ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
ጥያቄዎች


#አዘጋጅ :-መምህር አቤኔ ዘር ማሙሸት

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ


#ኛ ባለንጀራህን እንደ ራስህ አርገህ ውደድ የሚለው ትዕዛዝ የተሰጠው በዘመነ አዲስ ነው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ሕግጋትን መፈጸም ከክርስቶስ አልተማርንም።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ክርስቲያን ሰማያዊ ስለሆነ የመንግስትን ህግ መጠበቅ አይጠበቅበትም።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ መልካም ምኞት የኃጢአት ሥር ናት።

ሀ ሐሰት ለ እውነት

#ኛ ፍቅር የትእዛዛት ሁሉ ማሰሪያ ናት።

ሀ እውነት ለ ሐሰት


#ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ)የክርስቶስ ተከታይ
ለ )ክርስቶሳዊ
ሐ)መዐዛ ክርስቶስን የሚሸት
መ)ሁሉም

#ኛ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚመስለው በምንድን ነው?

ሀ)በአካሄድ በአለባበስ እና በአነጋገር
ለ)በኑሮ ሁሉ
ሐ) ሀ ና ለ መልስ ናቸው
መ)መልሱ አልተሰጠም

#ኛ ሕገ ልቦና የምንለው ዘመን እንዴት ያለውን ዘመን ነው?
ሀ የሙሴን ሕግ የጻፈበትን ዘመን
ለ ሕግ ያልተጻፈበትን ዘመን
ሐ የአዲስ ኪዳንን ዘመን
መ ኦሪትን

#ኛአሥርቱ ትእዛዛት ምን እና ምን ተብለው ይከፈላሉ? (በፍቅር)

ሀ)ፍቅረ ነዋይና ፍቅረ ሃብት
ለ )ፍቅረ እግዚአብሔር እና ፍቅረ ቢጽ
ሐ)እምነት ተስፋ ፍቅረ ተብለው
መ)አይከፋፈሉም

#ኛ ከሚከተሉት መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ ) ለመዳን ምግባር ብቻውን በቂ ነው።
ለ ) ሃይማኖት መሠረት ምግባር ደግሞ ጣራ ግድግዳ ነው።
ሐ) ሃይማኖት ብቻውን ለመዳን በቂ ነው።
መ ) ሁሉም መልስ ናቸው።

#በትምህርቱ መሠረት በአጭሩ አስረዱ

፲ ፩ #ኛ ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ዘርዝሩ

፲፪ #ኛ ሕገ ኦሪትን እና ሕገ ወንጌልን አነጻጽሩ

፲ ፫ #ኛ ክርስቲያናዊ ግዴታዎች የምንላቸውን ዘርዝሩ

፲ ፬ #ኛ የሚያዝኑ ብጹአን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉና። እንዴት ያለ ሀዘን ነው ብጽእናን የሚያስገኘው

፩ ፭ #ኛ እግዚአብሔር አንደኛውን ትእዛዝ (ከኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ የሚለውን ትእዛዝ) ያዘዘበት ምክኒያት ምንድን ነበር

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ድረስ በ👇👇👇👇👇
@abenma
@abenma
በኩል ይላኩልን

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የባሕረ ሐሳብ ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ፡፡

1 ካህናት አባቶች ባሕረ ሐሳብን የግድ መማር አለባቸው፡፡

2 ተንቀሳቃሽ በዓላት ዕለትን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡

3 አንድ ሱባዔ 10 ቀናትን ይይዛል፡፡

4 ለፍጥረት ስድስተኛ ቀን የሆነው ዕለተ አርብ የቃሉ ትርጉም ማካፈያ ማለትነው፡፡

5 ታህሳስ ማለት ፈለገ ማለት ነው፡፡

#ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1 የባሕረ ሀሳብ ስያሜ መካከል የማይደበው የቱ ነው?
ሀ. ሐሳበ ዘመን
ለ. አቡሽሀር
ሐ. የዘመን ሂደት
መ. መርሐ እውር

