ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ። መዝ 4:3
ሰማዕት ጻድቅ ማለት እውነተኛ ማለት ነው:: የሚገኘውም በክርስቶስ ጌትነት ፈጣሪነት አምኖ እንደ እርሱ በመመላለስና የጽድቅ ሥራ በመስራት ነው። በክርስቶስ እኖራለው የሚል ክርስቶስ እንደተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል 1ዮሐ 2:6 ልጆች ሆይ ማንም አያስታችሁ ክርስቶስ ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው 1 ዮሐ 3 :7 እንዲል :: በክርስቶስ ማመን ማለት በእርሱ አምኛለሁ እያሉ ዓመጽ የተባለ ኃጢዓትን እየፈፀሙ መመላለስ ሳይሆን በጎ ሥራ እየሠሩ እርሱን መከተል ነው 1ዮሐ 2:6 እግዚአብሔርን የምትወዱት ሁሉ ክፋትን ጥሉ መዝ 96:10 እንዲሁም ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ ዮሐ 14:15 እንደተባለ ነቢዩ እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ ሲልም በመጀመርያ ጻድቃን በደስታቸውና በምቾታቸው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራቸውና በኃዘናቸው ጊዜም ጭምር እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑ የሚያስረዳ ነው። ኢዮብ 1:1-22 እንባ 3:17 ዳግመኛም በጻድቁ መልካም ሥራ በጎነት ታማኝነት ታላቅ እምነት ቅንነት ተጋድሎ እንደታወቅ እንደተወደሰ እወቁ ተረዱ ማለት ነው:: በቅዱሳን የቅድስና ሥራ እግዚአብሔር ይመሰገናልና ማቴ 5:16 ገላ1:23 ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እግዚአብሔር ቅዱሳን በስፋትና በጥልቀት የሚነግሩን በእነርሱ አኗኗር እግዚአብሔር ስለሚነበብ ነው :: ስለሆነም ቅዱሳንን ማሰብ እግዚአብሔርን ማሰብ ነው ቅዱሳንን ማክበር እግዚአብሔርን ማክበር ነው ሮሜ 13:7 - 8 : 30 ቅዱሳንን መውደድ የመረጣቸውን እና የወደዳቸውን እግዚአብሔርን መውደድ ነው ኤፌ 5:1 ዮሐ 13:2 ከጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከጻድቃን ከሰማዕታት ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን !!

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ መላእክት አንዱ ሚካኤል ነው ሔኖክ 6÷1-2

የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያ የቅዱስ ያዕቆብ ወንድም የሆነ ይሁዳ መናፍቃኑ አንቀበልም ብለው የዓመጽ ቃል ካንደበታቸው ከሚወረውሩበት ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ከሆነና አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉ ሞተ ሥጋ ሳያገኘው ከተሠወረ ከነቢዩ ሔኖክ የትንቢት መጽሐፍ ጠቅሶ ሲናገር "ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ በኃጢአተኛነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም በእርሱ ላይ ስለተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳን ጋር መጥቶአል" ይሁዳ 1÷14 ሔኖክ 1÷9 ብሎ

የሔኖክን መጽሐፍ ጠቅሶ ስለጌታችን ፈራጅነት ስለእኩያን ሰዎች የክፋት ሥራና ክርስቶስ ከቅዱሳን ጋር የሚመጣበትን ነገረ ምጽዓትን አንስቶ ይነግረናል፡፡ እኛም የሐዋርያው ልጆች ነንና እርሱን ተከትለን ነቢዩ ስለ ቅዱስ ሚካኤል የተናገረውን ቃል ጠቅሰን ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ፡፡ በነቢዩ ሔኖክ መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል

* ለሰው በጎን የሚያደርግ መልአክ ነው *

ቅዱሳን መላእክት ከተፈጠሩበት ዓላማዎች መካከል አንዱ ለሰው በጎ ነገርን ማድረግ ነው ፡፡ ከእነዚህ በጎ ነገሮች መካከል አንዱ በእግዚአብሔር የታመኑና የሚታመኑ ሰዎችን ከሚቃጣባቸው ክፉ ነገር ሁሉ ማዳንና መታደግ ነው ፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል ያድናቸውማል" መዝ 33÷7 ብሎ እንደመሠከረ ፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ታቃኝቶ በቃል የመሠከረውን የቅዱሳን መላእከት ሰዎችን ከክፉ ነገር የመታደግ ሥራ የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ያዕቆብ በተግባር እንደተፈጸመለት ሲመሠክር "ከልጅነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፉ ነገርም ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነዚህ ብላቴኖችን ይባርክ" ዘፍ 42÷12-16 ብሏል፡፡ በዚህ የቅዱስ ያዕቆብ ምስክርነት የጌታችን የኢየሱስ መላእክት ሰዎችን ከክፉ እንደሚያድኑና ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ እንደሚባርኩ እንረዳለን ፡፡ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምርጥ ዕቃ የዓለም ብርሃን ብሎ የመሠከረለት ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን መላእክት ለሰው የሚያደርጉትን በጎ ሥራ አንስቶ ሲያስተምር "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መላእክት አይደሉምን?" ዕብ 1÷14 ይላል፡፡ የቅዱሳን መላእክት ታላቅ ትጋትና ማገዝ የሰው ልጅ መዳን የተባለ መንግሥተ ሰማያትን ይወርስ ዘንድ እንደሆነ ከተነገረን ይህን ለመቀበል ሰዎች ለምን ቸገራቸው ? ቅዱስ ሚካኤልም ለሰው በጎ ነገርን በማድረግ የሚታወቅ መልአክ ነው፡፡ ይህ ለሰው የሚያደርገው በጎነትን መጻሕፍት አምልተው ይመሰክራሉ፡፡ ነቢዩ ዳንኤል "በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል" ዳን 12÷1 ይላል ፡፡ ይህ የነቢዩ ቃል አስጨናቂ የተባለው የምጽዓቱ ቀን ዋዜማ እየቀረበ ሲመጣ ፈታኙም ሲበረታ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለምእመናን እንደሚለምን በግልጽ ያሳየናል ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ለሰው በጎ ነገር ነገር ማድረግ የት አለ ? ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስ ስለ ሙሴ ሥጋ የማይገባውን እየተናገረ በወሻከተም ጊዜም በእግዚአብሔር ስም ገሥጾታል ይሁዳ 1÷9 ፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነቢዩ ዳንኤልን ሊረዳው በመጣ ጊዜ የፋርስ መንግሥት አለቃ ዲያብሎስ ሊቋቋመው እንደሞከረና ቅዱስ ሚካኤል እንዴት እንደረዳው ሲገልጽ "ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ" ዳን 10÷13 ብሏል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ለሰዎችም ለመላእክትም በጎ ነገርን የሚያደርግ የዋህ ፈጣሪው በሰጠው ኃይልም ብርቱ መልአክ መሆኑን ከዚህ መረዳት ይቻላል ራእይ 10÷1፡፡

