው መከላከል ፅሁፎቻቸውን እንዴት ቢያሰራጩ እንደሚሻል፣ እና ይህን የመሳሰለ ነገር ሲነግራቸው ይውላል። ማታ ማታ ፋሺስቶቹን በየጠባቡ መንገድ ሲደበድባቸው ያመሻል፡፡ በአምስተኛው ቀን ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኘሁት፡፡ ስለአምቧጓሮው ሲነግረኝ፣ ስለኳስ ጨዋታ የሚያወራልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ በደስታ እየገነፈለ፣ ማድፊጡን መዝለሉን፣ እጁን እንደ ሰይፍ አርጎ አንገት መምታቱን፣ እንደ ዳንስ አድርጎ ገለፀልኝ

"ማኑ ይህን ሁሉ ስስራ አይቶኝ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር!
ያስተማረኝን ብልሀት በሙሉ ተጠቅሜበታለሁ» አለ

«ደህና ሁን» ብዬው ወደ ኤክስ ልመለስ ስል፣ ከኪሱ አንድ
እቃ አውጥቶ አሳየኝ። የፀጉር መቁረጫ መኪና «ቶንዶዝ»፡፡
ምንድነው? አልኩት፡፡ እየሳቀ «ፋሺስቶቹ ካፌ ሂድና እቺ ነገር
ኮሙኒስት መሆንዋን ትገነዘባለህ» ብሎኝ ተለያየን ኤክስ እንደደረስኩ ፋሺሰቶቹ ካፌ ገባሁ። ብዙዎቹ እጃቸውን ወይም ጭንቅላታቸውን በፋሻ ጠምጥመዋል፡፡ ግማሾቹ ፂማቸውን ላጭተዋል። ፂማቸውን ያልላጩት ደሞ ጥቁር «ቤሬ ቆብ
አርገዋል። ለካ ባህራም ኣንድ ፋሺስት በደበደበ ቁጥር ራሱን
ወይም ፂሙን ይላጭለት ኖሯል
(እኔና ባህራም ኣንድ ግሩም የሆነ ሀራኪሪ» የተባለ የጃፓን ፊልም አይተን ነበር። እዚያ ፊልም አንዱ ጎበዝ እየዞረ የጠላቶቹን
ፀጉር ይላጫል።)

ባሀራም በሄደ በአራተኛው ቀን፣ አንዲት ኮሙኒስት ልጅ ካፌ
ቁጭ ብዬ ሳለሁ መጣችና ወደ ኤክስ አንድ ነብሰ ገዳይ መጥቷል
አለችኝ። ምን አንደሆነ ማለቴ የቱ እንደሆነ አናውቅም። ግን መምጣቱን እናውቃለን፡፡ ፋሺስቶቹ ናቸው ከማርሰይ ያስመጡት። ባህራምን ሊደበድበው ወይም ሊገድለው ነው የመጣው::»
«ፋሺስት ነው?» አልኳት
«አይደለም። የተገዛ ነብሰ ገዳይ ነው» አለችኝ
ያን ጊዜውኑ ሲልቪ ቤት ሄድኩ። በአቶቡስ እንዳልሄድ
ምናልባት ፋሺስቶቹ ይከታተሉኛልና፡ ካንቺ ጋር ለሽርሽር የምንወጣ አስመስለን እንሂድ አልኳት።በመኪናዋ ሄድን። ለባህራም ነገርኩት።
ሲልቪ ቤቷ ወስዳን እራት በላን። ከዚያ ሶስታችንም ሄደን
ፋሺስቶቹ ካፌ ገብተን ሁለት ሰአት ያህል አሳለፍን። ይህን ሁሉ
ጊዜ ባህራምና ሲልቪ ያወሩ፣ ይቀልዱ፣ ይስቁ ነበር፡፡ እኔ ግን
ምንም ያህል አላወራሁም። ለባህራም ፈርቼለት ነበር፡፡ ሰውየው የቱ እንደሆነ ብናውቅ እንኳ ለመከላከል እንሞክር ነበር። አሁን ግን ከማንኛውም አቅጣጫ ጦር ሊወረወርበት በሚችልበት
ውስጥ፣ ባህራም ብቻውን የሚራመድ መስሎ ተሰማኝ
አብሬያቸው ባለማውራቴ፣ የኔ ፍርሀት ቀስ እያለ ወደ ሲልቫ
ተላለፈባት

“ፈራሁ። በጣም ፈራሁ» አለች

ባህራም «ምን ያስፈራሻል?» አላት፡፡ ግን ድምፁ እንደ ድሮ
ልዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ትንሽ እሾህም ሆኗል

«ማን እንደሆነ ወይም የት እንደሆነ አናውቅም፡፡ አንድ
ብቻውን መሆኑን እንኳ በእርግጥ አናውቅም፡፡»

«እና?»

አንድ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ?» አለችው

እኔ? ትቀልጂያለሽ? የኛ ቤተሰብ”ኮ እስኪጃጅ ካላረጀ
አይሞትም፡፡ የኔ ወንድ አያት፣ ያባቴ አባት፣ በዘጠና ሰባት
አመታቸው ብቻቸውን ሜካ መዲና ደርሰው ተመልስዋል። ታድያ
እንደተመለሱ የቤታችን ጣራ ዝናብ ማስገባት ሲጀምር ጊዜ፣
ሊያበጁት በመስሳል ወጡ። አበጅተውት ሲወርዱ ከመሰላል ወደቁና እግራቸው ወለም ብሏቸው ሁለት ሳምንት ሙሉ እንዲተኙ ሀኪም አዘዛቸው:: ታድያ ሁለት ሳምንት እንዴት ይለፍ? ውሽማቸው ናፈቀቻቸው። እና ገና አንድ ሳምንት ሳይተኙ፣ ሌሊት ጠፍተው ውሽማቸው ቤት ሄዱ። መኝታ ቤቷ በመስኮት እገባለሁ ሲሉ ባልየው በጥይት ልባቸውን አፈረሰላቸው:: ስንቀብራቸው የኔ አባት
«አይ አባባ! አይ አባባ! እኛ ያረጀነው እያለን አንተ ወጣት
ተቀጨህ!» ብሎ አለቀሰ፡»
ስንስቅ ሲልቪ በጆሮዬ እኔ ፍርሀት አቁነጠነጠኝ፡፡ ሽንቴ መጣ» ብላኝ ወደ ሽንት ቤት ሄደች
ባህራምን «የጀምሺድን የሚመስል ታሪክ ከየት አመጣህ?» አልኩት
( ከጀምሺድ ነዋ!» አለኝ «ስማኝ፡፡ እንድ ነገር አርግልኝ።
እዚያው ትደር፡፡ እና ነገ በሌሊት ተነስቶ ማርሰይ እንዲወስዳትና
ለአንድ ሳምንት ያህል ተደብቀው እንዲቆዩ ንገረው::

ቀፈፈኝ። በባህራም ትእዛዝ ኒኮልን ጀምሺድ ቤት ወስጄ ለጀምሺድ ላስረክበው ለአንድ ሳምንት ሙሉ! በጣም ቀፈፈኝ፡፡ ግን
ምን ማድረግ እችላለሁ?
አንተም ይህን ሰሞን ተጠንቀቅ። ማታ ብቻህን አትውጣ»
አለኝ። ሲጋራ አቀጣጠለ። እጁ ትንሽ ትንሽ ይንቀጠቀጣል። ፍርሀት አሳደረብኝ
ሲልቪ ተመለሰች። ደህና እደሩ ብያቸው ሄድኩ ኒኮልን ቤቷ እገኘኋት። ጀምሺድ ቤት ስንሄድ አጣነው፡፡ ቤቱ ቁልፍ ነው። ካፌ ዶርቢቴል ሄደን ጠያየቅን፡፡ ተካ፣ ጀምሺድና ሉልሰገድ ኒስ ሄደዋል አሉን። ኒኮልና እኔ የመጨረሻውን የማታ አቶቡስ ተሳፍረን ማርሰይ ወረድን፡፡ አንድ ወሻቃ ቦታ ሆቴል
አገኘን። ባለ ሁለት አልጋ ክፍል ተከራየን። ሁለታችንም ለባህራም
ሰግተናል። አንቅልፋችን እንደማይመጣ ግልጽ ነው:: አንድ ቆሻሻ ብጤ ጭር ያለ ካፌ ገብተን ከልቫዶስ እየጠጣን፣ እያወራን፣
እየተያየን ሳቃችን እየመጣ፤ እየተሳሳቅን፣ ድንገት ሳቃችንን
አቋርጠን በፀጥታ እየተያየን፣ ስንተያይ ኒኮል በሚያስጐመጅ አኳኋን እየቀላች፣ እየቀላች፣ እየጠጣን እያወራን፤ ከአንድ ሰእት በላይ አሳለፍን፡ ሰከርን፡፡ የተረፈንን ግማሽ ጠርሙስ ካልቫዶስ ይዘነው ሞቃት ሰማይ መሀል
ሆቴላችን ስንደርስ፤ እንዳንተያይ መብራቱን አጥፍተን፣
👍20
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ጥሪ
የሳጥናኤል ኮከብ

የሴሰኝነት ጥሪ
ሲልቪ

እኔና ሲልቪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፓሪስ ተጓዝን። በሷ መሪነት
ከፓሪስ ጋር ይበልጥ ተዋወቅኩ። በሲልቪ አስተማሪነት ከቅናት ጋር
ይበልጥ ተዋወቅኩ፡፡ ራሴንም ይበልጥ አወቅኩ ፓሪስ በገባን በሁለት ቀናችን፣ እንደ ልማዷ አንድ ደስ የሚላት ጎረምሳ አየችና አጣድፋ ወደ ሆቴላችን ወሰደችኝ፡፡ መብራቱን አጠፋች፡፡ እንደ “ልማዷ በኔ ገላ ጎረምሳውን ተደሰተችበት፣
አቃሰተች፣ ነገሩ ሊያልቅ ሲል ጮኸች። ተኛን፡፡ ያን ጊዜ እኔም
እሷም አላወቅነውም እንጂ፣ ከኔ ጋር እንዲህ ስትሆንና ስታደርግ
የመጨረሻ ጊዜዋ ነበር ነቃሁ። ጭለማ ውስጥ ነኝ። ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ:: ከጎኔ
ተንቀሳቀሰች፡፡ በእንቅልፍ ልቧ «“Non! Non! Non!" እያለች
እየተጨነቀች ተፈራገጠች። በጣም የሚያስፈራ ህልም መሆን
አለበት። እየቀሰቀስኳት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ከኔ ጋር ነሽ» አልኳት ራሷን እየደባበስኩ።
በሀይል እየተነፈሰች ተጠጋችኝና
«አንድ ነገር አስደነገጠኝ፡፡ መብራቱን አብራልኝ አለችኝ
አበራሁት። አይኔ ብርሀኑን ከለመደው በኋላ ታየችኝ፡፡ ጥቁር
ረዣዥም ፀጉሯ ጉንጭና አንገቷ ላይ ተጠምጥሟል፣ተለጣጥፏል። ግምባሯ ላይ ላቡ ያብለጨልጫል፡ ጠረግኩላት፣
ፀጉሯን ወደ ኋላዋ ሰበሰብኩሳት
ውሀ» አለችኝ፡፡ ራስጌ ካለው ጠርሙስ አጠጣሁዋት
«ደህና ነሽ?» ስላት፣ ሳቅ ብላ
«አጥፋው» አለችኝ። አጠፋሁት፣ አቀፍኳት
«ቅዠት ነበር፡፡ ኮሙኒስቶች የኢራንን ሻህ መንገድ ላይ
አግኝተውት በጩቤ ሲገድሉት አየሁ፡፡ በኋላ ግን ባህራም ሆነ።
«አይዞሽ ነቅተሻል፡ አይዞሽ» እያልኩ እጄን ጀርባዋ ላይ
ሳንሸራትት ትንሽ ከቆየሁ በኋላ
Tu es plutôt une mére Française qu' un sauvage Africain"
አለችኝ («ፈረንሳዊት እናት ነህ እንጂ አፍሪካዊ አረመኔ
አይደለህም ኮ») ሁለታችንም በሳቅ መንፈርፈር ጀመርን። ታድያ'ኮ ያን ያህል የሚያስቅ አልነበረም፤ ያን ጊዜ መሳቅ ስላስፈለገን ነው
እንጂ፡፡ እየተጠመጠመችብኝ፣ ደስታ ባፈነው ድምፅ
«መኖር እንዴት ጥሩ ነው!» አለችኝ
ካንቺ ጋር ሲሆኑማ!»
የኔ ካስትሮ፣ ይልቅ ካንተ ጋር ሲሆኑ ነው እንጂ፡፡»
እቅፍ አድርጌ ጉንጯን ሳምኳት። በጭለማው ላዬ ላይ ወጣች፡
እንደምትወደው ጀርባዋንና አንገቷን እያሻሸሁ
«ምን ይሰማሻል?» አልኳት
እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል»
«የተለየ ስጦታህ ምን እንደሆነ ልንገርህ?»
«ምንድነው?»
«የሰላም
ተሰጥዎ ነው ያለህ፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል። ካንተ ጋር ስሆን ፀፀትና ንስሀ አያስፈልገኝም፡፡»
«ፀፀትና ንስሀ?»
በተለወጠ ድምፅ
«ቅድም ስለበደልኩህ ገላህን ለጋራ ጥቅማችን ሳይሆን ለግል
ደስታዬ ስላዋልኩት»
ፀፀት ሊጀምራት እንደሆነ ገባኝ፡ አሳዘነችኝ
«የኔ ቆንጆ፡ ቂል አትሁኚ። አንቺ ገላሽን እንድደሰትበት
ትሰጪኝ የለ?» አልኳት
«አዎን»
«ታድያ እኔ ገላዬን እንድትደሰቺበት ብሰጥሽ ምናለበት?»
«ከዚያ ይለያላ»
«አስር ጊዜ ልዩ ይሁን። በናንተ አገር ፍቅር ማለት ምንድነው?
መስጠትና መቀበል አይደለም?»
«ነው»
«ታድያ ገላዬን ብሰጥሽና ተቀብለሽ ብትደሰቺበት ምን ፀፀት
ያስፈልገዋል? እኛ አገር መስጠት ማለት መስጠት ነው። ገላዬን
ከሰጠሁሽ የራስሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ የራስሽ ከሆነ ደሞ የፈለግሽውን ልታረጊበት ትችያለሽ ማለት ነው።
«እንደሱ ሆኖ ነው እሚታይህ?»
«ነው እንጂ»
«እንዴት ጥሩ ነህ! እኔ ግን እንዴት መጥፎ ነኝ!»
እንዴት?
«ውሸታም ነኛ!»
«ውሸታም?»
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ስትጠይቀኝ የሌላ ሰው ገላ
እያቀፍሽ በሰውየው ገላ ከኔ ጋር ተኝተሽ ታውቂያለሽ ወይ?”
አላልከኝም? እኔ ምን አልኩህ? »
«በጭራሽ አድርጌው አላውቅም አልሽኝ»
«አዎን። ግን ውሽቴን ነበር። ላንተ
መዋሸቴ በጣም ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ አሁን አንድ ውል እንግባ። አንተ ላለፈው ውሸቴ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ ደሞ ለወደፊቱ ሁልጊዜ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡»
«ስሚኝ የኔ ቆንጆ:: ለኔ ምንም ነገር መንገር የለብሽም፡፡»
“አውቃለሁ። ለዚህ ነው ልነግርህ የምፈልገው:: ከዚያም በላይ፣
አንተ ልትረዳኝ ትችል ይሆናል፡፡ እውነቱን ልንገርህ?»
«እሺ»
«አትጠላኝም?»
«በጭራሽ አልጠላሽም»
እሺ፡፡ ያኔ ታስታውሳለህ?»
የኔ ሻህራዝድ የኔ ቆንጆ፣ እንዴት ልረሳው እችላለሁ?»
“ተመስገንን ፍለጋ የምመጣ ይመስልህ ነበር፡፡ እኔ ግን አንተን
ለማግኘት ነበር የምመጣው፡፡ ሳይህ በጣም ደስ ትለኝ ነበር።
ካስትሮን ትመስለኝ ነበር። ስንቀልድ ስንስቅ ጥርስህን አፍህን ሳየው
አንቀህ እንድትስመኝ እመኝ ነበር፡፡ ታድያ አንተ እምቢ አልክ።
ስለዚህ ካንተ ስለይ፡ ተመስገን ጋ እሄድና አይኔን ጨፍኜ አንተን
እያሰብኩ አቅፈው ነበር፡፡»
«ያውቅ ነበር?»
«ምስኪን ተመስገን! እንዴት አርጎ ይወቅ?»
እንጃ፣ ነግረሽው ሊያውቅ ይችላል ምናልባት?»
«እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ሊገባው ይችላል?»
»እሺ ቀጥዪ»
«ትጠላኛለህ»
«እንግዲህ ቂል አትሁኚ፡፡ በኔ የመጣ ስለምንም አለመግባባት
አትስጊ። ንገሪኝ፡፡»
«እንዴት አርጌ ልንገርህ?»
«እንደመጣልሽ»
ከነገርኩህ በኋላ ምን እንደሚመስልህ ትነግረኝ እንደሆን»
“Parole d'honneur?'' (የከበሬታ ቃልህን ሰጥተሃል?»)
“Parole d'honneur” («የከበሬታ ቃሌን ሰጥቻለሁ»)
«እሺ። እንዲህ ነው:: አየህ፣ ካንተ ጋር ግብረ ስጋ በጣም
ደስ ይለኛል። ደጋግሜ ነግሬሀለሁ፡፡ ያንተን ግማሽ እንኳ ያህል እኔን ማስደሰት የቻለበት የለም፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን
በሽታዬ ይመጣል። ሲመጣ ደሞ መከላከያ የለኝም። ገባህ?»
«ገና አልገባኝም
«እንዳልኩህ፤ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን በሽታዬ ይመጣል፡፡ በጣም
ታምረኛለህ፣ በሀይል እመኝሀለሁ
«ታድያ አለሁልሽ አይደለም?»
“እንደሱ አይደለማ የምታምረኝ»
ልቤ መምታት እየጀመረ
“ታድያ እንዴት ነው?» አልኳት፣ ጐሮሮዬም መድረቅ ጀምሯል
በሀይል ታምረኛለህ፣ ምኞቱ ያንገበግበኛል። ግን ስትተኛኝ
በገዛ ገላህ እንዳይሆን ያስፈልጋል። የሌላ ወንድ ገላ ተውሰህ፣ በሱ ገላ አንተ እንድትተኛኝ ፈልጋለሁ። እንደዚህ ያማርከኝ ጊዜ፣ ካንተ
ተለይቼ መሄድ ይኖርብኛል።»
«ወዴት?» ጉሮሮዬ ጨርሶ ደርቋል
“አንተን ፍለጋ፣ ሌላ ወንድ ፍለጋ»
«ታገኚዋለሽ?»
«ምን ይመስልሀል?» ጉሮሮዋ ውስጥ ወፍራም ተንኮለኛ ሳቅ
ተሰማኝ ቅናት ማለት ይሄ ይሆን እንዴ? ታድያ ንዴቱና ብስጭቱ
የታለ? እኔን የሚሰማኝ ጥልቅ የሆነ እሳት የሆነ የሚያቃጥል
ቅንዝር! እንደ ዛሬም አንገብግቦኝ አያውቅ! ተለይታኝ ስትሄድ፣
ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች፣ ውብ ኣይኖቿን ክፍት ክድን
እያረገች፣ በፍትወተ ስጋ እስኪፈነዱ ብልታቸውን በሚያሳብጠው ፈገግታዋ የመረጠችውን እድለኛ ወንድ ስትጣራ ታየችኝ። ስጋዬ
አላስታግስ አላስችል አለኝ፣ እላዬ ላይ እንደተጋደመች በጥድፊያ
ገለበጥኳትና ጭኖቿን ፈልቅቄ ስገባ፣ በሙዚቃዊ ፈረንሳይኛዋ፣
በቅንዝር ድምፅዋ
“Ah. cheri, comme tu es sauvage! C'est delicieux"
👍20
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...«ዛሬ እንዳትለየኝ አለችኝ
እቅፍ አደረግኳት። ብዙ ነገር ልነግራት ፈለግኩ። ግን የመናገር
ጊዜ አልነበረም፡፡ እንደተቃቀፍን እንቅልፍ አቀፈን .

