#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ
“እንዲያውም የእህትህን ቆንጆ ፀጉር የምትሸልተው አንተ
መሆን አለብህ!” ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ ብልጭ አደረገችና በመልበሻው አናት ላይ መቀሱን አስቀመጠች: “ተመልሼ ስመጣ እህትህ ፀጉሯ ተቆርጦ ካገኘሁ
ብቻ አራታችሁም ምግብ የማግኘት እድል ይኖራችኋል።" ስትል ክሪስ እኔ ላይ፣ እኔም ክሪስ ላይ እንዳፈጠጥን ጥላን ሄደች:...
ክሪስ ፈገግ አለ: “አይዞሽ ካቲ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም።እናታችን በየትኛውም ሰአት ተመልሳ ስለምትመጣ እንነግራታለን፡ አይዞሽ አትፍሪ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም::” ሊያቅፈኝ ወደኔ መጣ፡ “በዛ
ላይ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል አንድ ካርቶን ብስኩትና አይብ መደበቃችን መታደል አይደል? ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ይህንን ስለማታውቅ ለዛሬ ምግብ
ይኖረናል:” አለ።
ድንገት እናታችን ካልመጣች ብለን በመስጋት ያን ዕለት ትንሽ ብቻ በላን።ግማሹን ወተትና ጥቂት ብርቱካኖች አስቀመጥን፡ ይሁንና እናታችን ሳትመጣ ቀኑ አለቀ: ምሽቱን ሙሉ አንዴ ስተኛ፣ አንዴ ስነቃ እንዲችው ስገላበጥ
ሌሊቱ ተጋመሰ፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገኝ አሰቃቂ ቅዠት ይመጣብኛል።ኮሪና ኬሪ ጠፍተውብን ክሪስና እኔ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ በጨለማ ስንፈልጋቸው አየሁ ስማቸውን እየጠራን ብንፈልጋቸውም እነሱ
ግን መልስ አይሰጡንም፡ በፍርሀት ውስጥ ሆነን በጨለማ እየሮጥን ነበር።
በጣም የሚያስጨንቅ ህልም ነበር። ስነቃ ክሪስም መንትዮቹም ተኝተዋል።እንደገና እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ፈለግኩ፡ ልከላከለው ሞከርኩ፡ ቀስ እያልኩ
እየሰመጥኩ እየሰመጥኩ እንደገና ጥልቅ ቅዠት የተቀላቀለበት አስፈሪ ህልም ውስጥ ገባሁ፡ በጨለማ እየሮጥኩ በደም የተሞላ ኩሬ ውስጥ ወደቅኩ ደሙ ልክ እንደሬንጅ ያጣብቃል ሽታውም እንደ ሬንጅ ነው: በአልማዝ ያሸበረቀ፣ጭንቅላቱ የወርቅና አይኖቹ ቀይ የሆኑ አሳ እየሳቀ ደም በደም አደረገኝ፡
ከዚያ ደጋግሞ የሚያስተጋባ ድምፅ “እይ! እይ! ማምለጥ አትችይም!” እያለ ጮኸ፡
ማለዳው ቢጫውን የተስፋ ብርሃን ከዘጋው ከባድ መጋረጃ ጀርባ የገረጣ መስሎ ይታያል፡ ኬሪ በእንቅልፍ ልቧ ወደኔ እየተጠጋች “እማዬ፣ ይህንን ቤት አልወደውም” ስትል አጉረመረመች: ኬሪ ያለ እረፍት ስትገላበጥ ላቅፋት ፈልጌ ክንዴን ለመዘርጋት ብሞክርም ማንቀሳቀስ አልቻልኩም:: ምን ሆኛለሁ? ራሴ ልክ ድንጋይ እንደተጫነ አይነት ከበደኝ፡ ከህመሙ የተነሳ ጭንቅላቴ
ሊከፈል መሰለኝ፡ የእግሮቼና የእጆቼ ጣቶች ላይ ይወረኛል። ሰውነቴ ድርቅ ብሏል ግድግዳዎቹ ሁሉ የተጣመሙ ይመስሉኛል። ሁሉም ነገር ቀጥ ያለ መስመር የለውም።
ከአልጋው ባሻገር ባለው በሚያብረቀርቀው መስተዋት ራሴን ለማየት ሞከርኩ::
ሆኖም የከበደኝን ጭንቅላቴን ዞር ላደርገው ብሞክርም አልንቀሳቀስ አለኝ::ሁልጊዜ ከመተኛቴ በፊት ጭንቅላቴን እንደልብ ማዘዋወር እንድችል ፀጉሬን ትራሱ ላይ እበትነዋለሁ ግማሹ ጉንጬ ላይ ያርፋል: እና ደስ የሚል ሽታውና ልስላሴው በጣም ደስ ይለኛል። የፀጉሬ ጉንጬ ላይ መነስነስ ወደ
ጣፋጭ የፍቅር ህልም ይወስደኛል።
ዛሬ ግን ትራሱ ላይ ፀጉር የለም: ፀጉሬ የት ሄዶ ነው?
