ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ውድ የትምህረተ ሃይማኖት እና የዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን እንደምን ከረማችሁልን🙏

እንደሚታወቀው የዓውደ ምህረት እህት ቻናል የነበረው ትምህርተ ሃይማኖት የተባለው ቻናል ከሰኞ #06 -09-2010 ዓ.ም ጀምሮ #የኔታ የተባለ የአብነት ትምህርት ቤት ሆኗል:: በፊት ያስተላልፈው የተበረው መርሐ ግብራት #ማለትም

ሰኞ #ትምህርተ ሃይማኖት
ማክሰኞ #ክ .ሥነምግባር
ረቡዕ #የመ ጥናት
ሀሙስ #ነገረ ማርያም
አርብ #ሥነ ፍጥረት
እሁድ #ባሕረ ሐሳብ የተሰኙት ሲሆኑ ሁሉም መርሐ ግብራት ይዘታቸውን ሳይለቁ በፊት የዓውደ ምህረት የኮርስ መርሐ ግብራት በሚተላለፉበት ውል ጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ በዕለተ አርብ በዓውደ ምህረት ከሚተላለፉት ኮርሶች ጋር በመሆን የሚቀጥሉ ይሆናሉ::በዚህም መሠረት #ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዘወትር አርብ #አርብ ከምሽቱ 2:30 ጀምረን ኮረርሶቹን ካቆሙበት ክፍል የምንጀምራቸው ይሆናሉ:: በአንድ የመሆናቸው ታላቁ ሚስጢር በትምህርት ይዘታቸውና ዓላማቸው ተመሳሳይነት ስላላቸው ነው::

👉በዚሁ አገጋጣሚ ለቀደምት #የዓውደ ምህረትና #የትምህርተ ሃይማኖት ቻናል ታደዳሚወዎቻችን ሁሉንም ኮርሶች ከአንድ ቦታ የማግኘት ዕድል ስለገጠማችሁ #እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን🙏

#ዘወትር አርብ ከ#2:30 ጀምሮ

#1🎤 ነገረ ድኅነት
#2📢ነገረ ማርያም
#3🎤ነገረ ቅዱሳን
#4📢ሥነ ፍጥረት
#5🎤ትምህርተ ሃይማኖት
#6📢ሥነምግባር (አንድ ክፍል ብቻ ይቀራል)
#7🎤መ ጥናት (ሁለት ክፍል ብቻ ይቀራል )
#8📢ባሕረ ሐሳብ

❤️ ዘወትር ቅዳሜ

🧙‍♂እንደተለመደው #ምን እንጠይቅልዎ??? የተሰኘው መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል🙏

❤️ዘወትር እሁድ

በቀድሞ ፕሮግራም አርብ ከተላለፉት ኮርሶች እርሶን የምንጠይቅበትና ልዮ ልዮ የመጻሕፍት ሽልማቶችን የምንሸልምበት ነበር ነገር ግን አዳዲሶች ኮርሶች ስለተጨመሩ ያን ለማድረግ ይከብዳል ሆኖም ስለዚህ ለ ተከታታይ 3ሳምንታት ምንም ዓይነት ከኮርሱ የተወጣጡ ጥያቄዎችን አንጠይቅም ::ይህን አጋጣሚ በመጠቀምም አዳዲሶቹን ኮርሶ በሚገባ አድምጠው ከሦስት ሳምንት በኃላ በምናደርገው ወርሃዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ተሳትፈው አሸንፈው" #ገድለ ተክለ #ሃይማኖት "እንዲሸለሙ ከወዲሁ ይዘጋጁ እንላለን እናመሰግናለን🙏

👉እስከዛሁ ግን በእሁድ መርሐ ግብረራችን ተጠይቀው ትከክክለኛ ምላሻቻው ያልተነገሩ ጠጥያቄዎች ስላሉ የእነርሱን ትክክለኛ መለሶች ይዘነን የምንቀርብበት ይሆናል::