ቀኑን በብዙ ስትስቅና «ዥማንፉ» የሚለውን ፈረንሳይኛዋን
ስትደጋግም ዋለች፡፡ እኔ አንድ የሆነ ነገር በምመለከትበት ጊዜ እሷ ያላወቅኩባት መስሏት ስትመለከተኝ ብዙ ጊዜ ተሰማኝ፡፡ እንደዚህ ስትመለከተኝ፣ አንድ ሁለት ጊዜ ድንገት ዘወር ብዬ አየኋት ያዘነና የናፈቀ ገፅታ አየሁባት፡ በአይኗ እንደምትጠጣኝ ይመስል ነበር፡፡ የማላውቀው እፍረት ተሰማኝ። ይህን ያህል የሚወደድ ምን አለኝና ነው?

ማታ ከእራት በኋላ «ለቫር ሳን ሚሼልኦ ወሰድኳትና አንድ
ሁካታ ያነሰበት ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ እጄን ዘርግቼ
ጉንጫን አየዳሰስኩ
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«እኔ እንጃ፡ አዝኛለሁ። እዝን ብያለሁ» አለችና፣ እጄን በሁለት
እጇ ይዛ ሳመችው:: አሁንም እፍረት ተሰማኝ። እጄን መሳሟ
ሳይሆን አሳሳሟ
«አውራልኝ አለችኝ
«ስለምን ላውራልሽ?»
«ስላንተ። ዛሬ ውስጤ አንድ ትልቅ ቀፎ ተከፍቷል፡ ባዶውን
ነው፡፡ ባንተ ልሞላው እፈልጋለው:: ከልጅነት ጀምሮ አውራልኝ።
ምንም ሳታስቀር በሙሉ ንገረኝ፡፡»
ጧት ልነግራት ፈልጌ የነበረውን ነገርኳት። ፍርሀቴን፣ ስጋቲን፣
ጭንቀቴን ዘረዘርኩላት። ስጨርስ አንድ እጄን እያሻሽች
«ውይ የኔ ካስትሮ! ሰው ነህ ለካ!» አለችኝ፡፡ በሊላው እጄ ፀጉሯን እየደባበስኩ
«ምን መስዬሽ ኖሯል?» አልኳት
«የማትፈራ፣ የማትጨነቅ፣ የማትታመም፣ የማትሞት መስለህ
ነበር ምትታየኝ፡፡ አትሳቅብኝ! ሰው እንደመሆንህ፣ ሟች መሆንህን
አውቅ ነበር። ግን እውቀት ዋጋ የለውም፡፡ ስሜት ነው ዋናው፡፡
ስሜቴ ደሞ ስላንተ ሌላ ነገር ነበር የሚነግረኝ፡፡ ተው አትሳቅ
እየው፤ እንዲህ አስበው እስቲ።
ጊ ደ ሞፓሳን የደረሰውን
«ቤል አሚ» የተባለውን ልብወለድ ታሪክ አንብበህ የለ? ቤል አሚ
እጅግ የተዋበ፣ ሽንቅጥ የሆነ ጎረምሳ ነው። ታስታውስ የለ፣ መፅሀፉ የሚያልቀው፥ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሄ አይናማ ጎበዝ በብዙ ሰው እየተደነቀ፣ ሀብታሟን ልጅ ሲያገባ ቄሱ ወዳሉበት ሲራመድ ነው።
ታድያ ቤል አሚን ባስታወስከው ጊዜ፤ ሲያረጅ ወይ ሲታመም ወይ
ሲሞት አስበኸው ታውቃለህ? ሁልጊዜ ወጣት እንደሆነ አይደለም የሚታይህ? . . እንደሱ ነው አየህ፡፡ ሳስብህ፣ ዘለኣለም ወጣት፣ ዘለአለም ጤነኛ ዘለአለም ኩሩ ሆነህ ነበር የምትታየኝ»

«አሁን ግን ሰው ሆነህ ትታየኝ ጀመር፡፡ ጧት እንደነገርኩህ!
ማንም ሰው፣ ምንም ነገር ሊያሸንፍህ የማይችል ይመስለኝ ነበር፡፡ የብረት ሰው ትመስለኝ ነበር። አሁን ግን እንደ ቢራቢሮ ሆነህ ነው የምትታየኝ። በጣም ቆንጆ ነህ፣ ነጭ ፈገግታህ ጥቁር ፊትህ ላይ ሲያበራ፣ አልማዝ መሳይ አይኖችህ በሳቅ ብልጭ ብልጭ ሲሉ ወይም በምኞት ሲግሉ፣ በወጣትነት ፀሀይ ውስጥ የሚበር ውብ ቢራቢሮ ነህ። እንደ ቢራቢሮ በቀላሉ የምትጠፋ ነህ። ከዚህ ወጥተን መንገድ ስንሻገር መኪና ቢገጭህ ትሞታለህ፣ በባቡር ስንሄድ ከሌላ ባቡር ጋር ብንጋጭ ትሰባበራለህ፣ በኤሮፕላን ብትበር፣ እና
ኤሮፕላኑ አንድ ነገር ቢሆን፣ እንደ ወረቀት ትቦጫጨቃለህ፡፡
አንዲት ጥይት ብትመታሀ ትሞታለህ፡፡ ...»
«አይዞሽ አይዞሽ»

«ምን አይዞሽ ትለኛለህ? መሞትህ ነው ። አይታይህም?»
ሌላውም ይሞታል ኮ፡፡ አንቺም ጭምር»

ሌላውን የት አውቀዋለሁ? ምኔ ነው? አንተ ግን አንተ ነህ፡፡
ማንንም አትፈራም፡፡ እንደ ሲራኖ ደ ቤርዤራክ ነህ፡፡ ጀግና ነህ።
ወንድ ነህ። የኔ ነህ። እወድሀለሁ፡፡ የኔን የራሴን ማርጀትና መሞት
በሀሳቤ ልቀበለው እችላለሁ፡፡ አንተ ታረጃለሀ ትሞታለህ ቢሉኝ ግን አልቀበልም፡፡ ይሄ አንፀባራቂ ፈገግታህ ሲጨልም፣ እነዚህ ብሩህ አይኖችህ ሲፈዙ ለማየት አልፈልግም፡፡ አልቀበልም፡፡ እምቢዮ! ኤክስ ውስጥ ፀሀይ እየሞቁ በባዶ ብርጭቆ አይን ሞታቸውን ከሚመለከቱት ሽማግሌዎች አንዱ እንድትሆን እልፈቅድልህም፡፡
አልፈቅድልህም! ይገባሀል? አልፈቅድልህም! ወጣት መአዛህን
ወስደው የእርጅና ሽታ ሲለጥፉብህ እንዳትቀበል!»

«እሺ የኔ ቆንጆ፣ እሺ ይቅር፣ ረጋ በይ አይዞሽ። አሁን
ወጣት ነኝ፣ ካንቺ ጋር ነኝ»
«አሁን ብቻ ነዋ!»
«አሁን ብቻ አይደለም፡፡ አይዞሽ አይዞሽ»
«ከዚህ ውሰድኝ»
«እሺ»
«ውሰደኝና ልብሴን አውልቀህ እቅፍ አርገኝ። ከድሮ ይበልጥ
እቀፈኝ፡፡ ፍርሀት ይዞኛል፣ ሀዘን ተጫጭኖኛል፡፡ መወደድ መታቀፍ
እፈልጋለሁ፡፡»
«እሺ የኔ ሲልቪ»
«እንሂዱ»
«እሺ»
«በል እንሂድ»
«እሺ የኔ ፍቅር፣ ይኸው መሄዳችን ነው።»
ሆቴላችን እንደደረስን፣ ቶሎ ልብሷን አውልቄ እቅፍ አረግኳት
«እወድሻለሁ የኔ ፍቅር፣ ከልቤ እወድሻለሁ» አልኳት
«በላ አሳየኝ፣ በስጋህ አሳየኝ፣ በነብስህ አሳየኝ
«ይኸው የኔ ፍቅር፣ ይኸው»
በጭለማው፣ በሹክሹክታ
«አማልክቱ ሁሉ ሞተዋል፡፡ እኛ ብቻ ነን የቀረነው:: አንተ ለኔ
አምላኬ ነህ። እኔስ አምላክህ ነኝ?»
«አዎን አምላኬ ነሽ»
«ድገምልኝ»
«አምላኬ ነሽ፡፡ አምላኬ ነሽ፡ የኔ አምላክ ነሽ»
አፌ ውስጥ እየተነፈሰች «በላ መስዋእት አቅርብልኝ»
«እሺ። ምን መስዋእት ትፈልጊያለሽ?»
«ሁልጊዜ ከላይ ሆነህ ወደታች ታየኛለህ፡፡ ዛሬ ታች ውረድና
እኔ አዘቅዝቄ ልመልከትህ ክብርህን ሰዋልኝ»
«እሺ፡፡ ክብሬን ውሰጂው:: ላንቺ ክብሬን ብሰዋ ደስ ይለኛል።
በጭለማው በሹክሹክታ
«በላ»
«እዘዢኝ»
«እንዳታመነታ ልባርግ»
«ዝግጁ ነኝ፡፡ ንገሪኝ፡፡ ምን ላርግሽ? ምን ልሁንልሽ?»
«ወደታች ውረድና ከእግሬ ጥፍር ጀምረህ እየሳምከኝ አየላስከኝ
ወደላይ ና፡፡»
«እሺ የኔ መቤት»
ከእግሯ ጥፍር ጀምሬ እስከ አፏ ሳምኳት ላስኳት። በአፉ
ተቀበለችኝና እየሳመችኝ፣ በጭለማው በሹክሹክታ
«ጥሩ ነበር፣ ግሩም ነበር፡፡ ግን አይበቃም። በጭራሽ
አይበቃኝም» አለችኝ
«የፈለግሽውን ንገሪኝ። አደርገዋለሁ፡፡ አምላኬ ነሽ»
«እንዴት ነው ጭኖቼ መሀል ስመኘኝ የማታውቀው?»
«አድርጌው አላውቅማ»
«በጭራሽ አርገኸው አታውቅም?»
«በጭራሽ»
«በጭለማው፣ በሹክሹክታ
ውረድና ጭኖቼ
ሳመኝ። ልክ አፌን
እንደምትስመኝ አርገህ ሳመኝ፤ በከንፈርህ፣ በጥርስህ፣ በምላስህ
ሳመኝ፡፡ አምላክህ ነኝ፡፡ ካንተ ምፈልገው መስዋእት እሱ ነው::»
«እሺ»
ሳረገው አልቀፈፈኝም፡፡ በጭራሽ አልቀፈፈኝም፡፡ እንዲያውም
በጣም ነው ደስ ያለኝ። ስስማት፣ በማክበርና በማምለክ ስስማት፣
እያቃሰተች ራሴን ስታሻሽ ቆይታ ቆይታ፣ በጭንቅላቴ ስባ ወደ ላይ
ወሰደችኝና
«ትወደኛለህ፡፡ በእውነት ትወደኛለህ፡፡ እንዴት ግሩም ነው!
ትወደኛለህ፡፡ አንተ እኔን ትወደኛለህ!» አያለች ስታቃስት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ያንቺው ነኝ» እያልኩ አባበልኳት
«እንዴት እድለኛ ነኝ! እንደ ዛሬ ደስ ብሎኝ ኣያውቅም»
«ገዝተሽኛል»
«ገዝቼሀለሁ። እወድሀለሁ፡፡ አንተም ገዝተኸኛል። እንዴት ጥሩ
«አሁን ተኚ። ደክሞሻል፡፡»
«እሺ፣ አቅፈህ አስተኛኝ።»
ከትንሽ ዝምታ በኋላ
«እንደዚህ ጥሩ ልጅ ሆነህ ሽርሙጣ መውደድህ አያሳዝንም?»
👍21😁1
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...ዛሬ ግን ሲልቪ አላዘነችም፡
የተለመደው ሳቋ አይኖቿን እየደጋገመ ያበራቸዋል፣ ከንፈሮቿን
ያለማቋረጥ ይከፋፍታቸዋል። እራት ላይ ሁለት ጠርሙስ ወይን
ጠጥተን ነበር፣ አሁን ሁለት ጠርሙስ ቢራ ስንቀላቅልበት ጊዜ ወሬአችን ሞቀ.
«አቤት እንዴት ነው ያማርሽኝ!» አልኳት
«ሱሪ ስለለበስኩ ነው?»
«ግማሽ»
«ግማሽስ?»
«ከስሩ ሙታንቲ ስላላረግሽ ነው። ለምን ሙታንቲ
አልለበስሽም?»
«ለምን ይመስልሀል?» አይኖቿኸ ውስጥ ያ የሚያሰክረኝ ቅንዝር
ይታያል
«እኔ እንጃ፡፡ ለምንድነው?»
«ግማሹ አንተ እንዳሁን እንድትመኘኝ ነው»
«ግማሹስ?»
«አይ! አይነገርም፡፡ በብርሀን አይነገርም፡፡» የአፏ አከፋፈት!
«ንገሪኝ። ንገሪኝ፡፡ ለምንድነው ሙታንቲ ሳትለብሺ
የመጣሽው?»
«ልንገርህ?»
«ንገሪኝ!»
«ተው ይቆጭሀል!»
«ንገሪኝ!»
«ሱሪው ጠባብ ነው:: ያለሙታንቲ ስለብሰው ቂጤ የበለጠ
አያምርም? የበለጠ አያስጐመጅም?»
«ያንገበግባል»
«እና ስራመድ ወንዶቹ እንዴት እንደሚያዩኝ አላየህም?»
ቅናቱ ጀመረኝ
«አላየሁም» አልኳት
«ያዩኝ ነበር። ይታወቀኛል'ኮ፡፡ ስራመድ ከኋላዬ ሆነው
ሲያዩኝ፣ አይናቸው ከዳሌዬ ጋር ሲንከራተት ይታወቀኛል፡፡»
«እና ምን ይሰማሻል?»
«ደስ ይለኛል፣ ዛሬ በሀይል አላምርም?»
«ታምሪያለሽ፡፡ ግን ከሌላ ጊዜ ይበልጥ እንደምታምሪ እንዴት
አወቅሽ?»
«ይታወቀኛላ»
«እንዴት ይታወቅሻል?»
«ውስጤ ይሰማኛል፡፡ አየህ፣ ዛሬ ወንድ አምሮኛል። በሀይል
አምሮኛል። ስለዚህ፣ ፊቴ፣ ገላዬ፣ አረማመዴ ሁሉ ወንድ ሊስብ
ይፈልጋል። ስለዚህ በሀይል አምራለሁ።»
የትላንቱ ሌሊት አይነት ቅናት ውስጤ መንቀሳቀስ ጀመረ
«እንዴት ነው የምታየኝ አንተ!?»
«እንዴት ነው?»
«አማርኩህ መሰለኝ»
«በጣም አምረሽኛል»
«እኔም አምረኸኛል። ግን ዛሬስ ልታጠግበኝ የምትችል
ኣይመስ ለኝም፡፡ ዛሬ የያዘኝ ምኞት እንደ እሳት ነው:: ለማጥፋት
ብዙ ብዙ ውሀ ይፈልጋል፡፡ አንተ ብቻህን ልታጠፋልኝ መቻልህን
እንጃ የትላንቱ ሌሊት ቅናት እንቅ አደረገኝ፣ ሌላ
ወንድ እንዲያምራት ተመኘሁ
«እና ምን ትፈልጊያለሽ? ንገሪኝ እስቲ»
«ትቆጣለሁ!»
«ይልቅ ንገሪኝ»
«ንገሪኝ፡፡ ምን ያምርሻል?»
«ወንድ ያምረኛል። ሶስት አራት ቆንጆ ቆንጆ ወንድ ባጎኝ
እፈቅዳለሁ፡፡
«እንድ አይበቃሽም?»
«አይበቃኝም። አልጠግብም፡፡ ዛሬስ አንተ እንኳ ብትሆን
እታጠግበኝም፡፡»
እና ምን ይሻላል?»
«አንተ ባትኖር መፍትሄ ነበረው»
«እኔ ባልኖር እንዲህ አይነት ስሜት ሲመጣብሽ ምን ታረጊያለሽ?»
ጠረጴዛ ላይ ያለውን ጥቁር ቦርሳዋን መታ እያደረገች
«ማስታወሻ ደብተሬ ውስጥ የቴሌፎን ቁጥሮች አሉኝ»

«የወንዶችሽ?»