2 ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

3 ከሚከተሉት መካከል የጌታችን ዓበይት በዓል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጌታችን በዓለ ግርዘት
ለ. በዓለ እንቁጣጣሽ
ሐ. በዓለ ደብረ ታቦር
መ. በዓለ ጰራቅሊጦስ

4 ጥንተ ቀመር ተብሎ የሚጠራው ቀን፡
ሀ. ሰኞ
ለ.ማክሰኞ
ሐ.ረቡዕ
መ.ሰኑይ

5 ‹‹አማረ›› የሚል ትርጉም ያለው የወር ስያሜ የትኛው ነው?
ሀ. ሰኔ
ለ. ሀምሌ
ሐ. ነሀሴ
መ. መስከረም

#በትምህርቱ መሰረት ትክክለኛውን መልስ ስጡ፡፡

1 ቋሚ በዓላት ከሚባሉት ውስጥ ቢያንስ አራቱን ጥቀሱ፡፡

2 የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

3 አውደ ዕለት የምንለው የቱን ቀን ነው?

4 የአንድ አመት አራት ክፍላተ ዘመን የምንላቸውን ዘርዝሩ፡፡ እያንዳንዳቸው ከመች እስከ መቼ አንደሆነ ጥቀሱ፡፡

5 መጋቢት ምን ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው? የወሩ ስያሜ ምንን ያመለክታል?

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇
@Midyam
@Midyam
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#ትምህርተ ሃይማኖት ጥያቄዎች

#አዘጋጅ :- አቤኔ ዘር ማሙሸት

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ መታመን ለማመን የሚሰጥ ተግባራዊ መልስ ነው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ሃይማኖት ለዚህ ዓለም ፈጣሪ ገዢ አስተዳዳሪ አለው ብሎ ማመን ነው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ አንድ ሰው በድንጋይ ቢያምን ሃይማኖት ይባላል።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ዶግማ ሊሻሻል ሊቀየር ሊለወጥ ከሁኔታዎች ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ነው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት

#ኛ ሥላሴ አንድ እና ሦስት ናቸው።

ሀ እውነት ለ ሐሰት


#ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ የጸጋ ምሥጢር የሆነው የቱ ነው?

ሀ) ምሥጢረ ሥላሴ
ለ) ምሥጢረ ሥጋዌ
ሐ) ምሥጢረ ጥምቀት
መ) ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን

#ኛ ለምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ የሆነው ሥነ–ፍጥረት የቱ ነው?

ሀ) ፀሐይ
ለ) አሳ
ሐ) የማክሰኞ እርሻ
መ) ሁሉም መልስ ናቸው።

#ኛ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር የሚናገረው ምሥጢር የቱ ነው?

ሀ ምሥጢረ ሥላሴ
ለ ምሥጢረ ቁርባን
ሐ ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
መ ምሥጢረ ሥጋዌ

#ኛ የሥላሴ ሦስትነት የሆነው የቱ ነው?

ሀ) በአገዛዝ
ለ) በሥልጣን
ሐ) በገጽ
መ) በሕልውና

#ኛ አምላክ እንዴት ሰው ሆነ?

ሀ ) በህድረት
ለ ) በተዋሕዶ
ሐ) ውላጤ
መ) በትድምርት

#በትምህርቱ መሠረት በአጭሩ አስረዱ

፲ ፩ #ኛ የጋለ ብረት ነገረ ተዋሕዶን የሚየስረዳው እንዴት ነው

፲፪ #ኛ ሚጠት ማለት ምን ማለት ነው? አምላክ በሚጠት ሰው አለመሆኑን አስረዱ።

፲ ፫ #ኛ አምላክ ለምን ሰው ሆነ

፲ ፬ #ኛ "ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እንዳይሰማ ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።" ዘፍ 11:7 ይህ ኃይለ ቃል ምሥጢረ ሥላሴን እንዴት እንደሚያስረዳ አብራሩ።

፩ ፭ #ኛ የሥላሴን የስም፣ የግብር እና የአካል ሦስትነት አስረዱ?

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ድረስ በ👇👇👇👇👇
@abenma
@abenma
በኩል ይላኩልን

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit