ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
ጥያቄዎች


#አዘጋጅ :-መምህር አቤኔ ዘር ማሙሸት

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ


#ኛ ባለንጀራህን እንደ ራስህ አርገህ ውደድ የሚለው ትዕዛዝ የተሰጠው በዘመነ አዲስ ነው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ሕግጋትን መፈጸም ከክርስቶስ አልተማርንም።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ክርስቲያን ሰማያዊ ስለሆነ የመንግስትን ህግ መጠበቅ አይጠበቅበትም።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ መልካም ምኞት የኃጢአት ሥር ናት።

ሀ ሐሰት ለ እውነት

#ኛ ፍቅር የትእዛዛት ሁሉ ማሰሪያ ናት።

ሀ እውነት ለ ሐሰት


#ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ)የክርስቶስ ተከታይ
ለ )ክርስቶሳዊ
ሐ)መዐዛ ክርስቶስን የሚሸት
መ)ሁሉም

#ኛ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚመስለው በምንድን ነው?

ሀ)በአካሄድ በአለባበስ እና በአነጋገር
ለ)በኑሮ ሁሉ
ሐ) ሀ ና ለ መልስ ናቸው
መ)መልሱ አልተሰጠም

#ኛ ሕገ ልቦና የምንለው ዘመን እንዴት ያለውን ዘመን ነው?
ሀ የሙሴን ሕግ የጻፈበትን ዘመን
ለ ሕግ ያልተጻፈበትን ዘመን
ሐ የአዲስ ኪዳንን ዘመን
መ ኦሪትን

#ኛአሥርቱ ትእዛዛት ምን እና ምን ተብለው ይከፈላሉ? (በፍቅር)

ሀ)ፍቅረ ነዋይና ፍቅረ ሃብት
ለ )ፍቅረ እግዚአብሔር እና ፍቅረ ቢጽ
ሐ)እምነት ተስፋ ፍቅረ ተብለው
መ)አይከፋፈሉም

#ኛ ከሚከተሉት መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ ) ለመዳን ምግባር ብቻውን በቂ ነው።
ለ ) ሃይማኖት መሠረት ምግባር ደግሞ ጣራ ግድግዳ ነው።
ሐ) ሃይማኖት ብቻውን ለመዳን በቂ ነው።
መ ) ሁሉም መልስ ናቸው።

#በትምህርቱ መሠረት በአጭሩ አስረዱ

፲ ፩ #ኛ ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ዘርዝሩ

፲፪ #ኛ ሕገ ኦሪትን እና ሕገ ወንጌልን አነጻጽሩ

፲ ፫ #ኛ ክርስቲያናዊ ግዴታዎች የምንላቸውን ዘርዝሩ

፲ ፬ #ኛ የሚያዝኑ ብጹአን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉና። እንዴት ያለ ሀዘን ነው ብጽእናን የሚያስገኘው

፩ ፭ #ኛ እግዚአብሔር አንደኛውን ትእዛዝ (ከኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ የሚለውን ትእዛዝ) ያዘዘበት ምክኒያት ምንድን ነበር

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ድረስ በ👇👇👇👇👇
@abenma
@abenma
በኩል ይላኩልን

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የባሕረ ሐሳብ ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ፡፡

1 ካህናት አባቶች ባሕረ ሐሳብን የግድ መማር አለባቸው፡፡

2 ተንቀሳቃሽ በዓላት ዕለትን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡

3 አንድ ሱባዔ 10 ቀናትን ይይዛል፡፡

4 ለፍጥረት ስድስተኛ ቀን የሆነው ዕለተ አርብ የቃሉ ትርጉም ማካፈያ ማለትነው፡፡

5 ታህሳስ ማለት ፈለገ ማለት ነው፡፡

#ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1 የባሕረ ሀሳብ ስያሜ መካከል የማይደበው የቱ ነው?
ሀ. ሐሳበ ዘመን
ለ. አቡሽሀር
ሐ. የዘመን ሂደት
መ. መርሐ እውር

2 ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

3 ከሚከተሉት መካከል የጌታችን ዓበይት በዓል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጌታችን በዓለ ግርዘት
ለ. በዓለ እንቁጣጣሽ
ሐ. በዓለ ደብረ ታቦር
መ. በዓለ ጰራቅሊጦስ

4 ጥንተ ቀመር ተብሎ የሚጠራው ቀን፡
ሀ. ሰኞ
ለ.ማክሰኞ
ሐ.ረቡዕ
መ.ሰኑይ

5 ‹‹አማረ›› የሚል ትርጉም ያለው የወር ስያሜ የትኛው ነው?
ሀ. ሰኔ
ለ. ሀምሌ
ሐ. ነሀሴ
መ. መስከረም

#በትምህርቱ መሰረት ትክክለኛውን መልስ ስጡ፡፡

1 ቋሚ በዓላት ከሚባሉት ውስጥ ቢያንስ አራቱን ጥቀሱ፡፡

2 የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

3 አውደ ዕለት የምንለው የቱን ቀን ነው?

4 የአንድ አመት አራት ክፍላተ ዘመን የምንላቸውን ዘርዝሩ፡፡ እያንዳንዳቸው ከመች እስከ መቼ አንደሆነ ጥቀሱ፡፡

5 መጋቢት ምን ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው? የወሩ ስያሜ ምንን ያመለክታል?

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇
@Midyam
@Midyam
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የለ ፣ አከበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ "ዑሰት " ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል::ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው


ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጢያንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥያንን
መ ) ኃጥያንንና ኃጥያንን

#ኛ_የቅዱሳ መላዕክት አገልግሎት ያልሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም


#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የፀጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
ሐ) የአስተብርኮ ስግደት
መ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ?የመላእክቱ የነገድ ስምና ሹማምንቶቻቸውስ እነማን ናቸው


፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የሥነ _ፍጥረት ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #ኛ_ ሥነ ማለት ያማረ ፣ የተዋበ ፣ የተቆነጀ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ከመፍጠር ያረፈው በዕለተ እሁድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

3 #ቅዱሳን መላእክት የተፈጠሩት ከእሳት እና ከነፋስ ነው::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

4 #የቅዱሳን መላእክት ነገድ ፲ ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

5 #በገቢር(በሥራ) የተፈጠረ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ!!