ጭንቅላቷን በኣዎንታ ነቀነቀች
«አሁንም ልትደውይሳቸው ትችያለሽ' ኮ»– ደነገጠኩ፡፡ እንዲህ ማለት መቼ ፈለግኩና? በጭራሽ አልፈለግኩም፡፡ ምን ነካኝ? እስቲ
አሁን እንዲህ ይባላል? ምን አይነት ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት!?
እጇን ቶሎ ሰዳ እጄን በሀይል ጨበጠች። አይኖቿ ውብ ብርሀን
ለበሱ፣ ቀያይ ከንፈሮቿን በምላሷ አረጠበች፣ ከውስጥ ወተት መሳይ
ጥርሶቿ ይብለጨለጫሉ፡፡ ማማሯ ማስጐምጀቷ ስሜት ባፈነው
ወፍራም ድምፅዋ
«ትፈቅድልኛለህ? ልደውልላቸው? አትጠላኝም? በኋላ
አታባርረኝም? ልደውልላቸው? አንተን ነው የምወደው:: ግን በሽተኛ ነኝ። መሄድ አለብኝ። ግን የምትጠላኝ ከሆነ አልሄድም፡፡ ልደውል?
ልሂድ? ትፈቅዳለህ?»
አቅበጠበጣት፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ ደሞ በሀይል አማረችኝ፡፡ እንደዛሬ
አምራኝ አታውቅም፡፡ ግን አሁን ላገኛት ኣልፈለግኩም፡፡
ከሆነልኝና ወደ ሌሎቹ ከሄደችልኝ፣ ከሌላ ጋር መሆኗን እያሰብኩ
መሰቃየት አማረኝ፡፡ እሷ ወንዶች ያማሯትን ያህል እኔ መሰቃየት
አማረኝ፣ መቅናት፣ መቃጠል አሰኘኝ፡፡ ራሲንም ለማወቅ ተጠማሁ፡፡ማን ነኝ? ፍቅር ይዞኛል? እና ፍቅር ምንድነው? ቅናትስ? የሁለቱስ ዝምድና እንዴት ያለ ነው የሚያፈቅሩዋት ሴት ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ ሌላ ወንድ ፍለጋ ስትሄድ ማየት፣ ሄዳ ስትመለስ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሶስት ወንድ በየተራ ሲደሰትባት፣ ሲስማት፣ ሲልሳት፣ ሲያለፋት ከቆየ በኋላ፣ ከዚያ ተቀብለው ይህን ሁሉ እያወቁ ያችን የሚወዷትን ሴት ማቀፍ፣
መሳም፣ መላስ፣ በቅናት እየነደዱ ሴትዮዋን መተኛት
ይሄ ደሞ ከሁሉ የጠለቀ፣ ከሁሉ የላቀ፣ ከሁሉ የደመቀ ከሁሉ የጨለመ፣ የሚያቃጥል፣ የሚበርድ፣ የሚያስደስት፣ የሚያበሳጭ፣ የሚገድል፣
የሚያድን፤ ከስሜት በላይ የሆነ ስሜት ይሰጥ ይሆን?

«ልሂድ ትፈቅዳለህ?» አለችኝ
«ብኋላ የት አገኝሻለሁ?» አልኳት፡፡ ድምፁ የኔው አይመስልም
ሆቴላችን»
«ከስንት ሰአት በኋላ?»
ሰአቷን አየች
«ከአምስት ሰአት በኋላ፡፡ ልክ በሰባት» አለችኝ
በጠረጴዛው ተንጠራርታ ግምባሬን ሳመችኝ
«አግባኝ፡፡ እባክህን አግባኝ! ይቅር እሺ። ይቅር፡፡ “nous nous
reverons bientôt'' (“አሁን አሁን እንገናኛለን») ብላ እጄን ስማኝ ተነስታ ከካፌው ወጣች። ስትሄድ ረዥም አንገቷን እያወዛወዘችው፣
ወደኋላዋ የተለቀቀው ፀጉሯ ዥዋዥዌ ይጫወታል። ከቀጭን ወገቧ ስር ወፍራም ዳሌዋ ይወዛወዛል፣ ስትራመድ ጠባቡ ሱሪዋ የቂጧን ውብ ቅርፅ ያሳያል ከውስጥ ሙታንቲ አልለበሰችም!!
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ፣ ከካፌው ወጥቼ ሲኒማ ገባሁ
እንደ አጋጣሚ ኢንግግር በርግማን የተባለው ገናና የስዊድን ፊልም አዘጋጅ የፈጠረው «ሰባተኛው ማህተም» የተባለው እጅግ የተመሰገነ ፊልም ነበር አንድ የጥንት ስዊድናዊ አርበኛ፣ ከኢየሩሳሌም የመስቀል ዘመቻ ሲመለስ፣ ልክ የክርስትያን ኢውርፓን መሬት እንደረገጠ፣ ሞት የተራ ሰው መልክ ለብሶ ይመጣና
«ልወስድህ መጥቻለሁ» ይለዋል
አርበኛው
«አሁን ካንተ ጋር መምጣት አይሆንልኝም፡፡
ላደርጋቸው የሚገባኝ፣ ግን ገና ያልፈጸምኳቸው፣ አንድ ሁለት ጉዳዮች አሉ» ይለዋል
ሞት «ልወስዳቸው ስመጣ ሰዎች ሁሉ ይህንኑ ነው የሚሉኝ ይለዋል

አርበኛው «እኔ ግን እውነቴን ነው:: ላደርጋቸው የሚገባኝ
ነገሮች አሉ፡፡ . . . በቼስ ጨዋታ የሚችልህ የለም ይባላል» ይለዋል
«እውነት ነው»
አርበኛው «እኔ ግን የምችልህ ይመስለኛል። ይዋጣልን እስቲ።
ምን ቸገረህ? በመጨረሻ ማሸነፍህ አይቀር» ይለዋል
“እሺ እንጫወት»
“እስክሽነፍ ድረስ ልኑር ፍቀድልኝና፣ እኔን ለማሸነፍ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብህ እናያለን
«እሺ»
ጨዋታቸውን ይጀምራሉ
እንደሱ ያለ አስደናቂ ፊልም አይቼ አላውቅም።
እጭለማው ውስጥ ሲልቪን አንድ አምስት ጊዜ ብቻ በድንገት
እያስታወስኳት በሀይል ድንግጥ አልኩ:: ግን ያኔውኑ ፊልሙ ከሀሳቢ ያባርራታል። ግሩም ፊልም ነበር። ሲያልቅ ደገምኩት፡፡ በጭራሽ አልጠገብኩትም፡፡ ግን ሶስተኛ ላየው አልቻልኩም፡፡ ሲኒማ ቤቱ ተዘጋ፡፡ ወጥቼ ስለፊልሙ እያሰላሰልኩ ስራመድ ሰአቴን አየሁ። ሰባት ከሩብ ልቤ በሀይል መምታት ጀመረ፡፡ ባለሁበት ቆምኩ።ሲልቪ እንዴት እስካሁን የሷ ሀሳብ አላስጨነቀኝም? ይሄ
ኢንግማር በርግማን እንዴት ያለ ፍፁም አርቲስት ቢሆን ነው?!
እስካሁን ከሱ ጋር ነበርኩ። ከሱ ጋር ስለሞትና ስለህይወት ሳስብ፣
👍24
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...ስለነሱ ስትነግሪኝ ለምን ልቤ እንደሚጠፋ ልንገርሽ»

«ለምንድነው?»
«ከነገርሽኝ ነገሩን አወቅኩት ማለት ነው። ካወቅኩት ደሞ
አያስፈራኝም፡፡ ጭለማ ሲሆን፣ ምን ይመጣብኝ ይሆን? በማለት
እፈራለሁ እንጂ፡ በብርሀን ካየሁት ማንም ሰው ቢሆን አያስፈራኝም፡፡ ማለቴ ሳላውቀው አንድ ሰው ይተኛሽ ይሆን? ብዬ እፈራለሁ እንጂ፣ እያወቅኩ ከሆነ፣ አስር ሰው ቢተኛሽም አልፈራም፡፡
እያወቅኩት ከተደረገ ድርጊቱ የኔ ሆነ ማለት ነው፡፡ የኔ ከሆነ
ሊጎዳኝ አይችልም .. እንዴት እንደተኙሽ ስትነግሪኝ፣ እኔ እነሱን
ሆኜ ተኛሁሽ፣ ተወስዶብኝ የነበረውን ገላሽን፣ ቃላትን መለሱልኝ ማለት ነው። ... ስለዚህ ነው የተኙሽ ወንዶች ቁጥር እንደመብዛቱ መጠን የኔ ደስታ የሚበዛው፡፡»

«አልገባኝም»
«አየሽ፣ ማንም አልተኛሽም ማለት ያስፈራኛል፡፡ ጭለማ ውስጥ
ነኝ ማለት ነው። .. አንድ ሰው ተኝቶኛል ብትይ፡ ትንሽ ይሻለኛል። ግን አሁንም አንድ ሰው ደብቀሽኝ ሊሆን ይችላል። አራት ወንድ ተኛኝ ብትይ የበለጠ ይሻላል። ምክንያቱም የደበቅሽኝ ነገር
የለም ማለት ነው። ስለዚህ መፍራት አያስፈልገኝም፤ ምክንያቱም የተወሰደብኝ ሁሉ ተመልሶልኝ አቅፌዋለሁ ማለት ነው፡፡»

«ገባኝ። አንድ ጥያቄ፡፡»
«ምን?»
«እኔም እነሱም ያው ነን ካልክ፣ ምን እንዳረጉኝ ባታውቅስ ምን
ልዩነት ያመጣል?»
«ይህን አትጠይቂኝ። ላስረዳሽ አልችልም፡፡ እኔም ራሴ
አይገባኝም፡፡ ምናልባት እኔም እነሱም ያው ለመሆን የምንችለው፣ እነሱ ያረጉትን ካወቅኩ ብቻ ይሆናል፡፡»
ዝም ዝም ሆነ፡፡ ታችኛ ከንፈሯን እየነከለች ስታስብ ቆየች
«ልንገርህ?» አለች
«ምን?»
«እኔ በበኩሌ ሌላ ሆኖ ነው የሚታየኝ»
እንዴት ሆኖ ነው ሚታይሽ?»
“በጭራሽ በሽታ አልያዘህም፡፡ እንደሌላ ወንድ ነህ»
ሌሎች ወንዶች ከሌላ ጋር ተኝተሽ ነይልኝ ይሉሻል?»
« አይሉኝም
እኔም የሚሉሽ አልመሰለኝም
«ስማኝ እንግዲህ:: ክርክሩን ተውና አድምጠኝ። በግብረ ስጋ
በኩል ስለሴቶች ታውቃለህ እንጂ፣ በጥቅሉ ስለ ሴቶች ምን
ታውቃለህ? እነሱ ካልነገሩሀ ስለነሱ ለማወቅ አትችልም፡፡ እነሱ ደሞ የውስጡን አይነግሩህም። ለምሳሌ፣ አንተ እኔን ከሌሎች እየተቀበልክ እንደምትደሰትብኝ ለሰው ትነግራለህ ይመስልሀል? ለማንም አትናገርም። ሌሎችም ወንዶች ውስጣዊውን ምስጢር አይነግሩህም፡፡
ስለዚህ ሴት ካልሆንክ ወንዶችን በዚህ በኩል ልታውቃቸው
አትችልም። እኔ ልንገርህ

“ብዙ ጋብቻዎች መቀዝቀዝ ሲጀምሩ፣ ሴትዮዋ ተስፋ
ትቆርጥና ውሽማ ትይዛለች። ባልየው ሲያውቅ ምን እንደሚያደርግ ታውቃለህ? ለጊዜው ይናደዳል፣ ይደበድባታል፣ እንፋታ ይላል።
በኋላ ግን ታርቀው ይቅርታ ያደርግላትና፣ በጣም ሊወዳት
ይጀምራል። ቀዝቅዞ የነበረው ጋብቻ ይሞቃል፣ ይታደሳል። ለምን? ሴትዮዋ ሌላ ወንድ ጋ ስለሄደች ነው

መንገድ ዳር ውጣና ጎረምሶቹን ሴት ሲያድኑ እያቸው።
ሴትዮዋ በጣም ጨዋ ከመሰለቻቸው፣ ምንም ቆንጆ ብትሆን አይከተሏትም፡፡ ትንሽ በመጠኑ ስድ ብጤ ከሆነች ግን
አስተያየቷ፣ አረማመዷ፣ ወይም አለባበሷ በቂ ልቅነት ካሳየ
ጎረምሶቹ ይሻሟታል። በቀላሉ ሊያገኙዋት ስለሚችሉ ብቻ
እንዳይመስልህ፡፡ ዋናው ምክንያት ሌላ ነው። ባለጌ ከመሰለች፣
እንግዲያው ብዙ ወንድ ኣውቃለች ማለት ነው:: ለዚህ ነው
የሚሻሟት
«እየው፣ የሰው ልጅ ፍጥረቱ እንደዚህ ነው:: አንድ የለመድከው ሰው ሊለይህ የሆነ እንደሆነ ልትወደው ትጀምራለህ።
ለህይወትህ የሚያስፈራ በሽታ የያዘህ የመሰለህ እንደሆነ፣ በፊት
ከምንም የማትቆጥራትን ህይወትህን በሀይል ልትወዳት ትጀምራለህ

ሀኪም ጨው እንዳትበላ ያዘዘህ : እንደሆነ፣ ጨው ምንኛ ግሩም
ቅመም እንደሆነ ትገነዘባለህ ሴትህ ወደሌላ የሄደችብህ
እንደሆነ፣ እንዴት ቆንጆ እንደሆነች እንደ አዲስ ሊታይህ ይጀምራል
በራሲ የሚያጋጥመኝን ለምን አልነግርህም? በዚህ ሰሞን
ከማያቸው ወንዶች ሁለቱ እንዴት እንደሚሆኑ ላጫውትህ፡፡ ሁለቱም
ያው ናቸው። ስለዚህ ስለአንዱ ልንገርህ፡፡ ማርሴል ይባላል። በጣም ቆንጆ ነው። ብዙ ሴት ያወቀ ወጣት ነው። ማታ ከእራት በኋላ ካንተ እንደተለየሁ፣ በቀጥታ ወደሱ የሄድኩ እንደሆነ፣ ንፁህ ነኝ፣ የማንም ላብ አልነካኝም፣ ጠረኔ የራሴ ነው፡፡ ልብሴን አስወልቆ ያቅፈኛል! በደምብ ያስደስተኛል፡፡ አንዳንዴ ታድያ፣ ካንተ እንደትለየሁ በቀጥታ ወደሱ እልሄድም፡፡ በፊት ሌላጋ እደርሳለሁ። እና እሱጋ ስሄድ የሌላ ወንድ ላብ ነክቶኛል፣ ጠረኔ የብቻዬ ሳይሆን ከጎረምሳ ጠረን ጋር ተቀላቅሏል። አሁንም ልብሴን ያስወልቀኝና ያቅፈኛል፤ ግን እንደነብር ይሆናል፣ ይጨፈልቀኛል፣ ይነክሰኛል።
ስለሌላ ወንድ አንነጋገርም ግን ሌላጋ እንደነበርኩ በማወቁ የበለጠ እንደሚጣፍጠው ግልፅ ነው፡፡ ይታይሀል?"

