ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
" #የጻድቅ_መታሰቢያ_ለበረከት_ነው ፤ የኀጥኣን ስም ግን ይጠፋል።"

#ምሳሌ_10÷7
#አቡነ_ጴጥሮስ_ጳጳሰ_ዘምሥራቅ_ኢትዮጵያ_ተላዌ_አሰሩ_ለአቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ

በ1885 ዓ/ም ፍቼ ከተማ ተወለዱ፤ የዓለም ስማቸውም፤ ኃይለ ማርያም ተባለ። በ1909 ዓ/ም መንኩሰው፤ “በ1910 ዓ/ም በወላሞ ወረዳ የደብረ መንክራት ገዳም መምህር ተብለው ተሾሙ። በ1916 ዓ/ም በዝዋይ ደሴት የገዳሙ መምህር ሆኑ። በ1921 ዓ/ም በእስክንድርያ ቅዱስ ማርቆስ ከአራት ጳጳሳት ጋር ጳጳስ ሲሆኑ ስማቸውም ጴጥሮስ ተባለ።” (ጳዎሎስ ኞኞ፤ “የኢትዮጵያና የኢጣልያ ጦርነት”፤ ገጽ 156)።

የጣልያንን ወረራ ለመከላከል በ1928 አዋጅ በታወጀ ጊዜ በወቅቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ ንጉሠነገሥቱንተከትለው ወደማይጨው ዘመቱ።
#በ1928 ሐምሌ21 ቀን የተባበሩት የአርበኞች ግምባርአዲስ አበባ ላይ የሠፈረውን የጠላት ጦርለመዋጋት በአደረገው ቀጠሮ መሠረት አቡነጴጥሮሥ በነደጃዝማች አበራ ካሣ ይመራከነበረው የሰላሌ ጦር አብረው ወደ አዲስአበባ ገቡ። ይህ ጦር ግን የሚፈለገው ውጤጥ አለመምጣቱን በመገንዘብ ወደመጣበት ሢያፈገፍግ አቡነ ጴጥሮሥ የአዲስአበባን ህዝብ ሰብከው በጠላት ላይ ለማስነሳት እና ሀገሩንና ሃይማኖቱን እንዳያጣ ለማንቃት በማሰብ ከጦሩ ተለይተው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ አንድ ቀን ብቻ እንደቆዩ ተይዘው የጦር አለቆች ፊት ቀረቡ።

ብፁእነታቸው ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስየነበረውን ሂደት 'ኮርየር ዴላሴራ' (corrieredella sera) የተባለው ጋዜጣ ወኪል እና የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው 'ፖጃሌ' የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15ቀን 1936 ዓም አዲስ አበባ በነበረ ጊዜሂደቱን ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ፅፎ ነበር
"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸውም ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሠየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል 'ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐ ምፀዋል፣ ሌሎችንም አንዲያምፁ አድርገዋል' የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቂርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ አርስዎ ለምን ዐመፁ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?' ሲል ጠየቃቸው ፡፡ #አቡነ_ጴጥሮስም የሚከተለውን #መለሱ''፡፡
#አቡነ_ቄርሎስ_ግብፃዊ ናቸው፣ #ስለ_ ኢትዮጵያና_ኢትዮጵያውያን_የሚገዳቸው_ነገር የለም፡፡#አኔ_ግን_ኢትዮጵያዊ_ነኝ፡፡ #አላፊነትም_ያለብኝ_የቤተ_ክርስቲያን_አባት_ነኝ፡፡ ስለዚህ #ስለ_ሀገሬና_ስለ_ቤተ_ክርስቲያኔ _አቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ #ለፈጣረዬ_ብቻ _የምናገረውን አናገራለሁ፡፡ #እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ #ስለዚህ_በእኔ_ላይ_ _የፈለጋችሁትን_አድርጉ፡፡ #ግን_ተከታዮቼን_አትንኩ' አሉ፡፡
ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእከት አስተላለፉ፡፡
'#'አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት #ቤተክርስቲያንን_ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ #እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ #ለዚህ_ለግፈኛ_አትገዙ !!!፡፡ ስለ ውድ #ሀገራችሁስለ ቀናች #ሃይማኖታችሁ_ተከላከለ
#ነጻነታችሁ_ከሚረክስ_ሙታቹህ_ስማችሁ_ሲቀደስ_ታላቅ_ዋጋ_ያለው_ክብር_ታገኛላችሁ#የኢትዮጵያ_ሕዝብ ለዚህ ለጠላት #እንዳይገዛ_አውግዣለሁ_የኢትዮጵ_መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። #በፈጣሪየ_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ስም_የተገዘተች ትሁን።''