ሽልማቱ በPDF format ሳይሆን በአካል ወይም በወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንደሚሰጥ ለማሳወቅ እንወዳለን::

"መልካም የኮርስ ሳምንት"
ማንኛውንም ሀሳብ ጥቆማና አስተያየታችሁን በ @YeawedMeherte @YeawedMehert በኩል ያድርሱን


🍒ሌላውና #አስደሳቹ ነገር ከእንግዲ ወዲ በዓውደ ምህረው ምንም ዓይነት የሊንክ ጋጋታ እንደማይኖርና ከዕርዳታ ጥሪ ወይም ከቤተ ክረርስቲያናት ምረቃ ጋር የተገናኘ ማስታወቂያ ካልሆነ በቀር በሳምንት ከአንድ በላይ promotion የማንሰራ መሆኑን #በደስታ እንገልጻለን::

📢ዓውደ #ምህረት🎤
የእናንተ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit📢
📢 @AwediMeherit📢
📢📢📢📢📢📢📢📢
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን!🙏


#እንደምን ከረማችሁልን ውድ የዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ደህና #እግዚአብሔር ይመስገን እንዳላችሁ ተስፋ እናደርጋለን ....እሰከ እዚች ሰዓት በደንነት የጠበቀን አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን አትለይምና እመ አምላከሸ ድንግል ማርያምም ከልጆ ከወዳጇ ጋር የከበረች የተመሰገነች ትሁን ጻድቃን ሰማዕታትም እንደየ ክብራቸው የከበሩ የተመሰገኑ ይሁኑ ለዘለዓለሙ አሜን!!🙏

👉ነገረ ድኅነት
👉ነገረ ማርያም
👉ነገረ ቅዱሳን #መምህር አቤኔ ዘር ማሙሸት እና በዓውደ ምህረት አስተባባሪዎች

👉የመጻሕፍ ቅዱስ ጥናት #በመምህር መስፍን አዳነ

👉ሥነ ፍጥረት #በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው
👉ትምህርተ ሃይማኖት #በመምህር ኢዮብ ክንፈ
👉ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር #በመምህር አቤኔዘር ማሙሸት
👉ባሕረ ሀሳብ #በመምህር ማርቆስ ዓለማየሁ የተሰጡ ሲሆን

#ቅዳሜ ቅዳሜ በሚተላለፈው #ምን እንጠይቅልዎ??? በተሰኘው መርሃ ግብራችን ደግሞ #ኦርቶዶክሳዊ መልሶችን በመስጠት እያገለገሉን የሚገኙት

የተለመዱ ዓይነት ጥያቄዎች በተርቢኖስ(በኃ/ማርያም) እና በአቤኔዘር (በተክለ ማርቆስ)በኩል የሚመለሱ ሲሆን

#ጠንካራና ሕይወት ነክ የሆኑ ጥያቄዎችን ደግሞ

#በመምህር ቢትወደድ ወርቁ እና
#በዲ/ን ሃብታሙ ፍቃዱ በኩል
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ስናስመልስ ቆይተናል ::


ለመምራኖቻችን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን የነፍስ ዋጋ ያድርግልን አሰበ መምህራንን ይክፈልልን !!🙏

#በዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ስምም #ምስጋናችንን እናቀርባለን::

🍒በቀጣይ በምዕራፍ ሁለት ቆይታችንም የጀመሩትን ኮርሶች አጠናቀው #አዳዲስ_ኮርሶችንም እንደሚቀጥሉልንም ስለነገሩን ስለ በጎ ምግባራቸው #በእግዚአብሔር ስም ከልብ እና መሰግናቸዋለን

#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የተጠናቀቁ #ኮርሶች

👉#ነገረ_ድኅነት(ምዕራፍ አንድ)
👉#የመጻሕፍ ቅዱስ ጥናት
👉#ክርስቲያናዊ ምግባር

❤️ #አዲስ የሚተኩ ኮርሶች

👉 #ነገረ_ድኅነት (ምዕራፍ ሁለት)
👉 #የቤተ_ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
👉 #ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