«በሚገባ! እና እኔ እንዲህ የምሆንበት ምክንያቱ ምን
ይመስልሻል?» ቀላል ነው። አንደኛ፣ ሌላ ወንድ ከተኛኝ ቆንጆ ነኝ ማለት ነው። ብዙዎች ከተኙኝ እጅግ በጣም ቆንጆ ነኝ፡፡ ስለዚህ የቀለጠ ትፈልገኛለህ፡፡ ሁለተኛ፣ ሌላው ተኝቶኝ አንተ ቀጥለህ ከተኛኸኝ፣ ከሱ ቀምተህ ወሰድከኝ ማለት ነው:: እኔ በሀይል ቆንጆ ሆኜ ከሌሎቹ ሁሉ ቀምተህ ከወሰድከኝ፣ ከሌሎቹ ሁሉ የበለጠ ወንድ ነህ።በወንድነት ከሁሉ በላይ ሆንክ፣ ስለዚህ ደስ ይልሀል፡፡ በጣም ደስ ይልሀል። ወንዶች ሁላችሁም እንደሱ ናችሁ። ግን አየችኝ..

«ግን ምን?» አልኳት
አብዛኛዎቹ ወንዶች ውጪውን ጎበዝ ቢመስሉም ውስጡን ፈሪ
ናቸው፡፡ የውስጥ ስሜታቸውን አይተው መቀበል ይፈራሉ። ስለዚህ ከራሳቸው ይደብቁታል። ሁሉም ወንድ አብዛኛው ወንድ ልበል የራሱን ሴት ሌሎች ሲቀምሱበትና እሱ ነጥቋቸው መልሶ የራሱ ሲያረጋት፣ የበለጠ ወንድነት ይሰማዋል። በሀይል ደስ ይለዋል። ግን ይህን እንደ ጉድ አርጎ ስለሚቆጥረውና ስለሚያፍርበት፣ እያየውም
አውቆ አይኑን ይጨፍናል። ስለዚህ ያስመስላል፤ ያስመስላል፡
ያስመስላል። አቤት ስንት ማስመሰል አለ!

«እዚህ ላይ ነው አንተን ከልቤ የማደንቅህ፡፡ እቺን
ያህል አትፈራም። ወደነብስህ ውስጥ አትኩረህ ትመለከታለህ፡፡ እዚያ ውስጥ ምንም ቀፋፊ ነገር ብታይ አይንህን አትጨፍንም፡፡ ስለዚህ ያለማስመሰል ትኖራለህ ውስጣዊውን ኑሮ ማለቴ ነው። እንግዲህ ወደ ውስጥህ ተመለከትክ፣ ውስጥህ እኔን ሌሎች ቢተኙኝ ከነሱ
ቀምተህ ስትተኛኝ ደስ እንደሚለው ነገረህ። ስለዚህ እኔን 'ሂጂ ወንዶችሽ ጋ አልከኝ። ሄድኩ፡፡ ተመለስኩ። ተደሰትክብኝ፡፡ ወንድ
ነህ። አንተ እውነተኛ ወንድ የሆንከውን ያህል እኔ እውነተኛ ሴት ሆኜ እንደሆነ እጅግ ኩራት ይሰማኛል።»

«አንቺ እንደምትይኝ ከሆንኩ፣ አንቺም እንደኔ አይነት ነሽ።
ልክ እንደኔ አይነት! አብዛኛዎቹ ሴቶች፣ ፍቅር ከያዘኝ ወንድ ጋር
ብቻ ነው ግብረ ስጋ ደስ የሚለኝ ይላሉ። ይህም ማስመሰል፣
ማስመሰል፣ ማስመሰል ነው። አንቺ ግን ለራስሽ አትዋሺም። ቆንጆ ወጣት ሆኖ ቆንጆ ወንድ እያቀያየሩ መደሰት እንዴት ያለ ገነት ነው!' ትያለሽ። እኔኮ አልችልም፣ ቆንጆ ወንድ ሳይ አያስችለኝም፣ቁንጅናውን መንካት መዳሰስ አለብኝ፣ በወጣትነቱ መደሰት አለብኝ ትያለሽ

“አንድ ቀን አንድ ነገር አልሽኝ። አስከመቼም አልረሳውም፡፡»

«ምን አልኩህ?»
👍23👎1
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

በሰፊ ውብ አፏ እየሳቀችብኝ፡ እየወደደችኝ ድንገት ሳቁን እየተወች አንድ ነገር ልነግርህ እፈልግ ነበር» አለችኝ ንገሪኝ
እንዳትቆጣ፡፡ ወንድ ሆነህ አትስማኝ፡ ደራሲ ሆነህ አዳምጠኝ እንጂ
«እሺ»
"Parole d'honneur?"
"Parole d'honneur!"
«አንተን እወድሀለሁ። ከልቤ አፈቅርሀለሁ፡፡ ግን ፖልን ልረሳው
አልችልም። የመጀመሪያዬ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ሳልጠግበው
ስለሄደብኝ ጭምር ይመስለኛል። «ይገባሀል?»
«ይገባኛል»
«እና አንድንድ ጊዜ ይናፍቀኛል፡፡ ይመስለኛል፣ በውስጤ
የልጃገረድነቴ ጊዜያት ከሱ ጋር ተዋህዷል፡፡ እና ያ ጊዜያት
ሲናፍቀኝ፣ ፖል ይናፍቀኛል። ከልቤ ላወጣው ልረሳው እሞክራለሁ።
ግን የምችል አይመስለኝም፡፡ የምልህ ይገባሀል?»
«ይመስለኛል»
«ስለዚህ ፖልን የሚመስል ሰው ሁሉ ደስ ይለኛል፤ ይስበኛል።
... እና ስለ ባህራም ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡»
ይናገራል ብላ ዝም አለች። መናገሩ እየከበዳት ሄዷል። ዝም
ብዬ ሳያት ቀጠለች
«አንተ ነህ ባህራምን እንድወደው ያረግከኝ፡፡ ስለሱ ብዙ ብዙ
አወራህልኝ። አራት ወር ሙሉ አወራህልኝ፡፡ ከወሬህ እንዳየሁት፣
በጣም በጣም ታከብረዋለህ። ግን እንደማውቅህ አንተ ማንንም
አታከብርም፡፡ ስለዚህ፣ ይሄ ባህራም እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው? አልኩ። አንዲት ሴት እንዲህ ካለች ደሞ መመለሻ የላትም። ይህን ያባሰው ምንድነው? ከወሬህ እንደተገነዘብኩት ባህራም እንደ ፖል ያለ ሰው ነው። እንደሌላው ሰው ከተራ ጭቃ ተጠፍጥፎ አልተሰራም፡፡ ጀግናዎቹ ከሚሰሩበት ከልዩ ጭቃ ተቀርፆ፣ በልዩ ንፁህ እሳት ውስጥ ነው የተጠበሰው። ባህራምን እንደዚህ አድርገህ
ነው ያሳየኸኝ
«አንተ ያንን ያህል እያከበርከው፣ ከፖል ጋር ያንን ያህል
እየተመሳሰለ፣ እንዴት ላይለኝ ይችላል? እኔ ደሞ
እንደምታውቀኝ ነኝ:: እንዴት ላልመኘው እችላለሁ?»
«ፍቅር ይዞሻል?»
ራሷን በሀይል
እየነቀነቀች፡ ከኋላዋ ጥቁር ሀር ፀጉሯ እየተወዛወዘ፣ የደስታ ሳይሆን የመሰቃየትና የመደናገር ፈገግታ ውብ አፏን እየሸመቀቀው

እኔ እንጂ! እኔ እንጃ! እኔ እንጃ!» አለችና ራሷን ጠረጴዛው ላይ
ደፋች
ረዥም ፀጥታ
እጄን ሰድጄ ራሷ ላይ አሳረፍኩት። ቀና ብላ አየችኝ፡፡ እምባዋ
ይወርዳል
«ሶስት ፍቅር አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል?» አለችኝ
“ሴትዮዋ ተራ ከሆነች አይችልም» አልኳት
ጠረጴዛው ላይ የነበረ እጄን ወስዳ ከጎንጯ ጋር እያተሻሸት፣
በእምባዋ እጄን እያረጠበች፡ በተጨነቀ ድምፅ
«ብዙ ጎዳሁህ፣ የኔ ቢራቢሮ?» አለችኝ
ግድ የለሽም አልኳት
«አለኝ እንጂ። ላንተ ብዙ ግድ አለኝ፡፡ ለዚህ እኮ ነው
የምነግርህ፡፡»
«አውቃለሁ»
ለኔ እንዴት ጥሩ ነህ! አሁን ምን ይሻለኛል?»
ቆንጆ ነሽ። ተወዳጅ ነሽ፡፡ ለምን አትወጂውም?»
በመሀረቤ እምባዋን እየጠረገች
«አንተስ? አትቀየምም?»
ሌሎች ጋ ትሂጂ የለ? ስለዚህ ለኔ ያው ነው»
ውይ! እንዴት ደግ ነህ!?»
«ለምን?»
ውሸትክን ነዋ» ተናፈጠች
እኔ እንድደሰት ብለህ
ትሰቃያለህ፡፡»
«የምን ስቃይ?»
መሀረቤን አጥፋ እየመለሰችልኝ
«እንግዲህ አትዋሽ። ይበቃሀል። አውቅሀለሁ'ኮ። ከምትገምተው
በላይ አውቅሀለሁ፡፡ ፊትህ ላይና አይኖችህ ውስጥ ስንትና ስንት ነገር ይታየኛል መስለህ።»
«ምን ይታይሻል?»
«ስለባህራም ስነግርህ በብዙ ነው ያዘንከው::
«ላንቺ ነዋ ያዘንኩልሽ፡፡
«እሱም ታይቶኛል። ግን ለራስህም በሀይል በመሰቃየት ላይ ነህ፡፡ እና በጣም አዝናለሁ፡፡ እንዲህ በመሆኔ በጣም አዝናለሁ፡፡»
«በማዘን የትም አይደረስም፡፡»
አውቃለሁ የኔ ቆንጆ:: ግን ማዘን አይቀርም፡፡»
ዝም ዝም ሆነ
«በኔ ብቻ ሳይሆን በባህራምም ጭምር ነው ያዘንከው። ልክ
ዝም አልኳት
«እንግዲህ ልንገርህ፡፡ እውነቱን ብታውቅ ይሻላል። ልንገርህ?»
«እሺ፡፡»
«ያን እለት ማታ ያ ሰውዬ ባህራምን ሊገድለው አልመጣም?
እና አንተ ኒኮልን ይዘህ ማርዕይ አልሄድክም? ከኒኮል ጋር
ምንም አልሰራችሁም? እውነት ተናገር፡፡»
«ምንም አልሰራንም፡፡ ይልቅ ቀጥዪ።»
«እና ሰውየውን ሲገድለው አላየሁም? እሱን ነግሬሀለሁ። እና
ከዚያ ወደ ቤት ሄድን፡፡ ባህራም ልክ ምንም እንዳልስራ በእርጋታ
ሶፋ ላይ ተቀመጠ። እኔ መጠጥ ሰጠሁትና ሶፋው ላይ አልጋ ብጤ
አነጠፍኩለት፡፡ አንጥፌ ስጨርስ 'እንግዲህ እዚህ ውስጥ ይተኛል።
ነብስ ገድሏል፤ ግን እዚህ ውስጥ ይተኛል። ከጀግና ጋር ነው'ኮ
ያለሁት። ከነብሰ ገዳይ ጋር ነው ያለሁት ብዬ አሰብኩ፡፡ ዘወር ብዬ
አየሁት። አንተ እንደ ነገርከኝ ነው። ዝም ሲል የኢራንን ሻህ
ይመስላል። ግን ማን ያውቃል? ጀግና ስለሆነ አንድ ቀን የኢራንን
ሻህ ይገድለው ይሆናል'ኮ!' ብዬ አሰብኩ
«እና በሀይል ተመኘሁት፡፡ ፍትወት ያንን ያህል አንቆ ይዞኝ
አያውቅም፡፡ ራሴን 'ተይ እንደሱ አታርጊ! - ተይ!'
እያልኩ
ከተቀመጠበት ሄድኩና እግሩ አጠገብ ተምበርክኬ ወደላይ አየሁት።
እንደ ቄስ እጁን ራሴ ላይ አሳረፈና
«ምን ሆነሻል?» አለኝ
ቀስ ብዬ ተነሳሁና አፉ ላይ ሳምኩት
አሁንም «ምን ሆነሻል?» አለኝ። ግን ገብቶታል
«ፈልጌሀለሁ» አልኩት
«እኔ አልፈልግሽም» አለ
«አውቃለሁ ትፈልገኛለህ፡፡ ትፈልገኝ የለ?»
«አዎን፡፡ ካየሁሽ ጀምሮ እንደፈለግኩሽ ነው::»
«ይኸዋ፡፡ አለሁልህ!»
«አይሆንም!»
«ለምን አይሆንም?»
«ምክንያቱን መቼ አጣሽው» አንተን ማለቱ ነው
«እሱ ንደሆነ ግድ የለውም» ኣልኩት
«እኔ ግድ አለኝ!»
«ለምን?»
«ጓደኛዬ ነው:: እፈልግሻለሁ፡፡ ግን እሺ አልልሽም። ስለዚህ
እርሺው!»
«አልረሳውም፡፡ ልረሳው አልችልም፡፡ ልረሳው አልፈልግም።
ሌሊት እመጣለሁ!» አልኩትና ሄጄ አልጋዬ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልተወው
ቆረጥኩ። ምናልባት አንድ ሰአት ያህል ቆየሁ። ከዚያ በላይ ግን
ልቆይ አልቻልኩም፡፡ እንደዚህ አላስችል ያለኝ እሱ ስለሆነ ብቻ
ነበር፣ ወይስ ሰው ሲገድል ስላየሁት ነበር? አላውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እሱ እዚያ ተጋድሞ እኔ እዚህ ሆኜ ልታገስ አልቻልኩም
ራቁቴን ወጣሁ፡፡ ሽቶ ተቀባሁ፡፡ ከመኝታዬ ወጣሁ፡፡ የንግዳ
ቤቱን መብራት አበራሁ። እንቅልፍ አልወሰደውም ነበር። በቀጥታ
ሄድኩና ከበላዩ ቆምኩ፡፡ ወደላይ አየኝ፡፡ ሲያየኝ ብዙ ጊዜ ቆየ፡፡
እጁን ሰደደ። ጭኔን ይዞ ወደታች ጎተተኝ
ካሸነፈኩት በኋላ ወደ አልጋዬ ሄድን፡፡»
ዝም አለች፡፡ ያችን ሌሊት እንደምታስታውስ ያስታውቃል፡፡
እንዴት ያለች ሌሊት ነበረች ይሆን? ብጠይቃት እንደማትነግረኝ
እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ስለሌሎቹ ወንዶች በሰፊው ትንገረኝ እንጂ፣
ስለነሱ ጥቃቅኑን ስጋዊ ተግባር ሳይቀር ትዘርዝርልኝ እንጂ፣
ስለፖልና ስለ ባሀራም አትነግረኝም፡፡ እኔም ስለነሱ መጠየቅ ልክ አልመሰለኝም፡፡ ዝም አልኩ። ቀጠለች

«ስለሌሊቱ ልንገርህ እንዴ?» አለችኝ
«ልትነግሪኝ ትፈልጊያለሽ?»
«አልፈልግም። ከፈለግክ ግን እነግርሀለሁ።»
ይህን ያለችኝ «ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም»
እንደምላት አውቃ ነው እንጂ፡ ንገሪኝ ብላትም እንደማትነግረኝ
አውቃለሁ
«ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም» አልኳት
👍16🤔3
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

የሞት ጥሪ

አማንዳ

ወደ ኤክስ ልንመለስ ሶስት ቀን ሲቀረን ሲልቪ ቤቶቿን ለመሰናበት ሄደች። ጊዜው ንፁህ ብርህንና ለስላሳ ሙቀት በዝግተኛው ነፋስ የሚንሳፈፉበት ውብ የፀደይ ቀን ነበር። የፓሪስ ሴቶች ወደ ሰፊው ስመ ጥሩ ጎዳና ወደ ሻንዜሊዜ እንደሚጎርፉ ታወቀኝ፡፡ በሜትሮ ወደዚያው ሄድኩ ሱቆቹ የፀደይ ሞድ ልብሶቻቸውን መስኮቶቻቸው ላይ ዘርግተዋል፤ ካፌዎቹ ጠረጴዛ ወምበሮቻቸውን ወደ መንገዱ
አውጥተው ከአብዛኛዎቹ ጠረጴዛዎች በላይ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጡ ሰፋፊ ጃንጥላዎችን ዘርግተዋል። ሰዉ ይንጋጋል፤ ትራፊኩ ይፈሳል። አንዱ ካፈ ውጪ ሰዉ የሚተላለፍበት ቦታ አንዲት ትንሽ ጠረጴዛ አጠገብ ተቀመጥኩ