* ለሕዝቡ ታዛዥ መልአክ ነው *

ቅዱስ ሚካኤል ለሕዝቡ በጎ ነገርን ለማድረግ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ መልአክ ነው "ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል" መባሉም ይህን ያጠነክርልናል ፡፡ ሊቃነ መላእክት ሠራዊተ መላእክት ለፈጣሪያቸው ይታዘዛሉ የመታዘዛቸውም ዓላማ የእግዚአብሔር ሕዝብን ከክፉ ነገር ሁሉ መታደግ ነው ፡፡ ታዛዥነት ከማገልግል ጋር በእጅጉ ይያያዛል ፡፡ ቅዱሳን መላእክት "ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም" ዕብ 1÷14 መባላቸውም በእውነት ለክርስቲያኖች ደኅንነት የሚታዘዙና ትሑታን መሆናቸውን ያመለክተናል፡፡

* የከበረ መልአክ ነው *

ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሔኖክ ቅዱስ ሚካኤል የከበረ መልአክ መሆኑን መሠከረ ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልን ያከበረ እግዚአብሔር ነው ሮሜ 8÷30-31፡፡ ክብር ጌትነት ከፍተኛነት ዋጋ ጥቅምና መወደድ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሰጣቸውን ክብር መግለጽ ከቃላት ከሐሳቦችና ከስብከትም በላይ ነው ምሳ 28÷12 1ጢሞ 5÷17 በመሆኑም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በፍጥሞ ደሴት ከሰማይ ሲወርድ ያየውን መልአክ ክብር ሲገልጽ "ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች" ራእይ 10÷1 ራእይ18÷1 ብሏል ፡፡ የቅዱሳን መላእክት ክብር ምድር የተባለ የሰውን ፍጹም ልብ በእውነት እንደሚያበራ ወደ ብርሃን ክርስቶስም እንደሚበራ ያሳየናል ፡፡ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ያከብራሉ ስለሚያከብሩትም እርሱም ያከብራቸዋል "ያከበሩኝን አክብራለሁ የናቁኝም ይናቃሉና" ብሎ እንደተናገረ 1ሳሙ 2÷29-30፡፡ የጌታ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የጌቶቹ ጌታ ነገሥታቱ ንጉሥ የሆነ እርሱ ፈጣሬ ፍጡራን አምጻኤ ዓለማት ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ክብርን ሰጥቶታልና ከምጽዓቱ አስቀድሞ "አንተ የምትተኛ ንቃ ክርስቶስ ያበራልሃል" የሚለውን የወንጌል መለከት ድምጽ እያሰማ ምጽዓቱን እንዲያበሥር ሹሞታል ማቴ 24÷31 ማቴ 25÷31 ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሲመሠክር "ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ (በቅዱስ ሚካኤል) ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና" 1ተሰ 4÷16 ይሁዳ 1÷9 ብሏል ፡፡
ይቆየን።