መቀሱ አሁንም መልበሻው አናት ላይ እንደተቀመጠ ነው: በድንግዝግዝ ይታየኛል፡ ጉሮሮዬን ለማርጠብ ምራቄን ደጋግሜ ዋጥኩና በግድ ትንሽ ድምፅ
አውጥቼ የክሪስን ስም ተጣራሁ። ወንድሜ ክሪስ እንዲሰማኝ እንዲያደርግ ወደ እግዚአብሔር ፀለይኩ። በመጨረሻ እንግዳ በሆነ ድምፅ “ክሪስ፣ የሆነ
ነገር ሆኛለሁ፡” ብዬ በሹክሹክታ መናገር ቻልኩ። ደካማዎቹ ቃላቶቼ እንዴት እንደተሰሙ ባላውቅም ክሪስን አነቁት ከእንቅልፉ በደንብ ሳይነቃ አይኖቹን እያሻሽ ካቲ ምን ፈልገሽ ነው?” አለኝ።
ከአልጋው ላይ አስፈንጥሮ ያስነሳው የሆነ ነገር አልጎመጎምኩ፡ አልጋዬ
አጠገብ ደረሰ፡ ትንፋሹን ውጦ በድንጋጤና በፍርሀት ድምፅ አወጣ፡
“ካቲ… ወይኔ አምላኬ ሆይ!”
ጩኸቱ በፍርሀት አሳቀቀኝ
'ካቲ ‥. ወይኔ ካቲ" ሲል አቃሰተ።
አይኖቹ እንዲህ በድንጋጤ እንዲፈጡ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ አልታዘዝ ያሉኝን ክንዶቼንና ያበጠ የመሰለኝን ከባድ ጭንቅላቴን ለማንቀሳቀስ
ሞከርኩ፡ እንደምንም እጄን ማንሳት ቻልኩ ከዚያ ለመሰማት የሚችል ጮክ ያለ ድምጽ አገኘሁና የእውነት ጮህኩ። ደግሜ ደጋግሜ ጮህኩ ክሪስ
በክንዶቹ አቅፎ እስኪያባብለኝ ድረስ ልክ አእምሮው እንደተነካ ሰው እየጮህኩ ነበር።
“እባክሽ አቁሚ… እባክሽ” ተንሰቀሰቀ። “ስለ መንትዮቹ ስትይ... የባሰ አታስፈራሪያቸው.
እባክሽ ካቲ አትጩሂ፡ ያሳለፉት
ይበቃቸዋል።እስከመጨረሻው ፈሪ እንዲሆኑ እንደማትፈልጊ አውቃለሁ: ካልተረጋጋሽ
ይደነግጣሉ። እመኚኝ በህይወቴ እምልልሻለሁ። ዛሬ እንደምንም ሬንጁን ከፀጉርሽ ላይ አስለቅቅልሻለሁ "
አያትየው ከእንቅልፌ እንዳልነቃ የሆነ መድኃኒት የወጋችኝን ምልክት ክንዴ ላይ አገኘሁ እና እንደተኛሁ ትኩስ ሬንጅ ፀጉሬ ላይ አፍስሳብኛለች: አንድም
ዘለላ እንዳይቀር ሬንጁን ከመጠቀሟ በፊት ፀጉሬን በደንብ ሳትሰበስበው አልቀረችም።
ክሪስ መስተዋት እንዳላይ ቢከለክለኝም ገፍትሬው መስታወቱ ላይ ተሰየምኩ።
ጭንቅላቴ አስፈሪ ጥቁር ጓል የተቀመጠበት መስሎ ሳይ አፌ በድንጋጤ ተከፈተ በመጀመሪያ የነቃው ኮሪ ነበር የተዘጋውን መጋረጃ ገለጥ አድርጎ ከእሱ
የተሸሸገችውን ፀሀይ ለማየት ከአልጋው ወጥቶ ወደ መስኮቱ እየሮጠ ሳለ ድንገት ሲያየኝ አይኖቹ ፈጠጡ፡ ከዚያ ትንንሽ እጆቹ አይኖቹን ለማሻሽት
ከፍ አሉና ባለማመን እንደገና አተኩሮ ተመልክቶኝ፡-
"ካቲ አንቺ ነሽ?” አለ፡
“አዎ”
“ፀጉርሽ ለምን ጥቁር ሆነ?"
