ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የባለፈው ሳምንት ጥያቄዎቻችንና መልሶቻቸው::
ጥያቄዎቹን ለማስታወስ ያክል

🍁የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተላለፉት ትምህርቶች መሰረት መልስ ስጡበት

1/ በተዋሕዶ አዳነን ስንል ምን ማለታችን ነው ?

2/በኦሪት ከነበሩ የእመቤታችን ምሳሌዎች መካከል ቢያንስ አምስቱን ጥቀሱ
2.1
2.2
2.3
2.4
2.5

3/ቅዱሳን ከምን ከምን ፈተና ይደርስባቸዋል? ቢያንስ ሦስቱን ጥቀሱ
3.1
3.2
3.3

4/ አራቱ ባህያተ ሥጋ የሚባሉት እነማን ናቸው? የእግዚአብሔርንስ ባህሪ እንዴት ይገልጣሉ
4.1
4.2
4.3
4.4





መልሶቻቸው



1/ በተዋሕዶ አዳነን ስንል ዘይትና ውኃ እንደሚቀላቀሉት መለኮትና ሥጋ በመቀላቀል በመደባለቅ ሳይሆን መነጣጠል መለያየት በሌለበት ሁለትነትን አጥፍቶ አንድነትን ባሰገኘ ያለ መደራረብ ያለ ያለ መወዳጀት ያለ እድረት ያለ ሚጠት ያለ ቱሳዬ በፍጽም ተዋሕዶ አዳነን ማለታችን ነው:: ይህን ነገረ ተዋሕዶን ያለ እንከን የሚያስረዳ ፍጽም ምሳሌ ባይኖረም ለተዋሕዶ በሚቀርቡ ምሳሌያት እንመልከት::

የነፍስና ሥጋ መዋሕድ=ሰው
የአይድሮጅንና የኦክስጅን ወኃደት =ውኃ
የብረትና የእሳት መዋሕድ =የፍም ብረት

ነገረ ተዋሕዶን በጋለ ብረት መስሎ መናፍቃንን የረታው ቅዱስ ቄርሎስ ሲሆን ብረትን እንደ ሥጋ መለኮትን እንደ እሳት መስሎ አንድ የጋለ ብረት ብረት ብቻ ነው እንዳንል እሳትነት አለው ያቃጥላል:: አይ እሳት ብቻ ነው እንዳንልም ቅርጽ የሌለው እሳት በብረቱ በመገለጡ የብረቱን ቅርጽ ይዞ ብረት መስሏልና ብረት ብቻ አይባልም እሳትም ብቻ አይባልም ::ልክ እንዲሁ ደግሞ ሥጋን በመንሳቱ የሥጋን በህሪ በህሪው አድርጓልና በሥጋ ጠባይ ተራበ ተጠማ ተያዘ ተጨበጠ ተገረፈ ተሰቀለ ሞተ እንደ አምላክነቱ የመለኮትን ባህሪ ባህሪው ሆኗልና ማዕበል ገሰጸ ሙት አስነሳ በፍቃዱ ሞቶ በሥልጣኑ ተነሳ ስለሆነም ክርቶስም ሰው(ሥጋ)ብቻ ወይም አምላክ(መለኮት)ብቻ ነው አይባልለትም በትንሳኤውም ቢሆን ሐዋርያው ቶማስ ጎኑን ቢዳስሰው እንደአምላክነቱ(መለኮትነቱ) አቃጥሎታል እንደ ሰውነቱ (ሥጋ እንደመንሳቱ) አቀዝቅዞ መልሶ ፈውሶታል አድኖታል:: ስለዚህ ሰው እንደ ቶማስ ሐዋርያ የዳነው በፍጽም ተዋሕዶ ነው::


2/በኦሪት ከነበሩ የእመቤታችን ምሳሌዎች መካከል ቢያንስ አምስቱን ጥቀሱ
2.1 የመጀመሪያይቱ ምድር
2.2 የማክሰኞ እርሻ
2.3 የአቤል ደግነት
2.4 እጸ ሳቤቅ
2.5 በይስሐቅ ፈንታ የታረደው በግ ወዘተ......

3/ቅዱሳን ከምን ከምን ፈተና ይደርስባቸዋል? ቢያንስ ሦስቱን ጥቀሱ
3.1ከሥጋቸው
3.2 ከአላዊያን ነገስታት
3.3 ከጠንቆዮች
3.4ከዲያቢሎስ
3.5 ከመናፍቃን.....

4/ አራቱ ባህያተ ሥጋ የሚባሉት እነማን ናቸው? የእግዚአብሔርንስ ባህሪ እንዴት ይገልጣሉ?

4.1እሳት:-ካዕሌ ኩሉ ሁሉን ቻይነቱን ያሳያል
4.2ነፋስ:-ፈታዬ በጽድቅ(እውነተኛ ዳኛ ነቱን ፈራጅነቱን
4.3ውኃ:-ቸርነቱንና እርህራኤውን
4.4መሬት:-ትዕግስቱን

ለበለጠ መረጃ የተላለፉትን ኮርሶች መመልከት ይቻላል... ይቆየን..

👉ለተሳታፊዎቻን እና ለታዳሚዎቻችን ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን የነፍስ ዋጋ ያድርግልን በእድሜ በጤና🙏 ይጠብቅልን::
ለማንኛውም ሀሳብና አሰተያየት አንዲሁም ጥቆማና ጥያቄ በ @YeawedMeherte ያድርሱን::
#የሥነ _ፍጥረት ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #ኛ_ ሥነ ማለት ያማረ ፣ የተዋበ ፣ የተቆነጀ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ከመፍጠር ያረፈው በዕለተ እሁድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

3 #ቅዱሳን መላእክት የተፈጠሩት ከእሳት እና ከነፋስ ነው::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

4 #የቅዱሳን መላእክት ነገድ ፲ ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

5 #በገቢር(በሥራ) የተፈጠረ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ!!


6 #ኛ_ከሚከተሉት መካከል የእሁድ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው

ሀ አፈር
ለ ጠፈር
ሐ እጽዋት
መ መልስ የለም።

7 #_በነቢብ (በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው

ሀ መላእክት
ለ ብርሃን
ሐ እሳት
መ መሬት

8 #_የኃይላት አለቃቸው ማነው

ሀ ቅዱስ ሚካኤል
ለ ቅዱስ ገብርኤል
ሐ ቅዱስ ሱሪያል
መ ቅዱስ አናንኤል

9 #_ከጠፈር በላይ የሚገኘው ብጥብጥ ውኃ ምን ተብሎ ይጠራል

ሀ ባቢል
ለ ውቂያኖስ
ሐ ሀኖስ
መ ሰማይ

10 #_እግዚአብሔር አምላክ በዕለተ ሰኑይ(ሰኞ) ስንት ፍጥረታትን ፈጠረ

ሀ ምንም አልፈጠረም
ለ አንድ
ሐ ሁለት
መ ስምንት

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_አራቱን ባህሪያተ ሥጋ በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው

፲ ፪ #_አራቱ በህሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባህሪያት ይመሰላሉ ::እንዴት የትኛው የትኛውን ባህሪውን ይመስላል የሚሉትን አስረዱ

፲ ፫ #ኪሩቤልና ሡራፌል የተሰኙት ነገደ መላእክት የእግዚአብሔርን ይሸከማሉ::ለመሆኑ እንዴት #እግዚአብሔርን ችለውት ነው የሚሸከሙት? በኮርሱ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት አስረዱ

፲ ፬ #_ሥነ _ፍጥረታት የተፈጠሩበትን ሦስት ዐላማዎች አስረዱ


፲ ፭ #_ጨለማ_የእግዚአብሔር ባህሪ እንዴት አንደሚገልጥ በትምህርቱ መሠረት አስረዱ

#መልሶቻችሁን እስከ ዛሬ ሳምንት ብቻ
👇👇👇👇👇👇👇
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ላይ ይላኩልን ::

#መልካም_ዕድል
🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የሥነ ፍጥረት መልስ

እውነት ወይም ሐሰት

1 እውነት
2 ሐሰት (ምክኒያቱም በዕለተ ቀዳሚት ሰባተኛው ቀን ነው፡፡ ዘፍ 2፡2-3)
3 ሐሰት (ምክኒያቱም ካለመኖር ወደ መኖር የመጡ ናቸው እንጂ ለመፈጠራቸው ነቅ ወይም ምክኒያት የላቸውም ግን እንደ እሳት ረቂቃን እንደ ነፋስ ፈጣን ናቸው፡፡)
4 ሐሰት (ምክንያቱም 100 ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ነገር ግን አሥር አሥር አድርጎ ለአሥር ከፍሏቸዋል፡፡ 40ውን ነገድ በኢዮር 30ውን በራማ 30ውን በኤረር አስፍሯቸዋል፡፡)
5 እውነት (ዘፍ 2፡7)

ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

6 ሀ ፡- አፈር (አፈር (መሬት) ከአራቱ ባሕሪያተ ሥጋ አንዱ ነው፡፡)
7 ለ ፡- ብርሃን (ዘፍ 1፡3)
8 ሀ ፡- ቅዱስ ሚካኤል
9 ሐ ፡- ሀኖስ
10 ለ ፡- አንድ ሥነፍጥረት እርሱም ጠፈር ነው፡፡

በአጭር መልሱ፡፡

11 አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ የሚባሉት
* እሳት
* ነፋስ
* ውኃ
* መሬት

12 አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባሕሪያት የሚመሰሉት፡
* እሳት ረቂቅ ነው እግዚአብሔርም በባሕሪው ረቂቅ አምላክ ነው፡፡ አንድም እሳት ብርቱ ነው ሁሉን ላጥፋ ቢል ውኃ ካልገደበው በቀር ሁሉን ያጠፋል እግዚአብሔርም ሁሉን ማጥፋት የሚችል ብርቱ አምላክ ነው፡፡
* ነፋስ ፍሬን ከገለባ እንደሚለይ እንዱሁ እግዚአብሔርም በባሕሪው ኃጥኡን ከጻዲቁ የሚለይ እውነተኛ ዳኛ ነው፡፡
* ውኃ እሳት ሁሉን እንዳያጠፋ እንደሚከለክል እንዲሁ እግዚአብሔር በባሕሪው ሩህሩህ ነው፡፡ የሰው ልጅን እንዳያጠፋ ርሕራሔው ይገድበዋልና ነው፡፡
* መሬት የእግዚአብሔርን ባለጸጋነት የሚያስረዳ ነው፡፡ አንድም መሬት በላይዋ ሁሉን እንደምትሸከም እግዚአብሔርም በባሕሪው ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑን ያጠይቃል፡፡