6 #ኛ_ከሚከተሉት መካከል የእሁድ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው

ሀ አፈር
ለ ጠፈር
ሐ እጽዋት
መ መልስ የለም።

7 #_በነቢብ (በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው

ሀ መላእክት
ለ ብርሃን
ሐ እሳት
መ መሬት

8 #_የኃይላት አለቃቸው ማነው

ሀ ቅዱስ ሚካኤል
ለ ቅዱስ ገብርኤል
ሐ ቅዱስ ሱሪያል
መ ቅዱስ አናንኤል

9 #_ከጠፈር በላይ የሚገኘው ብጥብጥ ውኃ ምን ተብሎ ይጠራል

ሀ ባቢል
ለ ውቂያኖስ
ሐ ሀኖስ
መ ሰማይ

10 #_እግዚአብሔር አምላክ በዕለተ ሰኑይ(ሰኞ) ስንት ፍጥረታትን ፈጠረ

ሀ ምንም አልፈጠረም
ለ አንድ
ሐ ሁለት
መ ስምንት

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_አራቱን ባህሪያተ ሥጋ በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው

፲ ፪ #_አራቱ በህሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባህሪያት ይመሰላሉ ::እንዴት የትኛው የትኛውን ባህሪውን ይመስላል የሚሉትን አስረዱ

፲ ፫ #ኪሩቤልና ሡራፌል የተሰኙት ነገደ መላእክት የእግዚአብሔርን ይሸከማሉ::ለመሆኑ እንዴት #እግዚአብሔርን ችለውት ነው የሚሸከሙት? በኮርሱ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት አስረዱ

፲ ፬ #_ሥነ _ፍጥረታት የተፈጠሩበትን ሦስት ዐላማዎች አስረዱ


፲ ፭ #_ጨለማ_የእግዚአብሔር ባህሪ እንዴት አንደሚገልጥ በትምህርቱ መሠረት አስረዱ

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት ጥያቄዎች

እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #_መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአንድ ጊዜ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

2 #_መዝሙረ ዳዊት በከተማ ስም ከተሰየሙ መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

3 #_የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ ትንቢተ ዳንኤል ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

4 #_መጽሐፈ አስቴርን የጻፈችው አስቴር ነች።

ሀ ) እውነት ለ) ሐሰት

5 #_የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ይዘት ምርጫ

6 #_ከሚከተሉት መካከል የታሪክ መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው

ሀ) ግብረ ሐዋርያት
ለ )የማቴዎስ ወንጌል
ሐ )ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች
መ) ሀ እና ለ

7) #ከተዘረዙት መጻሕፍት መካከል #_ሊቀ _ነቢያት ቅዱስ ሙሴ #ያልጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው

ሀ ) መጽሐፈ ኩፋሌ
ለ ) ኦሪት ዘፍጥረት
ሐ ) ኦሪት ዘዳግም
መ ) መጽሐፈ አክሲማሮስ

8) #_የኦ/ተ ቤተ ክርስቲያናችን ምትቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥራቸው ስንት ነው

ሀ ) 46
ለ ) 27
ሐ ) 35
መ ) 81

9 #_መጽሐፈ ምሥጢር ከየትኛው የአዋልድ መጽሐፍ ጋር ይመደባል
ሀ )ድርሳን
ለ )ነገረ ሃይማኖት
ሐ )የሥርዓት
መ )የታሪክ

10 #_"ገና እንደተወለዱ ልጆች የቃሉን ወተት ተመኙ።" 1ጴጥ 2:3 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል

ሀ )መጽሐፍ ቅዱስ ዳኛ መሆኑን
ለ ) መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጽድቅ የሚመራ መሆኑን
ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ ምግበ ነፍስ መሆኑን
መ)መጽሐፍ ቅዱስ የሕግ እና የአስተዳደር ምንጭ መሆኑን

#በአጭሩ መልስ ስጡ

11 #መጽሐፍ_ቅዱስን_ቅዱስ ካሰኙት ነገሮች መካከል ቢያንስ ሦስት ጥረሱ::

12 #ከመጻሕፍ_ቅዱስ ባህል መካከል ቢያንስ 2ቱ ጠቅሰህ(ሺ)ከሀገራችን ተመሳሳይ ባህል ጋር አንድነቱንና ልዮነቱን አነጻጽር(ሪ)::

13 #አዋልድ_መጻሕፍት ከሚባሉት መካከል 3ቱን ጥቀስና ጥቅማቸውን በአጭሩ አብራራ(ሪ)

14 #የመጻሕፍ_ቅዱስ ዕድሜ ሰንት ነው? መጀመሪያ የተጻፈውስ የመጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?በምንስ ቋንቋ ተጻፈ?

15 #መጻሕፍ_ቅዱስን እንደ ምንኖርበት ሀገር ባህል ፣ እንደ ደረስንበት የዕውቀት ደረጃ ፣ በሥጋዊ ሀሳብና ፍልስፍ ማንበብእና መተርጎምና የሚያስከትለውን ጥፋት በራስህ(ሺ) አገላለጽ አስረዳ(አስረጂ)


#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #_መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአንድ ጊዜ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

2 #_መዝሙረ ዳዊት በከተማ ስም ከተሰየሙ መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

3 #_የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ ትንቢተ ዳንኤል ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

4 #_መጽሐፈ አስቴርን የጻፈችው አስቴር ነች።

ሀ ) እውነት ለ) ሐሰት

5 #_የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው።

ሀ ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ይዘት ምርጫ

6 #_ከሚከተሉት መካከል የታሪክ መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው

ሀ) ግብረ ሐዋርያት
ለ )የማቴዎስ ወንጌል
ሐ )ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች
መ) ሀ እና ለ

7) #ከተዘረዙት መጻሕፍት መካከል #_ሊቀ _ነቢያት ቅዱስ ሙሴ #ያልጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው

ሀ ) መጽሐፈ ኩፋሌ
ለ ) ኦሪት ዘፍጥረት
ሐ ) ኦሪት ዘዳግም
መ ) መጽሐፈ አክሲማሮስ

8) #_የኦ/ተ ቤተ ክርስቲያናችን ምትቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥራቸው ስንት ነው

ሀ ) 46
ለ ) 27
ሐ ) 35
መ ) 81

9 #_መጽሐፈ ምሥጢር ከየትኛው የአዋልድ መጽሐፍ ጋር ይመደባል
ሀ )ድርሳን
ለ )ነገረ ሃይማኖት
ሐ )የሥርዓት
መ )የታሪክ

10 #_"ገና እንደተወለዱ ልጆች የቃሉን ወተት ተመኙ።" 1ጴጥ 2:3 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል

ሀ )መጽሐፍ ቅዱስ ዳኛ መሆኑን
ለ ) መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጽድቅ የሚመራ መሆኑን
ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ ምግበ ነፍስ መሆኑን
መ)መጽሐፍ ቅዱስ የሕግ እና የአስተዳደር ምንጭ መሆኑን

#በአጭሩ መልስ ስጡ

11 #መጽሐፍ_ቅዱስን_ቅዱስ ካሰኙት ነገሮች መካከል ቢያንስ ሦስት ጥረሱ::
#በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሱ ቅዱሳን ሰዎች ስለጻፉት
#ወደ ቅድስና ስለሚመራ
#በቅዱሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለተጻፈ
#ዘመን የማይሽረው መሆኑ
#መጻኤዉንና አላፊውን በትክክልና በእርግጠኛነት የሚናገር ሰለሆነ
#የሌሉሎች መጻሕፍት ዋኘና ምንጭ በመሆኑ

12 #ከመጻሕፍ_ቅዱስ ባህል መካከል ቢያንስ 2ቱ ጠቅሰህ(ሺ)ከሀገራችን ተመሳሳይ ባህል ጋር አንድነቱንና ልዮነቱን አነጻጽር(ሪ)::

እረኝነት:-
ሰርግ:-
ጫማ ማውለቅ:-


13 #አዋልድ_መጻሕፍት ከሚባሉት መካከል 3ቱን ጥቀስና ጥቅማቸውን በአጭሩ አብራራ(ሪ)

#መልስ
#አዋልድ መጻሕፍ የሚባሉ
#ገድል :-
#ተአምር :-
#ድርሳን :-
#መልክዕ :-

#ጥቅማቸው
ከአባታቸው ከመጻሕፍ ቅዱስ ጠባይ ሳይወጡ የቅዱሳንን ተጋሎ ድንቅ ድንቅ ተአምራት እና ተራዳይነት እንዲሁም ክብርን የሚገልጡ በመሆን መጻሕፍ ቅዱስ በጥቂቱ እና በመጠኑ በፍንጭ መልክ የገለጠውን አነርሱ አምልተውና አስፍተው ይተነትኑታይ ማለት ነው::#በአጠቃላይ በደረቁ በንባብ የተጻፈውን ወንጌል በሕይወት ተተግብሮ እያሳዮ ሃይማኖት ያጸናሉ ምግባር ያቀናሉ ይሕወት ይሆናሉ::

14 #የመጻሕፍ_ቅዱስ ዕድሜ ሰንት ነው? መጀመሪያ የተጻፈውስ የመጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?በምንስ ቋንቋ ተጻፈ?

#መልስ

ዘመኑ በትክክል በውል አይታወቅም መጀመሪያ የተጻፈውም መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተጻፈበት ቋንቋም እንደ ኢትዮጲያዊያን ሊቃውንት ገለጻ #በግዕዝ_ቋንቋ ነው

15 #መጻሕፍ_ቅዱስን እንደ ምንኖርበት ሀገር ባህል ፣ እንደ ደረስንበት የዕውቀት ደረጃ ፣ በሥጋዊ ሀሳብና ፍልስፍ ማንበብእና መተርጎምና የሚያስከትለውን ጥፋት በራስህ(ሺ) አገላለጽ አስረዳ(አስረጂ)

#መልስ

*ወደ ክህደትና ምንፍቅና ይከታል #በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይለያል የሚል መሰል ምላሾችን የሰጣችሁ ሁሉ ትክክል ናችሁ!::

#ለበለጠ_መረጃ የተላለፉ ኮርሶችን ያድምጡ

#በመልሶቻችሁን ዙሪያ ላላችሁ ማንኛውም አሳብ ጥያቄና ጥቆማ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በዓውደ ምህረት መንፈሳዊ የኮርስ መማርያ የቴሌግራም ቻናል ላይ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተቋርጠው የነበሩ እና አዳዲስ ትምህርቶችን ይዘን የምንቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጥያቄዎች ይሞክሩ።
👇👇👇👇👇👇


ጥያቄ #1
ከሥነ ምግባር ሕግጋት መካከል የማይመደበው የቱ ነው?
ሀ አምላካዊ ሕግ
ለ የተፈጥሮ ሕግ
ሐ ሥጋዊ ሕግ
መ መንፈሳዊ ሕግ

ጥያቄ #2
የነገረ ማርያም ትምህርትን መማር ለምን አስፈለ?
ሀ ጸጋዋን አውቀን እንጠቀም ዘንድ
ለ በብሉይ በሐዲስ በሊቃውንት መጽሐፍ ሁሉ ስለምትገኝ
ሐ የድኅነታችን ምክኒያት በመሆነኗ
መ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

ጥያቄ #3
ቅዱሳን አማልክት ናቸው ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ መፍጠር ይችላሉ ማለት ነው፡፡
ለ የአምልኮት ስግደት ሊሰገድላቸው ይገባል ማለት ነው፡፡
ሐ የመፍረድ ስልጣንን ከአምላካቸው ዘንድ በስጦታ አግኝተዋል ማለት ነው፡፡

ጥያቄ #4
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አይመደብም፡፡
ሀ አዋልድ መጽሐፍት
ለ የእግዚአብሔር መጽሐፍ
ሐ ቅዱስ መጽሐፍ
መ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ

ጥያቄ #5
ከሚከተሉት መካከል እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ የትኛው ነው?
ሀ ገሐንብ
ለ ሲዖል
ሐ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡
መ ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡

ጥያቄ #6
ሰባቱ ሰማያት ከምን ተፈጠሩ?
ሀ ከምንም
ለ ከእሳት
ሐ ከውሀ
መ ከእሳት እና ከንፋስ

ጥያቄ #7
ሕልውና ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ አኗኗር ማለት ነው፡፡
ለ መጥፋት ማለት ነው፡፡
ሐ ሥራ ማለት ነው፡፡
መ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

ጥያቄ #8
ከሚከተሉት መካከል አሥራው መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው?
ሀ ገድለ ተክለሃይማኖት
ለ ድርሳነ ገብርኤል
ሐ የሐዋርያት ሥራ
መ የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ

ጥያቄ #9
አምላክ ዘበሐሰት የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ቅዱስ ገብርኤል
ለ ቅዱሳን
ሐ ውበት


ጥያቄ #10
እግዚአብሔር መኖሩን በምን እናውቃለን?
ሀ በሕሊና ምስክረነት
ለ በታሪክ እና በቅዱሳት መጻሕፍት
ሐ በተፈጥሮ ሥርዓት
መ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

ጥያቄ #11
ጨለማ በባሕሪው የትኛውን የእግዚአብሔር ባሕሪይ ይገልጥልናል?
ሀ የእግዚአብሔርን ፍጹምነት
ለ የእግዚአብሔርን ረቂቅነት
ሐ የእግዚአብሔርን ቅዱስነት
መ የእግዚአብሔርን ጻዲቅነት

ጥያቄ #12
መጽሐፍተ ምኑናት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ ዓለማዊ የትምህርት መጽሐፍት
ለ የጥንቆላ መጽሐፍት
ሐ ዝሙትን የሚያሰሩ መጻሕፍት
መ መጽሐፍ ቅዱስ

ጥያቄ #13
ከአሥርቱ ትእዛዛት መካከል የመጀመሪያው ትእዛዝ ምን ይላል?
ሀ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡
ለ የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ፡፡
ሐ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ፡፡
መ እናት እና አባትህን አክብር፡፡

ጥያቄ #14
እግዚአብሔር በሰማይ ይኖራል ቢባል ምኑን ይገልጻል?
ሀ ከሰማይ ውጪ ሌላ ቦታ የለም ለማለት ነው፡፡
ለ መኖሪያው ሰማይ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
ሐ ስለ ልእልናውና ስለ ክብሩ በሰማይ ይኖራል ማለት ነው፡፡
መ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

ጥያቄ #15
መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን መማር ለምን አስፈለገ?
ሀ ለቅዱሳት መጽሐፍት የሚገባቸውን ክብር ለመስጠት
ለ የመጽሐፍትን ትርገጓሜ ለማወቅ
ሐ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት
መ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

መልሶቻችሁን፣ ያላችሁን አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ አድርሱን፡፡

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ጥያቄዎቹ ላይ መልስ በመስጠት የተሳተፋችሁ አባላቶቻችን አግዚአብሔር ያክብርልን፡፡ ዋጋችሁን አምላከ ተክለሃይማኖት ይክፈልልን እያልን መልሶቹ ከነማብራሪያቸው ወደ መስጠቱ እንገባለን፡፡

ጥያቄ #1
ከሥነ ምግባር ሕግጋት መካከል የማይመደበው የቱ ነው?
መልስ ለ - የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ የሥነ ምግባር ሕግጋት በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም አምላካዊያን (መንፈሳዊያን) እና ሥጋዊ (ዓለማዊያን) ይባላሉ፡፡ የተፈጥሮ ሕግ የምንለው እግዚአብሔር አምላክ ለሥነ ፍጥረቱ የሰራቸው የማይለወጡ ሕግጋት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፀሐይ በሥስራቅ ወጥታ በምዕራብ መግባት ሁሌም የሚኖር የማይለወጥ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ሕግ ከሥነ ምግባር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡

ጥያቄ #2
ነገረ ማርያምን መማር ለምን አስፈለ?
መልስ መ - ሁሉም መልሶች ናቸው፡፡ ነገረ ማርያምን መማር ለምን አስፈለ ቢሉ ጸጋዋን አውቀን እንጠቀም ዘንድ፣ በብሉይ በሐዲስ በሊቃውንት መጽሐፍ ሁሉ ስለምትገኝ፣ እርሷን ስንጠራ አብረን አምላካችንንም አብረን ስለምንጠራ እንዲሁም የድኅነታችን ምክኒያት በመሆነኗ ነው፡፡

ጥያቄ #3
ቅዱሳን አማልክት ናቸው ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ ሐ - የመፍረድ ስልጣንን ከአምላካቸው ዘንድ በስጦታ አግኝተዋል ማለት ነው፡፡ ለቅዱሳን የጸጋ አምላክነት ተሰጥቷቸዋል ማለት አምላክ የመሆን ስልጣንን ከእግዚአብሔር ዘንድ አግኝተዋል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት የጸጋ ስግደት እንዲሰገድላቸው፣ በዳግም ምጽዐት የመፍረድ ስልጣንን፣ በስማቸው እንድንለምን እንድንማጸን ባለሟልነትን ከእግዚአብሔር ዘንድ አግኝተዋል ማለት ነው እንጂ ይፈጥራሉ ማለት አይደለም፡፡ ማቴ 19፡28 ሉቃ 11፡31 ራዕ3፡9

ጥያቄ #4
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አይመደብም፡፡
መልስ ሀ - አዋልድ መጽሐፍ ነው፡፡ አዋልድ መጽሐፍት ማለት ልጆች መጽሐፍት ማለት ሲሆን ልጅነታቸውም ለመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ እነርሱም ድርሳናት፣ ገድላት፣ መልኮች፣ የትርገጓሜ መጽሐፍት ወዘተ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የእግዚአብሔር መጽሐፍ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ እንዲሁም ቅዱሳት መጽሐፍ እየተባለ ይጠራል፡፡ 2ኛ ጢሞ 3፡15-17

ጥያቄ #5
ከሚከተሉት መካከል እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ የትኛው ነው?
መልስ ሐ - በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር በባሕሪው በሁሉ የሞላ ነው፡፡ በዓለምም ከዓለም ውጪ ያለ ነው፡፡ በሲዖልም፣ በገሀንብም በሁሉም ቦታ አለ፡፡ መዝ 139፡7

ጥያቄ #6
ሰባቱ ሰማያት ከምን ተፈጠሩ?
መልስ ለ - ከእሳት ነው የተፈጠሩት፡፡ በሐልዮ በዕለተ እሁድ የተፈጠሩ ሲሆን ዓለማተ እሳት ተብለው ከሚጠሩት መካከል እነዚህ ሰባቱ ሰማያት ይገኙበታል፡፡

ጥያቄ #7
ሕልውና ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ ሀ - አኗኗር ማለት ነው፡፡ ሐለወ (ኖረ) ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ተርጉሙም አኗኗር ማለት ነው፡፡

ጥያቄ #8
ከሚከተሉት መካከል አሥራው መጽሐፍ የሆነው የቱ ነው?
መልስ ሐ - የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ነው፡፡ አሥራው መጽሐፍት የሚባሉት ሰማንያ አሐዱ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ናቸው፡፡ ሌሎቹ መጻሕፍት አዋልድ መጽሐፍት ይባላሉ፡፡ መሠረታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምሮ ያለቀቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች መጻሕፍት አዋልድ መጻሕፍት ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነርሱም ገድላት፣ ድርሳናት፣ የአንድምታ (የትርጓሜ መጻሕፍት)፣ መልኮች፣ የዜማ መጻሕፍት ወዘተ...