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
+++ እስራኤልን #የሚያድን #አዳኝ +++
መጽሐፍ ቅዱስ "እስራኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ እግዚአብሔርም የሚያድናቸው አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሳላቸው" ይላል። መሳ: 3:9 መሥፍኑ ጎቶንያል እግዚአብሔር ያስነሳው አዳኝ የሚያድን መባሉን ትመለከታላችሁን? ማዳን የማነው? የእግዚአብሔር! መስፍኑ ጎቶንያልን የሚያድን አዳኝ አድርጎ ያስነሳው ማነው? እግዚአብሔር! ጎቶንያል የሚያድን አዳኝ መባሉ የእግዚአብሔርን አዳኝነት ያስተሐቅራልን? በፍጹም! ታድያ ድንግል ማርያምን በጸጋ የተሞላች መድኃኒት ክርስቶስን የወለደች በጀርባዋ ያዘለች ጡቶቿንም ያጠባች በማዳኑም ጉዞ ያልተለየች የደስታ መፍሰሻ ምክንያተ ድኂንም በመሆኗ የምታድን አዳኝ ብንላት ችግሩ ምንድነው ? ከጎቶንያል የሚልቅ ጸጋ አልተሰጣትምን? እርሷ መድኃኒት ቤዛ የምታድን መባሏን የምትቃወሙ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴን ቤዛ ጎቶንያልን አዳኝ የሚያድን ሲልስ ምን ትሉ ይሆን? ስህተት ነውን?
*** ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስን "ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ በእነዚህም ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ" 1ጢሞ 4:16 በማለት ይመክረዋል:: ጢሞቴዎስ ታድናለህ ሲባል ማንን ነው የሚያድነው? ሰዎችን አይደለምን? እንዴት ነው የሚያድነው? በእምነት የሚያጸና በምግባር የሚያቀና መልካም አኗኗርን እንድንኖር የሚያደርግ ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ትምህርት በማስተማር አይደለምን? ሰዎችን ወደ መድኃኒት ክርስቶስ በትምህርትም በኑሮም የሚመሩ አዳኞች የሚያድኑ ታድናላችሁ አድኑ ተባሉ:: ሐዋርያትን ጌታችን ወደ ዓለም ሲልካቸው በሰጣቸው የማዳን ጸጋ ሰዎችን ከርኩሳን መናፍስት ከእኩያን አጋንንት እንዲታደጉ እንዲያድኑ በማዘዝ ነው "ሂዱ አጋንንትን አውጡ ሕሙማንን ፈውሱ(አድኑ)" ማቴ 10: 8 እንዲል። በዚህ ሐዋርያዊ ተልእኳቸው በደዌ ሥጋ በአጋንንት እስራት የተያዙትን በተአምራት በደዌ ነፍስ በኃጢአት የተያዙትን በትምህርት አድነዋል። እንደ እነርሱ ያሉ የእነርሱን ፍኖት የተከተሉ እውነተኞች ቀሳውስትም በጸሎታቸው የተቀደሰውን ቅብአት እየቀቡ ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ በደዌ ሥጋ በደዌ ነፍስ(በኃጢአት) የተያዙትን እንዲያድኑ ታዘዋል በዚህም የሚያድኑ ተብለዋል ያዕ 5:14-15 እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከናንተ በፊት ሰድዶኛል :- ቅዱስ ዮሴፍ ዘፍ 45:5 ዮሴፍ የንጽህና ምሳሌ ነው:: የጴጥፋራ ሚስት ለኃጢአት ብትጋብዘው እምቢ ብሏታልና:: ዘፍ 39:7-17 ዮሴፍ ይቅርታ የማድረግ ምሳሌ ነው በከንቱ የጠሉትን ለእስማኤላውያን በሃያ ብር የሸጡትን በጉድጏድ የጣሉትን ወንድሞቹን ሊበቀል እየቻለ ይቅርታ አድርጎላቸዋልና:: ዘፍ 45:1 ዮሴፍ የበረከት ምክንያት ነው " እግዚአብሔር የጴጥፋራን ቤት ውስጡንም ውጭውንም ስለ ዮሴፍ ባረከው የእግዚአብሔርም በረከት በውጭም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ " እንዲል ዘፍ 39:5 :: በዚህም " የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው " ምሳ 10:7 "በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው" ምሳ 10:6 "በጻድቃን በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች" ምሳ 11:11 የሚሉትም ቃላት እውነተኞች መሆናቸውን አወቅን:: ዮሴፍ ከተደረገበት ነገር አንዱ በክፋት አንዳች ክፉ ሳይገኝበት በገዛ ወንድሞቹ በከንቱ መጠላቱ ከዚያም ባለፈ መጀመርያ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች ኇላም ለግብጻውያን መሸጡ ነው። ዮሴፍ ወንድሞቹ ከሸጡት በኇላ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ እግዚአብሔር ረድቶት ምሥጢርን ገልጦለት በግብጽ ቤተ መንግሥት ታላቅ ለመባል በቃ:: ዓለም በሙሉ እህል ፍለጋ ከረጢቱን ይዞ ወደ እርሱ ተመመ:: ወንድሞቹም መጡ በክፋት። ሳይጠላቸው ሊበቀላቸው እየቻለ ሳይበቀላቸውም "እኔን በመሸጣችሁ አትዘኑ እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከናንተ በፊት ሰድዶኛልና" ዘፍ 45:5 አላቸው ይላል መጽሐፍ ቅዱስ:: "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ድንቅ ነው" መዝ 67(68) :35 እንዲልም እግዚአብሔር ማዳን እየተቻለው ፈቃዱን የፈጸሙ ቅዱሳኑን ምክንያት አድርጎ ማዳኑን እንደሚፈጽም ከዚህ ታሪክ እንማራለን:: ዮሴፍ "ህይወትን ለማዳን ተላክሁ" እንዳለ አትሰሙምን? ዮሴፍ እኮ የእግዚአብሔር ህይወትን ለማዳንም የላከው እግዚአብሔር ነው:: እነሆ ከዮሴፍ የምትበልጥ ከዚህ አለች እርሷ የዮሴፍን የአብርሃምን ፈጣሪ ክርስቶስን የወለደች ናትና ሉቃ 1:28-49 ። የዮሴፍን ፈጣሪ ክርስቶስን የወለደች ብርሃን የወጣባት ምሥራቅ ናትና :: ኢሳ 9:2 :6 ዮሐ።4:12-15 :: በረከትን የሚያድል የበረከት አባት ክርስቶስን ወልዳለችና ሉቃ 2:1-15 ። "ዮሴፍ ሕይወትን አዳነ" ብሎ መጽሐፍ ከነገረን እመቤታችን በተሰጣት ጸጋ ህይወታችንን ከመተተኞችና ከክፉዎች ታድናለች ብንል ችግሩ ምንድነው? መናፍቃኑ ተሸክመውት ያለውን መጽሐፍ አያስተውሉትም እንጂ ቅዱሳን ሐዋርያት " እንዲሁ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን።ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለው ብሎ አዞናል "ብለው የተልእኮቸው ዓላማ ምን እንደሆነ እንደተናገሩ ይመሠክርላቸዋል የሐዋ 13:47 ። ሐዋርያት ለምን ወደ ዓለም ተላኩ? ሰዎችን።የክርስቶስን ቃል አስተምረው መክረውና ገስጸው በትምህርታቸው።ለክብር ለማብቃት ነው:: በዚህም "ለማዳን የተላኩ" "ብርሃናት" ተባሉ ማቴ 10:1-16። ሐዋርያት ለማዳን ተልከናል ሲሉ ራሳቸውን ከክርስቶስ ጋር እያፎካከሩ ነውን ? አይደለም !! ቅዱሳን እንዲሁም እመቤታችን "መድኃኒት ቤዛ የሚያድኑ ለማዳን የተላኩ" ለምን እንደተባሉ መርምሮ በቀና አእምሮ መረዳት መልካም ነው::

የእናቱ የእመቤታችን አማላጅነት የልጇ ቸርነት አይለየን !!
መልካም በዓል!!
በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

@AwediMeherit
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Audio
"እውን መጽሐፈ ሲራክ ሴቶች እህቶቻችንን የሚዘልፍ የሚያጥላላ እና የሚነቅፍ መጽሐፍ ነው?"

