አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
494 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

በስራ ጉዳይ ወዲህና ወዲያ ስሯሯጥ ቆይቼ ከምሽተ 3 ሰዓት ካለፈ በኃለ ነው ወደ ቤት የገባሁት፡፡ያው የተለመደ የወንደላጤ ቤቴን አየከፈትኩ ሳለ ስልኬ ተንጣረረ...በአንድ እጄ እየከፈትኩ በሌለው እጄ ከኪሴ አወጣሁና አየሁት፡፡ ልጄ ነች፡አነሳሁትና

‹‹ሄሎ የእኔ ጣፋጭ››

‹‹ያንተ ጣፋጭ አይደለሁም..ማለት እናቷ ነኝ››

‹‹ውይ እሪች ይቅርታ …ተአምር መስላኝ ነው››

‹‹አውቃለሁ..አንተ አልተሳሳትክም እኮ የደወልኩት በእሷ ስልክ ነው…አባትና ልጅ ግን የምትገርሙ ሴረኞች ናችሁ››

‹‹እንዴት ማለት››በራፉን ከፍቼ ወደውስጥ ከገባሀ በኃላ አልጋዬ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብዬ ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡

‹‹ምን እንዴት አለው…ሁሉን ነገር ሰማሁ….በሚስጥር መገናኘትና መደዋወል ከጀመራችሁ መከራረማችሁን….አረ ጭካኔያችሁ…. ከአንተ  ደግሞ የእሷ አይገረምም፡፡››

‹‹እንዴት?››

‹‹ሰው እንዴት ከገዛ እናቱና አያቱ እንዲህ አይነት ሚስጥር ሰውሮ መቆየት ይችላል….ለዛውም በዚህ እድሜዋ››

‹‹ያው የአባት ጉዳይ ሲሆን ይችላል.ልጄን ደግሞ ታውቂያታለሽ… ልክ እንደአባቷ እስማርት ነች፡፡››

‹‹ይሀቺ ጉራ አሁንም አለቀቀችህም››

‹‹ምነው ተሳሳትኩ አንዴ?››

‹‹አላልኩም….ለማንኛውም በጣም እንዳስደመማችሁኝም እንዳስቀናችሁኝም መናገር እፈልጋለሁ…ለመሆኑ አንተስ እንዴት ነህ…?››

‹‹ይመስገነው… ህይወት እንደጢባ ጢቢ አንቀርቅባ አንቀርቀባ ገና  አሁን በቅርብ ቀን ነው  እያረጋጋቺኝ ያለው››

‹‹በጣም አዝናለሁ››

‹‹ለምኑ?››

‹‹ከእኔ ጋር የሆነው ነገር ባይሆን ኖሮ አንተ አንዱንም ችግር አታይም ነበር…››

‹‹ተይ ተይ ..ችግሩር ያየሁት እኮ ሀገሪቱ ተምሬ በተመረቅኩት ሞያ ስራ ልትሰጠኝ ስላልቻለች ነው››

‹‹ያ እውነት እንዳልሆነ ሁለታችንም እናውቃለን››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹አንተ ስራ አጣሁ የሚለውን እንደሽፋን ተጠቅመህ እራስህን እየቀጣህ ነበር...ቤተሰቦቼ ላይ ከሰራሁት መጥፎ  ስራ አንፃር የተሻለ ህይወት ፈፅሞ አይገባኝም ብለህ በመወሰን ነው በዝቅተኛ ህይወት ውስጥ እራስህን ዘፍቀህ በችግር በመዳከር እራስህን ስትቀጣ የኖረከው…እንጂ ሌላውን ተው አዲስአባ ወላጆችህ ትተውልህ የሞቱት ቤት እንዳለ ታውቃለህ….ባንክ ውስጥም ቢያንስ ከግማሽሚሊዬን ብር በላይ ትተው መሞታቸውን ከቤት ኪራይ እየተሰበሰበ ለዘመናት የተጠራቀመው ብር  እንዳለ ታውቃለህ… ይሄ ሁሉ ሀብት ያለው ሰው በጤናው የፓርኪንግ ሰራተኝነት እና የሆቴል አስተናጋጅ ሆኖ የወጣትነት ህይወቱን አይገፋም…ለዛውም ባለዲግሪ ሆኖ..