ጥያቄ #9
አምላክ ዘበሐሰት የሆነው የትኛው ነው?
መልስ ሐ - ውበት ነው፡፡ አምላክ ዘበሐሰት ማለት የሐሰት አምላክ ወይም አምላክ ሳይሆን የሰው ልጆችን የሚገዛ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ሰይጣን ዳቢሎስ፣ አጋንንት፣ ገንዘብ፣ ዕውቀት፣ ሥልጣን፣ ጉልበት፣ ጣዖታት ወዘተ.. አማልክት ዘበሐሰት ይባላሉ፡፡ ሰው በውበቱ የሚመካ ከሆነ እንዲሁ ውበቱን እያመለከ ነው ማለት ነው፡፡ ምሳሌ 31፡30

ጥያቄ #10
እግዚአብሔር መኖሩን በምን እናውቃለን?
መልስ መ - ሁሉም ነው፡፡ እግዚአብሔር መኖሩን በሥነ ፍጥረቱ፣ በተፈጥሮ ሥርዓት፣ በቅዱሳት መጽሐፍት እና በታሪክ እንዲሁም በሕሊና ምስክርነት እናውቃለን፡፡

ጥያቄ #11
ጨለማ በባሕሪው የትኛውን የእግዚአብሔር ባሕሪይ ይገልጥልናል?
መልስ ለ - የእግዚአብሔር ረቂቅነትን፡፡ በጭለማ ያለ ነገር እንደማይመረመር እግዚአብሔርም ረቂቅ የማይመረመር አምላክ መሆኑን ይገልጥልናል፡፡

ጥያቄ #12
መጽሐፍተ ምኑናት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
መልስ ሀ - ዓለማዊ የትምህርት መጽሐፍት ናቸው፡፡ መጽሐፍተ ምኑናት የምንላቸው ሥጋዊ ጥበብን የሚያስተምሩ ለሥጋዊ ህይወታችን የሚጠቅሙ ነገር ግን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የማይጠቅሙ እንዲሁም መንፈሳዊ ሕይወታችንን የማይጎዱ መጽሐፍት ናቸው፡፡

ጥያቄ #13
ከአሥርቱ ትእዛዛት መካከል የመጀመሪያው ትእዛዝ ምን ይላል?
መልስ ሐ - ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአምላክነቱ ቀናተኛ ስለሆነ ያዘዘው የመጀመሪያ ትዕዛዝ ነው፡፡ ዘጸ 20፡2-6

ጥያቄ #14
እግዚአብሔር በሰማይ ይኖራል ቢባል ምኑን ይገልጻል?
መልስ ሐ - ሰማይ ከሁሉ ከፍ እንደሚል እንዲሁ እግዚአብሔርም ስለ ልዕልናው ስለ ክብሩ በሰማይ በሰማይ ይኖራል ይባላል እንጂ እግዚአብሔር በሰማይ ብቻ ይኖራል ማለት አይደለም፡፡

ጥያቄ #15
መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን መማር ለምን አስፈለገ?
መልስ መ - ሁሉም መልስ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን መማር ያስፈለገበት ምክኒያት እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሊያስተላልፍ የፈለገውን ነገር ለመራዳት፣ ለቅዱሳት መጽሐፍት የሚገባቸውን ክብር ለመስጠት፣ የመጽሐፍትን ትርገጓሜ ለማወቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እና በመሳሰሉት ሌሎች ምክኒያቶች መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን መማር አስፈልጓል፡፡

ያላችሁን አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ፣ ይሄ ይጨመር፣ ይሄ ይቀነስ የምትሉትን ሁሉ አድርሱን፡፡ አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ይጠብቀን፡፡ የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡ ይቆየን ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የሥነ _ፍጥረት ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #ኛ_ ሥነ ማለት ያማረ ፣ የተዋበ ፣ የተቆነጀ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ከመፍጠር ያረፈው በዕለተ እሁድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

3 #ቅዱሳን መላእክት የተፈጠሩት ከእሳት እና ከነፋስ ነው::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

4 #የቅዱሳን መላእክት ነገድ ፲ ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

5 #በገቢር(በሥራ) የተፈጠረ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ!!


6 #ኛ_ከሚከተሉት መካከል የእሁድ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው

ሀ አፈር
ለ ጠፈር
ሐ እጽዋት
መ መልስ የለም።

7 #_በነቢብ (በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው

ሀ መላእክት
ለ ብርሃን
ሐ እሳት
መ መሬት

8 #_የኃይላት አለቃቸው ማነው

ሀ ቅዱስ ሚካኤል
ለ ቅዱስ ገብርኤል
ሐ ቅዱስ ሱሪያል
መ ቅዱስ አናንኤል

9 #_ከጠፈር በላይ የሚገኘው ብጥብጥ ውኃ ምን ተብሎ ይጠራል

ሀ ባቢል
ለ ውቂያኖስ
ሐ ሀኖስ
መ ሰማይ

10 #_እግዚአብሔር አምላክ በዕለተ ሰኑይ(ሰኞ) ስንት ፍጥረታትን ፈጠረ

ሀ ምንም አልፈጠረም
ለ አንድ
ሐ ሁለት
መ ስምንት

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_አራቱን ባህሪያተ ሥጋ በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው

፲ ፪ #_አራቱ በህሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባህሪያት ይመሰላሉ ::እንዴት የትኛው የትኛውን ባህሪውን ይመስላል የሚሉትን አስረዱ

፲ ፫ #ኪሩቤልና ሡራፌል የተሰኙት ነገደ መላእክት የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ::ለመሆኑ እንዴት #እግዚአብሔርን ችለውት ነው የሚሸከሙት? በምሳሌ መሠረት አስረዱ

