ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የባሕረ ሐሳብ ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ፡፡

1 ካህናት አባቶች ባሕረ ሐሳብን የግድ መማር አለባቸው፡፡

2 ተንቀሳቃሽ በዓላት ዕለትን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡

3 አንድ ሱባዔ 10 ቀናትን ይይዛል፡፡

4 ለፍጥረት ስድስተኛ ቀን የሆነው ዕለተ አርብ የቃሉ ትርጉም ማካፈያ ማለትነው፡፡

5 ታህሳስ ማለት ፈለገ ማለት ነው፡፡

#ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1 የባሕረ ሀሳብ ስያሜ መካከል የማይደበው የቱ ነው?
ሀ. ሐሳበ ዘመን
ለ. አቡሽሀር
ሐ. የዘመን ሂደት
መ. መርሐ እውር

2 ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

3 ከሚከተሉት መካከል የጌታችን ዓበይት በዓል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጌታችን በዓለ ግርዘት
ለ. በዓለ እንቁጣጣሽ
ሐ. በዓለ ደብረ ታቦር
መ. በዓለ ጰራቅሊጦስ

4 ጥንተ ቀመር ተብሎ የሚጠራው ቀን፡
ሀ. ሰኞ
ለ.ማክሰኞ
ሐ.ረቡዕ
መ.ሰኑይ

5 ‹‹አማረ›› የሚል ትርጉም ያለው የወር ስያሜ የትኛው ነው?
ሀ. ሰኔ
ለ. ሀምሌ
ሐ. ነሀሴ
መ. መስከረም

#በትምህርቱ መሰረት ትክክለኛውን መልስ ስጡ፡፡

1 ቋሚ በዓላት ከሚባሉት ውስጥ ቢያንስ አራቱን ጥቀሱ፡፡

2 የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?

3 አውደ ዕለት የምንለው የቱን ቀን ነው?

4 የአንድ አመት አራት ክፍላተ ዘመን የምንላቸውን ዘርዝሩ፡፡ እያንዳንዳቸው ከመች እስከ መቼ አንደሆነ ጥቀሱ፡፡

5 መጋቢት ምን ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው? የወሩ ስያሜ ምንን ያመለክታል?

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇
@Midyam
@Midyam
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#የባሕረ ሐሳብ መልሶች

የእውነት ሐሰት
1.እውነት
2.እውነት
3.ሐሰት
4.ሐሰት
5.እውነት

ምርጫ
1.ሐ
2.ለ
3.ሐ እና መ (ቦነስ)
4.ለ
5.ሀ

አጭር መልስ
1.ዘመንመለወጫ፡መስቀል፡ገና፡ጥምቀት፡ደብረታቦር፡ወርሃዊና አመታዊ በአላት
2.ሊቀ ጳጳስ ዲሜጥሮስ
3.ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉት ሰባት ዕለታት
4.1መጸው ከመስከረም 26--ታህሣሥ 25፡ 4.2 በጋ ከታህሣሥ 26----መጋቢት 25፡
4.3 ጸደይ ከመጋቢት 26----ሰኔ 26:
4.4 ክረምት ሰኔ 26---መስከረም 25
5.መገበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን መመገብ የሚለውን የአማረኛ ፍቺ ይይዛል፡፡

መልሶቹ ላይ ግር የሚል ያልገባችሁ ጥያቄዎች ካላችሁ @Midyam ላይ ይላኩልን።

ዓውደ ምህረት የእናንተ!!!!!