ለዚያ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት ኬሪ ነቃች። “ወይኔ!” ስትል ጮኸች። ካቲ ጭንቅላትሽ ምን ሆኖ ነው?! ትልልቅ እምባዎች ከአይኖቿ ወደ ጉንጮቿ ወረዱ፡ “አሁን ጭንቅላትሽን አልወደድኩትም” ስትል ሬንጁ እሷ
ፀጉር ላይ እንደሆነ ሁሉ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።
“ተረጋጊ ኬሪ” አለ ክሪስ በተረጋጋ ድምጽ። ካቲ ፀጉር ላይ ያለው ሬንጅ ነው: አሁን ስትታጠብና ሻምፑ ስታደርግበት ልክ እንደ ትናንቱ ይሆናል፡ እሷ ስትታጠብ እናንተ ሁለታችሁ ደግሞ ቁርስ እስኪቀርብ ብርቱካን እየበላችሁ
ቲቪ ተመልከቱ፡ በኋላ የካቲ ፀጉር ንፁህ ሲሆን ሁላችንም ቁርሳችንን
እንበላለን፡" አለ፡ ስለ ሁኔታችን የባሰ ፍርሀት እንዳይሰማቸው በማለት የአያታችንን ስም አልጠቀሰም ስለዚህ ወለሉ ላይ ተጠጋግተው በመቀመጥ
እርስ በርስ እየተረዳዱ ብርቱካኑን እየላጡ እየበሉ ራሳቸውን በቴሌቭዥን በሚተላለፈው የቅዳሜ ጠዋት የካርቱን ፊልም ውስጥ ከተቱ..
ክሪስ ገንዳው ውስጥ የሞቀ ውሀ ሞላልኝ: በዚያ በሚፋጅ ውሀ ውስጥ ፀጉሬን ደግሜ ደጋግሜ ነከርኩት። ክሪስ ደግሞ ሬንጁ እንዲላላ ለማድረግ ሻምፑ እያደረገ ነበር። ሬንጁ ቢላላም ከፀጉሬ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም:
ጣቶቹ በሚያጣብቀው የሬንጅ ክምር ውስጥ ገቡ። ፀጉሮቼን ሳይነቅል ሬንጁን
ለማውጣት እየሞከረ ነው: ግብግቡ ስላደከመኝ ማሰብ የቻልኩት ስለ መቀሱ ብቻ ነው: አያትየው መልበሻው አናት ላይ ስላስቀመጠችው የሚያንፀባርቅ
መቀስ።
ክሪስ ገንዳው አጠገብ ተንበርክኮ የሬንጁን ክምር ከፀጉሬ ውስጥ ሲያወጣ ሬንጁ በፀጉሮቼ የተሸፈነ ነበር፡ ሬንጁን ከፀጉሬ ውስጥ ለማውጣት ስንሞክር
ከሁለት ሰዓት በላይ ሆኖን ነበር። “መቀሱን መጠቀም አለብህ!” ብዬ ጮህኩ።
“አይሆንም መቀስ የመጨረሻ ምርጫችን ነው” አለ እናታችን ያመጣችለትን የኬሚስትሪ ዕቃዎች በመጠቀም ፀጉሬ ሳይጎዳ ሬንጁን የሚያሟሟ ኬሚካል መቀመም እንደሚችል አስቧል።

👍30❤3👏3
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ
...ልታገኝ ስለምትፈልገው ነገር ስትል ድራማ የምትሰራ አድርጌ የማስባት ለምንድነው? እኔን ችላ ብላ ክሪስን ተመለከተች።
ለሚቀጥለው ልደትህ ኢንሳይክሎፒድያ አዝዤልሀለው። ማተምያው ድረስ ራሴ ሄጄ ነው ያዘዝኩት ስምህንና ቀኑን ሰጥቺያቸዋለሁ ግን ወደዚህ በቀጥታ መላክ አይችሉም:: የሆነ ሰው ሊቀበላቸው ይገባል ልክ ሁልጊዜ ራስህን ለማስተማር ምርጡን ልሰጥህ እንደምፈልግ ሁሉ የሚያስደስትህን ስጦታ ሳስብ ሳስብ ቆይቼ ነው ያዘዝኩልህ”
ክሪስ የሚናገረውን አጣ ፊቱ ላይ የሚታየው ድብልቅልቅ ስሜት ነበር፤አይኖቹ ግራ የተጋቡና የፈዘዙ መሰሉ። አምላኬ! ካደረገችው ነገር በኋላ እንኳን ይወዳታል ማለት ነው::
ስሜቶቹ ቀጥታ ናቸው:: በቁጣ ነደድኩ እንደዚህ አይነት መፅሀፍት ከአንድ
ሺ ዶላር በላይ ይፈጃል: ምናልባትም ሁለት ወይም ሶስት ሺም ሊፈጅ ይችላል። ይህንን ገንዘብ ለምን የማምለጫ ገንዘባችን ውስጥ አትጨምረውም?