‹‹ትክክል ልትሆኚ ትቺያለሽ…..እኔ ግን በዚህ መንገድ አይቼው አላውቅም…እኔ ያምትይውን ብር ሆነ ቤት መጠቀም ያልቸልኩት ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን እሱን ለመጠቀም የእቴቴን አይን ማየት ስላልፈለኩ ነው፡፡››

‹‹ተው ተው..ትንሽ ካሰብክበት እኮ የእቴቴን አይን ሳታይ የሚገባህን ንብረትህን እጅህ ማስገባት ትችል ነገር››

‹‹ተይ ተይ .እንደምታስቢው ቀላል አልነበረም››

‹‹አውቃለሁ… ግን ያደረከው ያልኩትን ነው እራስህን መቅጣት.እኔም አኮ ስላደረኩት ነው እንደዛ የምልህ…..?››

‹‹እንዴት?››

‹‹ያው እደምታየኝ አምሮብኛል ሰውነቴ አብረቀርቆል..ግን አሜሪካ ያሳለፍኳቸውን ስድስት አመቶች እንደምታስበው  እንዳይመስልህ.. ከጥዋት እስከ ሊሊት ከሶስት በላይ ስራ እሰራለሁ..ብዙ ብዙ ገንዘብ አገኛለሁ..የማያስፈልገኝን ገንዘብ ለማግኘት ማለት ነው እንደዛ እለፋ የነበረው..  ማንንም አላገኝም ..የትም ሄጄ መዝናናት አልፈልግም….የሳምንት እረፍቴ ከስድስት ሰዓት አይበልጥም ነበር…ማን መሆኔን እራሱ ዘንግቼ በድኔ ልክ እንደሮቦት ሆኜ ነበር የምንቀሳቀሰው…አሁን በቅርብ ጊዜ ግን ይህ ጉዳይ እንዴት ነው..?ለምድነው እንደዚህ የምለፋው..?የምሰበስበው ገንዘብ ለማን ብዬ ነው….?ብዬ ሳስብ  በጣም ግራ ተጋባሁ እና ባለሞያ ጋር ሄድኩ.. ባለሞያውም የህይወት ታሪኬን ካስለፈለፉኝ በኃላ በስተመጨረሻ የደረሰበት መደምደሚያ የምሰራው ስራ ሁሉ እራስን መቅጣት እንደሆነ እና  ከዚህ ወጥመድ የመውጫው መንገድ ግን ይሄ እንዳልሆነ መከረኝ….ለዛ ነው ካለእቅዴ ድንገት ወደሀገሬ ፈጥኜ የመጣሁት..መድሀኒቱ እዚህ ስለሆነ…››

‹‹አልገባኝም›አልኳት

የእውነትም ስላልገባኝ፡፡
‹‹አየህ ያባለሞሞው ውሳኔዬ በጣም ትክክል ነበረ..ይሄው ወደ ሀገሬ ከተመለስኩ በኃላ ካስብኩት በጣም በፈጠነ ጊዜ መድሀኒቱን አግኝቼ እየታከምኩ ነው…አንተን ማግኘትና ያለህበትን ሁኔታ መረዳት ችያለሁ….ይህ ማለት በእየለቱ የት ወድቆ ይሆን በሚል እምሮዬን ሲበላኝ የነበረው ነገር አሁን ድኖልኛል….ሌላው የእቴቴን ይቅርታ ማግኘት ችያለሁ…ያ ደግሞ ምን ያህል የአእምሮ ሰላም እንደሚሰጥ በራስህ ታውቀዋለህ…በነገራችን ላይ አባዬንም ይቅርታ ጠይቄዋለሁ.. አሁን የቀረኝ ትንሽ ነገር ነው…አንተን እና አባዬን ማገናኘት..››