#አባታችን_ብጹዕ_አቡነ_ጴጥሮስ _ሐቀ _ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣሊያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርገ፡ም በቀር አባታችን የሚናገሩትን ሐቀኛ ንግግር አላስተረጎመም፡፡ አኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበበ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ሐላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቢ ተቀምጦ ስለ ነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለ ገለጠልኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተስበስቡት ጣሊያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበበ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰማ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር"።
ሆኖም አስተርጓሚው በጳጳሱ ላይ ተጽዕኖ ስላሳደረበቸው እውነተኛ ንግግራቸው ሳይገለጥ ቀረ። ቀጥሎም ብፁእነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ ርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ። ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣልያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሣ ታዘዘ። በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ስዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃትም በፈቱ ላይ ይታይ ነበር።
ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉኖ ደከሞአቸው ስለ ነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲ ቀመጡም ፈቀደላቸው፡፡ በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኩዋቸው። ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር፡፡
የሀገራቸው በጠላት መወረር የሕዝበቸው መገደልና መታስር የቤተ ከርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል ሊወስዱ ጥይት አልፎ ሌላ ስው እንዳይጎዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወስዱ። ከገዳዮቹም አንዱ 'ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉገ?' ሲል ጠየቃቸው፡፡ 'ይህ የአንተ ሥራ ነው' ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ'፡፡ ከመግደያውም ቦታ እንደ ደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ እድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ።
ከዚያ በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ ርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ 'ተኩስ' በማለት ትእዛዝ ሲስጥ ስምንቱም ተኩስው መቱዋቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አላመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡
የብፁዕነታቸው አሰክሬን ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአዲስ አበባ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር አንዲቀበር ተደሪገ። በዚያች ሌሊት በአዲስ አበባ ውስጥ በየቤቱ ልቅሶና ዋይታ ሆነ" በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ "አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ" ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቆአቸው እርስቸውም

የሚክተለውን ተናግረዋል። "አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳ ቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት
#ስለ_ቅዱሳን_የሚናገሩ_መጻሕፍት_ያስፈልጉናል

ስለ ቅዱሳት መጻህፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና
ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻህፍት አሥራው መጻህፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል
የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ።›
ኤፌ 5፤1 ‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እነዳትደክሙ እነዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ።› ዕብ 12 ፤ 2-5 በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት
የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል ፡፡
1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት
የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት
የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤የኤልያስን
፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና
መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን ፡፡
2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን
ታሪክ ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን
ታሪከ ፤ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል
መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ
ቃላትትን ለማየት ‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ
ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች
መረዳት እነችላለን
👉የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

👉የእግዚአብሔር ቅዱሳን ተአምራት ወ መንክራትን መፈጸም
ይችላሉ ሰለሞን ያደረገውም እንዲል ይኀውም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ
የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ፡፡› መዝ 67፤ 35 እያለ ይዘምራል፡፡ በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10 ፤12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር
እንደከፈሉ 14 ፤16 2ነገ 2 ፤8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ
የሐዋ 19፤11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እንደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5፤15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

👉ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው ፡፡‹በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ › አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት
ነው፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች
የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ
ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን የቸገራሉ?
በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹የንጉሱም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።› 1ዜና 29፤29
ተብሎ ተጽፋል፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል
1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ
አታንብቡ ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን።
ይቆየን።

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
መዝሙር #በሕብረት

#ስለ_እኛ_ብሎ

ስለ እኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ
ልብሽ በሀዘን ተወግሮ ቆስሎ(2)
ከመስቀሉ አውርደውት
ባንቺ ደረት ደግፈውት
ያለቀሽው የእንባሽ ብዛት
ይጠብልን የኛን ኃጢአት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ድኅነት ጥያቄ #መልሶች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ሐሰት
#ምክንያቱም :-ሰው ለመዳን ከማመን ያለፈ የተግባር ሰው (ምግባራትን እና ምሥጢራትን የሚፈጽም) መሆን አለበት:: ምግባራት የሚባሉትም በዋናነት #ጾም #ጸሎት #ስግደት #ምጽዋት ሲሆኑ ምሥጢራቱም #ምሥጢረ_ሜሮን #ቅዱስ_ጥምቀት እና #ቅዱስ_ቁርባን ይጠቀሳሉ #ሃይማኖት ያለ #ምግባራት ጥቅም አልባ የሞተ ነው::
"፤ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ #ከሥራ (ከምግባራት )የተለየ እምነት የሞተ ነው።" (የያዕቆብ መልእክት 2: 26)


#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :-በተለየ አካሉ #ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሶ ነፍስን ተስቶ በፍጽም ተዋህዶ #ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና:: #በምስጢረ ሥላሴ ትምህርታችን #አብ አባት #ወልድ ልጅ #መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ብለን ተምረናል እንዲህም እናምናለን:: ቅዱሳት መጻሕፍትም በተዋህዶ ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት ይነግሩናል:: ለምሳሌ "እግዚአብሔር አንድያ #ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶልና" ዮሐ3÷16