13 እግዚአብሔርን ይሸከማሉ ሲባል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይሸከማቸዋል እንጂ እነሱ የሚሸከሙት ሆኖ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጫማችን እኛን አይሸከመንም፡፡ ይልቁንም እኛ እንሸከመዋለን እንጂ፡፡ ኪሩቤልም ልክ እንደ ጫማ ናቸው፡፡

14 ሥነ ፍጥረት የተፈጠሩበት ዓላማ
* ለምስጋና፡- ሰው እና መላእክት የተፈጠሩበት ዓላማ እግዚአብሔርን አመስግነው የመንግሥቱ ወራሽ የክብሩ የስሙ ቀዳሽ ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡
* ለአንክሮ ለተዘክሮ፡- ሥነ ፍጥረትን አይተን የእግዚአብሔርን ሥራ እናደንቅ ዘንድ፡
* ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ፡- እንመገባቸው እና ለቁመተ ሥጋ ይሆኑ ዘንድ አንድም ለሥጋው ወደሙ ለነፍሳችን ምግብ ይሆኑ ዘንድ
* እንማርባቸው ዘንድ

15 ጨለማ እግዚአብሔር በባሕሪው የማይታይ የማይመረመር አምላክ መሆኑን ያጠይቅልናል፡፡ በጨለማ ያለ እንደማይታይ እንደማይመረመር እንዲሁ እግዚአብሔርም በባሕሪው የማይመረመር ረቂቅ አምላክ መሆኑን ይገልጽልናል፡፡ መዝ 17 (18)፡11

መልሶቹ ላይ ግር ያለ መጠየቅ የምትፈልጉትን @Abenma ላይ ያድርሱን።

ዓውደ ምህረት የናንተ!!!!!!!
#አራቱ_ወንጌላዊያን_በወንጌል_ላይ_ስለ_ጌታችን_ትንሳኤ_የጻፉት_ድርጊቶች_እና_ትዕይንቶች_እርስ_በእርሳቸው_ይጋጫሉ?

አራቱ ወንጌላዊያን ከየራሳቸው የትኩረት አቅጣጫ በዕለተ ትንሳኤ የተከናወኑትን ድርጊቶች እና የተፈጸሙትን ትዕይንቶች እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ እንደገለጠላቸው የሚፈልጉት ነገር ላይ ብቻ የትኩረታቸውን ማዕከል በማድረግ ጽፈዋል።

#ማቴዎስ
👉 በሰንበት ሲነጋ ማርያም መግደላዊት እና ሁለተኛይቱ ማርያም መጡ ይላል። ማቴ 28:1
👉 ሲደርሱም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ድንጋዩን እንዳንከባለለና ትንሳኤውንም አብስሮ ለደቀመዛሙርቱ ሄደው እንዲነግሩ አዘዛቸው። ማቴ 28–2—8
👉 በመንገድ ሲሄዱም ክርስቶስን እንዳገኙትና እንደሰገዱለት ይናገራል። ማቴ 28:9

#ማርቆስ
👉 ሰንበት ካለፈ በዋላ ሰሎሜ፣ መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብ እናት ማርያም ሽቶ ገዝተው ሊቀቡት መምጣታቸውን ይናገራል። ማር 16:1–2
👉 ከሳምንቱ በፊተኛው (እሁድ) ቀን እጅግ ማልደው ፀሀይ ከወጣ በኋላ መጥተው መልአኩ አብስሯቸው ሄደው ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሯቸው አዘዛቸው። ማር 16:3–8
👉ከዛም በኋላ ለማርያም መግደላዊት ብቻ እንደታያት ይናገራል። ማር 16:9

#ሉቃስ
👉በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሽቶ ይዘው ማርያም መግደላዊት፣ ዮሐና፣ የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ማልደው እንደመጡና መቃብሩም ጋር ሁለት መላእክት እንዳዩ ጽፏል። ሉቃ 24:1–8

#ዮሐንስ
👉መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን እሁድ እንደመጣች የመቃብሩን ባዶ መሆን አይታ ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለዮሐንስ ሄዳ መናገሯን እነርሱም መጥተው እንዳረጋገጡ ይናገራል። ዮሐ 20:1–10
👉 ማርያም መግደላዊት ግን የጌታን ሥጋ ወስደውታል ብላ እያለቀሰች እዛው እንደቆየች እና ሁለት መላእክት እንዳየች ጌታ ራሱም ተገልጦ እንዳነጋገራት አትንኪኝ እንዳላት ይናገራል። ዮሐ 20:11–17

ከላይ የተጻፉትን ስንመለከት እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ይመስላሉ ነገር ግን በፍጹም ግጭት የለባቸውም። በአንድ ቀን እንዴት እንዲህ የተለያየ ሁኔታ ሊፈጠር ቻለ የሚያስብል ይመስላል። ነገር ግን ፍጹም ስህተት የሌለው ነው። እያንዳንዱ ከተፈጸመው ነገር የተወሰነውን ወስደው በአገላለጽ አለያይተው ጻፉት እንጂ። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች እግር ኳስ ለማየት ስታዲየም ቢገቡ አንዱ ሜዳ ላይ ስለተደረገው ጨዋታ ቢዘግብ ሌላው ደግሞ ስለ ደጋፊውና ስለ ስታዲየሙ ድባብ ቢናገር ሁለቱ ተጋጭተዋል ማለት አይደለም። አራቱ ወንጌላዊያንም ስለጌታችን ትንሳኤ ሲተርኩ ከተለያየ የትኩረት አቅጣጫ አንድ ነገር ላይ ማዕከል አድርገው ዘገቡት። እንዴት እንደሆነ እንመልከት እስኪ:

#የሰዎቹን_አካሄድ_በተመለከተ

👉ቅዱስ ማቴዎስ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም አለ። ይህ ማለት ወደ መቃብሩ ሌሎች ሰዎች አልመጡም ማለት አይደለም። እነርሱ "ብቻቸውን" መጡ ብሎ አልተናገረምና።

👉ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ማቴዎስ ያልጠቀሳትን ሰሎሜን ጨመራት።

👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ በአጠቃላይ ወደ መቃብሩ የመጡትን ሴቶች ጠቀሳቸው።

👉የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ ማርያም መግደላዊት ከሁሉም ቀድማ (በጭለማ) መምጣቷን ይናገራል።

#ስለተከሰቱት_ትዕይንቶች

👉የቅዱስ ማቴዎስን ዘገባ ስንመለከት መልአኩ ድንጋዩን አንከባሎ ሲቀመጥ ሴቶቹ ተመልክተዋል። ከዛም መልአኩ የመቃብሩን ባዶ መሆን ካዩ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲያበስሩ ነገራቸው። በታዘዙት መሰረት ሄደው ለደቀመዛሙርቱ ሲያበስሩ ዮሐንስ እና ጴጥሮስ መጥተው አረጋግጠው ሄደዋል። ቅዱስ ማቴዎስ ግን መቃብሩን ደቀ መዛሙርቱ መተው ማረጋገጣቸውን ሳይናገር አልፎታል።
በመልአኩ ብስራት ሴቶቹ ለደቀመዛሙርቱ ሊያበስሩ ሲሄዱ በመንገድ ጌታችንን አይተው እንደሰገዱለት ተጽፏል። ይህን ስንመለከት ደግሞ ዮሐንስ ማርያም መግደላዊትን ጌታችን እንዳናገራትና አትንኪኝ እንዳላት የተጻፈውን ሳይገልጥ ሴቶቹ ጌታን እንዳገኙት ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ንገሯቸው ሚለውን ብቻ ጽፏል። ይህ ማለት ግን ሌሎች ድርጊቶች አልተፈጸሙም ማለት አይደለም።

👉ቅዱስ ማርቆስ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሳይገልጥ መቃብሩን መልአኩ እንዳሳያቸው እና ሄደው ትንሳኤውን እንዲያበስሩ እንዲሁም ጌታ መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት መታየቱን ገለጸ።

👉ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ መልአኩ ድንጋዩን ማንከባለሉን ሴቶቹንም መላእክቱ እንዳናገሯቸው ሄደውም እንዲያበስሩ እንደነገሯቸው ጻፈ። ደቀ መዛሙርቱም በሴቶቹ ብስራት መጥተው ማረጋገጣቸውን ቅዱስ ጴጥሮስ ብሎ ቅዱስ ዮሐንስን ሳይጠቅስ ጽፏል። ቅዱስ ጴጥሮስ ብቻውን ነው የሄደው ማለት ግን አይደለም። ምክኒያቱም "ጴጥሮስ ብቻ" አይልምና።

👉ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሌሎቹ ሴቶች ዘግይተው የመጡ ቢሆንም ቀድማ የመጣቸው ግን ማርያም መግደላዊት ስለነበር ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት መጣች ብሎ ተናገረ። ይህ ማለት ከእርሷ በኋላ ሌሎቹ ሴቶች አልመጡም ማለት አይደለም። የድንጋዩን መፈንቀል የመቃብሩን ባዶ መሆን ሄዳ ለደቀ መዛሙርቱ (ለጴጥሮስ እና ለዮሐንስ) ተናገረች። እነርሱም መተው አረጋግጠው ሄዱ። እርሷ ግን እዛው እያለቀሰች ቆየች መላእክቱም ስለ ምን እንደምታለቅስ ጠየቋት ጌታችንንም አገኘችው። አትንኪኝ አላት። ከሁሉም ቀድማ ትንሳኤውን አየች።