‹‹አንተን እና አባዬን…?››ደንግጬ

‹‹አዎ ምነው ያንን ማድረግ አትፈልግም እንዴ?››

‹‹አረ በጣም ፈልጋለሁ..ግን እንዴት ብዬ አይኑን አያለሁ ?››

‹‹ልክ የማዬን አይን እንዳየህ..ደግሞ እኔ አፍጥጬ ሄጄ እሱን ማናገር ከቻልኩ አንተስ እንዴት ያቅትሀል?፡፡:ከዛ ከእማዬ ጋር መልሰን እናጋባቸዋለን…አንድ ላይ ሆነን ወላጀቻችንን ሆነ እህቶቻችንን አንክሳቸዋለን… በእኛ ምክንያት የቆሰለው ልባቸው ፈፅሞ እንዲድን የተቻለንን እናደርጋለን..ከዛ የእኛም ቁስል ቀስ እያለ ሙሉ በሙሉ ይድናል…ምን ይታወቃል የፈረሰ ተስፋችን መልሶ ይገነባ ይሆናል…እርግጠኛ ነኝ በመጨረሻ እራሳችንንም ይቅር እንላለን፡፡

‹‹አሜሪካ ተመልሰሽ እትሄጂም ማለት ነው?››

‹‹ሄዳለሁ.. ግን ለመኖር አይደለም…ሁኔታዎችን አመቻችቼ አንደኛዬን ጠቅልዬ እመጣለሁ..››

‹‹የእውነትሽን ነው?››
‹‹ምነው ደነገጥክ…እዛ ብኖር ይሻላል እንዴ?››

‹‹አረ እንደዛ ስለወሰንሽ በጣም ደስተኛ ነኝ››

‹‹በጣም ደስተኛ ለምን እንደሆንክ ማወቅ እችላለሁ?››

‹‹እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ…አንድ ቀን ታአምርን ወደአሜሪካ ልውሰድሽ ብትላት ምንድነው የማደርገው? በሚል ስጋት እንዴት እየተሰቃየሁ እንደነበር ግምቱ የለሽም››

‹‹ይገርማል?››

‹‹ምኑ?››

‹‹መልስህ ያልገመትኩት ነው..ለልጅህ ባለህ ፍቅር ቅናት አደረብኝ››

‹‹እሷ እኮ የከሰመ ህይወቴን መልሳ ያለመለመችልኝ  ካሳዬ ነች. .ለእሷ ስል ህይወቴን እሰጣለሁ..››

‹‹በነገራችን ላይ አዲስአበባ ሪል እስቴት ገዝቼያለሁ..ስለዚህ ልክ ጉዳዬን ጨርሼ ከአሜሪካ እንደተመለስኩ ሁለችንም አንድ ላይ እንኖራለን ማለት ነው..››

‹‹አንድ ላይ ስትይ….?ማለት….?እንዴት…?››

የፈራሁት ነገር ዞሮ ሊመጣ ነው ብዬ በማሰብ ተርበበተበትኩ.

‹‹አይዞህ አትደንግጥ…ይሄውልህ እዬቤ እኔ አሁንም በጣም አፈቅርሀለሁ…እሱን ስሜቴን ካንተም ሆነ ከማንም መደበቅ አልችልም፡፡ደግሞም .አንተን ማፍቀር መቼም አላቆምም…ግን ደግሞ ከዚህ በፊት የሰራነውን ስህተት መቼም ደግመን እንድንሰራ አልፈልግምም፤ አልፈቅድምም….፡፡ይሄንን ደግሞ በቀደም እማዬ ሁለት  ጡቶቾን እስይዛ 
ነው ያስማለችኝ..ስለማልኩ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያውም ስህታችን ያስከፈለንን መከራ አይቼ ዳግመኛ ተመሳሳዩን ስህተት ለመፈፀም ጥንካሬው የለኝም፡፡.ቢያንስ ለእናቴ ስል….ለእህቶቼ ስል..ለአንተ ስል…፡፡ስለዚህ ምንም ስጋት አይግባህ
👍797🔥1🥰1😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጥዋት የበረፍ መንኳኳት ነው ከእንቅልፌ ያባነነኘ…በርግጌ ተነሳሁና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ…አሁንም በራፉ ይንኳኳል ግን የውጭ በራፍ ሳይሆን ከአያቴ ጋር የምንወሰነበት ተከፍቶ ያማያውቀው የውስጡ በራፍ ነው የሚንኳኳው…‹‹ውይ ልጅቷን ረስቼያት… በፈጣሪ ምን አይነት ዝፍዝፍ ሰው ነኝ? .እስከ አሁን እንግዳ እያለብኝ እንዲህ ነገር አለሙን ችላ ብዬ እተኛለሁ…?ይሄኔ እኮ እርቧት ይሆናል….?››

