ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ስከረም ፲ ቀን ነው ወደ ኢትዮጵያም የገባው በመስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ አሁንም በመጨረሻ ግሸን አምባ የገባው መስከረም ፳፩ ቀን ሲሆን ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱ አከበሩ። አፄ ዘርዓያዕቆብ ከግማደ መስቀሉ በተጨማሪ በተቆለፈ ሳጥን የተቀበሉትን ቅዱሳን ነዋያት በፅሑፍ በመዘርዘር ለመላው ኢትዮጵያዊያን መስከረም ፳፩ ቀን ገለጡላቸው፡፡

በነቢዮ በዳዊት ቃል“ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።” ተብሎ የተነገረው ትንቢት ዳግም በኛ በኢትዮጵያውያን ስለተፈጸመ ሁል ጊዜ በመስቀሉ ደስ ይለናል ከጠላት ቀስት ሁሉ እናመልጥበታለንእና መዝ60፥4።
............ ይቆየን ..........
ከእፀ መሰቀሉ እረድኤትና በረከት ያድለን ......አሜን!

#መስከረም ፩፭/ ፳፻-፩፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)