በፀደይ ቀን ሻንዚሊዜ ጎዳናው ዳር ቁጭ ብሎ ቢራ እየጠጡ
አላፊ አግዳሚዋን ፈረንሳዊት እና የስንትና ስንት ሌላ አገር ሴት
መቃኘት። ከዚህ የበለጠ ምን ደስታ ይገኛል? ሴቶቹ የፀደዩን
ብርሀንና ነፋስ ለመቀበል የፈነዱ አበባዎች ይመስላሉ፡፡ የወፍ ቋንቋ
መሳይ ፈረንሳይኛቸውን በልዝብ ድምፃቸው እንደዘፈን እየተቀባበሉ፣የተነጠፈውን ድንጋይ በረዥም ተረከዛቸው ኳ! ኳ! እያረጉ፤ ውብ ዳሌያቸውን እያወዛወዙ ወደላይና ወደታች ይተላለፋሉ፡፡ አይኔ
አብሯቸው ይመላለሳል
ቀስ እያለ አይኔ ሰከረ፡፡ ውበት በዛበት። የአንዷን ኩሩ አረማመድ ሳደንቅ ትንሽ እንደ ተራመደችልኝ፡ ህዝቡ መሀል ገብታ ትጠፋለች፡፡ የሌላዋ ግሩም ቅርፅ አይኔን ይስባል፡ ከዳሌዋና ከባት ከተረከዟ የቱን እንደምመርጥ ገና ሳልወስን ህዝቡ ይውጣታል። ደሞ
የአንዷ ፀጉርና አንገት ልቤን ይወስደዋል። የምትቀጥለዋ ወጣት ነጭ ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ ስታልፍ አይኔ በዳሌዋ እንቅስቃሴ ላይ ይተከላል። እሷንም ሚንጋጋው ህዝብ ይውጣታል። ሌላ ወበት ሌላ ሴት ላይ ተጭኖ ሲሄድ አይኔን ይስባል። እንደዚህ ሰል አይኔ ሰከረ

የቢራዩን ሂሳብ ከፍዬ ወደ ፕላስ ደ ሌትዋል በኩል ስራመድ
የአንዷ ፀጉር አይኔን ማረካው:: ሴትዮዋ ከኋላ ሲያዩዋት ምንም
አትል አረ ሻንለዚ ስላየሁዋት ነው እንጂ ሌላ ቦታ ባያት በጣም ደስ ትላለች። አጠር ያለች ወጣት ናት። ቀይ ቦርሳ አንጠልጥላለች። ገላዋን እቀፍ አርጎ የሚሸፍን፣ ነጭ ባለ ሽንሽን የፀደይ
ቀሚስ ለብሳለች። ወገቧን ሰፊ ቀይ ቀበቶ አቅፎታል። ቀይ
ባለረዥም ተረከዝ ጫማ የረገጡት እግሮቿ ወፈር ብለው፣ ቀለማቸው ወደ ቡናማ የሚያደላ ነው። ወፍራም ዳሌዋ ከነጭ ልብሷ
ስር ሲመዛዝ ያስታውቃል፣ ምኞት ይቀሰቅሳል። ግን ዋናው ውበቷ
ፀጉሯ ነው:: ይሄ ንፁህ ነጭ ፀጉሯ ወደኋላዋ ትከሻዋ ድረስ ተለቆ፣
ፀሀዩ ውስጥ ይብለጨለጫል። የረጋ የጨረቃ ብርህን የሚመስል
ንፁህ ፀጉር ከዚህ በፊት የት ነው ያየሁት? የት? መቼ? የት?
ሴትዮዋ ወደ ቀኝ በኩል ተጠምዛ ከሻንዜሊዜ ወጥታ፣ አንድ
ሌላ መንገድ ይዛ ወደሳይ በኩል መራመድ ጀመረች። ለምን
ተከተልኳት? አላውቅም
መንገዱ ዳር ብዙ መኪናዎች ቆመው ነበር፡ እሷ አንድ ጥቁር
ጃጉዋር ስፖርት መኪና ውስጥ ገባች። አልፌያት ወደ ላይ በኩል
መንገዴን ስቀጥል፣

“Hi there!” አለችኝ። ባለሁበት ቆምኩ፡፡ የአማንዳ፥ ድምፅ!
ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም፡፡ ግን ፀጉሩ የሷ ነው። አሁንም
አስታወስኩ። ወደሷ ዞርኩ፡፡ ከመኪናዋ ወጥታ እየሮጠች መጣችና ተጠመጠመችብኝ። ሽቶዋ በጣም ደስ ይላል።
“አማንዳ ነሽ እውነት?
«እዎን»
«ታድያ ያ ሁሉ ጮማ የት ሄደ?»
«ሸጥኩት» አለችና ትንሽ ከኔ ራቅ ብላ አንድ ሁለት ጊዜ
እየተሽከረከረች ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«ተአምር ነው፡፡ በአይኔ ባላይሽ ኖሮ አላምንም ነበር»
"Thank you"
«እውነቴን ነው:: አሁንኮ ማን እንደሆንሽ ሳላውቅ ከኋላሽ
በኩል ሳይሽ የማናት ቆንጆ ፈረንሳይ? እያልኩ ስከተልሽ ነበር»
«አንዲት ሴት ምን መስማት እንደምትወድ ብጥር አርገህ
ታውቃለህ መቸስ፡»
«እውነቴን ነው ኧረ!»
«ደስ ካልኩህ አብረኸኝ ምሳ ብላ እስቲ»
«ጥሩ»
ወደ ቆንጆ ጥቁር መኪናዋ ገባን፡፡ አማንዳ ድሮ ቁምቡርስ
ነበረች፣ አሁን ግን ቢራቢሮ ሆናለች። ትርፍ እገጯ ጠፍቷል፣
አንገቷ ዙርያ ተጠፍጥፎ የነበረው ጯማ ረግፏል። ፊቷ ሙሉ ነው፡
ግን ደስ ይላል፡፡ ከንፈሮቿ ሮዝ ብጤ ቀለም ተቀብተው፣ ሰማያዊ
አይኖቿ በጥንቃቄ ተኩለው፣ ቀይ ጉትቻዋ ከነጭ ፀጉሯ አጠገብ
ሲታይ በረዶ አጠገብ የተንጠለጠለ እንጆሪ ይመስላል።
ከአስቀያሚዎቹ ሴቶች ማህበር ወጥታ፣ ቆንጆዎቹ ማህበር
ገብታለች፡፡ ድምፅዋ ሳይቀር ተለውጧል። ድሮ አልቃሻ ብጤ ነበር፤አሁን ግን ልስልስ ያለ ቆንጆ ድምፅ ነው
«ንገሪኝ እስቲ፡ ምን እንደዚህ ለወጠሽ?» አልኳት
«አንድ ሰካራም አለችኝ
«ምን?»
«ሉን ተሰናብቼ ወደ አገሬ ስሄድ፡ ኤሮፕላኑ ውስጥ አንድ
ሰውዬ አጠገብ ተቀመጥኩ፡፡ ሰውየው ሰክሮ ነበር። ሉ ትዝ እያለኝ ለብቻዬ ሳለቅስ
« ምን ያስለቅስሻል? የወደድሽው ሰውዬ እምቢ አለሽ? ደግ አረገ! በዚህ እድሜሽ ምን እንዲህ አወፈረሽ? አለኝና ያኔውኑ
ረሳኝ፣ እንቅልፍ ወሰደው
«እኔ ግን ቃላቱን እስከ መቼም አልረሳቸውም። ለመጀመርያ
ጊዜ አንድ እውነት ተገለፀልኝ። ይኸውም፣ ጅል ሆኜ ነው እንጂ፣
ውፍረቴን እንደ ጭነት ተሸክሜ መዞር የለብኝም፡፡ ጭነቱን አውርጄ ልጥለው እችላለሁ። ልጥለው ቆረጥኩ። ሳን ፍራንሲስኮ ሄጄ ሙያቸው ክብደት መቀነስ ከሆነ ሰዎች ጋር አራት ወር ሙሉ ሰራሁ። ውጤቱን አንተም አመሰገንክልኝ አለች። ሳቋ ውስጥ ወጣትነትና የህይወት ድል አድራጊነት ይጨፍራል!

ባለ አራት ኮከብ (ማለት ከሁሉ ይበልጥ ምቾት ያለበት) ሆቴሏ
ወሰደችኝ። ክፍሏ ሆነን በቴሌፎን ሁለት ምሳ አዘዘች። አሁንም
አስደነቀችኝ። ኤክስ ሳውቃት ፈረንሳይኛውን በአስቀያሚ የአሜሪካን ቅላፄ ነበር የምታዜመው፣ አሁን ግን የፓሪስ ፈረንሳይኛ ሊሆን ምንም አልቀረው:: እያየችኝ ስትስቅ
“እንደዚህ የሚያስደስት ለውጥ አይቼ አላውቅም።

"Thank you, you re really sweet" አለችኝ

ከምሳ በኋላ «ፓሪስ ምን ትሰራለህ?» አለችኝ፡፡ ነገርኳት፡፡
«አንቺስ?» አልኳት።
«ከኒው ዮርክ የዛሬ ሳምንት መጣሁ፡፡ ይሄ ጃጉዋር ከኢንግላንድ እስኪመጣልኝ ነበር " ምጠብቀው። ነገ ወይም ተነገ ወድያ ወደ ኤክስ መሄዴ ነው:: . . ሉን ማግኘት አለብኝ፡፡ ደህና ነው? አሁንስ የሚፈልገኝ ይመስልሀል? ለጊዜው ሴት አልያዘ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ይዞ እንደሆነ፣ ነጥቄ መውሰድ ይኖርብኛል።»

«ምን?»
«ነጥቄ እወስደዋለሁ። ምነው ገረመህ? የድሮዋ አማንዳ
መስዬህለሁ እንዴ? ተለውጫለሁኮ:: ተዘጋጅቼ ነው የመጣሁት፡፡ ቢያንስ አርባ የሳይኮሎጂ መፅሀፍ አንብቤያለሁ። ደሞ ሉን
አውቀዋለሁ፡፡ ግብረ ስጋ በጣም ይወዳል። ለሱም ተዘጋጅቻለሁ፡፡»

«እንዴት?»
«ለሌላ ሰው ቢሆን ይህን አልነግረውም። አንተ ግን
ትወደኛለህ። ወፍራም ሳለሁም ትወደኝ ነበር፡፡ ለኔ ግድ ነበረህ፡፡
የተሻልኩ ሰው ሆኜ ስላየኸኝ ደሞ በጣም ደስ ብሎሀል። ይሄ ለኔ
ትልቅ ስጦታ ነው። በጣም ተወዳጅ ነህ፡፡ እና ለምን እንደሆነ
ሳላውቅ በጣም አምንሀለሁ፡፡ ለምንድነው እማምንህ?»
👍14🤔2
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....እኔ ፓሪስ ሄጀ ቅናት ውስጥ ስንፈላሰስ ኤክስ ውስጥ ምን ምን
ተደረገ? ከባህራም፣ ከተካና ከኒኮል የሰማሁትን ሳገጣጥመው እንደ እሚከተለው ሆነ፡-.

አንድ ማክሰኞ ከሰኣት በኋላ (ኒኮል ከፋሺስቶቹ ተደብቃ
ሰንብታ ከተመለሰች በኋላ) ባህራም የሚሰራበት ትምህርት ቤት ዲሬክተር ቢሮው አስገባውና ከስራዎ ላሰናብትዎ ነው» አለው።
ባህራም «ምነው?» ቢለው “በስራዎ በጣም ተደስቼ ነበር፤ ግን የጋርደን ከተማ የፖሊስ ሹም እንዳሰናብትዎ አዘዘኝ» አለው

«እዚህ ውስጥ የፖሊስ ሹም ምን አገባው?» አለ ባህራም

«አዩ፣ እርስዎ የውጭ አገር ዜጋ እንደመሆንዎ መጠን፣ እዚህ
አገር ስራ ለመያዝ ልዩ ፈቃድ ያስፈልግዎታል። እስካሁን ያለ
ፈቃድ ወረቀት ስለስሩ እርስዎም እኔም ልንቀጣ እንችል ነበር፡፡ ግን
የፖሊስ ሹሙ ጓደኛዬ ነው፡፡

የስራ ፈቃድ እንደሌለኝ እንዴት አወቀ?» አለ ባህራም

ሰው ነገረው:: ይመስለኛል፣ ኤክስ ውስጥ ጠላቶች አሉዎት።»
ባህራም ገባው። ፋሽስቶቹ መሆን አለባቸው

«እሺ ደመወዜን ይስጡኝ አለ። የሁለት ወር ከሶስት ሳምንት
ደመወዝ አለው። ዲሬክተሩ ገንዘቡን ከቢሮው ጠረጴዛ ኪስ አውጥቶ አቀበለው። ባህራም ገንዘቡን ቆጠረ። የተዋዋሉት ገንዘብ ሲሶ ነው።
«ሌላውስ?» አለ ባህራም
ዲሬክተሩ ከጠረጴዛው ኋላ እንደተቀመጠ፣ ቅዝቅዝ ባለ ክፉ
ድምፅ
«የምን ሌላ?» አለው
«ይሄ ሙሉ ደመወዜ አይደለም፡፡ አንድ ሶስተኛው ነው::
«ማን ነው ያለው? ደመወዝህን ሰጥቼሀለሁ፡፡ ከፈለግክ ውሰደው፣
ካልፈለግክ ተወው:: ድሮ አልጄርያ ሳለሁ አረቦቹን ከዚህ ባነሰ
ደመወዝ ነበር የምናሰራችሁ»
ባህራም ረጋ ባለ ድምፅ አረቦቹን ቅኝ ግዛት ስላደረጋችኋቸው
በካልቾ ብለው ካገራቸው አስወጧችሁ፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እኔ አረብ አይደለሁም፡፡ የኢራን ሰው ነኝ፡፡ የኢራን ሰው ሰውን አይነካም። ግን ማንም ሰው የኢራንን ሰው አይበድልም፡፡ ስለዚህ አለና ድንገት
በጠረጴዛው ተንጠራርቶ ሰውዬውን አነቀው፡፡ ሰውየው ራሱን ለማስጣል አልሞከረም፡፡ ባህራም ሲያፈጥበት፣ በደነገጠ ድምፅ

«አይነቁኝ፡፡ አስም በሽታ አለብኝ» አለው ባህራም ለቀቀው፡፡ ሰውዬው ከጠረጴዛው ኪስ ሌላ ገንዘብ አውጥቶ ባህራም ፊት ቆጠረው። ባህራም ገንዘቡን አንስቶ ኪሱ ከተት። ሰውየውን አየው፡፡ ወምበሩ ላይ ተቀምጦ ወደ ላይ ይመለከተዋል። ባህራም አፉ ውስጥ ብዙ ምራቅ ሰበሰበ፡፡ ሰውዬው ፊት ላይ ተፋው፡፡ ሰውዬው መሀረብ ሊያወጣ እጁን ወደ ኪሱ ሲከት ባህራም ትቶት ወጣ

ከዚያ እየጨሰ ወደ ኤክስ የሚወስደውን አቶቡስ ተሳፈረ
ያን ቀን ተካን ባያገኘው ጥሩ ነበር
ተካ በበኩሉ ከአንድ ወር በላይ ሲበሳጭ ሰንብቷል። ጀርመንዋ
ልጅ እየባሰባት ሄደ። በፊት እንኳ ከዚያ ካገሯ ልጅ ጋር የምትወጣው አልፎ አልፎ ነበር፡፡ አሁን ግን ቢያንስ በሳምንት አራት ማታ ከሱ ጋር ነች። ተካ እንግዲህ ቢበዛ በሳምንት ሁለት ማታ ቢያገኛት ነው። ለዚያውም ሁለቱም ማታ የንትርክ ማታ ነው።
ሁልጊዜ ስለጀርመኑ ይጨቃጨቃሉ

«ከሱ ጋር ምን ትሰሪያለሽ?»
በራሴ ህይወት ምን አገባህ?»
አብራችሁ ትተኛላችሁ?»
«ምን አገባህ?»
በጥፊ እየመታት «ንገሪኝ! ይተኛል?» ይላታል
በንዴት «አዎን ይተኛኛል! በል ምን ትሆን!?» ትለዋለች
እንደገና አንድ ሁለት ጥፊ ያቀምሳትና፣ በግድ ታግሎ
ይተኛታል
አንድ ማታ ግን፣ ዝግ ባለ ድምፅ
«ልሰናበትህ ነው የመጣሁት» አለችው
ልቡ እየፈራ «ምነው? የት ልትሄጂ ነው?» አላት
«የትም አልሄድም፡፡ እስቲ
ዛሬ እንኳ ሳንጣላ እንደር፡፡
የመጨረሻችን ሌሊት ነው፡፡ ሄርማን ሊያገባኝ ቆርጧል፡፡ እኔም እሺ ብየዋለሁ።»