ልክ ኬሪ ስትቃወም እንደምታደርገው ልጮህ ስል ክሪስ አይኖች ላይ ያየሁት ነገር አፌን እንድዘጋ አደረገኝ፡ ሁልጊዜ እነዚያ መፃህፍት እንዲኖሩት ይፈልግ ነበር፡ በዚያ ላይ አንድ ጊዜ ታዟል: አሁን ለሷ ገንዘብ ምኗም አይደለም፧
ምናልባት እንዲያው ምናልባት አያታችን ዛሬ ወይም ነገ ሊሞት ስለሚችል አፓርታማ መከራየትም ሆነ ቤት መግዛት አያስፈልጋት ይሆናል፡
ጥርጣሬዬ ተሰምቷታል።
እናታችን ጭንቅላቷን ቀና አደረገችና ወደ በሩ ተራመደች። ስጦታዎቻችንን
ገና አልከፈትንም፤ ስንከፍት የሚኖረንን ስሜት ለመመልከትም አልቆየችም።
እየጠላኋት ለምንድነው በውስጤ የማለቅሰው? አሁን አልወዳትም አልወዳትም።
በሩጋ ደርሳ እየከፈተች “ዛሬ ስለፈጠራችሁብኝ ህመም ስታስቡና እንደገና
በፍቅርና በአክብሮት ልታስተናግዱኝ ስትችሉ ተመልሼ እመጣለሁ ከዚያ
በፊት ግን አይሆንም::” አለች።
መጣች።
ሄደች።
መጥታ ስትመለስ
ኬሪና ኮሪን አልነካቻቸውም አልሳመቻቸውም አላናገረቻቸውም ለምን እንደሆነ አውቄያለሁ፤ ሀብት ማግኘት መንትዮቹን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው ማየት መቋቋም ባለመቻሏ ነበር።
ከጠረጴዛው አጠገብ ተነስተው እየሮጡ ወደ እኔ መጡና ቀሚሴን እየጎተቱ
ፊቴ ላይ አፈጠጡ ትንንሽ ፊቶቻቸው ጭንቀትና ፍርሀት አጥልቶባቸዋል።
እነሱም ደስታ እንዲሰማቸው መደሰቴን ለማየት ፊቴን እያጠኑ ነው:
ተንበርክኬ እሷ የጎዳቻቸውን በመሳምና በማቀፍ አጥለቀለቅኳቸው።
መልካችን ያስጠላል?" ጠየቀች ኬሪ በመጨነቅ፤ ትንንሽ እጆቿ እጄን
ይዘውኛል
“አይ በጭራሽ! አንቺና ኮሪ ቤት ውስጥ ብዙ በመቆየታችሁ ትንሽ የገረጣችሁ ትመስላላችሁ”
“በደንብ አድገናል?”
“አዎ፣ አዎ አድጋችኋል” እየዋሸሁ እንኳን ፈገግ ብያለሁ: በዚያ የማስመሰል
ደስታና የውሸት ፈገግታ ወለሉ ላይ ከክሪስና ከመንትዮቹ ጋር ተቀምጠን
አራታችንም ልክ እንደ ገና ቀን ስጦታዎቻችንን መክፈት ጀመርን። ሁሉም
በውድ የስጦታ ወረቀቶች በሚያምር ሁኔታ የታሸጉ ናቸው።
ወረቀቱን ቀደድን ሪቫኑን ጥለን የታሸጉበትን ካርቶኖች ገነጣጥለን ውስጡ ያለውን አወጣን... በውስጡ ለእያንዳንዳችን የሚያማምሩ ልብሶች ነበሩ:
አዳዲስ መፃህፍት፣ መጫወቻዎች፣ አንድ አይነት ቅጠል የሚስል ቅርፅ ያላቸው በትልቅ ካርቶን ውስጥ የታሸጉ የስኳር ከረሜላዎች።
እንደምታስብልን ማሳያው ይኸው! ሁላችንንም በደንብ ታውቀናለች።ከመጠኖቹ በስተቀር ፍላጎታችንን፣ ማድረግ የምንፈልገውን ሁሉ ታውቃለች።