‹‹ማራናታ… ደህና አደርሽ?.››

‹‹አዎ ደህና አድሬያለሁ….ልግባ…ልብስህን ለብሰሀል?፡፡››ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቀቺኝ፡፡

‹‹ውይ እሱ በራፍ የታሸገ ነው …ቆይ በፊት ለፊት ዞሬ መጣሁ..››

‹‹አይ እሽጉን ትናንት አያቴ አስነስቶት ነው የሄደው››…ከሚል ድምፅ ጋር የበር መንሳጠጥ ተሰማና ወለል ብሎ ተከፈተ..ውይ የተሰማኝ ስሜት…. በቅዱሳን መላዕክቱ የገነት በር ሲከፈት ፊት ለፊት በአይኖቼ እያየሁ  ያለሁ   ነው የመሰለኝ...እና ከበሩ መከፈትም በላይ በተከፈተው በራፍ አንገቷን አስቀድማ በማስገግ ብቅ ብላ ወደእኔ ግዛት የገባቸው ልጅ…  በፈጣሪ ሰይጣን አይደል እንዴ የምትመስለው፣ሰይጣን ክብሩን ከመገፈፉ በፊት…ለነገሩ ክብሩን ከተገፈፈም በኃላም ውበቱን አልተነጠቀም…

‹‹አንቺ ይገርማል..አያቴን አይደል እንዴ የምትመስይው?››ሳላስበው አድናቆት ከአንደበቴ አፈትልኮ ወጣ
‹‹ሽማግሌ ፊት ነው ያለሽ እያልከኝ ነው?››

‹‹ይቅርታ …ማለቴ በጣም ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው….››አዎ እውነቴን ነው …ልጅቷ ልክ አያቴን ነው የምትመስለው…ልቅም ያለች የጥቁር   ልጥልጥ  ውብ ነች…፡፡ልክ እንዳየኋት ልቤ ቢጫ ወባ እንደነደፈው ሰው ነው በደቂቃ ውስጥ ፍርፍር ስትል የተሰማኝ፡፡
‹‹ለማንኛወም ቁርስ መብላት ከፈለክ ና ቀርቧል….››ብላኝ በራፉን ክፍት ጥላ ተመልሳ ወደውስጥ ገባች፡፡እንግዳ ሲያፍር ባለቤት ይጋብዛል አሉ….ሲሆን ሲሆን ለሊት ተነስቶ ቁርስ በመስራት እሷን መቀስቀስ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ..ዳሩ አጅሪቷ በየት አሲይዛ …በሁሉ ነገር ጥድፍ ጥድፍ ትላለች፡፡በፈጣሪ በዚህ አይነት አጀማመር ይህቺን አንድ ወር እንዴት ነው ተቋቁሜ የምዘልቀው…? አያቴ ምን ነካቸው..?ይሄንንማ አውቀው ሆነ ብለው እኔን ለመፈተን ያደረጉት ነገር ነው፡፡ወይ እዳዬ ለዘመናት ከዳከርኩበት እና ፍዳዬን ካየሁበት የፍቅር ታሪክ ገና ትናንትና መደምደማሚያ አበጅቼለት ተገላገልኩ ስል….

‹‹እዬቤ...››ጥሪው ከተዘፈዘፍኩበት ሀሳብ መዞ  አነቃኝ

‹‹አቤት››

‹‹ቁርሱ ቀዘቀዘ እኮ….በዛ ላይ እርቦኛል››

ተንደርድሬ ተነሳሁና ፊቴን ተለቃልቄ ልብሴንም ሳልቀይር በለበስኩት ቢጃማ ተንንርድሬ ሚቀጥለው ክፍል ገባሁ…..እንግዲህ ይታያችሁ እዚህ ቤት መኖር ከጀምርኩ ሶስተኛ አመቴ ውስጥ ብሆንም አሁን ያለሁበትን ክፍል ስረግጥና የውስጥ ገፅታውን ሳይ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኔ ነው፡ክፍሉ በስርአት ቦታቸውን ይዘው በተቀመጡ የቤት እቃዎች የተሞላ ነው፡፡ ቢያንስ ሶስት ቦታ በመፅሀፎች የተሞሉ መደርደሪያዎች ይታያሉ…አልጋው በስርኣት ተነጥፏል፡፡  አልጋውን ተጠግቶ ያለው መካከለኛ መጠን ያለው ጠረጴዛ በምግብ ተሞልቷል…