#ሌሎቹ እዳሉ ይቀጥላሉ ማለት ነው


#ምን_እንጠይቅልዎ ዘወትር ቅዳሜ
👉ፍቅር
👉ንቅሳት
👉ውርጃ
👉የቅርብ ዝምድናና ትዳር
ወዘተ የመሳሰሉት #ከእናንተ_የሚመጡ_ማንኛውም_መንፈሳዊ ጥያቄዎች እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቂ ምላሽ ይሰጥበታል::
እንዲሰጥ የምትፈልጉት ሌላ የኮርስ ዓይነት ካለ ሀሳባችሁን በ

@abenma
@abenma
ወይም
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ብትልኩልን #እግዚአብሔር ከፈቀደ ነገሮችን አስተካክለን የምንጨምርላችሁ መሆኑን #በደስታ እንገልጻለን::
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ከዚህ ቀደም በዓውደ ምህረት ዘተዋሕዶ በ #ምን_እንጠይቅልዎ ከተሰኘው አምዳችን ካስተናገድናቸው ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹን በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሱትን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

#ጥያቄ ሰላም ለእናንተ ይሁን የክርስቶስ ቤተሰቦች እንኳን ለዳግመ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
እኔ የምጠይቀው ጥያቄ የወቅቱ ባይሆንም ግን ሁል ጊዜ በልቤ የሚመላለስ ጥያቄ ነው ዛሬ ያነሳሁት ሰሞኑ በመንፈሳዊ እና በአለማዊ የቴሌቪዥን መስኮት ያየሁ ነገር የበለጠ እንድጠይቅ አስገድዶኝ ነው።
ጥያቄ ከስርአተ ቤተ ክርስቲያን የተያታዘ ነው እኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ስንማር የሚዘመሩ መዝሙሮች እንኳን ተለይቶ ተሰጥቶን ነው ምንዘምረው የነበረው ዛሬ ዛሬ ግን የማንም ተራ አርቲስት ተነስተው መዝሙር ይዘምራሉ ዘምረው ዘማሪት ዘማሪ ይባላሉ ንስሀ ግብተው ወደ እግዚአብሔር ቤት ተመልሰው ነው እንዳንል በሌላኛው ቀን በሜካፕ በአጭር ቀሚስ በቃ ምን አለፋሽ በአጭሩ በአለም ውስጥ እናያቸዋለን ይባስ ብለው ማህተባቸውም አውልቀው አይተናል ይሄ ነገር ከተዋህዶ ስርአተ አስተምሮ እንዴት ይታያል ቤተክርስቲያናችን ይሄ ነገር እንዴት ታየዋለች

#መልስ
ጠያቂያችንን ከልብ እናመሰግናለን የሕይወትን ቃል ያሰማልን!!

ቤተ ክርስቲያናችን ባህረ ጥበባት የጥበባት ባህር ናት በመሆኑም ጥበብንና ጥበበኞችን አትቃምም አትደግፍም : :አብዛኛውን ጊዜ እንደውም ለጥበብ ባለ ውለታ ሆና ትገኛለች በየ ቴሌ ቪዥን መስኮት የምንመለከታቸው አብዛኞቹ አርቲስቶችም ከቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህር ቤቶች የተገኙ የማህጸኗ ፍሬ ናቸው:: እዚህ እየዘመሩ እዚያ መዝፈናቸው እዚህ የሀገር ልብስ ለብሰው እዛ ሚኒ እስከርት እዚይህ በማዕተም እዛ ማውለቃቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጥርጥር የሌለው ስህተት ነው:: ሆኖም እንደዚህ ከሆናችሁ አንዱን ያዙት ወይ ዝፈኑ ወይ ዘምሩ ብለን ግን ልንፈርድባቸው አይገባንም ዝም ብሎ ከመዝፈን እየዘመሩ መዝፈን የተሻለ ነው :: ማን ያውቃል ይመልሳቸው ይሆናል