በፈቃደኝነት ሞተን ስንቀበር ማየት ደስ በሚላት ጠንቋይ አያታችን ጥበቃ ስር የተተውንባቸውን እነዚያን ባዶና ረጃጅም ወራት በስጦታዎቹ ከፈለችን።
በዚያ ላይ እናቷ ምን አይነት እናት እንደሆነች እያወቀች... የምትሰራው ሁሉ በልቧ ትክክል እንዳልሆነ እያወቀች በመጫወቻዎቹና በአሻንጉሊቶቹ
ልትደልለንና ይቅርታ ልትጠይቀን ፈለገች
በጣፋጭ የስኳር ከረሜላ መራራውን ብቸኝነታችንን ከአፋችን፣ ከልባችንና
ከአእምሯችን ልትወስድ ተስፋ አደረገች ምንም እንኳን ክሪስ መላጨት
የሚያስፈልገው እኔም ጡት መያዣ መልበስ የሚገባን እድሜ ላይ የደረስን
ቢሆንም በእሷ አስተሳሰብ አሁንም ልጆች ነን ልክ በምታመጣው መፃህፍት
ርዕስ ትንሽ አድርጋ ለዘለዓለም ልታስቀምጠን ትፈልጋለች፡
ኬሪን አዲስ ቀይ ቀሚስ ሳለብሳትና ሀምራዊ ሪቫን ሳደርግላት ፈገግ እንዳልኩ
ነበር አሁን ሁልጊዜ እንደምትፈልገው አይነት ለብሳለች የምትወዳቸውን
ቀለማት እግሮቿ ላይ ሀምራዊ ካልሲ ከነጭ አዲስ ስኒhር ጋር አለበስኳት “በጣም ታምሪያለሽ ኬሪ” እሷም ብሩህ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሷ ተደስታለች።
ቀጥሎ ኮሪን ቀይ አጭር ሱሪና ኪሱ ቀይ የሆነ ነጭ ካኒቴራ አለበስኩት፡
ከዚያ “አንተንም ላልብስህ ክሪስቶፈር?” ስል ቀለድኩ
“ልብሽ ከፈቀደ ቆዳዬን ገልብጠሸ ማልበስ ትችያለሽ”
“ጋጠ ወጥ አትሁን!”
ኮሪ ሌላ የሙዚቃ መሳሪያ መጣለት፡ እሱ የሙዚቃ መሳሪያውን እየነካካ ኬሪ
ትዘፍንለታለች።
ሁሉም ነገር ላይ ያለኝን ደስታ የሚወስዱብኝ እግዚአብሔር የሰጠኝ ክፉ
ሀላቦች ነበሩኝ: ማንም የማያያቸው ከሆነ ቆንጆ ልብሶች ምን ይጠቅማሉ?
እኔ የምፈልገው በሚያምሩ ወረቀቶች ያልተጠቀለሉ፣ በሪቫን ያልታሰሩ፣ ሱቆች ውስጥ በካርቶን ያልተቀመጡ ነገሮችን ነው፧ የምፈልገው ገንዘብ
ሊገዛቸው የማይችላቸውን ነገሮች ነው: ጸጉሬ ከፊቴ በአጭሩ መቆረጡን
አስተውላለች? እንዴት እንደሳሳ አይታለች?የገረጣና የሳሳው ቆዳችንን እያየች
ጤነኛ እንደሆንን ታስባለች?
ለእኔ የተባሉትን ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች ተመለከትኩ፡ ሰማያዊ ቬልቬት ቀሚስ፣ ለግብዣ የሚለበስ ሮዝና ሰማያዊ የምሽት ጋዋን አብሮት ከሚሄድ ጫማ ጋር፧ እዚያ ተቀምጬ ከረሜላውን እየበላሁ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
“ኢንሳክሎፒዲያ!” ለዘለዓለም እዚህ ልንኖር ይሆን?