መጽሐፈ ሲራክ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ:

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ


👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
5. ይሆንልኛል ይደረግልኛል ብላችሁ እመኑ አትጠራጠሩ
እምነት አመክንዮ አይደለም በአመክንዮ የምንመረምራቸው ብዙ
ነገሮች እንዳሉ በእምነት ብቻ የምንረዳቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፡፡
እነዚህም ነገሮች የእምነት ጉዳዮች ናቸው ፡፡ ባህሩን እንደየብስ
ትረግጣላችሁ ስንባል በእምነት አዎን እንላለን ‹‹ ብሰጥምስ
ባይሆንስ እንዴት ? ›› ባልን ጊዜ እንሰጥማለን ማቴ 14 ፡ 30 ፡፡
አመክንዮ እንዴት ? ሲለን መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ይለናል፡፡
አመክንዮ የማይመስል የማይሆን ሲለን መጽሐፍ ሆኗል ይሆናልም
ይለናል ፡፡ ጌታችን በወንጌል ሐዋርያቱን ካስተማራቸው በኋላ
በእምነት እንደተቀበሉት አውቆ ያገኙትን ጸጋ ሲነግራቸው ‹‹ እናንተ
ስለነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ ›› ዮሐ 15፡4 ብሏቸዋል
፡፡ ንጹሐን መሆናቸውን የሚያሳየን መነጽር የሚያስረዳን አስረጂ
እምነት እንጂ ሌላ አይደለም ::
ይቆየን
የእርሱ ቸርነት የእናቱ አማላጅነት አይለየን !!

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
የነነዌ ሰዎች ግን በእምነታቸው በንስሐቸውና በጾማቸው እግዚአብሔር አስደሰቱት በዚህም በሐዲስ ኪዳን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንስሐ በማይገቡ ላይ እንደሚፈርዱ ሲመሠክርላቸው "የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና" ማቴ 12÷41፡፡ ስለሆነም ከጥፋት እንድንድን ከክፉ ሐሳባችን ንግግራችንና ተግባራችን ተመልሰን ንስሐ እንግባ ፡፡ የንስሐ ኃዘን መዳንን የዓለምም ኃዘን ሞትን ያመጣልና 1ቆሮ 7÷10 ፡፡ እምነትን ንስሐንና እውነተኛ ጾምን ገንዘብ አድርገን ለክብር ለመብቃት እንድንችል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን!! እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱሳንም ሁሉ በጸሎታቸው አይለዩን አሜን!!

በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
"እግዚአብሔር ሆሴዕን። ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው። " ሆሴ 1: 2

ጋለሞታ ሴት ለነቢይ ትገባለች ወይ ለሚለው ጥያቄ የተሰጠ መልስ

በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
Audio
#ዓውደ_ስብከት

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

"መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል።" 1ኛ ጢሞ 6:12

ገድልን ለሚቃወሙ ሰዎች የተሰጠ ትምህርትና መልስ።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ዓውደ_ስብከት

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።" ምሳ 10:7

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

✟ለአዕዛኒከ

ሰላም : ለአዕዛኒከ : እለ : ያጸምዓ : ምሳሌ : ዘሐዋርያት : ቡሩካን : ወዘነቢያት : ሰብአ ኩፋሌ ፤ ተክለ ሃይማኖት ምድራዊ ወመልአክ : ዘሉዓሌ ።
ምሥጠኒ : ውስተ ቤትከ : ዘአረፈቲሀሃ : ቢረሌ ። ከመ : አዕርፍ : ባቲ : እምብካይ : ወወይሌ ።

ትርጉም :- ✟ ለአዕዛኒከ ( ለጆሮሆችህ )

ተክለሃይማኖት ሆይ ፤ በክቡራን ነቢያት የተነገረውን በክቡራን ሐዋርያት የተሰበከውን መልካሙን ምሣሌ ነገር ለሚያደምጡ አዕዛኖችህ ሰላም እላለሁ ።
ቅዱስ አባቴ ሆይ በተፈጥሮ ጠባይህ ምድራዊ ሰው ስትሆን ፤ በሥነ ምግባርህ ሰማያዊ መልአክ ነህኮን ።
ከለቅሶና ከዋይታው በእርሷ ዐርፍ ዘንድ በወርቅና በዕንቁ በተሠራችው በሉዓላዊት ቤትህ
በዚያ ወስደህ አስቀምጠኝ

📜 መልክአ ተክለሃይማኖት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ሆሴ 1፥2

#ጋለሞታ እንዴት ለነቢይ ልትሆን ትችላለች? ጋለሞታ ማለት ምን ማለት ነው?