ተዋናይነት ለአንዳንዶች ሕይወታችው መደበኛ ስራቸው የሆኑ ብዙ ተዋንያን ሊኖሩ ይችላሉ ስለሆነም አንዱን ያዙ ወይ ዘምሩ ወይ ዝፈኑ ብሎ ማስጨነቁ ግሮሮዋቸው ላይ ቆሞ የሕይወታቸው እልውና መፈታተን ነው:: እግዚአብሔር አምላክ በስተ መጨረሻ ሥራ ሊሰራባቸው ይችላል ስለዚህ እየተወኑ ይዘምሩልን እየዘፈኑ ያመስግኑልን በታሪክ እንደምናውቀው አንዳንዶች በስተ መጨረሻ ንስሐ ሲገቡ ዘማሪ ሲሆኑ ይታያል በዚህም እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ተከታዮቻቸው(አድናቂዎቻቸውንም ) ጭምር የሚመልሱ ይሆናሉ:: የሚገርመው የተዋንያኖቹ ሳይሆን የአዘጋጆችና ካሜራ ማን የሆኑ ሰዎች አመለካከት ነው ሰይጣን ክርስቲያኖችን አብዝቶ መፈተኑ አይቀርም:: የየ ሰንበት ትምህር ቤቱ ወጣት ሁሉ ተዋንያን ለመሆን ሲፈልግ ለምን መስቀሉን ከአንገቱ እንዲያወልቅ ይገደዳል? ትወና ማለት እኮ ማስመሰል እንጂ መሆን አይደለም :: አንዳንድ ዘፋኖች ሲዘፍኑ እጃችሁን ወደላይ ወደላይ ይላሉ አሉ ሕዝቤም እውነት መስሎት እጁን ሲያነሳ ጓደኞቻቸው ኪስ እየገቡ ብዙዎችን እንደሚያጥቧቸው ሰምቻለሁ ታድያ አዘጋጆችስ (producer ) ምን ነካቸው ለቀረጻ ስለማይመች መስቀልህን መስቀልሽን አውልቂ አውልቅ እያሉ ለሌባው ዲያቢሎስ ሕይወታችንን የሚሰርቁት ለምንድነው? ከሳጥናኤል ጋር ተመሳጥረው ይሆን???


ሌላውን ትተን ሁል ጊዜ በየ ምሽቱ ቤታችንን እያንኳኳ "ቤቶች" የሚለንን ተከታታይ ሲት ኮም የቴሌ ቪዢን ድራማን እንኳን መስቀል አድርገው እንዳይቀረጹ ተዋንያን ይከለከሉ ነበር:: የሰውን ዘር ሁሉ እንዳይጠፋ የሚጠብቅ መስቀል አውልቁ ካልሆነ አትሰሩም እያለ ዘሩ ዘራችንን አቀለጠ::ለነገሩ መስቀል የሌለው ስለ መስቀል ክብር ሊያውቅ ሊረዳ አይችልም::

በዚህ ሁኔታ ታድያ በአገኙት አጋጣሚ ዕውቅናቸውን ለእግዚአብሔር ዕውቅና ያዋሉ ተዋንያን ዘማሪዎቻችንን ልናመሰግናቸውና በርቱ ጠንክሩልን ልንላቸው ይገባል እንጂ ልንወቅሳቸው አይገባም ባይ ነኝ::
እንደውም ዝማሬ መላእክትን ያሰማለን እስከ መጨረሻው በቤቱ ይትከልልን🙏አሜን

#ጥያቄ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉሻል የተባለው ለድንግል ማርያም ነው ወይስ ለኢየሩስ አሌም ነው?

#መልስ
ቃሉ የተናገረችሁ እሯሷ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት የተናረገችሁም ስለ እራሷ ነው

"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 48)


እንዴ ስለ እሯሷ እንዲ ተናገረች ቢሉ
1) እውነተኛው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሴቶች ሁሉ የተለየች እንደሆነች ስለነገራት

2) እመቤታችን ነቢይት ስለሆነች ፀጋን የተሞላች ነችና የጉደላት ፀጋ የለም በመሆኑም ወደፊት የሚሆነውን የሚደረገውን አውቃ በአንድ በቅዱስ ገብርኤልና በአንድ ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል አለች በዚም እውነት ተናገረች ትውልዱ ሁሉ ብጽይት እንላታለንና

ምነው ይህ ሁሉ ሃይማኖት ይህ ሁሉ መናፍቅ ባለበት ዓለም እንዴት ሁሉ ብጽይት ይሉኛል አለች ብለው ቢጠይቁ

ሁሉ ያለችሁ

1) አማኝ ትውልድን ሁሉ ማለቷ ነው ወላዲተ አምላክነቷን ዘላለማዊ ድንግልናዋን አማላጅነቷን ያመኑ ሁሉ ምዕመናን ያመሰግኑኛል ማለቷ ነው:: ይህም የመጻሕፍ ቅዱስ የአገላለጽ ባህል ነው ለምሳሌ በሉቃስ ወንጌል 2÷1 ላይ እንዲ ተብሎ ተጽፎል

"፤ በዚያም ወራት 👉ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች። "

አውግስጦስ ቄሳር ዓለምን በሙሉ አልገዛም በዓለም ታሪክም እስከ ዛሬ ድረስ ዓለምን አንድ ንጉስ ጠቅልሎ አልገዛትም


አውግስጦስ ቄሳር ትዛዙን ያወጣው ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ብሎ ነው :: ምን ማለቱ ብለን ልንጠይቅ ይገባል አውግስጦስ ቄሳር ዓለሙ ሁሉ ይጻፍ ዘንድ ያለው በግዛቱ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሳይቀሩ ለማለት ነው እንጂ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያሉ ሰዎች ሁሉ ይጻፉ ማለቱ አይደለም

በዚሁ በንጉሡ ትዕዛዝ እና በቅዱስ ሉቃስ አገላለጽ ዓለሙ ሁሉ የተባለው በግዛቱ ሥር የሚገኙት ሰዎች ለማለት እንደሆነ እመቤታቸንም ትውልዱ ሁሉ ስትል ሁሉን በአንድ ጨፍልቃ ሳይሆን አማኝ ትውልድ ሁሉ ማለቷ መሆኑን መገንዘብ ያሻል:: በእርግጥ በስተ መጨረሻ እመቤታችንን የማያመሰግናት ትሁልድ የለም ክብሯ ሲገባው አማላጅነቷ ሲታወቀው ሁሉ ብጽይት ይሏታል ይሰግዱላታልም::
"፤ የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። " ተብሎ በነቢይ ተነግሮላታልና::

(ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 14)
#ምን_እንጠይቅልዎ
#ጥያቄዎቻችሁን በሚከተሉት አድራሻዎች መስደድ ይችላሉ

👇👇👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
" #በቸርነትህ_ዓመታትን_ታቀዳጃለህ።"
____________________________

እግዚአብሔር አምላክ ለሰዎች ከሰጣቸው መልካም ስጦታዎች አንዱ ጊዜ ነው። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የዘመናት ጌታ የጊዜ ባለቤት እግዚአብሔር አምላካችን እንደቸርነቱና እንደ ምሕረቱ ብዛት ዓመትን እንደሚያቅዳጅ፣ እንደሚሰጥ ሲገልጥ "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ" በማለት ዘምሯል።

ዘመን ለሰው ልጆች የተሰጠ ድንቅ ስጦታ ነው። ይህን ድንቅ ስጦታ አስረዝሞ የመጠቀም አልያም አሳጥሮ መጎዳት ያለው በሰው እጅ ላይ ነው።