‹‹ምን ይገትርሀል አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በል ››አለችኝ

የእሷን  ግብዣ ችላ አልኩና ግድግዳ ተደግፎ ያተቀመጠ አንድ ደረቅ ወንበር በማንሳት ወደምግብ ጠረጴዛው አስጠግቼ በመቀመጥ አንዴ የቤቱን ዙሪያ መልሼ ደግሞ እሷን ከስር አስከላይ መቃኘት ጀመርኩ… አቀራርባ ስትጨርስ ፊት ለፊቴ አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በማለት እሷም ለመብላት ዝግጁ ሆና እጇን ወደምግቡ እየሰደደች‹‹..በል ብላ››.አለችኝ..

‹‹ይሄን ሁሉ ምን ጊዜ ሰራሺው?››የገረመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት.፡፡

‹‹እቤትህ ሰዓት የለም እንዴ..?ሶስት ሰዓት ሊሆን እኮ ነው››አመሏ ከመልኳ ተቃራኒ ነው..እስከአሁን እንዳየሆት ለየትኛውም ጥያቄ ቀና መልስ መስጠት አይሆንላትም…

‹‹ይቅርታ .እንቅልፍ ጣለኝ››

‹‹አያቴ ጠንካራ ሰራተኛ ነው እያለ ሲፎክርብህ የነበረው እንዲህ እየተኛህ ነው እንዴ?››

‹‹አጋጣሚ ሆኖ ነው..›› የጠቀለልኩትን ምግብ እየጎረስኩ መለስኩላት፡

‹‹እሺ ቢሾፍቱ ዛሬ ትወስደኛለህ ?››አዲስ ርዕስ ከፈተች

‹‹ለምን…?መሄድ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አይ የስራህ ቦታ እዛ አይደለ? ስራ ከሄድክ አብሬህ ለመሄድ ብዬ ነው››
‹‹እ ….እንደዛ ነው….ዛሬ ሳይሆን ነገ ነው የምሄደው ….ነገ አብረን እንሄዳለን….ዛሬ የሆነ ጓደኛዬን ከአገር ውጭ ስለምትሄድ እሷን እንሸኛለን››

‹‹እ… .ጄኔራሏን?››

‹‹ምን….?በምን አወቅሽ…?››.ደንግጬ

‹‹ይሄውልህ ስለአንተ የማላውቀው እንዲህ ቆንጆ መሆንህን ብቻ ነበር… አሁን ደግሞ እሱኑም አወቅኩ››ብለኝ እርፍ
‹‹እንዴት…?አሀ ይሄን ሁሉ የነገሩሽ አያቴ ናቸው?››

‹‹አዎ  አያትህ…በነገራችን ላይ አያቴ በየደብዳቤው ስለአንተ ሲዘበዝብልኝ በጣም እበሳጭበት ነበር››

‹‹ለምን? ቀንተሸ?››

‹‹አዎ ብቀና ይፈረድብኛል..?እኔ በአያቴ ቀልድ አላቅም...እና ብቸኛ የልጅ ልጁ ሆኜ መቀጠል ነበር ምፈልገው..››

‹‹እና አሁንስ?››ስል ጠየቅኳት በመገረም፡፡

‹‹አሁንማ አንደኛ አባቴ ከዛች የተረገመች ሚስቱ ሌላ ልጅ ስለወለደ ብቸኛ የልጅ ልጁ መሆኔ ማክተሙን አምኜ ተቀበልኩ ….ሁለተኛ እኔም ሳላስበው ታሪክህን ቀስ በቀስ ሲያስጠናኝ የእውነትም አያቴ አያትህ ይመስለኝ ጀመር…››

ተበሳጨሁ… ልጎርስ አፌ ላይ ያደረስኩትን ምግብ መልሼ ትሪው ላይ በትኜ ተነሳሁና‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው..?››አፈጠጥኩባት

‹‹አቦ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ማለት ምን ማለት ነው?››እሷስ መች የዋዛ ሆነችና በተቀመጠችበት መልሳ አፈጠጠችብኝ፡፡