ሙስሊሞች ላነሱት ጥያቄ የተሰጠ መልስ።

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
አድኗል 2ነገ 13፡20 ፡፡ ይህ ታላቅ ነቢይ ተመርዞ የምድሪቱንም የሴቶቹንም ፍሬ ሲጨነግፍ የነበረውን የኢያሪኮን ውሃ አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ ብሎና በማሰሮው ጨው ጨምሮ ወደ ሚያጨነግፈው ምንጭ ጨዉን ጨምሮ ውሃውን ከፈወሰው በኋላ በቤቴል የነበሩ ብላቴኖች ተሰብስበው ‹‹ አንተ መላጣ ውጣ አንተ መላጣ ውጣ ›› ብለው አፌዙበት እነሆም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥተው ዐርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው ይላል 2ነገ 2፡2-25 ‹‹ለነገር ሁሉ ምሳሌ አለው›› ዕብ 10፡1 እንዲል ዓለም የተፈወሰበትን ጨው ክርስቶስን የወለደች አዲሲቷን ማሰሮ ድንግል ማርያምን የምትሳደቡ እነደ ኤልሳዕ ያሉ አገልጋዮቹንም በስድብ የምታጥረገርጉ መጨረሻችሁ ምን ይሆን ?
+++ ቅዱስ ሚካኤል አልተሳደበም!! +++
መችም የቅዱስ ሚካኤል ስም ሲነሳ ዓይናችሁ በደምፍላት እንደሚፈጥ ጆሯችሁ በክፋት እነደሚቀላ አንደበታችሁ ለስድብ እንደሚሳል ይታወቃል ፡፡ የተባረኩት በምድር እንደ አእማድ ከሚታዩት አንዱ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲሁም የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ የእናንተ ድፍረት የተሞላበት ስድብ ከቅዱስ ሚካኤል ትኅትና ጋር በማነጻጸር እንዲህ ይላሉ ‹‹ ደፋሮችና ኩሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም ›› 2ጴጥ 2፡10-12፡፡ ‹‹ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም ›› ይሁዳ 1፡9 የውጭዎቹ ሉተራውያን እንዲሁም የከፋችሁት የውስጦቹ መልማይ አቀባዮቻቸው ተሐድሶዎች ሆይ ክርስቶስ ያልተከለው ተክል ይቆረጣል እናንተ ግን አስተውላችሁ ስድባችሁንና ንቀታችሁን ካልተዋችሁ ለስድባችሁም ንስሐ ካልገባችሁ በስማቸው አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ ባላፈረባቸው በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንደምትቆሙ ይህን ዕወቁ ዕብ 11፡ 16 ሮሜ 14፡ 10 ያን ጊዜም ነቢዩ እንደተናገረው በእርሱ ፊት ድዳዎች ትሆናላችሁ፡፡‹‹ በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ::›› መዝ 30፡18 እንዲል ፡፡ ከጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
5. ይሆንልኛል ይደረግልኛል ብላችሁ እመኑ አትጠራጠሩ
እምነት አመክንዮ አይደለም በአመክንዮ የምንመረምራቸው ብዙ
ነገሮች እንዳሉ በእምነት ብቻ የምንረዳቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፡፡
እነዚህም ነገሮች የእምነት ጉዳዮች ናቸው ፡፡ ባህሩን እንደየብስ
ትረግጣላችሁ ስንባል በእምነት አዎን እንላለን ‹‹ ብሰጥምስ
ባይሆንስ እንዴት ? ›› ባልን ጊዜ እንሰጥማለን ማቴ 14 ፡ 30 ፡፡
አመክንዮ እንዴት ? ሲለን መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ይለናል፡፡
አመክንዮ የማይመስል የማይሆን ሲለን መጽሐፍ ሆኗል ይሆናልም
ይለናል ፡፡ ጌታችን በወንጌል ሐዋርያቱን ካስተማራቸው በኋላ
በእምነት እንደተቀበሉት አውቆ ያገኙትን ጸጋ ሲነግራቸው ‹‹ እናንተ
ስለነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ ›› ዮሐ 15፡4 ብሏቸዋል
፡፡ ንጹሐን መሆናቸውን የሚያሳየን መነጽር የሚያስረዳን አስረጂ
እምነት እንጂ ሌላ አይደለም ::
ይቆየን
የእርሱ ቸርነት የእናቱ አማላጅነት አይለየን !!

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አካሄዶችን ሲጥስ ነው::
5. ይሆንልኛል ይደረግልኛል ብላችሁ እመኑ አትጠራጠሩ
እምነት አመክንዮ አይደለም በአመክንዮ የምንመረምራቸው ብዙ
ነገሮች እንዳሉ በእምነት ብቻ የምንረዳቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፡፡
እነዚህም ነገሮች የእምነት ጉዳዮች ናቸው ፡፡ ባህሩን እንደየብስ
ትረግጣላችሁ ስንባል በእምነት አዎን እንላለን ‹‹ ብሰጥምስ
ባይሆንስ እንዴት ? ›› ባልን ጊዜ እንሰጥማለን ማቴ 14 ፡ 30 ፡፡
አመክንዮ እንዴት ? ሲለን መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ይለናል፡፡
አመክንዮ የማይመስል የማይሆን ሲለን መጽሐፍ ሆኗል ይሆናልም
ይለናል ፡፡ ጌታችን በወንጌል ሐዋርያቱን ካስተማራቸው በኋላ
በእምነት እንደተቀበሉት አውቆ ያገኙትን ጸጋ ሲነግራቸው ‹‹ እናንተ
ስለነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ ›› ዮሐ 15፡4 ብሏቸዋል
፡፡ ንጹሐን መሆናቸውን የሚያሳየን መነጽር የሚያስረዳን አስረጂ
እምነት እንጂ ሌላ አይደለም ::
ይቆየን
የእርሱ ቸርነት የእናቱ አማላጅነት አይለየን !!

በመምህር #ቢትወደድ ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ገድላትን መንቀፍ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ነው!!

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ› ኤፌ 5፤1
‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ› ዕብ 12 ፤ 2-5፡፡
በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል፡፡

1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤ የኤልያስን ፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን፡፡

2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን ታሪክ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል:: መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል። ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ ቃላትትን ለማየት
‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች መረዳት እነችላለን

2.1 የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

2.2 የእግዚአብሔር ቅዱሳን ድንቅ ድንቅ ተአምራት መፈጸም
ይችላሉ "ሰለሞን" ያደረገውም እንዲል። ይኽውም ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል። ልበ
አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው" መዝ 67÷35 እያለ ይዘምራል፡፡በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10÷12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር እንደከፈሉ ዘጸ 14÷16 2ነገ 2÷8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ የሐዋ 19÷11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እነደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5÷15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

2.3 ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው፡፡ "በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ" አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን ይቸገራሉ? በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
"የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።" 1ዜና 29÷29 ተብሎ ተጽፋል ፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል።

1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል ሰዎቹ "አታንብቡ" ይሉናል ማንን እንቀበል? ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!

#በመምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
+++ ታማልደናለች +++

ሐዋርያው ስለ ቅዱሳን “ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።” (2ኛ ቆሮ 9፥14) በማለት የተናገረውን ያነበበ የአምላክ እናት ምልጃን እንዴት ያስተባብላል?
+++++
እመቤታችን የነገሥታቱን ንጉሥ የጌቶቹን ጌታ የኃያላኑን ኃያል የጸጋ አማልክት የተባሉ የቅዱሳኑን አምላክ እርሱን የወለደች ውሆችን በእፍኙ የሠፈረ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ የእርሱ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ናትና እንወዳታለን እናከብራታለን ።(ኢሳ 40:12 ራእይ 19:16 1ጢሞ 6:15) ጠላት የክርስቶስ እናቱ የድንግል ማርያም ወዳጆችን በባሕር አሸዋ በተመሰለ በዚህ ዓለም እንደ አሸን ፈልተው በተበተኑ እኩያን ሰዎች ልቡና አድሮ እንደሚዋጋቸው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል። (ራእይ 12:17) ጥላቻ ደረጃ አለው ዲያብሎስ ሁሉንም የሰው ዘር ይጠላል ከፍ ሲልም ቅዱሳንን አምርሮ ይጠላል ለድንግል ማርያም ያለው ጥላቻ ግን ወሰን ገደብና ጥግ የለውም ። የጥላቻው መገለጫ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ደግሞ ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣትን ምሉዕ ጸጋ ማስተባበል ማጠራጠር ማስካድና እርሷንም መሣርያ ባደረጋቸው ሰዎች አንደበት ማሰደብ ነው:: የምልጃዋን ጣዕም የቀመሰ ደግሞ ስለ አማላጅነቷ ከሕይወቱ በላይ ምስክር የለውምና እንዲህ ይላል :-
++ ታማልጅን ዘንድ ላንቺ ይገባል ++
የእመቤታችንን አማላጅነት መቃወም እግዚአብሔርን መቃወም መጻሕፍትንም ማስተባበል ነው:: ለምን ? ቢሉ
፩. በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዎች መማለድ መለመን ታላቅ ጸጋ ነው :: የእግዚአብሔር ጸጋ ያልተሰጠው ያልበዛለት በእርሱ ፊት ቆሞ እርሱን ሊለምን አይችልምና :: አባታችን አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ቢያገኝ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዶምና ለገሞራ እንደማለደ መጽሐፍ ይመሰክራል ። (ዘፍ 18:18-29) ሊቀ ነቢያት ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለምኖላቸዋል ። (ዘጸ 32:1-32) ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ይህን ታሪክ አውስቶ ሲናገር "እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ ባይቆም (ባይለምን) ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።" (መዝ 105(106)÷23) ማለቱ ሐሳባችንን ያጠነክርልናል:: የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሉዕ ጸጋን አግኝታለች:: ከሰማያውያኑ ቅዱስ ገብርኤል ከምድራውያኑ ቅድስት ኤልሳቤት "ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ ።" (ሉቃ 1÷30:43) ብለው እንደመሠከሩ:: ድንግል ማርያም ያልተሰጣት የቀረባት ምን ጸጋ አለ? እርስዋ አታማልድም የሚሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በመቃወም ክብር ይግባትና "የሚጎድላት ጸጋ አለ" እያሉ እንደሆነ እንገንዘብ:: ይህ ደግሞ ራሳቸው ምን ያህል ከጸጋው እንደተራቆቱ ያሳያል:: ከቅዱሳን ሁሉ ክብር የማርያም ክብር ይበልጣልና ::
፪. በሐዲስ ኪዳን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማማለድን ጸጋ ለቅዱሳን እንደሰጠ ሐዋርያው ሲመሠክር "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ (ህልው ሆኖ) ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር :: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ።" 2ቆሮ 5÷17-20 ብሏል:: ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ በሙሉ ለእመቤታችን ተሰጥቷታል ለእርሷ የተሰጠ ጸጋ ግን ለሐዋርያት አልተሰጠም:: ከፍጥረታት ወገን " ጸጋን የተሞላሽ" የተባለ ከእርሷ ሌላ ማን አለ? ታዲያ ማማለድ ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ ተልእኮም ከሆነ ድንግል ማርያም ደግሞ በጸጋ የተሞላች ከሆነች "አታማልድም" የሚሉ አያፍሩምን? የቅዱሳን ሐዋርያትን የማማለድ ጸጋ መጽሐፍ እየነገረን የእርስዋን ማማለድ ለመቀበል መቸገር ምን ይሉታል?
፫ . በሐዲስ ኪዳን ስለ ክርስቶስ በዓላውያን ነገሥታት የታረዱ በሰማይ በክብር የተገለጡ ሰማዕታት በክፉዎች ላይ እንደለመኑባቸው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል ። (ራእይ 6÷9)ስለ ልጇ "በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ።" (ሉቃ2÷35) የተባለች የሰማዕታት እናት ድንግል ማርያም ሰይጣን ክፉ ዓለም የሥጋ ፈቃድ ለሚፈትናቸው ክርስቲያኖች አትማልድምን ?
፬. ደፋሮች በድፍረትና በትእቢት በመናቅም እንደ ተራ ታሪክ ቢመለከቱትም ቅዱስ ዮሐንስ "የምልክቶች መጀመሪያ ጌታችንም ክብሩን የገለጠበት" ብሎ በመሠከረበት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ልጅዋን ወዳጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ለምና ተራውን ውሃ ወደሚጣፍጥ ወይን እንዲለወጥ አድርጋለች ። (ዮሐ ፪÷፩-፲፪)ክብርና ጸጋዋ ያልተገለጠላቸው ሰዎች የእርሷን የማማለድ ጸጋ እያስተባበሉ "እንጸልይላችሁ" "እናድናችሁ" "እንፈውሳችሁ" ሲሉ ማየትና መስማት " ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ ።" (ምሳ 30÷13) ተብሎ የተነገረው ትንቢታዊ ኃይለ ቃለ እንዲፈጸምባቸው እየተጉ መሆኑን ያሳየናል:: ዛሬም በኑሯችን በሥራችን በትዳራችን በትምህርታችን ጣዕም ያጣን ሁሉ በአማላጅነቷ በጥዑም ስሟና ከልጇ በተሰጣት ጸጋ አምነን እንቅረብ !! እርሷ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የክርስቶስ እናቱ ናትና::

አዘጋጅ መምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ ሉቃ ፩÷፲፱

ቅዱስ ገብርኤል በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ዘንድ ከፍ ያለ መወደድ ያለው መልአክ ነው::ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን አብዝተን የምንወድበት ብዙ ምክንያቶች አሉን

፩. ቤተሰብኡን የሚጠላ ማን አለ ?