እንደተመለከትነው አራቱም ወንጌላዊያን መጥቀስ የፈለጉትን ነገር ብቻ ጠቅሰው ተናገሩ እንጂ ታሪኩን አላፈለሱትም እርስ በእርሳቸውም አልተጋጩም።

#እስኪ_ሙሉ_ታሪክ_እና_ትዕይንቱን_እንመልከት

ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ጭለማ ሳለ በማለዳ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሥጋ ሽቱ ልትቀባ መጣች። ከእርሷም ተከትለው ሌሎቹ ሴቶች ወደ መቃብሩ መጡ። የጌታ መልአክ ወርዶም ድንጋዩን አንከባለለው። መቃብሩም ባዶ መሆኑን ሴቶቹ ተመለከቱ። መላእክቱም መቃብሩ ባዶ መሆኑን እርሱም መነሳቱን ነገሯቸው ለደቀመዛሙርቱም እንዲነግሯቸው አዘዟቸው። ሴቶቹም ሄደው መቃብሩ ባዶ መሆኑንና ጌታም መነሳቱን ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ነገሯቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስም መጥተው አረጋገጠው ተመለሱ። ከእነርሱ ኋላም ሴቶቹ መጥተው ነበር ማርያም መግደላዊትም ጭምር መቃብር ውስጥ መላእክት ተገልጸው ከሴቶቹ ጋር ሲነጋገሩ ውጪ ደግሞ ለማርያም መግደላዊት ጌታ ተገለጠላት። መነሳቱንም ተጠራጥራ ነበርና አትንኪኝ አላት። ውስጥ የነበሩት ሴቶች የምስራቹን ለማብሰር በመንገድ ሲሄዱ ጌታ ራሱ ተገለጠላቸው። እነርሱም ሰገዱለት። (ለማርያም መግደላዊት ሲታያት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።) የሆነውን ለደቀ መዛሙርቱ ነገሯቸው። በዚህ መሰረት አራቱም ወንጌላዊያን የጻፉትን ስንመለከት ምንም ግጭት እንደሌለ መረዳት እንችላለን።

ይቆየን።
በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ሃያ
አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆኖ እግዚአብሔርን እንዳመሰገነ
የሚናገር የገድሉ ዜና ይህ ነው፡፡

ሱራፌል ማለት አጠንተ መንበሩ
ለልዑል ማለት ነው፡፡ ተፈጥሯቸው ከብርሃን አካላዊ ነው፡፡
በቁጥር ሃያ አራት ናቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት
ክንፎች አሏቸው በሁለቱ ክንፎች ፊታቸውን ይሸፍናሉ አንተን ማየት
አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ወዲያና ወዲህ ይላሉ የወርቅ አክሊል
ተቀዳጅተው ብርሃን ተጎናጽፈው ማዕጠንተ ወርቅ ይዘው መንበሩን
እያጠኑ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሰግናሉ፡፡
"ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር አብን እናመስግነው
ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ወልድን
እናመስግነው ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር
መንፈስ ቅዱስን እናመስግነው ይል ነበር በብርሃኑም ልክ በስተቀኝ
ሰባት አክሊሎች አሉ የሰባቱም አክሊሎች ኅብራቸው
አይመሳሰልም አብሮኝ ያለውንም መልአክ ይህን ቤት ከማየት
የተነሣ ፍርሃት በልቤ አደረብኝ አልኩት፡፡ የቤቱን ነገር ልንገርህ እኔ
ተልኬያለሁ አትፍራ አለኝ ይህንንም ባለኝ ጊዜ ፍርሃት ከኔ እራቀ
በቃሉም አጸናኝ ቀድሞ ያልሰማሁት የዚህ ቤት ትልቅነቱ ምን ያኅል
ነው በውስጡስ ያለው የተቀመጠውስ ማነው አልሁት፡፡አስቀድሞ
ያየኸውን ያይደለ እይ ኋላ የቤቱን ጌታ እነግርሃለሁ አለኝ በዚያም
ዙፋን ፊት ለፊት የተተከለውን የብርሃን ዓምድ አየሁ የብዙ ሰዎች
ስም ተጽፎበት ነበርና ጌታዬ እሊህ ምንድን ናቸው የአዕማዱስ
ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የዙፋኖቹስ ስራቸው ምንድነው
አልሁት፡፡
ይህ ቤት ያንተ ቤት ነው ከሌሎችም ይልቅ እጅግ የከበረው
የመካከለኛው ዙፋን ልዩም ልብስም በላዩም የተቀመጡት
አክሊሎች ያንተ ናቸው በግራ በቀኝ ያሉ ዙፋኖች ግን ትእዛዝህን
በመጠበቅ በወንበርህ ለሚቀመጡ ካንተ በኋላ ለሚነሱ ልጆችህ
ነው፡፡በዙፋኖች በስተቀኝ ያሉ አእማድ ቁጥራችው ዓርባ አምስት
ሺህ በግራም ያሉ የመላዕክት ፈጣሪ እንደሠራቸው ዓርባ አምስት
ሺህ ናቸው የብዙ ሰዎችም ስም በዓምዱ ተቀርጾ የሚታየው ይህ
ዓለም አስኪያልፍ ድረስ ከመንፈስ ቅዱስ ላንተ የሚወለዱ ልጆችህ
ናቸው ለነዚህም አንተ አባት ትሆናቸዋለህ አለኝ፡፡
ይህቺ ታላቅ ጸጋ ክብር ትሰጠኝ ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ አልሁት
እግዘኢብሔር ለወደደው ባለሟልነትና ክብርን ይሰጣልና ነው
አለኝ ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃ ውስጥ አግብቶ
ከሥላሴ ዙፋን ፊት ለፊት አቆመኝና ሰገድኩለት ከዚያ አስቀድሞ
በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡
ተክለሃይማኖት ክፍልህ ከሃያ አራቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን የሚል
ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና
አንድነት አጠንኩ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደ
ልብሳቸው ሆነ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ ራእይ
4÷ 6-11 እንደወደድከኝ እወድሃለሁ እንዳከበርከኝ አከብርሃሁ
ስምህንም ልዑል ክቡር አደርገዋለሁ በጸሎትህም የሚታመን ሰው
ሁሉ ስላንተ ይድናል መታሰቢያህንም እንደተቻለው ያደረገ እኔ
በሰማይና በምድር አገነዋለሁ ባንተ ክብር እንዲከብር አደርገዋሁ
ብዬ እነግርሃለሁ፡፡ ጭንቅ መከራ ያገኘውም ቢሆን በስምህ
ቢጠራኝ እኔ ከጭንቀተቱ ሁሉ አደነዋለሁ ከሰባቱ ከመላዕክት
አለቆች ጋር መቆምን እኔ እከፍለዋለሁ የገድልህ መጽሐፍ
በተነበበበት ስምህም በተጠራበት ቦታ ለዘላለም ይቅረታዬና
ቸርነቴ በዚያ ይኖራል አለ፡፡
አመሰገንኩት ሰገድኩለትም በስራዬ ሳይሆን በፈቃድህ ይህንን ሁሉ
ለሰጠኸኝ ላንተ ምስጋና ይግባህ አልኩት ከዚህ በኋላ መልአኩ
ወደ ቀደመ ኑሮዬ መለሰኝ አለ ብፁዕ አባታች ይህንን አይቶ
በሰማይ በምድር ፈጣሪው ፍቅር እንደ እሳት ልቡ ነደደ ዘወትር
የዳዊትን መዝሙር ሌሎቹንም የነቢያትንና የሐዋርያትን መጽሐፍ
ያነብ ነበር እነጂ ሌሊትና ቀን አይተኛም ነበር … ፡፡" ከጻድቁ
አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት ይክፈለን! አሜን!
ምንጭ፡- ገድለ ተክለሃይማኖት ዘዓርብ ምዕራፍ 43
አዘጋጅ፡-በአዲስ አበባ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት
ቤተክርስቲያን
የምክሐ ደናግል ማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር (ሰንበት ት/
ቤት)
የመረጃ መዛግብትና ኦድዮቪዥዋል ክፍል መካነ ድር ማስተባበሪያ የተዘጋጀ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
ኅዳር ፳፻፲፩ ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ኢኦተቤ02_06.amr
690.3 KB
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክ

#ክፍል አሥራ አምስት

#በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ይዘት
👉 የመራ ተክለሃይማኖት (ዛግዌ) መነሳት ጠጠውድም ጃንስዩምና ግርማ ስዩም
👉 አራቱ ቅዱሳን ነገሥት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥነ_ፍጥረት

#ክፍል_ሁለት

#ዲያቆን #ኢዩኤል_ዳኛቸው

#ይዘት
👉 የዕለተ እሁድ ሥነ ፍጥረት አራቱ ባሕርያት

#አድማጮች የምትሳተፉባቸው ከትምህርቱ የተወጣጡ ጥያቄዎች

አራቱ ባሕርያት ከምን ተፈጠሩ?
አራቱ ባሕርያት የእግዚአብሔርን ባሕሪይ እንዴት ይገልጻሉ?
አራቱ ባሕርያተ ሥጋ እንዴት የሰው ልጅን የዕድሜ እርከን ይገልጣሉ?

መልሳችሁን

👉 @Abenma

ላይ አድርሱን።

እንዲሁም ትምህርቱ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ

👉 @Midyam
👉 @Estiffit
👉 @Abenma

ላይ ያድርሱን። ትምህርቱን ለወዳጆችዎ ማጋራቱን አይዘንጉ።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዝኦ ለአዳም
ሠላም
እም ይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

እርሶ የሚሳተፉባቸው የትንሳኤ ጥያቄዎች

1 አራቱ ወንጌላውያን የክርስቶስን ትንሳኤ ሲተርኩ እርስ በራሳቸው የሚጋጩ ይመስላሉ። እነዚህን የተጋጩ የሚመስሉ ነገሮች እንዴት ይታያሉ? ለምሳሌ የሰዎቹ አከሀሄድ፣ ጊዜው፣ የመላእክቱ ቁጥር ወዘተ…

2 ጌታችን በከርሰ መቃብር 3 ቀን 3 ሌሊት ማደሩን አስረዱ።

3 ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በራሱ ሥልጣን ሆኖ ሳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋ 2:24 ላይ "እግዚአብሔር አስነሳው።" ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው? እግዚአብሔር አስነሳው ማለት ምን ማለት ነው?