‹‹አያቴ ስል ለማሾፍ ወይም ለፉገራ ይመስልሻል…?የእውነት አንቺ ከእኔ በላይ እራስሽን ባለመብት አድርገሽ መጎረርሽ ነው..?››ወረድኩባት
‹‹ባለመብቱንማ በተግባር አየነው እኮ…. እኔ እኮ አይደለሁም የአንድ ሚሊዬን ብር ቼክ የተፃፈልኝ…አሁን እንብር እንብር አትበል ቁጭ በልና ቁርስህን ጨርስ .ደግሞ አያቴን የነጠቅከኝ ሳያንስ ስድብ ትመርቅልኛለህ….አረ አይነፋም…››

በንግግሯ ተሸነፍኩና ተመልሼ ቁጭ አልኩ…ገና በመጀመሪያው ቀን ይሄን ያህል ከተጮጮህን ዋል አደር ስንል..ወይኔ ጉዴ…ጨነቀኝ፡፡

አንድ ክፍል ቀረው
👍17915😁11🥰4👎3🔥2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

ከቁርስ ቡኃላ ልብስ ቀያየርንና ተያይዘን ወጣን….የተወሰኑ ጉዳዬች ስለነበረኝ እዚህም እዛም እሷን አንጠልጥዬ ስራራጥ ሰባት ሰዓት ሆነ…. ቁርስ ሰዓት ላይ ያቆምነውን ወሬ ሆቴል ገብተን ምግብ አዘን ምሳችንን እየበላን ቀጠልነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ወሬውን ድንገት የጀመረችው እሷ ነች….
‹‹አሜሪካዊቷ እስከመጨረሻው ቀይ አሻረችህ አይደል?››
‹‹ማ…?ለእኔ….?አልገባኝም››
‹‹ባክህ ማታ በስልክ ስታወሩ ሰምቼያለሁ››
‹‹አንቺ የሰው ሚስጥር ጆሮን ግድግዳ ላይ ለጥፎ ማዳመጥ ነውር አይደል እንዴ?››
‹‹እናንተ የመሀል ሀገር ሰዎች ደግሞ ኮተታ ኮተቱንም ሚስጥር ታደርጉታላችሁ..ግን የእውነት ሁለታችሁም አንጀቴን ነው የበላችሁት››
‹‹እንዴት?››
‹‹በቃ ፎንቃ ክፍኛ ነው የጠለፋችሁ….ታድላችሁ?››
‹‹እንዴ በዚህ ፍቅር ምክንያት ምን ያህል መከራ እንደተቀበልን ብታውቂ እንደዚህ አፍሽን ሞልተሸ ታድላችሁ አትይም ነበር….››