የስኳር ከረሜላ በጣም ከምወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህንን የከረሜላ
ካርቶን ያመጣችው ለኔ ነበር ለኔ፡ እኔ ግን መብላት የቻልኩት አንድ ብቻ
ነበር። ያንንም በጣም በችግር።
የከረሜላው ካርቶን መሀል ላይ ተቀምጦ ክሪስ ኮሪና ኬሪ ከበውት ተቀምጠው
በጣም በመደሰት ከረሜላዎቹን እያጣጣሙ ነበር፡ “ከረሜላዎቹን ሁሉ
መጨረስ አለባችሁ ለረጅም በጣም ለረጅም ጊዜ የማታዩት የመጨረሻ
ከረሜላችሁ ነው፡” አልኳቸው በመረረ ጥላቻ
ክሪስ አየት አደረገኝ ሰማያዊ አይኖቹ ደስተኛና የሚያበሩ ሆነዋል።
እምነቶቹና መተማመኑ ሁሉ እናታችን ለአጭር ጊዜ ባደረገችው ጉብኝት
እንደተመለሱለት ለማየት ቀላል ነበር፡ ስጦታዎቹ እሷ ከዚህ በኋላ ለእኛ ግድ የሌላት የመሆኑን ሀቅ የመደበቂያ መንገድ እንደሆነ ለምን ማየት አልቻለም? ከዚህ በፊት እንደነበርነው አሁን ለእሷ እውነት እንዳልሆንን እኔ
እንዳወቅኩት እንዴት አያውቅም? እኛ ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንዳሉት አይጦች፣ ሰዎች ሊነጋገሩባቸው ከማይፈልጓቸው ደስ የማይሉ ርዕሶች ውስጥ ነን፡
“እዚያ ቁጭ ብለሽ የማይናገር ምሰይ” አለ፡ ክሪስ ደስታውን እኔ ላይ እያንፀባረቀ: “እኛ ሶስታችን አይጦቹ መጥተው ከመብላታቸው በፊት አምሮታችንን ስንወጣ አንቺ ከረሜላውን እምቢ በይ: አንቺ ቁጭ ብለሽ ስታለቅሺ፣ ለራስሽ
ስታዝኚና ራስን መስዋዕት በማድረግ ሁኔታችንን መለወጥ እንደምትችይ ስታስመስይ ኮሪ፣ ኬሪና እኔ በልተን ጨርሰን ጥርሶቻችንን እናፀዳለን፡ ቀጥይ
ካቲ አልቅሺ! ሰማዕት ሁኚ! ተሰቃይ! ጭንቅላትሽን ከግድግዳ አላትሚ! ጩኺ እኛ እንደሆነ ወንድ አያታችን እስኪሞት እዚህ መሆናችን የማይቀር ነው::በዚያ ላይ ከረሜላዎቹ ሁሉ ያልቃሉ! ያልቃሉ! ያልቃሉ”

👍42❤3
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አራት
፡
፡
#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ
በፍሎሪዳ ወርቃማ የፀሀይ ብርሃን ውስጥ ደስተኛ ህይወት እንደሚኖረን ያቀድነውን እቅድ በቀስታ እየነገርኳት ነበር።
ክሪስ ልብሶቹን በደንብ ለብሶ በሚወዛወዘው ወንበር ላይ የኮሪን ጊታር እየነካካ ተቀምጧል። በቀስታ እያንጎራጎረ ነበር፡ ድምፁ መጥፎ አይደለም: ምናልባት ኬሪ ተሽሏት እንደገና እንደበፊቱ ከሆነች ሶስታችን አብረን ሙዚቀኞች እንሆን ይሆናል።
እጄ ላይ ያሰርኩት ስዊዘርላንድ ውስጥ የተሰራ ባለ ሀያ አራት ካራት የወርቅ
ሰዓት አለ። መቼም እናታችንን ብዙ ገንዘብ ሳያስወጣት አልቀረም፤ ክሪስም ሠዓት አለው ጊታር አለን፣ የክሪስ ካሜራና የውሀ ቀለሞችም አሉ… ስለዚህ እነሱን መሸጥ እንችላለን በዚያ ላይ አባታችን ለእናታችን ሰጥቷት የነበሩት
ቀለበቶችም አሉ።
ነገ ማለዳ የማምለጫ ቀናችን ሆኖ ተይዟል ግን የሆነ አስፈላጊ ነገር የረሳሁ
እንደሆነ አድርጌ የማስበው ለምንድነው?
ከዚያ ድንገት የሆነ ነገር አስተዋልኩ! እኔም ክሪስም ችላ ያልነው ነገር አያትየው የተዘጋውን በር ከፍታ እኛ ሳናያት በፀጥታ መቆም ከቻለች ሌላም ጊዜ እንደዚህ ታደርግ ይሆን? የምታደርግ ከነበረ አሁን እቅዳችንን አውቃ ሊሆን ይችላል። የእኛን ማምለጥ ለማስቆም የራሷን አቅድ አዘጋጅታ ሊሆን
ይችላል!
ይህንን መናገር ይገባኝ እንደሆን እያሰብኩ ወደ ክሪስ ተመለከትኩ አሁን
በማመንታት እንድንቆይ ምክንያት አልፈልግም: ስለዚህ ጥርጣሬዬን
ነገርኩት። ምንም ሳይረበሽ ጊታሩን መነካካቱን ቀጠለ “እሷን ባየሁበት ደቂቃ
ያ ሀሳብ አእምሮዬ ውስጥ ብልጭ ብሎ ነበር።” አለኝ: “ያንን ጆን የተባለ
ሠራተኛ ልትተማመንበት እንደምትችል አውቃለሁ። እንዳናመልጥ በማሰብ
ደረጃው ላይ እንዲጠብቀን ልታደርግ ትችል ይሆናል። ተይው ይሞክር! ምንም ነገር ሆነ ማንም ነገ ጠዋት ከመሄድ አያቆመንም!”