መልሶቻችሁን

@Abenma እና @Estiffit

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
የትንሳኤ መልስ አንድ.mp3
1.8 MB
#የጥያቄ_መልስ

ክፍል አንድ

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዝኦ ለአዳም
ሠላም
እም ይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

እርሶ የሚሳተፉባቸው የትንሳኤ ጥያቄዎች

አራቱ ወንጌላውያን የክርስቶስን ትንሳኤ ሲተርኩ እርስ በራሳቸው የሚጋጩ ይመስላሉ። እነዚህን የተጋጩ የሚመስሉ ነገሮች እንዴት ይታያሉ? ለምሳሌ የሰዎቹ አከሀሄድ፣ ጊዜው፣ የመላእክቱ ቁጥር ወዘተ…

በወንድማችን #አቤኔዘር

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
#የሥነ _ፍጥረት ጥያቄዎች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

1 #ኛ_ ሥነ ማለት ያማረ ፣ የተዋበ ፣ የተቆነጀ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ከመፍጠር ያረፈው በዕለተ እሁድ ነው::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

3 #ቅዱሳን መላእክት የተፈጠሩት ከእሳት እና ከነፋስ ነው::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት

4 #የቅዱሳን መላእክት ነገድ ፲ ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

5 #በገቢር(በሥራ) የተፈጠረ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ!!


6 #ኛ_ከሚከተሉት መካከል የእሁድ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው

ሀ አፈር
ለ ጠፈር
ሐ እጽዋት
መ መልስ የለም።

7 #_በነቢብ (በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው

ሀ መላእክት
ለ ብርሃን
ሐ እሳት
መ መሬት

8 #_የኃይላት አለቃቸው ማነው

ሀ ቅዱስ ሚካኤል
ለ ቅዱስ ገብርኤል
ሐ ቅዱስ ሱሪያል
መ ቅዱስ አናንኤል

9 #_ከጠፈር በላይ የሚገኘው ብጥብጥ ውኃ ምን ተብሎ ይጠራል

ሀ ባቢል
ለ ውቂያኖስ
ሐ ሀኖስ
መ ሰማይ

10 #_እግዚአብሔር አምላክ በዕለተ ሰኑይ(ሰኞ) ስንት ፍጥረታትን ፈጠረ

ሀ ምንም አልፈጠረም
ለ አንድ
ሐ ሁለት
መ ስምንት

#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_አራቱን ባህሪያተ ሥጋ በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው

፲ ፪ #_አራቱ በህሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባህሪያት ይመሰላሉ ::እንዴት የትኛው የትኛውን ባህሪውን ይመስላል የሚሉትን አስረዱ

፲ ፫ #ኪሩቤልና ሡራፌል የተሰኙት ነገደ መላእክት የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ::ለመሆኑ እንዴት #እግዚአብሔርን ችለውት ነው የሚሸከሙት? በምሳሌ መሠረት አስረዱ

፲ ፬ #_ሥነ _ፍጥረታት የተፈጠሩበትን ሦስት ዐላማዎች አስረዱ


፲ ፭ #_ጨለማ_የእግዚአብሔር ባህሪ እንዴት አንደሚገልጥ በትምህርቱ መሠረት አስረዱ

🙏🙏🙏🙏🙏
@AwediMeherit
@AwediMeherit
@AwediMeherit
የሥነ ፍጥረት ጥያቄዎች መልስ

እውነት ወይም ሐሰት

1 እውነት
2 ሐሰት (ምክኒያቱም በዕለተ ቀዳሚት ሰባተኛው ቀን ነው፡፡ ዘፍ 2፡2-3)
3 ሐሰት (ምክኒያቱም ካለመኖር ወደ መኖር የመጡ ናቸው እንጂ ለመፈጠራቸው ነቅ ወይም ምክኒያት የላቸውም ግን እንደ እሳት ረቂቃን እንደ ነፋስ ፈጣን ናቸው፡፡)
4 ሐሰት (ምክንያቱም 100 ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ነገር ግን አሥር አሥር አድርጎ ለአሥር ከፍሏቸዋል፡፡ 40ውን ነገድ በኢዮር 30ውን በራማ 30ውን በኤረር አስፍሯቸዋል፡፡)
5 እውነት (ዘፍ 2፡7)

ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

6 ሀ ፡- አፈር (አፈር (መሬት) ከአራቱ ባሕሪያተ ሥጋ አንዱ ነው፡፡)
7 ለ ፡- ብርሃን (ዘፍ 1፡3)
8 ሀ ፡- ቅዱስ ሚካኤል
9 ሐ ፡- ሀኖስ
10 ለ ፡- አንድ ሥነፍጥረት እርሱም ጠፈር ነው፡፡

በአጭር መልሱ፡፡

11 አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ የሚባሉት
* እሳት
* ነፋስ
* ውኃ
* መሬት

12 አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ በእግዚአብሔር ባሕሪያት የሚመሰሉት፡
* እሳት ረቂቅ ነው እግዚአብሔርም በባሕሪው ረቂቅ አምላክ ነው፡፡ አንድም እሳት ብርቱ ነው ሁሉን ላጥፋ ቢል ውኃ ካልገደበው በቀር ሁሉን ያጠፋል እግዚአብሔርም ቸርነቱ ርሕራሔው ካልገደበው ሁሉን ማጥፋት የሚችል ብርቱ አምላክ ነው፡፡
* ነፋስ ፍሬን ከገለባ እንደሚለይ እንዱሁ እግዚአብሔርም በባሕሪው ኃጥኡን ከጻዲቁ የሚለይ እውነተኛ ዳኛ ነው፡፡
* ውኃ እሳት ሁሉን እንዳያጠፋ እንደሚከለክል እንዲሁ እግዚአብሔር በባሕሪው ሩህሩህ ነው፡፡ የሰው ልጅን እንዳያጠፋ ርሕራሔው ይገድበዋልና ነው፡፡
* መሬት የእግዚአብሔርን ባለጸጋነት የሚያስረዳ ነው፡፡ አንድም መሬት በላይዋ ሁሉን እንደምትሸከም እግዚአብሔርም በባሕሪው ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑን ያጠይቃል፡፡

13 እግዚአብሔርን ይሸከማሉ ሲባል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይሸከማቸዋል እንጂ እነሱ የሚሸከሙት ሆኖ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጫማችን እኛን አይሸከመንም፡፡ ይልቁንም እኛ እንሸከመዋለን እንጂ፡፡ ኪሩቤልም ልክ እንደ ጫማ ናቸው፡፡

14 ሥነ ፍጥረት የተፈጠሩበት ዓላማ
* ለምስጋና፡- ሰው እና መላእክት የተፈጠሩበት ዓላማ እግዚአብሔርን አመስግነው የመንግሥቱ ወራሽ የክብሩ የስሙ ቀዳሽ ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡
* ለአንክሮ ለተዘክሮ፡- ሥነ ፍጥረትን አይተን የእግዚአብሔርን ሥራ እናደንቅ ዘንድ፡
* ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ፡- እንመገባቸው እና ለቁመተ ሥጋ ይሆኑ ዘንድ አንድም ለሥጋው ወደሙ ለነፍሳችን ምግብ ይሆኑ ዘንድ
* እንማርባቸው ዘንድ
* የሕልውናው መገለጫ ይሆኑ ዘንድ

15 ጨለማ እግዚአብሔር በባሕሪው የማይታይ የማይመረመር አምላክ መሆኑን ያጠይቅልናል፡፡ በጨለማ ያለ እንደማይታይ እንደማይመረመር እንዲሁ እግዚአብሔርም በባሕሪው የማይመረመር ረቂቅ አምላክ መሆኑን ይገልጽልናል፡፡ መዝ 17 (18)፡11

መልሶቹ ላይ ግር ያለ መጠየቅ የምትፈልጉትን @Amtcombot ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የቃልኪዳን ልጆች የጻዲቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳኑ ሁሉ ወዳጆች በሩቅም በቅርብም ያላችሁ እንደምን ቆያችሁ? አሜን እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘላለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረና የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሳምንታዊው ከሁሉም ትምህርት የተወጣጡትን ጥያቄዎች እነሆ ይዘን ቀርበናል፡፡

#1
ከሚከተሉት አንዱ አምላክ ሰው የሆነበት ምክኒያት ነው፡፡
ሀ. ለሰው ልጆች አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ
ለ. ፍቅሩን ይገልጽልን ዘንድ
ሐ. በኃጥአን ላይ ይፈርድባቸው ዘንድ
መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡

#2
ወንጌል የቃሉ ትርጉም ምን ማለት ነው?
ሀ. ሀዘን ማለት ነው፡፡
ለ. የምስራች ማለት ነው፡፡
ሐ. ስብከት ማለት ነው፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#3
የመጽሐፈ ሶስና እናት መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. 2ኛ ዜና መዋልእ
ለ. ትንቢተ ኤርሚያስ
ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
መ.መጽሐፈ አስቴር

#4
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መቼ ተጸነሰች?
ሀ. ሀምሌ 7
ለ. ሰኔ 7
ሐ. ነሐሴ 7
መ. ግንቦት 7

#5
ከሚከተሉት ሥነ ፍጥረት መካከል በነቢብ(በመናገር) የተፈጠረው የቱ ነው?
ሀ. ብርሃን
ለ. መላእክት
ሐ. 7ቱ ሰማያት
መ. አራቱ ባሕሪያተ ሥጋ

#6
‹‹ስለዚህ የድያብሎስ ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡9 ይህ ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል?
ሀ. አምላክ ሰው የመሆኑ ምሥጢር የዳቢሎስን ጥበብ በጥበቡ ይሽር ዘንድ መሆኑን፡፡
ለ. አምላክ ሰው ሳይሆን የዲያብሎስን ሥራ ማፍረሱን፡፡
ሐ. አምላክ ሰው የሆነው የሰው ልጆችን ያስተምር ዘንድ መሆኑን፡፡
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