ክርስቲያኖች ከቅዱሳን መላእክት ጋር የአንድ ቤተሰብእ ሀገር አባላት አካላት ነን:: በሐዋ ፱÷፲፭ መምህረ አሕዛብ ብርሃነ ዓለም ተብሎ የተመሠከረለት ቅዱስ ጳውሎስ "እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና (ባለሀገሮችና) ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" እንዳለ ኤፌ ፪:፲፱:: ሐዋርያው በዚህ ክፍል ቅዱሳን ከተባሉ መላእክት ጋር ቤተሰብእ እንደሆንን ነገረን ሀገራችንም አንድ መሆኑን ሲመሠክር "ከእነርሱ ጋር ባለሀገሮች ናችሁ " አለን:: ሀገራችን የት ነው ? ብለን ብንጠይቅም ራሱ በፊልጵዩስ መልእክቱ "ሀገራችን በሰማይ ነው" ብሎናል ፊልጵ ፫፥፲፰-፲፱ ::የመላእክት ሀገር መንግሥተ ሰማይ እንደሆነ የእኛም ሀገር በሰማይ ነው::ሐዋርያው "እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም" ያለው ቅዱስ ጴጥሮስ "እንግዶችና መጻተኞች ናችሁ" ፩ጴጥ ፪:፲፩ ብሎ በዚህ ኃላፊ ዓለም እንግዶች መሆናችንን የገለጠበትን የዚህ ዓለም እንግዳነታችንንና መጻተኛነታችንን ሳይሆን በሰማይ መንግሥት እንግዶች አለመሆናችንን ለመግለጥ ነው:: ይህ ዓለም ቢበዛ 70 ቢበረታም 80 ዘመን ብቻ የምንኖርበት ጊዜያዊ መኖሪያችን ነው መዝ 89÷10 ::ቅዱሳን መላእክት ቤተሰቦቻችን (እንደ ወንድም አባት እናት እህት) ስለሆኑ በአንዳችን የልብ ንስሐና መመለስ እንኳን ተደስተው በሰማይ ሀሴትን ያደርጋሉ ይዘምራሉ ያሸበሽባሉም :: ይህም የጌታችን በሥጋዌው ወራት ምሥክርነት ነበር ሉቃ ፲፭:፲::ቅዱሳን መላእክት ከምእመናን የማይለዩ እንደ እውነተኛ ወንድም አሳቢ እንደ አባት ጠባቂና ከክፉ የሚያድኑ አገልጋዮችም ናቸው:: መዝ 90÷11 ዳን 4÷12 የሐዋ 12÷5 የሐዋ 27÷23

2. ቅዱስ ገብርኤል መምህራችንም ነው

ቅዱስ ገብርኤል በቅዱሳት መጻሕፍት ከተገለጡልን ሥራዎቹ አንዱ የቅዱሳን ነቢያት እንዲሁም ምእመናን አስተማሪ መካሪ ጥበብ ገላጭ መሆኑ ነው :: እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን ያለውን ነገር በምልአት በስፋት የተናገረ ነቢዩ ዳንኤል "ገብርኤል ወደ እኔ እየበረረ መጣ በማታም በመሥዋእት ጊዜ ተናገረኝ አስተማረኝም እንዲህም አለኝ ዳንኤል ሆይ ጥበብና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ" ዳን 9:22 እንዳለ :: ቅዱስ ገብርኤል ምሥጢርን ጥበብን የመግለጥ ጸጋ ሀብት እንደተሰጠው ትመለከታላችሁን ? ዛሬ ላለን ምእመናን የክርስቶስ እናቱ እመቤታችንን "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ" እያልን እናመሰግናት ዘንድ ያስተማረን እርሱ አይደለምን ? ሉቃ 1:26-40 :: "በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን" ማለታችንም ለዚሁ ነው::

3 . አረጋጊ አጽናኝ ፍርሃትንም የሚያርቅ መልአክ ነው

አንዱ የቅዱስ ገብርኤል ሥራ ፍርሃትን ማራቅ የታወኩትንም ማረጋጋት ነው :: ስለሆነም ወደ ሰዎች በመጣ ጊዜ "አትፍሩ" እያለ ያረጋጋቸዋል :: እንኮዋ በዚህ ዓለም ሀሳብና የሥጋ ነገር የታወክነውን ቀርቶ መንፈሳዊውን ሰው ነቢዩ ዳንኤልን "አትፍራ" ብሎ ፍርሃትን አርቆለታል ዳን 8:15 ; 10:12 :: የአምላክ እናት ድንግል ማርያምንም ሲያበሥራት "ማርያም ሆይ አትፍሪ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና" ሉቃ 1:29-40 እያለ ነበር ::

4 . ስለ ምእመናን በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም (የሚለምን የሚማልድ) መልአክ ነው "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ" እንዳለ ሉቃ 1:19

5 . ደጋግ ሰዎችን ለንስሐ እንዲበቁ ከስህተታቸው እንዲታረሙ እንደ አባት የሚቀጣ መልአክ ነው :: ካህኑ ዘካርያስን ዲዳ እንዲሆን እንደቀጣውና ልጁ በተወለደ ጊዜም አንደበቱ እንደሚፈታለት እንደነገረው መጽሐፍ ይነግረናል ሉቃ 1:19-25 :: "ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት በፊቱም ተጠንቀቁ" ተብሎም ከኃጢአታቸው የማይመለሱትን እንደሚቀጣ ተነግሮናል ዘጸ 23:20

6 . በእባቦች ላይ በገነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው ተብሎም ተነግሮናል ሔኖክ 6:7-8 :: እንግዲህ ምን እንላለን ? የመላእክት አለቃ የአብሣሬ ትስብእት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃ አይለየን አሜን!!