የአያትየውና የሰራተኛው ደረጃው ስር የመጠበቅ ሀሳብ ሰላም ሊሰጠኝ
አልቻለም። ኬሪ አልጋው ላይ እንደተኛች ክሪስም የሚወዛወዘው ወንበር ላይ
ተቀምጦ ጊታሩን እየነካካ ትቻቸው ለመሰናበት ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ወጣሁ።
በሚወዛወዘው አምፑል ስር ቆሜ ዙሪያውን ተመለከትኩ፡ ሀሳቤ ወደዚህ ወደመጣንበት የመጀመሪያ ቀን ተጓዘ... እኛን... አራታችንን. እጅ ለእጅ
እንደተያያዝን ግዙፉን የጣሪያ ስር ክፍልና ውስጡ ያሉትን ጣዕረሞት
የሚመሳስሉ እቃዎቹን በመገረም ዙሪያውን ስንመለከት፣ ክሪስ ለመንትዮቹ ዥዋዥዌ ለመስራት ራሱን አደጋ ላይ ሊጥል የነበረበትን ሁኔታ በሀሳቤ ተመለከትኩ ከዚያ ወደ መማሪያው ክፍል ገብቼ መንትዮቹን አስቀምጠን
የነበረውን በሀሳቤ እየተመለከትኩ ሳለ ክሪስ በደረጃው በኩል ተጣራ ካቲ
መሄጃችን ደርሷል።"
ማንበብና መፃፍ ያስተማርንባቸውን መቀመጫዎች አየሁ። ብቻዬን ስደንስ
ፈጠን ብዬ ወደ መማሪያ ክፍሉ ተመለስኩና በጥቁር ሰሌዳው ላይ በጠመኔ
በትልልቁ እንዲህ ብዬ ጻፍኩ…
ጣራው ስራ ባለው ክፍል እንኖር ነበር።
እኔ፣ ክሪስቶፈር፣ ኮሪና ኬሪ።
አሁን ሶስት ብቻ ነን።
ከዚያ ስሜንና ቀኑን ፃፍኩ። በልቤ የአራታችን መንፈስ ከዚህ ጣራው ስር
ያለው መማሪያ ክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው የነበሩ የሌሎች ልጆችን መንፈስ እንደሚበልጥ አውቃለሁ የሆነ ሰው ወደፊት እንዲፈታው አንድ እንቆቅልሽ ትቻለሁ።
የሞተውን አይጥ ከሁለቱ የተመረዙ ዶናቶች ጋር ኪስ ወረቀት ውስጥ ከትተን ክሪስ በኪሱ እንዲይዘው ተደረገ፡ ከእንጨት በተሰራው ቁልፍ የእስር
ቤታችንን በር ለመጨረሻ ጊዜ ከፈተ። አያትየውና ሠራተኛው ታች እየጠበቁን
ከሆነ እስከሞት እንታገላለን ክሪስ ልብሶቻችንና ዕቃዎቻችን የተሞሉባቸውን
ሁለት ሻንጣዎች ያዘ ትከሻው ላይ ደግሞ የኮሪን ጊታር አንጠለጠለ፡ ጨለም
ባለው አዳራሽ ውስጥ እየመራ በጀርባ ወዳለው ደረጃ ወሰደን። ኬሪ በከፊል
እንደተኛች አቅፌያታለሁ ትንሽ ከበድ ትላለች። ነገር ግን ከሶስት አመታት
በፊት በእነዚህ ደረጃዎች ላይ ተሸክሜያት ስወጣ ከነበራት ክብደት ምንም
ያህል አልጨመረችም። ወንድሜ የያዛቸው ሁለቱ ሻንጣዎች ልጆች ሳለን
በጣም አፍቃሪና ሰውን የምናምን በነበረበት ወቅት፣ ከረጅም ጊዜ በፊት በዚያ
ቀፋፊ ምሽት እናታችን ያሸከመችን ሻንጣዎች ነበሩ።
በልብሶቻችን ስር በሁለት ትንንሽ ቦርሳዎች ከእናታችን የሰረቅናቸውን ገንዘቦች
እኩል ለእኩል ተከፋፍለን ይዘናል የተካፈልናቸው ምናልባት የሆነ ነገር
ተፈጥሮ እኔና ክሪስ ብንለያይ አንዳችን ባዶ እጃችንን እንዳንቀር ለማድረግ ነበር። ኬሪ ደግሞ በእርግጠኝነት ከአንዳችን ጋር ትሆናለች በሁለቱ ሻንጣዎች