#7
ወደ መግደል የሚያደርስ መንገድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከንቱ የሆነ ቁጣ
ለ. ወደ ሴት መመልከት
ሐ. መመኘት
መ. መሐላ

#8
ከሚከተሉት መጻሕፍት መካከል በጸሐፊው እና በይዘቱ የተሰየመው መጽሐፍ የቱ ነው?
ሀ. የዮሐንስ ራዕይ
ለ. መዝሙረ ዳዊት
ሐ. የሐዋርያት ሥራ
መ. የማቴዎስ ወንጌል

#9
ጥንተ አበቅቴ ስንት ነው?
ሀ. 7
ለ. 11
ሐ. 19
መ. 21

#10
አንድ ሱባኤ ስንት ቀናቶችን ይይዛል?
ሀ. 10
ለ. 9
ሐ. 8
መ. 7

#11
የጥንተ አበቅቴ እና የጥንተ መጥቅዕ ቀመር አዘጋጅ ቅዱስ አባት ማነው?
ሀ. ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ
ለ. ቅዱስ ዲሜጥሮስ
ሐ. ቅዱስ ኤፍሬም
መ. ቅዱስ ያሬድ

#12
የእመቤታችን ሀያት ማን ተብላ ትጠራለች?
ሀ. ቅድስት ሀና
ለ. ቅድስት ደርዲ
ሐ. ቅድስት ሄሜን
መ. ቅድስት ሄርሜላ

#13
መዝሙር ዘሠልስቱ ደቂቅ የሚለው መጽሐፍ አቆጣጠሩ ከየትኛው መጽሐፍ ጋር ነው?
ሀ. ከመጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ ጋር
ለ. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር
ሐ. ከትንቢተ ኤርሚያስ ጋር
መ. ከትንቢተ ኢሣይያስ ጋር

#14
የዕለተ ሰኑይ ሥነ ፍጥረት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ውሃ
ለ. ባህር
ሐ. ውቂያኖስ
መ. መልሱ አልተሰጠም፡፡

#15
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየት ተወለደች?
ሀ. በደብረ ዘይት ተራራ
ለ. በሊባኖስ ታራራ
ሐ. በእናት በአባቷ ቤት
መ. በቤተልሔም በከብቶች ግርግም።

መልሶቻችሁን

👉 @Amtcombot

ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ካህናት ልክ እንደ ሀያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲህ አጥነውታል።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ጷጉሜ የተባለችው ወር ከየት መጣች?
______ (በአለቃ ዕፁብ ማናዬ)____________

ብዙዎቻችን ስለ ዓመት ስንናገርና ለልጆቻችን ስናስተምር አንድ ዓመት 365 ¼ ቀንት፣ 52 ሳምንታት እና 12 ወራት በማለት እንናገራለል፡፡ እውነትም ልክ ነው፤ ነገር ግን 365 ¼ ማለት ምን ማለት ነው? ¼ የሚባል ቀን አለን? 12 ወራት በሠላሳ በሠላሳ ቀናት የተከፋፈሉ ሆነው ድምራቸው 12X30 = 360 ነው፡፡ ታዲያ 5ቀናት እና ¼ የተባለው ከየት መጣ? ጷጉሜስ የተባለችው ወርስ ከየት መጣች? ለሚባሉትን ጥያቄዎች አስተዋዮች ይጠይቃሉ፡፡ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን እንደሚከተለው ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ አስቀምጠውልናል፡፡(ይህ መልስ ብዛት ካላቸው የብራና ጽሑፎች ተውጣቶ ቀለል ባለ ዘዴ የቀረበ ነው፡፡) ይህ ትምህርት የሚገኘው አቡሻኽር በተባለው የቤተክርስቲያን ትምህርት ነው ፡፡ ትምህርቱ ሰፊ ነው፡፡ አብዛኛውም የሒሳብ ስሌት ያለበትም ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደተነሳንበት ስንመለስ ስንት ወቅቶች አሉን ከተባለ አራት ናቸው፡፡ እነሱም
#1 ክረምት(ከሰኔ26 መስከረም25)፣
#2 መፀው/መከር(ከመስከረም26- ታኅሣሥ25)፣ #3 በጋ/ሐጋይ (ከታኅሣሥ26 - መጋቢት25)፣
#4 ጸደይ/በልግ(ከመጋቢት26 - ሰኔ25) ነው፡፡ እያንዳንዱ ወቅት ደግሞ ሦስት ወራትን ይዟል፡፡ 3X30=90 ነው፡፡ 90 ሲባዛ በ4 ደግሞ 360 ነው፡፡ እንግዲህ የስሌቱ ነገር የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ከላይ አንድ ወቅት 90 ቀን ሳይሆን 91 ቀን 7ሰዓት እና 30 ደቂቃ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው የየወሩ ቀን ማጠር እና መርዘምን ተከትሎ በሚመጣ ልዩነት ነው፡፡ #ለምሳሌ
መስከረም ላይ 12 ሰዓት አይመሽም ብርሃን ነው፡፡
ታኅሣሥ ላይ ግን 12 ሰዓት ጭልምልም ይላል፡፡ ሌሊቱም ረዥም ነው፡፡ ለምሳሌ እነዚህ ቀረቡ እንጂ እያንዳንዱ ወር የተለያየ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ጠቅላላውን አራቱንም ወቅቶች ስንደምራቸው የምናገኘው ውጤት አንድ ዓመትን ያስገኙልናል፡፡
🚩ክረምት 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩መፀው 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩በጋ/ሐጋይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩ጸደይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
::::::::::::::::::::::::::
ጠቅለል አድርገን ስንደምረው ዘጠና ዘጠናው ቀን ስንደምረው 90 X 4 = 360 ይሆናል፡፡ ይህ የአሥራሁለት ወሩን ያዘ ማለት ነው፡፡ የየወቅቱን አንዳንድ ቀን ስንደምር 1 X 4 = 4 ይሆናል፡፡ ይህም የጷጉሜ አራቱ ቀናት ናቸው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የቀሩትን 7 ሰዓት እና 30 ደቂቃዎች ስንደምራቸው 30ሰዓት ይመጣል፡፡ ወደ ዕለት ሲቀየር 1 ቀን እና 6 ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከላይ ካገኘነው 4 ጋር ሲደመር 5 ቀናት እና 6 ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡
#በጠቅላላ አንድ ዓመት 365 ከ6ሰዓት ወይም ¼የሚባለው ለዚህ ነው ይህ ስድስት ሰዓት በአራት ዓመት አንድቀን ሆኖ ጷጉሜ ስድስት እንድትሆን ያደርገዋል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጳጉሜ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ጭማሪ” ማለት ነው ፡፡ በግእዝ “ወሰከ – ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ተውሳክ (ተጨማሪ) ማለት ነው፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የዓመት ተጨማሪ ወር አድርገናታል፡፡ ይህቺ ወር በ600 ዓመት 7 ትሆናለች ነገር ግን ሊቃውንት ይቺን የትርፍ ትርፍ ናትና ከስሌት ውጪ የማይኖርባት በማለት ይገልጧታል፡፡

#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit

ጷጉሜ ፫/፳ ፻- ፲፪ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#ሐዲስ_ሱራፊ_ተክለ_ሃይማኖት

#ሱራፊ ማለት መልአክ፣ ከካህናተ ሰማይ አንዱ ማለት ነው፡፡ ሱራፌን፣ ሱራፌል፣ ሱራፌም (በፅርዕ ሴራፊም፣ በዕብራይስጥ ስራፊም) ማለት የነገድ ስም፣ ልዑላን መላእክት፣ ሊቃናት፣ የሚያጥኑ፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ቀዳሾች ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/ ከዚህ ላይ ሱራፊ ነጠላ ቍጥርን ሲያመለክት፤ ሱራፌል ደግሞ ብዙ ቍጥርን ያመለክታል፡፡ ሱራፌል ለቅዱሳን በሰው አምሳል በመገለጣቸው ሽማግሌዎች ተብለው ተጠርተዋል /ኢሳ.24፥23፤ መሳ.13፥2-25፤ /፡፡ በግእዝ ቋንቋ ደግሞ ካህናተ ሰማይ ይባላሉ፡፡ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ቁጥራቸው 24 እንደሆነ ባለ እራዮ ዮሐን ጽፎልናል ይህ ግን 24ሰዓት ያለ እረፍት የሚያመሰግኑ መሆናቸውን ለማመልከት የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጂ ቁጥራቸውስ 24ብቻ ሆኖ አይደለም ።


ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ አቅሮቦላቸዋል። በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ24ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው / መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ እንደተረጎመው)

ዛሬ በዚህች መጠነኛ ጽሁፍ ኅዳር 24ቀን ከነዚህ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ጋር ተደምሮ የሥላሴን መንበር ያጠነ አዲሱን ምድራዊ ሱራፊን ተክለ ሃይማኖት /ተክለ ኤልን /እናስተዋውቃችዋለን። ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ከዘር የተገኙ ምድራዊያን አይደለም ተክለ ኤል ተክለ ሃይማኖት ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ምድራዊ ሰው የሆነ ሐዲስ ሱራፊ ነው።
‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ ፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.15፥13/፡፡

"ኤል" ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘሉ በመሆናቸው የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው ለምሳሌ ከላይ የጠቀስናቸው የሃያራቱን ካህናተ ሰማይ የሱራፌልን ስም መመልከት ይቻላል :- አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል ወ.ዘ.ተ ስለዚህ "ተክለ ኤል " ማለታችንም ይህ ሐዲስ ሱራፊ ስሙ ከስማቸው ጭምር የሚገጥም መሆኑን ለመግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ተክል ተክለ እግዚአብሔር ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ " ተክለ ኤል" ተክለ እግዚአብሔር ሲባልም የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል የሚል ትርጉም ይሰጣል ።


#አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ (የአብ ሥጦታ) ከሚባል ካህን እና ሣራ ወይም እግዚእ ኅረያ(እግዚአብሔር የመረጣት)በመባል ከምትታወቅ ደጋግ ከሆኑ ባልና ሚስቶች በመላእክ አብሳሪነት መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ገደማ ነው።
ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጺዮን ።(የፂዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ለህጻኑ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡ ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ነበር ቀን ከለሊት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ማመስገን የመላእክት መገለጫ ነውና ኢሳ 6÷6 ። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚእ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምስጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ ዐይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር በዱር ፈረስ ሲጋልብ ጦር ሲሰብቅ ተገናኝቶት ፍስሐ ጺዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ለውጦ ከእንግዲህ ወዲህ "ተክለሃይማኖት" እየተባልክ ተጠራ እንጂ ስም ፍስሐ ጺዮን አይሁን አላቸው አበው ስምን መላእክ ያወጣዋል እንዲሉ ፡፡ አያይዞም ፈረስ መጋለብ ጦር መስበቅ ቀስት መወርወር እንሰሳት ማደንን ተው ከእንግዲህ ወዲህ መስቀል ጨብጥ በወንጌል ስበክ ከአፍህ በሚወረወር በቃለ እግዚአብሔር መረብነት ሰው አድን አለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመላእኩ ክንፍ ላይ ተገልጦ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁ ብሎ በሐዋርያት ሾመት ሐዋርያ አድርጎ ሾመው። ጓደኞቹም ከያሉበት ተሰብስበው ወደ ተክለ ሃይማኖት ቀረቡ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ግን አላስተያይ አላቸው ስለዚህ ፊትህን ማየት አቃተን ተሸፋፈንልን ሲሉ ተማጠኑት። ሙሴ ከሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ በወረደ ጊዜ አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴ ሆይ ከፊትህ የሚወጣው ብርሃን አላስተያይ ብሎናልና እባክህ ፊትህን ሸፍንልኝ እንዳሉት ዘጽ 34÷29_35

#ጻድቁ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (ከአባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡ ሐዋርያዊ ተግባርንም በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታ፣በአምሓራና በሸዋ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ በመላዋ ኢትዮጵያ ወንጌልን አስፍተዋል።
ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ዛሬም በአጸደ ነፍስ ሆነው የሚፈውሱ ሐዲስ ሐዋርያ ሐዲስ ሱራፊ ናቸው።


በየ ደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ከሥራቸው ጽናት ከተአምራታቸው ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን ወይስ መላእክ ነህን ንገረን ይሏቸው ነበር። እርሳቸውም ከንቱ ውዳሴን ነፍሳቸው አጥብቃ ትጸየፈው ነበርና አባቶቼ እንደ

#ቀጣዮይ ይመልከቱ
👇👇👇👇
👆👆👆👆👆
ከላይ የቀጠለ

እናንተ ምድራዊ ሰው እንጂ መላእክ እሆን ዘንድ እኔ ማነኝ? እያሉ የሚያቃጥል የትዕትናን እንባ ከዐይኖቻቸው ይፈስ ነበር ። “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ” 1ጴጥ 5÷ 5 እንደተባለ ይህንን ይህን የትዕትና ሥራ ሲከተል ትዕትናው ፀጋውን አብዝታለት ያኔ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ሥላሴን በአንድነት ሦስትነቱ በማመስኑ ተደንቆ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲህ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው ብሎ የመረቀው የአባቱ ምርቃት ደርሳለት ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከፀሐይ ይልቅ ወደ ምታበራ ሀገር አደረሰው ።

#አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ አባታችንም ደግሞ እንደነርሱ ያዘ በምድር ብቻ ያይደለ በሰማያዊ መቅደስ ጭምር ገብቶ ከሱራፌል ጋር ሱራፊ ሆኖ ክንፉን ከክንፋቸው ገጥሞ ምስጋናው ከምስጋናቸው አንድ ሆኖ በወርቁን ማዕጥንት ይሰልስ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ ራእይ 5፥8 የቅዱስ ጳውሎስን ነገሩን ትምህርቱን የተከተለ ብጹህ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰማይ በመመንጠቅም ተከተለው፡፡ በመከራው መስሎታልና በክብሩ መሰለው “ ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገረው የማይገባወን የማይነገረውንም ቃል ሰማ ተብሎ እንደ ተጻፈ 2ቆሮ 12÷4 ስለዚህ በገድሉ መጻሕፍ እንዲ ሲል ሰማነው "ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከሃያ አራቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር በአንንድነት አጠንኩ ምስጋዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደ ልብሳቸው ሆነ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት" ገ/ተ ሃይማኖት ዘአርብ 43÷ 29

#የሐዲሱ_ሱራፊ_የአባታች_የቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት እረድኤትና በረከታቸው በአገራችን በኢትዮጵያና በሕዝበ ክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ጸንቶ ይኑር ! በወርቅ ጥናውም ዘወትር እያጠነ መዓዛ ክርስቶስን የምንሸት እውነተኛ ክርስቲያኖች አድርጎ የመንግሥቱ ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን!


............. ይቆየን............