#ዘመናችን እንዴት ይርዘም?
___________________


አንደበትን ከክፉ እንከልከል ፡ አንደበታቸውን ክፉ ከመናገር ያልከለከሉ ብዙዎች በጎውን ዘመን አላዩም። በዙዎች ዘመናቸው እንደ ምድረ በዳ አበባ ቶሎ ረግፏል። ሐናንያ እና ሰጲራ በአንደበታቸው ሐሰት ቢገኝ ከሰይጣን ጋር ተወዳጅተዋልና በጎውን ዘመን እንዳያዩ ዘመናቸው አጥሮ በሞት ተሸኝተዋል። የሐዋ 5፡1 በአንደበታቸው ክፋት የገባባቸው ሌሎችም እግዚአብሔር ዘመናቸውን አሳጥሮባቸዋል። መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር 34፡12 ላይ"ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ? አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።" በማለት ይናገራል።

ሌላው ዘመንን ማርዘሚያ ብርቱ መድኃኒት እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እግዚአብሔርን መፍራት ከሚያስገኛቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አንዱ ዘመንን ማስረዘም ነው። "እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፤ የኀጥኣን ዕድሜ ግን ታጥራለች።" ምሳ 10፡27

ከኃጢአት መጠበቅ ራስን በቅድስና ሕይወት ኖር ፡ በዘመነ አበው የነበሩ ቅዱሳን ከአዳም አንስተን ብንመለከት በዘመናቸው እጅግ የሸመገሉና በርካታ ዓመታትን የኖሩ ነበሩ። ለአብነትም አዳም 930 ማቱሳላ 969 ኖህ 950 ወዘተ ... የእነዚህ ሰዎች ረጅም ዘመን በምድር ላይ የመኖራቸው ምሥጢር ምንድን ነው ብለን ብንመረምር በአካሄዳቸው እግዚአብሔር አምላካቸውን ማስደሰታቸውና ከኃጢአት መጠበቃቸው በቅድስናም መኖራቸው ነው። የሰው ልጅ በሚሠራቸው ገቢር ኃጢአት ምክንያት ዘመኑ ማጠር ጀመረ። በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ አባቶቻቸው ዘጠኝ መቶ የሚቆጠር ዓመትን መኖር አልቻሉም። ይልቁንም የኃጢአት ግድግዳ ከእግዚአብሔር ቢለያቸው የዘመናቸውና የዕድሜ ጣርያ 120 ዓመት ሆነ። ዘፍ 6፡3 "እግዚአብሔርም፦ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ።" በዚህም አላበቃም በዳዊት ዘመን ይህ የዕድሜ ጣርያ ወደ 70 እና 80 ዓመት ወረደ። "የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው።" መዝ 90፡10 እነ አዳም 900 ዓመት ኖረው ያልደከሙት በዚህ ዘመን በ80 እና 90 ዓመት የሚደከምበት ምሥጢሩ የሰው እግዚአብሔርን መበደልና ኃጢአትን የሙጥኝ ማለት ነው። በእምነታቸው በምግባራቸው እግዚአብሔርን ያስደሰቱት ቅዱሳኑ ግን ዘመናቸው ረዝሞ ዕድሜያቸውን ጠግበው አልፈዋል። 1ኛ ዜና 29፡28 ፣ 2ኛ ዜና 24፡15 ፣ ኢዮ 42፡ 17

#ምን_እናድርግ?
____________
እግዚአብሔር አምላካችን አዲሱን ዘመን እናይ ዘንድ አድሎናል። በቸርነቱም ዘመናትን አቀዳጅቶናል። ያቀዳጀንን ዘመን የመቀደስና የመጠቀም ኃላፊነቱንም አብሮ ሰጥቶናል። ይህን ዘመን እንዴት እንቀድሰዋለን? ቅድስናን በመጨመር፣ ኃጢአታችንን በመቀነስ ፣ ንስሐን በማብዛት ፣ ያለንን በማካፈል ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠንከር ዘመኑን መቀደስ እንችላለን።

ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን እግዚአብሔር አምላካችን ክብር ምስጋና ይግባው። ዘመኑ የሰላም የጤና የንስሐ በሥጋው ወደሙ ምንታተምበት በጎውን ምንሰማበት ቤተ ክርስቲያናችን ምታብብበት ያድርግልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

(አቤኔዘር ወልደ ተክለሃይማኖት)

05/13/2013 ዓ.ም