፲ ፬ #_ሥነ _ፍጥረታት የተፈጠሩበትን ሦስት ዐላማዎች አስረዱ


፲ ፭ #_ጨለማ_የእግዚአብሔር ባህሪ እንዴት አንደሚገልጥ በትምህርቱ መሠረት አስረዱ

🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ፣ የተበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ "ሁሰት " ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው።

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው


ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጢያንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥያንን
መ ) ኃጥያንንና ኃጥያንን

#ኛ_የቅዱሳ መላዕክት አገልግሎት ያልሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም


#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት አማልክት ዘበጸጋ ናቸውና
ሐ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ) ።

፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ


፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልሶቻችሁን
👇👇👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ ፣ የተከበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

ምክንያቱም:- #የባህሪ ቅድስና ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው

#ኛ_ "ሁሰት" ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት


#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

ምክንያቱም :-ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር
#ለቅዱሳን መላእክት
#ለቅዱሳን መጻሕፍት
#ለቅዱሳን መካናት ይቀጸላልና

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት
ከፍቃደ ሥጋ ብቻ ሳይሆን #ለበረከት_ከእግዚአብሔር ለማሰናከል #ከሰይጣን #ከአላዊያን ነገስታት #ከጠንቆዮች ጭምር ይገጥማቸዋልና


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

ሐ)በፍጽምነት የሚገኝ ማዕረግ ነው

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው


ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጥዐንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥዐንን

#ኛ_የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት የሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም


#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
ሐ) የአስተብርኮ ስግደት
መ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

#መልስ
#ከእግዚአብሔር ለበረከት
#ከሥጋ ፍቃዳቸው
#ከአላዊያን ነገስታት
#ከጠንቆዮች
#ከሰይጣን


፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#መልስ
#ጸጣኒነት (ጀማሪ)
#ማዕከላዊነት
#ፍጽምነት
ወይም
#ንጽሐ ሥጋ
#ንጽሐ ነፍስ
#ንጽሐ ልቡናም ተብለው ይጠራሉ
፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
#ሊቀ_ነቢያት_ቅዱስ_ሙሴ በዘመኑ ባልነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መለመኑ እና መልስ ማግኘቱ
"፤ ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ #የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም #አስብ።"
#እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው #ክፋት_ራራ።"
(ኦሪት ዘጸአት 32÷14-14)


፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ

#መልስ
#ኢዮር
#ራማ
#ኤረር


፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
"፤ #እግዚአብሔር#በቅዱሳኑ ላይ #ድንቅ_ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።"
(መዝሙረ ዳዊት 67÷35)


"፤#እግዚአብሔር_በጻድቁ_እንደ_ተገለጠ_እወቁ፤ ።"
(መዝሙረ ዳዊት 3(4)÷3)


#መልሶቹ ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት
👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን ::

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሳምንታዊው ከሁሉም ትምህርት የተወጣጡትን ጥያቄዎች እነሆ ይዘን ቀርበናል፡፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡
ሀ. ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ
ለ. ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ
ሐ. በኃጥአን ላይ ይፈርድባቸው ዘንድ
መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ምን ማለት ነው?
ሀ. ሀዘን ማለት ነው፡፡
ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ሐ. ስብከት ማለት ነው፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. 2ኛ ዜና መዋልእ
ለ. ትንቢተ ኤርሚያስ
ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መ.መጽሐፈ አስቴር

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?
ሀ. ሀምሌ 7
ለ. ሰኔ 7
ሐ. ነሐሴ 7
መ. ግንቦት 7

#5
ከሚከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?
ሀ. ብርሃን
ለ. መላእክት
ሐ. 7ቱ ሰማያት
መ. አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስ ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?
ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዳቢሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
ለ. አምላክ ሰው ሳይሆን የዲያብሎስን ሥራ ማፍረሱን፡፡
ሐ. አምላክ ሰው የሆነው የሰው ልጆችን ያስተምር ዘንድ መሆኑን፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ለ. ወደ ሴት መመልከት
ሐ. መመኘት
መ. መሐላ

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ለ. መዝሙረ ዳዊት
ሐ. የሐዋርያት ሥራ
መ. የማቴዎስ ወንጌል

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?
ሀ. 10
ለ. 9
ሐ. 8
መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?
ሀ. ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ
ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ
ሐ. ቅዱስ ኤፍሬም
መ. ቅዱስ ያሬድ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?
ሀ. ቅድስት ሀና
ለ. ቅድስት ደርዲ
ሐ. ቅድስት ሄሜን
መ. ቅድስት ሄርሜላ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?
ሀ. ከመጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ ጋር
ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር
ሐ. ከትንቢተ ኤርሚያስ ጋር
መ. ከትንቢተ ኢሣይያስ ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ውሃ
ለ. ባህር
ሐ. ውቂያኖስ
መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ሀ. በደብረ ዘይት ተራራ
ለ. በሊባኖስ ታራራ
ሐ. በእናት በአባቷ ቤት
መ. በቤተልሔም በከብቶች ግርግም።

መልሶቻችሁን

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡

በሳምንታዊው ጥያቄዎቹ ላይ ለተሳተፋችሁ አባላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን በአምላከ ቅዱሳን ስም እያቀረብን የጥያቄዎቹን መልሶች እነሆ፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡

#መልስ መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
አምላክ ሰው የሆነው ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ፣ ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ፣ የዲያብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ ነው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ማለት ምን ማለት ነው?

#መልስ ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ኤቫንጋሊዮን ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መጽሐፈ ሶስና የሚቆጠረው ከትንቢተ ዳንኤል ጋር አብሮ እንደ አንድ ነው፡፡

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?

#መልስ ሐ. ነሐሴ 7

#5
ከሚከከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ብርሃን
እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን ብሎ በመናገር ብርሃን ፈጠረ፡፡ ዘፍ 1፡3

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?

#መልስ ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዲብሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
የዲያብሎስ ጥበብ በእባብ ቆዳ ተሰውሮ አዳም እና ሄዋንን ማሳት ሲሆን ጌታችን ይህንን ጥበብ ይሽረው ዘንድ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?

#መልስ ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ጌታችን በወንጌል ‹‹አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡... እኔ ግን እላችኋለው በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡›› ማቴ 5፡21 በማለት ከንቱ ቁጣ ወደ መግደል የሚያደርስ በመሆኑ እንዳንቆጣ አርቆ አጥሮልናል፡፡

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?