ኀዳር 24/2013ዓ.ም
+ #እመ_ዕረፍት +
ዛሬ እመ ዕረፍት ዐረፈች፤እመ ሕይወት ዛሬ ሞትን ቀመሰች፤ዛሬ አማናዊት ዕፀ ሕይወት
ከዕፀ ሕይወት ሥር ዐረፈች።ዲያቢሎስ በክፋት ግብሩ ጥል ፣ሞት እየተባለ እንደሚጠራ
(ኤፌ 2፥16፤1ኛ ቆሮ 15፥26) እንዲሁ እግዚአብሔርም በጽድቁ ንጹህ ብቻ ሳይሆን
ንጽሕና ሕያው ብቻ ሳይሆን ሕይወት እየተባለ ይጠራል።ዛሬ "የአሸናፊ እግዚአብሔር እናቱ"
ድንግል ማርያም ዐረፈች።አራቱ ባሕርያተ ሥጋን አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕዶ የፈጠረ
(ዘፍ 2፥7) የጌታችን እናቱ ዛሬ ቅድስት ነፍሷ ከክቡር ሥጋዋ ተለየ።"እንደ እመቤታችን
እንደ ማርያም የአብ ማረፊያ የሆነ ማን ነው?እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የወልድ
ማደሪያ የሆነ ማን ነው?እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የመንፈስቅዱስ ንጹሕ አዳራሽ
የሆነ ማን ነው?"(ተአምረ ማርያም)።እኛም በአንክሮ በተደሞ "እንደ እመቤታችን እንደ
ማርያም ሞት እንግዳ ነገር ምንድን ነው?" ስንል እንጠይቃለን።"ሞት የኃጢአት ደሞዝ
ነዋ"(ዘፍ 2፥17፤ሮሜ6፥23)።በክብር ሁሉ ጌጥ ያጌጠ እርሱ ያደረባት ንጽሕት የሰርግ ቤት
ታዲያ ለምን ታርፋለች?ይህስ መርምረን የማንዘልቀው ድንቅ የመለኮት ሥራ ነው።አዳምና
ሔዋን የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለው ምክረ ሰይጣንን ሰምተው ሞትን ወደ ዓለም
አገቡ።ድንግል ማርያም ግን በመልአከ ብሥራት በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ቃለ
እግዚአብሔርን ሰምታ ሕይወትን ለዓለም ሰጠች።(ሮሜ 5፥12-17)።ታዲያ እመቤታችን
እንዴት ዐረፈች?ይህንን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል።
ሰንበተ ክርሰቲያን ድንግል ማርያም በሰንበተ ክርስቲያን እሑድ ዐረፈች።ዕለተ እሑድ
የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው።በዕለተ እሑድ የፍጥረታት መሠረት የሆኑ አራቱ ባሕርያተ
ሥጋ(አሥራወ ፍጥረታት) ተገኝተዋል።ከድንግል ማርያምም የፍጥረታት ሁሉ አስገኚ ጌታ
ተገኝቷል።ዕለተ እሑድ የፍጥረታት መጀመሪያ ነው ድንግል ማርያም ግን ለጠፋው ፍጥረት
ሁሉ "የደኅንነት መጀመሪያ" ናት።በዕለተ እሑድ ገነት ተፈጠረልን "ስለ ሔዋን የተዘጋብን
የገነት ደጅ" "በምትናገር ገነት" በድንግል ማርያም "ዳግመኛ ተከፈተልን"
በዕለተ እሑድ መንግሥተ ሰማያት ተፈጠርልን በድንግል ማርያም ግን ዕለት ተዕለት
"መንግሥትህ ትምጣ" "መንግሥት የአንተ ናትና" እያልን የምንማጸነው መንግሥቱን
የሚያወርሰን አምላካችን አማኑኤል ተገኘልን።በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ ውኃን
ፈጠረ በፈጠረው ውኃም ላይ መንፈሱን አሰፈረ።መንፈስ ቅዱስ የጠበቃት ኃይለ ልዑል
የጋረዳት ድንግል ማርያም ግን "ማንም የተጠማ" ከእርሱ የሚጠጣ ጠጥተውት ዳግመኛ
የማያስጠማ ማየ ሕይወት ክርስቶስን ወለደችልን።በዕለተ እሑድ መላእክት ተፈጠሩ
በአማናዊት እሑድ በድንግል ማርያም ግን"ኪሩቤል በፍርሃት የሚሰግዱለት ሱራፌልም
የሚያመሰግኑት" "የመላእክት ደስታቸው"መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኘ።በዕለተ
እሑድ "እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ።"(ዘፍ 1፥3)በድንግል ማርያም ግን
"በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ" ለምንኖር ለእኛ "ታላቅ ብርሃን ወጣልን።"በዕለተ እሑድ
መንግሥተ ሰማያት ለጻድቃን ትሰጣለች ጌታችን ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ ግን
ወርሰውት ለዘላለም ይኖራሉ።እመቤታችን ሆይ በማንና በምን እንመስልሻለን?ሰንበት
ድንግል ማርያም ሆይ ሰንበት ከሚባል የሰንበታት ጌታ ከሆነ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን
እንዳይነሣን ለምኚልን።
እመቤታችን ካረፈች በኋላ ለምቀኝነት የማያርፉ አይሁድ በፊት ልጇ ከሞተ በኋላ ተነሥቷል
ዐርጓል እያሉ አወኩን።አሁን ደግሞ እሷን ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን?
ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ ሥጋዋን እናቃለጥለው ተባባሉ።ምቀኝነት ትርፉ ይህ
ነው።መታወክ።"ዓለም እንደሚሰጠው ሰላም ያይደለ እውነተኛ ሰላም የሚሰጠን የሰላም
አለቃ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ" ግን ዕረፍተ ኅሊናን እናገኝ ዘንድ "ጠላቶቻችሁን
ውደዱ" ብሎ አስተማረን።ማኅደረ ሰይጣን የሆነ ታዖፋንያ የሚባል ከእነርሱ አንዱ ክቡር
ሥጋዋን አቃጥላለሁ ብሎ የአልጋዋን አጎበር ቢይዝ መልአከ እግዚአብሔር እጆቹን በሰይፍ
ቆርጧቸዋል።አላወቃትማ "ቢያውቃትስ ኖሮ የክብርን እናት ሥጋ ለማቃጠል ባልደፈረ
ነበር።" በመስቀል ላይ"አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸው"ብሎ የለመነ
የፍቅር እናቱ የምትሆን ድንግል ማርያም ግን በከበረ ምልጃዋ እጆቹን አሰጠችው።እሱ
ቅዱስ ሥጋዋን ለማቃጠል እጆቹን ዘረጋ እመቤታችን ግን በሥጋዉም ሆነ በነፍሱ ታድነው
ዘንድ የምህረት እጆቿን ዘረጋችለት።ወንጌልን ያስተማርሽን ንጽሕት ፊደላችን ሆይ
እናመሰግንሻለን።የድንግል ማርያም ትንሣኤ ያውካልን?አዎን፤ በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ
"ከኪሩቤልና ከሱራፌል የሚበልጥ የመወደድ ግርማ" ያላት ድንግል ማርያም
በአጋጋንት፣በአይሁድና በመናፍቃን ዘንድ ግን "ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል
የሚበልጥ የማስፈራት" ግርማ አላት።
ከከበረ ዮሐንስ ጋር ወደ ዕፀ ሕይወት ተነጠቀች።"ዓለም አልተገባቸውምና።"(ዕብ
11፥38)ጌታን ከሁሉ አብልጦ ለወደደ ዮሐንስ ከሁሉ አብልጦ የሚወዳት ድንግል
ማርያምን በዕለተ ዓርብ ሰጠው።ከወንድሞቹ ሐዋርያት ተለይቶ ከእመቤታችን ጋር ከእግረ
መስቀሉ ሥር የተገኘ ዮሐንስ አሁን ደግሞ ከእነርሱ ተለይቶ ከእመቤታችን ጋር ከዕፀ
ሕይወት ሥር ተገኘ።ቅዱስ ዮሐንስ ከሕይወት ከክርስቶስ ደረት እየተጠጋ ጌታውን ያነጋግር
እንደነበረም ቅዱስ ወንጌል ነግሮናል።የቅዱስ ዮሐንስ እናት ማርያም ጌታ ሆይ በዙፋንህ
በተቀመጥህ ጊዜ አንዱ ልጄን በቀኝህ አንዱን በግራ አስቀምጥልኝ ብላ ለምናው
ነበር።በዙፋኑ "በአባቱ ቀኝ"የተቀመጠውም ቅዱስ "በቀኙ በምትቆመው" በአማናዊቱ ዙፋን
በድንግል ማርያም አጠገብ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖረው።ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን
በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ከተቀበለ በኋላ "ወደ ቤቱ ወሰዳት"(ዮሐ19፥27) እሷ ደግሞ አሁን
በዕለተ እሑድ "ወደ ቤቷ ወሰደችው"። የዓርብ መከራ ተካፋይ ቅዱስ ዮሐንስ የእሑድ ደስታ
ተካፋይም ነበር።ዕፀ ሕይወት አዳምን ከእርጅናው(ከኃጢአቱ) ልታድሰው አልቻለችም።ዕፀ
ሕይወት ድንግል ማርያም ግን "በአዲስ ተፈጥሮ" ዳግመኛ የሚፈጥረዉን ሕይወቱ
ክርስቶስን ወለደችለት።ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል "ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን
ይኸውም... የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ነው።"
ሞቷ እንደ ልጇ ሞት ነው።እሱ መላ ዘመኑን አዝኖ "ነፍሱ እስከሞት ድረስ ያዘነች" ሆና
ሞተ።(ማቴ 26፥38)
እሷም ከእሱ ጋር ተንከራታ "በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል"እንዳላት ቅዱስ ስምዖን አረጋዊ(ሉቃ
2፥34-35) እንደ ሰይፍ ነፍስን ከሥጋ ሊለይ የሚችል ጽኑ ኀዘንና መከራ ገጥሟት
ሞተች።የጌታችን ሞት ቅዱሳን መላእክትንና ሰዎችን አንድ አደረገ።የእመቤታችንም ሞት
እንዲሁ ነው።
ትንሣኤዋም እንደ ልጇ ትንሣኤ ነው። እንደ ልጇ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር
ቆይታ ተነሥታለችና።"ከመ ትንሣኤ ወልዳ" "እንደ ልጇ ትንሣኤ" ያሰኘውም ይህ
ነው።"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር የተባበረች ድንግል ማርያም ትንሣኤውን
     +++🙏  የጉጠቱ ፍም 🙏+++
 🙏 እግዚአብሔርን በመለኮቱ ልዕልና ያየው ማንም የለም ነገር ግን እርሱን መስለው ለኖሩ ቅዱሳን በአቅማቸው ልክ ይገለጥላቸዋልያናግራቸውማል።
ለአብርሃም በሽማግሌ ፣ ለሙሴ በሃመልማል እንዲሁም ለእነ ዳንኤል ዕዝራ ኢሳይያስ አይቶ በቃላት ድርድር ማስረዳት በማይቻልበት ክብር ተገልጦላቸዋል።
    🙏የጉጠቱን ፍም ስናስብ ከክርስቶስ ልደት በፊት ንጉስ ዖዝያን የሞተበትን ዓመት እናስታውሳለን መጽሐፍ እንደሚነግረን የይሁዳ ሕዝብ እስራኤልን እንዲመራ ዖዝያንን ገና የ16 ዓመት ጎልማሣ እያለ ነበር የቀቡት የንግስናን ዘውድ ደፍተው የወርቅ ካባን የደረቡለት።በንግስናውም ዘመን መልካሙንም ክፋውንም አሳልፏል።ከፍልስጥኤማውያን ጋር በነበረው ጦርነት እግዚአብሔር ረድቶት እነርሱን ድል አድርጎል በኋላ ዝናው እና ስሙ በዓለም ሁሉ ተሰማለት በደስታውም ተነሳስቶ ሦስት መቶ ሰባ ሺ አምስት መቶ ለሚሆኑ ጭፍሮቹ ልዩ ልዩ የሆኑ ጋሻና ጦር ቀስቶችን ሰርቶ አስረከባቸው ነገር ግን ይህን ሁሉ የስኬት ጫማ ሲጫመት የረዳውን አምላክ በመዘንጋቱ ልቡ ታበየ አምላኩንም በደለ በዙፋኑ በቀኝ አብሮት የሚቀመጠውን ካህኑን አዛርያስን ለምን በቀኜ ትቀመጣለህ በማለት ሠማያዊ ወምድራዊ ሥልጣን ካለው ጋር ይፎካከር ጀመረ እርሱም መልሶ "ካህን ይነብር በየማንከ(ካህናት በቀኝ ይቀመጣሉ)" ይልብሀል ህጉ ይለውና ደንቡን ነግሮ ዝም የስብለዋል ቀኝ የክብር መገለጫ ነውና።ኋላ ግን ዖዝያን በድፍረት ቤተመቅደስ ገብቶ ያለ ሥልጣኑ በዕጣን መሰዊያ ላይ አጠነ ያኔ እግዚአብሔር አምላክ በለምጽ መታው ከሰው ተለይቶ  በተለየ ቤት ለምጻም ሆኗልና ተቀመጠ ጊዜውም ደረሰና የንግስናውን ዘውድ ለልጁ አስረክቦ ከዚች አለም በሞተ ተለየ።
     🙏ንጉስ ዖዝያን በሞተበት አመት ልጁ ኢዮአታም በምትኩ በነገሰበት ዘመን ነበር ነብዮ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ በሚያስፈራ ዙፋን የልብሱ ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት የተመለከተው። ቅዱሳን የቅድስናቸው ደረጃ ጥግ ሲደረስ እግዚአብሔርን የማያት ክብር ላይ ይደርሳሉ። እንዴት መታደል ነው! እግዚአብሔርን ማየት! ማነው ይህንን ክብር'ስ የማይፈልግ? ነቢዩ በዙፋኑ ላይ ለማመን የሚከብዱ ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የመጠቁ ዕጹብ የሚያስብሉ ድንቆችንም ተመልክቷል፤ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማያ ስድት ክንፍ ያላቸው በመቅደሱ ዙሪያ ረበው አንተን ማየት አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ በአንተ ፊት መቆም አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን ሸፍነው በቀሪው ሁለት ክንፋቸው እየበረሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሠግናሉ። ምግባቸው መጠጣቸው ህይወታቸው ምስጋና! የእኛስ ህይወት? በምስጋና የተሞላ ወይስ በማማረር? መልሱን ለእራሳችን ። የሚደንቀው ነገር ሱራፌልም እኛም እርሱን ብናመሰግን ለእግዚአብሔር የምንጨምረው የምንቀንሰው ባለመኖሩ ነው ይልቁንስ አመስግነን መንግስቱን እንወርሳለን እንጂ።
🙏በመላእክቱ የምስጋና ቃል ጩኸት የመድረኩ መሠረት ተናወጠ ቤቱም በጢስ ተሞላ ነብዪም ተጨነቀ እጅግም ፈራ “እንዲህም ሲል ተናገረ፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! "
ትሁት አነጋገር! እግዚአብሔርን አይቻለሁ በቅቻለሁ ብሎ አልታበየም ነብዩ ኢሳይያስ ዖዚያን ከብርያለው ገንኛለሁ ብሎ እንደታበየ ይልቁን እራሱን ከነፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሰዎች ጉባኤ መሀል ወረወረ ራሱን ዝቅ አደረገ የሠራዊት ጌታ ዝቅታውን ፀፀቱን ተመልክቶ አንዱን ሱራፌል ላከለት ያም መልአክ በእጁ ከመሠዊያው በጉጠት ፍም ወስዶ አፋንም ዳሰሰለት ቀጠለና ታላቅ የድኅነት ቃል አሰማው " እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ።” በነብዩ ኤርሚያስ የተነገረው “እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ” የሚለው ትንቢት ተፈጸመ።