#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :- ምንም እንኳን ድኅነት በዕለተ አርብ በቀራኒዮ አደባባይ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ ለሰው ልጆች የተሰጠ ቢሆንም ከዚህ ከተሰጠው ድኅነት ግን ለመካፈል ሰው የራሱን ጥረት ማድረግ ይገባዋል። ድኅነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተፈጸመ ስለሆነ ብቻ ሰው ሁሉ ያመነውም ያላመነውም በግዴታ ይድናል ማለት አይደለም:: ለመዳን የወደደ ብቻ ከተፈፀመለት የድኅነት ሥራ በምግባራት ተሳትፎ ድኅነትን ያገኛል:: ስለዚህ በድኅነት ውስጥ ሰውም ሊፈጽመው የሚገባ ሂደት ነው::
"፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ #እንደ_ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ፤"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 12)

ልናስተውለው የሚገባን #የታዘዛችሁትን_በመፈጸም የምትለዋ እና #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ የምትለዋን ነው

በመሆኑም የእራሳችንን መዳን መፈጸም የምንችለው እና ከተሰራልን የድኅነት ሥራ የምንካፈለው የታዘዝነውን በመፈፀም ነው:: #የታዘዝነውም 10ቱ ትዕዛዛት 6ቱ ቃላተ ወንጌል ናቸው እነዚህን ለመፈፀም ደግሞ ጊዜ ዘመን ያስፈልገናል:: ይህ ደግሞ ድኅነት በሂደት የሚፈፀም እንጂ በአንድ ቀን በአንድ ቦታ በሰዓት ጌታን በመቀበል ብቻ አለመሆኑን ያስገነዝበናል:: በጥቅሉ ለመዳን ሰው የራሱ ድርሻን መወጣት ይገባዋል።

#ኛ እውነት

#ኛ ሐሰት
ምክንያቱም:-ያልተመለሰለት ጸጋ የለምና::
ፀጋ:-
ልጅነትን:- ከእንግዲ ወዲ ባሮች አትባሉም
ወራሽነትን:-
ገዢነትን(ሥልጣንን):- ግዛ ንዳ የተባለሁ ዓለምና በዓለም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ዛሬም ሰው ከትዕዛዙ ካልራቀ ሕጉን ከጠበቀ ከተፈጥሮ ሁሉ በላይ መግዛት መንዳት የሚችልና ሥልጣኑ ያለው መሆኑን በቅዱሳን ሕይወት መመልከት ይቻላል::


#በአጭሩ መልሱ

#ኛ #ስለ_ፍጽም_ፍቅሩ
#ለካሳ ለቤዛ
#የዲያብሎስ ጥበብ #በጥበቡ #ለመሻር
#ለምሳሌነት_ለአራያነት
#ድኅነት ሥርዓት ስላለው…

#ኛ #ማመን
#ሥራ (ምግባራት)
#ምሥጢራትን መፈጸም ማር 16:16 ዮሐ 6:54


#ኛ "፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ #በእርሱም ቍስል #እኛ ተፈወስን።"

(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 5)
"፤ #እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ #ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም #የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 6)

ነብዩ ስለ እኔ ብቻ አላለም #እኛ ብሎ አብዝቶ ተናገረ እንጂ:: እኛ ብሎ አብዝቶ መናገሩ የዓለምን ኃጢያት የተሸከመ የዓለም መድኀን መሆኑን ሲገልጥ ነው::

"እነሆ #የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1: 29)