#መልስ ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ጸሐፊው ዮሐንስ ወንጌላዊ ሲሆን ይዘቱ ደግሞ ያየው ራዕይ ነው፡፡

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?

#መልስ ለ. 11
ጥንተ አበቅቴ ማለት የሌሊቱ ሱባኤ ሲባዛ በሰባት ሲካፈል በሰላሳ የሚመጣው ትርፍ ማለት ነው፡፡ ይህም 23*7 = 161 ይመጣል፡፡ 161/30 ደግሞ 5 ደርሶ 11 ይቀራል፡፡ ቀሪው ጥንተ አበቅቴ ይባላል፡፡


#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?

መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?

መ. ቅድስት ሄርሜላ
እመቤታችን -› ቅ. ሃና -› ቅ. ሄርሜላ -› ቅ.ሲካር -› ቅ.ቶና -› ቅ.ደርዲ -› ቅ.ሄሜን -› ቅ.ቴክታ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?

ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?

መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡
በዕለተ ሰኑይ የተፈጠረው ብቸኛ ሥነ ፍጥረት ጠፈር (በተለምዶ ሰማይ እየተባለ የሚጠራው) ሲሆን የተፈጠረውም ከውሀ ነው፡፡ አዲስ ሥነ ፍጥረት ያሰኘውም አዲስ ባሕሪ ይዞ ስለተፈጠረ ነው፡፡ ውቅያኖስ እና ባሕር ውሀ በመሆናቸው የእለተ እሁድ ሥነ ፍጥረት ናቸው፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ለ. በሊባኖስ ታራራ