በሰላም አደሩ፡፡ ከዚያ በኋላ አነጋግራው አታውቅም
ጀርመንዋ ያስለመደችው ሲቀርበት ጊዜ ያንገበግበው ጀመር፡፡በቶሎ ሴት ማግኘት እንዳለበት ገባው:: ቢመለከት፣ ኒኮል አለች::መልኳ እጅግም ነው፡ ወንድ በብዙ ልትስብ አትችልም፡፡ ለዚህ አይደል ባህራምን በገንዘቧ 'ምታኖረው? ግን አሁን ባህራም
አብዛኛውን ጊዜ ከኤክስ ውጪ ነው:: ስለዚህ ሌላ ወንድ መፈለጓ
አይቀርም። እንድያውም ይህን ጊዜ እሱ (ተካ) ሴት ያስፈለገውን
ያህል እሷም ወንድ መፈለጓ አይቀርም፡፡ ሌላ ሴት እስኪያገኝ ማቆያ ትሆነዋለች። እሷም በበኩሏ ባህራም እስኪመጣላት ማቆያ ይሆናታል፡፡ የጋራ ጥቅም!
ማክሰኞ ከምሳ በኋላ ቤቷ ሄደ
ቡና አፈላችለትና «ዛሬስ ምን ሰማህና ልትጎበኘኝ መጣህ?»
አለችው
«እንድ ነገር አስቤ ነው» አላት
«ምን?»
«እኔንና አንቺን የሚጠቅም ሀሳብ ነው»
«ንገረኛ»
«ደስ ትዪኛለሽ፡፡ ስለዚህ ባህራም በሌለበት ጊዜ እዚህ ብመጣ
ጥሩ ይመስለኛል»
«መጥተህስ?»
«እናወራለን፤ እንጫወታለን» እያለ እጁን እጇ ላይ አስቀመጠ
እጇን እያሸሸች «ለኔ የሚሆን ጨዋታ ያለህ አይመስለኝም»
አለችው
«አለኝ»
«የለህም»
«ከባህራም በምን አንሳለሁ?»
በሁሉም ነገር»
«ሞኝ ነሽ። ይልቅ አንድ አቃጣሪ አረብ እየከፈልሽው
ከሚተኛሽ፣ እኔ ያለ ገንዘብ ብተኛሽ አይሻልሽም?» አላት
ፊቷ በቁጣ እሳት መሰለ፣ ግን ድምፅዋ አልተለወጠም
«ወንድ ከሆንክ ሂድና ባሀራምን አቃጣሪ አረብ ነህ በለው። እኔ
ወንድ ስላልሆንኩ የሚገባህን ቅጣት ልሰጥህ አልችልም። ግን ቆሻሻ ነህ፡፡ አንጎልህም ቆሻሻ ነው፣ ሰውነትህም ቆሻሻ ነው። እግርህ ይገማል፣ አፍህ ከሬሳ እኩል ይቆንሳል። አሁን ቤቴ ሳይገማ ተነስና ሂድልኝ አለችው
ተነሳ። ቁጭ እንዳለች ሳታስበው በጥፊ መታት። ከወምበሯ
ተከነበለች። ከወለሉ ላይ በፀጉሯ ጎትቶ እነሳትና እንገቷን ሳማት።
ስትፍጨረጨር እጁን ጠምዞ ወደ አልጋዋ ወሰዳት። አልጋው ላይ
ጣላትና አንድ ጡቷን ጭብጥ አርጎ ያዘ፡፡ መፍጨርጨሯን ተወች
በኣፏ ብቻ

ተወኝ! ብትተወኝ ይሻልሀል!» እያለች ትፎክራለች እጁን ሰደደና ሙታንቲዋን ሊያወልቅ ሲል እንደገና መፍጨርጨር ጀመረች፡፡ ጡቷን የባሰውን በሀይል ዉበጠው:: ፀጥ አለች፡፡ ሙታንቲዋን አወለቀው። እምባዎ ይወርድ ጀመር፡፡ ቁጣዋ
ወደ ልመና ተለወጠ
እባክህ ተወኝ፡፡ ምን አረግኩህ?»
ልመናዋን ከምንም አልቆጠረውም። ጡቷን ጨብጦ እንደያዘ የሱሪውን ቀበቶ ፈታ
አሁንም እምባዋ እየወረዳ «እባክህን ተወኝ፡፡ እርጉዝ ነኝ፡፡
የሁለት ወር ነብሰ ጡር ነኝ» አለችው

የሱሪውን ቁልፍ ይፈታ የነበረው እጁ ባለበት ደረቀ። ጡቷን ይዞ የነበረው እጁ ለቀቃት፡፡ ሱሪውን መልሶ ቆለፈ፡፡ ትቷት ወጣ

አልጋዋ ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ባህራም ደረሰ፡፡ ከጋርደን
እያበሽቀ መምጣቱ ነበር። በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቷን አየ፡፡
እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ ነገረችው
ተናዶ ተካን ፍለጋ ወጣ፡፡ ኒኮል ተከተለችው። ምናልባት
ኣደገኛ ነገር እንዳይስራ ፈርታለች። እሱ በረዥሙ ሲራመድ እሷ
አልደርስበት ብላ ከኋላው ከሩቅ ሱክ ሱክ ስትል፤ ኤክስን አቋርጠው ሲቴ አጠገብ ሲደርሱ ባህራም ተካን አየው፡፡ ጠራው፡፡ ተካ ቆመ፡፡አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ነበር። ባህራም ደረሰና ቃል ሳይናገር በጥፊ መታው። ተካ ቡጢ ሰነዘረበት። ባህራም ጎምበስ ብሎ አመለጠና፡
በፍጥነት የተካን እጅ ይዞ ጠምዞ በሀይል ወረወረው: ከዛፉ ጋር
አጋጨው። ከዚያ በኋላ ተካ ሊካላከል አልቻለም፤ አንጎሉ ዞሮበታል፡ ባህራም እጅ ውስጥ እንደ ህፃን ሆነ። ባህራም ጭንቅላቱን ይዞ ፊቱን
ከዛፉ ጋር ደጋግሞ ደጋግሞ አጋጨው። የተካ ፊት በደም ተበከለ።ኒኮል ደርሳ ባታስጥለው ኖሮ ምናልባት ይገድለው ነበር
👍211
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


የቀይ ኮከብ ጥሪ
ባህራም

ባህራም እየተለወጠ ሄደ፡፡ እነ ማኦ ትዜ ቱንግ የደረሱዋቸውን
መፃህፍት ማንበብ ተወ:: ስለኮሙኒዝም ማውራት ተወ፡፡ ክፍል መግባት ተወ:: እኔንም ይሽሸኝ ጀመር። እንደቀስተ ደመና ውብ የነበረውን የሬቮሉሽን ተስፋውን በብዙ የእሳት ቃላት ይነግረኝ ስለነበረ' አሁን ቀስተ ደመናው ተሰባብሮ ወድቆ ከበሰበሰ በኋላ፣ እንደገና
ሊያነጋግረኝ አልፈቀደም፡፡ ኒኮልም ፊት ነሳችኝ፡፡የባህራምን ክንፍ እንደሰበረችው ስላወቅኩ ፊት ነሳችኝ

የኤክስን ሰማይ የሉልሰገድና የጀምሺድ መቀሰፍ አላስደነገጠውም፡ የአማንዳ ጉብዝና አላስደነቀውም፡ የኒኮል ማርገዝ አላናደደውም፡ የባህራም መታሰር አላሳዘነውም፡፡ የኤክስ ሰማይ ለዚህ ሁሉ ደንታ የለውም
የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ እንደ አማንዳ አይን ብሩህ
ሰማያዊ ነው፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ኒኮል አይን ውሀ አረንጓዴ
ይሆናል፡ ወደ ማታ ጊዜ እንደ ሲልቪ ጉንጭ ይቀላል
የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፤ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው! ሁልጊዜ ውብ ነው፡ ሁልጊዜ ሰላማዊ ነው። ሌሊት የአልማዝ
ከዋክብትና የሰላም ፀጥታ ለብሶ ያድራል

የኤክስ የፀደይ ፀሀይ እየበረታች ሄደች። ንፁህ ብርሀኗ ቀስ
እያለ ወደ ብጫ ሀሩር ተለወጠ፡ ለስላሳውን የፀደይ ንፋስ
አደከመው፡ የሚወብቅ የአየር ባህር አደረገው፡፡ በጋ መጥቶ ኤክስ ውስጥ እንደ ሰፊ ድካም ተንሳፈፈ። አሮጊቶቹና ሽማግሌዎቹ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው በዝግታ እያለከለኩ፣ የሞትን ምህረት የሚጠብቁ
ይመስሉ ጀመር

እንዳንድ ጊዚ ባህራምንና ኒኮልን ምግብ ቤቱ ሲገቡ ወይም
ሰወጡ አያቸዋለሁ። ባህራም ከስቷል፡ አይስቅም፣ በፍጥነት
አይራመድም። ሽበቱም የበዛ መሰለኝ፡፡ ኒኮል ግን ወፈር ብላ፣
እርግዝናዋ በጣም አምሮባታል፡ በዝግታ ስትራመድ ታስጎመጃለች
ቀስ በቀስ ምግብ ቤት መምጣቱን ተዉት ተካ የኒኮልን ማርገዝ ለመሸሸግ ያሉት ነው» አለኝ፡፡ ሌላ
ነገር ነገረኝ ባህራም ማታ ማታ ኒኮልን ቤቷ ትቷት ይወጣና
ሲኒማ ይገባል ከሲኒማ ወጥቶ ካፌ 'ሰንትራ' ይሄዳል፡ እዚያው
ያድራል፤ ሲነጋ ወደ ኒኮል ቤት ይኳትናል፡ ተኝቶ ይውላል

አንድ ማታ ወደ ስድስት ሰአት ላይ ከሲኒማ ወጥቼ ወደ ቤቴ
በኩል ስራመድ፡ ከኋላዬ እንደ ፈጣን እርምጃ ሲከተለኝ ተሰማኝ።
እንዳልሰሙ መንገዴን ቀጠልኩ። ደረሰብኝ፡፡ ባህራም፡፡ ወደ ካፌ
ሰንትራ ሄደን ቢራ ካዘዝን በኋላ
ቁጭ ብለን ካወራን ብዙ ጊዜ ሆነን አለኝ፡፡ አይኖቹ እንደ
መድከም ብሏቸዋል፡ ፊቱ ላይ የአምስት አመት ያህል እድሜ
ተጨምሯል
"አንተ አትገኝም አልኩት"
በገዛ ራሴ ጥፋት በታሰርኩ' አንተ ጋ መጥቼ ባለቅስብህ ተገቢ
ማስሉ አልተሰማኝም

ጥሩ እድል አጋጥሞህ ቢሆን ኖሮ ግን መጥተህ ታጫውተኝ
ነብር፡ ደስታህን ታካፍለኝ ነበር»
አዎን። ይኸውልህ፡ ልክ ከፓሪስ እንደተመለስክ እንድንጋገርበት አቅጄ ነበር፡፡ ግን ገና ሳትመለስ ጣጣ ውስጥ ገባሁ። ስትመጣ ታድያ፤ መንፈሴ ተሸንፎ ስለነበረ ያቀድኩትን ችላ አልኩት፡፡ አሁን ፈቃደኛ ከሆንክ ብንነጋገርበት ጥሩ ይመስለኛል።»
"ጥሩ"
መጀመር አስቸገረው። ሲጋራ አቀጣጠለ።
ስለሰልቪ ጉዳይ ነው። ነግርሀለች?»
«አዎን፡፡
«ምን አለችህ?»
የነገረችኝን ባጭሩ አጫወትኩት። ዝም ብሎ ሰማኝ። ስጨርስ
«ውሸቷን ነው» አለኝ
«እንዴት?
«እኔ ነኝ የለመንኳት፡፡ እሷ እምቢ ብላኝ ነበር። ለብዙ
ተለማመጥኳት። 'አሁን አሁን ከሞት ጋር ስታገል ነበር፡ ውስጤ
በፍርሀት ተሞልቷል፡ ብቻየን ነኝ፡ የሰው ሙቀት ያስፈልገኛል፣
በጣም ያስፈልገኛል አልኳት። እሺ አለችኝ። ግን እሺ ያለችኝ ብዙ
ከተለማመጥኳት በኋላ ነው»
«ማንኛችሁን ልመን?»
«እኔን
«ለምን?»
«ውሸት አልነግርህማ»
«እሷስ ለምን ውሽት ትነግረኛለች?»
«እንዳንጣላ ብላ»
ዝም አልኩ። ንዴቱ ውስጤ ሲጠራቀም ይሰማኛል
«ከፈለግክም አገጣጥመን» አለኝ፡፡ ቁጣዬን ለመግታት ስል
መዋሽት ጀመርኩ
«ግድ የለም ይቅር። አሁን ስላንተ ንገረኝ አልኩት። ድምፁ
እንደተለወጠ ተሰማኝ
«ይቅርታ አርገህልኛል ማለት ነው?» አለኝ
«እንርሳው» አልኩት
«እፍረት ይሰማኛል። አይንህ ውስጥ ንቀት ይታየኛል»
«ንቀት አይደለም» አልኩት
«ታድያ ምንድነው?»
«ስሜቴን ልግለፅልህ?»
«አዎን»
እኔ ሳላውቀው የተጨበጠ ቀኝ እጄ በፍጥነት ሄዶ አገጩን
መታው:: ከነወምበሩ ወደኋላ ተገለበጠ። እጆቼን እንደ ጨበጥኩ ከበላዩ ቆምኩ፡፡ የተገለበጠው ወምበር አጠገብ እንደተጋደመ ወደ ላይ ያየኛል። ማንኛችንም አልተንቀሳቀስንም። ወደ ላይ እያየኝ ቀስ ብሎ መሀረቡን ከኪሱ አወጣ፡፡ መሀረቡ ውስጥ ተፋ። ደም፡ ቀና
ብሉ ቀይ ፈገግታ ሰጠኝ፡፡ እጁን ዘረጋልኝ። ጨበጥኩት፣ ወደ ላይ
ሳብኩት። በየቦታችን ተመልሰን ተቀመጥን

ካፌው ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዳሉና እንደሚያዩን ገና አሁን
ታወቀኝ። አፈርኩ፡፡ ግምባሬን አላበኝ፡፡ መሀረቤን አውጥቼ
ጠረግኩት። ባህራም እንደገና መሀረቡ ውስጥ ተፋ፡፡ ሳቅ እያለ
«እንደሱ እንኳ ይሻላል» አለኝ
አንድ ነገር አስታወስኩ፡፡ ባህራም ቢፈልግ ነብሴ እስኪመጣ
ሊደበድበኝ ይችል ነበር! እንደገና አላበኝ። በመሀረቤ ጠረግኩት
ከዚህ በኋላ ከባህራም ጋር እንደ ድሮው ማውራት ጀመርን።
የደረሰበትን እጫወተኝ። ኒኮል ማርገዟን ስታውቅ መበሳጨት
ጀመረች፡፡ ባህራም ከስራ ሲወጣ ብስጭቷ እየባሰባት ሄደ።
ሉልሰገድና ጀምሺድ ከሞቱ በኋላ፣ ብስጭቱ ወደ እምባ ተለወጠ፡፡
ማታ ማታ ታለቅሳለች። ባህራም ያባብላት፣ በስጋ ይገናኛትና
ያስተኛታል እሷ ስትተኛ እሱ ሲጋራ አቀጣጥሎ በጨለማው ስለ ኢራን
ያስባል። ከንቱ! ያ ሁሉ ዝግጅት ከንቱ ቀረ፡፡ ያ ሁሉ አመታት
በከንቱ አለፈ፡፡ ማኑ ያ ኢራን ሳሉ የ«ፍሬ አለቃው የነበረ
ስለአምባጓሮ ያስተማረው ውድ ጓደኛው ማኑ በሱ ቦታ ቢሆን
አሁን ምን ባደረገ ነበር? ለመሆኑ፣ ማኑ የት ይሆን? እዚያው
እንግሊዝ አገር ይሆን?
«ይገርምሀል” አለ ባህራም ሲነግረኝ አንድ አስር ቀን ያህል
በተርታ፣ ማታ ማታ ስለማኑ ብዙ ብዙ አሰብኩ። እና አንድ ቀን
ከሱ ደብዳቤ መጣልኝ። አይገርምህም? አድራሻዬን እንዴት እንዳገኘ

«ደብዳቤው ምን ይላል?» አልኩት፡፡

ከኪሱ ሁለት በአረብ ፊደላት የተፃፉ ደብዳቤዎች አውጥቶ
አንዱን ተረጎመልኝ

«ብዙ ብዙ የምነግርህ አለኝ፡፡ ግን በደብዳቤ አይሆንም።ስንገናኝ ነው። እዚህ ለንደን ውስጥ ሶስት ሚልዮን ፓውንድና ኣንድ
ዘመናዊ ማተሚያ ቤት አለን፡፡ ገንዘቡ ከቻይና፣ ከሶቭየት ህብረትና ከሌሎች ወዳጆች የተሰጠን ነው፡፡ ብዙ ሌላ እርዳታም ተሰጥቶናል፡፡
አስራ አምስት ሺ ካላሽኒኮቭ ጭምር! እንግዲህ ጊዜው ደረሰ፡፡
ፎቶግራፍህን ላክልኝና ፓስፖርት ይዤልህ እመጣለሁ። እኔና አንተ
አገራችን እንገባለን፡፡ እዚያ ብዙ ብዙ ስራ ይጠብቀናል። ዝግጁ ነህ?እንዲያው ነው የምጠይቅህ እንጂ ዝግጁ እንደሆንክ እርግጠኛ ነኝ፡፡ይህን ሁለት አመት የት የት ነበርኩ መሰለህ? ፒኪንግ፣ ሞስኮ፣ፕራግ፣ ቡዳፔስት ብቻ ስንገናኝ እነግርሀለሁ። ቶሎ ፎቶህን ላክልኝ»

ባህራም ደብዳቤውን እጥፎ ኪሱ ከተተ። ረዥም ዝምታ ሰዎቹ ካፌው ውስጥ ያወራሉ። አንዷ ኮረዳ ከሽንት ቤት ወጥታ
👍181
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ካንድ አመት ተኩል በፊት፣ በክረምት፣ ቤቱ ማሞቂያ
ስላልነበረውና የክረምቱ ብርድ ስለበረታበት፣ ካፌ «ሴንትራ» ያድር
ነበር፡፡ አሁን ደሞ የኒኮል እምባ እያባረረው ካፈ «ሴንትራ»
ያድራል። ሲጋራ እያጨሰ ሲተክዝ ያድራል፡፡ ስለ ኢራን ሲያሰላስል
ያድራል። ከንቱ ሀሳብ ሲያወጣ ከንቱ ሀሳብ ሲያወርድ ከንቱ
ሌሊቶችን ያነጋል