ውስጥም እንደዚሁ ሳንቲሞቹን እኩል ቦታ ከፍለን በሁለት ቦርሳዎች ውስጥ አድርገናል
እኔና ክሪስ ሁለታችንም ውጪ ምን እንደሚጠብቀን አውቀናል። ረጅም ጊዜ ቴሌቭዥን ማየታችን የዋህና ምንም ለማያውቁ ሰዎች የአለም ጨካኝ
ውሸቶች እንደሚጠብቋቸው አስተምሮናል። ልጆች፣ ተጠቂዎች፣ ደካሞችና
በከፊል የታመምን ነን ነገር ግን ከአሁን በኋላ የዋህ ወይም ምንም የማናውቅ
አይደለንም።
ክሪስ የጀርባውን በር እስኪከፍት ስጠብቅ የሆነ ሰው ሊያስቆመን እየመሰለኝ በእያንዳንዷ ሰኮንድ በፍርሀት ልቤ ቀጥ ብላ ነበር። ወደ እኔ ዞር ብሎ ፈገግ እያለ ወደ ውጪ ወጣ:
ውጪው ይበርዳል። መሬቱ ላይ እየቀለጠ ያለ በረዶ ይታያል: ግራጫው
ሰማይ በረዶ እንደገና ሊጥል እንደሆነ ይጠቁማል ቢሆንም ግን ጣራው ስር
ካለው ክፍል በላይ አይቀዘቅዝም፡ መሬቱ ከእግራችን ስር ያሙለጨልጫል።
ለብዙ አመታት ጠንካራና የተስተካከለ የእንጨት ወለል ብቻ ረግጠን
የምናውቅ በመሆኑ፣ መሬት ላይ መራመድ እንግዳ ስሜት አሳድሮብናል።
ደህንነት አልተሰማኝም: ምክንያቱም ጆን ሊከተለንና ሊመልሰን ይችላል
ወይም ይሞክራል ብዬ ፈርቻለሁ።
ንፁሁንና ጠንካራውን የተራራ አየር ለመሳብ ጭንቅላቴን ቀና አደረግኩ።
ትንሽ እስክንሄድ ድረስ ኮሪን አቅፌያት ነበር። ከዚያ በእግሮቿ አቆምኳት።
እርግጠኛ ባለመሆን እየተንገዳገደች ዙሪያውን አማተረች: ግራ የተጋባችና
የተገረመች ትመስላለች።
ትንሽና ቆንጆ ቅርፅ ያላትን የቀላች አፍንጫዋን ጠረገች። አምላኬ! ብርድ
ያማት ይሆን? ካቲ…” ሲል ክሪስ ተጣራ። “ሁለታችሁ መፍጠን አለባችሁ!
ገና ረጅም መንገድ ከፊታችን ስላለ ኬሪ ከደከማት እቀፊያት” አለ፡ ትንሽዬ እጇን ይዤ እጎትታት ጀመር። “ኬሪ ጥልቅና ረጅም ትንፋሽ ውሰጂ!
ሳታውቂው ንፁህ አየር፣ ጥሩ ምግብና የፀሀይ ብርሃን እንደገና ጠንካራና
ደህና ያደርግሻል:” አልኳት
ትንሽዋን የገረጣችውን ፊቷን ወደ እኔ ቀና አደረገች: በመጨረሻ ያቺ ተስፋ
አይኖቿ ውስጥ አንፀባረቀች: “ኮሪን ልናገኘው ነው?"
የኮሪን መሞት ካወቅንበት አሳዛኝ ቀን በኋላ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው። የውስጥ ፍላጎቷ ኮሪ መሆኑን ስለማውቅ አተኩሬ ተመለከትኳት የተስፋ ብልጭታዋን ላጠፋባት ስላልፈለግኩ አይደለም ማለት አልቻልኩም
ኮሪ ከዚህ በጣም በጣም ሩቅ ቦታ ነው ያለው: አባታችንን የሚያምር
የአትክልት ቦታ ውስጥ አየሁት ብዬ ሳወራ አልሰማሽኝም? አባታችን ኮሪ እንዳቀፈውና አሁን እሱ እየተንከባከበው እንደሆነ ስናገር አልሰማሽም እነሱ እዚያ እየጠበቁን ነው: አንድ ቀን እንደገና እናገኛቸዋለን፡፡ ግን በቅርብ አይደለም" አልኳት።

👍43😢13🥰6❤1🔥1