#ኛ #መንግስቱን_ሲወርስ_ስሙን_ሲቀድስ


#ኛ ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው ማለት እንጂ ቅዱሳን አያድኑም ወይም መድኀኒት አይባሉም ለማለት አይደለም:: በቅዱስ መጽሐፍ ሰዎች ሆነው አዳኝ ተብለው የተጠሩ አሉ #ለምሳሌ "፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ #እግዚአብሔርም_የሚያድናቸውን_አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ #ጎቶንያልን_አስነሣላቸው።"
(መጽሐፈ መሳፍንት 3: 9) ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎችን አዳኝ መድኀኒት አድርጎ እንደሚያስነሳ ነው:: መዳን በሌላ በማንም የለም ማለቱ የቅዱሳን አዳኝነት (መድኀኒትነት) ጠፍቶት አይደለም:: ቅዱሳን የጸጋ አዳኝ ናቸው:: ጸጋ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፣የተቸረ ፣የተለገሰ ስጦታ ማለት ነው:: ስለዚህ ቅዱሳን መድኀኒት ቢባሉ በስጦታ ያገኙት ነው። "#እድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን #ሌላ ስም የለም" ማለቱ ደግሞ ቅዱሳን ሲያድኑም በእራሳቸው ኃይል ሳይሆን ማዳንን በሰጣቸው በፈጣሪያቸው ስም ነው ማለቱ ነው:: ቅዱሳን መላእክት አዳኝ (መድኅኒት )ናቸው። ስማቸው ስመ እግዚአብሔር ተሸክሞልና:: ስለሆነም ቅዱስ ሚካኤል አዳነ ማለት እግዚአብሔር አደነ ማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ (ቅዱሳን ሰዎችም) ቢያድኑ የፈጣሪን ስሙን ጠርተው ነው "፤ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ #በናዝሬቱ_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።"
(የሐዋርያት ሥራ 3: 6)
ከዚህም ባሻገር ቅዱሳን ወደ ቅድስና ሲጠሩ ስማቸው ይለወጣል ስመ እግዚአብሔርም ይሆናል:: በመሆኑ እነርሱም በስማቸው ማዳን ይቻላቸዋል "፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #በእኔ_የሚያምን_እኔ_የማደርገውን_ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ #ከዚህም_የሚበልጥ_ያደርጋል፥" (የዮሐንስ ወንጌል 14: 12)
ከእርሱ አብልጦ የሚሰራ የለም ነገር ግን በስሙ ላመኑ እርሱ ያደረገውን ሁሉ የማድረግ ሥልጣን አላቸው ማለቱ ነው።

ይቆየን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ስለጠየቁ እናመሰግናለን በተለይ ደግሞ ወቅቱንና ጊዜውን ያገናዘበ ዘመኑን የዋጀ ጥያቄ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው ::በርቱልን:: የቤተ ክርስቲያን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሕይወትን ቃል ያሰማልን::
ምላሽ :- ወደ አተታውና ወደ መደመደሚያው ከመሄዳችን በፊት አጠር ያለና ቀጥተኛ ምላሽ እንስጥ :: ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ግድያ እንዴት ታየዋለች ? ለሚለው ጥያቄ ቤተ ክርስቲያን የልጆቿን ሞት እንደ ሰማዕታት ሞት ታየዋለች:: የሚል ግልጽ መልስ እንሰጣለን :: ሰማዕታት ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የሐዘኟ ምንጮች ፣የጠባሳዋ ማስታወሻዎች ፣ የቁስሏ ጥዝጣዜዎ ሳይሆኑ ጌጦቿ ናቸው ::ጌጥን ደግሞ ሁል ጊዜ ስለ እርሱ እያወሱ ያጌጡበታል ይዋውበታል እንጂ አፍረው አይሸሽጉትም ቤተ ክርስቲያንም በጌጦቿ አታፍርባቸውም ከዛ ይልቅ ቤተ ክርስቲያ አንጻ ፣ታቦት ቀርጻ፣ ገድል ጽፋ ፣ቀን ቆጥራ ዘላለም ስታዘክራቸው ትኖራለች::