ያን ሰሞን የሲልቪ መፅህፍ ለሶስተኛ ጊዜ እምቢ አለ።
ለሶስተኛ ጊዜ አባረረችኝ። እኔም መፃፍ አቃተኝ፡፡ እንዴትስ ላያቅተኝ ይችላል? ሲልቪ በጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ብርሀን ካላየችኝ፡
በውብ ሰፊ አፏ ሙቀት ካልሳመችኝ፣ ሰለስላሳ ገላዋ ካላቀፈችኝ እንዴት ልስራ እችላለሁ? መስራቱን ተውኩት
ዩኒቨርሲቲው አጠገብ ያለው መናፈሻ ውስጥ የኤክስ አዛውንት
በስጋው አቧራ ውስጥ “boule” ሲጫወቱ፡ በኮሚክ የደቡብ
ፈረንሳይኛቸው እየፎከሩ አንዷን የብረት ኳስ በሌላ እያነጣጠሩ
ወርውረው እየገጩ እየተሳደቡ ወይም እየተሳሳቁ ሲንጫጩ አያለሁ
ከዚያ ወደ ኩር ሚራቦ ሄጄ Monoprix የተባለው ትልቅ ሱቅ
ፊት ለፊት ከአንዱ ሽማግሌ ወይም ከአንዷ አሮጊት አጠገብ
አግድም ወምበር ላይ እቀመጥና፣ የኤክስ ሚስቶችና እናቶች
ከመንገዱ ወደ ሱቁ እየገቡ፣ ከውስጥ “Monoprix የሚል
የታተመባቸው የሞሉ ቡኒ የወረቀት ከረጢቶች ይዘው ወደ መንገዱ ሲጎርፉ አያለሁ፡፡ አስተያየታቸውም ሆነ አለባበሳቸው ወይም
አረማመዳቸው የጎረምሳ አይን አይስብም፡፡ ድሮ የጎረምሳ አይን
ስበው፣ ፍቅረኛ ይዘው፣ አግብተው ወልደው በቅቷቸዋል። አሁን
ወይም አርጅተዋል፣ ወይም ወፍረዋል ወይም ተዝረክርከዋል
ኮረዳዎቹ ጡታቸውን አሹለው! ዳሌያቸውን አሳብጠው፤
አይናቸውን ተኩለው፣ ፀጉራቸውን ተሰርተው ሽቶ አርከፍክፈው
እጅጌ የሌለው የበጋ ልብስ እየለበሱ፣ የብብታቸውን የተለያየ ከለር ፀጉር እያሳዩ፣ በጎረምሳ ታጅበው እየሳቁ እያወሩ በኩር ሚራቦ ይመላለሳሉ፡፡ ወይም ካፌዎቹ በር አጠገብ መንገዱ ላይ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ግማሽ ጭናቸውን እያሳዩ ልዩ ልዩ ቀዝቃዛ
እየጠጡ ያወራሉ

አሮጊቶቹና ሽማግሌዎቹ አግድም ወምበር ላይ ፈዘው ቁጭ
ብለው ፀሀይ ይሞቃሉ። እኔም ቁጭ ብዬ ስለሲልቪ ስለባህራም፣ስለኒኮል፣ ስለሉልሰገድ፣ ስለአማንዳ እያሰብኩ አላፊ አግዳሚውን
እመለከታለህ
ሲልቪ መቼ መጥታ ወደ እቅፏ ትጠራኝ ይሆን? ጊዜው አላልፍልህ ይለኛል። ወደ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሲኒማ " እገባለሁ።
ከሲኒማ ወጥቼ አንዱ ካፌ እሄድና ኣንድ ቢራ ጠጣለሁ

አንድ ቀን ወደ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ነበር። ሰማዩ ቀልቶ፣
ፀሀይዋ እንደ ቀይ ብርቱካን ከምእራባዊው አድማስ በላይ
ተንጠልጥላለች፡ ግን ገና አትጠልቅም፡ እስከ ሁለት ሰአት ተንጠልጥላ ኤክስን ታስውባታለች
አየሩ የሚለሰልስበት ጊዜ፣ ብቸኝነት የሚፈለግበት ሰአት ነው፡
የትዝታ የትካዜ ሰአት
ካፈ ኒኮል ሄድኩና በረንዳው ላይ ፊቴን ወደ ፀሀይዋ አድርጌ ቁጭ ብዬ ቡና አይነቱን ቢራ አዘዝኩ፡፡ አሮጊቷ ቢራውን እያቀረቡልኝ
"Ça fait longtemps qu'on vous a pas vu monsieur" አሉኝ ብዙ ጊዜ ሆነን ካየኖዎት)
Oui, madame." አልኳቸው
ጓደኛዎትስ ደህና ናቸው?»
ደህና ነው። አገሩ ገብቷል
ትምህርታቸውን ጨረሱ?»
"Il était tres gentil, votre ami“ (በጣም ጥሩ ሰው ነበር ጓደኞት")
"Oui, madame"
አሮጊቷ ሄዱ፡፡ ብቻየን ቀረሁ፡፡ ከቀይዋ ፀሀይ ጋር፣ ከቡናማው
ቢራ ጋር። ከሉልሰገድ ትዝታ ጋር መንግስተ ሰማያት ማለት
ሴት በየዛፉ ስር፣ በየግድግዳው ጥግ የሚበቅልበት ማለት ነው
አየህ፣ የኒኮል ጡት እንደ ነጭ ውብ ሰማይ ነው፡፡ ሰማዩ መሀል ላይ በሮዝ ቀለም የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች እኔ 'ምልህ! ከኒኮል ጋር አልጋ ላይ የወጣህ ጊዜ' በቅዱስ ብልግናዋ ትባርክሀለች
አይ አንተ ባላገር መባዳት ቁላን እምስ ውስጥ መክተት ይመስልሀል። ስንት ሳይንስና ስንት አርት እንዳለው ባወቅክ! ኒኮልን
በቀመስክ!.....
ፀሀይዋን ከለለኝ፡ ከሉልሰገድ ነጠለኝ፡፡ ቀና ብዬ አየሁት፡፡
ባህራም። አጠገቡ አንድ ቀጭን ባለመነፅር ሰውዬ ቆሟል። ቁመቱ
ከባህራም ትንሽ ይበልጣል። ያገሩ ልጅ ይመስላል ብድግ አልኩ፡፡ ሰውዬው ፈገግ አለ። ፈገግታው ደስ ይላል። የልጅ ፈገግታ ይመስላል። እጁን እየዘረጋ፣ በጣም ወፍራም በሆነ
ድምፅ በእንግሊዝኛ ከለንደን መምጣቴ ነው አለኝ
ጨበጥኩት፡፡ አጨባበጡ ልዩ ሆኖ ተሰማኝ። እጁ አይመችም።
በኋላ ሳየው መሀል ጣቱ ወደ አንድ በኩል ተጣሟል አይታጠፍም።ሌሎቹ ጣቶቼ ረዣዥም ቀጭን ቆንጆ ናቸው
እንኳን ደህና መጣህ!» አልኩት። ቁጭ አልን፡፡ባህራም ግን አልተቀመጠም። እኔን «ይሄ ማኑ ነው።የፈለግከውን ልትነግረው ትችላለህ» አለኝና ወደ ካፌው ውስጥ ገባ የማኑ ግምባር በጣም ጠባብ ነው: ወደኋላ የተበጠረው ፀጉሩ ከቅንድቦቹ ጋር ሊገናኝ ምን ያህል አይቀረው
ሳቅ አለ፡፡ የላይኛ የፊት ጥርሱ ሁለቱ የራሱ አለመሆኑን አስተዋልኩ ሰው ሰራሽ የአጥንት ጥርስ ነው። ጥያቄው አመለጠኝና

ጥርሶችህ የት ሄዱ?» አልኩት። የልጅ ሳቁን እየሳቀ ሰባራ
መሀል ጣቱን በግራ እጁ እያሻሸ
“አገሬ ትቻቸው መጣሁ:: እስር ቤት ውስጥ ኣለኝ፡፡ ወፍራም
ድምፁ ውስጥ መመረር አያሰማም፡፡ ሲስቅ ከመነፅሩ ኋላ አይኖቹ ጥፍት ይላሉ

«አህ! » አልኩት፡፡ ምን ማለቴ እንደሆነ እንጃ

«አሁን ጥርሶቼን ፍለጋ አገሬ መመለስ አለብኝ፡፡ ባህራም
ቢያፋልገኝ ቶሉ አገኛቸው ነበር። እሱ ግን ኣላግዝህም አለኝ»

«የጥርስ ኣዳኝ መሆን አልፈልግም አለ? »

“እህስ! ያውም የኔን የጓደኛውን ጥርሶች! አይገርምህም?»
በጣም እንጂ» ይሄ ምን አይነት ንግግር ነው? የሚል ሀሳብ
ጨረፈኝ

“ካንተ ጋር ብተዋወቅና በሰፊው ባወራ ደስ ይለኝ ነበር። ግን
እቸገራለሁ። ጥርሶቼ ናፍቀውኛል» አለ። ይስቃል
«ይገባኛል» አልኩት እየሳቅኩ
ባሀራም እንደሚያስፈልገኝስ ይገባሀል?»
“አዎን"
ሳቁ ከፊቱ ጠፋ፡፡ ጉንጮቹ ወደ ውስጥ የጎደጎዱ ናቸው፡፡ በብዙ
የሚመገብ አይመስልም። ቆንጆ ጣቶቹን አየሁዋቸው፤ ንፁህ ናቸው፤ የሲጋራ ልማድ አልተለጠፈባቸውም

አሮጊቷ ሲመጡ ማኑ ቀዝቃዛ ወተት አዘዘ፡፡ አንዲት ኮረዳ
ባጠገባችን ስታልፍ ሽቶዋ አንድ ጊዜ አወደን፡፡ ነጭ ሸሚዝና
ሰማያዊ ቁምጣ የለበሰው ቅርፅዋ አይን ይማርካል፡ የሚወዛወዝ ዳሌዋ ያስጎመጃል፡፡ ማኑ አይኑን ጣል አረገባት፡ ያኔውኑ ረሳት፡ ወደ
ካፌው ውስጥ እስክትገባ በአይኑ አልተከተላትም። ለምግብም፤
ለሲጋራም፣ ለመጠጥም፡ ለሴትም ጊዜ ያለው አይመስልም። ጊዜውን
በሙሉ ለሬቮሉሽኑ መድቧል? ስራውም፤ ጨዋታውም፣ እረፍቱም
ያው ሬቮሉሽን ይሆን?
እንዲህ አይነቶቹ ታጥቀው ሲነሱ፤ በሁለት አመት ውስጥ ሞስኮ፤ ፒኪንግ፣ ቡዳፔስት ወዘተርፈ እየዞሩ ሶስት ሚልዮን
ፓውንድና አስራ አምስት ሺ መትረየስ የሚያከማቹ ጎልማሶች
ታጥቀው ሲነሱ፡ እስር ቤት ውስጥ ጣታቸው ተሰብሮ ጥርሳቸው
የተሽረፈ ሰዎች ታጥቀው ሲነሱ፣ ለሴትም ለመጠጥም ጊዜ የሌላቸው ጎረምሶች ታጥቀው ሲነሱ፡ የኢራን ሻህ ለምን ያህል ጊዜ ዙፋኑ ላይ ሊቆይ ይችል ይሆን?

ማኑ እንዲህ አለኝ
👍311
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


....ከዚህ በፊት መፅሀፌ " እምቢ
ሲለኝ፣ አንተን አባርሬ ምን ነበር የማረገው መሰለህ?»

«ከመፅሀፍሽ ጋር የምትታገዪ ነበር የሚመስለኝ»

ተሳስተሀል። በየቀኑ ከምሳ በኋላ ማርሰይ እወርድና፡ ከሰአት
በኋላውን፣ ማታውን፣ አንድ አራት አምስት ወንድ ተኝቶኝ፣ ወደ
እኩለ ሌሊት ላይ ድክም ብሎኝ ወደ ኤክስ እመለሳለሁ:: በቀን
በቀኑ ይህን አረጋለሁ። አንድ ቀን ልሄድ ስዘጋጅ ፃፊ ፃፊ ይለኛል፡፡
መፃፍ እጀምራለሁ፡፡ ወንዶቹ በቁኝ ማለት ነው። በፊት እንዲህ ነበር
የማረገው

«አሁንስ?»

“አሁንም ላደርገው ተነሳሁ። ማርሰይ ወረድኩ። ግን ምንም
ሳላረግ ተመለስኩ።
«ወንዶችሽ እምቢ አሉሽ?»
በጉሮሮዋ ውስጥ ቅንዝረኛ ሳቋን እየሳቀች
“ትቀልዳለህ?» አለችኝ ተለውጬ ነው እንጂ። ወንድ መሄድ
ሱስ መሆኑ ቀረ»
«ሱስ መሆኑ ቀረ እንጂ መደረጉ ግን አልቀረም፣ እ?»
«መደረጉማ ለምን ይቀራል? የስሜት ደስታ አይደለም እንዴ?»
ይህን ጊዜ ቤቷ ልንደርስ አንድ መቶ ሜትር ያህል ቀርቶናል፡፡
ታሻሽው የነበረውን እጄን ለቀቀችና
ማን ይቅደም?» ብላ ትታኝ ሮጠች፡፡ እንዳልቀድማት ብዬ
ጫማዬን በሀይል እያስጮህኩ ተከተልኳት። እሷ እየጮኸች፣ እኔ
እየሳቅኩ ቤቷ ጋ ስንደርስ፣ በሩን ቀድማኝ በእጇ ነካችው
ቀደምኩህ!» አለችና በሩን ተደግፋ ቁና ቁና ስትተነፍስ፣
ጉንጮቿን በእጆቼ ይዤ ግምባሯን ሳምኳት እንደዚህ ለዋውጠኸኝ፣ በኋላ ያላንተ እንዳት ልሆን ነው?»
አለችኝ፡፡ በሀይል አሳዘነችኝ፡፡ ሆዴ ሽምቅቅ አለ፡፡ ወደኔ አስጠግቼ
ራሷን እየደባበስኩ ውይ የኔ ቆንጆ! እንድተውሽ አትፈልጊም እንዴ?» አልኳት
«አልፈልግም አልፈልግም አልፈልግም!» እያለች በጣም
ተጠጋችኝ፡ ራሷን አንገቴ ውስጥ ሸሸገች፡፡ እምባዋ አንገቴን ነካኝ
«እኔም ልተውሽ አልፈልግም፣ የኔ ቆንጆ፣ አልተውሽም፡፡
እስከመቼም አልተውሽም፡፡ ምንም ቢመጣ አልተውሽም» አልኳት
«እፈራለሁ፡፡ ካንት መለየቱን ሳስበው እፈራለሁ፡፡ አንተ አገርህ
ትሄድና፣ ከዚያ በኋላ አንገናኝም። እስከመቸም አላይህም፡፡ በቃ
ለዘለአለም?! ውይ! እቀፈኝ! እቀፈኝ!. . . መኖር እንዴት አስቸጋሪ
ነው!»
«አይዞሽ አንለያይም፣ የኔ ሲልቪ»
«አንለያይም?»
«አንለያይም። አይዞሽ አታስቢ። አሁን እንግባ»
አልጋ ውስጥ ላዬ ላይ አደረግኳትና፣ ጀርባዋንና አንገቷን
ጭንቅላቷን እየደባበስኩ ብዙ ጊዜ ከቆየን በኋላ፤
«አሁን ተለያይተን በወድያኛው ህይወት የምንገናኝ እንኳ
ቢሆን፣ ምናልባት እችለው ነበር» አለችኝ ግን መለያየቱ ለዘለአለም
ቢሆን፡ አንድ ጊዜ አይህና ከዚያ በኋላ ለዘለአለም ለዘለአለም
እስከመቸም የማንተያይ ስንሆን፣ በጣም ያስፈራኛል!» ብላ ተጠመጠመችብኝ