‹‹እንደእኔ በምቾትና በእንክብካቤ ዝም ብሎ አይነት ኑሮ ከመኖር በፎንቃ ተጠልፎ ስቅይትይት ማለት አይሻልም…?ምናለ በእሷ ቦታ እኔ በሆንኩ››
‹‹ጭረሽ….አንቺ ልጄ ቀልደኛ ነሽ ..››
‹‹እውነቴን እኮ ነው..››
ስልኬ ጠራ…የምጎርሰውን ጋብ አደረኩና አነሳሁት…. ጄኔራሏ ነች
‹‹እሺ ዜና..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ..››
‹‹ዝግጅትስ?››
‹‹ያው ሁሉን ነገር አጠናቅቄ አንተን መምጣት እየጠበቅኩ ነው››
‹‹የት ነሽ?››
‹‹እቤት ነኝ…››
‹‹ያው እንግዳ አለብኝ…እና ማታ ስመጣ ከእንግዳ ጋር ብመጠ ቅር ይልሻል?፡፡
‹‹አረ ፍፅም….ስራ ከሌላችሁ ለምን አሁን አትመጡም..››
‹‹አሁን?››
‹‹ምነው ስራ አለብህ እንዴ?››
‹‹አይ የለብኝም….ግን እንግዳ ያልኩሽ..››
‹‹አውቃለሁ ስለአያትህ የልጅ ልጅ ነው አይደለ የምታወራኝ…በቃ እጠብቃችኋለው… ይዘሀት ና..የእኔም እንግዳ እኮ ነች..ደግሞም ቆንጆ ነች አሉ…እንዴት ነው እውነት ነው እንዴ?›
‹‹አረ ተይኝ..ለማንኛውም እንመጣለን ቸው››ስልኩ ተዘጋ
ጭው አለብኝ..በዙሪያዬ ምን እየተካሄደ ነው…?እኔ መምጣቷን ሳላውቅ ማታ እቤት ስገባ ስላየኋት ጥቁር እንግደ ጄኔራሏ ቀድማ ታውቃለች…፡፡እንዴት..?እኔ ከነጋ ጀምሮ አሁን እንዴት ነው የማደርገው? እንግዳዋን እንዴት እሷ ጋር ይዤት ሄዳለሁ…?ጥያትስ አንዴት ሄዳው…?ምን ብዬስ መጥቼ እቤትሽ አድሬ እሸኝሻለሁ ካልኩ በኃላ እቀራለሁ …››እያልኩ ስብሰለሰል ቆይቼ ይሄው እሷ ሁለታችንንም በእንግድነት እሷ ቤት ሄደን እንደምናድርና አብረን እንደምንሸኛት ትናንትናውኑ ታውቅ ነበር
‹‹ምነው ፊትህን አጨማደድከው?››
‹‹አይ ነገሮች ግራ አጋብተውኝ ነው…ቅድም የነገርኩሽ ጎደኛዬ ጋር አብረን አንሄዳለን…››
‹‹ጄኔራሏ ጋ››
‹‹አዎ ጄኔራሏ ጋ››
‹‹ታፈቅራታለህ አይደል.?››
‹‹ማለት…?››
‹‹አትደንግጥ..ታድለሀል..ፍቅር በፍቅር የሆንክ ሰው ነህ…እኔንስ አንድ ቀን ምታፈቅረኝ ይመስልሀል?››
‹‹ምን አልሽ?››
‹‹አረ አትደንግጥ…ለፈገግታ ነው…ምነው ይሄን ያህል ፍቅር አንገሽግሾሀል እንዴ..?››
ወይ ጉድ ይህቺ ልጅ በቅርቡ እጄ ላይ ምትፈነዳ አደገኛ ፈንጅ ነች‹…አቶ እዬብ ፈተናህ ገና አላለቀም….ወይ አያቴ ከችግሮችህ ሁሉ ቀስ በቀስ ተላቀቅ ብለው መክረውኝ እንድወጣም አግዘውኝ ከብዙ ጥረት በኃላ አብዛኛው ተሳክቶልኝ ነፃ ልወጣ የድል ሪባኑን ልበጥስ መቀሱን እያስተካከለልኩ እያለሁ እራሳቸው ወደተመሳሳይ ችግር የሚጎተት ሌላ ፈተና ያስታቅፉኛል..?ምሳ ጨርሰን ሂሳብ ከፍለን በራይድ ወደ ጄኔራሏ ቤት እየሄድን ሳለ
‹‹እዬቤ በርጫ ገዝተን ብንሄድ ጄኔራሎ ይደብራታል?››ስትል ቀለል አድርጋ ጠየቀቺኝ፡፡
‹‹ትቅሚያለሽ እንዴ?››
‹‹ምነው ?መቃም እንዲህ ያስደነግጣል እንዴ?››
‹‹አይ…ስላልመሰለኝ ነው….ችግር የለውም ስንቃረብ እንገዛለን.››
ወዲያው ስልኬ ጠራ….ወይ ልጄ ደወለች አልኩና አነሳሁት