ሰማዕትነት የራሱ የሆነ ሃይማኖታዊ ፋይዳና ረብ ያለው የቅድስና ማግኛ አንዱ መንገድ ነው :: ቢሆንም ግን ሁሉም ክርስቲያን አንገቱን ለሰይፍ ሰቶ ሃይማኖቱን ያለ ተከታይ ቤተ ክርስቲያንን ያለ ቀዳሽ ሀገርን ያለ ወራሽ ባዶ አርጎ ያስቀራት ማለት አይደለም :: ክርስትና ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ግራህን ደግሞ አዙረህ ስጠው የምትል የፍቅር ሕግ ብትሆንም ቅሉ ዝም ብለህ ስትጠፈጠፍ ሁለ ግባ ማለት ግን አይደለም የእግዚአብሔር መቅደስ የሆነ ሰውነታችን ማንም እንዲጠፈጥፈው አይደለም በአምሳሉ አክብሮ የፈጠረን :: እንዲያውም አንድ አባት አንድ ወጠጤ መቶ በጥፊ ፊታቸውን ይመታቸዋል እርሳቸውም እንደ ወንጌሉ ብለው ሌላው ጉንጫቸውን አዙረው ይሰጡታል ያም ደፋር ወጠጤ ያለ እርህራሄ ደግሞ በዚህ በኩልም ይመታቸዋል ጥፊው በጣም ያመማቸው አባም መልሰው የሁለት ጥፊ እጥፍ በሚሆን ቦክስ መተው መሬት ላይ ይዘርሩታል ወጠጤውም እንዴ አባ ወንጌል ተላለፉ እኮ ቢላቸው ውይ ልጄ አዙረ ስጠው እንጂ ደጋግመህ ስጠው አላለም አሉት ይባላል። ሰማዕትነት የራሱ ወግና ሥርዓት ያለው እንጂ ዝም ብሎ ሄዶ ከእሳት መማገድ፣ በሰይፍ ማለቅ በጥይት መደብደብ ማለት አይደለም ስለዚህ ክርስቲያኖት በወንድሞቻችን እየደረሰ ያለሁን መከራ እያየን እየተሳቀቅን ሃይማኖት መለወጥ ወደ ኃላ ማፈግፈግ ወይም እንደ ሰማዕታት ብለን ደግሞ ተገዝግዘን ማለቅ ብቻ የለብንም ክርስቲያን አንድ የሀሳብ ጽንፍ ይዞ የሚቆም ጽንፈኛ አይደለም ነገሮችን በማገናዘብ በሚዛናዊነት ይቆማል እንጂ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያስተማረን “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።” ብሎ ነው ማቴዎስ 10፥16 ::
በተአምረ ኢየሱስ ላይ ተጽፍ እንደምናነበው ህጻኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ህጻናት ጠባይ ሲጫወት ሲታዘዝ ሲወድቅ ሲነሳ እናያለን በዚሁ የህጻናት ጠባይም ትምህርት ቤት ገብቶ ሳለ የመምህሩን የመጻፊያ ቀለም ሳያውቅ ጥቁሩን ከነጩ ይደባልቀዋል መምህሩም ቁጡ ነበርና የምጽፍበትን ቀለም ደፋህ ይልቁኑ ጥቁሩን ከነጩ ደባለክብኝ ብሎ ህጻኑን ኢየሱስ ክርስቶስን በጥፊ መታው ይህን ጊዜ ግን ግራ ጉንጭህን ለሚመታህ ቀኝህን ደግሞ አዙረ ስጠው ብሎ የሚያስተምር አምላክ ሆኖ ሳለ አዙሮ ግይ ጉንጩን ሲሰጠው አንመለከትም ከዛ ይልቅ መምህሩን ጠየቀው :: እንዲ ሲል መምህር ያጠፋሁብህ እንደሆነ አስተካክል ትለኛለ እንጂ ለምን ትመታኛለህ ??? አለው ። የተደባለቀውንም ጥቁርና ነጭ ቀለምም በተአምራት ለየ ብቻ ለይቶ ሰጠው:: እንደ ሰውነቱ አጠፋ እንደ አምላክነቱ ጥቁሩን ከነጭ ለይቶ ሰጠው :: ታዲያ ከዚህ የምንማረው ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታ ግራህን ደግሞ አዙረ ስጠው የሚለውን ይዞ ሲጠፋጠፉሁ መዋል ፍጽም አግባብ አይደለም ሰማዕታትም አያሰኝም ከዛ ይልቅ ለምን ትመታኛለህ ማለቱና እራስን ማስከበሩ የተገባ ነው ። ዛሬም በልዮ ልዮ ዱላ የሚመቱን ቁጡ መመህራኖች በዝተውብናል ለምን ትመቱናላችሁ ብለን ልንጠይቅ ይገባል።። “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።” ሮሜ 8፥36 ::

ታድያ ምን እናድርግ?
#ስለ ቀናች ሃይማኖት #መጋደል አለብን::
ክርቲያኖች በሃይማኖታችን ጸንተን መሞት ብቻ ሳይሆን መኖርም ተፈቅዶልናል “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” ይሁዳ 1÷3
ማስታወሻ :- መጋደል ሲባል ቆሞ መገደል ማለት አይደለም ባንገል እንኳ እንዳንሞት እራሳችንን መከላከል መቻል ማለት ነው :: ልክ ድብድብ ስንል የሁለት ሰዎች ሱታፌ ያለበት ኩነት እንደሆነ ሁሉ መጋደልም እንዲሁ ማለት ነው አንዱ ወገን ብቻ የሚያጠቃበት ከሆነ ድብደባ እንጂ ድብድብ አያሰኘውም ::
እኛ ክርስቲያኖች ሙስሊሙ ያርደናል ፖለቲካው ያቃጥለናል ሰይጣን ይሸምቅብናል መለያየት ያተኩሰናል ጴንጤው ያሰናክለናል ነገር ግን ይህ የክርስቲያኖች ጠባይ ነው በመቱን ቁጥር እንደ ሚስማር እንጠብቃለን በገፉሁን ቁጥር እንደ ቅቤ ከፍ እንልና የራስ አክሊል እንሆናለን የሰማዕታት ደም ዘር ነውና ሊቀንሱን ሲያርዱን 30፣60፣100 ፍሬ ሆነን በዝተን እናፈራለን ።
#በጸሎት እንትጋ
ክርስቲያኖች በሃይማኖት ነቅ የሌለባቸው ጻድቃኖች(እውነተኞች) ናቸው ። በመሆኑም በእምነት ሆነው የሚጸልዮት ጸሎት ተሰሚነት አለው ጸሎት የክርስቲያኖች ዋነኛ መሳሪያ ነው::“እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።” ያዕቆብ 5፥16
#ስለ ሀገራችን ጸልዮ
#ሰለ ሃይማኖታችን ጸልዮ
#ስለ አንድነታችን ጸልዮ
“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” ማቴ26፥41
“በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤” ኤፌሶን 6፥18
#ቀርበን እንወቃት እንማራት
የማያውቁትሀገር አይናፍቅም ነውና ይበልጥ ተቆርቋሪዎቿ ለመሆን ከፈለግን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀርበን እንማር ታሪኳን እናጥና ያሳለፈችሁን የመከራ ዘመን እንዴት እንዳለፈችሁ መርምረን ለነገ ችግሯ መፍትኤ እናብጅላት::

" የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ #እርሱም_የእግዚአብሔር ቃል ነው።" ኤፌ 6 ÷11-17 ይቆየን

ሐምሌ 26 ቀን ዕለተ እሁድ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ ማርያም
@YEAWEDIMERITE

ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#ስለ ሆሳዕና ከተማ የሆነ ነገር በሉ እንጂ?


“ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?”
ሐዋ9፥4
ክርስቲያኖችን ማሳደድ ክርቶስን ማሳደድ ነው !። ይህ ደግሞ የመውጊያውን ብረት እንደመቃወም የሚብስ ነው።
# ክርቶሳዊያን በሆሳዕና ሲከለከሉ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም ያኜ በክርስቶስ ዘመን የተጀመረ ነው::
# ወደ_ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ # እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው ነበር። "በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር" አሉ ። ይህን ጊዜ ከሕዝብም መካከል #ከፈሪሳውያን_አንዳንዱ፦መምህር ሆይ፥ደቀመዛሙርትህን ዝም እንዲሉ ገሥጻቸው አሉት። # እርሱም መልሶ፦እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው። ሉቃ19÷37-40

#ገዢዎቻችን ባልሰማ ዝም ቢሉም እንኳ #በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው እያለች ሆሳዕና ዛሬም ትጮሃለች !
#የከበረ ዘር ማነው?

አንተ ሞኝ አማራ ነው! ፣ኦሮሞ ነው! ፣ ትግሬ ነው!፣ ጎራጌ ነው!፣ አረ ከንባታ ነው! የለም አድያ ነው? ትል ይሆናል ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አይደሉም የከበረው ዘር "ሰው" ነው። እነዚያማ ሰዎች ልማዳቸውን ባህላቸውን ቋንቋቸውን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት አድራጎታቸውን ከቀደምቶቻቸው የወረሱበት የትውፊታቸው መገለጫ የሆነ ስመ ስያሜ ነው። አማራ ሥጋ የለችም ! ኦሮሞ ነፍስም አልተፈጠረችም ! ሁላችን ሰው ሆነን ተፈጠርን ሰው ሆኖ መኖርና ሰው ሆኖ መሞት ግን አቃተን።

የሰው ዘር የከበረ ዘር ነው:: የከበረ ዘር ማነው ? #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ዘር አይደለምን?
የሰው ዘር የጐሰቈለ ዘር ነው ጐስቋላ ዘር ማነው? #የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ዘር አይደለምን? መ.ሲራክ 10÷19-20

ለቀደሙት አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። #ማቴ 5÷21-22

በፖለቲካና በብሔር ሰበብ ክርስቲያን በመሆናችን ብቻ የምንፈናቀል እኛ የምንገደል እኛ ቤት ንብረታችን የሚወድም የእኛ የባለ ማዕተሞቹ ብቻ ነው።

ክርስትናን ዝም ብሎ በሰበብ በአስባቡ ማጥፋት አይቻልም !። ጠላት ይህን ቢያውቅ ኖሮ ዝናሩን ባልታጠቀ ቀስቱንም በከንቱ ባልጨረሰ ነበር። ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። 1ኛ ጴጥ 1፥23

" #ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? #ስለ_አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። የምገደለው ስለማን እንደሆነ እናውቀዋለን ስለ አንተ ስለ ማዕተማችን ነው! ስለ አንተ በክርስቶስ ክርስቲያኖች ስለመባላችን ስለ ስም ነው !

በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።” #ሮሜ 8 ፥35_37
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (toolkit)
መዝሙር #በሕብረት

#ስለ_እኛ_ብሎ

ስለ እኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ
ልብሽ በሀዘን ተወግሮ ቆስሎ(2)
ከመስቀሉ አውርደውት
ባንቺ ደረት ደግፈውት
ያለቀሽው የእንባሽ ብዛት
ይጠብልን የኛን ኃጢአት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ስለ_ታቦቲቱ የባዕዳኑ ምልከታ !
______________________________

( The sign and the seal /ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ )
ግራሃም ሐንኰክ

ታላቁ የመጻሕፍ ቅዱስ ምሥጢር
________________________ ገጽ 3-4

#በዘመነ ኦሪት እስራኤልላዊያን የቃል ኪዳኑን ታቦት የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆኑ የሚያመልኩትና በምድር ላይ ያኖረው ምልክቱንና ማኀተሙን እንዲሁም የኃይሉ መገለጫ ነው ብለው ያምኑ ነበር።
አሥርቱ ቃላት የተፃፉባቸው ሁለት ክንድ ርዝማኔ አንድ ክንድ ተኩል ቁመትና ወርድ ያለው በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ነው ከተቀጠቀጠ ንፁህ ወርቅ የተሠሩ ሁለት ኪሩቤል አንዱ ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛው ኪሩብ በሌላ ወገን ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ወደ መክደኛው በትይዮ ሲመለከቱ የሚያሳይ ነው ።
#መጽሐፍ_ቅዱስና ሌሎችም ጥንታውያን መዛግብት እንደሚሉት ታቦተ ሕጉ በሚንቀለቀል ብርሃኑና እሳቱ በነቀርሳ በእባጭ ና በለምጽ የመምታት የማቃጠል ተራራዎችን ወደ ሜዳማነት የመለወጥ ፣ ወንዞችን የማድረቅ ታላላቅ ሠራዊትን የመደምሰስ ፣ከተማዎችን የማፈራረስ ኃይል አለው።
እነዚሁ ምንጮች አክለውም ታቦተ ሕጉ የአይሁዶች የእምነት መሠረት እንደሆነ ና ንጉሥ ሰሎሞንንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ያሠራው ይህንኑ ታቦት በክብር ለማኖር አስቦ መሆኑን ይገልጻሉ።
#ይሁንና_ከክርስቶስ_ልደት በፊት በአንድ ሺህና ስድስት መቶ ዓመታት መካከል በገበረው ጊዜ ይህ እጅግ ድንቅና ተአምራዊ ታቦት የትና ወዴት እንደሄደ ሳይታወቅ በመሠወሩ ጉዳዩ ለብዙ ሺህ ዓመታት እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል ማስረጃው እንደሚጠቁመው በ587ዓመቸ ዓለም የናቡ ከደ ነጾር ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ባቃጠለ ጊዜ ታቦቱ በቦታው አልነበረም ።
በጦርነቱ የተማረኩት እስራኤላውያን ከባቢሎን ወደ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በ538ዓመተ ዓለም ተመልሰው ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ በሠሩበት ወቅትም ታቦቱ በዚያ አልነበረም ። ይህም ቀደም ሲልታቦቱ በባቢሎናዊያን አለመዘረፉን ያረጋግጣል።
#በካሊፎርኒያ ዮኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ኤሊየት ፍሬድማን በ1987ይህን ጉዳይ አስመልክተው ሲጽፋ "የታቦቱ መጥፋት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂው ምሥጢሮቾ እንደ አንዱ ይቆጠራል"ብለዋል።
ብሉይ ኪዳን መጻሕፍ ውስጥ እስከ ንጉሥ ሰሎሞን ዘመነ መንግሥት (970-931 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ድረስ ከሁለት መቶ ጊዜ በላይ ስለ ታቦቱ ተጠቅሷል። ከዚህ ብልህና አስተዋይ መሪ ዘመነ መንግሥት በኋላ ግን ታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን ተነስቶ አያውቅም። ይህን የመሰለ ክቡርና ውድ ቅርስ በተለይም ደግሞ ሃይማኖታዊ ከበሬታ ያለው በብሉይ ኪዳን የኋለኞቹ መጻሕፍት ጨርሶ አለመወሳቱ የሚያስገርም ነው።
#በዚህ የተነሳ በዘመኑ የነበሩ ጸሐፍትና ቀሳውስት የዚህን ቅዱስ ቅርስ የመሰወር ምሥጢር ላለማሳወቅ ከፍተኛ የሆነ የመሸፋፈን ጥረት ያደረጉ አስመስሎባቸዋል። የተሰወሩ ቅርሳ ቅርሶችን የሚያስሱ ወገኖች የዚህን ታላቅ ቅርስት መሰወር አውቀው በርካታ ዘመቻዎችን ቢያካሂዱም አንዳቸውም አልተሳካላቸውም።
በ1981/የጠፋው ታቦት ዘራፊዎች/( #Raiders_of_the_Lost_Ark ) በሚል ርእስ ሐሪሰን ፎርድ እንደኢንዲያና ጆንሰ ሆና የተወነችበት የሆሊውድፊልም ውስጥ በአሜሪካና በአውሮፓ ለዕይታ ቀርቦ ነበር። እኔም 1983 ናይሮቢ ውስጥ ይህንኑ ፊልም የማየት ዕድሉ አጋጥሞኝ ነበር።
#ፊልሙን ካየው በኋላ የታቦቱን ዱካ አነፍንፌ የለማግኘት ሀሳብ አደረብኝ።ከጥቂት ወራት በኋላም ሀሳቤን ለመተግበሮ ወደ ኢትዮጵያ አመራሁኝ። ጉዞዬንም ወደ ትግራይ አቅንቼ የኢትዮጵያውያን ቅድስት ከተማ የምትባለውን አክሱምን ጎበኘሁ። በዚህ ጊዜ ነበር ጠባቂውን መነኩሴ ያገኘኋቸው።
( The sign and the seal /ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ)
በግራሃም ሐንኰክ
............... #ይቀጥላል ..........
በቀጣይ
#ታቦቲቱ በኦሪቱ_ምልከታ
#ታቦቲቱ በአዲሳት ምልከታ
#ታቦቲቱ_በኢትዮጵያውያን እምነትና መልከታ
#በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል

❝... እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ..❞
—2ኛ ነገሥት 18: 30

ይህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከሚነድ ዕቶን እሳት ያዳነበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው፡፡

ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገሥት ወገን ናት፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በ20 ዓመት በአባ ባጋግዮስ ምክንያት ‹‹የጣዖታት ቤቶች ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ›› ብሎ አሳወጀ፤ በዚህ ጊዜ ግማሾቹ ተሰደዱ ቅድስት ኢየሉጣም ልጇ የ3 ዓመት ሕፃን ነበርና ለርሱ ብላ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች፡፡

በዚያም
ሀገረ ገዢው። :- ‹‹ክርስቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ›› ቢላት
እርሷም: - ‹‹ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም›› ብላ መለሰችለት፡፡
እርሱም መልሶ :- ‹‹እምቢ ካልሽ በሰይፍ እቀጣሻለሁ›› ብሎ ቢያስፈራራትም
እርሷ ግን :- ‹‹ይህን ሕፃን ጠይቀው›› አለችው፡ከዚያም
ሕፃኑን :- ‹‹ወርቅ እሰጥሃለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ›› አለው፡፡
ሕፃኑ ቂርቆስ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ‹‹ራሳቸውን እንኳ ማዳን ለማይችሉ ጣዖታትህ አልሰግድም›› ብሎ በመለሰለት ጊዜ ንጉሡ ተበሳጭቶ ‹‹በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሏቸው›› ብሎ አዘዘ፡፡

የውኃው መፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ 42 ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር፡፡ የንጉሡ አገልጋዮች ሊከቷቸው ሲወስዷቸው የቅድስት ኢየሉጣ ልቧ በፍርሃት ታወከባት፤ ቅዱስ ቂርቆስ ግን የእናቱን ፍርሃት እንዲያርቅላት ይጸልይ ነበር፤ እርሷንም ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ በርቺ ፣ ጨክኚ፤ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልን ያዳነ እኛንም ያድነናል›› በማለት እያጽናናት ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ፡፡

ከዚህ በኋላ ቅድስት ኢየሉጣ ጨክና በፍጹም ልብ ሆነው ተያይዘው ከእሳቱ ገብተዋል፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው ሳይቃጠል ተመልክተው ከአሕዛብ ብዙዎቹ አምነው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሚፈላ ውኃ ያወጣቸው ሐምሌ 19 ቀን ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበሉት ግን ጥር 15 ቀን ነው።

የቅድስት ኢየሉጣ እና የቅዱስ ቂርቆስ በረከታቸው ይደርብን

ሀገራችን ኢትዮጲያ ከሚነደው እሳት መልአኩን ልኮ ይጠብቅልን ! ላዘኑ ሰዎች መጽናናትን ያድልልን።

#ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ !

ዲ/ን እስጢፋኖስ ደ.
18/11/2014 ዓ.ም
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን።

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም

ዛሬ ....
#ለክርስቶስ ጸሀይ ምስራቅ ድንግል #ማርያም የተወለደችበት ቀን ነው ።
(አንቲ ምስራቁ ለክርቶስ እንዲል ቅዱስ ህርያቆስ)

#ለክርስቶስ ዝናብ ደመና ድንግል #ማርያም የተዘረጋችበት ነው ።
(አንቲ በአማን ደመና እንተ አስተርያ ለነ ማየ ዝናም እንዲል ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው)

#ለክርስቶስ መብል ፍሬ ድንግል #ማርያም የተተከለችበት ነው ።
(እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን እንዲል ቅዳሴ ማርያም )

#መልካም_በዓል
#የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው
#ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ


©️ ከመምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