ያላችሁን አስተያየት እና ጥያቄዎች

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ከቅዱስ ያሬድ በተገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት የዐቢይ ጾም አራተኛው ሰንበት “መጻጉዕ” ይባላል፡፡ መጻጉዕ ማለት “በሽተኛ” ማለት ነው፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ ስዳ መጻጉዕን ማዳኑን ቤተክርስቲያን ትሰብካለች፡፡ ለ 38 ዓመታት ያህል የፈውስ ተስፈኛ ሆኖ በመጠመቂያው አጠገብ የኖረ መጻጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ ‹‹አዎን›› እንደሚለው እያወቀ መጻጉዕን ‹‹ልትድን ትወዳለህን?” አለው። መጻጉዕም ‹‹ሰው የለኝም›› በማለት የመዳን ጉጉቱን ከወዳጅ አልባነቱ ጋር ገለጠ። ጌታም ‹‹ተንስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው፡፡ ወዲያው አፈፍ ብሎ በፍጥነት ያን ሁሉ ዘመን የተሸከመችውን ጠንካራ አልጋ ተሸክሟት ሄደ (ዮሐ 5፡1-5)።
ጌታችን መጻጉዕን ‹‹ ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ›› ያለው ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ቅዱስ ኤስድሮስ እንዳለው አልጋው ጠንካራ የብረት አልጋ ነበረና ጽንዓ ተአምራቱን ለማሳየት ነው፡፡ ሁለተኛው ‹‹ታዲያ ቢያድነኝ በከንቱ መች ሆነና የገዛ አልጋዬን ትቼለት የመጣሁ
ለመዳኔ ዋጋ የከፈልኩበት አይደለምን?›› እንዳይል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያለህን ይዘህ ሂድ እኔ ከአንተ አንዳች አልሻም›› ባሰኘ ቃል ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› ብሎታል።
ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው። የሰንበቱም ስያሜ በዕለቱ የሚነበቡትን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ ነው፡፡ በመልእክታቱ የሚነበቡት (ገላ 5፡1 እና ያዕ 5፡14) ስለ ድውያን መፈወስ የሚያወሱ ናቸው፡፡ ከሐዋርያት ሥራ የሚነበውም እንዲሁ (ሐዋ 3፡1)፡፡ የዕለቱ ምስባክ እንዲሁ የድውያንን መፈወስ የሚሰብክ ሲሆን “እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሳ ይለውጥለታል፡፡ እኔስ “አቤቱ ይቅር በለኝ፤ አንተን በድያለሁና ለነፍሴ አስተስርይላት” አልሁ፡፡” ይላል (መዝ 40:3)
ጌታችን መጻጉዕን የፈወሰባት ቦታ ቤተ ሳይዳ ሳትሆን ቤተ ስዳ ናት፡፡
ቤተ ስዳ (Bethesda) በይሁዳ ግዛት ከሚገኙና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን ከፈጸመባቸው ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡ ቤተ ሳይዳ (Bethesaida) ደግሞ በገሊላ አውራጃ የምትገኝ ከተማ ነበረች፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በይሁዳ ኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ ያለችዋን ቤተ ስዳን ‹‹በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ስዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። (ዮሐ 5፥2)›› ብሎ ሲገልጻት በገሊላ የምትገኘዋን ቤተ ሳይዳን ደግሞ ‹‹እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት(ዮሐ 12፥21)›› ብሎ ገልጿታል፡፡
ቤተ ስዳና ቤተ ሳይዳ የተለያዩ ቦታዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ የስማቸውም ትርጉምም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ ቤተ ስዳ ማለት ‹‹ቤተ ሣህል (የጸጋ/የምህረት ቤት)›› ማለት ሲሆን፣ በግሪኩ ቤተ ዛታ ወይም ቅልንብትራ ትባላለች፡፡ ቤተ ስዳ ባለ አምስት በር መመላለሻ አምስት ዓይነት ድውያን ፈውስን ከመጠመቂያው ውኃ ሲጠባበቁ የሚኖሩባት የጌታችን ማዳን የተገለጠባት ሥፍራ ናት። የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርክ/ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ የሚነጻባት በዕለቱ ከአንድ በቀር ለሌላው ፈውስ የማይደገምባት ቦታ ነበረች። ለዚህም ነው ይህች ስፍራ መጠመቂያና መመላለሻ ያላት በመሆኗ የምህረት ቤት የተባለቸው፡፡ እንደስሟ ትርጓሜ ‹‹ቤተ ስዳ›› የተባለችበትም ምክንያት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ አጠገቧ የሚገኝ ሲሆን ለቤተመቅደሱ መስዋእት የሚሆኑ በጎች ሁሉ በዚህ መጠመቂያ ሳይጠመቁ ወደ መስዋእቱ መሰዊያ ቦታ አይቀርቡ ስለነበረ ነው (ዘሌ 9፡2)። ጌታችን በቤተ ስዳ መዳንን ይጠባበቅ የነበረውን መጻጉዕን ፈውሷል፡፡
በቤተ ስዳ መጠመቂያ ይፈጸም የነበረው ድኅነት ምሳሌው እንዲህ ነው፡፡ ውኃውን ያናውጥ (ይባርክ) የነበረው መልአክ የቀሳውስት ምሳሌ፣ ውኃው የጥምቀት ምሳሌ፣ አምስቱ መመላለሻ (እርከን) የአምስቱ አዕማደ ምስጢር፣ የአምስቱ ድውያንና የአምስቱ ፆታ ምዕመናን ምሳሌ ናቸው፡፡ ቤተ ስዳ በዕለተ ቀዳሚት የሚፈወሰው አንድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ አንድ ብቻ መሆኑ አለመቅረቱን ሲያሳይ አለመደገሙ ደግሞ ፍጹም እንዳልነበረ ያሳያል፡፡
በአንጻሩ ቤተ ሳይዳ ማለት ደግሞ “የማጥመጃ ቤት” ወይም ‹‹የዓሳ ቤት›› የሚል ትርጉም ያላትና በተለይ ከሐዋርያቱ አሳ አጥማጆቹ ወንድማማቾች እና ቅዱስ ፊልጶስ የነበሩባት መንደር ነበረች (ዮሐ·1፡45)። ይህች ከተማ ‹‹የዓሳ ቤት›› የተባለችውም ከገሊላ ባህር ዳር የምትገኝ ስለሆነችና ዓሳ የሚያሰግሩ ሰዎች የሚነግዱባት ስለሆነበረች ነው። በዚህ በሞቀ ንግዷ የተነሳ ከተማዋ የተሰበከላትን ወንጌል ለመስማት ባለመቻሏ ጌታችን በተናገረው ትንቢት መሰረት ከሌላዋ ከተማ ከኮራዚን ጋር አብረው ጠፍተዋል (ማቴ 11፣21)፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ሳይዳም ድውያንን ፈውሷል (ማር 8፡22-25)፡፡
መጻጉዕ ግን ያዳነውን ረሳ፤ በሐሰትም መሰከረበት፤ ወደቀደመ “ደዌውም” ተመለሰ፡፡
መጻጉዕ ቀድሞ በቤተ ስዳ እያለ የነበረበትን ያንን ሁሉ ጭንቅ ኋላ በሊቶስጥሮስ አደባባይ ሲቆም ረሳው፡፡ ይህ ምስኪን መጻጒዕ “ሰው የለኝም” ብሎ የደረሰለትን ሰው ረሳ፡፡ ያዳነው ማን እንደሆነ ሲጠየቅ እንኳ አላወቀም። ወንጌላዊውም ‹‹የዳነው ያዳነውን አላወቀውም›› ( ዮሐ.5፥13) ይለዋል። በምኩራብ አግኝቶት ያዳነውን እንዳወቀውም ሄዶ ለአይሁድ ያዳነኝ እርሱ “ጌታ ኢየሱስ ነው” ብሎ ነገራቸው፡፡
ጌታችን መጻጉን ‹‹ ልትድን ትወዳለህን ›› ያለው አስፈቅዶ ለማዳን እንዲሁም በዕለተ ዓርብ ‹‹አድነኝ ሳልለው አድኖኝ›› እንዳይል ሲሆን መጻጉዕ ግን ‹‹ ሰው የለኝም›› ያለው ያድነኛል ብሎ ሳይሆን ‹‹ወደ መጠመቂያው ያደርሰኛል›› ወይም ‹‹ከሚከተሉት አንዱን አዝዞ ወደ መጠመቂያው እንዲያደርሰኝ ያደርጋል›› ብሎ ነበር፡፡
አንድ ሊቅ ይህን ‹‹ታሞ የተነሳ ፈጣውን ረሳ›› የተባለለት መጻጒዕ እና በሐሰት የተከሰሰውን ይቅር ባይ አምላኩን እያደነቀ በጉባዔ ቃናው እንዲህ ተቀኘ፡፡ ” ይትዐረቅ ምስለ ብእሲት ደዌሁ፤ ሠላሳ አዝማነ እስመ ነበረት ምስሌሁ ” (ትርጉም፡ መጻጒዕ ከሚስቱ ከደዌ ጋር ይታረቅ ፤ ሠላሳ ዓመታት ከእርሱ ጋር ኑራለችና)፡፡ ለብዙ ዓመታት አብረው የኖሩ ባልና ሚስት ሲፋቱ ከናፍቆት የተነሳ መለያየቱ እንደሚከብዳቸውና ተመልሰው እንደሚታረቁ ሁሉ ‹‹ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ አትበድል›› ተብሎ ከጌታ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መጻጉዕም ያዳነውን ጌታ በጥፊ መትቶ ዳግመኛ ወደ 38 ዓመት “የአልጋ ወዳጁ” ደዌ ተመልሶ ከእርስዋም ጋር መታረቁን የቅኔው ምስጢር ያስተምረናል። ጌትችን ከደዌው ነጻ አወጣው፤ እርሱ ግን ከደዌው ተለያይቶ መኖር ከብዶት ተመልሶ ታረቃት፡፡ኋላም በአውደ ምኩናን የሐሰት ክስ የቀረበበትን ጌታችንንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀድሞ ወደ መጠመቂያው እንኳ ለመቅረብ አቅም ያልነበረው ዛሬ ግን አልጋ ለመሸከም በበቃውና ያለ ተረፈ ደዌ በጸናው ኃይሉ የጌታውን ጉንጮች በጥፊ የመምታት ጉልበትና ድፍረት አገኘ ። አምላከ ምሕረት የክብር ጌታ ቀድሞ ‹‹ከዚህ የጠናው” ስለ ደዌ ሥጋ ፈንታ ደዌ ነፍስ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል” (ዮሐ 5፡14) ያለውን ዘንግቶ ደዌ ዘኃጢአትን ጠርቶ ተወዳጃት፤ በዕለተ ዓርብ የጌታውን ጉንጮች የጸፉች እጁም ደርቃ ቀርታለች፡፡
የዐቢይ ጾም አራተኛው