«አይዞሽ እንለያይም»
«አንለያይም?»
በሩ ተንኳኳ። ድንግጥ አለች
«አይዞሽ አይዞሽ»
በሩ እንደገና ተንኳኳ
«ማነው በይ» አልኳት
«ማነው?» አለች ጮክ ብላ
«ባህራም!»
ድንጋጤዋ ወደ ብሽቀት ተለወጠ። እየተነጫነጨች ተነስታ የሌሊት ካፖርቷን ራቁት ገላዋ ላይ ጣል አርጋመቀነቱን እየታጠ
ቀች ሄዳ በሩን ከፈተች
ባህራም «ይቅርታ በዚህ ሰአት ስላስቸገርኩ» እያለ ገባ። ጥቁር
ሙሉ ሱፍ ልብስ፣ ውሀ ሰማያዊ ሸሚዝ፣ ደማቅ ሰማያዊ ክራቫት::
ፂሙን ተላጭቶ፣ ፀጉሩን ወደ ኋላ አበጥሯል፡፡ ከጎንና ከጎን የበቀለው
ሽበት' የእርጅና ምልክት መሆኑ ቀርቶ ልዩ ጌጥ መስሏል፡፡ የድል
አድራጊነት ፈገግታ የሚጨፍርበት ፊቱ ወጣትነት ተላብሷል መጥቶ የተጋደምኩበት አልጋ አጠገብ ወምበር ላይ ሲቀመጥ
«እንዲህ ዘንጠህ የት ልትሄድ ነው? » አልኩት
ሲልቪ መጥታ ከጎኔ አልጋው ውስጥ ገባች
«እገሬ መግባቴ ነው» ከለ
“ልሰናበታችሁ ነው የመጣሁት»
«መሄድህ ነው በቃ?» አለችው ሲልቪ
“አዎን"
«ቆይ ዊስኪ ላምጣልህ» ብላ፣ ከአልጋው ወጥታ ወደ ወጥ ቤት
ሄደች፡፡ ቶሎ ከኪሱ አንድ ወረቀት አውጥቶ፣ ወምበር ላይ
የተሰቀለው ኮቴ ኪስ ውስጥ ከተተና፣ በሹክሹክታ
«ለብቻህ አንብበህ ቅደደው » አለኝ
"ላንተም ላምጣልህ? » አለች ከወጥ ቤቱ
«ለኔም ላንቺም አምጪ» አልኳት
ይዛ መጣች። ከልጋ ውስጥ ገባች። ዊስኪውን አነሳሁና ባሀራምን
«መልካም ጉዞ!» አልኩት
ፉት አልን
«ከመሄዴ በፊት ጥቂት ልነግርህ የሚገባኝ ነገር አለ» አለኝ።
ሲልቪ ትታን ልትሄድ ስትል «ካንቺ የሚደበቅ ያለበት አይደለም»
አላት
«እሺ» አልኩት
ብዙ ልነግርሀ በፈቀድኩ። ግን አብዛኛው የኢራን ኮሙኒስት
ፓርቲ ምስጢር ነው፡፡ አንተን አምንሀለሁ፡፡ ግን ፓርቲው
እንድነግርህ አይፈቅድልኝም»
«ይገባኛል፡፡ ምንም መናገር የለብህም»
«አውቃለሁ፡፡ ሁለት ነገር ብቻ በጠቅላላ ባጭሩ ልንገርህን
«ሁለት አመት ሙሉ በይሩት ነበርኩ፡፡ ግን ዩኒቨርሲቲው
ውስጥ የህክምና ትምህርት አልተማርኩም፡፡ ሌላ ስራ ነበረኝ። በቅርብ ምስራቅ ውስጥ ያሉትን የኢራን ኮሙኒስቶች ሳደራጅ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደሞ ከሻህ ሰላዮችና ከሲ.አይ.ኤ ጋር ረዥም ጦርነት ስናካሂድ ነበር። ሲ.አይ.ኤ ሊገድለኝ ሲሆን ጊዜ፣ ቱዴህ (የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ) እንድሸሽ አዘዘኝ። ወደ ኤክስ መጣሁ። እውነተኛ ስሜን
ልነግርህ አልችልም፡ ግን ባህራም አይደለም። ባሀራም ከፍሻር
በይሩት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ህክምና ይማር ነበር። በሱ ስም የውሽት ፓስፖርት አውጥቼ ነው፡፡

«ቤቶችህ ይህን ያውቃሉ?»
«ታላቅ ወንድሜ ያውቃል። ስም በቀየርኩ ቁጥር አዲስ ስሜን
በደብዳቤ ነግረዋለሁ፣ ከቤት ገንዘብ ሲመጣልኝ እሱ በአዲሱ ስሜ እየላከው ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር አለኝ የምነግርህ»
ምን?»
«ደጋግመህ መልክህ የኢራንን ሻህ ይመስላል ብለኸኛል።
እውነትክን ነው:: ሻህ የስጋ ዘመዴ ነው»
አጭር ዝምታ
«ላሳየኸኝ ጓደኝነትና ለዋልክልኝ ውለታ ላመሰግንህ አልችልም፡፡
ስለዚህ ሳላመሰግንህ መሄዴ ነው» አለኝና ተነሳ፡፡ በቁሙ ዊስኪውን ጨልጦ፣ ብርጭቆውን ኮሞዲኖ ላይ አኖረው:: ልሸኘው ካልጋ ልነሳ ስል
«አትነሳ። ማኑ እዚህ ውጭ ይጠብቀኛል። አብረኸኝ ብትመጣ
ያለቅስብኛል፡፡ እሱ ሁልጊዜ እንደተጠነቀቀ ነው። ወዴት በኩል
እንደምንሄድ አንተ'ንኳ እንድታውቅ አይፈልግም» ይስቃል፡፡ ማኑን
ስለሚወደው ይስቅበታል። ከማኑ ጋር ለመሆን በመቻሉ እጅግ ደስ
ብሉታል፡፡ ወጣትነቱን እንደገና አግኝቷል። እጄን ዘረጋሁ:: ጨበጠኝ። በኔ በኩል ተንጠራርቶ ሲልቪን ሳማት። ሊሄድ ወደ በሩ በኩል ከዞረ በኋላ
«ለመሆኑ አልኩት ዞረ። ፊቱ ላይ ፈገግታ የለም፡፡ የኢራንን ሻሀ ይመስላል።አፍንጫው ትልቅ ነው
«ለመጀመሪያ ጊዜ
ሳገኝህ ሶስት አሜሪካኖች
ይዘውህ ሊደበድቡህ መጀመራቸው ነበር» አልኩት
“A bas les Yankecs!” አለኝ እየሳቀ
“A bas!" አልኩት
ሰአቱን አየ፡፡ ቸኩሏል
“ሊደበድቡህ ይዘውህ ሳለ፣ ማኑ ያስተማረሀን የመከላከል ዘዴ
ለምን አልተጠቀምክበትምን» አልኩት
«ተማሪዎች ይሁኑ ወይ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ይሁኑ እርግጠኛ አልነበርኩም። ምናልባት እኔን ፍለጋ የመጡ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ቢሆኑስ? ያን አይነት ያምባጓሮ ዘዴ ማወቄን ካወቁ ባህራም አለመሆኔን ይጠረጥራሉ። ለዚህ ነው:: በሎ ደህና ሁኑ። ማኑ ይጠብቀኛል»
👍30🥰1👏1😁1
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከሲልቪ ቤት ወጥቼ ወደ
ሲቴ አመራሁ፡፡ ትላንት “ማታ ባህራም ኪሴ ውስጥ ያስቀመጠውን ወረቀት መንገድ ላይ አነበብኩት፡፡ ኒኮል የፃፈችለት ደብዳቤ ነው
«ውድ ባህራም
«እንዴት ልጀምር? አስቸጋሪ ነው። እወድሀለሁ፣ ከልቤ እወድሀለሁ። አሁን የምነግርህ ነገር የማልወድህ ሊያስመስለኝ
ይችላል። ግን እወድሀለሁ፤ ከልቤ አፈቅርሀለሁ
«ያለሬቮሉሽን መኖር አትችልም። ከኔ ጋር መኖር አትችልም። ስለዚህ እኔን ትተኸኝ መሄድ አለብህ
«እኔ ስለሪቮሉሽን በጭራሽ ሊገባኝ የማይችል ብዙ ብዙ ነገር
አለ። ለምሳሌ ደም ማፍሰስ። ብዙ ተከራክረንበታል፣ ታስታውሳለሁ::
ደጋግመህ አይገባሽም! ስለሪቮሉሽን በጭራሽ አይገቤሽም ብለኸኛል። እውነትክን ነው:: አይገባኝም። ግን በደምብ የገባኝ አንድ ነገር አለ። አንተ ያለ ሬቮሉሽንህ መኖር አትችልም። ስለዚህ መለያየት አለብን።

“ከዚህ ቀጥሎ የምነግርሀ ሊገባህ አይችልም። ስለዚህ እንዲገባህ ለማድረግ አትሞክር። ዝም ብለህ እመነው። ይኸው የማፈቅረው አንተን ነው። የተረገዘው ልጅ ግን ያንተ አይደለም። የሉልሰገድ ነው። ልነግርህ ሞክሬ ነበር። ብዙ ጊዜ ሞከርኩ፣ አቃተኝ፡፡ አሁንም
ቢሆን መነፅራሙ ጓደኛህ ባያግዘኝ ኖሮ አልችልም ነበር

አዝናለሁ:: ስላደረስኩብህ ሁሉ ችግር በጣም አዝናለሁ።
ብትችል በልብህ ይቅር በለኝ። ባትችል ጥላኝ፡፡ ብቻ ሂድና
ሬቮሉሽንህ ውስጥ ኑር። ደስታ ሊስጥህ የሚችል እሱ ብቻ ነው።
በሄድክበት ይቅናህ፡፡ ደህና ሁን።
ያንተ ኒኮል።
P S ልታገኘኝ አትሞክር። አታገኘኝም። ልሰናበትህ ባለመቻሌ አዝናለሁ። ግን ፊትህ ላይ ቂም ማየት እፈራለሁ። ደህና ሁን። ይህን ደብዳቢ ሶስት ጊዜ ደጋግሜ አነበብኩት፡፡ ኒኮል ለምን
ፃፈችው ይህን? ቀዳደድኩት። ቁርጥራጮቹን በተንኳቸው:: ሲቲ ሄጄ ገላዬን ታጥቤ፣ ልብሴን ቀይሬ ወደ ኒኮል ቤት ሄድኩ አልጋዋ ላይ ተጋድማ ሲጋራ እያጨሰች ሙዚቃ ትሰማለች ታቹን ነጭ ክሮሽ እንደ ሸማኔ ጥለት የከበበው ቡና አይነት ቀሚስ ለብሳለች። ስገባ ፈገግ እያለች
«እንኳን መጣህ! ጭር ብሎኝ ነበር» አለችኝ
ደህና ነሽ?
«ደህና ነኝ፡፡ በጣም ደህና ነኝ። ግን ሌላ ሰው ማየት
አልፈልግም። እባክህን በሩን ቆልፈው።
ቆልፌው ስመጣ፣ የተጋደመችበት አልጋ ላይ እንድቀሙጥ በእጇ አመለከተችኝ። ጥፍሮቿ ሀምራዊ ተቀብተው ያብለጨልጫሉ።
ተቀመጥኩ፣ አየሁዋት። በጣም የተለወጠች መሰለኝ፡፡ ከንፈሮቿ እንደ ጥፍርቿ ሀምራዊ መሳይ ቀለም ተቀብተዋል፡ ቅንድቦቿን ወደ ሰማያዊ የሚወስድ ጥቁር ቀለም አድምቋቸዋል፣ ከግምባሯ ንጣት ጋር ሲታዩ በጣም ያምራሉ። የአይኖቿ ቆዳ ልክ የአይኖቿን
የሚመስል ውሀ እረንጓዴ ኩል ተቀብቶ፣ አይኖቿ ውስጥ ተነክሮ
የወጣ ይመስላል። ከመጠን በላይ አምሮባታል። ከጥንታዊት
ግብፃዊት ጋር ያለሁ መሰለኝ። ፀጉሯ እንደ ድሮው አመዳም
አይደለም፡ ንፁህ ቡናማ ቀለም ተነክሯል
«ምን ነካሽ?» አልኳት
«ምነው?»
«እንደዚህ የምታምሪ አይመስለኝም ነበር»
"Merci
«እውነት ግን ምንድነው?» አልኳት
«እንደዚህ ነኝ፡፡ ሳዝን ሰው እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። አሁን
ያዘንኩ እመስላለሁ?»
በጭራሽ
«ለዚህ ነው አይኔንም የተኳልኩት፣ ፀጉሬንም የተነከርኩት»
«አዝነሻል?»
«እንደ ዛሬም አዝኜ አላውቅ፡፡ ሲሄድ ደህና ዋል አለህ?»
«አዎን»
የፃፍኩለትን አሳየህ?»
«አዎን፡፡ ለምን ፃፍሽው?»
«እንዴት እንደፃፍኩት ልንገርህ?»
«ንገሪኝ»
«ከትላንት ወድያ ማታ፣ እንደዚህ ተጋድሜ ሙዚቃ ስሰማ፣
አንድ ሰው መጣ፡ መልኩ ሰው ይመስላል እንጂ እንደኔና እንዳንተ
ህዋሳቱ ውስጥ ደም እንደሚፈስ ልምልልህ አልችልም። ምናልባት
ከነሀስ የተሰራ ሰው ሊሆንም ይችላል። ረዥም ቀጭን ነው፡ መነፅር ያረጋል። ግምባር የለውም፡ ከአይኑ ቀጥሎ አናቱ ይመጣል፡፡ ድምፁ ወፍራም ከመሆኑ የተነሳ ከሆዱ እንጂ ከጉሮሮው የሚወጣ
አይመስልም»
«ጠልተሽዋል እ?»
«መጥላት አይደለም፡፡ ፈራሁት። ቀፈፈኝ፡፡ አየህ፣ ገባና
በወፍራም ድምፁ
ኮል ማለት እርስዎ ነዎት?» አለኝ
ነኝ» አልኩት
“ጥሩ። እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ተልኬ የመጣሁ ነኝ
«ታድያ እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ምን አለኝ?
«እርስዎ አይናገሩ፡፡ ጊዜ የለኝም» አለኝ፡፡ ድምፁ በጭራሽ
አይለዋወጥም፡፡ ምንም ነገር ሲናገር በዚያው በወፍራም ድምፅ ነው
“የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ባህራምን ይፈልገዋል፡፡ በጣም
ይፈልገዋል። እኔን ፓርቲው ልኮኛል። ከትእዛዝ ጋር፡፡ ወያም
ባህራምን ይዘኸው ና፣ ወይም ገድለኸው ተመለስ ተብያለህ
ግደለው? ለምን?» አልኩት
ቀላል ምክንያት፡፡ የኛን ምስጢር ያውቃል፡፡ ምስጢራችንን
በሙሉ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፣ ወይም ከኔ ጋር ይምጣል፡ ወይም
ይሞታል። ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ግን አንድ ነገር አለ» አለኝ
ምን?»
ባህራም አልመጣም የሚለው በእርስዎ ምክንያት ነው:: እርስዎ
ባይኖሩ ይመጣል፡፡ ስለዚህ እርስዎ እንዳይኖሩ ማድረግ፡፡»
ሆዱ እየፈራ፤ «እንዴት?» አልኩት
«መግደል» አለኝና፣ ከኪሱ አንድ የታጠፈ ጩቤ አወጣ፡፡ ጫን
ሲለው ጩቤው እንደ ብልጭታ ክፍት አለ ሻህን ልግደለው!' አለኝና፤ ያንን የኢራን
ስእል አመለከተኝ፡፡ ባህራም ነው እዚያ የለጠፈው፡፡ ልተኛ ስልና ልነሳ ስል፣ ሻህ እንዲታየኝ እፈልጋለሁ ብሎ ሰቀለው::»
ግድግዳው ላይ የኢራን ሻህ የጦር ጠቅላይ አዛዥ የማእረግ
ልብሱን ለብሶ ቆሞ በከለር የተነሳው ትልቅ ፎቶ አለ
"ለምሳሌ ሻህ እርስዎ ነዎት። ጉሮሮውን ይመልከተቱ" አለና
ጩቤዋን ወረወራት። የሻህ ጉሮሮ ላይ ስክት አለች። ሰውየው ወደ
ስእሉ ሄዶ ጩቤውን ነቀለና አጥፎ ኪሱ ከተተ መንገድ ላይ እርስዎ ሲራመዱ ወይም ሲሮጡ እኔ በፈጣን መኪና እየሄድኩ ጩቤ ብወረውር፣ ጉሮሮዎትን እልስተውም፡፡ ገባዎት?» አለኝ። በድምፁ ሊያስፈራራኝ በጭራሽ አልሞከረም፡ ልክ የጂኦሜትሪ ፕሮብሌም እንደሚያስረዳኝ ያህል ነበር ገባኝ» አልኩት። እንደዚያን ጊዜ ፈርቼ አላውቅም
«ለባህራም ይንገሩት»
«ምን ብዩ?»
«ያረገዝኩት ካንተ አይደለም፣ ይበሉት
«ታድያ ከማን ነው ልበለው?»
« እንደፈለጉ። ለምሳሌ እጀምሺድ ወይም ከሉልሰገድ ነው
ሊሉት ይችላሉ፡፡ እነሱን ሊጠይቃቸው አይችልም»
«እሺ» አልኩና ደብዳቤውን ፃፈኩ። አጣጥፎ ኪሱ ሲከተው
«ባሀራም ይህንን ካነበበ በኋላም ከርስዎ ጋር መሄድ ባይፈቅድስ?»
አልኩት
«እምቢ አይልም»
«ቢልስ?»
«እገድለዋለሁ። ደህና እደሩ» አለኝና ወጣ። እንደሱ ያለ
ከሰውነት የራቀ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም
ኒኮል ዝም አለች፡፡ ዝም ብዬ እየኋት። በጣም ታምራለች።
ውሀ እረንጓዴ ኩሏና ሀምራዊ የከንፈር ቀለሟ የፈርኦን ዘመን
ግብፃዊት አስመስሏታል። ሳቅ አለች
«ምነው ትኩር ብለህ ታየኛለህ?»
«አማርሽኝ» አልኳት። ውስጡን ደነገጥኩ። እንደዚህ ለማለት
አላሰብኩም ነበር። ውሀ አረንጓዴ ቆዳ ሽፍን ግልጥ በሚያደርጋቸው
ውህ እረንጓዴ እይኖቿ አየችኝ፡፡ ሀምራዊ ከናፍሯ በፈገግታ
ተላቀቁ። እጄን ጉልበቷ ላይ አሳረፍኩ፣ አልከለከለችኝም
«ጫማዬን ላወልቅ ነው» አልኳት
👍285