#ቢትወደድ ወርቁ
የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ ም
ድጋሚ የተለጠፈ
++ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግዶ በዓለም ላይ ያበራ ፀሐይ ++

#በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ

የመልክዐ ተክለሃይማኖት ደራሲ በመልክዑ አርኬ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን "ቅዱስ አባት ሆይ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግደህ በዓለም የምታበራ ፀሐይ አንተ መዓዛህ የተወደደ ደብረ ከርቤን ነህ? ወይስ መሠወር የማይቻላት ደብረ ጽጌን ነህ? " በማለት ያመሰግናል፡፡ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም በየዘመኑ የተነሡ መምህራን ዋና ተልዕኮ ጣዖት አምልኰን በቃለ ወንጌል ማስወገድ ነው፡፡ በሰዎች ዘንድ የሚታይ የሚዳሰስ ጣዖት አለ፡፡ እንዲሁም የማይታይ የማይዳሰስ ልብም የማይባል ረቂቅ ጣዖትም አለ፡፡

በኑሯችንና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ልብ ሳንላቸው ከእግዚአብሔር አስቀድመን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ሳናውቃቸው ጣዓታት እንደሆኑብን ልናስተውል ይገባናል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን በየዘመናቸው ከሰዎች ልቡና የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ጣዖታት በቃለ እግዚአብሔር ሲያጠፉ ኑረዋል፡፡ በዚህም በነቢዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ "ጥበበኞቹ እንደሰማይ ፀዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡" (ዳን 12፡4) ተብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በገድላቸው እንደተጻፈልን በዘመናቸው ጣዖታትን አጥፍተዋል፡፡ በጣዖታቱ ላይ አድረው ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃቸውን ሰዎች ሲያታልሉ የኖሩትንም እኵያን አጋንንት በወንጌል ትምህርት ሲያሳፍሩና ሲበቀሏቸው ኑረዋል፡፡ በዚህም ለብዙዎች ብርሃን ሆነዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምን ያህል ጣዖታትን እንዳጠፉ ስንቶችን ከጣዖት አምልኰ እንዳላቀቁና አጋንንትን በወንጌል ትምህርት እንዴት እንዳወጡ ለመረዳት ገድላቸውን በእምነት ሆኖ ማንበቡ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይኽን በሕሊናችን እንያዝና በዚህ ክፍል ጻድቁ የተገለጡበትን የምስጋና ቃል እንመልከት፡፡

+++ ተክለሃይማኖት ፀሐይ +++

በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ብርሃን ፀሐይ ተብሏል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "እግዚአብሔር ብሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማነው?" (መዝ 26፡1) በማለት ዘምሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡፡" (ዮሐ 8፡12) በማለት አስተምሯል፡፡ ጌታችን ጨለማ ያለው እርሱን አለማወቅ እንደፈቃዱ አለመመላለስ በኃጢአትና በክሕደት መኖርን ነው፡፡ (ሮሜ 13፡11-13) ብርሃን የተባለ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእምነት ጸንተው በምግባር ቀንተው በትሩፋት አጊጠው እንደፈቃዱ የተመላለሱትንና ያገለገሉትን ወዳጆቹችንም ብርሃናት መሆናቸውን "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" በማለት መስክሮላቸዋል፡፡ ጌታችን ወዳጆቹ የዓለም ብርሃን የሚባሉት ብርሃን ሲሆኑ መሆኑን ሲናገርም "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡" (ማቴ 5፡14-16) ብሎዋል፡፡ በመነሻችን እንደተመለከትነው ጻድቁ ጨለማ ጣዖትን በማስወገድ ለዓለም ብርሃን ሆነዋል፡፡ ሰዎች ልቡናቸውን ከጣዖታት መልሰው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩትም ምክንያት ሆነዋል፡፡ በመሆኑም ደራሲው የጌታችንን ቃል ይዞ ጻድቁን "ብርሃን ፀሐይ" በማለት አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡"(ያዕ 1፡17-18) በማለት የብርሃናት አባት ብሎ ጠርቶታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ብርሃናት ብሎ የጠራቸው የብርሃን ክርስቶስ ልጆች ወዳጆቹ ቅዱሳን መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ አምልኮ ጣዖትን እንዲያስወግዱ ኑፋቄንና ክሕደትንና እንዲያጠፋ የሰዎች ልጆችን ሕይወት በቅዱስ ቃሉ አማካኝነት እንዲያርሙና እንዲያስተካክሉ ወደ ዓለም የተላኩ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት በኋላ ዘመን የተነሡ ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ "እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ እግዚአብሔር አዞናል፡፡" በማለት በአንድ ቃል ተናግረዋል፡፡ (የሐዋ 13፡47) ቅዱሳን ጨለማ (ኃጢአት) በሞላው በሰው ልቡና ብርሃን ክርስቶስን የሚያበሩ ብርሃናት መሆናቸውን ትመለከታላችሁን? ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የንስሐ ስብከትን እየሰበከ የንስሐ ጥምቀትን እያጠመቀ በመንገድ የተመሰለ የሰውን ልቡና እያስተካከለ የተቀበለውን መጥምቁ ዮሐንስን "የሚነድና የሚያበራ ብርሃን" ብሎ ጠርቶታል፡፡ (ዮሐ 5፡35) መጥምቁ ዮሐንስ በጌታችን አንደበት የሚነድና የሚያበራ መብራት ተብሎ ስለምን ተመሰገነ? ወንጌልን በመስበኵ ጣዖታትን በማጥፋቱ ሰዎችን ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በመመለሱ አይደለምን? ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፍቅር ነድደው ሰይጣንን ድል ነሥተዋል፡፡ በሕይወታቸው ክርስቶስን አብርተው በሰው ልቡና ነግሦ የነበረውን ጨለማ ኃጢአት ደርምሰዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ (የእውነት ፀሐይ) እንደሆነ መንገዱን የተከተሉ ወዳጆቹም ፀሐይ ሆነው ፀሐይ ተብለዋል፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘሪውን ምሳሌ ባስተማረበት ክፍል "በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡" (ማቴ 13፡44) በማለትም ጭምር አስተምሮዋል፡፡ እርሱ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሐይ ሲሆን ወዳጆቹ ደግሞ ጨረቃ ናቸው፡፡ ጨረቃ ብርሃንን የምታገኘው ከፀሐይ እንደሆነ ቅዱሳንም ጸጋን ክብርን ሥልጣንንም ያገኙት ከክርስቶስ ነውና ጌታችን "እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡" ብሎ አስተማረ፡፡ እንግዲህ በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔርን ተከትለው ጨለማ ጣዖትን ያጠፉ ደጋግ አባቶችና እናቶች ብርሃናት ፀሐይ ከዋክብት መባላቸውን ስንመለከት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ብርሃን ፀሐይ ብለን እንጠራቸዋለን እንጂ በጥርጥር መንፈስ ሆነን እንዴት? ለምን? ብለን አንጠይቅም፡፡

በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ
ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ ም