‹‹የእኔ ማር… የእኔ ጣፋጭ እንዴት ነሽ?››
‹አለሁ አባዬ….እሁድ እንደምንመጣ ታውቀለህ አይደል?››
‹‹አዎ አውቃለሁ…እናትሽ ነግራኛለች.እናም በናፍቆት እየጠበቅኩሽ ነው››
‹‹እሺ እሱን ልንግርህ ነው የደወልኩት…››
‹‹ስለደወልሽ ደስ ብሎኛል››
‹‹የት ነህ አባዬ መኪና ውስጥ ነህ እንዴ..ድምፅ ይሰማኛል››
‹‹አዎ የእኔ ልጅ ….ታክሲ ውስጥ ነኝ….አያቴን ታውቂያቸዋለሽ አይደል?
‹‹አዎ አውቃቸዋለህ… ከእሷቸው ጋር ነህ?››
‹‹አይ ከእሳቸው ጋር ሳይሆን ከልጃቸው ጋር የሆነ ቦታ እየሄድን ነው…ማራናታ ትባላለች ፡፡ስትመጪ ከእሷ ጋር አስተዋውቅሻለሁ››
‹‹እሺ አባዬ ሰላም በልልኝ››
‹‹ቸው እሺ ልጄ›ሥልኩ ተዘጋ
ጊዜ ሳታባክን ጥዝጠዛዋን ቀጠለች‹‹ከልጅህ እያስተዋወቅከኝ ነው እንዴ?››
‹‹አዎ እሁድ ቤተሰቦቼ ሁሉ ይመጣሉ ….ልጄም ትመጣለኝ …አብራን ስታየን ማን ነች ብላ ስትጠይቀኝ በቀላሉ አስረዳታለሁ ማለት ነው፡፡››
‹‹ለእሷ ብቻ ነው..ወይስ ለቤተሰብህ ሁሉ ነው የምታስተዋቀውቀኝ ?››
‹‹አሁን ይህ ምን የሚሉት ጥያቄ ነው፡፡አዎ…የአያቴ የልጅ ልጅ ነሽ….እቤተሰቤ ነሽ ማለት ነው፡ስለዚህ ከሁሉም ጋር አስተዋውሻለሁ››
‹‹እንደዛ ስላልክ ደስ ብሎኛል…..አክስትህ ግን የአያቴ ልጅ ነች ብለህ ብታስተዋውቀኝ ብዙም ደስ አይላትም››
‹‹ለምን…?አክስቴ ምን እንደምትፈልግ በምን ተውቂያለሽ….?አክስቴ እኮ ከአያቴ ጋ ተዋውቀዋል…አያቴ ማለት ለእኔ ምን እንደሆነ እና ምን እዳደረገልኝ በዝርዝር ነግሬታለሁ፤ በዛም የተነሳ በጣም የምታከብረው ሰው ነው……እንደውም አንቺ የእሱ የልጅ ልጅ በመሆንሽ በደስታ ነው የምትተዋወቅሽ››
‹‹አውቃለሁ ግን ፍቅረኛህ ብሆንና ይህቺ ፍቅረኛዬ ነች ብለህ ብታስተዋውቀኝ እንዴት ፍፅማዊ ደስታ እንደምትደሰት ይታየኛል››
‹‹እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ?አክስቴን እኮ በደንብ ምታውቂያት ነው ያስመሰለሺው››
‹‹እኔን ከስጋት ትገላግለኛለች ብላ ተስፋ ታደርግ ነበር .እሷ እኮ አሁንም እነዚህ ልጆች መልሰው ይሳሳቱ ይሆን ብላ እንቅልፍ ተኝታ አታድርም…ታዲያ አንተ እኔን የመሰለች ፍቅረኛ አግኝተህ ወስደህ ብታስተዋውቃት… ታየኝ፡፡እንዲሁ ስለምታሳዝነኝ እንደዛ ብለህ ብታስተዋውቀኝ አይከፋኝም….ምን ችግር አለው? አያታችን ከሄደበት እስኪመለስ የእቃቃ ፍቅረኛ ፍቅረኛ እንጫወትና ከእዛ ተጣልተን ተለያየን ብለን እናውጃለን…እስከዛ ሴትዬህም ወደአሜሪካዋ ተመልሳ ስለምትሄድ ችግር አይኖረውም..
‹‹ውይ ምን አይነት ጉድ ነሽ.?ሳትቅሚ እንደዚህ የለፈለፍሽ ከምርቃና ቡኃላ እንዴት ልትሆኚ ነው?››
‹‹አይዞህ ሀሳብ አይግባህ…ከመረቅንኩ ስሬ ኒዩክልር ብታፈነዳ እንኳን ከአንደበቴ ቃል አይወጣም….››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ጫቱን አሁኑን ልግዛልሽ ‹‹.ሹፌር ምቹ ቦታ ስታገኝ ታቋምልኝ….?እቃ ገዛለሁ››

ተፈፀመ
👍149🤔52👎10👏6😱52😢2