     🙏+ ጌታ ሆይ እንደ ነብዩ የተተረኮሰ አንደበት ስጠን ለእርሱም የላከውን ፍም እሳት ላክና ከአርያም የሚያቃጥለንን በደል ኃጢአት የሚያሰራንን በውስጣችን ያለውን እንክርዳድ አቃጥልልን። +
    15/02/2014
     ድሬዳዋ ኢትዮጵያ
       ተጻፈ በባሮክ ዘ አሚን
#ሐዲስ_ሱራፊ
_________
#ተክለ_ሃይማኖት
_____________
#ሱራፊ ማለት መልአክ፣ ከካህናተ ሰማይ አንዱ ማለት ነው፡፡ ሱራፌን፣ ሱራፌል፣ ሱራፌም
(በፅርዕ ሴራፊም፣ በዕብራይስጥ ስራፊም) ማለት የነገድ ስም፣ ልዑላን መላእክት፣
ሊቃናት፣ የሚያጥኑ፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ቀዳሾች ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/ ከዚህ
ላይ ሱራፊ ነጠላ ቍጥርን ሲያመለክት፤ ሱራፌል ደግሞ ብዙ ቍጥርን ያመለክታል፡፡
ሱራፌል ለቅዱሳን በሰው አምሳል በመገለጣቸው ሽማግሌዎች ተብለው ተጠርተዋል /
ኢሳ.24፥23፤ መሳ.13፥2-25፤ /፡፡ በግእዝ ቋንቋ ደግሞ ካህናተ ሰማይ ይባላሉ፡፡ ካህናተ
ሰማይ ሱራፌል ቁጥራቸው 24 እንደሆነ ባለ እራዮ ዮሐን ጽፎልናል ይህ ግን 24ሰዓት ያለ
እረፍት የሚያመሰግኑ መሆናቸውን ለማመልከት የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጂ
ቁጥራቸውስ 24ብቻ ሆኖ አይደለም ።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር
በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ አቅሮቦላቸዋል። በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ
ለ24ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም
ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣
ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣
መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣
እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ
ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና
ትርጓሜው / መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ እንደተረጎመው)
ዛሬ በዚህች መጠነኛ ጽሁፍ ኅዳር 24ቀን ከነዚህ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ጋር ተደምሮ
የሥላሴን መንበር ያጠነ አዲሱን ምድራዊ ሱራፊን ተክለ ሃይማኖት /ተክለ ኤልን /
እናስተዋውቃችዋለን። ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ከዘር የተገኙ ምድራዊያን አይደለም ተክለ
ኤል ተክለ ሃይማኖት ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ምድራዊ ሰው የሆነ ሐዲስ ሱራፊ ነው።
‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ
፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /
ማቴ.15፥13/፡፡
"ኤል" ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘሉ
በመሆናቸው የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው ለምሳሌ ከላይ
የጠቀስናቸው የሃያራቱን ካህናተ ሰማይ የሱራፌልን ስም መመልከት ይቻላል :- አካኤል፣
ፋኑኤል፣ ጋኑኤል ወ.ዘ.ተ ስለዚህ "ተክለ ኤል " ማለታችንም ይህ ሐዲስ ሱራፊ ስሙ
ከስማቸው ጭምር የሚገጥም መሆኑን ለመግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ተክል ተክለ
እግዚአብሔር ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ እግዚአብሔር
ባልኩ ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ " ተክለ ኤል" ተክለ
እግዚአብሔር ሲባልም የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል የሚል ትርጉም ይሰጣል ።
# አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል
በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ
አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ዘርዐ ዮሐንስ
ወይም ጸጋ ዘአብ (የአብ ሥጦታ) ከሚባል ካህን እና ሣራ ወይም እግዚእ ኅረያ
(እግዚአብሔር የመረጣት)በመባል ከምትታወቅ ደጋግ ከሆኑ ባልና ሚስቶች በመላእክ
አብሳሪነት መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ገደማ ነው።
ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጺዮን ።(የፂዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ
በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ
እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት
መጥባት ነው" ብላ ለህጻኑ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡ ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን
ገና በህጻንነት የገለጠ ነበር ቀን ከለሊት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ማመስገን የመላእክት
መገለጫ ነውና ኢሳ 6÷6 ። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን
ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚእ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን
ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምስጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ
ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ
መቅደስ ስትቀድስ ዐይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።ከዚህም በኃላ ፍስሐ ጺዮን በሰውና
በእግዚአብሔር ፊት በጥበብና በሞገስ አደገ።
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር በዱር ፈረስ ሲጋልብ
ጦር ሲሰብቅ ተገናኝቶት ፍስሐ ጺዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ለውጦ
ከእንግዲህ ወዲህ "ተክለሃይማኖት" እየተባልክ ተጠራ እንጂ ስም ፍስሐ ጺዮን አይሁን
አላቸው አበው ስምን መላእክ ያወጣዋል እንዲሉ ፡፡ አያይዞም ፈረስ መጋለብ ጦር መስበቅ
ቀስት መወርወር እንሰሳት ማደንን ተው ከእንግዲህ ወዲህ መስቀል ጨብጥ በወንጌል
ስበክ ከአፍህ በሚወረወር በቃለ እግዚአብሔር መረብነት ሰው አድን አለው ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስም በመላእኩ ክንፍ ላይ ተገልጦ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁ ብሎ
በሐዋርያት ሾመት ሐዋርያ አድርጎ ሾመው። ጓደኞቹም ከያሉበት ተሰብስበው ወደ ተክለ
ሃይማኖት ቀረቡ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ግን አላስተያይ አላቸው ስለዚህ ፊትህን ማየት
አቃተን ተሸፋፈንልን ሲሉ ተማጠኑት። ሙሴ ከሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ
በወረደ ጊዜ አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴ ሆይ ከፊትህ የሚወጣው ብርሃን
አላስተያይ ብሎናልና እባክህ ፊትህን ሸፍንልኝ እንዳሉት ዘጽ 34÷29_35
# ጻድቁ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው
ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (ከአባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡ ሐዋርያዊ ተግባርንም
በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታ፣በአምሓራና በሸዋ
በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ
ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ
አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ በመላዋ
ኢትዮጵያ ወንጌልን አስፍተዋል።
ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣
እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና
በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ
በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ
እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን
በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ዛሬም በአጸደ ነፍስ ሆነው የሚፈውሱ
ሐዲስ ሐዋርያ ሐዲስ ሱራፊ ናቸው።
በየ ደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ከሥራቸው ጽናት ከተአምራታቸው ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን
ወይስ መላእክ ነህን ንገረን ይሏቸው ነበር። እርሳቸውም ከንቱ ውዳሴን ነፍሳቸው አጥብቃ
ትጸየፈው ነበርና አባቶቼ እንደ እናንተ ምድራዊ ሰው እንጂ መላእክ እሆን ዘንድ እኔ ማነኝ?
እያሉ የሚያቃጥል የትዕትናን እንባ ከዐይኖቻቸው ይፈስ ነበር ። “እግዚአብሔር
ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ” 1ጴጥ 5÷ 5 እንደተባለ ይህንን
ይህን የትዕትና ሥራ ሲከተል ትዕትናው ፀጋውን አብዝታለት ያኔ በተወለደ በሦስተኛው ቀን
ሥላሴን በአንድነት ሦስትነቱ በማመስኑ ተደንቆ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲህ እያልክ
በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው ብሎ የመረቀው የአባቱ ምርቃት ደርሳለት
ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ድንገት ነጥቆ ወስዶ
ከፀሐይ ይልቅ ወደ ምታበራ ሀገር አደረሰው ።
# አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና
የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ አባታችንም ደግሞ እንደነርሱ ያዘ
በምድር ብቻ ያይደለ በሰማያዊ መቅደስ ጭምር ገብቶ ከሱራፌል ጋር ሱራፊ ሆኖ ክንፉን
ከክንፋቸው ገጥሞ ምስጋናው ከምስጋናቸው አንድ ሆኖ በወርቁን ማዕጥንት ይሰልስ
ይቀድስ ዘንድ ጀመረ ራእይ 5፥8 የቅዱስ ጳውሎስን ነገሩን ትምህርቱን የተከተለ ብጹህ
አባታችን ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰማይ በመመንጠቅም ተከተለው፡፡ በመከራው መስሎታልና
በክብሩ መሰለው “ ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገረው የማይገባወን የማይነገረውንም
ቃል ሰማ ተብሎ እንደ ተጻፈ 2ቆሮ 12÷4 ስለዚህ በገድሉ መጻሕፍ እንዲ ሲል ሰማነው
"ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከሃያ አራቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ
የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር በአንንድነት አጠንኩ ምስጋዬ ከምስጋናቸው
ጋር ልብሴም እንደ ልብሳቸው ሆነ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት" ገ/ተ
ሃይማኖት ዘአርብ 43÷ 29
# የሐዲሱ_ሱራፊ_የአባታች_የቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት እረድኤትና በረከታቸው በአገራችን
በኢትዮጵያና በሕዝበ ክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ጸንቶ ይኑር ! በወርቅ ጥናውም ዘወትር እያጠነ
መዓዛ ክርስቶስን የምንሸት እውነተኛ ክርስቲያኖች አድርጎ የመንግሥቱ ወራሾች የስሙ
ቀዳሾች እንድንሆን ያድርገን ለዘላለሙ አሜን!
............. ይቆየን............
ኀዳር 24/2013ዓ.ም